You are on page 1of 2

ድግሪ፣ ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው የአካዳሚያችን ሰራተኞች በመንግስት ፖሊሲና

ስትራቴጂ ዙሪያ በተሰጠው ስልጠና ላይ በውይይት ወቅት የተነሱና ተጨማሪ

ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው የተመረጡ ጥያቄዎች፤

የስልጠና ሰነዱ ርዕስ፡- በሁሉም ሰነዶች ላይ የተነሱ ጥያቄዎች፤

1. የአመለካከት ጥያቄዎች

1. ኒዩ ሊብራሊዝም በተለያዩ ሃገራት ልማትና ዴሞክራሲን ማረጋገጥ ከቻለ በእኛስ ሃገር ተግባራዊ ማድረግ ለምን
አልተቻለም?

2. የምንከተለው የአብዩታዊ ደሞክራሲ መስመር እውነት ልማትና ደሞክራሲን በሃገራችን አረጋግጧል ወይ? የልማት
አቅጣጫዎችና ፖሊሲዎች በሰነድ ደረጃ ከመስፈራቸው ባሻገር ምን ያህል ተፈፃሚ ሆነው ወደ ህዝቡ ወርደዋል?
 የመልካም አስተዳደር ችግርንና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍስ ምን ተሰርቷል? አመራሩን በማሰልጠንና
በማብቃት የአመራሩን የአፈፃፀም ችግሮች በመቅረፍ ረገድ የእኛ አካዳሚም ትልቅ ሚና የተጣለበት
ቢሆንም የሚጠበቅበትን ያህል አልሰራም፡፡ ይህን ተልዕኮ ለማሳካት በሚያስችል አቅም ላይ የሆነ
ባለሙያም ተቋሙ አላበቃም፡፡ ይህ እስከ መቼ ነው? አካዳሚውስ በሙሉ አቅሙ መቸ ወደ ስራ
ይገባል? ይህስ በማኔጅመንት ኮሚቴው ምን ያህል ትኩረት ተሰቶታል?

3. ልማትና ዴሞክራሲ የማይነጣጠሉ ናቸው እንላለን፡፡ ነገር ግን ለተለያዩ የልማት ስራዎች ሲባል ዜጎችን ያለ በቂ
ካሳ በማፈናቀልና የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ባልጠበቀ መልኩ ልማት እየተሰራ ባለበት ሁኔታ
ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ነን ማለት ይቻላል ወይ?

4. አሁን በትክክል በህገ- መንግስቱ መሰረት ክልሎች የተሰጣቸውን ስልጣን እየተገበሩ ነው ወይ? የፌደራል መንግስት
በክልሎች ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እየገባና እነሱም የፌደራል መንግስት ተላላኪ እየሆኑ አይደለም ወይ?

5. በሃገራችን በፖለቲካ ስልጣንና በኢኮኖሚ ሴክተር በተለይም በፌደራልና በአ/አ ተቋማት የትግራይ ክልል
ተወላጆች ከሌሎች ይበዛሉ፡፡ ይህ የአንድ ብሔር የበላይነትን (የትግራይን) አያሳይም ወይ?

2. የግንዛቤ፣የእውቀት/መረጃ/ ክፍተት ጥያቄዎች

1. ልማታዊ ዶሞክራሲያዊ መንግስታችን በተመረጠ አኳኋን በገበያው ውስጥ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል የነፃ ገበያ ስርዓት
እንከተላለን ተብሏል፡፡ በመንግስት ይዞታ ስር ያሉ እንደ ኤፈርትና ሜቴክ ያሉ ትልልቅ ተቋማት የነፃ ገበያ
ስርዓቱን አያውኩም ወይ? ይህ ጣልቃ ገብነቱስ ለኪራይ ሰብሳቢነት እያጋለጠ አይደለም ወይ? ምሳሌ የስኳር
ፋብሪካዎች ፕሮግራም፤
 ለኢንዱስትሪው ዘርፍ እኩል ተወዳዳሪነትን ከመፍጠር አንፃርስ በመንግስት እጅ ያሉ ኢንዱስትሪዎችና
ሌሎች በግሉ ዘርፍ ያሉ ኢንዱስትሪዎች እንዴት እኩል ይስተናገዳሉ?
 አሁን ባለው ሁኔታ ጥቃቅንና አነስተኛ፣ የከተማና የገጠር መሬት ልማት ለአመራሩ በከተማም ሆነ
በገጠር የኪራይ መሰብሰቢያ ምንጭና የፖለቲካ መሳሪያዎች አይደሉም ወይ? ምሳሌ፡- የሸድ ምሪት ጋር
ተያይዞ ወዘተ…ይህን ችግርስ ለመፍታት በቀጣይ ምን ታስቧል?
2. አሁን በሃገራችን የሚታየው የብሔር መልክ ያለው ግጭት፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብት መገደብ
ሁኔታና በብሔርተኝነት ስሜት መከፋፈል እንጅ ሃገራዊ ስሜት መጥፋቱ መንስኤው በምንከተለው የፌደራል
ስርዓት ምክንያት በአንድነታችን ላይ ሳይሆን በልዩነታችን ላይ ስለተሰራ አይደለም ወይ?
 የውስጣዊ ሰላም ችግር እያለስ ውጫዊ ሁኔታን መቆጣጠርና ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠርስ
እንዴት ይቻላል?
 ይህ ረብሻና ሁከት የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ላይ ያለው ተፅዕኖ እንዴት ይታያል?
3. በሃገር ውስጥ ገበያችን የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ክፍተት እያለ ኤክስፖርት መር የኢንዱስትሪ ልማት
ስትራቴጂ ለምን ተመረጠ? ከውጭ የምናስገባቸውን በሃገር ውስጥ ተፈላጊ የሆኑትን በራሳችን ማምረትና
መተካት ከቻልን በኃላ ኤክስፖርትን ማበረታታት (Import substitution then Export Promotion Strategy)
ስትራቴጅን ለምን አልመረጥንም?
4. በገጠር ያለው ማህ/ሰብ ያልተማረ በመሆኑ ቴክኖሎጅን በቶሎ ተቀብሎ የመላመድ ሁኔታው ዝቅተኛ ከመሆኑ
የተነሳ በገጠር የታሰበውን ፈጣን ልማት ለማምጣት አያደናቅፍም ወይ?
5. በፖሊሲው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግብርናው ኢንዱስትሪውን መመገብ በሚችልበት ፍጥነት እያደገ ነው
ወይ? ትስስሩስ በሚፈለገው መልኩ አለ ወይ?
6. የት/ርት ተቋማት ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ከማስረፅ አንፃር ያላቸው ሚና ለምን ዝቅተኛ ሆነ?
7. ከጅቡቲ ወደብ በተጨማሪ የአሰብ ወደብን መጠቀም ለምን አልተቻለም? በዚህስ ዙሪያ በቀጣይ ምን እየተሰራ
ነው?
8. ከውጭ እርዳታና ብድር ማግኘቱ ለልማታችን አጋዥ ቢሆንም እርዳታ ሰጭ ሃገራትስ የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት
ከማራመድና ከማስረፅ አንፃር በእኛ ሃገር ምን ያክል ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው?
9. የአባይ ግድብ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቀው በግብፅ ስትራቴጅክ ተፅዕኖ ነው ወይስ በሌላ ምክንያት?

You might also like