You are on page 1of 46

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
አራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት


ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ 2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ያግኙን

Email
office@eotc-gssu.org
YouTube
https://www.youtube.com/channel/
UCZlWxxCvV2UzcSz1Qxh6UAg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/
Twitter
https://twitter.com/tibeb_felege

Copyright ©
2015 E.C

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ብጹዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ


ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ብጹዕ አቡነ አቡነ አብርሃም


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር
ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ
ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ
መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

መክሥተ ርዕስ (ማውጫ)

ምዕራፍ አንድ
ክርስቲያን እና ክርስትና ፩
፩.፩. ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው? ፪
፩.፪. የክርስቲያን መገለጫዎች ፪

ምዕራፍ ሁለት
የመንፈስ ፍሬዎች እና የሥጋ ፍሬዎች ፭
፪.፩. የመንፈስ ፍሬዎች ፮
፪.፪. የሥጋ ፍሬዎች ፮
፪.፫. የኃጢአት ምንነትና ውጤት ፰

ምዕራፍ ሦስት
ስግደት ፲፩
፫.፩. የስግደት ትርጉም ፲፪
፫.፪. የስግደት አይነቶች ፲፪
፫.፫. የስግደት ጥቅም ፲፬

ምዕራፍ አራት
ዘላለማዊ ሕይወት ፲፭
፬.፩. ዘላለማዊ ሕይወት ምንድን ነው? ፲፮
፬.፪. እግዚአብሔርን መፍራት ፲፰
፬.፫. ዘላለማዊ ሕይወት ለማግኘት ምን
እናድርግ? ፳

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

አጠቃላይ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ሲያጠናቅቁ

• የክርስቲያንና ክርስትናን ጽንሰ ሐሳብ በአግባቡ


ይረዳሉ፡፡
• የዘላለማዊ ሕይወትን ምንነት ይገነዘባሉ፡፡
• የመንፈስ ፍሬዎችና የስጋ ፍሬዎች የተባሉትን ይለያሉ፡፡
• የስግደትን ጠቀሜታ ይረዳሉ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አንድ
ክርስቲያን እና ክርስትና

አጠቃላይ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የክርስቲያንና ክርስትናን ጽንሰ ሐሳብ በአግባቡ


ይረዳሉ።
• ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነና መገለጫዎቹን
ያውቃሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

• ክርስትያን በእናንተ እሳቤ የሚባለው ማነው ?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፩.፩. ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?


ልጆች ሁላችንም ክርስትያኖች ነን እንዴት ካላችው ክርስትያን የሚባለው፡
• ወንድ ከሆነ በ ፵ ቀን ሴት ከሆነች በ፹ ቀን የተጠመቀ የእግዚአብሔርን
ልጅነት ያገኘ ፣
• እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፤ (ሁሌም ቤተክርስትያን የሚሄድ፤
የሚዘምር፤ ቤተሰቦቹን የሚያከብር እና የሚታዘዛቸው፤ትምህርቱን
የሚየጠና፤ጉዋደኞቹን የሚወድ)
• የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚፈጽም (የሚጾም፤ የሚጸልይ፤የሚሰግድ)
• ክርስቶስ አምላክ ነው ፣ ጌታ ነው ፣ ፈጣሪ ነው ፣ ፈራጅ ነው ብለን
የምናምን ክርስቲያን ተብለን እንጠራለን፡፡
• የክርስቶስ ሐዋርያትም ለመጀመሪያ ጊዜ በአንፆኪያ ክርስቲያን ተባሉ፡
፡ [የሐዋርያት ስራ ፲፩ ፥ ፳፮]

፩.፪. የክርስቲያንነት መገለጫዎች


፩. በነገሮች ሁሉ እግዚአብሔርን ያስቀድማል
• ልጆች ምንም ነገር ከማድረጋችን በፊት እግዚአብሔርን ማስቀደም
አለብን ፡፡ምክንያቱም እርሱን የምናስቀድም ከሆነ ያሰብነው ሁሉ
ይሳካልናል የፈለግነውን እናገኛለን፡፡
• እግዚአብሔርን በሁሉ የምናስቀድመውም
• ጥዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ፤ምግባችንን መመገብ ስንጀምርም ሆነ
ተመግበን ስንጨርስ፤ትምህርታችንን ማጥናት ስንጀምርም ሆነ
አጥንተን ስንጨርስ አማትበን አባታችን ሆይ ብለን መጀመር
• እግዚአብሔር በትምህርታችን ጎበዞች ቤተሰቦቻችን የሚወዱን ጥሩ
ልጆች እንድነሆን እና ወደፊት መሆን የምንፈለገውን እንዲሰተን
ሁሌም ቤ/ን እየሄድን መጸለይ አለብን፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፪. ጠንካራ እና በኃይል የተመላ ነው


ክርስቲያን ሰው ጠንካራ ነው ሲባል አካላዊ ጥንካሬ ሳይሆን
የመንፈሳዊ ሕይወቱን ጠንካራነት የሚያመለክት ነው፡፡ ብርቱ
የሆነውም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስለሆነና ከመንፈስ ቅዱስ ካገኘው
ኃይል የተነሳ ነው፡፡ የጥንካሬው መሰረትና ምንጭ እግዚአብሔር ነው፡
፡ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡” ፊልጵ፡- ፬፥ ፫
“ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ፡
፡” መዝ፡-፯(፰)፥፬ ጥንካሬውም በአቅም የደከሙትን በመጨቆንና
በማሰቃየት ሳይሆን በትግስት ለይቅርታ ባለው ልብ ፣ ሌሎችን
በመርዳት;በታታሪነት፤በትምህርቱ፤ቤተሰብን በማገዝ፤ቤተክርስቲአን
በመሔድ ጠንካራ ነው፡፡
፫. እራሱን የሚጠብቅ፡
ልጆች ይህም ሲባል፡-
ሀ. ውሸትን ከመናገር፡-
ልጆች እግዚአብሔር ውሸትን አይወድም፡፡ ውሸት እውነት የሆነውን ነገር
እውነት እንዳልሆነ አድረገን ስንናገር ፤አንድን ነገር አድርገን አላደረግንም
ስንል ይህ ውሸት ይባላል ፡፡በዚህ ደሞ የዋሸናቸው ሁሉ ያዝኑብናል ፡፡
ለ. ከመጣላት፡-
የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔርን በሁሉ ይመስላሉ መጣላት
ሰውን አለመውደድ የሰይጣን ስራ ነው ልጅ ደሞ አባቱን ስልሚመስል
እኛም እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚወድ ልንዋደድ እና ከጉደኞቻችንም
ጋር በፍቅር መማር፤ማንበብ፤መጫወት እንጂ መጣላት አይገባንም፡፡
ማጠቃለያ፡- በዛሬው ትምህርታችን ክርስቲአን የሆነ ሰው፡- እግዚአብሔርን
የሚያስቀድም እግዚአብሔርን ለማስደሰት ሁሌም የሚጥር በጠንካራ
ኃይል የተሞላ ራሱን የሚጠብቅ መሆኑን ተምረናል፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

የተግባር ልምምድ

መምህር ተማሪዎችዎ በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ


ጽሑፍ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡና በክፍል ውስጥ
እንዲወያዩበት አድርጉ፡፡
፩.እግዚአብሔርን በምን በምን ደስ ማሰኘት ይቻላል?
፪.እኛ ክርስቲያን ነን የምንለው ምን ምን አለን?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሁለት
የመንፈስ እና የስጋ ፍሬዎች ፍሬዎች

አጠቃላይ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የመንፈስ እና የሥጋ ፍሬዎች የሚባሉትን


ይለያሉ።
• የመንፈስን ፍሬ ያፈራሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

• የመንፈስ ፍሬ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፪.፩ የመንፈስ ፍሬዎች


በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ማንኛውም ክርስቲያን ሊኖረው
የሚገባ ነገር ቢኖር የመንፈስ ፍሬ ነው፡፡ ይህ የመንፈስ ፍሬ የሌለው
ሰው ግን በመንፈሳዊ ሕይወቱ መልካም ስራ አልተገኘበትም ማለት ነው፡
፡ ይህን የመንፈስ ፍሬ ማፍራት የሚቻለው በእግዚአብሔር እረዳትነት
ብቻ ነው፡፡ አንድ የብርቱካን ፍሬ ማብቀል የሚያፈልግ ሰው የብርቱካን
ዘር መዝራት አለበት እንጂ የቲማቲም ዘር ቢዘራ የብርቱካን ፍሬ ሊያገኝ
አይችልም፡፡
የዚህ ፍሬ አመራረት ለውበትና ለእይታ ማራኪነት ተብሎ ሳይሆን
አፍርቶ እንዲበላ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የፍቅር፣ የደስታ፣ የሰላም እጦት
አለባቸው፡፡ መልካም ፍሬ በእኛ ላይ የሚያዩ ሰዎች በሕይወታቸው
የጎደላቸውን ከእኛ ያያሉ ማለት ነው፡፡
ልጆች እኛ ጎበዞች ጨዋዎች ለናት ላባታችን የምንታዘዝ ቤተክርስቲየን
ሁሌም የምንሄድ ሲንሆን ይህን ሁሉ የማያደርጉ ልጆች ከኛ መልካምን
ነገር ይማራሉ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መለክቱ ላይ የመንፈስ ፍሬ
ብሎ የዘረዘራቸውም የቅድስና ፍሬዎች፦ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥
ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን
መግዛት ነው።” ገላ ፭ ፥ ፳፪

፪.፪ የሥጋ ፍሬዎች


የሥጋ ፍሬዎች የሚባሉት ሰው በዚህ ምድር ላይ ሲኖር የሚሰራቸው
የሐጢአት ሥራዎች ናቸው፡፡ ይሄ ሲባል ግን መብላት፣ መጠጣት፣
መጋባት፣ ትምህርት መማር.... ሁሉ የሥጋ ተግባራት ቢሆኑ ከዚህኛው
ጋራ ተመድበው የኃጢአት ፍሬ ተደርገው አይታሰቡም፡፡

ምክኛቱም በልክና በስርአት ከተደረጉ ለመንፈሳዊው ሕይወት የራሳቸው


አስተዋጽኦ ስለሚያደርጉ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ ሰው ከበላ ጠንካራና ጤንኛ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ይሆናል፤ ጤነኛ ከሆነ እና ከጠነከረ ደግሞ ለመጸለይ እና መንፈሳዊ ስራ


ለመስራት የበረታ ይሆናል፡
የሥጋ ስራ የተባሉት እኛን ከእግዚአብሔር ከመለየት በስተቀር
ምንም መልካም ጎን የሌላቸው ናቸው፡፡ እነዚህንም ቅዱስ ጳውሎስ
ሲዘረዝራቸው፦ “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥
ርኵሰት፥ መዳራት፥ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥
ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥
ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ
ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።”እንዲል
ገላ ፭፥፲፱-፳፩
ለ.የኃጢአት ምንነት እና ውጤት
• ኃጢአትማለት ማጣት ማለት ነው ፡፡ይህም የፈጠረንን ሚመገበንን
ሁሌም የሚጠብቀንን የሚወደንን አምላካችንን እግዚአብሔርን ማጣት
ነው፡፡አምላካችንን የምናጣው በምንድነው ካላችው እሱ የማይወደውን
ስራ ስንሰራ ቤተሰቦቻችን የማናከብር የማንታዘዝ ከሆነ ቤተክርስትያን
የማንሄድ የማንጾም የማንጸልይ ከሆነ ከእግዚአብሔር እንለያለን እርሱም
ከኛ ይለያል፡፡
የኃጢአት ውጤቱ፡
• ሰው ኃጢአት በሰራ ቁጥር ከእግዚአብሔር ጋራ ይጣላል፡ምሳሌ
አባታችን አዳም በኃጢአቱ ምክንያት ከአምላኩ እንደተለየ እና እንደተጣላ
• እግዚአብሔርን ያሳዝናል ፡፡

ማጠቃለያ
ልጆች በዚህ ትምህርታችን
• የመንፈስ ፍሬዎች የተባሉትን ፍቅር ሰላም በጎነት ቸርነት ደስታ
የመሳሰሉት ሲሆኑ እኚህን ማድረግ እግዚአብሔርን ማስደሰት
እንደሆነም በተጨማሪ የስጋ ፍሬዎች የሚባሉ መጣላት ቁጣ ክርክር
ቅናት የመሳሰሉት ደሞ እኛን ከእግዚአብሔር የሚለዩን እንዲሁም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

አምላካችንን የማያስደስቱ እንደሆኑ ተምረናል፡፡


• ኃጢአት ማለት ከእግዚአብሔር የሚለይ ወይም እግዚአብሔርን
የሚያሳጣ ነው ልንል እንችላለን፡፡
• ስለሚያደርጉ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ ሰው ከበላ ጠንካራና ጤንኛ ይሆናል፤
ጤነኛ ከሆነ እና ከጠነከረ ደግሞ ለመጸለይ እና መንፈሳዊ ስራ
ለመስራት የበረታ ይሆናል፡
• የሥጋ ስራ የተባሉት እኛን ከእግዚአብሔር ከመለየት በስተቀር
ምንም መልካም ጎን የሌላቸው ናቸው፡፡ እነዚህንም ቅዱስ ጳውሎስ
ሲዘረዝራቸው፦ “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥
ርኵሰት፥ መዳራት፥ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥
ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ምቀኝነት፥
መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም
እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት
አይወርሱም።”እንዲል ገላ ፭፡፲፱-፳፩

፪.፫ የኃጢአት ምንነት እና ውጤት


• ኃጢአትማለት ማጣት ማለት ነው ፡፡ይህም የፈጠረንን ሚመገበንን
ሁሌም የሚጠብቀንን የሚወደንን አምላካችንን እግዚአብሔርን ማጣት
ነው፡፡አምላካችንን የምናጣው በምንድነው ካላችው እሱ የማይወደውን
ስራ ስንሰራ ቤተሰቦቻችን የማናከብር የማንታዘዝ ከሆነ ቤተክርስትያን
የማንሄድ የማንጾም የማንጸልይ ከሆነ ከእግዚአብሔር እንለያለን እርሱም
ከኛ ይለያል፡፡
የኃጢአት ውጤቱ፡
• ሰው ኃጢአት በሰራ ቁጥር ከእግዚአብሔር ጋራ ይጣላል፡ምሳሌ
አባታችን አዳም በኃጢአቱ ምክንያት ከአምላኩ እንደተለየ እና
እንደተጣላ
• እግዚአብሔርን ያሳዝናል ፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ማጠቃለያ
ልጆች በዚህ ትምህርታችን
የመንፈስ ፍሬዎች የተባሉትን ፍቅር ሰላም በጎነት ቸርነት ደስታ
የመሳሰሉት ሲሆኑ እኚህን ማድረግ እግዚአብሔርን ማስደሰት እንደሆነም
በተጨማሪ የስጋ ፍሬዎች የሚባሉ መጣላት ቁጣ ክርክር ቅናት
የመሳሰሉት ደሞ እኛን ከእግዚአብሔር የሚለዩን እንዲሁም አምላካችንን
የማያስደስቱ እንደሆኑ ተምረናል፡፡
ኃጢአት ማለት ከእግዚአብሔር የሚለይ ወይም እግዚአብሔርን
የሚያሳጣ ነው ልንል እንችላለን፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሦስት
ስግደት

አጠቃላይ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የስግደትን ምንነት ፣ ዓይነቶችን እና ጥቅሙን ይረዳሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

• የመንፈስ ፍሬ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?

፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፫.፩. የስግደት ትርጉም


ስግደት ፡- ሰገዱ፣ ስገድ፣ አጎንብስ፣ ተንበርከክ ካለው የግዕዝ
ቃል የተወሰደ ሲሆን
• ቃል ለቃል ትርጉሙ መዋረድ፣ ማጎንበስ፣ መንበርከክ፣ በግምባር
መውደቅ፣ ግንባርን መሬት አስነክቶ ስሞ መነሳት ማለት ነው፡፡
• የገዥ እና የተገዥ የመታዘዝና የትሕትና ምልክት (መገለጫ) ነው፡፡
• በጉልበቴም ተንበርክኬ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እጄን ዘረጋሁ፡
፡ ሕዝ፡- ፱፥፭

ሥዕል ፩ የሚሰግድ ሕጻን

፫.፪. የስግደት ዓይነቶች


• ስግደት የአምልኮና የአክብሮት ወይም የባህርይና የጸጋ ተብሎ በሁለት
ይከፈላል፡፡

፫.፪.፩. የአምልኮና የባህርይ ስግደት የፍጡር ነገር ሳይቀላቀልበት ጌትነት፣


ገዥነት፣ የባህርይ ገንዘቡ ለሆነ አምላክ ለልዑል እግዚአብሔር በንጹህ
መንፈስ፣ በፍጹም እምነት ይቀርባል
፲፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

• ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የሚመግብ ከሁሉ በላይ ነግሶ የሚኖር በባህርዩ


ሞት፣ በመንግስቱ ኅልፈት፣ በስልጣኑ ሽረት የሌለበት ስለሆነ
ይሰገድለታል፣ ይመለካል፣ ይመሰገናል፡፡
“እግዚአብሔርን ብቻ ልታመልክ ለሱም ብቻ ልትሰግድ ጽሑፍ አለ ….
እግዚአብሔር አምላክ ታላቅ ነውና…. ኑ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ
በእርሱም በሰራን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፡፡” ዘዳ፡-፮፥፰፫ ፣ማቴ፡
-፬፥፰ ፣መዝ፡-፳፬(፳፭)፥፪-፭
• የአምልኮ ስግደት የሚገባው የባህርይ አምላክ እርሱ ብቻ መሆኑን
ቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ይገልፃሉ፣ ያስተምራሉ፡፡
“ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል ምላስም ሁሉ በእኔ ያምናል” ኢሳ፡-
፵፭፥፳፫

፫.፪.፪. የአክብሮት ወይም የጸጋ ስግደት፦ እግዚአብሔር በመልኩና


በምሳሌው የፈጠረውን ሰውን አክብሮታል የጸጋ ገዥነትና የጌትነት
ስልጣንም ሰጥቶታል፡፡
“እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው
ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው እግዚአብሔር ባረካቸው፣…. ብዙ ተባዙ
ምድርንም ምሉአት ግዙአትም… አላቸው፡፡” ዘፍ፡- ፩፥፳፯-፳፰
• ስግደት የአክባሪና የተከባሪ፣ የገዢና የተገዢ ምልክት እንደመሆኑ
ለሰው ከእግዚአብሔር በተሰጠው የጸጋ ጌትነት ፣ አክብሮትና የጸጋ
ስግደት ይሰጣል፡፡
• ልዑል እግዚአብሔር በልዩ ጥበቡና በማይሰፈር ስጦታው አብዝቶ
ያከበራቸውና በማይለወጥ ቃል ኪዳን ባለሟል ያደረጋቸውን ቅዱሳን
ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃንና ሰማዕታትን ማክበር ይገባል፡
፡ የአክብሮትና የጸጋ ስግደትም ሊቀርብላቸው የሚገባውም ስለዚህ
ነው፡፡
• ከነቢያት እነ ዳዊት እነ ዳንኤል ከህዝብ እነ ማኑሄ ከወንጌላውያን
እነ ቅዱስ ዮሐንስን የመሳሰሉ ብዙ ደጋግ ሰዎች ለቅዱሳን መላዕክት
፲፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

የሚገባ የጸጋ ስግደት አቅርበዋል፡፡ ከእግዚአብሐር ዘንድ የተላከውን


የመልካም የምስራች ድምጽ ሰምተዋል በጎ በጎ በረከትንም አግኝተዋል፡
፡ 1ኛ ዜና፡-፳፩፥፲፮ ፣ ት/ዳን፡-፰፥፲፭ ፣ መጽ/መሳ፡-፰፫፥፳ ፣ ራዕ፡-፲፱፥፲

፫. ፫ የስግደት ጥቅም
ስግደት ለምን ይጠቅማል (እንሰግዳለን)?
“የእግዚአብሔር እውቀት የጥበቡ ምላት ስፋት ምን ይርቅ ! ምን
ይጠልቅ ! …” ተብሎ እንደተጻፈ ከሃሊነቱን በማድነቅ ፣ በስጦታው
በማመስገን ከቸርነቱ የሚገኝን በረከት በመሻት በመለመን እንሰግዳለን፡፡
ሮሜ፡-፰፩፥፴፫ ፣ ዘጸ፡-፴፫፥፲፩
• ሰው ከእግዚአብሔር የሚጠይቀውን እርዳታ እና በረከት ለማግኘት
ራሱን በትሕትና ዝቅ አድርጎ በስግደት የተደገፈ ጸሎት ማቅረብ
አለበት፡፡
• “ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና ብትወድስ ልታነጻኝ
ትችላለህ ብሎ ለመነው ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና
እወዳለሁ ሂድ አለው …… ለምጹም ለቀቀውና ነጻ፡፡” ማር፡-፩፥፵-፵፪
“ኑ እንሰግድለት ፣ እንገዛለት በፈጠረን በእግዚአብሔር ፊት እናልቅስ
አሉ ፈጥሮናልና (ፈጣሪያችን) ነውና፡፡ መዝ፡- ፺፬(፺፭)፥፮
• ወደ ቤተ ክርስቲያን አዘውትረው የሚማልዱ በጸሎት በስግደት
እግዚአብሔርን የሚለምኑ ሰዎች የጠየቁትን ያገኛሉ ድንቅ ድንቅ
ተዓምራትም ይደረግላቸዋል፡፡ “ቤቴ የጸሎት ቤት ናት” ብሎ ሰየማት
አምላክ በቤቱ የሚቀርበውን ደጅ ጥናት ይቀበላል፡፡ በእውነትና
በእምነት በንጹህ ልቡና የሚጠሩትንም ይሰማል፡፡ ለልመናቸው በጎ
ምላሽ ያገኛሉ፡፡
• “ወደ ህዝቡም ሲደርስ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበረከከ
ጌታ ሆይ ልጄን ማርልኝ … ብሎ ለመነው ኢየሱስም አምጡት አለ
ጋኔኑንም ገሰጸው ፣ ከእርሱ ወጣ ብላቴናውም ከዚያ ሰዓት ጀምሮ
ተፈወሰ” ማቴ፡- ፲፯፥፲፬-፲፰
፲፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አራት
ዘለዓለማዊ ሕይወት

አጠቃላይ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የዘለዓለማዊ ሕይወት ምንነትን የሚገኝባቸው መንገዶችን


እግዚአብሔርን ስለመፍራትና ዘለዓለማዊ ሕይወትን
ለማግኘት ምን ማድረግ እንደሚገባ ይረዳሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

• ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዴት ይገኛል?

፲፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፬.፩ ዘለዓለማዊ ሕይወት ምንድን ነው?

በቃል የሚጠና ጥቅስ

«የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት ቀላል የሆነ


የጊዜው መከራችን የክብርን የዘለዓለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ
ያደርግልናልና የሚታየው የጊዜው ነውና የማይታየው ግን የዘለዓለም
ነው፡፡»፪ኛቆሮ፡-፬ ፥፲፰

፩. ዘለዓለማዊነትህ
ስለምድራዊ ሕይወት ብቻ የሚያስቡ አሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የሚያስቡት
በዚህ ምድር ስላለው ሕይወታቸው ብቻ ነው፡፡ ምኞቶቻቸውም ሁሉ
በምድራዊው ሕይወት ላይ የተጠመዱ ናቸው፡፡ ጥረታቸውና ድካማቸው
ሁሉ ለዚህኛው ሕይወት ብቻ ነው፡፡ ስለ ዘለዓለማዊነታቸው ምንም
ላያስቡ ይችላሉ፡፡ በምድር ላይ የምታሳልፈው ሙሉ የሕይወት ዘመንህን
መጨረሰሻ ከሌለው ዘለዓለማዊነትህ ጋር ስታነፃፅረው የዓይን ጥቅሻ
ያህል ነው፡፡ በምድር ላይ ያለ ሕይወትህ እንዲህ ላለው ዘለዓለማዊነት
ይኸውም ሕያው ለሆነ ሕይወት የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡

ዘለዓለማዊነትን አስብ
ልጆች ስለ ዘለዓለማዊነትሁሌም ማሰብ ያስፈልጋል ፡፡ ማንኛውም ዓለማዊ
ነገር ከዘለዓለማዊነት ጋር ሲነፃፀር ዋጋው በጣም ትንሽ ነው፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን አስመልክቶ የላከው መልዕክት ምንኛ ድንቅ ነው፡
፡ «“የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት ቀላል የሆነ የጊዜው
፲፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

መከራችን የክብርን የዘለዓለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና


የሚታየው የጊዜው ነውና የማይታየው ግን የዘለዓለም ነውና”» ፪ኛ ቆሮ፡
-፬ ፥፰

፪. እግዚአብሔርን በሚያምኑ እና በማያምኑ ሰዎች መሀል የዘለዓለማዊነት


እይታ ልዩነት አለው፡፡
በፈጣሪ የማያምን የሆነው ሰው እይታ ቅርብ ነው እይታው ከሚታዩት
ነገሮች አልፎ አይሄድም፡፡የሚያምን ሰው ግን አርቆ ይመለከታል ፣
ከሞት በኋላ ያለውን ስለሚመለከትም እንዲህ እያለ ያሰላስላል፡፡ ከዚህ
ሥጋዬ ስላቀቅ ምን ይገጥመኛል? ወዴት እሄዳለሁ?ምን እሆናለሁ?
የሚያምኑ ሰዎች የሚጠብቁት “እግዚአብሔር የሰራትንና የፈጠራትን
ከተማ….” (ዕብ፡-፩፥፩-፪) ነውና፡፡

፫.መንገዳችሁን መርምሩ
ልጆች መንገዳችን እውነት ሁሌም እግዚአብሔርን የሚያስደስት መሆኑን
ማረጋገጥ አለብን ምክንያቱም ከዘላለማዊ ሕይወታችን እናዳንለይ፡፤

ማጠቃለያ፡-
ሰዎች ዘለዓለማዊ ሕይወት አለን ፡፡ ይህን አውቀን ራሳችንን ማዘጋጀት
መቻል አለብን፡፡ ይህንን ለማድረግ ዘወትር ራሳችሁን መርምሩ፡

ጥያቄዎች

• ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚያሳጡ ነገሮች ምንድን ናቸው?


• ለዘለዓለማዊ ሕይወት ራስን ለማዘጋጀት ምን ማድረግ

፲፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፬.፪. እግዚአብሔርን መፍራት (ፈሪሃ እግዚአብሔር)


በምድራችን ብዙ እውቀት አለ፡፡ ጥበብ እንደሚበዛም አስቀድሞ
ተነግሮናል፡፡ «እውቀትም ይበዛል፡፡» ዳን፡- ፲፪፥፬ በተባለበት ዘመን ላይ
ስለሆንንም እውቀት በዝቷል፡፡ በተለያየ ሙያና ደረጃ ሰዎች እውቀት
ሊኖራቸው በጣም ጠቢብም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡የጥበባት ምንጭና መሰረት
ግን እግዚአብሔርን መፍራት መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት
የሌለበት እውቀት ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላል፡፡ በዛሬው ትምህርታችን
እግዚአብሔርን ስለ መፍራት እንማራለን፡፡

ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው።


• እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ምን ማለት ነው?
• እንዴት እናዳብረዋለን?
• እግዚአብሔርን በመፍራት አለመኖር ምን ያስከትላል?

አባታችን እግዚአብሔር የሚወደንና የሚንከባከበን አምላክ ነው፡፡ እርሱ


ፈጥሮናል፡፡ ሲጠራንም ወደ እርሱ እንሄዳለን፡፡ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ
ስንሳሳትና የዘለዓለም ሞት ስናመጣም እስከሞት ወዶናል፡፡ የምንወዳቸውን
ቤተሰቦች ፣ ሕይወታችንንና በጎዎችን ነገሮች ሁሉ የሰጠን እርሱ ነው፡፡
ለወደፊቱም ያሰበልንና ያዘጋጀልን መልካም ነገሮች አሉ፡፡ ይህንን አምላክ
ማምለካችን ደስ ያሰኛል እርሱን መውደድ እና ማመንም ታላቅ በረከት
ነው፡፡ ታዲያ እርሱን መፍራት ማለት ምን ማለት ነው?

፲፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

እግዚአብሔርን መፍራት ማለት፡-


• እግዚአብሔርን አክብሮ መከበር ማለት ነው፡፡ አምላካቸን እንደሚወደን
እንደሚጠብቀን ሁሌም አምነን እሱ የሚየስደስተውን ስንሰራ
አምላካችን ያከብረናል፡፡”ስለዚህ የማይናወጥን መንግስት ስለምንቀበል
በማክበርና በፍርሐት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን
ፀጋ እንያዝ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና፡፡” ዕብ፡
-፲፪፥፳፰-፳፱፡፡
• ክፋትንና ኃጥያትን እንደሚጠላ ማወቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ
ነው እና ቅዱሳን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ “ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና
ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተፃፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ
ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ” 1ኛ ጴጥ፡-፩፥፲፭-፲፯ ኃጥያትና
ርኩሰት በእርሱ ዘንድ የተጠላ ነው፡፡ “እግዚአብሔርን መፍራት
ክፋትን መተው ሁሌም በፍቅር መኖር ነው፡፡
• እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ መሆኑን ማሰብ ነው፡፡ ለሰዎች ክፉና
መልካም ሥራ ዋጋ ይሰጣል፡፡ “እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም
እንደ ስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡ አልፋና
ዖሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ፡፡
” ራዕ፡-፳፪፥፲፪ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ስንፈራ እርሱ እንዳለ
እንደሚያየንና እንደሚሰማን ለክፋትና ለበጎነትም ዋጋ እንደሚሰጥ
ስለምናምን ነው፡፡ “ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋት
ይመለሳል፡፡” ምሳ፡-፲፮፥፮ እግዚአብሔርን መፍራት ታላቅ ጥበብ ነው፡፡

፲፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፬.፫.ዘለዓለማዊ ሕይወት ለማግኘት ምን እናድርግ

ሀ. ክርስቲያናዊ ፍቅር
“በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ” ፩ኛ ዮሐ፡-፫፥፲፰
፩ኛ ቆሮ፡- ፲፫፥፥ እና ፩ኛ ዮሐ፡- ፬፥፯-፲፩
ፍቅር ማለት “አፈቀረ” ወደደ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን
መውደድ ልብን መስጠት ማለት ነው፡፡ ፍቅር ፍጹምነት ፣ ርሕራሔና
ቅድስና የሚገለጡበት አደባባይ ነው፡፡ ፍቅር የታላላቆችን ምስክርነት
ያገኘ ፣ የኃያላንን ጉልበት ያንበረከከ ወልድን ከዙፋኑ የሳበ ሕያውና
ኃያል ነው፡፡ ፍቅር ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ (ሰብዕ) ተብሎ
በሁለት ይከፈላል፡፡
፩. የእግዚብሔር ፍቅር (Agape)
እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ መገለጫ
ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ጊዜ አይሽረውም ሁኔታም አይወስነውም
ወረት አይለውጠውም፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ ሕያው ነወ፡
፡ እግዚአብሔር የዘመናችን ሁሉ ወዳጅ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር
በእኛ ሁኔታ አይመሰረትም፡፡ እግዚአብሔር እንዲሁ ወደደን፡፡ ዮሐ፡
-፫፥፲፮ እንዲሁ የሚባል ፍቅር ከፀሀይ በታች የለም፡፡ የዓለም ፍቅር
በሁኔታዎችና በተፈቃሪው ማንነት ይመሰረታል፡፡ እግዚአብሔር ግን ያለ
ቅድመ ሁኔታ ወደደን፡፡ አብ አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ያደረሰው ኃያል
ወልድን ከዙፋኑ ስቦ ለመስቀል ሞት እንዲታዘዝ ያደረገው ለሰው ልጆች
ያለው ፍጹምና ዘልዓለማዊ ፍቅር ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶቹ ሳለን
ለእኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ያሳያል፡፡ ሮሜ፡-፭፥፰፡
፡ ስለዚህ አስቀድመን በፍፁም ልባችንና በፍፁም ነፍሳችን ልንወደው
ይገባል፡፡ ሉቃ፡- ፩፥፲፯፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፪. የሰው ፍቅር
ይህ ፍቅር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
• የጓደኛ ፍቅር (Filia)
• የቤተሰብ ፍቅር ናቸው፡፡

የጓደኛ ፍቅር
ይህ ፍቅር በተፈጥሮ እኩያነት ጓደኛ ፣ በሃይማኖት ዝምድና
ወንድም የሆኑን የሰው ዘርን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ኦሪት ባልንጀራህን
ወንጌል ጠላትህንም ውደድ ይሉናል፡፡ የሚወዱንን ብቻ ሳይሆን
የሚጠሉንንም በመውደድ የክርስትናችንን ብልጫ ማሳየት አለብን፡፡
ማቴ፡- ፭፥፯ የማናየውን እግዚአብሔርን መውደዳችንን የምናስመሰክረው
የምናየውን ወንድማችንን በመውደድ ነው፡፡ ፩ኛ ዮሐ፡- ፬
ጉአደኛችንን የማንወድ ከሆነ እግዚአብሔርን አውቃለሁ ማለት
አንችልም፡፡ ፩ኛ ዮሐ፡- ፬ ፥፰፡፡ ዮሐንስ ወንጌላዊ በሽምግልና ወራቱ በሰው
ታግዞ ወደ አማኞች ጉባኤ ሲመጣ በትምህርቱ መክፈቻ ቃል “ይህን ቃል
ለምን ትደጋግማለህ?” አሉት፡፡ ዮሐንስም “ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ
የመልካምነት ድምዳሜ ነው፡፡” አላቸው፡፡ እውነት ነው ፍቅር የሕግ ሁሉ
ፍፃሜ ነው፡፡ ሮሜ፡- ፫፥፡፡ ፍቅር የፍፃሜ ማሰሪያ ነው፡፡ ቆላ፡- ፫፥፬፡፡
ፍቅራችን ያለ ግብዝነት ይሁን፡፡ ሮሜ፡- ፪፥፱፡፡ ፍቅር የልብ ነገር እንጂ
በአንደበት ብቻ የሚወሰን በንግግር ብቻ የሚገለጽ አይደለም፡፡ ለዚህ
ነው ሐዋርያው “በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ”
ያለው፡፡ የምድሪቱ ርኃብ ፍቅር ነው፡፡ የምድር ቁስል እንዲፈወስ ከፈለግን
የመውደዳችን ማስመስከሪያ ነው፡፡ መዋደድ የክርስትና መታወቂያ ነው፡
፡ ዮሐ፡- ፲፫፥፭፡፡ ፍቅር የኃጥያትን ብዛት ይሸፍናል፡፡ ፩ኛ ጴጥ፡- ፬፥፰፡፡

፳፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

የቤተሰብ ፍቅር
ይህ ፍቅር በደም የተከፈሉ ወይም በአንድ ቤት ያደጉ ቤተሰቦችን
ይመለከታል፡፡ የአባት ፣ የእናት ፣ የእህት ፣ የወንድም ፣ የልጆችና ሌሎች
የስጋ ዘመዶች ወይም አብሮ የሚኖሩ ሰዎች ፍቅር በዚህ ይጠቃለላል፡
፡ የተገኘንበትን ቤተሰብ በደስታ መቀበል ማክበር እና ትክክለኛ የፍቅር
ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ሌላው የዘለዓለም ሕይወት እንድናገኝ ሊኖረን የሚገባው ነገር እምነት
ነው፡፡
እምነት እና የእምነት ደረጃዎች
በመንፈሳዊ ሕይወት የሚመራ ሰው እምነት አለው ምክንያቱም
ቅዱስ መጽሐፍ ያንን እምነት ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ “እምነት”
ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ ይለዋል፡፡
በመሰረተ እምነትና በተግባር ማመን
እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ መኖሩን እና ዓለምን በሙሉ
መቆጣጠሩን ስናምን እንደሚመለከተን አውቀናልና ከክፉ የኃጥያት ስራ
እንርቃለን ማለት ነው፡፡ ዘፍ፡- ፴፱፥፱
በእግዚአብሔር ጥበቃና ኃይል በትክክል የምታምን ከሆነ
አትፈራም ፍርሃት የደካማ እምነት ማስረጃ ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ
ማዕበሉን በፈራበት ጊዜ መስጠም ጀመረ ስለዚህ ጌታ “አንተ እምነት
የጎደለህ ስለምን ተጠራጠርክ?” ማቴ፡-፲፬፥፴፩ አለው፡፡ በ፪ኛ ነገ፡-፮፥፲፯
ላይ ያለውን ታሪክ ስንመለከት ግያዝ ከተማውን ከብቦ የነበረውን
የጠላት ሰራዊት ፈርቶ እንደነበር እናነባለን፡፡ ነገር ግን ነቢዩ ኤልሳዕ
የእግዚአብሔር ሰራዊት ሲያሸንፋቸው አየ፡፡ ስለዚህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን
እንዲገልጥለት ለግያዝ ጸለየለት እውነት ነው በሰብዓዊ ዓይኖቹ ሳይሆን
በእምነት ለማየት በቃ ፡፡ ከእርሱ ጋር ያሉትም ከጠላት ጋር ካሉት
እንደሚበልጡም ማየት ቻለ ማለት ነው፡፡
ይኸው እምነት ለሚከተሉት ነገሮች በግድ ያስፈልጋል፡፡

፳፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፩. ጸሎትን በሚጸልዩበት ጊዜ፡-


፪. ማንኛውም መንፈሳዊ ስራ በምንሰራበት ጊዜ፡- ነሕ፡- ፪፥፳፣ “የሰማይ
አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሮቹ ተነስተን እንሰራለን”
፫. ከእግዚአብሔር ፈውስና ጸጋ በሚያስፈልገን ጊዜ
ለ. ተስፋ እና የተስፋ ሕይወት
ክርስትና የተስፋ ሕይወት ነው፡፡ ተስፋውም በምድር ስንኖር
የምናምነው እና ጌታችን ይመጣል ብለን የምንጠብቀው የዘለዓለም
ሕይወት ነው፡፡ ይህን ለማግኘትም የአሁኑ ዘመን መከራ እና አጋጣሚ
አያታልለንም፡፡
ለምን ተፈጠርን?
ስለ ተስፋ ስንማር ለምን ተፈጠርን? እና ወዴት እንሄዳለን?
የሚሉትን ጥያቄዎች መመልከት አለብን፡፡ የብዙዎች የዘመናት
ጥያቄ የሆኑት እነዚህ ጥያቄዎች አንዳንዴ በተዛባ መንገድ ሲመለሱና
የተሳሳተ ድምዳሜ ሲሰጥባቸው ማየት የተለመደ ነው፡፡ በስነ ፍጥረት
ታሪክ ትምህርታችን የሰው ልጅና ዓለሙ ከውስጡ ጋር መፈጠሩን
ተመልክተናል፡፡
በዚህም መሰረት ለጋስ የሆነው እግዚአብሔር የሰውን ልጅ
ሲፈጥር በምድር የሚመላለሱትን “ግዙአቸው” ብሎ ያሰለጠናቸው ሲሆን
ፍፃሜውም “ሕያው ሆኖ እንዲኖር “ ነው፡፡ በመጨረሻም የመንግስተ
እግዚአብሔር ወራሾቹ የክብሩም ተካፋዮች እንድንሆን ነበር፡፡ ነገር ግን
የሰው ልጅ «አታድግ» የተባለውን በማድረጉ ወደቀ፡፡ ውድቀቱም ሞተ
ሥጋ እና ሞተ ነፍስ አመጣበት፡፡ ከዚህ ለመውጣት ያደረገው ጥረት
ስለአዳነው በተስፋ አምላኩን ለመነ እግዚአብሔርም የማዳን ተስፋ
ሰጠው፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በሰጠው ተስፋ መሰረት ጌታችን
ተወልዶ አዳነን በኋላ መጥቶም ጽድቅ ያለበትን ምድር እንደሚያወርሰን
ተስፋ ሰጥቶናል፡፡ ያንንም ተስፋ እንጠባበቃለን፡፡ ተስፋ በእግዚአብሔር
ሕልውና ያለንን እምነት እና መታመን የሚያመጣልን ኃይል ነው፡፡
፳፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

በእርሱ በእግዚአብሔር ያለንን ሕይወትም ያስረግጥልናል፡፡ መዝ፡-፳፫፥፬


፣ዕብ፡-፲፫፥፰ የተፈጠርነው የእግዚአብሔር ክብር ወራሾች ሆነን በዘላለም
ሕይወት ለመኖር ነው፡፡
የተስፋ ውጤት፡-
ሀ. ተስፋ አዳዲስ ሐሳብ እና ሥራ የማመንጨት ኃይል ነው፡፡
ተስፋ ትክክለኛ ግብ ይሰጣል፡፡ ወደ ግብ ለመድረስ እና
ፍፃሜውን ለማግኘትም ጥረት ይኖራል ነገን በተስፋ የሚያይና የሚጥር
ከሚያጋጥሙት ችግሮች አልፎ መፍትሔ ያስባል፡፡ ተስፋ በሥራችንና
በሕይወታችን በጎ አመለካከት ይፈጥርልናል፡፡ ቅዱሳን ለሚያሰቃዩዋቸው
ምህረት እና ፍቅርን የመመኘት ኃይል ያገኙት ከተስፋቸው ከኢየሱስ
ክርስቶስ ነበር፡፡ (የሐዋ፡-፯) ተስፋ በመከራዎች በትዕግስትና በጽናት
እንድንቆም ያበረታናል፡፡ “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር
ፍቅር በልባችን ስለፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም፡፡” ሮሜ፡-፭፥፭
ለ. ተስፋ ሙሉ እይታ እና ሰፊ አመለካከት ያመጣል
በአንድ አቅጣጫ ብቻ በማየት መሳሳት በጠባብ አመለካከት
መወሰን ችግሩ ብቻ ምድራዊነት ብቻ የሰዎች ድካም እና ክፋት ብቻ
እንዲታየን ያደርጉናል፡፡ ይህ ግን ጎዶሎ እይታ ነው፡፡ ምክንያቱን ከችግሩ
በኋላ መፍትሔ አለ ሰዎች ምድራውያን ብቻ ሳንሆን ሰማያውያንም ነን፡
፡ ማንኛውም ሰው ከድካሙ የሚበልጡ ጠንካራ ጎኖች አሉት እነኚህን
አለመረዳት ሙሉ እይታ እና ሰፊ አመለካከት ከማጣት ይመነጫሉ፡
፡ ተስፋ ግን የዛሬውን እና የወደፊቱን ጊዜያዊውን እና ዘልዓለማዊውን
ችግሩን እና መውጫውን ችግሩን እና መውጫውን ለራስ እና ለሌሎች
ማሰብን ይሰጣል፡፡
ሐ. እውነተኛ ተስፋ በእምነት ተመስርታ በፍቅር ትፀናለች
ሕሙማን በእግዚአብሔር አምነው ይድናሉ፡፡ እውነተኛ ተስፋም
በእምነት ይመሰረታል በፍቅር ይፀናል፡፡ አንድ ሰው በእግዚአብሔር
አምኖ የሚኖረው ተስፋ በእውነተኛው ታማኝ ላይ ስለሆነ እንደማያፍር
ተስፋውንም እንደሚያገኝ እርግጠኛ ነው፡፡ ይህንኑ በጽኑ መሰረት የተጣለ
፳፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ተስፋም ለአምላኩ እና ለሰዎች በሚሰጠው ፍቅር ይገልጠዋል፡፡ ለሌሎች


ስናካፍል፣ስናገለግል እና ለክፉዎችም ስንፀልይ ተስፋውን እንዲያገኙ
ካለን ፍቅር ነው፡፡

የተግባር ልምምድ

መምህር ተማሪዎችዎን በቡድን ከፋፍለው መድቧቸው፡


፡ ከዚያም ቀጥሎ በቀረበው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በክፍል ውስጥ
ከተማሩት መጻሕፍትን አንብበውና ሌሎች መምህራንን
ጠይቀው የተረዱትን /የተገነዘቡትን/ በጽሑፍ አቅርበው
በክፍል ውስጥ ማብራሪያ ይስጡ ወይም ገለጻ ያድርጉ፡፡

፩. የሰው ልጅ «አታድርግ » የተባለውን ትዕዛዝ በመጣሱ ምን


መጣበት?
፪. በእግዚአብሔር የተሰጠው የመዳን ተስፋ ምንድን ነው?

፳፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

መ የዋህነትና ቅንነት
የውሃት ራስን ዝቅ ማድረግ አለመመካት እሺ ባይነት ከራስ ይልቅ
ለጓደኛ ማሰብ ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ የዋህነት የመንፈስ ፍሬ ነው፡፡ ጌታችን
ስለተባረኩ ከተናገረው ዓረፍተ ነገር ግንባር ቀደም መሆኑን ሲገልፅልን
“የዋሆች ብፁዓን ናቸው ምድርን ይወርሳሉና “ ሲል አስተምሮአል ማቴ፡
- ፭፥፳፫፡፡
አንዳንድ ቅዱሳን አባቶች በየዋህነት በመኖር አገልግለው
አሳልፈዋል፡፡ የዋህነት ወይም ደግነት ጌታ ከእርሱ እንማረው ዘንድ
የጠየቀን እጅግ ጠቃሚ ምግባር ነው፡፡ ማቴ፡- ፲፩፥፳፱ “ከእኔ ተማሩ
እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝ እና” ከእርሱ ስብከትን ተአምራትን ፣
መምህርነትን ፣ ትሕትናን ፣ ፍቅርን ፣ አገልግሎትን ፣ ምህረትን
፣ ጥበብን እና ሌሎች ምግባራትን እና ፍጹምነትን ሁሉ እንድንማር
ጠይቆናል፡፡ ፍፁምነትን እና ምግባርን ሁሉ ይወክላልና ነገር ግን
በየዋህነት እና ቸርነት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ይህንን ለሚማሩት
ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁ ብሏቸዋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ኤፌ፡- ፬፥፲፩ “እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ
እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ
እለምናችኋለሁ በትሕትና ሁሉና በየዋሕነት በትዕግስትም እርስ በራሳችሁ
በፍቅር ታገሱ” ገላ፡- ፮፥፩ “ወንድሞች ሆይ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ
ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየዋህነት
መንፈስ አቅኑት አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ”፡፡

የየዋህ ሰው ጠባይ ስለ የዋህነት እና ስለየዋህ ይህን ሁሉ ካወቅን


የዋህነት ምድርን ነው? የዋህ ወይም የገር ሰው ጠባያት ምንድን ናቸው?
የሚሉትን እንመልከት፡-
የዋህ ሰው መልካም ጠባይ ያለው እና ሰላማዊ ሰው ነው፡፡ እርሱ
ሁል ጊዜ በነገሮች ሁሉ የተረጋጋ ነው፡፡ በጠባዩ የረጋ ነው ንግግሩ
ስሜቶቹ እንዱሁም አጠቃላይ እንቅስቃሴው ሰላማዊ ነው፡፡ ውጪያዊ
፳፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ገፅታ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ እሱነቱም እርጋታ የተሞለበት ነው፡፡ ልቡና


ስሜቶቹ የረጉ ናቸው ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚያደርጋቸው ውይይቶች
እና ንግግሮች የረጋ ነው፡፡ ዳግመኛም ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች
ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ነው፡፡
የየዋህ ሰው ድምጽ ሁል ጊዜ የዋህ ነው ድምጹ ፈጽሞ ከፍተኛና
ኃይለኛ አይደለም ንግግሮቹ ጎጂም ፣ አስቸጋሪም አይደሉም የረጋ እና
አነስተኛ ድምጽ የየዋህ ሰው ጠባይ ነው፡፡ ይህም የየዋሁ ጌታችን ድምጽ
የሚመስል ነው፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን ከአጭበርባሪዋ ከንግስት
ኤልዛቤል ሲሸሽ ባገኘው ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ
ነፈሰ እግዚአብሔር ግን በነፍሱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ከምድር መናወጥ
በኋላም እሳት ሆነ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፡፡
ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምጽ ሆነ ድምጹም ኤልያስ ሆይ
በዚህ ምን ታደርጋለህ? የሚል የእግዚአብሔር ድምጽ ነበር ፩ኛ ነገ፡
-፲፱፥፲፩

የየዋህ ሰው ችሎታ ምንድን ነው?


የየዋህ ሰው ችሎታዎች ተብለው የሚገለጹ አሉ፡፡ የዋህ ሰው
ሁከት አይፈጥርም አይከራከርም አይጮህም ድምፅንም በአደባባይ
አያሰማም፡፡ ንግግሮቹ እርካታ ያላቸውና ጣፋጭ ናቸው፡፡ ቃላቱ እጅግ
ትሑት እና ጥሩ መሆናቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ የአንድ ሰው ጠባይ
ምንም ይሁን ምን የማንንም ስሜቶች ፍጹም አይጎዳም ይህንን ሁሉ
የሚያደርገው ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ሳይሆን ከየዋህነቱ የተነሳ ነው፡፡

ሁለት ዓይነት የዋህነት አለ


• የዋህ ሆኖ የሚወለድ ገና ከልጅነቱ የሚጀምር ነው፡፡
• በትምህርት ፣ በትግል ፣ በመልካም ስራ እና በውስጡ ባለ ጸጋ የዋህ
የሚሆን ሰው ነው፡፡

፳፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ቅዱስ ጳውሎስ “እያንዳንዱ ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና


ይቁጠር እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልንጀራው
ደግሞ እንጂ” ፊል፡-፪፥፫ ተመልከት፡፡ ይህ ሁኔታ በአብርሃምና በሎጥ
መካከል ተፈጽሟል፡፡ ዘፍ፡-፲፫፥፭

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዋህ መሆኑን ሐዋርያት ከማስተማራቸው


ሌላ ራሱ ጌታም ገልፆታል እንዲያውም የዋህነትን በተግባር በስቅለቱ
ወቅት በግልጽ አሳይቷል፡፡
የዋሆች ስንሆን
• እግዚአብሔር ጸሎታችንን አይንቅም፡-
• ብንበደል እግዚአብሔር ይፈርድልናል ፡- መዝ፡- ፳፭፥፩(አቤቱ
እኔ በየዋሃቴ ሄጃለው እና ፍረድልኝ)
• አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር እንወርሳለን፡- ማቴ፡-፭፥፭
የዋሆች ብጹአን ናቸው ምድርን ይወርሳሉና።

ሠ ምጽዋት እና በጎነት
ምጽዋት
ምጽዋት ማለት ካለን ነገር ለሌሎች ማካፈል ማለት ነው፡፡ ምጽዋት
ችግረኞችን በማሰብና በመርዳት በእግዚአብሔር የምንታሰብበት እና
በረከት የምናገኝበት የትሩፋት ሥራ ነው፡፡ እኛ ከእግዚአብሔር ተቀብለን
እግዚአብሔር ደግሞ በድሆች በኩል ይቀበለናል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ለድሃ
ቸርነት የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል” በማለት እንዳስተማረን
ለድሆች ማድረግ ለእግዚአብሔር ማድረግ ነው፡፡ ብድራት ሳንጠብቅ
የተቸገሩትን እንርዳ የድሆች ዕዳ ከፋይ እግዚአብሔርበምድር በረከትን
በሰማይ ገነትን ያወርሰናል በትንሳኤ ዘጉባኤ ዋጋችንን ይከፍለናል፡፡
ምጽዋት መመጽወት ከተቀባዩ በላይ ለሰጪው ይጠቅማል፡፡
እግዚአብሔር ሰጪ ካደረገን በደስታ እንስጥ፡፡ እግዚአብሔር ሰጪውን
ተቀባይ ፤ ተለማኙን ለማኝ ፤ ባለጠጋውን ድሃ ፤ንጉሱን ተራ ሰው
፳፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ማድረግ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር የምንሰጠው አያሳጣን እንጂ ከሰጠን


በደስታ መስጠት አለብን፡፡ ምጽዋት ሌሎች የሚታሰቡበትና የሚጎበኙበት
የትሩፋት መንገድ ነው፡፡ አብርሃም እንግዶቹን በመቀበል ፣ ኢዮብ
ድሆችን በመንከባከብ ፣ክርስቶስ ሰው የራቃቸውን በመርዳት ምሳሌ
ሆነውልናል፡፡ ጠያቂና ደጋፊ ሰው ለሌላቸው ረዳት ሰው ሆኖ መገኘት
ትልቅነት ነው፡፡ ልጆች በጎ ማድረግ ጥቅሙ ለራስ ነው፡፡ ዛሬ በጎ
የሚያደርጉ በጎውን ዘመን ዓይኖቻቸው ያያሉ የእግዚአብሔር ጥበቃ
ከክፉ ይጋርዳቸዋል፡፡ የድሃውን ጩኸት ያልሰማ ሰው እግዚአብሔር
ልመናውን አይሰማለትም፡፡
ምጽዋት ካለን ነገር ለድሆች ማካፈል ማለት ነው፡፡ የድሃውን
ጩኸት ቸል ሳይል የሚሰማው አምላክ ድሆችን በኑሮ እንድናግዛቸው
ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ምጽዋት በመመጽወት እግዚአብሔርን እናስደስት፡፡

ጥያቄዎች
• ምጽዋት ምንድን ነው?
• ለድሆች ምን መመጽወት እንችላለን?
• እንግዶችን በመቀበል የሚታወቀው አባት ማነው?
• ለድሃ የሚሰጥ ለማን ያበድራል?
• ምጽዋት ከተቀባዩና ከሰጪው ለማን ይጠቅማል?

፳፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

በጎነት
በገላቲያ ምዕራፍ ፭ ከተገለጹት የመንፈስ ፍሬዎች መካከል አንዱ
በጎነት ነው፡፡ በጎነት ለሰዎች ያለን መልካም አመለካከትና የምናደርገው
ማንኛውም መልካም ሥራ ሁሉ ነው፡፡ በጎነት ማንኛውንም መልካምና
ጥሩ ፣የበጀ የተወደደ ሥራን ያካትታል አምላካችን እግዚአብሔር
በባሕርዩ እና በሥራው በፈጠረው ፍጥረት መደነቁ ሁሉ የበጎነቱ
አይነተኛ ምልክት ነው፡፡ ሁሉንም በየወገኑ በመፍጠሩ ማለት ነው፡፡

ሰ.. የደስታ ሕይወት


ልጆች ደስታ ማለት እግዚአብሔርን እና ሰዎችን ማስደሰት ነው፡እኛም
የምንፈልገውን ማግነት ነው፡፡
ደስታ በምናየውና በምንሰማው ፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈፀሙ
ድርጊቶች የሚሰማን ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር
የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ ደስታ ነው፡፡
የክርስቲያኖች ልዩ ደስታ የሚሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በአምላካዊ ፍቅሩ ዓለምን በማዳኑ በሚሰማን
ደስታ ነው፡፡ ይህም መልአኩ ለእረኞች እንደነገራቸው “ታላቅ ደስታ”
ተብሏል፡፡ ሉቃ፡- ፪፥፲
ለጌታችን እናት ለድንግል ማርያምም ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት
“ጸጋ የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ” ብሏታል ሉቃ ፩፥፳፰ እርሷም የጌታችን
እናት ስለ ደስታ ስትናገር “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ
እና በመድሐኒቴ ሐሴት (ደስታ) ታደርጋለች” ብላለች ሉቃ1፥47
ልጆች ደስ የሚለን በምን በምን ጊዜ ነው? ምንስ በመስረት
• የአምላካችንን ትእዛዝ በፈጸምን ጊዜ
• ወደ እግዚአብሔር ቤት በሄድን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ
ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ፡-፻፳፩፥፲፫
• የክርስቶስ ወንጌል በተማርን እና በዘመርን ጊዜ
• እግዚአብሔር በሕይወታችን ታላቅ ነገርን ባደረገልን ጊዜ መዝ፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

-፻፳፭፥፲፫
በጌታ ያገኘነውን ደስታ የምንገልጠው እንደ ዓለም በዘፈንና በስካር
ሳይሆን አምላካችንን በመዝሙር በማመስገን ነው፡፡ ኢሳ ፶፪፥፱ ይህንንም
ቅዱስ ያዕቆብ “ደስ የሚለው ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር” በማለት
ገልጿል፡፡ ያዕ ፭፥፩፫

ሸ. ሰላማዊ ኑሮ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከገለጸው የመንፈስ ፍሬ ፍቅርና ደስታን
አስቀድመን ተመልክተናል፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ሰላም እንሸጋገራለን፡፡
በቅድሚያ በቅዱስ መጽሐፍ በጸሎት እና በሕይወታችን ሰላም ያለውን
አስፈላጊነት እና ጥቅም በግልፅ እንጀምር፡፡ ሰላም በአጭሩ ለሰዎች
ሕይወት በጣም አስፈላጊ እና የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ በመቀጠልም
ስለ ሰላም ሦስት መሰረታዊ ነገሮችን እንመልከት፡-
• ሰላም ከእግዚአብሔር ጋራ
• ሰላም ከሰዎች ጋር
• ሰላም ከራስ ጋር

ሰላም ለሰው ልጆች ሕይወት በጣም ወሳኝና አስፈጊ ነው፡፡


ከሰላምውጪቤተሰብምሆነማህበረሰብሊረጋጋአይችልም፡፡በዓለም ውስጥ
በጸጥታ የሚኖር ሰው የለም አይኖርም፡፡ምክንያቱም በዓለም መኖር
የምንችለው ከብዙ ውጣ ውረድ ጋር በመሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ያለሰላም
በጸጥታ መኖር አይታሰብም፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለደቀመዛሙርቱ “ሰላምን እተውላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ልባችሁ
አይታወክ አይፍራም” ዮሐ ፲፬፥፳፯ ብሏቸዋል፡፡
ቅዱሳን መላዕክት በጌታችን ልደት ዕለት “ክብር ለእግዚአብሔር
በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር …” ሉቃ ፫፥፲፬ በሥርዓተ ቅዳሴ
“ሰላም ለሁላችሁ ይሁን” የሚለው ቃል በሚቀድሰው ካህን ቅዳሴው
እስኪያልቅ ድረስ ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ የሚሰጥ ቡራኬ ነው፡፡ በሌላ
፴፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

መልኩ ሰላም ስንል አንድ ሰው በውስጡ የሚሰማው የእረፍት ስሜት


ሰላም ይባላል፡፡ ሰላም ከሌለው ጋር በስምምነት እና በአንድነት መኖር
ነው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን በውስጡ የጭንቀት መንፈስ አይኖርበትም
በማህበራዊ ኑሮ ከቤተሰቡ ጋር ፣ ከሚሰራበት መ/ቤት ሰራተኞች ጋር ፣
ከጎረቤት ጋር ፣ ከትምህርት ቤት ጓደኞች ጋር ከሰው ሁሉ ጋር በኑሮ
ውስጥ ሁከት አይፈጥርም፡፡
ቀ. ታዛዥነት
መታዘዝ የትሕትና ፍሬ ነው፡፡ መታዘዝ ለእግዚአብሔር ያለንን
ፍቅር እና ለሰው ያለንን ክብር ያሳያል፡፡ የጽድቅን በረከት እየተቀዳጁ
በመንፈሳዊነት ዘልዓለማዊ ክብር ለማሳደግ መሰረቱ መታዘዝ ነው፡
፡ መታዘዝ ማለት የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ፣ ሥልጣኑን
መቀበልና ትዕዛዙን አክብሮ መፈጸም ነው፡፡ ዘጸ ፬፥፭፡፡ ለሚታዘዙት
በረከቱ ይደርሳቸዋል፡፡ ለማይታዘዙት ደግሞ መርገም በመንገዳቸው
ይጠብቃቸዋል፡፡

ለእግዚአብሔር መታዘዝ፡-
እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር መታዘዛችን
የምንገልጠው ድምጹን በመስማት ፣ ሕጉን በመጠበቅ ፣ በፍቅሩ በመኖር
፣ በምህረቱ በመተማመን ፣ በፈቃዱ በመመላለስና ፍጥረቱን (ሥራውን)
በማክበር ነው፡፡
የአዳም አለመታዘዝ በሰው ልጆች ላይ ጥፋት አመጣ፡፡ የእስራኤል
አለመታዘዝ በምድረ በዳ አስቀራቸው፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስ በሥጋ ሲገለጥ
በሥጋ ለባሾች መካከል እንደ እግዚአብሔር እየሰራ እንደሰው ሲመላለስ
ያስተማረን የጽድቅ ሥርዓት መታዘዝ ነው፡፡ ይስሐቅ ለአባቱ እስከሞት
እንደታዘዘ ክርስቶስም ለመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ፡፡ በመታዘዙ
ዓለምን አዳነ፡፡ ፡፡ ለምናምነው ሁሉ ፍለጋውን ትቶልናል፡፡

፴፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

እግዚአብሔር የሚታዘዙትን
• ይባርካል ያከብራልም፡፡
• በእግዚአብሔር መንግስት እንደ ፀሐይ የሚያበሩት በምድር
ታዘው ያከበሩት ናቸው፡፡
• እግዚአብሔር ወዳጆቹን የሚለይበት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ትዕዛዙን
በደስታ ተቀብሎ መፈጸም በረከትን ያስገኛል፡፡ በእግዚአብሔር
ያለን ፍቅር የሚገለጸው በመታዘዛችን ነው፡፡

ሥዕል ፪ ለቤተሰቡ የሚታዘዝ

፴፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ለወላጆች መታዘዝ፡-
ወላጆች ደክመው ያሳደጉን ባለውለታዎቻችን ናቸው፡፡ ወላጆቻችንን
እንድንታዘዝ፣ ህግና ነቢያት፣ ተፈጥሮና ወንጌል መክረውናል፡፡ መታዘዝ
ሁለቱም ኪዳናት በማዕተም ያጸኑት ቃል ነው፡፡ ኦሪት “አባትህንና
እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር እድሜህ
እንዲረዝም” ትላለች ዘጸ ፳፥፪ ሐዲስ ኪዳን “ ልጆች ሆይ ለወላጆቻችሁ
በጌታ ታዘዙ ይህ የሚገባ ነውና” ይለናል፡፡ ኤፌ፡-፮፥፩ ክርስቶስ ለእናቱ
ይታዘዝ ነበር ሉቃ ፪፥፩፡፡ ለወላጆች ስንታዘዝ ፍቅራቸው ይበዛልናል፣
እግዚአብሔር ይባርከናል፣ እድሜያችን ይረዝማል፣ ወደፊት ለእኛም
ልጆቻችን ይታዘዙልናል፡፡

ለመሪዎች መታዘዝ፡-
የእግዚአብሔር ልጆች ለስጋዊው ዓለምና ለመንፈሳዊው ዓለም/
ለቤተክርስቲያን/ መሪዎች እንዲታዘዙ እግዚአብሔር አዟል፡፡ መሪዎችን
መልካም በሆነ ሁሉ መታዘዝ ይገባል፡፡ ነገር ግን እንደ ናቡከደነፆር
እና ብልጣሶር “እግዚአብሔር ካዱ ለጣዖት ስገዱ” ለሚሉት ትዕዛዝ
እንደ ሦስቱ ወጣቶች “በዕምነት እምቢ” ማለት አለብን፡፡ ከሰው ይልቅ
ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባልና፡፡ ሐዋ ፭፥፱ ዳን ፫፥፫፡፡ ለአለም መሪዎች
የምንታዘዘው ሃገራዊ ሕጎችን በመጠበቅና በመፈፀም ነው፡፡ ሮሜ፡-፫፥፩ ፩ኛ
ጴጥ፡-፪፥፫ ፡፡ ለቤተክርስቲያን መሪዎች የምንታዘዘው የእግዚአብሔርን
ሕግ በመፈጸም የሐይማኖት ቤተሰቦችን በሚያስፈልጋቸው በጎ ነገር
በመርዳትና ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገውን በማሟላት ነው፡፡ ፊል
፪፥፪ ፣ ዕብ ፫፥፯፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰራተኞች ለአሰሪዎቻቸው እንዲታዘዙ
፣ ሽማግሌዎችንም እንድንታዘዛቸው ያዛል፡፡ ኤፌ ፮፥፭ ፣ ፩ኛ ጴጥ፭፥፭፡፡

፴፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

ማጣቀሻ መጽሐፍት
፩.መጽሐፍ ቅዱስ
፪.ለሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀ ማስተማሪያ መጽሐፍ
፫.ከፍትሕ ነገስት
፬.የቤተ ክርስቲያን ጸሎት
፭.መርሐ ሕይወት
፮. ጾምና ምጽዋት
፯.ዐበይት ሥነ ምግባራት
፲. እግዚአብሔርን መፍራት
፱. ክርስቲያናዊ ሕይወት
፲. ጸሎት ለመንፈሳዊ ሕይወት
፲፩. የመንፈስ ፍሬዎች
፲፪. የዚህ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያ እንዲሆን ከታተመው
የመምህራን መመሪያ ላይ

፴፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አራተኛ ክፍል

፴፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
የሰንበት ት/ቤት አመራር እና መምህራን
እንዲሁም ተማሪዎችና ወላጆች በመጽሐፉ ላይ
ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት እና ግብዓት
በሚከተለው አድራሻ ላኩልን

office@eotc-gssu.org
https://t.me/GSSUCurricu-
lum_bot

You might also like