You are on page 1of 44

ምዕራፍ ሶስት፤ የመረጃ ትንተናና የውጤት ማብራሪያ

ቀደም ሲል እንደተገለጸው ይህ ጥናት ሶስት ዓላማዎችን ለማሳካት የተከናወነ ሲሆን ዓላማዎቹ ግባቸውን እንዲመቱ
ያገለገሉ መረጃዎች በጽሑፍ መጠይቅ ተሰብስበዋል። በጽሑፍ መጠይቁ የተሰበሰቡት መረጃዎች አይነታዊና መጠናዊ
ሲሆኑ መረጃዎቹን ለመተንተን አመች በሆኑ የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች መተንተን አለባቸው። በመሆኑም መረጃዎቹ
በዚህ ምዕራፍ ተገቢዎቹን የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች በመጠቀም ተተንትነዋል ትንተናው የሚያመለክተው ውጤትም
ተብራርቷል፡፡

3.1. የመረጃ ትንተና


የጽሑፍ መጠይቅ የሞሉ ተማሪዎች መረጃ
ተ.ቁ የተማሪዎች ክፍል የተሰራጨው መጠይቁን በትክክል ምርመራ
መጠይቅ ብዛት በትክክል የሞሉ ያልሞሉ
ተማሪዎች ተማሪዎች
1 9 10 8 2
2 10 40 32 8
3 11 15 10 5
4 12 15 11 4
ድምር 80 61 19

ለጥናቱ ያገለገሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ያገለገለው የጽሑፍ መጠይቅ 31 ጥያቄዎቸን የያዘ ሲሆን ጥያቄዎቹም
በሁለት ክፍሎች ቀርበዋል። በመጀመሪያው ክፍል 24 ዝግ ጥያቄዎች ሲኖሩ እያንዳንዳቸው 4 የመስማማት ደረጃን
የሚያመለክቱ አማራጮች አሏቸው (ከፈጽሞ አልስማማም እስከ በጣም እስማማለሁ) ። እንዲሁም ቀሪዎቹ 7
ጥያቄዎች ደግሞ ክፍት ሲሆኑ ተማሪዎቹ ያላቸውን መልስ ያለገደብ የሚገልጹባቸው ናቸው። በዚህም መሰረት
ተማሪዎቹ በዝግ ለቀረቡት ጥያቄዎች በትምህርት ቤቱ ያጋጠሟቸው ችግሮች ያሏቸውን ደረጃዎች ከተሰጡት አራት
አማራጮች አንዱን ብቻ መርጠው እንዲመልሱ ተደርጓል። እንዲሁም በክፍት ጥያቄዎቹ በተለያዩ የትምህርት ቤቱ
ጉዳዮች ላይ ያጋጠሟቸውን ችግሮችና መፍትሄዎቻቼውን እንዲገልጹ ተደርጓል።
ቀደም ባሉት ክፍሎች እንደተገለጸው ለተማሪዎቹ ከተበተኑት 80 የጽሑፍ መጠይቆች ውስጥ 61 ዱ በትክክል ሲሞሉ
ቀሪዎቹ 19 ቱ ደግሞ በሚገባ አልተሞሉም። በመሆኑም በትክክል ያልተሞሉት 19 የጽሑፍ መጠይቆች ከትንተናው
ውጭ ተደርገው 61 ዱ ብቻ ተተንትነዋል። ከ 61 ዱ መጠይቆች ውስጥ 8 ቱ በ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች፣ 32 ቱ በ 10 ኛ
ክፍል ተማሪዎች፣ 10 ሩ በ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች እና 11 ዱ በ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሞሉት የጽሑፍ መጠይቆች
ለመረጃ ትንተና በግብዓትነት አገልግለዋል። የመረጃ ትንተናው የተከናወነው በሁለት ክፍሎች ሲሆን በመጀመሪያው
ክፍል የዝግ ጥያቄዎቹ ምላሾች፣ እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል የክፍት ጥያቄዎች ምላሾች ተተንትነዋል።

3.1.1 የዝግ ጥያቄዎች ምላሾች ትንተና

ከሰላሳ አንዱ የጽሑፍ መጠይቅ ጥያቄዎች ውስጥ 24 ቱ ዝግ ጥያቄዎች እንደሆኑ ከላይ ተገልጿል። ዝግ ጥያቄዎቹ
እያንዳንዳቸው አራት አማራጮች ሲኖሯቸው ምላሾቹም በቁጥር ተወክለዋል። አማራጮቹ ከፈጽሞ አልስማማም (1)
እስከ በጣም እስማማለሁ (4) ደረጃ ይገልጻሉ። በዚህ መንገድ ለቀረቡት ልዩ ልዩ ጉዳዮችን የሚያነሱ 24 ጥያቄዎች
ተማሪዎቹ የሚስማሟቸውን ምላሾች ሰጥተዋል። በጽሑፍ መጠይቁ የቀረቡት ጉዳዮች ባላቸው መመሳሰል በ 3
ክፍሎች የተመደቡ ሲሆኑ እነሱም የሚከተሉት ናቸው።

1. መምህራንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች፤

2. ርዕሳነ መምህራንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች፤

3. የትምህርት ቤቱን አጠቃላይ አስተዳደርና አሰራር የሚመለከቱ ጥያቄዎች

4. የተማሪዎችን ጠቃላይ ስርአትና ስነ ልቦና የሚመለከቱ ጥያቄዎች።

ቀጥሎ እነዚህ ርእሰ ጉዳዮች ለየብቻ በተከታታይ ይተነተናሉ።


3.1.1.1 መምህራንን በተመለከተ በዝግ ለቀረቡ ጥያቄዎች ተሰጡ ምላሾች ትንተና
በዝግ ጥያቄዎቹ ከቀረቡት ርእሰ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ መምህራንን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን የያዘው የመጠይቅ ክፍል
ነው። መምህራንን የተመለከቱት የጽሑፍ መጠይቁ ጥያቄዎች ሶስት ሲሆኑ እነሱም በጥያቄ ቁጥር 1፣ 2 እና 5
ቀርበዋል። ለእነዚህ ጥያቄዎች የተሰጡት ምላሾች ቀጥሎ ባሉት ሶስት ተከታታይ ሰንጠረዦች ቀርበዋል።

ሰንጠረዥ አንድ፡ መምህራን ስለሚያስተምሯቸው የትምህር አይነት ይዘቶች ያላቸው እውቀት (ግንዛቤ)
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
አብዛኛዎቹ መምህራን ስለሚያስተምሯቸው 1 9 0
ትምህርቶች በቂ እውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ 10 0
11 0
12 0
ድምር 0
መቶኛ 0
2 9 1
10 3
11 2
12 0
ድምር 6
መቶኛ 9.8
3 9 1
10 11
11 4
12 8
ድምር 24
መቶኛ 37.1%
4 9 6
10 18
11 4
12 3
ድምር 31
መቶኛ 50.3%
በሰንጠረዥ አንድ የቀረበው ጥያቄ "አብዛኛዎቹ መምህራን ስለሚያስምሯቸው ትምህርቶች በቂ እውቀት ያላቸው
ናቸው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 1 ቁጥርን በምንም ተማሪ አልተመረጠም። በአንጻሩ ደግሞ 2 ቁጥርን 6 ተማሪዎች
(9.8%)፣ 3 ቁጥርን 24 ተማሪዎች (37.1%)፣ 4 ቁጥርን 31 ተማሪዎች (53.1%) መርጠዋል። ከተማሪዎቹ ምላሽ
መገንዘብ እንደሚቻለው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች (55 ተማሪዎች /88.2%) መምህሮቻቼው በሚያስተምሩት
ትምሀርት ይዘቶች በቂ እውቀት እንዳላቸው ያምናሉ።

ሰንጠረዥ ሁለት፡ የመምህራን የማስተማር ስነ ዘዴ


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
የመምህራን የማስተማር ስነ ዘዴ ከተማሪዎች 1 9 0
የአረዳድ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ነው፡፡ 10 0
11 0
12 0
ድምር 0
መቶኛ 0
2 9 1
10 8
11 2
12 6
ድምር 17
መቶኛ 27.9%
3 9 6
10 12
11 3
12 3
ድምር 24
መቶኛ 39.3%
4 9 1
10 12
11 5
12 2
ድምር 20
መቶኛ 32.8%

በሰንጠረዥ ሁለት የቀረበው ጥያቄ "የመምህራን የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ከተማሪዎች የአረዳድ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ
ነው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 1 ቁጥር በምንም ተማሪ አልተመረጠም። በአንጻሩ ደግሞ 17 ተማሪዎች (27.9%)
2 ን፣ 24 ተማሪዎች (39.3%) 3 ን እንዲሁም 20 ተማሪዎች (32.8%) 4 ን መርጠዋል። ይህም ማለት 17 ቱ
ተማሪዎች (27.9%) መምህሮቻቸው የሚያስተምሩባቸው ዘዴዎች የማይመቿቸው ሲሆኑ ለቀሪዎቹ 44 ተማሪዎች
(72.1%) የመምህሮቻቼው ዘዴዎች ይመቿቸዋል ማለት ነው።

ሰንጠረዥ ሶስት፡ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ቅርበት


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በተማሪዎችና በመምህራን መካከል ያለው ግንኙት 1 9 0
በጣም ጥሩ ነው፡፡ 10 2
11 0
12 1
ድምር 3
መቶኛ 4.9%
2 9 0
10 1
11 0
12 2
ድምር 3
መቶኛ 4.9%
3 9 2
10 15
11 5
12 3
ድምር 25
መቶኛ 40.9
4 9 6
10 14
11 5
12 5
ድምር 30
መቶኛ 49.2

በሰንጠረዥ ሶስት "በመምህራንና በተማሪዎች መካከል ያለው ቅርበት በጣም ጥሩ ነው" የሚል ጥያቄ ቀርቧል። ለዚህ
ጥያቄ 1 ቁጥርና 2 ቁጥር እያንዳንዳቸው 3 ተማሪዎች በድምሩ 6 ተማሪዎች (9.6%) መርጠዋቸዋል፤ እንዲሁም 3 ን
25 ተማሪዎች (42.9%) እና 4 ን ደግሞ 30 ተማሪዎች (47.5%) መርጠዋቸዋል። ከዚህ መረጃ መገንዘብ
እንደሚቻለው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከመምህሮቻቼው ጋር ጥሩ ቅርበት ሲኖራቸው የተወሰኑት ተማሪዎች ግን
መምሮቻቸው ጋር ያላቸው ቅርበት አጥጋቢ አይደለም።

3.1.1.2. አጠቃላይ የትምህርት ቤቱን የአሰራር ስርአት ለተመለከቱ ዝግ ጥያቄዎች ተማሪዎች የተሰጧቸው ምላሾች
ትንተና
በዝግ ጥያቄዎች ከቀረቡት መጠይቆች ውስጥ አጠቃላዩን የትምህርት ቤቱን የአሰራር ስርአት የሚመለከቱት ጥያቄዎች
17 ሲሆኑ ጥያቄዎቹ በ 4 ንዑሳን ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ። ርእሰ ጉዳዮቹም የትምህርት ቤቱን ደንብና መመሪያዎች
የሚመለከቱ አምስት ጥያቄዎች (ጥያቄ ቁጥር 3፣ 4፣ 6፣ 7 እና 8)፤ የትምህርት ቤቱን ነባራዊ ሁኔታዎች የሚመለከቱ
ሶስት ጥያቄዎች (ጥያቄ ቁጥር 11፣ 12 እና 21)፤ የመኝታና የመመገቢያ ቤት ስርአትን የተመለከቱ አምስት ጥያቄዎች
(ጥያቄ ቁጥር 15፣,16፣ 17፣ 18 እና 19)፤ የትምህርት ቤቱን ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጻህፍት፣ ክሊኒክ እና የክበባት
እንቅስቃሴዎችን የሚመለከቱ አራት ጥያቄዎች (ጥያቄ ቁጥር 20፣ 22፣ 23 እና 24) ናቸው። እነዚህን ጉዳዮች
ለተመለከቱት ጥያቄዎች ተማሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ቀጥሎ በተከታታይ ይቀርባሉ።

3.1.1.2.1. የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ ለተመለከቱ ዝግ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ትንተና

የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ የተመለከቱት ጥያቄዎች አምስት ሲሆኑ እነሱም በጥያቄ ቁጥር 3፣ 4፣ 6፣ 7 እና 8
ቀርበዋል። ለእነዚህ ዝግ ጥያቄዎች ተማሪዎቹ ከተሰጡት አማራጮች መካከል በመምረጥ የመለሱ ሲሆን የተማሪዎቹ
ምላሾች እንደሚከተለው ተተንትነዋል።
ሰንጠረዥ አራት፡ የትምህርት፣ የፈተና እና የእረፍት የጊዜ ሰሌዳዎች አወጣጥ
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
ለፈተና ዝግጅት፣ ለግል ጥናትና እረፍት ለማድረግ 1 9 4
በትምህርት ቤቱ የሚወጡት የጊዜ ሰሌዳዎች 10 15
የተማሪዎችን ፍላጎት ያማከለና ለመማር ማስተማር 11 2
ሂደቱ የተመቸ ነው፡፡ 12 0
ድምር 21
መቶኛ 34.4%
2 9 2
10 11
11 0
12 5
ድምር 18
መቶኛ 29.5
3 9 1
10 4
11 4
12 3
ድምር 12
መቶኛ 19.3
4 9 1
10 2
11 4
12 3
ድምር 10
መቶኛ 16.4

በሰንጠረዥ አራት የቀረበው ጥያቄ "ለፈተና ዝግጅት፣ ለግል ጥናትና እረፍት ለማድረግ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡት
የጊዜ ሰሌደዎች የተማሪዎችን ፍላጎት ያማከለና ለመማር ማስተማር ሂደቱ የተመቸ ነው።" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ
1 ቁጥርን 21 ተማሪዎች (34.4%)፣ 2 ቁጥርን 18 ተማሪዎች (29.5%)፣ 3 ቁጥርን 12 ተማሪዎች (19.3%)፣
እንዲሁም 4 ቁጥርን 10 ተማሪዎች (16.%) መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው ብዙዎቹ ተማሪዎች በትምህርት
ቤቱ በሚዘጋጁት የትምህርት፣ የፈተና እና የእረፍት የጊዜ ሰሌዳ ደስተኛ አለመሆናቸውን ነው።
ሰንጠረዥ አምስት፡ የትምህርት፣ ከዓመቱ ትምህርት ቀድሞ የተሰጠው የክለሳ ትምህርት
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
ዋናው ትምህርት ከመሰጠቱ በፊት የተደረገው ክለሳ 1 9 1
በቂ ነው፡፡ 10 5
11 0
12 3
ድምር 9
መቶኛ 14.8
2 9 1
10 4
11 4
12 2
ድምር 11
መቶኛ 18.03
3 9 5
10 13
11 3
12 1
ድምር 31
መቶኛ 50.8
4 9 1
10 10
11 3
12 5
ድምር 19
መቶኛ 31.1

በዘንጠረዥ አምስት የቀረበው ጥያቄ "ዋናው የዓመቱ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የተሰጠው የክለሳ ትምህርት በቂ
ነው" የሚል ነው። ለዚሀ ጥያቄ 19 (31.1%) ተማሪዎች 4 ን፣ 31 ተማሪዎች (50.8%) 3 ን፣ 11 ተማሪዎች
(18.03%) 2 ን፣ እንዲሁም 9 ተማሪዎች (14.8%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ እንደሚያመለክተው ብዙዎቹ
ተማሪዎች የተሰጠው ክለሳ በቂ እንዳልሆነ ያምናሉ፤ በአንጻሩ የተወሰኑ ተማሪዎች በተሰጠው ክለሳ ደስተኞች ናቸው።

ሰንጠረዥ ስድስት፡ የትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ስርዓት ከተማሪዎች ፍላጎት ጋር ያለው መጣጣም


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በትምህርት ቤቱ ያለው አጠቃላይ የአስተዳደር ስርዓት 1 9 0
ከመማር ማስተማር ሂደት፣ ከተማሪዎች ፍላጎት፣ 10 4
ከመምህራን ፍላጎት እና ከወላጆች ፍላጎት ጋር 11 0
የተጣጣመ ነው፡፡ 12 1
ድምር 5
መቶኛ 8.2
2 9 2
10 13
11 2
12 1
ድምር 18
መቶኛ 29.5
3 9 6
10 10
11 6
12 8
ድምር 31
መቶኛ 50.8
4 9 0
10 5
11 2
12 1
ድምር 7
መቶኛ 11.5

በሰንጠረዥ ስድስት የቀረበው ጥያቄ "በትምህርት ቤቱ ያለው አጠቃላይ የአስተዳደር ስርአት ከመማር ማስተማር
ሒደት፣ ከተማሪዎች፣ ከመምህራንና ከወላጆች ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ነው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎች
የሰጡት ምላሽ 7 ተማሪዎች (11%) 4 ን፣ 31 ተማሪዎች (50.8%) 3 ን፣ 18 ተማሪዎች (31%) 2 ን እንዲሁም 5
ተማሪዎች (8.2%) 1 ን መምረጣቸውን ያመለክታል። ከዚህ መረጃ በመነሳት በትምህርት ቤቱ የጊዜ ሰሌዳ አብዛኛዎቹ
ተማሪዎች ደስተኞች እንደሆኑ ማረጋገጥ ይቻላል።

ሰንጠረዥ ሰባት፡ ተማሪዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሚሰጣቸው ምላሽ


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
ተማሪዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በመምህራንና 1 9 0
በአስተዳደር በኩል የሚሰጡት ምላሾች ተገቢና 10 4
ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ተገናዘቡ ናቸው፡፡ 11 0
12 0
ድምር 4
መቶኛ 6.6
2 9 5
10 14
11 5
12 2
ድምር 26
መቶኛ 42.6
3 9 1
10 6
11 0
12 6
ድምር 13
መቶኛ 21.3
4 9 2
10 8
11 5
12 3
ድምር 18
መቶኛ 29.6

በሰንጠረዥ ሰባት የቀረበው ጥያቄ "ተማሪዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በመምህራንና በአስተዳደር በኩል የሚሰጡት
ምላሾች ተገቢና ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ተገናዘቡ ናቸው፡፡" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 18 ተማሪዎች (29.6%) 4 ን፣ 13
ተማሪዎች (21.3%) 3 ን፣ 26 ተማሪዎች (42.6%) 2 ን እንዲሁም 4 ተማሪዎች (6.6%) 1 ን መርጠዋል። ይህ የመረጃ
ትንተና እንደሚያመለክተው ግማሾቹ ተማሪዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢ መልስ የሚያገኙ ሲሆን ግማሾቹ
ደግሞ ተገቢ መልስ አያገኙም።

ሰንጠረዥ ስምንት፡ በትምህርት ቤቱ የሚወሰዱ የዲሲፕሊን እርምጃዎች


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በትምህርት ቤቱ የሚወሰዱት የዲሲፒሊን 1 9 2
እርምጃዎች በቂ፣ ተመጣጣኝና አስተማሪ ናቸው፡፡ 10 2
11 2
12 3
ድምር 9
መቶኛ 14.8
2 9 0
10 4
11 0
12 0
ድምር 4
መቶኛ 6.6
3 9 2
10 20
11 0
12 2
ድምር 24
መቶኛ 39.3
4 9 4
10 6
11 8
12 6
ድምር 24
መቶኛ 39.3

በሰንጠረዥ ስምንት የቀረበው ጥያቄ "በትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሚወሰዱ የዲሲፒሊን እርምጃዎች በቂ፣
ተመጣጣኝና አስተማሪ ናቸው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 24 ተማሪዎች (39.3%) 4 ን፣ 24 ተማሪዎች (39.3%)
3 ን፣ 4 ተማሪዎች (6.6%) 2 ን እንዲሁም 9 ተማሪዎች (14.8%) መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው
አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ የሚወስዳቸውን የዲሲፒሊን እርምጃዎች እንደሚስማሙባቸው ሲሆን
የተወሰኑት ተማሪዎች ግን አይስማሙባቸውም ማለት ነው።

3.1.1.2.2. የትምህርት ቤቱን ነባራዊ ሁኔታዎች ለተመለከቱ ዝግ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ትንተና

በጽሑፍ መጠይቁ ከተካተቱት ዝግ ጥያቄዎች ውስጥ ሶስቱ የትምህርት ቤቱን ነባራዊ ሁኔታዎች የሚመለከቱ ሲሆኑ
እነሱም በተራ ቁጥር 11፣ 12 እና 21 የቀረቡት ናቸው። ለእነዚህ ጥያቄዎች ተማሪዎቹ የሰጧቸው ምላሾች ቀጥሎ
ተተንትነዋል።

ሰንጠረዥ ዘጠኝ፡ የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ለተማሪዎች ውጤት ያለው አወንታዊ አስተዋጽኦ
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
የተማሪዎች የአጠናን ስርአት፣ የመምህራን 1 9 0
የማስተማሪያ ዘዴና የግቢው አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ 10 0
በትምህርት ውጤታማነትሽ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ 11 0
አሳድሮብሻል።
12 1
ድምር 1
መቶኛ 1.64
2 9 3
10 7
11 0
12 4
ድምር 14
መቶኛ 22.95
3 9 1
10 16
11 5
12 3
ድምር 25
መቶኛ 40.98
4 9 4
10 9
11 5
12 3
ድምር 21
መቶኛ 34.4
በሰንጠረዥ ዘጠኝ የቀረበው ጥያቄ የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ለተማሪዎች ውጤት ያለው አወንታዊ
አስተዋጽኦ በሚመለከት ነው። ለዚህ ጥያቄ 21 ተማሪዎች (34.4%) 4 ን፣ 25 ተማሪዎች (40.98%) 3 ን፣ 14
ተማሪዎች (22.95%) 2 ን፣ እንዲሁም 1 ተማሪ (1.64%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው አብዛኛዎቹ
ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቱ ያለው የአጠናን ስርአት፣የመምህራን የማስተማሪያ ዘዴና የግቢው አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ
ውጤታቸው ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማሳደሩን አመላክተዋል ። ሆኖም ግን ጥቂት ተማሪዎች በአሉታዊነት አስቀምጠዋል፡፡

ሰንጠረዥ አስር፡ የተማሪዎች ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸው ችግሮች ስለመኖራችው


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በፈለጉት መጠን 1 9 0
ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጓቸው ችግሮች አሉ። 10 1
11 0
12 1
ድምር 2
መቶኛ 3.3
2 9 1
10 3
11 1
12 1
ድምር 6
መቶኛ 9.8
3 9 5
10 15
11 5
12 6
ድምር 31
መቶኛ 50.8
4 9 2
10 13
11 3
12 4
ድምር 22
መቶኛ 36.1
በሰንጠረዥ አስር የቀረበው ጥያቄ "የተማሪዎች የአጠናን ስርዓት፣ የመምህራን የማስተማር ዘዴ እና የግቢው አጠቃላይ
ነባራዊ ሁኔታ በትምህርት ውጤታማነትሽ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳድሮብሻል" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 22
ተማሪዎች (36.1%) 4 ን፣ 31 ተማሪዎች (50.8%) 3 ን፣ 6 ተማሪዎች (9.8%) 2 ን እንዲሁም 2 ተማሪዎች
(3.3%) 1 ነ መርጠዋል። ከዚህ መረጃ መረዳት የሚቻለው በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በፈለጉት መጠን ውጤታማ እንዳይሆኑ
የሚያደርጓቸው ችግሮች እንዳሉ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ያስቀመጡ ሲሆን ጥቂት ተማሪዎች ግን ተጽእኖ እንሰሌለው አመላክተዋል፡፡
ሰንጠረዥ አስራ አንድ፡ በትምህርት ቤቱ በቂና ፍላጎትን ማእከል ያደረጉ የመዝናኛ ቦታዎች በተመለከተ።
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በግቢው ውስጥ በቂና ፍላጎትን ማእከል ያደረጉ 1 9 5
የመዝናኛ ቦታዎች አሉ። 10 10
11 5
12 3
ድምር 23
መቶኛ 37.7
2 9 1
10 19
11 5
12 2
ድምር 27
መቶኛ 44.3
3 9 1
10 1
11 0
12 2
ድምር 4
መቶኛ 6.6
4 9 1
10 2
11 0
12 4
ድምር 7
መቶኛ 11.3

በሰንጠረዥ አስራ አንድ የቀረበው ጥያቄ 'በግቢው ውስጥ በቂና ፍላጎትን ማእከል ያደረጉ የመዝናኛ ቦታዎች አሉ" የሚል
ነው። ለዚህ ጥያቄ 7 ተማሪዎች (11.3%) 4 ን፣ 4 ተማሪዎች (6.6%) 3 ን 27 ተማሪዎች (44.3%) 2 ን እንዲሁም
23 ተማሪዎች (37.7%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ በቂ
እና ፍላጎት መሰረት ያደረጉ የመዝናኛ ቦታችዎች አለመኖራቸውን ገለጸዋልን፤ የተወሰኑ ተማሪዎች ግን በግቢው
ይዝናናሉ።

3.1.1.2.3. የመኝታና የመመገቢያ ቤት ስርአትን ለተመለከቱ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ትንተና

በትምህርት ቤቱ ህገ ደንብ ከሚከናወኑ ጉዳዮች ውስጥ የመኝታና የመመገቢያ ስርአት ይገኙበታል። እነዚህ አገልግሎቶች
ሲሰጡም የየራሳቸው ደንብና መመሪያዎች አሏቸው። እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ተማሪዎች ሊያጋጥሟቸው
የሚችሉ ነገሮች መኖራቸው እሙን ነው። ይህንን ለመፈተሽም በጽሑፍ መጠይቁ አምስት ጥያቄዎች (ጥያቄ ቁጥር
15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19) ቀርበዋል። ለእነዚህ ጥያቄዎች ተማሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ቀጥሎ ይተነተናሉ።
ሰንጠረዥ አስራ ሁለት፡ የመኝታና የምግብ ቤት ስርአት ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ መሆን
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በትምህርት ቤቱ ያለው የመኝታ ክፍልና የአመጋገብ 1 9 0
ስነ ስርአት ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ነው 10 1
11 3
12 0
ድምር 4
መቶኛ 6.6
2 9 0
10 3
11 3
12 0
ድምር 6
መቶኛ 9.8
3 9 3
10 15
11 2
12 4
ድምር 24
መቶኛ 39.3
4 9 5
10 13
11 2
12 7
ድምር 27
መቶኛ 44.3

በሰንጠረዥ አስራ ሁለት የቀረበው ጥያቄ "በትምህርት ቤቱ ያለው የመኝታ ክፍልና የአመጋገብ ስነ ስርአት ከወቅታዊው
ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ነው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 27 ተማሪዎች (44.3%) 4 ን፣ 24 ተማሪዎች (39.3%) 3 ን፣ 6
ተማሪዎች (9.8%) 2 ን እንዲሁም 4 ተማሪዎች (6.6%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው አብዛኛዎቹ
ተማሪዎች የመኝታ እና የምግብ ቤት ስርአቱ ወቅታዊውን ሁኔታ ያማከለ መሆኑን እንደሚያምኑና የተወሰኑት
ተማሪዎች ግን እንደማያምኑ ነው።

ሰንጠረዥ አስራ ሶስት፡ የመኝታ ክፍሎች የጸጥታ ሁኔታ


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በመኝታ ክፍል ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ለጥናት 1 9 1
አመች ነው። 10 5
11 0
12 3
ድምር 9
መቶኛ 14.8
2 9 1
10 10
11 4
12 2
ድምር 17
መቶኛ 27.9
3 9 1
10 9
11 2
12 3
ድምር 15
መቶኛ 24.6
4 9 5
10 8
11 4
12 3
ድምር 20
መቶኛ 32.8

በሰንጠረዥ አስራ ሶስት የቀረበው ጥያቄ "በመኝታ ክፍል ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ለማጥናት አመቺ ነው" የሚል
ነው። ለዚህ ጥያቄ 20 ተማሪዎች (32.8%) 4 ን፣ 15 ተማሪዎች (24.6%) 3 ን፣ 17 ተማሪዎች (27.9%) 2 ን
እንዲሁም 9 ተማሪዎች (14.8%) 1 ን መርጠዋል። ከዚህ መረጃ መሠረት አብዛኞቹ መልስ ሰጪ ተማሪዎች የመኝታ ቤቱ
ጸጥታ ጥሩ እንደሆነና ግማሾቹ ደግሞ ጥሩ እንዳልሆነ እንደሚያምኑ ማረጋገጥ ይቻላል።
ሰንጠረዥ አስራ አራት፡ በመኝታ ቤት ውስጥ ያሉ መጸዳጃዎች ንጽሕና እና ለአጠቃቀም አመችነት
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በመኝታ አዳራሽ ያሉ መጸዳጃ ቤቶች ንጽሕናቸው 1 9 1
የተጠበቀና ለአጠቃቀም ምቹ ናቸው። 10 2
11 0
12 2
ድምር 5
መቶኛ 8.2
2 9 1
10 0
11 3
12 4
ድምር 8
መቶኛ 13.1
3 9 3
10 12
11 4
12 3
ድምር 22
መቶኛ 36.1
4 9 3
10 18
11 3
12 2
ድምር 26
መቶኛ 42.6

በሰንጠረዥ አስራ አራት የቀረበው ጥያቄ "በመኝታ አዳራሾች ያሉ የመጸዳጃ ቤቶች ንጽህናቸው የተጠበቀና
ለአጠቃቀም ምቹ ናቸው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 26 ተማሪዎች (42.%) 4 ን፣ 22 ተማሪዎች (36.1%) 3 ን፣
8 ተማሪዎች (13.1%) 2 ን እንዲሁም 5 ተማሪዎች (8.2%) 1 ን መርጠዋል። በዚህ መረጃ መሰረት በመኝታ
አዳራሾች የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች ጽዱና ምቹ ሲሆኑ ለተወሰኑት ተማሪዎች ደግሞ
አይደሉም ማለት ነው።

ሰንጠረዥ አስራ አምስት፡ በመኝታ ክፍል ውስጥ ያሉ ቁሳቁሶች አመችነት


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
ለመኝታ የሚያገለግሉት ቁሳቁሶች ለመኝታ የተመቹ 1 9 1
ናቸው 10 3
11 2
12 2
ድምር 8
መቶኛ 13.1
2 9 0
10 5
11 2
12 5
ድምር 12
መቶኛ 19.7
3 9 2
10 14
11 3
12 2
ድምር 21
መቶኛ 34.4
4 9 5
10 10
11 3
12 2
ድምር 20
መቶኛ 32.8

በሰንጠረዥ አስራ አምስት የቀረበው ጥያቄ "ለመኝታ የሚያገለግሉት ቁሳቁሶች ለመኝታ የተመቹ ናቸው" የሚል ነው።
ለዚህ ጥያቄ 20 ተማሪዎች (32.8%) 4 ን፣ 21 ተማሪዎል (34.4%) 3 ን፣ 12 ተማሪዎች (19.7%) 2 ን እንዲሁም 8
ተማሪዎች (13.1%) 1 ን መርጠዋል። ከዚህ መረጃ መገንዘብ የሚቻለው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የመኝታ ቁሳቁሶቹ
ምቹ ሲሆኑ ለተወሰኑት ደግሞ ምቹ አለመሆናቸውን ነው።

ሰንጠረዥ አስራ ስድስት፡ የምግብ ቤት አቅርቦትና ጥራት


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
የምገባ ስርዓቱ ከአቅርቦትና ከጥራት አንጻር በጣም 1 9 0
ጥሩ ነው። 10 1
11 0
12 0
ድምር 1
መቶኛ 1.64
2 9 1
10 5
11 0
12 1
ድምር 7
መቶኛ 11.5
3 9 1
10 9
11 5
12 4
ድምር 19
መቶኛ 31.1
4 9 6
10 17
11 5
12 6
ድምር 34
መቶኛ 55.7

በሰንጠረዥ አስራ ስድስት የቀረበው ጥያቄ "የምገባ ስርዓቱ ከአቅርቦትና ከጥራት አንጻር በጣም ጥሩ ነው" የሚል ነው።
ለዚህ ጥያቄ 34 ተማሪዎች (55.7%) 4 ን፣ 19 ተማሪዎች (31.1%) 3 ን፣ 7 ተማሪዎች (11.5%) 2 ን እንዲሁም 1
ተማሪ (1.64%) 1 ን መርጠዋል። ከተማሪዎቹ ምላሽ መገንዘብ እንደሚቻለው የምገባ ስርዓቱ አቅርቦትና ጥራት
ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች በጣም ጥሩ ሲሆን ለጥቂት ተማሪዎች ደግሞ ጥሩ አለመሆኑን ነው።

3.1.1.2..4. የትምህርት ቤቱን ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ ክሊኒክ እና ክበባት ለተለከቱ ዝግ ጥያቄዎች የተሰጡ
ምላሾች ትንተና

በትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ ክሊኒክ እና ልዩ ልዩ ክበባት ይገኛሉ። በእነዚህ አገልግሎት ማግኛ ክፍሎች
ተማሪዎች ልዩ ልዩ ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል። በመሆኑን እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ተማሪዎች ችግር
ያጋጠማቸው መሆን አለመሆኑን ለመፈተሽ በጽሑፍ መጠይቁ አራት ዝግ ጥያቄዎች (ጥያቄ ቁጥር 20፣ 22፣ 23 እና
24) የተካተቱ ሲሆን ለጥያቄዎቹ የተሰጡት ምላሾች እንደሚከተለው ተተንትነዋል።
ሰንጠረዥ አስራ ሰባት፡ የትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ነባራዊ ሁኔታ
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
የቤተ መጻሕፍት ነባራዊ ሁኔታ ከመጻሕፍት አቅርቦት፣ 1 9 0
ለንባብ ካለው ምቹነት፣ ከመስተንግዶና ከጸጥታ 10 3
አንጻር በጣም ጥሩ ነው። 11 0
12 2
ድምር 5
መቶኛ 8.2
2 9 1
10 7
11 8
12 0
ድምር 16
መቶኛ 26.2
3 9 5
10 12
11 2
12 4
ድምር 23
መቶኛ 37.7
4 9 2
10 10
11 0
12 5
ድምር 17
መቶኛ 27.9

ሰንጠረዥ አስራ ሰባት የቀረበው ጥያቄ "የቤተ መጻሕፍት ነባረዊ ሁኔታ ከመጻሕፍት አቅርቦት፣ ለንባብ ካለው ምቹነት፣
ከመስተንግዶና ከጸጥታ አንጻር በጣም ጥሩ ነው" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 17 ተማሪዎች (27.9%) 4 ን፣ 23
ተማሪዎች (37.7%) 3 ን፣16 ተማሪዎች (26.6%) 2 ን እነዲሁም 5 ተማሪዎች (8.2%) 1 ን መርጠዋል። ከዚህ
መረጃ መረዳት የሚቻለው ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች ቤተ መጻሕፍቱ ምቹ እንደሆነና ለጥቂት ተማሪዎች ደግሞ ምቹ
እዳልሆነ ነው።

ሰንጠረዥ አስራ ስምንት፡ የትምህርት ቤቱ ክሊኒክ ነባራዊ ሁኔታ


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በትምህርት ቤቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች 1 9 3
ለሚታመሙ ተማሪዎች ተገቢውን እንክብካቤና 10 9
ህክምና ይሰጣሉ። 11 3
12 2
ድምር 17
መቶኛ 27.9
2 9 4
10 5
11 2
12 3
ድምር 14
መቶኛ 22.95
3 9 1
10 10
11 4
12 4
ድምር 19
መቶኛ 31.1
4 9 0
10 8
11 1
12 2
ድምር 11
መቶኛ 18.03
በሰንጠረዥ አስራ ስምንት የቀረበው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ለሚታመሙ ተማሪዎች
ተገቢውን እንክብካቤና ህክምና ይሰጣሉ" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 11 ተማሪዎች (18.03%) 4 ን፣ 19 ተማሪዎች
(31.1%) 3 ን፣ 14 ተማሪዎች (22.95%) 2 ን፣ 17 ተማሪዎች (27.9%) 1 ን መርጠዋል። ከዚህ መረጃ መገንዘብ
የሚቻለው ግማሾቹ ተማሪዎች በክሊኒኩ ደስተኛ ሲሆኑ ግማሾቹ ደግሞ ደስተኛ አለመሆናቸውን ነው።

ሰንጠረዥ አስራ ዘጠኝ፡ የትምህርት ቤተ ሙከራ ነባራዊ ሁኔታ


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
የትምሀርት ቤቱ ቤተ ሙከራዎች ተገቢዎቹን 1 9 1
አገልግሎቶች በመስጠታቸው ደስተኞች ነን። 10 0
11 0
12 1
ድምር 2
መቶኛ 3.3
2 9 1
10 10
11 2
12 7
ድምር 20
መቶኛ 32.8
3 9 4
10 17
11 8
12 2
ድምር 31
መቶኛ 50.8
4 9 2
10 5
11 0
12 1
ድምር 8
መቶኛ 13.1

በሰንጠረዥ አስራ ዘጠኝ የቀረበው ጥያቄ "የትምህርት ቤቱ ቤተ ሙከራዎች ተገቢዎቹን አገልግሎቶች በመስጠታቸው
ደስኛ ነኝ" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 8 ተማሪዎች (13.1%) 4 ን፣ 31 ተማሪዎች (50.8%) 3 ን፣ 20 ተማሪዎች
(32.8%) 2 ን፣ እንዲሁም 2 ተማሪዎች (3.3%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያሳየው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች
በትምህርት ቤቱ ቤተ ሙከራ አገልግሎት መርካታቸውን እና ከፊሎቹ ደግሞ በአገልግሎቱ ያልረኩ መሆናቸውን ነው።

ሰንጠረዥ ሀያ፡ የትምህርት ቤቱ የክበባት እንቅስቃሴና አሳታፊነት


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
ተማሪዎች በክበባት እንዲንቀሳቀሱ ትምህርት 1 9 0
ቤቱ የተመቸ ነበር 10 2
11 0
12 0
ድምር 2
መቶኛ 3.3
2 9 1
10 8
11 0
12 1
ድምር 10
መቶኛ 16.4
3 9 0
10 12
11 0
12 6
ድምር 18
መቶኛ 29.5
4 9 7
10 10
11 10
12 4
ድምር 31
መቶኛ 50.8

በሰንጠረዥ ሀያ የቀረበው ጥያቄ "ተማሪዎች በክበባት እንዲሳተፉ ትምህርት ቤቱ የተመቸ ነው" የሚል ነው። ለዚህ
ጥያቄ 31 ተማሪዎች (50.8%) 4 ን፣ 18 (29.5%) 3 ን፣ 10 ተማሪዎች (16.4%) 2 ን እንዲሁም 2 ተማሪዎች
(3.3%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያሳየው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ትምህርተ ቤቱ ተማሪዎችን በማሳተፉ
ደስተኞች መሆናቸውንና ጥቂት ተማሪዎች ደግሞ አሳታፊ አለመሆኑንና ደስተኞች አለመሆናቸውን ነው።

3.1.1.3. የተማሪዎችን አጠቃላይ ስርአትና ስነ ልቦና ለሚመለከቱ ዝግ ጥያቄዎች ተማሪዎች የሰጧቸው ምላሾች
ትንተና
በዝግ ጥያቄዎቹ የቀረበው የመጨረሻው ርእሰ ጉዳይ የተማሪዎችን አጠቃላይ ስርአትና ስነ ልቦናዊ ሁኔታዎች
የሚመለከት ነው። ስለዚህ ርእሰ ጉዳይ የሚያነሱት ዝግ ጥያቄዎች አራት (9፣ 10፣ 13 እና 14) ሲሆኑ ተማሪዎች በአዳሪ
ትምህርት ቤት መማራቸው ያሳደረባቸውን ስነ ልቦናዊ ጫና ወይም ያገኙትን ስነ ልቦናዊ እርካታ እና ተማሪዎቹ
ያላቸውን ስርአት የሚያነሱ ናቸው። ለአራቱ ጥያቄዎች ተማሪዎቹ የየራሳቸውን ምለሽ የሰጡ ሲሆን የተመሪዎቹ
ምላሾች ቀጥሎ አንድ በአንድ ይተነተናሉ።
ሰንጠረዥ ሀያ አንድ፡ በትምህርት ቤቱ መማር የሚያሳድረው ስነ ልቦናዊ ጫና
ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በአዳሪ ትምህርት ቤት በመማሬ ያሳደረብኝ የስነ ልቦና 1 9 3
ጫና አለ። 10 11
11 8
12 2
ድምር 24
መቶኛ 39.3
2 9 1
10 9
11 2
12 1
ድምር 13
መቶኛ 21.3
3 9 3
10 8
11 0
12 1
ድምር 12
መቶኛ 19.7
4 9 1
10 4
11 0
12 7
ድምር 12
መቶኛ 19.7

በስንጠረዥ ሀያ አንድ የቀረበው ጥያቄ "በአዳሪ ትምህርት ቤት በመማሬ ያሳደረብኝ ስነ ልቦናዊ ጫና አለ" የሚል ነው።
ለዚህ ጥያቄ 4 ን እና 3 ን እያንዳንዳቸው 12 12 ተማሪዎች በድምሩ 24 ተማሪዎች (39.4%) መርጠዋቸዋል።
በአንጻሩ ደግሞ 1 ን 24 ተማሪዎች (39.3) እና 2 ን 13 ተማሪዎች (19.7%) መርጠዋቸዋል። ከዚህ መረጃ መገንዘብ
የሚቻለው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቱ በመማራቸው ስነ ልቦናዊ ጫና ያሳደረባቸው መሆኑንና
የተወሰኑ ተማሪዎች ደግሞ ስነ ልቦናዊ ጫና እንዳላሳደረባቸው ነው።

ሰንጠረዥ ሀያ ሁለት፡ በትምህርት ቤቱ መማር ያለው ስነ ልቦናዊ እርካታ


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በትምህርት ቤቱ በመማሬ ያገኘሁት ስነ ልቦናዊ 1 9 1
እርካታ አለ። 10 0
11 0
12 3
ድምር 4
መቶኛ 6.6
2 9 0
10 11
11 2
12 3
ድምር 16
መቶኛ 26.2
3 9 3
10 12
11 4
12 3
ድምር 22
መቶኛ 36.1
4 9 4
10 9
11 4
12 2
ድምር 19
መቶኛ 31.1

በሰንጠረዥ ሀያ ሁለት የቀረበው ጥያቄ "በትምህርት ቤቱ በመማሬ ስነ ልቦናዊ እርካታ አግኝቻለሁ" የሚል ነው። ለዚህ
ጥያቄ 19 ተማሪዎች (31.1%) 4 ን፣ 22 ተማሪዎች (36.1%) 3 ን፣ 16 ተማሪዎች (26.2%) 2 ን እንዲሁም 4
ተማሪዎች (6.6%) 1 ን መርጠዋል። ከዚህ መረጃ መገንዘብ የሚቻለው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ
በመማራቸው ስነ ልቦናዊ እርካታ ያገኙ ሲሆን የተወሰኑ ተማሪዎች ደግሞ ስነ ልቦናዊ እርካታ አለማግኘታቸውን ነው።

ሰንጠረዥ ሀያ ሶስት፡ የተማሪዎች የእርስ በእርስ ማህበራዊ ግንኙነት


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በተማሪዎች መካከል ያለው ማህበራዊ ሕይወት 1 9 0
በጣም ጥሩ ነው። 10 0
11 0
12 2
ድምር 2
መቶኛ 3.3
2 9 3
10 2
11 2
12 1
ድምር 8
መቶኛ 13.1
3 9 3
10 11
11 4
12 6
ድምር 24
መቶኛ 39.3
4 9 2
10 19
11 4
12 2
ድምር 27
መቶኛ 44.3

በሰንጠረዥ ሀያ ሶስት የቀረበው ጥያቄ "በተማሪዎች መካከል ያለው ማህበራዊ ግንኙነት በጣም ጥሩ ነው" ለዚህ ጥያቄ
27 ተማሪዎች (44.3%) 4 ን፣ 24 ተማሪዎች (39.3%) 3 ን፣ 8 ተማሪዎች (13.1%) 2 ን እንዲሁም 2 ተማሪዎች
(3.3%) 1 ን መርጠዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እርስ በእርስ ያላቸው ማህበራዊ ግንኙነት
በጣም ጥሩ መሆኑንና የተወሰኑ ተማሪዎች ደግሞ ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነት እንደሌላቸው ነው።

ሰንጠረዥ ሀያ አራት፡ ትምህርትን የሚያውኩ የተማሪዎች ተግባራት


ጥያቄ አማራጮች የመላሾች የክፍል የመላሾች ቁጥር
ደረጃ
በተማሪዎች በኩል የመማር ማስተማር ስርአቱን 1 9 4
የሚረብሹ አላስፈላጊ ተግባራት ሲፈጸሙ 10 6
ይስተዋላሉ። 11 2
12 2
ድምር 14
መቶኛ 22.95
2 9 0
10 10
11 4
12 5
ድምር 19
መቶኛ 31.1
3 9 2
10 10
11 2
12 1
ድምር 15
መቶኛ 24.6
4 9 2
10 6
11 2
12 3
ድምር 13
መቶኛ 21.3

በሰንጠረዥ ሀያ አራት የቀረበው ጥያቄ "በተማሪዎች በኩል የመማር ማስተማር ስርአቱን የሚረብሹአላስፈላጊ
ተግባራት ሲፈጸሙ ይስተዋላሉ" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ 13 ተማሪዎች (21.3%) 4 ን፣ 15 ተማሪዎች (24.6%)
3 ን፣ 19 ተማሪዎች (31.1%) 2 ን እንዲሁም 14 ተማሪዎች (22.95%) 1 ን መርጠዋል። ከዚህ መረጃ መገንዘብ
የሚቻለው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች መማር ማስተማሩን የሚያወኩ ተግባራትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ያመላከቱ
ሲሆን ተማሪዎች ደግሞ አዋኪ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ነው

3.1.2. ለክፍት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ትንተና

ከላይ የቀረበው ትንተና በዝግ ለቀረቡት ጥያቄዎች ተማሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ናቸው። ከዝግ ጥያቄዎች በተጨማሪ
የጽሑፍ መጠይቁ ክፍት ጥያቄዎችንም የያዘ ሲሆን የክፍት ጥያቄዎቹ ዓላማም በትምህርት ቤቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች
የሚታዩትን ችግሮች ያለምንም ገደብ እንዲያብራሩ ማድረግ ነው። በዚህም በዝግ ጥያቄዎቹ የተገኙትን መረጃዎች
ትክክለኛነት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችንም ማግኘት ተችሏል። በክፍት የቀረቡት ጥያቄዎች ሰባት
ሲሆኑ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያነሳሉ። ሶስቱ ርእሰ ጉዳዮችም የትምህርት ቤቱን ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንን እና
በትምህርት ቤቱ የሚሰጡ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን የሚመለከቱ ናቸው። ለክፍት ጥያቄዎቹ የተሰጡት ምላሾች ቀጥሎ
በሶስቱ ክፍሎች ተከፋፍለው በገላጭ ትንተና ተተንትነዋል።

3.1.2.1. ርእሳነ መምህራንን ለሚመለከቱ ክፍት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ትንተና


በጽሑፍ መጠይቁ ተራ ቁጥር 1 የቀረበው ጥያቄ የትምህርት ቤቱን ርእሳነ መምህራን የሚመለከት ሲሆን ጥያቄውም
"በትምህርት ቤቱ አስተዳደር (ርእሳነ መምህራን) ላይ የሚታዩት ችግሮች ምን ምን ናቸው? ችግሮቹን ለመቅረፍ ምን
አይነት መፍትሄ መሰጠት አለበት?" የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ ርእሳነ መምህራን ላይ ያስተዋሏቸውን
ችግሮችና የመፍትሔ ሀሳቦች ገልጸዋል። ከተጠየቁት 61 ተማሪዎች ውስጥ 12 ተማሪዎች (19.7%) በርእሳነ
መምህራኑ ላይ ምንም ችግር እንዳላዩ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ 49 ተማሪዎች (80.3%) በርእሳነ መምህራኑ ላይ ይታያሉ
ያሏቸውን ልዩ ልዩ ችግሮች ገልጸዋል። በተማሪዎቹ የተገለጹት አንኳር አንኳር የርእሳመ መምህራን ችግሮች በሁለት
መመደብ የሚቻል ሲሆን በሁለቱ ችግሮች ምክንያትም ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተነስተዋል። ሁለቱ አንኳር የርእሳነ
መምህራን ችግሮችም የሚከተሉት ናቸው።

1. በተለያዩ ውሳኔዎች ላይ ተማሪዎችን አለማሳተፍና ውሳኔዎቹ የተማሪዎቹን ፍላጎት ያላማከሉ መሆን

2. ስራዎችን ርእሰ መምህራን እርስ በእርሳቸው ተግባብተውና ተቀናጅተው አለመስራት

በአራቱም የክፍል ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች በብዛት የገለጹት ችግር ተማሪዎችን በውሳኔዎች ላይ አለማሳተፍና
ተማሪዎችን ያማከሉ ውሳኔዎችን አለመስጠት ነው። ተማሪዎቹ አበክረው እንደገለጹት ተማሪዎችን የሚመለከቱ ልዩ
ልዩ ውሳኔዎች ሲወሰኑ በተማሪዎች ዘንድ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከተማሪዎቹ አንደበት ከመረዳት ይልቅ የራሳቸውን
ግምት ወስደው ነው የሚወስኑት። ይህም ውሳኔዎቹ ከነባራዊ ሁኔታው ጋር ያልተዛመዱ ከማድረጉም በላይ በተማሪዎቹ
ላይ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተማሪዎቹ ጨምረው እንደገለጹት
ውሳኔዎቹን በማስመልከት ተማሪዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት አስተያየት እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ሆኖም ግን
አስተያየታቸውን በበጎ ተመልክተው ከማሻሻል ይልቅ በአስተያየቱ መበሳጨትና አስተያየት የሚሰጡ ተማሪዎችን
አመናጭቆ ማባረር ይቀናቸዋል።
የተወሰኑ ተማሪዎች እንደገለጹት አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ተማሪዎች ይሳተፋሉ። ሆኖም ግን የተማሪዎቹ ተሳትፎ ለስም
ብቻ ሲሆን የሚያነሷቸው ሀሳቦች ተቀባይነት እንደማያገኙ አያይዘው ገልጸዋል። ይህም ችግሮቹን ከመቅረፍ ይልቅ
እንዳባባሳቸው ተማሪዎቹ ይናገራሉ። አያይዘውም የተማሪዎቹ ሀሳብ ተቀባይነት የማያገኝ ከሆነ ወይም ተቀባይነት
ያላገኘበትን ምክንያት በአሳማኝ ምክንያት አስደግፈው ማስረዳት ካልቻሉ መሳተፋቸው ከጥቅሙ ጉዳቱ
እንደሚያመዝን ገልጸው ተሳትፏቸው እርባና ቢስ መሆኑን አሳስበዋል።

ከአሳታፊነት ጋር በተገናኘ ሌላም ችግር እንዳለ ተማሪዎቹ ገልጸዋል። ይህም ተማሪዎችን ባለማሳተፋቸው ምክንያት
ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሔ አለመስጠት ነው። እንደተማሪዎቹ ገለጻ ተማሪዎች ለጠቆሟቸው ችግሮች አፋጣኝ
መፍትሔ አይሰጥም። ሆኖም ግን ችግሩ እየተባባሰ ሲሄድ የችኮላ መፍትሔ የሚሰጥ ሲሆን በችኮላ የተሰጠው መፍትሔ
ግን ችግሩ ስር በመስደዱ ምክንያት ሊፈታ አይችልም። ይህም በተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሆነ
ተማሪዎቹ አሳስበዋል።

ሁለተኛው የርእሳነ መምህራኑ አንኳር ችግር እርስ በእርሳቸው ተግባብተውና ተቀናጅተው አለመስራት እንደሆነ
ተማሪዎቹ የገለጹ ሲሆን በዚህ ችግር መነሻነትም የተለያዩ ችግሮች እንደተፈጠሩ ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ በአጽንኦት
እንደገለጹት አንድን ጉዳይ በማስመልከት ርእሳነ መምህራን በተናጠል ሲጠየቁ የሚሰጧቸው ምላሾች አንድ አይነትና
እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው። በዚህም ምክንያት ለተማሪዎች የሚደርሱት መረጃዎች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ
እንደሆኑባቸው ተማሪዎቹ አሳስበዋል። ከዚህ ጋር በተገናኘ አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ ወቅታቸውን ጠብቀው ወደ
ተማሪዎች እንደማይመጡ ተማሪዎቹ አስረድተዋል። ይህም የጥናት ጊዜያቸውን ከማፋለሱም በተጨማሪ
በውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳሳደረባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

ርእሳነ መምህራኑ ተግባብተው ባለመስራታቸው ምክንያት ሌላም ችግር እንደተፈጠረባቸው ተማሪዎቹ አስረድተወል።
ተማሪዎች እንደሚያስረዱት ርእሳነ መምህራኑ ባለመግባባታቸው ምክንያት የሆነ ችግር ሲፈጠር ተማሪዎቹ
ስለችግሮቹ ይጠይቃሉ። ተማሪዎቹ በሚጠይቁበት ወቅት ግን አግባብ ያለው መልስ አያገኙም። ከዚህ ይልቅ አንድኛቸው
ሌላቸው ላይ በመጠቋቆም እራሳቸውን የችግሩ ምንጭ ላለማድረግ ይጥራሉ። ይህም ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ
ይበልጡኑ እያባባሳቸው እንደሆነ ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

ከላይ የቀረቡት ሁለት አንኳር አንኳር ችግሮች በአብዛኛዎቹ ተማሪዎች የተገለጹት ሲሆኑ በጥቂት ተማሪዎች የተገለጹ
ጥቂት ችግሮችም አሉ። እነዚህ ችግሮችም የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ ተማሪዎችን የሚያጨናንቅ መሆኑ፣ ብዙውን
ጊዜ ለተማሪዎች የሚነገራቸው ግዴታቸው እንጂ መብታቸው አለመሆኑ፣ ከአንዳንድ ተማሪዎች የሚሰሟቸውን
መረጃዎች ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ መናገር፣ የዘረኝነት ችግር (ተማሪዎችን በዘር ለይቶ ትኩረት መስጠትና ትኩረት
መንሳት)፣ ሁሉንም ተማሪዎች በእኩል አይን አለማየት ሲሆኑ ችግሮቹ ስር ሳይሰዱ በፍጥነት ቢፈቱ ጥሩ እንደሆነ
ተማሪዎቹ አሳስበዋል።
3.1.2.2. የትምህርት ቤቱ መምህራንን በተመለከተ ለቀረበው ክፍት ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ ትንተና
በሁለተኛ ደረጃ በክፍት የቀረበው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ መምህራን በብዛት የሚስተዋሉ ችግሮችንና
መፍትሔዎቻቼውን የሚጠይቅ ነው። ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ ችግር ያሏቸውን ሀሳቦች በግልጽ የሰጡ ሲሆን መፍትሔ
ይሆናሉ ያሏቸውንም ሀሳቦች ገልጸዋዉው። አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በመምህሮቻቸው ላይ የጎላ ችግር እንዳላስተዋሉ
የገለጹ ሲሆን የመምህራንን ችግሮች የዘረዘሩት ተማሪዎች ቁጥርም ጥቂት አይደለም። በመምህራኑ ላይ የተጠቆሙት
ችግሮች በርካታ ሲሆኑ ችግሮቹን በሁለት ክፍሎች መድቦ መመልከት ይቻላል። ሁለቱ ምድቦችም የሚከተሉት ናቸው።

1. በመምህራን ግላዊ ባህርይ ላይ ያየሚያተኩሩ ችግሮች


2. በመምህራን እውቀትና የማስተማሪያ ዘዴ ላይ የሚያተኩሩ ችግሮች

የመምህራንን ችግር በለጹት ተማሪዎች በተደጋጋሚ የተገለጹት ችግሮች የመምህራን ግላዊ ባህርይ ላይ ያተኮሩ ችግሮች
ናቸው። ይህም ሲባል አብዛኛዎቹ በተማሪዎቹ የተገለጹት የመምህራን ችግሮች መነሻቸው የመምህራኑ ግላዊ ባህርይ
ሲሆን ችግሮቹም በተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ተማሪዎቹ ገልጸዋል። የተማሪዎቹ ምላሽ
እንደሚያመለክተው በአንድ የክፍል ደረጃ የተለያዩ ምድቦች (sections) የሚያስተምሩ መምህራን የሚያደርጓቸው
ያልተገቡ ድርጊቶች በተደጋጋሚ የተገለጸው የመምህራን ችግር ነው። በመምህራኑ የሚደረገው ያልተገባ ድርጊትም
ፈተናዎች ከመሰጠታቸው በፊት በተወሰኑ ምድቦች የሚያስተምሩ መምህራን የፈተናውን መልሶች በልዩ ልዩ መንገዶች
ለተማሪዎች መንገር ነው። አንዳንዶቹ መምህራን ይህንን አድርገው ሌሎቹ ደግሞ አለማድረጋቸው በተማሪዎቹ መካከል
ጤናማ የውጤት ፉክክር እንዳይኖር ማድረጉን ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

ሌላው በተለያዩ ምድቦች በሚያስተምሩ መምህራን የሚፈጽሙ ያልተገባ ተግባር የውጤት አሞላላቸው የተለያየ መሆኑ
ነው። ተማሪዎቹ እንደገለጹት በተለያዩ ምድቦች የሚያስተምሩ መምህራን ለአንድ አይነት የፈተና ጥያቄዎች የተለያዩ
የውጤት አያያዞችን ይጠቀማሉ። ከዚህም በተጨማሪ አንድን የትምህርት ይዘት በተመለከተ መምህራኑ በሚገቡባቸው
ክፍሎች የሚሰጧቸው ማስታወሻዎችና ገለጻዎች የተለያዩ መሆናቸውን ተማሪዎቹ ያስረዳሉ። ከዚህም ሌላ መምህራን
እርስ በእርሳቸው ባለመግባባታቸው ምክንያት የተማሪዎችን ውጤት እንደሚቀናንሱ ተማሪዎቹ አሳውቀዋል። ይህንን
የመሳሰሉት ችግሮች በብዛት የተገለጹት በ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን የተወሰኑ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎችም የችግሩ
ሰለባዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። በአንጻሩ የ 11 ኛ እና የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ተመሳሳይ ችግር አልገለጹም።

ተማሪዎቹ የገለጿች ከመምህራኑ ግላዊ ባህርይ የሚመነጩት ችግሮች እነዚህ ብቻ አይደሉም፤ በተወሰኑ ተማሪዎች
የተገለጹ የተለያዩ ችግሮችም አሉ። እነዚህ ችግሮችም ለተለያዩ የግልና የቡድን ስራዎች ተመጣጣኝ ውጤት
አለመስጠት፣ ለተማሪዎች ሞራል አለመጨነቅ (የተለያዩ የተማሪዎችን ሞራል የሚጎዱ ንግግሮችን መናገርና
ድርጊቶችን ማድረግ)፣ ጥያቄዎችን ከጉግል አውርደው በቀጥታ ለተማሪዎች በወርክሽት ወይም በፈተና መልክ
መስጠት፣ ተማሪዎችን በዘር ለይቶ ማዳላት፣ ሲያስተምሩም ሆነ ጥያቄ ሲጠየቁ መሰላቸት፣ ለሚጠየቁት ትምህርታዊ
ጥያቄዎች ተገቢ መልሶችን አለመስጠት፣ ከተማሪዎች ጋር አለመቀራረብ ወይም አለመግባባት ናቸው። በእነዚህና
በመሳሰሉት ያልተገቡ የመምህራን ባህርያት ምክንያት ተማሪዎቹ ከፍተኛ ችግር እንደተፈጠረባቸው ተማሪዎቹ
ገልጸዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የተገለጸው የመምህራን ችግሮች ከመምህራን እውቀትና የማስተማሪያ ዘዴ ጋር የተያያዙ ናቸው። በዚህ
ምክንያት የተፈጠሩት ችግሮችም አንዳንድ መምህራን ስለሚያስሀምሩት ትምህርት በቂ እውቀት አለመኖር፣
የሚጠቀሙባቸው የማስተማሪያ ዘዴዎች ለተማሪዎች አመች አለመሆናቸው፣ የፈተና አወጣጣቸው የተማሪዎችን
ግንዛቤ መመዘን አለመቻል፣ የተማሪዎችን እውቀት በይዘቶች ጽንሰ ሀሳብ ሳይሆን በሽምደዳ መለካት፣ ፈተናዎችን
ተማሪዎችን ለመመዘን ሳይሆን ተማሪዎችን ለመጣል መጠቀም፣ ሀሉም ተማሪዎች እኩል እውቀት እንዳላቸው
አድርገው በማሰብ በአንድ አይነት መንገድ መግለጽ፣ በክፍል ውስጥ ስለሚያስተምሩት ትምህርት ቀድመው
አለመዘጋጀት፣ የግል፣ የቡድን እና የቤት ራዎችን ማብዛት፣ በፈተና ወቅት የጥናት ጊዜን የሚሻሙ የግልና የቡድን
ስራዎችን ማብዛት ናቸው።

በአጠቃላይ የሚያስተምሩ መምህራን ከላይ የተገለጹት ችግሮች እንደሚታይባቸው ተማሪዎቹ ገልጸው ችግሮቹ
በተማሪዎቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዳሳደሩባቸው አስገንዝበዋል። መምህራኑ ችግሮቹን በመቅረፍ
ለተማሪዎቻቸው ውጤታማነት መትጋት እንደሚገባቸው ተማሪዎቹ አሳስበዋል።

3.1.2.3. የትምህርት ቤቱን ልዩ ልዩ ክፍሎች ለተመለከቱ ክፍት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ትንተና
በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ ክፍሎችን የሚመለከቱት ክፍት ጥያቄዎች አምስት ሲሆኑ በዋናነት አራት ጉዳዮችን
የሚያነሱ ናቸው። አራቱ ጉዳዮችም የትምህርት ቤቱን ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ ክሊኒክ እና የመኝታና የመመገቢያ
ክፍሎች ናቸው። እነዚህንጉዳዮች በተመለከተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተማሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ቀጥሎ
ተተንትነዋል።

በዝግ ጥያቄው ተራ ቁጥር ሶስት የቀረበው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ የሚገኘው ቤተ መጻሕህፍት የሚታዩት ችግሮችና
መፍትሔዎቻቸውን እንዲገልጹ የሚጠይቅ ነው። ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ የሰጡት ምላሽ የሚያመለክተው በቤተ
መጻሕፍቱ በርካታ ችግሮች እንዳሉ ነው። ተማሪዎቹ የገለጿቸው ችግሮች ቀጥሎ ያሉትን ይመስላሉ።

በቤተ መጻሕፍት ላይ እንደሚስተዋሉ በተማሪዎቹ ከተገለጹት ችግሮች መካከል በብዛት የተገለጹት የቤተ መጻሕፍት
ባለሙያ አለመኖር፣ በቂ መጻሕፍት አለመኖር እና የጸጥታ አለመኖር ናቸው። ብዙዎቹ ተማሪዎች እንደገለጹት
የትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ዋና ዋና ችግሮች ከላይ የተገለጹት ሶስት ችግሮች ሲሆኑ እነዚህ ችግሮች ቤተ
መጻሕፍቱን ለማንበብ የማይመች አድርገውታል።

ከነዚህ ችግሮች በተጨማሪ አንዳንድ መጻሕፍት በተማሪዎች እጅ ላይ መገኘታቸውና ለተማሪዎች ልቅ ነጻነት መሰጠቱ
በርካታ መጻሕፍት እንዲጎሳቆሉ እንዳደረጓቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል። እንዲሁም አንዳንድ መጻሕፍት ላይ ማህተም
አለመመታት፣ ቤተ መጻሕፍቱ ሁሌም (ከጧት እስከ ማታ) ክፍት አለመሆን፣ በተራ እንዲያስተናግዱ የተመደቡት
ተማሪዎች በተግባር አለመሰራትና ለሁሉም ተማሪዎች እኩል አገልግሎት አለመስጠት (ለጓደኞቻቼው ማዳላት)፣
የመጻሕፍቱ በአይነት በአይነታቸው አለመደርደር ከቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ችግሮች
እንደሆኑ ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

በ 3 ኛው የጽሑፍ መጠይቅ ክፍት ጥያቄ የቀረበው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ ቤተ መከራዎች የሚታዩትን ችግሮችና
መፍትሔዎቻቼውን የሚጠይቅ ነው። ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ በርካታ ችግሮችን በማንሳት መልስ የሰጡ ሲሆን
ተማሪዎቹ የሰጧቸው ምላሾች የሚከተሉት ናቸው።

በበርካታ ተማሪዎች የተገለጹት የቤተ ሙከራ ችግሮች በቂ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች አለመኖር፣ ያሉት ውስን ቁሳ ቁሶችና
ኬሚካሎችም ቢሆኑ አብዛኛዎቹ የተበላሹና ጊዜ ያለፈባቸው መሆናቸው እና የቤተ ሙከራዎቹ ንጽሕና አለመኖር
የሚሉት ናቸው። እነዚህ ችግሮች በሁሉም የክፍል ደረጃ ባሉ በርካታ ተማሪዎች የተነሱ ሲሆን ችግሮቹ በጉልህ
እንደሚስተዋሉ በተማሪዎቹ ተገልጿል።

ከእነዚህ ችግሮች በተጨማሪ በቤተ ሙከራዎቹ ያለው የወንበር አቀማመጥ ምቹ አለመሆን፣ ለቤተ ሙከራ የሚሰጠው
ጊዜ ማነስ፣ የቤተ ሙከራዎቹ አጠቃላይ ለመማር ተማሪዎችን የሚጋብዝ አለመሆን፣ ሳቢና ማራኪ አለመሆን፣ የቤተ
ሙከራ ትምህርቱ በውስን የትምህርት አይነቶች የተገደበ መሆን በተወሰኑ ተማሪዎች የተገለጹ የትምህርት ቤቱ ቤተ
ሙከራዎች ችግሮች ናቸው።

ሌላው በዝግ ጥያቄ የተጠየቀው የአገለግሎት መስጫ የትምህርት ቤቱነ ክሊኒክ የሚመለከት ነው። ይህ ጥያቄ በክፍት
መጠይቁ ጥያቄ ቁጥር 4 የቀረበ ሲሆን በክሊኒኩ የሚታዩ ችግሮችንና መፍትሔዎቻቼውን እንዲገልጹ የሚጠይቅ ነው።
ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የተማሪዎቹ ምላሾች በሁለት ምድቦች መመደብ ይቻላል። ሁለቱ
ምድቦችም የሚከተሉት ናቸው።

1. ከህክምና ባለሙያዎቹ የሙያ ብቃትና ስነ ምግባር ማነስ የሚመነጩ ችግሮች

2. ከክሊኒኩ ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች አለመሟላት የሚመነጩ ችግሮች

ከሁለቱ የችግሮች ምንጮች ውስጥ በብዙዎቹ ተማሪዎች የተገለጹት ከህክምና ባለሙያዎች የሙያ ብቃትና ስነ ምግባር
ማነስ የሚመነጩት ናቸው። አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እንደገለጹት አብዛኛዎቹ የህክምና ባለሙያዎች የሙያ ብቃትና
የስነ ምግባር ማነስ ችግር አለባቸው። ከህክምና ሙያ ብቃት ማነስ ጋር በተያያዘ ባለሙያዎቹ ከፍተኛ የሙያ ብቃትና
ልምድ ማነስ ይታይባቸዋል። ከባለሙያዎቹ የሙያ ብቃት ጉድለት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ በቂና ተገቢ ምርመራ
አለማድረግ፣ ማንኛውም ታካሚ ሲሄድ አንድ አይነት መድኃኒት መስጠት (የህመም ማስታገሻ ብቻ መስጠት)፣ መርፌ
በወጉ አለመውጋት፣ ታመው ወደ ክሊኒኩ ለሚሄዱ ተማሪዎች ተገቢውን ምርመራ ከማድረግ ይልቅ ሁሉንም
ተማሪዎች የትምህርት ጭንቀት (tension) እንደሆነ በመግለጽ ለህመማቸው መፍትሔ አለመስጠት፣ በሙያው በቂ
ልምድ አለመኖር እና ጥንቃቄ የጎደለው ህክምና መስጠት የሚሉት ናቸው።
የህክምና ባለሙያዎቹ ካለባቸው የሙያ ብቃት ማነስ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የስነ ምግባር ጉድለት እንደሚታይባቸው
ተማሪዎቹ ተናግረዋል። ተማሪዎቹ እንደገለጹት በተለይ ወንድ የህክምና ባለሙያዎች ከህክምናው ጋር ተያያዥ
ያልሆኑና ተገቢ ያለሆኑ ተግባራትን በታካሚዎቹ ተማሪዎች ላይ ይፈጽማሉ። ከዚህም በተጨማሪ አብዛኛዎቹ ሀኪሞች
ለታካሚዎቻቼው ተገቢውን ክብርና እንክብካቤ አይሰጡም። ብዙውን ጊዜ ከማክበር ይልቅ ማመናጨቅና መሰላቸው
እንደሚቀናቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል። ህክምና ሲሰጡ ተገቢዎቹን የመመርመሪያ መሳሪያዎቸ ካለመጠቀማቸው ጋር
ተያይዞ እነዚህን ያልተገቡ ተግባራተ ሀኪመቹ በመፈጸማቸው ህክምናውን ጥራት የሌለውና ታካሚዎችን መፈወስ
የማይችል እንዳደረገው ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

ሁለተኛው የትምህርት ቤቱ የችግሮች መነሻ የቁሳቁሶች አለመሟላት ነው። ተማሪዎቹ እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ
ክሊኒክ በቂ የህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች የሉም። ይህም ህክምናውን በተገቢዎቹ የመመርመሪያ መሳሪያዎች
ያልታገዘና ጥራት የሌለው እንዲሆን አድርጎታል። በዚህም ምክንያት ታካሚዎቹ ተገቢውን ህክምና እና ፈዋሽ
መድኃኒቶችን እንዳያገኙ ማድረጉን ተማሪዎቹ ገልጸዋል። በክሊኒኩ የሚገኙት ውስን መሳሪያዎችና መድኃኒቶችም
ቢሆኑ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆናቸውን ተማሪዎቹ ጨምረው ገልጸዋለ።

በጽሑፍ መጠይቁ ክፍት ጥያቄ የመጨረሻ ክፍል የተነሱት አገልግሎት መስጫ ክፍሎች የመመገቢያ ክፍልንና የመኝታ
ክፍልን የተመለከቱ ናቸው። እነዚህ ጉዳዮች የተነሱት በክፍት ጥያቄው ተራ ቁጥር 6 እና 7 ነው። ለእነዚህ ሁለት
ጥያቄዎችም ተማሪዎች ተገቢ ምላሾችን የሰጡ ሲሆን በተማሪዎቹ የተሰጡት ምላሾች ቀጥሎ ተራ በተራ ይተነተናሉ።

በጥያቄ ቁጥር 6 የቀረበው ጥያቄ በሁለቱ አገልግሎት የማግኛ ክፍሎች የሚስተዋሉትን ችግሮች እንዲገልጹ
ተጠይቀዋል። ለጥያቄው ተማሪዎቹ የተለያዩ ችግሮችን በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል። በተማሪዎቹ የተገለጹት
በመመገቢያና በመኝታ ክፍሎች የሚታዩት ችግሮች ቀጥሎ ለየብቻ ይተነተናሉ።

በርካታ ችግሮች የተገለጹበት የመጀመሪያው አገልግሎት የማግኛ ክፍል የመመገቢያ ክፍል ነው። በዚህ ክፍል ተማሪዎቹ
ያስተዋሏቸው ችግሮች ከምግብ ጥራትና አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው። ከምግብ ጥራት ጋር በተገናኘ በርካታ ችግሮች
እንዳሉ በርካታ ተማሪዎች ገልጸዋል። በብዛት የተገለጹት ችግሮችም የምግቡ ንጽሕና መጓደል፣ ንጽሕና የሌለውና
የማይጥም ምግብ ማቅረብ፣ ምግቡ ላይ እንደ ጸጉርና ትላትል የመሳሰሉ ባእድ ነገሮችን ማግኘት፣ በቁርስ ሰአት
የሚቀርበው ምግብ ምቹ አለመሆንና የመመገቢያ ሰአቱ ተማሪዎችን ያላማከለ መሆን የሚሉት ናቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ ከምግብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ በርካታ ችግሮች በመመገቢያ ክፍሉ እንደሚስተዋሉ ተማሪዎቹ
በዝርዝር ገልጸዋል። ተማሪዎቹ የገለጿቸው የምግብ አቅርቦት ችግሮች ብዙውን ጊዜ አንድ አይነት ምግብ በተደጋጋሚ
ማቅረብና የመመገቢያ አዳራሹ ጠባብ መሆን ናቸው። በተማሪዎቹ በኩልም የተመገቡባቸውን እቃዎች በአግባቡ
የመመለስ ችግር እንዳለ ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

በሁለተኛው በጥያቄ ቁጥር 6 የተጠየቀው አገልግሎች መስጫ የመኝታ ክፍል አገልግሎት ነው። በዚህ ክፍል የተለያዩ
ችግሮች እንዳሉ ተማሪዎቹ ገልጸዋል። የተነሱት ችግሮችም እንደ ፍራሽ፣ ትራስና ብርድልብስ የመሳሰሉት የመኝታ ቤት
ቁሳቁሶች ጥራት አለመኖር፣ ቁሳቁሶቹ ሲበላሹ በፍጥነትና በጥራት አለመጠገን፣ በአንዳንድ መኝታ ክፍሎች ዝናብና
ብርድ መግባት፣ እንደ አይጥና እንሽላሊት የመሳሰሉ ባእድ እንስሳት በየመኝታ ቤቱ መኖር፣ በአንዳንድ መኝታ ክፍሎች
ያሉ ተማሪዎች አለመግባባት፣ የጸጥታ አለመኖር፣ የመኝታ ክፍል ሰራተኞች በሌሊት ተማሪዎችን መቀስቀስ፣ አንዳንድ
ተማሪዎች በተራቸው መኝታ ክፍሎችን አለማጽዳት፣ የመጸዳጃ ቤቶች ንጽሕና መጓደል የሚሉት ናቸው። እነዚህ
ችግሮች በሙሉ የተገለጹት በ 9 ኛ፣ 10 ኛ እና 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች በመመገቢያም
ሆነ በመኝታ ክፍሎች ችግር እንደሌለ ገልጸዋል።

የመጨረሻው የጽሑፍ መጠይቁ ዝግ ጥያቄ በተራ ቁጥር 7 የቀረበው ሲሆን የተማሪዎቹ የመኝታ ቤት ድልድል
የተማሪዎቹን የክፍል ደረጃ ያማከለ አለመሆኑና መሰባጠሩ የፈጠረውን ችግርና አደላደሉ እንዴት ቢሆን ለተማሪዎቹ
እንደሚመች የሚጠይቅ ነው። ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ የየራሳቸውን ምላሽ የሰጡ ሲሆን የተማሪዎቹ ምላሽ ቀጥሎ
ተተንትኗል።

አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የመኝታ ቤቱ ድልድል በተማሪዎች የክፍል ደረጃ መሰባጠሩ እንደተመቻቸውና ምንም ችግር
እንዳልፈጠረባቸው የገለጹ ሲሆን ሁለት የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች ብቻ አደላደሉ ለተማሪዎች የሚመች እንዳልሆነ
ገልጸዋል። ሁለቱ የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደገለጹት የተማሪዎች የክፍል ደረጃ የተሰባጠረ መሆኑ እየተጠያየቁ
ለማጥናት እንቅፋት እንደሆነባቸው ገልጸዋል። በተጨማሪም ከሁለቱ ተማሪዎች አንዷ በክፍል ደረጃ መሰባጠሩ ጥሩ
ቢሆንም ከሁሉም የክፍል ደረጃ በአንድ የመኝታ ክፍል ውስጥ ቢያንስ ሁለት ተማሪዎች አለመመደባቸው ሀሳቦችን
ለማንሸራሸር እንዳላስቻላት ገልጻለች።

ከሁለቱ ተማሪዎች ውጭ ያሉት 59 ተማሪዎች በሙሉ የተሰባጠረ የመኝታ ቤት ምደባ በመኖሩ ደስተኞች መሆናቸውን
ገልጸዋል። ጥሩ ያስባሏቸውን የየራሳቸውን ምክንያቶችም ገልጸዋል። ተማሪዎቹ እንደገለጹት በተለያዩ የክፍል
ደረጃዎች መሰባጠራቸው ከተለያዩ ተማሪዎች ጋር ለመግባባት፣ በላይኛው የክፍል ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች
በታችኛው የክፍል ደረጃ ከሚገኙት ያለፈውን ትምህርት ለመከለስ፣ የታችኛዎቹ ደግሞ ከላይኛዎቹ ለወደፊቱ
ትምህርት ቀድመው እንዲዘጋጁ፣ በተለያዩ መምህራን ከሚማሩ ተማሪዎች የተለያዩ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ለማግኘት፣
ሀሳቦችን በተማሪዎች መካከል ለማንሸራሸር፣ ያለአንዳች አሉታዊ ፉክክር ለመረዳዳት፣ ጠቃሚ የሀሳብ ልውውጦችን
ለማድረግ ጠቅመዋቸዋል። ወደፊትም የመኝታ ቤት ድልድሉ በተመሳሳይ መንገድ ቢሆን እንደሚመርጡ ተማሪዎች
አሳስበዋል።

3.2. የጥናቱ ውጤት ማብራሪያ


በዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያ ክፍል ከጽሑፍ መጠይቅ የተገኙት መረጃዎች ተተንትነዋል፡፡ ትንተናው የተከናወነው የጽሑፍ
መጠይቁን ምላሽ ዝግ ጥያቄዎችንና ክፍት ጥያቄዎችን ለየብቻ በማደራጀት ሲሆን በመጀመሪያው ክፍል ለዝግ
ጥያቄዎች የተሰጡት ምላሾች፣ እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል ለክፍት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ተተንትነዋል፡፡ በዚህ
ክፍል ደግሞ የመረጃ ትንተናው የሚያመለክተው ውጤት ተብራርቶ ይቀርባል፡፡
የመጀመሪያው በጽሑፍ መጠይቁ የተካተተው ርእሰ ጉዳይ መምህራንን የሚመለከት ነው፡፡ መምህራንን በተመለከተ
በጽሑፍ መጠይቁ ሶስት ዝግ እና ሁለት ክፍት ጥያቄዎች በድምሩ አራት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች
ተማሪዎቹ የሰጡት ምላሽ የሚያመለክተው ውጤት ቀጥሎ ይብራራል፡፡

ለሶስቱ ዝግ ጥያቄዎች ተማሪዎቹ የሰጧቸው ምላሾች ትንተና እንደሚያመለክተው መምህራን በሚያስተምሯቸው


የትምህርት አይነቶች ያላቸውን እውቀት በተመለከተ የጎላ ችግር አይታይም፤ ይህንን በተመለከተ ከተጠየቁት 61
ተማሪዎች ውስጥ 6 (9.8%) ተማሪዎች ብቻ መምህራኑ ችግር እንዳለባቸው ሲገልጹ ቀሪዎቹ 55 (90.2%)
ተማሪዎች ደግሞ በመምህራኑ ላይ የእውቀት ችግር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው በመምህራን የእውቀት
ማነስ ረገድ ብዙዎቹ ተማሪዎች ችግር እንዳላጋጠማቸው ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ መምህራኑን በተመለከተ የቀረበው ጥያቄ የመምህራንን የማስተማሪያ ስነ ዘዴ የተመለከተ ሲሆን በዚህ
ረገድ 17 ተማሪዎች (27.7%) መምህራኑ ላይ ችግር እንደሚታይ ሲገልጹ ቀሪዎቹ 44 ተማሪዎች (72.3%)
የመምህራኑ የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ላይ ችግር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት አብዛኛዎቹ መምህራን
የሚጠቀሙት የማስተማሪያ ዘዴ በአብዛኛዎቹ ተማሪዎች ላይ ችግር እንዳልፈጠረባቸው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን
የማስተማር ስነ ዘዴ ችግር የሚታይባቸው መምህራን ቁጥር ጥቂት አይደለም፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ የተወሰኑ
ተማሪዎች ችግር እንዳጋጠማቸው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የመጨረሻው መምህራንን በተመለከተ የቀረበው ዝግ ጥያቄ መምህራኑ ከተማሪዎቹ ጋር ያላቸውን ቅርበት የሚመለከት
ነው፡፡ይህንን ጉዳይ በተመለከተ 6 ተማሪዎች (9.8%) ብቻ መምህራን ከተማሪዎች ጋር ያላቸው ቅርበት ጥሩ እንዳልሆነ
ሲገልጹ ቀሪዎቹ 55 (90.2%) ተማሪዎች ግን መምህራኑ ከተማሪዎቻቸው ጋር ጥሩ ቅርበት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በዚህ መረጃ መሰረት አብዛኛዎቹ መምህራን ከአብዛኛዎቹ ተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው መቀራረብ በጣም ጥሩ እንደሆነ
ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ መምህራንን የተመለከተ አንድ ክፍት ጥያቄ በጽሑፍ መጠይቁ ተካትቷል፡፡ በክፍቱ ጥያቄ የቀረበው
መምህራንን የሚመለከተው ጥያቄ በመምህራን ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውን እንዲገልጹ የሚጠይቅ
ነው፡፡ ለዚህ ዠጥያቄ ተማሪዎች ልዩ ልዩ ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡ በመምህራኑ ላይ የተነሱት ችግሮችም ከመምህራኑ ግላዊ
ባህርይ የመነጩ እና ከትምህርት እውቀትና አቀራረብ ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ የገለጿቸው በመምህራን ላይ
የሚስተዋሉ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 በአንድ የክፍል ደረጃ የተለያዩ ምድቦች (sections) የሚያስተምሩ መምህራን የሚያደርጓቸው ያልተገቡ
ድርጊቶች በተደጋጋሚ የተገለጸው የመምህራን ችግር ነው፤

 ፈተናዎች ከመሰጠታቸው በፊት በተወሰኑ ምድቦች የሚያስተምሩ መምህራን የፈተናውን መልሶች በልዩ ልዩ
መንገዶች ለተማሪዎች መንገር፤
 በተለያዩ ምድቦች የሚያስተምሩ መምህራን ለአንድ አይነት የፈተና ጥያቄዎች የተለያዩ የውጤት አያያዞችን
መጠቀም፤

 አንድን የትምህርት ይዘት በተመለከተ መምህራኑ በሚገቡባቸው ክፍሎች የሚሰጧቸው ማስታወሻዎችና


ገለጻዎች የተለያዩ መሆን፤

 መምህራን እርስ በእርሳቸው ባለመግባባታቸው ምክንያት የተማሪዎችን ውጤት መሸራረፍ፤

ይህንን የመሳሰሉት ችግሮች በብዛት የተገለጹት በ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን የተወሰኑ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎችም
የችግሩ ሰለባዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። በአንጻሩ የ 11 ኛ እና የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ተመሳሳይ ችግር አልገለጹም።
እነዚህ ችግሮች በበርካታ ተማሪዎች የተገለጹ ሲሆኑ ከእነዚህ ችግሮች በተጨማሪ በተወሰኑ ተማሪዎች የተገለጹ
የተለያዩ ችግሮችም አሉ። በተወሰኑ ተማሪዎች የተገለጹት የመምህራን ችግሮችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

 ለተለያዩ የግልና የቡድን ስራዎች ተመጣጣኝ ውጤት አለመስጠት፤

 ለተማሪዎች ሞራል አለመጨነቅ (የተለያዩ የተማሪዎችን ሞራል የሚጎዱ ንግግሮችን መናገርና


ድርጊቶችን ማድረግ)፤

 ጥያቄዎችን ከጉግል አውርደው በቀጥታ ለተማሪዎች በወርክሽት ወይም በፈተና መልክ መስጠት፤

 ተማሪዎችን በዘር እየለዩ ማዳላት፤

 ሲያስተምሩም ሆነ ጥያቄ ሲጠየቁ መሰላቸት፤

 ለሚጠየቁት ትምህርታዊ ጥያቄዎች ተገቢ መልሶችን አለመስጠት፤

 አንዳንድ መምህራን ስለሚያስሀምሩት ትምህርት በቂ እውቀት አለመኖር፤

 የሚጠቀሙባቸው የማስተማሪያ ዘዴዎች ለተማሪዎች አመች አለመሆናቸው፤

 የፈተና አወጣጣቸው የተማሪዎችን ግንዛቤ መመዘን አለመቻል፤

 የተማሪዎችን እውቀት በይዘቶች ጽንሰ ሀሳብ ሳይሆን በሽምደዳ መለካት፤

 ፈተናዎችን ተማሪዎችን ለመመዘን ሳይሆን ለመጣል መጠቀም፤


 ሁሉም ተማሪዎች እኩል እውቀት እንዳላቸው አድርገው በማሰብ በአንድ አይነት መንገድ መግለጽ ወይም
ማስረዳት፤

 በክፍል ውስጥ ስለሚያስተምሩት ትምህርት ቀድመው አለመዘጋጀት፤

 የግል፣ የቡድን እና የቤት ራዎችን ማብዛት፤

 በፈተና ወቅት የጥናት ጊዜን የሚሻሙ የግልና የቡድን ስራዎችን ማብዛት፤

 ከተማሪዎች ጋር አለመቀራረብ ወይም አለመግባባት ናቸው።

በእነዚህና በመሳሰሉት ያልተገቡ የመምህራን ባህርያት ምክንያት ተማሪዎቹ ከፍተኛ ችግር እንደተፈጠረባቸው
ተማሪዎቹ ገልጸዋል። ለእነዚህ ችግሮችም ተማሪዎቹ የመፍትሄ ሀሳብ የጠቆሙ ሲሆን በተማሪዎቹ ጥቆማ መሰረትም
መምህራን ያልተገቡ ተግባራቸውን በመተው መምህራዊ ስነ ምግባር ተላብሰው እንዲያስተምሩ አስተያየታቸውን
ሰጥተዋል፡፡

በመቀጠልም በጽሑፍ መጠይቁ የተዳሰሰው ጉዳይ ርዕሳነ መምህራንን የሚመለከት ነው፡፡ በጽሑፍ መጠይቁ ክፍት ጥያቄ
ርዕሳነ መምህራኑ ላይ የሚታዩት ችግሮች ምን ምን እንደሆኑና መፍትሔውስ ምን እንደሆነ ተጠይቀዋል፡፡ ርእሳነ
መምህራንን ለሚመለከቱ ክፍት ጥያቄዎች በተጠየቁት ተማሪዎች የተሰጡት ምላሾች የሚያመለክቱት ውጤት ቀጥሎ
ይብራራል፡፡

በጥናቱ ከተጠየቁት ተማሪዎች ውስጥ 19.7 መቶኛ የሚሆኑት ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን ላይ ምን
አይነት ችግር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ቀሪዎቹ 80.3 መቶኛ የሚሆኑት ተማሪዎች ርዕሳነ መምህራኑ ላይ
የተለያዩ ችግሮች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ እንደተማሪዎቹ ገለጻ ርዕሳነ መምህራኑ ላይ የሚስተዋሉት ችግሮች በተማሪዎቹ
ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ፈጥረዋል፡፡ ተማሪዎቹ የገለጿቸው በርዕሳነ መምህራኑ ላይ የሚስተዋሉት ችግሮች የሚከተሉት
ናቸው፡፡

 የተለያዩ ውሳኔዎች ላይ ተማሪዎችን አለማሳተፍና ቢያሳትፉም እንኳን ውሳኔዎቹ የተማሪዎችን ፍላጎትና


ነባራዊ ሁኔታዎች አለማማከል፤

 ውሳኔዎችን ከነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ሳይሆን እነሱ ይሆናል ብለው በገመቱት ላይ በመመስረት መወሰን፤

 ተማሪዎች የሚሰጧቸውን ልዩ ልዩ አስተያየቶች በበጎ መልክ በመውሰድ ነገሮችን ከማሻሻል ይልቅ አስተያየት
በሚሰጡ ተማሪዎች ላይ በመበሳጨት ማመናጨቅ፤

 በየጊዜው ለሚከሰቱ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሔ አለመስጠትና ችግሮቹ ስር ከሰደዱ በኋላ በጥድፊያ ችግሩን
ለመፍታት ቢሞከርም ችግሮቹ ግን አይፈቱም፤
 የርዕሳነ መምህራኑ እርስ በእርስ ተግባብተውና ተቀናጅተው አለመስራት፤

 ተግባብተው ባለመስራታቸው ምክንያት አንድን ጉዳይ በማስመልከት ተማሪዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች


የተጣረሱ መረጃዎችን መስጠት፤

 አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ ወቅታቸውን ጠብቀው ወደ ተማሪዎች አለማውረድ፤

 በትምህርት ቤቱ ለሚስተዋሉ ችግሮች አንድኛቸው ሌላኛቸውን በጥፋተኛነት መውቀስ፤

 የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ ተማሪዎችን የሚያጨናንቅ መሆኑ፤

 ብዙውን ጊዜ ለተማሪዎች የሚነገራቸው ግዴታቸው እንጂ መብታቸው አለመሆን፣

 ከአንዳንድ ተማሪዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን መቀበል፤ የሚሰሟቸውን መረጃዎች ትክክለኛነት ሳያረጋግጡም


መናገር፤

 ተማሪዎችን በዘር ለይቶ ትኩረት መስጠትና ትኩረት መንሳት፤

 ሁሉንም ተማሪዎች በእኩል አይን አለማየትና ለሚቀርቧቸው ተማሪዎች ብቻ ትኩረት መስጠት፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች ከ 80 መቶኛ በላይ በሆኑት ተጠያቂ ተማሪዎች የተገለጹ ሲሆኑ እነዚህ በርዕሳነ
መምህራኑ የሚታዩት ችግሮች በተማሪዎቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ተማሪዎቹ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ ችግሮቹ
ላይ ርዕሳነ መምህራኑ ተወያይተው መፍትሔ መስጠት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

በጽሑፍ መጠይቁ የተነሳው ሌላው ጉዳይ የትምህርት ቤቱን አጠቃላይ አስተዳደርና አሰራር የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ
ርእሰ ጉዳይ ስር የተለያዩ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በአራት ንዑሳን ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ስር
የተገኙት መረጃዎች ውጤት ቀጥሎ ይብራራል፡፡

የመጀመሪያው ንዑስ ርዕሰ ጉዳይ የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብን የተመለከተ ነው፡፡ ይህንን ርእሰ ጉዳይ የሚያነሱ
አምስት ዝግ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች ተማሪዎቹ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የተማሪዎቹ ምላሽ ትንተና
የሚያመለክተው ውጤት ቀጥሎ ይብራራል፡፡

የመጀመሪያው የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ እንዲሁም አሰራር የሚመለከተው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ የሚዘጋጁትን
የትምህርት፣ የፈተናና የእረፍት የጊዜ ሰሌዳዎችን የሚመለከት ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎች የሰጡት ምላሽ
እንደሚያመለክተው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የትምህርት ቤቱ ልዩ ልዩ የጊዜ ሰሌዳዎች ችግር እንደሚፈጥሩባቸው ነው፡፡
ከግማሽ በላይ የሆኑት ተማሪዎች የትምህርት ቤቱ የተለያዩ የጊዜ ሰሌዳዎች ከፍላጎታቸው ጋር የተጣጣሙ እንዳልሆኑ
ገልጸዋል፡፡
ሁለተኛው የትምህርት ቤቱን የአሰራር ስርዓት የሚመለከተው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ ያለው አጠቃላይ የአስተዳደር
ስርዓት ከመማር ማስተማር ሂደት፣ ከተማሪዎች ፍላጎት፣ ከመምህራን ፍላጎት እና ከወላጆች ፍላጎት ጋር
ስለመጣጣም የተመለከት ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎች የሰጡት ምላሽ አብዛኛው ተማሪዎች ደስተኛ እንደሆኑ የሚያመለክት
ቢሆንም የተወሰኑ የጥናቱ ተሳታፊዎች ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ፍላጎት አንጻር መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ
ያሳያል፡፡

ሦስተኛው ተማሪዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በመምህራንና በአስተዳደር በኩል የሚሰጡት ምላሾች ተገቢና ከነባራዊ
ሁኔታዎች ጋር የተገናዘቡ ስለመሆናቸው የተመለከተ ነው፡፡ በዚህም ግማሽ የሚሆኑት ተሳታፊዎች ለጥያቄው አዎንታዊ
ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ግማሽ ተማሪዎች ደግሞ መሻሻል የሚገባው እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡

አራተኛው ጥያቄ የ 2013 ዓ.ም ዋና ትምህርት ከመሰጠቱ በፊት በ 2012 ዓ.ም የነበረው ወረርሽኝ የተቋረጠውን
ትምህርት መከለስን የሚመለከት ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ የሰጡት ምላሽ እንደሚያመለክተው አብዛኛዎቹ
ተማሪዎች የተሰጠው ክለሳ ተመችቷችዋል፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑ ተማሪዎች የተሰጠው ክለሳ በቂ እንዳልነበር የሰጡት
መልስ ያሳያል፡፡

አምስተኛው ጥያቄ በትምህርት ቤቱ የሚወሰዱት የዲሲፒሊን እርምጃዎች በቂ፣ ተመጣጣኝና አስተማሪ


ስለመሆናቸው የሚመለከት ሲሆን፤ በዚህም አብዛኛው ተሳታፊዎች በትምህርት ቤቱ የሚወሰዱ የዲሲፕሊን እርምጃዎች
አግባብነት ያላቸው ስለመሆናቸው የጠቆሙ ሲሆን ጥቂት ተሳታፊዎች ደግሞ አግባብነት እንደሌለው አመላክተዋል፡፡

የትምህርት ቤቱን ነባራዊ ሁኔታዎች ለተመለከቱ 3 ዝግ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ስንመለከት የመጀመሪያው የግቢው
አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ማለትም የተማሪዎች የአጠናን ስርዓትና የመምህራን ማስተማር ስነዘዴ በተማሪዎች
ውጤታማነት ላይ ያላቸው በጎ ተጽእኖ እንዳለ የሚጠይቅ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎች የሰጡም ምላሽ
እንደሚያለክተው የትምህርት ቤቱ ነባራዊ ሁኔታ በተማሪዎች ውጤት ላይ አወንታዊ ተጽዕኖ እንዳለው 75 ከመቶ
የጥናቱ ተሳታፊዎች አመላክተዋል፡፡

ሁለተኛው የዚህ ርእሰ ጉዳይ ጥያቄ በትምህርት ቤቱ ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጓቸው ችግሮች መኖር
አለመኖራቸውን የሚጠይቅ ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ የሰጡት ምላሽ እንደሚያመለክተው 86 ከመቶ
የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች አሉታዊ ተጽእኖ ያሳደሩባቸው ጉዳዮች በትምህርት ቤቱ ገጥሟቸዋል፡፡ በአንጻሩ
ደግሞ 14 ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ እንዳላደረባቸው የተማሪዎቹ ምላሽ ያመለክታል፡፡

የመጨረሻው የዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጥያቄ የመዝናኛ ቦታዎችን የተመለከተ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎቹ የሰጧቸው
ምላሾች ትንተና እንደሚያመለክተው 82 ከመቶ የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ በቂና
የተማሪዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ የመዝናኛ ቦታዎች አይገኙም፡፡ ይህም በአንድም ሆነ በሌላ የተማሪዎቹ ውጤት
ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው፡፡
በመቀጠል የተነሳው ንዑስ ርዕሰ ጉዳይ የትምህርት ቤቱን የመኝታና የመመገቢያ ቤት ስርአት የሚመለከት ነው፡፡ ይህንን
ጉዳይ በተመለከተ በጽሑፍ መጠይቁ አምስት ዝግ እና አንድ ክፍት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ለጥያቄዎቹ ተማሪዎች
የሰጡት ምላሽ ቀደም ባለው ንዑስ ርዕስ ስር ተተንትኗል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ የትንተናው ውጤት ይብራራል፡፡

የመጀመሪያው ዝግ ጥያቄ የመኝታና ቤትና የምግብ ቤት ስርዓት ከወቅታዊ ሁኔታ ማለትም ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ
መከላከያ ፕሮቶኮል አተገባበር ጋር የተጣጣመ መሆን አለመሆኑን የሚጠይቅ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ተማሪዎች የሰጡት
ምላሽ እንደሚያመለክተው ስርዓቱ ከሞላ ጎደል ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡ ይህም ማለት አብዛኛዎቹ ተማሪዎች
(83.6%) የመኝታና የምግብ ቤት ስርዓቱ ከወቅቱ ሁኔታ አንጻር ተግባራዊ እየተደረገ እንዳለ ገልጸዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ
የተወሰኑ ተማሪዎች አተገባበሩ ተገቢና በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

ሁለተኛው ጉዳይ የመኝታ ቤት ፀጥታ ለጥናት መመቸቱን የተመለከተው ሃሳብ ሲሆን ብዙ ተማሪዎች (57.4 መቶኛ)
ለጥናት በሚመች መልኩ ፀጥታ እንዳለው ያመላከቱ ቢሆንም ቀሪዎቹ ተማሪዎች (42.6 መቶኛ) ችግር እንዳለ
አመላክተዋል፡፡ ይህም ማለት ከግማሽ በጥቂት የሚያንሱት ተማሪዎች የመኝታ ክፍል ጸጥታው ምቹ አለመሆኑን የገለጹ
ሲሆን ይህ ጉዳይ ይቀረፍ ዘንድ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ከዝግ ጥያቄው በተጨማሪ በመኝታ ክፍሎች የሚታዩ ችግሮችን እንዲገልጹ በክፍት ጥያቄ ተጠይቀዋል፡፡ ለዚህ ጥያቄ
ተማሪዎች የተለያዩ ችግሮችን የገለጹ ሲሆን በተሳታፊዎቹ ተማሪዎች የተገለጹት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የፍራሽ፣ ትራስ፣ ብርድ ልብስና የመሳሰሉት የመኝታ መገልገያ ቁሳቁሶች ጥራት አለመኖር፤

 የተበላሹ ቁሳቁሶች በአግባቡ አለመጠገን፤

 በአንዳንድ መኝታ ክፍሎች ዝናብና ብርድ መግባት፤

 በአንዳንድ መኝታ ክፍሎች እንደ እንሽላሊትና አይጥ የመሳሰሉ ባእድ እንስሳት መኖር፤

 በአንድ መኝታ ክፍል ውስጥ አንዳንድ ተማሪዎች አለመግባባት፤

 የመኝታ ክፍሎች ጸጥታ አለመኖር፤

 የመኝታ ክፍል ተቆጣጣሪዎች (ፕሮክተሮች) ተማሪዎችን በጧት መቀስቀስ፤

 አንዳንድ ተማሪዎች በተራቸው መሰረት የመኝታ ክፍልን አለማጽዳት፤

ከላይ የቀረቡት የመኝታ ክፍል ችግሮች የተገለጹት በ 9 ኛ፣ በ 10 ና እና በ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን የ 11 ኛ ክፍል
ተማሪዎች በመኝታ ክፍል ውስጥ ምንም ችግር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የመኝታ ክፍሎቹ ድልድል ላይ ተማሪዎች ያላቸውን አስተያየት እንዲገልጹ በክፍት ጥያቄ
ተጠይቀው ነበር፡፡ የመኝታ ክፍል ድልድሉ ከየክፍል ደረጃው የተሰባጠረ እንደሆነ ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ድልድሉ
የተሰባጠረ መሆኑ በተማሪዎቹ ላይ ችግር መፍጠር አለመፍጠሩን ተማሪዎች ተጠይቀዋል፡፡ ለዚህ ጥያቄም ከሁለት
የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች በስተቀር ሌሎቹ ችግር እንዳልፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንደገለጹት የመኝታ ቤት
ድልድሉ የተሰባጠረ በመሆኑ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ተማሪዎቹ የገለጿቸው ጠቀሜታዎችም የሚከተሉት
ናቸው፡፡

 ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው እንዲግባቡ ጠቅሟቸዋል፤

 በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚማሩ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው እንዲረዳዱ አድርጓቸዋል፤

 በተለያዩ መምህራን ከሚማሩ መምህራን ከሚማሩ ተማሪዎች ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ለመጋራት እድል
ፈጥሮላቸዋል፤

 ሀሳቦቻቸውን እርስ በእርስ ለማንሸራሸርና አሉታዊ ፉክክር እንዳይኖር እረድቷቸዋል፡፡

በአንጻሩ ደግሞ ሁለት የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች በመኝታ ክፍል ድልድሉ አልተመቻቸውም፡፡ ለዚህም የሰጡት ምክንያት
በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች መደልደላቸው እርስ በእርሳቸው እንዳይጠያየቁ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
በእያንዳንዱ የመኝታ ክፍል በተመሳሳይ የክፍል ደረጃ ያላቸው ቢያንስ ሁለት ተማሪዎች ቢኖሩ ጥሩ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ሦስተኛው ጥያቄ ደግሞ በመኝታ ቤትና መፀዳጃ ቤት ውስጥ ስላለው የንጽሕና ጉዳይ የሚያነሳ ሲሆን አብዛኛዎቹ
ተማሪዎች (78.7 መቶኛ) ንጽሕናው የተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቀሪዎቹ ተማሪዎች (21.3 መቶኛ) ደግሞ መኝታ
ክፎሎቹና መጸዳጃ ቤቶቹ ንጽሕና እንደሚጎድላቸው ገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው ከተጠየቁት ተማሪዎች ውስጥ
ወደ 25 መቶኛ የሚጠጉት የጽዳት ችግር እንዳለ መግለጻቸውን ሲሆን ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተማሪዎቹ
አሳስበዋል፡፡

አራተኛው ጥያቄ ደግሞ በመኝታ ቤት ያሉ ቁሳቁሶች ለመኝታ ያላቸውን ምቹነት በተመለከተ የሚጠይቅ ነው፡፡ ለዚህ
ጥያቄ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች (67.2 መቶኛ) አዎንታዊ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የተቀሩት ተማሪዎች (32.8 መቶኛ)
ደግሞ አሉታዊ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ውጤት የሚያመለክተው ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ ተማሪዎች የመኝታ ቤቶቹ
ቁሳቁሶች ምቹ እንደሆኑ ቢገልጹም ምቹ ያልሆነላቸው ተማሪዎች ቁጥር ጥቂት እንዳልሆነ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ
የተማሪዎቹ ምቾት እንደተጓለ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

አምስተኛው ጥያቄ ደግሞ ለተማሪዎች የሚቀርበው ምግብ ጥራቱና አቅርቦቱ የተሟላ ስለመሆኑ የሚጠይቅ ሲሆን
አብዛኛዎቹ ተማሪዎች (86.8 መቶኛ) ምግቡ ጥራት ያለውና አቅርቦቱም በቂ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ
ቀሪዎቹ ውስን ተማሪዎች (13.2 መቶኛ) የምግቡ አቅርቦትም ሆነ ጥራት የተሟላ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
ከዝግ ጥያቄዎች በተጨማሪ የትምህርት ቤቱን መመገቢያ ክፍል ችግሮች እንዲገልጹ በክፍት ጥያቄ ተጤቀዋል፡፡ ለክፍት
ጥያቄው ተማሪዎች መልስ የሰጡ ሲሆን የትምህርት ቤቱ የምግብ ስርዓት የተወሰኑ ችግሮች እንደሚታዩበት ገልጸዋል፡፡
በተማሪዎቹ የተገለጹት የዚህ ክፍል ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የምግቡ ንጽሕና መጓደልና እንደ ጸጉር የመሳሰሉ ባዕድ ነገሮች በምግቡ ላይ መገኘት፤

 የምግብ አለመጣፈጥ፤

 በቁርስ ሰአት የሚቀርቡት ምግቦች ለመመገብ ምቹ አለመሆን፤

 የቁርስ መመገቢያ ሰዓት ተማሪዎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ያማከለ አለመሆን፤

 ብዙውን ጊዜ አንድ አይነት ምግብ ማቅረብና ማሰልቸት

 የመመገቢያ አዳራሹ ከተማሪዎች ቁጥር አንጻር ጠባብ መሆንና ለመስተናገድ ምቹ አለመሆን

 በተማሪዎች በኩል የተመገቡባቸውን እቃዎች በአግባቡ አለመመለስ፡፡

በአጠቃላይ ምንም እንኳን የብዙዎቹ ተማሪዎች ምላሽ የትምህርት ቤቱ የምገባ ስርዓት መልካም እንደሆነ
ቢያመለክትም ከአቅርቦትና ጥራት አንጻር የተወሰነ ችግር ይታይበታል፡፡

ቀጣዩ ጥያቄ የትምህርት ቤቱን ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ ክሊኒክ እና ክበባት የሚመለከት ነው፡፡ ለዚህ ርእሰ ጉዳይ
በዝግ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች እንደሚያመለክተው በትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ከ 65 በመቶ በላይ
የሆኑ መላሾች በአገልግሎቱ መርካታቸውን ያመላከተ ሲሆን ቀሪዎቹ 35 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች በቤተ መጻሕፍት
አገልግሎቱ አልረኩም፡፡ ይህም የሚያመለክተው በትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ያልረኩት ተማሪዎች ቁጥር ጥቂት
አለመሆኑን ነው፡፡

ከዝግ ጥያቄው በተጨማሪ በቤተ መጻሕፍት ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች እንዲገልጹ በክፍት ጥያቄ ተጠይቀዋል፡፡ ለዚህ
ጥያቄ ተማሪዎች የየራሳቸውን ምላሾች የሰጡ ሲሆን ችግሮቹ ይቀረፉ ዘንድም መፍትሄ ያሏቸውን ሀሳቦች ሰጥተዋል፡፡
በተማሪዎቹ የተገለጹት የቤተ መጻሕፍት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የቤተ መጻሕፍት ባለሙያ አለመኖር፤

 በቂ አጋዥ መጻሕፍት አለመኖር፤

 ለማንበብ የሚያመች ጸጥታ አለመኖር፤


 ለተማሪዎች ልቅ ነጻነት መስጠት፤

 የመጻሕፍት በስነ ስርዓት አለመያዝና መጎሳቆል፤

 አንዳንድ መጻሕፍት ላይ የትምህርት ቤቱ ማሕተም አለመኖር፤ ይህን ተከትሎም መጻሕፍቱ ለመጥፋት


መዳረግ፤

 ቤተ መጻሕፍቱ ከጧት እስከ ማታ ክፍት አለመሆን፤

 የሚያስጠቅሙ ተማሪዎች ሁሉንም ተጠቃሚዎች እኩል አለማስተናገድ፤ ወይም ለሚቀራረቧቸው


ተማሪዎች ማዳላት፤

 በጻሕፍቱ በአይነት በአይነታቸው አለመደርደር (በካታሎግ የተደረደሩ አለመሆን)

ከላይ የቀረቡት በትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍት የሚሰተዋሉ ችግሮች እንደሆኑ ተማሪዎች የገለጹ ሲሆን በእነዚህ
ችግሮች ምክንያት ጥናታቸው እንቅፋት እንደገጠመውና መፍተሔ ቢሰጠው መልካም እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከቤተ መጻሕፍት አገልግሎቱ በመቀጠል የተጠየቀው ጥያቄ የትምህርት ቤቱን ክሊኒክ ይመለከታል፡፡ የህክምና አገልግሎት
አሰጣጥን በተመለከተ በዝግና በክፍት ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ ለጥያቄዎቹ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ለዝግ
ጥያቄው የተሰጠው ምላሽ እንደሚያመለክተው ከተጠየቁት ተማሪዎች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በህክምና
አገልግሎቱ መርካታቸውን ሲገልጹ ቀሪዎቹ 51 በመቶ የሚሆኑት አለመርካታቸውን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ክሊኒክ ያለበትን ችግር በተመለከተ ከዝግ ጥያቄው በተጨማሪ በክፍት ጥያቄ ተጠይቀዋል፡፡ ለዚህ ጥያቄ
ተማሪዎች የተለያዩ ችግሮችን በመግለጽ መልስ የሰጡ ሲሆን በክሊኒኩ የሚስተዋሉት ችግሮች ከህክምና ባለሙያዎቹ
የሙያ ብቃትና ስነ ምግባር ማነስ እና ከቁሳሱሶች እጥረት የሚመነጩ ናቸው፡፡ በተማሪዎቹ የተገለጹት የክሊኒኩ
ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የጤና ባለሙያዎቹ የህክምና ልምድና ብቃት ማነስ፤

 ለታካሚዎች ተገቢ ምርመራዎችን አለመስጠት፤

 ህመምተኞችን በሚገባ ከመመርመር ይልቅ ለሁሉም ታካሚዎች የህመም ማስታገሻዎችን ብቻ መስጠት፤

 መርፌ በአግባቡ አለመውጋት፤

 ሁሉንም ታካሚዎች በደንብ ሳይመረምሩ የትምህርት መጨናነቅ (tension) እንደሆነ በመደምደም ለመምከር
መሞከር፤
 ጥንቃቄ የጎደለው ህክምና መስጠት፤

 ወንድ የጤና ባለሙያዎች በታካሚዎች ላይ ከህክምና ጋር የማይዛመዱና ከሙያ ስነ ምግባር ውጭ የሆኑ ነውር
ተግባራትን መፈጸም፤

 ለታካሚዎች ተገቢ ክብርና እንክብካቤ አለመስጠት፤

 ታካሚዎችን በሚገባ ከማከም ይልቅ መሰላቸትና ታካሚዎችን ማመናጨቅ፤

 ተገቢዎቹን የህክምና መስጫ መሳሪያዎች ተጠቅሞ አለማከም፤

 የህክምና መስጫ ቁሳቁሶችና መድሀኒቶች እጥረት መኖር፤

 ያሉት ውስን ቁሳቁሶችና መድሀኒቶች የተበላሹና ጊዜ ያለፈባቸው መሆን፡፡

በአጠቃላይ በትምህርት ቤቱ የህክምና መስጫ ክፍል አገልግሎት አሰጣጥ በርካታ ተማሪዎች ደስተኞች አይደሉም፡፡
ከዚህም በመነሳት የትምህርት ቤቱ የህክምና አሰጣት ከፍተኛ የሆነ ችግር እንዳለበት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ቀጣዩ ጥያቄ የትምህርት ቤቱን ቤተ ሙከራ አሰጣጥ የተመለከተ ነው፡፡ ቤተ ሙከራን በተመለከተ አንድ ዝግ እና አንድ
ክፍት ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎቹ ለጥያቄዎቹ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ለዝግ ጥያቄው ተማሪዎቹ የሰጡት ምላሽ
እንደሚያመለክተው 64 በመቶ የሚሆኑት ተሳታፊዎች በአገልግሎቱ ረክተዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ቀሪዎቹ 36 መቶኛ
የሚሆኑት በአገልግሎቱ አልረኩም፡፡ ከዚህም በመነሳት ምንም እንኳን በአገልግሎቱ የረኩት ተማሪዎች ቁጥር ካልረኩት
ተማሪዎች ቁጥር የሚበልጥ ቢሆንም በአገልግሎቱ ደስተኛ ያልሆኑት ተማሪዎች ቁጥር ጥቂት አለመሆኑን መገንዘብ
ይቻላል፡፡

ከዝግ ጥያቄው በተጨማሪ ተማሪዎቹ ለክፍት ጥያቄው መልስ ሰጥተዋል፡፡ የተማሪዎቹ ምላሽ እንደሚያመለክተው
የትምህርት ቤቱ ቤተ ሙከራ በርካታ ችግሮች አሉበት፡፡ ተማሪዎቹ የገለጿቸው ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ሰ

 በቂ የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች አለመኖር፤

 አብዛኛዎቹ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች ጊዜ ያለፈባቸው መሆን፤

 የቤተ ሙከራ ክፍሎቹ ንጽሕና አለመኖር፤

 የወንበሮቹ ለአቀማመጥ ምቹ አለመሆን፤

 ለቤተ ሙከራ ትምህርቱ የተሰጠው ጊዜ በቂ አለመሆን


 የቤተ ሙከራ ክፍሎቹ ለመማር ማስተማር ሒደቱ ምቹና ሳቢ አለመሆን፤

 የቤተ ሙከራ ትምህርት የሚሰጠው በውስን የትምህርት አይነቶች ብቻ መሆን (ሁሉንም የተፈጥሮ ሳይንስ
ትምህርቶች በቤተ ሙከራ የታገዘ ትምህርት አለመስጠት)፡፡

በአጠቃላይ በትምህርት ቤቱ የሚሰጠው የቤተ ሙከራ አገልግሎት የተለያዩ ችግሮች እንዳሉበትና እነዚህ ችግሮች
መቀረፍ እንዳለባቸው በጥናቱ የተሳተፉ ተማሪዎች አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ቤቱን እንቅስቃሴ በተመለከተ ከተጠየቁት ተማሪዎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት አዎንታዊ ምላሽ የሰጡ
ሲሆን ቀሪዎቹ 20 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ደግሞ አሉታዊ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት በትምህርት ቤቱ
ያለው የክበብ እንቅስቃሴ በአመዛኙ መልካም ቢሆንም የተወሰነ ክፍተት እንዳለበት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የተማሪዎችን አጠቃላይ ስርአትና ስነ ልቦና ለሚመለከቱ ዝግ ጥያቄዎች ተማሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ሲጠቀለሉ
የሚከተለውን ይዘው ይገኛሉ፡፡ 60 ከመቶ የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎቸ እዚህ መማራቸው የስነልቦና ጫና
እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል፣ በአንጻሩ ደግሞ ቀሪዎቹ 40 በመቶ የሚሆኑት ተሳታፊዎች ምንም አይነት የስነ ልቦና ጫና
እንደሌለባቸው ገልጸዋል፡፡ ይህም ማለት ብዙዎቹ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ በመማራቸው የስነ ልቦና ጫና
አሳድሮባቸዋል ማለት ነው፡፡ሰ

በሌላ በኩል ደግሞ 67 ከመቶ የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ በመማራቸው የስነ ልቦና እርካታ
እንዳገኙ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ 33 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ደግሞ አለመርካታቸውን ገጸዋል፡፡ ይህም
የሚያመለክተው አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ በመማራቸው ደስተኞች መሆናቸውን ነው፡፡ ሆኖም ግን
በትምህርት ቤቱ ደስተኞች ያልሆኑት ተማሪዎች ቁጥር ጥቂት አይደለም፡፡

ሶስተኛው ተማሪዎችን የሚመለከተው ጥያቄ ተማሪዎች ያላቸውን መስተጋብር የሚመለከተው ጥያቄ ነው፡፡
ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ያላቸውን ማህበራዊ ግንኙነት በተመለከተ 83.6 ከመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች
በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች መካከል ጥሩ ማህበራዊ መስተጋብር እንዳለ ገልጸዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ 16.7 በመቶ
የሚሆኑት ተማሪዎች ጥሩ ማህበራዊ መስተጋብር እንደሌለ ያምናሉ፡፡

በመጨረሻም ተማሪዎችን የሚረብሹ ጉዳዮች በትምህርት ቤቱ መኖር አለመኖሩን የተጠየቁት ተማሪዎች እንደገለጹት
54 ከመቶ የሚሆኑትን ተማሪዎች የሚረብሹ ጉዳዮች ሲኖሩ ቀሪዎቹ 46 በመቶ ለሚሆኑት ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ
ያሉት ሁኔታዎች የመማር ማስተማር ስርዓቱን አይረብሹም፡፡ ከዚህም በመነሳት በትምህርት ቤቱ ባሉ ጉዳዮች
የሚረበሹት ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

You might also like