You are on page 1of 3

ረመዷን

ለአመት ስንመኝህ …. ለአንድ ወር ስንፆምህ

እኛ ሙስሊሞችን …. መስጊድ አስገብተህ

ገሀነም ተዘግቶ …. ገነት ተከፍቶብህ

ወስዋስን አራግፈህ …. ሸይጧን ታስሮብህ

ተራቡ ተጠሙ …. ጹሙኝ ትለናለህ

የአሏህን እዝነት …. ከፊትለፊት ታጥቀህ

የጀሊሉን ምህረት …. በጉያህ ሽጉጠህ

የቅጣቱን ነጃ …. ከኋላህ ደብቀህ፤

ረመዷን

ይቅር አባብለህ …. ጎሚ የያዘዉን

ረገብ አድርገህ …. ገንፋይ ተቆጭዉን

መለያህ አድርገህ …. ማካፈል ምፅዋቱን

ምንም ሳታስቸግር …. አራስ በሽተኛን

አፍታ አንሠለችህም …. ደጋግመህ ጎብኘን

ቅንጣት ቅር አይለንም …. አንተ ብታስጠማን

ሸህዋችን ሲደክም …. ሀሴት ነው ራባችን

ግና አስለቀስከን …. በጣሙን ተከፋን

መሆኑን ስናዉቀዉ ….. ልትሄድ ጥለኸን

መልሠህ ልሰጠን ….. ለዚያ ለስጋችን

ደግመህ ልትተወን …. ለዚያ ለሸህዋቺን

ረመዷን … እኔስ ተጠራጠርኩ …. አንድ ወር መሆንህን

በጣም እየጣፈጥክ፣ ምኑንም ሳልጥግብህ፣ ጥልኸን ልትሄድ ነዉ …. ሆነው አንድ ሠሞን፣


ረመዷን

ለወራቶች ቅናት …. አንድ ዋልታ ለኢስላም

አርግዘህ ቀናቶች …. የአሏህን ሠላም

ሙስሊሙን ስታደርግ …. የአኺራ ሀብታም

ደመወዝህ ብዙ …. ቁጥር አይገልፀዉም

ከጀሊሉ በቅር …. ማንም አይለካኽም

መጭ አመት ስትመጣ …. ሊፁምህ በሀረም

ልጠማህ በመካ …. ልራብህ በሀረም

እንዲያምርልኝ በአሏህ ….. ዱኒያም አኼራዬም

ረመዷን

ስጋዬ ሲከሳ …. ነብሴ ስትወፍር

ተራዊህ ስሰግድ …. በመስጊድ በህብር

ሳጠራዉ አሏህን …. ሳልቀዉ በክብር

ቁርዓን ስቀራ …. በተጅዊድ በተክሪር

ነብዩን ሳነሳ …. ከሀዲስ ማህደር

ሲዋክ እጄ ገብቶ …. ጥርሴም ለሳቅ ሲያምር

ድንገት አለክብኝ …. አንተ የበረካ ወር

ማክተሚያህ ሆነብኝ …. ኢደል- የውመል- ፊጥር

ዝም ብዬ አልቸኝህም …. ጌታዬን ላክብር

ደግሜ ደግሜ ….. ልበል አሏሁ አክበር

ደግሜ ደግሜ ….. ልበል አሏሁ አክበር

አሏሁ አክበር፣ አሏሁ አክበር፣ አሏሁ አክበር!!!!!!!፤

ቀለበት አደም - ዋሽንግተን ዲሲ - ረመዷን 28፣ 1431 / ጷጉሜ፣ 2002

You might also like