Professional Documents
Culture Documents
Hermenutics Handout For PTC
Hermenutics Handout For PTC
1፡20)
Hermeneutics
Compiled by
1
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
የትምህርቱ ዓላማ
የዚህ ኮርስ ዋና ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለንተናዊ ጥቅም ለመረዳት የሚያግዙ መሮሆዎችን በማቅረብና በማብራራት
ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ታማኝነት በተሞላበት መንገድ በመተርጎም በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ተግባራዊ
የትምህርቱ አጭር ገለጻ፡-የዚህ ኮርስ ትኩረት በዋናነት የሥነ አተረጓገምን (Hermentuics)ችግርን በተመለከተ መጽሐፍ
ቅዱስ ለእኔ ምን ይላል ከማለታችን በፊት መጽሐፍ ቅዱስ ለቀድሞዎቹ ተቀባዮች ምን ብሎ ነበር ብሎ በመጠየቅ
ከሐቲት(Exgesises) በመጀመር እና ለዛሬውስ ምን ዓይነት ትርጉም ይሰጣል የሚልን መርህ በመከተል ተማሪዎች
መጽሐፍ ቅዱስን ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ በመረዳት በግል ሕይወታቸውና በአገልግሎታቸውም እንዲተገብሩ ማበረታታት
ነው፡፡
የትምህርቱ ማስተማሪያ
መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለንተናዊ ጥቅሙ ማጥናት፡ ከጎርደን ዲ.ፊ. እና ዳግላስ ስቱአርት SIM ማተምያ፡
USA:1993
2
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
the course
የመተረጎም
አስፈላጊነት
ለትርጉም መሠረታዊ
መሣርያ
መልእክቶች ዓውደ ጥያቄና ሙከራ 1(10%)
ንባባዊ አስተሳሰብ መልስ
መልእክቶች የሥነ ውይይት
አፈታት ጥያቄዎች ገለጻ
የብሉይ ኪዳን ጥያቀና
ትረካዎችና ተገቢ መልስ
አጠቃቀማቸው ውይይት
ገለጻ
እሁድ የሐዋርያት ሥራ ፡- ጥቄና መልስ
የታሪካዊ አርኣያነት የቡድን ሥራ
ጥያቄ ገለጻ
ወንጌላት፡- ብዙ
አቅጣጫዎች ያሉት
አንድ ታሪክ
ምሳሌዎች፡- ጥያቄና ሙከራ 2(10%)
መልእክቱን አገኘህ? መልስ
ውይይት
ገለጻ
ሕግ(ሕግጋት)፡- ጥያቀና
የእስራኤል የቃል መልስ
ኪዳን ትዕዛዝ ውይይት
ገለጻ
ቅዳሜ ነቢያት፡-በእስራኤል ጥያቄና
የቃል ኪዳን መልስ
አስከባሪዎች ውይይት
ገለጻ
መዝሙረ ዳዊት ፡- ጥያቀና Relection (10%)
የእስራኤልና የእኛም መልስ
ጸሎቶች ውይይት
ገለጻ
ጥበብ፡-ያኔ እና ጥያቄና
አሁን መልስ
ውይይት
የዮሐንስ ራእይ፡- የቡድን ሥራ የመጨሻው የቡድን
እሁድ የፍርድና የተስፋ ገለጻ ሥራ(Final Project)
ምስሎች ገለጻ (30%)
የመጨረሻ ፈተና(Final)
(30%)
ጠቅላላ ዉጤት እና
አስተያየት(Feedback)
3
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
የስም ጥሪ ደንብ
ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚቀርቡ የመማር ማስተማር ሥራዎች፣በጥያቄና መልስ፣በቡድን ውይይት እና ከሌሎች ተግባሮች
ያገኙትን አዲስ ዕውቀት በአንድ ገጽ ወረቀት ላይ ፍሬ ሐሳቡን ያቀርባሉ፡፡ከአንድ ገጽ መብለጥ የለበትም፡፡
4
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
የመጨረሻው የቡደን ሥራ ከመልእክት ክፍሎች ቡድኑ ተስማምቶ በምመርጠው ክፍል ተመርኩዞ የሚሠራ ይሆናል፡፡ስለዚህ
የመጀመሪያው እርምጃ ክፍሉን ተስማምቶ መምረጥ ይሆናል፡፡
በመቀጠልም በክፍል ውስጥ ስለ መልእክቶች በተነጋገርነው መሠረት የመልእክቶችን ዓውደ ንባባዊ አስተሳሰብን እና
የመልእክቶችን ሥነ አፈታት ጥያቄዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የተማሩትን ተግባራዊ ለማድረግ እርምጃ ይወሰዳል፡፡
1. ሐቲት(Exegetical idea)
2. ሥነ አፈታት(Hermeneutical idea)
3. ተዛምዶ(Application)
አንደኛው ቀን
ብዙውን ጊዜ “መጽሐፍ ቅዱስን መተረጎም አያስፈልግም ዝም ብለህ አንብበውና የሚለውን ፈጽም” ሲባል መስማት
የተለመደ ነው፡፡በመጀመሪያ መገንዘብ ያለብን የመተርጎም ዓላማው ልዩ ምሥጢር መፈለግ እንዳልሆነ መሆኑን ነው፡፡
የምንባቡን ግልጽ ፍች ማግኘት ነው እንጂ፡፡
5
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
1. የአንባቢ ባሕርይ
አንባቢ ሁሉ ተርጓሚ ነው
አንባቢው ሁልጊዜም በአከባቢ የሚሆነውን ከማስተዋልም ግንዛቤ ሊያገኝ ይችላል
ሁሉም ግልጽ ፍችዎች ለሰው ሁሉ እኩል ግልጽ አይደሉም
ለምሳሌ 1 ቆሮ.14፡34-35
2. የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ
መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደ ክርስቶስ ሰብአዊና መለኮታዊ ባህርይ አለው፡፡
በሰው ልጆች ታሪክ፣ባህል እና ቃላት የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
ሁለት ደራስዎችም አሉት
እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ሰብአዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጽታዎች ለጠቅላላ የሰው ልጆች ሁኔታዎች የሚናገር
መሆኑ ነው፡፡
እግዚአብሔር አሉ የተባሉትን የተግባቦት መንገዶችን ሁሉ ለመጠቀም መርጦአል
እነዚህም የታሪክ ትረካ ፣ የዘር ሐረግ፣ ዜና ፣ሁሉም ዓይነት ሕግጋት፣ሁሉም ዓይነት
ግጥሞች፣ምሳሌዎች፣መልእክቶች፣ስብከቶች እና ገላጭ ትንበያዎች ናቸው
ለ 1500 ዓመታት በተለያዩ ሰዎች እና ሁኔታዎች አልፎ መምጣቱ ትርጉም የሚሻ ያደርገዋል
የተርጓሚ ሥራዎች
6
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ሁለተኛ ቀን
7
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
የመልእክቶቹ ባሕርይ
1. አንድ ምንባብ ለደራሲው ወይም ለተደራሲያኑ ያስተላለፈውን መልእክት ለእኛ ማስተላፍ አይችልም፡፡ ለዚህም ነው
ሁልጊዜም ከሐቲት መጀመር ያለብን፡፡
2. ከመጀመሪያው ምዕተ ዓመት መቼት ጋር በሚጣጣም ሁኔታ ውስጥ በሚንሆንበት ጊዜ ለእኛ የሚለው
የእግዚአብሔር ቃል ለእነርሱ ያገለገለው ነው፡፡ ሮሜ 3፡23፣ኤፌ 2፡8 እና ቆላ.3፡12 ዛሬም ያው ነው
8
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
5. በጥንቃቀ ማድረግ እስከተቻለ ድረስ በየትኛው የአዲስ ኪዳን ጸሐፍ ፊት ክፍት የነበሩትን ባህላዊ አማራጮችን
መወሰን
6. አንዳንድ ጊዜ በግልጽ የማይታዩትን የመጀሪያውና የሃያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን ባልላዊ ልዩነቶቸን ለመለየት መጣር
7. በመጨረሻም በዚህ ጉዳይ ላይ ክርስቲያናዊ ቸርነትን መላበስ
ሦስኛው ቀን
የቡድን ውይይት ጥያቄዎች
1. በብሉይ ኪዳን ትረካዎች ውስጥ የሚታስታውሱአቸውን ገጸ ባህርያት ተወያዩና ዘርዝሩ(4 ደቂቃ)
2. ብዙውን ጊዜ ሰባኪዎች እና አስተማሪዎች የብሉይ ኪዳን ታሪኮችን ስሰብኩ ምን ዓይነት ስህተቶችን ስፈጽሙ
ታስተውላላችሁ?(5 ደቂቃ)
9
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ በመፈለግ የሚፈጽሟቸው ስምንት በጣም የተለመዱ ስህተቶች
1. ስውር ፍች መፈለግ(allegorizing)
2. ዓውደ ንባቡን መጣስ(decontextualizing)
3. ምርጫ(selectivity)
4. የተሳሳተ ወህደት(false combination)
5. ዳግማዊ ብያኔ መስጠት(redefinition)
6. ከቀኖናዊ ያለፈ አተረጓገም(extracanonical authority)
7. ምንባቹን ሥነ ምግባራዊ ማድረግ(moralizing)
8. ግላዊ ማድረግ(personalizing)
መጽሐፍ ቅዱስን በግድ የለሽነት አታንብበው! ሁሉንም የራስህ አታድርገው! እግዚአብሔር የሚያዝህን ጉዳይ ፈጽሚ፡፡
አራተኛው ቀን
የሐዋርያት ሥራ ፡ የታሪካዊ አርኣያነት ጥያቄ
10
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
እንደ ታሪክ መጽሐፍ ሁሉ የሐዋርያት ሥራንም ስናጠና ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡እንደ ብሉይ ኪዳን ትረካዎች
ሁሉ ሐዋርያት ሥራን ሙሉ በመሉ ለሕይወታችን ምሳሌ ለማድረግ የሚናጠና ከሆነ ግራ መጋባታችን አይቀረ ነው፡፡
የሐዋርያት ሥራ ሒቲት
የሐዋርያት ሥራን ሐቲት ለመሥራት መጠየቅ ያለብን ጥያቄዎች ሁለት ናቸው
1. ምን ተከሰተ?(ታሪኩን ከዓውዱ መመልከት)
2. ለምን ተከሰተ?(የክስተቱን ዓላማ ከጸሐፍው ፍላጎት አንጻሪ መመልከት)
የሐዋርያ ሥራ ቅኝት(አሰሳ)
ለምን የሚለውን ጥያቄ ሉቃስ ራሱ በሰጠን አከፋፈል ተመሥርተ እናነሳለን፡፡ ብዙውን ጊዜ የሐዋርያት ሥራን ሉቃስ
በጴጥሮስ ምዕ.1-12 እና
ጳውሎስ 13-28 ተመሥርቶ ባደረገው ትኩረት ላይ ተመሥርቶ ሲከፈል ኖሮአል፡፡ወይም ደግሞ በወንጌሉ
መልክዓ ምድራዊ መስፋፋት ላይ በመመሥረት አልያም ቁልፍ ቃሉን 1፡8 በማድረግ መክፈል የተለመደ
ነው፡፡ይኼውም፡-
ም.1-7 ኢየሩሳሌም
11
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
በክርስቶስ አገልግሎት ውስጥ የእግዚብሔር መንግሥት ጽንሰ አሳብ ምን እንደሆነ ሳትገነዘብ ወንጌላትን
በአግባቡ እተረጉማለሁ ብለህ አታስብ፡፡
ይህም የሆነው በመጀመሪያ ደረጃ የጠቅላላው አዲስ ኪዳን መሠረታዊ የሥነ መለኮታዊ መዋቅር ሥነ
ፍጻሜያዊ(Eschatological) መሆኑን መገንዘብ ይኖርብሃል፡፡
ሥነ ፍጻሜ እግዚአብሔር ይህንን ዘመን ወደ ፍጻሜ የሚያመጣበት ጊዜ ነው፡፡በክርስቶስ ዘመን የነበሩት
አይሁድ በአብዘኛው ሥነ ፍጻሜያዊ አስተሳሰብ ነበሩአቸው፡፡ይህም ማለት እግዚአብሔር ወደ ታሪክ ምዕራፍ
በመዝለቅ ይህን ዘመን ከፍጻሜ በሚያደርስበትና መጭውን ዘመን ተግባራዊ በሚያደርግበት የጊዜ ቋፍ ላይ
እንደሚገኙ ያስቡ ነበር፡፡
ባህርይው ባህርይው
12
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ፍጻሜ
ተጀመረ ተግባራዊ ሆነ
መጭው ዘመን
ይህ ዘመን (እያለፈ) (ፍጹም የማያልፍ)
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለሚገኙ ብዙ ምንባቦችና በተለይም ለክርስቶስ ትምህርት ሥነ አፈታት ቁልፉ በዚህ
ዓይነት ውጥረት ውስጥ መገኘት ነው፡፡
አምስተኛው ቀን
ምሳሌዎች ለረዥም ዘመናት በተሳሳተ መንገድ ሲተረጎሙ የቆየበት ምክንያት ክርስቶስ ራሱ እንደ ተናገረው ከዓላማቸው
አንጻር ልሆን ይችላል(ማር.4፡10-12፣ማቴ.13፡10-13 እና ሉቃስ 8፡9-10)፡፡በምሳሌ የማስተማሩ ዓላማ ምን እንደሆነ
13
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
በተጠየቀ ወቅት በውስጥ ላሉት ምሥጢራዊ መልእክት እንደያዙና በውጭ ያሉትን ሰዎች ልብ እንደሚያደነድኑ የሚያመለክት
ምላሽ የሰጠ ይመስላል፡፡
እነዚህን መንፈሳዊ ምሥጢሮችን በጥንቃቄ ትርጉም ካልፈለግን በቀላሉ የራሳችንን መላምት እንዲንሰጥ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡
ኦገስትንን የመሰለ ምሁር የቤክርስቲያን መሪ ስለ ርኅሩኁ ሳምራዊ የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶአል፡-(ገጽ 139-140)
የምሳሌዎችን ሐቲት ለመረዳት የመጀመሪያ ሰዎችን ማወቅና እነርሱ በሰሙበት መንገድ መስማት እንዳለ ሆኖ የምሳሌዎችን
ባህሪይም ለይቶ ማወቅ አለብን፡፡
ምሳሌ ተብሎ የተተረጎሜው የግርኩ ቃል “ሜታል” ሲሆን በአማርኛ “ምሳሌ”ዎችን ብቻ ለማመልክት ሳይሆን ለይቤያዊ
አነጋሮችና እንቆቅልሾችም ጭምር የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
የምሳሌዎች ባሕርይ
በእኛ ዓውድ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች ገጠመኞታቸውን እና ቀልዶችን እየተናገሩ አውዱ በደንብ ስገባን በሳቅ ወይም በሀዘን
ምላሽ ልንሰጥ እንችላለን፡፡(ዋናው መስመር ተይዞአል…) ምሳሌዎችም ኢየሱስ በተናገረበት ዓውድ እንዲሰጡ የተፈለገው
ምላሽ እንዲሰጡ አስችሎአቸዋል፡፡እኛም የማጣቀሻ ነጥቦችን ወይም የታሪኩን ባለቤቶቸን ማግኘት ይጠበቅብናል፡፡
ስምኦን የተባለው ፈሪሳዊ ለክርስቶስ ያዘጋጀው ግብዣ(ሉቃስ 7፡40-42) በዚህ ምሳሌ ውስጥ የማጣቀሻ አሳቦች አሉ፡-
እነዚህም ገንዘብ አበዳሪውና ሁለቱ ተበዳሪዎች ናቸው፡፡ ዝምድናቸውም ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደ አበዳሪው ነው፡፡
ጋለሞታይቱና ስምኦን እንደ ሁለቱ ተበዳሪዎች ናቸው፡፡
ሁለቱም የተለያየ ነገር ከምሳሌ እንደሰሙ ማስተዋል አያዳግትም፡፡ የፍርድ ቃል እና የእግዚአብሔርን ምህረት
2. አድማጭን መለየት
የአንድ ምሳሌ ፍች መጀመሪያ ከተደመጠበት ሁኔታ ጋር ስለሚያያዝ አድማጮችን መለየት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡በእንዲህ
ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ የአተረጓገም ተግባር ሦስት ነገሮችን ያካትታል
14
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ሉቃስ 10፡25-35 ርኅሩኅ ሳምራዊ ፡- የማጣቀሻ ነጥቦች ሁለት ብቻ ናቸው፡፡የጠጎዳው ሰውዬውና ሳምራዊው፡፡ ዋናው
ትምህርቱ ፍቅር እንደሌለው የሚታየው የተጎዳውን ሰውዬ ባለመርዳቱ ሳይሆን ሳምራዊያን በመጥላቱ (እና ካህናትን በመናቁ)
ነበር
የጠፋው ልጅ ታሪክ (ሉቃስ 15፡11-32)፡- ሦስት ማጣቀሻ ነጥቦች ያሉት ሲሆን እነዚህም አባትና ሁለት ልጆቹ ናቸው፡፡
መልእክቱ እግዚአብሔር የጠፋትን ኃጢአተኞችን ይቅር ማለቱ ብቻ ሳይሆን በደስታ ይቀበላቸዋል የሚል ነው፡፡ራሳቸውን
እንደ ጻድቅ ሚቆጥሩ ሰዎች የጠፋውን ልጅና የአባቱን ደስታ ካልተጋሩ ጻድቃን አለመሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
ዋናው መርህ የማጣቀሻ ነጥቦቸንና የመጀመሪያ አድማጮችን የመለየት ጉዳይ ነው፡፡ለዚህም ቁልፉ የማጣቀሻ ነጥቦችን
በግልጽ እስከሚታዩበት ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ ማንበብ ነዉ፡፡ይህም በበኩሉ የመጀመሪያ አድማጮቹ እነማን እንደ ነበሩ
ፍንጭ ይሰጣል፡፡
ማቴ 20፡1-16 ሦስት የማጣቀሻ ነጥቦች አሉት፡- የመሬቱ ባለቤት፣ቀኑን ሙሉ የሠሩና አንድ ሰዓት የሰሩ ሲሆን መልእክቱ
ከጠፋው ልጅ ታሪክ ጋረ ተመሳሳይ ሲሆን እግዚአብሔር ቸር እንደሆነና ጻድቃን በልግስናው ቅር መሰኘት እንደማየገባቸው፡፡
ከማጣቀሻ ነጥቦቹ ወይም ዝርዝሮቹ አንዱ ሳይሆን ጠቅላላው ምሳሌ ስለ እገዚአብሔር ባሕርይ አንድ ነገር ይነግረናል
የሚለውንና
ከኢየሱስ መምጣት ጋር የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ ሰዎች እንደቀረበ ክርስቶስ ያስተማረባቸው መሆኑን መገንዘብን
ይጠይቃል
እንደ ሁልጊዜው ምሳሌዎቹ አሁን ባሉባቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዓውዶች መርካት አለብን
ሌላው ሥነ አፈታታዊ አሳቦችን የክርስቶስ ምሳሌዎች ሁሉ በሆነ መንገድ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሚያስተምሩ
መሣርያዎች ከመሆናቸው ጋር የተዛመደ ነው፡፡ስለዚህ ቀድሞውኑ እና ገና የሚሉ ሀረጎችን ያስታውሱ፡፡
ስድስተኛው ቀን
በውልና ማስረጃ ሰነድ እና በጋብቻ ቃል ኪዳን ሰነድ መካካል ያለውን አንድነት እና ልዩነትን ተወያዩና አቅርቡ፡፡
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከስድስት መቶ የሚበልጡ ትእዛዛት አሉ፡፡እነዚህም እስራኤላዊያን ለእግዚአብሔር ታማኞች
መሆናቸውን ለማሳየት የሚፈጽሟቸው ናቸው፡፡የሚገኙትም በዘጸ፣ዘሌ፣ዘኁ፣እና ዘዳ ውሰጥ ነው፡፡
15
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን ሕግ ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ስድስት የመነሻ መርሆዎች ማኖሩ ተገቢ ነው፡፡(ገጽ 156-
160)
እነዚህን መርሆዎች መጠበቁ የተሳሳተ የብሉይ ኪዳን ተዛምዶ በማስወገድ ፤ የሕግን የማስተማሪና እምነት- ገንቢ ባሕርያት
እንድትከተል ይረዳሃል፡፡(ገጽ 170)
1. የብሉይ ኪዳን ሕግ ሙሉ በሙሉ በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር በልጽጎ እንደ መጣልህ ቃል አስበው፡፡ የብሉይ ኪዳን ሕግን
ለአንተ እንደ ተላከ ቀጥተኛ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት አትውሰደው፡፡
2. የብሉይ ኪዳን ሕግ የአሮጌው ኪዳን መሠረት እና ከዚህም የተነሳ የእስራኤላዊያን ታሪክ መሠረት አድርገህ ተመልከት፡፡
በግልጽ እስካልታደሰ ድረስ የብሉይ ኪዳን ሕግ ለክርስቲያኖች እንደሚሠራ አድርገህ አትመልከት፡፡
3. የብሉይ ኪዳንን ሕግጋት እንደ ሙሉ ሕግጋት ሳይሆን እንደ ሞዴል አድርገህ ተመልከት፡፡
4. በብሉይ ኪዳን ሕግጋት ውስጥ የተገለጹትን የእግዚአብሔር ፍትሕ፣ፍቅርና ታላላቅ መመዘኛዎች በትኩረት
አስተውላቸው፡፡የእግዚአብሔር ምህረት ከመመዘኛዎቹ ትክክለኛነት እኩል መሆኑን አትዘንጋ፡፡
5. የብሉይ ኪዳንን ሕግጋት በነቢያት ወይም በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ እንዲጠቀስ አትጠብቅ፡፡
6. የብሉይ ኪዳን ሕግጋት የእስራኤል ሕዝብ በሚታዘዙአቸው ጊዜ በረከትን የሚያመጡ ለእስራኤል የተሰጡ መልካም
ስጦታዎች እንደሆኑ አስብ፡፡
የቡድን ወይይት፡ ትንቢት ምንድነው? ብዙ ጊዜ የትንቢት መጽሐፍትን መረዳት የሚያቅተን ለምን
ይመስላችኋል?
ነቢያት፡በእስራኤል የቃል ኪዳን አስከባሪዎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትንቢትን ርዕስ ይዘው የሚመጡ መጽሐፍት ከሌሎቹ ሁሉ በላይ በቁጥር በርከት
ያሉ ናቸው፡፡
እነዚህ የነቢያት መጽሐፍት ከ 760 እስከ 460 ዓ.ዓ በጥንቷ እስራኤል ዘመን የተከሰተ ታሪክ ነበር፡፡
እነዚህን መጽሐፍት በተሳሳተ መንገድ የሚንረዳባቸው ምክንያቶች ከአገልግሎታቸውና ከቅርጻቸው ጋር
በተያያዘ ነው፡፡
16
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ትንቢቶችን ለመረዳት ከሚያስፈልጉት ቁልፎች አንዱ ትንቢቶቹ ተፈጽመው እንዳለፉ መገንዘብ ነው፡፡ወደ
ኋላ ተመልሰን ለእነርሱ ገና የወደ ፊት ለእኛ ግን ያለፉትን ጊዜያት መመልከት ይኖርብናል፡፡
ነቢያት ቃል አቀባዮች
የታሪክ ችግር
ስለ ትንቢቶቹ ያለንን ግንዛቤ የሚያወሳስበው ሌላው ነገር ታሪካዊ ርቀት ነው፡፡ ከነገሮቹ ባሕርይ ሳቢያ ያን ጊዜ
ከነቢያቱ በጆሮአቸው ከሰሙአቸው እስራኤላዊያን ይልቅ በዛሬ ዘመን ያለን እኛ የእግዚአብሔርን ቃል
ለመረዳት እንቸገራለን፡፡ብዙውን ጊዜ ቃላቱ ምንን እንደ ተመለከቱና ለምንስ እንደሚያመለክቱ ማወቅ
ይሳነናል፡፡
የትንቢት አገልግሎት
እግዚአብሔር በእነዚህ የተጻፉት ቃላት ምንን እንደሚነግረን ለመረዳት በእስራኤል የነቢይ ሚናና አገልግሎት
ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡በእነዚህ ረገድ ሦስት ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል፡፡
ሐቲታዊ ተገግባር
በአጠቃለይ የትንቢት መጻሐፍት ጊዜንና ጥናትን የሚጠይቁ ናቸው፡፡ስለሆነም እነዚህን የትንቢት መጽሐፍትን
በሚንተረጉምበት ጊዜ ሦስቱን ውጫዊ የእርዳታ ምንጮች መዘንጋት የለብንም፡፡
1. የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
17
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
2. መጻሕፍት(Commentaries)
3. የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ(The Biblehandbooks)
ሰፊው ዓውድ፡-አስራ ስድስቱም የትንቢት መጻሕፍት ከረዥሙ የእስራኤል ታሪክ ውሰጥ ጥቅቶቹን ብቻ
(760-460 ዓ.ም) የሚሸፍኑ መሆናቸው አስገራሚ ነው፡፡
አሞጽ በ 760 ዓ.ዓ አካባቢ መልእክቶቻቸውን በጽሑፍ ካቆዩት ነቢያቶች የመጀመሪያው ሲሆን ሚልክያስ 460
ዓ.ዓ የመጨረሻው ነው፡፡ ቀጣዩን ጥያቄ መጠየቁ ተገቢ ነው፡፡በእነዚህ ሦስት መቶ ዓመታት ውስጥ የነቢያት
መልእክቶች የበረከቱት ለምንድነው? ወቅቱስ ምን ይመስል ነበር?
ከዚሁ ጋር በተያያዘ 760 አካባቢ እስራኤል ለረዥም ጊዜ በቆየው እርስ በእርስ ጦርነት ለሁለት ተከፍላ የሰሜኑ
መንግሥት (እስራኤል) የደቡብ መንግሥት(ይሁዳ)በመባል የተሰየሙበት ጊዜ ነበር፡፡
ከዚህም የተነሳ፡-
አሞጽ 765 ዓ.ም እና ሆሴዕ 755 ዓ.ም እስራኤል (የሰሜኑ) ክፍል ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ የማስጠንቀቂያ
መልእክት ቢያመጡም አንሰማም በማለታቸው በ 722 ለአሦር መንግሥት ተማረኩ፡፡
በመቀጠልም ይሁዳ(የደቡብ)መንግሥት ኃጢአቷ እየባሰ በመሄዱ እንደ ኢሳያሰ፣ኤርምያስ፣ኢዩኤል፤
ሚክያስ፤ናሆም፣ዕንባቆም፣ሶፎንያስ እና የመሳሰሉት ለአገልግሎት ተሰማሩ፡፡
በእንቢተኝነቷም ስለቀጠለች 587 ለባቦሎን ታልፋ ተሰጠች፡፡ ነቢያቶቹ ለእነዚህ ክስተቶች በቀጥታ ሰፊ
መልእክቶችን ያስተላለፉት ሲሆን መልእክታቸውን ለመረዳት ወቅቱን መገንዘቡ ወሳኝ ነው፡፡
በተጨማሪም የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት የትንቢት መልእክቶችን ለመረዳት ጠቃሚዎች
ናቸው፡፡
ቅርጾቹ
የሕግ ችሎት
ዋይታ
የተስፋ ቃል እና
ግጥም ናቸው፡፡
18
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
የዕብራይስጥ የግጥም ስልት ምን እንደምመስል ለመረዳት በብሉይ ኪዳን ግጥም ውስጥ ተደጋጋሚመው
የሚታዩትን ቀጣይ ሦስት ገጽታዎችን መመልከቱ ጠቃሚ ነው፡፡
“ከልባቸው ወደ እኔ አይጮሁም፤
በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ እግዚአብሔር ከእሰራኤልና ከይሁዳ የፈለገው ከእኛም የሚፈልገው ነው፡፡የሚልክያስ
4፡6 ማስጠንቀቂያ ዛሬም አልተነሳም፡፡
19
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ስምንተኛው ቀን
የቡድን ውይይት፡- የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ በአብዘኛው የአማኙ ማህበረተሰብ ተወዳጅ የሆነው ለምን
እንደሆነ ተወያዩና አቅርቡ፡፡
የመዝሙረ ዳዊት አተረጓገም ችግር የሚነሳው በቀማዊነት ከባሕርዩ ነው፡፡በቀዳማዊነት ዶክትሪንን ወይም
የሥነ ምግባርን ባሕርይን ለማብራራት አይደሉም፡፡ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች ይህንን ካለመረዳታቸው የተነሳ
በተሳሳተ መንገድ በሕይወታቸው ያዛምዱታል፡፡
የመዝሙራት ዓይነቶች
ሰቆቃዎች
20
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
የምስጋና
የውዳሴ
የደህንነት
የበዓላት
የጥበብ
የመተማመን
የእርግማን መዝሙሮች
ሐተታዊ ናሙና
የአንድን መዝሙር ቅርጽና መዋቅር መገንዘብ መልእክቱን ለመረዳት እንዴት እንደሚያግዝ ለማሳየት ሁለት መዝሙሮችን
መርጠናል፡፡
መዝሙር 3፡ ሰቆቃ
የምስጋና መዝሙር
የምስጋና መዝሙር ከሰቆቃ መዝሙር የተለያ ዓላማ ያላቸው ሲሆን 138 እንደ ምሳሌ ቀርቦአል፡፡
መግቢያ ቁ. 1-2
መከራ ቁ.3
ልመና ቁ.3
ነጻ መውጣት ቁ.6-7
ምስክርነት ቁ.4-5 እና 8
ማስጠንቀቅያ ፡-መዝሙራት ለመልካም ሕይወት ዋስትና አይሰጡንም፡፡በምድር ላይ ያለን ሕይወት ከመከራ ነጻ አይደለም፡፡
አንዳንድ ጊዜ በመዝሙራት የተሰጡ የዋስትና ቃላትን የመዝሙራትን ባሕርይ በአግባቡ ካለመረዳት በተሳሳተ
መንገድ በመተርጎም ግራ መጋባቶች ይስተዋላሉ፡፡
21
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ዘጠነኛው ቀን
ጥበብ ያኔ እና አሁን
የዕብራዊያን ጥበብ ብዙዎች የአሁኑ ዘመን ክርስቲያኖች ያልለመዱት ዓይነት ሥነ ጽሑፍ ነው፡፡
1. ጥበብ ምንድነው?
2. የጥበብ(የቅኔ መጽሐፍት) ምንድናቸው? ስንት ናቸው? ለእኛስ ምን ፋይዳ አላቸው?
3. ሰዎች ብዙውን ጊዜ የጥበብን መጽሐፍት በአግባቡ መረዳት የሚሳናቸው ለምን ይመስላችኋል?
ጥበብ በሕይወት መንፈሳዊ ምርጫዎችን ማካሄድና ትክክለኛውን እርምጃ መውሰድ ነው፡፡የጥበብ መጽሐፍት
በተለምዶ ሦስት ሲሆኑ አነርሱም መክብብ፣ምሳሌና ኢዮብ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ መዝሙረ ዳዊት፣መኃልየ
መኃልየ፣እና ሰቆቃዊ ኤርምያስም የጥበብ መጽሐፍ እንደሆኑ ማሰቡ ትክክል ነው፡፡
ጠቢብ ማነው
የጥበብ አስተማሪዎች
በጥንቷ እስራኤል አንዳንድ ሰዎች ጥበብን ለመማር ብቻም ሳይሆን ለማሳተማሪም ይተጉ ነበር፡፡
ከዚህም የተነሳ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ እነዚህ ይልኳቸውና እነርሱም እንደ ልጆች ያስተምሩአቸው
ነበር፡፡ከእነዚህም መካከል በጥንቷ እስራኤል በተለይም በራስ ንጉሥ መመራት ከጀመረችበት 1000 ዓ.ዓ
አካበቢ ከተነገሩት ጥቅቶቹ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተጽፎ ተሰጥቶናል፡፡(ዘፍ.48፡8) ላይ ዮሰፍ
የፈሪኦን አባት ተብሎ ሲጠራ ዲቦራም (መሳ.5፡7) የእሰራኤል እናት ተብላለች፡፡
22
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
ጥበብ በቤት
ከላይ የተነሱ አሳቦች እንዳለ ሆኖ የጥበብ ዋናው ቦታ ቤት ውስጥ በወላጆቻቸው በኩል ነበር፡፡
የጥበብ ገደቦች
መክብብ፡ጭፍግ ጥበብ
ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ መጽሐፍ ለምን መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ ተሰጠን የሚል ጥያቄ ከተነሳ ከሌሎች
የመጽኸፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር እንዲናነጻጽሪ እና አጠቃላይ መልእክቱን እንዲናገኝ ነው፡፡
ስለዚህ አንባቢ በሰባኪው ጥበብ ባለመርካት የጠቅላላውን የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍል ለማግኘት
ምርመራ ማካሄድ ይጠበቅበታል፡፡በእርግጥ በማሰርያው ላይ 12፡13 የነገር ሁሉ ፍጻሜ እግዚአብሔርን
መፍራትና ትዕዛዙን መጠበቅ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡
በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር እውነት በተነጻጻርነት የቆሙ የተሳሳቱ አሳቦች የሚገኙት በመክብብ
ውስጥ ብቻ አይደለም፡፡በመጽሐፌ ኢዮብ ጓደኞቹ ብዙ የተሳሳቱ ምክሮችንንና የማጠቃለያ አሳቦችን
ሲያቀርቡ እንመለከታለን፡፡
23
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
1. መከራ እና ሥቃይ ሁልጊዜም የኃጢአት ውጤት አይደሉም ሮሜ 8፡34-እና በዓለም ሳላች መከራ
አለባችሁ
2. እግዚአብሔር ክፋንና ደጉን የሚቆጣጠር ልዑል አምላክ ነው፡፡
3. እግዚአብሔር ጥያቄዎቻችንን ሁሉ የመመለስ ግዴታ የለበትም
4. እግዚአብሔር ክፉውን ለበጎ መለወጥ የሚችል አምላክ ነው
መጽሐፈ ምሳሌ ዋነኛ የጥበብ ምንጭ እና ሚዛናው በሆኑ የሕይወት ተግባራዊ እሰቶች ላይ ቅዲሚያ የሚሰጥ
ነው፡፡በንጽጽሪነቱም የታወቀ ነው፡፡ሞኙን ከጠቢብ፣ኃጢኡን ከጻድቁ….
24
“ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም…” (2 ጴጥ.1፡20)
መኃልየ መኃልይ ረጅም የፍቅር መዝሙር ነው፡፡መዝሙሩም በጥንታዊ የምሥራቅ አገሮች የስሜት መግለጫ
ስልት የተጻፌ ረጅም ፍቅር ግጥም ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም የገቡት ማንን ላፍቅር እና እንዴት ላፍቅር
የሚሉ ጥያቄዎች በሕይወት ውስጥ እጅግ ወሳኝ በመሆናቸው ነው፡፡ለእነዚህ ሁለት ወሳኝ ውሳኔዎች መንሳዊ
ምርጫዎችን ማድረግ ደግሞ ለአማኝ እጅግ አሰፈላጊ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዋናው መልእክት ትክክለኛ ምርጫዎ ከተካሄዱ ፍቅርና ወስብ እግዚአብሔር መጀመሪያ የወጠነውን
ዕድል በመፈጸም ለእርሱ ክብር ሊውል ይችላል የሚል ነው፡፡
25