You are on page 1of 1

የዓድዋ ድል ትልቅ ድል ነው። የአጼ ምኒሊክ እና የኢትዮጵያዊያን የማንነት ገጽታ ተንጸባርቆበታል። በተራቀቁት

የአውሮፓ አገሮችና በቀኝ ግዛት ውስጥ ለሚማቅቁ ህዝቦች ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ስሜቶችን ፈጥሮአል። ሀፍረትን እና
ድፍረትን።
ገሀድ የወጣው የኢትዮጵያኑ ዝና ለተጨቆኑ ጥቁር ህዝቦች አርአያ ሆኖ ድቅድቁን የጭቆና ዘመን የተስፋ ብርሃን
የፍነጠቀበት ነው።
በምኒልክ የንጉሰ ነገስትነት ዘመን በተለይ በዓድዋ ጦርነት ዋዜማ ኢትዮጵያዊያኑ ሙሉ ለሙሉ አንድነታቸውን
ያረጋገጡበት ዘመን ወቅት ነበር። ይህ አንድነት በዓድዋ ላይ ለዘወትር ጥቁር ህዝቦችን ሊያኮራ የቻለና ሲያኮራ የሚኖር
ድል ያስመዘገበ ነው።
ሰራዊቱ ለአገሩ ውድ ሂዎቱን መስዋዕት ለማድረግ ይሽቀዳደም የነበረው በምኒልክ ዘመን ተፈጥሮ በነበረው የህዝቦች
ትስስር እና ፍቅር ነበር ለማለት ይቻላል።
እንኳን ለ 125 ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።

You might also like