You are on page 1of 99

እስልምና ኮርስ

አለምገና ቤቴል ቃለ ህይወት ቤ/ክርስቲያን


መጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት
ክፍል አንድ
የእስልምና ታሪክ

የእስልምና ታሪካዊ ዳራ
1. ከእስልምና በፊት የአረቢያ ሁኔታ፡-
ሀ. የፖለቲካ ሁኔታ
- አረቦች የተከፋፈሉ ነበሩ

- አረቢያ ተከባ የነበረችው በክርስቲያን ግዛቶች ነበር ነገር ግን የተረሳች


ምድር ነበረች፤
- የማያቋርጥ የጎሳ ግጭት ነበረባት
ለ) ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ
- ሴቶች፤ ወላጆቻቸው ያጡ ልጆች በማህበረሰቡ ውስጥ
የተገለሉና የተጨቆኑ ነበሩ
- አብዛኛው ህዝብ የሚተዳደረው በከብት እርባታ ሲሆን
የከተማ ነዋሪዎች ነጋዴዎች ነበሩ
- ጎሰኝነት የተጠናከረ ነበር
ሐ) ሀይማኖታዊ አውድ
- ክርስቲያኖችና አይሁዶች በአረቢያ ይኖሩ ነበር
- አብዛኛው ሕዝብ ግን የሚያመልከው ጣኦት ነበር
- ሐኒፍ የሚባሉ አንድ አምላክ የሚያመልኩ የሐይማኖት
ቡድኖችም ነበር
2. የመሐመድ ታሪክ (570-632)
- የመሐመድ አስተምህሮና ህይወት በእስልምና እምነት ውስጥ
ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው፤
- የመሀመድን ታሪክ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን ማየት ተገቢ
ነው፡-
ሀ) በመካ የነበረው ህይወት፡-
ውልደቱ፤ እድገቱ፤ የነብይነት
ጥሪው፤ የመጀመሪያዎቹ የአገልግሎቱ
10 አመታት (570-622)
ለ) በመዲና የነበረው ቆይታ፡- ወደ
መዲና ከተማ ከተሰደደ በኃላ
የነበረው የሀይማኖትና የፖለቲካ
መሪነት ዘመን (622-632)፡፡
ሐ) መሐመድ ከአይሁዶች ጋር ግጭት ውስጥ ሲገባ የተቀየሩ
ነገሮች
• የጸሎት አቅጣጫ ከኢየሩሳሌም ወደ • ወደ መካ ኃይማኖታዊ ጉዞ ተጀመረ፡፡ ካዕባን

መካ ተቀይሯል (ሱራ 2፡142- (ጥቁር ድንጋይ) መሳምና ሌሎች በሐጅ ጊዜ

145፤ 149-15ዐ)፡፡ የሚደረጉ ተግባራት ኃይማኖታዊ ስርዓቶች

ሆነው ተደነገጉ፡፡
• በአይሁድ የስርየት ቀን የነበረው
• በመዲና የተገለጡት የቁርዓን ሱራዎች
ፆም ወደ ረመዳን ወር ተቀየረ፡፡
ይዘታቸው ከሥነ-መለኮት ይልቅ ማሕበራዊ፤
• እስልምና የአብርሃም እምነት ነው
ፖለቲካዊና ሕገ ነክ ጉዳዮችን የሚያንፀባርቁ
መባል ተጀመረ፡፡ ሆኑ፡፡
• የአዛን ጥሪ ደወልን ተክቶ ማገልገል • ሰላት በቀን ሦስት ጊዜ የነበረው አምስት ጊዜ
ጀመረ፡፡ ተደረገ፡፡
3. ከመሐመድ በኃላ የተነሱ ሙስሊም መሪዎች

ሀ) አቡ በክር (632-634 ዓ.ም) ለ) ኡመር ኢብን አል- ኸጣብ (634-


644 ዓ.ም)
• አቡ በክር ቀድመው እስልምናን
• ኡመር ከመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች አንዱ እና

ከተቀበሉ ሰዎች አንዱ ሲሆን፤ የነብዩ የመሐመድ ሦስተኛ ሚስት የሐፍሳ አባት ነው፡፡

• ኡመር በእምነቱም ሆነ በማስተዳደር ብቃቱ


መሐመድ ሚስት የአይሻ አባትም
የተመሰገነ ሰው ነበር፡፡
ነው፡፡
• ሶሪያ (636)፤ ኢየሩሳሌም (638)፤

• እስልምናን የካዱ አረቦችንና፤ ደቡባዊ ምዕራብ ኢራቅና ፐርዥያ (641)፤ እና

ባሉቺስታንና፤ ግብጽ በ642፤ ኑቢያ (ሱዳን)


ኤራቅንም ወደ እስልምና ቀይሮአል፡፡
በ643 ተይዞአል፡፡
ሐ) ኡስማን ኢብን አፋን (644-656 ዓ፣ም) መ) አሊ አብን ሳቢት (656-661 ዓ.ም)

 ኡስማን ከመካ ገዥዎች (ኡማያድ) ቤተሰብ የተገኘ  አሊ የመሐመድ የአጎት ልጅና የልጃቸዉ
ሲሆን፤ ከመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ውስጥ አንዱ /ፋጡማ/ ባል ነዉ፡፡
ነው፡፡
 ከቀደምት የእስልምና እምነት ተከታዮች
 በሥልጣን ዘመኑም ቁልፍ በሆኑ የሥልጣን
አንዱ ሲሆን በሕይወት እያሉ የጸሎት /ስላት/
እርከኖች ላይ ዘመዶቹን አስቀምጦ ስለነበር ይህ
ሥርዓት እንዲመራ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር
ዓይነት አሠራር የቀድሞዎቹን ካሊፋቶች ፈለግ
ነገር ግን በኡስማን መገደል እጁ እንዳለበትም
ያልተከተለ በመሆኑ ከተለያየ አቅጣጫ ተቃውሞ

አስነስቶበታል፡ ይጠረጠራል፡፡

 ቁርዓን ማሰባሰብ ፤ አዘርባጃን፤ የኤራንን የተወሰነ  የማስተዳደር ብቃቱ ደካማ ስለነበር በእርሱ

ክፍል እና አርሜንያን ፤ ቆጵሮስን ይዟል፡፡በምዕራብ የሥልጣን ዘመናት ሙስሊሙን ኅብረተሰብ


በኩልም ሰሜን አፍሪካ እስከ ትሪፖሊ ድረስ ወደ ክፍፍልና አለመረጋጋት ዉስጥ እንዲገባ
ተቆጣጥሮአል፡፡ አድርጓል፡፡
4. የኡማያድ ካሊፋቶች ዘመን (661-749 ዓ.ም)
• አሊ ሲሞት ስልጣኑን የተረከበዉ ሙአዊያህ የተባለዉ የሶሪያ አገረ ገዥ የነበረዉ ሰዉ
ነዉ፡፡

• በእነዚህ ዘመናት የተለያዩ መሪዎች ተነስተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሙአዊያ (661-


680 ዓ.ም)፤ ያዚድ 1ኛ (680-683 ዓ.ም)፤ መርዋን 1ኛ (683 - 684
ዓ.ም) መርዋን (684-685)፤ አብድ አል-ማሊክ (685-705 ዓ.ም) አል ዋሊድ
(705-717 ዓ.ም)፤ ኡማር 2ኛ (717-720 ዓ.ም)፤ ያዚድ 2ኛ (720-724
ዓ.ም) እና ሒሻም 1ኛ (724-743 ዓ.ም)፤ መርዋን 2ኛ (744-749 ዓ.ም)
ናቸዉ፡፡

• በኡማያድ ስርወ መንግስት /ካሊፌት/ እስልምና በምዕራብ በኩል ሰሜን አፍሪካን አልፎ
እስከ ፈረንሳይና ስፔን ደርሷል፡፡
በዚህ ዘመን የተገነቡ ሁለት ማዕከላት

አል-አቅሳ መስጊድ በ691 ዓ.ም የደማስቆ ትልቁ መስጊድ


የተሰራ ከ705-715 ዓ.ም
የእስልምና ተግዳሮት በቤተክርስቲያን ላይ
 እስልምና ወደ ተለያዩ ስፍራዎች በሀይል ሲስፋፋ በቅድሚያ
የተቆጣጠረው የክርስቲያን አከባቢዎችን ነበር
 እስልምና በክርስትና ላይ ስነ-መለኮታዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮት
ደቅኖአል
ለእስልምና መስፋፋት አስተዋጽኦ ያደረጉ ነገሮች

 ክርስቲያኖች የወንጌል ስርጭት  ሙስሊሞች በጦር ኃይል


እና የደቀመዛሙርትነት መስፋፋት
መዳከም፡፡ • ክርስቲያኖች ስለእስልምና
 የቤተክርስቲያነ ክፍፍልና ስነ- የነበራቸው የተዛባ ግንዛቤ
መለኮታዊ ክርክር • መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቋንቋ
አለመተርጎሙ
5. የአባሲድ ስርወ መንግሥት /ካሊፌት/
(750-1258 ዓ.ም)
• የኡማድ ስርወ መንግስት ከውጭና ከውጥ ከነበረበት ተግዳሮች

የተነሳ ሲዳከም በ750 ዓ.ም አብድ አል-ራህማን የተባለው

የኡማድ ካሊፍ ሌሎች የእስልምና ግዛቶችን ትቶ ወደ ስፔን በመሸሽ

ኮርዶቫ በተሰኘ ከተማ ማስተዳደር ጀመረ፡፡

• ነገር ግን የተቀሩት የእስልምና ግዛቶች በአባሲድ ኃይሎች ቁጥጥር

ስር ወደቀ፡፡
• በአባሲድ ስርወ መንግሥት ዘመን ብዙ ነገሥታት የተፈራረቁ ሲሆን

የአስተዳደር ማዕከላቸዉን ከደማስቆ ወደ ባግዳድ አዙረዋል፡፡

• አነዚህ መሪዎች ኃይልን የሚጠቀሙ ሲሆን ቁሳዊነትና ዓለማዊነት

ያጠቃቸዉ ነበር፡፡ አንዳንዶቹም ወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፡፡

• እንዲሁም ስልጣን ከአረቦች እጅ ወጥቶ አረብ ያልሆኑ

ሙስሊሞችም በአስተዳደር እርከን ዉስጥ የገቡበት ጊዜ ነዉ፡፡


• ባግዳድና ኮርዶቫ (ስፔይን) ሁለቱ ትላልቅ የሙስሊም የባህል ፤

የትምህርት፤የንግድ እና የአስተዳደር ከተሞች ሆኑ፡፡

• በከተሞች የቀለም ትምህርት እየተስፋፋ መጣ፤ በተለይም ቁርዓንና አረብኛ

ጽሑፎችን ማጥናት በሰፊው ተስፋፋ፡፡

• ከቁርዓን ቀጥሎ የሙስሊሞች የእምነታቸዉ መሠረት የሆነዉ ሐዲስ የተሰበሰበዉ

በአባሲድ ስርወ መንግሥት ጊዜ ነበር፡፡

• ብዙ የእስልምና ሊቃውንት የተነሱበት ዘመን ስለነበር የእስልምና ስነ-መለኮት


የዳበረበት እንዲሁም እስልምና ጠንካራ ሀይማኖታዊ ቅርጽ እንዲይዝ የተደረገበት
ጊዜ ነው፡፡
• በፐርዥያዊዉ አል-ኸዋርዝሚ በተባለዉ ሊቅ በ850 ዓ.ም የተዘጋጀዉ

አስትሮኖሚካል ሰንጠረዥ (astronomical table) በኋላም ለተሰራዉ


የሒሳብ ህጎች (Aljebra) መሠረት ጥሏል፡፡

• በመድኃኒቶች ጥናትም የአረቡ ዓለም ከአዉሮፓና ከሌላዉ ዓለም በተሻለ ደረጃ

ነበር፡፡

• በተጨማሪም የግሪክ ፍልስፍና ጥናቶች ወደ አረብኛ የመተርጎም ሥራ በከፍተኛ

ሁኔታ አድጎ ነበር፡፡

• በተለይም በካሊፍ ሐሩን አልረሲድ (786-809 ዓ.ም) እና በልጁ አል ማሙን

(813-833 ዓ.ም) ዘመን የአረቡ ዓለም በስልጣኔና በብልጽግና ከፍተኛ ደረጃ


የደረሰበት ጊዜ ነው፡፡ ይህም “ወርቃማው የእስልም ዘመን” ተብሎ ይጠራል፡፡
6. እስልምና በቱርኮች አስተዳደር ዘመን (1258-1924 ዓ. ም)
 የአባሲድ ስርወ መንግስት በመስቀል ጦርነትና በሌሎችም ችግሮች እየተዳከመ ሲመጣ

በቱርኮች እጅ ወደቀ፡፡

 ቱርኮች ከማዕከላዊ እስያ ፈልሰው የመጡ አረብ ያልሆኑ ህዝቦች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ

የሙሰሊም ግዛቶች ወረው ከመያዛቸው በፊት እስልምናን ተቀብለው ነበር፡፡

 ከዚህም የተነሳ የእስልምና አስተዳደር ለሶስት ዋና ዋና ግዛቶች ተከፍሏል፡፡

እነርሱም፡-

የማምሉክ ግዛት (1254-1517 ዓ.ም)፡- የማምሉክ ገዢዎች በእነዚህ ዓመታት


ግብጽን ያስተዳደሩ ሲሆን መሪዎቹም ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለወታደራዊ
አገልግሎት ከቱርክና ከአውሮፖ የመጡ ባሪያዎች ነበሩ፡፡
የሰልጁኮች ግዛት፡- ከ97ዐ ዓ.ም ጀምሮ ከመካከለኛው እስያ አካባቢ በመነሳት
ሰልጁክ በተባለ መሪ አማካይነት በፐርዢያ (ኤራን) ሰፍረው ነበር፡፡ ነገር ግን
ከተወሰኑ አመታት በኃላ ወደ እስልምና በመለወጥና ወደ ሙስሊም ግዛቶች
በመስረግ የተወሰኑትን ግዛቶች የተቆጣጠሩ ናቸው፡፡

ኦቶማን ቱርኮች፡- ኦቶማን ቱርኮች ከ1300-1924 ዓ.ም የሙስሊሙን አለም


ያስተዳደሩ ሲሆን ግዛታቸውም የተመሰረተው የሰልጁክ አስተዳደር በ1307
በወደቀበት ስፍራ እንዲሁም የማምሉክ ግዛት በ1517 ዓ.ም በወደቀበት ግዛት
ላይ ነበር፡፡ የግዛታቸውም ዋናው ከተማ በ1453 ዓ.ም በተቆጣጠሩት
ቁስጥንጥንያ ከተማ ሲሆን ስሙንም ኢስታንቡል በማለት ቀይረውታል፡፡
የእስልምና ታሪክ በኢትዮጵያ

1. እስልምና ከ7ኛ-19ኛ ክፍለ ዘመን

- የነብዩ መሐመድ ስደተኞች በ615 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጡ

- እስልምና ወደ አትዮጵያ በመጡ አረብ ነጋዴዎችና በጋብቻ ቀስ በቀስ ወደ

መሐል ሀገር ተስፋፋ፡፡

- ከ12ኛ-16ኛ ክፍለ ዘመን የአክሱም ስርወ መንግስት እየተዳከም ሲመጣ

የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በምስራቁ የአገሪቱ ክፍል እየጠነከረ መጣ፡፡


-
- በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል የንግድ መስመሮችን
ለመቆጣጠር ግጭቶች መደረግ ተጀመሩ፡፡
- ይህ ግጭት እያደገ መጥቶ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የአህመድ
ግራኝ ጦርነት ከ1529-1543 ተካሂዶአል፡፡
- ሙስሊሞች በጦርነቱ በመሸነፋቸው የክርስቲያኖች የበለይነት
ተረጋገጠ፡፡
- ከ18-19ኛው ክፍለ ዘመን በመሳፍንት ዘመን እስልምና
በኦሮሚያ፣ በወሎ እና የጁ አከባቢዎች እየተስፋፋ መጣ፡፡
- በ1875 ዓ.ም ግብጽ ሐረር በመቆጣጠርዋ እስልምና በሐረር
ኦሮሞዎች ዘንድ እንዲሰፋፋ ምክንያት ሆኖአል፡፡
- አጼ ዮሐንስንና አጼ ሚኒሊክ ሙስሊሞችን በግድ የማስገደድ
እርምጃዎችን ወሰዱ፡፡
- የአጼ ሚኒሊክ መስፋፋት የአርሲ ሙስሊሞች ወደ እስልምና
እንዲቀየሩ ምክንያት ሆኖአል፡፡
- በአጠቃላይ ከ16-19ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው
የሙስሊሞችና የክርስቲያኖች ግንኙነት የተበላሸ ነበር፡፡
2. የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን
- በደርግ ዘምን ለሙስሊሞች የዝግጅት ጊዜ ነበር፡፡

- የሙስሊም በአላቶች (አረፋ፣ ኢድ አል ፈጥር እና


መውሊድ) በብሄራዊ ደረጃ መከበር ጀመሩ፡፡
በኢህአዴግ መንግስት ዘመን ቀጥሎ ያሉትን ለውጦች
ተስተውለዋል፡-

ሀ) መንፈሳዊ ለውጦች

ለ) የህትመትና የትርጉም ስራዎች እድገት

ሐ) የመስጊዶች፣ የትምህርት ቤቶች፣ ቁርአን ት/ቤቶች

መ) የፖለቲካና የኢኮኖሚ እድገት

ሠ) የቁጥር እድገት
የቤተክርስቲያን ምላሽ

1. የወንጌል ሰራተኞችን ማሰማራትና መደገፍ

2. የክርስቲያኖች በፖሊቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች

መሳተፍ

3. ተማሪዎችን ማሰልጠን

4. የህትመት ስራዎችን መስራት


5. ጸሎት

6. ከእስልምና የሚመጡትን አማኞች ደቀመዝሙር

ማድረግና ለወንጌል ስራ ማሰማራት

7. የቤተክርስቲያን የልማት ስራዎች ከወንጌል ስርጭት ጋር

ማቆራኘት

8. ለወንጌል ስርጭት የሚረዱትን የስልጠና ማዕከላትን

መገንባት
ክፍል ሁለት
የእስልምና ስነ-መለኮት
1. የእስልምና መጻህፍት
ቁርአን
- የነቢያት መጽሐፍት የተላኩበት አላማዎች፡- 1) ለጸድቃን ሽልማት

እንዳላቸው ለማብሰር፤ 2) ለአመጸኞች ለማስጠንቀቅ፤ 3) ከዚህ በፊት


የተላኩ መልዕክቶች ለማስታወስ፤ 4) በሰዎች መካከል ፍርድ ለመስጠት፡፡
- በ23 አመታት ውስጥ ለነብዩ መሀመድ ቃል በቃል የተገለጠ ሲሆን በ114

ምእራፎች የተከፋፈለ ነው፡፡


- ቁርአን የመካ (86 ሱራዎች) እና የመዲና (28 ሱራዎች) ሱራዎች

በመባል በሁለት ይከፈላል


- እንዲሁም ቁርአን በ30 ጁዝ ይከፈላል

- ስለሌሎች ርዕሶች ይተርካል፡፡


- የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችንም ይዛል፡፡

- ቁርአን በሙስሊሞች ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ አለው፡፡

- ቁርአን የሚጠናው ከሀዲስ መጽሐፍ ጋር በማዛመድ ነው፡፡

- ቁርአን ስለ ፍጥረት፤ ስለ ፈጣሪ አምላክ፤ ስለሰዎች፤

ስለመላዕክት አለም፤ ስለወደፊት ፍርድ፤ ስለሀጢአት፤


ስለድነት፤ ስለክርስትናና ስለአይሁድ እምነት፤ ስለእምነትና
ሐይማኖታዊ ተግባራት እንዲሁም
ሀዲስ
- ሀዲስ ማለት የነብዩ መሐመድ ንግግሮች፡ አባባሎችና ተግባራት የያዘ

መጽሐፍ ነው፡፡
- የሀዲስ ዋና አላማ ሙስሊሞች የነቢዩን ፈለግና ትምህርት እንዲከተሉ
ማድረግ ነው፡፡
- ስድስት የሀዲስ መጽሐፍ ስብስቦች ያሉ ሲሆን በስድስት የተለያዩ ሙስሊም
ምሁራን ተሰብስበው የተጻፉ ናቸው፡፡
- የሀዲስ መጻህፍት የተጻፉት ከነብዩ እረፍት 200 አመታት በኃላ ነው፡፡
- መጻህፍቱ ሲሰበሰቡ አባባሎቹ የነብዩ መሐመድ መሆናቸው ለማረጋገጥ
2. ስድስቱ የእስልምና የእምነት አቐሞች
ሀ) ስለ አላህ አንድነት ማመን
አላህ በአካልና በመለኮት አንድ እንደሆነ ማመን ያስፈልጋል፡፤
 ቁርአን የስላሴን አስተምህሮ ይቃወማል (ሱራ 4፡171፤ 5፡73፤
17፡11)
 የአላህ ባህርያት፡- ትልቅነት፤ የሩቅና የቅርብ አምላክ መሆኑ፤
ህይወት ነው፤ ሁሉን ያውቃል፤ ሁሉን ቻይ ነው፤ የወደደውን
ያደርጋል፤ ሁሉን ይሰማል፤ ሁሉን ያያል፤ ይናገራል፤ ይወዳል፤ ወዘተ…
 አላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት

 አላህ ፈቃዱን እንጂ ራሱን አይገልጥም


ለ) በቅዱሳን መጻህፍት ማመን

 ሙስሊሞች በአላህ የተላኩ አራት ቅዱሳት መጻህፍት እንዳሉ ያምናሉ (ሱራ

3፡3፤ 3፡84፤ 2፡136፤ 4፡136፣ 163፤ 5፡46-48፤ 10፡94፡፡

እነርሱም፡-

1. ተውራት

2. ዘቡር

3. ኢንጂል

4. ቁርአን/ፉርቃን
ሐ) በመላዕክት ማመን
መላዕክት በሁለት የከፈላሉ፡-
1. ቅዱሳን መላዕክት፡-
- የተፈጠሩት ከብርሃን ሲሆን አላህን ቀንና ሌሊት የሚያገለግሉ ናቸው
- ዋና ዋና መላዕክት ጅብሪል፤ ሚካኤል፤ ኢስራፊል፤ አዝራኢል፤
ሙንከርና ናኪር፤ በቀኝና በግራ ትከሻ ተቀምጠው የሰውን መልካምና ክፉ
ስራ የሚመዘግቡ መላዕክት፤ እና ገሀነምን የሚጠብቁ መላዕክት ናቸው፡፡
2. የወደቁ መላዕክት፡
- ጅኒዎች፡- ጭስ ከሌለው እሳት ከአዳም መፈጠር 2000 አመታት
በፊት የተፈጠሩ ናቸው፡፡
- በየብስ፤በውኃ አካላትና በአየር ላይ ይኖራሉ
- ጥሩና መጥፎ ጅኒዎች በመባል በሁለት ይከፈላሉ
- አንዳንዶችም ሙስሊሞች ናቸው
ሰይጣን፡- ኢብለስ ወይም ተቃዋሚ ተብሎ ተጠርቶአል
- የተፈጠረው ከእሳት ነው (ሱራ 7፡12)፤
- ለአዳም ለመስገድ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በትዕቢቱ ምክንያት
ወድቓል፤
መ) በመልዕክተኞች/ነብያት ማመን

- መልዕክተኞች በሁለት ይከፈላሉ፡-

ሀ) ነብያት- መጽሐፍ ያልተሰጣቸው

ለ) መልዕክተኞች - ለተለየ አላማ የተላኩና አንዳንዶቹ መጽሐፍ

የተሰጣቸው ናቸው

- 315 መልዕክተኞች ሲኖር 28ንቱ በቁርአን ውስጥ በስም

ተጠቅሰዋል፡፡
ቁርአን ስለ አል-መሲህ ኢሳ ምን ይላል?
 አል-መሲህ ኢሳ ከመልዕክተኞች ውስጥ አንዱ ነው

 ስለ ማንነቱ፡- ከድንግል መወለዱ (ሱራ 19፡34-35)፤ በመስቀል ላይ


አልሞተም (ሱራ 4፡157)፤ ዳግም ይመለሳል (ሱራ 43፡63)፤
የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም (ሱራ 112)፤ ሐጢአት አልሰራም (ሱራ
19፡19)
 ስለ አገልግሎቱ፡- ነብይ ስለሆነ እስልምናን ሰብኮአል (ሱራ 3፡84፤
19፡24-25)
 ተአምራት አድርጎአል (ሱራ 3፡49፤ 5፡110፤ 5፡112-115)
ሠ) በመጨረሻው ቀን ማመን
 አላህ የመጨረሻ ፍርድ ቀን ቀጥሮአል (ሱራ 75፡1-40)

 የፍርድ ሂደቱ በሦሥት የተከፈለ ነው፡-

ሀ) በቀብር ውስጥ

ለ) በማቆያ ስፍራ

ሐ) በመጨረሻው ቀን
 የመጨረሻ ቀን ምልክቶች፡- እምነት መቀነስ፤ አለማዊነት መብዛት፤
የጎግና ማጎግ መነሳት፤ መሐዲ መነሳት፤ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት
ረ) መጀመሪያ በተወሰነ እጣ ፈንታ ማመን
 አላህ መልካምንና ክፉውን በመጀመሪያ ወስኖአል
 የሰው ዕጣ ፈንታ ቀድሞ ተወስኖአል
 አላህ ለወደደው ምህረት ያደርጋል ያልወደደውን ይቀጣል
3. ሐይማኖታዊ ተግባራት በእስልምና

ማንኛውም ተግባር በአምስት ይከፈላል፡-

1) ግዴታ መፈጸም ያለባቸው ተግባራት (ፈርድ)

2) ግዴታ ያልሆኑ ነገር ግን ቢፈጸሙ ዋጋ ያላቸው (ሱና)

3) ቢፈጸሙ ጥቅምም ጉዳትም የሌላቸው (ሙባህ)

4) እንዲፈጸሙ የማይመከሩ ተግባራት (ማክሩህ)

5) ክልክል ተግባራት (ሐራም)


አምስቱ መፈጸም ያለባቸው ግዴታ ተግባራት

ሀ) ሸሐዳ
 የእስልምና የእምነት መግለጫ ሲሆን ማንኛውም ሙስሊም
የአላህን አንድነትና የመሐመድ ነብይነት መመስከር አለበት፡፡
 አንድ ሰው ወደ እስልምና መቀየሩ የሚገልጸው ሸሀዳ በማለት
ነው፡፡
 መንግስተ ሰማያት መግቢያ ቁለፍ ነው

 ደጋግሞ ሸሀዳ ማለት እንደ መልካም ስራ ይቆጠራል፡


ለ) ሰላት
ስለ ሰላት በሱራ 2፡43 ላይ ተጽፎአል፤

 ሰላት ደንቡ ተጠብቆ በቀን አምስት ጊዜ መሰገድ አለበት (ፈርጅ፤


ዙሁር፤ አስር፤ መግሪብ እና ኢሻ ናቸው)፤

 ከስግደት በፊት መጠበቅ ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አሉ


(መታጠብ፤ አለባበስ፤ የሰላት ሰአት፤ የሰላት ቦታ፤ የሰላት
አቅጠጫ፤ የስግደት ቅደም ተከተል)

 ለየት ያሉ የሰላት አይነቶች አሉ (የአርብ /ጁምአ ሰላት፤


በአስክሬን ላይ የሚሰገድ ሰላት፤ የኢድ ሰላቶች እና ሱና ሰላቶች)
ሐ) ዘካ
ስለ ዘካ በሱራ 2፡43 ተጽፎአል፤
 ዘካ ሙስሊሞች ከአመታዊ ገቢያቸው 2.5% ለድኃ እንዲሰጡ
የታዘዙት ኃይማኖታዊ ግዴታ ነው፤
 ዘካ ሰጪው ሙስሊመ፤ የአእምሮ በሽተኛ ያልሆነ፤ ባሪያ ያልሆነ፤
እንዲሁ ለአንድ አመት ራሱ የሆነ ንብረት ያለው መሆን አለበት፤
 ዘካ ተቀባዮች ድሆች፤ ዘካ የሚሰበስበው ሰው፤ አዳዲስ አማኞች፤
ከባርነት ነጻ መውጣት ለሚፈልጉ፤ብድር ያለባቸው፤ ለጅሀድ
ጦርነት ለመሳሪያ መግዘዣ እንዲውል፤ እና መንገደኞች ናቸው፡፡
መ) ሮመዳን ፆም
 በአረቦች የሮመዳን ወር ለ30 ቀናት የሚጾም ጾም ነው፤

 ከጸሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያ ሰአት ድረስ ይጾማል ነገር ግን


በማታ መብላትና መጠጣት ይፈቀዳል
 በዘህ ወር ለጸሎትና ለቁርአን ንባብ ትኩረት ይሰጣል፤

 ላለመጾም ፈቃድ ያላቸው - እርጉዞች፤ መንገደኞች፤ በሽተኞች፤


አጥቢ እናቶች፤ የወር አበባ የመጣባቸው ሴቶች፤ሽማግሌዎችና
አሮጊቶች፤ እና ህጻናትና ልጆች
 ሱና ጾሞችም አሉ- ለምሳሌ ሸዋል ጾም፤ አሹራ ጾም
ሠ) የሐጅ ጉዞ
 ማንኛውም ጤነኛና መካ ደርሶ ለመምጣት በቂ ገንዘብ ያለው ሰው
የሀጅ ጉዞ እንዲያደርግ ይገደዳል፤
 በሀጅ ጉዞ የተለያየየ ሀይማኖታዊ ስርአቶች ይፈጸማሉ፡ -
ለምሳሌ ሁሉም ወንዶች ተመሳሳይ ልብስ ይለብሳሉ፤ መታጠብ፤
ጸጉር መላጨት፤ በካባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ መዞር፤ በሶፋና መርዋ
ኮረብታዎች መካከል ጉዞ ማደረግ፤ በሚና ሸለቆ የእንስሳ
መስዋዕት ማቅረብ
4. ሙስሊሞች ስለ ሐጢአት እና ደህንነት ያላቸው እምነት
 የውርስ ሐጢአት የለም

 ሰው ደካማ ፍጥረት ስለሆነ ምሪት ያስፈልገዋል (ሱራ 4፡26-


28፣ 2፡37-38፤ 20፤122-123)
 አዳምና ሔዋን ሐጢአት ከሰሩ በኃላ ንስሐ ገብተዋል

 ሰው ሐጢአት የሚሰራው ማወቅ ከጀመረበት ጊዜ በኃላ ነው

 ሐጢአት መልካም ስራ በመስራት ሊፋቅ ይችላል

 ለሐጢአት ስርየት አዳኝ አያስፈልግም


ሐጢአት በሶስት ይከፈላል፡-
1. ትንሽ ሐጢአት
2. ትልቅ ሐጢአት
3. ይቅርታ የሌለው ሐጢአት
የደህንነት ትርጉሞች

1. ደህንነት (ነጃት)

2. ስኬት (ፈውዝ)

3. ብልጽግና (ፈላህ)

4. ደስታ (ሰአዳ)

ደህንነት

5. ከምድራዊ ችግሮች መዳን

6. ከዘላለም ቅጣት መዳን


ደህንነት በሶስት መንገዶች ሊገኝ ይችላል፡-

ሀ) ሰማዕት የሆኑ ሰዎች ያለ ጥያቄ ጀነት ይገባሉ፤

ለ) መልካም ስራ የሰሩ

ሐ) ከተወሰነ ቅጣት በኃላ በምህረት አሊያም ለወንጀላቸው


ተመጣጣኝ ቅጣት ከተቀጡ በኃላ ጀነት ይገባሉ
በምልጃ የሚድኑት

1. ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በመሐመድ አማላጅነት ያለፍርድ


በቀኝ በኩል በር ወደ ጀነት ይገባሉ

2. ከፍርድ በኃላ የተለያዩ ነብያትና ቅዱሳን በሚሰጡት


አገልግሎት ወደ ጀነት ይገባሉ

3. ብዙ ከመቃጠላቸው የተነሳ ከሰል ወደ መምሰል ከደረሱ


በኃላ በአማላጆች ጸሎት ወደ ጀነት ይገባሉ፡፡
5. የተለያዩ የሙስሊም አይነቶች
ሀ) ሱኒ ሙስሊሞች

 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ካሊፋቶችን የሚቀበሉ ናቸው

 ሀዲስና ቁርአን የእምነታቸው መሰረት አድርገው ይቀበላሉ

 ቁርአን የሚተረጉሙት ሙስሊም ሙሁራን ናቸው

 አራት የሱኒ ክፍሎች አሉ

 ሀነፊይ፡- የተመሰረተው በአቡ ሃኒፋ ሲሆን ግማሽ ያህሉን የሱኒ ሙስሊም ይይዛሉ፡፡

ከሌሎች እምነቶችም ጋር ተስማምተው ይኖራሉ፡፡ በግብጽ፤ በቱርክ፤ በመካከለኛው

እስያ፤ በሰሜን ህንድ፤ በኤርትራ በኢትዮጵያ ጠረፍ አከባቢዎች ይኖራሉ፡፡


 ማሊኪያህ፡- የተመሰረተው ማሊክ ኢብን አናስ በተባለ ሰው ነው፡፡ አጥባቂ

የሱኒ ቡድን ሲሆን ሸሪአ ህግን ለመመስረት ኢጅማ፤ ቁርአን እና ሀዲስ

ተጠቅመዋል፡፡ በምእራብና ሰሜን አፍሪካ፤ በምስራቅ አረቢያ፤ በኤራን፤

በኤርትራ፤ በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ አገሮች ይገኛሉ፡፡

 ሻፊኢያ፡-አል ሸፊኢያ በተባለ ሰው የተመሰረተ ሲሆን የለዘብተኛ ሀነፊይ

እና የወግ አጥባቂው ማሊኪይ መዝኸብ መካከለኛ እንዲሆን በማሰብ

የመሰረተው ነው፡፡ ይህ ቡድን በግብጽ፤ በሶማሊያ፤ በፍልስጢኤም፤

በምእራብና ደቡብ አረቢያ፤ በኢንዶኔዥያ፤ በህንድ እና በኢትዮጵያ አፋር ፤


ሐንበልያ፡- በአህመድ ኢብን ሐንበል የተመሰረተ ሲሆን በጣም
አክራሪ የሙሰሊመ ቡድን ነው፡፡ ከፍተኛ ትጽዕኖ እየፈጠረ ያለ
ቡድን ሲሆን የሸሪአ ህግ የመሰረቱት ቁርአንና ሀዲስን በመጠቀም
ነው፡፡ በብዛት የሚገኙት በመካከለኛ ምስራቅ እንዲሁም በአለም
ሁሉ ተሰራጭቶአል፡፡
ለ) ሺአ ሙስሊሞች
 ሺአ ማለት የአሊ ቡድኖች ማለት ነው፡፡

 ቁርአን መተርጎም ያለበት ኢማም ብቻ ነው፡፡

 ኢጅማን ይቃወማሉ፡፤

 ካሊፍ የሚመረጠው በአላህ ነው፡፡

 አንድ የቁርአን ክፍል ሁለት አይነት ትርጉም ሊኖረው ይችላል፡፡


 ሰው ነጻ ፈቃድ አለው እንጂ አላህ ሁሉንም ነገር ቀድሞ
አልወሰነም፡፡
 ግዚያዊ ጋብቻ ይፈቅዳሉ

 የቅዱሳን አምልኮ ያዘወትራሉ፡፡

 በአብዛኛው በኤራን፤ በኤራቅ ሲገኙ በሌሎች የመካከለኛ


ምስራቅ፤ በሰሜን አፍሪካና በእስያ አገሮች ይኖራሉ፡፡
ሐ) ሱፊ ሙስሊሞች
 በኢትዮጵያ በባሌና አርሲ በብዛት የሚገኙ ሲሆን ከሌሎች
ሙስሊሞች ይልቅ በመንፈሳዊ ልምምድ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡
 የመጀመሪያዎቹ ሱፊዎች መሐመድ፤ አቡበክርና አሊ እንደሆኑ
ያምናሉ፡፡
 ለተመስጦና ለጸሎት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡
 ነፍስ የስጋ እስረኛ ነው፤ ሞት ደግሞ ለነፍስ ነጻነትን ይሰጣል፡፡

 ከአላህ ጋር ለመገናኘት ረጅም ሰአት በተመስጦና በመዝሙር


መቆየት ያስፈልጋል፡፡
 የስጋ ፍላጎትን በመገደብና መንፈሳዊ ረሀብተኛ በመሆን ለአላህ
ፈቃድ በር መክፈት ያስፈልጋል፡፡
 ከአላህ ጋር ለመገናኘት የሱፊ መንፈሳዊ ጉዞ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡
መ) ባህላዊ ሙስሊሞች

 እምነታቸው መሰረት ያደረገው በቁርእን፤ በሀዲስ፤ ከእስልምና በፊት

በነበረው ባህላዊ እምነት እና በአከባቢያቸው ባለው ባህል ላይ ነው፡፡

 የእስልምናን እምነት የሚፈጽሙት ከክፉ መንፈስ ለመጠበቅ፤

ከበሽታ ፈውስ እና በረከት ለማግኘት ነው፡፡

 አለምን የሚያዩት በባህላዊ እምነት መነጽር ነው፡፡

 የቅዱሳን መቃብር ዘወትር ይጎበኛሉ፡፡


 ተህሊል የተባለ ቅዱስ ውኃ ይጠጣሉ፡፡

 የጅኒዎች ጥቃት አጥብቀው ይፈራሉ፡፡

 በጠላቶቻቸው ላይ አስማት ይሰራሉ፡፡

 ክፉ አይን ያላቸው ሰዎችን ይፈራሉ፡፡

 በዛር ወይም በክፉ መንፈስ የተያዘን ሰው የማወጣት ስራ ሼኮቻቸው


ይሰራሉ፡፡
 ህልም የአላህ ምሪት እንደሆነ ያምናሉ፡፡

 የሳምንቱ ቀናት ለቅዱሳን (አውሊያዎች) ከፋፍለው በመስጠት


ይዘክራሉ፡፡
ሠ) ወሀብያ (ሰለፊያ) ሙስሊሞች
 ይህ ቡድን የተመሰረተው አሕመድ ኢብን ሐንበል በተባለ ሰው በ9ኛው ከ/ዘመን

ሲሆን በ14ኘው ከ/ዘመን የኖረው ኢብን ታይሚያህ እና በ19ኛው ክ/ዘመን


የኖረው አብድል ወሐብ ይህንን አስተምህሮ እንዲቀጥል አድርገውታል፡፡

 ይህ ቡድን በ1803 የሳአውዲን መንግስት በኃይል በመገልበጥ የወሀቢ መንግስት

መስርቶአል፡፡ ከዚያ በኃላ ወደ አለም መስፋፋት ጀመረ፡፡

 ይህ ቡድን በቀድሞ የእስልምና አስተምህሮ ላይ የሚደረግን ማንኛውም አይነት

ጭማሪን የቃወማል፡፡

 ሙስሊሞች ወደ ቀድሞው እስልምና፤ ቁርአንና ሀዲስ እንዲመለሱ ጥሪ ያደርጋል፡፡


 የተሀድሶ እንቅስቃሴዎችን በሚቃወሙ ሙስሊሞችንና ሌሎች

አካላት ላይ ጥቃት እንዲፈጸምም ያዛል፡፡

 ማንኛውም ሙስሊም ቁርአንን መተርጎም ይችላል፡፡

 ለቅዱሳን የሚደረግ አምልኮን ይቃወማሉ፡፡

 የቅዱሳን መቃብር መጎብኘትም ይቃወማሉ፡፡

 በሙስሊሞች መከበር ያለባቸው በአላት ኢድ አለ-ፈጥር፤ ኢድ

አል-አድሃ፤ አል-ለይል አል-ሙባረክ ብቻ ናቸው፡፡

 ከቦታና ከእቃ ጋር የተያያዘ ቅድስናን ይቃወማሉ፡፡


ክፍል ሶስት
ወንጌል ለሙስሊሞች እንዴት እንመስክር?
1. የወንጌል ስርጭት እንቅፋቶችን መለየት

ሀ) ውስጣዊ እንቅፋቶች
- የጥላቻና የዘለፋ አቀራረብ

- ፍርሀት

- መሀመድና እስልምናን ማንቐሸሽ

- ስለእስልምና ግንዛቤ ማነስ

- ለሙስሊም ወንጌል ስርጭት ትኩረት አለመስጠት


ለ) ውጫዊ እንቅፋቶች
- ስነ-መለኮታዊ ልዩነቶች
- ጥላቻ
- የአክራሪነት ዝንባሌዎች
- ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ
- ማህበራዊ ተጽዕኖ
2. ወንጌልን በህይወትና በቃል እንመስክር
ሀ) የክርስቶስን ምሳሌያዊ ህይወት ማንፀባረቅ
(ፊል 2፡6-8)
- ትህትና
- ፍቅር
ለ) በሙሰሊሞች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ገጽታ ሊኖረን ይገባል
- አምልኮአችን

- ዝማሬውቻችን፤

- አለባበሳችን፤

- ንግግራችን፤

- አመለካከታችን
ሐ) ቐንቐቸውን ማወቅና መናገር
- ቐንቐቸው ስንናገር ለእነሱ ያለንን ክብር ማሳያ ሊሆን ይችላል

- በሚገባቸው መንገድ ለመናገር ይረዳል

- አንዳንድ በክርስትና ውስጥ የምንጠቀማቸው ቃላት በእስልምና


አምሳያ ቃላት ስላላቸው እነዚህን ቃላት መጠቀም አለብን
- ቃላቶቹን ክርስቲያናዊ ትርጉም በመስጠት ለሙስሊሞች
ማስረዳት ይኖርብናል
መ) ተቀባይነት ያለው ማህበራዊ ሕይወት ሊኖረን
ይገባል
- ወንድ ከሴት ጋር የሚኖርን ግንኙነትን በተመለከተ
- እንግድነትን መቀበል በተመለከተ
- በችግራቸው ቀን መርዳት
- መልካም የቤተሰብ ህይወትን በመምራት

- ወጋቸውና ልማዳችውን ማክበር (ለቅዱሳን

መጻህፍት አክብሮት መስጠት፤ በግራ እጅ

አለመብላት፤ ሼኮችና የማህበረሰብ መሪዎችን

ማክበር)

- በህመማቸው ወቅት መጎብኘትና መጸለይ


ሠ) ጓደኝነት መመስረት
- መተማመንን ይፈጥራል
- መቀራረብን ያጠናክራል
- መደጋገፍን ያጠናክራል
- የውይይት በሮችን ይከፍታል
ሠ) ለሐይማኖታዊ ጭውውት አመቺ ቦታና ጊዜ ምረጡ
- ጊዜ ካለመምረጥ የተነሳ ሰዎች ላያዳምጡን ይችላሉ

- ሻይ እየጠጣችሁ

- የቦታ መረጣ ለምስክርነት በጣም አስፈላጊ ነው፤

ለምሳሌ፡- ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ፤ በጉድጋድ አጠገብ ከሳምራዊተ


ሴት ጋር፤ ከኢማኦስ መንገደኞች ጋር የነበረው ውይይት

ረ) እግዚአብሄር በልባቸው ባስቀመጠው እውነት ላይ መገንባት


አለብን (ሮሜ 2፡15፤ ሐዋ 17፡22-34)
- ስለ እግዚአብሄር ማንነትና ስራዎቹ

- ስለነብያት

- ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት

- ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ስራዎቹ

- ስለ ሐጢአት

- ስለፍርድ ቀን
ሰ) አውዳዊ አገልግሎት ማገልገል (1ኛ ቆሮ 9፡19-23)
- መልዕክቱን አውዳዊ ማድረግ

- መልዕክተኛውን አውዳዊ ማድረግ

- ማስተላለፊያ መንገዱን አውዳዊ ማድረግ

ሸ) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን በቅደም ተከተል ማስተማር


- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን

- ስነ-መለኮታዊ አስተምህሮችን

- እነዚህ ሐሳቦች ከቁርአን ጋር በንጽጽር አስተምራቸው


ቀ) የራሳችሁን የህይወት ምስክርነት እና ባህላዊ ታሪኮችን
በመጠቀም መስክሩ
- ኢየሱስ ምሳሌዎችን ይጠቀም ነበር፡- ለምሳሌ ስለ ሐብታሙ
ሰውና አላዛር (ሉቃ 16፡19-31)
- ምሳሌዎቹና ምስክርነታችሁ የምትመሰክሩላቸው ሰዎችን ችግርና
ጥያቄ ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት
በ) በልግስና ስራዎች አማካይነት መስክሩ

- በግል በምታደርጉት ቸርነት (በሰርግ፤ በሐዘን እና በተለያዩ


የችግርና የደስታ ግዜያት)

- በቡድን በምታደርጉት ቸርነት (እስረኞችን በመጠየቅ፤ ት/ት


ቤቶችን በመገንባት እና የተቸገሩትን አረጋዊያን በመርዳት)
ደቀመዝሙር ማድረግ
በደቀመዝሙርነት ሂደት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች

1. በእስልምናና በክርስትና መካከል ያሉ ስነ-መለኮታዊ ልዩነቶች

2. የባህል ልዩነቶች (አለባበስ፤ ምግብ፤ ባህል)

3. የክርስቲያን ማህበረሰብ አዳዲስ አማኞች ተገቢውን ማህበራዊና


ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ አለማድረግ

4. ስደትና የሐይማኖት ነጻነት ማጣት


5. ጌታን እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ምክንያት ተግዳሮት ሊሆን
የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል (ገንዘብ/ትዳር፤ በረከት፤
ህብረት/አዲስ ማህበረሰብ)
6. ቅይጥነት (መሐመድ/ኢየሱስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ/ቁርአን . . .)
7. በገንዘብ ፍቅር መጠመድ
መፍትሄዎች

1. የአዲስ አማኞችን ሀይማኖታዊና ባህላዊ አውድ መረዳት

2. የአማኞችን ማህበራዊ አውድ መረዳት

3. የአማኞችን እሴትና ንጽረተ አለም መረዳት

4. መንፈሳዊ ውጊያን መከላከል እንዲችሉ በእግዚአብሄር ላይ እንዲደገፉ


ማስተማርና በጸሎት መደገፍ፡፡

5. አዳዲስ አማኞች ብቸኝነት ስለሚሰማቸው፤ ስለወደፊት ህይወታቸው እርግጠኛ


ስለማይሆኑ፤ በክርስቲያን ማህበረሰብ ተቀባይነት እንዳላገኙ ስለማያስቡ ስነ-
6. ስነ-መለኮታዊ ጥያቄያቸውን ተገቢ በሆነ መንገድ መመለስ፤

7. በትዳር ህይወታቸው ውስጥ ያሉ ችግሮች ካሉ ማማከርና


ከችግራቸው እንዲወጡ መርዳት

8. የኢኮኖሚ ችግር ካጋጠማቸው ድጋፍ ማድረግ

9. የማንነት ቀውስ እንዳይገጥማቸው መስራት

10. በስደት ውስጥ ጸንተው እንዲቆሙ ማበረታታት

11. የእግዚአብሄር ቃል በተከታታይ ማስተማር


3. የሙስሊሞችን ጥያቄዎች እንዴት እንመልስ?

1ኛ ጴጥ 3፡15 እንዲህ ይላል፡- “በእናንተ ስላለ ተስፋ


ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር
የተዘጋጃችሁ ሁኑ”
መጽሐፍ ቅዱስ

1. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ቃል ነውን?


 የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት፡-

እንዴት እንደተገለጠ፡- 2ኛ ጴጥ 1፡20-21

አላማውም፡- 2ኛ ጢሞ 3፡16
 ቁርአን ምስክርነት ይሰጣል፡-

ሱራ 5፡44 - ተውራት መመሪያና ብርሃን ያለበት


መጽሐፍ ነው
ሱራ 5፡46 - ኢንጂል መመሪያና ብርሃን ያለበት
መጽሐፍ ነው
 ሌሎች የቁርአን ክፍሎች ምስክርነት፡- ሱራ 3፡3፤
2፡136፤ 4፡136፤ 4፡163
2. መጽሐፍ ቅዱስ ተበላሸቶአልን?
 የቁርአን ምስክርነት፡-

ሱራ 22፡52፡- መጽሐፍ ቅዱስን ከስህተት የሚጠብቀው


አላህ ራሱ ነው
ሱራ 4፡46፤ 2፡75፡- መጽሐፉ አይሁዶችና ክርስቲያኖች
ያበላሹት በጽሑፍ ደረጃ ሳይሆን በምላሶቻቸው ያጣምማሉ
 ታሪካዊ መረጃዎች፡- ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች

1. የአሌክሳንደሪያ ጽሑፍ (Codex Alexandrinus) -

በ5ኛው ክ/ዘመን የተጻፈ ነው፡፡

2. የሲናይቲከስ ጽሑፍ (Codex Sinaiticus)፡- በ4ኛው

ክ/ዘመን የተጻፈ ነው፡፡

3. የቫቲካን ጽሑፍ (Codex Vaticanus)፡- ከሁለቱ

ጽሁፎች ቀደምትነት ያለው ሲሆን በሮም ቫቲካን ላይብረሪ ይገኛል፡፡


4. የእብራይስጥ ማዞራይቲከ መጽሐፍ (Hebrew

Massoretic Text)፡- ከክርስቶስ ልደት በፊት


በእብራይስጥ ቐንቐ የተጻፈ ነው

5. የሙት ባህር ጥቅልል (Dead Sea scroll)፡-


በሙት ባህር አከባቢ በቁፋሮ የተገኘ መጽሐፍ ነው
6. ስፕቱጅንት (Septuagint)፡- ከእብራይስጥ ወደ ግሪክ
የተተረጎመ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ነው
7. የላቲን ቩልጌት (Latin Vulgate)፡- በ4ኛው ክ/ዘመን
ወደ ላቲን የተተረጎም መጽሐፍ ቅዱሰ ነው፡፡
3. ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሌሎች ተቃውሞዎች፡-
ሀ) ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መጻሕፍት ስላሉ የተለያየ
መልዕክት ያስተላልፋሉ?
ለ) መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ሳይሆን ሶስት አይነት
ንግግሮችን የያዘ ነው
ሐ) አሳፋሪ ታሪኮች የያዘ ነው
4. መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫልን?

መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ አይጋጭም፡፡ ነገር ግን ሰዎች መጽሐፍ


ቅዱስ እርስ በርሱ የሚጋጭ የሚመሰላቸው፡-

ሀ) የመጽሐፍ ቅዱስ አውድ ባለመረዳት

ለምሳሌ፡- ዮሐ 5፡31 እና ዮሐ 8፡14 - የኢየሱስ


ምስክርነት እውነት ነው ወይስ አይደለም?
ለ) ስዕላዊ አገላለጾችን ቀጥተኛ ትርጉም ስንሰጥ መጽሐፍ ቅዱስ

እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሊመስለን ይችላል

- ኢሳ 54፡5 - ፈጣሪሽ ባልሽ ነው

- ኢሳ 7፡20 - ከወንሱ ማዶ በተከራየው ምላጭ

ሐ) የደራሲው/የጸሐፊው እይታ አለመረዳት

- ማቴ 27፡5 - ይሁዳ ታንቆ ሞተ

- ሐዋ 1፡18 - በግንባሩ ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ …


መ) ተመሳሳይ ቃላት እንደአውዳቸው መተርጎም ይኖርባቸዋል

- ሰማይ የሚለው ቃል - ማቴ 3፡1 እና ዮሐ 3፡13

- ልጅ የሚለው ቃል - ዮሐ 3፡16 ፤ 1፡12 ፤ ዘፍ 22፡1-

መለኮታዊ ልጅ፤ ሰብአዊ ልጅ እና መንፈሳዊ ልጅ

You might also like