You are on page 1of 69

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ለርቀት ትምህርት

የተዘጋጀ የሐዲስ ኪዳን መድበል፪: መቐለ

ማውጫ
ሀ. የዚህ መድበል አስፈላጊነት............................................................................................................ xiii
ለ. የዚህ መድበል መዘጋጀት ዓላማ....................................................................................................... xiii
ክፍል አንድ: የሐዋርያትሥራ................................................................................................................ 1
1. መግቢያ................................................................................................................................... 1
1. 2. የጻፈበት ዓላማ................................................................................................................... 1
ምዕራፍ 1.................................................................................................................................... 1
1.1.1-12 የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ለሐዋርያት ስለ መነገሩ......................................................................1
1.2. 13–14 የ 120 ው ቤተ ሰብ የአንድነት ጸሎት.................................................................................1
1.3. 15–26 ጴጥሮስ በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ ይመረጥ ዘንድ ሐሳብ አቀረበ.................................................2
ምዕራፍ 2.................................................................................................................................... 2
2.1. 1–4 መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ ወረደ..................................................................................... 2
2.2. 5-13 የተለያዩ አይሁዳውያን በ 120 ው ቤተሰብ ልዩ ልዩ ቋንቋ መናገር ተገረሙ..........................................2
2.3. 14–21 ቅዱስ ጴጥሮስ በ 120 ቤተሰብ ላይ የተሰነዘረውን ተቃውሞ ተቃወመ............................................2
2.4. 22–36 ክርስቶስ ለእስራኤላውያን በተአምርም በትሩፋትም የተገለጠ እንደነበር ጴጥሮስ ተናገረ........................3
2.5. 37-42 የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ማመን.................................................................................... 3
2.6. 43-47 በእመናን መካከል የነበረ ሕይወት....................................................................................... 3
ምዕራፍ 3.................................................................................................................................... 3
3.1. 1–11 ጴጥሮስና ዮሐንስ በክርስቶስ ስም ሸባ ሁኖ የተወለደውን ልጅ ፈወሱ................................................3
3.2. 12–26 ሕዝቡ በዚህ ሰው መዳን ምክንያት ለአቀረቡት አድናቆት የጴጥሮስ መልስ........................................4
ምዕራፍ 4.................................................................................................................................... 4
4.1. 1–7 በሐዋርያት ላይ የተደረገው የአይሁድ መምህራን ተቃውሞ.............................................................4
4.2. 10–12 በቀረበው ተቃውሞ የሐዋርያው ጴጥሮስ መልስ.....................................................................4
4.3. 13–18 በጴጥሮስና በዮሐንስ በድጋሚ የተሰነዘረ ተቃውሞ...................................................................4
4.4. 19–23 ጴጥሮስና ዮሐንስ አቋማቸውን አሳወቁ...............................................................................4
4.5. 24–31 ለሐዋርያት በሚደረግላቸው ድል የ 120 ው ቤተሰብ ምስጋና......................................................5
4.6. 32–37 የአማኞች ኅብረት....................................................................................................... 5
ምዕራፍ 5.................................................................................................................................... 5
5.1. 1–14 የሐናንያና የሰጲራ ውሸት.............................................................................................. 5

1
ሐዲስ ኪዳን ማስተማሪያ መድበል፪: አዘጋጆች: ሊ/ሊቃውንት ያሬድ ካሣና መ/ር ፍሬ ስብሐት አባዲ.
5.2. 5–16 ጴጥሮስ ሕሙማንን በጥላው መፈወስ ጀመረ........................................................................5
5.3. 17–28 በሐዋርያት ትምህርት ላይ የተደረገ ቅንዓት........................................................................5
5.4. 29–33 ጴጥሮስና ዮሐንስ ለተቃዋሚዎች የሰጡት መልስ..................................................................6
5.5. 34–39 ገማልያል ሐዋርያትን የሚቃወሙ ሰዎችን ተቃወመ..............................................................6
5.6. 40–42 ሐዋርያት ጠላትን ስለ ማሳፈራቸው................................................................................ 6
ምዕራፍ 6.................................................................................................................................... 6
6.1. 1–7 የሰባቱ ዲያቆናት መመረጥ................................................................................................. 6
6.2. 8–15 በእስጢፋኖስ ላይ የተደረገ የሐሰት ክስ.................................................................................. 7
ምዕራፍ 7.................................................................................................................................... 7
7.1. 1-53 እስጢፋኖስ በምዕራፍ 6 ለተነገረበት የሐሰት ምስክርነት መልስ የሰጠበት ክፍል.....................................7
7.2. 54–60 የእስጢፋኖስ መገደል.................................................................................................... 8
ምዕራፍ 8.................................................................................................................................... 8
8.1. 1–4 የቤተክርስቲያን መሰደደና መበታተን...................................................................................... 8
8.2. 5–8 ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ የሆነው ፊልጶስ ሰማርያ በሚባል ሀገር ማስተማር ጀመረ....................................8
8.3. 9–13 ጠንቋዩ ሲሞን ስለ የሚያደርገው ምትሐትና በፊልጶስ ትምህርት ማመኑ..........................................8
8.4. 14–25 ጴጥሮስና ዮሐንስ ከሐዋርያት ወደ ሰማርያ ስለ መላካቸው.......................................................8
8.5. 26–40 ፊልጶስና ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ.................................................................................... 9
ምዕራፍ 9.................................................................................................................................... 9
9.1.1–2 ጳውሎስ በምእመናን ላይ ሲያደርስ የነበረው ማሳዳድ....................................................................9
9.2.3–9 የጳውሎስ መጠራት.......................................................................................................... 9
9.3.10–16 የደማስቆው ነዋሪ ሐናንያ ጳውሎስን ያጠምቅ ዘንድ ታዘዘ...........................................................9
9.4.17–26 የጳውሎስ መዳንና የመጀመርያ ምስክርነት..........................................................................10
ምዕራፍ 10................................................................................................................................ 10
10.2. 3-8 ለቆርኔሎዎስ መልአክ ተገለጠለት...................................................................................... 11
10.3. 9-16 የጴጥሮስ ራእይ........................................................................................................ 11
10.4. 17-22 ከቆርኔሌዎስ የተላኩ ሰዎች ጴጥሮስ ካለበት ቦታ እንደ ደረሱ....................................................11
10.5. 23-29 ለጴጥሮስ የተደረገለት አቀባበልና ጴጥሮስ ስለ ጉዳዩ ያደረገው ንግግር..........................................11
10.6. 30-33 ቆርኔሌዎስ ወደ ጴጥሮስ የላከበትን ምክንያት መግለጹ...........................................................11
10.7. 34-43 ጴጥሮስ ተናገር በተባለው መሠረት ተናገረ........................................................................11
10.8. 44–48 ቆርኔሌዎስና ቤተ ሰቦቹ መንፈስ ቅዱስ ን ስለ መቀበላቸው.....................................................12
ምዕራፍ 11................................................................................................................................ 12
11.1. 1 የቆርኔሌዎስና ቤተሰቦቹ ማመን በምእመናን ዘንድ ተሰማ..............................................................12
11.2. 2–3 በጴጥሮስ ላይ የደረሰ ተቃውሞ........................................................................................ 12
11.3. 4–18 ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ቤት የገባበትን ምክንያት ለወንድሞቹ አሳወቀ.............................................12
11.4. 19–21 በእስጢፋኖስ ሞት ስለተበተኑ ምእመናን.........................................................................12
11.5. 22–24 በርናባስ ወደ አንጾኪያ ተላከ........................................................................................ 12
11.6. 25–26 በርናባስ ጳውሎስን ፍለጋ ወደ ጠርሴስ መጣ......................................................................13
11.7. 27–30 ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ.......................................................................13
ምዕራፍ 12................................................................................................................................ 13
12.1. 1–5 የሐዋርያው ያዕቆብ መገደል............................................................................................ 13
12.2. 6-11 በእግዚአብሔር መልአክ ለጴጥሮስ ስለ ተደረገው እርዳታ..........................................................13
12.3. 12-17 ጴጥሮስ ከወንድሞቹ ጋር ተገናኘ................................................................................... 13
12.4. 18- 20 ጴጥሮስ በእስር ቤት በመታጣቱ ምክንያት ድንጋጤ ተፈጠረ...................................................14
12.5. 21-24 የሄሮድስ መሞትና የእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት................................................................14
12.6. 25 የጳውሎስና የበርናባስ ከኢየሩሳሌም መመለስ..........................................................................14
ምዕራፍ 13................................................................................................................................ 14
13.1. 1-3 የበርናባስና የጳውሎስ መመረጥ........................................................................................ 14
13.2. 4-12 የጳውሎስና የበርናባስ የመጀመርያው ሐዋርያው ጉዞ...............................................................14
ምዕራፍ 14................................................................................................................................ 15
14.1 ተልእኮውና አስተምህሮው..................................................................................................... 15
ምዕራፍ 15................................................................................................................................ 15
15.1. 1-3 ጳውሎስና በርናባስ በአስተማሯቸው ምእመናን ላይ ችግር ተፈጠረ................................................15
15.2. 4-5 የጳውሎስና የበርናባስ ኢየሩሳሌም መድረስ...........................................................................15
15.3. 6-12 የኢየሩሳሌም ጉባኤ.................................................................................................... 16
15.4. 13-21 የያዕቆብ ንግግር...................................................................................................... 16
15.5. 22-29 ወደ አሕዛብ የተላከ ደብዳቤ........................................................................................ 16
15.6. 30-35 ይሁዳና ሲላስ ደብዳቤውን ለአንፆኪያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሰጡ...............................................16
15.7. 36-41 የጳውሎስና የበርናባስ መለያየትና የ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ መጀመር............................................16
ምዕራፍ 16................................................................................................................................ 17
16.1 ተልእኮውና አስተምሮው....................................................................................................... 17
ምዕራፍ 17................................................................................................................................ 17
17.1 ተልእኮውና አስተምህሮው................................................................................................... 17
ምዕራፍ 18................................................................................................................................ 18
18.1. 1-17 ተልእኮውና አስተምህሮው............................................................................................ 18
18.2. 18-23 ጳውሎስ ከቆሮንቶስ ወደ ሦሪያ ፣ ኤፊሶን ፣ ቂሣርያና አንጾኪያ ደረሰ..........................................18
18.3. 24-28 ስለ አጵሎስ ማንነት................................................................................................. 18
ምዕራፍ 19................................................................................................................................ 18
19.1. 1-7 ጳውሎስ በዮሐንስ የተጠመቁ ደቀ መዛሙርትን ማግኘቱ............................................................18
19.2. 8-10 ጳውሎስ ለሦስት ወርና ሁለት ዓመት ያህል ያስተማረው ትምህርት..............................................18
19.3. 11-17 ለጳውሎስ የተሰጠው የመፈወስ ሀብትና የአስቄዋ ልጆች ሐፍረት..............................................18
19.4. 18-20 የጠንቋዮች ማመን.................................................................................................. 19
19.5. 21-23 ጳውሎስ ሮሜን ለማየት ስለ ማሰቡ...............................................................................19
19.6. 24-27 የድሜጥሮስ ስጋትና የአርጤምስ ክብር መቅረት..................................................................19
19.7. 28-32 የኤፌሶን ሰዎች ጩኸት............................................................................................. 19
19.8. 33-34 የእስክንድሮስ አለመሰማት.......................................................................................... 19
19.9. 35-40 የእነ ጳውሎስ ቅንነትና የከተማይቱ ጸሐፊ ኃላፊነት..............................................................19
ምዕራፍ 20................................................................................................................................ 19
20.1. 1-6 የጳውሎስ ወደ ተለያዩ ቦታዎች መሄድ................................................................................19
20.2. 7-12 የአውጤክስ ከደርብ መውደቅ........................................................................................ 20
20.3. 13-17 የጳውሎስ በተለያዩ ቦታዎች መዞር................................................................................. 20
20.4. 18-32 ለኤፌሶን ሽማግሌዎች (ቀሳውስት) የተሰጠ አደራና ማስጠንቀቅያ............................................20
20.5. 33-35 ከፍቅረ ንዋይ መራቅ እንደሚገባ................................................................................... 20
20.6. 36-38 በስንብት ምክንያት የተደረገ ልቅሶ................................................................................20
ምዕራፍ 21................................................................................................................................ 20
21.1. 1-16 የጳውሎስ ከቦታ ቦታ መጓዝ.......................................................................................... 20
21.2. 17-25 የጳውሎስ ኢየሩሳሌም መድረስ ፣ በሐዋርያት የተደረገለት አቀባበልና የታዘዘው ትእዛዝ......................20
21.3. 26-27 ጳውሎስ በሐዋርያት የታዘዘውን አደረገ...........................................................................21
21.4. 28-32 ጳውሎስ ተከሰሰ..................................................................................................... 21
21.5. 33-36 ጳውሎስ ወደ እሥር ቤት ተወሰደ.................................................................................. 21
21.6. 37-40 ጳውሎስ ስለ ራሱ ተከላከለ......................................................................................... 21
ምዕራፍ 22................................................................................................................................ 21
22.1. 1-23 ጳውሎስ ለሻለቃውና ለሕዝቡ ሰፊ ንግግር አደረገ..................................................................21
22.2. 24-26 ጳውሎስ ለተወሰነበት ውሳኔ ጥያቄ ማቅረቡ......................................................................21
22.3. 27-30 ሻለቃው የጳውሎስን ዜግነት መጠየቁና ጳውሎስን መፍታቱ.....................................................22
ምዕራፍ 23................................................................................................................................ 22
23.1. 1-5 ሊቀ ካህናት ሐናንያ ጳውሎስ በጥፊ ይመታ ዘንድ ትእዛዝ አስተላለፈ..............................................22
23.2. 6-10 በጳውሎስ ንግግር ምክንያት በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል መከፋፈል ተፈጠረ.........................22
23.3. 11.ለጳውሎስ ጌታ ተገለጠለት.............................................................................................. 22
23.4. 12-15 አይሁዳውያን ጳውሎስን እስኪገድሉ ድረስ እህልና ውሀን እንደማይቀምሱ ተማማሉ........................22
23.6. 23-24 ጳውሎስ እሥረኛ ሆኖ ወደ ቂሣርያ ወረደ.........................................................................23
23.7. 25-30 ስለ ጳውሎስ ጉዳይ ከሉስዮስ ወደ ፊልክስ የተላከ ደብዳቤ.......................................................23
23.8. 31-35 ጳውሎስ ከፊልክስ ቤተ መንግሥት ደረሰ..........................................................................23
ምዕራፍ 24................................................................................................................................ 23
24.1. 1-9 ጠርጠሉስ የተባለ ጠበቃ ጳውሎስን መክሰስ ጀመረ...................................................................23
24.2. 10-21 ጳውሎስ በፊልክስ ፊት የተከሰሰበትን ተከላከለ...................................................................23
24.3. 22-23 ፊልክስ የጳውሎስን ጉዳይ ሉስዮስ እስኪመጣ ድረስ እንዲዘገይ አደረገ.........................................23
24.4. 24-25 ፊልክስና ሚስቱ ድሩሲላ የጳውሎስን አስተምህሮ ሲከታተሉ...................................................23
24.5. 26-27 ፊልክስ ከጳውሎስን ገንዘብ ፈልጓል................................................................................ 23
ምዕራፍ 25................................................................................................................................ 24
25.1. 1-5 የጳውሎስ ጉዳይ በፊስጦስ መታየት ጀመረ............................................................................24
25.2. 6-8 ፊስጦስ ተከሳሹ ጳውሎስንና ከሳሾቹን አገናኘ........................................................................24
25.3. 9-12 ጳውሎስ ወደቄሣር ይግባኝ ማለቱና ፊስጦስ ለከሳሾች ማድላቱ..................................................24
25.4. 13-22 ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለአግሪጳና ለበርኒቄ ተናገረ...........................................................24
25.5. 23-27 ጳውሎስ ከአግሪጳ ፊት ስለ መቆሙ............................................................................... 24
ምዕራፍ 26................................................................................................................................ 24
26.1. 1-23 ጳውሎስ ከአግሪጳ ፊት ቆሞ የተናገረው ንግግር.....................................................................24
26.2. 24-29 ጳውሎስ አብደሃል መባሉና የወደፊት ዓላማውን መግለጹ.......................................................25
26.3. 30-32 የጳውሎስ ጉዳይ በአግሪጳና በበርኒቄ ዘንድ እንኳን ለሞት ለእሥራት የማያበቃ ነው ተባለ....................25
ምዕራፍ 27................................................................................................................................ 25
27.1. 1-44 ጳውሎስና ጓደኞቹ ወደ ሮሜ መጓዛቸውና በጉዞው የገጠማቸው ችግር...........................................25
ምዕራፍ 28................................................................................................................................ 25
28.1. 1-2 በመላጥያ የነበሩ አረማውያን ለጳውሎስና ለጓደኞቹ መልካም ሥራ አደረጉላቸው................................25
28.2. 3-6 የጳውሎስ እጅ በእፉኝት መነደፍና ከአሕዛብ የደረሰበት ሐሜት.....................................................25
28.3. 7-10 ጳውሎስ የፑፕልዮስን አባትና ሌሎች በሽተኞችን ፈወሰ..........................................................26
28.4. 11-16 ጳውሎስ ሮሜ ስለ መድረሱ........................................................................................ 26
28.5. 17-20 ጳውሎስ ስለጉዳዩ በሮሜ ለሚኖሩ ለአይሁድ ታላላቆች ተናገረ.................................................26
28.6. 23-31 ጳውሎስ በሮሜ አስተማረ.......................................................................................... 26
26.7 የሐዋርያት ሥራ ማጠቃለያ................................................................................................... 26
ክፍል ሁለት: የሮሜ መልእክት............................................................................................................ 28
2.1 መግቢያ............................................................................................................................ 28
2.2 መልእክቱ የተጻፈበት ቦታና መልእክት ወሳጅ................................................................................... 28
2.3 መልእክቱ የተጻፈበት ጊዜና የተጻፈላቸው ሰዎች.............................................................................. 28
2.4 የተጻፈበት ዓላማ................................................................................................................. 28
2.5 የመልእክቱ ልዩ ባሕርያት......................................................................................................... 28
2.6 በመልእክቱ ትኩረት የተሰጠባቸው ነገሮች...................................................................................... 28
ምዕራፍ 1.................................................................................................................................. 29
1.1.1-7 ጳውሎስና የሮም አማኞች................................................................................................. 29
1.2.8-12 ስለ ሮም አማኞች የጳውሎስ ጸሎትና ምስጋና.........................................................................29
1.3.13-17 ጳውሎስ ወደ ሮም አማኞች ለመሄድ የሚተጋበት ምሥጢር.......................................................29
1.4.18-25 እውነትን በዓመፃ በሚለውጡ ሰዎች ላይ ከሰማይ ቁጣ ይመጣል..................................................29
1.5.26-32 አስነዋሪው ምኞትና ተግባር............................................................................................ 30
ምዕራፍ 2.................................................................................................................................. 30
2.1.1-6 እውነተኛው የእግዚአብሔር ፍርድ........................................................................................ 30
2.2.7-12 ለመልካም ሰዎች የሚሰጥ ሕይወትና በክፉ ሰዎች ላይ የሚደረግ ቅጣት............................................30
2.3.13-16 ሕግን በማድረግ እንጂ ሕግን በመስማት መጽደቅ አይቻልም.......................................................30
2.4.17-24 አይሁድና ሕግ........................................................................................................... 30
2.5.25-29 አይሁድና ግዝረት (ሕግ)............................................................................................... 30
ምዕራፍ 3.................................................................................................................................. 31
3.1.1-4 የይሁድነት ብልጫና የግዝረት ጥቅም ምንድን ነው?....................................................................31
3.2. 5-9 በጳውሎስ ዓመጽ የሚገለጥ የእግዚአብሔር ክብር ስለ መባሉ.........................................................31
3.3.10-18 የጻድቅ መታጣት........................................................................................................ 31
3.4.19-26 ኦሪትና ነቢያት የመሰከሩለት የእግዚአብሔር ጽድቅ.................................................................31
3.5.27-31 አይሁድ በየትኛው ሕግ መካሉ?....................................................................................... 31
ምዕራፍ 4.................................................................................................................................. 32
4.1.1-5 አብርሃም የጸደቀው በእምነት ነው........................................................................................ 32
4.2.6-12 ግዝረትና ብፅዕና.......................................................................................................... 32
4.3.13-18 አብርሃምና ዘሩ ዓለምን ይወርሳሉ የተባለው በሕግ ሳይሆን በእምነት ነው........................................32
ምዕራፍ 5.................................................................................................................................. 32
5.1.1-5 ከእምነት ጽድቅ በኋላ ሰላምን ስለመያዝ.................................................................................32
5.2.6-11 ሰዎች የእግዚአብሔር ጠላቶች ሲሆኑ ክርስቶስ ስለ እነርሱ ስለ መሞቱ............................................32
5.3.12-16 የአዳም በደልና የክርስቶስ አዳኝነት ሲነጻጸር.........................................................................32
5.4.17-20 አዳምና ክርስቶስ በሞትና በሕይወት..................................................................................33
ምዕራፍ 6.................................................................................................................................. 33
6.1. 1-7 ከክርስቶስ ጋር መሞትና መነሣት......................................................................................... 33
6.2. 8-14 ከክርስቶስ ጋር መሆን................................................................................................... 33
6.3. 15-23 አማኞች ለሚታዘዙለት ባርያዎች እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው.................................................33
ምዕራፍ 7.................................................................................................................................. 33
7.1.1-6 ከሕግ መፋታት.............................................................................................................. 33
7.2.7-13 ሕግና ኃጢአት............................................................................................................ 34
ምዕራፍ 8.................................................................................................................................. 34
8.1.1-5 በክርስቶስ የተገኘው ነፃነት................................................................................................. 34
8.2.6-11 ስለ ነፍስ ፈቃድና ስለ ሥጋ ፈቃድ ማሰብ..............................................................................34
8.3.12-17 ከክርስቶስ ጋር መውረስ................................................................................................ 34
8.4.18-25 ለሰው የሚሰጠው ክብርና የሚቀበለው መከራ.......................................................................35
8.5.26-30 የመንፈስ እርዳታ....................................................................................................... 35
8.6.31-34 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነውን ሰው ማን ይቃወመዋል?......................................................35
8.7.35-39 አማኞችን ከክርስቶስ ፍቅር የሚለያቸው ነገር የለም...............................................................35
ምዕራፍ 9.................................................................................................................................. 36
9.1.1-6 በእግዚአብሔር የተመረጡት እስራኤል................................................................................... 36
9.2.7-13 በይስሐቅ በኩል ለአብርሃም የሚጠራው ዘር........................................................................... 36
9.3.14-29 የእግዚአብሔር ምርጫ በሰዎች ላይ እንዴት እንደሚፈጸም የቀረበ ማስረጃ......................................36
9.4.30-33 የእስራኤል አለመጽደቅና የአሕዛብ መጽደቅ.........................................................................36
ምዕራፍ 10................................................................................................................................ 37
10.1. 1-4 እስራኤል ይድኑ ዘንድ ጳውሎስ ይፈልጋል............................................................................. 37
10.2. 5-13 ድኅነት ለሁሉ ነው..................................................................................................... 37
10.3. 14-21 መስማት፣ ማመንና ስሙን መጥራት...............................................................................37
ምዕራፍ 11................................................................................................................................ 37
11.1. 1-5 የእስራኤል መውደቅ ጊዜአዊ መውደቅ ነው...........................................................................37
11.2. 6-12 ትሩፋን ያገኙት ጸጋና ኢትሩፋን ያላገኙት ጸጋ......................................................................37
11.3. 13-16 ጳውሎስ በአይሁድና በአሕዛብ ላይ ያለውን አመለካከት ለአሕዛብ ስለ ማሳወቁ...............................38
11.4. 17-24 አሕዛብ በእስራኤል ላይ እንዳይኩራሩ በምሳሌ ሲያስረዳ.........................................................38
11.5. 25-36 መላው እስራኤል ይድናሉ........................................................................................... 38
ምዕራፍ 12................................................................................................................................ 38
12.1. 1-8 ሰውነትን ቅዱስ መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብና እንደ ተሰጠህ ጸጋ ማገልገል........................................38
12.2. 9-21 የእውነተኛ ክርስቲያን ምልክት....................................................................................... 39
ምዕራፍ 13................................................................................................................................ 39
13.1. 1-7 ለባለ ሥልጣናት መገዛት ይገባል........................................................................................ 39
13.2. 8-10 ሌላውን ስለ መውደድ................................................................................................. 39
13.3. 11-14 በፍጥነት መንቃት ያስፈልጋል....................................................................................... 39
ምዕራፍ 14................................................................................................................................ 39
14.1. 1-12 በሌላው ወንድም ላይ አለመፍረድ................................................................................... 39
14.2. 13-23 ለሌላው እንቅፋት መሆን አይገባም................................................................................40
ምዕራፍ 15................................................................................................................................ 40
15.1. 1-6 ራስን ሳይሆን ሌላውን ደስ ማሰኘት ይገባል........................................................................... 40
15.2. 7-13 ክርስቶስ አይሁድንና አሕዛብን እንደ ተቀበለ እርስ በርሳቸው መቀባበል አለባቸው...............................40
15.3. 14-21 ይህን መልእክት የጻፈበትን ምክንያት ስለ መናገሩ................................................................40
15.4. 22-29 ጳውሎስ ሮሜን ለማየት እቅድ አለው.............................................................................41
15.5. 30-33 የሮም ምእመናን ስለ ጳውሎስ ጉዞና ስለ የሚሰጠው እርዳታ መጸለይ እንዲገባቸው ማሳሰቡ................41
ምዕራፍ 16................................................................................................................................ 41
16.1. 1-24 መንፈሳዊና ግላዊ ሰላምታ............................................................................................ 41
16.2.25-27 ምስጋና................................................................................................................ 41
16.3.የሮሜ መልእክት ማጠቃለያ................................................................................................... 41
ክፍል ሦስት: የ 1 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት................................................................................................ 43
3.1 መግቢያ............................................................................................................................ 43
3.2 የተጻፈበት ቦታ.................................................................................................................... 43
3.3 መልእክት አድራሾች.............................................................................................................. 43
3.4 መልእክቱ የተጻፈበት ጊዜ........................................................................................................ 43
3.5 መልእክቱ የተጻፈላቸው ሰዎች.................................................................................................. 43
3.6 ዓላማው........................................................................................................................... 43
ምዕራፍ 1.................................................................................................................................. 44
1.1.1-9 ጸጋና ሰላም ለቆሮንቶስ ምእመናን........................................................................................ 44
1.2.10-17 በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው መከፋፈል...................................................................44
1.3.18-25 የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ.......................................................................................... 44
1.4.26-31 የቆሮንቶስ ምእመናን መጠራታቸውን መመልከት አለባቸው.......................................................44
ምዕራፍ 2.................................................................................................................................. 45
2.1.1-5 የጳውሎስ የስብከት ማእከል ክርስቶስ ነው...............................................................................45
2.2.6-16 እውነተኛው የእግዚአብሔር ጥበብ...................................................................................... 45
ምዕራፍ 3.................................................................................................................................. 45
3.1.1-15 የቆሮንቶስ ምእመናን በመከፋፈል ምክንያት እንደ ሕፃናት ሁነዋል...................................................45
3.2.16-23 የቆሮንቶስ ምእመናን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ናቸው..........................................................46
ምዕራፍ 4.................................................................................................................................. 46
4.1.1-13 የእነጳውሎስ ሐዋርያነትና በሌላው ላይ አለመፍረድ...................................................................46
4.2.14-21 ጳውሎስ ለምእመናኑ የሚጽፍላቸው ሊያሳፍራቸው ሳይሆን ሊገሥጻቸው ነው..................................46
ምዕራፍ 5.................................................................................................................................. 46
5.1.1-8 በቆሮንቶስ አማኞች መካከል በአሕዛብ ስንኳ የማይደረግ ዝሙት እየተደረገ ነው.....................................46
5.2.9-13 የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በምግባረ ብልሹነት በሚመላለሰው ላይ መፍረድ ይገባታል.............................47
ምዕራፍ 6.................................................................................................................................. 47
6.1. 1-11 በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር መፍታት ያለባት ቤተክርስቲያን ናት..............................47
6.2. 12-20 የምእመናኑ ሰውነት የክርስቶስ አካል ስለ ሆነ ለዝሙት መዋል የለበትም.........................................47
ምዕራፍ 7.................................................................................................................................. 48
7.1.1-40 የጳውሎስ ምክር፦ በትዳር፣ በድንግልና ኑሮና በማግባት ዙርያ ላይ....................................................48
ምዕራፍ 8.................................................................................................................................. 49
8.1.1-13 ለጣዖታት ስለ ቀረበ ምግብ.............................................................................................. 49
ምዕራፍ 9.................................................................................................................................. 49
9.1.1-18 የሐዋርያ መብት.......................................................................................................... 49
9.2.19-23 የጳውሎስ መንፈሳዊ ጥበብ............................................................................................ 50
9.3.24-27 ለዋጋ መሽቀዳደም..................................................................................................... 50
ምዕራፍ 10................................................................................................................................ 50
10.1. 1-13 ከእስራኤል ታሪክ ለምእመናኑ የቀረበ ማስጠንቀቅያ...............................................................50
10.2. 14-22 እግዚአብሔርን ማስቀናት አይገባም...............................................................................50
10.3. 23-33 ጳውሎስ ሁሉን ይበላ ዘንድ ተፈቅዶለታል........................................................................50
ምዕራፍ 11................................................................................................................................ 51
11.1. 1-16 ትንቢት ለሚናገር ወንድና ለምትናገር ሴት የተሰጠ መመሪያ......................................................51
11.2. 17-26 በጌታ ራት ላይ የተፈጸመ መድሎ (ጥፋት)........................................................................51
11.3. 27-34 ሳይበቁ የጌታን ቅዱስ ቁርባን (ሥጋ ወደሙ) መቀበል ቅጣት ያስከትላል.......................................51
ምዕራፍ 12................................................................................................................................ 52
12.1. 1-11 ልዩ ልዩ ጸጋዎች (ስጦታዎች)........................................................................................ 52
12.2. 12-31 አንድ አካል ብዙ ሕዋሳት............................................................................................ 52
ምዕራፍ 13................................................................................................................................ 52
13.1. 1-13 ስለ ፍቅር የበላይነት................................................................................................... 52
ምዕራፍ 14................................................................................................................................ 52
14.1. 1-25 በተለያየ ቋንቋ መናገርና (ሌላ በማይሰማው) በአንድ ቋንቋ (ሌላ በሚሰማው) መናገር.........................52
14.2. 26-40 ለአምልኮ በሚሰባሰቡበት ጊዜ መደረግ ያለበት ጉዳይ.............................................................53
ምዕራፍ 15................................................................................................................................ 53
15.1. 1-11 የክርስቶስ ትንሣኤ..................................................................................................... 53
15.2. 12-34 ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል..............................................................................53
15.3. 35-50 የሚነሣ አካል (የሙታን ትንሣኤ)..................................................................................... 54
ምዕራፍ 16................................................................................................................................ 54
16.1. 1-4 ለድሀ አማኞች ገንዘብ ማሰባሰብ....................................................................................... 54
16.2. 5-12 የጉዞ ዕቅድ............................................................................................................. 54
16.3.13-24 የማጠቃለያ መልእክትና ሰላምታ....................................................................................55
16.4.የ 1 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ማጠቃለያ......................................................................................... 55
ክፍል አራት የ 2 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት.................................................................................................. 57
4.1.መግቢያ............................................................................................................................ 57
4.2.የተጻፈበት ጊዜና ቦታ............................................................................................................. 57
4.3.የተጻፈላቸው ሰዎችና መልእክቱን የወሰዱ ሰዎች............................................................................. 57
4.4.ዐላማው........................................................................................................................... 57
ምዕራፍ 1.................................................................................................................................. 57
1.1.1-11 ምስጋናና ስለ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን መከራ መቀበል...............................................................57
1.2.12-24 ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንን ይጐበኛል.....................................................................57
ምዕራፍ 2.................................................................................................................................. 58
2.1.1-11 እውነትን ስለ መናገር..................................................................................................... 58
2.2.12-17 ጳውሎስ ቲቶን ባለማግኘቱ ምክንያት ዕረፍት አጥቻለሁ አለ......................................................58
ምዕራፍ 3.................................................................................................................................. 58
3.1.1-6 የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሁሉም የሚያነባት የተጻፈች መልእክት ናት...............................................58
3.2.7-18 ወንጌልና ኦሪት............................................................................................................ 58
ምዕራፍ 4.................................................................................................................................. 59
4.1.1-6 የክርስቶስ አስተምህሮ ስላለ ከክፉ ሥራ መቆጠብ ይገባል...............................................................59
4.2.7-16 ስለ ሙታን ትንሣኤ...................................................................................................... 59
ምዕራፍ 5.................................................................................................................................. 59
5.1.1-10 ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በሰማይ የሕይወት ተስፋ አላት...........................................................59
5.2.11-21 ሁሉም በክርስቶስ አዲስ ሁኗል........................................................................................ 60
ምዕራፍ 6.................................................................................................................................. 60
6.1.1-13 ስለ ክርስቶስ ስም መጋደል እንደሚገባ.................................................................................. 60
6.2.14-18 የእግዚአብሔር መኖሪያ ቤተ መቅደስ................................................................................. 60
7.1.1-16 በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ተደረገው ንስሐ የጳውሎስ ደስታ....................................................60
ምዕራፍ 8.................................................................................................................................. 61
8.1. 1-15 ለድሆች ምእመናን መዋጮ (ገንዘብ) መስጠት እንደሚገባ...........................................................61
8.2.16-24 ቲቶ ወደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ይላካል ስለ መባሉ..............................................................61
ምዕራፍ 9.................................................................................................................................. 62
9.1. 1-15 በኢየሩሳሌም ላሉ ድሆች ምእመናን ስለሚሰጥ መዋጮ.............................................................62
ምዕራፍ 10................................................................................................................................ 62
10.1. 1-18 መንፈሳዊ ኃይል........................................................................................................ 62
ምዕራፍ 11................................................................................................................................ 63
11.1. 1-5 የባእድ ትምህርትን ስለ አለመቀበል.................................................................................... 63
11.2. 6-15 ወንጌልን ያለ ዋጋ ስለ ማስተማር.................................................................................... 63
11.3.16-33 መመካት አይገባም እንጂ መመካት የሚገባ ቢሆን ከጳውሎስ በላይ ማንም አይመካም ነበር...................63
ምዕራፍ 12................................................................................................................................ 64
12.1. 1-10 ጳውሎስ ያየው ራእይ................................................................................................. 64
12.2.11-21 የጳውሎስ በደል በመከራ ሊገሥጻቸው ወደ አማኞቹ ካለመምጣቱ በቀር ሌላ አይደለም.......................64
ምዕራፍ 13................................................................................................................................ 65
13.1. 1-10 የሩቅ ማስጠንቀቅያና ጸሎት.......................................................................................... 65
13.2. 11-14 የማጠቃለያ መልእክትና ሰላምታ...................................................................................65
13.3. የ 2 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ማጠቃለያ....................................................................................... 65
ዋቢ መጻሕፍት............................................................................................................................. 65
ሀ. የዚህ መድበል አስፈላጊነት
የሐዋርያት ሥራ ለሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መሸጋገሪያን ያበጃል፤ መጽሐፉ የሉቃስ 2 ተኛ መጽሐፍ ሁኖ በወንጌላት
ውስጥ እንደምናየው ክርስቶስ ሊያደርገውና ሊያስተምረው የጀመረውን ከመንፈስ ቅዱስ መውረድ በኋላ በሐዋርያት
ስብከትና በቤተ ክርስቲያን ምሥረታ አማካይነት መቀጠሉን ያስረዳል፤ የወንጌላትን ትረካ በአንድ በኩል፣ የሐዋርያትን
መልእክቶች በሌላ በኩል ከማገናኘቱ በተጨማሪ ስለ መልእክቶች ልናገናኝ የሚገባንን መረጃዎችና ስለ ጳውሎስ
የሕይወት ታሪክም ከመጽሐፉ ማግኘት ይቻላል፤ የትረካው መልክዐ ምድር አቀማመጥ፣ ቤተ ክርስቲያን
በተጀመረችበት በኢየሩሳሌምና የሮማውያን የፖለቲካ ማእከል በነበረችው በሮም መካከል ያለውን አካባቢ የሚዳስስ
ነው፤ መጽሐፉ የቤተ ክርስቲያንን የመጀመሪያ ሠላሳ ዓመት ታሪክን ያካትታል፤ ከዚህም በላይ የቤተ ክርስቲያንን
አጀማመር ከዝያ በኋላ ካለው ዘመን ጋር የሚያዛምድ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ዘመን ልትመራበት የሚገባትን
መርሕ ከዚህ መጽሐፍ ማግኘት ይቻላል፤ ስለዚህ ተማሪዎች ይህን ታሪክ ያውቁ ዘንድ መድበሉ ተዘጋጅቷል::

ለ. የዚህ መድበል መዘጋጀት ዓላማ


በሐዋርያት ሥራ የተዳሠሠ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ብዙ ነው፤ በተለይም ጳውሎስ በ 1 ኛው፣ በ 2 ኛው፣ በ 3 ኛውና
በመጨረሻም እሥር ሁኖ ወደ ሮማ ፍርድ ቤት በአቀና ጊዜ የተደረገውን አጠቃላይ ፍጻሜ በስፋት የሚያትት ነው፤
ስለዚህ ተማሪዎች ይህን ሂደት ያውቁ ዘንድ ነው::
ክፍል አንድ: የሐዋርያትሥራ

1. መግቢያ
ጸሐፊው የሉቃስን ወንጌል የጻፈ ራሱ ሉቃስ ነው። የወንጌላዊው ሉቃስ ሥራ ምን እንደሆነ፣ ትውልዱና ሀገሩ ከምንና
የት እንደሆነ በሉቃስ ወንጌል መግቢያ ተጽፏል። ይህ መጽሐፍ ለሉቃስ ሁለተኛ ጽሑፉ ነው። ይህ የታሪክ መጽሐፍ
የተጻፈለት ሰው የሉቃስ ወንጌል የተጻፈለት ቴዎፍሎስ ነው:: ይህም የሚያስታውቀው ”በመጀመሪያ የጻፍኩልህን
ታውቃለህ’’ የሚለው ቃል ነው። የተጻፈበት ዘመን በግልጽ ባይታወቅም ሁለት አስተያየቶች አሉ።

 የመጀመርያው አስተያየት ከ 60–65 ተጽፏል የሚል ሲሆን


 ሁለተኛው አስተያየት ደግሞ ከ 70 ዓ/ም በኋላ 80 ዎቹ በ 90 ዎቹ ዓ/ም እንደተጻፈ ያስቀምጣል።

1. 2. የጻፈበት ዓላማ
1. ሐዋርያት ያስተማሩትን ትምህርት፣ የሠሩትን ትሩፋትና ያደረጉትን ተአምራት ለማሳወቅ ነው::

2. ቅዱሳን ሐዋርያት የተገባላቸውን የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዙረው እንዳስተማሩ መግለጽ
ነው።

3. 120 ው ቤተሰብ በአንድነት ሳሉ መንፈስ ቅዱስ እንደ ወረደላቸው ማስረዳት ነው::

4. ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ ወንጌል አገልግሎትና ስለ ክርስቶስ በመመስከር ልዩ ልዩ መከራን እንደ ተቀበሉና በሰማዕትነት
እንደ ሞቱ መተረክ ነው::

5. የመጀመርያዎቹ ክርስቲያን መልካም ሥራ ለቤተ ክርስቲያን መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበረው ማሳወቅ
ነው::

6. በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን የተቀጣጠለው የወንጌል ብርሃን ከኢየሩሳሌም ወደ አንፆኪያ፣ ከአንፆኪያ ወደ ሰማርያ፣


ከሰማርያ ወደ ኤፌሶን፣ ከኤፌሶን ወደ ሌሎች ቦታዎች እየተስፋፋ ከሮም ቤተመንግሥት እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ
ደረሰ ማስረዳት ይገኙበታል::

ምዕራፍ 1

1.1.1-12 የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ለሐዋርያት ስለ መነገሩ


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ከ 48-51 ያለውን አጭር ምንባብ ሰፋ አድርጎ የሚያትት
ነው::

1.2. 13–14 የ 120 ው ቤተ ሰብ የአንድነት ጸሎት


ወንጌላዊው ሉቃስ በዚህ ክፍል የ 11 ደቀመዛሙርት ስም አንሥቷል ፤ ቀጥሎም እነዚህ የጌታ እናት እመቤታችንና
36 ቱ ቅዱሳት አንስት በአንድነት ጸሎት ያደርጉ እንደነበር ገልጾአል። በሐዋርያትም ዝርዝር ልብዲዮስ የተባለው
ታዴዎስን”የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም’’ በማለት ስሙን ቀይሮ አንሥቶታል 72 ቱ አርድእት አይጥቀስ እንጂ ከሐዋርያቱና
ከሴቶቹ እንደማይለዩ የታወቀ ነው።
1.3. 15–26 ጴጥሮስ በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ ይመረጥ ዘንድ ሐሳብ አቀረበ
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የይሁዳን ሐዋርያነት ከ 72 አርድእት መካከል ከነበሩት ከበርናባስና ከማትያስ ለአንዱ
እንዲሰጥ ሐሳብ አመንጭቷል፤ ሐሳቡንም ያመነጨው በመዝ 68፥25 ና 108፥8 ያለውን ሐሳብ መሠረት በማድረግ
ነው፤ በዚህ ክፍልም ያለው ይሁዳን የሚመለከት ንግግር አድርጓል፤ ንግግሩ የይሁዳ ከሐዋርያት መውጣት በምን
ምክንያት እንደሆነና በዚህ ስፍራ ሌላ ሰው መግባት እንዳለበት ያመለክታል፤ እንደ ጴጥሮስ አነጋገር ይህን ስፍራ
የሚይዝ ሰው ከመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ አረገባት ጊዜ ከሐዋርያቱ ጋር አብሮ የነበረ መሆን
አለበት:: ሌላን ሰው የመምረጡ ዓላማ ከእነርሱ ጋር ሁኖ የክርስቶስን ትንሣኤ ይመሰክር ዘንድ ነው፤ ለመመረጥ
መመዘኛ የሆነው ደግሞ ከላይ እንደ ተገለጸው ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ እስከ ክርስቶስ እርገት ድረስ መኖር ሁኖ
ቀርቧል፤ ይሁን እንጂ መመዘኛውን አሟልተው የተገኙ ኢዮስጦስ የሚሉት በርስያን የተባለው ዮሴፍና ማትያስ ሲገኙ
ከሁለቱ አንዱን መምረጥ አስቸጋሪ ነበር:: ምክንያቱም ሁለቱም በመመዘኛው መሠረት ተሿሚ ሁነው ተገኝተዋል፤
ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ እገዛ አስፈላጊ ነበር፤ ከዚህ በመነሣት ከብዙ ጸሎት በኋላ በሁለቱ አካላት ላይ ዕጣ ሲጣል
ዕጣው በማትያስ ላይ ወጥቷል፤ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የይሁዳን ስፍራ በመያዝ ሐዋርያነት ተሹሟል::

ምዕራፍ 2

2.1. 1–4 መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ ወረደ


ጌታ ለሐዋርያት የሰጠውን ተስፋ በአረገ በ 10 ኛው ቀን ልኳል። እዚህ ላይ የተጠቀሰው የመንፈስ ቅዱስ መምጣት
በእሳትና በነፋስ አምሳል ሲሆን እንደ እሳት ላንቃ እየተጎራረደ በ 120 ው ቤተሰብ ላይ አርፏል። የመንፈስ ቅዱስ ሀብቱ
120 ው ቤተሰብ የነበሩበትን ቤት ሞልቶታል፤ ከዚህ የተነሣ 120 ው ቤተሰብ በማያውቁት ልዩ ልዩ ቋንቋ
የእዚአብሔርን ቸርነት መናገር ጀምረዋል::

2.2. 5-13 የተለያዩ አይሁዳውያን በ 120 ው ቤተሰብ ልዩ ልዩ ቋንቋ መናገር ተገረሙ


ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በበዓለ 50 ጊዜ ነበርና ይህን በዓል ለማክበር ከየክፍላተ ዓለም (ከ 15 አገሮች
በላይ) ተውጣጥተው የመጡ ልዩ ልዩ ወገኖች ነበሩ፤ ታድያ እነዚህ ልዩ ልዩ ወገኖች የራሳቸውን ቋንቋ በ 120 ቤተሰብ
ሲነገር በሰሙ ጊዜ ከሚገባው በላይ ተገርመዋል ፤ በአንፃሩ ደግሞ ያፌዙ ሰዎች ነበሩ፤ ፌዙ”ጉሽ ጠጅ ጠጥተው
ሰክረዋል’’ በሚል አነጋገር የተገለጠ ነበር::

2.3. 14–21 ቅዱስ ጴጥሮስ በ 120 ቤተሰብ ላይ የተሰነዘረውን ተቃውሞ ተቃወመ


በእነዚህ ሰዎች ላይ የተሰነዘረው ፌዝ ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረዋል የሚል እንደ ነበር ከላይ ተገልጿል፤ ነገር ግን እውነቱ
እንዲህ አልነበረም፤ የተገባላቸው ተስፋ ተፈጻሚነት ቢያገኝ እንጂ:: በእግዚአብሔር መንፈስ እንደተሞሉ ከ 120 ው
ደቀመዛሙርት ጋር በመቆም ቅዱስ ጴጥሮስ ሁኔታውን አስረዳ፤ 120 ው ቤተሰብ በልዩ ልዩ ቋንቋ ተርጉመው
እንደሚናገሩ የተነገረ ትንቢት ከዚህ በፊት ተነግሯል፤ (ኢዩ.2፥28-32) ይህን በመጥቀስ ነው ጴጥሮስ እውነታውን
የገለጸው፤ ጴጥሮስ በወንድሞቹ መካከል ቁሞ ይህን የተናገረው ከዚህ በፊት የተሰጠውን ስልጣን መሠረት በማድረግ
ነው::

2.4. 22–36 ክርስቶስ ለእስራኤላውያን በተአምርም በትሩፋትም የተገለጠ እንደነበር ጴጥሮስ ተናገረ
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በተሰጠው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ታሪክ ለእስራኤል ይናገራል ማለት
በተአምራት፤ በትሩፋት፣ በድንቃ ድንቆችና በስልጣን በእስራኤል ፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጠና የታወቀ እንደ
ነበር፤ ይህ ሁኖ ሳለ በተቃዋሚዎችና በጠላቶቹ እጅ ሙቷል፤ በዚህ ድርጊት እነርሱም እንዳሉበት አስታውቋል፤ ነገር
ግን ክርስቶስ ቢሞትም በመዝሙር 15 (16)፥8–16 ያለውን ቃል በመጥቀስ ነቢዩ ዳዊት ስለ ራሱ እንዳልተናገረው
ማስረጃ አድርጎ አቅርቧል፤ ጴጥሮስ ይህን ይጠቅስ ዘንድ ያስቻለው እስራኤላውያን ይህን ጥቅስ ነቢዩ ዳዊት ስለ ራሱ
እንደተናገረው አድርገው እንዳይተረጉሙት ነው። ነቢዩ ግን ይህን ያለው ነቢይ ስለ ሆነና እግዚአብሔር ክርስቶስን
ከሞት ያሥነሣው ዘንድ እንዳለው ያውቅ ስለ ነበር ነው:: ከላይ እንደ ተገለጸው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ነቢዩ
ዳዊት አስመልክቶ ሲናገር ዳዊት እንደ ሞተና ወደ ሰማይ እንዳላረገ ያስረዳል። እስራኤላውያን ከ 25–28 ያለውን ቃል
ለዳዊት ሰጥተው እንዳይናገሩ፤ ጴጥሮስ ደግሞ ዳዊት ከየት እንዳለና ወደ ሰማይ እንዳልወጣ ስለ ክርስቶስ መነሣትና
ፈርሶ አለመቅረት ይናገራል፤ ለዚህ ንግግር ምስክር ያደረገው ራሱንና ሐዋርያትን ነው፤ እንዲህ ሲሆን እስራኤላውያን
እግዚአብሔር ክርስቶስን ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው ይወቁ ይላል፤ ከዚህ የጴጥሮስ ንግግር በኋላ ደጋጉ አይሁድ
በጴጥሮስ ስብከት አመኑ፤ ለዚህ ማመን ጴጥሮስና መሰሎቹ መንገድን ኣሳይተዋል።

2.5. 37-42 የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ማመን


እዚህ ላይ በጴጥሮስ ስብከት የተማረኩት ሰዎች ለማመን ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል፤ እንደ ሉቃስ አጻጻፍ እነዚህ
ሰዎች ከመንፈስ ቅዱስ መውረድ በኋላ የመጀመርያ አማኝ መሆናቸው ነው፤ ለዚህ መልካም ፈቃዳቸውም ሐዋርያትን
”ወንድሞች ሆይ ምን እናድርግ’’? በማለት ተናግረዋል፤ ጴጥሮስም ይህን በመመልከት ከቍ.38–40 ያለውን ኃይለ
ቃል ተናገረ፤ ይህን ጊዜ አማኞች እየበዙ ይሄዱ ነበር::

2.6. 43-47 በእመናን መካከል የነበረ ሕይወት


ወንጌላዊው ሉቃስ እንደጻፈው የእነዚህ ምእመናን ሕይወት እጅጉም የሚማርክ ነበር፤ እንዲህ በማድረጋቸው
ሥራቸው ዕለት ዕለት አማንያንን ይጨምር ነበር፤ በሚያይዋቸውም ሰዎች ትልቅ ሞገስ ነበራቸው፤ በሚሠሩት ሥራና
በሚበሉት በሚጠጡት ነገር ሁሉ አንድነት ነበራቸው፤ በዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ በዝቶላቸዋል፤ የክርስቶስንም
ሥጋውንና ደሙን በየጊዜው በመቀበልና በማቀበል ይፈጽሙ እንደ ነበር ተገልጿል።

ምዕራፍ 3

3.1. 1–11 ጴጥሮስና ዮሐንስ በክርስቶስ ስም ሽባ ሁኖ የተወለደውን ልጅ ፈወሱ


የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ለመጀመሪያ ጊዜ በክርስቶስ ስም ስልጣናቸውን የገለጡበት ይህ ሽባ ነው። ሽባነቱ የያዘው
ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ እንደ ነበር ጸሐፊው ሉቃስ ግልጽ አድርጓል። በዚህ ምክንያት ”መልካም’’ በምትባል ምኩራብ
ተቀምጦ በልመና ሕይወቱን ሲመራ ኑሯል። ጴጥሮስና ዮሐንስ ጸሎት ሊያደርጉ በዘጠኝ ሰዓት ወደዚህ ምኩራብ
ሲገቡ ከጴጥሮስና ከዮሐንስ የፈለገው ነገር ገንዘብ ነበር፤ ጴጥሮስ ግን ገንዘቡ በክርስቶስ ስም መፈወስ መሆኑን አውቆ
ሁኔታውን ኣስረድቶታል። በዚህ ጊዜ ነበር የሽባው መፈወስ እውን የሆነው። ድሮ ሲያውቁት የነበሩት ሕዝቦች በዚህ
ልጅ መዳን ተገርመዋል፤ ይህንንም ”የሰሎሞን መመላለሻ’’ ወደሚባለው ቦታ በመሮጥ ገልጠዋል፤ ልጁ ከፈውሱ በኋላ
ከምኩራብ ገብቶ እግዚአብሔርን ሲያመሰግን ታይቷል።

3.2. 12–26 ሕዝቡ በሽባው ሰው መዳን ምክንያት ለአቀረቡት አድናቆት የጴጥሮስ መልስ
እነዚህ ሰዎች ይህ ሰው የተፈወሰው በጴጥሮስና በዮሐንስ ስልጣን መስሏቸዋል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ይህ ሀሳብ ትክክል
አለመሆኑና ሰውየው የተፈወሰው በክርስቶስ ስም በማመን እንደ ሆነ በመጠቆም በዚህ ክፍል ያለው የክርስቶስ
አምላክነትንና አዳኝነትን በመናገር፤ ሰዎቹም ራሳቸው የነማንና የማን ልጆች መሆናቸውን ኣስረድቷል። እንደ ጴጥሮስ
ገለጻ እነዚህ ሰዎች፦

1. የነቢያት ልጆች ናቸው::


2. እግዚአብሔር ለአባቶች የሰጠው ተስፋ ልጀች ናቸው::

ምዕራፍ 4

4.1. 1–7 በሐዋርያት ላይ የተደረገው የአይሁድ መምህራን ተቃውሞ


ሐዋርያት የክርስቶስን ትንሣኤ በሚሰብኩበት ጊዜ በእነዚህ መምህራን ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፤ ተቃውሞው
ሐዋርያትን ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በወኅኒ ቤት የሚያውል ነበር። የእነዚህ ተቃዋሚዎች ተቃውሞ
እየጨመረ ሲሄድ ታይቷል፤ ይሁን እንጂ ይህ ተቃውሞ በተደረገበት ቀን እንኳ አምስት ሺ ሰዎች አምነዋል። ሐዋርያት
የተአምራትን ኃይል የሚያደርጉት በማን ስምና በማን ሥልጣን እንደሆነ ተጠይቀዋል። ይህን ጥያቄ የጠየቁት ካህናት
አላስተዋሉም እንጂ በምዕራፍ 3፥16 ተነግሯቸው ነበር።
4.2. 10–12 በቀረበው ተቃውሞ የሐዋርያው ጴጥሮስ መልስ
ከላይ በአይሁድ መምህራን የተጠየቀውን ጥያቄ በዋናነት የመለሰው ጴጥሮስ ነው፤ መልሱም ከዚህ በፊት መላልሶ
የተናገረውን ነው (3፥12-16)::

4.3. 13–18 በጴጥሮስና በዮሐንስ በድጋሚ የተሰነዘረ ተቃውሞ


ጴጥሮስና ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ግልጽ አድርገው በመመስከራቸው በተቃዋሚዎች ዘንድ ያልተማሩ ሰዎች ተብለዋል።
እንደ አይሁዳውያን አመለካከት ከክርስቶስ ጋር መሆን እንደ ስንፍና ድንቁርና ይቆጠራል፤ የተፈሰው ሽባ በዚህ ጊዜ
ከነዚህ ደቀመዛሙርት ጋር ቆሞ ነበር፤ ይህን የተመለከቱት የአይሁድ መምህራን የሐዋርያት ስብከት በኢየሩሳሌምና
አካባቢዋ እንዳይነገር አስጠነቀቁ፤ እነዚህ ተቃዋሚዎች ደቀመዛሙርቱ እንዳይሰብኩ ብቻ ሳይሆን ስማቸውም
እንዲጠፋ ጭምር ያስቡ ነበር። ይሁን እንጂ ትምህርቱ በዚህ ተቃውሞ የተገታ አልነበረም።

4.4. 19–23 ጴጥሮስና ዮሐንስ አቋማቸውን አሳወቁ


እነዚህ ደቀመዛሙርት ከሚደርስባቸው ተቃውሞ ይልቅ መነገር ስላለበት ጉዳይ ያሳሰባቸው ነበር፤ በመሆኑም
በተቃውሞ ምክንያት የሚመሰክሩትን ምስክርነት እንደማያቋርጡ ቁርጥ ኣቋማቸውን ገልፀዋል። እስከ አሁን ድረስ
ይህ ተቃውሞ የተነሣው በዝያ በተፈወሰው ሽባ ምክንያት ነው። አይሁዳውያኑ አንዳንድ ጊዜ ሕዝቡን ይፈሩ ስለነበር
ሐዋርያቱን የሚለቁበት አጋጣሚ ነበር፤ ይህን መሠረት አድርገው ሲፈቷቸው ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ወንድሞች
በመሄድ የደረሰባቸውን ተቃውሞ ለወንድሞቻቸው ኣሳውቀዋል።

4.5. 24–31 ለሐዋርያት በሚደረግላቸው ድል የ 120 ው ቤተሰብ ምስጋና


እነዚህ 120 ቤተሰብ በአንዱ ላይ የደረሰው መከራ መከራቸው፣ ለአንዱ የተደረገለት ድል ድላቸው አድርገው
ይቆጥሩት ነበር። አሁንም ለጴጥሮስና ለሐዋርያት የተሰጠው የፈውስ ሥልጣን ለእነሱ እንደተሰጠ አድርገው
ቆጥረውታል። ከዚህ በተጨማሪ በእነዚህ ተቃዋሚዎች የተደረገውን ሴራ ሰምተዋል። በዚህ ምክንያት ስለ ተሰጠው
ድልና ስለተደረገው ሴራ ከመጻሕፍት በመጥቀስ ሁኔታውን በጸሎት መልኩ ገልፀዋል:: ሴራው በክርስቶስ መነሣት ላይ
እና ሞት ላይ የተደረገ ነው። እነዚህ ሰዎች በዚህ ምንባብ ያለውን ጸሎት ሲጸልዩ ሁሉም በአንድ ቤት ውስጥ ነበሩ።
ጸሎታቸውም ተሰሚነት እንዳገኘ ለማመልከት የነበሩበት ቤት ተነዋውጧል። እንዲህ ሲሆን እነዚህ 120 ቤተሰቦች
ከዕለት ዕለት ገልጠው ያስተምሩ ነበር።

4.6. 32–37 የአማኞች ኅብረት


ይህ ምንባብ በምዕራፍ 2፥42–47 ያለውን ምንባብ ይመስላል።

ምዕራፍ 5

5.1. 1–14 የሐናንያና የሰጲራ ውሸት


እነዚህ ባልና ሚስት ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን በክፉ አሠራራቸው ለቀድሞዎቹ ክርስቲያኖች
የክፋት አርአያ ሆነዋል። የእነዚህ ሰዎች ክፋት በውሸት የተደረገ አሠራር ነው። ቢሆንም ሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስ ይህ
አሠራር ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ማታለል እንደሆነ አስረድቷል። ከእነዚህ ሰዎች ክፋት በፊት የቀድሞዎቹ
ክርስቲያን ሕይወት ምን ይመስል እንደ ነበር ከዚህ በፊት አይተናል፤ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ማንም ሳያስገድዳቸው
በራሳቸው ፈቃድ በመስጠት እውነቱን መናገር የነበረባቸው ቢሆንም ለጥንቷ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሂደት መበላሸት
ምክንያት ሁነዋል ፤ ድርጊቱ ውሸት እንደ ነበር ለማስረዳት ግን እንደ እጃቸው ሥራ ተገቢውን ቅጣት ተቀብለዋል።
በእነዚህ ሰዎች ቅጣት 120 ው ቤተሰብ በሰው ስለነበራቸው እይታ ሞገስና ግርማ ሆኖ ጨምሯል። ለእነዚህ ምእመናን
ቁጥር መጨመር በዋናነት ሁለት ምክንያቶች ነበሩ እነዚህም፦

1. የሐዋርያት ስብከት፣
2. በሐዋርያት የሚደረገው ተአምራት ናቸው።
5.2. 5–16 ጴጥሮስ ሕሙማንን በጥላው መፈወስ ጀመረ
ወንጌላዊው ሉቃስ በዚህ ምንባብ ያሳለፈው መልእክት ደቀመዛሙርቱ ልዩ ልዩ ተአምራትን ያደርጉ እንደ ነበር ነው።
እንዲያውም ሌላው ቀርቶ በጥላቸው ይፈውሱ እንደ ነበር ገልጾአል። የጴጥሮስ በጥላ አማካኝነት መፈወስ
የሚገኘውም በዚህ ውስጥ ነው::

5.3. 17–28 በሐዋርያት ትምህርት ላይ የተደረገ ቅንዓት


በዚህ ምንባብ የተገለጹ ተቃዋሚዎች ከልዩ ልዩ ቡድን የተውጣጡ ናቸው። እነዚህ ቡድኖች ሐዋርያት በክርስቶስ ስም
እንዳያስተምሩ የተለያዩ ሐሳቦችንና አሠራሮችን ይሠሩና ያቀርቡ ነበር። በዚህ ምንባብ ያለው የእነዚህ ቡድኖች ቅንዓት
ሐዋርያትን እስከ እስር ቤት ድረስ ያደረሰ ነው። ቢሆንም እግዚአብሔር መልአኩን ሰዶ ፈታቸውና የሕይወትን ቃል
እንዲያስተምሩ አደረጋቸው። መላእክት ለእግዚአብሔር ዓላማና ለሰው ልጅ መዳን የሚላላኩ እንደ ሆኑ በተለያዩ
መጻሕፍት ተጽፎ ይገኛል:: በሐዋርያት ላይ በተደረገው እርዳታ በካህናቱ ዘንድ ትልቅ ሽብር ሁኗል፤ ከብዙ ጥረት በኋላ
ግን ሐዋርያቱን በማግኘት ነገሩን በዘዴ ለማየት እንደ ሞከሩ ተገልጿል፤ እዚህ ላይ ያለው የካህናቱ ጠብ ተንኮል
የተሞላበት አነጋገር ሁኖ ቀርቧል::

5.4. 29–33 ጴጥሮስና ዮሐንስ ለተቃዋሚዎች የሰጡት መልስ


እነዚህ ደቀመዛሙርት ከላይ እንዳለፈው ምንባብ ከእስር ቤት ወጥተው ቃሉን አስተምረዋል:: ታዲያ በዚህ ጊዜ
የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ አንዳችም በክርስቶስ ስም እንዳያስተምሩ ነው፤ የምኩራቡ አለቃና መሰሎቹ እነዚህን
ደቀመዛሙርት እንዳታስተምሩ ተከልክላችሁ አልነበረም ወይ? ብሏቸዋል። ይህን ጥያቄ (ንግግር) ለመመለስ ነበር
ጴጥሮስና ዮሐንስ በዚህ ክፍል ያለውን ገጸ ንባብ የተናገሩት፤ ጴጥሮስና ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ሁለት
ምስክሮችን አቁመዋል፤ እነዚህም፦

1. ራሳቸው ሐዋርያት ናቸው::


2. መንፈስ ቅዱስ ነው::

5.5. 34–39 ገማልያል ሐዋርያትን የሚቃወሙ ሰዎችን ተቃወመ


ይህ መምህር በእነዚህ እስራኤል እጅግ የተፈራና የተከበረ መምህር እንደ ሆነ ጸሐፊው ሉቃስ ይገልጻል። ገማልያል
አይሁዳውያኑ በሐዋርያት ላይ የሚፈጽሙት ግፍን አይቷል፤ እንደዚህ መምህር አነጋገር ግፉ ከባዶ የተነሣ ነበር፤
በአንጻሩ ደግሞ የሐዋርያት አሠራር መጨረሻው ምን እንደሚሆን ሁለት ታሪኮችን በመጥቀስ ጥያቄ ምልክት
አስቀምጦታል። እስራኤላውያን በነዚህ ሐዋርያት ላይ የሚያደርሱት መከራ ማቆም እንዳለባቸው መከረ።
እንደገማልያል አነጋገር ሐዋርያትን መግፋት ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነው፤ በዚህ ምክንያት ደቀመዛሙርቱ የሞት
ቅጣት ታስቦባቸው የነበረ ቢሆንም በግርፋትና በዛቻ ተልለቀዋል።

5.6. 40–42 ሐዋርያት ጠላትን ስለ ማሳፈራቸው


ሐዋርያት ልዩ ልዩ መከራ ቢደርስባቸውም ጸሐፊው ሉቃስ እንዳስረዳው ግን ይህ መከራ ደስታቸው ነው፤ በየቀኑ ስለ
ክርስቶስ በቤተ መቅደስና በየቤቱ ይሰብኩና ይመሰክሩ ነበር ብሏል።
ምዕራፍ 6

6.1. 1–7 የሰባቱ ዲያቆናት መመረጥ


በጥንት ቤተ ክርስቲያን የምእመናን ቁጥር እየበዛ ሲሄድ አለመግባባት ተፈጥሯል፤ ይህ የቤተ ክርስቲያን ማኅበር የነበሩ
አማኞች ከኢየሩሳሌምና ከግሪክ አገር የተሰባሰቡ ናቸው፤ በዚህ ማኅበር ውስጥ የነበሩ ባል አልባ የሆኑ እናቶች
በሐዋርያት ይከፋፈል የነበረ ምግብ በአግባቡ ኣይደርሳቸውም ነበር፤ በዚህ ምክንያት ከግሪክ የመጡ አይሁዳውያን
በእስራኤል ላይ አጒረመረሙ:: ሐዋርያት ይህን ሲያውቁ ምግቡን በአግባቡ ለማከፋፈል የሚሠሩ በመልካም ሥነ
ምግባርና በሃይማኖት የታወቁ ሰባት ሰዎች በሕዝቡ እንዲመረጡ ሀሳብ አቀረቡ፤ ሀሳቡ ተቀባይነት አግኝቶ ለዚህ ሥራ
(ለማከፋፈሉ) ሰባት ሰዎች ተመርጠዋል፤ ስማቸውም በክፍሉ ውስጥ ተዘርዝሯል::

እነዚህ ዲያቆናት በ 12 ቱ ደቀመዛሙርት እግር ሁነው ስለ ወንጌል አገልግሎት እና ማኅበሩ ለማስተዳደር የተመረጡ
ናቸው።

6.2. 8–15 በእስጢፋኖስ ላይ የተደረገ የሐሰት ክስ


ከእነዚህ ሰባት ዲያቆናት በጥበብ፣ በሃይማኖትና በእውቀት በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠ እስጢፋኖስ ነው። በዚህ መሠረት
የአይሁድ መምህራን ይቃወም ነበረ፤ እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብና በአዕምሮ ጠባይዕ የተካነ ሰው ነው:: ይህን
ለመቃወም ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ አይሁዳውያን በተለይም ከኢየሩሳሌም የመጡ አይሁዳውያን በክርክር
ሳይሳካላቸው ሲቀር በሐሰት::

1. በሙሴ ሕግ ላይ
2. በእግዚአብሔር ላይ
3. በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላይ የስድብ ቃልን ይናገራል
4. ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ (ቤተ መቅደስን) ያፈርሳል
5. ሙሴ ያስተላለፍንን ሥርዓት ይለውጣል እያለ ያስተምራል በማለት ከሰውታል::

ምዕራፍ 7

7.1. 1-53 እስጢፋኖስ በምዕራፍ 6 ለተነገረበት የሐሰት ምስክርነት መልስ የሰጠበት ክፍል
በአርእስቱ እንደ ተጻፈው ከ 2–53 ያለው ምንባብ እስጢፋኖስ ስለ እስራኤል ታሪክ ጠቅሶ ለሊቀ ካህናቱ የሰጠው
መልስ ሲሆን እስጢፋኖስ ይህን ታሪክ መጥቀሱ እስራኤላውያን ሙሴን እንዳልተቀበሉት ሁሉ አይሁድም ክርስቶስን
እንዳልተቀበሉት ለማረጋገጥ ፈልጎ ነው። በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ በሙሉ በኦሪት ያለ ምንባብ ነው። ምንባቡም
ዘጠኝ ዋና ዋና ክፍሎችን ያካትታል ፤ እነርሱም፦

1. 1–8 የአብርሃም እምነት፣ ስደትና የተሰጠው ተስፋ


2. 9–10 ስለ ዮሴፍና ወንድሞቹ
3. 15–19 ያዕቆብ በረሀብ ምክንያት ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ
4. 20–22 ስለ ሙሴ መወለድና አስተዳደግ
5. 23–29 የሙሴ ስደት (ከግብፅ–ምድያም መኮብለል)
6. 30–34 ለሙሴ በቁጥቋጥ መካከል የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ተገለጠለት
7. 35–43 የሙሴ ወደ ፈርዖን መላክ
8. 44–50 የምስክር ድንኳን
9. 51–56 የእስጢፋኖስ የመጨረሻ ንግግር ናቸው::

እስጢፋኖስ ከ 1–53 ያለውን ታሪክን ከነገራቸው በኋላ ተቃዋሚዎቹን መገሠጽ ጀምሯል፤ አባቶቻቸው እና እነርሱ
የነቢያትና የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መሆናቸውን አስረድቷል። ክፋታቸው ምን እንደሆነም ገልጾባቸዋል፤ በመንፈስ
ቅዱስ ተሞልቶ የጌታን ክብር እያየ መሆኑንም ነገራቸው።
7.2. 54–60 የእስጢፋኖስ መገደል
አይሁዳውያኑ የእስጢፋኖስን ተግሣጽና ንግግርን በሚሰሙበት ጊዜ በታላቅ ድምፅ እየጮሁና እየሮጡ ከከተማ ወደ
ውጭ አስወጥተው በድንጋይ ደብድበው ገድለውታል። ልብሳቸውም ሳውል በሚባል ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ።
እስጢፋኖስ ግን የጌታን ክብር ያይ ነበር። ወደ ሞት በአዘነበለበት ጊዜም ይህን አትቁጠርባቸው እያለ ሲጸልይላቸው
ተሰምቷል፤ ይህን ከተናገረ በኋላ አርፏል::

ምዕራፍ 8

8.1. 1–4 የቤተክርስቲያን መሰደደና መበታተን


በእስጢፋኖስ ይመራ የነበረ ማኅበር ከእስጢፋኖስ ሞት በኋላ ተበትኗል። ይህ መበታተንና መሰደድ ሐዋርያትን
አያካትትም። መበተኑና መሰደዱ የተከሰተው በእስጢፋኖስ ሞት ምክንያት ነው። መበታተኑና መሰደዱ ግን
ለእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው። የጳውሎስ በክርስቲያን ላይ የነበረው ጥላቻም በቍ.3
ተገልጿል::

8.2. 5–8 ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ የሆነው ፊልጶስ ሰማርያ በሚባል ሀገር ማስተማር ጀመረ
ከተበተኑትና ከተሰደዱት መካከል አንዱ ፊልጶስ ነው፤ በዚህ ሂደት ምክንያት ወደ ሰማርያ ቢሄድም ግን ቃሉን
ከማስፋፋት ወደ ኋላ አላለም፤ እንደተገለጸው ከላይ ከተጠቀሰችው ቦታ በመገኘት ወንጌልን በሚገባ አስፋፍቷል። ከዚህ
ጎን ለጎን የተለያየ ደዌ ያለባቸው ሰዎችን እንደ ፈወሰም ተጽፏል። ይህን ያዩ የሰማርያ ሰዎች በእግዚአብሔር
የሚያምኑ ሁነዋል። ከነዚህ መካከል ጠንቋዩ ሲሞን አንዱ ነበር።

8.3. 9–13 ጠንቋዩ ሲሞን ስለ የሚያደርገው ምትሐትና በፊልጶስ ትምህርት ማመኑ


ሲሞን የተባለው ጠንቋይ በሰማርያ የጥንቆላ ሥራ በመሥራት ሕዝቡን በሐሰት ያታልልና ያሳምን እንደ ነበር
ተገልጿል። በሰማርያ ሰዎች ለጠንቋዩ የተሰጠው ክብርም ታላቅ እንደ ነበር በአጽንኦት ተገልጿል። ፊልጶስ ወደ ሰማርያ
በገባ ጊዜ ግን ሕዝቡ ሲሞንን ትተው በፊልጶስ ተአምራትና ትምህርት አመኑ፤ የፊልጶስ ተአምራትና ትምህርትም
ለጊዜው ሲሞንን አሳምኗል። በሰማርያ የተሰጠው የፈልጶስ አስተምህሮ መላውን ሕዝብ ያሳመነና ያጠመቀ ነበር::
ሲሞንም ከላይ እንደ ተገለጸው ለጊዜው የዚህ መንፈሳዊ ነገር ተካፋይ መስሎ ታይቷል::

8.4. 14–25 ጴጥሮስና ዮሐንስ ከሐዋርያት ወደ ሰማርያ ስለ መላካቸው


ፊልጶስ በሰማርያ ከተማ ያሉትን አሕዛብ ያስተምርና ያጠምቅ እንደ ነበር ከላይ ገልጸናል። ይህን አገልግሎት
ለማጠናከርና በፊልጶስ ባመኑት ላይ መንፈስ ቅዱስን ለማሳደር ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ሰማርያ ወርደዋል፤ ይኸውም
ጥምቀተ ዮሐንስን ብቻ ተጠምቀው በነበሩት አማኞች ላይ በጸሎትና እጅን በመጫን መንፈስ ቅዱስን ለማሳደር
ነው። ሲሞን ጴጥሮስና ዮሐንስ ባደረጉት ነገር ቀንቷል። የመንፈስ ቅዱን ጸጋ በወርቅና በብር ለመግዛት ፈለገ።
ጴጥሮስ የሲሞን ሀሳብ በተንኮል መርዝ የተሞላ መሆኑን ስለ አወቀ ነገሩ ንስሐ የሚያስፈልገውና ከክፋት በላይ እንደ
ሆነ አሳውቋል። ሲሞን ከዚህ በፊት በፊልጶስ ስብከት እንደ አመነና እንደ ተጠመቀ አይተን ነበር፤ ይሁን እንጂ ከላይ
እንደ ተገለጸው ይህ ነገር ጊዜአዊ ስለ ነበር በቅርብ ጊዜ ይህን ተንኮል አድርጓል:: አሁንም ተንኮሉን ሳይተው ከዚህ
ክፋት እንደሚመለስ ሐዋርያትን ሲማጸን ይታያል፤ እነዚህ ሁለት አበጋዞች ሐዋርያት የሲሞንን ጉዳይ በዚህ ሁኔታ
በመተው ሰማርያን ይዘው እግረ መንገዳቸው እያስተማሩ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰዋል።

8.5. 26–40 ፊልጶስና ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ


ይህ ”የኢትዮጵያ ሰው’’ የተባለው ጃንደረባ ሉቃስ እንደ ጻፈው ለመስገድ ኢየሩሳሌም ሄዷል። በጊዜው ከተለያዩ
ሀገሮች እየሄዱ ኢየሩሳሌም መስገድ የተለመደና ሃይማኖታዊ መገለጫ እንደ ነበር ታሪክ ያመለክታል፤ ይህ ጃንደረባ
”ህንደኬ’’ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ራስ ቢትወደድና በገንዘቧ ሁሉ ላይ የሰለጠነ ሰው እንደ ሆነ ተገልጿል፤
ሥራውን ጨርሶ ወደ ሀገሩ እየተመለሰ ሳለ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ በመመልከት ላይ ነበር (ኢሳ.53፥7–8)፤
ፊልጶስ በመልአክና በመንፈስ ቅዱስ ነጋሪነት ወደ ጃንደረባው ሲቀርብ ከላይ የተገለጸውን መጽሐፍ ሲያነብብ
ተመለከተ:: ስለሁኔታው ሲጠይቀው ግን ከማንበብ በቀር ነቢዩ ይህን ያለው ስለማን እንደሆነ የሚያውቀው ነገር
እንደሌለ አስረዳው፤ ጃንደረባው የማያውቀው ነቢዩ ስለማን እንደሚናገር እንጂ ምንባቡንና ቋንቋውን ግን ያውቀው
ነበር፤ የመጽሐፉ ይዘት የሚናገረው ስለ ክርስቶስ ሕማምና ሞት ነው:: ፊልጶስም ሁኔታውን በማስረዳት በክርስቶስ
አምኖ መጠመቅ እንዳለበት ሲናገር በፊሊጶስ እጅ ተጠምቋል። ከዚህ ክንውን በኋላ ሁለቱም አካላት ወደየቦታቸው
ሂደዋል::

ምዕራፍ 9

9.1.1–2 ጳውሎስ በምእመናን ላይ ሲያደርስ የነበረው ማሳዳድ


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ የጳውሎስን የቀድሞ ሥራ በትንሹ ያመለክታል።

9.2.3–9 የጳውሎስ መጠራት


ጳውሎስ በደማስቆ የእግዚአብሔር ጥሪን ከመስማቱ በፊት በምን ዓይነት ሥራና ሕይወት ይጓዝ እንደ ነበር
በመጀመርያው ክፍል አይተናል፤ ቢሆንም ክርስቲያንን ለማሳደድ ደማስቆ በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔር ጥሪ በመብረቅ
ብርሃን አምሳል መጥቶለታል። ይህ የመብረቅ ጥሪ ለጊዜው ጳውሎስን ቢያስደነግጥም ኋላ ግን የሕይወቱ መሪ ሆኗል።
ጥሪው ጳውሎስ በምን ዓይነት ሕይወት እየተጓዘ እንዳለና ወደፊት ምንን ማድረግ እንዳለበት የሚያመላክት ነው፤
በጥሪው ሳይደናገጥ አልቀረም፤ ነገር ግን የጥሪው መምጣት ዓላማ ለምን እንደ ሆነ ከጠሪው አካል ጋር ተነጋግሮ
ተረድቷል:: በተረዳው መሠረትም የተባለውን ነገር እንዳደረገ ጸሐፊው ሉቃስ ጨምሮ ገልጿል፤ ነገሮችን ሁሉ
እስኪያረጋግጥ ድረስ ግን ለሦስት ቀናት ያህል እህል ውሃ ሳይቀምስ እንደታወረ በደማስቆ ከተማ ተቀምጧል።

9.3.10–16 የደማስቆው ነዋሪ ሐናንያ ጳውሎስን ያጠምቅ ዘንድ ታዘዘ


በዚህ መጽሐፍ 3 ሐናንያ የተባሉ ሰዎች አሉ፤ ሁለቱ በምዕራፍ 5 ላይ ያለው ሲሆን አንዱ ደግሞ እዚህ ላይ ያለው
ነው፤ 3 ኛው ደግሞ በምዕራፍ 23፥2 ላይ ያለው ነው:: ጳውሎስ ዓይነ ስውር ሁኖ በደማስቆ 3 ቀን ሲኖር
እግዚአብሔር ጳውሎስን ያጠምቅ ዘንድ ይህን ሐናንያ በራዕይ ታይቶ ልኮታል። የሚያጠምቀው አካል ያለበት ቦታም
ተነግሮታል። ሐናንያ ወደ ጳውሎስ ከመድረሱ በፊት በሐናንያ አምሳል እግዚአብሔር እጁን ሲጭንበት ያይ እንደ ነበር
ሉቃስ አሳውቋል። ለሐናንያ እንደ ተነገረው የጳውሎስ መጠራት ዓላማ የእግዚአብሔርን ስም በአሕዛብ፣
በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ይሸከም ዘንድ ነው፤ እዚህ ላይ ጳውሎስ ለወደፊት በሚያደርገው ምስክርነት
ምርጥ ዕቃ ተብሎ ተነግሮለታል። ከምስክርነቱ ጎን ለጎንም መከራውን ተነግለታል።

9.4.17–26 የጳውሎስ መዳንና የመጀመርያ ምስክርነት


ያ ደቀ መዝሙር ሐናንያ በተላከው መሠረት ሁኔታውን በመግለጽ ማለት ከማን እንደተላከና ለምን ዓላማ ወደ እርሱ
እንደ መጣ በማስረዳት ጳውሎስን አጥምቋል። በዚህ ጊዜ በጥሪው ጊዜ በጳውሎስ ላይ የወረደው በሽታ ከጳውሎስ ላይ
ተወግዷል፤ ከዚህ በኋላ ጳውሎስ በደማስቆ ምኩራብ ገብቶ የቀድሞ አስተምህሮውን በመተው ስለ ክርስቶስ የባሕሪይ
ልጅነት መስክሯል፤ ይህ የጳውሎስ ምስክርነት ቀድሞ በሚያውቁት ዘንድ ድንቅ ነገር ሁኖ ታይቷል። የጳውሎስ
የመጀመርያ ስብከቱ ”እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው‘ የሚል ነው።

9.5.23–31 የደማስቆ አይሁድ በጳውሎስ ላይ ምክርን መከሩ

ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ በመመስከሩ በደማስቆ ከተማ በአይሁድ ዘንድ ትልቅ ተቃውሞ ገጥሞታል፤ ተቃውሞውም
ሕይወቱን የሚፈታተን ስለነበር በዚህ ከተማ የነበሩ ክርስቲያን ወንድሞቹ፣ አይሁድ በማያውቁት መንገድ ወደ
ኢየሩሳሌም አሸሹት። በዝያም ማስተማሩን አልተወም፤ በጊዜው በኢየሩሳሌም ሐዋርያትና ብዙ ደቀ መዛሙርት ነበሩ፤
ከዚያ ሲደርስ በክርስቶስ ስም በማስተማሩ ተቃውሞ እንደገጠመው በርናባስ ለሐዋርያት ነግሮለታል፤ ይሁን እንጂ
እውነታው እስኪታወቅ ድረስ ሐዋርያት የጳውሎስን ማመንና በዚህ ምክንያት የደረሰውን ተቃውሞ መቀበል
ተቸግረዋል። በደማስቆ የነበረው ተቃውሞ ግን በኢየሩሳሌምም ቀጥሏል። ከዚህ በኋላ ወደ ጤርሴስና ቂሣርያ ተሰደደ።
ይህን ጊዜ ቤተክርስቲያን ታድግና ትበዛ እንደ ነበር ተገልጿል::

9.6.32–35 ጴጥሮስ ኤንያ የተባለ ሰውን እንደ ፈወሰ

ይህ ምንባብ በአርእስቱ እንደተገለጸው ጴጥሮስ ልዳ በተባለ ቦታ ለ 8 ዓመታት ያህል የታመመ ኤንያ የተባለውን ሰው
እንደ ፈወሰ ይናገራል፤ ልዳ በከነአን ግዛት የምትገኝ ቦታ ናት::

9.7.36–46 ጴጥሮስ የኤዮጴዋን ጣቢታ ከሞት እንደ አሥነሣ

ይህች ጣቢታ የተባለች ሟች ሴት ለልዳ ቅርብ በሆነ ኢዮጴ በሚባል ቦታ የምትኖርና ደግነቷ ሁሉ በመላው ሕዝብ
የታወቀላት ሴት ናት፤ ሴቲቱ ጴጥሮስ በልዳ ባለበት ጊዜ ሙታለች፤ የጴጥሮስን በልዳ መኖር ያወቁ ሰዎች ሁለት
ሰዎችን ወደ እርሱ በመላክ አስመጥተውታል፤ በዚህ ጊዜ ነበር ነገሮችን በማመቻቸትና በጸሎት ከሞት ያሥነሣት።
የጣቢታ ከሞት መነሣት ለብዙ ሰዎች ማመን ምክንያት ሆኗል።

ምዕራፍ 10
10.1. 1–2 ቆርኔሌዎስና ደግነቱ

ቆርኔሌዎስ በቂሣርያ ”ኢጣሊቄ‘ ለሚባል ጭፍራ መቶ አለቃና አሕዛባዊ ሰው ሲሆን አንድ አማኝ የሚሠራውን
መልካም ሥራ በመሥራት የሚታወቅ ደግ ሰው እንደ ነበር ጸሐፊው ሉቃስ በአጽንኦት ይጽፋል:: በዚህ ሥራውም
ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳጅነትን መሥርቷል፤ ይሁን እንጂ በመጠመቅ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጠውን ልጅነት
በማግኘት የዳነ ሰው አይደለም::

10.2. 3-8 ለቆርኔሌዎስ መልአክ ተገለጠለት


ቆርኔሌዎስ በእግዚአብሔር ፊት ምን ዓይነት ሰው እንደ ነበር በመጀመርያው ክፍል ተገልጿል ማለት ከመልካም
ሥራዎቹ መካከል አንዱ ጸሎት ነው፤ ለዚህ ተግባር በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ ሳለ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መልአክ
ተገልጦለታል፤ መልአኩ የተገለጠለት፦

1. ጸሎቱና ምጽዋቱ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ደረሰለት ለማብሠር ነው::


2. እርሱና ቤተ ሰቦቹ በሚድኑበት ዙርያ ማድረግ ያለበትን ነገር ያደርግ ዘንድ ለመንገር ነው::

በዚህ ሁኔታ የመዳን መንገዱን የሚነግረው ጴጥሮስ ስለ ነበር የጴጥሮስን አድራሻ ነግሮታል፤ ይህን በመቀበል የተባለውን
ሁሉ በመተረክ መልእክተኞችን ወደ ጴጥሮስ ላከ::

10.3. 9-16 የጴጥሮስ ራእይ


በዚህ ክፍል ያለው ራእይ በቆርኔሌዎስ ላይ ያነጣጠረ ነው፤ የዚህ ራእይ ምሥጢራዊ ትርጉሙ ከ 26-29 ባለው
ምንባብ ስለተብራራ ያነን ማየት በቂ ይሆናል::

10.4. 17-22 ከቆርኔሌዎስ የተላኩ ሰዎች ጴጥሮስ ካለበት ቦታ እንደ ደረሱ


መልእክተኞቹ ኢዮጴ የደረሱት ጴጥሮስ ስለአየው ራእይ እያወጣና እያወረደ ባለበት ጊዜ ነው፤ ከመገናኘታቸው በፊት
ግን መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስን 3 ሰዎች እንደሚፈልጉት ነግሮታል፤ በቅድሚያ ለጴጥሮስ ስለጉዳዩ መንገር ያስፈለገበት
ምክንያት ኋላ በነገሩ እንዳይደናገር ነው፤ ስለዚህ መልእክተኞቹ አድራሻውን ጠይቀው ሲያገኙት ስለመጡበት ጉዳይ
ይነግሩት ዘንድ ጥያቄን አቀረበ፤ መልእክተኞቹም በተባሉት መሠረት አስረድተዋል፤ አሁን ነገሮች ሁሉ ለጴጥሮስ ግልጽ
ሁነውለታል::
10.5. 23-29 ለጴጥሮስ የተደረገለት አቀባበልና ጴጥሮስ ስለ ጉዳዩ ያደረገው ንግግር
የተደረገለት አቀባበልና ያደረገው ንግግር እንዴት እንደ ነበር ምንባቡን በማየት ማስተዋል በቂ ነው:: እዚህ ላይ ያለው
ምንባብ ቆርኔሌዎስ የላከበትን ምክንያት እንደተናገረና የጴጥሮስን ቃል ለመስማት ልቡ ክፍት እንደሆነ መግለጹን
ይናገራል::

10.6. 30-33 ቆርኔሌዎስ ወደ ጴጥሮስ የላከበትን ምክንያት መግለጹ


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ በክፍል ሁለት ያለውን ምንባብ ያብራራል::

10.7. 34-43 ጴጥሮስ ተናገር በተባለው መሠረት ተናገረ


እዚህ ላይ ያለው የጴጥሮስ ንግግር ቆርኔሌዎስንና ቤተሰቦችን የእግዚአብሔር ልጅነት ባለቤት ያደረገ ሲሆን ንግግሩም፦

1. እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ


2. ማዳኑን በክርስቶስ በኩል ወደ እስራኤል ልጆች እንደ ላከ
3. ክርስቶስ በዚህ ዓለም የመፈወስ ሥራውን እንዳከናወነ
4. ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሢሕ እንደ ሆነ
5. ክርስቶስ በአይሁዳውያን እንደ ተገደለ
6. ክርስቶስ በ 3 ኛው ቀን ከሞትእንደ ተነሣ
7. በክርስቶስ ላይ ለተደረገውና ክርስቶስ ላደረገው ሁሉ እነርሱ ምስክሮች እንደ ሆኑ
8. በክርስቶስ የሚያምን የኃጢአት ሥርየትን እንደሚያገኝ ነቢያት እንደ መሰከሩለት ያስረዳል::

10.8. 44–48 ቆርኔሌዎስና ቤተ ሰቦቹ መንፈስ ቅዱስ ን ስለ መቀበላቸው


ቅዱስ ጴጥሮስ በቆርኔሌዎስ ቤት ተገኝቶ ስለ እግዚአብሔር ቸርነት ሲናገር ሕዝቡ አምኗል። በዚህ ሁኔታ
የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ ለማስረዳት፦

1. መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል::


2. ሐዋርያት በበዓለ ሀምሳ በተናገሩት ቋንቋ ተናግረዋል::

ምዕራፍ 11

11.1. 1 የቆርኔሌዎስና ቤተሰቦቹ ማመን በምእመናን ዘንድ ተሰማ


እዚህ ላይ ያለው ዋና ነገር በይሁዳ የነበሩት ምእመናንና ሐዋርያት ቆርኔሌዎስና ቤተሰቦቹ በእግዚአብሔር እንዳመኑ
መስማታቸው ነው።

11.2. 2–3 በጴጥሮስ ላይ የደረሰ ተቃውሞ


ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው በአሕዛብ ላይ ያላቸውን አመለካከት እስከ አሁን ድረስ አላነሡም ፤ ምንም እንኳ በመንፈስ
ቅዱስ ቢታደሱና ጠንካራ ቢሆኑም እንደ ርኲስ ይቆጥሯቸዋል፤ በመሆኑም ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ቤት ገብቶ
በመብላቱና በመጠጣቱ ከወንድሞቹ ዘንድ ተቃውሞ ደረሰበት።

11.3. 4–18 ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ቤት የገባበትን ምክንያት ለወንድሞቹ አሳወቀ


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ ጴጥሮስ በምዕራፍ 10 ከ 9-48 ያለውን ምንባብ ለወንድሞቹ በዝርዝር እንዳሳወቀ
ያስረዳል::

11.4. 19–21 በእስጢፋኖስ ሞት ስለተበተኑ ምእመናን


እዚህ ላይ ያለው ምንባብ በእስጢፋኖስ ሞት ምክንያት የተበታተኑት ወንድሞች፦

1. እያስተማሩ ከተለያዩ ቦታዎች እንደ ደረሱ


2. በሚሠሩት ሥራ ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ ከእነርሱ ጋር እንደ ነበረች ያመለክታል።
11.5. 22–24 በርናባስ ወደ አንጾኪያ ተላከ
በአንጾኪያ ከተማ የእግዚአብሔር ቃል ተስፋፍቶ ነበር፤ ይህ መልካም ነገር ደግሞ በወንድሞች ዘንድ ተሰምቷል::
ስለዚህ ነገሮችን ሁሉ እንዲያረጋግጥ በርናባስ ወደዚች ከተማ ተላከ፤ የተላከበት ዓላማ በየቦታው የተስፋፋውን
የእግዚአብሔርን ቃል ለማስፋፋት ነው። ወንጌላዊው ሉቃስ በርናባስ ከዚህች ከተማ በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ
በዝቶ እንዳየ ይመሰክራል፤ ጸጋውም የቃሉ መስፋፋት ነበር።

11.6. 25–26 በርናባስ ጳውሎስን ፍለጋ ወደ ጠርሴስ መጣ


በርናባስ ጳውሎስን ፍለጋ ከአንጾኪያ ወደ ጠርሴስ ሄዷል፤ የሄደበት ዓላማ ጳውሎስን ወደ አንጾኪያ ለማምጣት ነው፤
አንጾኪያ ምእመናን ለመጀመሪያ ጊዜ ”ክርስቲያን’’ ተብለው የተጠሩባት ከተማ ናት።

11.7. 27–30 ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ


እነዚህ ነቢያት በኢየሩሳሌም የነበሩ ሲሆን የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ወደ አንጾኪያ እንደ ወረዱ ወንጌላዊው
ሉቃስ ይመሰክራል። ከእነዚህ አንዱ አጋቦስ ነው። ይህ ነቢይ በቀላውዴዎስ ቄሳር ዘመን ይመጣ ዘንድ ስላለው ረሀብ
ትንቢት ተናግሯል። ቢሆንም ረሀቡ በወንድሞች መረዳዳት ምክንያት የተቃለለ ይመስላል::

ምዕራፍ 12

12.1. 1–5 የሐዋርያው ያዕቆብ መገደል


ሐዋርያት ከክርስቶስ ማረግ በኋላ የእግዚአብሔርን ቃል በመስበካቸው ልዩ ልዩ መከራ ይደርስባቸው እንደ ነበር
በየቦታው ተገልጿል። በተለይም በሮማ ነገሥታት በኩል ይደረግ የበረው ተቃውሞ በቀላሉ የሚታይ አልነበረም፤
ምክንያቱም እነዚህ ነገሥታት ራሰ አምላክ በመሆናቸው ምክንያት በአዲሱ እምነት ትልቅ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል፤
ስለዚህ ይህን ስጋት ያስወግዳል ብለው ያሰቡትን እርምጃ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ መውሰድ ጀምረዋል:: ከዋናዎቹ
ሐዋርያት በመጀመርያ የሞት ጽዋዕን የቀመሰው የዮሐንስ ወንድም ያዕቆብ ነው፤ በዚህ ክፍል እንደተጻፈው የታላቁ
ሄሮድስ ልጅ ሄሮድስ አንቲጳስ ከላይ የተጠቀሰውን ደቀ መዝሙር በሰይፍ ቀልቶታል፤ በዚህ ንጉሥ የታዘዘው የራሰ
አምላክነት ቁጣ በያዕቆብ ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በመላው ደቀመዛሙርትም ላይ እንጂ:: በዚህም እንደተገለጸው
በይበልጥ ቁጣው ወደ ዋናው አለቃ ጴጥሮስ ተላልፏል፤ ይህ ድርጊት ለጥንቷ ቤተ ክርስቲያን እድገትና መስፋፋት ትልቅ
ፈተና ነበር፤ ይሁን እንጂ ማንኛውንም ፈተና በጸሎትና በእምነት ሲያሸንፉ ታይቷል:: በወንድሞች ዘንድ ስለጴጥሮስ
የተደረገው ጸሎትም ይህን ያመለክታል::

12.2. 6-11 በእግዚአብሔር መልአክ ለጴጥሮስ ስለ ተደረገው እርዳታ


ጴጥሮስ በወህኒ ተጥሎ በሰንሰለት ታስሮ በወታደሮች ይጠበቅ እንደ ነበር በአጽንኦት ተገልጿል፤ የጴጥሮስ መታሠር
እንደ ሄሮድስ ፍላጎት የፋሲካ በዓል እስኪያልፍ ነው። ከፋሲካው በኋላ በጴጥሮስ ላይ የታሰበው ነገር እስከ ሞት ድረስ
የሚያደርስ ነው፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የራሱ የሆነ ሥራን ይሠራ ስለነበር በመልአክ ረዳትነት ጴጥሮስ
በሚያስደንቅ ሁኔታ ከወኅኒ ቤት ወጥቷል::

12.3. 12-17 ጴጥሮስ ከወንድሞቹ ጋር ተገናኘ


ሐዋርያው ጴጥሮስ የመልአኩን እርዳታ ያስተዋለው ቆይቶ ነበርና ባስተዋለ ጊዜ ግን ምእመናን ተሰብስበው
ወደነበሩበት ቤት ሄደ። ይህ ቤት በቀድሞ ዮሐንስ ይባል የነበረው የማርቆስ እናት ቤት እንደሆነ ጸሐፊው ሉቃስ
ገልጿል፤ ምእመናን ጴጥሮስን በጸሎት ይጠባበቁ እንደ ነበር ከላይ ተገልጿል። ወደእነርሱ በመጣ ጊዜ ግን ከደስታ
የተነሣ በቀላሉ ማመን አልቻሉም። እርሱ ግን በእስር ቤት የተደረገለትን ሁሉ ነግሯቸው ወደ ሌላ ስፍራ ሂዷል።

12.4. 18- 20 ጴጥሮስ በእስር ቤት በመታጣቱ ምክንያት ድንጋጤ ተፈጠረ


ሄሮድስ ጴጥሮስን አሳሥሮ ወደ ሥራው ሄዷል። ታማኝ የሆኑ ጠባቂዎችን ሹሞ ሁኔታውን አመቻችቷል። ጠባቂዎቹ
ግን ለጴጥሮስ የተደረገውን የመልአክ እርዳታ አላወቁም። ሄሮድስ የወሰደው እርምጃ ጠባቂዎችን በሞት ቀጥቶ ወደ
ቂሣርያ መውረድ ነው፤ ይህን ጊዜ ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎች ተጣልቶ እንደ ነበር ተገልጿል:: ቁጣው ድርብ በመሆኑም
በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚደረገው ድርጊት ከባድ ይሆናል:: ነገር ግን ቢትወደዱ በላስጦስን አስታራቂ በማድረግ
አገራቸውን ከረሀብ አድነዋል። አገራቸው ከሮማ ምግብን የሚታገኘው በሄሮድስ እጅ በኩል አድርጎ ነበር።

12.5. 21-24 የሄሮድስ መሞትና የእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት


እዚህ ላይ ያለው ምንባብ ሄሮድስ አንቲጳስ ሕዝቡን እቀጣለሁ ብሎ በቀጠረበት ቀን ራሱ እንደ ተቀጣና የእግዚአብሔር
ቃል እየተስፋፋ እንደሄደ ያመለክታል፤ ሄሮድስ የተቀጣው በእግዚአብሔር መልአክ ሲሆን የተቀጣበት ምክንያት ደግሞ
የእግዚአብሔር ቃል በመናቁ ነው::

12.6. 25 የጳውሎስና የበርናባስ ከኢየሩሳሌም መመለስ


በምዕራፍ 11፥30 ጳውሎስና በርናባስ ለደቀመዛሙርት እርዳታ ወደኢየሩሳሌም እንደተላኩ አይተናል:: እዚህ ላይ
ደግሞ ያንን ጉዳይ አሳክተው ወደ አንጾኪያ እንደ ተመለሱ ነው የተጻፈው፤ በዚህ ጊዜ ማርቆስ የተባለው ዮሐንስን
ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ይዘውት እንደ መጡ ተገልጿል::

ምዕራፍ 13

13.1. 1-3 የበርናባስና የጳውሎስ መመረጥ


በዚህ ክፍል አምስት ነቢያት አሉ፤ እነዚህም፦

1. በርናባስ
2. ኔጌር የተባለው ስምዖን
3. ቀሬናዊው ሉክዮስ
4. የሄሮድስ ባለሟል ምናሔ
5. ሳውል (ጳውሎስ) ናቸው::

ወንጌላዊው ሉቃስ እነዚህን ነቢያትና መምህራን ይላቸዋል፤ እነዚህ አንድ ላይ ሲጾሙና ሲያመልኩ የእግዚአብሔር
መንፈስ ድንገት የጳውሎስንና የበርናባስን መመረጥ ተናግሯል፤ ለይሉኝ ያለበት ዓላማም ለወንጌል አገልግሎት እንደሆነ
”እኔ ለወደድኩት ሥራ ለይሉኝ’’ ባለው ንግግሩ ታውቋል::

13.2. 4-12 የጳውሎስና የበርናባስ የመጀመርያው ሐዋርያው ጉዞ


እነዚህ ሁለቱ መምህራን የመጀመሪያው ሐዋርያዊው ጉዞ ለማድረግ በጸሎትና እጅ በመጫን ከወንድሞቻቸው
ተሰናብተዋል፤ የመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉዞ ክንውን ያለው ከምዕራፍ 13፥4 እስከ ምዕራፍ 14፥26 ድረስ ሲሆን
በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያሉ ክንውኖች ሁሉ በመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉዞ የተደረጉ ናቸው፤ ስለዚህ ክንውኖቹን
አሳጥረን ስለገለጽናቸው እንዴት እንተከናወኑ ለማስተዋል ማንበብ የሚጠይቅ ይሆናል፤ ዋና ዋናዎቹ ግን ከዚህ በታች
ተዘርዝረዋል::

ተልእኮውና አስተምህሮው

1. 4–12 የተገለጸው ክንውን


2. 13–15 ጳውሎስና በርናባስ በአንጾኪያ
3. 16–23 ጳውሎስ በእስራኤል ላይ የተደረገን ቸርነትና የክርስቶስን ነገር መናገሩ
4. 24–26 የዮሐንስ ምስክርነትና የመዳን ቃል
5. 27– 43 በክርስቶስ ላይ የተደረገው የአይሁድ ክፋትና የክርስቶስ መነሣት
6. 44–45 በጳውሎስና በበርናባስ ላይ የተደረገ ታቀውሞ
7. 46–52 ጳውሎስና በርናባስ አይሁድን ማስጠንቀቅና የአይሁድ ጳውሎስን ከሀገራቸው ማስወጣታቸውና
የመሳሰሉት ናቸው::
ምዕራፍ 14

14.1 ተልእኮውና አስተምህሮው


1. 1–3 በኢቆንዮን የሰጡት ትምህርትና ያጋጠማቸው ተቃውሞ
2. 4–7 ልስጥራን፣ ደርቤንና ሊቃኦንያ ወደተባሉት ከተሞች ያደረጉት ሽሽትና በእነዚህ ከተሞች ያስተማሩት
ትምህርት
3. 8–10 በደርቤን አንድ አንካሳ ሰውን ማዳናቸው
4. 11–13 እነጳውሎስ አማልክት መባላቸው
5. 14–18 እነጳውሎስ ሕዝቡ ያደረጉላቸውን የማይገባ አምልኮ መቃወማቸው
6. 19–20 የእነጳውሎስ መደብደብና ከደርቤን መውጣት
7. 21–28 የእነጳውሎስ ወደ አንጾኪያ መመለስና የመሳሰሉት ናቸው::

ምዕራፍ 15

15.1. 1-3 ጳውሎስና በርናባስ በአስተማሯቸው ምእመናን ላይ ችግር ተፈጠረ


ጳውሎስና ባርናባስ በመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉዞ አሕዛብን ወደ አዲሱ የክርስትና እምነት መልሰዋል፤ በዚህ የተናደዱ
ወግ አጥባቂና የሙሴን ሕግ እንጠብቃለን የሚሉት አንዳንድ አይሁዳውያን ያመኑትን አሕዛብ የሙሴን ሥርዓት
እንዲጠብቁ አስተምረዋቸዋል፤ ሥርዓቱ በሙሴ ሕግ መሠረት ካልተገዘሩ መዳን እንደማይችሉ ያመለክታል፤ በዚህ
ምክንያት በእነጳውሎስና በቢጽ ሐሳውያን መካከል ብዙ ክርክር ተደርጓል፤ ይሁን እንጂ ክርክሩን የሚፈታ አካል
ስለአልነበረ የክርክሩ ሁኔታ በሐዋርያት እንዲታይ ጳውሎስና በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ተልከዋል::

15.2. 4-5 የጳውሎስና የባርናባስ ኢየሩሳሌም መድረስ


እነዚህ ሁለት ሐዋርያት የታዘዙትን ነገር ይዘው ኢየሩሳሌም ሲደርሱ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያትና ቀሳውስት
መልካም አቀባበል አድርገውላቸዋል፤ በዚህ ጊዜ ነበር እነጳውሎስ የተላኩበትን ምክንያት፣ እግዚአብሔር በመጀመርያው
ሐዋርያዊ ጉዞ ያደረገላቸውንና ለአሕዛብ የተደረገላቸውን ሁሉ የተናገሩት::

15.3. 6-12 የኢየሩሳሌም ጉባኤ


በዚህ ጉባኤ የቀረበው ጉዳይ በአይሁድ ምእመናንና በአሕዛብ ምእመናን መካከል የተፈጠረው ክርክር ነው፤ ክርክሩ
ከይሁዳ የወረዱ ወግ አጥባቂዎች የፈጠሩት ችግር እንደ ነበር ከላይ አይተናል፤ በዚህ መሠረት ጉዳዩን ያዩ ዘንድ
በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ቀሳውስት ትልቅ ጉባኤን አድርገዋል፤ በጉዳዩ በጉባኤው መካከል ትልቅ ክርክር እንደ
ተደረገ ተገልጿል፤ ነገር ግን ጴጥሮስ ለክርክሩና ለጉዳዩ መፍትሄ የሚሆን መልካም ሀሳብን አመነጨ፤ መፍትሄው
በአሕዛብ ላይ ሸክም እንዳይበዛ የሚያሳስብ ነው::

15.4. 13-21 የያዕቆብ ንግግር


ይህ ያዕቆብ የጌታ ወንድም እየተባለ የሚጠራ ሲሆን የጉባኤውም አፈ ጉባኤ ነበረ፤ ያዕቆብ ስለዚህ ክርክር ሲናገር
ሁለት አካላትን እንደ አብነት አቅርቧል:: ይኸውም፦

1. ጴጥሮስ ነው።
2. ነቢዩ አሞጽ ነው::

የጴጥሮስ ንግግር በአሕዛብ ላይ የተጫነው ቀንበር መነሣት እንዳለበት የሚያመላክት ነበረ፤ የነቢዩ አሞጽም ትንቢት
የቤተ እስራኤልን እንደገና መታነጽንና የአሕዛብን ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚያመላክት ነው (አሞ.9፥11)፤
ስለዚህ ያዕቆብ የጴጥሮስን ንግግርና የነቢዩ አሞጽን ትንቢት የአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር መመለስ መሆኑን ማስረጃ
አድርጎ በማቅረብ ለጉዳዩ መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን መፍትሄዎች ተናገረ፤ መፍትሄዎቹ፦

1. ከዝሙት መራቅ እንዳለባቸው


2. ከጣዖትና ከርኲሰት መራቅ እንዳለባቸው
3. ከታነቀ መራቅ እንዳለባቸው
4. ደም ከመብላት መራቅ እንዳለባቸው
5. ለራሳቸው የሚጠሉትን በሰው ላይ እንዳያደርጉ የሚያሳስቡ ናቸው::

15.5. 22-29 ወደ አሕዛብ የተላከ ደብዳቤ


እዚህ ላይ ያለው ሐሳብ የሚያስረዳው ሐዋርያት ጉባኤው በተስማማው መሠረት የቀረበውን መፍተሄ ለአንጾኪያዋ
ቤተክርስቲያን ጽፈው እንደ ሰደዱ ነው:: ውሳኔው ትክክል እንደ ነበረም ”እኛና መንፈስ ቅዱስ አንድ ሁነን በይነናል’’
በማለት አስረድተዋል።

15.6. 30-35 ይሁዳና ሲላስ ደብዳቤውን ለአንፆኪያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሰጡ


እነጳውሎስ ደብዳቤውን ወስደው ሰጥተዋል፤ በዚህ ወንድሞች ደስ እንዳላቸው ተገልጿል፤ በዚህ ምክንያትም በደስታ
ሦስቱም አካላት (ጳውሎስ፣ ሲላስና በርናባስ) በአንጾኪያ ብዙ ጊዜ ተቀምጠዋል፤ ይሁዳ ግን ወድያው ወደ ኢየሩሳሌም
ተመልሷል::

15.7. 36-41 የጳውሎስና የበርናባስ መለያየትና የ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ መጀመር


በመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉዞ ጳውሎስና በርናባስ አብረው እንደተጓዙና እንደሄዱ ግልጽ ነው፤ በ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ
ግን የመጀመርያው አንድነት አልተደገመም:: በርናባስ የአጎቱ ልጅ ማርቆስን ይዞ ወደ ትውልድ አገሩ ቆጵሮስ ሲሄድ
ጳውሎስ ደግሞ ሲላስን ይዞ ወደ ትውልድ አገሩ ቂልቂያና ጠርሴስ ሄዷል፤ ለመለያየታቸው ምክንያት የሆነው የማርቆስ
በመጀመርያ ሐዋርያዊ ጉዞ እነርሱን ትቶ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ ነው፤ ከዚህ የተነሣ የየራሳቸውን ቦታ በመምረጥ
ለማስተማር ሂደዋል::

ምዕራፍ 16

16.1 ተልእኮውና አስተምሮው


2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ የሚጀምረው በምዕራፍ 15፥40 ላይ ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ በምዕራፍ 18፥18 ላይ ነው፤
ስለዚህ አሁንም ለመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉዞ እንደተደረገው ያለ አገላለጽ ስለሚደረግ (አጠር ባለ አገላለጥ
ስለሚገለጥ) ጠቅላላ ምንባቡን በሚገባ ማንበብ ይጠይቃል:: አገላለጹም እንደሚከተለው በዋና ዋና ሐሳቦች ይሆናል፤
ይኸውም

1. 1–3 የጢሞቴዎስ ከጳውሎስና ሲላስ ጋር መቀላቀል፣


2. 4–8 በኢየሩሳሌም የወጣው ሥርዓት መጠናከሩና የእነጳውሎስ ወደ ጢሮአዳ መውረድ
3. 9–12 ለጳውሎስ የታየው ራእይና የእነጳውሎስ ፊልጵስዩስ መድረስ
4. 13–15 የልድያ ማመንና የእነጳውሎስ በልድያ ቤት ማደር
5. 16–18 የአንዲት ልጃ ገረድ ከርኲስ መንፈስ መላቀቅ
6. 19–21 ትርፍ የቀረባቸው ጌቶች እነጳውሎስን መክሰሳቸው
7. 22–24 የእነጳውሎስ መደብደብና መታሠር
8. 25–34 የእሥር ቤት ጠባቂ ማመንና የእነጳውሎስ በእሥር ቤት መጸለይ
9. 35–40 የእነጳውሎስ ከእሥር ቤት መውጣትና በሮማ ዳኞች ላይ ጫና ስለ ማሳደራቸው ይገኙበታል::

ምዕራፍ 17

17.1 ተልእኮውና አስተምህሮው


1. 1–4 በአንፊጶል፣ በአጶሎንያና በተሰሎንቄ ያስተማሩት ትምህርት
2. 5–9 በእነጳውሎስ ላይ የተደረገ ተቃውሞና የኢያሶንና የወንድሞች መደብደብ
3. 10–12 በቤርያ ያስተማሩት ትምህርትና የቤርያ ሰዎች ልበ ሰፊነት
4. 13–15 የተሰሎንቄ አይሁድ እስከ ቤርያ ያደረጉት ተቃውሞና የጳውሎስ ወደአቴና መሄድ
5. 16–17 የጳውሎስ በአቴና ሰዎች ሥራ መበሳጨትና ከመሰል ጓደኞች ጋር መነጋገር
6. 18–21 አንዳንድ ፈላስፎች በአርዮስፋጎስ ጉባኤ በጳውሎስ ላይ ያነሡት ተቃውሞ
7. 22–31 ጳውሎስ ፈላስፎች ላነሡበት ተቃውሞ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነትና መጋቢነትን በመግለጽ የሰጠው
ሰፋ ያለ ትምህርት
8. 32–34 በአርዮስፋጎስ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ማመንና ትንሣኤ ሙታንን በማስተማሩ የተደረጉ ፌዝ ናቸው::

ምዕራፍ 18

18.1. 1-17 ተልእኮውና አስተምህሮው


1. 1-3 የጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ መሄድና ከአቂላና ጵርስቅላ ጋር መገናኘት
2. 4–6 የሲላስና የጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ ወደ ቆሮንቶስ መውረድና የጳውሎስ አይሁድን ማስጠንቀቅ
3. 7-8 የቀርስጶስ ከቤተሰቡ ጋር ማመንና የቆሮንቶስ ሰዎች ማመን
4. 9-11 ለጳውሎስ የታየው ራእይና የጳውሎስ በቆሮንቶስ 1 ዓመት ከ 6 ወር መኖር
5. 12–13 የአይሁድ ጳውሎስን ከጋይዮስ ዘንድ መክሰስ
6. 14–16 ጋልዮስ በጳውሎስ ላይ የተነሣውን ክስ ውድቅ ማድረጉ
7. 17 የሶስቴንስ መደብደብና የጳውሎስ ወደ አንጾኪያ መመለስ ናቸው::

18.2. 18-23 ጳውሎስ ከቆሮንቶስ ወደ ሦሪያ ፣ ኤፊሶን ፣ ቂሣርያና አንጾኪያ ደረሰ


የጳውሎስ ሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ (53–57 ዓ/ም) በኤፌሶን ይጀምራል:: ኤፌሶንን ሲለቅ የተስፋን ቃል ተናግሮ
ሂዷል፤ 3 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ከምዕራፍ 18፥23-ምዕራፍ 21፥17 ያለው ነው፤ በዚህ ሐዋርያዊ ጉዞም ሐዋርያዊ
ተልእኮን አከናውኗል።

18.3. 24-28 ስለ አጵሎስ ማንነት


ይህ ገጸ ምንባብ አጵሎስ በአዲሱ የክርስትና እምነት ከማመኑ በፊት ምን ዓይነት ሰው እንደነበረና በአዲሱ የክርስትና
እምነት ካመነ በኋላ ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ ያስረዳል::

ምዕራፍ 19

19.1. 1-7 ጳውሎስ በዮሐንስ የተጠመቁ ደቀ መዛሙርትን ማግኘቱ


ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሳለ እነዚህ ደቀ መዛሙርት በዮሐንስ ጥምቀት የተጠመቁ ነበሩ:: በዮሐንስ ጥምቀት መጠመቅ
ማለት ወደ እውነተኛው የክርስቶስ ጥምቀት የሚያደርስ ጥምቀት መጠመቅ ማለት ፤ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን በመጣ
ጊዜ ግን ስለ መንፈስ ቅዱስ መቀበል ሲጠይቃቸው ምንም የሚያውቁት እንደሌለ አስረድተውታል:: ስለዚህ
እውነታውን በመንገር በመሲህ እንዲያምኑና የመንፈስ ቅዱስ ባለቤት እንዲሆኑ አደረጋቸው::

19.2. 8-10 ጳውሎስ ለሦስት ወርና ሁለት ዓመት ያህል ያስተማረው ትምህርት
በዚህ የትምህርት ዘመን ሁለት ነገር ተከሥቷል፤ ይኸውም፦

1. ማመን ነው::
2. አለማመን ነው::

ጳውሎስም ከላይ የተባለው 2 ኛው ነገር በበረታ ጊዜ የራሱ የሆነ ጥበብን መርጧል፤ ጥበቡ ከተቃዋሚዎች ርቆ
ደቀመዛሙርትን መለየት ነው::

19.3. 11-17 ለጳውሎስ የተሰጠው የመፈወስ ሀብትና የአስቄዋ ልጆች ሐፍረት


ጳውሎስ በተሰጠው ሀብተ ፈውስ መሠረት አጋንንትን ሲያወጣ ሰባቱ የአስቄዋ ልጆች ጠንቋዮች ጳውሎስ ያደረገውን
ማድረግ ሲሞክሩ አልተሳካላቸውም፤ ጠንቋዮቹ ከዚህ በፊት የማታለል ሥራን ሲሠሩ የነበሩ ናቸው፤ ጳውሎስ ይህን
ሥራ ሲሠራ ደግሞ በበለጠ የምታት ሥራቸውን ሊሠሩ ሲሞክሩ በክርስቶስ ስም ውጣ ያሉት ጋኔን በበላያቸው ላይ
ተነሥቷል፤ ይህም ድርጊት በመላው ኤፌሶንና በእስያ ሕዝብ የተሰማ ሁኗል::

19.4. 18-20 የጠንቋዮች ማመን


እነዚህ ጠንቋዮች በጳውሎስ ትምህርት ባመኑ ጊዜ ለጥንቆላ የሚጠቀሙባቸውን መጻሕፍት ማቃጠል ችለዋል::
ሌላው ሕዝብም የቀድሞ ሥራውን በመናገር ወደ እምነት ይገባ እንደነበር ተገልጿል::

19.5. 21-23 ጳውሎስ ሮሜን ለማየት ስለ ማሰቡ


ጳውሎስ ሮሜን ያይ ዘንድ የምን ጊዜም ፍላጎቱ ነው:: ይሁን እንጂ ሁኔታዎች አልተመቻቹለትም:: ቢሆንም እዚህ
ላይ ያለው ሐሳቡም ሮሜን በማየት ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ ነው፤ በዚህ ሐሳብ ምክንያት በወንድሞች መካከል ብዙ
ተቃውሞ ተከሥቷል::

19.6. 24-27 የድሜጥሮስ ስጋትና የአርጤምስ ክብር መቅረት


በዚህ ክፍል ያለው ገጸ ምንባብ በድሜጥሮስ የተነገረ ሲሆን በስጋት ላይ ያተኮረ ነው፤ ስጋቱም ከጳውሎስ ትምህርት
አንጻር ሲሆን ስጋቱ ደግሞ የጳውሎስን ትምህርት ለማስቆም፤ የራሱን ገቢና የአርጤምስን ክብር ለማስጠበቅ ያለመ
ነው::

19.7. 28-32 የኤፌሶን ሰዎች ጩኸት


እነዚህ ሰዎች ድሜጥሮስ ባመነጨው ስጋት ነው የጮሁት፤ በጭሆቱ ምን ያህል ግርግር እንደተፈጠረ ምንባቡን በማየት
መረዳት ይገባል::

19.8. 33-34 የእስክንድሮስ አለመሰማት


ይህ ሰው አይሁዳዊ ሲሆን ጳውሎስን እንዲሟገትላቸው መርጠውት ነበር፤ ነገር ግን አይሁዳዊ መሆኑን ሲያውቁ
እርሱን ገፍተው መጮኽ መርጠዋል፤ እዚህ ላይ ያለው ጭሆት ከላይኛው ክፍል ጭሆት የቀጠለ ሲሆን ለ 2 ሰዓታት
ያህል ወስዷል::

19.9. 35-40 የእነ ጳውሎስ ቅንነትና የከተማይቱ ጸሐፊ ኃላፊነት


እነ ጳውሎስ ባስተማሩት ትምህርት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው እንደ ነበር ግልጽ ነው፤ ነገር ግን የከተማው ጸሐፊ
ሁኔታውን በማየት የእነ ጳውሎስን ቅንነት ማረጋገጥ ችሏል፤ በመሆኑም የመጋቢያ ቀኑን ለሌላ ጊዜ በማራዘም
ጉባኤውን ፈትቷል::

ምዕራፍ 20

20.1. 1-6 የጳውሎስ ወደ ተለያዩ ቦታዎች መሄድ


ቦታዎቹ በክፍሉ የተጠቀሱ ሲሆን በእነዚህ ቦታዎች የአይሁድ ሴራ ስለበዛበት በክፍሉ የተጠቀሱ ደቀ መዛሙርት
በሽኝትና በመንፈሳዊ እርዳታ ተባብረውታል፤ በዚህ ከተጠቀሱት ቦታዎች መድረሻ የሆነቻቸው ጢሮአዳ ናት::

20.2. 7-12 የአውጤክስ ከደርብ መውደቅ


ይህ ልጅ የወደቀው በእንቅልፍ ምክንያት ሲሆን ለእንቅልፉ ደግሞ የጳውሎስ ረዥም ስብከት መነሻ ነው ፤
በመጨረሻም ጳውሎስ ልጁን አድኖታል::

20.3. 13-17 የጳውሎስ በተለያዩ ቦታዎች መዞር


እዚህ ላይ ሉቃስ እንደ ጻፈው ጳውሎስ ከከተማ ወደ ከተማ እየተዘዋወረ እንዳስተማረና መድረሻው ደግሞ ሚሊጢን
የተባለች ከተማ እንደሆነች ነው የተገለጸው:: ጉዞውም በችኮላ እንደነበር ታውቋል፤ ምክንያቱም በዓለ ሐምሳን
ለማክበር ኢየሩሳሌም ለመሄድ ይቸኩል ነበርና::
20.4. 18-32 ለኤፌሶን ሽማግሌዎች (ቀሳውስት) የተሰጠ አደራና ማስጠንቀቅያ
ክፍሉ በአርእስቱ እንደተገለጸ ለኤፌሶን ቀሳውስት ስለ አደራና ማስጠንቀቂያ የሚናገር ሲሆን ስለጳውሎስ የወደፊት
መከራም በሚገባ ይናገራል፤ አደራው ምእመናንን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው የሚያስረዳ ሲሆን ማስጠንቀቅያው
ደግሞ ራሳቸውን ይመለከታል::

20.5. 33-35 ከፍቅረ ንዋይ መራቅ እንደሚገባ


ጳውሎስ በሚዞረው ቦታ ሁሉ ከማንም ገንዘብ አይቀበልም ነበር፤ በዚህ መሠረት ሰው ራሱን ችሎ ሌላውን መርዳት
እንዳለበት ይመሰክራል፤ እዚህ ላይ ለኤፌሶን ቀሳውስት ያስተላለፈው መልእክትም ይህን ያስረዳል::

20.6. 36-38 በስንብት ምክንያት የተደረገ ልቅሶ


ጳውሎስ ለኤፌሶን ካህናት ከኤፌሶን መውጣቱን ሲነግራቸው በመሳም ፍቅራቸውን ገልጸውለታል፤ ፍቅሩ የተገለጠው
እየተላቀሱ ነበር፤ በተለይም ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩኝም ሲላቸው መንፈሳዊ ስሜታቸው እጅግ ተጎድቶ ነበር::

ምዕራፍ 21

21.1. 1-16 የጳውሎስ ከቦታ ቦታ መጓዝ


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ ሉቃስና ጳውሎስ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የነበሩ ደቀመዛሙርት ከወዴት ተነሥተው ወዴት
እንደደረሱ የሚናገር ሲሆን በጉዞው ውስጥ ዋና ዋና የሆኑ ሐሳቦች ደግሞ፦

1. የጢሮስ ነዋሪዎች ለእነጳውሎስ ያደረጉላቸው መልካም አሸኛኘት


2. አጋቦስ የተባለው ነቢይ ስለጳውሎስ መያዝና መታሠር የተናገረው ትንቢት
3. ደቀመዛሙርት ጳውሎስ ወደኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ያቀረቡት ልመና
4. ጳውሎስ ለማንኛው መከራ ያለው ዝግጁነት ያሳየው ቁርጠኝነት ናቸው::

21.2. 17-25 የጳውሎስ ኢየሩሳሌም መድረስ ፣ በሐዋርያት የተደረገለት አቀባበልና የታዘዘው ትእዛዝ
ከላይ ባለው ምንባብ እንደተገለጸው የተለያዩ ከተማዎችን ሲያቆራርጡ ተመልክተናል፤ በመጨረሻ ደግሞ መዳረሻ
የሆነቻቸው ኢየሩሳሌም ናት፤ ምክንያቱም በዓለ ሐምሳን ለማክበር ወደኢየሩሳሌም የሚያደርገው ጉዞ እጅግ አስፈላጊ
ነበር፤ በዚህ መሠረት ኢየሩሳሌም ሲደርሱ በሐዋርያቱ ዘንድ፦

1. መልካም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ በዚህ አቀባበል የኢየሩሳሌም ኤጵስቆጶስ ያዕቆብም ነበር::


2. በአንዳንድ ወንድሞች የሚታማበት ነገር ያስቀር ዘንድ 4 ወንድሞችን ይዞ መንጻት እንዳለበት ታዝዟል፤
የሚታማበት ነገር በቍ.21 ተገልጿል::

21.3. 26-27 ጳውሎስ በሐዋርያት የታዘዘውን አደረገ


እዚህ ላይ ያለው ምንባብ የሚያስረዳው ጳውሎስ የተባለውን ነገር እንደፈጸመ ነው::

21.4. 28-32 ጳውሎስ ተከሰሰ


እዚህ ላይ ያለውን ክስ ያቀረቡ ከእስያ የመጡ አይሁድ ናቸው፤ ክሱም፦

1. ሕዝብን አውኳል
2. ሕግን ሽሯል
3. ቤተ መቅደስን አርክሷል
4. ግሪካዊው ጢሮፊሞስን ወደ መቅደስ አግብቷል የሚል ሲሆን በአካሉ ላይም ብዙ ድብደባ አድርሰውበታል::

በዚህ ምክንያት ኢየሩሳሌም ፈጽማ እንደታወከች ወደ አገረገዥ ሲደርስ ገዡም ሁኔታውን ለማየት ችግሩ
በተፈጠረበት ቦታ ተገኝቷል::
21.5. 33-36 ጳውሎስ ወደ እሥር ቤት ተወሰደ
በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ የሚያስረዳው ጳውሎስ እሥረኛ ሁኖ ወደ እሥር ቤት እንደተወሰደ ነው፤ በዚህ ጊዜም
ትልቅ የሕዝብ ጫጫታና ውካታ እንደነበር ተገልጿል::

21.6. 37-40 ጳውሎስ ስለ ራሱ ተከላከለ


ጳውሎስ እየተደረገበት ያለውን ክስ በማየት ላይ ነው፤ ክሱ ቃሉን ከመናገር የማይከለክልበት መሆኑን በሚረዳበት ጊዜ
ግን ሻለቃውን በመጠየቅ ስለመብቱና የተከሰሰበት ጉዳይ መናገር ፈልጓል፤ በዚህ መሠረት ከሻለቃው የመናገር ፈቃድን
ሲያገኝ ስለአጠቃላይ ሁኔታ መናገር ጀምሯል፤ በመጀመርያ ግን በሻለቃው ዘንድ አራት ሺ ሰዎችን አሸፍቶ ወደ ግብጽ
በረሀ ባወጣው ሰው ተመስሏል::

ምዕራፍ 22

22.1. 1-23 ጳውሎስ ለሻለቃውና ለሕዝቡ ሰፊ ንግግር አደረገ


በዚህ ክፍል ለከሳሾቹና ለሻለቃው የተናገረው በምዕራፍ 9፥1-28 ያለው ታሪክን ነው፤ ጳውሎስ ይህን ታሪክ መናገሩ
ምን ዓይነት ሰው እንደሆነና ሥራው ምን ዓይነት ሥራ እንደሆነ ለማስረዳት ስለፈለገ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ
ንግግሩን ከመቀበል ይልቅ በታላቅ ጭኸት እየጮኹ ክሳቸውን ቀጥለዋል::

22.2. 24-26 ጳውሎስ ለተወሰነበት ውሳኔ ጥያቄ ማቅረቡ


እርምጃው በሕዝቡ ብቻ ሳይሆን በሻለቃውም ተጀምሮበታል፤ እርምጃው እየተወሰደበት ያለው በእሥር ቤት ውስጥ
ነው፤ እርምጃው ግን ከምክንያት የተነሣ አልነበረም፤ እርምጃው እግሩን በመጎተትና በአካላቱ ላይ በተደረገ ግርፋት
የሚገለጽ ነበር፤ በመሆኑም እየተወሰደበት ያለው እርምጃ ምክንያቱ ከምን የተነሣ እንደሆነ ለማወቅ ሲል ጥያቄ
አቅርቧል፤ ምክንያቱም ምንም ምክንያት ሳይገኝ በሮሜ ዜጋ ላይ እርምጃን መውሰድ እንደማይቻል በሀገሪቱ ሥርዓት
ነበርና::

22.3. 27-30 ሻለቃው የጳውሎስን ዜግነት መጠየቁና ጳውሎስን መፍታቱ


ሻለቃው የጳውሎስ ዜግነት የሮሜ ዜግነት መሆኑን ጳውሎስን በጠየቀበት ሰዓት አረጋግጧል፤ እርምጃው ራሱን
የሚያስጠይቅ መሆኑን ሲያውቅ ግን ጉዳዩን በሰፊው ለማየት ከእሥራቱ ፈትቶ በፊታቸው አቁሞታል::

ምዕራፍ 23

23.1. 1-5 ሊቀ ካህናት ሐናንያ ጳውሎስ በጥፊ ይመታ ዘንድ ትእዛዝ አስተላለፈ
ጳውሎስ እሥር ሁኖ ከሕዝብና ከሐላፊዎች ፊት ቢቀርብም በሁሉም ፊት እውነት መናገሩን ቀጥሏል፤ እርሱ
በማንኛውም ነገር የሚከሰስበት ምክንያት አልነበረበትም፤ ይህን መሠረት በማድረግ በሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ፊት
እስከዚች ቀን ድረስ በበጎ ሕሊና እግዚአብሔርን እያገለገለ እንዳለ ሲናገር ሐናንያ አፉን ይመቱት ዘንድ አዘዘ፤ ይህ ሊቀ
ካህናት ከአይሁድ ወገን ነው፤ ጳውሎስ ግን ሁኔታውን በማየት ሊቀ ካህናቱን ሰደበ፤ ለስድቡ መሠረት ያደረገው
የሐናንያ እውነት አለመፍረድን ነው፤ የሐናንያ ደጋፊዎች ስለ ስድቡ ጳውሎስን የተቃወሙ ሲሆን ለተሳደበው ስድብ
ፈሊጣዊ ንግግርን ተጠቅሟል::

23.2. 6-10 በጳውሎስ ንግግር ምክንያት በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል መከፋፈል ተፈጠረ
ስለ ትንሣኤ ሙታን ሲያስተምር የተለያየ ተቃውሞ ይደርስበት ነበር፤ እንደአጋጣሚ ፈሪሳውያንና ሱዱቃውያን
በአንድነት ሳሉ ለትምህርቱ ድጋፍ የሚሆንለትን ነገር አስቧል፤ ይህም ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያንን እርስ በእርስ
የሚለያይ ትምህርት መስጠት ነው፤ በዚህ መሠረት ለዓላማው ሲል ፈሪሳዊነቱን ተናግሯል፤ በዚህ ጊዜ ነበር በሁለቱም
ቡድኖች መለያየት የተፈጠረው፤ ለመለያየት ምክንያት የሆናቸው በቍ.8 ተገልጿል::
23.3. 11.ለጳውሎስ ጌታ ተገለጠለት
በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ የሚያስረዳው ጌታ በራዕይ ጳውሎስን እንዳደፋፈረ ነው ::

23.4. 12-15 አይሁዳውያን ጳውሎስን እስኪገድሉ ድረስ እህልና ውሀን እንደማይቀምሱ ተማማሉ
በዚህ ክፍል እንደተገለጠው ጳውሎስን ሳይገድሉ መብላትና መጠጣት እንደማይችሉ ወስነዋል፤ ይህ ውሳኔ
በሐላፊዎቻቸው በኩል አድርጎ ከሻለቃው ዘንድ መድረስ እንዳለበት ተማክረዋል፤ ውሳኔው ጳውሎስን ከአደባባይ
ከመድረሱ በፊት በመንገድ እንዲሞት የሚያደርግ ነው::

23.5. 16-22 ጳውሎስ በእኅቱ ልጅ አማካኝነት ከተመከረበት ምክር አመለጠ

ልጁ አጎቱ ጳውሎስን እንዴት እንደታደገ ምንባቡ የሚያስረዳና ግልጽ ስለሆነ ምንባቡን ብቻ ማየት በቂ ይሆናል::

23.6. 23-24 ጳውሎስ እሥረኛ ሆኖ ወደ ቂሣርያ ወረደ


የጳውሎስ ጉዳይ እስከ አሁን ድረስ ሉስዮስ በተባለ ዳኛ ሲታይ መጥቷል፤ ከአሁን በኋላ ግን በሌሎች ዳኞች የሚታይ
ይሆናል፤ በዚህ መሠረት ሉስዮስ ጳውሎስን በዚህ ክፍል ከተጠቀሱ ሰዎች ጋር ወደ ቂሣርያ ሰደደው ፤ በጊዜው
በቂሣርያ ያለው ፊልክስ ነው::

23.7. 25-30 ስለ ጳውሎስ ጉዳይ ከሉስዮስ ወደ ፊልክስ የተላከ ደብዳቤ


በአርእስቱ እንደተገለጸው ደብዳቤው ስለ ጳውሎስ ማንነት ለከሳሾቹ ሐሰት ይናገራል::

23.8. 31-35 ጳውሎስ ከፊልክስ ቤተ መንግሥት ደረሰ


በሉስዮስ የታዘዙ ሰዎች ጳውሎስንና የተጻፈውን ደብዳቤ ከፊልክስ ቤተ መንግሥት አድርሰዋል፤ ፊል ክስም የጳውሎስ
ከሳሾች እስኪመጡ ድረስ ”የሄሮድስ ግቢ’’ በተባለው እሥር ቤት እንዲቆይ አድርጓል::

ምዕራፍ 24

24.1. 1-9 ጠርጠሉስ የተባለ ጠበቃ ጳውሎስን መክሰስ ጀመረ


ፊልክስ የጳውሎስን ጉዳይ ከሳሾች እስኪመጡ ድረስ እንዳዘገየው ከላይ ተገልጿል፤ ከሳሾቹ ሲመጡ ጉዳዩን ማዳመጥ
ጀምሯል፤ በዚህ መሠረት ጠርጠሉስ የተባለው የከሳሾች ጠበቃ ዳኛው ፊልክስን በሚገባ በማመስገን ጳውሎስን
ወደመክሰስ ተሸጋግሯል፤ ክሱ ከዚህ በፊት ከተከሰሰበት እምብዛም የተለየ አይደለም::

24.2. 10-21 ጳውሎስ በፊልክስ ፊት የተከሰሰበትን ተከላከለ


ጳውሎስ በዚህ ክፍል ለፊልክስ የተናገረው በምዕራፍ 21፥26–28 ያለውን ታሪክ ሲሆን

1. የሙታን ትንሣኤ እንዳለ እያስተማረ መሆኑን


2. ነውር የሌለበት ሕሊና ይኖረው ዘንድ እየተጋ መሆኑን
3. የሚያመልከው እነርሱ (ከሳሾቹ) የሚያመልኩት አምላክ መሆኑን ጨምሮ አሳውቋል::

24.3. 22-23 ፊልክስ የጳውሎስን ጉዳይ ሉስዮስ እስኪመጣ ድረስ እንዲዘገይ አደረገ
ፊልክስ የጳውሎስን ጉዳይ በሚገባ አውቋልና ሉስዮስ እስኪመጣ ድረስ መመርመር አልፈለገም፤ ምንም እንኳ
እውነታው ግልጽ ቢሆንለትም ዋናው ነገር በሉስዮስ ነዋሪነት እንዲታይ ፈልጓል፤ እስከዝያው ግን በእሥር ቤት መቆየት
እንዳለበት አዝዟል::

24.4. 24-25 ፊልክስና ሚስቱ ድሩሲላ የጳውሎስን አስተምህሮ ሲከታተሉ


እዚህ ላይ ፊልክስና ሚስቱ የጳውሎስን አስተምህሮ ተከታትለዋል፤ ይሁን እንጂ አስተምህሮው ስለጽድቅ፤ ራስን
ስለመግዛትና ስለሚመጣው ኲነኔ የሚመለከት በመሆኑ ፈርተዋል፤ ስለዚህ ይህን ላለመስማት ትምህርቱን እንዲያቆም
አደረገ::
24.5. 26-27 ፊልክስ ከጳውሎስን ገንዘብ ፈልጓል
ጉዳዩ ወደእርሱ ተመርቶ ሳለ ሉስዮስ እስኪመጣ ድረስ ይቆይ ማለቱ፣ ጠያቂ ዘመድ እንዳይከለከልበት ብሎ ማዘዙ፣
መቶ አለቃው እንዲያደላለት ማድረጉና በሌላ ቀን አስጠርሃለሁ ማለቱ ለገንዘብ ብሎ እንደነበር ጸሐፊው ሉቃስ
አሳውቋል፤ በዚህ ምክንያትም ጉዳዩ ለሁለት ዓመት ያህል ዘግይቷል፤ በመጨረሻው ፊስጦስ ተተክቶ እንደታሠረ
ትቶታል፤ ከአሁን በኋላ ጉዳዩ በፊስጦስ የሚታይ ይሆናል::

ምዕራፍ 25

25.1. 1-5 የጳውሎስ ጉዳይ በፊስጦስ መታየት ጀመረ


በጳውሎስ ላይ የተያዘው ጉዳይ በመቀጠል ላይ ነው፤ ፊልክስ የጳውሎስን ጉዳይ ለገንዘብ ሲል ውዝፍ አድርጎ
እንደተወው ከላይ ተገልጿል፤ በእርሱ ምትክ የገባው ፊስጦስ ስለነበር ጉዳዩ ወደፊስጦስ ተሸጋግሯል፤ የከሳሾቹ ዓመጽ
ምንም አልተለወጠም፤ በመሆኑም በፊስጦስም ፊት ያነን ዓመጽ ሲያራምዱ ታይተዋል፤ ቢሆንም ፊስጦስ ነገሮችን
በአስትዋይነት በማየት ጉዳዩ በሕግ መሠረት እንዲታይ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፤ ጉዳዩም የደረሰለት ወደኢየሩሳሌም
በወጣበት ጊዜ ነው::

25.2. 6-8 ፊስጦስ ተከሳሹ ጳውሎስንና ከሳሾቹን አገናኘ


ጉዳዩ የደረሰለት በኢየሩሳሌም ሳለ እንደነበር ከላይ ተመልክተናል፤ ከስምንት ወይም ከአሥር ከማይበልጥ ቀን
ከኢየሩሳሌም ወደ ቂሣርያ በመውረድ ከሳሾቹንና ተከሳሹ ጳውሎስን አገናኝቷል፤ በዚህ ጊዜ እነዚያም መርታት
በማይችሉበት የከሰሱት ሲሆን ጳውሎስም ስለጉዳዩ መልስ ሰጥቷል::

25.3. 9-12 ጳውሎስ ወደቄሣር ይግባኝ ማለቱና ፊስጦስ ለከሳሾች ማድላቱ


ፊስጦስ ምንም እንኳ ጉዳዩን በአስተዋይነት ቢይዘውም ለከሳሾች ማድላቱ ግን አልቀረም፤ በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ከዚህ
በፊት ሲናገረው የመጣውን ንግግር በመናገር ወደቄሣር ይግባኝ ጠይቋል፤ ይግባኙም ተቀባይነት እንዳገኘ በቍ.12
ተገልጿል::

25.4. 13-22 ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለአግሪጳና ለበርኒቄ ተናገረ


እዚህ ላይ ያለው አግሪጳ ዳግማዊ ሄሮድስ ሲሆን ታላቁ የዚህ አግሪጳ አባት ቀዳማዊ አግሪጳ በ 44 ዓ/ም ሙቷል፤
በርኒቄ ተብላ የተጠራችው ሴትም የዳግማዊ አግሪጳ እኅትና የታላቁ አግሪጳ ታላቅ ሴት ልጅ ናት፤ እነዚህ ሁለት
ወንድምና እኅት የደስታ ጊዜን ለማሳለፍ ወደቂሣርያ በሚወርዱበት ጊዜ ፊስጦስ የጳውሎስን አጠቃላይ ሁኔታ
ነገራቸው::

25.5. 23-27 ጳውሎስ ከአግሪጳ ፊት ስለ መቆሙ


በዚህ ክፍልም ጉዳዩን እያብራራ ያለው ፊስጦስ ነው፤ አግሪጳና በርኒቄ ደግሞ የጉዳዩ ሰሚዎች ናቸው፤ ፊስጦስ በዚህ
ክፍል የተናገረው በላይኛው ክፍል ከተናገረው ተመሳሳይነት አለው፤ በዚህም አነጋገሩ ጳውሎስን ጥፋተኛ ማለት
ከብዶበት እንደነበር ማወቅ ይቻላል፤ ጉዳዩ ከበላይ ሐላፊዎች መድረስ ስላለበት ግን ከጋልዮስ ጀምሮ ነገሮች ሁሉ
ወደላይ (ቄሣር) ሲባሉ ይታያሉ::

ምዕራፍ 26

26.1. 1-23 ጳውሎስ ከአግሪጳ ፊት ቆሞ የተናገረው ንግግር


በዚህ ክፍል ያለው ንግግሩም በምዕራፍ 9፥1–28 ና በምዕራፍ 22፥3–21 ከአለው ንግግሩ ጋር ተመሳሳይ ስለ ሆነ
በ 3 ቱ ክፍሎች ያለውን ንግግሩ በሚገባ ማንበብ ይገባል በማለት ማብራራቱ ትተነዋል::
26.2. 24-29 ጳውሎስ አብደሃል መባሉና የወደፊት ዓላማውን መግለጹ
ጳውሎስ እውነቱን ሲናገር በፊስጦስ እንደ እብድ ተቆጥሯል፤ ጳውሎስ ግን አሁን እንደተባለው የሚያብድ ሳይሆን
እውነትን የሚገልጽ ሰው ነበር፤ ለዚህ ተቃውሞና ስድብም መልሱን ያስቀመጠ ሲሆን በአግሪጳ ዘንድም እውነቱ
የታወቀለት እንደሆነ ገልጿል:: አግሪጳ ግን ስለእርሱ አስመልክቶ የተናገረው አልተዋጠለትም፤ ምንም እንኳ አይሁዳዊና
ነቢያትን የሚያምን ቢሆንም ለጳውሎስ ንግግር እውቅና ላለመስጠት ሲል በቍ.28 ያለውን ቃል ሊናገር ችሏል፤
የጳውሎስ ዓላማ ግን እርሱ ብቻ ሳይሆን ከእሥራቱ በቀር ሌላውም ሰው የእግዚአብሔር ወገን ይሆን ዘንድ ነው፤
በመሆኑም ይህን ብሎታል::

26.3. 30-32 የጳውሎስ ጉዳይ በአግሪጳና በበርኒቄ ዘንድ እንኳን ለሞት ለእሥራት የማያበቃ ነው ተባለ
በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ አጠር ባለመልኩ በአርእስቱ የተገለጸውን ሐሳብ ይዟል::

ምዕራፍ 27

27.1. 1-44 ጳውሎስና ጓደኞቹ ወደ ሮሜ መጓዛቸውና በጉዞው የገጠማቸው ችግር


የጳውሎስ ጉዳይ በተለያዩ የሮማ ገዥዎች ሲታይ እንደመጣ ግልጽ ነው፤ በዚህም ስንኳን ለሞት ለመታሠር የሚበቃ
ጉዳይ እንዳልሆነ ገዥዎቹ ራሳቸው ሲመሰክሩ ታይተዋል፤ ይሁን እንጂ ገዥዎቹ ቁርጥ የሆነ ፍርድ ባለመስጠታቸው
ምክንያት ጳውሎስ ይግባኙን ቀጥሎበታል:: አሁን ከጓደኞቹ ጋር እሥር ሁኖ ወደ ሮማ ጉዞ ጀምሯል፤ በጉዞው ስማቸው
የተጠቀሰና ያልተጠቀሰ ደቀመዛሙርት አሉ፤ የዚህን የታሪክ መጽሐፍ ጸሐፊው ሉቃስም እንደነበረ ጉዞውንና አጠቃላይ
ሁኔታውን በባለቤትነት ያነሣዋል፤ እንዲያውም እኛ የሚለው አነጋገር የጀመረው በምዕራፍ 16፥10 ላይ ነው፤ ጉዞው
ምንያህል አስቸጋሪና ከባድ እንደ ነበር ጠቅላላ ምዕራፉን በማንበብ ማወቅ ይገባል:: ጉዞውም በጠቅላላ በባሕር ላይ
እንደ ነበር በስፋት ተገልጿል፤ በመሆኑም በምዕራፉ ውስጥ ያለው ሐሳብ ተመሳሳይና በጉዞው ወቅት የተከሠተ በመሆኑ
አጠር ባለመልኩ ከላይ በተገለጸው አነጋገር ተጠቃልሏል፤ ምንባቡን ግን በሚገባ ማንበብ ይጠይቃል::

ምዕራፍ 28

28.1. 1-2 በመላጥያ የነበሩ አረማውያን ለጳውሎስና ለጓደኞቹ መልካም ሥራ አደረጉላቸው


እነጳውሎስ፣ የመርከቢቱ አገልጋዮችና እሥረኞችን የያዙ ወታደሮች ከብዙ ውጣ ውረድና ከባድ ጉዞ በኋላ ያለአንዳች
ጉዳት መላጥያ ከምትባል ደሴት በሰላም ደርሰዋል፤ በተለይም ይህን ጊዜ እጅግ በርዷቸው ስለነበር ከላይ በተጠቀሰችው
ደሴት ነዋሪዎች አሕዛብ እጅግ የሚያስገርም ቸርነት ተደርጎላቸዋል፤ ድርጊቱ እሳት አንድዶ በማሞቅና በሌላም ደግነት
የተገለጠ ነው::

28.2. 3-6 የጳውሎስ እጅ በእፉኝት መነደፍና ከአሕዛብ የደረሰበት ሐሜት


ጳውሎስ በነደደላቸው ጭራሮ ላይ ሌላ ጭራሮን ሲጨምር ሌላ ክሥተት ተፈጠረ፤ ይኸውም ከጭራሮው ውስጥ
የወጣች እፉኝት የጳውሎስን እጅ መንደፏ ነው፤ ይህ ድርጊት ደግሞ በተከሰሰበት ላይ ሌላ ሰበብ የሚፈጥር ነበረ፤
ያስተናገዷቸው አሕዛብም ያሉት ከተከሰሰበት ጋር የሚመሳሰል ነው (ቍ.4):: እንዲያውም ወድያው የሚሞት
መስሏቸው እንደነበር ሉቃስ ይገልጻል፤ አንዳች ጉዳት ሳይደርስበት ሲቀር ግን ”ይህስ አምላክ ነው’’ በማለት
ሐሳባቸውን በመለወጥ ተአምራቱን አድንቀዋል::

28.3. 7-10 ጳውሎስ የፑፕልዮስን አባትና ሌሎች በሽተኞችን ፈወሰ


ጳውሎስ የተለያዩ በሽተኞችን እንደ ፈወሰ ከዚህ በፊት አይተናል፤ እዚህም ላይ ይህን ድርጊት በአርእስቱ በተጠቀሱት
ላይ ያከናወነ ሲሆን በዚህም አማካኝነት በፑፕልዮስ ቤት 3 ወር እንደ ሰነበቱና እጅግ እንደተከበሩ ተገልጿል::
28.4. 11-16 ጳውሎስ ሮሜ ስለ መድረሱ
ጉዞው ምንያህል አስቸጋሪና ከባድ እንደ ነበረ በየቦታው ተገልጿል:: ከዚህ የተነሣም በየደረሱበት የተወሰኑ ቀናትን
ሲያሳልፉ ታይተዋል፤ በመላጥያ ደግሞ ለ 3 ወራት ያህል ተቀምጠዋል:: ከእነዚህ ወራት በኋላ ግን የተለያዩ ቦታዎችን
በማቆራረጥ ሮሜ ደርሰዋል፤ በዚህ ጊዜ ሮሜ በሚኖሩ ክርስቲያን ወንድሞች በተደረገላቸው አቀባበል ተጽናንቷል::

28.5. 17-20 ጳውሎስ ስለጉዳዩ በሮሜ ለሚኖሩ ለአይሁድ ታላላቆች ተናገረ


በሮም የሕግ ምሁራን የሆኑ ታላላቅ የአይሁድ ወገኖች ነበሩ፤ እነዚህ፦ራሱ ጉዳዩን ከመናገሩ በፊት እርሱ ስለ ተከሰሰበት
ነገር የሚያውቁት ነገር አልነበረም፤ በምን ምክንያት ወደ ሮሜ እንደመጣ ሲነግራቸው ግን ለጉዳዩ እንግዶች እንደሆኑ
ነው የተናገሩት:: ጉዳዩን የነገራቸው ራሱ ጳውሎስ ነው::

28.6. 23-31 ጳውሎስ በሮሜ አስተማረ


ወደ ሮሜ የሄደው እሥረኛ ሁኖ እንደ ነበር ሲገለጽ መጥቷል፤ ቢሆንም በሮሜ እምብዛም የከፋ ተቃውሞ
አልገጠመውም፤ ባንድ ወገን ጉዳዩ ከምን እንደ ደረሰም ለመረዳት አስቸጋሪ ሁኖ ተገኝቷል:: በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስ
በቍ.31 ባለው ምንባብ ያለቀ ሁኖ ሲገኝ በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ምንባቡን እስከ ቍ.34 በማድረስ (የግእዙ
መጽሐፍም እስከ ቍጥር 34 ይደርሳል)

1. በጉዳዩ እንዳሸነፈ
2. ከእሥር ቤት በሰላም ወጥቶ 2 ዓመት በውጭ እንዳስተማረ (በተከራየው ቤት)
3. የኔሮንን ዘመዶች እንዳጠመቀ
4. በመጨረሻም በኔሮን እንደ ተገደለ ተገልጿል::

26.7 የሐዋርያት ሥራ ማጠቃለያ


ይህን መጽሐፍ የጻፈ ወንጌላዊው ሉቃስ እንደ ሆነ በ 1፥1-12 በስፋት ተገልጿል፤ መጽሐፉ፦

1. ቤተ ክርስቲያን በበዓለ ሐምሳ ቀን እንዴት እንደ ተመሠረተችና እንዴት እንዳደገች፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ
መካከል በመጀመርያ ምን ዓይነት ሕይወት እንደ ነበረ፣ ከዝያም ምን ዓይነት ችግር እንደ ተከሠተና ለተለያየ
ስደት እንዴት እንደ ተዳረገች ይገልጻል::
2. ስለ የጳውሎስ ሕይወት ታሪክ (አሳዳጅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ከአመነ በኋላ እስከ ሮማ ቤተ መንግሥት
የአከናወነውን የወንጌል አገልግሎት) በስፋት ያትታል፤ ይህም በዋናነት በመጀመርያው፣ በሁለተኛውና
በሶስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው የተገለጸ ነው::
3. የሮማ ባለ ሥልጣናት በአዲሱ እምነት ላይ የግድያና የማሳደድ ዘመቻን በሰፊው ያካሂዱ እንደ ነበር ይናገራል::

ውድ ተማሪ ሆይ ከዚህ በታች ከሐዋርያት ሥራ የተውጣጡ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውልሃል፤ ስለዚህ የሐዋ.ሥራን
በማንበብ እንደ ቀረቡልህ ዓይነት መልስ::

መልመጃ አንድ: ምረጥ

1. እንደ ጴጥሮስ አነጋገር ሰዎች ይድኑበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠ የድኅነት ስም?
ሀ/የጻድቃን ለ/የክርስቶስ ሐ/የድንግል ማርያም መ/የሁሉም
2. የማይታመነውን አምነው ያለቁ 400 ሰዎች የማን ተከታዮች ነበሩ?
ሀ/የገሊላው ይሁዳ ለ/የግብጹ ቴዎዳስ ሐ/የሊቀ ካህናት ሐናንያ መ/የሲሞን
3. ለሐናንያና ለሚስቱ ሰጲራ ሞት ምክንያት የሆነው ምንድነው?
ሀ/ከሽያጭ ከፍሎ ማስቀረት ለ/ውሸት ሐ/የመሬቱ መሸጥ መ/ሁሉም መልስ ይሆናል
4. ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል ተርታ ያልተሰለፈው ዲያቆን?
ሀ/ኒቃሮና ለ/ጳርሜና ሐ/ፊልጶስ መ/መልስ አልተሰጠም
5. በተሰሎንቄ ከሚኖሩ ሰዎች በቤርያ የሚኖሩ ሰዎች ልበ ሰፊዎች የተባሉት በምን ምክንያት ነው?
ሀ/ጸጥ ብሎ በመስማት ለ/መጻሕፍትን መርምሮ በማረጋገጥ ሐ/ባለመቃወም መ/በሁሉም
መልመጃ ሁለት: እውነት ወይም ሐሰት::

1. እንደ አቴናውያን እይታ ”ለማይታወቅ አምላክ’’ ተብሎ የተጻፈው ጽሑፍ እግዚአብሔርን ያመለክታል::
2. በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ደስታ በኢየሩሳሌም ላለችው ቤተ ክርስቲያን በተሰማ ጊዜ ወደአንጾኪያ
የተላከው በርናባስ ነው::
3. ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ በመናገራቸው ምክንያት ከሰሚው ወገን ሁለት ዓይነት አስተያየት ተሰንዝሯል::
4. ለማእድ አገልግሎት ሰባት ሰዎች ይመረጡ ዘንድ ሐሳብ የቀረበው በሐዋርያት ሳይሆኑ በሕዝቡ ነበር
5. ለጴጥሮስ የታየው ራዕይ ስለየሚበላና የማይበላ በተመለከተ የሚናገር ነበር::

ክፍል ሁለት: የሮሜ መልእክት

2.1 መግቢያ
የዚህ መልእክት ጸሐፊ ጳውሎስ መሆኑ በ 1፥1 ተገልጾአል፤ የሮሜን መልእክት መጻፍ የፈለገበት ምክንያት በሮሜ
ሰዎች መካከል ስላለው የጠባይ መለዋወጥ፣ የእምነትና የምግባር መፋለስን ለማስተካከል ነው፤ ይች ከተማ የተለያዩ
አገሮች ሰዎች የሚኖሩባት በመሆኗ ምክንያት የተለያየ ምግባረ ብልሹነት የሚታይባት ከተማ ነበረች፤ በተለይም
በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት ለሕዝቡ መከፋፈል ትልቅ አስተዋጽዖ ነበረው፤ በዚህ ምክንያት ጳውሎስ
በአይሁዳዊና በአረማዊ መካከል ስላለው መከፋፈል አጉልቶ ይጽፋል (2፥1)::

2.2 መልእክቱ የተጻፈበት ቦታና መልእክት ወሳጅ


መልእክቱን የጻፈው በቆሮንቶስ አገር ሁኖ ሲሆን ለመጻፍ ምክንያት የሆነው ደግሞ ፌቨን የተባለች ደግ ሴት
የተናገረችው ሂደት ነው፤ ይህች ሴት የሮማ ዜጋ ስትሆን በትዳር ምክንያት በቆሮንቶስ ትኖር ነበር፤ በሮማውያን
መካከል ስላለው ልዩነት ሁልጊዜ ለጳውሎስ ትነግራለች፤ በተለይም በአይሁዳውያን ክርስቲያንና በአረማውያን መካከል
ያለውን ልዩነት በግልጽ ትነግረዋለች፤ ከዚህ በመነሣት መልእክቱን ጽፎ ሴቲቱ እንድትሰጣቸው አድርጓል፤ መልእክቱ
በአይሁዳዊና በአረማዊ መካከል የተፈጠረውን አለመግባት በሚገባ የሚዳኝ ሁኖ ቀርቧል።

2.3 መልእክቱ የተጻፈበት ጊዜና የተጻፈላቸው ሰዎች


የተጻፈበት ጊዜ በ 57 ዓ/ም እንደሆነ ታውቋል፤ የተጻፈላቸው ደግሞ በሮም ከተማ ለሚኖሩ ሰዎች ነው::

2.4 የተጻፈበት ዓላማ


1. ከዚህ በፊት ብቁ ሐዋርያዊ ትምህርትን ያላገኘች የሮም ከተማ ይህን እንድታገኝ ማድረግ ነው::
2. መልእክቱን ከሰደደ በኋላ በአካል ሄዶ ይጠይቃቸዋልና ከመሄዱ በፊት ሁኔታዎች ተመቻችተው እንዲጠብቁት
ማድረግ ነው::
3. በአሕዛብና በአይሁድ ላይ የእግዚአብሔር ቸርነት እንዴት እንደሚፈጸም ማሳወቅ ነው::

2.5 የመልእክቱ ልዩ ባሕርያት


1. ከጳውሎስ መልእክታት ሁሉ እጅግ የተቀናጀ የአጻጻፍ ሥርዓትን ይከተላል
2. ከመልእክትነት ይልቅ ዝርዝር ሐተታዎችን ያካተተ የትምህርተ መለኮት አጻጻፍ ባሕርይ ይታይበታል::
3. በክርስትና አስተምህሮ ላይ ያተኩራል::
4. ብሉይ ኪዳንን በስፋት ይጠቅሳል::
5. ለእስራኤል እጅግ የማሰብ ሁኔታ ይታይበታል::

2.6 በመልእክቱ ትኩረት የተሰጠባቸው ነገሮች


እነዚህም፦ ኃጢአት፣ ድኅነት፣ ጸጋ፣ እምነት፣ ጽድቅ፣ መጽደቅ፣ ቅድስና፣ ቤዛነት፣ ሞትና ትንሣኤ ናቸው:: ከእነዚህ ጎን
ለጎን የተጠቀሱና የተነሡ ደግሞ ክርስቶስ፣ አይሁድና አሕዛብ ናቸው::

ምዕራፍ 1

1.1. 1-7 ጳውሎስና የሮም አማኞች


ጳውሎስ የሮም አማኞች የክርስቶስ ባርያና እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢያት አፍ ለአናገረው የወንጌል

ተስፋ የተጠራ ሐዋርያ እንደ ሆነ ሊያውቁለት ይፈልጋል፤ ይህም የወንጌል ተስፋ በሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ልጅ
እንደ ሆነ በአስመሰከረውና በተገለጠው ክርስቶስ በኩል የተሰጠ እንደ ሆነ ያሳውቃቸዋል፤ ታድያ እነርሱም የክርቶስ
ይሆኑ ዘንድ በዚህ ለወንጌል መጠራት እነርሱም እንዳሉበት በመግለጽ ”ከእግዚአብሔርና ከክርስቶስ ጸጋና ሰላም
ይሁንላችሁ’’ በማለት እርሱና እነርሱ የአንድ እግዚአብሔር መሆናቸውን ያሳውቃል::

1.2. 8-12 ስለ ሮም አማኞች የጳውሎስ ጸሎትና ምስጋና


ጳውሎስ እነዚህን አማኞች ለማብቃትና ለመሳብ ሲል እውነታ ያላቸውና የተለያዩ ቃላትን ይጠቀማል፤ በመሆኑም
ጸሎቱ እግዚአብሔር ወደ እነርሱ በሚመጣበት ጊዜ መንገዱን ያቀናለት ዘንድ ሲሆን ምስጋናው ደግሞ እምነታቸው
በመላው ዓለም በመሰማቱ ምክንያት እንደ ሆነ ገልጿል፤ የመጸለዩና የማመስገኑ ዓላማም በሁለቱ መካከል ባለችው
እምነት መጽናናት ይገኝ ዘንድ ነው::

1.3. 13-17 ጳውሎስ ወደ ሮም አማኞች ለመሄድ የሚተጋበት ምሥጢር


ጳውሎስ ወደ እነዚህ ምእመናን ለመሄድ ከማሰቡ በፊት ብዙ አሕዛብን በማስተማር መንፈሳዊ ፍሬን አግኝቶ ነበር፤
አሁንም ይህን ፍሬ በእነዚህ አማኞች ለመድገም በማሰቡ ማንኛውንም ሰው ለማስተማር ቆርጦ ተነሥቷል፤ ምንም
እንኳ ወደ ሮም ለመሄድ ሲያስብ ብዙ ጊዜ ቢከለከልም:: የሚያስተምራቸው ሰዎች ዓይነትና ደረጃ በቍ.14 የተገለጸ
ሲሆን እነዚህንና እነርሱን ለማስተማር እንደ ተዘጋጀ ይነግራቸዋል:: ይህም የሆነበት ምክንያት ለአይሁድም ሆነ
ለሚያምኑ አሕዛብ ወንጌልን ማስተማር የማያፍር በመሆኑና የእግዚአብሔር ኃይል በዚህ የሚገለጥ በመሆኑ እንደ ሆነ
ያሳውቃል::

1.4. 18-25 እውነትን በዓመፃ በሚለውጡ ሰዎች ላይ ከሰማይ ቁጣ ይመጣል


እዚህ ላይ ጳውሎስ በአርእስቱ በተገለጡ ሰዎች ላይ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንደሚታዘዝባቸው ይናገራል፤ በዓመፃ
የተለወጠው እውነት እግዚአብሔር በፍጥረቱ በኩል የተገለጠው መገለጥና የታወቀው መታወቅ ሲሆን ይህ ሂደት ግልጥ
የሆነላቸው ሰዎች እርሱን እንደ ጌትነቱና አምላክነቱ ከማመስገንና ከማክበር ይልቅ ፍጥረቱን በማምለክ ክብሩን፦

1. በሰው
2. በወፎች
3. በእንስሳትና በሚጠፋ ነገር በመለወጣቸው ምክንያት እንደ ሆነ ተናግሯል::

በዚህ ምክንያትም ጥበበኞች ነን ሲሉ ለድንቁርና እንደ ተዳረጉና እግዚአብሔርም ለርኵሰትና ለሥጋዊ ፍትወት አሳልፎ
ሰጣቸው ይላል፤ ርኵሰቱና ሥጋዊ ፍትወቱ በልዩ ልዩ ኃጢአት የሚገለጽ ሲሆን ለዚህ አሳልፎ የሰጣቸው እግዚአብሔር
ደግሞ ለዘለዓለሙ የተባረከ አምላክ እንደ ሆነ አሳውቋል::

1.5. 26-32 አስነዋሪው ምኞትና ተግባር


እዚህ ላይ ያለው አስነዋሪው ምኞትና ተግባር ተመሳሳይ ፆታ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር በሚያደርጉት ድርጊት መልክ
የተገለጸ ሲሆን ይህን ”አስነዋሪ’’ በማለት ገልጾታል፤ በዚህም ይህን በሚያደርጉ ላይ ብድራት አለባቸው ይላል፤
ጳውሎስ ሲናገር ይህን የሚያደርጉ ሰዎች ክፋት በዚህ ብቻ የሚያበቃ እንዳይደለ ካስረዳ በኋላ ስለሌላው ክፋታቸውም
ከ 29-31 ባለው ምንባብ ተናግሯል::

ምዕራፍ 2

2.1.1-6 እውነተኛው የእግዚአብሔር ፍርድ


እንደ ጳውሎስ አነጋገር ይህ እውነተኛ ፍርድ እግዚአብሔርን በማያውቁ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ፍርድ ነው፤ ጳውሎስ፦
አይሁድ አሕዛብን እንዴት እንደሚንቁና እንዴት እንደሚያቃልሉ ያውቃል፤ ይህን መልእክት መጻፍ ያስፈለገበት ዋና
ምክንያትም ይህን ተግባር ከመካከላቸው ያስወግድ ዘንድ ነው፤ ከዚህ በመነሣት አይሁድ በአሕዛብ ላይ የሚጸየፉትን
ራሳቸውም መልሰው የሚሠሩት በመሆናቸው ይህን በማድረጋቸው በመንቀፍና እውነተኛው የእግዚአብሔር ፍርድ
እንዴት እንደሚጠብቃቸው በመግለጽ ከንስሐ ይልቅ በልበ ደንዳናነት በመጽናታቸው ለጌታ መምጣት ቀን ቁጣን
እያካማቹ እንደ ሆነ ያሳውቃቸዋል::

2.2.7-12 ለመልካም ሰዎች የሚሰጥ ሕይወትና በክፉ ሰዎች ላይ የሚደረግ ቅጣት


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ ለመልካም ሰዎች ሕይወት እንደሚሰጣቸውና ለክፉ ሰዎች ቅጣት እንደሚደረግባቸው
የሚያስረዳ ሲሆን አይሁድም ሆነ አሕዛብ በሕይወቱም ሆነ በቅጣቱ ተካትተውበታል፤ ምክንያቱም ሁለቱም ወገኖች
በእግዚአብሔር ፊት አንድ ወገን ናቸው፤ እንዲህ ሲሆን ግን ለሕይወቱም ሆነ ለቅጣቱ በመጀመርያ ያሉት አይሁድ
እንደ ሆኑ ጳውሎስ ይጽፋል::

2.3.13-16 ሕግን በማድረግ እንጂ ሕግን በመስማት መጽደቅ አይቻልም


እዚህ ላይ አይሁድና አሕዛብ እኩል የሚቀጡበት ምክንያት በቍ.12 ከገለጸ በኋላ የአይሁድ ሕግን በመስማት መጽደቅ
ይቻላል የሚለውን ዝንባሌ ዋጋ ቢስ በማድረግ ሕግ ያላቸው አይሁድ ይቅርና ሕግ አልባ አሕዛብ ስንኳን እንደ ሕግ
ሰዎች እንደሚሠሩ ይናገራል፤ አሕዛብ በልባቸው ካለው ሕግ የተነሣ የሕግ ሰዎች የሚሆኑበት አጋጣሚ ይታያል::

2.4.17-24 አይሁድና ሕግ
በዚህ ምንባብ አይሁድና ሕግን በማነጻጸር አይሁድ የሕግ ሰዎች ነን በማለት በአሕዛብ ላይ የሚያሳዩትን አመለካከት
በመግለጽ ሕግን እንዴት እየሻሩ እንዳሉ ይነግራቸዋል፤ ንግግሩ በነቀፋ መልክ የቀረበ ሲሆን በእነርሱ ክፉ ሥራ
አማካኝነትም የእግዚአብሔር ስም እየተሰደበ እንደ ሆነ ተናግሯል (ኢሳ.52፥5 ሕዝ.36፥20)::

2.5.25-29 አይሁድና ግዝረት (ሕግ)


ጳውሎስ አይሁድ ለግዝረት ያላቸው ትኩረት ከማንም በላይ እንደ ሆነ ያውቃል፤ በዚህ አመለካከታቸውም ክርስቲያን
የሆኑ አሕዛብ እንዲገዘሩ ያስገድዱ ነበር፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሕጉ በግዝረት ይደገፋል ሳላሉ ነው፤ ይሁን እንጂ
በጳውሎስ አመለካከት ሕግ በግዝረት አይደገፍም፤ በመሆኑም ሕግን ቢጠብቁ ግዝረቱ ጠቃሚ እንደ ሆነ ካስረዳ በኋላ
አይሁዳዊነት የሚረጋገጠው ሕግን በመጠበቅ እንደ ሆነ ይናገራል፤ ሕግ አፍራሽ ከሆነ ግዙርም ሕግ አክባሪና ኢግዙር
አሕዛብ እንደሚበልጥ ጽፏል::

ምዕራፍ 3

3.1.1-4 የይሁድነት ብልጫና የግዝረት ጥቅም ምንድን ነው?


ጳውሎስ፦አይሁድ በይሁድነትና በግዝረት ላይ ያላቸው የጸና አቋምን መንቀፍና መመርመር ቀጥሎበታል፤ አይሁድ
በአይሁድነታቸውና በግዙርነታቸው እጅግ በጣም የሚመኩ ናቸው፤ ይህም አመለካከት ከትክክለኛው ሕግ እንዲወጡ
ምክንያት ሁኗል፤ ከዚህ በመነሣት አፍኣዊው አይሁዳነትና ግዝረት ብልጫውና ጥቅሙ ምንድን ነው? በማለት ነገሩን
በግርምት ይገልጸዋል፤ እንደ ጳውሎስ አመለካከት ከእነዚህ ሁለት ነገሮች መቅደም ያለበት በእግዚአብሔር ቃል ማመን
ሲሆን ኢአማኝ ሰው ቢኖርም የእርሱ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት እንደማያስቀረው ግልጽ አድርጓል::
3.2. 5-9 በጳውሎስ ዓመጽ የሚገለጥ የእግዚአብሔር ክብር ስለ መባሉ
እዚህ ላይ ጳውሎስ ሰዎች በእርሱ ላይ ከሚሰነዝሩት ሐሳብ በመነሣት ይናገራል፤ የሚሰነዝሩት ”መልካም እንዲሆንልን
ክፉ እንሥራ ይላል’’ ብለው ነው፤ ነገር ግን በእርሱ ስብከት የእግዚአብሔር ክብር እየላቀ በመሆኑ እንዴት እርሱን
(ጳውሎስን) ኃጢአተኛ ያደርገዋል?እንዲህ ከሆነማ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዴት ይፈርድ ይሆን? ይህን ሂደት
በአግራሞት በማየት ሰዎች በእርሱ ላይ የሚሰነዝሩት ነገር ምክንያታዊ እንዳልሆነ ይገልጻል፤ ምክንያቱም አይሁድና
አሕዛብን ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ ቀድሞ ከሷቸዋልና (ቍ.23)::

3.3.10-18 የጻድቅ መታጣት


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ የሚያስረዳው አይሁድና አሕዛብ (ሁሉም) በድለዋል ብሎ በቍ.9 ለተናገረበት ሂደት እንደ
ማስረጃ አድርጎ ይህን እንደ ተናገረ ነው::

3.4.19-26 ኦሪትና ነቢያት የመሰከሩለት የእግዚአብሔር ጽድቅ


ጳውሎስ ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ከሕግ በታች ላሉ እንደ ሆነ በመግለጽና
ይህም የሆነበት ምክንያት ሰው ሁሉ ሕግን በመሥራት የማይጸድቅ እንደ ሆነ ካስረዳ በኋላ ኦሪትና ነቢያት የመሰከሩለት
ጽድቅ እንደ ተገለጠ ያሳውቃል፤ ይህም ለሚያምን ሁሉ የሚሆንና ክርስቶስን በማመን የሚገኝ የእግዚአብሔር ጽድቅ
ሲሆን ክብር በጎደለባቸው ሁሉ ይሆናል፤ ምክንያቱም አይሁድም ሆኑ አሕዛብ በድለዋልና:: እንዲህ በመሆኑ በክርስቶስ
በኩል በተከናወነው ቤዛነት እንዲሁ በጸጋው እንደሚጸድቁ ይናገራል፤ ይህም ቤዛነት በእምነት የሚገኝና በደሙ የሆነ
ማስተሥሪያ አድርጎ እንዳቆመው ጽፏል፤ ይህን ያደረገበት ዓላማም፦

 የፊት ኃጢአት እንደ ቀረ ቸርነቱን ያሳይ ዘንድ ነው::


 በክርስቶስ የሚያምነውን እንደሚያጸድቅ በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው::

3.5.27-31 አይሁድ በየትኛው ሕግ መካሉ?


ጳውሎስ አይሁድም ሆነ አሕዛብ የሚጸድቁት በሕግ ሳይሆን በክርስቶስ ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው እንደሚጸድቁ
ተናግሯል፤ የነገሩ እውነታ እንዲህ ከሆነ አይሁድ በየትኛው ሕግ ይመካሉ? በሕግ እንዳይመኩም ሰው ያለ ሕግ በእምነት
መጽደቅ እንደሚችል ጳውሎስ በመናገር ላይ ነው፤ በሕግ መጽደቅ የሚቻል ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ
አምላክ ሊባል ነው፤ ስለዚህ ይህን ሂደት ለአይሁድ እንደ ጥያቄ በማቅረብ በሕግ ሳይሆን ግዙርንና ኢግዙርን በእምነት
የሚያጸድና የሁለቱም አምላክ አንድ እንደ ሆነ በአጽንኦት ያስተምራል::

ምዕራፍ 4

4.1.1-5 አብርሃም የጸደቀው በእምነት ነው


እዚህ ላይ ያለው ምንባብ የሚያስረዳው አብርሃም የጸደቀው በሕግ ሳይሆን በእምነት እንደ ነበር ይህን እንደ ማስረጃ
እንደ አቀረበላቸው ነው:: በአብርሃም ዘመን ሕግ አልተሠራም ነበር::

4.2.6-12 ግዝረትና ብፅዕና


በዚህ ምንባብ ደግሞ እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ስላልያዘባቸው ሰዎች ብፅዕና ከመዝሙረ ዳዊት በመጥቀስና
አብርሃም የከበረው መቼ እንደ ሆነ በመጠየቅ የአብርሃም ብፅዕና ከመገዘር በፊት እንደ ነበር በድጋሚ ያረጋግጣል፤
ግዝረት ለአብርሃም የተሰጠው ይጸድቅበት ዘንድ ሳይሆን የጽድቅ ምልክት ይሆነው ዘንድ ነበር፤ የዚህ ዓላማ ደግሞ
አብርሃም ሳይገዘሩ ለሚያምኑ ሰዎች አባት ይሆን ዘንድ ነው::

4.3.13-18 አብርሃምና ዘሩ ዓለምን ይወርሳሉ የተባለው በሕግ ሳይሆን በእምነት ነው


አብርሃም የብዙ አሕዛብ አባት እንደሚሆን፣ በሽምግልናው ጊዜ እንደሚወልድና ዘሩም ምድረ ርስትን እንደሚወርሱ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ተስፋ ተነግሯል፤ ታድያ ይህ ተስፋ መውረስ የሚችሉት ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በእምነት
እንደሚሆን ካስረዳ በኋላ ይህ በእምነት የተቆጠረው ጽድቅ ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን
ባስነሣው ለሚያምኑም ጭምር እንደ ሆነ ያረጋግጣል::
ምዕራፍ 5

5.1.1-5 ከእምነት ጽድቅ በኋላ ሰላምን ስለመያዝ


በምዕራፍ 4 ስለ እምነት አስፈላጊነት ከተናገረና ሰዎቹ በእምነት መጽደቅ እንዳለባቸው ከገፋፋ በኋላ ሰላምን እንያዝ
በማለት ይመክራል፤ በዚህም በእምነት ምክንያት አሁን ወደአሉበት ጸጋ መግባትን እንዳገኙና በእግዚአብሔር ክብር
ተስፋም እንደሚመኩ ተናግሯል::

5.2.6-11 ሰዎች የእግዚአብሔር ጠላቶች ሲሆኑ ክርስቶስ ስለ እነርሱ ስለ መሞቱ


እዚህ ያለው የጳውሎስ ሐሳብ በዋናነት በሚከተሉት ሐሳቦች ይጠቃለላል፤ ይኸውም፦

 ዘመኑ በደረሰ ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች እንደ ሞተ ነው::


 ሰዎች የእግዚአብሔር ጠላቶች ሲሆኑ ክርስቶስ ስለ ጠላቶቹ እንደ ሞተ ነው::
 በእርሱ ከተገኘው ጽድቅ ይልቅ በልጁ ሞት ከቁጣው ይበልጥ እንደሚንድን ነው::

5.3.12-16 የአዳም በደልና የክርስቶስ አዳኝነት ሲነጻጸር


እንደ ጳውሎስ አነጋገር ኃጢአት በአዳም በደል አማካኝነት ወደ ዓለም ገብታለች፤ ሞት ደግሞ በኃጢአት አማካኝነት
በሰው ሁሉ ላይ ደርሷል፤ በአንድ አዳም በደል ምክንያት ሞት በበደለውና ባልበደለው ላይ የደረሰበት ምክንያት ሁሉም
ሰው አዳማዊ ባሕርይ ያለው በመሆኑና ይመጣ ዘንድ ያለው አዳም የቀደመው አዳም ምሳሌ በመሆኑ እንደ ሆነ
አስታውቋል:: ይሁን እንጂ በሰው ልጆች ላይ የተደረገው የእግዚአብሔር ቸርነት እንደ አዳም በደል መጠን እንዳልሆነ
ገልጿል፤ ቸርነቱ በዝቶ ተደርጓል::

5.4.17-20 አዳምና ክርስቶስ በሞትና በሕይወት


እዚህ ላይ ብዙ ሰዎች በአዳም በደልና አለመታዘዝ አማካኝነት ኃጢአተኞች እንደሆኑ እንዲሁ በክርስቶስ መታዘዝ
አማካኝነት ብዙ ሰዎች ጻድቃን እንደ ሆኑ ይናገራል::

ምዕራፍ 6

6.1. 1-7 ከክርስቶስ ጋር መሞትና መነሣት


በምዕራፍ 5፥21 ላይ ጸጋ ከመጠን በላይ እንደበዛ ተናግሮ ነበር፤ ይህም ጸጋው ለሰዎች በዝቶ በመሰጠቱ ምክንያት
ነው፤ በመሆኑም ሰዎቹ ጸጋው በዝቷልና በኃጢአት እንኑር እንዳይሉ ይህን እሳቤ ቀድሞ በማየት ጸጋው ስለ በዛ
በኃጢአት እንኑርን? በማለት ሁኔታውን ይናገራል፤ ይሁን እንጂ ነገሩ እንዲህ አይደለም፤ ከዚህ ፈንታ አማኞች
ከክርስቶስ ጋር በሞት አንድ ይሆኑ ዘንድ በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር እንደ ተቀበሩ ያሳውቃል:: ከክርስቶስ ጋር የመሞትና
የመነሣት መመዘኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር መተባበር እንደ ሆነ አድርጎ ተናግሯል::

6.2. 8-14 ከክርስቶስ ጋር መሆን


እዚህ ላይ ደግሞ ከክርስቶስ ጋር የሚሞቱ ከሆነ ከእርሱ ጋር እንደሚኖሩ በመግለጽ ክርስቶስ፦

1. አንድ ጊዜ እንደ ሞተና ዳግመኛ እንደማይሞት


2. በሕይወት ለእግዚአብሔር እየኖረ እንዳለ ካስረዳ በኋላ ሕዋሶቻቸውን የጽድቅ ጦር ዕቃ አድርገው
ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንዳለባቸው ይመክራል፤ ምክንያቱም ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደሉምና::

6.3. 15-23 አማኞች ሚታዘዙለት ባርያዎች እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው


በቍ.14 አማኞች ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች እንዳይደሉ አመልክቷል፤ በዚህ ምክንያት ኃጢአት እንሥራ
እንዳይሉ ለሚታዘዙለት ሁሉ ባርያዎች እንደሚሆኑ ማሳወቅ ፈልጓል፤ በመሆኑም ለሚታዘዙለት ሁሉ ባርያዎች
እንደሚሆኑ ካስጠነቀቀ በኋላ የድሮ ሕይወታቸውና የአሁኑ ሕይወታቸው እንዴት እንደ ነበረና እንዴት እንዳለ
አስረድቷል፤ እንደ ገለጻው የድሮ ሕይወታቸው ውጤት ሞት ሲሆን የአሁኑ ሕይወታቸው ውጤት የዘለዓለም ሕይወት
ነው::

ምዕራፍ 7

7.1.1-6 ከሕግ መፋታት


አይሁድ የቀድሞ ሕጋችንን አንተውም በማለት በእንቢተኝነት የጸኑ ሰዎች ነበሩ፤ በዚህም ከጳውሎስና ከመሰል ጓደኞቹ
ተጣልተዋል፤ ስለ ሆነም ጳውሎስ ኦሪትን እየተናገረ ያለው ኦሪትን ለሚያውቁ እንደ ሆነ በመግለጽ ከኦሪት ተፋትተው
ለክርስቶስ ይሆኑ ዘንድ በባልና በሚስት እየመሰለ ያስተምራል፤ ከሕግ መፋታት ያስፈለገበት ምክንያትንም ሲገልጽ
ሰውን ባለማዳኑ ምክንያት ኃጢአት በሰዎች ላይ ነግሦ ስለ ነበር እንደ ሆነ ጽፏል፤ በመሆኑም ኑሮአቸው በፊደል
(በሕግ) ኑሮ ሳይሆን በመንፈስ (በእምነት) ኑሮ መሆን እንዳለበት በአጽንኦት ያሳውቃል::

7.2.7-13 ሕግና ኃጢአት


ጳውሎስ በኦሪት ላይ ድክመት እንዳለ ቢናገርም ድክመቱን የሚደመድመው በኦሪት ላይ ሳይሆን በሰዎቹ ላይ እንደ ሆነ
ነው፤ በመሆኑም ኦሪትንና ኃጢአትን በማነጻጸር ኦሪት ድክመት አለባት በማለት በኦሪት ላይ ሰበብ እንዳይፈጥሩ ሕግ
ኃጢአት እንዳይደለ ያስገነዝባል፤ ይሁን እንጂ ሕግ፦

 ለኃጢአት መምጣት ምክንያት እንደ ሆነ


 ለኃጢአት መኖር የመታወቅያ መንገድ እንደ ሆነ
 ለኃጢአት ሕያውነትና ለጳውሎስ ምውትነት ምክንያት እንደ ሆነ በአጽንኦት ገልጿል::

7.3.14-21 ውስጣዊ ግጭት

በዚህ ክፍል ደግሞ ሕግ መንፈሳዊ ነው ካለ በኋላ በማንነቱ ውስጥ የፍላጎት ፍጭት እንደ ከተመ ይመስክራል፤ ፍጭቱ
በማንነቱ የተነሣ ውጊያ እንደ ሆነ ሲገልጽ በዚህ ውጊያ አሸናፊ የሚሆነው የሥጋ ፍላገቱ እንደሆነ ተናግሯል፤ ለዚህም
እንደ ምክንያት ያቀረበው የሚወደውን ሳይሆን የማይወደውን የማድረጉ ሂደት እንደ ሆነ ነው፤ ይሁን እንጂ እርሱ ጥቁ
ሰው ሲሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በተደረገው ቤዛነት ነፃ እንደ ወጣ ይናገራል::

ምዕራፍ 8

8.1.1-5 በክርስቶስ የተገኘው ነፃነት


ጳውሎስ በሕግ ውስጥ መኖር ከሕግ በታች መኖር እንደ ሆነ አድርጎ ማሳየት የምን ጊዜም የሮም መልእክት ንግግሩ
ነው፤ ይህም ሰው ሕግን ካለመፈጸሙ የተነሣና ሕጉ ኃጢአትን ካለማራቁ የተነሣ የሕግ ባርያ ሁኗል፤ በክርስቶስ ኢየሱስ
ያሉትን ግን የሕይወት መንፈስ ሕግ ነጻ እንዳወጣቸው ይመሰክራል፤ ”የሕይወት መንፈስ ሕግ’’ የተባለው በክርስቶስ
የተሰጠው ሕግ ነው:: ይህ ሕግ ኃጢአትን በክርስቶስ አማካኝነት የቀጣ ሲሆን እንዲህም የተደረገበት ምክንያት ሕግን
ያልፈጸሙ ሰዎች ሕግን እንደ ፈጸሙ ይቆጠርላቸው ዘንድ ነው::

8.2.6-11 ስለ ነፍስ ፈቃድና ስለ ሥጋ ፈቃድ ማሰብ


በዚህ ክፍል ስለ ሥጋና ስለ ነፍስ ማሰብ ውጤቱ የተለያየ እንደ ሆነ ይገልጻል ማለት ስለ ነፍስ ማሰብ ሕይወት እንደ ሆነ
ሲገልጽ ስለ ሥጋ ማሰብ ግን መጨረሻው ሞት እንደ ሆነና ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንደ ሆነ ተናግሯል፤
በመሆኑም ምእመናኑ የክርስቶስ መንፈስ ያለበት ሰው የክርስቶስ ወገን እንደ ሆነ የሌለው ግን ወገን እንዳልሆነ
እንዲያውቁለት በመፈለጉ የክርስቶስ መንፈስን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ይመክራል::

8.3.12-17 ከክርስቶስ ጋር መውረስ


በዚህ ምንባብ ደግሞ እንደ ሥጋ መኖር ሞት እንደ ሆነ ካስረገጠ በኋላ፦
1. የሥጋን አሠራር በመንፈስ ቢገድሉ በሕይወት እንደሚኖሩ
2. እግዚአብሔርን ለመጥራት የነጻነት መንፈስ እንጂ የባርነት መንፈስን እንዳልተቀበሉ
3. የእግዚአብሔር ልጆች ከሆኑና ከክርስቶስ ጋር መከራን ቢቀበሉ የእግዚአብሔር ወራሾች እንደሚሆኑ ጽፏል::

8.4.18-25 ለሰው የሚሰጠው ክብርና የሚቀበለው መከራ


ጳውሎስ የእነዚህን ሁለት ነገሮች ተመጣጣኝነት ያስቀምጣል፤ ስለ እነዚህ ሁለት ነገሮች መናገር የፈለገበት
ምክንያትም አይሁድ ”የምንከብረው በኦሪት ነው’’ ስለሚሉ ነበር:: ስለዚህ ሰዎች በዚህ ዓለም የሚቀበሉት ስቃይና
በላይኛው ዓለም የሚሰጣቸው ክብር ቢመዛዘን መከራው ከምንም አይቆጠርም በማለትና የጸጋውን ቸርነት የበላይ
በማድረግ የአይሁድን ሐሳብ ውድቅ ያደርጋል:: ምክንያቱ ደግሞ ፍጥረት ለከንቱ ስለ ተገዛ የእግዚአብሔር ልጆች
መገለጥን (ትንሣኤ ዘጉባኤን) በተስፋ ይጠባበቃል፤ በዚህም ምእመናኑ ብቻ ሳይሆን ራሱ ጳውሎስና መሰል ጓደኞቹ
እንዳሉበት መስክሯል::

8.5.26-30 የመንፈስ እርዳታ


በዚህ ክፍል ያለው ጽንሰ ሐሳብ ከታች ባሉት ሁለት ጽንሰ ሐሳቦች የተጠቀለለ ነው:: ይኸውም፦

 ሰዎች እንዴት እንደሚጸልዩ ስለማያውቁ መንፈስ ቅዱስ በማይነገር ሁኔታ እንደሚያግዛቸው ነው::
ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ በመሆኑ ልጁ በኲር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ
በእግዚአብሔር ስለ ተወሰኑ ነው::
 እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰናቸውን፣ የጠራቸውንና ያጸደቃቸውን እንዳከበራቸው ነው::

8.6.31-34 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነውን ሰው ማን ይቃወመዋል?


ጳውሎስ በሮም ምእመናን ላይ ምን ዓይነት ታቀውሞ እየወረደ እንዳለ ያውቃል፤ በዚህም ምእመናኑ እምነታቸውንና
አምልኮአቸውን ቸል ማለት አይተዉም፤ ከጠላት ጫና ውስጥ መውደቃቸውም የማይቀር ነው፤ ይህን ለማቃለልና
ብርታትን ለመስጠት በመጀመርያ ደረጃ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነውን ሰው ማንም መቃወም እንደማይችል
ያሳውቃል፤ ለሰው ልጆች ክርስቶስ ድኅነት ሁኖ ተሰጥቷል፤ ከክርስቶስ ደግሞ ለእግዚአብሔር ሌላ ዋና የለውም፤
በመሆኑም ይህ ስጦታ (ክርስቶስ) ለእነርሱ እንደ ተሰጠ በመግለጽ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማንም
እንደማይከሳቸው ተናግሯል::

በሁለተኛ ደረጃ የሚያጸድቅ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ሲገልጽ የሚኮንንስ ማን ነው? ብሎ በመጠየቅ ኮናኙ በቍ.34
እንደ ተጻፈው ክርስቶስ እንደ ሆነ ገልጿል:: እዚህ ላይ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ”ስለ እኛ የሚማልደው’’ በማለት
ተናግሯል:: እንዲህ ማለቱ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ሙቶ የዘለዓለም መሥዋዕት ሁኗልና ይህ አንድ ጊዜ በሞተው የተገኘው
መሥዋዕት ዘለዓለማዊ መሆኑን ለማስረዳት ነበር::

8.7.35-39 አማኞችን ከክርስቶስ ፍቅር የሚለያቸው ነገር የለም


ጳውሎስ ከክርስቶስ ፍቅር ማንም እንደማይለየው አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፤ እንደ ጳውሎስ ገለጻ በዚህ ምንባብ
ሰዎችን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩ የሚችሉ 17 ነገሮች ተጽፈዋል፤ አማኞችን ግን ከክርስቶስ ፍቅር መለየት አይችሉም፤
መለየት የማይችሉበትን ምክንያት ሲገልጽ ደግሞ በክርስቶስ ፍቅር ከአሸናፊዎች የሚበልጡ አሸናፊዎች በመሆናቸው
እንደ ሆነ ገልጿል::

ምዕራፍ 9

9.1.1-6 በእግዚአብሔር የተመረጡት እስራኤል


ጳውሎስ ለእስራኤል ከአለው ፍቅርና ተስፋ የራሱን ሕይወት ለእስራኤል ተስፋ እውን መሆን እስከ መክፈል
እንደሚደርስ ይመሰክራል። ለዚህ ተስፋ ቤዛ መሆን የሚያቀርበው ምክንያት ከ 4-5 ያሉትን ለእስራኤል የተደረገ
ድርጊቶች ነው። እስራኤላውያን እነዚህን 6 ነገሮች በእግዚአብሔር ተደርገውላቸዋል። ይህ መደረጉ በእግዚአብሔር
ዘንድ የተመረጡ ስለነበሩ ነው፤ ነገር ግን እነዚህን ተስፋዎች የሰጣቸውን አምላክ ትተው በሌላ አካል ማምለክ
ጀምረው ነበር። ከሁሉም በላይ ክርስቶስ በሥጋ የመጣው ከእነዚህ ነውና። ይህን ፍቅር (አሳቢነት) እነርሱ
ባያውቁለትም ለዚህ ፍቅሩ (አሳቢነቱ) መንፈስ ቅዱስን ምስክር አድርጓል።

9.2.7-13 በይስሐቅ በኩል ለአብርሃም የሚጠራው ዘር


እዚህ ላይ እስራኤላውያን በኃጢአት ምክንያት ከአብርሃም መንፈሳዊ ልጅነት በመውጣታቸው ምክንያት
የእግዚአብሔር ቃል እንዳልተሻረና በይስሐቅ በኩል ለአብርሃም ዘር እንደሚጠራለት ያሳውቃል፤ እግዚአብሔር ”በዘርህ
የምድር አሕዛብ ይባረካሉ’’ ብሎ ተስፋውን ነግሮታል፤ ይህ ዘር ክርስቶስ ነበር:: በተመሳሳይ ሁኔታ ለአብርሃምና ለሣራ
የተነገረው ተስፋ ለርብቃም እንደ ተነገረ ጽፏል፤ ከርብቃ በተስፋው መሠረት የሚወለደው ኤሳው ሳይሆን ያዕቆብ
እንደ ሆነም ግልጽ አድርጓል፤ የኤሳውና የያዕቆብ ማንነት ከመወለዳቸው በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነበር፤
ይህም የሆነበት ምክንያት ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ ነው
ይላል::

9.3.14-29 የእግዚአብሔር ምርጫ በሰዎች ላይ እንዴት እንደሚፈጸም የቀረበ ማስረጃ


ጳውሎስ፦ ሰዎች በያዕቆብና በኤሳው ላይ የተገረውን ትንቢት በማየት እግዚአብሔር ”የሚያዳላ አምላክ ነው’’
የሚለውን አመለካከት እንዳይዙ አስቧል:: ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ያዕቆብና ኤሳው ገና ሳይወለዱ ዕድል
ፈንታቸውን መወሰኑ ምርጫው እንዴት እንደሚፈጽም ስለሚያውቅ ነው:: ስለዚህ ይህን በመገንዘብ እግዚአብሔር
”የመረጠውን ያደርጋል’’ የሚለውን ሂደት ለማሳየት በፈርዖን ላይ ያደረገውን ድርጊትንና ያናገረውን እንደ ማስረጃ
አድርጎ ያቀርባል::

ቀጥሎም ሸክላ ሠሪ በሸክላው ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው በምሳሌ ካስረዳ በኋላ እግዚአብሔርም እንደዚህ
እንደሚያደርግ አሳውቋል:: ስለዚህ ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ሥልጣንና ምርጫ ላይ መመራመር እንደሌለበት
ለማስረዳት ከላይ የተባሉትን ምሳሌና ድርጊት ተናግሯል:: ምክንያቱም ሁሉም በክርስቶስ ፊት ይቆም ዘንድ አለውና::
ነገር ግን እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በምርጫ የሚሠራ ቢሆንም ጥሪውን ግን ለሁሉም አድርጓል:: ለዚህም እንደ
ማስረጃ የቀረበው ከ 25-29 ያለው የሆሴዕና የኢሳይያስ ትንቢት ነው::

9.4.30-33 የእስራኤል አለመጽደቅና የአሕዛብ መጽደቅ


እዚህ ላይ ስለ እስራኤል አለመጽደቅ ሲናገር እስራኤል መጽደቅ የተሳናቸው ሕግን የተከተሉት በእምነት ስላልነበረ
እንደ ሆነ ሲገልጽ አሕዛብ ግን የጸደቁት በእምነት እንደ ሆነ ያሳውቃል:: እስራኤል ”መክበር በሕግ ነው’’ የሚል
አመለካከትን የያዙ ሰዎች ናቸው::

ምዕራፍ 10

10.1. 1-4 እስራኤል ይድኑ ዘንድ ጳውሎስ ይፈልጋል


ጳውሎስ እስራኤልን ከመጠን በላይ ቢዘልፍና ቢያስጠነቅቅም ለእስራኤል የማሰብ ሁኔታ ይታይበታል:: ስለዚህ
ልመናውና ፍላጎቱ ሁሉ እስራኤል ይድኑ ዘንድ ነው:: ምንም እንኳ በራሳቸው ጽድቅ ሊጸድቁ ቢፈልጉም ይጸድቁ ዘንድ
ብርሃናቸው እርሱ ነውና:: እስራኤል በሕግ መጽደቅ የተሳናቸው ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ መሆኑን ባለ ማወቃቸው
ነው:: ይህን በማምራርያ መልክ አስቀምጧል::

10.2. 5-13 ድኅነት ለሁሉ ነው


እዚህ ላይ ሙሴ በኦሪት ምን ብሎ እንዳስተማረና የእምነት ሕግ ደግሞ ምን በማለት እያስተማረ እንዳለ ይናገራል::
ሙሴ፦

 በኦሪት ያለውን ሠርቶ የፈጸመ ይጸድቅበታል ብሏል::


 በአፉ የመሰከረና በልቡ ያመነበት ይጸድቅበታል ብሏል::
በዚህም በአይሁዳዊም ሆነ በአረማዊ ልዩነት የለም:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ለጠራው ሁሉ የሚሆን ባለጸጋ
በመሆኑ ነው:: ስለሆነም ስሙን የጠራ ሁሉ ይድናል:: ጳውሎስም የሚሰብከውና የሚያስተምረው ይህንን ነው::

10.3. 14-21 መስማት፣ ማመንና ስሙን መጥራት


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ የተናገረው በቍ. 13 ለተናገረው ሐሳብ ማብራርያ ነው:: የምንባቡ ጽንሰ ሐሳብ ደግሞ
ስለ መስማት፣ ማመንና መጥራት ሲሆን ማመንም በእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ነው::

ምዕራፍ 11

11.1. 1-5 የእስራኤል መውደቅ ጊዜአዊ መውደቅ ነው


ጳውሎስ ስለ እስራኤል ሕግን በእምነት ካለመፈጸም የተነሣ ከተስፋ መውጣት በተመለከተ ሲናገር ይህ ከተስፋ
መውጣት (መጣል) ጊዜያዊ ያደርገዋል፤ ምክንያቱም የእስራኤል መውደቅ የአሕዛብ ሙላት እስኪፈጸም ነውና::
ለመጨረሻው ተጥለው ላለመቅረታቸውምና ዳግመኛ ወደ ተስፋው ለመግባታቸውም እንደ ምክንያት ያቀረበው
የትሩፋንን (የቅሬታን) መኖር ነው፤ ለዚህም ኤልያስ እስራኤልን በእግዚአብሔር ፊት የከሰሰበትን ታሪክ አንሥቷል፤
ከዚህ በተጨማሪም በእግዚአሔር ፊት ያለው ራሱ ጳውሎስ የእነርሱ ወገን በመሆኑ የእርሱን በተስፋው ውስጥ መኖር
የእነርሱ በተስፋው መኖር አድርጎ አቅርቧል:: እነዚህ ቅሬታዎች (ትሩፋን) ቅሬታ (ትሩፋን) የሆኑት በጸጋው
አማካኝነት ነው፤ ሕግን በእምነት ያልያዙት ግን ከዚህ ቅሬታነት (ትሩፍነት) አልተካተቱም::

11.2. 6-12 ትሩፋን ያገኙት ጸጋና ኢትሩፋን ያላገኙት ጸጋ


እዚህ ላይ በማመን የተመረጡ በመመረጣቸው ምክንያት ጸጋን እንዳገኙ፣ በማመን ያልተመረጡ ግን ባለመመረጣቸው
ምክንያት ጸጋን እንዳላገኙ ይናገራል፤ያልተመረጡት ይህን ጸጋ ያለ ማግኘት ምክንያት በመዝ 69፥22-23 እንደ
ተጻፈው ልባቸው ስለ ደነዘዘ ነው:: ከ 11-12 ያለው ደግሞ በመጀመርያው ክፍል የሰፈረው ጽንስ ሐሳብን ይጋራል::

11.3. 13-16 ጳውሎስ በአይሁድና በአሕዛብ ላይ ያለውን አመለካከት ለአሕዛብ ስለ ማሳወቁ


ጳውሎስ የአይሁድና የአሕዛብ መምህር ነው፤ አሕዛብም ይህን ያውቁለታል፤ ታድያ የእነርሱ መምህር እንደ ሆነ ሁሉ
በአይሁድ ላይ ያለውን ዓላማ መንገር ፈልጓል፤ በዚህ መሠረት አይሁድ ቀንተው ይመለሱ ዘንድ በእነርሱ (በአሕዛብ)
ዘንድ ያለውን የወንጌል አገልግሎት በጥንቃቄ እየፈጸመ እንደ ሆነ ያሳውቃቸዋል፤ ምክንያቱም የአይሁድ መውደቅ
ለአሕዛብ መመለስ ሕይወት የሆነ፦ መመለሳቸው ምን ያህል ሕይወት ይሆን! ብሎ ስለአሰበ ነው::

11.4. 17-24 አሕዛብ በእስራኤል ላይ እንዳይኩራሩ በምሳሌ ሲያስረዳ


በዚህ ክፍል እስራኤል በቤት ወይራ፣ አሕዛብ በበረሃ ወይራ (እስራኤል በሥር፣ አሕዛብ በቅርንጫፍ) ተመስለው
ቀርበዋል፤ በምሳሌው ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት እስራኤል ዋናው የተስፋው ባለቤቶች፣ አሕዛብ የዚህ ተስፋ
በሁለተኛ ደረጃ ተካፋይ መሆናቸውን ነው፤ እንደ ምሳሌው ገለጻ እስራኤል ለጊዜው ከዋናነቱ (ከሥርነት) ተነሥተው
አሕዛብ በዋናነት ሥፍራው (በሥሩ) ገብተዋል፤ ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤል ባለማመናቸው ምክንያት ሲሆን
አሕዛብ ደግሞ በማመናቸው ምክንያት ነው፤ ስለዚህ ጳውሎስ፦

 አሕዛብ በእስራኤል ላይ እንዳይኩራሩ ያስጠነቅቃል::


 እንደገናም ራሳቸው አሕዛብ ከእምነት ፈቀቅ የሚሉ ከሆነ ከተስፋው እንደሚወጡ ያሳውቃል::
 እስራኤል ደግሞ ወደ ተስፋው የመመለስ እድል እንዳላቸው ይናገራል::

11.5. 25-36 መላው እስራኤል ይድናሉ

በዚህ ክፍል ደግሞ በእስራኤል ባንዳንዱ ላይ የልብ ድንዳኔ የደረሰው የአሕዛብ ሙላት (መመለስ) እስኪረጋገጥ ድረስ
እንጂ እስራኤል እንደሚድኑ ይናገራል፤ ለዚህ ደግሞ ማስረጃ አድርጎ ያቀረበው ”መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል
ከያዕቆብም ኃጢአትን ያስወግዳል’’ (ኢሳ 59፥20) የሚለውን የትንቢት ቃል ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ወገኖች
በአብርሃም በኩል ይህን የመዳን ተስፋ የሰሙ ነበሩና:: ይህም መሆኑ የተመረጡ ወገኖች ስለ ሆኑ ነበር፤ በመሆኑም
እግዚአብሔር እነርሱን በአብርሃም በኩል በመምረጡ አይጸጸትም፤ ምንም እንኳ በወንጌል በኩል የአሕዛብ ጠላቶች
ቢሆኑም በተስፋው በኩል የአሕዛብ ወንድሞች ናቸው:: ስለዚህ ነው ጳውሎስ አሕዛብን እናንተን ቀድሞ በአለመታዘዝ
ዘግቷችሁ እንደ ነበረ እንዲሁ ዛሬ እስራኤልን በአለመታዘዝ ዘግቶ ሁሉን በአንድ ጊዜ ይቅር ማለት ፈልጓል ያለው::
ለዚህ የርኅራኄና የአምላክነት ሥራና ጥበብ ደግሞ ከ 33-36 ባለው ምንባብ ምስጋናውን አቅርቧል::

ምዕራፍ 12

12.1. 1-8 ሰውነትን ቅዱስ መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብና እንደ ተሰጠህ ጸጋ ማገልገል
እዚህ ላይ የሮም ምእመናን እንዴት መኖርና ማገልገል እንዳለባቸው ይናገራል ማለት፦

1. ሰውነታቸውን ቅዱስና ሕያው መስዋዕት አድርገው ማቅረብ እንዳለባቸው


2. ይህን ዓለም መምሰል እንደሌለባቸው
3. ምንም እንኳ ምእመናኑ በቍጥር ብዙ ቢሆኑም በክርስቶስ ግን አንድ እንደ ሆኑ
4. በተሰጣቸው ልዩ ልዩ ጸጋ ማገልገል እንዳለባቸው ይመክራል::

12.2. 9-21 የእውነተኛ ክርስቲያን ምልክት


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ ሙሉ በሙሉ መንፈሳዊ ምክር ነው፤ ስለ ሆነም ምንባቡን በማየት ምክሩ እንዴት እንደ
ቀረበ ማስተዋል ይገባል::

ምዕራፍ 13

13.1. 1-7 ለባለ ሥልጣናት መገዛት ይገባል


ጳውሎስ በሮም ምእመናንና በሮም ባለ ሥልጣናት መካከል ምን ዓይነት ግንኙነት እንዳለ ያውቃል፤ ስለዚህ ምእመናኑ
ለባለ ሥልጣናት መገዛትን ቸል እንዳይሉ”ሰው ሁሉ ለባለ ሥልጣናት ይገዛ’’ በማለት ይመክራል፤ ይገዛ ለሚለው ምክር
ያቀረበው ምክንያት ደግሞ ሥልጣን ሁሉ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነው የሚል ነው፤ እዚህ ላይ ተገዙ ያለው
ለበጎውም ለክፉም ባለ ሥልጣን ነው፤ ባለ ሥልጣናቱ በጳውሎስ አነጋገር ይሠሩና ይቀጡ ዘንድ ተሹመዋል፤ በመሆኑም
ስለ ቁጣ ብቻ ሳይሆን ስለ ሕሊና መገዛት የግድ ስለ ሆነ ለሁሉም በተገቢው ያደርጉ ዘንድ በቍ.7 ግልጽ የሆነ ምክሩን
አስቀምጧል::

13.2. 8-10 ሌላውን ስለ መውደድ


በሮም ከተማ እየተፈጸመ ያለው የሥነ ምግባር ብልሹነት ለጳውሎስም ሆነ ለምእመናኑ ግልጽ ነው፤ ምእመናኑ በዚህ
እንዳይታለሉና በማንም ዕዳ እንዳይኖርባቸው ያስጠነቅቃል፤ ከዚህ ይልቅ በሌላው ላይ ፍቅርን መያዝ ይገባቸዋል፤
ምክንያቱም ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ነውና::

13.3. 11-14 በፍጥነት መንቃት ያስፈልጋል


በዚህ ምንባብ ያለ መዳን ጊዜ አልፎ የመዳን ጊዜ እንደ ደረሰ ለማስረዳት ያለ መዳን ጊዜን በሌሊት፣ የመዳን ጊዜን
በቀን መስሎ አቅርቧል፤ ያለ መዳን ጊዜው በሕግ፣ የመዳን ጊዜው በሕገ ወንጌል ተመስሏል፤ በመሆኑም በዝያ የጨለማ
ዘመን አሠራር መመላለስን ትተው በብርሃን ዘመን አሠራር ይመላለሱ ዘንድ በዚህ ምንባብ ያለውን ትምህርት
ተናግሯል::
ምዕራፍ 14

14.1. 1-12 በሌላው ወንድም ላይ አለመፍረድ


እዚህ ላይ የሰፈረው የጳውሎስ ትምህርት በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለውን አለመግባባት መሠረት ያደረገ ነው፤
አለመግባባቱ፦

 ይህ ርኩስ ነው አይበላም፤ ይህ ንጹሕ ነው ይበላል ከሚል የተነሣ ነው::


 ርኩስ የሚባል ነገር የለም ሁሉም ይበላል ከሚል የተነሣ ነው::
 የተለየ ቀን አለ፤ የተለየ ቀን የለም ከሚል የተነሣ ነው::

ታድያ ትምህርቱ ለዚህ ግጭት አስታራቂ ሐሳብ ሁኖ ቀርቧል፤ ምክንያቱም አይሁድም ሆኑ አሕዛብ በእግዚአብሔር
ፊት እኩል ስለ ሆኑ ነው፤ ስለ ሆነም አይሁድ (የማይበላው) በአሕዛብ ላይ (በማይበላው ላይ) ”ሁሉንም ይበላል‘
ብለው መፍረድ የለባቸውም፤ (የለበትም) ከዚህ ይልቅ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ሁሉን ነገር አጥብቀው መረዳት
ይገባቸዋል፤ ለምን ቢባል ሁለቱም ወገኖች እየኖሩት ያለው ለእግዚአብሔር ነውና:: ለዚህም እንደ ማስረጃ ያቀረበው
ከ 7-12 ያለው የራሱን (የእነጳውሎስን) አኗኗር ነው፤ ስለዚህ ሁሉም በክርስቶስ ፊት የሚቆሙበት ጊዜ ስላለ አንዱ
በሌላው ላይ መፍረድ የለበትም ይላል፤ እዚህ ላይ ያለው መብላትና አለመብላት ከመጾምና ካለ መጾም አንጻር ሳይሆን
”ይህ ርኩስ ነው አይበላም ይህ ንጹሕ ነው ይበላል፤ ሁሉንም መብላት ይገባል’’ ከሚለው አመለካከት አንጻር የተነገረ
ነው::

14.2. 13-23 ለሌላው እንቅፋት መሆን አይገባም


አሁንም ደግሞ ጳውሎስ በዚህ ክፍል የሚናገረው እምነት ደካሞች የሆኑትን የመናቅና የማቃለል ቃልን እየሰነዘሩ
ለሚገኙ ጠንካራ አማኞች ነው፤ ይህ ሂደት በእምነት ጠንካራ የሆኑት አማኞች በእምነት ያልጠነከሩትን
እንዲያበረታቱና እንዲሸከሙ ለማድረግ ነው፤ ነገር ግን ክርስቶስ የሞተው ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብም ጭምር
ነበር፤ በተለይም አይሁድ በአሕዛብ ላይ ጠባቸውን ያከረሩት ከሚበላውና ከማይበላው አንጻር የተነሣ ስለ ነበር ጳውሎስ
ይህን ድርጊት በጽኑ ይኰንነዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር መንግሥት መብልና መጠጥ ሳትሆን ፍቅርና ሰላም መሆኗን
ከአስረዳ በኋላ አንድም አይሁዳዊ በማንኛውም አሕዛባዊ ሰው ፊት እንቅፋት አይሁን ሲል ይመክራል::

ምዕራፍ 15

15.1. 1-6 ራስን ሳይሆን ሌላውን ደስ ማሰኘት ይገባል


በዚህ ምንባብ ደግሞ በጠንካራ እምነት ውስጥ ያሉ አማኞች በደካማ እምነት ውስጥ የሚኖሩት አማኞችን መሸከምና
ደስ ማሰኘት እንዳለባቸው ይመክራል፤ አይሁድ አሕዛብን የሚሸከሙበት መመዘኛ የላቻውም፤ አሕዛብ ግን አይሁድን
የመሸከም ዓቅም አላቸው፤ ይኸውም ሳይጠራጠሩ ፈጽሞ ማመናቸው ነው፤ ስለዚህ የክርስቶስ ሌላውን የመሸከምና
ደስ የማሰኘት አርዓያን ተመልክተው እርስ በርሳቸው በአንድ ልብ ሁነው እግዚአብሔርን በማመስገን መኖር
እንዳለባቸው ይናገራል::

15.2. 7-13 ክርስቶስ አይሁድንና አሕዛብን እንደ ተቀበለ እርስ በርሳቸው መቀባበል አለባቸው
በዚህ ክፍል ሁለቱን ቡድኖች (አይሁድና አሕዛብን) ይመክራል፤ ምክሩ እርስ በርሳቸው መፋቀር እንዳለባቸው
የሚያስረዳ ሲሆን ክርስቶስ አይሁድና አሕዛብን የተቀበለው ለአባቶች (ለእነ አብርሃም) የሰጠውን ተስፋ ያጸና ዘንድ
እንደ ሆነም አስረድቷል፤ስለዚህም (ስለ ተስፋው መፈጸም) ሲል የመገረዝ አገልጋይ ሁኗል ይላል:: አሕዛብም
የተስፋው ተካፋዮች ለመሆናቸው ማስረጃ የሚሆን ከ 10-12 ያለውን የትንቢት ቃል ከኢሳ 66፥10 ጠቅሶ
አስረድቷል::
15.3. 14-21 ይህን መልእክት የጻፈበትን ምክንያት ስለ መናገሩ
ጳውሎስ የሮም ምእመናንን በዓይን ለማየትና በአካል ለማስተማር እጅግ የላቀ ፍላጎት አለው፤ ይሁን እንጂ ይህ ፍላጎት
ስላልተሳካለት በአካል ሂዶ ያስተምረው ዘንድ የነበረውን ትምህርት በዚህ መልእክት እንዳሰፈረ ያሳውቃል፤ በተለይም
ይህን መልእክት የጻፈላቸው፦

1. የመገሠጽና የመምከር ችሎታ ስላላቸው ይህን በማየት ለማሳሰብ ሲል በድፍረት እንደ ጻፈላቸው
2. በዚህ መልእክት ውስጥ የሰፈረውን ትምህርት የጻፈላቸው በተሰጠው ጸጋ መሠረት እንደ ሆነ
3. ክርስቶስ ከአስተማረው በቀር ሌላ ትምህርትን በመልእክቱ ውስጥ እንዳላሰፈረ
4. ሌላው በመሠረተው መሠረት ላይ እንዳይሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ እንዳላስተማረ
5. የክርስቶስ ነገር በአልተሰማበት ስፍራ ብቻ እንደ አስተማረ ያውቁ ዘንድ እንደ ሆነ ተናግሯል::

15.4. 22-29 ጳውሎስ ሮሜን ለማየት እቅድ አለው


ጳውሎስ የሮም ምእመናን ሊያውቁለት የሚፈልገው እውነታ አለ፤ ይኸውም ሮሜን መጎብኘት የምን ጊዜም ፍላጎቱ
እንደ ሆነ ነው፤ ነገር ግን እንደ አሰበው መሠረት አልሆነለትም፤ ስለዚህ በአካይያና በመቄዶንያ ምእመናን
የተውጣጣውን እርዳታ በኢየሩሳሌም ለነበሩ ድሀ ምእመናን አድርሶ ወደ እነርሱ እንደሚመጣ ያለው እምነትን
ያሳውቃቸዋል::

15.5. 30-33 የሮም ምእመናን ስለ ጳውሎስ ጉዞና ስለ የሚሰጠው እርዳታ መጸለይ እንዲገባቸው ማሳሰቡ
እዚህ ላይ ለምእመናኑ ማሳወቅ የፈለገው እውነታ፦

 በይሁዳ መንደር ብዙ ጠላቶች አሉበትና የሚያደርገው መንፈሳዊ ጉዞ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ


 የወሰደው እርዳታም ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ እንዲጸልዩለት ነው::

ምዕራፍ 16

16.1. 1-24 መንፈሳዊና ግላዊ ሰላምታ


ጳውሎስ ለሮም ምእመናን እየጻፈ ያለውን ትምህርት በመጨረስ ላይ ነው፤ ስለ ሆነም የመጨረሻ ትምህርቱን
ያደረገው ሰላምታ ነው፤ በመልእክታቱ ውስጥ በመጀመርያና በመጨረሻ አከባቢ ሰላምታ ያስቀምጣል፤ በመሆኑም
በዚህ ክፍል በስም ላልተጠቀሱ፣ እንዲሁም በስም የተጠቀሱ ከ 25 በላይ ለሆኑ ደቀ መዛሙርት ሰላምታን አቅርቡልኝ
ሲል ከእርሱ ጋር ያሉ ደቀ መዛሙርትም እንደ እርሱ ሰላምታን እያቀረቡላቸው እንዳለ አስታውቋል፤ ከሰላምታው
ውጭ ያለ ትምህርትም ምእመናኑ እንዴት መኖር እንዳለባቸው ያሳስባል::

16.2.25-27 ምስጋና
በመጨረሻ ያቀረበው ምሥጋና ነው፤ ምሥጋናውም የቀረበው ተሠውሮ የነበረው የዘለዓለም ድኅነት ምሥጢር
ለአሕዛብ ከመገለጡ የተነሣ ነው::

16.3.የሮሜ መልእክት ማጠቃለያ

የሮም ከተማ በጥንት ዘመንና በጳውሎስ ዘመን የባሕል፣ የወግ፣ የሥልጣኔ፣ የንግድ፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችና
የምግባረ ብልሹነት ማእከል ነበረች፤ ጳውሎስ ይህን ፍጻሜ በሚገባ ያውቃል፤ ታድያ ይህ ሁሉ (በተለይም ምግባረ
ብልሹነቱ) በእርሷ ውስጥ ላለው አማኝና ኢአማኝ ሕብረተሰብ ፈተና ሁኖ ኑሯል፤ በሮም በዋናነት አይሁድና አሕዛብ
ይኖራሉ፤ አይሁዳውያኑ ሕግ ያላቸው ሰዎች በመሆናቸው ምክንያት እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ እንተገብራለን
ብለው ያምናሉ፤ በተለይም እንደ ሙሴ ሕግ መሠረት ካልተገዘሩና ይህ ንጹሕ ነው ይበላል፣ ይህ (ርኩስ ነው) ንጹሕ
አይደለም አይበላም በማለት ይናገራሉ፤ በዚህ ምክንያትም ከአመኑ አሕዛብ ጋር ተጋጭተዋል፤ ምክንያቱም አሕዛብ
ይህ ሁሉ የላቸውምና:: በመሆኑም ከላይ እንደ ተገለጸው አሕዛብን ተስፋ የለሽና አምላክ የለሽ በማለት ንቀዋል
አቃልለዋል:: ይሁን እንጂ ክርስቶስ የሞተው ለሁሉም ነበር፤ በመሆኑም ጳውሎስ በዚህ መልእክት ማስተላለፍ
የፈለገው ጉዳይ አለ፤ ይኸውም ሁለቱም ወገኖች በክርስቶስ ደም እኩል እንደ ተዋጁና እግዚአብሔር የሁሉም አምላክ
እንደ ሆነ ነው:: ስለ ሆነም የክርስቶስን መቤዠት በሁለቱም ወገኖች መካከል በማስቀመጥ ሁለቱን ወገኖች
ያስታርቃል፤ ምክንያቱም ሁለቱም ወገኖች እኩል በድለዋልና::

ውድ ተማሪ ሆይ ከዚህ በታች ከመልእክቱ ውስጥ የተውጣጡ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውልሃል፤ ስለዚህ የሮሜ
መልእክትን በማንበብ እንደ ቀረቡልህ ዓይነት መልስ::

መልመጃ አንድ: ምረጥ

1. ሰዎች በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ የተገደሉት ለማን ሊሆኑ ነበር?


ሀ/ለሰይጣን ለ/ለኦሪት ሐ/ለክርስቶስ መ/ሀና ለ መልስ ናቸው
2. በአዳም በደል ምክንያት ምን መጣ?
ሀ/ሞት ለ/ኃጠአት ሐ/ጽድቅ መ/እርቅ
3. የዚህ ዓለም መከራ ከላይኛው ዓለም ክብር ሲመዛዘን?
ሀ/ተመጣጣኝ ነው ለ/ምንም አይደለም ሐ/በጣም የራቀ ነው መ/በጣም ይመሳሰላል
4. ከሚከተሉት ቃላት ቅደም ተከተልን በትክክል የያዘ ፈደል?
ሀ/መስማት፣ ማመን፣ መጥራት ለ/ማመን፣ መጥራት፣ መስማት ሐ/መስማት፣ መጥራት፣ ማመን
5. እንደ ጳውሎስ አገላለጽ የእግዚአብሔር ቸርነትና ጭከና በምን ታወቀ?
ሀ/በአሕዛብ ጥፋት በእስራኤል ድኅነት ለ/በእስራኤል ጥፋት በአሕዛብ ድኅነት

ክፍል ሦስት: የ 1 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት

3.1 መግቢያ
የ 1 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ጸሐፊ ጳውሎስ እንደ እንደ ሆነ በ 1፥1፣ በ 16፥21 ላይ ባለው ኃይለ ቃል ታውቋል፤
በቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶችም ተረጋግጧል፤ ከእነዚህ አንዱ የሆነው በ 88 ዓ/ም የነበረው የሮሙ ቀሌምንጦስ
መልእክቱ የጻፈው ጳውሎስ መሆኑ ጽፏል::

3.2 የተጻፈበት ቦታ
ይህ መልእክት የተጻፈበት ቦታ ኤፌሶን ነው፤ በኤፌሶን ለ 3 ዓመታት ያህል ሐዋርያዊ አገልግሎትን ሲሰጥ በነበረበት
ወቅት ሮሜን ለመጎብኘት የምን ጊዜም ፍላጎቱ ነበር፤ ነገር ግን ሁኔታዎች ስላልተመቹለት በጊዜው ሮሜን ማየት
አልቻለም፤ በዚህ ምክንያት ሂዶ ሮሜን እስኪጎበኝ ድረስ ይህን መልእክት በኤፌሶን ሳለ ጽፎ ሰድዷል::
3.3 መልእክት አድራሾች
መልእክቱን ከኤፌሶን ወደ ቆሮንቶስ ያደረሱ ደቀ መዛሙርት በማንኛውም ሐዋርያዊ አገልግሎቱ ሲራዱት የነበሩት
ደቀ መዛሙርት ሲሆኑ እነዚህም፦

 ጢሞቴዎስ
 እስጢፋኖስ
 ፈርዶናጥስ
 አካይቆስ ናቸው::

3.4 መልእክቱ የተጻፈበት ጊዜ


መልእክቱ የተጻፈበት ጊዜ በውል ባይታወቅም ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ግን ሁለት አስተያየቶች ቀርበዋል።
ይኸውም በ 47 ና በ 55 ዓ/ም ነው የሚል ነው።

3.5 መልእክቱ የተጻፈላቸው ሰዎች


መልእክቱ የተጻፈላቸው ሰዎች በቆሮንቶስ የነበሩ ምእመናን ናቸው። እነዚህ ምእመናን በከተማዪቱ በነበረው ምግባረ
ብልሹነት ሳይበከሉ አልቀሩም። ቆሮንቶስ በጊዜው የሥልጣኔ፣ የተለያዩ ባሕሎች፣ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የተለያየ ጣዖታዊ
ሥራና አመለካከት ማእከል ነበረች። በተለይም የሮማ ፖለቲከኞች ራሰ አምላክ የሆኑባት ከተማ ነበረች።

3.6 ዓላማው
ይህን መልእክት የጻፈበት ዓላማ ብዙ ቢሆንም በዋናነት እንደሚከተለው ነው። ይኸውም፦

1. በምእመናኑ መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል ማስወገድ ነው (1፥11-13)።


2. ከማንኛውም ምግባረ ብልሹነት እንዲታቀቡ ማድረግ ነው (5፥1)።
3. በክርስቶስ የተከፈለላቸውን ዋጋ እንዲመለከቱ ማድረግ ነው።

ምዕራፍ 1

1.1.1-9 ጸጋና ሰላም ለቆሮንቶስ ምእመናን


ጳውሎስ በየትኛውም መልእክቱ በመጀመርያ የሚያነሣው ሐሳብ ተመሳሳይ ነው፤ ይህም በመጀመርያ የራሱን ስም
በማንሣት ከዝያ ቀጥሎ የተደራሹን ስም፣ ሰላምታ፣ ምስጋና፣ ዋና ፍሬ ነገርንና መደምደምያን ያስከትላል። እዚህ ላይ
ያለው ኃይለ ቃልም ይህን የሚያመለክት ሲሆን ተደራሾቹ ሰዎች፦

1. በፍጹም እውቀትና ትምህርት ለክርስቶስ ስለ ሆኑ አንድም መንፈሳዊ ጸጋ እንደማይጎድልባቸው ይናገራል።


2. ወደ ልጁ ኅብረት የጠራቸው እግዚአብሔር የታመነ እንደ ሆነ ያሳውቃል።

1.2.10-17 በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው መከፋፈል


ይህ መከፋፈል የተፈጠረው እኔ የአጵሎስ ነኝ፣ እኔም የጳውሎስ ነኝ፣ እኔም የኬፋ ነኝ፣ እኔም የክርስቶስ ነኝ በሚል
አመለካከት ነው፤ አመለካከቱ ክርስቶስን ከሰዎች (ከእነ ጳውሎስ) ጋራ የሚያነጻጽር በመሆኑ አደገኛ ነበር። ታድያ ይህን
አነጋገር ትተው አንድን ቃል ይናገሩ ዘንድ ይለምናቸዋል፤ ይኸውም እኔ የክርስቶስ ነኝ ይሉ ዘንድ ነው፤ ምክንያቱ ስለ
እነርሱ የተሰቀሉት አጵሎስ፣ ኬፋና ጳውሎስ ሳይሆኑ ክርስቶስ ነበርና። ከተመኩባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ራሱ ስለ
ነበርም ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእነርሱ መካከል ብዙ እንዳላጠመቀ ተናግሯል።

1.3.18-25 የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ


በጳውሎስ ዘመን የግሪክ ፍልስፍና እጅግ ተስፋፍቶ ነበር፤ በክርስትናው እምነት ላይም ትልቅ ጫናን ፈጥሯል፤ በጊዜው
ጥበብ ተብሎ ሲገለጽ የነበረውም ከፍልስፍናው ጋር የተያያዘ አስተምህሮ ነበር፤ በዚህም ምክንያት የክርስቶስ ሥጋ
መሆንና አጠቃላይ ቤዛነት እንደ ሞኝነትና እንደ እብደት ሲቆጠር ታይቷል፤ ይህ የሆነበት ምክንያት ሰዎች
የእግዚአብሔር ጥበብ በዚህ መልክ (ሥጋ በመሆን) አይገለጽም ብለው ስለ ደመደሙ ነበር፤ ይሁን እንጂ የአምላክ
(የክርስቶስ) ሥጋ መሆንና አጠቃላይ ዓለምን በዚህ ሂደት ማዳን ዓለም በጥበብዋ የማታውቀው ጥበብ ነው። ስለዚህ
ጳውሎስ እዚህ ላይ ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት በሰዎች (በአይሁዳውያንና በግሪካውያን) እንደ እብደት
የተቆጠረው ነገር ግን ጥበብ የሆነው ክርስቶስን እየሰበከ እንዳለ ነው። ይህን ለመስበክ የተገደደበት ምክንያት ሲገልጽም
ከጠቢባን ጥበብና ኃይል የእግዚአብሔር ጥበብና ኃይል ስለሚበልጥ ነው ብሏል።

1.4.26-31 የቆሮንቶስ ምእመናን መጠራታቸውን መመልከት አለባቸው


እንደ ጳውሎስ አስተምህሮ ምእመናኑ በክርስቶስ ደም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የተጠሩ ሰዎች ናቸው፤
የመጠራታቸውም ምክንያት እግዚአብሔር በዓለም ዘንድ የተናቁትን በመምረጡ ምክንያት ነበር፤ ምክንያቱም
በፍልስፍናው ውስጥ ያሉት ሰዎች ከፍልስፍናው ውጭ ያሉትን ሰዎች እጅግ ይንቁ ነበርና። ታድያ እግዚአብሔር
ጥበበኞቹን ያሳፍር ዘንድ እነርሱን ስለ ጠራ ይህን መጠራት መመልከት አለባቸው፤ በመሆኑም ምእመናኑ፦ ሰዎች
በፈልላስፎች (በጠቢባን) እንደሚመኩ ሳይሆን በእግዚአብሔር ይመኩ ዘንድ ይገባል።

ምዕራፍ 2

2.1.1-5 የጳውሎስ የስብከት ማእከል ክርስቶስ ነው


በቆሮንቶስ ምእመናን መካከል በራስ ወዳድነትና በማታለል የሚያስተምሩ ሌሎች አታላይ መምህራን እንዳሉ ጳውሎስ
ይጠቁማል፤ እነዚህ የስብከት ማእከላቸው ክርስቶስ ሳይሆን ራስ ወዳድነትና አታላይነት ነው፤ እንዲሁ ዓይነት
አስተምህሮ በማታለልና በራስ ወዳድነት ወደ ምእመናኑ እንደ መምጣት ይቆጠራል፤ ነገር ግን ጳውሎስ ወደ እነዚህ
ምእመናን የሚሄደው እንደ እነዚህ መምህራን በመሆን ሳይሆን ክርስቶስንና የክርስቶስ ኃይልን ማእከል በማድረግ
ይሆናል፤ ይህን አስቀድመው ያውቁለት ዘንድ በመፈለጉ ”ወደ እናንተ የምመጣው በቃል ጥበብና አታላይነት ሳይሆን
ኃይልንና መንፈስን በሚገልጥ አመጣጥ ይሆናል’’ በማለት ግልጹን ይነግራቸዋል፤ ይህን የማድረጉ ምሥጢርም
እምነታቸው በሰው ጥበብና ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ እንዳይሆን ለማድረግ መሆኑን ገልጿል።

2.2.6-16 እውነተኛው የእግዚአብሔር ጥበብ


እዚህ ላይ ጳውሎስ፦ እርሱና መሰል ደቀ መዛሙርት የሚያስተምሩት ጥበብ ከዓለም ጥበብ የተለየ ጥበብ መሆኑን
ግልጽ ያደርጋል፤ በጊዜው ”ጥበብ’’ ተብሎ ሲነገር የነበረው፦ በግሪክ ፈላስፎችና መሰል አታላይ መምህራን ሲነገር
የነበረ ከንቱ አስተሳሰብ ነበር፤ እንዲህ በመሆኑም ነበር ”ዓለም በጥበብቧ የእግዚአብሔርን ጥበብ ማወቅ አልቻለችም’’
የተባለው። በዚህ ክፍል ጥበብ ተብሎ የተገለጸው የእነጳውሎስ ጥበብ ከዘመናት በፊት ለምእመናን ተወስኖ የነበረ፤
እንዲሁም ከዓለም በፊት ተሠውሮ የነበረ ነው ተብሎ ተነግሯል፤ ይህም የክርስቶስ ሥጋ መሆን ነው። ይህን ጥበብ
(የክርስቶስ ሥጋ መሆንን) ለሚያምኑ የሚያስተምሩት ሲሆን የዓለም ጠቢባን ግን ይህን ጥበብ አላወቁም።
ያላወቁበትም ምክንያት ለማወቅ እንደ ማስረጃ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ስላልያዙ ነው። እነጳውሎስ ግን ይህን
ማስረጃ ስለ ያዙ አውቀው ያስተምራሉ። ይህን ዓይነት ሰው ማንም እንደማይመረው (በፍዳ እንደማይያዝ) ይህን
ትምህርት ያልያዘውን ግን እንደሚመረመር (በፍዳ እንደሚያዝ) ከ 14-15 ባለው ምንባብ አስታውቋል።

ምዕራፍ 3

3.1.1-15 የቆሮንቶስ ምእመናን በመከፋፈል ምክንያት እንደ ሕፃናት ሁነዋል


በመካከላቸው የተፈጠረው መከፋፈል እኔ የአጵሎስ ነኝ፣ እኔ የጳውሎስ ነኝ በሚል አመለካት እንደ ነበር በ 1፥12 ላይ
ተገልጿል። ይህ የሚያመለክተው በክርስቶስ ብቻ ማመን ትተው በእያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ማመን መጀመራቸውን
ነው። እንዲህ በመሆኑ ገና ሥጋውያን ናቸው፤ ስለ ሆነም ጳውሎስ ይህን መከፋፈል ከመካከላቸው የሚያስወግደው
እነርሱን እንደ ሕፃናት (አላዋቂ) ወተትን በመጋት (አንድ ብሎ በማስተማር) ነው፤ እርግጥ ነው እነጳውሎስ
የእግዚአብሔር እንደ ራሴ በመሆናቸው ሊከበሩ ይገባል፤ ነገር ግን ሊመለኩ አይገባም፤ እንዲያውም ራሱ ሲናገር እነዚህ
ደቀመዛሙርት እንደየሥራቸው ዋጋቸውን እንደሚቀበሉ ካስረዳ በኋላ እነርሱ የተከሉትንና ያጠጡትን እግዚአብሔር
እንደሚያሳድግ ግልጽ አድርጓል። ምእመናኑ ግን የእግዚአብሔር እርሻና ሕንፃ ናቸው፤ በዚህ ሕንፃ ላይ መሠረትን
የሚጥለው ጳውሎስ ሲሆን አጵሎስ ደግሞ ቀጥሎ የሚያንጽ ነው፤ ሁለቱም እንደ ሥራቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ፤
ይህን ሂደት ከ 10-15 ባለው ምንባብ በምሳሌ መልክ አስቀምጧል።

3.2.16-23 የቆሮንቶስ ምእመናን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ናቸው


እንደ ጳውሎስ አነጋገር ምእመናኑ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሆናቸው በማንኛውም ነገር ይህን ቤተ መቅደስ
ማፍረስና ማርከስ የለባቸውም፤ በተለይም እኔ የአጵሎስ ነኝ፣ እኔም የጳውሎስ ነኝ በሚለው አነጋገራቸውና እኔ
ጥበበኛ ነኝ በሚል አመለካከት መመካት የለባቸውም፤ ምክንያቱም የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት
ነውና። ስለዚህ ማንም (ምእመናኑ) በሰው (በአጵሎስና በጳውሎስ) መመካትን በመተው የክርስቶስ መሆናቸውን
ሊያውቁ ይገባል።

ምዕራፍ 4

4.1.1-13 የእነጳውሎስ ሐዋርያነትና በሌላው ላይ አለመፍረድ


በዚህ ክፍል የሚከተሉትን መልእክቶች ያስተላልፋል፤ ይኸውም ምእመናኑ፦

1. የእነጳውሎስን ሐዋርያነት ሊያውቁ ይገባል።


2. ማንም በሌላው ላይ መፍረድና መታበይ የለበትም።
3. እነጳውሎስ ራብተኞችና ለመላእክት (ለዚህ ዓለም ዓለቆች) መዛበቻ ሆኑበት ድርጊት እየተፈጠረ እንዳለ፤
እነርሱ ግን ነገሥታትና ባለ ጸጎች መስለው የሚታዩበት ጊዜ እየመጣ እንደ ሆነ መግለጽ ነው። ይሁን እንጂ ያለ
እነጳውሎስ ይህን ክብርና ሥልጣን አላገኙም።
4. ጳውሎስ በሰው ዘንድ መመስገንና መከበርን እንደ ውርደትና እንደ መናቅ አድርጎ እንደሚመለከተው መረዳት
እንዳለባቸው፤ ይህንንም በምሬትና በምጸት ተናግሯል።

4.2.14-21 ጳውሎስ ለምእመናኑ የሚጽፍላቸው ሊያሳፍራቸው ሳይሆን ሊገሥጻቸው ነው


በዚህ መልእክት ውስጥ ጠንከር ጠንከር ያሉ ቃላትን አስፍሯል (3፥1-4)። በተለይም በ 4፥8-10 ላይ። እንደዚህ
ዓይነት ቃላትን የሚጠቀመው ግን ለማሳፈር ሳይሆን ለመገሠጽ ነበር፤ ስለ ሆነም በክርስቶስ ዘንድ ብዙ አእላፍ
መግዚቶች ማለትም አጵሎስንና ጳውሎስ ደቀመዛሙርት ቢኖሯቸውም እነዚህን ጌቶች ማድረግ የለባቸውም። እኔ
የአጵሎስ ነኝ፣ እኔ የጳውሎስ ነኝ ማለት ብዙ ጌቶች ማድረግ ነውና። ጌታቸው ግን ስለ እነርሱ የተሰቀለ አንድ
ክርስቶስ ነው፤ ይህን ያውቁ ዘንድ ጢሞቴዎስ ይህን መልእክት ይዞ ወደ እነርሱ ተልኳል።

ምዕራፍ 5

5.1.1-8 በቆሮንቶስ አማኞች መካከል በአሕዛብ ስንኳ የማይደረግ ዝሙት እየተደረገ ነው


በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እጅግ አስጸያፊ የሆነ ምግባረ ብልሹነት በመደረግ ላይ ነው። ይህም ተግባር ስንኳን
በክርስቲያኖች፣ በአሕዛብ ስንኳ ይደረጋል ተብሎ አይታሰብም፤ ይሁን እንጂ ተደርጓል፤ ይኸውም ልጅ የአባቱን ሚስት
ማግባቱ ነው፤ አሕዛብ ከሌላው ሚስት ቢያመነዝሩ እንጂ ከአባታቸው ሴት አያመነዝሩም፤ እንዲህ ሁኖ ሳለ
ክርስቲያኖቹ አንድም እርምጃ መውሰድ አልቻሉም፤ በመሆኑም ይህን ተግባር በሚፈጽም ሰው ላይ በሥጋው
የሚቀጣበትን (ንስሐ) እርምጃ ይወስዱበት ዘንድ ወይም አውግዘው ይለዩት ዘንድ ይነግራቸዋል፤ በሥጋ መቀጣት
(ንስሐ መግባት) ለሰይጣን ፍርድ ተላልፎ እንደ መሰጠት ተቆጥሯል። እንዲህ ዓይነቱ ሰው (የአባቱን ሚስት ያገባ)
ከዚህ የሞራል ውድቀት ደረጃ የደረሰው ትንሿ ኃጢአት ከትልቅ ኃጢአት እንደምታደርስ ባያውቁ ነበር፤ ታድያ የድሮ
ኃጢአትን ትተው አዲሱን ሕይወት ይይዙ ዘንድ ይገባል፤ ይህም የሆንበት ምክንያት ኃጢአትን ለማስወገድ ክርስቶስ
ተሰቅሏልና። እስራኤላውያን በፋሲካቸው የሚበሉት ቂጣ ከከረመው እርሾ የተጋገረውን ቂጣ አይደለም፤ ከአዲሱ ሊጥ
የተጋገረውን ቂጣ ነው የሚበሉት። ስለዚህ ምሳሌው (ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና የሚለው) የሚያስረዳው
በአሮጌው የሞት ኑሮ ሳይሆን በአዲሱ ኑሮ (በክርስቶስ ሞት በተገኘው ሕይወት) መኖር እንደሚገባ ነው።

5.2.9-13 የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በምግባረ ብልሹነት በሚመላለሰው ላይ መፍረድ ይገባታል


እዚህ ላይ የጻፈላቸው ከሴሰኞች ጋር እንዳይተባበሩ እንደ ሆነ ካስረዳ በኋላ የሥነ ምግባር ብልሹነት በታየበት ሰው ላይ
እርምጃ (ንስሐና አስተምህሮ) መውሰድ እንዳለባቸው ያሳስባል፤ ከምእመናኑ ውጭ ባሉት ክፉ ሰዎች ላይ ግን
እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል ብሏል።

ምዕራፍ 6

6.1. 1-11 በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር መፍታት ያለባት ቤተክርስቲያን ናት
እንደዚህ ምንባብ ገለጻ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረው ችግር በውጭ ላለው ኢአማኝ የተሰማ
ይመስላል፤ ይህም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቅ ሐፍረት ነው፤ ምክንያቱም ከዚህ ሁሉ የደረሰው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ
ይህን ችግር መፍታት የሚችል አዋቂ አማኝ ባለመገኘቱ ነበር። ከዚህ ፈንታ ችግሩ በኢአማኝ የሚዳኝ ሁኖ ተገኝቷል፤
ስለዚህ ጳውሎስ እዚህ ላይ እያለ ያለው ችግሩን በራሷ እንድትዳኘው ነው። ሌላው ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ ከእነርሱ
አንዳንዱ በመጀመሪያ እንደ አሕዛብ (ዓመፆኞች) የነበሩ ቢሆኑም አሁን ግን ሁሉም በክርስቶስ ስም ከኃጢአት
ታጥበው ወደ መጽደቅና መቀደስ እንደ ደረሱ ነው። በዚህ ክፍል ቅዱሳኑ (የቆሮንቶስ ምእመናን) ስንኳን በትንሹ ጉዳይ
ላይ በዓለምና በመላእክት ላይ የመፍረድ ሥልጣን እንዳላቸው ተናግሯል፤ እዚህ ላይ ”ዓለም’’ የተባለው ከአማኙ ውጭ
ያለውን ሕብረተሰብ ሲያመለክት፣ ”መላእክት’’ የሚለው ቃል ደግሞ ርኩሳን መናፍስትን ያመለክታል፤ ምክንያቱም
ምእመናን በአጋንንት ላይ የመፍረድ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋልና(ሉቃ.10፥17)።

6.2. 12-20 የምእመናኑ ሰውነት የክርስቶስ አካል ስለ ሆነ ለዝሙት መዋል የለበትም


እዚህ ላይ ከአይሁድና ከአሕዛብ አስተሳሰብ በመነሣት ነገሮችን ያነሣል። አይሁዳውያን ሁሉም የምግብ ዓይነት
(በተለይም ሥጋ) ሊበላ አይገባም የሚል አመለካከት አላቸው፤ ይህም የመነጨው በሙሴ ሕግ መሠረት ነው
(ዘሌዋ.19)። አሕዛብ ግን ከዚህ ወጣ ባለ ሁኔታ ሁሉም ነገር መበላት እንዳለበት ያምናሉ፤ የሁለቱም አመለካከት
ለሁለቱ ወገኖች መጣላት ምክንያት ሁኖ እንደ ነበር በሮም መልእክት ተገልጿል (14፥1-4)። ጳውሎስም በዚህ ጉዳይ
ላይ ያለውን አመለካከት ይናገራል። ይኸውም ምንም እንኳ ሁሉም ነገር በክርስቶስ አዲስ ቢሆንም ነገር ግን ሁሉም
እንደማይጠቅም ነው። ይህም የመሆኑ ምሥጢር ሆድ ለመብል፣ መብል ለሆድ ስለሚሆን ነው፤ ማለት መብሉም ሆነ
ምግቡ ይጠፋሉ።ሰውነት ግን የክርስቶስ አካል በመሆኑ ለዝሙት መዋል የለበትም፤ ምክንያቱም ሰው እግዚአብሔርን
የሚያገለግለው በመብል ወይም በሆድ ሳይሆን በሥጋው ንጽሕናን በመያዝ ነውና። ስለዚህ በክርስቶስ ደም የተገዛውን
አካል ለጋለሞታ እንዳያደርጉት ይመክራል፤ ከዚህ ይልቅ በሥጋቸው ንጽሕናን ይዘው እግዚአብሔርን ማክበር
አለባቸው።

ምዕራፍ 7

7.1.1-40 የጳውሎስ ምክር፦ በትዳር፣ በድንግልና ኑሮና በማግባት ዙርያ ላይ


በዚህ ምዕራፍ በዋናነት በአርእስቱ ላይ ስለ ተዘረዘሩት ነገሮች ይናገራል፤ ይኸውም፦

ሀ/ስለ ትዳር
በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በአሕዛብ ስንኳ የማይፈጸም ዝሙት እየተፈጸመ እንዳለ ተነግሯል (5፥1)። ይህም ጉዳይ
እንደ ተነገረው በዚሁ ተናግሯል (7፥1)፤ ታድያ ለዚህ ምግባረ ብልሹነት እንዳይዳረጉ መፍትሔውን ያስቀምጣል፤
ይኸውም እያንዳንዱ አማኝ ማግባትና በሚስት በሚስቱ መኖር ነው። በባልና በሚስት መካከልም ምን ዓይነት
መተሳሰብና ሂደት መኖር እንዳለበት መክሯል (3-6)። ሌላው ስለባልና ሚስት ያስቀመጠው ትእዛዝ ሴት ከባልዋ
መለየት እንደሌለባት፣ ባል ደግሞ ሚስቱን መፍታት እንደሌለበት ነው።

ለ/ስለ አላገቡና ስለ መበለቶች (ፈት ሁነው ስለሚኖሩ)

ለእነዚህ የሰጠው ምክር ቢቻላቸው እንደ እርሱ ሁነው እንዲኖሩ ነው፤ ነገር ግን የማይቻላቸው ከሆነ ማግባት
እንዳለባቸው ነው። ምክንያቱም እየተቃጠሉ ከመኖር ማግባት መፍትሔ መሆኑን አምኗል።

ሐ/አማኝ ባል ከኢአማኝ ሴት፣ አማኝ ሴት ከኢአማኝ ባል የሚኖሩ ከሆነ፣ በትዳራቸው ውስጥ መስማማት ካለ
አይለያዩ ብሏል፤ ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረበው ምናልባት እርሷ በእርሱ፣ እርሱ ደግሞ በእርሷ ሃይማኖት ይድኑ
ይሆናል የሚል ነው፤ በዚህ ምክንያት የማይድኑ ከሆነ ግን አማኞች ለዝሙት ብቻ አይጋቡምና ይለያዩ ብሏል።

መ/ማንም ሳይገረዝ ያመነ እንደ ሆነ ግድ ካልተገረዝኩ አይበል ብሏል፤ ምክንያቱም መገረዝ በመንፈስ እንጂ በሥጋ
አይደለምና።

ሠ/አርነት ሳይወጣ እግዚአብሔርን ለማገልገል የተጠራ ካለ በቅድሚያ ከባርነት ወጥቶ እግዚአብሔርን ማገልገል
እንዳለበት ተናግሯል።

ረ/ስለ ደናግል

ስለ ደናግል በተመለከተ ያስተላለፈው ምክር ከተቻለ በድንግልና ይኖሩ ዘንድ ሲሆን ካልሆነ ግን ቢያገቡ ኃጢአት
እንደማይሆንባቸው ነው። ይሁን እንጂ አሁንም ወደ አለማግባቱ ያደላል፤ ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት ያቀረበው ካገባ
ያላገባ እግዚአብሔርን ያስደስታል የሚል ነው።

ምዕራፍ 8

8.1.1-13 ለጣዖታት ስለ ቀረበ ምግብ


በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ማለት አንዳንዱ እምነተ ጠነካራ ሲሆኑ አንዳንዱ ደግሞ
እምነተ ደካማ ናቸው፤ በተለይም ለጣዖት በተሠዋው ሥጋ ዙርያ። በእምነት ጠንካሮች ነን የሚሉት ለጣዖት ምን
ገንዘብ አለው? ብለው የጣዖት መሥዋዕትን ሲበሉ ደካማዎቹ ደግሞ ቢበሉ የሚረክሱ ይመስላቸዋል፤ በመሆኑም
ጠንካራዎቹ በደካማዎቹ ላይ ታብየዋል፤ እንዲህ ግን መሆን አልነበረበትም፤ ምክንያቱም ከሁሉም ፍቅር ስለሚበልጥ
ከመታበይ ደካማውን በፍቅር ማስረዳት ነበረባቸው። ጳውሎስም ከዚህ በመነሣት በቅድሚያ ፍቅርን ይይዙ ዘንድ
ይመክራል፤ ለጣዖት ግን እንደ ጳውሎስ አመለካከት የራሱ የሆነ ገንዘብ የለውም፤ ምንም እንኳ በሰማይ ባሉና በምድር
ብዙ አማልክት ያሏቸው ሰዎች ቢኖሩም አንድ አምላክ ብቻ አለ፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፤ ቢሆንም ግን ይህ እውቀት
በሁሉም የታወቀ አይደለም፤ ስለዚህ የመብላት መብታቸው ለደካሞቹ እንቅፋት እንዳይሆን ይጠነቀቁ ዘንድ
ያስተምራል፤ ምክንያቱም ለደካሞቹም ክርስቶስ ሙቷልና። የመብላት መብትን (እውቀትን) ተጠቅሞ ደካማውን
ከማሰናከል ግን ለዘለዓለሙ ሥጋን አልበላም ብሏል።
ምዕራፍ 9

9.1.1-18 የሐዋርያ መብት


ጳውሎስ በዚህ ክፍል ስለ የሐዋርያ መብት በተመለከተ ይናገራል፤ በእነጳውሎስ ላይ የሚሰነዘሩ ነገሮች ብዙ ሲሆኑ
ከነእርሱ ደግሞ በዚህ ምንባብ በውስጠ ወይራ (በግልጥ ባልተገለጠ ሐሳብ) ተንጸባርቀዋል፤ እነዚህም፦

1. ሐዋርያ አይደለም የሚል ነው።


2. ክርስቶስን አላየም የሚል ነው።
3. ሴትን ያስከትላል የሚል ነው።

ከተራ ቁጥር 1- ተራ ቁጥር 3 ላለው ተቃውሞ፦ ከ 1-5 ባለው ምንባብ መልሱን አስቀምጧል።

ሴትን ያስከትላል ማለታቸው አማኞች ሴቶችን በማስከተሉ ምክንያት ነው፤ እነጴጥሮስም 36 ቱ ቅዱሳት አንስትን
ያስከትሉ ነበር፤ ግን ሚስቶቻቸው አልነበሩም፤ ስለዚህ ”እህት ሚስቶቻችን’’ ማለቱ ከዚህ አንጻር ነበር፤ በግእዙ ግን
”እህት ሚስቶቻችን’’ ሳይሆን የሚለው ”ወትትልወነ እህትነ እምአንስት’’ ከሴቶች ወገን (የእምነት) እህታችን
ልትከተለን አይገባምን? ነው የሚለው።

4. አስተምረው ዋጋ ይበላሉ የሚል ነው።

ለተራ ቁጥር አራት ተቃውሞ ያስቀመጠው መልስ ደግሞ ከ 7-14 ያሉ ምሳሌዎችና እውነታዎች ነው፤ እነዚህም፦

 በወታደርነት የሚያገለግል ሰው ደመወዝ ምሳሌ


 ወይኑን ተክሎ ፍሬውን የሚያገኝ ሰው ምሳሌ
 መንጋውን ጠብቆ ወተቱን የሚጠጣ ሰው ምሳሌ
 በሬ በሚያበራይበት ጊዜ አፉን አትሠር የተባለው ትእዛዝ
 ቤተመቅደስን የሚያገለግሉ የካህናት ምግብ እውነታ
፤ ካህናት ምግባቸው ከሚያገለግሉበት ቤተ መቅደስ እንዲሆን ታዝዟል፤ ጌታም ለሚያገለግል ዋጋው ይገባዋል
ብሏል (ማቴ 10፥10)።

ጳውሎስ ግን አስተምሮ ዋጋ መብላት እንደሚገባ በዚህ ምሳሌ መልክ ቢያስረዳም እርሱ ይህን አይፈልገውም፤ በራሱ
ጥረት ሕይወቱን መምራት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ድንኳን በመስፋት የራሱንና የደቀመዛሙርቱን ሕይወት ሲመራ
ታይቷል (የሐ.ሥራ 20፥33)። እንዲያውም በዋጋ ምክንያት ሰማያዊ ደመወዙ ከሚቀርበት ሞት እንደሚሻለው
ተናግሯል።

9.2.19-23 የጳውሎስ መንፈሳዊ ጥበብ

እዚህ ላይ ሁሉን ወደ እርሱ ይስብ ዘንድ መሆን የሌለበትንና መምሰል የሌለበትን እንደ ሆነና እንደ መሰለ ይናገራል፤
ይህም መንፈሳዊ ስልትና ጥበብን ያመለክታል።

9.3.24-27 ለዋጋ መሽቀዳደም


በዚህ ምንባብም ሥጋዊ ሩጫንና መንፈሳዊ ሩጫን በማነጻጸር በመንፈሳዊው ሩጫ በመሮጥ ዋጋን ማግኘት እንደሚገባ
ያስተምራል፤ በመንፈሳዊው ሩጫ ራሱም ገብቶበታል።
ምዕራፍ 10

10.1. 1-13 ከእስራኤል ታሪክ ለምእመናኑ የቀረበ ማስጠንቀቅያ


ይህ ምንባብ ሙሉ በሙሉ ስለ ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡ እስራኤል በተመለከተ የሚናገር ሲሆን በዚህ ጊዜ
እግዚአብሔር እነዚህን ወገኖች ከግብጽ ባርነት በታላቅ አምላካዊ እንክብካቤ እንዳወጣቸው ተገልጿል፤ ነገር ግን እንደ
ተደረገላቸው አምላካዊ እንክብካቤ መጓዝ ሳይችሉ በቀሩ ጊዜ በታላቅ ቅጣት ተመትተዋል፤ ታድያ ጳውሎስ ይህን
ታሪክ ለቆሮንቶሷ ቤተ ክርስቲያን እንደ መጥፎ አርዓያ በማቅረብ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፤ ዓላማውም እነዝያ መጥፎ
ታሪካቸው ለቆሮንቶሷ ቤተክርስቲያን የተነገረባቸው እስራኤል እንደ ጠፉ እንዳይጠፉ ነው።

10.2. 14-22 እግዚአብሔርን ማስቀናት አይገባም


የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በተለያየ የአምልኮ ጣዖት የተበላሸ ሕይወትን እንደ ያዙ ያውቃል፤ በአንድ በኩል የፍቅር
ማዕድን ሲቆርሱ በሌላ በኩል ደግሞ የአጋንንት ማዕድን ሲቆርሱ ታይተዋል፤ በሚቆርሱት ማዕድ በሚሳተፉት ተሳትፎ
የቆረሱበት ማዕድ ተሳታፊዎች (ማኅበርተኞች) ይሆናሉ፤ ስለዚህ የአጋንንትንና የእግዚአብሔርን ጽዋ በአንድ ጊዜ
መጠጣት ስለማይቻል ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ያሳስባቸዋል፤ ምክንያቱም በዚህ እግዚአብሔር ይቀናልና።
እግዚአብሔር በአምልኮቱ የሚቀና አምላክ ነው ተብሎ ተገልጿል።

10.3. 23-33 ጳውሎስ ሁሉን ይበላ ዘንድ ተፈቅዶለታል


እዚህ ላይ ያለው ጽንሰ ሐሳብ ስለሚበላና ስለማይበላ ሳይሆን እያስረዳ ያለው ለሌላው እንቅፋት ስለ መሆንና አለ
መሆን በተመለከተ ነው፤ አንዳንድ እምነተ ጠንካራ ክርስቲያኖች ለጣዖት የቀረበውን መሥዋዕት (ሥጋ) መብላት
ይገባል ሲሉ ደከማዎቹ ደግሞ መብላት አይገባም ይላሉ፤ ይሁን እንጂ እንደ ጳውሎስ አመለካከት ለጣዖት ገንዘብ
ስለሌለው ሁሉን መብላት ይገባል፤ ይህም ሁሉ በክርስቶስ አዲስ መሆኑን ያመለክታል፤ ምንም እንኳ ”ሁሉ
ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም’’ ቢልም። ይህን ያለው ሁሉን መብላት አይገባም የሚሉ ወገኖች ስላሉ
እነርሱን በፍቅር ለመያዝ ተብሎ ነው። በገበያ የቀረበውን ሁሉ ሳይጠይቁ መብላት እንደሚገባ ተናግሯል፤ ይህ ለጣዖት
የቀረበ ነው የሚል እስከሌለ ድረስ። ካለ ግን እንቅፋት ላለመሆንና ሃይማኖትን ላለማስነቀፍ መተው ይገባል ብሏል።

ምዕራፍ 11

11.1. 1-16 ትንቢት ለሚናገር ወንድና ለምትናገር ሴት የተሰጠ መመሪያ


በዚህ ክፍል ትንቢትን ጸሎት፣ ጸሎትን ትንቢት በማለት ይናገራል፤ ተከናንቦ ለሚጸልይና ወንድ ሳትከናነብ ለምትጸልይ
ሴት መመሪያን ያስቀምጣል፤ ይኸውም ከላይ የተገለጹት ወንድና ሴት በዚህ ሁኔታ መጸለይ የለባቸውም፤ ለሴቲቱ
ተከናንቢባ መጸለይ አለባት ላለበት ምክንያት መልስ ሲያስቀምጥ በበላይዋ ወንድ ስላለ ነው የሚል ነው፤ የማትከናነብ
ከሆነች ግን በበላዬ ሌላ አካል የለብኝም እንደ ማለት ይቆጠርባታል፤ ነገር ግን ሴት የተገኘችው ከወንድ ነው። ይህም
ተፈጥሮን የሚመለከት ነው፤ ለወንዱ ደግሞ ተከናንቦ መጸለይ የለበትም ላለበት ምክንያት መልስ ሲያስቀምጥ ወንድ
የክርስቶስ ምሳሌ ስለ ሆነ ነው የሚል ነው፤ አለመከናነቡ በክርስቶስ ላይ ሌላ አካል እንደሌለ ያስረዳል፤ ይህ እንዳይሆን
አይከናነብ ብሏል፤ ሌላም ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማብራሪያዎችን ተናግሯል።

11.2. 17-26 በጌታ ራት ላይ የተፈጸመ መድሎ (ጥፋት)


የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን በዕለተ ሐሙስ በክርስቶስ የተመሠረተውን ቅዱስ ቁርባን እንደ መነሻ በማድረግ በዕለታዊ
መንፈሳዊ እንቅስቃሴዋ (በተለይም እሑድ በተባለው ቀን) የፍቅር ማዕድን ታከናውን ነበር፤ የምታከናውነው
በመጸለይና የእግዚአብሔርን ቃል በመማር ነው፤ ይሁን እንጂ በዚህ መካከከል ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው አማኞች ስፍራ
አልተሰጣቸውም፤ የፍቅሩ ማዕድ የድሀና የሀብታም መለያ ተደርጎ ተወስዷል፤ ይህ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ታላቅ ፈተና
ሁኗል፤ ድሀውን ትተው መብላት የተጀመረውም ስስት ስለ ተፈጠረ ነው፤ በመሆኑም ይህ መሰባሰባቸው ለጌታ
መምጣት እንደሚገባ ሳይሆን በመቅረቱ ይህን ያስተካክሉ ዘንድ ወቀሳውን በማቅረብ ያስተምራቸዋል። ቀጥሎም
ከ 23-26 እንደ ተጠቀሰው ክርስቶስ በዕለተ ሐሙስ ያደረገውን የቅዱስ ቁርባን ድኅነትና ሥርዓት ነግሯቸዋል።
11.3. 27-34 ሳይበቁ የጌታን ቅዱስ ቁርባን (ሥጋ ወደሙ) መቀበል ቅጣት ያስከትላል
የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ከ 17-22 እንደ ተገለጸው የጌታ ቅዱስ ቁርባን ምሳሌ በሆነው ራት ላይ የማይገባ ተግባርን
ፈጽመዋል፤ በመሆኑም በዚህ ሂደት የጌታን ቅዱስ ቁርባን በማያምን ሰው ላይ ታላቅ ቅጣት እንዳለበት የማጠቃለያ
ማስጠንቀቂያውን ያስተላልፋል፤ እንዲያውም በዚህ አሠራር ቅጣት የተቀበሉ ሰዎች ብዙ እንደ ሆኑ ገልጿል (ቍ.30)፤
ይህ ዓይነት ተግባር እንዳይፈጸም ደግሞ መፍትሔው ከቤት በልቶ መሄድ እንደ ሆነ አስታውቋል።

ምዕራፍ 12

12.1. 1-11 ልዩ ልዩ ጸጋዎች (ስጦታዎች)


የቆሮንቶስ ሰዎች በድሮ ሰብእናቸው መናገር ወደማይችሉ ጣዖታት ይሄዱ እንደ ነበር በቍ.2 ተገልጿል፤ ሰዎቹ ይህን
ማድረጋቸው በእግዚአብሔር መንፈስ መጓዝ ባለመቻላቸው ነበር፤ ምክንያቱም በቍ.3 እንደ ተገለጸው ማንም
በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ”ክርስቶስ ጌታ ነው’’ የሚል ስለሌለ ነው፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦
”ክርስቶስ የተረገመ ነው’’ የሚል የለም ብሏል፤ የአማኞቹ ሰብእና እንዲህ በመሆኑ ከአንድ እግዚአብሔር የሚሰጡ ልዩ
ልዩ ጸጋዎች እንዳሉ ያስታውቃቸዋል፤ ለጊዜው በዚህ ክፍል ያሉ ጸጋዎች 9 ናቸው (8-9)።

12.2. 12-31 አንድ አካል ብዙ ሕዋሳት


የዚህ ክፍል ምንባብ የሚያስረዳው ምንም እንኳ አማኞቹ ከተለያየ ዘርና ጎሳ፣ እንዲሁም ከተለያየ የኑሮ ደረጃ
የተውጣጡ ቢሆኑም በክርስቶስ አንድ አካል መሆናቸውን ነው፤ ምክንያቱም ሁሉም አንድ መንፈስን ጠጥተዋልና።
አንዱ አማኝ ለሌላው አማኝ እጅግ አስፈላጊ እንደ ሆነም የአንዱ ሕዋስ ለሌላው ሕዋስ አስፈላጊነት እንዴት
እንደሚሆን በምሳሌ የተናገረበት ሁኔታ አለ፤ አንዱ ሕዋስ ሌላውን ሕዋስ አታስፈልገኝም ማለት አይችልም፤
እንዲሁም አንዱ ሕዋስ ከታመመ ሌላው ሕዋስ አብሮ ይታመማል፤ የአንዱ አማኝ ሕመምም (መከራ) የሌላው አማኝ
ሕመም (መከራ) ነው። በተጨማሪም የአንዱ ሕዋስ ደስታ የሌላው ሕዋስ ደስታ እንደ ሆነ፦ የአንዱ አማኝ ደስታ
የሌላው አማኝ ደስታ ነው። እንዲህ የሆነበት ምሥጢር ምንም እንኳ ሕዋሳቱ ብዙ ቢሆኑም በአካል አንድ ስለ ሆኑ
ነው፤ አማኞቹም በክርስቶስ አንድ አካል ናቸው፤ ቢሆንም እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን እንደ ሰጠው ጸጋ መሠረት
እያንዳንዱ የሁሉ ጸጋ ባለቤት እንዲሆን ያደርጋልን? በማለት ጥያቄ ያቀርባል።

ምዕራፍ 13

13.1. 1-13 ስለ ፍቅር የበላይነት


ይህ ምዕራፍ ሙሉ በሙሉ ስለ ፍቅር የሚናገር ሲሆን በማንኛውም መልካም ሥራና ክንዋኔ ላይ ፍቅር ካልተጨመረበት
ውጤቱ ከንቱ እንደ ሆነ ያስረዳል፤ ከፍቅር ጋር ጸንተው ይኖራሉ የተባሉ ሁለት ነገሮች አሉ፤ እነዚህም ተስፋና እምነት
ናቸው፤ ይሁን እንጂ እነዚህም ያለ ፍቅር ዋጋ የላቸውም ብሏል። ለዚህ ነው ”ደግሞ ከሁሉ የሚበልጠውን መንገድ
አሳያችኋለሁ’’ ያለው (12፥31)።

ምዕራፍ 14

14.1. 1-25 በተለያየ ቋንቋ መናገርና (ሌላ በማይሰማው) በአንድ ቋንቋ (ሌላ በሚሰማው) መናገር
ይህ ክፍል ሰፋ ያለ ምሳሌአዊ አነጋገርና መልእክት የያዘ ክፍል ነው፤ የሚያተኩረውም በትርጉም በመናገርና ያለ
ትርጉም በመናገር ላይ ነው፤ አንድ ሰው ሌላው በማይሰማው ቋንቋ አሥር ጊዜ ቢናገርና ቢያስተምር ዋጋ የለውም፤
እንዲህ ዓይነቱ ሰው ራሱን ብቻ እንጂ ሌላውን ማነጽ አይችልም፤ ለአድማጩም ወገን እንደሚናገር ሳይሆን
እንደሚለፈልፍ ይመስለዋል፤ በመሆኑም በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን እንዲህ ዓይነት ክሥተት እዳይፈጠር አስቀድሞ
መፍትሔን ይናገራል፤ መፍትሔው ተርጉሞ መናገር የሚችል አማኝ ካለ እንዲያስተምር ማደፋፈር ነው፤ ምክንያቱም
ትርጉም በሌላቸው እልፍ አእላፋት ቋንቋ (ልሳኖች) ከመናገር ትርጉም ያላቸው አምስት ቃላቶችን መናገር
ይበልጣልና። በቋንቋ (በልሳን) መናገር ለማያምኑ ሰዎች ምልክት ነው ብሏል፤ ምክንያቱም ተአምራት መስሏቸው
ሊሳቡ ስለሚችሉ ነው፤ በትርጉም መናገር ግን ለሚያምኑ ሰዎች ነው፤ በአጠቃላይ ጳውሎስ በዚህ ክፍል ያለውን ልዩ
ልዩ ምሳሌና አነጋገር የተናገረበት ዓላማ ቤተክርስቲያኒቱ በትርጉም የመናገር ጥቅምን ታውቅ ዘንድና በትርጉም ትናገር
ዘንድ ነው።

14.2. 26-40 ለአምልኮ በሚሰባሰቡበት ጊዜ መደረግ ያለበት ጉዳይ


እዚህ ላይ ያለው ሐሳብ የሚያስረዳው ለአምልኮ በሚሰባሰቡበት ጊዜ፦

1. በቋንቋ መናገሩም ሆነ በትርጉም መናገሩ ሁሉም ለማነጽ መሆን እንዳለበት ነው።


2. ሴቶች በማኅበር ማስተማር እንደሌለባቸው ነው፤ መማር ቢፈልጉም ከቤት ከባሎቻቸው ይማሩ ተብሏል፤
ይህም የሆነበት ምክንያት በጊዜም ከነበረው ባህል የተነሣ ሊሆን ይችላል።
3. ሁሉም ነገር በሥርዓትና በፍቅር መሆን እንዳለበት ነው።

ምዕራፍ 15

15.1. 1-11 የክርስቶስ ትንሣኤ


ጳውሎስ የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን ባንድም በሌላም ስለ ክርስቶስ ቤዛነት በተመለከተ አስተምሯል፤ አሁንም
እያስተማረ ያለው በዚህ ባስተማራቸው ትምህርት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ ነው፤ ስለዚህ እዚህ ላይም እያለ ያለው
ክርስቶስ ተነሥቶ ለተለያዩ ደቀ መዛሙርት ከታየ በኋላ በመጨረሻ ለእርሱ እንደ ተገለጸ ነው፤ ድሮም ሐዋርያቱ
ሲያስተምሩት የነበረው ስለ ክርስቶስ ነው፤ አሁንም እርሱ እያስተማረ ያለው ያንን ነው።

15.2. 12-34 ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል


የዚህ ክፍል ዋና ዋና ጭብጥ ሐሳቦች የሚከተሉት ናቸው፤ እነዚህም፦

1. ለሙታን በኩር ሁኖ ክርስቶስ ከሞት እንደ ተነሣ ነው።


2. የክርስቶስ የሆኑት ሁሉ ከሞት እንደሚነሡ ነው። ቢሆንም ኃጥአንም አብረው ይነሣሉ።
3. ክርስቶስ መንግሥቱን ለአባቱ አሳልፎ በሰጠበት ጊዜ ፍጻሜ እንደሚሆን ነው።

ምክንያቱም አሁን ባለው እውነታ የቤተ ክርስቲያን ገዥ ክርስቶስ ነው፤ ማለት ጠላቶቹ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ
ጊዜ ሊነግሥ ይገበዋል፤ በዚህ መገዛት ውስጥ ሞትም ጭምር አለበት፤ ይሁን እንጂ ”ሁሉን አስገዝቶለታል’’ ሲል ያለ
ክርስቶስ ነው፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉን ለአባቱ ባስረከበ ጊዜ እርሱም ለአባቱ ይገዛል ይላል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ
በለበሰው ሥጋ መጥቶ ዓለምን የሚያሳልፍ በመሆኑ ነው፤ ይህን እንደ ተልእኮ አድርጎ ስለ አየው እንጂ በክርስቶስስ
መገዛት የለበትም።

4. ጳውሎስም ሆነ ሌሎቹ በአገልግሎትና በመከራ ውስጥ የሚኖሩት የሙታን ትንሣኤ ስለ አለ ነው።

በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን መካከል”የሙታን ትንሣኤ የለም’’ የሚሉ አካላት ተገኝተዋል፤ ይህም ለቤተክርስቲያኒቱ
ከባድ ፈተና ነበር፤ ነገር ግን ሙታን ይነሣሉ በሚል ተስፋ (እምነት) ብዙዎች ስለ መነሣት ሲሉ መከራን (ጥምቀትን)
እየተቀበሉ (እየተጠመቁ) ነው፤ የእነ ጳውሎስም አኗኗር እንደዚሁ ነው፤ እንዲያውም ”ሙታን ይነሣሉ’’ በሚል
አስተምህሮው በኤፌሶን ከተማ ከአውሬ (ከእስክንድሮስ) ጋራ (ሐዋ.ሥራ 19፥33) ተጣልቷል፤ በመሆኑም ”ሙታን
አይነሡም’’ የሚል አመለካከት በቤተ ክርስቲያኒቱ መካከል እንዳይኖር ይህን መልእክት ያስተላልፋል።

15.3. 35-50 የሚነሣ አካል (የሙታን ትንሣኤ)


በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሙታን ትንሣኤ ያለው ግንዛቤና እምነት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፤ ታድያ ጳውሎስ
ይህን በጥልቀት በማየት የሙታን ትንሣኤ እንዴት እውን እንደሚሆን የተለያዩ ምሳሌዎችን ያመጣል፤ ይኸውም፦
 ዘር ካልተዘራ መብቀል እንደማይችል ሁሉ ሰዎችም ካልሞቱ መነሣት እንደማይችሉ ነው።

ይህም በማንኛውም ሰው የሚታወቅ እውነታ ነው፤ ስለዚህ ሰዎች ይነሡ ዘንድ መሞት አለባቸው፤ ደግሞ ይነሣሉ፤
በመሆኑም የሰው ሥጋ መቀበርና መነሣትን በዘር መዘራትና መብቀል መስሎ ተናግሯል፤ ይህን የሚያደርግ ደግሞ
እግዚአብሔር ነው ብሏል።

 የእንስሳት፣ የወፎች፣ የዓሣ ሥጋ፣ የሰማያውያን አካል፣ የምድራውያን አካል፣ የፀሐይ፣ የጨረቃና የከዋክብት
ክብር የተለያየ እንደ ሆነ የሰው ሥጋም በተለያየ መከራ፣ በሽታና ሌላም ቢሞትም በክብርና በኃይል ይነሣል
የሚል ነው።
 ምድራዊ አካል (ሥጋ) እንዳለ ሁሉ ሰማያዊ አካል (በሕይወት መኖር) ስላለ ነው።
 መሬታዊ አዳምን እንደ መሰልን ሁሉ ሰማያዊ ክርስቶስን ልንመስል የግድ ስለሚሆን ነው።

ይህም ስለ የሙታን ትንሣኤ በተመለከተ (የኋላ ሕይወት) ስለ ሆነ እየተናገረ ያለው የተለያዩ ንግግሮችና ምሳሌዎች
ተጠቅሟል፤ ለሙታን መነሣት እንደ ማስረጃ ሁኖ የቀረበው የክርስቶስ መነሣት ነው፤ በዚህም በኵረ ሙታን ተብሏል፤
ሙታን ይነሡ ዘንድ የሚደረግ አዋጅ አለ፤ ይኸውም ምሳሌና ሰው ሰውኛ አነጋገር ሲሆን የመለከት መነፋት ነው፤
በዚህም ጊዜ ሙታን እንደ ዓይን ጥቅሻ ወድያው ይነሣሉ ያለ ሲሆን የሙታን መነሣትን ”ምሥጢር’’ በማለት
ገልጾታል፤ ሙታን በመነሣት የሚያሸንፉት ሞት ”የኋላ ጠላት’’ ተብሎ ተገልጿል።

ምዕራፍ 16

16.1. 1-4 ለድሀ አማኞች ገንዘብ ማሰባሰብ


ጳውሎስ በየደረሰበት ቦታ (በተለይም በገላትያ፣ በአካይያና በመቄዶንያ) ለተቸገሩ ምእመናን ከምእመናን እርዳታ
በማሰባሰብ ያካፍላል፤ ምእመናኑ በዚህ ተግባር ክርስትናቸውን ይገልጹበታል፤ ምክንያቱም በእምነት ከመሰሏቸው
በመንፈስ ቅዱስ ሥራ (በእርዳታ) ይመስሏቸው ዘንድ ጳውሎስ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በዚህ ያለው ሐሳብ
የሚያመለክተው ከቤታቸው ከፍለው እያስቀሩ መስጠት እንዳለባቸው ነው።

16.2. 5-12 የጉዞ ዕቅድ


ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንን ለማየት ዕቅድ አለው፤ ይሁን እንጂ እስከ በዓለ ኀምሳ ቀን በኤፌሶን መቆየት
ፈልጓል፤ ስለ ሆነም ነገሮች አልተመቻቹለትም፤ ከዚህ በመነሣት ጢሞቴዎስ ወደ እነርሱ ይመጣልና በማንኛውም ነገር
እንዲራዱትና ያለ ፍርሃት በነፃነት ይኖር ዘንድ ያሳስባቸዋል፤ ስለ አጵሎስም በተመቸው ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል
ይነግራቸዋል።

16.3.13-24 የማጠቃለያ መልእክትና ሰላምታ


በዚህ ምንባብ ያለው ኃይለ ቃል የሚያስረዳው፦ የመጨረሻ ምክርና ሰላምታ እንደ አደረገ ነው፤ ይህም የተለመደው
የማጠቃለያ ሐሳቡ ነው።

16.4.የ 1 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ማጠቃለያ


ይህ መልእክት፦ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያለውን ችግር በራስዋ መፍታት እንደ ተሳናት፣ በውስጧ ታላቅ
መከፋፈል እንደ ተፈጠረ፣ የሥነ ምግባር ጉድለት እንደ ተገኘባት፣ በተለያየ የግሪክ ፍልስፍናና ጣዖታዊ ሥራ እንደ
ተዋጠች ያብራራል።

ውድ ተማሪ ሆይ ከዚህ በታች ከ 1 ኛ ቆሮንቶስ የተውጣጡ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውልሃል፤ ስለዚህ 1 ኛ


ቆሮንቶስን በማንበብ እንደ ቀረቡልህ ዓይነት መልስ::

መልመጃ አንድ: እውነት ወይም ሐሰት በል


1. በምዕ.15 መላው ምንባብ 100% ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ የሙታንና የክርስቶስ ትንሣኤ ነው
2. በትንቢት መናገር ለማያምኑ ምልክት ሲሆን በልሳን(ቋንቋ) መናገር ለሚያምኑ ምልክት ነው
3. እንደ ጳውሎስ አነጋገር ለቆሮንቶስ ምእመናን ጳውሎስን መምሰል በቂ ይሆናል
4. ጳውሎስ ለዚህ ዓለም ጠበብት የሚነግረው ጥበብ ተሠውሮ የነበረና ተገልጦ ያለ ነው
5. በቆሮንቶስ ምእመናን መካከል እየተደረገ ያለው ዝሙት በአሕዛብ እንኳ የማይደረግ ነው

መልመጃ ሁለት: ምረጥ

1. ማንም በሰው አይመካ :: የተሰመረበት ሰው ከሚከተሉት ማንን ያመለክታል?


ሀ/ጳውሎስን ለ/አጵሎስን ሐ/ጴጥሮስን መ/ሁሉን
2. ጳውሎስ ሌላውን ሰው ላለመጉዳት ብሎ የሚተወው ነገር?
ሀ/አለ ለ/የለም ሐ/አይኖርም መ/እንደ ሁኔታው ነው
3. ሙሉ በሙሉ ስለ የፍቅር የበላይነት የሚናገር ምዕራፍ ምዕራፍ_____ ነው
ሀ/14 ለ/13 ሐ/12 መ/11
4. ከሥጋዊ ሞትና ሥጋዊ ትንሣኤ አንጻር ሥጋዊ አካልና መንፈሳዊ አካል ከታች የሚወክሏቸው?
ሀ/ ፊተኛው አዳም ለ/ኋለኛው አዳም ሐ/ፊተኛው አዳምና ኋለኛው አዳም መ/ሁሉም መልስ ነው
5. የሞት መውጊያ ኃጢአት ሲሆን የኃጢአት ኃይል ምንድነው ተባለ?
ሀ/ሞት ለ/ኃጢአት ሐ/ዲያብሎስ መ/ሕግ

መልመጃ ሦስት: (የጻፍ ጥያቄ) ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች ባጭር ባጭሩ ግለጥ

1. የዚህ ዓለም ጠበብት በጥበባቸው የማያውቁት የእግዚአብሔር ጥበብ የትኛው ጥበብ ነው?
2. የእግዚአብሔር ጥበብ በዚህ ዓለም ዘንድ ሞኝነት እንደ ሆነች የዓለም ጥበብስ በእግዚአብሔር ዘንድ ምን
ሆነች?
3. በምእመናኑ መካከል ያሉት አጥፊዎችን ራሳቸው ምእመናኑ ይፈርዱባቸዋል፣ በውጭ ያሉትንስ (አሕዛብንስ)
ማን ይፈርድባቸዋል?
4. ከሥጋው ውጭ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ ከሥጋው ውጭ ኃጢአት ይሠራል፣ በሥጋው የሚያመነዝር ግን በምኑ
ላይ ኃጢአት ይሠራል?
5. ተክል የቆሮንቶስ ምእመናንን የተከለ፣ ውኃን ያጠጣና ያሳደገ ማን ነው? ተካይ_______ አጠጪ ____
አሳዳጊ__________ ::
ክፍል አራት የ 2 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት

4.1.መግቢያ
የዚህ መልእክት ጸሐፊ ጳውሎስ ነው (1፥1፣10፥1)። መልእክቱ የጳውሎስ የአጻጻፍ ስልት ጎልቶ የሚታይበት ሲሆን፣
ከሌሎች መልእክቶቹ ይልቅ በዚህኛው ሰፋ ያለ ነገር ስለ ራሱ ተጽፎ እናገኛለን።

4.2.የተጻፈበት ጊዜና ቦታ
የተጻፈበት ጊዜ ከሞላ ጐደል 55 ዓ/ም ገደማ መሆኑ የተገኙ መረጃዎች ያስረዳሉ፤ ከ 1 ኛ ቆሮ.16፥5-8
እንደምንረዳው የመጀመሪያው የቆሮንቶስ መልእክት የተጻፈው ከበዓለ ኀምሳ በፊት በኤፌሶን ሳለ ሲሆን፣ ሁለተኛው
ደግሞ የተጻፈው በኋላ ክረምት ከመግባቱ በፊት በዝያው ዓመት ነው፤ የተጻፈበት ቦታ በመቄዶንያ ፊልጵስዩስ ነው።

4.3.የተጻፈላቸው ሰዎችና መልእክቱን የወሰዱ ሰዎች


የተጻፈላቸው ሰዎች በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ያሉ ምእመናን ሲሆኑ መልእክቱን ከመቄዶንያ ፊልጵስዩስ ወደ
ቆሮንቶስ የወሰዱ ሰዎች ደግሞ ሉቃስና ቲቶ ናቸው።

4.4.ዐላማው
በቆሮንቶስ የጳውሎስን ሐዋርያዊ ክብር የሚነኩና ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያታልሉ ሐሰተኛ መምህራን ሠርገው
ገብተዋል፤ በዚህም ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ እነዚህ ሐሰተኛ መምህራን ትምህርት ማዘንበልዋ አይቀሬ ነው፤ ስለዚህ ይህ
ከመሆኑ በፊት ሁኔታውን በመረዳት በሐዋርያዊ አስተምህሮ ጸንታ እንድትኖር ማድረግ ነው።

ምዕራፍ 1

1.1.1-11 ምስጋናና ስለ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን መከራ መቀበል


ጳውሎስ ከ 1-2 ባለው ምንባብ ስለ ራሱ አድራሻና ስለ ምእመናኑ አድራሻ ከተናገረ በኋላ፣ እንዲሁም ስለ ሁሉም ነገር
ለእግዚአብሔር ምስጋናን ካቀረበ በኋላ፦

1. እግዚአብሔር በአስቻለው ችሎታ በመከራ ጊዜ እንደሚጸናና ሌሎችንም እንደሚያጸና


2. መከራ የሚቀበለው እነርሱ ይድኑ ዘንድ እንደ ሆነ
3. በእስያ የደረሰበትን ስቃይ ሊያውቁለት እንደሚፈልግ
4. ምንም እንኳ በየቦታው ስቃይ ቢኖርበትም በእግዚአብሔር ተስፋ እንደ አደረገ ተናግሯል።
1.2.12-24 ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንን ይጐበኛል
የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንን ለመጐብኘት ካቀደ ብዙ ጊዜ ሁኖታል፤ ይሁን እንጂ ሁኔታዎች ስላልተመቹለት መጐብኘት
አልቻለም፤ ቢሆንም አንድ ቀን ይችን ቤተ ክርስቲያን እንደሚጐበኝ ተስፋ አለው፤ ይህም የሆነበት ምክንያት
የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት መመኪያው ስለ ሆነች ነው፤ ምክንያቱም በእርሷ ልብ ውስጥ ያደረው
በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር፤ ስለዚህም በተመለከተ ”እናንተ ታስተውሉ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ’’
ብሏል። ስለዚህ በእነርሱ የተሰበከው ክርስቶስ አዎን (እውነት) ብቻ ስለ ሆነ ይህን አዎን (እውነት) አጥብቀው ሊይዙ
ይገባል፤ በዚህ ክርስቶስ እርሱንና እነርሱን እግዚአብሔር ቀብቷቸዋል (ቀድሷቸዋል)፤ የመንፈስ ቅዱስንም መያዣ
(የመጀመሪያ ክብር) ሰጥቷቸዋል፤ ጻድቃን ከትንሣኤ ዘጉባኤ በፊት የሚያገኙት ክብር መያዣ (የመጀመሪያ) ይባላል።

ምዕራፍ 2

2.1.1-11 እውነትን ስለ መናገር


ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ጠንካራ ጠንካራ የሆኑ ቃላትን በየቦታው ሲናገር ተሰምቷል፤ ይህን ያደረገበት
ምክንያት ደግሞ ወደ ቆሮንቶስ በመጣ ጊዜ በምእመናኑ መካከል አንዳችም ችግር (መለያየት) እንዳይቆየው ነው፤
ስለዚህ ምእመናኑ በእነዚህ ጠንካራ ቃላቶች ማዘን የለባቸውም፤ ከዚህ ይልቅ እነርሱን አብዝቶ የሚወድበትን ፍቅር
ሊያውቁለት ይገባል። የሚያዝንበት ክፍል (አካል) ካለ ግን ኀዘኑ የእነርሱም እንደሚሆን የገለጸ ሲሆን ይህን ዓይነቱ ሰው
ደግሞ ይቅር ማለት እንዳለባቸው ተናግሯል፤ ምክንያቱም የሚያሳዝናቸው ከሰይጣን የተነሣ መሆኑን አይስቱትምና።
ስለዚህ አዝኖ ወደ እነርሱ እንደማይመጣ እውነቱን ይነግራቸዋል።

2.2.12-17 ጳውሎስ ቲቶን ባለማግኘቱ ምክንያት ዕረፍት አጥቻለሁ አለ


እዚህ ላይ ጢሮአዳ በደረሰ ጊዜ ብዙ ሰማዕያን (የተከፈተ በር) ቢያገኝም ቲቶን ባለማግኘቱ ምክንያት እንደ አዘነ፣ ነገር
ግን ለኃጥአን የሞት ሽታ፣ ለሚድኑት ደግሞ የሕይወት ሽታ እንደ ሆነ ይነግራቸዋል፤ እንዲህ የሆነበት ምክንያትም
የእግዚአብሔር ቃልን እንደሚሸቃቅጡ ሳይሆን በቅንነት በክርስቶስ ፊት ስለሚናገር ነው።

ምዕራፍ 3

3.1.1-6 የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሁሉም የሚያነባት የተጻፈች መልእክት ናት


በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንና በጳውሎስ መካከል እጅግ የጠበቀ መንፈሳዊ መወዳጀት አለ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት
ሌሎች ሐሰተኛ መምህራን በተንኮል እንደ አስተማሩ ሳይሆን በቅንነት በማስተማሩ ምክንያት ነው፤ ሌሎቹ፦ ከሐሰተኛ
መምህራኑ ወደ አማኞቹ፣ ከአማኞቹ ወደ ሐሰተኛ መምህራኑ አንዳንድ መሰናክል የሚሆኑ ቃላትን በመጻጻፍ ነው
የሚያስተምሩት፤ በእነ ጳውሎስ ዘንድ ግን ይህ ሁሉ የሌለ በመሆኑ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን፣ በእነ ጳውሎስ ልብ
ውስጥ የተጻፈችው በቀለም ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ቀለምነት ነው፤ ይህን ሂደት ”በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ
መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው’’ በማለት ሲገልጽ፣ እንዲህ የሆነበት ምክንያትም በፊደል (በሕግ) ሳይሆን
በመንፈስ (በሕገ ወንጌል) በማስተማሩ ምክንያት እንደ ሆነ ግልጽ አድርጓል። ምክንያቱም ፊደል (ሕግ) ይገድላልና።
መንፈስ (ወንጌል) ግን ያድናልና።

3.2.7-18 ወንጌልና ኦሪት


በዚህ ክፍል ያለው ምንባብ የሚያስረዳው ኦሪትና ወንጌል በክብር ደረጃ እንደ ተነጻጸሩ ሲሆን በንጽጽሩ ወንጌል
የበላይነቱን ደረጃ ይዛለች፤ ጳውሎስ ይህን ንጽጽር ማቅረቡ ከሕግ ወንጌል እንደምትበልጥ (በወንጌል ሕይወት እንደ
ተገኘ) ማስረዳት ነው፤ ምክንያቱም ወንጌል ባለችበት ሁሉ አርነት አለና።
ምዕራፍ 4

4.1.1-6 የክርስቶስ አስተምህሮ ስላለ ከክፉ ሥራ መቆጠብ ይገባል


በ 3፥7-18 ባለው ምንባብ ስለ ክርስቶስ አስተምህሮ (ወንጌል) በተለመከተ ተናግሮ ነበር፤ ይህን የመናገሩ ምክንያት
ይህ (ወንጌል) ስላለ ከውሸት እንራቅ ለማለት ነው፤ በዚህ መሠረት ”የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም’’
በማለት ያስተምራል፤ ይህ አስተምህሮ የክርስቶስ የብርሃን ወንጌል ላልበራላቸው (ለማያምኑት) ሰዎች ሥውር ነው
ተብሏል፤ ለእነ ጳውሎስ ግን የብርሃንና የእውቀት ፋና በመሆን የተገለጠ ነው፤ ምክንያቱም ”በጨለማ ብርሃን ይሁን‘
ያለ እግዚአብሔር፦ ክርስቶስ በልባቸው እንዲሳል አድርጓልና።

4.2.7-16 ስለ ሙታን ትንሣኤ


ጳውሎስ ከእግዚአብሔር የሚደረግለትን እገዛ ምን ጊዜም በፊት ያስቀድማል፤ ያን ያህል የወንጌል አገልግሎት እየሰጠ
ያለው እግዚአብሔር ስለሚያግዘው ነውና፤ ይህም የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእርሱ ስላልሆነ ነው፤ ከዚህ
በመነሣት የእግዚአብሔር የኃይሉ ታላቅነት በእርሱ ዘንድ የሌለ መስሎ እንዳይታያቸው በሸክላው (በሥጋው) ውስጥ
መዝገብ ማለት ሃይማኖትና እውቀት ሰፍሯል፤ ከዚህ የተነሣ ምንም እንኳ በዓለም ዘንድ የተለያየ ችግር ቢገጥምበትም
የክርስቶስን ሞትና ሕይወት በሥጋው ተሸክሞ ስለሚሄድ የአሸናፊነቱን ኃይል ይዟል፤ እነዚህ ምእመናንም ይህን ያውቁ
ዘንድ ይወዳል፤ ስለዚህ፦

1. የሚያምነውን እንደሚናገር
2. ክርስቶስን ከሞት ያስነሣ አምላክ እነርሱንም እንደሚያስነሣ
3. በዓለም ዘንድ የሚቀበሉት ልዩ ልዩ መከራ የዘለዓለም ሕይወትን እንደሚያደርግላቸው
4. ሥጋቸው ቢጠፋ ስንኳ መንፈሳቸው ዕለት ዕለት እንደሚታደስ
5. የሚታየው ጊዜአዊ እንደ ሆነ፤ የማይታየው ግን ዘለዓለማዊ እንደ ሆነ አስታውቋቸዋል።

ምዕራፍ 5

5.1.1-10 ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በሰማይ የሕይወት ተስፋ አላት


በዚህ ምንባብ ሥጋን ምድራዊ ድንኳን ነፍስን ሰማያዊ ድንኳን አድርጎ ያቀርባል፤ ድንኳን ለጊዜው ተተክሎ ኋላ ቆይቶ
የሚነቀል ነው፤ በተለይም በስደት ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች በየደረሱበት ስፍራ የሚገለገሉበት መሣሪያ ነው፤
ጳውሎስም ምድራዊውን ሥጋ በዚህ ሂደት ያየዋል፤ ሰማያዊው ድንኳን ግን ሰማያዊውን ሥጋ ይመለከታል፤ ጳውሎስ
ይህን ምሳሌ የመሰለበት ዐላማ፦

 ምድራዊው ድንኳን (ሥጋ) ቢፈርስ ስንኳ ሰማያዊ ድንኳን (ሥጋ) አለን ለማለት ነው።
 ሰዎች ምን ጊዜም የሥጋቸው ስደተኞች እንደ ሆኑ ለማስረዳት ነው።

በዚህ ድንኳን (ሥጋ) መኖር ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነም ”በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን’’ በማለት
ተናግሯል፤ በመጨረሻም እያንዳንዱ በዚህ ድንኳን (ሥጋ) የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁሉም በክርስቶስ
የፍርድ ወንበር ፊት ይቀርብ ዘንድ እንዳለው አስረድቷል።

5.2.11-21 ሁሉም በክርስቶስ አዲስ ሁኗል


ጳውሎስ በመልእክታቱ ውስጥ ማእከል የሚያደርገው እውነታ አለ፤ ይኸውም የክርስቶስ ቤዛነት ነው፤ ይህን ከሰው ልብ
ለማስረጽ ሲል ደግሞ የተለያዩ ምሳሌዎችንና ድርጊቶችን ያካትታል፤ እነዚህ ”የትምህርቱ ማስደገፊያ’’ በመባል
ይታወቃሉ፤ ስለዚህ ይህን ለማስረዳት ሲል፦

1. በእውነት ሳይሆን በውሸት የሚመኩ ሰዎችን ታሳፍሩ ዘንድ ይህን አስተምራችኋለሁ ይላል።
2. በዓለም ዘንድ እብዶች ቢባሉም በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንዳላቸው ግልጽ ያደርግላቸዋል።
3. አንድ ክርስቶስ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ ይነግራቸዋል።
4. ሁሉም በክርስቶስ ሞት እንደ ታደሰ ያስታውቃቸዋል።
5. እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ እንዳስታረቀ ግልጽ ያደርግላቸዋል።
6. እግዚአብሔር በእነርሱ አድሮ ያስተምርና ይማልድ ዘንድ እንዳለው ይነግራቸዋል።
7. እግዚአብሔር ስለ ሰዎች ፈንታ ክርስቶስን እንደ ኃጢአተኛ እንዳደረገው ያስተምራቸዋል።

ምዕራፍ 6

6.1.1-13 ስለ ክርስቶስ ስም መጋደል እንደሚገባ


ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አማኞች የእግዚአብሔርን ጸጋ ያለ አዋቂነት እንዳይቀበሉ ስጋት አለበት፤
ምክንያቱም ጸጋው የተሰጣቸው ለምን ዐላማ እንደ ሆነ ካላወቁ ለከንቱ ይሆናልና፤ ስለዚህ በቍ.2 እንደ ተናገረው
የእግዚአብሔር ማዳን፦ ማዳን በሆነበት ወራት ስለ ተደረገላቸው ይህን የመዳን ቀን ያውቁ ዘንድ ይፈለጋል፤ ስለዚህም
አገልግሎታቸውን በንጽሕና ሊያሳኩ ይገባል፤ ምክንያቱም በሁሉም ነገር የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደ ሆኑ
ይቆጠራልና። ይህ አገልግሎት ከ 5-10 ባለው ምንባብ እንደ ተገለጠው በልዩ ልዩ የዓለም መከራና በልዩ ልዩ መልካም
ሥራዎች የሚገለጽ እንደ ሆነ አስታውቋል፤ ከዚህ የተነሣ የእነ ጳውሎስ ልቡና ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሰፊ ሜዳ
(የአስተምህሮ ስፍራ) በመሆኑ ሆዳቸውን (ልባቸውን) ማጥበብ (መዝጋት) የለባቸውም፤ ከዚህ ይልቅ መንፈሳዊ
ብድራትን መመለስ (መስማት) አለባቸው።

6.2.14-18 የእግዚአብሔር መኖሪያ ቤተ መቅደስ


በዚህ ምንባብ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከማያምኑ ሰዎች ጋር በማንኛው ክፉ ሥራ መጠመድ እንደሌለባት
ያስጠነቅቃል፤ ለዚህም ”ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው?
ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው?’’ በማለት በምሳሌ መልክ ያስረዳል፤ ምክንያቱም
የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናትና።

ምዕራፍ 7

7.1.1-16 በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ተደረገው ንስሐ የጳውሎስ ደስታ


እንደ 2 ኛ ቆሮንቶስ 6፥16-18 ምንባብ ገለጻ ጳውሎስና የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ
መቅደስ ናቸው፤ ይህ ተስፋ ለጳውሎስና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ነው፤ ስለዚህ ይህን የመሰለ ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ
ካላቸው ከማንኛውም ኃጢአት ራሳቸውን ሊያነጹ ይገባል፤ ከዚህ በመነሣት ልባቸውን ለእግዚአብሔር ቃል ክፍት
ማድረግ እንዳለባቸው ካሳየ በኋላ፦

 በመጀመሪያው መልእክት ጠንካራ ቃላትን ቢናገራቸውም ምንም እንዳላጠፋና ማንንም እንዳላታለለ


ያስታውቃቸዋል።
 ስለ እነርሱ እምነቱ ታላቅ እንደ ሆነና ትምክህቱም ታላቅ እንደ ሆነ ይገልጽላቸዋል።
 በመቄዶንያ ታላቅ ፈተና ቢደርስባቸውም በቲቶ መምጣት እንደ ተጽናኑ ይነግራቸዋል።

ቲቶ ይህን መልእክት ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ያደረሰ ደቀ መዝሙር ነው፤ የአማኞቹን ስለ ጳውሎስ ማዘንና
ማልቀስ ለጳውሎስ አስረድቷል፤ ይህ ድርጊት እነ ጳውሎስን የሚያጽናና ነበር።

 ከዚህ በፊት በጠንካራ ቃላት ቢያሳዝናቸውም እንደማይጸጸት ያስታውቃቸዋል።

በመጀመሪያው መልእክት በጠንካራ ቃላት ገሥጿቸው ነበር (1 ኛ ቆሮ.3፥1-4፣ 6፥1-8)፤ ቢሆንም ይህ ተግሣጽ
ለንስሐና ለሕይወት ስለ አበቃቸው አይጸጸትም።

 ስለ እግዚአብሔር ብለው የገቡት ንስሐ (ያዘኑት ኀዘን) ወደ መዳን እንደሚያደርስ ይገልጽላቸዋል።


 መልእክቱን እየጻፈላቸው ያለው ስለ በዳይና ተበዳይ ጉዳይ ሳይሆን ትጋታቸው በእግዚአብሔር ፊት ይገለጥ
ዘንድ እንደ ሆነ አጽንኦት ሰጥቶ ያስረዳቸዋል።
 ስለ እነርሱ የሚመካው መመካት ቲቶን በመቀበላቸው ምክንያት እንደ ተረጋገጠለት ይነግራቸዋል።

ምዕራፍ 8

8.1. 1-15 ለድሆች ምእመናን መዋጮ (ገንዘብ) መስጠት እንደሚገባ


የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በድሆች ምእመናን ላይ ያላትን መልካም እሳቤ ከቲቶ ሰምቷል፤ በቲቶ መምጣት ደስ
ከተሰኘበት ተግባር አንዱም ይህ እርዳታ(አስተዋጽኦ) ነው፤ ታድያ በዚህ እንዲቀጥሉበት የመቄዶንያ ቤተ ክርስቲያን
ለድሆች ምእመናን የሰጠችውን እርዳታ (አስተዋጽኦ) እንደ አርዓያ ያቀርብላታል፤ እንደ ጳውሎስ አነጋገር የመቄዶንያ
ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳ በተለያየ ችግር ውስጥ ብትሆንም ይህን ከምንም ሳትቆጥር በጳውሎስ ግፊት ሳይሆን
በራሷ መልካም ፈቃድ ለድሆች ምእመናን መዋጮን ሰጥታለች፤ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንም ይህን (ጸጋ) መዋጮ
እንዳላትና እንደ ራሷ ፈቃድ ልትቀጥልበት ይገባል፤ ምክንያቱም ”ብዙ ያከማቸ አላተረፈም፣ ጥቂትም ያከማቸ
አላጎደለም’’ ተብሏና (ዘጸ.16፥18) የእርሷ ትርፍ የሌላውን ጉድለት፣ የሌላው ትርፍ የእርሷን ጉድለት መሙላት
ይችላልና። በተጨማሪም እርሷ ባለ ጸጋ ትሆን ዘንድ ክርስቶስ ድሀ ሁኗልና። በመሆኑም ይህ መልካም ጅምር ከፍጻሜ
ይደርስ ዘንድ ከማብራሪያ ጋር ነግሯታል።

8.2.16-24 ቲቶ ወደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ይላካል ስለ መባሉ


ቲቶ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የሚደርሰውን መልእክት ያደርስ ዘንድ በጳውሎስ ተመርጧል፤ በሁለተኛ ደረጃ
የተመረጠ ወንድምም አለ፤ ይህ ወንድም በግልጽ ስሙ ባይጠቀስም ከሉቃስ እንደማያልፍ ብዙ ሊቃውንት ይስማማሉ፤
ከዚህ አንጻር ነው በመግቢያ መልእክቱ፦ መልእክት አድራሾች ቲቶና ሉቃስ ናቸው የተባለው። እንደዚህ ምንባብ ገለጻ
እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት በጳውሎስና በመላው አብያተ ክርስቲያናት የተመሰገኑና የታወቁ ናቸው፤ ከዚህ የተነሣ
ነው ወደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን (ወደ እናንተ) ይመጣል (ይመጣሉ) ያለው፤ በመሆኑም የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን
መዋጮውን (ጸጋዋን) በእነዚህ ደቀ መዛሙርት ፊት ልታረጋግጥ ይጠይቃታል፤ ስጦታውም (መዋጮው) በነቀፋ
የሚያልፍ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንደሚገባት ያስጠነቅቃል።

ምዕራፍ 9

9.1. 1-15 በኢየሩሳሌም ላሉ ድሆች ምእመናን ስለሚሰጥ መዋጮ


በ 8፥1-15 ባለው ምንባብ የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን ስጦታ (መዋጮ) ለመቄዶንያ ቤተ ክርስቲያን የተናገረ
ይመስላል፤ ምክንያቱም የቍ.2 ጽንሰ ሐሳብ ይህን ያመለክታል፤ የመቄዶንያ ቤተ ክርስቲያን ስጦታም ለቆሮንቶስ ቤተ
ክርስቲያን በተመሳሳይ መነገሩ ይታወቃል (8፥1)፤ ስለዚህ በዚህ ክፍል ውስጥ ያለው አጠቃላይ ዋና ሐሳብ፦ የቆሮንቶስ
ምእመናን በማድረግ ላይ ባሉት ስጦታ በዝያው እንዲቀጥሉበት ማደፋፈሩንና ማወደሱን ያስረዳል፤ ሲሰጡ ግን፦
ፍጻሜው ያምር ዘንድ ያለ አንዳች ጽነት (የሐሳብ መከፋፈል) መሆን እንዳለበት በምሳሌና ከመዝሙረ ዳዊት ጠቅሶ
አስረድቷል (ቍ.6-9)፤ በተጨማሪም ይህ ልግስናቸው ነዳያኑን ምእመናን ብቻ ሳይሆን ደስ የሚያሰኘው
እግዚአብሔርንና እርሱን ደስ እንደሚያሰኝ አስረድቷቸዋል። በዚህ ምክንያትም ”ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር
ይመስገን’’ በማለት የመዋጮውን ጉዳይ ይደመድማል።

ምዕራፍ 10

10.1. 1-18 መንፈሳዊ ኃይል


በእነ ጳውሎስ ላይ የሚሰነዘር የተለያየ ተቃውሞና ስድብ አለ፤ ይህን ተቃውሞና ስድብ በዋናነት የሚያደርሱት ደግሞ
የአይሁድ (እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዙ መዳን አይቻልም የሚሉ) መምህራን ናቸው፤ እነዚህ ምን ጊዜም
ከጳውሎስና ከመሰሎቹ ጋር እጅግ የከረረ ጥላቻ አላቸው፤ ይህን ደግሞ ጳውሎስና አማኞቹ ያውቃሉ፤ ታድያ ለእነዚህ
የሚደረገው ዘመቻ ሥጋዊ ዘመቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዘመቻ ይሆናል፤ ይህም የሚሆነው በሥጋዊ አስተሳሰብ አይደለም
ማለት በሰው ልማድ መዋጋት አይሆንም፤ ምክንያቱም የጳውሎስ የጦር ዕቃ ሥጋዊ የጦር ዕቃ ሳይሆን የጽድቅ ጦር ዕቃ
ነው፤ በዚህ የጽድቅ ጦር ዕቃ ሁሉን ወደ ክርስቶስ መማረክ ይችላሉ፤ ስለዚህ እውነቱ ይህ በመሆኑ መታዘዛቸው
በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ሊበቀል እንደ ተዘጋጀ ይነግራቸዋል፤ እነርሱም በፊታቸው ያለውን ጸጋ ሊያውቁ
ይገባቸዋል፤ ይህን መልእክት ማስተላለፉም እነርሱን ለማፍረስ ሳይሆን ለማነጽ ነው፤ ከዚህም በላይ ”ጳውሎስ ደካማ
ነው’’ የሚል አመለካከት እየተሰነዘረበት በመሆኑ ይህን ማስተባበል ፈልጓል (10-12)፤ ይህንንም እንደ ትምክሕት
በማየት አይደለም፤ እግዚአብሔር እንደ ወሰነለት መጠን እንደ ሆነ ከ 13-17 ባለው ምንባብ አስረድቷል፤ ምክንያቱም
እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና። በዝያውም ላይ
ጳውሎስ ”የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ’’ ብሎ የሚያስተምር ሐዋርያ ነው። በመሆኑም የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን
ይህን ታውቅለት ዘንድ ይህንና የመሰለውን ሁሉ እዚህ ላይ ጽፏል።

ምዕራፍ 11

11.1. 1-5 የባእድ ትምህርትን ስለ አለመቀበል


ጳውሎስ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያስተውለው እውነታ አለ፤ ይኸውም፦

1. እርሱን እንደ እብድ የምታይበት ሁኔታ እንዳለ ነው።


2. ሌላ ክርስቶስን፣ ሌላ ትምህርትንና ሌላ መንፈስን ልትቀበል እንደምታሰብ ነው።

ይህ ሁኔታ ስለ አሳሰበው እንደሚከተለው ያስተምራቸዋል፤ ይኸውም፦

ሀ/ እንደ እብድ ቢያዩትም በእብድነቱ ያስተምራቸው ዘንድ ጥቂት ይታገሡት ዘንድ ነው።

ለ/ እንደ ንጽሕት ድንግል ለክርስቶስ እንደ አጫቸው ነው።

ሐ/ እርሱ ያልነገራቸው ሌላ ክርስቶስን ለመቀበል ቢዘጋጁም ጥቂት ይጠብቁት ዘንድ ነው።

ነገር ግን ይህን በማለት ቢያስረዳቸውም መማር ካለባቸው እውነታ ሁሉ አንዳችም እንደ አላጎደለባቸው ጨምሮ
አስታውቋል።

11.2. 6-15 ወንጌልን ያለ ዋጋ ስለ ማስተማር


ጳውሎስ በጊዜው በነበሩ ሐሰተኛ መምህራን ገንዘብ እየተቀበለ ያስተምራል እየተባለ ነበር፤ ይህን ሐሰት ደግሞ ራሱ
ያውቀዋል፤ በአማኞቹ መካከልም ይህ ሐሰተኛ ወሬ ሳይስተጋባ አይቀርም፤ ይሁን እንጂ ጳውሎስ ከዚህ ሁሉ ሐሰት ነጻ
ሐዋርያ ነበር፤ ስለ ሆነም ይህን እንደ ግብአት በመጠቀም እንዴት እንደሚያስተምር ማሳወቅ ፈልጓል፤ በዚህ መሠረት
እውነታውን አስቀምጧል፤ ይኸውም፦

1. ያለ ዋጋ እንደ አስተማራቸው ግልጽ አድርጓል (ቍ.7)።


2. ያስተምራቸው ዘንድ ዋጋ የተቀበለበት ጊዜ እንደሌለና ለገንዘባቸውን እንዳልሳሳ ተናግሯል (ቍ.8)። ለዚህም
አስተምሮ ዋጋ መቀበል እንደሚገባ ከዚህ በፊት አስረድቷል (1 ቆሮ.9፥3-12)።
3. ዋጋ የሚገባው ቢሆንም ላለመክበድ ሲል እየተቀበለ እንዳልሆነ አስረድቷል (ቍ.9)።
4. ለጠላት ምክንያት ላለመስጠት ሲል አሁንም ዋጋ እንደማይቀበል አስታውቋል። የሐሰተኞቹ መምህራን አባባል
ግን እንደማይደንቅ በምሳሌ አስረድቷል (14-15)።
11.3.16-33 መመካት አይገባም እንጂ መመካት የሚገባ ቢሆን ከጳውሎስ በላይ ማንም አይመካም ነበር
ጳውሎስ ከምንም በላይ ትምክሕትን ያወግዛል፤ ይሁን እንጂ ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን በማለት ለሚመኩት ሐሰተኞች
የመመካትን በር መዝጋት ስለ ፈለገ እርሱም የሚመካበት እውነታ እንዳለ ይናገራል፤ የሚመካባቸው ነገሮችም ከ 22-
33 ባለው ምንባብ ተዘርዝረዋል፤ ይህም በሐረገ ትውልዱና በደረሰበት አጠቃላይ መከራ ላይ የሚያጠነጥን ነው።
ምናልባት ይህን እንደ መመኪያ አድርጎ ማቅረቡ፦ እነዝያ ሐሰተኞች መምህራን የሚመኩት በዚህ ሁኔታ ሁኖ ሊሆን
ይችላል፤ ቢሆንም ከላይ እንደ ተባለው የመመኪያ በሩን ለመዝጋት ነው እንጂ የጳውሎስ መመኪያ አሁንም አንድ
እግዚአብሔር ነው። ምክንያቱም እርሱ የሚናገረው እግዚአብሔር ያዘዘውን ነውና። ይህንንም ”ሞኝ ብሆንም
በሞኝነት እናገር ዘንድ ስሙኝ‘ ካለ በኋላ ማንኛውንም እንዴት መታገሥ እንዳለባቸው በመከረ ጊዜ አብራርቷል።

ምዕራፍ 12

12.1. 1-10 ጳውሎስ ያየው ራእይ


ጳውሎስ እነዝያን የሐሰት መምህራን መሞገትን አላቆመም፤ በዚህ መሠረት እዚህ ላይም የሚመካበት ነገር አለው፤
ይኸውም እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ የተነጠቀው መነጠቅ ነው፤ ጳውሎስ በእግዚአብሔር ራእይና መገለጥ
ምክንያት ወደ ሦስተኛው ሰማይ እንደ ተነጠቀ ያውቃል፤ ነገር ግን ራእዩና መገለጡ ከዓቅሙ በላይ ስለ ነበረ፦
የተነጠቀው ሰው እርሱ እንደ ሆነ በሚያሳምንና በማያሳምን አነጋገር ከ 14 ዓመት በፊት (ካመነ በኋላ) የሚያውቀው
ሰው እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ እንደ ተነጠቀ ይናገራል፤ እርሱ እንደ ሆነ እርገጠኛ ነገር ያለ ማስቀመጡ ምክንያት፦
የተነጠቀው ከነፍሱና ከሥጋው በየትኛው እንደ ሆነ እርግጠኛ አለመሆኑ ነው፤ ይህን በትክክል የሚያውቅ እግዚአብሔር
ነው። በዝያም ማንም መስማት የማችለውን ንግግር ሰምቷል፤ ይሁን እንጂ እርሱ በሰው ሰውኛ አነጋገር እንዲህ ቢልም
እውነቱ ግን ራሱ ጳውሎስ ነው፤ ይህ ጸጋ እውነት በመሆኑ በዚህ ይመካል፤ ቢሆንም በሁለት ምክንያቶች በፍጹም
አይመካም፤ ይኸውም፦

1. ሲመካ ያየውና የሰማው ሁሉ በይበልጥ ሞኝ ነው ብሎ እንዳይቆጥረው ነው።


2. በዚህ ጸጋ እንዳይመካ (እንዳይታበይ) የሥጋው መውጊያ ስለ ተሰጠው ነው።

ይህ የሥጋ መውጊያ የሰይጣን መልእክተኛ ተብሎ ተተርጉሟል፤ ይኸውም እነዝያ ሐሰተኛ መምህራን ናቸው፤ እነዚህ
ጳውሎስን በተቃውሞ የሚያጠነክሩ ናቸው፤ ሰው በጎኑ ጠላት ያለበት ከሆነ ጠንካራ ይሆናል፤ ይህም ብቻ አይደለም፤
ሥጋው የድካም ምንጭ በመሆኑ፦ ጳውሎስ ደካማ ለመሆኑ ማሳያ ነው። ስለዚህ እንደ ልቡ ተኩራርቶ የሚመካበት
ሁኔታ የለውም፤ ምንም እንኳ መንፈሳዊ ድካሙ ኃይል እየሆነው እንዳለ ቢገልጽም። ሌላው በዚህ ክፍል የገለጸው
ሐሳብ ጸጋዬ ይበቃሃል እንደ ተባለ ነው፤ ይህም የጳውሎስ ኃይል በደዌ (በድካም) ያልቃልና የሚል ነው።

12.2.11-21 የጳውሎስ በደል በመከራ ሊገሥጻቸው ወደ አማኞቹ ካለመምጣቱ በቀር ሌላ አይደለም


በጳውሎስና በምእመናኑ መካከል መለያየት ያለ ይመስላል፤ ምክንያቱም ወደ እነርሱ ካልመጣ የሚያዝኑ ይመስላሉና።
እንዲያውም በግልጥ ያዘኑ ነበሩ፤ ከዚህ ሌላ ግን በሁለቱም ፍጹም መለያየት የለም፤ ከዚህ በመነሣት አጠቃላይ
ሁኔታውን ያስታውቃቸዋል፤ይኸውም፦

 ከዋናዎቹ ሐዋርያት ትምህርት አንዳችም እንዳላጎደለባቸው ነው።


 በደሉ ወደ እነርሱ ካለመምጣት በቀር ሌላ እንዳልሆነ ነው።
 እርሱ የፈለገው ገንዘባቸውን ሳይሆን እነርሱ እንደ ሆነ ነው።
 ገንዘብ ይቅርና ነፍሱን ስለ እነርሱ አሳልፎ እንደሚሰጥ ነው።
 በገንዘቡ (በመዋጨው) ዙርያ በጥበብ እንደ ያዛቸው ነው።
 ቲቶን መላኩና ጠንካራ ቃላትን መናገሩ እነርሱን ለማነጽ እንደ ሆነ ነው።
 ምናልባት ከ 20-21 ያሉ ሥራዎች በእነርሱ እየተሠሩ ካሉ የሚያዝንበት ጊዜ እንደሚኖር ነው።
ምዕራፍ 13

13.1. 1-10 የሩቅ ማስጠንቀቅያና ጸሎት


ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ካሰበ ብዙ ጊዜን አድርጓል፤ ይሁን እንጂ መምጣት አልተቻለውም፤
በዋናነት ለመምጣት ጫፍ ላይ የደረሰበት ጊዜ ሦስት ጊዜ ያህል እንዳሰበ ተናግሯል፤ ይህን እንደ መምጣት በመቍጠር
”ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው’’ ይላል፤ ቢሆንም እንደ ዋናው መምጣት አይቆጠርም እንጂ መምጣቱ ግን
ሁለት ጊዜ እንደ መጣ ይመሰክራል፤ ይህን የተናገረበት ምክንያት ነገር ሁሉ በሦስት ምስክር ስለሚጸና የሚነግራቸው
ነገር ምን ያህል የጸና እንደ ሆነ ለመንገር ነው፤ ማስጠንቀቅያው፦

1. እንደ ገና በመጣ ጊዜ ለማንም እንደማይራራ ያመለክታል።


ሳይህደክም እየተመላለሰ ሊያስተምር እንደሚችል የሚናገረው፦ ክርስቶስ እነርሱን ለማስተማር ስለማይደክም
ነው፤ ጳውሎስም ከእርሱ ጋር በመድከም ከእርሱ ጋር በሕይወት ይኖራልና።
2. ራሳቸውን መፈተን (ማየት) እንዳለባቸው ያስገነዝባል።

ሌላው ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት፦

1. ክፉን እንዳያደርጉ እየጸለየ እንደ ሆነ ያውቁ ዘንድ ነው።


2. ጠንካራ ቃላትን መናገሩ ያስፈራራቸው ዘንድ ሳይሆን እውነት ሊናገር ስለ ፈለገ እንደ ሆነ ይረዱ ዘንድ ነው።
ሐዋርያዊ ሥልጣኑን ያገኘው ከክርስቶስ ስለ ሆነ በእውነት ላይ ተመሥርቶ እየጻፈላቸው እንደ ሆነ ሊያውቁ
የግድ ነው፤ ካልሆነ ሌላን ሰበብ ሊፈጥሩበት ይችላሉ።
3. ጠንካራ ቃላትን መናገሩ እነርሱን ለማነጽ እንደ ሆነ ነው።
4. እርሱ ደካማ (የማይረባ) መስሎ የሚታየው እነርሱ መልካምን ያደርጉ ዘንድ እንደ ሆነ ነው።

13.2. 11-14 የማጠቃለያ መልእክትና ሰላምታ


በዚህ ያለው ጽንሰ ሐሳብ በመልእክታቱ ማጠቃለያ አከባቢ የሚመክረውና የሚለው ሲሆን በተለይም እዚህ ላይ ልዩ
የሚያደርገው ”የክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅርና የመንፈስ ቅዱስ ኅብረትም ከሁላችሁ ጋር ይሁን’’ የሚለው
ንግግሩ ነው፤ ይህም ሦስቱን አካላት ማንሣቱ ነው።

13.3. የ 2 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ማጠቃለያ


ይህ መልእክት በውስጡ በያዘው ፍሬ ሐሳብ የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን ከልዩ ልዩ የሥነ ምግባር ብልሹነትና ክፉ
አሠራር የሚመልስ ነው፤ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በተለያየ የሥነ ምግባር ብልሹነት ወድቃ እንደ ነበረች በመልእክቱ
ውስጥ በብዛት ተጠቅሷል፤ በመሆኑ ጳውሎስ ይህን መልእክት በራሱ በመወከል የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከገባችበት
የሞራል ውድቀትና ምግባረ ብልሹነት ትወጣ ዘንድ አዘጋጅቶ ልኳል፤ መልእክቱን የወሰዱ ደቀ መዛሙርት ሉቃስና ቲቶ
እንደ ነበሩ ይታወቃል።

ዋቢ መጻሕፍት
 Lapsley/Brooks Foundation Dalas Texas USA- Addis Ababa Ethiopia 1994
 መጽሐፈ ግእዝ: ማኅበረ ሐዋርያት ፍሬ በ፲ወ፱፻ ፹ወ፩ ዓመተ ምሕረት
 መጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሐፍ ጋር በኢንተርናሽናል መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር
በ 1993 ዓ/ም የታተመ

ውድ ተማሪ ሆይ ከ 2 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት የተውጣጡ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውልሃል፤ 2 ኛ የቆሮንቶስ


መልእክትን በማንበብ እንደ ቀረቡልህ ዓይነት መልስ::

መልመጃ አንድ: እውነት ወይም ሐሰት በል


1. ጳውሎስ በዚህ መልእክት ውስጥ ጠንካራ ጠንካራ የሆኑ ቃላትን አልተጠቀመም።
2. የዚህ መልእክት አድራሽ ሉቃስና ቲቶ ናቸው።
3. መመካት የሚገባ ከሆነ ከጳውሎስ ወድያ የሚመካ የለም።
4. የመቄዶንያ ምእመናን መዋጮ ለቆሮንቶስ ምእመናን፣ የቆሮንቶስ ምእመናን መዋጮ ለመቄዶንያ ምእመናን
እንደ አርዓያ ሁኖ ተነግሯል።
5. በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አንዳችም የሥነ ምግባር ጉድለት አልታየም።

መልመጃ ሁለት: ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች መልስ

1. 2 ኛ የቆሮንቶስ መልእክት የተጻፈበት ቦታ የት ነው?


2. ጳውሎስ በመቄዶንያ ታላቅ ችግር በአጋጠመው ጊዜ በማን መምጣት ተጽናናሁ ይላል?
3. ጳውሎስ በራእይ እስከ ስንተኛው ሰማይ ደረስኩ ይላል?
4. በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትልቅ ጸጋ አለ ተብሏል፤ ይህ ትልቅ ጸጋ ምንድን ነው?
5. በዚህ መልእክት ማጠቃለያ ምዕራፍ በመጨረሻ ቍጥር የ 3 ቱ አካላት ስም እንዴት ተጽፏል?

የሐዋርያት ሥራ መልመጃዎች መልስ፦

መልመጃ አንድ: 1.ለ 2.ለ 3.ለ 4.መ 5.ለ

መልመጃ ሁለት: 1.ሐሰት 2.እውነት 3.እውነት 4.ሐሰት 5.ሐሰት

የሮሜ መልእክት መልመጃ መልስ፦ 1.ሐ 2.ሀ 3.ለ 4.ሀ 5.ለ

የ 1 ኛ ቆሮንቶስ መልእክት መልመጃዎች መልስ፦

መልመጃ አንድ: 1.እውነት 2.ሐሰት 3.እውነት 4.እውነት 5.እውነት

መልመጃ ሁለት: 1.መ 2.ለ 3.ለ 4.ሐ 5.መ

የ 2 ኛ ቆሮንቶስ መልመጃ፡

መልመጃ አንድ: 1.ሐሰት 2.እውነት 3.እውነት 4.እውነት 5.ሐሰት

መልመጃ ሁለት: 1.መቄዶንያ 2.በቲቶ 3.እስከ 3 ኛው ሰማይ ድረስ 4.መዋጮ 5.የክርስቶስ ጸጋ፣
የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት በሚል አገላለጽ።

You might also like