You are on page 1of 2

በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ ስልጠና ላይ ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው የአካዳሚያችን

ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና ላይ በውይይት ወቅት የተነሱና

መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው ጥያቄዎች፤

የስልጠና ሰነዱ ርዕስ፡- የኢት/ያ ፌደራሊዝም ስርዓት ግንባታ ስኬቶችና ተግዳሮቶች

1. የአመለካከት ጥያቄዎች

 ልማትና ዴሞክራሲ የማይነጣጠሉ ናቸው እንላለን፡፡ ነገር ግን ለተለያዩ የልምት ስራዎች ሲባል
ዜጎችን ያለ በቂ ካሳ በማፈናቀልና የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ባልጠበቀ
መልኩ ልማት እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ነን ማለት ይቻላል ወይ?

 አሁን በኢት/ያ ዴሞክራሲ አለ ወይ?


 የተለያዩ የህዝብ ጥያቄዎች ሲነሱ ምላሽ የምንሰጥበት ሁኔታ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መብቶች
የሚገፋ መሆቻቸው፤
 በወረቀት ላይ ብቻ እንጅ በቡድን ተቀምጦ ማውራትና ሃሳብን በነፃነት /በተለይ የሚዲያ ነፃነት/
እንኳን አይቻልም፡፡ ለምን?

 አሁን በትክክል በህገ- ምንግስቱ መሰረት ክልሎች እራሳቸውን የቻሉ ናቸው ወይ? የፌደራል
መንግስት ተላላኪ አይደሉም ወይ?

 በየተቋማቱ የብሔር ተዋፅኦ አሰራር ተግባራዊነቱ ምን ያህል ነው? በፌደራልና በአ/አ የትግራይ
ክልል ተወላጆች ከሌሎች ይበልጣል፡፡ ይህ የአንድ ብሔር የበላይነትን አያሳይም ወይ?

2. የግንዛቤ፣የእውቀት/መረጃ/ ክፍተት ጥያቄዎች


 ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ ማለት ምን ማለት ነው? ትርጓሜተቸውና ልዩነታቸው በህገ- መንግስታችን
ውስጥ ለምን በግልፅ አልተቀመጠም?
 ሃገራችን በዘጠኝ ክልሎች እንደተዋቀረች ህገ መንግስቱ ቢያወራም ሀገሪቱን የሚመራው ፓርቲ ግን አራቱን
ክልል ብቻ ነው ግንባር የፈጠረው። ቀሪ አምስቱስ ለምን አልተካተቱም?
 ሀይማኖትና መንግስት የትለያዩ ናቸው። ነገር ግን በጋራ ይሰራሉ። የሚዳኙበት የህግ አግባብ አለ ወይ?
 የፌደራል ስርዓታችን ግጮቶችን ይቀንሳን አንድነትን ያጠናክራል ተብሏል፡፡ነገር ግን አሁን
በየቦታው የሚታየው የብሔር መልክ ያለው፤ በቅርቡም በእግር ኳስ ሜዳ ሳይቀር እየተከሰተ
ያለው ግጭት ምክንያቱ ምንድን ነው? ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት ሁኔታም እየከበደ
ነው፡፡ በብሔርተኝነት ስሜት መከፋፈል እንጅ ሃገራዊ ስሜት ጠፍቷል፡፡ ብሔርን መሰረት
ያደረጉ የታጠቁ ሃይሎችም አሉ፡፡ታዳ ይህ ለምን ሆነ?
 ክልሎች የየራሳቸው ባንድራ አላቸው፡፡ይህ የሃገር አንድነትን አያደበዝዝም ወይ? አንድ ሃገር
አንድ ባንድራ ብቻ ቢኖረንስ? አንቀፅ 39 እና የሃገር አንድነት እንደት ይጣጣማል?
 ህገ መንግስታችን ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው ቢልም ከተጠያቂነት አንፃር አመራሮች በህግ የሚጠየቁበት
ሁኔታ የለም። ይሄ ከምን የተነሳ ነው?
 የፌደራል መንግስት ሁሉንም ክልሎች እኩል በልማት ለማመጣጠን እየሰራ ነው ወይ?
 ኢህአዴግ ምሁራንን በምርምርና በተለያዩ ጉዳዩች እንድሳተፉ ለምን ምቹ ሁኔታ አይፈጥርላቸውም ?
 አዲስ አበባ የማን ናት? የፌደራልም የኦሮምያ ክልልም ከተማ ናት ይባላልና፡፡
 በባለፉት መንግስታት የተሰሩ ተቋማትና ከተሞች ስም እየተቀየሩ ነው፡፡ይህ ለምን አስፈለገ?
ምሳሌ፡- ተፈሪ መኮነን ት/ቤት፣ ኢት/ያ ትቅደም ት/ቤት ወዘተ….
 መንግስት በአሁኑ ወቅት ህዝቡን ምን ያህል በብቃት እየመራው ነው? ለምሳሌ፡- ውጭ ሃገር
ያሉ ድያስፖራዎች ህዝቡን/በተለይም የኦሮሚያን/ እንዳሻቸው ሲያዝዙት ይታያል፡፡
 በሃገራችን ችግር ሲከሰት ብቻ ተሃድሶ ይካሄዳል፡፡ ይህ እስከመቼ አዋጭ ነው? ለምንስ ጠንካራ
ዴሞክራሲ አይገነባም?

You might also like