You are on page 1of 19

የአልሙኒየም ፕሮፋይል አይነቶች

እና አክሰሰሪዎች

አዘጋጅ ሚካኤል ጋሻው


 የአልሙኒየም አይነቶች በ 2 እንከፍላቸዋለን
 1 አኖዳይዝ ( መብራት ሲበራበት የሚያንጸባርቅ)
 2 ማት (ፈዛዛ)

የአልሙኔየም ፕሮፋይሎችን በተለያዩ ቀለም ልናገኝ እንችላለን


1 ሲልቨር 5 ኮፊ ከለር
2 ብሮንዝ 6 አረንጓዴ
 ሻምፓኝ 7 ሰማያዊ
 ዳርክ ብሮንዝ 8 ነጭ
 ጎልደን 9 አይቮሪ (ክሬም ከለር)
3 ውድን ከለር (እንጨት ከለር) 10 ግራጫ
4 ጥቁር
 የአልሙኒየም የስራ አይነቶች በ 5 ይከፈላሉ
1 የአልሙኒየም L T Z ስራ
2 የአልሙኒየም ተንሸራታች ስራ
3 ከርቴን ዎል
4 ክላዲንግ
5 ሃንድ ሬል
 1.የአልሙኒየም L T Z ስራ
የአልሙኒየም L T Z ስራ የምንለው በሌላ ስሙ ሂንጅድ ይባላል ምክንያቱም የማይንቀሳቀስ ስለሆነ ነው። የአልሙኒየም L T Z ስራ
የምንጠቀመው ለበር ለመስኮት ለሽንት ቤት መስኮት ለፓርቲሽን ስራዎች ነው።
ይሂን ስራ ለመስራት የሚያስፈልጉን የፕሮፋይል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው።
1. L ፕሮፋይል፦ ይህ ፕሮፋይል ግድግዳ ላይ በመሰፋት እንደ መቃን ያገለግለናል
የ L ፕሮፋይል ስፋት 50mm ነው
 2. T ፕሮፋይል፦ ይህ ፕሮፋይል በ 4 ይከፈላል
 1. T እስሞል፦ እንደ አካፋይ የምንጠቀምበት የፕሮፋይል አይነት ነው ስፋቱም 66mm ነው
 አንዳንዴ ወደውጭ ተከፋች በር ልንሰራበት እንችላለን።

2. T ኮምፐንሴሽን፦ ይህ ፕሮፋይል ባለሁለት ተከፋች በር በምንሰራበት ጊዜ ከቋሚው በር ጋ በመገጠም በሁለቱ በሮች መካከል
የሚፈጠረውን 6mm ክፍተት የሚሞላልን ነው። የፕሮፋይል ስፋቱም 60mm ነው።
3. T እስትራክቸር፦ vertically ረጅም ስራ በምንሰራበት ጊዜ ቋሜ ብቻ ሁኖ የሚገጠም በሁለቱም በኩል መስታወት የሚቀበል
ፕሮፋይል ነው።
4. T ኢንቨርተር፦ ወደውጭ ተከፋች በር ለመስራት ስንፈልግ ከ L ላይ በመግጠም የምንሰራበት ፕሮፋይል ነው።
 3. Z ፕሮፋይል፦ የዚህ ፕሮፋይል ጥቅም L,T,Z ስራ ላይ ተከፋቹን ፓርት ለመስራት ብቻ ነው የፕሮፋይል ስፋቱም 44mm
ነው።

 Big Z፦ ቢግ Z የምንለው በሳይዙ ከኖርማሉ Z የሚበልጥ ሲሆን ፋሻ እና ዘኮሎ አይገጠምበትም ቁልፉ እና እጀታው ሚሰራው ራሱ
Z ላይ ነው
 4. ፋሻ (Mid Rail)፦ በር በምንሰራበት ጊዜ የበራችን 1.10m ላይ የሚገጠም የበራችን አካፋይ ነው ስፋቱም 155mm ነው።

 5. ዘኮሎ (kik plate)፦ ለበር እና ለፓርቲሽን ስራ ከታች የሚገጠም የፕሮፋይል አይነት ነው። የዘኮሎ ስፋት 155mm ሲሆን ከፋሻ
የሚለየው በአንድ በኩል ብቻ መስታወት የሚቀበል በመሆኑ ነው።
 6. ሆሪዞንታል ፌርማ horizontal Glass Bed ferma or 90 degree Ferma)፦ የፌርማ ዋነኛው ጥቅም ለመስታወት
ማፈኛነት ነው።
 ሆሪዞንታል ፌርማ የሚገጠመው አግድም ላይ ነው። የሚገጠመውም መጀመሪያ ላይ ነው።

 7. ቨርቲካል ፈርማ (Vertical Glass Bed Ferma Or Oval Ferma)፦ ኦቫል ፌርማ ሆሪዞንታል ፌርማችንን ከገጠምን
በሁአላ በቁም የምንገጥመው የፈርማ አይነት ነው።
 ለአልሙኒየም L T Z ስራ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ( Acssesories)
 1. አንግል ኮኔክተር (Angle connector)፦ ሁለት በ 45 ዲግሪ የትቆረጡ ፕሮፋይሎችን ለማገናኘት የምንጠቀምበት ማቴሪያል
ነው።

 2. T ኮኔክተር ( T Connector)፦ T ፕሮፋይላቺንን ከሌላ ፕሮፋይል ጋር ለማሰር እንጠቀምበታለን።


 3. ክሮስ T ኮኔክተር ( Cross T Connector)፦ T ፕሮፋይል ከ T ፕሮፋይል ጋር ለማሰር ይጠቅማል።

 4. ማጠፊያ (Hinge)፦ የበር ወይም የመስኮት ማጠፊያ


 5. አርም (Arm)፦ ለሽንት ቤት መስኮት እንዳይወድቅ ደግፎ የሚይዝልን

 6. የሽንት ቤት መስኮት ቁልፍ (Plastic Kerketo)


 7. Z ጋስኬት( Z Gasket)፦ Z ፕሮፋይላችን ላይ በመገጠም በራችን እንዳይጮህ የሚያደርግልን
 8. የበር እጀታ (Door Handle)
 9. የበር ቁልፍ (Door Lock)፦

 10. የመስኮት እጀታ( Window Handle)


 11. ብሎን (Screw)
 12. መስታወት ማፈኛ (4 or 5mm Gasket)
 13. RHS 45*45 (Rectangular Hollow Section)
2. ለአልሙኒየም ተንሸራታች ስራ የሚያስፈልጉ የፕሮፋይል አይነቶች
1. ኤክስተርናል (External)፦ በተንሸራታች ስራ ላይ እንደ መቃን ሆኖ ያገለግለናል።
2. ኢንተርናል (Internal)፦ በተንሸራታች ስራ ላይ ተከፋቹ ወይም የሚንሸራተተው አካል ነው። ሲንሸራተት ድምጽ እንዳያወጣ
Brush ይገባለታል።የተንሸራታች ቁልፍ እና Roller ሚገጠመው ከዚህ ፕሮፋይል ላይ ነው።
3. ካፕ (Cup)፦ ሁለቱ ተንሸራታቾች በሚደራረቡበት ጊዜ እንደ ቁልፍ ያገለግላል።

4. Central or Butterfly Cup፦ ባለ 4 ተንሸራታች ስንሰራ የምንጠቀመው የካፕ አይነት ነው።


 ለአልሙኒየም ተንሸራታች ስራ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ( Acssesories)
1. የተንሸራታች ኮኔክተር (Sliding Connector)

2. የተንሸራታች ቁልፍ (Sliding Key)


3. Roller

4. Brush፦ ተንሸራታቹ ድምጽ እንዳያወጣ


5. 6mm መስታወት ማፈኛ (Gasket)
 3. ለከርቴይን ዎል ስራ የሚያስፈልጉ የአሉሙኒየም ፕሮፋይሎች
 1. መለን (Mellon፦ማለት ቨርቲካል ወይም ቋሚው የአልሙኒየም ፕሮፋይል ነው፡፡

2. ትራንዘም (Transom)፦ትራንዘም ማለት አግዳሚው ወይም ሆሪዞንታሊ ከመለን መለን የሚገጠም የፕሮፋይል አይነት ነው፡፡
3. ፕሬዤር ፕሌት (pressure plate)፦ ማለት በአግድም የሚገጠም መስታወቱን እንዳይንሸራተት የሚከላከል ፕሮፋይል ነው ፡፡
4. ፊንሺንግ ካፕ (Finishing Cup)፦ ማለት ፕሬዤር ፕሌቱ ከተገጠመ በኃላ የሚገጠም ፕሮፋይል ሲሆን ለከርቴይን ዎላችን
ውበትን ይሰጠዋል።
5. እስታፋ (staffa)፦ ማለት ቋሚውን ወይም መለኑን ከግድግዳ ጋር አጣብቆ የሚይዝልን የፕሮፋይል አይነት ነው ከኮንክሪት ጋር
በብሎን ይታሰራል።
6. ከርቴይን ኤል (curtain L)
7. ከርቴይን ዜድ (curtain Z)
የከርቴይን ዎል አክሰሰሪዎች (Aaccessories)
1. ረበር (rubber)
2. ሲሊከን (silicon)
3. ኮኔክተር (connecter)
4. አርም (Arm)
5. ሀንድል (Handl)
4. የአልሚኒየም ክላዲንግ ሥራ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች እና አክሰሰሪ
1. አልሚኒየም ኮምፖዚት ፓኔል
2. አር ኤች ኤስ 40*20
3. ክላዲንግ ቲ
4. እስክርው 4.8*19

You might also like