0% found this document useful (0 votes)
107 views71 pages

ADSWE New 4th Round Collective Agreement

ADSWE agreement

Uploaded by

abinet mengistu
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd
0% found this document useful (0 votes)
107 views71 pages

ADSWE New 4th Round Collective Agreement

ADSWE agreement

Uploaded by

abinet mengistu
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd

ማውጫ

መግቢያ ............................................................................................................................................. 1

ክፍል አንድ ጠቅላላ ........................................................................................................................... 1

አንቀጽ አንድ (1) የኀብረት ስምምነቱ ዓላማ ...................................................................................... 1

አንቀጽ ሁለት (2) አጭር ርዕስ........................................................................................................... 2

አንቀጽ ሶስት (3) የቃላት ትርጓሜ ..................................................................................................... 2

አንቀጽ አራት (4) በህብረት ስምምነቱና አግባብ ባላቸው ህጎች መሀል ያለው ግንኙነት ....................... 5

አንቀጽ አምስት (5) የሕብረት ስምምነት ሕጋዊነትና የተፈፃሚነት ወሰን ............................................ 5

አንቀጽ ስድስት (6) የድርጅቱ መብትና ግዴታዎች ............................................................................ 6

አንቀጽ ሰባት (7) የማህበሩ መብቶችና ግዴታዎች .............................................................................. 9

አንቀጽ ስምንት (8) የሰራተኛ መብትና ግዴታዎች........................................................................... 11

ክፍል ሁለት ..................................................................................................................................... 15

አንቀጽ ዘጠኝ (9) ቅጥር፣ ምደባ፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ ትምህርትና ስልጠና .............................. 15

አንቀጽ አስር (10) የሥራ መታወቂያ ደብተር .................................................................................. 22

አንቀፅ አስራ አንድ (11) የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሁኔታ ............................................................... 23

ክፍል ሦስት ..................................................................................................................................... 24

አንቀጽ አሥራ ሁለት (12) ስለ መደበኛ የሥራ ሰዓት ...................................................................... 24

አንቀጽ አሥራ ሶስት (13) የትርፍ ሰዓት የሥራ ክፍያ ..................................................................... 25

አንቀጽ አሥራ አራት (14) የሕዝብ በዓላት ...................................................................................... 25

አንቀጽ አሥራ አምስት (15) ልዩ ልዩ ፈቃዶች ................................................................................ 25

አንቀጽ አስራ ስድስት (16) ደመወዝና የደመወዝ ብድር ................................................................... 32

አንቀጽ አስራ ሰባት (17) የደመወዝ ጭማሪና ጉርሻ (ቦነስ) ............................................................... 32

አንቀጽ አሰራ ስምንት


ስምንት (18) የደመወዝ እርከን ጭማሪ እና የቦነስ አሰጣጥ.......................................... 33

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ (19) ልዩ ልዩ አበል ......................................................................................... 35

አንቀጽ ሃያ (20) ሕክምና መድህንና ጡረታ ..................................................................................... 38

አንቀጽ ሃያ አንድ (21) የማህበራዊ ጉዳዮች ...................................................................................... 41


i
አንቀጽ ሃያ ሁለት (22) ትራንስፖርትና መጓጓዣ ............................................................................. 42

አንቀጽ ሃያ ሶስት (23) የመስክ አገልግሎት ...................................................................................... 43

ክፍል አራት..................................................................................................................................... 44

አንቀጽ ሃያ አራት (24) የዲስፕሊን የእርምጃ አወሳሰድ ሥነ-ሥርዓት ............................................... 44

አንቀጽ ሀያ አምስት (25)


(25) የሥራ ውል ስለማቋረጥ ............................................................................ 47

አንቀጽ ሀያ ስድስት (26) የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ወይም በማስጠንቀቂያ ከሚያቋርጡ የዲስፕሊን


ጥፋቶች በስተቀር ሌሎች ጥፋቶች ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ .... 50

አንቀጽ ሃያ ሰባት (27) የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያዎች ............................................................ 56

አንቀጽ ሀያ ስምንት (28) የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓትና የሥራ ክርክር ...................................... 64

አንቀጽ ሀያ ዘጠኝ (29) የሥራ ውጤት ምዘና ................................................................................... 65

አንቀጽ ሰላሳ (30) ሰራተኛ በተወሰነ ጊዜ/ ሥራ (ኮንትራት) ስለመቅጠር ........................................... 67

አንቀጽ ሰላሳ አንድ (31) ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ............................................................................... 67

አንቀጽ ሠላሳ ሁለት (32) ማሻሻልና ማደስ....................................................................................... 68

ክፍል አምስት .................................................................................................................................. 68

አንቀጽ ሰላሳ ሶስት (33) ኃላፊነትና የስምምነቱ ተፈፃሚነት .............................................................. 68

ii
መግቢያ
አማራ የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት በአማራ ብሄራዊ ክልል የመንግስት ልማት
ድርጅቶች አመሰራረት፣ አደረጃጀት፣ አመራርና ድጋፍ አሰጣጥን ለማቋቋም በወጣ አዋጅ ቁጥር
236/2008 ዓ.ም አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) መሰረት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
መስተዳድር ምክር ቤት መጋቢት 22 ቀን 2010 ዓ.ም ባወጣው ደንብ ቁጥር 161/2010 ዓ.ም
እንደገና የተቋቋመ መንግስታዊ የልማት ድርጅት ነው፡፡

በመሆኑም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 "አሰሪ" እየተባለ በሚጠራው
በአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት እና "የሠራተኛ ማኀበር" ወይም “ማህበር” ተብሎ
በሚጠራው የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት መሰረታዊ የሠራተኛ ማኀበር
መካከል ይህ አራተኛ (4ኛ) ዙር የኀብረት ስምምነት ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈረመ፡፡

ክፍል አንድ ጠቅላላ


አንቀጽ አንድ (1) የኀብረት ስምምነቱ ዓላማ
1.1 የድርጅቱንና የሠራተኛውን ደህንነት፣ ሰብዓዊ ከብርና ህልውና ለማስጠበቅ፣ ለማጠናከርና
ለማሳደግ እንዲሁም ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማ ግቡን እንዲመታ ለማድረግ፣
1.2 አገሪቱ አሁን እያራመደች ካለችበት የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንፃር በነፃ ገበያው ብቁ ተወዳዳሪ
በመሆን የሰራተኛውን የስራ ዋስትና በዘላቂነት እንዲከበር ማስቻል፣
1.3 በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጁ በህብረት ስምምነት እንዲወሰኑ የተባሉ ጉዳዮችን በህብረት
ስምምነቱ ሽፋን እንዲያኙ ለማድረግና በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያለው የሥራ
ግንኙነታችን ዘርዘር ብለው በተቀመጡ መብቶችና ግዴታዎች ላይ እንዲመሰረት
በማድረግ በድርጅቱ ውስጥ ኢንዱስትሪ ሰላም ለማስፈን፣
1.4 የሰራተኛው ተጠቃሚነት በድርጅቱ ትርፋማነትና ደህንነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን
በመረዳት ሰራተኛው በመልካም ስነምግባር ታንፆ የድርጅቱን ሀብትና ንብረት እንደራሱ
ንብረት ተገንዘቦ ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ በማድረግ ድርጅቱን በዘላቂነት ትርፋማ
ለማድረግ፣
1.5 ሰራተኞች ሙሉ አቅማቸውንና ችሎታቸውን አሟጠው ለመጠቀም እንዲችሉ የሰራተኞችን
አቅምና የስራ ተነሳሽነት በማሳደግ የድርጅቱን የምርታማነት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ
በመጨመርና የድርጅቱን ትርፋማነት ከፍ በማድረግ በውጤቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ለማስቻል፡፡

1
አንቀጽ ሁለት (2) አጭር ርዕስ
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር ይህ የህብረት ስምምነት ‹‹አራተኛው
(4ተኛው) የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅትና የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች
ድርጅት መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የህብረት ስምምነት›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

አንቀጽ ሶስት (3) የቃላት ትርጓሜ


የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ፡-
3.1 "አዋጅ" ማለት የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ነው፡፡
3.2 “ድርጅት” ማለት በአማራ ብሄራዊ ክልል ዝክረ ሕግ ደንብ ቁጥር 161/2010 ተሻሽሎ
የተቋቋመ አማራ የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት ነው።
3.3 "ማኀበር" ወይም "የሰራተኛ ማኀበር" ማለት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀጽ 113 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 (ሀ) መሰረት የተቋቋመ አማራ የዲዛይንና
ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት መሠረታዊ የሠራተኞች ማኀበር ነው፡፡
3.4 “አሰሪ” ማለት በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 1
ላይ የተገለፀው ትርጉም ይኖረዋል፡፡
3.5 “የሥራ መሪ” ማለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የተደነገገው
ትርጉም የሚኖረው ሆኖ በድርጅቱ ተጨባጭ ሁኔታ የድርጅቱን ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ ሥራ
አስፈፃሚዎች፣ ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑና የማኔጅመንት
አባል የሆኑ ኃላፊዎችን፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆችና ዘርፍ ሀላፊዎች እንዲሁም
የሰው ሀብት አስተዳደር ሀላፊዎችንና የከፍተኛ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጆችን የሚጨምር
ይሆናል፡፡
3.6 “ሠራተኛ” ማለት በኢፌዴሪ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2
ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል፡፡ ነገር ግን በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ
አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 10 የተመለከቱትን የስራ መሪዎች
አያካትትም፡፡
3.7 “የዲስኘሊን ቅጣት/ እርምጃ” ማለት አንድ ሠራተኛ የሕብረት ስምምነቱን፣ የአዋጁንና
የድርጅቱን ደንብና መመሪያ በመተላለፉ ለፈፀመው ጥፋት የሚወሰንበት ቅጣት ነው፡፡
3.8 “ውሎ አበል” ማለት አንድ ሠራተኛ ለሥራ ጉዳይ ከምድብ የሥራ ቦታው የውሉ አበል
በሚያስከፍል ሌላ ቦታ ስራ እንዲሰራ ታዞ በሚሰራበት ወቅት ወይም ከስራ ባህሪው አኳያ

2
ታይቶ በልዩ ሁኔታ በሚወሰነው መሰረት በእየለቱ ለቁርስ፣ ለምሣ፣ ለእራትና ለመኝታ
እንደቆይታው የሚከፈለው ክፍያ ነው፡፡
3.9 “ቤተሰብ” ማለት የሠራተኛው/ዋ ሕጋዊ ሚስት/ ባል፣ ልጆች፣ እናት፣ አባት፣ ወንድምና
እህት፣ አክስት፣ አጎት የሆነ የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ ማለት ነው፡፡
3.10 “ማስጠንቀቂያ” ማለት ለአንድ ሠራተኛ የቅርብ ሀላፊው ወይም የበላይ ሀላፊው የጥፋቱን
ዓይነትና አድራጎት እንዲሁም የደንቡን አንቀጾች ጠቅሶ ጥፋቱ እንዳይደገም በቃል
ወይም በጽሑፍ የሚሰጥ ተግሳጽ ነው፡፡ በቃል የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ በፁሑፍ
የሚገለፀ ይሆናል፡፡
3.11 “የሕክምና ፈቃድ” ማለት በመንግስት ህጋዊ ዕውቅና ከተሰጣቸው ከግልም ሆነ
ከመንግስት የሕክምና ተቋማት የሚገኝ በፁሁፍ የተረጋገጠ የህመም ፈቃድ ነው።
3.12 “የደመወዝ እርከን ጭማሪ” ማለት በድርጅቱ ውስጥ ቢያንስ ለአስራ ሁለት ተከታታይ
ወራት ላገለገሉ ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) እና ለተወሰነ ጊዜ/ ስራ (ኮንትራት) ሰራተኞች
በየበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሀምሌ ወር ጀምሮ የደረጃ ለውጥ ሳይኖር በያዙት የደመወዝ
ደረጃ ከፍታ የድርጅቱን ትርፋማነት መሰረት አድርጎ በሚወሰነው መሰረት ወደ ጎን
እርከን ከደመወዛቸው ላይ የሚጨመር የደመወዝ እርከን ጭማሪ ነው፡፡
3.13 “የትርፍ ስዓት ስራ” ማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጁና በዚህ የህብረት ስምምነት
ከተወሰነው የቀኑ መደበኛ የሰራ ስዓት በላይ የሚሰራ ስራ የትርፍ ስዓት ስራ ነው፡፡
3.14 “የሥራ” ወይም “የደንብ ልብስ” ማለት አንድ ሰራተኛ ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ
እንደ ሰራው ፀባይ ለስራው ማከናወኛ ወይም ለሰራተኛው ደህነነትና ንፅህና
እንዲያገለግል የሚሰጥ ልብስ፣ ጫማ ወይም ሌላ ለስራ ሲባል የሚሰጥ የስራ መገልገያ
መሳሪያ ነው፡፡
3.15 “የአደጋ መከላኪያ መሳሪያ” ማለት የድርጅቱን ንብረትና ሰራተኛውን ከአደጋ ለመከላከል
የሚሰጥ ወይም የሚተከል ወይም የሚቀመጥ የመከላከያ መሳሪያ ነው፡፡
3.16 “ቅሬታ” ማለት በዚህ ስምምነት ወይም በህግ ትርጉም ወይም አፈፃፀም ችግር ምክንያት
በድርጅቱና በሰራተኛው ወይም በድርጅቱና በማህበሩ መካከል በሚፈጠረው
አለመግባባት ጉዳይ ለሚመለከተው አካል የሚቀርብ አቤቱታ ማለት ነው፡፡
3.17 “የሰራተኛ ተጠሪ” ማለት የማህበሩ የስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴና በቅሬታ አቀራረብ ስነ
ስርዓት ውስጥ ለተጠቀሰው በማንኛውም ደረጃ ሰራተኛውን በመወከል ጉዳዩን
ለመከታተል ወይም ከሰራተኛው ጋር ለመመካከር እንዲችሉ ኮሚቴው የሚወክላቸው
ሰራተኞች ወይም ሌሎች ህጋዊ ውክልና ያላቸው ናቸው፡፡

3
3.18 “የደረጃ ዕድገት” ማለት አንድን ሰራተኛ ከነበረበት የስራ ደረጃና ደመወዝ ወደ ተሻለ
የስራ ደረጃና ደመወዝ ከፍ አድርጎ ማሳደግ ወይም መመደብ ማለት ነው፡፡
3.19 “የስራ መደብ” ማለት በድርጅቱ አደረጃጀት የተካተተና በአዋጅ ቀጥር 1156/2011
አንቀፅ 9 እና 10 በተገለፀው መሰረት በተደረገ የስራ ውል ሰራተኛ የተቀጠረበት ወይም
የተመደበበት ወይም የሚቀጠረበት የስራ መደብ ነው፡፡
3.20 “ተዋዋዩች” ማለት በዚህ የህብረት ስምምነት ላይ የተደራደሩና ስምምነታቸውን
በፊርማቸው ያረጋገጡ የድርጅቱና የማህበሩ ተወካዮች ማለት ነው፡፡
3.21 “የአስተዳደር ኮሚቴዎች” ማለት ለደረጃ ዕድገት፣ ለቅጥር፣ ለትምህርት፣ ለዲስኘሊንና
የመሳሰሉ መታየት ያለባቸውን አስተዳደር ነክ ጉዳዩችን ተመልክተው የውሳኔ ሀሳብ
ለማቅረብ ከድርጅቱና ከሰራተኛው ወገን ተመርጠው የሚሰሩ የተለያዩ ኮሚቴዎች
ናቸው፡፡
3.22 “ዝውውር” ማለት ከአንድ የስራ መደብ ወደ ሌላ ይሰሩበታል ተብሎ በሚታመንበት የስራ
መደብ ወይም ከአንድ የስራ ቦታ ወደ ሌላ የስራ ቦታ ተመሳሳይ መነሻ ደመወዝና ደረጃ
(ደመወዝ ደረጃ ከፍታ) ባላቸው እንዲሁም ተመሳሳይ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ
በሚጠይቁ የሰራ መደቦች ላይ የሚፈፀም ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ዝውውር ነው፡፡
3.23 “ትምህርት” ማለት ለድርጅቱ የስራ ዕድገት በማሰብ ሰራተኛው ችሎታውንና ዕውቀቱን
በማሻሻል የተሟላና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችል ሲባል በሀገር ውስጥም ሆነ
ከሀገር ውጭ የሚሰጥ ነው፡፡
3.24 “ቦነስ” ማለት ድርጅቱ በአንድ በጀት ዓመት ካገኘው ትርፍ አንጻር እየታየ እያንዳንዱ
የድርጅቱ ሰራተኛ ባስገኘው የስራ አፈጻጸም ውጤትና የስራ ላይ ቆይታ ጊዜ አንጻር
እየተመዘነ፣ ወደፊት ለድርጅቱ የላቀ ትጋት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ለሰራተኛው
ሊከፈል የሚችል ጉርሻ /bonus/ ነው፡፡
3.25 "ደመወዝ" ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው
ትርጉም ይኖረዋል፡፡
3.26 "የአየር ፀባይ አበል" ማለት አንድ ሠራተኛ በተመደበበት የሥራ ቦታ ያለው የአየር
ፀባይ ለመኖር አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በመንግሥት በረሀ/ ቆላ ተብለው ተለይተው
በሚታወቁ ቦታዎች ተመድቦ ለሚሰራ ሰራተኛ ከሚከፈለው የወር ደመወዝ ወይም የቀን
ውሎ አበል ተመን ላይ በተጨማሪ የሚከፈል የማካካሻ ክፍያ ነው፡፡

4
3.27 ’’ተጠባባቂ’’ ማለት በአንድ በተለያዩ ምክንያቶች ክፍት የሆነ የሥራ መደብ ሲፈጠር
በቦታው ላይ በቋሚነት ሰው እስኪመደብ ድረስ የግድ ስራው መሰራት ስላለበት
በጊዜያዊነት ቦታውን ሸፍኖ የሚሰራ ሰራተኛ ነው፡፡
3.28 ’’ተወካይ’’ ማለት አንድ ሰራተኛ/ የስራ መሪ በተለያዩ ምክንያቶች ለተወሰነ ጊዜ ከስራው
ሲለይ በምትኩ የስራ መደቡን በመወከል ከያዘው ስራ ጋር ደርቦ እንዲሰራ አግባብ ባለው
አካል የሚመደብ ሰራተኛ ነው፡፡
3.29 በዚህ ኅብረት ስምምነት አደጋ የሚለው ቃል ድርጅቱ በገባው የኢንሹራንስ ፖሊሲ
መሠረት በአንድ ሰው ላይ ሳይፈቅደውና ሳይፈልገው የሚደርስበት ድንገተኛ የአካል
ጉዳት ወይም ሞት ነው፡፡
3.30 ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለፀው የሴትንም ጾታ ይጨምራል፡፡

አንቀጽ አራት (4) በህብረት ስምምነቱና አግባብ ባላቸው ህጎች


መሀል ያለው ግንኙነት
4.1. ስምምነቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እንዲሁም አግባብ ባላቸው
ሌሎች ህጎች በድርጅቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ በተዋዋያዮች
ላይ እንደ ሕግ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
4.2. ስምምነቱ መንግስት ካወጣቸው አግባብ ባላቸው ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም
ወደፊት ከሚወጡ አግባብ ባላቸው ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በሚጣጣም ሁኔታ
እየተተረጎመ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
4.3. በዚህ ህብረት ስምምነት ያልተጠቃለሉ ጉዳዮች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አሰሪና ሰራተኛን በተመለከተ ስራ ላይ ባሉና ወደፊት በሚወጡ የድርጅቱና
አግባብ ያላቸው የመንግስት ህጎችና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎች የሚሸፈኑ ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ አምስት (5) የሕብረት ስምምነት ሕጋዊነትና የተፈፃሚነት ወሰን


ይህ የህብረት ስምምነት በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ተፈፃነት ያለው ሲሆን የስራ መሪዎችንና
በቀን ሂሳብ ተከፋይ የሆኑ ሰራተኞችን አይመለከትም፡፡

5
አንቀጽ ስድስት (6) የድርጅቱ መብትና ግዴታዎች
6.1. የድርጅቱ መብቶች
ድርጅቱ ይህንን የህብረት ስምምነትና አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ
የተደነገጉትን ሳይቃረን የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡፡
6.1.1. በስራ ውል መሰረት የሰራተኛውን የስራ እንቅስቃሴና ክንውን የመምራት የማስተዳደርና
የመቆጣጠር፣
6.1.2. የድርጅቱን የስራ ፕሮግራም በማዘጋጀት የአሰራር ስልቶችን፣ መመሪዎችንና ደንቦችን
የማውጣት፣ የመፈፀም፣ የማስፈፀም፣
6.1.3. ሰራተኛን የመቅጠር፣ በስራ ደረጃ የማሳደግ፣ ጥፋት ሲኖር ከስራ ደረጃ ዝቅ ማድረግ፣
የማዛወር፣ የዲስፕሊን እርምጃ የመውሰድ፣ የማገድ፣ የማሰናበት፣
6.1.4. የስራ ደረጃዎችን ማውጣት፣ ማሻሻል፣ መለወጥ፣ መሰረዝ፣ የስራ ውክልና መሰጠት
እንዲሁም የደመወዝ ተመን ወይም ሌላ ክፍያ መወሰን፣
6.1.5. ለድርጅቱ ጥቅም ሲባል ያሉትን ሠራተኞች የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅን እንዲሁም
ሌሎች አግባብ ያላቸውን ህጎችና ይህን የህብረት ስምምነት በማይቃረን ሁኔታ እየሰሩ
ካሉበት ሥራ በሌላ ሥራ ላይ ለማሠራት ወይም ካሉበት የስራ ቦታ ወደ ሌላ የስራ ቦታ
አዛውሮ ማሰራት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አዛውሮ ማሠራት ይችላል። የተዛወረው
ሠራተኛም ቀደም ሲል የተመደበበትን የሥራ ደረጃና ደመወዝ እንዲሁም በተዛወረበት
የስራ መደብ የሚገኝ ጥቅም ካለ ያገኛል። ይሁን እንጂ ከሙያው ጋር ባልተዛመደ
ሁኔታ ሠራተኛን አያሰራም።
6.1.6. በኦዲት የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ወይም የንብረት ጉድለት ወይም ማናቸውም
ከሰራተኛው የሚጠየቅ የድርጅቱ ገንዘብ ካለ ሌሎች እርምጃዎችና የድርጅቱ ፋይናንስ
አሰራር እንደተጠበቁ ሆነው ከሰራተኛው ደመወዝ ከ1/3ኛ ያልበለጠውን በቀጥታ
በመቀነስ ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ ይችላል፡፡
6.1.7. ያለአግባብ የደመወዝ፣ አበልና ጥቅማጥቅም ብልጫ ጭማሪ የተሰጠው ሠራተኛ
ሲያጋጥም የተሰጠውን ብልጫ ጭማሪ በየወሩ ከደመወዙ 1/3 እየቀነሰ ገቢ የማስደረግ
መብት አለው ፡፡
6.1.8. በሀኪም ቦርድ የቦታ ለውጥ የታዘዘለት ሠራተኛ ሊሰራ ወደሚችልበት ሌላ ቦታ ወስዶ
በዝቅተኛም ሆነ በተመሳሳይ የስራ መደብ አሰማርቶ የማሰራት መብት አለው፡፡
የሚመደብበት ቦታ ከጠፋ አስተያየት ጠይቆ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ይችላል፡፡
በሰራተኛው ላይ የተከሰተው የጤና ሁኔታ ታይቶ ከአንድ ዓመት በኋላ ምርመራ
6
እንዲያካሂድ ተደርጎ የጤናውን ሁኔታ ያገናዘበ ማስረጃ ሲቀርብ እንደገና የሚታይና
ምደባ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
6.1.9. ድርጅቱ የሰራተኛውን የሙያ ፈቃድ ለመጠቀም ሲፈልገው የመጠቀም መብት አለው፤፤

6.2. የድርጅቱ ግዴታዎች


ድርጅቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 12 ከንዑስ አንቀጽ 1-12
እና አንቀጽ 92 ከንዑስ አንቀጽ 1-8 እንዲሁም አግባብነት ባላቸው ህጉች ከተጠቀሱት
ግዴታዎች በተጨማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡
6.2.1. ስለ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ የወጡትን አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪዎችን ይህንን የህብረት
ስምምነትና በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ወደፊት የሚወጡ ማሻሻያዎችን ያከብራል፣
ተግባራዊም ያደርጋል፡፡
6.2.2. ሠራተኛው በሥራ ላይ አደጋ ወይም የጤንነት ጉድለት እንዳይደርስበት ተገቢውን
ጥንቃቄ ያደርጋል። የአደጋ መከላከያ ያቀርባል ወይም ያዘጋጃል።
6.2.3. ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ በአንድ የበጀት ዓመት የሚሰጠው የሥራ ወይም የደንብ ልብሶች
ቁጥር ከአንድ በላይ ከሆነ፡-
ሀ/ የመጀመሪውን የበጀት ዓመቱ በገባ በ3ኛው ወር ማለትም በመስከረም ወር ላይ፣
ለ/ ሁለተኛውን ደግሞ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ የመጀመሪያው ወር ማለትም በጥር
ወር ላይ ለሠራተኛው አድሎ ያጠናቅቃል፤
6.2.4. በሠራተኛውና በድርጅቱ መካከል የተለየ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ለድርጅቱ
ሥራ አስፈላጊ የሆኑ መሣሪያዎችን፣ የሰው ሀይልና ጥሬ ዕቃዎችን በዕቅድ መሰረት
በወቅቱ ያቀርባል።
6.2.5. ሠራተኛው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንዲያገኝ ለተቋቋሙት ለብድርና ቁጠባ
የህብረት ሥራ ማህበርና ሰራተኛ ማህበሩ የሚሰበሰበውን ገቢ ከማህበሮች ጋር
በሚደረገው የስምምነት አግባብ ከማህበሩ አባላት (ሰራተኞች) ደመወዝ በመቀነስ
በማህበሮች ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ገቢ ያደረጋል፡፡ ማህበሮችም ገቢ ለተደረገለት
ገንዘብ ህጋዊ ደረሰኝ ይሰጣሉ እንዲሁም የማህበራዊ አገልገሎት ለማጠናከር ለሚደረገው
ጥረት ትብብር ያደርጋል።
6.2.6. ሠራተኛው የተቀጠረበትን ቀን፣ የቅጥር ማስረጃውን፣ የደመወዙን ልክ፣ በየጊዜው
የወሰዳቸውን ፈቃዶች፣ የጤንነት ሁኔታዎች፣ የጡረታ ዋስትና፣ ለልዩ ልዩ ማህበራዊ
ጉዳዮች የሚከፍላቸውን ሂሳቦችና የመሳሰሉትን በግልጽ የሚያሳይ ማህደር ይይዛል።

7
6.2.7. ሠራተኛው የሰራበትን የሥራ መደብ፣ ደመወዝና የአገልግሎት ጊዜ የሚገልጽ ማስረጃ
እንዲሰጠው በጽሁፍ ከጠየቀ መስጠት፡፡
6.2.8. ሠራተኛው በዓመት ሁለት ጊዜ የግል ማህደሩን ለማየት በጽሁፍ ሲጠይቅ ለሰው ሀብት
አስተዳደርና ቡድን መሪ ወይም እርሱ የሚወክለው ባለሙያ ባለበት እንዲያይ ድርጅቱ
ይፈቅዳል፡፡
6.2.9. ማንኛውም ሠራተኛ በሥራ ላይ እንዳለ የምስክር ወረቀት ወይም የድጋፍ ደብዳቤ
እንዲሰጠው ምክንያቱን ገልፆ በጽሁፍ ሲጠይቅ ጥያቄው ተገቢ መሆኑ ከማህደሩ
ተመሳክሮ የጠየቀው እንዲሰጠው ይደረጋል።
6.2.10. በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙት የሥራ መደቦች ተጠንተው ዝርዝራቸው ተዘጋጅቶ ከፀደቀ
በኋላ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ኃላፊነቱንና ተግባሩን የሚገልጽ የሥራ መዘርዝር (Job
Description) እንዲደርሰው ያደርጋል። በፕሮጀክቶች ላይ ሠራተኞች ሲመደቡ
ድርጅቱ ደብዳቤና የሥራ መመሪያ ይሰጣል።
6.2.11. ድርጅቱ ለድርጅቱ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ቋሚ ጽ/ቤት ያሟላል፡፡
6.2.12. ከሰራተኛ ማህበሩ ጋር በመተባበር ሰራተኞች የህብረት ስምምነቱን አንቀፆች ትርጉምና
አፈፃፀም በሚገባ እንዲረዱ አሰፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡
6.2.13. የሰራተኛውን ጤንነት፣ ደህንነትና ሞራሉን ለመጠበቅ የስራ አካባቢውን ተገቢውን
ጥንቃቄ ያደርጋል፤ ከማህበሩ ጋርም በመመካከር አሰፈላጊ የሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎች
ይወስዳል፡፡
6.2.14. ድርጅቱ የድርጅቱ ሰራተኞችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት
የድርጅቱ የወደፊት ዕቅድና ስልጠና ፍላጎት እና የስልጠና መመሪያ መሰረት
በማድረግ እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፡፡
6.2.15. በዚህ የህብረት ስምምነትና በድርጅቱ መመሪያ መሰረት የሰራተኛውን የደረጃ ዕድገት፣
ደመወዝ ጭማሪ በየጊዜው እየተከታተለ ይፈጽማል፡፡
6.2.16. ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የውጤት ተኮር ዕቅድና የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት በዚህ
ስምምነት በአንቀፅ 29.1 እንዲሁም 29.2 መሰረት መሰጠቱን ያረጋግጣል፡፡
6.2.17. ድርጅቱ ለሰራተኞች በጠዋት በመግቢያና በማታ በመውጫ ሰዓት የትራንስፖርት
አገልግሎት ያቀርባል፡፡ የሰርቪስ መኪናው ሰራተኞችን የሚያሳፍርበት ቦታ
በድርጅቱና በማህበሩ በጋራ ይወሰናል፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ከአቅም በላይ በሆኑ እንደ
መኪና ብልሽት፣ በሀገራዊ ወይም ክልላዊ ግዳጆች ድርጅቱ የትራንስፖርት አገልግሎት
ማቅረብ ካልቻለ ሰራተኛው በራሱ ትራንስፖርት ሥራ መግባት ይኖርበታል፡፡

8
ድርጅቱም ሰርቪስ መኪና ሳይኖር ሲቀር የድርጅቱ ሰራተኞች እንዲያውቁት በውስጥ
ሰሌዳ ማስታወቂያ ይለጥፋል፡፡
6.2.18. ድርጅቱ የበጀት አመቱ ሂሳብ በመዝጋት በውጭ ኢዲተር አስመርምሮ የውጤቱን ኮፒ
ለማህበሩ የሚያሳውቀው ከሀምሌ 1 ቀን ጀምሮ ባሉት 90 ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ይህም
ተግባራዊ የሚሆነው ለቦርድ ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ነው፡፡
6.2.19. ሰራተኛ ሲቀጠር፣ ሲመደብ፣ የደረጃ እድገት ሲያገኝ፣ የዲሲፕሊን እርምጃ ሲወሰድበት፣
የስራ ምስጋና የተሳትፎ ደብዳቤ ሲሰጠው፣ ለትምህርት ሲሄድ፣ ሲዛወር፣ ሲሰናበትና
ሲሞት ድርጅቱ ለማህበሩ ያሳውቃል፡፡
6.2.20. በድርጅቱ ውስጥ አስተዳደር እንዳይዛባ፣ የምርት ጊዜ በክርክር እንዳይባክን፣
የአስተዳደር ፍትሕ እንዲሰፍን፣ ሠራተኛው መላ ኃይሉን፣ ችሎታውን እና ሙያውን
በሥራ ላይ እንዲያውል በበኩሉ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፣
6.2.21. በማንኛውም ምክንያት የሥራ ውሉ ለተቋረጠበት ሠራተኛ የርክክብ ማስረጃ ሲያቀርብ
ድርጅቱ ሥራውን፣ ሙያውን፣ የሠራበት ዘመን፣ ደመወዙን ገልፆ እንደአስፈላጊነቱ
ፎቶግራፍ ያለበት የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡
6.2.22. የዓመቱን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የሥራ መግለጫዎች እንዲሁም የሚቀጥለውን
የበጀት ዘመን የሥራ ዕቅድ ለማኀበሩ እንዲደርሰው ያደርጋል፣ ድርጅቱም ለማኀበሩ
ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ማኀበሩ ሲጠይቅ ይሰጣል፤
6.2.23. ይህን የህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም ማህበሩ ሊሳተፍባቸው በሚገባቸው
በአዳዲስ የስራ ሁኔታዎች (የአሰራር ስርዓቶችና ማሻሻያዎች) ላይ ማህበሩን ለውይይት
ማሳተፍ፡፡

አንቀጽ ሰባት (7) የማህበሩ መብቶችና ግዴታዎች


7.1 የማህበሩ መብቶች
7.1.1 በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ ስለተመለከቱትም ሆነ ወይም ከስምምነቱ ውጭ
በድርጅቱ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ማናቸውም የስራ ሁኔታዎች ሰራተኛውን ወክሎ
ከድርጅቱ ጋር ይነጋገራል፡፡
7.1.2 በዚህ የሕብረት ስምምነት መሠረት በሚቋቋሙ ኮሚቴዎች ውስጥ ሠራተኛውን
የሚወክሉ አባላትን መርጦ የማሳተፍ፡፡

9
7.1.3 የሰራተኛ ማህበሩ ለድርጅቱ ስራ መሻሻል እና ሁለንተናዊ ዕድገት በድርጅቱ ዕቅድ፣
የስራ አፈፃፀም ክትትል እና ግምገማ ላይ እንዲሁም ትምህርትና ስልጠና፣ በዝውውር‹
በደረጃ እድገት፣ በቅጥር፣ በዲሲፕሊን፣ ኮሚቴዎች ላይ ይሳተፋል፡፡
7.1.4 አሰፈላጊ በሆነ ጊዜ ከደርጅቱ ጋር በመመካከር ማህበሩ በህጋዊ መንገድ ጠቅላላ ጉባኤ
የመጥራት ወይም የመሰብሰብ መብት አለው፡፡ ስብሰባም ሲጠራ በቅድሚያ ለድርጅቱ
ከ3 ቀናት በፊት አሳውቆ ሁለቱም በጋራ በሚስማሙበት ቀን ይሆናል፡፡
7.1.5 ለማህበሩ ስራ በድርጅቱ የተዘጋጀውን ማስታወቂያ ሰሌዳ የመጠቀም መብት አለው፡፡
7.1.6 ማንኛውም የስራ ሁኔታዎች በተመለከተ የድርጅቱ ሰራተኞች በመወከል የህብረት
ስምምነት መደራደር፡፡
7.1.7 ማሀበሩ ለሰራተኛው አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መዝናኛዎችን ጨምሮ ሌሎች የገቢ
ማስገኛ ፕሮጀክት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከድርጅቱ ጋር በመመካከር በሰራተኛውና
በድርጅቱ ስራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የማያሳድሩ መሆኑን በማረጋገጥ የማቋቋም መብት
አለው ድርጅቱም አዋጭነቱን ሲያምንበት አስፈለጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
7.1.8 ለሰራተኛው ደህንነት ሲባል ካምፕ ባላቸው ፕሮጀክቶች ከድርጅቱ ጋር ሆኖ የካምፕ
አስተዳደር መመሪያ ያወጣል፡፡

7.2 የማህበሩ ግዴታዎች


ማህበሩ በዚህ የህብረት ስምምነት እና አግባብነት ባላቸው ህጉች የተደነገጉት እንደተጠበቁ
ሆነው የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡-
7.2.1 ስለ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጡትን አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ይህንን
የሕብረት ስምምነት ያከብራል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፡፡
7.2.2 ሠራተኞች የሚጠቀሙባቸውን የምርት መሣሪያዎችና ንብረቶች በቁጠባና በእንክብካቤ
እንዲያዙ የድርጅቱን የሥራ ውጤት በብዛትም ሆነ በጥራት እንዲያዳብርና ምዝበራና
ብኩንነት እንዲወገዱ ማኀበሩ ያስተምራል፣ ያበረታታል፣ ያግዛል፤
7.2.3 ማህበሩ ሰራተኛውን በህብረት ስምምነት አንቀፆች ትርጉምና አፈፃፀም በመንግስት እና
በድርጅቱ የሚወጡ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን በሚገባ እንዲረዳና ጠንካራ የስራ
ዲስፕሊን እንዲኖረው አሰፈላጊውን ሁሉ ያደረጋል፡፡ ለድርጅቱ ኢንዱስትሪ ሰላም
መሰፈን ሲባል በቅን መንፈስ ለችግሮች መፍትሄ የመሻት ግዴታ አለበት፡፡
7.2.4 ይህን የህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም በአዳዲስ የስራ ሁኔታዎች (የአሰራር
ስርዓቶችና ማሻሻያዎች) ላይ ድርጅቱ ለውይይት ሲጠራ ቀርቦ የመወያየት ግዴታ
አለበት፡፡
10
7.2.5 የድርጅቱ ምርታማነትና ትርፋማነት ከፍ እያለ እንዲሄድ እንዲሁም የሰራተኛ የፈጠራ
ችሎታ እንዲዳብር ያነቃቃል፣ ያበረታታል፣ ይከታተላል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ የስራ
ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰራተኞች የተመደቡበትን ተግባር እና ሀላፊነት በጥራትና
በታማኝነት እንዲወጡ ያግዛል፡፡
7.2.6 በድርጅቱ ሰራተኞች መካከል የሚፈጠሩና የኢንዱስትሪ ሰላምን የሚያውኩ የተዛነፉ
አስተሳሰቦችን፣ አሉባልታዎችንና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን የመታገል፣ የማስተካከልና
የማረም፣
7.2.7 ከድርጅቱ ጋር በጋራ ኮሚቴነት በሚሰሩ ስራዎች ላይ በቅንነት፣ በታማኝነትና በትኩረት
የመስራት፣
7.2.8 ማህበሩ ማንኛውንም ሰራተኛውን የሚመለከት በህብረት ስምምነቱ የተጠቀሱትን
ጉዳዮች በግሉ ማሻሻል፣ መሰረዝ ወይም መለወጥ አይችልም፡፡

አንቀጽ ስምንት (8) የሰራተኛ መብትና ግዴታዎች


8.1 የሰራተኛ መብቶች
8.1.1 አግባብ ባለው ፍርድ ቤት በድርጅቱ ላይ ክስ ከማቅረቡ በፊት ቅድሚያ የሠራተኛ
ማህበሩ እንዲያደራድረው ቅሬታውን በጽሁፍ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
8.1.2 የሰራተኛው መብት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም በዚህ የህብረት ስምምነት
የሚከለከልበት ምክንያት እስከሌለ ድረስ ማንኛውንም በዚህ የህብረት ስምምነት
የተጠቀሱ መብቶችና ጥቅሞችን ያገኛል፡፡
8.1.3 የራሱን ዕድገት የሚቃረን ድርጊት ባጋጠመው ጊዜ በቅሬታ አቀራረብ ሰነ ስርዓት
መሰረት ለሚመለከተው የስራ ሀላፊ ቅሬታ ማቅረብ ይችላል፡፡
8.1.4 ሰራተኞች ሲያገቡ ከሙሽራ ማጀብ ውጭ ላለ አገልግሎት ለባህርዳር ከተማ እንዲሁም
ለምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት ደሴ ከተማ አንድ መኪና ከድርጅቱ ነዳጅና ሹፌር በነፃ ለ1
ቀን ይጠቀማሉ፡፡
8.1.5 ሰራተኛው ሳያውቅ ወቀሳ፣ ማስጠንቀቂያ፣ ቅጣት በግል ማህደሩ ውስጥ አይቀመጥም፡፡
በዚህም ሰራተኛው በግል ማህደሩ ላይ ጥርጣሬ ሲኖረው ጠይቆ በማናቸውም ጊዜ
የማየት መብት አለው፡፡

11
8.2 የሠራተኛ ግዴታዎች
ሰራተኛው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 13 ከንዑስ አንቀጽ 1-7
እና አንቀጽ 93 ከንዑስ አንቀጽ 1-5 እንዲሁም አግባብነት ባላቸው ህጉች ከተጠቀሱት
ግዴታዎች በተጨማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡
8.2.1. በተመደበበት ሥራ ሙሉ ችሎታውንና ዕውቀቱን በመጠቀም ለድርጅቱ ምርታማነት
ማደግ እንዲሁም ለሥራ አፈፃፀም ጥራት አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል።
8.2.2. በዚህ ደንብ መሠረት የተዘረዘሩትን የዲሲፒሊን ሁኔታና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-
ሥርዓት ደንቦችን ያከብራል።
8.2.3. ድርጅቱ በየጊዜው የሚያዘጋጃቸውን ክትባቶችና የጤና ምርመራዎች ከኤች አይ ቪ
ኤድስ (HIV/ AIDS) በስተቀር ይፈጽማል።
8.2.4. ሠራተኛው የሥራ ሰዓትን በሚገባ ያከብራል፣ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር አስቀድሞ
ፈቃድ ሳያገኝ ከመደበኛ ሥራው አይለይም።
8.2.5. ድርጅቱ ለመዝናኛና ለመመገቢያ ስፍራዎች የሚያወጣውን የሥነ-ሥርዓት
መመሪያዎችና ደንቦች ያከብራል።
8.2.6. ድርጅቱ ለሚይዘው የሠራተኛ ማህደር አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የመስጠትና
በሰጣቸው መረጃዎች ላይም ለውጥ ባደረገ ቁጥር ይህንኑ በጽሁፍ ለድርጅቱ ያሳውቃል።
8.2.7. አንድ ሠራተኛ በልዩ ልዩ ምክንያት ከሥራው ሲለይና በቦታው ተተክቶ የሚሠራ
ሠራተኛ ሲያስፈልግ ሠራተኛውን ተክቶ ይሠራል።
8.2.8. ካምፕ በሚሠራባቸው አካባቢዎች ድርጅቱና የሰራተኛ ማህበሩ የሚያወጣቸውን የካምፕ
አስተዳደር ደንቦችና ሥነ-ሥርዓቶች ያከበራል።
8.2.9. ሠራተኛው ሥራውን በትጋት ያከናውናል፣ በድርጅቱ የሥራ ሰዓት የግል ሥራ
ማከናወን አይችልም።
8.2.10. በድርጅቱ ውስጥ ሠራተኛው በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመደብ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ
ይሰራል። በዚህ መልክ የሚሠሩ ሠራተኞች ለኮሚቴው አገልግሎት የሚያውሉት ጊዜ
በኮሚቴው ሰብሳቢ በኩል ለሥራ ኃላፊው እንዲቀርብ ይደረጋል።
8.2.11. የድርጅቱ ሰራተኛ ሆኖ እያለ ድርጅቱን ሳይለቅ በሌላ መ/ቤት በመደበኛ የስራ ሰዓት
ሰራተኛ ሆኖ ማገልገል አይችልም፡፡ ይህ ሆኖ ከተገኘ ድርጅቱ ከስራ ያሰናብታል፡፡
8.2.12. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ከሥራ መልቀቅ ቢፈልግ ከአንድ ወር በፊት ለድርጅቱ
በጽሁፍ የማሣወቅ ግዴታ አለበት፡፡ በዚህ የተገለፀውን ያላሟላ ሰራተኛ ከመልቀቁ
በፊት የወር ደመወዙን ለድርጅቱ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ከ15 ቀናት በላይ የማስጠንቀቂያ

12
ጊዜ ሰጦ የቆየ ሰራተኛ ከሆነ ማስጠንቀቂያ የሰጠበት ጊዜ ተቀንሶለት የቀሪውን ቀናት
ደመወዝ ለድርጅቱ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ 15 (አስራ አምስት) ቀናትና ከዚያ በታች
ከሆነ ግን ሙሉ የ30 (ሰላሳ ቀናት) መክፈል ይኖርበታል፡፡
8.2.13. በማናቸውም ጊዜ ቢሆን የድርጅቱንና የእርሱን ክብር እንዲሁም ሚስጥር ይጠብቃል፡፡
8.2.14. ሰራተኛ ህገወጥ ሰነዶችን አያሰራጭም፣ አይልክም በድርጅቱና በሰራተኛ ማህበሩ
መካከል አለመግባባትን የሚፈጥር፤ ወይም የድርጅቱን መልካም የስራ ሁኔታ የሚጎዳ፤
ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በተገናኘ የድርጅቱንም ሆነ የማንኛውንም የስራ ሃላፊ/
ሰራተኛ ስም የሚያጎድፍ በማስረጃ ያልተረጋገጠ የሃሰት ወሬ፣ ሃሜት፣ ስም የማጥፋት
ተግባር ከመፈጸም መቆጠብ አለበት፡፡ ይህ አይነት ድርጊት በማንኛውም የመገናኛ
መንገድ መፈጸሙን ያወቀ ሰራተኛ ችግሩን ለድርጅቱና ለማህበሩ ማሳወቅ አለበት
8.2.15. ሰራተኛው ከቅርብ ሀላፊው የሚሰጡትን ማንኛውም የስራ የጽሁፍ ሰነዶች ይቀበላል
መልስ ያቀርባል፡፡ እንዲሁም ከቅርብ ሀላፊው የሚሰጠውን በስራ ውሉና በስራ ደንቡ
መሰረት ህጋዊ ትዕዛዞች አክብሮ ይሰራል፡፡
8.2.16. ሠራተኛው ከድርጅቱ በኃላፊነት የተረከባቸውን ወይም በስራ አጋጣሚ በእጁ የገቡ
ሰነዶች፣ ዕቃዎችና መሣሪያዎችን ወይም ሌሎች ንብረቶችን በጥንቃቄ ይይዛል፣
ይንከባከባል፣ ይጠብቃል፣ ሥራው ሲፈፀም መመለስ የሚገባውን መልሶ ለድርጅቱ
ያስረክባል፣ የድርጅቱን ንብረት ሆነ ብሎ ካበላሸ፣ ካጠፋ ወይም በድርጅቱ ንብረት
ወይም ጥቅም ላይ ማናቸውንም ሆነ ብሎ ጉዳት ካደረሰ ተጠያቂ ይሆናል፤
8.2.17. በሠራተኛው ላይ የተለዬ ፍርሃት፣ ጭንቀትና የመንፈስ መረበሽን የሚያሣድሩ፣ የሥራ
መንፈስና ምርታማነትን የሚፃረሩ ድርጊቶችን፣ ነውጥን፣ አድመኝነትን፣ በሠራተኛው
ውስጥ ከማስፋፋት መቆጠብ፤ ሌላው ሲያደርግ ቢያገኝ ወይም ቢሰማ የመታገል እና
ለድርጅቱ በወቅቱ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡
8.2.18. በሥራው ምክንያት የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት አይሞክርም፣ ማማለጃ ወይም ጉቦ
አይሰጥም ወይም አይቀበልም፡፡
8.2.19. ከድርጅቱ በሰነድ የወሰደውን ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ የተጠቀመበትን በሕጋዊ የወጪ
ማስረጃዎች በወቅቱ የማወራረድ፣ በሥራው ያልተጠቀመበትንም ገንዘብ በድርጅቱ
የፋይናንስ ደንብ መሠረት ተመላሽ ማድረግ አለበት፡፡
8.2.20. የሥራ ውሉ ተቋርጦ ከድርጅቱ ሲሰናበት በእጁ የሚገኘውን የድርጅቱን ንብረት ወይም
ገንዘብ በሙሉ ያስረክባል ወይም ገቢ ያደርጋል እንዲሁም ዕዳ ካለበት ድርጅቱ
ለሰራተኛው የሚከፍለው ገንዘብ ካለ ዕዳውን ሙሉ ለሙሉ ቀንሶ ማስቀረት ይችላል፡፡

13
8.2.21. ሠራተኛው በኦዲት የተረጋገጠበት ዕዳ ሲኖርበት ድርጊቱ ከስራ የማያሰናብት ከሆነ
ድርጅቱ በየወሩ ከሰራተኛው ደመወዙ ላይ 1/3 እየቆረጠ ያስቀራል፡፡ ሠራተኛውም
የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ይህ ከአስተዳደራዊም ሆነ ከወንጀል ተጠያቂነት
አያድነውም፡፡
8.2.22. ድርጅቱ የሰራተኛውን የሙያ ፈቃድ ሲፈልገው ሰራተኛው የመስጠት ግዴታ አለበት፤፤

14
ክፍል ሁለት
አንቀጽ ዘጠኝ (9) ቅጥር፣ ምደባ፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣
ትምህርትና ስልጠና
9.1 ቅጥር
9.1.1 በድርጅቱ ውስጥ የሰራተኛ ቅጥር የሚፈፀመው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011፣ በዚህ ህብረት
ስምምነትና ይህን ህብረት ስምምነት መሰረት በማድረግ በወጣው በድርጅቱ የሰው ሀብት
ሥራ አመራር መመሪያ መሰረት ይሆናል፡፡ መመሪያው ለሰራተኛ ማህበሩ በቅጅ
እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡
9.1.2 ከስራ መሪና ከዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ ውጭ በቀላሉ ገበያ ላይ በማይገኙ፣ ለከፍተኛ
ፕሮጀክቶች ለሚያስፈልጉና በተመሳሳይ ደረጃ ባሉ የፕሮፌሽናልና የቴክኒክ ሙያ የስራ
መደቦች ላይ ለድርጅት ጥቅም ሲባል በድርጅቱ ማኔጅመንት ውሳኔ ያለውድድር በፈታና
ወይም ያለፈተና ቀጥታ ቅጥር ይፈፀማል፡፡
9.1.3 ከላይ በ9.1.2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድን ከተሿሚ፣ ከሥራ መሪና ከአማካሪ
ውጭ ያለ ክፍት የሥራ መደብ ከድርጅቱ ስራተኞች ውስጥ በዝውውር እና በደረጃ
እድገት መሙላት ሳይቻል ሲቀር የውጭ ተወዳዳሪዎች ለቅጥር በማስታወቂያ ሊጋበዙ
ይችላል፡፡
9.1.4 የሰራተኛ ቅጥር የሚፈፀመው በግልፅ ውድድር ሲሆን ለተጠየቀው ቦታ ተፈላጊውን
መስፈርት እና በቅጥርና የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ የሚሰጠውን መመዘኛ አሟልቶ ሲገኝ
ቅጥሩ ይከናወናል፡፡ ለቅጥር በሚሰጥ የተግባርም ሆነ የጽሁፍ ፈተና ተወዳዳሪዎች
ቢያንስ 60 (ስልሳ) ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
9.1.5 በማጭበርበር፣ በስርቆትና በሌሎች የሙስና ጉዳዩች በዲስኘሊን የተባረረ ሰራተኛ
በድጋሚ በድርጅቱ መቀጠር አይችልም፡፡ ሆኖም በሌሎች የዲስኘሉን ጉዳዩች የሥራ
ውላቸው የተቋረጠ ሠራተኞች እስከ 2 (ሁለት) አመት ድረስ በድርጅቱ መቀጠር
አይችሉም፡፡
9.1.6 ላልተወሰነ ጊዜ (በቋሚ) በሚወጣ ክፍት የሥራ መደብ ላይ በድርጅቱ ለተወሰነ ጊዜ/
ሥራ (በኮንትራት) የተቀጠረ ሰራተኛ ስራ ላይ እያለ ላልተወሰነ ጊዜ (በቋሚ) ቅጥር
ማስታወቂያ ቢወጣ መስፈርቱን እስካሟላ ድረስ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ ተመዝግቦ
መወዳደር ይችላል፡፡ ካለፉ የተወሰነ ጊዜ ቅጥሩ በስምምነት ተቋርጦ ባለፉበት ቋሚ የስራ
መደብ ላይ በአዲስ መልክ ሊቀጠሩ ይችላል፡፡

15
9.1.7 በድርጅቱ ለተወሰነ ጊዜ/ ሥራ (በኮንትራት) የተቀጠረ ሰራተኛ ሆኖ በድርጅቱ ቢያንስ
አንድ ዓመት ያገለገለ ስራ ላይ እያለ ሌላ ካለበት ደረጃ የተሻለ የተወሰነ ጊዜ/ ስራ
(ኮንትራት) ቅጥር ማስታወቂያ ቢወጣ መስፈርቱን እስካሟላ ድረስ እንደማንኛውም
ተወዳዳሪ ተመዝግቦ መወዳደር ይችላል፡፡ ካለፈ የተወሰነ ጊዜ/ ስራ ቅጥር ውሉ
በስምምነት ተቋርጦ ባለፈበት የተወሰነ ጊዜ/ስራ የስራ መደብ ላይ በአዲስ መልክ
ሊቀጠር ይችላል፡፡
9.1.8 በድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) የተቀጠረ ሰራተኛ ሆኖ በድርጅቱ ቢያንስ አንድ
ዓመት ያገለገለ ስራ ላይ እያለ ሌላ ካለበት ደረጃ የተሻለ የተወሰነ ጊዜ/ ስራ (ኮንትራት)
ቅጥር ማስታወቂያ ቢወጣ መስፈርቱን እስካሟላ ድረስ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ
ተመዝግቦ መወዳደር ይችላል፡፡ ካለፈ ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) ቅጥር ውሉ በስምምነት
ተቋርጦ ባለፈበት የተወሰነ ጊዜ/ ስራ የስራ መደብ ላይ በአዲስ መልክ ሊቀጠር
ይችላል፡፡ የተወሰነ ጊዜ ቅጥሩ ሲጠናቀቅ በውሉ መሰረት የሚቋረጥ ይሆናል፡፡ የቋሚ
ጥያቄ ቢያነሳ ተቀባይነት የለውም፡፡
9.1.9 በአንድ የስራ መደብ ላይ በቅጥር ተወዳድሮ ከማለፊያ ነጥብ በታች ያመጣ (የወደቀ)
ተወዳዳሪ በዚሁ የስራ መደብ ላይ በድጋሚ መወዳደር የሚችለው ውጤቱ ከታወቀ ከ3
ወር በኋላ ነው፡፡

9.2 የሰራተኛ ምደባ


ድርጅቱ አዲስ መዋቅር በሚሰራበት ጊዜ ሰራተኞችን ባላቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ
አፈጻጸም ውጤትና የስራ ልምድ መሰረት ግልፅና አሳታፊ በሆነ መንገድ ስራና ሰራተኛን
ሊያገናኝ በሚችል ሁኔታ ምደባ ይካሂዳል፡፡ በዚህም ምደባ የሰራተኛ ማህበሩ ይሳተፋል፡፡

9.3 በተጠባባቂነት ወይም በውክልና ሰራተኞችን ስለመመደብ


9.3.1 ክፍት የሥራ መደብ በሚፈጠርበት ወይም በተለያየ ምክንያት በስራ መደቡ ላይ የነበረ
ሠራተኛ/ የስራ መሪ በማይኖርበት ጊዜ ቦታውን በተጠባባቂነት ወይም በውክልና ሸፍኖ
እንዲሠራ የሚመደብ ሠራተኛ ለመመደብ የማያስችል ተጨባጭ ምክንያት ወይም
የአቅም ችግር እስከሌለ ድረስ በክፍሉ ውስጥ ለሥራ መደቡ በደረጃ ቀጥሎ ያለው
ይሆናል። ከአንድ በላይ ተመሳሳይ ባለሙያ ቢኖር ለክፍት የሥራ መደቡ የተሻለ
ቀረቤታና ብቃት የሚኖረው ይመረጣል።

16
9.3.2 በተለያየ ምክንያት በስራ መደቡ ላይ የነበረ ሠራተኛ/ የስራ መሪ በማይኖርበት ጊዜ
በሰራተኛው የቅርብ ሀላፊ ወይም በራሱ በስራ መሪው ውክልና የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ተጠባባቂነት ግን በዋና ሥራ አስፈፃሚ/ በጽ/ቤት ሀላፊ ውሳኔ ተፈፃሚ ይሆናል።
9.3.3 ማንኛውም ውክልና ከዝቅተኛ የኃላፊነት ደረጃ ወደ ከፍተኛ ወይም ተመሳሳይ ወይም
ትይዩ የስራ ደረጃ ይሆናል፡፡ ይህም ከስራ ጋር የተያያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡
9.3.4 በማንኛውም ክፍት በሆኑ የሥራ መደቦች ላይ በተጠባባቂነት ሰራተኛው ከሰራ
በተጠባባቂነት ከተመደበበት ጊዜ ጀምሮ ለስራ መደቡ የተፈቀደ የሀላፊነት አበል ካለ
ይከፈለዋል፡፡
9.3.5 በፈቃድ፣ በህመምና በሌሎች በማንኛውም ምክንያት ለጊዜው ቀሪ የሆነ የሥራ መሪን
ወክሎ ከ30 ቀን በላይ ለሰራ ሰራተኛ ለስራ መደቡ የተፈቀደ የሀላፊነት አበል ብቻ ካለ
ይከፈለዋል፡፡ ክፍያው የሚፈጽመው ሠራተኛ በቦታው ተወክሎ እስካገለገለ ድረስ ብቻ
ነው፡፡
9.3.6 የተጠባባቂ ምደባ ከስድስት ወራት አይበልጥም። ሆኖም ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ
ሲያጋጥም ለተጨማሪ ስድስት ወራት ሊራዘም ይችላል።
9.3.7 በአንቀጽ 9.3.6 በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ድርጅቱ ቋሚ ምደባ ካላደረገ
ሠራተኛው ይህንኑ በጽሁፍ በመግለጽ የተጠባባቂነት ኃላፊነትን ሥራ የመተው መብት
ይኖረዋል፡፡

9.4 የደረጃ ዕድገት


9.4.1 የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የራሱን አማካሪ፤ ሹፌርና ፀሀፊ በድርጅቱ ውስጥ ካሉና
የስራ መደቡን ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ መስፈርት ከሚያሟሉ ሰራተኞች መካከል
ያለውድድር መርጦ በቀጥታ ይመድባል፡፡
9.4.2 በድርጅቱ ውስጥ ከሥራ መሪ፣ ከዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ፣ ሹፌርና ፀሐፊ የስራ
መደቦች ውጭ ያለ ክፍት የሥራ መደብ (ቦታ) ሲገኝ ሠራተኛ እንዲሟላለት
የሚፈልገው የስራ ክፍል ለድርጅቱ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት። ድርጅቱም ጥያቄውን
ተቀብሎ ሲፈቅድ መስፈርቱን የሚያሟሉ የድርጅቱ ሠራተኞች ተወዳድረው
እንዲሞሉት ያደርጋል። ሆኖም በቀላሉ ገበያ ላይ በማይገኙ ለከፍተኛ ፕሮጀክቶች
ለሚያስፈልጉና በተመሳሳይ ደረጃ ባሉ የፕሮፌሽናልና የቴክኒክ ሙያ የስራ መደቦች
ላይ ለድርጅት ጥቅም ሲባል በድርጅቱ ማኔጅመንት ውሳኔ ያለውድድር በፈተና ወይም
ያለፈተና ቀጥታ ቅጥር ሊፈፀም ይችላል፡፡

17
9.4.3 ከላይ 9.4.1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ክፍት የሥራ መደቦች ሲፈጠሩ/ ሲኖሩ
ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) ሠራተኞች ለመመዝገብ እንዲችሉ ድርጅቱ ማስታወቂያ
ይለጥፋል። በተጨማሪም በወቅቱ መስክ ላይ ላሉ ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) ሠራተኞች
የመገናኛ ችግር እስካላጋጠመ ድረስ እንዲያውቁት ይደረጋል። በማስታወቂያውም
የመመዝገቢያ ቀን፣ ሰዓትና ቦታ እንዲሁም መመዘኛዎችና ምዝገባው የሚጠናቀቅበት
ቀንና ሰዓት ይገለፃል። ሆኖም የመገናኛ ችግር ካለና ደረጃ እድገቱ የሚመለከተው
ሰራተኛ ሆኖ ከተገኜ በቅርብ ሃላፊው በኩል እንዲመዘገብ ይደረጋል፡፡
9.4.4 በውስጥ ማስታወቂያ ለደረጃ ዕድገት የሚወጣ ክፍት የሥራ መደብ ለ5 (አምስት)
ተከታታይ የሥራ ቀናት መቆየት ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ እጩ ተወዳዳሪ
ካልቀረበ በስራ መደቡ ላይ እስከ 1 (አንድ) ወር ጊዜ ውስጥ የውጭ ቅጥር ማስታወቂያ
እንዲወጣ ይደረጋል። ከአንድ ወር በላይ ከዘገየ ግን ድጋሚ የደረጃ ዕድገት ሊወጣ
ይገባል፡፡
9.4.5 የደረጃ እድገት ማስታወቂያዎች ወጥተው ለሥራው ተፈላጊ ሰው ከተመዘገበ በኋላና
የምዝገባው ጊዜ ካለቀበት ቀን ጀምሮ ኮሚቴው ከ10 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የውሳኔ
ሀሳቡን ያቀርባል።
9.4.6 የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይም ውክልና የተሰጠው አካል በቅጥር፣ እድገትና
ዝውውር ኮሚቴ የቀረበለትን የደረጃ ቅደም ተከተል እና የውድድር አካሄዶችን አጥንቶ
በ5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ይሰጣል።
9.4.7 የደረጃ እድገት ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ውክልና በተሰጠው
አካል ከፀደቀ በኋላ የሁሉም ውጤት በማስታወቂያ ሰሌዳ ይለጠፋል።
9.4.8 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ውክልና የተሰጠው አካል ከደረጃ እድገት ኮሚቴ የቀረበው
የውሳኔ ሀሳብ ውሳኔ ለመስጠት የማያስችል ሆኖ ሲያገኘው ወይም ኮሚቴው
ያላገናዘባቸው ነጥቦች ሲኖሩ ወይም ምዘናውና የኮሚቴው አሰራር ግልጽ ሆኖ ሳይቀመጥ
ሲቀር ይህንኑ በመጥቀስ እድገቱ እንደገና እንዲጠና ለኮሚቴው ይመራል። ዋና ሥራ
አስፈጻሚ ወይም ውክልና የተሰጠው አካል ከኮሚቴው በድጋሚ የቀረበለትን አስተያየት
በመመርመር የመጨረሻ ውሳኔ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ይሰጣል።
9.4.9 የቅጥር፣ የደረጃ እድገትና ዝውውር ኮሚቴ በሚከተለው ሁኔታ ይመሰረታል።
 የሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ----------------------------------------------------- ሰብሳቢ
 የሰው ሀብት ኦፊሰር/ ባለሞያ---------------------------------------------------------------- አባል
 የሰራተኛ ማህበር 2 (ሁለት) ተወካይ------------------------------------------------------- አባል

18
 ክፍት የሥራ መደቡ በቅጥር/ በደረጃ እድገት እንዲሟላለት የጠየቀው የስራ ዘርፍ/
ክፍል ኃላፊ ወይም ተወካይ------------------------------------------------------------------ አባል
9.4.10 ለአንድ ክፍት የስራ መደብ (ቦታ) መስፈርቱን አሟልቶ የተገኘ አንድ ወይም ብቸኛ
ተወዳዳሪ ቢሆን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከተገኘና በተሰጠው ፈተና
እና በአጠቃላይ የማወዳደሪያ መስፈርት ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ካስመዘገበ እድገቱን
ማግኘት ይችላል፡፡ ለደረጃ ዕድገት በሚሰጥ የተግባርም ይሁን የጹሁፍ ፈተና
ተወዳዳሪው/ዎች ወደ ሚቀጥለው ውድድር ለማለፍ ቢያንስ 50 (ሀምሳ) በመቶ
ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
9.4.11 የደረጃ እድገት የተፈቀደለት ሠራተኛ የደረጃ እድገቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ለሥራ
መደቡ የተወሰነውን መብትና ጥቅም ያገኛል።
9.4.12 የደረጃ እድገት የሚያገኝ ሠራተኛ የሚያገኘው የደመወዝ ጭማሪ በድርጅቱ የሰው
ሀብት ሥራ አመራር ወይም የምልመላና መረጣ መመሪያ መሠረት ይሆናል።
9.4.13 ለደረጃ እድገት የሚወዳደር ሰራተኛ የቅርብ ጊዜ ተከታታይ የ2 ጊዜ የስራ አፈፃፀም
ምዘና ውጤት እያንዳንዱ ከ60% በታች መሆን የለበትም፡፡ የ2 ጊዜ ከሌለ የአንድ ጊዜ
ከበቂ ምክንያት ጋር ሊያዝ ይችላል፡፡
9.4.14 አንድ ስራተኛ የደረጃ ዕድገት ካገኘ አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ከሆነው በሌላ የደረጃ
ዕድገት ሊወዳደር ይችላል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ግን ሊወዳደር አይችልም፡፡
9.4.15 አዲሰ ሰራተኛ ተቀጥሮ በድርጅቱ ውስጥ አንድ ዓመት ከሰራ እና መስፈርቱን ካሟላ
የደረጃ ዕድገት ሊወዳደር ይችላል፡፡
9.4.16 በአንድ የስራ መደብ ላይ በደረጃ እድገት የተመደበ ሰራተኛ ከ3 ወር በፊት ቢለቅ
የደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ ቀደም ሲል በዚህ የስራ መደቡ ላይ
ተወዳድረው ከነበሩት ሰራተኞች መካከል የማለፊያ ነጥብና በላይ ካመጡት ውስጥ
በውጤታቸው ቅደም ተከተል መሰረት የደረጃ ዕድገቱ ይሰጣል፡፡
9.4.17 በአንድ የስራ መደብ ላይ ተወዳድሮ ከማለፊያ ነጥብ በታች ያመጣ (የወደቀ) ተወዳዳሪ
በዚሁ የስራ መደብ ላይ በድጋሚ መወዳደር የሚችለው ውጤቱ ከታወቀ ከ3 ወር በኋላ
ነው፡፡
9.4.18 በማንኛውም በድርጅቱ ውስጥ በሚሰጠው የደረጃ እድገት ቅሬታ ያለው ህጋዊ በሆነ
መንገድ ቅሬታውን በወቅቱ በ3 (ሶስት) የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡
9.4.19 በዚህ የህብረት ሥምምነት ስለቅጥርና ደረጃ እድገት የተገለፁትን በማያፈርስና
በማይቃወም ሁኔታ ሌሎች ያልተጠቀሱ ዝርዝር የዝውውር፣ የደረጃ እድገት እና

19
የቅጥር አፈፃፀሞች በድርጅቱ የሰው ሀብት አስተዳደር ወይም የምልመላና መረጣ
መመሪያ መሠረት የሚፈፀሙ ይሆናል፡፡

9.5 የውስጥ ዝውውር


9.5.1 ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ የሠራተኛ ዝውውር የሚያደርገው ሥራና ሠራተኛን
ለማገናኘት የድርጅቱን ሥራ ለማሳደግና ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ ባለው ዓላማ
ወይም ተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ እንዲሁም ተፈላጊ ችሎታ መስፈርት ባለው የስራ
መደብ ሰራተኛው በሚያቀርበው የዝውውር ጥያቄ መሠረት ድርጅቱ ሲስማማ ብቻ
ይሆናል፡፡ ሆኖም ደረጃው ተመሳሳይ ሆኖ ደመወዙ የበለጠ ቢሆን ለዝውውር
ከመወዳደር አያግድም፡፡
9.5.2 ለስራው አስፈላጊ መሆኑ በአሰሪው ከታመነበት ሰራተኛን ከአንድ የስራ መደብ ወደ ሌላ
ተመሳሳይ የስራ መደብ ወይም ቦታ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት በያዘው
ደመወዝና ደረጃ አዛውሮ ማሰራት ይቻላል፡፡ ሆኖም ለቦታው የተመደበ ጥቅማጥቅም ካለ
ከተዛወረበት ወይም ከተመደበበት ቀን ጀምሮ ታስቦ ይከፈለዋል፡፡
9.5.3 ድርጅቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ወይም ጥያቄው በሰራተኛው ቀርቦ በድርጅቱ
ከታመነበት ይህን ህብረት ስምምነትና አግባብ ያላቸው ህጎችን ሳይቃረን ሰራተኛው
ቀድሞ የሚያገኘውን ደመወዝና የስራ ደረጃ ሳያጎድል አዛውሮ ሊያሰራው ይችላል፡፡ ነገር
ግን ከአንድ የስራ ቦታ ወደ ሌላ የስራ ቦታ በቋሚነት ማዛወር የሚቻለው ይህን ህብረት
ስምምነትና አግባብ ያላቸው ህጎችን ሳይቃረን ለስራው አስፈላጊ መሆኑ በድርጅት ደረጃ
ታምኖበት በድርጅቱ ስራ አመራር ኮሚቴ ሲወሰን ነው፡፡
9.5.4 አንድ ሠራተኛ ካለበት የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ በቋሚነት ሲዛወር ለራሱና
አብሮት ለሚሄደው ቤተሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅቱ ይሰጠዋል፡፡ ድርጅቱ
የትራንስፖርት አገልግሎት ለማዘጋጀት በማይችልበት ጊዜ የመድረሻ ትራንስፖርት
ወጪ፣ ውሎ አበልና እስከ 800 ኪሎ ግራም የሚመዝን የቤት ዕቃ በወቅቱ ሕጋዊ የየብስ
ትራንስፖርት ታሪፍ መሠረት ለሠራተኛው ይከፍላል፤ ሆኖም በራሣቸው ጠያቂነትና
ፍላጐት የሚዛወሩ ሠራተኞች የውሎ አበልና የትራንስፖርት ወጪ አይከፈላቸውም፡፡
9.5.5 አንድ ሰራተኛ ከአንድ የስራ መደብ ወደ ሌላ የስራ መደብ ለመዛወር በመጀመሪያ
በተዛወረበት ወይም በተቀጠረበት ወይም ባደገበት የስራ መደብ ላይ ቢያንስ 6 ወራት
የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡

20
9.5.6 በኤች አይቪ /ኤድስ/ በደሙ ውስጥ ለመኖሩ ማስረጃ ያቀረበ ሰራተኛ ወደ ሚስማማው
ወይም ቤተሰብ ወዳለበት ቦታ ዝውውር ሲጠይቅ ቦታ እስካለ ድረስ ቅድሚያ ተሰጥቶት
እንዲዛወር ይደረጋል፡፡

9.6 ትምህርትና ሰልጠና


9.6.1 ሰራተኛው በሙያው፣ በዕውቀቱና በችሎታው ተሻሽሎ ለተመደበበት ሥራ ብቁ ሆኖ
እንዲገኝ ድርጅቱ አስፈላጊውን እገዛ ያደርግለታል፡፡ ለዚህም ድርጅቱ ዕቅድ በመያዝ
ሰራተኛው እንዲማር ያደርጋል፡፡
9.6.2 ድርጅቱ እንዲማሩ ወይም እንዲሰለጥኑ የሚፈቅድላቸው ሠራተኞች ድርጅቱ በነፃ
በሚያገኘው ትምህርት ወይም ድርጅቱ በሚፈልገው የሙያ መስክ ሲሆን አፈፃፀሙ
በትምህርትና ሥልጠና መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
9.6.3 ድርጅቱ ልዩ ልዩ የሙያ ማሻሻያ ሴሚናር ለሰራተኛው ይሰጣል፡፡ እንዲሁም የድርጅቱን
ሥራ፣ ሙያና የተቋቋመበትን ክፍለ ኢኮኖሚ የሚገልጽ ትምህርታዊ የሆነ መጽሔት
ያዘጋጃል፡፡
9.6.4 ሠራተኛው በግሉ የውጭ አገር ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ ድርጅቱ ለሚመለከተው
አካል የጽሁፍ ማስረጃ (በድርጅቱ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ስፖንሰርነትን አይጨምርም)
እንዲሰጥለት ሲጠይቅ ይጽፍለታል፡፡ ትምህርቱም ለድርጅቱ ሥራ ጠቃሚ መሆኑን
የድርጅቱ ማኔጅመንት ከዕቅዱ ጋር አገናዝቦ ለድርጅቱ ስራ አመራር ቦርድ አቅርቦ
በማስፀደቅ እንዲማር ይፈቅድለታል፡፡ ሰራተኛውም በድርጅቱ ስልጠና መመሪያ መሰረት
በቅድሚያ የስልጠና ውል የመግባት ግዴታ ይኖርበታል፡፡
9.6.5 በድርጅቱ ድጋፍ ከመጀመሪያ ዲግሪ እና በላይ ተምሮና ተመርቆ የትምህርት
ማስረጃውን ላቀረበ ሰራተኛ የትምህርት ማስረጃውን ካቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ሰራተኛ
ከያዘው የስራ መደብ ደረጃ አንድ ደመወዝ ደረጃ ከፍታ ከፍ ያለና የሚያሟላ ክፍት
የስራ መደብ ካለ በዚሁ የስራ መደብ ላይ የአንድ ደረጃ ጭማሪ ተደርጎለት ይመደባል፡፡
የሚያሟላ ክፍት የስራ መደብ ከሌለ በያዘው ደመወዝ ደረጃ ከፍታ ወደ ጎን 3 (ሶስት)
እርከን ደመወዝ ጭማሪ ይደረግለታል፡፡ የደመወዝ ጣሪያ እርከን ከደረሰ ግን ጭማሪ
አይደረግለትም፡፡ ይህ ጭማሪ መደበኛውን የእርከን ጭማሪውን አያግድም፡፡
9.6.6 ሰራተኛው ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ በግሉ ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ትምህርት
ለመማር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ድርጅቱን ጠይቆና ድርጅቱም የሚማረው
የትምህርት ዓይነት ለድርጅቱ ጠቃሚ መሆኑን አይቶ ከፈቀደለት ትምህርት አጠናቆ/
ተመርቆ የትምህርት ማስረጃውን ካቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከያዘው የስራ መደብ ደረጃ
21
አንድ ደመወዝ ደረጃ ከፍታ ከፍ ያለና የሚያሟላ ክፍት የስራ መደብ ካለ በዚሁ የስራ
መደብ ላይ የአንድ ደረጃ ጭማሪ ተደርጎለት ይመደባል ከሌለ በያዘው ደመወዝ ደረጃ
ከፍታ ወደ ጎን 3 (ሶስት) እርከን ደመወዝ ጭማሪ ይደረግለታል፡፡ የደመወዝ ጣሪያ
እርከን ከደረሰ ግን ጭማሪ አይደረግለትም፡፡ ይህ ጭማሪ መደበኛውን የእርከን
ጭማሪውን አያግድም፡፡
9.6.7 ድርጅቱ የሠራተኛውን የእውቀት አድማስ ለማስፋት በዋናው መሥሪያ ቤት ቤተ
መጽሐፍት (ላይብራሪ) ያቋቁማል፡፡
9.6.8 ድርጅቱ የትምህርት ወጭ የሚሸፍነው ሰራተኛው በሚያቀርበው የፈተና ውጤት መሰረት
ወደ ሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ ማለፉን የሚያረጋግጥ የውጤት ማስረጃ ሲያቀርብ
ነው፡፡ ሆኖም ዝቅተኛ ውጤት በማምጣትም ሆነ በማንኛውም ምክንያት ድጋሜ
ለሚወሰዱ ኮርሶች ድርጅቱ ወጭ አይሸፍንም፡፡
9.6.9 የድርጅቱ ማኔጅመንት በልዩ ሁኔታ አይቶ ካልወሰነ በስተቀር የትምህርት ወጪ
የሚሸፈነው ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) ቅጥር ሰራተኞች ብቻ ነው፡፡
9.6.10 የትምህርት ዕድል አግኝቶ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሰራተኛ ግዴታውን ሳይጨርስ ሌላ
ትምህርት መጀመር አይችልም፡፡

አንቀጽ አስር (10) የሥራ መታወቂያ ደብተር


10.1 ለማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኞች የሙከራ ጊዜውን እስከሚጨርስ ድረስ ጊዜያዊ
መታወቂያ ሲገለገል ቆይቶ ቋሚ ሲሆን መታወቂያው ተሰርቶ ይሰጠዋል።
10.2 ማንኛውም ሠራተኛ የድርጅቱ መታወቂያ ቢጠፋበት በአቅራቢያው ለሚገኘው የፖሊስ
ጣቢያ ወይም ፍ/ቤት አስታውቆ መመዝገቡን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲያቀርብ
የማሳተሚያውን ወጭ ከፍሎ ሌላ መታወቂያ ካርድ መውሰድ ይችላል።
10.3 ማንኛውም ሠራተኛ የሥራ ውል ሲያቋርጥ የድርጅቱን መታወቂያ ይመልሳል።
10.4 ሠራተኛው በደረጃ እድገት ወይም በምደባ ወይም በዝውውር የሥራ መደብ መጠሪያ
ለውጥ ሲደረግለት ይህንኑ የሚገልጽ አዲስ መታወቂያ ይሰጠዋል። ነባሩንም መታወቂያ
ይመልሳል።
10.5 ሰራተኛው መታወቂያው ቢሰበር ወይም ቢበላሽ የማሳተሚያውን ከፍሎ ሌላ መታወቂያ
ይስራለታል።

22
አንቀፅ አስራ አንድ (11) የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሁኔታ
11.1 የማንኛውም ሠራተኛ የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 እና በዚህ የህብረት ስምምነት መሰረት ይሆናል፡፡
11.2 ሠራተኛው ከድርጅቱ ከሚፈለግበት ንብረት ወይም ገንዘብ ነፃ ስለመሆኑ ድርጅቱ
ባዘጋጀው የማረካከቢያ ወይም ክሊራንስ ቅጽ የሚመለከታቸው ክፍሎችን አስፈርሞ
እንዳመጣ የአገልግሎት የምስክር ወረቀትና ሌሎች ለሠራተኛው የሚገቡት ክፍያና
ጥቅሞች በሰባት (7) ቀናት ጊዜ ውስጥ ተሟልተው ይሰጡታል፡፡
11.3 የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ ከማንኛውም ዕዳ ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥና የሥራ ምስክር
ወረቀት እንዲሰጠው በጽሁፍ ሲጠይቅ የሚሰጠው የሥራ የምስክር ወረቀት በአማርኛና
በሰራተኛው ፍላጎት በእንግሊዝኛ ጭምር የሠራተኛውን ሙሉ ሥም ከነአያቱ፣ በድርጅቱ
የሰራባቸውን የሥራ አይነቶችና የሠራባቸውን ቦታዎች፣ የመጨረሻ ወር ደመወዙን፣
ሠራተኛው በድርጅቱ ውስጥ በሰራባቸው ጊዜያት የሥራ ግብርና ሌሎች መዋጮዎችን
መክፈሉን፣ የቅጥሩን ሁኔታና እንደአስፈላጊነቱ ሰራተኛው የሥራ ውሉ የተቋረጠበትን
ሁኔታ በመጥቀስ ይፃፍለታል፤ የድርጅቱ ማህተምም ይታተምበታል፡፡ ሰራተኛው በተለያየ
መ/ቤት የሰራበት ወይም በተለያየ የስራ መደብ ተቀጥሮ ወይም ተወክሎ ወይም ደርቦ
የሰራ እና ስለመስራቱ ከማህደሩ መኖሩ ሲረጋገጥ ይኸው ተገልፆ የስራ ልምዱ
ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ሠራተኛውን የሚጐዳ አስተያየት በስራ ልምድ ማስረጃ ላይ
አይገለጽም፡፡

23
ክፍል ሦስት
አንቀጽ አሥራ ሁለት (12) ስለ መደበኛ የሥራ ሰዓት
12.1 የማንኛውም ሠራተኛ መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ8 ሰዓት በሣምንት ከ48 ሰዓት
መብለጥ የለበትም፤
12.2 የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ከሰኞ እሰከ ሀሙስ
ከሰኞ እሰከ ሀሙስ ጧት ከ2:30-6:30
ከሰዓት ከ7:30-11:30 ይሆናል፡፡
አርብ ጧት ከ2:30-5:30
ከሰዓት ከ7:30-11:30
ቅዳሜ ጧት ከ2:30-6:30 ይሆናል፡፡
ከሰዓት ከ7:30-11:30 ብቻ ይሆናል፡፡
12.3 ከላይ በተ.ቁ 12.2 የተጠቀሰው ቢኖርም ከመስክ ስራና ከፕሮጀክት በስተቀር የድርጅቱ
ዋናው መ/ቤት እና የምዕራብ አማራ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኝበት ባህርዳር ከተማ እንዲሁም
የምስራቅ አማራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚገኝበት ደሴ ከተማ ቅዳሜ ቀን መደበኛ የቢሮ
መግቢያና መውጫ ሰዓት ጧት ከ2:30-5:30 ይሆናል፡፡ ሆኖም ቅዳሜ ከሰዓት ከ7:30-
11:30 ሥራ ኖሮ ማንኛውንም የድርጅቱን ሠራተኛ ሥራ እንዲገባ ሲጠየቅ የመግባት
ግዴታ አለበት፡፡ በዚህም መሠረት የሰራተኛ የቅርብ ሀላፊ ሠራተኞችን በግል፣ በከፊልና
ሙሉ በሙሉ ሥራ ካለው እንዲገቡ ማድረግ ይችላል፡፡ የሚገቡ ሠራተኞችንም የቅርብ
ኃላፊው አስቀድሞ መንገር ይገባዋል፡፡
12.4 ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በምንም ሁኔታ የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማይጠየቅበት ነው፡፡
12.5 ለድርጅቱ ሥራ ሲባል በሳምንት የሚሰራበትን ጠቅላላ የሥራ ሰዓት መጠን ሳይጨምር
የመግቢያና የመውጫ ሰዓት ሊለወጥ ይችላል፡፡
12.6 በመስክ የሚሠሩ ወይም/ እና የፕሮጀክት ሠራተኞች የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
ሆኖ ከ48 ሰዓት ሳይበልጥ ቅዳሜ ሙሉ ቀን እንደመደበኛ የሥራ ሰዓት ተቆጥሮ እንዲሰሩ
ይደረጋል፡፡ የመግቢያና የመውጫ ሰዓት እንደስራው ባህሪና እንደ አካባቢው የአየር
ጠባይ ድርጅቱና ማህበሩ ተስማምተው በሚያወጡት የሥራ መግቢያና መውጫ መሠረት
ይሆናል፡፡
12.7 የጥበቃ ሠራተኞች የሚሰሩበት የሥራ ሰዓት በአማካይ በቀን 8፡00 ሰዓት በሳምንት
48፡00 ሰዓት የማይበልጥ ይሆናል፡፡

24
12.8 ድርጅቱ ለሰራተኞች የሻይ ዕረፍት የሚሆን ከመደበኛ የስራ ሰዓት የሚቆጠር በቀን 30
ደቂቃ ዕረፍት ይሰጣል፡፡ ይኸውም ጧት 4.15 እስከ 4.30 አስራ አምስት ደቂቃ ከስዓት
9.30-9.45 አስራ አምስት ደቂቃ ይሆናል፡፡
12.9 የተለየ የስራ ባህሪ ካላቸው የስራ መደቦች ላይ ተመድበው ከሚሰሩ ሰራተኞች በስተቀር
የድርጅቱ ሰራተኞች የሳምንት ዕረፍት ቀን እሁድ ይሆናል፡፡ የሣምንት የዕረፍት ጊዜ
ለድርጅቱ ሠራተኞች በሙሉ በአንድ ላይና በአንድ ጊዜ ይሰጣል፤ ይሁን እንጅ በሥራ
ፀባያቸው ምክንያት በፈረቃ ወይም በሽፍት የሚሠሩ ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በአዋጅ
ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 64 መሠረት መደበኛ የሥራ ሰዓቶችን አማካይ በማድረግ
የሚደለደል ሲሆን የዕረፍት ጊዜያቸውም በሚወጣው የሥራ ፕሮግራም ድልድል መሠረት
ይሆናል፡፡
12.10 ወላድ ሴት ሰራተኞች የወለዱት ህፃን አንድ ዓመት እስኪሞላው ድረስ ጡት አጥብተው
ስራ ለመግባት እንዲችሉ የምሳ መውጫ ሰዓታቸው 6፡00 እና መግቢያ ሰዓታቸው 8፡00
ይሆናል፡፡ ይህ የሚሆነው ድርጅቱ የራሱን የህፃናት ማቆያ አገልግሎት እስኪያቋቁም
ድረስ ነው፡፡

አንቀጽ አሥራ ሶስት (13) የትርፍ ሰዓት የሥራ ክፍያ


13.1 ትርፍ ሰዓት ለሚሠራ ሠራተኛ ድርጅቱ በምሽት የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አሥራ አራት (14) የሕዝብ በዓላት


14.1 መንግሥት በሚያወጣቸው ህጎች መሰረት ለሚከበሩ የህዝብ በዓላት ቀናት ሠራተኛው
ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡
14.2 በስራ ባህሪያቸው ምክንያት በህዝብ በዓላት ቀን ተረኛ ሆነው ስራ ለሚገቡ የጥበቃ
ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 75 መሰረት
ተገቢው ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡

አንቀጽ አሥራ አምስት (15) ልዩ ልዩ ፈቃዶች


15.1 የዓመት ፈቃድ
15.1.1 በድርጅቱ አንድ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ 20 (ሀያ) የሥራ ቀኖች ከደመወዝ ጋር
ያገኛል፡፡
15.1.2 በድርጅቱ ከአንድ አመት በታች ያገለገለ ሰራተኛ የሰራባቸው ወሮች ታሰቦ በአገልግሎቱ
ልክ ተመጣጣኝ የሆነ ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡

25
15.1.3 ሰራተኛው የስራ ልምድ በሚጠይቅ የስራ መደብ ላይ ሲቀጠር በቅጥር ወቅት/ ጊዜ
ያስያዘው በሌላ መ/ቤት የሰጠው አገልግሎት ወይም የስራ ልምድ ካለ እስከ 10 (አስር)
ዓመት ድረስ ብቻ ለእያንዳንዱ ሁለት የአገልግሎት ዓመታት አንድ የስራ ቀን
እየተጨመረ ይያዝለታል፡፡ ሆኖም የስራ ልምድ በማይጠይቅ (ዜሮ ዓመት) የስራ
መደብ ላይ የተቀጠረ ከሆነ የስራ ልምዱ ለዓመት ፈቃድ አሰላል ጥቅም ላይ
አይውልም፡፡
15.1.4 በደርጅቱ ከአንድ ዓመት በላይ ላገለገለ ሠራተኛ በተራ ቁጥር 15.1.1 እና 15.1.3
የተመለከተው እንዳለ ሆኖ በድርጅቱ ለሰራበት ለእያንዳንዱ ሁለት የአገልግሎት
ዓመታት አንድ የስራ ቀን እየተጨመረ ያገኛል፡፡ የ2011 እና የ2012 በጀት ዓመት
ፈቃድ በነበረው አግባብ የሚሰላ ሆኖ የ2013 በጀት ዓመት በዚህ ህብረት ስምምነት
መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
15.1.5 ሰራተኛው ከሌላ መ/ቤት ያልተጠቀመበት የአመት ፈቃድ ቢኖርው ደርጀቱ
ስላልተጠቀመበት ፈቃድ አይመለከተውም፡፡
15.1.6 በእረፍት ላይ ያለ ሠራተኛ ከዕረፍቱ ላይ ለሥራ ሲጠራ በሠራተኛው ምርጫ በገንዘብ
ሊተካለት ወይም ሊተላለፍለት ይችላል፡፡ ይህም ሲሆን የነበረበት ሥፍራ ከመደበኛ
የሥራ ቦታው ውጭ ከሆነ ወደ መደበኛ የሥራ ቦታው ሲመለስ እንዲሁም እረፍቱን
እንደገና እንዲቀጥል ሲደረግ በድርጅቱ መመሪያ መሠረት የትራንስፖርት ወጪና የጉዞ
ቀናት የውሎ አበል ይከፈለዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተቋረጠ እረፍቱ ለመቀጠል ካልፈለገ
እረፍቱ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል፡
15.1.7 የድርጅቱንና የሠራተኛውን ጥቅሞች በማስማማት የዓመት እረፍት ከዓመቱ ውስጥ
በድርጅቱ ፈቃድ በአንድ ላይ ወይም በሁለት ጊዜ ከፋፍሎ ምቹ በሆነ ወራት
ይወሰዳል፡፡ ድርጅቱ ከሠራተኛው ጋር በመመካከር የዓመት ፈቃዳቸውን መቼ
እንደሚወስዱ የሚያሳይ ሠንጠረዥ ያዘጋጃል፡፡ ሆኖም የድርጅቱና የሠራተኛው የጥቅም
ግጭት ከተፈጠረ የድርጅቱ ጥቅም ቅድሚያ ይኖረዋል፡፡ ሰራተኛው ባለመጠየቁ
ምክንያት በእቅዱ መሰረት እረፍት ካልወሰደ ድርጅቱ በፈለገው ጊዜ ሰራተኛው
እረፍቱን እንዲወስድ ያደርጋል፡፡
15.1.8 አንድን ሰራተኛ በሥራው ባህሪ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የሚሰራው ስራ ከሌለው
ድርጅቱ አስቀድሞ የ5 (አምስት) ቀናት ማስጠንቀቂያ በመስጠት የዓመት ፈቃድ
መስጠት ይችላል፡፡

26
15.1.9 የዓመት ፈቃድ አቆጣጠር የሕዝብ በዓላትን እና የሳምንት የእረፍት ቀንን ማለትም
ቅዳሜ ከሰዓት በኋላና እሁድን አይጨምርም፡፡
15.1.10 የዓመት ፈቃድ የተሰጠው ሠራተኛ በደመወዝ ክፍያ ወቅት የአመት ፈቃድ ላይ
በመሆኑ የቅድሚያ ደመወዝ ክፍያ የሚጠይቅ ከሆነ ደመወዙንም ጭምር ከፈቃዱ ጋር
መውሰድ ይችላል፡፡
15.1.11 ሰራተኛው ከድርጅቱ ምንም ዓይነት ሀላፊነት/ ተጠያቂነት ሳይኖርበት በህጋዊ መንገድ
ስራ ሲለቅ ወይም ሲሰናበት ያልተጠቀመበት ህጋዊ ቀሪ የዓመት ዕረፍት ቀናት ካለው
በህጉ መሰረት በገንዘብ ተቀይሮ ይሰጠዋል፡፡
15.1.12 በመደበኛ /በቀን/ በክረምት ፕሮግራም ስራ ትተው እንዲማሩ የተፈቀደላቸው
ሰራተኞች በትምህርት ቆይታ ላይ እያሉ ወይም ለትምህርት ቆይታ ጊዜው የዓመት
ዕርፍት ፈቃድ አይታሰብላቸውም፡፡
15.1.13 በየበጀት ዓመቱ በድርጅቱ የሥራ ባህሪ ምክንያት በክረምት/ በአየር ፀባይ ችግር
ምክንያት ፕሮጀክት ሲዘጋ የፕሮጀክት ሰራተኞች (የተሽከርካሪ ኦፕሬተሮችን ጨምሮ)
በዋናው መ/ቤት ወይም ሌላ በክረምት ወቅት ባልተዘጋ ፕሮጀክት ላይ ለሥራ
እስካልተፈለጉ ድረስ ያልተጠቀሙበትን የዓመት ፈቃድ ቀናት እንዲወስዱ
ይደረጋል፡፡

15.2 የሕመም ፈቃድና የክፍያ ሁኔታ


15.2.1 የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ማንኛውም ሠራተኛ ቢታመም በመንግስት ዕውቅና
ከተሰጣቸው ከመንግሥትና ከግል ህክምና ተቋማት የሐኪም ፈቃድ ሲያገኝ የህክምና
ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም የሚሰጠው የፈቃድ ቀናት ብዛት የሚወሰነው ለሕክምና
ባለሙያዎች እንደሙያቸው ደረጃ በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ወይም በክልሉ
የጤና አጠባበቅ ቢሮ በተወሰነው መሰረት ይሆናል፡፡
15.2.2 ማንኛውም ሰራተኛ የህመም ፈቃድ የሚያገኘው በመንግስት በታወቀ የህክምና
ድርጅቶች ማለትም ከመንግስት ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያና ክሊኒክ ወይም ከግል ህጋዊ
የህክምና ተቋም ተገቢ የሆነ ህጋዊነት ያለው የህክምና የምስክር ወረቀት ሲያቀርብ
ነው፡፡
15.2.3 የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ማንኛውም ሠራተኛ ቢታመምና ይኸውም ከማናቸውም
የመንግስትና የግል ህጋዊ የህክምና ድርጅቶች ተገቢ የሆነ የሕክምና የምስክር ወረቀት
ማቅረቡ ሲረጋገጥ ህመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው በ1 (በአንድ)
ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት በሪኮርድ የተያዘው ተደምሮ
27
የሚሰጠውም የሕመም ፈቃድ ከ10 (አስር) ወራት አይበልጥም፡፡ ለህመም ፈቃድ
የደመወዝ ክፍያ አፈፃፀምም፡-
ሀ) ለመጀመሪያ 3 (ሶስት) ወራት ሙሉ ደመወዝ፣
ለ) ለሚቀጥለው 3 (ሶስት) ወራት 75% ደመወዝ፣
ሐ) ለሚቀጥለው 2 (ሁለት) ወራት 50% ደመወዝ፣
መ) ለሚቀጥለው 2 (ሁለት) ወራት ደመወዝ የማይከፈልበት የሕክምና ፈቃድ
ይሰጠዋል፡፡ ከዚህ በኋላ የማይሻለው ከሆነ ውሉ ይቋረጣል፡፡
15.2.4 የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ህሙማን የሆኑ ሠራተኞች በሀኪም የተረጋገጠና ይህንኑ ማስረጃ
ላቀረቡ ሰራተኞች ህመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ባለው በ1 (በአንድ)
ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት በሪኮርድ የተያዘው ተደምሮ
የሚሰጠውም የሕመም ፈቃድ ከ1 (አንድ) ዓመት አይበልጥም፡፡ ለህመም ፈቃድ
የደመወዝ ክፍያ አፈፃፀምም፡-
ሀ. ለመጀመሪያ 6 (ስድስት) ወራት ሙሉ ደመወዝና ለቀሪዎች፣
ለ. ለሚቀጥሉት 3 (ሶስት) ወራት ደግሞ 75% ደመወዝ፣
ሐ. ለሚቀጥሉት 3 (ሶስት) ወራት 50% ደመወዝ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡ ከዚህ
በኋላ የማይሻለው ከሆነ የሥራ ውሉ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
15.2.5 ማንኛውም ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ አደጋ ሲደርስበት ይህም በመንግስት ወይም
በታወቀ ህክምና ተቋም ሲረጋገጥ፤
ሀ) ጊዜያዊ የአካል ጉዳቱ እስከሚወገድ የመጀመሪያ 12 ወራት ሙሉ ደመወዝ
ለ) ለሚቀጥለው 6 ወራት ግማሽ ደመወዝ የሚከፈልበት የሕክምና ፈቃድ ያገኛል፡፡
ከዚህ በኋላ ሠራተኛው ድኖ ሥራውን መቀጠል አለመቻሉ በሀኪም ሲረጋገጥ
የጡረታ መብቱን በማስከበር ወይም የሥራ ሥንብት ክፍያውን በመክፈል የሥራ
ውሉ እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡
15.2.6 ሰራተኛው ከስራው ጋር ግንኙነት በሌለው ህመም ምክንያት ወደ ሌላ የህክምና ቦታ
ሄዶ እንዲታከም በሐኪም ሲታዘዝ ሐኪሙ ካዘዘው ቀን ማግስት ጀምሮ ለደርሶ መልስ
እንደቦታው ርቀት ከ3 (ሶስት) ቀናት ያልበለጠ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሰጠዋል በሚያቀርበው የህክምና ማሰረጃ መሰረት የህክምና ክፍያ እና የትራንስፖርት
ወጭ ይከፈለዋል፡፡

28
15.3 የአስታማሚ ፈቃድ
በድርጅቱ የምትሰራ ወይም የሚሰራ ሰራተኛ ህጋዊ ባል፣ ሚስት፣ ልጅ፣ እናት እና አባት

ለሆኑት በህጋዊ ህክምና ተቋም ተኝተው ለሚታከሙና ይህንን የሚገልጽ ማስረጃ ካቀረቡ 2
(ሁለት) ቀን የአስታማሚ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ተኝቶ የሚታከመው የሴት ሰራተኛዋ
ከአንድ ዓመት በታች የሆነ ህፃን ከሆነ ለሰራተኛዋ በምታቀርበው ህጋዊ የሀኪም ማስረጃ
መሰረት የ5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ይሰጣታል፡፡

15.4 የወሊድ ፈቃድ


የወሊድ ፈቃድን አስመልክቶ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 88
የተደነገገው ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም
15.4.1 ሰራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች
ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት
ይደረጋል፡፡
15.4.2 ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ
እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የምትቆይበት እረፍት በበጀት ዓመቱ
ካላት የዓመት እረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት እረፍት ፈቃድ የሌላት
እንደሆነ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት የእረፍት ፈቃዷ ይተካል፡፡
15.4.3 ሠራተኛዋ የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ
የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ የህመም ፈቃድ ትወስዳለች፡፡
15.4.4 ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ

ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ


ስታቀርብ ፅንሱ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ የ30 (ሰላሳ) ተከታታይ ቀን የድህረ ወሊድ
ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
15.4.5 የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ

ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ ጽንሱ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ የ45 (አርባ


አምስት) ተከታታይ ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
15.4.6 የድርጅቱ ሰራተኛ የትዳር ጓደኛው ከወሊድ ጋር በተያያዘ ባለቤቱን ለመንከባከብ
ደመወዝ የሚከፈልበት 5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ይህ
ተግባራዊ የሚደረገው ከሰራተኛው የግል ማህደር ላይ ባለትዳር መሆኑን የሚያረጋግጥ
ማስረጃ ሲኖር ነው፡፡ ሆኖም ፈቃዱ ባለቤቱ በወለደች በ10 (አስር) ቀናት ጊዜ ውስጥ
ካልተወሰደ ቀሪ ይሆናል፡፡
29
15.5 የሀዘን ፈቃድ
15.5.1 የሠራተኛው የትዳር ጓደኛ፣ የሠራተኛው ወይም የትዳር ጓደኛው ልጅ፣ እናት፡ አባት፣
ወንድም ወይም እህት ለ5 (አምሰት) የስራ ቀኖች እንዲሁም አያት፣ አጎት፣ አክስት፣
የእህት ልጅ፣ የወንድም ልጅ እንዲሁም ከነዚህ ሌላ ከመኖሪያ ቤቱ ሰው ሞቶ አስክሬን
ከቤት ሲወጣ ለ3 (ሦስት) የሥራ ቀኖች ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
15.5.2 የተጠየቀው የሐዘን ፈቃድ ትክክለኛ ሆኖ ባይገኝ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡
15.5.3 ሰራተኛው/ዋ ሲሞት ከየክፍሉ የተውጣጡ ሰራተኞች በቀብሩ ስነ-ስርዓት ላይ እንዲገኙ
የቀብሩ ስነ-ስርዓት እስኪፈፀም ድረስ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ በቀብር
ስነስርአቱ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች ድርጅቱ ሠርቪስ መኪና ይመድባል፡፡ ይህም
የሚሆነው የቀበሩ ስነ-ስርዓት በድርጅቱ ፅ/ቤት በሚገኝበት ስፍራ ሲፈፀም ነው:፡
15.5.4 በዚህ የህብረት ስምምነት አንቀፅ 15.5.1 ላይ በተጠቀሰው ሀዘን ምክንያት ከስራ ቦታው
ውጭ የሚሄድ ከሆነ በአንቀፅ 15.5.1 ከተፈቀደው የሀዘን ፈቃድ በተጨማሪ ለጉዞ ደርሶ
መልስ እንደ ቦታው ርቀት ከ6 ተከታታይ ቀናት ያልበለጠ ደመወዝ የሚከፈልበት
ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
15.5.5 ሟች ቤተሰብ ሆኖ ሬሳ ከቤቱ የሚወጣ ከሆነ አሰከሬኑን የሚያደርስ አንድ መኪና
ይመደባል፡፡
15.5.6 የሀዘን ፈቃድ ለመስጠት ሰራተኛው አስቀድሞ የቤተሰብ ፎርም ሞልቶ ከግል ማህደሩ
ጋር ያላያያዘ ከሆነና ቀብሩ የሚፈጸመው ከሚሰራበት ቦታ/ ከተማ ውጭ ከሆነ ማስረጃ
ከእድር/ ከማህበራዊ ፍርድ ሸንጎ/ የቀብር ስነ ስርዓቱ ከተፈጸመበት ተቋም/ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ተግባራዊ አይደረግም፡፡ ፈቃድ አይሰጥም፡፡
15.5.7 ሟች ሰራተኛ የቀብር ስነ-ሥርዓቱ የሚፈፀመው ከመደበኛ የሥራ ቦታው ወይም
ከሞተበት አካባቢ ውጭ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት የሚሄድ ከሆነ አስከሬኑን አጅበው
ለሚሄዱ አራት ሰራተኞች አድርሰው እንዲመጡ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ የቀኑ ብዛት በቦታው
እርቀት ይወሰናል፡፡
15.5.8 በኘሮጀክት ሥራ ላይ የሚሰራ ሰራተኛ ቤተሰብ ሞቶበት ጥሪ ከደረሰው ኘሮጀክቱ
ሰርቪስ መኪና ካለው አዘጋጅቶ የህዝብ ትራንስፖርት እስከሚገኝበት ቦታ ድረስ
ያደርሰዋል፡፡

30
15.6 የትምህርት ፈቃድ
15.6.1 ሠራተኛው በትርፍ ጊዜው በሚከታተለው ትምህርት ፈተና የሚሰጠው በሥራ ሰዓት
ከሆነ ሠራተኛው በሚያቀርበው ማስረጃ መሠረት ድርጅቱ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ
ይሰጠዋል፤
15.6.2 ድርጅቱ ፕሮግራም ይዞ ከሚያሰተምረው ውጭ እየተማረ ያለ ሰራተኛ ከተገኘ
የድርጅቱን የስራ ስዓት በድሎ ከሆነ ለዲስፕሊን ቀርቦ እንዲወሰንበት ይደረጋል፡፡
15.6.3 በድርጅቱ ተፈቅዶ በማታው ክፍለ ጊዜ የዲግሪ ትምህርቱን የሚከታተል ሰራተኛ
ኮርሱን ለማጠናቀቅ በሚቀረው የ1 (አንድ) ዓመት የመጨረሻ ትምህርት ኮርሱ
የሚሰጠው በቀን መሆኑ በተቋሙ ሲረጋገጥ ኮርሱ ለሚፈጀው ጊዜ ሙሉ ቀን ፈቃድ
ከሙሉ ደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡

15.7 የጋብቻ ፈቃድ


ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ የጋብቻ ስነ ስርአቱን በሚፈጽምበት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ
የ5 (አምስት) ለሁለተኛና ከዚያ በላይ ከሆነ የ3 (ሶስት) የስራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ለዚህም
የጋብቻ ሰርተፊኬት ያቀርባል፡፡

15.8 ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ


15.8.1 ሠራተኛው የተጠራቀመ የዓመት ዕረፍት ከመጠቀሙ በፊት ደመወዝ የማይከፈልበት
ፈቃድ አይሰጠውም፡፡
15.8.2 ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ እንደጉዳዩ ክብደት እየታየ በድርጅቱ ዋና ስራ
አስፈፃሚ ይሰጣል፡፡ ሰራተኛው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም ችግር
ሲደርስባቸው የዓመት እረፍታቸውን ጨርሰው ድርጅቱ ሲያምንበት በዓመት ከ30
ቀናት ያልበለጠ ያለደመወዝ (ነፃ) ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡

15.9 ልዩ ፈቃድ
ማንኛውም የዓመት ፈቃዱን የጨረሰ ሠራተኛ ልዩና አሳሳቢ ሁኔታ ሲያጋጥመውና ለዚህም
ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ደመወዝ የሚከፈልበት በተከታታይ ከሁለት ቀን ያልበለጠ በዓመት
ውስጥ በአጠቃላይ ከሦስት ቀናት ያልበለጠ ልዩ ፈቃድ ድርጅቱ ሲያምንበት ይሰጠዋል፡፡

31
አንቀጽ አስራ ስድስት (16) ደመወዝና የደመወዝ ብድር
16.1 የደመወዝ ክፍያ ቀን በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር በወሩ መጨረሻ ከ25ኛው አስከ 28ኛው
ቀን ይከፈላል፡፡ ሆኖም የሕዝብ በዓላት ሲኖሩ ድርጅቱ በዓሉ የሚውልበትን ቀን መሰረት
አድርጎ በቅድሚያ ሊከፍል ይችላል፡፡
16.2 የድርጅቱ አቅም አስከፈቀደ ድረስ በድርጅቱ ውስጥ ከተቀጠረ ጀምሮ አንድ ዓመት
ያገለገለ ሰራተኛ ያልተጣራ የ3 ወር ደመወዙን በሁለት ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ
ከወለድ ነፃ በሆነ መንገድ ሊበደር ይችላል፡፡ ለዚህም በቂ ዋስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
16.3 ሠራተኛው የወሰደውን የደመወዝ ብድሩን ለድርጅቱ በየወሩ ከደመወዙ ላይ 1/3
እየተቆረጠ ገቢ ይደረጋል፡፡ የሠራተኛው የሥራ ውል የተቋረጠ ከሆነ ያለበትን ቀሪ ዕዳ
ከሚከፈለው ማንኛውም ገንዘብ ላይ ሙሉ ለሙሉ ቆርጦ ያስቀራል፡፡
16.4 በድርጅቱ በሚሰጡ የብድር አገልግሎቶች በሚቋቋም ኮሚቴ ውስጥ የሰራተኛ ማህበር
ተወካይ በኮሚቴ አባልነት እንዲኖር ይደረጋል፡፡

አንቀጽ አስራ ሰባት (17) የደመወዝ ጭማሪና ጉርሻ (ቦነስ)


17.1. ጠቅላላ
17.1.1 ሠራተኛው በጡረታ፣ በስንብት፣ በሞት፣ በትምህርት ወዘተ በሥራ ገበታው ባለመገኘቱ
በዓመቱ ሁለት ጊዜ የሚሞላ የሥራ አፈፃፀም ምዘና የአንድ ጊዜ ብቻ ተሞልቶ ሌላውን
ለመሙላት ሳይቻል ሲቀር በአንድ የሥራ አፈፃፀም ምዘና መሠረት ተገቢውን ክፍያ
ሊፈጽም ይችላል፡፡ በትምህርት፣ በረጅም ጊዜ ፈቃድ (ከደመወዝ ነፃ ፈቃድን
ሳያካትት) በመሳሰሉት ምክንያቶች የሁለቱም ጊዜ የሥራ አፈፃፀም ካልተሞላ
ለሠራተኛው በአማካይ B ይሰጠዋል፡፡
17.1.2 ለቦነስ ወይም ለደመወዝ ጭማሪ አፈፃፀም ሲባል አሥራ አምስት ቀናትና ከዚያ በላይ

ያገለገለ ሠራተኛ ሙሉ ወር እንደሰራ ይቆጠራል፡፡


17.1.3 ቦነስም ሆነ የደመወዝ ጭማሪ የሚፈጸመው የድርጅቱ የሂሳብ ሪፖርት በውጭ ኦዲተሮች

ከተመረመረና አትራፊነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡


17.1.4 በበጀት ዓመቱ የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ከ50 በመቶ በታች ነጥብ ያገኘ የደመወዝ

ጭማሪም ሆነ ቦነስ አያገኝም፡፡


17.1.5 በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞች በድርጅቱ ወጪ በማኔጅመንቱ

ውሳኔ መሰረት ይሸለማሉ፡፡

32
አንቀጽ አስራ ስምንት (18) የደመወዝ እርከን ጭማሪ እና የቦነስ
አሰጣጥ
18.1. የደመወዝ እርከን ጭማሪ እና የቦነስ አሰጣጥ
18.2.1 ድርጅቱ በአንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከስራ ጋር በተያያዘ ከሚያገኘው
ያልተጣራ ትርፍ ላይ የትርፍ ገቢ ግብር ተቀንሶ ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ ሕጋዊ
መጠባበቂያ 5% በመቀነስ ለሠራተኞች የደመወዝ እርከን ጭማሪ ወይም የደመወዝ
እርከን ጭማሪ እና ቦነሰ ይሰጣል፡፡ አፈፃፀሙም ከታች ከአንቀጽ 18.2.2-18.2.17
በተጠቀሰው መሰረት ይሆናል፡፡
18.2.2 በአንቀጽ 18.2.1 መሠረት የሚሰጠው የደመወዝ ጭማሪ ወይም ቦነስ ወይም የደመወዝ
ጭማሪና ቦነስ አፈፃፀም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

የትርፍ ዕቅድ አፈፃፀም


ቦነስ የደመወዝ እርከን ጭማሪ
ድርጅቱ ለሰራተኛ መክፈል ካለበት አይሰጥም የአንድ እርከን ደመወዝ ጭማሪ
የአንድ ዓመት የእርከን ጭማሪ
ወጭ እጥፍ የተጣራ ትርፍ ካተረፈ
(ዓመታዊ የእርከን ወጭ X 2)
90%-130% የ1 ወር ደመወዝ የአንድ እርከን ደመወዝ ጭማሪ
130%-165% የ1.5 ወር ደመወዝ የአንድ እርከን ደመወዝ ጭማሪ
165%-200% የ2 ወር ደመወዝ የአንድ እርከን ደመወዝ ጭማሪ
200% የ2.5 ወር ደመወዝ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ

18.2.3 ለሰራተኛው የሚሰጠው ቦነስም የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤትን መሠረት አድርጎ
እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
 ከ86ና በላይ A 100%
 ከ81-85 B+ 95%
 ከ75-80 B 90%
 ከ65-74 C+ 85%
 ከ50-64 C 80%
18.2.4 ሙሉ የበጀት ዓመቱን ለድርጅቱ ትርፋማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰራተኞች በስራ
አፈጻጸማቸው ቀመር መሰረት ቦነስ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የሙከራ ጊዜያቸውን
የጨረሱ ሆነው ለበጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ትርፍ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰራተኞች
በአገልግሎት ጊዜ ልክ እየተሰላ ቦነስ ይከፈላቸዋል፡፡
33
18.2.5 በበጀት ዓመቱ 9 (ዘጠኝ) ወር እና ከዚያ በላይ ያገለገለ ሰራተኛ የደመወዝ እርከን
ጭማሪ ያገኛል፡፡ የደመወዝ እርከን ጭማሪ ተግባራዊ የሚሆነው ትርፍ በተገኘበት
በጀት ዓመት መጨረሻ ወር ቀጥሎ ባለው በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወር
ሀምሌ 1 ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡
18.2.6 በሞት ወይም በጡረታ ምክንያት የስራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ የበጀት አመቱ ሙሉ
ቦነስ እና ስራ ላይ ለቆየበት ጊዜ የደመወዝ እርከን ጭማሪ ይከፈለዋል፡፡
18.2.7 በበጀት አመቱ ለረጅም ጊዜ በሕመም ፈቃድ ላይ ያሳለፋ ካሉ ጉዳዩ ከአቅም በላይ
በሆነ ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን በማየት የስራ ውላቸው ለተቋረጠ ቦነስና የስራ
ውላቸው እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ብቻ የደመወዝ ዕርከን ጭማሪ እንዲሁም በሥራ
ላይ ያሉ ካሉ ደግሞ የተፈቀደውን ቦነስም ሆነ የደመወዝ ዕርከን ጭማሪ ያገኛሉ፡፡
18.2.8 በራሳቸው ጥያቄ/ ፈቃድ ከድርጅቱ የተሰናበቱ ወይም የስራ ውላቸው የተቋረጠ
ሠራተኞች ስድስት ወርና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ከሆነ ለሰሩበት ጊዜ ተሰልቶ ቦነስ
ይከፈላቸዋል፡፡ ነገር ግን የእርከን ጭማሪ አያገኙም፡፡ ሆኖም በዲስፕሊን ጉድለት
የተሰናበቱ ሠራተኞች አይከፈላቸውም፡፡ ይህ ተፈጻሚ የሚሆነው ክፍያው እንዲከፈል
በተወሰነ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ጥያቄው ከቀረበ ብቻ ነው፡፡
18.2.9 እርከን በተገኘበት በጀት ዓመት በደረጃ ዕድገትም ይሁን በምደባ የ1 (አንድ)
ደመወዝ ደረጃ ከፍታ ወይም የ3 (ሶስት) እርከን እና በላይ ዕድገት ወይም የደመወዝ
ጭማሪ ያገኙና በበጀት ዓመቱ ቢያንስ 6 (ስድስት) ወር ያላገለገሉ ሰራተኞች
የደመወዝ እርከን ጭማሪ አይከፈላቸውም/ አያገኙም፡፡
18.2.10 ቦነሱ የሚመሰረተው ሰራተኛው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሰኔ ወር ላይ በተከፈለው
ደመወዝ ላይ ይሆናል፡፡
18.2.11 የድርጅቱ ትርፍና ኪሳራ የሚመሰረተው የድርጅቱ የበጀት ዓመት ሂሳብ በውጪ
ኦዲተሮች ተመርምሮ መግለጫ ከተሰጠበት በኋላ ነው፡፡
18.2.12 ድርጅቱ የበጀት ዓመቱን ሂሳብ ዘግቶ በውጪ ኦዲተሮች አስመርምሮ ትርፍና
ኪሳራውን ማወቅ ያለበት ከሐምሌ አንድ ቀን ጀምሮ ባለው ሶስት (3) ወር ጊዜ
ውስጥ ይሆናል፡፡
18.2.13 ትርፍ በተመዘገበበት ወይም ቦነስ በሚከፈልበት በጀት ዓመት በመደበኛ ትምህርት
ላይ ላለ ሰራተኛ ቦነስም ሆነ የደመወዝ እርክን ጭማሪ አይከፈለውም፡፡

34
18.2.14 ትርፍ በተመዘገበበት ወይም ቦነስ በሚከፈልበት በጀት አመቱ ከ1-5 ቀናት ደመወዝ
የተቀጡ ሰራተኞች የተፈቀደውን ቦነስ መጠን 75% እና የተፈቀደውን የደመወዝ
ዕርከን ጭማሪ ያገኛሉ፡፡
18.2.15 ትርፍ በተመዘገበበት ወይም ቦነስ በሚከፈልበት በጀት አመቱ ከ6-30 ቀናት ደመወዝ
የተቀጡ ሰራተኞች የተፈቀደውን ቦነስ መጠን 50% እና የተፈቀደውን የደመወዝ
ዕርከን ጭማሪ ያገኛሉ፡፡
18.2.16 ትርፍ በተመዘገበበት ወይም ቦነስ በሚከፈልበት በጀት አመቱ ከ30 ቀናት በላይ
ደመወዝ የተቀጡና ከዚያ በላይ የዲስፕሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ግን የተፈቀደውን
ቦነስም ሆነ የደመወዝ ዕርከን ጭማሪ ሙሉ ለሙሉ አያገኙም፡፡
18.2.17 ከላይ በተጠቀሰው አግባብ የእርከን ጭማሪም ሆነ ቦነስ የሚሰጠው የድርጅቱ የተጣራ
ትርፍ ቢያንስ ዓመታዊ የእርከንና የቦነስ ጭማሪ ወጭውን ሊሸፍን ከቻለ ብቻ ነው፡፡
18.2.18 መንግስት የኑሮውን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ
ካደረገ መስሪያ ቤቱ ይህንኑ የኑሮ ሁኔታ በማየት አቅም ባገናዘበ ሁኔታ የደሞዝ
ጭማሪ ያደርጋል፡፡ ሆኖም ጥያቄው ለቦርድ ቀርቦ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ (19) ልዩ ልዩ አበል


19.1 የአየር ጠባይ አበል
የበረሀ/ ቆላ አበል ክፍያ አፈፃፀም የፌደራል/ የክልሉ መንግስት ባወጣው/ በሚያወጣው
መመሪያ መሰረት መሠረት ይፈፀማል፡፡

19.2 የውሎ አበል


19.2.1 ሰራተኛው ከምድብ የሥራ ቦታው ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ሥራ እንዲያከናውን ሲታዘዝ
በሚሄድበት ቦታ ለሚያጋጥመው የምግብና የመኝታ ወጪ ለመሸፈን ውሎ አበል
ይከፍለዋል፤ አከፋፈሉም የድርጅቱ ስራ አመራር ቦርድ በሚወስነው መሠረት ወይም
በድርጅቱ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
19.2.2 ማንኛውም ሠራተኛ ከመስክ እንደተመለሰ ሂሳቡን ማወራረድ ይኖርበታል፡፡ በመስክ
ላይ ላሉ ሠራተኞች ሂሳብ የሚወራረድበትን ሁኔታ ድርጅቱ ያመቻቻል፡፡
19.2.3 የውሎ አበል ቀጥሎ ባለው መሠረት ተሰልቶ ይከፈላል፡፡
ሀ/ ማንኛውም ሠራተኛ ከጠዋቱ አንድ (1:00) ሰዓት በፊት ከተመደበበት ከተማ ክልል
ውጭ ለሥራ ከተንቀሳቀሰ የቁርስ አበል ይከፈለዋል፡፡ እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት

35
ካልተመለሰ የምሳ አበል ይከፈለዋል፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ተመደበበት
ከተማ ክልል ከተመለሰ የእራት አበል ይከፈለዋል፡፡
ለ/ ማንኛውም ሠራተኛ ከተመደበበት ከተማ ክልል ውጭ የአየር ጠባይ አበል ወደ
ሚከፈልበት ቦታ ለሥራ ከተላከ በክልሉ ለሚኖረው ቆይታ ለቦታው የተመደበው
የአየር ጠባይ አበል በመደበኛ የውሎ አበል ላይ ተደምሮ ይከፈለዋል፡፡

19.3 የሞያ አበል


19.3.1 የሲቪል፣ የውሀ ሀብት፣ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የመስኖ መሐንዲስ፣ ጅኢሎጅስት፣
ሀይድሮጂኦሎጂስት፣ ሌሎች መሀንዲሶች፣ ቀያሽ፣ የድራፍቲንግ ባለሙያ፣ አይቲ፣ የህግ፣
የመካኒክ፣ በያጅ፣ ቦዲማን፣ ኤሌክትሪሽያን እና ሁለገብ የጥገና ባለሙያ ሆነው
የተመደቡበት የስራ መደብ የተጠቀሰውን የትምህርት ዝግጅትና ደረጃ የሚጠይቅ ከሆነ
የትምህርት ደረጃቸው፡-
ሀ) ኮሌጅ ዲፕሎማ ወይም 10+3 ወይም ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ነገር ግን
ከመጀመሪያ ዲግሪ በታች የትምህርት ደረጃ ላላቸው ብር 250.00 (ሁለት መቶ
ሀምሳ ብር)፣
ለ) የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ላላቸው ባለሞያዎች ብር 400.00
(አራት መቶ ብር) ከደመወዛቸው ጋር ይከፈላል፡፡ ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ግን
የተመደቡበት የስራ መደብ የተጠቀሰውን የትምህርት ደረጃ የሚጠይቅ ከሆነ ብቻ
ነው፡፡

19.4 ለታታሪ ሠራተኛ የሚከፈል ማትጊያ


19.4.1 ድርጅቱ በነፃ ገበያው ውስጥ ተወዳድሮ ከፍተኛ የሥራ ውጤትና ቅልጥፍና ማሣደግ
ከሠራተኛው የሥራ ዋስትና ጋር የተያያዘ መሆኑን ድርጅቱና ማኀበሩ ተረድተውታል፤
ይህንንም በሥራ ለመተርጎም እንዲቻል ሠራተኛው በየተሰማራበት የሥራ መስክ
የሥራ ፍላጎት በይበልጥ እንዲዳብር የሥራ ጥራትና ፍጥነት ከፍ እንዲል፤ በአጠቃላይ
የድርጅቱ ሠራተኞች ፍሬያማ የሥራ ውጤት ሲያስገኙ የማበረታቻ ስጦታና የምስክር
ወረቀት ሊሰጥ ይችላል፡፡
19.4.2 ለታታሪ ሠራተኛ የሚከፈል ማትጊያ/ ማበረታቻ ለአንድ ጊዜ ወይም በዘላቂነት
የሚከፈል ሆኖ በድርጅቱ የማትጊያ መመሪያ (Incentive Scheme Manual) ተጠንቶ
በሚዘጋጀው የአፈፀፀም መመሪያ (Implementation Guide Line) ወይም የድርጅቱ
ማኔጅመንት ኮሚቴ በሚወሰነው መሠረት ይሆናል፡፡

36
19.5 የካዝና መጠበቂያ
ለገንዘብ ያዥዎች የሚከፈል የገንዘብ መጠባበቂያ አበል (Cash Indemnity Allowance) ገንዘብ
ያዦች በምንዛሪና በአሰጣጥ ስህተት ገንዘብ ሊጎልባቸው ስለሚችል በዚሁ ምክንያት ለገንዘብ
መጠባበቂያ ይረዳን ዘንድ ድርጅቱ በየወሩ የሚከፍለው ሲሆን የክፍያ አፈፃፀሙም ከዚህ በታች
በተመለከተው መሠረት ይሆናል፡፡
19.5.1 ድርጅቱ በዋና መስሪያ ቤትና በጽ/ቤቶች ለሚገኙ ዋና ገንዘብ ያዦች በየወሩ ብር 250
(ሁለት መቶ ብር) እንዲሁም ለረዳት ገንዘብ ያዦችና ለዕለት ገንዘብ ተቀባዮች በየወሩ
ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) ወርሃዊ የገንዘብ መጠባበቂያ አበል ለአሥራ ሁለት
ወራት በሠራተኛው ስም በመጠባበቂያ ገንዘብ (Fund) መልክ ያጠራቀማል፡፡ ከዚህ
በኋላ ግን የመጠባበቂያ ገንዘብ ክፍያው በየወሩ ለገንዘብ ያዥ ይከፈላል፡፡
19.5.2 ገንዘብ ያዥ የተረጋገጠ የገንዘብ ጉድለት ሲገኝበት ድርጅቱ በስሙ ከተያዘው
ከተጠራቀመው መጠባበቂያ ገንዘብ ተቀናሽ በማድረግ ጉድለቱን ወዲያውኑ አሟልቶ
ከመጠባበቂያ ገንዘብ ላይ የተቀነሰውን ሂሣብ ከገንዘብ ያዥ ወርሃዊ መጠባበቂያ ክፍያ
ተቀናሽ በማድረግ ይሞላል፡፡ ይሁን እንጂ ያጎደለው ገንዘብ ከማካካሻ ገንዘብ በላይ
ከሆነ የጉድለቱን ልዩነት በሚሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሠራተኛው አሟልቶ እንዲከፍል
ይደረጋል፡፡
19.5.3 ገንዘብ ያዥ ከድርጅቱ ሲሰናበት ወይም ከገንዘብ ያዥነት የሥራ መደብ ወደ ሌላ
የሥራ መደብ ሲዛወር ከእዳ ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ በስሙ/ሟ የተጠራቀመው ገንዘብ
በአንድ ጊዜ ይከፈለዋል፡፡
19.5.4 በህመም ወይም በዓመት ዕረፍት ምክንያት ገንዘብ ያዥ በምድብ ሥራ ላይ ከ15
ቀናት በላይ በማይኖርበት ጊዜ እና በሌላ ሲተካ የወሩ የመጠባበቂያ ክፍያ ለተተኪው
ይከፈላል፡፡
19.5.5 በየፕሮጀክቶቹ የሚመደቡ ገንዘብ ያዦች የመጠባበቂያ ክፍያ ከላይ ከአንቀጽ 19.5.1
እስከ 19.5.4 መሠረት ይሆናል፡፡

19.6 በኘሮጀክት ለሚመደቡ ሠራተኞች /ካምኘ ፋሲሊቲ/


በቦታው/ በስራው/ ላይ ለማቆየትና ለማበረታታት ሲባል በድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ
ሲታመንና ሲፈቀድ ፍሪጅ፣ ቴሌቪዥን፣ ዲቪዲና ዲሽ የመሳሰሉት የዕለት መገልገያ
ቁሣቁሶችን ጨምሮ በካምኘ እንዲሟላ ይደረጋል፡፡

37
19.7 የወተት አበል
ላቦራቶሪ ማዕከል የሚሰሩ ላብ ቴክኒሻኖች፣ ሶይል ኬሚስቶች፣ ሶይል ሚካኒክስ የስራ መደብ ላይ
ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያዎች፣ ማቴሪያል መሀንዲሶች (ዳታ አናሊስት ሆነው የሚሰሩትንና
ሀላፊዎችን አያካትትም)፣ ንብረት ኦፊሰር (ዕቃ ግምጃ ቤት ሰራተኛ)፣ መዝገብ ቤት ሰራተኛ፣
ፎቶ ኮፒና ማባዣ፤ በያጆች፤ ብሉ ፕሪነት ሰራተኞች፤ የአካል ቅጥቀጣ ባለሙያ (ቦዲማን)፣
ባትሪ አሲድ የሚሞሉ ሰራተኞች፣ ላይበራሪያን፣ የሂሳብ ሰነድ ያዥ፤ ቆፋሪ/ ድሪለር በሰው ሀብት
አስተዳደር ስር ያሉ መዛግብት ወይም የግል ማህደር ያዥ ሰራተኞች፣ ስራ ላይ ባይሆኑም
ሳይቆራረጥ በቀን አንድ ሊትር ወተት ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት አንድ ወር
ሙሉ ከስራ ገበታው ላይ ከሌለ አይሰጥም/ አይከፈልም፡፡

19.8 ጡረታ የሚወጡ ሰራተኞችን በተመለከተ


በድርጅቱ 5 (አምስት) ዓመትና ከዚያ በላይ አገልግለው ከድርጅቱ ጋር ያላቸው የስራ ውል
በጡረታ ለተቋረጠ ሰራተኞች በድርጅቱ ወጭ 5 (አምስት) ግራም 21 (ሀያ አንድ) ካራቲ ወርቅ
ተገዝቶ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ ሃያ (20) ሕክምና መድህንና ጡረታ


20.1 ሕክምና
20.1.1 ሠራተኛው ወደ ታወቀ የመንግሥት ሆስፒታል ወይም በማንኛውም በሀገር ውስጥ
በሚገኙና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የግል ጤና ተቋማት ሄዶ መታከም ይችላል፡፡
20.1.2 በመንግስት የጤና ተቋማት ለሚታከም ለማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኛ የመድሀኒት
መግዣ ጨምሮ የህክምና ወጪ በድርጅቱ 100% ይሸፈናል፡፡ እንዲሁም በግል የጤና
ተቋማት ለሚደረግ ማንኛውም ህክምና ወጪ የመድሀኒት መግዣ ጨምሮ 75%
በድርጅቱ ይሸፈናል፡፡ ለአንድ ሰራተኛ በአንድ በጀት ዓመት የሚሸፈነው የህክምና
ወጪ በድምሩ ከብር 60,000.00 (ሰልሳ ሽህ ብር) አይበልጥም፡፡
20.1.3 ከላይ በአንቀጽ 20.1.2 የተጠቀሰው ቢኖርም በዚህ ህብረት ስምምነት ለታቀፉ የስራ
ሀላፊዎች (ቡድን መሪዎችና የፕሮጀክት ሀላፊዎች) በመንግስትም ሆነ በግል የጤና
ተቋማት ለሚደረግ ማንኛውም ህክምና ወጪ የመድሀኒት መግዣ ጨምሮ በድርጅቱ
የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ይሸፈናል፡፡
20.1.4 በዓይን ሕመም ምክንያት ሐኪም ለሠራተኛው መነጽር ሲያዝ እስከ ብር 1,750.00
(አንድ ሺ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) ድረስ የመነጽር መግዣ ድርጅቱ ይከፍላል፡፡

38
እንዲሁም የመነፀር ሌንስ እንዲቀየር በሀኪም ሲታዘዝ ሙሉ ወጭውን በመሸፈን
ይቀይራል፡፡
20.1.5 የጥርስ ማስሞላት ሕክምና ለሠራተኛው እንዲደረግ ሐኪም ሲያዝዝ የጥርስ ማስሞላቱ
ሂደት በማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል የጤና ተቋማት ሲከናወን ወጪውን 50
(ሀምሳ) በመቶ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡ ሆኖም ግን የስራ ላይ ጉዳት ካልሆነ በስተቀር ሰው
ሰራሽ ጥርስ ማስተከልን አይጨምርም፡፡
20.1.6 የጀሮ ማዳመጫ ሠራተኛው እንዲያደርግ ሐኪም ሲያዝዝ ከብር 5000 (አምስት ሺ ብር)
ያልበለጠ ለአንድ ጊዜ ብቻ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡
20.1.7 ሰራተኛው ሕመሙ በሆስፒታል የሚያስተኛው መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ በመንግስት
ሆስፒታልም ሆነ የግል የሕክምና ተቋማት ተኝቶ ሊታከም ይችላል፡፡ የወጭ
አሸፋፈኑም በአንቀጽ 20.1.2 እና 20.1.3 መሰረት ይሆናል፡፡
20.1.8 መስክ የሚገኙ ሠራተኞች በአቅራቢያቸው በሚገኙ በመንግሥት ወይም በመንግሥት
እውቅና ባገኙ ማናቸውም የሕክምና ተቋማት መታከም ይችላሉ፡፡ ወጪዉም በአንቀጽ
20.1.2 መሰረት ይሸፈናል፡፡
20.1.9 በመንግስት የሕክምና ተቋማት ወይም ሕጋዊ በሆነ የግል የህክምና ተቋም ትዕዛዝ
(Referal) መሠረት ሠራተኛው ከሚሠራበት የሥራ ቦታ ወደ አዲስ አበባ ወይም ሌላ
ቦታ ሂዶ/ዳ እንዲታከም/ እንድትታከም ቢደረግ ይኸው ማስረጃ ታይቶ ከውሎ አበል
በስተቀር የመጓጓዣውንና የህክምና ወጪውን ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ ሆኖም በልዩ ሁኔታ
በድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካልተፈቀደ ወይም በሀኪም ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር
የመጓጓዣ ወጭው የሚሸፈነው በየብስ ትራንስፖርት ሆኖ ከህጋዊ የትራንስፖርት
ተቋም ህጋዊ የትራንስፖርት ደረሰኝ ሲቀርብ ብቻ ነው፡፡
20.1.10 በሰራተኛው ላይ የደረሰው ህመም ለሂወት አስጊ መሆኑ በሀኪም ሲረጋገጥና በየብስ
ትራንስፖርት ማጓጓዝ የማይቻል መሆኑ በሀኪም ሲረጋገጥ ድርጅቱ የሰራተኛውን
ሂወት ለማትረፍ ሲባል በሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት ወጭውን ይሸፍናል፡፡
20.1.11 ድርጅቱ ሠራተኞችን ለሥራ የሚያሰማራበት ቦታ ቢጫ ወባ ክትባት የሚስፈልግ ሆኖ
ካገኘው የቢጫ ወባ ክትባት ወጭውን ችሎ ያስከትባል፡፡
20.1.12 በስራ ላይ እያለ አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ በድርጅቱ መኪና ወደ ህክምና ተቋም
ይወሰዳል፡፡
20.1.13 ከላይ የተጠቀሱት የህክምና ወጭዎጭች የሚሸፈነው ለሀገር ውስጥ ህክምና ብቻ ነው፡፡
የውጭ ሀገር ህክመና አያካትትም፡፡

39
20.1.14 ለእኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) ድርጅቱ እስከ ብር 20,000.00 (ሃያ ሽህ) ብቻ ወጭ
ይሸፍናል፡፡ ከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በላይ ግን ድርጅቱ ሊሸፍን አይችልም፣
20.1.15 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ህክምናዎች የህክምና ወጭ በድርጅቱ አይሸፈኑም፡-
ሀ) የኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) ከተፈቀደው የገንዘብ በላይ፣
ለ) ሰው ስራሽ (አርቴፊሻል) ቀዶ ጥገና ወይም ንቅለተከላ፣ ከስራው ጋር ግንኙነት
ከሌለውና በስራ ላይ እያለ ጉዳት ካልደረሰበት፣
ሐ) ከሰው ጋር በመደባደብ የሚከሰት ጉዳት፣
መ) በመጠጥ፣ በአደንዛዥ ዕጽ… ወዘተ ምክንያት በሚደርሱ በሽታዎች/ አደጋ፤
ሠ) የአባላዘር በሽታዎች፣
ረ) ሰው ሰራሽ ጥርስ ማስተከልን ወይም ማስተካከል፣ ጉዳቱ የደረሰው ከስራው ጋር
ግንኙነት የሌለው ከሆነ፣
ሰ) ሴት ሠራተኛ በራሷ ፈቃድ ሆን ብላ በምታደርገው ውርጃ ለሚመጣ ሕመም፣

20.2 የአደጋ ዋስትና/ ኢንሹራንስ


20.2.1 በስራ ላይም ሆነ ከስራ ውጭ በድርጅቱ ሠራተኛ ላይ በማንኛውም ጊዜ ለሚደርስ የሞት
ወይም የአካል ጉዳት አደጋ የሃያ አራት ሰዓት የአደጋ ዋሰትና ኢንሹራንስ ይገባለታል፡፡
ጉዳቱ የደረሰው በስራ ላይ ከሆነ ካሳው በአዋጁ መሰረት ይፈፀማል፡፡
20.2.2 ሠራተኛው በሞት በሚለይበት ጊዜ ሕጉ ለሚፈቅድለት የሟች ወራሽ ድርጅቱ ከመድን
ዋስትና በሚገባው የዋስትና መጠን መሰረት ከአደጋ ውጭ ለሆነ ሞት ብር 30,000.00
(ሰላሳ ሺ ብር) እንዲሁም በማንኛውም አደጋ ምክንያት ለሚመጣ ሞት ብር 60,000.00
(ስልሳ ሺህ ብር) ካሣ እንዲከፈል ያደርጋል፡፡ ተግባራዊ የሚሆነው አሁን የተያዘው ውል
ተጠናቆ ቀጣይ አዲስ ውል ሲገባ ይሆናል፡፡
20.2.3 ሠራተኛው በስራ ላይ አደጋ ምክንያቶች ቋሚ የአካል ጉዳት ደርሶበት በሰለጠነበት
ሙያ ለመሥራት አለመቻሉ ሲረጋገጥ ድርጅቱ በገባው የመድን ዋስትና እና በአዋጁ
መሠረት ተገቢው ካሣ ይከፈለዋል፡፡
20.2.4 በስራ ላይ አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ መሥራት አለመቻሉ በህክምና ቦርድ እስኪረጋገጥ
ድረስ በዚህ የህብረት ስምምነት ላይ ለተጠቀሰው ጊዜ ድርጅቱ ደመወዝ ለሠራተኛው
ይከፍላል፡፡
20.2.5 ድርጅቱ በመደጋገም አደጋ የሚደርስበትን ቦታ ወይም ሁኔታ በመከታተልና ለይቶ
በማወቅ አደጋውን ለማስቀረት የሚቻልበትን ዘዴ መፈለግና ሠራተኞችም ተገቢውን
ትብብር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
40
20.2.6 ሰራተኛው በስራ ላይ እያለ አደጋ ቢያጋጥመው ከአቅም በላይ እስካልሆነ ድረስ አደጋው
በደረሰበት ቀን ቢዘገይ አደጋው በደረሰ በ12 ሰዓት ውስጥ አደጋው የደረሰበትን ቀን፣
ሰዓት፣ የስራ ቦታ፣ የደረሰውን አደጋ፣ አደጋውን ያደረሰው አካል /ካለ/፣ አደጋው
በደረሰበት ቦታ የነበሩ እማኞችንና ሌሎች ሁኔታዎችን ያካተተ የጹሁፍ ማመልከቻ
ማቅረብ አለበት፡፡ በተባለው ቀንና ሰዓት ማመልከቻ ባያቀርብም በስራ ላይ እያለ ጉዳት
ለደረሰበት ሰራተኛ ድርጅቱ ሀላፊነት ይወስዳል፡፡
20.2.7 ሰራተኛው የስራ ደህንነት መጠበቂያ (Safety) ቀርቦለት ባለመጠቀሙ ለሚከሰት ጉዳት
ድርጅቱ ለማሳከምና አስፈላጊውን ለመፈፀም ግዴታ የለበትም፡፡
20.2.8 ማንኛውም ሰራተኛ ሲሞት ድርጅቱ የቀብር ማስፈፀሚያ የሚሆን በዚህ የሕብረት
ስምምነት በአንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 20.2.2 ከተጠቀሰው በተጨማሪ የሰራተኛው የ3
(ሶስት) ወር ደመወዝ ይከፈላል፡፡ አከፋፈሉም ሰራተኛው በህይወት ሳለ በጽሁፍ
ላስመዘገባቸው ቤተሰቦች (ጥገኞች) ይሆናል፡፡ ሆኖም በህይወት እያለ ያስመዘገባቸው
ቤተሰቦች ከሌሉ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 11ዐ/2/ እና /3/ መሠረት
ይከፈላል፡፡

20.3 ጡረታ
20.3.1 ማንኛውም የድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ)/ የተወሰነ ጊዜ/ሥራ (ኮንትራት) ሠራተኛ
በመንግሥት የጡረታ አዋጅ መሰረት የሚተዳደር ይሆናል፡፡
20.3.2 በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 59 1 ’’ሀ’’ ና ’’ለ’’
መሠረት ይሆናል፡፡
20.3.3 ሠራተኛው በጡረታ ከመገለሉ በፊት ሊሰጠው የሚገባና ያልተሰጠው ማንኛውም
ጥቅማጥቅም ተጠናቆ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
20.3.4 ሠራተኛው በጡረታ የመገለያ ጊዜው ከመድረሱ አስቀድሞ ድርጅቱ ቢያንስ ከአንድ
ዓመት በፊት ማሳሰቢያ ይሰጠዋል፡፡

አንቀጽ ሃያ አንድ (21) የማህበራዊ ጉዳዮች


21.1 የቀብር ሥነ-ሥርዓት ማስፈፀሚያ አገልግሎት
21.1.1 አንድ ሠራተኛ "ከቤተሰብ" አባላት ውስጥ የሞት አደጋ ቢደርስበት ለቀብርና
ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ድርጅቱ የተሽከርካሪ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
21.1.2 ማንኛውም ሠራተኛ በሃዘን ጊዜ ሰራተኛው የሚደርስበት አንድ መኪና ይመድባል፡፡

41
21.1.3 አንድ የድርጅቱ ሠራተኛ በሞት ከዚህ ዓለም በሚለይበት ወቅት ድርጅቱ ለሐዘንና
ለቀብር ሥነ-ሥርዓት ማስፈፀሚያ እንዲረዳ ብር5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
በማሕበሩ አማካኝነት ለቤተሰብ ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ በቀብሩም ሥነ-ሥርዓት ላይ
ተገኝቶ የአበባ ጉንጉን ያኖራል፡፡
21.1.4 ከመደበኛ የመኖሪያ ሥፍራ ውጭ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሌላ ቦታ የተላከ ሠራተኛ ቢሞት
ድርጅቱ በራሱ መጓጓዣ ወይም የትራንስፖርት ወጪውን በመቻል ወደ መደበኛ
የመኖሪያ ሥፍራ ወይም ቤተሰቡ በሚፈልገው ቦታ ድረስ አስክሬኑን ያጓጉዛል፡፡
21.1.5 በሃዘን ጊዜ የድርጅቱ ስራተኛ/ ቤተሰብ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ባህርዳር/ ደሴ ከተማ
ከሆነ ለሬሳ መውሰጃ የሚሆን አንድ ፒካፕ እና ለቀብር ስነ ስርዓት ማስፈፀሚያ
ለሰራተኛው የሚሆን አንደ ባስ ይፈቀዳል፡፡

22.1 ስፖርትና የመዝናኛ አገልግሎት


22.1.1 ማሕበራዊ ግንኙነቶችን ለማሳደግ ድርጅቱ ከሠራተኞች ጋር በመተባበር ስፖርት ነክ
እንቅስቃሴዎችንና ሌሎች አገልግሎቶችን በመስጠት ይተባበራል፡፡
22.1.2 ሠራተኛው በዕረፍት ጊዜው የሚዝናናበት የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ማሕበሩ
ያስተዳድረዋል፣ ይቆጣጠረዋል፣ ገቢውንም በአግባቡ ለማሕበሩና ለሠራተኛው
ግልጋሎት እንደሁም ለመዝናኛ ክበቡ መሻሻል እንዲውል ያደርጋል፤ ድርጅቱ
ለሠራተኛው መዝናኛ ክበብ መሻሻል ጥገናና የውስጥ ማቴሪያሎች ማሟላት እገዛና
ትብብር ያደርጋል፤ የድርጅቱ ሠራተኞች የሣይንስና ቴክኖሎጂ የጥናት እውቀታቸውን
ለማስፋት በተለይም የጥናትና ዲዛይን ችሎታቸውን ለማሣደግ የሚረዳ ቤተመፃሕፍት
ከማሕበሩ ጋር በመተባበር አጠናክሮ ያደራጃል፡፡

አንቀጽ ሃያ ሁለት (22) ትራንስፖርትና መጓጓዣ


22.1 ድርጅቱ በዋናው መስሪያ ቤት የትራንስፖርት አበል ለማይከፈላቸው ሠራተኞች ጠዋት
በሥራ መግቢያና ማታ በስራ መውጪያ ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት (ሰርቪስ)
ይሰጣል፡፡ ሆኖም ስለአፈፃፀሙ ማለትም የመነሻና የመድረሻ ቦታዎችና የጉዞ መስመሮች
ድርጅቱና የሠራተኛ ማህበሩ በጋራ አጥንተው ይወስናሉ፡፡
22.2 በስራ ባህሪያቸው ምክንያት የጋራ ሰርቪስ መጠቀም ለማይችሉ ሰራተኞች ድርጅቱ
ገንዘብ ይሰጣል፡፡ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል::
22.3 በድርጅቱ ተመርጦ ለስልጠና ወይም ለትምህርት የሚንቀሳቀስ ሰራተኛ ድርጅቱ
ትራንስፖርት ወይም የትራስፖርት ወጪውን ይሸፍናል፡፡

42
22.4 አዲስ አበባ ከተማ ለስልጠና ሳይሆን መኪና ሳይዙ ለመስክ ስራ ለሚላኩ ሰራተኞች አዲስ
አበባ ከተማ ለቆዩበት ቀናት ብቻ ታስቦ በቀን ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) የታክሲ/
የትራንስፖርት ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡

አንቀጽ ሃያ ሶስት (23) የመስክ አገልግሎት


ለድርጅቱ ሥራ በመስክ ተሠማርተው በድንኳን ለሚኖሩ ሠራተኞች ታጣፊ አልጋ፣
የመመገቢያ ቁሣቁሶች፣ በኬሚካል የተነከረ የወባ መከላከያ አጐበር፣ የወባ ትንኝ መከላከያ
ቅባቶች እና የተሟላ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ መስጫ ኪት ድርጅቱ ያቀርባል፡፡

43
ክፍል አራት
አንቀጽ ሃያ አራት (24) የዲስፕሊን የእርምጃ አወሳሰድ ሥነ-ሥርዓት
24.1 በአንድ ሠራተኛ ላይ የዲሲኘሊን እርምጃ የሚወሰደው ሠራተኛውን ከጥፋቱ በማረም
ሥራው እንዳይበደል ለመቆጣጠርና ሌሎች ሠራተኞች ከተመሳሳይ ጥፋቶቸ እንዲቆጠቡ
ለማድረግ ስለሆነ የዲሲኘሊን እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የጥፋቱ ክብደት፣ ሠራተኛው
ከጥፋቱ በፊት የነበረው ፀባይ፣ ያለው መልካም አገልግሎትና ለጥፋቱ መንስዔ የሆኑበት
ተጨባጭ ሁኔታዎች በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው፡፡
24.2 ማንኛውም ሠራተኛ በሥራ ላይ እንዳለ የሚያደርሰው ጥፋት በማስረጃ የተረጋገጠና
ጥፋቱም የዲሲኘሊን እርምጃ የሚያስወስድ ሆኖ ከተገኘ የሚወሰድበት ቅጣት በአዋጁና
በህብረት ስምምነቱ ያለማስጠንቀቂያና በማስጠንቀቂያ ከሥራ ከሚያሰናብቱ ጥፋቶች
በስተቀር በአንድ ሠራተኛ ላይ ዲሲፕሊን እርምጃ ሲወሰድ የሚወሰደው ቅጣት በዚህ
ህብረት ስምምነት ስለጥፋትና ቅጣት ዓይነቶች በሚያመለክተው ሠንጠረዥ መሠረት
ይሆናል፡፡ ሠራተኛው ሲቀጣ የተወሰደበት እርምጃ በወቅቱ በጽሁፍ እንዲደርሰው
ይደረጋል፡፡ በግልባጭም ሠራተኛ ማህበሩ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
24.3 በድርጅቱና በማኀበሩ የሚወከሉ እኩል አባሎች (ሰብሳቢውን ሳይጨምር) የሚገኙበት
የዲስፕሊን ኮሚቴ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ወይም በሥሩ ባሉ ጽ/ቤቶች ይቋቋማል፡፡
ሰብሳቢው በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም ጽ/ቤት ኃላፊ ይወከላል፤
24.4 ማንኛውም የዲሲፕሊን ጉዳዩች ከአንቀጽ 24.6 በስተቀር በድርጅቱ ወይም በጽህፈት ቤቱ
በተቋቋመው የዲስፕሊን ኮሚቴ አማካኝነት ይታያሉ፡፡ ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ
በየደረጃው ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ ከሥራ ላይ በመቅረት ምክንያት የሚወሰድ የዲስፕሊን
እርምጃ ከደመወዝ ቅጣት እስከ ሥራ ውል ማቋረጥ (ስንብት) ድረስ ያለው በሰው ሀብት
አስተዳደር ኦፊሰሮች በኩል አስተያየት እየቀረበ በሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ
የሚወሰን ይሆናል፡፡
24.5 ድርጅቱ አንዳንድ መጣራት ያለባቸውን ጉዳዮች በሚመለከት በሰው ሀብት ስራ አመራር
የስራ ሂደት/ ቡድን በኩል ተጣርቶ ለድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ/ ሀላፊ ይቀርባል፡፡
ሠራተኞች ጥፋት መፈፀማቸው ለሰው ሀብት ስራ አመራር ደጋፊ የስራ ሂደት/ ቡድን በጽሁፍ
ሲደርሰው ለዲስኘሊን ኮሚቴ ክስ ይመሰርታል፡፡ የዲስፕሊን ኮሚቴ ያጣራቸውን ጉዳዮች

ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም ለጽ/ቤት ኃላፊው የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡


የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የጽ/ቤት ኃላፊ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ሙሉ

44
በሙሉ በከፊል ሊቀበለው ወይም ሊሽረው ይችላል፡፡ በመጨረሻም የራሱን ውሳኔ
ያስቀምጣል፡፡
24.6 የሰራተኛው የቅርብ ሀላፊ ወይም ከቅርብ ሀላፊ በላይ ያለ ሀላፊ እስከ ጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ድረስ ያሉትን የዲስፕሊን እርምጃዎች ለዲስፕሊን ኮሚቴ ማቅረብ ሳያስፈልግ በራሱ
ቀጥታ ሊወስድ ይችላል፡፡
24.7 አንድ ሠራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብት ጥፋት ሲፈፅም አስፈላጊ ሆኖ
ከተገኘ ቅድሚያ እንዲጣራ ይደረጋል፡፡ ሆኖም የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ሥራ
ላይ በመቆየቱ መረጃዎችን የማጥፋት ወይም በድርጅቱ ሥራና ህልውና አደጋ ያደርሳል
ተብሎ ከታመነ ጉዳዩ ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በዋናው ሥራ አስፈፃሚ ሊታገድ
ይችላል፡፡ ሠራተኛው ከተጠረጠረበት ጥፋት ነፃ ሆኖ ከተገኘ ከሥራ ለታገደበት ጊዜ
ሙሉ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡
24.8 ለውሣኔ መዘግየት ሠራተኛው እራሱ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከ30 (ሰላሳ) ቀናት በላይ
ከሥራ አግዶ ማቆየት አይቻልም፤ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ውሣኔ ካላገኘ ደመወዝ
እየተከፈለው ውሣኔውን ይጠባበቃል፡፡
24.9 በሠራተኛው ምክንያት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ መስጠት ካልተቻለም ይህም
በማስረጃ ሲረጋገጥ ድርጅቱ ደመወዝ ሳይከፍለው ከሥራ ሊያሰናብተው ይችላል፡፡
24.10 በዚህ ህብረት ስምምነት አባሪ ሰንጠረዥ ሁለት (2) ላይ በግልጽ ያልተመለከቱት ሌሎች
ጥፋቶች ሠራተኛው ቢፈጽም በሰንጠረዡ ላይ በተመለከተው ተመሣሣይ ጠባይና
ክብደት ባላቸው የጥፋት ዓይነቶች ላይ በተወሰነው የቅጣት መጠን መሠረት የዲሲኘሊን
እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ ሆኖም የፈጸመው ጥፋት ዓይነትና ክብደት ከቅጣቱ ሠንጠረዥ
ጋር በማነጻጸር ረገድ አጠራጣሪና መረጃ የሚጠይቅ ሆኖ ሲገኝ እርምጃ ከመውሰዱ
በፊት ጉዳዩ በኮሚቴ ተጠንቶ የውሳኔ ሃሣብ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
24.11 እንደ ጥፋቱ ዓይነት ቅለትና ክብደት እንዲሁም ድግግሞሽ እየታየ በዚህ ህብረት
ስምምነት የተመለከቱት የዲስፕሊን ጉድለቶች (ጥፋቶች) ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ
የዲስፐሊን ቅጣቶች፡-
ሀ. የቃል ማስጠንቀቂያ፣ መ. ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ ማድረግ፣
ለ. የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ሠ. ከሥራ ማሰናበት ናቸው፡፡

ሐ. የገንዘብ/ ደመወዝ ቅጣት፣

45
24.12 የዲሲፕሊን ቅጣት ወይም አፈፃፀም በሰራተኛው ማህደር ውስጥ በሪከርድነት ተይዞ
በሰራተኛው ላይ ሊጠቀስ ወይም የደረጃ እድገት ሊያሳግድ ወይም ነጥብ ለማስቀነስ
የሚቻለው ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት ይሆናል፡፡
ሀ/ ከባድ የዲስኘሊን ቅጣትና እስከ አንድ ወር የደመወዝ ቅጣት የሚደርስ ቀላል
የዲስኘሊን ቅጣት የተወሰነባቸው ከዚህ በታች የተገለፀውን የእገዳ ጊዜ እስኪጨርሱ
ድረስ ለደረጃ እድገት ውድድር መቅረብ አይችሉም። የደረጃ እድገት እገዳ ጊዜውን
ከጨረሱ በኋላ ከዚህ በታች በተመለከተው ሠንጠረዥ ላይ የተመለከተው ነጥብ
እየተቀነሰባቸው ሊወዳደሩ ይችላሉ።
ለ/ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ የተወሰነባቸው ሠራተኞች በማንኛውም ጊዜ ከውድድር
የማይታገዱ ሆኖ የቅጣቱ ውሣኔ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች
እስከተጠቀሱት የጊዜ ገደብ ቀን ድረስ በሠንጠረዡ ላይ የተመለከተው ነጥብ
እየተቀነሰባቸው ሊወዳደሩ ይችላሉ።

የቅጣት ጊዜ
ለማህደር
ለደረጃ ለደረጃ እድገት
እድገት ታግደው የቆየበትን ጥራት
ታግደው የቅጣት ጊዜ ከጨረሱ የሚስጥ
ተ. የተወሰደው የዲስኘሊን የሚቆዩበት በኋላ ነጥብ እተቀነሰ የቅጣት ጊዜ ነጥብ
ቁ እርምጃ የቅጣት ጊዜ የሚወዳደሩበት ጊዜ ድምር ከ10%
ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ ለ1 ዓመት ለ1 ዓመት ለ2 (ሁለት) 4
1
ማድረግ (ከባድ) ዓመት
ከአንድ ወር በላይ እስከ ለ6 ወር ለ6 ወር ለ1 (አንድ) 6
2 ሦስት ወር የደመወዝ ዓመት
ቅጣት (ከባድ)
እስከ አንድ ወር የደመወዝ ለ3 ወር ለ3 ወር ለ6 (ስድስት) 8
3 ቅጣት (ቀላል) ወር
የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ __ 3 ወር __ 9
4
ቅጣት (ቀላል)
የቃል ማስጠንቀቂያና __ __ __ 10
5 ምንም ሪከርድ
የሌለበት/ባት

24.13 ደረጃ ዕድገት ታግዶ ሚቆይበትን የቅጣት ጊዜ የጨረሰ ሠራተኛ ገደቡ ካለቀበት ጊዜ
ጀምሮ የደረጃ ዕድገት በህብረት ስምምነቱ መሰረት የማህደር ጥራት ነጥብ እየተቀነሰበት
የመወዳደር መብቱ ይጠብቅለታል፡፡

46
24.14 ባለበት የስራ መደብ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ የተደረገ ሰራተኛ የያዘውን የስራ መደብ
እንደያዘ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ ተደርጎ የሚሰራ በመሆኑ አጠቃላይ የቅጣት ጊዜውን
(ከደረጃ ዕድገት ታግዶ የሚቆይበት ሲደመር ነጥብ እየተቀነሰ የሚወዳደርበት) ሲጠናቀቅ
በዚያው የስራ መደብ ላይ ከሆነ ወደ ነበረበት ደረጃና ደመወዝ እንዲመለስ ይደረጋል፡፡
24.15 ካለበት የስራ መደብ ተነስቶ በቅጣቱ መሰረት ዝቅ ያለ ደረጃ ያለው የስራ መደብ ላይ
ተመድቦ እየሰራ ያለ ሰራተኛ በደረጃ ዕድገት አግባብ ካልሆነ በስተቀር ወደ ነበረበት
ደረጃና ደመወዝ ተመልሶ አይመደብም፡፡
24.16 የቃል ማስጠንቀቂያ በሚሰጥበት ጊዜ የጥፋቱ ዝርዝርና ቀን ከሰፈረ በኋላ ሠራተኛው
የቃል ማስጠንቀቂያ ለመሰጠቱ በተለየ መዝገብ ሠራተኛው እና ማስጠንቀቂያ
የሚሰጠው የሥራ ኃላፊ በጋራ ይፈርማሉ፡፡ መዝገቡም በበጀት ዓመቱ በጥንቃቄ
በክፍሉ ይያዛል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ለመፈረም ፈቃደኛ ሆኖ ካልተገኘ የቃል
ማስጠንቀቂያው ወደ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተቀይሮ በፅሁፍ የተሰጠ የቃል ማስጠንቀቂያ
በሚል በጹሁፍ ተሰጥቶ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
24.17 ከቃል ማስጠንቀቂያ በላይ በዚህ አንቀፅ 24.11 “ለ-ሠ” ያለው የሥነ-ሥርዓት እርምጃ
ከሆነ ለሠራተኛው በፅሑፍ ሆኖ ሠራተኛው ፈርሞ እንዲቀበል ይደረጋል፡፡ ሠራተኛው
የማይፈርም ሆኖ ከተገኘ በድርጅቱ የውስጥ ሰሌዳ ላይ ለ5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት
ተለጥፎ ይቆያል፡፡ አድራጐቱም ተጨማሪ የሥነ-ሥርዓት ጉድለት እንደፈፀመ
ይቆጠራል፣
24.18 አንድ ሠራተኛ በፈጸመው ጥፋት የተነሣ በዚህ ኀብረት ስምምነት መሠረት የሚወሰዱ
የዲሲፕሊን እርምጃ በወንጀል ወይም በፍትሐብሔር ከመከሰስ አያግደውም፡፡

አንቀጽ ሀያ አምስት (25) የሥራ ውል ስለማቋረጥ


25.1 የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 24-
28 ወይም በዚህ ኀብረት ስምምነት በተገለጸው የዲሲፕሊን ጉድለት ለስንብት የሚያበቃ
ጥፋት መፈፀም ይሆናል፡፡

25.2 የሥራ ውል በማስጠንቀቂያ ስለማቋረጥ


25.2.1 የሥራ ውል በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት
በማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ ይችላል፤

47
25.2.2 በንብረት እና ገንዘብ ላይ የተመደበ ሰራተኛ ገንዘብ ወይም ንብረት ማጉደሉ በኦዲት
ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ እንደክብደቱ መጠን ታይቶ ውሉ በማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ
ይችላል፡፡

25.3 በመጀመሪያ ዙር ወይም በአንደኛ ደረጃ የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ


ስለማቋረጥ
ሥራ ውል በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1155/2011 አንቀጽ 27፣ 28 እንዲሁም 32
መሠረት ያለማስጠንቀቂያ ወይም በማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ሊቋረጥ ይችላል፤ በተጨማሪም
በዚህ ኀብረት ስምምነት መሠረት የሚከተሉት ሁኔታዎች በአንደኛ ደረጃ ከሥራ
ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብቱ/ የስራ ውል የሚያቋርጡ ጥፋቶች ይሆናሉ፤
25.3.1 የድርጅቱን ንብረት፣ ገንዘብ፣ ሰነድ በማጭበርበርም ሆነ በቀጥታ የሰረቀ፣ ያጠፋ፣ የሰረዘ
ወይም የደለዘ፡፡
25.3.2 ለግል ወይም ለሦስተኛ ወገን ጥቅም ለማስገኘት ወይም ድርጅቱን ለመጉዳት
በድርጅቱ ሠነድ ወይም ድርጅቱን በሚመለከት በማናቸውም ሠነዶች የተጠቀመ
ወይም ለመጠቀም የሞከረ ወይም ያጠፋ ወይም ያበላሸ ወይም የደለዘ ወይም የቀደደ
ወይም የደበቀ ወይም የሌላ ሰው ፊርማ አስመስሎ በመፈረም ሥራ ላይ ያዋለ ወይም
ለማዋል የሞከረ
25.3.3 የድርጅቱን ማህተም አስመስሎ የተጠቀመ ወይም የድርጅቱን ማህተም ለግል ጥቅም
ወይም ለሌላ ወገን ጥቅም ያዋለና በተመሳሳይ መንገድ የተጠቀመ፡፡
25.3.4 ከሰራተኛ የግል ማኀደር ውስጥ የሚገኝ ማስረጃዎችን ወይም ለድርጅቱ የሚቀርቡ
ወይም ከድርጅቱ የሚወጡ ወይም በመዝገብ የሚገኙ ደብዳቤዎች ወይም ጽሁፎች ሆን
ብሎ ወይም በቸልተኝነት የሰወረ ወይም የቀደደ ወይም የደለዘ ወይም የፋቀ ወይም
ያጠፋና በድርጅቱ ወይም በሠራተኛው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፡፡
25.3.5 በተጭበረበሩ ወይም በሐሰት የምስክር ወረቀቶች ወይም የሥራ ልምድ ወይም
የትምህርት ማስረጃ ወይም ግለሰቡን ሊጠቅሙ የሚችሉ ማናቸውም ማስረጃዎች
በማቅረብ ወይም ስሙንና ማንነቱን በመደበቅ ተቀጥሮ ወይም እድገት አግኝቶ
የተገኘ፡፡ ማስረጃዎችን አያይዞ የተገነ፡፡
25.3.6 ሆን ብሎ የተጭበረበረ የሐሰት ሰነድ ወይም የምስክር ወረቀት እንዲሰጥ ያደረገ
ወይም የተባበረ፡፡

48
25.3.7 ለግል ወይም ለሌላ ወገን ጥቅም ወይም ድርጅቱን በሚጎዳ በማናቸውም አኳኋን
በድርጅቱ ስም ወይም በድርጅቱ መታወቂያ ባለሥልጣን በመምሰል የተጠቀመ፡፡
25.3.8 የድርጅቱን ወይም የሥራ ባልደረቦቹን ወይም የደንበኞቹን ንብረት ወይም ገንዘብ
የሰረቀ፣ የዘረፈ ወይም ለመስረቅ የሞከረ ወይም ሆነ ብሎ ያጎደለ ወይም በእነዚህ
አድራጎት የተባበረ፡፡
25.3.9 ለድርጅቱ ሥራ እንዲውሉ የተሰጡትን የአደጋ መከላከያና ሌሎች ንብረቶች የሸጠ
ወይም የለወጠ ወይም ለሌላ ተግባር ያዋለ፡፡
25.3.10 ሆን ብሎ የግል ጥቅሙን በመፈለግ የድርጅቱን ንብረት ከተፈቀደው በላይ ከመጋዘን
ወጪ ያደረገ፡፡
25.3.11 ያልተሰራውን ሥራ ተሰርቷል ብሎ የሐሰት ሪፖርት ያቀረበ ወይም እንዲቀርብ
ያስደረገ፡፡
25.3.12 ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት የኤሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የስልክና የሬዲዮ መገናኛ
መስመሮች እንዳይሠሩ አድርጎ በሥራ፣ በሠራተኛና በድርጅቱ ንብረት ላይ ከባድ
ጉዳት ያደረሰ፡፡
25.3.13 ማንኛውም ሠራተኛ ከሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ከባለጉዳዩ ወይም ከሌላ ሠራተኛ
የማይገባውን ልዩ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት አስቦ ከባለጉዳዩ ወይም
ከሠራተኛው መማለጃ ጉቦ በጥሬ ገንዘብ ወይም በዓይነት የተቀበለ ወይም የሰጠ
ወይም መቀበሉም ሆነ መስጠቱ የተረጋገጠበት፡፡
25.3.14 ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኞች በሥራ ቦታ ወይም በሥራ ላይ ግድያ መፈፀሙ
ወይም ለመፈፀም መሞከሩ ወይም ዝሙት መፈፀሙ ወይም ለመፈፀም መሞከሩ
ወይም እርስበርስ መደባደቡ ወይም ለመደባደብ መዛቱ ወይም መሰዳደቡ ወይም
ጠብ ማስነሳቱ ወይም በማናቸውም ሁኔታ ፀጥታና የሥራ ሰላም እንዲደፈርስ
ማድረጉ ወይም የዚህ ድርጊት ቀስቃሽ ወይም አነሳሽ ወይም ምክንያት ሆኖ መገኘቱ
በተጨባጭ ሲረጋገጥ፡፡
25.3.15 በአልኮል ወይም በእጽ ወይም በሌሎች ተመሳሳይ መጥፎ ሱሶች ተመርዞ ወደ ሥራ
የገባ ወይም ወደ ሥራ በመግባት በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ የድርጅቱ
ንብረት ላይ አደጋ ለማድረስ የሞከረ፣
25.3.16 በሥራና በሠራተኛ ወይም በድርጅቱ ንብረት ላይ አደጋ ሊያስከትል የሚችል
ድርጊት ሆን ብሎ የፈፀመ፡፡

49
25.3.17 በማንኛውም ሁኔታ በድርጅቱ ላይ የተቃጣውን ከባድ አደጋ እያወቀ ሆን ብሎ ወይም
በቸልተኝነት ለድርጅቱ ካላሣወቀ ወይም የተቻለውን ያህል አደጋውን ለመከላከል
(ለመመከት) ጥረት ያላደረገ፡፡
25.3.18 በሥራ ፀባዩ ለስራ የተሰጠውን የጦር መሣሪያ ያበላሸ ወይም ያጠፋ ወይም ያባከነ
ወይም የሸጠ ወይም የለወጠ ወይም ለማይመለከተው ሰው ያስያዘ፤ ያስታጠቀ ወይም
ወንጀል እንዲሠራበት ያደረገና የጥበቃ አባል ሆኖ ለጥፋት፣ ለሌብነት ወይም
ለጉዳት የተባበረና ያመቻቸ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠበት፡፡
25.3.19 እንዲጠብቅ የተመደበበትን የዘብ ቦታ የቅርብ ኃላፊውን ፈቃድ ሳያገኝ ወይም ተተኪ
ዘብ ሳይኖር ጥሎ የሄደ፤
25.3.20 የሠራተኛው የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ውጤት ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛ ሆኖ ሲገኝ
የድክመቱ ምክንያት እየተጣራ ምክር፣ ስልጠናና የሥራ ላይ ልምምድ ተሰጥቶት
የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ውጤቱ ለ2ኛ ጊዜ ዝቅተኛ ከሆነ፡፡
25.3.21 ዋስትና ለሚጠይቁ የስራ መደቦች ሰራተኛው የመጀመሪያ ዋሱ ዋስትናውን
እንዲያወርድ ከጠየቀበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 30 ቀን ጊዜ ውስጥ ተተኪ
ዋስ ካላቀረበ፡፡

አንቀጽ ሀያ ስድስት (26) የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ወይም


በማስጠንቀቂያ ከሚያቋርጡ የዲስፕሊን ጥፋቶች በስተቀር ሌሎች
ጥፋቶች ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት ተፈፃሚ
ይሆናሉ፡፡
26.1. በሁለተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች
ሁለተኛ ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ደረጃ ቅጣት
ቅጣት
1 ድርጅቱ የሚያበረክተውን አገልግሎት እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ ስንብት
ሊያቃውስበት በሚችል በማናቸውም የውጭ ቀን ደመወዝ ቅጣት እስከ
ሥራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ደመወዝና ደረጃ ዝቅ
የግል ጥቅም ለማግኘት የድርጅቱን ሥራ ማድረግ
በሚበድል ተግባር ተሳትፎ ያደረገ
2 የድርጅቱን ሥራ የሚጎዳ እንቅስቃሴ ማካሄድ እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ ስንብት
ወይም የድርጅቱን ሥራ የሚያደናቅፍ ቀን ደመወዝ ቅጣት እስከ
ጭቅጭቅና ውዝግብ መፍጠር ደመወዝና ደረጃ ዝቅ
ማድረግ

50
ሁለተኛ ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ደረጃ ቅጣት
ቅጣት
3 በድርጅቱ መኪና ላይ በመኪናው የቴክኒክ በመድን ድርጅት በመድን ድርጅት
ጉድለት ሳይሆን በአሽከርካሪው ቸልተኝነት የማይሸፍነውን ወጭ የማይሸፍነውን
ያለጥንቃቄ በመንዳት ወይም የትራንስፖት ከፍሎ የ15-30 ቀን ወጭ ከፍሎ
ሕግን ባለማክበር በመኪናው ላይ ወይም ደመወዝ ቅጣት ከሥራ ስንብት
በጫነው ንብረት ወይም ሰው ላይ ወይም
በማናቸወም ላይ ጉዳት ያደረሰ
4 በሀላፊነት ከተረከበው የድርጅቱ መኪና የወሰደውን ወይም የወሰደውን
ወይም ለድርጅቱ ሥራ መገልገያ ንብረቶች ያጎደለውን ንብረት ተክቶ ወይም
በመውሰድ ከድርጅቱ ሥራ ውጪ ለሌላ እንደ ጥፋቱ ክብደት እስከ ያጎደለውን
ተግባር ያዋለ ወይም ያጎደለ ወይም ለራሱ አንድ ወር ደመወዝ ንብረት ተክቶ
ጥቅም የተገለገለ ቅጣት ከሥራ ስንብት
5 በድርጀቱ ላይ በድርጅቱ ንብረት ወይም ላደረሰው ጉዳት ኃላፊና ለደረሰው ጉዳት
በሥራ ላይ ከባድ ጉዳትና በደል ተጠያቂ ሆኖ እንደ ጥፋቱ ኃላፊና ተጠያቂ
የሚያስከትል አግባብ ያልሆነ ተግባር የፈፀመ ክብደት እስከ አንድ ወር ሆኖ ከሥራ
ደመወዝ ቅጣት ስንብት
6 የድርጅቱ ሀብት በዓይነት ወይም በገንዘብ እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ ስንብት
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የስርቆት ወይም ቀን እስከ የአንድ ወር
የማታለል ወይም ለግል ጥቅም ሲውል ወይም ደመወዝ ቅጣት
በማናቸውም ሁኔታ ጉዳት ሲደርስበት
እያወቀ ለሚመለከተው ክፍል ያላሳወቀ

7 የድርጅቱን ወይም የሰራተኛ ማኅበሩን ሥራ እንደጥፋቱ ክብደት ከ15


በሚመለከት ለሠራተኞች የሚተላለፍ ቀን ደመወዝ ቅጣት እስከ ከሥራ ስንብት
ማናቸውንም ዓይነት መልዕክቶችን ደመወዝና ደረጃ ዝቅ
ለማስተላለፍ ስልጣን ወይም የስልጣን ማድረግ
ውክልና የሌለው ሠራተኛ በማስታወቂያ
ሰሌዳዎች ወይም በማናቸውም ድርጅቱ
የሥራ ቦታዎች ወይም በሌላ ሁኔታ
ማስታወቂያ ወይም ሌሎች ጽሁፎችን
በመለጠፍ ወይም በማስነገር ያለ ፈቃድ
የተጠቀመ
8 ከግል ጥቅሙ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሕጋዊ
የመፈተሻ ኬላ የያዘውን ወይም የጫነውን እንደጥፋቱ ክብደት ከሥራ ስንብት
ጭነት ያላስፈተሸ ወይም የፍተሻ ኬላን ጥሶ ከአንድ ወር ደመወዝ
የሄደ ወይም በሌላ ዘዴ ሳይፈተሽ ያመለጠ ቅጣት እስከ ደመወዝና
ወይም ለማምለጥ የሞከረ ወይም በፍተሻ ደረጃ ዝቅ ማድረግ
ደህንነት ላይ አደገኛ ሁኔታን የሚያስከትል
ድርጊት የፈፀመ ሆኖ ከሚመለከተው ክፍል
በመረጃ የተረጋገጠበት
9 በድርጅቱ ቤቶች፣ መጋዘኖችና ሌሎች የሥራ እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ ስንብት
ቦታዎች መግቢያ ላይ መፈተሽ የሚገባቸውን ቀን ደመወዝ ቅጣት እስከ
መኪናዎች ወይም ሰዎች በመስማማት ወይም ደመወዝና ደረጃ ዝቅ
መደለያ በመቀበል ወይም በግደለሽነት ማድረግ
ተገቢውን ፍተሻ ሳያደርግ ያሳለፈ

51
ሁለተኛ ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ደረጃ ቅጣት
ቅጣት
10 የሚመለከተው የድርጅቱ ባለሥልጣን እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ ስንብት
ሳያውቀውና ሳይፈቅድ የድርጅቱን ዶክመንት ቀን እስከ የአንድ ወር
በቀጥታም ሆነ በተዘወዋሪ መንገድ ደመወዝ ቅጣት
ለማይመለከተው ሰው ወይም ድርጅት የሰጠ
11 በስራ ሰዓት ያለ ድርጅቱ ፈቃድ ወረቀት እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ ስንብት
እያዞረ ሌሎችን ሰራተኞች ያስፈረመ ወይም ቀን ደመወዝ ቅጣት
ስብሰባ መጥራት ወይም አድማ የሚያስነሳ እስከ ደመወዝና ደረጃ
ወይም በተጠቀሱት ህገወጥ ተግባራት ላይ ዝቅ ማድረግ
መሳተፉ በማስረጃ የተረጋገጠ
12 ተገቢ የመንጃ ፈቃድ ሳይኖረው ወይም አድራጎቱ ያስከተለው ከሥራ ስንብት
ከድርጅቱ የማሽከርከር ፈቃድ ሳይሰጠው ወጪና ጉዳት ካለ ከፋይና
የድርጅቱን መኪና ለማንቀሳቀስ የሞከረ ወይም
ተጠያቂ ሆኖ እንደጥፋቱ
ያሽከረከረ ወይም በኃላፊነት የተረከበውን ክብደት ከአንድ ወር
የድርጅቱን መኪና ተገቢ መንጃ ፈቃድ ላለውደመወዝ ቅጣት አስከ
ወይም ለሌለው ሰው አሳልፎ የሰጠ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ
ማድረግ
13 የድርጅቱን ስራ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ከሥራ ስንብት
መጨረስ እየቻለ አጠናቆ ያላስረከበ ወይም ሆኖ እስከ አንድ ወር
በተቀመጠው የጥራት ደረጃ መሰረት መስራት ደመወዝ ቅጣት
እየቻለ የጥራት ጉድለት ያስከተለ

26.2. በሶስተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች


ሦስተኛ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ደረጃ ቅጣት ሁለተኛ ደረጃ ቅጣት
ደረጃ ቅጣት
1 ሳያስፈቅድ ወይም ያለበቂ የባከነው ጊዜ ደመወዝ የባከነው ጊዜ ደመወዝ ከሥራ
ምክንያት በ6 ወር ጊዜ ተመላሽ ሆኖ ተመላሽ ሆኖ የደመወዙን ስንብት
ውስጥ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ የደመወዙን 5 ቀን 15 ቀን ደመወዝ ቅጣት
እየተሰጠው 5 (አምስት) ደመወዝ ቅጣት በሰው በሰው ሀብት ቡድን መሪ
የስራ ቀን ከሥራ የቀረ ሀብት ቡድን መሪ ይሰጠዋል
ይሰጠዋል
2 በጥበቃ ሥራ ጊዜ ሥራን እንደጥፋቱ ክብደት እንደጥፋቱ ክብደት ከሥራ
በተገቢው መንገድ ያላከናወነ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ስንብት
ወይም በጥበቃ ጊዜ ያንቀላፋ እስከ 5 ቀን ደመወዝ እስከ 6-15 ቀን ደመወዝ
ወይም ተቀያሪ ዘብ ሳይኖር ቅጣት ቅጣት
የጥበቃ ቦታውን ትቶ የሄደ
ወይም ያልተፈቀደለትን ሰው
ያሳደረ

52
ሦስተኛ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ደረጃ ቅጣት ሁለተኛ ደረጃ ቅጣት
ደረጃ ቅጣት
3 ከድርጅቱ ሥራ ጋር እንደጥፋቱ ክብደት እንደጥፋቱ ክብደት ከሥራ
በተያያዘ ሁኔታ በሥራ 5 እስከ 15 ቀን ከአንድ ወር ደመወዝ ስንብት
ኃላፊዎች ወይም ደመወዝ ቅጣት ቅጣት እስከ ደመወዝና
በማናቸውም የድርጅቱ ደረጃ ዝቅ ማድረግ
ሠራተኛ ላይ ማስፈራራት
ወይም ተጽዕኖና የማስገደድ
ሙከራ ያደረገ
4 በድርጅቱ ደብዳቤዎች እንደጥፋቱ ክብደት እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ
ወይም ጽሁፎች ወይም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቀን እስከ አንድ ወር ስንብት
በማናቸውም ዓይነት ሰነዶች እስከ 10 ቀን ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት
ላይ በማናቸውም ሁኔታ ቅጣት
ጉዳት ሊደርስ ወይም
እንደሚደርስ እያወቀ የሥራ
ኃላፊነቱን ያልተወጣ ወይም
ተገቢ ጥበቃና እንክብካቤ
ያላደረገ ወይም ሁኔታው
ከአቅም በላይ ሆኖ በወቅቱ
ለሚመለከተው ክፍል
ያላሳወቀ፡፡
5 በሥራ አጋጣሚ ያየውን እንደጥፋቱ ክብደት እንደጥፋቱ ክብደት እስከ
ወይም የሰማውን ሚስጥር ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ15 ቀን ደመወዝ ቅጣት ከሥራ
ሳይፈቀድለት ለሌላ አካል እስከ 15 ቀን ደመወዝ እስከ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ ስንብት
የነገረ ወይም ያሰራጨ ቅጣት ማድረግ
6 በማናቸውም የድርጅቱ እንደጥፋቱ ክብደት እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ከሥራ
የሥራ ቦታ ቁማር መጫወት እስከ 10 ቀን ደመወዝ ቀን እስከ አንድ ወር ስንብት
ወይም ሌሎች ማናቸውንም ቅጣት ደመወዝ ቅጣት
ዓይነት አስነዋሪ ድርጊቶች
መፈጸም
7 በድርጅቱ ማንኛውም መኪና የጭነቱ ኪራይ የጭነቱ ኪራይ ተገምቶ የጭነቱ
ከተፈቀደለት ጭነት ውጭ ተገምቶ ገቢ ገቢ እንዲሆንና ኪራይ
ገቢ በሚያስገኝ ሁኔታ እንዲሆንና እንደጥፋቱ ክብደት ከ15 ተገምቶ
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንደጥፋቱ ክብደት ቀን እስከ ከአንድ ወር ለድርጅቱ
መንገድ የግል ጥቅም እስከ 10 (አስር) ቀን ደመወዝ ቅጣት ገቢ
ለማግኘት ሰው ወይም ደመወዝ ቅጣት እንዲሆንና
ንብረት ወይም ሌላ ጭነት ተደርጐ
የጫነ ከሥራ ስንብት

53
26.3. በአራተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች
አራተኛ
አንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ሶስተኛ ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት ደረጃ
ቅጣት ቅጣት ቅጣት
ቅጣት
1 በጊዜው ተሰርቶ መጠናቀቅ የጥፋቱ አፈፃፀም የጥፋቱ የጥፋቱ አፈፃፀም ከሥራ
የሚገባውን ሥራ መወዘፍ ሁኔታ ተገምግሞ አፈፃፀም ሁኔታ ሁኔታ ተገምግሞ ስንብት
ወይም ማቀዝቀዝ ወይም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተገምግሞ 6-15 16-30 ቀን
ያልተሠራውን ሥራ እስከ 5 ቀን ደመወዝ ቀን ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት
እንደተሠራ አደርጎ ማቅረብ ቅጣት ቅጣት
2 ለሚመለከታቸው የሥራ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደጥፋቱ እንደጥፋቱ ከሥራ
ክፍሎች እንዲደርስ ክብደት አስከ ክብደት አስከ ስንብት
የተሰጠውን የጽሁፍ 15 ቀን 16-30 ቀን
መልዕክቶች ወይም ትዕዛዝ ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት
ሆን ብሎ ያዘገየ ወይም
ቅጣት
ያላደረሰ፣
3 አግባበ ባላቸው የድርጅቱ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደጥፋቱ እንደጥፋቱ ከሥራ
የሥራ ክፍሎች ወይም የሥራ ክብደት አስከ ክብደት አስከ ስንብት
ኃላፊዎች የሚጠየቁትን የቃል 15 ቀን 16-30 ቀን
ወይም የጽሁፍ ማስረጃዎች ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት
ወይም መረጃዎች ከአቅም
ቅጣት
በላይ ካልሆነ በስተቀር
በጊዜው ለመስጠት ፈቃደኛ
አለመሆን ወይም ማዘግየት
ወይም በማጉላላት
ትክክለኛውን ያለመግለጽ
ወይም በወቅቱ መቅረብ
የሚገባቸውን ሁኔታዎችና
ጉዳዮች አለማቅረብና
አለማሳወቅ
4 ኃላፊው በቃልም ሆነ በጽሁፍ እንደጥፋቱ ክብደት እንደጥፋቱ እንደጥፋቱ ከስራ
የሚሰጠውን ትዕዛዝ ወይም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ክብደት ከ6-15 ክብደት ከ16-30 ስንብት
መመሪያ ባለማክበር ወይም እስከ 5 ቀን ደመወዝ ቀን ደመወዝ ቀን ደመወዝ
የሥራ ኃላፊነት ለመቀበል ቅጣት ቅጣት ቅጣት
ፈቃደኛ አለመሆን ወይም
ሥራውን ላለመሥራት
ምክንያት መፍጠርና የሥራ
ጊዜን በማባከን
5 አግባብ ያልሆነ ክፍያን
የወሰደውን ተመላሽ የወሰደውን የወሰደውን የወሰደውን
የሚያስከትል የትርፍ ሰዓት አድርጎ የ5 (አምስት) ተመላሽ ተመላሽ አድርጎ ተመላሽ
ሥራ የሠራ ወይም ያሠራ ቀን የደመወዝ ቅጣት አድርጎ እንደጥፋቱ አድርጎ
ወይም ተገቢ ያልሆነ የውሎ እንደጥፋቱ ክብደት ከ30 ከሥራ
አበል የወሰደ ወይም ያስወሰደ ክብደት የ15 ቀን ደመወዝ ስንብት
ወይም እንዲከፈል ያደረገ (አስራ አምስት) ቅጣት እስከ
ሠራተኛ ቀን ደመወዝ ደመወዝና ደረጃ
ቅጣት ዝቅ ማድረግ
6 ለድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ የጎደለውን ገንዘብ የጎደለውን የጎደለውን ከሥራ

54
አራተኛ
አንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ሶስተኛ ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት ደረጃ
ቅጣት ቅጣት ቅጣት
ቅጣት
የተሰጠውን ገንዘብ ያለ በቂ ከፍሎ የ5 (አምስት) ገንዘብ ክፍሎ ገንዘብ ክፍሎ ስንብት
ምክንያት ለግሉ የተጠቀመ ቀን ደመወዝ ቅጣት የ15 (አስራ የ30 (ሰላሳ) ቀን
አምስት) ቀን ደመወዝ ቅጣት
ደመወዝ ቅጣት
7 ለድርጅቱ ሥራ/ ደንብ ልብስ ድርጅቱ ለደንብ ድርጅቱ ድርጅቱ ለደንብ ከሥራ
እንዲውሉ የተሰጡትን የሸጠ ልብሱ ያወጣውን ለደንብ ልብሱ ልብሱ ያወጣውን ስንብት
ወይም የለወጠ ወይም ለሌላ ገንዘብ መልሶ እስከ 5 ያወጣውን ገንዘብ መልሶ
ተግባር ያዋለ (አምስት) ቀን ገንዘብ መልሶ የ30 (ሰላሳ) ቀን
ደመወዝ ቅጣት የ15 (አስራ ደመወዝ ቅጣት
አምስት) ቀን
ደመወዝ ቅጣት

26.4. በአምስተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች


አምስተኛ
አንደኛ ሁለተኛ ሦስተኛ ደረጃ አራተኛ ደረጃ
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት ደረጃ
ደረጃ ቅጣት ደረጃ ቅጣት ቅጣት ቅጣት
ቅጣት
1 ዘግይቶ ወደ ሥራ የባከነ ሰዓት የባከነ ሰዓት የባከነ ሰዓት የባከነ ሰዓት ከሥራ
የሚመጣና በወር ተቀንሶ ተቀንሶ የ5 ተቀንሶ የ15 ተቀንሶ የ30 ስንብት
ውስጥ የዘገየባቸው የጽሁፍ (አምስት) (አስራ (ሰላሳ) ቀን
ሰዓት ተዳምረው የባከነ ማስጠንቀቂያ ቀን ደመወዝ አምስት) ቀን ደመወዝ ቅጣት
የሥራ ሰዓት ከ8:00 በሰው ሀብት ቅጣት በሰው ደመወዝ
ሰዓት በላይ ከሆነ ቡድን መሪ ሀብት ቡድን ቅጣት
ይሰጣል መሪ ይሰጣል
2 ለድርጅቱ ሥራ የቃል የጽሁፍ የ5 ቀን የ15 ቀን ከሥራ
እንዲውሉ የተሰጡትን ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት ስንብት
ማናቸውንም የአደጋ ቅጣት
መከላከያ መሳሪያዎች
ወይም የሥራ
መገልገያ መሣሪያዎች
ወይም ንብረቶችን
ተገቢ ጥበቃና
እንክብካቤ ያላደረገ
ወይም በአግባቡ
ያልተጠቀመ
3 ለድርጅቱ ሥራ የቃል የጽሁፍ የ5 ቀን የ15 ቀን ከሥራ
የተሰጡ የደንብ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ደመወዝ ቅጣት ስንብት
ልብሶችን ለብሶ ቅጣት
ያልተገኘ

55
አንቀጽ ሃያ ሰባት (27) የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያዎች
27.1 ሠራተኛውን ከሥራ ጋር ከተያያዘ አደጋ ወይም በሽታ ለመከላከል ድርጅቱ የሥራ
ልብስና የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች ከታች በ27.10 በተገለፀው አግባብ ይሰጣል፡፡
27.2 በየወሩ የሚሰጡ ካልሆነ በስተቀር የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያዎች አዲስ በጀት
ዓመት ከተጀመረበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ መሰጠት ይኖርበታል፡፡
27.3 ድርጅቱ ተገቢ የሆነ የመፀዳጃ አገልግሎትና ሁኔታ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
27.4 የሙከራ ጊዜያቸውን ያልጨረሱ አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኞችም ከታች በ27.10 በተጠቀሱ
የስራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ በዚህ አንቀጽ የተጠቀሱ የአደጋ መከላከያ
መሳሪያዎችን ማግኘት ይገባቸዋል፡፡
27.5 ብትን ጨርቅ ተገዝቶ የሚሰጥ ከሆነ ለኮትና ሱሪ 3.5 ሜትር (ሶስት ሜትር ከግማሽ)
ጨርቅ ለአንድ ሙሉ ልብስ ይሰጣል፡፡ ለካፖርት፣ ለሸሚዝና ሱሪ፣ ለጃኬትና ጉርድ ቀሚስ
ከሆነ 3 (ሶስት) ሜትር ለአንድ ሙሉ ልብስ ይሰጣል፡፡
27.6 የደንብ ልብስ በሚሰጥበት የስራ መደብ ላይ ተመድቦ የሚሰራ አንድ ሰራተኛ የደንብ
ልብስ በሚሰጥበት በጀት ዓመት 9 (ዘጠኝ) ወርና ከዚያ በላይ ከሰራ የተፈቀደውን የደንብ
ልብስ በሙሉ ያገኛል፡፡
27.7 የደንብ ልብስ በሚሰጥበት የስራ መደብ ላይ ተመድቦ የሚሰራ አንድ ሰራተኛ የደንብ
ልብስ በሚሰጥበት በጀት ዓመት ከ9 (ዘጠኝ) ወር በታችና ከ3 (ሶስት) ወር በላይ ከሰራ
የተፈቀደው የደንብ ልብስ መጠን በዓመት 2 (ሁለት) ከሆነ የተፈቀደውን 50 በመቶ
ወይም ግማሹን እንዲሁም የተፈቀደው የደንብ ልብስ መጠን በዓመት አንድ ብቻ ከሆነ
የተፈቀደውን 100% ወይም ሙሉውን ያገኛል፡፡ ነገር ግን አገልግሎቱ ከ3 (ሶስት) ወር
በታች ከሆነ አያገኝም፡፡
27.8 ከታች በ27.10 የተጠቀሱ የደንብ ልብሶች ከድርጅቱ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ
በስተቀር መሰጠት ያለባቸው ተገዝተውን መሰፋት ያለባቸው ተሰፍተው ነው፡፡
27.9 በመደበኛ ትምህርትም ይሁን በሌላ በማናቸውም ምክንያት በበጀት ዓመቱ በመደበኛ
ስራ ላይ ለሌሉ የስራ ሀላፊዎችም ሆነ ሰራተኞች የደንብ ልብስ አያገኙም፡፡

56
27.10 ለሠራተኛው የሚሰጥ የሥራ ደኅንነት መጠበቂያና የሥራ
ልብሶች
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
1 የጥበቃ ሽፍት መሪ እና  ላይት ብሎ ቴትሮን ኮትና ሱሪ  በዓመት ሁለት
ወንድ ጥበቃ ከተንጠልጣይ ባጅ ጋር
 ሸሚዝ በሀገር ውስጥ የተመረተ ነጭ  በዓመት ሁለት

 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ


ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ካፖርት  በሦስት ዓመት አንድ

 የዝናብ ልብስ  በሦሰት አመት አንድ

 የጭቃ ጫማ (ረዥም ኘላስቲክ ቦት  በሦስት አመት አንድ


ጫማ) ጥራት ያለው በሀገር ውስጥ
የተመረተ
 ኮፍያ ከልብሱ ጋር የሚመሣሠል  በሁለት አመት አንድ
የትራፊክ ኮፊያ አይነት
 ከራቫት /ላይት ብሎ/  በዓመት አንድ

 የልብስ ሣሙና 250 ግራም  በወር ሁለት

 ቀበቶ  በዓመት አንድ

2 ሴት ፈታሽ  ላይት ብሉ ቴትሮን ጃኬትና ጉርድ  በዓመት አንድ


ቀሚስ በሀገር ውስጥ የተመረተ
ከተንጠልጣይ ባጅ ጋር
 ወጥ ሸሚዝና ሱሪ (ነጭ ሸሚዝና  በዓመት አንድ
ላይት ብሉ ሱሪ) በሀገር ውስጥ
የተመረተ
 ሸሚዝ በሀገር ውስጥ የተመረተ ነጭ  በዓመት አንድ
 የውስጥ ልብስ (ቦኘሊን)  በዓመት አንድ
 ካፖርት  በዓመት አንድ

 የዝናብ ልብስ  በሦስት አመት አንድ

 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ


ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ኮፍያ ከልብሱ ጋር የሚመሣሠል  በዓመት ሁለት ጥንድ
የትራፊክ
 ካራቫት /ላይት ብሉ/  በዓመት አንድ

57
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
 የልብስ ሣሙና 250 ግራም  በወር ሁለት

3 ሾፊር  ቱታ ካኪ ቴትሮን (ብሉ ብላክ)  በሁለት ዓመት አንድ


 ቴትሮን ኮትና ሱሪ /ላይት ብሉ/  በዓመት ሁለት

 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ


ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የዝናብ ልብስ  በሦስት አመት አንድ
 ሸሚዝ ነጭ በሀገር ውስጥ የተመረተ  በዓመት ሁለት
 የልብስ
ነጭ ሣሙና 250 ግራም  በወር አንድ
4 ሞተረኛ ፖስተኛ  ቆዳ ጃኬት  በሁለት ዓመት አንድ
 ሱሪና ሸሚዝ ካኪ ቴትሮን /ላይት  በዓመት ሁለት
ብሉ/
 አጭር ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት ሁለት ጥንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የዝናብ ልብስ  በሦስት አመት አንድ
 የብረት ቆብ የድርጅቱ ንብረት  እንዳለቀ የሚተካ
የሆነ
 የቆዳ ጓንት  እንዳለቀ የሚተካ
5 መዝገብ ቤት ሠሪተኞች  3/4 ካኪ ቴትሮን ካፖርት ጥራት  በዓመት አንድ
ወይም የሰራተኛ የግል ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
ማህደር አከናዋኝ  ወተት  በቀን 1 ሊትር

6 የሂሳብ ሰነድ ያዥ  3/4 ካኪ ቴትሮን ካፖርት ጥራት  በዓመት አንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ወተት  በቀን 1 ሊትር
7 ማባዣ ሠራተኞች  3/4 ካኪ ቴትሮን ካፖርት ጥራት  በዓመት ሁለት
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ፎጣ  በዓመት አንድ
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ

 የገላ/ የእጅ ሣሙና ከ175-200  በወር አንድ


ግራም
 ኦሞ ከ175-200 ግራም  በወር አንድ
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት አንድ ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ወተት  በቀን አንድ ሌትር
 ከኘላሲቲክ የተሠራ ማስክ  እንዳለቀ የሚተካ

58
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
 ከኘላሲቲክ የተሠራ የእጅ ጓንት  እንዳለቀ የሚተካ
8 የቢሮ ተላላኪ (ሴት)  ነጭ ሸሚዝ በሀገር ውስጥ የተመረተ  በዓመት አንድ
 የውስጥ ልብስ ጥራት ያለው በሀገር  በዓመት አንድ
ውስጥ የተመረተ
 ቴትሮን ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ  በዓመት አንድ
(ላይት ብሉ)
 ወጥ ሸሚዝና ሱሪ (ላይት ብሉ)  በዓመት አንድ
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ
9 የቢሮ ተላላኪ (ወንድ)  ነጭ ሸሚዝ በሀገር ውስጥ የተመረተ  በዓመት ሁለት
 ላይት ብሎ ቴትሮን ኮትና ሱሪ  በዓመት ሁለት
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ
10 የቢሮ ጽዳት ሠራተኞች  ካኪ ቴትሮን ቀሚስ፣ ከቀሚሱ ጋር  በዓመት ሁለት
(ሴት) ተመሣሣይ የሆነ ሙሉ ሽርጥ
እንዲሁም የውስጥ ልብስ፣
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የልብስ ሣሙና 250 ግራም  በወር አንድ
 የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
 የጨርቅ ማስክ  በዓመት ሁለት
 የፀጉር መሸፈኛ ቆብ ጨርቅ  በዓመት ሁለት
 የዝናብ ልብስ  በሦስት አመት አንድ
 የመፀዳጃ የእጅ ጓንት /ላስቲክ/  እንዳለቀ የሚተካ

12 የቢሮ ጽዳት ሠራተኞች  ካኪ ቴትሮን ኮትና ሱሪ /ላይት ብሉ/  በዓመት ሁለት


(ወንድ)
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የልብስ ሣሙና 250 ግራም  በወር አንድ

 የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ


ግራም
 የጨርቅ ማስክ  በዓመት ሁለት

59
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
 የፀጉር መሸፈኛ ቆብ ጨርቅ  በዓመት ሁለት

 የዝናብ ልብስ  በሦስት አመት አንድ



 የመፀዳጃ የእጅ ጓንት /ላስቲክ/  እንዳለቀ የሚተካ አንድ

13 አትከልተኛ  ካኪ ቴትሮን ኮትና ሱሪ (ላይት  በዓመት ሁለት


ብሉ)
 ነጭ ሸሚዝ በሀገር ውስጥ የተመረተ  በዓመት ሁለት
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት ሁለት ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ቱታ ካኪ ቴትሮን (ዳርክ ብሉ)  በዓመት ሁለት
 ላስቲክ ቦት ጫማ ጥራት ያለው  በሁለት ዓመት አንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ ጥንድ
 የዝናብ ልብስ  በሦስት ዓመት አንድ
 የጨርቅ ቆብ  በዓመት ሁለት

 የገላ/ የእጅ ሣሙና ከ175-200  በወር ሁለት


ግራም
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር ሁለት

 የእጅ ጓንት/ሸራ/  እንዳለቀ የሚተካ

14 ላይብራሪያን  ¾ ነጭ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ

 ፎጣ  በዓመት አንድ
 ወተት  በቀን አንድ ሊትር
15 ንድፍ ሠራተኞች  ¾ ነጭ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ
 ፎጣ  በዓመት አንድ
 የገላ/ የእጅ ሳሙና ባለ ከ175-200  በወር አንድ
16 ላቦራቶሪ ቴክኒሽያኖች፣  ግራም
¾ ነጭ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት ሁለት
ሶይል ኬሚስቶች፣ ሶይል  ወተት  በቀን አንድ ሊትር
ሜካኒክስ የስራ መደብ ላይ  ፎጣ  በዓመት አንድ
ተመድበው የሚሰሩ  የጀሮ ሴፍቲ  በዓመት አንድ
ባለሙያዎች፣ ማቴሪያል  ኦሞ  በወር አንድ
መሀንዲሶች፣ ዳታ አናሊስት  የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ
እና የላቦራቶሪ ሀላፊዎች፡፡
 የገላ/ እጅ ሣሙና ከ175-200 ግራም  በወር አንድ
የላቦራቶሪ ሀላፊዎችና ዳታ
 ጫማ ከኬሚካል የሚከላከል (አፈር  በአመት አንድ ጥንድ
አናሊስት ባለሙያዎች
ኬሚስትሪና ውሀ ጥራት ለሚሰሩ

60
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
ወተት አያገኙም፡፡ ባለሙያ)
 ጫማ ከኬሚካል የሚከላከል  በአመት አንድ ጥንድ
ከሚያገኙት ባለሙያዎች ውጭ
ለሌሎች ባለሙያዎችና ሀላፊዎች
ሴፍቲ ጫማ በሀገር ውስጥ
የተመረተ
 የዝናብ ልብስ  በሶስት ዓመት አንድ
 የጨርቅ ቆብ  በአመት አንድ
 የእጅ ጓንት (የፕላሰቲክና የሸራ)  እንዳለቀ የሚተካ
 የአፍንጫና የአፍ ማሰክ  እንዳለቀ የሚተካ
17 ሁለገብ ጥገና ባለሙያ  ¾ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ

 የዝናብ ልብስ  በሦስት አመት አንድ

 ቱታ ካኪ ቴትሮን  በዓመት 2 (ሁለት)


 ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት 2 (ሁለት)
በሀገር ውስጥ የተመረተ ጥንድ
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ
 የገላ/ እጅ ሣሙና ባለ 100 ግራም  በወር አንድ
18 ማንኛውም የመሰክ ሰራተኛ  አጎበር በኪሚካል የተነከረ እንዳለቀ የሚተካ
መሰክ ሲወጣና በመሰክ ላይ ፊሊት በወር ሁለት ትልቁ
እንዳለ
19 ቆፋሪ/ ድሪለር/ ሪግ  ቱታ ካኪ ጥቁር ሰማያዊ  በዓመት ሁለት
ኦፕሬተር
 የዝናብ ልብስ  በሦስት ዓመት አንድ

 ላስቲክ ቦት ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት አንድ ጥንድ


በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ቦት ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው በሀገር  በዓመት ሁለት ጥንድ
ውስጥ የተመረተ
 ወተት  በቀን አንድ ሊትር
 የገላ/ የእጅ ሣሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ
 ፎጣ  በዓመት አንድ
 ሄልሜት  እንዳለቀ የሚተካ
 የእጅ ጓንት ሸራ  እንዳለቀ የሚተካ

61
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
20 ጂኦሎጂስቶች እና  ¾ ነጭ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ
ጂኦፊዚክስ
 የዝናብ ልብስ  በሦስት ዓመት አንድ
 ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት አንድ ጥንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ
21 የጋራዥ ክፍል ቴክኒሽያኖች  ቱታ ካኪ ቲትረን ጥቁር ሰማያዊ  በዓመት ሁለት
(መካኒኮች፣ ኤሌክትሪሽያን)  ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት ሁለት ጥንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የእጅ ጓንት ሸራ  እንዳለቀ የሚተካ
 የልብስ ሣሙና 250 ግራም  በወር ሁለት
 የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
 ኦሞና አጃክስ  እንዳለቀ

 ፎጣ  በዓመት ሁለት
 የአይንና የፊት ማስክ  እንዳለቀ

22 የስምሪት ባለሙያና  ¾ ነጭ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ


የንብረት፣ጠአ/የተሽ/ጥ/ስ/  የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ
ቡድን መሪ ግራም
 ፓራተሮፐር መሰል (ሴፍቲ) ቅዳ  በዓመት አንድ ጥንድ
ጫማ ጥራት ያለው በሀገር ውስጥ
የተመረተ
23 ቀያሽ  ካኪ ሱሪና ሸሚዝ ከነኮፍያው  በዓመት አንድ
 ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት አንድ ጥንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የዝናብ ልብስ  በሦስት ዓመት አንድ
24 የእቃ ግምጃ ቤት ሰራተኛ  ¾ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት አንድ ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
(የላቦራቶሪ ዕቃ ግ/ቤት ሰራተኛን
አያካትትም)
 የገላ/ የእጅ ሣሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
 የልብስ ሣሙና 250 ግራም  በወር አንድ

 ወተት  በቀን አንድ ሊትር


 ጫማ ከኬሚካል የሚከላከል  በዓመት አንድ ጥንድ
(ለላቦራቶሪ ስቶር ሰራተኛ ብቻ)

62
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
 የእጅ ጓንት የፕላሰቲክና የሸራ  እንዳለቀ የሚተካ
(ለላቦራቶሪ ስቶር ሰራተኛ ብቻ)
 የአፍንጫና የአፍ ማሰክ (ለላቦራቶሪ  እንዳለቀ የሚተካ
ስቶር ሰራተኛ ብቻ)
 ፎጣ  በዓመት አንድ

25 ግዥ ሰራተኛ  ¾ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ


 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በዓመት አንድ ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
26 የአይቲ ባለሙያዎች  ¾ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ

 ጎግል መነፀር  እንዳለቀ

 የፕላስቲክ ጓንት  እንዳለቀ

 የአይንና የአፍንጫ ማሰክ  እንዳለቀ

27 ገንዘብ ያዥ  የገላ/ የእጅ ሣሙና ከ175-200  በወር አንድ


ግራም
 ፎጣ  በዓመት አንድ
 አልኮል  በ3 ወር አንድ ሊትር
በግል
28 የምህንድስናና የሴክቶራል  ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት አንድ ጥንድ
ጥናት ባለሙያዎችና በሀገር ውስጥ የተመረተ
ሀላፊዎች  የዝናብ ልብስ  በሶስት ዓመት አንድ

29 መሬት አጠቃምና የአካባቢ  ሴፊቲ ጫማ ጥራት ያለው በሀገር  በዓመት አንድ ጥንድ
ጥናት እና የገበያ ጥናት ውስጥ የተመረተ
ባለሙያዎችና ሀላፊዎች  የዝናብ ልብስ  በሶስት ዓመት አንድ

30 ኦዶቪዥዋል ባለሙያ  ¾ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ


 ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት አንድ ጥንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ
31 ለሁሉም የድርጅቱ  ሶፍት  በወር አንድ
ሰራተኞች  የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
32 የአፈር ቅየሳ ባለሙያ  ሴፍቲ ቆዳ ጫማ ጥራት ያለው  በዓመት አንድ ጥንድ
በሀገር ውስጥ የተመረተ
 ካኪ ቲትረን ቱታ  በዓመት አንድ

 የእጅ ጓንት  እንዳለቀ

63
ተ. የሠራተኛው የሚሠጠው የሥራና የደንብ ልብስ
ብዛት
ቁ የሥራ መደብ ዓይነት
33 የመረጃ ዴስክ ሰራተኛ  ¾ ካኪ ቴትሮን ካፖርት  በዓመት አንድ
34 ቱልስ ሰራተኛ  3/4ኛ ካኪ ቲተሮን ካፖርት በሀገር  በአመት አንድ
ውስጥ የተመረተ
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በአመት አንድ ጥንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር አንድ
 የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
 ፎጣ  በዓመት አንድ

35 በያጅ/ ቦዲ ማን  ካኪ ቲትረን ቱታ  በዓመት ሁለት

 ሴፍቲ ጫማ ጥራት ያለው በሀገር  በዓመት ሁለት ጥንድ


ውስጥ የተመረተ
 የበየዳ መከላከያ የዓይን መነፀር  እንዳለቀ
 ከቆዳ የተሰራ ሽርጥ  እንዳለቀ
 የልብስ ሳሙና 250 ግራም  በወር ሁለት
 የገላ/ የእጅ ሳሙና ከ175-200  በወር አንድ
ግራም
 ወተት  በቀን አንድ ሊትር
 ኦሞና አጃክስ  እንዳለቀ
 ፎጣ  በዓመት አንድ
37 ጠቅላላ አገልግሎት ባለሙያ  3/4ኛ ካኪ ቲተሮን ካፖርት በሀገር  በአመት አንድ
ውስጥ የተመረተ
 አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ ጥራት  በአመት አንድ
ያለው በሀገር ውስጥ የተመረተ

አንቀጽ ሀያ ስምንት (28) የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓትና የሥራ


ክርክር
28.1 ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ በድርጅቱ በየትኛውም ደረጃ በሚወሰድበት አስተዳደራዊ
እርምጃ ወይም የሥራ ሁኔታ፣ የሥልጠናና ትምህርት፣ ፈቃድ ወይም ጥቅማጥቅም
አፈፃፀም ቅሬታ ካለው አቤቱታውን በፅሁፍ ለቅርብ ተጠሪው ያቀርባል፡፡ የቅርብ
ተጠሪው በሚሰጠው መልስ ቅር ከተሰኘ ወይም ካልረካ ቀጥሎ ላለው የሥራ ኃላፊ ወይም

64
ቅሬታ ሰሚ (ካለ) በፅሁፍ ያቀርባል፡፡ በዚህ ውሳኔ አሁንም ቅር ከተሰኘ ሂደቱን እየጠበቀ
የሚያቀርብ ሲሆን በመጨረሻ ለዋና ሥራ አስፈፃሚ በፅሁፍ ያቀርባል፣
28.2 በየደረጃው ያሉ ቅሬታ ሰሚዎች (ቅሬታውን ተቀብለው የሚያዩ የሥራ ኃላፊዎች)
ውሳኔውን እንደ ጉዳዩ አስቸኳይነት እየታየ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ እስከ አምስት (5)
ተከታታይ የሥራ ቀናት ያሳውቃሉ፡፡ በዚህ የጊዜ ገደብ ምላሽ ካላገኘ ለሚቀጥለው የሥራ
ኃላፊ ያቀርባል፡፡ ሆኖም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ
ይሆናል፡፡
28.3 ደረጃውን ጠብቆ ያልቀረበ ቅሬታ ተቀባይነት የለውም፡፡
28.4 ሠራተኛው ለቅሬታው ምላሽ በፅሁፍ በተሰጠው ውሳኔ ውሳኔውን በተቀበለ በ10 የሥራ
ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለሚቀጥለው የሥራ ኃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡ ውሳኔው በቃል
የተሰጠው ከሆነ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በፅሁፍ አድርጐ ለሚቀጥለው
ማቅረብ አለበት፡፡
28.5 የተወሰነው የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ከማለፉ አስቀድሞ ሠራተኛው በህመም ወይም ህጋዊ
ማስረጃ በሚቀርብበት በሌላ የግል ችግር ወይም በድርጅቱ ለሥራ ታዝዞ ለመስክ ሥራ
በመሄዱ ምክንያት በሥራ ቦታ ባለመገኘቱ ቅሬታውን ማቅረብ ባይችል በሥራ ቦታ እያለ
ያባከነው ጊዜ ካለ ተቀንሶ የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜው ወደ ሥራ ቦታ (ወደ ድርጅቱ)
ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ይጀምራል፡፡
28.6 ሠራተኛው ቅሬታውን በዚህ ሥነ-ሥርዓት በተወሰነው ጊዜ እና ሁኔታ ካላቀረበ ቅሬታውን
በአስተዳደራዊ መልኩ እንዲታይለት ድርጅቱን ለመጠየቅ የሚኖረው መብት በይርጋ
ይታገዳል፡፡
28.7 ቅሬታ የቀረበለት የሥራ ኃላፊ ወይም የሥራ ኃላፊው ፀሐፊ ሠራተኛው በፅሁፍ
የሚያቀርበውን ቅሬታ ፈርመው የመቀበል እና የሥራ ኃላፊው በወቅቱ ምላሽ የመስጠት
ግዴታ አለባቸው፡፡

አንቀጽ ሀያ ዘጠኝ (29) የሥራ ውጤት ምዘና


29.1. የሥራ አፈፃጸም ምዘና ውጤት አስፈላጊነት
29.1.1 ሠራተኞችን በሥነ-ምግባር ለማነጽ፣ ጠንካራ ጐናቸውን ለማጐልበት፣ ድክመታቸውን
ለማረም፣ የሥራ ችሎታቸውንና የግል ሙያን ለማዳበር በዚህም አንፃር ድርጅቱን
ትርፋማ በማድረግ የሥራ ውጤት ያለማቋረጥ እድገት እንዲያሳይ ለማድረግ፣እያንዳንዱ

65
ሠራተኛ ባስመዘገበው የሥራ ውጤት መሠረት ማበረታቻ ለማድረግና የሥራ ውድድር
በሠራተኞች መካከል ለመፍጠር፣ የሥራ ውጤትንም ለማሳደግ፣
29.1.2 ከፍተኛ የሥራ ችሎታና ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ለይቶ ለማወቅና ተገቢውን
ሥልጠና በመስጠት ለከፍተኛ ሀላፊነት ለማዘጋጀት፣
29.1.3 ለተመደቡበት የሥራ ቦታ ውጤታማ ያልሆኑ ሠራተኞችን በመለየት የችግሮቻቸውን
ምንጭ ለይቶ በማወቅ ሥልጠና የሚያስፈልጋቸው ከሆነ የሥራ ላይ ሥልጠና
ለመስጠት፣ ለተመደቡበት የሥራ ቦታ ብቃት የሌላቸውን ሠራተኞች ወደሚመጥኑበት
ሥራ ለማዛወር እንዲሁም በሚመደቡበት የተለያዩ ሥራዎች ላይ ተከታታይ የችሎታ
ማነስ የሚታይባቸውን ከደረጃ ዝቅ ለማድረግና ከሥራ ለማሠናበት፡፡

29.2. የሠራተኛው የሥራ ውጤታማነት መመዘኛ ሥርዓት


29.2.1. የሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት የሚለካው በድርጅቱ የውጤት ተኮር ዕቅድ
አዘገጃጀትና የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት አሞላል መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
29.2.2. ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና በዓመት ሁለት
ጊዜ በቅርብ አለቃው ይሞላለታል፤
29.2.3. የሠራተኛው ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና የሚካሄደው በቅርብ የሥራ ኃላፊው
መሪነት ሆኖ በቅርብ የሥራ ኃላፊውና በፈፃሚው ሠራተኛ በየወቅቱ ክትትል በተያዙ
የዕቅድ አፈፃፀም መረጃዎች ላይ በመመስረት ይሆናል፤

29.2.4. አፈጻጸም ምዘና ውጤቱ በሠራተኛው የቅርብ ኃላፊ ይሞላል፡፡ ሰራተኛው በተሰጠው
የሥራ አፈፃጸም ምዘና ውጤት ካልተስማማ ቅሬታውና አስፍሮ የሥራ አፈጻጸም ምዘና
ውጤቱ የመፈረም ግዴታ ያለበት ሲሆን የሰራተኛው ቅሬታም ውጤቱን በሞላው ሀላፊ
የቅርብ ኃላፊ ታይቶ ከፀደቀ የሚያዝ ይሆናል፡፡ የቅሬታውን ውጤትም ውጤቱን
ያፀደቀው ሀላፊ ሰራተኛውን አስጠርቶ በአካል ሊያስረዳው ይገባል፡፡ ሰራተኛው
በውጤቱ ላይ ቅሬታ አቅርቦ ተቀባይነት ካላገኘ ውጤቱን እንደተቀበለው ይወሳዳል፡፡
የሠራተኛው የቅርብ ኃላፊ ማለት መስክ ላይ ላሉት የመስክ ተጠሪ መሐንዲሱ ወደ
መደበኛ የሥራ ክፍላቸው እስኪመለሱ ድረስ መመዘኛውን በቅድሚያ ይሞላል፡፡
29.2.5. ለሠራተኛው የሚሰጥ የሥራ አፈፃጸም ምዘና ውጤት እንደሚከተለው ይመደባል፡፡
ከ86ና በላይ A
ከ81-≥86 B+
ከ75-≥81 B

66
ከ65-≥75 C+
ከ50-≥65 C
29.2.6. በተሰጠው የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት > 86 ላገኘ ወይም ከ60 በታች ለተሰጠው
ሠራተኛ የቅርብ ኃላፊው በቂ መግለጫና ማብራሪያ በግምገማው ቅጽ ላይ በተዘጋጀው
ቦታ ያስፍራል፡፡
29.2.7. የስራ አፈፃጸም ውጤቱ የመጨረሻ ውጤት ላይ ከመድረሱ በፊት ሠራተኛው ነጥቡን
እንዲያየው ወይም እንዲያውቀው አይደረግም፡፡
29.2.8. የሠራተኛው የሥራ አፈጻጸም ውጤት መመዘኛ ቅጽ የሰው ሀብት አስተዳደር አውቆት
ከግል ማሕደሩ ጋር ከተያያዘ በኋላ ለማንኛውም እድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ፣
የትምህርት፣ ሥልጠና… ወዘተ መገምገሚያና ለሌሎች ተመሳሳይ ጉዳች ጥቅም ላይ
እንዲውል ይደረጋል፡፡
29.2.9. አንድ ሠራተኛ ቀድሞ ከነበረበት የሥራ ቦታ ወይም መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብና
ቦታ ቢዛወርና የቅርብ ኃላፊው አዲስ ከሆነ ሠራተኛው ከቀድሞው ኃላፊው ጋር አራት
ወርና ከዚያም በላይ ከሠራ የሥራ አፈፃፀሙን የቀድሞው ኃላፊው ይሞላለታል፡፡
አዲስ በተዛወረበት የሥራ ቦታ ከተጠቀሰው ጊዜ በታች እና ከሁለት ወር በላይ ከሠራ
የሥራ አፈፃፀሙን የሚሞላው በአዲስ ሀላፊው ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰላሳ (30) ሰራተኛ በተወሰነ ጊዜ/ ሥራ (ኮንትራት)


ስለመቅጠር
30.1 በአዋጁና በህብረት ስምምነቱ የተጠቀሱትን የተወሰነ ጊዜ/ ሥራ (ኮንትራት) ቅጥር
አፈፃፀም መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ለድርጅቱ ስራ አስፈላጊ የሆኑና በገበያ ላይ በቀላሉ
የማይገኙ ወይም ልዩ ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎችን እንደ አሰፈላጊነቱ በተወሰነ ጊዜ/
ሥራ (በኮንትራት) ቅጥር መፈጸም ይቻላል፡፡ በዚህ መልክ የተቀጠሩ ሰራተኞች ቋሚ
ሰራተኞች የሚያገኙትን ጥቅማጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሆኖም ይህ አንቀጽ የቀን ወይም
የጉልበት ሰራተኞችን አይጨምርም፡፡

አንቀጽ ሰላሳ አንድ (31) ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች


31.1 ይህ ህብረት ስምምነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያልዳሰሳቸው ጉዳዩች ቢኖሩ በአሠሪና
ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡

67
31.2 በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ ያልተጠቀሱት ጉዳዮች አግባብ ባለው ህግና የድር
መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል ፡፡
31.3 በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ ስለተመለከቱትም ይሁን ስለሌሎች የሥራ ሁኔታዎች
መንግስት የሚያወጣቸው ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ ሠላሳ ሁለት (32) ማሻሻልና ማደስ


32.1 በዚህ የሕብረት ስምምነት ውስጥና በድርድሩ ወቅት የታለፉ ወይም የሚጨመሩ ጉዳዮች
ቢኖሩ ድርጅቱና ማኅበሩ በሙሉም ሆነ በከፊል ለማረም ተስማምተዋል፡፡ ማሻሻያው
ወይም እርማቱ በሁለቱ ወገኖች ከተፈረመ በኋላ በሚመለከታቸው መ/ቤቶች ሲጸድቅና
ሲመዘገብ የሕብረት ስምምነቱ አካል በመሆን ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
32.2 ከላይ በተራ ቁጥር 30.1 የተጠቀሰው ሁኔታ ቢኖርም ድርጅቱ በበጀት እጥረት ወይም
የኢኮኖሚ ለውጥ ሲያጋጥመው ይህ የሕብረት ስምምነት ወይም በተለይ የሚመለከተው
አንቀጽ እንዲሻሻል ወይም እንዲቀየር ሲጠየቅ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች የጋራ ስምምነት
እንዲለወጥ፣ እንዲሻሻል ወይም እንዲቀየር ይደረጋል፡፡

ክፍል አምስት
አንቀጽ ሰላሳ ሶስት (33) ኃላፊነትና የስምምነቱ ተፈፃሚነት
33.1 ኃላፊነት
33.1.1 ይህን ህብረት ስምምነት እያንዳንዱ ሰራተኛ ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን የመቆጣጠር ኃላፊነት የድርጅቱ የሥራ አመራር እና
የሰራተኛ ማህበሩ ይሆናሉ፡፡
33.1.2 በዚህ የህብረት ስምምነት የተመለከቱ መብትና ግዴታዎች ላልተወሰነ ጊዜ (ቋሚ) እና
ለተወሰነ ጊዜ/ ስራ (ኮንትራት) ሠራተኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

33.2 ህብረት ስምምነቱ የሚፀናበት ጊዜ


ይህ ህብረት ስምምነት ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት (3) ዓመት የፀና ይሆናል፡፡

68
33.3 ተደራዳሪ ወገኖች
በድርጅቱ በኩል
ሙሉ ስም ሀላፊነት ፊርማ ቀን
1. ----------------------------- ----------------------------- ------------------ -------------
2. ----------------------------- ----------------------------- ------------------ -------------
3. ----------------------------- ----------------------------- ------------------ -------------

በሰራተኛው ማህበር በኩል


ሙሉ ስም ሀላፊነት ፊርማ ቀን
1. ----------------------------- ----------------------------- ------------------ -------------
2. ----------------------------- ----------------------------- ------------------ -------------
3. ----------------------------- ----------------------------- ------------------ -------------

69

You might also like