You are on page 1of 11

በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

በመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ


የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት

ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸው የአካዳሚው ሰራተኞች

የስልጠና አጀማመር ሪፖርት

ታህሳስ /2010 ዓ.ም


አ/ አ

ማውጫ

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 0


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

ተ.ቁ ርዕስ ገጽ

1. ክፍል አንድ
የቅድመ ስልጠና ስራዎች

1.1. መግቢያ---------------------------------------------------------------------------------------2
1.2. የቅድመ ዝግጅት ስራዎች--------------------------------------------------------3

1.2.1. በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬትየተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች-------4


1.2.2. በሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ ስራዎች----------------------6

1.2.3. በአ/አ ስራ አመራር እንስቲትዩት የተከናወኑ ተግባራት---------------------5

2. ክፍል ሁለት
የሰልጣኞች አገባብ፣ አቀባበልና የስልጠና አጀማመር

2.1. መሰልጠን ያለባቸው ሰልጣኞች ድልድልና አገባብ--------------------------------7

2.2. የሰልጣኞች አቀባበል---------------------------------------------------------------------9

2.2.1. በልዩ ስልጠናና በሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት


የተከናወኑ የአቀባበል ስራዎች-------------------------------------------------10
2.2.2. የአ/አ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የተከናወኑ ተግባራት------------------10
2.3. የስልጠና አጀማመር----------------------------------------------------------------------10

3. ክፍል ሶስት

ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎች

3.1. ያጋጠሙ ችግሮች----------------------------------------------------------------------11


3.2. የተወሰዱ መፍትሔዎች---------------------------------------------------------------11
3.3. ማጠቃለያ--------------------------------------------------------------------------------12

ክፍል አንድ

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 1


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

የቅድመ ስልጠና ስራዎች

1.1. መግቢያ

ሀገራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ድህነትን ተረት በማድረግ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ
የአመራሩንና የፈፃሚ አካሉን/ባለሙያውን/ በአመለካከት፣ በክህሎትና በእውቀት መገንባት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን

በማመን መንግስት በየደረጃው ያለውን አመራርና ባለሙያዎችን አቅም በስልጠናና በተለያዩ የተሞክሮ ልውውጥ

መድረኮች የመገንባት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚም በየደረጃው ያሉ አመራርና ባለሙያዎችን በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች
እንዲሁም የልማት አቅጣጫዎች ላይ የምንከተለውን ልማታዊ አስተሳሰብ የማስተማር፣ የማስረጽና
የማሳወቅ በሂደቱም በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር ሚናውን የመጫወት
ተልዕኮ የተሰጠው የመንግስት ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ተቋሙ የተሰጠውን ይህን ትልቅ ሃገራዊ
ተልዕኮ ለማሳካት የተቋሙን የውስጥ አቅም ማብቃትና ማጎልበት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም የአካዳሚው
አመራርና ባለሙያ በዋና ዋና ሀገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ዙሪያ የጠራ ግንዛቤና የጋራ አመለካከት
እንድይዙ ከዚህ በፊት ስልጠና ያልወሰዱትን ድፖሎማና ከዚያ በታች ያላቸውን የአካዳሚው ሰራተኞችን
በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እንዲሁም አካዳሚው ሀገራችን በተያያዘችው የህዳሴ ጉዞ ላይ ባለው ጉልህ ሚና ላይ
በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ በታቀደው እቅድ መሰረት ሰልጣኞችን በአካዳሚው ውስጥ ካሉ 10 ዳይሬክቶሬቶች በማከፋፈል
መረጃዎቹ ተደራጅተው እንዲመጡ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ስልጠናውን የማደራጀት ስራ ተከናውኗል፡፡

ይህ ለድፖሎማና ከዛበታች ላላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና ከህዳር 20/2010 እስከ ታህሳስ 06/2010 ዓ.ም
ለመስጠት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ 47 ሰልጣኞችን ለማሰልጠን የታቀደ ቢሆንም ወደ ስልጠና ማዕከሉ (አ/አ ስራ አመራር
ኢንስቲትዩት) ቀርበው የተመዘገቡና ስልጠናቸውን መከታተል የጀመሩት ወንድ 17፣ ሴት 20 በድምሩ 37 (መሰልጠን
ካለባቸው 78.7%) ሰልጣኞች ናቸው፡፡ የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር
የሰልጣኞችን ዝርዝር በማሰባሰብ የተለያዩ የስራ ዳይሬክቶሬቶችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ በቡድን የመደልደል ስራ
እንዲከናወን በማድረግ ሰልጣኞች ወደ ስልጠና ቦታ ሲመጡ ለምዝገባ በሚመች መልኩ የማደራጀትና ሰልጣኞችን
የመመዝገብ ስራ ተከናውኗል፡፡

በዚሁ መሰረት የዚህ ስልጠና ከቅድመ ዝግጅት እስከ አቀባበልና አጀማመር የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት

ለቀጣይ ስልጠናና ሰነድ ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል በሚያስችል መልኩ በስልጠና አገባብ ወቅት የተሰሩ

ስራዎችን በዝርዝር በሦስት ምዕራፍ በመክፈል የአቀባበል ሪፖርቱ እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

1.2. የቅድመ ዝግጅት ስራዎች

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 2


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት ለድፖሎማና ከዛበታች ላላቸው ባለሙያዎች የሚሰጠውን ስልጠና ስኬታማ በሆነ አግባብ
ለማከናወን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ያከናወነ ሲሆን በዋናነት የዚህን ዙር ስልጠና ማስፈፀሚያ እቅድ
የማዘጋጀት፣ የሰልጣኞች ምልመላን የማደራጀት እንዲሁም ስልጠናውን ለማከናወን ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት
ከሰው ሃይል ልማትና ከት/ርትና ስልጠና ዘርፍ ጋር በቅንጅት በመስራት የሰልጣኞችን መረጃ በተገቢው ሁኔታ ተጣርቶ
እንዲመጣ፣ የሰልጣኞች ቡድን ድልድል፣ የሎጅስቲክና የፋይናንስ ሂደቶችን የማጠናቀቅና ዝግጁ የማድረግ ስራ
ተሰርቷል፡፡

የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የስልጠና ስራው ሲጀመር ለቡድኖች፣ ለህዋስ እና ለ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እቅድ ዝግጅት
መነሻ የሚሆን እቅድ የማዘጋጀት፣ ለምዝገባ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ቅፃ ቅፆች እንዲሁም የቡድንና የህዋስ መገምገሚያ
መስፈርቶች እንዲዘጋጁ ተደርጓል፡፡

ሰልጣኞችን በመመልመል ረገድ ከሰው ሃይል ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን ተገቢውን ክትትል ማድረግ የተቻለ ሲሆን
የተመለመሉ ሰልጣኞችን ለስልጠናው ራሳቸውን እንድያዘጋጁ የማሳወቅ ስራም ተሰርቷል፡፡ በቅድመ ስልጠና ወቅት
በዳይሬክቶሬታችን፣ በሰው ሃይል ልማትና በአ/አ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የተከናወኑ ተግባራት እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

1.2.1. በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ ቅድመ ስልጠና ተግባራት

የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት በዋናነት ከሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር እንድሁም በተዋረድ ጉዳዩ
ከሚመለከታቸው ሌሎች ዳይሬክቶሬቶች ጋር በመተባበር ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የጋራ እቅድ በማቀድ ወደ
ስራ ለመግባት ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም ስልጠናው የተቀመጠለትን የውስጥ አቅምን የመገንባት ግብ ማሳካት
እንዲቻል የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር፣ አፈፃፀማቸውን የመገምገምና ኦረንቴሽን የመስጠት ስራ
ተሰርቷል፡፡ ከዚህም አንፃር ዳይሬክቶሬቱ እነዚህ ሰነዶች ሲሰጡ ያከናወናቸው ተግባራት ከእቅድ አንፃር
ተግባራትን በመገምገም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

በጥንካሬ፤

 ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸው ሰራተኞችን ለማሰልጠን ተግባራትን ለመመዘን በሚያስችልና ከሰው

ሃብት ልማትና ከሌሎች ዳይሬክቶሬቶች ጋር በቅንጅት ሊያሰራ በሚያስችል መልኩ የስልጠና

ማስፈፀሚያ እቅድ መዘጋጀቱ፤

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 3


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

 ከአካዳሚያችን የስራ ባህሪና ከሰልጣኞች የት/ርት ደረጃና አቅም ጋር የሚመጣጠኑ የስልጠና


አጀንዳዎች መምረጥ መቻሉ፤
 ከዚህ በፊት የተካሄዱ ስልጠናዎች አፈፃፀም ላይ የተገኙትን ልምድና ተሞክሮዎች እንደ ግብአት

መጠቀም መቻሉ፤

 አስፈላጊ መረጃዎችን የያዘ የሰልጣኞች መመዝገቢያ ቅጽ በማዘጋጀት የሰልጣኞች ምዘገባ መደረጉ፤


 በምዝገባ ወቅት ለስልጠናው የተመለመሉትን ሰልጣኞች የማጣራት ሥራና ፈጣን ምዝገባ መካሄዱ፤
 የተለያዩ የስልጠና ቅፃቅፆችንና ሰነዶችን በማባዛት ለሁሉም ቡድኖችና ሰልጣኞች ማዳረስ መቻሉ፤

 የቡድን አወያዮችን በመሰብሰብ በስልጠና ወቅት አብረን የምንሰራቸውን ስራወችና የአደረጃጀትና


የአቅም ማጎልበቻ ሪፖርት ፎርማቶችን እንደት እንደሚሞሉልንና እንደሚልኩልን ገለፃ የማድረግና
የማስረዳት ስራ መሰራቱ፤
 መረጃዎችን የማጥራትና ያልተሟሉትን እንዲሟሉ የማድረግ ስራ መከናወኑ፣

 የኢንተርኔት አገልግሎት ለሰልጣኙ ምቹ እንዲሆን ለማመቻቸት መሞከሩ፣

 የሰልጣኞች፣ የቡድን እንደ አካል፣ የቡድን መሪ እና የረዳት ቡድን መሪዎች የየራሳቸው መመዘኛ
(መገምገሚያ) ነጥቦች ከሰልጣኞች አንፃር መዘጋጀቱ፤
 የስልጠናውን የእለታዊ የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት መቻሉ፤
 የስልጠናውን ቦታና ቀን መወሰኑ፤
 ስልጠናውን የሚያስተባብሩ ንዑስ አደረጃጀቶችን በማዋቀር ወደ ስራ መገባቱ፤
 በመስፈርቱ መሰረት አወያዩችን መመልመላቸውና መመደባቸው፤
 ከስልጠናው ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን የስልተናውን ሂደት በመገምገም እርምጃ እስከመውሰድ የደረሱ
መፍትሄዎች ላይ በጋራ መስራት መቻሉ፤

በድክመት፤
 የስልጠና ሰነዶች ኮፒና በእጅ ስቴፕለር የተመቱ በመሆናቸው ለእይታ የማይስቡና ለማንበብ አመች
ያለመሆናቸው፤

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 4


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

1.2.2. በከሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ ስራዎች

በጥንካሬ
 በአካዳሚችን ውስጥ ባሉ ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ስር ያሉ ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸውን
ሰራተኞች መረጃ በዝርዝር በመለየት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ መግባት መቻሉ፤
 ስልጠናውን በጋራ የሚያሰራን የጋራ እቅድ መታቀዱ፤
 የቡድን ዋና አወያዮችንና ረዳት አወያዮችን እንዲሁም ሰልጣኞች (በስብጥር) በየቡድኑ
የመደልደሉ ስራ በጋራ መሰራቱ፤
 ለስልጠና የተመለመሉ ሰልጣኞችን ዝርዝር በስዓቱ ማሳወቅ መቻሉ፤
 የበጀት ፕሮፖዛል ማዘጋጀትና ማስወሰን መቻሉ፤

በክፍተት

 የለም

1.2.3. በአ/አ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የተከናወኑ ተግባራት

ኢንስቲትዩቱ ከሚሰጣቸው የስልጠና ፕሮግራሞች ጋር በማጣጣም ለዚህ ዙር ስልጠናችን የሚያስፈልጉ


የመወያያ ክፍሎችንና የሃይል መድረክ አዳራሹን በተገባ ውል መሰረት ዝግጁ የማድረግ ስራ ሰርቷል፡፡

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 5


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

ክፍል ሁለት

የሰልጣኞች አገባብ፣ አቀባበልና የስልጠና አጀማመር

2.1. መሰልጠን ያለባቸው ሰልጣኞች ድልድልና አገባብን በተመለከተ


በተያዘው የውስጥ አቅምን ማጎልበት እቅድ መሰረት መሰልጠን ያለባቸው የሰልጣኞች ድልድል በሁሉም
የአካዳሚያችን ዳይሬክቶሬቶች የተደረገ ሲሆን ሰልጣኞች በመስፈርቱ መሰረት ተመልምለው ወደ ስልጠና
እንዲላኩም የክትትል ስራ ተሰርቷል፡፡ የስልጠና ኮሚቴውም ዳይሬክቶሬቶች የተመለመሉ ሰልጣኞችን በወቅቱ
ወደ ስልጠናው እንድልኩ የማድረጉን ስራ ለማከናወን የሞከረ ቢሆንም አንዳንድ ሰልጣኞች ዘግይተው
የመግባትና የመንጠባጠብና ከናካቴው የመቅረት ሁኔታ በሰፊው ታይቷል፡፡ በተለይ የሰልጣኞች አለመምጣት
ችግር ሰፊ ነበረ ብሎ ማየት ያስችላል፡፡ ይህም በቀጣይ ሊሻሻል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት
ለዳይሬክቶሬቶች የተሰጠ የሰልጣኞች ድልድል፣ የገባ ሰልጣኝና የቀረ ሰልጣኝ በየዳይሬክቶሬቶች
እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 6


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

ሰንጠረዥ 1፤ በአካዳሚያችን ዳይሬክቶሬቶች ስር ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸውና መሰልጠን ያለባቸው


ሰልጣኞች ድልድል፣ ወደ ስልጠናው የገቡና ያልገቡ ሰልጣኞች መረጃ፤

መሰልጠን የገባ ሰልጣኝ የገቡ ወደ


ተ.ቁ የስራ ዘርፍ ያለባቸው ወ ሴ ድ በ% ስልጠናው ያልገቡ
ያልገቡ በ%
1 ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት 3 1 2 3 100 - -
2 ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 5 1 2 3 60 2 40
3 ጠቅላላ አገ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት 21 10 4 14 66.7 7 33.3
4 እቅድ ክትትልና ግምገማ 2 - 2 2 100 - -
ዳይሬክቶሬት
5 ት/ርትና ስልጠና ዘርፍ 2 - 2 2 100 - -
6 የውስጥ ኦድት 1 - 1 1 100 - -
7 የስልጠና አመራር ዳይሬክቶሬት 6 4 2 6 100 - -
8 የአመራር አቅም ማጎልበት 1 - 1 1 100 - -
ዳይሬክቶሬት
9 የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት 4 1 2 3 75 1 25
10 ምርምርና ልማት ዳይሬክቶሬት 2 - 2 2 100 - -
ድምር 47 17 20 37 78.7 10 21.3

ከመረጃው ለማየት እንደሚቻለው በአካዳሚው ያሉት ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በተሻለ ሰልጣኞችን ወደ


ስልጣናው የላኩ ሲሆን ነገር ግን አንዳንድ ዳይሬክቶሬቶች ለስልጠናው የተመለመሉ ሰራተኞቻቸውን
ለስልጠናው መላክ ሲገባቸው ያልላኩ አሉ፡፡ መሰልጠን ያለባቸውን ሰልጣኞች ከመላክ አንፃር በሰፊው ክፍተት
የታየባቸው ዳይሬክቶሬቶችን ስናይ፤

 ከጠቅላላ አገ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት (መሰልጠን ካለባቸው ውስጥ 7 ሰራተኞች ወይም 33.3%) ፣


ከፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (2 ሰልጣኝ ወይም መሰልጠን ካለባቸው 40%)፣ ከሰው ሃብት ልማት
ዳይሬክቶሬት (1 ሰልጣኝ ወይም መሰልጠን ካለባቸው 25%) በድምሩ መግባት ከነበረባቸው ውስጥ
10 ሰልጣኞች(21.3%) የሚሆኑ ሰልጣኞች ከነዚህ ዳይሬክቶሬቶች ከስልጠናው የቀሩ ሲሆን፤

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 7


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

 በአንፃሩ ከሰንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለው ሌሎች የተቀሩት 7 ቱ ዳይሬክቶሬቶች መሰልጠን


ካለባቸው ሰልጣኞች ውስጥ ሁሉም የመጡ ወይም ምንም ከስልጠናው የቀረ ሰልጣኝ የሌለባቸው
ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ስልጠና መሰልጠን ካለባቸው 47 ሰልጣኞች መካከል 37 ቱ (78.7%) በስልጠናው የተገኙ
ሲሆን፤ 10 ሰልጣኝ ወይም ከጠቅላላው 21.3% የሚሆኑ ሰልጣኞች ወደ ስልጠናው አልገቡም፡፡ ስለሆነም
በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ ስልጠና ያልተገኙ ሰራተኞች በቀጣዩ ዙር ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ስልጠና
እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ይኖርበታል፡፡

2.2. የሰልጣኞች አቀባበል

ሰልጣኞች በ 19/03/10 ዓ.ም የምዝገባ ሂደቱን በማጠናቀቅ የስልጠናውን አሰራርና አደረጃጀት እንዲያውቁ ለማድረግ
ዝርዝር ኦረንቴንሽን እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡ በእለቱም ሰልጣኞቹ በስልጠናው ቆይታቸው ደስተኛ እንድሆኑ በመልካም
ምኞት መግለጫና በእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሰልጣኞችን መቀበል ተችሏል፡፡

2.2.1. በልዩ ስልጠና ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬትና ሰው ሃብት ልማት የተከናወኑ የአቀባበል ስራዎች
 ለስልጠናው የተመለመሉ ሰልጣኞችን በስልጠና ማዕከሉ በመገኘት በጋራ አቀባበል ማድረግ
መቻሉ፤
 የሰልጣኞች ምዝገባን ከዳይሬክቶሬታችን ጋር በጋራ በመተባበር መመዝገብ መቻሉ፤
 ሰልጣኞች በቡድን በመደልደልና በመስራት ለሰልጣኞች በሚታይ አመች ቦታ መለጠፉ ተችሏል፤
 የተቀየሩና የቀሩ ሰልጣኞች ዝርዝር በመለየት በተቻለ ፍጥነት ለስልጠናው እንድደርሱ መደረጉ፤
 ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ሊያደርጓቸው ስለሚገቡ ጉዳዩች ግልፅና ጥብቅ ኦሬንቴሽን
መሰጠቱ፤
2.2.2. አ/አ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት አቀባበል

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 8


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

የስልጠና ማዕከሉ ሰልጣኞች በሚገቡበት ወቅት ሰልጣኞችን በመቀበል ወደ ተያዘልን የስልጠና አዳራሽና
መወያያ ክፍል የማሳየት ስራ በጥሩ ሁኔታ ተሰርቷል፡፡

2.3. የስልጠና አጀማመር

የስልጠና ስራው በ 19/03/10 ጧት በምዝገባና በኦሬንቴሽን፤ እንድሁም ለመነሻነት በተዘጋጀው የአደረጃጀት እቅድ
መሰረት የቡድንና እያንዳንዱ ሰልጣኝ ራስን የማብቃት እቅድ እንዲያቅዱና ከአወያዮቹ ጋር የጋራ እንድያደርጉ
ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የቡድን እና የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች ተግባርና ኃላፊነት እና የሪፖርት ቅጾች ግልጽ
እንድሆኑላቸው ለቡድን አወያዩች ገለፃ ተደርጓል፡፡ ቡድን መሪዎች የቡድን አባላት ሰልጣኞችን ጥብቅ የሆነ ክትትል
ማድረግ እንደሚገባቸው ኦሬንቴሽን ተሰቷል፡፡ ከስዓትም የመግቢያ ፈተና በመስጠት በፈተናውም ሰልጣኞች ያመጡትን
ውጤት እንዲያዩ ተደርጓል፡፡

ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ሊከተሉት ስለሚገባ የስልጠና ድሲፕሊኖችን በተመለከተ ግልፅና ጥብቅ ኦሬንቴሽን
በሁለቱም (በሰው ሀብት ልማትና በልዩ ስልጠና) ዳይሬክቶሬት ኃላፊዎች ከተሰጠ በኃላ በቀጣይ ቀን በ 20/03/10 ዓ.ም
የመጀመሪያው የስልጠና ሰነድ በሆነው የህዳሴው መስመርና የኢት/ያ ህዳሴ አጀንዳ ገለፃ ተጀምሯል፡፡

ክፍል ሶስት

ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎች

3.1. ያጋጠሙ ችግሮች

የተመደቡ የቡድን አወያዩች በተለያዩ ምክንያቶች ባለመገኘታቸው ምክንያት ባልተሟሉ የቡድን


አወያዩች ወደ ስልጠናው ለመግባት መገደድ፤
የሰልጣኞች ከስልጠናው መቅረት ያጋጠመ መሆኑ፤በተለይ በጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በስፋት ያጋጠመ
መሆኑ፤
ኢንስቲትዩቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ፈጣን ያለመሆን/በጣም ቀርፋፋ/ እና አልፎ አልፎም
የመቆራረጥ ችግር መኖሩ፤

3.2. የተወሰዱ መፍትሔዎች

የተገኙትን አወያዩች በማቀያየር/በመበተን/ መጠቀምና የአወያይ እጥረት ያለበትን አስተባባሪ


ኮሚቴዎችም እየገቡ እንድያግዙ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 9


በኢፌድሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የ 1 ኛ ዙር የ EBC አመራርና ባለሙያዎች የስልጠና አቀባበል ሪፖርት

ያልመጡ ሰልጣኞችን መረጃ በማጥራት ወደ ስልጠናው እንድገቡ ለማድረግ ተሞክሯል፤


የኢንተርኔት አገልግሎቱ እንድስተካከል ከስልጠና ማዕከሉ ጋር በመነጋገር ለስልጠና አስተባባሪዎች የኔትወርክ
ኬብል እድሰጥ ማድረግ ተችሏል፤

3.3. ማጠቃለያ

የውስጥ አቅማችንን ለማብቃት ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው የአካዳሚያችን ባለሙያዎች የሚሰጠውን ስልጠና
በዳይሬክቶሬታችን አመታዊ እቅድ መሰረት ስልጠናው በወቅቱ እንድሰጥ ማድረግ መቻሉ በጥንካሬ የሚጠቀስ ነው፡፡
በዚህ የስልጠ ያጋጠሙትን ችግሮችን በመለየትና ከችግሮች በመማር አሁን የታየው የሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬቶችና
የስልጠና አስተባባሪ ኮሚቴው ቅንጅታዊ አሰራር በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

በሌላ በኩል የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት በስልጠናው የሚሳተፉ ሰራተኞችን ቀድሞ ያሳወቀ ቢሆንም አንዳንድ
ሰልጣኞች ለስልጠናው ያለመምጣታቸው በሰፊው የተስተዋለ ችግር ሆኖ ታይቷል፡፡ ይህ አካሄድ መሰልጠን ያለባቸውን
ሰራተኞች እንዳይሰለጥኑና አቅም እንዳይፈጥሩ በማድረግ አካዳሚያችን የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት በሚደረግ
ጥረት ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ቀላል ባለመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ስልጠና 47 ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸው ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን እቅድ የተያዘ ቢሆንም
37 (78.7%) ሰልጣኞች ሲገቡ 10(21.3%) ሰልጣኞች ወደ ስልጠናው ሳይገቡ የቀሩ በመሆኑ ይህ ችግር በቀጣዩ ዙር
እንዳይከሰት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ Page 10

You might also like