You are on page 1of 31

አድርገህልኛልና

አድርገህልኛልና በቸርነትህ
2x
አመሰግንሃለሁ እልል እልል
ለዓለም ዓለም አማኑኤል 2x
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም
ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
የችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ
እረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈፅሞ አራቅህልኝ የልቤን ትካዜ

1
አድርገህልኛልና
አድርገህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሃለሁ እልል እልል
ለዓለም ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቂያለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ

2
አድርገህልኛልና
አድርገህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሃለሁ እልል እልል
ለዓለም ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ
በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባህሪ እፁብ ለአንተ ስራ

3
አድርገህልኛልና
አድርገህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሃለሁ እልል እልል
ለዓለም ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም
አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይገባሀል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሀል
ደሀ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎድል እንደገና

4
አድርገህልኛልና
አድርገህልኛልና በቸርነትህ
2x
አመሰግንሃለሁ እልል እልል
ለዓለም ዓለም አማኑኤል 2x
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም

5
ቅዱስ ሚካኤል ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ቅዱስ ሚካኤል /3/
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ 2x
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
አንተ ስለሆንክ ………………ሚካኤል
የአምላክ ባለሟል……………ሚካኤል
ልመናህ ፈጥኖ………………..ሚካኤል
ከአምላክ ያቀርባል……………ሚካኤል
የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው
ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው
6
ቅዱስ ሚካኤል ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ቅዱስ ሚካኤል /3/
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ 2x
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
ደዌ የፀናበት………………….. ሚካኤል
በአንተ ይድናል……………….. ሚካኤል
በአደባባይህ ……………………ሚካኤል
ምስክር ሆኗል ………………….ሚካኤል
በቤትህ መጥቶ የተማፀነ
በቃል ኪዳንህ ከሞት አፍ ዳነ
7
ቅዱስ ሚካኤል ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ቅዱስ ሚካኤል /3/
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ 2x
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
ከአምላክ ተሰጥቶህ………………. ሚካኤል
ክብርህ ያበራል……………………. ሚካኤል
ለጎስቋላው ሰው ………………………ሚካኤል
መጠጊያ ሆኗል…………………… ሚካኤል
ትንሽ ትልቁ ደሃው ሀብታሙ
ለምኖ አግኝቷል ከአምላክ በስሙ
8
ቅዱስ ሚካኤል ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ቅዱስ ሚካኤል /3/
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ 2x
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
በብሉይ ኪዳን .................. ሚካኤል
ከአምላክ ተልከህ ………………ሚካኤል
ህዝብ እስራኤልን ………………ሚካኤል
ነፃ ያወጣህ ……………………..ሚካኤል
በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ
በታምራትህ ትፈውሳለህ
9
ቅዱስ ሚካኤል ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ቅዱስ ሚካኤል /3/
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ 2x
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
ባለመድኃኒት………………………..ሚካኤል
ያቃተውን …………………………..ሚካኤል
ፈዋሽ ፀበልህ …………………….. ሚካኤል
ሆኖኛል ኃይል…………………….. ሚካኤል
እንደ መፃጉ ድህነት አገኘው
ፈውሰህኛል በአንተ ተመካው
10
ቅዱስ ሚካኤል ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ቅዱስ ሚካኤል /3/
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ 2x
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ

11
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
በአካለ ስጋ እና በአካለ ነፍስ 2x
በአካለ ነፍስ ያሉ
ለፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
የእግዚአብሔር አይኖቹ ጻድቃንን ከማየት
ጆሮቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች
በምልጃቸው እንመን አናመንታ አንዳች

12
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
በአካለ ስጋ እና በአካለ ነፍስ
በአካለ ነፍስ ያሉ
ለፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
የዚህ ዓለም መከራ ሳያሳቅቃቸው
እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው
ሰማያዊ ተስፋ ስለሚታያቸው
በፈተና ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው

13
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
በአካለ ስጋ እና በአካለ ነፍስ
በአካለ ነፍስ ያሉ
ለፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
ኃጥኡ ነዌ እንኳን በሲኦል እያለ
ስለወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ
እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ
ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ

14
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
በአካለ ስጋ እና በአካለ ነፍስ
በአካለ ነፍስ ያሉ
ለፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
ቀዝቃዛ ውኃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም
የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም
ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል
አምነን እንፈፅመው ዋጋ ያሰጣል

15
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
በአካለ ስጋ እና በአካለ ነፍስ
በአካለ ነፍስ ያሉ
ለፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

16
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደ ደረሰ 2x
ከ’ራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ

ሕልምንም አለመ ታላቁን ራዕይ


መሰላል ተተክሎ ከምድር እስከ ሰማይ
ሲወጡ ሲወርዱ መላእክት በእርሷ ላይ
እግዚአብሔርም ቆሞ ከላይ ከጫፏ ላይ
17
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደ ደረሰ
ከ’ራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ

የአባቶችህ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ


ይህንን ምድር ለእርስትህ እሰጥሃለሁኝ
ዘርህ እንደ አሸዋ በምድር ይዘራል
በአራቱም ማእዘን ሕዝብህም ይሆናል
18
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደ ደረሰ
ከ’ራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ

አበው በምሳሌ እንደ ተናገሩት


ከምድር እስከ ሰማይ አምላክ የዘረጋት
በላይዋ ተቀምጦ በግልፅ የታየባት
የያዕቆብ መሰላል እመቤታችን ናት፤
19
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደ ደረሰ
ከ’ራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ

ሰማይና ምድር የሚታረቁባት


ወልደ እጓለ እመሕያው የተወለደባት
መላእክት ከሰማይ በአንድ የዘመሩላት
ታላቋ መሰላል እመቤታችን ናት፤
20
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደ ደረሰ
ከ’ራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ

21
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
2x
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
ምሳሌ የሌለሽ ……………………….ነይ እመቤቴ
ዘመዴ ነሽ ……………………………ነይ እመቤቴ
ያን ክፉ ዘመን …….……………….ነይ እመቤቴ
ያለፍኩብሽ ………………………….ነይ እመቤቴ
በፍቅርሽ እሳት ……………………….ነይ እመቤቴ
ልቤ ነደደ ………………………………ነይ እመቤቴ
እናትነትሽን …………………………….ነይ እመቤቴ
ስለወደደ ……………………………….ነይ እመቤቴ
22
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
የሰውስ ጉልበት ……………………….ነይ እመቤቴ
ምን ይረባኛል…………….……………ነይ እመቤቴ
ሰረገላዬስ…….………………………...ነይ እመቤቴ
መች ያድነኛል …………………………ነይ እመቤቴ
ከተሠወረ……………………………...ነይ እመቤቴ
ክፉ መከራ………………………………ነይ እመቤቴ
እድናለሁኝ …………………………….ነይ እመቤቴ
አንችን ስጠራ ………………………….ነይ እመቤቴ
23
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
ለስንፍናዬስ……………………….ነይ እመቤቴ
መቼ ልክ አለው…………….……ነይ እመቤቴ
ስለ በደሌ…….……………………ነይ እመቤቴ
እተክዛለው …………………………ነይ እመቤቴ
ለአነጋገሬ ……………………………ነይ እመቤቴ
ማጣፈጫ ነሽ…………………………ነይ እመቤቴ
ተሰምቻለው…………………………ነይ እመቤቴ
ድንግል ሆይ ስልሽ……………………ነይ እመቤቴ
24
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
ለመንገዴ ስንቅ……………………….ነይ እመቤቴ
ለራቤ መርሻ…………….……………ነይ እመቤቴ
ለታመመ ሰው.………………………...ነይ እመቤቴ
ነሽ መፈወሻ …………………………ነይ እመቤቴ
የተማጸነ ……………………………...ነይ እመቤቴ
በስምሽ አምኖ …………………………ነይ እመቤቴ
ማን አፍሮ ያውቃል ………………….ነይ እመቤቴ
ፊትሽ ለምኖ………………………….ነይ እመቤቴ
25
በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ

በጎ መዓዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ 2x
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ

26
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የናሆም መድኃኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ 2x
ማርያም እወድሻለሁ
ተጨንቂያለሁ ልንገርሽ
ምስጢረኛዬ እናቴ ነሽ
ሰው ያልሰማውን ብርቱ ምስጢር
ድንግል ሆይ ላንቺ ላማክር
ለቁስለኛውም መድኃኒቱ
የአዳም ዘር ሁሉ ነሽ ሕይወቱ
መፍትዬ አለ በእጅሽ
ተንበርክኬ ልማጸንሽ
27
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የናሆም መድኃኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ
ማርያም እወድሻለሁ
ሳልናገረው ይገባሻል
የውስጤ ሁሉ ይታይሻል
ድረሽ እናቴ ተራጅኝ
ያላንቺ ለኔ ማን አለኝ
ደስታዬ ደስታ የሚሆነው
በሃዘኔም የምጽናናው
አንቺ ከእኔ ጋር ስለሆንሽ
ተጽናንቻለሁ በስምሽ
28
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የናሆም መድኃኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ
ማርያም እወድሻለሁ
ወንድሞቼ እንኳን ቢሸጡኝ
ሰው ሁሉ ጠላት ቢሆነኝ
በእመአምላክ ሃይል ተምሬሃለሁ
በጠላቴ ላይ ሰልጥኛሃለሁ
የረሱኝ በሙሉ ያስቡኛል
የተጣሉኝም ያከብሩኛል
አንች አንግሰሽኝ አልወድቅም
እቆማለሁ ዘለዓለም
29
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የናሆም መድኃኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ
ማርያም እወድሻለሁ
መንገዴ ረዝሞ ደክሜብሽ
መከራው በዝቶ ታምሜብሽ
ወድቄ ሳዝን ድረሺልኝ
ለባሪያሽ ሃይሉን እንድትሰጪኝ
ፍቅርሽ በውስጤ ተንሰራፋ
በእናትነትሽ ልቤ ሰፋ
የሚለያየን ማንም የለም
ማርያም ልበልሽ ለዘለዓለም
30
የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ

የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ


የናሆም መድኃኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ 2x
ማርያም እወድሻለሁ

31

You might also like