Professional Documents
Culture Documents
የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር
የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር
በ ዘይነብ ሐሰን
1 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
የተቀደሰው የፍልስጤም
ምድር
-በ ዘይነብ ሐሰን
2 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ማውጫ
መግቢያ ገጽ
ምዕራፍ አንድ
አራዲል ሙቀደሣ
የፍልስጤማውያን አመጣጥ 1
አልቁድስ ሙስሊማዊት ከተማ 2
የቁድስ ሐረምነት በቁርአንና በሐዲስ 4
በይተል-መቅዲስ የእስላም ምሽግ 9
ምዕራፍ ሁለት
አልቁድስ/ኢየሩሣሌም
መዲነቱል ቁድስ 11
አል-ሐራም አሸ-ሸሪፍ 12
መስጂደል አቅሷ 12
የመስጂደል አቅሷ ደረጃ በኢስላም 13
የተባረከው የፍልስጤም ምድር 14
የቁድስ ሙስሊማዊት አገር መሆን 17
ዑመራዊ ቃል-ኪዳን 18
የአይሁድ የኃይል እርምጃ 18
በመስጂዱ ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች 19
የሠላም ቃል-ኪዳን 21
ድሉ የሙስሊሞች ነው 21
3 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ሻአላሁ ተአላ 22
ምዕራፍ -ሦስት
ዝክረ- ታሪክ
ቅድመ-ኑብዋ 23
ድህረ-ኑብዋ 24
ኢንቲሳር(የፍልስጤሟ ሙሽራ) 29
ፍልስጤም 33
እስከ መቼ ድረስ
ፒስ ፕሮሰስ
ይሉናል ፒስ ፕሮሰስ
ከበስተጀርባው ረሳስ
ሕዝቡን ለመጨረስና መሬቱን ለመውረስ
4 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
መግቢያ
የተቀደሠው የፍልስጤም ምድር መቼም ቢሆን የአይሁድ ይዞታ ሆኖ አያውቅም፡፡
ለዚሁ አንድ ማስረጃ “ለአይሁድ የተለየ አገር ቤት /separate homeland” የመፍጠሩ ሀሳብ
ሲንሸራሸር በነበረበት ወቅት ከፍልስጤም ውጭ ሌላም ቦታ ታስቦ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ
ምዕራባውያን የተቀረውን ዓለም ለማደናገር እንደሚሞክሩት የፍልስጤም ምድር ከድሮም
የአይሁድ የነበረ ቢሆን ኖሮ፤ ለነሱ አገር ቤት በመፍጠሩ ሀሣብ ውስጥ እንደ አርጀንቲናና
ዑጋንዳ የመሳሰሉትን ሀገራት ማካተቱ ባላስፈለገም ነበር፡፡
ይሁንና ለ‘አይሁድ የብቻ አገር ቤት’ የመፍጠሩ ሀሣብ የአውሮፓውያንን ይሁንታ
አግኝቶ በዋናነት ፍልስጤም ተመረጠች፡፡ ዓላማውን እውን የማድረጉ እንቅስቃሴም ተጀመረ፡
፡ ጊዜው በ 8ተኛው መቶ ሂጅሪያ1 ማብቂያ ላይ ነበር፡፡ የምዕራብ ኃይላት የዑስማንያ ቱርክ
ኢስላማዊ መንግሥትን ለመጣል የተጠናከረ ርብርቦሽ እያደረጉበት የነበረ ወቅት ነው፤ ይህንኑ
አጋጣሚ በመጠቀምና ገጸ በረከትም በመያዝ አንድ ከማኅበረ-አይሁድ የተውጣጣ የልዑካን
ቡድን በአውሮፓውያን ድጋፍ ሰጪነት ወደ ወቅቱ የዑስማንያ ኻሊፋት ሡልጣን ዐብዱል
ሐሚድ አመራ፡፡ አይሁዳውያን ፍልስጤም ውስጥ መሥፈር እንዲችሉና የመግቢያ ፈቃድም
እንዲሰጣቸው ተማጽኖ አቀረበ፡፡
ሡልጣን አብዱል ሐሚድ ግን በጊዜው መንግሥታቸው ላይ እየተደረገ በነበረው
አፍራሽ ግፊት ሳይበገሩ፤ በቀረበላቸው የከበረ ሥጦታም ሳይደለሉ የአይሁዶችን ጥያቄ ውድቅ
አደረጉት፡፡ የሁዶች አንዴ እንደምንም ብለው ፍልስጤም ውስጥ እግር መትከል ከቻሉ አገሪቱን
ከተቀረው ኢስላማዊ ዓለም በቀላሉ መነጠል ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ ከዚህም
በመነሳት ይመስላል፤ በ1900 እና 1901 መካከል በነበረው ጊዜ ተጨማሪ ደንቦችን በማውጣት
ማንኛውም የአይሁድ ተጓዥ ከሦስት ወር በበለጠ ፍልስጤም ግዛት ውስጥ ውሎ ማደር
እንደሌለበት ይደነግጋሉ፡፡ ከዚህም ሌላ ምንም ዓይነት የመሬት ሽያጭ ለአይሁድ እንዳይደረግ
ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡
የአይሁድ ጥረት ግን በዚህ አልተገታም፡፡ ሰላሣ አምስት ሚሊዮን የወርቅ ዲናሮችን
በመቋጠር እንደገና በ1920 ወደ ሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት አቀኑ፡፡ በጊዜው የዑስማንያ
ኢስላማዊ መንግሥት ካዝና በብዙ ወጪዎች ተራቁቶ እንደነበረም ያውቃሉ፡፡ እንደዛም ሆኖ
ግን የኢስላማዊውን መንግሥት ይሁንታ በወርቅ ሣንቲሞች ለመግዛት ያደረጉት ጥረት
በሡልጣኑ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የጉዳዩ ዋና አስተባባሪ ለነበረው ለቴዎዶር ሄርዞል
በላኩት ማስታወሻ ግልጽ እንዳደረጉት፡- “… ከፍልስጤም መሬት ላይ ስንዝር መስጠት
አልችልም፡፡ ምክንያቱም የግል ንብረቴ አይደለምና፡፡ ይልቅ ባለመብቱ ሕዝቡ ነው፡፡ ሕዝቦቼ
1
. ሂጅሪያ ማለት የዐረብኛ ቃል ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙም ‹‹ስደት›› ማለት ነው፤ ስደቱም የሚያመለክተው የነብዩ
ሙሐመድ(ሶ.ዐ.ወ) ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ታሪካዊ ክስተት መሆኑ ልብይለዋል፡፡ (ይህ የግርጌ ማስታወሻ
ከታተመው ዋና መጽሐፍ የሌለ ሲሆን ለአንባቢ በማሰብ በመልሶ ተያቢ የተጨመረ መሆኑ ማስታወስ
እንወዳለን፡፡)
5 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
6 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
7 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
የመከላከሉ ጦርነት
ፍልስጤሞች ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሕልውናቸው ላይ የመጣባቸውን ባዕድ
ኃይል በከፍተኛ የሕይወት መሥዋዕትነት በመከላከል ላይ እንዳሉ ናቸው፡፡
8 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
9 | ገገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
10 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
12 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
14 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ኢንቲፋዳ ጀዲዳ
ሴብቴምበር 2000
በ2000 ሴብቴምበር ወር ውስጥ አሪል ሻሮን የተቀደሠውን የሐረም አሸ-ሽሪፍ ስፍራ
የመጐብኘቱ ድፍረት ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡ ፍልስጤማውያን ወጣቶች ያስቀመጡትን ድንጋዮች
እንደገና አነሱ፡፡ ኢንቲፋዳው ቀጠለ፡፡ የአል-አቅሷ ኢንቲፋዳ፡፡ እንደገናም በኢስራኤል
ወታደሮች ጆሮ ግንድ ስር ድንጋይ ማፋጨቱን ቀጠለ፡፡
ኢንቲፋዳ ማለት በመሠረቱ በገዛ ቤት ንብረት ላይ የሚደረግ የሞት ሽረት መከላከል
ነው፡፡ በህልውና ላይ የመጣውን ጠላት የመመከት ርምጃ፡፡ ከምድር ተነስቶ የራሱን እኩይ
ዓላማ ለማሣካት ሲል ብቻ የሌላውን መኖር በሚክድ፣ ቤት በሚንድ፣ ዛፍ በሚነቅል፣ ሕጻናትን
በሚፈጅ፣ ሴትን ልጅ በሚያሰቃይ፣ አዕሩግ በሚያቀል እርጉም ኃይል ላይ ፍልስጤሞች
የጀመሩትን አመጽ “ኢንቲፋዳ” ይሉታል-ሕዝባዊ መነሳሳት ነው፡፡ ታዲያ ሐቁ ይሄ ሆኖ ሳለ
የኢስራኤል መንግሥት ለዚህ ያልታጠቀ ሕዝባዊ ተቃውሞ ምላሽ እየሰጠ ያለው ጨርሶ
ባልተመጣጠነ ኃይል (በአምሪካን ሠራሽ አፓቼ ሄሊኮፕተሮች፣ ከሰማይ ወደ መሬት
ተወንጫፊ ሳሩኾች፣ ታንኮችና ኤፍ 16 ተዋጊ ጀቶች) የመሆኑ ነገር የፍልስጤምን ሕዝቦች
ፈጅቶ መሬታቸውን ለመውረስ ያለውን ቁርጠኛ ዓላማ አመላካች ነው፡፡
ሁለተኛው ኢንቲፋዳ ከተጀመረበት (ከሴብቴምበር 2000) ይህ ፅሑፍ
እስከተጠናቀረበት 2003 ማብቂያ ድረስ 35 ወሮች ተቆጥረዋል፡፡ ሰላሳ አምስት የሰቆቃ ወሮች፡
፡ የከዚህ በፊቱን ትተን በነዚህ 35 አስከፊ ወሮች ብቻ በተቀደሰው የፍልስጤም ምድር ላይ
በኢስራኤል ጦር እጅ ምን እንደተፈጸመ ስናይ በርግጥም የአይሁዶች ዓላማ ፍልስጤሞችን
ፈጅቶ የፍልስጤምን ምድር የራሳቸው ማድረግ እንደሆነ ይበልጥ ሳንረዳ አንቀርም፡፡
የተሰውና የቆሰሉ
እነሆ በጦር ኃይል ድንገት ሰብሮ በመግባት ግድያ መፈጸም፣ ከተሞችን መክበብ፣
መንገዶችን መዝጋት፣ መኖሪያ መንደሮችን (ከአየር ወይ ከመሬት) በከባድ መሳሪያ መደብደብ፣
ቤቶችን ማፍረስ፣ ፍሬያማ ዛፎችን መንቀል፣ ሰብሎችን በታንክ እግር መረመም፣ ሰዎችን
ማዋከብና ማሰር፣ እንቅስቃሴዎችን በማቀብ ሕዝቡ ለረጂም ቀናት እንዳይገናኝ፣ እንዳይሰራ፣
እንዳይሸምት፣ እንዳይታከም በማድረግ ጅምላውን መቅጣት ዓይነተኛው የአይሁድ ጥቃት
ስልት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በተጠቀሰው የ 35 ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ 2875 ፍልስጤሞች
ሙት፣ 41‚322 ቁስለኛ ሁነዋል፡፡ 403 ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆችም ሆን ተብሎ
በተነጣጠረ ተኩስ ተገድለዋል፡፡
አለፍርድ ሂደት የተገደሉ
Palestinian center for human rights / PCHR” የተሰኘ የፍልስጤማውያን
የሰብዐዊ መብት ማዕከል ባቀረበው ዝርዝር በሦስት ዓመት የአል-አቅሳ ኢንቲፋዳ ወቅት 309
15 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
16 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
17 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
18 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
The ministry mad clear, concerning the secret Israeli detention camps for
Palestinians,that since 1967 up to date,Israel army camps as special interrogation
wings in certain Palestinian cases. “safarand” Israeli military camp,for example
was used by Israeli after 1967 for detaining several Palestinian ‘fidayeens’
(freedom fighters), asserting that lawyers and red cross staff were denied access
into such camps.
As for the palesetinian political figures and leaders in detention, the ministry
declared that they’re constantly being held in solitary confinement since the day
they were arrested, as in the case in Fateh’s Secretary General in the west bank
and Palestinian Legislative Council member marwan Al Barghouti.
The ministry pointed out to the struggle and steadfastness of the Palestinian
prisoners behind bars, as they sent a letter of support and solidarity from within
their prison cells to the president Yasser Arafat, denouncing the Israeli decision
of expelling or killing him, and considering it as a true evidence to the Israeli
“Transfer” policy, adopted by the Israeli government since the beginning of its
occupation.
የፈረሱ ሕንጻዎች ተቋማትና
መኖሪያ ቤቶች
የኢስራኢል መንግሥት በፍልስጤማውያን ላይ ከሚያራምደው የጥፋት ፖሊሲ
አንዱ ቤቶችንና መኖሪያ አካባቢዎችን ተቀባይነት በሌለው ምክንያት (ያላግባብ የተገነቡ ናቸው
በሚል) እየተነሳ ማውደሙ ይጠቀሳል፡፡ ባይነቱ የተለየ የጦር ወንጀል ቢኖር ይኸው
የኢስራኢል ጦር በቤቶችና መኖሪያ አካባቢዎች ላይ በማንአለብኝነት ቀጥሎት ያለው
የመክበብና ቡልዶዝ የማድረጉ ተግባር ነው፡፡ ጦሩ ከተሞችን ሰብሮ ሲገባ ከታንኮቹ በስተጀርባ
ቡልደዘሮች ይከተላሉ፡፡ በከባድ መሣሪያ (በጄት፣ በሚሳኢል…) የተደበደበውን ቤት ከሥር
ቡልደዘሮቹ መሠረቱን በመናድ ያስተኙታል፡፡ ቤቶችን አላንዳች ቅድመ ማስጠንቀቂያ ማፍረሱ
ሳያንስ፣ ባለቤቶቹን የትም ድረሱ ብሎ ማባረሩ፣ ይባስ ብሎም አንዳንዱጋ ባለቤቶቹ እውስጡ
እያሉ ሠብሮ በመግባት ቤቱን ለወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያነት በኃይል የመገልገሉ ነገር በደሉን
ያባብሰዋል፡፡ እነሆ በዚህ ዓይነት 282 ት/ቤቶች 15 የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ 553
የአስተዳደርና የሕዝብ ህንፃዎች ወድመዋል፡፡ 53‚656 መኖሪያ ቤቶች ተደብድበው 3‚877
ሙሉ ለሙሉ እንዳልነበረ ሁነዋል፡፡
የጥበብን ችቦ የማጨለም እርምጃ
የኢስራኢል መንግስትና ጦሩ ፍልስጤምን እንዳገር ለማጥፋት
ከሚጠቀሙበት ዘዴ መሃል አንዱ ፍልስጤማውያንን የመሬት ብቻ ሳይሆን የዕውቀት ድሃ
19 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
20 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
21 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
22 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
እያየም-- እንዳላየ
እየሰማም - እንዳልሰማ
እንዲሆን ተደርጐ ነውማ
ይህ ዓለም ቀልቡን የተቀማ
ኢስራኢሎች (በተለይም በአምሪካን አይዞህ ባይነትና ያልተቆጠበ ድጋፍ) በፍልስጤምና
በሕዝቧ ላይ ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈፅሙና የማይረሳ በደል ሲያደርሱ ዓላማው ግልጽ ነው፡፡
1. ነዋሪውን ዐረብ ፍልስጤም የፈጁትን ፈጅተው፣ ያፈናቀሉትን አፈናቅለው፣
የተቀረውን በአፓርታይድ ግንብ(አሁን እንደጀመሩት) አጥረው -አገሪቱን የራሳቸው
ማድረግ፤
2. ሦስተኛውን የኢስላም ሐረም በመቆጣጠር ሙስሊሞች በዚያ ላይ ያላቸውን
የባለቤትነት መብት መንፈግ፤
3. ዐረቡ ዓለም መሃል እንደ አጥንት ተሸንቁረው ሲያደሙት መኖር
4. የአካባቢውን ገጽታ ለሙስሊሞች ሕብረት እንማይመች አድርጐ መቀየር…..
ይህ ነው ዓላማው፡፡ ከዚህ ውጪ ከታሪክ፣ ከሃይማኖት፣ ከሕግና ከሕሊና ፍርድም
አንጻር በቦታው ላይ አንድ ሐቅ ኖሮአቸው አይደለም -ኢስራኢሎች ይህን የሚያደርጉት
በአንፃሩ ዐረብ ፍልስጤማውያን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ መከራ እያዩና እየተዋደቁ
ያሉት ከታሪክ፣ ከሃይማኖት፣ ከህግና ከኅሊና ፍርድም አኳያ ከተቀረው ሙስሊም ዓለም ጋር
የሚጋሩት ሐቅ በቦታው ላይ ስላላቸው ነው፡፡ እነሆ በቀጣይ የሚቀርበው የዚህ መፃፍ
ጭብጥም ይህንኑ አመላካች ይሆናል፡፡
23 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
የፍልስጤማውያን አመጣጥ
ከዒሣ ኢብን መርየም ዐለይሂ ሰላም መምጣት ምናልባትም 25 ክፍለ ዘመናት ቀደም
ብሎ በቦታው ላይ አራምዩች ነበሩ፡፡ ቀጥሎ ከነዓኒዩች ወደ ስፍራው ፈለሱ፡፡በመቀጠልም
ከወደ ትንሹ አስያ ወይም ከሙተወስጥ የባሕር ደሴቶች ግድም ፍልስጤማውያን መጡ፡፡
የመስርን ጠረፋማ ከባቢዎች በመውረር ወደ ሰሜን አቅንተው በጁዲያ ተረተርና በባሕሩ መሀል
በሚገኘው ትልቁ ሸለቆ ላይ ሠፈሩ፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በቦታው ላይ የነበሩና ዛሬም ያሉ ናቸው፡
፡
ቬስፖሲየን፣ ቲትስ፣ ትራጃን እና ሐድሪያን እንዲሁም የተለያዩ ክርስትያን ነጋሢዎች
በየተራ ባደረሱባቸው አውዳሚ ጦርነት የተነሳ አይሁዶች ከነሥርዐተ-ወጋቸው ተንኮታኩተው
ስብርባሪያቸው በአራቱ የሰማይ መስኮቶች ተበትኗል፡፡
“….ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፣ አሁን ግን
ከዓይንሽ ተሰውሮአል፡፡ ወራት ይመጣብሻልና፣ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል
ይከቡሻልም፣ በየበኩሉም ያስጨንቁሻል፣ አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን
24 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
25 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
there, but it is well to remember that the historic city of Jerusalem has
been a muslim city, as it stiil predominantly is, for much longer than it
ever was either a jewish or a Christian city “stewart perowne: Jerusalem
& bethelehem, new York,1965.p2
“በኢየሩሳሌም ሦስት የአሃዳዊ እምነት ቅርንጫፎች አብበዋል፡፡ መጀመሪያ
የአይሁዶች ከዚያም የክርስትና፡፡ በመጨረሻም የሙስሊም፡፡ አስካሁንም እንዚህ ሶስቱ በዚያ
እንዳበቡ ይገኛሉ፡፡ነገር ግን ታሪካዊት ኢየሩሳሌም ልክ በዛሬው ግዜም በአመዛኙ ሆና
እንደምትገኘው፣ የአይሁድ ወይም የክርስትያን ከተማ ከነበረችው ይበልጥ ለረጂም ጊዜ
ሙስሊማዊት ከተማ እንደነበረች ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ “ ስቲዎርት ፔሩኒ እየሩሳሌም እና
በይትለሐም - ኒውዩርክ 1965 ገጽ 2፡፡
እነሆ አል-ቁድስ ሙስሊማዊት ከተማ ስለመሆኗ፣ በይት አል-መቅዲስና ዙርያው
የሻም መሬት ወይም “ትልቁ ሱርያ” በመባል የሚታወቀው አካባቢ “አርደል ሙቀደሣ (የተባረኩ
መሬቶች) ስለመሆናቸው ከበቂ በላይ አረባዊና ኢስላማዊ ማገናዘቢያዎች አሉ፡፡ በፊሊስጢን
ነዋሪ የሆኑት አረቦች ሥረ-መሠረታቸው ከራሱ ከክልሉ ቅድመ ታሪክ በፊት ነው፡፡ ከታሪክ
ንጋት ጀምሮ የከንዓን ምድር በመባል በሚታወቀው አገር የነሱ መኖር ከአስር ሺህ ዓመታት
በፊት የጀመረ ነገር ነበር፡፡ መላው ታሪክና የቁፋሮ ሠነዶች (እራሱን ብሉይ ኪዳንን ጨምሮ)
ይህንኑ እውነታ ያረጋግጣሉ፡፡
ከመቶ ዓመት በፊት ያውም ሣይንሳዊ የምርምር ባሕል ገና ዳዴ በሚልበት ዘመን ላይ
ጥናቱን ያካሄደውና “Palestine illustrated” በሚል ርዕስ የጥናት ውጤቱን ያቀረበው ሰር
ረቻርድ ቴምፕል በፍልስጤም ማዕከላዊ ተረተር ስለሚኖሩ ሕዝቦች እንዲህ ይላል “… they
are veritable descendants of the Canaanites described in the bible of the
jebusites and amorites”
“…እነሱ በመጽሃፍ ቅዱስ ከተጠቀሱት ዩቡሲዩች / ኢያቡሳውያንና አራምዩች / አሞራውያን
የከነዓን ወገኖች የመጡ ( መምጣታቸው የታወቁ) ናቸው፡፡”
በዚህ ጉዳይ ዙርያ ሰር ጄምስ ፍራዘር ‘folk-lore in the old testament’ በተሰኘው
መድብሉ ቅጽ 1 ገጽ 417 ላይ የሚከተለውን ብሏል፡፡ የጹሑፍ ጥንቅር የመጀመሪያው ታሪካዊ
ግኝት በ “ገዘር” ከተደረገ በኃላ ነበር፡፡ ከተናገራቸው ነገሮች ሁሉ “ It is the opinion of
competent judges that the modern fellahin of Arabic speaking peasants of
Palestine are descendants of the tribes which dwelt there before the Israelite
invasion and have clung to the soil ever since. Being submerged but never
destroyed by each successive wave of conquest which has swept over the land”
“ይህ የብቁ ሊቃውንት አስተያየት ነው፡፡ እነዚህ አረብኛ ተናጋሪ የሆኑ የፍልስጤም ገበሬዎች
(ዘመነኞቹ ፈላሒን) በቦታው ላይ የኢስራኢል ወረራ ከመካሄዱ በፊት ነዋሪ ከነበሩ ነገዶች
የመጡ ናቸው፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ዝንተ አለማቸውን አፈሩን የሙጥኝ ብለው፤ አካባቢው
26 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
27 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ቢሄድ፣ እውን ፍርድ ቤቱ እንደበቂ ሕጋዊ ሠነድ ቆጥሮለት የጠየቀውን ንብረት ሊፈቅድለት
ይችላል ወይ?... ፍርዱን ለአዕምሮ ባለቤቶች፡፡
በቁርአን
ከኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም በፊትም ቢሆን ሥፍራው መስዕዋት ማቅረቢያ ነበር፡፡
“እነሆ ያ አባት ወደዚህ ከፍታ በመውጣት በልጁ በኢስሐቅ ምትክ የበግ መስዕዋት አቀረበ” -
(the sacrificed son of Abraham is ismael and not isacc) የተሰዋው የአብራሃም ልጅ
ኢስማኢል እንጂ ኢስሐቅ አይደለም.stoddard, p.141)
በኢስላም የቁድስ ሐረምነት ከሁሉ አስቀድሞ ከቁርአን የመጣ ነው፡፡ በይት አል-
መቅድስን እና መስጂደል አቅሳን በተመለከተ አላህ ሱብሃን ወተዓላ እንዲህ ይላል
28 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
29 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
30 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
አል-ቁድሥ፣ በሐዲስ
የቁድስን ሐረምነት የሚያመለክቱ በርካታ ነብያዊ ሐዲሶች አሉ፡፡ በአቡበከር አል-
ኻቲብ በተዘጋጀውና The virtue of Al-Quds በሚለው ጥንቅር ውስጥ ብቻ 165 ሃዲሶች
ተጠቅሰዋል፡፡ የትኛውንም የሐዲስ መድበል ያገላበጠ ደሞ የቁድስንና የመስጂደል አቅሷን
ቅድስና የሚያወሱ ሃዲሶች ብዙ እንደሚገኝ ነው፡፡ ከመሠል ብዙ ብዙ ሐዲሶች በሲሐነቱ
የሚታወቀውና ነብዩ (ሰዐወ) በይት አል-መቅዲስንና የአቅሷ መስጂድ ያደነቁበት ሃዲስ ተጠቃሽ
ነው፡፡ ነብዩ (ሰዐወ) በዚህ ሃዲስ አማካይነት ወደ አቅሷ የሚደረገውን የተቀደሰ ጉዞ በድንጋጌ
እንዳፀኑት እናያለን፡፡
31 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
“አርባ ዓመት ካሉኝ በኃላ በማያያዝም የሰላት ወቅት በደረሰበት ቦታ የትም ቢሆን
ስገዱ፣ ምክንያቱም መላው ምድር መስገጃ ነውና አሉኝ - (ሙስሊም)
ነብዩ(ሰዐወ) እንዲህም ብለዋል
“ከመሬቶች ሁሉ የአላህ ምርጫ ኢየሩሳሌም ናት፡፡ በኢየሩሣሌም የወረደ ጤዛ
ለማንኛውም ህመም ፈውስ ነው፡፡ ምክንያቱም ከገነት የነጠበ ነውና” (ኢብኑል ጀውሲይ ታሪኽ
በይተል መቅዲስ)፡፡
አልቁድስ በኢስላም ልዩ ቦታ ናት፡፡ ሐረምነቷ /ቅድሥናዋ እስከቂያማ ቀን እንደተጠበቀ
ይቀጥላል፡፡ ሠዎች ሁሉ በምድር ሕይወት የሠሩትን ዋጋ ያገኙ ዘንድ በፍርዱ ቀን በሷ
ይሰበሰባሉ፡፡ ስለዚህ ሙስሊሞች ሊጎበኟትና በመስጂዳም ሊሰግዱ ተገባቸው፡፡ በዚህ ላይ
የነብዩ አቋም ግልጽ ነው-
መይሙናህ የምትባል ሴት ወደነብዩ (ሰዐወ) በመቅረብ “ስለቁድስ ይንገሩን”
አለቻቸው፡፡
“በፍርዱ ቀን የሰው ሁሉ መሰብሰብያ ስፍራ ናት ልትጐበኛትና በመስጂዷ (መስጂድ አል-
አቅሷ) ተገኝተሸ ልትሰግጂ ተገባሽ ፡፡ ምክንያቱም በመስጂደል አቅሷ ውስጥ የተሰገደ ሠላት
በሌሎች መስጂዶች ከሚሰገዱ 500 ሠላቶች ጋር በደረጃ እኩል ነው” አሉዋት፡፡ በመቀጠልም
መይሙናህ- “ወደዛ መሄድ ባልችልስ - ምን ላድርግ?” አለች፡፡ ነብዩ (ሰዐወ) “በፋኖሶቿ ውስጥ
የሚቀጣጠ”ል የዘይት ስጦታ ላኪ፡፡ ማንም ቢሆን እንደዛ ቢያደርግ፣ ልክ(በቦታው ላይ ተገኝቶ)
እንደጐበኛት ይቆጠራል” (ኢብን ማጃህ)
32 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
33 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ምዕራፍ ሁለት
አል-ቁድስ/ኢየሩሳሌም
አል-ቁድሥ ምንግዜም በሙስሊሙ ሃሣብ ውስጥ አለች፡፡ በአዕምሮአቸው ጓዳ
ትነዝራለች፡፡ በኡማው የዕድሜ ዘመን ሁሉ በያንዳንዱ ሙስሊም ትውልድ ህሊና ውስጥ
ኖራለች፡፡ ዛሬም ቢሆን የታሪካችንና የህልውናችን ሕያው አካል በመሆን እንደቀጠለች ናት፡፡
ምክንያቱም
1. ከአላህ የተላኩት ነብያት በሙሉ የኢስላም ነብያት በመሆናቸው፣
2. መላው ሙሥሊም በሁሉም ነብያት (ከኢብራሂም እስከ ሙሳ፣ ዒሣ እስከ
ነብያቱ መደምደሚያ እስከ ሙሐመድ ዐለይሂሙ ሰላም ድረስ በተላኩት)
ስለሚያምን፣
3. የሁሉም ነቢያት ደዕዋ በተልዕኳቸው ዘመን ባንድ ወይም በሌላ መልኩ
ከቁድስ የተገናኘ በመሆኑ ነው፡፡
በመሆኑም ሙስሊሞች ከቁድስ ጋር ያለን መንፈሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነልቡናዊ ትስስር
እንዲበጠስ ወይም እንዲላላ በጭራሽ አንፈልግም፡፡
አልቁድስ የታወቁት አሃዳዊ እምነቶች መገናኛ እንደመሆኗ መጠን በሙስሊሞች ዘንድ
የተውሂድ ማዕከል ናት፡፡ ኢማን ዒባዳና ግንዛቤ ባንድ ተገናኝተውና ነጥረው ብርሃን
እንደሚሰጡበት የአዕምሮ ልዩ ጓዳ ትታያለች፡፡
ይበልጥ ደሞ አል-ቁድሥ ለሙስሊሞች የጂሃድ ዓርማ ናት፡፡ ቀደምት ታሪኮቿና
የወቅቱም እውነታ ይህንኑ ያረጋግጣሉ፡፡ በተለይም አሁን በፍልስጤም ሙስሊሞች እየተካሄደ
ያለው ኢንቲፋዳ በሙስሊሙ ኡማህ ዘንድ የቀሰቀሰው መንፈሳዊና ስሜታዊ ማዕበል በውነትም
ቁድስ በሙስሊሙ ዓለም እስከልብ ሥር የዘለቀ ቦታ እንዳላት የሚያመለክት ነው፡፡ ይህ ሃቅ
34 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
35 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
36 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
37 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
3/ የነብያት አገር
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህ አካባቢ የአንቢዩቹን የሩሡሎቹ አገር ቤት እንዲሆን
መረጠው፡፡ የሱን ትዕዛዝና መልዕክት ተቀብለው በማስተላለፍ ለየወገናቸው ያስተማሩበት
38 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ነብዩ (ሰዐወ)፣ “ከኡመቴ የሆኑ ጭፍሮች የእውነት ሐዋሪያ በመሆን/ ለሃቁ በመሟገት
ይቀጥላሉ፡፡ ሰዐቲቱ /ቂያማ እስከምትቆምም ድረስ በጠላቶቻቸው ላይ እነሱ ሁሌም
ባለድል ናቸው፡፡"- ብለው ሲሉ፣ ከታዳሚዎች አንዱ "ያ ረሱሉሏህ! እነሱን የት
ልናገኛቸው እንችላለን? ሲል ጠየቃቸው
”እነሱ በበይተል መቅዲስ እና በዙርያው ይገኛሉ” አሉት፡፡ (አህመድ)
39 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
7/ የሸሂዶች መሬት
የዚህ ብሩክ መሬት አፈሩ በብዙ ሸሂዶች ደም የረጠበና የተቀመመ ነው፡፡በጣም ብዙ
የሆኑ ወሳኝ ጦርነቶች በፍልስጤም ምድር ተካሂደዋል፡፡ የሐቲን፣ ዓይን ጃሉት፣ የአካህ፣
የቁድስና ያካባቢው ጦርነቶች ይጠቀሳሉ፡፡ በነዚህ ታላላቅ ጦርነቶች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ
ሙስሊሞች ተሰውተዋል፡፡ ባለፈው 50 ዓመት ብቻ (ዛሬ ዓለም የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት
በሚል ሥም ሰጥቶ የሙስሊሙን እይታ ባጭበረበረበት) በዚሁ “የመካከለኛው ምሥራቅ”
ተብዬ ጦርነት በአረቦችና የሁዶች መሃል በተካሄደውና እየተካሄደም ባለው ፍልሚያ በሺዎች
የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ሸሂድ ሆነዋል፡፡ እስከዚህም ደቂቃም መሥዕዋትነትን እየከፈሉ ናቸው፡
፡ 2ኛው ኢንቲፋዳ (ኢንቲፋዳ ጀዲዳ) በ1421ሂ የሻዕባን ወር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶም በየቀኑ
ብዙዎች በሸሂድነት መውደቃቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡ እነሆ ጂሃድና ሸሂድነት የተባረከው
የፍልስጤም ምድር ልዩ እንደቀጠሉ ነው፡፡ እነሆ ጂሃድና ሸሂድነት የተባረከው የፍልስጤም
ምድር ልዩ መለያ እንደሆነ ይቀጥላል፡፡
40 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ዑመራዊ ቃል ኪዳን
በመቀጠልም ዑመር(ረዐ) ከሊቀ ካህናቱ ጋር የስምምነት ውል አፀደቁ፡፡ በስምምነቱ
መሠረት ለቁድስ ነዋሪዎች የሕይወት፣ ያምልኮ ነጻነት፣ የንብረትና የማምለኪያ ስፍራ ጥበቃ
ዋስትና ገቡላቸው፡፡ ሙስሊም ካልሆኑ የከተማይቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነትም
ውል ተበጀለት፡፡ ዛሬ ሁሉም የታሪክ ሊቃውንት እንደሚቀበሉት ዑመራዊ ቃልኪዳን ፍትሐዊና
ባካባቢው ታሪክ ወደር ያልነበረው ነው፡፡ ከኢስላማዊ አገዛዝ በፊት በቦታው ላይ የነበሩትና
በጂሃድ ጦርነት የተወገዱት ክርስትያን ቢዛንታይኖች የሁዶችን ሲያሳድዱ ነበር፡፡ ወደቁድስ
ድርሽ እንዳይሉም ማዕቀብ ጥለውባቸው ነበር፡፡ ሙስሊሞች መጡና ማዕቀቡን አነሱላቸው፡፡
የሁዶች ወደ ቁድስ መግባት ቻሉ፡፡ ወደቁድስ መግባት ብቻ ሳይሆን የኢስላማዊ ወቅፍ ይዞታ
ወደሆነው ”የኢየሩሳሌም ማርገጃ ግንብ“ ሄደው እንዲፀልዩም ተፈቀደላቸው፡፡
41 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ኦገስት 21‚1969 ሚሼል ሮሐን የተባለና እራሱን የ”church of god” አባል የሚል
አውስትራሊያዊ መስጂዱን ለማቃጠል ሙከራ አደረገ፡፡ እሱ በለኮሰው እሣት አንድ ሺህ ዓመት
ያስቆጠረ ሚንበር ወደመ፡፡ በገንዘብ የማይተመን፣ ከምርጥ እንጨትና ከዝሆን ጥርስ የተሰራ
ውድ ዕቃ ነበር፡፡ ሚንበሩ ከሀሊብ/ሱሪያ በሰለሃዲን አል አዩቢ ነበር የመጣውና ለመስጂዱ
የተበረከተው፡፡
ኦክቶበር 1982 የ“kach” ንቅናቄ አባል የሆነ ግለሠብ መስጂዱ ላይ ሊሸጥር አቅዶ
በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ዩኤል ለርነር “ቁበተል ኸድራን” ሊያጋይ በማቀድ ወንጀል ተከሶ የሁለት
ዓመት እስራት ተፈረደበት፡፡
42 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
43 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
የሠላም ቃል ኪዳን
ኢሥላም መቼም ፀረ-ሰላም ሆኖ አያውቅም፡፡ ኢስላም የሠላም ሃይማኖት ነው፡፡
አልቁድስ/ኢየሩሣሌም የሠላም ከተማ ናት፡፡ ጠላት ከልቡ ሠላም ከፈለገ ሙስሊሞችንም
ይህንኑ መቀበል አለባቸው፡፡ ነገር ግን ሠላሙ የይስሙላ ሣይሆን እውነተኛና ቀጥተኛ እንዲሆን
እንፈልጋን፡፡ ሙስሊሙ ኡማህ መልሶ ለሽንፈት፣ ለውርደትና የራሱን ሃቅ አሳልፎ እንዲሰጥ
ለሚገደድበት ሠላም ማደር የለብንም፡፡ ብቃት ያለው ሙስሊማዊ አመራር ጨርሶ በሌለበት
ሁኔታ የኢስራኢል መንግሥት በምዕራብ ሃያላን ድጋፍ ሰጪነት በሙስሊሞች ላይ ለመጫን
የሚሞክረው ሠላም በመሠረቱ ሠላም አይደለም፡፡ ፍትሃዊ፣ የሚሰራም አይደለም፡፡
የፍልሥጤም ባለስልጣናት እንዲቀበሉት ቢገደዱ እንኳን ባካባቢው ላይ ሠላምና መረጋጋት
ሊሰፍን አይችልም፡፡ የሰብዐዊ መብት ረገጣውና ብጥብጡ እንዳለ ይቀጥላል፡፡ ችግሩን
ከማባባስና የሕዝቡን ስቃይ ከማራዘም በስተቀር የሚፈይዱት የለም፡፡ የችግሩ መባባስና
የሕዝቡን ሥቃይ መራዘም ደሞ ቀጣዩን አመፅ የበለጠ ያደርገዋል፡፡ “ጠያራትና ደባባት“
አሁንም አልገቱት፣ ወደፊትም አያቆሙት-
ድሉ የሙስሊሞች ነው
ሙስሊሞች የተባረከውን መሬት ለማስመለስና የዳዕዋ ግዳጃቸውን ለመወጣት
በሚያደርጉት ትግል አሸናፊዎች እንደሚሆኑ በቁርአንና በሱና ብስራቱ ተነግሯል፡፡ በቅርብም
ይሁን በመጪው ጊዜ ድሉ የሙስሊሞች እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ ካሁኑ አመልካች
ሁኔታዎች እየታዩ ነው፡፡
44 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
በሚያስገኝ የሠላም ማዕቀፍ ውስጥ ገብተን መውተፍተፍ አንፈልግም፡፡ የዚህ ዓይነቱ አቋም
በሙስሊሞችና በየሁዶች መካከል እየተካሄደ ያለውን ትግል በምንም ዓይነት እንደማይወክል
ለወዳጅም ለጠላትም ግልጽ ይሁን፡፡
ኢንሻአሏሁ ተዓላ-
በቅርቡ ሌላውን ሰለሃዲን እናያለን፡፡ እሱ በ1187 (የደም ጎርፍ ሳይኖር) በተዋጣለት
ወታደራዊ ክህሎት የተባረከውን መሬት መልሶ በመቆጣጠር ሠላምና መረጋጋት እንዳሰፈነበት
ሁሉ እኛም ተጠናክረን፣ ደመናችን ሃይል አካብቶ በቦታው ላይ ሠላሙን የምናሰፍንበት ጊዜ
ሩቅ አይሆንም፡፡ እርግጥ ነው ሙስሊሞች አሁን ያሉበትን አስከፊ ገጽታ ለመቀየር በጣም ብዙ
መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለስራ ውጤት የለም፡፡
ምዕራፍ ሶስት
የታሪክ ማስታወሻ
በቅድመ ኑቡዋ (ነብዩ ከመላካቸው በፊት) ነብዩ አደም አለይሂ(ዐሰ) በመካ ካዕባን
ካቆሙ ካቆሙ ከ40 ዓመት በኃላ መስጂደል አቅሷን ሰሩ፡፡ እነዚህ ሁለት መስጂዶች
መጀመሪያ በመላዕክት እንደተሠሩም ይነገራል፡፡ ይህ ደሞ የሁዶች እንደሚሉት
መስጂደል አቅሷ ለነሱ የተለየ ያምልኮ ስፍራ አለመሆኑን ያሣያል፡፡ ምክንያቱም
መስጂዱ ህልውና ያገኘው ከኢብራሂም(ዐሰ)በፊት ነውና፡፡
ነብዩ ኢብራሂም (ዐሰ) እና ልጃቸው ኢስማኢል(ዐሰ) ካዕባን እንደገና ካነጹ ከ40
ዓመት በኃላ እሳቸውና ሌላው ልጃቸው ኢስሐቅ(ዐሰ) መስጂደል አቅሷን እንደገና
ገነቡት፡፡
45 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
46 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
47 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
48 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
49 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
በመሃል አልቻለም እሱ
አቃተው መላወሱ፡፡
ዛለ ደከመ ጉልበቱ
ኢንቲሳር ተጨነቀች በብርቱ፡፡
የሰው ስጋ የቀመሰ
አሞራውም በሰማይ ተመላለሰ
ይህንን ማየቱ ዘገነናት
ሙሽራው ባሏ (ገና ሳይፈፀም) ውሃ ውሃ እያላት
የገዛ ደሙን አትግተው ጨነቃት
ጭንቅ ጥብብ አላት
ደሙን አስቁማ…
ሥቃዩን አስታማ ሕይወቱን ለማትረፍ
እርግፍግፍ አለች እንስፍስፍ…
…ተጨነቀች ተጠበበች
ዕንባዋ ሳይቀር ባፉ አነጠበች
የሚቻላትን ሆነች
ከሚቻላትም በላይ ሞከረች
ዕንጥሉን ቢያርስለት ብላ ከንፈሮቹም ላይ አለቀሰች
የሚቻላትን ሆነች
ከሚቻላትም በላይ ሞከረች
51 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
በረደችናም- እንደመስከን ብላ
ደሞ ደፈረሰች እራሷን ነቅንቃ
የፊሊስጢኗ ምንጭ ያልተቀዳች ቡርቃ
ታትማ ያደገች በኢማን ተጠብቃ፡፡
እሷም ይሄኔ
ቁርጥን ማወቅ በለገሳት ወኔ
የሂጃባን ቅዳጅ እራፊ
ደም ያረጠበውን የጨርቅ ትራፊ
እፊቱ ላይ ጥላ
/ሥፍራው እንዳይጠፋት በበረሃው ማምሻ
ምልክጽ ብጤም አድርጋ
እያንገፈገፋት አደባባይ ቆማ
53 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
ያገኛትን ጉድ ስትናገር ጩኻ
ፍልስጤም
ገዛ ረፋእ ኢየሩሣሌም
የግፍ ዱላ ቅጥቃጤ ጥቁር ደም
በድርድር እማይታገም
የግፍ ዱላ ቅጥቃጤ እብጠቱ
በገዛ መሬት ላይ ነፃነት የማጣቱ
አስቆጥቶ አስጨንቆ ወኒ ሲያግት
በኢማን ሙላት ሲነሽጥ
በሠይፍ ስለት ነው ‘ሚወጣለት’
54 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
በጂሃድ ብቻ ነው ‘ሚለይለት’
ፍልስጤም
በይት ጃላ በይት ለሐም
የሙስሊሙ የዓመታት ሕመም
የቁጣው ንዝረት ትርታ
ከቁበተል ኸድራ ሚመታ
እያለ ኢላ- መታ
እስከ መቼ ድረስ
ፒስ- ፕሮሰስ
ይሉናል ፒስ-ፒርሰስ
ከበስተጀርባው ረሣስ
ሕዝቡን ለመጨረስና መሬቱን ለመውረስ
ፍልስጤም
ጦርነት ባንቺ ግድም
ድል የሚታፈስበት ነው ከጥንትም
እየወቃሽ ነው ዘንድሮም
55 | ገ ገ
[የተቀደሰው የፍልስጤም ምድር] በ ዘይነብ ሐሰን
አንቺማ ምን አለብሽ
እውስጥሽ እየተቀጣጠሉ እንደጥይት አረር ልጆችሽ
የጋለ ጠመንጃ አፈሙዝ ነው አይያዝም መሬትሽ
አይጨበጥም ግዛትሽ
ያቃጥላል ዛትሽ
56 | ገ ገ