You are on page 1of 14

ትምህርተ ሃይማኖት

፩ ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው? ከቃሉ ትርጉም እስከ ሚስጢራዊ ትርጉም አብራርተ ጻፍሁ?

. ሃይማኖት ፈጣሪና ፍጡር የሚገናኙበት ረቂቅ መንገድ ነው

. በ አንድ እግዚአብሔር ማመን በህላዌው በባህርየ መለኮቱ ፥ በመጋቢነቱ ፥ በከሃሊነቱ ፥ በልዩ ሦስትነቱ ፥ ዓለምን
ካለመኖር ወደ መኖር በማምጣቱ ማመን ነው .ሃይማኖት የሚለው ቃል ሃይመነ 'አሳመነ ከሚለው ግእዝ የተገኘ ግስ
ሲሆን ትርጉሙም ማመን፥መታመን፥ጽኑ ተስፋ ማለት ነው።

ይኸውም ቅድመ ዓለመ አሳልፎ የሚኖር ለእርሱ ግን አስገኚ አሳላፊ የሌለ መሆኑን በአንድነት በሦስትነት ያለ ሁሉን ቻይ
አምላክ እንዳለ ማመን ነው

"ማመን" ማለት ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ ለወሰነ ፥ለእርሱ ግን አስገኚ ፈጣሪ የሌለው ፥የሚወስነው አንዳች ነገር የሌለ
(የማይወሰን) ፥ በባህሪው የማይመረመር ፥ሁሉን ቻይና ሁሉን አዋቂ የሆነ የሚሳነው ነገር የሌለ ፥ከፈጠረው ፍጥረታት
ጋር በቸርነቱ ፥በረድኤቱ በፍቅሩ ሳይለይ ፍጥረታትን በሥርዓትና በነፃነት የሚገዛ የሚያስተዳድር አንድ አምላክ አለ ብሎ
ያለ ጥርጥር መቀበል ማመን ማለት ነው ።

"መታመን" ማለት በማመን ውስጥ በረቂቅ አሳብ የተረዳነውን አምላክ ያለጥርጥር ተአማኒ ሆኖ መገኘት ነው
፤ለቃሉና ለትህዛዙ በፍቅር ፍፁም መገዛት ተግባራዊ ምላሽ መስጠት መታመን ማለት ነው።

ሚስጢራዊ ትርጉም ለምሳሌ

ከዉሃና ከመንፈስ በጥምቀት ከእግዚአብሔር የፀጋ ልጅነት እንደምናገኝ አምኖ መቀበል ማመን ሲሆን ፥መጠመቅ
ልጅነት ማግኘት ደግሞ መታመን ነው ።

ሌላው እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ እስከ መቃብር እንደወደደን ያለጥርጥር አምኖ መቀበል ማመን ሲሆን
፥ባልንጀራችንን በመውደድና ትህዛዙን በመጠበቅ መግለፅ መታመን ነው።

"ጽኑ ተስፋ " ማለት አምነው ታምነው የኖሩለትን አምላክ በኋላ በመጣ ጊዜ ያመነውን የታመነውን ነገር ዋጋ
ይሰጠናል ብሎ ተስፋ ማድረግ ነው ። አንድም ከሞት በኋላ ሕይወት ከመቃብር በኋላ ትንሣኤ ይሰጠናል ብሎ እምነትን
አጽንቶ ምግባርን አቅንቶ በተስፋ መጠባበቅ ነው ።

X ፪ የሃይማኖትና የእምነት ልዩነትን አብራርተህ ጻፍ ?

. እምነት በቁሙ ሃይማኖት ፥ማመን፥ መታመን ፥አስተማመን፥እሙንነት ማለት ነው

እምነት ማለት “ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡ ዓለሞች
በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን (ዕብ 11፡1-
3)፡፡” ለምሳሌ መንግስተ ሰማያትን (የዘላለም ሕይወትን) ተስፋ እናደርጋለን፡፡እምነትም ይህንን ተስፋ ያረጋግጥልናል፡፡
የእግዚአብሔርን (የሰማዩን) መንግስት አላየነውም፡፡ እምነት ይህንን ያላየነውን ነገር ያስረዳናል፡፡ ሳይንስ ይህንን ሊያደርግ
አይቻለውም፡፡

ሃይማኖት " .ማለት ደግሞ እምነትና አምልኮን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ የእምነትና የአምልኮ ሥርዓት ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔርን አምነን የምናመልክበት ሥርዓት ሃይማኖት ይባላል፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔርን እናምናለን፡ እርሱንም
እናመልካለን፡፡ እርሱን ምን ብለን እንደምናምንና እንዴት እንደምናመልክ (የአምልኮ ሥርዓት እንደምንፈጽም) የሚገልጽ
ሃይማኖት ነው፡፡ ስለዚህ የእምነት መገለጫው ሃይማኖት ነው፡፡

X ፫ " ሃይማኖት የሚመሰልባቸው ምሳሌዎች ፬ (4) ነገሮችን አብራርተህ ጻፍ?

* ሃይማኖት በመንገድ ትመሰላለች

መንገድ ከዚህ ጫፍ ወድያ ማዶ ያሉትን እንደሚያገናኝ ሃይማኖትም በምድር ቤተክርስትያን ያሉትን በሰማይ ካሉት ጋር
ታገናኛለችና በመንገድ ትመሰላለች ።

* ሃይማኖት በቤት መሠረት ትመሰላለች

አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ " ሃይማኖትን በቤት መሠረት " ፥ ምግባርን በጣርያና ግድግዳ ይመስላቸዋል

. ሃይማኖት መሠረት ነው ለምግባር ሁሉ ምንጭ ነውና

. ቀድሞ የሚታነጸው መሠረት እንደሆን ከምግባርም የሚቀድመው ሃይማኖት ነው ።

. መሠረት የሌለው ቤት ጎርፍ እና ንፋስ ይጥሉታል ፤ ሃይማኖትም የሌለው ሰው ክህደትና መከራ ይጥሉታል ።

* ሃይማኖት በሰናፍንጭ ትመሰላለች

. ሰናፍንጭ ፍጽምት ናት ነቅ የለባትን ሃይማኖትም ፍጽምት ናት ነቅ የለባትም

. ሰናፍንጭ አንድ ጊዜ ከተዘራች በኋላ ሁል ጊዜ ታበቅላለች ( ታፈራለች) ሃይማኖትም አንድ ጊዜ ተሰጣ ለዘላለም
ትኖራለች

* ሃይማኖት በወርቅ ትመሰላለች

.ወርቅ ከማዕድናት ሁሉ ንጹሕ ፥ ጽሩይ ነው ። ሃይማኖትም ንጹሕ ፥ ጽሩይ ነው እንከን ፈጽሞ አይገኝባትም ።

. ወርቅ ወርቅነቱ የሚታወቀው በእሳት ተፈትኖ እንደሆነ ሁሉ የሃይማኖትም ጥንካሬው የሚታወቀው በፈተና ተፈትኖ
ነው ። ነገር ግን በእሳት ምን ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ነው ።፩ ጴጥ
፩፥፯

X ፬ ' ዶግማ እና ቀኖና ልዩነታቸው ምንድን ነው ? አብራርተህ ጻፍ?

* ዶግማ ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን " ዶከይን" በጥሬው ቃሉ አመለካከት ፥ አስተሳሰብ ፥ አዋጅ ማለት ነው

.በ ሚስጥራዊ ቤተ ክርስትያን አፈታት የሃይማኖት (የእምነት) መሠረት ማለት ።

ዶግማ የተደነገገ፥ ውሳኔ ማለት ሳይሆን የተገለጠ ማለት ነው ።

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የገለጠው በሙሉ ዶግማ ነው ።

ዶግማ ሊለወጥ ፥ ሊሻሻል አይችልም

"ማቴ ፭፥፲፯ ሕግና ነብያትን ልሽር የመጣው አይምሰላቹ ላፀናው እንጂ" ሕግን የሰራ ሕግን የደነገገ እርሱ እግዚአብሔር
ነው ሊለውጥ ይቻለዋል ፤ ነገር ግን ፈጽሞ ሊሻሻል ሊቀየር የማይቻል ነገር እንዳለ ሲነግረንም ነው
ምሳሌ ፭ አህማደ ሚስጢራት

_ እመቤታችን አምላክን በድንግልና ስለመውለዳ

_ አሥርቱ ትህዛዛት ዶግማ ናቸው

* ዶግማ የቤተክርስትያን ራስ የተባሉ ቅዱስ ሲኖዶስ እንኳን ሊያሻሽሉት አይችሉምና ምክንያቱም የእምነት መሠረት
ነውና

* ቀኖና ማለት ሕግ ፥ስርሀት ፥ደንብ ፥ ፍርድ ፥ ቅጣት፥ መጠን ፥ ልክ ማለት ነው ።

በግሪኩ ካኖን በእብራይስጡ ቃኒን ይሉታል ። ይህም አንድን ነገር ለመለካት ለመመዘን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን
ለማረጋገጥ መጠኑን ለማወቅ የሚያገለግል መለኪያ (መስፈርያ) ማለት ነው ።

* ለመፀሐፍ ቅዱስ ሲሆን ቀኖና ለቁጥር መለክያ የተወሰነ የተመጠነ የመፃህፍት ብዛት ልክ ይነግረናል ፤ ፹፩ አሐዱ
ከዚህ አትለፍ ቀኖና መጻህፍት እንላለን

* በንስሐ ደረጃ ያለ ቀኖና ማከሚያ ተብሎ ሲተረጎም በደል የሰራ የንስሐ ልጅ የንስሐ አባቱ በሚችለው በልኩ ቀኖና
(ቅጣት ) ይሰጡታል ይህም ለበደሉ ልክ ሆኖት ሳይሆን የአምላክ ቸርነቱን ማሳያ አድርገው የንስሐ ቅጣት ይሰጡታል።

* ቀኖና ከትምህርተ ሃይማኖት አንጻር ፥+ ከችግር አንጻር እንደ አስፈላጊነቱ ሊሻሻል የሚችል ነገር ማለት ነው ።

"ቀኖና አጥቢያዊ ፥ ገዳማዊ ፥ አገረ ስብከታዊ ፥ ሀገራዊ፥ ዓለም አቀፋዊ ሆኖ ሊደነገግ ይችላል " ።

* ቤተክርስትያን ቀኖና ለመስራት የተገደደችው በየጊዜው የሚያጋጥማትን አለመግባባት ለመፍታት አመቺ እንዲሆን
ነው (የአዋርያት ስራ ፲፭ ) የመጀመርያው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ

* ቀኖና ሊሻሻል የሚችለው በቅዱስ ሲኖዶስ ነው

በአጠቃላይ

ፆም ዶግማ ነው አፈጻፀሙ ግን ቀኖና ነው

X ፮ ሚስጢረ ሥላሴ ከመጸሐፍ ቅዱስ አብራርተህ ጻፍ ?

ምስጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን

*.እግዚአብሔርም አለ፡- «ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 እዚህ ላይ «እግዚአብሔርም አለ»
ሲል አንድነቱ፣ «እንፍጠር» ሲል ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በዚህ ንባብ እግዚአብሔር የሚለው ሥመ አምላክ
ከአንድ በላይ እንደሆኑ ያስረዳናል ። ስለ ሥላሴ ኃልወት በሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ከተጻፉት ምንባባት ጋር
በማገናዘብ ይህ ጥቅስ ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን እንደሚመሰክር በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ አንቀጽ
እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን የሚለው ንግግር የሦስት ተነጋጋሪዎች ነው እንጂ ያንድ ተናጋሪ ቃል አይደለም፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር፤ ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን፤ ሲል ሦስትነቱን ማስተማሩ ነው፡፡ ሙሴም ይህን
የእግዚአብሔርን ነገር ሲጽፍልን ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ያለውን የብዙውን አነጋገር ለአንድ
ሰጥቶ፤ እግዚአብሔር አለ፤ ብሎ መጻፉ በአካል ሦስት ሲሆን በባሕርይ በህልውና አንድ ስለሆነ በአንድ ቃል መናገሩን
ከእግዚአብሔር ተረድቶ ለእኛ ሲያስረዳን ነው፡፡
*.እግዚአብሔር አምላክ አለ፡- «እነሆ አዳም መልካሙንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ዘፍ.3-22
«እግዚአብሔር አለ» ሲል አንድነቱን፣ «ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ሲል ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
እግዚአብሔር ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ በማለቱ ሦስትነቱን ያስረዳል፡፡ ምንአልባትም እግዚአብሔር አለ፤ አዳም ከእኛ እንደ
አንዱ ሆነ፤ የሚለው ቃል ሦስት ተነጋጋሪዎች በአንድ ቦታ ቢኖሩ አንዱ ሁለቱን ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ብሎ ሲነገር ከአንድ
የበዙ ተናጋሪዎች ቃል መሆኑን ነው የሦስትነት ተነጋጋሪዎች መሆኑን ስለሚያስረዳ እግዚአብሔር ሦስት አካል መሆኑ
በዚህ አነጋገር ግልጽ ነው፡፡

*. በባቢሎን ግንብ ወቅት፡ እግዚአብሔርም አለ፡- «ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ
እንደባልቀው፡፡» ዘፍ.11.6-8፡፡ «እግዚአብሔር አለ» ብሎ አንድነቱን፣ «ኑ እንውረድ» ብሎ ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን
ያመለክታል፡፡በዚህ አንቀጽ እግዚአብሔር ኑ እንውረድ ብሎ በመናገሩ ከሁለትነት የተለየ ሦስትነቱን ያስረዳል፡፡
«በቀትርም ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት አብርሃም ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ» ዘፍ.18.1-15
በማለት እግዚአብሔር አንድ መሆኑንና ሦስት አካል ያለው መሆኑን ወስኖ ያስረዳናል፡፡

የነቢያት ምስክርነት፡ እግዚአብሔር ለሙሴ በተገለጠለት ጊዜ «እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣
የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ነኝ» ዘጸ.3-6 ሲል «አምላክ፣ አምላክ፣ አምላክ» ብሎ ሦስትነቱን፣ «እኔ እግዚአብሔር
ነኝ» ብሎ ደግሞ አንድነቱን ገልጾ ተናግሯል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊትም «የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን
ሞላች፣ በእግዚአብሔርም ቃል ሰማዮች ጸኑ፣ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ» በማለት የሥላሴን ምስጢር
ተናግሯል (መዝ.32-6)፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም «ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ
አየሁት… ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ
ይጨሁ ነበር፡፡» ኢሳ.6.1-8 በማለት ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ብሎ ሦስትነቱን፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአበሔር ብሎ ደግሞ
አንድነቱን አይቶ መስክሯል፡፡ እንዲሁም “የጌታንም ድምፅ ‘ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል’ ሲል
ሰማሁ” (ኢሳ. 6፡8) በማለት ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን አመልክቷል፡፡ የእግዚአብሔር ቀራቢዎች አገልጋዮች
ሱራፌል በምስጋናቸው ሦስት ጊዜ ብቻ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ማለታቸው የሦስትነቱን አካላት መጥራታቸው ነው፤
እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ በማለት በአንድ ስም ጠርተው ምድር ሁሉ ምስጋናህን መልታለች በማለት ያንድ
ተመስጋኝ ምስጋናን መስጠታቸው ሦስቱ አካላት አንድ ሕያው እግዚአብሔር፤ አንድ ገዥ፤አንድ አምላክ፤ አንድ
ተመስጋኝ አምላክ መሆኑን መመስከራቸው ነው፡፡ ሱራፌልም በዚህ ምስጋናቸው እግዚአብሔር በአካል ከሦስትነት
ያልበዛ ሦስት ብቻ እንደ ሆነ በባሕርይ በህልውና ከአንድነት ያልበዛ ሦስት አካል አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን
ይመሰክሩልናል፡፡

* ምስጢረ ሥላሴ በሐዲስ ኪዳን

በሐዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት /ምስጢረ ሥላሴ/ በምስጢረ ሥጋዌ (በጌታችን በተዋህዶ ሰው
መሆን) በሚገባ ታውቋል፡፡

በብስራት ጊዜ፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም እመቤታችንን ባበሠራት ጊዜ «መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣለ፣
የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንች የሚለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡» ብሎ የሥላሴን
ሦስትነት በግልጽ ተናግሯል፡፡ሉቃ.1-35፡፡

*.በጥምቀት ጊዜ፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ /ሰው ሆኖ/ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ፣ አብ
በደመና ሆኖ «የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚላችሁን ስሙት» ሲል፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በራሱ ላይ በርግብ አምሳል
ሲወድቅበት ታይቶአል፡፡ /ማቴ.3.16-17፣ ማር.1.9-11፣ ሉቃ.3.21-22፣ ሉቃ.1.32-34/ በዚህም እግዚአብሔር በአካል
ሦስት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
*.በደብረ ታቦር፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለፀበት በደብረ ታቦር ተራራም ምስጢረ ሥላሴ ተገልጿል፡፡ ወልድ
በተለየ አካሉ ሥጋን ተዋህዶ በደብረ ታቦር ተገኝቶ፣ አብ በሰማያት ሆኖ ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ እርሱ ነው፤ እርሱን
ስሙት›› የሚል ቃል ተናግሮ፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በደመና ጋርዷቸው ተለግጠዋል፡፡ ማቴ 17፡1-10

*.ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሲሠጥ፡ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከማረጉ በፊት
ለደቀመዛሙርቱ ቋሚ ትዕዛዝ ሲሰጥ «እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው» ብሏል ማቴ.28.19-20፡፡ በዚህም ‹‹ስም›› ብሎ አንድነታቸውን ‹‹አብ
ወልድና መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ ሦስትነታቸውን ይነግረናል ።

X "፯.ሚስጥረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው ? በዚህ የሚታወቁ መናፍቃን ሦስቱን ጥቀስ?

*ምስጢረ ሥጋዌ ማለት “ቃል ስጋ ሆነ በእኛም አደረ” በሚለዉ የወንጌል ቃል ላይ የተመሰረተ ታላቅየክርስትና ሃይማኖ
ት ምስጢር ነዉ ። ዮሐ ፩፥፲፬

ሥጋዌ : ተሰገወ ሰው ሆነ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ምስጢረ ስጋዌ ማለት የእግዚአብሔር

አካላዊ ቃል ወልድ ሰዉን ለማዳን ሲል ሰዉ የሆነበት ፤ ሰዉን ያዳነበት ፤ መለኮትና ትስብእት በተዋህዶ

አንድ የሆኑበት ምስጢር ማለት ነዉ።

ክርስቶስ በቃልነቱ በመለኮቱ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ከእግዚአብሔርም የተገኘ አምላክ ወልደ አምላክ

እንደሆነ፤ በስጋ ደግሞ ከአዳም ተገኝቷል። እኛን ሰዎችን ለማዳን ከእኛ ጋር ዝምድና መስርቷል ። ከቅድስት
ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ሰዉ በመሆኑና በመወለዱ ከአዳም

ልጆች ጋር ያለዉን ዝምድና በተዋሐደዉ ስጋ አጽንቶታል።ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ

የእግዚአብሔር ልጅ የሰዉ ልጅ ሆኗል፤ እርሷም የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን በመዉለዷ የአምላክ

እናት ሆናለች።

* በሚስጥረ ሥጋዌ ላይ የተነሱ መናፍቃን ?

ይኸውም *፩ ንስጥሮስ

1 ኛ ክርስቶስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አለው፤ 2 ኛ/ ክርስቶስ ፍጹም ሰው እንጂ ፍጹም አምላክ አይደለም፤
እንዲሁም 3 ኛ/ እመቤታችን ሰውን እንጂ አምላክን አልወለደችም፤ ስለዚህ እመቤታችን ወላዲተ ሰብእ እንጂ ወላዲተ
አምላክ ልትባል አይገባትም (ሕስወኬ ትሰመይ ወላዲተ አምላክ፣ በአማን ትሰመይ ወላዲተ ሰብእ) ብሎ በማስተማሩ ይህ
ኑፋቄ በ 431 ዓ.ም. ላይ በታላቁ መምህር በእስክንድርያው ፓትርያርክ በቅዱስ ቄርሎስ አማካኝነት በኤፌሶን ጉባኤ
ተወግዞ ችግሩ ተወግዶ ነበር፡፡ ሆኖም የንስጥሮስ የክህደት እምነት ጨርሶ ሳይጠፋ በዚያው በመካከ ለኛው ምሥራቅ
በተለይ በፋርስና በባቢሎን እንዲሁም በኤዴሳ ሲስፋፋ ቆይቷል፡፡ እንዲሁም ንስጥሮሳውያን በኤፌሶንና በቊስጥንጥንያ
በብዛት ይገኙ ነበር፡፡

አውጣኪና ትምህርቱ

የንስጥሮስን ትምህርት በጥብቅ ይቃወሙ የነበሩት የግብጽ መነኰሳትና ካህናት ነበሩ፡፡ በቊስጥንጥንያም ቢሆን አያሌ
የንስጥሮስ ተቃዋሚዎች ነበሩ፡፡ የንስጥሮስን ትምህርት አጥብቆ ይቃወም የነበረና ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት እጅግ ቀናኢ
የነበረ አውጣኪ የተባለ በቊስጥንጥንያ የአንድ ትልቅ ገዳም አበምኔት (መምህር) ነበር፡፡ *
*፪ አውጣኪ ‹‹ክርስቶስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አለው›› የሚለውን የንስጥሮሳውያንን ትምህርት አጥብቆ
በመቃወም እሱ ወደ ተቃራኒው የባሰ ክህደት ውስጥ ገባ፡፡ አውጣኪ በቊስጥንጥንያ ‹‹ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ
ብቻ አለው፤›› እያለ ያስተምር ጀመር፡፡ አባባሉ የቅዱስ ቄርሎስን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ይመስላል፡፡ አውጣኪ
ግን ‹‹አንድ ባሕርይ›› ሲል የክርስቶስን መለኮታዊ ባሕርይ ብቻ ማለቱ ነበር፡፡

በአውጣኪ አባባል ‹‹ሁለቱ ባሕርያት ማለት የሥጋና የመለኮት ባሕርያት በተዋሐዱ ጊዜ የመለኮት ባሕርይ የሥጋን
ባሕርይ ውጦታል፤ አጥፍቶታል፡፡ ሥጋና መለኮት ከተዋሐዱ በኋላ በክርስቶስ ላይ የሚታየው የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው፡፡
በክርስቶስ የሥጋ ባሕርይ ተውጦ የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው የሚታየው፤›› ይል ነበር፡፡ ይህ አባባል በእኛም ቤተ
ክርስቲያን ማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተወገዘ ነው፡፡ አውጣኪ በተጨማሪ ከሥጋዌ በኋላ
ክርስቶስ ፍጹም ሰው ነው ለማለት ‹‹ክርስቶስ ዘዕሩይ ምስሌነ በትስብእቱ›› ማለት ‹‹ክርስቶስ በትስብእቱ (በሥጋው)
ከእኛ ጋር አንድ ነው›› የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ አነጋገር አይቀበልም ነበር፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት
መሠረት ‹‹ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው፡፡›› ነገር ግን ፍጹም ሰው ካልሆነና እኛን ወክሎ በመስቀል ላይ
በሥጋው መከራን ካልተቀበለ፣ የእኛ የሰዎች ድኅነት አስተማማኝ አይሆንም፡፡ በክርስቶስ የሥጋና የመለኮት ባሕርያት
ተዋሕደው በመስቀል ላይ በአንድነት ባሕርዩ በተቀበለው መከራ ድኅነትን አግኝተናል፡፡

‹‹በክርስቶስ የሥጋ ባሕርይ ተውጦ ወይም ጠፍቶ የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው የሚታየው›› የሚል የኑፋቄ ትምህርት
ነበር አውጣኪ የሚያራምድ የነበረው ። ለዚህም አባቶች በሚገባ አብራርተው መልሰውለታል አልመለስ ቢል ተወግዛል።

፫* ኬልቄዶናውያን ጉባኤ( የውሾች ጉባኤ)

የጉባሄው ዓላማ 1 ኛ/ በመናፍቅነት የተከሰሰውንና የተወገዘውን አውጣኪን ነጻ አድርጎ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት


መመለስ ነው ፡፡

2 ኛ/ ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ጉባኤው ላይ እንዳይገኝ የመንግስት ወታደሮች በሩ ላይ አቁመው ነበር ( ለስውር ተንኮል )
መልሰውም ወደ ጉባሄው ያልመጣው የሮሙ ፖፕ ልዮን የላከውን የሃይማኖት መግለጫ ደብዳቤ (The Tome of Leo) ላለ
መቀበል እና ደብዳቤውንም ፖፕ ልዮንንም አውግዟል የሚል ነው፡፡

3 ኛ/ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ሦስት ጊዜ ተጠርቶ አልተገኘም የሚል ነበር፡፡

ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ከተወገዘና ከሥልጣን እንዲወርድ ከተወሰነበት በኋላ ንግሥት ብርክልያ በግል አስጠርታ ሐሳቡን
ለውጦ በልዮን ጦማር (Tome of Leo) ላይ እንዲስማማና እንዲፈርም ትእዛዝ አዘል ምክር ሰጥታው ነበር ይባላል፡፡ እሱ
ግን መንፈሰ ጠንካራ ስለነበር የንግሥቲቱን ትእዛዝና ምክር አልተቀበለም፡፡ በዚህ ተናዳ ንግሥቲቱ ቅዱስ ዲዮስቆሮስን
በወታደሮች በሚያሰቅቅ ሁኔታ አስደበደበችው፡፡ በዚህም ድብደባ ጥርሶቹ ወላልቀው ጽሕሙም ተነጫጭቶ ነበር፡፡
እሱም የተነጨ ጽሕሙንና የወለቁትን ጥርሶች በአንድ ላይ ቋጥሮ ‹‹ይህ የሃይማኖት ፍሬ ነው፤›› የሚል ጽፎበት ለግብጽ
ምእመናን ልኮላቸዋል።

X ፰ ****************

፲ . ወልድ ስንት ልደት አለው? እንዴት?አብራርተህ ጻፍ

የኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት

ወልደ እግዚአብሔር፣ ወልደ ማርያም (የእግዚአብሔር አብ ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት
ልደታት አሉት፡፡ የመጀመሪያው (ቀዳማዊ) ልደት ዘመን ከመቆጠሩ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ወልድ
ከእግዚአብሔር አብ ከሰው አእምሮ በላይ በሆነ ምሥጢር (አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ) የተወለደው ልደት ነው
(መዝ 2፥7 መዝ 109፥3 ምሳ 8፥25)፡፡ ሁለተኛው (ደኀራዊ) ልደቱ ደግሞ ዓለም ከተፈጠረ አዳም ከበደለ ከአምስት ሺ
አምስት መቶ ዘመን በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደው ልደት ነው (ገላ 4፥4 ኢሳ 7፥14 ኢሳ 9፥6 ዘፍ
3፥15 ፤18፥13 ፤ 12፥8 ፣ መዝ 106፥20)፡፡ ዘመን የማይቆጠረለት፣ በቅድምና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ፣
ዓለምንም በአምላክነቱ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አካላዊ ቃል መለኮታዊ አካሉን፣ መለኮታዊ ባሕርይውን ሳይለቅ
በተለየ አካሉ ንጽሕት፣ የባሕርያችን መመኪያ ከምትሆን ከድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምላካዊ አካልና
ባሕርይን ከሰው አካልና ባሕርይ ጋር ያለመጠፋፋት፣ ያለመቀላቀል ተዋሐደ እንጅ አካሉም ባሕርይውም አልተለወጠም፡፡

፲፩. ሃያው ዓለማት የሚባሉት እነማን ናቸው ? አብራርትህ ጻፍ?

ከእሳት፥ ከነፋስ ፥ ከውሀ ፥ ከመሬት የተፈጠሩ ሃያ ዓለማት አሉ እነሱም

* ዓለማተ እሳት ፡. ከእሳት የተፈጠሩ ናቸው እነዚህም ቁጥራቸው ዘጠኝ (፱) ነው እነዚህም

ሰባቱ ሰማያት ( ሰማይ ውዱድ ፥ መንበረ ስብሐት ፥ ጽርሐ አርያም ፥ መንግስተ ሰማያት ፥ እና ኢዮር፥ራማ ፥
ኤረር መላህክት የሚኖሩበት ሁለቱ የተቀሩት ደሞ ምጽንዓተ ሰማይ ፥ ገሃነመ እሳት ናቸው ።

* ዓለማተ ነፋስ ፥> ነፋስ የመላበት ፤ በነፋስ የጸና የረጋ ዓለም ማለት ነው።

፩ ሐኖስን የተሸከመ ባቢል የተባለ የረጋ ንፋስ

፪. ይህን ዓለም የተሸከመው የምድር ንጣፍ ጉዝጓዝ የሆነ ንፋስ ናቸው

* ዓለማተ ማይ ፥> ከውሀ የተፈጠረ ውሀ የመላበት ዓለም ማለት ነው ።

፩. ሀኖስ ( ከጠፈር በላይ የሚገኝ ስፍራ ነው)

፪. ጠፈር

፫. ውቅያኖስ

፬. ከምድር በታች ያለው ውሀ ናቸው

**ዓለማተ መሬት ፥> ከመሬት ከአፈር የተፈጠሩ ናቸው ። እስከ እልፈተ ኦኣለም ድረስ የተለያዪ አገልግሎቶች ለሰው
ልጆች ያበረክታሉ ።

እነሱም ፥> ፩. የምንኖርበት ዓለም

፪. ብሔረ ብፁዓን ፥> ከአጥያት በስተቀር የጽድቅ ስራዎች ሁሉ የሚሰራባት እና በውስጣ በውስታ በቅዱስ ጋብቻ
የፀኑ እንደሚኖሩባት ገድለ ቅዱስ ዞሲማስ ያስረዳል ። በደቡብ አቅጣጫ ይገኛል

፫.ብሔረ ሕያዋን ፥> በዚህ የሚኖሩ በጽድቅ ስራቸው ከዚህ ዓለም የተሰወሩና ሞትን ያላዩ ከዳግም ምፅዓት ቀደም
ብሎ ለሰማህትነት ይገለጣሉ ። በሰሜን አቅጣጫ ይገኛል ።

፬. ገነት ፥> ጻድቃን ፥ ሰማህታት ፥ ደናግላን በአካለ ነፍስ ይኖሩባታል ። እስከ ዳግም ምፅዓት ድረስ።

በምስራቅ አቅጣጫም ይገኛል።

፭. ሲኦል ፥> ድቅድቅ ጨለማ የመላባት ከምድር በታች የሆነች መካነ ኋጥአን በአካለ ነፍስ እስከ ምፅዓት ድረስ
ይኖሩባታል ። በምዕራብ አቅጣጫ ይገኛል።

አምስቱ ዓለማተ መሬት የሚባሉት በብርሃን መጠን ይበላለጣሉ ።


ሲኦል ድቅድቅ ጨለማ ናት ከሲኦል የምንኖርባት ዓለም ታበራለች ። ከምንኖርባት ዓለም ደግሞ ብሔረ ብጹዓን ከብሔረ
ብጹዓን ብሔረ ሕያዋን ከብሔረ ሕያዋን ደግሞ ገነት ታበራለች ።

X ፲፪ ሥላሴ ማለት ምን ማለት ነው ? ስለምንስ በሴት አንቀጽ ተጠሩ አብራርተህ ጻፍ ?

* ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹ቅድስት›› ተብሎ ደግሞ በሴት አንቀጽ /ቅድስት
ሥላሴ/ ይጠራል ።

‹‹ቅድስት›› የሚባልበትም ሃይማኖታዊ ምሥጢር፡-

. ቅድስት

ሥላሴ ‹‹ቅድስት›› ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት /እናት/ ልጅዋን መውለዷን እንደማትጠረጥረው ሁሉ
ሥላሴም ይህን ዓለም መፍጠራቸውን ስለማይጠረጥሩ ነው፡፡ ሁሉም ከእነርሱ፣ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ሆኗልና፡፡ ሴት
ወይንም እናት ልጅዋ ቢታመምባት እንዲሞትባት አትሻም፤ ሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳን በጠላት ዲያብሎስ
እንዲገዛባቸው አይፈቅዱም፡፡ ሴት ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ
አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እያልን እንጠራቸዋለን፡

X ፲፫. የቅድስት ሥላሴ የአካል ግብር ስም ከመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ጭምር አብራርተ ጻፍ

የመለኮት ባሕሪያት አንድ ሲሆን። ሦስትነት፦አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሲገለጽ፤

* የአካል ሦስትነት፦ ለአብ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ አለው፥ ለወልድም ፍጹም ገጽ፥ፍጹም

አካል፥ፍጹም መልክ አለው፥ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ አለው።

*የስም ሦስትነት፦አብ የአብ ስም ነው፥ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይጠሩበትም፥ወልድም የወልድ ስም ነው፥አብ


መንፈስ ቅዱስ አይጠሩበትም፥መንፈስ ቅዱስም የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፥ አብ ወልድ አይጠሩበትም።

*የግብር ሦስትነት፦የአብ ግብሩ ወልድን መውልድ መንፈስ ቅዱስን ማሥረጽ፥የወልድ ግብሩ፥ከአብ

መወለድ፥የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ ከአብ መሥረፅ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሰረጸ እንጂ ከወልድ አይደለም

፥ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም አያሰርጽም አይሰርጽም።

እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት፥ሦስት ሲሆን አንድ ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ

ይባላል እንጂ ሦስት አማልክት አይባልም። አብ ውልድን ስለወለደ መንፈስ ቅዱስን ስላሰረጸ አይበልጣቸውም

ከመጸሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ጭምር አብራርተ ጻፍ ))

የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት[ዘፍ 1፡26]እግዚአብሔርም አለ፦ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር


እግዚአብሔርም አለ ብሎ አንድነቱን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ሲል ደግሞ
ብዛትን《ሶስትነት》ይገልጻል።

[ዘፍ 3፡22]እግዚአብሔር አምላክ አለ።እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ከእኛ የሚለውና
እንደ አንዱ የሚለው እግዚአብሔር ከአንድ በላይ እንደሆነ የጠቁሙን ናቸው። [ዘፍ 11፡7] ኑ፥ እንውረድ አንዱ የአንድን
ነገር
እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው ኑ የሚለው ቃል የሚያስረዳን አንዱ አካል ሌሎችን ሁለትና ከዚያም በላይ
ሊሆን ይችላል መጥራቱን ነው [ዘፍ 18፡1-15] በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ድጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር
በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት ።ዓይኑንም አነሳና እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው
ከድንኳኑ ድጃፍ

ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፤ እንዲህም አለ ፦ አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ
እለምናለሁ።

[ኢሳ 6፡1-3] ቅዱስ፥ቅዱስ ፥ቅዱስ፥የሠራው ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
አንዱ ቅዱስ ለአብ፥ሁለተኛው ቅዱስ ለወልድ፥ሦስተኛው ቅዱስ ለመንፈስ ቅዱስ መሆኑን ልብ እንበል ይህንን በድጋሜ

[ራዕ 4፡]እናገኘዋለን።

[ኢሳ 48፡16]አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

[ ማቴ 3፡16] ኢየሱስም ከተጠመቀ በኃላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፥እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ
እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፥እነሆም ፥ድምፅ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ
ይህ ነው አለ።

[ማቴ 28፡19] እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ያዘዝኋችሁንም
ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፥እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድርስ ሁል ጊዜ
ከእናንተ ጋር ነኝ።

[ሉቃ 1፡35]መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣል፥የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ሰለዚህ ደግሞ ከአንች የሚወለደው ቅዱስ
የእግዚአብሔር ልጂ ይባላል። [ዮሐ 14፡25]

ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህንን ነግሬአችኋለሁ፥አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን
ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። [1 ኛ ቆሮ 12፡3]

X 14 (፲፬) ?????????????????????????

፲፭ ጌታ ለምን ተጠመቀ ? በማንስ ስም ተጠመቀ አብራርተህ ጻፍ ?

*ለምን ተጠመቀ?

መድኃኒታችን ኢየሱስ እንደ አይሁድ ሥርዓት ለመንጻት፣ እንደ ዮሐንስ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት አልነበረም። ነገር
ግን ስለሚከተሉት ምክንያቶች ተጠምቋል።

፩ ትሕትናን ለማስተማር

መምህረ ትሕትና የሆነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተከታዮቹ አርአያ ይሆን ዘንድ የእጁ ፍጥረት በሆነው
በአገልጋዩ በዮሐንስ እጅ ተጠምቋል። መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ እኔ በአንተ ልጠመቅ ይገባኛል እንጂ አንተ በእኔ እንዴት
ትጠመቃለህ? ብሎ ለማጥመቅ ፍቃደኛ አለመሆኑን ቢናገር ጌታ “አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም
ይገባናል” በማለት እንዲያጠምቀው ያዘዘው መጠመቁን ለተከታዮቹ ትሕትናን ለማስተማር እንደሆነ አስረድቷል። ማቴ
፫ ፥ ፲፭።

፪ አርአያ ለመሆን
ጥምቀት ዳግመኛ ከእግዚአብሔር የምንወለድበት ማለትም የልጅነት ጸጋን የምንጎናጸፍበት ምሥጢር ነው።
ያለጥምቀት የዘላለም ሕይወት አናገኝም ስለዚህ ሰው ሁሉ መጠመቅ ግድ ስለሆነ እርሱ ራሱ በመጠመቅ ለእኛ አርአያ
ሆኖናል።

፫ የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ

ጥንተ ጠላት ዲያብሎስ አዳምና ሔዋንን ካሳተ በኋላ በጨለማ መጋረጃ ጋርዶ አገዛዙን አጸናባቸው። ኋላም በሥቃይ ላይ
ላሉት አዳም እና ሔዋን የእርሱ ባሪያዎች መሆናቸውን አምነው የባርነት ማረጋገጫ ደብዳቤያቸውን በዕብነ ሩካብ
ጽፈው ቢያመጡለት አገዛዙን እንደሚያቀልላቸው ነገራቸው። እነርሱም እውነት መስሎአቸው “አዳም የዲያብሎስ
ወንድ አገልጋዩ ፣ ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋዩ” ብለው በሁለት ዕብነ ሩካም ጽፈው ሰጥተውታል። ዲያብሎስም
አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል አስቀምጦት ነበር። ጌታም በተጠመቀ ጊዜ ዮርዳኖስ ያለውን የዕዳ ደብዳቤ
እንደሰውነቱ ተረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አጥፍቶታል። በሲኦል የተጣለውን በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ
ነፍሳትን ሲያወጣ አጥፍቶታል። ቆላ. ፪ ፥ ፲፫ – ፲፭

፬ አንድነቱንና ሦስትነቱን ለመግለጥ

እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑ በዘመነ ብሉይ በሁሉም ዘንድ እንደ አዲስ ጎልቶ
የማይታወቅ ምሥጢር ነበር። በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ
በሥጋ በተገለጠ ጊዜ አንድነቱና ሦስትነቱን ገልጦ አስተምሯል። ሦስትነቱን በትምህርት ከመግለጡ በፊት በጥምቀቱ
ወቅት በገሃድ እንዲገለጥ አድርጓል። ሦስቱ አካላት በአንድ ቅጽበት በአንድ ቦታ ማንነታቸውን ገልጠዋል ሜቴ ፫ ፥ ፲፮
ይኸውም አብ በደመና ሆኖ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ብሎ ሲመሰክር፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ
አምሣል ወርዶ በራሱ ላይ አርፎ፣ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ቆሞ በመታየት ኅቡዕ የነበረው የሥላሴ
ምሥጢር ገሀድ ሆነ።

፭ . ጥምቀታችንን ይባርክልን ዘንድ

እንፈጽመው ዘንድ የሚገባንንና የሚያስፈልገንን ሥርዓት ሁሉ የሠራልን ፈጣሪያችን ነው፡፡ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀን
አርባ ሌሊት በመጾም ጾማችንን እንደባረከልን /ማቴ.4፥1-10/ በጥምቀቱ ጥምቀታችንን ይባርክልን ዘንድ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሉቃስ በወርኀ ጥር በ 11 ኛው ቀን ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት ተጠምቋል፡

** በማንስ ስም ተጠመቀ? *

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም ጌታን ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለው አንተን ግን በማን ስም ላጥምቅህ ብሎት
ጠይቆት ነበር ። ጌታም እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዘላለም ካህን ነህ ብርሃንን የምትገልጽ የአብ የባህርይ ልጅ
ሆይ ይቅር በለኝ ብለህ አጥምቀኝ ብሎታል። እንዳለውም ጌታን አጥምቆታል ( መዝ 109 ፥ 4 )

፲፮ የጥምቀት አይነቶች አብራርተህ ጻፍ

ሦስት ዓይነት ጥምቀት አለ

፩ የእግዚአብሔርን ልጅነትን የምናገኝበት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምንወለድበት፤ ወንድ ፵ ቀኑ ሴት በ፹ በሜሮን


የምንከብርበት በክብር ስጋና ደሙ የምንታተምበት

፪ ጥምቀተ እንባ ፥> በክርስቶስ አምነው የቤተክርስትያንን እምነት ተቀብለው በበደላቸው እያዘኑ እንባቸውን እያፈሰሱ
ይቅርታ ሲለምኑ ፥ በቤተክርስትያን ላይ በሚነሳ ችግር (ስደት) ፥ ካህን አጥተው በውሀ የሚደረገውን ጥምቀት
ሳይፈጽሙ ቢሞቱ እንባቸው እንደ ጥምቀት ይቆጠርላችዋል ።
፫ የደም ጥምቀት ፥> በክርስቶስ አምነው ሳይጠመቁ ቆይተው ስለ ክርስቶስ እየመሰከሩ ሰማህትነት የሚቀበሉ ደማቸው
ጥምቀት ይሆንላችዋል / ማቴ ፲፥ ፴፪ / ሉቃ ፲፪፥፶

፲፯ . በብሉይ ኪዳን የቁርባን ምሳሌዎችን አብራርተህ ጻፍ ?

፩ አብርሃም አባታችን ዮርዳኖስ ተሻግሮ ወደ መልከጽዴቅ ሲሄድ መልከጽዴቅም ሕብስተ አኮቴት እና ጽዋዕ በረከት ይዞ
መገናኘቱ የቁርባን ምሳሌ ነው ዘፍ ፲፬ ፥፲፯ መልከጼዴቅ የክርስቶስ፥ አብርሃም የምዕመናን ፥ ዮርዳኖስ የጥምቀት፥
ሕብስተ አኮቴት የሥጋው ፥ ጽዋዕ በረከት የደሙ ምሳሌ ናቸው ። አብርሃምም ዮርዳኖስን ተሻግሮ በረከት መቀበሉ
ምዕመናንም ከተጠመቁ በኋላ የጌታን ሥጋ እና ደም የመቀበላቸው ምሳሌ ነው

*. እስራኤላውያን በምድረ በዳ የወረደላቸው መና ( ዘጸ ፲፮፥፩፫ ) / ዮሐንስ ፮፥፳፭ እስራኤላውያን የምዕመናን


ደመናው የእመቤታችን ፥ መናው የቅዱስ ሥጋው ፥ ውሃው የክቡር ደሙ ፥ ከነዓን የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ናቸው ።
እስራኤላውያን መናውንና ውሃውን እየጠጡ ወደ ከነዓን እንደገቡ እኛም የጌታን ሥጋና ደም የተቀበልን የዘላለም
ሕይወት ለማግኘታችን መንግሥተ ሰማያት ለመግባታችን ምሳሌ ነው ።

*.ኢሳይያስ ከለምጽ የዳነባት ፍሕም ኢሳ ፮፥፮ መለአኩ የዲያቆናት አንድም የቀሳውስት ኢሳይያስ የምዕመናን
ጉጠቱ የዕርፈ መስቀል አንድም የሥልጣነ እግዚአብሔር ፤ ፍሕሙ የደሙ አንድም የሥጋ ወደሙ ለምጹ የፍዳ የመርገመ
አጢአት ምሳሌ ነው ። ኢሳይያስ ከለምጽ በፍሕሙ እንደዳነ ምዕመናንም ሥጋ ወደሙ ተቀብለው የአጥያት ሥርየት
የማግኘታቸው ምሳሌ መልአኩ ፍሕሙን በእጁ ሳይሆን በጉጠቱ መያዙ ዲያቆናትም ሥጋ ወደሙ በእጃቸው መንካት
አይቻላቸውምና

*.የፋሲካው በግ ( ዘጸ ፲፪፥ ፩_፶፪) ይህ የእስራኤላውያን ታሪክ በኋላ ዘመን ( ለሐዲስ ኪዳኑ የጌታ ሥጋና ደም )
ለሚሆነው ምሳሌ ነው ። ይኸውን ግብጽ የሲኦል ፥ ፈርኦን የዲያብሎስ ፥ እስራኤል ዘሥጋ ለእስራኤል ዘነፍስ ፥
የተሠዋው በግ የክርስቶስ ፥ በጉን ተሰብስበው የበሉበት ቤት የቀራንዬ ምሳሌ ነው ።

ምሳሌው በዝርዝር ስንመለከት ?

፩ ነውር የሌለበት የ ፩ ዓመት ተባዕት ጠቦት እስራኤል ዘሥጋ የተባሉት እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነፃ ለመውጣት
የተመገቡት በግ ቀንዱ ያልከረከረ ጥፍሩ ያልዘረዘረ ያላረጀ በመካከለኛ እድሜ ላይ ያለ ነውር የሌለበት ንጹህ በግ ነበር
ይኸም ምሳሌነቱ እስራኤል ዘነፍስ ያዳናቸው በፋሲካው በግ የተመሰለው ጌታ ነውር ነቀፋ ኃጢአት በደል የለበትምና
እንደዚህ አለ ፥>

.አጥንቱን አትስበሩ ሥጋውን ብሉ ። የፋሲካው በግ አጥንቱ እንዲሰበር አልተፈቀደም ነበር ። ለጊዜው በአጥንት
የተመሰሉት እስራኤላውያን መከራ አያገኛቸውም ለማለት ሲሆን ለፍፃሜው ግን ክፉ ንግግር አጥንት የመስበር ያህል
ይሰማልና የእግዚአብሔር በግ በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የክህደት ቃል አትናገሩ ሲል አንድም የፋሲካው
በግ አጥንቱ እንዳልተሰበረ ሁሉ ጌታ በዕለተ ዓርብ በቀራንዪ በሚሰቀልበት ጊዜ አጥንቱ አለመሰበሩ ምሳሌ ነው ።( ዮሐ
፲፱ ፥ ፴፬ )

. በእሳት የተጠበሰ ብሉ ፥>

የበጉ ጥሬ ሥጋ በውሃ ተቀቅሎ የፈረሰውን ሥጋ አትብሉ ተብለዋል ። ምክንያቱ ጥሬ ቢበሉ በስጋው ውስጥ ደም
ይኖራል በደም ውስጥ ደግሞ ነፍስ ታድራለችና ጥሬውን አትብሉ አለ ። የተቀቀለውን አትብሉ መባሉ የተቀቀለ ሥጋ
ይፈርሳልና ከአጥንቱ ይለያያልና እንደዚሁ ጌታ በመቃብር ሳለ ፈራርሶ ሙስና መቃብር ( መበስበስ) አገኘው አትበሉ ሲል
ነው ።

በእሳት የተጠበሰው ብቻ ብሉ መባሉ በበግ የተመሰለው የጌታ ሥጋ እና ደም መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው
መሆኑን አምናችሁ ተቀበሉ ለማለት ነው ።
*. ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት ፥>

ለጊዜው የበሉት እንዲዋሐዳቸው በኋላ ደግሞ የፋሲካን በዓል ባከበሩ ቁጥር ያንን የግብፅን መራራ መከራ ( ባርነት)
እንዲያስቡ እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳናቸው እንዲያስተውሉ ነው ። ለፍጻሜው ግን ጌታ ለእኛ ሲል መራኣ ሞትን
እንደተቀበለ ሥጋ ወደሙ ስንቀበልና እንድናስታውስ ነው ። (ዮሐ ፲፱፥ ፳፰ ) አንድም ሥጋው ወደሙ ከመቀበላቹ በፊት
አፋቹ ምሬት እስኪሰማው ድረስ (፲፰ ሰዓት ድረስ) ጾማችሁ ተቀበሉ ለማለት።

. ወገባቹን ታጥቃችሁ ጫማ አድርጋቹ በትር ይዛችሁ ተመገቡ ፥>

ለጊዜው እስራኤል መንገደኞች ነበሩና እንዲዘጋጁ ለፍጻሜም ግን የጌታን ሥጋ እና ደም ስትቀበሉ ወገባችሁን ታጥቃችሁ
አለ ንጽሕናን ቅድስናን ገንዘብ አድርጋችሁ ሲል ነው። ሉቃ፲፪፥፴፭ / ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁ የበራ ይሁን
እንደተባለ ጫማችሁን ታጥቃችሁ ሲል ወንጌል ተምራችሁ ፤ በትር ይዛችሁ መባሉ የጌታ መስቀል ጋሻ መከታ
አድርጋችሁ ሥጋሄን ደሜን ተቀበሉ ሲል ነው።

. ፈጥናቹ ተመገቡት ( ትበሉታላችሁ)

ከዚህ ተዓምር በኋላ ነፃ ስለምትወጡ ወደ ከነዓን ጉዞ ስለምትጀምሩ ጊዜ ሳታባክኑ ፈጥናችሁ ብሉ ተባሉ። ለፍጻሜው
ግን ምዕመናን ሞት እንዳለባቸው አውቀው ዛሬ ነገ ሳይሉ ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ተዘጋጅተው መጠበቅ እንዳለባቸው
ሲያጠይቅ ነው።

. ከቤት አትውጡ ደሙም ምልክት ይሁናችሁ

እስራኤላውያን በጉን ሠውተው ደሙን በመቃኑና በጉብኑ ላይ ረጭተው ነበርና መልአከ ሞትም ያንን አይቶ ያልፋቸው
ነበር ። እንደዚሁ የደሙ ምልክት እስራኤልን ከሞት መቅሰፍትእንዳዳናቸው እኛም እስራኤል ዘነፍስ ዘለዓለማዊ
ሕይወት ለማግኘት የሞት ሞት ላለመሞት የጊታን ሥጋና ደም መቀበል ግድ ይላልና ፤ ከቤት አትውጡ መባሉ
ከሃይማኖት አትናወጹ በአንዲት ሃይማኖት ጸንታቹ ኑሩ ( ዕብ ፫፥፲፬)

. ሰባት ሆናችሁ ብሉ መባሉ ሰባት በዕብራውያን ፍጹም ቁጥር ነው የጌታ ሥጋና ደም ስትቀበሉ በንስሐ ፍጹማን
ሁኑ ሲል ነው ።

. ለአንዱ የተሠዋው ለሌላ ቤት አትውሰዱ መባሉ አንዱ ቤተክርስትያን የተሠዋው ወደ ሌላ ቤተክርስትያን


አትውሰዱ ሲል ነው

. የፋሲካው በግ 430 ዘመን በባርነት የነበሩትን እስራኤልን ነፃ ለማውጣት ምክንያት እንዲሆን የጌታ ስጋና ደም
5500 ዘመን ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለመውጣት ምክንያት ነውና የፋሲካው በግ ለሐዲስ ኪዳን ለጌታችን ሥጋ ወደሙ
ምሳሌ ነው።

X ፲፰ . ጌታ ለምን ቁርባንን በስንዴና ወይን አደረገው ? አብራርተህ ጻፍ?

* በስንዴና በወይን መሆኑ ፥>

፩.ምሳሌው ይፈፀም ዘንድ ነው መልከፀዴቅ በወይን በስንዴ ያመሰግን ነበር ዘፍ ፲፬፥፲፰ ዕብ ፯፥፩ ይህም የሥጋ
ወደሙ (ቁርባን) ምሳሌ ነው ።

፪.ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ነው ። በልቤ ደስታን ጨመርኩ ከስንዴም ፍሬም ከወይን ከዘይትም በዛ " መዝ ፬፥፯

፫. ሚስጢር ስላለው ነው ፥>ይኸውም ስንዴ ስብ ሥጋን ይመስላል ፥ ወይን ደግሞ ትኩስ ደምን ይመስላል ። ስለዚህም
በሚመስል ነገር መስጠቱ ነው
በመብልና መጠጥ መሆኑ

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውንና ደሙን በወርቅ በብር ሳይሆን በመብልና በመጠጥ ያደረገበት
ምክንያት አለው ይኸውም ፥>

መብልና መጠጥ ከሰውነት ጋር ይዋሐዳሉ ወርቅና ብር ግን አይዋሐዱም ። ስለዚህ በሰውነት እንዲዋሐድ


ለማስረዳት ነው ። ሰው ተርቦ ሳለ ወርቅና ብር ከሚሰጠው ለርኅቡ ምግብ ለጥማቱ መጠጥ የሰጠውን እንደሚወድ
"እወዳችኋለው ትወዱኛላችሁ "ሲለን ሥጋውንና ደሙን በመብልና መጠጥ አደረገው።

X ፲፱. ትንሣኤ ልቦና እና ትንሣኤ ዘጉባኤ የሚባሉትን አብራርተህ ጻፍ?

*ትንሣኤ ልቦና በመጨረሻ ቀን ከመነሳታችን በፊት በንስሐ በጽድቅ አሁን የምንነሳበት ትንሳኤ ነው ። ለትንሣኤ ልቦና
ጥምቀት ፥ ቁርባን ፥ ንስሐ ወሳኝ ነገሮች ናቸው ።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ሥጋሄን የበላ ደሜንም የጠጣ በመጨረሻ ቀን ይነሳል በማለት ተናግራል ዮሐ ፮፥፶፬

፡> ጥምቀት ሞትና ትንሣኤ ጋር መካፈል እንደሆነ ተገልጻል ሮሜ ፮፥፬

፡> ሌላው ትንሣኤ ልቦና ማግኛ መንገድ ከሞትና ከኃጢያት በንስሐ መነሳት ነው ። ለዚህም ነው የጠፋው ልጅ አባት ስለ
ልጁ " ይህ ልጄ ሞቶ ነበር ደግሞም ሕያው ሆናል ሉቃ ፲፭፥፳፱

ቅዱስ ጳውሎስ ኃጥእ በኃጢአት ያቀላፋ የሞተ ስለሆነና በንስሐ የሚነሳ ስለሆነ " አንተ የሞትክ ንቃ ከሙታንም ተነሳ
ክርስቶስ ያበራልሃል ኤፌ ፭ ፥፲፬ ይህ በንስሐ የምናገኘው ትንሳኤ ወይም ትንሣኤ ልቦና ነው ፤ ፊተኛው ትንሣኤ ብሎ
ይጠራዋል ። በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብጹሕና ቅዱስ ነው ሁለተኛ ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣም የለውም ( ራዕ ፳
፥ ፭ ) ከጥቅሱ እንደምንረዳው የፊተኛው ትንሣኤ ትንሣኤ ልቦና ለሁለተኛው ትንሣኤ ለትንሣኤ ዘጉባኤ ዋስትና
እንደሆነ ነው።

.*ትንሣኤ ዘጉባኤ

ከዚህ ዓለም ኅልፈት በኋላ ለሰው ሁሉ እንደየሥራው ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሱበት ሲሆን እኩሌቶቹ
ለዘላለም ሞት እኩሌቶቹ ለዘላለም ሕይወት የሚጠሩበት የመጨረሻው ውሳኔ የሚሰጥበት ነው

X ፳ . ለዳግም ትንሣኤ ስንነሳ በምን ዓይነት ሁኔታ እንነሳለን አብራርተህ ጻፍ?

በመጨረሻው ዘመን በላይ ያለው በታች ያለው በባሕርና በየብስ ያለው አውሬ የበላው ገደል የገባው ውሀ የወሰደስ
እንዲሁም በልዩ ልዩ ሞት ፈጽሞ ያረጀና የጠፋ በምድር ላይ የወደቀ የሥጋ ቅርፍት ሁሉ ወደ ቀደመው ሰውነቱ
ይመለሳል የማይበሰብስ የማያረጅ የማይለወጥ የማይራብ የማይጠማ ሆኖ ይነሳል

አነሳሳቸውም እንዲህ ነው፥>

*.ትንሣኤ ዘለክብር፡- የሚነሡት ጻድቃን የሚወርሱት መንግሥተ ሰማያትን ሲሆን ሲነሡ ብርሃን ለብሰው ብርሃን
ተጎናጽፈው እንደ ፀሐይ እያበሩ ወንዶች የ 30 ዓመት ጎልማሳ ሴቶች የ 15 ዓመት ቆንጆ ሆነው ለዘላለም በደስታ
በሕይወት ለመኖር የሚነሡት ትንሣኤ ነው፡፡ (ራዕ 21÷1-5 ፤ 2 ተኛ መቃ 13÷8-14) የ 30 ዓመትና የ 15 ዓመት መባሉ
አዳምና ሄዋን ሲፈጠሩ የ 30 ዓመትና የ 15 ዓመት ሆነው ተፈጠሩ ብለው ሊቃውንት ከሚያስተምሩት ጋር በተመሳሳይ
መልኩ ለሰው በሚገባ ቋንቋ ሙሉ ሰው መሆናቸውን ለማስገንዘብ እንጅ ከትንሣኤ በኋላ የሚቆጠር እድሜ ኖሮ
አይደለም፡፡ እድሜ የሚቆጠረው በፀሐይ፣ በጨረቃ፣ በከዋክብት ነው፡፡ ከዳግም ምጽዓት በኋላ እነዚህ ሁሉ ፍጥረታት
ስለሚያልፉ በማይቆጠር እድሜ እንኖራለን፡፡
*.ትንሣኤ ዘለኃሣር ፡-ይህን ትንሣኤ የሚነሡት ሰዎች በዚህች ምድር ሳሉ እግዚአብሔርን ሲበድሉ በክህደት
በምንፍቅና የሚኖሩ ትንሣኤ ልቡና ያላገኙ ሰዎች የሚነሡት ትንሣኤ ነው፡፡ ትንሣኤ ዘለኃሣር የሚነሡት ኃጥአን ከቁራ
ሰባት እጅ ጠቁረው የግብር አባታቸውን ሰይጣንን መስለው ለዘላለም ትሉ በማያንቀላፋበት እሳቱ በማይጠፋበት
በገሃነመ እሳት ውስጥ ይኖራሉ፡፡ (1 ኛ መቃ 13÷9-11′ ማቴ 13÷-42)

You might also like