You are on page 1of 2

በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ ስልጠና ላይ ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው የአካዳሚያችን

ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና ላይ በውይይት ወቅት የተነሱና

መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው ጥያቄዎች፤

የስልጠና ሰነዱ ርዕስ፡- የኢት/ያ ፌደራሊዝም ስርዓት ግንባታ ስኬቶችና ተግዳሮቶች

1. የአመለካከት ጥያቄዎች

 ኤክስፖርት መር የኢንዱስትሪ ልማት ስትረሰቴጂ በሃገር ውስጥ የኑሮ ውድነትን አያባብስም


ወይ? የኛ የሃገር ውስጥ የገባያ ፍላጎት መቼ ተሟላ ነው እንድህ አይነት ፖሊሲ የተመረጠው?

 ለኢንዱስትሪው ዘርፍ እኩል ተወዳዳሪነትን ከመፍጠር አንፃር በመንግስት እጅ ያሉ


ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች በግሉ ዘርፍ ያሉ ኢንዱስትሪዎች እንደት እኩል ይስተናገዳሉ?
በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ እንደ ስኳርና ብረታብረት ባሉትም የኪራይ ሰብሳቢነት እየተስፋፋ
ይታያል፡፡ ይህ ልማታችንን እየጎዳ አይደለም ወይ?

 የኮንደሚንየም ልማት የመክፈል አቅም በሌለው በድሃውና አቅም ባለው በሃብታሙ መካከል
ይባስ ልዩነት እየፈጠረ አይደለም ወይ? የከተማዋን ታሪካዊ ገፅታዎችንም እያጠፋ አይደልም
ወይ? ጥራቱስ እንደት ይታያል?

 ለሰው ሃብታችን የሚከፈለው ክፍያ ይህን ያክል መውረዱ ለምን አስፈለገ? የሰለጠነ የሰው
ሃብታችን በብቃቱ እውነት ከሌላ ሃገራቶች ጋር ተወዳዳሪ አይደለም ወይ?

2. የግንዛቤ፣የእውቀት/መረጃ/ ክፍተት ጥያቄዎች


 መንግስት ኤክስፖርትን ለማበረታታት የውጭ ምንዛሬ ተመን ግሽበት ማስተካከያ /Exchange Rate
Devaluation/ አድርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ሰፊው ህዝብ ገቢ ምርቶችን የሚጠቀም ከመሆኑ አንፃርና
በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችም ላይ ቢሆን የሃገር ውስጥ ገበያው ላይ የዋጋ ግሽበትን
ስለሚያስከትል ሃገራዊ ጠቀሜታው እንደት ይታያል?
 እንደ ኑግ ሰሊጥ፣ ቡና ያሉ ምርቶችን እሴት ለመጨመር መንግስት ለምን ጣልቃ አይገባም?
 ብድር ለማግኘት ቅድሚያ ቁጠባ የሚጠየቅበት ሁኔታ እያለ እና የተመቻቸ የመስሪያና
የመሸጫ ቦታ በለሌበት ሁኔታ በጥቃቅንና አነስተኛ ለመስራት ምን ያህል አመቺ ነው?
የሚያመርቱት ምርቶቻቸው ወደ ሃገር ውስጥ ከሚገቡ ምርቶች የገበያ ውድድር ተፅዕኖ ስር
እንዳይወድቁስ ምን የማበረታቻ ከለላ አላቸው?
 የሃገራችን ከተሞቻችን በእኩል /ተመሳሳይ/ እድገት እያደጉ አይደለም፡፡ ለምን?
 ከተሞችን ለማስፋፋት ሲባል ገበሬውን ያለ በቂ ካሳ በማፈናቀል እየጎዱት ነው፡፡ ይህ
ከፖሊሲው አንፃር እንደት ይታያል?
 ሙሉ የግብርናው ውጤቶች ኢክስፖርት ላይ የተኩር ከተባለ እውነት የኢንዱስትሪውና
የግብርናው ዘርፍ ተመጋጋቢ ይሆናል ወይ?
 የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን/FDI/ ለመሳብ ከፍተኛ ትኩረት ሲሰጥ የሃገር ውስጡን
ባለሃብት ከውጭው ባለሃብት ጋር ተወዳዳሪ እንድሆን ምን ማበረታቻ አለ?
 የኮንስትራክሽን የጥርት ችግር እንደት ይታያል?
 አሁን ያለው የከተሞቻችን ትስስር ምን ያክል ጠንካራ ነው?
 በቴሌ፣ ውሃና መብራት ሃይል ላይ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማስተካከል መንግስት ምን እየሰራ
ነው? ቴሌስ ምን ሰርቶ ነው በአፍሪካ ተሸላሚ የሆነው?
 በከተሞቻችን በተለይም በአ/አ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ምን
ታስቧል?

You might also like