You are on page 1of 643

2 ተኛ

ዕት




“የአማልክቱ” ዐዋጅ!
ማሣኒ!

በጆንሰን እጅጉ

2013 ዓ.ም

i
ዐዲስ አበባ

©የደራሲው መብት በሕግ የተጠበቀ ነው። 2013 ዓ.ም.


በማንኛውም መንገድ ካለ ደራሲው ፈቃድ በከፊል ወይንም ሙሉ ለሙሉ ማባዛትና
ማሰራጨት በሕግ የተከለከለ ነው።
ማንኛውም አስተያየት፣ ጥያቄም ኾነ ኂስ ካለዎት፦
+251912634194
sonejigu@gmail.com
የመጀመሪያ ዕትም፤ አፍሪካ ኀ/የተወሰነ የግል ማተሚያ ቤት በ 2013 ዓ.ም ዐዲስ
አበባ፤ ኢትዮጵያ ታተመ።

“የአማልክቱ” ዐዋጅ! ማሣኒ

በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጠቀሱ ቀናትና ዐመታት ‘ዓ.ም’ የሚል መግለጫ ከሌለው


በስተቀር በአውሮጳውያን የቀን አቆጣጠር የተቀመጠ እንደሆነ ይታወቅ። ተጨማሪ
ማብራሪያ ካልታከለ በስተቀር የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ
የተወሰዱት በ 1954 ዓ.ም የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ካሳተመው
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

አከፋፋይ፦ ጆንሰን እጅጉ



+251912634194
sonejigu@gmail.com
የመጀመሪያ ዕትም 2013 ዓ. ም
ሁለተኛ ዕትም © 2014 ዓ. ም
ዐዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ።
መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።


“የሰውንም ዐሳብ በእግዚአብሔርም ዕውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ


ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ
እንማርካለን።”

(2 ቆሮ. 10÷5)

መግለጫ
ይህ ዕትም በመጀመሪያው ዕትም ላይ መጠነኛ መሻሻልና
ለውጥ ተደርጎበት የታተመ ነው። የፊደልና የዓረፍተ ነገር ዕርማትን
በማካተት ግልጽ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማብራራት ተሞክሯል።
ተጨማሪ ርዕሶች ተካትተው የመጽሐፉ ዐሳብ እንዲጎለብት
ተደርጓል። በሥነ - መለኮት ኮሌጆች አስተያየት መሠረት
ለትምህርት መርጃና ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲያግዝ
በየምዕራፉ መዝጊያ ላይ ተጨማሪ ማጠቃለያና ግንዛቤ
ማስጨበጫ ጥያቄዎች ታክለዋል።

ማሣሰቢያ

iii
መጽሐፉን በሚገባ ለመረዳት ከመጀመሪያው ገጽ
ጀምረው በማንበብ ያጠናቅቁ። በሕዳግ ላይ ወደ ኋላ የሚጠቁሙ
ማስታዎሻዎች የተቀመጡት ተያያዥነት ያላቸውን ሐሳቦች
ለማስታወስ ነው። ወደ ፊት የሚጠቁሙ ሕዳጎች የተቀመጡት
ደግሞ አንባቢው የሚያነብበውን ክፍል አቋርጦ ወደፊት እንዲሄድ
ለማድረግ ሳይሆን የተነሣው ዐሳብ በተጨማሪ ማብራሪያ
እንደሚነሣ ተገንዝቦ ንባቡን በትዕግሥት ለመቀጠል እንዲበረታታ
ነው። በተጨማሪም ርዕሶች በተያያዥነትና በቅደም ተከተል
የተቀመሩ ስለሆነ አደረጃጀቱን ሳይከተሉ ከመኻል ገብቶ ማንበብ
ወይም ጀምሮ መተው ሙሉ ግንዛቤ ለመጨበጥ እንደማይረዳ
ለማሳሰብ እወዳለሁ።

ምስጋና

ከሁሉ በላይ ይህንን መጽሐፍ እንዳዘጋጅ ምሕረቱን ላበዛልኝ፣


ትኩረቴን በመቈጣጠር በመንፈሱ አማካኝነት ማስተዋልን
እየሰጠ አዕምሮዬ ለመገንዘብ የሚቸግረውን ነገር እያስረዳ
እንድተጋ በለሊትና በቀን ላበረታታኝ፣ አብሮኝ ለነበረ፣ በጊዜና
በቦታ የማይወሰን ሆኖ ሁሉን ለሚገዛ፣ ብቻውን ምጡቅና
ቅሩብ የማይደረስበት አምላክ ለሆነ፣ ለዘላለም አምላክና አባት
ብዙ ክብርና ምስጋና ለዘላለም በትውልዶች ሁሉ ይሁንለት።
በመቀጠል ውድ ባለቤቴን ገነት ወልዴንና የተወደዳችሁ
ልጆቼን ባለፉት ሦስት ዐመታት ይህንን መጽሐፍ ለማዘጋጀት
ጊዜአችሁን ስወስድ ላሳያችሁኝ ትዕግስትና ይቅርታ
አመሰግናለሁ። የእግዚአብሔር ሰው አክሊሉ ኩማ ከልቤ
ላመሰግንህ እፈልጋለሁ። ይህንን መጽሐፍ ለመጻፍ
ከተነሣሁበት ጊዜ አንሥቶ ያለሁበት ቦታ ድረስ በመምጣት
ትሰጠኝ የነበረው አስተያየት የዕይታ አድማሴ እንዲሰፋና እጄ
ላይ ያለው ሥራ ትልቅ እንደሆነ እንዳስተውል አግዞኛል።
ባንተ ስላለው ልበ-ሰፊነት እግዚአብሔርን አከብራለሁ፤
ሁሌም አልቋል ብዬ ያስቀመጥኩትን ሥራ እንዳልጨረስኩት
ታሳየኝ ነበር። “አልገባኝም! ጽሑፍ መብራራት ይፈልጋል
አብራራው! ቆንጆ ነው! በጣም ቆንጆ ነው! የእውነቴን ነው!”
የሚሉት ንግግሮችህ ደግፈውኛልና መቼም አልረሳቸውም።
ለምታደርገው መልካም ነገር ጥሩ የፈገግታ ምላሽ እንኳ
የማትጠብቅ ምርጥ አበረታች ነህ። ከዕውቀትህና ከባሕርይህ
ብዙ አትርፌአለሁ፤ እግዚአብሔር ይባርክልኝ።

ኤርሚሻ በየነ በሽፋን ገፅ ንድፍና በርእስ ምርጫዬ ላይ እጅግ


ጠቃሚ አስተያየት በመስጠትና የመጽሐፌን ወቅታዊነት
በማጉላት ለማበረታታት የሄድክበትን መንገድ አደንቃለሁ።
የጽሑፉን ረቂቅ እየተመለከትክ በነበረበት ወቅት ወንድም
አሳየኸኝ ለገሠና ጓደኞቹ “ቅይጡ ወንጌል” በሚል ርእስ
የሠሩት ዘጋቢ ፊልም ለአየር በቅቶ ነበር። ዘጋቢ ፊልሙም
የያዘው ርእሰ ጉዳይ በመጽሐፌ ከተነሱ አንዳንድ ነጥቦች ጋር
ያለው ዝምድና ቢያስገርምህ ዕየው በማለት ቀድመህ
የደወልክልኝ አንተ ነበርክ። በእርግጥም ከአግራሞት ባሻገርም

v
መለኮት እየሠራ ላለው ሕዝቡን የማንቃት ሥራ ምልክት
ነበር የሆነኝ። መርሻ ሲሳይ በተደጋጋሚ ሳትሰለች ትሰጠኝ
ስለ ነበረው አስተያየትና ምክር አመሰግናለሁ፤ በችግሬም ከጎኔ
በመሆን መልካም ወንድምነትህን አሳይተኸኛል። ወንድሜ
ስምዖን ነጋሽ ካንተ ብዙ አትርፌአለሁ። ባሳለፍናቸው
በእያንዳንዱ ሰዓታት በሚነሱት የመወያያ ነጥቦች
የምትሰነዝራቸው ሐሳቦች ልቤን የበለጠ ያጠነክሩትና ከፍ
ያደርጉት ነበር። በተገናኘን ቍጥር ጕጕትህን በሚያስተላልፍ
ፈገግታህ “እንዴት እየሆነልህ ነው?” የሚለው ጥያቄህ
የጀመርኩትን ሥራ ሳልጨርስ ማረፍ እንደ ሌለብኝ ያሳስበኝ
ነበር። በቻልከው ሁሉ በመልካም ገንቢ ምክርህና የሰላ
ጠቃሚ ትችትህ ሁሌም ከጎኔ ነበርክ። እግዚአብሔር
ይባክርክህ፤ ይጠብቅህ።

ናትናኤል ብርሃን ከመመረቂያ ጽሑፌ ጀምሮ የነበረህ ቁጣና


ደስታ ባንተ ውስጥ አልፌ ብዙ ወጣቶችን ማየት እንድችልና
እንድራራ አድርጎኛል። በአክብሮት የምትሰጠኝ አስተያየት
የምጽፈውን ነገር ከመጻፌ በፊት ደጋግሜ እንዳስብበት
አድርጎኛል። ለእውነት ስለሚቀና ልብህ እግዚአብሔርን
አመሰግናለሁ። መርሻ አቤልና ናትናኤል የጽሑፍ ግድፈቶችን
በማየትና በሽፋን ሥዕል ንድፉ ላይ አስተያየት በመስጠት
ስላደረጋችሁት ዕገዛ አመሰግናለሁ። በመጨረሻም ያለቀውን
ሥራ ወስዳችሁ ጊዜ ሰጥታችሁ በማየትና መልካም
አስተያየታችሁን በማከል ለንባብ እንዲበቃ ዕገዛ
ያደረጋችሁልኝ፤ የብርሃነ ወንጌል ሥነ-መለኮት ኮሌጅ
ፕሪንሲፓል አክሊሉ ኩማ፣ የዐዲስ አበባ ሥነ-መለኮት ኮሌጅ
ፕሪንሲፓል ፓ/ር ተስፋዬ ዋጋሪ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ
መምህርና አርታዒ ጋሽ ንጉሤ ቡልቻ፣ የኢትዮጵያ ድኅረ
ምረቃ ኮሌጅ መምህራን (EGST) ዶ/ር ተካልኝ ነጋ፣ ዶ/ር
አፈወርቅ ኀይሉ እና መጋቢ ሰለሞን አበበ ገ/መድህን፣ ከባህር
ማዶ ዶ/ር ይርዳው ተሰማና ዶ/ር ሳሙኤል ጌታቸው፣
ለእናንተ ያለኝ አክብሮት ላቅ ያለ ነው።

ኤርሚሻ በየነ ብዙ እንድሠራ የሚያበረታቱ ምክሮችህ ድንቅ


ሥራ ሠርተዋል። ዶ/ር ተካልኝ እግዚአብሔር አንተን ሥጦታ
አድርጎ ስለሰጠን አከብረዋለሁ። መጽሐፌን እንድታይልኝ
ስጠይቅህ የነበረህ ፈቃደኝነት አልነበረም ያስደነቀኝ። በይደር
ልታቆየው አልፈለግህም ነበር። ትሑት ልብህን የሚያንፀባርቅ
አቀማመጥህ ዓይኔ ላይ ተሥሎ ቀርቷል። የማይመች ወንበር
ላይ አጠገቤ ሆነህ ለረጅም ሰዓታት በማስተዋልና በፍጥነት
አነበብከው። የሰጠኸኝ አጠር ያለ አስተያየት ያልደፈንኩትን
ቀዳዳ አመላክቶኛል። ጋሽ ንጉሤ ስለ አባታዊ ፍቅርህና
ትህትናህ አመሰግናለሁ። ያኔ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
እያለን ታሳየን የነበረውን መንፈሳዊ ቅንዓትና ርኅራኄ ከብዙ
ዐመታት በኋላ ሳገኝህም ትኩስ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ዶ/ር
አፈወርቅ ኀይሉ ስላዘጋጀሁት የጽሑፍ ሥራ ከዶ/ር ተካልኝ
ከሰማህ በኋላ ለማየት የነበረህ ፈቃደኝነትና ጕጕት እጅግ
አስደንቆኛል። በአንተ ላይ ስላየሁት ፍቅርና ትሕትና
እግዚአብሔርን አመስግኛለሁ። መጽሐፌን ስትመለከት እንደ
ራስህ የድካም ውጤት ነበር የጓጓኸው። የክርስቶስን ልብ
በአንተ ውስጥ ተመልክቻለሁና የተስፋ ብርሃን በልቤ
vii
ተጭሯል። ዶ/ር ሳሚ ስለ ፍልቅልቅ ደስታህና ማበረታታትህ
አመሰግናለሁ። ዶ/ር ይርዳው ስለ አድናቆትህና መንገድ ስለ
ማሳየትህ አመሰግናለሁ። መጋቢ ሰሎሞን መጽሐፌን
ለማየትና በልምድና በዕውቀት የዳበረ ምክረ ዐሳብህን
ለመለገስ ጊዜህን ስለሰጠኸኝ እግዚአብሔር ይባርክልኝ።
መጋቢ ተስፋዬ ከውድ ጊዜህ ላይ ቆርሰህ ከሰፊው ዕይታህ ስለ
ጨለፍክልኝ በተለይ ደግሞ አንዳንድ የፊደል ግድፈቶችን
ስለጠቆምኸኝ እግዚአብሔር ይባርክህ። ስማችሁን
ያልጠቀስኳችሁ መደሰታችሁን የነገራችሁኝ ወዳጆቼ ሁሉ
እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

የቀዳሚ አንባብያን አስተያየት

“የአማልክቱ ዐዋጅ” መጽሐፍ ደራሲ ወንድም ጆንሰን እጅጉን


(ጆንን) ከአሥራዎቹ የዕድሜ ዘመናችን አንስቶ ዐውቀዋለሁ።
የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበርንበት ወቅት የክርስቲያን
ተማሪዎችን መንፈሳዊ ኅብረት በመምራትና በማገልገል የልጅነት
የወንጌል አጋሬ ነበር። ጆን ከልጅነቱ ጀምሮ ለጌታ እና ለክርስቶስ
ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ቅንዓት ያደረበት ወንድም ነው። ይህ
መጽሐፉም የቀደመውን ትጋቱንና ለቃሉ ያለውን ታማኝ ልብ
ጭምር አመላክቶኛል። “የአማልክቱ ዐዋጅ” ጸሓፊው ድንገት
ራሱን ያገኘበት ዱብዳ ሳይሆን ለዓመታት አብሮት ከነበረው፤
ለጌታ እና ለቤተ ክርስቲያን ካለው ቅንዓት ውስጥ ፈልቆ የወጣ
በኩሩ ነው።

በመላው ዓለም ብሎም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ


“የእምነት ቃል እንቅስቃሴ ዐዎንታዊ ዐዋጅ” ትምህርት
የፈጠረውን ቀውስና መንፈሳዊ ግልሙትና መረዳትና ማስረዳት
የተከፈተ ዐይን፣ ለእግዚአብሔር የቀና ልብ፣ ለቃሉ ያለን
ታማኝነት እና ትጋትን ይጠይቃል። ጆን በዚህ መጽሐፉ የእምነት
ቃል ዐዎንታዊ ዐዋጅ ትምህርት ታሪካዊ አመጣጡን ከሥር
መሠረቱ ፈልፍሎ በማውጣት የትምህርቱን አደገኛነት
እንድንረዳው አድርጎ በትጋት ከትቦታል። ከዚህም በላይ
“አማልክቱ” አስገድደው ለራሳቸው ዐሳብና ትምህርት ደጋፊነት
የተጠቀሙበትን የመጽሐፍ ቅዱስ አስቸጋሪ ክፍሎች በዝርዝር
ዳስሷል። ወደ መጽሐፍ ቅዱስ አተኩሮ በመመልከት ዐውዱን
በጠበቀ መልኩ ክፍሎቹን ተንትኗል። ክፍሎቹ ሊሉት
የፈለጉትንም ትክክለኛ መልዕክት ሳያዛባ በጥንቃቄ ለተደራስያኑ
አሳይቷል። ይህ ድካሙም ተደራስያኑን “በተገደዱ” ጥቅሶች
ከመደናገር የሚያድን ሲሆን ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ
አፈታትንም ለመማር ይጠቅማል።

ጆን ተሓድሶ ይሻል ብሎ ለሚያነሳው ችግር ምን ያኽል ቅርብ


እንደሆንን በመጠቆም በዚህ ዘመን ያለን አገልጋዮችን
ተጠያቂዎች ነን፣ እንደ ንቁ መሪ ኀላፊነታቸንን እንወጣ፣ አንድ
ቀን በፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን፣ የምንጠብቀው ሽልማት
ያለው ከፍርድ ወንበር ማዶ ነው በማለት እያነቃቃ ይሞግተናል።
በዚህ መጽሐፍ ላይ ጸሓፊው አደራ እንደተቀበለ እንደ ክርስቶስ

ix
አገልጋይ በድፍረት ስሕህተትን በፍትሐዊነት ይሞግታል።
ተደራስያኑንም ያለፍርሃት የስሕህተትን ትምህርት በመጋፈጥ
የእውነትን ወንጌል በፍጹም ግልጽነት እና ድፍረት ማስተማር
እንዲችሉ ያደፋፍራል።

በአጠቃላይ “የአማልክቱ ዐዋጅ” የዲበ-አካል ሃይማኖትና የእምነት


ቃል እንቅስቃሴ ያለውን ትስስር፤ ከመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ጋር
ያለውን ልዩነት በሚገባ አሣይቶኛል። የማላውቀውን እንዳልናገር፤
የምናገረውንም አስቤና አስተውዬ እንድናገር አስጠንቅቆኛል፤
አሳስቦኛል። ቅዱሳንን በሙሉ በተለይም በአገልግሎት ላይ ያለን
ይህንን መጽሐፍ በማንበብ ራሳችንንና ሌሎችን ከዚህ አጥፊ
ትምህርትና ልምምድ እንድንታደግ ዐደራ እላለሁ። እግዚአብሔር
አምላክ ይህን መጽሐፍ ለእኛ መትረፊያና ማትረፊያ፤ ለስሙም
ክብርን የሚያመጣ ያድርገው።
ሬቨረንድ ሳሙኤል ጌታቸው (ዶ/ር)
በአዳምስ ተርማል ፋውንዴሽን የአፍሪካ ኦፕሬሽንና ሚኒስትሪ
ዳይሬክተር፡ ሱፎልስ ሳውዝ ዳኮታ።

በመጨረሻው ዘመን የምትገኝን የክርስቶስ ቤተ


ክርስቲያን ከዚህና ከዚያ የሚያላጓትና የሚያወናብዷት የትምህርት
የአመራር፣ የባህልና የልምምድ ተግዳሮቶች እጅግ ናቸው። ከዚህ
ም የተነሳ ኢትዮጵያ ቤተ
ክርስቲያንን መልኳንና ይዘቷን እያደበሱና እያመሰቃቀሉ ልጆቿን ግ

እያጋቡና እየተፈታተኑ በተልዕኮዋ ወደፊት እንዳትሄድ ሰቅዘው ይዘ
ዋት ይገኛሉ።
ወንድሜ ጆንሰን ይህን በመረዳት በሥነ
መለኮትና በልምምድ የተፈጠሩ ችግሮችን ከምንጫቸው በማጥና
ት፤ በአገራችንም ያለከልካይ ሜዳ
አግኝተው እየጋለቡ ያሉትን በእውነት እየሞገተ፤ ያቀረበበትን ይህ
ን መጽሐፍለመጻፍ የሄደበትን ርቀት አድንቄአለሁ። የቤቱ ባለቤት
ም በቍጣ ሳይገለጥ
አገልጋዮች ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ ያስተጋባውን ማስጠንቀቂ

ወድጄለታለሁ። እንደ ወጣት ጸሓፊነቱም ዕደግ ተመንደግ ብዬ
መርቄዋለሁ። አንባቢም በትዕግሥት መጽሐፉን ማንበብ እንዲችል
አሳስባለሁ።
ፓስተር ይርዳው ተሰማ ቃዴስ የክርስቶስ ቤተ
ክርስቲያን መጋቢ፤ ሎስ አንጀለስ።


ምን ተባለ?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት መስፋፋትን ተከትሎ
“የፌስ ቡክ” ድረ ገጽ ሰዎች ዐሳባቸውን በጽሑፍ ከሚገልጡበት መንገድ
አንዱ በመሆን ዐወንታዊ አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል። ታዲያ
“የአማልክቱ” ዐዋጅ! መጽሐፍ ለንባብ ከበቃ በኋላ በርካታ አስተያየቶች
በዚሁ ድረ ገጽ የግል ዊሂብ መለጠፊያ ላይ ሲዘዋወሩ ተመልክቻለሁ።
ከእነኚህ ገጾች መኻል የአንዳንዶቹን ባለቤቶች አስቀድሜ በአካልም
ይሁን በስም አላውቃቸውም ነበርና አስተያየታቸውን ከመቀበል ባሻገር
ማን ናችሁ? ብዬ ለመጠየቅና ለመተዋወቅ ዕድል ፈጥሮልኛል።
ተለጥፈው ካየኋቸው ጽሑፎች መኻልም የአሌክስ ዘጸአት “እንካ
መጽሐፍ” የሽመልስ ይፍሩ “አንደበታቸውን አምላካቸው ላደረጉ ሁሉ የተሰጠ
አጸፋ!” የዲቦራ ጌታቸው “ግሩም ጽሑፍ” በሚሉ ርእሶች የተጻፉ
መጣጥፎች ይገኙበታል። ጽሑፎቹ ለአንባብያን ትሩፋት እንዲሆኑም
ከዚህ ቀጥሎ አቅርቤአለሁ። ከዲቦራ ጌታቸው በስተቀር ሁሉም መጽሐፌ
ደርሷቸው ያነበቡ ወገኖች ናቸው። ዲቦራ “ግሩም ጽሑፍ” በሚል ርእስ

xi
የለጠፈችው ከመጽሐፉ ላይ ተቀንጭቦ የተነበበውን አጭር ትረካ በ YouTube
ገጼ ላይ ከተመለከተች በኋላ ነበር።

እንካ መጽሐፍ
በእምነት ቃል አስተምህሮ ወይም በብልጽግናና ጤንነት ወልጋዳ ስብከት ላይ
በፈረንጅኛው አፍ ጥንቅቅ ያለ ሥራ የተሠራው በዶ/ር ዳንኤል ማክኮኔል (Dr.
Daniel McConnell) እና በሐንክ ሐነግራፍ (Hank Hanegraaff)
ነው። ማክኮኔል “A Different Gospel” እና ሐነግራፍ “Christianity
in crisis: 21st century” በሚል ርእስ የጻፏቸው ኹለት መጻሕፍት
በርእሰ ጉዳዩ ላይ በሚጻፉ የጥናት ጽሑፎችና መጻሕፍት ላይ እንደ ጨው
እየተነሰነሱ ይጠቀሳሉ። ከእነዚህ ኹለቱ በተጨማሪ ያነበብኩት የተደራጀ ሥራ
ቢኖር Jones and Woodbridge የተባሉ ደራስያን የጻፉት "Health,
Wealth and Happiness” የተሰኘ መጽሐፍ ነው።

ወደ አገራችን ቋንቋ ስንመጣ በርእሰ ጉዳዩ ዙሪያ ዓይን ከፋች ምርጥ ሥራ


የተሠራው በቀዳሚነት በግርማዊ ነው። "የብልጽግና ወንጌል" የተሰኘው
የግርማዊ ጥናታዊ ሥራ ለእኔ የሁል ጊዜም ምርጥ! ነው። ከዚያ ቀጥሎ የእምነት
ቃል እንቅስቅሴ አንኳር ጽንሰ-ዐሳብ ከመሠረቱ በመፈተሽ፤ ከውልደቱ እስከ
ዕድገቱ ድረስ እንዴት ተጠፍጥፎ እንደተሠራና በትምህርቱም ሆነ በልምምዱ
ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ርቱዕ ቀኖና ያፈነገጠ "ሰርጎ ገብ ባዕድ" እምነት
እንደሆነ የሚነግረን ደግሞ ጆንሰን እጅጉ ነው።

ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት በርእሰ ጉዳዩ ጥንቅቅ ያለ የተሟላ ጥናታዊ ሥራ


በመሥራት ማክኮኔል ቀዳሚ ናቸው። ማክኮኔል ቅይጡ አስተምህሮ እንዴት
በኢ.ደብልዩ ኪኒየን ወደ ወንጌላዊው ክርስትና እንደገባ ሲነግሩን "ተጠምቆ
ክርስትና ተነሳ" በማለት ነው። ከማክኮኔል ባልተናነሰ መልኩ ወንድማችን ጆንሰን
ደግሞ ጥምቀተ-ሥርዓቱ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ጭምር ጥንቅቅ አድርጎ
በመሥራት ዐሳይቶናል።

በአሁኑ ጊዜ የእምነት እንቅስቃሴ አስተምህሮና ልምምድ ሳናውቀው ወደ


ወንጌላዊው ክርስትና ሰርጎ ገብቶ ደረቱን በመንፋቱና "ቤተኛ ነኝ" ብሎ
በመደንፋቱ ዕውቅና ሰጥተን የምንሟገትለት ወረርሽኝ እየሆነ ነው።
“የአማልክቱ ዐዋጅ!” መጽሐፍ ይህንን ሙግታችንን ገታ አድርገን ቆም
በማለት እንድናድብ የሚያደርግ የማንቂያ ደወልና የእንቅስቃሴው መርዝ
ማርከሻ መድኃኒት ነው። መጽሐፉ ጥቅስን እየመዘዙ ዐዎንታዊ ዐዋጅ የማውጣት
ልምምድ የአብዛኛዎቹ "ወንጌላውያን ነን" ባይ አብያተ ክርስቲያናት የሰርክ
የመድረክ ተግባር መሆኑን በመረጃ እያስደገፈ ያስቃኘናል። መድረካችን የእምነት
ቃል ትምህርት ወይም የብልጽግናና ጤንነት አስተምህሮ ልምምድ ሰለባ
መሆኑንም ቁልጭ አድርጎ በማሳየት ቁጭት ውስጥ ይከትተናል፤ መልሶም
መውጫውን ያስጨብጠናል።

ይሁን እንጂ እንዲህ የተደከመበትና የተዋጣለት ድንቅ ሥራ ሆኖ እያለ ብዙም


ማስታወቂያ ያልጮኸለት በመሆኑ ምክንያት የመነበብ ዕድሉን አናሳ
አድርጎታል። ይህም ደራሲው ያልሠራውን ሥራ የሚያሳይ ቢሆንም መጽሐፉን
የተዋወቅን ወገኖች ጭምር ይህንን ክፍተት ለመሸፈን የድርሻችንን መወጣት
ብንችል ጥሩ ነው ብዬ ዐስባለሁ። ምክንያቱም ቀኖናዊውን ክርስትና የሚከተሉ
“ወንጌላውያን ነን" የሚሉ አማኞች፣ መሪዎችና አገልጋዮች መጽሐፉን
ሊያነብቡት ይገባል። ይህንን ቢያደርጉም የእምነት ቃል ትምህርትና
ልምምድ በሽታ በመኃላቸው የቱጋ ሰርጎ እንደገባ ለማየት ይችላሉ።
በተጨማሪም ትምህርቱን ለመቃወም እንዲበረቱ የእምነት አቋማቸውንና
ልምምዳቸውን በመፈተሽ ቢጠቀሙበት አትራፊ ይሆናሉ!!
አሻም! ወንድም ጆንሰን እጅጉ። ጸጋ ይብዛልህ!
አሌክስ ዘጸአት
አንደበታቸውን አምላካቸው ላደረጉ ሁሉ የተሰጠ አጸፋ!
"የአማልክቱ አዋጅ" የተሰኘውን መጽሐፍ በገዛሁ ማግሥት ነው አንድ ባልንጀራዬ
ከእጄ ላይ የነጠቀኝ። ሆኖም በወፍ በረር ቃኘት ስላደረግሁትና የዋጋውን
ትልቅነት ለመተመን ዕድል ስላገኘሁ እንዲህ ያሉ ጠቃሚ መጻሕፍት ሲጻፉ "ነገረ
ክርስትና" መጽሔት ከክፍያ ነፃ የሆነ ማስታወቂያ ለመሥራት ከመረጠቻቸው
መጻሕፍት አንዱ ለመሆን በቅቷል። በቅጽ 6 ቀጥር 16 ዕትም ላይም ይኸው
ተግባራዊ ተደርጓል። በቅርቡ ከመጽሐፉ ደራሲ ጋር በነበረን ቆይታ ደግሞ በርእሰ
ጉዳዩ ላይ ኢ - መደበኛ ውይይት አድርገናል።

ከውይይታችን እንደተረዳሁት ደረጃው ይለያይ እንደሆነ እንጂ የአንደበት አምልኮ


በአገራችን ባሉ ሁሉም ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እግሩን ያስገባ
አደገኛ ልምምድ ስለመሆኑ አውግተናል። "የትኛው በተስኪያን ልሂድ?" የሚል
ጭንቅ እስኪገባን ድረስ መድረክ ላይ የቆመ ሰባኪ ቢሉ፣ አስመላኪ በቀጥታም

xiii
ሆነ በተዘዋዋሪ ስለ አንደበት ኃይል ሳይደሰኩር እንደማይወርድም ስምምነት ላይ
ደርሰናል።

የደራሲው የመጀመሪያ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ


የሚያጠነጥን በመሆኑም የነገሩን ግራና ቀኝ በጥልቀት ስለመፈተሹ ለመገንዘብ
ችያለሁ። መጽሐፉም የዚህ ምርመራ ትሩፋት ነውና እንዲህ ዓይነቱ ነፍሰ ገዳይ
አስተምህሮና ልምምድ በማን ተጠንስሶ፣ በነማን ተጠምቆ በአሁኑ ወቅት ሁሉ
የሚጋተው አስካሪ መጠጥ ወደ መሆን እንደመጣ ከታሪካዊ ዳራው አንስቶ
በስፋት ይተነትናል።

ጸሓፊው "አማልክቱ ሰባከያን" የሚላቸው አካላት የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ


አፈታት ህግ የማይከተሉ፣ ከአመክንዮ የተፋቱ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ በኅሩይ
ዐወንታዊ ቃል ዐዋጅ በተሞላ አንደበትና ደግ ደጉን ብቻ በሚያስብ አዕምሮ
የሚመኩ ስለመሆናቸው በርካታ አብነቶችን ይዘረዝራል። ዋናው ጉዳይ ዐወንታዊ
ቃል ዐዋጅ ይሠራል ወይስ አይሠራም የሚል ሳይሆን ምንጩ ከየትና የማነው
ብሎ የመመርመር እንደሆነ ጸናን ሙግቶችን ያቀርባል። "አማልክቱ ሰባኪያን"
በግላጭ አምላክ እንደሆኑ ባይናገሩም በትምህርታቸውና በግብራቸው ግና ያንን
ስለ ማንጸባረቃቸው ይጠቁማል።
ድርሳኑ ባህር ስለሆነ ወደ ዝርዝሩ አልገባም። ለወዳጆቼ ግን አንድ ምክር
እሰጣለሁ። ይኼንን መጽሐፍ አንብቡት! አንብቡትና ሰው እንዴት
በእግዚአብሔር ስም ከእግዚአብሔር ዓለም ተንሸራትቶ እንደሚወድቅ ግንዛቤ
አግኙበት። አማኝ ማንነታችሁን ወደ አድራጊ ፈጣሪነት ከማሸጋገር ታላቅ
ውድቀት ለመጠበቅ ተጠቀሙበት።
በሽመልስ ይፍሩ (የነገረ-ክርስትና መጽሔት ዋና አዘጋጅ አ.አ)

ግሩም ጽሑፍ
ግሩም ጽሑፍ የተዋጣለት ትረካ። ከሞቅታዎች ጋር አብሬ መሄድ ሲያቅተኝ፤
የዐዋጅ ጋጋታ ቢያባትለኝ፤ ራሴን እኔ ነኝ ወይስ እነሱ ናቸው መንገድ የሳቱት ብዬ
ብዙ ጊዜ ጠይቄአለሁ። ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ሆኖ በልብ ያደረ ነገር ታዲያ
እንዲህ አንጀት በሚያርስ መልኩ ተገልፆ ሲታይ እንዴት ደስ ይላል! በዚህች
“አስር ደቂቃ” የዘመናት ችግር የሆነውን የቤተ ክርስቲያንን ሕመም ማንሳት ብቻ
ሳይሆን የችግሩን ስር መሠረት ተንትነህ በማቅረብህ ብዙ ነገር እንዳጤን
ረድተኸኛል። እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዕርህ አይንጠፍ።
Can't wait to hear more of these! I used to and still listen to
Justin Peters, who strives to expose false teachers and show
the right way in the light of God's word. I am grateful that we
got such a person who reminds us of these in our very own
language, Amharic. What can I say? To God be all the glory
who sustains and sanctifies His church.
በዲቦራ ጌታቸው (ግራፊክስ ዲዛይነር ባሕር ዳር)

ማውጫ
የቃላት መፍቻ xvi

ቅኝት አንድ - 15 -
ቅኝት ሁለት - 19 -
ክፍል፩
ታሪካዊ አንደምታ
ምዕራፍ 1
የፍተሻ ጉዞ - 25 -
የዲበ-አካል ሃይማኖት ውልደትና ዕድገት - 33 -
ኢማኑኤል ሲውዲንበርግ (1688-1777) - 40 -
ፍሬንዝ አንቶን ሜዝመር (1735-1815) - 44 -
ፕሮፌሰር ጆን ታይንዶል (1820-1893) - 46 -
ፊኒየስ ፓርክሆረስት ኩዊምቢይ (1802-1866) - 47 -
ሜሪ ቤከር ኤዲ (1862-1881) - 49 -
ኢማ ኮርቲስ ሆፕኪን (1849-1925) - 52 -
ማሊንዳ ኢሊቶ ክሬመር (1844-1926) - 54 -
ቻርልስ ፊሊሞር (1854–1948) - 56 -
ኸርንስት ሆምስ (1887-1960) - 63 -
ኢ. ደብልዩ ኪኒየን (1867-1914) - 65 -
ኬኔት ሄገን (1933-2003) - 67 -

ክፍል፪
ዘመን ጠገብ ጥምር ተግዳሮት
ምዕራፍ 2
የዲበ-አካል ሃይማኖት ኪኒየንና ኬነት ሄገን - 75 -
የዲበ-አካል ሃይማኖትና መለኮት - 87 -
የተፈጥሮ ሕግ - 91 -
ልዕለ አዕምሮ - 98 -

xv
የአባት ሕግ - 103 -
የኅሩይ ቃል ዐዋጅ - 110 -
የኅሩይ ዐዋጅ ስኬት - 114 -
የዲበ-አካል ሃይማኖት መላምት ሥርጭት - 121 -
መለኪያ ዘንግ - 126 -

ምዕራፍ 3
የዲበ-አካል ሃይማኖት እርሾ - 139 -
የዲበ-አካል ሃይማኖት እርሾ በኢትዮጵያ - 143 -
መለኮታዊ እምነት - 154 -
እግዚአብሔርን መምሰል እንዲህ ነው - 164 -
የኢየሱስን ምሳሌነት መከተል - 166 -

ምዕራፍ 4
የምናባዊ ዕይታ ሕግ - 171 -
የዐይነ ኅሊና ሕግ - 173 -
ስሜትን የማሳደግ ሕግ - 176 -
የማየትና ማሳየት ሕግ - 181 -
የመንፈስ መግነጢስ ሕግ - 185 -
ሞኛ ሞኙ የቃል ዓለም - 188 -

ክፍል ፫
የዐዋጅ ቃል ልምምድ

ምዕራፍ 5

የዐዋጁ ጥቅል - 195 -


የእምነት ቃል ልምምድ - 198 -
ጸሎት ያልገባው - 200 -
የአንደበቴ ቃል መሬት ጠብ አይልም! - 207 -
ዋ! ቃል እንዳላወጣ! - 213 -
የርግማንና የሟርት ፍርኃት - 215 -
ንስኃ እንደ ሟርት - 217 -
አላምጥም አለችኝ - 220 -
እግዚአብሔርን መስማት ለምኔ? - 223 -
የምኞት እስር - 227 -
ክፍል ፬
የጥቅስ ገበያ
ምዕራፍ 6
ተገድደው የተሸጡ ጥቅሶች - 235 -
ምን ላውጅ? - 237 -
አማልክታዊ ዘረ-መል (DNA) - 246 -
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል - 259 -
የረገምካት በለስ ደርቃለች - 266 -
የረገምከው ርጉም ይሆናል - 275 -
የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል - 283 -
ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል - 291 -
በልቡ እንደ አሰበው እንደዛው ነው - 292 -
ለጻድቁ መልካም ይሆንልሃል በሉት - 295 -
አንደበት እሳት ነው! - 297 -
ችግሩ እያለ - 300 -
በገባዖን ላይ ፀሓይ ትቁም - 303 -
ቃል ተናገር ብላቴናዬም ይፈወሳል - 305 -
እንደ እንጀራ ይሆኑልናል - 310 -
ሌላ ዐይነት እምነት - 314 -
በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል - 318 -
መለኮትን የሚያንቀሳቅስ ችሎታ - 325 -

ክፍል፭
የተኃድሶ ደወል
ምዕራፍ 7

መናፍቃዊ ሰንኩል ጉዞ - 333 -


የእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ - 340 -
አማልክት አደለንም! - 349 -
ገደብ የሌለው ሥልጣን - 352 -
ጥገኛ ሥልጣን - 356 -
ድፍረትን የሚያኮስስ ሥልጣን - 358 -

xvii
ምዕራፍ 8
መለኮትን ይለምኑታል - 361 -
የበረከት የጊዜ ሰሌዳ - 364 -
የዕጣ ፋንታ ማኅተም - 366 -
መለኮትን የሚያዝ ልዩ ዐዋጅ - 367 -
የዕብራውያን ዐዋጅ ቃል - 369 -
የእምነት ቃል - 372 -
የዳዊት ዐዋጅ - 374 -
ትልቅ እምነት - 377 -

ተጠያቂዎች ነን - 381 -
የንቁ መሪ ኀላፊነት - 383 -
የተዘነጋው የፍርድ ወንበር - 387 -
“መገለጥን” ያላቁ ጆሮዎች - 389 -
አዕምሮ ያዘረፈ መገለጥ - 394 -
የውጫዊው መንፈስ ተቃርኖ - 397 -
የሰነፍ ሽሽት - 400 -
የትርጉም ተሰጥዖ - 402 -
ሐቲታዊ ሥልት - 405 -
መንፈስ ቅዱስን ማወቅ - 407 -
ጴንጥቆስጤያዊ ሥጦታ (glossolalia) - 410 -
ተኃድሶ - 420 -

ዋቢ መጻሕፍት - 431 -
የቃላት መፍቻ
ዲበ-አካል (metaphysics)፦
ዌብስተር መዝገበ ቃላት ‘ሜታፊዚክስ’ መኖር ምንድነው?
ዓለምስ እንዴት መኖርን ጀመረ የሚለውን ጥያቄ
የሚመልስ ፍልስፍና ነው በማለት አጭር ትርጓሜ
ይሰጠዋል።1 አቻ የአማርኛ ስያሜው ደግሞ ዲበ-አካል
ሲሆን ከግዕዝ የተዋለደ ነው። ዲበ ማለት በላይ
ከሚታየው ጀርባ ወይም ያለፈ ማለት ነው። አካል
ከሚለው ቃል ጋር ሲዳበልና ዲበ-አካል ሲሆን ከግዑዙና
በዐይን ከሚታየው አካል ጀርባ ወይም በላይ እንደማለት
ነው። ዲበ-አካል ፍልስፍና እንደመሆኑ መጠን የተለያየ
መልክና ክፍል ያለው ሲሆን በዚህ መጽሐፍ የሚነሣው ልዩ
ዲበ-አካል የሚባለው ነው።
የዲበ-አካል ሃይማኖት (New Thought) ፦
ዲበ-አካላዊ ሃይማኖት ወደ ክርስትና የሰረገ ክፍለ-
ዘመናትን የተሻገረ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ነው።
እንቅስቃሴው ክርስትናንና የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍናን
በአንድነት በማጣመር፤ ከሃይማኖታዊ አስተሳሰቦችና
ልምምዶች ጋር በማስማማት የተመሠረተ ሲሆን ራሱን
እንደ ሃይማኖትም፤ እንደ ሳይንስም ይመለከታል።
በማዕከላዊነትም ሁሉም ሃይማኖቶች የተለያየ መንገድ
ቢከተሉም አንድ የሚያደርጋቸው ሳይንሳዊ ወይም
ተፈጥሮአዊ የቃል ኀይል ጥምረት አለ ብሎ ያምናል።
1
Webster’s New World Dictionary. (1979, P, 461).
xix
እንቅስቃሴ፦
አንድን ዐስተሳሰብ፣ ፍልስፍና ወይንም እምነት በርካታ
ሰዎች ሲከተሉት፣ እየሰፋና እያደገ ሲሄድ።
የእምነት ቃል እንቅስቃሴ፦
“የእምነት እንቅስቃሴ” ወይም “የቃል እምነት እንቅስቃሴ”
አዲስ ፍጥረት የሆነ አማኝ በኅሩይ ቃል ዐዋጅ ኀይል
ድነትን፣ አካላዊ ጤንነትን እና የገንዘብ ብልጽግናን
ለማረጋገጥ ይችላል የሚል በክርስትና ስም ያለ የዲበ-አካል
ሃይማኖት እንቅስቃሴ ነው። ይህንንም ለማሳለጥ የዲበ-
አካል ሃይማኖት ፍልስፍናን ከበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥቅሶች ጋር በማጣመር ያስተምራል። ትምህርቱን
በአመክኒዮ ለማቅረብም ሲል የትምህርተ-ሰብዕንና
የትምህርተ-ክርስቶስን ያዛባል።
ክርስቶሳዊነት፦
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ክርስቶሳዊነት ክርስቶስን ወደ
መሆን ማደግ እንደሚቻል በማሰብና በማስተማር ትኩረት
የሚያደርግ ወይም የሚያንጸባርቅ ልምምድን ይገልጣል።
መላለም፦
ፍጥረታትን ሁለ ወይም ከዋክብትና ፕላኔቶችን ሁሉ
ጠቅልሎ የያዘ ግዙፍ ክልል (ዩኒቨርስ)።
ምጡቃዊነት (transcendentalism) ፦
ከጊዜና ከቦታ ውጪ የሆነ የማይወሰን ማለት ሲሆን፤
የሰው መንፈስ መለኮት ስለሆነ በጊዜና በቦታ ወይም
በአካል አይወሰንም የሚል የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና
ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
ልዕለ አዕምሮ (Divine mind) ፦
“ልዕለ አዕምሮ” የሰውን ዐቅል እንደ መለኮት የሚቆጥር
የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ጽንሰ-ዐሳብ ነው። ፍልስፍናው
“ልዕለ አዕምሮ” የሰው አዕምሮ ክፍል ሲሆን ከቦታና ከጊዜ
ውጪ የሆነ በመላለም ውስጥ ያለ ኀይል ወይም አምላክ
ክፍል ወይም ቁራጭ ነው ይላል። አዕምሮ ሲነቃም ከዚህ
መላለም ኀይል ወይም የመላለም አዕምሮ ጋር በመነካካት
የሰውን ጥያቄ ይመልሳል፤ ፈውስንም ያረጋግጣል ብሎ
ያምናል።
ማመልኮት፦
ሰብአዊ ፍጡርን መለኮት አድርጎ ወይም በውስጡ
የመለኮትነት ቅንጣት እንዳለው ማሰብና ክብር መስጠት
ወይም በመለኮት መመሰል፤ ማስመሰል።
አማልክት፦
አምላክ የሚለው ቃለ ብዜት ነው። በዚህ መጽሐፍ
የሚወክለው በግልጽ አማልክት እንደሆኑ ባይናገሩም፤
በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የዲበ-አካል ሃይማኖት
ዐስተሳሰብን በግብራቸው ወይም በትምህርታቸው
የሚያንጸባርቁትን ጭምር ነው።
የአማልክት ጎራ፦
ይህ ቃል በዚህ መጽሐፍ የሚወክለው በተወራረሰ
ዐስተሳሰብ አማልክትነትን የሚያስተምሩና
በምግብራቸውም የሚያንጸባርቁ የልዩ ዲበ-አካል ምሁራን
ወይንም የእምነት ቃል እንቅስቃሴ መሪዎችን ነው።
ንቁ አማልክት፦
በዚህ መጽሐፍ የሚወክለው የዲበ-አካል ሃይማኖት
ፍልስፍናን በሚገባ ተረድተውና ዐውቀው በጥልቀት
የሚለማመዱና መለኮት እንደሆኑ የሚቆጥሩትን ነው።

xxi
የእምነት ቃል፦
የእምነት ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ቃል ቢሆንም
በልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ላይ የተመሠረተና የአንደበት ቃል
የመፍጠር ዐቅም አለው የሚል ትርጓሜ የተሰጠው
የእምነት እንቅስቃሴ ዐስተሳሰብ ነው።
ልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ (Positive Confession) ፦
ኅሩይ የቃል አዋጅ፣ የእምነት ቃል ዐዋጅ፣ ቃል
ማውጣትና ዐዎንታዊ ቃል በሚል ተለዋዋጭ የቃላት
አጠቃቀም ይታወቃል። ተጠቃሚዎቹ በዚህ መልክ
ይጠቀሙበት እንጂ ልምምዱ መጽሐፍ ቅዱስ ዐዋጅ
በማለት ከሚጠቅሰው ጋር የተለየ መሆኑን ለአንባቢ
ለመግለጽ እንዲያመች ልዩ ዐዎንታዊ አዋጅ በሚል
ተክቸዋለሁ። ልምምዱ በስብከት፣ በትምህርት፣
በዝማሬ፣ በጸሎት፣ በትንቢትና በፈውስ አገልግሎት ላይ
ሥራ ላይ እንዲውል እየተደረገ ያለ የዲበ-አካል ሃይማኖት
ልምምድ ነው። በአጠቃላይ ልምምዱ ዐሉታዊ ቃላትን
እንደ ስኹት ወይንም ኃጢአት ይቆጥራል። በተቃራኒው
ዐዎንታዊ ቃላትን መናገር መልካም ነገር እንደሚፈጥር
ይቆጥራል።
መገለጥ፦
በዚህ መጽሐፍ ከዚህ በፊት በነብያቱና በሐዋርያቱ
ያልተገለጠና የማይታወቅ ነገር ግን ከመንፈሳዊ ዓለም
የሚገኝ አዲስ መረጃን ለማመልከት ውሏል።
ምርመራ፦
በዚህ መጽሐፍ የሚነሣው በእጃችን ላይ ያለውን መጽሐፍ
ቅዱስ ለመረዳት የሚደረግ ሐቲታዊ ጥናትን ለመግለጥ
ነው።
ሐቲት (exegesis)፦
በቁሙ መፍታት፣ መተርተር፣ መክፈት፣ ማውለቅ፣
ማናዘዝ ማለት ሲሆን፤ ደራሲው መልእክቱን
ባስተላለፈበት ወቅት የነበረው ሁኔታ ምን ነበር?
ተደራሲያኑ ምን እንዲረዱለት ፈልጎ ነበር? ወይም ምን
ተረድተው ነበር? የሚለውን በማንሳት የሚመረምር
ሥልት ነው።
ተኃድሶ፦
የመታዘዝና የመለወጥ ቁርጠኝነት፤ አሮጌውንና
የተበላሸውን በማንሣት ወይንም በማፍረስ ወደ ትክክለኛና
የቀድሞ መልክ መመለስ።
ልዩታ (ልዩትነት)፦
አምሳያና አቻ ወይም መልክ የሌለው፣ ከሌላው ሁሉ
ፍጹም የተለየ ባህርይና ማንነት ያለው፣ ፍጹም መሳይ
አልቦነት ወይም ብቸኛ። (unique)
ጮረቃ፦ በክረምት ዝናብ ምክንያት መንገድ ላይ የሚከትር ትንሽ
ቆሻሻ ውኃ።
አመስጥሮ (Allegory) ፦ ድብቅ፣ ፊት ለፊት የማይታይ፣
ምስጢራዊ።
መግነጢስ፦ የማግኔት ስበታዊ ጉልበት።
ማሣኒ፦ ፍራሽ፣ ጠፊ፣ በስባሽ፣ የሚጠፋ፤ የሚያማስን፥
የሚያደክም፣ የሚያለፋ፣ የሚያንከራትት።
መግነጢስ(magnetism)፦ የስበት ኃይል።
ድጥ፦ በውኃ የለሰለሰ አንሸራትቶ የሚጥል መሬት።
ዊሂብ፦ በቁጥር ወይም በፐርሰንት ሊቀመጥ የሚችል መረጃ
ወይም ዳታ።
ኅሩይ፦ የተመረጠ፣ ልዩ፣ ቆንጆ።
xxiii
ጎበረረ፦ ደረቀ።
መሠየት፦ መጎምጀት።
ሥርው፦ መሠረት፣ ሥር፣ መነሻ፣ ምንጭ።
ቅኝት አንድ
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1980 ዎቹ ወዲህ በአገራችን
የወንጌል አማኞች አብያተ
የእሳት ሳይሆን ወደ ውጪ
ክርስቲያናት የአጥቢያ ቤተ
የሚገፈትር የበረዶ ወላፈን እየተሰማኝ
ክርስቲያናት ቍጥር በየጊዜው ነው። በገባሁበት በአብዛኛው ጉባኤ
ሣለሁ ትምህርቱን በአግባቡ ከተማረው
በመጨመር ላይ ይገኛል። ወይም ካጠናው የተለየ የፈተና ጥያቄ
በርከት ያሉ አዳዲስ አብያተ ቀርቦለት እንደሚጨነቅ ተማሪ ልቤ
ይነሆልልብኛል።
ክርስቲያናትም ተከፍተዋል።
መሰብሰቢያ አዳራሾች በአንድ ጊዜ ብቻ ከአንድ ሺ ሰው በላይ
እያስተናገዱ ነው። ከመደበኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪ
ኮንፈረንሶች ላይ የሚቆሙ የሰባኪያንና የነብያት ዕጥረት ከቶ
አይታይም፤ እንደውም ተጨናንቋል። ብዙዎች የዜማና
የመሳሪያ ክኽሎት ማደጉን በደስታ ይናገራሉ። ለዚህም
ማስረጃ ሲያቀርቡ የአዳዲስ ዜማ ቅጂና ሽያጭ አገልግሎት
ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል ይላሉ።

በተጨማሪም የብዙ ዘማሪዎችና የአምልኮ መርኃ ግብር


መሪዎች ወደ አገልግሎቱ መግባት፣ መድረክ ማድመቅና
መቈጣጠር ከዚህ ጋር አያይዘው ያነሣሉ። በአብዛኛዎቹ
ጉባኤዎች ታዲያ ብዙ ሕዝብም ሲዘልል፣ ሞቅ ባለ ስሜት
ሲጮኽና ኅሩይ ቃል በማወጅ ሲደሰት መመልከት እየተለመደ

15
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነው። ይህንን እንቅስቃሴ አስመልክተው የሚጽፉ ጸሓፍትም


ታዲያ ይህ የመነቃቃት (የሪቫይቫል) ወላፈን ምልክቱ ነው
ብለው ከትበዋል። ይህም እሰየው ያድርገው ያስብላል።

ይሁን እንጂ ከአዲሱ ሚሊኒየም መግቢያ ወዲህ የእሳት


ሳይሆን ወደ ውጪ የሚገፈትር የበረዶ ቊር እየተሰማኝ ነው።
በገባሁበት በአብዛኛው ጉባኤ ሣለሁ ትምህርቱን በአግባቡ
ከተማረው ወይም ካጠናው የተለየ የፈተና ጥያቄ ቀርቦለት
እንደሚጨነቅ ተማሪ ልቤ ይንከራተትብኛል። ብዙ ጊዜ ሰው
እንደሚሆነው መሆን ያቅተኛል። ዞር ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ፤
ለምን ደስ አይለኝም? ለምን ሰዎች ሲዘልሉ አብሬአቸው
አልዘልም? ለምን አብሬአቸው አላብድም? ለምን እንደ
ቀድሞው ዘመን ወደ ጉባኤ አልሮጥም? በአነሰተኛ ጉባኤዎች
ውስጥ እንኳን ይሸትተኝ የነበረ የምልጃ ጠረን ለምን ሣሳ? ያ
እንደ ንብ መንጋ በአንድ ዐይነት መቀጣጠል የሚተምም ጉባኤ
ወዴት አለ? ገና እግሮቼ ጉባኤ ሲረግጡ ሰባኪና ዘማሪ
ባልቆመበት መድረክ እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝረኝ፤ እንደ
እናት እጅ የሚዳስሰኝ፤ በውስጤ የጌታን ፍቅር እያፍለቀለቀ
በደስታ ይፈነቅለኝ የነበረ መንፈስ ወዴት ሄደ? ችግሩ ያለው
እኔ ዘንድ ነው ወይስ ጉባኤው ዘንድ ብዬ ራሴን በድንጋጤ
እጠይቃለሁ።

16
ጆንሰን እጅጉ

ይሁን እንጂ ፈራ ተባ እያልኩ የተበላሸወን ተረድተን፣


መፍረስ ያለበትን አፍርሰን፣
አንዳንድ አማኞችን ተጠግቼ
መጣል ያለብንን ጥለን፣
ስጠይቅ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ የተሓድሶ እሳት ለመለኮስ
እንድንችል የችግሩን መንስኤ
መሆናቸውን የሚጠቁመኝን ፈልገን ማግኘት ይገባናል።
ስሜቴን የሚጋሩበት ምላሽ
እሰማለሁ። ደግሞም ዞር በማለት በትዝታ ሠረገላ ወደ ኋላ
ስመለከት ያ የምናፍቀው ጉባኤ የነበረበት ዘመን አሁን
የሚታዩት ለውጦችና መስፋፋቶች የማይታዩበት፤ እኔም
ጽድቅና ኃጢአትን በቅጡ ያልለየሁ ስሜት የሚነዳኝ
እንቦቃቅላ የነበርኩበት ዘመን ሆኖ ይታየኛል። በዚያን የቅርብ
ዕሩቅ በሆነብኝ ዘመን እኮ ቤተ ክርስቲያን ገና አልተስፋፋችም
ነበር። ብዙ ነብያትና ዘማርያንም አላፈራችም። አሁን ያላት
የኢኮኖሚ ዐቅምና የሙዚቃ ጥበብ አልነበራትም። አዳራሾቿ
ከአራት መቶና አምስት መቶ መቀመጫ በላይ የላቸውም
ነበር።

ታዲያ ምን ሆነናል? ምንድር ነው የጎደለን? ለውጥ መቀበል


ስላቃተን!? “ድሮ”ን ናፋቂዎች ስለሆንን? ወይስ በረከቱን
እንዳንካፈል በኤልሳዕ ዘመን ባለማመኑ ምክንያት መለኮት
ገለል እንዳደረገው አለቃ ዐይናችን ተጋርዶ ይሆን? (2 ነገ. 7፡
2)። በፍጹም! ይሄ እንዴት ይሆናል? ስለ አገራችን ክርስትና
ከፍ ማለት፣ ስለ ለውጥና ተኃድሶ ተጨንቀናል! የቤተ

17
የአማልክቱ ዐዋጅ

ክርስቲያንንም ሆነ የአገራችንን የከፍታ ዘመንን የሚጠቁሙ


ትንቢቶች ስንሰማ በደስታ ሲቃ በአሜንታ ጮኸናል።
አልቅሰንስ የጸለይን እኛን እንዴት የልመናችንን መልስ
እንዳናስተውል ንጉሡን ተደግፎ በኤልሳዕ ትንቢት
እንደዘበተው አለቃ መለኮት ዐይናችንን ይጋርደናል? ይሄ
በጭራሽ አይሆንም። አንዳች ከዚህ የተለየ ምሥጢር የሆነብን
በውል ያልተረዳነው ተጽዕኖ የጉበኤዎቻችንን መንፈሳዊ
ጣዕም እንዳጠፋብን ይሰማኛል። ስለዚህ ቅይጡን ለይተን፣
የጎደለንን ዐውቀን፣ የተበላሸውን ተረድተን፣ ማሣኒውን
አፍርሰን፣ መጣል ያለብንን ጥለን፣ በተኃድሶ እሳት መለኮስ
እንዲሆንልን የችግሩን መንስኤ ፈልገን ማግኘት ይገባናል እንጂ
በፍጹም ችላ ማለት አይገባንም።

በዐዲስ አበባ ሥነ - መለኮት ኮሌጅ (ABC) ተማሪ በነበርኩበት


ወቅት “የእምነት ቃል” ልምምድ ከነበራቸው ከተለያየ አብያተ
ክርስቲያናት ከመጡ ጥቂት ተማሪዎች ጋር በክፍል ውስጥና
ከክፍል ውጪ የመገናኘት ዕድል
ይኸው ፍለጋውም መለኮት
ነበረኝ። ከእነዚህም ተማሪዎች ዓለምን በፈጠረበትና
ጥቂቶቹ በኅሩይ ዐዎንታዊ ቃል በሚያዝበት ስልጣን እንደቀና
ቢያሳብቅበትም አስተሳሰቡን
ዐዋጅ ላይ የተለየ እምነትና ለማጽናት ይረዱኛል ያላቸውን
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ዐስተሳሰብ እንዳላቸው
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ድረስ
ተመለከትኩ። ከእነዚህም ውስጥ ቧጧል።
ጆንሰን እጅጉ

ጥቂቶቹ መንበርከክም ሆነ ልመናን ወደ እግዚአብሔር


ማቅረብ የተዉ ነበሩ።

ይህንንም የተማሪ ማደሪያ ክፍል ይጋራኝ የነበረ ወዳጄ


በማደሪያ ክፍሉ የታዘበውን ሲነግረኝ “ከእኔ ጋር ማደሪያ
የሚጋራ የትምህርት ጓደኛዬ በፍጹም ተንበርክኮ አይጸልይም፤
ወዲያና ወዲህ እየተዘዋወረ የእምነት ቃል ነው
የሚያውጀው” ነበር ያለኝ። ከዚያ በኋላ ታዲያ የልምምዱን
ባህርይ፣ ጥቅምና ጉዳት መለየት ስለፈለግሁ መከታተል
ጀመርኩ። ይህንን ልምምድ በትምህርት ቤት ውስጥ ብቻም
ሳይሆን በአብዛኛዎቹ ዐዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አብያተ
ክርስቲያናት ጉባኤ ስብከት፣ ጸሎት እና ዝማሬ ላይ
በተደጋጋሚ በመመልከቴ አስተሳሰቡ ሥር እንዲሰድድ
ያደረገ፤ ለስብከቶች፣ ለጸሎቶችና ለዝማሬዎች አንድ ዐይነት
መልክ የሰጠ መናኛ የሆነ ትምህርት እንዳለ ለመገንዘብ
ቻልኩ።

የትምህርቱ ተጽዕኖ እየደበዘዘ ለመጣው መልካም የጉባኤ


ጠረን አንዱ ምክንያት ይሆን? የሚል ቀለል ያለ ጥርጣሬም
ተጫረብኝ። ይህንንም መፈለግና መፈተሽ እንዳለብኝ
ስላመንኩ የመመረቂያ ጽሑፌን በዚሁ ርእሰ ጉዳይ ላይ
አድርጌ በስፋት ለማጥናት ወሰንኩ። በመጨረሻም የጥናቱ
ውጤት ሲጠናቀቅ ከምጠብቀው በላይ አሳሳቢ የግራፍ ምስል

19
የአማልክቱ ዐዋጅ

አመላከተኝ። ከወንጌላውያን የእምነት አቋምም (ዶክትሪንም)


ሆነ ልምምድ እጅግ ሩቅ እንደሆነ የምናስበው የዲበ - አካል
ሃይማኖት ሰፊ ወረራ በማድረግ መካከላችን እንደገባ
ተገነዘብኩ። የጥናት ሙግቴን ባቀረብኩበት ሰዓት መምህሬ
ኤርሚሻ በየነ “ተጨማሪ ጥናት የሚፈልግ ልብ ያልተባለ ችግር
ነው።” በማለት የሰጠኝ አስተያየት የበለጠ የገባንበት ችግር
በመመልከት በተኃድሶ ቅናት እንድነሳሳና ይህንን መጽሐፍ
ለመጻፍ እንድወስን ገፋፍቶኛል።

የኅሩይ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ልምምድን ውጤት በመመልከት


መመሰጥ ጭልጥ ወዳለ ጥፋት ያስገባል። ምንም ምልክት
እንደሌለው ማሰብም ዐዋጅ ወለድ የሆኑ ሐሰተኛ
ተዓምራትን የሉም ብሎ መሸምጠጥ ነው። ስለዚህም ነገሩን
ለመመርመር ቀዳሚው ጥያቄ መሆን ያለበት የኅሩይ ዐዋጅ
ቃል ልምምድ ይሠራል ወይስ አይሠራም የሚል ውጤት
ተኮር የሆነ ጥያቄ ሳይሆን በምን? ወይም ለምንድነው?
የሚሠራው የሚለው ምንጭን ወይም መነሻን የማጣራት
ጥያቄ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ሐሰተኛ ምልክቶች ለጊዜው
ያመጡት ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሚያስከትሉት ዘለቄታ
ያለው መንፈሳዊ ፋይዳ ወይም የውጤቱን ውጤት መመዘን
አለበት። በርሜል ቡኾ ውስጥ የገባች ጥቂት እርሾ ምንም
አታመጣም ብሎ ችላ ማለትና መናቅ እንደማይቻል ሁሉ ይህ

20
ጆንሰን እጅጉ

ስኹት ትምህርት በመንፈሳዊ ዕድገት ላይ የሚያስከትለውን


ተጽዕኖ መካድ አይቻልም። ስለዚህም ለሥነ - መለኮቱ መነሾ
ዘርና ለውጤቱ ውጤት ትኩረት በመስጠት መፈተሽ ይገባል።
ጠንከር ብለንም ከሥር ከመሠረቱ ለመንቀለል ስለሚያግዘን
በዚህ ደረጃ መመልከት አግባብ ነው።

ከእ.ኤ.አ 1960 አካባቢ ጀምሮ “የእምነት ቃል እንቅስቅሴ”


የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ በሚል መሸፈኛ በመሸፋፈን
ራስን የመካድና ስለ ጌታ ስም መከራ የመቀበልን እውነት ወደ
ጐን በመተው፤ ካመንንና ለቃሉ በመታዘዝ ካወጅን በምድር
ባሉ መልካም በረከቶች ሁሉ እንባረካለን የሚል ዓርማ ዐንግቶ
ተነሳ። ከኮሚኒስትና ከእስልምና አገራት ውጪ ባሉ አገራት
ውስጥ ፈርጣማ ዓለም አቀፍ ንቅናቄን በመፍጠር ለብዙ ቤተ
- እምነቶች መከፈትና የአባላት ቍጥር መጨመርም
ምክንያት ሆነ። እንቅስቃሴው ከኋላ ያስከተለውን እኩይ አደጋ
ችላ በማለትም በዐዎንታዊነት የተመለከቱም ብዙ ናቸው።

“የእምነት ቃል እንቅስቅሴ” ገና ከመነሻው በዲበ - አካል


ሃይማኖት ፍልስፍና ቀመር የተነከረ እንደነበር በርከት ያሉ
ጥናቶች ያመላክታሉ። ይህም ፍልስፍና “ለቃል” የሚሰጠው
ግምት ላቅ ያለ ነው። ሃይማኖቱ “ቃል” በመላለም ውስጥ
ከኒዩክለር ይልቅ ይበረታል ብሎ ያምናል። ይህንኑ የቃልን
የማድረግና የመወሰን መላምት ወደ “አምላካዊ ሙላት”

21
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወይም አማልክትነት የመድረሻ ተስፋ አድርጎ በመውሰድም


ለማሳመን ዳክሯል። ትምህርተ ሰብዕንና ትምህርተ መለኮትን
አጉድፏል። ይኸው ፍለጋውም መለኮት ዓለምን በፈጠረበትና
በሚያዝበት ስልጣን እንደቀና ቢያሳብቅበትም አስተሳሰቡን
ለማጽናት ይረዱኛል ያላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ድረስ ቧጦ ራሱን ደብቋል።
ወንጌላውያን አማኞችም የእንቅስቃሴውን ታሪካዊ ሥር
ፈልገው ከመንቀልና በክርስትና ላይ ያጠላውን አደጋ
አምርረው ከመቃወም ይልቅ ችላ ብለውታል። እንደ ዋዛ
በመመልከትም “ቀላል ስሕተት” ነው በሚል ወንጀል
ማቅለያ በመመልከት እየተዘፈቁበት መሆኑ የርትዕ
ትምህርትን ቀጣይነት አሳሳቢ አድርጎታል።

ቅኝት ሁለት
“የእምነት ቃል እንቅስቅሴ” መሪዎችና ፍልስፍናቸው በሩቅ
ምስራቅ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ የበቀለ ቢሆንም
በዚህ መጽሐፍ ትኩረት ተደርጎባቸዋል። የዚህም አንደኛው
ምክንያት ፍልስፍናቸው በዘመንና በስፍራ የራቀ ቢሆንም
ለአገራችን ክርስትና እጅግ ቅርብ በመሆኑ ምክንያት ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ብዙዎቻችን በቅርበት ወይም በርቀት
የምናውቀውን “የእምነት እንቅስቃሴ” ዋነኛ ስኹት ሥርው
መርምረን ለመረዳት ወደ ሩቅና መካከለኛው ምስራቅ

22
ጆንሰን እጅጉ

ጥንታዊና አሁናዊ የዲበ - አካል ሃይማኖት ፍልስፍና መሄድ


ግድ ስለሚሆንብን ነው። ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ
አብዛኛው የአገራችን አገልጋይ ወይም አማኝ እንዲሁ በጥቅሉ
ፍልስፍናን የጎሪጥ ከማየቱም በላይ እርሱ ከያዘው ክርስትና
ሩቅና ለክርስትና የማይጠቅም ወይም በክርስትና ላይም
ምንም ተግዳሮት የሌለው አድርጎ የሚቆጥር ቢሆንም ፈጽሞ
ስኹት እና ከእውነት የራቀ ስለሆነ ይህንን ግልጽ ለማድረግ
ነው። ይህ መጽሐፍ ይህንን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና
ይጫወታል። ስለዚህም ርእሰ ጉዳዩን የማንበብ ፍላጎት
ቢኖረንም ባይኖረንም የጠራ አቋም እንዲኖረን፣
የተበከልንበትን እንድንለይ ወይም እንዳንበከል ለራሳችንና
ለምንወዳቸው መጠንቀቅ እንድንችል የዲበ - አካል
ሃይማኖትን የታሪክ አንደምታ መመርመር ግድ ይሆንብናል።

ስለዚህም ቀለል ያለ ግንዛቤ ለማግኘት እንዲረዳን በማለት


በዚህ መጽሐፍ የዲበ - አካል ሃይማኖትን ታሪካዊ ዳራ
የሚዳስሱ በርካታ ጥናቶችን በመመልከትና በማካተት
ምርምሮች ይደረጋሉ። የራሴን አዲስ ግኝት በማካተትም
ግላዊ ትንታኔዬን በራሴ ልዩ አቀራረብ አስቀምጣለሁ።
በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ከመጽሐፉ ርእሰ ጉዳይ ጋር
ተያያዥነት ያላቸውን አገርኛ የጽሑፍ መረጃዎችንና

23
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአገራችን የሚታዩ ጥቂት ሥነ - መለኮታዊ ልምምዶችን


በተጨባጭ መረጃ አካትታለሁ።

በክፍል “1” ምዕራፍ “1” ላይ ከላይ እንደተጠቆመው ቀደምት


ጥናቶችንና መሰል ምንጮችን በመጠቀም የዲበ - አካል
ሃይማኖትን ታሪካዊ ዳራና የመሪዎቹን ሚና ለመገንዘብ
እንድንችል የአስተምህሯቸው ዕድገት በታሪክ ቅደም ተከተል
ይብራራል። የዲበ -አካል ሃይማኖት ግንባር ቀደም መሪዎች፣
ግዙፍ ድርጅቶቻቸውና ከፍተኛ አስተዋጽዖ ለማድረግ
የተጠቀሙባቸው መጻሕፍት ይጠቀሳሉ። ይህም ክፍለ ዘመን
ጠገብ ፍልስፍናው እንዴት በቤተ ክርስቲያን እንደሰረገ ለማየት
የምንችልበትን ዕድል ይፈጥርልናል። ይህም ጠለቅ ያለ የታሪክ
አንደምታን ለማወቅ ለሚፈልጉና የሥነ - መለኮት ጥናት
ለማድረግ ለሚሹ አንባብያን ጭምር እንዲረዳ ታስቦ
ተዘጋጅቷል።

በክፍል “2” ምዕራፍ “1” የዲበ - አካል ሃይማኖትና የእምነት


እንቅስቃሴ ጥምረት የፈጠሩበት ዋነኛ የጋራ ጽንሰ - ዐሳብና
ተግዳሮቱ ይተነተናል። በምዕራፍ “2” የዲበ - አካል ሃይማኖት
“የቃል ኀይል” ጽንሰ - ዐሳብ ፍልስፍና የእምነት እንቅስቃሴን
ቀኝ እጁ በማድረግ ወደ ክርስትና ያደረገው ሽግግርና ዓለም
አቀፋዊ ሥርጭቱ ይተነተናል። በምዕራፍ “3” “የቃል ኀይል”
ጽንሰ - ዐሳብ ሥነ - መለኮት በኢትዮጵያ ክርስትና

24
ጆንሰን እጅጉ

የሰረገባቸው መንገዶችና አመለካከቶች ይነሣሉ። በምዕራፍ


“4” ደግሞ “የቃል ኀይል” ጽንሰ - ዐሳብ ዋና ዋና የአሠራር
ዘውጎች ይተነተናሉ።

በክፍል “3” ምዕራፍ “5” የዲበ - አካል ሃይማኖት ፍልስፍና


የወለደው ልምምድ በኢትዮጵያ ክርስትና ላይ ያሳደረውን
ተጽዕኖ ለመታዘብ እንድንችል የሚያግዙ በነባር አብያተ
ክርስቲያናትና በአዲሶቹ የእምነት ቃል አራማጆች መኻል
ከሚታዩ ተመሳሳይ ልምምዶች ጥቂት አስረጂ ምሳሌዎች
ይነሣሉ።

በክፍል “4” በምዕራፍ “6” የዲበ - አካል ሃይማኖት ፍልስፍና


የተጣባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በስፋት ይነሣሉ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የሥነ - አፈታት ችግሮችን በማረም
ለአገልጋዮችም ሆነ ቃሉን ማጥናት ለሚወዱ ሁሉ የሚያግዝ
ሃቲታዊ የሥነ - አፈታት መርሕ በእግረ መንገድ ይመላከታል።
ይህንንም ለማሳለጥ የጥቅሶቹ ፍቺ በንጽጽርና በግልጽ
ይቀመጣል።

በክፍል “5” ራሱን በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት እንቅስቃሴ


ሥር እየደበቀ በሚሽሎከሎከው የእምነት እንቅስቃሴና የዲበ -
አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ላይ ቤተ ክርስቲያን የምትነቃበት
ደወል ይደወላል። በቀጣይነትም በምዕራፍ “7” እና “8” የዲበ -

25
የአማልክቱ ዐዋጅ

አካል ሃይማኖትም ሆነ የእምነት እንቅስቃሴን የኅሩይ ቃል


ዐዋጅ ጽንሰ - ዐሳብን ተቀባይነት የሚያሳጡት ሥነ -
መለኮታዊ ዕውነታዎች ይዳሰሳሉ። በመጨረሻም በምዕራፍ
“9” ላይ የርቱዕ ሥነ - መለኮትና የሥነ - አፈታትን መርሖ
የሚያዛቡ ዝንባሌዎችን በመኮነን ልጓም የሚሆኑ ጭብጦች
ተነሥተው ቤተ ክርስቲያንን ለተሓድሶና በመንፈስ ቅዱስ
ለሚሆን እውነተኛ መነቃቃት በማነሣሣት ይጠቃለላል።
ይህም ትክክለኛና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእምነት መሠረትና
የጸሎት ሕይወት እንዲኖራቸው የሚሹ የተሓድሶ አርበኞች
የራሳቸውን ሕይወትና በአካባቢያቸው ላይ ያለውን
እንቅስቃሴ ማየትና መለየት የሚችሉበትን ብርሃን
ለመፈንጠቅ ያኽል የተደረገ ነው።

ላለፉት ሦስት ዐመታት ሳልሰለች ያለማቋረጥ ይህንን


መጽሐፍ ያዘጋጀሁበት ዋነኛ ምክንያት የክርስቶስን አካል
ለማነጽና የድርሻዬን ለመወጣት በማሰብ ነው። ዐላማዬም
በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ስም እየተንሰራፋ ያለውን የዲበ
- አካል ሃይማኖት የቃል ኀይል ሥነ -መለኮትንና የልምምዱን
መሸፋፈኛ ገልጦ ማሳየት፣ የዲበ - አካል ሃይማኖት የቃል
ኀይል ፍልስፍና የእምነት እንቅስቃሴ ዋነኛ ሥርው እንደሆነ
ማረጋገጥ፣ የምንመለስበትን የንስኃ ዐቅም ማጎልበትና
የመጽሐፍ ቅዱስን ስልጣን ያማከለ አተረጓጎምንና ጤናማ

26
ጆንሰን እጅጉ

መንፈሳዊ ልምምድን በማነቃቃት የተሓድሶ ብርሃን


ለመፈንጠቅ ነው።

በአጠቃላይ “የአማልክቱ ዐዋጅ” መጽሐፍ ችግሮችን ከርቀት


ከመጠቆምና ከመነካካት ይልቅ በጥቅስ የተሠሩ
መሸፈኛዎችን በመግፈፍ፣ በቁርጠኝነትና በድፍረት ወደ
ሰልፍ በነፃነትና በግልጽነት ወደ ሰልፍ ዘው በማለት
እንዲጀግንና ሸንቆጥ የሚያደርግ ይዘት እንዲኖረው
ተደርጓል። ይህ ድፍረትን ከእውነት ጋር ያጣመረ አቀራረብም
መጽሐፉን በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለ
ዕድሜ ጠገብ የሰው ዐሳብ በማፍረስና የክርስቶስን ቤተ
ክርስቲያን አማልክቱ ካሰናዱላት ውድቀት በመታደግ ወደ
ተሓድሶ ክብር ለመግባት እንድትችል አጋዥ የሚሆንበት
ዐቅም እንዲኖረው ይረዳዋል። ከእግዚአብሔር ጐን ነኝ
ለሚል፤ ለእውነተኛ ተሓድሶ በፍጹም ቅናት መታጠቅ
ለሚወድ፤ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት እንዲቀጣጠልና
ሳይበከል እንዲዘልቅ ለሚሻ የእምነት አርበኛ ወንጌላዊ አማኝ
ይህ መጽሐፍ ጨለማን የሚገልጥ የብርሃን ወገግታ በመሆን
ከፍተኛ አበርክቶት ይኖረዋል።

እንደ ማሳሰቢያ ማንሳት የምፈልገው ይህ መጽሐፍ የመረጃና


የዐላማ ውስንነት የለውም ማለት እንደማይቻል ነው።
ለምሳሌ የሚቀርቡ ምሳሌዎችና ትምህርቶች በውድድር

27
የአማልክቱ ዐዋጅ

በልጠው ስለተገኙ ወይም መድልዎ ተደርጎባቸው ሳይሆን


በቅርብ ስላገኘኋቸውና የሚነሱ ሐሳቦችን ለማሣያነት በቂ
ስለሆኑ ብቻ የተቀመጡ ናቸው። ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር
ተያያዥነት ያላቸው የተለመዱ ደቂቅ ትምህርቶችም
እንዲሁ ከትኩረት አቅጣጫ ውስንነት የተነሣ ሁሉም
አይዳሰሱምና አንባቢ “ለምን አልተካተተም” የሚል ቁጭት
እንዳይገባው አሣስባለሁ። በጥቅሉ “የአማልክቱ ዐዋጅ”
መጽሐፍ ዐቃቢ እምነት ባሕርይ ያለው እንደመሆኑ መጠን
“የኅሩይ ዐዎንታዊ ዐዋጅ” ሥነ -መለኮትን ሥርና ዕድገት
ለማግኘት ወደ ሰፊው የታሪክ ዓለም ጠልቆ በመግባት
እንዲመረምር፣ እንዲዳብርና እንዲሞግት ለማድረግ
ይሞከራል። የሥነ - መለኮትና የሥነ-አፈታት ክፍተቶችን
ተከትሎ በመኻላችን የገባውን የእምነትና የልምምድ ጥመት
ማሣያ ምሳሌ የሚሆኑ መረጃዎችን በዐገር ውስጥ ጭምር
እንዲያካትቱና በታሪክና በእግዚአብሔር ቃል እዲፈተሹ
በማድረግ ሊያቀና የሚችለውን የቃሉን ምልዐት፣ እውነትና
መፍትሄ አስቀምጣለሁ።

በአጠቃላይ የእምነት ቃል እንቅስቃሴን ሥነ - መለኮት ዋነኛ


ሥርው ፈልቅቄ በማውጣት በትምህርተ ሰብዕ፣ በትምህርተ
መለኮትና በመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ - አፈታት ላይ የፈጠረውን
ተጽዕኖ በጥልቀት እቃኛለሁ። በመጨረሻ መጽሐፉ ከሩቅ

28
ጆንሰን እጅጉ

ታሪክ በመነሣት ቀስ እያለ ወደ መኻል እየገባና እየቀረበን


የሚመጣ ስለሆነ የአንባቢን ሰፊ ትዕግሥትና አስተውሎት
እንደሚፈልግ በማሳሰብ መልካም ንባብና የተሓድሶ ዘመን
እንዲሆንልን እመኛለሁ

መልካም ንባብ

29
የአማልክቱ ዐዋጅ

ክፍል፩
ታሪካዊ አንደምታ

  

30
ጆንሰን እጅጉ

ምዕራፍ 1

የፍተሻ ጉዞ

መቼም ለገበያ የሚሆኑ አትራፊና ተፈላጊ ምርቶችን


ማቅረብ የአቅራቢ ድርጅቶች ድርሻ እንደሆነ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የምርቶቹን ጤንነትና ጥራት የሚቆጣጠሩ
አካላት በማኅበረሰቡ ውስጥ መኖር አለባቸው። ይህም
አቅራቢው ክፍል ለትርፍ ካለው ጕጕት የተነሣ የማኅበረሰቡን
ኑሮና ጤንነት ጥራታቸው በወረደ ከብክለት ባልጸዱ ምርቶች
እንዳያቃውስ ለመገደብ ይጠቅማል። ይህም ክትትል
ከማምረቻ መሣሪያው እና ከምርት ግብዓቶች ጀምሮ
የሚደረግ ቢሆንም ዐልፎ ዐልፎ ከዚህ ክትትልና ቁጥጥር
አምልጠው ወደ ገበያ የገቡ ምርቶች ያጋጥማሉ።

31
የአማልክቱ ዐዋጅ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መስሪያ ቤት


(EFDA) ሐምሌ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ለፋና ብሮድ ካስት ኮርፖሬት
(FBC) መግለጫ ልኮ ነበር። ፋና ብሮድ ካስት ኮርፖሬት ይሀንን
መግለጫ ጠቅሶ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ባለስልጣን
መስሪያ ቤቱ ቁጥጥሩን አምልጠው ወደ ገበያ ዘልቀው በገቡ
ምግቦች ላይ ባደረገው ጥናት አደገኛነታቸውን ደርሼበታለሁ
ሲል 57 የሚሆኑ የምግብ ዓይነቶችን ኅብረተሰቡ
እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ ብሏል። ይኸው የጤና ቁጥጥር
ባለስልጣን መስሪያ ቤት የምግቦቹን ዝርዝር በመግለጥ
የምግቦቹን መሠረታዊ ችግርም በመግለጫው አስፍሯል።
በተጨማሪም ምርቶቹ የኅብረተሰቡን ጤንነት አደጋ ላይ
የሚጥሉ ስለሆነ ከገበያ እንዲሰበሰቡና እንዲወገዱ ትዕዛዝ
ማስተላለፉን ፋና ጨምሮ ጠቅሷል።2 ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ
ይህንን ያደረገው በባዶና በግብታዊ ስሜት አልነበረም።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል
ኃላፊነትና ስልጣን ብቻ ሳይሆን የገበያውን ምርት
የሚመረምርበት የተቀመረ መለኪያ ስላለው መረጃዎቹ
ብሔራዊ ተአማኒነትና ተቀባይነት ያላቸውም ናቸው።

የቤተ ክርስቲያንም መሪዎች፤ የመጋብያን፣ የአስተማሪዎች፣


የነብያትና የሌሎችም አገልጋዮች ቀዳሚ ድርሻም እንዲሁ

2
Fana Broadcasting Corporate S.C July, FBC, (10, 2011), at 11:04 AM.

32
ጆንሰን እጅጉ

ለሕዝቡ ጆሮና ልብ የሚደርሱ መልዕክቶች ሳይበከሉ


እንዲደርሱ ከመሠረቱ ጀምሮ በጥንቃቄና በትጋት መሥራት
ነው። ሁለተኛው የኃላፊነት ድርሻ ደግሞ በአንድም በሌላም
መንገድ የተበከሉ ትምህርቶች ተሰራጭተው ከሆነ
ሕዝባቸውን ማስጠንቀቅና ተለይተው እንዲወገዱ ማድረግ
ነው። ምክንያቱም የተበከሉ ትምህርቶችና ልምምዶች
በመድረክ እና ከመድረክ ውጪ ባሉ የመረጃ ግንኙነቶች
አማካኝነት አምልጠው ወደ ሕዝብ ሕይወት ስለሚገቡ ነው።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ


ቤት እንዳደረገው ቤተ ክርስቲያንም ሾልከው የገቡ
ትምህርቶችን የሚያጠና፣ የሚከታተልና የሚቃወም ፈታሽና
ጠያቂ የዐቅበተ እምነት አካል ሊኖራት ይገባል። በመጋብያን፣
በአስተማሪዎችና በወንጌላውያን ቢሮ ሥር የአምልኮ፣
የምስክርነት፣ የጸሎት፣ የስልጠናና የጋብቻ አገልግሎት
ቡድኖችንና መርሃ ግብሮችን እንደምታደራጅ ሁሉ የዐቅበተ
እምነት አገልግሎትንም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ትኩረት ሰጥታ
ልታደራጅና ልታበረታታ ይገባል። ይህ ሲሆን ስሕተትን
የመከላከል አገልግሎቷን በማነቃቃትና በማቀላጠፍ ከውስጥም
ይሁን ከውጪ የሚነሱ ትምህርቶችን በመመከት የአማኞች
ሕይወት ጤናማና የተረጋጋ እንዲሆን በቀላሉ ለመርዳት
ያስችላል።

33
የአማልክቱ ዐዋጅ

በብሉይ ኪዳን ዘመን የጣዖት ትምህርት የተጠላና ባዕድ


እንደሆነ እስራኤላውያን እንዲያውቁ ከመጀመሪያው ግልጽ
ተደርጎላቸው ነበር። ይሁን እንጂ የጣዖት አስተምህሮ በሕዝቡ
መኻል እየሰረገ ያውክ እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት
ይጠቁማሉ። ለእስራኤል ነብያትም ይህንን መቈጣጠር ከባድ
ፈተና ቢሆንም በየጊዜው የሕይወት ፍተሻና ማስተካከያ
በማድረግ ተሓድሶን ለማምጣት ካለማቋረጥ ደክመዋል።
በየጊዜው የህዝባቸውን ሕይወት እየተጫነ የሚያዘቅጠውን
የአህዛብ የጣዖት አምልኮ ልምምድና ትምህርት ተጽዕኖ
መታገል ቋሚ ሥራቸው ነበር። በአጠቃላይ ነብያቱ ጣዖታቱን
ያላፈረሱበት የትምህርቱን ከንቱነት በመዘርዘር
ያልተቃወሙበትና የሕዝባቸውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ
ለማረቅ ያልሞከሩበትና አልፈውም ከነገስታቱ ጋር
ያልተጋጩበት ዘመን አለ ለማለት ያስቸግራል። (ዘጸ.32፣20፣
ኢሳ.44፣10-20)።

በዘመን መጨረሻ ወደ ትምህርታቸው ለጆሮአችን


ተወለደችው የአዲስ ኪዳን ልምምዳቸው ለዓይናችን
ቅርብ ነውና ተሐድሷዊ ፍተሻ
ቤተ ክርስቲያንም ስንመለከት ለማድረግ ስንነሳ መጀመር
እንዲሁ፤ ፍተሻዋ ያለብን ከራሳችንና
ከጉባኤያችን መሆን አለበት።
በትምህርትና በሕይወት
አቅጣጫ ሊሆን እንደሚገባ እናስተውላለን። በሌላ ቋንቋ
ጆንሰን እጅጉ

ፍተሻው ለሕዝቡ ቅርፅ እየሰጠ ካለው የዐስተሳሰብ ወይም


የትምህርት ቅርፅ ማውጫ (ሞልድ) እና በሕዝቡ ላይ
ከሚንጸባረቀው መልክ በመነሣት ተሓድሶን ለማምጣት
የሚደረግ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ከሞራል መበላሸት
ተግዳሮት ባሻገር አጋንንታዊ የሆኑና ውስብስብ አሳች
ትምህርቶች እንደሚፈልቁና በመካከሏ እንደሚሆኑ ቅዱሳት
መጻሕፍት በስፋት ያሳስባሉ። ኢየሱስ ከሐሰተኞች
እንድንጠነቀቅ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቷል።
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን
ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነብያት
ተጠንቀቁ።”(ማቴ. 7፣15)። ኢየሱስ በዚህ ንግግሩ እነኝህን
ሐሰተኞች ለመመለስ ከመጣር ይልቅ የመጠንቀቅን
አስፈላጊነት አስምሮበታል።

አንዳንዶቻችን እንደምናስበው ሐሰተኞች ከቤተ ክርስቲያን


ርቀው ያሉና አጠገባችን የማይደርሱ አይደሉም። “ነገር ግን
ሐሰተኞች ነብያት ደግሞ በሕዝቡ መኻል ነበሩ እንዲሁም
በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤
እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት
በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ።”
(2 ጴጥ. 2፣1)። ትምህርታቸው ለጆሮአችን ልምምዳቸው
ለዓይናችን ቅርብ ነውና ተሐድሷዊ ፍተሻ ለማድረግ ስናስብ

35
የአማልክቱ ዐዋጅ

መጀመር ያለብን ከራሳችንና ከጉባኤያችን መሆን አለበት።


ምክንያቱም እነኝህ ሰዎች እንዴት ሾልከው እንደሚገቡ
ያውቃሉ። “ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች
ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና።” (ይሁ 1፣ 4)።

ሐዋርያቱን ያየን እንደሆን ከማስጠንቀቅ አልፈው መፈተሻ


የእምነት መርሖ ያስቀምጡ ነበር። ለምሳሌ በዘመኑ የነበረውን
የኖስቲዝም ትምህርት3 ለመለየት እንዲያስችላቸው “ኢየሱስ
በሥጋ እንደመጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር
አይደለም።”(2 ዮሐ. 1፡20፣ ሐሥ. 15፡23-29)። በማለት
አሳውቀው ነበር።

ሐዋርያቱ ይህንን የመሳሰሉትን


የእምነት መርኾች ሲያስቀምጡ ከሐዋርያት ልምድ በመነሳትም
‘የትኛው ትምህርት ከቀደሙት
መሠረታዊ መመዘኛቸው ሐዋርያትና ነቢያት ትምህርት
ከኢየሱስና ከነብያት ትምህርት የተለየ ነው?’ የሚለው መጠይቅ
መሠረታዊ የተሓድሶ መመዘኛ
ጋር መስማማቱን ወይም እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል።
ታሪካዊ ዝምድናውን አመሳክሮ
ማረጋገጥ ነበር። ለምሣሌ ያኽል በእግዚአብሔር የአድኅኖት
ገቢር አማካኝነት የእስራኤል መታደስ ተስፋ ፍጻሜ የአሕዛብ

3
የኖስቲሲዝም፦ ኖስቲሲዝም ቁሳዊ አካል ሁሉ ርኩስ መንፈስ ደግሞ ቅዱስ ነው፣
የሰው ነፍስ በእውቀት ከቁሳዊ አካል ነፃ በመውጣት ትድናለች የሚል የግሪክ
ፍልስፍና የሚከተል ሃይማኖት ነው።
ጆንሰን እጅጉ

መካተት Gentile Inclusion አስቀድሞ በነብያትም መነገሩን


በመጠቆም የኢየሩሳሌም ጉባኤ ወስኖ ነበር። የውሳኔውን
ትክክለኝነት በተመለከተ ያዕቆብ አጽንዖት ሲሰጥ “ከዚህም
ጋር የነብያት ቃል ይሰማል፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ።”
(ሐሥ. 15፡15)። በማለት አስረድቷል።

ከዚህ የሐዋርያት ልምድ በመነሣትም ‘የትኛው ትምህርት


ከቀደሙት ሐዋርያትና ነብያት ትምህርት የተለየ ነው?’
የሚለው መጠይቅ መሠረታዊ የተሓድሶ መመዘኛ እንደሆነ
ማስተዋል ይቻላል። (ገላ. 1፡8-9)። ይህንንም ሐዋርያው
ጳውሎስ ሲያጸና “በሐዋርያትና በነብያት መሠረት ላይ
ታንጻችኋል።” (ኤፌ. 2፡20) ይላል። ከዚህ መርሖና መመዘኛ
ለማምለጥና ወደ ልቅ ልምምድ ለመግባት እንዲያመች
“ከሐዋርያት በሰባት እጥፍ ብልጫ ባለው ቅባት ተቀብቻለሁ።”
ማለት ወይም ሐዋርያቱና ነብያቱ ያላወቁት ነገር ተገለጠልኝ
ማለት አያዋጣም። በተጨማሪም “ውሻ በቀደደው ጅብ
ይሾልካልና” መሠረታዊ የትምህርት ስሕተትና ጥቃቅን ሕጸጽ
በማለት መከፋፈሉ አይጠቅምም። የትኛውም
ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማማ ትምህርትም ይሁን
ልምምድ ከአጋንት እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል።

ጳውሎስ ፊት ለፊት ኬፋን እንደተቃወመውና ይህንን


በማድረጉ ያስከተለውን ትልቅ ለውጥ ስንመለከት ስሕተትን

37
የአማልክቱ ዐዋጅ

ፊት ለፊት መቃወም ሥነ - ልቦናዊና ማኅበራዊ ዋጋ


ሊያስከፍል የሚችል ቢሆንም ተገቢና አስፈላጊ የተሓድሶ
ሥራ እንደሆነ እንገነዘባለን። ጳውሎስ ጴጥሮስን የተቃወመው
ለምን ነበር? መአድ ላይ ያደርግ የነበረው እንደ ጌታ ቃል
ስላልነበረ ነው። ምክንያቱም ድርጊቱ የተለመደና ቀላል ሊባል
የሚችል ቢሆንም ድርጊቱን ይመራው የነበረው ትምህርት
አደገኛና ክፉ ነበር። ጴጥሮስ ከኢየሩሳሌም የመጡ አይሁዶችን
ሲመለከት ከአህዛብ ጋር አብሮ ከመመገብ ያፈገፍግ ነበር።
ይህም በአይሁድ ትምህርት “ከአህዛብ ጋር መመገብ ያረክሳል”
ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ይህ ደግሞ አህዛብ ከአይሁድ ጋር
አብረው የታረቁበትንና በክርስቶስ ደም በመቀደስ አንድ
ከሆኑበት የወንጌል አስተምህሮ ጋር ይቃረናል፤ በእንጭጩ
ሊቀጭ የሚገባው አደገኛ አካሄድ ነበር። (ኤፌ. 5፡5-6)።

ጴጥሮስ አመለካከቱን የተቆጣጠረውን ይህንን የአይሁድ


ዐስተሳሰብ በትምህርት መልክ ባያስተላልፈውም በድርጊቱ
እያስተላለፈ ነበር ማለት ይቻላል። ስለሆነም “መቼ አልኩ?
አላልኩም!” የሚል ማስተባበያ እዚህ ላይ አይሠራም።
ከእውነት የተፋለሰ ትምህርት ለጆሮአችን፣ ለልምምዳችንና
ለዓይናችን ቅርብ ስለሚሆን ተሐድሷዊ ፍተሻ ለማድረግ
ስናስብ ከራሳችንና ከጉባኤያችን ጨከን ብለን መጀመር
ያለብን ለዚህ ነው። “ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ

38
ጆንሰን እጅጉ

ፊት ለፊት ተቃወምሁት፣ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።”


(ገላ.2፡11-14)። በዚህ ታሪክ ላይ ጴጥሮስ ደረቅ ክርክርና
እልኽ ውስጥ ሲገባ አንመለከተውም። በመለኮታዊ ሸክም
ልባቸው የተያዘ ተሓድሶ ቀመስ የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን
የወቅቱ መሪዎችም እንዲሁ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ
መጽሐፍ ቅዱስን አይነኬ የተቀመረ መለኪያ አድርገው
በመጠቀም ስሕተትን ነቅሰው በመለየት፤ “ነገርን እንደ
አመጣጡ” እንደሚባል በንግግር ለሚተላለፍ በንግግር፤
በጽሑፍ ላለ ደግሞ በጽሑፍ መልስ እንዲሰጡ ይጠበቃል።
ይህ አቀራረብ በአንዳንዶች “ፍቅር የጎደለው!” ሊያስብላቸው
ቢችልም፤ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ የትምህርት መርኾች መጠበቅ
ተሟጋች መሆንም ይገባቸዋል። የሐዋርያትን ትኩረት
በተመለከተ መጋቢ ሰለሞን አበበ ገ/መድህን ሲናገር፦

የሐዋርያት መልዕክቶች ዋነኛ ትኩረታቸው በየጊዜው


የተነሱትን ኑፋቄዎች መጋፈጥ እንዲሁም
የአስተምህሮ ግድፈቶችንና የምግባር ዝንፈቶችን
ማረም ነበር። ከእርማቱ ተጋፍጦው ጐን ለጐን ደግሞ
ጤናማውን አስተምህሮ ማስተላለፍ ነበር። ይህ ደግሞ
የተሓድሶ ሥራ ነው። ለምሳሌ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ
ቅይጥነት ለገጠማቸው አብያተ ክርስቲያናት የጻፈው
የተሓድሶ መልክቶችን ነበር። 4 ብሏል።
4
የቱሩፋን ናፍቆት። (2007፣115) ።

39
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጠቃላይ ከነብያቱም ይሁን ከሐዋርያቱ ተጋድሎ መገንዘብ


እንደምንችለው ኑፋቄን ነቅሶ በመለየት ማፍረስ የተሓድሶ
ሥራ መሆኑን ነው። የብልሹ ሥነ - መለኮት መታደስ
የሕይወት ተሓድሶ መሠረት ነው። ይህ ሳይሆን ቀርቶ
መሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ መርሖ የማይመሩ ሲሆኑና ገበያ
መር ሲሆኑ ግን ኑፋቄን አቃፊ በመሆን ኢ - ተሐድሷዊ
ይሆናሉ። በተጨማሪም ከሚፈጥሩት ወቅታዊ የገበያ ግርግር
ባሻገር ዘልቆ የሚኖር ተአማኒነትም ይሁን ተቀባይነት
አያገኙም። ለመንጋቸው ኀላፊነት የሚሰማቸው መሪዎች ግን
መንጋቸውን የተበከለ ምግብ መመገብ ልባቸው አይፈቅድም።
ትክክለኛውን ሥራ በትክክለኛ መሣሪያ መሥራት ይመርጣሉ።
ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም በመከተል ለቃሉ
ባለቤት ታማኝ በመሆን የማያቋርጥ የሕይወትና የሥነ -
መለኮት ፍተሻ ያደርጋሉ። ብልህ መሪ ከወንጌል ጋር የተያያዘ
እንቅስቃሴ እየጨመረ እየሄደ እንደሆነ ሲመለከት ጤናማ
ቃናውን ያጣ የተበላሸ ልዩ ወንጌል አብሮ በመስፋፋት
እውነትን እንዳይከለክል ትጋትን ይጨምራል።

ያለንበት ዘመን የቤተ ክርስቲያን ይህ ሳይሆን ቀርቶ መሪዎች


በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎች
ተግዳሮት ምንድነው? ብለን የሚመሩ ሳይሆኑና ገበያ መር
ሲሆኑ ግን ኢ - ተኃድሷዊ
የጠየቅን እንደሆነ በዋናነት ራሱን ይሆናሉ። በተጨማሪም
ከዲበ - አካል ሃይማኖት ጋር ከሚፈጥሩት ወቅታዊ የገበያ
ግርግር ባሻገር ዘልቆ የሚኖር
ተአማኒነትም ይሁን ተቀባይነት
አያገኙም።
ጆንሰን እጅጉ

በመቀየጥ እየተስፋፋ ያለው የእምነት እንቅስቃሴ አስተምህሮ


ሆኖ ነው የምናገኘው። በመሆኑም ይህንን የርትዕ ሃይማኖት
ተግዳሮት ለመመከት እንዲቻል በመኻላችን ያለው
ትምህርትና ልምምድ ላይ ፍተሻና ክትትል ማድረግ
ይኖርብናል። ይህን ችላ የምንል ከሆነ ግን እውነተኛውን
ወንጌል ለትውልድ ማስተላለፍ ይቸግረናል። የምንወደውን
የጌታ ስም በየጊዜው በተለያየ መንገድ በመሸፈን የሚወረንን
የወንጌል ጠላት ፈጥነን በመንቃት የማንመክት እና
በመካከላችን ሾልኮ የገባውንም ኮቴውን ሰብረን የማንጥል
ከሆነ ውሎ አድሮ መንጋውን አስበልተን እኛም መበላታችን
የማይቀር ይሆናል። ከታሪክ ብንማርም፤ አንዳንድ የሃይማኖት
አባቶች ወደ ምትኃትና ድግምት አሠራር ዘወር ብለው
አብዛኛውን ሕዝብ ከእውነት የራቀ የሩቅ ተሳላሚ ብቻ
አድርገውታል። ስለዚህም የተዋዛ አካሄዳችንን ካላስተካከልን
የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር እኛም ጭልጥ ብለን
እንደማንጠፋ ምንም ዋስትና አይኖረንም።

ለወንጌላውያን የሥነ - መለኮትና የሕይወት ብክለት ቀዳሚና


ብቸኛው ተጠያቂ የእምነት እንቅስቃሴ መሪዎችና
ትምህርታቸው እንደሆነ ብዙዎቻችንን እንደሚያስማማን
ተስፋ አደርጋለሁ። የሥነ - መለኮት ተመራማሪዎች በጉዳዩ
ላይ ትኩረት አድርገው ማስተካከያ ለማድረግ የሚሠሩትም
ለዚሁ ነው። ይሁን አንጂ አስገራሚው ነገር ለዚህ ጥፋት

41
የአማልክቱ ዐዋጅ

የእምነት እንቅስቃሴ ወይም የብልጽግና ወንጌል እጁ


ቢኖርበትም ቀዳሚና ባለቤት አለመሆኑ ነው። የእምነት
እንቅስቃሴ ከራሱ የወለደው ወይም መሪዎቹ እንደሚሉት
ከእግዚአብሔር ቃል የተገለጠላቸው ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ
ሳይጣረስ የተወሰደ ሥነ - መለኮት እንደሌላቸው ጥናቶች
ያመላክታሉ።

የዚህ መጽሐፍ በጎ አስተዋጽዖ የእምነት እንቅስቃሴ የዲበ -


አካል ሃይማኖት (New Thought) ፍልስፍናና ልምምድ ወደ
ቤተ ክርስቲያን የመግቢያ በር ወይም መሸጋገሪያ ድልድይ
አልያም ማራገቢያ በመሆን ማቀጣጠሉን ማሳየት መቻሉ
ነው። ይህም የተደረገው የእንቅስቃሴውን አገርኛ ትምህርትና
ልምምድ በመቃኘትና ናሙናዎችን በመዘገብ ጭምር ነው።
መጽሐፉ የዲበ - አካል ሃይማኖትና የእምነት እንቅስቃሴ
ታሪካዊ ሥርው ጽንሰ - ዐሳብ “የቃል ዐዋጅ” ፍልስፍና እንደሆነ
ለማረጋገጥ በጥልቀት በመመርመር በአጽንዖት ይተነትናል።
ሰፊ ቦታ የተሰጠው ይህ ሙግት ደግሞ እስከ አሁን ድረስ
በርእሰ ጉዳዩ ላይ ከተሠሩ የውጪና የአገር ውስጥ ሥራዎች
የመጽሐፉን ይዘት ልዩ ያደርገዋል።

42
ጆንሰን እጅጉ

የዲበ-አካል ሃይማኖት ውልደትና ዕድገት


“የተኃድሶ መሠረቱ ቀዳሚ የነበረ እውነትን ዳግም መፈለግና ዘመን
የጫነበትን ድሪቶ ከከበረው ውርስ ላይ ማንሳት አይደለምን?” 5
መጋቢ ሰለሞን አበበ ገ/መድህን

የዲበ - አካል ሃይማኖት ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር ያለውን


ተዛምዶና ምንነቱን ለመገንዘብና በክርስትና ንጥር እውነት
ላይ ያረፉ ጫናዎቹን ለመረዳት ታሪክን ዘልቆ መመርመር
ግድ ነው። ክርስትና መሰሉ የዲበ-አካል ሃይማኖት በ 18 ኛው
ክፍል ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በኢማኑኤል ሲውዲንበርግ
ተጀምሮ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
ማደግ የቻለና እስካለንበት ክፍለ ዘመን ድረስ በመዝለቅ
በመላው ዓለም የተዳረሰ የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍና ነው።
በጥቅሉ ስለ መኖርና ቅድመ ኑባሬ ማለትም ከሚታየው ቁስ
አካል ዓለም ጀርባ ያለውን ምስጢር የሚተነትንና ምላሽ
የሚሰጥ ፍልስፍና ሁሉ ዲበ - አካል ሊባል ይችላል። ይሁን
እንጂ የዲበ - አካል ሃይማኖት የሚከተለው የፍልስፍና ዐይነት
ከዚህ የተለየና ልዩ ዲበ - አካል በመባል የሚታወቀውን ነው።

የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍና በአርስጣጣሊስ (Aristotle)


እንደተጀመረ ቢታወቅም አብዛኛዎቹ ቀጣይ ፈላስፎች
የየራሳቸውን የልዩ ዲበ - አካል መርሖ አዳብረዋል። ከዚህም
5
የቱሩፋን ናፍቆት። (2007፣ 106)።

43
የአማልክቱ ዐዋጅ

የተነሳ ፍልስፍናው ከተፈጥሮ ሳይንስ ዲበ - አካል ጋር ያለው


ልዩነት የዛኑ ያኽል ግልጽ እየሆነ ሄዷል። የዌስትሚንስተር
መዝገበ ቃላትን ዲበ - አካላዊውን ፍልስፍና በሁለት
ይከፍለዋል። በሚታይና በሚዳሰስ ጭብጥ ላይ የሚመሠረትን
የዲበ - አካል ፍልስፍናን ገላጭ ዲበ - አካል (descriptive
metapyhscis) ሲለው ሃይማኖታዊ ምልከታዎችን
በመሰብሰብና ዲበ - አካላዊ ትርጉም በመስጠት ራሱን
በማሻሻል ያቀረበውን የዲበ - አካል ፍልስፍናን ደግሞ
ልውጥና የተከለሰ ወይም ልዩ ዲበ - አካል (revisionary
metaphysics) በማለትም ያየዋል። ኢማኑኤል ካንትንና
አርስጣጣሊስንም ከገላጭ ዲበ - አካል ሲመድባቸው ሄግልን
ደግሞ ከተከለሰ ወይም ከልዩ ዲበ - አካል ይመድበዋል።6
ከዚህም አከፋፈል በመነሳት የኑባሬ ጥናት ዲበ - አካል (The
study of general ontology metaphysics) እና የመንፈሳዊ
አዕምሮ ጥናት ልዩ ዲበ - አካል (The study of divine Mind.
especial metaphysics) በሚል ስያሜ ከፍለን ብንመለከት
የዲበ - አካል ሃይማኖት የሚከተለውን ፍልስፍና ለመረዳት
ያቀልልናል። ልዩ ዲበ -አካል “ነፍስ መለኮታዊ ባሕርይ አላት”
ወይም “አዕምሮ መንፈሳዊ እና ምጡቅ የሆነ ክፍል አለው”
ስለሚል መንፈሳዊ አዕምሮ የሚሠራበትን ምስጢር

6
ማስታወሻ፦ በዚህ መጽሐፍ ላይ በተደጋጋሚ የሚተነተነው ልዩ ዲበ-
አካል (especial methaphysics) እንደሆነ የታወቀ ይሁን።
Westminster Dictionary of Christian Theology. (1983, p. 105).

44
ጆንሰን እጅጉ

ለመፈለግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና ዲበ - አካላዊ


ፍልስፍናን ለመጠቀም ይሞክራል።

የዲበ - አካል ሃይማኖት አቀንቃኞች ‘የልዩ ዲበ - አካል ሥነ -


መለኮታዊ ትንታኔ’ ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል ስልጣን እንዳለው
ይቆጥራሉ። እንደ እርሱም ልዩ ዲበ - አካል በመጽሐፍ
ቅዱስና በሥነ -አመክንዮ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን
በባለምጡቅ አዕምሮ ምሁርን የነፍስ መገለጥ ላይ ወይም
ግምታዊ የፍልስፍና እልባቶቻቸው ላይ የተመሠረተ በመሆኑ
መገለጣዊ ነው ማለት ይቻላል። ይሁን አንጂ የሥነ - ኑባሬ
ዲበ - አካል ፈላስፎች የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍናን
አይቀበሉትም። ለምሳሌ ታላቁ የተፈጥሮ ሳይንስ ወይም
የሥነ - ኑባሬ ዲበ - አካል ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት ልዩ ዲበ -
አካልን “አቅጣጫና ዐላማ የሌለው መርሖ የለሽ ዕውር
ዐስተሳሰብ ነው ይለዋል።”7 በአጠቃላይ ልዩ ዲበ - አካል ከሥነ
- ኑባሬ ዲበ - አካል የተለየና የዲበ -አካል ሃይማኖት ሁነኛ
መሠረት ነው ማለት ይቻላል። በዚህም የባራድል ዩኒቨርሲቲ
የታሪክ ተመራማሪ ሮበርት ሲ.ፉለርን ጨምሮ አብዛኛዎቹ
በዲበ - አካል ሃይማኖት (New Thought) ላይ ጥናት ያደረጉ
የታሪክ ተመራማሪዎች ይስማማሉ።

7
Kant, Immanuel Critique of Pure Reason. (1929. P,21).

45
የአማልክቱ ዐዋጅ

ልዩ ዲበ - አካልን አንዳንዶች እንደ ሥነ - ልቦና ሳይንስ


ቢመለከቱትም ይህ ግን ፈጽሞ እውነትነት የለውም።
ምክንያቱም ልዩ ዲበ - አካል የማይዳሰስ ዐስተሳሰብን
የሚከተል በመሆኑ ነው። ለምሳሌ ከአካዳሚው የሥነ - ልቦና
ሳይንስ ጋር ያለውን ግልጽ የሥነ - አዕምሮ ዐስተሳሰብ ልዩነት
ማንሳት ይቻላል። ይኸውም ልዩ ዲበ - አካል የሰው አዕምሮ
“ከልዕለ አዕምሮ”8 ጋር የተገናኘ ስለሆነ በራሱ ኀይል ማድረግ
ይችላል የሚል መላምት የሚከተል ሲሆን የሰውን ፍላጎት
በዚሁ ኀይል ጣልቃ ገብነት ተደራሽ ለማድረግ ወይም የሰውን
ፍላጎት ለመመለስ ይጥራል። በአንፃራዊነት የሥነ - ልቦና
ሳይንስ ደግሞ ዐቅልን የሚጎዱ የአመለካከት ተጽዕኖዎችን
በማስወገድና ዐሳብን በማቅናት ለተሻለ ውሳኔ ወይም ተግባር
ያነሣሳል። አዕምሮንም እንደ ቁሳዊ አካል በመመልከትና
ዐዎንታዊ ዐስተሳሰብና ንግግር በመጠቀም መልካም የሚባል
ተጨባጭ አገልግሎት ይሰጣል።

ምናልባት የተፈጥሮ ሳይንስ ጥናት ሥነ - ልቦናንና ልዩ ዲበ -


አካልን ሊያመሳስላቸው የሚችለው የሚከተሉት መርሖና

8
ልዕለ አዕምሮ (divine mind) ፦ የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ሲሆን መለኮት
(እግዚአብሔር) አዕምሮ ነው የሚል ዐስተሳሰብ ይከተላል። እንደ ፍልስፍናው ልዕለ
አዕምሮ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለ እውነተኛ የሰው ማንነት ሲሆን ከተፈጥሯዊ
ዐቅል የተለየ እና በእውቀት ወይም መንፈሳዊ ልቀት የሚንቀሳቀስና የሚገለጥ ነው
ይላሉ። በተለመደው ሁለትዮሽ ምልከታቸውም አዕምሮ ቁሳዊና መንፈስ ክፍል
አለው፤ ልዕለ አዕምሮም የመንፈስ ክፍል (መንፈስ) ነው ይላሉ።

46
ጆንሰን እጅጉ

ትልም ሳይሆን ሁለቱም መልካም ዐስተሳሰብን ወይም


ቃላትን መጠቀማቸው ነው። ይህም ከላይ እንደተነሣው
ተፈጥሯዊው ሥነ - ልቦና ሳይንስ አካላዊ አዕምሮን በመልካም
ንግግር ማከም ላይ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑና ልዩ ዲበ -
አካል ግን “በመንፈሳዊ አዕምሮ” ላይ ትኩረት ማድረጉ ነው።

ልዩ ዲበ - አካል አዕምሮ አካላዊና መንፈሳዊ ክፍል እንዳለው


ሲቆጥር “መንፈሳዊ አዕምሮ” የሚሠራው የሰው ልጅ
በሚያስበው ወይም በሚናገረው ዐዎንታዊ ወይንም ዐሉታዊ
ቃል ምስጢራዊ ኀይል አማካኝነት ነው የሚል መርሖ
ይከተላል። በዚህም ምክንያት ዲበ -አካላዊው ሃይማኖት
በሁሉም ዐይነት ሃይማኖትና እምነት ውስጥ የሚደረገውን
የጸሎት ልምምድ የዐቅልን ኀይል መጠቀም እንደሚያስችል
መሳሪያ በመቁጠር በአንድ መነጽር ይመለከተዋል። እንደ
ትምህርቱ ከሆነ ማንኛውም ጸሎት “ልዕለ አዕምሮን”
በማንቀሳቀስ በሌላው ሰው መንፈስ ላይ ተጽዕኖ ማድረግ
ይችላል። ከዚህም የተነሳ ሰዎች በዐሳባቸው ኀይል
እንዳይጎዷቸው ጭምር ከሰዎች የሚሸሹ ሰዎች
አጋጥመውኝ ያውቃል። እንደ ትምህርቱ ማንኛውም ሰው
የአዕምሮውን ኀይል በልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ አማካኝነት
ከተጠቀመበት ጤንነቱን ማረጋገጥና መበልጸግ ይችላል።9

9
Ostrander, R. The power of Prayer in a World of Science: (2000. p.141).

47
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይህም ልዩ ዲበ - አካል ሃይማኖታዊ መልክ ያለው የባዕድ -


እምነት ልምምድ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።

ስለዚህም የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍናን መሠረት የሚያደርግ


የትኛውም ሃይማኖት ቅይጥ፣ ባዕድ አምልኮ ወይም ኑፋቄ
ነው ማለት ይቻላል። ማኮኖኔል “ልዩ ወንጌል” (the different
gospel) በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ እንዳብራሩት ከሆነም
በማኅበራዊና ሥነ - ልቦና ጥናት (sociology or psychology)
ምልከታ መሠረት በመመዘን አንድን እንቅስቃሴ ባዕድ -
እምነት ወይም ኑፋቄ እንደሆነ መፈረጅ ይቻላል። እንዲህም
ሲሆን ከተለመደው ውጪ የሆነና ማኅበረሰቡ እንደ ነውር
የሚቆጥረው ትምህርትና ልምምድ ባዕድ - እምነት ሊባል
ይችላል ማለት ነው።

ይሁን እንጂ ይላሉ ማኮኔል የእምነት እንቅስቃሴን ለመፈረጅ


ይህ በቂ አይደለም። እንደ እርሳቸውም ታሪካዊና ሥነ -
መለኮታዊ መመዘኛ ያስፈልጋል። አያይዘውም ኢ ደብሊዩ
ኪኒየን የቃል እምነት ትምህርቱን ከዲበ - አካል ሃይማኖት
በመቅዳት የእምነት እንቅስቃሴ መሥራች እንደሆነ ታሪክን
ያመሳክራሉ። ከዚህም ታሪካዊ መመዘኛ የተነሣ የእምነት
እንቅስቃሴ ከባዕድ - እምነት ጋር የተቀየጠ (cultic) ወይም
ኑፋቄ ነው ይላሉ። አጽንፆት ሲሰጡም፤ የእምነት እንቅስቃሴ
የእኔ የሚለው የሥነ - መለኮት ፍሬ ቢኖረውም መሠረቱ

48
ጆንሰን እጅጉ

ባዕድ - እምነት ሰለሆነ ሥነ - መለኮቱም ያው ከባዕድ ጋር


የተቀየጠ ወይም ኑፋቄ እንደሆነ ያክላሉ።10

በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ሐንክ ሐነግራፍ


“የእምነት እንቅስቃሴ ባዕድ አምልኮ” እንደሆነ የሚስማሙ
ሲሆን ከማኅበራዊ (sociology) ጥናት፣ ከሃይማኖት ምልከታ
(religion) እና ከሥነ -መለኮት (theology) አንፃር መገምገምና
መወሰን እንዳለበትም ያትታሉ። ከማኅበራዊ ጥናት አንፃርም
የታዋቂውን የማኅበራዊ ጥናት ተማራማሪ የማልቶን ይንገርን
ዐሳብ ያጋራሉ። እንደ ይንገር ከሆነ ባዕድ አምልኮ በተረት ላይ
የሚመሠረትና ድርጅታዊ መዋቅር የሌለው ነው።

ሐነግራፍ ከሃይማኖታዊ ምልከታ አንፃር ደግሞ የታሪክ


ተመራማሪ የሆኑትን ጄ ጎርደን ማልቶንን ዐሳብ በማንሳት
ያቀርባሉ። እንደ ማልቶን ከሆነ ባዕድ አምልኮ ጎጂና የሰውን
አዕምሮና ማኅበራዊ ግንኙነቶች የሚወስን ወይም በሕዝብ
ላይ የሚሰለጥን እንቅስቃሴ ወይም ትምህርት ነው።
ቀጥለውም ሐነግራፍ በሥነ - መለኮት መመዘኛ ላይ ትኩረት
ያደርጋሉ። በዚህም የሚያነሱት ነጥብ ባዕድ አምልኮ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ከአውዳዊ ፍቺአቸው ውጪ
የሚጠቀም ወይም ለክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት
የራሱን ትርጉም የሚስጥ ነው የሚለውን ነው። ምሳሌም
10
The Different Gosple. (PP, 72-80).

49
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሲያጣቅሱ በተለያዩ ቡድኖች ለኢየሱስ የሚሰጠውን ትርጉም


ያነሳሉ። ለምሳሌ ይላሉ ሐነግራፍ “ኢየሱስ” የሚለውን ስም
ሁሉም መናፍቃን የሚጠቀሙ ሲሆን የሚሰጡት ትርጉም ግን
ይለያያል። ሞርሞኖች “ኢየሱስ የሉሲፈር ወንድም ነው”
ሲሉ የእምነት እንቅስቃሴ ልዑካን ደግሞ ዳግም እንደተወለደ
“አንድ ክርስቲያን ወንድም” ብቻ እንደሆነ በመቁጠር
ያኮስሱታል ይላሉ።11

በእርግጥም የዲበ - አካል ሃይማኖትም ይሁን የእምነት


እንቅስቃሴ መጽሐፍ ቅዱስን ከአውዱ ውጪ በመፍታት
የራሳቸውን “የእምነት ቃል” ወይም “የዐዋጅ ቃል” ትምህርት
ማደራጀታቸው ባዕድ ወይም ኑፋቄ ያደርጋቸዋል።
በአጠቃላይም ይህ አካሄዳቸው በልዕለ አዕምሮ ጽንሰ - ዐሳብ
ላይ የተመሰረተና የትምህርተ - ሰብዕን ርቱዕ ሥነ -መለኮት
የሚያፋልስ በመሆኑ ባዕድ አምልኮ መባሉ ትክክል ነው።
ይሁን እንጂ ኑፋቄው ዕድሜ ጠገብና የሻገተ ቢሆንም
በየዘመኑ በሚበቅሉ የማይናቅ ክህሎትና የትምህርት ደረጃ
ያላቸው አቀንቃኞቹ አማካኝነት እየገሰገሰና እየተስፋፋ
መምጣቱ ትኩረት ያስፈልገዋል። ሞስሊ ግሊን አር የተባሉት
ጸሓፊ የጄ ጎርደን ማልቶንን ጥናት በማጣቀስ እንደጻፉት
ለዲበ - አካል ሃይማኖት ንቅናቄ መቀስቀስና መስፋፋት

11
Christianity in crisis: 21st century. (PP, 80-90).

50
ጆንሰን እጅጉ

ምክንያት የሆኑ አያሌ መሪዎችን ዘርዝረዋል።12 በርካታ


ጥናቶች እንደሚያሳዩትም አብዛኛዎቹ መሪዎች ከምሁራን
የሚመደቡ ናቸው።

ከእነዚህም ተጽዕኖ ፈጣሪ ምሁራን መኻል የሥነ - መለኮት


ዐዋቂዎች፣ ፈላስፎች፣ ሳይኮሎጂስቶች፣
ሳይኮቴራፒስቶችና13 ሂፖቴኒስቶች14 ይገኙበታል። እነኝህ
ምሁራን በዘመናቸው ከነበራቸውም ተቀባይነት ክህሎት
የተነሣ ተጽኗቸው የገዘፈ ነው። ትምህርታቸው አወዛገቢና
ውስብስብ በመሆኑ በወንጌላውያን አማኞች ላይ ጭምር
ተጽዕኖ በማድረግ ለእምነት እንቅስቃሴ መፈብረክ ምክንያት
መሆን እንደቻሉ ኦስትረንደር፣ ሂላርና ሞስሊን ጨምሮ
በርካታ የታሪክ ጸሓፍትና አጥኚዎች ይስማማሉ።15 በነኚህም
ጥናታዊ መረጃዎች ላይ ባደረግሁት ጥናትና ዳሰሰሳ ለእምነት
12
. Mosley, R New Thought, Ancient Wisdom. (2006. Pp, .45-51, 131-139).
13
ሳይኮቴራፒ:- ሰፊና የተለያየ ትርጓሜ ቢኖረውም አዕምሮ ቀና ወይም ፖዘቲቭ ነገር
ብቻ እንዲያስብና ከዐቅም በላይ ቢሆንም እንኳ ትልልቅ ነገሮችን በማሰብ
እንዲሞላ በማድረግ ግለሰቡን ከጭንቀት ማውጣት፤ ጤናማ ወይም ሰላም
እንዲሆን ማድረግ ይቻላል የሚል የስነ -ልቦና ፍልስፍና ህክምና ነው።
14
ሂፖቴኒዝም:- በዐቅል እና በስሜት መኃል ያለውን ትዕዛዝ ወይም ግንኙነት
በማቋረጥ እንቅልፍ የሚመስል ሰመመን ውስጥ በማስገባት ወይም ሙሉ ለሙሉ
በማደንዘዝ ግለሰቡ በሃይፖቴኒስቱ የሚሰጠውን ትዕዛዝ ብቻ ካለፍቃዱ
እንዲቀበልና እንዲፈጽም የሚያደርግ አስገዳጅ የምትሃት “ጥበብ” ነው። ለምሳሌ
ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ከካዝናቸው ወይም ከባንክ ሂሳባቸው ላይ አውጥተው
ለማያቁት ሰው (ሂፖቴኒስት) በመስጠታቸው የሚቆጩ በርካታ ሰዎች
የሚያጋጥሙን በዚህ አሠራር አዕምሯቸው እየተሰረቀ ነው።
15
. Mosley, R New Thought, Ancient Wisdom. (2006. Pp. 45-51, 131-139).

51
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንት ዓይነተኛ መንስኤ የዲበ - አካል


ሃይማኖት ፍልስፍና እንደሆነና ሰፊ ሚና የነበራቸው መሪዎች
ደግሞ እነማን እንደነበሩ መለየትና ማረጋገጥ ችያለሁ።

በርካታ ጥናቶች ብዙ ቍጥር ያላቸውን የልዩ ዲበ - አካል


መሪዎችን ቢዘረዝሩም በዚህ መጽሐፍ ላይ ግን የጠቀስኳቸው
የዲበ - አካል ሃይማኖት አማልክታዊ ዐስተሳሰብን በማስፋፋት
ትልቅ ውጤት አስመዝግበው ያገኘኋቸውን አእማዳት ተጽዕኖ
ፈጣሪዎች ብቻ ነው። ከተጠቀሱት የዘመን መረጃዎች ውስጥ
አንዳንዶቹ የመሪዎቹን የልደትና የሞት ዊሂብ የሚያሳዩ ሲሆኑ
ጥቂቶቹ ደግሞ ተጽዕኖ የፈጠሩበትን ዐመታት የሚጠቁሙ
ብቻ ናቸው። በዝርዝር ከተቀመጡት ምሁራን መኃል
ኢማኑኤል ሲውዲንበርግ፣ ጆን ታይንዶል እና ፓንክሆረሰት
ኪዊምቢ ለዲበ - አካል ሃይማኖት እንቅስቃሴ መወለድ ግንባር
ቀደም ታሪካዊ ተጠቃሽ መሆናቸውን እስማማለሁ።

በዚህም ሲውዲንበርግ የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍናን በመፈልሰፍና


ወደ ሃይማኖት በማምጣት የአባትነት ቦታ ይዟል። ጆን ታይንዶል
ሲውዲንበርግ በጸሎት ላይ የጠቆመውን የልዩ ዲበ - አካል ምልከታ
ሳይንሳዊ ሙከራዎችን በማድረግ በምክንያታዊነት ለማብራራት
በመሞከር ይከተላል። ፍሬንዝ አንቶን ሜዝሜር ደግሞ ምትኃታዊ
የአዕምሮ ኀይል አሠራርን በማስተዋወቅ ልዩ ዲበ - አካላዊ ፈውስና
ተዓምራትን ወደ ሃይማኖትና ወደ ተፈጥሮ ሳይንስ ሥነ - ልቦና

52
ጆንሰን እጅጉ

ትምህርት ለማስታከክ ሞክሯል። ፓንክሆረሰት ኪዊምቢ ደግሞ


ፍልስፍናውን ሰብስቦ በማቀላጠፍ ሳይንሳዊና ኃይማኖታዊ መልክ
በማላበስና በማስፋፋት ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ አቅጣጫ
እንዲኖረው አድርጓል። በአጠቃላይ ከሲውዲንበርግ ጀምሮ እንደ ሜሪ
ቤከርና ቻርልስ ፊሊሞር ዐይነት በርካታ መሪዎችም ጭምር መጽሐፍ
ቅዱስን በልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍና መነፅር በመመልከትና በመተንተን
ክፍለ ዘመናትን የተሸጋገረና የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ዐቅም
የተፈታተነ ትልቅ ረብሻ እንዳስከተሉ ታሪክ ይመሰክራል።

ኢማኑኤል ሲውዲንበርግ (1688-1777)

ኢማኑኤል ሲውዲንበርግ ለዲበ - አካል


ሃይማኖት መፀነስ ፈር ቀዳጅ እና ተጽዕኖ
ፈጣሪ በመሆን የመጀመሪያ ሰው ነው።
አሜሪካውያንን ከቁስ አካላዊነት ወደ
መንፈሳዊነት እንደ አሸጋገረ የታሪክ
ጸሓፍት የሚናገሩለት ይህ ሰው ሲውድናዊ
ሲሆን ሳይንቲስት፣ ፈላስፋና የሥነ - መለኮት ዐዋቂም ነበር።
ተከታዮቹም የአብርሆት (Enlightenment)16 ሳይንስ መሣሪያ፤
የሰውን ልጅ መለኮትነት ወይም አማልክትነት ማኅተም የከፈተና
ያረጋገጠ በማለትም ዘክረውታል።

16
የአብርሆት (Enlightenmnet)፦ ሃይማኖትና ፖለቲካን ወደጐን ያደረገ የ 18 ተኛው
ክፍለ ዘመን ፍልስፍና ሲሆን እውነት በተጨባጭ ምክኒያት ላይ የተመሰረተች ናት
ብሎ ያምናል።

53
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሲውዲንበርግ እርሱ እንደሚመሰክረው በ 57 ዓመቱ ላይ


(1743 -1744)17 መንፈሳዊ ዓይኑ ተከፍቶለት ተደጋጋሚ
የህልም ጉዞ አድርጓል። ይህንንም ከግል ማስታወሻው
በተወሰደ “የህልም ጉዞዎች” በተሰኘው ጽሑፉ ላይ አስፈሪና
አነቃቂ የኤሮቲክ ልምምዱን ሳይቀር በዝርዝር በላቲን ቋንቋ
አስቀምጧል።18 ከሙት መንፈስ ጋር በተደጋጋሚ ተነጋግሯል፤
በህልም በተደጋጋሚ ካወራቸው የሙት መናፍስት ውስጥ
አባቱ፣ ብዙ ሴቶችና የፈረንሳዩ ንጉስ ቻርልስ ስድስተኛ
ይገኙበታል። ይህንም በመሰለው ልምምዱ፤ ከመንፈሳዊው
ዓለም አገኘሁ በሚለው መገለጥና ከመላእክት ጋር ባደረገው
ንግግር በመታገዝ አስራ ስምንት መንፈሳዊ ይዘት ያላቸውን
ሥራዎቹን ለኅትመት አብቅቷል። በተጨማሪም ለኅትመት
ያልበቁ የልዩ ዲበ -አካል ጽሑፎችን እንዳበረከተም ጥናቶች
ያመለክታሉ19።

በርካታ ጹሁፎቹም የዓለምን ዐስተሳሰብ የቀረጹ ቅርፅ


ማውጫ (mold) እንደሆኑ የታሪክ ጸሓፍት መስክረውለታል።
ሲውድንበርግ እውነተኛ ዕውቀት የሚጀምረው ቁስ አካላትን
በዐይን በመመልከት ወይም በመፈተሽ አይደለም በማለት
ሞግቷል። የሥነ - ኑባሬን ዲበ - አካል ይፃረርና በመገለጥ
17
Lamm, M. Emanuel Swedenborg, The Devopment of His Thought. (2000).
18
Odhner. C. Journal of Dreams. (2016. no.120, no.171, no.261, no.175). ቀደምት
የእንግሊዘኛ ትርጓሜዎች ላይ አንዳንድ የህልም ገጠመኙ እንዳይካተት ተደርጓል፡፡
19
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, P. 33,34).

54
ጆንሰን እጅጉ

የበላይነት ይደገፍ የነበረው ይህ ሰው እውነተኛ ዕውቀት


የሚገኘው በመለኮት ነው ብሎ ያምን ነበር። ራሽናል
ሳይንስም ሆነ ሃይማኖት በልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍና መታገዝ
እንዳለባቸው ያምናል። በተጨማሪም እጅግ ጠቃሚ የሆነው
ሳይንስ የነፍስን ተፈጥሮ ማወቅና ነፍስ በአካል ውስጥ ያላትን
ሥራ ማጥናት ነው ይል እንደነበር ሄላር በጥናታቸው
ጠቅሰዋል።20

በአጠቃላይ የሲውዲንበርግን ፍልስፍናዎችን ስንመለከት


በአርስቶትልንና በአፍላጦን (Plato.429-347 B.C) የልዩ ዲበ -
አካል ዐስተሳሰብ ተጽዕኖ ሥር መውደቁን መገንዘብ
እንችላለን። ለምሳሌ የአፍላጦንን የሁለትዮሽ ዕይታ
በመጠቀም (በ 1758) በላቲን በተጻፈ መጽሐፉ ላይ
እንዳሰፈረው መላእክትን እንኳ የመንፈሳዊው ዓለም
መላእክትና የመንግስተ - ሰማይ መላእክት በማለት ለሁለት
እስከ መክፈል ይደርሳል።21 በሌላም ቦታ ደግሞ የመንግስተ
ሰማይ ውጫዊ እና ውስጣዊ መላእክት በማለት መልሶ
በሁለት ይከፍላቸዋል። ይህም የሆነው ሰማያት ውስጣዊና
ውጫዊ ክፍል አላቸው ብሎ በማመኑ ምክንያት ነበር።22

20
ibid., (p, 142).
21
Swedenborg, E. Haven and Hell. (2000, P, 17)
22
ibid., (P, 19).

55
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይኸው የሁለትዮሽ ምልከታው አባዜ መላእክቱን በሁለት ጾታ


ከፍሎ እስከ መመልከትም አድርሶት ነበር።23

ይህም ብቻ ሳይሆን አፍላጦን እንደሚል ተፈጥሯዊው ዓለም


የመንፈሳዊው ዓለም ምላሽ ወይም ነፀብራቅ ነው ብሎ
ስለሚያምን አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በራእይ መጽሐፍ ላይ
በሰማይ እንደታየች ሁሉ በምድር ላይ ያሉትን ከተሞች አንድ
እንኳ ሳይቀር በሰማይ እንደምናገኛቸው ተንትኗል። “የሰማይ
ጥንድ ነን” በሚል ርእሱ ላይ እንዳሰፈረውም እያንዳንዱ ሰው
ውስጥ ተፈጥሯዊና መንፈሳዊ ዓለም አለ ብሏል። እንደ
እርሱ ከሆነ መንፈሳዊው ጥልቅ አዕምሮ ሲሆን፤
ተፈጥሯዊው ደግሞ አካላችንና ስሜታዊ ድርጊታችን ነው።24
በርግጥ ሲውድንበርግ ይህ ዕውቀት በጥንታውያን ግብጾችና
ግሪኮች ይታወቅ ነበር ስለሚል አፍላጦን ተጽዕኖ
እንዳደረገበት አይክድም ማለት ይቻላል።

ሲውድንበርግ የአፍላጦን ብቻ ሳይሆን ምናልባትም ደግሞ


የረኔ ዴካርት (1596 - 1650) ፍልስፍና ተጽዕኖ ነበረበትም
ማለት ይቻላል። ዴካርት አዕምሮ የራሱ ተፈጥሯዊ ብርሃን
ስላለው በተመስጦ አማካኝነት በስሜት ህዋሳት ላይ ጥገኛ
ያልሆነ ዕውቀትን መሰብሰብ ይችላል በማለቱ የሞስሊንን

23
Ibid., (P, 211).
24
Ibid. (P, 51).

56
ጆንሰን እጅጉ

ጥርጣሬ ተአማኒ ያደርገዋል። እዚህ ላይ ዴካርት ከስሜት


አካላት ይልቅ ለአዕምሮ ከፍተኛ ቦታ በመስጠት ‘መኖሬን
የማቀው ስለማስብ ነው፤ ስለዚህም በአእምሯችን ውስጥ
የሚፀነስ ማንኛውም ግልጽ ዐሳብ እውነት ነው።’25 ማለቱን
እንደ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል። ሲውዲንበረግ ራሱም
ቢሆን በአዕምሮው ብርሃን አማካኝነት ከመላለም (Universe)
መረጃዎችን እንደሚያገኝ መናገሩ ይህንኑ የረኔ ዴካርት
ተጽእኖ ያሣያል ብዬ አምናለሁ። ሲውድንበርግ ከዴካርት ጋር
ያለው ልዩነት ዴካርት ዕውቀትን በሥነ -አመክንዮ
እንደሚረጋገጥ ማመኑና ሲውዲንበርግ ደግሞ ምናባዊ ግምት
በመገለጥ ወይም በመንፈሳዊ መረጃ እንደሚረጋገጥ ማመኑ
ብቻ ነው።

በዚህም ምክንያት ገና ከመጀመሪያው ሲውዲንበርግ


አዕምሮው የሚሰጠው መረጃ በአመክኒዮ የሚረጋገጥ
ተጨባጭነት ያለው ቢሆንም ባይሆንም ትኩረት
አልነበረውም ማለት ይቻላል። በዚህም ምክንያት የልዩ ዲበ -
አካል ፍልስፍናው በምንም መስፈሪያ የማይለካ ነው።
ይልቁንም የሁሉ መለኪያ በሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ
የሚሰነዝረው አመሥጥሯዊ ፍቺ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥነ -
ጽሑፋዊና መለኮታዊ ስልጣን የሚዳፈር እንደሆነ

25
Allen, Diogenes S. Philosophy for Underastanding Theyology. (2007. P.128-131).

57
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይታይበታል። ይህንንም አመሥጥሯዊ ምልከታውን


ሲያስረግጥ ቃል እንደ ሰው አካል ነው፤ ምስጢራዊ ፍቺው
ደግሞ ነፍስ ነው ብሏል።26

አመሥጥሯዊ ሥነ - አፈታት ችግሩ ተገለጠልኝ ከሚለው


ሰው በስተቀር የተገለጠው ነገር በሌላ ሰው የማይመረመርና
የማይታይ ወይም የማይደረስበት መሆኑ ነው። ሲውዲንበርግ
በሰው ስላልተደረሰበት ምጡቅ ልምምዱ ሲናገርም፦

“ለብዙ ዐመት በመለኮት ምህረት በላቀ ሁኔታ ውስጥ


ስለ ነበርኩ በተከታታይና ባልተቆራረጠ ሁኔታ
ከመንፈስና ከመላእክት ጋር ኅብረት አደርግና እርስ
በርስ ሲነጋገሩ፤ ከእኔም ጋር ሲነጋገሩ ሰምቻለሁ።
በዚህ መንገድ በማንም ሰው ያልታወቀና ያልታሰበ
እጅግ ግሩም የሆነ ነገር እንድመለከትና እንድሰማ
ተሰጥቶኛል”27

ብሏል። በዚሁ ለእኔ ብቻ “ተገለጠ” በሚለው ምስጢራዊ


ምልከታው የክርስትና ትምህርቶችን በራሱ መንገድ
ተንትኗል። የአዳማዊ ኃጢአትንና የኢየሱስን ቤዝዎት
አሽቀንጥሮ ጥሏል።28 በአጠቃላይ የሲውዲንበርግ ፍልስፍና
የክርስትና ሥነ - መለኮትና የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍናን
26
Swedenborg, E. Haven and Hell, (p,167).
27
Swedenborg. E. (2009). Arcana Coelestia. (P,12).
28
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, p.45).

58
ጆንሰን እጅጉ

ውሕደት በመፍጠር የዲበ - አካል ሃይማኖትን መውለድ


ችሏል። ይህንንም ሃይማኖት ፈረንጆቹ “New Thought”29
ይሉታል።30

በዚህ ክፍለ ዘመናትን በተሻገረ ፍልስፍናውም በቤተ


ክርስያንና በዲበ -አካል ሃይማኖት እንቅስቃሴ መሪዎች ላይ
ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳረፈ ሞስሊ ይስማማሉ። ለዚህም
ማስረጃ ሲውዲንበርግ የዲበ - አካል ሃይማኖት ከዋክብት
በሆኑት በሜሪ ቤከር ኤዲና በቻርልስ ፊሊሞር ላይ
ያሳደረውን ተጽዕኖ ሲገልጹ፦ “ሲውዲንበርግ በዲበ - አካል
ሃይማኖት ፍልስፍና ስሌት አማካኝነት ሜሪ ቤከር ኤዲ
‘ሳይንስና ጤንነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቁልፍ ጥቅሶች ጋር’
የተሰኘውን መጽሐፍ ለመጻፍ አስችሏታል። ቻርልስ
ፊሊሞር ደግሞ ዲበ - አካላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ መፍቻ31
የተባለውን ማብራሪያ ኮመንተሪ እንዲጽፍ አስችሎታል።”32
ብለዋል። በአጠቃላይ የኢማኑኤል ሲውዲንበርግ የልዩ ዲበ -
አካል ዐስተሳሰብ የአፍላጦንንና አርስቶትልን ፍልስፍና ስቦ
የተጠቀመ ሲሆን ከሜዝሜር ጀምሮ ያሉት ዐስተሳሰቦች
29
New Thought፡ ይህ ቃል በዚህ መጽሐፍ “የዲበ-አካል
ሃይማኖት” በሚል የአማርኛ ቃል በደራሲው ተተክቷል።
30
Haller, J. S. The History of New Thought:. (2012, P,5-34).
31
ዲበ-አካላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ መፍቻ (metaphysical Bible Dictionary) ፦ መጽሐፍ
ቅዱስ በምስጥር የተጻፈ ነው በማለት አመስጥሯዊ (Allegorism) አፈታትን
በመጠቀም ዲበ-አካላዊ ትንታኔ የሚሰጥ ማብራሪያ (commentary) ነው።
32
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, p.148).

59
የአማልክቱ ዐዋጅ

ደግሞ የሩቅ ምስራቅ ሃይማኖቶችን ፍልስፍና ወደ ራሳቸው


ቋት የሳቡ ናቸው።

ፍሬንዝ አንቶን ሜዝመር (1735-1815)


ለዲበ - አካል ሃይማኖት መዳበር
አሰተዋጽዖ በማድረግ ከሲውዲንበረግ
በመቀጠል ሊጠቀስ (Animal magnetism)
የሚችለው እንሰሳዊ መግኔጢስ33
እንቅስቃሴ መሥራችና መሪ የሆነው
ጀርመናዊው ፍሬንዝ አንቶን ሜዝመር ነው። ሜዝመር (ዶ/ር)
“አሜሪካዊው ፈዋሽ” በመባል የሚታወቅ ሳይካትሪስትና
ሂፖተኒስት ነው። እጅ በመጫን ወይም በንኪኪ “የአዕምሮ
ኀይል ከሰው ወደ ሰው በመተላለፍ ይሠራል” የሚል የልዩ ዲበ
- አካል ፍልስፍና አስተዋውቋል።

በዚሁ ዐስተሳሰቡ ላይ የመድኃኒት ዶክትሬቱን በቬና ዩኒቨርስቲ


ሲያጠናቅቅ የመመረቂያ ጽሑፉን የሠራ ሲሆን በቀጣዮቹ 70
ዐመታት በጤና ሳይንስ፣ ሳይኮሎጂና ሳይካትሪስት ምርምሮች
ላይ ይህ ነው የማይባል ተጽዕኖ ማሳረፍ ችሏል። ከቬና
ዩኒቨርስቲ ተመርቆ ከወጣ በኋላም የፈውስ ሙከራዎችን በቬና
መለማመድ ጀምሮ ነበር። ይሁን እንጂ በከተማዋ ውስጥ

33
እንሰሳዊ መግኔጢስ፦ (Animal Magnetism)፦ የሰው ልጅ ዐቅል የማይወሰንና
የማይገደብ ሙጡቅ የፈውስ ልዕለ ኀይል አለው ብሎ የሚያምን ፍልስፍና ነው።

60
ጆንሰን እጅጉ

በነበረው የህክምና ሥርዐት ተቀባይነትን በማጣቱና ከአንድ


ታካሚው ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ሙከራውን
መቀጠል ስላልቻለ ከቬና ወደ ፈረንሳይ ተጉዟል። ከዚህም
በኋላ በፓሪስ የእንሰሳዊ መግኔጢስ (animal magnatizem)
ክሊኒክ የከፈተ ሲሆን ህጋዊ ድጋፍንም አግኝቶ ነበር።34

ሜዝሜር ለጥንቆላ አሠራር ብዙ ትኩረት እንዳልነበረው


ቢነገርም ከምትኃታዊ አሠራር አልራቀም ነበር።
የሳይካትሪስቶች አካል ወይም አዕምሮ በመላለም ውስጥ
ያለውን መግኒጢሳዊ ኀይል መቀበልና ማስተላለፍ ይችላል
በሚለው ፍልስፍናው ለጨለማው ዓለም ትልቅ በር በማበጀት
አጋንታዊ ልምምዶችን አስተዋውቋል። እንደ እርሱም አዕምሮ
የፈውስ መግኔጢስ ፈሳሽ በማመንጨት በሽታን ይፈውሳል።
ገና ከልጅነቱ ጀምሮ እውነትን በራሱ መንገድ ማረጋገጥ ይወድ
እንደነበርም ይነገርለታል።

በፓሪስ የዐይን ምስክር የሆኑ የክሊኒኩ ታካሚዎች የሰጡትን


ምስክርነት ቢሊ የተባለ ታሪክ ጸሓፊን በመጥቀስ ኢንሲ ቢ
እንዳስቀመጠው የሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል፦

መግነጢሳዊው ሰው (ሜዝሜር) ታካሚው ላይ ዓይኑን


ያፈጣል፣ የበሽተኛውን ራስ ይይዛል፣ ታማሚ የሆኑ የአካል
ክፍሎችን ይነካካል ወይም በታካሚው ፊት ላይ እጁን ቀስ

34
Franz Anton Mesmer: His life and Teaching. (1920, Pp,1 7-20).

61
የአማልክቱ ዐዋጅ

እያለ ያንቀጠቅጣል፤ ነገር ግን ታማሚው ከዚህ በላይ በሆነ


የመግኒጢስ ኀይል ይነካል። በዚህ ጊዜ ታማሚዎቹ የተለያየ
ሁኔታ ያሣያሉ። ምንም ለውጥ የማያሣዩ ቢኖሩም
አንዳንዶቹ ግን የውጋት ስሜት፣ ትንሽ ህመም፣ የላብ
እርጥበት፣ እሳት ወይም ሙቀት ይሰማቸዋል፤ ሌሎች
ራሳቸውን በመሳት ይወድቃሉ። ሌሎች ደግሞ በራሳቸው
ፈቃድ የማይቆጣጠሩት እንቅስቃሴ ያሣያሉ፤ ይህም ሳቅና
መንገዳገድ ሊሆን ይችላል። ሌላው ምንም ዐይነት ራስ
የመሣት እንቅልፍ ውስጥ ቢገቡ እንኳ ስበታዊው ሰው
በሚያሰማው ድምፅ፣ የእጅ እንቅስቃሴ ወይም የዐይን ዕይታ
ያነቃቸዋል፤ እንደፈለገም ያንቀሳቅሳቸዋል። ሰዎችም
ለመገረምና እንደ ትርዒት ለመመልከት ይሰበሰባሉ። 35

ይህንን በመሰለ ሁኔታ ሜዝሜር የልዩ ዲበ - አካል አጋንንታዊ


የኀይል ልምምድን ተግባራዊ በማድረግ የፈውስ አገልግሎት
በመስጠት በዘመኑ ከበድ ያለ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ታሪክ
ጸሓፊው ሞስሊ በመጽሐፋቸው ጠቅሰዋል።36

ፕሮፌሰር ጆን ታይንዶል (1820-1893)


ታይንዶል የፊዚክስ ሳይንቲስትና የተፈጥሮ
ሳይንስ ፈላስፋ ሲሆን በለንደን የነበረው
የምሁራን ማኅበር (X. club) ማለትም
የአብርሆት ቡድን37 አባልም ነበር። የታሪክ
35
Ibdi, (P,18, 26).
36
Glenn, R. Mosley. New Thought, (2006 P. 131).
37
የምሁራን ማህበር (X. club) በ 19 ነኛው ክፍለ ዘመን በኢንግላንድ የነበረ ዘጠኝ
አባሎች ያሉት የሳይንቲስቶች የእራት ቡድን ነው። እንኝህ ሳይንቲስቶች በየ እለቱ

62
ጆንሰን እጅጉ

ጸሓፍት እንደጠቆሙት የሲውዲንበርግ ተጽዕኖ በአብርሆት


ሳይንቲስቶች ላይ ከፍተኛ ነበር። ስለዚህም እንደ ማንኛውም
የአብርሆት ቡድን አባል በዘመኑ የነበረው የሲውዲንበርግ ልዩ -
ዲበ - አካል ፍልስፍና ተጽዕኖ አርፎበታል ማለት ይቻላል።
ታይንዶል በ 1872 “የጸሎት መመዘኛ” በሚል ለንባብ ያበቃው
ጽሑፍ የልዩ - ዲበ አካል ፍልስፍናን ከተፈጥሮ ሳይንስ ጋር
ለማስተረቅ እንደሞከረ ያሳያል። ጥናቱ የጸሎት መልስን
በምክንያታዊ የሳይንስ ሙከራ ለማረጋገጥ የጣረና ክርስትናን
ለመፈተሽ የሞከረ ነበር።

ታይንዶል በለንደን የሚገኘው የአብርሆት ቡድን አባል


እንደመሆኑ መጠን ለጥናቱ መነሻ ያደረገው “ዓለማትን
የሚመራው የተፈጥሮ ሕግ ነው።” የሚለውን የወቅቱን
የተፈጥሮ ሳይንስ ግኝት ነበር።

እንደ ሞስሊና ሄለር ያሉ ምሁራን በጥናታቸው ላይ


አካትተውት ባልመለከትም ታይንዶል የጸሎትን መልስ
ከተፈጥሮ ሕግ ጋር ማገናኘቱ ለዲበ - አካል ሃይማኖት ማዕበል
መነሳት ዓይነተኛ ምክንያት በመሆን ማገልገል እንደቻለ
ተመልክቻለሁ። ምክንያቱም ከታይንዶል በኋላ የተነሱ እንደ
ቻርልስ ፊሊሞር ያሉ የዲበ - አካል ሃይማኖት አገልጋዮች

ለራት ይሰበሰቡና ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው ላይ ይወያዩ ነበር።

63
የአማልክቱ ዐዋጅ

የታይንዶል ጽሑፍ ተጽዕኖ ይታይባቸዋል።38 ስለሆነም የዲበ -


አካል ሃይማኖትን የተመለከትን እንደሆነ ሳይንሳዊ
ምርምሮችን የመቀበልና ከኢ - ምክንያታዊ መላ ምቶች ጋር
በማግባባት የመተንተን ባሕርይ ስላለው የታይንዶልን ምርምር
እንደ ሁነኛ ግብዓት እንደተጠቀመበት ይታያል። በተጨማሪም
የሪክ ኦስትራንደር ጥናት የታይንዶል ጽሑፍ ዐግቶት የተነሣው
የተፈጥሮ ሕግን ከጸሎት ጋር ያገናኘ ዐስተሳሰብ በቤተ
ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ውዝግብና የእምነት መዋዥቅ
እንዳስከተለ ያሳያል። በዚህም ምክንያት በዘመኑ የነበሩ
አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ከታይንዶል ዐሳብ ጋር
የመስማማት አዝማሚያ እስከ ማሳየት እንደደረሱ ይኸው
ጥናት ጠቁሟል።39

ፊኒየስ ፓርክሆረስት ኩዊምቢይ (1802-1866)


በቅጽል ስሙ “የዲበ - አካል ሃይማኖት
ምጡቅ ዐሳቢ” ወይም “የዲበ - አካል
ሃይማኖት አባት” በመባል የሚታወቀው
ፊናስ ፓርክሆረስት ኪዊምቢይ (ዶ/ር)
ቁልፍ የዲበ - አካል ሃይማኖት ተጽዕኖ
ፈጣሪ መሪ ነበር። ኪዊምቢይ ብቅ ያለው የታይንዶል ጽሑፍ

38
በዚሁ ምዕራፍ “ቻርልስ ፊሊሞር” በሚለው ንዑስ ርዕስ ገጽ 56-61 እና ”ራልፍ
ዋልኮዶ ኤመርሰን“ በሚለው ንዑስ ርዕስ ገጽ 62 ላይ ይመለኮቷል።
39
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science. (2000, P.19).

64
ጆንሰን እጅጉ

ለንባብ ከበቃ በኋላ መልስን በተመለከተ ጸሎትን የሚመልሰው


የተፈጥሮ ኀይል ነው የሚለውን የታይንዶል ዐስተሳሰብ እንደ
ድልድይ ተጠቅሞበታል።

ከዚህም በተጨማሪ ኪዊምቢይ የሜዝመርን “እንሰሳዊ


መግነጢስ” ጹሑፎችን በማጥናት “አዕምሮ አካልን ይፈውሳል”
የሚል ግንዛቤን እንዳዳበረ ሄለር ይጠቅሳሉ።40 ይህን ልምምዱ
ከመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ጋር የሚመሳሰል ስውር እጅ
እንዳለው የሚያስረግጡ ነጥቦችን በቀጣዩ ክፍል የምንቃኝ
ይሆናል። ኪዊምቢ የአንድ ሰው መንፈስ በሌላው ሰው
መንፈስ ላይ ተጽዕኖ በማሳደርና ከነፍሱ ጋር ግንኙነት
በመፍጠር መፈወስ መቻሉ በእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ውስጥ
ተመሳሳይ መለኮትነት እንዳለ ማረጋገጫ ነው በማለትም
ያምናል።41 ይህንንም የፈውስ ኀይል ሲያስረዳ “በአዕምሮ
ውስጥ ያለ የጥበብ ኀይል ነው” እንዳለም ዴሰር ደብሊዩ
የኪዊምባይን የመጨረሻ ደብዳቤ ጠቅሰው ጽፈዋል። “ጥበብ
በሁሉም ሰው ውስጥ አለ። በጠጨማሪም መለኮት በሁሉም
ሰው ውስጥ ያለ ፈጣሪ (ፈዋሽ) አዕምሮ ነው”42 ማለቱም
ተጠቅሷል። ፍልስፍናው የሰው አዕምሮ መንፈሳዊ ወይም
መንፈስ ክፍል እንደሆነና የመለኮት ምሳሌና መልክ እንዳለው

40
Haller, J. S. The History of New Thought. (2012, P.71).
41
Ibid., (p.71).
42
The Quimby Manuscripts. Phineas Parkhurst Quimby. (2018, P 70)

65
የአማልክቱ ዐዋጅ

እስከመተንተን ይዘረጋል።43 በአጠቃላይ የኪዊምቢይን


መሠረታዊ ምልከታ ስንመረምር የሰው መንፈስ፣ የአዕምሮ
ጥበብና መለኮት የሚሉትን ሦስት ቃላት በተለዋዋጭ
የሚገለገል ሆኖ እናገኘዋለን።

ኪዊምቢይ “በሽታ ስሕተት የሆኑ ደካማ እና ዐሉታዊ


የአዕምሮ ሐሳቦች ውጤት ነው” ይል ነበር። የፈውስ ጥበብ
በአዕምሮ ለውጥ የሚመጣ የኬሚካል ለውጥ እንደሆነም
ይቆጥራል። ይህንንም ሲናገር “የአዕምሮዬን ኀይል በመጠቀም
የታካሚዬን አዕምሮ በመለወጥ የኬሚካል ለውጥ በአካሉ
ውስጥ አደርጋለሁ። ለምሳሌ የዕጢ ዕብጠቶችን ማክሰም”
ብሏል።44 እንደ እርሱም ከሆነ ፈውስ በአዕምሮ ኀይል
ምክንያት የሚከሰት የኬሚካል ለውጥ ነው። በዚህም መሠረት
አንድን ታማሚ ለመፈወስ የታማሚውን ዐሉታዊ ዐስተሳሰብ
ማረቅ ያስፈልጋል የሚል የሳይኮተራፒ ወይም የልዩ ዲበ -
አካል ሳይኮሎጂ ትምህርት አስተዋውቋል።45

በቀጣይም በ 1838 በይፋ በፖርትላንድ የአዕምሮ ፈውስ ቢሮ


ለመክፈት ችሎ ነበር። ኪዊንምቢይ ይህንንም አጋንታዊ
የምትኃት ጥበብ በመጠቀምም በዓመት ውስጥ ከ 500 ላላነሱ
ሰዎች የፈውስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር። በዚህም የካሪዝማቲክ
43
Ibid., (p. 41).
44
Ibid., (P.174).
45
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, P. 48).

66
ጆንሰን እጅጉ

የፈውስ አገልግሎት በሚመስል እንቅስቃሴው የወንጌል


አማኞቹን ጨምሮ የብዙ የሃይማኖትና የሳይንስ ቡድኖችን
ቀልብ እንደ ሳበና እንዳደናገረ የታሪክ ጸሓፊው ጆን ኤስ ሃለር
ይስማማሉ።46

ሜሪ ቤከር ኤዲ (1862-1881)
ሜሪ ቤከር ኤዲ የኪዊምቢይ ተማሪ
ስትሆን ኪዊምቢይ በስብከትና በፈውስ
አገልግሎቱ ዕረፍት እያጣ ሲመጣ
በጽሑፍና በኅትመት ሥራ ታግዘው ነበር።
በኪዊምቢይ የፈውስ ጥበብ የተማረከችው
ኤዲ የኪዊምቢይ ተማሪ ከመሆኗ በፊት የጤንነት እክል
የነበረባት ሲሆን በ 1862 ሙሉ ለሙሉ ከተፈወሰች በኋላ
የኪዊምቢይን የልዩ ዲበ - አካል ፈውስ በራሷ መንገድ
በማሳደግ በ 1881 በቦትሰን “ክርስቲያን ሳይንስ” ትምህርት
ቤት ለመክፈት በቅታ ነበር። ኮሌጇም በኒዎርክ፣ ቺካጎና
በኮሎራዶ ብሮክሊን በአምስት ዓመት የባችለር እና
የዶክትሬት (CSD) የሰባት ዓመት ተግባራዊ የፈውስ ልምምድ
ሥልጠናን በማከል እስከማስመረቅ ደርሶ እንደነበር ጥናቶች
ያሳያሉ።47

46
Ibid., (p. 5, 46).
47
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom. (2006, P, 46).

67
የአማልክቱ ዐዋጅ

ኤዲ የሳይንስና ጤንነት ትምህርቷ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር


እኩል እንደሆነ ታምን ነበር። በሌላ በኩልም ለኤዲ ኢየሱስና
ክርስቲያን ሳይንስም ልዩነት የላቸውም። እንደ እርሷ ከሆነ
የዚህ ምክንያቱ ኢየሱስም ሆነ ክርስቲያን ሳይንስ ስለ
መንፈስና ጤንነት ስለሚያስገነዝቡ ነው። ክርስቲያን ሳይንስ
በተሰኘው መጽሐፏ ይህንን ስትገልጽ “መንፈስ
ከእግዚአብሔር እንደሚመጣ በትክክል እናውቃለን ማለትም
ከመለኮታዊ መርሖ፣ ይህንንም የምናውቀው በክርስቶስ እና
በክርስቲያን ሳይንስ ቅድመ ዕውቀት ነው።”48 ብላለች። ኤዲ
ለትምህርቷም ሆነ ለክርስቲያን ሳይንስ ከክርስቶስ ወይም
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መስተካከል የምታቀርበው ሌላው
ምክንያት በሳይንስ ጤንነትም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱም
የዓለምን መንፈሳዊ ተፈጥሮ በመግለጥ ዓለምን ነፃ ያወጣሉ
የሚል እንደሆነ ሞስሊ አንስተዋል49።

ኤዲ በኅሩይ ቃል ዐዋጅ ላይ ያላትን እምነት ስትገልጥም


“ያልተነገረ ዐሳብ በመለኮታዊ አዕምሮ አይታወቅም”
ብላለች።50 በሌላም ቦታ ይህንን ኢየሱስ እንዴት በተሳካ ሁኔታ
እንዳስተማረ ስታነሳ “ኢየሱስ የመጣው እንዴት ኃጢአት፣
በሽታና ሞት እንደሚወገዱ (በኅሩይ ዐዋጅ ቃል) ለሰው ልጆች

48
Mary Baker Eddy Science and Health with Key to the Scriptures. (2006, P, 185).
49
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, 86).
50
Mary Baker Eddy Science and Health with Key to the Scriptures. (2006, p,15).

68
ጆንሰን እጅጉ

ለማስተማርና ምሳሌ በመሆን ለማሳየት ነው። ፍሬ የማያፈራ


ዛፍ ይቆረጣል ነው ያለው።” ብላለች።51 በዚህም ኤዲ የሰው
ልጅ ንግግር ስርየትን፣ ፈውስንና ሞትን እንደሚያስወግድ
ኢየሱስ ምሳሌ በመሆን ማሳየቱን ለማሳመን ሞክራለች።
በሌላ በኩል ለኤዲ ይህንን አለመለማመድ ፍሬ አለማፍራትና
ከግንዱ ላይ የሚያስቆርጥ ነው። በእርግጥ በኢየሱስና በሰው
ልጆች መካከል ያለውን የማንነት ልዩነት ማጥፋት ቢቻል ኖሮ
የኤዲ ፍልስፍና እውነት ሊሆን በቻለ ነበር!

“አንታመምም ሆነ አንደኽይም” በማለት ታውጅ የነበረችው


ኤዲ ስለ በሽታ ያላትን እምነት ስትገልጥም “አዕምሮ ሁሉን
በሁሉ ነው ብቸኛው እውነት ልዕለ አዕምሮ ነው። ህመምና
በሽታ የህልም ጥላ ናቸው ወይም የአዕምሮ ጨለማ ዐሳብ
ውጤት ናቸው። ነገር ግን ይህ በሽታ ወይም ጭለማ በእውነት
ብርሃን (የአዕምሮ ብርሃን) ፊት ይሸሻል። በሽታና ሞት
የሥጋዊ አዕምሮ ወይም ኃጢአት ውጤት ናቸው።” በማለት
አስቀምጣለች።52 ይህ አባባሏም ኤዲ ‘ልዕለ አዕምሮ’ ስትል
ምን ማለቷ ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

51
Ibid., (p, 22).
52
Mary Baker Eddy. Christian Healing. (1936, P.21).

69
የአማልክቱ ዐዋጅ

ኤዲ በራሷ ጽሑፍ ክርስቲያን ሳይንስ ስለ ሰውነት እና ስለ


መለኮት ያለውን ምልከታ በማያያዝ ልዕለ አዕምሮ የልዩ ዲበ -
አካል መሠረት እንደሆነ አስፍራለች፦

“የሰው ፍልስፍና እግዚአብሔርን እንደ ሰው


ያደርገዋል። ክርስቲያን ሳይንስ ግን ሰውን እንደ
እግዚአብሔር ያደርገዋል። የመጀመሪያው ስሕህተት
ነው። ሁለተኛው ግን ትክክል ነው። ልዩ ዲበ - አካል
ከፊዚክስና ከቁስ አካል በላይ ነው። ልዩ ዲበ -አካል
የሚመደበው ባረፈበት መሠረት ወይም ልዕለ አዕምሮ
ነው” ብላለች።53

በዚህም ልዕለ አዕምሮ ያገዘፈ የዲበ - አካል ሃይማኖት


ምልከታዋ “እግዚአብሔር ልዕለ አዕምሮ ነው፤ ሁሉንም
54
ይገዛል…” በማለት ለመለኮት ማንነት የራሷን ግልጽ
ትርጓሜ ሰጥታለች። ሜሪ ቤከር ልዕለ አዕምሮን ከሰውነት
በመለየት “የማይወሰን ምጡቅና ዘላለማዊ እግዚአብሔር
ነው” እያለች በተደጋጋሚ ብታስቀምጥም በሌላ በኩል
መለኮትን በዚሁ ስልታዊ ቃል በመጠቀም ከሰውነት ጋር
ትቀላቅለዋለች። “እውነት መጀመሪያ የለውም። ልዕለ
አዕምሮ የሰው ነፍስ ነው። ይህም ሰውን በፍጥረት ላይ ሁሉ

53
Mary Baker Eddy. (2006. P, 283).
54
Ibid., (p, 163).

70
ጆንሰን እጅጉ

ገዥ ያደርገዋል።”55 ብላለች። በዚህም የሰውን አማልክትነት


ለማስረፅ ጥራለች። በኤዲ ማብራሪያ ‘ልዕለ አዕምሮ’
የሚለው ስያሜ ለሰው ነፍስ ተሰጥቷል። በአጠቃላይ ኤዲ
ራሷን ያስተዋወቀችበት የልዕለ አዕምሮ ወይም ክርስቲያን
ሳይንስ ትምህርት በራሱ የተወዛገበና ውኃ የማያነሳ ነው
ማለት ይቻላል። በአጠቃላይ አስተምህሮዋ የአፍላጦንን
(Plato, 429BC-347BC) የሚታየው ዓለም የማይታየው ዓለም
ጥላ ነው፤ ነፍስም የሥጋ (የቁስ) እስረኛ ነች የሚለውን
ፍልስፍና የቡድሃ ነፃ የመውጣት (ዐወንታዊ ካርማ56) ወይም
የሂንዱ የአትማን57 ወደ ባራህማን የመሻገር58 አስተምህሮ
ጭማቂ እንደሆነ የታየበት ነው ማለት ይቻላል። ይህ ደግሞ
የዲበ - አካል ሃይማኖት ወጥነት የሌለውና በራሱ መልክ
የማይገለጥ ተለዋዋጭ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ኢማ ኮርቲስ ሆፕኪን (1849-1925)

“የመምህራን መምህር” ወይም “የዲበ - አካል


ሃይማኖት ሐዋርያ” በመባል የምትታወቀው
ሚስ ኢማ ኮርቲስ ሆፕኪን ለኤዲ ኤዲተር
55
Ibid., (p, 321).
56
ፖዘቲቭ ካርማ፦ የተሻለ የሕይወት ዙር ዕድል
57
አትማን፦ የሰው ውስጣዊ ክፍል ወይም ነፍስ ሲሆን የባራህማ ክፍል ወይም
ቁራጭ አካል ነው።
58
ባራህማን፦ ዓለምን የፈጠረ ኃይል ወይም ዩኒቨርሳል ንቃተ ሕሊና ሲሆን
በየአንዳንዱ ነገር ውስጥ ያለ መለኮታዊ ባሕርይ ነው።

71
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመሆን “የክርስቲያን ሳይንስ” ዜና የሚል ጋዜጣ በተከታታይ


ለንባብ አብቅታለች59። ግልጽ የቋንቋ አጠቃቀም ችሎታ
እንዳላት የሚነገርላት ሆፕኪን ኋላ ላይ ከኤዲ በመለየት
የራሷን “ክርስቲያን ሳይንስ ኮሌጅ” የተባለ ትምህርት ቤት
ለመክፈት ችላ ነበር። ከኤዲም ይልቅ የተሻለችና ታዋቂና
ተሰሚ አስተማሪ ልትሆን ከመቻሏም በላይ በርካታ የልዩ ዲበ
- አካል ቁልፍ አስተማሪዎችን ልታፈራ ችላለች። ከእነኚህም
አስተማሪዎች መካከል ኸርነስት ሆምስ፣ ቻርልስ ፊሊሞርና
ክሬመር ተጠቃሽ ናቸው።
ሆፕኪን የጸሎትን ምላሽ ወይም የመበልጸግና የፈውስን
ምሥጢር ስታስረዳ፦

“የምናውጀውን ነገር ሁሉ እንደምናገኘው


እርግጠኞች ነን። አምላክ የፈጠረልን ሁሉ መልካም
ነው። የኛ ድርሻ እንዲሆኑ መናገር ብቻ ነው።
በዙሪያችን የኛ ቃል የሚያንቀሳቅሰው የማይታይ
ኀይል አለ። እንዲሆን የምንፈልገውን ነገር እንዲሆን
እናደርገዋለን። መጥፎ ነገሮችን ስንናገር እንደዛው
ይሆንብናል። ማንኛውንም ነገር እንደምንመኘውና
እንደምንፈልገው እንደዛው እንዲሆን መናገር
60
እንችላለን።”

59
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, P. 98).
60
Ibid., (p. 100).

72
ጆንሰን እጅጉ

ያለች ሲሆን በሽታና ሞትንም ሙሉ በሙሉ በመካድ ዕውን


አይደሉም፤ ሕልም ናቸው ትል ነበር። ይህም ሰዎችን ለኅሩይ
ቃላት ዐዋጅ ልምምድ ለማዘጋጀት ያግዛት ነበር። ሌላው
ሰውን ለዚሁ ዐዋጅ ልምምድ ማዘጋጃ መንገዷ ደግሞ ጥቅስ
መጥቀስና የሥነ - ሰብና የሥነ - መለኮትን ትምህርት
በማቃወስ ሰውን የማመልኮት ስልት ነበር። ኪዊምቢይም ሆነ
ኤዲ መለኮትን አዕምሮ ነው ብለው እንደሰየሙ ሁሉ
ሆፕኪንም ጥቅስ ጠቅሳ መለኮትን “አዕምሮ ነው” ብላለች።

እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።


እግዚአብሔር አዕምሮ ነው። አዕምሮ ሁሉም
መልካም እንደሆነ አየ። የሚያየው፣ የሚያሸተውና
የሚቀምሰው መልካም ነው። ምንም የሚጎዳ
የለም። ምንም የሚያጠቃ የለም። ይህ
የምንጠብቀው የእግዚአብሔር ኪዳን ነው። ከሞት
ጋር ከተስማማን ሞትን እንቀበላለን። 61

በዚህ ሁኔታም የስነ - ልቦና ቀረፃዋን ካካሄደች በኋላ


የዐወንታዊ ዐዋጅ ልምምድን ስታሰርጽ፦

“በሁሉ ቦታ መገኘት፣ ሁሉን ማወቅ፣ ሁሉን


መቻል የሚሉትን ቃላት ሳናቋርጥ ዝም ብለን
እንናገር። ይህንን ስናደርግ በፍጥነት ትልቅ
61
Emma Curtis Hopkins, 12 Lessons in Spiritual Healing. (2016, P. 160).

73
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደሆንን እጅግ ኃይለኞች እንደሆንን እና ጠቢብ


እንደሆንን ይሰማናል። በርግጥ ማንነታችን
እንደጨመረ ላናይ እንችላለን። ውሳኔያችን
የተሻለ ይሆናል፤ በርግጥ ደግሞ ወዲያው ይህንን
ለውጥ ላናይ እንችላለን።”62

ብላለች። ሆፕኪን እግዚአብሔርን አዕምሮ እንዳለች ሁሉ


‘ዐወንታዊ ዐዋጅ’ ለምትለው ቃል ትርጉሙንና አቅሙን
ያስቀመጠች ሲሆን ‘ዐወንታዊ ዐዋጅ’ ማንም ሰው
የሚፈልገውን መልካም ነገር ለራሱ መፍጠር የሚችልበት
የንግግር ጥበብ ሕግ እንደሆነም ትናገራለች። ይህንንም
ስታስረዳ “እንደ ነፃ ጤንነት ያለ የራሳችሁን መልካም መጥራት
ትችላላችሁ። የጠራችሁት የተጠማችሁት ነፃ ጤንነት ከሆነ
63
ተፈጥሮ ሁሉ ‘አሜን’ ይላል።” ብላለች። ይህንንም
የምትለው የሚታወጁ ኅሩይ ቃላት በራሳቸው ኀይል
እንዳላቸው ስለምታምን ነው። ይህንንም ስታስረዳ “በቃላት
ውስጥ ወደ ላይ የሚያነሳ ወይም ከፍ የሚያደርግ መልካም
ዐቅም አለ” ብላለች።64 በአጠቃላይ ሆፕኪን ልዕለ አዕምሮን
ይሠራል ብላ ያመነችበትን የንግግር ኀይል በስፋት

62
Ibid., (2016, P. 100).
63
Ibid., (P. 23).
64
Ibid., (P. 86).

74
ጆንሰን እጅጉ

አስተዋውቃለች። የታሪክ ምሁራን እንደሚናገሩት ከሆነም


ሆፕኪን ባትኖር የዲብ - አካል ሃይማኖት ይሞት ነበር።

ማሊንዳ ኢሊቶ ክሬመር (1844 - 1926)


ማሊንዳ ኢሊቶ ክሬመር በሆፕኪን
ትምህርት የተመሰጠች የሆፕኪን ተማሪ
ነበረች። በኋላ ላይም የራሷን “የመግለጥ
ሕግ” law of expression በማበልጸግ
ልታስተዋውቅ ችላለች። ክሬመር
በሰንፍራንሲስኮ “የመለኮታዊ - ሳይንስ
ቤተ ክርስቲያን” መስራችና የመጀመሪያዋ የመለኮታዊ ሳይንስ
ኢንስቲዩት ፕሬዝዳንትም ሆናለች። በክሬመር ትምህርት
ሥርው የመግለጥ ሕግ የማይታየውን መለኮት በሚታይ መልክ
የሚገልጥ ሲሆን፤ የአዕምሮ ስነ ምግባር፣ የተመስጦ እና
የባሕርይ ለውጥ ድምር ውጤት ነው።

እንደ ክሬመር እምነት “የአዕምሮ ለውጥ” ማለት ግን


ማንኛውንም ዐሉታዊ ዐሳብ ማስወገድና “በልዩ ዐዋጅ”
መተካት መቻል ማለት ነው። እንደ እሷም ይህ ሕግ የፈውስና
የብልጽግና ሕግ ቁልፍ ነው።65 ይህንንም ስታስረዳ “ፍጹም
እንደሆንክ ስታስብ ፍጹምነት ይገለጥብሃል ፍጹም
አለመሆንን፣ በሽታን፣ ኃጢአትን ስታስብ ያው ነገር
65
Haller, J. S. The History of New Thought. (2012, P,109).

75
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይሆንብሃል እውነትን አስቡና ሳታቋርጡ ለራሳችሁ ተናገሩ


ችግር የለም! አልፈራም በሉ የሚያስፈራ ነገር በፍጹም የለም
በሉ።”66 በማለት ሰው የሚፈልገውን ነገር ምላሽ ከንግግሩ
ድግግሞሽ የተነሣ እንደሚያገኝ አስተምራለች።

ትምህርቷንም የመግለጥ ሕግ ደረጃ በማለት ያስቀመጠች


ሲሆን እንደ እሷ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ያስቀመጠችው
መለኮትን የመግለጥ ጥበብን ነው። ይህንንም ስትገልጥ፦

እኔ በሰውነቴ አልወሰንም፣ በድርጊት አልወሰንም፣


በሥራዬ ውጤት አልወሰንም፣ አካሌ በማይወሰን ዐሳብ
ይዘት ያለ አካለ - መንፈስ ነው፣ ዓይኔ ለእውነት
ተከፍቷል፣ ፍጹም የነፃነት ሕግን ይዣለሁ፣ መለኮታዊ
ተፈጥሮዬ በመንገዶቼ ሁሉ የምገልጠው ሕግ ነው፣
በመንገዴ ሁሉ እውነትን አውቃለሁ፣ ጉዞዬ የሰላም ጉዞ
ነው፣ በትልቅ ዕድል ፋንታ ውስጥ ቆማለሁ፣ በእውነት
ሐይቅ ውስጥ ኖራለሁ፣ ፍጻሜ በሌለው ወርቃማ
የፍቅርና ወጣትነት ንጋት ውስጥ አድራለሁ። 67

ብላለች። እነኝህ የተሽሞነሞኑ ኅሩይ ቃላት የተሸከሙትን


ቀጥተኛ ትርጉም ልብ ላለው የክሬመር ጥበብ መለኮትን

66
Ibid., (P,124)
67
Cramer, M. Divine Science and Healing. (2018, P. 68).

76
ጆንሰን እጅጉ

መግለጥ ሳይሆን መለኮት ሆኖ መገለጥ እንደሆነ ማስተዋል


ከባድ አይሆንበትም።

ክሬመር የእምነትን አስፈላጊነት በማንሳት የእምነት


ትምህርት ያስተማረች ሲሆን፤ “እምነትን በትክክል መመስረት
ከመንፈስ ጋር አንድ እንደሆንን ማመን ነው። እምነት
መግለጥም እንደ መንፈስ መናገርና ማድረግ ነው።”68
ብላለች። ክሬመር ‘እምነት መለኮት እንደሚናገር መናገርና
ማድረግ ነው’ የሚለውን ፍልስፍና ለማስረዳት ኢየሱስ
‘ኃጢአትህ ተሰረየልህ’ ማለቱንና ‘አልጋህን ተሸክምህ ሂድ’
ማለቱን በምሳሌነት ታነሳለች። ይሁን እንጂ ይህ አቀራረቧ
ኢየሱስ መለኮትም ሰውም መሆኑን ማዘናጋትና ሰውን ሙሉ
ለሙሉ ከኢየሱስ ጋር እኩል ማድረግ ወይንም መለኮት
ማድረግ ይንፀባረቅበታል። እርግጥ የወጣችበት ከፍታ የሚናድ
ደረጃ መሆኑን ሳታስውል የሆፕኪንን መንገድ ተከትላለች።
እንደ መለኮት ለመናገርና ለማድረግ መለኮት መሆን
እንደሚጠይቅ ስለገባትም ይህንኑ ለማሳካት ጥራለች ማለት
ይቻላል።

ክሬመር በዚሁ ጫፍ በማያደርስ “የመግለጥ” ትምህርቷ


ፈውስን ስለማረጋገጥ ስትጠቅስም፦

68
Odhner. C. Journal of Dreams. (2016, P. 86.).

77
የአማልክቱ ዐዋጅ

የድነት እውነት የኔ ነው፣ እውነት አሁን የኔ ነው፣


የእግዚአብሔር መንግስት አሁን በኔ ውስጥ ናት፣
የመንግስተ ሰማይ የሆነው ሁሉ አሁን እጄ ላይ ነው፣
ከኃጢአት እምነት አሁን ነፃ ወጥቻለሁ፣ እኔ የዘላለም
ሕይወት ነኝ፣ አሁን ከሞት ነፃ ነኝ፣ የኢየሱስ
የሕይወት መንፈስ አሁን ነፃ አውጥቶኛል፣
እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ አሁን
አመልካለሁ፣ አሁን ምንም መልካም ነገር እንደማላጣ
አምናለሁ፣ እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር አሁን
የሚያስረግጥ ነው፣ አሁን በተረጋገጠ ነገር ውስጥ
ኖራለሁ። 69

ብላለች። ይህ የክሬመር ‘እንደ መለኮት መናገርና ማድረግ’


የሚለው “የመግለጥ ሕግ” ሁሉ ነገር በሰው ልጅ ፈቃድ ስር
እንደወደቀ ለሚያስመስለው የኅሩይ ቃላት ዐዋጅ ትምህርትና
ልምምድ ሥርው እንደሆነ መካድ አይቻልም። የእምነት ቃል
እንቅስቃሴ መሪዎች ተመሳሳይ አካሄድም ቢሆን እንደ ክሬመር
ባሉ የዲበ - አካል ሃይማኖት መሪዎች መንገድ እየተጓዙ
እንዳሉ ማየት አይቸግርም።

ቻርልስ ፊሊሞር (1854–1948)


በዲበ - አካል ሃይማኖት ላይ የተደረጉ
የታሪክ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፊሊሞር
69
Odhner. C. Journal of Dreams. (2016, 76).

78
ጆንሰን እጅጉ

ወደ ዲበ - አካል ሃይማኖት እንቅስቃሴ ዘው ያለው በኢሉኑስ


የልዩ ዲበ - አካል ኮሌጅ በሆፕኪን አማካኝነት በ 1886 ይሰጥ
በነበረውን “ክርስቲያን ሳይንስ” ኮርስ ላይ የዲበ - አካል
ሃይማኖትን ወይም “የመለኮት ሳይንስ” ትምህርት ከተከታተለ
በኋላ ነው። ታሪኩ እንደሚያሳየው በዚህ ወቅት ፊሊሞር
አርባዎቹ ላይ ቢደርስም ከአሥር ዓመቱ ጀምሮ ሁለቱም
እግሮቹ በአግባቡ የማይታዘዙለት ክራንች ተጠቃሚ ነበር።

እንደ ታሪኩም ከሆነ የፊሊሞርን ትኩረት የሳበው በሆፕኪን


የልዩ ዲበ -አካል የጸሎት ጥበብ ማለትም በኅሩይ ቃላት ዐዋጅ
ባለቤቱ መርትል ፊሊሞር በወቅቱ መድኃኒት ከሌለው የሳንባ
ነቀርሳ በሽታ በአንድ ዐመት የዐዋጅ ልምምድ መፈወስ
መቻሏ ነበር። በተጨማሪም ይህንኑ የመርትልን ምስክርነት
ሰምተው በሚመጡ በሽተኞች ላይ መርትል ራሷ
የተማረችውን የልዩ ዲበ - አካል ዐዋጅ ትምህርት ተግባራዊ
ስታደርግ በዐይኑ መመልከት ቻለ። ይህም ተደጋጋሚ ስኬት
ቻርልስ ፊሊሞርን በዚሁ የዐዋጅ ምትኃት ለመፈወስ
እንዲቋምጥ አደረገው። እንደተመኘውም በአጭር ጊዜ በኅሩይ
ቃል ዐዋጅ ልምምድ ሁለቱም እግሩ ተፈውሶ ጤነኛ ሰው
ለመሆን እንደቻለ ተጠቅሷል።70

70
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P, 6-8)

79
የአማልክቱ ዐዋጅ

በዚህም መሰረት የክሬመር ተወዳጅ ተማሪ ፊሊሞር በክሬመር


መለኮታዊ ሳይንስ ጥበብ (Divine science) ከተፈወሰ በኋላ
በክሬመር ተጽዕኖ ሥር ሊወድቅ ችሏል። ይህንንም ለመረዳት
1890 ፊሊሞር በጻፈው ጆርናል ላይ “ለአማልክት” ሆፕኪን
ያለውን አድናቆት ማየት በቂ ነው። ሞስሊ ይህንን የፊሊሞር
አድናቆት ሲጠቅሱ “በመንፈስ ካለማቋረጥ ትሰርፃለች
መገኘቷ ፈውስ ነው፣ እሷን ለመስማት ዕድል ያገኙ ሁሉ
በአዲስ ሕይወት ይሞላሉ”71 ማለቱን አንስተዋል። ይህ
አድናቆት የሆፕኪንን አማልክትነት ያረጋገጠ ወይም ሰው
ለአምላኩ የሚያቀርበውን አምልኮ ዐይነት እንደሆነ ማየት
አይቸግርም። ከፊሊሞር አስተያየት በመነሳት በአንድ ጊዜ
ከሺዎች በላይ ሊሰሟት የሚሰበሰቡላት ሆፕኪን ምን ያህል
ተጽዕኖ ፈጣሪ ተናጋሪ እንደነበረችም መገመት አይቸግርም።

ቻርልስ ፊሊሞር ከሆፕኪን በመቀጠል የኪዊምቢይን


ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልክ የማላበስ ሥራ የሠራ
ሲሆን፤ ፕሮፌሰር ታይንዶል ያስቀመጠውን የተፈጥሮ ሕግ
ወደ ሰው አዕምሮ ክፍል ጎትቶታል። በዚህም ፍልስፍናው
ለሰው ልጅ ክርስቶሳዊ ተፈጥሮን በመስጠት ሰው “አማልክት”
እንደሆነ በጥቅስ ለማረጋገጥ ሞክሯል። ለምሳሌ ያህል
የኢያሱንና የኢየሱስን የስም ትርጓሜ በመያዝ “የልዩ ዲበ -

71
Ibid., (P.9).

80
ጆንሰን እጅጉ

አካል የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት” በተባለው መጽሐፉ


ሲያስረዳ፦

‘ኢያሱ’ ማለት ‘አዳኝ’ ማለት ነው ‘ጆሆቫ’ ከሚለው


የእብራይስጥ ቃል የወጣ ነው። ጆሆቫ ‘ነፃ አውጪ’
ወይም ‘አዳኝ’ ማለት ነው። በእብራይስጥም ‘ኢየሱስ’
ከሚለው ስም ጋር አቻ ነው። እነኝህ ሁለት ቃሎች
‘ጆሆቫ’ከሚለው ቃል የተገኙ ናቸው። ይህም ‘እኔ እኔ
ነኝ’ ያለው እሱ ነው። በኢያሱና በኢየሱስ መካከል
ያለው ልዩነት ‘እኔ ነኝ ውስጥ የተገለጠው ሥውር
ሕሊና ልቀት ደረጃ ብቻ ነው። በሆነ የአዕምሮ ደረጃ
ላይ ‘እኔ ነኝ’ እጅግ ልቀት በማግኘት ኀይል
ይጨምራል። ይህ ኀይል በመንፈሳዊ መረዳት የራሱ
የሆነ መሠረት አለው። ኢያሱ የእስራኤልን ልጆች ወደ
ተስፋይቱ ምድር አስገብቷቸዋል። ስለዚህ በእኛ ‘እኔ
ነኝ’ ኀይል ወይም በውስጣችን ያደረውን ክርስቶስ
በመያዝ የሕይወት መዋጀት ኀይል እናገኛለን። 72

ብሏል። ፊሊሞር በዚሁ መጽሐፉ ክርስቶስ እያለ የሚጠራው


ግን መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በማለት የሚያሳየንን ማንነት
ሳይሆን እርሱ ራሱ “ዐሳባዊ ሰው” የሚለውን ነው። ይህንንም
አስመልክቶ “ክርስቶስ እግዚአብሔር በራሱ መልክ እና ምሳሌ
የፈጠረው ሰው ነው። ፍጹም የሆነ ዐሳባዊ ሰው፤ ይህ ደግሞ
72
Charles Fillimore. Metaphysical Bible Dictionary. (1931. P,531).

81
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሰዎች ሁሉ እውነተኛ ማንነታቸው ነው።”73 ብሏል።


በተጨማሪም በተደጋጋሚ ክርስቶስ የሰው ሁሉ መጠሪያ
እንደሆነ በጽሑፎቹ ጠቅሷል።

ፊሊሞር የኅሩይ ቃላት ዐዋጅ ትምህርትን ጥቅስ ጠቅሶ


ቢያስተምርም የቃል ኀይል መሠረቱ አዕምሮ እንደሆነና
በተጨማሪም በበሽታ ላይ ያለውን ዐቅም በተለየ ሁኔታ
ያምናል። ይህንንም ሲገልጥ:-“ማይክሮብስ ወይም ጀርም
የሚፈጠረው በዐሳብ ኀይል ነው። ዐሳብ በዐሳቢው ሰው
አዕምሮ አማካይነት ቅርፅና መልክ በመያዝ ዕውን ይሆናል፤
ዐሉታዊ ወይም የተሳሳተ ዐሳብ የበሽታ መንስኤ ህዋሶችን
ይፈጥራል። መልካም ዐሳብ ደግሞ አካል ገንቢ ጥሩ ነገር
ይፈጥራል”74 ብሏል።

እንደ ፊሊሞር ከሆነ የሰው ልጅ የአዕምሮውን ኀይል


መጠቀም የሚችለው አዕምሮው ከመለኮታዊ አዕምሮ ጋር
መዋሃድ ሲችል ነው። ይህንንም ሲናገር “የሰው ልጅ ኢየሱስ
እንዳደረገው በጥበቡ አዕምሮውን ከመለኮታዊ አዕምሮ ጋር
ሲያዋህድ፤ እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበትን የኀይል ሕግ
መጠቀም ይችላል።”75 ብሏል። እንደ እርሱ ከሆነ የሰው ልጅ
አዕምሮ ከመለኮታዊ አዕምሮ ወይም ልዕለ አዕምሮ ጋር
73
Ibid., (P, 907).
74
Ibid., (P, 648).
75
Ibid., (P, 819).

82
ጆንሰን እጅጉ

በመዋሃድ ከመለኮት ጋር አንድ የሚሆንበት ጥበብ ዐሉታዊ


ዐሳብ ማስወገድ ነው።76 እንደ እርሱ ይህ ሲሆን የሰው ልጅ
በገዥነት ዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ የኀይል አካላትም
ይታዘዙለታል።

ፊሊሞር የአዕምሮን ኀይል ከአንደበት ጋር በቀጥታ


ያያይዘዋል። ይህንንም ሲያስረዳ “ይህንም ብሎ በታላቅ
ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፣ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።” (ዩሐ.11፡
43)። የሚለውን ቃል በመጥቀስ ይህ የኢየሱስ ልምምድ
የቃል ኀይል የአዕምሮን ኀይል በማነሳሳት ፈውስን
እንደሚያረግጥ ያሳያል ብሏል።77 ፊሊሞር ቃል በሁለት
መንገድ ይሠራል ለመልካም ወይም ለህመም በማለትም
(ምሳ. 18:21)78 ጥቅስ ጠቅሷል።79 በሌላም ቦታ “ሰው
በአንደበቱ ቃል የራሱን ዓለም መፍጠር ይችላል።” ያለ ሲሆን
ይህንንም ለማስረዳት ደግሞ የምሳሌ መጽሐፍን ያነሳል።
(ምሳ. 12:18)። ይሁን እንጂ የተነሱት ጥቅሶች ዐሳቡን
አይደግፉትም።

ፊሊሞር ጸሎት የሚመለስበትን ሁኔታ ሲያብራራ ቴንዶል


ከተፈጥሮ ሕግ ጋር እንዳገናኘው ሁሉ እርሱም ከተፈጥሮ
76
Ibdi. (P, 768).
77
Ibdi. (P, 575).
78
በምዕራፍ አምስት ላይ “የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል” በሚለው ንዑስ ርዕስ
ሥር ይመለከቷል።
79
Ibdi. (P, 982).

83
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሕግ ጋር የማያያዝ ፍንጭ ይታይበታል። ፊሊሞር የጤንነት


ወይም የፈውስ ጸሎት ከሌላው ይልቅ በፍጥነት ይመለሳል
ሲልም ምክንያቱን ያብራራል፦

ይህ ጸሎት ከሁሉ ይልቅ በፍጥነት የሚመለስ ጸሎት


ነው፤ ምክንያቱም የተፈጥሮ ሕግ ለመለኮት ሕግ
አካላችን እንዲዘጋጅ ያደርገዋል። ሰው በጸጥታ
ውስጥ ሆኖ መንፈስ ጤንነቱን እንዲያድስ ሲጋብዝ
የአካሉን የተፈጥሮ ኀይል እንቅስቃሴ እንዲጨምር
ይጣራል። በጸሎት አዕምሮ ይታደሳል አካልም
ይለወጣል።80

ብሏል። እንደ ፊሊሞር ከሆነ አካል በመታደስ ጤንነትን


የሚቸረው በአካል ውስጥ ወዳለው የተፈጥሮ ሕግ ጥሪ
ስለተደረገና ይኸው ሕግም በዚህ ጥሪ ምክንያት
እንቅስቃሴውን ስለጨመረ ነው ማለት ነው። በአጠቃላይ
እንደ እርሱ ከሆነ ቀጥተኛ የፈውስ ምክንያት ወይም የጸሎት
መልስ ምክንያት በሰው አካል ውስጥ ያለ የተፈጥሮ ሕግ
መንቀሳቀስ ነው።

80
Charles Fillimore. Metaphysical Bible Dictionary. (1931. P, 771)

84
ጆንሰን እጅጉ

በአጠቃላይ ፊሊሞር የመለኮታዊ አዕምሮ እና የአንደበት


ኀይል መላምት ጽንሰ - ዐሳብን በመያዝ የዐዎንታዊ ዐዋጅን
አስፈላጊነት አስተምሯል።81ይህንን ሲያስረዳ፦

የአንደበታችሁን ከፍታ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ይሁን፣ ‘እኔ ...


አይደለሁም’ በሚል ዐዋጅ ጊዜ አታጥፉ። ‘አልፈራም’
ማለት አንዳንድ ጊዜ ይጠቅም ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህ
ይልቅ ሁል ጊዜ ማለት ያለባችሁ ‘እኔ ደፋር፣
የማልፈራ፣ ልበ - ሙሉ ነኝ የሚለውን ዐዎንታዊ ቃል
ዐዋጅ ነው።82ብሏል።

ፊሊሞር ይህን የልዩ ዲበ - አካል በዓለም ላይ በሰፊው


በማሰራጨት የተዋጣለት ለመሆን ችሏል። በአጠቃላይ
ፊሊሞር በትምህርቶቹ ክርስቶስን “ዐሳባዊ ፍጥረት”
ሲያደርገው ሰውን ደግሞ ክርስቶስ ያደርጋል። ይህንንም
በመሰለ የልዩ ዲበ - አካል ፍልስፍናው አያሌዎችን
አጥምቆ አሰማርቷል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት
በተደራጀ ሁኔታ ሚሽነሪዎችን አሠልጥኖ በመላክ
በ 2005 ዓ.ም ብቻ በመቶ ሥልሳ ዘጠኝ አገሮች የዲበ -
አካል ሃይማኖት ሚኒስትሪዎችን መክፈት ችሏል።
ሚኒስትሪዎቹ ታዲያ የጸሎት ኅብረቶችንና “የዩኒቲ ቤተ

81
Ibdi. (P, 997).
82
Ibdi. (P, 571).

85
የአማልክቱ ዐዋጅ

ክርስቲያን” አጥቢያዎችን በመክፈት በርካታ ጽሁፎችን


በመበተን ረድተውታል።83

በተለይ ደግሞ “የሜታፊዚክስ መዝገበ ቃላት” የተሰኘው


መጽሐፉ እንቅስቃሴውን ለማስፋፋት አግዞታል። ጽፎቹና
ትምህርቶቹም እስከ አሁን ድረስ በኤሌክትሮኒስ ጭምር
በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። በአጠቃላይ ፊሊሞር የወንጌል
አማኞችን የጸሎት ሕይወት የሸረሸረ የተሳካለት የዲበ - አካል
ሃይማኖት መሪ “የምጡቃዊነት” ማለትም
“የትራንሴንዴንታሊዝም” እንቅስቃሴ መሪ “የዩኒቲ ኮሚኒቲ
ትምህርት ቤት” መሥራች እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ።

ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን (1803-1882)፦ ይህ


ሰው የዲበ - አካል ሃይማኖት ቅርንጫፍ
የሆነው ምጡቃዊነት
(transcendentalism)84 ፍልስፍና መሪ
83
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, pp. 90-91).
84
ምጡቃዊነት(transcendentalism)፦ የአፍላጦን (Peleto) ፍልስፍና ተጽዕኖ
እና የዲበ - አካል ሃይማኖት አስተሳሰብ ቅርፅ ያለው የዐሳባዊነት እንቅስቃሴ ነው።
ፍልስፍናው “እውነትን እያንዳንዱ ሰው ማወቅ የሚችልበት መለኮት (ብርሃን)
በውስጡ አለ” የሚለው የኤመርሰን አስተሳሰብ መሠረቱ ነው። ይህ ደግሞ
“ለግላዊነት” አስተሳሰብ መሠረት ጥሏል። እንቅስቃሴው ዐሳባዊነትን፣ የኢማኑኤል
ካንትን ዲበ - አካል ፍልስፍናን፣ ልዩ ዲበ - አካልንና በተለመደው መንገድ የመጽሐፍ
ቅዱስ ጥቅሶችን በማጣመር በክርስትና ግንዛቤዎች ላይ ጫና ፈጥሯል። በአጠቃላይ
“ሰው በውስጡ ያለውን እውነተኛ ማንነት ወይም መለኮትነት ማለትም ምጡቅ
መንፈስ በነፍሱ ዓይን በማየትና በማወቅ ሲያድግ ከውስንነት ነፃ በመውጣት
ከመለኮት ጋር ይቀላቀላል” የሚል ፍልስፍና ይከተላል።

86
ጆንሰን እጅጉ

ሲሆን “አሜሪካዊው ነቢይ” በመባልም ይታወቅ ነበር።


በትምህርቱም ኢየሱስ ከማንኛውም ሰው የተለየ ማንነት
እንደሌለው አስተምሯል። አዳምንም “የአማልክት ዘር ፍጹም
ሞዴል” በማለት ከፊት ያሰልፈዋል።85 ኤመርሰን በ 1836
“ተፈጥሮ” የሚል መጽሐፍ የጻፈ ሲሆን፤ በመጽሐፉም ላይ
ወደ የማይወሰን አጥናፈ ዓለም (ቦታ የለሽ ዓለም) አርጋለሁ
ሁሉንም ነገር ዐያለሁ፣ እኔ የመለኮት ክፍል አካል ነኝ ማለቱን
ሂላር ዘግበዋል።86 ግብረ ገባዊነትም አንዱ የመለኮትነት
መንገድ እንደሆነ በዚሁ ፍልስፍናው ጠቁሟል። “በመታዘዝ
ራሳችንን በማኖር መለኮት (አምላክ) እንሆናለንም።” ብሏል።
87

ይህንን የመለኮትነትን ጽንሰ - ዐሳብ እስከ ሆፕኪን ድረስ ያሉ


መሪዎች በግልጽ ሲናገሩ ቢቆዩም ኤመርሰን አግንኖታል።
እንደ ሌሎቹ መሪዎችም ትምህርተ - ሰብዕንና ትምህርተ -
መለኮትን አፋልሷል። በጽሑፉም “ለገጣሚ፣ ለፈላስፋና
ለቅዱሳን ሁሉም ነገር ወዳጃዊና በረከት ሆኗል፣ ሁሉም
ነገሮች አትራፊ፣ ሁሉም ቀኖች ቅዱስ፣ ሁሉም ሰው መለኮት
ነው።”88 በማለት አረጋግጧል። በአጠቃላይ ኤመርሰን

85
Works of Ralph Waldo Emerson (P.76)
86
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, P,5).
87
The Complete Essays and Other Writings of Ralph Waldo Emerson. (1950, P.
190)
88
Ibid., (P. 124).

87
የአማልክቱ ዐዋጅ

በፕሮፌሰር ታይንዶል የተፈጥሮ ትንታኔ ላይ በመንጠላጠል


በተፈጥሮ ውስጥ የተጎለተ ሕግ ከያንዳንዱ ሰው ጋር ትስሥር
አለው፤ እያንዳንዱ ሰው በተናጠል በራሱ መንገድ ከዚህ ሕግ
ጋር ኅብረት በመፍጠር ወደፈለገበት መድረስ ይችላል በማለት
የግለ-ምጡቃዊነትን ልምምድ ማስረፅ ለድኅረ ዘመናዊነት
መሠረት ጥሏል።

ኸርንስት ሆምስ (1887-1960)


ኸርንስት ሆምስ የአዕምሮ ሳይንስ ጸሓፊና
የዐዎንታዊ ዐስተሳሰብ “positive
thinking” ፈላስፋ ነው። ሆምስ በ 1918
የልዩ ዲበ - አካል ትምህርት ቤት በቦትሰን
የከፈተ ሲሆን በሰው ሕይወት ውስጥ
የሚሠራ የአመክንዮና የውጤት ሕግ እንዳለ በስፋት
አስተምሯል።89 ቅዱሳት መጻሕፍት አንድ ድርጊት
የሚወልደው ሌላ ክሥተት ወይም ውጤት እንደሚኖረው
ቢናገሩም የክስተቱ ባለቤት ግን መለኮት እንደሆነ
ይጠቁማሉ። ሆምስ ግን በትምህርቱ ይህንን እውነት
በማዛባት የገኃዱ ዓለም ሥነ - አመክንዮም ይሁን ውጤት
ባለቤት አዕምሮ ነው በማለት አስቀምጧል።

89
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P, 137).

88
ጆንሰን እጅጉ

በዚህም የዐዎንታዊ ዐስተሳሰብ በተደጋጋሚ ለአዕምሯችን


ዐሳቦች መልስ የሚሰጥ ሕግ እንዳለ ያስተማረ ሲሆን
ኢየሱስም ይህንን ሕግ አስተምሯል ይላል። ይህንንም
ሲያስረዳ “የምናስበው ነገር ሁሉ ዲዛይን ነው። አዕምሮ
ደግሞ ፈጣሪ ነው። ኢየሱስ ይህንን ሕግ አስተዋውቋል።
ኢየሱስ ‘እንደምታምኑት እንደ እዚያው ይሆናል!’ ብሎ
90
ነበር።” በማለት አስፍሯል።91 በአጠቃላይም የሆምስን
ትምህርተ - ሰብዕን ያየን እንደሆነ የሰው ልጅ ፍጹም የሆነ
መንፈሳዊ ፍጥረት ስለሆነ በዐሳቡ ኀይል ብቻ የማይታይ
ነገርን ወደ መታየት ማምጣት የሚችል ፍጥረት ነው።
ይህንንም ሲገልጥ “የሰው ልጅ ዐሳቡን ወደ መንፈሳዊው
ዓለም በመልቀቅ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ መልሶ መቀበል
ይችላል።”92 ብሏል።93

ሆምስ የአስተሳሰቡ መሠረታዊ መመዘኛ “ሰው ፍጹም የሆነ


መንፈስ እንዲኖረው ሆኖ ተፈጥሯል” የሚል ከመሆኑ
በተጨማሪ ሰው አማልክት መሆኑን መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ

90
Ernest Holmes Creative Mind and Success. (1919. p. 10).
91
በምዕራፍ አምስት ላይ “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል” በሚለው ንዑስ ርእስ
የተሰጠውን መልስ ይመለከቷል።
92
Ernest Holmes Creative Mind and Success. (1919. p. 21).
93
በምዕራፍ ሦስት “መለኮታዊ እምነት” በሚለው ንዑስ ርእስ የተሰጠውን መልስ
ይመለከቷል።

89
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሰማንያ ሁለትን በመጥቀስ ለማጽናትም


94
ይሞክራል። ይህንንም ሲያብራራ፦

“እግዚአብሔር ምጡቅ መንፈስ እንደሆነ ሁሉ


እኛም በዚሁ መንፈስ ምሳሌና መልክ ነው
የተፈጠርነው። መለኮት ባለበት በዛው መርሖ
95
ውስጥ ነው የተፈጠርነው። በምጡቅ መንፈስና
በተመሳሳይ የድርጊት አመክንዮና ውጤት ሕግ
ተፈጥረናል።”96

ብሏል። ሆምስ እንደ አብዛኛዎቹ የዲበ - አካል ሃይማኖት


መሪዎች ሁሉ ህመም የዐሳብ ውጤት እንደሆነ ሲያምን
ዐስተሳሰብን በመለወጥ ውጤትን መለወጥ ይቻላል ይላል።
ይህንንም በጽሑፉ ሲገልጥ፦ “አንድ ሰው ህምም ሲሰማው
ህመሙን በጤንነት መተካት ከፈለገ አሁን ያለው ነገር ምንም
ቢሆን ግድ የለኝም ፍጹም ነኝ ይበል።”97 ብሏል። ስለዚህም
ሆምስ የዲበ - አካል ሃይማኖትን ቀደምት አማልክት
ተከትሏል ማለት ይቻላል። በተጨማሪም ዐስተሳሰቡ የከረመ
ቢሆንም እንኳ ዘመነኞቹ የእምነት ቃል አማልክት አንግበው
ይዘውታልና በቸልታ የምናየው አይደለም።
94
ibid., (p.12).
95
በምዕራፍ አምስት ላይ “የእግዚአብሔር መልክ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር
የተሰጠውን መልስ ይመለከቷል።
96
Ernest s. HomlesThe science of Mind. (nd. p.3).
97
ibid., (p. 13).

90
ጆንሰን እጅጉ

ኢ. ደብልዩ ኪኒየን (1867-1914)


ኪኒየን የዲበ አካል ሃይማኖት ማለትም
“የዘመናዊ አዲስ ዐስተሳሰብ” ወይም
የዐዎንታዊ ዐዋጅ (positive confession)
አራማጅና የቤቴል መጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርት ቤት መሥራችና ጸሓፊ ነው። ይህ ሰው በ 1892
“የዐወንታዊ ዐስተሳሰብ” (positive thinking) ፈላስፋ
በነበረው ኸርንስት ሆምስ የዲበ - አካል ሃይማኖት ትምህርት
ቤት በመግባት ተምሯል። በዚህም የትምህርት ቤት ቆይታው
ቻርልስ ኤመርሰን የተባለ ክርስቲያን ሳይንቲስት እና
የትምህርት ቤቱ ርእሰ - መምህር አስተምሮታል። በዚህም
ምክንያት ኪኒየን በዲበ - አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ደህና
አድርጎ እንደተጠመቀ የታሪክ ምሁራን ይስማማሉ።98
ኸርንስት ሆምስ የፊሊሞርን “ዐዎንታዊ ዐዋጅ” ፍልስፍና ወደ
“ዐዎንታዊ ዐስተሳሰብ” ቢመልሰወም ኪኒየን ግን የኸርንስት
ሆምስን “ዐዎንታዊ ዐስተሳሰብ” ፍልስፍና መልሶ ወደ
‘ዐዎንታዊ ዐዋጅ’ በመቀልበስ እንደገና ቀድሞ ወደነበረበት
ሊመልሰውና በራሱ መንገድ ሊያሳድገው ችሏል።99
ትምህርቱንም “የእምነት ቃል” በማለት የሰየመው ሲሆን
ዝናና ሐብትንም አትርፎበታል።

98
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, P, 269).
99
በምዕራፍ ሁለት ላይ መለኮትን ማነቃቃት በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል።

91
የአማልክቱ ዐዋጅ

በኪኒየን ትምህርት መሠረት የትኛውም የሚሠራ እምነት


ከዐዋጅ ቃል ጋር ይያያዛል። በሌላ አገላለጽ እምነት
በዐዎንታዊ ዐዋጅ ነው የሚሠራው። በዚህም ጽንሰ - ዐሳብ
ምክንያት ዐወንታዊ ዐዋጅ ወይም የኅሩይ ቃል ዐዋጅ
የእምነት እንቅስቃሴ ማዕከላዊ መርሖ ሊሆን ችሏል። ይህም
በየመስባኩና በየመጣጥፉ ላይ እየተደጋገመ እንዲሰፍር
በማድረግ በሰፊው እንዲሰራጭም ተደርጓል። ለምሳሌ፦
ኪኒየን ጽንሰ -ዐሳቡን ካነሳባቸው በርካታ ትምህርቶችና
ዐረፍተ - ነገሮች መኃል “እምነታችን የሚወሰነው
በምናውጀው ቃል ነው።”100 የሚለውን ቁልፍ ዐሳብ ማንሳት
ይቻላል። እንደ ኪኒየንም ከሆነ እምነት የሚለካው
በዐዎንታዊ ዐዋጅ ቃል ነው። በሌላም ቦታ “የእምነት ቃል
ዐዋጅ እግዚአብሔርን እንዲሠራ ያደርገዋል።”101 በማለት
እግዚአብሔር ለመሥራት እስከምንናገር ድረስ እንደሚጠብቅ
አንፀባርቋል። በዚህም የቃል ዐዋጅ ትምህርት ምክንያት
የእምነት እንቅስቃሴን የሚያራምዱ አብያተ ክርስቲያናት
የድምፅ ብክለት የሚያስከትል ከፍተኛ ጩኸትና መጯጯህ
መለያ ምልክታቸው ሊሆን ችሏል ማለት ይቻላል።

በተጨማሪም ኪኒየን “በአንደበታችን የምንናገረው ነገር


በትክክል የሚገዛን እርሱ ነው።”102 በማለትም የአንደበትን
100
E.W. Kenyon. The Power of Your Words. (1981, P. 50).
101
Ibdi. (p, 190).
102
Ibdi, (p,158).

92
ጆንሰን እጅጉ

ልዕልና ተናግሯል። ይህንንም ሲያብራራ ዐሉታዊ ነገር


የምንናገር ወይም የምናውጅ ከሆነ መንፈሳችንን የሚገዛው
ለእርሱ ነው። በሽታን የምንናገር ከሆነ በሽታ በአካላችን
ውስጥ መሥራት ይጀምራል ብሏል። “ዐዎንታዊ ዐዋጅ
ስታውጁ ሁሉም ነገር የእናንተ ይሆናል በዐሉታዊ ዐዋጅ
ደግሞ ሁሉንም ነገር ታጣላችሁ።”103 በማለትም የቃል ዐዋጅ
በሕይወታችን ላይ ከፍተኛ የመግዛትና የመወሰን ዐቅም
እንዳለው አስተምሯል።

ኪኒየን የዐዎንታዊ ቃል ዐዋጅ ትምህርትን ለማግነንና


የኢየሱስን ምሳሌነት እከተላለሁ ለማለት ሲል፤ ኢየሱስ
በሰበካቸው ስብከቶች ውስጥ ስለራሱ የተናገራቸውን ቃለት
በመልቀም፤ ኢየሱስ ማንና ምን እንደሆነ በተደጋጋሚ ያውጅ
ነበር ብሏል።104 ለምሳሌ ኢየሱስ “እኔና አብ አንድ ነን።” ብሎ
መናገሩ ለኪኒየን ዕውነትን የሚገልጥ ስብከት ሳይሆን ወደ
መለኮትነት ጫፍ ለመድረስ በሚደረግ ትግል የተነገረ የእምነት
ቃል ዐዋጅ ነው። በዚህም የኪኒየን የቃል ዐዋጅ ሥነ -
መለኮት ምክንያት የእምነት ቃል እንቅስቃሴ አብያተ -
ክርስቲያናት፤ ስብከቶች፣ የፈውስ ፕሮግራሞች እና
ዝማሬዎች የዐዎንታዊ ቃል ዐዋጅ ቅኝት እንዲኖራቸው ሆን
ተብሎ በስፋት ተሠርቷል።
103
E.W. Kenyon.The Hidden Man. (P. 126).
104
E.W. Kenyon. The Power of Your Words. (P, 78.).

93
የአማልክቱ ዐዋጅ

ኬኔት ሄገን (1933 - 2003)


ኬኔት ሄገን “የእምነት እንቅስቃሴ ሐዋርያ”
በመባል ይታወቃል። ይሁን እንጂ እንደ
ኪኒየን ከዲበ - አካል ሃይማኖት ፍልስፍና
ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም። ነገር ግን
የኪኒየን ሌላኛው አፍ በመሆን የኪኒየንን
ትምህርቶች ከ 50 ዐመታት በላይ በዘለቀ አገልግሎቱ
አስተምሯል። የሬማ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መሪ
እና የዓለም አቀፍ ሬማ አገልግሎት ፕሬዝዳንት በመሆንም
ሠርቷል። 1974 እ.ኤ.አ. የሬማ የርቀት መጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርት ቤትን የከፈተ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቱ
ትምህርቶቹን በጽሑፍ በቪዲዮና በኦዲዮ በመላው ዓለም
እንዲሰራጭ አግዘዋል። ሄገን በ 1933 ሦስት ጊዜ ለአሥር
ደቂቃ እንደሞተና ሲዖልን ዐይቶ እንደተመለሰ (I went to
hell) በተሰኘ መጽሐፉ ላይ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን
ይኸው ልምምድ ዳግም የተወለደበትን የእምነት ምስጢር
እንዲገለጥለት እንዳስቻለውም በዚሁ መጽሐፉ ላይ
105
ተናግሯል።

105
Kenat Hagin. I went to hell. (1982).

94
ጆንሰን እጅጉ

እንደ ኪኒየን ሁሉ ተጨባጭ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል


በምርመራ ከመረዳት ይልቅ በመገለጥ የበላይነት በመተርጎም
ያምን የነበረው ሄገን እ.ኤ.አ. በ 1934 ኢየሱስ በተለያየ ወቅት
ለስምንት ጊዜ ያህል ተገልጦለት የማርቆስን ወንጌል መሠረት
ያደረገ የእምነትን ቃል ትምህርት እንደገለጠለት የተናገረ
ሲሆን መገለጡ “ትምህርቴን አስቀየረኝ” ብሏል። (ማር. 11፡
23)። በዚህም ምክንያት ሄገን ይህ ክፍል ሕይወቱን
እንደለወጠው ይናገራል። ከዚህም በኋላ በ 1968 እ.ኤ.አ.
የመጀመሪያውን “የእምነት ቃል” የተሰኘ ትምህርት አሳትሞ
65 ሚሊዮን ቅጂ ተሽጦለታል። ሄገን “የዘመናዊ የእምነት
እንቅስቃሴ አባት” በመባል የሚታወቅ ልዩ ዐመታዊ ስብሰባና
በርካታ “የእምነት ቃል” ኮንፍረንሶችን በማድረግም
ይታወቃል።

በአጠቃላይ ኬኔት ሄገን ያራመደው እንቅስቃሴ “የእምነት ቃል


እንቅስቃሴ” ወይም “የብልጽግና ወንጌል” በሚል ይታወቃል።
ሥነ -መለኮቱም ድነት በኢየሱስ የሚገኝ እንደሆነ ይጠቅሳል።
ይሁን እንጂ እንደ እርሱ ከሆነ “ድነት” መንፈሳዊና ምድራዊ
ስኬትን ያካተተ “ጥቅል” ነው።106 ሄገን የልመና ጸሎትንም
እንደ እምነት ማነስ ይመለከተዋል። የልመና ጸሎትን
ከመለኮት ሉዓላዊ ፈቃድ ጋር በማገናኘት ለሚሞግቱት

106
በምዕራፍ ስድስት “አላምጥም አለችኝ” በሚለው ንዑስ ርእስ ይመለከቷል።

95
የአማልክቱ ዐዋጅ

አማኞችም መልስ ሲሰጥ፦ “ፈቃድህ ቢሆን ብለን መጸለይ


የለብንም፤ ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቃል
ገብቶልናል። የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ማለትም፤ መንፈሳዊ፣
አካላዊና ቁሳዊ ፍላጎታችን እንዲሟላልን እግዚአብሔር
ፈቅዷል”107 ብሏል።

ኪኒየን “የእምነት ቃል እንቅስቃሴ” መስራች እንደመሆኑ፤


በኬኔት ሄገን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳረፈ በርካታ የሥነ -
መለኮት አጥኚዎች ይስማማሉ። ለምሳሌ ማክኮኔል ኬኔት
ሄገን የራሱ የሆነ ትምህርት እንደሌለውና ከኪኒየን የተሰረቀ
ትምህርት እንደሚያስተምር ለማስረዳት ያስቀመጡት ሰፊ
ንጽጽር ይህንኑ ተጽዕኖ የሚያመለክት ነው።108

የኬኔት ሄገን ከሂይፖቶኒዝም ጋር እጅግ መመሳሰል ያለው


“በመንፈስ መውደቅ” ፣ “በመንፈስ መሳቅ” አሊያም
“በመንፈስ ራስን መሳት” ወይም “መጓዝ” የሚባሉ
ልምምዶቹ የትውልድን ቀልብ ገዝተዋል። በተጨማሪም
የተለመደውን “የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ የሚል” መሸፈኛ
አግኝተዋል። በአጠቃላይ ሄገን የኪኒየንን ልዩ ዲበ - አካል
ፍልስፍና ምሳሌና “መገለጥ” በታጀቡ ስብከቶቹ በማስቀጠል
ለቍጥር የሚያታክቱ በርካታ ሰባኪያንን ልብ በመስረቅና

107
Kennt Hagen. Praying to Get Results.1(983. P,6).
108
McConnell. A Different Gosspel. (1988, Pp, 8-12).

96
ጆንሰን እጅጉ

ከእምነት ቃል እንቅስቃሴ ኋላ በማስሰለፍ የተሳካለት መሪ


ለመሆን ችሏል። እንደ ጆይስ ማየር፣ ጆይል ኦስተንና ኀይሉ
ዮሐንስ የመሳሰሉ በርካታ አቀንቃኞች ራሳቸውን የትምህርቱ
ቅርጫት ቢያደርጉም ከጠቀስኳቸው ዋና መሪዎች ይልቅ
በጥልቀት ሊያብራሩልን ስለማይቸሉ አልተካተቱም።
በተጨማሪም የዐሳብ ድግግሞሽን በማብዛት ያሰለቹናል
በሚል ታልፈዋል።

የዚህ መጽሐፍ ዐላማም በትምህርቱ ውስጥ ያሉ ሰዎችን


ሁሉ ማጋለጥ አይደለም። ይልቁንም ትምህርቱን በጥልቀት
በመመርመር ከአርዮስ ትምህርት ያላነሰ ኑፋቄ እንደሆነ
ማሳየት ነው። ስለሆነም ከግለሰቦች ይልቅ በትምህርቱ ላይ
ትኩረት በማድረግ ለትምህርቱ መስፋፋት ቀዳሚና አንጡራ
ታሪካዊ ድርሻ ያላቸውን፤ ትምህርቱን በግልጽና በበቂ ሊያሳዩ
የሚችሉ መረጃዎች ብቻ ተተንትነዋል። በአጠቃላይ
አንዳንድ የትምህርቱ አቀንቃኞች የተጠቀሱት ትምህርቱን
ማንሳት ስለተፈለገ ወይም ድርሻቸው ሰፊ ስለሆነ ብቻ
ነው።

97
የአማልክቱ ዐዋጅ
ማጠቃለ
ያ ፕ ሮፌ ሰር
ሳይንቲስት
ጆ ን ታ ይንዶ ል
ኢማ ኑኤ ል ሲ ው ዲ ንበርግ
25 የዲ በ - አካል መጻሕ ፍት የጸሎ ት መ መ ዘኛ

ተፈ ጥሮ
ዲ በ - አካል መ ጽ ሐ ፍ ቅ ዱ ስ (ራ ልፍ ዋ ልዶ
መ ፍቻ ኤ መ ርሰን)
(ቻ ርልስ ፊ ሊሞ ር)
የክርስቲ ያ ን ሳይንስ
(ኢ ማ ኮርቲ ስ
ሳይንስና ሆፕ ኪን)
ጤንነት የአዕ ም ሮ
(ኤ ዲ ቤከር) ሳይንስ“positive
thinking”
(ኢርነሰት ሆምለስ)

ኅሩይ ቃል ዐዋጅ
(የኪኒየንና የኬኔት ሄገን በርካታ መጻሕፍት)
የ (ኬኒዮን+ሄገን)

ቤተ ክርስቲያን

ግራፍ አንድ፦ይህ ግራፍ ለዲበ - አካል ሃይማኖት ዕድገት ትልቅ


አስተዋጽዖ ያደረጉ መጻሕፍትና ታሪካዊ ትስስራቸውን ያሳያል።

98
ጆንሰን እጅጉ

የፍልስፍናው ማዕከላዊ ዐሳብ በአዕምሮ፥ በዐሳብና በአንደበት ቃል


መኃል ያለው ትስሥር ነው።
በደራሲው

ሜ ዝሜ ርዝም (አኒማ ል ማ ግኔቲዝም )


(ፍሬንዝ አንቶ ን ሜ ዝ መ ር)

የአዕም ሮ ፈ ው ስ
(ፊ ናስ ፓርክሆረስት ኪዊ ም ቢይ)

ትራ ንሴንደንታ ሊ ዝም
(ራ ልፍ ዋ ልኮዶ ኤ መ ርሰን)
ኢማ ኑኤ ል ሲውድንበርግ
ዲ በ-አካላዊ ሃይማ ኖት

(ልዩ ዲ በ-አካል )

ክርስቲያን ሳይንስ (divine science)


(ኢማ ኮርት ስ ሆፕ ኪን)

ዐዎ ንታ ዊ ዐስተሳሰብ
(ኢርነስት ሆም ለስ)

የመግለጥ ሕግ
(ማ ሊንዳ አሊቶ ክሬመ ር)

ዐዎ ንታ ዊ ዐዋጅ
(ቻ ርልስ ፊ ሊሞ ር)

የቃ ል ዐዋጅ በርካታ መጻሕፍት


(ኢ.ደብልዩ ኪኒየን+ኬኔት ሄገን)

99
የአማልክቱ ዐዋጅ

ግራፍ ሁለት፦ ይህ ግራፍ የዲበ - አካል ሃይማኖትን ዋነኛ


የፍልስፍና ማዕከልና ለመስፋፋት ያገዘውን መጻሕፍት ያሳያል።
መጻሕፍቱ እስከ አሁን ድረስ ሰፊ ተነባቢነት ያላቸው ሲሆን
አዳዲስ ጸሓፍያንም ዐሳባቸውን በየጊዜው ይገዙታል።
በደራሲው

የአዕ ም ሮ
ፈ ው ስ ቢሮ
(1838)
ፖርት ላንድ
ቤቴ ል መ ጽ ሐ ፍ (ሜ ዝ ሜ ር)
የክርስቲ ያ ን ሳይንስ
ቅ ዱ ስ (ኅሩይ ቃል
ት /ቤት (1881)
ዐዋ ጅ ) ት /ቤት
ቦት ሰን (ኤ ዲ )
(ኬኒዮን)

የዲ በ - አካል
መ ለኮታ ዊ ሃይማ ኖት የክርስቲ ያ ን
ሳይንስ ኮሌጅ
ሰንፍራ ንሲስኮ ፍልስፍና ሳይንስ ኮሌጅ
(በክሬመ ር) (ሆፕ ኪን)

የመ ልካም ዐስተ ሳሰብ ሆፕ ኪን


ት /ቤት (1918) ቦት ሰን
(ሆም ለስ )

ግራፍ ሦስት፦ ለዲበ - አካል ሃይማኖት መዳበርና መስፋፋት


ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉት እነኚህ ተቋማት ናቸው። ይህም

100
ጆንሰን እጅጉ

የትምህርት ተቋማት ዐሳብን ለማስረጽ ያላቸውን ዐቅም


ያመለክታል።
በደራሲው።

የምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ ጥያቄዎች


1. የእምነት እንቅስቃሴ ትምህርትን ወይም ልምምድን እንደ
ባዕድ እምነት ወይም ኑፋቄ መፈረጅ ተገቢ ነው ብለህ
ታምናለህ? በምን መለኪያ? በአገራችንን አውድ የእምነት
እንቅስቃሴ መሪዎችን ሳይጨምር ምዕመኑ ሁሉ
ትምህርቱን ተረድተውና ሆነ ብለው ተቀብለውታል
ማለት እንችላለን?
2. ጸሓፊው የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ዐዎንታዊና ዐሉታዊ
ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው በማለት ያጎላበትን ተጨባጭ
እውነታ መገንዘብ ምን ይጠቅማል?
3. ከኢማኑኤል ሲውዲንበርግ ጀምሮ እስከ ኬኔት ሃገን
ድረስ ያሉ መሪዎች የሚያስተሳስራቸው ዋና የፍልስፍና
ዐሳብ ምንድነው?
4. የዲበ - አካል ሃይማኖት ባይኖር የእምነት እንቅስቃሴ
አይወለድም ነበር ብሎ መደምደም ይቻላል? ለምን?
5. በዚህ ክፍለ ንባብህ ያገኘኸው ግንዛቤ ምንድነው? ከዚህስ
የተነሳ በግል ልምምድህና አገልግሎትህ ላይ ምን ለውጥ
ለማድረግ ወስነሃል?
6. የዲበ - አካል የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ትመህርት የቤተ
ክርስቲያን ችግር ነው ብለህ ታስባለህ? ለምን?

101
የአማልክቱ ዐዋጅ

ክፍል ፪

102
ጆንሰን እጅጉ

ጥምር ተግዳሮት

  

103
የአማልክቱ ዐዋጅ

ምዕራፍ 2

የዲበ - አካል ሃይማኖት ኪኒየንና ኬነት ሄገን


ምንም እንኳ የኪኒየንም ይሁን የሄገን ሥነ - መለኮት የዲበ -


አካል ሃይማኖትን ከክርስትና ጋር ያጣመሩ ጽንሰ - ሃሳቦችን
በስፋት የተከተለ ቢሆንም እንደ ጆይ ማክኢንታየር ያሉ
ጸሓፍት ይህንን እውነታ በማስተባበል ይከላከላሉ።
ማክኢንታየር የኪኒየንን የእምነት ቃል እንቅስቃሴ “ዘመናዊ
እንቅስቃሴ ነው” ብሎ በማሞካሸት ከዲበ - አካል ሃይማኖት
ፍልስፍና ጋር ክርስትናን አላቀላቀለም ሲል ተከራክሯል።
ይህንንም “ኪኒየን እና የእምነት ቃል መልዕክቱ” በተሰኘ
የማስተባበያ መጽሐፉ ሲገልጽ፦ “የመጽሐፍ ሥራዬን ስሠራ
የታተሙ መጻሕፍትንና ሌሎች የኪኒየንን መጽሔቶች መረጃ
ተጠቅሜአለሁ። ኪኒየን የልዩ ዲበ -አካል ፍልስፍናን እና
ክርስትናን እንዳላቀላቀለም አረጋግጫለሁ።”109 ብሏል። በዚሁ
ጽሑፉ “የኪኒየንን ትምህርት መሠረት ከልዩ ዲበ - አካል
ይልቅ የወንጌል አማኞች መሪዎች ናቸው” በማለትም

109
McIntyre, J. E.W. Kenyon and His Message of faith (2010, p, 21).

104
ጆንሰን እጅጉ

የኪኒየንን ትምህርት ወደ ወንጌል አማኞች የተኃድሶ


እንቅስቃሴ ለመወርወር ሞክሯል።

ይህንንም ሲያስረዳ “ትምህርቶቹ ከእርሱ በፊት የነበሩ


የወንጌል አማኞች መሪዎችን ትምህርት የሚያንፀባርቁ
ናቸው።”110 ብሏል። እርሱ ይህንን ይበል እንጂ በርከት ያሉ
የኪኒየን ሥራዎች ምስክርነቱን ውሸት በማድረግ ያጋለጡ
ናቸው። ቀጥሎም የኪኒየንን ትምህርት አስተዋጽዖ ሲያብራራ
“ትምህርቶቹ በብዙ መንገድ ልዩ ናቸው፤ ከ 19 ኛው ክፍለ ዘመን
ከወንጌላውያን እንቅስቃሴ ጋር በቀላሉ የሚገጥሙ ወይም
የሚስማሙ ናቸው። ኪኒየን የ 19 ኛውን የወንጌላውያን እና
የ 20 ኛውን ክፍለ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ (revival) እንቅስቃሴ
ካገናኙ ቁልፍ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው።”111 ብሏል።

ማክኢንታየር ራሱን እንደ ታሪክ ጸሓፊ በመመልከት ለኪኒየን


ትምህርት እንዲህ ከፍተኛ ቦታ በመስጠት የኪኒየንን
ትምህርት ከወንጌላውያን የቅድስና እንቅስቃሴ Higher life
movement እና ከመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ጋር
ሊቀላቅለውና ሊደብቀው ይሞክር እንጂ ዘይትን ከውኃ ጋር
እንደመቀላቀል ነው የሆነበት። በእርግጥም ማክኢንታየር

110
Ibid., (2010, p, 23).
111
Ibid., (p, 469).

105
የአማልክቱ ዐዋጅ

ታሪክን ለመዘገብ ብቁ አይደለም። ምክንያቱም እርሱ ራሱ


የእምነት ቃል እንቅስቃሴ አካልና አገልጋይ ስለሆነ ነው።

ራሱ ኪኒንየም ቢሆን ከልዩ ዲበ-አካል ጋር ያለውን ንክኪ


በመካድ ልዩ ዲበ-አካልን በማጣጣል112 ልዩ ዲበ-አካል ለአዲሱ
ክርስትና አያስፈልግም በማለት ይኮንናል።113 ይሁን እንጂ
ትምህርቶቹ ይህንን አይመሰክሩለትም። ማክኮኔል ለዚሁ
ክኽደት መልስ ሲሰጡ ሌሎች የታሪክ ጸሓፍት እንደሚያነሱት
ሁሉ ኪኒየን በኸርንስት ሆምስ የዲበ-አካል ሃይማኖት
ትምህርት ቤት ገብቶ መማሩን ጠቅሰዋል።114 ማክኢንታየር
ታዲያ የታሪክ ጸሓፊ ከሆነ ብዙዎች የሚያነሱትን ይህን
እውነት ለምን ሸሸገ? አንድ የታሪክ ጸሓፊ በገለልተኝነት
ተጨባጭ እውነታዎችን ሳይሸሽግ መዘገብ ይጠበቅበታል።
በተጨማሪም ኪኒየን ከሁለትዮሽ ዓለም (Dualism)115
ከአፍላጦን አስተሳሰብ ጋር መስማማቱንም ማኮኔል
ያነሳሉ።116 በእርግጥም ኪኒየን ሁለት ዓይነት ጽድቅ፣ ሁለት
ዓይነት ዕውቀትና ሁለት ዓይነት እምነት የሚሉት
ትምህርቶቹ ይህንኑ የልዩ ዲበ-አካል ሁለትዮሽ ትምህርት

112
E.W.K enyon. The Hidden Man. (Pp, 41, 116)
113
E.W. Kenyon. A New Type of Christianity. (p. 4).
114
McConnell. A Different Gospel. (1988, p.37).
115
የሁለትዮሽ ዓለም የሚታየው ዓለም የመንፈሳዊው ዓለም ነጸብራቅ ነው
የሚል ነው።
116
McConnell. A Different Gospel. (1988, P, 105).

106
ጆንሰን እጅጉ

የሚያረጋግጡ ናቸው።117 ይሁን እንጂ ማክኢንታየር ይህንን


ሐቅ መመልከት ወይም መመርመር የፈለገ አይመስልም።

በአጠቃላይ ኪኒየንና ትምህርቶቹን ስንመለከት ከልዩ ዲበ-


አካል የቃል ሕግ ፍልስፍና አላመለጡም። የ 19 ኛው ክፍለ
ዘመን የወንጌላውያን የቅድስና (የተሓድሶ) እንቅስቃሴ
ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደነበረ የታመነ ቢሆንም ኪኒየንን ከዲበ-
አካል ሃይማኖት ፍልስፍና አድኖታል ማለት በጭራሽ
አይቻልም። ኪኒየንም ተከታዮቹ እንደሚሰብኩለት የቅድስና
እንቅስቃሴና የተሓድሶ እንቅስቃሴ ድልድይ በጭራሽ
አልሆነም። ይልቁንም በተሓድሶ መንገድ ላይ የተጎለተ
እንቅፋት በመሆን የተሓድሶን ቀጣይነት አደናቅፏል ማለት
ይቻላል። የዚህ መጽሐፍ ጸሓፊ ከዚህ እውነት ጋር በጽኑ
ይስማማል።

ኪኒየንም ሆነ ሄገን በዕውቀት፣ በሰውነትና በእምነት ወይም


በቃል እምነት ላይ ያላቸው ዕይታ እንደ ልዩ ዲበ-አካል
አማልክቱ ሁሉ የተንሸዋረረና የሥነ-ሰብዕን መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ትምህርት በማፋለስ ሰውነትን የሚያመለኩት ኑፋቄ
ነው። ይህም መመሳሰል ኑፋቄው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
እንዳልተወለደ ይመሰክራል። ለምሳሌ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን
ተፈጥሮ በሚለው ጽሑፉ ላይ “እኔ የእግዚአብሔር ክፍል
117
E.W. Kenyon. The Hidden Man. (P, 72).

107
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወይም አካል ነኝ”118 እንዳለው ሁሉ ኪኒየንም እግዚአብሔር


ከሰው መንፈስ ጋር እኩል ተፈጥሮ አለው ማለቱን ማኮኔል
ያነሣሉ።119 በእርግጥ አብዛኛዎቹ የእምነት እንቅስቃሴ
መናፍቃን ይህንን በድፍረት ቢሉም ኬኔት ሄገን ግን የኪኒየንን
ኑፋቄ በመከተል “አማኞች የክርስቶስ አካል ናቸው፤
ክርስቶሶች ናቸው።”120 በሚለውና መሰል ትምህርቱ ጎልቶ
ይወጣል።

የእምነት እንቅስቃሴ መሪዎች መለኮት መሆናቸውን ሲናገሩ


እንደ እግዚአብሔር፣ እንደ ክርስቶስ ዐይነት ወይም አዲስ
ተፈጥሮ በሚሉ ግልጽ ቃላት ይጠቀማሉ። የልዩ ዲበ-አካል
አማልክቱ አገላለጽ ግን ልዩ ልዩና ሁሉንም አቃፊ ስለሆነ
አደናጋሪ ነው። አብዛኛዎቹ የዲብ-አካል ሃይማኖት
አቀንቃኞችም ተግባራዊ ልምምዱ ላይ እንጂ መጠሪያው
ምንም ቢሆን ግድ የሌለባቸው የላቸውም። እንደ እነርሱም
ከሆነ መለኮት የአዕምሮ ክፍል ነው። ለምሳሌ “አማልክት”
መርፊ መመልኮትን ሲገልጽ “ተፈጥሮ፣ ሕይወት፣ ፈጣሪ
(አምላክ)፣ የፈጠራ ብቃት ቢባሉም፤ እነዚህ በቀላሉ ውስጠ
ሕሊናን በመተካት የሚያገለግሉ መጠሪያዎች ናቸው።”121
ብሏል። አስቀድመን እንደተመለከትነው የዲበ-አካል
118
Ralph Waldo Emerson, Nature, nd, p,3.
119
McConnell, A Different Gospel (1988. P, 44).
120
በምዕራፍ ሦስት ”መለኮታዊ እምነት“ በሚል ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል።
121
ጆሴፍ ሙርፊ። አእምሮን የመጠቀም ጥበብ። (ገጽ.50) ።

108
ጆንሰን እጅጉ

ሃይማኖትም ሆነ የእምነት ቃል መሪዎች በዚህ ስልት


ትምህርተ-ሰብዕን በማፋለስ ሰውን የሚያመለኩቱት የኅሩይ
ቃል ዐዋጅ አስተምሮን የሰውን ልጅ ችግር መፍቻ ቁልፍ
እንደሆነ አድርገው መሠረት ለመጣል በማሰባቸው መሆኑ
ቀዳሚ ሥፍራ ይይዛል።

ለምሳሌ ኪኒየን “አዲስ ክርስትና” በሚለው መጽሐፉ ላይ


የፈውስን ፍላጎት ለማሳካት የቃል ዐዋጅ የሚሠራበትን ሂደት
ሲያስረዳ “የእምነት ቃል በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የሞቱ
ሴሎችን በማደስ ይገነባል።”122 ብሏል። ይህ ዐስተሳሰብ
በቻርልስ ፊሊሞር እና ክሬመር መሬት የወረደ ትምህርት
እንደሆነ ልብ ይሏል።123 ይህ እንዴት ይሆናል ቢሉ እንደ
እነርሱ ከሆነ ምስጢሩ የሰው ልጅ “አማልክት” በመሆኑ ነው።
እንደ እነርሱም ‘የቃል ዐዋጅ’ የኀይልና የፈውስ ስልጣን
ገቢራዊ ምስጥሩም ይህው ነው። ለዚህም የመመልኮት
ልምምድ መሠረት ምክንያት ተደርጎ በእምነት እንቅስቃሴ
አማልክት የሚቀርበው አንደኛው የሰው አፈጣጠር ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ የዳግም ልደት ምስጢር ነው።

ኪኒየን የሰውን ተፈጥሮ ሲያስረዳ ሰው በኤደን ገነት


በእግዚአብሔር መልክ በእግዚአብሔር ምድብ ውስጥ ነው

122
E.W. Kenyon. A New Type of Christianity. (P, 15).
123
ገጽ 52፣ ገጽ.56 እንዲሁም ገጽ. 109፣ገጽ. 209 እና ገጽ.219 ይመለከቷል።

109
የአማልክቱ ዐዋጅ

የተፈጠረው። ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኘውም በመንፈሱ


ነው፤ ሰው መንፈስ ነው የዚህም ምክንያቱም እግዚአብሔር
መንፈስ ስለሆነ ነው። ሰው በኃጢአት ሲወድቅ የሰይጣንን
ተፈጥሮ ተካፍሏል (ሰይጥኗል)። የአምስቱ ስሜት ህዋሳቱ
እስረኛ ሆኗል።124 ያለ ሲሆን የዳግም ልደትን ምስጢር ደግሞ
ሲያስረዳ ሰው በዳግም ልደትም ዳግመኛ (በውደቀት አጥቶት
የነበረውን) የመለኮትን ተፈጥሮ በመካፈል የመለኮት ልጅ
ሆኗል ይላል።125 በአጠቃላይ እንደ ኪኒየንና ሄገንን ከሆነ የቃል
ዐዋጅ የጸሎት መልስ፣ ዳግም የተወለደ መንፈስ ፍሬ፣
በእምነት ላይ ያለ እምነት፣ የድነት ቁልፍ፣ የፈውስ ምስጢር
ነው። እንደ እነሱም የዚህ ትምህርት ምንጩ መገለጥ ስለሆነ
በዚህ ጉዳይ ላይ ጠያቂ ቢኖር እንኳ ቦታ የላቸውም።

ኪኒየን እንደ ዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክት ሁሉ ዕውቀት


ከጥናት ይልቅ በመገለጥ እንደሚገኝም ደጋግሞ ይናገራል።
ስለዚህም መለኮትም ቢሆን ከሰው ጋር ኅብረት የሚያደርገው
በአዕምሮ በኩል ሳይሆን ሰው በመንፈሱ በኩል በሚያገኘው
መገለጥ እንደሆነ ይቆጥራል። ይህንንም ሲናገር፦ “ዕውቀት
በግሪክ ኢፒግኖሲስ ይባላል። ይህም ማለት ሙሉ ዕውቀት
124
መንፈስ የአምስቱ የስሜት ህዋሳት እስረኛ ነው በማለት፤ መንፈስንም ብቻ ለይቶ
መንፈስ ነው ከመለኮት ጋር ህብረት የሚያደርገው በማለት የሰውን ስሜት
የማጣጣል ዝንባሌ ፤ የሰው ነፍስ በሥጋ ውስጥ ታስራለች ነፃ የምትወጣውም
በዕውቀት ነው ከሚለው ከፕላቶ ዲበ-አካል ፍልስፍና የተወሰደ እንደሆነ ልብ
ይሏል።
125
E.W. Kenyon. The Hidden man. (Pp,5, 184).

110
ጆንሰን እጅጉ

ማለት ነው፣ ትክክል የሆነ እክል የሌለበት። እንዲህ ዓይነት


ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፣ ይህ የሚገኘው በመገለጥ ነው።”126
ያለ ሲሆን መገለጥን በማግነኑ ምክንያት ቃለ-እግዚአብሔርን
በመመርመር መረዳት እንደማይቻል አሳይቷል። ይህም ብቻ
ሳይሆን መገለጥ ፍጹም ዕውቀት ነው ብሎ በማመኑ
“መገለጥ” የሚላቸውን ትምህርቶቹን በምንም ነገር ሊለኩና
ሊመረመሩ የማይችሉ የእምነት መሠረት አድርጓቸዋል።
ማኮኔል ይኸው የኪኒየን ዕውቀት በመንፈሳዊ መገለጥ ብቻ
እንደሚገኝ ማመንና በጥናት ላይ የተመሰረተ ወይም የመረጃ
ዕውቀትን ማጣጣል፤ በዲበ-አካል ሃይማነኖት ፍልስፍና
ለመዘፈቁ ማስረጃ እንደሆነ ይስማማሉ።127 በርግጥም
ለኪኒየን በመገለጥ መመላለስ ምጡቅነት ነው።

የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክትም ቢሆኑ እውነተኛው


ዕውቀት ወይም ትክክለኛው መረጃ ከመንፈሳዊው ዓለም
የሚያገኙት “መገለጥ” ወይም በውስጣቸው የሚፈጥሩት
“ህልም” እንደሆነ ያምናሉ። የዓለማችን ትልልቅ
ሳይንቲስቶችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተሳካላቸው በእዚህ
መንገድ መሄዳቸው እንደሆነም ያትታሉ። በብዕር ሥሙ
ዳዊት ድሪም በሚል እራሱን የሚያስተዋውቀው
ኢትዮጵያዊው የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና አራማጅ ዕውቀት
126
E.W. Kenyon New Creation realites, (nd. p.131).
127
McConnell, A Different Gospel, (1988, P,108).

111
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወይም ሕልም የሚፈጠርበትን መንገድ ሲናገር “ዐይንህን


በመጨፈን የውጪውን ዓለምና የውስጥህን ዐሳብ የተዘጋ
አድርገው”128 ይላል። ይሁን እንጂ ይህ ጥበብ አዕምሮን ሙሉ
ለሙሉ ንቁ እንዳይሆን በማድረግ ራስን ለውጫዊው ኀይል
(አጋንት) የማዘጋጃ ጥበብ ነው። ሙሉ ለሙሉ ራስን
በመሳትም በክፉ መንፈስ ቁጥጥር ሥር ያደርጋል።129 የዲበ-
አካል ሃይማኖት ተከታዮች በዚህ ልምምድ ዕውቀት
ወይምሕልምም ሆነ ፈውስ ይገኛል ብለው ያምናሉ።

የዲበ-አካል ሃይማኖት አቀንቃኞች እምነትን ሲገልጹ


‘እምነት’ የዐስተሳሰብና የስሜት ውጤት ነው ይላሉ።
ለምሳሌ ሙርፊ ይህንን ሲገልጽ “እምነት ማለት በአዕምሮህ
ያለው ዐስተሳሰብ ውጤት ነው። የውስጠ ሕሊናህ ኀይል
በዐስተሳሰብህ ልምምድ ልክ ይህንን ውጤት ወደ አጠቃላይ
የሕይወት መስመር ያሰራጨዋል።”130ብሏል። በመቀጠልም
ከመጽሐፍ ቅዱስ(ማቴ.9:23)131 በመጥቀስ ሰው ማመን
ያለበትም በውስጡ ያለውን ም ጡቅ ልዕለ አዕምሮ ዕምቅ
ዐቅም እንደሆነ ለመጠቆም ሞክሯል። በእርግጥ የልዩ ዲበ-
አካል አማልክቱ የሚያነሷቸው ጥቅሶች የሚሉትን የሚያሳዩ
128
ዳዊት ድሪም። (ገጽ.2012፣154)
129
በምዕራፍ ዘጠኝ ላይ “የውጫዊው መንፈስ ተቃርኖ” በሚለው ንዑስ ርዕስ
የተሰጠውን ዝርዝር ዐሳብ ይመለከቷል።
130
ጆሴፍ ሙርፊ። አእምሮን የመጠቀም ጥበብ። አቤል ጸጋዬ ።(2012፣ገጽ.52)።
131
“ልጄ ሆይ፣ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት።“

112
ጆንሰን እጅጉ

አይደሉም። ለምሳሌ ማቴዎስ እንደዘገበው ልጅቱ ምንድነው


ያመነችው? እነርሱ እንደሚሉት ዕምቅ ብቃቷን ከሆነ
ያመነችው ለምን አለቀሰች? ኢየሱስስ ያበረታታ የነበረው
ምን ዐይነት እምነት ነበር? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።

አማልክት ናፖሊዮን ሂል ደግሞ እምነትን የአዕምሮ ሁናቴ ነው


በማለት ሲገልጠው እምነት በመላለም ውስጥ ያለውን ኀይል
መጠቀም የምንችልበት ብቸኛው መሳሪያ ነው ይላል።
በመቀጠልም እምነት ውስንነትን በማፍረስ የፈለግነውን ነገር
ማድረግ ያስችለናል፤ አንደ ማኅተመ ጋንዲ ዐይነት የፖለቲካ
መሪዎች እንኳን ኀያል የሆኑት የእምነታቸውን ኀይል
ተጠቅመው ነው ይላል። እንደ እርሱ ከሆነ የስውር ሕሊናችንን
ተግባር የሚወስነው እምነት ነው።132 በአጠቃላይ እንደ
አማልክቱ እምነት ስሜትና ቃል ካልተቀላቀሉ አመርቂ
ውጤት ማግኘት አይቻልም። ናፖሊዮን ሂል የዚህን ምክንያት
ሲያስረዳ ሕሊናችን የሚነቃውና የሚሠራው እነኝህ
ሲቀላቀሉ ብቻ ነው ብሏል።133 ይህንንም ዐሳብ በማጠናከር
ሰው በእምነት መንፈስ በማሸነፍ ማንኛውንም ቁሳዊም ሆነ
መንፈሳዊ ሐብት ማግበስበስ ይችላል ብሏል።134

132
Napolieon Hill, Think and grow Rich. (1938, Pp, 65-77)
133
Ibdi, (p, 88).
134
Ibdi, (p, 195).

113
የአማልክቱ ዐዋጅ

ኪኒየንም እንዲሁ በእምነት ላይ ያለውን እምነት “በእምነቴ


ላይ ያለ እምነት” በሚል ንዑስ ርዕስ በተጻፈ መልዕክቱ ላይ
ሲያብራራ፦

በሦስቱ ወንጌላት ውስጥ የሚገኙት አስደናቂ የኢየሱስ


የእምነት መልዕክቶች አሉ። እነኝህ ዓረፍተ ነገሮች
ኢየሱስ ሰዎች በርሱ እንዲያምኑ የሚሞግቱ ናቸው።
ነገር ግን መልዕክቶቹ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን
ለአይሁድ የተላለፉ ናቸው። አይሁድ የማያምኑና
ከዳተኞች ነገር ግን የኪዳን ሕዝብ ናቸው። ኢየሱስ
በእርሱ መሲህነት እንዲያምኑ ይጫናቸው ነበር።
ፈውሳቸው በርሱ ላይ ባላቸው እምነት ላይ
የተመሠረተ ነው። ወደ ጳውሎስ መልዕክቶች ስንመጣ
ግን እምነት በኢየሱስ ላይ እንዲሆን የሚያደርግ ጫና
አናገኝም። አንድ ሰው ንስሓ ገብቶ የክርስቶስ
ቤተሰብ ከሆነ ሁሉም ነገር የእርሱ ነው። በጳውሎስ
መልዕክቶች ውስጥ እምነት ይኑራችሁ የሚል
መልዕክት አታገኙም። ለምን? ምክንያቱም ሁሉም
ነገር የእኛ ነው። 135

ብሏል። እንደ ኪኒየን ከሆነ በእምነት ላይ ያለ እምነት ዳግም


የተወለደ መንፈስ ፍሬ ወይም ውጤት ነው።136 ሁሉም ነገር

135
Don Gossett. E.W. Kenyon. Keys to Reciving God’s Miracle (2011, p,25).
136
E.W. Kenyon. The Hidden Man. (P, 3).

114
ጆንሰን እጅጉ

የእኛ ስለሆነ በእምነት ላይ ያለ እምነት እንጂ ከመለኮት


የምንቀበልበት ወይም መለኮትን የምንጠብቅበት እምነት
አያስፈልገንም የሚለው ይህ የአማልክት አመለካከት የልመና
ጸሎታችን በዐዋጅ ቃል መተካት አለበት ወደሚል ማጠቃለያ
ገደል ብዙ ብርቅዬ ሰባኪዎችን ዐግቶብን ወርዷል። የብዙ
አማኞችን የምልጃ ሕይወት አሽመድምዶ ጥሏል። ‘ዳግም
የተወለደ የሰው መንፈስ መፍጠር የሚችል እምነት ኀይል
ምንጭ ነው’ በማለት በተደጋጋሚ የሚናገረው ኪኒየን
እምነትን እንደ ኀይል ማየቱ የመለኮትን ልዕለ ኀይል
በምሥጢር እንደካደ ያጋልጠዋል።137 በአጠቃላይ እንደ ኪኒየን
ላሉ አማልክት የእምነት ቃል ልዩ ዐዋጅ ከድነት በፊት የመዳን
ምክንያት ከድነት በኋላ ሲሆን ደግሞ በእምነት ላይ ያለ
እምነት ወይም ዳግም የተወለደ ሰው መንፈስ ፍሬ ወይም
ውጤት ነው።

ኪኒየን (በሮሜ.10፡10) መሠረት መዳኑ እንኳ በአንደበቱ ቃል


ላይ እንደሆነ ነው የሚያምነው። ይህ ደግሞ የክርስትናን
መሠረታዊ የድነት ትምህርት ስለሚያፋልስ ከኑፋቄ
ያስመድበዋል። ይህንንም ሲናገር “የዘላለም ሕይወት
እንዳለኝ እስካላወጅኩ ድረስ የዘላለም ሕይወት ሊኖረኝ
አይችልም”138 ብሏል። ሄገንም ይህንኑ(ሮሜ.10፡10)
137
Ibid., (P, 79).
138
Ibid., (P, 123).

115
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመጥቀስ ኪኒየን የተናገረውን በመድገም ሲያስረዳ “ሰው


በልቡ ማመኑና በአንደበቱ ማወጁ ጸሎቱ እንዲመለስለት
ያደርጋል።” ያለ ሲሆን፤ ቀጥሎም ከኪኒየን መውሰዱን
ለመካድ እንዲያመቸው “የቃል ዐዋጅ እምነትን እንዳስተምር
ተገለጠልኝ።” ብሏል።139 እነርሱ ተገለጠልኝ ይበሉ እንጂ
የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ትምህርት አስቀድሞ ሆፕኪንን በመሳሰሉ
የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር
ይሰጥ የነበረ ትምህርት እንደሆነ ልብ ይሏል።140 አገልጋይ
ዮናታን አክሊሉም ይህንኑ (የሮሜ.10፡10) መልዕክት
በማንሳት141 “በጣም ነው የማምነው በኮንፌሽን። እኔ እኮ
ብዬ ነው የዳንኩት። ዘላለምን እኮ ጆይን ያደረከው ብለህ
ነው። ዛሬ ማታ ትላለህ ነገርህ ይከፈታል።” ብሏል።142 እንደ
እርሱም ከሆነ ድነቱ የተፈጸመው በአንደበቱ ልዩ ዐዎንታዊ
ዐዋጅ ቃል ወይም ኮንፌንሽን ስለሆነ ቁሳዊ ነገሮችንም
በማወጅ የራስ ለማድረግ መሞከር ትክክል ነው። በአጠቃላይ
ዮናታን የቃል ዐዋጅ ትርጓሜን ከኪኒየን ወይም ከሄገን አፍ
በትክክል ወስዶ አስቀምጧል። የቃል ዐዋጅን በእነኝህ ሁለት
“ሰዎች መገለጥ” ልክ ወይም ከዛ በላይ ተረድቶ ለማስረዳት
የሚሞክር ሰው የእምነት ቃል አስተማሪ ሊባልና ከመናፍቅ
ሊቆጠር እንደሚችል ማወቅ ይገባል።
139
በምዕራፍ ሁለት “የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” በሚል ንዑስ ርዕስ ይመለከቷል።
140
ከገጽ. 52-ገጽ. 53 ይመለከቷል።
141
በምዕራፍ ስምንት ላይ የእምነት ቃል በሚለው ንዑስ ርዕስ መልስ ተሰጥቶበታል።
142
ዮናታን አክሊሉ። በአፍህ ቃል ተያዝክ። (መጋቢት 26፣ 2020)።

116
ጆንሰን እጅጉ

“ዘ ሂድን ማን” በተሰኘ መጽሐፉ ኪኒየን ፈውስም ቢሆን


አንዲሁ ነው፤ ህመሙ በውስጤ እያለ እንኳ “በመገረፉ ቁስል
ተፈውሻለሁ እያልኩ ማወጅ አለብኝ” በማለት ሰው
በአንደበቱ ቃል ልዩ ዐዋጅ ፈውስን ማድረግ እንደሚችል
ተናግሯል። ይህ ንግግሩ ታዲያ የጸጋ ስጦታን ያቃለለ ሊባል
የሚችል ነው። እንደ ኪኒየን ከሆነ ይህንን የልዩ ዐዋጅ ቃል
ፈውስ ለመቀበል አስቀድሞ አምስቱን የስሜት ህዋሳት
መረጃዎች መካድ ያስፈልጋል። እንደ ትምህርቱም በሽታን
መካድ የፈውስ ምሥጢር ነው። ሄገንም በተመሳሳይ ሁኔታ
በሽታን መካድ የፈውስ ቁልፍ እንደሆነ አስረግጧል።143
ዮናታንም እንዲሁ “ኢየሱስ ሬሳን እንኳ አንተ ጎበዝ ነው ብሎ
የሚጠራው።”144 በማለት ይህንኑ የመካድ መርሖ
ለማስተዋወቅ ሞክሯል። እንደ ቃል ኀይል ሥነ-መለኮት
ከሆነም ፈውስን ለመቀበል ተፈጥሮአዊ መረጃዎችን በመካድ
መንፈሳችን በመገለጥ የሚያገኘውን መረጃ ማወጅ አስፈላጊ
ነው። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስን የእምነት መርኧ የጣሰ
የዲበ-አካል ሃይማኖት ልምምድ ስለሆነ አጋንታዊ የፈውስ
ልምምድ እንደሆነ ልብ ይሏል።

143
በምዕራፍ ሁለት “የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” በሚል ንዑስ ርዕስ ይመለከቷል።
144
በአፍህ ቃል ተያዝክ። (መጋቢት 26፣2020)።

117
የአማልክቱ ዐዋጅ

ፓስተር ክሪስም እንዱሁ የተለመደውን(የማቴ.12፡37)145 እና


(የምሳ.18፡21)146 ጥቅሶች ካነሣ በኋላ “በፊታችሁ
የተቀመጠው ሥራ ምንም ይሁን ምን በጭራሽ ላደርገው
አልችልም አትበሉ። ክርስቲያን ዐሉታዊ ነገሮችን ሲያወራ
በመንፈሱ ላይ ይጋባል እናም በሕይወቱ ላይ የእግዚአብሔርን
ቃል ይቃረናል።”147 ብሏል። እንደ እርሱም ክርስቲያን
ማንኛውንም ሥራ ለመሥራት የሚያስችለው ክህሎት፣
የገንዘብ ወይም የትምህርት ዐቅም ባይኖረው እንኳ እውነታን
በመካድ፣ መልካም በማወጅና ያለውን መለኮታዊ ባህርይ
ወይም ብቃት በመረዳት ብቻ ሁሉን ማድረግ ይችላል።

ለዚህም ለትምህርቱ አጽንዖት ለመስጠትም(ፊሊ.4፡13)


በመጥቀስ “ማድረግ የማትችሉት ምንም ነገር የለም፤ ስለዚህ
ማንኛውንም ዐሉታዊነት ከቋንቋችሁ አስወግዱ”148 ብሏል።
የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክትም እንዲሁ በተመሳሳይ
መልክ ህመምን ተፈጥሯዊ ሞትንና እርጅናን ይክዱ እንደ
ነበር ልብ ይሏል።149
145
በክፍል አራት ምዕራፍ ስድስት “አንደበት እሳት ነው” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር
እና እንዲሁም በክፍል አምስት ምዕራፍ ሰባት ላይ አማልክት አይደለንም በሚለው
ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል፡፡
146
በክፍል አራት ምዕራፍ ስድስት “የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል” በሚለው ንዑስ
ርዕሥ ሥር ይመለከቷል፡፡
147
ክሪስ እና አኒታ ኦያኪሎሚ Rapsoid of reality (ጥር፣19፣2006).
148
Ibd, (ጥር፣19፣2006).
149
ሜሪ ቤከር ኤዲና “የክህደትና የእወጃ ሕግ” ብላ በማስተማር ተጠቃሽ ናት።
ሚልቴዝ ደግሞ ይህንኑ ትምህርት በመከተል ተፈጥሯዊ ሞትን ለማሸነፍ ሙከራ

118
ጆንሰን እጅጉ

ሄገን ከኪኒየን እጅ በመቀበልና “ተገለልጦልኝ ነው” በሚል


ሰበብ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ከልዩ ዲበ-አካል ጋር
በማቀላቀልና ወደ ክርስትና በማስረግ የጥፋት ከፍታ ላይ
ከኪኒየን ይልቅ መውጣት ችሏል። ትምህርቱ ከክርስትና ጋር
ካለው መጠነኛ መመሳሰልና በእንቅስቃሴ ደረጃ ያደገ ከመሆኑ
የተነሣ የአብዛኛውን ክርስቲያን ማኅበረሰብ ስብከት፣ ዝማሬ
እና መንፈሳዊ ልምምድ ቅኝት እስኪቆጣጠር ድረስ ገዝፏል።
እንደ ጎርደን ፊ፣ ማኮኔልና መሰል የጴንጥቆስጤ ርቱዕ
ትምህርት አስተማሪዎች በመጽሓፎቻቸውና በመድረካቸው
ቢቃወሙትም ተቃውሟቸው ወደ እንቅስቃሴ አላደገም።
ስለዚህም በክርስትና ላይ ያለውን የርቱዕ ትምህርት
አለመስፋፋት ክፈተት በመጠቀም በረጅም ገመዱ ጠልፎ
በማሰር በርካታ የዓለማችንን ሰባኪያን ከኋላው አስከትሏል።
ጌታ ኢየሱስም “ስንዴውን አብራችሁ እንዳትነቅሉ
እንክርዳዱን ተዉት።” እንዳለ ይኸው ከስንዴው ጋር አብሮ
እስከ ዛሬ ድረስ በውድቀት ከፍታው ላይ እየቦረቀ ነው እንጂ
አንገት አልደፋም።

በአጠቃላይ ከሲውድንበርግ ጀምሮ እስከ ኪኒየንና ሄገን ድረስ


ያሉት መሪዎች ትምህርት ክርስትናን በዲበ-አካል ሃይማኖት
ለመተካት የሚጥር ነው ማለት ይቻላል። ስለዚህም የዲበ-
አካል ሃይማኖት እንቅስቃሴን አሮጌ አሻራ መለየት
አድርጋለች። ከገጽ. 117-119 ይመለከቷል።

119
የአማልክቱ ዐዋጅ

የፍልስፍናው ሰለባና ተሳታፊ እንዳንሆን እንድንጠነቀቅ


ይረዳናል። በዚህ ክፍል ላይ ኪኒየን ስለሰውነት፣ ስለ እምነት
እና ስለ ኅሩይ ቃል ዐዋጅ የሚያነሳቸውን ዐሳቦች ለማስረዳት
የሮሜ መልዕክትንና የዘፍጥረት መጽሐፍትን እንደሚጠቅስ
በጥቂቱ ተመልክተናል። ትምህርቶቹ ቤተክርስቲያን ላይ
በማጥላት የሥነ-መለኮት ዕይታን ስለተገዳደሩ ማስተካከያ
ለማድረግ የተነሱትን ክፍሎች ትርጓሜ በምዕራፍ አምስትና
ሰባት ላይ የምንመለከት ይሆናል።

ማክኢንታየር እንደሚለው ኪኒየንም ይሁን ሄገንን የቅድስና


እንቅስቃሴ የኋላ ታሪክ አላቸው ብለን ብናምን እንኳ ከልዩ
ዲበ-አካል ፍልስፍና አቀንቃኝነት አላስመለጣቸውም።
እንዲሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ክርስትና በወንጌላውያን ሥነ-
መለኮት ዶግማ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ከመንፈስ ቅዱስ
እንቅስቃሴ ሥር ከሚወሸቀው ከእምነት እንቅስቃሴ የሻገተ
የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ተጽዕኖ እንዳልታደጋት
ይታያል። ለዚህም የበርካታ አገልጋዮች በዚሁ ትምህርት
መለከፍ በቂ ማስረጃ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዐቃቢ እምነት ላይ ያላት አቋም
ልል መሆኑ ዋነኛው ነው። ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎቱ
ለጥቂት ግለሰቦች የተተወ አገልግሎት ከመሆኑም ባሻገር
አገልጋዮቹ በሐሳዊያንና ደጋፊዎቻቸው እንደ ነቃፊና ጠበኛ
ሲቆጠሩና ሲገለሉ ምንም ዐይነት ግላዊና ተቋማዊ ድጋፍና

120
ጆንሰን እጅጉ

ከለላ ስለማይደረግላቸው ቤተክርስቲያንን መታደግ


የሚችሉበት ርቀት ድረስ መሄድ ያቅታቸዋል። ያም ቢሆን
እንደ ግርማዊ፣ ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌና ወንድም ዘላለም
መንግስቱ ያሉ ወንድሞች ጹሑፎችንና ስልጠናዎችን
በማዘጋጀት የራሳቸውን አሻራ ማስቀመጥ ችለዋል። ጥቂት
ለርቱዕ ትምህርት የሚጨነቁ ወገኖች እንዲሁ በማኅበራዊ
መገናኛዎች በሚያቀርቧቸው አጫጭር ጹሑፎች ይበል
የሚያሰኝ ጠንካራ ሥራዎቻቸውን ሲያቀርቡ
እየተመለከትንም ነው።

ይሁን እንጂ በእንቅስቃሴ ደረጃ ያለና ተመሳስሎ የሰረገ ስሁት


ትምህርትን ከመኻል ነቅሎ ለማስወገድ የሚቻለው በቡዙዃኑ
ንቁ ተሳትፎና በመሰል ተቋማዊ እንቅስቃሴ የታገልን
እንደሆን ብቻ እንደሆነ ከታሪክ መማር አለብን። በተናጥል
ካለ ትግል በኅብረት ወደሚሆንና ሕዝብን ተደራሽ ወደ
የሚያደርግ እንቅስቃሴ መሸገገር ይጠበቅብናል። እራሳችንን
እንደ ተሓድሶ ሰባኪያን የምንቆጥር ሁላችንም መፍረስ
ያለበትን ለይተንና መታደስ ያለበትን አውቀን መቆም
ካልቻልን ሚዛን የሚደፋ ውጤት አይኖረንም። ስለዚህም
መጋቢ ሰለሞን“ጥሪዬ ለመታደስም ለማደስም ነው።”150
እንዳለው እኛም ከዐሳቡ ጋር ተስማምተን በመታደስና
በማደስ የሚሆን የተሓድሶ እንቅስቃሴን መፍጠር እንድንችል

150
የቱርፋን ናፍቆት (2007፣ 116)።

121
የአማልክቱ ዐዋጅ

የዲበ-አካል ሃይማኖትን ተጽዕኖ ጠልቀን መፈተሽ ግድ


ይለናል። ለዚህም ክርስትናን የተዳበለውን ድሪቶ፤ ይህውም
የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍናን መርሖ፤ የኪኒየንንና የኬኔት
ሄገንን የዐዎንታዊ ቃል ዐዋጅ ትምህርት ከልዩ ዲበ-አካል ጋር
ያለውን ተወራራሽነት ልብ ማለት ወሳኝ ነው። የእምነት
እንቅስቃሴ የምንፍቅና ተቋማትን ከአመራሩ አቋምና
ከትምህርቱ ባሕርይ የተነሳ ለማደስ አስቸጋሪ ቢሆንም
በሥራቸው የተደራጁ አማኞች ሁሉ የትምህርቱን ኑፋቄ
በትክክል ስለማይረዱት በትህትና ለማቅናት ማሰብና
መዘጋጀት ያስፈልጋል።

የዲበ-አካል ሃይማኖትና መለኮት


ከሲውዲንበርግ ጀምሮ የነበሩትን የዲበ-አካል ሃይማኖት
አማልክት እንቅስቀሴን የተመለከትን እንደሆን
ቤተክርስቲያንን ተገዳድሮ ነበር ማለት ይቻላል። ለዚህም
ዋነኛ ድልድይ የሆነው የእምነት ቃል እንቅስቃሴ የዲበ-አካል
ሃይማኖት ፍልስፍናን በቀላሉ ወደ ቤተክርስቲያን አካልነት
ማሸጋገር የቻለ እንቅስቃሴ መሆኑ ነው። የዲበ-አካል
ሃይማኖትን ፍልስፍና ከቤተክርስቲያን ጋር ለማዋሃድ ቀላል
ያደረገለት ተለዋዋጭ ባሕርይ ስላለው ነው። በዚህም
ባሕርይው የሳይንስ ደጋፊ በመሆን እና ተፈጥሯዊ እውነቶችን
በመቀበል ከተፈጥሯዊ እውነቶች ጀርባ የማይጨበጥና
የማይታይ እውነታ አለ በማለት ትንታኔ ለመስጠት ይጥራል።

122
ጆንሰን እጅጉ

እንደ ሃይማኖት ደግሞ ሃይማኖቶችን ሁሉ እንደ አንድ


በመቀበል ይደምራል። በተለይም ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ
ላይ በልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና በመታገዝ ኢ-ምክንያታዊ የሆነ
ፍልስፍናዊ ትንተና በመስጠት የዲበ-አካል ሃይማኖትን
ያሰርጋል።

በዚህም አካሄዱ ወደ ሃይማኖት ቀኖና ዘልቆ በመግባትም


‘ጸሎት የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ሕግ ጋር በመነካካት ኀይል
ለማግኘት ያስችለዋል’ በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶችን
ጠቅሶ እስከማስረዳትም ይደርሳል። ከዚህም ሲዘልቅ ሥነ-
መለኮት ካለ እኔ ዕርዳታ ሙሉ መሆን አይችልም የሚል
አቋም በመከተል ሥነ-መለኮትን ለማገዝ አገለግላለሁ ይላል።
በአጠቃላይ ሁለገብና ተለዋዋጭ ባሕርይ የተነሣ ዲበ-አካላዊ
ሃይማኖትን የሚመሩትን ተቋማት ከስያሜያቸው እና
ከሚጠቅሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስና የፍልስፍና ትንታኔ
ብቻ በመነሣት የፍልስፍና ተቋማት ናቸው ወይም
የሃይማኖት ተቋማት ናቸው ለማለት ይቸግራል። እንዲሁ
ከልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ጋር የተጋቡ ሃይማኖታዊ ተቋማት
ናቸው ማለት ይቀላል። ይህ ቅይጥነት ማዕከላዊነት ወይንም
ሚዛናዊነትን (balance) ለሚያፈቅሩና መኻል ሰፋሪ
ለዘብተኛ አማኞች የተመቸ ነው።

123
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጠቃላይ ይህ ጥምር አካሄድ የዲበ-አካል ሃይማኖት


ፍልስፍናን በቀላሉ ከክርስትና ጋራ እንዲጣመር አስችሎታል
ማለት እንችላለን። ክርስትናም ሆነ የዲበ-አካል ሃይማኖት
እንዲሁ በድፍኑ ከተመለከትናቸው ሁለቱም የጸሎትን ምላሽ
ይጠባበቃሉ። ይህንንም ቀረብ ብሎ ለማይመረምር አንድ
መንገድ ላይ ያሉ መስለው እስኪታዩት ድረስ ለመለየት
ይቸገር ይሆናል። ቀርቦ ለሚመለከት ግን ክርስትናም ሆነ
የዲበ-አካል ሃይማኖት ለጸሎት ያላቸው ትርጉም እጅግ
የተለያየ መሆኑን ይረዳል። ምክንየቱም ሁለቱም ተቋማት
በጸሎት መልስ መንስኤ ግንዛቤም ይሁን በጸሎት መልስ
መንገድ ላይ ሰፊና ግልጽ ልዩነት አላቸው።

በእርግጥ ኪኒየን እና ሄገን የቃል ዐዋጅ ጽንሰ-ዐሳብን


በመጠቀም በዲበ-አካል ሃይማኖትና በክርስትና መኻል
በመግባት ድልድይ ለመሆን ሞክረዋል። የዲበ-አካል
ሃይማኖትንና የክርስትናን ልዩነት በጥቅስ በማጥፋትም ባዕድ
ዐሳቡን ካለችግር ለማስረግ ችለዋል። ይሁን እንጂ ለብዙ
የሥነ-መለኮት አጥኚዎችንና እውነት ወዳድ አማኞች ልብን
የሚያሳዝንና ሊዋጥ የማይችል የአሳር እንጀራ ነው። ለዚህም
ምክንያቱ ይህ ልዩ ወንገጌል ትምህርተ ሰብዕንም ይሁን
ትምህርተ መለኮትን ማዛባቱ ብቻ አይደለም። በዲበ-አካል
ሃይማኖትና በክርስትና መኻል ያለው ጋብቻም ይሁን የኅሩይ

124
ጆንሰን እጅጉ

ቃል ዐዋጅ ፍልስፍና መለኮትን ዝቅ በማድረግ የሰው ተገዥ


የሚያደርገው ስለሆነና ከመለኮት ጋር ያለን የፍቅር ትስስር
ስለሚፈታ ወይንም ስለሚያፈርስ ጭምር ነው።

በትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ትልልቅ ሥራ የሚሠሩ


ትልልቅና የተወሳሰቡ ማሽኖች ይገኛሉ። እነኝህ ማሽኖች
ከኤሌክትሪክ የሚያገኙትን ኀይል ወደ መካኒካል ኀይል
የሚለውጥ ሥርዐት የተገጠላቸው ናቸው። ማሽኖቹ
እንዲንቀሳቀሱና የተፈለገውን ምርት እንዲያመርቱ ብዙ
የሰው ኀይል አይፈልጉም። ፕሮግራማቸውን የሚያስጀምር
ዲጂታል ኮድ ወይም ቁልፍ ተገጥሞላቸዋል። ለመንቀሳቀስና
የተፈለገውን ሥራ ለማሠራት ይህንን ኮድ የሚያውቅ አንድ
ባለሞያ (Expert) ኮዱን እንዲሰጣቸው ወይም እንዲነካ ብቻ
ነው የሚጠብቁት። እንዲሁም በዲበ-አካል ሃይማኖት
ፍልስፍና መሠረት ከሆነ በመላለም ውስጥ ያለውን ኀይል
ወይም “መለኮትን” ለማንቀሳቀስና ምላሽን ለማግኘት
የሚያስፈልገው ኮዱን መንካት ብቻ ነው። እንደ ትምህርቱም
ይህ ኮድ እምነት፣ ስሜትንና ዐዎንታዊ ዐሳብን የሚያይዝ
የኅሩይ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ሕግ ነው።

እንደ ፍልስፍናው ይህ ሊሆን የሚችለው ሰው የመለኮት አካል


ክፍል ስለሆነ ወይም አማልክት ስለሆነ ነው። ጆሴፍ ሙርፊ
ሲናገር፦ “አንተን ወደ መለኮታዊነት የሚቀይርህ ኀይልና

125
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጥበብ አንተን ከፍ ያደርግሃል። ይህ ኀይል ነው ዓለምን


የሚያንቀሳቅሰው” ብሏል።151 በአጠቃላይ እንደ እርሱ ሰው
መለኮትን መንካትና ማንቀሳቀስ የሚችለው መለኮታዊ ክፍል
ስላለው ነው።

ይህንን መለኮታዊ ክፍል ፊሊሞር “የክርስቶስ አዕምሮ” ፣


“የሰው እኔነት” ፣ “ልዕለ አዕምሮ” በማለት ይጠራዋል።
ይህንንም ሲገልጥ፦

የእያንዳንዱ ሰው እውነተኛ ማንነት፤ እኔ ነኝ፣ እውነት


ወይም የክርስቶስ አዕምሮ ነው። እኔ ባዩ ማንነት፤
እግዚአብሔር ‘እኔ ነኝ’ ነው። ስለዚህ የሰው ዘሩም ‘እኔ
ነኝ’ ነው። ‘እኔ ነኝ’ የጌታን ሕይወት መቀበል ነው፣
ፍቅሩን ጥበቡን እና በልዕለ መለኮት ውስጥ ያለውን
ዐሳብ ሁሉ። 152

ብሏል። በዚህ ሁኔታ ፊሊሞር መለኮት ‘እኔ ባይ’ ነው በማለት


ማንነት እንዳለው ቢጠቁምም መልሶ ደግሞ እንደ እርዳታ
ቀለብ ለሰው ሁሉ በነፃ በማደልና የሰው ሁሉ ማንነት
በማድረግ የራሱ ብቻ የሆነ ልዩ መለኮታዊ ማንነቱን
ይገፈዋል። የእምነት ቃል “ምሁራኑም” ቢሆኑ የክርስትና
አስተምህሮ መለኮት አካላዊ ስብዕናና ፈቃድ ያለው እንደሆነ

151
ዶ/ር ጆሴፍ ሙርፊ። አእምሮን የመጠቀም ጥበብ። (2012፣34)።
152
Charles Fillimore. Metaphysical Bible Dictionary. (1931. P, 424).

126
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚያስተምር እንደማይሰወርባቸው ብናውቅም፤ እንደ


ኪኒየን፣ ሄገን፣ ክሪስና ማይልስ ሞንሮይ ያሉ አስተማሪዎች
ይህንን እውነት ወደ ጐን በማድረግ፤ ‘አዲስ ፍጥረት’153
የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ አሰተምሮ ከድነት ጋር
የሚያገናኙት ሲሆን “አምላካዊ ተፈጥሮ” በማለት “አማልክት
ነን” ወደሚል ፍቺ አሳድገውታል። ኪኒየን የሰው መንፈስ
በመለኮት ምድብ ውስጥ እንደ ተፈጠረና በዳግም ልደት
እንደገና ይህንን ተፈጥሮ እንደተጎናጸፈ እንደሚያወራ ሁሉ፤
ኬነት ሄገንም ይህንን ማወጅ እንዳለብን አጽንዖት የሚሰጥ
ሲሆን በመጨረሻም ክርስቶሶች ነንም ብሏል።154

የእምነት ቃል አማልክት የጸሎት ምላሽን ለማግኘት


“የመለኮትን ኀይል” ለማንቀሳቀስ ይጠቅማል በማለት
የሚታሰበውን የልዩ ዲበ-አካሉን ‘የኅሩይ ቃል ዐዋጅ’ መርሖ
በተመሳሳይ መንገድ ይከተላሉ።155 ከዚህም የተነሣ ሁለቱ
የአማልክት ቡድኖች የጋብቻቸውን ቀለበት በማድረግ
የተጣመሩት በጸሎት ምላሽ ጽንሰ-ዐሳብ ማለትም በኅሩይ
ቃል ዐዋጅ ትምህርትና ተያያዥ ሥልቶች አማካኝነት ነው
ማለት ይቻላል። መጋቢ ሰለሞን የእስራኤልን የቃልኪዳን

153
በምዕራፍ ሦስት ላይ “አማልክታዊ ዘረ መል (ጅን)” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር
ይመለከቷል።
154
ምዕራፍ ሦስት “መለኮታዊ እምነት” እና “የኢየሱስን ምሳሌነት መከተል”
በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል።
155
“የኅሩይ ቃለ ዐዋጅ” በሚለው ንዑስ ርዕስ የሚዳሰስ ይሆናል።

127
የአማልክቱ ዐዋጅ

ተሓድሶ ጠቅሶ “ሳይፈርስ የታደሰ አልነበረም”156 እንዳለው


ጋብቻውን አፍርሰን ቤተክርስቲያንን ለማደስ የጋብቻውን
ጥምረት ቀለበትና ተያያዥ ሥልቶቹን በሚገባ ማወቅ
ይጠበቅብናል። መጠነኛ ግንዛቤ ለመፍጠር መጽሐፍ
ቅዱሳዊውን የጸሎት ልምምድ ለማደብዘዝ ያጠሉ
መሠረታዊ ዐዎንታዊ ቃል ዐዋጅ መነሻዎችንና ተያያዥ
መላምቶች በዚህ ምዕራፍ እንመለከታለን።

የተፈጥሮ ሕግ
እንደ ዴቪድ ሂዩም ያሉ የታሪክና የፍልስፍና ተመራማሪዎች
መለኮት የተፈጥሮ ሕግን ጥሶ አይሠራም ወይም ተአምራት
አያደርግም፤ ካደረገም የራሱን ሕግ ያፈርሳል በማለት ፈጣሪን
ለፈጠረው ሕግ እስረኛ ካልሆነ የሚል የሰነፍ ሙግት
ይሞግታሉ። የእምነት እንቅስቃሴ አማልክት ደግሞ ፈጣሪ
እንዲሠራ የሰውን ልጆች ስልጣን ወይም “ቃል ማውጣት”
አሊያም ፈቃድ ያስፈልገዋል የሚል ክኽደት ያሰማሉ።

ሌሎች ማንኛውም የጸሎት መልስ ውጤት ፈጽሞ ከተፈጥሮ


ሕግ ጋር እንጂ ከመለኮት ጋር አይገናኝም በማለት
ይከራከራሉ። ለምሳሌ፦ በክርስቲያን ሳይንስ ሥር የተደራጁ
ወቅታዊ የሆነ የምክንያታዊነት ዐስተሳሰብ እናራምዳለን

156
የቱርፋን ናፍቆት (2007፣111)።

128
ጆንሰን እጅጉ

የሚሉ የዲበ-አካል ሃይማኖት አቀንቃኞች የጸሎትን መመለስ


ባይክዱም ‘ጸሎት የሚመለሰው የተፈጥሮ ሕግ በአንደበት ቃል
ስለሚንቀሳቀስ ነው።’ በማለት የመለኮትን ጣልቃ መግባት
አስፈላጊነት ያገላሉ። በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን ወደ
መለኮት የሚደረጉ ጸሎቶች ሳይንሳዊ ዐስተሳሰብ በሌለበት
ዘመን የተደረጉ በመሆናቸው ምክንያት ለዘመናዊው ክርስትና
ምሳሌ መሆን አይችሉም በማለትም ተአምራትን ያጣጥላሉ።
ሪክ ኦስትራንደር ይህንን ዐስተሳሰብ ሲያጣቅሱ፦

ኤሊያስ ወደ እግዚአብሔር ስለ ዝናብ የጸለየበትና


መልስ ያገኘበትን እውነት የሚመለከቱበት ሁኔታ ያየን
እንደሆን የብሉይ ኪዳን አይሁድ ሳይንሳዊ ንቃት
አልነበራቸውም። ስለዚህ የኤሊያስን የጸሎት
ልምምድን የሚመስሉ የጸሎት ታሪኮች ዘመናዊው
ክርስትና የሚከተላቸው ምሳሌዎች በመሆን ማገልገል
አይችሉም። መገለጥ እያደገ የሚሄድ ነው። አሁን
የሰው ልጅ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን በተሻለ መገለጥ
ባደገበት ጊዜ ላይ ይገኛል። የተፈጥሮ ሕግን ምንም
ከማያውቁ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በላይ ዘመናዊው
ክርስቲያን የጸሎት ግንዛቤውን ከፍ እንደሚያደርግ
ይጠበቃል ይላሉ ።157

157
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science: (2000, p.95).

129
የአማልክቱ ዐዋጅ

በማለት አስፍረዋል። የዚህ አመለካከት መሠረታዊ መነሾ


የምክንያታዊነት ዐስተሳሰብ ተግዳሮት መስፋፋት ነው።
በ 1872 በምክንያታዊነት (empirical)158 መንገድ
የሃይማኖትን ጸሎት በመፈተሽና በመጻፍ ታይንዶል ቀዳሚ
ነው። ከታይንዶል ሳይንሳዊ ሙከራዎች መኻል አንዱ
በሆስፒታል ውስጥ በተኙ ተመሳሳይ ህመምና የህክምና
ክትትል ይደረግላቸው በነበሩ ታካሚዎች ላይ የተደረገ ነበር።
በዚህም ሙከራ ከፊሎቹ ታማሚዎች በተለያየ እምነት ባሉ
ሰዎች ጸሎት ሲደረግላቸው ከፊሎቹ ደግሞ ካለምንም ጸሎት
ክትትል የሚደረግላቸው ነበሩ። በውጤቱም ጸሎት
የተደረገላቸው ካልተደረገላቸው ይልቅ የተሻለ የጤንነትና
መሻሻል እንዳሳዩ ታይንዶል ይገልጻል።159

በተለያየ ጊዜም ይህንን አጠናክረው የሚያሣዩ ተመሳሣሣይ


ጥናቶች ተደርገዋል። ለምሳሌ በ 1988 እ.ኤ.አ
በሰንፍራንሲስኮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ከአራት መቶ
ባላነሱ የልብ ታማሚዎች ላይ የተደረገውን ጥናት ማንሣት
ይቻላል። ጥናቱ እንደሚያሳሣየው ሙከራው ከታይንዶል
ሙከራ ጋር ተመሣሣይ የሆነ ውጤት አሣየ። እንደ ጥናቱ
158
በሦስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በአሌክሳንደሪያ የኢንምቴሪካል የሚባል
የሕክምና ፍልስፍና ትምህርት ቤት ነበር። ይህ የፍልስፍና ት/ቤት እውቀትን
በስሜት ሕዋሳት አማካኝነት የሚገኝ ነው ብሎ ሲያምን ከሚታየው ቁሳዊ ዓለም
ጀርባ ያለውን በአመክኒዮ የምንገነዘበው ዓለም መኖርን ይክዳል።
159
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science: (2000, p.22).

130
ጆንሰን እጅጉ

መግለጫ ከሆነ በውጤቱ ጸሎት ከተደረገላቸው ከሃያ ስድስት


የታማሚዎች ምድብ ውስጥ በሃያ አንዱ ምድብ ላይ የጤንነት
መሻሻል ማየት ተችሏል። 160

በዳክ ዩኒቨርስቲ የህክምና ማዕከል እንዲሁ ተመሳሳይ ጥናት


የተደረገ ሲሆን ሃሮልድ ኮኒግ እንዳስታወቁት ጸሎት
የተደረገላቸው ህመምተኞች ካልተደረገላቸው ይልቅ
ደስተኛና ጤነኛ ሆነዋል። ኮኒግ የተጸለየላቸው ታካሚዎች
ያሳዩተን ለውጥ ምክንያት ሲያስረዱ በጸሎት ወቅት
የአድሬናል ሆርሞን ይቀንሳል፤ ይህም የታካሚውን በሽታ
የመከላከል ዐቅም ወይም ኢሙኒቲ ከፍ ያደርገዋል ይላሉ።161
ይህንንም ከሚመስሉ የህክምና ጥናቶች የተነሣ ታዲያ
ህክምናንና ጸሎትን በአንድነት መጠቀም እንደሚረዳ
በአነንዳንድ ባለሞያዎች እና ሆስፒታሎች እንደሚታመን
መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዚህም ምክንያት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የህክምና


ተቋማት በቅጥር ክፍያ የሚያገለግሉ አገልጋዮችን
በተቋማቸው ውስጥ እንደሚያሰማሩ ይታወቃል። በእርግጥ
ይህ አገልግሎት በሚገባ በሰለጠኑ መንፈሳዊ አገልጋዮች ሥራ
ላይ ከዋለ ካለው መንፈሳዊ ጠቀሜታ ባሻገር የታካሚዎችን

160
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom. (2006, 83).
161
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom. (2006, 83).

131
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሥነ-ልቦና በመጠበቅ የሰውነታቸው ስርዐት እንዳይዛባ


በማድረግ ተፈጠሯዊ ጤንነታቸው ላይ ዐዎንታዊ ተጽዕኖ
እንደሚኖረው ዕሙን ነው። ምክንያቱም ጸሎትም ይሁን
የቃሉ አገልግሎት በሰው ሁለንተና ላይ ማለትም በስነ-ልቦና
ላይም ጭምር ዐዎንታዊ ውጤት ሰለሚኖረው ነው። ይሁን
እንጂ ትክክል የማይሆነው ይህንን ውጤት ከልዩ ዲበ-አካል
የሥነ-ልቦና ህክምና ዘርፍ ወይም ከተፈጥሮ ኀይል ጋር
ማያያዝ ነው።

ጤናማና ክርስቲያናዊ አገልግሎትን በሆስፒታሎች ውስጥ


የሚሰጡ ወገኖች ቢኖሩም ዘርፉ በልዩ ዲበ-አካል ዐስተሳሰብ
አራማጆች ዐይን መግባቱ አልቀረም። እራሱን መቀላቀል
የሚወደው ይኸው ፍልስፍና የሥነ-ልቦና ሳይንስ ነኝ
በማለትም አንገቱን በዚሁ የህክምና ዘርፍ ብቅ ማድረጉ
የተለመደ ነው። በአገራችን እየሰማናቸው ያሉ አንዳንድ
የህክምና ጥበቦችም ይህንን የሚጠቁሙ ናቸው። በቃል ኀይል
የሚንቀሳቀስ የተፈጥሮ ሕግ እንዳለ ወይም አዕምሮ መፈወስ
የሚችል ልዕለ ተፈጥሮ እንዳለው የሚያንጸባርቅ የትኛውም
ጽሑፍም ይሁን የህክምና ሥልት የልዩ ዲበ-አካል ሥነ-ልቦና
እንጂ የተፈጥሮ ሳይንስ ሥነ-ልቦና እንዳልሆነ መታወቅ
አለበት።

132
ጆንሰን እጅጉ

በአገራችን በብዙ ሺ ቅጂ ከሚሸጡ ትርጉም መጽሐፍት


መኻል ብንጠቅስ Ask and it is given (ጠይቅና ተቀበል)
አብርሃም ሂክስ (1988)፣ The secret (ምስጢሩ) ሮንዳ በርን
(2006)፣ “The Power of your Subconssions Mind”
(አዕምሮን የመጠቀም ጥበብ) ጆሴፍ ሙርፊ (2012)፣
“የስኬት ፍልስፍና” ናፖሊዮን ሂል (2012)፣ “ትልቅ ሕልም
አለኝ!” ዳዊት ድሪምስ (2012) እና እንደ Law of attraction
(የመግኔጢስ ሕግ) ያሉ መጽሐፍት የዲበ-አካል ሃይማኖት
ሥነ-ልቦና ፍልስፍና አካል ናቸው።

አብዛኛዎቹም የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ሥነ-ልቦና


ቀመስ መጽሐፍት በአሁኑ ጊዜ በአማርኛ ጭምር
እየተተረጎሙ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጩ እንደሆነ ከነኝኽ
መጽሐፍት የጦፈ ገበያ መረዳት ይቻላል። ነገሩን የበለጠ
አሳሳቢ የሚያደርገው መጽሐፍቱ በአብዛኛው የአገራችን
ታዳጊ ወጣት ተማሪዎች ሳይቀር ተነባቢ መሆናቸው ነው።
በስልጠና ጭምር በትልልቅ ድርጅቶች እንኳ ሳይቀር
“ምርታማነትን ለማሳደግና የፈጠራ ሥራዎችን
ለማበረታታት” በሚል ሰበብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰጡ
መሆናቸው ደግሞ የባስ በትውልዱ ላይ የተጋረጠውን ትልቅ
አደጋ ያመለክታል።

133
የአማልክቱ ዐዋጅ

መለስ ብለን ታይንዶል ስለ ጸሎት ያለውን ግንዛቤ ስንመረምር


አገኘሁ ከሚለው የሆስፒታል ሙከራ ውጤት ጀርባ ሌላ
አስቀድሞ የተደገፈበትን ጽንሰ-ዐሳብ እንዳለ እናገኛለን።
ይህም የ 19 ኛውን ክፍለ ዘመን ተመራማሪዎች ትኩረት የሳበ
የተፈጥሮ ሳይንስ ግኝት ጽንሰ-ዐሳብ ነው። ታይንዶል
ያገኘውን የሆስፒታል ሙከራ ውጤት ልዩ ዲበ-አካላዊ
መንገድን በመከተል ከተፈጥሮ ሳይንስ ንድፈ ዐሳብ ጋር
አዛምዶታል። በዚህ ምክንያት “ዓለማትን የሚመራ የተፈጥሮ
ሕግ አለ” የሚለው የተፈጥሮ ሳይንስ ንድፍ ዐሳብ
ስላንሸራተተው ጸሎትን የሚመልሰው የተፈጥሮ ሕግ ነው
ወደሚል ፍቺ አዘንብሏል። ይህንንም ሲገልጽ፦

እግዚአብሔር ጸሎትን የሚመልሰው ተፈጥሯዊ በሆነ


መንገድ እንደሆነ አምናለሁ። ይህ ገና ከመጀመሪያው
ተመድቦ የተቀመጠ ነው። ለቁሰአካል (matter) እና
ለአዕምሮ የራሳቸውን ሕግ ሲያስቀምጥ፤ ነገሮችን
ጥበባዊ እና ጠቃሚ ለሆነ የእራሱ ፍጻሜ ከሕግ ጋር
አቀናጅቷል። . . .ተቀባይነት ላለው ለሕዝቡ ጥያቄ
መልስ እንዲሰጡ አዘጋጅቷቸዋል። 162

ብሏል። በዚህም ታይንዶል አዕምሮ በውስጡ በተቀመጠው


ሕግ አማካኝነት ከተፈጥሮ ሕግ ጋር በመቀናጀት መልስ

162
Tyndall J. Prayer-Gauge. (1876, P. 142).

134
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚሰጥ አስቀምጧል። ይህም የአዕምሮን ሕግ የማመን


ዝንባሌ በልዩ ዲበ-አካል አማልክቱም ላይ በስፋት መታየቱን
ቀደም ብለን ተመልክተናል። የተፈጥሮ ሳይንስ መሠረታዊ
ዐሳብ ‘ቁሰ-አካል ሁሌ ወደ አዳዲስ ቅርፅ ይቀየራል፣ ምንም
የሚፈጠር አዲስ ኀይል የለም፤ ስለዚህም ተፈጥሮ ቋሚና
ያው ነው። የልዕለ ተፈጥሮ ኀይል ጣልቃ በመግባት በፍጹም
አይሰራም’163 የሚል እንደሆነ አንባቢ ያስተውል።

በርግጥ ፕሮፌሰር ታይንዶል የመለኮትን ጣልቃ መግባት


ወደጐን ገሸሽ ቢያደርግም የጸሎት ምላሾችንና ተአምራትን
በማመን የፈውስ ተጨባጭነትን የመቀበል አዝማሚያ
ይታይበታል። ይሁን እንጂ ከላይ የተጠቀሰውን የተፈጥሮ
ሳይንስ ንድፈ ዐሳብ በከፊል የሚያንፀባርቅ አደገኛ አስተያየት
አስቀምጧል። አስተያየቱም የጸሎትን ምላሽ ምክንያት
በግልጽ ያስቀመጠ ነው። ይህንንም ሲያስረዳ “የጸሎት መልስ
የተፈጥሮ ኀይል ወደሌላ ይዘት መቀየር ነው።”164 ብሏል።
በዚህም የታይንዶል ሳይንሳዊ ፍተሻና ማጠቃለያ መሠረት
ጸሎት የሚመለሰው በተፈጥሮ ሕግ ኀይል ስለሆነ ጸሎትን
ለመመለስ መለኮት ጣልቃ መግባት አያሰፈልገውም ማለት
ነው።

163
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science: (2000, p.18).
164
Ibid., (p.31).

135
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደ እርሱ ከሆነ በሆስፒታል ሙከራውም የታየው የጤንነት


ለውጥ በጸሎት አማካኝነት የተፈጥሮ ኀይል ወደ ሌላ ኀይል
መቀየር ነው ማለት ነው። ፕሮፌሰር ታይንዶል ይህንን
ሲያጠናክር መለኮትን ዞር በማድረግ በምትኩ የተፈጥሮ ሕግን
በማስቀመጥ የተፈጥሮ ሕግ ከመለኮት የተሻለና ንቁ እንደሆነ
ለማሳየት ይሞክራል። ይህንንም ሲተነትን “ዝናብ እንዲዘንብ
ወይም ፀሓይ እንዲወጣ ወይም ውቅያኖስ ከዳርቻው ገንፍሎ
165
እንዳይወጣ መጸለይ አያሰፈልገንም።” በማለት
ይሞግታል።

ይሁን እንጂ ይህ ንድፈ ዐሳብ ግራ መጋባት ይታይበታል


ምክንያቱም በአንድ በኩል “ጸሎት የተፈጥሮ ሕግ ምላሽ
ነው።” ይላል። በሌላ በኩል ደግሞ “ዝናብ እንዲዘንብ ወይም
መሬት በዛቢያዋ ላይ እንድትዞር መጸለይ አያስፈልገንም።”
ይላል። በመጀመሪያ ነጥቡ ላይ የተፈጥሮ ሕግ በጸሎት
እንደሚሰራ ሲያሳይ በሁለተኛ ነጥቡ ላይ ደግሞ ይህ ሕግ
በራሱ የተቀመጠና የተወሰነ ስለሆነ በጸሎት እንደማይሰራ
ወይም ምላሽ እንደማይሰጥ ማስረጃ ያቀርባል። እንደ
ታይንዶል ከሆነ የተፈጥሮ ሕግ ሁለት ዐይነት ነው። ይኸውም
ለጸሎት ምላሽ የሚሰጥና የማይሰጥ።

165
Ibid., (p.9).

136
ጆንሰን እጅጉ

በርግጥ የተፈጥሮ ሕግ በመለኮት የተቀመጠና በጸሎት


የማይቀየር ነው የሚለው ዐሳብ በተወሰነ መልኩ እውነት
ቢኖረውም በሌላ በኩል ደግሞ ጸሎት የተፈጥሮ ሕግ ምላሽ
የመስጠትና አለመስጠት ጉዳይ ሊሆን ግን በፍጹም
አይችልም። ምናልባትም የታይንዶል መሞገቻ ሊያስደነግጥ
የሚችለው “ለሚያአምን ሁሉ ይቻለዋል” የሚል ጥቅስ
በመጥቀስና አውዳዊ ፍቺውን ወደ ኋላ በመተው በእምነት
ሁሉን ማድረግ እንችላለን በማለት ገደብ የሌለው የእምነትና
ጸሎት ለመለማመድ የሚጥሩትን ነው። እነኝህ ወገኖች ልዩ
ዐዎንታዊ ዐዋጅ የሚለማመዱ በመድረክ የሸመገሉ ሕፃናት
ናቸው። ሕፃናቱ ሁል ጊዜ ተአምራት ሁሉ ማድረግ
እንደሚችሉ ወይም በራሳቸው ፀሓይን ማስቆም እንደሚችሉ
ያስባሉ። ነገር ግን አንድ ጊዜ እንኳ ተሳክቶላቸው አያውቅም።
በመለኮት ሉዐላዊ ፈቃድ እንደሚወሰኑ ፈጽመው ማመን
ስለማይፈልጉ ለምን እንዳልተሳካላቸው መመርመርም ሆነ
ስኬት ስለማጣታቸው በማንም እንዲጠየቁ አይፈልጉም።
ስለዚህም እራሳቸውን በማረም ስብከታቸውንም ሆነ
ትምህርታቸውን ለመቀየር አይፈቅዱም።

ኪኒየን የተፈጥሮ ሕግ ላይ ያለውን አመለካከትም ያየን


እንደሆን “በእምነት ቃል” ትምህርቱ የተፈጥሮ ሕግን
ከእምነት ጋር በማጣመር ያስቀምጣል። ሲያብራራውም

137
የአማልክቱ ዐዋጅ

“እግዚአብሔር የእምነት መንፈስ ነው። ዓለማትን ወደ መኖር


ያመጣው በእምነት ነው። ታውቃላችሁ የተፈጥሮ ሕግ
ለእግዚአብሔር ልጆች የእምነት ቃል ይታዘዛል።”166 ብሏል።
እንደ እርሱ ማብራሪያ ከሆነም ዓለማት የተፈጠሩት
የተፈጥሮ ሕግ ለእግዚአብሔር የእምነት ንግግር መልስ
ስለሰጠ ነው። ይህ ደግሞ ተቀባይነት የለውም ምክንያቱም
ተፈጥሮ ሳይኖር የተፈጥሮ ሕግ ሊኖር አይችልም።

እንደ ኬኒየን ትምህርት እንደ እግዚአብሔር ማመን “በኅሩይ


ቃል ዐዋጅ” የተፈጥሮን ሕግ በመቈጣጠር የፈለግነውን ነገር
እንድናደርግ ያስችለናል። ይህ የእምነት ዐይነት “እንደ
እግዚአብሔር ዐይነት እምነት” የተባለውም “ለእግዚአብሔር
እንደ ሠራ የሚሠራ እምነት ነው” ተብሎ ሰለሚታመን ነው።
ኪኒየን የእርሱን “የእምነት ቃል” ወይም ዐዎንታዊ ዐዋጅ
ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ለማስያዝ ጥረት
አድርጓል። ዋናውና ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ግን ከላይ
ባሉት ክፍሎች እንደተመለከትነው የኅሩይ ቃል ዐዎንታዊ
ዐዋጅ መርሖ መነሾ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን የተፈጥሮ ሕግ
ሥሌት መሆኑ ነው።

ለታይንዶል የተፈጥሮ ሕግና የጸሎት ግንኙነት ትንታኔ በዘመኑ


የነበሩ አንዳንድ የተወዛገቡ የቤተ-እምነት መሪዎች የሰጡትን
166
E.W. Kenyon. The Hidden Man. (P,41).

138
ጆንሰን እጅጉ

ምላሽ ያየን እንደሆነ የታይንዶልን ንድፈ ሃሳብ እንደ አዲስ


የጸሎት ዕይታ ወይም መለኮታዊ “መገለጥ” ሳይመለከቱት
የቀረ አይመስልም። በዚህ ሁኔታ እንደ በጎ ገጸ-በረከት
በመቁጠር በአድናቆትና በአግራሞት የተቀበሉት እንዳሉ ሁሉ
በሌላ በኩል ደግሞ ታይንዶልን የተቃወሙት የቤተ-እምነት
መሪዎችም ነበሩ። ይህንንም ሪክ ኦስትራንደር ሲያብራሩ
እንዲህ በማለት አስፍረዋል፦

የኒውዮርኩ ቤተ-እምነት መሪ ታይንዶልን


ሲያዳንቁት የሜቶዲስት ፕሬስፔትሪያን ቤተእምነት
መሪዎች በሚወጡት ጋዜጦቻቸው ይቃወሙትና
በጸሎት ቦታዎችም ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ
ጸሎት እንዲደረግለት ያደርጉ ነበር።167

የሜቶዲስት ፕሬስፔትሪያን ቤተ ክርስቲያን ለታይንዶል


በንስሓ መመለስ የምልጃ ጸሎት ከማድረግ አልፋ በጋዜጦች
እስከ መቃወም መድረሷ የነበራትን ጠንካራ አቋም አመልካች
ነው። በአጠቃላይ ፈውስን ወይም የጸሎትን መልስ ከተፈጥሮ
ሕግ ጋርም ይሁን ከዐዎንታዊ ቃል ዐዋጅ ሕግ ጋር ማያያዝ
መናፍቅነት እንደሆነ መታወቅ አለበት። የሥነ-ልቦና
ሳይንስንም ከልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ጋር በማጋባት የአዕምሮ

167
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science: (2000, p.22).

139
የአማልክቱ ዐዋጅ

ፈውስን መለማመድም እንዲሁ ምትሃት መሆኑን ማወቅ


ተገቢ ነው።

ልዕለ አዕምሮ
ጀርመናዊው ሜዝሜር እንሰሳዊ መግነጥስ (animal
magnetism) በሚል የአዕምሮን ኀይል በማስተዋወቅ
ፈውስና ተአምራትን በማድረግ በአገረ አሜሪካ “ፈዋሹ
አሜሪካዊ” በሚል ቅጽል ስም የታወቀ ሆኖ ነበር። በኋላ
ላይም ሰፊ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለው የሲውዲንበርግን
ፍልስፍና ከሩቅ ምስራቅ ሃይማኖታዊ ምልከታዎች ጋር
በማግባባት እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። በዚህም በዘመኑ
የቤተክርስቲያንን ጤናማ የጸሎት ልምምድ መረበሽ ችሎ
ነበር።

ይሀንን ትምህርት ፊንሃስ ፓንክረስ ኪዊምቢይ ደግሞ


አዕምሮ የመለኮት አካል ወይም ክፍል እንደሆነ በሰፊው
በማስተዋወቅ የሥነ-ሰብዕን ትምህርት አዛብቷል። በዚህም
ፍልስፍናው “መንፈሳዊ ልቀት” ወይም “መገለጥ” መልክ
እንዲኖረው በማድረግ ከሜዝሜር በተሸለ ሁኔታ ተቀባይነትን
ማግኘት ችሎ ነበር። በኪዊምቢይ ትምህርት መሠረት
እግዚአብሔር ጥበብ ሲሆን ክርስቶስም በየአንዳንዱ ሰው
ውስጥ ያለ መለኮታዊ ተፈጥሮ ማለትም ልዕለ አዕምሮ

140
ጆንሰን እጅጉ

(divine mind) ነው። ሙርፊ ይህንን የአዕምሮ ምጡቅነት


ወይም መለኮትነት ሲያብራራ “የአንተ ውስጠ ሕሊና
አንቀላፍቶም ሆነ ተኝቶ አያውቅም ሁሌ ሥራ ላይ ነው።
የአንተ ውስጠ ሕሊና የጊዜና የቦታ ነፃነትን የተቀዳጀ ነው።
ከምንም ዐይነት ሥቃይና ጭንቀት ነፃ ነው።”168 ብሏል።
እንደ እርሱ ከሆነ ውስጠ ሕሊና የተባለው የአዕምሮ ክፍል፤
በጊዜና በቦታ የማይወሰን፣ የማይደክመውና የማያልቅ ዕምቅ
ብቃት ያለው ተኣምር መፍጠር የሚችል ምጡቅ ነው።
ይሁን እንጂ ምጡቅ ለመሆን ከጊዜና ከቦታ ውጪ በመሆን
ከተፈጣሪነት ይልቅ ፈጣሪ መሆንን ይጠይቃልና ነጭ ውሸት
ነው ማለት ይቻላል።

ኪዊምቢይ አዕምሮ ባለው መለኮታዊ ተፈጥሮ ምክንያት


የአንድ ሰው አዕምሮ የሌላውን ታማሚ ሰው አዕምሮን
በማረቅ የፈውስ ሆርሞን እንዲሰራጭ በማድረግ ይፈውሳል
በማለት ያመናል። የኢየሱስን የፈውስ ምሥጢር ሲያስረዳም
ኢየሱስ ይፈውስ የነበረው ይህንኑ ልዕለ አዕምሮ ተጠቅሞ
እንደሆነ ያብራራል።169 ሌላው ይህ ሰው ከአገልግሎቱ
መስፋትና “ስኬት” የተነሣ ሰፊ የርቀት የፈውስ አገልግሎት
መስጠት ጀምሮ እንደ ነበር ይነገርለታል።

168
ጆሴፍ ሙርፊ፣ አእምሮን የመጠቀም ጥበብ። (2012, Pp,34-35).
169
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, p.56).

141
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይህንንም የፈውስ አገልግሎት ይፈጽም የነበረው ታዲያ


በኅሩይ ዐዎንታዊ በማወጅ ነው። ለዚህም ዐዋጅ ልምምድ
ምክኒያቱ ልዕለ አዕምሮን እንዲሠራ የሚያስችለው ቃል
እንደሆነ ስለሚያምን ነበር። ለምሳሌ ያኽል በአንድ ወቅት
ከአንድ በሽተኛ ለደረሰው የርቀት የፈውስ አገልግሎት ጥያቄ
መልስ የሰጠበት የደብዳቤ መልዕክት፤ የፈውስ አገልግሎት
ምላሽ ወይም “የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” እንዲህ ይነበባል። “ደስ
ይበልህ ድፍረትህን ጠብቅ። በእምነትህ ማዕበል ላይ
ስራመድና የህመምህንም ማዕበል ጸጥ በል በማለት ሳዘው
አሁን ታየኛለህ። ከዛም ማዕበሉ ዐልፏል በማት በደስታ
ትናገራለህ።”170 ይላል። እንደ እርሱ ከሆነ ህመም የእምነት
መናወጥ ምክንያት ሲሆን የኅሩይ ቃላት ዐዋጅ ይህንን
በመለወጥ ፈውስን ያረጋግጣል።

በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ለአንድ ታማሚ እንዲሁ የላከው


የፈውስ አገልግሎት ደብዳቤ እንዲህ ይላል፦

“አሁን ይህንን ደብዳቤ እያነበብክ ሳላህ ባልጋ ላይ ተኝተህ


በክፍልህ ውስጥ እያየሁህ ነው። አሁን! የቤትህን በር አልፌ
እንደ እግዚአብሔር መለአክ ልፈውስህ ወደ ቤትህ
እየተራመድኩ ገባሁ! በቃ ተፈውሰሃል ከአልጋህ ላይ
ተነሣ!”171
170
Ibid., (p.60).
171
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, p.66)

142
ጆንሰን እጅጉ

እንደ ኪዊምቢይ ከሆነ በፍቃዱና በአንደበቱ ዐዎንታዊ የቃል


ዐዋጅ አማካይነት ምጡቅ አዕምሮውን በማንቀሳቀስ
የፈለገውን ሁሉ በስፍራና በጊዜ ሳይወሰን ማድረግ ይችላል።

ሜሪ ቤከር ኤዲም ቁሳዊ አዕምሮና “ልዕለ አዕምሮ” በማለት


በተለመደው የአፍላጦን የሁለትዮሽ ንጽረተ ዓለም አዕምሮን
በሁለት በመክፈል አስተምራለች። እንደ ሌሎቹ የዲበ-አካል
ሃይማኖት አማልክት እርሷም አመስጥሯዊ ሥነ-አፈታትን
በመከተል ‘ደቀመዝሙር’ ማለት በላቲን ‘ተማሪ’ ማለት ነው።
ስለዚህም ኢየሱስ ደቀመዝሙሩን ከቁስ ይልቅ በልዕለ አዕምሮ
እንዲፈውሱ አዟቸዋል። ፈውስም ከእርሱ በመማር
የተላበሱት ክህሎት እንጂ ስጦታ አይደለም ብላለች።172

ቻርልስ ፊሊሞርም እንዲሁ ኢየሱስ ተዓምራት ስላደረገበት


ኀይል አስተያየት ሲሰጥ፦

እኛ ሁል ጊዜ እንደምንናገርለት ኢየሱስ የተለየ ልዕለ


ኀይል እንዳለው አልተናገረም። እርሱ አፈንድቶት
የነበረው ኀይል ‘የእግዚአብሔር መንግስት’ ብሎ
የሚጠራውን ኀይል ነበረ፤ የእርሱ መረዳት ከመደበኛው
የሰው ልጅ ያለፈ ነበር። ለማንኛውም ሌሎች ሰዎችም

172
Mary Baker Eddy. Science and Health with Key to the Scriptures.
(2006, p. 285).

143
የአማልክቱ ዐዋጅ

እርሱ ያደረገውን ማድረግ እንደሚችሉ ያውቅ ነበር፤


ደግሞም ያንን ተናግሯል።

ብሏል። በመቀጠልም ከሉቃስ ወንጌል በመጥቀስ፦ “ይህ


የእግዚአብሔር መንግስት በውስጣችን ነው። የመለኮት
አዕምሮ ነው።”173 (17:20,21)። በማለት አብራርቷል። ይኸው
ሰው ከአንድ የሬዲዮ ጣቢያ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠየቅ
በመጥቀስ ፊሊሞር በሰዎችና በኢየሱስ መከከል ያለው ልዩነት
አዕምሮን የማላቅ ልዩነት እንደሆነ መግለጡን ሞስሊ
አስፍረዋል። ይህንንም ሲጠቅሱ “ኢየሱስ መንፈሳዊ እምነቱን
የሰውነቱ አውቶሚክ ኃይል ለፍቃዱ እስኪታዘዝና በውኃ ላይ
እስኪራመድ ድረስ አሳድጓል።”174 ማለቱን አንስተዋል። ሞስሊ
እንደጠቆሙት ፊሊሞር በሰዎችና በኢየሱስ መኻል ያለውን
ልዩነት ማመልከት የፈለገው ሰዎች ወደ ክርስቶሳዊነት
የሚሸጋገሩበትን እርሱ “የመንፈሳዊ እምነት ዕድገት” በማለት
የሚጠራውን ድልድይ ለማሳየት ስለፈለገ ነው። በፊሊሞር
ዕይታ መሠረት የሰው ልጅ በአዕምሮው ላይ ያለውን እምነት
በማሳደግ ኢየሱስ የደረሰበት ደረጃ ላይ በመድረስ በእራሱ
ሁሉን ማድረግ ይችላል ማለት ነው። ፊሊሞር ለዚህ እምነቱ
መጽሐፍ ቅዱስን ቢያጣቅስም “እምነትን” ፣ “ቃልን” እና
“አባትን” የሚመለከተው ግን በተለየ መንገድ ነው።
173
Charles Fillimore. Metaphysical Bible Dictionary. (1931. P, 557).
174
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom. (2006, p,125).

144
ጆንሰን እጅጉ

እምነት ለፊሊሞራዊያን አዕምሮን ከማንቀሳቀስ የተለየ


ተግባር የለውም። እንደ እነርሱ አገላለጥ የእምነት ተግባር
በአዕምሮ ውስጥ ያለውን የተደበቀ ዕምቅ ብቃት መግለጥ
ነው። በሌላ አገላለጥ እምነት የአዕምሮን ኀይል መጠቀም
የሚያስችል መክፈቻ ቁልፍ ነው። ስለዚህም እምነት
“መለኮትን ወይም አባትን ያነቃቃል” ብለው ያምናሉ። ይሁን
እንጂ ለፊሊሞራዊያን መለኮት የመጽሐፍ ቅዱሱ ግለ ስብዕና
ያለው አካላዊ አምላክ ሳይሆን የአዕምሮ ክፍል አካል ነው።
ይሀንንም ፊሊሞር ሲገልጥ “ኢየሱስ አባቴ እያለ የሚጠራው
ልዕለ አዕምሮን (divine mind) 175 ነው።” ብሏል።

እምነትንም ሲያስረዳ የአዕምሮ ስሜት ክፍል እንደሆነ


ይናገራል። በዚሁ ትምህርት መሠረት ኢየሱስ የአዕምሮውን
ዕምቅ ኀይል በመጠቀም ተአምራት ያደረገ የምጡቅ ልዕለ
አዕምሮ ባለቤት ነው። እንደ እርሱ ማንኛውም ሰው
የኢየሱስን ትምህርትና ሞዴል በመከተልና በመለማመድ

175
ልዕለ አእምሮ (divine mind) ፦ አእምሮ መለኮታዊ ተፈጥሮ አለው የሚል
በፊንሃስ ፓንክረስ ኪዊንቢ የተጀመረ ዐስተሳሰብ ሲሆን በዚሁ ዐስተሳሰብ
በመመሰጥ የኪዊንቢ ተማሪ የነበረችው ሜሪ ቤከር ኤዲ “ዲቫይን ማይንድ” የተባለ
የፈውስ ጥበብ ኮሌጅ ለመክፈት በቅታለች። የኤዲ ተማሪ የነበረው ቻርልስ
ፊሊሞር ደግሞ ሳይንሳዊ ትንታኔን በመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ የበለጠ በማስደገፍ
የሰው ልጅ ይህንን አእምሮ በማነቃቃት ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል በማለት
ኢየሱስን በምሳሌነት ይጠቅሳል። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያደረጋቸውን
ተአምራት የአእምሮውን ኃይል በእምነት መጠቀም ስለቻለ ነው በማለት
የእምነትን አስፈላጊነት በስፋት አስተምሯል።

145
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወደዚህ ልቀት ወዳለው አማልክትነት ወይም ክርስቶሳዊነት


መድረስ ይችላል። ለምሳሌ ፊሊሞር የአዕምሮን ኀይል በግልጽ
ሲያስረዳ “የአዕምሯችንን ተፈጥሯዊ ክህሎት ትንሽ
ከተረዳንና እምነት የሚባለውን ክፍል ማሳደግ ከቻልን በዋናው
አእምሯችን ዐዋጅ አማካኝነት ምንም ነገር ለማድረግ
የሚሳነን ነገር የለም።” ይላል።176 እንደ እሱ ኢየሱስ እምነቱን
በማሳደግ የአዕምሮውን ክፍል በመጠቀም እንደላቀ ሁሉ፤
የሰው ልጅም በዐዎንታዊ ዐዋጅ አማካኝነት አዕምሮውን
በመጠቀም ወደ ሁሉን ቻይነት ይሸጋገራል ወይም
ይመለኩታል።

በአጠቃላይ ኪዊምቢይ ፕሮፌሰር ታይንዶል ያስቀመጠውን


የተፈጥሮ ሕግ ቀመር ወደጐን በማድረግ በምትኩ የልዕለ
አዕምሮ (Divine Mind) ፍልስፍና በማስቀመጥ የራሱን
ማሻሻያ አድርጎበታል ማለት ይቻላል። ነገር ግን ታይንዶልም
ሆነ ኪዊምቢይ መለኮትን ግላዊ ማንነትና የጸሎት ተደራሽነት
ያሳጡታል። ክርስቶሳዊነትን ወይም አማልክታዊነትን በስፋት
ያስተማረው ቻርልስ ፊሊሞር ደግሞ የሁለቱንም ዐሳብ
ሳይጣላ “የአባት ሕግ” የሚል ጽንሰ-ዐሳብ በማቅረብ
የአስታራቂ ሽማግሌነትን ቦታ ይረከባል። በዚህም ዐስተሳሰብ
ጸሎት ተደራሽ የሚያደርገው ይህኑኑ የአባት ወይንም

176
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, 143).

146
ጆንሰን እጅጉ

የአዕምሮ ሕግ ነው። በርግጥም ፊሊሞር የተሳካለት ሽማግሌ


በመሆን ትምህርቱን ወደ ቤተክርስቲያን በቀላሉ ለማስረግ
ከሲውድንበርግ ቀጥሎ ሁለተኛው ሰው ለመሆን ችሏል።

ፍሊሞራዊያን የሰውን የማይወሰን የመቻል ዐቅም ለማሳመን


እንዲረዳቸው ስለእምነት የሚናገሩ ታዋቂ የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎችን የእምነት እንቅስቃሴ አማልክት ሲጠቀሙ
በምንመለከተው መንገድ ተጠቅመዋል። ከነኝህም ጥቅሶች
ውስጥ ለምሳሌ ያክል(ማቴ.14፡31፣ ማር.9፡23፣ዩሐ.14፡
12)177እና(ማር.11፡23)178 ይገኙበታል። ይህ አቀራረባቸውም
ክርስቲያን እንዲመስሉ አድርጓቸዋል። በተጨማሪም የዲበ-
አካል ሃይማኖት እንቅስቃሴ ሁሉም አማልክት የወንጌል
አማኞች ኢየሱስን እንደሚጠቅሱና በኢየሱስ ሞዴልነት
እንደሚያምኑ ሁሉ እነርሱም በኢየሱስ ትምህርትና ሞዴልነት
እንደሚያምኑ በተደጋጋሚ መናገራቸው የበግ ለምድ የለበሱ
ተኩላዎች አድርጓቸዋል።

የአባት ሕግ
በፊሊሞር ታሪክ ተጠቅሶ እንደምናገኘው ከሆነ የቀድሞ
በባለቤቱ ከዛም በእራሱ መፈወስ ምክንያት መለማመድ

177
በምዕራፍ ሁለት “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል” ሐቲታዊ ዳሰሳ ሥር ይመለከቷል።
178
በምዕራፍ አምስት “የረገምካት በለስ ደርቃለች” በሚለው ንዕስ ርዕስ ሥር
ይመለከቷል።

147
የአማልክቱ ዐዋጅ

የጀመረውን የፈውስ ጥበብ ለተማሪዎቹ


የሚያስተዋውቅበትን መንገድ ስንመለከት በኢየሱስ ላይ ያለ
እምነት ሳይሆን በአዕምሮ ሕግ ላይ የተመሠረተ ነው።
ለምሳሌ ፊሊሞር በኢየሱስና በሰው ልጆች መኻል ያለው
ልዩነት በአዕምሮ ላይ ያለ የእምነት ልዩነት እንደሆነ
እንደሚያምንና ይህም ተከታዮቹን የጸሎትን አቅጣጫ ያስያዘ
እንደሆነ በሞስሊ ጥናት ተጠቅሷል። ለምሳሌ፦ በ 1892
እ.ኤ.አ ዩኒቲ ኮሚኒቲ ለእያንዳንዱ አባል ባሳተመው
ደብዳቤም “በአንተና በኢየሱስ መኻል ያለው ልዩነት ኢየሱስ
የአባት ሕግ ለቃሉ እንደሚመልስለት በፍጹም ልቡ ማመኑ
ነው።”179 ማለቱን ጠቅሰዋል።

ይህ የፊሊሞር ጹሁፉ ትምህርተ ክርስቶስን ከማመሰቃቀሉም


በላይ የጸሎት መልስ ስልጣን ከአባት በላይ የአባት ሕግ በማለት
ትምህርተ መለኮትን አፈር ያለበሰ ነው። እንደ እርሱም
“የአባት ሕግ” በተፈጥሮ ሕግን ምትክ የተቀመጠ ሲሆን ግለ-
ስብዕና ያለውን መለኮትን ገላጭ ሳይሆን የሰው ልጆችን
አዕምሮ ወካይ ነው። ይህም ዐስተሳሰብ ከሂንዱይዝም
ባራህማንን ጋር ያመሳስለዋል180። ይሁን እንጂ ታይንዶል ላይ
እንደተመለከትነው በዚህ የፊሊሞር ዐሳብ ላይም መምታታት
ይታያል። ምክንያቱም የአዕምሮ ሕግ ከአዕምሮ
179
New Thought, Ancient Wisdom. (p. 14).
180
ባራህማን፦ በገጽ.52 ላይ ያለውን ሓዳግ ይመልከቱ።

148
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚበልጥና ጸሎትን የሚመልሰውም እርሱ እንደሆነ


ይናገራል። በሌላ በኩል ደግሞ የአዕምሮ ሕግ በአንደበት ቃል
ይገዛል ይላል። ይህ ከሆነ ደግሞ የአንደበት ቃል ከአዕምሮ ሕግ
ብልጫ ስላለው የበላይነቱን ወይም የአባትነትን ቦታ
ስለሚወስድ ጸሎትን የሚመልሰው የአባት ሕግ ሳይሆን
የአንደበት ቃል ይሆናል። ስለዚህም እንደ ፊሊሞር ከሆነ
የአባትን ሕግ የሚያንቀሳቅሰው የአንደበት “ኅሩይ ቃል ዐዋጅ”
የሚበልጠውን ስልጣን ይይዛል ማለት ነው።

ከዚህ የፊሊሞር የቃል ኀይል ትምህርት በመነሣት የፊሊሞር


ተከታይ የሆነው ኢሚሊ ኬዲይ (ዶ/ር) የሰጠውን
“የአማልክት” የቃል ኀይል ልምምድ እንደሚከተለው
ተጠቅሷል፦

እግዚአብሔር ፍጥረትን ለመፍጠር በጀመረበት


መንገድ እንጀምራለን። ለዚህ ቅርፅ ለሌለው ዓለም
እንናገራለን። በአንደበታችን እንደተናገርን
እንደዛው ይሆናል። አሁን እንዲሆን እንዲገለጥ
እንናገራለን። በቃላችን ኀይል ወደ መኖር ይመጣል።
ይሆናል ይገለጣል። 181

181
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P.15).

149
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለዚህ ለኢሚሊ ኬዲይ ዞር ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ አፈታት


መሠረታዊ ምክኒያቱ ፊሊሞርን መከተሉ እንደሆነ መረዳት
አይቸግርም።

ለፊሊሞር መሣት መሠረታዊ ምክንያት ምንድነው? ብለን


የጠየቅን እንደሆነ ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ሊተረጎም
የማይችል ሙሉ ለሙሉ ምሳሌያዊና ምሰጢራዊ ነው
የሚለውን የሲውዲንበርግን አቋም መያዙ ነው። ፊሊሞር
ምስጢራትን ለመፍታት ባለው ጕጕት የተነሣ የመጽሐፍ
ቅዱስን ስልጣንም ይሁን የሥነ-ጽሑፍን ሕግ በመጣስ
መጽሐፍ ቅዱስን በልዩ ዲበ-አካል ስልት ለመተንተን ጥሯል።
በተጨማሪም ምስጢራዊ እውነታዎች በማለት መረጃ
የሌላቸውን መላምቶች ለመደርደር እንዲያመቸውም በከፊል
አመስጥሯዊ182 አተረጓጎም ይከተላል። ለዚህም እንደ
አውሮጳዊያን አቆጣጠር በ 1931 ለህትመት ያበቃው ዲበ-
አካላዊ ባይብል ዲክሽነሪ የተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ
ማብራሪያ ጥሩ ማሣያ ነው።183 ፊሊሞር በዚህ መጽሐፉ ላይ
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጽፋው በሚገኙ እያንዳንዳቸው
ነገሮች ላይ የራሱን ትርጉምና ትንታኔ ይሰጣል። በዚህም

182
አመስጥሮት (Allegory)፦ መጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራዊና ስዕላዊ ስለሆነ ድብቅ
ትርጉሙን በመፈለግና በመተርጎም የተመሠረተ ሥነ-አፈታት ነው።
183
. Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, Pp. 23-25).

150
ጆንሰን እጅጉ

መሠረት ፍቺዎችን ለሰዎች ስምና ለቦታ ሥሞች እንኳ


ሳይቀር አስቀምጧል።

ከፊሊሞር አመስጥሯዊ ትርጓሜዎች መኻል ጥቂት ስናነሳም


ከማቴዎስ ወንጌል ላይ የጲላጦስን ስም በመውሰድ
ሲተረጉም፦ “ጲላጦስ ማለት በመረጃ እና በአዕምሮ ዕውቀት
የተመሠረተ ዕቅድና የአገዛዝ ሥርዐት ወይም የሥጋ
ፈቃድማለት ነው” ብሏል።(ማቴ.27፡2)። ጲላጦስ ኢየሱስን
የአይሁድ ንጉስ ነህን ብሎ መጠየቁን በማንሣትም ይህ
የጲላጦስ ንግግር ንጉሥነት ለሁሉም ሰው የተሰጠ መሆኑን
ያሣያል ይላል በበማለት ተርጉሟል።(ዮሐ.18:33)።184
በተጨማሪም እንደ እርሱ ከሆነ ቃየልና አቤል የሚሉት ስሞች
አዕምሮን ይወክላሉ። ሲያብራራም አቤል ማለት ትንፋሽ
ማለት ስለሆነ የአይምሮ ዓለምን ይወክላል፤ ነገር ግን የእንሰሳ
አገልግሎትን እንጂ መንፈሳዊ አዕምሮን አይወክልም ይለል።
ለዚህም ምክኒያት የሚያደርገው ደግሞ አቤል የበጎች ጠባቂ
መሆኑን ነው።185 ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጫነ
የፊሊሞር የልዩዲበ-አካል ትርጉም ምን ያኽል አመስጥሮትን
የተከተለ እንደሆነ መረዳት ከባድ አይደለም።

184
Charles fillimore, Methaphysical Bible Dictionary. (1931, p, 761).
185
Ibid., (p, 5).

151
የአማልክቱ ዐዋጅ

በፊሊሞር የልዩ ዲበ-አካል ትርጓሜ መሠረት ፊሊሞሪያዊያኑ


የዘፍጥረት መጽሐፍ አዕማድ ትምህርት የአዕምሮ ዐሳብን
ዐቅም ወይም የቃልን ኀይል ምሥጢር የሚያሣይ ነው ብለው
ያምናሉ። ለምሳሌ እግዚአብሔርም አለ የሚለውን ቃል
ከዘፍጥረት መጽሐፍ በመጥቀስ ፊሊሞር የሚከተለውን
አስፍሯል፦

እግዚአብሔርን ወይም መላለማዊ አዕምሮን መረዳት


ለመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ለማንኛውም ሥነ-ጽሑፍ
ቁልፍ ነው። በዘፍጥረት ታሪክ ሙሴ እንዳስቀመጠው
ሁሉም ነገር ወደ መሆን የመጣው እግዚአብሔር አለ
በሚለው ነው ይህም የአዕምሮ ዐሳብ ነው።186

ይህንኑ ዐሳብ በሌላ ቦታ ደግሞ ሲያብራራ እግዚአብሔር አለ


የሚለው ዓለማትን ከምንም ነገር የከሰተ ቃል ከሰው ልጅ
አዕምሮ ዐሳብ ጋር አንድ ነው ብሏል፦

“‘እግዚአብሔርም አለ’ ይህ ሁሉም ነገሮች ወደ


መገኘት ከሚመጡበት ከአዕምሮ ዐሳብ ጋር
ተመሳሳይ ነው። ሰው ችግር ከደረሰበትና ከችግሩ ጋር
ከተስማማ ይህንን በራሱ ላይ ያመጣው ዐሳቡ ከቃሉ

186
Ibid., (p,654).

152
ጆንሰን እጅጉ

እና ከጌታ ጋር ወይም የመለኮት ሕግ ጋር


ስለተስማማ ነው።”187

ለፊሊሞር እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበት ዐቅም ከሰው


ልጅ አዕምሮ ዐቅም ጋር ልዩነት የሌለው ነው። በርግጥ
“የአዕምሮ ሕግን” መለኮት ብሎ ስለሚጠራውና የሰውን
አዕምሮ መለኮት ስለሚደርገው ይህ ድንቅ ባይሆንም የቃል
እምነትን ለማስረፅ የተሄደበት ረጅም መንገድ አስገራሚ
ነው።

ፊሊሞርያኑ የመለኮትን የማይወሰን የመፍጠር ችሎታ ለሰው


ልጅ “አትገደብም” በማለት ሲሰጡት ወይም አዕምሮ
“የማይወሰን ልዕልና አለው” በማለት መለኮታዊ ተፈጥሮ
ሲሰጡት አይጎረብጣቸውም። ይሁን እንጂ ቀርቦ ለመረመረው
በራሳቸው ዐውድም ቢሆን ትምህርቱ ወጥነት የሌለየውና
ዕብደት ሊባል የመሚችል ነው። ፊሊሞር ሙሴ የተደነቀበትን
የቁጥቋጦ እሳት በማጣቀስ ሲተነትን፦

ጥበብ ከልብ ማለትም ከዚህ ቁጥቋጦ ይወጣል ወይም


ከማይቃጠል ህዋስ። ይህ ቅዱስ ቦታ ነው ወይም
በመለኮታዊ አዕምሮ ውስጥ ያለ ነገር ነው። ሰው
ወደዚህ ቁጥቋጦ (መለኮታዊ አዕምሮ) ሲቀርብ ሙሴ

187
Ibid., (p, 346).

153
የአማልክቱ ዐዋጅ

‘ጫማህን ከእግርህ አውልቅ’ እንደተባለ የውስንነትን


ዐሳብ ማውለቅ አለበት።188

ብሏል። እንደእርሱም የሙሴን ጫማ ማውለቅ መወገድ


ያለበት የውስንነት ዐሳብ ነው። እውነቱ ግን ሰው ከልደቱ
ጀምሮ እስከ ሞቱ ድረስ በጊዜና በቦታ የተወሰነ፤ አንዲቱን
ጸጉሩን እንኳ ነጭ ወይንም ጥቁር ማድረግ የማይችል ውስን
ፍጥረት ነው። (ማቴ.5፡36) ። በሌላ በኩል ደግሞ ዐሳብና
መለኮታዊ አዕምሮ ሁለት የተለያዩ ነገሮችና አዕምሮም
በመገለጥ ሊደረስበት የሚችል ከሰውነት ወጪ ያለ የማይዳሰስ
ማድረጉ ውልና ወጥነት የሌለው ቅዠት ነው ማለት ይቻላል።
የሰውን አዕምሮ መልሶ እንዴት የሰውነት ክፍል
እንደሚያደርገው በሚቀጥለው ንዑስ እርዕስ የሚዳሰስ
ይሆናል።

አዕምሮን የአባት ሕግ ወይም መለኮት በማድረግ የልዩ ዐዋጅ


ቃል ትምህርትን መሠረት ለማስያዝ ከሚጥረው ከዚህ
የፊሊሞር ድፍረት ይልቅ ግን ግርምት የሚፈጥረው በወንጌል
አማኞች መድረክ ላይ የሚሰማው ‘አንወሰንም’ የሚለው
ሰውን ያመለኮተ የቃለ ዐዋጅ ነውጥ ነው። ለምሳሌ የእምነት
ቃል ሰባኪው ክሪስ ሲናገር “እኛ ማድረግ ለምንችላቸው
ነገሮች ምንም ገደብ የለብንም ማለት ነው። ለእኛ ምንም

188
የክሬመርን አልወሰንም እወጃን (ገጽ 55) ላይ ይመለቷል።

154
ጆንሰን እጅጉ

የማይቻል ነገር የለም፤ እኛ ልንሸነፍ የምንችል አደለንም።”189


ብሏል። እነኝህ ሰባኪያን አጢኖ ለሚመለከታቸው ከሰማይ
የወረዱ ትኩስ አማልክት ይመስላሉ። ከፊሊሞሪያዊያኑ
ባልተለየ ሁኔታ የዘፍጥረትን መጽሐፍ በመጥቀስ መንፈሳዊው
ዓለም የቃል ዓለም ነው በሚል ትርጉም ጡዘት በቃል ኀይል
በመጠቀም የሰውን የጸሎት ጥያቄ መልስ የመወሰን ሙከራ
በየመድረኩ ሲያደርጉ ማየት የተለመደ ነው። እነኝህ ወገኖች
አዕምሮን ወደ መለኮት ለማስጠጋት “የአባት ሕግ” የሚለውን
ቃላት ባይጠቀሙም የፊሊሞርን የዐዋጅና የአእምሮ ሕግ
ተግባራዊ ማድረጋቸውን በየመድረኩ የምናስተውለው እውነት
ነው።

ክርስቶስን ማነቃቃት

በዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ሥርው ቃል ዐዋጅ


በጤንነትም ይሁን በስኬት ላይ ውጤት የሚኖረው
“ክርስቶስን” ስለሚያነቃቃ ነው። ለምሳሌ ፊሊሞር ኅሩይ ቃል
ዐዋጅና ሜዲቴሽን በፍጥረት ውሰጥ ያለውን “መለኮት”
ወይም “ክርስቶስ” በማነቃቃት ከፍተኛ ውጤት ለማስገኘት
ይጠቅማል ይላል።190 እንደ እርሱ ትምህርት ከሆነ እያንዳንዱ
189
ክሪስ ኦያኪሂሎሚ፤ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ (2009፣ነሐሴ 11) ፡፡
190
ሜዲቴሽን፦ አእምሮን በአንድ በሚፈለግ ነገር ላይ ብቻ በማድረግ በተመሰጦ
ማሰብ ሲሆን ለምሳሌ፣ በተለያየ ርቀት ያሉ የዩኒቲ አባላት ዘወትር 9 ሰዓት የጋራ
የአእምሮ ትስስር ለመፍጠር በያሉበት በመገናኘት ለ 5 ደቂቃ የዝምታ ተመስጦ

155
የአማልክቱ ዐዋጅ

አማኝ በውስጡ ያለውን “መለኮት” የማነቃቃት ኀላፊነት


አለበት።191

ሪክ ኦስትራንደር የፊሊሞራዊያኑን አማልክትነት ወይም


የክርስቶሳዊነት እምነት መሠረታዊ ግንዛቤ ሲያስረዱ።
“ክርስቶስ የሚለው ስም የኢየሱስ መለኮታዊ ስም ሲሆን
ይህም በእያንዳንዱ ሰዉ ወስጥ ያለውን ተመሣሣይ መለኮታዊ
ተፈጥሮ ዐቅምን ያሣያል።”192 ማለታቸውን አጣቅሰዋል።
እንደ ፊሊሞር አተረጓጎም ከሆነ ክርስቶስ የሚለው ስም
መለኮታዊ ባሕርይን የሚገልጥና ለሰው ሁሉ የተሰጠ በመሆኑ
በኢየሱስ ብቻ የተወሰነ አይደለም። እንደ እነርሱ ኢየሱስ
የክርስቶሳዊነት193 ምሳሌ እንጂ የተለየ ማንነት ያለው መለኮት
አይደለም። ፊሊሞር በዚሁ የተበላሸ ትምህርተ ክርስቶስና
ትምህርተ ሰብዕ ትምህርቱ እንደሚለውም የሰው አዕምሮ
የመንፈስ ክፍል መለኮት ወይም ክርስቶስ ነው።194 ይህም
የሰው መንፈስ (የአዕምሮ ክፍል መሆኑ ነው) መለኮት ነው
የሚል ትርጉም የሚሰጥ ነው። እንደ ትምህርቱ በሰው ውስጥ
ያለውን መለኮት በማነቃቃት ታማሚውን ለመፈወስ አምላክ

ያደርጋሉ በማለት ሄለር ጆን ይገልጣሉ (ገጽ 105)::


191
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, p,119).
192
Ibid., (p, 105).
193
የክርስቶሳዊነት፦ ክርስቶስ መሆን ወይም አምላክ መሆን ማለት ነው።
194
ክርስቶስ፦ በፊሊሞር እምነት ክርስቶስ የኢየሱስ ብቻ የሆነ መጠሪያ ሳይሆን
የሁሉም ሰው መጠሪያና የመለኮታዊ አእምሮ ስያሜ ነው።

156
ጆንሰን እጅጉ

ሁሉን ማድረግ የሚችል አዕምሮ እንደሆነ ማመን ይገባል።


በመቀጠል ታማሚው “ማረጋገጥ” ወይም “ማወጅ” ስላለበት
ይህንኑ እንዲያደርግ ማዘዝ ያስፈልጋል።195

ትምህርቱን ግልጽ ለማድረግ “የቃል ዐወጅ” ጉልበት ወይም


ውጤት ምስጢሩ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለ “ክርስቶስ”
መነቃቃት ነው። ኦስትራንደር የዩኒቲ ተማሪዎችን የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ እምነት ሲገልጹ፦ “የዮኒቲ ተማሪዎች መለኮት በሰውና
በሁሉም ፍጥረት ውስጥ እንዳለ ሲያምኑ “ጸሎትም”196
ይህንን መለኮት በማነቃቃት እንዲንቀሳቀስ ያደርገዋል።”197
ይላሉ በማለት አስፍረዋል። ምንም እንኳን ዐስተሳሰቡ እንዲህ
ውል የለሽ ቢሆንም የወንጌል አማኞችን መድረክና ጉባዔ
ያጠመቀ ልምምድ መሆኑ አስደንጋጭ ነው። ሰባኪያኑ በውል
በማያቁት ወይም በግልጽ በማይስማሙበት በዚህ
የፊሊሞራዊያን የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ፎርሙላ ፈውስና
ተአምራት ለማድረግ ሲሉ በኩራት ይተገብሩታል። ወዳጆች፤
በዚህ መልክ ሰባኪኑ በወንጌላውያን መድረክ ላይ ወደ ሥኬት
ከፍታ ለመምጠቅ ሲጥሩ መመልከት ምን ያኽል ልብን
የሚሰብርና እግዚአብሔርንም የሚያሳዝን ይሆን?

195
Haller, J. S. The History of New Thought: (2012, p, 106).
196
ፊሊሞሪያዊያን “ጸሎት” የሚሉት የቃል ዐዋጅን ነው።
197
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science: (2000, p.118).

157
የአማልክቱ ዐዋጅ

በእርግጥ አማልክቱ ትምህርቱን በቃለ እግዚአብሔር


እንዲጣፍጥና እንዲሸፈን ስላደረጉት ልምምዱን
ስንመለከትም ይሁን ስንለማመድ ብዙም አይቆረቁረን
ይሆናል። ነገር ግን የቃል ዐዋጅ መርሖ በልዩ ዲበ-አካል
አማልክቱ በስውር ተቀምሮ የታደለን መሳሪያ ነው። የኅሩይ
ቃል ዐዋጅ ዋነኛ ስሌት ሰውነትን ለማነቃቃት ታስቦ የተቀመረ
አይደለም። እንደነእርሱ ከሆነ በሰው ውስጥ ያለ “መለኮታዊ
ክፍልን” ማለትም “አዕምሮን” ወይም “ክርስቶስን”
ለማነቃቃት ታስቦ የሚተገበር እንደሆነ ልናውቅ ይገባል።

የኅሩይ ቃል ዐዋጅ
ፊሊሞር የኅሩይ ቃል ዐዋጅ አስተምህሮን ከጀማሪው
ከሲውዲንበርግና ከፓንክሆረስት ኪዊምቢይ ተቀብሏል።
ሁሉም የዲበ-አካል ሃይማኖት መሪዎች የራሳቸውን ፍልስፍና
እያከሉ እንዳዳበሩት ሁሉ ፊሊሞርም ይህንኑ አድርጓል። እንደ
ፊሊሞር ከሆነ የኅሩይ ቃል ዐዋጅን ቅደም ተከተል በማወቅ
መተግበር “ጸሎት” እንዲመለስ ያደርጋል። ለምሳሌ ሞስሊ
ፊሊሞር በጽሑፉ ላይ ይህንን ማብራራቱን ሲያጣቅሱ፦
“በመጀመሪያ ዐሳብን በትክክል ማቀናጀት፣ በስልጣን መናገር፣
እንደተፈጸመ መቁጠር፣ ዘና ማለትና በመጨረሻ ለሕሊና
ያስተላለፍነው ትዕዛዝ ማለትም መልካምም ይሁን ክፉ

158
ጆንሰን እጅጉ

ያሰብነውን አዕምሮ ወደ ተግባር እደሚለውጠው መረዳት


አስፈላጊ ነው”198 በማለት ማስቀመጡን ያነሳሉ።

ከዚህም የተነሳ “የዩኒቲ ኮሚኒቲ” አባላት “የቃል ዐዋጅ”


የጸሎት መልስ እንደሆነ ያምናሉ። በዚህም መሠረት ብዙ
የጸሎት ጥያቄ መልሶችን እራሳቸው በቀጥታ በኢሜልና
በሥልክ ጭምር ትንቢት በሚመስል ዐዋጅ ይመልሱ እንደ ነበር
የሞስሊ ጥናት ያሣያል። ከነኝህም “የጸሎት” መልሶች
መኻልም የፊሊሞር ባለቤት ማርቲል “ጸሎትን”
የመለሰችበትን ጽሑፍ እንደሚከተለው አጣቅሰዋል፦

ባላችሁበት ቦታ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲፈስባችሁ


አውጃለሁ! በዛ ውስጥ ባዶነት ተስፋ መቁረጥ እና
ደካማነት የለበትም! የአዕምሮን የውሸት መረጃ ክፍል
በማሸነፍ ከናንተ ጋር በመሆን እንደሰታለን!
የሚያበረታታችሁን ታላቅ ቃል እናውጃለን! ድፍረትን፣
እምነትን፣ ጥንካሬን ጥበብን እናውጃለን!199

በዚሁ ጥናታቸውም ማርቲል በተደጋጋሚ እንደዚህ ዓይነቱን


የቃል ዐዋጅ ጮክ ብሎ መናገር በሽተኛን የሚፈውስ መርሖ
እንደሆነ በልበ ሙሉነት በተደጋጋሚ ታስተምር ነበር ብለዋል።

198
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, p.79)
199
Ibid., (P.18).

159
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደ ሞስሊ ከሆነ ማርቲል በዚህ መርሖ ውጤታማ


እንደሆነች የራሷን ፈውስ ጨምሮ ከተለያየ ቦታ በሚደርሷት
በርካታ የጸሎት መልስ ምስክርነቶች አረጋግጣለች።
በአጠቃላይ ይህ ልምምድ የማርቲል ፊሊሞር “ቃል ዐዋጅ”
ወይም ተከታዮቻቸው እንደሚሉት “የጸሎት መልስ” ውጤት
ልክ እንደ አምላክ በአፉቸው ላይ እንደሆነ እንደሚያምኑ
በግልጽ ያሣየ ነው። እንደርሷም ጸሎትም ሆነ የጸሎት መልስ
ያው የቃል ዐዋጅ ነው።

ይህ ትምህርቷም በከፍተኛ ሁኔታ ስለተስፋፋ በቸልታ


የሚታይ አይደለም። ሞስሊ የታሪክ ተመራማሪውን ጀምስ
ዳይሊትን ለማርቲል ውጤታማነት የሰጠውን ምስክርነት
ሲያጣቅሱ፦ “ማርቲል በሊጥ ውስጥ እንደተቀመጠ እርሾ
ሺዎችን እስክታቦካ ወይም እስክትባርክ ድረስ፤ ባለቤቷ
ፊሊሞር ለሚሊዎኖች የሚደርስ በረከት እስኪሆን ድረስ
መሥራት ችላለች።”200 ማለቱን አንስተዋል።

የፊሊሞር ተከታይ የሆነው ኢርነስ ሆምስ የቃል ዐዋጅ


ልምምድን በምን ስልጣን እንደሚያደርግ ሲጠየቅም የኢየሱስ
ስልጣን በሥራው እንደሆነ እንዲሁ ሥልጣኔ በሥራዬ ነው

200
Ibid., (p . 7).

160
ጆንሰን እጅጉ

ማለቱን አጣቅሰዋል።201 እንደ እርሱ ከሆነ የቃል ዐዋጅ ስልጣን


ጥገኛ ያልሆነና በግል ፍቀድ ብቻ የሚደረግ ልምምድ ነው።

የቃል ኀይል የሚሠራበትን ምክንያት የፊሊሞር ተከታይ የሆነ


ሚስተር ሮው ላንድ የተባለ ሰውም የተናገረውን ሲያጣቅሱም
“በምናውጅበት ጊዜ የተናገርነው ቃል በመላለም ውስጥ
ይንቀሳቀሳል፣ የህይወታችንን ቅርፅ ያበጃል፤ ስለዚህ አሁን
ያለውን ችግር እርሳውና ቃልህ እንዲሰራ ፍቀድለት።”202
ማለቱን ዘግበዋል። ፊሊሞራዊያኑ ለጸሎት መልስ በእነርሱ
ፈቃድ ቁጥጥር ሥር የሚሠራ የቃል ዐዋጅ በቂ እንደሆነ ካመኑ
ታዲያ እግዚአብሔርን ወይም ኢየሱስን መጥራታቸው
ፍልስፍናቸውን ከቤተክርስቲያን ጋር ለማጋባት
እንዲያመቻቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው ማለት ይቻላል።

በርግጥም አማልክታዊው የቃል ዐዋጅ እምነት በቤተክርስቲያን


ለመስረጉ ሁሉም የልዩ ዲበ-አካል መሪዎች የተለያየ
አስተዋጽዖ አድርገዋል። ኪኒየን ግን በተለየ ሁኔታ ተገለጠልኝ
በሚል በወንጌላውያን አማኞች መድረክ ላይ ሳይቀር እንደ ልቡ
ድክድክ እንዲል አስችሎታል። የኬኔት ሄገን ተመሳሳይ ክህደትና
የተገለጠልኝ ውሸትም ልምምዱ እንዲጠነክርና ተደላድሎ
መኮፈስ እንዲችል አስችሎታል። ትምህርቱም በበርካታ

201
Ibid., (p .50).
202
Ibid., (p, 20).

161
የአማልክቱ ዐዋጅ

የፕሮቴስታንት አማኞችና አገልጋዮች እንኳ ሳይቀር ሰፊ


ዕውቅና ተሰጥቶታል። ይህም ሊሆን የቻለው በኪኒየን
የተጀመረው ‘ኅሩይ ቃል ዐዋጅ’ የኢየሱስን ስም በመጥራትና
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በመናገር ማስደገፍ በሄገንም
በመቀጠሉ ነው። ለምሳሌ ኢ. ደብሊዩ ኪኒየን ይህንን
ልምምድ ሲያጸና፦ “የብዕር ጫፍ ከሴይፍ ስለት ይበረታል
እንደሚባለው የአንደበታችንን ቃል ብቻ መልቀቅ ብንችል
ሕይወታችን እንዴት ያማረ በሆነ ነበር። የአንደበታችን ቃል
የእግዚአብሔር ቃል በሚሆንበት ጊዜ የብዕራችን ጫፍ እና
የአንደበታቸችን ቃል ታላቅ ኀይል ይኖረዋል።”203 ያለ ሲሆን
በዚህ ንግግሩም ኪኒየን የአንደበታችንን ኀይል
አለመጠቀማችንን በቁጭት ማንሳቱ በልዩ ዲበ-አካሉ
ፍልስፍና መጠመዱን ጠቋሚ ነው። በልዩ ዲበ-አካል ትምህርት
ላይ የጨመረው አዲስ ነገር አንደበታችን የእግዚአብሔርን ቃል
በመጠቀም የበለጠ ኃይለኛ ይሆናል የሚለው መሆኑ ብቻ
ነው።

የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ያገኘው ድል እና ተቀባይነት ሲነሳ


የእምነት ቃል እንቅስቃሴ አርበኛውን “አማልክት” ሄገንን
አለማንሳት አይቻልም። ሄገን ጥቅስ ጠቅሶ የልዩ ዲበ-አካል
ፍልስፍናን በቤተክርስቲያን ውስጥ በማስተማርና በማስፋፋት

203
E.W Kenyon & Don Gossett. Speak life: Words that work wonder. (p. 22).

162
ጆንሰን እጅጉ

የሚያክለው የለም። ለምሳሌ፦ የጸሎትን ምላሽ ምሥጢር


(ሮሜ.10፡10) በመጥቀስ ሲያስረዳ “ሰው በልቡ ማመኑና
በአንደበቱ ማወጁ ጸሎቱ እንዲመለስለት ያደርጋል” ብሏል።
ሄገን በመቀጠልም ከሰማይ የሰማው ድምጽ ህዝቤን እምነት
አስተምርልኝ እንዳለው ከተናገረ በኋላ የዚህን መገለጥ
ማዕከላዊ ዐሳብ ሲያስቀምጥ፦ “በልባችሁ ውስጥ ያለውን ነገር
ካመናችሁና ከተናገራችሁ ታገኙታላችሁ” በማለት ከማር.11፡
23 ጋር በማያያዝ ያነሣል። ይሁን እንጂ ከኪኒየን ላይ የተወሰደ
እውነትን ያፋለሰ ድምዳሜ ነው። ይህንን በሚገባ ለመረዳት
የጥቅሱን ትንታኔ በምዕራፍ አምስት ላይ የምናየው ይሆናል።

የዲበ-አካል ሃይማኖት ምሁራንም ሆኑ የእምነት እንቅስቃሴ


መሪዎች ታዲያ በፈውስ ልምምዳቸውም ሆነ ትምህርታቸው
የኢየሱስን ስም አሊያም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ እንዲህ
እያጣቀሱ ማዋዛታቸው የአማኞችን አፍ አስከፍቶላቸዋል።
በተጨማሪም ፊሊሞራዊያን ቃል ዐዋጅን ለግላቸው ፈውስና
ጤንነትም የሚጠቀሙ ሲሆን እንደ እርሱም እወጃው በቀጥታ
ለአካላቸው ብልቶች በትዕዛዝ ቃል የሚተላለፍ ነው
የሚሆነው።

ለምሳሌ፦ ማርቲል ይህ የዐዋጅ መርሖ አካሌን በማደስ


ፈውስን ያደርጋል ማለቷን ሞስሊ ያነሣሉ።

163
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለአካሌ፣ ለሳንባዬ ሕይወትንና ጤንነትን እናገራለሁ፣


ለልቤ ሕይወትን እናገራለሁ፣ እኔ እንደፈለኩት እንደዛው
ይሆናል! ...ለጉበቴ ሕይወትን እናገራለሁ! ጉበቴ የተበላሸ
አይሆንም! ነገር ግን ጤናማና ጠንካራ ነው! በጨጓራዬ
ላይ ሕይወትን እናገራለሁ! ደካማ አይደለም! ነገር ግን
ጠንካራ ኃይለኛና ብርቱ ነው። 204

ብላለች። ይህም የማርቲል ኅሩይ ቃል ዐዋጅ (Positive


confession) ተከታዮቿ ከመታመማቸው አስቀድሞ
ከበሽታ እንዲከላከልላቸው ለማድረግ በማሰብ
የሚወጉት መድኃኒት መሆኑ ነው።205 እንዲሁ ሁሉ
ይህንኑ ትመህርት በከፍተኛ ሁኔታ እያስተማረ
የሚገኘው ክሪስም “በአንደበታችሁ ጤንነታችሁን
ጠብቁ። ዘወትር ጤንነትን፣ ስኬትን፤ እንዲሁም
ብልጽግናን ተናገሩ።”206 ብሏል።

ከወንጌል አማኞች መኻልም ይህንን ቃል የማወጅ “መከላከያ


መርፌ” በተመሳሳይ ሁናቴ በሽታን ወይም ድኽነት
እንዳይነካቸው በሚል የሚወጉ ወገኖች እንዳሉ
ተመልክቻለሁ። ጸሎታቸው ካለ ቃል ዐዋጅ የሚመለስ
204
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P,19).
205
“ዲበ-አካል፣ኬኒዮንና ኬኔት ሄገን” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር ኬኒዮንና ኬኔት ሄገን
ይኸው የኅሩይ ቃል ዐዋጅ መርሖ ለአካል የማወጅን አስፈላጊነት መናገራቸውን
ያስተውሏል።
206
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ፤ ክሪስ ኦኪያሂሎሚ (2013፣29) ፡፡

164
ጆንሰን እጅጉ

የማይመስላቸው ብዙ ናቸው። ስለዚህም የስብከታቸውና


የጸሎታቸው ማሳረጊያና ማጣፈጫ “ኅሩይ ቃል ዐዋጅ”
እንዲሆን ያደርጋሉ። በሚያሳዝን ሁኔታም ህዝቡን ቁጭ
ብድግ በማድረግና በማዋከብ ከእነርሱ ጋር እንዲያውጅና
እንዲለማመድ ያደርጋሉ።

የኅሩይ ዐዋጅ ስኬት


በኅሩይ ዐዋጅ ልምምድ ስኬት እንዳገኙ የሚናገሩ ክርስቲያኖች
አልፎ አልፎ ይሰማሉ። ልምምዱ የማይታይበትም ጉባኤና
አገልጋይም አይመቸንም ይላሉ። ልምምዳቸውን የሚቃወም
ወይም እንዲላቀቁ የሚሞግታቸው ምን አልባት የተገኘ
እንደሆነ ታዲያ የመንፈስ ቅዱስን እንቀስቃሴ እንደሚቃወም
ይቆጥራሉ። የዛኑ ያኽል ደግሞ በልምምዱ ግራ የሚጋቡ፣
ጤናማነቱን የሚጠራጠሩና በስኬቱም እውነተኝነት ላይ ጥያቄ
የሚያነሱ ብዙ ናቸው። ነገር ግን የቃል ዐዋጅ ልምምድ ስኬት
ተጨባጭነት ለማረጋገጥ ከማሰብ በፊት የልምምዱን ሥርው
ማጥናትና እንደ እግዚያብሔር ቃል መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል። ምክንያቱም ማንኛውም ልምምድ ይሥራም
አይሥራ እንደ ጌታ ቃል ካልሆነ ውድቅ ነው። ይህም መጽሐፍ
ታሪካዊ መሠረቱን ከመቃኘት ባሻገር ይህንን ፍተሻ ዳር
ለማድረስ ሰፊ ቦታ ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ንዑስ

165
የአማልክቱ ዐዋጅ

ርዕስ የቃል ዐዋጅ ልምምድን ስኬት ከመሪዎቹና ከውድቀቱ


አንፃር እንመለከታለን።

አማልክቱ ሰባኪያን ኅሩይ ቃል ዐዋጅ ከልመና ይልቅ እጅግ


አስፈላጊና ውጤታማ እንደሆነ ይታመናሉ። የመልካም ዐዋጅ
ቃላትን በህሙማን ላይ ማወጅ ፈውስን ያመጣል፤
ድኽነትንም ጠራርጎ በማስወገድ ያበለጽጋል በማለት ሁሉም
የዲበ-አካል ሃይማኖት አራማጆችም ሆኑ የእምነት እንቅስቃሴ
መሪዎች እንደሚስማሙ ጥናቶች ያሣያሉ። ታዲያ
መሠረታዊው ጥያቄ ይህ ዐስተሳሰብ እውነተኛ ውጤት አለው
ወይ የሚለው ብቻ ሳይሆን በእዚህ መርሖ መሠረት የሚታዩት
ውጤቶች ከወዴት ናቸው? የሚለውም ነው። የእግዚብሔርን
ቃል መርሖ የማይከተል ወይም የቃሉን መርሖ የሚያፋርስ
ማንኛውም ልምምድ ሁሉ የሥጋ፤ የአጋንትም ነው።

ለምሳሌ ብናነሳ፤ ክሪክስ ኦከህያሜ ሜጋ ቤተ-ክርስቲያን


የሚመራ በኅሩይ ዐዋጅ ቃል ትምህርትና የፈውስ ልምምዱ
በርካታ ዐዎንታዊ ምስክርነቶችን የሰበሰበ መሪ ነው። ነገር ግን
አገልግሎትን ‘ውጤታማ’ ለማለት ከሚሰሙ ምስክርነቶች
በላይ የሰዎች ሕይወት እየተገነባ ያለበት ሥነ-መለኮት እንደ
ጌታ ቃል መሆኑን መመዘን ያስፈልጋል። ምክንያቱም መጽሐፍ
ከግንባታው ይልቅ የሚሠራበት ግብአት ላይ ትኩረት ማድረግ
እንዳለብን ያስጠነቅቃል። (1 ቆሮ.3፡12-13)።

166
ጆንሰን እጅጉ

ክሪስ “ራፕሶይድ” የተባለ በየወሩ እየታተመ በመላው ዓለም


በተለያየ ቋንቋ የሚሰራጭ አነስተኛ መጽሐፍ አለው። በዚሁ
መጽሐፍም ወርሃዊ መልዕክት ላይ የቃል ዐዋጅ አስፈላጊነት
ላይ ትኩረት በመስጠት በቋሚነት ያቀነቅናል። በትምህርቱም
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ላይ ለውጥ ያላመጡት
ዐሉታዊ ንግግር ስለሚናገሩና ኅሩይ ዐዋጅን ስለማይለማመዱ
ነው፤ ዐሉታዊ ንግግር በሰው መንፈስ ላይ ያለውን መለኮታዊ
ባሕርይ ይጎዳል ይላል።207 ይህንንም ለማሣካት በእያንዳንዱ
የስብከት መዝጊያው ላይ “ጸሎት” እና “የእምነት ዐዋጅ”
የሚሉ ርዕሶች ያስቀምጣል። ትምህርቱ ትኩረት እንዲያገኝም
በየአጥቢያው በሚኖረው የዕሁድ አምልኮ ላይ የዕለቱ የምንባብ
ክፍል ከወርሃዊ መጽሔቱ ላይ በዕለቱ ተረኛ የሚነበብ ሲሆን
የዕለቱ “የእምነት ዐዋጅ” ወይም “ጸሎት” በጉባኤው
እንዲታወጅም ይደረጋል።

ይሁን እንጂ “ጸሎትም” ይሁን “የእምነት ዐዋጅ” በሚል ርዕስ


የሚያስቀምጠውን ዝርዝር ዐሳብ አንስተን የመረመርን
እንደሆን በሁለቱም ርዕስ ሥር የተቀመጠው ዝርዝር ዐሳብ
ምንም ልዩነት የሌለውና ከጸሎት ይልቅ የቃል ዐዋጅ ማለትም
“ልዩ ጸሎትን” የሚንጸባረቅበት ነው። ለምሳሌም ያኽል
የሚከተለውን እንመልከት፦

207
ክሪስ እና አኒታ ኦኪሂያሎሚ፤ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲ (2006፣ጥር፣ገጽ.19) ፡፡

167
የአማልክቱ ዐዋጅ

“እግዚአብሔር ለአኔ ካለው ፍጹም ፈቃድ ጋር


እንዲስተካከል የከበረውን ሕይወቴን አከባቢዬን
ለማቅናት በከንፈሬ ባለው የእግዚአብሔር የመፍጠር
ኀይል እጠቀማለሁ፡ ሕይወቴን፣ ጤናዬን፣ ገንዘቤን፣
ወዳጆቼን በተመለከተ የበረከት ቃል ስናገር፣ መንፈስ
ይሰፍባቸዋል እውንም ይሆናሉ። ዛሬ በረከትና
እየጨመረ በሚሄድ ክብር እመላለሳለሁ፣ በኢየሱስ
ስም።”208 (የእምነት ዐዋጅ)

“ቃሎቼ ኀይል ያላቸው፣ ድሎችን፣ ብልጽግናን፣


ዕድገትን እንዲሁም የተትረፈረፈ በረከትን ለእኔ
የሚሰጡ ናቸው። በመልካም ቃላቶቼ በክርስቶስ
ውብ የሆነ ያልተለመደ አስደሳች፣ አርኪ፣ ልዩ እና
በብልጽግና፣ በጤንነት፣ በደስታ እና በሰላም የተሞላ
የክብር ሕይወት እፈጥራለሁ፣ በክርስቶስ ክብር፣ ጸጋ
እና ጽድቅ እመላለሳለሁ፣ በኢየሱስ ስም።”209
(ጸሎት)።

በሁለቱም ምድብ የተዘረዘሩት ኅሩይ ቃላት መለኮትን


የመለመንን ዝንባሌ ሊያሳዩ የሚችሉ ባሕርያትን ፈጽሞ
ያስወገዱ ናቸው። ይህ ልመናን የመሸሽ ዝንባሌ የሚያሣየን
አንድ ክርስቲያን በቃሉ ዐዋጅ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ

208
ክሪስ እና አኒታ ኦያኪሎሚ፤ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲ (2013፣ገጽ.10)፡፡
209
Ibdi, (p.29).

168
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚችል ማመን እንዳለበት ነው። ይህ ተቀብሎ


የሚለማመድ ከሆነ ታዲያ ወደ መለኮት በትህትና በመቅረብ
ኅብረትን የሚያደርግበትንና ልመናን የሚያሰማበትን ዐቅም
በቀላሉ ይጥላል። በዚህ ትምህርትና ልዩ ጸሎት ልምምድ
የተጠቁ ሰዎችን የአንድ ደቂቃ ጸሎት በማድመጥ ልንለያቸው
እንችላለን። ይህን ስንመለከት የቃል ዐዋጅ ልምምድ
የክርስቶሳዊነት ባሕርይ ዋነኛ መገለጫ መሳሪያ በመሆን
ማገልገል መጀመሩን እንገነዘባለን። የመጽሐፍ ቅዱስን ርቱዕ
ትምህርት መሠረት ያላደረገ የትኛውም ልምድ የወለደው
ስኬት ጥፋት ስለሆነ ከእውነተኛ ስኬት አይቆጠርም።

እንዲሁ ሁሉ እንደ ሄገን ባሉ የእምነት ቃል ትምህርት


አስተማሪዎች የአዋጅ ቃል ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ
እንደሚሆን ቢሰበክም ትምህርቱን ተቀብለው በሚከተሉት
ጭምር ግራ መጋባታቸውን የሚያሣዩ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ለምሳሌ ሄገን የእምነት ቃል ትምህርትን ከእርሱ የተማሩ
ሰዎች ወደ እርሱ ተመልሰው በመምጣት “ሄገን እንዳልከን
አደረግን። የምንፈልገውን ነገር ደጋግመን አወጅን። ነገር ግን
ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም። አልሰራልንም።” ሲሉት
የሚሰጠውን ምላሽ በራሱ ብዕር እንዳስቀመጠው። “ደህና
የማይሠራ ከሆነ ኢየሱስ ዋሽቷል ማለት ነው?”
እንደሚላቸው የተናገረ ሲሆን፤ በመቀጠልም ሰዎቹም

169
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመደንገጥ፦ “አይ! ኢየሱስ አይዋሽም።” እንደሚሉት


210
ጠቅሷል።

የሄገን የቃል ዐዋጅ እንዳልሠራላቸው የሚያረጋግጠውን


ተከታዩቹ የሚያነሱትን ጥያቄ ወደጎን አድርገን፤ አግባብነት
በሌለው አቀራረቡ በሚሰጠው ምላሽ ማሳቀቁንም ትተን፤
መነሻ ያደረገውን የሮሜን ጥቅስ ስንመለከት ፈጽሞ ስለ
ጸሎት ያልተባለ ጥቅስ ሆኖ ነው የምናገኘው። በአጭሩ የሮሜ
መጽሐፍ “የእምነት ቃል” የሚል ርዕስ በማንሣት
የሚያብራራው የድነት ምሥጢርን ሆኖ ነው የምናገኘው።
ክፍሉ “የእምነት ቃል” በማለት የሚያነሳው የኢየሱስን ሞትና
ትንሳኤ ማመንን እና መስበክን ነው። ሄገን እንደሚሉት
የምንፈልገውን በልባችን ያለን አንድ ነገር ስለ ማመንና
ስለማወጅ በፍጹም እየነገረን አይደለም። እውነቱ ይህ ከሆነና
ልምምዱ የጌታን ቃል መርሖ የማይከተል ከሆነ ታዲያ ሄገንን
በድምጽ እየተገለጠ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያፈነገጠ ትምህርት
እንዲያስተምር የሚያዘው “ተገለጠልኝ” የሚለው ኢየሱስ
ማነው? የሚል ጥያቄ በጥርጣሬ ማንሣት ይገባል። መጽሐፍ
ሰይጣን እራሱን የብርሃን መልአክ አድርጎ እንደሚገልጥ
ስለሚናገር ሥጋታችን የሚበረታታ እንጂ የሚኮነን አይደለም።
(2 ቆሮ.11፡14)።

210
Hagin, K.E. (n.d). Understanding our Confession. (Pp, 56-75).

170
ጆንሰን እጅጉ

በተመሳሳይ መልኩም የዲበ-አካል ሃይማኖት መሪዎች የቃል


ዐዋጅ በሰው ልጆች ችግርና ሥቃይ ሞትና እርጅና ላይ እንኳ
ቢሆን በአሸናፊነት መራመድ የሚያስችላቸው ጥበብ እንደሆነ
አስተዋውቀዋል። መርሖ ቀምረው አስተምረዋል፤ ይሁን እንጂ
ካተረፉት ዝናና ሐብት በስተቀር ሙከራቸው ፍጹም ውጤት
አልነበረውም። ለምሳሌ ሜሪ ቤከር ኤዲ “የፈውስ ህጎች”
ወይም “የክህደትና የዐወጅ መርሖ” በማለት ዘርዝራ
በማስቀመጥና ተፈጥሯዊ ሞትን እስከ መካድ በመድረስ በዚህ
ድፍረቷ በአድናቂዎቿ ጎልታ ነበር። ህጎቿም ሥድስት መርኻ
ግብር ባላቸው ሥድስት ቀናት የተከፋፈሉ ነበሩ።

1. ቀን አንድ ተፈጥሯዊ ድካምን፣ ሥጋንና፣ ክፋቱን ማለትም


ምኞትንና የሥጋን ሥሜት፣ የወሲብ ፍላጎትን መካድ።
ሰው ከእግዚአብሔር የወረሳቸውን ነገሮች ማወጅ
ማለትም እውነተኛ ማንነትን ንጹህ ፍላጎትንና
መንፈሳዊነትን ማወጅ።
2. ሁለተኛ ቀን የክፋትን የሚያታልል ተጽዕኖንና የቁስን
ተጨባጭ እውነትነት መካድ። መንፈስ ብቻ ተጨባጭ
እውነት እንደሆነ ማመን፣ መልካምን ብቻ እንደምንቀበል
እና የመንፈስ ሕግ ብቸኛው ሕግ አንደሆነ ማወጅ።
3. ሦስተኛ ቀን የኃጢአትን ኀይል፣ የራስ ወዳድነትን ኀይል፣
ትዕቢትን፣ ቁጣና በቀልን መካድ።

171
የአማልክቱ ዐዋጅ

4. ፍርሃትን፣ በደለኝነትን እና እፍረትን መካድ፤ ሰላምና


እምነትን ማወጅ።
5. ድካምን፣ አለማወቅን፣ ሞኝነትን መካድ ዕውቀትንና
ፍትህን ማወጅ።
6. ፈውስን እና እርካታን ማወጅ። የሚሉ ናቸው።

እንደ ኤዲ ከሆነ የኅሩይ ቃል ዐዋጅ አስፈላጊነትን ከፍ


የሚያደርገው የፈውስ ቁልፍ ምክንያት መሆኑ ነው። የኤዲ
የክህደትና የዐዋጅ ትምህርት መሠረታዊ ምክንያት “ቁስ
እውነት አይደለም መንፈስ ብቻ ነው እውነት” የሚል ነው።
ተከታዮቿም ተፈጥሯዊ እርጅናን፣ ህመምንና ሞትን እስከ
መካድና የአካላዊ ሕይወት ቀጣይነትን እስከ ማወጅ
ይደርሳሉ። እንደ ትምህርቱም የቁስ-አካል መረጃ፤ ማለተም
የህመም ሥቃይን ጨመሮ እውነት ስላልሆነ መካድና በምትኩ
በዐዋጅ ቃል ጤንነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ኤዲ ይህን
በስፋት ታስተምር እንጂ ይህ ጽንሰ-ዐሳብ ጥንታዊው
የኖስቲስዝምን የቁስና የመንፈስ የሁለትዮሽ ዐስተሳሰብ
ጭምር የተቆናጠጠ ነው። ከዛም ከዚህ ብለው ሕግ ቀምረው
በታማኝነት ቢለማመዱትም ስኬት ብለው የሚቆጥሩት
ውድቀታቸውን ነው።

በ 1929 አኒ ሪክስ ሚልቴዝ (1856–1924) የተባለች


የሆፕኪን ተማሪ የኤዲን ክህደት ሕግ ላቅ ወዳለ ደረጃ

172
ጆንሰን እጅጉ

በማሽጋገር የዐዋጅን አስፈላጊነት ለማጉላት ሞክራለች።


ለዚህም የዐዋጅ ቃል ትምህርት የተጠቀመችው መጽሐፍ
ቅዱስን ሲሆን፤ ከፍ ያለ መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ልዩ
ችሎታ እንዳላት ትናገር ነበር። ሚልቴዝ አዕምሮን ለማሳደግ
በአንድ ነገር ላይ መመሰጥ አስፈላጊ ነው ትላለች።
ተመስጦንም ተግባራዊ ለማድረግ እንዲረዳ ክርስቲያን ዮጋን
አስተዋውቃለች።211 ሚልቴዝ አራቱን የዮጋ አይነቶች
መፈጸም ከተቻለ በሽታን ማሸነፍና የፈለግነውንም ማግኘት
እንችላለን የሚል አቋም ያላት ሲሆን ራስን ዘና ማድረግ ወደ
ክርስቶሳዊነት የምንገባበት ወይም የምንመለኩትበት በር ነው
ትላለች። እንደ እሷ ሰው በአካለ ሥጋው ሕያው መሆን ወይም
ለዘላለም በሥጋው መኖር ይችላል። ለዚህም ፍጽምና
ለማብቃትና ራስን ከተፈጥሮ ኀይል ተጽዕኖ ለማዳን ከወሲብ
መታቀብ ያስፈልጋል በማለት ታስተምር ነበር። እንደ ገዳማት
የምነና ትምህርት መሆኑ ነው።

ኋላ ላይ ሚልቴዝ በአካለ ሥጋ መኖር መቀጠል ሳይሳካላት


ይቀርና ትሞታለች። ትምህርቷ በመሞቷ ምክንያት ዋጋ
ማጣቱ የቆጫቸው ተማሪዎቿ ታዲያ ትምህርቷን በአስከሬኗ
ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ሞክረውት ነበር። ይህንን
በማድረጋቸውም ፍጹም አማኝ መሆናቸውን አስመሰከሩ።
211
ክርስቲያን ዮጋ፦ አራቱን የሂንዱ የዮጋ ሥርዓቶችንና የዐዋጅ ቃል ለክርስቶስ
መናገርን አቀላቅሎ የያዘ ልምምድ ነው።

173
የአማልክቱ ዐዋጅ

እነኝህ ታማኝ ደቀመዛሙርት ለሶስት ቀን አስከሬኗን


በመክበብ የኤዲን የቃል ዐዋጅ የፈውስ ሕግጋትን ፈጸሙ።
ከመሞቷ በፊት “ለምርጦቿ” በገባችው ቃል መሠረት
ከሄደችበት እንደ ኢየሱስ ትመለሳለች አልሞተችም በማለት
ሲያውጁ ተደመጡ። ይሁን እንጂ አስከሬኑ ባለመነሣቱ
ምክንያት ሳይሳካላቸው ቀረ። አይበገሬዎቹ ተማሪዎች ታዲያ
መጨረሻውን ይጠባበቅ ለነበረው ሕዝብ የሰጡት መልስ
ዐዋጃችን ውጤት የለውም የሚል ሳይሆን “ሚልቴዝ
በሄደችበት የምትወደውንና ያማረ፤ ለመኖር እጅግ የተመቸ
ቦታ ስላገኘች መመለስ ሥላልፈለገቸች አትመጣም የሚል
ነበር።”212

አንባቢ ሆይ ለሦስትና ለሁለት ምዕተ ዐመታት ያኽል


በዓለማችን ላይ ይህን የመሰለ በርካታ አስቂኝ ድራማዎች
የተሰሩ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ይህንን “የመካድና የማወጅ
የአማልክት መርሖ” ፈውስን፣ ተአምራትን እና ሐብትን
ከመንፈሳዊው ዓለም ለመቀበል መለማመድ ያስፈልጋል
በማለት የሚያራግቡ መሪዎች እንዳልጠፉ ማየት ምን ያኽል
ስሜትን የሚነካ ይሆን? በየቤተ-እምነቱ የሚደረገውን
የመካድና የማወጅ ባዓላትና ሥርዓቶች፣ የፈውስና ተዓምራት
ሥርዐቶች አካሄድ፣ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የሚታየው
212
John S. Haller Jr. The History of New Thought. (2012, Pp,31-132).

174
ጆንሰን እጅጉ

የመካድና የማወጅ ድግስ፣ በየወሩ በአማርኛ እየተተረጎሙ


የሚሰራጩ የክሪስ ኦያኪሎሚ ወርሃዊ መጽሐፎች ላይ
የሚወጡ የክህደትና የዐዋጅ ጸሎት ህጎች፣ በየቦታው
በአጽንዖት የማወጅና የመካድ መርሆችን ቀላቅለው የሚሰጡ
ስብከቶችና በጃችን ያሉ መጽሐፎች የዚህ ወረራ ማስረጃዎች
አይደሉምን? በርግጥ ወረራውን ለመረዳትና ለመቃወም
የእወጃው መርሖ የሚያስመዘግበው የተጭበረበረ የፈውስና
ተአምራት ውጤት እና የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ሥነ-ልቦና ሰረቃ
ልባችንን ያከብድብናል የሚል ፍርሀት አለኝ።

የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ልምምድ የአገልግሎት ጥሪ፣ የመጽሐፍ


ቅዱስ ጥናትም ሆነ የጸሎት ዝግጅት አይፈልግም። ተግባራዊ
መፈተሻው ደግሞ በህመም ሥቃይ ውስጥ ያሉ ህሙማንና
የኢኮኖሚ ችግርተኞች ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ ህሙማንም
ሆኑ ችግርተኞች የሚያገኙትን የሕሊና ዕፎይታ እንጂ
ዕፎይታው የሚመጣበትን መንገድ ስለማይፈትሹ ለዚህ
ዓይነተኛ ሜዳ ይሆናሉ። ለዚህም ቀድመን የተመለከትነው
የሜዝሜር፣ የፊሊሞር፣ የኪዊምቢይ እና የኤዲ የፈውስ
ተዓምራትና አያሌ ተከታዮችን የማፍራት “ስኬት” በቂ
ማስረጃ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ መጽሐፍ ለማየት
እንደምንሞክረው የአንድ ሥነ-መለኮት ሆነ ልምምድ ቀዳሚ
የስኬት መመዘኛ ከእግዚአብሔር ቃል ያለው ፍጹም ዝምድና

175
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንጂ የሚታዩ ተግባራዊ ልምምዶች ወይም የተከታዮች


መበራከት አይደለም።

የዲበ-አካል ሃይማኖት መላምት ሥርጭት


የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና በዚህ መጽሐፍ የተዳሰሰበት
ምክንያት ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር የጋራ መሠረቶችን
በመፍጠር በክርስትና ርትዕ ትምህርት ላይ ሰፊ ተጽዕኖ ያሳረፈ
ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ስለሆነ ነው። እንቅሴስቃሴው
በምሁራኑ ቢጀመርም ለአካለ መጠን የደረሰው በበርካታ
የዲበ-አካል ሃይማኖት እናት ድርጅቶች ጠንካራ ሥነ-
ጹሑፋዊና ተቋማዊ ቅብብሎሽ እንደሆነ ጥናቶች
213
ያሣያሉ። ከነኝህ እናት ድርጅቶች የፈር ቀዳጁ
የሲውዲንበርግ “አዲሱ ቤተክርስቲያንን” ጨምሮ የኮርቲስ
ሆፕኪን “ሆፕኪን ዲበ-አካል ኮሌጅ” ፣ የቤከር ኤዲ “ክርስቲያን
ሳይንስ ኮሌጅ” ፣ “የአዕምሮ ሳይንስ” መጽሐፍ ጸሓፊ የሆነው
የኸርንስት ሆምስ “ሳይንስ ቤተክርስቲያን” የዐዎንታዊ
ዐስተሳሰብ ኮሌጅ፣ የቻርልስ ፊሊሞር “ዩኒቲ ኮሚኒቲ ዓለም
አቀፍ ቤተክርስቲያን”፣ የማሊነዳ ኢሊኦት ክሬመር “መለኮታዊ
ሳይንስ ትምህርት ቤት” እና የኬኔት ሄገን “ቤቴል መጽሐፍ
ቅዱስ ኮሌጅ” ዋነኞች ናቸው።

213
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, pp, 45-51).

176
ጆንሰን እጅጉ

ለምሳሌ የዮኒቲ ኮሚኒቲ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያንን


ሥርጭት ብቻ በተመለከተ ሂለር ያስቀመጡትን መረጃ
እንቃኝ። በ 2001 እ.ኤ.አ ብቻ የቃል እምነት እንቅስቃሴን
የሚያራምዱ ከ 30 ያላነሱ የአመራር ማህበራት በናይጀሪያ፣
በኩባ፣ በጋና፣ በጃማይካ፣ በካናዳ፣ በእንግሊዝ በአርጀንቲና
በሜክሲኮ ነበሩ። በሚኒስትሪ ደረጃ ደግሞ በአሜሪካ፣ በካናዳና
ናይጀሪያ ብቻ 144 ደርሰው ነበር። ይህ የሚኒስትሪ ቍጥር
በ 2005 እ.ኤ.አ በ 42 አገራት ብቻ ወደ 1020 ከፍ ብሏል።
በዓለማችን 125 አገራት ላይ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እስከ
መክፈትም በስፋት መሰራጨት ችሏል።214

በአጠቃላይ ከ 18 ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አከባቢ ጀምሮ


የልዩ ዲበ-አካል ድርጅቶች ወረርሽኝ፣ የአንደበተ-ርቱዕ
መሪዎቻቸው ስብከትና በከፍተኛ ሁኔታ በነዚሁ ተቋማት
አማካኝነት የተሰራጩ ሥነ-ጹሁፎች በክርስትና ላይ ከፍተኛ
ተጽዕኖ አሳድረዋል። ምንም እንኳ እንቅስቃሴው ከሁለት
ምዕተ ዐመት በፊት በአገረ አሜሪካን ቢጀምርም እሰካለንበት
ክፍለ ዘመን ድረስ የተሻገረ ወደ ዓለም አቀፋዊነት ያደገ፤
እውነተኛውን የመንፈስ መነቃቃት ያዳፈነ ከፍተኛ
የመንፈሳዊ ልምምድ ብክለት ያስከተለ እንቅስቃሴ ለመሆን
ችሏል።

214
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P, 72).

177
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሥርጭት ጉዞውንም ቁልቁለት በማድረግ ያስፋፋው


የአስተምህሮ ጥንካሬ ወይም ተአማኒነት ስላለው ሳይሆን
የተደራሲያኑ ወቅታዊ በሆነ ችግር መጠመድና ከችግራቸውም
መውጫ ቀዳዳ መፈለግ ነው። እንቅስቃሴው ሳይንስም ይሁን
ሥነ-መለኮት የሰው ልጆችን ጥያቄ ሊመልስ ከሚችለው በላይ
የልዩ ዲበ-አካላዊ ዕውቀት ወይም የነፍስ መገለጥን መፍታት
ይችላል በማለት ማቅረቡ የሥርጭቱ ቁልፍ ነው። ለምሳሌም
ሲውዲንበርግም ይሁን ተከታዮቹ የነፍስና የአዕምሮን
ምንነትን እና የተፈጥሮ ሕግ ከዐዋጅ ቃል ጋር ያለውን
ዝምድና ለመተንተን መሞከራቸውን የዚህ አስረጂ ነው።
የፊሊሞርንና መሰል ተከታዩቹን ከነበረባቸው የግል ችግር
የመለቀቅ ፍላጎትም እንዲሁ ይህን ያስገነዝባል።

የፊሊሞር ተከታዬች ግለ ታሪክ እንደሚያሳየው እነርሱም


እንደ ፊሊሞር ትኩረታቸው ከነበረባቸው የጤንነትና
የኢኮኖሚ ችግር በአጭር ጊዜ በመላቅ ስኬታማ መሆን ነበር።
በዚሁ እንቅስቃሴውም በማህበረሰቡ መኻል የጋራ መሠረት
በማኖር ትምህርቱን ለማስፋፋት የተጠቀሙበትም
የሃይማኖት ክፍሎች በዐወንታ የሚቀበለውን ጸሎትን ነው።
ይሁን እንጂ ለዲበ-አካል ሃይማኖት ጸሎት ከክርስትና የተለየ
ትርጉም አለው። ለምሳሌ እንደ ፊሊሞር ትምህርት ጸሎት
‘የዝምታ’ እና ‘የንግግር’ በመባል በሁለት ክፍል ይከፈላል፤

178
ጆንሰን እጅጉ

ከዝምታ ጸሎትም የንግግር ጸሎት ይበልጣል። ይህንንም


የፊሊሞር ተከታይ የሆነችው ዶክተር ካንዲ ስታብራራ
እግዚአብሔር በፍጥረት ሥራ ላይ እንደጀመረ እንጀምራለን፣
ለዚህ ቅርፅ ለሌለው ዓለም እንናገራለን፣ እንደምንለው
ይሆናል፣ አሁኑኑ እንዲሆን እንዲገለጥ እንናገር፣ በቃላችን
ኀይል ይሆናል፣ ይገለጣል።215 ብላለች።

ታዲያ እነርሱ እንዲህ ጥቅስ መዘው ጸሎት ይበሉት እንጂ ልዩ


ጸሎት ወይም የቃል ዐዋጅ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ልዩ ጸሎት
እራስን ወደ መለኮትነት ከፍ በማድረግ ይክባል፤ የሰዎችን
ችግር ፈቺ በማስመሰል ያመጻድቃል። ይህ ሁሉ ሆኖም
መስፋፋቱ እግዚአብሔርን በማያውቁትም ይሁን በቅጡ
ባላደገ የክርስትና ሕይወት በሚመላለሱት መኻል የተሳካ ነው።

ቃል በቃልና በድፍረት የዘፍጥረትን ጥቅስ በመጥቀስ “እንደ


እግዚአብሔር እንናገራለን።” የማለታቸው ሚስጥሩ ተከታይ
ለማፍራት የቀየሱት ተራ ስልት አይደለም። ይልቁንም የቃል
ዐዋጅ ትምህርታቸው ክርስቶሳዊነት ካልታከለበት ትርጉም
ስለማይሰጥ ነው። ለዚህም የአማልክትነት ዐስተሳሰብ ጉልበት
የሆነው መሪዎቹ የሩቅ ምስራቅ ኃይማኖቶችንና
ፍልስፍናዎችን አጣምረው መነሳታቸው ነው። ይህም
በቀለላሉ ዓለማቀፍ ሥርጭቱን አፋጥኖላቸዋል።
215
Ibdi, (P,115).

179
የአማልክቱ ዐዋጅ

አማልክትነት ወይም ክርስቶሳዊነት በሁሉም ሰው ውስጥ አለ፤


ተመስጦም (meditation) ያነቃቃዋል የሚለው ጽንሰ-ዐሳብ
ፈጽሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተቀዳ አይደለም። እንደ ቡዲሂዝም
ካሉ የሩቅ ምስራቅ ፓንቴይስት ዐስተሳሰብ የተቀዳ ትምህርት
ነው። ምክንያቱም ቀደምት ቡዲሂስቶች የሰው ነፍስ
የመላለም አዕምሮ ወይም የመፍጠር ኀይል (አምላክ) አካል
ነው፤ ተመስጦ ከባራህማን ወይም ከአምላክ ጋር ለመቀላቀል
የምንጓዝበት መንገድ ነው ብለው ያምኑ ነበር።

መቼም የትምህርቱ መሠረት እንዲህ ከክርስትና የራቀ


እንደሆነ ጥናቶች ቢያሣዩም በክርስትና ውስጥ ለመስፋፋት
የሚያስችለው የጋራ መሠረት የሚሆነውን በርካታ ትምህርት
በቃለ-እግዚአብሔር አስደግፏል። ስለዚህም ልምምዱ
በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ጉባኤ ወይም
መድረክ እንዳይስፋፋና ዝር እንዳይል በር ይዞ መመከት
የሚችል የቤተ-እምነት መሪ ይኖራል የሚል ተስፋዬ ስስ ነው።
ከዚህ ይልቅ ከጥቅስ ጋር ተዋህዶ ሥር ከመስደዱ የተነሣ
ትክክል ነው ብሎ የሚሞግት የዋህ ይኖራል የሚል ነው ሰፊ
ጥርጣሬዬ። የእግዚአብሔር ቃል ከአጥፊው ፍልስፍና ጋር
ተደባልቆ እንዲሰበክ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ፈቅደናል
የሚል ነው ሙግቴ። “የሚጠራጠር አንዳች አይቀበልም!”
“የሚቃወመኝ መንፈስ ቅዱስን ይቃወማል!” በሚል ስብከትና

180
ጆንሰን እጅጉ

ጹሑፎች መበራከት ምክንያት እንድንፈራና እንድንደነግጥ


ስለተደረግን ስሕተትን ለይተን ለመቃወም ላልተናል ነው
ወቀሳዬ።

ስሕተትን በቃለ እግዚአብሔር ነቅሶ የሚቃወም ምናልበት


ቢገኝ እንኳ የመንፈስ ቅዱስን እንቅስቃሴ እንደሚቃወም
ፈላስፋ በመቁጠር ከመድረክ ማራቅ እየተለመደ መምጣቱ
የመማረካችን ምልክት ነው። ከትምህርቱ ድብቅ ባሕርይ
የተነሣ የመንፈስ ቅዱስን እንቅስቃሴ ከዲበ-አካል ሃይማኖት
እንቅስቃሴ ለመለየት መቸገራችን የመላላታችን ዓይነተኛ
ምክንያት እየሆነ ነው። የዲበ-አካል ሃይማኖት የሰዎችን
ወቅታዊ ፍላጎት ተደራሽ አድርጎ መሥራቱ ከካራዝማቲክ
የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ጋር በአንድ ዓይን እንዲታይ
አግዞታል። በዚህም የዋህ በሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች
ዐወንታዊ ድጋፍ አግኝቷል። እንደ ማክኢንታየር ዐይነት
ጸሓፊዎች ኪኒየን ያስፋፋውን የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና
“ከተሓድሶ እንቅስቃሴ ጋር አንድ ነው” በማለት የመንፈስ
ቅዱስ አፍቃሪ ወንጌላውያንን ለማግባባት መከራከራቸውና
ደጋፊ ማግኘታቸው ለዚህ በቂ ማሣያ ነው። እስከ አሁንም
ክርክሩ እንደቀጠለ ነው። ከካራዝማቲክ እንቅስቃሴ ጋር
መመሳሰሉ የፈጠረው ብዥታ ካለ ከልካይ የጀማ ጉባኤና

181
የአማልክቱ ዐዋጅ

የፈውስ አገልግሎት የትብብር መድረክ በመፍጠር


በወንጌላውያኑ መኻል ሳይቀር እንዲሰራጭ አስችሎታል።

በእርግጥ ክርስትና የሰው ልጆችን መንፈሳዊም ይሁን ቁሳዊ


ችግር ተደራሽ የሚያደርግበትና የሚፈታበት የራሱ ድንቅ
መንገድ አለው። ለምሳሌ የፈውስ አገልግሎት ከዚህ ውስጥ
አንዱ ነው። ይህ አገልግሎት ለህሙማን ዕፎይታ ነው።
የአባላት ቍጥር እንዲጨምር በማድረግም ዕልል የሚያስብል
ውጤት ያስከትላል። ይሁን እንጂ እውነተኛው የመንፈስ
ቅዱስ እንቅስቃሴ የፈውስ አገልግሎት በዲበ-አካል ሃይማኖት
የፈውስ ጥበብ የመዋጥ ትንቅንቅ ውስጥ እንዳለ
የሚያመላክቱ በርካታ ማሣያዎች አሉ። ግብታዊ ሥነ-
መለኮቱና ምትሃታዊ ልምምዶቹ ርቱዕ ሥነ-መለኮትንና
ልምምድ ከማኅበረ ምዕመናን መኻል ገፍትረው ወደውጭ
እስከማስወጣት እየደረሱ ነው። የክርስቶስን መልክና ምሳሌነት
የመከተል ትርጉምንም እስከ መለወጥ ይደርሳሉ።

እነኝህ ማጭበርበር የታከለባቸው ምትሃታዊ የፈውስ


ልምምዶች በሴይጣን የተሸነቆሩ ረቂቅ ወጥመዶች፤ በፈውስ
አገልግሎት ስም የሚዘሩ ጭለማዎች ናቸው። አንዳንዶች
በዚህ ስኹት አሰራር ከመማረራቸው የተነሣት የመንፈስ
ቅዱስን የጸጋ አሠራር እስከመካድ ይደርሳሉ። ይሁን እንጂ
የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የጨለማውን ሥርጭት ለመግታት

182
ጆንሰን እጅጉ

የመንፈስ ቅዱስን ልምምዶች መቃወም ወይም ወንጌል


የሰዎችን ችግር ተደራሽ እንደሚያደርግ መካድ የለባትም።
እውነተኛውን ብርሃን በማብራት ማሸነፍ ነው ያለባት።
በቀዳሚ የሚያስፈልገውም አሠራርን መለየትና መጽሐፍ
ቅዱሳዊ መርኾችንና ባሕሎችን በግልጽ ማስቀመጥ ነው።

ማጠቃለያ
ስሕተትም ሆነ ስኹት አሠራር በማንም እና የትም ቦታ
ቢነገርና ቢደረግ ያው ስሕተት ነው። መለኪያዎች ‘እዚያ
ማዶ’ያሉትንና ወገን አደሉም የምንላቸውን፤ የእኛ ወገኖች
ናቸው የምንላቸውን ‘እዚህ ማዶ’ ያሉትንም ተደጋጋሚ
ትምህርቶችና ልምምዶች ወይም ዶክትሪኖች እኩል
ካለመድሎ ይለካሉ። ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ
መለኪያ የትኛውንም የእምነት መርሖ ወይም ዶክትሪን እኩል
ሊለካ ይገባል። ስሕተት ከእኛ ኅብረት ውጪ በሆኑም ይሁን
በእኛ ኅብረት ውስጥ ባሉ ወገኖች ቢደረግና ውጤቱ ምንም
ያኽል ቢያምረን አሊያም ብንጠላው በእኩልና በተመሳሳይ
መስፈሪያ መለካትና መፈረጅ አለበት። እንዲህም ሲሆን
ብይናችን የሚሆነው በግለሰቡ ማን መሆን ወይም በውጤት
ትልቅነት ስለማይሆን ፍርዳችን አይዛባም። የግለሰቡ ዝና
ወይም ያለው ሰፊ ተቀባይነት ወደታች ተጭኖን
አያንገዳግደንም። በአንፃሩ በተአምራትና በምልክቶች ላይ
ብቻ በመመሥረት እውነትን መፈረጅ አደገኛ ነው።

183
የአማልክቱ ዐዋጅ

መጽሐፍ ቅዱስ አጋንት ታላላቅ ተአምራትና ምልክቶችን


እንደሚያደርጉ ይጠቁማል።(ራዕ.13፡14፣ 2 ቆሮ.2፡9-10)።
በግብጽ ጠንቋዮችና በሙሴ መኻል የውጤት ውድድር ነበር።
በውድድሩም ተመሣሣይ ውጤት ተመዝግቧል። ይህም ሙሴ
ተአምራትን እንደሚያደርግ የግብጽ ጠንቋዮችም ማድረግ
እንደሚችሉ እዛው ሙሴ ተአምራት ያደረገበት ቦታ ላይ
ማስረገጥ የቻለ ነው። የመጨረሻው ውጤትም ቢሆን የኀይል
ልዩነትን ነው እንጂ ያሣየው የግብጽ ጠንቋዮች ሙከራ ኀይል
አልባ ወይም ምንም ውጤት እንደሌለው አይደለም።
በቀጣይነትም ጠንቋዮቹ ያላቸውን ውጤት ለማሻሻል
ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገዋል።

ሙሴም ቢሆን የእርሱ አምላክ እንደሚበልጥ አሣያቸው እንጂ


ውጤት አልባ ናችሁ የሚል ሙግት አልገጠመም። በአጠቃላይ
በሙሴና በጠንቋዮቹ መኻል የተአምራት መመሣሰል ቢኖርም
የምንጭ ልዩነት ነበር። የጠንቋዮቹና የሙሴ የእምነት
መርኸም ለየቅል ነበር። የጠንቋዮቹን መሠረት የተመለከተ
የኀይላቸውን ምንጭ መረዳት አይቸግረውም። እንዲሁም
ሁሉ የሚከተሉትን የሃይማኖት መርኸም የተረዳ ምንም ያኸል
ተአማኒ ውጤት ቢያስመዘግቡም የኀይላቸውን ምንጭ
ለመረዳት አያዳግተውም። የግብጽን ጠንቋዮችና የዲበ-አካል
ሃይማኖትን የኀይል አሠራርና መርኸ መለየት በአንድም በሌላ
መንገድ ከአሠራራቸውና ከመርኻቸው ጋር ታሪካዊ ትስሥር
ያለውን የትኛውንም አሠራር ባዕድነት ለመረዳት ያስችላል።
የዲበ-አካል ሃይማኖት ሴጣናዊ ከሆነ ከቃል ዐዋጅ መርኹና

184
ጆንሰን እጅጉ

ልምምዱ ጋር የተዛመደ ወይም ታሪካዊ ንኪኪ ያለው ሁሉ


ሴጣናዊነት የተጠናወተው ነው።

በአጠቃላይ የእምነት እንቅስቃሴ የቱንም ያኽል የመንፈስ


ቅዱስን መነቃቃት እንቅስቃሴ በማስመሰል ቢንቀሳቀስም
ከዲበ-አካል ሃይማኖት ጋር ያለውን ታሪካዊ ትስሥር፣
የሚከተለውን ዶክትሪን ወይም መርኸና አሠራር በመመርመር
ከእውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ መለየት ይቻላል።
“ሁሉም ያው ነው” በማለት ሁሉን በአንድነት በመደዳው
የሚፈርጁ የዋኻን ለዚህ እውነት ትኩረት ሊሰጡና ከጅምላ
ፍረጃቸው በመውጣት ቀርበው ሊመረምሩና ክፉውን
ከመልካም፣ እርኩሱን ከቅዱሱ ሊለዩ ይገባል። የሐዋርያትን
የሃይማኖት መርሖ የማይከተልና የዲበ-አካል ሃይማኖትን
መርሖ የሚከተል የትኛውም መሪ ከሐዋርያት ጋር ታሪካዊ
ትስስር እንደሌለውና ሴጣናዊነት የተጠናወተው እንደሆነ
መታወቅ አለበት።

ማጠቃለያ ግራፍ፦ የዐዋጅ ቃል ልምምድ ጽንሰ-ሐሳብ


መሠረትና ታሪካዊ ዕድገቱ።

185
የአማልክቱ ዐዋጅ

የዐዋ ጅ ቃል ወ ይም ልዩ ጸሎ ት
(የእም ነት ቃል)

መ ለኮት ን ማ ነቃቃት

የአባት ሕ ግ

ልዕለ አዕም ሮ

የተ ፈ ጥ ሮ ሕ ግ

ምስል አራት፦ በተፈጥሮ ሕግ ጽንሰ-ዐሳብ የተጀመረው የዲበ-


አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ወደ ቃል ዐዋጅ (እምነት ቃል) ልምምድ
በማደግ የእምነት እንቅስቃሴ ዋነኛ መሠረትና መርኸ ሊሆን
ችሏል። (በደራሲው)።

186
ጆንሰን እጅጉ

የምዕራፍ ሁለት የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥያቄዎች

1. ኪኒዮን በዲበ-አካል ባዕድ ሃይማኖት ተጽዕኖ ሥር


ወድቋል ማለት ይቻላል? አስረዳ።
2. ፕሮፌሰር ጆን ታይዶል የጸሎትን ምላሽን
በተመለከተ በየትኛውም እምነት የሚደረግ ጸሎት
ከተፈጥሮ ሕግ ጋር ግንኙነት ስላለው የሚሆን ነው
ሲል መረጃዎችን አቅርቧል። ይህንን ዐስተሳሰብ
የሚሞግት ክርስቲያናዊ ምላሽ መስጠት ይቻላል?
አስረዳ።
3. ፊኒየስ ኪዊምቢ “አዕምሮ ምጡቅ መለኮት ነው” ያለ
ሲሆን የኢየሱስን የፈውስ ውጤቶች በማንሳትም
ከዚህ ጋር አመሳክሯል። ይህ ድኩም አካሄድ ወይም
ፍልስፍና ከምን የመነጨ ነው ትላለህ?
4. በክርስትናችን ላይ በዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና
ተጽዕኖ የተሸነቆሩና በእምነት እንቅስቃሴ የተጋረዱ
አጋንታዊ ቀዳዳዎችን ለማየትና ለመድፈን መጽሐፍ
ቅዱሳዊ የሆነ የጸሎትና የፈውስ መርሖ መከተል
አለብን ብለህ ታምናለህ?
5. በግል ሕይወትህና በቤተክርስቲያንህ የእምነት
እንቅስቃሴ ባነገበው የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና

187
የአማልክቱ ዐዋጅ

ተጽዕኖ ምክንያት የተሸነቆረ ምን ቀዳዳ ወይም እክል


ይታይሃል? ቀደዳውንስ ለመድፈን ምን ማድረግ
አለብን?
6. የዲበ-አካል ሃይማኖትም ሆነ የእምነት እንቅስቃሴ
የሥነ-ሰብዕንም ሆነ የሥነ-መለኮትን ርቱዕ
ትምህርት የሚያዛባበት ተመሳሳይ ዐላማ ወይም
ምክንያት ምንድነው?

ምዕራፍ 3

188
ጆንሰን እጅጉ

የዲበ-አካል ሃይማኖት እርሾ


አማልክቱ ሰባኪያን እንደሚሉት መለኮትን በፋብሪካ ውስጥ


እንደሚገኝ ግዙፍ ማሽን የመክፈቻ ቁልፉን በመጫን
እንዳናቀሳቅሰው እርሱ ሕያውና ፈቃድ ያለው አምላክ እንጂ
ግዑዝ አይደለም። ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሁታን ግን
ከእርሱ ጋር የሚተባበሩበትና የሚሠሩበትን የመንፈስ ቅዱስ
ኀይል ይሰጣቸዋል። በዐጽናፈ-ዓለም ውስጥ ያሉ ግዙፍና
ጥቃቅን ነገሮችን፤ የተፈጥሮ ሕግን ወይም ማንኛውንም
ምክንያትና ሥነ-አመክንዮ ያንቀሳቅሳል ይቆጣጠራል።

የሰው ልጆች ግን ይህንን ምጡቃዊነት የሚጋሩበት ጥበብም


ይሁን የመለኮት ቅንጣት ፈፅሞ የላቸውም። ነገር ግን በፊቱ
ራሳቸውን ቢያዋርዱ፣ ልመናቸውንና ጥቂቷን እምነታቸውን
በርህራሄ ይመለከታል። ትንሿ ልመናቸው አንጀቱን
ታላውሰዋለች። ዋጋ ለማይገባው ትንሽ ድካማቸው ትልቅ
ዋጋ ይሰጣል። የራሱ ፍቅር ያንቀሳቅሰዋል! ፍርድን ሊያደርግ
ከመከራቸውም ሊያድናቸው ይነሣል። ሳያዩት ቀድሞ
ይመለከታቸዋል! ሳይነኩት እጁን ዘርግቶ ይዳስሳቸዋል! እነርሱ
ባይረዱት እንኳ እርሱ ግን ልባቸውን ተጠግቶ ያደምጣል!

189
የአማልክቱ ዐዋጅ

እጀግ ከፍ ብለው የጭንቅላታቸው ጫፍ አጠገቡ ሳይደርስ


እርሱ ዝቅ ብሎ አጠገባቸው ነው!

ይህንን ያስተዋለ በልቡ መለኮትን ያፈቀረ አንድ ሰው ታዲያ


“ለምን ሰው ምጡቃዊነትን ይፈልጋል? ለምንስ ደርሶ
በመንገድ ወድቆ ሊቀር እራሱ በፈጠረው ማሣኒ የእምነት
አሳንሰር ለመጓዝ ይሳፈራል? ቀድሞውንስ መለኮት ምን
አሳጣውና? ደግሞ የያዘው ዐጉል መንገድ ቢያደርሰውና
ቢሳካለት መድረሱ ምን ይፈይድለታል?” ብሎ መጠየቁ
አይቀርም።

የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ፍልስፍና የዲበ-አካል ሃይማኖት ዋነኛ እርሾ


ነው። ይህንንም ከብብቱ ወስደን ልንደፋበት ብንችል ኖሮ
የዲበ-አካል ሃይማኖት በጠፋ ወይም ባልኖረ ነበር። ጠፋ ማለት
ደግሞ በዚሁ ፍልስፍና የተቃኙ የእምነት እንቅስቃሴ የቅኝት
አውታሮች ተበጣጠሱ ማለት ነው። አንድ ታዋቂ የእምነት
ቃል ሰባኪ ከወዳጄ መጋቢ ቴውድሮስ ተጫን216 ጋር የእምነት
ቃል ስብከትን በተመለከተ በነበራቸው የግል ውይይት ሲናገር፦
“የእምነት ቃል ትምህርትን ካላስተማርን ይህንን ሕዝብ ምን
እናስተምረዋለን?” ነበር ያለው። እርግጥም የትምህርታቸው
ማዕከል የሆነውን የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ትምህርት ከጃቸው
ማራገፍ ቢቻል ኖሮ በቦታው ወንጌል የሚነግስበት ዕድል
ይኖረው ነበር። የዲበ-አካል ሃይማኖት እርሾ ክፋቱ የሰውን
216
ቴውድሮስ ተጫን የባለደራ ትውልድ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መጋቢና ነው።

190
ጆንሰን እጅጉ

ቁስል እያከከ የእግዚአብሔርን ምጡቅ ሉዐላዊ ፈቃድ ወይም


ይሁንታ አድበስብሶ ከፍጡራን እግር ሥር በመጣል አካላዊና
ቁሳዊ ፈውስህ በጅህ ነው ማለቱ ነው። ትምህርቱ
በሚከተለው የቃል ዐዋጅ መርሖ ፈውስንና ብልጽግናን
ለማሳካት ሲል የሥነ-ሰብዕንና የሥነ-መለኮትን ትምህርት
እስከ ማዛባት የሚለጠጥ ነው። ምክንያቱም እንደ ትምህርቱ
ከሆነ ዐዋጅ የሚሠራው የሰው ልጅ አማልክታዊ ተፈጥሮ
ስላለው ነው።

እርሾው ምዕተ-ዐመታት የተሻገረ ከፕላኔታችን ጋር


የተጣበቀና የሻገተ አጋንታዊ ጥበብ ነው። የቤተ-እምነት
ጽሑፎችንና ሳይንሳዊ ጽሑፎችን ለዘመናት ተጣብቷል።
ሥነ-ልቦና አነቃቂ አቀራረቡም የስኬት ደረጃዎችን መቆናጠጥ
የሚወደውን የዓለማችን ሕዝብ ስሜት ሰቅስቆ የሚይዝ
ቀልብ አናቂ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። ለምሳሌ ገና
በልጅነት ዕድሜው ከመሬት ሲነሳ የዓለማችንን ሕዝብ
ከፍተኛ የብልጽግናና የፈውስ ፍላጎት በሁለት እጆቹ
ተንጠላጥሎ ነበር። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ተከትሎ
የተቀሰቀሰው የኢንፊሎዌንዛና የሳንባ ነቀርሳ ወርረሽኝም
መልካም አጋጣሚ ፈጥሮለት ነበር። ቀውሱ ያስከተለው
የፈውስ ፍላጎትና የድኽነት ማምለጫ ቀዳዳ የሚፈልግ ሕዝብ
ጭንቀት ቁርጭምጭሚቱን አጽንቶ እንደልቡ እንዲሮጥ
እንዳስቻለው ታሪክ ምስክር ነው።

191
የአማልክቱ ዐዋጅ

በዚህም ምክንያት አስቀድመን በምዕራፍ ሁለት ማጠቃላያ


ላይ እንደ ተመለከትን አማልክቱ የዓለምን ሕዝብ ስስ ስሜት
በቀላሉ ማግኘት ችለዋል። የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ
የሚችለው “የምጡቅ ወይም የመላለም አዕምሮ ኀይል ነው።”
በማለት ቀልቡን ያሳቅሉታል። ሲሻቸው ደግሞ “የዐሳብ ኀይል”
ነው በማለት ሲያዋክቡት ሲሻቸው ደግሞ “የኅሩይ ቃል ኀይል”
ወይንም “የተፈጥሮ ሕግ ኀይል ነው።” ሲሉት ሲሻቸው ደግሞ
“በሁሉም ሰው ውስጥ ያለ አምላክነት ወይም ክርስቶሳዊነት
ነው።” በማለት በብዥታ ውስጥ ይመሩታል። በዚህም ውል
በሌለው ሁለ ገብ ፍልስፍናቸው የ 18 ኛውን እና የ 19 ኛውን ክፍለ
ዘመን ሳይንቲስቶች ትከሻ በመደገፍ እውነትን ለመመርመር
የማይተጋውን ሕዝብ እጅ ጠፍንገዋው በመያዝ አእምሮውን
ገዝተውታል። እጁን መያዛቸው ግን ለጥቅማቸው እንጂ
አዝነውለትና ሊያነሱት አልነበረም። ይልቁንም ወዲያና ወዲህ
ሲያወዛውዙት፣ ሲያነሱ ሲጥሉት ክፍለ ዘመናት ተቆጥረዋል።
ኦስትራንደር ታሪክን አጣቅሰው ሲዘግቡ፦

በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አከባቢ የነበሩ


ታዛቢዎች አብዛኛዎቹ የ 19 ኛው ክፍለ ዘመን የቁስ
አካላት (naturalist) ተመራማሪ ሳይንቲስቶችና
ምሁራን ቡድኖች ወደ ኋላ ማለትም ወደ ኃይማኖት
ተመለሱ። በመላለም ውስጥ ያሉ ክስተቶች
መንፈሳዊ ምክንያት ይኖራቸዋል የሚል ዐሳብ

192
ጆንሰን እጅጉ

የመቀበል ፍላጎት አሳይተዋል። ዥዋ ዥዌው ወደ ኃላ


ተለጠጠ ማለትም በጸሎት ኀይል ወደ ማመን
ተመለሰ። 217

በማለት አስፍረዋል። ሳይንቲስቱ ወደ መንፈሳዊ ግንዛቤና


እምነት የመመለስ ፍላጎት ያሳዩ እንጂ ቀደም ብለን እንዳየነው
በልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ተነክረዋል።

ስለዚህም እምነትን ከቤተክርስቲያን ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ


ለመማር የሚፈቅድ ቀና ልብ አልነበራቸውም። ከዚህ ይለቅ
ግን ሲውዲንበርግ የጠቆመውን የመንፈስ ምሥጢር
በሳይንሳዊ መንገድ ለመረዳትና ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፍላጎት
ነበራቸው። የፕሮፌሰር ታይንዶልን ማለትም “ጸሎትን
የሚመልሰው የተፈጥሮ ሕግ ነው” የሚለውን የልዩ ዲበ-አካል
ፍልስፍና እንደ ምሶሶ ተክለውት ነበር። ስለዚህም
ቤተክርስቲያንን እንደ አምልኮ ማዕከል ሳይሆን እንደ
ቤተሙከራ ተጠቅመውባታል ማለት ይቻላል።

በአጠቃላይ ሳይንቲስቱ ጥርጣሬ የታከለበት እምነት ወይም


ለዘብተኝነት ነበራቸው። ይህም በወቅቱ ለሳይንቲስቱ
እንደሽንፈት ለቤተክርስቲያን ደግሞ እንደ ድል ተቆጥሯል።
ይሁን እንጂ ከዲበ-አካሉ ሃይማኖት ፍልስፍና ጋር የተቀላቀለና

217
Rick Ostrander. The Life of Prayer in a World of Science: (200. P.117).

193
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያልጠራ ስለ ነበር ቤተክርስቲያንን ሊያሳድፍ ችሏል። ይህም


ዲበ-አካላዊ ጅረት ጠንካራ “መዓበል” በመፍጠር
የቤተክርስቲያንን ደጃፉ ለመግፋትና የጸሎት አቅጣጫን
ለማስቀየር ጊዜ አልፈጀበትም። ኦስትራንደር ሲጠቅሱ
“የዓይን ምስክሮች ‘ትልቅ የዐሳባዊነት ፍልስፍና መዓበል'
የዓለምን ህዝቦች ሁሉ እስኪያጥለቀልቅ ድረስ ጎረፈ፣
አሜሪካዊያን ስለ መንፈስና ቁስ አካል ያላቸውን ዐስተሳሰብ
ለወጠ።”218 በማለት ሬይ ስታናርድ ቤከር (1909)
ማስፈራቸውን ያነሣሉ። ይህም ከፍተኛ ቍጥር ያለው ሳይንስ
ወዳድ ሕዝብ ወደ ቤተ-እምነት እንዲያፈልስ ቢያደርግም
ዐቅም የሌለውና በእውነት ላይ ባግባቡ ያልተገነባ ልዩ ዲበ-
አካላዊ ክርስትናን በማስፋፋትና ጤናማ መንፈሳዊ
ልምምዶችን በማዳፈን እጅግ የከፋ የጐንዮሽ ጉዳት
አስከትሏል።

ለምሳሌ፦ የዲበ-አካል ሃይማኖት የጸሎት መሠረታዊ ግንዛቤ፤


“ጸሎት የሚመለሰው በአዕምሮ ኀይል ነው” የሚል እንደሆነ
ሁሉ በሚገርም ሁናቴ አብዛኛዎቹ የእምነት እንቅስቃሴ
መሪዎች የፊት መሸፈኛ ሲገለጥ በዚህ የሚስማሙ ሆነው
እናገኛቸዋለን። ለምሳሌ ኬኔት ሄገን በብዕሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ጠቅሶ ይህንኑ የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ሲያፀድቅ “ብዙ

218
Ibid., (P. 66).

194
ጆንሰን እጅጉ

ነገሮች የሚሆኑት እንደሚሆኑ ስለምናስብ ነው።”219 ብሏል።


በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ኬነት ሄገንና ኪኒየን ያሉ የእምነት
እንቅስቃሴ “አማልክት” ከዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክት
ይልቅ አስገራሚና ግራ የሚያጋቡ ናቸው። ምክንያቱም
የጸሎት መልስን ለማግኘት በልዩ ዲበ-አካል ትምህርት
መሠረት የቃል ኀይልን መጠቀም አስፈላጊነት ሲነግሩን
ቆይተው መልሰው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገርለትን
የልዕለ መለኮት ኀይል እናምናለን ይላሉና ነው።

ይህንንም የዲበ-አካል ሃይማኖት ትምህርት ወደ አማርኛ


በተተረጎሙ መጽሐፍትና በተቀረፁ ምስሎች አማካኝነት
በአገራችን ላይ በስፋት እንዲሰራጭ አድርገዋል። ይህም
ከፍተኛ ሥርጭትና የዐስተሳሰብ መመሳሰል የዲበ-አካል
ሃይማኖት የቃል ዐዋጅ መርሖ በየዘመናቱ የሚያገኘውን
ትውልድ ሁሉ የነከሰ፤ በፋብሪካ ውስጥ የሚቀርብለትን ቅርፅ
ያጣ ቁስ ተመሳሳይ ቅርፅ እየሰጠ እንደሚተፋ ቅርፅ ማውጫ
(mold) ፤ ለሰው ልጆች አዕምሮ አንድ ዐይነትና ተመሳሳይ
የዐስተሳሰብ መልክ እየሰጠ እንደሆነ ያሣያል።

የዲበ-አካል ሃይማኖት እርሾ በኢትዮጵያ

219
Hagin, K.E You can have what you say. Rhema Bible Church. (1997, P.13).

195
የአማልክቱ ዐዋጅ

ዲበ-አካል ሃይማኖት ሰባኪያን የትኛውም የተነገረ ቃል


በመላለም ውስጥ እንደሚሠራ ያምናሉ። የእምነት
እንቅስቃሴ ሰባኪያን ደግሞ ከፊሉ ተመሳሳይ እምነት
ቢኖራቸውም አብዛኛዎቹ የአዲሱ ፍጥረት ወይም ዳግም
የተወለደው አማኝ ዐዋጅ የበላይ በመሆን እንደሚሠራና
እንደሚገዛ እንደሚያምኑ የሚፅፏቸው ጹሑፎችና
የሚያሰራጯቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያመለክታሉ።
በሁለቱም እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለውን ክርስትናን
የሚበርዝ የቃል ዐዋጅ ጽንሰ-ዐሳብ እርሾ ያጤንን እንደሆነ
መሠረታዊ አንድነት እንዳለው ለመለየት የሚቸግር
አይደለም። ይሁን እንጂ ሥነ-መለኮቱም ሆነ ልምምዱ
የክርስትና አካል እንደሆነ እስኪቆጠር ድረስ መላውን የአሜሪካ
ታላላቅ ቤተክርስቲያናት በማጥለቅለቅ የተስፋፋ ሲሆን ባህር
ተሸጋሪ ወይም ዓለም አቀፋዊ ወረርሽኝ መሆንም ችሏል።
በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞችም እንዲሁ በቅጡ
የታወቀና ተጽዕኖውም ይሁን በዐድነቱ ተስተውሎ ከምንፍቅና
የተቆጠረ አይደለም።

በ 2010 ዓ.ም የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሑፍ ሳዘጋጅ ከተወሰኑ


የአቢያተክርስቲያናት አጥቢያ አገልጋዮችና ምዕመናን ጋር
ያደረኩት ቃለ-መጠየቅና የሰበሰብኩት የጽሑፍ ዊሂብ ይህንኑ
ለማረጋገጥ እረድቶኛል።220 በዚህም ጥናት ወቅት ከአማኑኤል
220
Johnson Ejigu. The Infilunce of Positive Confession (2018).

196
ጆንሰን እጅጉ

ኅብረት ቤተክርስቲያን ሁለት አጥቢያ መጋቢዎችና አገልጋዮች


ጋር የጋራ (ፓናል) እና የተናጥል ውይይት አድርጌያለሁ።
የግንባርና የስልክ የተናጥል ውይይት ከጥቂት የዐዲስ አበባ
ከተማ ቤተክርስቲያናት አገልጋዮች ጋር አድርጌያለሁ። ከሙሉ
ወንጌል ሦስት አጥቢያዎች፣ ከመሠረተ-ክርስቶስ ሁለት
አጥቢያዎች፣ ከቃለ ሕይወት ሁለት አጥቢያዎች፣ ከመካነ-
ኢየሱስ ሁለት አጥቢያዎች፣ ከጉባኤ እግዚአብሔር ሁለት
አጥቢያዎች፣ ከገነት አንድ አጥቢያ፣ ከመማጸኛ ከተማ አንድ
አጥቢያ፣ ከተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አንድ አጥቢያና
ከኬብሮን አንድ አጥቢያ፤ በጥቅሉ ከአሥራ ስምንት የሙሉ
ጊዜ አገልጋዮችና ከሌሎችም ጋር ወይይት አድርጌያለሁ።
በተጨማሪም መቶ ሃምሣ የወረቀት መጠይቆችን በዐዲስ
አበባ ለሚገኙ የወንጌላውያን አጥቢያ አባላትና ለዐዲስ አበባ
ሥነ-መለኮት ኮሌጅ ተማሪዎች በትኜ ናሙና ሰብስቤያለሁ።
የጥናት ጥያቄዬ ትኩረት “የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” ልምምድ
ምንነትና ምንጭ ምን ያኽል በቤተክርስቲያን ይታወቃል? ምን
ያክልስ ይዘወተራል? ምንስ ተጽዕኖ ፈጥሯል? ምንስ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ድጋፍ አለው? የሚለውን ለመመለስ የተደረገ ነበር።

የአገልጋዮቹን ምላሽ ስሰማ የዲበ-አካል ሃይማኖት እንቀስቃሴ


በቤተክርስቲያን መሪዎች ፊት የተጋረጠ ፈተና እንደሆነ
መገንዘብ ችያለሁ። 80% የሚሆኑት የወንጌላውያን
አገልጋዮች የቃል ዐዋጅ የምትናገረው ነገር ይወርስሃል የሚል

197
የአማልክቱ ዐዋጅ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ዐሳብ የያዘ ትምህርት


እንደሆነ ይስማማሉ። ይሁን እንጂ አብላጫዎቹ ልምምዱ
በወንጌላውያኑ መኻል እንደማይተገበር ነው የሚያምኑት።
ለምሳሌ ከ 55%-60% የሚሆኑት ከሰጡትኝ ቃል
እንደተረዳሁት ልምምዱ የሚዘወተረው “ኢንዲፔንደንት”
ቤተ-እምነት የሚባሉት ቤተ-እምነቶች አከባቢ ብቻ ነው
የሚል ምልከታ አላቸው። እንዲሁም 20%-25% የሚያክሉት
የወንጌላውያን አገልጋዮች ትምህርቱም ሆነ ልምምዱ
በወንጌል አማኞች ቤተ-እምነት ውስጥ መደበኛ ባልሆነ ቅርፅና
ይዘት እንደሚተገበር ያምናሉ። ለዚህም ማስረጃ በየዓመቱ
የሚደረገውን የኅሩይ ቃል ዐዋጅ በዓልና ልምምድ ያነሣሉ።
ያምሆኖ ግን የትምህርቱም ሆነ የልምምዱ አሳሳቢነት ወይም
ችግር ትኩረታቸውን የያዘው አይመስልም። በሌላ በኩል
ደግሞ ልምምዱ በኢንዲፐንደንት ቤተክርስቲያን ይዘወተራል
የሚለው የወንጌላውያኑ ጥቆማ እውነትነት አለው። ለምሳሌ
የከኬብሮን ቤተ እምነት መሪ ከሆነው ፓስተር ሮን ጋር
ያደረኩት የስልክ ልውውጥ ልምምዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
እንደሆነ እንደሚያምኑና በግልጽ እንደሚለማመዱ
አረጋግጦልኛል።

አብዛኛዎቹ አገልጋዮች የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ልምምድ እንዴት


ወደ ወንጌል አማኞች ጉባኤ ሊደርስ እንደቻለ ሲናገሩ እንደ
ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1980 ዎቹ አከባቢ የኬኔት ሄገንና

198
ጆንሰን እጅጉ

የኪኒየን መጽሐፍት ወደ አማርኛ ተተርጉመው መበተናቸውን


ያነሣሉ። እንደ ነገሩኝ ከሆነ አብዛኛዎቹ የወቅቱ አገልጋዮች
እነኝህን መጽሐፍት አንብበዋል። በተጨማሪም ያነጋገርኳቸው
አገልጋዮች በጊዜው የነበረውን ሁኔታ በማስታወስ የግል
አስተያየታቸውን ያነሳሉ። በወቅቱ በትምህርት ደረጃ
ተዘጋጅተው በአማርኛ የሚሰራጩ ሌሎች መጽሐፎች ብዙም
አለመኖራቸው ለትምህርቱ እንዳጋለጣቸው ይጠቅሳሉ። እንደ
እነርሱም በወቅቱ እነኝህን መጽሐፎች ማንበብ አማራጭ
አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍቱ የትውልዱን
የትምህርት ፍላጎት በመለኮስ እንደጠቀሙ መልካም ጎንዮሽ
ነበራቸው በማለትም ይናገራሉ።

ከመጽሐፍቱ በተጨማሪ በእነኝሁ ዐመታት አከባቢ የሬማ


ቤተክርስቲያን መስራች ሐዋርያው ዘውዴ ልምምዱንና ሥነ-
መለኮቱን ማስፋፋታቸውን አንዳንድ አገልጋዮች ይናገራሉ።
ሬቨረንድ ብሉጽ ፍትዊ የሬማ ቤተክርስቲያን የእምነት ቃል
እንቅስቃሴን በኢትዮጵያ ውስጥ በማስፋፋት የነበራትን ድርሻ
የዳሰሰ ጥናት አድርገው ነበር። በዚህ ጥናታቸው ሐዋርያው
ዘውዴ እንግሊዝ ዐገር ሄዶ በኬኔት ሄገን ይሰጥ የነበረውን
የእምነት ቃል ትምህርት ተምሮ ከመጣ በኋላ ትምህረቱን
ማስፋፋቱን ጠቁመዋል። እንደ ቡሉጽ ጥናት ከሆነ በተቋም
ደረጃ ሬማ ቤተክርስቲያን በሐዋርያው ዘውዴ ገብረስላሴ

199
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከተመስተች በኋላ የኬኔት ሄገን ትምህርቶችን ታስተምር


ነበር።

ይህንንም ሲጠቅሱ በ 1991 እ.ኤ.አ. ዘውዴ በለንደን


ከሚገኘው የእምነት ቃል እንቅስቃሴ ጎጥ በተደረገለት ግብዣ
ወደ ለንደን በመሄድ በሄገን ይሰጥ የነበረውን ሥልጠና
ተካፍሏል። በዚህም ምክንያት ይላሉ ብሉጽ፦ ዘውዴ በሄገን
የቃል እምነት ተጽዕኖ ሥር ሊወድቅ ችሏል። ከዚህ በኋላም
በ 1994 እ.ኤ.አ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ሐዋርያ ተደርጎ
ተሾመ። በ 1995 እ.ኤ.አ. ሬማ ፌዝ ሚኒስትሪን መሠረተ።
በእዚሁ ዐመትም ሬማ ቤተክርስቲያን ተመሠረተች።
በአጠቃላይ በዚሁ ጥናታቸው ሬቨረንድ ቡሉጽ የቃል እምነት
ሥነ-መለኮት በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስፋፋቱ የሐዋርያውን
አስተምህሮ በግንባር ቀደምትነት አስቀምጠዋል።221

በተጨማሪም ካነጋገርኳቸው የወንጌል አማኞች የሙሉ ጊዜ


አገልጋዮች መኻልም የተወሰኑት ከሐዋርያው ጋር ከነበራቸው
ወዳጅነትና ትውውቅ የተነሣ የሬማ ቤተክርስቲያን ጉባኤን
ይካፈሉ እንደ ነበር ነግረውኛል። በወቅቱ ይካፈሉ በነበረበት
ጉባኤ ላይ የነበረውን የቃል ልምምድ እንዲያካፍሉኝ
ለጠየኳቸው ጥያቄ ሲመልሱልኝም ለራሳቸው የሚፈልጉትን

221
Bulutse Futuwi. An Introduction to Theology and Growth of Independent
Churches in Ethiopia: (Addis Ababa, June, 2002, pp, 70-71).

200
ጆንሰን እጅጉ

ነገር ያውጁ ነበር። በዐይነ ሕሊናቸውም የሚፈልጉትን መኪና


ሞዴልና ቀለም በመመልከት የዐሳብ መሪ ይዘው ‘ቩ…ቩ…
ቩ…ጲ…ጲጵ’ የሚል የተሽከርካሪ ድምጽ ያሰሙ እንደ ነበር
ነግረውኛል።222

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በቤተክርስቲያን አመራርና


አስተዳደር ላይ የሚገኙ ጥቂት አገልጋዮች እንደ ነገሩኝ
ጉባኤያቸው ላይ እንዲያገለግሉ የሚጋብዙዋቸውን አገልጋዮች
በጥንቃቄ ይመርጣሉ። ይሁን እንጂ የሚያስተላልፉትን
መልዕክትና ትምህርት አስቀድመው ስለማያውቁት የቃል
ኀይል ትምህርት ከመድረክ ወደ ሕዝብ አምልጦ ሊገባ
ይችላል። ይሁን እንጂ እንደዚህ ዐይነት ነገር ሲፈጠር ደግሞ
ወዲያው የማስተካከያ እርምጃ አይወሰድም። በዚሁ
በወንጌላዊ አማኞች መድረክ ላይ አምልጦ በሚወጣ የቃል
ኀይል ሥነ-መለኮት ላይ ታዲያ የሚወሰዱ መፍትሄዎች
ምንድናቸው የሚል ጥያቄ ለአገልጋዮቹ አቅርቤ ነበር።

ከአገልጋዮቹ ያገኘሁት መልስ ጉባኤ እንዳይረበሽ ከመድረክ


ላይ አገልጋይ አናስወርድም ነገር ግን ሕዝቡ እራሱን
እንዲጠብቅ እናስተምራለን የሚል ነው። ይሁን እንጂ ይህ
አሠራር ሙሉ ለሙሉ ወይም የሚበልጠውን ኀላፊነት
222
ማስታወሻ፦ ከላይ የተጠቀሰው የእምነት ቃል ልምምድ አሁን ላይ ያለችውን
የሬማ ቤተክርስቲያንም ይሁን አሁን ላይ ያለውን የሐዋርያው ዘውዴን አቋም
እንደማይገልጽ ይታወቅ።

201
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለምዕመኑ የሚሰጥ አካሄድ ስለሆነ ቅሬታ ፈጥሮብኛል።


ምክንያቱም “በጉን ለራስህ እረኛ ሁን” እንደማለት ነው።
በሌላ በኩል በአገራችን በአሁኑ ወቅት በተቋም ደረጃ
እንቅስቃሴውን የሚያራምዱ በርካታ ቤተ-እምነቶች
ተጽኗቸውን እያሰፉ ይገኛሉ። በተለይ ደግሞ የሄገን ት/ቤቶች
ቅርንጫፍ እንደሆነ የሚታወቀው “ቪክትሪ ስነ-መለኮት
ኮሌጅ”223 በየዋህነት ትምህርት ቤቱን የሚቀላቀሉ
የወንጌላውያን አማኞችና አገልጋዮች ላይ እየዘራ ያለው ክፉ
አረም በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

በመጨረሻም በዐዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መጽሐፍት


መደብሮችን ጎብኝቻለሁ። መታዘብ እንደቻልኩት በራዕይ
የመጽሐፍ መሸጫ መደብር የኪኒየንና የኬኔት ሄገን
መጽሐፎች ለሽያጭ አይቀርቡም። ይሁን እንጂ የተጠቀሱትን
መጽሐፍት በፁሁፋቸው ላይ በማጣቀሻነት የተጠቀሙ
መጽሐፍት በነኚሁ የሽያጭ ማዕከላት ለሽያጭ ቀርበው
ተመልክቻለሁ። ይህም በእጅ አዙር የነኪኒየን ዐስተሳሰብ
በከፍተኛ ሁኔታ ለወንጌላዊያን አማኞች እየተቸበቸበ እንደሆን
ያሣያል። በአንፃሩ ደግሞ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
የመጽሐፍት ማከማቻና ቁትጥር ቢሮ ሠራተኛ የሆነችውን

223
ቪክትሪ ስነ-መለኮት ኮሌጅ መኖሪያቸውን አሜሪካ ባደረጉትና የእምነት
እንቅስቃሴ አራማጅ በሆኑት መጋቢ አንፍሬ አሊጋዝ የሚመራ በዐዲስ አበባ
የሚገኝ ትምህርት ቤት ነው።

202
ጆንሰን እጅጉ

እሸት መኩርያ እንዳነጋገርኩትና እንደተረዳሁት ከሆነ የእምነት


እነቅስቃሴ መጽሐፍት እንዲሸጡ አይፈቀድም። መሰል
መጽሐፍትን ለማጣቀሻነት የተጠቀሙ መጽህፍትም እንዲሁ
እንዳይሸጡ ዕግድ ይደረግባቸዋል።

በመካነ-ኢየሱስ የመጽሐፍ መደብር ደግሞ ዲበ-አካላዊያኑ


መጽሐፍት ካለ ዕግድ ሽያጭ ላይ ይቀርባሉ። ከመጽሐፍ
መደብሩ ኀላፊ ሳሙኤል መንገሻ እንደተረዳሁት ይህንን
የሚያደርጉበት ምክንያት “በዕግድ ሕዝብን መጠበቅ
አይቻልም።” የሚለው አንዱ ምክንያት ሲሆን ሌላው
ምክንያት ደግሞ “ስኹት ትምህርቶችን ተረድተው መልስ
መስጠት የሚፈልጉ አገልጋዮች መጽሐፍቱን ይፈልጋሉ።”
የሚል ነው። በነኝህ መደብሮች ያስተዋልኩት መልካም ነገር
ደግሞ የሽያጭ ሰራተኞች በመግባባት ላይ የተመሰረተ
ለአንባቢያን መጽሐፍትን የማማረጥና የማማከር አገልግሎት
መስጠታቸውን ነው። በግል የመጽሐፍት መደብር ግን ሙሉ
ለሙሉ በእምነት እንቅስቃሴ መሪዎች የተፃፉና ስለ ዲበ-አካሉ
ባዕድ የእምነት ቃል የሚያስተምሩ በዐገር ውስጥና በውጭ
ዐገር ቋንቋ የተጻፉ መጽሐፍትን ካለምንም ዕገዳም ሆነ
የማማከር አገልግሎት ለገበያ ቀርበው ሲሸጡ ለመመልከት
ችያለሁ።224

224
Johnson Ejigu. The Infilunce of Positive Confession: (2018).

203
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጠቃላይ ከወንጌል አማኞች ጋር ባደረኩት ውይይት


ያገኘሁት መልስ ሁለት ነገር ያሣያል። አንደኛ የቃል እወጃ
ጸሎት ካለገደብ የሚተገበርባቸው ኢንዲፐንደንት ቤተ-
እምነት መድረኮች መኖራቸውን። ሁለተኛ በከፊል ቃል ዐዋጅ
የተፈቀደባቸው የሚመስሉ በተለይ ደግሞ ዓመታዊ ዐዋጅ
በሚል ልምምዱ የሚተገበርባቸው የወንጌላዊ አማኞች ቤተ-
እምነት መድረኮች መኖራቸውን ነው። ይህንንም አስመልክቶ
ተካልኝ ነጋ (ዶ/ር)“የዓመቱ ቃል በሚል የምናውጃቸው
ስንኞችና ጥቅሶች ትምህርቱ ልባችንን ምን ያኽል እንደገዛው
ጠቋሚ ምስክር ናቸው”225 በማለት አስረግጧል።

ተካልኝ በእዚህ ላይ በማከልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ


ወንጌላዊያንን ይወክላሉ የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች
የአማልክቱን ትምህርት ማሰራጨታቸው እና የወንጌላዊያን
ምዕመናን ለትምህርቱ ጆሮ መስጠታቸውን በዝርዝር
በማንሳት “ይህ ያለንበትን ቦታ ያሣያል” ብሏል።226
በተጨማሪም ትምህርቱ በተለያየ መንገድ ስለሰረገና ሰፊ
መነካካት ስላለው መቈጣጠር ለሚፈልጉ ጥቂት አገልጋዮች
እንኳ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። እንደ አገልጋዮቹ የመፍትሄ
ጥቆማ ከሆነ ደግሞ ነቅቶ ራስን መጠበቅ በዋናነት የምዕመኑ
ድርሻ ነው። ካደረኩት ጥናት ለመረዳት እንደቻልኩት በቃል
225
የጸሎት ቤት፡የንግድ ቤት?! (ገጽ. 121)::
226
Ibdi. (p. 22)

204
ጆንሰን እጅጉ

ዐዋጅ ትምህርት ያልተበከለና ያልተነካካ መድረክና ምዕመን


የለም ማለት ይቻላል።

በዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል ኀይል ትምህርትና ልምምድ ላይ


የወንጌላዊያን አማኞች ያላቸውን አቋም ስንመረምር ሁለት
ዐይነት ተመጋጋቢ ወይም ተቀራራቢ መልክ አለው። አንዳንድ
የወንጌላዊያን ቤተ-እምነቶች የተለሳለሰ ለዘብተኛ አቋም
አላቸው። እነኝህ ቤተ-እምነተቶች የዕለቱ ፕሮግራም
እንዳይበላሽባቸው ወይም ሁል ጊዜ “ጥሩ ፕሮግራም ነበር!”
የሚል ድጋፍ የሚናፍቁ ስለሆነ ስሕተትን መለየት ቢችሉና
ቢያውቁም እንኳ አሞካሽተው የሚያስጨበጭቡ እንጂ
ዕርምት የማይሰጡ ናቸው። ከነኝህም ቤተ-እምነት መሪዎች
አንዳንዶቹ የአማልክቱን የቃል ዐዋጅ ትምህርት በከፊል
ይቀበላሉ። የሚያሳዝነው እነኝህ መሪዎች ጥቂቱ እርሾ ሊጡን
ሁሉ ያቦካል የሚለው ብኺል ጠፍቶባቸዋል። የከፋው ነገር
ደግሞ በአንዳንድ ቤተእምነቶች አውቀውትም ይሁን
ሳያውቁት የልዩ ዲበ-አካሉ እርሾ ባለቤት ሆነው የሚታዩት
እራሳቸው መሪዎቹ መሆናቸው ነው። በመሪዎች እጅ ያለ
ትንሽ እርሾም በአጭር ጊዜ አገሩን ሁሉ የሚያቆመጥጥ ዐቅም
ስላለው የሚያደርሱት ጥፋት ከፍተኛ ስለሚሆን
የአብያተክርስቲያን ኅብረት ጽሕፈት ቤትም ሆነ ሌላ ባለድርሻ
አካል በዝምታ ማለፍ የለበትም።

205
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሌሎቹ ቤተ-እምነተቶች ደግሞ የዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል


ኀይል ትምህርት ከካሪዝማቲክ የኀይል መግለጥ ጋር
ተመሳሳይነት ያለው ልምምድ በመሆኑ ምክንያት የተወዛገበ
አቋም ውስጥ ያሉ ናቸው። ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነኝ
በ 2008 ዓ.ም የናዝሬት አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን
የቀድሞ መጋቢ ዳንኤል አለማየሁ ለሰጡት፤ የጥንቆላ አሠራር
ወደ ቤተክርስቲያን እየገባ ነው። ከካሪዝማቲክ እንቅስቃሴ ጋር
ተመሳሳይ ነውና እንለይ የሚል ማስጠንቀቂያ ያዘለ ስልጠና
ምክንያት በወንጌላውያን አማኞች መኻል የታየው
መከፋፈልና ቸልተኝነት ነው።

ምንም እንኳ ስልጠናው በተሟላ ዶክመንት የተደራጀ


ቢሆንም በወቅቱ የአማኑኤል ህብረት ቤተ-እምነት እንኳ
ከመወዛገቧ የተነሣ በቤተ እምነት ደረጃ አንድ አቋም መያዝ
አልቻለችም ነበር። ከዚህም ዐልፎ ጥቂት ሰዎች የመጋቢውን
ስልጠና በማክፋፋትና ኮንነዋል። የመጋቢውን ስብዕናውን
በሚነካ ሁኔታ አስተያየት እስከ መስጠትም ደርሰው ነበር።
ከነዚህም አንዳዶቹ “እርሱ ባለራዕይ ከሆነ ለምን
የሚያገለግለውን ሕዝብ ትቶ ኑሮውን በውጭ ዐገር አደረገ?”
የሚሉ ቃላቶችን ሲሰነዝሩ ተሰምተዋል። ነገር ግን ይህ
እርሱንና እርሱን ብቻ የሚመለከት ኀጢያትም ጽድቅም
የማይባል የግል ህይወቱና እርምጃው እንደሆነ ሊታወቅ ይገባ

206
ጆንሰን እጅጉ

ነበር። እንደ እኔ ከሆነ ግን ሥልጠናው ስኬታማና ዓይን ከፋች


ነበር።

በርግጥ የምትሃታዊውን አሠራር ንድፈ-ዐሳብ ምሥጢር


ወይም የትምህርቱን መሠረት ካልተረዳን ይህንን ዓይነቱን
ሥልጠና ወይም ትምህርት መቀበል ለማናችንም ቢሆን ከባድ
እንደሚሆንብን አውቃለሁ። በሌላ በኩል ግን ምንም እንኳ
አውቀውትና ተረድተውትም ቢሆን ለትርፋቸው ሲሉ
እውነትን የሚቃወሙ እንዳሉም መገንዘብ አያዳግተንም።
ያም ሆነ ይህ ቤተክርስቲያን “የአማልክቱን” የቃል ኀይል ሥነ-
መለኮት መሠረትና ምንነት አበጥራ ልታውቅና ጽኑና ግልጽ
አቋም ልትይዝና ህዝቧን ልትጠብቅ ይገባል።

እንደ ዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ከሆነ የሰውን መለኮታዊ


አካል ማለትም አዕምሮን ወይም በራህማን በማንቀሳቀስ
ተአምራት ማድረግ የሚችለው ዋነኛ ነገር የኅሩይ ቃል ዐዋጅ
ኀይል ነው። ይህንን ዐስተሳሰብ የወንጌል አማኞችም ብንሆን
‘የእምነት ቃል ማወጅ’ የሚል ተመሳሳይ ስም ተሰቶት
የነቢይነት መለያ ምልክት እስኪመስል ድረስ ‘ቼ በል ፈረሴ’
በማለት ክርስትናን ቁልቁል እንዲጋልብ አድርገነዋል። የቃል
ዐዋጅ ልዩ ጸሎት ከሌለ ጉባኤ እንደማይነቃቃ፣ መለኮት
እንደማይናገር፣ ጸሎት እንደ ማይመለስ፣ ጸጋው እንደ

207
የአማልክቱ ዐዋጅ

ማይንቀሳቀስና በሽተኞ እንደማይፈወስ እያሰብን እንደሆነ


ጥርጥር የለውም።

አንዳንድ የወንጌላዊያን መሪዎች መሠረታዊ የእምነት


መሠረታቸው የተበላሸ የክርስትና ተቋማት ሥነ-መለኮትን
በግልና በተቋም አምርረው መኮነን ሲገባቸው የማቀፍና
የመደመር አዝማሚያ እየታየባቸው ነው። ይህ አካሄድ ኬነት
ሄገን ከኪኒየን ኪስ የወሰደውን የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና
ከቤተክርስቲያን ጋር እንዳዋሃደ፤ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን
አማኞች ግልጽ ባልሆነ መንገድ የጀመሩትን የዲበ-አካል
ሃይማኖት ፍልስፍና ጥምረት ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ
ህጋዊነቱን ሊያረጋግጥ የሚችል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን
አንድነትን እንደሚሰብክ ሁሉ መራራቅንም እንደሚሰብክ
እናውቃልን። ለምሳሌ፦ የሥነ-መለኮትና የኑሮ ዘዬ ልዩነትን
በማንሳት ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቲዮስ በፃፈለት
ደብዳቤ ይህንን መክሯል፦ “በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም
አያውቅም …እንደነዚህ ካሉት ራቅ።” (1 ጢሞ.6፣4) ይላል።

ዓለምን በከፍተኛ ሁኔታ የበከለው የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ፍልስፍና


በዋናነት የፈውስ አገልግሎት፣ የብልጽግናና የጸሎት መርሖ
እንደሆነ ተደርጎ ይተገበራል። በኢትዮጵያም ቤተ-እምነቶች
ይህን የቃል ኀይል ቅርፅ ማውጫ (mold) በመቀበል ቅርፅ
የተዋረሱ ተቋማት መኖራቸው ምስጢር አይደለም። ይህ ነው

208
ጆንሰን እጅጉ

ብለን ያስቀመጥነው የመሠረታዊ ትምህርት ልዩነት


ባይኖረንም ከፍሬያቸውና ወጣ ካለ ልምምዳቸው የተነሳ
እዛው በፀበላችሁ ያልናቸው የእምነት ተቋማት በርካታ
ናቸው። የዛኑ ያኽል ደግሞ የማንለያቸውና የተንከባከብናቸው
ወይም በመድረካችን ላይ የደጋገምናቸው ብዙ ናቸው። ይህ
መመሳሰላችንም “ፍቅር ነው ያጣችሁት እንጂ ምንድነው የጎላ
ልዩነታችሁ? ለምን ኅብረት አይኖራችሁም” የሚል አስተያየት
ለወንጌላውያኑ ከተለያ አቅጣጫ በግልና በቡድን እንዲነሳ
እያደረገ ይገኛል። የአንድነት ጥያቄ ለውጥን ወይንም
ተሓድሶን ቀድሞ ሲመጣ አደጋው ከባድ እንደሚሆን ግን
በቅርብ ከተመለከትነው የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር መማር
ይቻላል።

ከአማልክት ማኅበር ከሆኑት አንዳንዶች ልዩነትን ከማስወገድ


ይልቅ ደብቀውና አንድነን የሚያስብላቸውን ድፍረት ነገር
ጨምረው ሲናገሩ፦

ከወንጌላዊያኑ ጋር አቅዋማችንን የምንገልጥበት


ዓረፍተ ነገር ካልሆነ በስተቀር ምንም ልዩነት የለንም፤
ለምሳሌ ሰው ሥጋ ነፍስ መንፈስ አለው የሚለውን
የተማርነው ከወንጌላዊያኑ ነው። እኛ ሰው መንፈስ
ነው ማለታችን ነው እንጂ ልዩነት የለውም። መንፈስ

209
የአማልክቱ ዐዋጅ

አለውና መንፈስ ነው ማለት ምንድነው ልዩነቱ፤


ሁለቱም ያው ነው። 227

ብለዋል። እንዲህ ተሓድሶ ባልነካው ውስጠታቸው ሲቀጥፉ


መመልከታችን ለአቅመ አንድነት ያልደረሰ እንጭጭ
ልቦናቸውን እንድንታዘብ አድርጎናል። ክርክራቸውም
እንጭጩን የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ካውንስልን ወደ ኅብረት
ለማሸጋገር እስከመታገል የደረሰ ነው። ያም ሆነ ይህ ባደረኩት
ጥናት የእምነት ቃል ዐዋጅ ልምምድ ከዲበ-አካል ሃይማኖት
የቃል እምነት ፍልስፍና ጋር በቀጥታ ተገናኝቶ ባገኘውም
ከ 70% በላይ የሚሆኑት የወንጌል አማኞች ልዩነቱን
እንደማይገነዘቡ ወይንም በጥርጣሬ እንኳ እንደማይመለከቱት
ካደረኩት ጥናት ተረድቻለሁ።

የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና የቃል ኀይልን ጽንሰ-ዐሳብ


መሠረት አድርጎ ልቅና የተለያየ አካሄድ እንደተከተለ ሁሉ፤
የእምነት እንቅስቃሴ ማኅበርተኞችም እንዲሁ ይህንኑ
ፍልስፍና ተጣብተው በአንድ ግንባር መስጥረዋል። የእምነት
እንቅስቃሴ አማልክቱ ሚስጥራዊ የሆነ የአንድነት ስኬት
ማግኘት የቻሉት የዲበ-አከል ሃይማኖት አማልክት ፍልስፍና
በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥምቀው ስላመነኮሱት ነው።
በዚህም “በተደጋጋሚ መናገር ወይም መድገም” ፣ “መለኮታዊ
227
ዘላለም ጌታቸው። GMM TV ቃለ መጠየቅ፣ ጥቅምት 4፣ 2፡00።

210
ጆንሰን እጅጉ

እምነትን መለማመድ፣ ልዕለ አዕምሮን በመልካም ዐስተሳሰብ


‘positive thinking’ መቈጣጠር ወይም ምናባዊ ምስል
በተመስጦ ማየት፣ የሚሉትን ጽንሰ-ሐሳቦች የአገልግሎታቸው
ዋና አካል እንዲሆኑ አድርገዋል። የቃል እምነት አማልክቱ
ይህንን ጽንሰ-ዐሳብ የማይነካና የማያስተጋባ የስብከት፣
የትምህርት ወይም የጸሎትና የዝማሬ አገልግሎት የላቸውም
ማለት ይቻላል። ከዚህም የተነሳ ፍልስፍናው የዲበ-አካል
ሃይማኖት ህልውና እንደሆነ ሁሉ ለእምነት እንቅስቃሴም
ህልውናው እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም።

በዚህ ክፍል (በምዕራፍ ሦስትና አራት) የእነዚህ ትምህርቶች


መሠረታዊ ዐሳብ የሚተነተንበት መንታ ምክንያቶች አሉት።
አንደኛውና ዋነኛው ምክንያት ትምህርቶቹ ከክርስቶስ
ትምህርት ጋር የማይገጥሙና የመጽሐፍ ቅዱስን ርቱዕ
ትምህርት የሚያፋልሱ እንደሆነ ማሳየት ነው። በዚህም
ትምህርቶቹ የእምነት እንቅስቃሴ ከዲበ-አካል ሃይማኖት ጋር
በመጣባት ያስተዋወቀው አጋንታዊ ትምህርት እንደሆነ
ያጋልጣል። ይህ ደግሞ እንቅስቃሴው ኑፋቄ እንደሆነ
ለመፈረጅና የክርስትናን ርቱዕ ትምህርት ለመታደግ
እንድንችል ያግዘናል። ሁለተኛው ምክንያት የትምህርቱን ሥር
ሳያውቁ እያስተማሩ ያሉ የእምነት እንቅስቃሴ ሰባኪያን
የዲበ-አካል ሃይማኖት ባለሟል እየሆኑ እንደሆነ እንጂ

211
የአማልክቱ ዐዋጅ

እግዚአብሔርን እያገለገሉት እንዳልሆነ አስተውለው


እንዲመለሱ ለመርዳት የሚደረግ ትግል ነው።

መለኮታዊ እምነት
ከሥነ-መለኮት ጥናት አንጻር ሲታይ “መለኮታዊ እምነት” ምን
ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ ለመረዳት ግር የሚያሰኝና አስቸጋሪ
ነው። ነገር ግን ከቃሉ ተጠቃሚዎች ለመረዳት ስንሞክር
“የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት” ወይም በእምነት ላይ ያለ
እምነት ማለት ሲሆን ይህም አሸናፊ፣ ገዥ፣ የበላይ፥ ወሳኝና
መፍጠር የሚችል ትልቅ “የአማልክት እምነት” ወይም
“እግዚአብሔር ያለው እምነት” ዐይነት እንደ ማለት ነው።
እንደእነርሱ ከሆነ እምነት ለእግዚአብሔር የመፍጠር አቅሙ
ወይም የኀይል ሁሉ ምንጭ ነው። የሰው ልጅም በተመሳሳይ
መንገድ እምነትን በመጠቀም መፍጠር ይችላል። የትምህርቱ
ጀማሪ ኢ ደብልዩ ኪኒየን ሁለት ዐይነት እምነት በሚለው
መጽሐፋ “ፈጣሪ እምነት” በሚለው ንዑስ ርዕስ
“የእግዚአብሔርን እምነት” ያነሣል። እንደ እርሱ ከሆነ
እግዚአብሔር በቃል ላይ ባለው እምነት ዓለማትን ፈጥሯል።

ይህንም ሲተነትን፡ “በመጀመሪያው የዘፍጥረት መጽሐፍ አንድ


ትልቅ ቃል ሥራ ላይ አውሏል። ይህም ‘ይሁን’ የሚለው ቃል
ነው። እምነት የተሞላ ቃል ዓለምን አስገኝቷል፤ እምነት

212
ጆንሰን እጅጉ

የተሞላ ቃል ዛሬም ዓለምን ያስተዳድራል።”228 ብሏል።


ሌላኛው የኪኒየን አፍ ሄገንም እንዲሁ እግዚአብሔር
ዓለማትን እንዴት ነው የፈጠረው? እግዚአብሔር የተናገረው
ነገር እንደሚሆን አምኖ ነበር። የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት
መሠረታዊ መርሖ በልብ ማመንና በአፍ መናገር ነው። በማለት
‘የእምነት ቃል’ ከሚለው በ(ሮሜ.10፡10)229 ላይ ከተቀመጠው
ቃል ጋር ለማግባባት ሞክሯል። በተጨማሪም(ከማር.11፡12-
14፣20-22) ያጣቅሳል።230 እንደ እርሱ በዚህ ክፍል ላይ
ኢየሱስ የበለሷን ዛፍ ያደረቃት የእግዚአብሔር ዐይነት
እምነትን በመግለጡ ወይም በመጠቀሙ ነው።231

“አማልክቱ” እንደሚሉት የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት


የሚገኝበት ሁለት ዐይነት መንገድ አለ። አንደኛው ልምምድ
ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማንነት፤ የምድብ ለውጥ ነው።
እንደ ትምህርቱ ከሆነ ሁለቱም መርሖ ይሠራል። ቢሊ ጆይ
ዳፍርቲ የልምምድ ውጤት ለሆነው እምነት በምሳሌነት
ከዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ላይ እግዚአብሔርንና ከወንጌላት
ላይ ደግሞ ኢየሱስን ለምሳሌነት ያሰልፋል።

228
E. w. Kenyon. The Two Kind of Faith. (p, 27).
229
በምዕራፍ ስምንት ላይ “የእምነት ቃል” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር ተብራርቷል።
230
በምዕራፍ አምስት ላይ “የረገምካት መለስ ደርቃለች” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር
የተብራራ ነው።
231
Kenneth E. Hagin. Exceedingly Growing Faith (1995, pp, 105-108).

213
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጆይ የኦራል ሮበርት የእምነት (faith) ዩኒቨርስቲ ሙሩቅ


ነው።232 ምንም እንኳ እምነት ጥገኛ ላልሆነ መለኮት
የማይመጥን መርሖ እንደሆነ ብንገነዘብም እርሱ ግን ከኪኒየን
በተማረው መሠረት አስቀድሞ የእግዚአብሔርን አማኝነት
ለትምህርቱ እንዲመቸው አድርጎ ያትታል፦

እግዚአብሔር ያልነበረ ነገር እንዲሆን ተናገረ፣ ይህም


ማለት፣ የማይታዩት ነገሮች እንዲታዮ። ነገር ግን
እግዚአብሔር ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ
በእምነት ዓይቷቸው ነበር። የህንን ያደረገው በራሱ
ቃል ስለሚያምን ነው። ቃሉ እንደሚፈጸም
እርግጠኛ ነበር።…እግዚአብሔር የእምነት (አማኝ)
አምላክ ነው። ያምናል፣ ይናገራል፣ ከዛ በኋላ ነገሮች
ይሆናሉ።

ጆይ እንዲህ ያደከመውን ጡዘት ማስተላለፍ


የፈለገበትን አዕማድ ነጥብ በማስቀመጥ
ሲያጠቃልልም፦ “እርሱ እንዳደረገ እንድናደርግ ቃሉ
ተሰጥቶናል።”233 ይለናል። ጆይ የተነሳበት የዘፍጥረት
መጽሐፍ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት የሚነግረን ነው።
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ለመፍጠር አስቀድሞ ማየት

232
ጆይ ቢሊ ከኦራል ሮበርት ዮኒቨርሲቲ ምሩቅ ሲሆኑ የቪክትሪ መጽሐፍ ቅዱስ
ኮሌጅና ቤተክርስቲያን መሪ ነው።
233
Joe, B. Faith Power: It works better with all the Parts. (1978. p. 50)

214
ጆንሰን እጅጉ

ከዛ ማመን በመጨረሻም መናገር አስፈልጎት ነበር


ይለናል። ተዛምዶ ሲያደራጅ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ይህ
መርሖ ለሰዎች እንደሚሰራ በማስረገጥ እንድንለማመድ
ይመክራል።

ጆይ ይህ የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት በቀላሉ


እንደማይገኝም ያስረዳል። እግዚአብሔር “እምነትን” የቱጋ
ተለማመዶ አጥናፈ-ዓለሙን ለመፍጠር ብቅ እንዳለ ለመናገር
አይድፈር እንጂ ሰው ወደ እግዚአብሔር እምነት እንደሚደርስ
አትቷል። እንደ እርሱም ከሆነ የእምነት ማደግ ፈጣሪን ወደ
መሆን ያደርሳል ማለት ይቻላል። ኢየሱስንም በምሳሌነት
ሲጠቅስ፦ “ኢየሱስም እምነቱን በማሳደግ ወደ እዚህ ደረጃ
ደርሷል።” ይላል። በመቀጠልም “የእግዚአብሔር ዐይነት
እምነት በአንድ ለሊት የሚያድግ አይደለም። ብዙ
ክርስቲያኖች የአሸናፊ እምነት፤ ደስታን ማጣጣም ለምን
እንደማይችሉ ታውቃላችሁ የእምነትን መርሖ በተደጋጋሚ
ስለማይፈጽሙ ነው።”234 ይላል። እንደ እርሱ ከሆነ እምነት
የሚያድገው የእምነት መርሖን በመፈጸም ነው፤ አንድ ነገር
እስኪሆን ድረስ ደጋግሞ ማወጅ። ትምህርቱ ልብ የመሰጠው
ካገኘ ቀስ እያለ ወደ ለየለት ገደል እያሞኘ ዐግቶ መውረዱ
የማይቀር ነው። የታደሰው ሰው እምነቱን ካሳደገ ‘የሚሳነው

234
Ibdi. (P, 54).

215
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነገር የለም’ ወይም ‘እንዲሆን የሚፈልገውን ነገር በቃሉ ዐዋጅ


እስከ መወሰን ሊደርስ የሚችል “አማልክት ነው” በማለት እስከ
ማሳመን ይደርሳል።

ጆይ ይህ የእምነት ደረጃ በኢየሱስ ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር


ከነገረን በኋላም የማንነት ለውጥ ውጤት እንደሆነ
ሁለተኛውን ገጽታውን ሊያሳየን ይሞክራል። ይህንንም
ሲያብራራ የእግዚአብሔርን እምነት መካፈል የምንችልበት
ምስጢር ድነት ያስከተለው የማንነት ለውጥ ውጤት እንደሆነ
አጣፍጦ ያቀርባል። “የመለኮት ሕይወትና ተፈጥሮ
ተቀብለናል፣ ለዚህም በደሙ አጥቦ ወደ መንግስቱ
አስገብቶናል።”235 ይላል። እንደ ጆይ ሁሉ “ንቁ አማልክት”
የሆኑ ሁሉ በእነዚህ ሁለት መሠረታዊ የመለኮታዊ እምነት
መርሖ ይስማማሉ። አዲሱ ፍጥረት እንደ እግዚአብሔር
ማመንና በቃል ዐዋጅ ማዘዝ የሚችለው የእግዚአብሔር
ዐይነት ተፈጥሮ ስላለው ነው በማለት በጽኑ ይሞግታሉ።

ባጭር ቃል እንደ እነርሱ አዲስ ፍጥረት መሆን ከሰውነት


ምድብ በመውጣት በአምላክነት ምድብ ውስጥ መቀላቀል
ነው። ይህም የመቀላቀል ዐስተሳሰብ ወደ ታላቁ ፈላስፋ
አፍላጦን የተጠጋ ነው። ምንም እንኳ አፍላጦን ‘አሐዳዊ’
(Oneness) በማለት የሚጠራውን የፍጥረታት ምንጭ አካላዊ
235
Ibid., ( Pp50-51).

216
ጆንሰን እጅጉ

ህላዌ ያለው መለኮት እንደሆነ ባያስረግጥም፤ ሰው በሞት


ወይም በዕውቀት አማካኝነት ከቁሳዊነት ነፃ ሲወጣ ወደ
መጣበት አሃዳዊ ሥነ-አመክንዮ በመመለስ በተቀላቅሎ
መኖርን ይቀጥላል በማለት ያአምን ነበር።

የእምነት እንቅስቃሴ መሪዎች አማልክትነትን ቢያስተምሩም


ሥነ-ልቦናቸውን በከፍተኛ ሁኔታ የተቆጣጠረው
የአማልክትነት ምኞት አደልም። ከዚህ ይልቅ መሠረታዊ
ምክንያታቸው ለመነቃቃት ወይም ለጸሎት ምላሽ ያላቸው
ጕጕት እንደሆነ እመለከታለሁ። በአንዳንድ “የእምነት ቃል”
አራማጆች የልዕለ አዕምሮን ኀይል በመልቀቅ መልስን መቀበል
የሚለው የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና “የእምነትን ኀይል”
በመጠቀም የምንፈልገውን ነገር መጨበጥ በሚል ሥልታዊ
አቀራረብ ሥራ ላይ መዋሉ የዚህ ዓይነተኛ ማሳያ ነው።

በአጠቃላይ አማልክቱ በእምነት ሁሉን ለመጨበጥ ሲሉ


በመጀመሪያ እግዚአብሔርን አማኝ ያደርጉታል። በመቀጠልም
ኢየሱስም እምነቱን እንዳሳደገ ከደሰኮሩ በኋላ ሰው በሁለት
መንገድ፤ በእምነት ማለትም በኅሩይ ቃል ዐዋጅ ልምምድ እና
በመደብ ለውጥ እንደሚመለኩት ወይም ወደ ክርስቶሳዊነት
እንደሚሸጋገር ይደመድማሉ። አስተሳሰቡንም ለማስረጽ
የሰውንትን ትምህርት በማዛባት ሰውነትን ከመለኮት ጋር

217
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደሚያዳብሉታል። እንዲሁም ትምህርተ መለኮትንም


በማፋለስ የሰውን ባሕርይ ለመለኮት ያሸክሙታል።

ለምሳሌ አማልክት ኪኒየን ሲናገር፦ “ሰው በእግዚአብሔር


ምድብ ውስጥ ነው የተፈጠረው። ሰው ዘላለማዊ መንፈስ
ነው።”236 ብሏል። ሌላኛው የኪኒየን አፍ ሄገንም እንዲሁ
በምዕራፍ ሦስት መለኮታዊ እምነት በሚለው ንዑስ ርዕስ
እንደተመለከትነው “ሰው ትንንሽ አምላክ ነው። በመለኮት
ምድብ ውስጥ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር የተጠቀመበትን
የእምነት ኀይል መጠቀም ይችላል። የራሳችንን ተጨባጭ
ዓለም በአንደበታችን ቃል መፍጠር እንችላለን።”237ብሏል።
ሄገን በዚህ መሠረታዊ ትምህርቱ ከአባቱ ከፊሊሞር እና
ከኪኒየን ጋር ተስማምቷል።

የኪኒየንን ትምህርት በመስረቅ እንዳስፋፋ የሚታማው ይህ


ሰው ይህንኑ ዐሳብ ምንም ሳይገደብ ሲያስረግጥ ክርስቶስ ነን
ይለናል። ብዙዎቻችን እንደዚህ ዓይነቱን ነገር ‘የአፍ ወለምታ
ነው እንጂ የታሰበበት አይደለም’ ብለን እንደምንከራከር
አውቃለሁ። ይሁን እንጂ በደንብ ታስቦበትና ተሰልቶ
የሚተላለፍ መልዕክት እንደሆነ ከፁሁፎቻቸውና ከስብሰባቸው
እንዲሁም ከተግባራዊ ልምምዳቸው ልብ የምንለው እውነት
236
E.W. Kenyon. The Hidden Man. (p,3).
237
Harrison, M.F. Righteous Riches: The Word of Faith Movement in
Contemporary African American Religion. (2005, p. 35).

218
ጆንሰን እጅጉ

እንደሆን ላሳስብ እወዳለሁ። ሄገን ይህንን ጥቅስ በመጥቀስ


ሲያስረዳ፦

ታውቃላችሁ አማኞች ጻድቃን ተብለዋል። የማያምኑ


ደግሞ ኀጥአን ተብለዋል። አማኞች ብርሃን ተብለዋል።
የማያምኑት ደግሞ ጭለማ ተብለዋል። በመጨረሻም
አማኞች ክርስቶስ ተብለዋል። የማያምኑ ደግሞ ሴጣን
ተብለዋል። ኢየሱስ ራስ ሲሆን እኛ ደግሞ አካሉ ነን።
ራሳችሁና አካላችሁ በተለያየ ስም የሚጠራ
ይመስላችኋል? አማኞች ክርስቶሶች ናቸው መጽሐፍ
ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል ወይም ብልት እንደሆነ
እንደሚናገር አታውቁም? ለምን ክርሰቶስ እንደተባልን
አሁን አይታችኋል? 238

ብሏል። ሄገን መሠረት ያደረገው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል


ነው።(2 ቆሮ. 6፣14-15)። ነገር-ግን ይህንን ጽንሰ-ዐሳብ
ፊሊሞር ክርስቶሳዊነትን ካስቀመጠበት ጽንሰ-ዐሳብ ጋር
ስናወዳድር ከአንድ ምንጭ ማለተም ከልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና
የተቀዳ እንደሆነ ማየት እንችላለን። ፊሊሞር “በኢየሱስና
በእኛ መኻል ያለው ብቸኛ ልዩነት ኢየሱስ አባት የተባለው
ሥርዐት ወይም የተፈጥሮ ሕግ ለአንደበቱ ቃል
እንደሚመልስለት በፍጹም ልቡ ማመኑ ነው” ማለቱን

238
Hagin, K.E. Understanding our Confession. (d.n. p. 67).

219
የአማልክቱ ዐዋጅ

በምዕራፍ ሁለት ተመልክተናል። በተጨማሪም “ኢየሱስ


የክርስቶሳዊነት ምሳሌ ነው” ማለቱን በዚሁ ክፍል መጠቀሱን
ልብ ይሏል። በተጨማሪም የእምነት ቃል ትምህርት
ከፊሊሞርያዊያኑ ጋር በተመሳሰለ መልኩ የዘፍጥረትን
የፍጥረት ታሪክ መነሻ ያደርጋል። በአጠቃላይ ይህንንም
የሚያደርጉት እግዚአብሔር እራሱ የእምነትን ኀይል
በመጠቀም ፍጥረትን እንደፈጠረ በማሣየት እምነትን
የማሣደግ ግብዣ ማድረግ ስለሚፈልጉ ነው።

እውነቱ ሲታይ ግን የዘፍጥረት መጽሐፍ እግዚአብሔር


ፍጥረትን ሲፈጥር “ይሁን” በማለት ሉዐላዊ ፍቃዱን እንደሰጠ
የሚያሣይ ነው እንጂ “የእግዚአብሔርን አማኝነት”
አያሣየንም። በሌላ በኩል ምንም ነገር ለማመን ወይም
ለመደገፍ የሚያስፈልገው ጥገኛ አምላክ አለመሆኑን ቅዱሳት
መጽሐፍት ግልጽ ያደርጋሉ። በሌላ አገላለጥ እምነት አንድ
የተሰጠን ተስፋ የምናደርገውን ነገር የሚያስረግጥ ነው።
ስለሆነም እግዚአብሔር ተስፋ ስለማይቀበልና ስለማይጠብቅ
እግዚአብሔር ያምናል ወይም አያአምንም ማለት
ስለማይቻል እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት ያፈጠጠ ውሸት ነው።
ቅዱሳት መጽሐፍትም የመለኮትን ልዩትነት በማንሣት ይህንን
በስፋት ይመሰክራሉ። ለምሳሌ ያኽል በኢሳያስ አፍ
እግዚአብሔር ሲናገር፦ “እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፣ ከእኔ

220
ጆንሰን እጅጉ

ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ


ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፣
የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።” (ኢሳ.44፡6) ይላል።
በሌላም ቦታ፦

እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሃለሁ፣


አንተም ተናገረኝ። ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ
ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።
ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፣ በላይዋስ የመለኪያ
ገመድ የዘረጋ ማን ነው? አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት
ሲዘምሩ፣ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልልሲሉ፣
መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር?
የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው? (ኢዮ.38፡4-
5)።

በማለት በመፍጠር ሥራው ውስጥ የነበረውን ብቸኛ


የመወሰን ድርሻ ይናገራል። እንግዲህ ከዚህ ቃል
እንደምንረዳው በዓጥናፈ-ዓለም ልደት ውስጥ ብዙ ዕውቀት፣
ድንጋጌና ሥራ ነበር። ይህም የዘፍጥረት መጽሐፍ
የማይነግረን ወይም “ይሁን” በሚለው ነጠላ ቃል ውስጥ
ተገልጦ የማናገኘው ሰፊና ጥልቅ ምሥጢር ነው ማለት
ይቻላል።

221
የአማልክቱ ዐዋጅ

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ዘፍጥረት ትረካ በፍጥረት ሥራ ላይ


እግዚአብሔር ቃል እየተናገረ እንደ ፈጠረ ሁሉ ቃል
ያልተናገረበት ጊዜም እንደ ነበረ መካድ አይቻልም። ለዚህም
ትልቅ ማሣያ የሚሆነው የፍጥረቱ ገዥ የሆነው የሰው ልጅ
ካለ ቃል ትዕዛዝ መፈጠሩ ነው። ይህም መንፈሳዊው ዓለም
ካለ ቃል አይንቀሳቀስም የሚለውን ከፊል ዕውነት ይሽረዋል።
እንዲሁም በየቀኑ እየሆነ ያለው ሚሊዬን ክሥተት፤ እየሆነ
ያለው በመጀመሪያ ቃል ስለተነገረ ነው ብሎ ማሰብም
ተዓማኒነት የሌለው ነው። ከሁሉ በላይ መለኮትን ለቃል ሕግ
ተገዥ ማድረግ የልዩ ዲበ-አካሉ ምሁራን እንዳደረጉት
ከልዕናው አውርዶ የቃልን ሕግ በምትኩ ማንገስ ነው
የሚሆነው።

አንድ ጓደኛዬ ከዚህ በፊት የአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን


አባል እንደነበረች የሚያውቃትን ወጣት መንገድ ላይ
ያገኛታል። ልጅቱ ብስራት ቡዛየሁ (ጃፒ) የሚሰጠውን
ትምህርት ረዘም ላለ ጊዜ ተከታትላለች። እርሱ እንደነገረኝ
ጊዜው ማለዳ ነበርና የተለመደውን ዐገርኛ ሰላምታ “እንደምን
አደርሽ?” በማለት ያቀርብላታል። መልሷ ግን ከተለመደው
ውጭ ግር የሚያሰኝ ነበር። ከራሱ አንደበት እንደሰማሁት
“እንደ እግዚአብሔር” በማለት ነበር ምላሽ የሰጠችው።

እናም የሰላምታው መልስ ያስደነገጠው ይህ ወዳጄ መልሶ

222
ጆንሰን እጅጉ

“በርግጠኝነት አንቺ ያደርሽው በተዘጋ ቤት ነው፤ ምክንያቱም


ትፈሪያለሽ! ለመሆኑ ማንንም የማይፈራው እግዚአብሔር
የት ነበር ያደረው?” በማለት ምናልባት ደንግጣ ወደ ማስተዋል
ትመለስ ይሆናል በማለት ጠየኳት ይላል። ልጅት ግን መች
ትፈራና “ከኔ ጋር ነዋ ያደረው!” በማለት መለሰችልኝ ይላል።

ይህ ወዳጄ የልጅቱ መልስ የባስ ግርምት ቢፈጥርበት “አይ!


ይቅርታ? እንዴት አደራችሁ?” በማለት ትቻት ሄድኩ ይላል።
መቸም ብስራት እንደዚህ ዓይነቱን የሰላምታ አሰጣጥ
ያስተምራል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጂ ሰዎች
በእነርሱና በመለኮት መኻል ያለው ልዩታ ጠፍቶባቸው
አንቀላፍቶ ለማያቅ፤ መኝታ ክፍል ለማያስፈልገው አምላክ
ለሰው የሆነውን “ማደር” በድፍረት ሊጠቀሙ የቻሉት ምን
ዐይነት ሚዛኑን ያጣ ትምህርት ቢማሩ ነው የሚል ግርምት
ማስነሣቱ አይቀርም።

ይህ ከሆነ ብዙም ሳይቆይ በጂ ኤም ኤም (GMM) ቴሌቪዥን


ጣቢያ ላይ ጥቂት አድማጭ ያለው ትንሹ የሄገን አፍ “እንደ
እግዚአብሔር ዐይነት እምነት” የሚለውን የአማልክት ሄገንን
ርዕሰ-ትምህርት ይዞ ሲያስተምር ተመለከትኩ።

የእምነት ኀይል አንደበት ነው። እምነት መንፈስ


ነው። እምነት ላለው ሁሉ ይቻላል። we are

223
የአማልክቱ ዐዋጅ

manifested God kind of faith የእግዚአብሔር


ዐይነት እምነትን እንገልጣለን። you know ይህ
የአዕምሮ እምነት አይደለም የመንፈስ እምነት ነው።
ምን ዐይነት እምነት እንደሆነ ታውቃላችሁ?
የምትፈልጉትን ነገር ከመንፈሳዊ ዓለም ላይ ይጠራል!
you know እግዚአብሔር ተናገረ ሆነም።
የምትናገሩት ነገር ሁሉ ይሆናል። Don’t worry!
አትጨነቁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ ከማይታየው
ዓለም ስበን እናመጣዋለን። ስሜታችሁን
239
አታድምጡ።

በማለት ጮክ ባለ ድምጽ ይናገር ነበር። እንግዲህ ይህንን


ከዲበ-አካል ሃይማኖት መሪዎችም ይሁን ከእነ-አማልክት
ኪኒየንና ኬኔት ከሄገን ስብከቶች የተቆነጣጠረ የቃላት ስብስብ
ያዘለ ትምህርት ያየን እንደሆነ “እንዴት አደርሽ?” ለሚለው
የሰላምታ ጥያቄ ምላሹ “እንደ እግዚአብሔር” መሆኑ
አያስደንቀንም። እርሱ “የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት”
የሚለው የምንፈልገውን ነገር ከመንፈሳዊው ዓለም የሚጠራ
ሲሆን ይህንንም እግዚአብሔር ዓለማትን በመናገር
ከፈጠረበት ኀይል ጋር ያነፃጽረዋል። እምነት ያስፈለገው
በመለኮት ላይ ጥገኛ ለሆነው ለፍጥረቱ እንደሆነ እየታወቀ
እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ቀላቅሎ “አምኖ ነው
239
ብስራት ቡዛየሁ (ጃፒ) ጂ. ኤም. ኤ ቴሌቪዥን (ሚያዚያ, 16፣ 7፣10, 2018) ።

224
ጆንሰን እጅጉ

የተናገረው” ማለት ምን ማለት ይሆን?

እንዲህ እነሱ እንደሚሉት እኛ ማለት ያቃተን፤ እጅግ የረቀቀ


“መገለጥ” ስለሆነና መድረስ የማንችል ዳዴን ያልጨረስን
ህፃናት ስለሆንን ይሆን? ተካልኝ ለእንዲህ ዓይነቱ መላምት
መልስ ሲሰጥ፦ “የእግዚአብሔር ዕውቀት ፍጹም በመሆኑም
ለእርሱ እምነት አያሻውም። በፍጹም ዕውቀት ውስጥ ምንም
ዐይነት መጠባበቅ ስለማይኖር አምላካችን ያምናል ብሎ
መናገር ትርጉም አይሰጥም።” ብሏል።240

በርግጥ ትምህርቱ “የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት” ወይም


“የመንፈስ እምነት” የሚል ስም ይሰጠው እንጂ ከልዩ ዲበ-
አካሉ “የቃል ኀይል” አስተምህሮ ጋር የተለየ አይደለም።
በምዕራፍ ሁለት ላይ እንዳየነው ፊሊሞራዊያኑም “ቃል
በማወጅ” ጸሎትን ይመልሱ ነበር። ሰውዬው እንዲሁ
ከመንፈሳዊው ዓለም ሰዎች የሚፈልጉትን ስቦ ማምጣት
እንደሚችል እየነገረን ነው። “የምትናገሩት ነገር ሁሉ ይሆናል።
Don’t worry! አትጨነቁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ
ከማይታየው ዓለም ስበን እናመጣዋለን።”241 እንደእርሱ ከሆነ
እርሱ ካለ ጭንቀትን ደህና ሰንብች ነው።

240
ዶ/ር ተካልኝ። የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! (ገጽ. 93)።
241
Harrison, M.F. Righteous Riches: The Word of Faith Movement in
contemporary AfricaneAmeerican Religion. (2005, P.68).

225
የአማልክቱ ዐዋጅ

“የአማልክቱ” የልዩ ዲበ-አካል ትምህርት ጥግ ጸሎትን


ለመመለስ “የእግዚአብሔር ዐይነት እምነት” ልምምድ
አይደለም። አስቀድመን እንዳየነው መሠረታዊ ፍላጎታቸው
ስኬትን መጓጓት ቢሆንም የትምህርቱ ጥግ ግን ሰውን
የመለኮታዊ ተፈጥሮ ባለቤት ማድረግ ነው። ይህንን
የክራይስት ኢንባሲ ቤተክርስቲያን መስራች የሆነው ፓስተር
ክሪስ የኪኒየንን ትምህርት በመውሰድ ሲያንጸባርቅ242“ይሄ
ማለት ከመለኮት ጋር አንድ ዐይነት ሕይወት አለን። አንድ
ዐይነት ተፈጥሮና ባሕርይይ አለን። በእግዚአብሔር ምድብ
ውስጥ ነን።”243 ብሏል። ፊሊሞር ወደ “ክርስቶሳዊነትነት”
እንደሚያድግ እንደሚያምን ወይም የዲበ-አካል ሃይማኖት
አራማጆች የሰው አዕምሮ መለኮታዊ ተፈጥሮ እንዳለው
እንደሚቀጥሩ ተመልክተናል። እንዲሁ ሁሉ አብዛኛዎቹ የቃል
እምነት እንቅስቃሴ አማኞችም የልምምዳቸውን መሸፈኛ
ገልጦ ለተመለከተው “ክርስቶሳዊነትን” እንደሚያምኑ ማወቅ
አይቸግርም።

በአጠቃላይ የእምነት ቃል “አማልክት” እግዚአብሔር የቃል


እምነትን ኀይል በመጠቀም ዓለማትን ፈጥሯል “መንፈሳዊው
ዓለም ካለ ቃል አይሠራም።” በሚል ትምህርታቸው

242
በምዕራፍ ሁለት ላይ “ዲበ-አካል ኪኒየንና ኬኔት ሄገን” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር
ይመለከቷል።
243
ክሪስ ኦካሂሎሚ Rapsoid of reality (2009 ግንቦት 27)።

226
ጆንሰን እጅጉ

የመለኮትን ልዕልና ዝቅ በማድረግ ከሰው ጋር ያስቀምጡታል።


የጸሎት መልስ የመመለስ ድርሻን ደግሞ ሙሉ ለሙሉ
ለሰዋዊ አማልክቶች እምነት ይሰጡታል። ተካልኝ እምነት
ድርጊት የሚወድቅበት እንጂ ድርጊት ፈጻሚ አይደለም
በማለት የግሪክ ሰዋሰው ሊቃውንትን በማጣቀስ ይሞግታል።
(በማር.11፡22) ላይ ተመሥርቶም ‘እግዚአብሔር ያምናል’
በሚል መነሻ እምነትን በእምነት ላይ ማድረግ የቋንቋና
የዐውድ ስምምነትን ያልተከተለ እንደሆነ በማንሣት
ኮንኗል።244 በአጠቃላይ ይህ የዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል
እምነት ፍልስፍና ሰዋዊ-አማልክቱ በራሳቸው የመወሰን፣
የመፍቅድ፣ የመፈወስና ተአምራት የማድረግ ስልጣን
ያላቸው በማስመሰል በተከታዮቻቸው እንዲመለኩ
አድርጓቸዋል። ነገር ግን በዚህ መንገድ የሚከሰቱ ቁሳዊና
መንፈሳዊ ምላሾች ሁሉ የመለኮትን የድርጊት ባለቤትነት
ሙሉ ለሙሉ ስለሚያገሉ የመለኮት እጅ እንደሌለባቸው
በግልጽ መታወቅ አለበት።

እግዚአብሔርን መምሰል እንዲህ ነው

244
የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! ( 233)።

227
የአማልክቱ ዐዋጅ

“በመልክና በምሣሌው ተፈጥራችኋል፤ በመንፈሳችሁ የእርሱ


ችሎታ አለ፤በከንፈራችሁ ደግሞ የእርሱ ችሎታ አለ።
የምትፈልጉትን ተናገሩና ፍጠሩ”245
ክሪስ ኦያኪሂሎሚ

የዲበ-አካል ሃይማኖት አስተምህሮ በእምነት ቃል እንቅስቃሴ


አማኞች የሚስተናገድበትን ሁኔታ ማለትም አንድነትና
ልዩነት ለመመልከት የጥቂቶቹን የእምነት እንቅስቃሴ
ሰባኪያን ማብራሪያ መመልከት በቂ ነው። ለዚህም ምክኒያቱ
ሁሉም የሚያነሱት ጥቅስና ማብራሪያ ነጥብ ተመሳሳይና
የተወራረሰ በመሆኑ ነው። ይሁን እንጂ ከኪኒየን ጀምሮ
አብዛኛዎቹ “የእምነት እንቅስቃሴ አማልክት” ትምህርታቸው
የበዐዱ የዲበ-አካል ሃይማኖት ቅጂ እንደሆነ ይክዳሉ።

ከዚህ ባሻገር ምንጫቸውን መጽሐፍ ቅዱስ፤ ምሳሌያቸውን


ኢየሱስ አድርገው ስለሚያቀርቡ የተቀየጠውን የዲበ-አካል
ሃይማኖት ጽንሰ-ዐሳብ ገልጦ ለማውጣትና ለመተማመን
አስቸጋሪ ይሆናል። እነርሱ ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ
እንደሆነ ቢያስመስሉም የኅሩይ ቃል ዐዋጅን በተደጋጋሚ
የማወጅን አስፈላጊነትን ያስተማረውንና ለዲበ-አካል
ሃይማኖት ፍልስፍናም ጭምር መነሻ ጽንሰ-ዐሳብ ያቀበለውን
ቡድሂዝምን የሚቀድመው የለም። ስለዚህ ወደ ግልጸት
245
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ፡፡ ክሪስ ኦኪሂሎሚ (2013፣ገጽ. 10)።

228
ጆንሰን እጅጉ

በመምጣት መጥቀስ የሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስን ሳይሆን


የቡድሃን ፍልስፍናዎች መሆን እንዳለበት አምናለሁ። ቡድሃ
የኅሩይ ቃል ዐዋጅ አስፈላጊነትን ቢያስተምርም እንደ
እምነት ቃል “አማልክቱ” ሰው በእግዚአብሔር መልክ
መፈጠሩን በማስረጃነት በማንሣት በቃለ ዐዋጅ ልንመስለው
እንደሚገባ ስለማይዘክር “ከእምነት ቃል አማልክቱ” የተሻለ
የሥነ-ጽሑፍ ግብረ-ገብ ይታይበታል።

ቡድሃ ‘ማንታራ’ የሚባል ጥንታዊ የጸሎት ማለትም የዐዋጅ


ልምምድ ያስተማረ ሲሆን የጸሎት ዓረፍተ ነገሩም “ኦ!
በአበቦች መኻል የተጎለተ! የከበረ የሚያብረቀርቅ ሐብት!”
የሚል የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ነው። በቡድሂዝም ይህንን የጸሎት
ዓረፍተ ነገር በተደጋጋሚ መድገም ወይም ማወጅ
የሚቀጥለውን ሕይወት ወይም የሕይወት ዙር ‘መልካም
ወይም ፖዘቲፍ ካርማ’ በመፍጠር የሚያስተካክል ነው በማለት
ይታመናል።246 ስለዚህ ኅሩይ ቃልን የማወጅ መሠረታዊ መርሖ
መነሾ የቡድሃ “ፖዘቲፍ ካርማ” ዐስተሳሰብ ነው ማለት
ይቻላል። ታሪክን ወደኋላ ስንመለከት የቡድሃ አስተሳሰቦች
ለአዲሱ ዐሳብ ዐስተሳሰብም ይሁን ለኒው ኤጅ ሙቭመንት
ትምህርቶች ዓለምን ለማዘጋጀት መንገድ ጠራጊ በመሆን
እንዳገለገሉ ማስተዋል ከባድ አይደለም።

246
Mosley J. & Hill. The Power of Prayer. (2000. P, 53)

229
የአማልክቱ ዐዋጅ

የቪክትሪ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ መምህር ቢሊ ጆይ ዳፍርቲ


(ዕብ. 10፡23) አስደግፈው የእግዚአብሔርን ቃል በተደጋጋሚ
የማወጅን አስፈላጊነት ይናገራሉ፡_ “የማያቋርጥ እምነትና
ቃል ዐዋጅ የእምነትን ኀይል እንዲለቀቅ ያደርጋል።”247
ይላሉ። እንደሳቸው ከሆነ “የእምነት ኀይል” በቃል ዐዋጅ
አማካኝነት ማንኛውንም ተአምራት ማድረግ ይችላል።
ቀጥለውም ይህን ልምምድ እግዚአብሔርን መምሰል ነው
በማለት ይሞግታሉ። መጋቢ ተዘራ ያሬድም ይህንኑ
ሲያንፀባርቁ፦

የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ምዕራፍ!


የመጀመሪያው ትምህርት! ጨለማ ሲያይ ብርሃን
ይናገራል፤ እግዚአብሔርን መምሰል ማለት እንግዲህ
አንዱ እንግዲህ ይህ ነው፤ እንደ አባታችን
እግዚአብሔር ያየነውን ሳይሆን በህይወታችን ልናይ
የምንፈልገውን መናገር ማለት ነው።

ብለዋል። እንደ እርሳቸው ከሆነ ልንመለከት የምንፈልገውን


ነገር መናገር እግዚአብሔርን መምሰል ነው። በአጠቃላይም
የእምነት ቃል “አማልክቱ” በእግዚአብሔር የመፍጠር ሥራ፤
‘ቃል’ ሥራ ላይ በዋለበት መንገድ በቃል ዐዋጃችን

247
Joe, B. Faith Power: It works Better with all the Parts: it power, (1978. p.51).

230
ጆንሰን እጅጉ

እግዚአብሔርን ልንመስለው እንደሚገባ ለማስረዳት


በተደጋጋሚ ሁለት ሐሳቦችን በማያያዝ ያነሣሉ፦

1. እግዚአብሔር ዓለማትን በቃል መፍጠሩን እና


2. የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩን።

ይህንም ሲያጠቃልሉ ሰው በእግዚአብሔር መልክ ስለተፈጠረ


እርሱ በቃሉ ዓለማትን እንደፈጠረ ሁሉ የሰው ልጅም
በአንደበቱ ቃል እንዲሁ ማድረግ ይችላል ይሉናል። የዚህን
ጥቅስ ችግርና እግዚአብሔርን የመምሰልን ጥያቄ በምዕራፍ
ሰባት ላይ የምንመለከት ይሆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን
በኅሩይ ቃል ዐዋጅ ልምምድ እግዚአብሔርን ስለምንመስለው
ምሳሌነቱን እንከተላለን ከማለት ይልቅ ፈጣሪውን ቡድሃን
ወይንም ፊሊሞርን እንከተላለን ማለት ይቀላል።

የኢየሱስን ምሳሌነት መከተል


ኢ.ደብልዩ ኪኒየን አንድን ቃል እስኪፈጸም ድረስ በተደጋጋሚ
መናገርን ወይም “የእምነት ቃል ዐዋጅን” አስፈላጊነት
ሲያስረዳ “ኢየሱስ የማያቋርጥ ቃል የማውጣት “continual
248
confession” ተግባራዊ ልምምድ ህይወቱ ነበረ ይለናል።
በዚህም ምክንያት ሌሎችም ይህንን የኢየሱስን ምሳሌነት
እንዲከተሉ በአጽንዖቶ ያበረታታል። ሌላኛው የኪኒየን አፍ

248
E.W. Kenyon and His Message of faith. (p. 425).

231
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሄገንም ይህንኑ ዐሳብ በመጋራት “ኢየሱስ ሁል ጊዜ ማን


እንደሆነ ያውጅ ነበር። ማን እንደሆናችሁ ሁል ጊዜ በመናገር
249
ምሳሌነቱን መከተል አለባችሁ።” በማለት አሳስቧል።
የአስተሳሰቡ አዕማድ አቀንቃኝ ኬንዮን ይህንን እንዴት
እንደተረዳ ሲያስረዳ፦

አንድ ቀን የዕብራዊያንን መልዕክት 4፡14 እያነበብኩ


ሳለ የትኛውን የእምነት ዐዋጅ ነው መያዝ ያለብኝ
ብዬ ጠየኩኝ፤ አዎ፣ መጽናት ያለብኝ መጽሐፍ
ቅዱስ በሚናገርለት ዐዋጅ ላይ ነው። አዲስ ፍጥረት
እንደሆንኩ፣ የእግዚአብሔርን ተፈጥሮና ሕይወት
ስለ መቀበሌ። 250

ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ኪኒየን በውስጣችን ያለውን


መንፈሳዊ ኀይል ከፍ ለማድረግ ወይም ለማሳደግም የኅሩይ
ቃል ዐዋጅን አስፈላጊነት ያወሣል። ይህንንም ሲገልጽ፦
“በውስጥህ ያለውን መንፈሳዊ ኀይል ማሳደግ የምትፈልግ
ከሆነ በውስጥህ ያለውን ማለት የምትፈልገውን ነገር
251
ተናገረው የእራስህም አድርገው።” ብሏል። ይህንንም
ለማጉላት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በህይወታችን
249
Hagin, K. E. In Him. (1980, p. 7).
250
E.W. Kenyon and His Message of Faith. (pp. 417- 418).
251
McIntyre, J. E.W. Kenyon and His Message of faith: the True Story. (2010,
p,339).

232
ጆንሰን እጅጉ

እዲፈጸሙልን በተደጋጋሚ የማወጅን አስፈላጊነት ሲናገር፦


“የምንናገረው እግዚአብሔር ስለተናገረ ነው። የተስፋ
ቃሎችን ይዛችሁ ስትናገሩ ከፍተኛ ኀይል ታገኛላችሁ።
ደጋግማችሁ ደጋግማችሁ ህይወታችሁ እስኪሆን ድረስ
ተናገሩ።”252 ብሏል።

ኪኒየን እንደሚለው አዲስ ፍጥረት እንደሆንና


የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ እንደተቀበልን ማወጅ የዚህን ያኽል
ትኩረት የሚፈልግ ከሆነ፤ ኪኒየን ከኢየሱስ ጋር አብረውት
በመኖር ይሰሙት የነበሩ ደቀመዛሙርት እንኳ ከተረዱት በላይ
ተረድቷል የሚያስብል ነው። ምክንያቱም ደቀመዛሙርቱ
ይህንን ተረድተው ቢሆን በጻፏቸው መልዕክቶች በአጽንዖት
በተደጋጋሚ ሊወተውቱን በተገባ ነበር። ወይም ደቀመዛሙርቱ
ከትንሳኤ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ አሣሣቢነት ወይም አብርሆት
ተረድተው በግልጽ ሊጽፉልን ሲገባቸው ነገር ግን ደብቀውናል
ወይም እንደ ኪኒየን ያሉ ጥቂት የሚገለጥላቸው ሰዎች ብቻ
እንዲረዱት አድርገው በምሥጢር ጽፈውታል። ዳሩ ግን
ኪኒየን ተገልጦለት ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። ነገር ግን
ከእርሱ “መገለጥ” በፊት ቡድሃ ወይም የልዩ ዲበ-አካሉ
ምሁራን ባለቤትነትን ስለያዙ የተኮረጀ እንደሆነ መተማመን
ይገባል።

252
McIntyre, J. E.W. Kenyon and His Message of faith: (2010, P. 414).

233
የአማልክቱ ዐዋጅ

እግዚአብሔርን የመምሰል ልምምድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ


በተደጋጋሚ ተጠቅሶ የምናገኘው ቢሆንም አማልክቱ ሰባኪያን
እንደሚሉት አንድም ቦታ እንኳ ከኅሩይ ቃል ዐዋጅ ከማወጅ
ጋር ተያይዞ አልቀረበም። ለምሳሌ ያኽልም ጥቂት ጥቅሶችን
እንመልከት፦

 ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤


እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት
ተስፋ ስላለው፣ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል (1 ጢሞ.4፡8)።
በተጨማሪም (1 ጢሞ.5፡4፣ 6፡4፣ 6፡6፣11)።
 በበጎነትም ዕውቀትን፣ በዕውቀትም ራስን መግዛት፣ ራስንም
በመግዛት መጽናትን፣ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል
(2 ጴጥ. 1፡6)።
 እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ (1 ቆሮ.1፡11)።

በአጠቃላይ መጽሐፍት ኢየሱስ የዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል


ኀይል አማኝ እንደሆነና እምነቱንም በዚህ ስልት ያሳድግ
እንደነበረ በማስተማር እኛም በዚህ መልክ እንድንመስለው
አይሰብኩም። ስለዚህም ይህንን የእምነት ቃል ሥነ-መለኮት
እንደማንኛውም ስኹት ትምህርት ወይም ኑፋቄ ውግዝ
ልንለው ይገባል።

234
ጆንሰን እጅጉ

ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ የእምነት ቃል ባዕድ ሥነ-መለኮት በኢትዮጵያ
ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት መኻል እንደተሰራጨ
ለማሣየት ጥረት ተደርጓል። ይህንንም ለማጠናከር
የመመረቂያ ጽሑፌ የጥናት ዊሂብና ትርጓሜ ሥርጭቱ ምን
ያክል ሥነ-መለኮታችንና ልምምዳችንን እንደረበሸ ለማሳየት
እንዲረዳ በዝርዝር ተቀምጧል። በኢትዮጵያ
አብያተክርስቲያናት ውስጥ የኪኒዮንና የኬኔት ሄገነን የአማርኛ
ዕትም መጽሐፍት የዲበ-አካል ሃይማኖትን የቃል ኀይል ጽንሰ-

235
የአማልክቱ ዐዋጅ

ዐሳብ አስራጭተዋል። በሐዋርያው ዘውዴ ይመራ የነበረው


የሬማ ፌዝ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴም በየዋህነት
ለትምህርቱ መስፋፋት ዋነኛ መሳሪያ በመሆን አገልግሏል።

የወንጌላውያን አብያተክርስቲያነት የእንቅስቃሴውን ግስጋሴ


ለመግታት የሚወስዱት እርምጃ ይህ ጥናታዊ ጹሑፍ
እስቀረበበት ጊዜ ድረስ የተለሳለሰ ነው። መጋውን ለራስህ
እረኛ ሁን በማለት ዳር መያዝ ምርጫቸው ነው። የእምነት
እንቅስቃሴ ሥነ-መለኮት የቃል ዐዋጅን ከእምነት፣
እግዚአብሔርን ከመምሰልና የክርስቶስን ምሳሌነት ከመከተል
ጋር አያይዞ ቢያስተምርም የትምህርቱ ሥነ-መለኮትም ይሁን
መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን የዲበ-አካል ሃይማኖት
ከመሆኑም በላይ ከመንፈሳዊ መስመር የሚያወጣና ምንም
ረብ የሌለው ነው።

236
ጆንሰን እጅጉ

የምዕራፍ ሦስት ግንዛቤ ማስጨበጫ ጥያቄዎች


1. ጸሓፊው የዲበ-አካል ሃይማኖት ‘እርሾ’ እና ቅርፅ
ማውጫ ‘mold’ በሚሉ ሁለት ቁልፍ ቃላተ
የሚገልጠው “የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” የእምነት ቃል ኑፋቄ
መሠረት እንዴት ሊሆን እንደቻለ አብራራ።

2. የእምነት ቃል በሚል መሸፈኛ የተጀቦነ ባዕድና ቅይጥ


የዲበ-አካል ሃይማኖት ትምህርት አንተ ባለህበት
አጥቢያ የመሰራጨት ዕድል አለው? በምን መንገድና
ደረጃ?

3. ጸሓፊው ባደረገው ጥናት የሰበሰበውን የመረጃ ውሂብ


መሠረት አድርጎ ሲያብራራ የወንጌላውያን
አብያትክርስቲያናትን በእምነት ቃል ትምህርት
ሥርጭት ላይ ሁለት ዐይነት አቋም እንዳላቸው
ጠቅሷል። በዚህ ላይ የቤተክርስቲያንህና የግልህ አቋም
ከየትኛው ሊመደብ ይችላል?

4. በእምነት ቃል ትምህርት አብያተክርስቲያናት


የመበከላቸውን ኀላፊነት መውሰድ አለበት የምትለው
ማንን ነው? ሥርጭቱንስ ለመግታት ምን መደረግ
አለበት ትላለህ? በበኩልህስ ምን ማድረግ ታስባለህ?

237
የአማልክቱ ዐዋጅ

5. “ክርስቶስን መምሰል” የሚለው የዲበ-አካል


ሃይማኖትና የእምነት እንቅስቃሴ ትርጓሜ ከመጽሐፍ
ቅዱስ አውዳዊ ትርጓሜ ጋር ያለውን መመሳሰልና
ተቃርኖ አብራራ።

6. በዲበ-አካል ሃይማኖትም ይሁን በእምነት እንቅስቃሴ


ሰባኪያን ግንዛቤ የኢየሱስን ምሳሌነት የመከተል
ትምህርት ላይ ምን እፀፅ ተመለከትክ? ለአንተ
ኢየሱስን መምሰልና ምሳሌነቱን መከተል ምንድነው?

ምዕራፍ 4

የምናባዊ ዕይታ ሕግ

ህንዶች “ሦስተኛውን ዐይን” ይወክላል በሚል


በቅንድባቸውና በቅንድባቸው መኻል ክብ ነጥብ ዐይነት

238
ጆንሰን እጅጉ

ምልክት በቀይ ቀለም በመቀለም ያስቀምጣሉ። “ሦስተኛው


ዐይን” በአከርካሪ አጥንት ነርቭ ውስጥ ባለ ፒናል በሚባል ዕጢ
ሥር ይገኛል ብለውም ያምናሉ። እንደነእርሱ ከሆነ
ሦስተኛው ዐይን የሁሉም ነገር በር ነው። ለምሳሌ፦
የሳይኪክ፣ የአስትራ ፕሮጀክሽን፣ የሃይፖተኒዝምና
የሜዝሜሪዝም ዋና መሳሪያ ነው። ዲበ-አካላዊ የሰው ክፍል
ከሦስተኛው ዐይን ጋር ግንኙነት አለው ብለውም ያምናሉ።
ሦስተኛው ዐይን በእውነተኛው ዓለም ውስጥ እንዲራመዱ
በማድረግ ከውስንነት መንጥቆ እንደሚያወጣቸውም በጽኑ
ያስባሉ። ይህንንም ሲያስረግጡ “ሦስተኛው ዐይን”
እውነተኛና በዐይን የማይታየውን ዓለም ይመለከታል፣
ከመንፈስ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ከመላለም ጋር ያዋህደናል
ይላሉ።

እንደ ትምህርታቸውም ማንኛውም ሰው ፒናል እጢንና


“ሦስተኛው ዐይን” እንዲገናኙ ሲያደርግ “ስድስተኛውን”
የስሜት ህዋሱን መጠቀም ይጀምራል። “ሦስተኛው ዐይን”
በተመስጦ፣ በዳንስና በዮጋ በመነቃቃት እያደገም ይሄዳል
ይላሉ። በአጠቃላይ ይህ የጥንታዊያን ህንዶች ዐስተሳሰብ
ለልዩ ዲበ-አካል ምናባዊ ምስል የማየት አስተምህሮ መሠረት
ነው ማለት ይቻላል። ከዲበ-አካል ሃይማኖት መስፋፋት በኋላ

239
የአማልክቱ ዐዋጅ

“በተመስጦ”253 ወይም ምናባዊ ምስልን በተደጋጋሚ ማየት


የህንዶች ብቻ ሳይወሰን ዓለም አቀፋዊ ልምምድ በመሆን
ሊስፋፋ ችሏል።

ገና ከጅምሩ ዲበ-አካላዊው ሃይማኖት ዓለም አቀፋዊነት


ምልከታ እንደ ነበረው ሞስሊ ሲውዲንበርግን በመጥቀስ
ሲገልጹ “ሲውዲንበርግ ዓለማቀፋዊነት ያለው ዐስተሳሰብ
ነበር የሚያራምደው። ሁሉም ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች
የራሳቸው የሆነ መለኮታዊ የሥራ ድርሻና ዐላማ አላቸው
ብሎ ያምናል።”254 በማለት አጣቅሰዋል። በዚህም
ዓለማቀፋዊ ዐስተሳሰብ ምክንያት ከዲቫይን ሳይንስ በስተቀር
ሁሉም የዲበ-አካል ሃይማኖት ቅርንጫፎች ምንም ዐይነት
የእምነት ዶግማ ወይም ወጥ መርሖ የላቸውም። ይሁን እንጂ
ዲቫይን ሳይንስም ቢሆን ሁሉም ሃይማኖቶች ትክክል
እንደሆኑ ያምናል።

ዶክተር አንቶኒ ይህንን አንድነት ሲገልጡ በሃይማኖት፣


በፊሎዞፊና በሳይንስ መኻል ያለው ልዩነት ትምህርት
የሚሰጡበት መንገድ ብቻ ነው ይላሉ። “ሃይማኖት ፊሎዞፊና
ሳይንስ በመጨረሻ ላይ ሁሉም በመላለም ውስጥ አንድ ኀይል

253
ተመስጦ፦ የሩቅ ምስራቅ ኃይማኖቶች ልምምድ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ አእምሮ
ማሰብ አቁሞ እስኪደነዝዝ ወይም እስኪፈዝ ድረስ ዐሳብን አንድ ነገር ላይ ብቻ
በማድረግ ሦስተኛውን ዓይን የማሰራት ጥበብ ነው።
254
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P,62).

240
ጆንሰን እጅጉ

እንዳለና እኛም ከዛ ኀይል ጋር አንድ እንደምንሆን በራሳቸው


መንገድ ያስተምራሉ። እያንዳንዳችንም ስለዚህ ኀይል
የራሳችን የሆነ ግላዊ አገላለጥ ነው ያለን።”255 ብለዋል።
ይህም ዓለም አቀፋዊነት አካሄድ ዲበ-አካላዊውን ሃይማኖት
ሁሉንም አቃፊ እንዲሆንና እንዲገዝፍ አግዞታል።

ከዚህም ጠንካራ እውነትነት ከሌለው ዓለማቀፋዊ የልዩ ዲበ-


አካል ቅርፅ ማውጫ ሞልድ ለጸሎት ከሰጠው መልክ የተነሣ፤
ዲበ-አካላዊው ሃይማኖት በማናቸውም ሃይማኖቶች ውስጥ
የሚደረጉትን የተመስጦ ወይም የጸሎት ልምምዶች በአንድ
መነጽር ይመለከታል። እንደ አስተሳሰቡ ከሆነ በሁሉም
እምነቶች ውስጥ የሚደረግ ጸሎት ወይንም ተመስጦ አንድ
ዐይነትና ልዩነት የሌላው ነው።

በአጠቃላይ አስተሳሰቡ ሰፊ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን


ያገኘበት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት። አንደኛው
ምክንያት ምናባዊ ምስልን በዐይነ ኅሊና የመመልከት
ልምምድ በብዙ ኃይማኖተኞች፣ ኢ-አማኞችና አሊያም
ፓንቴይዝም256 እምነቶች ውስጥ የተለመደ መሆን መቻሉና
እንደ ጸሎት የሚቆጠር ልምምድ መሆኑ ሲሆን። ሁለተኛው
255
Anthony, R. Beyond Positive Thinking. (2004 p,26).
256
ፓንቴይም፦ የሩቅ ምስራቅ እምነት ሲሆን ፓንቴይስቶች አምላክ በሁሉም
ውስጥ አለ ሁሉም አምላክ ነው ብለው ያምናሉ።

241
የአማልክቱ ዐዋጅ

ደግሞ ምናባዊ ምስልን ማየት እንደ ጸሎት ከመቆጠሩም


ባሻገር “የመልስ” ቁልፍ እንደሆነ ተደርጎ በሰፊው በዲበ-አካል
ሃይማኖት “አማልክት” ይሁን በእምነት ቃል “አማልክት”
የተሰጠ ትምህርት በመሆኑ ነው። በአጠቃላይ በምናባዊ ዕይታ
ወይንም በተመስጦ ኀይል የጸሎት ምላሽን መፈለግ
ከሂንዱይዝም እስከ ዲበ-አካላዊው ሃይማኖት፤ ከእስልምና
እስከ ክርስትና ባሉ እምነቶች ውስጥ የሚታይ ወጥ ልምምድ
ነው ማለት ይቻላል። ሐንክ ሐነግራፍ ይህንን መሰል ልምምድ
ሲገልጹ፦ “ከባዕድ ወይም ከሴጣናዊ እምነት ወደጥንቆላ
የተደረገ ሽግግር።”257 ብለውታል። ከዚህ ቀጥሎ ይህ የጥንቆላ
ልምምድ የሚተገበርባቸውን መንገዶች ዘርዘር አድርገን
እናያለን።
የዐይነ ኅሊና ሕግ
እንደ ዲበ-አካል ሃይማኖት ከሆነ ጸሎት የሚመለሰው በዐይነ
ኅሊና ዐቅም ነው። እንደ ትምህርቱ ይህንን ማድረግ ከባድ
አይደለም። ምክንያቱም አዕምሮ እንደ ማግኔት የሰው ልጅ
የሚፈልገውን ነገር ማለትም ሐብትም ይሁን ጤንነት
የመሳብና የመሰብሰብ ተፈጥሮአዊ ዐቅም አለው የሚል
እምነት አለ። መርፊ አር ይህንን ሲያስቀምጥ “የሰዎች ጸሎት
የሚመለስበትን መንገድ የማመን ጉዳይ ብቻ አይደለም።
257
Hank Hanegraaff. Christianity in Crisis: 21st Century (438).

242
ጆንሰን እጅጉ

የጸሎት መልስ ውጤት የሚፈጸመው የእየአንዳንዱ ሰው


ስውር ሕሊና ከአዕምሮ ክፍል ለደረሰው ትዕዛዝ ለሕሊና መልስ
ሲሰጥ ነው።”258 ብሏል። ይህ ብዙዎቻችን ከባዶ ፍልስፍና
ያልዘለለ ቅዥት መስሎ ቢታየንም የሚገርመው ነገር ብዙዎች
በዚህ የአእምሮ ስሌት በመጠቀማቸው የስኬትና የተአምራት
ሰዎች መሆን እንደቻሉ በማሳመን ተከታይ አፍርተዋል።
ለምሳሌ ማይለስ ሞንሮይ How to become a Leader. Break
away from your Struggling Mind Set ከሚለው ጹሑፉ
በመውሰድ አዶናይ መጽሔት እንዳስነበበው የሚከተለውን
ብሏል፦

አሁን ካለህበት የተለየ መኖር ትፈልጋለህ?


የዐስተሳሰብህን ሁኔታ ለውጠው። ሰዎች ካሉበት ከፍ
ያለማለታቸው ምስጢር በአስተሳሰባቸው ላይ
የተሠራው ግብታዊ እምነት ምክንያት ነው። ሕይወትህ
በምታስበው ልክ ነው የሚወሰነው። እየነገሩኳችሁ
ያለሁት የእኔ የስኬት ምስጥር እዚህ ነጥብ ላይ ነው
ያለው። ወለል ላይ ከመተኛት አንስቶ በራሴ
አውሮፕላን እንድበር ያደረገኝ ምስጥር ይህ ነው። ማን
እንደምትሆኑ እራሳችሁን ቀይራችሁ ስታስቡ ነው።
የአስተሳሰባችሁን ክፍል እንዴት እንሚሰራ አሠራሩን
ተረዱ። 259
258
Murphy, J. The Power of Your Subconscious Mind. (P. 5).
259
አዶናይ መጽሔት። ቁጥር 3። (ገጽ 18)።

243
የአማልክቱ ዐዋጅ

ማይልስ ይህን ይበል እንጂ የሐብቱ ምክንያት በተለያየ ሥልት


ይሰበስብ የነበረው ገንዘብ እንደሆነ የአደባባይ ምስጥር ነው።
ምናልባትም ይህ አቀራረብ የሐብት ምንጭ ጥያቄን እንዳይነሳ
ለማድረግ ይጠቅም ይሆናል። ግለሰቡ እደተለየ ዐቅል ባለቤት
እንዲቆጠር በማድረግም በተከታዮቹ የሚመለክ አማልክት
ያደርገዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በአድማጩ ላይ የሚያሳድረው
የሥነ-ልቦና ጫናና የማኅበራዊ ሕይወት እረብሻ ቀላል
አይደለም። ትምህርቱን የሚጋቱ ወገኖች የዐሳባቸውንኀይል
ተጠቅመው ስኬት ማማ ላይ ለመውጣት ለረጅም ዐመት
እንዲጥሩና ዘመናቸውን በከንቱ እንዲጨርሱ ያደርጋቸዋል።

የሂንዱ እምነት ተከታይ ሮሪ ሻሃንም እንዲሁ ለዐስተሳሰብ


ከፍተኛ ቦታ ሰጥቷል። አዕምሮአችንና እምነታችን እንዴት
አብረው በመስራት ነገሮችን እውን እንደሚያደርጉ ይናገራል።
ይህንንም ሲያስረዳ፦ “የምናምነው ነገር ሁሉ እውን ይሆናል።
ስናምን ወደ ህይወታችን እንዲከሰት እንጋብዘዋለን
ምክንያቱም ስናምን በሐሳባችን ላይ ያለውን ነገር ወደ
ህይወታችን እውን እንዲሆን ጠራነው ማለት ነው።”
ይላል።260 እንደ ሻሃን አገላለጥ እምነት የሚያርፈው የአዕምሮ
ዐሳብ ላይ ነው። ይሄም የሚሆንበት ምክንያት የታሰበውን ነገር

260
Mind Power, Connecting with Power of your Unconscious Mind. (2011. P, 11).

244
ጆንሰን እጅጉ

እውን የሚያደርገው “ኀይል” የሚፈልቀው በእምነት ስለሆነ


ነው። ሻሃን ይህንን ሲያብራራ “የምናምነው ማናቸውም ነገር
ሁሉ እውን ይሆናል። በሐሳባችን የተመለከትነውን ሁሉ ወደ
ህይወታችን እንጋብዘዋለን። ህይወታችንን በምንፈልገው ነገር
ለመሙላት ቀላሉ ስሌት የምንፈልገውን ነገር በመመልከት
ወደ ህይወታችን መጥራት ነው።”261ብሏል። እንደ ሻሃን
አስተምህሮ በዐይነ ኅሊና መመልከት የእምሮን ኀይል
ለመጠቀም ቁልፍ ሆኖ ያገለግላል።

በተጨማሪም በሻሃን አገላለጥ የምንፈልገው ነገር በገሃዱ


ዓለም እንዲገለጥ ለማድረግ “ከመጥራት” ወይም በእምነት
ቃል “አማልክት” አገላለጥ “ከማወጅ” በዐይነ ኅሊና መመልከት
ይቀድማል። ልብ ማለት ያለብን እንደእርሱ ይህ ኀይል ልዕለ
ፈቃድ ያለው አካል ባለቤት የለውም። ስለዚህ የምንፈልገውን
ነገር እንዲሆን ለማድረግ እራሳችን በመወሰንና በእምነታችን
አማካኝነት በዓይነ ሕሊናችን በማየት በአእምሯችን ላይ
ያለውን ዐሳብ በመቈጣጠር እንገዛዋለን ማለት ነው። እንደ
ሻሃን ከሆነ ይህን ለማድረግ እምነት አስፈላጊ ሲሆን እንደርሱ
‘እምነት’ በዕውቀት ላይ የሚመሠረትን የተስፋ እርግጥኝነት
ሳይሆን በዐይነ ኅሊና ልምምድ ምክንያት በአዕምሮ ውስጥ
የሚፈጠር የስሜት እድገት ነው።

261
Ibid., (p, 30).

245
የአማልክቱ ዐዋጅ

በሌላ በኩል ግን የሰው ልጅ የማሰብ፣ ያሰበውን በአዕምሮው


የማየት፣ አካል የሚለብስበትን መንገድ የማቀድ እና በቅደም
ተከተል የማስቀመጥ፤ በቦታና በጊዜ ውስጥ የታለመውን ነገር
በእጆቹ የመሥራት ተፈጥሯዊ ክህሎት አለው። ይህ ማለት
ግን እንደ ሻሃን ያሉ ጸሓፍት እንደሚነግሩን በተዘጋ ቤት ውስጥ
ቁጭ ብሎ በምኞት ዓለም ውስጥ ብቅ ጥልቅ ከማለት ጋር
የሚያገናኘው ነገር የለም።

ስሜትን የማሳደግ ሕግ
እንደ ልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ግንዛቤ ከሆነ እምነትና ስሜት
የተለያየ ትርጉም የላቸውም። “የስኬት ህጎች” የተባለው
መጽሐፍ ጸሓፊ ናፖሊን ሂል የቃል ዐዋጅ የሚሠራበትን
ሥርዐት ሲያብራራ፦

በከፍተኛ ፍላጎት ያሰብነውን መልካምም ይሁን


መጥፎ ነገር ስንናገር ከእምነት ጋር ይቀላቀላል ስውር
ሕሊናችን ተጽዕኖ ያርፍበትና ተቀብሎ ወደ
ጭብጥነት ወይም ወደ ገሃድ በሂደት ይለውጠዋል።
የሐሳባችን፣ የዕቅዳችን ወይም የትልምችን የንግግር
ዕርግብግቢት ወደ ስውር ሕሊናችን እሲኪደርስ ድረስ
በየቀኑ ደጋግመን መናገር አለብን። እምነትን ስሜትን
እና ዐሳብን መቀላቀል በመለማመድ ፍጹም

246
ጆንሰን እጅጉ

እንሆናለን። ይሄም ማለት የአእምሯችን ኀይል


በማደግና በሌሎች አዕምሮ ላይ ተጽዕኖ በማድረግ
አነቃቂ ባለቤት ወይም ጌታ እስከመሆን ያድጋል።
የሆንነው ነገር ሁሉ የሆንነው ስውር ሕሊናችን
ከከባቢያችን ወስዶ በዘገበው የንግግር ርግብግቢት
ምክንያት ነው። ራሳችንን ነፃ ማውጣትና የራሳችንን
ዓለም ሥርዐት መገንባት አለብን። 262

ብሏል። ይህ የዲበ-አካል ሃይማኖት ጽንሰ-ዐሳብ የሰውን


አዕምሮ የክስተት ሁሉ ባለቤት ወይም ምክንያት ያደርጋል።
የዚህም ዋነኛ ዐላማ የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር የክስተት
ባለቤትነት ግንዛቤ በማውጣት በመለኮት ላይ ያለውን እምነት
ማጥፋት ነው። በዚህም ዐስተሳሰብ የክስተት ባለቤት አዕምሮ
ቢሆንም ማስፈጸሚያ ዋና አካል ግን የቃል ኀይል ወይም
ተደጋጋሚ የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ነው። ናፖሊዮን ሂል የሰውን
አዕምሮ የመለኮት ቁራጭ አድረጎ ከልዕለ መለኮት የመፍጠር
ብቃት ጋር አንድ አድርጎ ሲመለከት በተጨማሪም ለስሜት፣
ለእምነት፣ ለዐሳብ እና ለኅሩይ ቃል ዐዋጅም ከፍተኛ ቦታ
ሰጥቷቸዋል።

እምነትን ወይም ስሜትን የሚያሳድገውም ደጋግሞ በማወጅ


ወይም በማዘዝ እንደሆነ ሂል ይናገራል። ይህንንም ሲገልጽ

262
Napolen Hill, Think and Growth. (1938, Pp, 54-56).

247
የአማልክቱ ዐዋጅ

“ትዕዛዝን ደጋግሞ በመናገር ማስረገጥ ስውር የአዕምሮአችን


ክፍል የእምነታችንን ፍቃደ ስሜት የሚያሳድግ ብቸኛ መንገድ
ነው።”263 ብሏል። በዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ውስጥ
እምነት በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ቢሆንም ልዩ እምነት
መሆኑን ልብ ማለት ይገባል። ምክንያቱም መጽሐፍ
ቅዱሳዊው እምነት በአዕምሮ ውስጥ በቃላት ዐዋጅ
አማካኝነት የሚፈጠር የስሜት ዕድገት ሳይሆን በዕውቀት ላይ
የተመሰረተ የተስፋ ርግጠኝነት ነው።“እምነትም ተስፋ
ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውንም ነገር
የሚያስረዳ ነው።”(ዕብ.11፡1)። በተጨማሪም ማንም ልዩ
እምነት ቢኖረው እንኳ ስጦታ እንጂ የስሜቱ ወይም የዕይታው
ማደግ እንዳልሆነ ማወቅ አለበት። “ለአንዱም በዚያው
መንፈስ እምነት፣ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ
ስጦታ፣ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ።” (1 ቆሮ.12:9)።

በወንጌል አማኞች ቤተ-እምነት መድረኮች ላይ ከፍተኛ ዝናና


ተቀባይነትን ካገኙ ሸጋ ከሚባሉ ዘማሪዎች አንዱ ነው።
በቅርቡ አጋጠሚ በሚመስል ሁኔታ ድንገት መንገድ አገናኘንና
መጨዋወት ጀመርን። ከብዙ መግባባት በኋላ መድረክ ላይ ገና
ሲታይ ጉባኤ እንደሚደምቅለት በዐዎንታዊ ስሜት
አነሳሁለት። ልክነህ በሚል ጭንቅላቱን ወደ ላይና ወደ ታች

263
Hill, N., Think and Grow Rich. (1937. p. 53).

248
ጆንሰን እጅጉ

እያወዛወዘ የደስታ ፈገግታ ለገሰኝ። ከዘማሪው ጋር ኮሮና


በአገራችን ከገባ ከአንድ ወር በኋላ ነበር የተገናኘነው።
አቢያተክርስቲያናት ተዘግተዋል፤ የመድረክ አገልግሎቶች
ተቋርጠዋል። ይህ ወጣት ዘማሪ አገልግሎቱ በስሜት ላይ
ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር እንደሆነ አውቃለሁ። ከዚህም የተነሳ
ታዲያ በቤተክርስቲያን መዘጋት ምክንያት የዝማሬ አገልግሎት
የተቋረጠበት የከተማችን ወጣት ሕይወት ያሳስበኛል።
አብሮት የሚቆይና የችግሩን ጊዜ የሚያልፍበት ዐቅም
የሚፈጥርለት ዕውቀት በዚሁ ዘማሪ አገልግሎት አማካኝነት
መሰነቁን እንደምጠራጠር አንስቼ ለውይይት ጋበዝኩት።
ያለኝንም አስተያየት እንደሚከተለው ሰነዘርኩ፦

ሕዝቡ ላንተ ያለው አቀባበልና ያለህም ሰፊ


የአገልግሎት መድረክ ብዙ ሕዝብ እየተከተለህ
እንዳለ ምስክር ነው። በተለይ ደግሞ ወጣቶች
ይከተሉሀል። ይሁን እንጂ የወጣቶቹን ስሜት እጅግ
በሚኮረኩር የሙዚቃ ስልትህና የቃል ዐዋጅ ስንኞችህ
እንደምታነሳሳ፤ ከዚህም የተነሣ ትውልዱን ስሜቱን
ብቻ በማሳደግ ስሜታዊ እንዳደረከው ትታማለህ።
በማስተዋልና በዕውቀት ወጣቱ ከአምላኩ ጋር
እንዲገናኝና እንዲጸልይ አላስለመድከውም። ‘ያ’
የጉባኤ ልምድ ደግሞ አቢያተክርስቲያናት በኮቪድ
19 ምክንያት በመዘጋታቸው ተቋርጧል። ስሜትን

249
የአማልክቱ ዐዋጅ

ማነቃቃት በአንድ በኩል ጥሩ ቢሆንም፤ በሌላ በኩል


ደግሞ ትውልዱ ክርስትናውን ሳይጥል የሚሻገርበት
የዕውቀትና የማስተዋል ዐቅምን ለመፍጠር ስሜትን
በማረጋጋት በዕውቀትና በማስተዋል ባለማሳደግህ
ተጠያቂ የምትሆን አይመስልህም?

ዘማሪውም ሲመልስ፦

“ታውቃለህ ብዙ ዘማሪዎች አሜሪካ ሄደው በየነዳጅ


ማደያው ነዳጅ ቀጂ ያደረግናቸው የተሰጡንን
ስጦታዎች ማድነቅ ስለማንችል ነው። ተቺዎች ነን።
ያስጨፍራል ነው የሚሉኝ አውቃለሁ! እንግሊዘኛው
ዳዊትም በአምላኩ ፊት ደነሰ ነው የሚለው። ገና
አስጨፍራለሁ!”

ይህንን ካለ በኋላ በመቀጠል ደግሞ ከወገቡ በታች ያለውን


የኋላ ክፍሉን እያወዛወዘ፦ “የናጄሪያዎቹን ዳንስ ታውቃለህ?
ገና እርሱን ሁሉ ነው አምጥቼ በመድረክ ላይ የምደንሰው
ወይም የማስደንሰው።” በማለት መለሰልኝ።

ዘማሪው እጅግ እየተሰላቸ የኢትዮጵያዊያን ባሕርይ ተቺ


እንደሆነ ይናገር እንጂ እርሱ እራሱ ወደ መድረክ ሲወጣ
በጉባኤያችን የሚሰማው ፉጨትና ጭብጨባ የሚያሳየው
አድናቂዎች መሆናችንን ነው። ትችትን መፀየፉም

250
ጆንሰን እጅጉ

ያመለከተኝ ትችት የሚጎለንን ነገር በመጠቆም የምንሠራበት


ጥበብ እንደሆነ አለማወቁን ወይም አለመልመዱን ነው።
እልህና ስሜት በተቀላቀለበት ምላሹ የውይይት መድረካችንን
ቢደረግምብኝም “ዘማሪዎች ምንም መተቸት የለባቸውም
ነው የምትለኝ?” በማለት ትንሽ ቦታ እንዲሰጠኝ ለማድረግ
ብሞክርም።

ቀጣዩ ምላሽ ግን፦ “አንድ ሰው እኔን ዝም ብሎ ከሜዳ ላይ


ተነስቶ መተቸት አይችልም። ለመተቸት መጀመሪያ ከእኔ ጋር
ኅብረት መፍጠርና ግንኙነት መመስረት አለበት። እንደዛ
ዐይነት ሰው ቢተቸኝ እሰማዋለሁ” በማለት የትችት መድረክ
ለማግኘት በዋዛ እንደማይቻልና የእርሱ ጓደኛ መሆን
እንዳለብኝ በመተረክ መልሶ ደረገመብኝ። የጓደኝነት
ግብዣውም ቢሆን ከልብ አይደለም። ምክንያቱም እንደ
እነርሱ ከሆነ ጓደኝነት ለመፍጠር ዝነኝነትን ይጠይቃል።

እንደእዚህ ወጣት ዘማሪ ሁሉም ዘማሪዎች ባይባልም


አብዛኛዎቹ ዘማሪዎች እና የእምነት እንቅስቃሴ “አማልክት”
ስሜት ላይ ብቻ በመሥራታቸው ምንም የጥፋተኝነት ስሜት
አይሰማቸውም። ለዚህም ምክንያቱ ከፍ ያለ የስሜት
መነቃቃትን ከፍ እንዳለ እምነት ስለሚቆጥሩት ነው። ስሜት
በሚቆሰቁሱ የሙዚቃ መሳሪያ በታጀቡ ዝማሬዎቻቸውና
የኅሩይ ቃል ዐዋጃቸው ላይ ጠንክረው ለመሥራት ቀን ከለሊት

251
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይለፋሉ። ይህ አልበቃ ብሏቸውም የተጠኑ ልሳኖችና


ድምጾችን ያክሉበታል። ሰፊ አድማጭ ያላቸውን ስሜት
አቀጣጣይ የዘፈን ዜማዎች ለማጥናት እንኳ አይመለሱም።
ወደ ጣራ ለመዝለል እንዲችሉ እስፖርት ይሠራሉ። እነዚህ
መሪዎች በእውነት ላይ የተመሰረተን ዕውቀት ወደ ጐን
አድርገው የስሜት መነቃቃትን ለማሳደግ እንዲህ የሚደክሙት
ምናልባት እምነትን እንደ ስሜት ማደግ የሚመለከተውን
የዲበ-አካል ሃይማኖትን ምክር እየተከተሉ ስለሆነ ይሆን? ብሎ
መጠየቅም ብልህነት ነው።

በርግጥ ስሜትን ከስብዕናችን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ


ባይቻልም እምነትን በቀጥታ ከስሜት ጋር ማገናኘትና
አጥብቆ በስሜት መነቃቃት ላይ መሥራት ጸያፍ ነው።
በእንደዚህ ዓይነቱ አካሄድ በማነቃቃት የሕዝብን ስሜት
ማሳደግ ይቻል ይሆናል። ይሁን እንጂ የሕዝቡን ስሜት ከፍ
በማድረግ አሳድገን ስናበቃ ግን ከትንሽ ቆይታ በኋላ ስሜት
እንደ ጤዛ መጥፋቱና መቀዝቀዙ የማይቀር ስለሆነ ለጊዜው
እምነት መስሎን የነበረው ነገር ከስሜት ጋር አብሮ ይተንና
የምንጨብጠው ፍሬ ሳይሆን ንፋስ ይሆናል። ተካልኝ ይህንን
ሲያስረዳ፦ “ስሜት ከመረዳት ባነሰ ነገር ከተቆሰቆሰ፣ ለረጅም
ጊዜ ሳይነድ ፈጥኖ ይከስማል።” ብሏል።264

264
የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! (ገጽ፣ 251)።

252
ጆንሰን እጅጉ

እምነት ግን ተስፋ ሰጪውን በማወቅ ላይ የተመሰረተ የታወቀ


ተስፋ እርግጠኝነት ነው እንጂ የስሜት መጋጋል አይደለም።
ተካልኝ ሚዛናዊነት በጎደላቸው ዝማሬዎች ላይ ያለውን ስጋት
ሲገልጽ፣ “ስሜታችንን የሚያሞቁ ነገር ግን አእምሯችንን
የሚያስተኙ ከሆኑ ያከስሩናል” ብሏል።265 የመልካም ዐዋጅ
ቃል የቀላቀለ ለስሜት የቀረበ ሙዚቃ ስሜት ሊነካና ደስታን
በመፍጠር ሊያዘልል ይችል ይሆናል። ነገር ግን ተካልኝ
እንዳለው እንዲህ ዓይነቱ በዕውቀት ላይ ያልተመሰረተ
መነቃቃት አደጋ አለው።

ማወቅ የሚገባን ነገር ቢኖር ስሜት በዕውቀት ሲነካ ወደ


ውሳኔና ድርጊት ይወስዳል። ስሜት ግን ዕውቀትን በመንካት
እምነትን መፍጠር አይችልም። ለምሳሌ፦ በዮሐንስ ወንጌል
ምዕራፍ ሥድስት ላይ እንደተዘገበው ኢየሱስ ያደረገውን
ተኣምር በመመልከታቸው ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው
ያሉት አይሁድ በተመለከቱት ተዓምር ስሜታቸው ስለተነካ
ነበር ቁ.14። ኢየሱስ ግን ይህንን ሲመለከት ጥሏቸው ሄዷል
ቁ.15። ይሁን እንጂ ኋላ ላይ ኢየሱስን ፈልገው
አግኝተውታል። ቁ.25። ኢየሱስ የመለሰላቸው መልስ
የስሜታቸው መነካት ወይም ጣራ መንካት ወደ እምነት
እንዳላደረሳቸው ጠቋሚ ነው። ቁ.29።

265
lbid. (p, 249).

253
የአማልክቱ ዐዋጅ

የኢየሱስ ከፊታቸው በመሰወር ቆም ብለው የሚያስቡበትን


ጊዜ ቢሰጣቸውም እነርሱ ግን ከስሜት ወጥተው ወደ
ማስተዋል አልደረሱም ነበር። ኢየሱስ ከስሜት አውጥቶ ወደ
ዕውቀት ሊያደርሳቸው አምርሮ ቢተጋላቸውም ወደ
ሚፈልገው እውነት አልደረሱም። (ከቁ.29-40)። ስለዚህ
ከኢየሱስ ልንማርና ዝማሬዎች ስሜትን ከማናር ይልቅ
ሰሚውን ወደ እውነት በጥበብ የሚመሩና ትክክለኛውን ዐውድ
በጠበቀ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት የተቃኙ እንዲሆኑ ልንሠራ
ይገባል። እንዲህ ሲሆን ዝማሬዎች ስሜትን አግነው
ከማውጣት ይልቅ ማስተዋልንና እምነትን የሚያሳድጉ
ስለሚሆኑ እንደ ቀድሞዎቹ ዝማሬዎች መንፈሳዊ ዐቅምን
የመፍጠር ተጽዕኗቸው ከፍተኛ ይሆናል።

የማየትና መሠየት ሕግ
የሰው ልጅ የአዕምሮውን ኀይል በመጠቀም ወደ ሚፈልገው
ስኬት እንደሚደርስ የዲበ-አካል ሃይማኖት “አማልክት”
ያምናሉ። በአንድ ወቅት አንዲት የወንጌል አማኞች
ቤተክርስቲያን አባል የሆነች እህት ቆንጆ ልጅ መውለድ
የምትፈልግ እናት የቆንጆ ህፃን ፎቶ ምስል መኝታ ክፍሏ
ብትለጥፍና ሁል ጊዜ ብትመለከተው ምኞቷ እንደሚሳካላት
በርግጠኝነት ሞገተችኝ። ይህንንም ስታስረዳኝ እህቷ

254
ጆንሰን እጅጉ

በመኝታ ክፍሏ የምታምር ቀይ መኪና እንደሰቀለችና ሁል


ጊዜ እንደምታያት ነገረችኝ።

ይህንን በማድረጓም እህቴ በቅርብ ጊዜ ቀይ መኪና


እንደሚኖራት እርግጠኛ ነች ትላለች። ይህንን እንዴት
በርግጠኝነት ልታምን እንደቻለች ስትነግረኝ ገና ልጅ ሆነን
“እህቴ ብዙ ጊዜ የምትፈልገውን ልብስ ዐይነት ፎቶ ወይም
ሥዕል እስከ ከለሩ ደብተሯ ላይ ትለጥፋለች። ብዙም ሳይቆይ
ታዲያ ያንኑ ዐይነት ቀለምና ዲዛይን ያለው ልብስ አባታችን
ገዝቶላት ይመጣ ነበር።” በማለት አስረዳችኝ። የሚገርመው
ነገር ታዲያ ይህቺ እህት መለኮትን ለምኖ ከመቀበል በዓይነ
ሕሊናዋ ሕግ የምትፈልገውን ነገር በመሳብ የምታምን
ቢሆንም ክርስቲያን አማኝ መሆኗንም ደግሞ ቅንጣት ያኽል
አለመጠራጠሯ ነው። ኢየሱስ ለሁለት ጌቶች መገዛት
እንደማይቻል ቢያስጠነቅቅም፤ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ
ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አይቻልም ቢባልም፤ አንደዚህች
እህት ታዲያ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መርሖ እና ዲበ-
አካላዊውን መርሖ አንድ ላይ አድርገው ለመጠቀም
የሚሞክሩ ብዙ ናቸው። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ይህንን
ማድረግ ሚዛናዊነት ነው። እምነታቸውንም በሳይንሳዊ
መንገድ እንዳስረገጡ እንጂ እርባና ከሌለው ፍልስፍና ጋር
እንደቀላቀሉ አያስቡም። በዚህ ሥልት ተጠቅመው ሰዎች

255
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚፈልጉትን ገንዘብ ተገደው እንዲሰጧቸው ማድረግ


እንደሚችሉ እንኳ ያስባሉ።

በዲበ-አካል ሃይማኖት አስተምህሮ መሠረት፤ የሰው ልጅ


ለፈውስም ይሁን ለማናቸውም ፍላጎቱ መሟላት
የሚያስፈልገው የአዕምሮውን ኀይል የሚሠራበትን መንገድ
ማወቅና መጠቀም ብቻ ነው። ሂል ይህንን ሲያብራራ፦

የሰው አዕምሮ ኀይል ነው። ልክ እንደ ባትሪ ድንጋይ


ነው። ከመላለም ኀይልን ይቀበላል ደግሞም ወደ
መላለም ኀይል ይለቃል። ሁለት ባትሪ ድንጋዪች
በመነካካት ብዙ ኀይል እንደሚያመነጩ ሁለት
ሰዎችም የአዕምሮ መነካካት በመፍጠር የነፍስ
ኀይል የገዥ አዕምሮ መስመር መዘርጋት ይችላሉ።
266

ብሏል። እንደ እርሱ ከሆነ አዕምሮ የክስተት መነሾ ገዥነትን


የሚወስደው የመላለምን ኀይል መቀበያና መልቀቂያ የተፈጥሮ
አውታር ስላለው ሲሆን ከሌላው ሰው አዕምሮ ጋርም
በመተባበር መሥራት ይችላል። እንደዚሁ ሁሉ የእምነት
እንቅስቃሴ አማልክትም አዕምሮ ከሚሠራባቸው መንገዶች
አንዱ፤ የአዕምሮን የማየት ዐቅም መጠቀም እንደሆነ
ያምናሉ። ለምሳሌ መጋቢ ተዘራ እሰከ ርዕሱ ከዮንግ ቾ
266
Hill, N., Think and Grow Rich. (1937, Pp, 177-178).

256
ጆንሰን እጅጉ

በተወሰደ “ሬማና ሎጎስ” በተሰኘ ትምህርታቸው የዐይነ ኅሊና


ሕግ እንዴት እንደሚሠራ ስሜትን በሚያሳድግ አቀራረባቸው
ሲያስረዱ “ኀይልህ ትኩረት ወደ ምታደርግበት ነገር ይሄዳል”
ካሉ በኋላ በመቀጠል፤ ያዕቆብ ሽመልመሌ በትር ለበጎቹ
አሳይቶ እንዲጸንሱ ማድረግ እንደቻለ ይጠቅሳሉ።(ዘፍ.30፡
39)። ይህን ተከትሎም “የምታየው ነገር ያድጋል፣ አብዝተህ
የምትመለከተው ነገር ይበዛል! ችግርህን አሊያም ችግርህን
ሊቀይረው የሚችለውን ሬማ ቃል የማየት ምርጫ አለህ!!!…
በረከትህን እየው! አሸናፊነትን እየው! ሳትደክም እየው!”267
ይላሉ።

እንደ እውነቱ ከሆነ መነሻ ያደረጉት የያዕቆብ ታሪክ የዕይታን


ሕግ ሥነ-መለኮት ለመመስረት በቂ አይደለም። ምክንያቱም
የአንድ ታሪክ ክስተት ወቅታዊ የማይደገም ተዓምር ብቻ
ሊሆን ይችላልና ነው። ደግሞም መጋቢው ሰዎች እንጂ
የያዕቆብ በጎች እንዳልሆንን ያስተዋሉ አይመስለኝም። በዛ
ላይ ደግሞ ለያዕቆብ የሰራ በጎቹ የጸነሱበት ሽመልመሌ በትር
መርሖ በመሆን ለይስሐቅ ለዮሴፍ ወይም ለእስራኤል ነቢያትና
ሕዝብ የሠራበት ቦታም እንደሌለ ቢረዱ መልካም በሆነ ነበር።
መጋቢው ግን ስሜታችንን እያባበሉ እንደ በጎች

267
ተዘራ ያሬድ። ሬማና ሎጎስ (2008፣ 113)::

257
የአማልክቱ ዐዋጅ

የምንፈልገውን ቁሳቁስ የፎቶ ምስል በራስጌያችን ላይ ሰቅለን


እንድንጎመጅ ሊያበረታቱን ይሞክራሉ።

በርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ትምህርት እንደ ዮንግ ቾ ያሉ


መሪዎች መሠረት ለማሲያዝ ሲሉ የጌታ ቃል በመጀመሪያ
ሎጎስ ኋላም ሬማ መሆን በመጨረሻም መታወጅ አለበት
ይላሉ።268 ለአብርሃም እግዚአብሔር የልጆቹን ብዛት
ለማስረዳት ክዋክብትን ማሣየቱን በማንሳት ትምህርታቸውን
ለማያያዝ ይሞክራሉ። ይሁን እንጂ ነገሩ ለየቅል ነው።
እግዚአብሔር አብርሃምን ክዋክብት ያስቆጠረው የዕይታውን
ኀይል ተጠቅሞ ክዋክብቱን ወደ መሬት እንዲስባቸው
አልነበረም። ማለቴ ‘ዘርህ እንዲሁ ይሆናል’ እንደተባለ ምድር
በአብርሃም ዘር እንድትሞላ ያደረገው የአብርሃም ዕይታ
ዐቅም ሳይሆን የእግዚአብሔር ሉዐላዊ ችሎታ ነው።(ዘፍ.15፡
5-6)። የዘፍጥረት መጽሐፍ ጸሓፊም ዮንግ ቾ እንደሚሉት
አብርሃም ክዋክብቶችን ከተመለከተ በኋላ የዕይታውን ኀይል
ለመጠቀም ሲል በዐይነ ሕሊናው የልጆቹን ፊት እንደ ሰዓሊ
እየሣለ መሳቅ እንደጀመረ በፍጹም አይነግረንም። ከዚህ ይልቅ
ግን ‘አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ’ በማለት አብረሃም
በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነት ከፍ እንዳለ ይነግረናል
(ዘፍ.15፡6)። በተጨማሪም እሳቸው ይህንኑ የዕይታ ሕግ

268
የእግዚአብሔር አድራሻ። (2020፣171)።

258
ጆንሰን እጅጉ

ለማስረጽ ብዙዎቹ የእምነት ቃል መምህራን ሳይነካኩ


የማያልፉትን269 የፍጥረትን ልደት በተለመደው መልኩ
ያነሣሉ።

እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ሲፈጥር ምድር ባዶ


ነበረች ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበር። ነገር ግን
እግዚአብሔር ባዶነትን አይቶ ባዶነትን አልተናገረም
መሆንን ማፍራትን ብርሃን ይሁን አለ። ብርሃን ይሁን
የሚለው ቃል እራሱ እንዴት ደስ ይላል! አንዳንድ
ጊዜ በንግግራችን ውስጥ የሚገለጠው ጨለማ
የእይታችን ውጤት ነው። ዓይናችን (ዕይታችን)
ታማሚ መሆኑን ጠቋሚ ነው። 270

በዚህ ንግግራቸው ሊጠቁሙን የፈለጉት የዕይታ ኀይል ምን


ያኽል ጨለማን እንደሚያበራ ወይም ነገሮችን እንደሚለውጥ
ነው። ለስኬታችንም በመጓጓት ለዕይታችን ጥንቃቄ ማድረግ
እንዳለብን ያሣስባሉ። ይህንንም ለማስረዳት ‘ብርሃን ይሁን’
የሚለው የእግዚአብሔር ንግግር ‘የእግዚአብሔር የዕይታ
ውጤት ነው’ የሚያሰኝ ከበድ ያለ የጨለመ መንገድ
ተጉዘዋል። መጋቢው በግልጽ ባይሉንም ነገር ግን ገለጻቸውን
ተከትለን እግዚአብሔር በዓይኑ የተመለከተውን ጨለማ ትቶ
ወይም ክዶ ብርሃንን በዐይነ ሕሊናው ተመለከተ፤ ከዛም ያንን
269
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲ። (2013፣10)።
270
ተዘራ ያሬድ። ሬማና ሎጎስ። (2008፣ ከገጽ. 105-107)::

259
የአማልክቱ ዐዋጅ

የተመለከተውን ብርሃን ጠራው፤ ወይም ተናገረ ብንል እንደ


እሳቸው ከሆነ ትክክል ነው የምንሆነው። ይሁን እንጂ ይህ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው የዲበ-አካል ሃይማኖት
ወይም የቡድሃ ፍልስፍና እንደሆነ የእምነት ቃል አማልዕክቱ
ሊያምኑልን ይገባል።

የመንፈስ መግነጢስ ሕግ
የልዩ ዲበ-አካል አማልክት የሰበት ሕግ የስኬት ቁልፍ እንደሆነ
ያምናሉ። እንደ እነርሱ ከሆነ የመግነጢስ ሕግ የሚሠራው
አንድን ነገር ደጋግሞ በማሰብ ነው። ለምሳሌ ብንጠቅስ
“ምስጢሩ” የሚለው የሮንዳ ባርን መጽሐፍ
እንደሚያስደንቀው እና ሕይወቱን እንደ ለወጠው የሚናገረው
ኢትዮጵያዊው የልዩ ዲበ-አካል አማልክት ዳዊት ድሪምስ
ይህንን ሲያስረዳ፦ “በመግኒጢስ ሕግ መሠረት ማንኛውም
ደጋግመህ የምታስበው አዎንታዊም ይሁን ዐሉታዊ ዐሳብ
ተመልሶ ወደ ራስህ ተስቦ ይመጣል።”271 ይላል። በመቀጠልም
በብዙ ሺ ቅጂ እየተቸበቸበ ባለው በዚሁ “ትልቅ ሕልም አለኝ”
በሚለው መጽሐፉ ዘርን እንደ ዐሳብ፤ አዕምሮን ደግሞ እንደ
እርሻ በመመልከት አንባቢዎቹን ለዘርና ለአጨዳ ያዘጋጃል።
ድብቁ አእምሯችን ማንኛውንም የምንዘራበትን ዘር

271
ዳዊት ድሪምስ፤ ትልቅ ሕልም አለኝ። (ገጽ. 2012‚ 334) ።

260
ጆንሰን እጅጉ

የማብቀል ዐቅም አለው በማለት በህይወታችን ያገኘነው


መልካምም ይሁን ክፉ ነገር የሐሳባችን ውጤት ነው ይላል።272

የእምነት ቃል “አማልክት” ይህን ከመሰለው የልዩ ዲበ-አካል


“አማልክት” ዐስተሳሰብ ባይርቁም፤ የመግነጢስ ሕግን
የባለቤትነት ድርሻ ከአዕምሮ ይልቅ ለመንፈስ መስጠታቸው
የተለመደ አካሄድ ነው። ለዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት
‘ሰው መንፈሱ ከእግዚአብሔር ስለተወለደ እንደ እግዚአብሔር
የመመልከት ዐቅም ያለው ስኬት መሳብ የሚችለው መንፈሱ
ነው።’ የሚል ነው። በመሠረቱ ሰው መንፈስ ነው ለማለት
መነሻ የሚያደርጉትን ዮሐንሰ ወንጌልን ያየን እንደሆን፤
‘ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው’ ማለቱ ሥጋንና ነፍስን
እየካደ ወይም እያሳነሰ ነው ብሎ ለማሰብ አይቻም።(ዮሐ.3፡
6)። ምክንያቱም ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ሲያወራለት
በተደጋጋሚ የሚያነሳው ሰውነትን ሳይከፋፍል ‘ሰው’ በማለት
ነው።

ይሁን እንጂ ከአይሁዳዊው መምህር ጋር ስለ ዳግም መወለድ


መግባባት ስላልቻሉ ሰውነትን በሁለት በመክፈል “ሥጋ” እና
“መንፈስ” በማለት ያስረዳዋል። ያም ቢሆን ኢየሱስ ይህንን
አቀራረብ የተጠቀመው ወደ መንግስተ-ሰማይ የመግባትንና
የዳግም መወለድን አስፈላጊነት ለማስረዳት ሊጠቀምበት
272
Ibdi, (p, 309).

261
የአማልክቱ ዐዋጅ

ስለወደደ ብቻ ነው እንጂ የሰውን ተፈጥሮ ለያይቶ


ሊያስተምር ወይም ‘ሰው መንፈስ ነው’ ለማለት አልነበረም።
ስኬትና ድልን በመስበክ የሚታወቁት ፓስተር ክሪስ ግን
መንፈስ የስኬት ምንጭ እንደሆነ ለማስተማር መንፈስን
ለይቶ ያነሣል። በትምህርቱም “እውነተኛ ሥኬት ከሰው
መንፈስ የሚወጣ ነው።”273 ብሏል። በዚህም መንፈስን
የስኬት ሁሉ ማከማቻ አድርጎ በማቅረቡ ከመግኒጢስ ሕግ
ትምህርት ጋር መተባበሩን ያሳሉ። ፓስተሩ በጹሁፉ ላይ
ከሚያነሳው ማብራሪያ ከታጀበበት ጥቅስና የቃለት ለውጥ
ወይም አቀራረብ በስተቀር ከቡዲህስቱ ሸሃንም ይሁን ከዲበ-
አካል ሃይማኖት አስተምህሮ ጋር ያላቸው ልዩነት ጠባብ ነው።

የቃል ኀይል እምነትም ይሁን የዐይነ ኅሊና ልምምድ የሰውን


ልጅ በልዕለ መለኮት ላይ ያለውን ተስፋና እምነት በቀላሉ
በማሟጠጥ ከአምላኩ ነጥሎ እንዴት እንደሚያስቀረው ልብ
ማለት ይገባል። እንደ ሸሃን ከሆነ አንድ ሰው ይህንን የአዕምሮ
ኀይል ልምምድ ተግባራዊ በሚያደርግበት ጊዜ ልዕለ አዕምሮን
በመቈጣጠር የራሱ አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለዚህም
ሌላ ሰሚ አምላክ ስለማያስፈልገው “አምላክ ለምኔ” ይሆናል።

ይህ በፓንቴይስቶቹ ላይ ሙሉ ለሙሉ ሠርቷል። የወንጌል


አማኞችንም ለመለኮት ያላቸውን የጋለ እምነት አቀዝቅዟል።
273
ክሪስ እና ኦኒታ ኦኪሎሚ፡ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲ (ጥር፣26፣2006) ።

262
ጆንሰን እጅጉ

በአንዳንድ አማኞች ላይ ሲንጸባረቅ የምንመለከተውም


‘ጸሎት ለምኔ?’ ዐይነት የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ወይም የልዩ ጸሎት
ልምምድ ወይም በመለኮት ላይ ጥገኛ የመሆን ስሜት
መጥፋት የዚህ ዓይነተኛ ማሳያ ነው። እነኝህ ወገኖች
በመለኮት ላይ ከመደገፍ ይልቅ በመሪዎቻቸው የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ ልምምድ ላይ መደገፍን ይመርጣሉ። ምክንያቱም
መሪዎቻቸው ፊሊሞር ያስተምር እንደነበረ ሁሉ እነሱም
የልምምዳቸው ውጤት ምክንያት ኢየሱስ በነበረበት የእምነት
ወይም የሕይወት ደረጃ ላይ መኖራቸው እንደሆነ ደጋግመው
በመናገር አሳምነዋቸልና ነው።

ይሁን እንጂ አገልጋይ በራሱ የሚፈልገውን ስኬት ወደ


እራሱም ሆነ ወደ የሚያገለግለው ሕዝብ የሚስብበት በዳግም
ልደት የተቀበለው ልዩ የዕይታ መብቃት እንዳለው ቅዱሳት
መጽሐፍት አያስተምሩም። በሌላ በኩል አገልጋዮች በብቃት
የሚያገለግሉበት ምሥጢር ከተሰጣቸው ጸጋና ኀይል የተነሣ
እንደሆነ በማያሻማ ሁኔታ ተጽፏል።

ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፣ እንደ እግዚአብሔር


ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፣ እግዚአብሔር
በሚሰጠኝ ኀይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ስልጣን
እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ

263
የአማልክቱ ዐዋጅ

ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር


ዘንድ፤ አሜን። (1 ጴጥ. 4፡11)።

ይህም ጸጋ የተሰጠበት ዐላማ አገልጋዮችን በማሳደግ ብጹዑ


ቅዱስ ለማድረግና ከሕዝቡ ኣርቆ ከፍታ ላይ ለብቻቸው
ለማስቀመጥ አይደለም። ይልቁንም ሕዝቡን ለማብቃት ነው።
“እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ
ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ
እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው።” (ቆላ.1፡28)። ጸጋው
ሕዝቡን ወደ ፍጹም ሙላት ለማድረስ ወይም አገልጋዩ
ከሕዝቡ ጋር አብሮ እንዲያድግ የሚሠራ ነው። አገልጋዩጋ ብቻ
የሚቀር፤ አገልጋዩን ለብቻ ነጥሎ ከፍ የሚያደርግና በሕዝቡ
ላይ ሁለንተናዊ ተጸዕኖ በማድረግ የማይፈስና የማያሳድግ ጸጋ
የመለኮት ሥጦታ አይደለም። ስለዚህ ነው ሐዋርያቱ ሁል ጊዜ
ሕዝቡ ሊቀበል ያለውን ጸጋ የሚያስተዋውቁት። “የመንፈስ
ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።” (ሐሥ.2፡18)። “ትጸኑ ዘንድ
መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና።”
(ሮሜ.1፡11)። “በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ
ስለ ፈሰሰ ተገረሙ።”(ሐሥ.10፡45)። . . . ወዘተ. የሚሉ
ተደጋጋሚ ጥቅሶች ይህንኑ የትኩረት አቅጣጫ ይጠቁማሉ።

በአጠቃላይ “የአዕምሮ መግኒጢስ ኀይል” ልምምድ ተፈጥሯዊ


ያይደለ አጋንታዊ የምትሃት ጥበብ ወይም ልምምድ ነው።

264
ጆንሰን እጅጉ

ይህንን አሰራር እንደ ጸጋ ማየትም ፈጽሞ ስሕተት ነው።


የእግዚአብሔር ጸጋ ሌሎችን የሚያሳድግ ተተኪዎችን
የሚያፈራ እንጂ የተወሰኑ አገልጋዩችን ብቻ በማግነን
በመድረክና በሕዝብ ኪስ ላይ የማንገስ ባሕርይ የለውም።

ሞኛ ሞኙ የቃል ዓለም
“የአፍህ ቃል ዐቅም አለው። ‘ከአፌ ቃል በኋላ ማንም አንዳች
አይጨምርም። እኔ ሁል ጊዜ እንደ ድግምት ነው የምደግመው
በላዬ ላይ።”274
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ

“የአማልክቱን” የቃል ዐዋጅ እና የዐይነ ሕሊና እምነትም ሆነ


ልምምድ ላጤነው ሰው መንፈሳዊው ዓለም ለቃልና ለዕይታ
ሕግ የተተወ ሊመስለው ይችላል። ተግዳሮቱ በክርስትና ላይ
ብቻ የተቃጣ ሳይሆን መለኮተን እንደ ፋብሪካ ማሽን ወይም
እንደ ሞኝ አባት ያስቆጠረ ነው። “አመልክቱ” መንፈሳዊ
ዓለም “ሞኝ አባት ልጆቹ ጭቃ ባቦኩበት እጆቻቸው ኮቱ ኪስ
ውስጥ ገብተው የሚፈልጉትን ሁሉ ሲወስዱ አያይም።”
እንደሚባለው መንፈሳዊው ዓለም በቃል ኀይል መጫወቻ
የሆነ ሞኛ ሞኝ እንደሆነ በግልጽ ሳይነግሩን በስውር
አግባብተውናል።

274
ዮናታን አክሊሉ። ማርሴል ቲቪ። በአፍህ ቃል ተያዝክ። (መጋቢት 26፣2020)።

265
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከዚህም የተነሣ “የእምነት ቃል አማልክቱ ጉባኤ” ሞኛ ሞኝ


አምላክ የሚመለክበት ወይንም ጭቃ ባቦኩበት እጃቸው ኪሱ
ዘው የሚሉ ህፃናት የሚቦርቁበት ጉባኤ ይመስላል። ሰባኪው
እያወጀ ሳለ ብድግ ብሎ ወደ መስባክ በመዘለል ከአፉ ላይ እንደ
ገብስ ቆሎ ዝግን ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። ይህም
የህዝቡ ስነ-ልቦና ተገደው በተሸጡ ጥቅሶች ትምህርት
እንደተያዘ ጠቋሚ ነው። ለምሳሌም ብናነሳ ዮናታን አክሊሉ
ሲናገር ‘በኢዮብ መጽሐፍ ላይ አንድ ደስ የሚለኝ ቃል አለ
‘ከአፌ ቃል በኋላ ማንም አንዳች አይጨምርም።’ በማለት
ጉባኤውን ሲያስደምም በዩቲዩብ ቻናሉ ላይ በተለቀቀው
ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ይታያል። ይሁን እንጂ ጥቅሱ
በ 1954 ቱ የአማርኛ ዕትም መጽሐፍ ቅዱስ ሲነበብ “ሰዎች
እኔን ሰምተው በትዕግሥት ተጠባበቁ፣ ምክሬንም ለማዳመጥ
ዝም አሉ። ከቃሌ በኋላ አንዳች አልመለሱም፤” (ኢዮ.29፡
22)። የሚል ሲሆን እርሱ እንደሚለው ግን የቃልን ዐቅም
የሚያሣይ ወይም ድግምት ዐይነት ልምምድን የሚያመለክት
ሳይሆን በክፍሉ ላይ ኢዮብ በበሽታ ከመመታቱና ከመደህየቱ
በፊት በሰዎች የነበረውን ተሰሚነትና ተቀባይነት ነው
የሚናገረው። ዮናታን ግን በበርካታ አድማጭ የመሰማት ዕድል
እንዳለው ሰው መጠንቀቅ ሲገባው ይህንን ያስተዋለ
አይመስልም። ከእዚህ ይልቅ ደግሞ ነባር የወንጌላውያን

266
ጆንሰን እጅጉ

አገልጋዮች ይህንን መሰሉን የቃል እምነት የጥቅስ ፍቺ መዛባት


ሲንጸባርቁ ማየት ግርምታ ይፈጥራል።

በአንድ ወቅት ነባር የወንጌል አማኞች ታዋቂ አገልጋይ የቃል


ዐዋጅን አስፈላጊነት ሲያስረግጥ “እርኩሳን መናፍስት እንኳ
መንፈሳዊው ዓለም የቃል ዓለም መሆኑን ስለሚያውቁ
በተደጋጋሚ ቃል በማውጣት ወይም በድግምት ነው
የሚሰሩት።” እንዳለኝ አስታውሳለሁ። ይህ ወዳጄ ክርስቲያን
ደጋሚ ሊያደርገኝ ቢያግባባኝም አልተሳካለትም ነበር። እንደ
እርሱ አባባል መንፈሳዊው ዓለም ለሴይጣናዊያን “ቃለ ዐዋጅ”
እንኳ የሚታዘዝና የሚገዛ እነርሱ እንደፈለጉ የሚያደርጉት
ሞኛ ሞኝ ነው።

እንደዚህ ዓይነቱን መላምት መከተል አምላክን ለመደገፍ እንደ


መጣር ወይም አምላክን እንደ መካድ ሊቆጠር የሚችል ነው።
አንድ ጥያቄ ላንሳ ደግፉኝ የሚል ደካማ እንዴት አምላክ
መሆን ይችላል? የተስፋው ቃል እንዲፈጸም የኛን ደጋግሞ
መናገር ይፈልጋል የሚለው የኪኒየን ባዶ ጩኸትስ
እግዚአብሔርን ያኮስሰዋል ብለን ከምንቃወመው “እርዱኝ
እረዳችኋለሁ ብሏል” ከሚለው ያገራችንስ ተረት ተረት
ልዩነቱ ምንድነው?

267
የአማልክቱ ዐዋጅ

“የእምነት ቃል አማልክት” ለጥርጣሬ ቦታ የላቸውም!


እምነታቸውም ይሁን ዕውቀታቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ
እንደደረሰ ይቆጥራሉ። ለልምምዳቸውም ያላቸው ስሜት
ሞቅ ያለ ነው! ከፍተኛ መተማመንና ድፍረት ይታይባቸዋል፤
ሐብታም ነኝ ወይም አላረጅም ለማለት ላለባበሳቸውም ሆነ
ለጸጉራቸው ቀለም እጅግ ይጨነቃሉ፤ “አዲስ ፍጥረት” የሆነ
ሰው ከማያምኑቱ ይልቅ የቃሉ እና የዓይነ ሕሊናው ኀይል ገዥ
እንደሆነ ታምነዋል። በሌላ በኩል ደግሞ እነርሱ እንደሚሉት፤
እነርሱ በደረሱበት “ከፍታ” (ሌቭል) አልደረሰም ብለው
ከሚያስቡት ምዕመንም ይሁን አገልጋይ ጋር ወዳጅነትም
ይሁን ኀብረት ማድረግ ቅር ይላቸዋል ወይም አክብሮትና
ፍቅር ያጥራቸዋል።

በሥነ-መለኮት ትምህርት ልዕለ መለኮት እግዚአብሔር


የማይደረስበት አቻ የሌለው ሆኖ መንፈሳዊውን ዓለም ሆነ
ቁሳዊውን ዓለም በእጁ የያዘ ኃያል እንደሆነ ማወቅ ቀደዳሚ
ነው። ምጡቅ ዐሳቢ ወይንም ሁሉን ዐዋቂ (omniscence)
እንደሆነ ማወቅም መሠረታዊ ነው። በእርግጥ “ከአማልክቱ”
ጥቂቶቹም ሆኑ ከወንጌል አማኞች አብዛኛዎቹ ይህን የሥነ-
መለኮት ግንዛቤ በግልጽ እንደማይክዱ ዕሙን ነው። ይሁን
እንጂ እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ በግልጽ ይናገራሉ
በሥራቸው ግን ይክዱታል እንደተባለ ሆኖባቸዋል።

268
ጆንሰን እጅጉ

ልምምዳቸውም ሆነ ትምህርታቸው የእግዚአብሔርን ሁሉን


ዐዋቂነት እና የሰውን ልጆች በዕውቀት መወሰንና ለመለኮትነት
አለመብቃት ሊያመለክት በተገባ ነበር ባይ ነኝ። በኢሳያስ አፍ
እግዚአብሔር ጣዖታት አምላክነትን አያሟሉም በማለት
የሚሞግትበት አንዱ ባዶነታቸውን አለማወቃቸው ሲሆን
የእራሱን አምላክነት ያስረዳበት አንዱ ሙላት ደግሞ
አስቀድሞ የማወቅ ችሎታውን ነው።

አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱ ጀምሬ


አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ
ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ
የለም ማንንም አላውቅም፤ የተቀረጸውን ምስል
የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፣ የወደዱትም ነገር
አይረባቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያዩምና
አያውቁም፤ ስለዚህ ያፍራሉ። (ኢሳ.44፡8-9)።

ሐናም እንዲሁ የእግዚአብሔርን ዐዋቂነት


ስትናገር፦“አትታበዩ፣ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር
ዐዋቂ ነውና፣ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን
ነውና።”(1 ሳሙ.2፡3)። ንጉሱ ዳዊትም ልጁ ሰለሞን
የመለኮትን ዐዋቂነት ልብ እንዲል ሲመክረው፦ “እግዚአብሔር
ልብን ሁሉ ይመረምራልና፣ የነፍስንም ዐሳብ ሁሉ
ያውቃልና።” (1 ዜና.28፡9)። ከሩቅ የሚመለከት ምጡቅ

269
የአማልክቱ ዐዋጅ

ዐዋቂነቱን መዝሙረኛው ሲናገር፦ “እግዚአብሔር ከፍ ያለ


ነውና ወደ ችግረኞችም ይመለከታልና፤ ትዕቢተኞችንም ከሩቅ
ያውቃል።” (መዝ.138፡6)። ይላል።

እንግዲህ የመለኮትን ምጡቅ ዐዋቂነት የሚጠቁሙ ይህንን


የሚመስሉ ብዙ ታሪኮችና ጥቅሶች ቢኖሩም አማልክቱ
መለኮትን ሞኛ ሞኝ ማስመሰላቸውን ለመኮነን እነኝህ
ጥቅሶች በቂ ናቸው። መለኮት ኪሱን ከፍጥረቱ መጠበቅ
የሚችልበት ዕውቀት የጎደለው፤ ፍጥረቱን በፍቃደ ዕውቀቱ
የማይቆጣር አይደለም። ስለዚህም ማንም የፈለገውን ነገር
ከመንፈሳዊው ዓለም እጁን እየዘረጋ ከኪሱ የሚነጥቀው ሞኛ
ሞኝ አባት አይደለም! ይህ ካልሆነና ፍጥረቱን የማይገዛና
የማይቆጣጠር ከሆነ ግን እንዴት አምላክ ልንለው እንችላለን?

በተመሳሳይ ሁኔታ ለክርስትና መሠረት የሆኑ የአዲስ ኪዳን


መጽሐፍትም ይህንን እውነት ያንጸባርቃሉ። “እግዚአብሔር
ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።” (1 ዮሐ.3፡
20)። “. . . ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ
ነኝ ይላል።” (ራዕ.1፡8)። በአጠቃላይ የክርስትና ሥነ-መለኮት
የሚያስተምረው ስለ አንድ ኀይል ሳይሆን ስለ አካላዊ መለኮት
ነው። ሁሉም ዐይነት ሃይማኖትም ሆነ ማንኛውም ዐይነት
ጸሎት ልዩነት የሌለው አንድ ዐይነት እንደሆነም ክርስትና
አይስማማም። በክርስትና ሥነ-መለኮት መሠረት የጸሎት

270
ጆንሰን እጅጉ

መመለስ ምክንያት የምናብ ዕይታ ወይም የቃል ዐዋጅ ሳይሆን


በመለኮት የመሰማትና ይሁንታ የማግኘት ጉዳይ ነው።
“በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች
ብንለምን ይሰማናል።” (1 ዩሐ.5፡14)። ከዚህ ጋር መስማማት
የሌለው የጸላዮች ሥብስብም ይሁን ጸሎት መሣይ ነገርም
ይሁን ዐዋጅ ቀልድ ነው።

እንደ ክርስትና ሥነ-መለኮት የተመስጦ ትርጉምን ያየን


እንደሆን አንድን ነገር በሚገባ መረዳት ወይም በጥልቀት
መገንዘብ ነው እንጂ አዕምሮን በማፍዘዝ የሚሆን የሦስተኛው
ዐይን መከፈት አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ “ተመስጦ
መጣብኝ” ሲል አዕምሮው እንደደነዘዘ እየነገረን ሳይሆን
ማስተዋሉን ከፍ የሚያደርግ የመለኮት ጸጋ እንደተቆጣጠረው
እየነገረን ነው። (ሐሥ.22፡17-22)። አዕምሮው ሥራ እንዳላቆመ
እዛው ክፍል፤ በቍጥር አሥራ ዘጠኝና ሃያ ላይ በተመስጦ
ውስጥ እያለ የእራሱንና የእስጢፋኖስን የኋላ ታሪክ እያሰበና
እያስታወሰ የሚናገረውን ማየት ይቻላል። ጳውሎስ በሌላ
ቦታም “የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ” በማለት ሲናገር ሦስተኛ
ዐይን እንዳለን እየጠቆመን ሳይሆን አእምሯችሁ ሲረዳ ወይም
ሲገነዘብ ለማለት ነው። ህዝቅኤልም እንዲሁ ልብን ከሰው
ልጅ የማሰብ ዐቅም ጋር አጣምሮ አስቀምጦታል።(ሐሥ.12፡7,
ኤፌ.1:18, ህዝ.11፡5)።

271
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጠቃላይ ተመስጦ ላቅ ወዳለ ማስተዋል በመንፈስ ቅዱስ


ጸጋ መግባት ነው። ልዕለ መለኮት እግዚአብሔርም በክሱት
ፍቃዱ ጸሎትን የሚሰማና የሚመልስ አምላክ ነው። ጸሎትም
ሊመለስ የሚችለው የኀጢአት መሥዋዕት ሆኖ በሰው ልጅ እና
በመለኮት መኻል ያለውን ጥል በማፍረስ የሰውን ልጅ ድነት
በፈጸመው በኢየሱስ ላይ ባለ እምነት በስሙ የተደረገ እንደሆነ
ብቻ ነው።(ዮሐ.14፡13)። ማንኛውም ጸሎት በኢየሱስ ደም
የሚሆን የኀጢአት ሥርየት በሌለበት ተመላሽ አይደለም።
የድነት ወይም የዕርቅ ወይም የንስሓ ጸሎትም ከማንኛውም
ጸሎት መቅደም ያለበተም በዚሁ ምክንያት ነው።

ማጠቃለያ
በዚህ ክፍል ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር የተዳበለው የዲበ-አካል
ሃይማኖት እርሾ የወንጌላውያንን ክርስትና ለመበረዝ እያደረገ
ያለውን የሥነ-መለኮት ግብግብ ተመልክተናል። ይህ ደግሞ የዲበ-
አካል ሃይማኖትን የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ሥነ-መለኮት አውቀን መፀየፍ
እንድንችል ያግዘናል። የእምነት እንቅስቃሴን ባዕድና ቅይጥ ሥነ-
መለኮት ለይተን በማውገዝ የክርርስትናን ርቱዕ ሥነ-መለኮት
ለማስቀጠል እንድንተጋ ያስችለናል። ባለማወቅ ወይም በየዋህነት
የዲበ-አካል ሃይማኖት ሕልውና የሆነውን የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ጽንሰ-
ዐሳብ እያገለገልን ያለን ወገኖች በዚህ ደረጃ በተብራራ አቀራረብ
መሠረቱን መመልከታችን እንድንደነግጥና እንድንመለስ ያግዘናል።

272
ጆንሰን እጅጉ

እርሾውን አውጥተ አንጠፍጥፈን ብንደፋው እውነት እላችኋለሁ


የክርስቶስን ትምህርቶች ለመረዳት ተቸግረን መልዕክት የሌለው
መልዕክተኛ አንሆንም። ስለዚህ የዲበ-አካል ሃይማኖትን ፈጥነን
እንዳንላቀቅ ‘ምን እናስተምራለን ታዲያ?’ የሚል ስጋት እያታለለ
አያዘግየን። በዲበ-አካል ሃይማኖት የተቃኙ አውታሮችን በጣጥሰን
ወዲያ እንጣላቸው።

በዚህ ክፍል ያየነውን ብርሃን ለማወፈር በቀጣዩ ክፍል አራት ላይ


ደግሞ ይኽው የዲበ-አካል ሃይማኖት እርሾ ምን ያክል በመካከላችን
እየሰረገ እንዳለና ክርስቲያናዊ አመለካከታችንና መንፈሳዊ
ልምምዳችንን ለመግራት እየታገለን እንደሆነ እንመለከታለን።
እንደ ወንጌላዊ አማኝነቴም የትግሉን አሳሳቢነትና በየአንዳንዳችን
ፊት ያለውን አደጋ መገንዘብ እንድንችል የግል ገጠመኜንና ልምዴን
ጭምር በመተረክ አብራራለሁ።

የምዕራፍ አራት ግንዛቤ ማስጨበጫ ጥያቄዎች


1. የምናባዊ ዕይታ ሕግ ፍልስፍና የዲበ-አካልን ሃይማኖት
እንዲገዝፍና ዓለም አቀፋዊ መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ችሏል
ብለህ ታምናለህ? ለምን?
2. እንደ ሸሃን ትምህርት ከሆነ እምነት በዓይነ ሕሊና ዕይታ
ምክንያት የሚፈጠር የስሜት ዕድገት ነው። ከክርስትና
ትምህርት አንፃር ሲታይ አዘውትሮ ስሜት ላይ የመሥራትና
ስኬት ላይ ለመድረስ ማወጅ ከእምነት ሊቆጠር ይቸላል?
3. አንተ የምታቃቸው ክርስቲያኖች በማየትና መጎምጀት ሕግም
ይሁን በመንፈስ መግነጢስ ሕግ የጸሎት መልስ ወይም ስኬት

273
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንዳገኙ ሲነገሩ ሰምተህ ታውቃለህ? እንዲህ ዓይነቱን ልምምድ


ከክርስትና አስተምህሮ አንፃር እንዴት ትመለከተዋለህ?
4. የእምነት ቃል አማልክት መንፈሳዊ ዓለም የሚሠራበት ቁልፍ
የዐዋጅ ቃል እንደሆነ ያምናሉ። ይህ ትምህርት መጽሐፍ
ቅዱሳዊ መሠረት አለው ብለህ ታስባለህ? አብራራ።
5. የእምነት እንቅስቃሴን ቅይጥና ባዕድ ትምህርት ለማምከን ምን
መደረግ አለበት ትላለህ? በነጥብ አስቀምጥ።

ክፍል ፫
የዐዋጅ ቃል ልምምድ

274
ጆንሰን እጅጉ

  

ምዕራፍ 5

የዐዋጁ ጥቅል

275
የአማልክቱ ዐዋጅ

ቀኑ ትልቅ ቀን እንደሆነ ገና ከብርድ ልብስ ሳልወጣ የነበረው


የስሜቴ መነቃቃት ማለዳ ላይ ዐወጀልኝ። ስለዚህም
የሚመጥን ጥሩ አለባበስ መልበስ እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩት።
ኮቶቼን በአልጋዬ ላይ በተንኳቸው። ይህኛው ኮት ከዚህኛው
ሸሚዝ ጋር ይሄዳል በማለት አማረጥኩ። ጫማውንም
እንደዛው። መቼ እኔ ብቻ ባለቤቴ ገኒ ትልቋ ልጄ ሄርሚ፣
መካከለኛው ፋዬና ትንሹ ማክም እንዲሁ እየተዋከቡ ነው።
ሸሚዜን ተኩሼ ሳልጨርስ መብራቱ ድርግም አለ። “ወይ ጣጣ
ጸጉሬን ሳልጨርስ” የገኒ ድምፅ ነበር። “ዳዲ ቶሎ በል እንጂ
የልጆች ቦታ እኮ አናገኝም።” ሔርሚዬ ናት። “ዳድ አዲሱን
ጫማ አያደርጉልኝም።” ትንሹ ማክ ነበር። “ዳዲ የትኛውን
ጫማ ላድርግ?” የፋዬ ጥያቄ ነው። “በቃ! በቃ!
እንዳይረፍድብን ቶሎ እንውጣ።” የቤተሰቡን ትርምስ
ለማስቆም የተሰነዘረ የእኔ ድንጋጌ ነበር። ልክ ነበርኩ
ምክንያቱም መቀመጫ ቦታ ለማግኘት ፈጥነን መውጣት
ነበረብን።

ወደ ጸሎት ቤቱ እንደተጠጋን የበዓል ስሜት የሚያስተጋባ


አለባበስ የለበሱ እንደኛው የዕለቱ ታዳሚ የሆኑ ሦስት
ወጣቶች የሚያካፋውን የመስከረም ዝናብ ለመሸሽ ሲሯሯጡ
ተመለከትኩ። ብዙም ሳይቈይ ድንገት አንደኛው

276
ጆንሰን እጅጉ

ከመካከላቸው ወደ ኋላው እረብ አለ። አብረው ካሉት ጓደኞቹ


አንደኛው ፈጥኖ እጁን አፈፍ አድርጎ ቢያነሳውም አንደኛው
ግን ባለበት ቦታ ቆሞ በግርምት ተንከተከተ። ሣቁ ሁኔታውን
ጫወታ አስመሰለው። ጓደኛውን ያነሣው ፈርጣማ ወጣት
የባልንጀራው ቀልድ ተጋባበት መሰለኝ ፊቱ ላይ የተረጨውን
ጮረቃ እየጠራረገለት “አይዞህ ይህ ዐመት ብትወድቅም እንኳ
የምትነሣበት የከፍታ ዐመትህ ነው!” በማለት ቀለደበት።
በወጣቶቹ ፌዝ መቆጣቴን የሚያሣብቅ ሰላምታ በጨፈገገ
ፊት ሰጥቻቸው አልፈናቸው ሄድን። ወደ ጉባኤው ደጃፍ
ደርሰን ስንመለከት የተፈጠረው የበዓል ድማም ደስታ
ጫረብን። ምነው ሁሌ እንዲህ በሆነ? ያስብላል። አዳዲስ
መብራቶች በርተዋል። መድረኩ በጌጣ ጌጥ አብዷል። ሰባኪያን
ቦታቸውን ይዘዋል።

ዲያቆናቱ ከበር ተቀብለው ወደፊት በመምራት ፊት ለፊት


ከተቀመጡቱ ጋር ቀላቀሉኝ። በሁሉም ሰው ፊት ላይ አዲሱን
ዓመታዊ ዐዋጅ መልዕክት የመጠባበቅ ስሜት ይነበባል።
የሚለቀቀው ቃል በአሮጌው ዐመት እኛን ያደከመን ኀይል
የሚሰበርበት በአዲሱ ዐመት ያለውን አዲስ ነገር ደግሞ
ለመናጠቅ የምንዘረጋበት እንደሚሆን ቆጥረን በእምነትም
በስሜትም ለመቀበል ተጋግለናል። አገልጋዩም ይህንን
ለማሳካት በማሰብ ሲደክም አድሯልና፣ እንቅልፍ በዓይኑ የዞረ

277
የአማልክቱ ዐዋጅ

አይመስልም። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1990 ዎቹ ወዲህ


እንዲህ ዓይነቱን በዓል በተደጋጋሚ አድርገናል። አምናም
እዚም እዛም ቤተክርስቲያን እንዲሁ ነበር። ካቻምናም
እንዲሁ ዐልፏል። ሁሌ በየዓመቱ እንዲህ ለማሳካት ጠብ
እርግፍ እንላለን። ስብከታችንን፣ ጸሎታችንንና ዝማሬያችንን
ከየት እንደመጣ ወይም ማን እንደሰጠን በውል የማናቀው
ክፉም መልካምም ብለን ለመፈረጅ የሚቸግረን ቅርፅ
ማውጫ ሞልድ275 ነገር ይዘውረዋል።

አምና ለበዓሉ ድምቀት መድረኩን በዲዛይን በማስዋቡ ላይ


በሰፊው ተሳትፌአለሁ። ዘንድሮ ደግሞ የዐዋጁን ጥቅል
በመያዝ ወደ መድረክ በመውጣት ባህላዊ አልባሳትን ከለበሱ
መዘምራን ጋር ተቀላቅያለሁ። ዓመታዊ መልዕክት ለማወጅ
የተዘጋጀው ፈጣን ሰባኪ ማይክ ጨብጧል። የሙዚቃው
መሳሪያና የሕዝቡ “ይከፈት” የሚል ጩኸት በጆሮዬ ሲደርስ
ልቤን እየኮረኮረ በደስታ ፈገግ ያስብለኛል። የማይታየውን
መንፈሳዊ ሀልዎት ለመዳሰስ ደግሞ ዓይኔን ጨፈን አድርጌ
እፈልገዋለሁ። ሲጠፋብኝ፤ በመንፈስ ማሽተት ሲያቅተኝ
መልሼ ዐይኔን እከፍታለሁ። ሕዝቡን ቃኘት ሳደርግ ሁሉም
ሰላም. . . ሰላም ነው። የአብዛኛው ሕዝብ ጕጕትና ደስታ
275
መልክ ማውጫ (Molds)፦ ለምሳሌ በጫማ ሥራ የሚያገለግል ሲሆን በሰው
እግር ቅርፅ ከጠንካራ ብረት የተሰራ ይሆንና የራሱ ዲዛይንና መልክ ይኖረዋል።
የሚቀርብለትን የጫማ ሶል ግብአትም ይሁን የቆዳ ልባስ በራሱ መልክ እየቀረጸና
እያተመ የተፈለገውን ያኽል ማውጣት ይችላል።

278
ጆንሰን እጅጉ

ቀልብ ይገዛል። ምን ነካኝ ታዲያ በማለት ራሴን ወቅስና ልቤን


በዐይኔ ከማየውና በጆሮዬ ከምሰማው ጋር ለማስታርቅ
እታገላለሁ።

የመጨረሻው ድምፅ እስኪሰማ ድረስ የውስጥ ትግሉ ቀጠለ።


የመጨረሻው ዕንቢልታ ተነፋ፤ “ሊከፈት ነው. . . ፣ ሊከፈት
ነው. . . ፣ ተከፈተ!” የያዝኩትን ጥቅል ተረተርኩት። ሰባኪው
እንደተለመደው በያዘው ማይክ ዓመታዊ ቃሉን ዐወጀ።
ድብልቅ ልቅ ያለ ጭፈራና አምልኮ፤ ልጅ ዐዋቂው ሁሉ ሽቅብ
መዝለል ጀመረ። አብሬ ለመዝለል ሞከርኩ ይሁን እንጂ
ብዙም አልዘለቅኩበትም። በእንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ ሌላው
አማራጭ በልሳን መጸለይ ነው፤ እርሱም ቢሆን
አልተሳካልኝም፤ ቃላቱ አንደበቴ ላይ ተንቀዋለሉብኝ።
ቢሆንልኝና ለድምቀቱ ተረረር ባደርገው በወደድኩ ነበር።
በማስመሰል ለተካኑ ግብዞች የተጠኑ እንግዳ ቃላትን በልሳን
ፋንታ መድገም መንፈሳዊነትን ማንጸባረቂያ እንደሆነ ይቈጠር
የለ? ይሁን እንጂ በመንፈስ መነዳት ካልሆነ የእውነት
አይሆንምና ጸጋውን የተቀበልኩበትን መንገድ የሚያውቀው
ልቤ ይሞግተኛል።

አንዳንዱ ግን ካለምንም ችግር ወደ ቆምንበት መድረክ ሁለት


እጁን እየዘረጋ እፍስ! እፍስ! ዝግን! ያደርጋል፣ ሌላው
ይጮኻል፣ ሌላው ያፏጫል፣ ሌላው ጣራ ጣራ እየተመለከትክ

279
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይስቃል፣ ሌላው ደግሞ ጸጥ ብሎ ይንበረከካል፣ ጥቂት


ወጣቶች ደግሞ እርስ በርስ እየተንሾካሾኩ ይሳሳቃሉ።
ምንድነው የሚያንሾካሽኩት? በጭራሽ አይገባም። መድረኩ
“ዐዋጅ. . .ዐዋጅ” በሚል ድምጽ ይነዋወጣል። እንዲህ
ድብልቅልቅ ባለ ጉባኤ ታዲያ የአንዳንዶቻችንን መቀዛቀዝ
ምን ይሉታል? ለምንስ ስሜታችን ይዋዥቅብናል? ዳሩ ወደን
አይደለም አንዳች ነገር ዐቅላችንን ዐግቶት ነው።
አንዳንዶቻችን አምና የወሰድነው የዐዋጅ ቃል መልዕክት
ዓመቱን ሙሉ አብሮን እንዲዘልቅ በመኪናና በቤት ዕቃችን
ላይ እንኳ ሳይቀር ብንለጥፍና ብንሰቅልም ገና ሳምንት
ሳይሞላው ከልባችን ስለወረደብን ከዓምናው ዐዋጅ ጋር
ለምን? በሚል ጥያቄ በቍጣ ተፋጠናል።

ሌሎቻችን ደግሞ በአንዱ ቤተ-እምነት ዐዋጅ አልረካ ብለን


በየአጥቢያው እየዞርን የሰበሰብናቸው ሥጋ ያልለበሱ የዐዋጅ
ቃሎች እንደ 7D ፊልም በዓይናችን ፊት እየተሽከረከሩ ተራ
በተራ የልባችንን ጕልበት ያብረከርኩታል። እንደ ልማዳችን
ታዲያ አዕምሯችን የሚያቀርበውን የመረጃ መዝገብ ደጋግመን
በመዝጋትና በመካድ የዘንድሮው ዐዋጅ ራቁት ተሰላፊ
አይደለምና ‘በእምነት ተቀበል!’ እያልን ቃል አውጥተን
በራሳችል ላይ ብንጮኽም ሕሊናችንን ማሸነፍ ያቅተናል።
በመጨረሻም ራሳችንን ደካማ፤ የማንጠግብ የዐዋጅ የቃል

280
ጆንሰን እጅጉ

ርኃብተኞች እንደሆንን እንቈጥራለን። ከዚህ ካለፍን ደግሞ


“ዘንድሮ ሰባኪው በጭራሽ ልክ አይደለም! ፣ ወርዷል!” ፣
አልጸለየም! ፣ ዘማሪው ነው ያበላሸበት!” በማለት
እናጉተመትማለን። እውነቱ ሲገለጥ ግን ችግሩ የሰባኪው
መውረድ ወይም አለመጸለይ ወይም ዘማሪው የፈጠረው
እንቅፋት አይደለም። ችግሩ እየተከተልን ያለነው መርሖ
ወይም ልምድ ከመለኮት ያልተሰጠን፣ መጽሐፍ ቅዱስን
ከከተቡት ቅዱሳን ያልተማርነው፣ ከክርስትና ያፈነገጠ
እንግዳና መሠረቱ የተበላሸ ፍርክስክስ ማሣኒ ልምምድ መሆኑ
ነው።

የእምነት ቃል ልምምድ
የዐዋጅ የቃል ልምምድ “የእምነት ቃል” የሚል መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ስም ሰጥተን ድግስ ደግሰን እስከምንታደምና ወደ
መድረክ ብቅ ለሚሉ “አዲሶቹ” ምሣሌ እስክንሆንላቸው ድረስ
በመኻላችን ሥር ሰዷል። ይብስ “አዳዲሶቹ” ወደ ቋሚ የዕለት
ልማድ እስኪያሳድጉትና የአገልግሎታቸው ማዕከል
እስኪያደርጉት ድረስ ምክኒያት የሆንላቸው እኛው እራሳችን
ነባርነን የምንለው ነን። በሌላ በኩል ጥቂት አማኞች በዚሁ
እንግዳ ልምምድ ግራ ተጋብተው እግራቸውን ከዘረጋነው
የአጥቢያ ጉባኤ እየሰበሰቡ ነው። ይሁን እንጂ እንደተለመደው
የኀላፊነትን ቃና በጣ አንደበታችን “ጠፋህ” ወይም “ጠፋሽ”

281
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከማለት በቀር የጠፉበትን ምክንያት መርምረን በማየት


የምንፈይድላቸው ነገር የለም።

ሌሎች በእኛና “በአዳዲሶቹ” መኻል ያለው ልዩነት ቀጥኖባቸው


ቢቀላቀሏቸውም ምላሻችን ዝምታ ሆኗል። አሉን
በምንላቸው “ስኬቶች” ዕይታችን ስላነሰ ልባችንን ጸጸት
አያውቀውም። “ኤፍሬም እንግዶች ጕልበቱን በሉት፣ እርሱም
አላወቀም፤ ሽበትም ወጣበት፣ እርሱም አላወቀም።” እንደተባለ
ሆኖብናል።(ሆሴ.7፡9)። ይሁን እንጂ እኛ ወንጌላውያን
አቢያተክርስቲያናት ከምንምና ከመቼውም ጊዜ ይልቅ
ዐይናችንን ከፍተን መንገዳችንን ልንመለከትና እየሆነ ላለው
ጥፋት ኀላፊነት ልንወስድ ይገባል። በዚህ መጽሐፍ በስፋት
ለመመርመር የተሞከረው የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና
አዕማድ አካል የሆነው “የእምነት ቃል” ሞልድ የክርስትናን
ሥነ-መለኮታዊ ዕይታ እንዴት እንደጨመደደ ነው።

እኛምጋ ይሁን “አዲሶቹጋ” አማልክታዊ የቃል ዐዋጅ ሥነ-


መለኮት በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የብልጽግና፣ የድነት፣
የፈውስ፣ የተአምራትና የትንቢት አገልግሎት ማዕከል
እንዲሆን ተደርጓል። ይህንን “የአማልክት” መልክ ማውጫ
እያስከተለ ያለውን ጥፋት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተ-
እምነት መሪዎች ልብ ያሉት አይመስልም። ምንም እንኳ

282
ጆንሰን እጅጉ

ወንጌላውያኑ ‘የተሓድሶ ያለህ’ እያሉ ቢጮሁም በተለያየ


መንገድና ደረጃ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ዲበ-
አካላዊውን የቃል እምነት ሲለማመዱትና ሲያስተምሩት
ይታያል። በየቦታው እየተቀዛቃዘ የመጣው ጸሎትና ምልጃ፤
በተለይ ደግሞ አንዱ ላንዱ የሚጸልይበት የጸሎት ድፍረት
እየኮበለለብን መምጣት፣ አንዱ የሌላውን ሸክም
የሚሸከምበት ክርስቲያናዊ ኅብረት መቀዛቀዝ፣ እንጸልይ
ሲባል ወደ መድረክ አፍጦ የሚመለከት ምዕመን መብዛት፣
መንበርከክ የሚጠላ ትውልድ መበራከት እና በሌላ መልኩ
ደግሞ ክርስቲያኒያዊ ኅብረት “ትንቢት በሚናገሩ” ወይም “ቃል
በሚያወጡ” ዙሪያ ብቻ ማገፋፋቱና ተወስኖ መቅረቱ
አካሄዳችን ትክክል እንዳልሆነ ጠቋሚ ነው።

በአጠቃላይ “ቃል የማውጣት” በመባል የሚታወቀው ልዩ


የጸሎት ልምምድ እግዚአብሔርን ደጅ የመጥናት ወይም
ፊቱን በቆይታ የመፈለግን እውነተኛ ልምምድ
ከቤተክርስቲያን ገፍቶ ለማስወጣት እያራቆተን ይገኛል።
ተሓድሶ ካላቆመው፤ መነቃቃትም ካላስወገደው ታዲያ ምን
መፍትሔ ይኖረዋል? ይህው እርሾ ፈልቶ ቁጥራችን ትንሽ ነው
የማንባል የወንጌል አማኝ ቤተ-እምነት አባላት ካልባረከኝ
አለቅህም የሚለውን የጓዳ ልምምዳችንን ወዲያ ብለን
“የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ቃል አውጣ” በማለት አገልጋዮችን

283
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሙጥኝ ማለት ከጀመርን ውለን አድረናል። ከልመናና ምልጃ፤


ከጾምና ጸሎት እልፍኛችን ቀስ በቀስ ተንሸራተን እንየኮበለልን
እንዳለ ከብዙዎቻችን የተሰወረ አይደለም።

በምልጃ የሚታወቁ የጸሎት ቡድኖች እንኳ በእንግዳው የኅሩይ


ቃል ዐዋጅ ልምምድ ሲጥለቀለቁ ይታያል። እርሾውን
ሳናስወግድ ይህን ችግር ለማቃለልና ሚዛን ለመጠበቅ
የምንዘረጋቸው የጾም ጸሎት ፕሮግራሞች ቡዙም ውጤት
የላቸውም። ወረርሽኙ ጸሎትን እየተካ እንደመጣ ሁሉ
ትንቢት በሰው ፈቃድ ይንገር ይመስል ከእግዚአብሔር
በመስማት የሚነገርን ትንቢትም እየተካ መጥቷል። አማኙ
የመለኮትን ሀልዎት በግልም ይሁን በጉባኤ ፈልጎ ከመንካት
ይልቅ በችግሩና በፍላጎቱ ላይ ቃል የሚያወጣለትን “የተቀባ
ነቢይ” ዕንባ ባቀረሩ ዓይኖቹ በየመድረኩ በመከራተት
ሲለማመጥ ማየት ቋሚ ትዕይንት እየሆነ ነው። ቀጥለን
ዙሪያችንን ለመቃኘት እንዲረዳን የልምምዱን ፈለግ ጥቂት
እንመለከታለን።

ጸሎት ያልገባው
አንዳንድ ጊዜ በመዝገበ ቃላት ወይም በመጽሐፍ
የምናውቃቸው ቃላትን ኅብረተሰቡ ከተለመደው ውጪ ወጣ
ባለ መንገድ ሲጠቀምባቸው ይስተዋላል። የቃላት

284
ጆንሰን እጅጉ

ትርጓሜያቸው ተለውጦ የማኅበረሰቡ ሁሉ መገልገያ


የሚሆኑት፤ ጥቂት በዕድሜ፣ በትምህርት፣ በሰፈር ወይም
በሃኃይማኖት የተቧደኑ ሰዎች በተደጋጋሚ ሲጠቀሙባቸው
ነው። እንዲህ ዐይነት ነገር ሲያጋጥም የቋንቋ ትርጉሙ
ተናጋሪውጋ ነው ያለው እንደሚባለው ለመግባባት ከተፈለገ
ተናጋሪው ለቃላቱ የሰጠውን ትርጉም ቀረብ ብሎ
በትዕግሥት መረዳት ይጠይቃል። ይሁን እንጂ አንዳንድ
የቃላት ትርጉም ለውጥ ቃላቱ የተሸከሙትን አንጸባራቂ ነባር
ትርጉም እስከ ማደብዘዝና እስከ ማጥፋት ሊደርስ ይችላል።
ስለዚህም ሁሉንም ዐይነት ለውጥ ወይም ትርጓሜ አሜን
ብለን የምንቀበለው አይሆንም።

ለምሳሌ ያኽል ትርጓሜያቸው ከተለወጡ ቃላት አንዱ


“ጸሎት” የሚለው ቃል ነው። ስለዚህም ሰዎች ‘ጸልዩልኝ’
ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? ብሎ መጠየቅና ትርጓሜያቸውን
መፈለግ ግድ ነው። እንዲህ ሳንጠይቅ በደፈናው የምንቀበል
ከሆነ ግን ጸሎት’ ከሚለው ቃል ጋር አብረን የምንወርሰው
አዲስ ትርጉም የጸሎትን ሥነ-መለኮት በማበላሸት የተለየ
ልምምድ ውስጥ ይከተናል።

በአንድ ወቅት በአንድ አነስተኛ ከተማ በምትገኝ አንዲት


አጥቢያ ውስጥ መጋቢ ሆኖ ጌታን በማገልገል የሚደክም አንድ

285
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወዳጄ ጸሎቱ ድንገት ተለወጠብኝ። ይህ ለውጥ ግራ


ቢገባኝም፦ “ምን ሆነኻል ጸሎትኽ እኮ እየተለወጠ ነው።”
የሚል አስተያየት ቀመስ ጥያቄ አቀረብኩለት።

መጋቢውም መልሶ፦ “አልገባኝም ምን ማለትህ ነው?”


በማለት ቁጣ ባዘለ ድምጽ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠየቀኝ።

እኔም እንዲረጋጋ ለማድረግ፤ የሚለማመጥ ፈገግታ እያሳየሁ፦


“አይ! ጸሎትህ ከዚህ በፊት ከማቀው ተለየብኝ። ጸሎትህ
‘የእምነት ቃል ትንቢት’ እንጂ ጸሎት አልመስል ቢለኝ ነው፤
የተማጽኖን ጸሎት እየተውክ ነው፤ ጸሎትህ ሁሉ እኮ
“በእምነት ቃል ዐዋጅ” እየተተካ እየመጣ ነው፤ ይህንን
አስተውለሃል?” በማለት የታዘብኩትን አብራራሁለት።

መጋቢው ወዳጄ ቁጣውን አረጋግቶ በአዎንታ ጭንቅላቱን


እየነቀነቀ “አዎ ልክ ነህ!” ካለኝ በኋላ አቅጣጫ የለወጠበትን
ቦታ ወደ ኋላ ተመልሶ የሚፈልግ በሚመስል ሁኔታ ጥቂት
አሰብ አደረገና ጥያቄዬን ለመመለስ ገጠመኙን ያወጋኝ
ጀመር።
ከዕለታት አንድ ቀን ቢሮዬ ቁጭ ብዬ እየሰራሁ እያለሁ
ከቤተክስቲያናችን ነባር አባላት አንዱ ወደ ቢሮዬ
አንኳክቶ በመግባት እንድጸልይለት ጠየቀኝ። እኔም
እጄን ጭኜ ላብ ጠብ የሚያደርግ ጸሎት ጸለይኩለት።

286
ጆንሰን እጅጉ

ይሁን እንጂ ሰውየው አመስግኖኝ ከቢሮ ይወጣል ብዬ


ስጠብቅ ወንበር ስቦ ቁጭ አለ። የሚያወራኝ ነገር
ይኖራል በሚል በደስታ ተከትየው ከተቀመጥኩ በኋላ
በጕጕት ስጠባበቅ አንዳች የጣለው ነገር ያለ በሚመስል
ስሜት ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወለሉ ላይ በዓይኑ
እያማተረ፦ ‘ሌላ የሚጸልዩ ሰዎች የሉህም?’ ሲል
ጠየቀኝ። የሚናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ ባይገባኝም
በጸሎቴ እንዳላመነ ስላሰብኩ በድንጋጤ ዝም ብዬ ዐይን
ዓይኑን ማየት ቀጠልኩ። በዚህን ጊዜ ንግግሩን
በመቀጠል ‘ማለቴ የትንቢት ቃል የሚናገሩ ኀይል
ያላቸው ሰዎች ካሉህ ቃል ቢያወጡብኝ ደስ ይለኛል።’
አለኝ። ወይ ልፋቴ በሚል ቁጭት ጭንቅላቴን ወደ
ግራና ቀኝ በማላጋት፦ ‘የሉንም! መጀመሪያውኑ እኮ
ሳልጸልይልህ ብትነግረኝ ትችል ነበር! በማለት
መለስኩለት።’እርሱ ግን መልሶ ‘አይ ደህና! ሌላ ጊዜ
አዘጋጅልኝና ትጸልይልኛለህ’ ብሎኝ ከቢሮዬ ወጣ።
የጸለይኩለት ጸሎት ትክክል እንደሆነ ባምንም ከዚያን
ጊዜ ጀምሮ ሳላውቀው ጸሎቴ ለራሴም እየተለወጠብኝ
መጣ።

በማለት አብራራልኝ። ከዚህ ታሪክ መረዳት እንደምንችለው


ይህ ወዳጄ ከቤተክርስቲያኑ አባል ጋር መግባባት ያልቻለው
ግለሰቡ “ጸሎት” ለሚለው ቃል የሰጠው ትርጓሜ የተለየ
ስለነበር ነበር። ኋላ ላይ ግን “ሌላ የሚጸልዩ ሰዎች የሉህም?”

287
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚለውን ጥያቄ ተከትሎ የተሰጠው የጸሎት ማብራሪያ


“ለጸሎት” የተሰጠውን እንግዳ ትርጓሜ እንዲረዳና ሳይፈልግ
እንዲቀበል ተጽዕኖ አድርጎበታል። ከግለሰቡ ማብራሪያ
መረዳት እንደሚቻለው ‘የሚጸልዩ’ ለሚለው ቃል ‘የትንቢት
ቃል የሚናገሩ’ ወይም ‘ቃል የሚያወጡ’ የሚል ትርጓሜ
ተሰጥቶታል። ይህ የቃላት ትርጉም ተግዳሮት ኋላ ላይ
የመጋቢውንም የቃል ትርጉም በማስለወጥ የጸሎት
ልምምዱን እስከ ማስቀየር ደርሷል። የዚህም ምክንያቱ
የምናስብበት መንገድ ቃላትንና ትርጉማቸውን ይቃኛልና
ነው።

በእንደዚህ ዐይነት ልውጥ ትርጓሜ የሚነዱ ወገኖች ‘የትንቢት


ቃል’ ወይም ‘ቃል ማውጣት’ የጸሎት ዋና አካል እንደሆነ
ያስባሉ። “ቃል ማውጣት” ወይም “የትንቢት ቃል” መናገር
የሚችሉ ወገኖች ብቻ መጸለይ እንደሚችሉ ስለሚቆጥሩ
ይህንን ማድረግ ለማይችሉ አገልጋዮች የጸሎት ዕድል
አይሰጡም። በዚህም ምክንያት ብዙ አገልጋዮች ከጸሎት
መድረኮች ይገፋሉ። ይህንን ዐስተሳሰብ የተገነዘቡና ያወቁ
አገልጋዮች ታዲያ “የእምነት ቃል” የማውጣት ወይም ኅሩይ
ቃል የማወጅ አሊያም ዐጉል የሆነ ትንቢት የመናገር ልምምድ
ውስጥ ሳይፈልጉ ለመግባት ይገደዳሉ። ካልሆነም ለጸሎት
እጃቸውን ከመዘርጋት ይሰበስባሉ። በዚህም የጸሎት ትርጓሜ

288
ጆንሰን እጅጉ

ለውጥ ተግዳሮት ምክንያት የአገልጋዩም የግል ጸሎት ሕይወት


በከፍተኛ ሁኔታ እየተመታ ይገኛል።

በቅርብ በሥነ-መለኮት ኮሌጅ በነበርኩበት ወቅት አንድ ሰው


የሚደነግጥለት ዐይነት የሆነ፤ የማቀው፤ መልካም ስብዕና
ያለው ወንድም ታሞ ቤቱ እንደተኛ ከአንድ ወዳጄ በስልክ
ሰማሁ። በሰማሁት ነገር ልቤ ስላዘነ “እባክህ ቤቱን
አላውቀውምና ይዘህኝ ሂድ።” በማለት ይህንኑ የነገረኝን
ወንድም ጠየኩት። የእሽታ ምላሹ ግን “አብሮን የሚሄድ ሌላ
የሚጸልይ ሰው ብታገኝም ጥሩ ነው።” የሚል ነበር። “ምን
ማለትህ ነው? እኛ መጸለይ አንችልም ማለት ነው?” በማለት
ባፋጥጠውም “አይ እሱማ እንችላለን በጸሎት የሚያገለግል
የፈውስ ስጦታ ያለው ሰው ካለ ማለቴ ነው።” በማለት
እንደመለሰልኝ አስታውሳለሁ። እንደዚህ ወንድሜ ከሆነ
ውጤት ያለው ጸሎት መጸለይ የሚችሉት በጸሎት
የሚያገለግሉ፤ የፈውስ ሥጦታ ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው።

በግል ጸሎት የጸሎት ምላሽን ከመለኮት መጠበቅ ቀስ በቀስ


እየቀረ፤ በምትኩ “ኀይል ያላቸው” ወይም “በጸሎት
የሚያገለግሉ” በሚባሉ ሰዎች በኩል መጸለይና ምላሽንም
መጠበቅ እየተለመደ ይገኛል። በሥጦታ ሰጪው ላይ ከመደገፍ
ይልቅ በጸጋ ስጦታዎች ላይ ጥገኞች እየሆንን ነው።
የሥጦታውን ምልክት የምናይባቸው ሰዎች በመካከላችን

289
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከሌሉ መለኮትን የመጥራት ድፍረት እያጣን እንደሆነ በርካታ


ጠቋሚ ነገሮች አሉ። መለኮትን “ቃል በሚያወጡ” ሰዎች
በኩል መፈለጋችን ትክክል እንደሆነና መንፈሳዊነት እንደሆነም
የምንቆጥር ብዙ ነን። ለዚህም ምክንያት አድርገን
የምናቀርበው ህዝበ እስራኤል ልመናውን ወደ ነቢያቱ ያደርግ
እንደነበር የሚያሳዩ ታሪኮችን ነው።

በእርግጥም መለኮት ከሰዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ


የጀመረበትን ጥንታዊ ታሪክ ስንመረምር የብሉይ ኪዳን
ሥርዐት እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ኅብረቱ ከጥቂት ሰዎች ጋር
ብቻ የተወሰነ እንደሆነ እናያለን። ከዚህም የተነሣ
እግዚአብሔር ስለ ዐገርም ይሁን ስለ ግለሰቦች የፍትህም
ይሁን የምህረት ወይም ሌላ ምላሾችን ይሰጥ የነበረው በነኝሁ
ጥቂት ሰዎች በኩል ነበር (ዘፍ.18፡20-33)። እናም ስለ ሕዝቡ
ሲጸልዩ መለኮት ይሰማቸዋል። መለኮት ሕዝቡን
የሚናገረውም በእነኚሁ ሰዎች በኩል ነው። ስለዚህ ሕዝቡ
ልመናውን በቀጥታ ወደ ጥቂት የእግዚአብሔር ሰዎች ያደርግ
ነበር።

ለምሳሌ ይህንን በግልጽ ከሚያሳዩ ክፍሎች ውስጥ ሕዝቡ ወደ


ኤርሚያስ ልመና ያቀረበበትን ክፍል እንመልከት፦

290
ጆንሰን እጅጉ

ነቢዩንም ኤርምያስን፦ ዓይኖችህ እንዳዩን ከብዙ


ጥቂት ቀርተናልና ልመናችን፣ እባክህ፣ በፊትህ
ትድረስ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የምንሄድበትን
መንገድና የምናደርገውን ነገር ያሳየን ዘንድ ስለ እኛ፣
ስለዚህ ቅሬታ ሁሉ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር
ጸልይ አሉት።”

ነቢዩም ይህንን ወደ እርሱ የተደረገ የሕዝብ ልመና ካደመጠ


በኋላ አልተቃወመም ነበር። “ሰምቻችኋለሁ፤ እነሆ፣ እንደ
ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤
እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ፣
ከእናንተም ምንም አልሸሽግም አላቸው።” (ኤር.42፡2-4)።

ሕዝቡ በቀጥታ ልመናውን ወደ እግዚአብሔር


የማያቀርብበትና ምላሽን የማይጠብቅበት ዋና ምክንያት
ሕዝቡ ከእግዚአብሔር የራቀ ሕይወት ስላለውና ኪዳኑም
ከኃጢአት ባርነት ፍጹም ነፃ ስለማያወጣውና ስለማያነፃው
ነበር። (ኢሳ.59፡2፣ ዕብ.9፡10፣ ዩሐ.8፡31-36)። እንዲሁም
ሕዝቡ እግዚአብሐርንም ከመፍራቱ የተነሣ እግዚአብሔርን
በቀጥታ መስማት አይፈልግም። “ሙሴንም፦ አንተ ተናገረን
እኛም እንሰማለን፤ እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን
አሉት።”(ዘጸ.20፡19)።

291
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያም ቢሆን ግን በዛው ኪዳን ሥርዐት ውስጥ መለኮትን


በግላቸው በቀጥታ ለመቅረብና ለማውራት የሚደፍሩ እንደ
ሐና ያሉ ጥቂት የጀገኑ ግለሰቦች ነበሩ። “እርስዋም በልብዋ
ትመረር ነበር፣ በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች፣ ጽኑ ልቅሶም
አለቀሰች።”(1 ሳሙ.1፡10)። ሐና ይህንን ያደረገችው ምንም
የክህነት ወይም የነቢይነት ስልጣን ሳይኖራት ነበር።
የሚገርመው ነገር በዛ አሮጌ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔርን
እንደ ንጉስ ሳዖል በነቢያት በኩል ሳይሆን በቀጥታ እንደነ ዳዊት
ለብቻቸው በሚፈልጉት ደስ ይሰኝና በኀይልም ይገለጥላቸው
ነበር። ዳዊት ነቢይም ንጉስም ሳይሆን ይህንን
አድርጎታል።(1 ሳሙ.17፡37፣ መዝ.42፡2)። ነገሩን ግልጽ
ለማድረግ፦ በብሉይ ኪዳን ለግል ፍለጋ ትንንሽ ግልጽ
ተስፋዎች ነበሩና ያንን የሚጠቀሙ ጥቂት የእምነት ሰዎች
ነበሩ። “በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው
ቢጸልዩ፣ ፊቴንም ቢፈልጉ፣ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፣
በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፣ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፣
ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።” (2 ዜና.7፡14፣ኢሳ.58፡9)።
በአጠቃላይ በጠባቡ ኪዳን ውስጥ እንኳ በሩ ሙሉ ለሙሉ ዝግ
አልነበረም ወይም ገርበብ ያለ ነበር ማለት ይቻላል። ሕዝቡ
ሲፈልገው ያገኘው፤ ሲጠራው ያገኘው ነበር። (ሆሴ.6፡3)።

292
ጆንሰን እጅጉ

በሌላ በኩል ደግሞ የአዲስ ኪዳን ሕዝብ በክርስቶስ ሞትና


ትንሳኤ በተመሠረተ ፍጹም ዕርቅ ምክንያት ልዕለ መለኮትን
ፈልጎ የሚያገኝበትና አባት ብሎ የሚጠራበት መንፈስና ልዩ
ዕድል የተሰጠው ሕዝብ ነው። “አባ አባት ብለን
የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና
ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።”(ሮሜ.8፡
15)። መለኮት በጥቂቶች ብቻ ላይወሰን ነቢያቶች ቀድሞ
የተነበዩለት ታላቁ የአዲስ ኪዳን ተስፋ ተፈጸመ። “ቃልም
ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፣ አንድ
ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።”
(ዩሐ.1፡14)። በዚህም ምክንያት “በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ
መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።” (ኤፌ.2፡18)። ይህ ትልቅ
ኪዳንና መገለጥ ባለበት “እግዚአብሔርን ፈልጉና አምጡልኝ?”
የሚል ዐይነት ወደ ነቢያት የሚደረግ ልመና እጅግ አሳፋሪ
ነው። አዲስ ኪዳን ላይ ሆነን ብሉይን እየኖርን ልመናን ለሰዎች
እያቀረብን ከሆነ የሚገለጥልን ኀይል እንኳ ቢኖር ከወዴት ነው
ብሎ ማሰብ ይገባል።

ለጸሎት ስንሰበሰብ በመካከላችን የጸጋ ሥጦታዎችን የተቀበሉ


ትንቢት የሚናገሩ ወይም ድምጽ የሚሰሙ ሰዎች ሊኖሩ
ይችላሉ። ነገር ግን ጸሎት ማለት ትንቢት ማለት አይደለም፤
ዋናው ያሰባሰበን ጉዳይ የጋራ ጸሎት ከሆነ ልንጸልይ እንጂ

293
የአማልክቱ ዐዋጅ

ትንቢት ሰምተን ልንበተን አይገባም። ትንቢት ጸሎትን ሊተካ


አይችልም! ወይም ጸሎት ትንቢትን ሊተካ አይችልም።
በአንድ ወቅት ይህንን ጸሎትና ትንቢትን የማምታታት
ችግራችንን እያሰላሰልኩ ከአንድ ወዳጄ ጋር በነበረን የሻይ
ሰዓት “ከሰው ጋር መጸለይ ስትፈልግ ምን ዐይነት ሰው
ትመርጣለህ?” በማለት ጥያቄ አቀረብኩለት።

ወዳጄ ግንባሩን ሰብሰብ የዓይኖቹን ሽፋ ሽፍት ጠበብ አድርጎ


በመነጽሩ ውስጥ እየተመለከተኝ፦ “አዲስ ክርስቲያን” በማለት
መለሰልኝ።

ያልጠበኩት መልስ ነበርና በመደመም ወንበሬ ላይ ወደ ኋላዬ


ተለጥጨ ከት ብዬ ሳቅኩኝ። ሐሳቤን በመሰብሰብም “ለምን?”
በማለት ንግግሩን እንዲቀጥል ጋበዝኩት። “ለምን መሰለህ?”
በማለት ቀጠለ፦

አዲስ ክርስቲያን ‘እንጸልይ’ ስትል ‘እንጸልይ’ ማለትህ


እንደሆነ ይገባዋል። ጴንጤው ግን እንጸልይ ስትለው
‘ተንብይልኝ’ ወይም ‘ልተንብይልህ’ እንዳልከው ነው
የሚያስበው። እንዴት አርገህ ትጸልያለህ? አብረሃቸው
ስትጸልይ ትንቢት የማትናገር ከሆነ ለመጸለይ አፍህን
መክፈት የለብህም። ዝም ነው ማለት ያለብህ። የጸሎት
ወይም የዝማሬ ድምጽ ያሰማህ እንደሆነ ደግሞ
የተቀበልካቸው ስለማይመስላቸው ሊቆጡና ሊጣሉህ

294
ጆንሰን እጅጉ

ይጀምራሉ። ከዛ ስምህን ያጠፋሉ! እርሱ ትንቢት


አይቀበልም ይሉሃል።

በማለት አብራራልኝ። ይኽን መሰሉ ጸሎትና ትንቢትን


ማምታታት አንዱ በአንዱን እንዲዋጥ አድርጎታል። የጸሎት
ትርጉም በመለወጥ እንዳንግባባ እያደረገን ከመምጣቱም
በላይ እርስ በርስ ያለንን መንፈሳዊ ኅብረት ጎድቶታል።
በየጸሎት ቤቱ የሚደረጉ የጸሎት ፕሮግራሞችን እወነተኛ
ጣዕም አጥፍቶብናል። በዚህም የተፋለሰ ትርጉም ምክንያት
በአንድ ቤት የሚኖሩ ባልና ሚስት እንኳ አብረው ለመጸለይ
የሚቸገሩበት ሁኔታ እስኪፈጠር ደርሰናል። ወደ አንድ አከባቢ
ወይም ወደ አንድ መኖሪያ ቤት በእንግድነት ሄደን አማኞችን
ስንተዋወቅ በደስታ እያፍለቀለቀን “እንጸልይ” ያስብለን
የነበረው የጋለ ስሜት ከደበዘዘና በቀልድና በጨዋታ ብቻ
መለያየት ከጀመርን ሰንብተናል። የ 80 ዎቹ ዘመን ጸሎት
እንዲህ አልነበረም በሚል እስከመቆጨት ያደረሰን አምላክ
ተለውጦ፤ ቅዱስ መንፈሱ ትቶን ሳይሆን የተለወጠውን
የጸሎት ትርጉም ተከትለን በአንድ መንገድ ስለነጎድን ነው።
ካስተዋልንና ከተመለስን የቀድሞውን ዘመን የጸሎት መንፈስ
የማንመልስበት ምንም ምክንያት የለም። እንደ እውነቱ ከሆነ
እንደ ወዳጄ ኺስ ጸሎት ያልገባው “የጸጋ አገልጋይ” ከመሆን

295
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ጸሎት የገባው አዲስ ክርስቲያን


መሆን የተሻለ ነው።

የአንደበቴ ቃል መሬት ጠብ አይልም!


አንድ ጊዜ ጤናማ ከሚባሉት አንዷ በሆነች በመዲናችን
በምትገኝ ቤተክርስቲያን ሳምንታዊ ጉባኤ ለመካፈል
ታደምኩ። ቤተክርስቲያኒቱ መልካም ተጽዕኖ በመፍጠራቸው
ከሚነገርላቸውና መልካም ስም ካላቸው አቢያተክርስቲያናት
አንዲቱ ናት። በዕለቱ ልዩ የጸሎት ምሽት ዝግጅት ነበር።
የአምልኮውና የቃል ስብከት ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ
የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢና ነቢይ ለሕዝቡ ለመጸለይ የዘይት
ብርሌ ይዘው ወደ መድረክ ወጡ። እንደተለመደው መድረክ
ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከጸለዩ በኋላ ዘይት እየቀቡ
ለመጸለይ ተዘጋጁ። ሕዝቡንም በሁለት መስመር በመሆን ወደ
እነርሱ እንዲመጣ ግብዣ አደረጉ።

እኔም በረከቱን ለመካፈል መጋቢው በቆመበት አቅጣጫ ቆሜ


ተራዬን እየተጠባበኩ እያለሁ በነቢዩ በኩል የተሰለፈው ብዛት
ያለው ሕዝብ ትኩረቴን ሳበው። በመጋቢው በኩል የተሰለፈው
ትንሽ ቍጥር ያለው ሰው ሕዝቡ ምርጫ እያደረገ እንዳለ
ጠቆመኝ። የዚህን ምርጫ ምስጢር ለመረዳት ስለጓጓኹ
ከጥቂት ቀን በኋላ ያገኘኋቸውን የተወሰኑ ታዳሚወች ለምን

296
ጆንሰን እጅጉ

እንደዛ እንዳደረጉ መጠየቅ ጀመርኩ። የተወሰኑት በመደናገጥ


“እንዲሁ ባጋጣሚ ነው” ፤ “አስቤበት አይደለም።” ከማለት
ያለፈ ግልጽ መልስ አልሰጡኝም። ጥቂቶቹ ግን የነቢዩን “ቃል
ማውጣት” ወይም ባርኮት ፈልገው እንደሆነ በግልጽ ነገሩኝ።
የጉባኤውን ዐውድ መሠረት በማድረግና ግንዛቤ ውስጥ
በማስገባት ለነኝህ ሰዎች ቀጣዮን ጥያቄዬ አቀረብኩላቸው።
“ከነቢዩና ከመጋቢው ማናቸው ናቸው የበለጠ የመባረክ
ስልጣን ያላቸው?” የሚል ነበር። በነቢዩ በኩል የተሰለፉትንም
ጨምሮ የብዙዎቹ መልስ ታዲያ “መጋቢው” የሚል ነበር።

በዚህ መልክ የመለሱልኝ በጥያቄ ስለወቀስኳቸው ይሆን?


ወይስ የምፈልገውን መልስ ስለተረዱ? ለምንስ
ልምምዳቸውና ሥነ-መለኮታቸው ተጋጨባቸው?
አላውቅም። ያም ሆነ ይኽ ሚዛን የማጣት ችግር
እንደገጠማቸው ለመገንዘብ ጊዜ አልወሰደብኝም። የዚህ
ችግር አንዱ ምክንያት ነቢያቱ በሕዝቡ ስነ-ልቦና ላይ
የሚፈጥሩት ጫና እንደሆነ አምናለሁ። ነቢያቱ ጸጋን
ከመለኮት እንደተቀበሉ ብንቆጥር እንኳ እንዲህ አይነቱን ጫና
የሚፈጥሩበትን ጥበብ ከመለኮት ነው የተቀበሉት ብሎ ማመን
ይቸግራል። የተለየ ስልጣን እንዳላቸው ለማሳመን
ከሚጠቀሙበት ስልት አንዱ የአንደበታቸው ቃል ያለውን
ትልቅ ስልጣን ማጉላት ነው። “የአንደበቴ ቃል መሬት ጠብ

297
የአማልክቱ ዐዋጅ

አይልም!” በማለት አስረግጠው ሲናገሩ ምስኪኑ ሕዝብ


በፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ ይወድቃል። ተስፋውንም
በአንደበታቸው ቃል ላይ ያደርጋል። ኅሩይ ቃል እንዲያወጡለት
ለመለማመጥ ከወንበሩ ተነስቶ በጭብጨባ እጅ ይነሣል።

አብዛኛዎቹ በየመድረኩ የምናያቸው አማልክት ነቢያት አንድ


ዐይነት ልብስ የለበሱ ናቸው። የተለየ ከምንምና ከማንም
ብልጫ ያለው ስልጣን እንዳላቸው ይተማመናሉ። ለራሳቸው
ያላቸውን የገነነ ዐስተሳሰብና እምነት ከንግግራቸው ቀድሞ
የሚያብረቀርቅ ልብሳቸው ያሳብቃል። በአንድ ወቅት የተለየ
ስልጣን ያጎናጸፈው ልዩ ቅባት እንደተቀባ የሚቆጠር አማልክት
ነቢይ ይህንን ምሥጢር ሲደሰኩር ሳምሶንን አንስቶ እንዳስረዳ
ትዝ ይለኛል። በዕለቱ ነቢዩ እንደተለመደው በጉባኤው ላይ
ከታደመው ሕዝብ ለየት ያለ የሚያብረቀርቅ ልብስ ለብሷል።
መቼም እንደዚህ ዓይነቱ ለየት ያለ አለባበስ ሠርግ ላይ
ሙሽራውን ከታዳሚ ለመለየትና የታዳሚውን ቀልብ
በሙሽራውና በሙሽሪት ላይ ለማሳረፍ ሆን ተብሎ ለአንድ
ቀን ብቻ እንደሚደረግ እናውቃለን።

በነገራችን ላይ ነቢያቱን ከሙሽሮች ለየት የሚያደርጋቸው


ዘወትር የክብር ቬሎ መጎተታቸው ብቻ ነው። አንባገነን
የአፍሪቃ መሪዎች በወርቅ በተሽቆጠቆጠ አልባሳት
በህዝባቸው ስነ-ልቦና ላይ ጫና ይፈጥራሉ እንደሚባለው

298
ጆንሰን እጅጉ

በተከታዮቻቸው ሥነ-ልቦና ላይ ዘወትር ጫና ያሳድራሉ።


ጫናቸውን ከፍ ለማድረግ ካስፈለገም ወደ ጉባኤ ሲገቡ
አጃቢ፤ ለመቀመጫቸውም ዙፋን መሳይ ነገር
እንዲዘጋጅላቸው ያዛሉ።

እናም በአሸብራቂ ልብሱ ትኩረታችንን የሳበው አማልክት


ነቢይ ማይኩን በጁ እንደጨበጠ የጥያቄያችን መልስ ሁሉ
እርሱጋ እንዳለ በሚያስመስል ንግግር ጉባኤውን አስጨበጨበ።
በሙሉ ድፍረት እንዲህ ነበር ያለን፦

ችግርህን ለመለወጥ ሦስት ወር ሙሉ ጾም ጸሎት


ልትይዝ ትችላለህ። ነገር ግን ተነቀል ብትለው
አይነቀልም። አንድ የተቀባ ነቢይ ግን ሶስት ወር
የደከምክበትን ችግር የሆነብህን ነገር፤ በሦስት
ደቂቃ ውስጥ ከስሩ ነቅሎ ይጥለዋል። ሶምሶን
የኢያሪኮን ከተማ መዝጊያ ከእነመቃኑ ነቅሎ
በኬብሮን ተራራ ራስ ላይ እንደጣለው እንዲሁ
ይሆናል!

ሕዝቡም ሞቅ አድርጎ በማጨብጨብ መስማማቱን


አበሰረው፤ ይሁን እንጂ በአምላኩ ዙፋን ፊት ተንበረክኮ
የመቆየት ድፍረቱን እየተነጠቀ እንዳለ ያስተዋለ የለም ነበር
ማለት ይቻላል።

299
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነቢዩ እያለ ያለው የተቀባ ነቢይ መፈለግና “እንዲጸልይልን”276


ማድረግ እንጂ በመጸለይ መድከም እንደማያስፈልገን ነበር።
በዚህ ሥልታዊ አቀራረቡም በእርሱ ቅባት ስልጣን ማመን
ችግራችንን ከስሩ ነቅሎ እንደሚጥል ማወቅ እንዳለብን
አግባብቶናል። ንግግሩ ቀላልና የሚናቅ አልነበረም።
ምክንያቱም መልዕክቱን ያስተላለፈው በእውነተኛ የመጽሐፍ
ቅዱስ ታሪክ ላይ ተደግፎ ነበርና ነው።

አማልክቱ ነቢይ መልዕክቱን ለማስተላለፍ የተጠቀመበት


የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዲህ የሚለውን ነበር።

ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ እኩለ ሌሊትም


በሆነ ጊዜ ተነሥቶ የከተማይቱን በር መዝጊያ ያዘ፣
ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያውም ጋር ነቀለው፣
በትከሻውም ላይ አደረገ፣ በኬብሮንም ፊት ወዳለው
ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ በዚያም
ጣለው።(መሳ.16፡3)።

ታሪኩ የሚያነሳው በዘመነ መሳፍንት በምድረ እስራኤል


የተፈጸመን ታሪክ ነው። በዘመኑ በእስራኤላውያን ላይ
ፍልስጤማውያን ግፍ ያደርጉባቸው ነበር። በእስራኤል ደግሞ
ሰራዊት አደራጅቶ የሚዋጋና የሚመራ መሪ አልነበረም።
276
የጸሎት ትርጓሜው “ቃል ማውጣት” በሚል እንደተተካ “ጸሎት ያልገባው”
በሚለው ንዑስ ርዕስ የተብራራ ነው።

300
ጆንሰን እጅጉ

መሪንም ያስነሳላቸው የነበረው እግዚአብሔር ነበር። ይህም


በቀጥታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሚያደርገው ምህረት ጋር
የተገናኘ ነው። የሳምሶን መፀነስና መቀባትም ከዚሁ ጋር
የተያያዘ ነው (መሳ.13)።

እግዚአብሔር ሶምሶንን ያስነሳበት ዐላማ ሕዝቡ በበደሉ


ምክንያት የተቀጣበት አርባ ዐመት ስላበቃ ፤
ከፍልስጤማውያን ግፍ ሕዝቡን እንዲታደግ ነው። አጠቃላይ
የታሪኩን ጭብጥ ስንመለከት የሶምሶን በእስራኤል ፊት ኀይል
ማድረግ የሕዝቡንም ሆነ የሶምሶን ጸሎት በመወከል ለጸሎት
ምሳሌ መሆን አይችልም። ሊያሳየን የሚችለው
የእግዚአብሔርን በምህረቱ ወደ ሕዝቡ መመለሱንና የማዳን
ኀይሉን ትልቅነት ነው።

በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር አገልጋዮችን የሰጠበትን ምክንያት


የተመለከትን እንደሆን ግን ከዚህ የተለየ ምክንያትና ዐላማ
አለው። ሕዝቡ ጸሎት እንዲያቆምና ነቢያቱም ስለሕዝቡ
እንዲዋጉና ደርሰው የሕዝቡን ችግር እንደ ኀያል አዳኝ
እንዲፈቱ አይደለም። ይልቁንም ሕዝቡ የኀይል መንፈስ
እንዲሞላና እንዲበረታ አቅጣጫ እንዲያሳዩና የመንፈስ ቅዱስ
ኀይል በተሞላ ህይወታቸው ምሳሌም ጭምር እንዲሆኑለት
ነው። “የገሐነም ደጆች አይችሏትም።” የተባለው ስለ አዲስ
ኪዳን ነቢያት ሳይሆን ስለ ቤተክርስቲያን ወይም ስለ ሕዝቡ

301
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደሆነ ማስተዋል ይገባል። በግል ወይም በነቢይ ጸሎት


የማይፈቱ ነገሮች በኅብረት ጸሎት የሚፈቱበትም ምስጢር
ይኽው ነው።(ማቴ.16፡18፥ ሐሥ.12፡5)።

የዚህም መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ የኀይል መንፈስ ለሕዝቡ


ሁሉ መፍሰሱ ነው። የመንፈስ ቅዱስን መፍሰስ ኢየሱስ
የሰጠው የመጨረሻ ተስፋ ነበር። “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ
በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ። …በዚያን
ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።”
የዚህንም ተስፋ ፍጻሜ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ ዘግቦት
እናገኛለን። (ሐሥ.1:8,8፡17፣ 2 ጢሞ.1:6, ሮሜ.15:13
ኤፌ.2:16-17)። እነኝህ ጥቅሶች በአማልክት ነቢያቱ
ተዘውትረው የሚጠቀሱ ቢሆኑም መልሰው ደገሞ
ይከድኗቸዋል።

አማልክቱ ነቢይ መልዕክቱን ያስተላለፈበት ሁኔታ ስንመለከት


የአዲስ ኪዳንን የአገልግሎት ትልም የሳተና የመጽሐፉንም
ዐውድ ያልጠበቀ ነበር ማለት እንችላለን። ምክንያቱም
ያነሳው የሶምሶን ታሪክ ለአዲስ ኪዳናዊ አገልግሎትም ይሁን
ለጸሎት ምሳሌ መሆን አይችልም። ያም ሆኖ ግን ንግግሩ
የነበረው የማስጨብጨብ ጉልበት ቀላል አልነበረም። እንደዚህ
ዓይነቱ ንግግር ለጊዜው ቢያስፈነድቅም የሚፈጥረው የስነ-
ልቦና ጫና የከፋ ነው። የጸሎት ድፍረትን በማስጣል ጥገኛና

302
ጆንሰን እጅጉ

የሰው ተከታይ ያደርጋል። የመንፈስ ቅዱስን እሳት ያዳፍናል።


እንደዚህ ዓይነቱ የትዕቢት አቀራረብ የአምባገነንነት ስሜትን
የሚንጸባርቅበትና የእግዚአብሔርን ጉባኤ አለማክበር ነው
ቢባል ስሕህተት ሊሆን አይችልም። ነቢያቱ ከመለኮት ጋር
ያለንን ህብረት ስሜትን በሚኮረኩር ንግግራቸው ቀስ ብለው
ወደ ጐን በማድረግ እንደዚህ ልመናችንን ለእነርሱ
እንድናቀርብ የሚያባብሉን ለምንድነው? አብዛኛዎቹ ነቢይ
እንደሆኑ የሚያምኑ አማልክት ሰባኪያን ብዙ ጊዜ እንደዚህ
ዓይነቱን ጫና ሳይፈጥሩ ከመድረክ እንዳይወርዱ የማሉ
ናቸው። ገና የስብከታቸውን መግቢያ ሲነግሩን የአንደበታቸው
ቃል መሬት ጠብ እንደማይል ያውጁልናል።

ወዳጆች ሆይ፣ አፍርሰውናል፤ ወደ እግዚአብሔር ልመና


የማቅረብና የማሰብ መብታችንን ገፈውናል፤ በእርግጥ
አገልጋዮች በአዲስ-ኪዳንም ይሁን በብሉይ-ኪዳን መንፈሳዊ
ስልጣን እንዳላቸው ይታወቃል። መንፈሳዊ ስልጣን ግን
የሌላውን ፈቃድ ለመርገጥና ለማፍረስ፤ የሕዝብን ቀልብ
ለመስረቅና ለራስ ክብር ለማሰለፍ ሳይሆን ለማነጽ የተሰጠ
እንደሆነ ግልጽ ነው። “ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና
ለመምከር ለማጽናት ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው
ይናገራል።” (1 ቆሮ.14፡3)። ስለዚህ መንፈሳዊ ስልጣን

303
የአማልክቱ ዐዋጅ

የምንፎካከርበት ሳይሆን ሥራ የምንሠራበት እንደሆነ


መታወቅ አለበት።

በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ የግል አቋሙንና ሥልጣኑን


ሲያንጸባርቅ የሥልጣኑ ዐላማ የሌሎችን መንፈሳዊ ሕይወት፣
ድፍረት፣ እምነት ማፍረስ እንዳልሆነ ያብራራልና። ስለዚህ
ለማፍረስ ከመትጋት ብንቆጠብ መልካም ነው ብዬ አምናለሁ።
“ጌታ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ
በሰጠው በሥልጣናችን ከፊት ይልቅ ብመካ እንኳ አላፍርም።”
ይላል። (2 ቆሮ.10፡8፣ 13፡10)። የሚገርመው ግን እንዲህ
መጫወቻ እያደረጉን በጩኸት ጉባኤ ማሞቃችንና አሜን
ከማለት አልፈን ደርሰን ልክናቸው በማለት ከልዩ ዲበ-አካል
ለተጣባ ስብከታቸው መሟገታችን ነው። አማልክቱ ነቢያት
የአንደበታቸውን ንግግር እንደ መለኮት ንግግር በመቁጠር
የሚንቀጠቀጡላቸውን መፈለጋቸው ለምንድነው? የነቢያት
አገልሎት ነብያቱን ለሚፈራና ከመለኮት ጋር የተስተካከለ
ስልጣን እንዳላቸው ቆጥሮ ለሚርበተበትስ ብቻ የተፈቀደ
የሚመስለው ለምንድነው? የሚናገሩት ሁሉ ምንም ስሕተት
የሌለውና መሬት ጠብ የማይል እንደሆነ ደጋግመው በመናገር
ተጽዕኖ ስለሚፈጥሩ አይደለምን?

ዋ! ቃል እንዳላወጣ!

304
ጆንሰን እጅጉ

ጊዜው 2000 ዓ.ም ሲሆን ቀኑ ፀሐያማ ነበር። የዚያን ጊዜው


ኃ/ማሪያም አሁን አዳማ ከተባለው ሆስፒታል አንዲት
በግምት ሰላሳ አራት ዐመት የሚሆናት ወጣት ስትወጣ አየሁ።
እጅግ ክፉኛ መታመሟን የሚቆራረጥ ትንፋሿ፣ የፊቷ
መገርጣትና የምታሰማው የማቃሰት ድምጽ ይናገራል።
የዘጠኝ ዐመት ልጅ አብሯት አለ። ደግፈኝ በሚል ዕይታ በዐይኖ
ተማጸነችኝ። ከመደገፍ ባለፈ ልመሰክርላትና ልጸልይላት
በመፈለግ ፈጥኜ በመጠጋት ደገፍኳት። ብዙ ሰዎች በመከራ
ውስጥ ሲሆኑ ለወንጌል ጆሯቸውን እንደሚሰጡ ሁሉ ጆሮዋን
ሰጠችኝ። የበለጠ ልትሰማኝና ንስሓ ላስገባትና ልጸልይላት
ቀጠሮ ያዝን። ቤቷ አድርሼያትም ተለያየን። ቀጠሯችን ደርሶ
እስካገኛት ድረስ፤ ለመዳን ያላት ጕጕትና የልጇ ጭንቀት ፊቴ
እየተደቀነ ረፍት ነሳኝ። በቀጠሯችን ቀን አብሮኝ እንዲሄድ
በማሰብ ስልኬን አንስቼ ስሙን መጥቀስ ወደ ማልፈልገው
አንድ አገልጋይ ጓደኛዬ ደወልኩ። አብረን ለመሄድም
ተስማማን።

የቀጠሮው ቀን ደርሶ ስደውልለት የሰጠኝ ምላሽ ግን ቀዝቃዛ


ነበር። ምክንያቱን ሲያስረዳኝ “ጆን ደክሞኛል። ሻወር ወስጄ
አረፍ ማለት አለብኝ።” የሚል ነበር።

“ኸረ እባክኽ በሞት አፋፍ ላይ ያለች ሰው ናት ልንረዳት


ይገባል” ብለውም አመረረብኝ። ይሄ የሚሆነው ከቀኑ ዘጠኝ

305
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሰዓት ነበርና መኪናዬን አስነስቼ ቡና ለመጠጣት ወደ


ሚያዘወትርበት ቦታ ፈጥኜ ሄድኩኝ።

በደረስኩም ጊዜ አረፍ ማለት አለብኝ በማለት የመለሰልኝን


ሰው ቁጭ ብሎ ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት ባገኘው እራሴን
መግዛት አቃተኝ። “የተቀጣጠርነው እዚህ ነው? በጣም
አዝናለሁ!” በማለት አንባረቅኹበት።

መልሱ ግን ገራሚ ነበር፤ ቁጣዬ ፍንክች አላደረገውም።


ይብሱን በቁጣ የሌባ ጣቱን እያወዛወዘ “ዋ! ጆን ቃል
እንዳላወጣ! ዋ! ነግሬሃለሁ!” ነበር ያለኝ።

የወዘወዛት ማስፈራሪያ በትር በእኔ ዘንድ ዋጋ አልነበራትምና


“አውጣ! አውጣ! አታስፈራራኝ!” በማለት መልሼለት በአንድ
ጠባብ ክፍል ወስጥ ከትንሽ ልጇ ጋር ትጠብቀኝ ወደ ነበረች
ምስኪን ብቻዬን አመራሁ።

በቅርብ የማውቀው ወንድሜ እንደዚህ በተለየ እንግዳ በትር


ለምን አስፈራራኝ? ይሄ ወንድሜ በጤናማ ቤተክርስቲያን
በሚሰጥ ጤናማ ትምህርት ያደገ አገልጋይ ቢሆንም ይህንን
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የልዩ ዲበ-አካል “የቃል ኀይል”
ልምምድ ሳያውቀው ወደ ውስጥ ጠልቆ በደመ-ነፍስ
እየተለማመደ ነበር ማለት ይቻላል።

306
ጆንሰን እጅጉ

“እውነትን መናገር በቂ ነው! ስሕተትን መናገር አስፈላጊ


አይደለም!” የሚለውን መርሖ ከ 1995 ዓ.ም አከባቢ ጀምሮ
በየመድረኩ በመጠቀም ስሕተቶችን አንስተን ከመገሰጽና
ከማረም ብንቆጠብም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖ ካለመሆኑም
ባሻገር ዛሬ ላይ ውጤቱ ዐሉታዊ ጣጣውን እየነገረን ነው።
ያም ቢሆን ፉርሽነቱን ከውጤቱ ተምረን እንኳ መታረም
አይታይብንም። “በቆሸሸ የብርጭቆ ውኃ ላይ ንጹሕ ውኃ
ብናቆረቁርበት እየነፃ ይሄዳል” ምሳሌያችን ነው። ሐዋርያትም
ሆኑ ነቢያት የነበሩበትን ትውልድ ስሕተት ለማረም
ወገባቸውን አሸንፍጠው የዐቅበተ እምነት ሥራ ሰርተዋል።
“እከሌን እንዳላሳዝነው! መድረክ እንዳይነሳኝ! መንገዴን
እንዳይዘጋ!” ሳይሉ ስኹት አሠራርን ነቅሰው መንቀፋቸው
በጃችን ላይ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ቢሆንም
ልንቀበለው አንወድም። አብዛኛዎቻችን ስሕተትን ለማደባየት
የሚችል ጭካኔ አይታይብንም። በእኛ ብሶም ዝምታችን
ሩኽሩኽ የፍቅር ሰዎች እንደሆንን ማሳያ እንደሆነ በማመካኘት
ለማሳመን እንቢልታ እንነፋለን።

የወዳጄን ማስፈራራት ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው አሁን ላይ


ለራሳቸው በፈጠሩት መድረክ ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ብዙ
ሲያጠፉ የምናያቸው ወጣቶች በቤተክርስቲያን እጅ እያሉ
እንዳላረምናቸው ይጠቁመኛል። ባለፉት አስራና ሃያ አመታት

307
የአማልክቱ ዐዋጅ

ስኽተቶችን ከማረም ይልቅ ዐባሪ ሆነን “የፍቅር መአድ”


አብረን እየቆረስን ቁልቁል ወርደናል። መድረክ እየተጋራንና
እያጋራን ቤተክርስቲያንን በቸልታ በመምራት ለአጋንታዊ
አሠራር ሕዝብን ያዘጋጀን መጋቢያን ዛሬ ላይ ትውልድ
እየገባበት ላለ ጥፋት ከተጠያቂነት እንደምናመልጥ ምን
ዋስትና አለን? ዛሬ ላይ ያለው ውጤት ላለፉት አሥርት
ዐመታት በመድረካችን ላይ የሠራነው ተሳሳተ ሥራ ማሳያ
እንደሆነ አምናለሁ።

የርግማንና የሟርት ፍርሃት


ባደረኩት ጥናት ላይ፤ ቃለ መጠየቅ ካደረኩላቸው
የወንጌላውያን ቤተ-እምነት አማኞች መኻል 50%
የሚያኽሉት ማንኛውም የሚነገር ዐሉታዊ ኔጌቲቭ ቃል
ሟርት እንደሆነ እና ፍጻሜያቸውን በመወሰን ሊጎዳቸው
እንደሚችል በጽኑ የሚያምኑ ሆነው አግኝቻለሁ።277 ለእነርሱ
መልካም እንደማያስቡ የሚጠራጠሯቸውን ሰዎች ከሰይጣን
ቀጥሎ በፍርሃት ይመለከቷቸዋል። በቃል ከታሰሩበት፤ ሰንሰለት
በቃል ለመፈታት በራቸውን ዘግተው የተመረጡ መልካም
ቃላትን በራሳቸው ላይ ያውጃሉ፤ ስኬታቸው ግን
የሚያስቡትን ያክል አይሆንላቸውም።

277
Johnson Ejigu The Infilunce of Positive Confession. (2018).

308
ጆንሰን እጅጉ

ስኬት የማጣታቸው ምክንያት የታሰሩበትን የቃል ሰንሰለት


ውል ስለማያውቁት እንደሆነ በማሰብ፤ የነቢያትን እርዳታ
ፍለጋ ሞቅ ባለ ፖስተር ተዋውቆ ያዩበትን መድረክ ሁሉ
ይቀላውጣሉ። እንደዚህ በፍርሃት የታሰሩ ወገኖች
የሚበዙበትን ጉባኤ ለመስበክ መድረክ ላይ የወጣ ብልጣብልጥ
ታዲያ ጉባኤውን አድምቆ “አቤት የነበረው የእግዚአብሔር
ክብር!” ለማስባልና ወፈር ያለ ፖስታ አፈፍ አድርጎ
ለመውጣት ቀላል ይሆንለታል። የሚጠበቅበት የተመረጡ
ቃላትን እየመዘዘ፤ በታወቁት የሰው ልጅ መሠረታዊ
ፍላጎቶችና የተለመዱ ችግሮች ላይ ማወጅ ብቻ ነው።
ከዚህም አለፍ ካለ ደግሞ ይስመርለትም አይስመርለት
“የሟርት አፎች ሲዘጉ አያለሁ! ርግማንን ሰበርኩ! ሞት
አይሆንም!” በሚል “የዐዋጅ ጸሎትን” ወይም “ትንቢታዊ ቃል”
ማውጣት ብቻ ነው የሚጠበቅበት።

እውነቱን ለመናገር ያተረፈው የፍራንክ ፍራንክ ጨዋታውን


ያወቀበት “ርግማን ሰባሪው” ሰባኪ ብቻ ነው። ሕዝቡማ ምን
ያተርፋል ከጉባኤ እንደወጣ መልሶ ለዛው የፍርሃት ሰንሰለት
እጁን ይሰጣል። ለምን ቢባል “ረጋሚዎችና ሟርተኛ ናቸው”
ብሎ የሚጠረጥራቸው ሰዎች በሄደበት ሁሉ በውሎው፣
በሰፈሩ እና በጎረቤቱ ይጠብቁታልና ነው። ይህ ትምህርት
ታዲያ ግራ የገባው ሥነ-መለኮት መሆኑን የማይበት አንዱ

309
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነገር በመሟርተኝነት የሚጠረጠሩት አማኞችና አገልጋዮች


ጭምር መሆናቸው ነው። የሆሊ ስፕሪት ቤተክርስቲያን
መሥራች ነቢይ ታምራት ደምስስ “የአማኝ ሟርት” በሚል
ርዕስ ባስተላለፈው የቀጥታ ሥርጭት መልዕክቱ ሟርት
በአገልጋዮች፣ በፓስተሮችና በነቢያት ንግግር ሳይቀር
እንደሚሠራ ይናገራል። በሌላ ቦኩል ከዚህ በተቃራኒው እርሱ
ደግሞ “ቃል አወጣባችኋለሁ” በማለት በቃል ዐዋጅ ጸሎት
ሟርትን ሲከላከል ይታያል።278 እንደዙሁ ሁሉ ብዙዎቻችን
በአንድም በሌላም መንገድ “የክርስቲያን ሟርት ከባድ ነው።”
የሚል ተመሳሳይ ንግግር እንደሰማን አስባለሁ። እንዲህ ዓይነቱ
ንግግር ታዲያ የሟርት እስረኛ ከማድረጉም በላይ
ክርስቲያኒያዊ ኅብረትን ይጎዳል። ባንድ ወቅት የምቀርበው
ክርስቲያን ወዳጄ ተስፋ ያደረገው የሽንኩርት መስኖ እርሻ
አከሰረው። ኪሳራውን በቀጥታ ያያዘው ታዲያ አስቀድማ
በፍርኀ-እግዚያብሔር እንዲመላለስ ትመክረውና
ታስጠነቅቀው ከነበረችው ባለቤቴ ጋር ነው። ፊት ለፊት
“አሟርታብኝ ነው።” ብሎ እስከ መናገር ደረሰ። ከዚህም ዐልፎ
አኮረፋት። በዚሁ የማይጨበጥ ጥርጣሬው ምክንያት መልካም
የነበረው ግንኙነታቸውም ተቋረጠ።

278
በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አስደናቂ መልዕክት። AMAZING DAY WITH MAN OF
GOD PROPHET TAMRAT DEMSIS.

310
ጆንሰን እጅጉ

በእንደዚህ ዐይነት የሟርት ፍራቻ የተጠቃ ክርስቲያን እፎይታ


ለማግኘት ሲል ቤት፣ ሰፈር፣ ቤተክርስቲያን ወይም ዐገር
እስከመቀየር ሊደርስ ይችላል። መጽሐፍ ግን በዐሉታዊ ቃል
ወይም በሟርት መታሰር ፍጹም ባልሆነው በአሮጌው ኪዳን
እንኳ እንደማይገባ ያረጋግጣል። ምክንያቱም አንደኛ
ሟርተኝነት ኀጢአት ስለሆነ ሟርተኛው በሟርቱ ተጠያቂ
ነው። ሁለተኛው እግዚአብሔርን አምላኩ ያደረገ ሕዝብ
የማይጣስ ከለላ አለው። እስራኤል ከሟዋርትና ከአስማት
እንደተጠበቀ የሚያረጋግጥ የሙሴ ቅኔ ይህንን ያሣያል።
“በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፣ በእስራኤልም ላይ ምዋርት
የለም።” (ዘኁል.23፡23)።279 በሌላ በኩል በተሸለ ኪዳን ውስጥ
የምናገለግል አገልጋዮች ይህንን እውነት ትተን ማኅበረ
ምዕመኑን የርግማንን ኀይል በሚያንጸባርቅ ስብከታችን
እያስበረገግን እንዲህ ዐይነት ፍርሃት ውስጥ እንዲመላለስ
ማድረጋችን የከፋ ኃጢአት እንደሆነ ይሰማኛል። እንዲህ
ዓይነቱ የስብከትም ይሁን በትንቢታዊ መገለጥ ስም የሚቀርብ
የተዛባ መልዕክት ምዕኑን የፍርሃት ተገዥ በማድረግና
ላልተፈለገ መንከራተትና ብዝበዛ ያዘጋጀዋል።

ንስሓ እንደሟርት

279
በምዕራፍ ስድስት “የረገምከው ርጉም ይሆናል” በሚለው ንዑስ ርዕስ
የምንመለከተው ይሆናል።

311
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከዐዲስ አበባ ወደ ናዝሬት ከአባቴ ቤተሰብ ጋር ኑሮችንን


ለማድረግ ከተንቀሳቀስንበት ጊዜ ጀምሮ (1989 ዓ.ም)
የናዝሬት አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ጉባኤ አፍቃሪና
ታዳሚ ነበርኩ። ለዚህ ምክኒያቴ ደግሞ በዐዲስ አበባ ገርጂ
ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ ይርዳው ተሰማ280 ይመራ
በነበረው የምስክርነት ቡድን ውስጥ ሳገለግል የተፈጠረብኝ
ተጽዕኖ ነበር። በዚያን ወቅት ከምስክርነት ኅብረቱ ጋር
ለረጅም ወራት ጾምና ጸሎት እየያዝን ስለኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን መለወጥ በዕንባና በታላቅ የርሃብና የመራራት
ስሜት እንጸልይ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ታዲያ በናዝሬት
ማርያም ቤተክርስቲያን የተነሣውን የተሓድሶ እንቅስቃሴ
መስማት ጀምረን ነበር። በዚህም ምክንያት የናዝሬት
አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን የዚሁ ምልጃ መልስ እንደሆነ
አስብ ስለነበር የተሓድሶ እንቅስቃሴውን በዓይኔ ማየት በቃላት
ከምገልጸው በላይ ልቤ ይናፍቅ ነበር።

የአማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን በናዝሬት ማርያምና


ኪዳነ-ምህረት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናት ውስጥ
በሚገኙ ወጣቶች መኻል በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የተከሰተ
መነቃቃት ውጤት ናት። በወቅቱ ታዲያ የአማኑኤልን ጉባኤ
ረግጦ በምድሪቱ ላይ እንደማዕበል የፈሰሰውን የሽብሸባ

280
አሁን በሎስአንጀለስ የምትገኝ ቃዴስ ቤተክርስቲያን ፓስተር።

312
ጆንሰን እጅጉ

መዘምራን የዝማሬ ቅኔ ለመስማት የማይመኝ የለም ነበር።


የመለኮት ህልውና እንደ ደመና አብሮት ይንቀሳቀስ የነበረው
መጋቢ ዳንኤል አለማየሁ የሚሰብከው ቃል ኃጢአተኛውን
ለንስሓ የሚያበቃ፥የወደቀውን የሚያነሳ፣ ተስፋ የቆረጠውን
ተስፋውን የሚቀጥል፣ የጠወለገውን የሚያለመልም ነበርና
ጉባኤውን የበለጠ ተናፋቂ ያደርገው ነበር። እኒዲሁም ሁሉ
ተወዳጅ ዲያቆናትና አስተማሪዎች የጉበኤው ውበቶች ነበሩ።

ከዕለታት አንድ ቀን ይህንኑ የቅዳሜ ምሽት አምልኮ በጕጕት


ታደምኩኝ። ከተለመደው ጣዕመ ዜማ በኋላ በወቅቱ
ከቤተክርስቲያኒቱ ብርቅዬ አገልጋዮች መኻል አንዱ የስብከት
መልዕክት ለማስተላለፍ ወደ መድረክ በመውጣት የኢየሱስን
የማዳን ኀይል ትልቅነት በሞቀ ስሜት መናገር ጀመረ፤
አሜንታችንን በሞቀ ጭብጨባ ገለፅንለት። ይሁን እንጂ
ብዙም ሳይቆይ መልዕክቱ ጉባኤ ወደ መውቀስና መዝለፍ
ተቀየረ። ወቀሳው የንስሓ ጸሎትን የሚቃወምና የሚከለክል
ነበር።

ሙሉ ስብከቱን ማስታወስ ባልችልም ድንገት ከወንበሬ


አስፈንጥሮ ያስነሳኝንና እጅግ አከብራውና እፈራው የነበረውን
ጉባኤ ለቅቄ እንድወጣ ያደረገኝን ንግግር ግን አልረሳውም።
እንደዚህ የሚል ነበር “ኢየሱስ አንድ ጊዜ ደሙን በማቅረብ
ቀድሶናል። እዚህ እየመጣችሁ ማረኝ እያላችሁ አታልቅሱብን!

313
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደዚህ አይነቱ ጸሎት ሟርት ነው። አታሟርቱብን!” ወጣቱ


ንግግሩን ያስተላለፈው ምንም ማዋዛት በሌለበት በሙሉ
ድፍረትና ቁጣ ጭምር ነበር።

ወደ ፍጹምነት ለማደግ የዳዴ ጉዞ የጀመሩ ህፃናት በሚበዙበት


ጉባኤ እንደዚህ ዓይነቱ ራስን መመርመርን የሚያጨናግፍ
ንግግር ምን ይሉታል? ንስሓንስ ሟርት ነው ብሎ አክርሮ
መናገር ምን ማለት ነው? ወቅቱ ቤተክርስቲያኒቱ ለቃለ
እግዚአብሔር ፍተሻ ከፍተኛ ትኩረት የምትሰጥበት ጊዜ ነበርና
ያንን ወጣት ሰባኪ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ደግሜ በቤተክርስቲያኒቱ
መድረክ ላይ አላየሁትም።

ዛሬ ላይ ቢሆን ግን ያ ወንድም ተመሳሳይ ነገሮችን


የሚናገርበት ብዙ የመድረክ ዕድል በብዙ ቤተ-እምነት
መድረኮች ባገኘ ነበር። በሌላ በኩል በዚያን ወቅት ማለትም
“እዛ ቤተክርስቲያን እንዳትሄዱ ስኹት ነው።” በሚባልበት፤
በተለይ ደግሞ አገልጋይ “እዚያ ውጉዝ ቤተክርስቲያን ሲሄድ
ታይቷል።” የሚል ወሬ ከተሰማበት ቢሮ በሚጠራበትና
ከአገልግሎት በሚታገድበት ዘመን፤ በመድረኮቻችን ላይ
እንዲህ ዐይነት እንግዳ ትምህርቶች ብቅ እያሉ ይታዩ ከነበረ፤
አብዛኛዎቻችን ለዘብተኛ በሆንበት ከትምህርትና ሕይወት
ጥራት ይልቅ ክህሎት ላይ ትኩረት ባደረግንበት በዚህ ዘመን፤
ምን ያኽል እንግዳ ትምህርቶችን እያስተናግድን ይሆን?

314
ጆንሰን እጅጉ

ይህ ከሆነ ከአሥር ዐመታት በኃላ በ 2009 ዓ.ም ይህንኑ ጉባኤ


አስጥሎ ያስወጣኝን ተመሳሳይ ንግግር የአንዲት
ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑ መጋቢ በቴሌቪዥን መስኮት ቤቴ
ድረስ ገብተው ሲናገሩ ሰማሁ። ይህ የተደገመ ስብከትም ነገሩ
አንድ ተመሳሳይ የሥነ-መለኮት ምንጭ እንዳለው
አረጋገጠልኝ። እንዲህ ዓይነቱን በስውር በሰው ልብ ላይ
የተዛመተን ስኹት ትምህርት ከትውልድ ላይ ማንሳት የዋዛ
አይደለም። እርግጥም ስሕተትን ማጥራት በኒኩለር ጨረር
የተበከለን አከባቢ ለማጽዳት እንደመሞከር አድካሚ እንደሆነ
እንዳስብ አድርጎኛል።

ዋኖቹ የእምነት እንቅስቃሴ “አማልክት” ንስሓን የሚጠሉበት


ምክንያት ዐሉታዊ ኔጌቲቭ ቃል እንዳይናገሩ መጠንቀቅ
ስለሚፈልጉ ነው። ለምሳሌ እንደ ኪኒየን ትምህርት ከሆነ
ኃጢአትን መናዘዝ እንኳ የሽንፈት ምክንያት ነው። ይህንንም
ሲናገር “የኃጢአተኝነትን ወይም የንስሓ ቃል አንናገርም።
በክርስቶስ የሆነውን እንናገራለን። ክርስቶስ በኛ ውስጥም ምን
እንደሆነ፤ በአፋችን ላይ ያለውን የእርሱን ቃል”281ብሏል።
የእምነት አባቶች ግን ንስሓ ሲገቡ የሚናገሩት ዐሉታዊ ንግግር
ክፉ ተጽዕኖ እንዳያስከትልባቸው አይፈሩም ነበር። ያሉበትን
ውድቀት አብራርተው በግልጽ ንስሓ ከመግባትም አይሸሹም።

281
E.W. Kenyon. The Hidden Man. (P. 120).

315
የአማልክቱ ዐዋጅ

“በጭንቀቴ ደክሜያለሁ፣ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፣


በእንባዬ አልጋዬን አርሳለሁ”(መዝ.6፡6)። ምናልባት ይህ
የብሉይ ኪዳን የእንሰሳት ደም ባለበት የነበረ ልምምድ ነው
ብለን የምናስብ የዋኻን ብንኖር (1 ዩሐ.1፡9) ብንመለከት
እደተሳሳትን እንገነዘባለን። ምክንያቱም ይህ ክፍል ለአማኞች
የተጻፈ ደብዳቤ እንደሆነ እናውቃለን።

በተጨማሪም ምንም እንኳ የድነት ንስሓ(ሉቃ.5፡32) አንድ


ጊዜ የገባን ቢሆንም እጸጽን የማረምና የመመለስ ንስሓን
ቤተክርስቲያን እንደታዘዘች የራዕይ መልዕክት
ያሳየናል።“እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ
አስብ፣ ጠብቀውም ንስሓም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ
ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ
አታውቅም።” (ራዕ.3፡3 ራዕ.2፡5,16,3፡19)። ከዚህ ለጥቆም
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አማኞችን ለንስሓ እንደሚወቅስና
እንዴት እንደሚያዘጋጃቸው ማየት ይቻላል።(2 ቆሮ.7፡8-
10)። ንስሓ የማያምኑ ሰዎች ከፈጣሪ ጋር የሚታረቁበት
የዕርቅ መንገድ ነው። አማኞች ደግሞ የአምላካቸውን ፊት
ዘወትር ለማየት የሚቀርቡበት የእንደገና ዕድል። በአጠቃላይ
ንሰሐ መለኮታዊ ትዕዛዝና የፍጽምና መንገድ እንጂ ሟርት
አይደለም።(ዕብ.4፡6)።

316
ጆንሰን እጅጉ

አላምጥም አለችኝ
ሐምሌ መጀመሪያ አከባቢ እንደወትሮው ሁሉ ዐዲስ አበባ ላይ
ከበድ ያለ ዝናብ እየጣለ ነበር። ዝናቡ ጋብ እንዳለ ቡና
እየጠጣን ከተጠለልንበት ካፍቴሪያ ከሳቂታው አቤል አየለ ጋር
መኪና ወዳቆምንበት የኢትዮጵያ ኢቫንግሊካል መጽሐፍ
ቅዱስ ኮሌጅ ግቢ አመራን። በካፊያ ውስጥ እየተራመድን
እየፃፍኩ ያለሁትን መጽሐፍ ዐሳብ አንስተን መጫወት
ጀመርን። አቤል የመጽሐፉን ዐሳብ ወዶታል። አቤል የቃል
ኀይል ሥነ-መለኮት የክርስትናን ድነት ትምህርት
እስከማበላሸት የሚደርስ የተለጠጠ አስተምህሮ ነው የሚል
አቋም አለው።

የዚህም የቃል ኀይል ሥነ-መለኮት ጽንሰ-ዐሳብ መሠረት


ከተናጋሪዎቹ አፍ ወስደን ያየን እንደሆን ‘ድነት ፓኬጅ ነው!
ከዛም ውስጥ የኃጢአት ይቅርታ አንዱ ጥቅል ነው! የምድር
በረከት ደግሞ ሌላው ጥቅል ነው። የፈለከውን መጥራትና
መክፈት ያንተ ድርሻ ነው’ የሚል ሆኖ እናገኛለን።282 አቤል
ይህንን ዐስተሳሰብ ሊያስረዳኝ እንደሞከረው የቃል ኀይል ሥነ-

282
ድነት በውስጡ መንፈሳዊና ምድራዊ በረከት “ጥቅል” የያዘ ነው የሚለው
ትምህርት የኪኒየንና የኬኔት ሄገን ስኹት ፍልስፍና እንደሆነ በምዕራፍ አንድ ላይ
“ኢ. ደብልዩ ኪኒየን” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል።

317
የአማልክቱ ዐዋጅ

መለኮት ገንዘብ ማግኘትንም ሆነ አለመታመምን የድነት ክፍል


እንደሆኑ ማመን እንዳለብንና ማንኛውንም ዐሉታዊ ንግግር
እውነትነት ቢኖረውም እንኳ መካድ እንዳለብን እስከ
ማስተማር እንደሚደርስ ነው። ይህንንም ለማስረዳት አቤል
ከወራት በፊት ያጋጠመውን ገጠመኝ ያወጋኝ ጀመር።

አቤል በቅርቡ በአንድ ጓደኛው ሰርግ ላይ ሚዜ ሆኖ ነበር።


ገጠመኙ በሰርጉ ላይ ሚዜ ከነበሩ ወጣቶች ጋር ከዐዲስ አበባ
ሃዋሳ፤ ከሃዋሳ ዐዲስ አበባ ይጓዙ ስለ ነበር በዚህ መኻል
የተፈጠረው የክርስትና እምነት ጭውውት ነበር። አቤል ብዙ
ማውራት የማይወድ ዝምተኛና ጥሩ አድማጭ ወጣት ነው።
አብረውት ይጓዙ ከነበሩ ወጣቶች አንደኛዋ አቤል
እንዳጫወተኝ ምናልባትም የቃልን ኀይል በመፍራት ይመስላል
ብዙም ሌላ ሰው በእምነቷ ላይ እንዲናገር የማትፈልግ ወጣት
ናት። እቺ ወጣት ታዲያ በጭውውታቸው መኻል አጥብቃ
የተከራከረችበት ነጥብ ነበራት።

ይህም ድነት ከመከራና ከኑሮ ትግል ነፃ ያወጣናል የሚል ነው።


አቤል ሲናገር ልጅቱ ይህንን ስታስረዳ በተደጋጋሚ “already
ድነናል” ትላለች ይላል። ይህንንም ስታብራራ “መከራ ወይም
ልፋት ርግማን ነው። የአዳም ውድቀት ውጤት ነው።
በክርስቶስ የተቀበልኩት ያለ-ልፋት እንድኖር ነው። ልፋት የኔ
አይደለም!” ትላለች። ልጅቱ የምትናገረው ነገር ከፊል

318
ጆንሰን እጅጉ

እውነትነት ቢኖረውም በጣም ተለጥጧል ይላል አቤል።


በግርምት እርሷን ለማስረዳት የሞከረበትን ሁኔታም ሲያነሳ፦

“ይህ ከሆነ ለምን ከልፋት፣ ከመከራና ከሥጋ ሞት


አናመልጥም? እሺ አማኝ ምንም ዐይነት ሥቃይና መከራ
እንደማይደርስበት እንስማማ። በወሊድ ጊዜ ያለውን
ተፈጥሯዊ ምጥ እንዴት ታይዋለዋሽ? ከአካላዊ ህመምና
ሞትስ ለምን አናመልጥም?” በማለት ጠየኳት ይላል።

አቤል ለዚህ ጥያቄው ልጅት የሰጠችውን ምላሽ ሲያስረዳኝ፦


“አላምጥም አለችኝ።” ይላል።

የአቤል ቀጣዮ ጥያቄ ታዲያ “እሺ . . . እንዴት ይሆናል ታዲያ?


ካላማጥሽ በቀዶ ህክምና ነው የምትወልጂው ማለት ነው?
ያም ደግሞ ህመምና ሥቃይ አለው!” የሚል ነበር።

አቤል የልጅቱን ቀጣይ መልስ ሳቅ እየታገለው ሲነግረኝ


“አስነጥሼ ነው የምወልደው!” አለችኝ ይላል።

በሳቅ የሚፍለቀለቀውን የአቤልን ቀይ ፊት በግርምት


እየተመለከትኩ “አልገባኝም ምን ማለቷ ነው?” በማለት
ጠየኩት።

319
የአማልክቱ ዐዋጅ

አቤል ሳቁን ለመግታት እየታገለ “ያው መጥፎ ሽታ


አፍንጫውን እንደሰረሰረው ሰው ‘አጥሴ’ ስል ወልዳለሁ ማለቷ
ነው” በማለት በትዕግሥት አስረዳኝ።

እኔም በግርምት “ምን ዐይነት ትምህርት ብትማር ነው


እንደዚህ አስቸጋሪ የሆነችብህ?” በማለት አቤልን ጠየኩት።

አቤል “ያው! ልጅቷ የጃፒ ተማሪ ነች!” በማለት መለሰልኝ።

በርግጥ ጃፒ ይህንን ዐይነት ትምህርት አስተምሮ ከሆነ በእነ


ክሬመር የዲበ-አካል ሃይማኖት ትምህርት ተጽዕኖ ሥር
ወድቋል ማለት ይቻላል። ብዙዎቹ የእምነት እንቅስቃሴ
መሪዎች ለሁለት ምዕተ-ዐመት ያኽል ይህንን ትምህርት
የሙጥኝ ብለውታል። እንዲህ ዓይነቱን የጨለማ ትምህርት
ጃፒም ሆነ እርሱን መሰሎቹ ተጋብተው የቅዠት ጀልባ ውኃ
በሌለበት የከተማ አስፓልት ላይ ለመቅዘፍ መሞከራቸው ቂል
አልያም እብድ እንደሆኑ ያስመሰክርባቸዋል።

ልጅቱ ማንኛውንም ክፉ የምትለውን ነገር፤ ተፈጥሯዊ


ክስተቶችን ጭምር እየካደች ነው ያለችው። ይህንንም
በማድረጓ በወሊድ ሰዓት ከሚፈጠር ህመም እንኳ
እንደምታመልጥ ታምናለች። እንደ እውነቱ ከሆነ ከሥር
መሠረቱ እንደተመለከትነዉ የዚህ ትምህርት ጀማሪ ጃፒ

320
ጆንሰን እጅጉ

ሳይሆን የዲበ-አካል ሃይማኖት “አማልክት” ስለሆኑ ትልቁን


የባለቤትነት ድርሻ ይወስዳሉ።283

እግዚአብሔርን መስማት ለምኔ?


ነቢይ ወይም የእግዚአብሔር ሰው መልካም ምኞቱን ወይም
የበረከት ቃል መናገር ይችል ይሆናል። ይሁን እንጂ መልካም
ንግግር ወይም የበረከት ቃል በፍጹም መለኮታዊ ትንቢትን
ሊተካ ወይም በእግዚአብሔር ፈቃድ ከሚነገር ትንቢት ጋር
ሊስተካከል አይችልም። እንዲህ ዓይነቱ ሚዛን ያልጠበቀ
አገልግሎትም ሆነ ልምምድ የሕዝብን ልብ ከመለኮት ላይ
ይሰርቃል። በእርግጥ አቤሴሎም የእስራኤልን ሕዝብ እያባበለ
ከንጉስ ዳዊት ላይ ይሰርቅ እንደነበር የቃል ዐዋጅን ልዩ ጸሎት
በመጠቀም ሆን ብለው የሕዝብ ልቦና ወደ ራሳቸው የሚሰርቁ
አገልጋዮች መኖራቸው ሐቅ ነው። “እንዲሁም አቤሴሎም
ከንጉሥ ፍርድ ሊሰማ ከእስራኤል ዘንድ በሚመጣ ሁሉ ያደርግ
ነበር፤ አቤሴሎምም የእስራኤልን ሰዎች ልብ
ሰረቀ።”(2 ሳሙ.15፡6)።

“የተቀቡት ነቢያት” አማኙ ዓይኑን ወደ እነርሱ ማድረጉ


ትክክልና ለችግሩ መፍትሔ የሚያጭድበት ብቸኛ መንገድ
እንደሆነ አድርገው በተቀነባበሩ የቪዲዮ ምስክርነት
283
ይህን ለማረጋገጥ በምዕራፍ ሁለት ላይ የተዘረዘሩትን የዲበ-አካል ሃይማኖት
መሠረታዊ ፍልስፍናዎች ይመለከቷል።

321
የአማልክቱ ዐዋጅ

ማስታወቂያቸው ሳይቀር እያስጎሰሙ በማሣየት ያባብሉታል።


ከፊሉ ዕድሉን አግኝቶ “ቃል ወጥቶለት” በተስፋ ልቡ ሞቆ፣
ስሜቱ ጣራ ነክቶ፣ በደስታ ጩኸት ጉባኤ ያደምቃል። ከፊሉ
ደግሞ ቃል ቢወጣለትም ውሎ አድሮ “የወጣው ቃል”
ሳይሰምርለት ይቀራል። ደግፎ የሚያጽናናው የጠቢብ ቃል
በልቡ ሲናፍቅ፤ አሳፋሪ ልምምዳቸው እንዳይጋለጥባቸው
ስለሚፈሩ ዳግም ወደ መድረክ እንዳይጠጋ ይገፈትሩታል።
እምነት የለህም በሚል ማመናጨቅ ሕሊናው ተነርቶና
ኮስምኖ ከጉባኤ ይለቃል። በክርስትናው ያፍራል! በደረሰበት
የልብ ስብራት ያቀረቅራል፤ በመጨረሻም እስከ ወዲያኛው
እግሩን ከጉባኤ ለመሰብሰብ ይወስናል። ጸሎትንም ሆነ
ትንቢትን ቃል ከማውጣት ጋር አቻ አድርገው አሳይተውናል።
በውጤቱም የጸሎት ትርጉም ተለውጦብናል! ትንቢት
ቀሎብናል! ብዙዎቻችን ይህንን የእንቦጭ አረም ከመንቀል
ይልቅ “አትፍረድ” በሚል ማስፈራሪያ ተታለንና “የቀባቸውን
አትንኩ” በሚል ማታለያ ተሸብበን ስኹትን የምናሳድግ
ተባባሪዎች ሆነናል!

“ቃል በማውጣት” ዝናን ካተረፉ የመድረክ ባላባቶች መኻል


አንዱ “አማልክት ሐዋርያ” ይህንንኑ ልምምድ ተግባራዊ
ሲያደርግ በግል ቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ መመልከት የተለመደ
ነው። ሰውየው እግዚአብሔርን መስማት ለምኔ? ያለ

322
ጆንሰን እጅጉ

ይመስላል። ይህ ሰው በብዙዎች “ምንም ትምህርት


የማያስተምርና አላዋቂ ነው” ቢባልም። የዲበ-አካል
ሃይማኖትን ረቂቅ የቃል ትምህርት ግን ያስተምራል፤
ይተገብራል። ቃል የማውጣት ትምህርቱንም“ጸሎት” ብሎ
ይጠራዋል። የእርሱ “ቃል ማውጣት” ልምምድ ከትንቢት
እኩል ምን ያኽል የሰውን አቅጣጫ የመወሰን ዐቅምም
እንዳለው ይናገራል። ለዚህ ምሳሌ እንዲሆነኝ ካስተላለፋቸው
የመድረክ ምስሎች መኻል ከዮቲዩብ ላይ ከወረደው
ከአንደኛው ላይ የወሰድኩትን ላስነብባችሁ። በመጀመሪያ
“ሐዋርያው” ሕዝቡን “እስቲ ከዚህ መኻል ነቢይ ለመሆን
የሚፈልግ ማነው? ትፈልጋላችሁ?” በማለት ይጠይቃል።
ሕዝቡም “አዎ” በማለት ከመቀመጫው ተነስቶ ይጮኻል።
በመቀጠል በሁለት መንገድ ነቢይ መሆን እንደሚቻል
ያስተምራል።

አንዳንድ ሰው ማለት ነው፤ ከማገለግለው


ከእግዚአብሔር ሰምቼ ማለት ነው፤ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል ብዬ የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምቼ ባንተ
ላይ ባመጣ ፀጋው አንተን ያገኝሃል። ጥሪ ያለባችሁ
ሰዎች አላችሁ፤ ነቢይ እንደምትሆኑ። ትሆናላችሁ!
በሌላ መንገድ ማለት ነው፤ ፈጽሞ ከእግዚአብሔር
ሳልሰማ፤ በራሴ ወጪ ብጸልይ ነቢይ ነው የምትሆነው።
እየሰማችሁ ነው? ላንዳንዱ ከጌታ ሰምቼ ማለት ነው፤

323
የአማልክቱ ዐዋጅ

ስሙ እንትና ይባላል፣ ሥራው ይሄ ነው፣ ይሄን ሥራ ትቶ


ወደ እዚህ ይሄዳል ብል ማለት ነው ነቢይ ይሆናል። ነቢይ
አደርጋለሁ ብሎ ጌታ ተናግሮኝ ከጌታ ሰምቼ ብጸልይ
ነቢይ ነው የምትሆኑት። ከጌታም ምንም ሳልሰማ
እንደው ተናድጀም ማለት ነው፤ ና ብዬ ብጸልይ ማለት
ነው፤ ነቢይ ነው የምትሆኑት። አንተን ነቢይ ለማድረግ
ከጌታ መስማት የለብኝም። አይጠበቅብኝም! አንተን
ነቢይ ለማድረግ እኔ በራሴ ወጪ ነቢይ ነህ ብል ማለት
ነው፤ ነቢይ ትሆናለህ።

በማለት ይናገራል። “አማልክቱ ሐዋርያ” ደጋግሞ “ብጸልይ”


በማለት የሚያነሳውን ድርጊት አመልካች ቃል “በራሴ ወጪ
ነቢይ ነህ ብል” በሚል ድርጊት አመልካች ዓረፍተ ነገር ተክቶ
ስለሚያብራራው፤ የጌታን ፍቀድ ወይም ይሁንታ መጠየቅ
እንዳልሆነ አንባቢ ያስተውል። ይሁን እንጂ በዚህ ማብራሪያ
ውስጥ ብጸልይ የሚለውን ድርጊት አመልካች ቃል ለአንድ
አይነት ዐሳብ ብቻ አይጠቀመውም። ትንቢት መናገር ጸሎት
እንዳልሆነ ብናውቅም እርሱ ግን ጌታን በመስማት ወይም
ፍቃዱን በመለየት ትንቢት መናገር ለሚለውም ዐሳብም
ያውለዋል። በአጠቃላይ እየተባለ ያለው “ጸሎት” በመጽሐፍ
የምናውቀው ጸሎት ሳይሆን “ከጌታ ሰምቶ ትንቢት መናገር”
ወይም “በራስ ወጪ ቃል ማውጣት” (“ትንቢት መናገር”)

324
ጆንሰን እጅጉ

ነው። ይህም ልዩ ጸሎት በማለት በተደጋጋሚ ያነሳነው የልዩ


ዲበ-አካል ልምምድ ነው።

በቪዲዮው ላይ እደሚታየው “ሐዋርያው” በዚህ ማብራሪያው


የእርሱ በእራሱ ወጪ (ፈቃድ)‘ከጌታ’ ሳይሰማ “ቃል
ማውጣት” ከትንቢት እኩል ፍላጎትን እውን የማድረግ
ጉልበትና ስልጣን እንዳላቸው በግልጽ አስረድቶ ሕዝቡን
ከመቀመጫ ማስነሳት ችሏል። “የሐዋርያውን” ንግግር የዋኽ
ንግግር ነውና እንደልማዳችን “በቅንነት” እንመልከተው ብለንና
‘ብጸልይ’ ለሚለው ቃል የራሳችንን የተስተካከለ ትርጉም
ሰጥተን ‘እግዚአብሔርን ብለምን’ ማለት ፈልጎ ነው ብንል
እንኳ “በራሴ ወጪ” የሚለው ተደጋጋሚ ስንኝ ያግደናል።
ይሁን እንጂ “ሐዋርያውን” ይሄ ይፋ ንግግሩ ግልፅነቱን
አመላክቶኛል። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የቃል ኀይል ብልጥ
ተለማማጆች “የአስማት ምስጢር ካልደበቁት ይከሽፋል”
እንደሚባለው የስሌታቸውን ሚስጥር አይናገሩም። የምትሃት
ምስጢራቸውን በልባቸው ሰውረው የሚነግሩን ላይ ላዩን
ስለሆነ እንዲህ በቀላሉ አናስተውላቸውም።

ከላይ እንዳሰፈርኩት የነቢይ “ቃል ማውጣትና” ትንቢት እኩል


ከሆኑ፤ በእምነቱ የደከመ ሰው የማይታየውን እግዚአብሔር
ከመፈለግና የእርሱን ይሁንታ ከመሻት በዐይን የሚታየውን
እንደኛ ሰው የሆነውን “ነቢይ” መማጸን የተሻለ መንገድ ነው

325
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሊል ይችላል። ምክንያቱም ሥጋ ለለበሰ የሰው ልጅ


የማይታየውን አምላክ ከመማጸን ሥጋ ከለበሰው ነቢይ ጋር
መደበኛም ይሁን መደበኛ ያልሆነ ድርድር በማድረግና ዋጋ
በመክፈል ምላሽ መጠበቅ ቀላል ስለሚሆንለት ነው። ስለዚህ
ብዙዎች በተለይም ደግሞ በገንዘብ ሀብታም የሆኑና በእምነት
የደኽዩ ይህንን መንገድ የተሻለ አቋራጭ መንገድ እንደሆነ
በማመን ይመርጡታል። እነኝህ ሰዎች ከገስት ሐውስ ክፍያ
አልፈው ለህንፃ ግንባታ የዳጎሰ ገንዘብ ቢለግሱ የሚያስገርም
አይሆንም።

ነገር ግን ካቀድነው የማያደርስ ከአምላክ የሚያርቅ ልምምድ


እንደሆነ ልብ ማለት ይገባል። ትንቢት ከሰው ቃል ጋር
ሊወዳደርም እኩል ሊሆንም በፍጹም አይችልም።
ምክንያቱም ትንቢት በመለኮት ሥልጣንና ፈቃድ የሚነገር
ነው። በአንፃሩ የሰውን ልጅ ከመለኮት ጋር እኩል የሚያደርገው
ሥልጣንም ይሁን ማንነት የለም። አሊያም መለኮትን
ሊያንቀሳቅሰው የሚችል የሰው ስልጣን ወይም የቃል ዐዋጅ
የለም! በሰው ፈቃድ ወይም ሰው በራሱ ወጪ በሚናገረው
ነገር የሚንቀሳቀስ ኀይል ካለ ግን ካለምንም ጥርጥር እርሱ
መለኮት ሳይሆን አጋንት ነው። ልንገስጸው እንጂ
ልናጨበጭብለት በፍጹም አይገባም። ምክንያቱም መለኮት

326
ጆንሰን እጅጉ

ፍቃዱን የማይሸጥና ለሌላው ፈቃድ የሚያስገዛ “ከአማልክት”


እንደ አንዱ አይደለም!

ትንቢት መናገር ቃል ከማውጣት ወይም ከማወጅ እጅግ የላቀ


መንፈሳዊ ስጦታ ነው። ምክንያቱም ትንቢት የሚነገረው
በመንፈስ ቅዱስ መነዳት ነው። “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ
አልመጣምና፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች
በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።”(2 ጴጥ.1፡21)።
የትንቢት አገልግሎት የሰው የይሁንታ ቃል የማይተካው፤
የተቆረጠ የሚፈጸም የእግዚአብሔር ዐሳብና ሙሉ ፈቃድ
ነው። እዚህ ላይ አንድ ሰው ጥቅስ ጠቅሶ “ከእርሱም ይልቅ
እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን።”(2 ጴጥ.1፡19) እንደሚል።
“ያወጣሁት ቃል የእራሴ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ነው።”
በማለት ይሞግት ይሆናል። በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል
የትንቢት ቃል መሆኑ ምንም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ
አይደለም። ያም ቢሆን ግን የትንቢት ቃል በተስፋ
የምንጠብቀውና የምንታዘዘው እንጂ እንዲፈጸም በማወጅ
የምናግዘው በጭራሽ አይደለም። በግልጽ ቃል “የዚህን
መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ።”(ራዕ.22፡
7) ነው የተባለልን እንጂ የሚያውጅ አልተባለልንምና
ብፅዕናውን ለማግኘት የሚያስፈልገን ማወጅ ሳይሆን መጠበቅ
ነው።

327
የአማልክቱ ዐዋጅ

የምኞት እስር
በ 1986 ዓ.ም የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ስለነበርኩኝ፤ የጂሴ
ትምህርት ቤት የተማሪ ኅብረት መሪ ሆኜ አገለግል ነበር።
በዚያ የልጅነት ዘመኔ በጥልቅ የኀላፊነት ስሜት የተማሪዎችን
ሕይወት በቅርበት መከታተል ሥራዬ ነበር። የብዙዎቹ
ክርስቲያን ተማሪዎች ሕይወት የተቀጣጠለና ሩቅ ለማረፍ
የሚምዘገዘግ ነበር። የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርታቸውን
በጥሩ ውጤት አጠናቀው ዩኒቨርስቲ የገቡ ወጣት ተማሪዎች
ለተማሪው ሞዴል እንዲሆኑልን ስለምናስብ እንዲጎበኙንና
እንዲያገለግሉን በተደጋጋሚ ዕድል እንሰጣቸው ነበር። ታዲያ
አንድ ቀን ከነዚሁ የቀድሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ተማርዎች መኻል ከነበረ አንድ ወጣት ጋር መንገድ አገናኘን።
ከዩኒቨርሲቲ እየመጣ ነበር። መንገዳችን አንድ ነበርና ረጅም
የመጨዋወት ዕድል አገኘን።

የዩኒቨርስቲ ቆይታውንና የክርስትናውን ሁኔታ


እንዲያጫውተኝ ጠየኩት የያዘውን ደብተር እንደማይረባ
ከንቱ ነገር እያጣጣለ ይነግረኝ ጀመር። “ይሄን ደብተር ከፈለኩ
እጥለዋለሁ። ለኔ ኢየሱስ ሁሉን ነው። ለመኖር መማር
አያስፈልገኝም። ሁሉ አለኝ። የምድሪቱ ሐብት የእኔ ነው!”

328
ጆንሰን እጅጉ

አለኝ። የማልጠብቀውን ነገር ነበርና በምሰማው እጅግ


ደነገጥኩ። አስፈራኝ! ኢየሱስን ከፍ ወዳለ ተራራ ላይ አውጥቶ
የምድር ነገስታት፤ ክብራቸውንም አሳይቶት ሁሉ የእኔ ነው
ወድቀህ ብትሰግድልኝ ላንተ እሰጥሃለው ያለው ሴጣን ዳግም
ተገልጦ የምኞት ወጥመዱን እየዘረጋ እንደሆነ ተሰማኝ። ይሄ
ወዳጄ ካለምንም ህጋዊ ፈቃድ የከተማዋን ሐብት ሁሉ
በምኞት ማግበስበሱ፤ ይልቁንም ለኑሮ የሚያስፈልገውን ገቢ
ለማግኘት እንዲችል የሚያበቃውን ትምህርት እንዲህ
ማጣጣሉ ለምን ነበር?

በወቅቱ በነበረኝ ዐቅም ያንን ወጣት እውነትን አስረድቶ


ከገባበት የህልም ዓለም ማውጣት ለእኔ ከባድ ነበር።
በዕድሜም፣ በትምህርት ደረጃም በአገልግሎትም ይቀድመኝ
ነበርና ዳገት ሆነብኝ። ከጥቂት ወራት በኃላ ታዲያ ያ የት
ይደርሳል የተባለ የደረጃ ተማሪ ከዩኒቨርስቲ ተባሮ የጎዳና
እብድ እንደሆነ ሰማሁ። ያን ዕለት ታዲያ ዕንባዬን አውጥቼ
ስቅስቅ ብዬ በጌታ ፊት አልቅሼያለሁ። እንደዚህ ሩቅ
ያሰብናቸው ስንቶቹ ብርቅዬ የቤተ-እምነት ልጆች በምኞት
ሠረገላ ሽቅብ ወጥተው ሲያበቁ፣ የሚጨብጡት ሲያጡና
ሁሉ ውሸት ሲሆንባቸው የአዕምሮ ህሙማን ሆነው
ልብሳቸውን ጥለው አዘቅት እንደወረዱ ታሪክ ይመስክር።

329
የአማልክቱ ዐዋጅ

እህህ . . . ስንቶቻችን ወንጌል በእንግሊዘኛ የሚናገሩ ፂማቸው


የረዘመ፣ ጸጉራቸው የተንጨበረረ፣ ውድቅዳቂ ጫትና ሲጋራ
በጃቸው የሰበሰቡ ወጣቶች በየጎዳና አጋጥመውን ያውቅ
ይሆን? ስንቶቻችንስ የምዬን ወደ አብዬ እንዲሉ፤ ከንፈር
መጠን “አይ የሰው ክፋት! አስደግመውበት ነው! መዳኃኒት
አስነክተውት ነው!” ብለን አልፈናቸው ይሆን? እኛጋ ያለውን
በየመስባኩ ላይ የቆመውን ወደ ዕብደት ዐግቶ የሚጋልበውን
ከንቱ የምኞት ፈረስ እንዳናይ ማነው ዓይናችንን ያሰረን?
በእዚህ አጭር እድሜዬ ክርስቲያን አያብድም ብዬ
በተከራከርኩበት አንደበቴ በተደጋጋሚ አፍሬያለሁ።

ሐብት ለማግኘት የሚያስፈልገው መሥራት ነው ለመሥራት


ደግሞ ሥራው የሚፈልገውን በቂ ክህሎት መያዝ ይጠይቃል።
ለዚህ ደግሞ መማር አንዱ መንገድ ነው። መጋቢ አመሉ ጌታ
መጋቢያዊ ምክራቸውን እንዲህ በማለት ያትታሉ።

ምትሃታዊ በሆነ መንገድ መበልጸግ የሚፈልጉ


ሰነፎች በበዙበት በዚህ ዘመን በጸሎት ማዕከላትና
በቤተክርስቲያናት ሰዎች በሥራ ላይ እንዲያተኩሩ፤
ሠርተው ለውጥ እንዲያመጡና እግዚአብሔር
የእጃቸውን ሥራ እንዲባርክላቸውና እንዲበለጽጉ
ማስተማር ያስፈልጋል!284
284
መጋቢ አመሉ ጌታ። የድሆችና የችግረኞች ጩኸት ወጣ። (2010፣ ገጽ፣ 129)።

330
ጆንሰን እጅጉ

የመጋቢው ጥቆማና አስተያየት ልብ ለሚለው ጠቃሚ ነው።


ምትሃት ዱሮ ዱሮ በበርሃ ውስጥ የሚደግሙ ደጋሚዎች
በድብቅ ይሰራሉ ሲባል ነበር የምንሰማው፤ አሁን ግን እንዲህ
አይደለም። መኻላችን ነው ያለው፤ መድረካችን ላይ እዚሁ
አጠገባችን ነው። ይህም ዘመኑ በምትሃታዊ ብልጽግና ምኞት
የተሞላ እንደሆነ ማሣያ ነው። በቴሌቪዥን መስኮት
የታዘብኩትን ቀጥሎ ላውጋችሁ፦

አንዱ ነቢይ ተብዬ ከጉባኤ መኻል አንዱን አስነስቶ


ያስቆመውና “ቤት እንዳለህ ዐያለሁ” ይለዋል።
ሲያብራራለትም “ለመሸጥ ፈልገኽ አልሸጥ ብሎሃል። አንተ
መሸጥ የምትፈልገው አምስት መቶ ሺ ብር ነው ደላሎችም
አይተው አያወጣም ብለውሃል።” ሻጭ ተብዬም “አዎ
የእግዚአብሔር ሰው” እያለ እንደተለመደው መንቀጥቀጥና
ማልቀስ ይጀምራል። ነቢይ ተብዬም በመቀጠል “ቃል
ላውጣበት” ይለዋል። ሻጭ አንገቱን ወደላይ ወደ ታች እያደረገ
“አዎ የእግዚአብሔር ሰው” ነቢይ ተብዬም “ስንት እንዲሸጥ
ትፈልጋለህ?” በማለት ይጠይቀዋል። ሻጭ “እግዚአብሔር
እንደ ፈቀደ” ማለት። ነቢይ ተብዬም በድጋሚ “ቃል ላውጣ
ታምናለህ?” በማለት በአጽንኦት ይጠይቀዋል። ሻጭ በድጋሚ
አንገቱን በመነቅነቅ “አምናለሁ የእግዚአብሔር ሰው ቃል
አውጣ።” ነቢይ ተብዬ “አምስት መቶ ሺ ብር ነው አደለ

331
የአማልክቱ ዐዋጅ

አልሸጥ ያለህ? አምስት ሚሊዬን ብር ሸጥኩት።” በየመካከሉ


ይሰማ የነበረው ማነቃቂያ የሙዚቃ መሳሪያው ተረረር. . .ዲሽ
የሚል ረጅም ሪትም ያሰማል። ሻጭ እጁን አንስቶ “አሜን!
አሜን!” በማለት ሲጮህ ይታያል። ጉባኤው በዕልልታ
ያዳምቃል።

በዚህም ትዕይንት የታዘብኩት የሽያጭና ግዥ ሥርዐት


መለወጡን ነው። በዚህም ሥርዐት ለመሸጥም ሆነ ለመለወጥ
በሥራው ውስጥ ያሉ ማለትም የደላሎች ምክኒያታዊና
ፍትሐዊ ወቅትን ያገናዘበ ግምት ሳይሆን የሚያስፈልገው
“የነቢይ ቃል ማውጣት” ልዩ ጸሎት መሆኑ ነው። “ነቢዩ ቃል
በማውጣት” ሥልጣኑ ተጠቅሞ ከቍጥር በኋላ የሚፈልገውን
ያኽል ዜሮዎችን መደርደር ለእርሱ እጅግ ቀላል ነገር ነው።
የቍጥር ተዓምራት መሆኑ ይሆን? አንባቢ ሆይ፦ ከሚስተው
ጋር መሳታችን ለምንድነው?“ቃል ማውጣት” ከሚባል ሥርዐት
ከሚያዛባ ምትሐት ጋር እንዲህ መተባበራችንና ጉባኤ
ማጣበባችን ለምንድነው? ልባችን በክፉ ምኞት ስለታሰረ
አይደለምን?

ወዳጆች ሆይ፦ ልጠይቃችሁ ከዚህ የሚብስ ምን ምትሃት አለ?


ምትሃትም ይሁን ምኞት ሁል ጊዜ አይሳካም እንጂ አምስት
መቶ ሺ የተገመተ ቤት ተሳክቶ አምስት ሚሊዬን ብር ቢሸጥ
በገዥ ቦታ ሆናችሁ ብታስቡ ምን ትላላችሁ? “አስነክተውት

332
ጆንሰን እጅጉ

ሸጡለት!” ነው የምትሉት “አምኖበት ገዛ”። አንባቢ ሆይ፦


ገዥ የአምስት መቶ ሺ ብር ቤት በአምስት ሚሊዮን ብር
ሲገዛ ሰሚ “እሰየው ቤት ገዛ ይላልን?” እግዚአብሔር
መንግስት መስፋትስ አንጻር ምን ትርፍ ይኖረዋል? “እነኝህን
ሰላቢዎች ተጠንቀቋቸው!” አያስብልምን? ሌላውን አደኽይቶ
በአቋራጭ መበልፀግ መመኘት በርግጥም ምትሃት ሊባል
የሚችል ነው።

ዛሬ ላይ በቤተክርስቲያን ውስጥ የምንተክለውን የዐመፅ ዛፍ


ነገ ላይ የሚመጣው ትውልድ በቤተክርስቲያን አድጎ ሲያገኘው
ዛፉን መልካም ፍሬውን ጽድቅ ብሎ እንዳይጠራው ያሰጋል።
የእምነት ቃል ልምምድ ብለን የሙጥኝ የተጣበቅነው
ዐስተሳሰብ የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና መሆኑን አውቀን
ሥር ሰዶ ሳያድግና ለመንቀል ሳያሰቸግር ከሥሩ ነቅለን
ልንጥለውና ልናጠፋው ይገባል። በምዕራፍ ሦስት ላይ
እንደተመለከትነው በዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል ዐዋጅ የጸሎት
ልምምድ የእግዚአብሔርንም ይሁን የክርስቶስን ምሳሌነት
እየተከተልን ነው የሚል መሸፈኛ ፈጽሞ ተቀባይነት
የለውም። በሚቀጥለው ምዕራፍ ላይ ለዚህ ልምምድ
የሚጠቀሱ በርካታ ጥቅሶች ቢኖሩም ስኹት ሥነ-አፈታትን
እንደተከተሉ እንመለከታለን።

333
የአማልክቱ ዐዋጅ

መቼም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖ መከተል እንዳለብን


ማናችንም እንዘነጋለን ብዬ አላስብም። ይሁን እንጂ የቃል
ኀይል ትምህርትን ለማጽደቅ ልባችንን የሚሞግቱ በርከት ያሉ
ጥቅሶች አእምሯችንን ያንኳኳሉ ብዬ እፈራለሁ። በርግጥ ይህ
ስሜት መፈጠሩ የዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል ዐዋጅ ልምምድ
አጠገባችን ወይንም በመካከላችን እንደሆነ አስረጂ ነው።
የእነኝህ ጥቅሶች አጠቃቀም የዲበ-አካሉን ሃይማኖት እርሾ
ማለትም መለኮታዊ እምነትን ማለተም ዐዋጅ መደጋገምን
እና ምናባዊ ምስል መመልከትን ለማጽደቅ የሚሞክሩ
ብዥታዎች ናቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ በእነኝህ ጥቅሶች
ስኹት ፍቺ አማካኝነት የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስና
በእምነት እንቅስቃሴ ጉያ ውስጥ እንዲሸሸግ አድርጎታል።
ይህንን መደበቂያ ማውገዝ ያቃተን እኛ ታዲያ ትምህርቱ
የስኬት ሁሉ በር እንደሆነ እንድንቆጥር ግፊት ተደርጎብናል።

ማጠቃለያ

የእምነት ቃል ባዕድ ሥነ-መለኮት ያጠላው ጥላ በኢትዮጵያ


የወንጌል አማኞች መንፈሳዊ ልምምድ ላይ አርፏል ማለት
እንችላለን። በዚህ ምዕራፍ ላይ እንዳየነውም በዕውቀትም
ይሁን ባለማወቅ የእምነት ቃል ኑፋቄ የሆነው የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ ልምምድ በዐዲስ አበባ በሚገኙ ወንጌላውያን
አብያተክርስቲያነት አዲስ ዘመን መቀበል በሚል በሰፊው

334
ጆንሰን እጅጉ

ይተገበራል። በፈውስ ጉባኤዎች፣ በጸሎትና በስብከቶች


ይዘወተራል። በናሙና ማሣያነትም በርካታ ልምምዶችንና
በየዓመቱ በተደጋጋሚ የሚፈጸም የቃል ዐዋጅ በዓል ምን
መልክ እንዳለው በትረካ መልክ ተመልክተናል። በትረካውም
ይህው ባዕድ ልምምድ በአማኞች ላይ እያሳደረ ያለውን ግራ
መጋባትና ሥቃይ በጥልቀት ዓይተናል።

በአጠቃላይ የእምነት እንቅስቃሴ ባዕድ የቃል ዐዋጅ ሥነ-


መለኮት የሚፈጥረው ተጽዕኖ ለዕርግማን፣ ለሥራና ለመከራ
ያለንን ግንዛቤ በማዛባት ብልሹ ልምምድ ውስጥ እንደሚከት
የቀረቡልን መረጃዎች የሚጠቁሙ ናቸው። ፍልስፍናው
የጸሎት፣ የእምነትና የንስሓ ልምምዳችንን ምን ያኽል
እንደሚያጎድፍ ተመልክተናል። ዐሉታዊ ተጽዕኖው እንዲህ
የከፋ ቢሆንም እራሱን በጥቅስ መደበቁ ረጅም ዘመን
ለመክረም አግዞታል።

ይሁን እንጂ የመንፈስ ቅዱስን እሳት ሽታ ለለመዱ


መንፈሳዊያን ብልሹ ዲበ-አካላዊ ጠረኑን መለየት
አይቸግራቸውም። የእንቅስቃሴው ረብ የሌለው አካሄድና
በቃለ እግዚአብሔር ላይ ቅጥ ያጣ ድፍረት ቁጣና የቃላት ጠብ
የማስነሣት ግብዣው ከፍ ያለ ነው። ያንን ማድረግ ግን
ማንንም አይጠቅምም። የሳተውንም ለመመለስ አይረዳምና
ይህ መጽሐፍ ያንን አይከተልም። ስለዚህም በቀጣዩ ምዕራፍ

335
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለዲበ-አካል ሃይማኖት ዐስተሳሰብ መደበቂያ የሆኑ የመጽሐፍ


ቅዱስ ክፍሎች በዝርዝር ይነሣሉ። ይህም ዐሳቡን
ከተጣበቀበት ጥቅስ ለማላቀቅ የሚደረግ ነው እንጂ ግለሰቦች
ላይ ያተኮረ አይደለም። የትምህርቱ አገልጋዮች
ያዘገሙበትንም ጨለምተኛ የሥነ-አፈታት ጉዞ ወደ ብርሃን
ለማውጣት እንዲረዳን በራሳቸው አፍ እንዲናገሩ በማድረግ
ሐቲታዊ (exegesis) ስልትን የተከተለ ምላሽ ይሰጥበታል።
በአጠቃላይ የአስተሳሰቡ አገልጋይም ይሁን ሰለባ የሆኑትን
ከተያዙበት ተጽዕኖም ይሁን ከተያዙበት የሰጠነ ሥነ-መለኮት
ለማውጣት የመንችልበትን ብርሃን ለማሣየት የሚያስችል
አካሄድን እንከተላለን።

የምዕራፍ አምስት ማጠቃለያ ጥያቆዎች


1. ተሳትፎ በምታደርግባቸው ክርስቲያኒያዊ ኅብረቶች የጸሎት
ትርጓሜን የለወጠና ኅብረቶችን የጎዳ የእምነት እንቅስቃሴ
የቃል ዐዋጅ ልምምድ አመላካች የሆነ ምን ዐይነት ልምምድ
አለ?
2. ዓመታዊ የቃል ዐዋጅ ልምምድ መሠረቱ ምንድነው
ብለህ ታስባለህ? ልምምዱ በግል ክርስትናህ ላይ
ያሳደረብህ ዐዎንታዊ ወይም ዐሉታዊ ተጽዕኖ ካለ
አብራራ።
3. አገልጋዮች የመባረክ ወይም የመርገም ስልጣን
አላቸውን? ይህ ስልጣን እንድንፈራቸውና

336
ጆንሰን እጅጉ

እንድንገዛላቸው ያስገድደናል ብለን ማሰብ


እንችላለን? ለምን?
4. በነቢይ የአንደበት ቃልና በትንቢት መኻል ያለው ልዩነት
ምንድነው?
5. አንተ ባለህበት አጥቢያ የንስሓ ጸሎት ምን ያኽል
በግልና በጉባኤ ይደረጋል? ንስሓን እንደሟርት
የሚቆጥሩ ሰዎች አጋጥመውህ ያውቃሉ?
6. ዐሉታዊ እውነታዎችን የመካድ ወይም አለመናገር
ልምምድ ምን ጉዳት ወይም ረብ አለው ብለህ
ታስባለህ? በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አቋም አለህ?

337
የአማልክቱ ዐዋጅ

ክፍል ፬

የጥቅስ ገበያ

  

338
ጆንሰን እጅጉ

ምዕራፍ 6

ተገደው የተሸጡ ጥቅሶች


ያለፉትን ሦስትና ሁለት ምዕተ ዐመታት የቤተክርስቲያን


ታሪክ ወደ ኋላ ዞር ብለን ስናጠና የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ሥነ-
መለኮት በወንጌላውያን አማኞች እርሻ ላይ በቀላሉ ተበትኖ
ለመብቀልና ለማደግ እንደቻለ እናስተውላለን። ቤተክርስቲያን
በእምነት እንቅስቃሴ ጽሓፍት መሪዎች አማካኝነት የልዩ ዲበ-
አካልን የአስተምህሮም ሆነ የልምምድ ስሕተት በሰፊው
ተግታለች። የዚህም ዋነኛ ምክንያት ተገደው ካለ ቦታቸው
እንዲውሉ የተወሰነባቸው ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች
በቤተ-እምነት መስባክ ላይ ሰፊ የገበያ ዕድል ማግኘታቸው
ነው። እጅግ ታዋቂና ዝነኛ አንደበተ ርቱዕ ሰባኪያን የዚህ ገበያ
ባለ ሟል በመሆንና ወደ ትምህርቱ ዘልቀው በመግባት በሙሉ
አቅማቸው ተሳትፈዋል።

ገበያው ግን የደራው የዛን ያኽል አጓጊና ፍሬ ያለው እንቅስቃሴ


ስለሆነ አይደለም። በቅጡ የሚጨበጥ ቅርፅና መልክ የለውም።

339
የአማልክቱ ዐዋጅ

አንድ ዐሳብ ላይ የሚገላበጥ በመሆኑም ምክንያት ልብ ላለው


ፍሬ የሌለውና ሊያጠግብ የማይችል አሰልቺ የህልም እራት
ነው። መሠረታዊ ችግሩም ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥነ-
አፈታት ሕግ የማይከተልና በተጨባጭ ሥነ-አመክንዮ ላይ
ያልተመሠረተና ማጭበርበር የሞላበት መሆኑ ነው።
አማልክቱ ሰባኪያን ጥቅሶችን እየገነጣጠሉ ለሚፈልጉት ዐሳብ
መደገፊያ ሲጠቀሙ ለእግዚአብሔር ክቡር ቃል ያላቸውን
ንቀት በአደባባይ ያሣያሉ። አድማጮቻቸውንም ከዲበ-አካል
ሃይማኖት በተቀበሉት የእምነት ቃል ቅርፅ ማውጫ ሞልድ
አእምሯቸውን በመግዛት ለመምራት ይጥራሉ።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ያለው ትልቅ የአደራ


መልዕክት እንደሆነ እናውቃለን። ስለዚህም በፍጹም ትህትና
ስሜትና ፍቃዳችንን በማስገዛት ከልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና
ራሳችንን አላቀን በጥንቃቄ መርምረን ልንረዳው ይገባል።
የፅሐፊው መልዕክት ላልተጻፈበት ዓላም እንዲቆም ማስገደድ
ታማኝነትን ማጉደል ወይንም የሥነ-ጽሑፍ ወንጀል መፈጸም
ነው።(2 ጴጥ.1:20)። የአማልክቱ ማኅበር አገልጋዮች
ከስሕተት ለመታረምና በትክክለኛው መንገድ ለመጓዝ
የሚረዳን ብቸኛው ሀብታችን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ
እያወቁ፤ ዐውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባል
ቃሉን በቸልታ ለመመልከት መምረጣቸው አሳዛኝ ነው።

340
ጆንሰን እጅጉ

ይህም ሆኖ ግን አምላካችን ብዙ የመመለስና የመታረም ዕድል


የሚሰጥ ሩኽሩኽ አምላክ ስለሆነ እስከ አሁን ስተንም ሆነ
አስተን ከሆነ፤ አሁን ግን መንፈስ ቅዱስን ሰምተን ለመመለስና
ለመታረም እራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል። ይህ ሣይሆን ቀርቶ
የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ ለመረዳትና ለማስተላለፍ
የማንጠነቀቅ ከሆነ ግን ለጥፋት እራሳችንን እና
የሚሰሙንንም እያሰናዳን እንደሆነ ማወቅ አለብን። ዕንቢታ
ግን ከሆነ ምርጫችን ያለምነው ከፍታ ላይ ሳንደርስ
የቆመንበት ከድቶን ዐዘቅት መውደቃችን የማይቀር ስለሚሆን
ጥፋታችን ዘግናኝ ይሆናል። “ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን
መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም
ታደርጋላችሁ።”(2 ጴጥ.1:19)።

ምን ላውጅ?
ዘመነኞቹ አማልክት የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ልምምድን በማሣደግ
የትኛውንም ጥቅስ ጠቅሰው ዐዋጅ የማድረግ አባዜ አላቸው።
ለምሳሌ የሄገን አፍ በመሆን በማቀላጠፍ ላይ ያለው ፓስተር
ክሪስ ማንኛውንም ጥቅስ ጠቅሶ መናገር ወይም ማወጅን

341
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለእግዚአብሔር ቃል ምላሽ መስጠት ነው በማለት


ያበረታታል። “ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ ለቃሉ ምላሽ
መስጠት፣ ያንኑ ነገር በመስማት መናገር። የእናንተ ቃሉን
መናገር ለቃሉ የምተሰጡት ምላሽ ነው። ይህ ነው እንግዲህ
ሕይወታችሁንም ይሁን ሁኔታችሁን የሚቀይረው።”285 እንደ
እርሱም ከሆነ ዐዋጅ ለቃሉ የሚሰጥ ምላሽ ስለሆነ አዕማድ
የሚባል የክርስትና አካል ነው።

የእግዚአብሔርን ቃል የማወጅን ትምህርት ያሰረፀው ኪኒየን


እንዴት ትምህርቱን እንደጀመረ ሲናገር (ዕበ.4:14) ሲያነብ
“ምን ላውጅ?” የሚል ጥያቄ እንደተፈጠረበት ይናገራል።
መንፈስም “አዲስ ፍጥረት” ወይም “የእግዚአብሔር ተፈጥሮ
እንዳለው ማወጅ” እንዳለበት አመለከተኝ ይላል። ይህንንም
ለማስረዳት ጥያቄ ፈጥሮበት የነበረውን ክፍል በማንሣት
ያብራራሉ። ይሁን እንጂ ኪኒየን እንደሚለው ክፍሉ አዲስ
ፍጥረት ወይም የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ማወጅን የሚመክር
አይደለም። ኪኒየንን ከመቃወማችን በፊት ግን ለዚህ
ዐስተሳሰብ መነሻ የሆነውን የዕብራዊያን መጽሐፍ አብረነው
እንመልከት።

285
ክሪስ ኦያኪሂሎሚ፣ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ። (2006፣ ጥር 13)።

342
ጆንሰን እጅጉ

“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር


ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ ጸንተን ሃይማኖታችንን
እንጠብቅ።”(1954 ዓ.ም. ዕትም)።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ የኪኒየንን ትኩረትና ስሜት የሳበው


“ሃይማኖታችንን እንጠብቅ” የሚለው ቃል ሲሆን ኪኒየን ግን
የተመለከተው የዚህን አቻ የኪንግ ጀምሱን እንግሊዘኛ
ትርጉም ብቻ እንደሆነ መታዝብ ይቻላል። ይህም “let us
hold fast our profession” የሚል ሲሆን ቀጥተኛ
ትርጉሙ “ዐዋጃችንን አጥብቀን እንያዝ” እንደማለት ነው።
ይህም ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ ከሚለው ከ 1954 ቱ
የአማርኛው ዕትም አጠቃቀም አንፃር ሲታይ አሻሚ ነው።
ይኸው ቃል በድጋሚ (በዕብ.10፣23) በተመሳሳይ ሁኔታ
ተጠቅሶ ብናገኘውም የተለየ ትርጉም ወይም ዐውድ ግን
የለውም ።

ስለሆነም የቃላት ትርጉም ልዩነት የሚንጸባረቅበት ክፍል


ስለሆነ የዓረፍተ-ነገሩን ዐሳብ ለመፍታት የቃሉን ማለትም
“ዐዋጃችንን . . .” ፍቺ በዐውዱ ውስጥ ከመፈለጋችን በፊት
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን መመልከት ይኖርብናል።
የተወሰኑት ትርጉሞች “ማወጅ” ከሚለው እንግሊዘኛ ኪንግ
ጀምስ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቃል የተጠቀሙ ሲሆን የተወሰኑት

343
የአማልክቱ ዐዋጅ

ደግሞ ወደ 1954 ቱ የአማርኛ ዕትም ቀርበው እናገኛቸዋለን።


ከእነዚህም ውስጥ፦
 therefore, let us never stop trusting him. (ስለዚህ
በርሱ ማመናችንን እንቀጥል።) ሊቪንግ ባይብል ።
 let us hold firmly to what we believe. (ያመንነውን
አጥብቀን እንያዝ።) ሊቪንግ ኒውስ ።
 እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ። (አዲሱ መደበኛ
ዕትም)

እንግዲህ አስቀድሞ እንደጠቆምኩት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ


ትርጉሞች በአንድ ዐይነት ቃል ስለማይስማሙ ያሻማሉ።
ይሁን እንጂ የትኛው የቃል አጠቃቀም ወደ ትክክለኛ ትርጉም
ይወስደናል የሚለውን ለመረዳት በቀጣይ ደግሞ ቃላቱን
በመጽሐፉ ዐውድ ውስጥ ማየት ይኖርብናል። ምክንያቱም
ቃሉ ከአውዱ ዐሳብ ውጭ የሆነ እንግዳ ዐሳብ ሊያስተናግድ
አይችልምና ነው።

የዕብራዊያን መጽሐፍ አንዳች የቀረባቸው የቤተ-መቅደስ


ሥርዐት መንፈሳዊ ትርፍ ያለ ለመሰላቸው የተፃፈ ነው።
እነኝህ ወገኖች ከእምነታቸው ወደ ቤተ-መቅደሱ ሥርዐት
ለማፈግፈግ ጫፍ ላይ የደረሱ ክርስቲያኖች እንደሆኑ
ከመልዕክቱ ትኩረት እንረዳለን። ጸሓፊው ሊመክራቸው
የፈለገው ወደኋላ መመለስ እንደሚያስቀጣና አሁን ያሉት

344
ጆንሰን እጅጉ

ከብሉይ በሚበልጥ ኪዳን ውስጥ ስለሆነ በእምነታቸው


እንዲፀኑ ነው። ይህንንም ብዙ ማስረጃ እያጣቀሰ ያስረዳል።

ስለዚህ የመጽሐፉ ዐውድ “እምነታችንን እናውጅ” ለሚለው


ኪኒየን ለተከተለው የእንግሊዘኛ ኪንግ ጀምስ ትርጉም ሩቅ
ሆኖ እናገኘዋለን ማለት ነው። በተቃራኒው ደግሞ
“እምታችንን እንጠብቅ ወይም እንያዝ” የሚሉት ከላይ
የጠቀስኳቸው ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አዲሱን
መደበኛ ትርጉም ጨምሮ ለአውዱ ቅርብ ሆነው
እናገኛቸዋለን ማለት ነው። ስለዚህ ከክፍሉ ዐውድ አንጻር
ትክክለኛው ትርጉም እምነታችንን እናውጅ የሚለው ሳይሆን፤
እምነታችንን እንያዝ የሚለው ነው ማለት ነው።

ይህ ከሆነ የኪኒየን እክል ቃላትን ከአውዳቸው ውጪ በመዝገበ


ቃላት ትርጉማቸው ብቻ መፍታት እንደሆነ መገንዘብ
እንችላለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘውን
የትኛውንም ቃል በራሱ መጽሐፍ ውስጥ የሚኖረውን ፍቺ
ሳንመለከት የመዝገበ ቃላትን ወይም የቋንቋ ትርጉምን
መፈለግ ስሕተት ነው። ምክኒያቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን
የመፍታት ከፍተኛ ስልጣን ያለው መዝገበ ቃላት ሳይሆኑ ራሱ
መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በተጨማሪም እነኝህ “አማልክት”
ስኽተታቸውን ከመጀመሪያው አለማረማቸው ወደ ከፋ
ስሕተት እንደወሰዳቸው እናያለን።

345
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመቀጠልም ኪኒየን የተስፋ ቃሎችን ማወጅ እንዳለብን


ይናገራል። ይህንንም የቃል እወጃ ልምምድ ሲያስረዳ፦
“በየዕለቱ እግዚአብሔር ስለቤተክርስቲያን፣ ስለ እራሱ እና
ስለእኔ ስለየ አንዳንዳችን የተናገረውን ደጋግሜ ደጋግሜ
እናገራለሁ። ይሄ ወደ ውስጤ ዘልቆ በመግባት ደስታና ድልን
ያጎናጽፈኛል።”286 ብሏል። ኪኒዩን ገደብ የለሽ ጉዞውን
በመቀጠል የምንፈልገውን ነገር እስከምንሆነው በተደጋጋሚ
መናገር እንዳለብን በአጽንዖት ይናገራል። “ልንናገረው ይገባል!
ተስፋዎች የህይወታችሁ አካል እስኪሆኑ ድረስ ደግማችሁ
ደጋግማችሁ በመናገር ትልቅ ኀይል ማግኘት ትችላላችሁ።”287
ይላል።

እንደ ኪኒየን ትምህርት የምናስብ ከሆነ የተስፋ ቃል


እንዲፈጸም የሚያስፈልገን ዋና ነገር የተስፋ ቃሉን ደጋግሞ
ማወጅ ወይም መድገም መሆኑ ነው። ያለበለዚያ አንድ ጊዜ
ብቻ የተነገረ ትንቢት ወይም ቃል መለኮታዊ ድጋፍ ኖሮት
አይንቀሳቀስም! ወይም አይፈጸምም። የኪኒየን ልዩ ዲበ-አካል
ታዲያ በአገራችን ያሉ ሰባኪያንን ቀልብ ገዝቷል። መጋቢ
ያሬድ ተዘራ የዐዋጅ የቃል የፈውስ መነሾ ምሥጢር እንደሆነ
ያትታሉ። ይህንንም ለማስረዳት የቤተክርስቲያናቸው አባል
የሆነ አንድ ሰውን ልምምድ አጋርተዋል፦
286
McIntyre, J. E.W. Kenyon and His Message of Faith. (2010, P, 420).
287
Ibid., (P. 414).

346
ጆንሰን እጅጉ

በመገረፉ ቁስል ተፈውሻለሁ እያልኩ የእምነት ቃል


አውጅ ነበር።…እኔ ዝም ብዬ ተፈውሻለው፤
በእምነት ፈውሴን ተቀብያለሁ በማለት ማመስገን
ጀመርኩ። እግዚአብሔር መልካም ነው። በእምነት
ፈውሴን ተቀብያው ስል አንድ ቀን…ፈውስ በእጄ
ሲያልፍ እጄም ሙሉ ለሙሉ ሲፈወስ ታወቀኝ።
ለካ ሰው በእምነት እያወጀ ያለምንም ዐይነት
መድኀኒት መፈወስ ይችላል። 288

ይህ የልዩ ዲበ-አካል ምትሃታዊ የፈውስ ጥበብ ሥልት እንደሆነ


በምዕራፍ ሁለት ላይ እንደተመለከትን ያስተውሏል።
“በመገረፉ ቁስል ተፈውሻላሁ” የሚለውም ጥቅስ ለልምምዱ
መደገፊያ እንዲሆን ካለ አውዱ ፍቺ የተሰጠው እንደሆነ
ተካልኝ በመጽሐፋ ላይ ጠቅሷል። በዚሁ ሰፋ ያለ ትንታኔውም
የአካላዊ ፈውስ ጸሎትን አስፈላጊነትን “እግዚአብሔር ፈዋሽ
ነው።” በማለት ሲያሰምርበት “በመገረፉ ቁስል ተፈውሻላሁ”
የሚለውን ቃል ነጥሎ በመውሰድ ከባቢያዊ እውነቶችን እና
አካላዊ ህመሞችን ጭምር ለመካድ መዋሉን ይኮንናል።
በመቀጠልም ከመገረፉ እና ከመቁሰሉ በፊት በትንቢተ ኢሳያስ
ላይ በመገረፉ ቁስል ተፈወስን መባሉ ምንን ያመለክታል?
በማለት ይጠይቃል። አያይዞም የሚያመለክተው የመሲሁን
ቤዝዎት ነው በማለት ማቴዎስም ፈውስን ከኃጢአት ስርየት
288
ተዘራ ያሬድ። ሬማና ሎጎስ (2008፣ ገጽ. 91)።

347
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጋር አያይዞ ማቅረቡን በማተት ፅሑፉን ያጠቃልላል። ተካልኝ


በዚሁ ፁሑፉ ለማስረዳት ‘ተሸከመ’ የሚለውን ሰብቱጀንት289
ኢሳያስ ‘53’ ላይ ሲጠቀሙ ‘ፌሮ’(ምትክ)የሚል ቃል
መጠቀማቸውን እና ማቴዎስ ደግሞ ‘ላምባኖ’(አስወገደ)የሚል
ቃል መጠቀሙን በማብራራት በቀጥታ ከመሲህ የነፍስ ድነት
ሥራ ጋር የተያያዘ ፍቺ አለው ብሏል።290

“እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው


ይፈጸም ዘንድ፣ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፣ የታመሙትንም
ሁሉ ፈወሰ።” (ማቴ.9:2-6)።

እርግጥም ጴጥሮስ ይህንን የኢሳያስ ‘53 ን’ ጥቅስ የተጠቀመ


ቢሆንም ተካልኝም እንዳነሳው በማያሻማ ሁኔታ የኃጢአት
መወገድን ለማብሰር ነው የተጠቀመው። “ለኃጢአት ሞተን
ለጽድቅ እንድንኖር፣ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን
በእንጨት ላይ ተሸከመ (አስወገደ)፤ በመገረፉ ቁስል
ተፈወሳችሁ።”(ጴጥ.2:24)። ኢየሱስ በዚህ መሲሂያዊ ቤዛነቱ
ኃጢአታችንን ያስወገደው ለጽድቅ እንድንኖር እንደሆነ ክፍሉ
በግልጽ ያሣያል። ይህም የኃጢአት መላቀቅና የጽድቅ ኑሮ፤
በሐዋርያው ጴጥሮስ ቋንቋ ተርጉመን ከተመለከትነው“ፈውስ”
289
ሰብቱጀንት፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባ ሊቃውንት አማካኝነነት
ከእብራይስይጥ ወደ ግሪክ የተተረጎከመ የብሉይ ኪዳን መጸሓፍት ሥብስብ
ነው።
290
የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት!? (ገጽ፣223-229)::

348
ጆንሰን እጅጉ

ይባላል። ስለዚህ “በመገረፉ ቁስል ተፈውሳችሁ” የሚለው ቃል


ነባራዊ ሁኔታን በመካድ የአካል ፈውስ መቀበያ የዐዋጅ ሥልት
ምሳሌ አድርጎ ማሰብ እራስንም ሰሚንም ማታለል እንደሆነ
መታወቅ አለበት።

የኪኒየን አጋር ዶን ጎሲትም እንዲሁ የምንፈልገውን ገንዘብ


ለማግኘት ማወጅ እንዳለብን ይናራል። እንደርሱ ከሆነ ደግሞ
የዐዋጅ መሠረቱ ፍላጎታቸን ሲሆን ነገር ግን ስናውጅ
በእግዚአብሔር ቃል አስደግፈን መሆን አለበት። ይህንንም
ሲያስረዳ “ቃል እስክናገር ምንም ነገር አልሆነም” በሚለው
ርዕሱ በሉቃስ ወንጌል 5:1-5 ላይ ኢየሱስን መረባቸውን ወደ
ጥልቁ እንዲጥሉ ለደቀ-መዛሙርቱ መናገሩን ያነሣል።
አያይዞም ሲናገር ኢየሱስ እስኪናገር ድረስ ምንም የሆነ ነገር
አልነበረም ይላል። ይህንንም “መገለጥ” ሲያብራራ የግል
ልምምዱን ያነሣል። በትረካውም የመኪና ካምፓኒ ዕዳውን
የማይከፍል ከሆነ ተጨማሪ ጊዜ ሳይሰጠው መኪናውን
እንደሚነጥቀው አስጠነቀቀኝ ይላል። ይህንንም ተከትሎ
ምንም የሚከፍለው ገንዘብ ስለሌለው ሲጨነቅ ድንገት
የፊሊጲሲዩስ መልዕክት ትዝ ይለዋል።

ጥቅሱም “አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር


በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።”
የሚል ነው። (ፊሊ.6፡9)። እርሱ እንደሚለው ወዲያው

349
የአማልክቱ ዐዋጅ

‘የሚያስፈልገኝን ገንዘብ አምላኬ ይሰጠኛል’ እያለ ደጋግሞ


ማወጅ ይጀምራል። ወዲያውም ኪሱ ውስጥ ገንዘብ እንደገባ
ተሰማው። ከደቂቃዎች በኋላም የቤቱ በር ይንኳኳል።
መኪናውን ለመውሰድ የተላኩ ሰዎች ግን አልነበሩም። በሩን
ያንኳኳው ሰው የመጣው ከገንዘብ ወኪል ድርጅት የተሰጠውን
መልዕክት ይዞ ነው። መልዕክቱም በርከት ያለ የዶን ጎሲትን ዕዳ
ሊከፍልለት የሚችል ገንዘብ ከአንድ ሰው እንደተላከለት
የሚያበስር ነበር። በመጨረሻም ጎሲት ገንዘቡን በመውሰድ
ከዕዳው ነፃ እንደወጣ ያትታል።291 ጎሲት ታዲያ ጥቅስ ጠቅሶ
ኢየሱስን ምሳሌው በማድረግ በራሱ ልምምድ አስደግፎ
በመጽሐፉ ቢከትበውም ለእርሱ ሠርቶለትም ቢሆን እንኳ
እውነትነት ግን የለውም።

እንደ እውነቱ ኢየሱስ ጎሲት እንዳደረገ በተደጋጋሚ


አላወጀም፤ የኢየሱስ ንግግር ለደቀመዛሙርቱ የተላለፈ
ተግባቦትን የሚፈጥር ትዕዛዝ እንጂ ዐዋጅ አልነበረም። ከደቀ-
መዛሙርቱም አንዳቸው እንኳ ከዚሁ ልምምዳቸው
በመነሣት የቃል ዐዋጅ አስፈላጊነትን በመማር ከኢየሱስ አፍ
ቃል አፈፍ በማድረግ፤ መረባቸው ብዙ አሳ እንዲይዝላቸው
“መሬቤን ወደ ጥልቅ እጥላለሁ፣ ብዙ ዓሳ እይዛለሁ፣ መሬቤን
ወደ ጥልቅ እጥላለሁ፤ ብዙ ዓሳ እይዛለሁ…” በማለት ጎሲት

291
Don Gossett. E.W. Kenyon. Keys to Reciving God’s Miracle. (2011, p, 182).

350
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚለው አማልክቱ የሚለማመዱትን ዐይነት ኅሩይ ቃል


አላወጁም ነበር።

እንደውም የሚሆን ነገር እንደሌለ ስላሰቡ ወይም ስላላአመኑ


ለመታዘዝ ብቻ መረባቸውን የጣሉ ነው የሚመስሉት።
“አቤቱ፣ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤
ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው።” ይህን
የጴጥሮስን ንግግር እንደ ዐዋጅ መቁጠር ዕብደት ነው፤
ምክንያቱም ለኢየሱስ የተሰጠ የእሽታ ምላሽ እንደሆነ ግልጽ
ነውና ነው። ደቀ-መዛሙርቱ ከቃል ዐዋጅ ይልቅ የተማሩት
በኢየሱስ ማንነትና በእነርሱ ማንነት መኻል የሰፋ ልዩነት
መኖሩን ነበር። “ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ
ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ
ተለይ አለው።”

ከዚህ ታሪክ በኋላም ደቀ-መዛሙርቱ ሲጎልባቸውና ሲቸገሩ


ወደ ባህር በመሄድና በማወጅ የተዓምራት ዓሳ ለማጥመድ
አንድም ቦታ አልሞከሩም፤ እንደውም እርዳታ ሲሰበስቡ ነው
የታዩት። ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ “በቀሪ ዘመኔ ላይ
ቃል ዘራሁበት” በማለት ሲያዜሙና የቃል ዐዋጅን
ሲለማመዱ አልተሰሙም። ኢየሱስ ማንነቱን ለመግለጥ
ባደረገው በዚህ ተዓምር ላይ ያስተማረው የቃል ዐዋጅ
ትምህርት የወንጌል ስብከት ስለነበር ደቀ-መዛሙርቱ ወደ

351
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሥብከት ሥራ ነበር የገቡት። “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ


ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ አለው።” የሚለውም የኢየሱስ
ንግግርም ይህን የሚያረጋግጥ ነው።

እንደ ጎሲት ከሆነ ግን ይህ ጥቅስ በቃል ላይ ያለ እምነትን


ወይም ዐዋጅን ነው የሚያስተምረው። ኪኒየን የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ ልምምድ ምን እንደሆነ ሲያስረዳ በመለኮት ላይ ያለ
እምነት ሳይሆን በእምነት ላይ ያለ እምነት እንደሆነ
አስረግጧል። ይህም ማለት ድርጊት ወይም ተኣምር
ፈጻሚው እምነት ራሱ ነው ማለት ነው። እንደ ኪኒየን ከሆነ
‘ቃል’ አስገዳጅና አማኙ የሚፈልገውን ነገር እንዲሆን
የሚወስንበት ዐቅም ነው። የጎሲት ትምህርት የዲበ-አካል
ሃይማኖት አስተምህሮ በቃል እምነት ላይ እንደተመሠረተ
ሁሉ የእርሱም ትምህርት እንዲሁ በቃል እምነት ላይ
የተመሰረተ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። የጎሲት
ትምህርተ ከዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ጋር የሚለየው
የጎሲት ትምህርት እንደ አለቃው ኪኒየን የቃል እምነት የልዩ
ጸሎት ልምምድን ለአማኞች ብቻ የተገባ ልምምድ እንደሆነ
መግለጹ ብቻ ነው።

ፓስተር ተዘራ የቃል ዐዋጅ ልዩ ጸሎትን እንደ ሥዕል መሣል


እንደሚመለከቱት ያነሣሉ። ይህንንም ሬማና ሎጎስ በተሰኘ
መጽሐፋቸው ላይ ሲያስረዱ፦ “የእግዚአብሔርን ቃል

352
ጆንሰን እጅጉ

ማወጅን የማየው ሥዕል እንደመሳል አልያም የሆነ ቅርፅ እንደ


መቅረጽ ነው”292። ይህንን ካሉ ኋላ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ
እንዲረዳቸው የደቡብ ኮሪያውን መጋቢ ዮንግ ቾ የግል
ልምምድ ያነሣሉ። አንድ የጉሮሮ ታማሚ ሴት ወደ ቾ
በመምጣት እንዲጸልዩላት ብትጠይቃቸውም እሳቸው ግን
የምጸልይልሽ በመገረፉ ቁስል ተፈውሻለው በማለት 10 ሺ
ጊዜ ፃፊና ነው ብለው ያዟታል። ኋላ ላይም ሴቲቱ ይህንን
በማድረጓ መፈወሷን እንደመሰከረች ያነሣሉ።

ፓስተር ተዘራ ይህንን ታሪክ እርሳቸው ሬማ ከሚሉት


የመገለጥ ትምህርት ጋር ካያያዙት በኋላ ፈጥነው ወደ
ዘፍጥረት መጽሐፍ በመሄድ፦ “እግዚአብሔ ጨለማውን
ብርሃን ይሁን ሲል በውሃ ላይ ሰፎ የነበረው የእግዚአብሔር
መንፈስ ብርሃኑን ይሰራዋል።” በማለት እግዚአብሔር
ዓለማትን የፈጠረበትን ሥርዐት ካነሱ በኋላ ይኸው ሥርዐት
በሰው ልጆች እንደቀጠለ ያስረዳሉ። “የእግዚአብሔር መንፈስ
አንድ ነገር እስክትናገሩ እየጠበቀ ነው። እግዚአብሔር
በእምነት ከምትናገሩት ቃል ጋር ይሠራል። ቃል አውጡበት።
የእግዚአብሔርን ቃል! የእምነት ቃል!” 293በማለት ያክላሉ።
ይህም ቀደምት የእምነት ቃል አስተማሪዎች መለኮትን በቃል
እንደሚገዛና እንደሚወሰን አድርገው አኩስሰው
እንዳስተማሩት ሁሉ የሚተርክና የሚሰቀጥጥ ትምህርት
ነው። ሐንክ ሐነግራፍ ይህንን መለኮትን የሚወስን በሽታ
292
ተዘራ ያሬድ። ሬማና ሎጎስ (ገጽ፣2008, 83)።
293
Ibdi. (2008፣ 84-85)።

353
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሲገልጡ፦“የእምነት እንቅስቃሴ አምላክ ክብደትና ቁመት


አለው፤ ያልተሳካለትም ይባላል። የመንፈሳዊው ዓለም
እስረኛ፤ የእምነት ኀይልም ጥገኛ ነው. . . በአጠቃላይ እርሱ
እውነተኛው እግዚአብሔር አይደለም”294 ብለዋል።

መጋቢው መለኮት ዓለማትን የፈጠረበትን ስልጣን ለሰው


መስጠታቸው የመለኮት ሉዐላዊ የማይወሰን ተሰብዖ እና
የሰው ልጅን ፍጥረታዊ ውሱን ተሰብዖ ልዩነት እንደዘነጉ
የሚያሳይ ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ቃል
መናገርንና የእምነት ቃልን መናገርን በተለዋዋጭነት
ማስቀመጣቸው በእግዚአብሔር ቃልና በእምነት ቃል መኻል
ያለው የስልጣን ልዩነት እንደ ተሰወረባቸው ያሣያል። ይሁን
እንጂ መጋቢው ቃል የማውጣትና የማወጅን አስፈላጊነት ግን
እርሳቸው አንባቢያን ዘንድ እንዲደርስላቸው በፈለጉት ሁኔታ
ማስተላለፍ እንደቻሉ ይታያል። ምክንያቱም ቃል የማወጅ
ልምምድ መለኮት ዓለማትን ከፈጠረበት ኀይል ጋር
በማመዛዘን በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እጅግ ወሳኝ
ልምምድ እንደሆነ ቀልብ በሚሰርቁ ምስክርነቶች በማጀብ
አቅርበዋልና ነው።

ኪኒየንም ሆነ ተከታዮቹ የልዩ ዲበ-አካሉ የቃልን ኀይል


ደጋግሞ በመናገር ወይም በቃል ድግምት መጠቀም

294
Christianity in crisis: 21st century. (P.458).

354
ጆንሰን እጅጉ

ትክክለኝነትን በጥቅስ ሊያረጋግጡልን ሞክረዋል። እሁን


እንጂ እነርሱ እንደሚሉት አዲስ ነገር አልተገለጠላቸውም
ወይም አዲስ ነገር ተረድተው አላስረዱንም። ከሆነም ከእርሱ
ቀድመው የተረዱት ፊሊሞናዊያን የበለጠ ተገልጦላቸዋል
ማለት ይገባናል። እዚህ ላይ መሰረታዊው ነገር ኪኒየን
እንደሚለው በተደጋጋሚ የምናውጀው ምንድነው? የሚለው
ሳይሆን ዐዋጅ ምንድነው? ይህስ መርሖ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ነው ወይ? ኪኒየንስ እንደሚለው ኢየሱስ የቃልን ኀይል
ተግባራዊ ለማድረግ ይህንን መርሖ ተጠቅሞ ነበር ወይ?
የሚለው ነው።

በአጠቃላይ ከላይ እንደ ተመለከትነው ኪኒየን ምን ላውጅ


የሚል ጭንቀት የተፈጠረበት እርሱ እንደሚለው
የዕብራዊያንን መልዕክት ሲያነብ ሳይሆን አስቀድሞ ነው።
ምክንያቱም ምን ላውጅ የሚለውን ጥያቄ ከማንሳቱ በፊት
የዐዋጅን አስፈላጊነት ከክፍሉ መማሩን በግልጽ ማሳየት
ሲኖርበት ይህንን ግን አላደረገም። የጠቀሰውን ክፍል ከማንበቡ
በፊት በኅሩይ ቃል ዐዋጅ ጽንሰ-ዐሳብ ባያአምን ኖሮ
የዕብራዊያንን ዐውድ ለመፈተሽ እንዲህ ባልተቸገረ ነበር።
እንደ እውነቱ ከሆነ ደቀመዛሙርቱም ኅሩይ ቃል ለማወጅ
የተጨነቁበት ወይም የችግር መፍቻ ቁልፍ እንደሆነ አድርገው
ያስተማሩበት ቦታ የለም። ስለዚህ ምን ላውጅ የሚለው

355
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጥያቄ እራሱ በተነሳው ክፍል መነሻነት መነሳት የሌለበት


ስለሆነ ጥያቄው በራሱ ስኹትና ግልጽነት የጎደለው ነው።
ፓስተር ተዘራም ቢሆኑ እንዲሁ የኪኒየንን ትምህርት
ለመታዘዝ ያኽል የእግዚአብሔርን ቃል የማወጅ አስፈላጊነትን
ለማስተማር ሞከሩ እንጂ ትምህርታቸውን የሚያስደግፉት
በምስክርነቶች ነው። በጭራሽ ተአማኒነት ባለው
የእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ አቀራረብ የላቸውም።

አማልክታዊ ዘረ-መል (DNA)


አብዛኛዎቹ የእምነት ቃል አስተማሪዎች ማለት ይቻላል
ሰዋዊ አማልክትነትን ለማረጋገጥ(2 ጴጥ.1፡3-4) ደጋግመው
ይጠቅሳሉ። ለምሳሌ ማይልስ ሞንሮይ ይህንን ጥቅስ
በማንሳት ሲደመድሙ “እኛ ደግሞ ባሕርይውን ተካፍለናል።
ከእግዚአብሔር ጋር እንደገና ስንገናኝ እርሱ የሆነውን ሁሉ
295
ለመሆን በተፈጥሮ ኀይል እናገኛለን። ብለዋል።
ተርጓሚው ወንድማገኝ ባሕርይውን በሚል ቃል ተካው እንጂ
ማይልስ ተፈጥሮውን በማለት ነው የሚያስቀምጡት። እንደ
እርሳቸው ከሆነ በዚህ ተፈጥሮ ምክንያት እርሱ የሆነውን

295
ማይነስ ሞንሮይ። የእምቅ ብቃትን የማውጣት ጥበብ። (2001 ገጽ፣49)።

ማስታወሻ፡- “መለኮታዊ ተፈጥሮ” የሚለው ፍልስፍና ጽንሰ-ዐሳብ አስቀድሞ በዲበ-


አካል ሃይማኖት መሪዎች እንዴት እንደተብላላ ልብ ይሏል። (ኪዊምቢ ገጽ. 47፣
ሆፕኪን ገጽ. 52፣ ክሬመር ገጽ. 54 ፊሊሞራዊያን ገጽ 57፣ እንዲሁም ጆይ ገጽ. 146)።

356
ጆንሰን እጅጉ

ሁሉ እንድንሆን ተደርገናል። ይህም ስለ ዳግም ልደት ወይም


አዲስ ፍጥረት ስለመሆን ያላቸው የተንሸዋረረ ዕይታ
መለኮትነት እንዳላቸው እንዲቆጥሩ በማድረግ የተለየ የጸሎት
ፎርሙላ ወይም የኅሩይ ወይም የመልካም ቃለ ዐዋጅ መርሖ
እንዲከተሉ አድርጓቸዋል።

በእርግጥ የእንግሊዘኛው ኪንግ ጀምስ ዕትም ትርጓሜ


‘ተፈጥሮ’ በማለት ያስቀመጠ ቢሆንም ለመናገር የፈለገው
ግን ከተበላሸው ዓለም ማምለጥ ስለምንችልበት ስለተሰጠን
መንፈሳዊ ዐቅም ወይም ‘ባህርይ’ ነው እንጂ ከመለኮት ጋር
ፍጹም አንድ ዐይነት በማድረግ አማልክት ስለሚያደርገን
ማንነት አይደለም። ስለዚህ በእንግሊዘኛውም መጽሐፍ
ቅዱስ የተጠቀሰው ‘ተፈጥሮ’ የሚለው ነጠላ ቃል በመዝገበ
ቃላት ፍቺ ሳይሆን በመጽሐፉ ዐውድ ፍቺ የታሰረ ስለሆነ
ማይልስንም ይሁን ክሪስን አያስኬዳቻውም። በተጨማሪም
ጴጥሮስ የተጠቀመበት ‘ተካፋዮች’ የሚለው ቃል ‘የማንነት
መደባለቅን ሳይሆን በአንድ ማኅበር ውስጥ ያለን የአንድ አባል
የራሱን ድርሻ መካፈል ወይም ተሳታፊ መሆንን የሚያሳይ
ነው። በዚህ ላይ ተካልኝ ‘ተፈጥሮ’ የሚለውን ቃል በማንሣት
ሲያስረዳ የግሪክ ምሁራንን የሰዋሰው ትርጓሜ ስምምነት

357
የአማልክቱ ዐዋጅ

በማንሣት መሆንን ወይም መደባለቅን ሳይሆን መካፈልን


የሚያሣይ ነው በማለት አስረግጧል።296

ክሪስ አማልክቱ ሰው ተካፍሎታል በማለት የሚያምኑትን


የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ወይም ማንነት የበለጠ ግልጽ
ለማድረግ(2 ቆሮ.5፣17) በመጥቀስ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን
አዲስ ፍጥረት ነው።” በማለት ይንደረደራሉ።
ቀጥለውም(1 ቆሮ 6፡17) በማጣቀስ በዝርዝር ሲያብራሩ
“ለሰይጣን፣ ለድኽነት፣ ለበሽታ፣ ለደዌና ለሞት ተገዥ የሆነ
አዲስ ፍጥረት አልፈጠረም እርሱ የሠራው አዲስ ፍጥረት
በዚህ ዓለም ላይ የበላይ የሆነ፣ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት
ያለው አዲስ ፍጥረት ነው።”297 በማለትም ይተነትናሉ።
በርግጥ የአዲስ ፍጥረትነት ፍሬ ዐሳብ ክርክር ውስጥ ባይገባም
የፓስተሩ ትርጉም ግን ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኗል።

በመቀጠልም ዐሳባቸውንእንደተለመደው ጥቅስ በመቀጣጠል


ሲያሰፉ “1 ጴጥ.2፡9 ሲናገር ‘እናንተ ግን የተመረጠ ትውልድ’
ትውልድ የሚለው ቃል ከዘር ግንድ ሥርወ-ቃል (ጅን) የወጣ
ነው።” በማለት ያስረዳሉ። ይህንንም ሲተነትኑ፦

የዘር ግንድ DNA ማለት የአንድን ፍጡር ህዋስ


የሚገነባና የሚጠብቅ ሲሆን፣ የዘር ባሕርያት
296
የጸሎት ቤት፤ የንግድ ቤት?!። (ገጽ፣ 185)።
297
ክሪስ እና አኒታ ኦያኪሎሚ Rapsoid of reality (ጥር፣10፣2006)።

358
ጆንሰን እጅጉ

(ክሮሞዞም)ከወላጅ ወደ ልጅ እንዲተላለፍ የሚረዳ


መረጃ የያዘ ነው። አንድ ፍጡር ከወላጆቹ
የሚወርሰውን አካላዊ፣ አዕምሮአዊ እንዲሁም
ሌሎች ባሕርያትን ይወስናል። ስለዚህ ቃሉ የተመረጠ
ትውልድ ብሎ ሲገልጽላችሁ የተፈጠራችሁበትን
መለኮታዊ ቅንጣት ያሣያል፤ የእግዚአብሔር ዘረ-መል
DNA አላችሁ ማለት ነው። ስለዚህ ነው መጽሐፍ
ቅዱስ ከአሸናፊዎች ትበልጣላችሁ
የሚለው። (ሮሜ.8፡37)። ይላሉ።
298

እርሳቸው ጥቅሶቹን አቀላቅለው ይህንን ይበሉ እንጂ


የተጠቀሱት ሦስት ጥቅሶች(1 ቆሮ.6፡17 1 ጴጥ.2፡9 ሮሜ.8፡
37 ከ 2 ቆሮ.5፡17) አብረው ሊታዩ የማይችሉና ለየቅል
ናቸው። በመጀመሪያ የቆሮንጦስ መልዕክትን ያየን እንደሆን
ክርስቲያን ኀጢአትን ለማድረግ አመክኖያዊ መሆን
አይችልም የሚል አንደምታ አለው።(1 ቆሮ.6፡17) “ከጌታ ጋር
አንድ አካል ነን።” የሚለው ኀረግ የማንነት ተቀላቅሎን
ለማሳየት የዋለ ሳይሆን በግብር አንድ መሆንን ለማሳሰብ
የዋለ ነው። ጌታ ኢየሱስ ኀጢአትን ሊሰራ አይችልምና!
የሚል የአመክኒዩ ግንዛቤ የተከተለ ነው። ይህንንም ማንሳት
የሚጀምረው ቍጥር ‘13’ ላይ ነው። “ሥጋ ግን ለጌታ ነው
እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው።” ይላል።
298
. ibdi, (ጥር፣10፣ 2006)።

359
የአማልክቱ ዐዋጅ

በቍጥር ‘15’ ላይ ደግሞ “ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ


ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ
የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም።” በማለት
አጽንዖት ከሰጠ በኋላ በቍጥር ‘17’ ላይ የዐሳቡን ማሰሪያ
“ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።” በማለት
ፍጹም አንድነትን ከቅድስና እና ከንጽህና ጋር ካለው ትብብር
አንጻር በማንሳት ያስራል። በአጠቃላይ ሐዋርያው እየደከመ
ያለው የቆሮንጦስ አማኞች የክርስቶስን ቅድስና እንደተካፈሉ
በማሳየት የተዝረከረከ አቋማቸውን ለማከም ነው።

ስለሆነም የትምህርቱ ትኩረት ስለሰው አፈጣጠር ማለትም


ስለ ተሰራንበትን ዘረ-መል (DNA) ማሳየት ሳይሆን ኃጢአትን
አትሥሩ የሚል ነው። መለኮትንም ኃጢአትን እንዳይሠራ
አይመክሩትምና የመለኮት ዘረ-መል እንዳለን የምናምን ከሆነ
እንዲህ ዓይነቱ ምክር አያስፈልገንም። እርሳቸው እንደሚሉት
የተሰራንበትን የመለኮት ዘረ-መል ካለን ግን መከራከር ያለብን
የሰውን አፈጣጠር የሚተርከውን ቀጥተኛ ጥቅስ ከዘፍጥረት
ጠቅሰን መሆን አለበት። ያም ቢሆን ግን የምድር አፈርን እንጂ
የእግዚአብሔር ዘረ-መል የሚል ነገር ተጠቅሶ
አናገኝበትም።“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር
አበጀው።” ነው የሚለው።(ዘፍ.2፡7)።

360
ጆንሰን እጅጉ

ያም ቢሆን የሰውን አፈጣጠር የሚተርከውን ቀጣይ ዓረፍተ-


ነገር በማጣቀስ ሲሞግቱ ይሰማል። ቀጣዩን ዓረፍተ ነገር ያየን
እንደሆነ “በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት
ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።” የሚል ነው። አማልክቱ
ይህንን ጥቅስ እንደ ተለመደው በቀጥታ ቃል በቃል ይፈቱታል።
በዚህም መሠረት ሰው ከእግዚአብሔር ውስጥ የወጣ ሕይወት
ስለተሰጠው የእግዚአብሔር ዐይነት ሕይወት (DNA) ወይም
መንፈስ ተሰጥቶታል፤ ለዚህ ነው “ሰው እንደ እግዚአብሔር
ዐይነት መንፈስ ነው” ብለን የምንከራከረው ይላሉ።

ለምሳሌ ክሪስ “ነገር ግን ሰው መንፈስ ነው። የሰው ልጅ


መንፈስ የተሰራው ከምድር አፈር አይደለም። የሰው ልጅ
መንፈስ የመጣው ከእግዚአብሔር መንፈስ ነው።”299 ብሏል።
ይህም ለሰው ልጅ ልዕልናን የሚያላብስ አደገኛ ፍቺ ነው።
ይሁን እንጂ ነገራቸው በጭራሽ ትክክል አይደለም።
ምክንያቱም ቃሉን ቀጥታ ቃል በቃል መፍታት እንደሌለብን
የሚጠቁመን አቅጣጫ በዘፍጥረቱ ጥቅስ ዓረፍተ-ነገር ውስጥ
ታስሯልና ነው። ይኸውም ‘እፍ አለበት’ የሚለው ቃል ነው።
ይህ ቃል ቀጥተኛ ትርጓሜው የእንሰሳትን የአተነፋፈስ
ሥርዐት የሚገልጥ ነው። ሳንባ ንጹህ አየር ወደ ውስጥ ካስገባ
በኋላ መልሶ በመኮማተር አካል የተጠቀመበትን የተቃጠለ አየር

299
ክሪስ ኦያኪሎሚ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ፡፡ (2009፣ነሐሴ 15)፡፡

361
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወደ ውጪ ያስወጣል። በአጠቃላይ ‘እፍ’ ማለት የሳንባ ግፊትን


በመጠቀም ወደ ውጪ አየር መገፍተር ማለት ነው።

‘እፍ አለበት’ የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጓሜ መጽሐፍ ቅዱስ


ስለ እግዚአብሔር ከሚያስተምረው አስተምህሮ ጋር
ይፋለስብናል። ምክንያቱም መለኮት መንፈስ ስለሆነ ሳንባ
እንዳለው ልናስብ አንችልም። በእርገጥ ጸሓፊው ‘የሕይወትን
እስትንፋስ’ የሚል አሻሚ ቃል ተጠቅሟል። ስለዚህ
እግዚአብሔር ‘እፍ’ ያለው አየርን ሳይሆን ሕይወትን ነው
የሚል ክርክር ያስነሣል። ይህም ቢሆን ታዲያ ‘እፍ’ ለማለት
አፍን ጨመሮ ሌሎች የመተንፈሻ አካለት ያስፈልጋሉና
መለኮት ሕይወትን ወደ ውጪ የሚያስወጣበት የአተነፋፈስ
ሥርዐት አለው ያስብለናልና ትክክል አንሆንም። እውነቱ ይህ
ከሆነ የዘፍጥረቱ ጸሓፊ ለማይተነፍስ አምላክ ‘እፍ አለበት’
የሚለውን ቃል መጠቀሙ ምን ማለቱ ነው? ‘የሕይወት
እስትንፋስ’ ሲልስ ምን ማለቱ ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ
ነው።

ከላይ የተመለከትነው ሐቲታዊ ዳሰሳ ክፍሉን በቀጥታ ቃል


በቃል መተርጎም ለስሕህተት እንደሚያጋልጠን ለመረዳትና
የጹሑፉን ባሕርይ መረዳት እንድንችል ያግዘናል። ክፍሉ
ትረካዊ አቀራረብ ስላለው ጸሓፊው ሙሉ ለሙሉ ሥዕላዊ
አገላለጥን ለመጠቀም መርጧል። በእንደዚህ ዐይነት ትረካ

362
ጆንሰን እጅጉ

ተራኪው ትኩረት የሚያደርገው ዋናውን መልዕክት


ማስተላለፍ ላይ ስለሚሆን የማይታየውን የሚታይ
ሊያደርገው እና አካል ለሌለው ደግሞ አካል በመስጠት
ሲንቀሳቀስ የሚያሣይ ሥዕል ሊፈጥር ይችላል። በዘፍጥረት
መጽሐፍ ላይም የተራኪው ዐላማ ሥዕላዊ ትረካን ተጠቅሞ
የሰው ልጅ የተሠራበትን ዘረ-መል(DNA)ማሣየት ሳይሆን
የመለኮትን ፈጣሪነትንና የሰውን ተፈጣሪነት ማሳያት ነው።

ክፍሉን ቃል በቃል ቀጥታ መተርጎም እንደሌለብንና የክፍሉን


ትረካዊ ባሕርይ ግምት ውስጥ ካስገባን ጥቅሱን ለመረዳት
እንሞክር። “በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ
አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።” በዚህ ጥቅስ ሥርው
መለኮት ድርጊት ፈፃሚ ሲሆን ድርጊቱ ያረፈው ደግሞ
‘አፍንጫ’ ላይ ነው። የተላለፈው ድርጊት ደግሞ ‘እስትንፋስ’
ነው። የድርጊቱ ውጤት ደግሞ ‘ሕያው’ መሆን ነው። አሁን
የክፍሉ ትረካ ግልጽ እንደሆነልን አምናለሁ።

ድርጊት ተቀባዩ አፍንጫ ሥራው አየር መቀበል ስለሆነ


መለኮት ወደ አፍንጫ የገፋው የከባቢውን አየር ነው ሊሆን
የሚችለው። ‘እፍ’ አለበት የሚለውም ቃል ድርጊቱ የአየርን
መገፍተር እንደ ተከናወነ ለማሳየት የዋለ እንጂ መለኮት
እንደሚተነፍስ ወይም ከመለኮት ውስጥ የወጣ አየርም ይሁን
ሕይወት እንዳለ የሚያሣይ አይደለም። ‘የሕይወት እስትንፋስ’

363
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚለውም ቃልም ይህንኑ የሰው የአተነፋፈስ ሥርዐት


መሥራት እንደ ጀመረ ያሣያል። ለዚህ ነው የሰው ልጅ ‘ሕያው
ነፍስ ያለው ሆነ’ በማለት የሚያበስረው። ይህ ማለት ግን
የነፍስ መፈጠርን እንጂ ነፍስ ከመለኮት ውስጥ እንደወጣ
የሚያመለክት በጭራሽ አይደለም። በተጨማሪም ነፍስ
መፈጠሩን ክፍሉ ቢነግረንም አማልክቱ እንደሚሉት ግን
እስትንፋስ መንፈስ ወይም ነፍስ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም።
እፍ አለበት የሚለውን ቃል ጸሓፊው የተጠቀመውም የሰውን
ሕያው መሆን የሚያሳይ ሥዕል ለማሣየት ብቻ ነው።

በአጠቃላይ መለኮት ወደ ሰው አፍንጫ እፍ ያለው(የገፋው)


‘የሕይወትን ‘እስትንፋስ’ የከባቢ አየር ከሆነ ሰውም ‘ሕያው
ነፍስ ያለው ሆነ’ የሚለው ቃል የሚያበስረን ሰው በሕይወት
የሚንቀሳቀስበት አካላዊ ሥርዐት ተገጥሞለት በመተንፈስ
መንቀሳቀስ መጀመሩን ሲሆን የነፈስንና የመንፈስን አፈጣጠር
ዝርዝር ግን አይነግረንም። ስለዚህ ሕያው መሆኑ ‘እፍ አለበት’
በሚል የተገለጠው የመጨረሻው ድርጊት ውጤት ብቻ
ሳይሆን የጠቅላለው “ሰው” በመለኮት የመፍጠሩ ውጤት
መግለጫ ነው። ስለዚህ የተጠቀሰው የዘፍጥረት መጽሐፍ ሰው
የመለኮትን ዘረ-መል (DNN) እንደተካፈለ በጭራሽ
አያሣይም።

364
ጆንሰን እጅጉ

ሰበኪው እንደሚሉት የጴጥሮስ መልዕክትም ቢሆን የዘረ-መል


(DNA) ባዮሎጂ ሳይንስ ትምህርት አያስተምርም። “እናንተ
ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት
እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ
ሕዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ።”(1 ጴጥ.2፡9)። ሰባኪው
መዘው ያወጡት ከላይ የተጠቀሰው “ትውልድ” የሚለው ቃል
በዘመነኛ መዝገበ ቃላት ዘረ-መል (DNA) የሚል ፍቺ መያዙ
ሐቅ ነው። ሆኖም መጽሐፉ በተፃፈበት ዘመን ዘረ-መል ገና
አልተገኘም ወይንም አልታወቀም። ጴጥሮስም የእኛን ዘመነኛ
መዝገበ ቃላት አያውቀውም። ከፓስተሩ ይህ እውነት ተሰወሮ
የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት በዘመነኛ መዝገበ ቃላት
ለመተርጎም መታገላቸው ግን የሚያሳዝን ነው።

የአንደኛ ጴጥሮስ መልዕክት አጭር ቢሆንም ከአሥራ ሰባት


ጊዜ በላይ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን የተጠቀመ መጽሐፍ ነው።
ስለዚህ ወደ ዘመነኛው መዝገበ ቃላት ፍች ከመንደርደራችን
በፊት ይህንን ማጤን ክፍሉን በቅጡ ለመረዳት ይጠቅመናል።
የጴጥሮስ መልዕክትን የብሉይ መጽሐፍት አጠቃቀም ስናጤን
ሁለት ዐይነት አጠቃቀም አለው። ይኸውም የብሉይ ቃላትን
በቀጥታ ከነዓረፍተ-ነገራቸው የመውሰድ አጠቃቀምና
አንዳንዴ ደግሞ የዓረፍተ-ነገሩን መሠረታዊ ዐሳብና የተወሰኑ

365
የአማልክቱ ዐዋጅ

ቃላትን ብቻ በከፊል በመውሰድ ከእራሱ አዲስ ቃላት ጋር


በማበር አዲስ ኪዳናዊ ፍቺን የማጉላት አጠቃቀም ነው።

ስለዚህም ‘የተመረጠ ትውልድ’ የሚለውን ቃል ስንመረምርም


ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት የተወሰደ ስለሆነ፤ የቃል
አጠቃቀሙንና ቃሉን ምን ዐይነት ዐሳብ ማሸከም ስለፈለገ
ወደ አዲስ ኪዳን እንደ ወሰደ ማየት አለብን። በአብዛኛዎቹ
የብሉይ መጽሐፍት ውስጥ “መመረጥን” ከቁሳ ቁስ መመረጥ
ጋር በስፋት ተጠቅሶ እናገኛለን። በዘጸ.19፣5 ላይ ግን በተለየ
ሁኔታ ከሕዝቡ መመረጥ ጋር ተጠቅሶ እናገኘዋለን። “አሁንም
ቃሌን በእውነት ብትጠብቁ፣ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ
ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ።” ይላል። በሌላ በኩል
ደግሞ “ትውልድ” የሚለው ቃል በብሉይ መጽሐፍት የታወቀ
ቃል ቢሆንም በዘጸአት ላይ “ርስት” ነው የሚለው።

ሐዋርያው ‘ርስት’ የሚለውን ቃል ‘ትውልድ’ በሚለው


ቢተካውም የሁለቱም ቃላት ትርጉም በመያያዝ ይስማማሉ።
‘ርስት’ የእከሌን ባለቤትነት ሲያሣይ ‘ትውልድም’ በተመሳሳይ
መልኩ የእከሌን ባለቤነትን ያሣያል። ልዩነቱ ለቁስና ለሰው
መዋሉ ብቻ ነው። ለምሳሌ፦ የአብርሃም ትውልድ ሲል
የአብርሃምን ባለቤትነት ያሣያል ማለት ነው። የናቡቴን ርስት
ሲልም እንዲሁ የናቡቴንን ባለቤትነት ያሣያል ማለት ነው።
ስለዚህም ጴጥሮስ “ትውልድ” የሚለውን ቃል ሲጠቀም

366
ጆንሰን እጅጉ

የብሉይን የባለቤትነት ትርጉም ሳያፋልስ ቃሉን ከነዐሳቡ


በመውሰድ ነው የተጠቀመው።

በብሉይ መጽሐፍት “ትውልድ” በብዛት አገልግሎት ላይ


የዋለው በአንድ ዕድሜና ጊዜ ውስጥ የኖሩ ህዝቦችንና በአንድ
ቤተሰብ ውስጥ ያሉ የቤተሰብ ዝርዝር አባለትን ለማመልከት
ነው። ከዚህም በተጨማሪ “የመመረጥን” እና “የትውልድን”
ንድፈ ዐሳብ አጣምረን በብሉይ መጽሐፍት መነጽር ያየን
እንደሆን፤ በመጀመሪያ መመረጥ ያለው በአብርሃም የዘር
ግንድ ወይም ትውልድ ውስጥ በመግባት ብቻ እንደሆነ
እንገነዘባለን። ምክንያቱም የአብርሃም ተስፋና ኪዳን
የሚፀናው ከአብርሃም በመወለድ ስለሆነ ነው። አይሁድ
ለመመረጥ የአብርሃም ትውልድ መሆን ዋና ነገር እንደሆነ
ያስባሉ። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን ጸሓፊዎች ይህንን ወደጐን
በማድረግ ዋናው ነገር ዘር ሳይሆን እምነት ነው በማለት
ይሞግታሉ።

እንደ ሙግታቸውም በእዚያ አሮጌ ኪዳንም ቢሆን ከዘረ-መል


ይልቅ እምነት ነው የሚበልጥ ዋጋ የነበረው። አይሁድ
በእምነት ግንድ ወይም ሥርዐት ውስጥ የሚገቡት ግን
ከአብርሃም በመወለድ ነው። ይህም የሚሆነው የአብርሃም
በሥራ የተገለጠ እምነት ስለሚቆጠርላቸው ነው እንጂ
የአብርሃም ዘረ-መል ስለሚቆጠርላቸው ፈጽሞ አልነበረም።

367
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከአብርሃም እምነት የተነሣ ለእግዚአብሔር የተመረጡ


ይሆናሉ። በአጠቃላይ በዚህም የአብርሃም ኪዳን የነበረውን
የመመረጥን ምሥጢር ያየን እንደሆን ዋናው ነገር የአብርሃም
ዘረ-መል ሳይሆን የአብርሃምን እምነት መካፈል ነበር።
እግዚአብሔር ይቆጥርላቸው የነበረው የአብርሃምን ዘረ-መል
ሳይሆን እምነቱን እንደነበር ግልጽ ሊሆንልን ይገባል።

ኢየሱስ የአብርሃምን ዘረ-መል የያዙ አይሁዳዊያንን


የአብርሃም ዘር ነን ቢሉትም የአብርሃምን እምነት
ስላላገኘባቸው ኮንኗቸዋል። “የአብሃም ልጆች ብትሆኑ
የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር . . .እናንተ ከአባታችሁ
ከዲያብሎስ ናችሁ።”(ዮሐ.8፡33፣39፣44)። በዚህም ንግግሩ
ዋናው ነገር ዘረ-መል መካፈል ሳይሆን እምነት መካፈል
እንደሆነ አሣይቷል። ስለዚህ ኢየሱስም ሆነ የአዲስ ኪዳን
መልዕክት ጸሓፊዎች የአብርሃምን የዘር ግንድ ሙሉ በሙሉ
ወደ ጐን ትተውታል ማለት እንችላለን። የአብርሃምን እምነት
ብቻም አንስተው በማሳየት ልጅነት በዘረ-መል በመዛመድ
ሳይሆን የዘረ-መል ትስሥር በማይፈልግ እምነት እንደሆነ
አሣይተዋል። በሌላ ቋንቋ የአማልክት ዘረ-መል እንደሌለን
በግልጽ አስቀምጠዋል ማለት ነው።

ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ


ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም

368
ጆንሰን እጅጉ

እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ


ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው፣ ለተገረዙትም
አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ
አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ
የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው።
(ሮሜ.4፡1-12)።

ሐዋርያው በዚህ መልዕክቱ የአብርሃምን አባትነት ከዘረ-መል


ሙሉ ለሙሉ ነጥሎ በማውጣት በእምነት ነው ይላል። የበለጠ
ለማስረገጥም አህዛብ ካለ ዘረ-መል እንዲሁ በእምነት ብቻ
አብርሃም አባት እንደሚሆናቸው ያብራራል።

ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት


ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና
እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦
ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፣
ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ
አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን
አባት ነው። (ሮሜ.4፡16-17)።

እንግዲህ ክፍሉ እንዲህ የማያሻማ አቀራረብ ልጅነት


ከተፈጥሯዊው የልጅነት ዘረ-መል ሽግግር ሥርዐት ውጪ
እንደሆነ የሚናገርን ከሆነ ሰባኪው ምን ነካቸው ያስብላል።

369
የአማልክቱ ዐዋጅ

እዚህ ላይ ግን ምናልባት ክሪስ የጴጥሮስን መልዕክት ሲተነትኑ


(ዩሐ. 1፡13) አስበው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ ማንሣት
እንችላለን። ምክንያቱም ዮሐንስ ከሰው መወለድና
ከእግዚአብሔር መወለድን ተፈጥሯዊ ቃላትን በመጠቀም
ያወዳድራልና ነው። “እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ
ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ
አልተወለዱም።” በዚህ ውድድር ውስጥ የሰው ዘረ-መል
በቀጥታ በሦስት የተለያዩ አጋዥ ቃላትን በመጠቀም
ይገልጠዋል። ይህም ከደም፣ ከሥጋ፣ ከወንድ የሚሉት ቃላት
ሲሆኑ ፈቃድ የሚለው የሰውን ዘረ-መል የሚጠቁመው ገላጭ
ቃል ግን ሳይለዋወጥ ከሦስቱም ቃለት ጋር አብሮ ተሰልፏል።

በሌላ በኩል ግን ‘ከደም’ ወይም ‘ከሥጋ ፈቃድ’ በማለት ከሰው


መወለድን እንደተናገረ በአንፃራዊነት ከእግዚአብሔር
መወለድን ሲገልጥ ግን ፈቃድ ወይም ዘር የሚል ተመሳሳይ
ቃል የመጠቀም ድፍረት ውስጥ አይገባም። ይህንን አድርጎ
ቢሆን ኖሮ እኛም “የእግዚአብሔርን ዘረ-መል” ወይም(DNA)
የማውራት ዕድል ይኖረን ነበር። ስለዚህ ዮሐንስም ቢሆን ዘረ-
መልን ከእግዚአብሔር ከመወለድ አንጻር የሚጠቁምበት ሰፊ
ዕድል ቢኖረውም አላደረገውም። አማልክት ክሪስ እንደሚሉት
የእግዚአብሔርን ዘረ-መል ተካፍለናል ለማለት የሚችልበትን
ሰፊ ዕድል ዘሎ ልጅነት በዘረ-መል ካለ የሥጋ ልጅነት

370
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚበልጥ ብቻ በመናገር ይደመድማል። ስለዚህ ይህ


ልጅነት በዘረ-መል ካለ ተፈጥሯዊ ልጅነት ሥርዐት ውጭ
እንደሆነና ከተፈጥሯዊው ልጅነት እጅግ የሚበልጥበት
መንፈሳዊ ምሥጢር እንዳለው እንረዳለን። በአጠቃላይ
ሐዋርያው የልጅነትን ተፈጥሯዊ ባህርይ በማንሣት ማነፃፀር
የፈለገው በእምነት የሚገኘውን የእግዚአብሔር ልጅነት
ስልጣን ትልቅነት ለማሳየት ብቻ ነው። “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣
በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ
ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” (ዮሐ.1፡11)። ስለዚህም
የባዮሎጂያዊው የዘረ-መል ትንታኔ አያዋጣም።

ወደ ጴጥሮስ ስንመለስ የብሉዩን ቋንቋ የወሰደው የአዲስ


ኪዳንን ቤተክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን ሕዝብ ጋር አወዳድሮ
ለመግለጥ ነው። ምክንያቱም የብሉይ ሕዝብ ከተመረጠበት
በተሻለ ሁኔታ የአዲስ ኪዳን ሕዝብ ከብዙ ትውልድና ሕዝብ
መኻል የመመረጥ ዕድል ያገኘ ሆኖ ስላገኘው ነው። ይህም
ምርጫ ዘርና ወገንን የማይለይ ምርጫ ነው። የአብርሃም
ተስፋና ኪዳን ለአዲስ ኪዳን ሕዝብ የኢየሱስን የመስቀል
የማዳን ሥራ በማመን ይቆጠራል። ስለዚህም ሐዋርያው
‘የተመረጠ ትውልድ’ ማለቱ የዚህን ዕድል ትልቅነት ለማጉላት
እንጂ ከመዝገበ ቃላት በመነሣት አዲስ ፍጥረት በመሆን

371
የአማልክቱ ዐዋጅ

የመለኮት ዘረ-መል (DNA) እንደተካፈልን በመገለጥ ለማሣየት


በፍጹም አይደለም።(1 ጴጥ. 1፡10-11)።

በመጨረሻ ክሪስ የአዲሱ ፍጥረትን (DNA)


ዘረ-መል
አሸናፊነትን ለማስረዳት የሚያነሱትን የሮሜ መጽሐፍ
ሥንመለከት እርሳቸው እንደሚሉት ሆኖ አናገኘውም። “በዚህ
ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች
እንበልጣለን።”(ሮሜ.8፡37)። ሐዋርያው እራሱንም
በመጨመር አሸናፊዎች እያለ የሚጠራቸው በቍጥር ‘35’ ላይ
በሰዋዊ ቋንቋ የሚዘረዝራቸውን ስደት፣ ረሃብ፣ ራቁትነት፣
ፍርሀት የሚላቸውንና ሰይፍ በማለት የሚያነሳቸውን
ሮማዊያን ገዳዮችን ነው።

እነኝህ የትግል መድረክ ላይ የወጡ አሸናፊዎች ናቸው።


ምክንያቱም እነኝህ ነገሮች ሁሉ በጳውሎስ ላይ ጡንቻውን
አሳርፈውበታል። የሚበልጥ ማሸነፍ በማለት ሊጠቁመን
የፈለገው ከነኝህ ነገሮች መሽሽ ወይም ማምለጥን ወይም
ክሪስ እንደሚሉት ከድኽነት ከረሃብና ከስደት መውጣትን
ሳይሆን በእዛው መከራ ውስጥ ሆኖ ያለን አሸናፊነት ነው።
ይህም ሚስጥራዊ ማሸነፍ በክርስቶስ ፍቅር ጸንቶ መኖር
ነው። በቍጥር ‘39’ ላይ አጽንዖት በመስጠት “ከፍታም
ቢሆን፣ ልዩ ፍጥረትም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ
ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቻለሁ።”

372
ጆንሰን እጅጉ

ይላል። የዚህም ምክንያቱ የእግዚአብሔር ዘረ-መል ስላለን


ሣይሆን፤ ኢየሱስን የወደድንበት ፍቅር ጽኑና በነኝህ ነገሮችም
ወይም በሮማ ጨካኝ መሪዎች ይሁን በሌላ ልዩ ፍጥረት
ሊጠፋ አለመቻሉ ነው።

በሌላ በኩል ክሪስ ሐዋርያው ጳውሎስ የተጠቀመውን “አዲስ


ፍጥረት” የሚለውን መሠረታዊ የድነት ቋንቋ አንስተዋል።
ጳውሎስ ይህን ቃል የተጠቀመው በቆሮንጦስ መልዕክቱ
ነው።“ሥለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤
አሮጌው ነገር ዐልፎ አል፤ እነሆ፣ ሁሉም ነገር አዲስ
ሆኗል።”(2 ቆሮ.5፡17)። ሐዋርያው ድነትን ከመለወጥ ጋር
በተደጋጋሚ ይመለከተዋል። በዚህም ክፍል በድነት ውስጥ
ያለውን መታደስ ወይም መለወጥ ምሥጢር ለማስረዳት
‘አዲስ ፍጥረት’ የሚል ቃል ዘረ-መል የሚል ዐሳብ ሣያነሳ
ሲጠቀም እናገኘዋለን። ክሪስ ግን የሚጠቅሱት በዚህ መልክ
አይደለም።

ክሪስ እንደሚሉት ሰው አዲስ ፍጥረት በመሆን የመለኮትን


“ዘረ-መል” ከተካፈለ “አማልክቱ” ሰው የእግዚአብሔርን
እምነት በመለማመድ የራሱን የህልም ዓለም ዕውን የማድረግ
ወይም የመፍጠር አማልክታዊ ዐቅም አለው። የሚለው
መደምደሚያቸው የሚያስረግጥ ነው የሚሆነው። እንግዲህ
እምነትን ወይም ቃል የማውጣት ልምምድን ከዘረ-መል

373
የአማልክቱ ዐዋጅ

ግንዛቤ አንጻር ስንመለከተው ከመለኮት ጋር በንፅፅር


በማቅረብና ወደ መለኮትነት ከፍታ በመጎተት ለምትሃታዊ
የርኩሳን መናፍስት ልምምድ በምሥጢር ለማዘጋጀት
እየተሰራ እንደሆነ አንባቢ ልብ ሊል ይገባል።

በአጠቃላይ ጳውሎስ ‘አዲስ ፍጥረት’ የሚለውን ቃል በሁለት


ምክንያት ተጠቅሞበታል። የመጀመሪያውን ቃል
የተጠቀመበት ምክንያት ቆሮንጦሳዊያኑ በተፈጥሮአዊ
አካላቸው እጅግ ይመኩ ስለነበርና ይህም አስተሳሰባቸው
ለሚሰብከው በወንጌል አምኖ መለወጥ ወይም መዳን
እንቅፋት ሥለሆነበት ትምክህታቸውን ማስረጀትና ከመንገድ
ማስወገድ ስለፈለገ ነው። ይህንንም ቍጥር ‘12’ ላይ ስለነኝህ
ሰዎች ባሕርይ የጠቆመውን በመመልከት መገንዘብ
እንችላለን። “በመልክ እንጂ በልብ ለማይመኩ።” ይህንንም
በማለቱ ልብ ከመልክ ያለውን ብልጫ አሳይቷል። እንዲሁ ሁሉ
ውድድሩን በማስፋት አዲስ ፍጥረትና አሮጌ በማለት የአዲሱን
ፍጥረት ብልጫን አያይዞ አመልክቷል። “ስለዚህ ማንም
በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፎ
አል፤ እነሆ፣ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”(2 ቆሮ.5፡17)።

ነገር ግን በጳውሎስ ዕይታ የአዲሱ ሰው ብልጫ የቃል ኀይል


የመጠቀም ብልጫ ሳይሆን አዲስ መሆኑ ወይም ያላረጀ
ማለትም ለማለፍ ያልቀረበ ወይም የማይጠፋ መሆኑ ነው።

374
ጆንሰን እጅጉ

ሁለተኛው ቃሉን የተጠቀመበት ምክንያት አዲስ ፍጥረት


መሆን ከመገረዝ የበለጠ ሥርዐት እንደሆነ በማሳየት በግዝረት
ያለውን የአይሁድ ሃይማኖት ትምክህት ማስረጀት ስለፈለገ
ነው። ይህንንም ለማድረግ በቆሮንጦስ እንዳደረገው አዲስ
ፍጥረት የመሆንን አስፈላጊነት ወይም ረብ ከመገረዝ ጋር
አወዳድሯል። በዚህም ትምህርቱ አዲስ ፍጥረት መሆንን
እንድናውጅ በፍጹም አልነገረንም። "በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ
ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ይሁን አለመገረዝ
አይጠቅምምና።“(ገላ.6፡15)።

ስለዚህ ሐዋርያው ያነሣው አዲስ ፍጥረት የሚለው ጽንሰ-


ዐሳብ ለአማልክትነትም ይሁን ለቃል ማወጅ ሥነ-መለኮት
መሠረት በጭራሽ መሆን አይችልም! የተጠቀሱት
የቆሮንጦስም ይሁን የገላቲያ መጽሐፍት አዲስ ፍጥረት
መሆንን ከአሮጌው ጋር እያነፃፃሩ ሲያነሱ ሰለተቀበልነው
“የእግዚአብሔር ተፈጥሮ” እየነገሩን ሳይሆን የመዳናችንን
ታላቅ ምሥጢር ወይም ከአሮጌው ሰው ‘ባለመጥፋት’ብልጫ
ያገኘንበትን እውነት እየነገሩን እንደሆነ ማወቅ ተገቢ ነው።

“የእምነት ቃል” አማልክት የቃል ዐዋጅን ትምህርት


ሲያጠናክሩ የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክት ሰውን በግልጽ
አምላክ እንደሚያደርጉት እነርሱም “አዲስ ፍጥረት” በማለት
የተዛባና የተወሳሰበ ትምህርት ለማስተማር ሙከራ ያደርጋሉ።

375
የአማልክቱ ዐዋጅ

የቃል ኀይል የሚሠራበት ምስጢር “ሰው መለኮታዊ ተፈጥሮ”


ስላለው እና “አዲስ ፍጥረት” ስለሆነ እንደሆነ አበክረው
ያስተምራሉ።

ይህ አዲስ ፍጥረት የምንፈልገውን ነገር መፍጠር ወይም


ፍጻሜን መወሰን እንደሚችል ይታመናሉ።‘እግዚአብሔር
በፍጥረት ታሪክ በእምነት የቃልን ኀይል እንደተጠቀመ ሁሉ
ሰው የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ስላለው በእምነት የቃልን ኀይል
በመጠቀም የሚፈልገውን ነገር መፍጠር ይችላል።’ የሚለው
ፍልስፍና እውነት ከሆነ ታዲያ ሰው የራሱን የጸሎት መልስ
የመፍጠር ዐቅም አለው እንደማለት ይሆናል። ስለዚህም
አዲሱ ፍጥረት ወደ መለኮት መጸለይ ሳይሆን የሚኖርበት፤
የሚናገረውን “የእምነት ቃል” የመፍጠር ዐቅም ማመንና
እንዲሆንለት የሚፈልገውን ነገር በመወሰን መናገር ብቻ ነው
የሚያስፈልገው ማለት ነው። ይህንን ነው እንግዲህ “ከፍተኛ
ደረጃ ያለው የመንፈስ እምነት” ወይም “እንደ እግዚአብሔር
አምኖ መኖር” በማለት ሲናገሩ የምንሰማው። በእነርሱ ልክ
የማናስብ ከሆነ ደግሞ “ያልገባው” በማለት ቁልቁል
የሚመለከቱን።

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል

376
ጆንሰን እጅጉ

ቀደም ባሉት ምዕራፎች ልዩ ዲበ-አካል ስለ እምነትና ስለ ሰው


ልጅ ዕምቅ ብቃት ያለውን ምልከታ ተመልክተናል። አንዱ
የፍልስፍናው አካል “ሰው ሁሉን ይችላል” የሚል ጽንሰ-ዐሳብ
ነው። ይህንንም ለመደገፍና ሰውን በውሸት ወደ ክርስቶሳዊነት
ለማሳደግ በርካታ ጥቅሶችን ይጠቅሳሉ። በዚህ ንዑስ ርዕስ
የሰውን ልጅ አማልክታዊ ዐቅም ለማሣየት ከሚውሉ ጥቅሶች
ዋነኛ የሆኑ ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይነሣሉ።(ማር.9፡
23፣ ዩሐ.14፡12፣ ማቴ.14፡29)።

ጥቅሶቹን ለመረዳት አስቀድመን ጥቅሶቹ የተወሰዱት


ከወንጌላት እንደሆነ ልብ እንበል። ወንጌላት ኢየሱስ ትምህርት
ከሰጠባቸው ክፍሎች በስተቀር አብዛኛው አካላቸው ታሪካዊና
ቀጥተኛ ትርክት ባህርይ አለው። በአንጻሩ ደግሞ መልዕክቶች
ቀጥተኛ የሆነ የትምህርት አካላቸው ሰፊ ነው። በዚህም
ምክንያት መልዕክቶች የሚያስተላልፉትን ትምህርት መረዳት
ከታሪክ ክፍሎች ከመማር ይልቅ ይቀላል።300 ይሁን እንጂ
አማልክቱ ቀጥተኛ ትምህርት ካላቸው ለመረዳትም ግልጽ
ከሆኑ መልዕክቶችና የኢየሱስ ቀጥተኛ ትምህርቶች ይልቅ
ታሪኮች ላይ ትምህርት የመሥራት ዝንባሌ አላቸው። ለዚህም
ምክንያቱ ጥሩ የመረዳት ዐቅም ስላላቸው ነው የሚል እምነት
የለኝም። ይልቁንም ታሪኮችን እንደፈለጉ አድርገው

300
Gordon D. Fee. New Testament Exegesis. (2002, P,20).

377
የአማልክቱ ዐዋጅ

በራሳቸው ትርጉም ለማቅረብ ስለሚያመቻቸው ነው ብዬ


አምናለሁ።

የመጀመሪያውን “ለሚያአምን ሁሉ ይቻላል አለው” የሚለው


የማርቆስን ዘገባ ስንመለከት። አማልክቱ ይህንን ጥቅስ ሥርው
በማድረግ የኢየሱስን የመቻል ዐቅም በአንፃራዊነት ከገልጋዬች
የመቻል ዐቅም ጋር በማመሳሰልና በማወዳደር ለማሳመን
ይጠቀሙበታል። ይሁን እንጂ ቃሉን በተነገረበት ታሪክ ውስጥ
ስንመለከት እውነቱ ከዚህ የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን።

ኢየሱስ የተጠቀሰውን ንግግር የተናገረው የብላቴናውን አባት፤


“ቢቻልህስ” የሚል ንግግር ተከትሎ እንደሆነ የክፍሉ ትረካ
ያሣያል። ኢየሱስ ለብላቴናው አባት ሲመልስለት “ለሚያምን
ሁሉ ይቻላል” ነበር ያለው። ስለዚህ የኢየሱስ ‘የይቻላል’ መልስ
ስለ እራሱ (ስለ ኢየሱስ) መቻል እንጂ ስለ አማኙ (መቶ
አለቃው) መቻል የተሰጠ አይደለም። ካለ እምነት ወደ
እግዚአብሔር መቅረብ አይቻልምና፤ “እኔን ለሚያምን ሰው
ሁሉን ማደረግ እችላለሁ” እንደ ማለት ነው። ከአውዱ
በመውጣት ነጥለን ካልተረጎምነው በስተቀር የሚያምን ሰው
ሁሉን ማድረግ ይችላል ወይም እምነት ሁሉን ማድረግ
ይችላል የሚል ትርጉም በጭራሽ የለውም።

378
ጆንሰን እጅጉ

ሁለተኛው የዮሐንስ ወንጌል ጥቅስ፦“እውነት እውነት


እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያአምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ
ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።” የሚለው
ነው። አማልክቱ ይህንን ክፍል ሁሉን የማድረግ ያልተገደበ
ችሎታ እንዳላቸው ለማስመሰል ይጠቅሱታል። ኪኒየን ይህ
ጥቅስ እውን የሚሆንበትን ምክንያት እንደ ተለመደው ሰው
በመለኮት ምድብ ውስጥ በመሆኑ ምክንያት በኢየሱስ ቦታ
ስለሆነ እንደሆነ ያነሣል።301 በርግጥም ክፍሉ ከላይ
ከተመለከትነው ከማርቆስ ይልቅ የእምነት ቃል አማልክትን
የሚያግዝ የተሻለ ጠንካራ መከራከሪያ የሚሆን ይመስላል።

ለዚህም ምክንያቱ ጥቅሱን በግርድፉ ስንመለከት አንደኛ


አማኙን የድርጊት ባለቤት ያደርገዋል። ሁለተኛ ገደብ የለሽ
የማስፈፀም መብት ለአማኙ ይሰጣል። ሶስተኛ ልቀት ያለውን
የማድረግ ወይም የመቻል ዕድል ለአማኙ ይሰጣልና ነው።
ኪኒየን ከዚህ ዐይነት ግርድፍ ግንዛቤ ተነስቶ አስተያየቱን
ሲያሰፍር፦ ጸሎት አዲስ ሥርው ይዟል።302 ጸሎት
የምንጮህበትና የምናለቅስበት ሳይሆን አንድ ትልቅ ስብሰባ
ላይ አስፈላጊ የሆነ ነገር ለመጠየቅ እንደተሰበሰቡ ባለስልጣናት

301
E.W. Kenyon, Two kinds of faiths (p, 24).
302
በምዕራፍ ስምንት ላይ መለኮትን ይለምኑታል በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የጸሎትን
ፍቺና ትርጉም ይመለከቷል።

379
የአማልክቱ ዐዋጅ

303
ጥያቄ የምናቀርብበት ነው። ብሏል። ይህም የልዩና እንግዳ
ጸሎት ዐስተሳሰብ እንደሆነ ልብ ይሏል።

በእርግጥ ወዳነሳነው ክፍል ተመልሰን ጥልቅ የሥነ-ጽሑፍ


ምርመራ ለማድረግ ስንነሳ በአንደኛው ነጥብ ላይ
እንደተመለከትነው የድርጊት ባለቤት አማኙን በማድረግ እንደ
ሚጀምር መካድ አንችልም። ይሁን እንጂ የዚህን ድርጊት
አፈፃፀም በቀጣዮቹ ጥቅሶች ላይ ሲያስቀምጥ “ያደርጋል”
የሚለው ግስ “አደርጋለሁ” በሚል ግስ ተለውጦና ተተክቶ
ስለምናገኘው “ያደርጋል” የሚለው ግስ ዘላቂነት እንደሌለው
ልብ እንላለን። ከዚህም በላይ ኢየሱስ የድርጊት ባለቤትነቱን
በማፅናት በተደጋጋሚ ከመናገሩም በላይ እኔ“እራሴ
አደርገዋለሁ” በማለት አጽንዖት ይሰጠዋል። ስለዚህ አማኙን
የድርጊቱ ዐባሪ እንጂ ባለቤት በማድረግ አያነግሰውም።

በዚህ አፈፃፀም ላይም እምነት በወልድ ክርስቶስ የመቻል


ዐቅም ወይም ማንነት ላይ ማረፍ ሲኖርበት ከሚፈለገው
ድርጊት ወይም ውጤት ጋር የመገናኛው መንገድ
‘የምትለምኑትን’ ስለሚል ልመና እንጂ ቃል የማውጣት ልዩ
ጸሎት ወይም ዐዋጅ አይደለም። ይህንን ተረድተን የክፍሉን
ዐውድ በመመርምር ዘላቂ የሆነ የድርጊት ባለቤትነትን
ለኢየሱስ ሰጥተን ስንወጣ በሁለተኛ ነጥብነት ያነሣነው ቃል
303
E.W. Kenyon, Two kinds of faiths, (p,125).

380
ጆንሰን እጅጉ

እዚያው ክፍል ላይ እግራችንን የሚይዝ ሌላ ችግር


ይሆንብናል።

ይህም ‘የምትለምኑትን’ ከሚለው ቃል ጋር ተከትሎ የመጣው


‘ሁሉ’ በሚለው ተቀጽላ ገደብ የለሽ የልመና መብት ለአማኙ
መስጠቱ ነው። ይሁን እንጂ ለዚህም ቃል በክፍሉ ውስጥ ቀላል
መፍቻ እናገኛለን። ይህም የኢየሱስ አድማጮች ወይም
የተደራሲያኑ ዐውድ ወይም አይሁዳዊ ማንነት ነው።
አይሁዳዊ ሐዋርያቱ ልመናቸው ገደብ እንዳለው አሳምረው
ያውቃሉና ፊሊሞራዊያን ባሉበት የዐስተሳሰብ ዐውድ
ልናስቀምጣቸው አይገባም። ለአይሁድ የእግዚአብሔር ፈቃድ
ገደባቸው ነው።

ስለዚህ የኢየሱስ ንግግር ይህንን መሠረታዊ ዐውድ ያልዘነጋ


ንግግር ስለሆነ የምትለምኑት ሁሉ የሚለው ንግግር “እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ” የሚል ታሳቢ ገደብ አለው ማለት
ይቻላል። ስለዚህም ክፍሉን የመጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ
ዐውድ የሚያገናዝብና የጠበቀ አፈታት ልንተረጉም ግድ
ይሆንብናል። “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ
ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።”(1 ዮሐ.5፡14)።

በአጠቃላይ ሐዋርያቱ በመለኮት ፈቃድ የተገደቡ እንጂ


የፈለጉትን ሁሉ የሚያደርጉ ወይም የሚያስደርጉ ሁሉን

381
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚችሉ ፈጽሞ አደሉም። የእግዚአብሔር ፈቃድ


የየትኛውም ልመናም ይሁን እምነት ገደብ ነው። ስለሆነም
የለመናችሁትን ሁሉ የሚለው ቃል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ
የለመናችሁትን ሁሉ የሚል አውዳዊ ማሰሪያ እንዳለው
ማወቅ ይገባናል። ይሁን እንጂ ከዚህ ጥያቄ እግራችንን አላቀን
ልንራመድ ስንል አሁንም በድጋሚ ሦስተኛው ነጥብ ላይ
የተነሣው ቃል ይይዘናል። ይህም ካደረኩት በላይ የሚለው ቃል
ነው።

ቃሉ ልዩ ልምምዶችን ካለ ገደብ እንደምንለማመድ


እንደሚያመለክት እንድናስብ ያስችለን ይሆናል። ይሁን እንጂ
እንደዚህ ዐይነት ግምት ለማሳደር የሚችል ክፍል ቢሆንም
ግምታችንን ግን በክፍሉ እንዲፈተሸ መፍቅድ ይኖርብናል።
ይህንን ለማድረግ ውድድሩ የዐይነት ነው የብዛት የሚል ቀላል
ጥያቄ እናንሳ። ውድድሩ የዐይነት ነው ብሎ ማሰብ ብዙ
አያስኬድም ምክንያቱም ኢየሱስ በዐይነት በሌላ በማንም
የማይደገሙ የእርሱን ከፍ ያለ የመቻል ዐቅም ብቻ የሚየሣዩ
ወይንም መለኮትነቱን የሚያንጸባርቁ ምልክቶችን አድርጓልና
ነው።

ለምሳሌ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለቱን ውሃውን ወደ


ወይን ጠጅ የቀየረበትን የቃና ዘገሊላውን ሰርግ ታሪክና
ማዕበልን በማዘዝ ፀጥ ያደረገበትን ታሪክ ማንሳት ይቻላል።

382
ጆንሰን እጅጉ

የብዛት ነው የሚለው ግን ያስኬዳል ምክንያቱም ኢየሱስ


አገልግሎቱ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ብቻ ለሶስት ዐመት
ያኽል የተወሰነ ሲሆን የሐዋርያቱ ተልዕኮ እስከ ዓለም ፍጻሜ
ድረስ ማለትም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የሰፋ ስለሆነ ነው።
ስለዚህ በአጭሩ እኔ ካደረኩት በላይ የሚለው ቃል ቀደም ብዬ
እንዳነሳሁት የሐዋርያቱን ያልተገደበ መቻል ሳይሆን
የተሰጣቸውን ሰፊ የተልዕኮ ዕቅድ የሚያሳይ ነው።

ሦስተኛው በማቴዎስ ወንጌል ላይ ተዘግቦ የምናገኘው ጴጥሮስ


በውኃ ላይ የተራመደበትን ክፍል ነው። ይህ ክፍል ምንም እንኳ
ቀጥተኛ የታሪክ ትርክት ባሕርይ ቢኖረውም አማልክቱ ግን
ቍጥር ‘29’ ለብቻው ከአውዱ በመነጠል የቃል ኀይልን ‘ሁሉን
የመቻል’ ሥነ-መለኮት ሲመሠርቱበት ይታያል። ኢየሱስ
ጴጥሮስን በውኃ ላይ እንዲራመድ ያደረገው “ና” በሚለው
የቃል ኀይል ነው በማለትም ይሞግታሉ።

የታሪክ ትርክቶች የሚያስተላልፉትን ትምህርት ለማግኘት፤


ታሪኩ ውስጥ በደንብ ገብተን ማየት ይኖርብናል። ማቴዎስ
እንደዘገበው ኢየሱስ ጴጥሮስ በውሃ ላይ እንዲራመድ
መፍቀዱን ተከትሎ ትንሽ እንደተራመደ ወደ ባህሩ ሲመለከት
እጅግ የሚያስፈራ ማዕበል እንዳለ አስተዋለ፤ ወዲያውም
መስጠም ይጀምራል። በዚህም ጊዜ “ጌታ ሆይ አድነኝ” ብሎ
ጮህ። ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ የጴጥሮስን እጅ በመያዝ

383
የአማልክቱ ዐዋጅ

“አንተ እምነት የጎደለህ፣ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው።”


ጴጥሮስንም ወደ ጀልባው አስገባው። ደቀ መዛሙርቱ ይህ
ሁሉ ሲሆን እዚያው ጀልባው ላይ ነበሩ። በሆነውና
በተመለከቱት ነገር ልባቸው እጅግ ተነካ። ከዚህ በፊት
ያልተማሩትን ትምህርት ተማሩ። ዋው! ቀድሞ
ያልተናገሩተንና ያላደረጉትን ለመናገርና ለማድረግ ተገደዱ
“በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት።”

ከዚህ ታሪክ በመነሣት “አማልክቱ” እንደሚሉት የኢየሱስን


ምሳሌነት ለመከተል የእምነት ቃል መርሖን መከተል ነው
የሚያስፈልገው። ይህም ማለት የእግዚአብሔር ሰዎች ኢየሱስ
እንዳደረገው ቃል በማውጣት ሁሉን ማድረግ ይችላሉ
ወይንም በውኃ ላይ ሊያራምዱን ይችላሉ ማለት ነው የሚል
ግንዛቤ ሊፈጥር ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ የእግዚአብሔር
ሰዎች የሚናገሩትን መጠራጠር እንድንሰምጥ ያደርገናል እንደ
ማለት ነው። ይሁን እንጂ ይህ ክፍል እንደዚህ ዐይነት መርሖ
አይሰጠንም።

ይህንንም ለመገንዘብ የሚያስችሉን አራት ነጥቦች አሉ።


በመጀመሪያ “በእግዚአብሔር ሰዎችና” በኢየሱስ መኻል ሰፊ
ልዩነት አለ። ከዚህ ታሪክ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ የተማሩትም
ይህንኑ ልዩነት ነው። በሁለተኛ ደረጃ የእግዚአብሔር ሰዎች
የቱንም ያኽል እምነታቸው ቢያድግ ፊሊሞር እንደሚለው

384
ጆንሰን እጅጉ

ወደ ክርስቶሳዊነት አያድጉም። ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን


የክርስቶሳዊነት ሞዴላቸው በማድረግ የመንጠራራትና የማደግ
ስሜት አልታየባቸውም። በሶስተኛ ደረጃ የተፈጥሮን ሕግ
እስከመጣስ የሚደርሱ ተአምራት የሚሆኑት በመለኮት ፈቃድ
እንጂ በሰዎች ፈቃድ ወይንም ይሁንታ አይደለም። ከዚህ
ተአምራዊ ክስተት በኋላ ደቀመዛሙርቱ ቃል በማውጣት
ከጀልባቸው እየተፈናጠሩ በመውጣት በውሃ ላይ የመራመድ
ሙከራ አላደረጉም ነበር።

አራተኛውና ዋናው ነጥብ ኢየሱስ በዚህ ክፍል ላይ ማስተማር


የፈለገውና ደቀ መዛሙርቱም የተማሩት እውነት ነው።
ይኸውም ሰው ሊደርስበት ስለሚችለው የእምነት ደረጃ
ወይም የማይወሰን የመቻል ዐቅም ሳይሆን ኢየሱስ በማዕበልና
ወጀብ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው የማይደረስበት የተለየ
ማንነት እንዳለው ማወቃቸው ነው። ይህንንም ከተአምራቱ
ያገኙትን ትምህርት ከራሳቸው አንደበትና ድርጊት መገንዘብ
እንችላለን “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው
ሰገዱለት።”(ማቴ. 14፡33)። አዎ! የተፈጠረው ነገር በእነሱና
በኢየሱስ መኻል ያለውን ልዩነት እንዲያስተውሉና
እንዲሰግዱለት አድርጓቸዋል። ማቴዎስ የዘገበው ይህ ታሪክ
በሐዋርያቱና በኢየሱስ መኻል ያለውን ልዩነት የሚያሰፋ እንጂ

385
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚያጠብ አይደለም። በእውነትም ኢየሱስ የማንነታችን


ሳይሆን የተካፈልነው የጽድቅ ባሕርይ ሞዴል ነው።

በአጠቃላይ የዲበ-አካል ሃይማኖት “አማልክት” እንደሚሉት


ኢየሱስ ጴጥሮስን በፍጹም በውሃ ላይ በእምነት ወይም በቃል
ኀይል የመራመድ የእምነት ልቀትን አላስተማረውም። ይህ
ቢሆን ኖሮ ጴጥሮስ ደጋግሞ ደጋግሞ በውሃ ወይም በአየር ላይ
በተራመደና ብዙ አስደማሚ ነገር ባሳየን ነበር። ይሁን እንጂ
ክፍሉ የሚያስተምረን በኢየሱስ የማድረግ ዐቅም ላይ ፍጹም
እምነት እንዲኖረን ነው።

“እምነት የጎደለህ ስለምን ተጠራጠርክ!” የሚለው ተግሳጽ


በጴጥሮስ ላይ የተሰነዘረበት በውሃ ላይ እንዲራመድ ያዘዘው
ሁሉን ማድረግ የሚችል መለኮት ስለነበር ነው እንጂ ሌላ
ምሥጢር የለውም። ከደቀመዛሙርቱ እንደምንማረው እርሱ
የሚሰገድለት መለኮት እንጂ እምነትን በማሳደግ የሚደረስበት
ፍጥረት አይደለም። ይህ ታሪክ የእግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉን
የማድረግ የቃል ዐቅም ማመን እንዳለብን የማስተማር ብቃት
የለውም። ስለዚህ ቃላቸውን የመጠራጠርም ይሁን
የመቃወም መብት ስላለን እምነት የጎደላችሁ የሚል ውንጀላ
አይገባንም።

386
ጆንሰን እጅጉ

በውሃ ላይ ከተራመደውና ከኢየሱስ ጋር አካላዊ ቅርርብ


ከነበረው ጴጥርስ የተሻለ ነገር ከታሪኩ የመማር ዕድል ያለው
የለም። ሐዋርያቱም ቢሆኑ ባለድርሻ ከነበሩበት ታሪክ
በመገንዘብ ሁሉን የሚያስችላቸው የተለየ የቃል እምነት
ምሥጢር እንደተረዱ አልነገሩንም። በአጠቃላይ ሁሉን
የሚችል አምላክ እንጂ ሁሉን የሚችል አማኝ የለም! እምነት
የቱንም ያኽል ከፍ ቢል ሰውን ወደ “አማልክትነት”
አያሻግረውም። ፍጹም የሆነ እምነት መጣል ያለብንም በቃል
ኀይል ላይ ሳይሆን የማይገደብ የማድረግ ዐቅም ባለው መለኮት
ላይ ነው።

ወዳጆች በቸልታ ተውጠናል። ብዙውን ጊዜ ልብ ብሎ


ለሚመለከተን የእግዚአብሔር ሰዎችን የእምነት ቃል ወይም
ስብከት “መጠራጠር እንደ ጴጥሮስ ያሰምጣል” በሚል ፍርሀት
ውስጥ የተቀመጥን እንመስላለን። አንዳንዶቻችን በእንደዚህ
ዐይነት የተወናበደ ትርጉም አእምሯችን ተይዟል። ከመድረክ
አድርጉ የምንባለውን ሁሉ ለማደረግ ራሳችንን አዘጋጅተን
ወደ ጉባኤ የምንሄድ ሆነናል። በስብከታቸው መኻል የአፋቸው
ቃል መሬት ላይ ወድቆ እንዳይቀር ከወንበራችን ተነስተን
የምንቀልብ ጎል ጠባቂ በረኛ መስለናል። እርስ በርሱ ለሚጋጭ
ስብከታቸው እንኳ ያለን ምላሽ “አሜን” ነው።

387
የአማልክቱ ዐዋጅ

የቃል እምነት ሰባኪያን አማልክቱ በእንደዚህ ዐይነት


ዐስተሳሰብ በማስፈራራት በሚቆጣጠሩት ጉባኤ ከታደምን
በምንም ነገር ላይ ፈቃድ ያለንና ምርጫ የማድረግ ዕድል
የሚሰጠን አደለንም። ኦ! ምንኛ የምናሳዝን ምስኪኖች ነን?
‘እንምቢ’ የማለት ወይም የመመርመር መብቱ ግን ነበረን።
ወዳጆች ሆይ፣ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ ነገር ግን መናፍስት
ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰኞች
ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።” የሚለውን ቃል
አስረስተውናል! (1 ዩሐ.4፡1)።

የረገምከት በለስ ደርቃለች


ይህ ጥቅስ ተጠቅሶልን “ቃል ኀይል አለው!” “ቃል ያደርቃል!”
“ቃል ያለመልማል!” ስንት ጊዜ ተብለን አሜን ብለን ይሆን?
ይህንን ማመን የእግዚአብሔርን ቃል የማድረግ ስልጣን ማመን
ሊመስል ይችል ይሆናል። በርግጥ ታሪኩ ተጨባጭና እውነተኛ
ነው። ይሁን እንጂ ታሪኩ ላይ የሚታየውን አንፀባራቂ ጭብጥ
ትቶ ላይ ላዩን ማለት ልጁን ትቶ እንግዴ ልጁን አነሱት
ስለሚሆን ሕይወት ወይም ትርጉም አይኖረውም።

ጎርደን ፊ በስነ-አፈታት ጥናት ሰፊ ተቀባይነትና ተአማኒነትን


ካተረፉ የስነ-መለኮት አጥኚዎች መኻል አንዱ ናቸው።
[“የአዲስ ኪዳን ሐቲት”] በተሰኘ መጽሐፋቸው የሥነ-አፈታት

388
ጆንሰን እጅጉ

መርሆችን ሲጠቅሱ የምናነበውን ክፍል ለመረዳት የክፍሉን


አወቃቀር፣ የስነ-ጹሁፉን ዘዬ፣ የተናጋሪውንና የሰሚውን
ባህል፣ የቃላትና የዓረፍተ ነገር ቅመራ፣ ተግባቦቶች እርስ በርስ
ያላቸውን የዐሳብ ስምምነትና ፍሰት የማየትን አስፈላጊነት
ያነሣሉ። በተጨማሪም ከምናነበው ክፍል መልዕክት ትኩረት
ሳንወጣም ከአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስና ሥነ-መለኮታዊ
ዐውድ ጋር ያለውን ዝምድና ማየት አለብን በማለት
ይመክራሉ።304 ይህንን መሠረት አድርገን ስናጠናና አጠቃላይ
የመጽሐፍ ቅዱስን ዐውድ ስንመለከት፤ የእስራኤል ነቢያት
የሚታይና የሚዳሰስ ድርጊትን በመልዕክት ተቀባዩ ፊት ምሳሌ
አድርጎ ማቅረብ ባህል እንዳላቸው እናገኛለን። ይህም
መልዕክት ከሚያስተላልፉባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ
ውበትና ሥኬት ያለው አቀራረባቸው ነው።

ለምሳሌ ያኽል ሆሴዕን ያየን እንደሆን የእስራኤልን ግልሙትና


ገልጦ ለመናገር ጋለሞታይቱን ጎሜርን አግብቶ ነበር።(ሆሴ.1፡
1-7)። ህዝቄል ደግሞ የእስራኤልን በደም መሞላትና
የእግዚአብሔርን የፍርድ ቅጣት ለማመልከት የሥጋና የአጥንት
ቁርጥራጭ በምንቸት እሳት ላይ ጥዶ እንዲቀቅል ታዞ
ነበር።(ህዝ.24፡1-14)። ኤርሚያስም እስራኤል በባርነት ሥር
እንደምትወድቅ ለማሳየት ቀንበር እንዲሰራና አንገቱ ላይ

304
Gordon D. Fee New Testament Exegesis, (2002, pp, 31, 41).

389
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንዲያስር ታዞ ነበር።(ኤር.27፡2)። እንዲሁም ነቢዩ ኢሳያስ


የወይን እርሻን በመጠቆም የእስራኤልን ሕዝብ በመመሰል
ለመግለጥ ተጠቅሟል። እስኪቆስል ድረስ በጥፊ እንዲመታ
ጉንጩን የሰጠ ነቢይም ነበር። (ኢሳ.6፡1-9 ኢሳ.65፡24 1 ነገ.
21፡37-43)።

ከእነዚህ ታሪኮች መኻል በነገስት መጽሐፍ ላይ የተጠቀሰው


ነቢይ የሚታይና የሚዳሰስ ክስተት በመፍጠር መልዕክቱን
እንዴት እንዳስተላለፈ እንመልከት። ክፍሉ ሲተርክ
ከነቢያትም ወገን አንድ ሰው በእግዚአብሔር ቃል
ባልንጀራውን፦

ምታኝ አለው ሰውዮውም ይመታው ዘንድ እንቢ


አለ። …ደግሞም ሌላ ሰው አግኝቶ፦ ምታኝ
አለው። ሰውዮውም መታው፣ በመምታቱም
አቈሰለው። ነቢዩም ሄዶ በመንገድ አጠገብ
ንጉሡን ቆየው ዓይኖቹንም በቀጸላው ሸፍኖ
ተሸሸገ። ንጉሡም ባለፈ ጊዜ ወደ እርሱ ጮኸ፦
ባሪያህ ወደ ሰልፍ መኻል ወጣ እነሆም፣ አንድ ሰው
ፈቀቅ ብሎ ወደ እኔ አንድ ሰው አመጣና፦ ይህን
ሰው ጠብቅ፣ ቢኰበልልም ነፍስህ በነፍሱ ፋንታ
ትሆናለች፣ ወይም አንድ መክሊት ብር ትከፍላለህ

390
ጆንሰን እጅጉ

አለኝ። ባሪያህም ወዲህና ወዲያ ሲመለከት ጠፋ


አለው። (1 ነገ.21፡37-43)።

ነቢዩ በእርሱና (አደራ ተቀባይ) በሌላው ሰው (አደራ ሰጪ)


መኻል ያለውን የአደራ ስምምነትን ተከትሎ በተፈጠረው
እምነት ማጉደል ምክንያት መሆን ያለበትን ፍርድ ንጉሱን
በማግባባት ያሳምነዋል። “የእስራኤልም ንጉሥ፦ ፍርድህ
እንዲሁ ይሆናል አንተ ፈርድኸዋል አለው።”

በመቀጠል እጅግ ቀላል ከሆነ ከዚህ የሁለት ሰዎች ፍትህ ብይን


ምሳሌ ከበድ ወዳለ በእግዚአብሔርና በንጉሡ መኻል ወዳለው
ስምምነት መስተጓጎል ይንደረደራል። የፊቱን መሸፈኛ
በማንሳትና የቆሰለ ፊቱን ገልጦ በማሳየት ከምሳሌው ወደ
መልዕክቱ በቀላሉ ይሻገራል። “ፈጥኖም ቀፀላውን ከዓይኑ
አነሣ የእስራኤልም ንጉሥ ከነቢያት ወገን እንደሆነ ዐወቀው።”
በመጨረሻም በአጭሩ ማስተላለፍ የፈለገውንም መልዕክት
ያስቀምጣል። “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እርም
ያልሁትን ሰው ከእጅህ አውጥተሃልና ነፍስህ በነፍሱ ፋንታ
ሕዝብህም በሕዝቡ ፋንታ ይሆናሉ አለው።” በዚህንም ጊዜም
ንጉሡ እርሱን የሚመለከት የፍርድ መልዕክት እንደሰጠው
ይረዳና እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ይመለሳል።

391
የአማልክቱ ዐዋጅ

“የእስራኤልም ንጉሥ እየተቈጣና እየተናደደ ወደ ቤቱ


ተመለሰ፣ ወደ ሰማርያም መጣ።” በአጠቃላይ የአይሁድ
ነቢያት እንዲህ ዐይነት የተሳካ የተግባቦት ባህል ነበራቸው።
ማለትም በምሳሌ ለማስተማር ሲሉ ድርጊት ይፈጥራሉ
ወይም በቅርበት የሚታዩና በሕዝቡ የሚታወቁ ነገሮችን
ይጠቀማሉ። ይህንን አይሁዳዊ ተግባቦት በምሳሌነት
ከተመለከትንና ካስተዋልን የማርቆስ ወንጌልን በዚህ ባህል
ውስጥ ሆነን እንድንመለከት ጋብዛለሁ።(ማር.11፡12-14፣ 20-
26)።

ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች


ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፣ ነገር ግን የበለስ
ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም
አላገኘባትም። መልሶም፦ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም
ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ
መዛሙርቱም ሰሙ። ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን
ከሥርዋ ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ትዝ ብሎት፦
መምህር ሆይ፣ እነሆ፣ የረገምሃት በለስ ደርቃለች
አለው።

ወቅቱ በለስ የሚያፈራበት ወቅት ባይሆንም ኢየሱስ ግን በለስ


ፍለጋ ወደ በለስ ዛፍ መሄዱ፤ በተለመደው በነቢያት መንገድ
ድርጊት ፈጥሮ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት እንዳለ

392
ጆንሰን እጅጉ

ይጠቁማል። የሚፈጥረው ድርጊት ደግሞ በእስራኤል


የሚታወቅና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት መሆን አለበት።
እስራኤላዊያን ከበለስ ዛፍ ጋር የተቆራኘ ታሪክ አላቸው።
የበለስን ጥፍጥፍ ለመድሐኒትነት ይጠቀሙበታል።(2 ነገ.20፡
7)። እግዚአብሔር የእስራኤልን አባቶች በሆሴዕ አፍ በበለስ
በመመሰል ተናግሯል። (ሆሴ.9፡10)። ኤርሚያስ እስራኤልን
በክፉና ሰው ሊበላው በማይችለው በለስ እና በጣፋጭ ሊበላ
በሚችል በለስ ተመስሎ በራዕይ ተመልክቷል።(ኤር.24)።

በሌላ በኩል ደግሞ አይሁድ በለስ በተወሰነለት በራሱ ወራት


እንደሚያፈራ ጊዜው ሲደርስ እናፈራለን (እንባረካለን) ብለው
ተስፋ ያደርጋሉ። ይሁን እንጂ ፍሬ ለነርሱ የእስራኤል
ፖለቲካዊ መንግስት ነው። ለእግዚአብሔር ግን መሲኽን
ማወቅና መቀበል መቻል ነው። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ
ደግሞ ለኢየሱስ ርሃቡ ነበር።(ማቴ.24፡32 ዮሐ.5፡34)። ከዚህ
የእስራኤላዊያን ቀደምት የበለስ ግንዛቤ ተነስተን ስንመለከት
ኢየሱስ የተከተለው የንግግር ባህል ወይም እየፈጠረ ያለው
ምሳሌ አግባብነት ያለው ነው።

ወደ ታሪኩም ስንመለስ ኢየሱስ የለመለመ በለስ በሩቅ


ተመልክቷል። ጸሓፊው የሚበላ ፍሬ ፍለጋ ወደ እርሷ እንደሄደ
ከተረከ በኋላ የበለስ ወራት አይደለም በማለተ የፍትህ
አስተያየቱን ያክላል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ይህንን የፍትህ

393
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጥያቄ ጥሎታል። ከዚህም ዐልፎ ማንም ካንቺ ፍሬ አይብላ


በማለት የፍርድ ድንጋጌ ሰጠ። በሁለተኛው ቀን ማለዳ
ሲልፉም ደቀመዛሙረቱ ከሥሯ ደርቃ ተመለከቱ። ነገሩ
ከኢየሱስ የርግማን ቃል ጋርም ስለተገናኘባቸው በመገረምም
ለኢየሱስ መድረቋን ነገሩት። እርሱ ግን “በእግዚአብሔር
እመኑ” በማለት መለሰላቸው።

ይህንን ክፍል በጥልቀት ለመረዳት በሁለት ከፍለን መመርመር


ይኖርብናል። የመጀመሪያው ዋና የታሪኩ መልዕክት ከቍጥር
(12-14) ያለው ከበለሷ መድረቅ ጋር የተገናኘ ወይም በለሷ
የተወከለችበት ለእስራኤል ሁሉ የተላለፈ ሥዕላዊ መልዕክት
ነው። ይህም ሚልክያስ የተናገረው የመሲሁ ድንገታዊ ጉብኝት
መፈሙን ይጠቁማል።305 ይህ ጉብኝት ድንገታዊና በመለኮት
የጊዜ ሰሌዳ የተፀመ እንጂ በእስራኤል የጊዜ ሰሌዳ ወይንም
ውጥን የሆነ አልነበረም። ስለዚህም በታሪኩ ላይ
እንደምንመለከተው የበለሷ ወራት ላይ ትኩረት
አልነበረውም። ኢየሱስ ጊዜን በተመለከተ ሊነሳ የሚችለውን
የፍትህ ጉዳይ ገሸሽ ያደረገው ለዚህ ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ የበለሷ ምሳሌ እስራኤል ከመለኮት ጋር


ያላትን ህብረት በመጠበቅ ውጤታማ መሆን እንዳለባት
ለማሳየት ወይንም የሚጠበቅባትን መልካም ፍሬ ለመጠቆም
305
እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል። (ሚል.3፥1)።

394
ጆንሰን እጅጉ

የተመሰለም ነው። በትንቢት እንደተነገረው ኢየሱስ ወደ


መቅደሱ በድንገት በራሱ ወራት ቢመጣም እንኳ
የሚፈልገውን ፍሬ ይሁን ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ይህንንም ለመጠቆም ማርቆስ በለሷን በዘገበበት ታሪክ መኻል
መቅደሱ በኢየሱስ መጎብኘቱን አስገብቶ ዘግቧል።306 ኢየሱስ
ወደ በለሷ በድንገት በራሱ ጊዜ ያደረገው ጉዞና በበለሲቱ ላይ
የተላለፈበት ርግማን፤ እስራኤል የሚጠበቅባት ፍሬ
ስላልተገኘባት የሚደርስባትን ትንቢታዊ ፍርድ (ርግማን)
ለማመልከት የተደረገ ነው።307

ይሁን እንጂ ኢየሱስ ይህንን በግልጽ የመሰለ ቢሆንም


የሚያሳዝነው ግን ደቀመዛሙርቱ የምሳሌው ፍሬ መልዕክትጋ
ሳይደርሱ መንገድ ላይ ቆመዋል። ትኩረታቸው ክስተቱጋ
ማለትም የበለሷ መድረቅጋ ተጣብቆ ቀርቷል። ለኢየሱስ
እየነገሩት ያሉትም ይህንኑ ግርምታቸውን ነው። ዳሩ ግን
ኢየሱስ በግንዛቤያቸው ማነስ ባይደሰትም ለእስራኤል
እያስተላለፈ ያለውን መልዕክት ወደጐን በማድረግ ክስተቱን
እነርሱን በቀጥታ የሚመለከታቸውን የጸሎት ትምህርት
ለማስተማር ለመጠቀም መርጧል። ስለዚህ ሁለተኛው
306
ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና
የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፣ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም
ወንበሮች ገለበጠ (ማር.11፣15)።
307

395
የአማልክቱ ዐዋጅ

መልዕክት ለደቀመዛሙርቱ ብቻ የተላለፈ መልዕክት እንደሆነ


እናያለን።

በነጋታው ማለዳ በነበራቸው ጉዞ ላይ ኢየሱስ ወደ በለሲቱ


ቀድሞ ሲመለከት አናየውም። ግርምት የወለደው
የደቀመዛሙርት ግብዣ ተቀብሎ ግን ወደ በለሲቱ
ተመልክቷል። ምናልባት የተፈጠረው ድርጊት ማለትም
የበለሲቱ መድረቅ በደቀመዛሙርቱ እንዲነሳ መፍቀዱ
የደቀመዛሙርቱን ፍላጎት ወይም ጥያቄ ተከትሎ ውጤታማ
ትምህርት ለማስተማር ስለፈለገ ይሆናል።

ኢየሱስ ሁል ጊዜ በአከባቢው ላይ የሚመለከተውን ወይም


የሚሰማውን ነገር ለማብራሪያ illustration እንደሚጠቀም
ሁሉ ይህንንም ክሥተት ለማስተማር ለመጠቀም
ፈቅዷል።(ቁ.20-26)። ነገር ግን በዚህ ትምህርት ላይ ብዙ ጊዜ
በቃል ኀይል ስለማመን ለብቻ ተነጥሎ የሚጠቀሰውና
ውዝግብ የሚያስነሳውን ሐረግ እናያለን።(ቁ.23)።308 ይህም
“እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት
ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፣ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ
ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።” የሚለው ነው። የዚህን
ኀረግ ችግር ለመፍታት፤ የበለሷን መድረቅና የደቀመዛሙርቱን
308
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኬኔት ሄገን የተለጠለትና ህይወቱን የለወጠው ክፍል
እንደሆነ እንደሚናገርና ኪኒየንም ቢሆን የቃል ዐዋጅ ትምህርቱን ለማስመር
የተጠቀመበት ክፍል እንደሆነ ልብ ይሏል።

396
ጆንሰን እጅጉ

ጥያቄ ተከትሎ ኢየሱስ ያስተላለፈውን አንኳር ትምህርት


እንመርምር።

ኢየሱስ እያስተላለፈ ያለውን መልዕክት ለመረዳት


በመጀመሪያ በክፍሉ ውስጥ ትኩረት የተሰጠውን ቁልፍ ቃል
እንፈልግ። ይህንን ለማድረግ ስንጓዝ (ከቁ.23-24) ባለው ክፍል
እምነት ሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ ተነስቶ እናገኛለን። ስለዚህ
እምነት የክፍሉ ቁልፍ ቃል ነው ብለን መወሰን እንችላለን።
ይህንን ከተስማማን እምነት የተነሳበትን ዐውድ ለመረዳት
እንሞክር። ምክንያቱም እምነት የተነሳበትን አውዳዊ
ምክንያት ካልተረዳን የትምህርቱን አዕማድ ዐሳብ ማግኘት
ይቸግራል።

በአጠቃላይ አውዳዊ ዐሳቡን ለማግኘት ሦስት ደረጃዎችን


ከማርቆስ ጋር አብረን ለመውጣትም እንገደዳለን። ማርቆስ
በመጀመሪያው ደረጃ ላይ (ቁ.21) በእግዚአብሔር የማመንን
አስፈላጊነት ኢየሱስ እንዳነሣ ያሣየናል። ኢየሱስ መነሾው ላይ
በእግዚአብሔር ማመንን ያነሣው ለመንደርደሪያ ወይም
ለመግቢያ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ “በእግዚአብሔር
እመኑ” የሚለው መልዕክት አድማጮቹ ወይም አይሁድ ሁሉ
የሚስማሙበትና የነቢያቱ ሁሉ መልዕክት ስለሆነ ነው።
ሁለተኛውን ደረጃ ስንወጣ አወዛጋቢውን ቍጥር እናገኛለን።
በዚህም ቍጥር ላይ(ቁ.23) አምኖ የመናገርን አስፈላጊነት

397
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጠቆም አድርጎ ያልፋል። የሚገርመው ግን ይህ ኀረግ የቃል


እምነት “አማልክቱ” ከዐመት ዐመት ውለው ቢያድሩበትም
ኢየሱስ ግን እዚህ ላይ ብዙ አለመቆየቱ ወይም ማብራሪያ
አለመስጠቱ ነው።

ኢየሱስ የምንወዛገብበት ኀረግ ላይ ብዙ ያልቆየው የበለሷን


በዕርግማን ንግግር መድረቅ ቀጥተኛ ታሪክ እና በቍጥር 24
ላይ የሚገኘውን የልመና ንግግርን ወይም የጸሎትን መልስ
ወይም መፈጸም ለማያያዝ ብቻ ሊጠቀምበት ስለፈለገ ነው።
ማለትም አማልክቱ እንዲልላቸው የፈለጉትን የቃል ኀይል
አሊያም የዕርግማን ኀይል ሊያስተምር አልፈለገም ማለት
ነው። አንዳንዶች በዚህ ክፍል የተጠቀሰው “ተራራ” የተባለው
ሴጣን ነው ሌሎች ደግሞ አይደለም “ተራራ” የተባለው
ማንኛውም ችግር የሚሆንብን ነገር ነው ሲሉ ይደመጣሉ።
ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ውዝግብ የክፍሉን ዋና ዐሳብ
የሚያዘናጋና ምንም ረብ የሌለው ነው።

በመጨረሻም ማርቆስ ሦስተኛውን ደረጃ ይዞን በመውጣት


(ቁ.24) ጸሎት ወይም ልመና እንደሚመለስ የማመን
አስፈላጊነትን በማሣየት ኢየሱስ ትምህርቱን እንዳጠቃለለ
ይነግረናል። የኢየሱስ ማጠቃለያ ትምህርት ጭብጥ
የአድማጩን ትኩረት በመሰብሰብ ለተግባር ወይም ለልመና
ጸሎት የሚጣራ ነው እንጂ የርግማንን ምሥጢር በማብራራት

398
ጆንሰን እጅጉ

ርግማንን የሚያበረታታ አይደለም። ክፍሉ ኢየሱስ ምንድነው


ደቀመዛሙርቱን ሊያስተምራቸው የፈለገው? እነርሱስ ምን
ገባቸው? የሚለውን ወሣኝ ጥያቄ ይመልሳል።

ኢየሱስ ትምህርቱን በፍጥነት በጸሎት ወይም በልመና ላይ


ለማሳረፍ ያደረገውን የአቅጣጫ ለውጥ ቆም ብለን ለምን
ይህንን አደረገ በማለት ስንጠይቅ የምናገኘው እውነት አለ።
ይኸውም በቍጥር ‘24’ መጀመሪያ ላይ ‘ስለዚህም
እላችኋለሁ’ በማለት ያሳየው የአቅጣጫ ለውጥና በዚሁ
ቍጥር ላይ ከክስተቱ ጋር የፈጠረው ተዛምዶና ያደረገው
የመልዕክት ድምድማት፤ የትምህርቱ አዕማድ ዐሳብ የቃል
ኀይል እምነት ትምህርት ሳይሆን በእምነት የልመና ጸሎት
ማድረግ የሚል መሆኑንን የሚያሳይ ነው። ሐዋርያትም የእዚህ
ትምህርት ቀጥተኛ ፍቺ እንደገባቸው አምናለሁ። ለዚህም
በሐዋርያት ሥራ ላይ የልመና ጸሎትን በተደጋጋሚ ሲያደርጉ
መታየታቸው ወይም በመልዕክታቸውም የልመናን ጸሎት
አስፈላጊነት በተደጋጋሚ ማስተማራቸው በቂ ማሣያ ነው።
የቃል እምነትንም ተምረው ቢሆን ኖሮ እንዲሁ ተመሳሳይ
ነገር ነበር የሚያደርጉት።

በአጠቃላይ ኢየሱስ በበለሷ ላይ ያወጣው የቃል ትዕዛዝ


እያስተማረ ካለው የልመና ጸሎት ጋር እንደማይጣጣም
አልጠፋውም። ስለዚህም በአስገራሚ የማስተማር ክህሎት

399
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመጠቀም በትምህርቱና በክስተቱ መኻል “ማንም ያለው ነገር


እንዲደረግለት ቢያአምን በልቡ ሳይጠራጠር፣ ይህን ተራራ፦
ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል” በማለት
የዐሳብ ጥምረት ፈጥሯል። በመጀመሪያ የደቀመዛሙርቱን
የበለስ መድረቅ ግርምት መነሻ ያደርግና አምኖ የመናገር
አስፈላጊነት በማንሳት ድልድይ ይሠራል። ከዛም ምሳሌውንም
ሆነ ድልድዩን በመተው አምኖ መናገር የሚለውን መለመን
አሊያም መጸለይ በሚል ተርጉሞ በመተካት፤ ወደ
ሚያስተላልፈው መልዕክት በፍጥነት ይሻገራል። በመጨረሻም
በእምነት የልመና ጸሎት ማድረግ አለባችሁ የሚል ትምህርት
ላይ በመድረስ ይቋጫል።

አሁን ማርቆስም ሆነ ኢየሱስ በእምነት የልመና ጸሎት


ማደርግን እንጂ የርግማን ኀይል ትምህርት ማስተማር
እንዳልፈለጉ ተገንዝበናል። ስለዚህ “አምናችሁ የምትናገሩት
ይሆናልና የምትፈልጉትን ዐውጁ” በማለት ጉባኤ ማስጨነቅ
በእግዚአብሔር ቃል ላይም ይሁን በሕዝቡ ላይ የሚሠራ
ኀጢአት መሆኑን መረዳት እንደማይቸግረን ገምታለሁ።
ይህንን እውነት ወደጐን አድርጎ ክፍሉን ‘የአማኞች የርግማን
ቃል ይሠራል’ ለሚልም ይሁን ለኅሩይ ቃል ዐዋጅ የጸሎት
ልምምድ መጠቀም ትክክል አይደለም። እንዲህ ማድረግ
የቤተክርስቲያንን ወርቃማ የጸሎትና የልመና ልምምድ

400
ጆንሰን እጅጉ

በቀጥታ የሚያጨልም ተግባር መሆኑን ማስተዋል አለብን።


የአማኞችን ርግማን ቃል ኀይልን ትምህርት የሚያቆምልን
ሌላ ጥቅስ ምናልባት የምናገኝ ከሆነ እንፈልግ እንጂ ማርቆስን
ብንተወው መልካም ነው።

በእግዚአብሔር የሚያአምን አማኝ አምኖ መናገር የሚለውን


ቃል አውዳዊ ትርጉም ካስተዋለ፤ ልመና ወይም ጸሎትን
ሰምቶ የሚመልስ አምላክ እንዳለ በመረዳት ንግግሩን
ከእግዚአብሔር ጋር እንጂ ከፍላጎቱ ወይም ከቁስ ጋር
አያደርግም። እምነታችንን በንግግራችን ላይ አድርገን ስናበቃ
“እግዚአብሔርን አምናለው” ማለት መሠረታዊውን የእምነት
መርሖ የሚያፋልስ ቃል አባይነት እንደሆነም መታወቅ
አለበት። የልዩ ዲበ-አካል አማልክቱንም ይሁኑ የእምነት ቃል
አማልክቱን የርግማን ቃል በመፍራት ልንሸማቀቅ አይገባም።
የምንፈራውና የምንቀጠቀጥለት አንድ እውነተኛ አምላክ
የሆነ፣ የሁሉ ጌታና አባት አለን።

የረገምከው ርጉም ይሆናል


“ነቢይ አማልክቱ” ከበረከት ጋር የማገናኘትም ይሁን ርግማን
የማጣበቅ ስልጣን እንዳላቸው በሰፊው ይታመናል ብል
ማጋነን አይሆንብኝም። “ርግማን ሰበራ” ወይም “የበረከት
ቃል ማውጣት” በሚል በተደጋጋሚ ጉባኤ ሰብስበው ሕዝብ

401
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚያስጨንቁም በርካታ ናቸው። እውነቱን ለመናገር


ከእግዚአብሔር ትንቢታዊ መልዕክት ወይም ቃል ይልቅ
በአንደበታቸው ቃል የመሆን ዐቅም የሚታመኑ አገልጋዮችም
ይሁኑ ተገልጋዮች ብዙ ናቸው። ከሰበሰብኩት ዳታ 60%
የሚሆኑት የወንጌላዊያን አማኞች የርግማን ፍርሀት
ዐስተሳሰብ ተጠቂዎች ሲሆኑ አብዛኛዎቹም ለዚህ ማስረጃ
ከምሳሌ መጽሐፍ ይጠቅሳሉ።309 (ምሳ.18፣20)310
ይጠቅሳሉ። ጥቂት የማይባል ሕዝብም“ቃል የማውጣት”
ልምምድን የሚያዘወትሩቱ ሐሰትን ሲናገሩ ቢሰማም እንኳ
በፊታቸው በፍርሃት ይንቀጠቀጣል።

አደባባይ ወጥቶ የሕዝብ ሕይወት የጎዳ ጥፋታቸውን


የሚኮንን ምናልባት የሚገኝ ከሆነ እኛን የነካ ወዮለት!
ለማለት የከንዓንን መረገም በማጣቀስ እስከ ማስፈራራት
ይደርሳሉ።(ዘፍ.9፤25)። ይሁን እንጂ ክፍሉ አደባባይ የወጣን
የአለቆች ስሕተት የወጣበት አደባባይ ላይ ቆሞ መገሰጽ
ርጉም እንደሚያደርግ አያሣይም። በተጨማሪም የኖህ
ስሕተትም እንደ አስተምሮ ስሕተት የሚቆጠር አይደለም፤
ስኽተቱም ቢሆን የማንንም ህይወት የሚጎዳም አልነበረም።
ነገሩን የተመለከቱም የከንዓን ዐይኖች ብቻ ናቸው፤ ከንዓን
ሰነፍ ስለሆነ አልተጠቀመበትም እንጂ መፍትሄው በእጁ
309
Johnson Ejigu. The Infilunce of Positive confession. (2018)
310
ይህንን ጥቅስ በሚቀጥለው ንዑስ ርዕስ በሰፊው የምንመለከተው ይሆናል።

402
ጆንሰን እጅጉ

ነበር። ከዚህ ይልቅ ግን አባቱ ላይ መሳለቅን ምርጫው


አድርጓል። ኖህ ስካርና እንቅልፍ ውስጥ ስለነበረ ፈጽሞ
ስኽተቱን ማረም ስለማይችልም ተጠያቂ አይደለም። ስለዚህ
ክፍሉን የአማልክቱን ስኹት አይነኬነት ለማጉላትና የርግማን
ማስፈራሪያ አድርጎ መጠቀም አግባብ አይደለም። ያም ሆኖ
በአዲስ ኪዳን መራገም የማይገባ እንደሆነ እናውቃለን(ያዕ.3፡
10)።

በሌላ በኩል ደግሞ መለኮት በመንፈሳዊ አገልግሎቶች መኻል


ጣልቃ ገብቶ የሚሠራቸውን ተአምራት የሥነ-መለኮት
ሥርው ማድረግ እንደማይቻል ቢታወቅም፤ የርግማን ቃል
ኀይል አስተምህሮን ለማረጋገጥ “የእግዚአብሔር ሰዎች”
የተባሉቱ አገልጋዮች“ቃል አውጥተው” የተፈጸሙላቸውን
ጥቂት አስደንጋጭና መሳጭ ማስረጃዎች በአንዳንድ የወንጌል
አማኞች በተደጋጋሚ ሲነሣ እንሰማለን። መጠይቅ
ያደረኩላቸው ጥቂት የወንጌል አማኞችም “የእግዚአብሔርን
ሰዎች” የአንደበት ቃል ከሁሉ ይልቅ እንደሚፈሩና
እንደሚያምኑ ተረድቻለሁ።

የዚህን እምነት መሠረታዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያት


ለመረዳት ከመፈለጌ የተነሣ ለአንዳንድ የወንጌል አማኞች፣
የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችና የእምነት እንቅስቃሴ መሪዎች
መጠይቅ አድርጌያለሁ። የርግማንን ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊነት

403
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሲያስረዱኝም፤ ከብሉይ ኪዳን (የዘኁ.22 እና 2 ነገስ.1፡10-


12) ታሪክ፤ ከአዲስ ኪዳን ደግሞ ኢየሱስ ረግሟት
የደረቀችውን በለስና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ
የሚገኘውን የሐናኒያና ሰጲራ ታሪክ
አንስተውልኛል።(በሐሥ.5)።

በእርግጥ እነኝህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተመለከትን


እንደሆን ታላላቅና አስደንጋጭ መለኮት የተገለጠባቸውን
ክስተቶችን ይዘው እናገኛቸዋለን። ቢሆንም ግን የታሪክ
ትረካዎች ላይ ዶክትሪን በመመሥረትና ታሪኮችን በቀጥታ
የእምነት መርሖ አድርጎ መውሰድ ለስሕተት ያጋልጣል።
ስለዚህ ከመነሻው የታሪክ ትረካዎችን የዶክትሪን ሥርው
ማድረግ አይገባም። ለዚህም ምክንያቱ ታሪክ በጊዜ፣ በቦታ
እንዲሁም በታሪኩ ባለቤቶችና ተሳታፊዎች የሚወሰንና
በድጋሚ የሚፈፀም ባለመሆኑ ነው። ጎርደን ፊ በታሪክ ላይ
ዶክትሪን መሥራት የማይቻልባቸውን ነጥቦች በማንሳት
ያስጠነቅቃሉ።311 ይህ ሲባል ግን የምንማረው እውነት ወይም
የምንወስደው መርሖ የለም ማለት አይደለም። ስለዚህም
የታሪኩ ጭብጥ ለርግማን ሥነ-መለኮት መርሖ መሆን
እንደማይችል ለማየት ክፍሎቹን በየተራ እንድንመለከት
እጋብዛለሁ።
311
ጎርደን ፊ እና ዳግላስ። መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለንተናዊ ጥቅሙ ማጥናት። (2000፣
ገጽ፣ 80)።

404
ጆንሰን እጅጉ

በመጀመሪያ የተነሣው ኤልያስ በአክዓብ መልዕክተኞች ላይ


እሳት ያወረደበትን ታሪክ ስንመለከት ኤልያስ ርግማኑ
የሚፀናለት የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ የሚችል አስፈሪ
አማልክት እንደሆነ ሊሰማን ይችላል። ለታሪኩ መፈፀም
መሠረታዊ ምክንያት የሆነውን በጊዜው የነበረው ሁኔታ
ምንድነው ብለን ስንጠይቅ ግን አክዓብ እስራኤልን በበአል
አምልኮ መሙላቱና ሕዝቡም እግዚአብሔርን እንዳይፈራ
ማድረጉ ሆኖ እናገኛለን። በወቅቱ የነበረው ጦርነት በበአልና
በእግዚአብሔር መኻል የሚደረግ ይመስል ነበር። ኤልያስም
ከአክዓብ ጋር የግል ጥል ባይኖረውም እግዚአብሔርን በመወከል
ጦርነት ውስጥ ገብቷል። በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ አክዓብ
ኤልያስን በቁጥጥሩ ሥር ለማድረግ ወታደራዊ ኀይል የላከው።
ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን፦ “እኔስ የእግዚአብሔር
ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፣ አንተንም፣
አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ
እርሱንና አምሳውን ሰዎቹን በላች”(2 ነገ.1፡10)።

ይህንን ክፍል ያጠኑ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ታዲያ በዚሁ


ታሪክ ላይ ዶክትሪናቸውን መሥርተው ነበር። ደቀመዛሙርቱ
አይሁድ ኢየሱስን በኢየሩሳሌም እንዳልተቀበሉት ሲመለከቱ
ተቆጥተው ነበርና የኤልያስን ልምምድ መድገም መፍትሄ
መስሎ ታይቷቸው ፈቃድ ይጠይቃሉ። “ጌታ ሆይ፣ ኤልያስ

405
የአማልክቱ ዐዋጅ

ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ


ትወዳለህን? አሉት።”(ሉቃ.9፡54)። ደቀመዛሙርቱ እንደዚህ
ዓይነቱን ልምምድ ለመለማመድ የመለኮት ልዩ ፈቃድ
እንደሚሻ ቢረዱና ቢጠይቁም ፈቃድ ግን አላገኙም ነበር።
“እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፦ ምን ዐይነት መንፈስ
እንደ ሆነላችሁ አታውቁም።” አላቸው። (ሉቃ.9፡55)።

በአጠቃላይ ከኢየሱስ ምላሽ እንደምንረዳው ኤልያስ ያንን


ድርጊት እንዲፈጽም የመለኮት ፈቃድ ያገኘ ቢሆንም
ለደቀመዛሙቱ ግን አልተፈቀደም ነበር። ይህም መለኮታዊ
ኀይልን ለመግለጥ የመለኮት ንቁ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ
ይጠቁማል። በሌላ በኩልም ኤልያስ “ቃል በማውጣት” ሁሌ
እሳት የሚያወርድ አስፈሪ አማልክት ሆኖ አለመቀጠሉም
የመለኮትን ንቁ ፈቃድ አስፈላጊነት አመልካች ነው። ለዚህም
በኤልዛቤል ፊት የነበረው ሽሽትና ፍርሃት በቂ ምስክር ነው።
በአጠቃላይ ከታሪኩ ዐውድ መገንዘብ እንደምንችለው ታሪኩ
በመለኮት ፈቃድ ወይም ሙሉ ቁጥጥር ሥር የተፈፀመ እንጂ
በኤልያስ ፍቃደ-ልቦና ወይም በአንደበቱ የመርገም ዐቅም
የተፈፀመ አልነበረም። ኤልያስ ልዩ የርግማን ተሰጦ እንዳለው
በማወቅ ወይም የአንደበትን ኀይል በመረዳት በጠላቶቹ ላይ
ሁሌ የእሳት ዝናብ ለማዝነብ የሚሞክር ሰውም አልነበረም።
ይህንን ማድረግ ቢችል ኤልዛቤልን አመድ ባደረጋት ነበር።

406
ጆንሰን እጅጉ

በአጠቃላይ ይህ ታሪክ የአማልክቱን የቃል ርግማን ሥነ-


መለኮት ቅቡል ለማድረግ በቂ አይደለም።

ሁለተኛው ስለ አንደበት ርግማን አደገኝነት ማሣያ ተደርጎ


የሚነሳው ክፍል የረጋሚውን የበለአምን ታሪክ የሚተርከው
የዘኁልቁ መጽሐፍ ነው። በርግጥ የዘኁልቁ መጽሐፍ
የበለዓምን አደገኛ የርግማን ልምምድ የምናይበትን ታሪክ
ይዟል። የበልዓም ርግማን፤ ሕዝብ እንደሚያጠፋ፣ ባርኮቱ
ደግሞ የጦርነት ድል እንደሚያቀዳጅ ታምኗል። ይሁን እንጂ
ይህ የበለዓም የአንደበት ዐቅም በነቢይ ወይም በቅዱሳት
መጽሐፍት የተነገረና የተረጋገጠ አይደለም። ከታሪኩ
እንደምንረዳው የበልዓምን የአንደበት ዐቅም ያመነው ገንዘብ
ሰጥቶ ያስጠራው የአህዛብ ንጉስ የነበረው ባላዓቅ ነው።
ባላዓቅ ነቢያትን የማይሰማ መጽሐፍትንም የማያውቅ ነበርና
በበልዓም የርግማን ኀይል ቢታመን ለምን አያስብልም።

ባላዓቅ የእስራኤል ሕዝብ በዙሪያው ያሉትን ነገስታት እንዴት


አድርጎ እንዳጠፉ ተመለከተ። ስለዚህ ይህንኑ በለዓምን
ለአማልክት መሥዋዕት አቅርቦ የርግማን ቃል በማውጣት
እንዲያግዘው ላከበት።(ዘኁ.23፡2)። “እባክህ፣ ና ርገምልኝ፤
አንተ የመረቅኸው ምሩቅ የረገምኸውም ርጉም እንደ ሆነ
አውቃለሁና ብሎ ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞቹን ላከ”
(ዘኁ.22፡5-6)። እንደ ባላዓቅ አመለካከት ከሆነ አማልክት

407
የአማልክቱ ዐዋጅ

መሥዋዕት ቀርቦላቸው ሕዝቡ በበለአም አንደበት ከተረገመ


የተነገረውን የርግማን ቃል አማልክቱ (መናፍስቱ) ያፀኑታል።
ባላዓቅ በበልዓም የርግማን ወይም የበረከት ቃል የማውጣት
ልምምድ ላይ የዚህን ያኽል ሊታመን የቻለው ከሰማቸው
ወይም ከተመለከተው የበልዓም ልምምድ ውጤት የተነሣ
እንደሆነ መገመት ይቻላል። ልናስተውል የሚገባው ግን
መጽሐፉ ሊነግረን የፈለገው ስለ በለዓም የርግማን ልምምድ
ትክክለኝነት ወይም ስኹት ባለመሆኑ ስለዚህ ጉዳይ ምንም
አስተያየት እንደማይሰጠን ነው።

ፍጥረቱን ሁሉ የመናገርና የማዘዝ መብት ያለው ሉዐላዊ


አምላክ እግዚአብሐር በለዓም መናፍስት ጠሪ ምዋርተኛ
እንደሆነ ቢያውቅም የምዋርት ልምምዱን ሳያአርም
ከበለዓም ጋር መነጋገርና በባላዓቅ ፕሮግራም ላይ እርሱ
የሚፈልገውን ብቻ እንዲያደርግ በማዘዝ እንደ እግዚአብሔር
ነቢይ ሊጠቀምበት ይጀምራል። በርግጥም ይህ ጊዜያዊ
ግንኙነት በለዓምን የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ አስመስሎታል።
እግዚአብሔርም በለዓምን፦ “ከእነርሱ ጋር አትሂድ፤ የተባረከ
ነውና ሕዝቡን አትረግምም አለው።”(ዘሁ.22፡12)። በለዓም
ግን የተላከለት የምዋርት ዋጋ ቢያጓጓውና እግዚአብሔር
በሉዓላዊነቱ ያለው የመቈጣጠርና የመወሰን ዐቅም
ባይገለጥለት፤ እስራኤልን ለመርገም ከባላዓቅ ጋር ተስማምቶ

408
ጆንሰን እጅጉ

ጉዞ ማድረግ ይጀምራል። ምናልባትም የእስራኤልን አምላክ


ከአማልክት እንደ አንዱ አድርጎ ዐስቦት ይሆናል።

ይሁን እነጂ መለኮት በልዕለ ኀይሉ የበለዓምን ፈቃድ


በመከላከል በለዓም የሚፈልገውን እንዳይናገር
ይወስነዋል።“እግዚአብሔርም ቃልን በበለዓም አፍ አድርጎ ወደ
ባላቅ ተመለስ፣ እንዲህም በል አለው።”(ዘሁ. 23፡5)። መለኮት
የዚህን ያኽል በለዓምን ይቆጣጠር የነበረው ባላዓቅ ስለ
ዕርግማን የሚያስበው ትክክል ስለነበርና በለዓም “ቃል
አውጥቶ”፤ ርግማኑ በሕዝቡ ላይ ፀንቶ፤ ሕዝቡ ሽባ ሆኖ
በምድረበዳ እንዳይቀርበት ስለፈራ አልነበረም። በርግጥ
እግዚአብሔር እንዲህ ፈርቶ ከሆነ አምላክ ባልተባለ ነበር።
እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ማንኛውንም የተነገረ
ወይም ሊነገር ያለ የርግማን ቃል ወይም ምዋርት የሚፈራ
ከሆነ በእርግጥ እግዚአብሔር ነው አምላኩ ለማለት
ይቸግራል። ረጋሚው በተናገረው ርግማን ይቀጣል እንጂ
ርግማኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ እንደማይፀናበት መጽሐፍ
ያረጋግጣል። “የሚባርኩህንም እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም
እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ
ይባረካሉ።”(ዘፍ.12፡3)።

ምዋርት ይሥራም አይሥራ ምዋርተኛው ለማሟረት እንኳ


የሚችለው ልዕለ መለኮት ሲፈቅድ ብቻ እንደሆነ የዘኁልቁ

409
የአማልክቱ ዐዋጅ

መጽሐፍ የባላዓቅን ምኞትም ሆነ የበለዓምን ልምምድ


በመቈጣጠርና ባዶ በማድረግ አብርቷል። እዚአብሔር በለዓም
ሕዝቡን እንዳይረግም የተቆጣጠረው ርግማኑን ስለፈራና
ሕዝቡን ከርግማን መጠበቅ ስለፈለገ ሳይሆን በልዕልናው
ሁሉን የሚገዛና የሚቆጣጠር አምላክ እንደሆነ ለአህዛብ
ነገስታት ማሳወቅ ስለፈለገ ነበር። ይህንን የማይገነዘቡ
አማኞች ግን የርግማን አንደበት እንዲዘጋላቸው አሊያም
የርግማን ቃል በበረከት ቃል እንዲሰበርላቸው ሲመኙ
ይታያል።

በመሠረቱ የበረከት ቃል ርግማን መስበሪያም አይደለም።


የበረከት ቃል በሰው ፈቃድና ፍላጎት የሚነገር ቃልም
አይደለም። ነገር ግን በመንፈስ የተገለጠውን እውነት
በማስተዋል፣ የመለኮትን ፈቃድ በመገንዘብ ሊመጣ ያለውን
ነገር የማሳወቂያ ወይም የመተንበያ መንገድ ወይም ወደፊትን
የመጠቆም ጥበብ እንደሆነ መጽሐፍት ይጠቁማሉ። በለዓምን
እግዚአብሔር ከተቆጣጠረው በኋላ ያደረገው ይህንኑ ነው።
በተናገረው የበረከት ቃል መለኮት በሚመጣው ዘመን
በእስራኤል ላይ ያለውን ዓለማ ተርኳል(ዘሁ.23፡8-10፣ዘፍ.48፡
14፣17-19 ዘፍ.49፡28)። በአጠቃላይ ክፍሉ የርግማንን
ፍርሀትን አያሰርፅም። እጆቻቸውን በሰዎች ላይ ጭነው
መልካም ምኞታቸውን ወይም ኅሩይ ቃል ዐዋጅን እንደ

410
ጆንሰን እጅጉ

ትንቢት በማስቆጠር ለሚናገሩም ማለፊያ ስሕተት ኣራሚ


ምክር ነው።

ሦስተኛው ክፍል ኢየሱስ የረገማት በለስ መድረቅ ሲሆን


ራሱን ችሎ በአንድ ንዑስ ርዕስ ስለተነሣ ድግግሞሽን ለመቀነስ
በዚህ ክፍል አይነሣም።312 የመጨረሻው የአንደበትን ርግማን
ኀይል ለማስረዳት የተነሣው ክፍል ሐናኒያና ሰጲራ የሞቱበት
ታሪክ ነው። ካደረኩት ቃለ መጠይቅ ለመረዳት እንደቻልኩት
ጴጥሮስ የቃልን ኀይል ወይም ርግማን ወይም የፍርድ ቃል
ተጠቅሞ ሐናኒያንና ሰጲራን በራሱ ፈቃድ እንደገደለ ተደርጎ
ይተረጎማል። “ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤
በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።”(ሐሥ.5፣5)።

ይሁን እንጂ ታሪኩን ስንመለከት ጴጥሮስ በሐናኒያ ላይ


የፍርድን ወይም የርግማን ቃል አወጣ ለማለት የሚያስደፍረን
ሆኖ አናገኘውም። “ጴጥሮስም፦ ሐናንያ ሆይ፣ መንፈስ
ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን
በልብህ ስለ ምን ሞላ? ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን?
ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ
ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም
አለው።”(ሐሥ.5፡3-4)።

312
“የረገምካት በለስ ደርቃለች” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ክፍሉ የእርግማን ቃል
ኃይል ትምህርትን ለማስተማር የማይበቃ እንደሆነ ይመለከቷል።

411
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሐዋርያው ሐናኒያ እንደዋሸ የተረዳው በመንፈስ ቅዱስ


እንደሆነ ግልጽ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ሐናኒያን መውቀስና
መጠየቅ ነበረበትና ያደረገው ይህንኑ ነው። ጴጥሮስ የሐናኒያን
ሞት አላወጀም ነበር። ይሁን እንጂ ለመሥራት የሰውን አፍ
ትዕዛዝ የማይሻ ወይም በሰው ምክር መደገፍ የማያስፈልገው
መለኮት የራሱን እርምጃ ነበር የወሰደው። በተመሳሳይ ሁኔታ
ጴጥሮስ ለሰጲራ ጥያቄ ቢያቀርብላትም እርሷ ግን በድጋሚ
ዋሸችው። ሐዋርያው ከመጀመሪያው ክስተት የተነሣ
የመለኮትን ፍርድ አስተውሎ ነበርና በባሏ ላይ የሆነው ነገር
በእርሷም ላይ እንደሚቀጥል የቅርብ ጊዜ ትንቢት ነገራት።
በባሏ ላይ እንደሆነ ሆነባት፤ ወድቃ ሞተች። ከዚህ ታሪክ በኋላ
ሐዋርያው አማልክት ሄገን እንደ አደረጉት “አዲስ ልምምድ
ላይ ደረስኩ” ወይም “አዲስ ቅባት ተቀበልኩ” ወይም “አዲስ
መገለጥ” በሚል የቃል ርግማን ኀይል በተደጋጋሚ
ለመለማመድ ሲሞክርም ሆነ ሲያስተምር ወይም “ቃል
ላውጣ?” በሚል ሲደሰኩር በጭራሽ አናገኘውም።

በአጠቃላይ ክፍሉ የአንደበትን ቃል ልዕልና አያሣይም።


ይልቁንም መለኮት ፍርድን ለማድረግ የሰውን ንግግር
እንደማይጠብቅ ይጠቁማል። ከዚህ ቃል በመነሣት
የምንፈልገውን ለመጣልና ለመሻር ወይም ለማዋረድ ወይም
ለማክበር የርግማን ቃል ማውጣት የአህዛብ ልምድ ወይም

412
ጆንሰን እጅጉ

አምላክ የሚፀየፈው ሟርት እንደሆነ ልናውቅ ይገባል። ይህንን


ስመለከት ምናለ ያላስተማሩንን ትተን ያስተማሩንን መከተል
ቢሆንልን የሚል ቁጭት ይይዘኛል?

ወዳጆች ርግማንን መፍራትም ሆነ መሸማቀቅ አይመጥነንም፤


ይህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ባሕርይ በፍፁም አይደለም።
እንዲህ የሚባል ነገር የለም እንጂ “የአንደበት ሕግ” የሚባል
ነገር አለ ብለን ብናምን እንኳ፤ እግዚአብሔር በበለዓም
አንደበት የሚሠራውን የርግማን ሕግ በጭራሽ አልፈራውም
ነበር። በታሪኩ ላይ እንዳየነውም እግዚአብሔር በመንገዱ ላይ
እየወጣ የተገዳደረው ሉዐላዊ ኀይሉን ሊያሳይ ስለወደደ
እንደነበር እንዳስተዋልን ተስፋ አደርጋለሁ። የዕብራዊያን
አምላክ ባላዓቅና በለዓም የእንሰሳት ስብ መሥዋዕት
ያቀረቡላቸው መናፍስት የማያስቆሙት ብርቱ አምላክ
እንደሆነ አሳይቷል። መናፍስቱ ተደግሶ የልምዳቸው
ቢደረግላቸውም በለዓም ባዘጋጀላቸው መድረክ ዝር አላሉም
ነበር።

413
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል


“የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል ከንፈሩም ከሚያፈራው ይጠግባል
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው የሚወዷትም ፍሬዋን
ይበላሉ።”
(ምሣ.18፡20-21)

“የአንደበት ቃል ኀይል” ወይም “ኅሩይ ቃል ዐዋጅ” ሰባኪያን


በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘው ዐሳብ ስለ አንደበት ቃል
ምስጢራዊ ኀይል እንደሚናገር ይስማማሉ ማለት ይቻላል።
ለምሳሌ ፓስተር ክሪስ ይህንን ጥቅስ ጠቅሶ ሲያበቃ “ይህ
የቃላት ኀይልና የመፍጠር ጉልበትን እንድንረዳ ያደርጋል።
ቃላችን በጣም ኀይለኞች ናቸው። ሊሰሩም ሊያበላሹም
ይችላሉ።” ብሏል።313 የዚህን ትምህርት ታሪካዊ መነሾ በክፍል
አንድና ሁለት ላይ እንደተመለከትነው ልዩ ዲበ-አካል እንደሆነ
አስረግጠናል። ይሁን እንጂ የእምነት እንቅስቃሴ አዕማድ አካል
ከመሆን አልፎ በካሪዝማቲክ ወይም በወንጌላውያን
እንቅስቃሴ ውስጥ እንኳ ሳይቀር መስረግ የቻለ ቆሻሻ ነው።
በተለያዩ የመንፈሳዊ ተቋማት ውስጥ ከዐገር ውስጥና ከዐገር
ውጪ የሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በቃል እምነት ላይ ያላቸው
መመሳሰል ዓለም አቀፍ መልክ ያለው የልዩ ዲበ-አካል

313
ክሪስ እና አኒታ ኦያኪሎሚ Rapsoid of reality. (ጥር፣19፣2006).

414
ጆንሰን እጅጉ

ዐስተሳሰብ ተጽዕኖ ውስጥ መውደቃቸውን ያሣያል። ለምሳሌ


ያኽል ከዲበ-አካል ሃይማኖት መሪዎች መኻል የሩዝልን
ከመንፈስ ቅዱስ ኀይል እንቅስቃሴ መሪዎች መኻል
የክርስቲያን ሃርፉችን፣ ከእምነት ቃል እንቅስቃሴ መሪዎች
መኻል የሬቨረንድ ተዘራ ያሬድን ከወንጌላዊያን አማኞች
መሪዎች መኻል የመጋቢ አመሉ ጌታን በተጠቀሰው ጥቅስና
ትምህርት ላይ የሰጡትን ማብራሪያ አንድነትና ልዩነት
እንመለከታለን።

የፊሊሞር ተከታይ የሆኑት ሩዝል ይህንን ክፍል ጠቅሰው


ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ።“ዐዎንታዊ ነገር በምናገርበት ጊዜ
ሕይወትን እናገራለሁ! ወይም እበላለሁ! ዐሉታዊ ነገርን ስናገር
ደግሞ ሞትን እናገራለሁ ማለት ነው።”314 ‘;;ሩዝል የጥቅሱን
ቀጥተኛና ጠባብ ትርጉም ብቻ ነው የወሰዱት። በዚህም
ምክንያት የአንደበታቸውን ፍሬ እንደሚበሉ ወይም
የሚናገሩትን ነገር እንደሚወርሱ ፍጹም እርግጠኛ ናቸው።

በሌላ በኩል ፔንትኮስታል እንቅስቃሴ አራማጅ፣ የሚራክል


ፌዝ ቤተክርስቲያን ፓስተርና ዓለም አቀፍ ሚራክል
ኢንስቲዮት የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማዕከል
መስራች፤ ክርስቲያን ሃርፉች (ዶ/ር) ይህንኑ ክፍል ጠቅሰው
ሲያብራሩ፦
314
Harrison, Righteous Riches. (2005, P, 68).

415
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይሄ ማለት አሸናፊ ናችሁ ስልጣን አላችሁ፣ ሴጣን


ይፈራችኋል፣ ሊይዛችሁ አይችልም፣ በእግዚአብሔር
ቃል ልባችሁን ብቻ አይደለም መሙላት ያለባችሁ!
አንደበታችሁንም ጭምር በእግዚአብሔር ቃል
መሙላት አለባችሁ። ከዛ በኋላ ከአፋችሁ የሚወጣው
ቃል አካላችሁን ሁሉ መንካት መባረክ ይጀምራል።
የአንዳንድ ሰዎች ችግር እኮ የንግግራቸው ዋጋ ነው
እግዚአብሔር ልባችሁ ውስጥ ሕይወትን አስቀምጧል።
ያ ሕይወት ጊዜያዊ ውበት አይደለም የሚሰጣችሁ።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የማትናገሩት ከሆነ ግን
አዕምሮአችሁን አይለውጥም፣ ነፍሳችሁን
አያጠነክርም፣ አካላችሁን አይፈውስም ህይወታችሁን
አይመራም ማለት ነው። 315

ብለዋል። እንደ እሳቸው አገላለጥ የአንደበታችን ቃል ስንናገር


ኀይል ኖሮት በዘረዘሯቸው በረከቶች እንሞላለን ወይም
እንጠግባለን። በእርግጥ ሰውየው ‘ተናገሩ’ የሚሉት
የእግዚአብሔርን ቃል ነው። ችግሩ ግን የእግዚአብሔርን ክቡር
ቃል የማንናገረው ከሆነ በፍጹም መሥራት እንደማይችልና
በህይወታችን ላይ ተጽዕኖ እንደሌለው በማንፀባረቅ ቃሉን
ከንግግር ሕግ በታች ማድረጋቸው ነው። አፅንዖት
ለመስጠትም ቃል የሚሠራበትን መሠረታዊ ነገር

315
Christian Harfouche, The hiden power of your words, (1993, P,55).

416
ጆንሰን እጅጉ

እግዚአብሔር በውስጣችን ሕይወትን ስላስቀመጠና የዚህ


ሕይወት የመስሪያ ብቸኛ መንገድ አንደበታችን ስለሆነ ነው
ብለዋል። ስለዚህ እንደ እሳቸው በውስጣችን ያለ ሕይወት ቃል
እና አንደበት ከፍተኛ ትስሥር በማድረግ ክስተቶችን
በመቈጣጠር ድርጊት የመፍጠር ስልጣን ይኖራቸዋል ማለት
ነው።

በእምነት እንቅስቃሴ አራማጅነታቸው የሚታወቁት መጋቢ


ተዘራ ያሬድም ይህንኑ በምሳ.18፡20 ላይ የሚገኘውን ጥቅስ
በመጥቀስ “የምትናገሯቸው የእግዚአብሔር ቃሎች
ተመልሰው ያረሰርሷችኋል” በሚል ርዕሳቸው ላይ
ሲናገሩ፦“እስቲ እነኝህን ቃሎች በእምነት ተናገሯቸው።
ለራሳችሁ ተናገሩ እግዚአብሔር ይወደኛል ባርኮኛል ያበዛኛል
ስለዚህ በምንም አልፈራም በሉ።”316 በማለት የአንደበትን
ፍሬ የመብላትን ልምምድ ይመክራሉ።

የወንጌውያን አቢያተክርስቲያናት መኻል የተሓድሶ


እንቅስቃሴ ፍሬ የሆኑ ቤተእምነቶች ቢኖሩም አጠገባችን
አይደርስም፤ ፈጽመንም አናውቀውም በሚሉት የልዩ ዲበ-
አካል የእምነት ቃል ልምምድ እየተያዙና ከተሓድሶ መስመር
በጥቂቱም ቢሆን ቀስ በቀስ እየተንሸራተቱ ይገኛሉ። ለምሳሌ
ከነኝሁ ቤተእምነቶች የአንዲቱ አጥቢያ ስመ-ጥር መሪ መጋቢ
316
ተዘራ ያሬድ። ሬማና ሎጎስ (2008፣ ገጽ 133)::

417
የአማልክቱ ዐዋጅ

አመሉ ጌታ ይህንኑ ሩዝልስ፣ ሃርፉችና ያሬድ ተዘራ የቃልን


ኀይል ለማሣየት የነካኩትን የምሳሌ መጽሐፍ ክፍል
በመጽሐፋቸው ላይ በተመሣይ ትርጓሜ ማንሣታቸው በጥቂቱ
ብናነሳ ማለፊያ አስረጂ ይሆንልናል። በዚሁ ጹሑፋቸውም
መልካምና የተመረጡ ቃሎችን በመናገር በረከትን የማወጅ
አስፈላጊነትን አበክረው ያሳስባሉ።
ሰው መረዳት ያለበት በዘመኑ ሁሉ የአንደበቱን ፍሬ
እንደሚበላ ነው። ክፉም ይሁን ደግ ሰው በዘመኑ
ሁሉ የሚጠግበው እንደተጻፈው ቃል የአንደበቱን
ፍሬ ነው። ክፉ ቃል በእኛና በእኛ ጉዳይ ላይ
ከተናገርን መርገም ሆኖ የህይወታችንን ፍጻሜ
ማሰር ይችላል። 317

ብለዋል። መጋቢው በዚህ ጥቁርና ነጭ በሚባል ግልጽ


አገላለጣቸው የአንደበት ቃል ፍጻሜን የማሰር ጉልበት
እንዳለው በመጠቆም አንባቢን በዚህ አደገኛ እስራት
እንዳይጠለፍ በመጓጓት ያስጠነቅቃሉ።

መጋቢው ይህንኑ የምሳ.18፡20 ን ጥቅስ በሌላም ቦታ በድጋሜ


አንስተዋል፤ በአንደበት ክፉ ንግግር ርግማን ምክንያትም
ለታሰሩ ወገኖች የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

317
መጋቢ አመሉ ጌታ ። ቅድመ ጋብቻ ጥበብ። (2008፣ገጽ. 93)።

418
ጆንሰን እጅጉ

እንግዲህ ሕግ በሕግ እንደሚሻር ሁሉ የተናገርነው ክፉ


ቃል መሻር የሚችለው አሁን አምነን በምንናገረው
መልካም (ኅሩይ) ቃል ነው። አስቀድሞ በቀልድ
መልክም ይሁን ሆን ብላችሁ ከአፋችሁ የወጣው
በነገራችሁ ላይ እስራትን አለመከናወንን ያመጣው ክፉ
ቃል ሕይወትን በሚዘራ ቃል መሻር አለበት። 318

ብለዋል። እንደ እሳቸው ከሆነ በቀልድ መልክ የተናገርነው ቃል


እንኳ በቃል ብቻ የሚፈታ እስራት ሆኖ ሊያሰቃየንና
ሊያሰናክለን ይችላል። ይህ ደግሞ እጅግ አስፈሪ ከመሆኑም
በላይ በልዕለ መለኮት ቁጥጥር ሥር የምንገዛ ሳንሆን ለአንደበት
ሕግ ተላልፈን የተሰጠን ምስኪኖች ያደርገናል።

በሌላ በኩል ደግሞ መጋቢው ለየት ባለ መልኩ የአንደበታችን


ክፉ ንግግር በራሱ እንደማይፈጸም ነገር ግን አስፈጻሚ ክፉ
መንፈስ እንዳለና መልካም ስንናገር መቀመጫ
እንደምናሳጣው ያክላሉ።319 በርግጥ ይህ ትንታኔያቸው ከዲበ-
አካል ሃይማኖት አራማጆች መርሖ ጋር አይስማማም።
ምክንያቱም የንግግራችን ድርጊት ባለቤትን “የተፈጥሮ ኀይል”
ወይም “የአዕምሮ ኀይል” ነው በሚለው የልዩ ዲበ-አካል ግንዛቤ
ምትክ “አስፈጻሚ ክፉ መንፈስ” የሚል ጽንሰ-ዐሳብ
318
Ibdi. (ገጽ. 104)።
319
Ibdi. (ገጽ, 105).
ራሚሽ። የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት። (2003 ገጽ. 20-35)::

419
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመጠቀም በዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ላይ ዕርማት


ሰንዝረዋል።

ይሁን እንጂ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት በአንደበት ቃል


ላይ ያላቸው ክፍሉን የተንተራሰና የተደጋገመ ትንታኔያቸው
ወደ ልዩ ዲበ-አካሉ ፍልስፍና የተጎተተ ነው። ከዚህም ባሻገር
መጋቢው የትምህርታቸው መነሾ የሆነውን የዚሁን ክፍል
አፈታት የተመለከትን እንደሆን ከሩዝል፣ ከያሬድም ይሁን
ከሃርፍሮች ሥነ-አፈታት የተለየ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-
አፈታት አልተከተለም። ይህም ስኹት የሥነ-አፈታት
ዝምድናም ለወንጌላውያን ሰባኪያን የማንቂያ ደወል ነው ብዬ
አምናለሁ።

ሩዝልስንና ፊሊሞርን በመሳሰሉት በዲበ-አካል ሃይማኖት


መሪዎች ዕይታ ከሆነ፤ የኅሩይ ቃል ዐዋጅ የሚሠራበት
ምሥጢር በውስጣችን ያለ የአዕምሮ ሕግ ወይም መለኮት
ማለትም ዲቫይን ማይንድ፣ የአንደበት ቃልና እምነት ከፍተኛ
ትስሥር በማድረግ በክስተቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የባለቤትነት
ስልጣን ስለሚኖራቸው ነው። እንደ ክርስቲያን ሃርፉች
ምልከታ ደግሞ ኅሩይ ቃል ዐዋጅ የሚሠራበት ምሥጢር
እግዚአብሔር በውስጣችን ያስቀመጠው ሕይወትና
የአንደበታችን ቃል ትስሥር በማድረግ የባለቤትነት ድርሻ
ስለሚወስዱ ነው። እንደ ሬቨረንድ ተዘራ ምልከታ ደግሞ

420
ጆንሰን እጅጉ

የሚነገሩ ቃሎች ወደ ተናጋሪው ተመልሰው የሚመጡበት


ለሳቸውም እንኳ ግልጽ ያልሆነ በእምነት የምንቀበለው
ሥርዐት ስላለ ነው። እንደ መጋቢ አመሉ ጌታ ዕይታ ከሆነ
ደግሞ የተናገርነው ከፉ ነገር የሚሆንብን አስፈጻሚ ክፉ
መንፈስ የባለቤትነት ድርሻ ስለሚወስድ ሲሆን በተቀራኒው
ደግሞ መልካም የሚሆነው አስፈጻሚ መልካም መንፈስ ስላለ
ነው። ከዚህም በተጨማሪ በተመሳሳይ መልኩ አብዛኛዎቹ
ወንጌል አማኞች ይህንን ክፍል የአንደበት ቃል ኀይልን ውጤት
እንደሚያሣይ እንደሚያምኑ ካደረኳቸው በርካታ መጠይቆች
መረዳት ችያለሁ።

የተነሣውን የምሳሌ ምዕራፍ 18፣20 ክፍል አብዛኛዎቹ


የወንጌል አማኞችም ጭምር እንደሚስማሙበት ስለ አንደበት
ቃል ኀይል የሚናገር ከሆነ አስተሳሰቡ ለምንድነው
የሚተቸው? ወይም ለምንድነው ሁላችን በዚህ ዐሳብ ላይ
የማንስማማው የሚል ጥያቄ በልበ ሰፊነት ማንሣት ይገባል።
በመጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ስልጣን እንደሚያምን አማኝ ግን
ሊያስማማን የሚችለው የዲበ-አካል ሃይማኖት መሠረታዊ
የቃል እምነት መርሖ ሳይሆን በትክክለኛ የሥነ-አፈታት ላይ
የተመሠረተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ብቻ ነው።

የዚህን ክፍል መልዕክት ለመረዳት እውነተኛ ጕጕት ያለው


ማንኛውም ሰው በመጀመሪያ የክፍሉን ዓረፍተ ነገር

421
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከመተርጎሙ በፊት አስቀድሞ የመጽሐፉን ባህርይ መገንዘብ


አለበት። የምሳሌ መጽሐፍ የጥበብ መጽሐፍ እደመሆኑ መጠን
ሥነ-ፁሁፋዊ ጥበቦችን የሚጠቀም ጥበባዊ ባሕርይ የተላበሰ
መጽሐፍ ነው። በቀጥታም ሰው ከመለኮት ጋር ያለውን
ግንኙነት ከማሣየት ይልቅ ሰው ከሰው ወይም ከማህበረሰቡ
ጋር ያለውን ግንኙነት በማንሣትና ማኅበራዊ አባባሎችንና
ተግባራዊ ልምምዶችን በመመርመር የሕይወትን ትርጉምና
ደስታ በምክንያት ያስቀምጣል።320 የመጽሐፉን ባሕርይ
ግንዛቤ ውስጥ ካስገባን በኋላ ከደረቅ ንባብ በመዝለቅ ጸሓፊው
ጽሁፉን ያቀናበረበትን ወይም ያደራጀበትን ሁኔታ መመልከት
አለብን። ከዛም በጹሑፉ ውስጥ ጎልተው ከወጡ እውነታዎች
በመነሣት መሠረታዊ እውነታዎችን መረዳትና የመጽሐፉን
መልዕክት አዕማድ ግንድ ወይም ቲም መገንዘብ ይኖርብናል።

ይህንን ካደረግን ትኩረታችን ወደ ሆነው ወይም ወደ አነሣነው


የምንባብ ክፍል ትርጉም ተቃርበናል ማለት ነው። በመቀጠል
የምንተረጉመውን ዓረፍተ-ነገር የቅርብ ዓረፍተ-ነገሮችን ፍሬ
ዐሳብ በመረዳት ወደ ትርጉም ለመሻገር እንዘጋጃለን።
በመጨረሻ ለመተርጎም የፈለግነውን ዓረፍተ ነገር ጥንድ
ስንኞች ወይም ከላይና ከታች ያሉ ተጣማጅ ኀረጎችን ዐሳብ
መረዳት ይኖርብናል። ይህ ሳይሆን ግን በቀላሉ አንድን ነጠላ

320
Steven L. Mckenzie. How to Read the Bible. (2005, P. 91)

422
ጆንሰን እጅጉ

ስንኝን ለብቻው ወስዶ መተርጎም ከማሳሳቱም በላይ ጥቅሱን


ለባዕድ ዐሳብ እንድንሸጥ ያደርገናል።

በዚህም ሥልታዊ አፈታት ሥርው አጠቃላይ የምሳሌ


መጽሐፍን ማዕከላዊ መልዕክት ምንድነው ብለን እንጠይቅ።
መልዕክቱ ‘እግዚአብሔርን መፍራትህ ወይም ጠቢብ አሊያም
ሞኝ መሆንህ በማህበራዊ ሕይወትህ ወይም ከባልንጀራህ ጋር
ባለህ ግንኙነት ይገለጣል’ የሚል ሲሆን ይህም በፍርድ ቤቶች
ሥርዐት እንደሚዳኝና እንደሚረጋገጥ ያመለክታል።
321
በዚህም መሠረት እግዚአብሔርን መፍራትና ከባልንጀራ ጋር
ያለ ግንኙነት የምሳሌ መጽሐፍ ዋና ማዕከላዊ መልዕክት
ይሆናል ማለት ነው። ይህንን ከተገነዘብን ለመተርጎም
ያነሣነውን ከላይ ለዲበ-አካል ሃይማኖት ቅርብ ተደርጎ
ተንጸባርቆ ያየነውን ክፍል እናንሣ።(ምሣ.18፡20)።

መተርጎም ለፈለግነው ቍጥር “20” ቅርብ የሆኑ ስንኞችን


ማለትም ቍጥር “17” እና ሌሎቹንም እንመርምር። ይህንን
ስናደርግ ቍጥር “17-19” የፍርድ ርዕስ እንደያዘ በቀላሉ
መረዳት እንችላለን። “ወደ ፍርድ አስቀድሞ የገባ ፃድቅ
ይመስላል፤ ባልንጀራው ግን መጥቶ ይመረምረዋል ዕጣ
ክርክርን ትከለክላለች በኃይላንም መኻል ትበይናለች።” ቍጥር

321
Murphy, E. Carm. Wisdom Literature; Job, Proverbs, Ruth, Canticles, and
Estger. (1981, P, 5).

423
የአማልክቱ ዐዋጅ

‘21’ ደግሞ “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው


የሚወዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።” በማለት የፍርድ ድንጋጌ ዋና
ባለ ድርሻ አካል ዳኛው ሳይሆን ለመዳኘት የቀረበው ሰው
እንደሆነ ይጠቁማል። ይህም የሚሆነው ከንግግሩ የተነሣ
ስለሚወሰንበት እንደሆነ ይገልጣል።

በመጨረሻ ቍጥር‘20’ የመጨረሻውን የፍርድ ውጤት ጣራ


‘ሞት’ ወይም ‘ሕይወት’ ማለትም ከሞት ቅጣት ነፃ የሆነ ኑሮ
ወይም ሕይወት እንደሆነ ያሣያል። የፍርድ ሂደቱን ዝርዝር
ሲያስረዳ ደግሞ ይህ የሚሆነው ከተቻለ በምርመራ ካልተቻለ
ደግሞ በዕጣ ሲበየን እንደሆነ ይጠቁመናል። ምክንያቱም ዕጣ
መደቧ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሆነ ስለሚታመን በምርመራ
ያልተገኘውን ጥንታዊው የእስራኤል የፍትህ ጉባኤ ወይም
ፍርድ ቤት በዕጣ እግዚአብሔር እንዲፈርድ ዕድል ስለሚሰጥና
በዚሁ ሥርው ሞት ወይም ሕይወት ስለሚበየን ነው።

በዚህ ፍርድ አሰጣጥ ቀድሞ ወደ ፍርድ ወንበር የገባው ንጹህ


ቢመስልም ባልንጀራው በደረሰ ጊዜ ይመረመራል ወይም
ማስረጃ ያቀርብበታል። ቀድሞ ወደ ፍርድ ወንበር የገባው
በባልንጀራው ለሚያቀርበው መስቀለኛ ጥያቄ ወይም
ለሚያቀርበው የቃል ኪዳን ውል ማስረጃ ወይም ስምምነት
በሚሰጠው መልስና አስቀድሞ በተናገረው የአንደበቱ ቃል
ምክንያት ሞት ሊፈረድበት ይችላል። በተመሳሳይ መልኩ

424
ጆንሰን እጅጉ

የዋስትና ኪዳንን የገባ ሰው ምን ያኽል በቃሉ ምክንያት እስከ


ፍርድ ውሳኔ ድረስ ሊያዝ ወይም ሊጠመድ እንደሚችል በሌላ
ቦታ ተመሣሣይ የፍርድ ድንጋጌን ተጠቅሷል። “በአፍህ ቃል
ተጠመድህ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ።” በማለት ይህንን ያስረዳል።
(ምሳ.6፡2)። ይሁን እንጂ በዚህም ጥቅስ ላይ የቃል ኀይልን
ለማስተማር ሲባል ተመሣሣይ ወንጀል ይፈጸምበታል።322

ስለዚህ ክፍሉ የፍርድ ቤትን የፍርድ አሰጣጥ የመጨረሻ


ስልጣን የሚይሳይ፤ ወደ ፍርድ ቦታ ፍርድ ለማጣመም
ተንቀልቅሎ መግባትና መናገር እስከ ሞት ድረስ ዋጋ
እንደሚያስከፍል የሚያስጠነቅቅ ነው። ስለሆነም የተጠቀሰው
ክፍል የአንደበት ኀይል ሕግን ወይም ከቃል ጀርባ ስለሚሠራ
ክፉ መንፈስ ወይም የርግማን አሠራር በጭላንጭል እንኳ
የሚያሳይ ሆኖ አናገኘውም ማለት ነው።

በአጠቃላይ ሆድን ወይም ሕይወትን የቃላትን ዳቦ በመግመጥ


ለመሙላት መሞከር ወይም የምንፈልገው የስኬት ጥግ
ለመድረስ ቃልን በቃል ለመሻር መጣር ትርጉም ያለው
አይደለም። ክፍሉ ሕይወትን ከማኅበራዊ ፍርድ መጠበቅ
እንችል ዘንድ፤ አንደበታችንን ወይም ንግግራችንን ፍርድን
ለማጣመም ከመጠቀም እንድንታቀብና እንድንጠነቀቅ

322
በዚሁ ምዕራፍ በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል በሚለው ንዑስ
ርዕስ ሥር ይመለከቷል።

425
የአማልክቱ ዐዋጅ

በድምቀት ያስተምረናል። ከዚህ ውጪ ግን ጥቅሱን ገንጥሎ


በመውሰድ “ተገለጠልኝ” በሚል ሰበብ በመቅጠፍ ለሌላ እንግዳ
ዐሳብ መደገፊያ አድርጎ ማዋል በመለኮት የሚያስኮንን ወንጀል
ነው።

በባልንጀራና በባልንጀራ መኻል ያለውን ፍትህ መለኮት ጣልቃ


ገብቶ ከበየነ ቃሉ ላይ ወንጀል በሚሰሩ ላይ እንዴት ይበይን
ይሆን? የአንደበትን ቃል ኀይል በማስተማር ሕዝብን
በዕርግማንና ፍርሃት ውስጥ መክተት ያስጠይቃል። መልካም
በመናገር ሕይወትን በመልካም መሙላት በሚል ቅዥት
የጸሎትን አቅጣጫ ከልመና ወደ ዐዋጅ ጸሎት መቀልበስ
በሐሰተኛ መንገድ ትውልድን መምራት ነው። በእግዚአብሔር
ቃል ላይ እንደዚህ አይነት ቀልድ መቀለድ አያሸልመንም።
እንዲህ ዓይነቱን የቃል እምነት ዐስተሳሰብ የቀዳንበት ምንጭ
ንጹህ አይደለምና አንጠፍጥፈን ብንደፋው ክብር ይሆንልናል።

ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል


“ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል።” (ምሳ.13፡2፣ 18፡21)።
“ቃላት የመፍጠር ኀይል ያላቸው ነገሮች ናቸው። አሁን
የምትኖሩት ሕይወት የቃላችሁ ውጤት ነው።”323
ክሪስ ኦያኪሂሎሚ

323
ክሪስ ኦያኪሂሎሚ (2013 ገጽ. 29)።

426
ጆንሰን እጅጉ

ከላይ የተነሣው የምሣሌ መጽሐፍ ጥቅስ የአንደበትን ኀይል


ውጤት ማለትም ሰው አምኖ በጸሎት የሚያውጀውን ነገር
እንደሚያገኝ እንደሚያሣይ በብዙ ይነሣል። ይሁን እንጂ
አስቀድመን እንዳየነው የምሳሌ መጽሐፍ በማህበረሰብ ውስጥ
የፍትህን አስፈላጊነት የሚያጎላ መጽሐፍ በመሆኑ ስለ ጸሎት
የሚያስተምር መጽሐፍ አይደለም። የተነሣው ክፍል ማለትም
የቍጥር ሁለት ጥንድ ዓረፍተ ነገር “የዓመፀኞች ነፍስ ግን
ግፍን ትሻለች።” በማለት በመጀመሪያው ሐረግ ውስጥ
የአንደበት ውጤት ወይም የሚበላ ፍሬ ሆኖ የተገለጠውን
‘መልካም’ በሁለተኛው ጥንድ ሐረግ ከተቀመጠው የአመፀኞች
ውጤት ከሆነው ‘ግፍ’ ጋር በአንፃራዊነት ያወዳድረዋል። ይህም
ዐመፅን ማድረግ የመልካም ተቃራኒ የሆነን‘ግፍ’ ወይም ክፉ
ቅጣትን እንደመሻት ነው እንደ ማለት ነው። የዐመፅ ፍሬ
የመልካም ተቃራኒ ማለትም የግፍ ቅጣት እንደሆነ ከተረዳን
የዚህን ውጤት ምክንያት የበለጠ ግልጽ የሚያደርግልንን
የቅርብ ዓረፍተ ነገር ቍጥር ሦስትን መመልከት መልካም
ነው። ቍጥር ሦስት “አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል
ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል” ይላል።

በመልካም የመጥገብም ይሁን የጥፋት ምክንያቱ አፍን


መጠበቅ ወይም “ማሞጥሞጥ” ሲሆን ይህም “ኅሩይ ቃል
ማወጅ” አሊያም “ቃል ማውጣት” ሳይሆን አግባብነት

427
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሌለውን ንግግር ሰዎችን በቀጥታ መናገር መሆኑ ነው።


የተጠቀሰው ጥጋብም ይሁን ጥፋት ምክንያቱ ማህበራዊ ፍትህ
ነው እንጂ የቃል ተፈጥሮአዊ ኀይል ውጤት አይደለም። ይህም
የእስራኤል ሕዝብ የፍትህ ሥርዐት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ
ወይም ሕግ የተመሠረተ ስለሆነና ሕጉን በመተላለፍ የማይገባ
ነገር በሌላው ላይ የሚናገር በሕጉ መሠረት ስለሚቀጣ ነው።
ቍጥር ‘13’“ትዕዛዝን የሚያቃልል በትዕዛዝ ተይዞ ይጠፋል!
ትዕዛዝን የሚፈራ ግን በደህንነት ይኖራል።” በማለት ይህንን
ዐሳብ ያፀናል። ይህም ጥፋት ወይም ደህንነት ማለትም ጥጋብ
አንደበትን በመጠበቅ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ፅድቅንም
ማድረግን ያካተተ እንደሆነ አክሎ እንደሚያብራራ ያሣያል።
ቍጥር 25 ላይ ደግሞ “ፃድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ
ይበላል፤ የኃጥኣን ሆድ ግን ይራባል” በማለት መጥገብና
መራብን ከኃጢአትና ከጽድቅ ጋር በማያያዝ የአውዱን ዐሳብ
ወደ ፊት ያመጣዋል።

እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፦ሆድ በንግግር የሚሞላ ቢሆን


ዝምተኞች በርኃብ ጠውልገው ፍግም ባሉ ነበር። እውነቱ ግን
ሕግን በማክበር የማይገባ ነገር ከመናገር ብንታቀብ ኅብረተሰቡ
ይህንን በማየት በሚሰጠን መልካም ምላሽ እንጠግባለን።
ጽድቅን ብናደርግ የፃድቅን በረከት እንጠግባለን። ከዚህ ውጭ
ግን የራሳችንን ትርጉም ለጥፈን፤ ጸሎትን ከንግገር ይልቅ

428
ጆንሰን እጅጉ

ልፍለፋ አድርገነው የምንመኘውን መልካም ነገር በማወጅ


ብንውል ከእውነትም ከጸሎትም ተነጥለን የወደቅን በራሳችን
ላይ የፈረድን ምስኪኖች እንሆናለን።

በልቡ እንደ አሰበው እንደዛው ነው


በአንድ ወቅት ጌታን እንደሚወድ የምመሰክርለት ወዳጄ በፌስ
ቡክ ድህረ-ገጹ ላይ ሰው የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እንደማግኔት
የሰው አዕምሮ ሲስብ የሚያሣይ ማብራሪያ ምስል አጋርቶ
በመመልከቴ ተደናገጥኩ። ይህን ወዳጄን ምን ማለትህ ነው?
ብዬ ብጠይቀው፤ “ሥዕሉ ደስ ስላለኝ ነው ያጋራሁት።”
በማለት መለሰልኝ። “እኮ ሥዕሉ ምን ማለት እንደሆነ
አስተውለሃል?” በማለት ደግሜ ብጠይቀውም “ያው መልካም
ማሰብ ጥሩ ነው ማለት መሰለኝ።” የሚል ቀለል ያለ መልስ
ነበር የሰጠኝ። ይህ ወንድሜ ያጋራው ምስል ሰው በአዕምሮው
ኀይል ሁሉንም ይቆጣጠራል የሚሉ የሂንዱይዝም
አስተሳሰቦችን በተደጋጋሚ የሚያጋራ የፌስ-ቡክ ተጠቃሚ
ያጋራውን ምስል ነበር። የሚያሳዝነው እንደዚህ ወንድማችን
ብዙዎቻችን የመልዕክቶችን መሠረታዊ መነሻና ምንነት በውል
ሳንረዳ ደጋፊ ወይም አስተላላፊ መሆናችን ነው።

“እውነተኛው ማንነትህ የሚወሰነው በልብህ በምታስበው


ዐሳብ ነው! የምትሆነው የምታስበውን ነው! ስለዚህ ነገህን

429
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለመቀየር መጀመሪያ አምሮህ መቀየር አለበት! ነገ የምትሆነው


ዛሬ የምታስበውን ነው!” የሚሉ ሥብከቶችን
በየመድረኮቻችን በተደጋጋሚ ሰምተን አንዳንዶቻችን ትልልቅ
ቤትና ዘመናዊ መኪና ወይም የአለቃችንን ወንበር በመቋመጥ
አስበን ይሆናል። ሌሎቻችን ደግሞ “አቤት መገለጥ” ብለን
ለሌሎች በመተረክ አስተላልፈን ይሆናል። በርግጥ በአዕምሮ
መለወጥ ብንስማማም የአዕምሮአችንን ኀይል ተጠቅመን
በቃል ዐዋጅ ልዩ ጸሎት ነጋችንን ለመቀየር መሞከር ግን
ሟርተኝነት እንደሆነ ልናስተውል ይገባል።

የአዕምሮ ሳይንስ መስራች የሆነው ኢርነስ ሆምስ እንዲህ


ይላል፦“እኛ ሰዎች ፍጻሜያችንን መቈጣጠር የምንችልበት
ዐቅም እንዳለን ለመረዳት ሺ ዐመታት ፈጅቶብናል። መጽሐፍ
ቅዱስ እንዲህ ይለናል ‘ሰው በልቡ እንዳሰበው እንዲሁ
ነውና።’(የምሳ.23፡7)። የማሰብ ሂደት በሰው ውስጥ የሚሠራ
የማያቋርጥ የመፍጠር ጉልበት ነው።”324 ኢርነስ ሆምስ ይህ
ጥቅስ ሰውን ሁሉ እንዲወክልለት ለማድረግ “ሰው” የሚል ቃል
በመደበኛው የምሳሌ ቍጥር ‘7’ ዓረፍተ-ነገር ላይ ጨምሮ
በማስቀመጥና በዚህም ምክንያት የትርጉም ለውጥ በማድረግ
የሥነ-ጽሑፍ ወንጀል ሠርቷል። ይሁን እንጂ ጥቅሱ
የተወሰደበት ቦታ ላይ ‘ሰው’ የሚል ቃል የለም። በተጨማሪም

324
Glenn R. Mosley. New Thought, Ancient Wisdom, (2006, P. 60).

430
ጆንሰን እጅጉ

ጥቅሱ አንድን አስመሳይ ገጸ ባህርይ ያለውን ሰው በምሳሌነት


በማቅረብ በልቡና በንግግሩ መኻል ያለውን መምታታት
በማሣየት በእውነት ላይ ያልተመሠረተ የሸንጋይ ግብዣን ክፉ
መሆን የሚያስተምር ነው እንጂ ሰውን ሁሉ አይወክልም።

የዚህን ጥቅስ ዐሳብ ለመተንተን ከመቸኮላችን በፊት ተያያዥ


ዐሳብ ያላቸውን የቅርብ ዓረፍተ ነገሮችን አብረን እንመልከት።
በመጀመሪያ ሙሉ ዐሳቡ እንዲህ የሚል ነው። “የቀናተኛን
ሰው እንጀራ አትብላ፣ ጣፋጩ መብልም አይመርሖ፤ በልቡ
እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፣ ልቡ ግን ካንተ ጋር
አይደለም። የበላህውን መብል ትተፋዋለህ፣ ያማረውንም
ቃልህን ታጠፋዋለህ።”(ምሳ.23፡6-8)። የዚህ ክፍል አዕማድ
መልዕክት የቀናተኛ እንጀራ አትብላ የሚለው የምክር ቃል
ነው። ለዚህ ደግሞ አሣማኝ ምክንያት ሲያቀርብ በአንደበቱ
ብላ ጠጣ ይልሃል ነገር ግን በልቡ እንድትበላ አያስብም፤
ምክንያቱም የምትበላው ያስቀናዋል ወይም በላብኝ ይላል።
እውነተኛው ነገር በአፉ እየተናገረ ያለው ሳይሆን በልቡ
የተሰወረው ድብቅ ዐሳብ ነው። ይህ አስመሳይ ሰው እንደ
አሰበው ነው እንጂ እንደተናገረው አይደለም ማለቱ ነው።

በአጠቃላይ አንደበቱን ከማመንህ በፊት ባሕርይውን


ተመልከት፤ የሚያስበው እንደ ባሕርይው ነውና የሚል
መልዕክት ይዟል። ቀናተኛ ባሕርይ ካለው መልካም

431
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደማያስብልህ እወቅ፤ ይህንን ዘንግተህ እንጀራውን ከበላህ


ግን የበላኸውን እስክትተፋ ድረስ ትደርሳለህና አስብበት ማለቱ
ነው። እውነቱን ለመናገር ክፍሉ ስለ ቀናተኛ ወይም አስመሳይ
ሰው የሐሰት ግብዥ ድራማ ነው የሚያሣየን። በልቡ
የሚያስበውና በአንደበቱ የሚያስበው አንድ አለመሆኑን
በመግለጥ እንዲህ ዓይነቱ ማስመሰል ምን ያኽል የባልንጀራን
ልብ እንደሚጎዳ በማሣየት የማኅበረሰብ ሥነ-ልቦና ጥበቃ
ያደርጋል።

ይህን ግንዛቤ ችላ በማለት እንደ ኸርንስት ሆምስ የምሳሌን


መጽሐፍ ጥቅስ በማንሣት የወደቀ ፍልስፍና መደገፊያ
ማድረግ አለማወቅ ሣይሆን ዓመጽ ነው! ምክንያቱም የክፍሉ
ዐሳብ ለማንኛውም ቅን ልቦና ላለው ሰው በአዕምሮው ዐሳብ
ፍጻሜው እንደሚወሰን ወይም የዐሳብን ኀይል እንደማያሣይ
ግልጽ ነው። በተጭበረበረ መንገድ የመጀመሪያዋን ኀረግ በልቶ
በማውጣትና የራስን ማጭበርበሪያ ቃል በማከል ድምዳሜ
መስጠት አግባብ አይደለም።

ማይክ ተሰጥቶን ንግግር እያደረግን እያለን ድንገት አቋርጠውን


ያልተቋጨ ሐሳባችንን አንጠልጥለው ይዘውና የራሳቸውን
ጨምረው “እንዲህ ማለት ዐስቦ ነው” ብለው በሐሳባችን ላይ
ቢቀጥሉብንና ቢያብጠለጥሉን ምን ይሰማናል? እንደዚህ
እንዲሆን ማናችንም አንፈቅድም! በምሳሌ መጽሐፍ ላይ

432
ጆንሰን እጅጉ

የሚሠራው አሳዛኝ የመቆራረጥና የመቀጣጠል ወንጀል


ከዚህም የባሰ አስከፊ ነው። በአጠቃላይ ‘በልቡ እንዳሰበው
እንዲሁ ነው።’ የሚለው ኀረግ በምሳሌው ላይ የተጠቀሰውን
አንድ ሸንጋይ ሰው ባሕርይና ምግባር እንጂ የሰውን ልጅ ሁሉ
አዕምሮ የሚወክል በጭራሽ አይደለም።

ለጻድቁ መልካም ይሆንልሃል በሉት


ይህ ጥቅስ በኢሳያስ መጽሐፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን መልካም
እንዲሆንልን መልካም መናገር አለብን የሚለውን ዐስተሳሰብ
ለማራገብ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። በቅን ልብ ክፍሉን
ለመገንዘብ ከታሰበ ግን ዓረፍተ-ነገሩን ከላይ ተገንጥሎ ከቀረው
ዓረፍተ-ነገር ጋር አብሮ የሚታይ ነው። ሙሉ ዓረፍተ ነገሩ
“የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ጻድቁን መልካም ይሆንልኃል
በሉት።” የሚል ነው።(ኢሳ 3፡10) በጥቅሱ ላይ በግልጥ
እንደሚታየው “ና” የሚለው አያያዥ ቃል የ “ሥራቸውን” እና
ተከታዩን “መልካም ይሆንልሃል በሉት።” የሚለውን በማያያዝ
የሥራችውን ውጤት ወይም ፍሬ ለመጠቆም የገባ አያያዥ
ስለሆነ ሁለቱን ኀረጎች በፍፁም መነጠል አይቻልም።
በዓረፍተ-ነገሩ ውስጥ “ሥራቸው” ምክንያት ሲሆን “መልካም”
ደግሞ ውጤት ነው።

433
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጭሩ ለማስቀመጥ ነቢዩ “እና” የሚለውን አያያዥ


መስተፃምር የተጠቀመው ሁለቱን ዐሳብ ማለትም ምክንያትን
(ሥራ) እና ውጤትን (መልካም) አገናኝቶ ለማሳየት ነው።
ነቢያቱ ግምት ዐሳቢያን ሳይሆኑ የህጉ ነፀብራቅ ዐሳቢያን
ናቸው። የሕጉን መጽሐፍ ሥርው በማድረግ ከተወሰነላቸው
አጥር ሳይወጡ አሁንና ወደፊትን ይመለከታሉ። ስለዚህም
ኢሳያስ “መልካም ለሚያደርግ መልካም ይሆንለታል” የሚል
ዐሳብ ያለው መልዕክት ሲያንፀባርቅ መሠረት የሆነውን
የዘዳግምን ወይም የሕጉን መጽሐፍ ዐውድ እያሰበ ነው ማለት
እንችላለን። (ዘዳ.10፡12-13)።

ስለዚህም “መልካም እንዲሆንልህ መልካም ተናገር” የሚለውን


የልዩ ዲበ-አካል መላ ምት እየተከተለ እንዳልሆነ ከክፍሉ ዐሳብ
በመነሣት እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ለፃድቁ መልካም
የሚሆንለት ነቢዩ ስለተናገረለት ወይም “መልካም ይሆንልሃል”
እንዲሉት የተነገረላቸው የእስራኤል ልጆች ስለሚሉለት
ስለሚያውጁለት በፍፁም አይደለም። ነቢዩ እያለን ያለው
ለፃድቁ በመልካም ሥራው ምክንያት (መልካም)
እንደደሚሆንለት ነው። የእስራኤል ልጆች ሕጉን የመጠበቅ
ውጤት የሆነውን የምስራች ሰምቶ እንዲደሰትና ከጊዜው
መከራ እንዲፅናና፤ የሥራውን ውጤትም በትዕግሥት
እንዲጠብቅ እንዲነግሩት ነው የታዘዙት። የሕጉን ውጤት

434
ጆንሰን እጅጉ

በማመልከት ሕዝቡን ማበረታታትና ማጽናናት የነቢያቱ ቋሚ


ሥራ ወይም አገልግሎት እንደ ነበረ ቅዱሳት መጽሐፍት ሁሉ
ያመለክታሉ።

በአጠቃላይ “ለጻድቁ መልካም ይሆንልሃል በሉት” የሚለው


ቃል ሕጉን በመጠበቅ የሚገኘውን መልካም ነገር የሚጠቁም
ትንቢት እንጂ “የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” እንዳልሆነ እያወቅን ቃሉን
ካላግባብ በመጠቀም፤ የምንናገረው ኅሩይ ቃል ይሆናል በሚል
ምኞት ራሳችንን ሞልተን በመጮህ ስኬትን መፈለግ ተላላነት
ነው። ምናልባት በዚህ መንገድ ተጠቅመን የምንቆጥራቸው
ስኬቶች ቢኖሩ እንኳ የስኬታችን ምንጭ እንደነ ፊንሃስ
ኪዊምቢይ ሌላ መንፈስ እንጂ ቃሉ ወይም ቅዱስ
እግዚአብሔር እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል።

አንደበት እሳት ነው!


“አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መኻል ዓመጸኛ
ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፣ የፍጥረትንም ሩጫ
ያቃጥላል፣ በገሃነምም ይቃጠላል።” ያዕቆብ 3፡6

435
የአማልክቱ ዐዋጅ

የያዕቆብ መልዕክት “ቃል ማውጣት” የልዩ ጸሎት አካል


በመሆን ምን ያኽል ወደ ፊታችንን የመወሰን ዐቅም እንዳለው
ለማስረዳት እንደተጻፈ በስፋት ይታመናል። ለምሳሌ ያኽል
ክርስቲያን ሃርፉች ያዕቆብን በመጥቀስ የሰጡትን ትንታኔ
እንመልከት።

ያዕቆብ አንደበት የፍጥረትን ሩጫ ያቃጥላል ይላል


‘የፍጥረት ሩጫ’ የሕይወትን ጉዞ እንደ ማለት ነው።
ይሄ ጥቅስ አንዳዶቻችሁ ችግር ውስጥ ለምን
እንደወደቃችሁ ያስረዳል። አሁን ያላችሁበት ችግር
ባለፈው የሕይወት ዘመናችሁ ስለራሳችሁ
የተናገራችሁት ትንቢት (“የእምነት ቃል ንግግር”)
ውጤት ነው። 325

ሃርፉሮች እንደሌሎቹ “የእምነት ቃል አማልክት” ሁሉ


ከአንደበታችን የሚወጣ ማንኛውም ቃል ከመለኮታዊ ትንቢት
እኩል በህይወታችን ላይ የሚሆነውን በመወሰን እንደሚፀና
ወይም እንደሚገዛ በማመን ዐሉታዊ ንግግሮችን እንዳንናገር
እያስጠነቀቁን እንደሆነ ግልፅ ነው። ይሁን እንጂ እየነገሩን
ያሉት የልዩ ዲበ-አካሉ ፍልስፍና ያቀበላቸውን መላምት ነው
እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የነገራቸውን በፍፁም አይደለም።
መጋቢ አመሉም እንዲሁ “ክፉ ቃል በእኛና በእኛ ጉዳይ ላይ

325
Harfouche C. The Hidden Power. (1993, P.51).

436
ጆንሰን እጅጉ

ከተናገርን መርገም ሆኖ የህይወታችንን ፍፃሜ ማሰር


326
ይችላል።” እንዳሉ ልብ ይሏል። በምሳሌ አስረጅነት
በተጠሰው መጽሐፍ ክፍል ላይ ጥቂት ማሣያ ማንሣት በቂ
ስለሆነ እንጂ ይህንን የመሰለ ብዙ ምሣያ መጥቀስ ይቻላል።

ፕሮፌሰር ቶማስ ኒኮላስ (N.T Wright) የያዕቆብን መልዕክት


ከአስተማሪዎች የአንደበት ተጽዕኖ ጋር በማያያዝ
ይመለከቱታል፦ ኒኮላስ አሁን የመረጡትን የሕይወት አቅጣጫ
ለምን እንደመረጡ በመገረም ይጠይቃሉ። በመቀጠልም
ከልጅነታቸው ጀምሮ የተለያዪ አስተማሪዎች
እንዳጋጠሟቸው ያነሣሉ። እነኝህ አስተማሪዎች አንዳንዶቹ
መጥፎ አንዳንዶቹ መልካሞች ቢሆኑም ከመልካሞቹ
አስተማሪዎች መኻል ሁለት ወይም ሦስቱ እንደ ጓደኛ
በመቅረብ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዲረዱና
እንዲቋቋሙ እንዳበረታቷቸው ያትታሉ። ኒኮላስ በመቀጠል
አንዳዶቻችሁ በሰማችሁት አንድ ወይም ሁለት ዓረፍተ ነገር
አዲስ ዓለም ውስጥ ገብታችኋል በማለት ቃላት
የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ ያብራራሉ። በመቀጠልም ሁለት
ወይም ሶስት አስተማሪዎች እንዴት አድርገው ተጨባጭ
ተጽዕኖ አድርገውባችሁ ይሆን? ምናልባትም አሁን እየሄዳችሁ

326
መጋቢ አመሉ ጌታ ። ቅድመ ጋብቻ ጥበብ። (2008 ገጽ. 93)::

437
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያላችሁበትን የሕይወት አቅጣጫ አሲይዘዋችሁ ይሆናል


በማለት ግለ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።327

ይህንን እውነት የሚክድ ሰው ያለ አይመስለኝም። እኔም ራሴ


ለዚህ ምስክር ነኝ። ሃይማኖታዊ ወግን ጥዬ አቅጣጫ
የቀየርኩት በሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ጌታን በማገልገል
ትተጋ የነበረች እህት አልማዝ ደምሴ “ኢየሱስም በታላቅ
ድምጽ ጮሆ ነፍሱንም ሰጠ። የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከላይ
እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ።” (ማር.15፡37-38)። የሚለውን
ጥቅስ ስታነብልኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። ወዲያው ክርክሬን
ሁሉ ትቼ ነበር ለንስሓ የተንበረከኩት።

የተነበበልኝ ቃል ዐሉታዊ ንግግርም ይሁን ኅሩይ ቃል ዐዋጅ


የሚባል አልነበረም። ይሁን እንጂ የድነትን ግንዛቤ በልቤ
በመጫር ፍጻሜዬን ወስኖታል። ምክኒያቱም የሰማሁት ቃል
ንስሓ ለመግባትና ጌታን ለመከተል እንድወስን አድርጎኛል።
ይኸው በዚሁ መንገድ ላይ አቅጣጫዬን በመቀየር ከሃያ አራት
ዐመት በላይ ተጓዝኩኝ። በርግጥ የያዕቆብን መልዕክት
ስንመለከት አንደበት ከሚያስከትለው እንዲህ ዓይነቱ ልምላሜ
ይልቅ በአንፃራዊነት በሚያስከትለው ጥፋት ወይም ፍርድ ላይ
ትኩረቱን አድርጓል።

327
N.T. Wright. James. (2012, Pp, 129-131).

438
ጆንሰን እጅጉ

ያዕቆብ ምዕራፍ ሦስት ቍጥር አንድ ላይ መልዕክቱን ሲጀምር


“ወንድሞች ሆይ፦ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ
የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁና።” በማለት
ይጀምርና በመቀጠል የፍርዱ ምክንያት አንደበትን መግዛት
አለመቻል እንደሆነ በብዙ ማብራሪያ ያስረዳል። ያዕቆብ
በመልዕክቱ አንደበት ትንሽ አካል ቢሆንም ያለውን አቅጣጫ
የማስለወጥ ዐቅም በማጉላት እንደ መርከብ መሪ፣ እንደ
እሳትና እንደ ፈረስ ሉጓም ይመለከተዋል። አንደበት ሁለት
ማልያ ለብሶ ለሁለት ተቃራኒ ቡድን እንደሚጫወት ተጫዋች
በሁለት ተቃራኒ ተግባር ላይ ሊሳተፍ እንደሚችል
ለማስጠንቀቅ ደግሞ ከአንደበት የሚወጣ የበረከትና የርግማን
ንግግርን ያነሣል። በርግጥም አንደበት ተለዋዋጭ ሊሆን
ስለሚችል አስቸጋሪ አካል ነው። አስተውለን የተከታተልን
እንደሆን፤ አንድ ሰባኪ በአንድ መድረክ ላይ እርስ በርሱ
የሚቃረን ሁለት ነገር ሲናገር ልንሰማ እንችላለን።

በአጠቃላይ ያዕቆብ በዋናነት ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት


ማንኛውም ግብታዊ ንግግር ወይም ትምህርት አቅጣጫ
የሚመራ ግንዛቤ በመፍጠር የፍጥረትን ሩጫ መዳረሻ ገሃነም
ሊያደርግ እንደሚችል ነው። እራሱ አንደበትም ወይም ንግግር
በገሃነም ፍርድ እንደሚቀጣ በመመሰል አንደበትን መግዛት
ወይም መቆጣጠር ተገቢ ነው ይለናል። ያዕቆብ ለዚህ

439
የአማልክቱ ዐዋጅ

ትምህርቱ ሥርው ኢየሱስ ያስተማረውን ትምህርት


ለማድረጉ ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም ኢየሱስ
“ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ
ይሰጡበታል” እንዳለ እናውቃለንና ነው። (ማቴ.12፡36)።

የያዕቆብ መልዕክት መጽሐፍ ቅዱስን በዘፈቀደ ለምኞታቸው


ማስፈፀሚያ ለማድረግ በሁለት ማልያ ለሚታገሉና
ሌሎችንም በተሣሣተ ትርጉማቸው ለሚመሩ “አማልክት”
ጭምር፤ የአንደበትን አቅጣጫ የማሲያዝ ዐቅም፤
የሚያመጣውንም ፍርድ ስለሚጠቁም ጠቃሚና ጥልቅ ምክር
ይለግሳል። የማይገባና የተሣሣተ ትምህርት ማስተማር
ትውልድን በገሃነም አቅጣጫ እንደሚመራ ያስጠነቅቃል።
ይህንን አስፈሪ አደጋ ጆሮ ዳባ በማለት የእግዚአብሔርን ቃል
በማዛባት ለበረከተም ለርግማንም መትጋት ያሳዝናል። ይባስ
ብሎ ደግሞ ይህንኑ መጽሐፍ መልሶ በመጠቀም ማሣት ዐይን
ያወጣ ድፍረት ነው። ቅን ልቦና ካለንና እራሳችንን የቃሉ
አገልጋዮች እንደሆንን የምንቆጥር ከሆነ ግን አቅጣጫችን ወደ
ፍርድ እንዳይሆን ቆም ብለን ደጋግመን ልናስብና
አንደበታችንን በእውነት ልንገራ ይገባል።

ችግሩ እያለ

440
ጆንሰን እጅጉ

በሁለተኛ ነገስት ምዕራፍ አራት ላይ እጅግ ልብ የሚነካ


አስተማሪ ታሪክ እናገኛለን። ልጅን በነቢይ ጸሎት ያገኘች
ሱናማይት ሴት ድንገት ልጇን ሞት መልሶ ይነጥቃታል።
የመረረ ሐዘኗን ተሸክማ ወደ ነቢዩ ኤልሳ ትከንፋለች። ኤልሳ
በሩቅ ሲመለከታት አመጣጧ በሰላም እንዳልሆነ ቢጠራጠር
እንዲያጣራለት ሎሌውን ግያዝን ወደ እርሷ እንዲበር
ይልከዋል። ግያዝም በደረሰ ጊዜ “በደኸናሽ ነውን? ባልሽ ደኽና
ነውን? ልጅሽስ ደኽና ነውን?” በማለት የደህንነት ጥያቄ
ያቀርብላታል። ይሁን እንጂ ሴቲቱ ነገሯን መደበቅ
ትፈልጋለች። ለምን መደበቅ ፈለገች? ብለን እንጠይቅ።
ከመካከለኛው ምሥራቅ ባህል እንደምንረዳው ከሆነ አስከሬን
ቤት ውስጥ ሳይቀብሩ ጥሎ መሄድ ነውር ነው። እንዲህ
የሚያደርግ ሰው እንደ እብድ ይቆጠራል። ሴቲቱ ከዚህ ባህል
ውጪ ስላልሆነች ማህበራዊ ፍረጃን እንደፈራች መገመት
ይቻላል።

ስለዚህ መደበቅ በመፈለጓ ከባህሏ አንጻር ትክክል ናት።


በዚህም መሠረት ለጊያዝ እውነታውን በመካድ ሳይሆን
በመደበቅ “ደኽና ነው” በማለት መለሰችለት። ወደ ተራራውም
ወደ ኤልሳ ወጣች ልጅን ያገኘችው በነቢዩ ጥያቄና ልመና
ነበርና እግሩን ይዛ “በውኑ ከጌታዬ ልጅን ለመንሁን? እኔም
አታታልለኝ አላልሁህምን?” አለችው። በዚህን ጊዜ ነቢዩ

441
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሆነውን ነገር ከሚስጥራዊ አቀራረቧ በመረዳት ችግሯን


ለመፍታት ጊያዝን ብትሩን በብላቴናው ላይ እንዲያስቀምጥ
ላከው። ሴቲቱ ግን ኤልሳን “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው
ነፍስህም እምላለሁ! አልተውህም።” በማለት አብሯት
እንዲሄድ ግድ ትለዋለች። ከዚህም የተነሣ ኤልሳ ተነሥቶ
ተከተላት። እንደ ደረሰም የብላቴናውን አስከሬን በአልጋ ላይ
ተጋድሞ ያገኛል። በመጨረሻም ሰባት ጊዜ በብላቴናው ላይ
ተኝቶ ሲጸልይ ብላቴናው እንደነቃ ታሪኩ ያሣየናል።(2 ነገስ.4፡
26-35)።

ሴቲቱ ችግሩ እያለ ‘ደኽና ነው’ ለምን አለች? አስከሬን ጥሎ


መሄድ ነውር እንደሆነ ስለምታውቅ? ወይም ከግያዝ ጋር ጉዳይ
ስሌላትና ልትነግረው ስላልፈለገች? ወይስ ኅሩይ ቃል ዐዋጅ
ተግባራዊ እያደረገች? ኤልሳስ አብሯት ለመሄድ የወረደው
የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ንግግሯን ስለሰማ ነው? ወይንስ “አታታለኝ
አላልኩህምን?” በማለት ስለወቀሰችውና አብሯት እንዲሄድ
ግድ ስላለችው? የልጇስ ከሞት መነሳት የእምነቷ ውጤት
አሊያም የኤልሳ ጸሎት ነውን? ወይስ የሴቲቱ የቃል ዐዋጅ?
አንዳንዶች እንደሚሉት ነቢዩ ኤልሳስ ሴቲቱን የልጇን መሞት
በመካድና በፋንታው መልካም መናገር ከቀጠለች ልጇ
እንደሚነሳ ነግሯት ነበር? እንዲህ አስባ ነበር ለማለት የዐሳቧን
መነሻ ትምህርት ማቅረብ የምንችልበት ምንጭ አለን?

442
ጆንሰን እጅጉ

በእርግጥ ሴቲቱ ጉዳዩዋን መሉ ለሙሉ ከነቢዩ ጋር ያደረገች


እና ልመናዋን ወይም ጸሎቷን ወደ ነቢዩ እያደረገች እንደሆነ
ጠቋሚ ዓረፍተ ነገር እናገኛልን። በፋንታው ደግሞ ወደ
መለኮት ስትጸልይና የሙጥኝ ስትል አትታይም።328 ሴቲቱ
ከጊያዝ ጋር የነበራትን የቃላት ልውውጥ ስንመለከትም
ለጊያዝ ጥያቄ መልስ እየሰጠች እንጂ የኅሩይ ቃል ዐዋጅ
እያወጀች አልነበረም። የኅሩይ ቃልን ጉልበት ለመጠቀም
እያሰበች ቢሆን በሯን ዘግታ ማወጅ እንጂ ወደ ኤልሳ መሮጥ
ባላስፈለጋት ነበር። ስለዚህ የአዋጅ ቃል ትምህርትም ይሁን
ዐሳብ ነበራት ማለት ስለማንችል እያወጀች ነው ማለትም
አንችልም።

ከአዋጅ ቃል በተቃራኒ “አታታልለኝ አላልኩህም?” የሚለው


ንግግሯም የልጇን ሞት የሚያረዳ ዐሉታዊ ንግግር የያዘ ቃለ
ወይራ ዘይቤ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ “ችግሩ እያለ ኅሩይ ቃል
ዐውጁ” በማለት እንደሚያጯጩሁን “የአማልክቱ” ባለሟሎች
ዕይታ ከሆነ ይህቺ ሴት ይህ ንግግሯ ዐሉታዊ ስለሆነ ቀድሞ
‘ደህና ነው’ በማለት የተናገረችውን መልካም ንግግር
አፋርሳለችና ልጇ ሊነሣላት አይገባም። ባጠቃላይ ሴቲቱ
የልጇን ሞት ለማርዳት የምትኖርበትን ህብረተሰብ ባህል እንጂ
ሞተ የሚለውን ቃል መናገር አልፈራችም ወይም ያለችበትን
328
ወደ ነቢያት የሚደረግ ጸሎትን በተመለከተ በምዕራፍ አምስት ላይ ”ጸሎት
ያልገባው“ በሚል ርዕስ የቀረበውን ዐሳብ ልብ ይሏል።

443
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሁኔታ አልካደችም። ‘በደህና ነውን’ ለሚለው ለሎሌው ጥያቄ


የሰጠችውም ‘ደህና ነው’ የሚለው መልስ ልትነግረው
ስላልፈለገች ነው እንጂ ችግሩ እያለ መልካም ማወጅ
ስለፈለገች አልነበረም። ይህንን ደግሞ የግል መብቷ ስለሆነ
ልናከብርላት ይገባል።

ለኤልሳም ‘አታታልለኝ አላልኩህምን’ የሚል መልስ መስጠቷ


ልጅ የማግኘቷንና ሞቱን በማያያዝ ኤልሳ ኀላፊነት
እንዲወስድ የተጠቀመችበት ጥበብ ነው። ልጇ ከሞት
የተነሣላትም ኤልሳ ሙሉ ኀላፊነት ስለወሰደና ወደ
እግዚአብሔር ስለጸለየ ነው እንጂ ‘ደህና ነው’ የሚል ቃል
ስላወጀች አልነበረም። ምናልባት ከዚህ እውነት አልፈን ታሪኩ
የዐዋጅ ቃልን ልዩ ጸሎት የሚጠቁም እንደሆነ ብንጠራጠር
እንኳ የሕጉን መጽሐፍ ባግባቡ ያልተማረችና በእስራኤል ባህል
ውስጥ ያላደገች የዚህችን ሴት ልምምድ መርሖ ማድረግ
አንችልም። ስለዚህም ‘ደህና ነው’ የሚለው ቃል ስላማረን
ወይም የኅሩይ ቃል ዐዋጅ እንደሆነ በማሰብ ብቻ “ሁሉ ሰላም
ነው” የሚል የዝማሬ ሥንኝ በመደርደር ቅጥ ባጣ ፉጨት
ሕዝብ ማደናቆር በፍጹም አግባብ አይደለም።

444
ጆንሰን እጅጉ

በገባዖን ላይ ፀሓይ ትቁም


“በገባዖን ላይ ፀሓይ ትቁም፣ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ።”
(ኢያሱ 10፡12)።

ይህንን ቃል የተናገረው ኢያሱ ነው። ጥቅሱ የእምነት ቃል


ጉልበትን ጣራ ለማስረዳት ከሚውሉ ታዋቂ ጥቅሶች አንዱ
ነው። እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት
ቀን “ይሁን” በማለት ወይም በተፈጥሮ ውስጥ ያለውን የቃል
ኀይል በመጠቀም እንደፈጠረ በመልኩ የተፈጠረ የሰው ልጅም
በአንደበቱ ቃል እንዲሁ ማድረግ ይችላል የሚለውን ለማጽናት
ይህ ታሪክ ይነሳል። በእርግጥም የኢያሱን ንግግር ተከትሎ
ፀሓይ ቆማለች። “ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ
ፀሓይ ቆመ፣ ጨረቃም ዘገየ። አንድ ቀንም ሙሉ ለመግባት
አልቸኮለም።” (ኢያሱ 10፡13) ።

በቀላልና ግልብ ንባብ ክፍሉን የተመልከትን እንደሆን፤


ካለመለኮት ጣልቃ ገብነት ወይም በኢያሱ የእምነት ቃል
ማስገደድ ኢያሱ እንደተናገረ ሆነ ወደሚል ድምዳሜ ውስጥ
ፈጥነን ልንገባ እንችል ይሆናል። ነገር ግን አውዳዊ ጥናት

445
የአማልክቱ ዐዋጅ

ልንከተል እንጂ እንዲህ ልናደርግ አይገባም። የክፍሉን ታሪክ


ስንመረምር በመጀመሪያ ጦርነቱ በዋናነት የኢያሱ ሳይሆን
የመለኮት ሆኖ ነው የምናገኘው። “ከእስራኤል ልጆች ፊት
እየሸሹ በቤትሖሮን ቁልቁለት ሲወርዱ፣ ወደ ዓዜቃ
እስኪደርሱ ድረስ እግዚአብሔር ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ
ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ። የእስራኤል ልጆች በሰይፍ
ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።” (ኢያሱ
10፡11)።

ኢያሱ በዚህ ጦርነት ውስጥ ሁለተኛ ባለድርሻ ነው። ስለዚህም


በጦርነቱ ውስጥ የመለኮት ሙሉ ድርሻና ፈቃድ እንደ ነበረ
ለመረዳት አያዳግትም። “እግዚአብሔርም ለእስራኤል ይዋጋ
ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን
ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።” (ኢያሱ 10፡14)።
እግዚአብሔር ኢያሱን የመስማቱ ምሥጢር እራሱ
እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ስለነበርና ኢያሱ ይህንን
የመለኮት አጀንዳ ለማስፈፀም ስለተሰለፈና ስለጸለየ እንደሆን
ልብ ይሏል።

በሁለተኛ ደረጃ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ ኢያሱ ወደ


እግዚአብሔር በቀጥታ ጸለየ ወይስ ለፀሓይና ለጨረቃ በቀጥታ
ተናገረ የሚለው ነው። ኢያሱ በነበረበት ዘመን ያለው ንፅረተ
ዓለም ግንዛቤ ፀሓይ እንደምትጓዝ ስለነበረ በንግግሩ ውስጥ

446
ጆንሰን እጅጉ

ሲንፀባረቅ የምናየው የፀሓይና የጨረቃን መቆም ጥያቄ ነው።


በዚህም ኢያሱ በቀጥታ ለፀሓይ ተናግሮ ቢሆን ምድር እንዴት
ሰምታ በዛቢያዋ ላይ ቆመች ፀሓይስ በኢያሱ ላይ አትስቅም
ወይ በማለት የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን አንባቢ መጠየቅ
ይገባዋል። የኢያሱን ጸሎት የመለሰ የምድር መስማት ወይም
የተፈጥሮ ሕግ አልነበረም። የኢያሱን ጸሎት የመለሰ የኢያሱን
ደካማ ንፅረተ ዓለም ንግግር ሳይሆን የልቡን ፋላጎት ወይም
ጥያቄ ያነበበ ሕያው አምላክ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር
የለውም።

በመጨረሻ “ኢያሱ ፀሓይና ጨረቃን እንደ አዘዘ ነገሮቻችሁ


ላይ ቃል አውጡ! በእምነት የምትፈልጓቸውን ነገሮች እዘዙ!”
በማለት ሕዝብን ለልዩ ጸሎት ማነሳሳት አግባብ እንዳልሆነ
ማወቅ አለብን። ይህንን አልቀበል ካልን ግን ኢያሱ የመለኮትን
ፈቃድ በመገንዘብ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት ወይም
ልመናን እንዳደረገ የሚያሳዮንን ግልፅ ቃላት የት
እንደብቃቸዋለን? “ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ:
በእስራኤልም ፊት እንዲህ አለ፦ በገባዖን ላይ ፀሓይ ትቁም፣
በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ።” (10፡12)። ጸሓፊው በቀጣዩ
ቍጥር ላይ ደግሞ ኢያሱ ለእግዚአብሔር መናገሩን ብቻ
ሳይሆን እግዚአብሔርም ኢያሱን መስማቱን በግልፅ

447
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያመለክተናል “እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ


ያለ ቀን አልነበረም።” (ኢያሱ 10፡14)።

እንግዲህ የመጽሐፉ ጸሓፊ በቀጥታ ከዘገበው እውነት ወጥቶ


በራስ መንገድ ለማብራራት መሞከር እውነትን ማጣመም
ነው። ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን ከጸሓፊው ስልጣን በላይ
በጹሑፉ ላይ ስልጣን እንዳለን በትዕቢት ለማሳየት መሞከርም
ጭምር ነው። ምክንያቱም ኢያሱ የተናገረው ለፀሓይና
ለጨረቃ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ስለነበር ጸሎቱን ሰምቶ
የመለሰለት እግዚአብሔር እንደ ነበር ክፍሉ አይደብቅም።

ቃል ተናገር ብላቴናዬም ይፈወሳል


የቃል የማውጣት ልምምድ ሥነ-መለኮት መሠረት ሆኖ
የሚጠቀሰው አንዱ በሉቃስ ወንጌል ላይ የሚገኘው መቶ
አለቃ ባሪያው እንዲፈወስለት ኢየሱስን የለመነበት “ቃል
ተናገር” የሚለው ዓረፍተ ነገር ነው። ይህንን የንግግር
ልውውጥ ለመመርመር በቀዳሚነት መገንዘብ የሚገባን ክፍሉ
አንድ በእስራኤል ምድር የተፈፀመ ታሪክ እየተረከልን እንደሆነ
እንጂ መሠረታዊ ትምህርት (ዶክትሪን) እያስተላለፈ
እንዳልሆነ ነው። የታሪክ ትረካ ዋናው ዐላማ የታሪኩን ጭብጥ
ማሳየት ነው። ከታሪኩ ጋር በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተያያዥነት
ያላቸው ነገሮች ወይንም ንግግሮች ሁሉ ትክክል ይሁኑም

448
ጆንሰን እጅጉ

አይሁኑ ሊነሱ ይችላሉ። የጸሓፊው ትኩረት እስካልሆኑ ድረስ


ደግሞ ምንም ዐይነት የድጋፍም ይሁን የተቃውሞ አስተያየት
ሳይሰጥባቸው በክፍሉ ላይ ተጠቅሰው ልናገኛቸው
እንችላለን።

በዋናው የትረካ ታሪክ ላይ በእግረ-መንገድ የገቡትን ነገሮች


ወይም ንግግሮች ትክክለኝነት የምናረጋግጠው በሌላ ቦታ
ነገሩን ሊያስረግጡ ወይም ሊያሳዩን የሚችሉ ትምህርቶች
ያሉ እንደሆን ብቻ ነው። ይህን ሳናደርግ በትረካ ውስጥ
የተባለውን ሁሉ ቆነጣጥሮ የስብከት ማጣፈጫ አሊያም
የትምህርት ሥርው ማድረግ ጸያፍ ነው። ለምሣሌ
በተጠቀሰው የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ሰባት ታሪክ ላይ ዋናውና
የመጀመሪያው ጭብጥ ብላቴናውን ኢየሱስ መፈወሱ ነው።
ሁለተኛው ጭብጥ ደግሞ ኢየሱስም ስለ መቶ አለቃው
እምነት የተናገረው ነው።መቶ አለቃው ኢየሱስን ለማግባባት
የተጠቀመበት መንገድ ግን በታሪኩ ጭብጥ ላይ ቡዙ ቦታ
የሚሰጠውና ለትምህርት መሠረትነት የማይበቃ ነው።

መቶ አለቃው ኢየሱስን ሲለምነው “ስለዚህም ወደ አንተ


ልመጣ እንዲገባኝ ሰውነቴን አልቈጠርሁትም፤ ነገር ግን ቃል
ተናገር፣ ብላቴናዬም ይፈወሳል።” ይለዋል።(ሉቃ 7፣7)።
በመቀጠልም የመቶ አለቃው እምነት አመክኖያዊ ሥርው
ወታደራዊ ልምምዱ እንደሆነ ያስረዳል፤ ቍጥር ስምንት “እኔ

449
የአማልክቱ ዐዋጅ

ደግሞ ከሌሎች በታች የምገዛ ሰው ነኝ፣ ከእኔም በታች


ወታደሮች አሉኝ፣ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፣
ሌላውንም፦ ና ብለው ይመጣል፣ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ
ብለው ያደርጋል።” ይህንን ተከትሎ በቍጥር ዘጠኝ ላይ
እንደተገለጠው ኢየሱስ አንድ መልካም ነገር ተመለከተና
ተደነቀ፤ ይህም መቶ አለቃው የእግዚአብሔር ቃል ካላቸው
ከእስራኤል ልጆች ይልቅ በተሻለ ሁኔታ በወታደራዊ ልምዱ
ላይ ብቻ በመመሥረት ኢየሱስ በሽታን መፈወስ የሚችል
ስልጣን እንዳለው ማመኑ ነበር።

መቶ አለቃው በንግግሩ ውስጥ የኢየሱስን የማድረግ ስልጣን


እንደ አመነ ኢየሱስ “በእስራኤል እንኳ እንደዚህ ዐይነት
እምነት አላገኘሁም።” በማለት መሰከረለት። ከዚህ በኋላ
በቍጥር ዘጠኝ ላይ የኢየሱስን መደነቅ ተከትሎ ኢየሱስ
የተጠየቀውን “ቃል” እንደተናገረ ወይም እንደ ዐወጀ ሳይነግረን
ብላቴናው እንደ ተፈወሰ ይተርካል። ይህም ኢየሱስ የመቶ
አለቃውን ከወታደራዊ ግብረገብ መነሻ ያደረገ ትምህርት ችላ
እንዳለው ወይም ዋናው የትኩረት ነጥብ የመቶ አለቀው
ንግግር ላይ የተመሠረተ ሳይሆን መቶ አለቃው ኢየሱስ ላይ
ያለው እምነት ላይ ያረፈ ነበር። ማለትም ኢየሱስ ልጁን
ሊፈውስለት እንደሚችል ማመኑ ላይና የኢየሱስ ብላቴናውን
መፈወስ መቻል ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያረጋግጣል።

450
ጆንሰን እጅጉ

ሉቃስም ይሁን ኢየሱስ የመቶ አለቃውን “ቃል ተናገር”


የሚለውን ንግገር ሲያርሙ ወይም ሲያጸድቁ
አለመመልከታችንም እንዲሁ በታሪኩ ውስጥ ትኩረት
የተሰጠው የመቶ አለቃው እምነትና የኢየሱስ የመፈወስ
ስልጣን እንደነበር ያሣያል።

በተመሳሳይ ታሪክ ማቴዎስ 8፡13 “ኢየሱስም ለመቶ


አለቃው፦ ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ” በማለት እንደመለሰለት
ይነግረናል። በመቀጠልም “ብላቴናውም በዚያች ሰዓት
ተፈወሰ።” በማለት የተከሰተውን ቅፅፈታዊ ፈውስ ይተርካል።
የኢየሱስ ንግግር እንደሚያሳየን ምላሹ በቀጥታ ወደ
ብላቴናው የሚጠቁምና የቃልን ኀይል የሚያሳይ አይደለም።
ማለትም ዛሬ ላይ አማልክቱ ፈውስን በዐዋጅ ቃል ለማደል
ሲተጉ እንደምንመለከተው “ደህና ነው!” ወይም “ደህና ሁን!”
“አይሞትም” . . . ወዘተ የሚል ዐዋጅ ሣይሆን የኢየሱስን
ዐዎንታዊ ፈቃድና መልስ ያዘለ ምላሽ ነበር። የኢየሱስ ንግግር
ለመቶ አለቃው የእምነት ጥያቄ በቀጥታ የተሰጠ መልስ
ወይም የተግባቦት (communicational conversation) ንግግር
ነው ማለት እንችላለን።

ከዚህ ሁሉ በላይ መስተዋል ያለበት ከላይ እንደተብራራው


ኢየሱስ የመቶ አለቃውን ንግግር ትክክለኝነት በመጠቆም
ትምህርት አልለመመሥረቱ ነው። አስቀድመን እንዳነሣን

451
የአማልክቱ ዐዋጅ

ኢየሱስ ያደነቀው የእርሱን (የኢየሱስን) የማድረግ ስልጣን


ባለቤትነት ያረጋገጠውን የመቶ አለቃውን እምነት ነው።
የአንድ አህዛብ መቶ አለቃ በታሪክ ውስጥ የተጠቀሰ ንግግር
በታሪኩ ውስጥ ያለውን ድርሻ ሳናስተውል የትምህርት
መሠረት አድርገን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ቃል አውጣ”
በሚል ጥያቄዎቻችንን ደረታችን ላይ ለጥፈን ስልጣን
አላቸው ብለን በምናስባቸው “ባለራዕይዎች” ደጅ ሁሉ
ልንሰለፍ አይገባም። ከዚህ ይልቅ ከክፍሉ ጭብጥ ተነስተን
ኢየሱስ በሽታን የመፈወስ ስልጣን እንዳለው ማመን ይገባል
የሚል መርሖ መያዝ አግባብ እንደሆነ አምናለሁ።

በሌላ በኩል ከመቶ አለቃው ወታደራዊ ልምድ ንግግር ይልቅ


ላቅ ባለ መልኩ “ቃል መናገር” በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ሥራ
ላይ ውሏል። ሥራ ላይ የዋለበትን ዐውድ የተመለከትን
እንደሆን ብዙውን ጊዜ ከዐዋጅ ቃል ጋር አቻ ትርጉም ይዞ
እናገኛለን። ይህም መተንበይ ወይም መልዕክት ማስተላለፍ
ወይም መስበክ እንደማለት ነው። ለምሳሌ ያኽል
የኤርሚያስን ልምምድ መመልከት እንችላለን። በአንድ ወቅት
እግዚአብሔር ኤርሚያስን በቀጥታ “ቃል ተናገር” ብሎ አዝዞት
ነበር።

በካርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም


ልጅ ሸለቆ ሂድ፣ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር፣

452
ጆንሰን እጅጉ

እንዲህም በል፦ የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም


የምትኖሩ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፦ የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው
የሚያደርግ ክፉ ነገር፣ እነሆ፣ በዚህ ስፍራ
አመጣለሁ። (ኤር.19፡2-3)።

በዚህ ክፍል በግልጽ እንደምናየው በመጀመሪያ ነቢዩ


የሚናገረው ዛሬ ላይ እንደምንመለከተው “የቃል ማውጣት”
የልዩ ጸሎት ልምምድ ለመናገር የወደደውንና የፈለገውን
ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሰማውን ነው። በሁለተኛ ደረጃ ነቢዩ
የሚናገረው ለወደደውና ለፈለገው ወይም በፈለገው ቦታና
ሰዓት ሳይሆን ለማን እንደሚናገርና የትቦታ እንደሚናግር
በተወሰነለት ሥርው ብቻ ነው።

በመጨረሻ ነቢዩ እንዲናገር የታዘዘው በራሱ ምርጫ ወይም


ኅሩይ ዐሉታዊ ንግግር አልነበረም። በአጠቃላይ ከመጽሐፍ
ቅዱስ ጠቅሰንም ቢሆን የምንናገረው ቃል ወደ ክስተት
የሚለወጠው እኛ ስለተናገርን ሳይሆን አስቀድሞ በመለኮት
ለዚያ ጊዜና ቦታ የተወሰነና የታቀደ እንደሆን ብቻ ነው።
የነቢዩ ቃል መናገር፣ መስበክ፣ ማወጅ ወይም ማሳወቅ
በመለኮት ቁጥጥር ውስጥ የሚሠራ ነው። ስለዚህ የሚሆነው
ክስተት ወይም ድርጊት ባለቤት ነቢዩ ወይም የነቢዩ አንደበት

453
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሳይሆን በበላይነት እየተቆጣጠረ ያለው መለኮት እንደሆነ


ማስተዋል ይገባል።

ከላይ ካየነው ጥቅስ ወረድ ብሎ “የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው


የሚያደርግ ክፉ ነገር፣ እነሆ፣ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ” ይላል።
ይህም ቀጣይ ዓረፍ-ተነገር መለኮት የክስተቱን ባለቤትነት
ለነቢዩ አንደበት አስረክቦ እንደተቀመጠ አያሳይም። ይልቁንም
ትንቢቱ ከተነገረ በኋላ እንኳ የፍጻሜው ክስተት በመለኮት እጅ
እንደሆነ ነው የሚያሳየን፤ ምክንያቱም “አመጣለሁ” በማለት
መለኮት ሙሉ ኀላፊነትን ይወስዳልና ነው። ስለዚህም ነቢያቱ
ቃልን በተደጋጋሚ በማወጅ የትንቢቱ ፈጸሚ ወኪል ሳይሆኑ
ትንቢቱን አስተላላፊ ብቻ ናቸው። ፈፃሚው መለኮት እራሱ
ነው። ስለዚህ ማንም ቢሆን ጥቅስን ደጋግሞ በመናገርም እንኳ
ቢሆን (ቃል በማውጣት) ትንቢት የማስፈፀም ኀላፊነት
ሰለሌለው ልንታለል አይገባም።

ነቢዩ ኤርሚያስ ትንቢት የተናገረው መለኮት ካለ ቃል


ስለማይሠራ ሳይሆን ወደፊት ሊሆን ያለው ነገር ለምን
እንደሚሆንና ማን እንደሚያደርገው ለሕዝቡ ለማሳወቅ
ስለተፈለገ ነው። ቍጥር አራት “ትተውኛልና፣ ይህንም ስፍራ
እንግዳ አድርገውታልና፣ እነርሱና አባቶቻቸውም
ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት አጥነዋልና የይሁዳም
ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋልና።” በማለት

454
ጆንሰን እጅጉ

የሚሆነው ክፉ ነገር የሚሆንበትን ምክንያት በማስረዳት


የሚሆነው ነገር ኀላፊነቱ የራሳቸው የሕዝቡ እንደሆን
ያሳያቸዋል።

በአጠቃላይ ቃል ማወጅ ወይም ቃል መናገር በዕብራዊያንም


ይሁን በጥንት ህዝቦች ትርጉም መስበክ፣ ትንቢት መናገር፣
መልዕክት ማስተላለፍ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን አራት
አካላትም ይኖረዋል።
 አንደኛ የዐዋጁ ባለቤት ወይም መልዕክቱን ያስተላለፈው
ባለስልጣን (ጌታ ወይም አምላክ) ።
 ሁለተኛ ራሱ የዐዋጁ ቃል (መልዕክት)።
 ሦስተኛ ዐዋጅ ነጋሪው (መልዕክተኛ)።
 አራተኛ ዐዋጅ ተቀባይ አካል ማለትም የሚሰማ ጆሮ
ያላቸው ምላሽ የሚሰጡ ጉዑዛን ያልሆኑ ተደራሲያን
ናቸው።

በአጠቃላይ በዕብራዊያን “ቃል ማውጣት” ፅንሰ-ዐሳብ የቃል


ሕግ ቦታ የለውም። በመሆኑም የልዩ ዲበ-አካሉ “ቃል
ማውጣት” ጽንሰ-ዐሳብ ከአእብራዊያኑ ዐስተሳሰብ እጅግ ዕሩቅ
ነው። በዚህም ምክንያት የልዩ ዲበ-አካሉን ጽንሰ-ዐሳብ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አድርጎ ለማቅረብ የዕብራዊያኑ አጠቃቀም
አያመችም። እንደ ዕብራዊያኑ ልምምድ ከሆነ ትንቢት
የሚናገር ነቢይ እንኳ ቢሆን የአስፈፃሚነት ድርሻን

455
የአማልክቱ ዐዋጅ

አይወስድም። የመቶ አለቃውን ንግግርም ያየን እንደሆነም


እርሱ እራሱ በወታደሮቹ ላይ ያለውን ስልጣን በማንሳት
ኢየሱስ በበሽታ ላይ ያለውን ስልጣን የሚያጎላ ነው።
በአጠቃላይ ከመቶ አለቃው ንግግር እንደምንረዳው “ቃል
አውጣ” የሚለው ጥያቄ የኢየሱስን ስልጣን እንጂ የቃል
ኀይልን የአስፈጻሚነት ድርሻ ለማሣየት የዋለ አይደለም።
መቶ አለቃው የቃል ኀይልን በሚያሳይ መልኩ ተጠቅሞ ቢሆን
እኳን በኢየሱስ ምንም ዐይነት የማረጋገጫ መግለጫ ወይም
ትምህርት ስላልተሰጠበት መቶ አለቃው ልክ ነበር ማለት
አንችልም።

እንደ እንጀራ ይሆኑልናል


“የእምነት ቃል ዐዋጅ ልዩ ጸሎት” ምሳሌ ተደርጎ ብዙ ጊዜ
“በአማልክቱ” የሚጠቀሰው በዘኁልቁ መጽሐፍ ላይ የሚገኘው
ከአስሩ ሰላዮች፣ ከኢያሱ፣ ካሌብና ከሕዝቡ ጋር የተያያዘው
ታሪክ ነው። ፓስተር ክርስቲያን ሃርፉሮች እንዲህ ይላሉ፦

የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ ምድር ያልገቡትና


በምድረበዳ የቀሩት እኮ የተሳሳተ ነገር መናገር
ስለመረጡ ነው። ሁል ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል
ይገምቱ ነበር። ከዚህ በኋላ ጥሩ ነገር እንደማይሆን

456
ጆንሰን እጅጉ

እገምታለሁ ካላችሁ እራሳችሁ በፈጠራችሁት እሳት


ህይወታችሁን እያቃጠላችሁት ነው። 329

ፓስተሩ ቀደም ብለን ከተመለከትነው (ከያዕ.3፡6) ጋር


የዘኁልቁን ታሪክ እያገናዘቡ ለመፍታት እየሞከሩ እንደሆነ
የተጠቀሙበት ቃል ይጠቁማሉ። ነገር ግን እውነቱን አውዳዊ
አፈታትን በመከተል በመጠኑ ለመረዳት እንሞክር።
በመጀመሪያ በታሪኩ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰውን
የሁለቱን ሰላዮች ዐዎንታዊ ንግግር እናነሣለን “ነገር ግን
በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና
የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፣ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፣
እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው አትፍሩአቸው ብለው
ተናገሩ።” ዘኁ 14፣9። ካሌብና ኢያሱ ይህንን የሚሉት ሙሴ
ወደ ከንዓን ገብተው እንዲሰልሉ በላካቸው መሠረት ሰልለው
ከተመለሱና የአስሩን ሰላዮች አስደንጋጭ ዐሉታዊ ንግግር
ካደመጡ በኋላ ነው።

አስሩ ሰላዮች ያዩትን ፈታኝና አስቸጋሪ ነገር ለሕዝቡ እንዲህ


በማለት ተናግረው ነበር። “ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች
ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም የጸኑ
ናቸው፤ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን።” (ዘሁ.13፡28)
። ሰዎቹ የተናገሩት እውነትና ምንም እክል የሌለው ነው።
329
Christian Harfouche. The hiden power of your words, (1993, P.51).

457
የአማልክቱ ዐዋጅ

የተላኩትም ይህንኑ በምድሪቱ ላይ ያዮትን እንዲናገሩ ነው።


ስሕተት የሰሩት ከተመለከቱት ነገር ተነስተው “በኀይል ከእኛ
ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም።” (ዘሁ.13፡
31) በማለት የራሳቸውን መደምደሚያና አስተያየት ለሕዝቡ
በመናገራቸውና ሕዝቡ እንዲፈራና እንዲደነግጥ በመጨረሻም
በአምላኩ ላይ ያለውን ድፍረትና ተስፋ እንዲጥል
በማድረጋቸው ነው። ጸሓፊው የራሱን አስተያየት አክሎ
ሲያጠቃልል፦

ስለ ሰለሉት ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች


እያወሩ፦ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን
ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ
ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው።
በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፣
የዔናቅን ልጆች፣ አየን፣ እኛም በዓይናችን ግምት
እንደ አንበጣዎች ነበርን፣ ደግሞም እኛ በዓይናቸው
ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ።” ይላል። (ዘሁ.13፡32-
33)።

አንዳዶች እንደሚሉት የእነኚህ ዕብራዊያን መሠረታዊ ችግር


“የእምነት ቃል” አለማወጃቸው ሳይሆን ታላቁን
እግዚያአብሔርንና ገናና ኀይሉን መርሳታቸውና በአምላካቸው
ላይ ሙሉ ለሙሉ እምነት ማጣታቸው ነው። ከዚህም

458
ጆንሰን እጅጉ

የሚብሰው ደግሞ ይህንኑ ስኹት ትምህርት (ወሬ) ለሕዝቡ


ማስተማራቸው ነው። በተጨማሪም ይህ ክፍል በአዲስም
ይሁን በብሉይ መጽሐፍት በተደጋጋሚ እንደሚነሳ
እናውቃለን። ይሁን እንጂ አንድም የብሉይ ኪዳን ወይም
የአዲስ ኪዳን ጸሓፊ የእምነት ቃል የማወጅ ችግር
እንደነበረባቸው አንስቶ አይከሳቸውም። ለምሳሌ የዕብራዊያን
ጸሓፊ የሚያነሳው ያለማመናቸውን ነው እንጂ ቃል የማወጅ
ችግር እንደነበረባቸው አይደለም። “ባለማመናቸው ጠንቅ
ሊገቡ እንዳልቻሉ እናያለን።” (ዕብ.3፡19)።

ኢያሱና ካሌብ ግን በተለየ ሁኔታ የአስሩን ሰላዮች ማጠቃለያ


በመቃወም “የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፣ ጥላቸው ከላያቸው
ተገፍፎአል፣ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው አትፍሩአቸው።”
በማለት የአስሩን ሰላዮች አስተያየት እየሞገቱ ይከራከራሉ።
በርግጥም በስለላ ተልዕኮአቸው ወቅት የተመለከቱትን እውነት
እየካዱ ሳይሆን ከመለኮት ውጥንና ዐቅም ጋር እያነፃፀሩ ነበር።
እግዚአብሔርም ይህንን አቋማቸውን ከተመለከተ በኋላ
ሀልዎቱን ከእነሱ ጋር እንደሚያደርግና ድል እንደሚሰጣቸው
ቃል ገብቶላቸዋል።

በአጠቃላይ ይህንን ታሪክ ወስዶ የቃል ዐዋጅ ልዩ ጸሎት ምሳሌ


አድርጎ ለማቅረብ በፍፁም የማይቻል ነው። የኢያሱና የካሌብ
ንግግር ለእምነት ዐዋጅ ልዩ ጸሎት ምሳሌ የማይሆንበት

459
የአማልክቱ ዐዋጅ

ምክንያት፦ አንደኛ የኢያሱና የካሌብ ንግግር ጸሎት ሳይሆን


ሕዝቡን ወደ ትክክለኛ ግንዛቤ የሚመልስ ስብከት በመሆኑ
ነው።330 ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ እንደፈራ ስለተመለከቱ
ሕዝቡ እምነቱን በእግዚአብሔር ላይ እንዲያደርግ
ለማበረታታት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ኢያሱና ካሌብ
ይህንን ያሉት “የኅሩይ ቃል ዐዋጅን” ኀይል በመረዳት
ለመጠቀም አስበው አልነበረም። ኢያሱና ካሌብ ይህንን
ያደረጉት በእግዚአብሔርና በሰጣቸው የማይሻር የፍቅሩ ኪዳን
ላይ ያላቸውን መታመን ለሕዝቡ ለማሳየትና ምሳሌ በመሆን
ሕዝቡን ለመመለስ ነው። ይህንንም ሲናገሩ፦ “እግዚአብሔር
ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር
ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል።” (ዘኁ.14፡8)። እንደ እነሱ
ከሆነ ወደ ከንዓን የመግባታቸው ምሥጢር እነርሱ የተናገሩት
የእምነት ቃል ኀይል ሳይሆን መለኮት ለነርሱ ያለው ፍቅርና
የመቻል አቅሙ ነው።

የእግዚአብሔር የቅሬታ ንግግር ይህንኑ በበለጠ ያስገነዝበናል


“እግዚአብሔርም ሙሴን ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል?
በፊቱስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያአምን
ብኝም?” (ዘኁ.14፡11)። እግዚአብሔር ቅሬታው በእርሱ
አለማመናቸውና ኀይሉን መናቃቸው ነበር። እውነታው ይህ
330
በምዕራፍ ስምንት ላይ “የዕብራዊያን ዐዋጅ ቃል” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር
የቀረበውን ይመለከቷል።

460
ጆንሰን እጅጉ

ቢሆንም ብዙ ጊዜ (በዘኁ.14፡ 28) ላይ “እኔ ሕያው ነኝና


በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት
አደርግባችኋለሁ” የሚለው ቃል ብቻ ተነጥሎ “መንፈሳዊው
ዓለም በቃል ኀይል ነው የሚሠራው።” ለሚል መሞገቻ
ይውላል። ይህ እውነት ከሆነና እንደ ሕግ ከተወሰደ ሁል ጊዜ
መስራት ነበረበት። ብዙም ሳይርቅ በቍጥር ‘31’ ላይ
“ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን
አገባቸዋለሁ፣ እናንተም የናቃችሁትን ምድር ይወርሳሉ።”
ይላል። እነኝህ ሰዎች ምንም እንኳ በልጆቻቸው ላይ ዐሉታዊ
ንግግር ቢናገሩም እንኳ ንግግራቸው ግን አልፀናም ነበር።

እዚህ ላይ “አመንኩ ተናገርኩ እንደ ተባለ ነውና የተናገሩት


ያመኑትን ነው እምነትን ከንግግር እንዴት
ትነጥለዋለህ?”(2 ቆሮ.4፡13)። የሚል ክርክር ይነሣ ይሆናል።
ይሁን እንጂ ጳውሎስ በቆሮንጦስ መልዕክቱ የሚናገረው
የኢየሱስን ትንሳኤና የሕይወት ኀይል ስለመናገር ወይንም
ስለመስበክ ነው እንጂ አማልክቱ እንደሚሉት የምንፈልገውን
ነገር ስለማወጅ ፈፅሞ አይደለም። በቁ.14 ላይ ይህ ንግግር
ምን እንደሆነ ሲገልጥ“ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ
ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን
እናውቃለንና።” በማለት በትንሳኤ ዕውቀት ላይ
የተመሠረተና ትንሳኤን የሚያመለክት ንግግር ወይም

461
የአማልክቱ ዐዋጅ

የወንጌል ስብከት እንደሆነ ያሣያል። በተጨማሪም ‘ንግግር’


እምነት ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ እንጂ ብቸኛ
መንገድ እንዳልሆነም ልብ ማለት ይገባል። እምነት
መገለጫው ብዙ ነው። እምነት በሥራ፣ በጽናት፣
በትዕግሥትና፣ በመታዘዝ፣ ኃጢያትን እንቢ በማለት . . .
ወዘተ ሊገለጥ ይችላል።

ሌላው የካሌብና የኢያሱ ንግግር ዐላማም ቢሆን ከላይ


እንደተገለፀው የሕዝቡን ልብ ለማንሳት እንጂ የቃልን ኀይል
በመላለም ውስጥ በመልቀቅ ለመጠቀም ወይም
መንፈሳዊውን ዓለም ለማንቀሳቀስ ወይም ለመግዛት
አልነበረም።331 በመጨረሻም አስቀድመን እንዳልን የካሌብና
የኢያሱ ንግግር ጸሎት ሳይሆን ስብከት ስለሆነ ለቃል ዐዋጅ
ጸሎት ምሳሌ መሆን ፈፅሞ አይችልም።

ሌላ ዐይነት እምነት
ፀጥ ረጭ ያለ ጉባኤ ድንገት ይተራመሳል። ሰው ሁሉ
ከተቀመጠበት መቀመጫ እንዲነሳ ይታዘዛል። በመቀጠልም
“የምትፈልጉትን ነገር የምታውጁበት ሰዓት ነው!” የሚል
331
ለተጨማሪ ግንዛቤ በዚሁ ምዕራፍ “አንደበት እሳት ነው” በሚለው ንዑስ ርዕስ
የተጠቀሰውን ልብ ይሏል።

462
ጆንሰን እጅጉ

ነጋሪት ይጎሰማል። ሰዎች ወዲያና ወዲህ እየተወራጩ መሆን


የሚፈልጉትን በአየሩ ላይ ያውጃሉ! የሚፈልጉትን ሁሉ
ይጠራሉ! ይናገራሉ። ሕዝቡን ከወንበር አስነስቶ እንዲህ
ያተራመሰው ግን ከሚያከብረውና ከሚወደው ከእግዚአብሔር
ሥልጣናዊ ቃል የተነበበለት ጥቅስ ነው። “ለአሕዛብ አባት
አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ
የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት
የሁላችን አባት ነው።” ይህንንም ተከትሎ የመድረኩ አለቃ
ፈጠን ባለ ወፍራም ድምጽ “አሁን የሌላችሁን፤ ነገር ግን
እንዲሆን ወይም እንዲኖራችሁ የምትፈልጉትን ነገር
እንጠራዋለን! አዲስ ነገር ይሆናል!” በማለት ያውጃል።
በመጨረሻም አሁን አድራሻችሁ ተቀየረ ሲል “ወንበር
ተቀያየሩ!” የሚል ትዕዛዝ ይሰጣል።

የዚህን ጊዜ ታዲያ የማይኩ ድምጽ ከፍ ይላል የሙዚቃ ድምጽ


ይከተላል። በመኻል በመኻልም “ነገራችሁ ተቀየረ! ሰፈራችሁ
ተቀየረ! አድራሻችሁ ተቀየረ! ወዘተ.” የሚል ልዩ ዐዋጅ
በተደጋጋሚ እንዲያስተጋባ ይደረጋል። ይኸው ነው የከፍታ
ጣሪያው! የጸሎት ማሳረጊያ መጨረሻው! የጸሎት መልስ
ማረጋገጫው! የአማልክት ጉባኤ ምልክቱ። ነገሩን እንደ
ትንግርት እንድንመለከተው የሚደረገው። ነገሩን ግራ
የሚያደርገው ይህ ሁሉ የሚሆነው እዛኛው . . . የእምነት

463
የአማልክቱ ዐዋጅ

አማልክት ጉባኤ መንደር ወይም “አዳዲሶቹጋ” አለመሆኑ


ነው። እዚሁ መካከላችን የወንጌላውያን አማኞች ጉባኤ ላይ
ነው።

ወዮ! እዚህ ያለነውና እዛ ያሉት፤ ሁላችንም ዐብረን፤


መለኮትን እንዲህ እኛ እንዳደረግነው የሚሆን ‘ና’ ስንለው
የሚመጣ ‘ሂድ’ ስንለው የሚሄድ የመድረክ አሻንጉሊት
አስመሰልነው። ዳሩ ግን ልዕለ መለኮት እግዚአብሔር ጊዜና
ቦታ የማይገዛው የተፈራ አምላክ ነው። እርሱ በጊዜና በቦታ
የሚከናወኑ ነገሮችን ሁሉ ይገዛል ይቆጣጠራል።
የማያውቀው፤ ቀድሞ የማይመለከተው ቅጽበታዊና
አስደንጋጭ ነገር በእርሱ ዘንድ አይኖርም። ለማድረግ
የወሰነውን ነገር እንዳያደርግ የሚገዳደረውና የሚሞግተው
ሌላ ልዕለ ኀይል የለም። በአንደበት ቃል ዐዋጅ እጁ
አይጠመዘዝም። “ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ
የለም፤ እሠራለሁ፣ የሚከለክልስ ማን ነው?” ያለ እርሱ
በእውነት ብርቱ ነው።(ኢሳ.43፡13)። የጸሎታችንና የልመና
ቃላችን መሰማት እውነተኛ የምስራች ጣራው የእርሱ
ይሁንታና የማድረግ ሥልጣኑ ወይም በጎ ፈቃድ ነው።

አብራም ልጅ የሌለውና መውለድ የማይችል ሽማግሌ


ቢሆንም ልጅ እንደሚወልድ ተስፋ ተሰጠው። ይህም ብቻ

464
ጆንሰን እጅጉ

ሳይሆን ተስፋው እንደሚጨበጥ ሊያስረግጥለት ወዶ ስሙን


“አብርሃም” ብሎ ጠራው። “ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ
አብራም ተብሎ አይጠራ፣ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፤
ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።” (ዘፍ.7፡5)። ይህ ታሪክ
ልዕለ መለኮት ምን ያኽል በጊዜ ውስጥ ያሉ ክስተቶችን
እንደሚቆጣጠር ከልካይ የሌለው እንደሆነ ያስተምረናል።

ገና ምንም ሳይኖር አንድ ልጅ እንኳ በሌለበት “የልጅ አባት”


ብሎ መጥራት የሚችል በዐጽናፈ-ዓለም ውስጥ ወይም ከዚያ
ውጭ ከእርሱ ሌላ ማንም የለም። ይህንን ታዲያ ማን
አስተዋለ? የመለኮትን ልዕለ ስልጣን እየተጋፋ እንደሆነ ማን
ተረዳ? “በመጀመሪያ መጨረሻውን፣ ከጥንትም ያልተደረገውን
እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ
እላለሁ።”(ኢሳ.46፡10)። ይህንን ልዕለ መለኮትን የማወቅ
የመወሰንና የማድረግ አቅሙን ያልተረዳ እምነቱን በቃል ኀይል
ላይ ቢያደርግና የላንቃው ግድግዳ እስኪፈርስ ቢጮህ ድንቅ
ባልሆነ ነበር። የመለኮት ሉዑላዊነት ተሰብኮለትና አምኖ
የተሰበሰበ ጉባኤ በዐዋጅ ጉልበት ሁሉን ለመቈጣጠር
ሲጯጯኸ ማየት ግን ድንቅ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም ነው።

አባታችን አብርሃም አማኝ እንደ ነበር ጥርጥር የሌለው ጉዳይ


ቢሆንም ይህ የምስራች ከተነገረውና ስሙ ከተለወጠ በኋላ
“በአዲስ መገለጥ” የሕይወት ልምምዱ ተቀይሮ ወደ ቃለ

465
የአማልክቱ ዐዋጅ

ዐዋጅ ልምምድ ውስጥ እንደገባ ፍንጮች የሉንም። “ዘርህ


እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፣ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ
አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ።” (ሮሜ.4፡18) ።
ምንም እንኳ መለኮት በጊዜና በክስተት ላይ ባለው ልዕለ
ስልጣን አማካኝነት ነገሩ ከመፈፀሙ በፊት በኀላፊ ግስ “የብዙ
ሕዝብ አባት” በማለት ቢጠራውም አብርሃም ግን የገባው ነገር
ቢኖር የተነገረው ተስፋ የማይቀር እንደሆነ ነበር። ባንፃሩ
እርሱም እንደ መለኮት በኀላፊ ጊዜ ግስ ቃል የማወጅ
አስፈላጊነትን አልተረዳም፤ ዛሬ እንደምናደርግ ቃል
ዐላወጀም፤ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጎ አልጠራም። ዮናታን
አክሊሉ ግን ይህን እውነት ወደጎን በማድረግ “የሌለን እንዳለ
አድርጎ በሚጠራ ማመንህ የሚታወቀው አንተ እራስህ የሌለን
እንዳለ አድርገህ ስትጠራ ነው።”332 ብሏል። እርሱ ይህንን
ይበል እንጂ ባለታሪኩ አብርሃም እንዲህ ዐይነት መለኮትነትን
የመጋራት ልምምድ አልነበረውም።

አብርሃም የራሱ ሥጋና የሣራ ማህጸን ሙት መሆኑን


አልካደም። ነገሩ እስኪፈጸም እየደጋገመ ጠዋትና ማታ
“አላረጅም” ፣ “ወጣት ነኝ! ወይም “ልጅ አለኝ!” እያለ
ሲያውጅ አልታየም። ገና ይስሐቅ ሳይወለድ “ይስሐቅ!
ይስሐቅ!” እያለ አንድም ቀን አልጠራም። ይልቁንም መጽሐፍ

332
ዮናታን አክሊሉ። ማርሴል ቲቪ። በአፍህ ቃል ተያዝክ። (መጋቢት 26፣2020)።

466
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚመሰክር ሙት በሆነው አካል ላይ መለኮት እንደተናገረ


ሕይወት እንደሚዘራ ተስፋ በማድረግ የመለኮትን የማይወሰን
የማድረግ ችሎታ አመነ። “የመቶ ዐመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ
እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት
መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ።”(ሮሜ.4፡19)።
በአጠቃላይ አብርሃም በእምነት የእርሱና የሣራ አካል ሙት
(ያረጀ) መሆኑን ነው ያየው እንጂ እውነታን በመካድ
ወጣትነትን አልተመለከተም። አንድ ሰው ታዲያ በእምነት
ተመለከተ ማለት ምን ማለት ነው? በማለት ይጠይቅ
ይሆናል። በእምነት ተመለከተ ማለት የተነገረውን ተስፋ አሁን
የሚታየው ሙት (ያረጀው) አካል እንደማያጨናግፈው
የመለኮትን ዐቅም በመገንዘብ ተረዳ ማለት ነው።

አብርሃም የእምነት ሕግ የተባለ የተወሳሰበ እምነት ወይም


ልምምድ ባይኖረውም “የእምነት አባት” ተብሏል። በዚህም
እምነቱ “ፅድቅ” የተባለ ትልቅ ዋጋ ተቀብሏል። ስለዚህ ደግሞ
ፅድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ይላል።(ሮሜ.4፡22)። ይህም ብቻ
ሳይሆን ይህ “እምነት” ለሁላችንም አንዲቆጠር መለኮት
ወሰነ። “ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ
የተጻፈ አይደለም፣ ስለ እኛም ነው እንጂ።”(ሮሜ.4፡23)።
ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱን ስለ ቃል ኀይል ምንም የማያወራ
ጥቅስ ይዞ፤ የፊሊሞራዊያንን አመሥጥሯዊ ትርጓሜ

467
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመጠቀም “የምትፈልጉትን ነገር ጥሩ፤ አሁን ላይ የሌለን


ወይም የሌላችሁን ነገር ለራሳችሁ ተናገሩ! በምናባችሁ
የሥራችሁን ውጥን ሣሉና እራሳችሁን እንደ ትልቅ ካንፓኒ
ባለቤት ቁጠሩና ዐውጁ።” ማለት እንዴት ይቻላል? እንዲህ
በድፍረት የእግዚአብሔርን ችሎታ ለሰው መስጠትስ እንዴት
አያስፈራም?

ይህንን ስል የሚመሩትን ሕዝብ ለማፅናናት ካለቸው ብርቱ


ፍላጎት የተነሣ በየዋህነት ስተው የሚያስቱን እንዳሉ
አልዘነጋም። በሌላ በኩል ግን ሌላ “አማልክታዊ አባትነትን”
ለራሳችው በሚፈልጉ፤ ሌላ ዐይነት እምነት በሚለማመዱ
መሪዎችም ብዙ እንደ ተቀለደብን አውቃለሁ። የእምነት
አባቶች ግን የከበሩት ባልተወሳሰበ እምነት ነበር። በዚህም
ምሳሌነታቸውን ትተውልናል። ስለዚህ እውነትን አስተውለንና
ከዚህ ማደናገሪያ አምልጠን፤ ከስህተታችን ሁሉ ታርመንንና
እውነትን ተገንዝበን፤ የአባቶችን መንገድ በመከተል
በልምምዳቸው መስለናቸው አብረናቸው እንድንከብር የልቤ
ምኞትና ጸሎት ነው።

468
ጆንሰን እጅጉ

በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል


“ቃላት በጣም ኀይለኞች ናቸው፣ ሊሰሩም ሊያበላሹም
ይችላሉ።”
ፓስተር ክሪስ ኦኪሂሎሚ

“የአፍ ቃል የመፍታትም የመያዝም የማበላሸትም የመስራትም


ዐቅም አለው።”
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ።

“በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም


የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።” (ማቴ.18፡18)።
“የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር
የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም
የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” (ማቴ.16፡19)።
“በአፍህ ቃል ተጠመድህ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ።” (ምሳ.6፣2)
“እኔ እላችኋለሁ፣ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ
ቀን መልስ ይሰጡበታል።” (ማቴ.12፡36)።

ፓስተር ክሪስ ምሳሌ 6፡2 ትን ካነሳ ኋላ “ይህ ጥቅስ ብዙዎች


ዛሬ የሚገኙበትን አደገኛ ሁኔታ ላይ አጽንዖት ሰጥቷል።
ብዙዎች የራሳቸው ቃላት እስረኞች ናቸው።”333 ብሏል።
ዮናታን አክሊሉም ይህንኑ አፈፍ አድርጓል። በዩቲዩብ
333
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ (2013፣29)።

469
የአማልክቱ ዐዋጅ

ጣቢያው ላይ በለቀቀው ትምህርት ላይ እንደሚታየው የልዩ


ዲበ-አካል አማልክትም ይሁኑ የእምነት ቃል አማልክት
የአንደበት ቃል ኀይል ጽንሰ-ዐሳብን በእግዚአብሔር ቃል
ለማስደገፍ የሚጠቀሙባቸውን በርካታ ጥቅሶች ሽምድድ
አድርጎ ከተጎነጨ በኋላ በጕጕት በሚያደምጠው በርካታ
ወጣት ጆሮ በመዘርገፍ አብራርቷል።(ምሳ.2፡6334ዘሁ.14፡
28፣335ማቴ.12፡36336 ያዕቆ.3፡6337ምሳ.18፡20338ሮሜ.10፡
10339ማቴ.26፡34-75)። እንደ እርሱም ከሆነ ኪኒየን እንዳለው
ሁሉ “የአንደበት ዐቅም” ድነትን እስከ ማስገኘት የሚደርስ
ሲሆን ኢየሱስም የአንደበትን ዐቅም በመጠቀም የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ አማኝና ምሳሌ ነው።340 ድግግሞሽን ለመቀነስ
እያንዳንዱ ጥቅስ ላይ የተሰጠውን መልስ በሓዳግ ማጣቀሻ
ላይ በምናገኘው አቅጣጫ እንድንመለከት ይሁን።

334
በዚሁ ምዕራፍ ላይ “የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይበላል” በሚል ንዑስ ርዕስ
ይመለከቷል።
335
በዚሁ ምዕራፍ ላይ “እንደ እንጀራ ይሆኑልናል” በሚል ንዑስ ርዕስ ይመለከቷል።
336
በዚሁ ምዕራፍ ላይ ላይ “አንደበት እሳት ነው” በሚል ንዑስ ርዕስ ይመለከቷል።
337
በዚሁ ምዕራፍ “አንደበት እሳት ነው” በሚለው ንዑስ ርዕስ የተሰጠውን መልስ
ይመለከቷል።
338
በዚሁ ምዕራፍ ላይ “የረገምከው ርጉም ይሆናል” በሚል ንዑስ ርዕስ ይመለከቷል።
339
በምዕራፍ ሁለት ላይ “ኅሩይ ዐዋጅ” በሚለው ንዑስ ርዕስና በምዕራፍ ስምንት ላይ
“የእምነት ቃል” በሚለው ንዑስ ርዕስ ላይ ይመለከቷል።
340
በምዕራፍ ሶስት ላይ “እግዚአብሔርን መምሰል እንዲህ ነው” በሚለው እና
“የኢየሱስን ምሳሌነት መከተል” በሚለው ንዑስ ርዕስ ላይ የተሰጠውን ምላሽ
ይመለከቷል።

470
ጆንሰን እጅጉ

በአጠቃላይ እንደ ዮናታን ከሆነ ኢየሱስ የአንደበቱን ኅሩይ ቃል


ዐዋጅ ተጠቅሟል። ለጴጥሮስም “ትወደኛለህን?” የሚል
ጥያቄ ሦስት ጊዜ ደጋግሞ በማቅረብ ሦስት ጊዜ እንዲናገር
አድርጎታል። ኢየሱስ ይህንን ያደረገው “የምትይውን ሰው
አላውቀውም” በማለትና በመማል ሦስት ጊዜ የፈጸመውን
የአንደበቱን “የክህደት ዐዋጅ” በጴጥሮስ መልካም ዐዋጅ
በመጠቀም ለመሻርና ለማደስ ስለፈለገ ነው። እንደ ዮናታንም
ሰው በአንደበቱ ከሚናገረው ክፉ ዐዋጅ መፈታት የሚችለው
በእራሱ አንደበት መልሶ መልካም ያወጀ እንደሆነ ነው። በዚህ
ትምህርትም ሁሉም የልዩ ዲበ-አካል አማልክትም ይሁኑ
የእምነት ቃል አማልክት ይስማሙበታል። በሌላ በኩል የልዩ
ዲበ-አካል አማልክት እንደሚሉትም ከሆነ ኢየሱስ የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ ዐቅምን ፖዘቲፍ ኢነርጂ በመጠቀም ተአምራትን
ያደርግ ነበር። ዮናታንም የቃልን ኀይልን ለማሣየት ኢየሱስ
ሙቱን እንኳ አንተ ጎበዝ ብሎ መጥራቱን በአጽንዖት
አንስቷል።

ዮናታን በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ አደናጋሪ በሆነ ጥበብ


(ምሳ.2፡6) እና (ማቴ.12፡36)341 በማጣቀስ አቀላቅሎ ያቀረበ
ሲሆን የተጠቀሰው የምሳሌ እና የማቴዎስ ክፍል የአፍ ቃል
ዐቅምን ነው የሚነግረን ብሏል።342 ማስደንገጥና ማስፈራራት
341
በዚሁ ምዕራፍ ላይ ላይ “አንደበት እሳት ነው” በሚል ንዑስ ርዕስ ይመለከቷል።
342
ዮናታን አክሊሉ። ማርሴል ቲቪ። በአፍህ ቃል ተያዝክ። (መጋቢት 26፣2020)።

471
የአማልክቱ ዐዋጅ

በሚንጸባረቅበት የስነ-ልቦና ሰረቃ በተላበሰ ስብከቱም የሕዝቡ


ስሜት ሲጦዝና ከወንበሩ ተነስቶ እጁን ሲዘረጋ ተንቀሳቃሽ
ምስሉ ያሣያል።

ከላይ የተጠቀሱትን እንደ ማቴ.18፡18 እና ማቴ.16፡19


ጥቅስም ይሁን ዮናታን ያነሳቸውን ጥቅሶች ቀደምት የልዩ
ዲበ-አካል አማልክት ተጠቅመውባቸዋል። ኋላ ላይም
የእምነት ቃል እንቅስቃሴ ግንባር መሪዎች በተመሳሳይ መንገድ
እንደተጠቀሟቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ቀደም ብለን
ተመልክተናል። ከአማልክቱ የጥቅሥ መዐድ እንደ ዮናታን
ዐይነት የዘመናችን አገልጋዮች ብቻ ሣይሆኑ ጥንታዊያን
የቤተክርስቲያን መሪዎችም ሳይቀር ተቋድሰዋል። ስለዚህም
ለትምህርት እንዲሆን የወጣቱን የዮናታንን በልዩ-ዲበ አካል
ፍልስፍና ማዕከላዊ ጽንሰ-ዐሳብ ውስጥ መዘፈቅን አነሣሁ
እንጂ ድንቅና አዲስ ነገር እንዳይደለ አንባቢ ያስተውል።

ለምሳሌ አንዳንድ የሃይማኖት ቀደምት ሊቃናት ለሐዋርያት


በቃላቸው የማሰርና የመፍታት ስልጣን አላቸው የሚል
እምነት እንደነበራቸው ቱፊቶች ይጠቁማሉ። ከዚህም የተነሣ
አባቶች በአደባባይ ፈጦ በወጣ ስህተታቸው እንኳ አይወቀሱም
ነበር፤ ይህም ለቤተክርስቲያን ውድቀት የራሱን አስተዋፅዖ
አድርጓል። እንደ ትምህርቱም ከሆነ የሃይማኖት አባቶች
(አገልጋዮች) እንዲሁ የማሰርና የመፍታት አማልክታዊ ስልጣን

472
ጆንሰን እጅጉ

እንዳላቸው በስፋት ይታመናል። ከዚህ ዐስተሳሰብ ዮናታን


ለየት የሚያደርገው የአንደበትን “የመፍታትና የማበላሸት ሕግ”
በአማኞች አንደበት ላይ ሁሉ እንደሚሠራ አስረግጦ መናገሩ
ነው።

ይሁን እንጂ ይህ ዐስተሳሰብ ቢሆንም በቀደምት የልዩ ዲበ-


አካል አማልክት ተንፀባርቋል።343 አንዳንድ ጥንታዊያን የታሪክ
ቱፊቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ጳጳሳቱ ብቻ በቃል የፈቱት
የተፈታ ወይም የተባረከ ይሆናል! በቃል ያሰሩት ደግሞ የታሰረ
ወይም የተረገመ ይሆናል። በርግጥ ይህ አመለካከት አሁን
ባለችውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም
ሰፊ ተቀባይነት አለው። ጥንታዊውን የጳጳሳት የቃል ኀይል
የማሰርና የመፍታት ስልጣን ሊመሰክር የሚችል ምሳሌ
ከመካከለኛው ዘመን ታሪክ (1000-1500) ላንሳ። ታሪኩ
የተፈጸመው በሮም ኢንፓየር ንጉስ ሄነሪ አራተኛ እና በሮም
ካቶሊክ ጳጳስ ግሪጎሪ ስድስተኛ መኻል ነው።

በዘመኑ ጳጳሳቱ ከሉዑላን ነገስታቱ ይልቅ ላቅ ያለና በፖለቲካ


ስልጣን ላይ እንኳ ሳይቀር የማዘዝ ስልጣን እንዳላቸው
ይታመን ነበር። በዚሁ ዘመን ታዲያ በሮሙ ንጉስ ሄነሪ እና
በጳጳሱ ግሪጎሪ መኻል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። በዚህም
ምክኒያት ሄነሪ አዲስ ጳጳስ እንዲመረጥ ለማድረግ ግሪጎሪን
343
Ibdi. (መጋቢት 26፣2020)።

473
የአማልክቱ ዐዋጅ

የማይፈልጉትን ሰዎች ሰብስቦ ሙከራ ቢያደርግም ሰዎቹ


የጳጳሱ የውግዝ ስልጣን ስላስፈራቸው ሳይሳካለት ይቀራል።
ይልቁንም ግሪጎሪ ንጉሱን እንደርጉም በመቁጠርና
ከቤተክርስቲያን ደጋግሞ በማስወጣት የቤተክርስቲያኒቱን
ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣዋል። ለመንግስቱም እውቅናን በመንፈግ
አድማጭና ተከታይ በማሣጣት ያዳክምበታል። ንጉስ ሄነሪ
ፍትህ ስላጣና ተጽዕኖው ስለከበደበት ጳጳሱን ምህረት
ከመጠየቅ ውጪ አማራጭ ያጣል።

ስለዚህም ንጉሱ ፍትሃት ወይም ምህረት ፍለጋ


ከቤተክርስቲያኒቱ ውጪ በጳጳሱ ፊት በበረዶ ላይ
ይንበረከካል። “አባት ይፍቱኝ” በማለትም ይማጸናል። ግሪጎሪ
ግን አምርሮበት ነበርና ጥያቄውን ሳይቀበለው ጥሎት ይሄዳል።
ንጉስ ሄነሪ በጳጳሱ እርምጃ ከማዘኑም በላይ፤ ተመልሶ ይቅር
ብያለው ብሎ እስኪያስነሳው ወይም እስኪፈታው ድረስ
በዚያው በተንበረከከበት በረዶ ላይ እያለቀሰ ለሦስት ቀን ያኽል
ለመጠበቅ ይገደዳል። በአጠቃላይ በዚህ ታሪክ ላይ
እንደምንመለከተው የሮማ ጳጳሶች የማሰርና የመፍታት
ስልጣን እንዲህ ነገስታቱን እንኳ በበረዶ ላይ የሚያንበረክክና
የሚያንቀጠቅጥ ነበር።344

344
Study.com. academy lesson.

474
ጆንሰን እጅጉ

ቀጥሎ ለዚህ የቃል ስልጣን ሥርው ተደርገው በሰፊው


የሚጠቀሱት ሁለቱን ጥቅሶች ማለትም (ማቴ.18፣18) እና
(ማቴ.16፣19) እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክፍሉ ላይ
ያስተማረውን ትምህርት አብረን እንድናጠና ጋብዛለሁ።

በመጀመሪያው ጥቅስ ላይ(ማቴ.18፡18) የምናገኘው ዐሳብ


ከቍጥር (15-17) ላለው ትምህርት ማሰሪያ ስለሆነ ዐሳቡን
ለመረዳት ወደ ላይ ከፍ ብለን ከ‘15’ ጀምሮ ለማየት
እንገደዳለን። ይህንን ስናደርግ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ወንድሙን የበደለን ወንድም በተበዳይ መወቀስ እንዳለበት
ያስተማረበትን ጥበብ እናገኛለን። ኢየሱስ ዕርቅን እያስተማረ
ቢሆንም የዕርቅ የአስፈፃሚነት ኀላፊነትን ግን ከበዳይ ይልቅ
ለተበዳይ ሰጥቷል። ይህንንም የተበዳይ ኀላፊነት በተመለከተ
አራት ደረጃዎችን በተፍታታ መንገድ ያስቀመጠ ሲሆን
አራተኛው ግን እጅግ አደገኛ መሆኑን በትምህርቱ አሳይቷል።

1. ለብቻው መውቀስ፤
2. ሁለትና ሶስት ምስክር ፊት መውቀስ፤
3. ወቀሳውን ለቤተክርስቲያን መንገር፤
4. እምነት እንደሌለው ሰው መቁጠርና መተው።

እንደ ኢየሱስ ትምህርት አራተኛው ደረጃ ላይ የደረሰ በዳይ


ከባድ አደጋ ውስጥ ወይም እስራት ውስጥ ነው። ይህ እስራት

475
የአማልክቱ ዐዋጅ

በክፍሉ ውስጥ ያለውን ትርጉም ያየን እንደሆነ የተበዳይን


ይቅርታ አለማግኘት የሚል ትርጉም ያለው ነው። መፍታት
የሚለው ደግሞ የተበዳይን ይቅርታ ማግኘት የሚል ትርጉም
ነው ያለው። ይህንን ሦስት ደረጃ ያለውን ወቀሳ ዐልፎ ከበደል
አለመመለስ በምድር ባለው ወንድሙ ይቅርታን አለማግኘትን
ያስከትላል። ይህም ብቻ ሳይሆን የሰማይ አምላክ ፊትም
በወንድሙ ላይ በሠራው በደል ይቅርታን አለማግኘት ወይም
እሥራት ያስከትላል። በተቃራኒው ደግሞ ወቀሳውን ተቀብሎ
ከበደል ተመልሶ ይቅርታ መጠየቅ በምድር ባለው ተበዳይ
ይቅርታ ያስገኛል። በሰማይ አምላክ ፊትም በወንድሙ ላይ
ለሠራው በደል ይቅርታ ያስገኛል። በሰማይ የተፈታ ይሆናል
የተባለውም ይኽው ነው።

በዚህም ትምህርት ውስጥ ሰማይ ከተበዳይ ጎን በመቆም


ስለፍትህ ይፋረዳል። ይህም በሰዎች ስንበደልና ስንከፋ
እራሳችን በዳይ ሆነን ቢሆን እንኳ ፈጥነን “አንተ ተመልከት”
“አንተ ፍረድ” በማለት የመለኮትን ፍርድ እንደምንጣራው
ዐይነት ቀልድ አይደለም። በመጀመሪያ ተበዳይ በዳይን
መውቀስ አለበት። ይህም ተቀባይነት የሚኖረው ፍርድን
በመመኘት ሳይሆን በዳይን ገንዘብ ለማድረግ በመመኘት
በርህራሄና በፍቅር የተደረገ እንደሆን ነው። በተዘረዘሩት ሦስት
መመሪያዎች መሠረት ተበዳይ በሚያመቻቸው መንገድ በዳይ

476
ጆንሰን እጅጉ

ቢመለስ ይቅር ሊለው ወይም ሊፈታው በሚፈቅድ የፍቅር


ልብ ነው የሚያደርገው። በሦስቱም ደረጃዎች ሙከራ በዳይ
ባይመለስ ግን በአራተኛ ደረጃ መርኸ መሠረት ተበዳይ የማሰር
ወይም ለፍርድ አሳልፎ የመስጠት ስልጣን ያገኛል። በዚህም
ሥርዐት ለዕርቅ አስቀድሞ መዘጋጀት ያለበት በዳይ ሳይሆን
ተበዳይ ነው ማለት ነው። በክርስቶስ ደም ከሚሆን የኃጢያት
ንስሓና ስርየተም በፊት የተበዳይን ፍትሃት ወይም ይቅርታ
ማግኘት ቀዳሚ ነው።

በአጠቃላይ ክፍሉ እንደሚነግረን ማንኛውንም የዕርቅ ፍለጋ


ኃለፊነቱን የተወጣ አንድ ተበዳይ ምዕመን የማሰርና
የመፍታት ስልጣን እንደሚኖረው ነው። በአንጻሩ ግን የእምነት
ቃል ሰባኪያኑ እንደ ካቶሊኩ ጳጳስ ምዕመናቸውን
አስፈራርተው ለመግዛት እንዲያመቻቸው እንደሚሰጡት ልዩ
ትርጉም የሃይማኖት አባቶችን ወይም የአገልጋዮችን ልዩ
ስልጣን ወይም የቃል የመፍታትና የማሰር ኀይል
አያመለክትም። ይህንን በዳይና በተበዳይ መኻል መሆን
ያለበትን መወቃቀስና ይቅር መባባል የሚየስተምር ትምህርት
በማስገደድ ስለአንደበት ቃል ስልጣን ነው የሚያስተምረው
በማለት አግባብ አይደለም። በዚህም መልክ መሳትና
ሌላውንም ማሣት በመንግስተ-ሰማይ የሚያስጠይቅ በደል
እንደሆነ ማወቅ የንስሓ ዕድል ይሰጣል።

477
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሁለተኛው ጥቅስ ማለትም ከተመለከትነው ጥቅስ ጋር


ተመሳሳይነት ያለው ነው።(ማቴ.16፡19)። ይህም ጥቅስ
እንዲሁ የመንፈሳዊ ሰዎችን የቃል ስልጣን የሚያሳይ
አይደለም። ክፍሉ ምንም እንኳ መመሳሰል ቢኖረውም
ከ(ማቴ.18፡18) የተለየ መልዕክት ተሸክሟል። በዚህ ክፍል ላይ
ኢየሱስ ንግግር የሚያደርገው ከጴጥሮስ ጋር ነው። የንግግሩ
ምክንያት “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?”
የሚለው የኢየሱስ ጥያቄ ነው። ጴጥሮስም መልስ “አንተ
ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ።” የሚል ነበር።
ይህንንም መልስ ተከትሎ ኢየሱስ ሁለት መሠረታዊ ነገሮች
ተናገረ፦

1. በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፣ የገሃነም


ደጆችም አይችሉአትም።
2. የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር
የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም
የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

በክፍሉ ላይ ሁለት ጥያቄ ማንሳት ይገባል። አንደኛው ጥያቄ


ኢየሱስ አለት ያለው ምንድነው? የሚል ሲሆን ሁለተኛው
ደግሞ የመንግስተ-ሰማያት ቁልፍ ምንድነው? የሚለው ነው።
ኢየሱስ ይህንን እንዲናገር ያደረገው “አንተ ክርስቶስ የሕያው
እግዚአብሔር ልጅ ነህ።” የሚለው የጴጥሮስ መልስ እንደሆነ

478
ጆንሰን እጅጉ

ግልጽ ነው። ስለዚህ “አለትም” ይሁን “ቁልፍ” የተባለው


“በዚህ” በሚል የቅርብ አመልካች ስለተገለጠ “አንተ ክርስቶስ
የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ።” የሚለውን የጴጥሮስ ንግግር
የሚያመለክት ነው የሚሆነው።

እውነቱ ይህ ከሆነ ጴጥሮስ ይህንን “አለት” ወይም “ቁልፍ”


ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ
ሁለት ላይ ነው።

ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፣


ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦
አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፣ ይህ
በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፣ ቃሎቼንም አድምጡ።
…ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፣ በዚያም ቀን ሦስት
ሺህ የሚያኽል ነፍስ ተጨመሩ።(2፡14፣ 41)።

በአጠቃላይ ማቴዎስ እየነገረን ያለው “የኢየሱስን ማንነት


የሚገልጥ የወንጌል ስብከት” የቤተክርስቲያን ሥርው
የመንግስተ-ሰማያት ቁልፍ እንደሆነ ነው። የሐዋርያቱም
ልምምድ ይህንኑ ነው የሚያሳየው። ከዚህ ውጪ ዛሬ ላይ
“አማልክቱ” እንደሚያደርጉት ቃል በማውጣት ወይም
በማወጅ ሰው ሲያስሩ ሲፈቱ የሚውሉበት ጉባኤ እንደነበር
በአዲስ-ኪዳን መልዕክቶች ውስጥ የሚጠቁመን ፍንጭ

479
የአማልክቱ ዐዋጅ

አናገኝም። ጳጳሳቱ ያስተምሩ እንደነበረውና የእምነት ቃል


አማልክቱ ሲያንጸባርቁ እንደሚታየው ቃል በማውጣት ወይም
በመገዘት ከሰማይ የመነጠል ስልጣን እንደነበራቸው አናይም።
ለመንፈሳዊ ሰዎች የማሰርና የመፍታት ስልጣን “አማልክቱ”
የሚጠቅሱት ሁለቱም ጥቅሶች የቃል የማውጣትን ወይም
የቃል ዐዋጅ ትምህርትን አያበረታቱም።

መለኮትን የሚያንቀሳቅስ ችሎታ


እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1980 እና 1990 ዎቹ መኻል
ነቢያቶች መልዕክት ሲናገሩ መልዕክት ተቀባዩ ግለሰብም ይሁን
ታዳሚ ምዕመን ራሱን በማቀርቀር ዓይኑን ይጨፍናል።
ከዚያም ዝግ ባለ ድምጽ ጉዳዩን ከአምላኩ ጋር በማድረግ
ጸሎቱን መቀጠሉ የተለመደ ነበር። የሚናገር የእግዚአብሔር
መንፈስ ነውና ለመመልከት መንቀዥቀዥም ሆነ ቀና ማለት
የሐበሻው ባህል ከአክብሮት አይቆጥረውምና ይህንን የሚደፍር
አልነበረም። ቀና ቢባልስ ሥጋ የለበሰ ሰው እንጂ ምን
ሊመለከት ይችላል? መንፈስን እንደሆን ዐያዩትም።
ምስክርነት ለመስጠት ወይም ከአገልጋዩ ጋር ለመነጋገር
ካስፈለገ ጸሎት ካለቀ በኋላ ነው የሚደረገው። አሊያም
የምስክርነት ጊዜ ተብሎ ተለይቶለት ነው። ምንም ዐይነት
ተኣምር ቢከሰት በምስክርነት ምክንያት ጸሎት እንዲረበሽና
እንዲቋረጥ አምልኮም እንዲስተጓጎል አይፈቀድም።

480
ጆንሰን እጅጉ

የጉባኤ አምልኮና ጸሎት የከበረ ነው! አማኞች ሁሉ በጋራ


ለፈውስም ይሁን ለተአምራት እጃቸውን አንስተው
የሚተባበሩበት እንጂ ቁጭ ብለው የሚደነቁበት፣ የሚስቁበትና
የሚጯጯሁበት ትርዒት አልነበረም። በእዛ ሥርዐት
የማይሰራና ውጤት የማይኖረው እምነት ወይም ውጤት
የሌለው ጸሎት የሚጸልይ አማኝ እንዳለ የሚቆጥር ስለሌለ
የምዕመኑ የጋራ ጸሎት ቆሞ ከሚያገለግለው ባልተናነሰ
ይከበራል። የሚገኘውም መንፈሳዊ ድል የጋራ ስለሆነም
አንድን ሰው ብቻ አያገንም። የጌታ መንፈስም ድንገት በጉባኤ
ካለው ምዕመን አንዱን አስነስቶ ድንቅ ሊናገርና ሊሰራ
ይችላል የሚል ተስፋም ስላለ ‘ያ ሰው እኔስ ብሆን’ የሚል
መጠባበቅና ዝግጅትም የነበረበት ነው።

አሁን ግን እንዲህ አይደለም ነቢዩ ሲተነቢይ የሚተነበይለት


ቀና ብሎ ካላናገረው ወይም መልስ ካልሰጠው ነቢዩ ይቆጣል
ወይም ጥሎት ይሄዳል። የትንበያው ሥርዐት እንዲቀጥል
ከተፈለገ ማቀርቀርም ዐይን መጨፈንም መጸለይም
አይገባም። እንዲህ ዓይነቱ ልምምድ ታዲያ
አቢያተክርስቲያናትን ሲኒማ ቤት እንዲመስሉ እያደረጋቸው
ነው። አሁን ላይ ባለው ሁኔታ“ሥጋን የለበሰ ሁሉ ጸሎትን ወደ
የምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።” የሚለውን ጥቅስ “ሥጋን
የለበሰ ሁሉ ጸሎትን ወደ ምትመልሰው ወደ እግዚአብሔር

481
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሰው ይመጣል።” ተብሎ ተተክቷል ብል ዋሽተሃል


የሚያስብለኝ አይደለም። መለኮታዊው ኀይል በሰዎች እጅ
እንደሚንቀሳቀስ ማሽን በሰዎች ቁጥጥር ሥር ያለ ይመስላል።
አሽከርካሪ መሪውን ወደ ሚዘውርበት የተሽከርካሪውን
አቅጣጫ እንደሚወስን እንዲሁ አገልጋዩ በቃሉ ዐዋጅ
የመለኮትን ኀይል ወደ ሚፈልገው ለማዞር በየመድረኩ
ይታገላል። ማህበረ ምዕመኑ ለችግሩ መፍትሄ ከአምላኩ ጋር
ያለው ግንኙነት ሳይሆን የአገልጋዩ ልዩ ጸሎት ወይም ቃል
ዐዋጅ እንደሆነ ስላአመነ የግል ጸሎትን በጉባኤ አይደለም
በጓዳውም እየተወ ነው ያለው።

ከናይጄሪያው ቲቪ ጆሽዋ ጀምሮ እስከ አገራችን በርካታ


ቻናሎች ድረስ ሰዎች መድረክ ላይ ወዳለው “የእግዚአብሔር
ሰው” ልመናና ጸሎት ሲያቀርቡና ብሎም እግር ላይ ወድቀው
ሲማፀኑ ማየት የተለመደ ነው። ብዙ ሕዝብ ባለበት ጉባኤ
“አሜን የእግዚአብሔር ሰው” እያለ ብድግ ቁጭ በማለት
የሚጮህ ሰው ካለ እመኑኝ ትንቢት የሚነገረው ለእርሱ ነው።
ይህንን ድርጊት ለምን ብሎ የሚጠይቅ ወይም የሚቃወም ግን
ብዙም አይታይም። ቀደም ብለን እንደተመለከትነው የዲበ-
አካል ሃይማኖት ምሁራን ሰው ተራራን መንቀል የሚችል
የእምነት ደረጃ ላይ ከደረሰ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም
ወይም የሰዎችን ልመና መፈጸም ይችላል ይላሉ።

482
ጆንሰን እጅጉ

ፊሊሞር ፊንሐስ ኪዊምቢ ያደርግ እንደ ነበረ እንደ አምላክ


የጸሎት ጥያቄዎችን ከዓለም ዙሪያ ያስተናግድ ነበር።
እነኝህንም የጸሎት መልሶችና ምልክቶች ያደርግ የነበረው
‘የአዕምሮውን ክፍል የእምነት ወይም የኅሩይ ቃል እወጃ ኀይል’
በመጠቀም እንደ ነበር ታሪኩ ያስረዳል። አብዛኛዎቹ ይላኩለት
የነበሩ ደብዳቤዎችም የፈውስና የሐብት ጥያቄዎችን የያዙ
ነበሩ። ጥያቄዎቹም በፊሊሞር የቃል ዐዋጅ ልምምድ
አማካኝነት ተግባራዊ ምላሽ ያገኙ ስለነበር ሰፊ ተቀባይነት
ማግኘት እንዲችል አስችሎት ነበር። ፊሊሞራዊያኑ አማልክት
ታዲያ የሰው ልጅ “የተፈጥሯዊ ውስንነቱ ጌታ ነው!”
የሚለውን ዐሳባቸውንለማስረገጥ ሲሉ ኢየሱስ ተራሮችን
እንኳ ማንቀሳቀስ እንደምንችል ተናግሯል እስከ ማለት
ይደርሳሉ ።

ቅልጥ ያልን ‘የሪቫይቫል’ ሰዎች ነን የሚሉ አንዳንድ ቤተ-


እምነት መሪዎች ይህንንኑ አማልዕክታዊ ሥልት
መጠቀማቸው ፀሓይ የሞቀው ጉድ ነው። የዓለም አቀፍ
‘ሪቫይቫል’ ሰባኪው እንደሆኑ ክርስቲያን ሃርፍሮች “ዘ ኃይድን
ፓወር ኦፍ ዮር ዎርድስ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ከላይ
የተጠቀሰውን የፊሊሞርን ዐሳብ በመጋራት ሲያብራሩ “ምድር
የተፈጠረችው እግዚአብሔር ስለተናገረ ነው። እንደዚሁም
ሁሉ፤ ኢየሱስ ሰው ሲናገር ተራሮች እንደሚንቀሳቀሱ

483
የአማልክቱ ዐዋጅ

ተናግሯል። እግዚአብሔር ጠንካራ የእምነት ቃላትን በመናገር


ወይም በማወጅ ኀይሉን የምናቀሳቅስበትን ችሎታ
ሰጥቶናል”345 ብለዋል። (ማር.11፡23)። ይሁን እንጂ ይህ
ግንዛቤ ማስጨበጫ ‘ሰባኪው ስለየትኛው እግዚአብሔር ነው
የሚያወሩት?’ የሚል ጥያቄ የሚያጭር ነው። ፊሊሞርም ሆነ
ሃርፉች የጠቀሱት ማርቆስ አስራ አንድ የእምነትን ወይም
የቃል “ዐዋጅ” ኀይል ስለመጠቀም እንደማያስተምር ቀደም
ብለን “የረገምካት በለስ ደርቃለች” በሚለው ንዑስ ርዕስ
በዝርዝር ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ እነኚህ ሰዎች ይህንን ጥቅስ ካለ-አግባብ


በመተርጎም ‘ጸሎትን’ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ባህልና ትርጉሙ
አውጥተው በቃል ዐዋጅ ልምምድ በመተካት ለማስተማር
በየጊዜው በመሞከር ላይ ናቸው። እኛ ግን የኀይል ባለቤት
የሆነው የዕብራዊያኑ አምላክ ልዕለ ኀይሉ በሰው ፈቃድና
ትዕዛዝ እንደማይንቀሳቀስ አውቀን አምነናል።346 ሐዋርያው
ግሪኮችን ሲያወራ “በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን
እንኖርማለን።” (ሐሥ.17፡28)። እንዳለው ፍጥረቱን
የሚያንቀሳቅስ እንጂ በፍጥረቱ የሚንቀሳቀስ አምላክ
የለንም።

345
Christian Harfouche, The hiden power of your words. (1993, P, 54).
346
Haller, J. S. The History of New Thought. (2012, Pp, 82, 130, 217).

484
ጆንሰን እጅጉ

የእግዚአብሔር ወዳጆች ሆይ፦ የቃል ዐዋጅ ጸሎት ልምምድ


በአዕምሮ ውስጥ ያለውን ኀይል በመግለጥ መልሳችንን
እንደሚያቀብለን የልዕልና መጎናጸፊያ ሆኖ ቀርቦልናል። ይሁን
አንጂ የጥቅስን ፍቺ በዚህ መልክ እያዛቡ መለማመድ
የመለኮትን ልዕልና መቃረን እንደሆነ እንደተገነዘብን እምነቴ
ነው። እንዲህ ዓይነቱ ልምምድ የመለኮትን ቁጣ
ከመቀስቀሱም በላይ ለአጋንታዊ የምትሃት ኀይል መንቀሳቀስ
አሳልፎ እንደማይሰጠን ምንም ዋስትና አይኖረንም። መለኮት
በቃል ዐዋጅ ሕግ የማይንቀሳቀስ ከሆነና፤ የሚነሱ ጥቅሶችም
የቃል ኀይልን ትምህርት ለማስተማር ብቁ ካልሆኑ፤ በዚህ
መንገድ የሚንቀሳቀስ ኀይል ካለ ባዕድ መንፈስ መሆኑን
መረዳት ይገባል።

እንደዚህ ዓይነቱን በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረግ


ምትሃታዊ የኀይል ልምምድ ምሥጢር መረዳት ለብዙዎቻችን
አስቸጋሪ እንደሚሆን አውቃለሁ። ይህንን መጽሐፍ እያነበብን
ያለን ሁላችንም ግን ምስጥሩ ገባንም አልገባንም በተዛባ
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የተመሰረተን ልምምድ
ከመነካካት እንድንሰበሰብ በጌታ ፍቅር አሳስባለሁ! ከቅርብ ጊዜ
ወዲህ በአገራችን መለኮትን ለማንቀሳቀስ የሚደረግ ልምምድ
እየተስፋፋ መጥቷል። በልምምዱም የወንጌላውያን አማኞች
ጭምር ተጠያቂዎች እየሆንን እንደሆነ በቂ አመላካች

485
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነጥቦችን ተመልክተናል። ለዚህም ጥቅሶችን ተረጉመን


እየተጠቀምን ያለንበት መንገድና መንፈሳዊ ልምምዳችን
መመሳሰል አስረጂ ነው። በልምምዱ እንግዳ ባሕርይ
እየታወክን እንኳ በመድረካችን ላይ ሲያቆጠቁጥና ሲገን
በዝምታ አልፈናል። በእንግዳው አካሄድ ጸሎት፣ ሥብከትና
ዝማሬ እየተረበሸ እንደሆነ ብናውቅም አካሄዱ የትዕይንትና
የታይታ ረሐባችንን ለማስታገስ ስለሚረዳን ካሜራ አስደቅነን
ሕዝብ አስጨብጭበን በመድረክ አነገሥን እንጂ ውረድልንን
አልደፈርንም። ይኸው ቸልታችን የለየላቸው የቃል ዐዋጅ
አማልክት ከመካከላችን ወጥተው ወንጌልን ወደ ንግድ
በመለወጥ ዐገር ለመበጥበጥ እንዲበቁ አድርጓቸዋል።
ሳናርማቸው፤ እውነትንም በወጉ እንደሚገባ ሳናሲዛቸው
ከጃችን አምልጠውናል።

486
ጆንሰን እጅጉ

ማጠቃለያ

በዚህ ሰፋ ያለ ዳሰሳ የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ትምህርት በዲበ-አካል


ሃይማኖት የሚያማስን ቅዥት እንጂ ጽኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ሥርው ያለው ትምህርት እንዳልሆነ እንደተረዳን ተስፋ
አደርጋለሁ። ልምምዱ “ተገለጠልን” በሚል ሰበብ ካለ
አውዳቸው እንዲናገሩ ከተደረጉ ጥቅሶች ውጪ አንድ እንኳ

487
የአማልክቱ ዐዋጅ

አሳማኝ ጥቅስ ማቅረብ የማይችል የለየለት የዲበ-አካል


ሃይማኖት ፍልስፍና ነው። ይህም ቢሆን የጠራ የወንጌል
አማኞች ሥነ-መለኮት እንከተላለን የምንለውም ጭምር
አውቀነውም ይሁን ሳናውቀው ከትምህርቱ ስውር እጅ ጋር
እንደተነካካን ተመልክተናል። አማልክቱ የሚጠቅሷቸውን
ጥቅሶች ከእነርሱ ባልተለየ መንገድ ተርጉመን በአንድ ገበያ
መዋላችን ግልጽ እንደሆነልን አምናለሁ።

አሁን ምን እናድርግ ቢሉ፤ በዚህ መጽሐፍ አምላካችን


የፈነጠቀልንን የእውነትን ብርሃን በአንክሮ ተመልክተን
ለመሠረታዊ ተሓድሶ እንነሳ። የዲበ-አካል ሕልውና የሆነውን
የቃል ዐዋጅ ትምህርት ከትምህርታችንና ከልምምዳችን
ጠርገን እናስወግድ። ለጤናማ ሥነ-አፈታት ትኩረት
በመስጠት ርቱዕ አስተምህሮን እናሰተምር። ተሓድሶን
መሻታችን ከልብ ይሁንና ይህንን ማሣኒ የልዩ ዲበ-አካል አቧራ
ከእግዚአብሔር ቃልና ከመድረካችን ላይ አራግፈን
እናስወግድ። ይህ ሳይሆን ግን ባልፀዳ ጉባኤና በተበከለ መድረክ
የመንፈስ በቅዱስ የሚሆንን መነቃቃት ተስፋ ማድረግ አደጋ
አለው። ምክንያቱም መለኮትን ከመርሖና ከባሕርይው ውጪ
መፈለግ ስለሆነ እራስን ማታለል ወይም ጊዜ መፍጀት ወይም
ለባዕድ አሥራር እራስን ማዘጋጀት እንደሆነ ማወቅ አለብን።

488
ጆንሰን እጅጉ

የምዕራፍ ሥድስት የግንዛቤ ጥያቄዎች


1. እንደ ቃል ዐዋጅ ትምህርት ከሆነ የዐዋጅ ቃልን በተደጋጋሚ
መናገር አስፈላጊ ነው። እንደትመህርቱ አስፈላጊ
የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው? (አራት ነጥቦችን
አስቀምጥ)
2. ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ተነስተን ከእግዚአብሔር ጋር
በዘረ-መል እንደተዋረስን ልናስብ አንችልም የምንልበትን
ምክንያት አስቀምጥ።
3. አገልጋዮች የማይገደብ ችሎታ እንዳላቸው ለማሳመን
በተሳሳተ መንገድ ከሚተረጎሙ ጥቅሶች መኻል ሁለቱን
ጥቀስ።

4. ኢየሱስ ረግሟት የጎበረረችው በለስ ታሪክ የቃልን የርግማን


ዐቅም ያሳያል? አብራራ።

5. በምሳ.18፡20 “መሠረት የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፣


ከንፈሩ ከሚያፈራው ይጠግባል፣ ሞተና ሕይወት በምላስ

489
የአማልክቱ ዐዋጅ

እጅ ናቸው፣ የሚወዷትም ፍሬዋን ይበላሉ” የሚለውን


ቃል ከዚህ በፊት እንዴት ትረዳው ነበር? ወይም በምን
ዐይነት ትርጓሜ ሰምተህው ታውቃለህ?

6. የማሰርና የመፍታት ስልጣን ምንድነው? ይህ ልምምድ


በአለህበት ቤተክርስቲያን የሚተገበርበት መንገድ ምን
ይመስላል? ከዚህ ክፍል አንፃር ምን ማድረግ እንዳለብህ
ወስነሃል? (ማቴ.18፡18)።

490
ጆንሰን እጅጉ

ክፍል ፭

የተሓድሶ ደወል

491
የአማልክቱ ዐዋጅ

  

ምዕራፍ 7

መናፍቃዊ ሰንኩል ጉዞ

የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ከኢማኑኤል ሲውዲንበርግ


ጀምሮ እስከ ቻርልስ ፊሊሞር፤ ከኪኒየን ጀምሮ እስከ የእኛ
አገሮቹ የእምነት ቃል አስተማሪዎች ድረስ የዘለቀና ያልጎበረረ
ዥረት ነው። ፍልስፍናው የተፈጥሮ ሕግን ግኝትና
የሂንዱይዝምን ዐስተሳሰብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር

492
ጆንሰን እጅጉ

በማቀላቀል፤ የጸሎት ምላሽ ባለቤትነትን ከመለኮት ላይ


በመውሰድ ለቃል ዐወጅ የጸሎት ልምምድ እንደሚሰጥ
ተመልክተናል። በዚህም ቅይጥና ባዕድ የዐዋጅ ቃል ሥነ-
መለኮት መርሖ ምትሃታዊ ተአምራቶችና ፈውሶችን
እያስፋፋ እንደሆነ አንባቢ መታዘብ እንደቻለ ተስፋ
አደርጋለሁ። የቃል ዐዋጅ ልምምድ ባገኘው መድረክ ሁሉ
የመለኮትን ሉዐላዊ ፈቃድ በምስጢር በመካድ፤ መለኮት
በፍጥረቱ ውስጥ ያለውን የመወሰንና የማድረግ ድርሻና
ስልጣን የተጋፋና ክርስትናን የሰነከለ ኑፋቄ ነው። የእምነት
እንቅስቃሴም ይህንኑ የዲበ-አካል ሃይማኖት ዐሳብ የተዋረሰ
እንቅስቃሴ በመሆኑ ምክንያት ማኮኔል እንዳሉት ባዕድ እምነት
(cultic) ወይም ቅይጥ ኑፋቄ ነው ማለት እንችላለን። 347

ቀደም ባሉት ክፍሎች በስፋት እንደተመለከትነው የእምነት


እንቅስቃሴ የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍናን ሥርው
በማድረግ የራሱን የሥነ-ሰብዕና የሥነ-መለኮት ትምህርት
በማስፋፋት ልዩ ሃይማኖትን አስተዋውቋል። በዚህም
የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎምን፣ ትምህርተ ድነትን፣ ትምህርተ
ጸሎትንና ትምህርተ እምነትን እስከ መበረዝ እንደሚደርስ
ተመልክተናል። እርግጥም በኢትዮጵያ ወንጌላዊት
ቤተክርስቲያን እንደ ጥቃቅን ስሕተት እንጂ እንደ ባዕድ የኑፋቄ
እንቅስቃሴ እንዳይቆጠር ለማድረግ ግልጽ ያልሆነና

347
Different Gosple. (P.78).

493
የአማልክቱ ዐዋጅ

የየተለሳለሰ አቀራረብን ይጠቀማል። ይህንንም በዚህ መጽሐፍ


ካቀረብኩት ጥናታዊ ዊኸብና ልምምዶቻችን ከተፈተሸበት
ዳሰሳ መረዳት እንደቻልን ተስፋ አደርጋለሁ።

በአጠቃላይ እንቅስቃሴው በስውር እጁ ወንጌላዊቷ


ቤተክርስቲያን ወደ ልዩና እንግዳ የዲበ-አካል ሃይማኖት
ልምምድ ውስጥ ቀስ በቀስ እንድትዘቅጥ እየገፈታተረና
መንፈሳዊ ጣዕሟን እየረበሸም እንደሆነ ለማመልከት ጥረት
ተደርገጓል። በክርስትና ተቋማት ዘንድ ተቀባይነትና
ተወዳጅነት የሚያተርፍበት ስሜት አነቃቂና ሰውን ከፍ
የሚያደርጉ ትምህርቶቹ ምን እንደሆኑ ዓይተናል። ለነኝህ
ትምህርቶች የሚሰጣቸውን የጥቅስ መሸፈኛ ለማጋለጥም
ተሞክሯል። ይህም የተደረገው የመሸፈኛው አለመገለጥ
እንቅስቃሴውን ለመቃወም የምናደርገውን ጥረት ሊያከሽፍ
ስለሚችል ነው። ጥምር ተግዳሮቱን ለመከላከል
የምንችልበትን ዕውቀት እንድናገኝ ሐቲታዊ (exegetical)
ዳሰሳዎች ተደርገዋል። በእያንዳንዱ ዳሰሳም የእንቅስቃሴውን
ዐቅም ለማዳከም እንዲቻለን ዝርዝር መልስ ተሰጥቷል። ይህ
አቀራረብ ደግሞ የእምነት እንቅስቃሴ ኑፋቄን አንድ እንዲሉ
ወይም እንዲያወግዙ ተስፋ ለተጣለባቸው፤ መሳሪያውን
እንደተቀማ ወታደር ምንም የማይሉ እየሆኑ ለመጡ መሪዎች
ማለፊያ የማንቂያ ደወል በመሆን እንደሚያበረታቸው
አምናለሁ።

494
ጆንሰን እጅጉ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ከእምነት ቃል እንቅስቃሴ የልዩ


ዲበ-አካል ፍልስፍና ሩቅ እንደሆንን ቢገመትም በተለይ ከቅርብ
ጊዜ ወዲህ የትምህርቱን ባዕድነት ብዙም ለይተን ስንረዳና
ስንቃወመው ዓይታይም። በዚህ መጽሐፍ እየተበራከቱ
በመጡት የቃል እምነት መምህራን ትንቢት መሳይ የዐዋጅ
ንግግር እየተሳብን ለመምጣታችን አመለካች የሚሆኑ እኛምጋ
ያሉ ክፍተቶችን ለመቃኘት ሞክረናል። እነኝህ መምህራን
በሚያቀርቡልን ቀለል ባለ ስሜትን በሚለኩስ ስብከትና
ልምምዳቸው ከመሳባችን የተነሣ ለዲበ-አካል ሃይማኖት
ጋብቻ ቅርብ ሆነዋል ማለት ይቻላል። ይሁን እንጂ ‘ፈጽመን
ተዋህደዋል’ በሚል እንዳንወቀስ የዲበ-አካል ሃይማኖት
አማልክት ‘የቃል ዐዋጅ’ የእምነትን ወይም የስሜት ማደግ
ልዕለ አዕምሮን ወይም መለኮትን ያነቃቃል እንደሚሉት
‘መለኮት ይነቃቃል’ አንልም። ያም ሆኖ በአንዳንድ የማነቃቂያ
መርሀ-ግብራችን ላይ የሚታየው የቃል ዐዋጅ አካሄድ
ሰውነትን ነው ወይስ መለኮትን ለማነቃቃት የታሰበው? የሚል
ጥያቄ እስከ ማስነሳት የሚደርስ መሆኑ ለጥምቀተ ኑፋቄው
መቅረባችንን ጠቋሚ ነው። መርሖ አፍራሽ ልምምዶች
በግብር የሚተላለፉ ትምህርቶች መሆናቸውን መዘንጋት
ይታይብናል። በአገራችን ያሉ ትንንሽ አማልክትን “ለአቅመ
ስሕተት አልደረሱም” በሚል ጉንጭ አልፋ ሙግት አማካይነት
እስከ ስኽተታቸው ለመታቀፍ መታገላችንም ይህንኑ አስረጂ
ነው።

495
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከዚህም ሲያልፍ፤ ጥቂት የማንባል ሰባኪያን፣ ነቢያትና


ዘማሪያን የቃል ዐዋጅ ላይ ትኩረት በማድረግ የሰውን ስሜት
በማነቃቃት ተጠምደናል። ሕዝቡ ልመናና ምልጃ
እንዳይለማመድ ማይክ ጨብጠን በኅሩይ ቃል ዐዋጅ
ጩህታችን ማደነቃቀፍን ተያይዘነዋል። በዚህም ምክንያት
ሕዝቡ የጸሎትን ምላሽ ወይም ትንቢትን እያንዳንዱን ሰው
መቅረብና መዳሰስ ከሚችለው ከመለኮት መጠበቅን እየተወ
መጥቷል። ለግል ጾሎትና ለቃል ጥናት ያለው ፍቅር ወርዷል።
የጸሎት መልስን በምንም የማይወሰኑ ባለስልጣናት
ከሚመስሉቱ አማልክት የአንደበት ዐዋጅ እንዲጠብቅ
አድርገነዋል። ይህም የዲበ-አካሉ ሃይማኖት ፍልስፍና
በክርስትና ውስጥ ያሉ አስተሳሰቦችን የሚቀርጽ መልክ
ማውጫ ሞልድ እየሆነ እንደመጣ የሚያረጋግጥ ነው።

በተጨማሪም ምንም እንኳ የእምነት ቃል አስተማሪዎችን


ነቅሰን የምንቃወምበትን ነጥቦች በመድረካችን ላይ
በተደጋጋሚ ብናሰማም ክፍተቶች ግን አሉብን። ምክንያቱም
በአንፃሩ ዲበ-አካላዊው ሃይማኖት ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር
የተጋባበትን የጸሎት ምላሽ መሠረታዊ ትምህርት
እናስተምራለን። ማለትም መጠኑ ይነስም ይብዛ፤ ታላቅ
እምነት ወይም መለኮታዊ እምነት፣ ኅሩይ ቃል ማወጅ፣
የእምነት ቃል፣ ዐዋጅን መደጋገም፣ ምናባዊ ምስልን ማየት

496
ጆንሰን እጅጉ

ለሚባሉና ይህንንም ለመሳሰሉ ልምምዶችንና ትምህርቶችን


በራቸንን ከፍት ነው። የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክት
የሚጠቀሟቸውን ጥቅሶች በተመሳሳይ ሁኔታ እስከ ሥነ-
አፈታት ችግሮቻቸው እንጠቀማለን። ነገር ግን ወዳጆች
ሆይ፤ ስሕተት የእምነት እንቅስቃሴ መሪዎች ሲናገሩትና
ሲላማመዱት ስሕተት እኛና የእኛ የምንላቸው ወይም
የምንወዳቸው ሰባኪያን ሲናገሩት ትክክል የሚሆንበት የስነ-
አመክንዮ ሕግ የለም። ስሕተት የትም ቦታ በማንም ቢነገር
ስኹትነቱን አይለውጥምና ልንነቅፈው ይገባል።

የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክት በሚጠቀሙበትና


በሚተረጉሙበት መንገድ የኅሩይ ቃል ዐዋጅን፣ የአዲሱ
ፍጥረት ጽንሰ-ዐሳብን፣ እምነትንና ስልጣን መተርጎማችን
አሳዛኝ ነው። በትምህርትና በጸሎት መርሃ ግብራችንም
በድርፍረት ስንለማመደው መታየታችን አንገት ያስደፋል።
በውጤቱም፤ የዲበ-አካል ሃይማኖት ልምምድ ልመናን
በዐዋጅ በመተካት ልዩ ጸሎትን በመካከላችን እስከ
ማስፋፋትት ቢደርስም የሚቆረቁረን ጥቂቶች ነን። የቃል
ዐዋጅ ልምምድ የዲበ-አካልም ይሁን የእምነት እንቅስቃሴ
ትምህርት ማዕከላዊና ዋና መርዛማ ሥር እንደመሆኑ መጠን
ልንደነግጥ በተገባን ነበር። ለዚህ ሁሉ ብክለት የዲበ-አካል
ሃደይማኖት መሪዎችና የእምነት ቃል ሰባኪያን ቀዳሚ ድርሻ

497
የአማልክቱ ዐዋጅ

ቢኖራቸውም የወንጌላውያን አማኞች ቤተ-እምነት


መሪዎችና ተከታዮችም መውሰድ ያለብንን ሰፊ ድርሻ መካድ
አንችልም። ስለሆነም ሳንዘገይ እራሳችንን በመፈተሽ ከዚህ
ሰንካላ ሃይማኖት ትምህርትና ልምምድ ማጥራት ይገባናል።
ይህንን ማድረግ ካልቻልን ግን በእምነት እንቅስቃሴ ደካማና
ቅይጥ ሥነ-መለኮት ፊት የምንቆምበት ዐቅም አይኖረንም።

ከእምነት እንቅስቃሴ ጀርባ ያለውን የዲበ-አካል ሃይማኖት


መመልከት አለመቻልም እንዲሁ አደጋ አለው። ምክንያቱም
የእምነት እነቅስቃሴን ከስሕተት ተርታ ለመመደብና
ወገባችንን አሸንፍጠን ፊት ለፊት በመሞገት ዐቅም
እንዳይኖረን ያደርጋል። ስለዚሀም በዚህ መጽሐፍ
የትምህርቱን ጀርባ ማየት የምንችልበትንና ከርተዑ ትምህርት
የተለየ እንደሆነ ማወቅ የምንችልበትን ዐቅም ለማሳደግ
በመጓጓት ሰፊ ጥረት ተደርጓል። በተጨማሪም የዲበ-አካል
ሃይማኖት ፍልስፍና ኢየሱስን እንደ ምሳሌው መውሰዱ
እንዴት በእምነት እንቅስቃሴ መሪዎች ዘንድ የማይሻክርና
ተስማሚ እንዲሆን እንዳስቻለው ለማሳየት ተሞክሯል።
ለዚህም የሚጋሯቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ተመልክተናለ፤ በዚህም የመጨረሻ ክፍል ይህንኑ በማስረገጥ
እንመለከታለን።

498
ጆንሰን እጅጉ

ቀደም ብለን እንዳነሳነው የኢየሱስ ምሳሌነት የሚወሰድበትን


ትርጓሜ ስንመለከት እንደ መለኮት በቃል ዐዋጃችን
እንፈጥራልን፣ እንፈውሳለን፣ እንወስናለን፤ ስለዚህም ደግሞ
በመለኮትነቱ እንመስለዋለን እስከሚል ጥግ ድረስ የሚዘልቅ
ነው። የእምነት እንቅስቃሴ ከዚህ የኑፋቄ ማረጋገጫ ማህተሙ
ባሻገር ከሚያስከትለው ውጤት አንጻር ስንፈትሸውም እንደ
ድመት እጅ በተደበቀ ጥፍሩ እየቧጨረ ያቆስላል። ማቁሰሉም
ለሞት የሚያደርስ እንጂ የዋዛ አይደለም። ምክንያቱም “ውሃ
ሲወስድ እያሳሳቀ ነው።” እንደሚባለው የሰውን ልጅ ከመለኮት
ጋር ካለው ኅብረት ቀስ በቀስ በመነጠል የውሃ ሽታ
ያደርገዋል። ይህ ውጤቱም መናፍቃዊነቱን አጋላጭ ነው።
ምክንያቱም እግዚአብሔርን ከመምሰልና ከፍጹም ሙላት ጉዞ
ማደናቀፍ የስኸተት ትምህርት መገለጫ ባሕርይ ነውና ነው።
ለዚህም መሠረታዊ ምክንያቱ የትምህርተ ክርስቶስን ርቱዕ
ሥነ-መለኮት ማፋፈለሱና ኢየሱስን ብቸኛና ምጡቅ መለኮት
መሆኑን መሸፈኑ ነው። እንዲሁ ሁሉ ትምህርተ ሰውንም
በማፋለስ የሰው ልጅን ወደ ምጡቅ መለኮትነት መድረስ
የሚችል ማንነት እንዳለው እንድንቆጥር እያዋዛ ማባበሉ
ሌላው መጋለጫው ነው። ከላይ እንደጠቆምኩትም ከዚህ
ትምህርት ጀርባ ያለው የዲበ-አካል ሃይማኖት ዋነኛ ማህተሙ
እንደሆነም መዘንጋት የለበትም።

ፊንሃስ ፓንክረስ ኪዊምቢ የኢየሱስን ልቀት ሲያረጋግጥ


“ይህንን እውነት ለዓለም በማስተዋወቅ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው

499
የአማልክቱ ዐዋጅ

ቢኖር ኢየሱስ ነው። እርሱ በምድር ላይ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ


ይልቅ የከፍተኛ ጥበብ ባለቤት ሆኗል።” እንዳለ ልብ ይሏል።348
ይሁን እንጂ ሰውዬው ኢየሱስን ያገነነው ሰውነትን
በተድበሰበሰ ስውር አካሄዱ ለማግነን እንዲያመቸው ስለፈለገ
ነው እንጂ የኢየሱስ ልቀት ገብቶት ሊያከብረው ነው ብሎ
ማሰብ ያስቸግራል። ምክንያቱም ይህን ‘እውነት’ በማለት
በስውር ብዕሩ የሚጠቁመው የዲበ-አካል ሃይማኖትን “ልዩ
የቃል ዐዋጅ” ጽንሰ-ዐሳብ ነውና ነው። እንዲሁ ሁሉ ኪኒየን፣
ሄገንም ይሁኑ ሃይሉ ዮሐንስ የመለኮት ዐይነት ነን፤
ክርስቲያኖች ‘ክርስቶስ’ ተብለዋል ማለታቸውን ልብ
ይሏል።349 የእግዚአብሔር ወዳጆች፤ እንዲህ ዓይነቱን
ትምህርትና ልምምድ ከኑፋቄ ከመመደብ ይልቅ “ጥቃቅን
ስሕተት” የሚል ስም በመስጠት የሚሸፋፍን ወይም የሚታገስ
ክርስትና ጤናማ ነው ብሎ ማሰብ የቸገረ አይደለም
ትላላችሁን?

ወዳጆች ሆይ፤ የጸሎትን ምላሽ ባለቤትን ከመለኮት ይልቅ


ለሰው አንደበት ከመሰጠ፣ የሰውነትን ሥነ-መለኮት ምልከታ
በማበላሸት በግልጽና በስውር “የክርስቶሳዊነትን” ዐስተሳሰብ
በከፍተኛ ደረጃ ከማስፋፋት የከፋ ምን የኑፋቄ ትምህርት
ይኖራል? አስተሳሰቡን ለሚያዳብሩ መሰል ፍልስፍናዎቹ
በአገራችን የእምነት ቃል እንቅስቃሴ ሰባኪያን ሳይቀር
348
The History of New Thought. (p,43).
349
ገጽ. 158 ይመለከቷል።

500
ጆንሰን እጅጉ

“መገለጥ” የሚል ትልቅ ስም ተሰጥቶታል። ይሁን እንጂ


ምንም የተለያየ ስም ቢሰጠውም ሙሉ ለሙሉ ከዲበ-አካል
ሃይማኖት የተሰረቀ ለክርስትና ባዕድ የሆነ ፍልስፍና ስለመሆኑ
ምንም ድርድር አይሻውም። ሥነ-መለኮቱን በክርስትና ውስጥ
ለማስረግና የቤተክርስቲያንን በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ወዝና
ጠረን ለማበላሸት እንዲያመች ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥቅሶች ቢመዘዙም በሙሉ የሥነ-አፈታት ችግር
እንዳለባቸው በዝርዝር የተመለከትን አይደለምን? ትምህርቱ
የሥነ-አፈታት ስሕተት የሚታይበት ቢሆንም በጥቂት
የወንጌል አማኞች ሰባኪያን ሳይቀር ትክክል እንደሆነ
የሚሞገትለት፤ አልፎም በመደበኛ ጉባኤዎች ላይ ስፍራ
በማግኘት የአደባባይ ልምምድ እስከ መሆን የደረሰ ነው።
ከዚህም ቋሚ አካሄዱ የተነሳ ታላቅ ኑፋቄ ስለሆነ በክርስትና
ርቱዕ አስተምሮ መሠረት ከጥቃቅን ስሕተት የሚቆጠረወና
በዋዛ የሚታለፍ ፈጽሞ አይደለም። ይሁን እንጂ
ተከራካሪዎቹም ሆኑ አብዛኛዎቹ የእምነት ቃል አስተማሪዎች
ትምህርቱን በዚህ ደረጃ በጥልቀት ስለማያውቁት
ልንራራላቸው ይገባል።

ቀደም ብሎ እንደተብራራው ርህራሄያችን እስከ ስኽተታቸው


ለማቀፍ ግን መሆን የለበትም። ርህራሄያችን ለጥናታዊ
መጽሐፍት፣ ተያያዥ ውይይቶችና ስልጠናዎች በር በመክፈት
ለግልጽ ሕዝባዊ ንስሓና ለውጥ ዕድል ለመፍጠር መሆን
አለበት። እርግጥም ለእውነት ራሳቸውን በመስጠት ሊመለሱ

501
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከወደዱና ኅብረታችንን ከፈለጉት የትምህርታቸውን ወልጋዳ


አካሄድ በግልጽ ማመን አለባቸው። ይህም መሠረታዊ ዕርማት
በመውሰድ መድረካቸውንም ሆነ ሥነ-መለኮታቸውን
አጽድተው እስከ ማሳየት ሊደርስ ይገባል።

በአጠቃላይ መለኮትን የምንመስልበትንና የማንመስልበትን


ምስጢር መገንዘብ ይገባል። ማለትም መለኮት የማይወሰንና
የማይታዘዝ መሆኑንና በአንጻሩ ደግሞ የአገልጋዮች መንፈሳዊ
ሥልጣንን ውስኑነት ወይም ጥገኝነት መገንዘብ አለብን።
ዕብራዊያን ለዐዋጅ ቃል የሚሰጡትና የዲበ-አካል ሃይማኖት
መሪዎች የሚሰጡት ትርጉም ልዩነት ምን እንደሆነ መለየት፣
የዲበ-አካል ሃይማኖት ለእምነት የሚሰጠውን ትርጓሜና
መጽሐፍ ቅዱስ ለእምነት የሚሰጠው ትርጉም ልዩነት ምን
እንደሆነ መለየት፣ የዲበ-አካል ሃይማኖት ለመገለጥና
ለእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠው ትርጉም ለእግዚአብሔር
ቃል ያለውን ባዕድነት፣ መሪነትን ከተጠያቂነት አንጻር
መረዳትና የዲበ-አካል ሃይማኖት የእግዚአብሄርን ቃል
የሚፈታበትን ስኹት አካሄድና የሃቲታዊ ሥነ-አፈታት ስልትን
መከትልን አስፈላጊነት መገንዘብ፤ ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር
የተዋሃደውን ዲበ-አካል ፍልስፍና መለየት የምንችልበትን
ጉልበት ለማግኘት ያስችለናል። ይህ እውቀት ዐይን ከፋች
በመሆንም የእምነት እንቅስቃሴን ከኑፋቄ ለመመደብም ሆነ
ከኑፋቄው ለመላቀቅና ለመጠበቅ እጅጉን ያስችለናል።

502
ጆንሰን እጅጉ

የእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ


“እኛ የታላቁ ፈጣሪ አዕምሮ መልክና ምሳሌ ነን። በተወሰነ
የአዕምሮአችን አፈጣጠር ልክ እንደ እርሱ ነን። በአዕምሮአችን
መስተካከል ልክ ኢየሱስ እንደ አደረገው የሕሊና አንድነት 350
እኛም መድረስ እንችላለን።” 351
አማልክት ቻርልስ ፊሊሞር።

“የዚህን እውነት ትርጉም ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲረዱ


እንዴት እመኛለሁ! ይህ ማለት እናንተ የእግዚያብሔር
ማንተት ካላቸው ምድብ ናችሁ።”352
አማልክት ክሪስ ኦያኪሂሎሚ

“አማልክት ነን!” የሚለው ሙግት መነሻ ምክንያትና መድረሻ


ትልም የሌለው ያልተደራጀ ክርክር አይደለም። “አማልክቱ”
ሲያነሱ እንደሚሰማው የዚህ ሙግት መነሻ የዘፍጥረት
መጽሐፍ የሰውን አፈጣጠር ሲዘግብ ባከለው ገላጭ ቃላት
ማለትም “በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር” የሚለው
እና (መዝ.82) ለሰው ልጆች የተጠቀመው “አማልክት ናችሁ”
የሚለው ገላጭ ቃል ነው። መድረሻ ትልሙው ደግሞ ሰው
350
ፊሊሞር ኢየሱስ ከአብ ጋር የነበረው አንድነት የሕሊና አንድነት ነው ይላል። እንደ
ፊሊሞር ከሆነም በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረው የሰው ዐቅል ቁሳዊ ሳይሆን
መንፈሳዊ ወይም መንፈስ ነው። በተጨማሪም ለፊሊሞር እግዚአብሔርም ልዕለ
አእምሮ ነው።
351
Charles Fillmore. Mysteries of Genesis. (1936, P,10).
352
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ። (ሚያዚያ 12፣ 2010) ።

503
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያለውን መለኮታዊ ዐቅም በማሳየት በቃሉ ኀይል


የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ለመፍጠር የሚችልበትን ዕውቀት
ማካፈል ነው። ይህንንም ትምህርት ልዩ ዲበ-አካላዊ
ገጽታውን በመሸፈን የክርስትና መልክ እንዲኖረው መሠረት
የጣለው ኪኒየን ቢሆንም ሄገን ብዙ ተከታይ ሊያፈራበት
ችሏል።353

ተካልኝ ሰውን መንፈስ ነው ወይም በእግዚአብሔር መልክ


የተፈጠረው መንፈሱ ነው የሚለው ትምህርት ሰውን
ከመለኮት እኩል ለማድረግ ታስቦ የሚደረግ እንደሆነ ካነሳ
በኋላ ይህንን ለማስረዳት ዊንስተን ቢልን ጠቅሷል።
ሰውየው የተጠቀመበትን ዓረፍተ ነገር ሲያጣቅስ፦
“በእግዚአብሔር መልክና አምሳል፤ በእርግጥም ለአዳምና
ለኛ ምን ማለት እንደሆነ አጽኖት ልስጥ። ትርጉሙ እኛ
የተሰራነው ልክ እንደ እግዚአብሔር እንድንቀሳቀስ ነው።”
354
ማለቱን አንስቷል። ተካልኝ በተሳለ ብዕሩ እንደጠቆመን
ከሆነ “የአማልክቱ” ሥነ-መለኮት ሰውን ወደ ተፈለገው
መለኮትነት ለማድረስ ተሰልቶ የተወረወረ ነው ማለት
ይቻላል።

ለዚህም ድፍረት “በጭራሽ፤ አማልክት አይደለንም!” የሚል


የተካረረ ምላሽ በመስጠት ማለፍ ቢቻልም “አማልክቱን”
353
በምዕራፍ አንድ ላይ “ኢ ደብልዩ ኪኒየን” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል።
354
የጸሎት ቤት የንግድ ቤት። (ገጽ፣ 182)።

504
ጆንሰን እጅጉ

ለማረምም ይሁን አንባቢን ለማነጽ ግን አይጠቅምም።


በተነሱት ጥቅሶች አስቸጋሪ አቀራረብ ላይ የልዩ ዲበ-አካሉ
ዐስተሳሰብ ተደምሮበት ብዙዎች ተቸግረውበታል። በዚህ
ንዑስ ርዕስ ሁለቱን መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ቀረብ
ብለን እንመረምራለን።

“ከአማልክቱ” ክርስቶሳዊነት ትምህርት በአንጻራዊነት


የአጥባቂ አማኞችን ምልከታ ስናነሳ “የሰው ልጅ አምላክ
ወይም አማልክት የመሆን ዕድል ፈጽሞ የለውም!” የሚል
መርሖ እናገኛለን። ይህንን እውነት ነው ብለን የተቀበልን
እኛ ታዲያ ሰው በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረበት
ምሥጢር ምንድነው? የሚለውን “የአማልክቱን” ጥያቄ
መመለስ ይገባናል። አስቀድሜ እንዳነሳሁት የዚህ ጥያቄ
ዋነኛ መነሾ የሰው አፈጣጠር ታሪክ እንደሆነ ይታወቃል።
“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን
እንፍጠር… እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው።” (ዘፍ.1:26-27)።
አማልክት ኪኒየን ይህንን ክፍል በመጥቀስና የተገለጠለት
በማስመሰል “በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረው የሰው
መንፈስ ነው።” ይበል እንጂ መጽሐፍትን ስንመረምር ግን
ይህንን ማረጋገጥ ፈጽሞ አንችልም።355

355
ሰው መንፈስ ነውን? ከገጽ. 79፣152፥157-158፥185-186፥249 ይመለከቷል።

505
የአማልክቱ ዐዋጅ

ተካልኝ በዚህ ክፍል ላይ የተጠቀሰውን ‘በእግዚአብሔር


መልክና ምሳሌ ሰው ተፈጠረ’ የሚለውን ቃል አንስቶ
ሲያብራራ የጥንታዊያን ህዝቦችና ነገስታት ባህላዊ የቃላት
አጠቃቀም ታሪካዊ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቷል። ይህንንም
ሥርው አድርጎ በሥነ-መለኮት አጥኚዎች ሰው
በእግዚአብሔር መፈጠሩን በተመለከተ የሚነሱ ሦስት
የሥነ-መለኮት ዕይታዎችን አስቀምጧል።
1. ሰው ከእግዚአብሔር የተካፈለውን ነፃ ፈቃድ፣ ግብረ
ገባዊነትና ምክንያታዊነት ያሳያል።
2. ከሌሎች ፍጥረታት በበለጠ ሰው ከአምላክ ጋር ኀብረት
ማድረግ የመቻሉን ዐቅም ያሳያል።
3. ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ገዥነትን (ምድርን
የማስተዳደር ስልጣን ያሣያል።356

ተካልኝ እንደጠቀሰው እንዲህ ዐይነት ታሪካዊ ጥናት


የአንድን ክፍል ዐሳብ በትክክል ለመረዳት አጋዥ እንደሆነ
አምናለሁ። ይሁን እንጂ ከታሪካዊ ጥናት በፊት ቃላቱ
በአውዳቸው ወይም በመጽሐፉ ውስጥ የተሸከሙትን ዐሳብ
ለመረዳት ማጥናት መቅደም አለበት የሚል እምነት አለኝ።
ይህም ሲሆን ከቃላት ፍቺው ጋር ታሪካዊ ጥናትና አውዳዊ

356
የጸሎት የንግድ ቤት?! (ገጽ. 89)።

506
ጆንሰን እጅጉ

ዳሰሳው በመደጋገፍና በመጣጣም የክፍሉን ዐሳብ በተሸለ


ሁኔታ እንድንረዳ ያስችሉናል።

እንደ እውነቱ ከሆነ የክፍሉን ዐሳብ ከመጽሐፉ ተነስተን


ለመረዳትና ትርጉም ላይ ለመስማማት ሁለቱ ቃላት
ማለትም ‘በምሳሌያችን’ እና ‘በመልካችን’ የሚሉቱ ቁልፍ
ቃሎች ክፍሉን ለመረዳት አስቸጋሪ ያደርጉታል።
ምክንያቱም እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ አካላዊ ቅርፅና
መልክ እንደሌለው ቢታወቅም ቃላቱ ቃላቱ ግን ከዚህ
በተቃርኖ ስለ አካላዊ መልክ፣ ቅርፅና ይዘት የሚያወሩ
ናቸውና ነው። የዕብራይስጥ ትርጉማቸውም ከዚህ ቁስ-
አካላዊ ትርጉም ውጪ ምንም አያሳይም። በተጨማሪም
ቃላቱ የመልክንም ይሁን የምሳሌነትን ገደብ ወይም
ውስንነት ዓያሳዩንምና ‘መምሰል’ን ‘አማልክት መሆን’ እስከ
የሚል የተለጠጠ ትርጉም ሊስጉዙ ይችላሉ። አማልክት
ኪኒየንም “በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረው የሰው
መንፈስ ነው።”357 በማለት ‘ሰው መንፈስ ነው’ ወደሚል
መቋጫ የተንጠራራው በዚሁ ቃላቱ በሚፈጥሩት ክፍተት
ምክንያት ነው። የሁለቱን ቃላት የቋንቋም ይሁን የመዝገበ
ቃላት ፍቺ የሚፈጥረውን ይህንን ውዝግብ ስንመለከት
አማልክቱ ለምን እንደሳቱ በመገንዘብ በልባዊ ሸክምና
ርህራሄ እንሞላለን እንጂ ደርሰን ለፍርድ አንቆጣም፦
357
ከገጽ 157 ይመለከቷል።

507
የአማልክቱ ዐዋጅ

 በምሳሌያችን ‫( הדגמה‬ዴሙት) ሞዴል፣ ቅርፅ


 በመልካችን ‫חולם‬ (ጼሌም) ተመሳሳይ፣
ዐይነት፣ ምድብ።

ቃላቱ በአንባቢው ዐቅል ውስጥ የሚፈጥሩት የትርጉም ግራ


መጋባትና እክል ግልጽ ነው። አውዳዊ አፈታትን ከመሰል
ችግር እንደ ማምለጫ መፍትሄ የሚጠቀም የመጽሐፍ
ቅዱስ ተማሪ እንኳ በዚህ መፈተኑ የማይቀር ነው። ይሁን
እንጂ የዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ አጠቃላይ አጭር የሰው
አፈጣጠር ዘገባም ሆነ የምዕራፍ ሁለት ዝርዝር አፈጣጠር
ዘገባ ዐውድ ሁለቱም ፈጣን መፍቻ የሚፈልግን ተማሪ
ሙሉ ለሙሉ ቃላቱን እንዲፈታ አያግዙትም። ስለዚህም
የልዩ ዲበ-አካል “አማልክትም” ሆኑ የእምነት ቃል
“አማልክት” የቃላቱን ቀጥተኛ ትርጉም በመውሰድና
ከ 2 ጴጥ.1፡4 ጋር በማገጫጨት “የእግዚአብሔር ዐይነት
358

ነን!” ወይም “በእግዚአብሔር ምድብ ውስጥ ነን!”359 የሚል


ፍቺ መስጠታቸው አወዛጋቢ ፍቺ ቢሆንም አማራጭ
በመሆን ይቀርብለታል። አማልክቱ ግን በዚህ ሳይቆሙ
“በልባችን ውስጥ ያለውን ነገር እንደ እግዚአብሔር በመናገር

358
በምዕራፍ ስድስት ላይ “አማልክታዊ ዘረ-መል” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር
ይመለከቷል።
359
በምዕራፍ ሦስት ላይ “መለኮታዊ እምነት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ይመለከቷል።

508
ጆንሰን እጅጉ

መፍጠር የምንችል አማልክት ነን!” በማለት ግርታውን


ያባብሰሱና እረፍት ያሳጡታል።

እንዲህ ዐይነት አሻሚ ቃል ሲያጋጥም ታዲያ በመሰለን


መንገድ ተርጉመን ወደ ቀለለን አማራጭ መንገድ ፈትለክ
ከማለት ይልቅ ቃሉን ወይም ክፍሉን ከአጠቃላይ የመጽሐፍ
ቅዱስ ዐውድ አንጻር መመርመርና “የአዲስ ኪዳን ጽሐፍትስ
እንዴት ነው የተረዱት?” ብሎ መጠየቅ ብልሀት ነው።
በተለይ ደግሞ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትን የአዲስ ኪዳን
ጽሐፍት እንዴት ነው የተረዱት ብሎ ማሰብ አግባብ ነው።
ምክንያቱም የአዲስ ኪዳን ጽሐፍት የብሉይ ኪዳን
መጽሐፍት ዕውቀት ነበራቸው። የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትን
ሲጽፉም የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትን ዐሳብና ቃላት
በተለያየ መንገድ ወስደው ተጠቅመዋል። በተጨማሪም ከኛ
ይልቅ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ለተጻፉበት ቋንቃና ባህል
ቅርብ መሆናቸውንም መዘንጋት የለብንም።

በመጀመሪያ ይህንን ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሞ


የምናገኘው ያዕቆብን ነው። ያዕቆብ “ምሳሌ” የሚለውን
ቃል ከዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ በቀጥታ ወስዶ የተጠቀመ
ብቸኛው የአዲስ ኪዳን ጸሓፊ ነው። ይሁን እንጂ ያዕቆብ
ቃሉን ለመረዳት የሚያስችለንን ምንም ዐይነት ፍንጭ
አይሰጠንም። “በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም

509
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች


እንረግማለን።” (ያዕቆ.3፣9)። በሌላ በኩል ግን የአዲስ ኪዳን
ጸሓፍት ‘ምሳሌ’ የሚለውንም ይሁን ‘መልክ’ የሚለውን
ቃል በመውሰድ በተለያየና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ
ተጠቅመውታል። የዘፍጥረቱን ቃላት የተጠቀሙበትን
ፍቺም በጠቀሱበት ዐውድ ወስጥ ፈልጎ መረዳት
የዘፍጥረቱን ቃላት የተረዱበትን ትርጉም ለመረዳት
የሚያስችል ጠቃሚ መንገድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የአዲስ ኪዳን ጸሓፍት ‘ምሳሌ’ የሚለውን ቃል ወኪል፣


አስተማሪ (አስረጂ)፣ ጽድቅ (ቅድስና)፣ ምስል (የአኗኗር ዘዬ)
፣ ዐዋቂ እና ሞዴል የሚል ትርጓሜ ባለው ዐውድ
ተጠቅመዋል። መልክ የሚለውን ቃል ደግሞ ምልክት፣
ሁኔታና ክብር የሚል አውዳዊ ፍቺ በመስጠት
ተጠቅመውታል። ‘ምሳሌ’ እና‘ባሕርይ’ የሚሉት ቃላት
ቀጥሎ በተዘረዘሩት ጥቅሶች ውስጥ የተቀመጡበትን
ትርጉም ያስተውሏል።

በምሳሌአችን

 ወኪል፦ “ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፣


እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ
በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና።” ሮሜ.8፡4።
‘በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ’ የሚለው ቃል ኢየሱስ

510
ጆንሰን እጅጉ

ኃጢያተኞችን እንደወከለ ያሣያል።ስለዚህም


‘ውክልና‘የሚል ትርጉም ይዟል ማለት ነው።

 አስተማሪ አስረጂ፦ “እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ


ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን።”1 ቆሮ.10፡6። ይህ
‘ምሳሌ ሆነልን’ የሚለው ቃል አስረጂ ወይም አስተማሪ
ሆነልን የሚል ትርጓሜ ይዟል።

 ጽድቅና ቅድስና፦ “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና


እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው
ልበሱ።” አፌ.4፣2 ። ‘ምሳሌ’ የሚለውን ቃል ‘ጽድቅና
ቅድስና’ በሚል ራሱ ስለተካው ለቃሉ የተሰጠውን ትሩጓሜ
መረዳት ቀላል ነው።

 ምልልስ ወይም የአኗኗር ዘዬ፦ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔን


የምትመስሉ ሁኑ፣ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ
እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ። ፊሊ.3፡17።
ምሳሌነቱን ‘ምልልስ’ በማለት ስለፈታው ለቃሉ የአኗኗር
ዘዬ የሚል ትርጓሜ እንደሰጠው ግልጥ ነው።

 ዐዋቂ፦ “የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን


ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።”
ቆላ.3፡10። ምሳሌነት ዕውቀት ከማግኘት ጋር በቀጥታ
ተነፃጽሯል። ስለዚህ ‘ምሳሌ’ የሚለው ቃል በእዚህ ክፍል
ላይ ዐዋቂነትን ጠቋሚ በመሆን ጥቅም ላይ ውሏል።

511
የአማልክቱ ዐዋጅ

 ሞዴል፦ “ስለዚህም በመቄጸዶንያና በአካይያ ላሉት


ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።” 1 ተስ.1፡7 ።

“ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ


እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፣ ያለ ስልጣን ስለ ሆንን
አይደለም።” 2 ተስ.3፡9 ።

“ስለዚህ ግን፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ


ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን ኢየሱስ ክርስቶስ
ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፣
ምህረትን አገኘሁ።” 1 ጢሞ.1፣16 ።

“ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም


በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፣
ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።” 1 ጢሞ.4፡12 ።

“ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኀይል


አትግዙ።” 1 ጴ.5፡3። የተዘረዘሩትን ጥቅሶች እንዳየነው
‘ምሳሌ’ የሚለው ቃል በስፋት የመልካም አንዋኑዋር
ማሣያ ወይም ሞዴል የሚል ፍቺ ለማሳየት ውሏል።

“በመልካችን”

 ምልክት፦ “በሕግም የዕውቀትና የእውነት መልክ ስላለህ


ሮሜ.2፡20። መልክ የሚለው ቃል እዚህ ጥቅስ ላይ
‘ምልክት’ በሚል ዐሳብ ሥራ ላይ ውሏል።

512
ጆንሰን እጅጉ

 ውበት፣ “የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና 1 ቆሮ.7፡31 ።


መልክ በማለት የተጠቀመው ውበትን ለማሳየት ነው።

 ክብር (ባሕርይ)፦ “ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ


ክብር እንለወጣለን።”2 ቆሮ.3፡18 ።

“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፣ ሁሉን


በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፣ ኃጢአታችንን በራሱ ካነፃ በኋላ
በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።” ዕብ.1፡3።

“እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር


ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር
አልቈጠረውም።” ፊሊ.2፡6። ሶስቱም ጥቅሶች ‘መልክ’
የሚለው ቃል ‘ክብር’ የሚል ትርጓሜ እንደያዘ ይስማማሉ።

 ሁኔታ፣ ምልክት፦ “የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን


ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።” 2 ጢሞ.3፡5 ። መልክ
የሚለው ቃል እዚህ ጥቅስ ላይ የመምሰል ሁኔታን ወይም
ምልክት ማሳየትን ለመግለጥ ውሏል።

ከእነኝህ ጥቅሶች ጋር ተመሳሳይ የቃላት አጠቃቀም


የተጠቀሰባቸው ሌሎች ክፍሎች ቢኖሩም ለእዚህ ጥናት ግን
የቀረቡት ጥቅሶች በቂ ናቸው።

513
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጠቃላይ ከጥቅሶቹ አዲስ ኪዳናዊ የቃላት ትርጉም


እንደምንገነዘበው፤ በዘፍጥረቱ ትኩረት ሳቢ ክፍል ውስጥ
የተጠቀሱትን ምሳሌና መልክ የሚሉትን ቃላት የአዲስ ኪዳን
ጸሓፍት በቀጥተኛ ትርጓሜያቸው ማለትም ‘ቅርፅ ተመሳሳይ፣
ዐይነት፣ ምድብ’ በሚል ፍቺ እንዳልተጠቀሙ መረዳት
እንችላለን ማለት ነው። ስለዚህም ሰው በእግዚአብሔር መልክ
የተፈጠረው መንፈሱ ነው አይደለም ነፍሱ ነው የሚለው
የኪኒየን360 ውዝግብም አያስኬድም። የእግዚአብሔር መልክ
በሰው መንፈስ ላይ ብቻ የሚንጸባረቅ ሳይሆን በሁለንተናው
ላይ የሚነጸባረቅ ባሕርይ ነው። ለዚህም ነው በሁለንተናችን
ማለትም በሥጋ በነፍስ በመንፈሳችን እግዚአብሔርን
የምናከብረው ወይም የምናመልከው (1 ተስ.5፡23)።

የእግዚአብሔር ምድብ ወይም “አማልክት” የሚለው ፍቺ


በአዲስ ኪዳን ጸሓፍት ፈጽሞ የማይታወቅና እንግዳ ነው።
ከላይ ያየናቸው የቃላት ትርጓሜዎች ሁሉ ችላ መባል
የሌለባቸው ከመዝገበ-ቃላት የተሻለ መልካም ፍቺ ማሳያ
ሲሆኑ፤ ከአጠቃላይ ከአዲስ ኪዳን ዐውድ አንጻር የተነሣንበትን
የዘፍጥረት ጥቅስ በተሸለ መንገድ ተርጉመን ለመረዳት
በእግዚአብሔር ክብር ምልክት ጽድቅ ወይም ቅድስና ሞዴል
ፈጠረው የሚል ፍቺ መውሰድ እንችላለን።

360
ገጽ 341 ይመለከቷል።

514
ጆንሰን እጅጉ

እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን ክብራችንንና ቅድስናችንን


እንዲያንጸበርቅ እንፍጠረው። እግዚአብሔርም ሰውን ለክብሩ ማሣያ
ፈጠረው፤ የእግዚአብሔርም የቅድስና እና የጽድቅ መልክት አድርጎ
በመፍጠር ምልክቱ አደረገው። (ዘፍ.1:26-27)። በደራሲው የተተካ።

ሥለዚህ ‘ምሳሌ’ የሚለውም ሆነ ‘መልክ’ የሚለው ፍቺ


ሞዴል፣ ምልክት፣ ሁኔታ፣ ወኪል፣ ቅድስና ጽድቅ፣ የኑሮ ዘዬ
የሚሉቱ፤ ሰው መለኮትነትን እንደተካፈለ የሚያሳዩ በጭራሽ
አይደሉም። ሰው የተሰራበትንና የተዋቀረበትን ንጥረ-ነገር
ለማሳየት የተቀመጡም አይደሉም። ከዚህ ይልቅ ሰው
የተፈጠረበትን ዐላማ የሚጠቁሙ ናቸው። በአጠቃላይ ሰው
በአኖኖር ዘየው ወይም ባሕርይው ቅድስናን በማንጸባረቅ
ለመለኮት ሞዴል እንደሆነ የሚያሳዮ ናቸው።

ይሁን እንጂ ከዘፍጥረት ምዕራፍ ሦስት በኋላም ይህ መልክና


ምሳሌነት እንደተበላሸ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ኪኒየን
እንደሚለው ግን ‘ሰው በውድቀት ምክኒያት መንፈሱ ነው
የተበላሸው’ በማለት የሰውን ሁለንተና መነጣጠል ፈጽሞ
የማይቻል ነው። በውድቀት ምክንያት የተበላሸው የሰው
ሁለንተና ነው። መታደስና መዋጀት ያለበትም ሁለንተናው
ነው እንጂ መንፈሱ ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ
ይህንን የተበላሸ መልክ ለማደስ ሁለንተናዊ ሰውነትንና
የእግዚአብሔርን መልክና ምሳሌነት በመያዝ ወደ ምድር

515
የአማልክቱ ዐዋጅ

መምጣቱንም ያስተምረናል። በዚህም ተልዕኮ ኢየሱስ


የተሳካለት ሊሆን ችሏል።

ከዚህም በመነሣት የኢየሱስን ሞዴልነት እንድንከተል የአዲስ


ኪዳን ጸሓፍት ሲመክሩ፤ ወደ ክርስቶሳዊነት እንድናድግ
እየጠቆሙን ሳይሆን የእርሱን የኑሮ ዘዬ ቅድስና እና ጽድቅ
እንድንከተል እያሳሰቡን ነው። ለምሳሌ ሐዋርያው ጳውሎስ፦
“ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር
ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” (ኤፌ.4፡24)።
በማለት አስፍሯል። ሐዋርያው በቆሮንጦስ መልዕክቱም
የቆሮንጦስ አማኞችንም የኑሮ ዘዬ ወይም ባሕርይ መበላሸትን
ተከትሎ ብዙ ከመከረ በኋላ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል
እኔን ምሰሉ።” ይላቸዋል 1 ቆሮ.11፣1። በአንጻራዊነት
ስለአምላክነቱ ግን እግዚአብሔርን የሚመስለው እንደሌለ
መጽሐፍት ደመቅ አድርገው ይጮኻሉና መለኮት ምሳሌና
መልክ የለውም።

በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር


ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር
ታስተያዩኛላችሁ? እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም
ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤
በፀሓይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም
ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፣ አንተ ግን

516
ጆንሰን እጅጉ

አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ


ማንም የለም። (ኢሳ.45፡5፣ 46፡5)።

አማልክት አደለንም!
ሰው በአፈጣጠሩ መለኮት ካልሆነ ለምንድነው ታዲያ
መዝሙረኛው “አማልክት ናችሁ” የሚለው? የሚል ጥያቄ
ማንሳት አግባብ ነው። አማልክታዊያኑ ይህ ጥቅስ እጅግ
እንደሚጎትታቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ ‘አማልክት’
የሚለው ቃል በአውዱ ውስጥ ያለው ፍቺ እነርሱ እንደሚሉት
ሳይሆን ‘ፈራጅ’ የሚል ትርጉም ነው ያለው። በዚህ ቦታ ላይ
“አማልክት” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት የእስራኤልን
ፈራጆች በትልቅ ስም ሊሰይማቸውና ሊወቅሳቸው ስለፈለገ
ብቻ ነው። ይህም የተሰጣቸው የፍርድ ሥራ የላቀ እንደሆነ
ለማሳየት የተደረገ ነው። በዚህም መሠረት “አማልክት”
የሚለውን ሥያሜያቸውን ግብራቸው እንደማይመጥን
በማሳየት መልሶ ወቅሷቸዋል።

መውቀስም ብቻ አይደለም ነገር ግን ፍርድ ውስጥ


እንደሚወድቁም ይጠቁማል። “እግዚአብሔር በአማልክት
ማኅበር ቆመ፣ በአማልክትም መኻል ይፈርዳል።” (መዝ.82፡
1)። የዚህ ፍርድ ምክንያትም እነኝህ ፈራጆች የሐሰት ፍርድ
ማድረግና ችግረኛና ድሆችን መግፋታቸው ነበር። “እስከ መቼ

517
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሐሰትን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼስ ለኃጢአተኞች ፊት


ታደላላችሁ?”(82፡2)። ካለ በኋላ በቍጥር አምስት ላይ “እኔ
ግን” በማለት ይጀምራል። ይህም የሚያሳየን “አማልክት”
ወይም የልዑል ልጆች ቢባሉም በግብራቸው በተሰጣቸው ስም
ልክ አለመገኘታቸውንና በተቃራኒው መዋላቸውን ነው።

“እኔ ግን፦ አማልክት ናችሁ፣ ሁላችሁም የልዑል ልጆች


ናችሁ።” ይላቸዋል። (መዝ.82:6) ። ስለዚህም ወቀሳው ‘እኔ
አማልክት” ብላችሁም እናንተ ግን ”አማልክት” (ፈራጅ) መሆን
አልቻላችሁም’ የሚል ውስጠ ወይራ መልዕክት ይዟል።
በመጨረሻም የአማልክት አምላክ በግብራቸው ላይ
ስለሚፍርድ፦ “ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ
አልሁ።”(82፡7) በማለት ያረዳቸዋል። በተጨማሪም
“አማልክት” የሚለው ቃል ከዚህ በፊት የማይታወቅና እንገዳ
ቃል እንዳልሆነም ልብ ይሏል። ቃሉ በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት
ውስጥ በሦስት የተለያዩ አውዶች ወይም ፍቺዎች ሥራ ላይ
ውሏል።

 ለጣዖት፦ የሐሰት አምላክ እንደሆኑ ለማመልከት።

 ለሰው ልጆች፦ ዳኝነትን ለማመልከት።

 ለእግዚአብሔር ፦ኃያል ፈጣሪ መሆኑን ለማመልከት።

518
ጆንሰን እጅጉ

ስለዚህ ስኹት የሚሆነው የእምነት እንቅስቃሴ “ዐዋቂዎች”


‘አማልክት’ የሚለውን ቃል መጠቀማቸው ሳይሆን
የተጠቀሙበት ዐውድ በሶስተኛው ዐውድ አጠቃቀም
ማለትም የእግዚአብሔርን ኃያል ፈጣሪነት በሚያመለክተው
ዐውድ ሰውነትን በመክተት በመጠቀማቸውና እራሳቸውን
በመለኮት ምድብ ውስጥ በማስገባታቸው ነው። አማልክት
የሚለውን ስያሜ ‘ዳኞች’ ወይም ‘ፈራጆች’ ነን በሚል ዐውድ
ቢጠቀሙበት ትክክል በሆኑ ነበር። ይሁን እንጂ ከዚህ ይልቅ
“አማልክት አደላችሁም” በማለት ሊሞግታቸው የሚወድ ሰው
ሲያጋጥማቸው፤ ኢየሱስ አይሁድን በተከራከረበት ሁኔታ
መከራከር ይመርጣሉ። ይሁን እንጂ እዚህም ላይ ኢየሱስ
የተጠቀመበትንም መንገድ ቢሆን እንደ ሳቱት ይታያል።

ሐዋርያው ዮሐንስ እንደዘገበው ኢየሱስ “እኔና አብ አንድ ነን”


ስላለ አይሁድ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱበት። ኢየሱስ ግን
“ስለየትኛው ሥራዬ ነው የምትወግሩኝ።” በማለት የዐሳብ
አቅጣጫቸውን ለመቀየር ጥያቄ አቀረበላቸው። አይሁድ ግን
የመጡበትን መስመር ሳይለቁ እራሱን በአምላክ ክብር
ማስተካከሉ እንዳስቆጣቸው ነገሩት። ኢየሱስ ግን ‘ስለ
የትኛው ሥራዬ?’ በማለት መጠየቁ እራሱን ከአብ
ማስተካከሉ፤ እነርሱ እንደሚሉት በቃል ወይም በንግግሩ
ሳይሆን በሥራው ስለ ነበረ ነበር። በመቀጠልም ከመጡበት

519
የአማልክቱ ዐዋጅ

መስመር መውጣት እንዳልፈለጉና ግትሮች እንደሆኑበት


ሲመለከት፤“መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን
የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው…”
በማለት ፈጥኖ ፊቱን ወደ መዝሙረኛው ዳዊት ሙሉ በሙሉ
በማዞር መሞገት ይመርጣል።(ዩሐ.10:35)።

ኢየሱስ ይህንን ያደረገበት መሠረታዊ ምክንያት እነርሱ


እንደመሰላቸው ስለ እራሱ በሚሰጠው ምላሽና
በመዝሙረኛው መኻል የቃለት ዝምድና ስለነበር ግን
አልነበረም። ይልቁንም የዐውድ ዝምድና ስለ ነበር ነው።
በመዝሙረኛው የሰው ልጆች “አማልክት” የተባሉት ስለ
ማንነታቸው ወይም ስለ ተፈጥሯቸው ሳይሆን ስለ ግብራቸው
ነበር። እንዲሁ ሁሉ ኢየሱስም በማንነቱ ከአብ ጋር
የተስተካከለ ቢሆንም ለአይሁድ ግን እየነገራቸው የነበረው
ከማንነቱ አንጻር ሳይሆን ከመልካም ሥራው አንጻር ከአብ
የተስተካከለ መሆኑን ነው። ይህንንም አስቀድሞ ‘ስለ የትኛው
ሥራዬ?’ በማለት የጠየቃቸው ጥያቄ አመልካች ነው።
በአጠቃላይ መዝሙረኛውም ይሁን ኢየሱስ “አማልክት”
የሚለውን ቃል ያዋሉት ዐውድ ስምምነት ሲኖረው፤ ግብርን
እንጂ ማንነትን አያመለክትም።

እንግዲህ ከዘፍጥረት ጀምረን እስከ ራዕይ መጽሐፍ ድረስ


ስንመረምር ሰው የአማልክትነት ማንነት ወይም አፈጣጠር

520
ጆንሰን እጅጉ

እንዳለው የሚያሳየን ክፍል አናገኝም። ተካልኝ ይህንን


በማስመልከት አስተያየቱን ሲያሰፍር፦ “ሰው በእግዚአብሔር
መልክ መፈጠሩ እውነት ቢሆንም በምድቡ ፍጥረት እንጂ
አምላክ (ፈጣሪ) አይደለም።” 361
ብሏል። በርግጥም
አምላክትነት ፈጣሪነትን መጠየቁ ዕሙን ነው። ስለዚህ በዚህ
መንገድ ሥነ-መለኮታዊ ትርጉሙን በማዛባት ሰው መለኮታዊ
ተፈጥሮ ወይም መደብ እንዳለው አድርጎ የኅሩይ ቃል ዐዋጅ
አስተምህሮን መሬት ለማሲያዝ መሞከር ዕርባና የለውም።
በግልጽ ቃል ለማስቀመጥ ሰውን “አማልክት” ለማድረግ ወይም
ወደ ክርስቶሳዊነት ለማሳደግ የሚጥር ትምህርት ፈጽሞ
ቅቡልነት የሌለው ወደ ለየለት አዘቅት የሚጥል ድንቁር
ጨለማ ነው። ሰዎች እንጂ በመለኮት ምድብ የምንመደብ
“አማልክት” እንደሆንን ይህ ክፍል በጭራሽ አያመለክትም።

ገደብ የሌለው ሥልጣን


የዲበ-አካል ሃይማኖት “አማልክት” መለኮት በቃሉ ስልጣን
መሥራቱ አስጎመጅቷቸዋል ማለት ይቻላል። ወደ እዚህ ጣራ
ለመድረስ የተፈጠረባቸው ጕጕት ትምህርተ ሰብዕንና
ትምህርተ መለኮትን በማፋለስ በምድርና በሰማይ መኻል
ስንኩል ደረጃ አዘርግቷቸዋል። የተከተሉት መላ ምት
ለሃይፖተኒዝምና ለአኒማል ማግኔትዝም መናፍስታዊ
361
የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! (ገጽ. 134)።

521
የአማልክቱ ዐዋጅ

ልምምድ በማጋለጥ መንገድ ላይ አስቀራቸው እንጂ


አንዳቸውም “አማልክት” አልሆኑም። የእምነት ቃል
ሰባኪያኑም ይህንኑ ትምህርት በመከተላቸውና
ከተፈጠረባቸው የኀይል ጥማት የተነሣ ከመናፍሱቱ ስውር
እጆች ጋር ተነካክተዋል። በምኞታቸውም ርቀው በመሄድ
“አንገደብም! አንወሰንም!” የሚል የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ሞፈክር
አስተጋብተዋል። ለትምህርታቸውና ለልምምዳቸውም
ሥርው የመለኮትን ምሳሌነት እንከተላለን በማለት በጥቅስ
ለመደገፍ ሙከራ አድርገዋል። ይሁን እንጂ የመለኮት ባሕርይና
ስልጣን የሆነው ሁሉ ለሰው ምሳሌ መሆን አይችልምና
መቆሚያቸው ማሣኒ፣ ስኬታቸው ውድቀት ነው።

ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠሩት በአጥናፈ ዓለም


ውስጥ በቃል የሚንቀሳቀስ ልዩ ዐቅም ስላለ ሳይሆን
እግዚአብሔር ፈጣሪ ስለሆነ ነው። “እርሱ የሁሉ ፈጣሪ
ነውና።”(ኤር.16፡10)። ይህም የመለኮት የመፍጠር ባሕርይ
ስልጣን የቃልን ኀይል በመለማመድ የማንደርስበትና ልንጋራ
የማንችለው የመለኮት ብቻ የሆነ ባሕርይና ስልጣን ነው።

አፅንዖት ስንሰጥ፤ መለኮት ዓለምን የፈጠረበት ስልጣን ለሰው


ልጆች “የመፍጠር ዐቅም” ሞዴል መሆን አይችልም።
‘እግዚአብሔር በፍጥረት ልደት ለመፍጠር እንደተናገረ
እንናገራለን።’ በማለት የዘፍጥረትን መጽሐፍ በመጥቀስ

522
ጆንሰን እጅጉ

የተሳሳተ የቃል ኀይል ግንዛቤ ዐግቶ መነሳት የመለኮትነትንና


ሰውነትን ምንነት አለማወቅ ችግር ሲሆን። በተጨማሪም
ፈጽሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥነ-አፈታት ባልተከተለ መሠረት
ላይ የቆመ ትምህርት ነው።

በዚህ መጽሐፍ ላይ ለማስረዳት እንደተሞከረው አዲስ


ፍጥረት የሚለው ጽንሰ-ዐሳብ የድነትን ምሥጢር ለማስረዳት
የዋለ ነው። የቃልን የመፍጠር ኀይል ለመጠቀም የሚያስችለን
የተለየ ተፈጥሮ ያለን “አማልክት” እንደሆንን አያስረዳም።
በዳግም ልደት አማካይነት ክርስቶሳዊነትን የተጎናጸፍንበት
የማንነት ሽግግር እንዳለም በጭራሽ የሚያሳይ አይደለም።

በአጠቃላይ “መንፈሳዊ ሥልጣን” ገደብ የሌለው የቃልን ኀይል


መጠቀም የሚያስችል መንፈሳዊ ወይም የአዕምሮ ክህሎት
አይደለም። መንፈሳዊ ስልጣን ለማዘዝና ለመግዛት
የሚያስችል ከአምላክ የሚሰጥ ሥጦታ እንደሆነ ቅዱሳት
መጽሐፍት ይስማማሉ። “ሁሉም፦ ይህ ምንድር ነው?
በስልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም
ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው? ብለው
እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።” (ማር.1፡17)። በዚህ ንግግር
ውስጥ እንደምንረዳው በጥንታዊያን አይሁዶች መንፈሳዊ
ስልጣን ቢታወቅም ገደብ ያለው ነው። ይኸውም የስልጣን
ገደብ የአይሁድን ሕዝብ መናፍስትን ለማዘዝ እንኳ ያላደረሰ

523
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነበርና ኢየሱስ መናፍስትን በማዘዝ ሲያስወጣ ይደነቁበት


ነበር። (ሉቃ.4፡36)።

የኢየሱስ ትዕዛዝ ከመናፍስቱ ጋር ተግባቦትን በመፍጠር


እንዲታዘዙት አድርጓል። ምክንያቱም መናፍስቱ የማዘዝ
ስልጣን እንዳለው አውቀው ነበር። “እርሱም፦ የናዝሬቱ
ኢየሱስ ሆይ፣ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን?
ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፣ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ
ጮኸ።”(ማር.1፡24፣5፡7-13)። ይህም ቢሆን የኢየሱስ ስልጣን
በተግባቦት የሚሠራ ብቻ ሳይሆን መናፍስቱ ለመታዘዛቸው
ወይም ለመውጣታቸው አስገዳጅም ነበር። ለዚህም ንቁ
የመንፈስ ቅዱስ ኀይል አብሮት ይንቀሳቀስ እንደነበር
እናያለን። “እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ
ከሆንሁ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ
ደርሳለች።” (ሉቃ 11፡20)።

ከካህናት ወገን የሆኑ አንዳንዶች ደግሞ ከመደነቅ ይልቅ


የሥልጣኑን ምንጭ በመጠየቅ ተከራክረውታል። ምክንያቱም
ኢየሱስ ለማስተማርም ሆነ ለመፈወስ ይጠቀምበት የነበረው
ስልጣን ታላቅና የተለየ ወይም ከዚህ በፊት ያልታየ ስለ ነበር
ነው።“በምን ስልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ስልጣን ማን
ሰጠህ?” ይሉታል (ማር 1፡27፣ ማቴ.21፡23)። አይሁድ ይህንን
ሲጠይቁ በምክንያት ነው። ኢየሱስ ሥልጣንን በቤተመቅደስ

524
ጆንሰን እጅጉ

ወይም በካህን እጅ ስላልተቀበለም ጭምር ተደናግረዋል።


ኢየሱስ የሥልጣኑ ምንጭ ወይም ዕውቅና ከሰው ወይም
ከመቅደስ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሊነግራቸው ቢፈልግም ይህ
ግን ሳይስማማቸው ቀርቷል።

ኢየሱስ አይሁድ ባይቀበሉትም በሙሉ ድፍረትና ገደብ


በሌለው ስልጣን ከመሥራት የሚከለክለው ምንም ነገር
አልነበረም። ማቴዎስ ይህንኑ የኢየሱስ ሙሉ ስልጣን ሲገልጥ
“ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ስልጣን ሁሉ
በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።” በማለተ አስቀምጧል።
(ማቴ.28፡18) ። በርግጥም ኢየሱስ በአጥናፈ ዓለም ውስጥ
ያለውን ስልጣን በሙሉ ጠቅልሎ ይዟል። ይህንን እውነት
የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት በወጥነት ሳያወላዱ አስቀምጠዋል።
እንዲህ ዓይነቱ ወሰን የሌለው ስልጣን በሰው ላይ መንጸባረቁ
ለአይሁድ አዲስና እንግዳ ሲሆን በጭራሽ ሊቀበሉትም
የማይችሉት ነው። (ማር፡2፡10 ማር.5፡2-15፣ ማቴ.8፡27፣9፡
8)።

ለምሳሌ አይሁድ የመግደልና ነፍስን የመውሰድ፤ ሕይወትን


የመስጠትና ከሞት የማስነሳት፤ የመፍረድና የፍጻሜ ድንጋጌ
የማድረግ የአብ መለኮታዊ ስልጣን ብቻ እንደሆነ ያምናሉ።
ይሁን እንጂ ኢየሱስ በነፍሱ ላይ ስልጣን እንዳለው
ያሳውቃቸዋል። “እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም

525
የአማልክቱ ዐዋጅ

አይወስዳትም። ላኖራት ስልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት


ስልጣን አለኝ ይህችን ትዕዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።” (ዩሐ.10፡
11)። ሕይወት እንደሚሰጥ ወይም ሙታን በእርሱ
እንደሚቀሰቀሱ ይነግራቸዋል። “ልጅንም አይቶ በእርሱ
የሚያአምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ
ፈቃድ ይህ ነው፣ እኔም በመጨረሻው ቀን
አስነሣዋለሁ።”(ዮሐ.6፡40)። እንደሚፈርድም ጭምር
ይነግራቸዋል። “የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ስልጣን
ሰጠው።” (ዮሐ. 5፡27)።

በአጠቃላይ ኢየሱስን በስልጣን ሊደርስበት ወይም


ሊስተካከለው የሚችል ፈጽሞ የለም። የመጨረሻው የሰው
ልጆች ዕጣ ፋንታም የሚወሰነው በእርሱ ነው።
“በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት።” (2 ጢሞ.4፣1)። በአጠቃላይ
ኢየሱስ እርሱ እንደተናገረው ሕይወቱም ሆነ ሥልጣኑ ጥገኛ
ያልሆነና መለኮታዊ ወይም አምላካዊ ነው።

በአንፃሩ የአማኝ ሕይወት ግን ጥገኛ ሕይወት ነው። ከእኛ


በራሱ ሕይወት ያለው ወይም የበቃ ማንም የለም። ኢየሱስ
ግን ህይወቱ ጥገኛ እንዳልሆነ ሁሉ ሥልጣኑም ጥገኛ
አይደለም። “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ
ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና። የሰው

526
ጆንሰን እጅጉ

ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ስልጣን ሰጠው።”(ዮሐ.5፡


27)።ስለዚህም ኢየሱስ በደረሰበት ከፍተኛ የሕይወት ደረጃ
ላይ እደርሳለሁ፤ የመለኮትንም ገደብ የሌለው ስልጣን
እለማመዳለሁ ብሎ ማሰብ የቀን ቅዠት ነው። ገደብ
የሌለውና ጥተገኛ ያልሆነ በራሱ የሚሠራ ስልጣን ያለው
መለኮት ብቻ ነው። ለዚህ ነው ዝቅ ብለን የምንሰግድለት፤
ልባችንን የምናስገዛለት።

ጥገኛ ሥልጣን
ኢየሱስ ልዩ የሚያደርገው በራሱ ያልተገደበ ሥልጣንን ስላለው
ብቻ ሳይሆን ሥልጣንን መስጠት መቻሉም ነው። “አሥራ
ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት
ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኀይልና ስልጣን ሰጣቸው።”
(ሉቃ.9፡1)። ይህ ስልጣን በትዕዛዝ ቃል የሚገለጥ ሲሆን
የሚሠራው ከስልጣኑ ባለቤት ጋር ባለ የማያቋርጥ ግንኙነትና
ቁጥጥር ስለሆነ ጥገኛ ስልጣን ነው። የስልጣን ሰጪውን ንቁ
ዕውቅናና የኀይል ድጋፍ ይፈልጋል። “እነርሱም ወጥተው
በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፣ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፣
በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።” (ማር.16፡20)።
በውክልና ወይም ከታላቁ ባለ ስልጣን ጋር አንድ ላይ
በመስማማት ወይም የማያቋርጥ ኅብረት በመፍጠር የሚሠራ
ስልጣን ነው እንጂ በራሱ ምንም ማረግ አይችልም። ስለዚህም

527
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነው አገልጋዩ ከመለኮት ጋር ያለው ኅብረት እንደተቋረጠ


ጠቋሚ የሆነ የሕይወትም ይሁን የትምህርት ልምምድ
ስንመለከት የሚሠራበትን መንፈስ ጤናማነት መጠራጠር
የሚያስፈልገው።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በእርሱ የተወሰኑና ጥገኞች


መሆናቸውን በምሳሌ ሲያስረዳ ቅርንጫፍ ከግንዱ ጋር ያለው
ግንኙነት ከተቋረጠ ፍሬ ማፍራት አይችልም የሚል አመክኒዮ
አቅረቧል።“እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ
አትችሉም።”(ዮሐ.15፡4)። ምንም ዐይነት ታላቅ መንፈሳዊ
ስልጣን የሚባል ቢኖር እንኳ ወደ ክርስቶሳዊነት በማደግ
የሚገኝና በመለኮት ላይ ጥገኛ ያልሆነ ስልጣን ሊሆን
አይችልም። የተሰጠን መንፈሳዊ ስልጣን ኢየሱስ በከፈለው
ዋጋ ምክንያት የተቀበልነው የጸጋ ስጦታ ሲሆን በአብ ስልጣን
የማድረግ ዐቅምና ፈቃድ በጥገኝነት የሚሠራ ነው። ይህንን
ባህርይ የማያሣይ አሠራር የመለኮት ምስክር የሌለውና በጌታ
ቃል ያልተረጋገጠ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስም በእርሱ ያለውን ስልጣን የማድረግ


ምሥጢር ምን እንደሆነ ሲያስረዳ “በመንፈስ ቅዱስም ኀይል
በእኔ አድርጎ ከሠራው በቀር ምንም ልናገር
አልደፍርም።”(ቆላ.1፡29፣ ሮሜ.15፡9) ይላል። ይህም
መንፈሳዊ ስልጣን ባለቤትና ገዥ እንዳለው ይጠቁመናል።

528
ጆንሰን እጅጉ

ከጌታ የሆነ ስልጣን መናፍስትን ለማስወጣትና በሽተኛ


ለመፈወስ የተሰጠ ቢሆንም በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም
ነገር ማድረግ ግን የሚያስችል እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል።
በአጠቃላይ መንፈሳዊ ስልጣን በማንኛውም ቦታና ሰዓት
በመገኘት ፈጣን ሆኖ ሊሰራ በሚችል በመለኮት ፍቃደ ኀይል
የሚሠራ እንጂ በሰው ተፈጥሮአዊ ቃል ኀይል የሚሠራ
አይደለም። በሰው ፈቃድ ውስጥ እንጂ በሰው ፈቃድ
የሚሠራም አይደለም። ቅዱሳት መጽሐፍት ፍቃዱን እንጂ
ፍቃዳችንን ልንፈጽም ዐርነት እንዳለን አያሳዩንም። በኢየሱስ
የፈውስ ልምምድ እንኳ ሳይቀር ይህ ታይቷል።

“ከእርሱም ኀይል ወጥቶ ሁሉን ይፈውስ ነበርና ሕዝቡ ሁሉ


ሊዳስሱት ይሹ ነበር።”(ኤፌ.1፡11)። ይህንን ቃል ስንመለከት
‘እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ።’ እንደሚል ከኢየሱስ
የወጣው ኀይል በኢየሱስ ሰብአዊ ትዕዛዝና ፈቃድ ሳይሆን
በልዕለ መለኮት ዕውቀትና ፈቃድ የወጣ እንደሆነ
እናስተውላለን። የሴቲቱን መቸገርና በእምነት የኢየሱስን
የልብስ ጫፍ መንካት የተመለከቱ የመለኮት ዓይኖች በስፍራው
ላይ እንደነበሩ መካድ አይቻልም። ምንም እንኳ ኀይል
የተሰጠን ቢሆንም እንደቤታችን ኤሌክትሪክ በቁጥጥራችን
ሥር የምናደርገው፤ ስንፈልግ የምናበራውና የምናጠፋው፤
እንደፈለገን የምንጠቀምበት እንዳልሆነ ልናውቅ

529
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይገባል።(ሉቃ.6፡19፣ሐዋ 1፡8፣6፡8)። በአጠቃላይ መለኮት


በባሕርይው ሉዐላዊ ፍቃዱንና ሥልጣኑን ለፍጥረቱ አሳልፎ
እንደማይሰጥ ልናውቅ ይገባል።

ድፍረትን የሚያኮስስ ሥልጣን


በጸሎት ጉባኤዎች ላይ ምዕመኑ ወደ አገልጋዮ ተጠግቶ
ለአገልጋዮ ለመጸለይ የማይደፍረው ለምንድነው? የሚል ጥያቄ
ማንሳት ተገቢ ነው። ምዕመኑ የመንፈሳዊ ሥልጣኑን ማነስ
በማሰብ “ውኃ ወደታች እንጂ ወደ ላይ አይፈስም።” በሚል
አመክኒዮ ተጠፍሯል። እንደ እውነቱ ከሆነ በየጸሎት ጉባኤው
ለቤተክርስቲያን መጋቢዎችና ነቢያት እጅ ጭኖ ለመጸለይ
ይቅርና ወደ ተንበረከኩበት ዙፋን መሳይ ወንበራቸው ቀርቦ
ለመንበርከክ የሚደፍር ምዕመን ብዙም አይታይም። እንደዚህ
ለማድረግ የሚደፍር ምናልባት ቢገኝ ፊታቸው
ስለሚገፈትረውና እንደነውረኛ በመቁጠር ስለሚሳሳቁበት
ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ አያደርገውም። ዳሩ በህዝባቸው ላይ
እጃቸውን መጫን ሱስ የሆነባቸው አገልጋዮች የምዕመናቸው
የጸሎት እርዳታ ይናፍቃቸዋል ብሎ ማሰብሕልም ነው።

በአንድ ወቅት በቤተክርስቲያኔ ውስጥ በሚዲያ ክፍል


የሚያገለግል አንድ ወጣት እንዲጸልይልኝ ስጠይቀው በጥያቄዬ

530
ጆንሰን እጅጉ

እንደተገረመ አስታውሳለሁ። እዲጸልይልኝ ለማድረግ ብዙ


መከራከርና ማግባባት ነበረብኝ። የወጣቱ መከራከሪያ“አንተ
ለኔ ትጸልያለህ እንጂ እኔ እንዴት ላንተ እጸልያለሁ?” የሚል
ነበር። በመጨረሻ ግን መግባባት ችለን ነበርና ጸልዩልኝ ጸጋን
ተካፍዬ ተለያይተናል። በመንፈሳዊ ስልጣን ልቀት በማመካኘት
የወንድሞችንና የእህቶችን የጸሎት ድፍረት የሚገዳደር
አመለካከት የውድቀታችን አመለካች ነው ብዬ አምናለሁ።
የአህዛብ ሐዋርያ በመሆን እጅግ በሰፊው ያገለገለው ጳውሎስ
ምንም እንኳ ሐዋርያ እንደሆነ ቢያምንም እንደፈለገው
ወይም ሁሉን ማድረግ የሚችልበት ሥልጣንና ኀይል እንዳለው
አማልክት አድርጎ እራሱን አያስብም ነበር። ስለዚህም እርሱ
በሚገለገልበት ሁኔታ ወይም መጠን ከማያገለግሉ ምዕመናን
የጸሎት ልመና ወይም እርዳታ ይናፍቀው ነበር።
እንዲለምኑለትም ያደፋፍራቸውና በጽኑ ያበረታታቸው
ነበር። “ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ
አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ። ”ኤፌ.6፡
9።

በአጠቃላይ የማይወሰንና የማይገደብ በራሱ ስልጣን ያለው፤


ጥገኛ ያልሆነ መለኮት ብቻ ነው። የተሰጠን መንፈሳዊ
ሥልጣንም ይሁን ኀይል በመለኮት ፈጣን ንቁ ቁጥጥር እና
ፈቃድ የሚሠራ ነው። በእግዚአብሔር መሰማት የተለየ

531
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወይም ታላቅ መንፈሳዊ ስልጣን አይፈልግም። የጸሎትን


ስኬት ወይም ምላሽ መለማመድ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ
የተሰጠ ስልጣን ነው። በምንም ዐይነት መንፈሳዊ ሥልጣንና
ኀይል የምናገልግል ብንሆንም እንኳ የምናገለግለውን ሕዝብ
የጸሎት ድፍረት እንዳናጠፋ ልንጠነቀቅ ይገባል። የመንፈሳዊ
ሥልጣንን ገደብ በመረዳት እግዚአብሔርን በመፍራትና
በፍጹም ትህትና የመለኮትን ፈቃድና ኀይል በመለመን
ማገልገል የእግዚአብሔር ሰዎች አዕማድ መገለጫ ባሕርይ
ነው።

ማጠቃለያ

“ሰውን በመልካችንና በምሳሌያችን እንፍጠረው” ከሚለው


ዓረፍተ ነገር በመነሳት “እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ
በመልክና በምሳሌው የተፈጠረው የሰው መንፈስ ነው፤ የሰው
መንፈስ ፍጹም የመለኮት መልክና ምሳሌ አለው።” የሚል
ትርጓሜ የያዘ ሥነ-መለኮት መከተል የዘፍጥረትን መጽሐፍ
የአጻጻፍ ስልት ካለመረዳትና የመዝገበ ቃላትን ፍቺ ከመከተል
የሚመጣ እንደሆነ ተመልክተናል። በአጠቃላይ ይህ ክፍል
የሰው ልጅ አፈጣጠር ሰው አማልክትነት እንዳለው
እንደማያረጋግጥ በማስገንዘብ ከመለኮት ጋር ጤናማ ኅብረት
እንዲኖረን እንዳበረታታን ተስፋ አደርጋለሁ። መንፈሳዊ

532
ጆንሰን እጅጉ

ሥልጣንም ገደብ እንዳለው በማስገንዘብም ሌሎችን


በትሕትና እንድናገለግል አቅጣጫ እንደጠቆመንም አምናለሁ።

የምዕራፍ ሰባት ግንዛቤ ማስጨበጫ ጥያቄዎች

1. የእምነት እንቅስቃሴ ሥነ-መለኮት ባዕድ ወይም ቅይጥነት


እንደተዳበለው ማሣያ የሚሆኑ ነጥቦችን በዝርዝር
አስቀምጥ። በእነኝህ ነጥቦች የተጠቀሱ ልምምዶች አንተ
ባለህበት አከባቢ ምን ያኽል ይታያሉ?

2. የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ለክርስትና ሥነ-መለኮት


አንድ ዐይነት ባዕድ መልክ እየሰጠ እየመጣ እንደሆነ ማሣያ
የሚሆኑ ነጥቦች ተዘርዝረዋል። አቢያተክርስቲያናት ከዚህ
ተጽዕኖ እንዲላቀቁ ምን ምን መደረግ አለበት ብለህ
ታስባለህ?

533
የአማልክቱ ዐዋጅ

3. ኢየሱስ አይሁድ የቀረበበትን “እራስህን ከእግዚአብሔር


እኩል ታደርጋለህ” የሚል ክስ መዝሙር ሰማንያ ሁለትን
በመጥቀስ ሞግቷል። በመዝሙር ሰማንያ ሁለትና በኢየሱስ
ሙግት መኻል ምን ዝምድና አለ? “አማልክት” ነን
የሚለውን ቃል መጠቀም እንችላለን? አብራራ።

4. በኢየሱስ ሥልጣንና በአገልጋዮች ስልጣን መኻል ምን


ልዩነት አለ? ይህንን ልዩነት ማወቅ ለአገልግሎትህ ምን
ይጠቅማል ብለህ ታስባለህ?

534
ጆንሰን እጅጉ

ምዕራፍ 8

መለኮትን ይለምኑታል

“አሁን ጌታ ሆይ በኀይል ሁሉ አበርታኝ ብሎ መጸለይ (መለመን)
ስሕተት ይሆናል፤ ይልቁንም እናንተ ማድረግ ያለባችሁ በተወሰነ ኀይል
ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በውስጥ ማንነታችሁ በኀይል
ሁሉ እንደበረታችሁ ማወጅ ነው።”362
ፓስተር ክሪስ ኦያኪሂሎሚ

“በአስተምህሮቱ (የእምነት ቃል አስተምህሮት) ምኞታችን ከፍቃዱ ጋር


ስለማይስተያይ፣ ጸሎታችን ይቀንሳል። ጸሎትን (ልመናን) የተካው ዐዋጅ
ደግሞ አድማጭ ይፈልጋል። ህይወታችን በግል ጌታን ከመፈለግ ይወጣና
የአደባባይ መፈክር ይሆናል።”363
ዶ/ር ተካልኝ ነጋ

362
ክሪስ ኦያኪሂሎሚ፤ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ (2009፣ነሐሴ፣5) በተጨማም ራፕሶዲ
ኦፍ ሪያሊቲስ 2013፣2 ይመልከቱ)።
363
የጸሎት ቤት፡ የንግድ ቤት (ገጽ. 237)።

535
የአማልክቱ ዐዋጅ

አማልክቱ የጸሎትን ትርጓሜ በማዛባት በኅሩይ ቃል ዐዋጅ


ማለትም በልዩ ጸሎት ቢተኩትም የአዲስ ኪዳን ሥነ-መለኮት
መዝገበ ቃላት ጸሎት የሚለውን ቃል ሲተረጉም ‘መለመን’
በሚል አቻ ቃል አስቀምጦታል። መዝገበ ቃላቱ
እንደሚያሳየው ጸሎት በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት
“proseuchomai” በሚል የግሪክ ቃል የተገለጠ ሲሆን በሌላ
በኩል ደግሞ deomai እና deesis በሚሉ ሁለት ቃልትም
ተገልጻል። ይህም እንደ መዝገበ ቃላቱ ትንታኔ aitema እና
aiteo እንደ ማለት ሲሆን ትርጓሜውም በትህትና ተንብርክኮ
መለመን ወይም መማጸን ማለት ነው። (ማቴ.5፡42 ቆላ 1፡9
ኤፌ.3፡13 1 ዩሐ 5፡14፣16 ዩሐ 14፡13-16፣23 ሉቃ.22፡32
ማቴ.6:8 ማቴ.7፡9)። ከዚህም በተጨማሪ መዝገበ ቃላቱ
እንደሚያሳየው በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ወደ
እግዚአብሔር መጸለይ “boe” እና “krazo” በሚሉ ግሶች
የተገለጠ ሲሆን ትርጉሙም እዬ እዬ ማለት፣ ማልቀስ ወይም
የጩኸት ለቅሶ ማሰማት ማለት ነው።

በአጠቃላይ የጸሎት አዲስ-ኪዳናዊ ፍቺ እጅግ አስፈላጊ ለሆነ


ጉዳይ አስቸኳይ ዕርዳታ ለማግኘት ለስላሳ የጩኸት ድምጽ
ማሰማት ማለት ነው።364 ስለዚህ ጸሎት ትዕዛዛዊ ቃል
ማውጣት ወይም ሥልጣናዊ ዐዋጅ ማሰማት ከሚለው የተዛባ
364
New International Dectionary of New Testament Theology, (Pp. 855-86).

536
ጆንሰን እጅጉ

ትርጉም በተቃራኒው ሌላ ስልጣን ያለውን አካል መለመን


ወይም ጥያቄን በትህትና ማሳወቅ የሚል ትርጉም ይይዛል
ማለት ነው።365 በአጠቃላይ የግሪክ ሰዋሰው ፍቺ ስለ ጸሎት
የሚሰጠው ትርጓሜ እንደሚያሳየው ጸሎት የሚያቀርበው
ሰው ጉልበት ያለውን አስገዳጅ ንግግር ወይም የኅሩይ ቃል
ዐዋጅ መጠቀሙን ሳይሆን በተለሳለሰ ቅላጼ ድምጽ መለመኑን
ወይም ጥያቄ ማቅረቡን ነው። ይህም ዐሳብ በአዲስ ኪዳን
ብቻ ሳይሆን በብሉይ ኪዳን መጽሐፍትም ተንጸባርቋል።

ለምሳሌ መዝሙረኛው በመልዕክቱ የጸሎትን ልመናነት ብቻ


ሳይሆን የመለኮትን የልመና ሰሚነትን አመልክቷል።
“ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል ልመናቸውንም ይሰማል
ያድናቸዋልም።”(መዝ.145፡19 20:1)። በዚህም መሠረት
የጸሎታችን መዳረሻ አድራሻ እና ምላሽ ወይም የማድረግና
ያለማድረግ ሙሉ ሥልጣንና ነፃ ፈቃድ ያለው ልዕለ መለኮት
እንጂ ግዑዝ ወይም የተፈጥሮ ሕግ እንዳልሆነ ያሳውቃል።
የብሉይ ኪዳን አባቶች በፍጹም ትህትናና ፍርሃት
የሚንበረከኩት የሃይማኖት ሥርዐት ስለሆነባቸው
አልነበረም። ነገር ግን መለኮት የማድረግም ይሁን ያለማድረግ
ፍጹም ነፃነት ያለው አምላክ እንደሆነ ስለሚያውቁ ነበር።
የቱንም ያኽል የመለኮት ኀይል ተገልጦባቸው ተአምራትን

365
Ibid., (p.164).

537
የአማልክቱ ዐዋጅ

ቢያደርግ በመለኮት ፊት የመንበረከክና የመለመን


ልምምዳቸውን አይቀይሩም ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስም
እንዲሁ ምንም ጸጋው በህይወቱ አልፎ ከፍ ያለን ነገር
ቢሠራበትም፤ የመለመን አስፈላጊነትን በመካድ የመናኛውን
የልዩ ዲበ-አካል ልምምድ አቅጣጫ አልተከተለም ነበር።
“በዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ
ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ።” ይላል (ኤፌ.3፡
14)።

እግዚአብሔር ጸሎትን በመስማት የታመነ ነው፤ ኃጢአተኛን


የሚሰማ ጻድቅ አምላክ መሆኑ ደግሞ ድንቅ ነው። ኢየሱስ
በትምህርቱ ከጸሎቶች ሁሉ ለኃጢአተኛ ሰው የንስሓ ጸሎት
ተሰሚነት ላይ አጽንዖት ሰጥቷል። በትምህርቱም ይህን
ሲያስረዳ“እላችኋለሁ፣ እንዲሁ ንስሓ በሚገባ በአንድ
ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”
ብሏል።(ሉቃ.15፡10)። ይህም በክርስቶስ የተሠራው የድነት
ሥራ ከእግዚአብሔር ጋር ዕርቅን ፍጹም በማድረግ ፍፃሜ
እንዲያገኝ ነው። “ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ
ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ
ዘንድ ነው።” (ኤፌ.2፡16)።

በሌላም ቦታ በድነት ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት


እንደተሰጠን ሲያረጋግጥ፤ “እርሱ ከጨለማ ስልጣን አዳነን፣

538
ጆንሰን እጅጉ

ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ


ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”(ቆላ.1፡13)ይላል።
ድነታችን ለራሳችን ጥቅም ቢሆንም መለኮት ይህንን
ያደረገው ለራሱ እንደሆነ ሲያስረዳም፦“በእርሱም በኩል
በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት
ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።”(ቆላ.1፡20)
ይላል።

በአጠቃላይ ድነታችን ከመለኮት ለመለኮት ነው እንጂ ከእኛና


ለእኛ አይደለም። ይህንንም ሲያስረዳ፦ “እንደ ምሕረቱ
መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ
በመታደስ አዳነን እንጂ፣ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ
ነበረው ሥራ አይደለም።”(ቲቶ.3፡5)። እንግዲህ ይህንን
የሚያክል ታላቅ ድነት በህይወታችን የተፈጸመው
ኃጢአተኞች ሆነን ሳለን ያቀረብነውን የንስሓ ጸሎት
ስለሰማን ነው። ይልቁንም ልጅ ከሆንን በኋላ እንዴት
አብዝቶ ልመናችንን ይሰማን ይሆን? እንዴትስ አብዝተን
በፊቱ መውደቅ ይገባን ይሆን?

ከእኛ መኻል አንዳንዶች በግዚአብሔር ላይ ያላቸው


መተማመን መስሎ የሚታያቸው ልመና ማቆማቸው ወይም
መንበርከክ መተዋቸው እንደሆነ እየተመለከትን ነው።
ልመናም ሆነ መንበርከክ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ

539
የአማልክቱ ዐዋጅ

መሸማቀቅ እንደሆነ አስበዋል። ስለዚህም መንበርከክን


በመንጎራደድ፣ ልመናን በኅሩይ ቃል ዐዋጅ ወይንም በስልጣን
ማዘዝ ተክተውታል። ለእንደዚህ ዓይነቱ ልምምድ መደገፊያ
ተደርጎ ብዙ ጊዜ በቀጥታ የሚጠቀሰው አንደኛው
ዐሳብ“የአዲስ ኪዳን ህዝቦች በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ
ተባርከናልና የምንለምነው ነገር የለም።” የሚል ጽንሰ-ዐሳብ
ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “እዘዙኝ ስላለ መለኮትን
የምንፈልገውን ነገር በእምነት ማዘዝ ነው ያለብን” የሚለው
ጽንሰ-ዐሳብ ነው። ከዚህ ቀጥሎ ልመናን የሚገዳደሩ ጽንሰ-
ሐሳቦችን እንመረምራለን።

የበረከት የጊዜ ሰሌዳ


አንዳንዶች በፊታቸው የቀረበን ማዕድ እንኳ ሳይቀር ገና
ከመመገባቸው አስቀድመው “ተባረኳል! በልተነዋል!” የሚሉ
ኀላፊ ቃላትን በመደርደር የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ጸሎትን
ሲያደርጉ ስንመለከት የመሠረታዊ ትምህርት ቀውስ ውጤት
እንደሆነ ስላላስተዋልን አሜን በማለት በርካታ ጊዜያት
ተሳስቀን አልፈናል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ የምንስቅበት ቀልድ
ሳይሆን የመሰረታዊ ትምህርት ተፋልሶ ውጤት ነው። ይህንን
የመሳሰሰሉ በርካታ ልዩ ጸሎቶች በኤፌ.1፡3 ያለውን ክፍል
በዋናነት መነሻ በማድረግ ይተገበራሉ። ክፍሉ “በክርስቶስ
በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን

540
ጆንሰን እጅጉ

የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።” የሚል ነው።


ይህንን ክፍል ስናጠና እየተናገረ ያለው የተባረክንበትን ድነት
መነሻ ከጊዜና ቦታ ውጪ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ
እንደሆነ እንረዳለን። በሌላ በኩል ደግሞ የድነታችንን ‘አሁንን’
እና መድረሻ ‘ወደፊትን’ የሚጠቁም የጊዜ ሰሌዳንም
ያሣየናል። ይህም የእኛ ድርሻ የሚታይበት ሳይሆን የመለኮት
ድርሻ የሚታይበት ነው።

 በመጀመሪያ ይህ በረከት የድነታችን መጀመሪያ ዓለም


ከመፈጠሩ በፊት በእግዚአብሔር አዕምሮ ውስጥ በዕቅድ፣
በምርጫና በውሳኔ ደረጃ መጠናቀቁን በኀላፊ ጊዜ ያመለክታል
(ቍጥር.3-5)።

 በመቀጠል ደግሞ ይህ በረከት ካገኘነው ስርየትና ቤዛነት የተነሣ


አሁን የተረጋገጠ እና የጨበጥነው እንደሆነ ያመለክታል
(ቍጥር.6-9፣11፣14)።

 በመጨረሻም ምንም እንኳ መባረካችን የተረጋገጠ ቢሆንም፤


ያላለቀ ስለሆነ አሁን ላይ ሆነን ለወደፊት ተስፋ የምናደርገው
እንደሆነ ይጠቁማል (ቍጥር. 12-13)።

 በቍጥር 10 ላይ ደግሞ የበረከታችንን መጨረሻ ወይም


መዳረሻ ምን እንደሆነ ይናገራል።

541
የአማልክቱ ዐዋጅ

በአጠቃላይ የኤፌሶን መልዕክት በረከት ከጊዜና ዘመናት በፊት


የተወሰነ በአሁንና በወደፊት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ የተቀመጠ
ሥጦታ እንደሆነ በማሳየት ለአምልኮና ለምስጋና ይጋብዘናል።

በሚገርም ሁኔታ ሐዋርያው የኤፌሶን ክርስቲያኖችን ይህንን


ሁሉ ካላቸው በኋላ በቍጥር ‘16’ ላይ “ስለ እናንተ
እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም።”
በማለት መናገሩ የጸሎትን ማለትም የልመናን አስፈላጊነት
ችላ አለማለቱን ያንጸባርቃል። በመቀጠልም በቍጥር ‘17’
በድጋሜ እግዚአብሔርን እንደሚለምን መናገሩ የልመና
አስፈላጊነትን አጽንዖት እንደሰጠው ያሣያል።“የክብር አባት
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ
የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።”
ይላል።

እንግዲህ የቃሉ ጸሓፊ ከእኛ ይልቅ የሚያስተላልፈውን


መልዕክት አቅጣጫ የመወሰን ስልጣን እንዳለው ካወቅን፤
ጸሓፊው ስለመባረክ ያለው እምነት ልመናን እንዳላስጣለው
ልናውቅም ይገባል። የኤፌሶንን መጽሐፍም ይሁን ሌላ ክፍል
በመጥቀስ “በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ተባርከናል” የሚል የልዩ
ጸሎት ፈሊጥን መለማመድን እናስወግድ። ለምነን
የምንቀበለው ምንም ነገር እንደሌለ በመቁጠር የልመና

542
ጆንሰን እጅጉ

ጸሎትን ወደጐን ማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት


የሌለው ከመሆኑም በላይ አላዋቂነትም እንደሆነ እንገንዘብ።

የዕጣ ፋንታ ማህተም


የሚነገሩ ቃሎች በራሳቸው ውጤት ከሌላቸው የበረከት ቃል
የመናገር ፋይዳው መንድነው? የአይሁድ መሪዎችና አባቶች
ህዝባቸውንና ልጆቻቸውን የበረከት ቃል በመናገር
የሚባርኩት ለምንድነው? የአንደበታቸውን ቃል ኀይል
መጠቀማቸው ይሆን? ልመናን ወደጐን የሚያደርግ ልዩ
ጸሎት እየተለማመዱ ይሆን? ዕጣ ፋንታን ለመወሰንና
ለማረጋገጥ ይሆን? በፍጽም አልነበረም።

ለምሳሌ ያኽል ይስሐቅ ለልጁ ለያዕቆብ የተናገረውን የበረከት


ቃል የተመለከትን እንደሆነ ልጁን ለመለኮት አደራ አሳልፎ
የሰጠበት ንግግር እንደሆነ ነው የምናስተውለው። “ሁሉን
የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን
ይባርክህ፣ ያፍራህ፣ ያብዛህ!” (ዘፍ.28፡3)። እንዲህ የበረከት
ቃል አይሁድ የሚለማመዱት የቃልን ኀይል ተጠቅመው
የህዝባቸውንና የልጆቻቸውን ዕጣ ፋንታ ለመወሰን
አልነበረም፤ በጭራሽ እንዲህ ዐይነት ፍጻሜን የመወሰን
ድፍረት አልነበራቸውም። በመልካም ቃላቶች የስነ-ልቦና
ጥገና ለማደረግ በመሰብም አልነበረም። መልካም ንግግር

543
የአማልክቱ ዐዋጅ

የስነ-ልቦና ግንባታ ማድረጉ እውነት ቢሆንም የበረከት ቃል


የሚናገሩት ግን በዚህ ዐላማ ታስረው በጭራሽ አልነበረም።

አባቶች የበረከት ቃል ሲናገሩ እጃቸውን በሚባርኩት ሰው


ላይ ያኖራሉ ወይም ወደ ሰማይ አምላክ ያነሣሉ።(ዘፍ.48፡
14)። የሚባረከው ደግሞ መንፈስ በሆነ ልዑል አምላክ ፊት
ይንበረከካል። የሚባርከው ሲባርክ ተባራኪው አሜን ይላል።
(1 ዜና.16፡36)። ይህ ሥርዐት ፍጹም ለእግዚአብሔር
መገዛትና በእርሱ ስልጣን ላይ በመታመን የተሞላ ነው።
ባርኮቱም በባራኪው አንደበት የሚያልቅና የሚገኝ
አይደለም። ድምዳሜውን፤ የፍጻሜ ማኅተሙን የማድረግ
ስልጣን ያለውን አምላክ በእምነት የሚጋብዝ ብቻ ነው።
የባርኮቱ ማዕከላዊ ፍሬና መቋጫም ‘እግዚአብሔር ይባርክህ’
የሚል ነው። ይህም “ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን
ልጆች እያንዳንዳቸው ባረካቸው።” እንደሚል በመለኮት ላይ
በመተማመን ተባራኪውን ለመለኮት ለማስተላለፍ የሚደረግ
መሆኑን ያመለክታል። (ዕብ.11፡21)።

በተጨማሪም የቃል ኀይልን የመጠቀም ዐስተሳሰብ የሌለበትና


ልመናን በእግዚአብሔር ፊት የማቅረቢያ ሥልት እንደሆነም
ያመለክታል። ይህንን አለመገንዘብና ቃሉን በግልብ ንባብ
ተመልክተን በመተረጎም አባቶች የቃልን ኀይል ተጠቅመው
የልጆቻቸውን ፍጻሜ ወስነዋል በማለት ያልኖሩበት ልምምድ

544
ጆንሰን እጅጉ

ባለቤት እያደረግናቸው የወንጀላችን ዐባሪ ልናደርጋቸው


አይገባም። ስለዚህ ልጆቻችን በትምህርታቸው ስኬታማ
እንዲሆኑ ቀንና ለሊት የበረከት ቃል ማወጅ አይጠቅመንም።
ነገር ግን የመለኮትን ባርኮት በሚማጸን የባርኮት ልመና
ለእግዚአብሔር በእምነት አሳልፈን በመስጠት ባለን ዐቅም
ልክ ማስጠናት ብንችል አትራፊ እንሆናለን።

መለኮትን የሚያዝ ልዩ ዐዋጅ


ትንቢተ ኢሳያስን መነሻ በማድረግ ልዩ ጸሎት የማድረግ
ልምምድ በወንጌላውያን አማኞች መኻል እንኳ ሳይቀር አልፎ
አልፎ ይስተዋላል። በዚህም መሠረት መለኮትን ለማዘዝ
ሰዎች ይሰበሰባሉ። (ኢሳ.45፡11)። የሚያሳዝነው ግን ይህንን
ክፍል ለዚህ ልዩ ልምምድ መሠረት አድርጎ ለመውሰድ
ተደጋጋሚና ተመሳሳይ ሌላ ጥቅስ የለንም። በተጨማሪም
የ 1954 ዓ.ም የአማርኛው ዕትም በተጠቀሰው ክፍል ላይ
የቃላት ግድፈት ይታይበታል።

የአማርኛው 1954 ቱ ዕትም እንዲህ ይነበባል፦“የእስራኤል


ቅዱስ ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለሚመጣው
ነገር ጠይቁኝ፣ ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም እዘዙኝ።"
አብዛኛዎቹን በሌላ ቋንቋ የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ
ትርጉሞች ያየን እንደሆን ግን“ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም

545
የአማልክቱ ዐዋጅ

እዘዙኝ።" በሚለው ቃል ፋንታ የሚቃረን የሚመስል ዓረፍተ


ነገር ተጠቅመዋል። የ 1980 ቱ የአማርኛ ዕትምም እንዲሁ
ከ 1954 ቱ ጋር አይስማም። ለምሳሌ ያኽልም ጥቂቶቹን
ብንመለከት፦

 “Concerning things to come, do you question me


about my children, or give me orders about the
work of my hands?” ስለ እጆቼ ሥራ ልታዙኝ ትችላላችሁን?
(NIV)።
 "Do you question what I do for my children? Do
you give me orders about the work of my hands?
ስለ እጆቼ ሥራ ትዕዛዝ ትሰጡኛላችሁን? (NLT)
 Israel's Creator, says: "What right have you to
question what I do? Who are you to command me
concerning the work of my hands? ስለ እጆቼ ሥራ
ልታዙኝ እናንተ ማን ናችሁ? (TLB)።

ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕትሞች ተነስቶ የአማርኛውን


(1954) ዕትም መጠራጠርና አውዳዊ አገባቡን መፈተሸ
አግባብ ነው።

እንግዲህ በአጠቃላይ ከኢሳያስ ‘45’ ዐውድ ተነስተን ያጤንን


እንደሆን እግዚአብሔር የክስተቶች ወይም የድርጊቶች ሁሉ
ባለቤት እንደሆነ በመናገር ስለ ሉዐላዊ አምላክነቱ

546
ጆንሰን እጅጉ

የሚሞግትበት ክፍል እንደሆነ እናስተውላለን። “ብርሃንን


ሠራሁ፣ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፣
ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ
እግዚአብሔር እኔ ነኝ።”(45፡7)። በተጨማሪም ሉዓላዊነቱን
ሊታገሉ የሚሞግቱትን ወይም በተፈጥሮ ላይ ለምን ሆነ
በማለት ክርክርና ጥያቄ የሚያነሱትን ያስጠነቅቃል።
“ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መኻል
ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ
ሥራህ፦ እጅ የለውም ይላልን?” (45፡9)።

በመጨረሻ በቍጥር(45፡11) ላይ ‘ልትጠይቁኝ ወይም


ልታዙኝ አትችሉም’ የሚል ማጠናከሪያ ዐሳብ በማቅረብ
የበለጠ ያጠናክራል። ከላይ ለመዘርዘር እንደተሞከረው
መለኮት የማይደፈር ሉዐላዊነት እንዳለው እየተናገረ ከወረደ
በኋላ ቁ ‘11’ ላይ ሲደርስ ግን ‘እዘዙኝ’ የሚል ከሆነ እየተናገረ
የመጣውን ዐሳብ ያፈርሰዋል። ስለዚህ “እዘዙኝ” የሚለውን
ቃል በቀጥታ ከአውዱ ውጪ ብቻውን ወስዶ መተርጎምና
ክፍሉን መፍታት ትክክል አይሆንም። እንዲህ አውዱን
በሚገባ ከአጤንን የአማርኛው 1954 ዕትም የቃል ግድፈት
መገንዘብ አይቸግረንም።

ሥለዚህ ጥቅሱ መለኮትን ማዘዝ እንደማይቻል ስለሚያሳይ


በዐዋጅ ቃልም ይሁን በእምነት ቃል መለኮትን መቈጣጠርም

547
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሆነ ማዘዝ ይቻላል የሚል ጽንሰ-ዐሳብ መደገፊያ መሆን


አይችልም። ከሥነ-አመክንዮም አንጻር የሚታዘዝ ለአዛዡ
አምላክ ሊሆን አይችልምና ይህንን ማሰብ ግብዝነት ነው።
ለዚህ ነው እግዚአብሔር በፍጥረቱ ላይ በሉዓላዊነቱ ወስኖ
የሚያደርገውን ነገር “ለምን” ብሎ የሚጠይቀውን ወዮ
በማለት ኢሳያስ የሚያስጠነቅቀው። በአጠቃላይ “ስለ እጆቼ
ሥራ የምታዙኝ እናንተ እነማናችሁ?” በማለት የሚሞግተው
እርሱ የማይታዘዝ አምላክ ስለሆነ እንደሆነ ልብ ማለት
ይገባል። ሉዐላይነቱን የሚነካ እንዲህ ዐይነት የልዩ ጸሎት
ልምምድ የመለኮትን ቁጣ የሚቀሰቅስ እንደሆነ ከተነሳው
የትንቢተ ኢሳያስ ዐውድ መገንዘብ ይቻላል።

የዕብራዊያን ዐዋጅ ቃል
በርግጥ ቃል ማወጅ የዕብራዊያንና የጥንታዊያን ነገስታት
ነባር ልምምድ እንደ ነበር የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ የልዩ ዲበ-አካል “አማልክትም” ይሁኑ
የእምነት ቃል አማልክት “የቃል ዐዋጅ” ወይም “ቃል
ማውጣት” ልምምድን በተመለከተ የሚጋሩት ጽንሰ-ዐሳብ
እንዳላቸው በስፋት ተመልክተናል። ይሁን እንጂ ከዕብራዊያን
ጋር የሚጠቀሙበት ቃል ተመሳሳይነት ቢኖረውም የጽንሰ-
ዐሳብ ስምምነት ግን በጭራሽ የለውም።

548
ጆንሰን እጅጉ

ልምምዱን ውስብስብና ለመለየት አስቸጋሪ የሚያደርገው


የልዩ ዲበ-አካል ሊቃወንቱም ይሁኑ የእምነት ቃል አራማጆች
የሚጠቀሙት ቃላትና ዓረፍተ ነገር ከዕብራዊያኑ ዓረፍተ
ነገርና ቃላት ጋር መመሳሰሉ ነው። ስለዚህም ይህንን ልዩነት
ለመለየት እንዲቻል ዕብራዊያንም ሆኑ የእምነት ቃል
ትምህርት አራማጆች ለሚጠቀሙት ቃልና ዓረፍተ-ነገር
የሚሰጡትን ትርጉም በጥንቃቄ ማስተዋል ይገባል።
ዕብራዊያን ቃል ማወጅ ለሚለው ስንኝ የሚሰጡት
ትርጉምና የልምምድ ቅርፅ ከልዩ ዲበ-አካል “አማልክትም”
ይሁን ከእምነት ቃል “አማልክት” ፈጽሞ የተለያየ ነው። በዚህ
መጽሐፍ ውስጥ ይህንን ለማጉላትና ለአንባቢ ለማመልከት
እንዲረዳ የተሳሳተ ትርጓሜያቸውና ልምምዳቸው በስፋት
ተብራርቷል።

በአጠቃላይ ጥንታዊውን የቃል ዐዋጅ አጠቃቀም ስንመረምር


“የቃል ዐዋጅ” ጥንታዊያን ነገስታት ለህዝባቸው በሙሉ
በመልዕክተኛ አንደበት መልዕክት ለማስተላለፍ የሚጠቀሙበት
መልዕክት ማስተላለፊያ መንገድ ሆኖ እናገኛለን።
መልዕክተኛው ዐዋጅ ነጋሪ ሲባል መልዕክቱ ደግሞ ዐዋጅ
ይባላል። እንደዚሁ ሁሉ “የዐዋጅ ቃልን” በዕብራዊያን ዐውድ
ውስጥም ስንመለከት የእግዚአብሔርን መልዕክት ሰዎች

549
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሰምተው ምላሽ እንዲሰጡ ለማድረግ በግልጽ መንገር፣


መስበክ ወይም መተንበይ እንደ ማለት ነው።

ለምሳሌ ትንቢተ ኢሳያስ፦ “የዐዋጅ ነጋሪ ቃል፦


የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ-በዳ ጥረጉ፣ ለአምላካችንም
ጎዳና በበረሃ አስተካክሉ” ይላል።(ኢሳ.40፣3)። በዚህ ዐውድ
ሥርው ዮሐንስ ዐዋጅ ነጋሪ የተባለ ሲሆን መልዕክቱ
ደግሞ‘ዐዋጅ’ የሚል ትርጓሜ ሊይዝ ይችላል። ይህም በቀጥታ
የመጥመቁ ዮሐንስን የንስሓ ጥሪና የስብከት አገልግሎትን
የሚጠቁም ነው። ሐዋርያው ጳውሎስም “ዐዋጅ” መናገርን
አንስቶ ለጢሞቲዎስ ሲጽፍለት ዐዋጅን የሚያነሳው ከስብከት
አንጻር ነው። “እኔም ለዚህ ነገር ዐዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ
በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን
ተሾምሁ፤ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም።” (1 ጢሞ. 2.7)
ይላል።

በተጨማሪም ዕብራዊያን “ዐዋጅን” በእግዚአብሔር ላይ


ያላቸውን መታመን በዝማሬ ወይም በጸሎት ለመግለጥ
ይጠቀሙበታል። ይህም ለጠላቶቻቸው ድንጋጤ፣
ለእግዚአብሔር ክብርና ለእነርሱ ደስታ መገለጫ ይሆናል።
በዚህም ዐውድ መሰረት አንድ አማኝ በአምላኩ ላይ ያለውን
መተማመን በቃላት በጸሎት ወይም በስብከት ቢገልጥ ምንም
እክል የሌለው እንደሆነ መታወቅ አለበት። “እግዚአብሔር

550
ጆንሰን እጅጉ

እረኛዬ ነው፣ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ


ያሳድረኛል፣ በእረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል”(መዝ.2፡1-2)።
በእርሱ ላይ በመታምን መወራረዳችንን አምላካችን
ይመለከተዋል። የእምነት ቃላችንንም ወደ ጆሮው ደርሶ
መልስን ዐግቶልን ይመጣል። ዳዊት በጎሊያድ ፊት ቆሞ
አንገቱን ቆርጦ እንደሚጥል የተናገረው በአምላኩ ላይ ታምኖ
ነበር። አምላኩም በእርሱ ላይ ያለውን መታመን ተመልክቶ
አከበረው፤ እንደተናገረውም አደረገለት፤ በወንጭፍ መትቶም
ጣለው። “ዳዊትም ፍልስጤኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ
አሸነፈው፣ ፍልስጤኤማዊውንም መትቶ ገደለው፤ በዳዊትም
እጅ ሴይፍ አልነበረም (1 ሳሙ.17፡50)።

በአጠቃላይ “ዐዋጅ” የሚለው ቃል በጥንታዊያን አይሁዶችም


ሆነ በአዲስ ኪዳን ፅሐፍት የተለመደ ቃል ቢሆንም አጠቃቀሙ
ወይም ትርጓሜው ግን የዲበ-አካል ሃይማኖት አማልክትም
ሆኑ የእምነት ቃል አማልክት እንዲሆንልን የምንፈልገውን
ነገር በአየሩ ላይ፣ በመንፈሳዊው ዓለም ላይ ወይም በነገሮች
ላይ ማወጅ ወይም መናገር እንደሚሉት የቃልን ጉልበት
መጠቀም በፈጹም አይደለም። ጥንታዊያን ነገስታትም ሆኑ
ዕብራዊያን ዐዋጅ ሲሉ መልዕክት ማስተላለፍ ወይም መስበክ
ማለታቸው ነው። ስለዚህ ቃሉ ምንም እንኳ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ቢሆንም እንግዳ ለሆነ የዲበ-አካል ሃይማኖት

551
የአማልክቱ ዐዋጅ

ዐስተሳሰብ ያለአግባብ ተዘርፎ ተሸጧልና ወደ መጽሐፉ


እውነተኛ ትርጉም ይመለስልን።

የእምነት ቃል
የዕብራዊያን ይሁኑ ጥንታዊያን ህዝቦች ‘ዐዋጅ’ የሚለውን
ቃል መልዕክትን ማስተላለፍ ወይም መስበክ በሚል ዐውድ
እንደተጠቀሙ ተመልክተናል። እንዲሁ ሁሉ በሮሜ
መልዕክትም ሐዋርያው ጳውሎስ “የእምነት ቃል” የሚል ስንኝ
“ስብከት” በሚል ዐውድ ተጠቅሟል። ሐዋርያው ቃሉን
የተጠቀመው የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ ሥብከት እንጂ ኪኒየን
ወይም ሄገን እንደሚሉት የኅሩይ ቃል ዐዋጅ ጸሎት
ትምህርትን ለማስተማር አይደለም። (ሮሜ.10፡8-13)።

ይህንንም ግልጽ ለማድረግ በቍጥር ‘8’ ላይ የምንሰብከው


በማለት የእምነት ቃል ምንነትን እንደሚጠቁም ይመለከቷል።
በመቀጠል የስብከቱን ምንነት ሲያብራራ፦ ቍጥር ‘9’ ላይ
ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እግዚአብሔር ከሙታን እንዳስነሳው
እንደሚል ይመለከቷል። በመጨረሻ ሥብከቱ በኃጢያተኛው
ልብ የወለደው እምነት የኀጢያአተኛው መጽደቅ ምክንያት
ይሆናል። ለኃጢያተኛው ድነት ወይም መጽደቅ ምክንያት
በልቡ ማመኑ እንደሆነ “ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል” ከሚለው
ስንኝ በግለጽ ተቀምጧል። ይህንንም ከቍጥር (10-14)

552
ጆንሰን እጅጉ

ይመለከቷል። አዳኙን የተረዳና አምኖ የጸደቀ ኀጢአተኛ የነበረ


ሰው የጌታን ስም በመጥራት ይድናል። ጽድቅን የሚከተል ይህ
መዳን ግን ምንድነው?

ይህን ውዝግብ የሚያስነሳው ስንኝ “በአፍህ ብትመሰክር


ትድናለህ” የሚለው ነው። ክፍሉ በአፍ መመስከርን ከመዳን
ጋር ያገናኘበት መንገድ ግልጽ አይደለም። ይሁን እንጂ በቁጥር
አሥር የተጠቀሰው ‘መመስከር’ የሚለው ቃል ብዙም ሳይርቅ
ከቁጥር አሥራ ሁለት ጀምሮ ‘መጥራት’በሚል ቃል ተተክቶ
በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።(ቁ.12፣13)። በቁጥር አሥራ ሦስት
ላይ መመስከር ከመዳን ጋር እንደተገመደው ሁሉ መጥራትም
ከመዳን ጋር ተገምዷል ስለዚህም በተመሳሳይ ፍች
እንደተቀመጠ እንገነዘባለን። በተቃራኒው ደግሞ የጌታን ስም
አለመጥራት ካለመታዘዝ ጋር ተገምዷል። (16፣21)።“የጌታን
ስም የሚጠራ ይድናል” የሚለው ስንኝ ስለመዳን መጠነኛ
ፍንጭ ይሰጠናል። ምክንያቱም የጌታን ስም መጥራት
እንግዳና አዲስ ቃል አይደለም። በብሉይ ኪዳን በርካታ ቦታ
ጥቅም ላይ ውሏል። ይህንን ስናጠና የጌታን ስም ለመጀመሪያ
ጊዜ የጠራው አብርሐም ሆኖ እናገኛለን። እንዲህ ተዘግቧል፦
“በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም
ስም ጠራ” (ዘፍ.12፡8፣ 13፡4፣21፡33)። ይህም አብርሐም
ከዑር በእምነት ታዞ ከወጣ በኋላ ያደረገው የቶሎ ድርጊት
ነው። ድርጊቱ ወይም የጌታን ስም መጥራቱ በቀጥታ
ከአምልኮና የእግዚአብሔርን ዐሳብ ከማገልገልና ከመታዘዝ ጋር
የተገናኘ ሆኖ ነው የምናገኘው። የሶሪያዊው ንዕማንንም

553
የአማልክቱ ዐዋጅ

ንግግር ያየን እነደሆን እንዲሁ አይሁድ የእግዚአብሔርን ስም


እየጠሩ ያገለግሉ እንደነበር መረጃ እንደነበረው ይጠቁማል
ስለዚህም የጌታን ስም መጥራት ከአገልግሎት ጋር ያለውን
ተያያዥነት እንመለከታለን። (2 ነገ.5፡11)።

ሐዋርያው ጳውሎስ የጌታን ስም መጥራትን ከመዳን ጋር


ቢገምደውም ይኽም አገላለጥ ቀድሞ በትንቢተ ኢዩኤል
የተጠቀሰ ነው። (ኢዩ.2፡32)። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን
ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ‘መዳን’ የሚለው ቃል ‘ጽድቅ’
እንደሚለው ቃል በአንድ ፍቺ ብቻ እንደማይጠቅሰው ነው።
ጽድቅ የኃጢአት ስርየትን፣ ከዘላለም ፍርድ መዳንን ወይም
በእግዚአብሔር ፊት ያለን ፍጹም ተቀባይነትን ሲያሳይ መዳን
ግን ከዓለማዊነት ወይም ከዓለም ዐመፅ፣ ከኃጥእ ሰዎች፣
ከአክሊል መቃጠል፣ ከአደጋና ከሴይጣን ፍላፃ መትረፍን
ሊያመለክት ይችላል።

በአጠቀላይ በብሉይ ኪዳን ዐሳብ መሠረት የጌታን ስም


መጥራት አምልኮ ማቅረብ፣ መታዘዝ ወይም ማገልገል ከሆነ
ሰው ይህንን በማድረጉ ከዘላለም ፍርድ ከሚድንበት ጽድቅ ጋር
ይገናኛል ብለን ልናስብ አንችልም። ምክንያቱም ጽድቅ
በእምነት የሚገኝ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው። (ሮሜ.5፡1)።
ታዲያ ሰው በማገልገሉ ከምንድነው የሚድነው ካልን
የአገልግሎቱን ዋጋ ከሚያሳጣው እሳት ነው የሚድነው።
(1 ቆሮ.3፡13-15)። ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የጌታን ስም
ሲጠራ ወይም ሲያገለግል ከዐመፅ የራቀ እንደሆነ ወይም
እግዚአብሔርን በመፍራት በንጹህ ልብ ያገለገለ እንደሆን ብቻ

554
ጆንሰን እጅጉ

ነው። “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ የሚለው


የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል” (2 ጢሞ.2፡19)።
የጌታን ስም መጥራት ከጽድቅ ጋር የዚህን ያህል ለምን
ተጠጋጋ? ያልን አንደሆን የጸደቀ ሰው ቀጣዩ ድርሻው
ያጸደቀውን አምላክ ማምለክና ማገልገል ስለሆነ ነው።

ስለዚህ የኀጢያን መጽደቅ ሥርውም በአየሱስ ሞትና ትንሳኤ


ላይ የተመሰረተ እምነት ነው እንጂ በምዕራፍ ሁለት ላይ
ኪኒየን ‘እስካውጅ ድረስ ደህንነቴ አልተፈጸመም’ እንደሚለው
መሠረት የልዩ ዐዋጅ የቃል አይደለም። አማልክት ሄገን
እንደሚለውም ‘የእምነት ቃል መናገር’ ማለት እኛ
እንዲሆንልን የምንፈልገውን ማንኛውንም ነገር መናገር
ማለትም አይደለም። ወይም ‘የእምነት ቃል’ ማለት አንድን
ደስ ያለንን ትንቢታዊ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ወስደን
በመሸምደድ ደጋግመን መናገር ማለት አይደለም። ነገር ግን
በሮሜ መጽሐፍ መሠረት ‘የእምነት ቃል’ የሚለው የኢየሱስን
ሞትና ትንሳኤ የጌታን ስም ለማይጠሩ ወይም ለማይታዘዙ
መስበክ (ማወጅ) እንደሆነ ማወቅ ይገባል። (14-21)።

የዳዊት ዐዋጅ

ዕብራዊያን በጸሎትና በዝማሬያቸው የእግዚአብሔርን


ትልቅነት በእርሱም ላይ ያላቸውን መታመን ለመግለጥ
የእምነት ቃል ዐዋጅን ይጠቀሙ እንደነበር ቅዱሳት መጽሐፍት

555
የአማልክቱ ዐዋጅ

ይጠቁማሉ። ይሁን እንጂ ይህንንም ልምምድ ያየን እንደሆን


ዐሉታዊ ንግግር ወይም የኅሩይ ቃል ዐዋጅ የሚባል ዐይነት
አይደለም። በአጠቃላይ ዐሉታዊ እውነታዎችን ለመካድ
አይሞክሩም ነበር። በተጨማሪም ያደርጉ የነበረው የቃል ኀይል
ስሌትን በመከተል ማለትም የነፍሳቸውን ጉልበት (አትማን)
ወይም ልዕለ ዓእምሮን (ዲቫይን ማይንድ) የተፈጥሮን ልዕለ
ኀይል (ባራህማን) ወይም የነፍሳቸውን ኀይል (psychic
energy) በመጠቀም የራስን ፈቃድ ለመፈጸም ወይም
መለኮትን ለማንቀሳቀስ አልነበረም።

ለምሳሌ ጥቂት የዝማሬና የጸሎት ይዘት ያላቸውን ስንኞች


ከመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ አንስተን የዳዊትን ልምምድ
በመመልከት ይህንን መረዳት ይቻላል። “እንደ ትቢያ በነፋስ
ፊት እፈጫቸዋለሁ፣ እንደ አደባባይም ጭቃ
እረግጣቸዋለሁ።” (መዝ.18፡42)። ከዚህ ስንኝ በግልጽ ማየት
እንደሚቻለው መዝሙረኛው በጠላቶቹ ላይ ያለውን
የበላይነት ወይም አሸናፊነት እየተናገረ ወይም እያወጀ ነው።
ነገር ግን የመዝሙረኛውን እምነት ስንመረምር ኀይሉ ንግግሩ
ላይ የተመሰረተ ሆኖ አናገኘውም። ምክንያቱም ወደዚህ
ዐዋጅ ከመድረሱ፤ በቍጥር ሁለት ላይ እምነቱ በእግዚአብሔር
ላይ እንደሆነ በሚያማምሩ ቃላት በማወጅ ይጀምራል።
“እግዚአብሔር ዓለቴ፣ አምባዬ፣ መድኃኒቴ፣ አምላኬ፣

556
ጆንሰን እጅጉ

በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፣ መታመኛዬና የደኅንነቴ


ቀንድ መጠጊያዬም ነው።” በተጨማሪም መዝሙረኛው
አንደበቱ ዐሉታዊ ነገር ተናግሮ እንዳይዋረድም የሚፈራና
የሚንቀጠቀጥ ወይም የሚጠነቀቅም አልነበረም።

እንደዚህ በአምላኩ ላይ ያለው መታመን ከፍ ያለ ቢሆንም


ያለበትን አስጨናቂ ወቅታዊ ሁኔታ ግን ሳይክድ ይናዘዛል።
ይህንንም ክፉ ክስተት ሊገልጡለት የሚችሉ የተመረጡ
ዐሉታዊ ቃላትን በቍጥር ሦስትና አራት ላይ ካለ ችግር
ይጠቀማል። “የሞት ጣር ያዘኝ፣ የዐመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤
የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።” ይሄ
ንግግሩ የነበረበት ሁኔታ ምን ያኽል ተስፋ አስቆራጭና ልብ
የሚሰብር እንደሆነ ያሣያል። ይህም ብቻ አይደለም ሊያመልጥ
የሚችልበት ምንም ዐቅም እንዳልነበረው በማመን የጣር
ድምጽ ያሰማል።

ይህ ከሆነ ታዲያ መዝሙረኛው ከዚህ ዜሮ ካደረገው ከበባ


ወጥቶ የድል ባለቤት ሆኖ ድልን ያአወጀበት ምሥጢር
ምንድነው? ብለን ስንጠይቅ በቍጥር ስድስት ላይ እንዲህ
በማለት ይገልጣል። “በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፣
ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፣
ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።” ምንም እንኳ ጩህቱ የድል
ሳይሆን የጣርና የጭንቀት ቢሆንም፤ ምንም እንኳ ቃሉ

557
የአማልክቱ ዐዋጅ

በዙሪያው ባለው ተፈጥሮ ወይም መላለም ላይ በማረፍ


ተጽዕኖ የማሳረፍ ዐቅም ባይኖረውም በእግዚአብሔር ጆሮ ግን
መሳቱን እርግጠኛ ነበር።

የመዝሙረኛው የድል ዐዋጅ የማዐወጅ ሚስጥሩ እንደ ዲበ-


አካል ሃይማኖት ሊቃውንቱ ወይም እንደ እምነት ቃል
አራማጆች በዐዋጅ ቃል ጠላቶቹን ድል ለመንሳት በመፈለግ
አልነበረም። በተጨማሪም የድል ዐዋጅ ማሰማቱ ድል
ለማድረግ ሳይሆን ድል ስላደረገ ነበር። የድሉም ምሥጢር
በአምላኩ መሰማቱ እንደሆነ ግልጽ ነው። በአጠቃላይ
እያዐወጀ ያለው አምላኩ ሰምቶት በመንቀሳቀሱ ምክንያት
በጠላቶቹ ላይ ያገኘውን ኀይል ለማሳወቅ ያኽል ብቻ ነው።
በመለኮት ኀይል ላይ ያለውን መታመንና የመለኮትን ኀይል
ታላቅነት በማብራራት በብዙ መንገድ በሰፊው ይተርካል።
“ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፣ የተራሮችም
መሠረቶች ተነቃነቁ፣ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና
ተንቀጠቀጡ። ከቍጣው ጢስ ወጣ፣ ከፊቱም የሚበላ እሳት
ነደደ።” (መዝ.18፡7-17)።

እግዲህ መለኮት ለማዳን እጁን የዘረጋው ዐቅም ላጣና


ጠላቶቹ ከእርሱ እንደበረቱ ተረድቶ መቸገሩንና መጨነቁን
ለሚናገር እንዲህ ዓይነቱ ምስኪን ሰው ነበር። መለኮትን
የትሁታን ልመና እንጂ የሰው ቃል ብርታት አስገድዶ

558
ጆንሰን እጅጉ

እንደማያንቀሳቅሰው ሊታወቅ ይገባል። “ከብርቱዎች ጠላቶቼ


ከሚጠሉኝም አዳነኝ፣ በርትተውብኝ ነበርና።” የሰው ልጅ
አዳኝ ያስፈለገው ራሱን ማዳን የማይችል ስለሆነ እንደሆነ
ግልጽ ነው። መለኮት የደካማውን ድምጽ ይሰማል በፍቃዱም
ማንም ሳይገፋው ወይም ሳያስገድደው ይንቀሳቀሳል!
ዕብራዊያን የሚናገሩት ቃል የቱንም ያኽል ዝቅታቸውን
የሚያሳይ ቢሆን ወይም የቱንም ያኽል ከፍ ያለ ቢሆን ድል
የማድረጋቸውና ድል የማወጃቸው ምሥጢር ግን
በእግዚአብሔር ጆሮ መሰማታቸው ስለሆነ ዐዋጅን
የሚጠቀሙት ለአምልኮ ዐላማ ነው።

መለኮት የሚያወጣው የትዕዛዝ ቃል ከሁሉ እንደሚበልጥና


ፍጥረቱን እንደሚያናውጥ ያውቃሉ። ቍጥር አሥራ ሦስት
“እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፣ ልዑልም ቃሉን
ሰጠ።” መዝሙረኛው በአምላኩ ላይ ያለውን መተማመን
በተደጋጋሚ ያውጃል። “እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች
የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።”
በጠላቶቹ ላይ ያለውን አሸናፊነትም የሚያውጀው
የሚታጠቀውን ይህንን ኀይል በመረዳት እንጂ የሚናገረውን
ኅሩይ ቃል ዐዋጅ በመተማመን በፍጹም አይደለም። “እንደ
ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፣ እንደ አደባባይም ጭቃ
እረግጣቸዋለሁ።”

559
የአማልክቱ ዐዋጅ

ከዕብራዊያን ልምምድ ወጥተን በአንጻራዊነት ቃሉን


በመንጠቅ አዲስ ዶግማ መስራት ያስጠይቀናል። ሰሚ
በሌለበት በጉባኤም ይሁን በተዘጋ ቤት ልባችን የፈቀደውን
“የኅሩይ ቃል ዐዋጅ” ወይም “የበረከት ቃል ማውጣትና”
ፍጻሜን ማረቅ ወይም “ኅሩይ ቃል በማወጅ” የጸሎት መልስን
ለመጨበጥ በሚል መለማመድ ለምትሃት አሠራር እራስን
መስጠት ነው። ይህንን ልዩ ጸሎት እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
የጸሎት ልምምድ መቁጠር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርው የሌለው
መንገድ መከተል እንደሆነና ይልቁንም ኪኒየን እንዳስተማረው
እምነትን በመለኮት ላይ ማድረግ ሳይሆን እምነትን በእምነት
ላይ ማድረግ እንደሆነ ልናስተውል ይገባል።

ያለንበትን ተጨባጭ ሁኔታ፤ ዝቅታም ይሁን ከፍታ ከቃል


ኀይል ፍርሃት ወጥተን ሊረዳን ለሚችል አምላክ እንተርክለት።
ማወጅ ካለብን ካሌብና ኢያሱ እንዳደረጉ የአምላካችንን
የኀይል ትልቅነትና በርሱ ኀይል ላይ ያለንንም መታምን
በማወጅ ነፍሳችንን እናጽና፤ በጉባኤም መኻል የአምላካችንን
ትልቅነት በማወጅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንንም
እናበርታ።

560
ጆንሰን እጅጉ

ትልቅ እምነት
እምነትን ከኅሩይ ቃል ዐዋጅ ልምምድ ጋር በማያያዝ
ማስተዋወቅ በሰፊው የተለመደ ነው። ይህንን
የማይለማመድና የልመና ጸሎትን የሚያዘወትር ሰውን ደግሞ
እንደ ደረቅ፤ መንፈስና እምነት እንደሌለው መፈረጅ
እንዲሁ። ኢየሱስ ወደ እርሱ ልመናቸውን ባቀረቡ ሰዎች
እምነት በተደጋጋሚ ተደነቀ እንጂ አንዳቸውንም ልመና
ማቅረባቸውን እንደ እምነት ማነስ ተመልክቶ
አልኮነናቸውም። “እውነት እላችኋለሁ፣ በእስራኤል እንኳ
እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።” (ማቴ.8፡10)። ወደ
እግዚአብሔር መቅረብም ሆነ ልመናን ማቅረብ የእምነት
“አማልክቱ” እንደሚሉት የእምነት ማነስ ሳይሆን እንደውም
ትልቅ እምነት የሚፈልግ ተግባር ነው። (ማር.12፡14)።
ይህንን የሚያመለክቱ ጥቂት ምሳሌዎችን ለመዘርዘር ያኽል፦

 የኢያኢሮስ የተባለ የሙክራብ አለቃ ታናሽቱ ልጁ


ብትታመምና ብትሞትም ከሞት ልትነሳ የቻለችው ኢየሱስ
እግር ላይ ወድቆ አጥብቆ ስለለመነ ነበር። “ታናሽቱ ልጄ
ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር
መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው።” (ማር.5፡
22-24)።

561
የአማልክቱ ዐዋጅ

 የቅፍርናሆሙ መቶ አለቃ ልጁ ከሥቃይ የተፈወሰለት ወደ


ኢየሱስ ቀርቦ ስለ ለመነ ነበር። “ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ
እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል ብሎ ለመነው።” (ማቴ. 8፡6)።

 በለምጽ በሽታ ተይዞ የነበረው ሰው ከለምጹ የነፃው በኢየሱስ


ፊት ወድቆ ስለለመነ ነበር። “እነሆ፣ ለምጽ የሞላበት ሰው
ነበረ፤ ኢየሱስንም አይቶ በፊቱ ወደቀና፦ ጌታ ሆይ፣ ብትወድስ፣
ልታነፃኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው።” (ሉቃ.5፡12)።

 ኢየሱስ ፈሪሳዊው ያደረገለትን ማህበራዊ ግብዣ ተቀብሎ


እንኳ በቤቱ በማዕድ የተቀመጠው ለምኖት ስለነበር ነው።
“ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤
በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ።” (ሉቃ. 7፡36)።

ይህንንም የሚመስል ልመናቸውን ወደ ኢየሱስ አቅርበው


ተቀባይነትን ያገኙ ብዙ ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል።
ከዚህም ልመና እና እምነት ተያያዥ እንደሆኑ እንማራለን።
ስለዚህም ማንም እምነት አለኝ የሚል ሰው እምነቱን
የልመና ጸሎትን በመለኮት ፊት በማቅረብ ሊያሳይ ይገባል።

በአጠቃላይ ቀደም ብለን እንዳየነው ጸሎት እርዳታ ፍለጋ


በታላቅ እምነት እና በትህትና መለመን ወይም መጮህ ማለት
ሲሆን ይህም በፈጣሪና በፍጥረቱ መኻል ወይም በመለኮትና
ባምላኪው መኻል ያለውን ልዩነትና የጠለቀ ትስሥር
አመልካች ነው። በእምነት በፊቱ በመውደቅ ለምነነው

562
ጆንሰን እጅጉ

መንቀሳቀሱን ተረድተን ከሆነ፤ አንቀሳቅሰነው ሳይሆን


ተንቀሳቅሶልን እንደሆነ ማወቅም ተገቢ ነው። ባርኮትም ሆነ
የእምነት ዐዋጅ የመለኮትን ፈቃድ ማስገደጃ መሳሪያዎች
መሆን ፈጽሞ አይችሉም።

ማጠቃለያ

ምንም እንኳ በአዲስ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ውስጥ


የምንኖር የአዲስ ኪዳን ህዝቦች ብንሆንም፤ አዲስ ኪዳን
በእምነት ሰበብ እንደፈለገን የምንኖርበትን ልቅ ሕይወት
አያስተምረንም። በአዲስ ኪዳን የመለኮት ባሕርይ
አልተለወጠም ስለዚህም ነቢዩ ኢሳያስ የመለኮትን ሉዐላዊነት
ባንድም በሌላም መንገድ ለተዳፈሩ ያመለከተው “ወዬ”
ለኛም ማስጠንቀቂያ የማይሆንበት ምክንያት የለም።
መለኮትን ማንቀሳቀስ የሚችል ትልቅ እምነት የለም!
ተራራን የሚነቅል አምላክ እንጂ ተራራ የሚነቅል ልዩ የዐዋጅ
ቃል ኀይልም የለም። “በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን
እንኖርማለን።"(ሐሥ.17፡28)። እንደተባለ መለኮት ሁሉን
ያንቀሳቅሳል! ዐጉል የተዳፈረና ግራ የተጋባ የቅዱሳት
መጽሐፍትን ትርጉም ያዛባ ሥነ-መለኮት ከመለኮት ጋር
ያጋጫል።

563
የአማልክቱ ዐዋጅ

የእግዚአብሔር መንፈስ ከቃሉ ጋር ያስማማናል እንጂ


በጭራሽ አያጣላንም። እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነ
የእምነት ልምምድ እየተለማመድን ስኬት እያገኘን ከሆነ
የስኬታችን ምንጭ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደሆነ
ብንመረምር መልካም እናደርጋለ። የእምነት ቃል ዐዋጅም
ይሁን የባርኮት ቃል መናገር ሥነ-መለኮታችንን
በእግዚአብሔር ቃል ልናበጥረው ይገባል። ልመናን ለመለኮት
ማሳወቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርው ያለውና የእምነት
መገለጫ መንገድ ስለሆነም ልመናና ምልጃን ከጣልንበት
ማንሣት ገባናል ።

የምዕራፍ ስምንት ግንዛቤ ጥያቄዎች

1. በእምነት ቃል የዐዋጅና መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ የጸሎት


ልምምድ ሥነ-መለኮት መኻል ያለውን ልዩነት አስረዳ።

2. የእምነት ቃል ዐዋጅ ልምምድ በርቱዕ ትምህርት ላይ


የተመሠረተን የጸሎት ልምምድ ይጎዳል ብለህ ታስባለህ?
አብራራ።

3. የእምነት እንቅስቃሴ የቃል ዐዋጅ ሥነ-መለኮትና ልምምድ


ከዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል ዐዋጅ ሥነ-መለኮትና

564
ጆንሰን እጅጉ

ልምምድ ጋር ያለው ታሪካዊ ትስሥርና ተዛምዶ


ምንድነው?

4. የዕብራውያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የዐዋጅ ልምምድና


የእምነት ቃል የዐዋጅ ልምድድ ምን መመሳሰልና የስነ-
መለኮት ልዩነት አለው?

5. ጤናማ የሆነ የቃል ዐዋጅ ልምምድን በምን መልክና ገደብ


መጠቀም እንችላለን ብለህ ታምናለህ? አብራራ።

ምዕራፍ 9

ተጠያቂዎች ነን

565
የአማልክቱ ዐዋጅ

ፈጽመን በእውነት ነግሰናል ብንልም ገና ነን፤ ምንም


አልተነካካንም ብንልም አድፈናል፣ በጭራሽ አልተደፈርንም
ብንልም ተወረናል። አዎ፤ እኛ የወንጌላውያን አማኞች
ሳናውቀው ከምንራበውና ከምንወደው ሀልዎት ቀስ ብለን
ርቀን እየሄድን ነው። የጸሎትና እግዚአብሔርን የመምሰል
ምስጢር ተዛብቶብናል። በዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና
ተሰንክለን አንክሰናል። ይባስ ብለን ደግሞ ይህንን አስተውለን
ኀላፊነት ከመውሰድ ይልቅ በሕሊናችን ጓዳ የሚደውለውን
የተጠያቂነት ጥያቄ የምናላክክበት ፍለጋ ሽቅብና ቁልቁ
እንሯራጣለን እንጂ የድርሻችንን አናነሳም። አሊያም ከእኛ
ዕርቆ ያለ ይመስል ደርሰን ወደ እምነት ቃል እንቅስቃሴ
አእማድ መሪዎች ጣታችንን እንጠቁማለን።

እነርሱም ቢሆኑ ሴጣናዊነት የተጣባው የጥፋት ደረጃቸው ከፍ


ያለ ቢሆንም ማስመሰልን ይመርጣሉ እንጂ አምነው
ሊቀበሉትና ሊለወጡ አይወዱም። ይብሱኑ ወንጌላውያኑን
መለኪያቸው ያደርጋሉ። ደርሰውም “አረ በጭራሽ እኛ ምን
አጠፋንና ወንጌላዊያኑ በስኬታችን ስለቀኑብን እንጂ የቱጋ ነው
ልዩነታችን? እነርሱ የሚያደርጉትን ነው የምናደርገው። እነርሱ
የሚሉትን ነው የምንለው።” በማለት ይሞግታሉ።
ከወንጌላውያን ወገን የሆንነውም ብንሆን ከመኻላችን የወጡ
እኛው ያሳደግናቸው ጥፍዋን ፍሬዎቻችን እንደሆኑ

566
ጆንሰን እጅጉ

ዘንግተነው ንጹህ ነን ለማለት እጃችንን እንደ ጲላጦስ


በመታጠብ “አይመለከተንም” ማለትን እንመርጣለን።

ሌሎቻችን የእምነት እንቅስቃሴ እውቀት በጎደላቸው የዋኽ


አማኞች ትምህርት እንደሆነ በመቁጠር ትንሽ ሥልጠና ቢጤ
ሰጥተን ለማደስ እንደክማለን። ውዝግቡ የሚያስቆመው
የእውነት ፋና እስኪበራና እውነተኛ ተሓድሶና የመንፈስ ቅዱስ
መቀጣጠል ድል ነስቶ መድረክ እስኪቆጣጠር ድረስ የተለያየ
መልክ እንደያዘ የሚቀጥል ይመስላል። በሌላ በኩል ደግሞ
የእምነት እንቅስቃሴ ሴጣናዊ ሃይማኖት ነው የሚሉ ወገኖች
ደግሞ ከረር ያለ ጦርነት ይገጥማሉ። እነኝኛዎቹ ኀላፊነት
ለመውሰድ አንገታቸውን የሚሰጡና “ሰዎቹ እነመን እንደሆኑ
ግድ ዐይለንም” የሚሉ ናቸው። ወንድማማች ከሚመስል
ኅብረት ይልቅ ለርተዕ ሥነ-መለኮት ቅድሚያ ሰጥተው
ይታገላሉ። ሐንክ ሐነግራፍ ከእምነት እንቅስቃሴ ጋር ጥቂቶች
የሚያደርጉትን ትግል በማስመልከት ሲናገሩ፦

አሁን ክርስትና ውስጥ ከበቀለው ቀውስ ጋር


ተፋጠናል። ነገር ግን ቀውሱ የካርዝማቲክ ተሓድሶ
እንቅስቃሴ የፈጠረው ስሕተት አይደለም። ትግሉ
የሞትና የሕይወት ትንቅንቅ ነው፣ በርትዕ ክርስትናና

567
የአማልክቱ ዐዋጅ

በመናፍቅነት መኻል፣ በክርስቶስ መንግስትና በሴጣናዊ


እምነት መኻል ያለ የሞት ሽረት ነው። 366 ይላሉ።

ሐነግራፍ በዚህ ጽሑፋቸው የገባንበት ቀውስ ብስለት የሌለው


ወይም ያላደገ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ የፈጠረው
እንዳልሆነ ጠቁመዋል። እንደርሳቸው ከሆነ የገባንበት ትግል
የእምነት እንቅስቃሴን የማደስ ሳይሆን የማጥፋትና ርትዕ
ትምህርትን ደግሞ የማስቀጠል ነው። ከሐነግራፍ አቅዋም ጋር
የምስማማ ቢሆንም ቅይጥነት የተዳበለን እኛ ወንጌላውያን
አማኞች አስቀድመን እራሳችን ልናጠራና ልንታደስ ይገባል
የሚል እምነት አለኝ።

መፍትሄው “በእጃችን ነው!” ጩኽቴ ነው። እኛ የወንጌላውያን


አማኞች ወይም አገልጋዮች የቆምንበትን ድጥና የወደቅንበትን
እርቀት ማየት፣ ማወቅ፣ ማመን፣ መጸጸትና ከበዓዱ
ትምህርትና ልምምድ ለመመለስ መደንገጥ ይገባናል። ርቱዕ
ትምህርት ልባዊ ትኩረታችንን ይሻል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ
መርሆችን መጣስ በዋዛ የሚታለፍ አደይደለም፤ ለመናፍስታዊ
ልምምድ መጋለጥ ፍፃሜው ነውና። ኢየሱስ የአይሁድን
የመጽሐፍት ትርጉምና መንፈስን የመለየት ችግር ተመልክቶ
“መጽሐፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ
የምትስቱ አይደለምን?” እንዳለው አቅለን የተመለከትነው

366
Christianity in crisis: 21st century. (P.104).

568
ጆንሰን እጅጉ

የስነ-አፈታት ችግርና ገሃድ ድክመት ለስሕተት አጋልጦናል፣


ባዕድ መንፈስና የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይቶ አለማወቅን
አስከትሎብናል። የመሣታችንም ይሁን ለሚስቱ ምሳሌ
የመሆናችን ምስጢር ይህው የስነ-አፈታት ግድፈት እንደሆነ
ልብ ያልን ጥቂት ነን። (ማር.12፡24)።

ይህ መጽሐፍ ርትዕ ክርስትናን ለማስቀጠል የሚደረገውን


ትግል ለመቀላቀል የሚያስችል የተሓድሶ ትልም ተሸክሟል።
በወንጌላውያን መሪዎችና ምዕመናን እንዲሁም ከእምነት
እንቅስቃሴ ጋር ንኪኪ ባላቸው መኻል ሰፋሪ አገልጋዮችና
ምዕመናን ላይም ትኩረት አድርጓል። የዚህም ጫና ምክንያቱ
ወንጌላውያኑ ከተዳበላቸው ቅይጥነት በመላቀቅ የትግል ኅብር
እንዲፈጥሩና የእውነተኛው መንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ አካል
የሆነውን የተሓድሶ ቁልፍ እንዲጫኑ ለማድረግ ነው። ይህም
የእምነት ጦርነት ለመዋጋትና የክርስቶስን ርትዕ ትምህርት
አደራን ለመቀበል የሚያዘጋጅ ነው ።

የንቁ መሪ ኀላፊነት
“ንቁ ጠባቂ አጥቶ ክፍቱን ባደረ ቤት ውስጥ መንገደኛው ሁሉ ዘው
በማለት ያሻውን ጉድፍ ሲጥልበት የቆሸሸ እንደሆን ጉድፍን የሚጠርግ
አዳሽ ያስፈልጋል።”367
መጋቢ ሰለሞን አበበ ገ/መድህን

367
የቱሩፋን ናፍቆት (2007፣ ገጽ፣ 109)።

569
የአማልክቱ ዐዋጅ

መሪ የሚፈጽመው ትንሽ ስሕተት ቡኾ ውስጥ ጠብ እንዳለ


ጥቂት እርሾ ዐገር የሚያናውጥ ይሆናል። መሪ ለሕዝብ
መታደስም ሆነ መሳትና መጥፋት የሚወስደው ድርሻ ትልቅ
ነው። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሕዝቡን ድርሻ ሲጠቁምና
ሲያሳስብ የእራሱን የመሪነት ድርሻ በጥንቃቄና በንፅህና
ከተወጣ በኋላ ነበር። “እነሆ፣ እናንተ ገብታችሁ
በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ
እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትንና ፍርድን
አስተማርኋችሁ።” (ዘዳ.4፡5)። መንፈሳዊ መሪን ከስሕተት
የሚጠበቀው ከመለኮት የተሰጠውን መመሪያ በትክክል
የተገበረ እንደሆነ ነው። ሙሴ ሕዝቡን ያስተማረው
እግዚአብሔር ያዘዘውን በጥንቃቄ በመስማትና በትክክል
ትርጓሜውን በመረዳት ነበር እንጂ ምኞቱን ወይም ትውልዱ
የሚፈልገውን አልነበረም። ሙሴም በመሪነት ዘመኑ አስቸጋሪ
የነበረውን የእስራኤል ሕዝብና መሪዎች ለማቅናት የከፈለው
ከባድ ዋጋ መሪዎች ኀላፊነታቸውን ለመወጣት መክፈል
ያለባቸውን ዋጋ ጠቋሚ ነው።

እንደ ሙሴ ካሉ መሪዎች በተቃራኒ ደግሞ እስራኤልን ያሳቱ፤


ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ቃል ወደ አህዛብ ትምህርት ዞር
ያደረጉ አያሌ መሪዎች በእስራኤል ታይተዋል። ከእነኝህም
መሪዎች አብዛኛዎቹ ከፍተኛ ሥልጣን፣ ዝና፣ ተቀባይነት፣

570
ጆንሰን እጅጉ

ክህሎትና ዕውቀት የነበራቸው ናቸው። በክፉ አካሄዳቸው


ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩት ኃያላን መኻል ከነገስታቱ የናባጥን ልጅ
የኢዮርብዓም፣ ኢዮአካዝ፣ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም፣
ፋቂስያስ፣ ዘካርያስ፣ ፋቁሔ፣ ሆሴዕ፣ ምናሴን ማንሳት
ይቻላል። ለነኝህ ሁሉ ነገስታት የክፋት ፈር ቀዳጅ በመሆን
ምሳሌ የሆነላቸው የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓም (2 ዜና.15፡18)
ሲሆን ምናሴ ደግሞ ክፋትን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯል።
“በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አሳለፈ፤ ሞራ
ገላጭም ሆነ፣ አስማትም አደረገ፣ መተተኛም ነበረ፣
መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም
ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።”
(2 ዜና.33፣6)።

በሕዝቡ መኻል የሚመላለሱ፤ የተመረጡና የተሾሙ አሳሳች


መሪዎች ጣዖትን ከሚያመልኩና ከሚከተሉ አህዛብ ይልቅ
ለእግዚአብሔር ሕዝብ አደገኞች መሆናቸውን ይኸው የምናሴ
ታሪክ ምስክር ነው። ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል
ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ
በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ(2 ዜና.3፡9)።
ጣዖትን የሚያመልኩ አህዛብን እንደማጥፋት በሕዝቡ
መካከከል ያሉ አደገኛ መሪዎችን ማጥፋት ቀላል አይደለም።
ምክንያቱም ዐገር ያለመሪ ትቀራለች ወይም ትፈርሳለችና

571
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነው። ንጉስ ሳኦልን ዞር ለማድረግ ዳዊት እስከሚያድግ


መጠበቅና ሁኔታዎችም ለለውጥ እስኪመቹ ድረስ ጊዜ
መውሰድ አስፈልጎ ነበር።

በአጠቃላይ የብሉይ መጽሐፍት በአሳቾችና በስሕተት ላይ


ያላቸው የከረረ አቋም አሳቹን እስከ መግደል ድረስ መሆኑ
ምን ያኽል መሪዎች ስሕተትን ማጥፋት እንደሚጠበቅባቸው
ጠቋሚ ነው። “ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ
በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት ስም የሚናገር
ነቢይ፣ እርሱ ይገደል።” (ዘዳ.18፡20)። መለኮት በተበላሸ
ትምህርትና ሕይወት ላይ ጽኑ አቋም አለው። መጋቢ ሰለሞን
የሐዋርያትን ይህንኑ የመለኮት አቋም መከተልና በሥኽተት
አስተምህሮ ላይ መጨከን እንደ ተሓድሶ መርሖ
ይመለከተዋል። ይህንንም ሲገልጽ “ተሓድሶን ለማምጣትና
ወደ እውነቱ ለመመለስ ሲባል የሐሰት ትምህርት ላይ
መጨከን ግዴታ ነው አንጂ፣ አማራጭ አልነበረም፤ ዛሬም
ሊሆን አይችልም።” ብሏል። ይሁን እንጂ ሁል ጊዜ እጸጽ
ባለቤት አለውና ስኸተትን ስንነካ ባለቤቱንም አብረን
መንካታችን የማይቀር ነው። ስለዚህ በደንብ አድምተን
ማለፍ አይሆንልንም ምክንያቱም ወዳጅነታችንን ያሳጣናል፤
መድረካቸው ይቀርብናል። “ጥበብ” በምንለው የሥጋ ምክር

572
ጆንሰን እጅጉ

በጥንቃቄ ሳንነካካ መተላለፍን እንመርጣለን። አትድረስብኝ


አልደርስብህም ምርጫችን ነው።

መጨከን አቅቶናል! በመካከላችን ያሉ ክፍለ ዘመናት የተሻገሩ


አደገኛ በካይ ትምህርቶችና ልምምዶችን ፍቅር ይበልጣል
በሚል የተንሸዋረረ ምልከታ በርሕራሄ አልፈናቸዋል። እነኝህ
ትምህርቶች እንዲህ ገርበብ ባሉ በሮች ላይ ይቅርና በተዘጉ
በሮች ላይ እንኳ ሳይቀር የግፊት አቅማቸውን ያሳርፋሉ።
ይህንንም ባነሳነው ረዥም የልዩ ዲበ-አካል ሃይማኖት ታሪክ
በመዳሰስ የተሞከረው ምን ያኽል ጨከን ያለ ጠንካራ
ተቃውሞ ማድረግ እንዳለብን ለማስገንዘብ ነው። ለስኸተት
መዘናጋትና ስምና ጥቅስ እየፈለጉለት መሸፋፈን ብሎም
ስኸተትን በንቀትና በቸልታ መመልከት የንቁ መሪ ወይም
የአስተዋይ ክርስቲያን ባሕርይ በፍጹም አይደለም።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ወንጌልን ከማስፋፋት ጐን ለጐን


ጤናማ ወንጌል የመስበክና የሚመሩት ሕዝብ በቃለ
እግዚአብሔር ላይ የጸና አቋም እንዲኖረው በማስተማር
መትጋት አለባቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን እንዲያደርግ
ጢሞቲዎስን ይመክረዋል። “እነዚህን አስተምርና ምከር።
ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ
ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል
በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን በትዕቢት ተነፍቶአል

573
የአማልክቱ ዐዋጅ

አንዳችም አያውቅም።” (1 ጢሞ.6፡3፣ 4፡13)። ሐዋርያው


በዚሁ መልዕክቱ በግልጽ “ልዩ ትምህርት” በማለት የበየነው
ትምህርት እንዳለ አሳይቷል። ይህም ትምህርት ኢየሱስ
ካስተማረው ጤናማ ትምህርት የተለየ እንደሆነና
እግዚአብሔርን ለመምሰልም የማይጠቅም እንደሆነ
ጢሞቲዮስን አስረድቶታል።

የእግዚአብሔር ወዳጆች፦ ከአዲስ ኪዳን ምክሮችና


ማስጠንቀቂያዎች በተጨማሪ የነቢያቱን የመሪነት ትግል
አጠር አድርገን ተመልክተናል። እንዲሁም የዜና መጽሐፍ
የናባጥን ልጅ ኢዮርብአም እስራኤልን በማሳት ፈር ቀዳጅ
እንደሆነና ምናሴ ደግሞ በኢዮርብአም የተጀመረውን ክፋት
እንዴት ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዳሻገረው መርምሮ እንደዘገበ
ዐይተናል። ይህ ታሪክ በኢማኑኤል ሲውዲንበርግ የተጀመረው
የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፋና በእምነት ቃል እንቅስቃሴ ሰባኪያን
በተለይም በኬኔት ሄገን ከፍ ወዳለ ደረጃ የተጓዘበትን
የውድቀት መንገድ በድጋሜ አሳይቷል።

ከዚህ ሁሉ የምንማረው ለተዛባ ሥነ-መለኮትና ልምምድ


የመሪዎች የተጠያቂነት ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን ነው።
ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጣለብንን ቆሻሻ የሚያስተውሉ
ጥልቅ ዕይታ ያላቸው “አዳሽ” ዐቃቢያን መሪዎች
ለቤተክርስቲያን ያስፈልጓታል። እያንዳንዱ አማኝም ግብታዊ

574
ጆንሰን እጅጉ

ልምምድንም ሆነ ትምህርት መነሻና ዕድገት በመፈተሽ


እራሱን መመርመር እንዲችል ወደ እራሱ የመመልከት
ኀላፊነት አለበት። በአጠቃላይ “የአማልክቱ” የልዩ ዐዎንታዊ
ዐዋጅ ፍልስፍና እየተበላሸ ለመጣው የቤተክርስቲያን ጠረንና
በአገራችን የወንጌል ሥራ ላይ ለጣለው ጨለማ የኢትዮጵያ
ወንጌል አማኞች መሪዎች እንዲሁም ምዕመናንም ጭምር
ተጠያቂዎች እንደሆንን አምናለሁ።

በእርግጥም የጠፋውን ለማረምና ለማቅናት ኀላፊነትን


መደበቅ ከተጠያቂነት አያድነንም። ኑፋቄን አትድረስብኝ
አልደርስብህም በሚል ብኺል ድል አንነሣውም። የፍቅር
መአድ በጋራ አብሮ መቁረስ አይለውጠውም። በሚገባ
የተቀመሩ መጽሐፍትን በማዘጋጀትና በማሰራጨት ፊት ለፊት
በመጋፈጥ ባዕድነት የተዳበለውን ሥነ-መለኮት ለማስተካለል
መሥራት አማራጭ አይደለም። ስኹት ሥነ-መለኮትን
ማስፋፋት ለእውነት እንቅፋት ማኖር ነው፤ እንዲሁ ሁሉ
ስኹት አስተምህሮን መግለጥና ማረም የእውነትን በር
መክፈት ነው። በዚህ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ የውድቀታችን
ዋና አካል የሆነውን የስነ-አፈታት መሠረታዊ ችግርና የግንዛቤ
ክፍተት የፈጠረብንን መዘናጋት በማንሣት የመፈትሄ አቅጣጫ
አስቀምጣለሁ።

የተዘነጋው የፍርድ ወንበር

575
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሐዋርያው ጳውሎስ ተደጋጋሚ በሆነ ማሳሰቢያው


የሚያስተምረን የሚሰብኩ ሰዎች ትልቅ ኀላፊነትና
ተጠያቂነት እንዳለባቸው ነው። ሐዋርያው ኀላፊነቱን
ስለተወጣ አክሊል እንደተዘጋጀለት ያምን ነበር። “ወደ ፊት
የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ
የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል።”(2 ጢሞ.4፡8)። ይህ
ቢሆንም በሌላ በኩል ሲታይ ከልክ ያለፈ ድፍረት
አልነበረውም።

አክሊል እንደሚጠብቀው በርግጠኝነት ቢናገርም ከአክሊሉ


በፊት በጌታ ፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናል በማለት
ተስፋውን ከፍርድ ወንበር ጀርባ ያኖራል። “መልካም ቢሆን
ወይም ክፉ እንዳደረገ፣ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን
በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር
ፊት ልንገለጥ ይገባናልና፤፤” (2 ቆሮ.5፡10)። ከዚህም
እንደምንረዳው በአዲስ ኪዳን ፈጣን ፍርድ ነው እንጂ የቀረው
ለፍርድ መቅረብ አይቀርም። ሐዋርያው ምንም እንኳ
ኀላፊነቱን እንደተወጣ ቢያምንም በፍርድ ዙፋን ፊት
እንደሚገለጥና ሥራው እንደሚመዘንም ያምን ነበር።

በዚህም ምክንያት ወደ እራሱ በሚመለከትበት ጊዜ ፍርድን


በፍርሃት ሲመለከት ወደ ጌታ በሚመለከትበት ጊዜ ደግሞ
ሽልማትን በናፍቆትና በጕጕት ይመለከት ነበር ማለት

576
ጆንሰን እጅጉ

ይቻላል። ያዕቆብም በተመሳሳይ ሁኔታ የኀላፊነትን አስፈሪነት


ይነግረናል። “ወንድሞቼ ሆይ፣ ከእናንተ ብዙዎቹ
አስተማሪዎች አይሁኑ፣ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል
ታውቃላችሁና።” (ያዕ.3፡1)። ይህ የያዕቆብ የአስተማሪ ቅነሳ
ማሳሰቢያ የነበረበትን የፍርድ ፍርሀት በግልጽ ያሣያል።

በአንጻሩ አሁን ላይ ያለን አገልጋዮች ልል አቋም የፍርድ ወንበር


እንደሚጠብቀን እንደማናምን ጠቋሚ ነው ማለት ይቻላል።
ከዚህም የተነሣ ለዘብተኛና መኻል ሰፋሪ ነን። በስኹት
አሠራሮች ወይም ትምህርቶች ላይ ቁጡዎች አደለንም።
ስለዚህም ደግሞ ጨክነን ያደባየነው ትምህርት የለም ማለት
ይቻላል። ሽልማት መናፈቃችን መልካም ቢሆንም ካለልክ
መመካታችን ግን አዘናግቶናል። እራሳችንን ተመልክተን
ከስኽተቶቻችን በግልጽ ከመታረም ይልቅ መድበስበስን
እንመርጣለን። ሽልማቱ የተቀመጠው ከፍርድ ወንበር ጀርባ
እንደሆነ ዘንግተናል። ሽልማቱን መታመናችን እንዳለ ሆኖ
በፍርድ ወንበር ፊት መገለጣችን የማይቀር እንደሆነ በማሰብ
ትንሽ ብንፈራ መልካም በሆነ ነበር።

577
የአማልክቱ ዐዋጅ

“መገለጥን” ያላቁ ጆሮዎች


“የመጽሐፍ ምርጫችን እና የምናነብበት መንገድ የሚወሰነው ጸሓፊው
በጻፈበት ዐላማና የትኩረት አቅጣጫ ነው።” 368
ጆን ስቶት

በአጠቃላይ ከሚሊኒየም ወዲህ የልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ


ትምህርትና ልዩ ጸሎት ልምምድ በኢትዮጵያ ወንጌል
አማኞች ቤተክርስቲያን ምዕመን መኻል እንኳ ሳይቀር
በስፋት እየተስፋፋ መጥቷል ማለት ይቻላል። ተተኪ
አገልጋዮች በትንቢት፣ በዝማሬና በሥብከት ለማገልገል የልዩ
ዐዎንታዊ ዐዋጅ ስልትን ማወቅና ማጥናት ቁልፍ እንደሆነ
እያሰቡ ነው። የልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ልምምድ ለስብከታችን፣
ለጸሎታችንና ለዝማሬያችን አንድ ዓይነተ ቅርፅ የሰጠ መልክ
ማውጫ ሞልድ ሆኗል። ይህም መንፈሳዊ እንቅስቃሴያችንን
ከእምነት ቃል እንቅስቃሴ ጋር እያመሳሰለው እየመጣ ነው።
ልምምዱ ብዙዎቻችንን ግራ ለምንጋባበት እንግዳ የሆነ
የጉባኤ ጠረን አንዱና ዋነኛ ምክንያት እንደሆነም ቅን ልቦና
ያለው የሚያስተውለው እውነት ነው። በሚመጣው ዘመን
ይህንን መልክ ማውጫ ሞልድ መስበር ካልተቻለ ተሓድሶን

368
John Stott, Understanding the Bible. (1984, P, 1).

578
ጆንሰን እጅጉ

ማሰብም ይሁን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ዕድገት ማሰብ


እንደማይቻል አስባለሁ።

የወንጌላዊቷ ቤተክርስቲያን ከሥነ-መለኮት ምልከታዋ ጋር


ለማይገጥም እንዲህ ዓይነቱ የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና ለምን
ተገዛች? የሚል ጥያቄና ቁጭት በልባችን ሊያቃጭልብን
ይገባል። በቃለ እግዚአብሔር መርምራና ፈትሻ እውነትን
ከሐሰት ለይታ ጽኑ አቋም ለምን አልያዘችም? በጉያዋ ያደጉ
የተሓድሶ ጉዞዬን ያስቀጥሉኛል ያለቻቸው ክዋክብቶቿ
ደርሰው የመሪነቱን ተረኝነት ሲጨብጡ ጉልበታቸው ላልቶ
በአማልዕክቱ “የእምነት ቃል” ግርግር ደርሰው መዘፈቃቸው
ለምንድነው? ምናልባት መገለጥን የሚያልቀው አዲስ ነገር
ናፋቂ ባህላችን ልባቸውን አርዶ እግራቸውን አንሸራቶ ዐቅም
ነስቷቸው ይሆን?

የዕድገታችን የኋላ ታሪክ እንደሚያሳየው የከረምንበት ባህል


መሠረቱን በውል ባልተረዳነው “መገለጥ” ላይ የተንጠለጠለ
ነው። በጃችን ያለውን የመረጃ ምንጭ ማለትም መጽሐፍ
ቅዱስ፤ የጸሓፊዎቹን ትልም ባማከለ መንገድ በመመርመር
የበሰለ አይደለም። ርቱዕ ትምህርትን ለሚያስተምሩን ሁነኛ
መጽሐፍትና መድረኮች ብዙም ግድ የለንም። በርከት ያለ
ቍጥር ያለው ሕዝብ የሚያስከትሉ መሪዎችን መጠራጠር
አንፈልግም። ተካልኝ ይህንን ጭፍንነት አስመልክቶ ሲናገር፦

579
የአማልክቱ ዐዋጅ

“የመረጡት ሰው መሠረታዊ የአስተምህሮ ጥመት እንዳለበት


ሳይገነዘቡ፤ በርካታ ተከታዮች እንዳሉት ካወቁ ትምህርቶቹን
ያለ ምርመራ ይጋቱታል።”369 በማለት ወቅሷል። ዳሩ ተካልኝ
እንዳለው ችግሩ መጋታቸው ብቻ ሳይሆን ለመመርመር ደፋ
ቀና የሚሉ ወገኖችን ማጥላላታቸውም ጭምር ነው።

በማክፋፋታቸውም፤ በመጽሐፍት ምርመራ ላይ የትምህርት


ሥርዐት ቀርጸው የሚሰሩ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤቶችን
በጥርጣሬ እንድንመለከት አድርገውናል። ቃሉን በማስተዋል
እንድንነቃና እንድንነቃባቸው ስለማይፈልጉ ሥነ-መለኮት
“ያደርቃል!” ይሉናል። “አማልክት” ባወረዱት ደረቅ ዝናብ
በስብሶ ከመበሳበስ፤ ከምንጩ አጠገብ ደርቆ መሰንበት
እንደሚሻል ማን በነገራቸው። ለነገሩ ጥያቄው ንጹህ ምንጭ
ማን ተጠጋ የሚለው ነው እንጂ ምንጩን የተጠጋ ረሰረሰ
እንጂ ማን ጎበረረ? ሥነ-መለኮትም ችግሩ እንደ ልዩ ዲበ-
አካል ካለ የሰው ፍልስፍና ጋር የተጣባና የተባረዘ እንደሆነና
መንፈስ ቅዱስን በማግለል በሰው ተፈጥሯዊ የአዕምሮ
ክህሎት ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ እንጂ በመንፈስ
ቅሰዱስ በሚደረግ የቃል ምርመራ ላይ የተመሰረተ ሥነ-
መለኮት አሳምሮ ያረሰርስ።

369
የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! (ገጽ.53)።

580
ጆንሰን እጅጉ

በአንድ በኩል ሁሉን መርምሩ እውነቱን ያዙ በሚለው


መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሖ ላይ አብዛኛዎቻችን
እንስማማለን። በሌላ በኩል ግን ተግባር ላይ እንዲህ
አደለንም። ይህ ክፍተታችን ደግሞ “አማልክቱ” እንዲንቁንና
ብሎም በመካከላችን እንደፈለጉ እንዲቦርቁ አግዟቸዋል።
ለቃለ እግዚአብሔር ሥነ-አፈታት ካለን ለዘብተኛ አቋም፤
ለመገለጥ ካለን ግነት የተነሣ “መገለጥ” የሚል ማስታወቂያ
ሲጎሰም ወደ ሰማንበት ሁሉ ክንፍ አውጥተን በረናል።
ከነበርንበት ቤተ-እምነት አጥቢያ ተነቅለን መንገደኛውን
ለመቀላቀል የሽኝት ደብዳቤ ለመቀበልና ስንብት ለማድረግ
እንኳ ትዕግሥት ያጣንበት ጊዜ ብዙ ነው።

በቀላሉም የሚነሳ፣ ከኛ ውጪ የሆነ ወይም የኛን ጥረት


የማይፈልግ ዋዘኛ እንቅስቃሴ (movement) ወይም መንፈሳዊ
መነቃቃት ናፋቂዎች መሆናችንን ስንፍና ሳይሆን
መንፈሳዊነት እንደሆነ ቆጥረናል። ሳንመረምር መሯሯጣችን
በልዩ ዲበ-አካል የቃል ዐዋጅ የሐሰት መነቃቃቶች ላይ
ጥዶናል። የተሣፈርነው አውቶቡስ መሆኑን ረስተን
እራሳችንን እንደ ብልጥ ቆጥረን ዘና ብለናል። ያም ሆኖ ግን
ብናተርፍ መልካም በሆነ ነበር። ዳሩ ግን ሰንብተን ሲከፋን
ፌርማታ ላይ መውረዳችን አልቀረም። “አንዳንድ የዐዲስ
አበባ መጋቢዎች እንደ አውቶብስ አሽከርካሪዎች ናቸው”

581
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንደሚባለው፤ አሽከርካሪው ዞር ብሎ ሳይመለከተን


አዲሶቹን ተሳፋሪዎች በፋንታችን አዝሎ ከዓይናችን ፊት
ጥሎን ነጉዷል። ስንት ጊዜ የያዝነው ተራግፎ የቀረበን ርቆን
ብቻችንን ቀርተናል!

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1980 ዎቹ ውስጥ በዐዲስ


አበባና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በነበረ አንድ እንቅስቃሴ
ተማርኮ ከነቤተሰቡ ቀኝ እጁን ሰጥቶ የነበረ አንድ ወዳጄ
ይህንኑ እያነሣ በቁጭት ሲያወሳኝ፦

በወቅቱ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ስተናል፤ ለዚህ


ምክንያቱ ደግሞ “የቃል መገለጥ” የሚል መርሖ
መከተላችን ነው። ወንጌል ስንመሰክር አጋንንት
ስለጮህልንና ልሳን ስለተናገርን ያመኑትንም እነዚህ
ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፣ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣
በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፣ እባቦችን ይይዛሉ የሚል ጥቅስ
አንስተን “በራልኝ” በሚል ከኛ በፊት የነበሩትን ለወንጌል
ትልልቅ ዋጋ የከፈሉ አገልጋዮችን፤ እነ ጋሽ ኪዳሞን
(የቃለ ሕይወት ወንጌላዊ) እንኳ ሳይቀር እንዳልዳኑ
እስክናስብ ድረስ ናቅናቸው። የኋለኛው ቤት ክብር
ከፊተኛው ቤት ክብር ይበልጣል የሚል ጥቅስ መዘን፤
ቀድሞ የነበሩት የወንጌል አማኞች ቤተ-እምነት የጸሎት
ቤቶች እንደ አረጁና እንደሚጠፉ በአዳዲሶቹም
የተሓድሶ ቤተ-እምነቶች እንደሚተኩ ቃል
“ተገለጠልን” ወይም “በራልን” በማለት ተነበይን።

582
ጆንሰን እጅጉ

ይህ ወዳጄ በወቅቱ የነበረውን እንቅስቃሴ የተቀላቀለው


መንፈሳዊ መነቃቃትን ስለናፈቀና “በራልኝ” የሚል ብሂል
የተሞላው በወቅቱ የነበረው ስሜትን ሞቅ የሚያደርግ
ስብከት ልቡን ስላንሆለለው ነበር። እንደዚህ ወንድማችን
ሁሉ ብዙዎቻችን “መገለጥ” ከተባለ ሊመረመርና ሊደረስበት
የማይቻል፤ ለተናጋሪው ብቻ የተሰጠ ልዩ ስጦታ እንደሆነ
ቆጥረን ዓይናችንን ጨፍነን ባደግንበት ተቋም ላይ እንኳ
ሳይቀር ክተት አውጀን ጦር መዘናል። የዚህ ወንድም ታሪክ
ብዙዎቻችንን ይወክለናል። ምክንያቱም ራሳችንን፣
ትዳራችንን፣ ሥራችንን፣ ገንዘባችን፣ ጊዜያችንንና
ወጣትነታችንን በተመሳሳይ ውሳኔ የሰዋን ብዙ ነን።
አብዛኛዎቻችን ብዙ ለመገንዘብ የሚያስቸግሩን መልስ
ያጣንላቸው ነገሮች ሲያጋጥሙን እንኳ መርምረን እውነቱን
ለመረዳት አንፈቅድም።

የዚህም ምክንያቱ ምናልባት ሰነፎች ስለሆንን ወይም


መመርመር ኃጢአት እንደሆነ ስለምናስብም ሊሆን ይችላል።
ወይም ለምንናፍቀው መነቃቃት እንቅፋት እንዳንሆን
በመፍራትም ሊሆን ይችላል። አሊያም “የመገለጥ መንፈስ”
ከሁሉ የሚበልጥ ስልጣን እንዳለው ስለምናምን ይሆናል።
ተካልኝ ስሜታዊነት አንዱ ከምርመራ የመራቃችን ችግር
እንደሆነ ይጠቁማል። ይህንንም አስመልክቶ “ነገሩን

583
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንዳንመረምር ትምህርቱ የፈጠረብን የደስታ ሲቃ


ስሜታችንን ገዝቶታል። የቢሆንልኝ ፍላጎታችንም
ከመርማሪነት ወደ ጠባቂነት የአዕምሮ ቅኝታችንን
ለውጦታል።” ብሏል።370 ያም ሆነ ይህ ግን ቃሉን
ከመመርመር ይልቅ “መገለጥን” የምንናፍቅ፣ የምንከተልና
የምንፈራ ሆነናል ማለት ይቻላል። ይህም “የመገለጥ”
ዝንባሌ፤ አደጋ ውስጥ መሆናችንን ጠቋሚ ነው። ተካልኝ
ይህንን በማስመልከት ሲያሳስብ፦ “ያልነው ነገር ድንገት
የተከሰተ (ሰደን ሬቬሌሽን) ሲሆን መጠንቀቅ መልካም ነው።
ከእኛ በፊት የጌታን መንገድ በጠበጠቡ የእምነት አባቶቻችን
ዘንድ ዱካው ካልታየ፣ ጥንቃቄያችንን እንጨምር።”371
በማለት አስፍሯል።

እውነቱን ለመናገር ብዙዎቻችን ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ


በህልሞቻንና በራዕዮቻችን ካለምንም ጥንቃቄ
እንታመናለን። ቃሉን ስንሰማ ወይንም ስናጠና ልባችንን
የምናዘነብለው ልምምዳችንን እንዲያጸድቅልን ወይም
የጎደለንን ለማሟያ ብቻ በመሆኑ ምክንያት ለቃሉ ያለን
ክብር ትንሽ ነው። ሰባኪዎቻችን ያዩትን ራዕይ ከነገሩን በኋላ
ወደ ቃሉ ሲሄዱና ያዩትን ራዕይ በቃሉ አስደግፈው
ሲተርኩልን ጆሯችን ይነቃቃል፤ አሜንታችን ይደምቃል።
370
ዶ/ር ተካልኝ። የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! (ገጽ. 136).
371
Ibid., (p,204).

584
ጆንሰን እጅጉ

በሌላ በኩል ደግሞ በህልም ወይም በራዕይ ወይም በትንቢት


ካላስደገፉልን በስተቀር ቃሉ ሙሉ እንደሆነ አንቆጥርም
ወይም መንፈስ ቅዱስ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አናምንም።
እንደዚህ ዓይነቱን “የመገለጥ ስብከት” የሚከሰትበትን ጉባኤ
ታዲያ የስብከቱን ጭብጥ ሳንመረምር በደፈናው
“የተቀጣጠለ” ወይም “ሪቫይቫል ያለበት” የሚል ስም
እንሰጠዋለን።

እውነቱ ሲገለጥ ግን ብዙ ጊዜ የምንሞግትለት ጉባኤ የዲበ-


አካል ሃይማኖት ልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ልምምድ የነገሰበት
እንጂ ሪቫይቫል የሚታይበት አይደለም። እውቁ አሜሪካዊ
ፈዋሽ፣ “የአማልክቱ” ማህበር ፊት አውራሪ፣ ፊንሃስ ፓንክረስ
ኪዊምቢ በዚህ ዘመን ቢሆን የኖረው ጉባኤውን “የሪቫይቫል
ማዕከል” እንደሆነ ቆጥረን፤ “እኔም ልቀባ” በሚል ምኞት
ከማጨናነቅ የሚመልሰን ነገር ያለ አይመስልም። ምክንያቱም
ኪዊምቢ ስብከቱ መገለጥ፣ ተአምራቱ የሚታይ እንደ ነበር
አንዳንድ የታሪክ ትርክቶች ያትታሉ።

ሞስሊ የዲበ-አካል ሃይማኖት መነቃቃትን እንደማይከላከል


ሲናገሩ፦ “ዲበ-አካላዊው ሃይማኖት ለሚፈልገው ነገር
372
ኀልወትን የመለማመድ ቅን ፍላጎት አለው።” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ይህ ፍላጎት ክፉ መንፈስንና ቅዱስ መንፈስን
372
Mosley, R New Thought, Ancient Wisdom፣ (2006, P, 50).

585
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያልለየና ለመለኮት ፍላጎት ደንታ የሌለውና በእራስ ፍላጎት


የታወረ እንደነበር ተመልክተናል። የእንቅስቃሴው በውጪያዊ
ኀይል መነቃቃት ፍላጎት፤ የሰውን መለኮታዊ ክፍል (አዕምሮ)
በማነቃቃት የሰው ፍላጎቶችን በቃል ዐዋጅ አማካኝነት
ለመመለስ የሚደረግ ነው። ስለዚህ መነቃቃቱ አባይና
የመለኮትን ትልም የማያሳካ ነው። “መገለጥም” ይሁን
“መነቃቃት” የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት ከመረዳት ይልቅ
ጆሮአችንን ካፈዘዘውና የመጽሐፉን ሰዎች በሕይወት ለውጥ
እንድንመስላቸው የማይመራን ከሆነ፤ እውነተኛ መነቃቃትና
ከቃሉም የተገኘ ዕውቀት አይደለምና ደንግጠን ልንሸሽው
ይገባል እንጂ ልንጠመድበት አይገባም።

አዕምሮ ያዘረፈ መገለጥ


የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት አንዱ ምልክቱ ጥልቅ ወደ ሆነ
የቃል ዕውቀት አገልጋዩንም ሆነ ምዕመናኑን መምራቱ ነው።
አእምሯችን ከፈጣሪ የተሰጠን ትልቅ ሥጦታ ነው። መጽሐፍ
ቅዱስ እንደ ባለ አዕምሮ እንድናስብ እንጂ አዕምሮን
አለመጠቀምን አያበረታታም። መንፈስ ቅዱስ አዕምሮን
በመክፈት ያግዘናል እንጂ አዕምሮን በመጋረድ ከፍቃዳችንና
ከዕውቀታችን ወጪ አይነዳንም። እውነተኛ የሆነ የመንፈስ
ቅዱስ መነቃቃት ሪቫይቫል በዕውቀት ያበለጽጋል እንጂ
አዕምሮን በማዳከም አያፈዝም። (1 ጴጥ.4፡7፣ 2 ቆሮ.5፡13)

586
ጆንሰን እጅጉ

አዕምሮን የሚያጣጥል የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና መጽሐፍ


ቅዱስን በመመርመር የሚገኝ ዕውቀትን አክፋፍቷል።
“መገለጥ” የሚል ፈሊጥ በማንገብም የቤተክርስቲያንን
እንቅስቃሴ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ለመገዳደር ችሏል።
ተጽዕኖው ዘመን ተሻግሮ አሁን ያለንበት ዘመን ድረስ
ተዘርግቷል። አባይ ነቢያቱ “እንደ ወረደ ላገልግላችሁ” ወይስ
“ከመጽሐፉ” በሚል ሕዝቡን ሲያማርጡና ቃሉን ከመንፈሱ
ሲያቃርኑ መመልከታችን የዚህ አስረጂ ነው። መገለጥ በሚል
መሸፈኛ አንዳንድ ጉበኤ ላይ የሚግተለተለው ባዶ ዐዎንታዊ
ዐዋጅ ናዳ የሚፈጥረው የስሜት ንረት ከመንፈስ ቅዱስ
መነቃቃት እንደራቅን ማረጋገጫ ነው። እንደውም
“ማነቃቃት የተፈለገው ሰውነትን ነው ወይስ የሰውን
አማልክታዊ ክፍል?” የሚል ጥያቄ እስከ ማስነሳት ይደርሳል።

“የአማልክቱ” ታሪክ እንደሚያሳየን አብዛኛዎቹ መሪዎች ወደ


መጽሐፍ ቅዱስ አጭርና ረጅም ጉዞ ያደረጉ ናቸው። አጭር
ጉዞ ያደረጉት በዚህ መጽሐፍ ላይ እንደተቀመጠው የተወሰኑ
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ብቻ ጨለምተኛ ማብራሪያ
የሰጡ ናቸው። ረጅም ጉዞ ያደረጉት ደግሞ እንደ
ስዊዲንበርግና ፊሊሞር፤ የክርስትና ዶክትሪን ላይ የራሳቸውን
የዕውር ድንብር ፍቺ ያስቀመጡና የመጽሐፍ ቅዱስ
ማብራሪያ ኮመንተሪ ለመጻፍ የሞከሩ ወይም ሙሉ የእምነት

587
የአማልክቱ ዐዋጅ

ዶግማ ከልዩ ዲበ-አካሉ ፍልስፍናቸው ጋር እንዲስማማ


አድርገው የፃፉ ናቸው። እነርሱ እንደሚናገሩት ከሆነ ይህንን
ሊያደርጉ የቻሉበት የዕውቀታቸው ምንጭ ከመንፈሳዊው
ዓለም የሚያገኙት “መገለጥ” ወይም መረጃ ነው። ይሁን
እንጂ ሥራዎቻቸውን ስናጤን፤ ምክኒያታዊነት የሌለው
የአዕምሮ መጨለም ወይም በውጪያዊ ኀይል የመነዳት
ውጤት እንደሆነ እንገነዘባለን።

በቤተክርስቲያንና በዙሪያዋ የነበሩ እንቅስቃሴ መሪዎችን


ታሪክ ስናጠና የተወሰኑት የዲበ-አካል ሃይማኖት
አቀንቃኞቸች የወንጌል ሰባኪያንም ነበሩ። እነኝህ ሰባኪያን
ታዲያ እንገዳውን ፍልስፍና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አዳብለው
ስለሚሰብኩ ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ “መገለጥ” እንዳላቸው
የሚነገርላቸው ናቸው። እንዲህ ዓይነቱን አቀራረብ ተካልኝ
‘መሸሸጊያ’ ብሎታል። “ሌላው መሸሸጊያ ከማንም
አልተማርኩትም በቀጥታ ከእግዚአብሔር አገኘሁት የሚል
ነው።”373 በርግጥም “መገለጥ” የሚለው ማመካኛ ዲበ-
አካላዊውን የሃይማኖት ፍልስፍና ለሚከተሉት
መሸሸጊያቸው ነው። ዐዋቂ ይባሉ እንጂ ትምህርታቸውን
አስተውለን ስንሰማና በቃለ እግዚአብሔር ስንመረምር
አዕምሯቸውን የተዘረፉና ምንም የማያውቁ ቂሎች እንደሆኑ
እንገነዘባለን።
373
የጸሎት ቤት-የንግድ ቤት?! (ገጽ. 54)፡፡

588
ጆንሰን እጅጉ

ከምርመራ መራቃቸው ሳይበቃ ትምህርታቸውን


ለመመርመር የሚነሳውን ቅንነት የጎደለው በማለት ጠላት
ያደርጉታል። እንዲህ ዓይነቱን ፍረጃ ተካልኝ ሲተች፦
“‘በአዕምሮህ ሳይሆን በመንፈስህ፤ በቅንነት ብቻ ለአራት
ሳምንት ስማኝ’ የመልዕክታቸው ክፍል ሆኗል። ቅንነት በሚል
የተጠየቅነው የነገሮችን አንደምታ ሳንመረምር ለሰማነው
አሜን እድንል ነው።”374 በማለት አስፍሯል። በርግጥም
ተከታዮቻቸውን ያየን እንደሆን አእምሯቸውን ቤታቸው
አስቀምጠው እንዲመጡ የታዘዙና የዐቅላቸውን ነፃነትን
የተገፈፉ ናቸው። በሌላ በኩል ዐሳቢያዊያን የተከማቹበትን
ጉባኤ ለመስበክ እግር ከጣላቸው ጉባኤው “ቅንነት
እንደጎደለው”፤ “መንፈስ ቅዱስ እንዳይንቀሳቀስ የሰው
አዕምሮ እንደያዘው” በማስመሰል መኮነንና መቆጣት
ልማዳቸው ነው። የሥነ-ልቦና ጫና አድርገው ከተሳካላቸው
የአድማጫቸውን ጆሮ ለማፍዘዝ ይሞክራሉ። የሪቫይቫል
መለኪያቸው “አሜንታና ጩኽት” ሞቅ እያለ ከመጣ ደግሞ
“አሁን ክብር ወደቀ” በማለትና በማወጅ ሕዝብን
ያደናብሩታል።

የዲበ-አካል ሃይማኖት ሊቃውንቱንም ሆነ ሰባኪያኑን ታዲያ


ይህ የዕውር ድንብር አካሄዳቸው ወይም የጉዟቸው ሁኔታ

374
lbid. (p, 56).

589
የአማልክቱ ዐዋጅ

ያመሳስላቸዋል። ይኸውም ጉዟቸው “ከመንፈሳዊ መገለጥ”


ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የተደረገ ጉዞ መሆኑ ነው። መጽሐፍ
ቅዱስን የሚያነሱት ከመንፈሳዊው ዓለም “የተገለጠላቸውን
ነገር” ለማብራራት እንዲያግዛቸው ብቻ ነው። ወይም
የገመቱተን ነገር እውነት ለማድረግ። ይህንኑ የተደነቃቀፈ
የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎምና አጠቃቀም እክል ተካልኝ
ሲያነሳ፦“የትርጓሜያቸው ችግር ጥቅሶችን ከተነገሩበት
ታሪካዊ ዐውድ ማላቀቅ፣ መጽሐፍቱ የተደረሱበትን
መሠረታዊ ዐላማ መዘንጋት፣ ዋነኛ ሐሳቦችን ወደ ጐን
ማድረግ ናቸው።”375 በማለት በዝርዝር አስቀምጧል።

እርግጥም በዚህም ጥቅስን ከአውዱ በሚያላቅቅ አካሄዳቸው


የመጽሐፍ ቅዱስን ስልጣን አቃለዋል። ለምሳሌ ያኽልም
ፊሊሞር ከመንፈሳዊው ዓለም በሚያገኘው መገለጥ እና
በልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍናው በመደገፍ የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥቅሶችን ከአውዳቸው በማላቀቅ ተርጉሞ መፃፉ በቂ
ማስረጃ ነው። ሲውደንበርግም እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር
ቢያደርግም በዘመኑ እንደ ታላቅ የሃይማኖት አገልጋይ
በመታየቱ የተቃወመው የሃይማኖት አካል አልነበረም።
በአጠቃላይ እውነትን መርምረን ከመረዳት የሚያዘናጋ

375
lbid. (p, 201).

590
ጆንሰን እጅጉ

አዕምሮን የሚዘርፍ “መገለጥ” ከአጋንት ስለሆነ ልንደነቅበት


ሳይሆን ልናስወግደው ይገባል።

የውጫዊው መንፈስ ተቃርኖ


ጥቅስን ከአውዱ በማላቀቅ ትርጉም የመስጠት አካሄድ
በሥነ-መለኮት ምልከታ ኢ-ሐቲት (eisegesis) ይባላል። ኢ-
ሐቲት በአዕምሮ ውስጥ በመገለጥም ይሁን በሌላ የመረጃ
ምንጭ የተገኘን ዕውቀት ወይም ትርጉም ወደ መጽሐፍ
ቅዱስ በማስገባት ማንበብ ማለት ነው። በዚህ መንገድ
መጽሐፍ ቅዱስ ሲተረጎም ትልቁ ስልጣን የመጽሐፉ ዐውድ
ሳይሆን የተርጓሚው ወይም ለተርጓሚው የሚገልጥለት
መንፈስ ነው። በዚህ መልክ ጥቅስን ከዐውድ የሚያላቅቅ
መንፈስን “ውጫዊ የመገለጥ መንፈስ” ልንለው እንችላለን።
ይህ መንፈስ ከቃሉ ውጪ በሆነ ውጫዊ መረጃ ቃሉን ለመግለጥ
የሚሠራ ክፉ መንፈስ ነው። እንዲህ ዓይነቱ አሠራር
ቤተክርስቲያንን ለስኹት አሠራር አሳልፎ ይሰጣታል፤
አልፎም እርስ በእርስ የመከፋፈልና የመለያየት ምክንያትም
ይሆናልና እጅግ አደገኛ ነው። ይህ አሠራር እስልምናን
ጨምሮ በርካታ ስኹት እንቅስቃሴዎችን የወለደ ትልቁ
የክርስትና ተግዳሮት ነው።

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ቃሉ ውስጥ ያለውን ትርጓሜ


ታሪካዊና ሥነ-ጹሑፋዊ እውነታውን እንድንገነዘብ

591
የአማልክቱ ዐዋጅ

በማድረገግ የአውዱን ፍቺ የሚያሳየንን መንፈስ “ውስጣዊ


የመገለጥ መንፈስ” ልንለው እንችላለን። እንዲህ ዓይነቱ
መንፈስ ወደ ቃሉ ውስጥ እንድንመለከት በማገዝ
ቤተክርስቲያንን ከእጸጽ ስለሚጠብቅና ስለሚያነፃት እጅግ
አስፈላጊ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ይህንን ውስጣዊ የመገለጥ
አሠራር ሳንገነዘብ ከመንፈሳዊ ዓለም መረጃ በመፈለግ ለመረዳት
መሞከር ለአደገኛ ስሕተት ያጋልጣልና ልንጠነቀቅ ይገባል።

ቅዱሳን ሐዋርያቱ እንደሚመሰክሩት የእግዚአብሔር ቃል


ውስጣዊ መንፈስ ያለው መጽሐፍ ነው። “የእግዚአብሔር
ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፣
የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና
ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ
ይጠቅማል።” (2 ጢሞ.3፡16)። ይህ በቃሉ ላይ የሚሰፍ
መንፈስ የማስተዋል መንፈስ ሲሆን አንባቢው የተጻፈውን
ነገር እንዲያስተውል አአምሮውን በመክፈት የቃሉን ፍቺ
በመጽሐፉ ዐውድ እንዲረዳ ይሠራል። “ይህንም ስታነቡ
የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ
ትችላላችሁ።” (ኤፌ.3፡4)። ይኸው የመጽሐፍ መንፈስ ነው
ለሐዋርያቱ አስቀድሞ በነቢያት መጽሐፍት የተነገረውን
የመገለጥ ጥግ በማሳየት እንዲረዱ ያገዛቸው። ይህንንም
ሲያስረዱ፦“ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን

592
ጆንሰን እጅጉ

እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች


አልታወቀም።” (1 ጴጥ.3፡6) ብለዋል።

ከዚህ በተቃራኒ ውጫዊ መንፈስ የትርጓሜ ድርሻ ሲወስድ


የመገለጥ ወይም የመረጃ ጫና በማድረግ ከውስጣዊው
መንፈስ ጋር የማይስማማ ዐውድን ይከተላል። ይህ መንፈስ
አንባቢው ቃሉን በራሱ ፈቃድና ስሜት እንዲተረጉምና
እንዲስት ያደርጋል። ለዚህ ነው ከውጫዊ መገለጥ ወደ
እግዚአብሔር ቃል መሄድ አደገኛ የሚሆነው። እንደ ኪኒየንና
ኬኔት ሄገን ያሉ አማልክት መሠረታዊ ችግራቸው በእንደዚህ
ዐይነት መንፈስ መለከፋቸውና ውጫዊ መረጃዎችን
ከህልሞቻቸውና ከራዕዮቻቸው በመቅዳት ቃሉ ላይ
መጫናቸው ነው። የትኛውም ከእግዚአብሔር ቃል
የማይነሳና ዐውድን የሚያፋልስ መንፈስ የእግዚአብሔር
መንፈስ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት።

በቅርብ አንድ ወዳጄ ልጆቹን መጽሐፍ ቅዱስ አብረውት


እንዲያጠኑ ሲጠይቃቸው የመለሱለት መልስ ግርምት
ፈጥሮብኝ ነበር። ልጆቹ ሲመልሱለት“አባቢ አንተው እራስህ
አጥናና ጠቅለል አድርገህ ንገረን!” ነበር ያሉት። በእርግጥ
ልጆቹ አይፈረድባቸውም። ምክንያቱም ይህንን
የሚያደርጉበት ተፈጥሮአዊ ዐቅም የላቸውም። አእምሯቸው
ለእንደዚህ ዓይነቱ ጥናት ዝግጁ አይደለምና ስልቹ ናቸው።

593
የአማልክቱ ዐዋጅ

ነገር ግን የዐዋቂዎች ለጥናት የተመቸ ልብ ማጣትና


መሰላቸት ግራ የሚያጋባና መፍትሄ ሊፈለግለት የሚገባ
ጉዳይ ነው። ሁል ጊዜ ሌሎች ደክመው “ዋና ዋና ነጥቦች”
በማለት በአጭሩ እንዲያስቀምጡላቸው የሚፈልጉ ወገኖችን
ምን እንበላቸው? ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር
ወይም በማጥናት መረዳት እንደማይቻል ለምን
እንደሚያስቡ አይገባኝም። መጽሐፍ ቅዱስ በመመርመር
የምንረዳው በሰው ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን
ለምንድነው የምንዘነጋው?

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ ለሰዎች ገልጦላቸው፤


ለሰዎች እንዲደርሳቸውና እንዲረዱት ተደርጎ በሰው ቋንቋ
የተጻፈ መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ባለቤት፤ መንፈስ ቅዱስ
ወይም የመጀመሪያዎቹ ጸሓፊዎች ሰዎች እንዳይረዱት
የማወሳሰብ ሥራ በፍጹም አልሠሩም። ይልቁንም በብዙ
ምሳሌና መንገድ በማስረዳት የሰው ልጆች ወደ መታዘዝ
እንዲደርሱ ረድተዋል። በእርግጥ ከጸሓፊዎቹና
ከመጀመሪያዎቹ ተደራሲያን ጋር የጊዜና የባህል ልዩነት ያለን
ስለሆነ በጥንቃቄ መመርመርና መተርጎም ይኖርብናል።

የትርጉምን አስፈላጊነትን ሳነሳ ሁልጊዜ ተርጓሚ


እንደሚያስፈልጋቸው የሚያምኑ አማኞች ይሄ ጉትጎታ
እንደማያስፈልጋቸው እንደሚያስቡ አውቃለሁ። ዳሩ ግን

594
ጆንሰን እጅጉ

እነኝህ ወገኖች ያውቃሉ በሚሏቸው ሰዎች ሁልጊዜ መደነቅ


የሚወዱ፣ ለራሳቸው የሚመቻቸውን አስተማሪ
የሚመርጡና ወደ እውነት ሊደርሱ የማይወዱ ሰነፎች
ናቸው። “ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት
ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፣
እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን
ያከማቻሉ።” እንደተባለ ሆኖባቸዋል።(2 ጢሞ.4፡3)።
በአጠቃላይ ለውድቀት ከሚያፈጥን፤ ከዐውድ ጋር ከሚያጣላ
ውጫዊ መንፈስ እራሳችንን እየጠበቅን እራሳችንን ለቃሉ
የውስጥ መንፈስ አሳልፈን እንድንሰጥ አደራ እላለሁ።

የሰነፍ ሽሽት
መጽሐፍ ቅዱስን በግል ጥናታቸው ተርጉመው ለመረዳት
የማይሹ ወገኖች ስንፍና የተጠናወታቸው ናቸው። እነኝህ
ወገኖች ምናልባትም ለስንፍናቸው ማምለጫ
ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ይጠቅሱ ይሆናል። በዕርግጥ
ጃንደረባው የሚረዳው ሰው ሳይኖር መረዳት እንደማይችል
ይናገራል። ይሁን እንጂ የሰውየው ችግር በኢየሩሳሌም
የነበረው ቆይታ አጭር መሆኑ ነው። በቆይታውም
በኢየሩሳሌም በነበረው የስግደት ሥርዐት ላይ ብቻ ትኩረት
አድርጓል። በሚያነበው የኢሳያስ መጽሐፍ ላይ በቂ ምርመራ

595
የአማልክቱ ዐዋጅ

ለማድረግ አጋዥ ስላልነበረውም በሚያነበው ክፍል ግራ


ተጋብቷል፤ እርዳታም ፈልጓል።

እውነታውን ስንመለከት እርዳታ የፈለገበት ምክንያት


የክፍሉን ታሪካዊ ዳራ ለመረዳት በራሱ ሁኔታ ምክንያት
ስለተቸገረ ነበር እንጂ ክፍሉ የተወሳሰበና በወፍ ቋንቋ የተፃፈ
ስለ ነበረ አልነበረም። ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳያስን
መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና፦ “በውኑ የምታነበውን
ታስተውለዋለህን? አለው። እርሱም፦ የሚመራኝ ሳይኖር ይህ
እንዴት ይቻለኛል? አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ
ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።. . . አፉን ከፈተ፣ ከዚህም መጽሐፍ
ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት።” (ሐሥ.8፡27-38)።

ከዚህ ጃንደረባ በተቃራኒ ደግም በቤሪያ የነበሩ ሰዎች


ለመመርመር የሚችሉበት የተፃፉ መርጃ መሳሪያዎችና
(የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት) ጥሩ የጥናት ልምድ ነበራቸው።
ለሚሰሙትም ታሪክ ቅርብና ጠያቂዎችም ናቸው።
የሰሙትን ለመረዳት እንዲችሉ በቂ የጥናት ጊዜ
በመውሰዳቸውም ምክንያት በቀላሉ ወደ እውነት መድረስ
ችለው ነበር። “እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ
ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት
መጽሐፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።”
(ሐዋ.17፡11)።

596
ጆንሰን እጅጉ

ወዳጆች ሆይ፦እንደ እውነቱ ከሆነ የእግዚአብሔርን ቃል


ማገልገል ለሰነፎች የተገባና የተሰጠ አገልግሎት አይደለም።
አስቀድመን እግዚአብሔር የትጉኹዋን እንጂ የሰነፎች
አምላክ እንዳልሆነ ልናውቅ ይገባናል። ጌታችን ኢየሱስ ዘይት
ያለቀባቸውን ቆነጃጅት “ሰነፎቹ” ያላቸው ለምን
ይመስላችኋል? ቆነጃጅቱ ሰነፎች የተባሉት ብዙ ዝግጅት
ለማድረግ የማይጨነቁና የማያስቡ ስለሆኑ ይሆን? “ሰነፎቹ
መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና።”
(ማቴ.25፡3)። የእግዚአብሔር ቃል የምታደርጉትን ሁሉ
በትጋት አድርጉት በማለት ይመክራልና በትጋት ልናገለግል
ይገባል እንጂ ለስንፍና ቦታ መስጠት የኢየሱስን ሞትና
ትንሳኤ አምኖ ከዳነ ሰው አይጠበቅም (ቆላ.3፡23)።
እውነተኛ የአገልግሎት ትጋት ቃሉን እንደሚገባ ከመረዳት
ይጀምራል።

እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተፃፈበት ትልምና


ምክንያት እንዳለው ከማሰብ መጀመር አለብን። ክፍሉ ለምን
ተፃፈ? ለማን ተፃፈ? የወቅቱ ጸሓፊ ምን እያስተላለፈ ነበር?
የወቅቱ ተደራሲያን ምን ገባቸው? የሚሉ ጥያቄዎችን
በማንሳት መመርመር ስንጀምር የመጽሐፉ የውስጥ መንፈስ
የትኩረትና የማሰብ ችሎታችንን ከፍ በማድረግ የጥያቄዎቹን
መልስ እንድናገኝ ማስተዋልን በመስጠት ያግዘናል።

597
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ዐይነት ማስተዋል አግኝቶ


እንደነበር ከፃፋቸው ፁሁፎች ግልጽ ሆኖ እንደሚታይ
ያስረዳል። ለምሳሌ “ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር
እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ።”(ኤፌ.3፡
4)ማለቱን ልብይሏል። እንግዲህ አማኝ የተቀበለው መንፈስ
ከቃሉ የውስጥ መንፈስ ጋር የሚስማማ ነው ስንል ከመጽሐፉ
አውዳዊ ፍቺ የሚያወጣ ውጫዊ መንፈስ ወይም መገለጥ
ከእግዚአብሔር አይደለም እያልን ነው።

ይህንንም የቃሉን የመንፈሱንና የአማኙን ግንኙነት


ሐዋርያው ዮሐንስ የመምህርና የተማሪ ግንኙነት ያደርገዋል።
የተማሪው ድርሻ ለመማር መፍቀድና መምህሩ
የሚያቀርብለትን ለመረዳት መመራመር ወይም መጠየቅ
ነው። የመምህሩ ድርሻ ተፅፎ በተማሪው እጅ ያለውን መረጃ
ተማሪው እንዲያስተውል መርዳት ወይም አቅጣጫ
መጠቆም ነው። ይህንንም ዮሐንስ ሲገልጠው፦ “እናንተስ
ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፣ ማንም
ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት
ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፣ እውነተኛም እንደ ሆነ
ውሸትም እንዳልሆነ፣ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፣ በእርሱ
ኑሩ።” (1 ዮሐ.2፡27)። ስለዚህ የተቀበልነው መንፈስ
የሚያስተምር መንፈስ ስለሆነ በጃችን ያለውን መረጃ

598
ጆንሰን እጅጉ

ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት በመመርመር በማስተዋል


ልንመላለስና ልናገለግል ይገባል።

የትርጉም ተሰጥዎ
በርካታ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም
ከመፍራታቸውም በላይ ለጥቂት የመተርጎም ተሰጥዎ
ያላቸው ቅቡዐን ብቻ የተሰጠ እንደሆነ ያስባሉ። ከዚህም
የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስን ቀረብ ብለው በማየት መተርጎምና
መረዳት ይፈራሉ። ለዚህም ቶሎ ወደ አዕምሮቸው
የሚመጣው የሐዋርያው ጴጥሮስ ማስጠንቀቂያ ነው። “ይህን
በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም
ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም።”(2 ጴጥ.1፡20)።
ስለዚህም ግልብ ንባብ ከማድረግ ውጪ ዘልቀው መመርመርና
መረዳት አይፈልጉም።

ይሁን እንጂ ይህ ክፍል ፈቃድ የሚከለክለው በራስ ፈቃድ


ወይም ፍላጎት ላይ የተመሰረተን ግምታዊ ወይም ውጫዊ
መገለጥ ያለውን ትርጉም ነው። ውስጣዊው የመገለጥ
መንፈስ ምርምርን ሲፈቅድ ውጫዊው የመገለጥ መንፈስ
ጥያቄን የማይፈቅድና አሜንታን ናፋቂና አስገዳጅ ነው።
ቀደም ብለን እንደተመለከትነው የልዩ ዲበ-አካል
ሊቃውንቱም ሆኑ የእምነት ቃል ሰባኪያኑ የጸሎት ግንዛቤና

599
የአማልክቱ ዐዋጅ

የመጽሐፍት ግንዛቤ ጥመት ምክንያት ውጪያዊ መገለጥን


መከተላቸው ነው።

አብዛኛዎቹ ይህንን መንገድ የሚከተሉ ሰባኪያን ታዲያ


እንዲታረሙ የማይፈቅዱና ለአስተያየቶች ዝግ ስለሆኑ
ለማረም አስቸጋሪዎች ናቸው። በጃቸው ካለው መረጃ
(መጽሐፍ ቅዱስ) ይልቅ ከመንፈሳዊው ዓለም በሚያገኙት
መረጃ ወይም “የእኔ መገለጥ” በሚሉት ይታመናሉ።
መንፈሳዊ ሚስጥራትን ከመንፈሳዊው ዓለም የሚቀበሉ
“አማልክት” ስለሆኑ ከሰዎች ጋር አይግባቡም።
ምዕመናቸውም ይሁን በስራቸው ያሉ አገልጋዩች እነርሱ
ያዘጋጁላቸውንት ትምህርት ብቻ እንዲያስተምሩና
እንዲሰሙ ይገደዳሉ።

ነገር ግን ቤተክርስቲያን አንድ ሰው “መገለጥ” በሚለው በራሱ


ዐሳብ ዙሪያ በጥንቃቄ ሰዎችን በማሰለፍ የሚገንባት ሳትሆን
አማኞች ሁሉ የቃሉን ምሥጢር በመመርመር የሚረዱባት፤
ብዙ አገልጋዮችም የእግዚአብሔርን ቃል በመመርመርና
በመረዳት የሚመክሩባት፣ የሚገስጹባት፣ ጸጋን
የሚያካፍሉባት ሰማያዊ ተቋም ናት።

በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው የኤፌሶንን መጽሐፍ በማንሳት


ሙግት ሊያነሳ ይችላል። “እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣

600
ጆንሰን እጅጉ

ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም


እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ።”(ኤፌ.4፡11)። ከዚህ
ጥቅስም በመነሣት “ሁሉም አማኝ መጽሐፍ ቅዱስን
መመርመር፣ መተርጎምና በትክክል መረዳት ከቻለ ሁሉ
አስተማሪ መሆን ይችላል ማለት ነው?” በማለትም ያነሣ
ይሆናል። እንዲህ ግን አይደለም። ሁሉ አስተማሪ አይደሉም።
ለምሳሌ፦ ሰዎች የዐይን መነጽር የሚጠቀሙት የዓይናቸው
ብሌን ሙሉ ለሙሉ ስለማይሠራ ወይም ማየት ስለተሳነው
አይደለም።

እንዲሁ ሁሉ አስተማሪዎች የተሰጡን ማህበረ ምዕመኑ


መመርመርና መረዳት የማይችል ልቦናው የጨለመ ስለሆነ
አይደለም። የማስተማርም አገልግሎት የሚፈልገው
መረዳትን ብቻ ሳይሆን የተረዳነውን ነገር የምናስረዳበትን
ጥበብና ጸጋንም ጭምር ነው። የአስተማሪዎች
ብልጫቸውም ይህ ነው። በተጨማሪም ከወንጌል
አስተማሪዎችና ሰባኪዎች በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በመታገዝ
ጠልቆ መቆፈር፣ መመርመርና ማስረዳት ይጠበቃል።

የውጫዊ መንፈስ መገለጥ ያጨለመውን ለማብራት


መጽሐፍትን የመመርመር አስፈላጊነትን ማመን እንደሚገባን
ሁሉ ብርሃኑ ሙሉ እንዲሆን መጽሐፍትን የመተርጎም
አስፈላጊነትንም ማመን አለብን። ይህም ማለት ክፍሉ ለእኛ

601
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚሰጠንን ትርጉም ወይም በጊዜና በቦታ የማይወሰን


መልዕክት ማለትም ዘላለማዊ እውነት መረዳት፤ ታሪካዊ
ዳራውን መገንዘብ፤ አስፈላጊ ሲሆን የሚያግዙንን መርጃ
ማብራሪያዎች ተጠቅመን በመተርጎም ፍቺ መስጠት ማለት
ነው። ጃንደረባው “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት
ይቻለኛል?” በማለት ግራ መጋባቱ፤ የሚመራው ሰው ወይም
መርጃ ማብራሪያ እጁ ላይ ስላልነበረም ጭምር ነበር። ዛሬ
ላይ ግን ይህንን እንዳንል ብዙ መርጃ መጽሐፍት ማለትም
የሥነ-አፈታት መመሪያዎችና ማብራሪያዎች በጃችን ላይ
ይገኛሉ። ለምሳሌ ያኽል ለመጥቀስ ቢያስፈልግ፦

 በጎርደን ፊ (ዶ/ር)። (How to read the bibile: for all


its worth) በሚል ርዕስ ተጽፎ“መጽሐፍ ቅዱስን
ለሁለተናዊ ጥቅሙ ማጥናት”በሚል ርዕስ በዳግማዊ
የተተረጎመ። ለሁሉም አማኝ እንዲመች ተደርጎ
የተዘጋጀ።
 በራሜሽ ሪቻርድ (ዶ/ር) ተጽፎ በገበየሁ አየለ የተተረጎመ
“የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት” (scripture sculpture)
ለሰባኪዎችና ለአስተማሪዎች እንዲረዳ ሆኖ የተዘጋጀ።
 በሃዶን ደብልዩ ሮቢንሰን(ፕ/ር) የተጻፈ “Biblical
Preachinging” ለሰባኪዎችና ለአስተማሪዎች እንዲረዳ
ሆኖ የተዘጋጀ።

602
ጆንሰን እጅጉ

 በያሬድ ሽፈራው። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ


(ቅጽ 2) ለሥነ-መለኮት ጥናት እንዲያግዝ ሆኖ የተዘጋጀ።
ጥቂቶቹ ናቸው።

በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ ለጥቂት “የቃል መገለጥ”


ላላቸው ተርጓሚዎች ብቻ የተሰጠ መጽሐፍ ሳይሆን
መርምረንና ተርጉመን በመረዳት ልንጠበቅ የምንችለው
መጽሐፍ ስለሆነ ስንስትም ሆነ ሲያስቱን ተጠያቂዎች ነን።
ስለዚህ ጊዜ ሰጥተን ማጥናትና ወደ ሕይወታችን ማምጣት
የእያንዳዳችን ኀላፊነት ጭምር ነው እንጂ ለጥቂት
“የመተርጎም ተሰጥዎ” አላቸው ለምንላቸው በውጪያዊ
መገለጥ ለሚመኩ “ቅቡዐን” የምንተወው ጉዳይ ፈጽሞ
አይደለም።

ሐቲታዊ ሥልት
ከጌታ የተቀበልነው በእኛ ያለው ቅባት እውነትን
የምንመረምረበትና የምንረዳበት ነው። የእግዚአብር ቃል
ሲናገር፦ “እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ
ይኖራል፣ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን
የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፣ እውነተኛም እንደ
ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፣ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፣ በእርሱ
ኑሩ”(1 ዮሐ.2፡27) ይላል። ስለዚህ የተቀበልነው ሕይወት
ብቃት አጥተን ሁል ጊዜ የአማልክቱን ድጋፍ ፍለጋ ደጅ

603
የአማልክቱ ዐዋጅ

የምንጠናበት ደካማ ሕይወት አይደለም። ይልቁንም


በሐቲታዊ ሥነ-አፈታት ሥልት (exegesis) እየታገዝን ጥልቅ
በሆነ የቃሉ መረዳትና ዕውቀት የምናድግበትና የምንበረታበት
ነው።

ሐቲታዊ (Exegssis) ትርጉም ወይም ፍቺ ያስፈለገበትም


ምክንያት ሥነ-ጹሁፉ የሚለውን ሳንረዳ፤ የተሣሣተ መረጃ
ወስደን እንድንሄድ የሚያደርግ ክፍተት በእኛና በመጽሐፉ
መኻል እንዳይፈጠር ስለሚረዳ ነው። ለምሳሌ፦ በእኛ እና
በመጽሐፉ ጸሓፊዎች መኻል የሥነ-ጽሑፍ ባህል ልዩነት
መኖሩና ሁሉም መጽሐፍ የተፃፉበት ትልም መለያየት
በዋነኝነት በእኛና በመጽሐፉ መኻል ክፍተት ሊፈጥሩ
የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው። በተጨማሪም ሐቲታዊ
የተርጉም ሥልት በመረጃ አያያዝ እና አስተላለፍ ምክኒያት
የሚከሰቱ ጥቃቅን ግድፈቶችን መለየት ስለሚያስችል፤
ክፍተቶችን ለማጥበብ ይጠቅማል። በመጽሐፉና በእኛ መኻል
የክፍተት ምክኒያት ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦችን ዘርዘር
ለማድረግ ያኽልም፦

 ጹሑፉ የተጻፈበት ቋንቋ ባለቤት አለመሆናችን፣


 የተጻፈበት ቋንቋ ጥንታዊና አሁን የማይነገር መሆኑ፣

604
ጆንሰን እጅጉ

 የጸሓፊውንና የመጀመሪያ ተደራሲያኑን ጥልቅ ስሜትና


ሁኔታ ለመረዳትና ለመገንዘብ አሁን የማናገኛቸው
መሆኑ፣
 በእኛና በመጀመሪያዎቹ ተደራሲያንና ጸሓፊዎች መኻል
የጊዜና የባህል ርቀት ያለ መሆኑ፣
 አሁን በጃችን ያለው መጽሐፍ ረጅም ዘመን የተሻገረ
የቅጂ ቅጂ በመሆኑ ምክንያት በአያያዝ እና በግልበጣ
ወቅት የአንዳንድ ቃላት መጥፋትና ጥቃቅን ትርጉም
ስሕተት ሊከሰት መቻሉ ተጠቃሽ ናቸው።

እነኝህን እውነታዎች ግልጽ ቢሆኑም፤ የልዩ ዲበ-አካል ምሁራኑም


ሆኑ የእምነት እንቅስቃሴ ሰባኪያን ለዚህ እውነት ደንታ
የላቸውም። በዚህም ምክንያት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ
የሚከተሉት አግባብነት የሌለው ሥነ-አፈታት የተንሸዋረረ ዕይታ
እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል። ይሁን እንጂ የሁሉም ትልም
መሣትና ማሣት ነው ብዬ ለማመን ደግሞ ይቸግረኛል።
የመጀመሪያው የመንሸዋረር ምክንያት በምዕራፍ ሁለትና ሦስት
ላይ እንዳየነው “መገለጥን” እየተቀበሉ ያሉት ከሚያስቱ መናፍስት
እንደሆነ አለማወቃቸው ነው።

ሁለተኛው ግን መጽሐፍ ቅዱስን ለመፍታት የተከተሉት


አመሥጥሯዊ ሥነ-አፈታት (Allegory) ነው። አመሥጥሯዊ ሥነ-
አፈታት ቃላትን ለብቻቸው ነጥሎ በቀጥታ የመፍታት ባሕርይ
አለው። በተጨማሪም ቃላቱን በተጠቀሱበት ዐውድ ውስጥ

605
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሳይሆን በዘመናዊ መዝገበ ቃላት ውስጥ የመተርጎም ዝንባሌ


አለው። ይህም አካሄድ አማልክቱን ከዐውድ በማውጣት ድንቁር
ጭለማ ውስጥ አስገብቷቸዋል፤ ለራስ ግምት ወይም ከክፉ
መንፈስ ወይም ውጫዊ መንፈስ ለሚመጣ “መገለጥ”
አጋልጧቸዋል።

ቻርልስ ፈራህ በእምነት እንቅስቃሴ ላይ ባደረገው ጥናት


የደረሰበትን ድምድማት ሲያሰፍር፦ “የእምነት እንቅስቃሴ
ኖስቲሲዝማዊ ሥነ-አፈታት መርሆችንና ሳይንሳዊ የዐውድ ዳሰሳ
ይከተላል።” ብሏል።376 ቻርልስ ሳይንሳዊ መንገድ ይበለው እንጂ
የእምነት እንቅስቃሴ የሚከተለው የልዩ ዲበ አካል ፍልስፍና ነው።
በሌላ በኩል ኖስቲሲዝም377 እንዲሁ የልዩ ዲበ-አካልን ሥነ-
አፈታትና አመሥጥሯዊ ሥነ-አፈታት እንደሚከተል ልብ ይሏል።

የሰው አፈጣጠር፣ አዲስ ፍጥረት፣ ዐዋጅ ቃል፣ የመርገም መስበርና


የበረከት ቃል ማውጣት የሚሉትን ትምህርቶች ሥር እንዲሰዱ
ያደረጋቸው ምንድነው? ብለን መጠየቅ ይገባናል። ጠቅለል ያለ
መልስ ስናስቀምጥ፦ እነኝህና መሰል ትምህርቶች ሥር ሊሰዱ
የቻሉት ሐቲታዊ ትርጉምን በጣለ አመሥጥሯዊ አተረጓጎም
ነው። ምንም እንኳ አንዳንዶቹ ርዕሶች አስፈላጊና ከመጽሐፍ
ቅዱስ የተወሰዱ ቃላት ቢሆኑም የተጠቀሙበት ሥነ-አፈታት
376
Charles Farah Jr, “A Critical Analysis: The ‘Roots and Fruits’ of Faith-Formula
Theology” (Spring 1981, P, 21).
377
ኖስቲሲዝም፦ ዕውቀትን ማዕከል ያደረገ በአፍላጦንና በአይሁዳዊው ፊሎ
ዐስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ፤ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አከባቢ የተጀመረ፤
ክርስትናን በከፊል የሚቀበል ፍልስፍና ነው፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ፡፡
ቅጽ 2 ያሬድ ሽፈራው 2010፣ ገጽ 162)

606
ጆንሰን እጅጉ

የሚያነሱትን ርዕስና የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በተሳሳተ መንገድ


እንዲረዱና ስኹት መርሖ እንዲከተሉ አድጓቸዋል። በውጤቱም
ትምህርተ ክርስቶስንና ትምህርተ ሰብዕን በማፋለስ የብዙ
አማኞችን መንፈሳዊ ሕይወት አሽመድመዷል፤ የቤተክርስቲያንን
መልካምና ቅዱስ ጠረን በመረበሽ የኹከት ምክንያት እየሆነ ነው።
እውነተኛውን የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት አዳፍኖ የራሱን እሳት
ለመለኮስ በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ በዐድ አመድ ለመነስነስ
እየሞከረ ይገኛል።

ተሓድሶ
“ማንኛውም ነገር ከመለኮታዊው አስተምህሮ በተጻሮ ሲቆም፣ ወይም
ቅይጥነት ሲዳበለው ተሓድሶ ያስፈልገዋል። የእግዚአብሔር ሰው ነኝ
የሚል ሁሉ አምልኮተ ባዕድን፣ ርኩሰትን፣ ጥንቆላን፣ ኑፋቄን፣ በወንጌል
ስም መነገድን ወዘተ ማፍረስ ግድ ይለዋል።” 378
መጋቢ ሰለሞን አበበ ገ/መድህን

ይህ መጽሐፍ መታደስ ያለበትን ችግር፣ የችግሩን መንስኤና


የመፍትሔ አቅጣጫ በጉልህ በማስቀመጥ የወንጌላዊያን
ቤተ-እምነትን የሚተነኩሰው ቤተክርስቲያንን ለተሓድሶ
ለማነሣሣት ነው። በተያያዝነው ሚኒሊየም የቤተክርስቲያንን
ስም የሚያጎድፍ ብልሹና ልዩ ልምምድ ጥግ ላይ ተደርሷል።
ይህ ደግሞ የተሓድሶን አንገብጋቢነት ጠቋሚ ነው። ተሓድሶ
የመታዘዝ መነቃቃትን በመከሰት ሲገለጥ ይጸድቃል፤ ተሓድሶ
378
የትሩፋን ናፍቆት፣ (2007, ገጽ.105)።

607
የአማልክቱ ዐዋጅ

ተብሎም ለውጥን ካለነገሠ ዐላማውን ስቷል፤ መነቃቃትም


አይደለም።

ከፊሎቻችን የወንጌላውያን አማኞች በተሓድሶ አስፈላጊነት


ላይ ቅንጣት ጥርጥር የለንም። ለዚህም አዘውትረን
የምንሰብክበት የስብከት ርዕስ፣ በጉባኤ የምንዘምረው ዝማሬ
እንዲሁም በየዓመቱ የምናከብረው የተሓድሶ መታሰቢያ
በዓል መልካም ማሳያ ናቸው። እዚህ ላይ ግን የተሓድሶ
ፍላጎት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ አስምረን ማለፍ አለብን።
መታደስ ያለበትን ነገር ለይቶ ማወቅና በግልና በተቋም ደረጃ
ለመታደስ ወይም ለውጥን ለመቀበል መፍቀድ፤ የተሓድሶ
እንቅስቃሴ ግቡን እንዲመታና ተቋማዊ እስኪሆን እንዲያድግ
ማድረግ አስፈላጊ ነው። ይህ ሳይሆን ለውጥን እየፈለግንና
እየሰበክን፤ በምንም የማይወሰን ቅጽፈታዊም ይሁን ሂደታዊ
ለውጥ የሚያመጣ የለውጥ ቁልፍ የሆነ ወንጌል በእጃችን
ይዘን፤ ወይም በራሳችን ብቻ ወስነነው፤ “የገነተረ” በሚል
የሞኝ ፈሊጥ ለተሸጋጋሪ ለውጥ አለመዘጋጀት ወይም ንቁ
አለመሆን በክርስትና ሃይማኖት የተኮነነ ነው።
ባለፈው ዘመን የዲበ-አካል ሃይማኖትና የእምነት እንቅስቃሴ
ቁንጮ ወይም የጋብቻ ቀለበት የሆነው የልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ
ልምምድ ወደ ቤተ-እምነታችን ሰርጎ ቁልቁል
እንዲያንደረድረን መፍቀዳችን ዋጋ አስከፍሎናል። አሁን ግን

608
ጆንሰን እጅጉ

ራሣችንንም ሆነ ተቋማችንን በመፈተሽና ከልዩ ጽኑ


የተሓድሶ አቋም ይዘን በግልም ይሁን በተቋም ደረጃ ያሉትን
“የእምነት እንቅስቃሴ” ተግዳሮቶች ለመቋቋም ልንነሣ
ይገባል። መለኮታዊ ትንቢትንና ልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅን እኩል
ያደረገውን፣ የጸሎት ምላሽን ከአማልክት አፍ ያስመኘንንና
የቃሉን አገልግሎት ቃና በማበላሸት ያቃለለውን አጋንታዊ
ደቦ ብልሹ ማሣኒ መወጣጫ ደረጃ እናስወግድ። በተለይም
ደግሞ እኛ የወንጌላውያን ቤተእምነት ሰባኪያን ያልተቀላቀለ
ወንጌል ለትውልድ የማስቀጠል አደራ አለብን። ስለዚህም
እውነትን ችላ በማለት ለክብራችንና ለጥቅማችን ቅድሚያ
ሰጥትን ከተሰለፍንበት የማስመሠልና የመመሣሰል ገበያ
አስቀድመን እንውጣ።

ታላቁ የተሓድሶ አርበኛ ሉተር በግል ሕይወቱ ልቡን


በመለወጥ የጀመረው ተሓድሶ ወደ ተቋማዊ እንቅስቃሴ
አድጎ በመስፋት የክርስትና ተቋማት ተሓድሶ ምክንያት
መሆን የቻለው በዘመኑ የነበረችውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን
የሥነ-መለኮት ችግሮችን ለይቶ በማወቁና ፊት ለፊት
በመጋፈጡ ነበር። በወቅቱ አብዛኛዎቹ ካቶሊካዊያን የሉተርን
የተሓድሶ ንቅናቄ እንደ በቅሎ የደነበሩበት ሲሆን፤
እንደበረከት ከመቀበል ይልቅም በመቃወምና በማግለል ኢ-
ተሓድሶአዊ አቅጣጫ ተከትለዋል። ሌሎች ለዘብተኝነትን

609
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሲከተሉ ጥቂቶች ግን ከሉተር ጐን በመሆን የተሓድሶው አካል


መሆናቸውን አስመስክረዋል። ዛሬም ቢሆን ያለን ምርጫ
ከሦስቱ አንዱ ነው የሚሆነው። በወደድነው መስመር
የመሰለፍ ምርጫ አለን፤ የተሓድሶ አቋም ይዘው ከተነሱ
ተቋማትና ግለሰቦች ጋር ማበር አሊያም መቃወም ወይንም
ለዘብተኛ መሆን።

የዲበ-አካልን ሃይማኖትን ከወንጌል ቀይጠን መአከላዊነትን


ወይንም ሚዛናዊነት እንከተላለን በሚል ፈሊጥ ማንንም
ላለመንካትና ላለማስከፋት ለዘብተኝነትን መከተላችን
ይብቃን። መኻል መሰፍረን ትተን የተሓድሶ አካል እንድንሆን
ከታሪክ በመማር ፈጥነን አሰላለፋችንን እናስተካክል። ከኛ
በፊት የነበሩ ታላቆቻችን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በሰዋዊ
“የአማልክትነት” ምኞት ተታለው ቢሳሳቡም ወደ መለኮት
ሳይጠጉ ማስነው ቀርተዋል። እኛም ታዲያ“ብልህ በሰው
ይማራል” እንደሚባለው ከሌሎች እጸጽ ተምረን ልናመልጥ
ይገባል። ከማሣኒው የአማልክት የቃል ዐዋጅ መወጣጫ
ልባችንንም እግራችንንም እንሰብስብ። የተዘረጋልን
እጃቸውን ብቻ ሳይሆን የቆሙበትንን ድጥ በማስተዋል
እንመልከት። ለምናገለግለው አገልግሎትም ይሁን ለራሳችን
ሕይወት ተጠያቂ እንደሆንን እናስተውል። ሽልማት
ተስፋችን እንደሆነ ሁሉ ፍርድ ወይም ተጠያቂነት

610
ጆንሰን እጅጉ

እንደሚጠብቀንም በማወቅ በቀረው ዘመናችን ተጠሪ


የሆንንለትን፤ የመንፈሳዊ ስልጣን ሁሉ ምንጭ የሆነውን
ቃሉን በፍርሃትና በታማኝነት እናገልግል።

የእምነት እንቅስቃሴ የዲበ-አካል ሃይማኖትን መሠረት


አድርጎ እንደተነሳና “መገለጥ” በሚል ማመካኛ ከጥቅስ ጋር
ቀይጦ የያዘው ትምህርት የልዩ ዲበ-አካል ፍልስፍና መሆኑን
ገልጠን ተመልክተናል። በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ
መርሆችን የሚጣረሱ ልምምዶቹ በዲበ-አካል ሃይማኖት
ፍልስፍና መሰንከሉን በብርቱ የሚያሳዩ እንደሆነ ዓይተናል።
በዚህም ንኪኪው በየዘመናቱ የክርስትናን ትምህርት
ለመበረዝ ከተገዳደሩ ስኹት ትምህርቶች
እንደሚያስመድበው አስረግጠናል። በልምምዱና
በትምህርቱ፤ ትምህርተ ክርስቶስን፣ ትምህርተ ሰውን፣
ትምህርተ ድነትንና ትምህርተ ጸሎትን ስለሚያፋልስም
የኑፋቄ ምድቡን እንደሚያጠነክረው በስፋት ዳሰናል።
የወንጌላውያን አማኞች ይህንን ድሪቶ ለይተን በማወቅ
ማስወገድና ወደ ተሓድሶ ማቅናት እንድንችል የዚህ መጽሐፍ
ጥሪ ነው። የዲበ-አካልን ትምህርትን የሚያስተምሩና
ልምምዱንም የሚለማመዱ፤ በተጨማሪም የዲበ-አካል
ሃይማኖት አካል የሆነውን የኪኒዮንና የኬኔት ሄገን ትምህርት
ትክክል እንደሆነ የሚሞግቱና የሚያሰራጩ ወገኖችን ለይተን
ማወቅ እንድንችል ጥረት ተደርጓል። እነኝህ ወገኖች በግልጽ
ንስሓ በመግባት የትምህርትና የልምምድ ለውጥ ካላደረጉ
በስተቀር እንደ እንቅስቃሴያቸውን እንደ ክርስትና መነቃቃት

611
የአማልክቱ ዐዋጅ

ወይም ሪቫይቫል መቁጠር እንደማይቻል ዐይተናል።


በመናፍቃኑ መርሀ ግብራቸው መሳተፍም ሆነ አብሮ
በአገልግሎት መጠመድ ለሚከሰተው የክርስትና መበረዝ
ተጠያቂ እንደሚያደርገን ከታሪክ እንድንማር በሠፊው
ተዳሷል።

“የአማልክቱ” ዐዋጅ! የሚያሰማውን ደማቅ ጩኸት በጽሞና


ያደመጥን ሁላችን በዲበ-አካል ሃይማኖት ልዩ ዐዎንታዊ
ዐዋጅ የቤተክርስቲያን ክብሯ እየነተበ፣ ባህሏ እየተቀየረ፣
ጠረኗ እየተለወጠና ከእውነት ያፈነገጠ ልምምድ ውስጥ
እየገባች እንዳለ እንገነዘባለን። ይህ ገባን የምንል ሁላችን
ታዲያ እውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት
እንዲቀጣጠል መንገድ የመጥረግና የማቅናት ወይንም በኅብር
ለተሓድሶ የመሥራት ኀላፊነት እንደወደቀብን ይሰማኛል።
መጋቢ ሰለሞን አበበ “ማፍረስም መሥራት ነው።”379
እንዳለው በዚህ መጽሐፍ የተገለጠውን የዲበ-አካል
ሃይማኖት ሕልውና የሆነውን ፍልስፍና ከብብቱ ነጥቀን
በመግደል በእምነት እንቅስቃሴ ማህበር የቆመ የተምህርት
ሐውልት እናፍርሰ፤ የእምነት እንቅስቃሴን የትምህርት
አውታሮች በጣጥሰን እንጣል።

ጎበዝ፤ የዲበ-አካል ሃይማኖትና የቤተክርስቲያን ምስጢራዊ


ጋብቻ ፈርሶ፤ የልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ጦስ ያስከተለው

379
የትሩፋን ናፍቆት፣ (2007፣ገጽ.119)።

612
ጆንሰን እጅጉ

የሚደብት መነቃቃት ድባብ ተገፎ፤ ለስብከት፣ ለትንቢት፣


ለጸሎትና ለዝማሬ አገልግሎት፤ ለጠቅላላ ክርስትና ሕይወትና
የአምልኮ ባህል ተሓድሶ ምክንያት እንድንሆን ቆርጠን
እንነሣ። በጥቂት ግለሰቦች ትጋት ለሚታዩ ዐቃቢያዊ ይዘት
ላላቸው መርሃ ግብሮች ትኩረት እንስጥ፤ ተቋማዊ ወይም
የቤተክርስቲያን አካል እንዲሆኑም እናግዝ። ቤተክርስቲያን
ሰዎች በመንፈስ የሚሰሩባትና ለወንጌል አደራ የሚበቁባት
የተሓድሶ ማዕከል እንጂ ከጭለማው አሰራር ጋር
የምትጠላለፍና የምትወዳጅ የውድቀት ማዕከል እንዳትሆን
እንጋደል! ኤሊያስ በዘመኑ እስራኤልን ያነተበውን የበአልን
ትምህርት ተረድቶ “አቤቱ፣ አምላክ እንደ ሆንህ፣
ልባቸውንም ደግሞ እንደ መለስህ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ
ስማኝ።” (1 ነገ.18፡37)። ብሎ ስለ እስራኤል ልብ መታደስ
ጸባዖት የገባ ጩኸት ቅናት ባቃጠለው ልቡ እንደጮህ፤ የዲበ-
አካሉን መሰዊያ አፈራርሰን በመጣል ለመለኮት እጅ መገለጥ
የምራችንን በመንፈስ ቅናት እንጸልይ፤ ኡ ኡ ብለን እንጩኽ።

ከግል ሕይወታችን ጀምሮ እየሳሳ የመጣውን የክርስትና ደመና


የማስመለስና እየተተካ ላለው አዲስ ትውልድ የማስተዋወቅ
አደራ እንደ ወደቀብን አስተውለን እንነሳ። አመሥጥሮትን
በሚከተል መንገዱን በሳተ የልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ስሜትን
ተደራሽ ማድረጋችን ያክትም። ያለማወቃችን ፈጽሞ

613
የአማልክቱ ዐዋጅ

እንዲከስም “ጌታ የሰጠኝ መገለጥ” የሚል መሸፈኛ ካለው


ገበያ መር ሥነ-አፈታት እንላቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስን
በተሻለና በጥልቀት የምንረዳበትን ዐውድና ታሪካዊ
እውነታዎችን ያገናዘበ ሐቲታዊ የአጠናን ሥልትን እንከተል።
መገለጥ ያደበዘዘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምርመራ
እንዲያበራው እንፍቀድ እንጂ የመንፈስ ቅናት
ለሚያቃጥላቸው የተሓድሶ ቅሬታዎች የመድረክ እንቅፋት
አንሁን። መለኮትን ከሰውነት በለየ ዕውቀትና ማስተዋል ሆነን
በሰከነ መንፈስ በጸሎትና በልመና አብረን በአንድ መንፈስ
የልጆቹን ልመና ሰምቶ በሚመልስ ጌታ ፊት ከልባችን
እንበርከክ፤ በተቀበልነው የልጅነት መንፈስ በአንድነት እንደ
ንብ መንጋ በምልጃ እንትመም!

ጥቂት ሰዎች በአጀብ እና በትወና በሚገኑበት የአማልክት


መድረክ የታደምንበትና የቲያትር ቤት የዳር ተመልካች
ያስመሰለን፤ የክርስቶስን መስቀል የወንጌል ዐዋጅ
የሚያኮስስና ቤተክርስቲያንን ሰማያዊ ተልዕኮ የሌላት የስነ-
ልቦና ህክምና ማዕከል ያስመሰላት መድረክ ይክሰም። የሥነ-
አፈታትና ርቱዕ መጽሐፍት ከቤተክርስቲያን ጋር
የሚተዋወቁበት አውደ-ርዕዮችን በማስፋፋትና እስከ ቤት
ኅብረት ጥናቶች በማውረድ “የአማልክቱን” የሐሰት እሳት
እናዳፍን! እናንተም ሰባኪያን ሆይ፤ ተነሱ! ቤተክርስቲያን

614
ጆንሰን እጅጉ

ለጸሎትና ለቃሉ ያለትን ርትዕ ትርጉም እናስመልስ! እነሆ፦


የሳተ ይመለስ! ያሳተም ንስሓ ይግባ! ሁላችን በአንድነት
ተሳታፊ ወደ የምንሆንበት የክብሩ ደመና ተያይዘን በመግባት
አብረን እንብረር! እንፈንጥዝ። የተመሰቃቀለ፤ መንፈሳዊና
አካላዊ የሰውን ሕይወት በመለወጥ የሚያስውበው
እውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ ወርቃማ እሳት ይቀጣጠል!
ሙታንን ሕያው የሚያደርግ ወንጌል ይታወጅ! የእውነት
ብርሃን እንደ ንጋት፤ የሀልዎቱ ሽታ እንደ አልባስጥሮስ ጠረን
ይውጣ፤ ልባችንንም ሞልቶት ወደ ውጪ የሚፈስ ጅረት
ይሁን!!

በቀረውስ፤ በእግዚአብሔር ቃልና በመንፈስ ቅዱስ ኀይል


የመታደስና የመነቃቃት ዘመን ለክርስተስ ቤተክርስቲያን
ይሁን። አሜን።

ማጠቃለያ

የዲበ-አካል ሃይማኖት መሻት የሰውን ልጅ መሠረታዊ ሊባሉ


የሚችሉ ችግሮችን መፍታት ነው ማለት ይቻላል። ለዚህ
ደግሞ ቁልፍ ነው ብሎ የሚያጠነጥነው የኅሩይ ቃላት ዐዋጅ
ያላቸውን ብልጽግናና ጤንነት የማከናነብ “ተፈጥሯዊ” ዐቅም
ነው። መሪዎቹ ይህንኑ “የኀይል ምስጢር” ለማሳመን
እንዲያመቻቸው ትምህርተ ሰብዕንና ትምህርተ መለኮትን
አፋልሰው አስተምረዋል። ይህንንም ለማድረግ

615
የአማልክቱ ዐዋጅ

የሚያግዟቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጠምዝዘዋል።


ለፍልስፍናው ዕድገትም በርካታ የዲበ-አካል ፍልስፍና
ልምምዶችን ተጠቅመዋል። የልዩ ዲበ-አካል ተቋማትና
መጽሐፍቶችም ያደረጉት አስተወዕፆ ቀላል የሚባል
አይደለም። በአጠቃላይ ዐስተሳቡ ለመዳበር ረጅም ዘመን
የፈጀበትና እስከ አሁንም ድረስ አፍላ ነው።

ኢ ደብልዩ ኪኒየን በኤመርሰን ትምህርት ቤት ገብቶ የዲበ-


አካል ሃይማኖት ትምህርትን ከመማሩም ባሻገር የትምህርቱን
ሥርው የቃል ዐዋጅ ዐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፎ
አስተምሯል። የኪኒየንን ኮቴ የተከተሉ ሰባኪያንም እንዲሁ
ርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን “መገለጥ” በሚል ሰበብ ልዩ
ዲበ-አካላዊ ፍቺ በመስጠት የእምነት እንቅስቃሴ መሠረት
እንዲሆኑ አድርገዋል። የእምነት እንቅስቃሴ ኅሩይ ቃል
ዐዋጅን እንደ ዲበ-አካል ሃይማኖት ሁሉ የሰው ልጆች
መሠረታዊ ችግሮች መፍቻ እንደሆነ ያስተምራል። ከዚህም
ሲዘልቅ የድነት ምስጢርም እንደሆነ ይታመናል። ይህንንም
ትምህርት ለማስፋት ሲል ትምህርተ ሰብንና ትምህርተ
መለኮትን እስከ ማዛባት ይደርሳል። ለትምህርቱ መስፋፋት
የቃል እምነት ሥነ-መለኮት ኮሌጆቹንና የኬኔት ሃገን
መጽሐፍትን በማሰራጨት በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቅሟል።
በዚህም ምክንያት ትምህርቱም ሆነ ልምምዱ
በወንጌላውያን አማኞች መኻል ሳይቀር በስፋት ተስፋፍቷል።

616
ጆንሰን እጅጉ

የዲበ-አካል ሃይማኖት የቃል ኀይል ልምምድ ተፈጥሯዊም


ይሁን ሳይንሳዊ በጭራሽ አይደለም። የኀይል ልምምዱም
ይሁን ትምህርቱ በእግዚአብሔር ቃልም ይሁን በተፈጥሮ
ሳይንስ ያልተረጋገጠና ሰይጣናዊ ነው። ስለዚህ
ከእግዚአብሔር ቃል ጥቅስ ስለሚጠቅስና በማስመሰሉም
እራሱን በሳይንስና በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ስለሚደብቅ
ልንለይ እንጂ ልንታለል አይገባም።

በአጠቃላይ የዲበ-አካል ሃይማኖት ፍልስፍና ከእምነት


እንቅስቃሴ ጋር በመጋባት የወንጌላውያንን ክርስትና
የሚቦሮቡር አጋንታዊ ሴራ ነው። ይህም ሊሆን የሚችለው
የተምህርቱ ማዕከል የሆነው የዐዋጅ ቃል ጽንሰ-ዐሳብና
ልምምድ የሥነ-ልቦና ሳይንስ በሚመስል ፍልስፍናና
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተለወሰ ስለሆነ ነው። ስለዚህ
ከሥውር ሴራው ለማምለጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ የዐዋጅ ቃል
ሥርው ዐሳብ ጋር ያለውን ዝምድናና ልዩነት በጥንቃቄ
ለመለየትና ለማጥራት በመሠረታዊ ትምህርት (Doctrine)
ላይ ጠንካራ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል።

617
የአማልክቱ ዐዋጅ

ማ ጠቃለያ
የታሪክ አንደምታ ግራ ፎ ች
የዲበ-አካል ሃይማኖትና
የክርስትና ለወንጌል አማኞች
ጥምረት የማንቂያ ደወል
የኅሩይ ቃል
የዲ በ-አካል
ዐዋ ጅ ሥነ-
ሃይማ ኖት ና መለኮት
የእም ነት ጽ ንሰ-ዐሳብ
እንቅ ስቃሴ ሥነ-
የተ ፈ ጥሮ ሕግ አፈ ታት
ልዕለ አዕም ሮ
የቃል ኀይል
አዲ ስ ፍጥረት
ሥነ- መለኮታዊ ሥብከት
መ ለኮት ና ጸሎ ት
ልም ም ድ ዕም ነት
ዘረ-መል ዝማ ሬ
መልክ (ም ድብ)
ክርስቶ ሳዊነት
መለኮት ን
ማ ነቃቃት (መመ
ልኮት )

ምስል አምስት፦ የእምነት እንቅስቃሴ የተዛባ ባዕድ ሥነ-መለኮት


መሰረታዊ መነሾ በየጊዜው እየተባባሰ የሚሄደው የዲበ-አካል ሃይማኖት
የቃል ኀይል ፍልስፍና ነው። በዚህ መጽሐፍ ቅይጥ ሥነ-መለኮቱን
ለማጽደቅ የሚኬድበትን ሰፊና ስንኩል የሚያማስን ጉዞ ዳሰናል። የዲበ-

618
ጆንሰን እጅጉ

አካል ሃይማኖትም ይሁን የእምነት እንቅስቃሴ በቃለ እግዚአብሔር ላይ


ያላቸው ተመሳሳይ ዕይታና ሥነ-አፈታት ሦስቱን የቤተክርስቲያን
ዕሴቶች (ሥብከት፣ ጸሎትና ዝመሬ) በማፋለስ ወንጌላዊያን
አብያተክርስቲያናትን ከሀልዎተ መለኮት እያራቀ ይገኛል። ለተስተካከለ
የሥነ-አፈታት መርሖ ትኩረት መስጠትና ለተሓድሶ ተግቶ በመሥራት
ካለንበት እክል መውጫ መፍትሄ ሆኖ ተቀምጧል። ይህ ባልሆነበት ግን
ሪቫይቫልን ተስፋ ማድረግ ባዶ ድካም ይሆናል።
የተ ፈ ጥ ሮ ሕ ግ

ፈ ውስ
የቃል ኀይል


ልዕለ አዕም ሮ

የልዩ ዲ በ-አካል የልዩ ዲ በ-አካል

መ ርሖ
የአባት
ኅሩይ ቃል ዐዋጅ ት
(የአዕም ሮ )ሕ ግ ን
መ ለኮታዊ
እም ነት ማ
ሥ ኬት ረ
መ ለኮት ን ጋ
ማ ነቃቃት


ምሥል ስድስት፡ መለኮትን የሚያነቃቃ የልዩ ዲበ-አካል ዐዎንታዊ
ዐዋጅ ልምምድ። “ዐዎንታዊ ቃል ዐዋጅን” ዋነኛ የትምህርቱ ማዕከል
በማድረግ መለኮትነትን ለማረጋገጥ ይሠራል።









619 ጋ

የአማልክቱ ዐዋጅ

ምሥል ሰባት፡ “አማልክትነትን” የሚያነቃቃ የእምነት እንቅስቃሴ


የልዩ ዐዎንታዊ ዐዋጅ ልምምድ። ይህ ልምምድ የእምነት እንቅስቃሴ
ሁሉም ትምህርቶች የቆሙበት ዋና መሠረትና ማዕከላዊ አገልግሎት
ነው። ፈውስን፣ ስኬትንና በመጨረሻም ድነትን (መንፈሳዊ ሥኬትን)
በማወጅ (በመለኮታዊ እምነት) የሰው ልጅ ጥግ ላይ እንደሚደርስ
በመቁጠርም ሰውነትን ያመለኩታል።

620
ጆንሰን እጅጉ

መ ስቀ ሉ ን ማ ዕከል
ያ ደረገ እም ነት (2ቆ ሮ. ድነት
4፣13)።

የወ ንጌል ዐዋጅ
አዲ ስ (ኢ የሱ ስን)
የወንጌ ላው ያ ን ፈ ውስ
መ ርሖ ፍጥ ረት ፡- መ ስበክ (ሮሜ .10፡
መ ለወጥ 8-10)

የጌ ታ መ ልክ፡-
ሥኬት
በም ሣሌነቱ መ ኖር

ምሥል ስምንት፦ እንደ ወንጌል አማኞች የእምነት ቃል መናገር


የወንጌል ስብከት (የኢየሱስን የማዳን ሥራ ማወጅ) የቤተክርስቲያን
ማዕከላዊ አገልግሎት ነው። ድነት በእምነት የሚገኝ ለውጥ እንደሆነ
ሲቆጠር በዚህ ዓለምም ይሁን በሚመጣው ዓለም እንደሚጠቅም
ይታመናል፤ፈውስም ይሁን ሥኬት እንደ ዋና ነገር አይታይም።
አገልግሎቱም በአማኞች መታነጽና በጌታ መክበር ላይ ትኩረት
ያደርጋል። (በደራሲው)

621
የአማልክቱ ዐዋጅ

ሁል ጊዜ ለሚሰማን “ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ


እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፣ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን
በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር
ይሁን፤ አሜን።” (ኤፌ.3፣20)።

የምዕራፍ ዘጠኝ ግንዛቤ ጥያቄዎች


1. አመስጥሯዊ መገለጥ ሥነ-አፈታት በርቱዕ ሥነ-መለኮትና
ልምምድ ላይ ምን እክል እንደፈጠረ ታስተውላለህ?

2. በአመስጥሯዊ መገለጥና በሐቲታዊ መገለጥ መኻል ያለው


ልዩነት ምንድነው?

3. የእግዚአብሔርን ቃል መርሖ የሚጣረስ ሥነ-መለኮት ለባዕድ


መንፈስ አሠራር በር ሊሆን ይቸላል ብለህ ታምናለህ? ለምን?

4. የእምነት እንቅስቃሴ ሥነ-መለኮትና ልምምድ ጠንከር ያለ


ተቃውሞ ካልገጠመው ለወንጌላውያን ክርስትና ስጋት ይሆናል
ማለት እንችላለን? ወንጌላውያን ቤተእምነቶች ይህንን
ተግዳሮት ለማሸነፍ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ትመክራለህ?

5. የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ክርስትና ተሓድሶ


ያስፈልጋቸዋል ብለህ ታስባለህ? ለምን? ተሓድሶን ለማምጣት
በግልና በኅብረት ምን አቋምና እርምጃ ለመውሰድ አቅደሐል?

6. ይህ መጽሐፍ ስለ እምነት እንቅስቃሴ ባለህ ግንዛቤና


ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ የግል ኅብረትና የአገልግሎት

622
ጆንሰን እጅጉ

ዝግጅትህ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሮብሃል? በግልህና


በአገልግሎትህስ በምን መንገድ ልትጠቀምበት ወስነሃል?

7. እውነተኛና ሐሰተኛ መንፈስን ወይም አሠራርን ለመለካትና


ለመለየት የሚጠቅሙንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርኾች
አስቀምጥ።

ዋቢ መጽሐፍት
ተካልኝ ነጋ። (2010)። የጸሎት ቤት፤ የንግድ ቤት። ሮሆቦት ማተሚያ ቤት።
ዐዲስ አበባ።
ራሚሽ ሪቻርድ። (2003)። ገበየሁ አየለ የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት። ዐዲስ አበባ።
(scripture sculpture. የላፕስሊ ብሩክስ ፋውንዴሽን፣ ዳላስ ቴክሳስ)።
ተዘራ ያሬድ (2008)። ሬማና ሎጎስ፣ ሲ.ኤን፣ ፒ.ኤን አ.የ፤ቀ .የ።
ግርማዊ (2000)። መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለንተናዊ ጥቅሙ ማጥናት፤ መጽሐፍ
ቅዱስን ለመረዳት የሚጠቅም መመሪያ። New Testament Exegesis:
A Hand Book for Students and Pastors. Lousisvilies:

623
የአማልክቱ ዐዋጅ

(Gordon F. & Daglas). Westminister John Knox pres.


(1993).
ዪንጊ ቾ (2020)። የእግዚአብሔር አድራሻ። አየ፣ አ.አ።
አቤል ፀጋዬ።(2012)። አዕምሮዎን የመጠቀም ጥበብ። ጆሴፍ ሙርፊ። (The
Powere of your Subconscious Mind). አ.የ፤ ቀ.የ።
አመሉ ጌታ (2008)። ቅድመ ጋብቻ ጥበብ። አ.የ፤ ቀ .የ።
_____። (2010)። የድሆችና የችግረኞች ጩኸት ወጣ። ሰሊሆም ማተሚያ ቤት፤
ዐዲስ አበባ።
ክሪስ ኦያኪሎሚ። (2006፣ጥር፣10)። Rapsoid of reality, Love World:
nd.
_____። (2009፣ነሐሴ 11)። Rapsoid of reality, Love World: nd.
_____። (2006,ጥር)። ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ። Randburg: Gauteng
World publishing.
_____። (2013, መስከረም). ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ።. Randburg:
Gauteng Love World Publisher.
_____።(2013,ጥቅምት)። ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ, Randburg: Gauteng
Love World Publisher.
ሰለሞን አበበ። (2007)። የትሩፋን ናፍቆት። ርኆቦት አታሚዎች፣ ዐዲስ አበባ።
ያሬድ ሽፈራው። (2010)። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ። (ቅጽ 2) አ.የ፣
ዐዲስ አበባ።
ራሴላስ ጋሻነህ። (2012)። የስኬት ፍልስፍና። (Think grow and rich).
ናፖሊዮን ሂል። (2004)። ቡክላንድ ፣ ዐዲስ አበባ።
ዳዊት ድሪም። (2012)። ትልቅሕልም አለኝ። አፍሪካ ማተሚያ ቤት፣ ዐዲስ
አበባ።

624
ጆንሰን እጅጉ

Eddy B. (2006). Science and Health with Key to the


Scriptures. Boston, Massachusetts፣ The Christian
Science Publishing Society.
Anthony, R. (2004). Beyond Positive Thinking. N.p:n.p.
Florida: Power House.
Allene Diogenes, S. (2007). Philosophy for Understanding
Theology: Louisville: Wstminster John Knox Press.
Atkinson, B. (1950). The Complete Essays and Others
Writings of Ralph Waldo Emerson. New York: Random
House.
Brown, C. (1986). New International Dectionary of New
Testament Theology V Grand Rapids: Michigan.
Charles Farah Jr. (1981). A Critical Analysis: The ‘Roots and
Fruits’ of Faith-Formula Theology. Spring: Pneuma.
Emerson, W. (1906) Works of Ralph. in 12 vols. New York:
Botsen.
Dunn, G. (1970). Babtizm in Hloy Spirit. Westminister:
press. pennsylvania.
E. W. Kenyon. (1981). The Power of Your Words. Whitaker
House. Nd.
______ (2013). Speak Life: Words That Work Wonders. New
Kensington: Whitaker.
______ (dn). The Two Kind of Faith. Faith’s secrit Revealed.
N.p: n.d.

625
የአማልክቱ ዐዋጅ

_______ (nd). The Hidden Man. Ununveling of subcoscions


Mind. N.p: n.d.
_______. (nd). A New Type of Christianity. N.p: n.d.
Gordon D. Fee. (2002). New Testament Exegesis: A
HandBook for Students and Pastors. Lousis vilies ፣
Westminister John Knox pres.
Fillmore C. (1931). Metaphysical Bible Dictionary. Kansas
City, Mo.: Unity School of Christianity.
______. (1936). Mysteries of Genesis. Global Grey ፣ Nd.
(2018).
Gossett D. (2011). E.W. Kenyon. Keys to Reciving God’s
Miracle. Whigtere House: Washington.
Hagin, K. E. (1979). You Can Have What You Say. Tulsa:
Faith Library Publications.
_______. (d.n). Zoe: the God Kind of Life. Faith Library
Publications፣ Tulsa.
_______. (d.n). Understanding Our Confession. Faith Library
Publications፣ Tulsa.
_______. (d.n). Commanding Power. Faith Library
Publications፣ Tulsa.
_______. (1980). In Him.Tulsa: Np: Faith Library Publications.
_______. (1983). Praying to Get Results. Faith Library
Publications: Tulsa.
Haller, J. S. (2012). The History of New Thought: from Mind
Cure to Positive Thinking and the Prosperity Gospel

626
ጆንሰን እጅጉ

Pennsylvania. Swedenborg Foundation Press: West


Chester.
Hanegraaff, H. (1982). Christianity in crisis: 21st century.
Nashville: Tennessee.
Harfouche, C. (1993). The Hidden Power: Your Worlds. Np:
Pensacola.
Harrison, M. F. (2005). Righteous Riches: the Word of Faith
Movement in Contemporary African American Religion.
Madison Avenue, New York: Oxford University Press.
Hill, N. (1937). Think and Grow Rich. Meriden, Conn:
Ralston Society.
Holmes, E. (1919). Creative Mind and Success. Center for
Spiritual Living: Ashevil.
Hopkins, C. (2016). 12 Lessons in Spiritual Healing. (Deidre
Michell). N.p: People’s Voice. (n.d).
Joe, B. D. (1978). Faith Power: It works Better with all the
Parts: Np.nd.
John Stott. (1984). Understanding the Bible. Scripture
Union: Valley Forge.
Klein, T. (2003). How Things are in the World: Metaphysics
and Theology in Wittgenstein and Rahner. Milwaukee:
Marquette University Press.
Lamm. M. (2000). Emanuel Swedenborg: The Devopment
of His Thought: (Spiers, T & Hallengren). A swednborg
Foundation: Pennsylvania. (1915).

627
የአማልክቱ ዐዋጅ

MacArthur, J. (2013, P.42). Strange Fire: The Danger of


Offending the Holy Spirit with Counterfeit Worship.
Nashville, Tennessee: Thomas Nelson.
McConnell, D. R. (1988). A different Gospel: A historical
and biblical analysis of the Modern Faith Movement.
Hendrickson: Massachusetts.
McIntyre, J. (2010). E.W. Kenyon and His Message of faith:
the True Story. c. n: Empowering Grace Ministries.
Murphy, J. (n.d). The Power of Your Subconscious Mind:
Unlock Your Master Key to Success. N.p: n.d.
Mesmer, A. (nd). His life and Teacing. London: (R.B. Inge).
William Rider & Son, Lid (1920).
Mckenzie, L. (2005). How to Read the Bible. New York:
Oxford University Press.
Miller, R. (2015). From Azusa to Africa to the Nations. AIA
Publications: Springfield.
______. (2013). Leading Believers into the Baptism in the
Holy Spirit. Springfield, MO: AIA Publications.
Mosley, G. R. (2006). New Thought, Ancient Wisdom: The
History and Future of the New Thought Movement.
Philadelphia, London: Templeton Foundation Press.
Murphy, E. & Carm. (1981). Wisdom Literature; Job,
Proverbs, Ruth, Canticles, and Estger. William B.
Eerdnans Publshing Company: Grand Rapids, Michigan.
N. T. Wright. (2012). James. Downers Grove: InterVarsity
Press.

628
ጆንሰን እጅጉ

Ostrander, R. (2000). The power of Prayer in a World of


Science: Protestants, Prayer, and American Culture,
1870-1930. Avenue New York: Oxford University Press.
Peale, N. (2006). The Power of Positive Thinking: A
Practical Guide to Mastering the Problems of Every day
Living. N.p: n.d.
Polkinghorne, J. (2000). Faith Science and Understanding.
YaleUniversity Press: New Haven and London.
Quimby, P. (2018). Parkhurst Quimby Manuscripts (Horatio
W. Dresser). Global Grey (1921).
Rook, E. (2009). Confession of an Invisible Illuminati. N.p:
n.d
Sheehan, R. (2011). Mind Power: Connecting with the
Power of Your Unconscious Mind. N.p: n.d.
Swedenborg, E. (2016). Journal of Dreams: And Spiritual
Expriences. (Odhner Th). Pennsylvania: FB & c Ltd.
(1918).
_____. (2009). Arcana Coelestia: The heavenly arcana
contained in the Holy Scripture or Word of the Lord
unfolded, beginning with the book of Genesis.
(Faulkner, J) West Chester, Pennsylvania. Swedenborg
Foundation. (1756).
______. (2000). Haven and Hell (Gorge F. Dole). London:
Sewdenborg foundation. (1758).

629
የአማልክቱ ዐዋጅ

Tyndall, J. (1876). Prayer-Gauge Debate. Boston:


Congregational Publishing society.

Unpublished Document
Bulutse Fuuwi. An Introduction to Theology and Growth of
Independent Churches in Ethiopia: With Special
Reference to Rhema Faith Church: A Critical Approach.
Thesis: Submitted to the Faculty of EGAST for the
Degree of Master of Theology. (Addis Ababa, June
2002).
Johnson Ejigu. (2021). Believe and Practice of “Positive
Confession” in Addis Ababa Evanglical Churches
Beleivers’ Prayer Life: Submited to the Faculty of Adiss
Abeba Bible College (ABC), Bibilical Theology (BA).
(May 17, 2018).

Media Document
ብስራተ ቡዛየሁ። ጂ. ኤ ም. ኤም. ቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ዐዲስ አበባ።(2018፣
መጋቢት፣16)።
ዮናታን አክሊሉ። ማርሴል ቲቪ ዓለም አቀፍ ዩቲዩብ ቻናል። የሥብከት ርዕስ
“በአፍህ ቃል” ተያዝክ።(2020፣ መጋቢት፣ 26)።

https://youtu.be/Q_V6wMq0kGw. (በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል


አስደናቂ መልዕክት)።
አዶናይ መጽሔት ቁጥር 3.ገጽ 18፤ 2011 ዓ.ም

Web Site Docment

630
ጆንሰን እጅጉ

Study.com/academy/lesson/pope-gregory-vii-henry-

iv.html.

ቀጣይ የደራሲው ሥራዎች

1. የአማልክቱ ተራሮች

2. የዲበ-አካል ሃይማኖት

3. አምልኮተ ማርያም



  

631
የአማልክቱ ዐዋጅ

632

You might also like