You are on page 1of 15

የደም አክሊል

ትዕይንት፩
ሶስት ህጻናት ከመጋረጃ ውጭ ሻማ እየለኮሱ ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም
ስለእግዚአብሔር አፈሰሱ ፣ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ (2) ከመጋረጃ ውስጥ በወንድ ድምጽ

‹‹ 8ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንበሳውድም ሽንፈት ገጥሟቸው ከሀገር ሸሹት ህዝበ ………………….. ስለ ተስፋ ቃሉ ፣ ስለ
እውነታችው ተሰደዱ ፣ ስለ ስሙ ትሰደዳላችሁ የተባለው ተፈጸመ ፣ ሁሉንም ጥለው መከራን ይታገሱ ፣ በንግስት ዮዲት ጦር
በመጋዝ ተሰንጥቀው ፣ በሰይፍ ተመትረው ፣ ተዘንትረው ፣ በስጋ መጥበሻ ተጥለው ፣ በእሳት ተቃጥለው እርሱን ብለው
……………………………………. ተዘንትሮ ፣ ህጻናት የእናታቸውን በድን ጡት የሙጥኝ እንዳሉ ተጨፈጨፉ ፡፡ ህዝበ ክርስቲያን
እረኛቸውን ተከትለው ስለ እርሱ ሞቱ ፡፡ ተሰየፉ ፣ ገዳማት ፈራረሱ ፣ የዘጉ አባቶች በግፍ የሰማዕትነት አክሊል ኑ . . . ቅመሱ
እያለች ቤተክርስቲያን ደውሏን ደግማ ደጋግማ ደወለች ፡፡

. . . . . ደወል ተደጋግሞ ይደወላል . . . መጋረጃው ሲከፈት ንግስት ዮዲት ከክብር ዙፋኗ ተቀምጣ መርዕድ በቀኝ ለገሱ
በግራ ሰይፍ ይዘው ይቆማሉ ፡፡ ደምስ በር ላይ ጦርና ጋሻ ይዞ ይቆማል ፡፡ ከንግስት ዮዲት ጎን ካባ እና ጎራዴ ተቀምጦ ይታያል ፡፡

ዮዲት ፡ (በቁጣ) ይህ ወንበር የሙሴን ህግ ያስከብራል ፣ ከእንግዲህ የንግስትን ወዳጅነት የማይሹትን ሁሉ ቁልቁል
ዘቅዝቃችሁ በመስቀል ፣ ቆዳቸውን በመግፈፍ አሰቃዩአቸው (ከጎን ያለውን ጎራዴና ካባ ለመርዕድ
እየሰጠችው)እንካ ቀኝ እጄን ተጠቀምባት ፡፡

መርዕድ ፡ ንግስት እነዚህን ሐሳዊ ክርስቲያኖች ለማጥፋት እና የሙሴን ህግ ለማስከበር ፣ ስርዓተ ኦሪቱን ለማስፋፋት
ቆርጬ መነሳቴን ይወቅልኝ ፡፡

ለገሰ ፡- እንግዲህ ንግስት ይህን ሥራ ስሩ ካሉን እንደ ካታኮምቦች ክርስቲያኖች . . . . . . . . . ከአውሬ ጋር ማታጋያ
ትርዒት አዘጋጅተን እነዚያን ክርስቲያኖች እየያዝን ከአውሬ ጋር በማታገል እንደሰት ፡፡ ስጋቸውን እየቀረደዱ ፣
ሙዳ ሙዳውን እየበጨቁ ጎመድ ጎመድ እያደረጉ ሲበሏቸው ለህዝቡ በማሳየት በትርኢቱ እየተዝናናን
ብንቀጣቸው ጥሩ ይመስለኛል፡፡

መርዕድ ፡ አዎ ንግስት ጥሩ ብልጠት ነው ይዘጋጅና እንደሰት ፡፡

ዮዲት ፡ እንግዲህ ጥሩ ፡፡ የጎራዴያችሁን ስለት ፈትኑት ፣ ጩቤያችሁን የክርስቲያንን ገላ በመተልተል እዩት ከደነዘ
ሳሉት ፡፡ እንዳላችሁት እሳቱም ሰይፉም ጉድጓዱም በፍጥነት ይዘጋጅና በሞታቸው እንሳቅ ፡፡ በእልቂታቸው
እንደሰት ፡፡ በሉ እንግዲህ እናንተም ወደ ክርስቲያን አደናችሁ እኔም ወደ እልፍኜ ፡፡

መርዕድ ፡ አተ . . . . ተ. . . . ተ. . . ተ. . . ተ. . . ዘራፍ ! ዘራፍ !

የንግስትን እምነት ማነው የሚነካው

አንበሳው መርዕድ መኖሩን ዘነጋው

ይቀላ አንገቱ ይመተር ይቀላ

ተገፎ ይተልተል የክርስቲያን ገላ

ፎክር ፎክር አለኝ ወኔዬ ተነስቶ

የአይሁድን ጠላት ጭንቅላቱን ሽቶ

ዘራፍ ዘራፍ ልበል ጠላትን ለመምታት

ጎራዴዬን ልሳል ወሬን ለሰብቃት

ለክርስቲያን ሁሉ ወዮለት ወዮለት


. . . . . . . የንግስት አሽከር መርዕድ . . . . . .

መርዕድ እና ለገሰ ወጥተው ሄደው አንዱን መነኩሴ እያሯሯጡት ይታያል ፡፡ መነኩሴው ብዙ መጽሐፍትን ይዞ ይታያል ፡፡

መነኩሴው ፡ አታገኟትም ! አዎ አታገኟትም ፡፡ ነፍሴን ከስጋዬ ለይታችሁ ያን ጊዜ ትወስዷታላችሁ ፡፡ እናንተ ከሀዲዎች


መስሏችሁ እኮ ነው ቤተ ክርስቲያንን ልታጠፉ የምትታገሉት . . . . ግን ተምሳሌቷ የኖህ መርከብ የሆነች
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አትጠፋም ! አዎ ቤተ ክርስቲያን አትጠፋም (ተንበርክኮ ወደ ሰማይ በማቅናት)
ምነው ፈጣሪዬ እውነት ልንጠፋ ነው ? ወይንስ ወርቅ በእሳት እንዲፈተን ልንፈተን ይሆን ? ምነው ደግነት
የተሞላበት ሕይወትህን ቢመለከቱ? ሲያሳድዱህ ፣ ሲያንገላቱህ ፣ አንተ እነርሱን ለማግኘት በማይገባህ ጎዳና

መጓዝህን አይነልቦናቸውን ብትከፍትና ቢያዩ ምናለ ? እረ አንተነትህን አሳያቸው ! ማንነትህን ግለጽላቸው ፡፡


(ከተምበረከኩበት በመነሳት መጽሐፍቱን ከክንዳቸው ላይ አትኩረው እየተመለከቱ) እውን አባቶቻችን
ቅዱሳን እንዳለፉብህ ልጠፋ ይሆን ? እውን የኢትዮጵያ እጅ ይታጠፍ ይሆን ? እውን ይቺ ፀሃይ የሆነች
ተዋህዶን ለመሰወር እኛ ከተገደልን በኋላ ፡፡ አሁን እነኚህን መጻሕፍቶች በየዋሻው ከሚቃጠሉ ልሰውራቸው
የእውነት አምላክ የፈቀደ ጊዜ ይግለጠው ፡፡ ዘመን ያውጣው ትውልድ ያግኘው ከእንግዲህ ማን ቁጭ ብሎ
ይጽፈዋል ? አባቶች በደማቸው አቆይተው ለኔ አስረክበዋል ፡፡ አሁን ደሞ በኔና በህዝበ ክርስቲያን ደም
ተጠብቆ የሚቆይ ከሆነ ለምን ራሴን አሳልፌ ለውርሴ አልሰጥለትም ? ያውላቸው ስጋዬ ያሻቸውን ያድርጉት
፡፡ የቅዱስ ያሬድን የሕይወት አደራ ተሸክሜ ከምጠፋ ለጊዜው ልሰውረው (ወደ ህዝቡ ዞሮ) ልጄ ውርሴን
በደሜ አትቤ ልሰውርልህ ነው ይህንን ሕብስት የሆነ ቃል አውጥህ ብላ አባቶችህ ሞተው ያወረሱህን ሞተህ
ለልጅ ልጅህ አውርስ ፡፡

ልጄ ! የሚበጀህ ስለሆነ ነው በዚህ የሞት አደራ የፈተነኩህ ልጄ ውርስህን ብትይዘው ያበራልሃል ፡፡


ብትለቀው ግን ሕይወትህ ይጨልምብሃል ፡፡

መርዕድ እና ለገሰ ፡ (በመጋረጃ ውስጥ ) ፡ ያዘው . . . ያዘው . . . ያውና ከዚያ ላይ . . . እለፈውና ከፊቱ ቁም

መኩሴው ፡ መጡ . . . መጡ እነዚህ አረመኔ እምነት በላዎች እምነቴን ሊወስዷት መጡ ፡፡ ልጄ ውርሴን ሊያጠፉ መጡ


(መጽሐፉን ይደብቃሉ) እንግዲህ ልጄ ሰውሬልሃለው አውጥቶ መብላቱን እወቅበት ብትተወው
ትሞታለህና ፡፡ ልጄ ውርሴ ለዝንት ዓለም እንዲያበራ አውጥተህ ብላው ፡፡ አበላሉ ጠፍቶብህ እንዳትሳሳት ፡፡
ያው . . . . . . . . . ስለ አበላሉ አባቶችን ጠይቅ ይነግሩሃል፤ ሽማግሌዎችን ጠይቅ ያስተምሩሃል ሽማግሌ
ካንደበቱ ውሸት አይወጣምና ልጄ አደራ ! አደራ ! (መነኩሴው በመርዕድ እና ለገሰ እጅ ተይዘው ይሄዳሉ )
፡፡

ትዕይንት ፪
መጋረጃ ሲከፈት ዕዝራ በዋሻው ውስጥ እንደተኛ ሆኖ እያለ ያባቱና የልጁ ድምጽ በግብአተ ድምጽ ይደመጣል ፡፡

ህጻን ልጅ ፡ አባ . . . አባዬ . . . አይ አድነኝ

ሽማግሌው ፡ / ጎላ ባለ የስቃይ ድምጽ / እ. . . . ህ. . . . ጌታ አፍርሶ በሶስት ቀን የሰራት ቤት አሁንም አትፈርስም ፡፡ እ. . .


ህ. . . አባቴ የሰጠኝን ሳልለቅ . . . ሲ. . . . . . ለልጄ የተፈተነች እምነትን የደም አክሊልን አወርሳለው ፡፡ እ. .
. እ. . .ልጄ . . . እንካ . . . እንካ . . . እንካ ዳዊቴን ድገመው እንካ ያሬድን ዘምረው . . . እንካ እውነትን
አጥብቅ ል. . . ጄ . . .እውነቴን እንደሰጠሁክ በሰማይ እጠይቅሃለው . . . ልጄ አደራ አደራ ! / ቀይ መብራት
ይጠፋል /

ዕዝራ ፡ አባን ፣ እማን ፣ ማሙሽን ፣ ባለቤቴን ፣ እኔንስ ለማን ? መጡ . . . መጡላችሁ ግፈኞች መጡላችሁ ፡፡ እኔማ
እብድ ነኝ ፡፡ እብድን ሰው ማን ይገለዋል ? ግን እናንተ በዋሻ ፣ በዱር በምድረበዳ ያላችሁ ሁሉ ከእውነት
ሊያፈናቅሏችሁ መጡ ፡፡ እውነትን ሊያሳድዷችሁ መጡላችሁ ፡፡ አንቺ ጀምበር ጠልቀሽ እርጂኝ ፡፡ በቀን
ብርሃንሽ ከምታጋልጭኝ በለሊት በዳፍንት ያዙኝ እያልኩ እንቅልፌን ልጣ ፡፡ ወገን እንዳባትህ ቆዳህን
እንገፍሃለን እያሉኮ አስፈራሩኝ ፡፡ አባቴ ቆዳው ተገፎ መሞቱ በዓይነ ሕሊናዬ እየተመላለሰ ፣ ሲታረድ ያየሁት
አንገቱ ከዓይኔ ሳይጠፋ እንገድልሃለን ይሉኛል ፡፡
አቤት ጭካኔ ! በተገደለ ፣ በተገፈፈ ቆዳው ላይ ሎሚ ጨመቁበት ፡፡ ለኔ መከታ የሆነ ክንዱን ጠፍንገው
በእንግርግሪት አስረው በሰይፍ ቀረደዱት፡፡

ሽማግሌው ፡- / በግብዓተ ድምጽ / ልጄ እንካ ዳዊቴን ድገመው ፣ እንካ ድጓውን ዘምረው ፣ እንካ ውርሴን ጠብቀው

ዕዝራ ፡ እንካ ድጓውን ! አለኝ ራሱን በሰይፍ መካከል አሳልፎ ፡፡ ይሁን እኔስ እስካሁን ተቀብዬ አቆየሁት ፡፡
ከእንግዲህ እኔ እብድ ስባል ወይንም ደግሞ እንደ አባቴ የሞት ጽዋን ስቀምስ ለማን ነው የማስረክበው ?
እንጃለት ለውርሱ ! ማን ነው እንደ አባባ ውርሴን አልለቅም በማለት ቆዳውን የሚገፈፍ ? ማን ናት እንደ
እማማ እምነትን ለመጠበቅ ጡቷን የምትቆረጥ ? የትኛው ልጅ ነው እንደ ማሙሽ አያቱን የሚከተል ? እስኪ
ንገሩኝ ? ለኛ አይደለም የዚያ ሰው ሁሉ ሞቱ ? ለውርሱ አይደለም ስደቱ ? አቤት ! ነጋልኝ ፡፡ አይሁድ
ከሃዲዎች ድጓውን ሊወስዱብኝ ? ማሙሽ . . . ማሙሽ ያ ቅብዝብዝ የንግስት አሽከር የመጣ እንደሆን
አልሰጥም ውርሴን በለው ፡፡ አልለቅም ውርሴን በለው ፡፡ አባቴ ሞቶበታል ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው
በለው ! አ. . .ሁ. . . ለካስ ማሙሽ ሞተሃል ፡፡ አየህ ልጄ ! አንተ ሞተህ አሳበድከኝ ? አዬ ልጄ ! / ቤቴል
መጥታ ትቆማለች / . . . ቤቴልዬ . . . እንዳያልሙብሽ ፣ እንደማሙሽ ትሞችብኛለሽ ፣ ቤቴልዬ ማሙሽ
ጥሎኝ ሄደ ! ግን አባም ፣ እማም ፣ ማሙሽም ፣ ባለቤቴም ይህን ዋጋ ጥለውልኝ አለፉ ፡፡

ቤቴል ፡ ወንድም ጋሼ ተው እባክህ ፡፡ እነሱን እያሰብክ ጨለማን ስትሸሽ ብርሃንን እንዳትለቅ

ዕዝራ ፡ ተው አልሽኝ ቤቴልዬ ? አይሁድ በጦር እና በጎራዴ ሲያስጨንቁን ፣ የነ አባባን አደራ የያሬድን ውርስ ስጦታ
አምጡ ሲሉን ፣ ሲያንገላቱን ምኑን ልተወው ? ቤቴልዬ ሊወስዱብን እያነፈነፉብን ነውና እንደብቀው ፡፡
ቤቴል ያን ለገንዘብ ሲል ራሱን ባንዳ ያደረገውን የዮዲትን አሽከር ለገሰን ያባቶቻችን ውርስ ነው አይበላም
በይው ፡፡ መስሯቿ ክርስቶስ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን አትጠፋም በይው ፡፡

ቤቴል ፡ ወንድም ጋሼ አይዞህ የአባባ ውርስ እኛ እያለን አይጠፋም ! ይልቅ ያረፉትን ዋኖች እያሰብክ በጭንቀት
ሕሊናህን አትወጥረው ፡፡ እነርሱ እኮ የእውነትን መንገድ አልለቀቁም ፡፡ ማዘንስ እውነትን ረግጠው በሐሰት
ለሚጠፉት ወገኖቻችን ነው ፡፡ ወንድም ጋሼ ይልቅ እነ አባባን ስለ እውነት ብለን እንከተላቸው ፡፡
በሕይወታችን እንምሰላቸው ደግሞም የቀረኸኝ አንተ ብቻ ስለሆንክ መስራት የሚገባንን ሳንሰራ ብትለየኝ
ሀዘኔ እጥፍ ይሆናል ፡፡

ዕዝራ ፡ አዎ የቀረሁሽ እኔ ነኝ ፡፡ ሌላው ቀሪሽ ደግሞ ውርሱ ነው ፡፡ ጠራኝ የጊዮርጊስ መንፈስ ፣ ጠራኝ የያሬድ
መንፈስ ፣ ቤቴል . . . ይጠራኛል ማሙሽ ና ይለኛል ልጄ ናፈቀኝ ማሙሽ አባትህ ና ይልሃል እብድ አባትህ
ይጠራሃል ፡፡ ልጄ ወ/ቂርቆስ ናልኝ ልጄ ና . . . የአባትህን ውርስ እንካ ልጄ ተቀበለኝ ፡፡ አቤት ! ብቻዬን
አስቀሩኝ ? ባለቤቴ ሆዷ ውስጥ እስካለው ሽል እቶን ውስጥ ተጣለች ፡፡ ማሙሽ ለጋ ሰውነቱ ለአንበሶች
ተሰጠ ፡፡

ቤቴል ፡ እማ ጥሪኝ ፡ እማ ሞትሽ ሞቴ ሊሆን ብርሃንሽ ሊያበራልኝ ይጠራኛል ስለ እውነት ስደትሽን ልቀበል ጥሪሽ
ይሰማኛል እማ የከሃዲዎች ሰይፍ በአንገቴ ቢዘረጋ ከአባቶቼ መንገድ ላልወጣ ከእውነት መንገድ ወደ ኋላ
ላልል አንቺ የቀመስሽውን የሞት ጽዋ ልቀምስ ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር!!!! ቅዱሳን አባቶች ለሰማዕትነት
ተሹማችሁ በደማችሁ የሕይወት ታሪክን ጻፋችሁ ፡፡ የድል አክሊልን አገኛችሁ ፡ አባቶች እኔም እንደናንተ
የአላውያንን የግፍ ስቃይ በመፍራት ከመንገዳችሁ ላልወጣ ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር . . . አባ ! አባዬ ?
ያሬድ አስታውሺ አትርሺ ስርዓትን እንዳትጥሺ ማለትህን አልዘነጋም ፡፡ ግን እግዚአብሔር እንደጠበቀህ
እንዲጠብቀኝ ፣ ድል ማድረግን እንዲሰጠኝ ለኔ ለደካማዋ ልጅህ ለምንልኝ ፡፡ አባ አሰረ ፍኖትህን ልከተል
አንተ ከሄድክበት ከእውነት መንግድ ፈቀቅ ላልል ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር ፡፡

ትዕይንት ፫
መጋረጃው ሲከፈት መነኩሴው በእስር ቤት ሆነው እጃቸው የኋሊት እግራቸው በሰንሰለት ታስረው ቁጭ ብለው ይታያሉ ፡፡

መነኩሴው ፡ እውነትም አልኩ ጠፈነጉኝ ወይ ነገር ! ወይ የኔ ነገር ! ላውርስ በልኩስ ስቃይ ይሁን እጣዬ ይሁና ግድ የለም
በደሜ መፍሰስ የክብርን አክሊል እቀዳጃለው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ! ቅዱስ ጴጥሮስ ! ቅዱስ እስጢፎኖስ !
እግዚአብሔር በዚች በትንሽ ስራዬ የእናንተን የደም አክሊል ሊያድለኝ ነው ! የኔ ሞት የክብር ሞት ነው
ውርስን እንደጠበቁ መሞት በእግዚአብሔር ፊት ክብርን የሚያሰጥ ታላቅ እረፍት ነው ፡፡ የሞት ሞት ውርስን
መተው ነው ፡፡ በራስ መንገድ መሄድ ግን የሞት ሞት ውዳቂ ሞት ነው ፡፡ ልጆቼ ! ይህን ሞት ሽሹት የሞትን
ድል መንሻ ትዕግስት ፣ ጽናት ፣ ምግባር ፣ ርትዕት የሆነች ተዋህዶ እምነታችሁን ያዙ ፡፡
ዮዲት ፡ ጅልነት ነው ለመሆኑ ጊዜው ሳይደርስ መሲሁ ተወለደ እያላችሁ አይሁድን በእምነታቸው እንዲወድቁ
የምታደርጉ እናንተ እነማንናችሁ ? እረ ከሌላው የተለየ ይህ ሚስጢር የተገለጸላችሁ እናንተ እነማን ናችሁ ?

መነኩሴው ፡ እኛማ በእውነት መሰረት ላይ የታነጽን ርትዕት የሆነች ተዋህዶን ያመንን የሥላሴ የእጅ ሥራዎች ለመመረጥ
የበቃን እድለኞች ነን ፡፡

መርዕድ ፡ ዝምበል ደግሞ መልስ ይሰጣል ዘልዛላ

ዮዲት ፡ ተው ቆይ እስኪ ይልቅ የእብደት ተግባርህን ትተህ የሰወርካቸውን ዕቃዎች መጽሐፍቶች ብታሳየን ይሻላል ፡፡
አላሳይም የምትል ከሆነ ግን ያለ ጊዜህ በሞት ትቀጣለህ ፡፡

መነኩሴው ፡ እሰየው ! እሰየው ! በከሃዲያን እጅ በሰማዕትነት ማረፍ እሰየው ! ስለ ተስፋ ቃሉ በአላውያን እጅ በሰማዕትነት
ማረፍ እሰየው ! ምን ጊዜም እኮ ወርቅ እና አማኝ በእሳት ነው የሚፈተነው ፡፡ ንግስት ! በስሙ መሰቃየት ፣
ስለ ስሙ መሞት እንዴት ያረካል መሰለሽ . . . ጌታም እኮ በስሜ መከራን ትቀበላላችሁ ብሎናል ፡፡ ስለዚህ
ስለ ስሙ በሰማዕትነት መሞት ሞት ሳይሆን ክብር ነው ፡፡ አውጣ የምትሉኝ ዕቃ እና መጽሐፍት ግን ከአባቴ
በውርስ የተቀበልኩት በመሆኑ እኔም ለልጄ የማስረክበው ነው ፡፡ ስለዚህ ላልሰጣችሁ ባታሰቃዩኝ ጥሩ ነው
፡፡ ልጄ የነፍስ ረሃብተኛ እንዲሆን አልፈልግም ፡፡

ዮዲት ፡ ለየቱ ልጅህ ? ከሰይፋችን ስለት ለሚያመልጠው ? ከእቶን እሳታችን ለሚተርፈው ? አሁን ሌላ ምንም ነገር
አልፈልግም ሞትን ወይም ነጻነትን ምረጥ ?

መነኩሴው ፡ ዓይን እያላችሁ የማታዩ ፣ ጆሮ እያላችሁ የማትሰሙ መሆናችሁን ጌታ በወንጌል አስፍሮታል

ለገሰ ፡ እረ ዝም በል ዝጋ የንግስት ጆሮ አይስማ እባኮን ንግስት ይህን ጥጋበኛ እንደ ዶሮ ብልት ገነጣጥለን ለአንበሶች
ቅርጫ እንጣለው ፡፡ ይዩት እስኪ ልቡ በትዕቢት አብጦ እርሶን እንኳ ንቆ ፡፡

መነኩሴው ፡ ወንድሜ መድህን በመስቀል ሆኖ ደሙን ሲያፈስልህ አንተ ግን ያን ያፈቀረህን መድህን ለመውጋት ጦርህን
ሰበቅህ ፣ ቀስትህን ገተርክ ፣ እሳትን አነደድክ አይደል ? እርሱ ግን አሁን ይፈልግሃል ና ይልሃል ሳውልን
አድርገኝ በለው ሂድና ፈልገው ፡፡

ዮዲት ፡ ውሰደው ስጋውን ለአንበሶች ስጠው ፣ አንበሶች እየቦጫጨቁ ሲቀራመቱት እያየ ወገኔ አይሁድ ይደሰት ፡፡

መነኩሴ ፡ ልጆች በጎቼን አደራ ! ጠቦቶቼን አደራ ! ውርሴን አደራ

ዮዲት ፡ እስኪ አሁን ወደ ሞት የሚያስጋልባቸው እብደት እንጂ እውነት ፍቅር ነው ? ይገርማል ! ይህ የሀሳዊ ፍቅር
እንዴት ልባቸውን ተክቶታል ፡፡

መርዕድ ፡ ምን ዓይነት የእምነት ጥንካሬ ነው ሲዘምቱባቸው ማይዘምቱ ፣ ሲገድሏቸው ለገዳዮቻቸው ይቅርታን


የሚለምኑ ታዲያ እንደዚህ ሆኖ እያየሁ ምን ባደርግ ይሻለኛል ? ለምን ከአሁን በኃላ እዘምትባቸዋለሁ ------
የለም የለም የንግስት ጆሮ አይስማው ------

ግን በገደልኳቸው ጊዜ ሁሉም ሳውልን ሁን እያሉኝ ያልፋሉ ፡ ይህ ሳውል የሚባል ማን ይሆን ? ዳሩ ለመዳን


ጦሬን ወደ አፎቱ መች መለስኩት --------- አቤት ! በየገዳማቱ መቁጠሪያቸውንና ዳዊታቸውን እንደያዙ
ስንቶቹ ረግፈው ቀሩ ? ለባዕድ አንገዛም በማለታቸው ስንቶቹ ቤት ተዘጋባቸው እና በእሳት አረሩ ! አቤት
ብዛታቸው / እጁን ዘርግቶ እያየ / አንተ እጅ የስንት ሰው ነፍስ በመዳፍ ውስጥ ይጮሃል አንድ ቀን ከሰይፍ
ይልቅ እውነትን ትፈልግ ይሆን ?

ለገሰ ፡ ምን እንዳስደሰተኝ ታውቃለህ ?

መርዕድ ፡ ሰይፍ በሚያነሱባቸው ላይ ሰይፍ የማያነሱትን ፣ በቀልን በበቀል የማይመልሱትን ክርስቲያኖች ከአንበሶች ጋር
ማታገል ይሆናላ ያስደሰተህ ፡፡

ለገሰ ፡ ትክክል ነህ የክህደት ዝማሬ በአንበሶች ክርን ጸጥ ሲል ፡ የአይሁድን እምነት አልቀበልም ብላ በእምቢታ
የተንጣጣች ምላስ ጌታ ሆይ ! ይቅር በላቸው ! ብላ ስትዘጋ አንበሶቹ ሙዳ ሙዳ ስጋቸውን እየቦጨቁ
ለንግስት ድልን በማሳየት ጎመድ ጎመድ እያደረጉ ሲቀራመቱ ከማየት ሌላ ምን የሚያስደስት እና የሚያረካ ነገር
አለ ትላለህ ?
መርዕድ ፡ ጌታ ሆይ ይቅር በላቸው አለ አልከኝ ! ምን አይነት ጠላትን ማፍቀር ነው ፡፡

ለገሰ ፡ ቀልደኞች በላቸው ! ይቅር በላቸው ብሎ ነገር ይልቅ ራሳቸው ይቅር ተብለው በምድር ላይ በኖሩ ይሻላቸው
ነበር፡፡ ይልቅ መርዕድ ንግስት እንዳሉህ በደብረ ዳሞና በአቅራቢያው ያሉትን ገዳማት በስለት ጎብኝ
ስልጣንህም ጣራ ላይ ደርሷል መቼም ወዳጅ ሲሾም እንደማየት የሚያስደስት ነገር በዚች ምድር የለም ፡፡ በል
እንግዲህ ወደዚያው ሂድ መቼም በነሱ ዘንድ በትር ማንሳት ፣ መከላከል ብሎ ነገር የለም ፡፡ እንደደረስክ እንደ
ጎመን መቀርደድ ነው ፡፡

መርዕድ ፡ ይሁና እነርሱም ከእምነታቸው ፈቀቅ ላይሉ እኛም ላንራራላቸው ተያይዘናል ፡፡ በል እሺ ቻው ፡፡

ለገሰ ፡ ወደዚያው ልታዘግም ነው ?

መርዕድ ፡ አዎ ወደዚያው መሆኑ ነው

ለገሰ ፡ ቆይ ቆይ እስኪ ከዚህ ቀደም በተደረገው አሰሳ አንዲት ወጣት ክርስቲያን ከእብድ ወንዶች ጋር በተራራው ስር
መኖራቸው ተረጋግጧልና ወደነርሱ ሄደን ብንይዛቸው ምን ይመስልሃል?

መርዕድ፡ እሽ ጥሩ እንሂድ

ትዕይንት ፬
ቤተል፡ / ቁጭ ብላ ወደ ተመልካች እያየች/ አንቺ መሬት የትኛዉ አይነት ነች?ኮረኮንች ወይስ ለም? ነጭ ነቀዝ ደግሞ
በዉስጥሽ ፈልቷል ቢዘራብሽ ታፈሪ ይሆን? የአባቴን ዘር የዠ ነበር ልዘራብሽ ፈለገሁ ግን ግን የአባቴ ዘር
እንክርዳድ የማያበቅል መሬት የሻል፡፡ --- ኦፍ! ባለአደራነት እንዴት የስጨንቃል ያዉም የህይወት አደራ
መጠበቅ ግን እኮ ይህ አደራ ህይወትን የሚሰጥ አደራ ነው፡፡ አለም ፈጥና ታስውባለች፡ ታከስምማለች፡፡
ታበቅላለች ታጠፋለች ነገር ግን የእዉነት አደራ ለመጠበቅ ይችን ዝንጉርጉር አለም ጥሎ መቅበዝበዝ ከድሎት
ወደ ስቃይ መግባት የወደፊት ብርሀንን እያዩና ተስፋ አያደረጉ ፍጥነትን ወደዚያ መጨመር እንዴት
ያረካል(ደወል ይሰማል) አቤት ይሰማኛል የሰማዕታት ጥሪ ሲያስተጋባ አንቺ ጀንበር ንጋት ነሽ ስል ልጠፊብኝ
ነው ገና እኮ አልጠገብኩሽም፡፡ ገና የማወርሰውን የአባቴን ዘር ማስቀመጫ ሳላዘጋጅ ተዋህዶ በሰማዕታት ደም
ፈንጥቃ ስታበቃ ሁሉም ሳይመገባት ልታጨልምብኝ ነው፡ ላይ ይሁን

ለገሰ፡ እስኪ ተመልከት በሓሳዊ ፍቅር ጭንቅላቷ ነውልሎ ሀብትን መተው እንደ አውሬ እየተቅበዘበዙ ዱር ለዱር
መኖር ደግሞ እኮ የሚገርምህ የዚያ የቱጃር ከበርቴ ልጅ ነች እኮ!

መርዕድ፡ የየቱ? የአገር ገዢው ልጅ ነች እንዳትለኝ?

ለገሰ፡ ታዲያስ በባለፈው አሰሳ የንግስት ወዳጅ አልሆንም አርፌ የያዝኩትን እየገዛሁ አልኖርም በማለት ከሀብት
ድህነትን፣ ከከተማ ዋሻን በመምረጥ በአይሁድ እምነት አላምንም ስል በሀሳዊ ፍቅር ጭንቅላቱ ነውልሎ
ስያስቸግር የተገደልዉ እኮ ነው፡፡

መርዕድ፡ ወይዳ የዚህ ሰው ነፍስም ለካ በመዳፌ ውስጥ ትጭሐልች፡፤

ለገሰ፡ እሽ የኛ መናኝ ይነሱአ /…… ተነሽ እንጅ/ አንቺን እኮ ነው! ስሚ አንድ ምርጫሽን እፈልጋለሁ እሳትን ወይም
የንግስት እምነትን፡፡

መርዕድ፡ እህቴ የንግስትን ወዳጅነት ንቀሽ ገና ባልተወለደው ተስፋ ባታደርጊ ጥሩ ነው፡፡

ቤቴል፡ ካልተወለደው የተወለደ እና ስለእኛ የሞተዉ የፍቅር ባለቤት ምኞት ህይወት መሰለህ!

ለገሰ፡ አሐ! ከንግስት እምነት ሞትን መረጥሽ? … ?በኔ እጅ የሰማዐትነት አክሊል ፈለጋ ከሆነ በዚህ ጎራዴ
ቀረጣጥፌሽ ያሻዉን ተስፋ አግኝ፡፡

መርዕድ፡ ቆይ ተዋት ስሚ ሁለት ምርጫ እሰጥሻለሁ፡፡ ክርስትናሽን ትተሽ የንግስት ወዳጅ በመሆን በኦሪት ህግ ፀንተሽ
ትኖሪያለሽ? ነው ወይስ እንዲህ የጎሰቆለ ስጋሽን ለሰይፍ አሳልፈሽ ትሰጫለሽ?

ቤቴል፡ በፍፁም! የኔ ወንድም አይሆንም ክርስቶስ ለእኔ ብሎ እንደሞተላኝ ስለኔ ክብር ብሎ ስለቆሰለልኝ ለፍቅሩ፣
ለመቁሰሉ፣ ለቸርነቱ፣ ስታሳድዱት ለመታገሱ ብሰየፍ/ ብቃጠል/ እንዴት ያረካኛል መሰለህ፡፡ እምነትን
ሳይክዱ ውርስን እንደጠበቁ በአባት መንገድ እየሄዱ መሞት እንዴት ደስ ያሰኛል መሰለህ? ይልቅ በጉብዝናህ
ወራት ፈጣሪህን አስብ፡፡ አሁን እሚጠራህ አለና ሳውልን አድርገኝ በለው፡፡

ለገሰ፡ ተነሽ ምስሽ እሳት ነው፡፡ መርዕድ ከዝች ከማታምን ጋር ክርክር መግጠም አያስፈልግም፡፡ ደግሞም እኮ
ንግስት ያዘዙንን አንዘንጋ፡፡

ቤቴል፡ እሔዳለሁ ልቀቀኝ ድሮም ቢሆን ከሰማያዊ ሞት የምድርን ሞት መርጬ ነው፡፡ ከአለም የወጣሁት ሞተ-ስጋ
ኢምንት ነው ይልቅ አንተ መፍራት ያለብህ ሰማያዊ ሞትን ነው/ሻሽዋን ጥላ ትሄዳለች/

ዕዝራ፡ ዛሬ ደግሞ በነዚያ አውሬወች ሰይፍ የሚወድቅ ተረኛ ክርስትያን ማን ይሆን? እስኪ ቤቴልየ እንድትጠነቀቅ
ልሂድና ልንገራት ከእንግዲህ እ በዚህ ምድር ያለችኝ መጠሪያ እሷ ብቻ፡፡ --- ታዲያ ያለግዜዋ እንዳይነጥቁኝ
ልንገራት፡፡ ----ቤቴል --- ቤቴልየ---- የትነሽ--- እህቴ---- ሚሚ---- ታናሽ--- ቤቴል አንቺም እንደ እማማ?
እኔ እኮ እብድ ነኝ ማን ያብላኝ? የእናንተን እብደሰ እናንተው ካልቻላችሁኝ ማን ይችልልናል ብላችሁ
ጥላችሁኝ ሄዳችሁ? እህቴ --- አንቺም እንደ ማሙሽ አንገትሽ ሲተፍ? በፍፁም --- አይሆንም ስቃዩን
አትችይዉም፡፡ አባም፤ እማም፤ ማሙሽም፤ ባለቤቴም ሰመዕታት ሁላችሁ ደማችሁ በዚህ ድጓ ሳልች
ይታየኛል፡፡ የአደራ ፊደላቱ በደማችሁ አሰፈራችሁልኝ፡፡ ግን ቤቴል አንቺስ አደራሽን ተወጣሽ ለእኔስ ማነው
አጋሬ ማነው አለሁልህ እሚለኝ?--- ባድነት ይሰማኛል ---- ቤቴል ሰይፍ አትፈራም ክርስቲያን ናት ሰይፍ
አትፈራም፡፡ቤቴል የስጋ ብርሀንዋ ጨለማ የነፍስ ብርሀንዋ ግን ለዘላለም ያበራል፡፡ --- ነጋላችሁ ክርስቲያኖች
ታዲያ ማን ነው በነ አባባ የደም መዝገብ ላይ የሚያሰፍር? ማን ነው የአማላኩን አርአያ የተከተለው? አባባን
ህያው የሚያደርግ ለውርሱ የቆመ ማን ነው? ---- ለአባባ ውርስ ትሞታላችሁ? ትሞታላችሁ? እንሞታለን
እንመሰላለን ይሉሀል አባባ ፡ ቤቴል --- እርስዋ እንደሞተች እኛም እንሞታለን ይሉሻል፡፡

ትዕይንት ፭
መጋረጃ ሲከፈት አባ ሳሙኤል ሚስታቸው ወ/ሮ ልኬ ልጆቻቸው አስቴር እና አብነት ተቀምጠው አስቴር እሳት ለማንደድ
ስትጣጣር ትታያለች፡፡

ወ/ሮ ልኬ፡ ተይው ልጄ ተነሽማ በተስፋ ይነዳል ብለን ስንደድም አንጀትሽን እስቃተትንሽ አይደል? ተይዉ ልጀ ተይዉ፡፡

አብነት፡ ተያትማ ታንድደው እና የተኮራመተ አንጀታችንን ታፍታታው፡፡ ግን እማ ስደት ማለት ርሀብ ማለት ነው
እንዴ? እኔ እኮ እረህቡ ከብዶኛል፡፡ በፍፁም መታገስ አልቻልኩም፡፡ አባባስ ምን አለበት ከገንዘብህ ይዘህ
ብትመጣ? ቅጠል እየበላን የቦይ ዉሀ እየጠጣን እስከመቸ እንቆያለን፡፡

አባ ሳሙኤል፡ ልጀ ግዜው የመሬት ነው፡፡ መሬት ደግሞ ልትጠባ በስባሽ ስጋን ልትጠባ አፏን በከፈተችበት በዚያ
አስከፊ ስአት ክርሰቲያን ለሆነ ሁሉ ጥጋብ የለዉም፡፡ አልዚህ ረሀቡም ይህ የስደት ግዜ እስኪያልፍ
ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የዘላለም ጥጋብ ደስታ ነው፡፡ / ወደ ህዝቡ ዙሮ / ልጀ አስቴር ይህ የማየው
ምነው ምነው አልደረሰም? የአሁኑ ገበሬ እንኳ ወቅት ያይ ነበር፡፡

አስቴር፡ ነበር አባባ ነገር ግን የህ የምታየው ዘርም ለም መሬት አላገኘም፡፡ ደግሞም እኮ የባለቤቱ አይደለም ጠላት
አውቆ የበተነው እንጅ ጥሩ ዘር የመሰለ ስንት እንክርዳድ ሞልቷል መሰለህ አባባ፡፡ ግማሹ አሜካላ ላይ ወድቆ
እየቆጨጨ እውነት ይጠፋል፡፡ ግማሹ አረም አንቆ ይዞታል ቀሪውን ደግሞ ነጭ ተምች ተነስቶ እያነቀዘው
ነው፡፡

ወ/ሮ ልኬ፡- አይ ይህ ማሳ ጣጣው የባለቤቱ ልጅ ነበር ግን ልጁ ሁሉ የአባቱን ትች እንደገና አዲስ ነው የማዘጋጀው ማለት
ጀምሯል፡፡ የአባቱን የማይከተል ከንቱ ትዉልድ፡፡

አብነት፡ አባባ ደብተራችን እኮ ተቃጠለ፡፡ ከእንግዲህ የት እየሄድን ልናሰቀድስ ነው? ግን እሱ የቤትህ ቅንአት
አቃጠለኝ እያለ ለምን ማራቸው?

አስቴር፡ ኧረ እንዲያውም አባም እኮ ያን ሁሉ እውቀታቸውን እንደያዙ ደብሬን አላቅም በማለት እሳት እየነደደ ግን
እያሸበሸቡ ገብተዉ ተቃጠሉ፡፡ ታዲያ አባባ እኛስ ለምን እንፈራለን? ለምን እነደነርሱ አንቃጠልም፡፡

አብነት፡ አባየ እነዚህ አይሁዶች ሲዘምቱብን እናስ ለምን አንዘምትባቸውም? ለምን አንገድላቸውም?
አባ ሳሙኤል፡ ልጄ በወንጌል ግራ ፊትህን ለሚመታ ቀኝህን አዙርለት፡፡ ክፉዉን በክፉ አትቃወሙ፡፡ አትግደል
በቀል የኔ ነው ይላልና እርሱ ግፋችንን ተመልክቶ ብድራችንን ይመልስልናል፡፡ ደግሞ አባም እኮ
አላሞቱም አሉ፡፡

አብነት፡ አባ የታሉ? ንገሩኝ አባባ! አባ የታሉ?

አባ ሳሙኤል፡ መጻሕፍትን እያሳዩ እኚኸው አባ፡፡ በስጋ ከኛ ቢለዩም ያለሞተ ታሪክ አላቸው ታሪካቸው በፈቃደ
እግዚአብሔር ለፍተው ደክመው የፃፉትን የደረሱትን መጸሕፍታቸውን አስረክበዉናል፡፡
እውነታቸውን፤ እምነታቸውን ፤ ፍቅራቸውን ፤ ትህትናቸውን በልባችን ቀርፀው አላፈዋል፡፡ እና
ልጆቸ የቅዱሳን ሞት ዕረፍት ስለሆነ ሞቱ ልንል አይገባም፡፡

አብነት፡ ታዲያ አባባ እኛስ እንዴ አባባ እኔ የቂርቆስን እማማ የእየሉጣን አንተ የጊዮርጊስን ሳምሶን ካሌብና አስቴር
ድግሞ የአናንያን የአዛርያን የሚሳኤልን የሰማዕትነት አክሊል በዮዲት እጅ ለምን አንቀበልም?

አባ ሳሙኤል ፡ ልጆቸ አባቶቻችን እኮ እኛን ተክተው ነው ያለፉት፡፡ እኛስ ዘር ሳንተካ አባቶቻችን የሰጡንን ዘር
ሳንዘራ እንዴት እንሙት? እሽ እኛስ ሞትን / ወደ ህዝቡ ዙረው/ ይህ ቡቃያ አይፈርድብንም?
እንዲሁም ለነጭ ነቀዝ ትተነው ስንሄድ አያሳዝንም? ልጆች የነ አትናቴዎስ የህይወት አደራ አለብን፡፡
ቡቃያው ማደግ ሲሻ ለነጭ ነቀዝ ትተነው ብንሄድ ያጠፋዋል፡፡ ልጆች እኔና እናታችሁ
አርጅተናል፡፡ ከእንግዲህ ለእናንተ አውርሰን የምናልፍበት ግዜ ነው፡፡ ልጆቸ--- ይህ ህይወትን
የሚሰጥ ለእኛ ለኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ለአለም የታሪክ አሻራ የሆነ ውርስ በአባቶቻችንና ለኛ
እንደበሩ እናንተም መቅረዝ ሁናችሁ እንድታበሩ፡፡ አደራ አለባችሁ የዕለተ አርብ አደራ፣የቅዱስ
ያሬድ አደራ፣ የሐዋርያት አደራ፣ የሊቃዉንት አባቶች አደራ፡፡ ልጆች አደራ ለጠባቂዉ መታመን
ሲሆን ለሚተወው ግን የባዶነት መገለጫ ነውና ያለዙት፡፡

ሳምሶን፡ /ከመድረክ ዉጭ ቆይቶ/ ጴጥሮስ መስቀልህ ወዴት አለ? ጳውሎስ መሰየፍህ የት አለ? እስጢፋኖስ መወገርህ
ወዴት አለ? --- አቤት ስለብርሀን ስንቶች ጠፋ! ወዳጀ እናቷን በመጥበሻ እንደአሳ ተጠበሰ! መነኮሳት ሁሉ
አለቁ! ገዳማት ተዘረፋ! የዘጉ አባቶች እንደዘጉ ተቃጠሉ! ነደዱ! ብናኛ ሆኑ! ነፍሳቸው ግን ወደ ሰማይ
ተነጠቀች! በክብር ተቀመጠች! አጌጠች! አቤት--- ጭካኔ! አቤት ግፍ! ለሰማዕታት ደወል ለህዝበ ክርስቲያን
እየደወሉ፣ ነጋሪት እየጎሰሙ፣ መለከት እየነፉ፣ የስንቱን አንገት ቀሉት፣ የስንቱን ገላ ገረፋት! አይግፍ!
አይጭካኔ! ነግሶ ደግሞ እነማን ይሆኑ ተረኞች! የሞት ዕድል ባለ ዕጣወች/ወደ መድረኩ እየገባ/ ሞትን በሞት
ልታሸንፉ ለድል የቆማችሁ ወገኖች እሳየው በሉ፡፡ ለክብሩ ዘምሩ ደስ ይበላችሁ አልል በሉ፡፡

አባ ሳሙኤል፡ ልጄ አሁን በእኛ ዘንድ ደስታ የለም ውርሳችን ተቀባይ አጥቷል፡፡ የእኛ ደስታስ የደከምንለት ውርስ
ተቀባይ ሲያገኝ ነው ይልቅ አረፍ በልና እርምህን አውጣ፡፡

አስቴር፡ አባባ እርምህን አውጣ የምትለው የልጁን ነገር----------

ሳምሶን፡ ምን ሆነ ልጄ? አስቴር የግፈኞች ሰይፍ ቀመሰና ሞተ?

አባ ሳሙኤል፡ ረጋ በል ልጄ ልጅህን ለእናቱ ማሳመኛ ሲሉ በወፍጮ ፈጩት፤ ይህ ሁሉ ስለ ጌታ ስም ነውና አ


ይዞህ ተፅናና ልጅህ ደግሞ የቂረቆስን ፈለግ በመከተሉ ደስ ሊልህ ይገባል፡፡

ሳምሶን፡ እንዴት ሆኑ አባባ? አይደረግም? ታሪኩ መሞት የለበትም እሱስ ታሪክን

የማኖርበት ማህደሬ ነው፤ ደግሞስ ያ ለጋ ሰውነቱ እንኳን ወፍጮ ዱላስ ይችላል? አባባ ታሪኩ እኮ ገና
እንቡጥ ነው፤ ታሪኩ እኮ ገና ልጅ ነው!!!

ካሌብ፡ /ከመድረክ ውጭ ሆኖ/ አቤት……..አቤት ሞኝነት ገና ለገና የተስፋ ቃልን በማመን አንገትን አሳልፎ መስጠት፤
ከተንደላቀቀ ቤት ወጥቶ ስቃይ? ከረሀብ ጥጋብ? ለምን? እኔ ግን አላደርገውም!!! ለምን ብዬ? (ከመድረክ
ገብቶ ሳምሶንን እያየ) አንተ ጨካኝ እዚህ አለህ ልጅህ ይህችን አለም ሳይጠግባት አስገደልከው አይደል፤
ልኑር እየለ በኮልታፋ አንደበቱ ሲማፀን መኖርን ከለከልከው፡፡ ሞት ላይቀርላት ሚስትህ ለሞቶ ቆርጣ
አስገደለችው ፡፡ጭካኔ ነው፤ አንትም ጨካኝ ነህ በጣም ጨካኝ !

ሳምሶን፡ ተወኝ !! ልጀን እወደዋለሁ ጌታየንም አፈቅረዋለሁ ! ከመውደድ ደግሞ ማፍቀር ይበልጣል፡፡በዝች ምድረ
ተሰቃይቶ ከሚኖረው እኳንም አረፉና ወደ አምላኩ ሄደ፡፡
ወ/ሮ ልኬ፡ ተው…ልጅ ካሌብ!! እነርሱ መችሞቱ ፤በክርስቶስ የሞቱ ሰወች አረፉ ይባላል እንጅ ሞቱስ አይባልም፤ ከዚህ
አለም ኑሮቸው በእረፍተ ሞት ቢገቱም በሰማይ ግን ህያዋን ናቸው፡፡የዚህ ምድር ኑሮ ደስታ ግን በሰማይ
ይጨልማል፤ ስለዚህ የወዲያኛውን ነው መሻት፡፡
ካሌብ፡ ኤዴያ…እንዲህ እያላችሁ ነው ተስፋችን ያጨለማችሁት ፡፡
አባ ሳሙኤል፡ በሉ ሌላውን ነገር ተውት ፤እንግዲህ ልጆቸእስከዛሬ የእናንተን እንዲህ መሰባስብ ነበረ ስጠብቅ የቆየሁት ዛሬ
ግን እንዲህ ተሰባስባቸሁ ስላገኘሆችሁ ውርሴን የማስረክብበት የመጨረሻ ቀን ይሆናል፡፡ልጆቸ የህች ተዋህዶ
እምነታችን ለዘላለም እንዳበራች ትኖራለች ፡፡ የተዘራው ዘርም የእግዚአብሔር ስለሆነ ጠላት ቢያጭደውም
አያልቅም ቢቀጥፈውም ያቆጠቁጣል ፤ የኛ ሞት ለኛ የማይጠፋ ብርሃን ይሰጠናል እናም ልጆቸ በብርሃናችሁ
አብሩ፤ብርሃን ስላላችሁ ተመላለሱ ብሎልና እግዚአብሔር /ድጎውን ያነሱና /ይህ ድጎ የቅዱስ ያሬድ የመንፈስ
ስጦታ ነው እንካ ሳምሶኔ የበኩርነትህን ስራ ስራበት.ሙትለት አደራ ውረሱ እንዳይጠፋ /ስንክሳሩን ያነሱና/
እነች ልጂ አስቴር ይህ ስንክሳር የቅዱሳን አበው ታሪክ ነው ራስሽን ከእርሱ አስቀድሚ ፡፡ /ዝማሬውን ያነሱና/
እንካ ልጄ አብነቴ ይህም እንዲሁ የቅዱስ ያሬድ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው ለውርሱ አንተነተህን መስዋት
አድርግለት………አደራራራ ልጆቸ…አደራ ውርሴን አደራ…
አስቴር፡ አባባ ሞትህ ሞት ሳይሆን ብርሃን እንዲሆን የመዳንን ብርሃን በውርስ ስጦታ እራሴ አብርቸ ለአለም እንዳበራ
ብርሃንን ሰጠኸኝ አባባ አንተ የቀመስከውን ሰማህትነት እኔም ሳለፍራና ወደኀላ ሳልል እንድቀምሰው ከጌታየ
ከፈጣሬየ ከክርሰቶስ ፅናትን ለምንልኝ የክርስትያን ሞት እኮ የክርሰትና መፍቻ ቁልፍ ነው በሰማህትነት
መሞት እነዴት ያረካል ፡፡
አባ ሳሙኤል፡ አዎ…ሌላው ደግሞ ልጆቸ ይህች ከግራ ና ከቀኝ ጦር የተሰበቀባት ተዋህዶ እምነታችን የእኛ ሰንሰለታችን
መሰላላችን ናት ፡፡ብንሞትባት ታበራለች ባንሞትባት ደግሞ አትጠፋም የእኛ ሞት ግን የእኛ ሞት ግን
ለመጭው ትውልድ ህያው ምስክር ነው፡፡እናም ልጆቼ ከእምነታችሁ ሳትሸሹ የፊተኛውን የክርስቶስንና
የአባቶቻችሁን መሰረት አጥብቃችሁ እንደ አባቶቻችሁ ብትፀኑ የክርሰቶስ ተካፋዮች ትሆናላችሁ /ፊታቸውን
ወደ ካሌብ አቅርበው መፅሐፈ አበውን በማንሳት / ልጀ ካሌብ እነካ መፅሀፍ አበው ለአንተ አብርተህ ለአለም
ለኩሰው ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ አድምቀህ አብራው በአንተ ትጋት የአባቶችን ታሪክ አሳውቅ አክብረው
ያከብረሀል ሙትለት ህይወትን ይሰጥሀል፡፡
ካሌብ፡ ሞታችሁ ላያጠግበኝ ችግራችሁ ላያስደስተኝ ህይወት እያለ ሞትን በመምረጥ ሃዘን የምታፈሩ አይናችሁ
በሞት ጭንብል የተጋረደ እምነት እያላችሁ እግሬን በሰነስለት አስራችሁ እደገትን እነዳላድጋት ኑሮን
እንዳልኖራት አንቆ የያዘኝ እርሱ ነው፡፡…….ይልቅስ አባባ ይህን የእምነት ሰንሰለት ፍታልኝ ነፃአድርገኝ በነጻነት
መኖር አፈልጋለሁ፡፡ ይህንም በአለም አገኘዋለሁ፡፡
ሳምሶን፡ በጤናህ ነው….ወይስ አብደት ቢጢ ይዞሀል ልበል……እእእ የማቅህን ያክል እንደማላቅህ አደረከኝ እኮ!!
እዝራ፡ /ከመድረክ ውጭ/ ይህ ሊሆን ግድ ነውና አትደነግጡ ዳሩ ግን መጨረሻዉ ገና ነ ዉ፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ
አሳልፈዉ ይሰጡቸዋል፡፡ ይገድሉአቸዋል ስለስሜም በአህዛብ ዘንድ የተጠላቸሁ ትሆናላችሁ ወዮላችሁ
ክርስትያኖች ለበጎች የማያዝኑ ጨካኞችና ተኩላዎች ወጥተዋልና፡፡
አስቴር፡ ማነዉ በዚህ ሞት በበረከተበት ወቅት የጌታን ቃል በአደባባይ የሚሰብከዉ.. ማነዉ ግን ስጋዉን ጠልቶ
ክርስቶስን የወደደዉ፡፡
እዝራ፡ /ከመድረክ ዉጭ/ ወገን አሁንስ አፌም ደረቀ፤አንጀቴም እህል አጣ፤ልብሰም በላየላይ ተቦጫጨቀ፡፡ የጌታን
ቃል አክብራ የኖረች እህቴን ቤቴልን፤ሚሚን አንድደዉ ገድለዉ እኔን በብቸኝት ረሃብ ቀጡኝ፡፡ ግን ቤቴል..
እማ ነች ነይያለችሽ.. የገድሉሻል ብላ አስባ እንደሆነ ግን እብድንስ የሚገለዉ የለም ወይ.. በያት፡፡ /ወደ
መድረኩ እየወጣ/ እንደምን አረፈዳችሁ አጎቴ ደህና ናችሁ.. አረመኔ ስያሳድዳችሁ ነጋባችሁ ሚጢየ ግን
መሸባት፡፡ አስቴርየ የአጎትሽ ልጅ መሸባት የምት ጉጠት ከአጠገቤ ነጥቆ ወሰዳት፡፡ አስቴርየ እንደ ልጅነትሽ
ልታጫዉትሽ መጥታ ጓዳ ዉስጥ እንደሆነች እይልኝ፡፡
አስቴር፡ አይዞህ ወንድም ጋሼ ቤቴልኮ አልሞተችም ህያዉ ነች፡፡
እዝራ፡ አንቺም እንደ ቤቴል ወንድም ጋሼ አልሽኝ .. አስቴር እንደ እኔ ብቻሽከመቅረትሽ ያድንሽ
ካሌብ፡ እስኪ ተመልከት አባባ ሞታችሁ ጤና ላይሆን አሳብዶት ሲያንከራትተዉ እያያችሁ ታድያ እኔም እንደ እርሱ
እንዳብድ ነዉ ፍላጎታችሁ፡፡
እዝራ፡ ካሌብ እኔ እብድ ነኝ.. እኔኮ እዝራ ነኝ አታዉቀኝም እንዴ.. አጎቴ እኔ እብድ ነኝ ..አሰቴር እ ኔ አብድ .. ወገኖቹ
በሰው ያልቁበት ብቸኛ እብድ ሊባል ይገበዋል እንዴ.. ወገን እነዚያ ጨካኞች ያለረዳት ብቻየን ስላስቀሩኝ
እብድ መባል አለብኝ ..እብድስ እነዚያ ከሃዲዎች እብደትእኮ ክህደት ነው፡፡ ታድያ እኔ አዝራ እብድ፤እኔ
እብድ /እያለ ወጥቶ ይሄዳል/
አብነት፡ እማማ እኔ ከእዝራ ጋር ሄጀ የሚበላ ቃርሜ ልምጣ፤
ልኬ፡ ተው…..ልጀ ያገኙህ እነደሆን የገድሉሃል፤
አባ ሳሙኤል፡- ይህድ ተይው እኛስ ባዋቂ አንጀታችን ቻልነው እሱ እንዴት ይቻለዋል..እንዲውም እሰካሁን መቆቱ
ያሰመስግነዋል፡፡ ሂድ ልጀ ሂድ አይሁዶችን ብታገኝ እነኳ ሞትን አትፍራ ይግደሉህ ከርሀብ ሞት ይሻላል
/አብነት ወጥቶ ይሄዳል/
ካሌብ ፡ በሉ እሽ እኔ ልሄድ ነኝ………
ልኬ፡- ተው ልጀ …..ካሌብ የአባትህን ውረስ ተቀበል. ይህን ውርስ በሆላ ብትፈልግው እንኳን አታገኝው ሽማግሌ
አባትህም በመጨረሻ ዘመኑ እረግሞህ እነዳይሞት ልጀ ስለጠባሀው ጡቴ ብለህ ውርሱን ተቀበል
ካሌብ፡ እማማ የኔ ውርስ እናንተ የምትሎቸው ተራ ነገሮች ሳይሆኑ አንደላቆ ሊኖረኝ የሚችለው ጥላችሁት
የመጣችሁት ሰፊ ርስታችሁ ነው፡፡….. አባባ እኔ የምፈልገው ገንዘብህን እንጂ ይህን ተራ መፅሐፍህን
አይደለም፤ የህን የእዳ አደራህን ለሌላ ሰው አውርሰው ….እእ …..በሉ እሽ ቻው /ወጥቶ ይሄዳል/
አባ ሳሙኤል፡ ተው ልጄ ተመለስ የዴማስን የጥፋት መንገድ አትመልከት ተው ተመለስ…………እባክህን ልጄ ….ተመለስ
/ዋሽንት/
ሳምሶን፡ አባባ ወንደሜ ሲሰናከል ዝም ብየ ማየት የለብኝም እኔም የጌታየን ፈለከ በመከተል ነብሴን በወንደሜ
መመለስ ለውጨ በሞቴ ከሄደበት ከጥፋት መንገድ እመልሰዋለሁ፡፡
አስቴር፡ አባባ እኔም ክርስቶስ እንደሞተልኝ ስለወንድሜ ሕይወቴን አሳልፌ ሰጥቸ ወንድሜን ከጠፋት መመለስ ፤
ከእሳት ማውጣት ፤መንገድ ከሚመስል ከተሰበረ ድልድይ ፈጥኝ ማውጣት …መመልሰ አለብኝ
ልኬ፡ አረረረረተው ልጆቸ አግኝተው እንዳይገሎችሁ ……
አባ ሳሙኤል፡ ተይ እንጂ እንዲህ አይነት ቃል ከአንደበትሽ አይውጣ በሉ ልጆቼ ሄዱ ካጠገባችሁ ያለውን ወንድማችሁን
ወዳችሁ ስለጥፋቱ ካልሞታችሁለት ያላያችሁትን አምላክ አፈቀርንህ፤ እንሞትልሃለን ብትሉት ምን ዋጋ
አለው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መቀለድ ነው የሚሆነው ፡፡ እናም ልጆቼ /ሀይማኖተ አበውን አነስተው/ እኔን
ሁናችሁ……..የአባትህን ውርስ እንካ በሉት አደራ ልጆቼ /ልጆቹ ሲሄዱ ይታያል/
ልኬ፡ በሉ ደህና ሁኑ ልጆቼ እግዚአብሔር በሰላም ይመልሳችሁ ስትሄዱ ተጠንቅቃችሁ ነው፡፡ ከእንግዴህ ምን
አደረጋልሁ እንቅፋት እኳንእንዳይመታችሁ የምሳሳላችሁ እናታችሁ፤ በሞታችሁ ጨክኝ ሰደድኳችሁ ፡፡ ግን
ይሁን አባቱ …….ወንድማችሁ በነፍሱ ከሜሞት የእናንተ በስጋ መሞት ይሻላል ፡፡
መርዕድ ፡- /ከመድረክ ውጭ/ በደብረ ዳሞ እና በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ መነኮሳት እንደ ንግስት ትዕዛዝ ፀጥ ረጭ
አደረኳችው ፡፡ ድምጥማጣቸውንአጠፈሆቸው አቤት የፈሰሰ ደም ………..አሁን ደግሞ በየዋሻው ያሉትን
እንዳድን ታዘዝኩ አዎ የንግሰት ትዛዝ ነው መፈፀም አለብኝ ፡፡ ካለበለዚያ እኔም ታዳኝ እሆናለሁ፡፡//ወደ
መድረኩ ሲገባ መጋረጃው ይዘጋል ፤ ሲከፈት ልኬና አባ ሳሙኤል ተሰይፈው ያጣጥራሉ፡፡ አባ ሳሙኤል
መፅሐፍ ቅዱስ ገልጠው የሀዋርያት ስራ ምዕ 9-1 ያለውነ ቃል አውጥተው //
አባ ሳሙኤል፡ ል………..ልጄ ጌታ በፍቅር ይቅር እንዲልህ …......ን………….ንስሃ ግባ ሰይፍህን ጥለህ ተከተለው እውነቱ
ይበራልሃል…….እእ…….እባክህን ተቀበለኝ ልጄ ….እንካ አንብበው //መርዕድ ተቀበሎ የሀዋርያት ስራን ምዕ 9፤1-
16 ያነብና//
መርዕድ፡ ሳውል ማንው..ይንገሩኝ አባቴ ሳውል ማነው ..ማን ይነግረኛል ..ሳውል ምንድነን ነው፡፡
አብነት፡- /ቃርሞ አየተመለሰ ከመድረክ ውጭ / እኔስ በልቸ ጠገብኩ እህል አጥቶ የቆየ የ እማማ እና የአባባ አንጀት
ትንስ እነኳ እንዲቀሳቀስ ይህችን ዳቦ ልውሰድላቸው // ወደመድረኩ ይገባና // አባባ፤ እማማ የት ነው
ያላችሁት //ወለል ውድቀው ሲያይ ይደነግጥ እና
አባባ ምነው …… እረ እማይ ብቻየን እኮነኝ አባባ.. እረ አይቻልም ተነሱ የሚበላ ይዠላችሁ መጥቻለሁ አባ
ማን ያኑረኝ እማዩ ጅብ ሲጮህ ከማን ጋር ልተኛልሽነው፡፡
መርዕድ፡- /ከጎዳ በመውጣት/ ማሙሽ ሳውል ማን ነው.. ንገረኝ
አብነት፡ አልፈልግም ዞር በልልኝ አንተ ነህ አይደል ያረድካችው ……….አትተጋኝ ዞር በልልኝ ከዚህ እነደ አባባ
ልታርደኝ ነው እማማን እንዳረደካት ልታርደኝ ነው አልፈልግም ዞር በልልኝ //እያለ ያፈገፍጋል ወደ ሆላ//
መርዕድ ፡ ልገድለህ አይደለም ማሙሽ እንካ የእናት እና አባትህን ደም በግፍ እንዳፈሰስክ የእኔንም ደም በአንተ እጅ
ይፍሰስ ፡፡ /ሰይፍን የሰጠዋል/ ግን ማሙሽ ሳውል ማን ነው፡፡../አብነት ሰይፉን ተቀብሎ ሊገድለው አጁን
ሲዘረጋ የአባቱ ቃል በግብአት ደምፅ ይሰማል ፡፡
ልጄ ጌታ በወንጌል ግራ ፊትህን ለሚመታህ ቀኝህን አዙርለት ክፉን በክፉ አትቃወም አትግደል በቀል የኔ ነው
ይላል እና እርሱ ግፋችንን ተመልክቶ ብድራታችንን ይመልስልናል …..ይህን ቃል ሲሰማ አብነት ሰይፉን ጥሎ
ከእናት እና አባቱ በድን ላይ ይወድቃል መርዕድ መፅሐፉን ሲገልጥ የሐዋ ስራ 9፤1-16 ያለው ቃል በግብአት
ድምፅ ይነበባል ተነቦ እነዳበቃ …..
መርዕድ፡ በቃኝ ሳውል ጳውሎስ መሆኑን በእውነት አወኩእያየሁ አለማየቴን፤ ብርሀናችሁ
በእኔም ላይ እንዲበራ ከፈጣሪ ለምኑልኝ

ትዕይንት ፮
ካሌብ፡- /ቤት ውስጥ ተቀምጦ / አቤት ! ከዚህ በላይ የሚሳደስት ምን ነገር አለ በአባቴ ሃብት ላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ አዛዠ
ተናዛዥ ሆንኩ ብቻ ምን ይደረጋል አባቴ በሰተርጅናአው እነደ
አልባሌ አቃ ወደቀ ፡፡እነርሱ እነኮ የራሳቸው ጉዳይ ግን ያንን ሕፃን
የት አግኝቸ ይህችን አለም ባጠገብኩት እንርሱ እነደሆኑ ካደሩበት
አይውሉም ከዋሉበት አያድሩም ፡፡ለማንኛውም አሁን ወደጌታ ለገሰ
ዘንድ ልሄድ ና የአባቴን ውርስ በውል ማግኝቴን ላረጋግጥ ፡፡
/ከመጋረጃው ውጭ ቁሞ እያለ የዮዲት አዋጅ ቃል ከመጋረጃው ደምፅ ይደመጣል/ ሕዝቤ ሆይ የአይሁድን
እምነት ክዶ በሀሳዌ ፍቅር ልቡ በኖ ለትዕዛዜ አልገዛም ብሎ የኮበለለውን የፊቱን ሹሜን መርዕድን ይዞ
ለመጣ ትልቅ ስጦታ ይሰጠዋል የመርዕድን ቦታ ይዞ ያሰተዳድራል ፤

ለገሰ፡ /አዋጁን ከሰማ በውሀላ / ሹም ለመሆን ሹም ማስያዝ በዚህ ሰሞን ንግስት እንዲት ያለ ማለፊያ አዋጅ አወጁ

አዎ! ብላ ሲሉት ያልበላ ለሚበላ ስወ ቦታውን መለቀቅ አለበት ገናለገና ጓደኛዩ ነው ብየ ለምን ብየ ሹመት
ያመልጠኛል፡፡ካለበት ጉድጎጓድ ምሼ አውጥቸ አንጠልጠየ አቀረበዋለሁ

ካሌብ፡ ከዉጭ ይመጣና ጤና ይስጥልኝ ጌታዬ

ለገሰ፡ ኡፍ! መጣህ እንዴ ጥሩ ስአት አክባሪ ነህ ስማ ካሌብ አሁን በአይሁድ እምነት ለማመንህ እና ስራህን ወደ
እምነቱ ለማስገባትህ በምን ማረጋገጫ ልመንህ፡፡

ካሌብ፡ ይመኑኝ እንጅ ጌታየ ይህን ሁሉ የማደርገው እኮ የንግስት ፍቅር ይዞኝ ነው፡፡

ለገሰ፡ እመነኝ ካልክ ------ የማላዉቅ መሰለህ! የነዛ ተፈላጊ ቀንደኛ ክርስቲያኖች መፅሐፍ ወራሽ የሆነ አይደል
ሞኙን ይፈልግ (ይህን ሲል ፊቱን ወደ ኋላ ዙሮ) ጥሩ ግን አንድ ነገር ልፈትንህ እፈልጋለሁ ትስማማለህ?

ካሌብ፡ ይፈትኑኝ ጌታዬ ለንግስት ፍቅር ስል የማልከፍለው መስዋዕትነት የለም ግን የአባቴን እርስት አደራ፡፡

ለገሰ፡ ለእርሱ ግድ የለም ለእኔ ጣለው ይኸውልህ አሁን በአካባቢያችን ድጓ፣ ስንክሳር፣ መፅሐፈ አበው፣---- የተባሉ
መፅሐፍትን ደብቀው በመዞር ሰላምን የገዙ ሁለት ሰዎች አሉ እነርሱን ከነመጻሕፍቶቻቸው በእጃችን ውስጥ
ከአስገባህልን ያለኸው ሁሉ ይደረግልሀል ያለበለዚያ ግን ታደኝነትህ ይፀናል ገባህ?

ካሌብ፡ እህቴን ወንድሜን/ወደ ተመልካቹ ዙሮ/--- ምን አደርጋለሁ እነርሱንም ታደኝነቱ ላይቀርላቸው አኔስ ለምን
የአባቴን ርስት ያመለጠኝ ------ ጌታዬ ባሉኝ ነገር ተስማማቻለሁ ነገ በ9 ስአት ከተራራው ጀርባ ያለውን ዋሻ
ያውቁት የለ ከዚያ ሁለቱንም ቁጭ አድርጌ እጠብቅዎታለሁ

ለገሰ፡ አዎ ደምስም እኔም እናውቀዋን አሁን ሂድ ባልከኝ ሰአት እመጣለሁ ሲል ለገንዘብ ብሎ ዘመዶቹን በእሳት
አሳለፎ የሚሰጥ ደግሞም እሽ ያን ያለውን የአባቱን እርስት ለእኔ ለላቤ ዋጋ ተሰጥቶኝ ወስኜዋለሁ፡፡ ከአፌ
የወጣውን ስጋ ምን ያወጣል ለሁሉም ጊዜ ይደረስ፡፡
ካሌብ፡ /ዋሻ ውስጥ ተቀምጦ / ከእንግዲህ ዙረው ዙረው ፈልገው ሲያጡኝ ተመልሰው ከዚህ መምጣታቸው
አይቀርም ሰለዚህ ከዚህ ቁጭ ብዬ ጠብቄ ሲወጡ ማስያዝ ነው፡፡

አብነት፡ / እጓዳ ውጭ/ ካሌብ አባዬና እማዬ እኮ ሞቱ ብቻዬን ጥለዉኝ ሄዱ፡፡

ካሌብ፡ አይዞህ እኔ አለሁልህ አሁን ወደ ጓዳ ግባ ምንም አይነት ነገር ብትሰማ እንዳትወጣ፡፡

ሳምሶን፡ አስቴር ወንድማችን ፈልገን አጣነው ከዚህ በላይ ካገኙን ጥሩ ስለማይሆን ወደ ዋሻው እንመለስ ሞታችን
በክብር ቢሆንም ማውረስ የሚገባንን ሳናወርስ ማለፍ የለብንም የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ደግሞ ከዚያው
እናገኘዋለን፡፡

አስቴር፡ ጥሩ እንግዲያው ወደ ዋሻው እንመለስ

ካሌብ፡ የመኖሬ በር ከፋቾች መጡ እንግዲህ ሸፍጥ ልጀምር ያዘንኩ መስዬ ቁጭ ከዚያ...ይዞ መቅረብ ነው አይዞህ
ካሌብ ድፈር መኖር በግሩ ዳዴ እያለ መጥቶአል፡፡

አስቴር፡ (ወደ እርሱ እየተጠጋች) የናቴ ልጅ ወንድም ጥላ ከዚህ አለህ እንዴ; እኛ እኮ አንተን ለመፈለግ ያልሄድንበት
ቦታ የለም!!

ካሌብ፡ ምነው ሞት እንዲህ በበዛበትና በረከሰበት ሰዓት መጣችሁ; እኔም እኮ ስለናንተ እያሰብኩ በጣም ተጨንቄ
ነበር፡፡

ሶምሶን፡ ወንድሜ በሰይፍ መካከል አልፈን የመጣነው የአባባን የውርስ መፅሐፍ ልንሰጥህ ነውና እንካ ስለእግዚአብሔር
ብለህ ተቀበለን (መፅሐፉን ይሰጠዋል)

ካሌብ፡ እሺ እቀበላለሁ!! (ተቀብሎ ይስመዋል)

አስቴር፡ የመንከራተታችን ዋጋ ሆኖ እግዚአብሔር ያንተን ልብ አራራልኝ፤ ለውርሳችንና ለፍቅሩ ተገዢ ሆንክ፡፡ በል


ከእንግዲህ ውርስህ እንዳይጠፋ በከንቱ እንዳይቀር ቃል ግባለት፤ በከንቱ እንዳይጠፋ ሙትለት፤ የአባትህን
አደራ ለልጅህ አስረክበው፡፡ ና ስለደስታችን እቀፈኝ፤ ደስ ብሎኛል፤ ( ይሳሳማሉ) ሶምሶን አባባና እማማ
የደስታችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ከጓዳ ጥራቸው፡፡

ካሌብ፡ እነሱማ ከንቱ ሀሳብ እያውጠነጠኑ በንግስት ሰይፍ ተሰይፈው ሞቱ፡፡

ለገሰ፡ ካሌብ!

ካሌብ፡ (ከነርሱ እየሸሸ) ዞር በሉ ውርስ ውርስ እያላችሁ ህይወቴን እንዳታበላሹት

ሶምሶን፡ (ለገሰንና ካሌብን እየተመለከተ) ለካስ ባንዳ ኑረሀል እንደ ዮሴፍ ትሸጠን? የአባባን ታሪክ ልታጨልም ብሀኑን
ልትገታ አሰብክ አይደል? ለኛስ ተወው ሞታችን ክብራችን ነው፡፡ አንተ ግን እንዲህ በወደድካት አለም ፀንተህ
እንደማትቆየባት እወቅ፡፡ ጨካኝ ነህ፤እምነትህን አደራህን ሸጠህ የበላህ ይሁዳ ነህ፡፡

ለገሰ፡ ዝምበል ዝጋ - - - ጥሩ ነው ካሌብ ከእንግዲህ የንግስት ወዳጂነትህም ተረጋግጦልሃል፡፡ (መጽሃፍትን ተቀብሎ


ሁለቱንም ወደ እስር ቤት ይወስዳቸዋል፡፡ አብነት ገጓዳ ወጥቶ)

አብነት፡ ወንድሜ እህቴ ከጅብ ማስደንገጥ፣ ከብቸኝነት አዳኑኝ ስል ይህ ሰው በላ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ አባ ተመልክት
ስስታም ልጅህን፣ እማ ተመልከች እምነትሽ በጡት ነካሽ ሲመረዝ፤ አባ ጥራኝ አባዬ አንተን የወሰደ ምት
ይውሰደኝ መሰየፍ ያግኘኝ ( ተንበርክኮ) ምንነው እግዚአብሔር አምልክ ቅርቆስን በሰማዕትነት የጠራህ
ምንነው እኔን በብቸኝነት ስሰቃይ እንደርሱ አልጠራ አልክኝ፤ ጨከንክብኝ (ይቀመጣል)

እዝራ፡ (ከመድረኩ ውጭ) አስቴር መሸባት፣ ያጎቴ ልጅ መሸባት፣ ወንድም ለወንድሙ ጨከነ፡፡ አስቴሬ ዮዲትን
እምነታችንን አንክድም በያት፤ ሶምሶኔ ቤተ ክርስቲያን ፅኑ አለት ስለሆነች አጥጠፋም በላት፡፡ እርጉም በላ፤
ሞት በስጋ ለክርስቲያኖች ተራ ነገር ስለሆነ እብዱ እዝራ አይፈራሽም በላት፡፡

አብነት፡ (ከተቀመጠበት እየተነሳ) እዝራዬ አትለየኝ፣ ብቸኛ ነኝ ዘመዶቼን ካሌብ በላቸው ግን ለምን የማያምን
አማኝን ያጠቃዋል?
እዝራ፡ ሰማሁ አብነቴ የአባትህን ውርስ ወሰዱት አይደል፤ አትረቡም በላቸው፡፡ እስኪ ተመልከቱ ይህን እንቡጥ ገና
በለጋነት እድሜው እንደኔ ብቸኛ ሲያደርጉት ጨካኝ ነሽ በላት፤ አብነቴ ህጻኑን ልጅ ብቻየን ስላስቀረሽን
እግዚአብሔር ፍጥረት ይንሳሽና ማህፀንሽ ይረር በላት፤ ዘር ያሳጣሽ በላት፤ አብነቴ አጎቴን የጨለማ ጉም
ዋጠው እናትህን የጅቦች ሰይፍ በላት፤ አስቴርንና ሶምሶምን ወንድማቸው በላቸው፤ አረመኔ! እምነት በላ ነህ
አትረባም በለው፡፡ ርስት አገኛለሁ ሲል ዘመዶቹን አስፈጃቸው አይደል? አትበላውም በለው፤ ወንድሞቼን
በግፍ አስገድሎ በግፍ ሊበላ? በፍፁም አይችልም! ሄጄ በማቃጠል እንዳልነበር አደርገዋለሁ፡፡

አብነት፡ ወንድም ጋሼ እንዳይገድሉህ እንጂ እንዲያ የጓጓለትን ሀብት አሳጥተህ ራቁቱን አድርገው ፤ እንሂድና አሁን
ሁለታችን እናቃጥለው፡፡ ( ወጥተው ሲሄዱ ካሌብና ለገሰ ከመድረክ ውጭ፡)

ለገሰ፡ ስማ ካሌብ እንቅጩን ልንገርህ የአባትህን ሃብት ለኔ የልፋት ዋጋ ተብሎ በበላይ አካል ተሰጥቶኝ
ወርሼዋለሁ፡፡ ነገር ግን ላደረግኸው ተጋድሎ መጠለያና ትንሽ ገንዘብ ይሰጥሃል፡፡ መታደን ግን ከአሁን በኋላ
ቀርቶልሃል፡፡

ካሌብ፡ ምነው ጌታዬ የአባቴን ሃብት ለምን? ኧረ ይተዉ ጌታዬ?

ለገሰ፡ ዝጋ በቃ ሌላውን ሁሉ እርሳው፤ አለበለዚያ በእጄ ነህ! ሆዳም ስግብግብ ሊበላ! መርዝ ብላ!!

ደምስ፡ (በጣም እየጮኸ) ተቃጠለ! ተቃጠለ! ጌታዬ ተቃጠለ!

ለገሰ፡ ምኑ ነው የተቃጠለ?

ደምስ፡ ሁሉም ነገር አንድም የቀረ ነገር የለም

ለገሰ፡ የምኑ ሁሉ ነገር ነው? እረጋ በል

ደምስ፡ በባለፈው የወረሱት ሃበት ሁሉ ተቃጠለ

ለገሰ፡ ማን ነው ያቃጠለው?

ደምስ፡ እሱንማ ባውቅ እኔስ መች እለቀው ነበር!

ለገሰ፡ ያ ካሌብ የሚሉት ከሃዲ የት ነው ያለው?

ደምስ፡ እሱ ከዛው እሳቱን ለማጠፋት ይታገላል፤ እሱ ባይኖርማ ሁላችንም ተቃጥለን ነበር

ለገሰ፡ ነፍሰ ስጋው ይቃጠልና እኔ እንዳለበላው ነው ያቃጠለው፤ የሱ ተንኮል ለኔጠፍቶኝ! ሂድ አሁን በፍጥነት
ይዘኸው ና! በቁሙ እንዳለ በእሳት አቃጥለዋለሁ፡፡

ደምስ፡ አ...ሀ... ለካ ይኽም አለ! ጌታዬ ይህን ደብዳቤ አንዲት አሮጊት ናቸው የሰጡኝ፤ (ለገሰ ደብዳቤውን ሲከፍት
በግብዓተ ድምፅ)

መርዕድ፡ ‹‹ውድ ወንድሜ ሆይ በአፈር ከመጫወት ከህፃንነት ጊዜያችን ጀምሮ በንግስት ቤት ተቀምጠን ባንዳ ሆነን
የክርስቲያንን ደም እስከ ማፍሰሳችን የነበረውን ጊዜ አስበው፡፡ ውድ ወንድሜ ያ ያሳለፍነው የጨለማ ጊዜ
የባንዳነት ዘመን በጣም አስጠልቶኝ፣ አንገፍግፎኝ፤ ያ ያፈሰስነው የንጹህ ወገኖች ደም እረፍት ነስቶኝ፣
ክርስቶስ የጠፋውን በግ እኔን ፈልጎ ስላገኘኝ እሱም ተደስቶብኝ እኔም ተከትዬው ሄጃለሁ፡፡ ወንድሜ ሆይ
ይህ ጊዜያዊ ደስታ ነገ በዋይታና በጩኸት ይተካል፡፡ ለማለት የፈለግሁት አንተም እንደኔ በሰራኸው ስራ
ተፀፅተህ በክርስቶስ አምነህ ብትመለስ ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ የኔ መዳን ሲያስደስተኝ የአንተ እንደጠፋህ መቅረት
ደግሞ በጣም እያሳዘነኝ ነው፡፡ እና ወንድሜ እባክህን ወደ አዳኝህ ተመለስ፤ ያፈሰስከው የብዙ ንጹሓን ደም
እንደ አቤልና ዘካርያስ ደም ፍረድልኝ እያለ በእግዚአብሔር ፊት እየጮኸ ነው፡፡ ሌላው የምልህ ነገር ቢኖር
ባለፈው ከሁለቱ ክርስቲያኖች ተቀብለህ የወሰድከውን መፅሐፍ ላክልኝ፤ በወንድምነታችን መጻሕፍቱን
ብትመልስልኝ ጥሩ ነው፤ ካልሆነ ግን መጻሕፍቱን በኔ ለውጠህ ለንግስት አቅርበኝና ሥልጣንን አግኝ፡፡ እኔ
ግን ከአሁን በኋላ በሰማይ ተሸሜአለሁ፡፡ መጻህፍቱን ስትልክልኝ ያን ጊዜ እመጣለሁ፡፡-----መዳን ሰይፌን
አስጥሎ የክርስቶስ ያደረገኝ እና ክርስቶስን ያስመረጠኝ ወንድምህ መርዕድ ነኝ...ከዋሻው፡፡››
ለገሰ፡ ሃብት አመለጠኝ ስል ሌላ ስልጣን መጣ? እነዲህ ነው እንጂ ልፋትን ሲቆጥር ከእነዚያ ተራ ነገር በሆኑ
መጻሕፍት እራሱን ለውጦ ከመጣ ምን ገዶኝ? በደስታ እቀበለዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ የንግስት አሽከር ለገሰ
ተብሎ ከተነገረ አቤት ሀብት፣ አቤት ክብር...አቤት ክብር... ብቻ እነጃ እሰኪደርስ ቸኮልኩያለሁ፡፡

ደምስ፡ (ካሌብን በጥፊ እየመታው) አንተ አስመሳይ ቀጥል! ቀጥል!

ካሌብ፡ ድሮም ላትረቡኝ አይሁድን ማመኔ

ደምስ፡ ምንም አይነት ቃል አያስፈልግም ዝም ብለህ ብትሄድ ነው የሚሻልህ

ለገሰ፡ መጣህ አንተ ከሃዲ! እኔ እንዳልጠቀምበት ነው አይደል ያቃጠልከው? በል ቆይ ማንነቴን አሳይሃለሁ፤ ደምስ!
በል ፈጠን በልና ከዘመዶቹ ጋር ወስደህ ጠፍንገው፡፡ ስትመለስ ለእሱ እህትና ወንድም የቀማናቸውን
መጻሕፍት ይዘህልኝ ተመለስ፡፡

ደምስ፡ (መጻሕፍቱን እየሰጠ) ይኸው...

ለገሰ፡ በል ከዚያ ዋሻ ሂድና እነዚህን መጻሕፍት ሰጥተህ ያን ከኀዲ ይዘኸው ና!

ደምስ፡ የቱን ከኀዲ?

ለገሰ፡ መርዕድ ነዋ! በፍጥነት ይዘኸው ና! እቤት እጠብቅሀለሁ፡፡

ትዕይንት ፯
መጋረጃ ሲከፈት ዕዝራ፣ መርዕድና አብነት ዋሻው ውስጥ ይታያሉ

መርዕድ፡ ዕዝራ! እናትና አባትህን፣ እህትና ወንድምህን፣ ሚስትህንና ልጅህን፣ በአጠቃላይ ወገንህን ገድዬ አንተን
ብቻህን በማስቀረት ለዚህ ሁሉ ችግር ስለዳረግሁህ ፀፀት የእግር እሳት ሆኖ እያቃጠለኝ ነውና እባክህን ይቅር
በለኝ (ጎንበስ ብሎ)

ዕዝራ፡ ማሙሽን ከኔ ካባቱ መለየት ሳይወድ ለይተኸው፤ ባለቤቴን ቅሪት ሳለች ከእቶን ውስጥ አንድደሀት፤ አባባን
ቆዳዉን ገፈህ ፣ እማማን እናቴን ጡቷን ቆርጠህ፣ ቤቴልን በእሳት በማቃጠል ናላዋን እንዳዞርከው ላንተ
ለነፍስ በላው ይቅርታ ላደርግልህ? ገድለኸኝ እያየሁእንዴት ብዬ ይቅር ልበልህ? የዘመዶቼን ተስፋ
ስላጨለምክባቸው ይቅርታ? የማይሆን ነገር ነው፡፡ (ወጥቶ እየሄደ)... ዘመዶቼን አስታወስኳችሁ ትዝታችሁ
ቀሰቀሰኝ፤ ማሙሽ ....የኔ ልጅ እባክህን ናልኝ! ቤቴልስ ለምን አትመጭም? አልናፍቅሽም እንዴ?

መርዕድ፡ ማሙሽ የእናት የአባትህን ደም በማፍሰስ አንተን ብቻህን እንድትቀር በማድረግ ስለ በደልኩህ አንተ እንኳን
ይህን ጊዜ በህይወት እያለህ ከልብህ ይቅር በለኝ፡፡

አብነት፡ ይቅርታ የማደርግልህ የአባባን የውርስ መጽሐፍ ስትሰጠኝ ነው፡፡

መርዕድ፡ ለእርሱ ከሆነ ምንም ችግር የለም ማሙሽ፤ መምጫው ጊዜ ዛሬ ነው እስከዛው ግን አንተ ከጓዳው አትውጣ፡፡

ደምስ፡ አንተ ከኀዲ! እንደኔ እንደኔ ይዤ ብገድልህ ነበር ፍላጎቴ፤ ነገር ግን አለቃዬ ያዘዘኝን አልጥስም፡፡(መጻሕፍቱን
እየወረወረ) ያውልህ ምናምንቴ መጽሀፋችሁ፤ አንተ ግን ና ፍዳህን ታያታለህ፡፡

መርዕድ፡ (መጻሕፍቱን ተቀብሎ) መጣሁ እሺ ጠብቀኝ (ከጓዳ ይገባና) ማሙሽ እንካ ውርስህን እንካ፣ ሃብትህን
ኑርበት፤ እኔም እውነትን አውቄ ስለእውነት መስዋዕት ልሆንእየሄድኩ ነው፡፡ ለካ እነዚያ አባቶች በሞታቸው
ይደሰቱ የነበረው ለእውነት መሞት ስለሚያስደስት ነው፤ በል ማሙሽ በይቅርታ ሸኘኝ......

አብነት፡ እግዚአብሔር ይስጥህ እርሱ ይቅር ይበልህ፡፡ እሳቱን ውሃ፣ ሰይፉን ለምለም ያድርግልህ፡፡ እኔ ይቅር
ብዬሃለሁ፡፡ (መጻሕቱን እያየ) አባባ እነዲያበራልኝ ውርስህን አደራ ብለኸኛልና እኔም አልጥለውም፤ አንተ
በስጋ ብትሞትም ብርሃንን አውርሰኸኛልና ለኔና ለመሰሎቼ ለዘላለም እንዳበራ ይኖራል፡፡

ትይንት፰
በእስር ቤትውስጥሶምሶን፣ አስቴር፣ መርዕድናካሌብየኋሊትታስረውለገሰናደምስቆመውሲጠየቁይታያል፡፡
ለገሰ፡ (አመድበእጁጨብጦእያሳያቸው)፡ ይታያችኋልየቄሳርንወዳጅነትጠልተውበክርስትናእምነትተሞልተው፡
ሞልተን፣ ተሰደደልን፣
ቅብጥርስእያሉአይናቸውእያየወደሞትጉጠታችንበመግባትበእቶንእሳትየነደዱየእናንተሰማእታትየነዛከሃዲያንብና
ኝ( አመዱንእየበተና) አመድይህችንዓለምበብናኝነት ፣ መሸኘት( ወደሶምሶን)፡-
የእኛታሪክአስተላላፊወገኛከእኛአምልጦበሚኖረውለየትኛውልጅህነውየምታስተላልፈው፡፡

ሶምሶን፡- እውነትትመነምናለችእንጅአትጠፋምስለምድርሃብትሁሉየሞቱእጥፍሞትንሞቱእኛግንበሞተልንሞትን፣
ያፈቀረንንአፈቀሩን፣ ሞታችንምደስታየሰፈነበትቀናመንገድነው፡፡

ለገሰ፡ (ወደመርዕድዞሮ፡-) የእኛለእምነትክብርን፡ ለህይወትን ሠጭ? ወገኛ! ለመሆኑ ምን አጠጣህና እንደዚህ ሆንክ?

መርዕድ፡ ወዳጅእርሱየሰበሰብከውምድራዊካባነገያልቃል፡፡ ይህአምሮየሚታየውሰውነትህምይረግፋል፡፡


በክርስቶስስለክርስቶስመሞትግንለዘለዓለምየማያልፍፀጋንያሰጣልእናወንድሜየክርስትናንእምነትመከራውንአይ
ተህአትጥላው፡፡ ቅመሰውናአጣጥመውትረካበታለህ፡፡

ለገሰ፡ በቃህአትዘላብድ

አስቴር፡ ምንድንነውእንደዚህየምታስጨንቀኝበሞታችንየቆረጥንሰዎችእኮነንለምንአትገድለንም?ግደለን፡
እግዚአብሔርንካልፈራህግደለን፡፡

ለገሰ፡ ቀስበይአትቸኩይበመሞቱትደርሽበታለሽ፡፡

ዕዝራ፡ ከመድረክውጭሞትንሻትኩ!ለዘመዶችየመጣሞትንወደድኩበቃኝ!በቃኝ!ፀሃዩ፣ ብርዱ፣ ረሃቡ፣


መራቆቱአንገፈገፈኝ!በቃኝከእንግዲህአልደበቅም!ወደእስርቤትሄዶአስቴርአሰቃዩሽ?ሶምሶንአንገላቱህ?ይታያችሁ
ወገንይታያችሁሰዎችበስቃይእንዲህተፈትነውሲያልፉ፤
ተዋህዶግንአለችለወደፊትምትኖራለችበየግዜውየተነሱከሃዲያንበፍፁምሊያጠፏትአልቻሉም፡፡ወደፊትየሚነሱት
ምሊያጠፉትአይችሉም፡፡
ይኸውአሁንየአጎቴልጆችተሰቃዩወደፊትምክርስቲያንወገኖችሁሉስለእምነታቸውይሰቃያሉ፡፡ፊቱንወደአስቴርአዙ
ሮጣቱንወደለገሰበመቀሰርይህንንባንዳየንግስትሎሌእውነትአትጠፋምበይውፊቱንወደሶምሶንዞሮሶምሶኔያችንጉድ
ያመጣችጉዲትንአንበሳውድምእየመጣነውበላት፡፡

ለገሰ፡ ምንንልታስፈራራነውአንተእብድ

ዕዝራ፡ ያችንየሴትአለቃህንጉዲትንከአንቺጋርካለውክእኛጋርካለውይበልጣልበላት፡፡
የክርስቲያንጦርያሸንፋልበላትየቤተክርስትያንንናየኢጥዮጲያንታሪክልታጠፊአስበሽከሆነጠብሽከእግዚአብሔርጋ
ርነውናአይሆንልሽምበላት!!

ለገሰ፡ ሌላስየለህም!

ዕዝራ፡ ወደካሌብበመሳቅእያየ፡- የእግዚአብሔርፍርዱንማንይመረምረዋል፡፡ አሁንይህንእምነትበላ፣ ውርስበላ፣


ወገንበላ!ማንበእንዲህአይነትይኖራልፀሎትነበር፡፡ አቤትየእግዚአብሔርጥበብ፡፡

ለገሰ፡ ቀጥልአህንምሌላካለህ፡፡

ዕዝራ፡ ሞት በስጋ ውዳቂ ነው! አንፈራም በላት ለሴት አለቃህ (ፊቱን ወደ አስቴር ዞር ብሎ) .........................................
እነቤቴልን፣ እነ አባባን እናገኛቸዋለን፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ክርስቶስንና እናቱን እመቤታችን ድንግል
ማርያምን እናገኛቸዋለን (ፊቱን ወደ ህዝቡ መልሶ) ያልረባ ዘመን አመጣሽ እምነት ይጠፋል፤ እውነተኛና
ቀጥተኛ የሆነች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን በሰማዕታት ደም ትፈካለች፡፡ ወገኖች መጠራታችሁን ተመልከቱ
እንደሰው ጥበብ ጠበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች፣ ባላባት የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም፡፡
ስጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ፤ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ፡፡

ለገሰ፡ በቃህ ዝጋ (ሰይፍን ይዘረጋበታል)

ዕዝራ፡ ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ሰይፍህን እንደጓደኛህ ወደ አፎቱ ብትመልሰው ይሻልሃል፡፡
ለገሰ፡ ማነህ ደምስ! ና ወዲያ ውሰድልኝ....እነዲያውም ቆይ ተወው እኔ ራሴ እቶን ውስጥ እማግደዋለሁ፡፡ አንተ
እነርሱን ወስደህ አንገታቸውን ቅላቸው፡፡

ካሌብ፡ ወንድሞቼንና እህቶቼ ይቅር በሉኝ!! በሰማይና በምድር በፊታችሁ በደልኩ፤ የስጋ ፍላጎቴ ይመቻችልኝ
መስሎኝ ለሀብት ስል ሸጥኋችሁ፤ እንደ ዴማስ ጠፍቼ እንደ ይሁዳ ሞቼ፣ እንዳልቀር እባካችሁ
ስለመኃኔአለም፣ ስለእመቤታችን ፣ ስለቅዱሳን መላዕክት፣ ስለጻድቃን ሰማዕታት ብላችሁ ይቅር በሉኝ!!!

ሶምሶን፡ አይዞህ ካሌብ ፀፀት ንስሐ ነው፡፡ እንኳንም መበደልህ ተሰማህ እንጂ እኛ ይቅር ብለንሃል፡፡

አስቴር፡ ተነስ ወንድሜ የኛ ሐዘናችን የነበረ እኛን መበደልህ ሳይሆን ጠፍተህ መቅረትህ ነበር፡፡ እንደ ፈያታዊ ዘየማን
በዚች ባለቀች ሰዓት ወደ ሞት ስንነዳ መመለስህ በጣም አስደስቶናልና ይቅር ብለንሃል፡፡

አብነት፡ (ወደ ሰማይ እየተመለከተ) እማማ፣ አባባ በሰይፍ ያለቃችሁ ወገኖች ደማችሁ ጎልቶ ታየኝ፤ ድምጻችሁ አካል
ነስቶ ተሰማኝ፤ ብክደው ሊከዳኘ፤ ብይዘው ሊያፅናናኝ፡፡ የሰጣችሁኝን ውርስ ለማን ላስረክበው? (ወደ ሕዝቡ
ዞሮ) ንገሩኝ እስኪ አባቴ እውን ሞተ? እማማ እውን ተለየችኝ? አጎቴስ ቆዳው ተገፈፈ? እስኪ ንገሩኝ! እዝራ
ብናኝ ሆነ? እነ አስቴር፣ እነ ቤቴል የት ገቡ? ንገሩኝ እንጂ በሉ ንገሩኝ!!
ተመልካች፡ ሁሉም ሞተዋል፡፡
አብነት፡ አልሞቱም በፍጹም አልሞቱም፡፡ በርግጥ በስጋ ሞተዋል፤ እኔ ግን አገኘኋቸው፤( ወደ ውርሱ እየተመለከተ)
አዎ አገኘኋቸው፤ የመሞታቸው ምክንያት በደማቸው ከትበው ለኛ ሊያስተላልፉ ያሉትን ይህ ንዋየ
ቤተክርሰቲያን ነው፡፡ (ወደ ሕዝቡ ዞሮ) አንተ ያባቴ ቡቃያ እዳ አለብህ፤ የነአባባ የሞት እዳ፤ የነ አባባ የውርስ
እዳ!! ማነው የአባባን የውርስ እዳ የሚጠብቅ? አንተ ቡቃያ ሰይጣን መጥፎ ዘርን ሊዘራብህ ክህደት
ሊጠናወትህ ተነስቷልና ላትክድ ቃል ግባ!!

You might also like