You are on page 1of 2

3.4.

5 የግብር ከፋይ ስምምነት ሠነድ (Taxpayer


Charter) አስፈላጊነት
አንድ በሥጋት መስፈርት ለኦዲት ተግባር የተመረጠ ግብር ከፋይ ስለ ኦዲቱ
ዓላማና አሰፈላጊነት በሚገባ በመረዳት በንግድ ሥራው እንቅስቃሴ ዙሪያ
ያለውን ሁኔታ ከኦዲተሮች ጋር በግልጽ ለመወያየትና ኦዲተሮችም
የመጡበትን ዋንኛ ዓላማ በግልጽ አሰረድተው በግብር ከፋዩ እና
በባልስልጣን መ/ቤቱ መካከል ግልጽ የሆነ መግባባት እንዲፈጠር
ለማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም የግብር ከፋይ የስምምነት ሠነድ
ከሚያካትታቸው ነጥቦች መካከል፡-
1. የግብር ባለሥልጣኑን ኃላፊነትና ግዴታ፤
2. የግብር ባለሥልጣኑን መ/ቤት መብት፤
3. የኦዲተሮችን ተጠያቂንት፤
4. ግብር ከፋዩ ለኦዲት ተግባር አስፈላጊ የሆኑ ሠነዶች ለኦዲት ምርመራ
በማቅረብ የማስረዳት መብትና ኃለፊነት እንዳለው ለማስገንዘብ፤
5. የኦዲት ተግባሩ ግልጽና ግብር ከፋዩም በሚገባ የተገነዘበውና ያመነበት
እንዲሆን ለማስቻል፤
6. ግብር ከፋዩ በኦዲት ተግባሩ ጥያቄ ከለው የመጠየቅና አስታየት መስጠት
መብት እንዳለው ለማሰገንዘብ፤
7. ከኦዲት ፍፃሜ በኋላ በተገኘው የግብር እና ታክስ ዕዳ የግብር ባለሥልጣኑን
ያማስከፈል መብትን እና የግብር ከፋዩን የመክፈል ግዴታ ግልጽ ለማድረግ
ሲሆን
በአጠቃለይ በግብር ከፋዩና በባለሥልጣን መ/ቤቱ መካከል ሊኖር የሚገባውን
ግንኙነት ጤናማና በመተማመን ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ለማድረግ
የሚያስችል በመሆኑ ይህ የግብር ከፋይ ቻርተር ሠነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ
ይሆናል፡፡ ስለሆነም የስምምነት ሰነዱን የኦዲት ተግባሩ ከመጀመሩ በፊት
ከግብር ከፋዩ ጋር በመወያያት መፈረም ይኖርበታል፡፡

You might also like