You are on page 1of 2

በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ ስልጠና ላይ ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው የአካዳሚያችን

ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና ላይ በውይይት ወቅት የተነሱና

መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው ጥያቄዎች፤

የስልጠና ሰነዱ ርዕስ፡- የግብርና ልማት ስትራቴጅና አቢዩታዊ ዴሞክራሲ

1. የአመለካከት ጥያቄዎች

 መሬት ይሸጥ ይለወጥ ብንል ምን ችግር ይፈጠራል? በልማት ምክንያት የሚነሱ ሠዎችስ አሁን ከምንለው ጋር
አይጋጭም ወይ?

 ልማትና ዴሞክራሲን በአንድ ላይ ማስኬዱ ጥሩ ቢሆንም አንዳንዴ ግን አብሮ ለማስኬድ


ያስቸግራል፡፡ ለምሳሌ መንገድ ለመስራት ህዝቡን አሳምነን ተወያይተን ካልተሳካልን ልማቱ
ይጓተታል፡፡ ይህንን ባማከለ መልኩ እንደት ፈጣን ልማት ማረጋገጥ ይቻላል?

 ከደርግ ጊዜ ጀምሮ 85% የኢት/ያ ህዝብ በገጠር ነው የሚኖር ይባላል፡፡ በግብርናችን ይህን
ያክል ለውጥ ካለ ታዳ ለውጡ ምኑ ጋ ነው? ለምንስ ከእርዳታ አልወጣንም?

 ግብርናችን ለምን የተበጣጠሰ መሬት ላይ ብቻ ይሆናል? ሜካናይዝድ የሆነ እርሻ ብንጠቀም


ጉዳቱ ምንድን ነው ?

2. የግንዛቤ፣የእውቀት/መረጃ/ ክፍተት ጥያቄዎች


 የጫት ምርት እና የቢራ ፋብሪካዎች በሃገራችን እየበዙ ነው፤ ይህ ደግሞ ሱሰኛና ጤናማ ያልሆነ ትውልድን
የሚፈጥር ከመሆኑ አንፃር የግብርና መር ስትራቴጂው ይህን ጉዳይ እንደት ያየዋል?

 ዝርያን የማዳቀል ስራ ከተፈጥሮ ውጭ ስለሆነ የጎንዮሽ ጉዳት የለውም ወይ?

 ገበሬውን ከማስተማር አንፃር የተቀመጠ ነገር አለ፤ ነገር ግን በትክክል በትምህርት ፖሊሲያችን ውስጥ የለም፤
የጎልማሶች ት/ርት የሚባለውም ቢሆን በደርግ ጊዜ የነበረ ነው፤ ይህ እንዴት ይታያል?

 የሞደል አርሶ አደር አመራረጥና ገበሬዎችን በህብረት ስራ ማህበር የማደራጀት ጉዳይ ከፖለቲካ
ጋር የተያያዘ ይመስላል፡፡ የሚመረጡትም አርሶ አደሮች ሁልጊዜ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሞደሎችን
ስንመርጥ ችግር የለም ወይ?

 የሚስተዋለውን ከፍተኛ የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ችግር እስከ አሁን ለምን መፍታት
አልተቻለም?

You might also like