You are on page 1of 2

በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ ስልጠና ላይ ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው የአካዳሚያችን

ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና ላይ በውይይት ወቅት የተነሱና

መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው ጥያቄዎች፤

1. የአመለካከት ጥያቄዎች
1.1 ኒዮ-ሊብራሊዝም ሞግዚታዊ አሠራርን ይፈጥራል ተብሏል፤ ነገር ግን የኛ ልማታዊ ዴሞክራሲ እኛን
በቻይና ቁጥጥር ስር አላደረገንም ወይ?
1.2 መንግስት እየተከተለ ያለው የኢኮኖሚ ጣልቃ ገብነት ወደ እዝ ኢኮኖሚ እያደላ ነው
ወይስ ወደ ነፃ የኢኮኖሚ ስርዓት?
1.3 ሁልግዜ ያለፉት መንግስታት ስህተቶች ላይ ነው፡፡ ለምን? አሁን ላይ ራሳችንን ከደርግ ጋር
ማወዳደራችን ምን ያህል ተገቢ ነው?መንግስት በሚሰራው ስራ ሳይሆን ሌሎችን
በማጥላላት ላይ ተጠምዷል ለምን?
1.4 የደርግ መንግስት ብዙ ፀረ-ደሞክራሲያዊ ድርጊቶች ነበሩት ተብሏል፡፡ ነገር ግን አሁን
በተግባር እያየነው ያለነው ሁኔታ ከዛኛው ስርዓት በምን ይሻላል?
1.5 የደርግ ሥርዓት መሬት ላራሹ ብሎ ለገበሬው ቢሠጥም ገበሬውን ግን ተጠቃሚ አላደረገም ተብሏል፤ ነገር
ግን የምንከተለው የልማታዊ ዴሞክራሲ መስመር የገበያ ስርዓት እውነት ገበሬውን ተጠቃሚ አድርጓል
ወይ? ገበሬው እውነት ከልማቱ ተጠቃሚ ከሆነ እየታየ ያለው ከተለያየ የሀገራችን ክፍል ወደ አ/አ (የገጠሩ
ወጣት ወደ ከተማ) የሚደረግ ፍልሰት መጨመሩ ይህን አያመላክትም ወይ?
1.6 አሁን የምንከተለው የነፃ ገበያ ከእዝኢኮኖሚ ምን የተሻለ ነገር ፈጥሯል ?
እንዲያውም ሃብታሙን የበለጠ ሃብታምና ደሃውን የበለጠ ደሃ በማድረግ በዜጎች መካከል ከፍተኛ የገቢ
ልዩነት ፈጥሯል፤ ታዲያ እንዲህ ከሆነ ደርግ ሲከተል የነበረው የሃብት ገደብ ለዚህ ችግር መፍትሄ ስለሚሆን
አሁንስ ለምን አንጠቀምበትም?
1.7 ቴሌን፣ መ/ሃይልንና ባንክን ወዘተ… ያሉትን ትልልቅ የልማት አውታሮች ለምን ለግሉ ዘርፍ መስጠት
አልተፈለገም? የመዓድን ዘርፉስ ለምን ለግሉ ዘርፍ ተሠጠ/ተፈቀደ?
2. የግንዛቤ፣የእውቀት/መረጃ/ ክፍተት ጥያቄዎች
2.1 የሊብራሊዝም፣ ኒዩ ሊብራሊዝም፤ የሶሻሊዝምና አብዮታዊ ደሞክራሲ ፖለቲካዊና
ኢኮኖሚያዊ አንድነታቸውና ልዩነታቸው ቢብራራ?
2.2 በሰነዱ ላይ ኒዮ-ሊብራሊዝም ጉዳት ብቻ ነው የተንፀባረቀው፤ እውነት ጥቅም የለውም ወይ ? ጥቅም
ከሌለውስ የበለፀጉት ሀገራት ለምን መረጡት?
2.3 የልማታዊ ዴሞክራሲ መስመር የሃገር አንድነትና ቀጣይነት ያለውን ዘላቂ ልማትን
ከማረጋገጥ አንፃር እንዴት ይታያል?
2.4 የምንከተለው ልማታዊ ዴሞክራሳዊ ስርዓት በራሱ ኪራይ ሰብሳቢነትን እንዲስፋፋ አላደረገም ወይ?
2.5 የግብር ስርዓታችን (ከደሞዝ፣ ካፌ… ወዘተ ጨምሮ) ድግግሞሽ አለበት፤ ይህ ለምን ሆነ?
2.6 እየተሰሩ ያሉት የልማት ስራዎች እርስ በርሳቸው ያለመናበብና ያለመቀናጀት ሁኔታአለ፤ አንዱ ድርጅት
የሰራውን ሌላው ያፈርሰዋል፤ ይህ ደግሞ ነዋሪው ላይ ከፍተኛ የአገልግሎት አቅርቦት ችግር ፈጥሯል፤ይህ
ለምን ሆነ? መንግስትስ ችግሩን ለመቅረፍ ምን አስቧል?
2.7 የምንከተለው የመሬት ፖሊሲ ዜጎቻችን ለልማት ተነሽ በማለት የሚመጥን ካሳ ሳይሰጥ ቤት አልባ
በማድረግ ችግር ላይ ጥሏል፤ ገበሬውንም በማፈናቀል ማሳ አልባ አድርጓል፤ ታድያ መሬት አይሸጥም
አይለወጥም የተባለው ገበሬው መሬት አልባ እንዳይሆነ ከሆነ ይህ ችግር ለምን ተከሰተ?
2.8 መንግስት በገበያ ውስጥ ገበያ የማረጋጋት ስርዓት እየሰራሁ ነው ይላል፡፡ ነገር ግን በተግባር
ነጋዴው ህዝቡን እንደፈለገ እየበዘበዘ ነው፡፡ ይህ እንዴት ይታያል?

You might also like