You are on page 1of 9

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ

የኢንዱስትሪ አክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር


ዳይሬክቶሬት

ረቂቅ ሰነድ

ጥቅምት 2011 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
ማውጫ ገፅ
1. መግቢያ 2

2. የሰነዱ አስፈላጊነት 2

3. ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎች 3

3.1. ዋና ዓላማ 3

3.2. ዝርዝር ዓላማዎች 3

4. የውድድሩ መርሆዎች 3

5. የሰነዱ ወሰን 3

6. ቴክኖሎጂ ለማወዳደር በቅደም ተከተል የሚከናወኑ ተግባራት እና ፈፃሚዎች 3

7. የዳኞች አመራረጥና ተግባር 4


7.1. ዳኞች ሊገኙ የሚችሉባቸው ተቋማት 4

7.2. የዳኞች አመራረጥ 4

7.3. የዳኞች ተግባርና ኃላፊነት 5

8. የውድድሩ ተሳታፊዎች 5

9. የተወዳዳሪዎች ምዝገባ 5

10. የውድድሩ የማስፈፀሚያ ስልቶች 5

11. የማወዳደሪያ መስፈርት 6

12. የቅሬታ አቀራረብ ሂደት 7

13. የሽልማት አሰጣጥ 8

14. የተሳትፎ ሰርቲፊኬት 8

15. ማጠቃለያ 8

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
1. መግቢያ

ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት በተከታታይ ያስመዘገበችውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል ልማታዊ
አስተሳሰብን በህብረተሰቡ ውስጥ በማስረፅና አምራች ዜጋን በመፍጠር የምርት/ማምረቻ እና
የአገልግሎት/የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን አቅርቦት ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት መንግስት ልዩ
ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ቀጣይነት ባለው መልኩ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት የሚቻለው የልማት ፕሮግራሞች መሪ መስሪያ
ቤቶችን ውጤታማነት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከተረጋገጠ ሲሆን ለዚህም በኢኮኖሚ የበለፀጉ
ሀገራት ሳይንሳዊ ትንታኔ እና ሰፋፊ ጥናትና ምርምርን በማካሄድ ያፈለቁትን ቴክኖሎጂዎች በተለያየ
መንገድ ወደ ሀገራችን አስገብቶ በመቅዳትና በመጠቀም የውጭ ምርትን መተካት (Import substitution)
የሚያስችል ፖሊሲ/ስትራቴጂ ተቀይሶ ትግበራ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ አደረጃጀት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ


ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዋነኛ ተልዕኮም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅቶ በየዘርፎቹ
በሚካሄድ ልማት ውስጥ ለተሳተፉ ዜጎች/አንቀሳቃሾች ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳትና በማቅረብ
ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ መቶ በመቶ የአቀዳድ ሰነድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ይሁን እንጂ ቴክኖሎጂ የቀዱትን አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞችም ይሁኑ የጥ/አ/ አንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች
እያንዳንዱ ክልል በራሱ መስፈርት አወዳድሮ ከሚያበረታታው ውጪ በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀ
የማወዳደሪያ መስፈርት አለመኖሩና በየክልሉ የሚካሄደው የተለያየ በመሆኑ ቴክኖሎጂውን ወጥ በሆነ
መንገድ መለካት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም ተቀድቶና ለኢንተርፕራይዝ ተሸጋግረው ሀብት ማፍራት ያስቻሉ
ቴክኖሎጂዎችን በክልል፣ በክላስተር እና በተቋማት ደረጃ በማወዳደር አሸናፊውን ቴክኖሎጂ የቀዳውን
አሰልጣኝ፣ ሰልጣኝ ወይም የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ ለማበረታታት ጥቅም ላይ እንዲውል ይህ ሰነድ
ተዘጋጅቷል፡፡

2. የሰነዱ አስፈላጊነት
በተለያየ ወቅት በየደረጃው በተደረገ ድጋፍና ክትትል በዘርፉ ያለውን ችግር ለማየት እንደተሞከረው ቴክኖሎጂ
መቶ በመቶ መቀዳቱን መለካት የሚያስችል አሰራርና መስፈርት የያዘ ሰነድ ባለመኖሩ በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኝ
እንዲሁም በአንቀሳቃሾች ተቀድተው የሚሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎችን በትክክል ከመለካት አንፃር ያለውን ክፍተት
ለመሙላት እንዲያስችል ይህን የቴክኖሎጂ ማወዳደሪያ ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

3. ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎች
3.1. ዋና ዓላማ
የሰነዱ ዋና ዓላማ ቴክኖሎጂን በመቅዳት የኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡትን በማበረታታት

ለቀጣይ በአሰልጣኙ፣ በሰልጣኙ እና በአንቀሳቃሹ ዘንድ የውድድር ተነሳሽነት መፍጠር እና ቴክኖሎጂን

የመቅዳት አቅምን ማሳደግ ነው፡፡

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
3.2. ዝርዝር ዓላማዎች

 አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና አንቀሳቃሾች ቴክኖሎጂን በመቅዳት ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ

ዕድገት የተሻለ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል፣

 የቴክኖሎጂ ሂደቱን ተከትሎ በማሸጋገር ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ያደረገን ተቋም በየደረጃው

(በፌደራል፣ በክልልና በክላስተር) ማበረታታት

 ቴክኖሎጂ በመቅዳት ሂደት ውስጥ የውድድር መንፈስ መፍጠር

 አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና አንቀሳቃሾች በቴክኖሎጂው ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ እውቀት እንዲያገኙና

ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር ማድረግ፣

4. የውድድሩ መርሆዎች
 ታማኝነት
 ግልጸኝነት
 ፍትሃዊነት
 ሚስጥር ጠባቂነት
 ቅንነት
 ተጠያቂነት

5. የሰነዱ ወሰን
ይህ የማወዳደሪያ ሰነድ ቴክኖሎጂ በመቅዳት የኢንተርፕራይዙን ተወዳዳሪነት ያረጋገጡ የቴክኖሎጂ

ባለቤቶችን በፌዴራል፣ በክልል እና በክላስተር ደረጃ በየበጀት አመቱ ዕቅድ መሠረት ለማወዳደር በሚከናወኑ

ዝግጅቶች ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

6. ቴክኖሎጂ ለማወዳደር በቅደም ተከተል የሚከናወኑ ተግባራት እና


ፈፃሚዎች
ተ.ቁ. ተግባራት ፈፃሚ አካላት
1. የሚወዳደሩ ቴክኖሎጂዎች ሰነዶችን የማጣራት ስራ በማከናወን ሰነዱን በፌዴራል፣ በክልል፣ እና
ላቀረበው አካል ግብረ-መልስ መስጠት ክላስተር ኮሌጅ/ተቋም
2. ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በፊት ለውድድር አለመቅረባቸውን ማጣራት፣ የሚመለከተው የስራ
3. ለውድድር በቀረቡት የቴክኖሎጂ ዓይነቶች ዳኞችን መምረጥ፣ አቅም ክፍል
መፍጠርና የማወዳደሪያ መስፈርቱን ማስረከብ
4. ለውድድር የሚቀርቡ ቴክኖሎጂዎችን የተሟላ ሰነድ በየሙያው ለተደራጁ
ዳኞች ማስረከብ
5. በቴክኖሎጂ ውድድር እና ሲምፖዚየም ምቹ ቦታ መገኘቱንና መሰረታዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ፡፡
6. ቴክኖሎጂ በሚወዳደርበት ቦታ በመገኘት ውድድሩን ይመራሉ፣ በየደረጃው ያሉ የስራው
ኃላፊዎች

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
7. በተዘጋጀው ማወዳደሪያ መስፈርት መሠረት ቴክኖሎጂዎችን ያወዳድራሉ፣ በየቴክኖሎጂ ዓይነቱ
የተደራጁ ዳኞች
8. የተቀዳውን ቴክኖሎጂ ሚስጥራዊነት መጠበቁን ይከታተላሉ ያስጠብቃሉ፣ በፌዴራል፣ በክልል፣ እና
ክላስተር ኮሌጅ/ተቋም
የሚመለከተው የስራ
ክፍል
9. ቃለ-ጉባኤ በመያዝ በውድድር ወቅት የነበረውን ሂደትና የተወዳዳሪዎችን የዳኞች ጉባኤ
ውጤት የያዘ እና የተፈረመበት ሰነድ ከአስፈላጊ ማስረጃ ጋር ለሚመለከተው
የስራ ክፍል ያቀርባል፣
10. የቀረበለትን ዝርዝር መረጃ ካጣራና ከገመገመ በኋላ ለስራ ክፍሉ የበላይ በፌዴራል፣ በክልል፣ እና
አካል አቅርቦ ያስፀድቃል፣ ክላስተር ኮሌጅ/ተቋም
የሚመለከተው የስራ
ክፍል
7. የዳኞች አመራረጥና ተግባር

7.1. ዳኞች ሊገኙ የሚችሉባቸው ተቋማት


ለውድድር የሚቀርቡ ቴክኖሎጂዎች በተለያዩ ዘርፎች ምርት ማምረት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚውሉ

በመሆናቸው የቴክኖሎጂዎቹን ጥራትና አገልግሎት ለመፈተሸና ለማወዳደር የሚቻለው ከየዘርፉ በቴክኖሎጂ

አጠቃቀም ላይ ዕውቀቱና ክህሎቱ ባላቸው ባለሙያዎች ነው፡፡ ስለዚህም ዳኞቹ ሊገኙባቸው የሚችሉ ተቋማት

የሚከተሉት ናቸው፡-

 የምርምር ተቋማት

 ኢንዱስትሪዎች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ኢንስቲትዩቶች

 የንግድ ዘርፍ ኢንዱስትሪ ማህበራት

 የዘርፍ መሪ መስሪያ ቤቶች

 የሙያ ማህበራት

 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች

 ኮሌጆች

7.2. የዳኞች አመራረጥ


የዳኞች ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት የሚታዩ ዋና ዋና መመዘኛ መስፈርቶች፡-

1) ከቴክኖሎጅው ምርት ወይም ኦፕሬሽን ተዛማጅ የትምህርት ዝግጅት


2) በተመሳሳይ ፕሮጀክት/ቴክኖሎጂ ምርት ወይም ኦፕሬሽን ላይ የስራ ልምድ
3) በተሰማራበት ሙያ ያለው ስነ ምግባር
4) የሙያ ብቃት ምዘና ልምድ
5) የአመራር ክህሎት

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
7.3. የዳኞች ተግባርና ኃላፊነት
1) ለቴክኖሎጂ ውድድሩ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች፣ ሰነዶች፣ ማወዳደሪያ ቼክሊስትና የሪፖርት ፎርማት
መሟላታቸውን ማረጋገጥ፣
2) ለቴክኖሎጂ ውድድሩ የተዘጋጀውን መስፈርት በአግባቡ መረዳትና መጠቀም
3) በውድድሩ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ያለውን ሂደት ለተወዳዳሪዎች ማሳወቅ
4) ለተወዳዳሪዎች ውጤቱን ሪከርድ በማድረግ ግብረ-መልስ በወቅቱ መስጠት
5) ከሚመለከተው የስራ ክፍል ጋር በመሆን የውድድሩን አፈጻጸም መገምገም
6) የሚወዳደረውን ቴክኖሎጂና የውድድሩን ሂደት ሚስጥራዊነት መጠበቅ
7) በውድድሩ ወቅት ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠት
8) በውድድሩ ዙሪያ ያሉትን መረጃዎች በተዘጋጀው የሪፖርት ፎርማት በማጠናቀር ለሚመለከተው አካል
እንዲደርሱ ማድረግ

8. የውድድሩ ተሳታፊዎች
 አስልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የውድድሩ አካላት ይሆናሉ፡፡

ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ይበረታታሉ፡፡

9. የተወዳዳሪዎች ምዝገባ
ማንኛውም ተወዳዳሪ በተቀመጠው የመመዝገቢያ መስፈርት መሰረት የሚከተለውን መረጃ አሟልቶ መስጠት

ይኖርበታል፡-

 የተወዳዳሪው ሙሉ ስም

 የመጣበት ተቋም/ኢንተርፕራይዝ

 የመጣበት ክልል

 የሚወዳደርበት ዘርፍ/ሙያ

 የሚወዳደርበት ቴክኖሎጂ ስም

10. የውድድሩ የማስፈፀሚያ ስልቶች


የቴክኖሎጂ ውድደሩ በተደራጀ መልኩ በተቋማት፣ በክላስተሮች፣ በክልሎችና በፌዴራል ደረጃ
እንዲፈጸም የሚከተሉት የማስፈጸሚያ ስልቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡-

 የቴክኖሎጂ ውድድር ዕቅድን ከፌዴራል ኤጀንሲ እስከ ተቋማት ለሚገኙ አደረጃጀቶች ማውረድ
 የአፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀትና ለፈጻሚዎች ማስተዋወቅ
 ከባላድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት መስራት
 የዳኞችንና የኮሚቴ አባላትን አቅም መገንባት
 በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት
 መረጃዎችን በተደራጀ ሁኔታ ለውሣኔ አሰጣጥ አመቻችቶ መያዝ፤

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
 የእውቅናና ሽልማት ሥርዓት ማስቀመጥ
 አጠቃላይ ሂደቱን መቀመር

11. የማወዳደሪያ መስፈርት


ቴክኖሎጂዎችን ለማወዳደር የሚያገለግሉ የመመዘኛ መስፈርቶች ከስር የተገለፁት ሲሆኑ አጠቃላይ

ፍረጃው በሚከተሉት የነጥብ ገደቦች መሠረት ይሆናል፡-

1= ዝቅተኛ (ከ 65% በታች)


2= መካከለኛ (ከ 65 –75%)
3= ከፍተኛ (ከ 75 – 90%)
4= የላቀ (ከ 90 –100%)

ክብደት የተሰጠ
ተ.ቁ መስፈርት
ከ 100% ነጥብ
1 ከማህበራዊ ጠቀሜታ አንፃር 20
1.1 የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽል መሆኑ 5
1.2 የስራ ዕድል በመፍጠር ላይ ያለው አስተዋፅኦ 5
1.3 የሴቶችን የስራ ጫና የሚቀንስ መሆኑ 5
1.4 የአካል ጉዳተኞችንና አቅመ-ደካሞችን ችግር ፈቺ መሆኑ 5

2 ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር 25


2.1 ከውጭ የሚገባ ምርት/አገልግሎትን የሚተካ 4

2.2 ውጭ ገበያ መግባት የሚያስችል ምርት/አገልግሎት መሆኑ 4

2.3 ከውጭ ከሚገባው ተመሳሳይ ምርት በዋጋ ያነሰ መሆኑ 4


2.4 የምግብ ዋስትና ለማረጋግጥና ድህነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያለው 5
መሆኑ
2.5 የምርት/አገልግሎት ጥራትና ምርታማነት መጨመሩ 4
2.6 የደንበኞች/ዜጎችን የመግዛት አቅምን ያገናዘበ መሆኑ 4
3 ከአካባቢ ደህንነት/አረንጓዴ ልማት አንፃር 15
3.1 የአካባቢ ብክለትን የሚቀንስ መሆኑ 3

3.2 የተፈጥሮ ሀብትን በተሻለ ሁኔታ መጠቀም ማስቻሉ 3

3.3 በአጠቃቀም ላይ የስራ ቦታ የጤናና የአካል ጉዳት የማያስከትል መሆኑ 3


(OHS)
3.4 የአካባቢውን የልማት ፀጋ መጠቀም የሚያስችል መሆኑ 4
3.5 ብሔራዊ ጥቅምና የደህንነት መረጃ ስርዓትን አደጋ የማያስከትል 2
መሆኑ

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
4 ከቴክኖሎጂ አንፃር 40
ክብደት የተሰጠ
ተ.ቁ መስፈርት
4.1 ከ 100%
6 ነጥብ
በእሴት ሰንሰለት ትንተና ችግሮችን ለይቶ የተነሳ መሆኑ

4.2 የአዋጭነት ትንተና የተዘጋጀለት መሆኑ 4

4.3 አሰራር ሰነድ (ንድፍ፣ ዝርዝር ንድፍ፣ የጥሬ ዕቃ ዝርዝርና ልኬት) 6


የያዘ መሆኑ
4.4 የቴክኖሎጂ ፍብረካ ዝርዝር መግለጫ (የጥሬ ዕቃ ስም ዝርዝር፣ ልኬትና 5
ዋጋ) መቅረቡ
4.5 የአመራረት ሂደቱ ተቀምሮ የቀረበ መሆኑ 3
4.6 የአገጣጠም ሰነድ (assembling manual) 3

4.7 የናሙናና የጥራት ፍተሻ ሪፖርት መቅረቡ 5

4.8 ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል መሆኑ 4


4.9 ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች ተሸጋግሮ ሀብት ማፍራት ማስቻሉን 4
ማረጋገጫ ሠነድ መቅረቡ
አጠቃላይ ውጤት 100

ያገኘው ደረጃ

12. የቅሬታ አቀራረብ ሂደት


ተወዳዳሪዎች በአሰራርና በውጤት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካላቸው አቤቱታቸውን ውድድሩን
በሚመራው የስራ ክፍል ለተመደበው አስተባባሪ ያቀርባሉ፤ አቤቱታቸው በመጀመሪያ በሙያው ዳኛ
ታይቶ ካልተፈታ ቀጥሎ በዳኞች ጉባኤ እንዲታይ ይደረጋል፤ በዚህ መፍታት ካልተቻለ
የመጨረሻው ውሳኔ ውድድሩን በሚመራው ስራ ክፍል ኃላፊ ከዳኞች ጋር በመምከር የሚሰጥ
ይሆናል፡፡ ለዚህም ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ጉዳዩን ለውድድሩ አስተባባሪ ውጤቱ በተገለጸ ሁለት
ቀናት ውስጥ ማመልከቻቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቅሬታው በቀረበ በሁለት ቀናት ውስጥ
ለአቅራቢው የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡

13. የሽልማት አሰጣጥ


በቴክኖሎጂዎች ውድደር አሸናፊዎች በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አስፈጻሚ አካላት በሚወስኑት መሰረት

የገንዘብ፣ የሜዳሊያ፣ የትምህርት ዕድል፣ የሰርተፊኬት፣ የውጭ ጉብኝት እንዲሁም ሌሎች የማበረታቻ

ሽልማቶች የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ
14. የተሳትፎ ሰርቲፊኬት
ውድድሩን ያጠናቀቁ ሁሉም ተሳታፊዎች በውድድሩ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳትፎ ሰርትፊኬት የሚያገኙ

ይሆናል፡፡

15. ማጠቃለያ
ይህ የማስተግበሪያ ሰነድ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ተግባርን በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት በሌለው ሁኔታ

የመፈጸም ክፍተትን እንደሚሞላ ይታመናል፡፡ ሆኖም በትግበራ ላይ የግልጸኝነትና የአጠቃቀም ችግሮች

ሊያጋጥሙ የሚችሉ በመሆናቸው ውድድሮችን የሚመሩ አካላት የራሳቸውን መፍትሄ እያስቀመጡ

ውድድሮቹን ከፍጻሜ ማድረስ የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ወይንም ለአፈጻጸም

ተጨማሪ ማብራሪያዎች ቢያስፈልጉ ግን የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲን ድጋፍ መጠየቅ የሚቻል

መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

አድራሻ፡-

ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡- 40/1080 አዲስ አበባ


ስልክ ቁጥር 0116291895
ኢ-ሜይል፡ kehulum_belay@yahoo.com

ፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ

You might also like