You are on page 1of 99

ECCSA

የንግድ ሥራ እቅድ አዘገጃጀት ስልጠና

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ


እና
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
የተዘጋጀ ኢትዮጵያ
ግንቦት 2013
1
ECCSA

አመቻች፤
--------

2
ስለ ስልጠናው ...... ECCSA

 የንግድ ስራ ስናከናውን በየእለቱ በሚያጋጥሙን ስራዎች፣ ችግሮችና ጉዳዮች


እንጠመድና ትልቁንና ዋናውን ስእል ማየት ይሳነናል፡፡ ይህ ሊከሰት የሚችለው የንግድ
እቅድ ሳይኖረን ሲቀር ነው። የንግድ ሥራ ዕቅድ፤ ስኬታማ ንግድ ለመጀመር፣
ለመገንባትና ለመምራት በጣም አስፈላጊ ሰነድ ነው። እንዲሁም አስፈላጊውን የስራ
ማስኬጃ ገንዘብ ለማሰባሰብ (ለማሳደግ) እና የንግድ ሸሪኮችን ለመሳብ (ለመያዝ)
ውጤታማ መሳሪያ ነው። የንግድ ሥራ እቅድ የንግዱን ግቦችና ዓላማዎች በግልፅና
በተጨመቀ መልኩ የሚጎልፅና ለእሱም ስኬት የአሰራር ስልቱን የሚያመለከት መሣሪያ
ነው። እንዲሁም የንግድ ሥራ እቅድ ለአምራቾች አገልግሎት ሰጭዎች ፍላጎት
ላላቸው የንግድ ሸሪኮችና አቅራቢዎች ለንግዱ ግቦች የላቀ የመገናኛ መሣሪያ ነው፡፡
በርካታ የንግድ ሥራዎች በእቅድ ዝግጅት እጥረት ምክንያት ይወድቃሉ ወይም ለኪሳራ
ይዳረጋሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ስልጠና ትክክለኛ እቅድ እንዴት ማዘጋጀት እንዳለብዎት
በማሳየት ስኬታማ ንግድ መምራት እንዲችሉ ያስችልዎታል።
3
የስልጠናው አላማ ECCSA

 ይህንን ስልጠና ሲያጠናቅቁ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፤


 ስለንግድ እቅድ ጠቀሜታ የተሻለ መረጃ ይኖርዎታል፤
 የንግድ እቅድ ደረጃዎችን ይዘረዝራሉ፤
 የንግድ እቅድ አስፈላጊ ክፍሎችን ይለያሉ፤
 የንግድ እቅድ ያዘጋጃሉ፤
 ንግድዎን ለማሻሻል እቅድዎን ይጠቀማሉ፤
 ውጤታማ የንግድ ሥራ እቅድ ለማውጣት የሚረዱዎትን ተጨማሪ ሀብቶች
ይለያሉ።
4
የስልጠና ርዕሶች ECCSA

 የንግድ ስራ እቅድ ምንድን ነው?


 የንግድ ስራ እቅድ ለምን አስፈለገ?
 የንግድ ስራ እቅድ የማዘጋጅት ሀላፊነት የማን ነው?
 የንግድ ስራ እቅድ ለማን ያስፈልጋል?
 የንግድ ስራ እቅድ መቼ ነው መዘጋጅት ያለበት?
 የንግድ ስራ እቅድ ምን ምን ያካትታል?

5
ትርፍ ECCSA
ደንበኛ
የንግድ ሥራ ምንድን ነው? ፈጠራ
ማጋራት

• የንግድ ሥራ ሰዎች በመሰባሰብ


አፈፃፀም
ግብ

(ድርጅት በመመስረት) ወይም


በተናጠል የሚያቋዉሙት የንግድ
ሀሳብ
ተወዳዳሪ
ዎች
ምርቶችን (እቃዎችን ወይም
የንግድ
አገልግሎቶችን) ለደንበኞች ተነሳሽነት
ክህሎት የንግድ
ስልት
በማቅረብ ትርፍ ለማግኝት
ገንኙነት/
የሚከናወን ተግባር ነው። ትስስር
መልካም
• ንግድ በበሀሪው ያለመታከት ብዙ በራስ
መተማመ
አጋጣሚ

መስራትን የሚጠይቅ ተግባር ነው። ን


ገበያ
የንግድ ስራ እቅድ ምንድን ነው? ECCSA

 የንግድ ስራ እቅድ
 ንግድ ስራ ለመጀመር፣ ለማሻሻል ወይም ለማስቀጠል ወደፊት ምን መስራት እንዳለብዎ አስቀድመው
ማሰብና ማዘጋጀት ነው፤
 ሁሉምን ውስጣዊ እና ውጫዊ አካላትን እና ስትራቴጂዎችን የሚገልጽ በጽሑፍ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፤
 የንግድ ሥራን እና ተያያዥ የመነሻ ታሳቢዎችን መሠረት ያደረገ መሠረታዊ ሃሳብን የሚያቀርብ
የጽሑፍ ሰነድ ነው
 የንግድ ትንታኔ
 የበፊት የንግድ አፈፃፀም
 ሽያጭ ሁኔታ፣ የግብይት ሁኔታ፣ ወጪዎች፣ የንግድ አቅም እንዲሁም ትርፍ
 በውጫዊ ሁኔታዎች ሊከሰቱ የሚችሉ፤ በንግድዎ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ለውጦችን መተንበይ
 ንግድዎ የተጋለጠባቸውን ስጋቶች ለይተው ማወቅ 7
ECCSA
የንግድ ስራ እቅድ ምንድን ነው?
 የንግድ እቅድ ምንድነው?
 በግልጽ የቀረበ፣ በቀላሉ ማንም ሊረዳው የሚችል፣ መረጃ-ሰጭ ዶሴ ነው
 ንድፈ-ሐሳባዊ፣ ረቂቅና የተወሳሰበ ወይም ምስጢራዊ መሆን የለበተም
 የንግድ ስራዎ ትርፋማ፣ ምርትና አገልግሎትዎ ተፈላጊ መሆኑን ለማሳየት
የሚጠቀሙበት ዶሴ ነው
 ሀሳብ የመሸጫ ሰነድ ነው

8
የንግድ ስራ እቅድ ምንድን ነው? ECCSA

 ማንኛውም ድርጅት ሊተገብር ያሰበው የንግድ ስራ ግብና ዓላማ ምን እንደሆነ፣ የስራው ሂደት ምን
እንደሚመስልና እንዴት እንደሚሠራ እንዲሁም እያንዳንዱ ክንውን መቼ እንደሚሰራ የሚያስረዳ ሰነድ
ነው፡፡
 የታለመውን ግብ ለመምታት የሚያስችል የአሰራር ሂደት/መመሪያን የያዘ ነው፡፡
 የንግድ ድርጅቱን የቢዝነስ /የንግድ ስራ አሰራር ፍኖተ ካርታ ያሳያል፡፡
 የንግድ ስራ ድርጅቱን ስራና ያለውን እድል ለገንዘብ ተቋማትና ባለሀብቶች ሊያስረዳ የሚችል ሰነድ ነው፡፡
 የንግድ ስራ ድርጅቱን ስራ ሊኖረው የሚችለውን ማንኛውንም እድል /ሁኔታ በመዘርዝር የሚታቀድበት በቂ
ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት ሰነድ ነው፡፡

9
ECCSA

የውይይት ጥያቄ
 የንግድ ስራ እቅድ አስፈላጊነት ወይም አስፈላጊነት ላይ ተወያዩ፡፡

10
ECCSA
የንግድ እቅድ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ?
 የንግድ እቅድ አስፈላጊ ነውን?
 አዎ
 እቅዱ ለድርጅቱ እና ሌሎች የድርጅቱን ዓላማዎች ለማወቅ ለሚሞክሩ
ሥራ ፈጣሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የስራ አጋሮች፣ አቅራቢዎች ወይም
ሠራተኞች ጠቃሚ መረጃ የሚያቀርብ ሰነድ ነው፡፡

11
የንግድ እቅድ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ?
ECCSA
 የንግድ ድርጅቱ ተግባሩን በአግባቡ ለማደራጀት እንደመነሻ ያገለግላል፤
 የባንክና ሌሎች የገንዘብ ተቋማትን ትብብር/ብድር ለማግኘት ያስችላል
 ሌሎች የንግድ ሸሪኮችን ለመሳብ
 ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ስልታዊ ግኑኝነት ለመመስረት
 ትልልቅ የተደራጁ ስራዎችን ከሌሎች ተቋማት ጋር ለመስራት፣ ትልልቅ ውሎችን ለመፈራረም
 ቁልፍና ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ሰራተኞች ለመሳብ
 ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ለመወሀድ
 ሌሎች ድርጅቶችን ለመግዛት ወይም ድርጅቱን ለመሸጥ
 የድርጅቱን የስራ መሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ሰራተኞች የሰራ ተነሳሽነት ለመጨመር
 ብዙ ገንዘብና ጉልበት ከማውጣት በፊት የንግድ ሥራውን አዋጭነትና ውጤታማነት ለመገምገም
 የድርጅቱን ርዕይ፣ተልዕኮ ፣ ዓላማዎችን እና ስልቶች ለማቀናጀት
 ለንግድ ስራው የሚያስፈልጉትን የሃብቶች መጠን ለማወቅ
12
የንግድ ስራ እቅድ ለምን ይዘጋጃል? ECCSA
 የንግድ ስራ እቅድ በተዘጋጀው ግብና ዓላማ ላይ ትኩረት / አጽንኦት በመስጠት ስራን ለማከናወን
ይረዳል፡፡
 የገንዘብ አቅምን ከተለያየ ምንጭ ለማግኘት ይረዳል፡፡
 የንግድ ስራው የሚጀመርበትንና ሊመራበት የሚገባውን ስርዓት በማሳየት አቅጣጫ ጠቋሚ ይሆናል፡፡
 በተነደፈው የንግድ ስራ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር
ይረዳል፡፡
 የተነደፈው የንግድ ስራ የስኬት እድል ያለው መሆኑን ለማሳየት ይጠቅማል፡፡
 የንግድ ስራውን ለማስተዳደር የሚያስፈልገው በቂ ችሎታ እንዳለ መኖሩንና ለሚመረተው ምርትና
አገልግሎት የገበያ እድል መኖሩን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡
 ስራው ከተጀመረ በኃላ በጊዜ ሂደት ውስጥ በእቅድ ደረጃ የተቀመጠውን ውጤት በተግባር ከሚሆነው
ጋር ለማወዳደር ይረዳል፡፡
13
የንግድ እቅድ ማዘጋጀት ንግድዎን የሚያሻሽለው እንዴት ነው? ECCSA

 የንግድ እቅድ መኖር ንግድዎ ጥራት ያለው መረጃ እንዲኖረውና በንግድዎ ጉዳዮች ላይ
ትክክለኛ ውሳኔ እንዲወስኑ እንዲሁም የንግድዎን እንቅስቃሴ፣ አፈፃፀም እንዲከታተሉ
ይረዳዎታል፡፡
 የንግድዎ አፈፃፀም ጥሩ ከሆነ የንግድ እቅድ በማዘጋጀት የወደፊት እንቅስቃሴዎን ይበልጥ የተሻለ እንዲያደርጉ
ይረዳዎታል፡፡
 የንግድዎ እንቅስቃሴ በትክክል እየተከናወነ ካልሆነና የተወሰኑ ችግሮች ካሉበት የንግድ እቅድዎ እንደችግር መፍቻ
ሆኖ ለያገለግልዎ ይችላል፡፡
 የንግድ እቅድ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች አስቀድመው በመገመት ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሄዎች
ለመፈለግና እንዳይከሰቱ ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
 በደንብ የተዘጋጅ የንግድ እቅድ ምን ያህል ገንዘብ ወደድርጅትዎ እንደሚገባና ምን ያህል ገንዘብ ከድርጅትዎ
እንደሚወጣ ያሳያል፡
14
ECCSA

የውይይት ጥያቄ
 የንግድ ስራዎ ምንድን ነው?
 በንግድ ስራዎ ውስጥ ምን አይነት ችግር አለ?
 በንግድ ስራዎ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የንግድ እቅድ እንዴት
ሊረዳዎ ይችላል?

15
የንግድ ዕቅድ ዓይነቶች ECCSA

1. የተጠቃለለ ወይም አጭር እቅድ


2. ሙሉ ወይም ረጅም እቅድ
3. ተግባር ተኮር የንግድ ዕቅድ

16
የንግድ ዕቅድ ዓይነቶች ECCSA

1. የተጠቃለለ ወይም አጭር እቅድ


 ስለ ንግድ ስራው በጣም አስፈላጊ መረጃን ብቻ የያዘ ሰነድ ነው
 ከ10-15 ገጽ የሆነ እጥር ምጥን ያለ ነው
 የንግድ ሥራ ስልቱ በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ይገለጻል
 በደንብ የታወቁ ድርጅቶች/ ባለሀብቶች ለብድር በሚያመለክቱበት ጊዜ ይጠቀሙታል።
2. ሙሉ ወይም ረጅም እቅድ
3. ተግባር ተኮር የንግድ ዕቅድ

17
የንግድ ዕቅድ ዓይነቶች
ECCSA
1. የተጠቃለለ ወይም አጭር እቅድ
2. ሙሉ ወይም ረጅም እቅድ
 የእቅዱ ዋና ዋና ክፍሎች ከ30-50 ገጾች ሊኖሩት ይችላል።
 ከ10-30 ገጾች የድጋፍ ሰነድ
 የድጋፍ ደብዳቤዎች ፣ የባለሀብቱ የመረጃ፣ የማስተዋወቂያ መረጃዎች .....
 የሰነዱ መግቢያ ዝርዝር ገላጭ ነው
 ቁልፍ ጉዳዮችን በጥልቀት ለማብራራት ካስፈለገ
 ብዙ ገንዘብን በመፈለግ ለመበደር ወይም ለማሰባሰብ
 ስልታዊ የንግድ አጋር ለመፈለግ
3. ተግባር ተኮር የንግድ ዕቅድ
18
የንግድ ዕቅድ ዓይነቶች
ECCSA

1. የተጠቃለለ ወይም አጭር እቅድ


2. ሙሉ ወይም ረጅም እቅድ
3. ተግባር ተኮር የንግድ ዕቅድ
 የድርጅት የውስጥ አሠራር በጥልቀት የሚያሳይ እቅድ ነው
 ለማዘጋጀት ብዙ ጊዜ ይወስዳል
 እቅዱ ስለ ምርትና አገልገሎቶች እና ስለሚሳተፉ ሰዎች ሰፊ ታሪካዊ አመጣጦችን የሚያካትት ነው
 ሰፊ ትንተና
 ሥራ አስኪያጆችንና ሰራተኞችን ለማነሳሳት
 ሲባል ለእድገቱ ትዕዛዝ ይሰጣል
 እንደ ዓመታዊ ግምገማ አካል ሆኖ ያገለግላል
19
ECCSA
የንግድ ስራ እቅድ እንዴት ይዘጋጃል?
 በንግድ ስራ ውስጥ የሚጠየቁ ማንኛውንም ጥያቄዎች በመዘርዘርና ለጥያቄዎቹ መልስ
በመስጠት
 ከተጠየቁት / ሊጠየቁ ከሚችሉት ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ
መረጃ በማሰባሰብ
 አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በሙሉ በማሰባሰብ
 የተለያዩ አማራጮችን በማወዳደርና የተሻለውን አማራጭ ለመውሰድ በመወሰን

20
በንግድ ስራ እቅድ ምን ሊደረግ ይችላል? ECCSA

 የንግድ ስራ እቅድ አስቀድሞ ማዘጋጀት ለክትትል ይረዳል፡፡


 ይህም ማለት በእቅድ የተያዘውን ስራ ከተከናወነው ስራ ጋር በማነጻጸር
ለመገምገም ይጠቅማል፡፡
 ከገንዘብ ተቋማት እንዲሁም ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ለሚደረግ ውይይት
የመነሻ ሃሳብ ይሆናል፡፡
 የንግድ ስራ እቅድ ለጅምላ ንግድ፣ ለችርቻሮ ንግድ፣ አገልግሎት የሚሰጥ የንግድ
ድርጀት፣ ምርት የሚያመርት (አምራች) ድርጅት፣ ማንኛውም የንግድ ድርጅት፣
ለገንዘብ ተቋማትና ለንግድ ዘርፍ ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

21
ECCSA
የንግድ ስራ እቅድ ገጽታ ምን ይመስላል?
 የተተየበና በጥራዝ የተቀመጠ፣ በንጽህና የተጠበቀ/የተያዘ፣ ማጠቃለያና እዝል ያለው
(ዋናውን እቅድ ላለማስረዘም ማለት ነው)፣ እያንዳንዱ ገጽ የገጽ ቁጥር የተሰጠው፣
በሚመለከተው አባል የተፈረመ መሆን የተገባው ሲሆን የንግድ እቅድ መድብል ብዙ
ወይም ጥቂት መሆን የሚወሰነው እንደ ንግዱ የዘርፍ ዓይነት ነው፡፡

22
ECCSA
የንግድ ስራ እቅድ ምንን ያካትታል?
 የንግድ ዘርፉ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችን፣
 በዘርፉ የሚሰሩ ተወዳዳሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣
 አቅራቢዎች፣
 ተቀጣሪዎች፣
 ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች፣
 የንግድ ስራው የሚካሄድበት ስፍራ ወይም አድራሻ፣
 ለንግዱ ስራ የሚያስፈልገው ቁሳቁስ. ወዘተ

23
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት ECCSA

 ስለንግድ ስራው አጭር መግለጫ  የንግድ ስራ ዓይነት


 የኢንተርፕራይዙ ስም  አምራች ፣ አገልግሎት ሰጪ ፣ ጅምላ ሻጭ፣ ችርቻሮ
ንግድ
 ኢንተርፕራይዙ በሕግ የሚኖረው የሰውነት ዓይነት
 በአንድ ሰው ባለቤትነት
 የንግድ ድርጅቱ ስለሚሰራው ንግድ ስራ አጭር
 በአጋርነት የሚሰራ
ዘገባ
 ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር
 የሚያመርተው የምርት ዓይነት እና የሚሰጠው
አገልግሎት
 ኮርፖሬሽን
 ገበያን በተመለከተ የድርጅቱ ትኩረት የሚሰጠው
 ይህ ሕጋዊ ሰውነት የተመረጠበት ምክንያት የህብረተሰብ ክፍል ወይም ተቋም
 የተጠሪ አድራሻ  ንግዱ ለአገሪቱ ምጣኔ ሀብት የሚያበረክተው
 ስልክ ቁጥር፣ ኢሜይል፣ ፋክስ..... አስተዋጽኦ

24
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት
ECCSA
 የድርጅቱ መስራቾች / አባላት ግለታሪክ መግለጫ
 ሙሉ ስም ከነአያት፣ አድራሻ፣ የትምህርት ደረጃ፣ በድርጅቱ ውስጥ ያላቸው የሥራ ኃላፊነት
 ገበያ ነክ እቅድ
 ድርጅቱ ምርቱን ስለሚያቀርብበት / ስለሚሸጥበት ገበያ ማብራሪያ (ገበያው የሚገኝበት አካባቢ፣ ታሳቢ የሚደረጉት የደንበኞች ዓይነት፣ ጠቅላላ የገበያ
ሽፋን፣ ተወዳዳሪ አምራቾች ካሉ ስለሚያቀርቡት ምርትና አገልግሎት አጭር ማብራረያ፣ ተመሳሳይ ምርትና አገልግሎት የሚቀርብ ከሆነ በገበያው ውስጥ
ስለሚኖረው ድርሻና የመሳሰሉት)
 ምርቱ /አገልግሎቱ በገበያ ውስጥ የሚኖረው ድርሻ
 ምርቱን ለማምረትም ሆነ ለመሸጥ የሚያስፈልጉት ግብዓቶች
 ድርጅቱ የሚያቀርበው ምርት በአካባቢው ካሉ ሌሎች ተመሳሳይ አምራቾች የሚለይበትና ገበያውን ወደራሱ የሚስብበት ገጽታ ምን እንደሆነ
 አገልግሎቱን ለማቅረብ / ምርቱን ለማምረት የሚያስፈልገው ግብዓትና የማምረቻ ዋጋ
 ምርቱንና አገልግሎቱን የመሸጫ ዋጋ
 የገበያ ዋጋን መተመን
 ድርጅቱ የሚያስባቸው ደንበኞች ለመክፈል የሚኖራቸው የገንዘብ መጠን ፍቃደኝነት.... ከፍተኛው ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን
 በአካባቢው የሚገኙ ተወዳዳሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን / አገልግሎታቸውን የሚሸጡበት ዋጋ ምን ያህል ነው?
 ድርጅቱ የሚያመርተውን / ያለውን ምርት የሚሸጥበት ዋጋስ ምን ያህል ነው? .......ከፍተኛው፣ መካከለኛ ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን
 ድርጅቱ የሽያጩን ዋጋ ለመወሰን ምክንያት የሆነው ምንድነው? 25
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት ECCSA

 ደርጅቱ የሚጠቀምበት ቦታ/ስፍራን ማቀድ


 የንግድ ስራው የሚከናወንበት ስፍራ / ቦታ
 ቦታው የተመረጠበት ምክንያት
 የተመረተው ምርት / ሸቀጥ ለደንበኞች እንዴት ይከፋፈላል ወይም እንዴት ሊደርሳቸው
ይችላል?
 ደንበኞች በቀጥታ ማግኘት ይችላሉ
 በጅምላ ሻጮችና በችርቻሮ በሚሸጡ ነጋዴዎች በኩል
 ይህንን የመሸጫ / የማከፋፈያ ዘዴ ለመጠቀም የተፈለገበት ምክንያት ምንድነው?

26
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት ECCSA

 ገበያ ለመሳብ / ምርቱን ለማስተዋወቅ ማቀድ


 ማስታወቂያ በመስራት
 ሽያጭ በማከናወን

27
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት
 የምርት እቅድ ECCSA
 ምርት የሚመረትበት ሂደት ዝርዝር (የሚያስፈልገው ግብዓት፣ የምርት ስራዎቹ ቅደም ተከተል)
 የሚያስፈልገውን ቋሚ እቃ ዝርዝር ከነዋጋው ይገለጽ
 የእቃው ዓይነት፣ ብዛት፣ ዋጋው
 በወር ሊመረት የሚችለው ምርት መጠን ይገለጽ
 የማምረቻው ቦታና መሳሪያ ይገለጽ
 ለምርት ተግባር የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች ዝርዝር
 የሚያስፈልገው የጥሬ እቃ ዝርዝር፣ መለያ፣ ብዛት፣ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ
 የሰራተኞች ክፍያ..... የስራ መደብ፣ ሙያ፣ ወርሀዊ ደመወዝ ....
 የኢንተርፕራይዙ የስራ ማስኬጃ ወጪዎች
 የስራ ማስኬጃ ወጪዎች ዝርዝርና የገንዘብ መጠን (በወር)
 የጊዜያዊ ሰራተኛ የጉልበት ዋጋ ክፍያ
 የመብራት ክፍያ (እንዲሁም ውሃ፣ ስልክ እና የመሳሰሉት ወጪዎች)
 የጥገና ወጪ
 የቋሚ እቃዎች የአገልግሎት ዘመን ዋጋ ቅናሽ

 የእያንዳንዱ ምርት የማምረቻ ዋጋ.... 28


የንግድ ስራ እቅድ ይዘት
ECCSA
 የአደረጃጀትና የአስተዳደር እቅድ
ዋና ስራ አሰኪያጅ
 የንግድ ስራው ዓይነት
 የድርጅቱ አወቃቀር የፋይናንስ የምርት የሽያጭና ግዥና
የሰው ሀይል
ስራ አስኪያጅ ክፍል ስርጭት ንብረት

29
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት
 የገንዘብ ፍሰት እቅድ ECCSA
 የሚያስፈልግ የገንዘብ መጠን / የፕሮጀክት ዋጋ የገንዘብ መጠን
 ቋሚ እቃ /ንብረት
 መሬት
 ህንጻ (የማምረቻና የመሸጫ ቦታ)
 መሳሪያ
 አጠቃላይ የቋሚ እቃ /ንብረት ዋጋ
 ምርት ከማምረት በፊት የሚኖር ወጪ
 የመስሪያ ወርሀዊ የማምረቻ ወጪዎች
 የጥሬ እቃዎች ዋጋ
 የአስተዳደር ወጪዎች
 ወርሀዊ የሰራተኛ ክፍያ
 አጠቃላይ የማምረቻ ዋጋ
 አጠቃላይ የካፒታል ዋጋ
30
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት
 የገንዘብ ፍሰት እቅድ ECCSA

 የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ( ለአምራቾች የንግድ ዘርፍ)


 ዓመታዊ የትርፍና ኪሳራ ግምት መግለጫ
 ጠቅላላ ሽያጭ
 (የሚቀነስ) ከሽያጭ ላይ ተመላሽ የሚሆን (ካለ)
 የተጣራ ሽያጭ
 (የሚቀነስ) የተሸጡ እቃዎች የመጀመሪያ ዋጋ
 የተጣራ ትርፍ
 (የሚቀነስ) የኦፕሬሽንና የአስተዳደር ወጪ
 የማስፈጸሚያ ትርፍ
 (የሚቀነስ) የወለድ ወጪ (የብድር ወለድ ክፍያ)
 ከታክስ በፊት ያለ ትርፍ
 (የሚቀነስ) የገቢ ታክስ ግምት
 ከታክስ በኃላ ያለ ትርፍ 31
የንግድ ስራ እቅድ ይዘት
 የገንዘብ ፍሰት እቅድ ECCSA

 የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ( ለአገልግሎት የቢዝነስ /


የንግድ ዘርፍ)
 ዓመታዊ የትርፍና ኪሳራ ግምት መግለጫ
 የገቢ መጠን
 ሽያጭ
 (የሚቀነስ): የኦፕሬሽን ወጪ
 የደመወዝ ክፍያ ወጪ
 የኪራይ ወጪ
 ከሽያጭ ጋር የተያያዘ ወጪ
 የወለድ ወጪ (የብድር ወለድ ክፍያ)
 ልዩ ልዩ ወጪዎች
 ከታክስ በፊት ያለ ትርፍ
 (የሚቀነስ) የገቢ ግብር ግምት
32

የንግድ ስራ እቅድ መቼ ይዘጋጃል? ECCSA

 የንግድ ስራ ለመጀመር ሲታሰብ


 የንግድ ስራ ከመጀመር አስቀድሞ
 የንግድ ስራውን ለማሳደግ ሲታሰብ
 የንግድ ስራውን በተመለከተ አዲስ ሀሳብ ሲገኝ
 አዲስ ልምድ ሲገኝ

33
ECCSA
የንግድ ስራ እቅድ ማን ይዘጋጃል/ በማን ይዘጋጃል?
 በንግድ ስራው ስራ አስኪያጅ ሊጀመር የታሰበውን የቢዝነስ / የንግድ ስራ ታሳቢ
ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡
 በዚህ ረገድ ድጋፍ ሰጪ በሆነ አካል እንዲሁም አማካሪዎች ድጋፍ ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
 የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን በመጠቀም እንደ አስፈላጊነቱ ለኢንተርፕራይዙ
እንደሚመች በመቀየር መጠቀም ይቻላል፡፡

34
ጠቃሚ የንግድ እቅዶች ECCSA

 የሽያጭና የግብይት እቅድ


 የምርትና ወጪዎች እቅድ
 የትርፍ እቅድ
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ
 የብድር እቅድ

35
ጠቃሚ የንግድ እቅዶች
ECCSA
 የሽያጭና የግብይት እቅድ
 ሽያጭና ግብይት በጣም ተቀራራቢ ድርጊቶች ናቸው
 የግብይት ተግባራት በንግድዎ ሽያጭ ላይ የማይቀር ተፅእኖ ይኖራቸዋል
 የሽያጭና የግብይት እቅድዎን ሲያዘጋጁ ንግድዎ በሰባቱ የግብይት ቅንብሮች ላይ ምን እንደሚሰራ ይተነብያሉ
 ምርት፣ ዋጋ፣ ቦታ፣ ማስፋፊያ፣ ሰዎች፣ ክንዋኔና አካላዊ ማረጋገጫዎች
 በእያንዳንዱ ወር ምን ያህል ሽያጭ ሊኖርዎት እንደሚችል ይተንብዩ፡፡
 ይህ እቅድ የደንበኞችዎን ፍላጎት ለማርካት የሚያስችሉዎትን ትክክለኛዎቹን እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ደንበኞች ሊከፍሉ
ፈቃደኛ በሚሆኑበት ዋጋ እንዲያቀርቡ ይረዳዎታል፡፡
 የምርትና ወጪዎች እቅድ
 የትርፍ እቅድ
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ
 የብድር እቅድ 36
ጠቃሚ የንግድ እቅዶች ECCSA
 የሽያጭና የግብይት እቅድ
 የምርትና ወጪዎች እቅድ
 የብዙዎቹ ንግዶች ከፍተኛ ወጪያቸው የሚሆነው የምርት ሂደቶች ላይ ነው
 ንግዱ ምን ያህል ብዛት ያለው ምርት ያመርታል?
 ለምርቱም ምን አይነት ጥሬ እቃዎች ያስፈልጋሉ?
 ወጭውስ?
 የምርት እቅድና የወጪዎች እቅድ ሲዘጋጅ ሁለቱንም አጣምሮ እንዲይዝ ተደርጎ ነው
 በምርትና ወጪዎች እቅድ ላይ የምርት ማሻሻያዎችን በመተለም ወጪዎችዎን በየወሩ ተከፋፍለው ይተነብያሉ
 የትርፍ እቅድ
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ
 የብድር እቅድ
37
ጠቃሚ የንግድ እቅዶች ECCSA

 የሽያጭና የግብይት እቅድ


 የምርትና ወጪዎች እቅድ
 የትርፍ እቅድ
 በትርፍ እቅድ አማካኝነት በእያንዳንዱ ወር ምን ያህል ያልተጣራ ትርፍና የተጣራ ትርፍ
እንደሚያገኙ ይተነብያሉ፡፡
 ንግድዎ ትርፍ የሚያገኘው እንዴት እንደሆነ እንዲያቅዱ ይረዳዎታል፡፡
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ
 የብድር እቅድ

38
ጠቃሚ የንግድ እቅዶች ECCSA

 የሽያጭና የግብይት እቅድ


 የምርትና ወጪዎች እቅድ
 የትርፍ እቅድ
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ ማለት በየወሩ ምን ያህል ገንዘብ ወደንግድዎ እንደሚገባና ምን
ያህል ገንዘብ ከንግድዎ እንደሚወጣ ይተነብያሉ፡፡
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ በማንኛውም ጊዜ ንግድዎ የጥሬ ገንዘብ እጥረት
እንዳይገጥመው ለማድረግ ይረዳል፡፡
 የብድር እቅድ
39
ጠቃሚ የንግድ እቅዶች ECCSA
 የሽያጭና የግብይት እቅድ
 የምርትና ወጪዎች እቅድ
 የትርፍ እቅድ
 የጥሬ ገንዘብ ፍሰት እቅድ
 የብድር እቅድ
 ንግድዎ ምን ያህል ሊበደር እንደሚችል፣ መቼ ብድሩ እንደሚያስፈልገውና ማንን ብድር
ሊጠይቅ እንዳሰበ ያቅዱበታል፡፡
 ይህ እቅድ ንግድዎ ጥሩ የገንዘብ ምንጮች እንዲያገኝ ያስችልዎታል፡፡

40
የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች ECCSA
 በተቻለ መጠን ቀለል ያድርጉት፤ ለማዘጋጀትና ለመጠቀም ቀላል ይሆንልዎታል፡፡
 ለእቅድዎ ይበልጥ ተስማሚ የሚሆነውን ክፍለጊዜ ይምረጡ፡፡
 ለሶስት ወር፣ ለአንድ አመት ወይም ለንግድዎ ተስማሚ በሆነ ለማንኛውም ክፍለጊዜ የንግድ እቅድ ማውጣት
ይችላሉ፡፡
 እቅድዎን በየወሩ ይከፋፍሉት፡፡
 ከብድር እቅድ በስተቀር ሁሉም እቅዶች በወር መከፋፈል አለባቸው፡፡
 በመሰረታዊ የሂሳብ መዝገብዎ ውስጥ የንግድ ሂሳብዎን በየወሩ ከፋፍለው ይመዝግቡ፡፡
 የንግድ እቅድዎን በየወሩ ሲከፋፍሉ የሂሳብ መዝገብዎን ከእቅድዎ ጋር በየወሩ ማመሳከር ይችላሉ፡፡
 ይህ ከሆነ ደግሞ የንግድዎን እንቅስቃሴ በእቅድዎ መሰረት መሆኑን መመልከት ይችላሉ፡፡
 የንግድ እቅዶችዎን የሚያዘጋጁት አስቀድመው ሊጠቀሙባቸው ከመፈለግዎ በፊት ነው፡፡
 የሚቀጥለውን እቅድ ለማዘጋጀት አሁን ያለው የእቅድ ወቅት እስከሚያበቃ ድረስ መጠበቅ የለብዎትም፡፡
41
የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች ECCSA

 መረጃ በመሰብሰብ እቅድ ሲያዘጋጁ ይጠቀሙበት፡፡


 ለምሳሌ፣ የእቃዎችንና ቁሳቁሶችን ወጪዎችን ሲተነብዩ የቀጣዩ አመት ዋጋ ምን ያህል ሊሆን
እንደሚችል አቅራቢዎችዎን ይጠይቁ፡፡
 በመላ ምት አይጠቀሙ፡፡
 የንግድ እቅድዎን ወቅታዊ መረጃ ተጠቅመው ያሻሽሉት፤ እርስዎ የሚያዘጋጁት የንግድ እቅድ
ረጅም ጊዜ ላያገለግልዎት ይችላል፡፡
 ምክኒያቱም ነገሮች በየጊዜው ስለሚቀያየሩ ነው፡፡
 ለምሳሌ፣ የጥሬ እቃ ዋጋ በድንገት ሊጨምር ይችላል፤ የደንበኞች ፍላጎት ደግሞ ሊቀንስ ይችላል፡፡
ይህ ደግሞ የሽያጭ፣ የወጪዎች ና የትርፍ እቅዱን ያፋልሰዋል፡፡ ስለዚህ ሁኔታዎች በሚቀየሩበት
ጊዜ በየጊዜው የንግድ እቅዱን ማየትና ማስተካከል ይኖርብዎታል ማለት ነው፡፡
42
የንግድ እቅድ ትንታኔ ECCSA

 ለንግድዎ የወደፊት እቅድ ከማዘጋጀትዎ በፊት ያለፉትን የንግድዎን አፈፃፀሞች አስቀድመው በሚገባ
ተንትነው ማወቅ ይኖርብዎታል፡፡
 የንግድ እቅድ ትንታኔ ለማድረግ የመረጃ ምንጭዎ የንግድ ሂሳብ መዝገብዎ ነው፡፡
 በንግድ ሂሳብ መዝገብዎ ተጠቅመው ያለፊትን ጊዜያት የንግድዎን አፈፃፀም በዝርዝር መዳሰስ
የንግድ ትንተና ይባላል፡፡
 ያለፉት ንግድ እንቅስቃሴዎች መረጃ ከሌለ እቅዳችን የምናዘጋጀው ያለበቂ መረጃ ወይም በግምት
ይሆናል፡፡

43
የንግድ እቅድ ትንታኔ ECCSA
 የንግድ ትንታኔ ዋነኛ አላማ ከዚህ በፊት ንግድዎ ውጤታማ ያልነበረባቸውን ጉዳዮች/ነገሮች ለመለየት፣
ውጤታማ የነበረባቸውን መልሶ ለማየትና ወደፊት ምንና እንዴት ይበልጥ የተሻለ መስራት እንደሚችል ለይቶ
ለማወቅ ነው፡፡
 መሰረታዊ የሂሳብ መዝገብዎ ንግድዎን ለመተንተን እጅግ በጣም ጠቃሚ የመረጃ ምንጭዎ ነው፡፡
 ሶስት አይነት አስፈላጊ ትንተናዎች አሉ፤
 የሽያጭና የግብይት ትንታኔዎች
 የምርትና የወጪዎች ትንታኔዎች
 የትርፍ ትንታኔዎች ናቸው፡፡
 ንግድዎን ለመተንተን የሚከተሉትን ሶስት ሂደቶች ይከተሉ፤
 ያለፉትን አመታተት የንግድ እንቅስቃሴ መረጃዎችን ያግኙ
 የንግድ ውጤቶችዎን ያነፃፅሩ
 ምክንያቶችን ይወቁ
44
የንግድ እቅድ ትንታኔ ECCSA

1. የሽያጭና የግብይት ትንታኔዎች


 ሽያጭዎ ምን ያህል እንደጨመረ ወይም እንደቀነሰ ለማወቅ እንዲችሉ የየወሩንና የየአመቱን
ሽያጮች ያወዳድሩ፡፡
 የግብይት እንቅስቃሴዎን በመተንተን ሽያጭዎ ከፍና ዝቅ የሚልበት ወይም የሚለዋወጥበትን
ምክንያቶች ይወቁ፡፡
 በዚህም ሂደት ሽያጭዎን ለመጨመርና ንግድዎን ለማሻሻል ማቀድ ይችላሉ፡፡
 የንግድ ወጤቶቸዎን መጠኖች ከታች ከተዘረዘሩት አንጻር ይተንትኑ
 ምርት፣ ዋጋ፣ ቦታ፣ ማስፋፊያ፣ ሰዎች፣ ክንዋኔዎች ....

45
የንግድ እቅድ ትንታኔ ECCSA
1. የሽያጭና የግብይት ትንታኔዎች
 በንግድ ሰራዎ ላይ ያሉ መሰረታዊ ችግሮችን ለመለየት በጥንቃቄ መመርምር ያስፈልጎታል፡፡
 ይህንን ሂደት በብቃት ለመወጣት ከታች የተመለከቱትን አይነት ጥያቄዎች ይጠይቁ፤
 ከዚህ በፊት ንግዴ ምን ያህል አምርቷል?
 የንግዴ የማምረት አቅም ተገቢ ነውን?
 የተከራየሁትን ቦታ በሚገባ ተጠቅሜበታለሁን?
 የቁሳቁሶች አጠቃቀሜ በቁጠባ ነበር ወይስ አባክን ነበር?
 የቁሳቁሶች ዋጋ ጨምሮ ነበር ወይስ ቀንሷል?
 ሰራተኞች ሙሉ ለሙሉ ስራቸውን ማከናወን ይችሉ ነበረን?
 ሰራተኞቼ በሙሉ ተሟልተው ነበር?
 የማምረት ሂደቴ ውጤታማ ነበርን?
 ሰራተኞቼ በቂ ክህሎት እና ተነሳሽነት ያላቸው ነበሩ?
46
ECCSA

የቡድን ዉይይት
 የንግድዎ ሽያጭ እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ነው?
ለምን?

47
የውጫዊ ሁኔታዎች ለውጦችን ትንበያ ECCSA
 የእርስዎ ንግድ ብቻውን መቆም አይችልም፤ የሚንቀሳቀሰው በገበያ ውስጥ ነው፡፡
 ስለዚህ የእርስዎ የንግድ እቅድ አዋጪ መሆኑን እርግጠኛ ለመሆን ውጫዊ ሁኔታዎችንም ያገናዘበ መሆን
ይኖርበታል፡፡
 የንግድ እቅዱ መሰረት ማድረግ ያለበት በገበያ ምን እንደተፈጠረ ብቻ የሚለውን ብቻ ሳይሆን በገበያ ውስጥ
ወደፊት ምን ሊፈጠር ይችላል በሚል ነው፡፡
 ይህ ማለት በውጫዊ አካባቢ ሁኔታዎች ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦችንና በንግድዎ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ነገሮችን
መተንበይ ያስፈልግዎታል ማለት ነው፡፡
 ትንበያ ምንድን ነው?
 የንግድ እቅድዎን ሲያዘጋጁ በውጫዊ ሁኔታዎች ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦችንና እንዴት በንግድዎ ላይ ተፅእኖ
ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ይተነብያሉ፡፡
 ወደፊት በእርስዎ ግብይት፣ ሽያጭ፣ የምርት ሂደት፣ ወጪዎች፣ ትርፍና የገንዘብ ፍሰት ላይ ለውጦች እንዴት ተፅእኖ
ሊያሳድሩ እንደሚችሉ መገመትዎ አይቀርም፡፡
48
የውጫዊ ሁኔታዎች ለውጦችን ትንበያ ECCSA
 በሽያጭዎና በግብይትዎ ላይ ተፅእኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ ውጫዊ አካባቢ ለውጦች

ውጫዊ
አካባቢ

49
ጥንካሬ፣ ድክመት፣መልካም አጋጣሚና ተግዳሮት ትንተና
ECCSA

አጋዥ ጎጅ

ጥንካሬ ድክመት

• .... • ...
• ...
ውስጣዊ

መልካም አጋጣሚ ስጋት/ተግዳሮት

• ... • ....
ውጫዊ
የውጫዊ ሁኔታዎች ለውጦችን ትንበያ ECCSA

 በንግድዎ ሽያጭና ግብይት ላይ ተፅእኖ ሊያመጡ ከሚችሉ አካባቢያዊ ለውጦች መካከል ጥቂት
ምሳሌዎች፤
 የደንበኞች ፍላጎቶች
 የተወዳዳሪዎች እንቅስቃሴ
 አማራጭ ምርቶች
 የኢኮኖሚ ለውጥ
 አዳዲስ ፖሊሲዎች፣ ህጎችና ደንቦች
 በንግድ የማምረት ተግባሮችና የወጪዎች ላይ ተፅእኖ ሊያመጡ ከሚችሉ ለውጦች ጥቂት ምሳሌዎች፤
 የጥሬ እቃ አቅርቦትና የተማረ ሰው ኃይል
 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች
 የኢኮኖሚ ለውጦች
 አዳዲስ ፖሊሲዎች፣ ህጎችና ደንቦች 51
ስጋቶችን መለየት ECCSA

 ስጋት ምንድን ነው?


 ስጋት ማለት ባልተጠበቁ አጋጣሚዎች ምክንያት ንግድዎ ጉዳት ውስጥ ሊወድቅ የሚችልባቸው
ሁኔታዎች ማለት ነው፡፡
 ስጋት በንግዱ በውስጥና በውጫዊ አካባቢዎች ሊነሳ ይችላል፡፡ በንግዱ ከውስጥ የሚነሱ ውስጣዊ
ስጋቶች ይባላሉ፡፡
 ከውስጣዊ ስጋቶች ጥቂት ምሳሌዎች ለመጥቀስ ፤ የንብረት መበላሸት፣ ማጭበርበር፣ አደጋና
የሰራተኞች ከስራ መልቀቅ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
 ከውጫዊ አካባቢዎች የሚነሱ ስጋቶች ደግሞ ውጫዊ ስጋቶች ይባላሉ፡፡
 ከውጫዊ ስጋቶች ጥቂት ምሳሌዎች ለመጥቀስ፤ የአቅርቦት እጥረት፣ የውጭ ምንዛሪ መዋዠቅ፣
የማይሰበሰቡ እዳዎች፣ አዳዲስ ህጎችና የተፈጥሮ አደጋዎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡

52
ስጋቶችን መለየት ECCSA

 የስጋት አያያዝ ምንድን ነው?


 የስጋት አያያዝ ማለት ንግድዎ ለየትኞቹ ስጋቶች እንደሚጋለጥ በመለየት እነዚህ ስጋቶች በንግዱ ላይ
የሚያስከትሉትን ተፅእኖዎች ለመቀነስ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች መንደፍ ነው፡፡
 የስጋት መከላከል ዝግጁነት የንግዱ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫና አንቀሳቃሽ መሆን የሚኖርበት
ከመሆኑም በላይ በንግዱ የእለት ተእለት ስራአመራር ውስጥ መሰካት ወይም መተከል
ያስፈልገዋል፡፡
 የስጋት አያያዝ ዘዴዎች አላማ ስጋት መውሰድን ለመከላከል ወይም ለመከልከል አይደለም፡፡
 ነገርግን ስለምንወስደው ስጋት በሚገባ እውቀቱ ኖሮንና ስጋቱን መቀበል የሚያስከትላቸውን
ውጤቶች በመረዳት ስለሚሆን ለስጋቱ ተገቢውን ምላሽ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

53
ስጋቶችን መለየት ECCSA
 የስጋት አያያዝ ደረጃዎች
1. ለአሁንና ለወደፊት ንግድዎ የተጋለጠባቸውን ስጋቶች ይለዩ፤
2. የስጋቶችን ሁነት (መከሰት) መገምገም
3. የስጋቶችን ቅደምተከተል መወሰን (በደረጃማስቀመጥ)፡፡
4. ለስጋቶች ምላሽ መስጠት
 አራት የተለመዱ የስጋቶች ምላሽ የመስጠት መንገዶች አሉ
 መቀበል
 የተወሰኑ ስጋቶች የማይቀሩ ናቸው
 ማስተላለፍ
 የተወሰኑ ስጋትን ለመቀነስ ለንግድዎ የመድህን ዋስትና መግባት
 መቀነስ
 የስጋት መከሰት እድሉን ወይም የሚያመጣውን ተፅእኖ መቀነስ
 ማራቅ

54
በንግድዎ ላይ የመከሰት እድል ያላቸውና ትልቅ ተፅእኖ ሊያመጡ የሚችሉ ስጋትን ማጥፋት
የቡድን ውይይት ECCSA
1. ንግድዎ በአሁን ሰአት የተጋለጠባቸውና ወደፊት የሚከሰቱትን ስጋቶች ይዘርዝሩ፡፡
2. ንግድዎ ለየትኞቹ ስጋቶች ቅድሚያ ይሰጣል?
3. ንግድዎ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ስጋቶች እንዴት ይቋቋማል?
4. ከላይ ያሉትን ጥያቄዎች ከመለሱ በኋላ የሚቀጥለውን ቅፅ ይሙሉ፡፡

ተ.ቁ ስጋት የመከሰት እድል ድግግሞሽ ተጽዕኖ ደረጃ የስጋት


ምላሽ
/መፍትሔ
1
2
3
4
5
55
ለንግድ እቅድዎ መረጃ የሚያገኙት ከየት ነው?
 የንግድ ልማት አገልግሎት ሰጪዎች፤ ECCSA

 እነዚህ ተቋሞች ከሚሰጡት የተለያዩ የንግድ አቅም ማሳደጊያ አገልግሎቶች መካከል የተለመዱትን ለመጥቀስ ያህል የስራ አመራር
ስልጠና፣ የገበያ ተደራሽነት መረጃዎች፣ የፋይናንስ ተደራሽነት መረጃዎችና የቴክኒክ ስልጠናዎች ይገኙበታል፡፡
 የንግድ ልማት አገልግሎቶች በመንግስት ተቋሞች፣ አማካሪዎች፣ ልዩ ፕሮጀክቶች ወይም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ሊሰጡ
ይችላሉ፡፡
 የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማህበሮች፤
 ከእነዚህ ማህበሮች ከዘርፉ ጋር ስለተያያዙ ህጎች፣ ታክስ፣ ደረጃዎችና ሌሎች ጉዳዮች በተለይ በእርስዎ ንግድ ላይ አንድምታ
ስለሚኖራቸው አዳዲስ ጉዳዮች መረጃዎች ሊያገኙይችላሉ፡፡
 የሂሳብ ባለሙያዎች፣ጠበቆችና የንግድ አማካሪዎች፤
 ከንግድ አቅዱ አንዳንድ ክፍሎች ጋር በተያያዘ ሊያግዙይችላሉ፡፡
 የፋይናንስ ተቋሞች፤
 እንደባንኮች፣ የህብረት ስራ ማህበሮች፣ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋሞች

56
ECCSA
 አለም አቀፍ ተቋሞች፤
 በተለይ ኢንተርፕርነሮችን ለማገዝ የሚያካሂዷቸው ፕሮጀክቶች መረጃ በመስጠት ሊያግዙ ይችላሉ፡፡
 የንግድ ማውጫዎች፤
 የተለያዩ የንግድ ጉዳይ ፈፃሚ አገልግሎቶች
 ለምሳሌ፣ ንግድ ፈቃድና ምዝገባ፣ ታክስና ለአነስተኛ ንግድ ተበዳሪዎች ተፈላጊ ሁኔታዎችን ለማሟላት የማመቻቸት
አገልግሎቶች፣
 ኢንተርኔት፤
 የንግድ እቅድዎን ለማጠናቀቅ የሚያግዙ በርካታ መረጃዎችን ከመረጃ መረቦች ማግኘት ይችላሉ፡፡

የንግድ ሥራ ዕቅድ መቼ ያስፈልጋል?


 አዲስ የንግድ ስራ ሲጀምሩ
 ነባር የንግድ ስራ ድርጅት በሚገዛበት ጊዜ
 ነባር የንግድ ስራ ድርጅት ወሳኝ የምርት ሂደት ለውጥ ካስፈለገ
57
ECCSA

የንግድ ሥራ ዕቅድ ማን ሊመለከተው ይችላል?


 ስራ መሪዎች/አስተዳዳሪዎች
 ባለቤቶች / የንግድ አጋሮች (የአሁን ...የወደፊት)
 አበዳሪዎች - እንደ ባንኮች ፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወዘተ
 መንግስት ...
 ማህበረሰቡ

58
የንግድ ሥራ እቅዱን ማን ሊያዘጋጀው ይችላል? ECCSA

 ስራ መሪዎች/አስተዳዳሪዎች
 ባለቤቶች / የንግድ አጋሮች
 አማካሪዎች
 ስራ ፈጣሪዎች

59
የንግድ እቅድ የማዘጋጀት ሂደት ECCSA

 የንግድ ስራ እቅድ መጻፍ በራሱ ትልቅ ፕሮጀክት ነው


 የሚከተሉትን ተግባራት ይጠይቃል
 ተለያዩ መረጃዎችን መሰብሰብ
 የመረጃ ትንተና ማከናወን
 የንግድ እቅዱን በተለያዩ ክፈሎች ከፍሎ መፃፅፍ
 ለተለያዩ አካለት በቃል ማቅረብ

60
የንግድ እቅድ የማዘጋጀት ሂደት
ECCSA
 መረጃ መሰብሰብ
 እቅዱን ለማዘጋጅት የመጀመሪያው ስራ መረጃ መሰብሰብ ነው
 የመረጃ ምንጮች የሚከተሉት ናቸው
 በይነመረብ
 የመንግስት ስታትስቲክስ;
 የገቢያ ምርምር ሪፖርቶች;
 ዩኒቨርሲቲዎች;
 የንግድ ማህበራት;
 የንግድ ሥራ ጋዜጦችና መጽሔቶች;
 የተፎካካሪ ድርጅቶች ሪፓርት;
 ከተለያዩ አካለት ጋር የሚደረጉ ቃለ-መጠይቆች
 የአቅራቢዎች ፣ የደንበኞች እና የተፎካካሪዎች አስተያየቶች

61
የንግድ ሥራ ዕቅድ ለማዘጋጀት ቁልፍ መመሪያዎች ECCSA

 ዕቅዱን በተቻለ መጠን አጭርና ግልጽ ያድርጉት


 እቅዱን በተገቢው ሁኔታ ያደራጁ፣ ይጠርዙ
 እቅዱ የወደፊት አቅጣጫን ማሰየት የሚችል መሆን አለበት
 እቅዱ ውስጥ የተጋነኑ ሀሳቦች መኖር የለባቸውም
 ወሳኝ ስጋቶችን ለይተው ያውጡ
 በጣም የተበታተኑ የንግድ አይነቶችን በአንድላይ አይጨምሩ
 ትኩረት የሚሻውን ገበያ ይለዩ
 የአንባቢውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ያዘጋጁ

62
የንግድ ሥራ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ሂደት የተለመዱ ስህተቶች
ECCSA
 ለእድገት ግልጽ የሆነ ዕቅድ አለማስቀመጥ
 እቅዱን በቀላል ቋንቋ አለማዘጋጀት
 በአግባቡ የገቢያ እና የተፎካካሪ ሁኔታ ትንታኔ አለማድረግ
 ያልተሟላ የገንዘብ መረጃ
 ብዙ ጊጽ ያላቸው አባሪዎች
 እቅዱ ማከተት ያለበትን ክፈሎች አለማካተት ወይም በሚፈለገው ደረጃ በዝርዝር ሀሳቦችን አለማስቀምጥ
 በጣም የተወሳሰበ፣ እዚህና እዚያ የሚረግት ረጅም ሰንድ
 አህጽሮተ ቃላት ከመጠን በላይ መጠቀም
 ዩሳብ ድግግሞሽ

63
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA
 የንግድ እቅድ ቅርጸት / ይዘት
 የንግዱ እቅድ ውስጥ ጥልቀት እና ዝርዝር በሥራ መጠን እና ስፋት ፣ የሚቀርበለት አካል እና በንግዱ ሁኔታ (አገልግሎት /
ማኑፋክቸሪንግ) ላይ የተመሠረተ ነው ፡
 የገበያው መጠን ፣ የፉክክር እና የንግዱ ዕድገት በንግድ እቅዱ ስፋትና ጥልቀት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ
 ምንም ይሁን ምን ፣ የንግድ እቅድ የሚከተሉትን ሶስት ጥያቄዎች መመለስ አለበት
1. አሁን የት ነን?
 የጥንካሬ፣ ድክምት፣ መልካም አጋጣሚና ተግዳሮት ትንተና
 ስለ የገበያ ቦታ ወቅታዊ ሁኔታ ፣ ስለ ውድድር ፣ ስለ ንግድ ሥራው ፅንሰ-ሀሳብ እና አስፈላጊ በሆኑ የመጀመሪያ እርምጃዎች
ውስጥ የተሳተፉ ሰዎችን ትንተና ፡፡
2. ወዴት ለመሄድ አስበናል?
 ሌሎች ለወደፊቱ ሊያካፍሉት ከፈለጉ ለንግዱ የታቀደው አቅጣጫ ግልጽ እና ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡
3. እንዴት እንደርሳለን?
64
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች
ECCSA
1. የመግቢያ ገጽ
2. ማጠቃለያ
3. የአካባቢ እና ኢንዱስትሪ ትንተና
4. ስለ ንግድ ስራው ሰፊ ማብራሪያ
5. የግብይት ዕቅድ
6. የምርት እና የሥራ ዕቅድ
7. የድርጅት መዋቅር
8. የስጋት ትንተና
9. የገንዘብ እቅድ

65
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA

1. የመግቢያ ገጽ
 የንግድ ሥራ ስም እና አድራሻ
 የዋና ዋና ተዋነዮች ስም እና አድራሻ
 የንግድ ሥራ አይነት
 ማውጫ

66
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች
ECCSA
2. ማጠቃለያ
 የተሟላ የንግድ ሥራ እቅዱን በማጠቃለል ከሁለት እስከ ሶስት ገጾች
 በጣም አስፈላጊ የሆነውን የንግድ እቅዱን ክፍል ያቀርባል፣ ምክንያቱም
 ወደ ዋናዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መረጃ ይሰጣል፣
 ስለድርጅትዎ አጭር መግለጫ ይሰጣል ፡፡
 ዋና ዋና መግለጫዎች እና መደምደሚያዎች እና የስኬት ምክንያቶች ይገልጻል
 ማጠቃለያው የሚከተሉትን ክፍሎች ማካትት አለበት
 የንግዱ ስትራቴጂ ዝርዝር
 የአስተዳደር ቡድኑ ቁልፍ ብቃቶች ገለፃ
 በገበያው ላይ አጭር መግለጫ ፣ የስኬት ቀመር እና ልዩ የመሸጥ ሀሳቦች
 የእርስዎ ተወዳዳሪ ጥቅሞች ጥቅል አቀራረብ
 ስለ ምርቶች እና አገልግሎቶች አጭር መግለጫ
 የገንዘብ ፍላጎቶችዎ መግለጫ 67
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA

3. የአካባቢ እና ኢንዱስትሪ ትንተና


 የወደፊቱ አመለካከት እና አዝማሚያዎች
 የተፎካካሪዎች ትንተና
 የገቢያ ክፍፍል
 ኢንዱስትሪ እና የገበያ ትንበያዎች

68
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA
4. ስለ ንግድ ስራው ሰፊ ማብራሪያ
 የንግዱን ምንነት
 ምንድነው ፣ ምን ያደርጋል? እንዴት ተመሰረተ? በማን? ለምን? ስኬት?
 ርዕይ / ተልዕኮ / ዓላማዎች
 ምርት እና አገልግሎት
 የንግድ ሥራ መጠን
 የሥራ አካባቢ
 የንግድ ሥራ ዓይነት

69
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች
4. ስለ ንግድ ስራው ሰፊ ማብራሪያ ECCSA
 የድርጅቱ ስልት/ስትራቴጂ
 መሠረታዊ ፍልስፍና እና አመክንዮ
 የውሳኔ አሰጣጥ ...... ያልተማከለ
 ድርጅቱን ለማሳደግ ከውጭ የሚመጣ የንግድ አጋር የመቀበል ፍላጎት

 አራት የስትራቴጂ የመርሆች


 አጠቃላይ የድርጅት ስትራቴጂ
 ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለማምረት እና ለመሸጥ፣
 ስኬትን ከፍ ለማድረግ
 ተልዕኮ መግለጫ ..... ድርጅቱ ለምን ተመሰረተ
 የድርጅት እሴቶች እና አጠቃላይ የመመስረት ዓላማን የሚያጠቃልል መግለጫ
 ቴክኖሎጂ / መረጃ ግምገማ
 ቴክኖሎጂን የመጠቀም እና መረጃን የማስተዳደር ችሎታ
 አመራር
70
 ስትራቴጂውን የሚወስን እና የሚተገብረው (ተዓማኒነት ሊኖረው ይገባል)
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA

4. ስለ ንግድ ስራው ሰፊ ማብራሪያ


 የተለያዩ የንግድ አደረጃጀት ዓይነቶች አሉ (እ.ኤ.አ. የ 1960 ን የኢትዮጵያ የንግድ ኮድ
ያንብቡ)
 ብቸኛ ባለቤትነት ፣
 አጋርነት ፣
 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና
 ኮርፖሬሽን / አክሲዮን ማኅበራት
 የህብረት ሥራ ማህበራት

71
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች
4. ስለ ንግድ ስራው ሰፊ ማብራሪያ
ECCSA
 ንግዱ የት ቦታ ይቋቋም
 ወጭዎችን ለመቀነስ ወይም የደንበኞች ምርቶችዎን ለመመልከት ወይም ቢያንስ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ የንግድ ሥራው ቦታ በጣም
አስፈላጊ ነው ፡፡
 ንግዱ የችርቻሮ ወይም የአገልግሎት ተኮር ከሆነ ከገበያ አቅራቢያ መሆን አለበት ፡፡
 ምርቱን ተኮር ከሆነ ወደ ጥሬ ዕቃ ምንጮች ወይም ወደ መሠረተ ልማት ተቋማት (ለምሳሌ ፣ ወደብ) ፣ የትራንስፖርት እና የፍጆታ
አገልግሎቶች (ለምሳሌ ፣ ኃይል) ማዕከላት አጠገብ መቅረቡ የተሻለ ሊሆን ይችላል ፡፡
 የንግድ በቦታውን ለመወሰን የሚከተሉት ጉዳዩች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው
 ለአስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች ያለ ቅርበት
 ለገቢያዎች እና ለማከፋፈል ያለ ቅርበት
 የትራንስፖርት ተቋማት መኖር
 ቀልጣፋ እና ርካሽ የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖር
 ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎች መኖር (ወደፊት / ወደ ኋላ ትስስር)
 የመሠረተ ልማት ተቋማት (ለምሳሌ ፣ መንገድ ፣ ኃይል ፣ ወደብ ፣ ወዘተ)
 የግንኙነት ተቋማት (ለምሳሌ ፣ ፖስታ ቤት ፣ ስልክ ፣ ፋክስ ፣ ቴሌክስ ፣ ወዘተ) 72
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች
4. ስለ ንግድ ስራው ሰፊ ማብራሪያ ECCSA

 ንግዱ የት ቦታ ይቋቋም
 ወጭዎችን ለመቀነስ ወይም የደንበኞች ምርቶችዎን ለመመልከት ወይም ቢያንስ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ የንግድ ሥራው ቦታ በጣም
አስፈላጊ ነው ፡፡
 ንግዱ የችርቻሮ ወይም የአገልግሎት ተኮር ከሆነ ከገበያ አቅራቢያ መሆን አለበት ፡፡
 ምርቱን ተኮር ከሆነ ወደ ጥሬ ዕቃ ምንጮች ወይም ወደ መሠረተ ልማት ተቋማት (ለምሳሌ ፣ ወደብ) ፣ የትራንስፖርት እና የፍጆታ
አገልግሎቶች (ለምሳሌ ፣ ኃይል) ማዕከላት አጠገብ መቅረቡ የተሻለ ሊሆን ይችላል ፡፡
 የንግድ በቦታውን ለመወሰን የሚከተሉት ጉዳዩች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው
 ለአስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች ያለ ቅርበት
 ለገቢያዎች እና ለማከፋፈል ያለ ቅርበት
 የትራንስፖርት ተቋማት መኖር
 ቀልጣፋ እና ርካሽ የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖር
 ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎች መኖር (ወደፊት / ወደ ኋላ ትስስር)
 የመሠረተ ልማት ተቋማት (ለምሳሌ ፣ መንገድ ፣ ኃይል ፣ ወደብ ፣ ወዘተ)
 የግንኙነት ተቋማት (ለምሳሌ ፣ ፖስታ ቤት ፣ ስልክ ፣ ፋክስ ፣ ቴሌክስ ፣ ወዘተ) 73
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA

5. የግብይት ዕቅድ
 አራት የግብይት ሁነቶች
 ምርት
 የዋጋ አሰጣጥ
 ቦታ (ስርጭት)
 ማስተዋወቂያ
 የሽያጭ ትንበያ

74
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA

6. የምርት እና የሥራ ዕቅድ


 ይህ ክፍል የሚከተሉትን ያጠቃልላል
 የማምረት ሂደት
 የማምረቻ ቁሳቁሶች አቀማመጥ
 ማሽኖች እና መሳሪያዎች
 የጥሬ ዕቃዎች አቅራቢዎች ስሞች
 የኩባንያ ሥራዎች መግለጫ
 ለሸቀጦች እና / ወይም አገልግሎቶች የትእዛዝ ፍሰት
 የቴክኖሎጂ አጠቃቀም (አቅም)

75
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች
ECCSA
7. የድርጅት መዋቅር
 ድርጅቱ ምን ያህል ሠራተኞች ፣ የሥራ መደቦች ፣ የሥራ አደረጃጀት አወቃቀር ፣ የባለስልጣኖች መስተጋብር መግለጫ ነው ፤
8. የገንዘብ እቅድ
 በጣም ጠቃሚ ክፍል
 ስለወደፊቱ ንግድ የፋይናንስ አካል ሁሉንም መሠረታዊ መረጃዎች ይይዛል
 የሚጠበቁ ገቢዎች እና ወጪዎች ፣ የፕሮጀክት ፋይናንስ መርሃግብር ፣ ፕሮጀክቱ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆን
ጠቋሚዎች
 በመጀመሪያ ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት ይህ ክፍል ነው;
9. ስጋቶች
 ከተወዳዳሪዎቹ እስከ ህሊና ቢስ አቅራቢዎች የፕሮጀክት አደጋዎች ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ
 ይህ ክፍል ሁሉንም ሊሆኑ የሚችሉ አደጋዎችን እና ለመቀነስ እና ለመቀነስ መንገዶችን ይገልጻል ፡፡

76
የንግድ እቅድ ወሳኝ ክፍሎች ECCSA
የድርጅት እቅድ... ስሌቱ የተገኘው ድርጅቱ ምን ያህል ሠራተኞች ፣ የሥራ መደቦች ፣ የሥራ አደረጃጀት
አወቃቀር ፣ የባለስልጣኖች መስተጋብር መግለጫ ነው ፤
የገንዘብ እቅድ... በጣም አስደሳች እና ጠቃሚ ክፍል። ስለዚህ ፣ ስለወደፊቱ ንግድ የፋይናንስ አካል ሁሉንም
መሠረታዊ መረጃዎች ይ containsል። የሚጠበቁ ገቢዎች እና ወጪዎች ፣ የፕሮጀክት ፋይናንስ መርሃግብር ፣
ፕሮጀክቱ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆን ጠቋሚዎች ፣ የእረፍት-ነጥብ ፡፡ በመጀመሪያ እርስዎ እና
ባለሀብቶች የሚስቡት ይህ ክፍል ነው;
አደጋዎች... ከተወዳዳሪዎቹ እስከ ህሊና ቢስ አቅራቢዎች የፕሮጀክት አደጋዎች ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ሊሆኑ
ይችላሉ ፡፡ ይህ ክፍል ሁሉንም ሊሆኑ የሚችሉ አደጋዎችን እና ለመቀነስ እና ለመቀነስ መንገዶችን ይገልጻል ፡፡

77
ECCSA

እናመሰግናለን!!

78
ECCSA

II. ራእይ ቅንብሮች /Vision Setting/

https://ethiopianchamber.com/
79
ECCSA

ሀ) ራእይ (Vision)እና የራእይ መግለጫ (Vision Statement)

ምንድን ናቸው?
ራእይ -
 ራዕይ - ስለወደፊቱ በአዕምሮ የማሰብ ወይም የማቀድ ችሎታ።
 ራዕይ ዕቅዶችን ለማዘጋጀት፣ ግቦችን እና ዓላማዎችን ለማውጣት ፣ ውሳኔዎችን
ለማድረግ እንዲሁም በማንኛውም ፕሮጀክት ላይ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሥራን
ለማስተባበር እና ለመገምገም የተግባራዊ መመሪያ ነው ፡፡
https://ethiopianchamber.com/
80
ECCSA

የራእይ መግለጫ /Vision Statement /ምንድን ነው?

 የአንድ ኩባንያ ወይም ድርጅት የወደፊት አቅጣጫውን ለማቀድ የሚጠቀምበት የግቦች


ስብስብ ወይም የተልእኮ መግለጫ ነው።
 የራዕይ መግለጫ አንድ ኩባንያ በረጅም ጊዜ ውስጥ በአጠቃላይ ከአምስት እስከ አስር ዓመት
ባለው ጊዜ ውስጥ ወይም አንዳንዴም ረዘም ላለ ጊዜ ለማሳካት ምን እንደሚፈልግ ይገልጻል።

https://ethiopianchamber.com/
81
ECCSA

የራእይ መግለጫ /Vision Statement/ጠቀሜታዎች


 ባለድርሻ አካላት በተለይም ሰራተኞች የንግድዎን ትርጉም እና ዓላማ እንዲገነዘቡ ይረዳል፡፡ በዚህ
ምክንያት ሠራተኞች የበለጠ ውጤታማ እና በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡
 የድርጅትዎን ጥረት የተፈለገውን የረጅም ጊዜ ውጤት ይገልጻል። ለምሳሌ ፣ ቀደምት የማይክሮሶፍት
ራዕይ መግለጫ የነበረው “ኮምፒተር በእያንዳንዱ ዴስክ እና በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ሲገባ“የሚለውን
ያሳያል።

 በከፍተኛ ደረጃ አንድ ድርጅት በጣም ተስፋ የሚያደርገው እና በረጅም ግዜ ስኬታማ የሚሆንበትን
መንገድ ያሳያል።
https://ethiopianchamber.com/
82
ተልዕኮ መግለጫ / Mission Statement / ECCSA

 ተልዕኮ መግለጫዎች - ንግዱ ለምን እንደተመሰረተ ለኩባንያው አባላትም ሆነ ለውጭው ማህበረሰብ

ለማስተላለፍ የተቀየሱ ናቸው ፡፡

 የሚያሳየው አሁን ስላለህበት ሁኔታ እና ለምን እንደምትስራ ነው ፡፡

https://ethiopianchamber.com/
83
ECCSA

ተልዕኮ እና ራዕይ መግለጫዎች /Mission and vision statements/

ተልዕኮ እና ራዕይ መግለጫዎች ሶስት ወሳኝ ሚናዎችን ይጫወታሉ-


(1) የድርጅቱን ዓላማ ለባለድርሻ አካላት ማሳወቅ ፣
(2) የስትራቴጂ ዝግጅትን ሁኔታን ማሳወቅ ፣ እና
(3) የድርጅቱን ስትራቴጂ ስኬታማነት ለመለካት የሚያስችሉ ግቦችን እና ዓላማዎችን ማዘጋጀት
፡፡

https://ethiopianchamber.com/
84
በራዕይ መግለጫ እና በ ተልዕኮ መግለጫ መካከል ልዩነት ECCSA

ተልዕኮ መግለጫ / Mission Statement/:

 ተልዕኮ መግለጫዎች - በአሁን ጊዜ (present based) የሚገለጽ ሆኖ ንግዱ ለምን


እንደተመሰረተ ለኩባንያው አባላትም ሆነ ለውጭው ማህበረሰብ ለማስተላለፍ የተቀየሱ ናቸው ፡፡

 የሚያሳየው አሁን ስላለህበት ሁኔታ እና ለምን እንደምትስራ ነው ፡፡

 ተልዕኮ መግለጫ በምርት ስሙ (purpose of the brand) ዓላማ ላይ ያተኩራል ፡፡

 ተልዕኮ ተግባር ተኮር ነው ፡፡

85 https://ethiopianchamber.com/
ECCSA
ራዕይ መግለጫ /Vision Statement/

 ለወደፊቱ የታሰበ (future-based) እና ከደንበኞች ይልቅ የኩባንያ ሠራተኞችን ለማበረታታት


እና መመሪያ ለመስጠት የታሰበ ነው ፡፡

 ራዕይ የወደፊት ግቦችዎን የሚገልጽበት እና እንዴትም እንደሚደርሱበት ነው


 ራዕይ ቡድኑ ለውጥ እንዲያመጣ እና ከራስ የበለጠ የትልቅ ነገር አካል እንዲሆኑ ሊያነሳሳ ይገባል
፡፡
 የራዕይ መግለጫው የዓላማ ፍፃሜን ትግበራንይመለከታል።
 ራዕይ ምኞት ነው
86
https://ethiopianchamber.com/
ማስታወሻ-በሚከተሉት ፅንሰ-ሀሳቦች መካከል ያለው ልዩነት-- ECCSA

 ራዕዩ ግብ ነው ፡፡ ከስትራቴጂ ጋር አንድ አይደለም;

 የንግድ ስትራቴጂ አንድ ኩባንያ የራሱን ራዕይ ለማሳካት (ወይም ለማቆየት) እንደሚቻል ይነግርዎታል። ስትራቴጂው
ራዕይ እንዴት እንደሚሳካ የሚገልጽ እቅድ ነው ፣ ታክቲኮቹ እቅዱ እንዴት እንደሚፈፀም እና ራዕዩ የመጨረሻ
ውጤት ነው ፡፡
 አንድ ጥሩ ስትራቴጂ በንግዱ ውስጥ ሰዎች ሊወስዷቸው የሚገቡትን (እና የማይወስዷቸውን) እርምጃዎች እና
ቅድሚያ የሚሰጧቸውን (እና ላለማስቀደም) የሚፈለጉ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ መመሪያዎችን ወይም ደንቦችን
የያዘ ግልጽ ፍኖተ ካርታ ይሰጣል ፡፡
 ግብ - አንድ ሰው ወይም የሰዎች ቡድን የሚገምቱት ፣ ሊያቅዱት እና ለማሳካት የሚፈልጉት ውጤት ሀሳብ ነው።
ሰዎች የጊዜ ገደቦችን በማውጣት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ግቦችን ለማሳካት ይጥራሉ
https://ethiopianchamber.com/
87
ራዕይ ECCSA
Vision

ተልዕኮ ስልት
Strategy
Mission

ግብ
Goal

ዓላማ
ተግባራት
Objective Activities
ECCSA
ለ) የአንድ ኩባንያ ራዕይ ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው ?

 ለንግዱ ዓላማ እና አቅጣጫን ይሰጣል ፡፡


 የድርጅቱን ዓላማ ፣ ኩባንያው ምን እየጣረ እንደሆነ እና ምን ማግኘት እንደሚፈልግ ይገልጻል
፡፡
 ለውጡን እውን ለማድረግ ጉልበትና ፍላጎት ይፈጥራል።
 ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን እንዲፈጽሙ ፣ እንዲፀኑ እና የተቻላቸውን ሁሉ እንዲሰጡ
ያነሳሳቸዋል ፡፡
 ራዕይ ዕቅዶችን ለማዘጋጀት፣ ግቦችን እና ዓላማዎች ለማውጣት ፣ ውሳኔዎችን ለመውሰድና
በማንኛውም ፕሮጀክት ላይ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሥራን ለማስተባበር እና ለመገምገም
ተግባራዊ መመሪያ ነው ፡፡
https://ethiopianchamber.com/
89
ECCSA
ሐ) የራዕይ መግለጫ እንዴት ይጽፋሉ / ያዳብራሉ /Write/Develop a Vision
Statement?

 ራዕይ መግለጫ ኩባንያዎን ይገልጹበታል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የወደፊቱን ፣


ያሳዩበታል ፡፡
 በመጀመሪያ ድርጅቱ ምን መሆን እና ማድረግ እንደሚፈልግ ራዕይን ማዳበር አለብዎት ፡፡
 ያንን ራዕይ ካዩ በሁዋላ ራዕይ እንዴት እንደሚያሳኩ የሚገልጽ ስትራቴጂ ወይም ሰፊ እቅድ
ማዘጋጀት ይችላሉ ፡፡
https://ethiopianchamber.com/
90
ECCSA

ደንበኞች ራዕይ መግለጫቸውን ለመለየት ይችሉ ዘንድ የሚጠቅሙ ጥያቄዎች፡-


 የእኔ የምርት ስም በማህበረሰቤ ፣ በኢንዱስትሪዎ ወይም በዓለም ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ
እንዲኖረው እፈልጋለሁ?
 የእኔ ምርት (brand) በመጨረሻ ከደንበኞች እና አጋሮች ር በምን መልኩ ይሠራል?
 የንግድ ሥራዬ ባህል ምን ይመስላል ፣ በሠራተኞች ሕይወት ውስጥስ እንዴት ተጽዕኖ
ይፈጥራል?

እነዚህን ጥያቄዎች ከመለሱ በኋላ በአሁን እና በወደፊትዎ መካከል የመንገድ ካርታ


(roadmap) ፈጥረዋል ማለት ነው…

https://ethiopianchamber.com/
91
ECCSA

የድርጅትዎን ልዩነት የሚያንፀባርቅ የራዕይ መግለጫ ሲቀርፅ ምን መደረግ አለበት-(አጭር


መግለጫ)
 ለወደፊት ከ 5 እስከ 10 ዓመታት ፕሮጀክት ያድርጉ

 የአሁኑን ጊዜ (present tense) ይጠቀሙ ፡፡


 ግልጽ ፣ እጥር ምጥን ያለ ፣ ከጃርጎን-ነፃ ቋንቋ ይጠቀሙ።
 በስሜት የተሞላ በፍላጎት የታጀበ እና ቀስቃሽ ያድርጉት።
 ከንግድ እሴቶችዎ እና ግቦችዎ ጋር ያስተካክሉ።
 ተፎካካሪዎትን ዋቢ ያድርጉ ወይም ተመሳሳይነት ይፍጠሩ።
 የእርስዎን ራዕይ መግለጫ ለሠራተኞችዎ ለማሳወቅ ዕቅድ ይፍጠሩ።
 ለሚመሠርቱት ራዕይ ጊዜና ሀብትን ለመስጠት ያዘጋጁ ፡፡
https://ethiopianchamber.com/
92
ECCSA
ራዕይዎን ማን ይቀርጻል?
ራዕይ መግለጫ ለመጻፍ የመጀመሪያው እርምጃ -
 እሱን በመቅረጽ ሚና የሚጫወተው ማን ነው?
Ö በትንሽ ንግድ ውስጥ የእያንዳንዱን የድርጅት አባል ግንዛቤ ለመሰብሰብ ቀላል ነው ፡
Ö በትላልቅ ንግድ /ክዋኔዎች ውስጥ የሰራተኛ ድምፆችን መያዙን በሚያረጋግጡበት ጊዜ የበለጠ ተመራጭ
መሆን ሊኖርብዎት ይችላል ፡፡
ይህንን ለማሳካት የድርጅታችሁን ክፍል ከሚወክሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይ አውደ
ጥናቶችን ማስተናገድ ይመከራል ፡፡
https://ethiopianchamber.com/
93
ECCSA

 ተለዋጭ የአረፍተ ነገሩን ስሪቶች ለመፍጠር ቡድኖችን መሰብሰብ እና ከቀሪው ኩባንያ


ግብረመልስ መቀበል ይችላሉ ፡፡
አንድ ድርጅት በሠራተኞች ተሳትፎ አማካይነት ዓላማውን ፣ ዋና እሴቶቹን እና የወደፊቱን ራዕይ
በመለየት በጋራ ዓላማዎች እና እሴቶች ላይ በመመርኮዝ አማራጮቹን እና ዕድሎቹን ይገመግማል
፡፡

https://ethiopianchamber.com/
94
ECCSA
መ) የእርስዎን ራዕይ መግለጫ እንዴት ይጠቀሙበታል?
የሚከተሉትን ይወስኑ!
 የ ራዕይ መግለጫዎ የት እንደሚታይ!
 በድርጅትዎ ውስጥ ምን ሚና እንደሚጫወት!
(በእውነቱ ከኩባንያው ባህል ጋር ካልተዋሃደ በአዳራሹ ውስጥ የራዕይ መግለጫ መስቀሉ ወይም
በማኅበራዊ አውታረ መረቦች ላይ ማስተዋወቅ ፋይዳ የለውም)

ሰራተኞችዎ ራዕዩን የማይገዙ ከሆነ በጭራሽ በሰራ ላይ ማከናወን አይችሉም ፡፡ “የራዕይ መግለጫው
ሰራተኞችዎ የሚያምኑበት መሆን አለበት ፡፡ ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ውሳኔዎችን የሚወስዱ እና
የንግድዎን ራዕይ የሚያንፀባርቁ እርምጃዎችን የሚወስዱት ፡፡
https://ethiopianchamber.com/
95
ECCSA

ሰራተኞችን የራዕዩን ባለቤትነት እንዲወስዱ የሚረዳበት አንዱ መንገድ የድርጅት ወርክሾፖችን እና


የአእምሮ ማጎልበት ስብሰባዎችን ማካሄድ ነው ፡

በእነዚህ ስብሰባዎች ውስጥ ሰራተኞች የራዕዩን መግለጫ እሴቶችን በዕለት ተዕለት ሥራዎቻቸው
ውስጥ ማካተት የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲለዩ ያበረታቱ ፡፡

ከዚያ በኋላ ሰራተኞችን ራእዩን ሲይዙ እውቅና መስጠት እና ሽልማት መስጠት ይችላሉ ፡፡

https://ethiopianchamber.com/
96
ECCSA
የማነቃቂያ ራዕይ መግለጫዎች ምሳሌዎች
አንዳንድ የማይረሱ እና የተለዩ የራዕይ መግለጫዎችን መፈተሽ የራስዎን ለመጻፍ ለሚፈልጉት
መነሻዎች ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ በጣም ጥቂቶቹ፡-

AMAZON - ደንበኞች በመስመር ላይ ለመግዛት የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር የሚያገኙበት እና


የሚያገኙበት የምድር በጣም ደንበኛ-ተኮር ኩባንያ ለመሆን ፡፡

Caterpillar: ራዕያችን እንደ መጠለያ ፣ ንፁህ ውሃ ፣ ንፅህና ፣ ምግብ እና አስተማማኝ ኃይል


ያሉ ሁሉም ሰዎች መሰረታዊ ፍላጎቶች በአከባቢ ዘላቂነት የሚከናወኑበት እና እኛ የአከባቢን እና
የህብረተሰቡን ጥራት የሚያሻሽል ኩባንያ ነው ፡፡ ኑርና ሥራ ፡፡

https://ethiopianchamber.com/
97
ECCSA
 Google: በአንድ ጠቅታ የዓለም መረጃን ተደራሽነት ለማቅረብ ፡፡
 Hilton Hotels & Resorts: ምድርን በእንግዳ ተቀባይነት እና ሙቀት ለመሙላት ፡፡
 Oxfam: ድህነት የሌለበት ዓለም ፡፡
 Samsung: ዓለምን ያነሳሱ ፣ የወደፊቱን ይፍጠሩ ፡፡
 McDonald's: ምርጥ ፈጣን የምግብ ቤት አገልግሎት ተሞክሮን ማሳየት፡፡
 EAL: ደህንነቱ በተጠበቀ ፣ በገበያ ላይ የተመሠረተ እና በደንበኞች ላይ ያተኮረ ተሳፋሪ እና የጭነት ትራንስፖርት በማቅረብ
በአፍሪካ ውስጥ በጣም ተወዳዳሪ እና መሪ የአቪዬሽን ቡድን ለመሆን ...

98
¥ጠቃለያ ECCSA

Yÿ SLጠና ድርጅትን ዉጤታማ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነጥቦች


የተካተቱበት በመሆኑ ተበዳሪዎች ብድር ከማግኘታቸዉ በፊት ስልጠናዉን መዉሰድ
ይኖርባቸዋል፡፡

ስልጠናዉም ተበዳሪዎች ዉጤታማ ሆነዉ ብድራቸዉን በተገቢዉ ሁኔታ መክፈል


እንዲችሉ ያግዛቸዋል፡፡

https://ethiopianchamber.com/
99

You might also like