You are on page 1of 2

The Gibson School Systems

P.O. Box 15564 Addis Ababa, Ethiopia info@gyaschool.com Phone Numbers: 0116 61 01 50/011628312

ሇጊብሰን ትምህርት ቤቶች ሥርዓት 12ኛ ክፍሌ ተማሪዎች ወሊጆች/አሳዳጊዎች

በቅድሚያ ሰሊምታችንን እናቀርባሇን፡-

መግቢያ

ዋናዉ ጉዳይ የ12ኛ ክፍሌ ተማሪዎቻችን ሊይ የሚታዩ ከመስመር የወጡ ተግባራትና የብሔራዊ ፈተና ውጤት

ማስመዝገብ ሊይ ያተኩራሌ፡፡ ጊዜ ወስደዉ እንዲያነቡ አበክረን እናስገነዝባሇን፡፡

የጊብሰን ትምህርት ቤቶች ሥርዓት የ12ኛ ክፍሌ ተማሪዎችን ሇብሔራዊ ፈተና እያዘጋጀ መሆኑ ይታወቃሌ፡፡ የዚህ የ2015

የትምህርት ዓመት የ12ኛ ክፍሌ ብሔራዊ ፈተና ደግሞ እጅግ ውድድር የበዛበት፣ የማሇፊያ ጣሪያዉ ከፍተኛ የሚሆንበት፣

ካሇፉት ዓመታት ሲታይ በርካታ ተማሪዎች ሇፈተናው የሚቀርቡበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዉድድር በአሸናፊነት መወጣት
የሚቻሇዉ ደግሞ ትምህርት ቤትና ወሊጆች በቅርበት ሆነው ሇተማሪዎች ውጤት በአንድነት ሲሰሩ እንደሆነ በግሌፅ
ይታወቃሌ፡፡

በዚህ መሰረት ተማሪዎቻችን ሇብሔራዊ ፈተና የሚያደርጉትን ዝግጅት ሇማደናቀፍ እየተደረጉ ያለትን የሚያዘናጉ
መንገዶችን በመዝጋትና ወደ ትምህርታቸዉ ብቻ እንዲያተኩሩ ሇማድረግ የወሊጅና የትምህርት ቤት ግዴታ ስሇሆነ
ተማሪዎችን ከመጥፎ ጎዳና አሊቆ ወደ ትክክሇኛ የትምህርት መስመር ማስገባት ከሁለም የትምህርት ቤት ባሇድርሻ አካሊት
ይጠበቃሌ፡፡ በአሁን ሰዓት እየሆነ ያሇው እንደሚከተሇዉ ቀርቧሌ፡፡

1ኛ) ትምህርት ቤቱ እንደደረሰበት በአንዳንድ ተማሪዎች ቅስቀሳ የ12ኛ ክፍሌ ተማሪዎች ሇፓርቲ መደገሻ በሚሌ
ገንዘብ የማሰባሰብ ሙከራ መኖሩን ሇማስተዋሌ ችሇናሌ፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎችን በጣም የሚያዘናጋ፣ የተማሪዎችን
የትምህርት ፍሊጎትና ሥነ-ሌቦና የሚሰርቅ፣ሇማይታሰብ ክፉ መንፈስ የሚያጋሌጥ፣ የወደፊቱን ተስፋ የሚያጨሌም
አካሄድና ትምህርት ቤቱና ወሊጆች የሇፉበትን፣ የተጓዙበትን፣ መስዋዕትነት የከፈለበትን በአጠቃሊይ ድካማቸውን
የሚያመክን ነው፡፡ ወሊጆች ሇዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተዉ በአስቸኳይ ይህንን ድርጊት ሇማስቆም ሌጆቻቸውን በመገሰፅ
ከትምህርት ቤቱ ጋር መተባበር አሇባቸው፡፡ ይህንን ጉዳይ በሚያስተባብሩ እና ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎች ሊይ
ት/ቤቱ ያሇምንም ቅድመ ሁኔታ ከት/ቤት የሚያሰናብት ይሆናሌ፡፡

2ኛ) በአሁኑ ጊዜ በውጭ ሀገር ዕድሌ ያገኙ የ12ኛ ክፍሌ ተማሪዎች በላልች ተማሪዎች ሊይ መጥፎ ተፅዕኖ
እየፈጠሩ ያለ መሆናቸው ደግሞ ላልች ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተለና እንዲዘናጉ
ማድረጋቸው ላሊው ያሌተሇመደ ተግባር ነዉ፡፡ ዕድሌ ማግኘታቸውና የራሳቸውን መስመር ማዘጋጀታቸው ግን
መሌካም ሆኖ ሳሇ ሇብሔራዊ ፈተና ራሳቸውን እያዘጋጁ ባለ ተማሪዎች ሊይ ችግር መፍጠራቸው እኩይ ተግባር
ነው፡፡ ይህንንም በሁሇቱም በኩሌ ያለትን ችግሮች በጋራ መፍትሄ መፈሇግና ወደ ትክክሇኛ መስመር ማስገባት
ከወሊጆችና ከትምህርት ቤት ይጠበቃሌ፡፡

3ኛ) የተማሪዎች ዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ከምንግዜውም በሊይ እየጨመረ ባሇበት ወቅት ከትምህርት ጋር
ባሌተያያዙ ላልች አሊስፈሊጊ ሁነቶች ውስጥ መሳተፍ ጎጂነቱ ሇማንም የተሰወረ አይደሇም፡፡ በጊብሰን የመሌካም
ባሕርይ ዋጋ አሇው መርሐ ግብር ውስጥ ሇዓመታት ሊሳሇፉ ተማሪዎች ይህንን ማጤን የሚከብድ አይደሇም፡፡ ስሇዚህ
ሇተስሇፋበት የትምህርት ዓሊማ ቅድሚያ በመስጠት መሊ ትኩረታቸውን በትምህርታቸው ሊይ እንዲያደርጉ ወሊጆችንም
ተማሪዎችንም አጠንክረን እናሳስባሇን፡፡ ዓሇም የውድድር መድረክ ናት፡፡ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣው ግን ጠንክሮ የሠራ
ብቻ ነው፡፡

4ኛ) ትምህርት ቤቱ የ12ኛ ክፍሌ ተማሪዎች ውጤታማ ሇማድረግ በተሇያዩ መንገዶች የትምህርት የስራ ሀይልችን
በማስተባበር እየሰራ ይገኛሌ፡፡ ይህ ፍሬያማ መሆኑ የሚረጋገጠው ደግሞ የጊብሰን ተማሪዎች የውጤት ባሇቤት
ሲሆኑና በድሌ ወደ ዩንቨርስቲ ሲገቡ ነዉ፡፡ በዚህ መሰረት ወሊጆችና ትምህርት ቤት በጋራ ሆነዉ የደከሙበት
የዓመታት ሌፋት ዋጋ እንዳያጣ የትምህርት ቤትም ሆነ የወሊጆች የዘወትር ክትትሌ መተኪያ የላሇዉ የዕሇት ዕሇት
ተግባር መሆኑ ሇአፍታ ሉዘነጋ አይገባም፡፡ ትምህርት ቤቱ በትምህርት ቤት ቁጥጥሩን ያጠናክራሌ፡፡ ወሊጆች ደግሞ
ከትምህርት ቤት ዉጪ የሌጆቻቸዉን ውል በቅርበት መከታተሌ ይጠበቅባቸዋሌ፡፡ ተማሪዎች ተሰባስበዉ በራሳቸዉም
ይሁን የትምህርት ቤቱን ስም ተጠቅመዉ ምንም ዓይነት ፕሮግራም እንዲያዘጋጁ አሌተፈቀደሊቸዉም፡፡ ትምህርት
ቤቱ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁለ ተማሪዎችን የሚያሳትፉ የተሇያዩ ትምህርታዊ እና አነቃቂ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት
ተማሪዎችን ሇመፅሄት የሚሆን የፎቶ ግብአት ማግኘት ይችሊለ፡፡ እንደተሳትፏቸዉም ሰርተፍኬት አዘጋጅተን
እንሰጣሇን፡፡

5ኛ) የተማሪዎች ስነምግባር አንዲሁም በትምህርት ገበታ ሊይ መገኘት (attendance) በተማሪዎች ትራነስክሪፕት ሊይ
የሚሰፍር በመሆኑ ተማሪዎች ሳይዘናጉ እስከመጨረሻዉ የትምህርት ቀናት ድረስ ትምህርታቸዉን በንቃት
በመከታተሌ ረገድ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ስንሌ አበክረን እንመክራሇን፡፡

ተማሪዎች በትምህርታቸዉ ስኬታማ የሚሆኑት በስነምግባር ታንፀዉ ሲያድጉ ብቻ መሆኑን የጊብሰን ትምህርት
ቤቶች ሥርዓት ያምናሌ፡፡ ሇዚህም ትምህርት ቤቱ ክትትሌና ድጋፍ ያደርጋሌ፡፡ ይሁን እንጂ ተማሪዎች
ትምህርታቸዉን በአግባቡ እንዲከታተለ በማያደርጉ እና በተሇያዩ ኢ-ስነምግባራዊ እንቅስቃሴዎች ሊይ በሚሳተፉ
ተማሪዎች ት/ቤቱ ጥብቅ የሆኑ የማስተካከያ እርምጃዎች ሇመዉሰድ የሚገደድ መሆኑን ደግመን ሇማሳሰብ
እንወዳሇን፡፡

በመጨረሻም በዝርዝር የተጠቀሱትን ነጥቦች ትኩረት ሰጥቶ በማጤን ተማሪዎቻችን በተስተካከሇ ጎዳና ሊይ ተሰማርተው
የነገ የሀገር ባሇዉሇታ እንዲሆኑና የወሊጆቻቸውን ድካም እጥፍ ድርብ አድርገው የሚከፍለ እንዲሆኑ በጋራ እንድንሰራ
ትምህርት ቤቱ በአጽንኦት ይጠይቃሌ፡፡ እንደገናም በዚህም መሌዕክት ይዘት የተጠቀሱትን ነገ ሊይ ጠባሳ ሉሆኑ የሚችለ
እኩይ ተግባራትን አሁኑኑ በማምከን ተማሪዎችን ወደ ጤናማ መንገድ ሇማስገባት መስራት ይጠበቃሌ፡፡ ሇዚህም የወሊጆች
ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱም ክትትለን አጠንክሮ ይገፋበታሌ፡፡

እናመሰግናሇን!

የጊብሰን ትምህርት ቤቶች ሥርዓት፡፡

You might also like