Professional Documents
Culture Documents
Cover of Clincs
Cover of Clincs
Law school
Tewedros Kassa.............UGR/9148/13
በተጨማሪም አሁን ፍርድ የተሰጠበትና አፈጻጸም የተከፈተበት ሰነድ አልባ ይዞታ የአቶ አደፍርስ መሆኑን የሚያስረዱ
የሚከተሉት ማስረጃዎች በአቶ አደፍርስ እጅ ይገኛሉ፡-
1) በአቶ አደፍርስ ከበደ ይዞታውን ከአቶ ገ/ኪዳን መካከል በሚያዝያ 16 ቀን 1996 ዓ/ም የገዛበት የመኖሪያ ቤት
ሽያጭ ውል 01፡፡
2) የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት አሁን በአቶ አደፍርስ ከበደ እጅ የሚገኘው ይዞታ ከ 1997 ዓ/ም በፊት ጀምሮ በአቶ
አደፍርስ እጅ ይገኝ እንደነበር በኮሚቴ አረጋግጦ የላከበት ሰነድ 03 ገጽ፡፡
ጥያቄዎች
1) ለአቶ አደፍርስ ከበደ ፍ/ቤት የሚገባ የተሟላ የመቃወም አቤቱታ አዘጋጅ፤
2) ለአቶ አደፍርስ ፍ/ቤቱ የሰጠው ፍርድ እንዳይፈጸም አቤቱታ ጠይቅ፤
ቀን፡-29/11/2014
መዝገብ ቁጥር፡-1234
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት
ለልደታ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ
የመ/አመልካች፡- አቶ አደፍርስ ከበደ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የመ/ተጠሪዎች ፦1. አቶ አለን አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
2. አቶ ኤልያስ ካሳ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 1234 ላይ በሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው
ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 እና 359 መሰረት የቀረበ የመቃወም
አቤቱታ ነው
ሀ. ፍ/ቤቱ ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን አለው፡፡
ለ. የፍ/ቤቱን መጥሪያ ለመቃወም ተጠሪ የመ/አመልካች አደርሳለሁ፡፡
ሐ. የመቃወም አመልካች የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ችሎታ አለኝ፡፡
መ. በመ.ቁ 1234 በቀን 25/10/2014 ዓ.ም የተሰጠ ወሳኔ ተያይዞ ቀርቧል፡፡
ቀን፡-29/11/2014
መዝገብ ቁጥር፡-1234
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለልደታ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ
የመ/አመልካች፡- አቶ አደፍርስ ከበደ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የመ/ተጠሪዎች፦ 1.አቶ አለን አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
2. አቶ ኤልያስ ካሳ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 223 መሰረት ከመቃወም አመልካች የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ
1.የሰነድ ማስረጃ
1) በአቶ አደፍርስ ከበደ ይዞታውን ከአቶ ገ/ኪዳን መካከል በሚያዝያ 16 ቀን 1996 ዓ/ም የገዛበት የመኖሪያ
ቤት ሽያጭ ውል 1 ገጽ ዋና ።
2) የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት አሁን በአቶ አደፍርስ ከበደ እጅ የሚገኘው ይዞታ ከ 1997 ዓ/ም በፊት
ጀምሮ በአቶ አደፍርስ እጅ ይገኝ እንደነበር በኮሚቴ አረጋግጦ የላከበት ሰነድ 3 ገጽ፡፡
2. የሰው ምስክር
1. ወ/ሮ .............................. አድራሻ፡-.....................
2. አቶ ...................................አድራሻ፡-....................
3. ወ/ሮ .................................አድራሻ፡-....................
ከላይ የቀረበው የማስረጃ ዝርዝር እውነት መሆኑን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 92/3/ መሰረት አረጋግጣለሁ፡፡
የመቃወም አመልካች
ቀን፡-29/11/2014
መዝገብ ቁጥር፡-1234
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለልደታ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ
የመ/አመልካች፡- አቶ አደፍርስ ከበደ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የመ/ተጠሪዎች፦1. አቶ አለን አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
2. አቶ ኤልያስ ካሳ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
በፍሥ/ሥ/ህ/ቁ. 359(3) እና 205 መሰረት በቃለ መሀላ ተደግፎ የቀረበ አቤቱታ
የመቃወም ተጠሪዎች የእኔ የመቃወም አመልካች የሆነውን የቤት ይዞ፣ የእኔ ነው፥ የእኔ ነው በማለት በፍርድ ቤት ይወሰንልኝ
ጥያቄ አቅርቦ ስከራከሩ ቆይቶ ፍርድ ቤቱም ምስክር ሰምቶ የመቃወም 2 ተኛ ተጠሪ የይዞታው ባለቤት ነው ብሎ የአለበት
ቤት ፈርሶ ለ 2 ተኛ መቃወም ተጠሪ እንድይመለስ ወስኗል። ነገር ግን የመቃወም 2 ተኛ ተጠሪ የይዞታው ባለቤት አይደለም፡፡
በመሆኑም ይህ ውሳኔ የመቃወም አመልካች መብትና ጥቅሜን የሚጎዳ በመሆኑ የመቃወም 2 ተኛ ተጠሪ የይዞታው ባለቤት
ሳይሆን ባለቤት ነኝ በሚል በዚሁ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 1234 በቀን 25/10/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሻር እና
የመቃወም አመልካች የክርክሩ ተካፋይ ሳልሆን ለመቃወም ተጠሪ የተሰጠው ውሳኔ የእኔን ህጋዊ መብት እና ጥቅም በእጅጉ
ስለሚጎዳ በተገለጸው ቀን የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮና የክርክሩ ተካፋይ ሆኜ ክርክሩ እንደገና ተሰምቶ ውሳኔ እንዲሰጥልኝ
በመቃወም ያቀረብኩት አቤቱታ እውነት መሆኑን በመሃላ ቃል አረጋግጣለሁ፡፡
የመቃወም አመልካች
ቀን፡- ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 333 እና 335 መሰረት የእግድ ትዕዛዝ ለማሰጠት በቃለ-መሃላ ተደግፎ የቀረበ አቤቱታ
ለተጠሪ የተወሰነው የይዞታ ባለቤትነት እንድሻርልኝ እና ቤቱ የይፍረስ ውሳኔ እንድሻርልኝ አቤቱታ አስገብቻለሁ። ተጠረ
አቤቱታ እንደ አስገባው አውቆ ወይም ሳይአውቅ የእኔ የአመልካች ይዞታ በሆነው ቤት ላይ ሊተካ የማይችል ጉዳት
ሊያደርስብኝ ይችላል። በመሆኑም የእኔ የአመልካች ይዞታ የሆነው ቤት ማለትም አሁን ለተጠሪ የተወስነው 40 ቆርቆሮ 2
ክፍል ቤት ያረፈበት 280 ካ.ሜ እንዳይፈርስ ለአዲስ አበባ ቤቶች ባለስልጣን የእግድ ትእዛዝ ይሰጥልኝ፡፡ ለተጠሪ የተወሰነው
እና እንድፈርስ የተወሰነው እንዳይፈርስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 333 እና 335 መሰረት የእግድ ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ በማክበር
እጠይቃለሁ፡፡
አመልካች