You are on page 1of 205

ትዝታ

ሀዱስ አሇማየሁ

፲፱፻፴፭ ዒ.ም

ii
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ማውጫ

መቅድም .................................................................................................................................................... 1

ምእራፍ አንድ .............................................................................................................................................. 2

የወልወል ግጭት .......................................................................................................................................... 2

ምእራፍ ሁለት ............................................................................................................................................. 9

ቅድመ - ዝግጅት .......................................................................................................................................... 9

ምእራፍ ሶስት ............................................................................................................................................ 16

ዝግጅት ..................................................................................................................................................... 16

ምእራፍ አራት ........................................................................................................................................... 27

የዘመቻው ጉዞ ........................................................................................................................................... 27

ምእራፍ አምስት ........................................................................................................................................ 31

ደባት......................................................................................................................................................... 31

ምእራፍ ስድስት......................................................................................................................................... 38

ደባጉና....................................................................................................................................................... 38

ምእራፍ ሰባት ............................................................................................................................................ 46

ተከዜ ........................................................................................................................................................ 46

ምእራፍ ስምንት ........................................................................................................................................ 51

ከደባጉና እስከ እንዳስላሴ ............................................................................................................................ 51

ምእራፍ ዘጠኝ ........................................................................................................................................... 55

የሰለክላካ ጦርነት ....................................................................................................................................... 55

ምእራፍ አስር ............................................................................................................................................ 62

ሽሽት ........................................................................................................................................................ 62

ምእራፍ አስራ አንድ ................................................................................................................................... 75

ሌላ ዘመቻ................................................................................................................................................. 75

ምእራፍ አስራ ሁለት .................................................................................................................................. 78

ከደባርቅ እስከ ሱዳን................................................................................................................................... 78

iii
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምእራፍ አስራ ሶስት ................................................................................................................................... 90

ሱዳን የቆዬንበት ጊዜ .................................................................................................................................. 90

ምእራፍ አስራ አራት ................................................................................................................................. 102

ከካርቱም እስከ ጎሬ................................................................................................................................... 102

ምእራፍ አስራ አምስት ............................................................................................................................. 109

ጎሬ .......................................................................................................................................................... 109

ምእራፍ አስራ ስድስት .............................................................................................................................. 117

ከጎሬ እስከ (ጎይ?) ..................................................................................................................................... 117

ምእራፍ አስራ ሰባት ................................................................................................................................. 125

ከጉይ እስከ ጉማ ....................................................................................................................................... 125

ምእራፍ አስራ ስምንት ............................................................................................................................. 133

ጌራ ......................................................................................................................................................... 133

ምእራፍ አስራ ዘጠኝ................................................................................................................................. 140

ጎጀብ....................................................................................................................................................... 140

ምእራፍ ሃያ ............................................................................................................................................. 150

ቦንጋ ....................................................................................................................................................... 150

ምእራፍ ሃያ አንድ .................................................................................................................................... 155

አዲስ አበባ............................................................................................................................................... 155

ምእራፍ ሃያ ሁለት ................................................................................................................................... 162

ካዲስ አበባ እስከ ፓንዛ ............................................................................................................................. 162

ምእራፍ ሃያ ሶስት .................................................................................................................................... 171

ፓንዛ ...................................................................................................................................................... 171

ምእራፍ ሃያ አራት .................................................................................................................................... 177

ሊፓሪ ..................................................................................................................................................... 177

ምእራፍ ሃያ አምስት ................................................................................................................................ 182

ሎንጎቡኮ ................................................................................................................................................. 182

ምእራፍ ሃያ ስድስት ................................................................................................................................. 194

ነፃነት....................................................................................................................................................... 194

iv
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሰው ቢሞት ፌቅር አይሞትም!!

ይህ ትንሽ መፅሏፌ ፊሽስት ኢጣሌያ የኢትዮጵያን ነፃነት ሇማጥፊት በተነሳችብን ጊዜ ሇመከሊከሌ


ስንወጣ አብረውኝ ወጥተው አብረውኝ ሳይመሇሱ በጦርነቱ፥ ወዴቀው ሇቀሩት ወንዴሞቼ ሇዘሪሁን
ወጋየሁና ገሊው ተገኝ መታሰቢያና እነሱ በሞት፥ ቢሇዩኝም እኔ በህይወት እስካሇሁ ዴረስ ፌቅራቸው
አብሮኝ የሚኖር መሆኑን የምገሌፅበት ነው።

ዯራሲው።

መቅድም
በዚህ ትዝታ ብዬ በሰየምኩት ትንሽ መፅሀፌ የተፃፇው ሁለ እውነተኛ ታሪክ ነው። መፅሀፈን «ታሪክ»
በማሇት ፇንታ ትዝታ ብዬ የሰየምሁት «ታሪክ» ሇመባሌ የሚጎዴለት ነገሮች ስሊለ ነው። እኒያን
«ይጎዴሊለ» የተባለትን ነገሮችና የጎዯለበትን ምክንያት በሚከተለት መስመሮች እገሌፃሇሁ።

በ1928 የፊሽስት ኢጣሌያ ጦር ኢትዮጵያን መውረሩ እንዯ ታወቀ በሙለ ኢትዮጵያጵያ


የጦርነት አዋጅ ሲታወጅ በዚያ ጊዜ የጎጃም እንዯራሲ የነበሩት (ሁዋሊ ሌኡሌ) ራስ እምሩም
የጎጃምንጦር አስከትተው በዚያ ሊይ በዯጃዝማች አያላው ብሩ ይመራ የነበረውን የሰሜንን ጦር
ጨምረው ትግራይ ውስጥ «የሽሬ ግምባር» በመባሌ ወዯ ታወቀው የጦር ግንባር ዘመቱ። ከዚያ እዚያው
ሽሬ በመባሌ ወዯ ታወቀው የጦር ግንባር ዘመቱ። ከዚያ፥ እዚያው ሽሬ ውስጥ «ሰሇክሇካ» በተባሇው ቦታ
ሊይ ከጠሊት ጋር ዋናውን ጦርነት ገጥመው ዴሌ ከሆኑ በሁዋሊ ተመሌሰው በምእራብ ኢትዮጵያ
በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው፥ በጅማና በከፊ ውስጥ ጎጀብ በሚባሇው ወንዝ ሊይ ተያዙ። ታዱያ እኔ፥ ሽሬ
ግንባር ጦርነትም በምእራቡ ያርበኝነት ትግሌም አብሬያቸው ስሇ ነበርሁ በየቀኑ የተዯረገውንና የሆነውን
ሁለ እየተከታተሌሁ ዝርዝር ማስታወሻ እይዝ ነበር። ነገር ግን እኛ ከጎጃም ሽሬ እስክዯርስ የያዝሁት
ዝርዝር ማስታወሻ እዚያው ሽሬ ውስጥ ዯባጏና ከተባሇው ኢጣሌያኖች መሽገው ተቀምጠውበት ከነበረው
ቦታ አጠገብ ጠሊት ሰፇራችንን ባይሮፕሊን በዯበዯበበት ጊዜ ዴንኩዋኔና በውስጡ የነበረው ሁለ በቦምብ
ሲቃጠሌ አብሮ ተቃጠሇ። 2ኛ - ያ የመጀመሪያው ማስታወሻዬ ከተቃጠሇ በሁዋሊ እንዯ ገና የፃፌሁት
ማስታወሻ ዯግሞ፥ በምእራብ ኢትዮጵያ ካርበኝነቱ ትግሌ በሁዋሊ እኔ ከራስ ጋር ተይዤ ወዯ ጣሉያን
አገር እስር ቤት ስወስዴ ሇዘመድቼ እንዱያዯርስሌኝ የሰጠሁት ሰው ሳያዯርስሌኝ እንዯያዘው ወዯ
አርበኝነቱ ተመሌሶ እዚያ ሲሞት አብሮት ጠፊ። እንግዱህ ከዚያ ሁለ የተረፇኝ ከራሴው ውስጥ
ሳይጠፊ ቆይቶ ከብዙ በጥቂቱ የማስታውሰው ወይም ትዝ የሚሇኝ ብቻ ነው። ቢሆንም ያው
የማስታውሰው በጊዜ በቦታና በሰው ስም እንዱሁም ባንዲንዴ ዝርዝር ነገር በኩሌ የተሙዋሊ ስሊሌሆነ
«ራሱን የቻሇ ሙለ ታሪክ» ባይባሌም «የጦርነቱን ሙለ ታሪክ የሚፅፈ ሰዎች አንዲንዴ

1
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚፇሌጉዋቸውን ነገሮች ያገኙበት ይሆናሌ» ብዬ ተስፊ በማዴረግ እኔ ሳሌፌ ያውም ጥቂቱ ጠፌቶ
እንዲይቀር ትዝታ የሚሌ ስም ሰጥቼ ሳሳትመው አሰብሁ።

ከመጽሀፈ የመጀመሪያው ምእራፌ ሇጦርነቱ መነሳት ምክንያት ስሇ ሆነው ስሇ ወሌወሌ ግጭት


ባጭሩ የሚሌፅ በማስረጃ የተዯገፇ ታሪክ ነው። ከታሪክነቱም ላሊ፤ ኢጣሉያ ወሰን አሌፊ ኢትዮጵያ
ውስጥ ወሌወሌ ሊይ ጦርነት አዴርጋ ብዙ ኢትዮጵያውያንን በመፌጀትዋ የኢትጵያ መንግስት ሇአሇም
መንግሥታት ማህበር አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ ማህበሩ ከህግና ከፖሇቲካ ማናቸውን አንዯሚመርጥ መወሰን
አቅትቶ አስር ወራት ሙለ ሲያመንታ ከኖረ በኋሊ የተረፇው ሊይቀር - ሙሶሉኒ ከሂትሇር ጋር
እንዲይተባበር የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያን መስዋዔት አዴርጎ ማቅረቡን የሚያሳይ ነው። ባጠቃሊይ
«የአሇም መንግሥታት ማህበር» የሚባሇው ሀያሊን መንግስታት ወዯዬግባቸው ሇመዴረስ የፖሇቲካ
ጨዋታቸውን የሚጫወቱበት ሜዲ መሆኑንና «አሇም አቀፊዊ ህግ» የሚባሇውም እንዯ ብሄራዊ ህግ
ስሌጣን ሊሊቸው ሀይሇኞች የፖሇቲካ መሳሪያ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በዚህ ትንሽ መፅሏፌ ስሇ
ጦርነቱ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በሁዋሊ እስከ 1936 ሰባት አመታት ያህሌ ጣሉያን አገር በግዞት
ስሇቆየንበትም ትዝ የሚሇኝን ፅፋያሇሁ። በጣም የማዝነው ቀዯም ብዬ እንዯገሇፅሁት የፃፌሁት
ማስታወሻ በመጥፊቱና መፅሀፈን የፃፌሁት የጦርነቱም የግዞቱም ጊዜ ካርባ አመታት በሊይ ካሇፇ
በሁዋሊ በመሆኑ የብዙ ጀግኖችን ስምና ስራቸን በዚህ መፅሀፌ ውስጥ ቦታ ሰጥቺኤ ከተከታታይ
ትውሌድች ጋር ሇማስተዋወቅ ሳሌችሌ ስሇ ቀረሁ ነው።

ምእራፍ አንድ

የወልወል ግጭት
ኢጣሉያ በ1888 አዴዋ ሊይ ከኢትዮጵያ ጋር ባዯረገችው ጦነት ዴሌ ከተመታች በሁዋሊ እንዯገና
ኢትዮጵያን ወግታ ዴሌ ሇመቀዲጀትና ያዴዋን ቂም ሇመበቀሌ፣ ከዚያም ወዯ አይነተኛ ግብዋ ሇመዴረስ
ማሇትም ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛትዋ ሇማዴረግ ፅኑ ፌሊጎት የነበራት መሆኑ ሇፖሇቲካ ተመሌካች ሁለ
ስውር አሌነበረም። ይህ ፅኑ ፌሊጎትዋ ፊሽስቶች መንግስቱን ስሌጣን ከመያዛቸው በፉት የነበረና እነሱም
ስሌጣን ከያዙ በሁዋሊ የቀጠሇ ነበር። ቀዯም ብሊ፥ በብዙ የኢትዮጵያ ክፌልች ካሠራጨቻቸው
ሚሲዮኖችዋ ላሊ፥ የንግዴ፣ የባህሌ፥ ወይም ኢትዮጵያንና ኢጣሌያን የሚያገናኙ ጉዲዮች ቅንስሊዎችዋን
አቁዋቁማ በነሱ አማካይነት መኳንንቱም የቤተ ክርስቲያንን አሇቆችም በገንዘብና በመሳሪያ ስጦታ
እንዱሁም በሹመት ተስፊ እያባባሇች ሇረዥም ጊዜ አሊማዋ አንዱረዴዋት አጥብቃ ስትሰራ የኖረች
ሇመሆንዋ ጦርነቱ በተነሳ ጊዜ ያባበሇቻቸው ሁለ ባይሆኑም ከነሱ መሀከሌ ብዙ አገራቸውን እየከደ
ሇስዋ ይገቡ መኖራቸው ምስክር ነው።

2
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይሌቁንም፥ በኢትዮጵያ ሰሜንና ዯቡብ (በኤርትራና በሱማላ) በንግዴ ኩባንዮችዋ አማካይነት
ትንንሽ ቦታዎች ከያዘችበት ጊዜ ጀምራ እስከ ወሌወሌ ግጭት ዴረስ ስታዯርገው የኖረችው ኢትዮጵያን
ቅኝ ግዛትዋ ማዴረግ የረዥም ጊዜ አሊማዋ የነበረ ሇመሆኑ ላሊው አይነተኛ ምስክር ነው።

በሰሜን «ሩባቲኖ» በተባሇው ኩባንያዋ ስም ከያዘችው ከአሰብ ተነስታ አንዲንዴ መንግስቶች


በተሇይ የእንግሉዝ መንግስት ረዴተዋት ምፅዋን ከያዘች በሁዋሊ በ«ድጋሉና በሰሀጢ» እንዲዯረገችው
በጦርነት ሳይሳካሊት ሲቀር በማባበሌና በማታሇሌ ቀስ እያሇች፥ ኤርትራን በሙለ ያዘች። በዯቡብም
እንዱሁ ከዛንዚባር ሱሌጣንና ከእግሉዝ መንግስት ጋር ተስማምታ የ«በናዱር ኩባንያ» በተባሇ ኩባንያዋ
ስም በህንዴ ውቅያኖስ ጠረፌ ሇጠረፌ «በናዱር» የሚባሇውን የሱማላ ክፌሌ ያዘች። ከዚያ
ሇከብቶቻቸውም ሇግመልቻቸውም ሳርና ውሀ ፌሇጋ ወዯ ኢትዮጵያ ኦጋዳን የሚዘምቱትን የሱማላ
ዘሊኖች አስቀዴማ ሁዋሌ ሁዋሊ እየተከተሇች የበናዱርን ወሰን አሌፊ ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እነ «ለ -
ፊርንዱን» እና ባካባቢው ያለትን ላልች ቦታዎች መያዝዋ ታወቀ። ስሇዚህ አፄ ምኒሌክ ምንም እንኳ
ሇአውሮፓ መንግስታት መሊሌሰው ከፃፈት እንዯሚታየው የኢትዮጵያ ወሰን ባህር መሆኑን ቢያምኑም
ያን የማያቋርጥ ግፉትዋን ሇመግታት የወሰን ስምምነት ሇማዴረግ በመገዯዲቸው ካዴዋ ጦርነት በሁዋሊ
እንዯ አውሮፓ አቆጣጠር በ1897 በኢትዮጵያና በኢጣሉያ መንግስቶች መሀከሌ አንዴ የወሰን ስምምነት
ተዯረገ። ያ ወሰን በዯቡብ ምእራብ ከጁባ ወንዝ «ባርዯራ» ከሚባሌ ስፌራ አጠገብ ተነስቶ ቀጥታ
መስመር እየተከተሇ ሄድ ሰሜን ምስራቅ ሲዯርስ የእንግሉዝንና የጣሉያንን ሱማላዎች ከሚሇየው ወሰን
ጋር የሚገናኝ ነበር።

«የ1897 ስምምነት» የሚባሇው እንዯ ላልች ስምምነቶች በዝርዝር ተፅፍ የተፇረመ አሌነበረም።
አንዴ የጀርመን ሰው በሰራው «የሀበኒክት ካርታ» በመባሌ በታወቀ የጂዎግራፉ ካርታ ሊይ አፄ ምኒሌክ
ከጁባ ወንዝ የእንግሉዝና የጣሉያን ሱማላዎች እስከሚገኙበት ወሰን ዴረስ በቀይ ቀሇም አስምረው
ማህተማቸውን አትመው የ«ሻሇቃ ኔራስኒ» ሇተባሇ የጣሉያን መንግስት እንዯራሴ የሰጡት ቀጥ ያሇ
መስመርና ያን የወሰን መስመር የጣሉያን መንግስት የተቀበሇው መሆኑን ያስታወቀበት ቴላግራም
ባንዴነት ተጣምረው ነው።

ከ11 ዒመት በሁዋሊ እንዯ አውሮፓ አቆጣጠር በ1908 በኢትዮጵያና በኢጣሉያ መንግሥቶች
መሀከሌ አዱስ የወሰን ስምምነት ተፇረመ። አዱሱ ስምምነት በዯቡብ ምእራብ በኩሌ በ1897 ስምምነት
የጣሉያን ሱማላ የሰሜን ወሰን የሆነውን «ባርዯራን» ወዯ ዯቡብ ትቶ ወዯ ሰሜን እስከ «ድል»
ይዯርስና ከዚያ ወዯ ምስራቅ ሄድ ዋቢሸበላ ሊይ ከ1897 መስመር ጋር ይገናኛሌ። ይህ የ1908
ስምምነት በጁባና በዋቢሸበላ መሀከሌ ያሇውን ሰፉና ሇም አገር ሁለ «ባይዲዋ» የሚባሇውን የርሻ አገር
ጭምር ሇኢጣሉያን አገር ሱማላ የሚሰጥ ነበር። ያንጊዜ የጣሉያን የውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር የነበሩት
ሲኞር ትቶኒ «ባዱሱ ስምምነት ኢጣሉያ ያገኘችው አገር 50.000 ኪል ሜትር ወይም ከሲሲሉ ከሁሇት

3
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጊዜ የሚበሌጥ ነው» ብሇው እንዯ አውሮፓ አቆጣጠር የካቲት 13 1908 ሇፓርሊሜንት መናገራቸው
ስምምነቱ ሇጊዜው ጣሉያኖችን ዯስ አሰኝቶዋቸው የነበረ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ነገር ግን ያሰኛቸው
ወዯ አይነተኛ ግባቸው ሇመዴረስ አንዴ ትሌቅ እርምጃ በመሆኑ ወንጂ የሱማላ ግዛታቸው የሚያሰፊ
በመሆኑ ብቻ አሌነበረም። አይነተኛ ግባቸው ኢትዮጵያን በጦርነት ዴሌ መትቶ ቅኝ ግዛት ማዴረግ አሇ
ነበረ በስምምነት ያገኙትን እጅ ካዯረጉ በሁዋሊ ከዚያ ተነስተው ወዯ ፉት መግፊታቸውን ቀጠለ። እንዯ
አውሮፓ አቆጣጠር በ1987 የኢትዮጵያ መንግስት ከኢጣሉያ መንግስት ጋር እንዲዯረገው ከእንግሉዝ
መንግስት ጋርም በኢትዮጵያ ኦጋዳንና በእንግሉዝ ሱማላ መሀከሌ ስሊሇው ወሰን ስምምነት አዴርጎ
ነበር። በዚያ ስምምነት መሰረት እንዯ አውሮፓ አቆጣጠር በህዲር ወር 1934 የኢትዮጵያና የእንግሉዝ
መንግስቶች የወሰኑን መስመር እየተከተሇ በመሬት ሊይ ምሌክቶችን የሚያዯርግ የጋራ የወሰን ኮሚሽን
ሾሙ። የኮሚሽኑ አባሊት መሪዎች በኢትዮጵያ መንግስት በኩሌ ዯጃዝማች ተሰማ ባንቴ፣ በእንግሉዝ
መንግስት በኩሌ ኮልኔሌ ክሉፍርዴ ነበሩ።

ኮሚሽኑ የወሰን ምሌክቶችን ካዯረገ በሁዋሊ እንዯ ስምምነቱ የእንግሉዝ ሱማላ ጎሳዎች
በየጊዜው ወዯ ኢትዮጵያ ኦጋዳን እየገቡ ግጦሽ የሚያግጡባቸውንና ውሀ የሚያጠጡባቸውን ቦታዎች
እየዞሩ ሲያዩ ወሌወሌን ባንዴ «ሻምበሌ ሮቤርቶ ችመሩታ» የተበሇ መኮንን የሚመራ የባንዲ ጦር ተይዞ
አገኙት። የባንዲው ጦር ምሽግ መሽጎ፥ ከምሽጉ አጠገብ በከፌተኛ ቦታ ሊይ የኢጣሉያ ሰንዯቅ አሊማ
ተሰቅል ነበር። ሇወሰኑ ኮሚሽን ጠባቂ የነበሩት የጅጅጋው አገረ ገዥ ፉታውራሪ ሽፇራው ባሌቻና
ምክትሊቸው ግራዝማች አፇወርቅ ከጦራቸው ጋር ቀዴመው ወሌወሌ ዯርሰው ከጣሉኢያን የባንዲ ጦር
ጋር እንዯ ተፊጠጡ ኮሚሽኑ ዯረሰ።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዲይ ሚኒስትር የነበሩት ብሊቴን ጌታ ህሩይ በጊዜው ሇነእብረው የአሇም
መንግስታት ማህበር እንዲስታወቁት ወሌወሌ በ1987 እና በ1908 ከተፇረሙት የወሰን ክሌሌ
ስምምነቶች 60 ኪል ሜትር ኢትዮጵያ ኦጋዳን ውስጥ ገብቶ የሚገኝ ቦታ ነው ያውም አፄ ምኒሌክ
በ«ሀበኒክት» ካርታ ሊይ በቀይ አስምረው ማህተማቸውን አትመው ሇጣሉያን መንግስት የሊኩትና
የጣሉያን መንግስትም የተቀበሇው መሆኑን በቴላግራም ያስታወቀው የወሰን መስመር በዚያን ጊዜ
ብሊቴን ጌታ ህሩይ ጠፌቶባቸው ይሆናሌ እንጂ ወሌወሌ ስምምነት ከተዯረገበት ወሰን 60 ኪል ሜትር
ብቻ ሳይሆን 130 ኪል ሜትር ያህሌ ኢትዮጵያ ኦጋዳን ውስጥ ገብቶ የሚገኝ ቦታ ነው። እንዱህ
መሆኑን ሇማረጋገጥ ከስምምነቱ በሁዋሊ የኢጣሉያ መንግስት የውጭ ጉዲይ ሚኒስትር ያወጣውን
«ኦፉሻሌ» ካርታ ‹ካሮሴሉ› የተበሇ ኢጣሉያዊ ፀሀፉ ባሳተሙት «FERROE FUOCO In SOMALIA
(ሰይፌና እሳት በሶማላ) ከተባሇ መፅሀፌ ማየት ይቻሊሌ።

የፉታውራሪ ሽፇራው ጦር ከኢጣሉያ የባንዲ ጦር ተፊጦ እንዲሇና ኮሚሽኑ ባጠገቡ እንዯ ሰፇረ
የባንዲው መሪ ሻምበሌ ችመሩታ የኮሚሽኑንና የጠባቂውን ጦር ወሌወሌ መዴረስ ሞካዱሾ ሇሱማላ አገረ

4
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ገዥ ‹ሇማውሪስዮ ራቫ› (MAURIZIORAVA) አስታውቆ አገረ ገዡ አይሮፕሊኖች ስሇ ሊከበት እኒያ
አይሮፕሊኖች የኮሚሽኑ አባልችና ጠባቂያቸው ጦር የሰፇሩበትን ቦታ እየዞሩ ያስፇራሩ ጀመር።

የኮሚሽኑ መሪዎች ዯጃዝማች ተሰማና ኮልኔሌ ክሉፍርዴ ወሌወሌ ከዯረሱ ጀምሮ ያዩት ሁለ
ከማሳዘን አሌፍ ስሊስገረማቸው፥ የኢጣሉያን መንግስ ጦር በኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ መመሸጉና
በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ሇስራ የተሊኩትን የኢትዮጵያና የእንግሉዝ የወሰን ኮሚሽን አባልች
በአይሮፕሊን ማስፇራራቱ ህገ ወጥና የእብሪት ስራ መሆኑን ሇሻምበሌ ችመሩታ ፃፈሇት። ነገር ግን
የሻምበለ መሌስ ካይሮፕሊኖች ላሊ ተጨማሪ ጦር ከታንኮችና መዴፍች ጋር ማመጣት ሆነ። ከዚያ
በሁዋሊ የጣሉያን ባንዲ አሇቃም ሆነ ያገረ ገዡ አዴርጎት ሁለ ጠብ ሇመጫር የተነሱ መሆናቸውን
የሚያመሇክት ስሇ ነበረ የኮሚሽኑ መሪዎች የማይቀረው የሚቀር መልዋቸው - ነገሩ አዯገኛ ሁኔታ ሊይ
ሳይዯርስ በመንግስት ዯረጃ ንግግር ተዯርጎበት እንዱወሰን ሇማመሌከት ከወሌወሌ ተነስተው «አድ» ወዯ
ሚባሇው ቦታ ሇመሄዴ ወሰኑ።

የኢትዮጵያና የእንግሉዝ የጋራ ኮሚሽን አባልች ከጠባቂው ጦር ጥቂት አስከትሇው የቀረውን


እዚያው እንዱጠብቅ ትተው ወዯ አድ መሄዲቸውን ሻምበሌ ችመሩታ እንዲወቀ እንዯ አውሮፓ
አቆጣጠር ታህሳስ 5 1934 በ9:30 ሊይ ያይሮፕሊን የታንክ የመዴፌና የላሊም የሌዩ ሌዩ መሳሪያውን
ሀይሌ አስተአብብሮ እዚያ በቀረው የኢትዮጵያ ጦር ሊይ አዯጋ ስሇ ጣሇ መራራ ጦርነት ተዯረገ።
የኢትጵያ ጦር የጋራ ኮሚሽኑን ሇመጠበቅ እንጂ እንዱያ ሊሇ ከባዴ ጦርነት የተሰናዲ ባይሆንም ብዙዎች
አገር የሚያኮራ የጅግንነት ስራ ሰርተው እዚያው ወዯቁ።

የወሌወሌ ግጭጥ አዱስ አበባ እንዯ ታወቀ የውጭ ጉዲይ ሚኒስትር የነበሩት ብሊቴን ጌታ ህሩይ
ወሌዯ ስሊሴ በጊዜው የጣሉያን ጉዲይ ፇፃሚ የነበሩትን «ስኞር ሞምቤሉን» ጠርተው የጣሉያን ጦር
ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ብቶ ያሊንዲች ምክንያት የወሰን ኮሚሽንን እንዱጠብቅ በታዘዘው የኢትዮጵያ ዘብ
ሊይ ጦርነት አንስቶ ብዙ ሰው በመፌጀት የመንግስታቸውን ፅኑ ሀዘን በቃሌ ካስታወቁ በሁዋሊ እንዯ
አውሮፓ አቆጣጠር 1928 በሁሇቱ መንግስታት መሀከሌ በተፇረመው የወዲጅነትና የሽምግሌና ስምምነት
መሰረት ግዲዩ፥ በሽምግሌና (Arbitration) እንዱታይ የፃፈትን ሇመንግስታቸው እንዱያስተሊሌፈ
ሰጡዋቸው። ሮም በነበሩ የኢትዮጵያ መንግስት እንዯራሲ በኩሌም ተመሳሳይ ጥያቄ ሇጣሉያን መንግስት
ቀረበ። ነገር ግን ሇጣሉያን መንግስት የወሌወሌ ግጭት ኢትዮጵያን ወግቶ ቅኝ ግዛቱ ሇማዴረግ ሊቀዯው
የረዥም ጊዜ እቅደ በር ከፊች ወይም የመጀመሪያ እርምጃ እንጂ ዴንገተኛ አዯጋ አሇመሆኑን በስኞር
ሞምቤሉ በኩሌ የተሰጠው መሌስ ዯህና አዴርጎ ያሳያሌ።

መሌሱ ባጭሩ፦

5
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«1ኛ፦ በሀረሩ ገዥ ዯጃዝማች ገብረ ማርያም ወሌወሌ ምሽግ ዴረስ ሄዯው በኢትዮጵያ መንግስት
ስም የጣሉያንን ጦር አዛዥ ይቅርታ እንዱሇምኑ፥

«2ኛ፦ በጦርነቱ ምክንያት ከጣሉያን የባንዲ ጦር ውስጥ ሇሞቱትም ሇቆሰለትም ካሳና ሇፇረሰው
ምሽግ ዋጋ፥ የኢትዮጵያ መንግስት 200.000 ጠገራ ብር አዱስ አበባ ባሇው የጣሉያን ሇጋሲዮን በኩሌ
ሇጣሉያን መንግስት እንዱከፌሌ፥

«3ኛ፦ ሇዯረሰው አዯጋ ሀሊፉዎች የሆኑት የኢትዮጵያ የጦር መኩዋንንት ከወታዯሮቻቸው ጋር


ሇጣሉያን ሰንዯቅ አሊማ የክብር ሰሊምታ ከሰጡ በሁዋሊ በፌጥነት ተይዘው ማእረጋቸውን እንዱገፇፈና
እንዲገሩ ሌማዴ ተቀጥተው እንዱታሰሩ» የሚሌ ነበር።

እንዱያ ያሇ እብሪትና ንቀት ዯራርቦ የተሸከመ ጥያቄ ሉውጡት የማይቻሌ መራራ ከመሆኑ ላሊ
«በዴል ካሱኝ ሾህ ይዞ እጄን ዲስሱኝ ሇነገር ነው» እንዯሚለት የጣሉያን መንግስት ሇነገር የታጠቀ
መሆኑን በመረዲት እንዯ አውሮፓ አቆጣጠር ታህሳስ 14 1934 የኢትዮጵያ መንግስት በሱና በኢጣሉያ
መንግስት መሀከሌ የተፇጠረውን አስጊ ሁኔታ በዝርዝር ገሌፆ ሇአሇም መንግስታት ማህበር ዋና ፀሀፉ
አስታወቀ። ከዚያ እንዯ ገና በዚያው ወር 24 1934 ኢጣሉኢያ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ወሌወሌን
ከያዘች በሁዋሊ ዯግሞ «ኦፌዯብን» «አድን» እና «ጌርልጏቢን» መያዝዋን ሇዋናው ፀሀፉ አስታወቀ።
ኢጣሉያም ወሌወሌም ሆነ ላልች የተቆጠሩት ቦታዎች በግዛትዋ ውስጥ መሆናቸውንና ኢትዮጵያ ግዛት
ውስጥ አሇመግባትዋን ገሌፃ መሌስ ሰጠች።

እንዯ አውሮፓ አቆጣጥገር ትር 3 1935 የኢትዮጵያ መንግስት የአሇም መንግስታት ማህበር


(League of Nations) በተቋቋመበት ቃሌ ኪዲን (Covenant) መሰረት በኢትዮጵያና በኢጣሉያ መካከ
የተፇጠረውን አስጊ ሁኔታ ማህበሩ መርምሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጥያቄ አቀረበ። ከዚያው ወር 17
1935 ማህበሩ በጉዲዩ ሇመነጋገር ወስኖ አጀንዲው ፃፇው። ነገር ግን የኢጣሉያ መንግስት በኢትዮጵያ
ሊይ ሉያዯርገው ሊሰበው ጠቅሊሊ ጦርነት በቂ ዝግጅት ሇማዴረግ ጊዜ እንዱያገኝ አንዴ ጊዜ «ከኢትዮጵያ
መንግስት ጋር በቀጥታ የተጀመረው ንግግር ስሊሊሇቀ ወዯ ሽምግሌና የመተሊሇፈ ጊዜ አሌዯረሰም» ሲሌ፥
ላሊ ጊዜ «ኢጣሉያና ኢትዮጵያ እንዯ አውሮፓ አቆጣጠር በ1928 የፇረሙት የወዲጅነትና የሽምግሌና
ስምምነት መሰረት ሌዩነታቸውን ራሳቸው ተስማምተው ሇሚያቋቁሙት የሽምግሌና ፌርዴ ቤት
(Arbiitration) አቅርበው ማስወሰን እንጂ ሇማህበሩ ማቅረብ የሚያስፇሌግ አዯሇም» እያሇ ሌዩ ሌዩ
ምክንያቶች እየሰጠ ነገሩ (League Council) የኢትዮጵያ መንግስት ባቀረበው አቤቱታ ሊይ ንግግር
አሊዯረገም። ምክንያቱ በጉዲዩ የማህበሩ ምክር ቤት ተነጋግሮ ውሳኔ እንዲይሰጥበት የኢጣሉያ መንግስት
ተንኮለን ሇመሸፇን ከሚፇጥረው ዘዳ ላሊ፥ ጀርመን አውሮፓ ውስጥ ጦርነት ሇማዴረግ መሰናዲቱ
መታወቅ ጀምሮ ስሇ ነበር፥ «ማህበሩ ሙሶሉኒን የሚያስቀይም ነገር ያዯረገ እንዯሆነ ከጀርመኑ መሪ
ከሂትሇር ጋር እንዲይተባበር ተፇርቶ» ነው ይባሊሌ።

6
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በግንቦት 25 1935 የማህበሩ ምክር ቤት (Council) በጉዲዩ ተነጋግሮ ፇራ ተባ እያሇ
«የኢትዮጵያና የጣሉያን ሌዩነት በማህበሩ ውስጥ ሁሇቱ ተስማምተው በሚያቋቁሙት የሽምግሌና ፌርዴ
ቤት (Arbitratiion) እንዱወሰን 2ኛ ጉዲዩ በሽምግሌናው ፌርዴ ቤት በተያዘበት ጊዜ፥ የጦርነት መሰናድ
እንዲታዯርግ» የሚሌ ውሳኔ (Resolution) አሳሇፇ።

በማህበሩ ውሳኔ መሰረት የኢትዮጵያና የኢጣሌያ መንግስቶች የሽምግሌና ዲኞቻቸውን መርጠው


ፌርዴ ቤቱ (Arbitration Tribunal) ተቁዋቁዋመ። የኢጣሉያን መንግስት ሇዲኝነት የመረጠው «ልይጂ
አሌዴሮቫንዱ» እና «ራፊየላ ሞንታኛ» (Luigi Aldrovandi e Raffoele Montagna) የተባለትን ሁሇት
ጣሉያኖች ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ፕሮፋሰ ጂዎፌር ዯሊ ፕራዯሌ» (Professor Geouffre de la
Pradelle) የተባለትን ፇረንሳዊና «ፕሮፋሰር ፔትማን ፖተር» (Professor Pittman Potter)
የተባለትን አሜሪካዊ መረጠ። በሽምግሌናው ፌርዴ ቤት የኢጣሉያ መንግስት ወኪሌና ነገረ ፇጅ
«ፕሮፋሰር ሴሶና» የኢትዮጵያ መንግስት ወኪልችና ነገረ ፇጆች ፕሮፋሰር ጋስቶን ዥዝ የተባለት
ፇረንሳዊና በፓሪስ የኢትዮጵያ ሚኒስትር በዥሮንዴ ተክሇ ሀዋርያት ነበሩ። የፌርዴ ቤቱን ፅህፇት ቤት
እንዱመሩ የተሾሙ ሶስት ጣሉያኖችና በኢትዮጵያ በኩሌ አንዴ ፇረስንሳዊ (ሬሞ ዯሊ ፕራዯሌ፥ የዲኛው
የጂዎፌር ዯሊ ፕራዯሌ ሌጅ) ነበሩ።

ፌርዴ ቤቱ በዚህ አሆሁዋን ተቋቁሞ ከተዯራጀ በሁዋሊ የኢትዮጵያ ነገረ ፇጆች «ሇግጭቱ
ምክንያት ሆኖ ክርክሩን ያስከተሇው ወሌወሌ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ሇመሆኑ ማስረጃ እናቅርብ»
አለ። ነገር ግን የኢጣሉያ መንግስት ነገረ ፇጅ «ወሌወሌ በማን ግዛት ውስጥ መሆኑ ጨርሶ መነሳት
የሇበትም» ብሇው ስሇ ተቃወሙ፥ የኢጣሉያን መንግስት የመረጣቸው (ኢጣሉያን) ዲኞችየጣሉያንን ነገረ
ፇጅ አቁዋም፣ የኢትዮጵያ መንግስት የመረጣቸው ዲኞች የኢትዮጵያን ነገረ ፇጆች አቁዋም ዯገፈ።
ስሇዚህ ነገሩ መውጫ የላሇው ዝግ መንገዴ ሆነና ወዯ ማህበሩ ምክር ቤት ቀርቦ መመሪያ እንዱሰጥበት
ተዯረገ። ምክር ቤቱ ጉዲዩ ቀርቦሇት ከተነጋገረበት በሁዋሊ ሀምላ 31 1935 ወሳኝ ዴምፅ (Castiing
Vote) የሚኖረው አምስተኛ ዲኛ እንዱመረጥ መመሪያ ሰጥቶ በፓሪስ የግሪክ ሚኒስቴር የነበሩት «ሙሴ
ፖሉቲስ» ተመረጡ። ከዚያ አምስቱ የሽምግሌና ዲኞች (Arbitration Tribunal) ተሰብስበው የሁሇቱን
ወገኖች የማይቀራረቡ አቁዋሞች ሇማቀራረብ ወይም ህግንና ያመፅ ስራን ማስማማት አስቸግሮዋቸው
ዘሇግ ያሇ ጊዜ ጉዲዩን ይዘው ከቆዩ በሁዋሊ በመጨረሻ መስከረም 3 1935 የሚያሳዝንና የሚያስገርም
ውሳኔያቸውን ሰጥተው ተነሱ። ውሳኔው ባችሩ እንዯሚከተሇው ነበር።

«1ኛ. የኢትዮጵያ መንግስትም የኢጣሉያን መንግስትም ወሌወሌ በየራሳቸው ግዛት ውስጥ


መሆኑን ያምኑ ስሇ ነበረ እዚያ ሊይ ሇተነሳው ግጭት ሁሇቱም በዯሇኞች ሉባለ አይችለም።

7
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«2ኛ. በወሌወሌ ግጭት ምክንያት በቦምብና በላሊ በሌዩ ሌዩ መሳሪያ የተዯረገው ጦርነትም
እንዱያ ባለ ቦታዎችና እንዱያ ባለ ሁኔታዎች ዘወትር የሚዯርስ ተራ ነገር ስሇ ሆነ ‹ሇአሇም ሰሊም
ያሰጋለ› ተብሇው ከሚያሳስቡት ጉዲዮች ተራ የሚገባ አይዯሇም»

የሽምግሌናው ፌርዴ ቤት፥ የኢጣሉያን መንግስት ከጉሌህ ያመፅ ስራው አጥቦ ከማጥራቱ ላሊ
ኢትዮጵያን ወርሮ ሇመያዝ የሚያስችሇውን የጦር ሰራዊትና ዘመናዊ መሳሪያ ካገሩ አጉዞ፥ በኤርትራና
በሱማላ ውስጥ ሇማከማቸት ተጨማሪ ጊዜ ሰጠው። በዚያ ረዥም ጊዜ ውስጥ፥ የኢጣሉያ መንግስት
ወታዯሩንና መሳሪያውን በኤርትራና በሱማላ ወሰን ዴረስ፥ ያከማቸውን የጦር ስራቶችና መሳሪያ
ሇማጉዋጉዋዝ መንገዴ፥ በላሇባቸው ክፌልች መንገዴ ሇመስራትና የኢትዮጵያን ወሰን ሰብሮ ሇመግባት
ባቀዯባቸው ቦታዎች ሁለ ምሽጎቹን ሇመመሸግ ቻሇ።

የጣሉያን መንግስት የጦርነት መሰናድውን በገሀዴ ሲያሰናዲ ረዥም ጊዜ ቆይቶ ኢትዮጵያን


በሰሜንና በዯቡብ መውረር ሲጀምር የአሇም መንግስታት ማህበር «ምንም አሊዯረገም» እንዲይባሌ
ሇኢጣሉያም ሇኢትዮጵያም (ሊጥቂዋና ሇተጠቂዋ) የጦር መሳሪዑያ እንዲይሸጥሊቸው ወይም
እንዲይሰጣቸው የሚያግዴ ውሳኔ አሳሇፇ። ውሳኔው የተሰሩትን የጦር መሳሪያዎች እንጂ፥ ሇጦር መሳሪያ
የሚሆኑትን ጥሬ እቃዎች ጭምር ስሇማያግዴ፥ «እገዲው የተዯረገ በኢትዮጵያ ሊይ ብቻ ነው» ማሇት
ይቻሊሌ። ኢጣሉያ ጥሬ እቃ እስካሌተከሇች ዴረስ ሇጦርነቱ የሚያስፇሌጋትን መሳሪያ ሁለ የምትሰራበት
ፊብሪካ ስሇነበራት እገዲው እስዋን የሚነካ አሌነበረም።

የኢትዮጵያ መንግስት ሇዘመናዊ የፖሇቲካ ውስብስብ እንግዲ ስሇ ነበረ ኢትዮጵያ የአሇም


መንግስታት ማህበር አባሌ መሆንዋን ብቻ ወሰንዋ እንዲይዯፇርና ነፃነትዋ እንዱከበር የታመነ ዋስ
መሆኑን ከሌብ ያምን እንዯ ነበረ የጊዜው ባሇስሌጣኖች ከሚናገሩትም፥ በጋዜጣም ከሚፃፇውም ይታወቅ
ነበር። እንዱያውም ኢትዮጵያ ሇአሇም መንግስታት ማህበር አባሌ የሆነችበት ዋና ምክንያት ማህበሩ
የተመሰረተበት «ቃሌ ኪዲን» (Convenant) አይነተኛ አሊማው ያባልቹን ዯህንነትና የአሇም ሰሊም
ሇመጠበቅ በመሆኑ «አፌሪካን ተከፊፌሇው ቅኝ ግዛታቸው ሇማዴረግ ከሚሽቀዲዯሙት የአውሮፓ ታሊሊቅ
መንግስታት ይጠብቀኛሌ» ብሊ በማመን ነበር ይባሊሌ።

የኢትዮጵያ መንግስት አሇም አቀፊዊ ህግ እንዯ ብሄራዊ ህግ ስሌጣንና ሀይሌ ሊሊቸው


መንግስታት የሚያገሇግሌ መሳሪያ መሆኑን አያውቅም ነበር። ስሇዚህ በዚያ ረዥም ጊዜ ውስጥ የጣሉያን
መንግስት ወታዯሩንና መሳሪያውን ካገሩ እያጉዋዘ በኤርትራና በሱማላ አከማችቶ ከዚያ ጦርነት
ሇመክፇት ባቀዯባቸው ግንባሮች ሁለ ወዯ ኢትዮጵያ ወሰን መንገድችና ዴሌዴዮች ሲሰራ፥ በኢትዮጵያ
ወሰን ሊይ ምሽጎችንና ላልችንም ሇጦርነቱ የሚያስፇሌጉትን መሰናድዎች ሁለ ሲያሰናዲ የኢትዮጵያ
መንግስት በመጀመሪያ ዯረጃ እምነቱን በአሇም መንግስታት ማህበር ሊይ በመጣሌ 2ኛ የነበረውን
መጠነኛ የመሳሪያ ሀይሌ እንኳ በሚያስፇሌገው ጊዜና በሚያስፇሌግበት ቦታ የማዯራጀት ችልታ

8
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ስሇሌነበረውና የሚያዯርገው ስሇ ተዯናገረው አንዲች መስናድ ሳያዯርግ እጅ እግሩን ሰብስቦ አገሩ በይፊ
እኪወረር ዴረስ ይጠብቅ ነበር።

የኢጣሉያ የጦር ሰራዊት - በሱማላ ግንባር መቸም ቀዯም ብል ነው ኦጋዳን ውስጥ ብዙ


ቦታዎች የያዘ - በሰሜን ግንባር፥ መረብን ተሻግሮ ትግራይ ውስጥ ብዙ ቦታዎችን ከያዘ በሁዋሊ እንዯ
ኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥቅምት ወር 1928 የኢትዮጵያ መንግስት ሇጦርነት «የክተት አዋጅ» አወጀ።
የአሇም መንግስታት ማህበር በገባው ቃሌ ኪዲን መሰረት የጣሉያን መንግስት ኢትዮጵያን እንዲይወር
ሇማዴረግ ፇቃዯኛ ሳይሆን ቀርቶ ጦርነቱ ባዋጅ ከተጀመረ በሁዋሊ እንኳ በማህበሩ ፉት በዯሇኛ ወይም
አጥቂ ሆኖ ሊሇመገኘት ትእዛዙን ባይኔ አሊየሁም እንጂ፥ «ጠሊት ሲያጠቃ ከመከሊከሌ በቀር የኢትዮጵያ
ጦር ሇማጥቃት እንዲይሞክር በየግንባሩ ጦሩን ሇሚመሩት የኢትዮጵያ የጦር አሇቆች የመንግስቱ ጥብቅ
ትእዛዝ ተሰጥቶዋሌ» እየተባሇ በሰፉው ይነገር ነበር። እንዱያ ያሇ ትእዛዝ መስጥቱ እውነት መሆኑን
ትእዛዙን ከተቀበለት የጦር አሇቆች አንደ በጭፌሮቻቸው ፉት ሲናገሩ (ጭፌሮቻቸውን በፇንታቸው
ሲያስጠነቅቁ) ሰምቻሇሁ። ግን ጦርነት ሇመዋጋት ተሰሌፍ «ካሌተጠቃችሁ እንዲተጠቁ» የሚሌ ትእዛዝ
እንዳት ያሇ የሚያስገርም የየዋሆች ትእዛዝ ነው! ታዱያ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ፌፁም የዋህነት ከአሇም
መንግስታት ማህበር በሇውጡ አንዴ ብጣሽ ነገር ሳያገኝ ኢትዮጵያን ውዴ ዋጋ፥ በጣም ውዴ ዋጋ
ነፃነቷን ጭምር አስከፇሊት።

ምእራፍ ሁለት

ቅድመ - ዝግጅት
የወሌወሌ ግጭት ሲዯረግ እኔ ጎጃም አገው ምዴር ውስጥ ዲንግሊ በምትባ ትንሽ ከተማ ያንዴ
ትንሽ ትምህርት ቤት አስተማሪና ስራ አስሂያጅ ነበርሁ። በዲንግሊና በአዱስ አበባ መሀከሌ ካንዴ ፖስታ
ቤት በቀር የስሌክ ይሁን ወይም የመኪና መንገዴ መገናኛ ስሊሌነበረ፥ ዲንግሊ እንኖር የነበር ሰዎች
እንኩዋንስ ስሇ «ወሌወሌ ግጭት» ስሇ አዱስ አበባም የምንሰማው ወሬ እጅግ ጥቂት ነበር። ያውም
ጥቂት አዱስ አበባ ዯርሰው እስኪመሇሱ ከሶስት ወራት ያሊነሰ ጊዜ ከሚወስዴባቸው ሲራራ ነጋዳዎችና
እጅግ ፇጠነ ሲባሌ በወር አንዴ ጊዜ ከሚዯርሰው እግረኛ ፖስታ አመሊሊሽ የሚገኝ ነበር። ስሇዚህ
አንዲንዴ ጊዜ ተጨምሮበት አንዲንዴ ጊዜም ተቀንሶሇት፥ በዚያም ሆነ በዚህ መሌኩ ተሇውጦ ካሌሆነ
እውነተኛው ወሬ ዯርሶን አያውቅም። የሆነ ሆኖ፥ በነበርሁበት አገርና ባካባቢው የሚኖረው ህዝብ ስሇ
ወሌወሌ ግጭትም ሆነ ስሇ ላሊው ኢትዮጵያ ከውጭ መንግስታት ጋር ስሊሊት ግንኙነት የሚከታተሌና
በጠቅሊሊው የፖሇቲካ ጉዲይ የሚያሳስበው ስሊሌነበረ ሇኔም እዚያ በቆየሁበት ጊዜ፥ ግጭቱ የሁዋሊውን
ያህሌ ከብድ አሌተሰማኝም ነበር። እርግጥ የፖስታ ቤቱ ሹም፣ አቶ ይትባረክ ተገኝ በወር አንዴ ጊዜ ስሇ
ነበረና ከሳቸው ጋር ግንኙነት ስሇ ነበረኝ ጊዜ ያሇፇ ጋዜጣ በማንበብም ከዯብዲቤዎች ያገኙትን ያረጀ ወሬ

9
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እየነገሩኝም፥ ከላልች የተሻሇ አውቅ ነበር። ግን ካቶ ይትባረክ አገኘው የነበረው ወሬ የግጭቱን አስጊነት
የሚያሳይ አሌነበረም።

የወሌወሌ ግጭት በህዲር ወር መጨረሻ 1927 ከተዯረገ በሁዋሊ በዚያው አመት በመጋቢት ወር
ሊይ ከዲንግሊ ወዯ ዯብረ ማርቆስ ትምህርት ቤት ተዛወርሁ። ዯብረ ማርቆስ የትምህርት ቤቱ
ሹማምንትና መምህራንም ሇየመስሪያ ቤቱ አሊፉዎችና ሰራተኞች ሆነው ካዱስ አበባ የተሊኩት ሰዎችም
ስሇ ፖሇቲካ ጉዲይ የመወያየት ሌማዴ የነበራቸው ስሇ ነበሩ፥ የወሌወሌ ግጭት ከዲንግሊ የበሇጠ
ውይይት ሲዯረግበት አሌፍ አሌፍ ይሰማ ነበር። ይሁን እንንጂ እዚያም ቢሆን፥ ባዱስ አበባና በዯብረ
ማርቆስ መሀከሌ የመኪና መንገዴ ስሊሌነበረ፥ የሇት ቀርቶ የማግስት ወሬ ሇጠቅሊሊው ህዝብ የሚያዯርስ
ላሊ መገናኛ ስሇሌነበረ ካዱስ አበባ ትክክሇኛ ወሬ የሚያገኙ የስሌክና የራዱዮ ሰራተኞችና በነሱ
አማካይነት መሌእክቱ የሚተሊሇፌሊቸው የበሊይ ሹሞች ብቻ ነበሩ። እነሱም በምስጢርና በተራ ወሬ
መሀከሌ ያሇውን ሌዩነት ባሇማወቅ ይሁን ወይም በላሊ በማይታወቅ ምክንያት፥ ከበሊይ የሚሊከውን ነገር
ሁለ ምስጢር አዴርገው ስሇሚይዙት፥ ስሇ ወሌወሌ ግጭት ትክክሇኛውን ሁኔታ ከነሱ በቀር የሚያውቅ
አሌነበረም። የቀረው ሰው ጫፌና ጭምጭምታ ወሬ እየያዘ በዚያ ሊይ የየራሱን ግምት እየጨመረ ነበር
ሲያወራና ሲተች የሚሰማው። ብቻ በጠቅሊሊው «በኢጣሉያና በኢትዮጵያ መሀከሌ ጦርነት ይዯርጋሌ»
ብል የሚገምት አሌነበረም።

ነገር ግን ወዯ ሁዋሊ ኢጣሉያ ወሰን አሌፊ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ጦርነት ማዴረግዋንና ብዙ
ህዝብ ፇጅታ አንዲንዴ የኢትዮጵያን አገሮች መያዝዋን የኢትዮጵያ መንግስት ሇአሇም መንግስታት
ማህበር አስታውቆ፥ ማህበሩ በጉዲዩ በመነጋገር ሊይ መሆኑ ይሰማ ጀመር። እሱንም የሚያወሩት አሌፍ
አሌፍ ከሚዯርሰው ጋዜጣ ያነበቡና «የአሇምን ፖሇቲካ እንከታተሊሇን» የሚለ ሰዎች ነበሩ። ታዱያ እኒያ
ሰዎች ግምታቸውንና ምኞታቸውን ከጋዜጣ ያነበቡት ወይም ካዋቂዎች የሰሙት አስመስሇው እያጋነኑ
ሲናገሩ ኢጣሉያ፥ የምትቀጣ መሆንዋን እንዯማያከራክር የተረጋገጠ ነገር ቆጥረውት ክርክሩም ሆነ
ትችቱ ስሇ ቅጣቱ አይነትና ስሇ ካሳው መጠን ነበር።

የአሇም መንግስታት ማህበር አሰራር እንኩዋንስ ዯብረ ማርቆስ ከነበሩት ሹማምንትና ሰራተኞች
አዱስ አበባ የመንስቱ አባሊት ከሆኑት ሰዎች መሀከሌም ጠንቅቀው የሚያውቁ አሌነበሩም። የአሇም
መንግስታት ማህበር ከማህበሩ፥ አባሊት ሀይሇኞች የሆኑት ታሊሊቅ መንግስታት ታናናሾችን በእርዲታ
ተስፊ እያባበለም እያስፇራሩም እንዱተባበሩዋቸው አዴርገው መፇፀም የሚፇሌጉትን መሌካም ይሁን
ክፈ ህጋዊ መሌክ እንዱኖረው ሇማዴረግ የሚጫወቱበት መዴረክ መሆኑን ያን ጊዜ በኢትዮጵያውያን
መሀከሌ የሚያውቅ አሌነበረም። ከዚህ ሁለ ላሊ «የማህበሩ ውሳኔ ከህግና ከህግና ከህሉና ፌርዴ የራቀ
ይሆናሌ፤ ወይም አንዴ አባሌ የቀሩትን መንግስታት ሁለ ፇቃዴ ጥሶ ያመፅ ስራውን ሇመፇፀመ
ዴፌረትም አቅምም ሉኖረው ይችሌ ይሆናሌ» ብል የሚጠረጥር ኢትዮጵያዊ አሌነበረም። ስሇዚህ፥

10
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የማህበሩ ምክር ቤት (League Council) የኢትዮጵያና የኢጣሉያ ጉዲይ፥ በማህበሩ ስር በሽምግሌና
ፌርዴ ቤት (Arbitration) ታይቶ የፌርዴ ቤቱ ውሳኔ እንዱቀርብሇት ውሳኔ (Resolution) ማሳሇፈ
ከታወቀ በሁዋሊ የኢትዮጵያ መንግስትም ከሹማምንቱና ከሰራተኞች ወገን ጉዲዩን የሚከታሇው ክፌሌም
ፌፃሜውን በታሊቅ ተስፊና በጉጉት ይጠባበቅ ነበር። ሇጥንታውያኑ መኩዋንንትና ሇጠቅሊሊው ህዝብ ግን፥
ጉዲዩ እንኩዋንስ ሇውይይት ሇአሳብም ሩቅ ስሇ ነበር በነሱ መሀከሌ ሲነሳ እምብዛም አይሰማ ነበር።

የአሇም መንግስታት ማህበር ውሳኔ ቅን ፌርዴን የተከተሇ እንዯሚሆን በማመን፥ የኢትዮጵያ


መንግስትና የፖሇቲካ ጉዲይ የምንከታተሇው ሁለ ውሳኔውን በናፌቆት በመጠባበቅ ሰፉው፥ ህዝብ
በግዳሇሽነት ሊይ እንዲሇን፥ ትምህርት ቤት የሚዘጋበት ጊዜ ዯረሰ። ስሇዚህ እኛ በትምህርት ቤት ስራ
የተሰማራነው ሁለ አስተማሪዎች፥ ፇተና ሇማሰናዲትና ሇማረም ላልች ሰራተኞች የመዝጊያው በአሌ
የሚከበርበትን ስነ ስራት ሇማዯራጀት በነበረው ውጥረትና ጥዴፌያ ምክንያት አሳባችንም ጊዜያችንም
በሙለ በዚያ ስራ ተውጦ፥ የወሌወሌ ግጭት ያስከሌተሇውን መዘዝም ሆነ ላሊውንም ነገር ሁለ
ሇጊዜው ወዯ መርሳት ዯርሰን ነበር። የፇተናው ውጤት፥ በዚያ ጊዜ ይሰጡ በነበሩት ትምርቶች ሁለ፥
በጣም ጥሩ ስሇ ነበረ፥ አስተማሪዎች ትጋትና ብርታት እንዱህም ሊስተማሪዎች የትምህርት አሰጣጥ
ችልታ እንዯ ምስክር ሆኖ ታይቶ በረከቱ ካሌዯረሳቸው ጥቂት አስተማሪዎችና ከቤተሰቦቻቸው በቀር
ባጠቃሊይ ሁለንም ዯስ አሰኝቶ ነበር።

የትምርት ቤታችነን የመዝጊያ በአሌ ካከበርን በሁውሊ ወዯ ዯብረ ማርቆስ ትምህርት ቤት


ከተዛወርሁበት ጊዜ ጀምሬ ሳስበበት የቆየሁት ጉዲይ ሊሇቃዬ፥ ሇጎጃም የትምህርት ክፌሌ አሊፉ፥ ሊቶ
(ሁዋሊ ፉታውራሪ) ወሌዯ ጊዮርጊስ ተዴሊ ገሌጨ፥ ትምህርት ቤታችን በተዘጋበት በረፌቱ ጊዜ
ያሰብሁትን ሇመፇፀም ፇቃዴ እንዱሰጡኝ ጠየቅሁዋቸው። አሳቤ የተወሇዴሁበት አገር እንድዲም ኪዲነ
ምህረት ከዯብረ ማርቆስ ቅርብ ስሇ ሆነ እዚያ በሬዎች ገዝቼ ሁሇት ጥማድች ባስጠምዴ በህሌ በጥራ
ጥሬና በላልች ሇኑሮ አስፇሊጊዎች በሆኑ ነገሮች በኩሌ የሚኖርብኝን ችግር የሚያቀሌሌኝ ከመሆኑ ላሊ
ዴሀ ዘመዴ ሇመርዲትም የሚያስችሇኝ ስሇ መሰሇኝ ይህን ሇማዴረግ ነበር።

አቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ፥ በመሰረቱ አሳቤን ዯግፇውና አበረታተው፥ በተከታዩ አመት አዲዱስ


ትምህርት ቤቶች በሚከፇቱባቸው አንዲንዴ አውራጃዎች ሇጊዜው ስሇሚያስፇሌጉት አስተማሪዎችና
ላልች አስቸኩዋይ መሰናድዎች ተመካክረን መወሰን ስሊሇብን፥ እስከ ነሀሴ አጋማሽ ዴረስ ቆይቼ
እንዴሄዴና ትምህርት ቤት እስከሚከፇትበት ጊዜ ዴረስ ያሰብሁትን ፇፅሜ እንዴመሇስ ፇቀደሌኝ።
እንዱያውም ያሌጠይቅሁዋቸውን ገንዘብ የሚያጥረኝ እንዯሆነ በየወሩ ከዯመወዜ እየተቀነሰ የሚከፇሌ
ብዴር ሉፇቅደሌኝ የሚችለ መሆናቸውን ገሇፁሌኝ። ስሇዚህ ሇመመካከር በትምርት ቤት ውስጥ
ከምሰበሰብበት ስንነሳ፥ ወይም ስብሰባ በላሇን ጊዜ፥ እንድዲም ሄጄ ስሰነብት የሚያስፇሌጉኝን ሳዘጋጅ
ሰነበትሁ።

11
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አንዴ ቀን የስብሰባ ጊዜ ስሊሌዯረሰ ወንበር አውጥቼ እዯጄ እንዯ ተቀመጥሁ እስከ ዛሬ
ሲያስገርመኝ የሚኖር «አንባቢዎችንም ሳያስገርማቸው አይቀርም» ብዬ የምገምተው ነገር ዯረሰ።

ሀምላ 28 1927 ጤናው መንገሻ የሚባሌ ወዲጄ ካገው ምዴር እኔን ፇሌጎ እቤቱ ዴረስ መጣ።
ጤናውን ዲንግሊ ሳሇሁ መጀመሪያ ያወቅሁት በሽፌታነቱ ነበር። በጀግናነቱ የሚያውቁት ሁለ ተባብረው
የሚያዯንቁት ነበር። ምንም እንኩዋ ትንሽ ከመንገዲችን የወጣን ቢመስሌ፥ ጤናውና እኔ የተወቅንበት
ሁኔታ አንባቢዎች ቢያውቁት የሚከፊ ስሊሌመሰሇኝ ባጭሩ፥ እንዯሚከተሇው መግሇፅ እወዲሇሁ።

ዲንግሊ የመጨረሻው የእንግሉዝ ቆንስሌ የነበሩት ሜጀር ችዝማን ከዚያ ሇቅቀው ሲነሱና በሳቸው
እግር ላሊ ቆንስሌ እንዯማይተካ ሲታወቅ ቆንስሊው ትምህርት ቤት ሆኖ፥ እኔ ወዯዚያ ተዛውሬ
ትምህርት ቤቱን እናቁዋቁም እስኪዯረግ ዴረስ በጉምሩክ፥ ውስጥ የተቆጣጣሪነት ስራ ነበር የምሰራው።
በተቆጣጠሪነቴ በየወሩ መጨረሻ ሂሳብ በሚወራረዴበት ጊዜ ካሆነ ብዙ ስራ አሌነበረኝም። ስሇዚህ
አሇቃዬ ያገው ምዴርና ያቸገር የጉምሩክ ስራ አሊፉ የነበሩት፥ ብሊታ፥ ህሇተወርቅ እሸቴ፥ ከጉምሩክ
ሹምነታቸው ላሊ «የባሪያ ነፃ» ሹም ክሌፌም እንዴረዲ ጠይቀውኝ «ቦወድገባነት» ሉተባበሩኝ ከፇቀደ
ጉዋዯኞቼና እሳቸው ሇዚያ ስራ ከመዯቡዋቸው ወታዯሮች ጋር ባንዴነት ሆነነ እንሰራ ጀመር። ምንም
እንኩዋ በባሪያ ሲነግደ የተያዙ ሰዎች በስቅሊት እንዯሚቀጡ ቀዯም ብል የታወጀ አዋጅ ቢኖርም በዚያ
ጊዜ፥ ብርቱ የባሪያ ንግዴ በምስጢር ይሀሂዴ ስሇ ነበር ስራችን «ባሪያ ፇንጋዮችንና» በጠቅሊሊው ባሪያ
ነጋዳዎችን እያዯኑ የያዙዋቸውን ባሮች ነፃ ማዴረግ ስሇ ነበረ ብዙ ባሮች ነፃ አዯረግን። ከጤናው
መንገሻ ጋር የተዋወቅንም ያን ጊዜ ነበር። ጀግንነቱን ብዙ ሰዎች ሲያዯንቁሇት እሱማ ስሇ ነበረ፥ «እሱ
ከኛ ጋር የሆነ እንዯሆነ ከባሪያ ፇንጋዮችና ነጋዳዎች ጋር በነበረን ጦርነት ሀያሌችን ይበረታሌ» ብዬ
በማመን እኔ ነበርሁ ፇሌጌ የተዋወቅሁት። ብቻ በመነጋገር ሊይ እንዲሇን እኔ ከጉምሩክ ወዯ ትምህርት
ቤት በመዛወሬ ንግግራችን ፌፃሜ ሳያገኝ በጅምር ቀረ። ይሁን እንጂ ወዲጅነታችን አሌተቋረጠም፤
ዲንግሊ ትምህርት ቤት በቆየሁበት ጊዜ ሁለ ቶሌቶል እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር።

«ጤናው ዛሬ ምን እግር ጣሇህ?» አሌሁት፥ እዯጅ እንዯ ተቀመጥሁ ወዯኔ ሲመጣ ሳየው ገና
ተገናኝተን ከመሳሳማችን በፉት።

«አንተን ሌጠይቅ ነው የመጣሁ» አሇ ከተሳሳምን በሁዋሊ።

«እኔን ሇመጠየቅ ብቻ ካገው ምዴር እዚህ ዴረስ?»

«ወዲጅነታችን ካገው ምዴር እዚህ ዴረስ አያስመታም ማሇትህ ነው?»

«እንዱያ ማሇቴ እንኩዋ አይዯሇም፤ ላሊ የዯረሰብህ ችግር እንዲሇ ሇማወቅ ነው እንጂ።»

12
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«የዯረሰብኝ ችግር የሇም፤ አንተን ሇመጠየቅና ወዱያውም የፌሌሰታን ፆም እዚህ ሇመያዝ ብዬ
ነው የመጣሁ።»

ይዠው እቤት ገብቼ ቁርስ እንዱያዯርግ ብሇምነው «አዴርጌ አሇሁ» ብል «እንቢ» ስሊሇኝ አንዴ
ብርጭቆ ጠጅ ከጠጣ በሁዋሊ፥ ስብሰባ እንዲሇብኝ ነግሬው ሇምሳ እንዱመጣ ተቃጠርንና፥ እኔ ወዯ
ስብሰባ፥ እሱ ወዯሚሄዴበት ሄዴን። ከስብሰባ ስመሇስ ቀዴሞኝ እዯጅ ቁጭ ብል አገኘሁት።

«ሇምን እቤት ገብተህ አሌተቀመጥህ?» አሌሁት።

«ሌጆች እንኩዋ እንዴገባ ሇምነውኝ ነበር፤ ነገር ግን ብቻዬን እቤት ከመቀመጡ፥ እዚህ ተቀምጨ
እንዱህ አካባቢውን ስመሇከት መቆየቱን ስሇ መረጥሁ ነው አሌገባም ያሌሁዋቸው።»

ከዚያ ገብተን ስሇ አገው ምዴርም ስሇ ዯብረ ማርቆስም፥ እያወራንም ምሳ በሇን። ከቀትር በሁዋሊ
ስብሰባ ስሊሌነበረኝ ስንጫወት እንዴንውሌና እዚያው እኔ ቤት እንዱያዴር ሇመንሁት።

«የሇም የሚያስቸኩሌ ጉዲይ ስሊሇብኝ እሄዲሇሁ» አሇኝ።

«ምን?»

«ማታ ከላልች ሰዎች ጋራ እራት እንዴንበሊ አስቀዴሜ ስሇ ተቀጣተጠርሁ፥ እዚያው ነው


የማዴር፥ አሁን ከዚህ ሄጄ ሽንብራና የንፌሮ መቀቀያ፥ አንዲንዴ የሚያስፇሌገኝን እቃዎችም ስገዛዛ
አመሻሇሁ፤ ነገ ዯህና መቃብር ቤት ባገኝ ፇሌጌ አስንዲዲሇሁ፤ ስሇዚህ ጊዜ የሇኝም» አሇ፤ እንዯሚያፋዝ
ጥርሶቹን በከፉሌ ገሇጥ አዴርጎ።

«ትቀሌዴብኛሇህ መሰሇኝ!» አሌሁት፥ የተናገረው እውነቱን ይሁን ቀሌደን ማወቅ ስሊሌቻሌሁ።

«ቀሌዴ አይዯሇም፤ ውነቴን ነው። ከመጣሁሇት አንደ ዋና ጉዲይ፥ በፌሌሰታ ፆም እዚህ ሱባኤ
ሇመግባት ነው።»

«ስንት ነፌሰ ገዲይ ስንት ንብረት የዘረፌህ ሀጢያተኛ እንኩዋንስ አስራ አምስት ቀን፥ አስራ
አምስት አመት ሽንብራ እየበሊህ ሱባኤ ብትገባ ምህረት አገኛሇሁ በሇህ ተስፊ ታዯርጋሇህ?» አሌሁት።
ሇምቀሇዴ ያህሌ ነው አንጂ፥ ከጅግናነቱና ላልች ሽፌቶች ሳይቀሩ ይፇሩት የነበረ ከመሆኑ ላሊ፥
እንኩዋንስ ብዙ አንዴ ነፌስ ያጠፊ መሆኑን ሰምቼ አሊውቅም።

«ሀጢያተኛ መሆኔን ስሊወቅሁና ፇጣሪዬን ምህረት እንዱያዯርግሌኝ ብሇምነው እንዯሚምረኝ


ስሊመንሁ ነውኮ ምህረት ሌመና ሱባኤ የምገባው። ጌታችን፥ ‹ሀጥአንን እንጂ ፃዴቃንን ሌፇሌግ

13
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሌመጣሁም› አሊሇምን?» ብልኝ ተነሳ። ጤናው ዜማም፥ ቅኔም አዋቂ ነበር። ሌሸኘው ወጥተን እዯጅ
ስንዯርስ።

«ያቺ ዲዊትህ አሇች እንዯሆነ እባክህ ስጠኝ» አሇኝ።

«የትዋ ዲዊቴ?»

« ‹በብርሃንና ሰሊም ማተሚያ ቤት ታተመ› የሚሌ የተጻፇበት የኪስ ዲዊትህ፤ ሇሰው


ሰጠሀት?»

«ሇሰው እንኳን አሌሰጠሁዋትም፤ ብቻ የት እንዲስቀመጥሁዋት አሊውቅም» ብዬ ገብቼ የነበሩኝን


ጥቂት መፃህፌት ወዯ ዯረዯርሁበት ክፌት ሳጥን ብሄዴ በቅርብ ስሊገኘሁዋት አምጥቼ ሰጥቼው ፆሙ
ሲፇሰክ፥ ነሀሴ አስራ ስዴስት ቀን ምሳ እኔ ቤት አብረን ሌንበሊ ተቃጠረን ተሰነባበትን።

ነሀሴ አስራ ስዴስት ከምሳ ሰአት ትንሽ ቀዯም ብል መጣ። ትንሽ ቀጠን ከማሇቱ በቀር፣ መሌኩ
ምንም ያክሌ ስሊሌተሇወጠ አስራ አምስት ቀም ሙለ ሽንብራ - ያውም በቀን አንዴ ጊዜ ብቻ እየበሊ -
ሲፆም የሰነበተ አይመስሌም ነበር።

«ትንሽ የቀጠንህ ትመስሊሇህ እንጂ፥ ላሊ የመጎዲት መሌክ አይታይብህም፤ ፉትህማ እንዱያውም


ካስራ አምስት ቀን በፉት የመጣህ እሇት ሳይህ ከነበረውም ቁሌጭ ብል ዯምህ ጠርቶ አምሮብሀሌ»
አሌሁት፤ ምሳ እየበሇና ስናወራ።

«አቀበት መወጣት፥ ቁሌቁሇት መውረዴ የሇ፤ ሽምብራ ቦቀሌት ቀቅል አንዴ ጊዜ በዘጠኝ ሰአት
በሌቶ ጥሩ ውሀ ጠጥቶ መተኛት ብቻ ነው። ታዱያ ምን ጎዯሇብኝና የጉዲት መሌክ ይታይብኝ?
እንዱያውም ሲሳማማ ብታይ፤ እንዱህ እንዲይመስሌህ!» አሇኝ። የማፋዝበት መስልት እንዲይሰማው
ከዚያ አሌፋ ስሇ ሱባኤው አሊነሳሁበትም፤ እሱም አሊነሳም፤ ላሊ ወሬ እያወራን ምሳ በሌተን ስንጨርስ
ዯክሞት እንዯ ተኝቶ ትንሽ እንዱያርፌ ጠየቅሁት።

«ምንም አሌዯከመኝም፤ ይሌቅ ተነስ ውትርን እንውረዴ» አሇኝ እጁን ታጥቦ ተነሳና፡ ውትርን
ከትምህርት ቤታችን በታች ያሇ ወንዝ ነው። በቀኙና በግራው ሰፉ ሜዲ ስሊሇ፤ ዯስ ያሰኛሌ። እዚያ
ወርዯን ዙሪያውን ዯህና አዴርጎ በሚያሳይ ጉብታ ሊይ ተቀምጠን ስንጫወት እንዯቆየን የሰጠሁንት
ዲዊት ከኪሱ አውጥቶ፣ እዚያ ውስጥ ያስቀመጠውን የተፃፇበትን ወረቀት ገሌፆ ይመሇከት ጀመር።
ከዚያ፥ ዲዊትዋን አጥፍ እፉቱ አስቀመጠና ቅር ያሇው ፉቱን ቀና አዴርጎ ከወንዙ ወዱያ ማድ
‹አረዯዥን› የሚባሇውን ተራራ እየተመሇከተ ዝም አሇ።

14
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ምንዴነው?» አሌሁት፤ ወረቀቱን ካነበበ በሁዋሊ ፉቱን ቅር ሲሇው ስሊየሁ፥ የመርድ ወረቀት
የያዘ መስልኝ ሌቢኤ እየፇራ።

«ፇርንጁ በቅርቡ ጦርነት ሉያዯርግብን ነው። እና የሚቀናን አይመስሇኝም፤ ዴሌ አዴርጎ


አገራችንን የሚይዝ ይመስሇኛሌ። ብቻ ይዞ ብዙ አይቆይም፤ ይወጣሌ፤ አንተም የምትዘምት
ይመስሇኛሌ» አሇ፤ በቅርታ የከበዯ ፉቱን ካረዯዥን ተራራ ወዯኔ መሌሶ።

የዘመዴ ሞት ሉያረዲኝ ብዬ ስፇራ ከወረቀቱ ሲያነብ የቆየው ሱባኤ ገብቶ ያየውን ህሌም
መሆኑን ከሰማሁ በሁዋሊ ሌቢኤን ተጭኖት የነበረው ፌራት ገሇሌ ሲሌሌኝ ተሰማኝና ዯስ ብልኝ
ሳይታወቀኝ እንዴ እመሳቅ አሌሁ። ከዚያ የዯስታ ስሜቴ ከፉቴ እንዲይታይ፥ ነገሩ ያሳሰበኝ ሇመምሰሌ
አንገቴን ዯፌቼ ቆይቼ፥

«እሲት ሁለም ይሁን፤ የኔ መዝመትስ ምን ይባሊሌ? ወታዯር አዯሇሁ!»

«በምን ምክንያት እንዯምትዘምት እኔ አሊውቅም።»

ህሌም የሚባሇውን ነገር ተፇሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብቼ ከቆየሁበት ጊዜ ጀምሬ ማመኑን
ስሇ ተውሁ ያንሇት ጤናው የነገርኝንም አሊመንሁ። ነገር ግን እጅግ ብርቱ ምስጢር አዴርጎ እቤት
እንዲይነግረኝ ቤቱን እንኩዋ ስሇ ጠረጠረ እጠራ ሜዲ ሊይ ወስድ የነገረኝን ያሇመንሁት አስመስል
የሚያሳይ ነገር እንዲሌናገርና እንዲሊስቀይመው በነገርኝ ህሌም ሊይ መተቸት አሌፇሇግሁም። እሱ ግን
አሇማመኔ እንዯ ገባው ከፉቱና ከጠቅሊሊው ሁኔታው ይታይ ነበር።

ወዯ ቤት ተመሌሰን ወዯ ህሌሙ የሚመራ ነገር እንዲንናገር እኔም እሱም እየተጠነቀቅን ላሊ


ወሬ ስናወራ ከቆየን በሁዋሊ፥

«መቸም ዛሬ ስንጫወት አምሽተን እራትም አብረን በሌተን እዚህ ነው የምታዴረው» አሌሁት።

«የሇም እዚህ አሊዴርም። ወዯ አገው ምዴር ከሚሄደ ሰዎች ጋር አብረን አዴረን፥ ነገ ከጥዋቱ
ቀዯም ብሇነ ሇመነሳት ስሇ ተቃጠርንና የምፇፅመው ብርቱ ጉዲይ ስሊሇኝ ሌሂዴ፤ እንዱያውም ጊዜ
ሳሌፋያሇሁ» ብልኝ ተነሳ። አጥብቄ ብሇምነውም ያካፇሇኝን ብርቱ ምስጢር ዯስ ብልኝ ባሇመቀበላ
አዝኖ ይሁን፥ ወይም እንዲሇው ሇማግስቱ የጥዋት ጉዞው እንዱመቸውና ያንሇት የሚፇፅመው ጉዲይ
ኖሮት በዚያ ምክንያት ይሁን «እንቢ» አሇኝ። ስሇዚህ አብሬው ወጥቼ ስንሰነባበት፥

«ታዱያ ነገ ጥዋት የምትሄዴ ከሆነ መቼ ነው የምንገናኝ? እንግዱህ አንገናኝም ማሇት ነው?»


አሌሁት።

15
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«በቅርቡ እንገናኛሇን፤ ወዯ ዘመቻ ከመሄዴህ በፉት መጥቼ አይሀሇሁ» አሇ፤ ያሽሙር ፇገግታ
ፇገግ ብል። «የነገርሁህን አሁን ባታምን፥ በቅርቡ ሲዯርስ ታያሇህ!» ማሇቱ ነው። እኔም ያሽሙሩ
ትርጉዋሜ ገባኝና ሳቅሁ።

ከተሇያየን በሁዋሊ እዯጅ፤ እንዯ ቆምሁ ካይኔ እስኪጠፊ ስመሇከተው ቆይቼ፥ የነገረኝን ህሌም
እያሰሊሰሌሁ እቤት ገብቼ ቁጭ ስሌ፥ ዲንግሊ ሳሇሁ ጣሉያኖች «ይሰራለ» እየተባሇ ይወራ ስሇ ነበረ
አንዴ የተንኮሌ ስራ የሰማሁት ትዝ አሇኝ።

ጣሉያኖች እንዯ ባህታውያንም እንዯ ባሇዛሮችም ሇብሰው ጠጉራቸውን አሳዴገው ወዯየምኩዋንንቱና


በዝህብ ዘንዴ ተሰሚዎች ወዯ ሆኑ ሰዎች እየሄደ፥ «በኢትዮጵያና በኢጣሉያ መሀከሌ ጦርነት ተዯርጎ
ኢጣሉያ እንዴታሸንፌና ኢትዮጵያ ሊጭር ጊዜ ይዛ ቆይታ እንዴትሇቅ እግዚአብሔር አዝዞዋሌ» እያለ
የሚሰብኩ ሰባኪዎች ገዝተው በዚያ ክፌሌ ያሰራጩ መሆናቸው ይወራ ነበር። ባህታዊዎች የነገሩዋቸው
ስዎች ራሳቸው «ነገሩን» እያለ የሚያወሩም ነበሩ። ስሇዚህ ጤናው «ህሌም አየሁ» ብል የነገረኝ
የጣሉያን ሰባኪዎች «በምስጢር ይስበካለ» እየተባሇ ይወራ ከነበረው ስብከት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ
ታየኝና ሇጊዜው ዯነገጥሁ። ነገር ግን ትንሽ ሳስብ ከቆየሁ በሁዋሊ «ጤናው እንዱያ ያሇ ነገር ያዯርጋሌ»
ብል ማመኑን ሌቤ አሌቀበሇው ስሊሇ አሳቡን ቶል ከራሴ ውስጥ አባረርሁት። ያን ዴንገት ትዝ ብል
ያዯነገጠኝን ነገር ብቻ ሳይሆን ሇጊዜው ጤናውንም ህሌሙንም ረስቼ እንድዲም ሄጄ ስቆይ
ስሇሚያስፇሌጉኝ ነገሮች ወዯ ማሰቡና ወዯ ማሰናዲቱ ገባሁ። ብቻ ጤናውንና ህሌሙን ይረሳሁዋቸው
ሇጊዜው ነው። ጤናው «በህሌም መሌክ ታየኝ» ብል የነገረኝን የሚያስገርም ትንቢት ወዱያው ሲፇፀም
ስሊየሁት እሱም ህሌሙም ተመሌሰው መጥተው እንዯማይጠፈ ሆነው ባእምሮዬ ተቀርፀው ይኖራለ።

በጦርነቱ ጊዜ ሲዯረገ ካየሁትና፥ እኔ ራሴ እንኩዋ ካዯረግሁት ብዙ ተረስቶኛሌ። ሀምላ 28


1927 ከጤናው መንገሻ ጋር የተነጋገርነውን ግን፥ ከዚያ ከሚያስገርም ትንቢት ጋር የተያያዘ ስሇ ሆነ፥
አንደን አሌረሳውም። እንኩዋንስ የተነጋገርነው ጤናው ሲናገር በጁ፥ በከንፇሮቹ ባይኖቹ ያዯርገው
የነበረውን እያንዲንደ ትንንሽ እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ ይታየኛሌ።

ከጤናው ከተሇያየንበት ቀን ማግስት ይሁን ሳሌስት፥ ትምህርት ቤት ከመከፇቱ በፉት በሬዎችን


ሇመግዛት አሇቃዬን ተሰናብቼ ወዯ እንድዲም ኪዲነ ምህረት ወረዴሁ።

ምእራፍ ሶስት

ዝግጅት
እንድዲም፥ የናቴ አባት፥ አያቴ እናቴና ሁሇት እህቶቼ ባንዴ ሊይ የሚኖሩበት ከመሆኑ ላሊ ብዙ
የቅርብና የሩቅ ዘመድቼ የሚኖሩበት አገር ነው። ስሇ ሄዴሁበት ጉዲይ ዘመድቼን ሳማክራቸው፥ በመሰረቱ

16
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሳቤን ዯግፇው፥ ወራቱ ያዝመራ ወራት በመሆኑ መሬቱ ሁለ የተዘመረ ስሇሆነና አዝመራው
እስኪሰብሰብ ማረስ ስሇማይቻሌ፥ በዚያ ጊዜ ከብቶችን የመግዛት ትርፈ፥ እነሱን ሲጠብቁ መቆየት ብቻ
መሆኑን አስረዴተው፥ አዝመራ እስኪሰበሰብ ቢያንስ እስከ ጥቅምት መጨረሻ ቆይቼ እንዴገዛ ስሇ
መከሩኝ ምክራቸውን ተቀበሌሁ። ከዚያ በኋሊ፣ የረፌት ጊዜዬን እዚያው ከዘመድቼ ጋር ሇማሳሇፌ ወስኜ
ጥቂት ቀናት እንዯ ቆየሁ አንዴ ቀን ያሇቃዬ ያቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ መሊክተኛ መጥቶ፥ «ቶል ዴረስ
በሌውሀሌ» አሇኝ። ምክንያቱን ያውቅ እንዯሆነ ብጠይቀው፥

« ‹ዛሬ ባይችሌ ነገ እንዲይቀር ንገረው› አለኝ እንጂ ምክንያቱን አሌነገሩኝም» አሇኝ።

በማግስቱ ጥዋት ከንድዲም ተነስቼ ዯብረ ማርቆስ እንዯ ዯረስሁ በችኮሊ የተጠራሁበትን
ምክንያት ሇመጠየቅ ወዯ አቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ ፅህፇት ቤት ሄዴሁ። አቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ ሇምን እንዯ
ጠሩኝ እኔ እስክጠይቃቸው አሌቆዩም፤ ሰሊምታ ሰጥተው ካስቀመጡኝ በሁዋሊ፤ ወዱያው የሄዴሁሇትን
ሳሌፇፅም እንዴመሇስ ሇማዴረግ የተገዯደበትን ምክንያት ሉገሌፁሌኝ ጀመሩ።

«ጣሉያኖች ጦርነት ሉያዯርጉብን ታጥቀው መነሳታቸው ተረጋግጦዋሌ። ጦራቸውን በሰሜን


በኩሌ መረብ ወንዝ ሊይ አሰሌፇዋሌ፤ እንዱያውም ባንዲንዴ ቦታ «ወንዙን ተሻግረዋሌ» ይባሊሌ።
በዯቡብም ቀዯም ብሇው ኢትዮጵያ ውስጥ የያዙዋቸውን ቦታዎች አሌፇው፥ ወዯ ፉት ገፌተዋሌ ይባሊሌ።
ይህ እርግጥ ነው፤ ራስ እምሩ ናቸው አስጠርተው የነገሩኝ። ብቻ እስካሁን ከሳቸውና ካቶ ገብረ መስቀሌ
ሀብተ ማርያም በቀር እዚህ አገር ያወቀ የሇም። ሇኔም የነገሩኝ ህዝቡን ካሁን ጀምረህ ስሇምቀሰቅስበት
ዘዳ ሉያማክሩኝ ነው። ስሇዚህ ከሊይ በይፊ እስኪገሇፅ ዴረስ ምስጢር ነውና፥ ሇማንም ቢሆን ካፌህ
እንዲይወጣ አዯራህ። አሁን እንዲሌሁህ ከራስና ካቶ ገብረ መስቀሌ እዚህ ትምህርት ቤት ከኔና ካንተ
በቀር የሚያውቀው የሇም። ካስተማሪዎች እንኩዋ አንዴ የሚያውቅ የሇም» አለ። አቶ ገብረ መስቀሌ
እዚህ ትምርት ቤት ከኔና ካንተ በቀር የሚያውቀው የሇም። ካስተማሪዎች እንኩዋ አንዴ የሚያውቅ
የሇም» አለ። አቶ ገብረ መስቀሌ ሀብተ ማርያም (ሁዋሊ ዯጃዝማች) የዯብረ ማርቆስ ራዱያ ጣቢያ ሹም
ነበሩ።

«ታዱያ ጣሉያኖች ጦራቸውን አሰሌፇው አገራችን ውስጥ ቦታ ከያዙ እስከ መቼ ዴረስ ነው


ነገሩ ምስጢር ሆኖ የሚቆይ? ሇምን ቶል የዘመቻ አዋጅ አይታወጅ?» አሌሁዋቸው።

«የዘመቻ አዋጅ መቸ እንዯሚታወጅ አሊውቅም፤ መንግስት አዋጁን ያቆየበት ምክንያት


ይኖረዋሌ።»

«ሇመሆኑ ያሇም መንግስታት ማህበር ፇቅድሊቸው ነው? ወይስ ፇቃደን ጥሰው ጣሉያኖች በኛ
ሊይ ጦርነት የሚያዯርጉ?» አሌሁዋቸው፤ ኢጣሉያ በኢትዮጵያ ሊይ ጦርነት ሌታዯርግ መነሳትዋ

17
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እርግጥ መሆኑን ሲነግሩኝ ስሇ አሇም መንግስታት ማህበር ስሰማው ከኖርሁት ጋር አሌጣጣምሌኝ
ስሊሇ ግራ ገብቶኝ።

«መፌቀዴማ እንዳት አዴርጎ ይፇቅዴሊቸዋሌ? ፇቃዴን ጥሰው ይሆናሌ እንጂ። ብቻ


‹ማህበርተኞች ከሆኑት መንግስታት መሀከሌ እንግሉዝና ፇረንሳይ ማስተረቂያ አሳብ አቅርበው አሳቡ
የኢትዮጵያን አገር ከፌል ሇኢጣሉያ የሚሰጥ ስሇ ሆነ፥ የኛ መንግስት አሌተቀበሇውም› ይባሊሌ። ይህ በኔ
ግምት ማህበተኞች መከፊፇሊቸውን በማህበርተኞች መሀከሌ እኛን የማይዯግፈ መኖራቸውን የሚያሳይ
ይመስሇኛሌ» አለና ትንሽ ዝም ብሇው ቆይተው፥

«ሌክ ባርባ አመታቸው ተመሌሰው መጡብን! አይገርምህም? ያዴዋ ጦረንት ሌክ አርባ አመቱ
ነውኮ!» አለኝ።

«አዎ፤ አርባ አመት ነው። ነገር ግን አሁን ያንጊዜ የዯረሰው ውርዯት እንዲይዯርስባቸው ዯህና
ሆነው ተሰናዴተው ስያመጡ አይቀሩም።»

«እውነትህን ነው፤ ዯህና ሆነው ስሇ ተሰናደ አቅማቸው ከዚያን ጊዜው የበረታ መሆኑን
ቢተማመኑ ነው ተመሌሰው የመጡብን። እኛ ግን እንኩዋንስ ከዚያን ጊዜው ሌንበረታ እንዱያውም
ዯከምናሌ!» አለ።

«እንዳት?»

«ያዴዋን ዴሌ ባስገኙት የዴሮ መሪዎችና በጦር ሰራዊታችወ መሀከሌ የነበረው የተቀራረበ


ግንኙነት በዛሬዎቹ መሀከሌ የሇም። የዴሮ መሪዎች ተወሌዯው ባዯጉበት አገር፥ ከትውሌዴ ወዯ
ትውሌዴ ሲወርዴ ሲዋረዴ የመጣ የገዥነት ወይም የመሪነት ስሌጣናቸውን ከዘር የወረሱ በመሆናቸው
ከመኩዋንንታቸውና ከጦር አሇቆቻቸው ጋር እርስ በእርሳቸው ብቻ ሳይሆን አባት ሊባት አያት ሊያትና
ታሪክ ሇታሪክ ጭምር የሚተዋወቁ ስሇ ነበሩ፥ ግንኙነታቸው የጠበቀ ነበር። ዛሬ ግን እኒያ በያገራቸው
ከመኩዋንንቱ ከጦር አሇቆችና በጠቅሊሊው ከጦር ሰራዊቱ ጋር በቅርብ ይተዋወቁ የነበሩት መሪዎች
እየተነሱ፥ አዲዱስ መሪዎች ካዱስ አበባ ተሌከው ስሇ ተተኩ፥ በያገሩ ያሇው የጦር ሰራዊት
‹ያውራዎቻችን ሌጆች አውራዎቻችን› በሚሊችው መሪዎች ፇንታ የማያውቃቸውና የማያውቁት
እንግድች መሪዎቹ እንዱሆኑ በመዯረጉ ቅር ያሇው መሆኑ ይሰማሌ።

«እንዯምታውቀው ከኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ውስጥ በጣም የሚበዛው ከውጭ ጠሊት ጋር


በጀግንነት ሲዋጋ የኖረው ከሊይ እስከ ታች በየዯረጃው ስጋ አብሌቶ ጠጅ ሇሚያጠጣው ሇሚሾመውና
ሇሚሸሌመው ጌታው ሲሌ ነው እንጂ ሊገሩ ወይም ሇባንዱራው ብል የሚዋጋ ቢኖር በጣም ጥቂት
ይሆናሌ። በጥንቱ ሌማዴ የኢትዮጵያ ወታዯር ታማኝነቱ ሇጌታው እንጂ፤ ሊገሩ አይዯሇም! ሌብ አዴርግ

18
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይህን ክፈ ሌማዴ መዯገፋ እንዲይመስሌህ! ክፈ ሌማዴ መሇወጥ የሚገባው መሆኑ መቸም የታወቀ
ነው! ነገር ግን ክፈም ቢሆን ሌማዴ ሆኖ ስራት ሆኖ አጋእራንን እስከ ዛሬ በነፃነት ያቆያት ስሇሆነ
ታማኝነቱ ሊገሩና ሇባንዱራው የሆነ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት አሰሌጥኖ ሳይተኩ የነበረውን ማዴከም
ወይም ማፌረስ ባድ እጅ የሚያስቀር ስሇሆነ ይህን ነው የጠሊሁት። ዛሬ ያሇንበት ሁኔታ፥ ከጥቂት ሽህ
የክብር ዘበኞች በቀር ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ተሰናዴቶ ሳይተካ የጥንቱ የዯከመበት ነው። ሇዚህ ነው፤
‹እንኩዋንስ ከጥንቱ ሌንበረታ እንዱያውም ዯከምናሌ› ያሌሁህ» አለ።

«ብቻኮ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ሇማሰሌተን አሁን እንዲለት በክብር ዘበኞች ተጀምሮ ነበር።
ሆሇታም የጦር መኮንኖች በብዛት ይሰሇጥናለ ይባሊሌ። ዯግሞ ኢትዮጵያ የአሇም መንግስታት ማህበር
አባሌ እስከ ሆነች ዴረስ ጠሊት ሉያጠቃት እንዲማይችሌ ፅኑ እምነት ስሇ ነበረ ይመስሇኛሌ፤ የጦር
ሰራዊቱን በሙለ ከጥንታዊው ወዯ ዘመናዊው ሇመሇወጥ መንግስት ያሌቸኮሇበት» አሌሁዋቸው።

«የቸሌተኛነት ይሁን ወይም ያቅም ማነስ ወይም ላሊ ምክንያቱን ስሊማሊውቀው ሌነግርህ


አሌችሌም። ብቻ መተኪያውን ሳናሰናዲ፥ የጥንቱን ስራት እያፇረስን በሚያሰጋ ሁኔታ ሊይ መሆናችንን
ነው ሌነግርህ የፇሇግሁ። የሆነ ሆኖ አሁን እሱን እንተውና የሄዴህሇትን ስራ ትተህ እንዴትመጣ
ሇማዴረግ የተገዯዴሁበትን ምክንያት ሌንገርህ» ብሇው ወዯ ተጠራሁበት ጉዲይ ተመሇስን።

«ቅዴም እንዲሌሁህ፥ ራስ አስጠርተውኝ ካሁን ጀምሮ ህዝቡን መስቀስቀስ አስፇሊጊ መሆኑን


ከተስማማን በሁዋሊ የሳቸው አሳብ እኛ እዚህ ትምርት ቤት ትያትር አዘጋጅተን እሳቸው፥
መኩውንንቱንና የጦር አሇቆችን፥ እንዱሁም ከከተማው ነዋሪዎች የታወቁትን ሰዎች ጠርተው እግቢ
እንዱታ ይሁሇተኛ የሚያነቃቃ ንግግር እየተዘጋጀ፥ ህዝብ በሚሰበስባቸው ቦታዎች እንዱነገር ነው።
ስሇዚህ የጠራሁህ፥ ከመሀከሊችን ካሁን ቀዯም ካዱስ አበባ ትያትር ሰርተህ ያሳየህ አንተ ስሇ ሆንህ ራስ
የጣለብኝን ከባዴ አዯራ ባንተ ሊይ ሇመጣሌ ነው» አለ። እውነትም፣ እንኩዋንስ ስራው ወሬው ከባዴ
ስሇ ነበረ ከብድኝ አንገቴን ዯፌቼ ቆይቼ አሌሁና፥

«ሇመሆኑ ትያትር አዘጋጅተን አስጠንተን ሇማሳየት የሚበቃ ጊዜ ይኖረናሌ?»

«ጊዜውስ አጭር ነው፤ ከሚመጣው ወር (መስከረም) መጨረሻ በፉት መታየት ይኖርበታሌ፤


ብቻ በኔ አሳብ አዱስ አበባ ማጀስቲክ ሆቴሌ የታየውን ትያትር አሁን ሇተፇጠረው ሁኔታ እንዱስማማ
አዴርጎ ማሻሻሌ የተቻሇ እንዯሆነ ባሇን አጭር ጊዜ ውስጥ ሇማሳየት የሚዯርስ ይመስሇኛሌ፤ እንዱህ
ማዴረግ አይቻሌም?»

«አዱስ አበባ የታየው ትያትር ፅሁፌ በጄ ስሊሇ፥ እስቲ አሁን ሇተፇጠረው ሁኔታ እንዱስማማ
አዴርጌ ማሻሻሌ እችሌ እንዯሆነ ዛሬ አይቸው ነገር ሌንገርዎና ከዚያ በሁዋሊ ስሇምናዯርገው እንነጋገር»
ብያቸው ተሰነባበትን።

19
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እውነትም አቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ እንዲለት አዱስ አበባ ማጀስቲክ ሆቴሌ የታየው «ያበሻና
የወዯሁውሊ ጋብቻ» የተባሇ ትያትር የመጨረሻው ክፌሌ ያጥራሌ እንጂ በጊዜው ሇተፇጠረው ሁኔታ
የሚስማማ ሆኖ አገኘሁት።

ከዚያ ረዥም ትያትር የሚበዛ፥ «አበሻና ወዯ ሁዋሊ» ተዋዯው ፌቅራቸውን በግጥምና በሌዩ ሌዩ
የፌቅር መግሇጫዎች ሲገሊሇፁ ከዚያ እንዱጋቡ ወስነው ከጋብቻ በፉት የሚዯረገው ስነ ስራት ተፇፅሞ፥
በዘፇን በዯስታና በሆታ ሲጋቡ ከዚያ በጋብቻ ኑሮዋችወ ወዯ ሁዋሊ ያበሻን ሀብትና ንብረት እየሸጠ
መስከሪያና መዯሰቻ አዴርጎ ጨርሶ እሷ ዯህይታ፥ አይነ በሽተኛ ሆና ስታሇቅስ የሚታይበት ነበር።
በመጨረሻው ክፌሌ አበሻን፥ ከጥንት ጀምሮ የሚያውቃት አቶ ‹አእምሮ› የተባሇ አስተዋይ ሽማግላ
ሌጆችዋን ሰብስቦ እናታቸው እዴኒያ ስትንገሊታ ዝም ብሇው በመመሌከታቸው ወቅሶ ከወዯሁዋሊ
እንዱያሇያይዋት የመክራቸውና ያበሻ ሌጆች ባንዴነት ሆነው ወዯ ሁዋሊ እናታቸውን በሰሊም አሌፇታም
ስሊሇ እሱን ገዴሇው እናታቸውን ነፃ ሲያወጡ ዯስታ ችፇራ ቀረርቶና ፈከራ ይሆናሌ። ይህ የመጨረሻው
ክፌሌ ከማጠሩ በቀር፥ «በወዯሁዋሊ» ፇንታ «ፊሽስት ኢጣሉያን» ተክተን እንዱስማማ የማሻሻያ
ሇውጦች ተዯርገውሇት ሇታሰበው ስራ ሉሆን እንዯሚችሌ ሊቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ ነገርሁዋቸው። ወዱያው
ከማሻሻያው ጋር ተባዝቶ የሚሰሩት ሌጆች እንዱያጠኑት ተሰጣና ሌጆቹ ያን ሲያጠኑ፥ እኔ አንዴ
ሳምንት ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ ሇዚኢያ ተጭማሪ የሚሆን አጠር ያሇ ትያትር አዘጋጅቼ አዯረስሁ። መቸም
ቀስቅሶ ሇማሸሇሌና ሇማስፍከር ያክሌ የሚበቃ ከመሆን አሌፍ በኪኢነት መሌኩ ሲታይ ‹ከትያትር ተራ
ገብቶ የሚቆጠር ነበር› ሇማሇት አያስዯፌርም። ያዱሱ ትያትር የታሪክ ንዴፌ ባጭሩ እንዯሚከተሇው
ነበር።

አንዴ የፇረንጅ አገር ንጉስ፥ ባገሩና በኢትዮጵያ መሀከሌ የወዲጅነት ግንኙነት እንዱመሰረት የሚሻ
መሆኑን ገሌፆ ሇኢትዮጵያ፥ ንጉስ ይፅፊሌ። የኢትዮጵያ ንጉስም አሳቡን በዯስታ የተቀበሇ መሆኑን
አስታውቆ፣ መሌስ ይሰጣሌ። ከዚያ የፇረንጁ ንጉስ ግብዣ ቢዯረግሇት ኢትዮጵያን ሇመጎብኘት የሚወዴ
መሆኑን መሆኑን ሇኢትዮጵያ ንጉስ ይፅፌና ተጋብዞ መጥቶ፣ ሇንጉስ የሚገባ አቀባበሌ ተዯርጎሇት
ኢትዮጵያን እየዞረ ሲያይ ሰንብቶ፥ ዯስ ብልት ይመሇሳሌ። አገሩ ከዯረሰ በሁዋሊ ስሇ ተዯረገሇት
የወዲጅነት አቀባበሌና መስተንግድ አመስግኖ በጉብኝቱ ጊዜ እንዯ ተመሇከተው፥ ኢትዮጵያ መሬትዋ ሰፉ፥
ህዝብዋ ጥቂት ሲሆን፥ የሱ አገር መሬቱ ትንሽ ህዝቡ ብዙ ሆኖ ብርቱ ችግር ስሇ ገጠመው የኢትዮጵያ
ንጉስ መሌካም ፇቃዴ ሆኖ ከሰፉ ሀገሩ አንዴ ክፌሌ ከፌል ቢሰጠው መሬት የጠበበው ህዝቡን እዚያ
አስፌሮ ወዱኢያው ኢትዮጵያንም በዘመናዊ ስሌጣኔ ኢትዮጵያን በሙለ በጦር ሀይሌ ሇመያዝ የሚገዯዴ
መሆኑ አስታውቆ ይፅፊሌ። የኢትዮጵያ ንጉስ፥ የፇረንጁ ንጉስ እንዯ ወዲጅ ተጋብዞ መጥቶ ያገሩን
መግቢያና መውጫ ካጠና በሁዋሊ እንዱያ ያሇ የክህዯትና እብሪት መሌእክት ስሇ ሊከበት ተገርሞ
መኩዋንንቱንም የጦር አሇቆችንም ሰብስቦ ስሇ ዯረሰው የፌሌሚያ ጥሪ ሲነግራቸው ሁለም ይቆጡና
ሇጦርነት የተዘጋጁ መሆናቸውን ሇተፊሊሚው ሳይውሌ ሳያዴር እንዱጻፌሇት ይነግሩታሌ። ከዚያ፥

20
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የኢትዮጵያ ንጉስ «አንተ በዘመናዊ መሳሪያና በሰሇጠነ ወታዯርህ ብትመካ፥ እኔ እንዯ ሰማይ ከዋክብትና
እንዯ ባህር አሸዋ በበዛው የሰራዊቴ ጀግንነትና በእግዚአብሔር ሀይሌ ተማምኜ እጠብቃሇሁ፤ ና» ብል
ሇፇርንጁ ንጉስ ይመሌስሇታሌ። ከዚያ ጦርነት ይሆንና ኢትዮጵያውያን ዴሌ አዴርገው፣ክ፣ እያቅራሩና
እዬፇከሩ የማረኩትን፥ የጠሊት ወታዯርና መሳሪያ ከንጉሳቸው ፉት ሲያቀርቡ ይታያለ።

ሁሇት ትያትሮች እንዱሰሩ የተመረጡት ተማሪዎች በብርቱ ትጋት አጥንተውና በትምህርት


ቤቱ አዲራሽ ውስጥ ሲያሇዝቡ ሰንብተው ከተገመተው ጊዜ በፉት እግዝቢ፥ በ«ሰንተራ ሜዲ» ስም
በተሰየመው ሰፉና፥ ረዥም አዲራሽ ውስጥ አሳዩ።

ራስ እምሩ ከመኩዋንንቱና ከጦር አሇቆች ላሊ፥ በከተማው የታወቁ ሰዎች፥ በንግዴ፥ በሚሲዮንና
በተሇያዩ ስራዎች እዚያ ይኖሩ የነበሩት ጥቂት የውጭ ዜጎች እንዱሁም አዲራሹ እስከ ቻሇ ዴረስ
ወታዯሩ ተጠርቶ እንዱያይ አዴርገው ስሇ ነበረ፥ የተቀመጠው ተቀምጦ፥ የቆመው በግንቡ ዙሪያ
ተዯራርቦ ቆሞ አዲራሹን እስኪጨንቀው ሞሌቶት ነበር። ትያትሮች ሲጀምሩ አዱስ አበባን ማጀስቲክ
ሆቴሌ «ያበሻና የወዯሁዋሊ ጋብቻ» የተባሇው ትያትር በታየ ጊዜ ሇሱ መክፇቻ እንዱሆን አሰናዴቼ
ያስዘመርሁት መዝሙር ተዘመረ። ያ «ተነሱ ታጠቁ» የተባሇው መዝሙር ከዚህ የሚከተሇው ነበር።

«ተነሱ ታጠቁ፤ ኢትዮጵያን፥

እንጀምር ስራ በስመ አብ ብሇን፥

ርቀው ሄዯዋሌ፥ ጉዋዯኞቻችን፥

እንዴረስባቸው በጣም ተፊጥነን፥

አሁን በብርሃኑ ጨሇማ ሳይሆን

ወዯ ሁዋሊ ቀርተን አውሬ እንዲይበሊን፤

ኢትዮጵያ አገራችን ስሇ ነፃነትሽ ይፇሳሌ ዯማችን»

«ምስጋና ይዴረሰው ሇሰማዩ ጌታ፥

ጠብቆ ሊቆየን በሰሊም በዯስታ፥

ውዴ ሀገራችንን ከብዙ ወስሊታ፥

እንግዱህ እንጠንክር በጣም እንበርታ

እንዲናወሊውሌ እንዲናመነታ

21
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ህይወታችን ይሇፌ ባንዱራችን ፇንታ፤

ኢትዮጵያ አገራችን ስሇ ነፃነትሽ ይፇሳሌ ዯማችን»

«እናት ኢትዮጵያ ውዱቱ ውዱቱ፥

በሶስቱ ቀሇሞች የተሽሇምሽቱ፥

ነፃነት የሚዯፌር ቢመጣብሽ ብርቱ፥

ዯማችን ይፇሳሌ አይቀርም በከንቱ፥

ሊንቺ የማይረዲ ሳሇ በህይወቱ፥

በረከትሽን ይንሳው እስከ እሇተ ሞቱ፤

ኢትዮጵያ አገራችን ስሇ ነፃነትሽ ይፇሳሌ ዯማችን።»

ሁሇቱንም ትያትሮች ተመሌካችሁ ሁለ በጣም ነበር የወዯዲቸው። ይሌቁንም መጀመሪያ ያበሻ


ሌጆች ወዯ ሁዋሊ ገዴሇው ሲያቅራሩና ሲፍክሩ፥ በሁዋሊ ከፇረንጁ ጠሊት ጋር በተዯረገው ጦርነት
ኢትዮጵያውያን ዴሌ አዴርገው እያቅራሩና እየፍከሩ ምርኮዋቸውን በንጉሳቸው ፉት ሲያቀርቡ
በተጫዋቾች ሊይ ይታይ የነበረው ግሇት በተመሌካቾች ተጋብቶ ወኔያቸውን የቀሰቀሰ መሆኑ በግሌፅ
ይታይ ነበር። ከትያትር ተጫዋቾች አንዴ ዴምፃዊ ‹የነሲብ› ሌጅ ምርኮኛውን እንዯ ያዘ በሚሸጥ ዴምፅ
አቅራርቶ አቅራቶ መፍከር ሲጀምር ወዱያ ታች ያዲራሹን ጥግ ይዘው ከቆሙት ወታዯሮች አንደ
የተቃጠሇ ስሚዓቱን አፌኖ መያዝ አቅቶት፥

«አ - ህ! ቡር -! አካኪ ዘራፌ!» ብል ጎራዳውን መዝዞ እያወናጨፇ ወዯ ፉት ሲሮጥ ሁለም


ፉቱን ከትያትር ሰራተኞች ወዯ ሱ አዞረ። ያ ወታዯር የሚያብረቀርቅ ጎራዳውን እያወናጨፇ፥ ሮጦ ራስ
በግንባር ከተቀመጡበት ሉዯርስ ትንሽ ሲቀረው እዚያ በግንባር ከተቀመጡት የውጭ ዜጎች አንዲንድቹ -
ነገሩ እንግዲ ስሇ ሆነባቸው እንዯ ሆነ አይታወቅም - ከተቀመጡበት ተፇንጥረው እየተነሱ ሇመሸሽ
ቃጥተው ነበር። ወዱያው ራስ ሇጊዜው ተቆጥተው ወታዯሩ ተይዞ እንዱቆይ ስሊዯረጉ ሰሊም ሆነና
ጭዋታው ቀጠሇ። ነገር ግን ጭዋታውም ወዯ መጨረሻው ዯርሶ ስሇ ነበረ እንዲሇቀ ተይዞ የቆየው
ወታዯር እንዱሇቀቅና እፉታቸው ቀርቦ እንዱፍክር ፇቅዯውሇት ፈከራውን ያንዯቀዴቀው ጀመር። እዬተን
በረከከ እየተነሳ፥ ዙሪያ እየዞረ እየዘሇሇ፥ ቆሞ እንዯ ባሊውላ እየተንዘረዘረ ሲፍክር በፉቱ ይወርዴ የነበረው
ሊክ ከውስጡ እየፇሊ በራሱ ገንፌል ፉቱን የሚያጥሇቀሌቅ ውሀ እንጂ ሊብ አይመስሌም ነበር! ከዚያ ምን
እንዯሚፇሌግ ሲጠየቅ፥ የሚጠይቀው ጠፌትቶ ዝም ብል ቆይቶ፥

22
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ገዴዬ እፉትዎ የምሞትበት አንዴ አዱስ ጠመንጃ ብቻ ነው የምፇሌገው ራስ ሆይ፤ ሇጌታዬ
ላሊ የምፇሌገው ነገር የሇም!» አሇ። ወዱያው አንዴ ጠመንጃ ከሚያስፇሌገው ጥይት ጋርና ሀያ ብር
እንዱሸሇም ታዝዞሇት ዯስ ብልት ወዯ ቦታው ተመሇሰ። ከዚያ የውጭ ዜጎች እንዱሰናበቱ አዯርጎ እነሱ
ከወጡ በሁዋሊ ሇኢትዮጵያውያን ብቻ የሚነቃቃ ንግግር እኔ እንዲዯርግ ታዝዤ ስሇ ነበረ፥ ያሰናዲሁትን
ንግግር አዯረግሁ።

ያንሇት በረዥሙ ያዯረግሁትን ንግግር አሁን መሇስ ብዬ ሳስታውሰው ይገርመኛሌ! ስሇ


ኢትዮጵያ ታሪክና ስሇ ዘመናዊ መሳሪያ ሲነገር የሰማሁት እውነቱም ስህተቱም ባንዴነት፥ የተዯባሇቅበት
ወሬ በመኡለ እውነት መስልኝ ያን እያስፊፊሁና እያጋነንሁ በዴፌረት መናገር «የማያውቁ አፌረ
አይጨነቁ» እንዯሚለት ስሊሊወቅሁ እንኩዋንስ እፌረት ሉሰማኝ የምናገረው ሁለ እውነት ሇመሆኑ
ትንሽ የጥርጥር ምሌክት አይታይብኝም ነበር! አዲራሹን የሞለት ሰሚዎቹም የምናገረው እውነት
መሆን አሇመሆኑን ከመመርመር ይሌቅ፥ - በንግግሩ ማማር ተማርከው ይሁን ወይም ከኔ የተሻሇ
የማያውቁ ስሊሌነበሩባቸው እንዯ ሆነ አይታወቅም - ሁለም የዯስታና ያዴናቆት ምሌክት ነበር
የሚታይባቸው።

በሙለ አፌሪካ ከሚኖሩት አገሮች ሁለ፥ ኢትዮጵያ ብቻ ወሰንዋ ታፌሮ፥ ነፃነትዋ ተከብሮ
የኖረች በሌጆችዋ ጀግንነት እንጂ በመሳሪያ ጥራት አሇመሆኑ ኢትዮጵያውያ በመሳሪያችው ትራት
እየተመኩ በየጊዜው የመጡባቸውን ጠሊቶች ሁለ በጦርና በጎራዳ ዴሌ እየመቱ፥ መሳሪያቸውን ማርከው
ውርዯት እያከናነቡ ሲኢመሌሱ የኖሩ መሆናቸውን ኢጣሉያ ራስዋ ከዚያ በፉት ከታንክና ካይሮፕሊን
በቀር በጊዜው በነበረው ዘመናዊ መሳሪያዋ እንዯ ላልቹ ተመክታ ሰሀጢ ድጋሉ መቀላና አዴዋ ሊይ
ከኢትዮጵያ ጋር ባዯረገቻቸው ጦርነቶች ዴሌ ተመትታ፥ መሳሪያዋንና ሰዎችዋን አስማርካ የተመሇሰች
መሆንዋን ያን ሁለ ካስረዲሁ በሁዋሊ ታንክና አይሮፕሊን ወሬያቸው የሚያስፇራውን ያክሌ
አሇመሆናቸውን ሇመግሇፅ እያጋነንሁ ከተናገርሁት ትዝ የሚሇኝ ከሞሊ ጎዯሌ እንዯ ሚከተሇው ነበር።

«ታንክ እንዯ ኢትዮጵያ ተራራማ በሆነ፥ አገር ሇሚዯረግ ጦርነት የተሰራ መሳሪያ አይዯሇም።
ታንክ ተራራ ወጥቶ፥ ገዯሌ ወርድ ሉዋጋ የማይችሌ እንዯ ወይዘሮ ባሌተዯሇዯሇ ጉርብጥብጥ መሬት ሊይ
የማይንቀሳቀስ ዘበናይ መሳሪያ ነው። አይሮፕሊንም የጦርነት ግጥሚያ ሲሆን ሇማስፇራራት እሊይ ሆኖ
ከማጉራራት በቀር፥ ወገኑን ጭምር እንዲይመታ፥ ቦምብ ሇመጣሌ አይፇቀዴሇትም፤ በጥብቅ የተከሇከሇ
ነው። ሁሇተኛ የጠሊቱን የጦር ሰራዊት ከወገኑ ሩቅ በሆነ ቦታ እሜዲ ሊይ ሰፌሮ ካሊገኘ ሉያጠቃ
አይችሌም። ሶስተኛ በጠመንጃ ይቅርና በሽጉጥ እንኩዋ ከተመታ ወይም ዝቅ ብል ሲበር ክንፈን የዛፌ
ቅርንጫፌ ከነካው ሰሇሉት እንዯ በሊው ሸክሊ ተንኮታኩቶ የሚወዴቅ ግብዝ ነገር ነው። ስሇዚህ ዞሮ፥ ዞሮ፥
ጦርነቱን የሚወስነው ጀግነነት ስሇ ሆነና ጀግንነትም ማንም የማይከፇሊቸው የኢትዮጵያውያን የተፇጥሮ
ሀበት ስሇ ሆነ አሁንም እንዯ ሁሌጊዜው ዴለ የኢትዮጵያውያን እንዯሚሆን አይጠረጠርም!» እያሌሁ

23
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዯዚያ እንዯ ፍከረው ወታዯር ፉቴ በሊብ ባይታጠብም፥ ሊብ ሊብ እያሇኝ ዯረቴን ነፌቼ ስናገር
ያይሮፕሊንና የታንክን መሌክ ብቻ ሳይህን ውስጠ ምስጢራቸውን ሁለ አንዴ ባንዴ የማውቅ እመስሌ
ነበር! የተፇሪ መኮንን ትምርት ቤት ተማሪ በነበርሁ ጊዜ፥ የመጀመሪያው ይሁን ሁሇተኛው አይሮፕሊን
መጥቶ ጃንሜዲ ሲያርፌ ብዙ ተማሪዎች እየሮጥን ሄዯን እሜዲው ውስጥ እንዲንገባ ስሇ ተከሇከሌን፥
በውጭ ቆመን አይሮፕሊኑን ከሩቅ አይተን ተመሌሰናሌ። እንግዱህ ያይሮፕሊን እውቀቴ ያን ያክሌ ነው።
ከዚያ በፉትም ሆነ ከዚያ በሁዋሊ እስከ ዘመቻው ዴረስ ጎጃም በቆየሁበት ጊዜ አይሮፕሊን የሚባሌ አይቼ
አሊውቅም። እንዱያውም የታንክንማ ከስሙ በቀር መሌኩን እንኩዋን አንዴ ቀንም አይቼ አሊውቅ! ይሁን
እንጂ ያዯረግሁት ንግግር አሊማውን ግሩም አዴርጎ መታ! መኩዋንንቱም የጦር አሇቆችና ወታዯሩም
ጠሊታቸውን ዴሌ እንዯሚመቱ ሙለ እምነት አዴሮባቸው ያኔውኑ ሲቃ እንዯ ያዛቸው ከሁኔታቸው
ሁለ ይታይ ነበር። ከዚያ በሁዋሊ መስከረም 22 1928 አዱስ አበባ ወዱያው ተከታትል ዯብረ ማርቆስ
የጦርነት አዋጅ ታወጀ።

የክተት አዋጁ ከተነገረ በሁዋሊ ዯብረ ማርቆስ በግቢ፥ በገብያ ወይም በላሊ ሰው በርከት ብል
በምገኝበት ቦታ ሁለ ሲወራ የሚሰውማው ስሇ ዘመቻው ሲዯረግ የሚታየው ሇዘመቻ የሚያስፇሌገው
ነገር ሆነ። ትምርት ቤት እንኩዋ ምንም ሇስሙ ቢከፇት በዚያ ጊዜ ካስተማሪዎችም ከተማሪዎችም ስሇ
ትምርት የሚነጋገሩ አሌነበሩም፤ ሁለም የሚነጋገሩና የሚከራከሩ ስሇ ጦርነቱ ነበር። ከመሸ በሁዋሊ
መጠጥ ቤቶች ወዲለበት ወዯ መሌሀ ከተማ የተሄዯ እንዯ ሆነ እዚያ የሚሰማው በዘፇን ፇንታ «ሰንጎ
መንጋ» «እረ ቸ በሇው» ወይም እነሱን የመሰሇ ወኔ የሚቀሰቅስ ጭዋታ ነበር። እንዱሁም ማታ ማታ
በትምርት ቤታችን አቅራቢያ ከነበሩት የመኩዋንንት ሰፇሮች ባንዲንድቹ ከዚያ በፉት ተሰምቶ የማያውቅ
ቀረርቶና ፈከራ ይሰማ ስሇ ነበረ፥ ብዙዎቻችን እዯጅ ቁጭ እያሌን ያን ቀረርቶና ፈከራ ስንሰማ ማምሸት
እንወዴ ነበር።

የከተማው ብቻ ሳይሆን የባሊገሩ ዘማች፥ ሇጠመንጃው ጥይት ሇላሇው ጥይት ሉገዛ ዴንኩዋን
የላሇው ሇዴንኩዋኑ አቡጀዱዴ ሉገዛ፥ ሇስንቁና ሇዴንኩዋኑ መጫኛ የላሇው በቅል ወይም፥ አህያ ሉገዛ
በያካባቢው ወዯ ዯብረ ማርቆስ መጥቶ፥ በየሱቁና በየገብያው ሲጣዯፌ የሚታየው ሁለ ወዯ ሞት
ሳይሆን ዯስ ወዯሚያሰኝ የጭዋታ ቦታ ሇመሄዴ የሚሽቀዲዯም ይመስሌ ነበር።

ታዱያ በወጣሁ ቁጥር ያን፥ ጠቅሊሊ የህዝብ እንቅስቃሴ አይቼ ተመሌሼ ወይም ማታ ከቤቴ ዯጅ
ተቀምጬ ባካባቢዬ ከመኩዋንንቱ ሰፇር የሚስማማውን ቀረርቶና ፈከራ ስሰማ ቆይቼ ገብቼ ስተኛ ያ፥
ሇዘመቻ የሚያስፇሌጉትን ነገሩች ሇመግዛት ሲሽቀዲዯም ያየሁት ሁለ ያ፥ ሲያቅራራና ሲፍክር
የሰማሁት ሁለ፥ ከጥቂት ጊዜ በሁዋሊ ወዯ ጦርነቱ ሲጉዋዝ እዚያ ከጠሊት ጋር ገጥሞ ሲዋጋ ሲኢገዴሌ
ሲሞት፥ ቅስል፥ ሲጨነቅ፥ ስእለ ይታየኝና መንፇሴ እረፌት አጥቶ እየተወራጨሁ ስነሳ፥ ተመሌሼ ስተኛ
ቆይቼ «ሌዝመት ወይስ ሌቅር?» እሊሇሁ። ሇዚህ ጥያቄ በቀሊለ መሌስ ሇማግኘት አሌቻሌሁም። ካንዴ

24
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወገን ጭፌራ የላሇኝ ነጠሊ ሰው ብቻዬን ዘምቼ በጦርነቱ ሜዲ ሊይ ሊዯርገው ከምችሇው ይሌቅ
ያስተማሪነት ስራዬን ስሰራ ብቆይ ሊገር የበሇጠ የሚጠቅም መሆኑ ይሰማኛሌ። ከላሊ ወገን፥ ያ ሁለ
እንዱሁ በተሇምድ ወይም «ሀይማኖር የሚያስሇውጥ ርስት የሚነቅሌና ነፃነት አሳጥቶ እንዯ ባሪያ
የሚገዛ ጠሊት መጣብህ» ተብል የተነገረውን እንዱሁ በጭፌኑ አምኖ ሇመዋጋት ሲዘምት እኔ የነፃነትን፥
ትርጉም ከብዙዎቹ የተሻሇ የማውቀው ወዯ ሁዋሊ መቅረት የማይገባ መስል ይሰማኛሌ። ይሌቁንም
ትያትር ያሳየን እሇት ወኔ በሚቀሰቅስ ንግግር የላልችን ሇጦርነት ታጥቀው እንዳንሱ አዯፊፌሬ እነሱ
ታጥቀው ሉዋጉ የኔን ወዯ ሁዋሊ መቅረት ሳስብ በሌጅነቴ ጎበዛዝት በርከት ብሇው በሚገኙባቸው የዴግስ
ቤቶች ስሇ ፇሪ፥ «እሸረረ» ግጥም እየገጠሙ ሲጫወቱ እስማቸው ከነበሩት ግጥሞች አንዲንድቹ ትዝ
ሲለኝ ያን ጊዜ በኔ ሊይ እንዯ ገጠሙዋቸው ሁለ እረፌት ይሰማኛሌ። ከኒያ የ«እሸረረ» ግጥሞች ትዝ
ያለኝ የሚከተለት ናቸው።

«የማይመጣ መስልት እያሇ ሲያቅራራ ‹ጎራው ና፥ ጎራው ና›

ይመስሇን ነበረ ሌቡ ሙለ ጅግና፤

ሆዴ ቁርጠት አመመው፥ የጎራውን መምጣት ከመስማቱ ገና፥

ሇካስ አሞት የሇሽ ፇሪ ኖሮዋሌና!»

«አብረን ሌንሰሇፌ እሱ ምል ነበር፤ እኛንም አምለ፥

ማየቱን ፇራና መሬት ጢሳ ስትነዴ፥ በጥይት ቃጠል፥

እንዯ ባቄሊ አሹቅ፥ ቀረ ሹሌክ ብል!»

«ባምስት ፇጅ እንካቦ ጠሊውን ከሌብሶ፥

ተነስቶ ሲፍክር ግንባሩን ከስክሶ አይኑን ዯም አጉርሶ

ጀግና መስልን ነበር ጠሊት አሸባሪ ምሽጉን ጣጥሶ፤

‹ጦር መጣብህ!› ቢለት አእምሮው ተቃውሶ

ሆድኡ እየተንጉዋጉዋ እንዯ ጠጣ ኮሶ

ተሸሸገ እማጀት የናቱን ነት ሇብሶ!»

«ምን ያሇው ፇሪ ነው ምን ያሇው ወራዲ፥

25
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እኛን ገፌቶ ሰድ ወዯ ጦሩ ሜዲ

እሱ ተሸሸገ ገብቶ እናቱ ጉዋዲ!»

ያን ሁለ ባሳቤ እያወጣሁ እያወረዴሁ መወሰን አቅቶኝ ሁሇት ቀናት ያህሌ ስቸገር ቆይቼ፥
በመጨረሻ ሇመዝመት ቆረጥሁና እሳቸው ፇቅዯው ራስ እምሩን እንዱያስፇቅደሌኝ አሇቃየን፥ አቶ ወሌዯ
ጊዮርጊስን ሇመንሁዋቸው። መጀመሪያ እሳቸውም ራስም አሳቤን አሌተቀበለም ነበር። ሁዋሊ ግን
ብቀርም የመንፇስ እረፌት ስሇላሇኝ ስራዬን በሙለ ሌብ ሌሰራ የማሌችሌ መሆኑን ሊስረዲቸው
ፇቅዯውሌኝ፤ ስንቅ ሇማሰናዲት ከዯብረ ማርቆስ ዲንግሊ የሚሻሌ ስሇ ነበርና ወዱያውም የዘመቻው
መንገዴ በዚያ ስሇ ነበረ እዚያ ሌቆያቸው ከራስ ተሰናብቼ ወዯዚያ ሇመሄዴ አሰብሁ።

ከዯብረ ማርቆስ ከመነሳቴ አንዴ ቀን ቀዴሞ ጤናው መንገሻ መጣ። እሱን እንዯ ገና እስካየው
ዴረስ፥ የንገረኝን ህሌም መጀመሪያ ከቁም ነገር ስሊሌፃፌሁት፥ ሁዋሊም በሰነበትሁበት ግርግር ምክንያት
ረስቸው ነበር። እሱን ሳይ ትዝ አሇኝና ዯነገጥሁ፤ እንዱያውም ጤናውን ፇራሁት።

«ከየት መጣህ?» አሌሁት።

«ዛሬ ከዚሁ ከከተማ ነው፤ ካገውምዴር ትናንት መጥቼ እዚህ እዘመዴ ቤት አዯርሁ።»

«ካገው ምዴር ሇምን ጉዲይ መጣህ?»

«ሇዘመቻ ከመነሳትህ በፉት መጥቼ አይሀሇሁ! ብዬህ አሌነበረም? ሇዚያ ነው የመጣሁ» አሇ፤
ሇመሄዴ በመሰናዲት ሊይ መሆኔን ሰምቶ ኖሮ፤ ያሽሙር ፇገግታ በፉቱ እየታየ።

ምሳ አብረን ከበሊን በሁዋሊ ትንሽ ስንጫወት እንዯ ቆየን ከኔ ጋር ሇመዝመት መወሰኑን ነገረኝ።
መጀመሪያ እውነት አሌመሰሇኝም፤ የሚቀሌዴ መስልኝ ነበር። ሁዋሊ እውነቱን መሆኑን ስረዲ ሌዩ ሌዩ
ምክንያቶች እየፇጠርሁ አሳቡን ሇማስሇወጥ ያዯረግሁት መከራ፥ ከኔ ጋር መሄደን ያሌፇቀዴሁ
አስመስል አሳይቶት ቅር አሇውና ከኔ ጋር ባይሆን ከላልች ጋር መሄደ የማይቀር መሆኑን ነገረኝ።
እኔም ቅር ያሇው መሆኑን ሳይ፥ እንዱቀር ሇማሳመን ነበር እንጂ ማስረጃ ምክንያቶችን ያቀረብሁሇት
የማይቀር ከሆነ ከኔ ጋር ቢሄዴ እንዱያውም ብርቱ ዴጋፌ ስሇሚሆነኝ ዯስታውን የማሌችሇው መሆኔን
አረጋግጨሇት አብረን ሌንዘምት ተስማማን። እንዱሁም ከዚያ በፉት አዋጁ ተነግሮ የኔ መዝመት እንዯ
ታወቀ ያክስቴ የወይዘሮ ይታክቱ ቦጋሇ ሌጅ፥ ‹ገሊው ተገኘ› የሚባሇው ካስራ ስዴስት አመት
የማይበሌጠው ሌጅዋ ካሌዘመትሁ ብል አስቸግሮዋት ኖሮ፥ ጠፌቶ ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር
እንዲይሄዴባት ሰግታ ከኔ ጋር እንዱዘምት አጥብቃ ስሇ ሇመነችኝ ዯስ ሳይሇኝ ተቀበሌሁ። ሶስተኛ
ከተፇሪ መኮንን ትምህርት ቤት ከወጣሁ ጀምሮ አራት አመት ሙለ አብሮኝ የኖረው ‹ዘሪሁን ወጋየሁ‹
መቸም ከኔ የማይሇይ አብሮኝ ዘማች መሆኑን አስቀዴሜ አውቅ ነበር። ስሇዚህ ከኔ ጋር አራት ዘማቾች

26
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሆነን፥ ራስ እምሩ ከዯብረ ማርቆስ ከመነሳታቸው ቀዯም ብሇን ወዯ ዲንግሊ ሄዴን። ዲንግሊ ከዯረስን በኋሊ
ዯግሞ አንዴ ላሊ ዘሪሁን የተባሇ ረዥም ወጣት (ያባቱን ስም ረስቸዋሇሁ) መጥቶ የጌታ አዯረሌኝ። ያን
ሁዋሊ የመጣውን ዘሪሁን ፉት ከነበረው ዘሪሁን ሇመሇየት «ረዥም ዘሪሁን፥ አጭር ዘሪሁን» እንዱባለ
እነሱም እኛም ተስማማን። በመጨረሻ አቶ ‹ዘውዳ ወሌዯ ተክላ› መጥቶ ከኛ ጋር ተጨመረ። አቶ
ዘውዳ ባቶ ህሇተወርቅ እሸቴ ውስጥ ባቸፇር ክፌሌ ግብግቢት (ዯንገሌ - በር) ሇሚባሇው ኬሊ የጉምሩክ
ሹም ነበር። እኔ ሌጁን ክርስትና አንስቼ አበ ሌጁ ነኝ። ከዘመቻ የማይቀርበትን ሌዩ ምክንያት ሊቶ ህሇተ
ወርቅ ገሌፆሊቸው ምንም እንኩዋ እሳቸው ዘማች ቢሆኑ ከኔ፥ ጋር እንዱዘምት ስሇ ፇቀደሇት ነበር
ወዯኔ የመጣ። ስሇዚህ ዲንግሊ ስንዯርስ፥ ዘማቾች ከኔ ጋር ስዴስት ሆንን ማሇት ነው።

አቶ ዘውዳ ጤናውና እኔ፥ የየራሳችን ጠመንጃና ጥይት ነበረን። ሇረዥም ዘሪሁንና ሊጭር
ዘሪሁን ሁሇት ጠመንጃዎች ከሚያስፇሌጋቸው ጥይት ጋር እኔ እዚያው ዲንግሊ ገዛሁ። እንዱሁም አንዴ
መጠነኛ ሸራ ዴንኩዋን ሇራሴ፥ አንዴ መጠነኛ አቡጀዱዴ ዴንኩዋን ሊቶ ዘውዳና ሇጤናው ላሊ
አቡጂዱዴ ዴንኩዋን ሇሁሇቱ ዘሪሁኖችና ሇገሊው ገዛሁ። የኮርቻ በቅል ፉቱንም ስሇ ነበረኝ፥
ሇዴንኩዋኖቻችንና ሇስንቅ መጫኛዎች የሚሆኑ አንዴ የበቅል አጋሰስና አንዴ ስናር አህያ ገዛሁ። በዚያ
ጊዜ ማናቸውም ነገር ርካሽ ስሇ ነበር እኒያን የገዛሁዋቸውን ነገሮች ሁለ ሇመግዛትና ስንቅ ሇማሰናዲት
ብዙ ገንዘብ አሊወጣሁም። ሇምሳላ ሇቁዋንጣ የምትሆን አንዴ መሲና ሊም የገዛ ቆዲ ምሊሽ ባምስት ብር
ነበር።

ምእራፍ አራት

የዘመቻው ጉዞ
በ1928 ኢጣሉያ በኢትዮጵያ ሊይ ጦርነት እስካዯረገችበት ጊዜ ዴረስ የጎጃም የጦር ሰራዊት
ከሞሊ ጎዯሌ በሁሇት ምዴብ የተመዯበ ነበር ማሇት ይቻሊሌ። አንዯኛው ዋናው ምዴብ ከሊይ ከሻሇቃው
ወይም ከጠቅሊይ ግዛት ሰጥቶ፥ ግዛት ሊሌሰጠው ወይም ግዛት መስጠት የማይችሌ ሲሆን እቤቱ ግብር
እያበሊ ሌብሱንም መሳሪያውንም ችል የሚያኖረው ወታዯር ነበር። በዚያ ምዴብ ውስጥ ግዛት
ከነበራቸው በቀር ሇግብረ በሊ ወታዯሮች በዘመቻ ጊዜ የሚያስፇሌጋቸውን ስንቅና ትጥቅ የሚችለ
ጌቶቻቸው ነበሩ።

በሁሇተኛው ምዴብ ውስጥ የሚገኙት መዯበኛ ስራቸው እርሻ፥ ወይም ላሊ ስራ ሆኖ ሇገዢዎች


ኩዲዴ ከመኮዯዴ ቤት ከመስራት አጥር ከማጠር ወይም ከላሊ የጉሌበት ስራ ነፃ ሇመሆን በሻሇቃው
ወይም ከሻሇቃው በታች ባለት ታሊሊቅ አገረ ገዥዎች መዝገብ ገብተው የዯንብ ብረት የሚይዙት ነበሩ።
እኒያ የዯንብ ብረት ያዦች ብረታቸውን እቤታቸው አስቀምጠ፥ ባመት አንዴ ጊዜ የዘብ ተራቸውን
እየተወጡ ዘመቻ ካሌመጣ መዯበኛ ስራቸውን (እርሻ፥ ወይም ላሊ ስራ) እየሰሩ የሚኖሩ ዘመቻ ሲመጣ

27
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ብቻ የሚዘምቱ «የዘመቻ ባሇዲዎች» ነበሩ። ስንቃቸውን መሰነቁም ሆነ የስንቃቸውን መጫኛ
እንዯየአቅማቸው - በቅል ወይም አህያ - መግዛቱ የራሳቸው ጉዲይ ነው። ከነዚህ የጦር ሰራዊቱ
ከተመዯበባቸው ሁሇት ምዴቦች ላሊ፥ ሻሇቃው ወይም ከበታቹ ያለት ታሊሊቅ አገረ - ገዢዎች ሇስንቅ
ሇዴንኳን ወይም ሇዘመቻ አስፇሊጊዎች ሇሆ፥ ሇላልች ነገሮች መጫኛ፥ አጋሰሶችና ጫኞች
የማይበቁዋቸው ሲሆኑ ባንዴ ነጋዴራስ የሚተዲዯሩ ነጋዳዎች በገዛ አጋሰሶቻቸው ጭነው እንዱዘምቱ
ይታዘዙ ነበር። ሇስሙ ‹ዋጋ ይከፇሊችኋሌ› ይባሊለ ግን መክፇለ የማያጠራጥር ነው።

በ1928 በራስ እምሩ አዝማችነት ወዯ ሽሬ ግንባር የዘመተው የጎጃም የጦር ሰራዊትም


እንዯዚያው እንዯ ጥንቱ ከሻሇቃው ጀምሮ እንዯ የዯረጃው የመኩዋንንቱ አሽከር የዘመቻ ባሇዲ የሆነው
ባሊገርና ስንቅ ጫኙ ነጋዳ ነበር። ከዚያ ሊይ የተጨመረው አዱስ ዘማች ‹ሌጅ ግዛው ቡኔ› በተባለ
መኮንን የሚታዘዝ ከ800 -1000 አባልች የነበሩበት የክብር ዘበኛ ጦር ነበር። በግምት ሰሊሳ አምስት
ሺህ ያክሌ ይሆናሌ ይባሌ ነበር። የያዘው መሳሪያም፥ ከክብር ዘበኛው በቀር እንዱዑሁ ከያይነቱ
የተዯበሊሇቀ ከመሆኑ ላሊ አብዛኛው፥ የማያስተማምን አሮጌ፥ ነበር። ባሊገሩና ከተራው ወታዯር የሚበዛው
የያዘው ጠመንጃ ናስ ማሰር ውጅግራ፥ ወጨፍ ስናዱር መስኮብና እነሱን የመሳሰሇ ጊዜው ያሇፇበት
መሳሪያ ነበር። ሇዚያውም በቂ ጥይት የነበራቸው ጥቂት ይሆናለ። መኩዋንንቱና ባሇሙዋልቻቸው ብቻ
እንዯ - መውዜር ዱሞትገር (ሇሚትፇር) ሇበን ያሇ ጠመጃና በቂ ጥይት ነበራቸ። በመሳሪያ በኩሌ
ከሁለም የክብር ዘበኞች በጣም ይሻለ ነበር። ያን ጊዜ አባልች ከነበሩት መሀከሌ አንደ አሁን እንዯ
ነገሩኝ፥ ጠመንጃቸው መውዜርና ሇበን ነበር፤ በዚያ ሊይ ስዴስት መትረየሶችና አንዴ ያይሮፕሊን ማውረጃ
ነበራቸው።

ከጎጃም የጦር ሰራዊት ላሊ፥ በዯጃዝማች ‹አያላው ብሩ› ይታዘዝ የነበረውም የሰሜን የጦር
ሰራዊት በክቡር ራስ እምሩ ውስጥ እንዱዘምት ተዯርጎ ስሇ ነበረና የዯጃዝማቹ ጦር አስር ሽህ ክሌ
እንዯሚሆን ይገመት ስሇ ነበረ የሁሇቱ መሪዎች የጦር ሰራዊት ባንዴነት አርባ አምስት ሽህ ይሆን ነበር
ማሇት ነው። የጣሉያን የሰሜኑ ግንባር የጦር ሰራዊት አዛዥ የነበረው ማርሻሌ ፔትሮ በድሉዮ ግን፥
«የኢትዮጵያ ጦርነት» (La Guerra di Ethiopia) በተባሇው መፅሀፈ «የራስ እምሩና የዯጃች አያላው
የጦር ሰራዊት ባንዴ ሊይ አምሳ ሽህ ይሆን ነበር» ብል ፅፎሌ።

በዚያን አንፃር ማርሻሌ ባድሉዮ በተጠቀሰው መፅሀፈ እንዯ ገሇፀው በሽሬ ግንባር የተሰሇፇው
የጣሉያን የጦር ሰራዊት ካይሮፕሊን ከታንክ ላሊ፥ አምስት ዱቪዥን (ክፌሊተ - ጦር) እና አንዴ ብርጌዴ
ነበር። ያ ሰራዊት 173 መሀከሇኛና ቀሊሌ መዴፍች እንዯ ነበሩ ማርሻለ በዚያው መፅሀፈ ፅፎሌ።
መቸም እያንዲንደ አገር በዱቪዥኑ እና በብርጌደ ውስጥ የሚዯሇዴሇው የሰው ቁጥር የተሇያዬ ስሇሆነ
በሽሬ ግንባር የተሰሇፇው የጣሉያን አምስት ዱቪዥን እና አንዴ ብርጌዴ ሰራዊት በቁጥር ስንት ሰው
እንዯ ነበረ እርግጠኛ ማወቅ ያስቸግራሌ። ነገር ግን፥ ባጠቃሊይ እንዯ «ኢንሳይክልፒዱያ ብሪታኒካ»

28
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
(ENCYCLOPEDIAN BRITANICA) የጦር ሰራዊት አመዲዯብ፥ ባንዴ ዱቪዥን ውስጥ 17,000 –
20,000 ሰው፥ ባንዴ ብርጌዴ ውስጥ 6,000 – 7,000 ሰው ስሇሚመዯብ ዝቅተኛው ምዴብ የሚያዝ
ቢሆን እንኩዋ ማርሻ ባድሉዮ የጦር ሰራዊት በዴምሩ ከ90,000 (ከዘጠና ሺህ) ወታዯር በሊይ ነበር
ማሇት ነው። ስሇዚህ በሽሬ ግንባር የጣሉያን የጦር ሰራዊት በመሳሪያ ዒይነት፥ ጥራትና ብዛት ብቻ
ሳይሆን በወታዯር ብዛትም ከኢትዮያ ሰራዊት ብሌጫ ነበረው ሇማሇት ያስዯፌራሌ። ከዚያም ላሊ
የሚያሳዝነውም የሚያስገርመውም ራስ እምሩ ገና ከጎጃም ከመነሳታቸው በፉት፥ የጣሉያን የጦር
ሰራዊት ወሰኑን፥ መረብን አሌፍ ትግራይ ውስጥ ምቹ ቦታዎች እየመረጠ ምሽጉን አጠንክሮ ሰርቶ
ይጠብቅ ስሇ ነበረ፥ ጦርነቱ የተዯረገው በኒያ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንክረው በተሰሩት የጣሉያን ምሽጎች
ሊይ መሆኑ ነው። ያ ሁኔታ፥ ጣሉያኖችን ከመሳሪያቸውና ከሰዋቸው ብዛት ያሊነሰ ወይም የበሇጠ
የጠቀማቸውን ያክሌ ኢትዮጵያውያንን የጎዲ መሆኑ የማይጠረጠር ነው። እንዱያ ያሇው ሁኔታ፥ በሽሬ
ግንባር ብቻ ሳይሆን በላልች የጦር ግንባሮችም የዯረሰ ስሇ መሆኑ ማርሻ ባድሉዮ በተጠቀሰው መፅሀፈ
እንዱህ ይሊሌ።

«የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ተሰብስቦ እስኪንቀሳቀስ ረዥም ጊዜ በመውሰደ ተጠቅመን


በሙሶሉኒ ትእዛዝ መረብን ጥቅምት 3, 35 አዴዋ ጥቅምት 6, 35 መቀላን ህዲር 8, 35 አንዴ ጥይት
ሳይጮህብን ያዝን። ባጠቃሊይም ያሇብዙ ችግር ከትግራይ ብዙዎችን ክፌልች (Nuona Parte de
Tigrai) በቁጥጥራችን ውስጥ አዯረግን»።

አሁን ከመስመሬ ወጥቼ ወዯ ጠቅሊሊው የጦርነት ታሪክ በሚያመራው መንገዴ በመግባቴ


ይቅርታ ይዯረግሌኝና ወዯ ጀመርሁት፥ ወዯ ሽሬ ግንባር ሌመሇስ።

ክቡር ራስ እምሩ፥ ያን በምኑም በምኑ ካቅማቸው ጋር የማይመጣጠን የጠሊት ሀይሌ ሇመግጠም


በጥቅምት ወር 1928 የመጀመሪያ ሳምንት ከዯብረ ማርቆስ ተነስተው በዚያው ወር አጋማሽ አካባቢ
(ቀኑን ረስቸዋሇሁ) ዲንግሊ ሲዯርሱ ብሊታ ህሇተወርቅ እሸቴ፥ የጉምሩክ ጭፌሮቻቸውንና የከተማውን
ህዝብ አሰሌፇው ተቀበለዋቸው። እኔና ከኔ ጋር የሚዘምቱ ጉዋዯኝኖቼም ከሳቸው ጭፌሮች ጋር
ተሰሌፇን ነበር።

ራስ እዴንኩዋናቸው ገብተ ትንሽ እንዲረፈ፥ የዲንግሊንና ያካባቢውን ዘማች ሰሌፌ እንዱመሇከቱ


ሲጠየቁ እኔን አስጠርተው ዯብረ ማርቆስ ትያትር ያሳየን ዔሇት ያዯረግሁትን ንግግር ይዤው እንዯ ሆነ፥
እዚያም ከሰሌፈ በሁዋሊ እንዴዯግመው ስሇ ነገሩኝ ያረፌሁበት ቤት ከሰፇሩ አጠገብ በመሆኑ ሮጨ
አመጣሁት። ከዚያ ሰራዊቱ ተሰሌፍ በያሇቃው እየተመራ በፉታቸው አሌፍ ሲጨርስ ያ ያንሇት መጥቶ
ሰሌፌ ያሳየውና አብሮዋቸው የመጣው ሰራዊት ባንዴነት ተሰበሰበበት ከቁመቴ ባይበሌጥ የማያንስ
ረዥም ሇበኔ አንግቼ ዯብረ ማርቆስ ያዯረግሁትን ወኔ የሚቀሰቅስ ንግግር አንዴ ቃሌ ሳሌጨምርበት
ወይ ሳሌቀንስበት እንዱሁ እንዲሇ ዯገምሁት። ሌዩነት ቢኖር ዯብረ ማርቆስ ስናገር የነበረኝ ዴንፊታ፥

29
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የነበረኝ ግሇትና ሊብ ሊብ ማሇቱ ያንሇት አሇመኖሩ ነው። ሆኖም ያ ንግግር ሇኔ ፉት የሰጠኝን የጋሇ
ስሜት አይሰጠኝም እንጂ ላልችን አስፍከራቸው። እንዱያው ዯብረ ማርቆስ የፍከረው አንዴ ወታዯር
ሲሆን ዲንግሊ ያንሇት ስሇፌ ካሳዩትም ከራስ ጋር ከመጡትም መሀከሌ ብዙ፥ ወታዯሮችና መኩዋንንት
የጀግንነት ስሜታቸውን ሌብ በሚነኩ ቃሊት እየገሇፁ ሲፍክሩ ማየቱ እንዳት ሌብ የሚሞሊ ነበር! ዴሌን
በጅ ያስጨበጠ ይመስሌ ነበር! ከፇከሩት መኩዋንንት አንደ ዴሌን በጅ ያስጨበጠ ይመስሌ ነበር!
ከፇከሩት መኩዋንንት አንደ፥ «ያገሬ መሬት የጠሊት መቃብር እንጂ፥ የጠሊት ግዛት እንዯማትሆን
በራሴና ባሽከሮች ስም ቃሌ ሇምዴር ሇሰማይ!» ብሇው የሚለትንና ሲፇክሩ በፉታቸው ሊይ ሲነዴ ይታይ
የነበረውን የወኔ ስሜት ሌረሳው አሌችሌም።

የራስ እምሩ ሰራዊት ከዲንግሊ ባቸፇር በደርቤቴና በዯንገሌ በር አሌፍ፥ ቤገምር ግዛት እስኪገባ
ዴረስ በየሰፇሩበት ቦታ አካባቢ የሚኖረው ዘማአች እየመጣ ሰሌፌ ባሳየ ቁጥር፥ ረዥም ሇበኔም
እያነገትሁ ያን ረዥም ንግግሬን ስዯግም አፋ፥ እንዯ «አቡነ ዘበሰማያት» ሇምድት አይኔን ንግግሩ ወዯ
ተፃፇበት ወረቀት መመሇሱን እንኩዋ ትቼ ነበር።

የቤገምዴር እንዯራሴ የነበሩት ዯጃዝማች ወንዴወሰን ካሳ ቀዯም ብሇው ያገሩን የጦር ሰራዊት
ይዘው አባታቸው፥ ሌኡሌ ራስ ካሳ ወዯ ዘመቱበት የትግራይ ግንባር ሄዯው ስሇ ነበረ ክቡር ራስ እምሩ
ጎንዯር ሲዯርሱ የተቀበለዋቸው የቤገምዴርና የሰሜን ጳጳስ አቡነ አብርሃምና አገር ሇመጠበቅ ከዘመቻ
የቀሩት መኩዋንንት ከነጭፌሮቻቸው ነበሩ።

ራስና ዘማች ሰራዊታቸው፥ ከጎንዯር ተነስተው ጉዞዋቸውን ሲቀጥለ አቡነ አብርሃምም ያንዴ
ይሁን የሁሇት ቀን ጉዞ አብረው ተጉዘው ነበር። እንዱያውም «አብረው ሇመዝመት ራስን ቢሇምኑዋቸው
ራስ ከሚዘምቱ ይሌቅ ጎንዯር ቆይተው ሇዘማቹ ሰራዊት እንዱቀናው ፀልት ቢያዯርጉና ጦርነቱ
መርዘሙ ስሇማይቀር ስንቅ እየተሰናዲ ነጋዳ በኪራይ ወዯ ጦሩ ግንባር እንዱያዯርስ ቢያዯርጉ የበሇጠ
የሚጠቅም መሆኑን አሰረዴተው ሇስንቅ ማሰናጃ የሚሆን ገንዘብ ሰጥተው እንዱመሇሱ አዯረጉዋቸው»
ብሇው ራስና ጳጳሱ ሲነጋገሩ እዚኢያው የነበሩ ሰዎች ነገሩኝ። ጳጳሱ ገንዘብ ተቀብሇው መመሇሳቸው
እርግጥ መሆኑ ወዯ ፉት በላሊ ምእራፌ ይታያሌ።

የሰሜንን ግዛት ከገባን በሁዋሊ ተከዜን ‹በትክሌ ዴንጋይ› በኩሌ ሇመሻገር አፊፈን ወረዴ ብሇን
እወገቡ ሊይ ዯረስን « ‹ትእዛዝ እስኪዯርስዎ ባለበት ይቆዩ› የሚሌ የራዱዮ መሌእክት ሇራስ ዯረሳቸው»
ተብል እዚያ ሰፌረን ሰነበትን። ታዱያ ከመስፇሪያው ጥበትና ከሰራዊቱ ብዛት የተነሳ ከመጠን ያሇፇ
መተፊፇግ ስሇ ነበረ፥ የተቅማት ወረርሽኝ (በሽታ) በሰፇሩ ገብቶ ሰራዊቱን ክፈኛ ጎዲው። ዯብረ ማርቆስ
የነበሩትና በዘመቻው ግዚኤ ከሰራዊቱ ጋር የዘመቱት ግሪካዊ ሀኪም ቀን ብቻ ሳይሆን እስከ ማታ
እየሰሩ፥ ጉዲቱን ሇማቅሇሌ ብርቱ ጥረት አዴርገዋሌ። ነገር ግን በረዲቶችና በመዴሀኒት እጥረት ምክንያት
ርዲታቸው ሇበሽተኛው ሁለ ሉዯርስ አሌቻሇም። ከዚያ ክፈ በሽታ ካመሇጡት ጥቂት ሰዎች መሀከሌ

30
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እኔና ሰዎቼ ነበርን። ከዲንግሊ ስንነሳ፥ አንዴ የእንግሉዝ ቆንሲሌ ዘበኛ የነበሩ ሰው፥ ቆንስለ ወዯ
ሀገራቸው ሲሄደ የሰጡዋቸውን አራት ጠርሙስ መራራ አረቄ (ፇርኔት) ሰጥተውኝ ስሇ ነበረ ከዚያ
አንዲንዴ መሇኪያ ከምግብ በሁዋሊ እየጠጣን እሱ ረዴቶን ይሁን ወይም በእዴሊችን እኛ ሰፇር በሽታው
አሌገባም። እንዱያ ባሇ ችግር ከሰነበትን በሁዋሊ፥ ፉት እንዯ ታሰበው ተከዜን ‹በትክሌ ዴንጋይ› በኩሌ
መሻገራችን ቀርቶ፥ ሊዩን ‹በሇማሇሞ› በኩሌ እንዴንሻገር ስሇ ተዯረገ ወዯዚያ ሇመሄዴ እንዯ ገና
ተመሌሰን አፊፈን ወጥተን ወዯ ዯባት አመራን።

ምእራፍ አምስት

ደባት
ሰራዊቱ ከሰነበቱበት ወጥቶ የዯባትን ከተማ ወዯ ግራ እየተወ አሌፍ ተከዜ አፊፌ አቅራቢያ
እስኪዯርስ ተከዜ አፊፌ አቅራቢያ እስኪዯርስ የተጉዋዘበት አገር በጠቅሊሊው ደር የሚባሌ ነገር
የማይታይበት ሇጥ ያሇ ሜዲ ነው።

በዚያ ሜዲ ሊይ የራስ አጀብ ጥንታዊውን ያጀብ ስነ - ስራት ተከትል መጉዋዝ ሲጀምር ሌዩ


መስል ታየ፤ እንዯ ያንሇት አምሮ ታይቶ አያውቅም። ሜዲው ይሁን አጀቡን ያሳምረው ወይስ አጀቡ
ሜዲውን አይታወቅም፤ ብቻ ግሩም ነበር!

እንዯ ሌማደ ፉታውራሪ ጦር፥ ራስ ከሚሰፌሩበት ቀዯም ብል ወዯ ፉት መስፇር ስሊሇበት


ጥዋቱን ቀዴሞ ሄድአሌ። ከፉታውራሪው ጦር በሁዋሊ ራስ ሰፇር ዴንኩዋን አስተክሇው ግብር
አሰናዴተው የሚቆዩት ሹማምንት ከመሶበኞቻቸውና ከገንቦኞቻቸው ጋር ቀዴመው ሄዯዋሌ። ዯጀኑ
ጦርም ራስ ከሚሰፌሩበት ራቅ ብል ወዯ ሁዋሊ መስፇር ስሊሇበት ገና አሌዯረሰም፤ ወዯ ሁዋሊ ነበር።
ስሇዚህ ያ ወዯ ፉትም ወዯ ሁዋሊም አይን ሉዯርስ እስከሚችሌበት ዴረስ ሜዲውን አሳምሮት የሚታየው
የራስ አጃቢ ሰራዊት ብቻ ነበር!

የፉት አጃቢው ባሇብረት ሰራዊት ግንባሩን ይዞ ይጉዋዝ ነበር። ከሱ በሁዋሊ ማሇፉያ ፇረሶችና
ማሇፉያ ፇረሶችና ማሇፉያ በቅልዎች እንዯ ተጫኑ መሬት በሚጠርግ ባሇ ሌዩ ሌዩ ቀሇም ቀሚስ
አሸብርቀው ይሳቡ ነበር። ከነሱ በሁዋሊ አንጋቾች ባሇሙዋልችና የሌፌኝ አሽከሮች ምርጥ ምርጥ
መሳሪያዎችን እያነገቱ ራስን ከብበው ያጅቡ ነበር። ከዚያ ራስ ጥሌፌ ዔቃ በተጫነች ረዥም በቅልዋቸው
ሊይ ተቀምጠው ከመኩዋንንቱም ከባሇሙዋልቻቸውም አንዲንድቹን በተራ እያስጠሩ፥ - ፉታቸውን
ተመሌክቶ መገመት የሚቻሇውን ያክሌ - ካንደ ጋር ቁም ነገር እየተነጋገሩ ከላሊው ጋር ተራ ጨዋታ
እየተጫወቱና እየተሳሳቁ ይሄደ ነበር። ከራስ በሁዋሊ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ማሇፉያ መሳሪያዎቻቸውን ባሇ
ሌዩ ሌዩ ቀሇም ቀሚስ እያሇበሱ ይዘው ይከተለ ነበር። ከጋሻ ጃግሬዎች በሁዋሊ፥ መኩዋንንቱ
በየበቅልዋቸው እየተቀመጡ እንዯ የማእረጋቸው የቅዯም ተከተሌ ተራቸውን ይዘው ይጉዋዙ ነበር።

31
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከመኩዋንንቱ በሁዋሊ፥ ባጀብ ውስጥ የተመዯበ ቦታ የላሇው ወታዯር ባሇ ብረቱ ጀላው የጫነው፥
ያሌጫነው ሁለም ባንዴ ሊይ ይጥመሇመሌ ነበር።

ያን ሁለ ሰራዊት ታጃቢውንም አጃቢውንም ባንዴነት ጥሩንበኞች እንቢሌተኞች፥ መሌክተኞችና


ነጋሪት መቺዎች መሳሪያቸውን አስተባብረው በጉዞ ሙዚቃ እያጫወቱና እያስዯስቱ ጉዞው በመቀጠሌ
ሊይ እንዲሇ ከሩቅ የሚሰማ የብቸኛ ንብ «ህሞታ» የመሰሇ ዴምፅ ይሰማ ጀመር። ያን ጊዜ የሁለም ጆሮ
ከሙዚቃውና ከጭዋታው ወዲዱሱ ዴምፅ ተመሇሰ። ያ ዴምፅ እየቆየ እየጎሊ እየጎሊ ሲሄዴ ያይሮፕሊን
ዴምፅ መሆኑ ታወቀ። ወዱያው አይሮፕሊንዋ ስትመታ መሌክዋም ታየ። ወዯ ሊይ ከመራቅዋ የተነሳ
ትንሽ አሞራ መስሊ ነበር የምትታይ! ያቺ አይሮፕሊን የራስ እምሩን ሰራዊት ሇመፇሇግ ሰፌሮ
በሰነበተበት ቦታ ዯርሳ ከዚያ ወጥቶ የሄዯበትን መንገዴ ስታገኝ ተከትሊ መምጣትዋ ነበር።

ከዚያ «ተበታተኑ በሌ! ተበታተኑና ተኩሱባት በሌ!» የሚሌ ትእዛዝ ከራስ አጠገብ እንዯ ተሰማ
ያን ትእዛዝ ፉት ያለት ሇፊፉዎች ወዯ ፉት፥ ሁዋሊ ያለት ወዯ ሁዋሊ እየተቀባበለ አስተሊሇፈ። ያን
ጊዜ፥ ያ ስነ - ስራቱን ተከትል ይጉዋዝ የነበረው ሰራዊት ብትንትን ብል ሁለም ከያሇበት መተኮስ
ጀምሮ እስኪቆም ዴረስ እዚያ ሜዲ ሊይ የጦርነት ግጥሚያ የተዯረገ መስል ቆየ። የክብር ዘበኞች
ያይሮፕሊን ማውረጃ መዴፌ ተኩዋሽም ተኩሱን ከጀመሩት ሰዎች መሀከሌ ነበር። መዴፈን ተኩዋሽም
ተኩሱን ከጀመሩት ሰዎች መሀከሌ ነበር። መዴፈን ተኩዋሹ መዯገኛውን ከመሬት ተክል፥ በዚያ ሊይ
መዴፈን ጠመዯና ሽቅብ አነጣጥሮ መጀመሪያ ሁሇት «አመሌካች ጥይቶች» (Tracer Bullets)
አከታትል ተኮሰ። እኒያ አመሌካች ጥይቶች በሰማይ ሊይ የሚምዘገዘግ ጅራታም ኮከብ ረዥም ነጭ
አመሌማል የመሰሇ ነገር በሁዋሊቸው እየተጎተተ፥ አንደ ባይሮፕሊንዋ ሁዋሊ ሁሇተኛው በፉትዋ
ጠፇሩን ሰንጥቀው ወጥተው እንዯ ገና ወዯ መሬት ተመሌሰው እስኪወዴቁ ሲታይ በጣም ያምሩ ነበር።
ብቻ ሁሇቱም ካይሮፕሊንዋ ሩቅ ነበሩ፤ ኢሊማቸውን ሳቱ ማሇት ነው። ከዚያ መዴፇኛው «ባገኝ
ባጣውን» ጥቂት መምቻ ጥይቶች ከተኮሰ በሁዋሊ መዴፈን ተሰናከሇበትና አንዯኛውን አቆመ።

አይሮፕሊንዋ ወዯ ሊይ በጣም ርቃ ትበር ስሇ ነበረ፥ በላሊው ጠመንጃ የተተኮሰው ጥይት ሁለ


የዯረሰባት አይመስሌም። የሚበዛው ጠመንጃ አሮጌ የነበረ በመሆኑ በዚያ አሮጌ ጠመንጃ የተተኮሰው
ጥይትማ ግማሽ መንገዴ መዴረሱም የማያጠራጥር ነበር! ስሇዚህ ያቺ አይሮፕሊን የያዘችውን ቀጥታ
መስመር ትንሽ ሳታቃውስ ቀጥ ብሊ የሰራዊቱ ፉታውራሪ ጦር እስከ ዯረሰበት ቦታ ሄዯች። ከዚያ
ከሄዯችበት መንገዴ ተመሌሳ እንዯ ገና ወዯ ዯጀኑ ጦር ሄዯች። እንዱያ ወዯ ፉትና ወዯ ሁዋሊ
እየተመሊሇሰች ዙሪያ እየዞረች የጦር ሰራዊታችንን ሌክ ካጠናች በሁዋሊ የትግራይን አቅጣጫ ይዛ ሄዲ
እዚያው ቀረች።

ሰራዊቱ በተበታተነበት እንዲሇ፥ ስሇ አይሮፕሊንዋ በየጉዋደ ሌዩ ሌዩ ትችት ሲተች ዘሇግ ያሇ


ሳትመሇስ ስሇ ቆየች ሁለም ያጀብ ቦታ ቦታውን እንዱይዝና ጉዞውን እንዱቀጥሌ ተሇፇፇ።

32
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
‹ይቺ አይሮፕሊንዋ ቦምብ የምትተኩስ ናት› ይባሌ የሇ? ታዱያ ዛሬ ያሌተኮሰች ሇምን ይሆን?»
ባጠገቤ ከነበሩት ሰዎች አንደ እኔን እያየ። ራሴ ፉት ሰሌፌ በታየ ቁጥር ስሇ አይሮፕሊን ስናገር ውስጠ
- ምስጢርዋን ሁለ የማውቅ እመስሌ ስሇ ነበረ፥ ያነሇት ቦምብ ያሌጣሇችበትን ምክንያትም የማውቅ
መስልት ነበር ይመስሇኛሌ።

«ወቴ በሄዯችበት በጥይት ሲያዋክባት መቸ ፊታ አገኘች! ሇመተኮስ ትንሽ ቆም ብል ማነጣጠር


ያስፇሌጋሌ!» አሇ ጉዋዯኛው፤ እኔ ፌርጥም ብዬ ዝም ስሊሌሁ።

«ሇመሆኑ ተመትታ ይሆን በሄዯችበት የቀረች?» አሇ ሶስተኛው።

«ብትመታማ እዚህ ነበር የምትወዴቅ፤ ባትመታ ነው እንጂ!» አሇ ሇፉተኛው ጥያቄ መሌስ


የሰጠው ሰው።

«ምናሌባት ሰሌሊ እንዴትመሇስ የተሊከች ሰሊይ ትሆናሇች» ብዬ ትቻቸው ሄዴሁ።

ከዚያ ጥዋት ቀዴመው የሄደት ሹማምት ሰፇር መርጠው የራስን ዴንኩዋን አስተክሇው
በሚጠብቁበት ቦታ ሇመዴረስ ብዙ ጊዜ አሌፇጀም። ሰፇሩ ወዯ ትግራይ ሇመሄዴ ከዲባት ከተማ በስተቀኝ
አሇፌ ብል ፌንትው ባሇ ሜዲ ሊይ ነበር። በዚያ ሜዲ ሊይ አንደ ከላሊው በጣም እየተራራቁ በቅሇው
ከማታዩ ብቸኛና አጫጭር ግራሮች በቀር ላሊ የንጨት ምሌክት የሇም።

ሰራዊቱ እዚያ እንዯ ዯረሰ፥ የራስን ዴንኩዋን እያየ፥ ያስፊፇሩን ስነ - ስራት ተከትል ወዯ ፉት
የሚሰፌረው ወዯ ፉት በቀኝና በግራ የሚሰፌረው በቀኝና በግራ ወዯ ሁዋሊ የሚሰፌረው ወዯ ሁዋሊ ቦታ
ቦታውን እየያዘ ሰፇረ።

የሰሜኑ አገረ ገዥ ዯጃዝማች አያላው ብሩ ሇዘመቻው ቀዯም ብሇው ወዯ ተከዜ አፊፌ


በመሄዲቸው ዲባት ስሊሌነበሩ፥ ወዯ ሰፇር መጥተው ራስን የተቀበለ አገር ጠባቂ ሆነው የቀሩት
የዯጃዝማች ታናሹ ሌጃቸው «ፉታውራሪ መርሶ» ነበሩ። ፉታውራሪ መርሶ፥ የጦርነቱ ጊዜ የሚረዝም
የሆነ እንዯ ሆነ በየጊዜው ስንቅ እየተሰናዲ ሇሰራዊቱ እንዱሊክ ከራስ ጋር ሲነጋገሩ ቆይተው ሇዚያ
የሚሆን እንዯ አቡነ አብርሃም ገንዘብ ተቀብሇው መሄዲቸውን ሁዋሊ ሰማሁ።

በማግስቱ ጥዋት ገና ፀሀይ ሳትወጣ ሰራዊቱ ቅሩስ ቀምሶ ጉዞውን ሇመቀጠሌ ከሜዲው ኩበት
ሇቃቅሞ በየምዴጃው እሳት ማንዯዴ እንዯ ጀመረ ያይሮፕሊን ዴምፅ ተሰማ። ከዚያ፥

«እሳታችሁን እያጠፊችሁ፣ ተበታትናችሁ ያይሮፕሊንዋ ሊይ ተኩሱ!» የሚሌ ትእዛዝ ይሇፇፌ


ጀመር። ወዱያው እንዯ ትናንቱ አንዴ ብቻ ሳትሆን፥ ብዙ አይሮፕሊኖች በሁሇትም በሶስትም ቡዴን
እየሆኑ በግንባር - ቀዯሙ (በፉታውራሪ) ጦር ሰፇር ሊይ መጥተው በመሀከለ (ራስ ባለበት) ጦር ሰፇር

33
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሌፇው ምንም ሳያዯርጉ እስከ ዯጀኑ ጦር ሰፇር የመጨረሻ ዲርቻ ዯረሱ። ዴምፃቸው ባንዴነት
«የሰማይ ቁጣ» ይመሌስ ስሇ ነበረ አይሮፕሊን መሆናቸውን ባይነግርባቸው ወዯ ሊይ ከመራቃቸው
የተነሳ፥ ትናንሽ አሞሮች እንጂ አይሮፕሊኖች አይመስለም ነበር። ሲመሇሱ ከዯጀኑ ጦር ሰፇር ጀምረው
የቦምብ ነጎዴጉዋዴ እያወረደ በመሀከለ ጦር ሰፇር አሌፇው እስከ ፉታውራሪ ጦር ሰፇር ዯረሱ። እንዯ
ገና ከፉታውራሪው ጦር እስከ ዯጀኑ ጦር! እንዱያ ከሁዋሊ ወዯ ፉት፥ ከፉት ወዯ ሁዋሊ ከቀኝ ወዯ ግራ
ከግራ ወዯ ቀኝ እየተመሊሇሱ ያን ያሊንዲች መጠሇያ፥ በጠራ ሜዲ ሊይ የተሰጣ ሰራዊት ሲዯበዴቡ
አረፇደ። መቸም የተኩሱ ነገር «ይህን ይመስሌ ነበር» ሇማሇት ምሳላ ማግኘት አይቻሌም። እንዱያው
ባጭሩ «ከሰራዊቱ ጠመንጃ የያዘው ሁለ ሳይተኩስ የቀረ አይመስሌም» ቢባሌ ያ፥ ተኩስ ምን ይመስሌ
እንዯ ነበረ ሇመገመት አሳብ ይሰጥ ይኆናሌ! ያን ያክሌ ከተተኮሰው ጥይት ጥቂቱ እንኩዋ፥ አይሮፕሊኖች
በሚበሩበት የሚዯርስ ቢሆን ኖሮ አንዲቸው ባሌተመሇሱ፤ ሁለም ባሇቁ ነበር! ነገር ግን እንኩዋንስ
በሚበዛው አሮጌ ሇሱ፤ ሁለም ባሇቁ ነበር! ነገር ግን እንኩዋንስ በሚበዛ አሮጌ ጠምንጃ የተተኮሰው
ጥይት በጥሩ ጠመንጃ የተተኮሰው ጥይትም ሉዯርስ ከማይችሌበት ሩቅ ከፌታ ስሇ ነበረ ቦምብ
የሚጥለት፥ አንዲቸውንም ጉዲት ሳያገኛቸው እዯረቅ ርፊዴ ሊይ ዴምፃቸውን ባንዴነት አስተባብተው
እያንጎረጎሩና እየፍከሩ የትግራይን አቅጣጫ ይዘው በመጡበት መንገዴ ተመሌሰው ሄደ።

ቦምብ ሲጥለ ከመፌጠናቸውም ላሊ ተበታትነው ወዯ ፉትና ወዯ ሁዋሊ፥ ወዯ ቀኝና ወዯ ግራ


ይዋነቡ ስሇ ነበረ፥ ትክክሇኛ ቁጥራቸውን ሇማወቅ አስቸጋሪ ነበር። እኔ፥ «አስራ ሁሇት» መስሇውኝ
ነበር። ላልች ያነጋገርሁዋቸው ሰዎች ግን ተስማምተው «አስራ ስምንት ናቸው» አለኝ። ሇኔ እንዯ
መሰሇኝ «አስራ ሁሇት» ቢሆኑም ጥቂት አዯለ፤ ብዙ ናቸው! ነገር ግን እንዯ ብዛታቸው ሰፇሩን
ሲዯበዴቡ እንዯ ቆዩበት ረዥም ጊዜና እንዲወረደት የቦምብ መአት ሰው ተርፍ የሚቀር እይመስሌም
ነበር። ነገር ግን ቦምብ ይጥለ የነበረ ወዯ ሊይ በጣም ከፌ ብሇው ከሩቅ ከመሆኑና ከመፌጠናቸው ላሊ
ሰራዊቱም በዚያ ሰፉ ሜዲ ሊይ ተበታትኖ ስሇ ነበረ ያዯረሱት ጉዲት የተፇራውን ያክሌ አሌነበረም፤
መጠነኛ ነበረ። የሞቱት ጉዲት የተፇራውን ያክሌ አሌነበረም፤ መጠነኛ ነበረ። የሞቱትን «አስራ አራት»
ሰዎችና «አርባ» አጋሰሶች ነበሩ። የቆሰለትን ሰዎች ቁጥር ረስቸዋሇሁ። ብቻ ከሞቱት ሰዎች ቁጥር
ቢበዛም ብዛቱ እጅግ የሚባሌ እንዲሌነበረ ትዝ ይሇኛሌ።

የባሰባቸው ቁስሇኞች ወዯ ግሪኩ ሀኪም ዴንኩዋን እየተወሰደ የህክምና ርዲታ ከተዯረገሊቸው


በሁዋሊ ሰራዊቱ ወዱያው ከሰፇረበት ቦታ ተነስቶ ጉዞውን ቀጥል የፍገራን፥ ሜዲ ሲጨርስ አስር ሰአት
ግዴም ቁጥቁዋጦና አንዲንዴ ከፌ ያለ ዛፍች የበቀለበት ቦታ ስሇ ተገኘ እዚያ ሰፇረ። ያነሇት በሚበዛው
ሰው ፉት ይታይ የነበረው የሀዘን የብስጭትና የቀቢፀ - ተስፊ ምሌክት ነበር። እውነትም ጦርነት ገጥሞ
ከጠሊት በኩሌ አንዴ እንኩዋ የተገዯሇና የቆስሇ ሳያዩ ከወገን ብቻ የተገዯሇና የቆሰሇ ማየት የሚያሳዝንም
የሚያበሳጭም ነው! እኔንማ እንዯ ላልች ሀዘንና ብስጭት ብቻ ሳይሆን ብርቱ እፌረት ጭምር ነበር
የተሰማኝ! አይሮፕሊንን ያን ያክሌ ዋጋ እያሳጣሁ ስሰብክ ኖሬ፥ ያንሇት እኒያ አይሮፕሊኖች እኔ ዋጋ

34
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዲሳጣሁዋቸው አሇመሆናቸውን በሰሩት ስራ ሲያመሰክሩ አሊዋቂነቴን ገሇፀብኝና ቀና ብዬ የሰው ፉት
ማየቱን እንኩዋ አፇርሁ።

ዴንኩዋናችንን ተክሇን እቃችንን ቦታ ቦታውን ካስያዝን በሁዋሊ፥ እኔንና አጭሩ ዘሪሁንን


እዴንኩዋን ትተው ላልች ጉዋዯኞቻችን ከብቶችን ይዘው ውሀ ወዲሇበት ሄደ። እኔ እዴንኩዋኔ ውስጥ
ዘሪሁን እውጭ እንዲሇን ‹ፉታውራሪ ዲምጠው ተሰማ› መጡ። ፉታውራሪ ዲምጠው ከታሊቁ አባታቸው
ከፉታውራሪ ‹ተሰማ ጎሹ› ጀምረው በጎጃም ቤተ መንግስት የታወቁና የተከበሩ ነበሩ። ክቡር አስ እምሩ
የጎጃም አገረ ገዥ ጀምሮም ፉታውራሪ ዲምጠው ያንዴ ትሌቅ ወረዲ አገረ ገዥ በመሆናቸው ሊይ
‹የወረገኑ ሹም› ጭምር ነበሩ። ስሇዚህ፥ ከግሌ ወታዯሮቻቸው ላሊ ሇወረዲውና ሇወረገኑ የዯንብ ብረት
ያዦችም አዝማች ስሇ ነበሩ ከታሊሊቅ የጭፌራ አሇቆች አንደ ነበሩ። ከማውቃቸው የጎጃም መኩዋንንት
ሁለ ፉታውራሪ ዲምጠው ዘመናዊውን አስተሳሰብና አሰራር ይከተለ ስሇ ነበረ ከዯብረ ማርቆስ ትምርት
ቤት መምህራን ጋር የተቀራረበ ግንኙነት ነበራቸው። እኔንም ወዯ ዯብረ ማርቆስ ከተዛወርሁበት ጊዜ
ጀምሮ በጣም ያቀርቡኝ ነበር። ብዙ ጊዜ ወዯ ቤታቸው እያስጠሩኝ አንዲንዴ ጊዜም እኔ ቤት እየመጡ
ስንጫወት ማምሸቱን ሌማዴ አዴርገነው ነበር። በዘመቻው ጉዞ ሊይ ግን የሳቸውን ዴንኩዋን የሚከብበው
- ልላውም ጭፌራውም - ስሇሚበዛ ከኔ ጋር መነጋገር ሲፇሌጉ ጋሻ ጃግሬያቸውን ብቻ አከትሇው
ወዯንኔ ዴንኩዋን ነበር የሚመጡ። ያንሇትም ጠመንጃቸውንና በነጭ እራፉ ቁዋንጣ የያዘ ጋሻ
ጃግሬያቸው ተከትልዋቸው መጥተው እዴንኩዋን ያን ቁዋንጣ እየበሊን ስንጫወት በርከት ያለ ሰዎች
እየተነጋገሩ ወዯ ዴንኩዋናችን ሲቀርቡ ተሰማን። እዯጅ ያለት የፉታውራሪ ጋሻ ጃግሬና ዘሪሁን ብቻ
ናቸው፤ ዴምፁ ግን ከሁሇት ሰዎች ዴምፅ የበዛ ነው። ፉታውራሪና እኔ ጭዋታችንን አቁመን ስናዲምጥ፥

«አንተ ያ ተማሪ የት ነው?» አሇ አዱስ ከመጡት ሰዎች አንደ፤ ዴምፁን ከፌ አዴርጎ።

«የቱ ተማሪ?» አሇ ዘሪሁን።

«ያ ያንተ ጌታ»

ዘሪሁን አሌመሇሰም።

«የት አሇ ነውኮ እምሌህ!» አሇ ሰውየው በቁጣ።

«እዴንኩዋን ውስጥ ናቸው» አሇ ዘሪሁን።

«ጥራው!»

ዘሪሁን አሌተንቀሳቀሰም፤ ዝም ብል ተቀመጠ።

«አትጠራውም?» አሇ ሰውየው፤ አሁንም ተቆጥቶ። ዘሪሁን ንቅንቅ አሊሇም።

35
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እስቲ ሌውጣና ማን መሆኑን ሌይ» ስነሳ፥

«አፇረህ ተቀመጥ፤ የሰከረ ሰው ይመስሊሌ!» አለ ፉታውራሪ።

«ወዯሱ አሌሄዴም፤ እበር ቆሜ ሇማየት ነው» ብያችወ ሽጉጤን እመንገዴ አሌጋየ ሊይ


ካኖርሁበት አንስቼ ታጥቄ፥ ዴንኩዋኑን ገሇጥ አዯረግሁና ወጣሁ። እንዱያ አጥብቆ የሚፇሌገኝ ሌጅ
‹ዲኛቸው ተሰማ› ነበር።

ሌጅ ዲኛቸው ተሰማ የፉት ‹ምን ያምር› የሚለት አይነት አይሁን እንጂ ቁመቱ ዘሇግ ያሇ ውሀ ጠይም
ጠጉረ ሊዛ፥ ሽንጥና ወገቡ ልጋ፥ በጠቅሊሊው ዯስ የሚሌ የወንዴ ቅርፅ ያሇው፥ ወጣት መኮንን ነው።
ትውውቃችን ተቀራርበን ሇመጫወት ያክሌ ባይሆንም እንዱሁ በሩቁ እንተዋወቃሇን። ጠመንጃውን የያዘ
ጋሻ ጃግሬውና አራት ወይም አምስት የሚሆኑ ባሇ ብረት ወታዯሮች ተከትሇውታሌ። እሱ ጥይት የሞሊ
ዝናሩን እሊይ ረዥም ጎራዳውን ከታች አዴርጎ ታጥቆ ያን ትጥቁንና ልጋ ወገቡን ሇማሳየት
እንዯሚፇሌግ ሁለ፥ ቀጭን ኩታውን ከታች ወዯ ቀኝና ግራ ትከሻዎቹ መሇስ አዴርጎ ረዥም ዘንጉን
በግራ እጁ ይዞ፥ እነዘሪሁን ከተቀመጡበት ራቅ ብል ቆሞዋሌ።

«እኔን ነው መሰሇኝ የምትፇሌግ ሌጅ ዲኛቸው፤ ሇምን ፇሇግከኝ?» አሌሁ ከዴንኩዋኔ በር ቆሜ።

«ዛሬ ሌፊረዴህ ነው የመጣሁ!» አሇ፤ በቀኝ እጁ የጎራዳውን ውሊጋ ጨብጦ።

«ሇምኑ?» አሌሁ።

«ዯሞ ሇምኑ ይሇኛሌኮ! ‹አይሮፕሊን እንኩዋንስ በጠመንጃ በሽጉጥ ይወዴቃሌ› እያሌህ ሰውን
ሁለ አታሌሇህ ማስፇጀትህ ጠፌቶህ ነው አሁን ሇምኑ የምትሇኝ? አንተ አታሊይ ቀጣፉ!» አሇ
ጎራዳውን ነቅነቅ እያዯረገ።

«አዎ፤ ‹እንኩዋንስ በጠመንጃ በሽጉጥም ከተመታ ይወዴቃሌ› ብያሇሁ፤ ግን አሌተመታምኮ ሌጅ


ዲኛቸው!» አሌሁት። እንዱያ ስሌ ሇካስ ሳይታወቀኝ ፇገግ ብዬ ኖሮዋሌ።

«ጥርስህን ያርግፇውና ዯሞ ‹ጥርስ አሇኝ› ብሇህ መሳቅህ ነው? በሌ አሁን ና ወዱህ!» አሇ


ጎራዳውን እየነቀነቀ።

«ሇምን ነው የምመጣ? አሌመጣም! አሌሁት» ፇገግ እንዲሌሁ። ፉታውራሪ ዲምተው እውስጥ


ሆነው ሲስቁ እሰማቸዋሇሁ።

«ካንተ ወይ ከኔ፥ ማን ወንዴ እንዯ ሆነ ዛሬ ይሇይሌናሌ! በሌ ና!» አሇ አሁንም ጎራዳውን


እየነቀነቀ።

36
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ታዱያ ወንዴነታችንን ሇማሳየት አንተና እኔ እዚህ ከመጋዯሌ ያን ወንዴነት እፉታችን ተሰሌፍ
በሚጠብቀን ጠሊት ሊይ ብናሳይ አይሻሌም? አንተና እኔኮ ወንዴማሞች ነን» አሌሁት።

«ወንዴማሞች! ዯሞ አንተ ነህ የኔ ወንዴም? እንዲንተ ያሇ ወንዴም የሇኝም!» አሇ የኔን


ወንዴምነት እየተፀየፇ ሁለ ከፇንሩን አበሊሌጦ።

«የኔን ወንዴምነት ካሌፇሇግህ፥ እኔም ያንተን ወንዴምነት አሌፇሌግም ያንተን ወንዴምነት


እፀየፇዋሇሁ! አሁን ሂዴ ወግዴ ከዚህ! ወግዴ ብየሀሇሁ!» አሌሁ ሇጀመሪያ ጊዜ ግሌፌ አዴርጎኝ፥ እጅጄን
በሽጉጤ ሊይ አዯረግሁና። የዴምፄን መሇዋወጥ ሲሰሙ ፉታውራሪ ወጥተው መጡና እኔን ወዯ
ሁሊቸው ገፌተው፥

«አንተ ዲኛቸው ዛሬ ዯህና አይዯሇህም? በሌ አሁን ሂዴ ከዚህ» አለ።

«እኔ ጉዲየ ከሱ ጋር ነው፤ እርስዎን የሚያገባዎ አይዯሇምና አርፇው ይቀመጡ። እሱን ግን


አሳየዋሇሁ!» አሇ የጎራዳውን ወሇጋ እንዯ ጨበጠ እግሮቹን አፇራጦ ቆሞ።

«አዎ ታሳየዋሇህ፤ ሞሌፊጣ! እሱን ጎራዳህን መዝዘህ እዚህ እስክትዯርስ ሶስት ጊዜ


ይገዴሌሀሌ!» አለት።

«የሱ ጥይት እንክዋንስ ሉገዴሇኝ አይነካኝም!» አሇ። ያን ጊዜ ፉታውራሪ ነጥቀው የዘሪሁንን


ሽመሌ ከጁ ነጠቁና፥

«ሂዴ ወግዴ ከዚህ በዚህ ደሊ ሳሊበራይህ፥ አንተ ሰካራም!» አለ የሚያበራዩበትን ደሊ እያሳዩ።

ሌኡሌ ራስ ኃይለ የጎጃም አገረ ገዥ በነበሩት ጊዜ ፉታውራሪ ዲምጠው ከታወቁት ታሊሊቅ


መኩዋንንት አንደ ሲሆኑ ሌጅ ዲኛቸው የራስ የእሌፌኝ አሽከር ሆነው አብረው የኖሩ ነበሩ። በክቡር
(ሁዋሊ ሌኡሌ) ራስ እምሩ ጊዜም፥ ፉታውራሪ ያንዴ ትሌቅ ወረዲ አገረ ገዥ ከመሆናቸው በሊይ
‹የወረገኑ› ሹም በመሆናቸው ሇራስ የቅርብ ረዲትና ስሇ ጎጃም ምክር ከሚሰጡት ታሊሊቅ መኩዋንንት
አንደ ነበሩ። ስሇዚህ ሌክ ዲኛቸው መቆጣታቸውን ሲያይ፥ ፇርቶዋቸው ይሁን ወይም አክብሮዋቸው
በረዴ ብል እጁን ከጎራዳው ውሊጋ ሊይ አወረዯ። ወዱያው አብረውት ከነበሩት ሰዎች ፀና ፀና ያለት
እንዯ መገሊገሌም እንዯ ማባበሌም እያዯረጉ ይዘውት ሄደ።

በማግስቱ ጥዋት፥ ዯጃዝማች ‹ገሰሰ በሇው› ላሉቱን ጠፌተው ወዯ አገራቸው ወዯ ጎጃም


መመሇሳቸው ታወቀ። ሌጅ ዲኛቸው ተሰማም ከሳቸው ጋር መመሇሱን ሰማን።

37
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምእራፍ ስድስት

ደባጉና
ሇቁስሇኞች ህክምና እንዱዯረግሊቸው አጋሰሶች የሞቱባቸው ሰዎች በካባቢው ካሇው ባሊገር
ፇሌገው እንዱገዙና ወዱያውም ዯጃዝማች አያላው ብሩ የሚገኙበትን ሇማጠያየቅ ቢያንስ ያንዴ ቀን
ውል ማዴረግ አስፇሊጊ ሆኖ ስሇ ተገኘ ውልው እዚያው ሰራዊቱ ሰፌሮ ባዯረበት ቁጥቁዋጦና አንዲንዴ
ዛፍች ባለበት ቦታ እንዱዯረግ ተወሰነ።

ዯጃዝማች አያላው ስሇሚገኙበት ቦታ፥ የተጠየቁት ባሊገሮች ከጥቂት ቀናት በፉት እዚያ
አቅራቢያ ሰፌረው የነበር መሆናቸውንና ከዚያ ተነስተው ተከዜ አፊፌ መስፇራቸውን ከመስማታቸው
በቀር የተከዜ አፊፌ ወንዙን በቁሙ ተከትል የሚሄዴ ስሇሆነ የት ቦታ እንዯ ሰፇሩ የማያውቁ
መሆናቸውን ተናገሩ።

ስሇዚህ፥ ራስ እኔን አስጠርተው ሇዯጃዝማች የፃፈሊቸውን ወረቀት ሰጥተው ያለበትን ፇሌጌ ያን


ወረቀት እንዲዯርስሊቸውና የሚሰጡኝን መሌስ ይዤ ቶል እንዴመሇስ አዘዙኝ። ሇዯጃዝማች እንዱዯስር
በሰጡኝ ወረቀት የፃፈሊቸው ሁሇቱ የሚገናኙበትን ቦታ ቀን እንዱያስታውቁዋቸው መሆኑንም በቃሌ
ገሇፁሌኝ።

ርፊዴ ሊይ ጤናውና ረዥሙ ዘርይሁን እኔና ገሊው ከሰፇራችን ተነስተን የሇማሇሞን መንገዴ
ይዘን ስንገሰግስ፥ ከቀትር በሁዋሊ ሰባት ሰአት ግዴም ተከዜ አፊፌ ዯረስን። እዚያ አንዴ ትንሽ መንዯር
አጠገብ ጥቂት ሰዎች ተሰብስበው ስሊየን ወዯነሱ ሄዯን ዯጃዝማች አያላው የሰፇሩበትን ቦታ
እንዱያመሇክቱን ብንጠይቃቸው መጀመሪያ በጥርጣሬ መሌክ እስ - በሳቸው ከተያዩ በሁዋሊ፥

«እኛ ዯጃዝማች አያላው የሰፇሩበትን የት እናውቃሇን ጌቶች አለ ከመሀከሊቸው አንዴ ሸምገሌ


ያለ ሰው።

«ሇክፈ ነገር አይዯሇምኮ የዯጃዝማችን ሰፇር የምንፇሌገው ጌቶች፥ ይህን ከክቡር ራስ እምሩ
የተፃፇሊቸውን ወረቀት ሌናዯርስሊቸው ነው» አሌሁ ማህተም ከሊይ የታተመበትን አንቨልፕ ከኪሴ
አውጥቼ እያሳየሁ። ከዚያ እስ - በሳቸው በሹክሹክታ ሲነጋናገሩ ትንሽ ቆዩና፥

«ያቺን መንገዴ ሳትሇቁ አፊፌ - ሇአፊፌ ስትሄደ ዘበኞቻቸውን ታገኛሊችሁና እነሱ


ይመሩዋችሁዋሌ» አለ ሽማግላው ሰው፥ መንገዴዋን በሽመሊቸው እያሳዩ። «ብቻ - እኛ መንገደን
እንዲመሇከትናችሁ እንዲትናገሩ አዯራችሁ!» አለ ሽማግላው ቀጠለና።

38
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ግዳሇም አትስጉ፤ አንናገርም ብያቸው አመስግነን ዘወር ስንሌ «ያ ሮቢሊው የራስ እምሩን ሰው
ክፈኛ ጎዲው የሚባሇው እውነት ነው?› አለ። «የተፇራውን ያኽሌ አይዯሇም እንጂ መጉዲትስ ጏዴቶዋሌ
ነገር ግን ከሰው የበሇጠ የጎዲ ከብቱን ነው» አሌሁዋቸው።

«ይገርማሌ! የእዴሌ ነገር ሆኖ ነው እንጂ የእኛን ጌታ ዯጃዝማችን ዲባት ከከተማቸው ሲኖሩም


ከዚያ ሰራዊታቸውን ይዘው ወጥተው እዚህ አካባቢ ሰፌረው ሲሰነብቱም እያሇፇ ከመሄዴ በቀር አንዴ
ቀን አስዯንግጦአቸው አያውቅም» አለ ሽማግላው።

ከዚያ የሇማሇሞን መንገዴ ወዯ ቀኝ ትተን ወዯ ግራ ባሊገሮች ያሳዩንን ቀጭን መንገዴ ይዘን


አፊፌ ሊፊፌ በግምት ሁሇት ኪል ሜትር ያህሌ እንዯ ሄዴን፥

«ቁሙ!» የሚሌ ከፌተኛ የትእዛዝ ዴምፅ ሰማን። ያዘዘንን ሰው ግን፥ ሁሊችንም ዙሪያውን
ባይናችን ፇሌገን ሌናየው አሌቻሌንም። ስሇዚህ ምንም እንኩዋ እዚያ አካባቢ ዘበኞች መኖራቸውን
ባሊገሮች ቢነግሩን ያን ትእዛዝ ዘበኞች ይስጡን፥ ወይም ላልች ማወቅ ስሊሌቻሌን ሰግተን እኔ ከበቅልዬ
ወርጄ የጏረሰ ጠምንጃዬን ከገሊው ተቀብዬ ጤናውና ዘሪሁንም እንዯ ኔ የጏረሰ ጠመንጃ ጠመንጃቸውን
እንዯ ያዙ ፇንጠር ፇንጠር ብሇን ቀጥል የሚመጣውን ተጠንቅቀን እንጠብቅ ጀመር። ካዛዣችን
ተጨማሪ ዴምፅ ሳይመጣ፥ እኛም እንዱያ በስጋት ሊይ እንዲሇን ዘሇግ ያሇ ጊዜ ካሇፇ በሁዋሊ፥

«ሂዴና ጠይቃቸው!» አሇ እንዯ ፉተኛው ጏርነን ያሇ ዴምፅ።

«ሰውየው ያውና እዚያ ዛፌ ውስጥ!» አሇ ጤናው፤ ሁሇተኛው ትእዛዝ ከመስጠቱ አንገቱን ዝቅ


አይኑን ጭንቁር አዴርጎ ወዲንዴ ዛፌ ባገጩ እያመሇከተ። ያ ሰው ከመንገደ ጏን ትንሽ ራቅ ብሊ
በበቀሇች ቅጠሊም ዛፌ ሊይ እንዲይታይና ቅጠለን ሇብሶ ጠመንጃውን ወዯ መንገደ ዯግኖ ተቀምጦዋሌ።
ወዱያው እንዱጠይቀን የታዘዘው ሰው እመንገደ ዲር ከነበረ ቁዋጥኝ ዴንጋይ ጀርባ ከተሸሸገበት ወጥጦ
ጠመንጃውን በፉቱ አስቀዴሞ ወዯኛ መንገዴ ሲጀምር፥

«ትተኩሱና ክፈ ነገር ይዯርስባችሁዋሌ፤ እኛ የክብር ጌታችን የዯጃዝማች አያላው ዘብ


ጠባቂዎች ነን!» አሇ እዛፈ ሊይ የነበረው ሰው።

«እኛም ከክቡር ራስ እምሩ ይህን መሌእክት ሇክቡር ዯጃዝማች አያላው ብሩ እንዴናዯርስ


የተሊክን መሊክተኞች ነን» አሌሁ፤ መሌእክት የያዘውን አንቨልፕ ከኪሴ አውጥቼ ከሩቅ እንዱያዩት
እያወሇበሇብሁ። ያሌሁትን ሲሰሙና አንቬልፑን ሲያዩ ጠመንጃውን በፉቱ አስቀዴሞ ወዯኛ መንገዴ
የጀመረው ሰው ወዯ ትከሻው መሌሶ አንግቶ እዛፌ ሊይ ተቀመጠ ትእዛዝ ሲሰጥ የነበረው ሰውና ከላሊ
ወገን በላሊ ዛፌ ሊይ ቅጠሌ ሇብሶ ተቀምጦ ሳናየው የቆየ ላሊ ሰውም እንዱህ ጠመንጃቸውን እያነገቱ
ወርዯው መጡ። ከዚያ ሰሊምታ ተሰጣተን፥ ዲባት እሰፇራችን ሊይ ስሇ ዯረሰው የቦምብ አዯጋ ትንሽ

39
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከተነጋገርን በሁዋሊ ከሶስቱ አንደ እየመራ ወስድ ሁሇተኛውን በር ከሚጠብቁት ዘበኞች ጋር አገናኘን፤
ከዚያም አንዴ ላሊ ዘበኛ ወዯ ዯጃዝማች ሰፇር ወሰዯን።

ዯጃዝማች አያላው የሰፇሩበት ቦታ ተከዜ አፊፌ ሊይ እንዯ መሆኑ ቁጥቁዋጦና በርከት ያለ


ዛፍች ያለበት ነው። ስሇዚህ ከሳቸው ሰፇር ራቅ ባሇ ቁጥቁዋጦ ውስጥ እኛ ያሊየነው የወታዯር ሰፇር
ኖሮ እንዯሆነ እንጂ እኛ እንዲየነው፥ እዚያ እሳቸው በሰፇሩበት ሊይ የነበሩት የመኩዋንንትና የወታዯር
ዴንኩዋኖች ይህን ያህሌ ብዙ የሚባለ አሌነበሩም።

አጋፊሪው ዯጃዝማች አያላው ወዯ ተቀመጡበት ዴንኩዋን አስገብቶኝ እጅ ስነሳ እሳቸውና


ዯጃዝማች ‹ገብረ መዴህን› የሚባለ ከትግራይ የመጡ የሌኡሌ ራስ ስዩም ታሊቅ መኮንን ጏን ሇጏን
በተነጠፈ ዴሌዲልች ሊይ ተቀምጠው ነበር። በሁሇቱም ፉት፥ ባንዴ ጠረጴዛ ሊይ ጠጅ የያዙ ብርላዎች
ተቀምጠዋሌ። ከራስ የተሊከሊቸውን በአንቬልፕ የተዯፇነ መሌእክት ሇዯጃዝማች አያላው ሰጥቻቸው
አንብበው በጎናቸው እዴሌዲለ ሊይ ካስቀመጡት በሁዋሊ፥

«ጠጅ አምጣሇት» አለት፥ ያስገባኝን አጋፊሪ።

«ጌታዬ ይቅርብኝ» አሌሁ፥ እጅ ነስቼ።

«ሇምን?»

«ጠጅ አሌጠጣም»

«ብርዝም አትጠጣም?»

«ብርዝ እጠጣሇሁ»

«ብርዝ አምጣሇት» አለና አጋፊሪው ሲመጣ፥

«ተቀመጥ» አለኝ።

ዴንኩዋኑ ከዲር እስከ ዲር ስጋጃ ምንጣፌ ግጥም ብል የተነጠፇበት ነበር። ይሁን እንጂ ጥይት
ሙለ ዝናሬንና ሽጉጤን እንዯ ታጠቅሁ እግሬን አጣጥፋ እመሬት ሊይ መቀመጥ አስቸጋሪ ስሇ ነበረ፥
ቆሜ ብቆይ በወዯዴሁ ነበር። ነገር ግን ትእዛዛቸውን አሇማክበር መስል ይታይብኝ ይሆናሌ ብዬ ፇርቼ
በግዴ እግሮቼን አጣጥፋ እምንጣፈ ሊይ ተቀመጥሁ።

ሇኔ የታዘዘው ብርዝ እስኪመጣ ዴረስ እዚያ ዴንኩዋን ውስጥ ትንፊሽ አይሰማም ነበር።
ዯጃዝማች አያላው ሽቅብ አንጋጠው የዴንኩዋኑን ጣራ እየተመሇከቱ ዯጃዝማች ገብረ መዴህን አንዲንዴ
ጊዜ ዯጃዝማች አያላውን አንዲንዴ ጊዜ እኔን አንዲንዴ ጊዜ መሬቱን እያሇዋወጡ እያዩ፥ እኔም አንዲንዴ

40
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጊዜ ብቻ ስርቅ እያዯረግሁ ሁሇቱን ዯጃዝማቾች ከማየቴ በቀር አንገቴን ዯፌቼ የተቀመጥሁበትን መሬት
እየተመሇከትሁ ከባዴ ዝምታ ሰፌኖ ቆየ። ብርዝ እንዱያመታሌኝ የታዘዘው ሰው አምጥቶ እፉቴ
አስቀምጦሌኝ ከወጣ በሁዋሊ፥

«ይገርማሌ መቆየት ብዙ ያሳያሌ ብዙ ያሰማሌ! መቆየታችን እኛ የምንጠረጥር እኛ የማንታመን


መሆናችንን አሳየን፤ አሰማን!» አለ ዯጃዝማች አያላው አይናቸውን ከዴንኩዋኑ ጣራ መሌሰው እኔን
ፌጥጥ አዴርገው እያዩ። «ሇመሆኑ» አለ ቀጠለና «ሇመሆኑ የምኒሉክ አሌጋ የጣይቱ አሌጋ የሀይሇ
ስሊሴ አሌጋ፥ የኔ አሌጋ ሳይሆን ቀርቶ ነው እኔ አያላው በገዛ ሊሌጋዬ፥ ‹ዯባ ይሰራሌ› ተብዬ
የምጠረጠረው? ግዳሇም እንዱያ ያሇውን ወሬ ካስወሩብኝ ጠሊቶች ጋር፥ ሌብና ኩሊሉት መርምሮ
የሚያውቀው አምሌካ ያፇራርዯኛሌ። እኔም እውነት እንዱያ ያሇውን ዯባ የምሰራ ከሆንሁ እሱ ዯሜን
እንዱህ ያፌስሰው!» አለና ጠጅ የያዘ ብርላያቸውን አንስተው በጠረጴዛው ሊይ ሲከሰክሱት ጠጁ ከሳቸው
አሌፍ ተርፍ፥ በዯጃዝማች ገብረ መዴህን ሊይ ተረጨ! ያን ጊዜ እኔ በጣም ዯነገጥሁ። ይሌቁንም ያን
የተናገሩትን ሁለ ሲናገሩ እኔነ ፌጥጥ አዴርገው ያዩ ስሇ ነበረ ‹ምናሌባት እሳቸውን ሇመሰሇ የተሊክሁ
መስያቸው ይሆን?› ብዬ አሳብ ገባኝ።

«ማነው ዯግሞ እርስዎን የሚጠረጥር? ይህ እንዱያው ከንቱ የማይረባ ነገር ነው! ‹ይጠረጠራለ›
ብል የነገረዎ ሰው ካሇ ይሌቅ እሱ ነው ጠሊትዎ እንጂ እስዎን የሚጠረጥር ይኖራሌ ብሇው አያስቡ»
አለ ዯጃዝማች ገብረ መዴህን።

«እርስዎ የሚድሇትብኝን ሁለ አያውቁምና ዝም ይበለ ዯጃዝማች፤ እኔ ነኝ የማውቀው እኔ


ሁለንም ተከታትዬ ዯርሼበታሇሁ» ብሇው በቁጣ ሲያጨበጭቡ አጋፊሬው ገባ።

«ገሰስን ጥራው!» አለ ዯጃዝማች አያላው፤ እንዯ ተቆጣ አንበሳ የሚያፇራ ፉት። ከዚያ
ግራዝማች ይሁን ወይም ቀኛዝማች «ገሰሰ» የሚባለት ጠና ያለ መኮንን ኩታቸውን በካኪ ኮታቸው
ሊይ አዯግዴገው የጠመንጃቸውን አፇሙዝ ዘቅዘቀው ሲገቡ፥

«ገሰሰ» አለ ዯጃዝማች በተቀመጡበት እንዲለ እየተንቆራጠጡ። «ገሰሰ እኔ አያላው


በታዘዝሁበት የጦር ሜዲ ሁለ የመንግስቴን ጠሊት እያስጨነቅሁ መሬት እያስጋጥሁ ሳሳምን
የመንግስቴን ክብር ሳስጠብቅ የኖርሁ አይዯሇሁም? ‹በመንግስቱ ሊይ ዯባ ይሰራሌ› ተብዬ የምጠረጥር
ነኝ? በታዘዝሁበት የጦር ሜዲ ሁለ ተሇይተውኝ ከማያውቁት አሽከሮቼ አንደ አንተ ነህ፤ እስቲ
መስክር!»

«እንዳት! ዯግሞ ማነዋ ጌታየን ‹በመንግስቱ ሊይ ዯባ ይሰራሌ› የሚሌ! በመንግስት ሊይ ዯባ


የሰሩትን ‹ካይዲኖች› እያሳዯዯ ሲቀጣ የኖረ ማን ሆኖ ነዋ ጌታዬ ‹በመንግስት ሊይ ዯባ ይሰራሌ› የተባሇ!
ያንተን ታማኝነትና ጀግንነት እኛ አሽከሮችህ ብቻ ነን የምንመሰክር? ያንተን ታማኝነታ ጀግንነት አሇም

41
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሁለ ያወቀው አሇም ሁለ ተናግሮ ያበቃው አዯሇም? ጌታዬን ‹በመንግስት ሊይ ዯባ ይሰራሌ› የሚለት
ራሳቸው ዯባ የሚሰሩ ካይዲኖች ናቸው! አንዴ ትንሽ ምሌክት ብቻ አሳየንና እኒያን ስምህን በሀሰት
የሚያካፈትን ጠሊቶችህን እኒያን ካይዲኖች አስጨንቀን ያንተን ታማኝነትና የነሱን ካይዲንነት በገዛ
አፊቸው እንዱመሰክሩ እንዱናዘዙ እናዴርጋቸው! አንዴ ምሌክት ብቻ አሳየን! ዘራፌ ያንተ አሽከር! ዘራፌ
ገሰሰ….!» እያለ የጠመንጃቸውን አፇሙዝ ዘቅዝቀው ይዘው የፈከራ ግጥማቸውን እየዯረዯሩ በዴንኩዋኑ
ውስጥ ሲንጎራዯደ ሇሳቸው ቦታ ሇመሌቀቅ ያሰብሁ መስዬ ከዚያ በይለኝታ ተገዴጄ እግሮቼን አጣጥፋ
ከተቀመጥሁበት መሬት ብርዜን ይዤ ተነሳሁና ዴንኩዋኑን ተጠግቬ ቆሜ አይ ጀመር።

ግራዝማች (ወይም ቀኛዝማች) ገሰሰ እንዱያ ወዱያና ወዱህ እየተመሊሇሱ ፈከራቸውን ጨርሰው
እጅ ነስተው ከወጡ በሁዋሊ ትንሽ ቆይቶ አጋፊሪው ገብቶ «ከፉታውራሪ ሽፇራው ወረቀት የያዘ
መሊክተኛ መጥቶዋሌ» አሇ።

«ከየት ከግንባር» ጥራው!» አለ ዯጃዝማች የስጋት ምሌክት በፉታቸው እየታየ። ፉታውራሪ


ሽፇራው ጌታሁን ተከዜ አጠገብ፥ ዯባጉና የተባሇውን ጣሉያኖች መሽገው የተቀመጡበትን ቦታ ከብበው
እንዱጠብቁ ከተሊኩት ሶስት የጦር አሇቆች አንደ፤ ተከዜን በሇማሇሞ በኩሌ ተሻግረው የምስራቁን
ግንባር እንዱይዙ የታዘዙት ነበሩ። ‹በአዱያቦ› በኩሌ የምእራቡን ግንባር ይዘው ሇመጠበቅ የሄደት የጦር
አሇቃ የዯጃዝማች አያላው ትሌቁ ሌጃቸው (ስማቸውን ረስቻሇሁ) የነበሩ መሆናቸውን ያንሇት ዯጃዝማች
ራሳቸው ሲናገሩ ሰምቻሇሁ። የመሀከለን ግንባር ይዘው ሉጠብቁ ታዝዘው የሄደት ላሊ ትሌቅ የጦር
አሇቃ ነበሩ።

የፉታውራሪ ሽፇራው መሊክተኛ ገብሮ እጅ ከነሳ በሁዋሊ የያዘውን ወረቀት ከኪሱ አውጥቶ
ሇዯጃዝማች አያላው ሰጥቶ እንዯ ቆመ፥ ዯጃዝማች ስሜታቸው መታወኩ በፉታቸው እየታየ ወረቀቱን
አንብበው በጎናቸው እዴሌዲለ ሊይ ጣለና፥

«እንዳት! መሊሌሼ ነግሬው ያን ያክሌ አዯራ ብዬው እንዱህ ያዯርገኛሌ?» አለ በብርቱ ቁታ


አይናቸውን በመሊክተኛው ሊይ አፌጥጠው። «ጠሊት አስቀዴሞ ካሊጠቃ አንተ የምታዘው ጦር በምንም
ምክንያት ቀዴሞ እንዲያጠቃ» ብዬ በጥብቅ አስጠንቅቄው፥ አዯራ ብዬው፥ ይህ እብዴ «ትእዛዝ
ተሊሌፇሀሌ ብሇው ጃንሆይ እንዱጣለኝ እንዱህ ያዯርገኛሌ?»

«ማጥቃት ጀመርን› ነው የሚሇው ፉታውራሪ?» አለ ዯጃዝማች ገብረ መዴህን። ዯጃዝማች


አያላው ሇተጠየቁት መሌስ ፉታውራሪ ሽፇራው ጌታውሁን የፃፈሊቸውን ወረቀት ከጣለበት አንስተው
ሇሁሊችንም እንዱሰማ አዴርገው አነበቡት። ወረቀቱ የሚሇው - ከሞሊ ጎዯሌ - እንዯሚከተሇው ነበር።

«ላሉቱን ተከዜን ተሻግረን አፊፈን ከወጣን በሁዋሊ ተሸሽገን የምንቆይበት ጫካ ፌሇጋ ወዯ ፉት


ስንሄዴ፥ ዯባጉና አጠገብ እንዯ ዯረስን ስሇ ነጋብን፥ ትንሽ ቁትቁዋጦ አግኝተው እዚያ መስፇር ግዴ

42
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሆነብን። ይህ የሰፇርንበት ቦታ ትንሽ ቁጥቁዋጦ እንጂ፥ ጫካ የላሇበት በመሆኑ ዛሬ ሳንታይ ብንውሌ
ነገ ሳንታይ ሌንውሌ አንችሌም። ስሇዚህ ጦራችን ጠሊት ባሇበት እንኩዋ ሳይዯርስ ባይሮፕሊን ተዯብዴቦ
እንዲያሌቅ ነገ እንጋት ሊይ ዯባጉናን እንመታሇንና ረዲት ጦር ቶል እንዱዯስሌን»

«ፉታውራሪ ሽፇራው ያሇው እውነት ነውኮ ጌታዬ፥ የትግራይን ምዴር ጣሉያን በቦምብ
አቃጥልት ዛሬ እንኩዋንስ ሰው ወፌ የሚሸሽግ ጫካና ቁጥቁዋጦ አይገኝም። ስሇዚህ ጦሩ አንዴ ስራ
ሳይሰራ በሰፇረበት ባይሮፕሊን ተዯብዴቦ ሳያሌቅ ቀዴሞ ባዯጉናን ሇመምታት ማሰቡ ማሇፉያ አሳብ
ነው» አለ ዯጃዝማች ገብረ መዴህን።

«ያሌሁትን አሌሰሙኝም መሰሇኝ!» አለ ዯጃዝማች አያላው ቆጣ ብሇው። «ያሌሁትኮ ‹እኔ


የታዘዝሁት እሱንም ያዘሁት ጠሊት ቀዴሞ ካሊጠቃ በምንም ምክንያት እሱ የሚያዝዘው ጦር ቀዴሞ
እንዲያጠቃ› ነው! ይህን ነበር በጥብቅ ያስጠነቀቅሁት፤ አሁን ጉዴ አዯረገኝ! ከንግዳህማ እንዱያውስ ምን
ሊዴርግ እችሊሇሁ! አሁን መሊክተኛ ቢሊክ ከንጋት በፉት እዚያ ዯርሶ ወዯ ሁዋሊ እንዱመሇስ ማዴረግ
ይቻሊሌ!»

«ዋይ! እንዱህ ያሇው ነገር እዚህም አሇ? እንዱህ ያሇው ነገር እርስዎም ዘንዴ መኖሩን ባውቅ
መች እመጣ ነበራ!» አለ ዯጃዝማች ገብረ መዴህን እሳቸውም ተቆጥተው። «ጌታየ ሌኡሌ ራስ ስዩም
ወዯ ሄደበት መሄደን ትቼ ወዯርስዎ የመጣሁ እንዱህ ያሇው ነገር አበሳጭቶኝ መሆኑን
ነግሬዎታሇሁ። ‹መረብን ጠሊት እንዲይሻገር ተከሊከሌ› ተብየ ከተሊክሁ በሁዋሊ ‹ጠሊት ካሌተኮሰብህ
እንዲትተኩስ› ስሇ ተባሌሁ እጄን አጣጥፋ እንዯ ተቀመጥሁ፥ ጠሊት በኔ ሳይተኩስ እኔነ አሌፍ አዴዋን
ባይሮፕሊን ሲዯበዯብ ራስ ሇቅቀው ወዯነራስ ካሳ ስሇ ሄደሇት አንዴ ጥይት ስናጮህበት መረብን ከኛ
ትንሽ ራቅ ብል ተሻግሮ አዴዋን ያዘ። ሇምን? ‹ካሌተኮሰባችሁ እንዲትተኩሱበት› ስሇ ተባሇን! ሇመሆኑ
ሇጦርነት ተሰሌፍ ‹ጠሊት ካሌተኮሰባችሁ እንዲትተኩሱ› ማሇት ምን ፇሉጥ ነው? ፌራት ነው? ወይስ
ምን?»

«እንኔ አያላው ነኝ የምፇራ? አያውቁኝም ማሇት ነዋ፤ ዯጃዝማች!»

«ጀግንነትዎን ዯህና አዴርጌ አውቃሇሁ እንጂ! ጀግናነትዎን ዯህና አዴርጌ ስሇማውቅ ነበርኮ
ከርስዎ ጋር ሆኜ መረብ የተሳሳትሁትን ስህተት ሇማረም ወዯርስዎ የመጣሁ! ነገር ግን አሁን ሲናገሩ
የሰማሁትን ከስዎ ሰምቸው የማሊውቅ፥ እንግዲ ነገር ሆነብኝና ግራ ገባኝ!»

« ‹ጠሊት ሲያጠቃ ከመከሊከሌ በቀር እናንተ ቀዴማችሁ እንዲታጠቁ› የሚሌ ነው ትእዛዛችን፤


እንዱህ ያሇው ትእዛዝ የተሰጠበትን ምክንያት የሚያውቁት ከኛ በሊይ ያለት ናቸው፤ እኛ አይዯሇምን!»

43
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ጠሊታችን ወሰን ጥሶ ሲገባ ካሌተኮስንበት እንዱሁ ሰተት እያሇ አገራችንን አንዴ ባንዴ ይዞ
ይጨርሳሌ እንጂ፤ ሇምን ብል ይተኩሳሌ? ሇምን ጥይቱን ያባክናሌ!»

«ስማ ወዲጄ!» አለ ዯጃዝማች አያላው ሇዯጃዝማች ገብረ መዴህን መመሇሳቸውን ትተው፥ ወዯ


ኔ ባገጫቸው አመሇከቱና። «ዯባጉናን ከብበው እንዱጠብቁ ከሊክሁዋቸው የጦር አሇቆች አንደ፥ ‹ነገ
እንጋት ሊይ ጦርነት እንገጥማሇሁና ረዲት ጦር ይሊክሌኝ› ብል የፃፇሌኝን አሁን ሳነብ ሰምተሀሌ። ነገር
ግን ያሇኝን ጦር ሁለ በሶስት ከፌየ ሇዚያው ሇከበባው ስሇ ሊክሁ፥ እኔን ሇመጠበቅ ከቀሩት ጥቂት
ዘበኞች በቀር በተጨማሪ የምሌክሇት ጦር የሇኝም። ‹አዱያቦንና› መሀከሇኛውን ግንባሮች ይዘው
እንዱተብቁ የሄደትም ሇርዲታ እንዲይዯርሱሇት ያለበት የተራራቀ ነው። ስሇዚህ ከራስ ላሉቱን ብርቱ
ረዲት ጦር ተሌኮ ሇነገ እንዱዯርስሇት በጥብቅ አዯራ ማሇቱን እንዴትነግርሌኝ! ስሇዚህም
ስሇምንገናኝበትም ወረቀት እሰጥሀሇሁ»

ከዚያ ብርዜን ጠጥቼ እጅ ነስቼ ወረቀቱን ተፅፍ እስኪሰጠኝ ከሰዎቼ ጋር እውጭ ቆየሁና አስር
ሰአት ግዴም ተነስተን ስንገሰግስ፣ ሲጨሌም ሰፇራችን ዯረስን።

ጤናው ረዥሙ ዘሪሁንና ገሊው ወዯ ዴንኩዋናችን ሲሄደ፥ እኔ በቀትታ ወዯ ራስ ዴንኩዋን


ሄዴሁ። እዚያ ‹ሉጋባው› ፉታውራሪ ሀይለ እምሩ ተቀብሇው ወዱያው ከራስ ጋር አገናኝተውኝ
ዯጃዝማች አያላው ያሌኩትን ወረቀት ከሰጠሁዋቸውና በቃሌ ‹አዯራ› ያለኝን ከነገርሁዋቸው በሁዋሊ
እዯጃዝማች ዴንኩውና ገብቼ እስክወጣ ዴረስ ያየሁትን ትያትር የሚመስሌ ነገር እንዱሁም በሁሇቱ
ዯጃዝማቾች መሀከሌ ተነስቶ የነበረውን ክርክር በዝርዝር ተረክሁሊቸው።

«በወረቀት የፃፌሁሊቸው ሊንተ በቃሌ ከነገርሁህ የተሇየ አዯሇም። ስሇዚህ እሳቸው የሚያውቁት
እኛ የማናውቀው ነገር ይኖር እንዯሆን እንጂ፥ እኔ በፃፌሁሊቸው ‹ተጠርጠርሁ› አሰኝቶ የሚያስቆጣ ነገር
የሇበትም» አለ ራስ፤ እንዯ ማገረም ብሇው።

እኔ ተሰናብቼ ወዯ ዴንኩዋኔ ከሄዴሁ በሁዋሊ ምክር ተዯርጎ ፉታውራሪ ‹ክፌኔ ማንያህሌሀሌ› ላሉቱን
በግስጋሴ ተከዜን ተሻግረው ሇፉታውራሪ ሽፇራው ርዲታ እንዱዯርሱ ታዝዘው በነጋው አፌሊ ጦርነት
ሊይ የዯረሱሊቸ መሆኑን ሰማሁ። ፉታውራሪ ክንፋ ማንያህሌሀሌ ሇጎጃም ፉታውራሪ ጦር አዛዥ ነበሩ።

የዯባጉና ጦርነት ታህሳስ 6 1928 ነበር የተዯረገው። በሰው ቁጥር ዯባጉና መሽጎ ከተዋጋው
የጣሉያን ጦር የፉታውራሪ ሽፇራውና የፉታውራሪ ክንፋ ጦር ባንዴነት ይበዛ እንዯ ነበረ፥ በጦርነቱ
ተካፊዮች የነበሩ ሰዎች ይናገራለ። በመሳሪያ በኩሌ ግን በሁሇቱ ወገኖች መሀከሌ የነበረው ሌዩነት
የሰማይና የምዴርን ያክሌ የተራራቀ ነበር! የኢትዮጵያውያን መሳሪያ አብዛኛው ያው አሮጌ ጠመንጃ
ነበር። በዚያ አንፃር የጣሉያኖች ጦር ምሽጉን አጠንክሮ ሰርቶ ይዋጋ የነበረ ከመሆኑ ላሊ መዴፍች ብዙ

44
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከባዴና ቀሊሌ መትረየሶች እንዱሁ የጅ ቦምብ በብዛትና ታንኮች ነበሩት። ያም ሆኖ በመጨረሻ ዴለ
ሇኢትዮጵያውያን ሆነ።

በጦር ሜዲ፥ እንኩዋንስ የጠሊትን ሙታንና ቁስሇኞች የራሳችንንም ቆጥሮ የመያዝ ሌምዴ
ስሇሉዓሇን በዯባጉና ጦርነት ከኛም ከጠሊትም ምን ያክሌ ሞተው ምን ያክሌ እንዯ ቆሰለ በኛ በኩሌ
እርግጡን የሚያውቅ ያሇ አይመስሇኝም መቸም እኔ አሊውቅም። ማርሻሌ በድሉዮ ግን ቀዯም ብየ
በጠቀስሁት መፅሀፈ ከጣሉያን ጦር ወገን የሞቱና የቆሰለ 392 ወታዯሮችና 9 መኮንኖች በምዴር 401
መሆናቸውን ፅፍዋሌ። ታዱያ ዯባጉና ጦር ሜዲ ሊይ ከሞቱት ተርፇው የእንዲ ስሊሴን መንገዴ ይዘው
ሲሸሹ እስከ ብዙ ኪል ሜትር ዴረስ ወዴቀው ይታዩ የነበሩት የጣሉያንና የመሇዮ ሇባሽ «አሽከሬ»
ሬሳዎች ቁጥር ተይዞ ሲገመት ማርሻ ባድሉዮ የሰጠውን የሙታንና የቁስሇኞች ቁጥር የሚያስተባብሌ
ሆኖ ይገኛሌ፤ ከጣሉያንም ከኢትዮጵያም ወገን የሞቱትና የቆሰለት ትክክሇኛ ቁጥራቸው ባይታወቅም
ብዙ ነበሩ። ከጣሉያኖች የተማረከው መሳሪያም እጅግ ብዙ ነበር። ከባደና ቀሊለ መትረየስ ጠመንጃው
የመተረየሱና የጠመንጃው ጥይት በሳጥን በሳጥን እንዲሇ ሁለም ብዙ ነበር። ሉሬው ከወታዯሩ ተርፍ
በባሊገሩ እጅ በብዛት ይገኝ ስሇ ነበረ እኛ ስንዯርስ፥ ባንዴ ብር እስከ ሺህ ሉሬ ይሇወጥ ነበር።
የተሰባበሩም ያሌተሰባበሩም ታንኮችና ብረት ሇበስ ካሚዎኖች በጦሩ ሜዲ በእንዲ ስሊሴ መንገዴ
ቆመውም ተገሌብጠውም በብዛት ይታዩ ነበር።

ማርሻሌ ባድሉዮ ስሇ ጦርነቱ በመፅሀፈ ሲተች «የዯባጉና ጦርነት ከጠቅሊሊው ጦርነት አንፃር
ሲታይ ከቁም ነገር የሚቆጠር አይዯሇም» ብልዋሌ። እርግጥ ከጠቅሊሊው ጦርነት አንፃር ሲታይ የዯባጉና
ጦርነት ትንሽ ነው። ነገር ግን ብቻውን ሲታይ፥ - ብቻውን መታየትም ይገባዋሌ - ታሪካዊ ነው።
የዯባጉና ጦርነት የተዯረገበት ቦታ የተዯረገበት ቀን በጦርንቱ ዴሌ ያዯረጉት ኢትዮጵያውያንና ዴሌ
የሆኑት ጣሉያኖች የራሳቸው የሆኑ መሌክና ጠባይ ያለዋቸው ናቸው። ስሇዚህ፥ ኢጣሉያ በመጨረሻ
በጠቅሊሊው ጦርነት ዴሌ አዴራጊ ሆኖ ኢትዮጵያን መያዝዋ የዯባጉናን መሌክና ጠባይ አይሇውጠውም።
ኢጣሉያ በመጨረሻ ኢትዮጵያን ዴሌ አዴርጋ መያዝዋ ዯባጉና ያሇቁንት ሽማምንትዋንና ወታዯሮችዋን
ከሞቱበት በግዘሪ - ሥጋ አያስነሳቸውም፤ አካሊተ ጎዯልዎች የሆኑትን በሇሙለ አካሊት
አያዯርጋቸውም። ይህ የተዯረገ ጎዯልዎች ስሇ ሆነ፥ የተዯረገው እንዴ እገና እንዲሌተዯረገ ሉሆን
አይችሌም! እርግጥ በላልች ቦታዎችና በላልች ቀኖች ኢጣሉያ ዴሌ አዴርጋ ኢትዮጵያን ይዛሇች። ነገር
ግን ያ ሁለ ጀግናው ፉታውራሪ ሽፇራውና ጀግኖች ተከታዮቻቸው ምሽግ አፌርሰው የመዴፌና
የመትረየስ አጥር ጥሰው ታንክ ሰባብረው የሚበዙትን ጣሉያኖች ገዴሇው የተረፈትን መሳሪያቸውን
እያስጣለ አባርረው የዯባጉናን ዴሌ የተቀዲጁ መሆናቸውን በምንም መንገዴ ሉሇውጠው አይችሌም!
ኢጣሉኢያ ኢትዮጵያን ዴሌ አዴርጋ መያዝዋ የሽፌራውን ጀግናነት ሉቀማው አይችሌም! ሽፇራው ዴሌ
ባዯረገበት ቦታ፥ ዯባጉና ሊይ ቢወዴቅም ምዴርን ከነታሪክዋ የሚያጠፊ መአት እስካሌመጣ ዴረስ
ጀግናነቱና ስሙ ከዯባጉና ተራራ ጋር ሇሁሌጊዜ ይኖራለ።

45
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምእራፍ ሰባት

ተከዜ
የጎጃም ጦር ዲባት ሜዲ አጠገብ ቁጥቁዋጦ ባሇበት ቦታ ሰፌሮ ከቆየበት ተነስቶ በሁሇተኛው
ይሁን በሶስተኛው (እርግጡን እረሳሁት) ቀን፥ ከቀትር በሁዋሊ በዯህና ጊዜ ተከዜ ሸሇቆ ውስጥ ሰፇረ።
የተከዜን አፊፌ ወጥቶ ትግራይ ውስጥ ሽሬ ሇመስፇር የሚበቃ ጊዜ እያሇ ሰፇር እሸሇቆ ውስጥ እንዱሆን
የተመረጠበትን ምክንያት አሊውቅም። ምናሌባት ከዚያ በፉት ሰፇር በተዯረገባቸው አንዲንዴ ቦታዎች
ሇሰውና ሇከብቱ የሚበቃ ውሀ ሳይገኝ እየቀረ ችግር ይፇጠር ስሇ ነበረ፥ እንዱያ ካሇ ችግር ሇመዲንና
ወዱያውም ዴንገት አይሮፕሊን ቢመጣ ሇመጠሇያ ጫካውም ዋሻውም እዚያ የሚመች በመሆኑ ሉኆን
ይችሊሌ።

የጎጃሙ ፉታውራሪ ጦር አዛዥ ፉታውራሪ ክንፋ ማንያህሌሀሌ፥ ሇዯባጉናው ጦርነት ይዘውት


የሄደት ጦር ቢቀነስሇትም የቀረው ብዙ ስሇ ነበረ፥ የተከዜን ወንዝ በቀኝና በግራ ተከትል ሸሇቆውን
በወርደም በቁሙም እስከ ሩቅ ዴረስ ሞሌቶ ሰፇረ። የራስ ሰፇር ወንዙን ተሻግሮ ወዯ ግትራይ ግንባር
ነበር። የኛ ሰፇርም ከሳቸው ሰፇር በጣም ሩቅ አሌነበረም። ዴንኩዋኖቻችንን ተክሇን እቃችንን ቦታ
ቦታውን አስይዘን ካሰነዲዲን በሁዋሊ ሇማረፌ እንዯተቀመጥን እኔ «ራስ ይፇሌጉሀሌ» ብል መሊክተኛ
መጥቶ ስሇ ነገረኝ ሇመሄዴ ተነሳሁ። ገሊውም እንዯ ሌማደ ሉከተሇኝ ጠመንጃየን ይዞ ሲወጣ አይቼ፤
የራስ ሰፇር ቅርብ ስሇ ነበረ፤ «ተመሇስ» ብዬው ብቻዬን ሄዴሁ።

ራስ አነጋግረውኝ ስወጣ፤ እዚያ ውጭ በቡዴን በቡዴን እየሆኑ ቆመው የሚያወሩ ብዙ ሰዎች


ስሇ ነበሩ እኔም ከወሬው ሇመጋራት ወዲንደ ቡዴን ጠጋ ከማሇቴ ያይሮፕሊን ዴምፅ ተሰማ። ወዱያው
«ተበታትናችሁ ወዯ አይሮፕሊኖች ተኩሱ» ሇማሇት ምሌክት የሆነው የክብር ዘበኞች ጥሩንባ ይነፊ
ጀመር። ከዚያ «ተበታትናችሁ ወዯ አይሮፕሊኖች ተኩሱ» ሇማሇት ምሌክት የሆነው የክብር ዘበኞች
ጥሩንባ ይነፊ ጀመር። ከዚያ ራስ ባቅራቢያው ወዯ ተሰናዲሊቸው መጠሇያ ሲሄደ እኛም ወዯ ዛፈ ስር
እየሄዴን እንዯ ተጠጋን፤ ዴምፃቸውን ከሩቅ ያሰሙን አይሮፕሊኖች ታዩ። እኔና አብረውኝ የነበሩት
ሰዎች የተጠጋንበት ዛፌ ትሌቅ ስሇ ነበረ እዚያ ስር ሆኖ እይሮፕሊኖችን ሇመቁጠር ያስቸግር ነበር።
ቢሆንም እኔ ሇመቁጠር እስከቻሌሁት ዴረስ አመት መሇውኝ ነበር። ላልች ግን እንዯኔ አምስት ናቸው
ያለም ሰባት ናቸው ያለም ነበሩ። ያም ሆነ ይህ ዯባት ሜኢዲ የዯበዯቡንን ሲዯበዴቡን አሌቆዩም።
የተጫኑትን ቶል ቶል አራግፇውብን ቶል ተመሇሱ መቸም በጦሩ ሰፇር ሊይ የጣለትን ጥሇው
እስኪመሇሱ ዴረስ የነበረው ተኩስ ከመብዛቱ የተነሳ ጠመንጃ ያሇው ሁለ የሚተኩስ ይመስሌ ነበር።
ያንሇት የተጣሇው ቦምብ ዯባት ሜዲ ከተጣሇው የተሇየ በጣም ትሌሌቅ ነበር። ስሇዚህ ካይሮፕሊኖች
አካሊት አንዲንዴ ክፌሌ እየተሰበረ የወዯቀ መስልት ብዙ ሰው ወዯዚያ «ያይሮፕሊን ስባሪ» ወዯ ተባሇው
ነገር እየሮጠ እየሄዯ ከብቦ ሲመሇከት ቆየ።

46
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በኒያ የአይሮፕሊን ስባሪ መስሇውት ሰው ተሰብስቦ በሚመሇከታቸው ነገሮች አካባቢ አየሩ እንዯ
ሰናፌጭ በሚከነክን ትናኝ ተበክል እዚያ የተሰበሰቡትን ሰዎች ሁለ አይናቸውን እየሇበሇበ ወዱያው
ያስሊቸውና ያስነጥሳቸው ጀመር። የዛፍች ቅርንጫፌ ቅጠለና ሳሩም ሁለ የዘይት ጠባይ ያሇው ፇሳሽ
አቁሮ ስሇ ነበረ ያ ስረሳሽ እየተንጠባጠበ ራቁት አካሊታቸውን የነካቸው ሁለ የተነካው አካሊታቸው እሳት
እንዯ ፇጀው መጉረብረብና ማበጥ ጀመረ። ከዚያ ግሪኩ ሀኪም አይተው ያንሇት የተጣሇው «ማስታርዴ
ጋዝ» የተባሇው የመርዝ ጋዝ ስሇ ሆነ ሰውም ከብትም ካጠገቡ እንዱርቅ ካስታወቁ በሁዋሊ ይህ በየሰፇሩ
ተሇፇፇ።

የሀኪሙ ማስታወቂያ ከመሇፊፈ በፉት አይሮፕሊኖች እንዱሄደ የሰዎቼን ዯህንነት ሇማወቅ


ቸኩዬ ተጠግቼ ከቆየሁበት ዛፌ ስር ወጥቼ ወዯ ሰፇሬ እየሮጥሁ ብሄዴ ከገሊው በቀር ሁለንም
ተቀምጠው ስሇ ዯረሰው አዯጋ ሲያወሩ አገኘሁዋቸው።

«ገሊውስ?» አሌሁ፥ እሱን ብቻ ሳጣው ስጋት ተሰምቶኝ።

«አይሮፕሊን ተስብሮ ወዯቀ» እያለ ሰዎች ሉያዩ ሮጠው ሲሄደ አይቶ፥ እሱም እንዯ ሄዯ
አሌተመሇሰም» አሇኝ ከመሀከሊቸው አንደ፤

«ሇምን ሇቀቃችሁት?» ብዬ «ስባሪው ወዯቀ» ወዯ ተባሇበት ቦታ ስሄዴ አቶ ዘውዳ ተከትልኝ


መጣ። እዚያ ስንዯርስ አይናቸውን እየፇጃቸው እያነጠሳቸውና እያሳሊቸው እንዱሁም ዘይታማው ፇሳሽ
በራቁት አካሊታቸው ሊይ የፇሰሰባቸው እያቃጠሊቸው በዬዛፈና በየዯንጋዩ ስር ተቀምጠው የሚጨነቁት
ሰዎች ብዙ ነበሩ። ገሊውን አንዴ ቁዋጥኝ ዯንጋይ ተጠግቶ ተቀምጦ አይኖቹን በሁሇት እጅጅጆቹ ይዞ
ያሇማቁዋረጥ ሲያስሇውና ሲያስነጥሰው ሱሪው ቁምጣ ስሇ ነበረ ከጭኖቹ በታች ዘይታማው ፇሳሽ
የነካቸው እግሮቹ እሳት የሇበሇባቸው መስሇው አገኘነው። አይሮፕሊኖች መርዝ ጥሇው ከሄደ በሁዋሊ
የሰናፌጭ ሽታ በሸሇቆው ውስጥ ሁለ ቢሰማም በተሇይ የመርዙ ጋዝ በወዯቀበት አቅራቢያ ሁለ በጣም
ከብድ ይሰማ ነበር። ስሇዚህ ምንም እንኩዋ የመርዝን ጋር ከስሙ በቀር ሽታውንም ላሊ ጠባዩንም
ባሊውቅ ያንሇት አይሮፕሊኖች የጣለብን ያስከተሇውን ሌዩ ሌዩ ጠንቅ ሳይ የመርዝ ጋር መሆኑን
ጠረጠርሁ። ገሊውን ከጠቀመጠበት አንስተን በቀኝና በግራ ዯግፇን ወዯ ሰፇራችን ስንሄዴ በመንገዴ ሊይ
እንዲሇን የሀኪሙ ማስታወቂያ ሲሇፇፌ ስሇ ሰማን ወዯ ዴንኩዋናችን መሄደን ትተን ወዯ ሀኪሙ
ዴንኩዋን ሄዴን። እዚያ ሀኪም ሇሳለና ሇማስነጠሱ መዴሀኒት ከሰጡት በሁዋሊ አይኑንም እግሮቹንም
በሽንት እንዴናጥበውና በማግስቱ ወዯሳቸው መሌሰን እንዴንወስዯው ነግረውን ሄዯን እንዲለን ንበሽንት
አጠብነው። ማምሻውን ማሳለንም ማስነጠሱንም ባይተወውም ትንሽ ፊታ ሰጠው ያይኖቹና የግሮቹ
ስቃይም ትንሽ መሇስ አሇሇት፣ ነገር ግን እግሮቹ በጣም አብተው ሉቆምባቸው አይችሌም አይኖቹንም
መክፇት አይችሌም ነበር።

47
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያንሇት ማታ ጦሩ ከላለቱ ቀዯም ብል የተከዜን ሸሇቆ እንዱሇቅና እንጋት ሊይ ፊፈን ወጥቶ
ቁጥቁዋጦ ባሇበት ቦታ እንዱዑሰፌር ሲሇፇፌ አመሸ። ነገር ግን ሰፇር ሲሆን፥ ላሉትም ቢሆን
የሚያስፇሌገውን ከያሇበት እየፇሇጉ መፌታቱና ማቅረቡ ሰፇር ሲሇቀቅ ተፇትቶ የተበታተነውን
አጠረቃቅሞ ማሰሩና መቻኑ ካሰቡት የበሇጠ ጊዜ የሚወስዴ ነው። ስሇዚህ እንጋት ሊይ ሁለም የተከዜን
አፊፌ ወጥቶ በየቁጥቁዋጦው ውስጥ ሰፇሩን እንዱይዝ ከታዘዘው ሰራዊት እስከ ርፊዴ ዴረስ ገና
አፊፈን እየወጡ ሲመጡ የሚታዩ በጣም ብዙ ነበሩ። እንዱያውም እስኪመሽ ዴረስ ከሸሇቆው ያሌወጡም
ነበሩ ይባሊሌ።

ራስ ምን ጊዜ የተከዜን ሸሇቆ ሇቀው እንዯ ወጡ ትዝ አይሇኝም እኛ ግን ከላሉቱ አስር ሰዒት


ግዴም ተነስተን ገሊውን በኔ በቅል አስቀምጠን ቀስ ብሇን እያዘገምን ሲነጋጋ አፊፈን ወጣን። ከዚያ
ትንሽ ስንሄዴ እንዯቆየን ሇመንገደ ቀረብ ባሇ ቦታ ቁጥቁዋጦ በስሱ የከበበው ትሌቅ የግራር ዛፌ ስሊየን
ያ ቦታ ሇሰፇር የሚስማማ መሆኑንና ወዱያውም ያሌተያዘ መሆኑን ሇማረጋገጥ አቶ ዘውዳ ሮጦ ሄድ
ሲመሇስ ተስማሚ መሆኑንም አሇመያዙንም ነገረን። ስሇዚህ፥ ወዯዚያ ሂዯን ቶሌ ቶል ጭነታችንን
አራግፇን ጀንበር ሳትወጣ ዴንኩዋኖቻችንን ተክሇን እቃችንን አሰነዲዴተን ጨረስን። እውነትም ያ ቦታ
ከትሌቅ ግራር ላሊ ባጠገቡ ከሩቅ ያሌታዩን ትንንሽ ግራሮችም ያለበት ስሇ ነበረ፤ ምንም እንኩዋ
የሁለንም ቅጠሌ የቦምብ እሳት ቢያቃጥሇው ቅርንጫፊቸው ባንዴነት ችፌግ ያሇ በመሆኑ ስፌራችንን
ከሊይ አይሮፕሊን ያየዋሌ ተብል የሚያሰጋ አሌነበረም።

በጠቅሊሊው ጦሩ የሰፇረበት ዯባጉናን ወዯ ፉት አዴርጎ ጦርነት በተዯረገበት ቦታ ሳይዯርስ


በቁጥቁዋጦዋማው ቦታ ሊይ ነበር። ያ ቦታ ፉታውራሪ ሽፇራው ጦርነት ከመግጠማቸው በፉት
ሰፌረውበት የነበረው መሆኑን ሰዎች ነገሩን። በዚያ ቦታና በዯባጉና ምሽግ መሀከሌ ያሇው አንዴ ሚኤዲ
ብቻ ስሇሆነ፥ እውነትም ፉታውራሪ ሽፇራው እንዲለት «እዚያ ሰፌረው አንዴ ቀን ሳይታዩ ቢውለ
በሁሇተኛው ሳይታዩ እንዯማይቀሩ» የታወቀ ነበር!

እቃችንን በየቦታው አዴርገን አሰነዲዴተን ቁርስ ስናዯርግ ገሊውም ትናንቱን ምሳ ከበሊ በሁዋሊ
ምንም ሳይቀምስ አዴሮ ስሇ ነበረ የማር ተሌባ በወፌራሙ በጥብጠን ሰጥተነው ጠጣ፤ ማስነጠሱንም
ተወው። ሳለ የላለትን ያክሌ ባይሆንም ያስሇው ነበር። ነገር ግን፥ ምንም እንኩዋ አይኖቹንና እግሮቹን
ሀኪሙ መክረውን እንዯ ተመሇስንም ጥዋት ጉዞ ከመጀመራችን በፉትም በሽንት ብናጥበው የማቃጠለን
ስቃይ አስታገሰሇት እንጂ አይኖቹን መግሇጥ አሌቻሇም፤ ይሌቁንም እግሮቹ ይብሱን አብተውና
ተጉረብርበው እንኩዋንስ ሉቆምባቸው ከተዯጋገቡበት ማንቀሳቀሱም በጭንቅ ነበር።

ከቁርስ በሁዋሊ ገሊውን ወዯ ሀኪም ከመውሰዲችን የራስን ሰፇር አይቼ ምናሌባት እኔን
የሚፇሌጉበት ጉዲይ ቢኖርም ታይቼ ቶል እመሇስሇሁ ብዬ ሄዴሁ። እዚያ እንዲሇሁ አይሮፕሊኖች
መጥተው ቦምብ ሲጥለ ቆይተው ሄደ። ያን ጊዜ ከራስ ጋር እመጠሇያቸው ውስጥ ስሇ ነበርሁ

48
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ቁጥራቸው ስንት እንዯ ነበረ አሊየሁም፤ ያዩትን ሰዎችም ቀጥል በሚገሇፀው ምክንያት ሇመጠየቅ ጊዜ
አሌነበረኝም። ከራስ ጋር ቆይቼ ስወጣ ፉታውራሪ ሀይለ እምሩ ወዯ ጎን ሳብ አዴርገው፤

«ከሰፇርህ ሰው ተሌኮ መጥቶ ሰዎችህ እንዴትሄዴሊቸው መፇሇጋቸውን ነግሮን ሄዯ። እስቲ -


የተቸገሩበት ነገር ቢኖር ይሆናሌና ሂዴሊቸው። ብቻ - ቀሊሌ ነገር ሳይሆን አይቀርም አይዞህ
አትዯንግጥ» አለ ወዱያው ቀጥሇው መዯንገጤን ከፉቴ ሲያዩ።

ክፈ ነገር እንዯ ዯረሰ ወዱያው ገባ። ከዚያ በፉት በላሇሁበት ክፈም ሆነ በጎ ቢዯርስ ከሄዴሁበት
ስመሇስ ይነግሩኛሌ እንጂ ሰዎቼ አንዴም ቀን ካሇሁበት ዴረስሌን ብሇው ጠርተውኝ አያውቁም። ስሇዚህ
ከክፈም ክፈ ቢዯርስ ነው እያሌሁ አሳቤን ሇራሴ እየነገርሁ ከራስ ሰፇር የሮጥሁ እሰፇሬ አጠገብ ስዯርስ
ከግራሮቹ ስር ዴንኩዋኖች በነበሩበት ቦታ ያመዴ ክምርና ባመደ ክምር ዙሪያ የሚጤስ ጢስ ብቻ
ይታያሌ! ላሊ ነገር ምንም የሇ። የኔ ሰዎችና በሰፇራችን አቅራቢያ ካለት አንዲንዴ ሰዎች መጥተው
ሁለም አንገታቸውን እየዯፈ ቆመዋሌ። ያን መአት ሳይ ራሴን በከባዴ ነገር የተመታሁ መስል
ተሰማኝና በቆምሁበት እንዲሇሁ ዯንዝዤ ቀረሁ። በዚያ ጊዜ እዚያ የቆሙት ሰዎች ሁለ የሰዎች ጥሊ
እንጂ ሰዎች መስሇው አይታዩኝም ነበር! አቶ ዘውዳ ወዯኔ ሲመጣ፥ የሚንቀሳቀስ የሰው ጥሊ መስል
ነበር የሚታየኝ እጄን ይዞ ሉያነጋግረኝ ሲጀምር ብቻ መሌኩ ጥርት ብል ይታየኝ ጀመር።

«ተው እንጂ ጦርነት ነውኮ ሇዚህ መመጣታችንን ረሳሀው?» አሇ ትሌሌቅ የዯረፇሱ አይኖቹ
እንባ ምሌተው ሳግ እየተናነቀው አሊሇቀስሁ፤ ክርር ብዬ ከመቆም በቀር አንዴ ቃሌ እንኩዋ
አሌተነፇስሁ፤ ፉቴና ጠቅሊሊ ሁኔታዬ ምን መስል ታይቶት እንዱያ እንዲሇ አሊውቅም። ሰዎችን
አጥርቼ ማየት ስጀመር ሁለንም አንገታቸውን እየዯፈ ቆመው አየሁ። ገሊውን ብቻ አይኔ ዙሪያውን
ቢፇሌግ አጣው።

«ገሊው የት አሇ? ሞ - ተ?» አሌሁ አፋ እየፇራ። አቶ ዘውዳ አሌመሰሇኝም፤ አንገቱን ዯፌቶ


ዝም አሇ።

«ሬሳውም የሇ? ተቃጠሇ?» አሌሁ ገሊው ሲቃጠሌ ታየኝና አዴርነው ይመስሌ ሳይታወቀኝ
እጆቼን ዘርግቼ ወዯ አመደ እየሮጥሁ። ያን ጊዜ ሁኔታዬን ሲያዩ የኔ ሰዎችም እዚያ የነበሩት ላልች
ሰዎችም ሁለ ዴምፃቸውን ከፌ አዴርገው እየጮሁ ያሇቅሱ ጀመር። ሲቃጠሌ እናቶ ዘውዳ ከሰውነቱ
ሉያተርፈ የቻለትን ትንሽ ቁርጥራጭ ሰብስበው በትንሽ ጨርቅ አስረው አንዴ ዛፌ ስር አስቀምጠውት
ነበር ፇትቼ ሇማየት አሌቻሌሁም፤ ዴፌረት አነሰኝ።

የዯረሰብንን አዯጋ የሰሙት ወዲጆቻችን ሁለ ከቅርብም ከሩቅም ሰፇር ተሰብስበው ስናሇቅስ


የቆየን በሁዋሊ የኛ እቃ ሁለ ተቃጥል ምንም የተረፇን ነገር ስሊሌነበረ ሰዎቼ ስንቅ የተጋባሊት ትንሽ

49
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሳጥን በግዢ ይሁን በሌመና ፇሌገው አግኝተው ያን በትንሽ ጨርቅ የታሰረ የገሊው የሰውነት ፌርፊሪ
በዚያ ከትተን ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ባሇመገኘቱ እዚያው እሰፇራችን ከትሌቁ ግራር ስር ቀበርበነው።

ገሊውና አንዲንዴ እንዯሱ መተኪያ የላሊቸው አሌተተኩም እንጂ ላሊውን የተቃጠሇ እቃና ስንቅ
ሁለ፥ ራስ፣፤ ብዙ መኩዋንንት ወዲጆቼም የመጡት እያስያዙ መጥተው ያሌመጡት እየሊኩ ያንሇት
እስከ ማታ ዴረስ ተኩሌኝ። እንዱያውም የምንጭንባቸው ከብቶች የማይችለሌን በመሆናቸው
እያመሰገንሁ ባሌመሌሰው ኖሮ ወዲጅ ያመጣሌን ሌዩ ሌዩ ስንቅ፥ ከኛ ተርፍ ሇብዙ በበቃ ነበር።

«እዚያ ግራር ስር ዴንኩዋን የተተከሇ መሆኑን አይሮፕሊን እንዳት አውቆ ሰፇራችንን ቦምብ
መታው?» ብዬ ሁዋሊ ሰዎቹን ብጠይቅ አይሮፕሊኑ እዚያ ግራር ስር ሰፇር መኖሩን አውቆ ሳይሆን
እሸሇቆው ውስጥ አርፌዯው እየወጡ ይመጡ የነበሩ ብዙ ሰዎች አይሮፕሊን ዴንገት ሲመጣ ስሊዩት
መጠሇያ ፌሇጋ እኛ ወዯ ሰፇርንበት ቁጥቁዋጦና ዛፌ ሲሸሹ በነሱ ሊይ አከታትል የጣሇው ቦምብ ከነሱ
አንዲቸውንም ሳይነካ፥ የኛን ሰፇር ያቃጠሇ መሆኑን ነገሩኝ።

ገሊው አስቀዴሞ በመርዝ ጋር አይኖቹ ባይዯፇኑና እግሮቹ ባይስነከለ ኖሮ አይሮፕሊኑ


የመጣበትን አቅጣቻ ሲያይ፥ እንዯ ላልቹ ሸሽቶ ያመሌጥ ነበር እንጂ እዴንኩዋን ውስጥ እንዯ ተኛ
በቦምብ አይቃጠሌም ነበር። ስሇዚህ የገሊው መቃጠሌ ጠንቁ አስቀዴሞ በመርዝ ጋዝ ሇመንቀሳቀስ
እንዯማችይሌ ሆኖ መጎዲቱ ነው እሊሇሁ። ምናሌባት ከቦምቡ ቃጠል ቢተርፌም በመርዝ ጋዝ ክፈኛ
ስሇተጎደ እንዯ ሞቱ ሰዎች፥ ይሞት ኖሮ ይሆናሌ። በመርዝ ጋዝ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር አሊውቅም
እንጂ ብዙ መሞታቸውን ሰምቻሇሁ። ክፈኛ የቆሰለትንና በታምር ካሌሆነ ‹ሉተርፈ ይችሊለ›
የማይበለትን ግን፥ ብዙ ባይኔ አይቻሇሁ። መርዙ በበዛት የፇሰሰባቸው ሰዎች የቆሰሇ አካሊታቸው ሌብስ
እንኳ አሊስነካ ብል ራቁታቸውን ተጋዴመው ጉማሬዎች እንጂ ሰዎች ስሇማይመስለ፤ ከሩቅ ማየቱም
ያሰቅቅ ነበር። እኒያ ሰዎች የጣእራቸውን እዴሜ ከማስረዘም በቀር መቸም እንዱያ ከፇራረሱ በሁዋሊ
የመትረፌ እዴሌ እንዯማይኖራቸው የታወቀ ነው።

በውነት እንዱያ ያሇውን መሳሪያ ምንም ጠሊት ቢሆን በሰው ሊይ ሇማዋሌ የሚጨክን ሰው፥
በሌብ ሰባዊ ስሜት የላሇው፥ አሇት ዴንጋይ የተፇጠረበት መሆን አሇበት፤ እንዱያ ያሇውን መሳሪያ
በሰው ሊይ ማዋሌ ሰባዊ ህሉና ሉሸከመው የማይችሌ እጅሌ ከባዴ መሆኑን አሇም ሁለ ያወቀውና
ያወገዘው በመሆኑ የኢጣሉያ መንግስት በኢትዮጵያ ሊይ ከማዴረጉ በቀር ‹ላሊ መንግስት በላሊ አገር ሊይ
አዯረገ› ሲባሌ ተሰምቶ የሚያውቅ አይመስሇኝም። ታዱያ መንግስታት በጦርነት ጊዜ በመርዝ ጋዝ
እንዲይዋጉ የሚከሊከሇውን፥ እንዯ አውሮፓ አቆጥጣጠር 17 1925 ጀኔቭ ሊይ የተፇረመውን
«ፕሮቶኮሌ» (ስምምነት) ፇርመው ካፀዯቁ መሀከሌ አንደ፤ የጣሉያን መንግስት ነው! የጣሉያን
መንግስት ሰውን እንዯ ክፈ ተባይ በመርዝ መፌጀት የሰው ባህሪ ያሇው ይሌቁንም እንዯ ጣሉያን
በስሌጣኔው የሚኮራ ህዝብ ሉያዯርገው የማይገባ መሆኑን አይክዴም። እስከ ዛሬም ዴረስ የሚክዯው

50
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ማዴረጉን ነው። ግን ምን ይሆናሌ! ሙታንን አስነስቶ የሚያስመሰክር ምዴራዊ ዲኛ የሇ! ቢኖርማ
ገሊውንና እንዯሱ በጣሉያን መርዝ ያሇቁትን ኢትዮጵያውያን ሁለ አስነስቶ ባስመሰከረ ነበር!

ምእራፍ ስምንት

ከደባጉና እስከ እንዳስላሴ


የጏጃም ጦር፥ ከዯብረ ማርቆስ ተነስቶ ትግራይ ውስጥ «ሰሇክሇካ» አጠገብ «እንዲስሊሴ» እስኪዯስ
ከጥቅምት እስከ የካቲት 1928 አምስት ወራት ያክሌ ፇጀበት። ከዚያ ጊዜ ውስጥ ከሁሇት ወራት በሊይ
ያሳሇፇው ሽሬ አውራጃ ውስጥ ከዯባጉና እንዲስሊሴ እስኪዯርስ ነበር። አንዲንዴ ጊዜ በሰፇረባቸው
ቦታዎች እንዱሰነብት የሚያስገዴደት ምክንያቶች ይገጥሙት እንዯ ነበረ ባይካዴም ያን ያክሌ ጊዜ
ይሌቁንም ትግራይ ባንዴ አውራጃ (በሽሬ) ውስጥ፥ ከሁሇት ወራት በሊይ ማሰሇፌ በምንም ምክንያት
ባሌተገባ ነበር። የጉዞው ጊዜ ያን ያክሌ መርዘሙ ጠሊትን የጠቀመውን ያክሌ በኛ ሰራዊት ሊይ ችግር
ማዴረሱ በሰራዊቱ መሀከሌ ሲናገር ይሰማ ነበር።

ሇጠሊት መንገዴ ባሌነበረባቸው ክፌልች መንገዴ እየሰራ ሰራዊቱንም ሇሰራዊቱ የሚያስፇሌገውን


መሳሪያና ስንቅም ሇማጉዋዝ ጠቅሞታሌ። እንዱሁም ትግራይ ውስጥ በቁሌፌ ቦታዎች ምሽጎቹን
አጠንክሮ ሇመስራትና የያዘውን አገር ህዝብ በገንዘብም በስብከትም ሇማባባሌ ያመቸው መሆኑ ግሌፅ
ነበር። ባንፃሩ የኛ ሰራዊት የሻሇቃውና የታሊሊቁ መኩዋንንት ግብረ - በሊዎች እየኆኑ ከዘመቱት በቀር፥
የገዛ ስንቁን እያሰናዲ ባህያ ጭኖ የዘመተው ሰራዊት ሁለ፥ ጉዞው በረዘመ መጠን ከጦሩ ግንባር
ሳይዯርስ ስንቁ እያሇቀ በመሄደ መቸገር ጀምሮ ነበር።

በዴሮው ሌማዴ ዘማች ሰራዊት ዘመቻ ሲሄዴ ስንቁን ቆጥቦ፥ በሚያሌፌባቸው አገሮች ወይም
በሚሰፌርባቸው ቦታዎች ከሚኖረው ባሊገር ቤት ገብቶ በውዴም በግዴም እየበሊ እየጠጣ፥ ተጨማሪ
ስንቅም እየያዘ ስሇሚሄዴ በሚዋጋበት ቦታ ዯርሶ እስኪመሇስ ዴረስ በስንቅ በኩሌ እምብዛም አይቸገር
ነበር። ዘማች በሚያሌፌባቸው አገሮች የሚኖር ባሊገርም ዘማች ሰራዊት ባገሩ የሚያሌፌ መሆኑን ገና
ከሩቅ ሲሰማ ከብቱንና ገንዘቡን እንዱሁም ሉይዘው የሚችሇውን ሁለ እየያዘ ሉይዘው የማይችሇውን
እየሸሸገ ራቅ ወዲሇ ቦታ ሸሽቶ ይቆያሌ። ብቻ ያን ማዴረጉ ከሚያስከትሇው ችግር ይሌቅ በየቤታቸው
ቆይተው ወታዯሩን አብሌቶ አጠጥቶ የሚይጠይቀውን ስንቅ ሰጥቶ መሸኘቱ የሚመርጡ ስሇሚኖሩ
የስንቅ ችግር ከብድ አይከብዴም ነበር።

ራስ እምሩ ግን ዘመናዊውን አስተሳሰብ በመከተሌ ባሇፈባቸው አገሮችና በሰሩባቸው ቦታዎች


ሁለ እባሊገር ቤት ገብቶ የሚዘርፌ ወይም በምንም አይነት የሚያስቸግር ወታዯር ብርቱ ቅጣት
የሚቀጣ መሆኑንና ባሊገርም ሇስንቅ የሚሆን እህሌም ከብትም ገብያ አውጥቶ ሇወታዯር በዋጋ እንዱሸጥ
አዋጅ ያስነግሩ ስሇ ነበረ፥ ወታዯር እባሊገር ቤት ገብቶ ያስቸግራሌ ሲባሌ ወሬ አይሰማም ነበር። ይሁን

51
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንጂ ሰፇር በሚዯረግባቸው ቦታዎች ከሚኖረው ባሊገር አዋጁን በሙለ ሌብ ባሇማመን የሚበዛው ቤቱን
እየዘጋ ከብቱን ነዴቶ ሸሽቶ በመንዯርም ሆነ በገብያ የሚታየው ሰው ጥቂት ነበር። ገብያ የሚወጣው
እህሌና ከብትም በዚያው መጠን ጥቂት ነበር። ያንኑም መግዛት የሚችለት ገንዘብ ያሊቸው እንጂ
የላሊቸው ስሊሌሆኑ ዞሮ ዞሮ የጉዞው መርዘም በተሇይ መጠነኛ ስንቅ እየያዙ በተነሱት ዘማቾች ሊይ
የስንቅ ችግር ማዴረሱ አሌቀረም።

አንዴ ቀን ሽሬ ውስጥ ሰፌረን በሰነበትንበት ቦታ፣ የባሊገር ዘማቾች «ጠሊት ባሇበት ቦታ ዯርሰን
ጦርነቱን ሳንጀምር በመንገዴ ስንቃችን አሌቆ ራብ ሳይገዴሇን አይቀርም» እያለ ሲያማርሩ የሰማሁትን
ሇፉታውራሪ ሀይለ እምሩ ነግሬ ሳያስፇሌግ ባንዲንዴ ቦታ ሰፇር እየተዯረገ ያን ያክሌ የሚሰነበትበን
ምክንያት ጠየቅሁዋቸው።

«ሳያስፇሌግ እንኩዋ አይዯሇም» አለኝ ፉታውራሪ።

«ምንዴነው አስፇሊጊ ያዯረገው?»

«በሰፇርንባቸው ቦታዎች ጥቂት ጥቂት እየቆየን ቀስ ብሇን ብንሄዴ ይሻሊሌ ከተባሇባቸው


ምክንያቶች አንደ እንዱያውም ስንቅ ያሇቀባቸው ወይም ያነሳቸው ዘማቾች ገብያ ሉያገኙ ያሌቻለትን
አገር ሊገር ዞረው ሇመግዛት ጊዜ እንዱያገኙ ታስቦ ነው። ሁሇተኛው አይነተኛው ምክንያት ግን አሁን
ጦርነት ወዯ ምንገጥምበት ቦታ እየተቃረብን በመሄዲችን ከመግጠማችን በፉዑት የተቻሇውን ያክሌ ስሇ
ጠሊት ዴርጅት አሰሊሇፌ መረጃ ሇማግኘት ነው»

«ጠሊት ሰሇክሇካን አጠንክሮ መሽጎ መሰሇፈ ገና ዴሮ ታውቆዋሌ፤ ላሊ ምን መረጃ ነው ማግኘት


የሚያስፇሌገው?»

«መቸም የሰሇክሊካን ተራራ ሁላ መመሸግ አይቻሌ፤ ዞረን ማጥቃትን የምንችሌባቸው ክፌት


ቦታዎች ይኖራለ። እንዱሁም በግንባር መሽጎ ሊሇፇው ወታዯር ጥይትና ስንቅ የሚያቀብሌባቸውን
መንገድችና በጀርባ የመሳሪያም የስንቅም ማከማቻዎች ያለበትን ትክክሇኛ ቦታ ማወቁ፥ እነሱን
ሇማጥፊት ያስችሇናሌ። ያን ማዴረግ ከተቻሇ ዯግሞ ጣሉያኖችን የሚጎዲውን ያክሌ እኛን እንዯሚጠቅም
አይጠረጠርም። ታዱያ እንዱያ እንዱያ ያሇውን መረጃ ካገሩ ሰው በቀር ማንም ሉያውቅ ስሇማይችሌ
የሚያውቁ ሰዎች እየተፇሇጉ በቡዴን በቡዴን ሆነው በያቅጣጫው ተሌከው የነሱ መሌስ እስኪዯርስ
መጠበቁ ነው ጉዞዋችንን የሚጎትተው» አለ ፉታውራሪ።

«በዘመናዊ የጦር ትምህርት ከሰሇጠነውና በዘመናዊው የጦር መሳሪያ ሁለ ከታጠቀው የጣሉያን


ጦር ሰራዊት ጋር ግንባር ሇግንባር ከመግጠም ይሌቅ ከጀርባው መንገድችን እያፇረሱ፥ የመሳሪያና የስንቅ
ማከማቻዎችን እያቃጠለ የዴብቅ ጦርነት መዋጋቱ ኢጣሉያን የበሇጠ እንዯሚጎዲና ኢትዮጵያን የበሇጠ

52
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዯሚጠቅም የውጭ አገር የጦርነት ስሌት አማካሪዎች ሇኢትዮጵያ መንግስት ምክር ሰጥተዋሌ»
እየተባሇ ሲነገር እሰማ ነበር፤ ራስ እምሩ በዚያ ጊዜ ያን ዘዳ በስራ ሇማዋሌ በመሞከር ሊይ
መሆናቸውን ግን ያንሇት ፉታውራሪ ሀይለ መማቴ ነበር።

እውነትም ሁዋሊ የጣሉያን ዋና ጦር መምሪያ ጦርነቱን ይመራበት የነበረውን መንገዴ እንዯ


ተመሇከትሁት - ቀዯም ብል ታስቦበት - የኢትዮጵያ ጦር የጣሉያንን ጦር በግንባር መግጠሙ ሳይቀር
ወዱያው ከዚያ ጋር ተጣምሮ በጦር ግንባሮች አካባቢ ከሚኖሩት ባሊገሮችና ከወታዯሩ ክፌሌ
ተውጣጥተው በቡዴን በቡዴን እየተዯራጁ በጀርባው ተሰማርተው መንገድቹን የሚያፇርሱና የነዲጅ
የመሳሪያና የስንቅ ማከማቻዎችን የሚያቃጥለ ዴርጅቶች ቢኖሩ ኖሮ የጦርነት ጠባይም ሆነ የመጨረሻ
ውጤቱ የተሇየ ይሆን እንዯ ነበረ የሚያምኑ ሰዎች ቢኖሩ ከነሱ አንደ እኔ ነበርሁ። ነገር ግን በዴሜየም
የጭፌራ አሇቃ ባሇመሆኔም ምክንያት ስሇ ጦርነቱ ጉዲይ ምክር ሲዯረግ ተካፊይ ሆኘ ስሊማሊውቅ፥
አሳቤን በግሌ ሊንዲንዴ መኩዋንንት ወዲጆችና አጋጣሚ ሳገኝ ሇራስ ከመግሇፅ በቀር በስብሰባ ሇመግሇፅ
እዴሌ አሌነበረኝም። በዚያ ዘዳ መዋጋት ጣሉያንን የሚጎዲ መሆኑን በጭዋታ ሊይ ከገሇፅሁሊቸው
መኩዋንንት አንደ «ጠሊቱን በዴብቅ የሚያጠቃ ላባ፥ ወይም አጋሚድ ነው እንጂ፥ እንኩዋንስ
የመንግስት ጦር አንዴ ጀግና ጎበዝ ተሸሽቶ ጠሊቱን አያጠቃም» ብሇው ያፋዙብኝ ትዝ ይሇኛሌ።

የጣሉያን ጦር ሰራዊት በሚዋጋበት የጦር ግንባር ይዞት የሚሰሇፇው መሳሪያ ጥይት ነዲጅ
ስንቅና ላሊውም ሇውጊያ አስፇሊጊ የሆነው ነገር ሁለ ሇጥቂት ቀናት ያክሌ ነው እንጂ እንዯ ኢትዮጵያ
ጦር ሰራዊት ጥይቱን ሁለ በወገቡ ዝናር ታጥቆ ስንቁን ባጠገቡ አዴርጎ አይሰሇፌም። በግንባር
የሚዋጋውን የጣሉያን ጦር ሰራዊት በማናቸውም ነገር (በመሳሪያ በነዲጅና በስንቅ) የሚመግበው
ዴርጅቱ (ልጅስቲክስ) አዯጋ እንዲይዯርስበት በግንባር ከሚዋጋው ሰራዊት ርቆ ወዯ ሁዋሊ መሆን
አሇበት። የጣሉያን 4ኛ ጦር ሰራዊት (አርሚ ኮር) «ሰሇክሇካ» ግንባር ሲሰሇፌ ባክስምና ባዴዋ አጠገብ
ከነበረው መጋቢ ዴርጅት ይዞት የሄዯው ሇ3 ቀን የሚሆን የወታዯር ስንቅና ያጋሰስ ገፇራ ሇ2 ቀን
የጠመንጃና የመትረየስ ጥይት ሇ1 ቀን የሚሆን የመዴፌ ጥይት መሆኑን «ማርሻሌ ባድሉዮ» ቀዯም
ብዬ በጠቀስሁት መፅሀፊቸው ይናገራለ። እንዱሁም «የሌኡሌ» ራስ ካሳ «ጦር በከፉሌ መገናኛ ቆርጦ»
የመጀመሪያውን የተንቤን ትሌቅ ጦርነት «ዴሌ ባዯረገ ጊዜ» ማርሻሌ ባድሉዮ እንዱህ ይሊለ፦

«በመጀመሪያው የተንቤን ጦርነት የጠሊት ሀየሌ በማየለ፥ የኛ አዛዥ ሇጊዜው የጦሩን ሜዲ


መሌቀቅ አስፇሊጊ ሆኖ ሲሇቅ ከመቀላ 70.000 ወታዯር 14.000 የጭነት አጋሰስና 300 መዴፌ ወዯ
ሁዋሊ ሇመመሇስ ጥናት ስናዯርግ ከዚያ ጋር እዚያ ተይዞ የነበረውን ከሁሇት እስከ ሶስት ቀን የሚበቃ
ጥይት፥ ሇስዴስት ቀን የሚሆን የወታዯር ስንቅና ያጋሰስ ገፇራ ሇዚያ ያክሌ ቀን የሚሆን የነዲጅና ሌዩ
ሌዩ መሳሪያ ሇማጉዋዝ መንገደ በከፉሌ ዯህና ስሊሌነበረ ተቸግረን ነበረ። ዯግነቱ የራስ ካሳ ጦር እዚያው
በመቆሙ ሁኔታው ቀስ በቀስ እየተረጋጋ ሄድ አስግቶን የነበረው ችግር ሳይዯርስብን ቀረ።»

53
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይህ ማርሻለ ያሇው ስንቅ ጥይት፥ ነዲጅና እነሱን የመሰሇውን ሇጦርነት የሚሆነውን አሊቂና
ሊሇቀ ነገር መተኪያ ሁለ ሇጥቂት ቀናት ከሚያስፇሌገው በቀር የቀረው አይነተኛው በግንባር ከሚዋጋው
ጦር ሰራዊት ተሇይቶ በመጋቢ ዴርጅቶች (በልጅስቲኮች) ውስጥ የሚቆይ መሆኑን ስሇሚያስረዲ መጋቢ
ዴርጅቶች (ልጅስቲኮች) ከተቃጠለ ወይም አቀባባይ መንገድች ከፇረሱ ተዋጊው ሠራዊት ሇውጊያ
የሚያስፇሌገው ነገር ሁለ ይቁዋረጥበትና ጦርነቱን መቀጠሌ አይችሌም ማሇት ነው።

ስሇዚህ የኢትዮጵያ መንግስት በግንባር የሚዋጋ ጦር ሰራዊት እንዲዯራጀ እንዱሁም ከጠሊት


ሁዋሊ በመጋቢ ዴርጅቶችና (ልጅስቲክስ) በመንገድች ሊይ የዴብቅ ጦርነት ሇማዴረግ የሰሇጠኑ ብርቱ
ሀይልች ቢያዯራጅና በሁሇት ግንባር (በፉትና በሁዋሊ) ቢዋጋ ኖሮ ኢጣሉያ ቶል ዴሌ ባትሆን ግንባር
ምናሌባት ጦርነቱ ሁሇተኛው ያሇም ጦርነት እስከ ተጀመረበት ጊዜ ተራዝሞ በኢትዮጵያ ሊይ
ያዘመተችውን የጦር ሰራዊት ወዯ አውሮፓ ሇመመሇስ ትገዯዴና ኢትዮጵያም ሊጭር ጊዜም ጊዜም
ቢሆን የነፃነት ክብርዋን ሳትገፇፌ ትቀር ነበር እሊሇሁ። ይህ መቸም የኔ አስተያየት ነው። ስሇዚህ እዚህ
ሊይ ሊቁመውና አሁን ፉታውራሪ ሀይለ «ከጠሊት ጦር ጀርባ ስሇ ነበሩት መጋቢ ዴርጅቶችና መንገድች
መረጃ ሇማምጣት በያቅጣቸው ተሌከዋሌ» ወዲለዋቸው ሰዎች ሌመሇስ።

ከኒያ «በያቅጣጫው ተሌከዋሌ» ከተባለት የመረጃ ቡዴኖች አንደ የሰሇክሇካን ተራራ መሽጎ
ከተሰሇፇው የጣሉኢያን ጦር ጀርባ በጣም ራቅ ብል በሰፉው በሽቦ የታጠረና በወታዯር በጥብቅ
የሚጠበቅ - ባሌሳሳት - «ራማ» የተባሇ ጦርና የመሀንዱስ መሳሪያ የነዲጅና የስንቅ መጋቢ ማከማቻ
ሇማቃጠሌ ይወስንና አቶ ‹ዮሀንስ አብደ› (ሁዋሊ ሻሇቃ) የሁሇት ግራዝማቾች ጦር አስተባብሮ ሄድ
እንዱያቃጥሇው ይታዘዛሌ። ከሁሇቱ ጋራዝማቾች አንደ ግራዝማች ባያብሌ ዯስታ ያፄ ቴዎዴሮስ የሌጅ
ሌጅ «የዯስታ መሸሻ» ሌጅ ነበሩ። ግራዝማች «ግራዝማች ዯሴ» (ያባታቸውን ስም ረስቻሇሁ) ዲሞት
ውስጥ አንዴ የጭፌራ አሇቃ ነበሩ።

ያባቶ ዮሀንስ የተመራው የሁሇት ግራዝማቾች ጦር ቀን በዋሻ ውስጥ ተሸሽጎ እየዋሇ ላሉት
እየተጉዋዘ ራማ ዯርሶ ሇጥበቃ የተመዯበው የጣሉያን ጦር ሊይ ዴንገት አዯጋ ይጥሌና ከብርቱ ጦርነት
በሁዋሊ ዴሌ አዴርጎ መጋቢ ዴርጅቱን አጥፌቶ ይመሇሳሌ። በዚኢያ ጦርነት ከኢትዮጵያውያን የሞቱና
የቆሰለ ስንት እንዯ ነበሩ ሊውቅ አሌቻሌሁም። እዚያ ከጣሉያን ሹማምንትና ወታዯሮች የሞቱና የቆሰለ
141 (አንዴ መቶ አርባ አንዴ) መሆናቸውን ፅፍዋሌ። ታዱያ ማርሻለ «በዚያ ጦርነት ጣሉያኖች
ኢትዮጵያውያንን ዴሌ አዴርገው አባርረው እንሰኡ ከ2ኛው ጦር ሰራዊት (አርሚ ኮር) ጋር ተጨመሩ»
ይሊሌ። 2ኛው ጦር ሰራዊት «ሰሇክሇካ» መሽገው ከተሰሇፈት የጣሉያን ጦር ሠራዊቶች አንደ ነበር።
ነገር ግን ጣሉያኖች ማሸነፊቸው እውነት አይዯሇም። እውነቱ ጥንቱንም ኢትዮጵያውያን መጋቢ
ዴርጅቱን ሇማጥፊት እንጂ ሇመያዝ ስሊሌሄደ የሄደሇትን ፇፅመው ብዙ ጣሉያኖችን ገዴሇውና አቁስሇው
ጥቂት ጣሉያኖችንም (5 ይሁን 6 ረስቻሇሁ) ማርከው በሄደበት አሆሁዋን ላሉት ላሉት ተጉዘው ወዯ

54
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሰፇራቸው መመሇሳቸው ነው። ማርሻሌ ባድሉዮ እንዯሚሇው ጣሉያኖች «ራማ» ወይም አፌጋጋ ሊይ
ዴሌ ቢያዯርጉ ኖሮ፥ ከነሱ ከሞት የተረፈት ቦታቸውን ትተው ወዯ 2ኛው የጣሉያንጦር ሰራዊት ባሌሸሹ
ነበር። ኢትዮጵያውያንም የማረኩዋቸውን ጣሉያኖች ይዘው ወዯ ሰፇራቸው ባሌተመሇሱ ነበር።

ባቶ ዮሀንስ አስተባባሪነት ራማን ሇማጥፊት የታዘዘው የግራማች ባያብሌና የግራዝማች ዯሴ


ጥምር ጦር ቀንቶት መመሇሱንና ራስ ሰፇር የሚዯርስበትን ጊዜ ገና በመንገዴ ሳሇ አስቀዴሞ አስታውቆ
ስሇ ነበረ ራስ መኩዋንንቱና ሰፇር ከቀረው ሰራዊት ብዙው ወጥተው ተቀበለት። ዴሌ አዴራጊው ጦር
የማረካቸውን ጣሉያኖች እመሀሌ አዴርጎ በሰሌፌ «አዴራጊው ጦር የማረካቸውንጣሉኢያኖች እመሀሌ
አዴርጎ በሰሌፌ «አሞሌማሌጉሚ» እያሇ እያረበረበ በራስና በተቀባዩ ሰራዊት ፉት ሲያሌፌ ጣሉያኖችም
ያሞሌማሌጉሚን ቅኝት በግዴ ተምረው ከማራኪዎቻቸው ጋር ተሰሌፇው ሲያረበርቡ ምንም እንኩዋ
ያይን የተያዙበትን ወጥመዴ ያጠመደት ራሳቸው ቢኢሆኑ ያሳዝኑ ነበር። ከመሀከሊቸው አንደ ክንደን
ሉቆረጥ ትንሽ እስኪቀረው በጎራዳ ተመትቶ ያን ሉቆረጥ ትንሽ የቀረው ክንደን በግዴ አያይዘው
አስረው ወዯ ሊይ ባንገቱ አጥሌቀውሇታሌ። ታዱያ ያን ተሸክሞ እሱም ከማራኪዎቹ ጋር ሲያረበርብ
ማየቱ ከማሳዘን አሌፍ የሚያስቆጣ ስሇ ነበረ ራስ ተቆጥተው ጣሉያኖች ከሰሌፈ እንዱወጡና ቁስሇኛው
ቀዯ ግሪኩ ሀኪም ተወስድ ህክምና እንዱዯረግሇት አዘዙ።

ከዚያ እኒያ የተማረኩ ጣሉያኖች ባዱስ አበባና በዲባት መሀከሌ አሌፍ አሌፍ በሚመሊሇሰው
የኢትዮጵያ አይሮፕሊን ወዲዱስ አበባ እንዱሄደ በማግስቱ ይሁን በሳሌስቱ ወዯ ዲባት ተሊኩ። ሁዋሊ
ከዘመቻው መሌስ አቶ ዮሀንስ አብደና እኔ ዲባት ተሊኩ። ከዘመቻው መሌስ አቶ ዮሀንስ አብደና እኔ
ዲባት ሁሇት ቀናት በቆየንበት ጊዜ ስሇ ጣሉያን ምርኮኞች ብንጠይቅ «አይሮፕሊኑ ካዱስ አበባ እስኪዯርስ
ባንዴ ቤት ውስጥ ሲጠበቁ እንዱቆዩ ተዯርጎ የቁስሇኛው ሽታ ጉዋዯኞቹን በማስቸገሩ ሇብቻው ዴንኩዋን
ተተክልሇት በተቀመጠበት አንዴ ቀን የጣሉያን አይሮፕሊን መጥቶ በዲባት አንዴ ላሊ ነገር ሳይነካ እሱን
ብቻ በቦምብ ገዴል ሄዯ ላልች ወዯ አዱስ አበባ ተሊኩ» አለን።

ምእራፍ ዘጠኝ

የሰለክላካ ጦርነት
ሰሇክሊካ በአክሱምና በእንዲስሊሴ መሀከሌ፥ ከምስራቅ እስከ ምእራብ በበዙ ኪል ሜትር ርዝመት
ተዘርግቶ የሚታይ፥ ትሌቅ ተራራ ነው። ማርሻሌ ባድሉዮ ዯጋግሜ በጠቀስሁት መፅሀፌ እንዯ ገሇፀው
የጣሉያን 2ኛው ሰራዊቶች (አርሚ ኮርስ) ያን ተራራ፥ ከአክሱም ወገን እስከ አናቱ ዴረስ መሽገው
ተሰሌፇውበት ነእብር። 2ኛውና 4ኛው ሰራዊቶች በመሀከሊቸው አምስት ክፌሊተ ጦር (ዱቪዥንስ) እና

55
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አንዴ «ብርጌዴ» ነበራቸው ሇሁሇቱ ሰራዊቶች አስተባባሪ ራሱ መሆኑን ማርሻሌ ባድሉዮ ሲገሌፅ እንዱህ
ይሊሌ። «ሁሇቱን ሰራዊት አስተባብሮ ሇመሥራት እንዱመቸኝ የመምሪያ ቦታየን ከጀርባ ቀረብ እንዱሌ
አዴርጌ ነበር።»

የራስ እምሩ ጦር፥ እየዘገመ ሲጉዋዝ ብዙ ወራት ካሳሇፇ በሁዋሊ የካቲት 19 ወይም 20 1928
(ትክክሇኛው ቀን ረስቻሇሁ) እንዲስሊሴ ዯረሰ። ሰሇክሇካ አናት ሊይ የመሸገው የጣሉያን ጦር፥ ጠሊት ወዯ
ተራራው እንዲይጠጋ ሇመከሊከሌ ቀንና ላሉት ሳያቁዋርጥ መዴፈን ከሩቅ ሲስሙት የሰማይ ነጎዴጉዋዴ
እንጂ እውነት የመዴፌ ተኩስ አይመስሌም ነበረ። የባውዛው መብራትም ላሉቱን ሙለ እንዱሁ
ሳያቁዋርጥ ከሰሇክሇካ ተራራ ወዯ እንዯስሊሴ ወገን ያሇውን አገር ሁለ ከምስራቅ ወዯ ምዔራብ እንዯገና
ወዯ ምስራቅ እየተሽከረከረ እንዲበራ ያዴር ነበር።

የራስ እምሩ ጦር እንዯስሊሴ በዯረሰበት እሇት ማታውን ፉታውራሪ ጦርና የተቆጠሩ ያውራጃ
ገዥዎች የግሌና የየግዛታቸውን እይዯንብ ጦር ይዘው መሽጎ የሚጠብቀውን የጣሉያን ጦር ሇመግጠም
ታዝዘው የሄደት ዴጋፌ እንዱሰጡ ስሇ ታዘዙ፥ እየተከታተለ ይሄደ ጀመር። በመጨረሻ የካቲት 22፥
1928 ማታ ይመስሇኛሌ ራስ ባጠገብ ሆነው ጦርነቱን ሇመምራት ከሳቸው ጋር የቆየውን ጦር ይዘው
ወዯ ግንባር ሄደ። ከመነሳታቸው በፉት ሁለም ጉዋዙንና ጉዋዝ ጠባቂውን እዚያው እንዲስሊሴ ትቶ
ከመሳሪያው ጋር የእሇት ስንቁን ብቻ እየያዘ ወዯ ጦርነቱ ግንባር እንዱሄዴ በየሰፇሩ ስሇ ተሇፇፇ በቅል
ያሇው የሇት ስንቁን በከረጢት አዴርጎ በኮርቻ ዴሀራው እያነገበ እግረኛው የስንቅ ቀረጢቱን ባንገቱ
አግብቶ በብብቱ ስር እያንጠሇጠሇ ዯረቅ ጦር ሆኖ ወዯ ግንባር ገሰገሰ። እኛም አጭሩ ዘሪሁንን ሇጉዋዝ
ጥበቃ እንዯስሊሴ ትተን አቶ ዘውዳና ጤናው እኔና ረዥሙ ዘሪሁን እንዯ ትእዛዙ የሇት ስንቃችንን
ይዘን ተከተሌን።

የራስ መምሪያ፥ ከንዲስሊሴ ወገን አንዴ ትንሽ ወንዝ ከግርጌው አዴርጎ፥ ከሰሇክሇካ ተራራ ጥግ
ነበር። ያ ቦታ ሇዚያ ጦርነት ሲባሌ ካይሮፕሊን ቦምብና ከመዴፌ ጥይት እንዱጠብቅ ቀዯም ብል ታስቦ
በጥናት የተሰራ እንጂ ባጋጣሚ የተገኘ አይመስሌም። እዚያ ስንዯርስ እጦሩ ግንባር የመዴፈ
የመትረየሱና የጠመንጃው ተኩስ አንዴ አፌታ እንኩዋ ጋብ ሳይሌ መዯዲውን ይንጎዯጎዴ ስሇ ነበረ፥ ሰው
ተርፍ የሚያዴር አይመስሌም ነበረ። ነገር ግን፥ ያ ሁለ ተኩስ ጣሉያኖች የኛ ጦር ምሽጋቸውን ሰብሮ
እንዲይገባባቸው የኛ ጦር በበኩለ ጣሉያኖች ከምሽጋቸው ወጥተው የተሰሇፇበትን ቦታ እንዲይዙበት
ሇመከሊከሌ እንጂ ሁሇቱ ወገን ጠሊቶች እስበሳቸው እየተያዩ፥ ወይም አንዲቸው ባንዲቸው ሊይ
እያነጣጠሩ የሚተኯሱት ስሊሌነበረ ከሁሇቱም ወገን ጉዲት ቢኖር ከስንት አንዴ ነበረ። በማግስቱ ግን
የካቲት 23 1928 ከንጋት ጀምሮ የመከሊከለ ተኩስ እያበቃ በሱ ፇንታ የመገዲዯለ ተኩስ ሲተካ
ሁኔታው ተሇውጦ የካቲት 23 ከንጋት ጀምሮ የዋሇው ጦርነት እንዯ ቁዋያ እሳት በፉት የተማገዯውን
ብቻ ሳይሆን አሌፍ ባካባቢው ያሇውንጭምር የሚፇጅ ነበር። ዯግነቱ ጦርነቱ በጣሉያን ምሽግ ሊይና

56
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ባካባቢው ስሇ ነበረ እዚያ፥ ኢትዮጵያውያንን ሇይቶ መምታት አስቸጋሪ በመሆኑ ያይሮፕሊን ቦምብና
የከባዴ መዴፌ ጥይት አሌነበረም። አይሮፕሊኖችና ከባዴ መዴፍች የሚዯበዴቡ ሰፇራችነንና ከሰፇር ወዯ
ጦሩ ግንባር የሚሄደትን ነበር። በምሽጉና ባካባቢው የጦርነቱ ግጥሚያ በጣሌያኖች በኩሌ በቀሊሌ
መዴፌ በከባዴና በቀሊሌ መትረየስ እንዱሁም በጅ ቦምብና በጠመንጃ ሲሆን በኢትዮጵያውያን በኩሌ
በጠመንጃና በጎራዳ ነበር።

ራስ እመምሪያቸው ውስጥ እንዲለ፥ በግንባር ከሚያዋጉት ኢትዮጵያውያን አዛዦች ሌዩ ሌዩ


መሌእክቶች ይዯርሱዋቸው ነበር። ታዱያ እኒያ መሌእክተኞች በተሰሙ ቁጥር እዚያ በነበረው ሰው ሁለ
ጊት አንዲንዴ ጊዜ ፇገግታ አንዲንዴ ጊዜ ቅሬታ ይታይ ነበር። አንደ ጠሊትን ከምሽጉ ወዯ ሁዋሊ
እንዱያፇገፌግ ማዴረጉንና እሱ ምሽጉን መያዙን አስታውቆ ጠሊት ሀይለን አጠንክሮ የተመሇሰ እንዯሆነ
ሇመመከት የሚያስችሇው ጦር እንዱጨመርሇት ይጠይቃሌ። ቆየት ብል ላሊው ጠሊት በሰውና በመሳሪያ
ብዛት ያየሇት በመሆኑ ትንሽ ሇማፇግፇግ ስሇተገዯዯ ተጨማሪ ጦር እንዱሊክሇት ይጠይቃሌ። ዯግሞ
ላሊው በወታዯሩ ሊይ ከባዴ የሞትና የመቁሰሌ ጉዲት ስሇ ዯረሰ ረዲት ጦር እንዱሊክሇት ይጠይቃሌ።
አሁንም ላሊው ከሰዎቹ የሚበዙት ስሊሇቁ ከተረፈት ጋር እንዲይከበብ ቶል ከመከበብ የሚያዴነው ርዲታ
እንዱዯርስሇት ይማጠናሌ። ከዚያ ላሊው ከምሽግ ውጭ በጎን የጠሊት ብርቱ ጦር ዴንገት ስሊሇ፤ ቶል
የሚመሌሰው፥ ወይም ባሇበት የሚያግዯው ከሱ የበረታ ሀይሌ ካሌተሊከሇት እሱ ያሰሇፇውን ጦር
ከመክበብ አሌፍ ዋናውን መምሪያ የሚያሰጋ መሆኑን ያስጠነቅቃሌ። ራስም እንዱያ ሊሇው ሁኔታ
መጠባበቂያ ተቆትቦ ከቆየው ጦር ወዯየተጠቀበት ግንባር በያሇቃው እንዱሄዴ ተቆጥቦ ከቆየው ጦር
ወዯየተጠየቀበት ግንባር በያሇቃው እንዱሄዴ ትእዛዝ ይሰጣለ። እንዱያ ሲሆን ቀኑ ወዯ ቀትር ግዴም
ሆነ። እስከዚያ ዴረስ፥ ሶስቱ ጉዋዯኞችና እኔ የጭፌራ አሇቆችም ያሇእቃ ጭፌሮችም ስሊሌነበረርን ወዯ
ግንባር ከታዘዙት ጋር እንዴንሄዴ ባሇመታዘዛችን እዚያው እራስ መምሪያ ሆነን ከግንባር የመጡት
የሚያወሩትን ስንሰማና ወዯ ግንባር ታዘው የሚሄደትን ስናይ ዋሌን።

ያንሇት፥ ዯጃዝማች አያላው ብሩም ራስ መምሪያ ውስጥ አብረዋቸው ነበሩ። ዯጃዝማች ተከዜ
አፊር የራስን መሌዔክት ሊዯርስሊቸው ሄጄ ካየሁዋቸው በሁዋሊ ከያሇሇት በቀር አይቻቸው አሊውቅም
ነበር። እንዱያውም ከራስ ጋር ተቀምጠው ከግንባር አዛዦች የተሊኩ መሌእክተኞች እየመጡ «ጠሊት
አየሇብን ሰው አሇቀብን ሌንከበብ ነው ከምሽግ ውጭ የሚያየው ብርቱ የጠሊት ጦር ዋናውን ምሽግ
እንዲይከብ ያሰጋሌ።» እያለ መሌእክታቸውን በተናገሩ ቁጥር አሽከሮቻቸውን አንዴ ባንዴ እያስጠሩ
ተከዜ አፊፌ እኔን የተቀበለ እሇት እንዲፇረጉት ያስፇክሩ ነበር።

እዚህ ሊይ እንዲመሇከትሁት ወዯ ቀትር አካባቢ አቶ ዘውዳ ጤናውና እኔ ባንታዘዝም


የመጣንሇት ተግባራችን ስሇሆነ ወዯ ጦርነቱ ግንባር እንዴንሄዴ ተመካክረንና ዘሪሁን ረዥሙ በቅልዋን
ይዞ እዚያው ራአስ መምሪያ እንዱቆዬን ትተነው ከታዘዙት ወታዯሮች ጋር ወዯ ግንባር ሇመሄዴ

57
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከመምሪዑያው ወጣን። የተጉዋዯንናቸው ወታዯሮች በከርት ማሇታቸውን አይተን ተከተሌናቸው እንጂ
በምን ዯንብ ውስጥ እንዯሆኑና ማንኛውን የግንባር አዛዥ ሉረደ እንዯሚሄደ አሊወቅንም ሇመጠየቅም
ጊዜ አሌነበረንም። ከመምሪያው ዋሻ እንዯ ወጣን ባካባቢው ያሇውን ቁጥቁዋጦና ቅጠለ የተቃጠሇ ዛፌ
ብቻ የሚታይበትን ክፌሌ አሌፇን ወዯ ጦርነቱ ቦታ የተቃረንብ ስንሄዴ አንዴ ቦታ ሊይ እሩምታ
የተተኮሰ የከባዴ የቀሊሌ መሳሪያ ጥይት ከሊይ እንዯ ናዲ ወረዯንብ። ያን ጊዜ ሁሊችንም በያሇንበት
ወዯቅን። ያ ቦታ ካካባቢው ሁለ ገሇጥ ያሇ በመሆኑ ሌንቆይ የምንችሌበት አሌነበረም። ፉቱንም እንዴያ
ብዙ ሆነን ተበታትነን መሄዴ ሲገባን እንዯ ሰርገኛ ባንዴነት እጅብ ብሇን ስንሄዴ እዚያ ገሊጣ ቦታ ሊይ
የጠሊት ቃፉር ከሩቅ አይቶን ይሆናሌ መሳሪያውን አስተባብሮ የተኮሰብን። ትንፊሼን አስተጋብቼ
መተንፇስ እንዯቻሌሁ የተሻሇ ቦታ ሇፉቴ አንዴ ትሌቅ ቁዋጥኝ ዴንጋይ ስሊየሁ በጉንብሴ እየሮጥሁ ሄጄ
እሱን ተጠጋሁ። ወዱያው ጉዋዯኞቼ አብረውኝ መሆናቸውን ሇማረጋገጥ በቀኝም በግራም ባይ ጤናው
ብቻ ተከትልኛሌ፤ አቶ ዘውዳ የሇም።

«አቶ ዘውዳስ ተመትቶ ይሆን የቀረ?» አሌሁት ጤናውን በጣም ዯንግጨ።

«ኧረ እንጃ! አንተን ወዯ ፉት ስትሮጥ ሳይህ ጊዜ ተከትዬህ ሮጥሁ እንጂ ወዯሱ ዘወር ብዬ
አሊየሁም። ግን የተመታ አይመስሇኝም እንዱያውም ሰው ያሇ አይመስሇኝም» አሇ ጤናው።

«የተመታ ሰው አሇመኖሩ እንዳት ይታወቃሌ?»

«የቆሰሇ ሰው ቢኖር እዚያው እንዲሇን የስቃይ ዴምፅ እንሰማ ነበር??

«እስቲ ሇማናቸውም ወዴቀንበት ወዯ ነበረው ቦታ ተመሌሰን እንፇሌገው፤ ተመትቶ እዚያው


ካሌቀረ ከላልች ጋር በላሊ አቅጣጫ ወዯ ግንባር ቢሄዴ ነው» አሌሁ።

«እዚህ ቆይ እኔ ዯርሼ ሌምጣ» አሇ ጤናው። ግን ቦታውን ራሴ ካሇየሁት የሌብ ርጋታ የማገኝ


ስሊሌመሰሇኝ ከጤናው ጋር አብሬ ሄጄ ወዴቀንበት የነበረውን ቦታ ብቻ ሳይሆን ባካባቢው ሁለ ፇሌገን
አቶ ዘውዳን አሊገኘነውም፣ ጤናው እንዲሇው ላሊ ቁስሇኛም በቦታው አሌነበረም። ከዚያ በላሊ አቅጣጫ
ሄድ እጦርነቱ ውስጥ መግባቱን አምነን እኛም ወዯዚያው ሄዴን። ጠሊት የሚተኩሰው የሌዩ ሌዩ
መሳሪያ ጥይት በፉት የተሰሇፈትን አሌፍ ከጀርባ ያሇውን ዛፌና ቁጥቁዋጦ ይጨፇጭፌ ስሇ ነበረ
እግንባር ዯርሶ ቦታ መያዙ ቀሊሌ አሌነበረም። ሆኖም እንዯ ምንም ብሇን በግንባር ቦታ ያዝን። ብቻ ያ
ቦታም፤ ከሱ በሁዋሊ ሁሇት ጊዜ ያክሌ ሇውጠን የያዝናቸው ቦታዎችም አንዲንድቹ ከጠሊት ጥይት
ሉተግኑን የማይችለ መስሇው እየታዩን አንዲንዴ ዯግሞ አሊማችንን ሇመምታት የማይመቹ እየሆኑብን
ቢያንስ ከሶስት ጊዜ ያሊነሰ ቦታ ሇውጠናሌ። ግንባሩን ስንሇቅ ወዯ ምእራብ ሰሜን የተሻሇ ቦታ ያየን
ሲመስሇን ተኩሱ ትንሽ ፊታ እስኪሰጥ እንጠብቅና አጎንብሰን እየሮጥን፥ ወይም በሆዲችን እየተሳንን
ከቆየንበት ቦታ ወዲዱሱ እንዛወራሇን። የጦርነቱ ግንባር ከምእራብ ሰሜን እስከ ዯቡብ ምስራቅ ሲሆን

58
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እኛ ወዯ ምእራብ ሰሜን መጠጋቱን የመረጥንበት ምክንያት በተሇይ፥ እኔን ቶሌቶል ውሀ ይጠማኝ
ስሇነበረና ከራስ መምሪያ ግርጌ የተሻገርናት ወንዝ የምትወርዴ ከዚያው ከምእራብ ሰሜን አቅጣጫ
ስሇሆነ ከዚያች ወንዝ ሊሇመራቅ ከዚያው ከምእራብ ሰሜን አቅጣጫ ስሇሆነ፥ ከዚያች ወንዝ ሊሇመራቅ
ነበር። ውሀ ጥሙ ሲጠናብኝ ጤኢናው ኮዲ ይዞ ስሇ ነበረ በሆደ እየተሳበ ሁሇት ጊዜ ወዴ ወንዝ እየሄዯ
የራሱን እዚያው ጠጥቶ ሇኔ ኮዲውን እየሞሊ ሲያመጣሌኝ ቆየ። ነገር ግን ሶስተኛ ሲሄዴ ጣሉያኖች ከሊይ
ቆርጠውብን ይሁን ወይም ውሀው አሌቆ «አፌህን ታረጥብበት እንዯሆን» ብል ጭቃ ይዞሌኝ መጣ።

መቸም ሰው አስቦና አቅድ ከሞት የሚዴንበትን መንገዴ እንጂ ወዯ ሞት የሚወስዯውን መንገዴ


እንዯማይከተሌ የታወቀ ነው። ነገር ግን ይሌቁንም ብዙ ህዝብ ባሇበት ቦታ የቁጣ የሲቃ ወይም
የፌርሀት ስሜት የሚያስነሳ ሁኔታ ተፇጥሮ አእምሮን እንዲያስብና እንዲያመዛዝን ሲሸፌን የሚከተለት
መንገዴ ወዯ ሞት ወይስ ወዯ ዯህንነት የሚወስዴ መሆኑን ሇይቶ ማየት አይቻሌም። ያን ጊዜ እንዯ በግ
መንጋ በስሜት ብቻ ተነዴቶ ፉት የቀዯመውን ተከትል ወዯ ጥፊት ቢሆን እየተንጋጉ መሄዴ ነው። ይህ
እውነት መሆኑን ያንሇት በምእራብ ሰሜን ያየሁት ትርእይት የሚያሳምን ነበር፤ እስከ ዛሬም። ያ
ትርእይት ሇብዙ ጊዜ በህሌሜ ይመጣብኝ ነበር፤ እስከ ዛሬም ስሇ ጦርነቱ ሳስብ ባይነ - ህሉናዬ ፉት
በጉሌህ እየተዯነቁ ከሚታዩኝ ስእልች አንደ እሱ ነው።

ቀዯም ብዬ እየዯጋገምሁ እንዲመሇከትሁት ጣሉያኖች፥ ምቹ ቦታ እየመረጡ አሇፌ አሇፌ


አዴርገው በሰሩዋቸው ምሽጎቹ ሊይና ባካባቢያቸው ነበር ጦርነቱ የሚዯረገው። የኢትዮጵያውያን ምሽጎች
ግን እግዚአብሔር ከፌም ዝቅም አዴርጎ ሰርቶ እዚያ ያስቀመጠሊቸው ዯንጋዮችና አሇፌ አሇፌ አዴርጎ
ያበቀሇሊቸው ቅጠሊቸውን የቦምብ እሳት ያቃጠሊቸው ግንድች እንዱሁም ውሀ ሸርሽሮ ያጎዯጎዲቸው
ጉዴባዎች ብቻ ነበሩ፤ በጥንቃቄ የተሰሩ ምሽጎች አሌነበሩዋቸውም። ታዱያ እኒያ ዯንጋዮች፤ ግንድችና
ጉዴባዎች ጠሊት ከከፌተኛ ምሽጉ በከባዴና በቀሊሌ መሳሪያ ከሚወርዴባቸው ጥይትና የጅ ቦምብ በቂ
መንዴ ሉሆኑ ስሇማይችለ እዚያ እንዲለ የሚገዴለና የሚቆስለ ብዙ ነበሩ። ባንፃሩ። ጠሊት አንዲንዴ
ጊዜ ኢትዮጵያውያን ጉዲት በዝቶባቸው ወዯሁዋሊ ሇማፇግፇግ ሲገዴደ እንዲይመሇሱ ቦታ ሉይዝ
ከመውጣቱ በቀር የሚበዛውን ጊዜ በጥንቃቄ በተሰራ ምሽግ ውስጥ ተጠብቆ ስሇሚዋጋ ያን ያክሌ ጉዲት
አያገኘውም አግኝቶትም እንዯሆን አይታይም። ይህ ኢትዮጵያውያንን ሳያናዴዴና ሳያስቆጣ እንዲሌቀረ
የታወቀ ነው። ጠሊት የሚተኩሰው ጥይት ሳያስቆታ እንዲሌቀረ የታወቀ ነው። ጠሊት የሚተኩሰው
ጥይት ሳያስቆጣ እንዲሌቀረ የታወቀ ነው። ጠሊት የሚተኩስ ጥይት ጠሊትን ሲገዴሌና ሲያቆስሌ
አሇማየታቸው እነሱ የሚተኩሱት ጥይት ካገራቸው ዯንጋይ ጋር ሉዋጋ የዘመቱ ይመስሌ በጠሊት ፇንታ
የምሽግ ዯንጋይ ሲዯበዴብ ማየታቸው ይህ ሁለ የያንዲንዲቸውን ሌብ አስቆጥቶና ሁለንም ተስፊ
አስቆርጦ ተስፊ የቆረጡ ሁለ የሚያዯርጉትን እንዱያዯርጉ የስሜት መገናኛ አስተባብሮ አስነሳቸው።

59
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከሁሇቱም ወገን ተኩስ እንዯ ተፊፊመ ሳሇ፥ ምንም ትእዛዝ ሳይሰማ፥ ፉትም ሁዋሊም ከተሰሇፈት
ኢትዮጵያውያን ብዙዎች አሇቃና ጭፌራ እንዯ ተማከሩ ሁለ ባንዴነት «ሆነ!» ብሇው አውክተው
በመንገዴ ተመትተው የወዯቁት ወዴቀው የቀሩት ኢጣሉያኖች ምሽግ ውስጥ ገብተው የጨበጣ ጦርነት
ገጠሙዋቸው እዚያ ከኢትዮጵያውያን ሽጉጥ ያሇው በሽጉጥ ላሊው በጎራዳና በጩቤ ያ የላሇው
በጠመንጃው አፇሙዝ ጣሉያኖች በሳንጃ በጅ ቦምብና ባሊቸው መሳሪያ ሲጨፇጭፈ ሲተራረደ ከቆዩ
በሁዋሊ፥ ጣሉያኖች ያን የግንባር ምሽጋቸውን ሇቀው ከሁዋሊ ሇማፇግፇጊያ ወዯ ተሰራ ምሽጋቸው ሸሹ።
ብቻ የግንባር ምሽጋቸውን ሇጊዜው ቢሇቁም በሁዋሇኛው ምሽግ ውስጥ የግንባር ምሽጋቸውን ሇጊዜው
ቢሇቁም በሁዋሇኛው ምሽግ ውስጥ ከነበሩት ጋር ሀይሊቸውን አስተባብረው ኢትዮጵያውያንን እንዯ ገና
ወዯ ነበሩበት ባንዲንዴ ቦታም ከዚያ አሳሌፇው ወዯ ሁዋሊ መሇሱዋቸው። እዚያ ምሽግ ውስጥ ስንት
ኢትዮጵያውያንና ስንት ጣሉያኖች እንዯሞቱ ስንት እንዯቆሰለ ጣሉያኖች ቦታውን ይዘው ስሇ ቀሩ
መቸም ያውቃለ እኛ፤ ግን አሊወቅንም። እኔና ጤናው ሇጨበጣው ጦርነት ተካፊዮች ሳይሆኑ አወዯ
ሁዋሊ ከቆዩት መሀከሌ ነበር። ጤናው «ሆ!» ብል የተነሳው ወታዯር ሲቃ ተጋብቶበት ተነስቶ ሩጫ
ጀምሮ ነበር። ነገር ግን ተከትዬ ይዤው ብዙ ከታገሌን በሁዋሊ አሸንፋ አስቀረሁት።

ጤናውና እኔ እቀትር ሊይ ወዯ ግንባር ከሄዴን ጀምሮ ጦርነቱ የይባህር ማእበሌ ይመስሌ


እንዱያው ወዯ ፉት ሲሄዴና ወዯ ሁዋሊ ሲመሇስ ግንባሩ ምንም ያክሌ ሳይሇወጥ በነበረበት እንዲሇ ቀኑ
እየመሸ ሄዯ። ጨሇምሇም ሲሌ ከኛ ወገን ተኩስ እየተቀነሰ ይሄዴ ጀመር። ባቅራቢያችን በየዴንጋዩና
በየግንደ ስር አዴፌጠው ይተኩሱ ከነበሩት ሰዎችም አንዲንድቹ በቦታቸው አይታዩም ነበር። የጣሉያኖች
ተኩስ ግን ምናሌባት የኛው መቀነሱን ጎሌቶ እንዱሰማ አዴርጎት እንዯሆን እንጂ እንዱያውም የጨመረ
ይመስሌ ነበር።

«ወዯ መምሪያው ሄዯን እዚያ ምን እንዯሚዯረግ ብናይ ምን ይመስሌሀሌ? አሁን ስሇጨሇመ


ጣሉያኖች ከምሽጋቸው ወጥተው ወዯ ፉት ሇመግፊት የሚዯፌሩ አይመስሇኝም» አሇኝ ጤናው።

«ዯህና አስበሀሌ እንሂዴ» አሌሁት። ወዯ መምሪያው የመሄዴ አሳብ ስሇ ተነሳ እንዯሆን


አሊወቅም፤ ራብ ተሰማኝ። ከነጋ እህሌ አሌቀመስንም ነበር። ከዚያ የጠሊት ጥይት እንዲያገኝ ቀስ ብሇን
ካንዴ ተገን ወዯ ላሊ እየተሊሇፌን እወንዝዋ ስንገባ አንዯኛ ከየአቅጣጫው እየመጣ ወንዝዋን ተከትል
ወዯ መምሪያው አኩዋያ የሚወርዯው ወታዯር ብዙ ሆኖ አገኘነው። ትንሽ እንዯ ሄዴን አቶ ዘውዳንም
ከኛ ዝቅ ብል ከነበረ ግንባር ከሚመሇሰው ወታዯር ጋር ሲመጣ አገኘነውና ጤናውም እኔም ከዯስታችን
ብዛት የተነሳ እስኪጨንቀው እያቀፌን ሳምነው። ሽሽት የተጀመረ መሆኑን የነገረን አቶ ዘውዳ ነበር።

«አይዯረግም! መች ዴሌ ሆነና ነው የምንሸሸው? ወታዯሩ ግንባሩን ይዞ እየተዋጋ!» አሌሁ


በጣም ዯንግጨ።

60
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ጠሊት በብዙ ግንባር ከማየለም ላሊ በጎን ብርቱ ሀይሌ አውጥቶ ዋናውን መምሪያ ሇመክበብ
በማስጋቱ ነው ወዯ ሁዋሊ ማፇግፇግ ግዳታ የሆነው ይባሊሌ። ስሇዚህ ጠሊት መሸሻችንን አውቆ
እንዲይከተሌ አንዲንዴ የጭፌራ አሇቆች ሰዎቻቸውን ይዘው እስከ እኩሇ ላሉት ግንባር ሳይሇቁ ሲተኩሱ
እንዯቆዩ ተዯርጎ የቀረው ጦር ቀስ እያሇ እንዱመሇስ በመነገሩ ገና በጊዜ ነው ሰው መመሇስ የጀመረ፥
እኛ ከፉተኞችም ከመጨረሻዎችም አዯሇንም፤ ከመሀከሇኞች ነን» አሇ አቶ ዘውዳ።

«እኛ በነበርንበት ግንባር አሁን ያሌኸው ትእዛዝ መነገሩን አሌሰማንም ወታዯሩም ግንባሩን
ሳይሇቅ በመዋጋት ሊይ እንዲሇ ነው ትተነው የመጣን፤ ታዱያ እንዳት ነው ባንዲንዴ ግንባር ሇሚዋጋው
ወታዯር እንዱመሇስ ሲነገረው በላሊው ግንባር ሊሇው የማይነገረው?» አሌሁ ግራ ገብቶኝ።

«እንጃ፤ ምናሌባት የናንተ ግንባር ወታዯሮች እስከ እኩሇ ላሉት ሲተኩሱ ቆይተው ሁዋሊ
እንዱከተለ ከተመዯቡት ክፌልች ሉሆኑ ወይም ተረስቶ ትእዛዝ ሳይዯርሳቸው ቀርቶ ሉሆን ይችሊሌ»
አሇ አቶ ዘውዳ።

«ወዱያውምኮ እኛ ከሄዴን ጀምረን ግንባራችንን ይዘን ስንተኩስ ዋሌን እንጂ ከሰዎች ጋር


ተቀራርበን ሇመነጋገር ጊዜ ስሊሌነበረን የዯረሰ ትእዛዝ ቢኖርም ካሌተሇፇፇ ሌናውቅ አንችሌም» አሇ
ጤናው።

የራስ መምሪያ ወዯ ነበረው ዋሻ ስንዯርስ እዚያ ማንም አሌነበረም እውነትም ሽሽት ሆኖዋሌ!
ትናንት ላሉቱን ሙለና ያንሇት እስከ ስዴስት ሰአት ግዴም ጢስ እንዲጤስበት የቀፍ ንብ ያን ዋሽሻና
አካባቢውን ሞሌቶ ሲዋነብ ሲተራመስ ከነበረው ሰራዊት ሁለ ያን ጊዜ አንዴ አሌነበረም። ሁለም
ሲተራመስ ከነበረው ሰራዊት ሁለ ያን ጊዜ አንዴ አሌነበረም። ሁለም ሸሽተዋሌ። ከዚያ ዝም ብዬ ወዯ
ዋሻው በራፌ ስሄዴ አቶ ዘውዳና ጤናው ተከተለኝ። ሇምን እንዯ ሄዴሁ አሊውቅም። ብቻ እዚያ በራፌ
ቆሜ ወዯ ውስት ሳይ ማስፇራራቱ! የዋሻው ውስጥ በላሉቱ ጨሇማ ሊይ የሲኦሌን ግርማ እንዯ ዯረበ
ሁለ በጣም ያስፇራ ነበር።

«አሁን እዚህ ዋሻ ውስጥ ምን የሚኖር መስልህ ነው ሌታይ የመጣህ? እባክህ ና እንሂዴ»


አሇኝ አቶ ዘውዳ እጄን ይዞ። ከዚያ ስንመሇስ ከዋሻው በራፌ ትንሽ ፇንጠር ብል አንዴ ትሌቅ ዯንጋይ
አየሁና ወዯሱ ኄጄ እስሩ ስቀመጥ አቶ ዘውዳ እፉቴ ቆሞ ሇተናገረው መሌስ ስሊሌሰጠሁት እሱም
ጤናውም ዝም ብሇው ባጠገቤ ተቀመጡ። ያቶ ዘውዳ ዴምፅ እንጂ የተናገረው ምን እንዯ ሆነ
አሌተሰማኝም ነበር። ያን ጊዜ የማዯምጠው አሳቤ መሌስ ሳያገኝ እያከታተሇ የሚጠይቀውን ጥያቄ ነበር።
«እንግዱህ ዴሌ ሆነ ማሇት ነው? ዴሌ መሆን እንዱህ ነው? በዯባጉናና በራማ ጠሊትን ዴሌ መትቶ
መሳሪያውን ገንዘቡን ሰውንም የማረከ የኛ ጦር ነበር። እኔ ባየሁት መጠን እስከ ዛሬም ዴረስ ቀኙ የኛ
ነበር። እስከ ዛሬ ዴረስ አሸናፉው የኛ ጦር ነበር። ዛሬም ቢሆን የላሊውን ግንባር አሊውቅም እንጂ፥ በኛ

61
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ግንባር የተሰሇፇው ወታዯር ከተሰሇፇበት ግንባር ስንዝር ሳይሇቅ በመዋጋት ሊይ እንዲሇ ነው። ታዱያ
ዴሌ መሆን እንዱህ ነው? የጠሊት ጦር ዋናውን መምሪያ ሇመክበብ ስሊሰጋ ወዯ ሁዋሊ መሸሽ ግዳታ
ሆነ የተባሇውስ ሇመክበብ ያሰጋው የጠሊት ጦር የት አሇ? ጠሊት ያሰራቸው የውሸት ወሬ ታምኖ
የጠሊት የወሬ ጦርነት አስፇርቶ ይሆን ሽሽት የሆነ? እና ኢጣሉያን በመሳሪያ ብዛት ባይሆንሇት በወሬ
ጦርነት ዴሌ አዴርጋ ኢትዮጵያን ሌትይዝ ነው? እና እንግዱህ የኢትዮጵያ የነፃነት ታሪክ መጨረሻ
ሉሆን ነው?» እንዱህ እንዱህ ያሇውን ጥያቄ ዝም ብዬ ብዝነ ህሉናየ ሳዲምጥ ቆየሁና «እንዳት!»
አሌሁ ሳይታወቀኝ ዴምፄን አሰምቼ

«ምኑ ነው እንዳት?» አሇኝ አቶ ዘውዳ።

«ጦርነቱ አሌቀ ማሇት ነው? ዛሬ የጦርነቱ መጨረሻ ሆነ ማሇት ነው?» አሌሁ።

«አ - ይ የጦርነቱ መጨረሻ አዯሇም። ጠሊትን ሇመቁዋቁዋም የሚያስችሌ የተሻሇ ቦታ ይዞ


ሇመዋጋት ወዯ ሁዋሊ ማፇግፇግ ነው ሲባሌ እንጂ የመጨረሻ ሽሽት ነው ሲባሌ አሌሰማሁም» አሇ አቶ
ዘውዳ። ታዱያ እኔን ሇማፅናናት የተናገረው ነገር እንጂ እውነቱ አሌነበረም ያ እሇት የጦርነቱ መጨረሻ
ነበር።

የሰሇክሇካ ጦርነት በሶስት ቀን ብቻ ያሇቀ ይመስሇኛሌ። ማርሻሌ ባድሉዮ ግን በፇርንጆች


አቆጣጠር የካቲት 29 ተጀምሮ መጋቢት 3 1935 ማሇት ባራት ቀን ማሇቁን ፅፍዋሌ። ከዚያ ጦርነት
ከሁሇቱ ወገኖች የሞቱትና የቆሰለት ስንት እንዯሆኑ በኛ በኩሌ አይታወቅም። ማርሻሌ ባድሉዮ
«የሞቱትና የቆሰለት ከኢትዮጵያ ወገን 4.000 ከኢጣሉያ ወገን 63 መኮንኖችና 906 ወታዯሮች ዴምር
969 ነበሩ» ይሊሌ። መቸም ጣሉያኖች በምሽግ ውስጥ ሆነው ከመዋጋታቸው ላሊ የመሳሪያ ብሌጫቸው
- ባይነትም ሆነ በብዛት - ኢትዮጵያውያን ከነበራቸው ጋር የማይቀራረብ እጅግ የሊቀ ስሇ ነበረ
በኢትዮጵያውያን ሊይ የዯረሰው ጉዲት የሚበሌጥ መሆኑን አይቻሌም። ይሁን እንጂ በጣሉያኖች ሊይ ስሇ
ዯረሰው ጉዲት ማርሻለ የሰጠው ቁጥር ትክክሇኛ መሆኑ ያጠራጥራሌ፤ ያሳነሰው ይመስሊሌ።

ምእራፍ አስር

ሽሽት
«እንሂዴ እንጂ፥ እስከ መቼ እዚህ እንቀመጣሇን?» አሇ አቶ ዘውዳ።

«ወዳት?» አሌሁት።

«ሰው ሁለ ወዯሚሄዴበት።»

«ሰፇራችን ዯርሰን ዘሪሁን ምን እንዯ ሆነ ሳናውቅ?»

62
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ረዥሙ ዘሪሁንም በቅልውን ይዞ ወዳት እንዯ ሄዯ አሊወቅንምኮ። የሚሸሸውን ሰው ተከትል
አሌሄዯ እንዯሆነ ምናሌባት፥ ወዯ ሰፇር ሄድ ይሆናሌ። ስሇዚህ ሇማናቸውም ሰፇር መዴረሱ
የሚያስፇሌግ ይመስሇኛሌ» አሇ ጤናውም።

ከዚያ ተነስተን ወዯ እንዲስሊሴ ስንሄዴ ከኛ በቀር ወዯዚያ የሚሄዴ ሰው አሊየንም፤ ሁለም ሊዩን
ወዯ ዯቡብ - ምስራቅ የሚወስዯውን መንገዴ ይዞ ነበር የሚጎርፌ። የንዲስሊሴን መንገዴ እንዲጋመስን
ከሰፇራችን የሚመጡ ወታዯሮች አግኝተን ብንጠይቃቸው ሰፇሩ በሙለ መቃጠለንና እዚያም አንዴ
ሰው አሇመኖሩን ሁለም መሸሹን ነገሩን። ቢሆንም እሰፇር ዯርሰን የተባሇው እውነት መሆኑ
እንዴናረጋግጥ ተስማማንና ሄዴን። እውነትም ሰፇር በነእብረበት ቦታና ባካባቢው የዴንኩዋንም፤
የሰውም ምሌክት አሌነበር ባድ ነበር። «ሰፇሩ በሙለ በቦምብ ተቃጥልዋሌ» የተባሇው ግን ወታዯሮች
አጋንነው ያወሩሌንን ያክሌ ሆኖ አሊገኘነውም። ምንም እንኩን ጊዜው ማታ ቢሆንና እኛም ሰፇሩን ሁለ
ዞሮ ሇማየት ጊዜም ፌሊጎትም ባይኖረን ያው በጨረቃ ብርሃን ማየት የቻሌነውን ክፌሌ ያክሌ ብዙ
የቃጠል ምሌክት አይታይበትም፤ መጠነኛ ነበር። ቢሆንም የኛ ዴንኩዋኖች ተተክሇውበት ወዯ ነበረው
ቦታ ስንዯርስ እስክናይ ዴረስ ዯባጉና የዯረሰብን ጉዲት ገና ባሳባችን ውስጥ እንዲሇ ስሇ ነበረ እየፇራን
ነበር የሄዴን። ግን እዚያም የቃጠል ምሌክት አሌነበረም፤ ዴንኩዋኖች ተነቅሇው እቃው ሁለ
ተጠቅሌል ተነስቶዋሌ። ስሇዚህ አጭሩ ዘሪሁን ጉዋዙን ይዞ ሰው ሁለ የሄዯበት መንገዴ ተከትል የሄዯ
መሆኑን አምነን እኛም ወዯዚያው ተመሇስን።

ሰው በሚሸሽበት መንገዴ ስንዯርስ ከግንባር እየተመሇሰ ያን መንገዴ ይዞ የሚሄዯው በጣም ብዙ


ነበር። አቶ ዘውዳ እንዯ ነገረን እስከ እኩሇ ላሉት ዴረስ ግንባሩን ሳይሇቁ ሲተኩሱ እንዱቆዩ የታዘዙ
ካለ እንዱያውም ከግንባር የሚመሇሰው ገና እስከ እኩሇ - ላሉትና ከዚያም በሁዋሊ ይቀጥሊሌ ማሇት
ነው።

ሇካስ ሽሽቱ የተጀመረ ገና በቀን ኖሮ አይሮፕሊን እየተከታተሇ በቦምብ ሲዯበዯብ ከሞተው ላሊ


ከመንገደ ቀኝና ግራ በየዛፈም በየቁዋጥኙም ስር ወዴቆ «እግዚኦ» የሚሇውን የሚማጠነውን ቁስሇኛ
መገመት ያስቸግራሌ፤ እጅግ ብዙ ነበር። አንደ «እባካችሁ አይኔ እያየ አውሬ አይብሊኝ፤ አንስታችሁ
ሰፇር አዴርሱኝ» ይሊሌ። አንደ «እባካችሁ ከወዯቅሁበት ቀና አዴርጋችሁ ዛፈን ወይም ዯንጋዩን
አስዯግፈኝ» ይሊሌ። ላሊው ‹ስሇ በሊኤ - ሰብ እምበኤት በጠብታ ውሀ አፋን አርጥቡሌኝ» ይሊሌ። ዯግሞ
ላሊው «በወንዴ ሌጅ አምሊክ አንዴ ጥይት አትንፇጉኝ፤ ገዴሊችሁኝ ሂደ» ይሊሌ። እኒህን ሇምሳላ ያክሌ
ጠቀስሁዋቸው እንጂ የሌመናው አይነት ብዙ ነበር። ታዱያ ምንም እንኩዋ ያን ከመንገደ ቀኝና ግራም
ከየዛፈና ከየቁዋጥኙ ስርም የሚሰማውን የተሇያየ ሌመና ያን የስቃይና የጣር ሌመና ሇመጀመሪያ ጊዜ
ሲሰሙት ሌብን በጣም የሚያስጨንቅና የሚያሰቅቅ ቢሆን እንዱያ ማስጨነቁም ሆነ ማሰቀቁ ሇጊዜው
ብቻ ጆሮ እስኪሇምዯው ብቻ ነው! እግዚኦታውና ምጥነታው እየተዯጋገመ ከዚያም እየበዛ በሄዯ መጠን

63
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጆሮ ይሇምዯውና ዴምፁን እንጂ፥ ቃለን እስከ መስማቱም ይተወዋሌ! ስሇዚህ ከዚያ መንገደን ሞሌቶ
ተርፍ በቀኝና በግራ ቁጥቁዋጦውን እየጣሰ ይሄዴ ከነበረው ሰራዊት መሀከሌ ከያቅጣጫው የተሇያየ
ርዲታ የሚሇምኑትን ቁስሇኞች መርዲቱ ቀርቶ ሇመጠየቅ እንኩዋ መሇስ ወይም ጎንበስ የሚለ ቢኢንሩ
ከስንት አንዴ ነበሩ፤ እነሱም የቅርብ ዘመዴ ወይም ወዲጅ ጠፌቶባቸው የሚፇሌጉ ሳይሆኑ አይቀሩ!
የቀረው የሚበዛው መንገደን ሞሌቶ እስበሱ እየተገፊፊ ከመንገደ ቀኝና ግራ ቁጥቁዋጦውን እየጣሰ ዝም
ብል ወዯ ፉት መሄዴ ብቻ ነው። በፉቱ ምን እንዯሚቆየው ያውቅ ይመስሌ አይሮፕሊን በፉቱ
እንዯማይቆየው እርግጠኛ የሆነ ይመስሌ ካይሮፕሊን ሇመሸሽ እስበሱ እየተገፊፊ ዝም ብል እውር
ዴንበሩን ወዯ ፉት መሄዴ ብቻ ነው!

መቸም አንዴ ሰራዊት ዴሌ ሆኖ እምሸሽ ሲጀመር እያንዲንደ ሰው ነፌሱን ሇማዲን ብቻ


በዯመነፌስ እየተነዲ ተያይዞ እንዯ በግ መንጋ መንጋጋት ነው እንጂ በዚያ ጊዜ «ሊዯርገው የሚገባኝን
አሊዯረግሁም» ብል የህሉና ወቀሳ ወይም «የምን ይለኝ» ስሜት የሚሰማው አሇመኖሩ የታወቀ ነው።
ሇመሆኑ ህሉናው ወቅሶት ሇመርዲት የሚፇሌግ ቢኖርስ ስንቱን ሉረዲ ይችሊሌ? ወይስ ማነኛውን ረዴቶ
ማነኛውን ይተዋሌ? መፌረደ የሚያስቸግር ነው። እንዱያ ባሇ ጊዜ እንዱያ ያሇ ሁኔታ ሲፇጠር የላልች
ጦር ሰራዊቶች ሇውጊያው ተካፊዮች የማይሆኑና ዴሌ አዴርጊው ጦር ጉዲት እንዲያዯርስባቸው ባሇም -
አቀፌ ህግ እየተጠበቁ ቁስሇኞችን የሚረደ እንዯ «ቀይ መስቀሌ» ያለ ዴርጅቶች ይኖሩዋቸዋሌ። የኛ
ጦር ሰራዊት ግን እንዱያ ያለ ዴርጅቶች ስሊሌነበሩት ቁስሇኞቻችን የማዲን ወይም የመግዯሌ ርዲታ
ሇማግኘት የሚጠብቁት ከጠሊቶቻቸው ነበር! ስሇዚህ ጠሊቶቻቸው የሚያዯርጉዋቸውን እንዱያዯርጉዋቸው
በየወዯቁበት እንዲለ ሲጮሁ እየሰማን ትተናቸው እንሄዴ ነበር!

ከመንገዴ ቀኛን ግራ ወዴቀን ከሚጮሁት ቁስሇኞች መሀከሌ ያንዲንድቹ ዴምፅ ሌክ ያጭሩ


ዘሪሁንን ይመስሌ ነበር። ዘሪሁን ከትምህርት ቤት ከወጣሁበት ቀን ጀምሮ ያሌተሇየኝ አብሮኝ የኖረ ስሇ
ነበረ መሌኩን ሳሊይ ከሩቅ በዴምፅ የማውቀው ነበር። ታዱያ ያን ላሉት «እባካችሁ ርደን» እያለ
ከሚጮሁት መሀከሌ የሱን ዴምጽ የሰማሁት ሲመስሇኝ ቆም ብዬ፤ «በዚያ በኩሌ ‹ሊውሬ ትታችሁኝ
አትሂደ የሚሇው ዘሪሁን ነው» እሊሇሁ። ከዚያ እኔ ቀዴሜ አቶ ዘውዳና ጤናው ተከትሇውኝ ዴምፅ
ወዯ ሰማሁበት እንሮጥና ቁስሇኛው ዘሪሁን አሇመሆኑን ስናይ አንስተን ሌንወስዯው አሇመቻሊችንን
ነገርነው፤ ከወዯቀበት ቀና ወይም ጋዯም እንዴናዯርገው ፇሌጎ እንዯ ሆነ ጋዯም አዴርገን ወይም ቀና
አዴርገን አንዴ ዴንጋይ ወይም ዛፌ አስዯግፇን እዚያው ትተነው እንሄዲሇን። አሁንም ትንሽ እንዯ ሄዴን
የዘሪሁንን የመሰሇ ዴምፅ ስሰማ ቆም እሌና «ያ ‹ውሀ› እያሇ የሚጮኸው ላሊ ሉሆን አይችሌም ዘሪሁን
ነው» እሊሇሁ። ወዱያው ‹ውሀ› ወዯ ሚሇው ቁስሇኛ ሮጠን እንሂዴና፤ በግንባሩ ተዯፌቶ እንዯሆነ
ግሇበጥ አዴርገን አይተነው ዘሪሁን አሇመሆኑን ስናውቅ በጀርባው አስተኝተን ትተነው እንሄዲሇን! ዯግሞ
ስንሄዴ ቆይተን የዘሪሁንን ዴምፅ የሰማሁ ሲመስሇኝ «በዚያ በኩሌ ‹ገዴሊችሁኝ ሂደ› እያሇ
የሚማጠነው ያሇ ጥርጥር ዘሪሁን ነው» እሊሇሁ። አሁንም ሶስታችን እየሮጥን ሄዯን ቁስሇኛው

64
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በጀርባው ወዴቆ በዯም እየዋኘ ሲሰቃይ ጎንበስ ብሇን በጨረቃ ብርሃን በሊብ የጠሇቀ ፉቱን አይተን
ዘሪሁን አሇመሆኑ ስናረጋግጥ ከፇራችንን እየመጠጥን ብቻ ትተነው እንሄዲሇን! እንዱያ የዘሪሁንን
ዴምፅ የሰማሁ በመሰሇኝ ቁጥር ከሁሇቱ ጉዋዯኞቼ ጋር መንገዲችንን እያሳበርን ያን ዴምፅ ወዯ
ሰማሁበት ቦታ እየሮጥን እየሄዴን ቁስሇኞችን ስናገሊብጥ ስናቃናና፤ ስናስተኛ ዘሪሁንን ሳናገኘው ላሉቱ
ነጋ! ያን ላሉት ሁሇቱ ጉዋዯኞቼና እኔ ዘሪሁንን ፌሇጋ ወዴቀው እንዯሆነ ቀና ዴርገን ዯንጋይ ወይም
ዛፌ አስዯግፇን አስቀምጠን የተውናቸው ዯንጋይ ወይም፥ ዛፌ ተዯግፇን ተቀምጠን እንዯሆነ ዝቅ
አዴርገን አስተኝተን የተውናቸው ካንዴ ጎናቸው ወዯ ላሊው መገሊበጥ ፇሌገው እንዯሆነ አገሊብጠን
የተውናቸው ቁስሇኞች ስንት እንዯሆነ እግዜር ይወቅ እንጂ እኔ እንኩዋንስ አሁን ያን ጊዜ ባፌሊውም
ሊውቅ አሌችሌ ነበር!

የበጋ ንጋት ከሰአቱ ብርሃን ስሇሚቀዴም ሰአቱ ገና ሳሇ፥ ብርሃኑ ቀዯም ብል አገሩን በሙለ ቀን
አዯረገው። ወዱያው ያይሮፕሊን መሌክ ሳናይና ዴምፅ ሳንሰማ ከሁዋሊችን በሩቁ፥ ቦምብ እየተከታተሇ
ሲፇነዲ ተሰማን። መጀመሪያ እንዱያ ሲንጎዯጎዴ ከሩቅ የሰማነው የመዴፌ እሩምታ ተኩስ መስልን
ነበር። ነገር ግን ካጭር ጊዜ በሁዋሊ አይሮፕሊኖች በሁሇትም በሶስትም ቡዴን ሆነው መንገደን ሞሌቶ
እየተተራመሰ በሚሸሸው ሰራዊታችን ሊይ ከባዴ ቦምባቸውን እያወረደበት ሲመጡ ታዩ። ያንሇትና
በተከተለት ቀናት ይጥለዋቸው የነበሩት ቦምቦች ባሇ ስንት ኪል ግራሞች መሆናቸውን አሊውቅም
እንጂ፤ ከዚያ በፉት ይጥለዋቸው ከነበሩት በጣም ከፌተኞች ነበሩ። አንደ ቦምብ ተጥል በፇነዲ ጊዜ
መሬቱን በሊዩ እስከ በቀሇው ዛፌና ቁጥቁዋጦ ጎርድ ብዙ ሜትር ወዯ ሰማይ ሲያጉነው፤ እስሩ ተቆፌሮ
የሚቀረው ጉዴጉዋዴ ጎርድ ብዙ ሜትር ወዯ ስማይ መጠነኛ የቤት ክፌሌ ባይበሌጥ የማያንስ በጣም
ሰፉ ነበር። ጥሌቀቱም በዚያው መጠን ነበር። ታዱያ እኒያ አይሮፕሊኖች ሰራዊታችንን ከዯጀኑ እስከ
ፉታውራሪው ጦር ዴረስ እንዱያ በቡዴን በቡዴን ሆነው እየተከታተለ በቦምብ ሲዯበዴቡ ተስፊ መቁረጡ
አፌዝዞን እንዯሆነ አሊውቅም፤ ከመሀከሊችን ወዯነሱ የሚተኩስ አሌነበረም። የሚበዛው ሰው እንኩዋንስ
መተኮሱን አይሮፕሊኖች አሌፇው እስኪሄደ ዴረስ እንዯ ፉቱ ተበታትኖ በየዛፈና በየቁዋጥኙ ስር
ተተግኖ መቆየቱን ረስቶ ከሊዩ ቦምብ እየወረዯ ዝም ብል ወዯ ፉት ብቻ ይሄዴ ነበር። ዯግነቱ፥
አይሮፕሊኖች ቦምብ የሚጥለ ከፌ ካሇ ርቀት በባድው ቦታ ሊይ ነበር የሚወዴቅ። ስሇዚህ ምንም እንኩዋ
ራሱን መርሳትና ይወርዴ ከነበረው የቦምብ ብዛት አንፃር ሲመሇከቱት «በሰውም ሆነ በከብት ሊይ
የዯረሰው ጉዲት ሉዯርስ ይችሌ ከነበረው ያነሰ ነበር» ማሇት ይቻሊሌ።

ያንሇትና ከዚያ በፉት በነበረው ላሉት፥ ከዚህ በሊይ ባጭሩ እንዯ ተረክሁት መንገዴ ይታይ
የነበረውን የመከራና የስቃይ ትርኢት ሳስታውስ ከሁለም ጎሌቶ ባይነ ህሉናየ ፉት የሚታየኝ ባንዴ ሴት
ሊይ ሲዯርስ ያየሁት ነው። አንዴ ያይሮፕሊን ቡዴን ዯብዴቦን ካሇፇ በሁዋሊ ዛፌና ቁዋጥኝ ወይም ላሊ
ተገን ወዲሇበት መሸሹን ያሌረሳን ሰዎች ከየተሸሸግንበት ወጥተን ስንሄዴ እንዯቆየን አይሮፕሊኖች
ከሁዋሊችን እንዯ ገና ቦምብ እየጣለ ሲመጡ ሰማን። ያንጊዜ የዯረስንበት ቦታ የዘንባባ ዛፍችና ላልች

65
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ዛፍች አሇፌ አሇፌ ብሇው የበቀለበት ስሇ ነበረ ወዲለበት እየሸሸን ተጠጋን። በበቅል ተቀምጣ ጥቂጣችን
ዛፍች ወዲለበት እየሸሸን ተጠጋን። በበቅል ተቀምጣ ከሰራዊቱ ጋር የምትሄዴ አንዴ ሴት ነበረች። ይች
ሴት ባሇማህዯር ዲዊት ባንገትዋ አግብታ ካንዴ ብብትዋ ስር አንጠሌጥሊ አንዴ አጭር ዱሞትፇር
ጠመንጃ እንዱሁ ባንገትዋ ስር አንጠሌጥሊ አንዴ አጭር ዱሞትፇር ጠመንጃ እንዱሁ ባንገትዋ አግብታ
በጀርባዋ አዝሊ ባንዴ እጅዋ የተቀመጠችበትን በቅል ዛብ በላሊ እጅዋ የተጫነች አጋሰስ በረዥም ሇኮ ይዛ
ከሁዋሊዋ እየሳበች ትሄዴ ነበረ። በክፈ አጋጣሚ አይሮፕሊኖች እዚያ ቦታ ሉዯርሱ ሲቃረቡ፥ አጋሰስዋ
ገረገረችባት፥ (ቆማ ወዯ ሁዋሊ ሳበቻት።) ዘውር ብትሌ ያጋሰስዋ ጭነት ባንዴ ወገን አጋዴል ከጀርባዋ
ወዯ ሆዴዋ ወርድዋሌ። ከዚያ ሴትዬዋ ከበቅልዋ ወርዲ ያጋዯሇውን ጭነት ወዲጋሰስዋ ጀርባ ሇመጫን
ትታገሌ ጀመር። ያን ጊዜ ሁሊችንም ያይሮፕሊኖችን መዴረስ አይተን «ሴትዮ አይሮፕሊኖች መጡብሽ
በቅልዎችን ተያን ነይ! እባክሽ ተያቸውና ወዱህ ነይ!» እያሇን ከያሇንበት ጮህን። እሷ የኛን ጩኸትም
ሆነ ቦምብ እየጣለ የመጡትን አይሮፕሊኖች አይታም አትሰማም ነበር። አይንዋም ጆሮዋም አሳብዋም
ሁለ ተሰብስቦ ያተኮረው ያን ያጋዯሇ ጭነት መሌሳ ሇመጫን በጀመረችው ትግሌ ሊይ ብቻ ነበር።
ከየዛፈና ከየቁዋጥኙ ስር ስንጮህ ከነበርነው መሀከ አንዴ ሰው ሴትዮዋን ሇማዲን ወዯስዋ ሮጦ ነበር።
ነገር ግን አይሮፕሊኖች ስሇ ቀዯሙት ከመሀሌ መንገዴ ወዯ መሸሸጊያው ተመሇሰ። ያች ሴት እንዱያ
ካጋሰስዋ ጭነት ጋር በመታገሌ ሊይ እንዲሇች አይሮፕሊኖች ከጣለትዋቸው ቦምቦች አንደ እስዋና
በቅልዎችዋ በቆሙበት መሀሌ ወዯቀ። ወያው ያ፥ የቆሙበትና በዙሪያው የነበረው መሬት ሁለ ተጎርድ
ብዙ ሜትር ወዯ ሰማይ ሲነሳ የስዋና የበቅልዎችዋ የመሬቱ፥ የዯንጋዩ የሳሩና የቁጥቁዋጦው ብጥስጣሽ
ባንዴነት ተዯባሌቶ ባየር ውስጥ ከጉዋነ በሁዋሊ ተምሇሶ ቦምቡ መሬቱን ጎርድ ሲያነሳው እስር ተቆፌሮ
በቀረው ሰፉ ጉዴጉዋዴ ዙሪያ ተበተነ። ታዱያ የሚያስገርመው አይሮፕሊኖች እዚያ ባጠገባችን በጣለት
ብዙ ቦምብ ከዚያች ሴትና ከበቅልዎችዋ በከዚያ ሁለ ሰራዊት ሞቶ ወይም ቆስል ሲወዴ ያየነው
አሌነበረም።

አይሮፕሊኖች ከሄደሌን በሁዋሊ ከየዛፈ ስር ወጥተን መንገዲችንን ስንቀጥሌ ሴትየውና ሇማዲን ሩጫ


ጀምሮ የነበረው ሰው እንዯ ነገረን፥ ያቺ ሴት ያንዴ መኮንን በጣም የሚወደዋት የጭን ገረዴ ኖራሇች።
ከሁሇት ቀን በፉት የመኮንኑ አሽከሮች እጦርነቱ ውስጥ አሌቀው እሳቸውም ክፈኛ ሲቆስለ፥ ከሞትም
ከመቁሰሌም የዲኑ እስዋና አንዴ ወንዴ አሽከራቸው ብቻ ኖረዋሌ። ጌትየው በፅኑ ቆስሇው በጣእር ውስጥ
እንዲለ እስዋ ባጠገባቸው ሆና ስታስታምማቸው እንዯማይተርፈ ተረዴተው ኖሮ «አንቺና ተስፊው
(ወንደ አሽከራቸው) ከሞት ተፊችሁ አገራችሁ ሇመግባት የበቃችሁ እንዯሆነ፤ መሳሪያየንና አባቴ
ሲሞቱ ሇመታሰቢያቸው የሰጡኝን ዲዊቴን ሇሌጄ ሇንጋቱ እንዴታዯርሱሌኝ አዯራ። እሱ እስኪያዴግ
የናቱ ወንዴም ብሊታ በየነ ባሊዯራ ሆነው ይጠብቁሇት» ብሇው ተናዘው ሞተዋሌ። እንዱኢህ ያቺ ሰው
ሁለ ነፌስዋን እንዴታዴን ያን ያክሌ ሲማጠናት አይንዋ እያየ በቦምብ ተቃጥሊ የሞተች የወዲጅዋን

66
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያዯራ ኑዛዜ ሇመፇፀም ኖሮዋሌ! ምን አይነት እስከ ሞት የሚያዯርስ ታማኝነት ምን አይነት ሀይሌ
ፌቅር ቢሆን ነው!

«ሇሀይማኖትዋ ብሊ ሇማተብዋ ብሊ እንዱያ ተቃጥሊ ሞተች!» አሇ ሰውየው የሴትየዋን ታሪክ


ከተረከሌን በሁዋሊ እየተከዘ።

«እንዳት ሇሀይማኖትዋ ብሊ? ያይሮፕሊን ቦምብ ስንቱን አቃጥል ሲጨርስ እያየች ካጋሰስ
ጭነት ጋር ስትታገሌ መሞትዋ ‹ሀይማኖተኛ› የሚያሰኛት መስልዋት ነው? እንዱህ ያሇው ሞኝነት
ወይም እብዯት ነው እንጂ ሀይማኖተኝማነት አዯሇም!» አሇ ጤናው ከማዘኑ የተነሳ ቆጣ ብል፤ ግን
ሀያሌ ፌቅር ሞኝም እብዴም ሀይማኖትም ሁለንም ያዯርጋሌኮ!

ከዚያ ራስና ከሰራዊቱ አብሮዋቸው የሚጉዋዘው ክፌሌ በሰፇሩበት ዋሻ አጠገብ ዯረስንና ከኛ ጋር


ከነበሩት የሚበዙት ሰራዊቱ የሚሄዴበትን ዋና መንገዴ እንዯ ያዙ ሲቀጥለ ሁሇቱ ጉዋዯኞቼና እኔ
አንዲንዴ ሰዎች ጭምር ወዯ ራስ ሰፇር አመራን። እህሌ ከቀመስን ሁሇት ላሉትና አንዴ ቀን አሌፇው
ሁሇተኛው ቀን መጀመሩ ስሇነበረ ዝሇን እግራችንን እየጎተትን ነበር የምሄዴ። ስሇዚህ እሰፇር እንዯ
ዯረስን ራስን ከማየታችን በፉት ትንሽ ሇማረፌ አንዴ ዛፌ ስር ገዯም ባሌንበት ዴካምና እንቅሌፌ
ተዯራርበው ተጨንውን እኩሇ ቀን ሲሆን ነቃን። ከዚያ ወዯ ራስ ሄዯን እጅ ነስተን ተመሌሰን ትንሽ
እንዴ እቆየን ሁሇት አሳሊፉዎች አንደ እንጀራ በጥራር፥ ሁሇተኛው አገሌግሌ ሙለ ፌትፌት ይዘው
መጡ። ያንጊዜ ሇኔ ያ አሳሊፉዎች ይዘው የመጡት እንጀራና ወጥ ዘወትር የምንበሊው አንዲንዴ ጊዜም
ተርፍን የምንጠው መስል አሌታየኝም ነበር። በመሌኩም ገና ሳሌቀምሰው በጣሙም ከማውቀው እንጀራ
ወጥ ሁለ የተሇየ ተበሌቶ የማይጠገብ መሌሶ ነበር የታይኝ። ወዱያው ባጠገባችን በርከት ያለ ሰዎች
ስሇ ነበሩ በኛና በነሱ መሀከሌ ሲከፊፇሌ ሇያንዲንዲችን የሚዯርሰን ያሇ ጥርጥር ትንንሽ መሆኑን
አሰብሁና፥ እኒያ ሰዎች ሊይ አንዴ አይነት የጥሊቻ ስሜት ተሰማኝ። ከዚያ ሇኒያ ሰዎችና ሇኛ፥ ባሇጥራሩ
እንጀራ እየቆረሰ በጅ በጃችን ሲያሲዘን ባሊገሌግለ እጁ እስኪሞሊ ፌትፌቱን እያፇሰ በያዝነው እንጀራ ሊይ
አዴርገውሌን ሄደ። ያን ከቀማመስን በሁዋሊ እዚያ ባጠገባችን ሌትነጥፌ ምንም ያክሌ ያሌቀራት ትንሽ
ወንዝ ስሇ ነበረች ጤናው ሄድ የራሱን እዚያው ጠጥቶ ሊቶ ዘውዳና ሇኔ እንዯ ምንም አጠራቅሞ ግማሽ
ኮዲ ውሀ አምጥቶሌን መጣንና እንዯ ገና ተኝተን ከመሸ በሁዋሊ ነቃን። «እክሌ ያፀንኦ ሇሰብ» አዯሌ? ያ
አንዲንዴ እፌኝ ጉርሻም ከምግብ ተቆጥሮ ነፌስ ዘራብንና በርታ በሇን ተነሳን። ምግቡን የተካፇለን ሰዎች
ግን ስንነሳ አሌነበሩም ሄዯዋሌ። የነሱን መሄዴ ሳይ ወዱያው አሳሊፉዎች እንጀራና ፌትፌት ይዘው
መጡ እዚያ በመኖራቸው የተሰማኝ ጊዜያዊ የጥሊቻ ስሜት ትዝ አሇኝና ሰውነቴን ታዝቤው ሳይታወቀኝ
ራሴን እየወዛወዝሁ ፇገግ አሌሁ።

«ምን ታስቦህ ነው ራስህን እየወዘወዝህ የምትስቅ?» አሇኝ ጤናው ያየኝ ሳይመስሇኝ አይቶኝ
ኖሮ።

67
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ምንም አዯሌ እንዱያው፥ ነው» አሌሁት፥ ዴንገት ስሇ ጠየቀኝ የምሰጠ መሌስ አጥቸ
እውነቱንም እንዲሌናገር አፌሬ።

ላሉቱን ከራስ ጋር ከዚያ ሰፇር ተነስተን ሲነጋጋ ሇተከታዩ ቀን ሰፇር እንዱሆን መሪዎች
በመረጡት ቦታ ዯረስን። ያ ቦታ ካንዴ ትሌቅ ተራራ ስር - ሇስር የተራራው ርዝመት ተከትል እስከ
መጨረሻው የሚዯርስ ዋሻ ነበር። እዚያ ዋሻ ውስጥ ራስን የተከተሇው ሰራዊት ሁለ ጥቅሌሌ ብል
ገብቶ ሰውም ሆነ ከብት አይታይ ነበረ። ጠቁዋሚ ካሊመሇከተው በቀር፤ «ጠሊት እዚያ ቦታ ሰው
መኖሩን ጠርጥሮ ቦምብ ይጥሌ ይሆናሌ» ተብል የሚያሰጋ አሌነበረም።

ቀኑን አርፇን የምንውሌበት ቦታ ሇመምረጥ ስንዘዋወር ከሌጅ (ሁዋሊ ቀኛዝማች) አሇማየሁ


ቦጋሇ ጋር ተገናኝተን እሱ ከያዘው ቦታ አጠገብ ሰው ያሌያዘው ባድ ቦታ አግኝተን እዚያ አረፌን። ሌጅ
አሇማየሁ ከጉዋዙና ከጉዋዝ ጠባቂዎቹ ጋር አንዯኛ እንዲስሊሴ ቢሇያዩም፤ በቅልና ስንቅ ከያዘሇት አሽከሩ
ጋር አሌተጠፊፊም ኖሮዋሌ። ስሇዚህ እጭዋታ ሊይ የጦርነቱን ግንባር ከሇቀቅን ጀምሮ በቅልየንና
ስንቃችንን ከያዘው ሰው ጋር መጠፊፊታችንን ስነግረው በጣም አዝኖ የተረፇውን ትንሽ ስንቅ አብረነው
እንዴንከፊፇሌ አጥብቆ ሇመነን።

«የተረፇህን ስንቅ ትንሽ ከሆነ ያኑ ትንሹን አሁን አራግፇህ ሇኛ አካፌሇህ ሁዋሊ አንተም እንዯኛ
ከመራብ በቀር የምትቀምሰው የት ታገኛሇህ? እኛስ እንዯዚያ እንዯ ምቀኛው ነጋዳ ካሌሆነ በቀር ከንቱ
ሊንጠግብ አንተንም እንዯኛ ስትራብ ማየቱ ምን ይጠቅመናሌ?» አሌሁት «ምቀኛው ነጋዳ ተናገረ»
የተባሇው ትዝ ስሊሇኝ እንዯ መሳቅ ብዬ።

«የምን ምቀኛ ነጋዳ ነው?» አሇ ሌጅ አሇማየሁ።

«ያ ወረቱን ወንበዳዎች ዘርፇውት ሰዎች ተሰብስበው ሲያስተዛዝኑት ‹ከመዘረፋ የባሰ


የሚያስቆጨኝ አብረውኝ የነበሩት ነጋዳዎች ሁለ አንዴ ነገር ሳይወሰዴባቸው እኔ ብቻ መዘረፋ ነው›
ያሇው አሌሁት።

«ሊህኑ የማይበቃ መሆኑ ነው እንጂ የሚያሳዝን ሇሁዋሊውስ ግዳሇም እግዜር ያውቅሌናሌ» አሇ


በተረቱ ሲስቅ ቆይቶ። «ሇሁዋሊውስ…..» አሇ ቀጥል። «ሇሁዋሊውስ ከዚህ ተነስተን ከተከዜ ወዱያ ማድ
እጋራው ጥግ ስንሰፌር እንዲስሊሴ የተውነው ጉዋዛችንም ሰዎቻችንም ከቦምብ ቃጠል ተርፇው እንዯሆነ
እዚያ እንገናኝ ይሆናሌ።»

«እስካኍን ያሌተገናኘን እዚያ እንዯምንገናኝ እንዳት ይታወቃሌ?»

«ሰራዊቱ ሇየብቻ ተበታትኖ ጋራውን እንዲይወጣና የዯጋውን አገር ህዝብ እንዲይበዴሌ ግንባር
ቀዯሞ ጦር እንዱያግዯው ትእዛዝ ተሰጥቶዋሌ። ስሇዚህ መንገዴ ሇመንገዴ ከዯረሰው የቦምብ አዯጋ

68
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የተረፇው ሁለ እዚያ ሳይገናኝ አይቀርም» አሇ። ሌጅ አሇማየሁ፤ ራስ ከሹማምንቱ ጋር ምክር ሲያዯርጉ
ተካፊይ በመሆኑ እኛ የማናውቀውን ያው ነበር።

ከዚያ የነበረውን ትንሽ በሶና ዲቦ ቆል አሽከሩ አምጥቶ እፉታችን አራግፍ አቅርቦን ከሄዯ
በሁዋሊ፤ «ሇሱስ ምን ቀረው ሌንጨርስበት ነውኮ!» አሌሁ።

«ዴንገት በመንገዴ የተጠፊፊን እንዯሆነ እንዲንቸገር ሁሊችንም ዴርሻችንን ተከፊፌሇን ይዘናሌ፤


ስሇዚህ እሱም ላልችም ትንንሽ ይኖራቸዋሌ ይህ የኔ ዴርሻ ነው» ሲሇኝ የሱን ጥንቃቄ በሌቤ አዴንቄ
እኔም እንዯሱ ባሇማዴረጌ ራሴን ነቀፌሁ።

የሌጅ አሇማየሁን ስንቅ ሁሇቱ ጉዋዯኞቼና እኔ ከሱ ጋር ተከፊፌሇን በሌተን የላሉቱን ፊንታ


በየቦታችን ሌንተኛ ስንሰናዲ መንገደን ይዞ በሚጉዋዘው ሊይ ቦምብ እየጣለ ወዯ ተከዜ የሚያሌፈትን
አይሮፕሊኖች ዴምፅ ከመስመታችን ሶስት ወይም አራት ጊዜ ያክሌ ተዯጋግሞ ሲተኮስ ሰማን። ተኩሱ
ዯከም ያሇ ስሇ ነበረ ከኛ ራቅ ብል ባይሮፕሊኖች ሊይ የተተኮሰ መስልን ነበር። ግን ባይሮፕሊኖች ሊይ
የተተኮሰ አሌነበረም «ባሇቃ አምሳለ የተመኙ» ሊይ የዯረሰ ዴንገተኛ አዯጋ ነበር። አሇቃ አምሳለንና
«ዴማሀገነት (ሁዋሊ መሊከ ፀሀይ) ታዬን፤ አሇቃና ሉቀ ጠበብት ሆነው ዯብረ ኤሌያስንና ያካባቢውን
ገጠሮች ሲገዙ በሌጅነቴ አውቃቸዋሇሁ። ያሇቃ አምሳለን ጉብዝናም በቅርብ የሚያውቃቸው ሰዎች
ሲያዯንቁ ሰምቻሇሁ። በዴሮው የጌቶች ባህሌ ሲያበለና ሲያጠጡ አይናቸው የማይሳሳባቸው ሇጋስ
መሆናቸውን እኔም አይቻሇሁ። የሌኡሌ ራስ ሀይለ ፀሀፋ ትእዛዝ በነበሩ ጊዜ ልላዎቻቸውንና ዘመዴ
ወዲጃቸውን ብቻ ሳይሆን ወዯ ራስ ሀይለ ሊቤቱታና ሇዯጅ ጥናት ከሚሄዯው ሰው ሇሚበዛው ባሌዯረባ
(ጉዲይ አስፇጻሚ) እሳቸው ስሇ ነበሩ ያን ሁለ ሰው ጉዲዩን ጨርሶ እስኪመሇስ በዬሇቱ ግብር እያገቡ
ሲያበለና ሲያጠጡ የሚኖሩ ሇጋስ መሆናቸው በሰፉው የታወቀሊቸው በመሆኑ «አባ ባህር» ይባለ ነበር

ያነሇት አሇቃ አምሳለና ዴማሀገነት ታዬ ከጦርነቱ ሚዑኤዲ ሲመሇሱ፥ ራስ እዚያ ተራራ ስር


መሆናቸውን ሰምተው ወዯሳቸው ሇመሄዴ ከዬበቅልዋቸው ወርዯው አፊፌ ሊፊፌ እየሄደ ተራራውን
የሚወርደበት መንገዴ ሲፇሌጉ አይሮፕሊን ይመጣባቸዋሌ። አሇቃ አምሳለ አይናቸውን ታመው በቅጥ
ማየት አይችለ ኖሮ፥ ዴማሀገነት ፉት ፉታቸውን ሲሄደ እሳቸው እዬተከተለ ይሄደ ኖሮዋሌ።
ዴህማገነት ባቅራቢያቸው አንዴ ዛፌ ያዩና እዚያ ተጠግተው አይሮፕሊኖችን ሇማሰስሇፌ «ና ወንዴሜ
ብሇው ሲሄደ አሇቃ በሳቸው ሇመዴረስ ቸኩሇው የሚቆሙበትን ሳያዩ ባንዴ ዴንጋይ ሊይ ይቆሙና
ዴንጋዩ ተገሌብጦ ይጥሊቸዋሌ። ከዚያ ዴማሀገነትም የተከተለዋቸው አሽከሮችም ሉያነሱዋቸው ሲሮጡ
ቁሌቁሇት ስሇ ነበረ አምሌጠዋቸው እየተንከባሇለ ከገዯለ አፊፌ ይዯርሳለ። ከዚያ ገዯለ ብዙ እርከኖች
ስሇ ነበሩት፤ ካፊፌ ተወርውረው በመጀመሪያው እርከን ሊይ ሲወዴቁ ያ አንጥሮ ወዯ ታችኛው እርከን
ይወርውራቸዋሌ። እንዱያ ከሊይኛው እርከን ወዯ ታችኛው እየተወረወሩ በወዯቁ ቁጥር የታጠቁት ሽጉጥ
እየተተኮሰ ራስ በሰፇሩበት ከገዯለ ስር ወርዯው ይወዴቃለ። ሇካስ ያ ቀዯም ብል በአይሮፕሊኖች ሊይ

69
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እየተዯጋገመ የተተኮሰ መስልን የነበረው ዯከም ያሇ ተኩስ ካሇቃ አምሳለ ሽጉጥ የተተኮሰው ኖሮዋሌ!
እኛ ወሬውን የሰማን ትንሽ ቆይተን ነበር።

ሌጅ አሇማየሁና እኔ ከጉዋዯኞቻችን ጋር አሇቃ አምሳለ ከገዯለ ስር በወዯቁበት ቦታ ስንዯርስ


አሽከሮቻቸው ቀዯም ብሇው ዯርሰውሊቸው ቅጠሌ ጎዝጉዘው በሊይ ምንጣፌ አንጥፇው በጀርባቸው
አስተኝተዋቸው ነበር። እንዱያ ተኝጠው ሲንቀሳቀሱ፥ ወይም ሲተነፌሱ ስሇማይታዩ የህይወት ምሌክት
የማይታይባቸው የሞቱ ይመስለ ነበር። ጎንበስ ብዬ ስዲስሳቸው ግን ሰውነታቸው ይሞቃሌ፤ ወዯ
አፌንጫቸው ጠጋ ብዬ ሳዲምጥ በጣም ዯካማ ትንፊሽ እየቆየ ይሰማሌ። ብቻ እንኩዋንስ ቀኑን ውሇው
ሉያዴሩ ከጥቂት ሰአቶች በሊይ የሚቆዩ አይመስለም ነበር። ከዚያ ሰዎቻቸውን አያፅናናን አብረናቸው
ቆይተን ያን ቀን የከፊ ነገር የዯረሰ እንዯ ሆነ ቢያስታውቁን የምንረዲቸው መሆናችንን ነገረናቸው
ሌንተኛ ሄዴን። ግን የዯረሰ ክፈ ነገር አሌነበረም። በማግስቱ ከተከዜ ማድ ሰፇር በተዯረገበት ያሇቃ
አምሳለ ሰዎች አሌጋ ሰርተው በዚያ ሊይ አሇቃን አንገታቸውን ቀና አዴርገው አስተኝተው
ሲያመጡዋቸው አይቸ፥ ሄጄ ብጠይቃቸው ፇገግ ብሇው በጎ መሆናቸውን ሲነግሩኝ ገረመኝ። ከብዙ
አመታት በሁውሊም አዱስ አበባ ተገናኘን። እምቸም ከዚያ ገዯሌ ወዴቆ ወዱያውኑ መሞት ቢቀር
የእዴሜ ሌክ አካሇ - ስንኩሌ ሳይሆን መቅረት፥ ወይ በታምር ያሇዚያም ከብረት የተሰራ አካሌና በምንም
ሁኔታ የማይሸነፌ ፅኑ መንፇስ ያሇው ሰው መሆን ያስፇሌጋሌ!

ላሉት በዋሻው ከዲር እስከ ዲር ጫጫታ ሆነ። ራስና አጃቢ ሰራዊታቸው ጉዞ ሇመጀመር
መነሳታቸው ነበር። ሌጅ አሇማየሁና ሰዎቹም ቀስቅሰውን ወዯ ራስ ሄደ። እኛ ግን ከተኛንበት መነሳት
አቅቶን እዚያው ብዙ ቆይተን ሰው ሁለ ሄደ። እኛ ግን ከተኛንበት መነሳት አቅቶን እዚያው ብዙ
ቆይተን ሰው ሁለ ሄድ ሰፇሩ ባድ ከሆነ በሁዋሊ ነበር የተነሳን። ከዚያ ተራራውን በወረዴንበት መንገዴ
እያዘገምን ወጥተን ከሰራዊቱ ጋር ተጨምረን ጉዞዋችነን ጀመርን። ወዯ ተከዜ አፊፌ እዬተቃረብን
በሄዴን መጠን መሬቱ ዯሌዲሊ መሆኑ እዬቀረ ከመንገደ ባንዴ ወገን አቀበት በላሊው ወገን ቁሌቁሇት
እየሆነ በመሄደ፥ ይሌቁንም ላሉት ከመንገዴ ወጥቶ በቀኝ ወይ በግራ የሚሄዴ አሌነበረም ሁለም
እመንገደ ውስጥ ታጉሮ፥ እስበሱ እየተገፊፊ ነበር የሚሄዴ። እዚያ ውስጥ መሄዴ ከመንገደ ይሌቅ
መጋፊቱ ያዯክማሌ! እዚያ ውስጥ ከቀኝ ከግራ ከፉት ከሁዋሊ ጆሮ የሚሰማው «ሂደ ሂዴ ሂዴ እንጂ!
አትሄዴም?» ብቻ ነበር። እዚያ ግፉያ ውስጥ አንዴ ሰው ዯክሞት ወይም አነቅፍት ቢወዴቅ በሊዩ ቆሞ
መሄዴ ነው እንጂ ሇመርዲት የሚሞክር አሌነበረም። እንዱዑያ እየተጋፊን ስንሄዴ ከላሉቱ በዘጠኝና
ባስር ሰዒት መሀከሌ ግዴም አንዴ ዯረቅ ወንዝ ዯረስን። ወንዝዋን ተሻግሮ ከትግራይ ወገን የተከዜን
አቀበት ነው። ያን አቀበት አሻግሬ ሳይ የተረፇኝ አቅም ሁለ ተሙዋጦ ያሇቀ መስል ተሰማኝና፤ «እዚህ
ትንሽ ካሊረፌን አቀበቱን መውጣት አሌችሌም» አሌሁ፤ ሇጉዋዯኞቼ። ከዚያ መንገደን ሇቀን፤ ወዯ ሊይ
ወገን ትንሽ እንዯ ሄዴን ጠርቦ ያሇሰሇሱት የመሰሇ ሰፉ አሇት ዯንጋይ አገኘንና ሶስታችንም እዚያ
ተጋዯምን።

70
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ትንሽ አርፇን ጉዞዋችነን ሇመቀጠሌ በተጋዯምንበት በዚያው እንቅሌፌ ተጫጭኖን ጤንው
ቀዴሞ ነቅቶ ሲቀሰቅሰን ጀንበርዋ የምትወጣበትን አዴማስ የወርርቅ ቀሇም የተቀባ አስመስሊ አሳምራ
አገሩ ሁለ ወገግ ብልዋሌ ቀን ሆኖዋሌ። በዚያ የንጋት ወጋገን ከከዯረቅዋ ወንዝ ባሻገር ሳር ቅጠለ
የተቃጠሇው የተከዜ ዲገት ከቁዋጥኞቹ ጋር ከግር እስከ ራሱ ራቁቱን ይታያሌ። ሰማዩ በሙለ የዯመና
ምሌክት የማይታይበት እነእ ወሇወለት መስታዋት የጠራ ነበር። በመንገዴ የሚሄዯው ሰራዊት የላሉቱን
ያክሌ አይሁን እንጂ ያንጊዜም እስበሱ እየተገፊፊ የሚሄዴ፥ ብዙ ነበር። ጤናው ተኝቶበት ከነበር አሇት
ወርድ ከግርጌያችን ቆሞ የሚጉዋዘውን ሰራዊት ይመሌከት ነበር።

«አሁን አይሮፕሊኖች የሚመጡበት ጊዜ ነው፤ እንዱያውም ዛሬ ቆይተዋሌ እንጂ መሰንበቻቸውን


ከዚህ ቀዴመው ነበር የሚመጡት። ስሇዚህ ከሰራዊቱ መሀሌ ገብተን እዬተገፊፊን ስንሄዴ የመጡብን
እንዯሆነ በግራና በቀኝ መጠሇያ የሚሆን ነገር ስሇማይታይ፥ እዚያ ማድ ከሚታዩት ትሌሌቅ ቁዋጥኞች
ወዲንደ እንዴሂዴና እስሩ ተቀምጠን እስከ ቀትር እንቆይ። ከዛሬ ቀዴመ እንዯ ተመሇከትነው ከቀትር
እስከ ዘጠኝ ሰዒት አካባቢ አይሮፕሊኖች መጥተው ቦምብ አይጥለም» አሇ አቶ ዘውዳ።

«እውነትህን ነው እኔም ከቀትር በሁዋሊ አመሻሽ ሊይ ካሌሆነ መጥተው ቦምብ የጣለበት ቀን


ትዝ አይሇኝም። ያን ጊዜ እነሱም ነጂዎቻቸውም ሆዲቸን ሞሌተው የሚያርፈበት ይሆናሌ። ወዱያውም
ትናንት ሌጅ አሇማየሁ እንዯ ነገረን ሰፇሩ ከተከዜ ማድ አፊፈ ጥግ ከሆነ ቆይተን መንገደን ሰው ሇቀቅ
ሲያዯርግሌን ብንሄዴ እንዯርሳሇን» አሌሁ። ጤናውም ተስማማ።

እኛ ስንነጋገር ሰማዩ የዯመና ምሌክት የማይታይበት ጥሩ ነበር። ነገር ግን በቅፅበት «ከዚህ


መጣ» ሳይባሌ ከባዴ ጉም የተከዜን ሸሇቆ ከሊይ እስከ ታች አዲፇነው። ከዚያ በዚያ አራራ በጋና የዝናብ
ቀርቶ የዯመና ምሌክት በሰማይ ሳይታይ እንዱያ ያሇ ከባዴ ጉም በመውረደ እየተገረምን ሰራዊቱ
የሚሄዴበትን መንገዴ አቁዋርጠን እንዯ ተማርከርነው እስከ ቀትር ወዯምንቆይበት መሄዴ ስንጀምር፥

«አያ ጤናው አያ ጤናው» አንዴ ሰው ከሰራዊቱ መሀሌ። ሶስታችንም ዘወር ስንሌ ረዥሙ
ዘሪሁንን በቅልውን እየሳበ ከሰራዊቱ ተሇይቶ ወዯኛ ሲመጣ አዬነው። ያንጊዜ ዘሪሁን ከሞተበት ተነስቶ
የመጣ እንጂ ጠፌቶን ሰንብቶ የተገኘ አሌመሰሇንም። እሱ ወዯኛ ሲመጣ እኛም ወዯሱ ሄዯን ሶስታችንም
በተራ እያቀፌን አስጨንቀን ከሳምነው በሁዋሊ ሳሌጭሩ ዘሪሁን ክፈ ወሬ እንዲይነግረኝ እየፇራሁ
የሚያውቀው ነገር እንዲሇ ብጠይቀው ምንም የሚያውቀው ነገር አሇመኖሩን ነገረኝ። ከጦርነቱ ሰፇር
ቀዴሞን ተነስቶ ያነሇት ከሁዋሊችን የመጣበት ምክንያት አዯጋ አግኝቶት ኖሮ እንዯሆነ ጠይቄው መሌስ
በቅጡ ሳይሰጠኝ አይሮፕሊኖች ሲመጡ ዴምፃቸውን ስሇ ሰማን ቶል እዯረቅዋ ወንዝ ገብተን ቅጠሌ
በላሊቸው ዛፍች ስር ተጠጋን። ግን የሚበርሩት ከጉሙ በሊይ ስሇ ነበረ እንኩዋንስ እኛን መንገደን
ሞሌቶ እንዯ ውሀ ሙሊት ይጥመሇመሌ የነበረውን ሰራዊት ሳያዩ ወዯ ፉት እዬተከታተለ አሌፇው ሩቅ
ቦታ ቦምብ ሲጥለ እንሰማ ነበር። እኛም በሊያችን ሲያሌፈ ዴምፃቸውን ከመስማት በቀር በጉም

71
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምክንያት መሌካቸውን አሊዬን። ከዚያ ወጥተን ከተከዜ አፊፌ ጥግ አንዴ ትሌቅ ቁዋጥኝ አገኘንና
ባጠገባችን ቦምብ የፇነዲ እንዯሆነ ፌንጣሪው እንዲያገኘን እዚያ ከመሊው ዴንጋይ ቶሌቶል ሰብስበን
በግንባር ጥሬ ካብ ክበን በቅልው የዘሪሁንን ወይባ የነተነከረ ኩታ እንዯ ተከናነበ እፉታችን ካንዴ ዛፌ
ግንዴ ጋር አስረን እምሽጋችን ውስጥ ገብተን ተቀመጥን። ዘሪሁን የስንቅ መያዣውን የሸራ ከረጢት
ሲያመጣሌን ሇዚያ ጊዜ በቅቶ የሚተርፌ በሶ ጭኮና ዲቦና ቆል አገኘን። ብቻ ውሀ ስሊሌያዝንና
ባጠገባችንም ስሊሌነበረ በሶ ሌንበሊ አሌቻሌምንም። ከጭኮውና ከዲቦ ቆልውም ቢሆን የራበንን ያክሌ
አሌበሊንም ከቀትር በፉት ቢያንስ ዯከመንና ተኛን። እዚያ እንዲሇን አይሮፕሊኖች ከቀጥር በፉት ቢያንስ
ሶስት ጊዜ ያክሌ መጥተው ቦምብ እዬጣለ ሄዯዋሌ። ግን የሚጥለትን ቦምብ እንዱሁ «ባገኝ ባጣውን»
ባቀበቱ ሁለ ሊይ ዘርተውት ይሄዲለ እንጂ፥ መንገደን ይዞ እንዯ ጉንዲን ሰራዊት እየተዯራረበ
የሚርመሰመሰውን ሰው ሉያዩት ስሊሌቻለ ያነሇት እዚያ ዲገት ሊይና ከዚያም አሌፍ እስከ ተከዜ ወንዝ
ዴረስ በሰውም ሆነ በከብት ሊይ ያዯረሱት ጉዲት ከስንት አንዴ ነበር። ያነሇት የጣለትን ቦምብ ሁለ
በሚጓዘው ሰራዊት ሊይ አነጣጥረው ቢጥለት ኖሮ ሰው ባሌተረፇ።

ርፊዴ ሊይ ካምስት በሁዋሊ ጀምሮ እስከ ቀትር ዴረስ ያ ከባዴ ጉም እዬሳሳ ሄድ በመጨረሻ
በንኖ ጠፊና ሸሇቆው በሙለ ግሌጥ ሆነ። ያይሮፕሊን ዴምፅ ከሰማንም ዘሇግ ያሇ ጊዜ አሇፇ። በዚያ ጊዜ
መንገደን ሞሌቶት የነበረው ሰው በመጠኑ ቀሇሌ ብልዋሌ። ስሇዚህ ከቆየንበት አቀበት ወርዯን እዋናው
መንገዴ ስንዯርስ የበሊነው ጭኮና ዲቦ ቆል ፅኑ ውሀ ጥም ሇቆብን ስሇ ነበረ እኔ በበቅልየ ተቀምጩ
ተከዜ ወንዝ እስክንዯርስና ውሀ እስክንጠጣ ቸኩሇን ስንሄዴ፥ ሌጅ ሀብቴ አሻግሬን ከመንገዴ ወጣ ብል
አንዴ ዛፌ ስር ተቀምጦ አዬነው። ባጠገቡ አንዴ ሰው ቆሞ ነበር። ሌጅ ሀብቴ በቅርብ የማውቀው ክቡር
ራስ እምሩ ሰው ነበር። ከበቅልዬ ወርጄ ምን እንዯሆነ ብጠይቀው መታመሙን ስሇ ነገረኝ በቅልዬን
ሇሱ ሰጥቼ እኔ እንዯ መሰንበቻዬ በግሬ እየሄዴሁ ተከዜ ወንዝ ዯረስን። እዚያ ያየነው ዯግሞ ስሇ ሽሬ
ግንባር ጦርነት ሳስብ ባይነ - ህሉናዬ ፉት ጎሌተው ከሚታዩኝ ክፈ ትርኢቶች አንደ ነው።

የተከዜ ውሀ እመሻገሪያው ሊይ ሰፉና ፀጥ ያሇ ነው። ታዱያ ያ ሰፉ ውሀ፤ ገና ከሩቅ ሲያዩት


ቀይ ቀሇም በከባደ የተበጠበጠ ይመሌሳሌ። «ምን ነገር ነው ምን ጉዴ ነው?» እየተባባሌን ቀረብ ስንሌ
መሻገሪያው በቁሙም በወርደም ከዲር እስከ ዲር ሬሳ ሞሌቶበት የዚያ ሬሳ ዯምና ፇርስ ነው! የሰው
ሬሳ የፇረስና የበቅል ሬሳ ያህያ ሬሳ ያውሬ ሬሳ ሬሳ፥ ሬሳ ብቻ! እግር ከራስ ራስ ከግር እዬተመሰቃቀሇ
እየተዯራረበ ሞሌቶበት፥ የዚያ ሁለ ሬሳ ዯምና ፇርስ ነው። ያን ሳይ ውሀ ጥሜ ተቆረጠ። ከዚያ በሁዋሊ
የመጠጣቱ አሳብ ቀረና አሳሳቢ የሆነው እዚያ ገብቶ መሻገሩ የሚዘገንን ነበር። ግን፤ መሻገር የማይቀር
ግዳታ ስሇ ነበረ የሬሳው ብዛት ቀሇሌ ያሇ በሚመስሌበት በስተ ሊይ በኩሌ ጥርሳችንን ነክሰን ገብተን
ተሻገርን። ያ የሬሳ ክምር መቸም ያንዴ ቀን ሉሆን አይችሌ፤ ከጦርነቱ ግንባር ሽሽት ከተጀመረበት ቀን
ጀምሮ መሰንበቻውን ሰውና ከብቱ ሉሻገር ሲገባው አውሬው ውሀ ሉጠጣ ወይም ሬሳ ሉበሊ ሲመጣ
ሁለም ባንዴ ሊይ እዚያ በቦምብ ሲያሌቅ የሰነበተበት መሆን አሇበት!

72
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከዚያ እዬሄዴንም ተቀምጠን እያረፌንም አስር ሰአት አቅራቢያ የወንዙን ዲገት ሌንወጣ ትንሽ
ሲቀረን አይሮፕሊኖች መጡብን ግን ብዙ አሌቆዩም፤ ጥቂት ቦምቦች ጥሇው ሲሄደ ተሸሽገን ከቆዬንበት
ወጥተን ቀስ እያሌን ጉዞዋችንን ስንቀጥሌ ሰፇር ከተዯረገበት አጠገብ አንዴ ትንሽ ወንዝ አገኘን። እዚያ
ውሀ ጠጥተን የተከዜን ውሀ ስንሻገር የተበሊሸ ያካሊት ክፌሊችነን ከነሱሪያችን አጥበን ከወንዝዋ ዲር
አርፇን ሇመቆዬት ጋዯም ባሌንበት አጭሩ ዘሪሁንን ሲመጣ ከሩቅ አዬነው። «ዯስታ ቀሉሌ» የሚለት
አሰት አዯሇም። ዘሪሁንን በህይወት ባገኘው ዯስታውን የምችሇው አሌመሰሇኝም ነበር። ግን ዯስታው
ያሰብሁትን ስሜት አሌሰጠኝም። ዘሪሁንን ፉት ክስሌ ብል ጠቅሊሊ ሰውነቱ ተጎሳቅል ሳየው፥
እንዲሰብሁት በሚያስቅና በሚያስፇነዴቅ ዯስታ ፇንታ፥ ዯስታ አይለት አዘን፥ የውስጥ ህዋሳቴን ሁለ
የሚያውክ ሌዩ ስሜት ተሰማኝና ሳሊስበው አይኖቼ እምባ ሞለ፤ ከዚያ እሱ እኛ ዘንዴ እስኪዯርስ
ሳሌጠብቅ፥ ተነስቼ ወዯሱ ስሄዴ፥ ላልች ጉዋዯኞቻችንም ተከተለኝ።

«አዋዋ አሇህ? ዯህና ነህ?» አሇኝ ዘሪሁን ገና ሳንገናኝ ተጣርቶ። ዘሪሁን «አዋዋ» ነበር
የሚሇኝ። መሌስ መስጠት ስሊቃተኝ አሌመሇስሁሇትም፤ ዝም ብዬ ሄጄ አንገቱን አቅሬ ከሳምሁትት
በሁዋሊ እንዱያ እንዯ ያዝሁት አሳቤ ፀጥ እስኪሌ ቆይቼ፤

«አዯጋ ዯርሶብህ ኖሮዋሌ? ሇምን እንዱህ ሆንህ?» አሌሁት።

«አህያየን እንዯ ተጫነ ቦምብ አቃጠሇብኝ እንጂ እኔስ ዯህና ነኝ ምንም አሌሆንሁ» አሇ። ቦምብ
ያቃጠሇው የኔን አህያ ነበር። ግን ዘሪሁን እኔን እንዯ ራሱ ቆጥሮ የኔ የሆነ ማናቸውም ነገር ሁለ የሱ
መሆኑን በፌፁም ሌብ የሚያምን ስሇ ነበረ የኔን አህያ «ያህያየ» የኔን በቅል «በቅልየ» የኔን ቤት
«ቤቴ» እያሇ መናገሩ የተሇመዯ ነበር።

«እንኩዋን አንተ ዯህና ሆንህ» ብዬ አንገቱን ስሇቅሊቸው ዝም ብሇው ይመሇከቱን የነበሩት


ጉዋዯኞቻችን ሁለ በተራ «እንኩዋን እግዚአብሔር አተረፇህ!» እያለ ከሳሙት በሁዋሊ ከወንዝዋ ዲር
አርፇንበት ወዯ ነበረው ቦታ ተመሌሰን ተቀምጠን ረዥሙ ዘሪሁን በሶ አዘጋጅቶ አቅርቦሇት ይበሊ
ጀመር።

«አህያውን ቦምብ ያቃጠሇው እመንገዴ ሊይ ነው?» አሇው አቶ ዘውዳ።

«አዎ ትናንት እመንገዴ ሊይ ነው» አሇ ዘሪሁን።

«ታዱያ አንተና አጋሰስዋ እንዳት ተረፊችሁ?»

«በቅልዬን እዬሳብሁ አህያየን ፉት ፉት እዬነዲሁ ስንሄዴ የበቅልዋ ጭነት ሲያጋዴሌብኝ ጊዜ


ጭነቱን አስተካክዬ ሇማጥበቅ እስዋን ከመንገደ ወዯ ዲር አዴርጌ እስክጭን ዴረስ አህያው ከሚጉዋዘው
ብዙ ሰውና ከብት ጋር ከኔ ትንሽ ራቅ ብል ነበርና ያን ጊዜ አይሮፕሊኖች መጥተው እዚያ እሱ

73
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በነበረበት የጣለት ቦምብ ብዙ ሰውና ከብት ሲጨርስ ነው እሱም አብሮ የተቃጠሇ። እንግዱያ እኔ
በነበርሁበትና ባጠገቤማ ከሰውም ከከብትም የቦምብ ፌንጣሪ እንኩዋ የዯረሰበት አንዴ አሌነበረም።
እሱንም ጭነቴን እስካስተካክሌ ባጠገቢኤ ባቆዬው ኖሮ አይሞትም ነበር» አሇ ዘሪሁን መብሊቱን ትቶ
እዬተከዘ።

«ብቻህን ምን ማዴረግ ትችሌ ኖሮዋሌ አጋሰስዋን ትጭን ወይስ አህያውን ትይዝ አንተ ምንም
ማዴረግ አትችሌም ነበርና አሁን ማዘኑን ትተህ ብሊ። እንኩዋን አንተ ዯህና ሆነህ እንጂ እሱን
በማጣታችን ማዘንና ማማረር አይገባንም» አሌሁት። እውነቴን ነው መንገዴ ሇመንገዴ በቦምብ እንዯ
ቅጠሌ ሲረግፌ እዬረገጥነው የመጣ ነውን የሬሳና የቁስሇኛ ብዛት ሳስብ ከዚያ ሁለ መሀከሌ ዘሪሁን
ሳይሞት ሳይቆስሌ በዯህና ከኛ ጋር መገናኘቱ እንኩዋንስ ያህያውን ብቻ የበቅልዋን ጭምር መጥፊት
ኢምንት አዴርጎ የሚያሳይ ነው።

የራስ እምሩ ሰራዊት ከሰሇክሇካ የጦር ግንባር ሸሽቶ የተከዜን ወንዝ እስኪሻገር ያይሮፕሊን ቦምብ
እዬገዯሇና እያቆሰሇ መንገዴ ሇመንገዴ የጣሇውን የሬሳውን የሬሳና የቁስሇኛ ብዛት፥ እንኩዋንስ ያንጊዜ
ሲያዩት ካሇፇ በሁዋሊም ቢያስቡት ሌብ የሚያስጨንቅና የሚያሰቅቅ ነው! የጣሉያን ሰራዊት በኢትዮጵያ
ሰራዊት ሊይ በጦር ግንባር ካዯረሰው ጉዲት ገና ከጦርነቱ ግንባር ሳይዯርስና ከግንባር ሳይሸሽ ያዯረሰበት
ጉዲት «የከፊ ነው» እሊሇሁ። በጦርነቱ ሊይ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሞትና የመቁሰሌ ጉዲት ይዴረስበት
እንጂ በመጠኑም ቢሆን ጠሊቱን ገዴልና አቁስል ሲጥሌ ማየቱ ትንሽ የመበቀሌ ርካታ ይሰጠዋሌ።
የጣሉያን አይሮፕሊን ከጦር ግንባር ውጪ በኢትዮጵያ ሰራዊት ሊይ ያዯርገው የነበረው ጦርነት ግን
ሲገዴሌና ሲያቆስሌ እንጂ ሲሞትና ሲቆስሌ የማይታይበት በመሆኑ አካሌ ብቻ ሳይሆን መንፇስ ጭምር
የሚገሌዴ ነበር። እሽሽት ሊይ ከሰሇክሇካ የተከዜን ወንዝ እስክንሻገር በሞትና በመቁሰሌ የዯረሰብንን
ጉዲት እዚያ ወዴቆ የቀረውን ህዝብ ብዛት የያንዲንደ ቤት ይወቀው እንጂ እኛ መቸም አናውቀ! ማርሻሌ
ባድሉዮ 3000 መሆኑን ፅፇዋሌ።

በተቀመጥንበት እንዲሇን ዘሪሁን እስኪያርፌ እንዲስሊሴ ከተሇያዬንበት ጊዜ ጀምሮ ጉዋዝ ጠባቂው


ሰራዊት ስሇ ሰንተተበትና ሁዋሊም ከዚያ ሲነሳ ስሇ ነበረው ሁኔታ በጠቅሊሊው እንዱያወራን እየጠየቅነው
ሲነግረን ቆይቶ ከዚያ ተነስተን ከወንዝዋ ሩቅ ያሌሆነ ቦታ ፇሌገን ሰፇርን።

ሰፇሩ የተከዜን ወንዝ ዲገት ወጥቶ ከጠቅሊሊው የተከዜን ሸሇቆ ዲገት ግርጌ በሁሇቱ ዲገቶች መሀከሌ
ከሊይ እስከታች ገዯም ብል የሚወርዴ ቁጥቁዋጦም አንዲንዴ ቅጠሊቸው ያሌተቃጠሇ ዛፍችም የነበሩበት
ቦታ ነው። የሸሇቆው ዲገት በስተምስራቅ በኩሌ አናቱ «ራስ ዲሽን» ተራራ ነው። ስሇዚህ የሱ ቅዝቃዜ
ስሇሚሰማው ሰፇሩ በጣም ብርዲም ነበር። እዚያ በቂ አዬር (ኦክሲጂን) ባሇመኖሩ እንጨት ማንዯዴ
አይቻሌም። አንዴ እንዯ ሸንበቆ ውስጡ ክፌት ሆኖ ጥቃቅን ቅጠልች ያለት የንጨት አይነት በብዛት
ስሊሇ እሱን ብቻ እዬነቀለ ማንዯዴ ይቻሊሌ። ግን ያ አይነት እንጨት አንዴ ጊዜ «ግሌብሌብ» ብል

74
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ተቃጥል ፌም ወይም ከሰሌ ሳይተው አመዴ ብቻ ሆኖ የሚያሌቅ ነው። ስሇዚህ ከብርደ ሇመከሊከሌ
እሱን በሊይ በሊዩ እዬዯራረቡ እያቃጠለ ሇመሞቅ ካሌሆነ ውሀ ሇማሞቅ ወይም ምግብ ሇማብሰሌ
አይሆንም። የዚያ ቦታ ብርዴ መቸስ ሇብቻው ነው። አንዴ ቆሇኛ በክፈ አጋጣሚ እንዱያ ባሇ ቦታ
ተገኝቶ «እጅ ቢገኝ የንፌጥ ማሇቂያው አሁን ነበር!» እንዲሇው አውራ ጣትን ባጠገቡ ካለት ላልች
ጣቶች ጋር አቀራርቦ አፌንጫን መያዝ አይቻሌም እንጂ፥ ቢቻሌ ኖሮ እውነትም ከንፌጥ ሇሁሌጊዜ
መገሊገሌ የሚፇሌጉ ሁለ መሄጃው ያ ቦታ በሆነ!

ምእራፍ አስራ አንድ

ሌላ ዘመቻ
ከሰሇክሇካ የጦር ግንባር ተመሌሰን ከተከዜ ማድ በሰፇርን ማግስት፣ እጥዋቱ ሊይ የራስ
መሊክተኛ መጥቶ እንዯሚፇሌጉኝ ነግሮኝ ሄዯ።

እኔ እራስ ዴንኩዋን ስዯርስ አቶ ዮሀንስ አብደ (ሁዋሊ ሻሇቃ) ከሳቸው ጋር ቆይቆ ይወጣ ነበር።

«እኔና አንተ አብረን እንዴንሰራ የታዘዝነው ስራ አሇ፤ ሇሱ ነው የተጠራህ» አሇኝ እጁን


ሇሰሊምታ ወዯኔ ዘርግቶ።

«ምን ስራ ነው?» አሌሁት እጁን ጨብጨ።

«ስትገባ ራስ ቢነግሩህ ይሻሊሌ» አሇ፤ እንዯ መሳቅ ብል። ወዱያው አጋፊሪው ራስ ወዲለበት
አስገብቶኝ እጅ ስነሳ የቃሌ ሰሊምታ ሰጡኝና፤

«እጦርነቱ ሊይ ወይም ከዚያ እመሌስ ሊይ የተጎዲብህ ሰው አሇ?» አለኝ።

«የሇም፤ ሁሊችንም ዯህና ነን» አሌሁ።

«ትሌቅ እዴሌ ነው!»

«መቸም - በጦርነቱ ግንባር ሊይ ከተጎዲብን ሰው ይሌቅ እሽሽቱ ሊይ ባይሮፕሊን ቦምብ የተጎዲው


ሳይበሌጥ የሚቀር አይመስሇኝም!» አሌሁ፤ ሌጠይቃቸው ሊሰብሁት አይነተኛ ነገር መንገዴ ሇመክፇት
ብዬ።

«ይመስሌሀሌ?»

«አዎ፤ ሇኔ ይመስሇኛሌ። ምክንያቱም የላሊውን ግንባር አሊውቅም እንጂ እኔ ከቀትር ጀምሬ


እስኪጨሌም ዴረስ በዋሌሁበት በምእራቡ ግንባር እዬሞቱና እዬቆሰለ የወዯቁት ብዙ ቢሆኑም

75
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ብዛታቸው ከጠሊት የመሳሪያ አይነትና ብዛት አንፃር ሲታይ ይህን ያክሌ ‹ከመጠን ያሇፇ ነው› የሚባሌ
አይዯሇም መጠነኛ ነው። ዯግሞ በዚያ ሁለ ጊዜ ጣሉያኖች ከምሽጋቸው ወጥተው የኢትዮጵያ ወታዯሮች
ከያዙት አንዴ ትንሽ ቦታ እንንኩዋ አስሇቅቀው መያዝ አሌቻለም። እንዱያው አንዴ ጊዜማ የኢትዮጵያ
ወታዯሮች «ሆ!» ብሇው ኢጣሉያኖች ምሽግ ውስጥ ገብተው በጨበጣ ጦርነት አሸንፇው ከምሽጋቸው
አባረዋቸው ነበር! ብቻ ከሁዋሊ ተጨማሪ ሀይሌ ስሊገኙ በሱ ርዲታ እንዯገና ወዯ ምሽጋቸው ሇመመሇስ
ቻለ። ያም ሆኖ ከጨሇመ በሁዋሊ እኔ ጉዋዯኞቼ ስሇ ጠቅሊሊው የጦርነት ሁኔታ ሇመረዲት ወዯ ዋናው
መምሪያ እስክንመሇስ ዴረስ እንኩዋንስ የኛን ሰራዊት ዴሌ አዴርገው ወዯ ፉት ሉገፊ ከምሽጋቸው
አሌወጡም። ሰራዊታችንም እቀትር ሊይ እኛ ስንሄዴ የነበረበትን ቦታ ሳይሇቅ በመዋጋት ሊይ እንዲሇ ነው
ትተነው የመጣን። ታዱያ ይህ ሁለ ሲታይ ‹በግንባር የተሰሇፇው ሰራዊታችን የዯረሰበት ጉዲት ከመጠን
ያሇፇ ነው› የማይባሌ ከመሆኑ ላሊ ተዋግቶ ጠሊቱን ዴሌ የማዴረግ ፌሊጎቱና ሲቃው ያሌተቀነሰ
የመሸነፌና ተስፊ የመቁረጥ ምሌክት የማይታይበት ነው የሚመስሌ ከግንባር ተመሌሰን መንገዴ
ሇመንገዴ ባይሮፕሊን ቦምብ ተገዴልና ቆስል የወዯቀውንና የሚሸሸውን ሰራዊት ስንመሇከት ግን በግንባር
ከሚታዬው በፌፁም የተሇዬ ተስፊ የሚያስቆርጥ ነው።»

«አዎ፤ በላሊው ግንባርም ቢሆን ጣሉያኖች የኛን ሰራዊት ዴሌ አዴርገው ወዯ ፉት የገፈበት


ቦታ እምብዛም የሇም» አለ ራስ እንዯ መተከዝ ብሇው።

«እንግዱያ - ሇምን ሸሸን?» አሌሁ ሽሽት የሚባሇውን ቃሌ የራስ አፌ እንዯ ተፀየፇው ስሇ


ተሰማኝ ጥያቄየ ተገቢ መሆን አሇመሆኑን አዬተጠራጠርሁ። ይሁን እንጂ ወታዯሩ መስመሩን ሳይሇቅ
በመዋጋት ሊይ እንዲሇ የሸሸበትን ምክንያት ከመጀመሪያ ጀምሮ ስሊሌገባኝና ከንክኖኝ ስሇ ነበረ፥ መጠዬቅ
ነበረብኝ።

«ሰራዊታችን በግንባር ዴሌ ስሇሆነ አሌነበረም ወዯ ሁዋሌ ሇማፇግፇግ የፇሇግን። ጠሊት ከሁዋሊ


መንገዲችንን ቆርጦ ሇመክበብ ብርቱ ሀይሌ አሰናዴቶ በጎን መሆኑን ስሇ ተረዲን እወጥመደ ውስጥ
እንዲንገባ ወዯ ሁዋሊ ምቹ ቦታ ይዘን ሇምሳላ ተከዜን በግንባራችን አዴርገን ሇመዋጋት ነበር አሳባችን።
አሁን ግን ከሰራዊቱ የሚበዛው ተስፊ የቆረጠና ሇመዋጋት ፌሊጎት የላሇው ሆኖ ስሊገኘነው የፉተኛውን
አሳባችንን ትተን ላሊ አዱስ አሳብ አስበናሌ። አንተንም የተራህን ስሊዱሱ አሳባችን ሌናነጋግርህ ነው።
አሳቡ አዱስ ቢሆንም ያው ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ነው። ስሇዚህ ወድ - ዘማች ነህና አሁንም በዚኢያው
በወድ - ዘማችነትህ ሇመቀጠሌ ትፇቅዴ እንዯሆን ላሊ ዘመቻ ሌናዝህ አስበናሌ ትፇቅዲሇህ?» አለ
የቅርታ ፇገግታ ፇገግ ብሇው።

«መቸም ጦርነቱ የሚቀጥሌ ከሆነ የምችሇውን ሁለ እያዯረግሁ እስካሇሁ ዴረስ ከመቀጠሌ


በቀር ላሊ አሳብ የሇኝም» አሌሁ።

76
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እኛም ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ነው አሳባችን፤ ግን ፉት እንዲሰብነው እዚህ አካባቢ ሳይሆን፤
ያገራችንን ምእራብና ዯቡብ - ምእራብ ይዘን መዋጋት ሇኛ ምቹ የሚሆነውን ያክሌ ሇጠሊት የማይመች
በመሆኑ ወዯዚያ ሇመሄዴ ወስነናሌ። ያ ክፌሌ ዯን የሞሊበት ስሇ ሆነ ጠሊት እንዯ ሌብ ባይሮፕሊንና
በታንክ ሉዋጋበት የማይችሌ ከመሆኑ ላሊ እኛ የመክበብ ስጋት እንዲይኖርብን እንግሉዞች
የሚገዙውቸውን አገሮች ሱዲንና ኬንያ በጀርባችን አዴርገን እግዚአብሔር ፉቱን እስኪመሌስሌን ዴረስ
ስንታገሌ ብዙ ጊዜ ሌንቆይ እንችሊሇን። ስሇዚህ አሁን አንተን ወዯ ፇሇግንበት ጉዲይ እንመሇስና
«በትግራይ ምዴር የምንዋጋው ጦርነት ረዢም ጊዜ የሚወስዴ መስልን በስንቅ በኩሌ እንዲንቸገር
በዬጊዜው እዬተሰናዲ እንዱሊክሌን የሚያዯርጉበት ገንዘብ ዲባት አገር ጠባቂ ሆኖ ሇቀረው ሇዯጃዝማች
አያላው ሌጅ ‹ሇፉታውራሪ መርሶ› እና ጎንዯር ሇጳጳሱ ‹ሊቡነ አብርሃም› ሰጥተን ነበር። አሁን ይኸው
እንዲየህው ጦርነቱ በጥቂት ቀናት ስሊሇቀ ያን ገንዘብ ሊንተና ሊቶ ዮሀንስ አብደ እንዱያስረክቡዋችሁ
ሇሁሇቱም እንፅፊሇንና ሲያስረክቡዋችሁ ይዛችሁት ወዯ ሱዲን እንፅፊሇንና ሲያስረክቡዋችሁ ይዛችሁት
ወዯ ሱዲን እንዴትሄደ ነው ያሰብነው። አቶ ዮሀንስ ከንግሉዝኛ ላሊ አረብኛ ቁዋንቁዋም ሰዎችም
ሰሌሚያውቅ ከሚረደህ ሰዎች ጋር አገናኝቶህ ተመሌሶ በመንገዴ ሳሇን እንዱዯርስብን ነው የሚሄዴ።
አንተ ግን እኛ ባገራችን ምእራብ ‹ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ይመቻሌ› ብሇን የምንመርጠውን ዋና ሰፇር
እስክናስታውቅህ ዴረስ ገንዘቡን ይዘህ እዚያው ትቆያሇህ። ዋና ሰፇራችንን ስናስታውቅህ ከሱ ጋር
ሇወታዯራችን ሌብስና ዴንኩዋን የሚሆን ካኪ ሇስንቅ የሚሆን ዯረቃ ዯረቅ ነገርና መዴሀኒት እንዱሁም
በዚያ ጊዜ ሁኔታውን አይተን አስፇሊጊ ሆኖ የምናገኘውን ሁለ በዝርዝር ፅፇን እንሌክሌሀሇን ገንዘብ
እስከ በቃ ዴረስ ገዝተህ ገንዘቡ እንዲይጠፊብህ በኛ ስም ባንክ ሇማግባትም ሇምትገዛው ነገር ሁለ
ሇማውጣትም የሚያስችሌ የስሌጣን ወረቀት ያሌገባህ ነገር እንዲሇ ወይም ሇራስህ የምትጠይቀው ነገር
እንዲሇ አሁን ጠይቅ» አለ።

«የነገሩኝ ሁለ ግሌፅ ነው፤ ገብቶኛሌ። ሇራሴ የምጠይቀውም የሇ። ነገር ግን ከዚህ ሄዯው
ጦርነቱን ሇመምራት የሚመርጡት ሰፇር እኔ ከምቆይበት ከሱዲን ጋር መገናኛ መንገዴ የላሇው
እንዯሆነ የኔ መመሇሻ ችግር እንዲይሆን አስቀዴሞ ቢታሰብበት ዯህና ይመስሇኛሌ። እንዱያውም የሚቻሌ
ቢሆንማ፤ እኔም ባውቀው ዯስ ይሇኝ ነበር» አሌሁ። በጦርነት ጊዜ ‹የሚሄደበትን አስቀዴመው
ይንገሩኝ› ማሇት የማይገባ መሆኑ ትዝ ያሇኝ ከተናገርሁት በሁዋሊ ነበር።

«መቸም - ከኢለባቦርና ከከፊ አንደ ሳይሆን አይቀር፤ ታዱያ ሁሇቱም ከሱዲን ጋር


እንዯሚገናኙ ታውቃሇህ» አለኝ ትንሽ ፇገግ ብሇው።

«አዎ፤ ይገናኛለ»

«ዯመወዝህን እስከ መቼ ተቀብሇሀሌ?» አለኝ፤ ሁሇታችንም ሊጭር ጊዜ ዝም ብሇን ከቆዬን


በሁዋሊ።

77
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እስከ ጥቅምት ወር ዴረስ ዯብረ ማርቆስ ተቀብያሇሁ»

«የወሩ ስንት ነው?»

«አምሳ አምስት ብር ነው»

«ፃፌና ከህዲር እስከ ሚያዝያ አሁን እዚህ እንዱከፇሌህ ይዯረጋሌ» አለኝ» በመጋቢት ወር
መጀመሪያ ግዴም ስሇ ነበርን የሁሇት ወር ቅዴሚያ ተከፇሇኝ ማሇት ነው።

ያነሇት ከቀትር በሁዋሊ አቶ፥ ዮሀንስ አቡደና እኔ ከጉዋዯኞቼ ጋር፥ ወረቀቶቹ ሁለ ተጠናቅቀው
ተሰጥተውን አብረውን እንዱሄደ የታዘዙት «ያምሳ አሇቃ አበበ ወሌዯ ማርያም» ከክብር ዘበኞች
ጭፌሮቻቸው ጋር ጭምር ራስን ተሰናብተን፥ ከዚያ ብርዲም ሰፇር ወጥተውን አዯርን።

ምእራፍ አስራ ሁለት

ከደባርቅ እስከ ሱዳን


ራስ ከሰፇሩበት ተነስተን የተከዜን ሸሇቆ ዲገት ወጥተን ያዯርንበት ቦታ፥ ከዯባርቅ ግንባር እዲገቱ
አንዴ ትንሽ ወንዝ አጠገብ ነበር። ወንዝዋ እንዲቅምዋ ሸሇቆ ስሇ ነበራት ሰፇራችን ትናንቱን ባዯርንበት
ሰፇር አይን ሲታይ ሞቃት ነበር። ስሇዚህ ያሇፇው ላሉት የንቅሌፌ ውዝፌ ባሇቱ እንቅሌፌ ሊይ ተዯርቦ
ሁሊችንንም ከብድን በማግስቱ ጀንበር እስክትወጣ ዴረስ ከመሀከሊችን የነቃ አሌነበረም። ጥዋት ስንነሳ፥
የኔን ሁሇት በቅልች ያገሩ ላቦች ላሉት ሰርቀዋቸው አገኘን።

ከሁሇት በቅልዎቼ የኮረቻ በቅልየ «የግራጭ» መጥፊት ነበር በጣም ያሳዘነኝ። በዘመቻው
ካዬሁዋቸው በቅልዎች ሁለ አፋን ሞሌቼ «የግራጭን የመሰሇ አሌነበረም» ማሇት እችሊሇሁ።
በትሌቅነቱ ከሩቅ ሇሚያየው ፇረስ እንጂ በቅል አይመስሌም። እዴሜው እዬገፊ በመሄደ ጠጉሩ ጨርሶ
በመንጣቱ ከግራጭነቱ ወዯ ዲሇቻነት ቢሇወጥም በዴሮ መሌኩና ስሙ «ግራጭ» እንሇው ነበር። ግራጭ
በሙያውም ሆነ ባመለ ሌዩ ነበር። ገና ተጭኖ ወዯሚቀመጥበት ሰው ሲቀርብ አንገቱን ሰበር ጆሮዎቹን
እንዯ ተዯገነ ጣምራ ቀስት ወዯ ፉት ቅስር ጭራውን ነሰነስ አዴርጎ ሰሌፈን አሳምሮ ይቆይና
ከተቀመጡበት በሁዋሊ ሲሰግር፥ ቆሞ ስግሪያውን እዬተመሇከተ ሳይዯነቅ የሚሄዴ አሊፉ መንገዯኛ
አሌነበረም።

አንዴ ቀን ተቀምጨበት እያሰገርሁት ስሄዴ አንዴ እግሩ ሳር ሇብሶ በማይታይ ጉዴጉዋዴ ሊይ


ቆሞ እስከ ጉሌበቱ ጠሇቀና ወዯ ፉት ዯፊ ሲሌ እኔ ከሊዩ ተወርውሬ በፉት ወዯቅሁ። እንዱያ
እንዯወዯቅሁ ዘወር ብዬ ከሁዋሊየ ሲፇራገጥ አይቼ በሊየ እንዲይወዴቅብኝ ፇርቼ ነበር። ነገር ግን እሱ
እንዯ ምንም እዬተፌገመገመ እግሩን ከገባበት ጉዴጉዋዴ አውጥቶ እኔን አሳሌፍ ከሄዯ በሁዋሊ የተጎዲ

78
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጉሌበቴን እያሻሸሁ በወዯቅሁበት እንዯ ተቀመጥሁ ስሇ ነበርሁ ከሄዯበት ተመሌሶ ወጥቶ ሲያሸተኝ ቆዬና
ባጠገቤ ቆመ። ዘሪሁንም አንዴ ቀን ወሀ ሇማጠጣት ወዯ ወንዝ እዬጋሇበው ሲሄዴ ወዴቆ ሌክ እኔ
የወዯቅሁ እሇት እንዲዯረገው፥ ርቆ ከሄዯበት ተመሌሶ እሱን እያሸተተ ባጠገቡ መቆሙን ነግሮኛሌ።
እንዱህ የሚያዯርጉ በቅልዎች አይቼ አሊውቅም አይተናሌ ከሚኢለ ሰዎችም ሰምቼ አሊውቅ! በቅልዎች
ከሊያቸው የጣለዋቸውን ሰዎች ባይረግጡዋቸው እንዯኔ ጥሇዋቸው ይጋሌባለ እንጂ ከሄደበት
ተመሌሰው ቁስሇኞቻቸውን አያስታሙም፤ ይህ በተሇይ ሇግራጭ የተሰጠ ባህሪ ነበር።

ከዚህ ሁለ በሊይ ግራጭ እንዯ አንዲንዴ ቀን የጣሊቸው ባሇማእረጎች ቀን ጥልት፥ በኔ በዴሀው


እጅ እስኪወዴቅና መጨረሻ የሰረቀው ላሊ ያንጋሬ ወይም የላሊ መናኛ ነገር መጫኛ አጋሰስ
እስኪያዯርገው ዴረስ፥ ጥንት ከንግስተ - ነገስታት ዘውዱቱ ምኒሌክ ማሇፉያ የኮርቻ በቅልዎች አንደ
የሆነ በወርቅ ዴግዴግ መረሻት የሚያጌጥ ባሇማእረግ በቅል ነበር።

ጎጃም የንጉስ ተክሇ ሀይማኖት ሌጅ፥ ወይዘሮ ንግስት ተክሇ ሀይማኖት አዱስ አበባ ብዙ ቆይተው
ወዯ አገራቸው ሲመሇሱ፥ ንግስተ ነገስታት ዘውዱቱ ከሸሇሙዋቸው የክብር ሽሌማት መሀከሌ አንደ
የጭን በቅልዋቸው ግራጭ ነበር። ሁዋሊ፥ ወዘሮ ንግስት ተክሇ ሀይማኖት ግራጭን የዲንግሊ ተወሊጅ
ሇሆኑት ሹማቸው ሇ«ቀኛዝማች ሙለነህ ቦጋሇ» ሸሇሙዋቸው። ቀኛዝማች ሙለነህ ዲንግሊ በነበርሁበት
ጊዜ ሇኔ ሸጡሌኝ። ግራጭን ከኔ የሰረቀው ላባ፥ ወይም እሱ የሚሸጥሇት ሰው፥ የምን መጫኛ አጋሰስ
እንዯሚያዯርገው መቸም የሚያውቅ የሇ!

ባቶ ዮሀንስ አብደ በቅልዎች ሊይ በተዯራቢ ሉጫን ከተቻሇው የተፇውን እቃየን የኔ ሰዎችም


ወታዯሮችም እንዱይዙት ካዯርግን በሁዋሊ ሁለም ወዯ ዯባርቅ ጉዞ ሲጀምሩ አቶ ዘውዳ ወሌዯ ተክላና
እኔ፥ በቅልዎቹን ሇመፇሇግ፥ ወንዝዋን ተከትሇን ወዯ ታች ብዙ ከወረዴንና ከዚያም ሰፌረን ካዯርንበት
ማድ ወዯ ነበረች መንዯር ተመሌሰን ጠያይቀን ምንም ፌንጭ ካጣን በሁዋሊ እኛም አወራውን መንገዴ
ይዘን ወዯ ዯባርቅ ጉዞ ጀመርን።

ትንሽ እንዯ ሄዴን በወርደም በቁሙም እንዯ ኩዲዴ እርሻ በጣም ትሌቅ የሆነ ዙሪያውን
በቁጥቁዋጦ የተከበበ እርሻ አገኘን። አወራው ጎዲና ያን እርሻ እኩሌ ሰንጥቆ ነበር የሚያሌፌ። እርሻው
መሀከሌ እንዯ ዯረስን ዙሪያውን፥ ከከበበው ቁጥቁዋጦ የጥይት እሩምታ ወዯኛ ተተኮሰብን። ከያቅጣጫው
የሚተኮብንን የተኩስ ብዛት ስናት በብዙ ሰው መከበባችነን አወቅን። መጀመሪያ ሲተኮስብን በወዯቅንበት
እንዲሇን ትንሽ ቆይተን ከኛ ራቅ ብል አንዴ ትሌቅ የግራር ዛፌ ስሇ ነበረ ሄዯን እሱን እንዴንጠጋ
ተመካክርንና፥ በጉንብሳችን እዬሮጥን ሄዯን፥ ግራሩን በመሀከሊችን አዴርገን ሁሇታችንም ጀርባችንን ወዯ
ግራሩ ፉታችን ወዯ ጠሊቶቻችን አዴርገን ተኝተን እንታኮስ ጀመር። ካቶ ዘውዳም ከኔም ፉት ሇፉትና
ከግራ ቀኛችን የሚተኮሰው ጥይት ስሇ እኛ ባሇንበት ሳይዯርስ ካጠገባችን ራቅ ብል እርሻቸውን ሲፇሌስ
ስሊዬን ጠሊቶቻችን ሁለ የሚተኩሱት ባሮጌ ጠመንጃ መሆኑን ተረዲን። ባንፃሩ የኔ ጠመንጃ ረዥም

79
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇበን ያቶ ዘውዳ ረዥም ምኒሽር ስሇ ነበሩ፥ እኛ የምንተኩሰው ጥይት ጠሊቶቻችነን አሌፍ ይሄዲሌ።
ስሇዚህ ሌባችን እንዯ መርጋት አሇና ጥይት እየቆጠብን እንዴንተኩስ ተመካከርን።

ከዚያ በሁዋሊ እንዯ ተመካከርነው «የጠሊቶቻችነን ተኩስ በተኩስ እንመሌስ» እነሱ ሲተኩሱ
አዴፌጠን እንቆይና ከቁጥቁዋጦው ብቅ ያሇ ሰው ስናይ እንተኩስበታሇን፤ እንዯ ገና ወዯ ቁጥቁዋጦው
ተመሌሶ ጉዋዯኞቹ ጭምር ሲተኩሱብን አዴፌጠን እንቆያሇን። እንዱህ ወዯ እርሻው ብቅ ሲለ ተኩሰን
እዬመሇስናቸው እቁጥቁዋጦው ውስጥ ሆነው ሲተኩሱ አዴፌጠው እዬቆዬን፥ ስንተኩስ ረዥም ጊዜ ካሇፇ
በሁዋሊ እግዚአብሄር ከገባንበት ወጥመዴ ሉያወጣን ሲፇሌግ በክፌሌ በክፌሌ እዬሆነ ከሚጉዋዘው ዘማች
ሰራዊት አንዴ ክፌሌ አውራውን ጎዲና ይዞ ከሁዋሊ ብቅ አሇ። እሱን ስናይ አስፇርቶን ከነበረው አዯጋ
ሇመዲናችን እርግጠኞች ሆንና በጣም ዯስ አሇን። ሰራዊቱ ሳይዯርስ በነበርንበት ሁኔታ እንዲሇን ቀኑን
ሙለ ብንውሌ ኖሮ፥ ምንም እንኩዋ እዬቆጠብን ብንተኩስ ጥይታችን ማሇቁ ስሇማይቀር እኒያ የከበቡን
ሰዎች እኛን ገዴሇው ወይም ከነነስፊችን መሳሪኢያችነን መግፇፊቸው አይቀርም ነበር። መቸም የነሱ
አሊማ እንዱህ በተናጠሌ የሚያገኙዋቸውን ዘማቾች ገዴሇውም ይሁን ከነነስፊቸው መሳሪያቸውን
መግፇፌ ነው።

ዘማቹ ሰራዊት በብዛት መምጣቱን ሲያዩ ከብበው ይተኩሱብን የነበሩ ሰዎችም ዯብዛቸው ስሇ
ጠፊ፥ ከሰራዊቱ ጋር ተጨምረው ወዯ ዯባርቅ ተጉዋዝን። ዯባርቅ አጠገብ በሰፇርንበት የጡት፥ አባቴን
«ቀኛዝማች አሇማየሁ ሀይሇ ማርያምን» አግኝቼ የበቅልዎቸን መሰረቅ ስሇ ነገርሁዋቸው ከነጋዳዎች
ይሁን ከዘማቾች ሁሇት በቅልዎች አስገዙሌኝና ሰራዊቱ «የባህር ዲርን» መንገዴ ይዞ ጉዞውን ሲቀጥሌ
አቶ ዮሀንስና እኔ ከሰዎቻችን ጋር ወዯ ዲባት አመራን።

ዲባት አገር ጠባቂ ሆነው ሇቆዩት፥ ሇዯጃዝማች አያላው ሌጅ (ሇፉታውራሪ መርሶ) ከራስ እምሩ
የተፃፇሊቸውን ወረቀት ሰጥተን ሁሇት፥ ይሁን ሶስት ቀን ያክሌ እዚያው ቆዬን። ዲባት በቆየንበት ጊዜ
ባቶ ዮሀንስ አብደ መሪነት «ራማ» የተባሇው የጣሉያኖች የመሳሪያና የስንቅ ማከማቻ ሲመታ
ተማርከው ወዯዚያ (ወዯ ዲባት) ስሇ ተሊኩት ጣሉያኖች ጠይቀን ክንደን በጎራዳ ተመትቶ የነበረው
ቁስሇኛ ጣሉያን በቁስለ ሽታ ምክንያት ከጉዋዯኞቹ ጋር ባንዴ ቤት ሉቀመጥ ባሇ መቻለ ሇብቻው
ዴንኩዋን ተተክልሇት በተቀመጠበት የጣሉያን አይሮፕሊን መጥቶ በቦምብ ገዴልት መሄደንና ላልች
በኢትዮጵያ አይሮፕሊን ወዲዱስ አበባ መሊካቸውን ሰማን። እንዱሁም እዚያው ዲባት እንዲሇን አንዴ
የኢትዮጵያ አይሮፕሊን መጥታ አረፇች። ነጂዋ «ዯምሴ ኃይላ» የተባሇ የትምህርት ቤት ጉዋዯኛየ
ነበር። ያችን አይሮፕሊን ከማረፉያው ወዯ ዲር አወጥቶ አቁሞ ከጣሉያን ቦምብ ሇመሰወር፥ ያካባቢውን
ቁጥቁዋጦ እንዴትመስሌ ቅጠሌና ቁጥቁዋጦ እያስቆረጠ አሌብሶ ተዋት። ዯምሴ ያን ሁለ ካዯረገ በሁዋሊ
ከተማ ገብቶ ከማረፈ፥ አንዴ የጣሉያን አይሮፕሊን መጣና «ቀኝ ወይ ግራ» ሳይሌ ያሇችበትን አስቀዴሞ

80
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዲወቀ ሁለ (አውቆም ሉሆን ይችሊሌ) በቀጥታ ወዯስዋ ሄድ አመዴ አዴርጎዋት ላሊ ነገር ምንም
ሳይነካ ወዯ መጣበት ተመሇሰ።

የዯጃዝማች አያላው ሌጅ፥ ስንቅ እየተሰንዲ እንዱሊክበት ከራስ የተቀበለትን ሰሊሳ ሺህ (30.000)
ጠገራ ብር ስሇ ሰጡት ያን ጭነን ወዯ ጎንዯር ተጉዋዝን። ጎንዯር ሇቤገምዴርና ሇሰሜን የትምህር
ሚኒስቴር ሹም የነበሩት አቶ (ሁዋሊ ፉታውራሪ) «ዲባ ወላ» ተቀብሇው፥ አቶ ዮሀንስንና እኔን
እንዱዑኢያውም እቤታቸው በምቾት አስቀምጠው ዯህና አዴርገው ሲያስተናግደን ሰነበቱ። ጎንዯር በገባን
ማግስት አቶ ዮሀንስና እኔ ወዯ ጳጳሱ ወዯ፥ ወዯ አቡነ አብርሃም ሄዯን ከራስ እምሩ የተፃፇሊቸውን
መሌእክት ሰጥተውናቸው ከተመሇከቱት በሁዋሊ «ነገ እቤተክርስቲያን ስሇምውሌ እስቲ - ሇሁለም ነገ
ወዯ ማታ ተመሇሱ» አለ የቅርታና የማመንታት መሌክ እዬታየባቸው። ጊዜው «አቢይ ፆም» ስሇ ነበረ
እቤተክርስቲያን መዋሊቸው እውነት ሉሆን ይችሊሌ። በማግስቱ ወዯ ማታ እንዯ ተቀጠርነው ወዯ
አባታችን ቤት ሄዯን አገኘናቸው።

«ይህን ጉዲይ - ትናንት እናንተ ከሄዲችሁ ጀምሬ፥ አውጥቼ አውርጄ፥ አገሊብጨ፥ ባየው አስቸጋሪ
ሆኖ አገኘሁት» አለ ካስቀመጡን በሁዋሊ። «እንዳት ነው አስቸጋሪ የሆነብዎ አባታችን?» አሊቸው
ዮሀንስ። «አያችሁ ሌጆቼ ይህ የመንግስት ገንዘብ በኔ እጅ መሆኑን ብዙ ሰው ያውቃሌ። ስንቅ
ተሰናዴቶ ወዯ ጦርነቱ ግንባር የሚሊክበት ጊዜ ሲዯርስ ሲዯርስ ሇማሰናዲቱም ሇማስጫኑም «ይረደኛሌ»
ብዬ ሊሰብሁዋቸው ነጋዳዎችና አንዲንዴ ታሊሊቅ ሰዎች እንዱያውም እኔ ራሴ ነኝ የነገርሁዋቸው። እና
መቸም አሁን - ራስ እምሩ በጦርነቱ ዴሌ ሆነው መመሇሳቸውን ከማንም የበሇጠ እናንተ
ታውቃሊችሁ። በተንቤን ግንባርም፥ እነራስ ካሳ በርግጥ ዴሌ መሆናእችው እዚህ ከታወቀ ቆይተዋሌ።
ጃንሆይም ዴሌ ሆነው መመሇሳቸው በሰፉው ይነገራሌ። ታዱያ፤ እግዚአብሔር አያዴርገው እንጂ
ጣሉያኖች ዴሌ አዴርገው የመንግስቱን ስሌጣን ከያዙ ‹አንተ ዘንዴ የተቀመጠውን የመንግስት ገንዘብ
አምጣ› ቢለኝ ምን እመሌሳሇሁ? ብርቱ ችግር ይዯርስብኛሌኮ! መቸም እኔ እችግር ውስጥ ብገባ
እንዯማትወደ አውቃሇሁ። ራስ እምሩም ቢሆኑ እኔ እንዴቸገር የሚፇሌጉ አይመስሇኝም!» አለ ጳጳሱ።

«የላሊውን ግንባር ሁኔታ አሊውቅም እንጂ ራስ እምሩኮ አሁን አባታችን እንዲለት ዴሌ ሆነው
ጦርነቱ አሌቆ መመሇሳቸው አዯሇም። እስከ ዛሬ የተዯረገው ጦርነት ጠሊት ምሽጉን አጠናክሮ መሽጎ
እስከ ምሽጉ ዴረስ የወታዯር የመሳሪያና የስንቅ ማመሊሇሻ መንገድች ሰርቶ ባሰናዲቸው ሇሱ ምቹ በሆኑ
ቦታዎች ሊይ በመሆኑ ሰው ስሇ ተጎዲባቸው ሇሰራዊታቸው ምቹ በሆነ ቦታ ይዘው እዚያ ሊይ መሸገው
ጠሊትን ከመሸገው ምሽግና ከሰራው የመንገዴ ሩቅ በሆነ ሇሱ በማይመች ቦታ ሇመዋጋት ወዯ ሁዋሊ
ማፇግፇጋቸው ነው። የኛም መሌእክት የሚቀጥሇው ጦርነት በዚህ ገንዘብ ሇወታዯር ትጥቅና ስንቅ
መዴሀኒት ገዝተን ሇማቅረብ ነው» አሌሁ ራስ የነገሩኝን ከሞሊ ጎዯሌ ዯግሞ። «እኛም የምንመኘው
እኛም ቀን ከላት አምሊካችነን በፆምና በፀልት የምንማጠነው መጨረሻ ዴለ የኛ እንዱሆን ነው። እኛ

81
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እግዚአሄር የሚያዯርገው አይታወቅምና የፇራነው የማንወዯው ክፈ ነገር የዯረሰ እንዯ ሆነ እኔ ምን
እሆናሇሁ? ነው የምሊችሁ።»

«መቸም ገንዘቡን ሊባታችን የሰጡ ራስ እምሩ መሆናቸው የታወቀ ነው። አሁን ያን ገንዘብ ሇኛ
እንዱያስረክቡን ማህተማቸው የታተመበትና ፉርማቸው የተፇረመበት ፅሁፊቸው ዯርሶዎታሌ። ራስ
እንዯፃፈሌዎ ሇኛ ሇሚያስረክብንም አስፇርመው ነው። ስሇዚህ በኛ አስተያየት ባዯራ ያስቀመጡትን
ገንዘብ ሇባሇገንዘቡ መመሇስ ምንም ችግር የሚያመጣብዎ አይመስሇንም» አሇ አቶ ዮሀንስ።

«ነገሩ ሁለ እንዱህ አንተ እንዲሌኸው ቀሌሊ ቢሆንማ እንዳት መሌካም ነበር! ግን ሊንተ
መሰሇህ ቀሊሌ አዯሇም። እስቲ አስቡበት፤ እኔም አስበበታሇሁ። አሁን የቀጠርሁዋቸው እንግድች
የሚመጡበት ጊዜ ስሇ ዯረሰ ሂደ» ብሇው አሰናበቱን።

የጃንሆይን ዴሌ መመሇስ ጎንዯር እስክንዯርስ ዴረስ አሊወቅንም ነበር። ከሰማን በሁዋሊ ግን


የጳጳሱን አነጋገርና ጠቅሊሊ ሁኔታቸውን ስናይ ገንዘቡን እንዯማይሰጡን ሁሇታችንም ገመትን። ይሁን
እንጂ «አስብበታሇሁ» ብሇው ስሇ ነበረ፥ ከቤተክርስቲያ የሚመሇሱ ከቅዲሴው በሁዋሊ በዘጠኝ ሰአት
አካባቢ መሆኑን አረጋግጠን ቁርጡን ሇማወቅ በማስቱ ቀዯም ብሇን ሄዯን፥ ከግቢያቸው አጥር ውጭ
ቆመን ስንጠብቃቸው በበቅል ተቀምጠው በርከት ያለ ሰዎች አጅበዋቸው መጡ። አጥሩን ገብተው
ከበቅል እንዯ ወረደ፥

«ትናንት ተነጋግረን ጨርሰን አሌነበረም? ዛሬ ሌታዯርጉ መጣችሁ? ላሊ የምታነጋግሩኝ ጉዲይ


አሊችሁ?» አለ፥ አጅበዋቸው ከመጡት ሰዎች መሀከሌ እዯጅ በቆምንበት።

«ሇዚያው ሇተሊክንበት ጉዲይ ነው እንጂ ላሊ ጉዲይስ የሇንም። ትናንት አባታችን ‹ሊሰብበት›


ብሇው አሰናብተውን ስሇ ነበረ አስበው የወሰኑትን እንዱነግሩን ነው ዛሬ የመጣን» አሊቸው ዮሀንስ።

«አስቤ የወሰንሁትን ትናንት ነግሬያቸዋሇሁ፥ ላሊ አስቤ የምወስነው ነገር የሇም። እና - እባካችሁ


እዚህ እዬተመሊሇሳችሁ አታስቸግሩኝ» አለና ዘበኛቸውን ጠርተው «እነዚህን ሁሇት ሰዎች እዚህ
እንዲታዯርሳቸው! ዲግመኛ የመጡ እንዯሆነ ወዱያ ማሇት ነው! እንዳት ያለ - አስቸጋሪዎች ናቸው!»
ብሇው እያጉረመረሙ ወዯ ቤታቸው ሲገቡ ዘበኛው ብቻ ሳይሆን እዚያ ከነበሩት ሰዎች «ሂደ፤ ወግደ፤
ሂደ እንጂ ምን ታዯርጋሊችሁ? የተባሊችሁትን አሌሰማችሁም?» የሚለን ስሇበዙ እዬተጉረምን ወዯ
ማረፉያችን ተመሇስን። ጳጳሱ እዚያ ባዯባባይ ያን ያክሌ የማያስፇሌግ ነገር ከመናገር፥ ሁሇታችንን ይዘው
ገብተው ውሳኔያቸውን ነግረው በጭዋነት ሉያሰናብቱን ሲችለ እንዱያ ያሇ «እዩሌኝ ስሙሌኝ!»
አዴራጎት ያዯረጉበትን ምክንያት ሇጊዜው አቶ ዮሀንስም እኔም ሌናስተውሇው አሌቻሌንም ነበር።
ጣሉያኖች ኢትዮጵያን ከያዙ በሁዋሊ እኒያ ጳጳስ፥ የኢትዮጵያ «ፓትርያርክ» ሆነው ተሾሙ።

82
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ራስ እምሩ ሇዯጃዝማች አያላው ሌጅም ሇጳጳሱም የፃፈሊቸው ወረቀቶች በተዯፇርኑ አንቬልፖች
ሆነው ስሇ ተሰጡንና በቃሌም ስሊሌነገሩን በሁሇቱ ሰዎች እጅ የነበረው ገንዘብ ምን ምን ያክሌ እንዯ
ነበረ አናውቅም ነበር። የዯጃዝማች አያላው ሌጅ ገንዘቡን ሲሰጡን የተከቡበትን ሰነዴ ስሊሳዩን 30.000
ብር መሆኑን ተረዲን። ነገር ግን፥ በጳጳሱ እጅ የቀረው ገንዘብ ምን ያክሌ እንዯ ሆነ አሊውቅነውም።

ጃንሆይ ዴሌ ሆነው መመሇሳቸውና ጣሉያኖች ያሊንዲች ተቃውሞ አዱስ አበባ ሇመግባት


ከያቅጣጫው በመጉዋዝ ሊይ መሆናቸውን ጎንዯር እዬተጋነነ ስሇ ተወራ እዚያ ከነበሩት ሹማምት
አንዲንድቹ ወዯ ሱዲን ሇመሸሽ መሰናዲታቸውን ሰማን። መጀመሪያ ከሄደት መሀከሌ አሁን
የማስታውሳቸው የጎንዯር ከንቲባ የነበሩት፥ ከንቲባ ዯስታ ምትኬ እና የጎንዯር ባንክ ሹም የነበሩት አቶ
ተክላ ሮሮ ነበሩ። ከነሱ ጋር በሽሬ ግንባር የኢትዮጵያን የጦር ሰራዊት ሇመርዲት ተሌኮ ጦርነቱ ቶል
ስሊሇቀ ከጎንዯር ወዲገሩ የሚመሇስ አንዴ የሱዲን «የቀይ መስቀሌ» ቡዴን ነበር። ሇቡዴኑ ያስተዲዯር
አሊፉና ወዱያውም እንዯ አነጋጋሪ ሆኖ የሚረዲ ሱዲን ተምሮ እዚያው ብዙ ጊዜ የቆየ፥ አቶ ሀብቴ ዯስታ
የሚባሌ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነበር። ሀብቴ ዯስታ ሱዲን በተሇይ ካርቱም በቆዬሁበት ጊዜ፥ እዚያ ከነበሩት
ኢትዮጵያውያን ጋር ያስተዋወቀኝና ችግር በገጠመኝ ቁጥር ስጠራው ይዯርስሌኝ የነበረ ወዲጄ ነበር።

ጎንዯር አንዴ ሳምንት ያሌሞሊ ጊዜ ካሳሇፌን በሁዋሊ አቶ ዲባ ወላን አመሰግንና ተሰናብተን እኔ


አጭሩ ዘሪሁንን ሱዲን አብሮኝ እንዱቆይ አቶ ዘውዳ ወሌዯ ተክላን እዚያ ዴረስ ሸኝቶኝ ከናቶ ዮሀንስ
ጋር እንዱመሇስ ይዤ፥ ከላልች ጉዋዯኞቼ ጋር እዚያው ጎንዯር ተሰነባብተን ከሚሸሹት ሹማምትና
ከቀይ መስቀሌ ሰዎች ጋር በጭሌጋ በኩሌ ተጉዘን ኢትዮጵያና ሱዲን ወሰን ዯረስን። ወሰኑ በኢትዮጵያ
በኩሌ «መተማ» በሱዲን በኩሌ «ገሊባት» ናቸው። መተማና ገሊባት በበጋ ወራት በሚዯርቅ ወንዝ
የተሇያዩ ከመሆናቸው በቀር እንዯ አንዴ ከተማ የሚቆጠሩ ናቸው።

እወሰኑ እንዯ ዯረስን የሱዲን ቀይ መስቀሌ ሰዎች ተሻግረው ገሊባት ገሊባት ሲሰፌሩ እኛ
ኢትዮጵያውያን መተማ፥ ከከተማው አጠገብ አርፇን፥ ወዯ ሱዲን ክፌሌ ሇመሻገር ገሊባት የነበሩትን
እንግሉዛዊ የወረዲ ገዢ ፇቃዴ ጠዬቅን። ወዱያው መሳሪያ የያዙት በኢትዮጵያ ክፌሌ (መተማ)
ቆይተው፥ እኛም የያዝነውን መሳሪያ እዚያ ትተን መሻገር የምንችሌ መሆናችን ስሇተነገረን፥ ያምሳ አሇቃ
አበበ ወሌዯ ማርያምን ከጭፌሮቻቸው ጋር መተማ ትተን ዮሀንስ ከአንዴ ሌጅ ጋርና እኔ ከዘሪሁን ጋር
ጀላያችነን፥ ተሻግረን ገሊባት ሰፇርን። ያምሳ አሇቃ አበበ፥ አቶ ዘውዳና ላልችም ቢሆኑ መሳሪያ ይዘው
መሻገር ተከሇከለ እንጂ ጀላያቸውን ማሻገር ስሊሌተከሇከለ ወዯ «ገዲሪፌ» እስክንሄዴ ዴረስ
አሌተሇዩንም፤ አብረን ነበርን።

እንግሉዛዊው አገረ ገዢ ማታ ሇራት ጋብዘውን ነበር። የመሄጃው ጊዜ ከመዴረሱ በፉት፥ አቶ


ዮሀንስ ወዯ ዴንኩዋን ጠርቶኝ ስሄዴ ከግራጫ ብርዴ ሌብሱ በቀጭኑ የቆረጠውን እዬጠቀሇሇ ይሰፊሌ።

83
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«የምን ጥብጣብ ነው የምትሰፊው?» አሌሁት።

«ና ተቀመጥ» አሇና፥ ያን ቀጠን አዴርጎ በረዢሙ የሰራውን ጥብጣብ የሚመስሌ ነገር ባጭር
ባጭር ቆርጦ፥

«በሌ ከላሊው ወገን እንዱህ እያዯረግህ ስፊ!» ብል ቁራጮቹን ባንዴ ወገን በኮቱ ትከሻ ሊይ
እያጋዯመ በተራ አስቀምጦ ይሰፊ ጀመር። እኔም የሰጠኝን ቁራጮኝ የሱን እያዬሁ በሁሇተኛው የኮቱ
ትክሻ ሊይ ሰፊሁ። በዯረቱ ኪስ ሊይም አንዴ ነገር ሰፊ፥ ከዚያ ያን የብርዴ ሌብስ ቁራጮች በትክሻዎቹና
በዯረቱ ኪሱ ክዲን ሊይ የተሰፊበት ኮት ሲሇብስ የወታዯር ሹም ሆነ።

«የምን ምሌክት ነው ይሄ?» አሌሁት።

«ይህ የምን ምሌክት መሆኑን አታውቅም?»

«አሊውቅም» አሌሁት። እውነቴን ነበር፤ እንኩዋንስ ያን ጊዜ፥ ዛሬም የወታዯርን ሹማምንት


«የመቶ አሇቃ ሻምበሌ ሻሇቃ፥ ወ.ዘ.ተ» እያለ ሲጠሩዋቸው ካሌሆነ መሇያ ምሌክቶቻቸውን ሆነ ብዬ
ስሊሊጠናሁዋቸው አሊውቃቸውም።

«ይህ የሻሇቃ ምሌክት ነው» አሇኝ።

«እና አሁን አንተ ራስህን የሻሇቃ አዴርገህ መሾምህ ነው?»

«ታዱያስ! የሻሇቃነት ይበዛብኛሌ?»

« ‹ያሌሆንኸውን› ማሇቴ ነው እንጂ፥ እሱስ ባያንስህ አይበዛህም!»

እንዱያ እየተቀሊሇዴን ስንሳሳቅ ቆይተን ወጥቼ ከዴንኩዋኔ በራፌ እንዯ ተቀመጥሁ፥ «‹ጊንጥ»
የሚለዋት መርዘኛ ነገር ነዴፊ ከተቀመጥሁበት አዘሌሊ አስነሳችኝ። ጩኸቴን ሲሰሙ ዮሀንስም፥ እዚያ
የነበሩት ላልች ሰዎችም እዬሮጡ መጥተው «መርዝዋ በሰውነትህ ሁለ እንዲይሰራጭ የነዯፇችው ገሊህ
ዙሪያውን መበጣት አሇበት» ብሇው በጥተውኝ ሄደ። በዚያ ምክንያት እንኩዋንስ አገረ ገዢው ግብዣ
ሌሂዴ ላሉቱን እንቅሌፌ ባይኔ ሳይዞር «እግዚኦ» እንዲሌሁ አዴሬ በማግስቱ ነበር የተሻሇኝ። ዮሀንስ
ግን፥ የሻሇቃ ሌብሱን ሇብሶ ሄድ በክርብር ራቱንም፥ ውስኪውንም ሲጋበዝ ካመሸ በሁዋሊ የሄዴንሇትን
ጉዲይ ሊገረ ገዢው ነግሮ፥ ገዲሪፌ ዴረስ የሚያዯርሰን ካሚዮን አሳዝዞ፥ በዯስታ እዬፇነጠዘ ተመሇሰ።
በማግስቱ ይሁን በሳሌስቱ ሁሇቱን በቅልዎቼን እዚያው ገሊባት በውዴ ዋጋ፥ ያውም በሱዲን ብር
ሸጥናቸው። ከዚያ ዘሪሁንና እኔ፥ ካቶ ዘውዳ ወሌዯ ተክላ ካምሳ አሇቃ አበበ ወሌዯ ማርያምና
ከጭፌሮቻቸውም ተሰናባብተን ካቶ ዮሀንስና ከተከተሇው ሌጅ ጋር በታዘዘሌን ካሚዮን ገንዘባችንን ጭነን
ወዯ ገዲሪፌ ሄዴን። የቀይ መስቀሌ ሰዎችም በራሳቸው መጉዋጉዋዣ እስከ ገዲሪፌ አብረውን ሄዯው ወዯ

84
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ካርቱም በባቡር ጉዞዋቸውን እስኪቀጥለ እዚያው ገዲሪፌ ሆቴሌ ይዘው አረፈና አቶ ሀብቴ ዯስታ፥ እኛን
ወስድ «አቶ ዘውዳ» (ያባታቸውን ስም ረሳሁ) ከሚባለ ኢትዮጵያዊ ጋር አገናኘን።

አቶ ዘውዳ ገዲሪፌ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን ጉዲይ እንዱፇፅሙ በእንግሉዝ ባሇስሌጣኖች


ተሹመው በዚያ ስራ ረዢም ጊዜ የቆዩ ነበሩ። በዚያ ጊዜ፥ ገዲሪፌ ይኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያውያን፥
ከፌተኛ ስራ የነበራቸው በመጠኑ ቢሆኑም በጉሌበት ስራ የሚተዲዯሩ ሴቶችና ወንድች በጣም ብዙ
ነበሩ። ከወንድችም ይሌቅ ሴቶች! ታዱያ አቶ ዘውዳ የሁለንም ገመና እንዯያመለ ሸሽገው የሚኖሩ
ወገኖቻቸውን ወዲጅ በመሆናቸው እዚያ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ሁለ የሚወደዋቸውና
የሚያከብሩዋቸው ነበሩ።

አቶ ዘውዳ እግቢያቸው ውስጥ አንዴ የተሇዬ ቤት ሰጥተውን እዚያ አረፌን። በማግስቱ አቶ


ዮሀንስና እኔ ወዯ ሱዲን ስሇ ተሊክንበት ጉዲይ ሇመነጋገር ወዯ አገረ ገዢው ከመሄዲችን በፉት የተጎሳቆሇ
ሰውነታችነን እና ሌብሳችነን ስናፀዲዲ እንዴንውሌ እንዱሁም የጎዯሇንን ሌብስ እንዴንገዛ ተመካከርን እሱ
«ቀዯም ብዬ የምዯርስበት ሰው አሇ» ስሊሇ ተሇያይተን እኔ ወዯ ገበያ ሄዴሁ። ከዚያ ሀብቴ ዯስታ
የምፇሌገው ነገር በሚገኝበት እያዞረ የምገዛውን ከገዛሁና ጠጉሬን ካስተካከሌሁ በሁዋሊ ምሳየን እሱ
ባረፇበት ሆቴሌ ጋብዞኝ በሌቼ፥ አመሻሽ ሊይ አቶ ዘውዳ ግቢ አጠገብ አዴርሶኝ ተመሇሰ።

«ምሳህን በሊህ?» አሌሁት ዘሪሁንን እንዯ ገባሁ የያዝሁትን እቃ ሲቀበሇኝ።

«እኔስ ስጠብቅህ ቆይቼ ስትቀር ጊዜ በሊሁ፤ አንተ ጦምህን ዋሌህ እንጂ! ሇመሆኑ በጤንነት
ነው ይህን ያክሌ የዋሌህ?» አሇኝ።

«ዯህና ነኝ ምሳየን ካቶ ከብቴ ጋር በሌቼ እዚያው ስንጫወት ቆዬን፤ ዮሀንስ አሌተመሇሰም?»


አሌሁት።

«አቶ ዮሀንስማ ጥዋት ከወጣችሁ በሁዋሊ ትንሽ ቆይተው በመቶቢሌ ተመሌሰው ገንዘቡን
ወዳት እንዯ ወሰደት አሊውቅም ይዘው ሄዯው እንዯ ገና መጡና እዚህ ከባሇቤቱ ጋር ሲነጋገሩ ቆይተው
ወዯ ገሊባት መሄዳንና ነገ የምመሇስ መሆኔን ሇሀዱስ ንገረ በሇውኝ ሄደ» አሇኝ።

ምን እንዯ ዯረሰ ማወቅ ስሊሌቻሌሁ፥ ግራ ገብቶኝ ዝም ብዬ ከቆየሁ በሁዋሊ ወዯ አቶ ዘውዳ


ሄጄ ዮሀንስ ምን ነግሮዋቸው እንዯ ሄዯ ጠዬቅሁዋቸው።

«አገረ ገዡ (ዱስትሪክት ኮሚሽነር) መስርያ ቤት ሄድ፥ ጣሉያኖች መተማን ሇመያዝ በግስጋስ


ሊይ መሆናቸውን ስሇ ነገሩት እዚያ እዱቆዩ የተዋቸው ወታዯሮች ከነመስሪያቸው በጣሉያኖች
እንዲይማረኩ፤ ሰዋራ ቦታ አስይዞዋቸው ነገ የሚመሇስ መሆኑን ነግሮኝ ሄዯ» አለኝ።

85
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ሇስራ ያመጣነውን ገንዘብ በኦቶሞቢሌ ጭኖ መውሰደን ከኔ ጋር ያሇው ሌጅ ነገረኝ፤ ወዳት
ወስድ እንዲስቀመጠው የነገረዎ ነገር አሇ?» ብሊቸው፤

«ስሇ ገንዘቡ የነገረኝ ነገር የሇም፤ ወዯ ገሊባት የሚወስዯው ካሚዮን እውጪ ቆሞ ይጠብቀው
ስሇ ነበረ በታም ቸኩል ነበር። እኔን ያነጋገረኝ ከግዛቱ መስሪያ ቤት በቀጥታ እንዯ መጣ ነበር። ስሇዚህ
ምናሌባት ገንዘቡን እዚያ አስቀምጦት እንዯሆን?» አለኝ አቶ ዘውዳ።

አቶ ዮሀንስ በማግስቱም በሳሌስቱም አሌተመሇሰ። ባራተኛው ቀን አቶ ዘውዳን ወዯ ግዛቱ


መስሪያ ቤት እንዱወስደኝ ሇመንሁዋቸውና ወስዯው ከዋናው ፀሀፉ ካቶ «ሚካኤሌ በኪት» ጋር
አገናኙ። አቶ ሚካኤሌ በኪት፥ ከኢትዮጵያውያን ወሊጆች ሱዲን ውስጥ ተወሌዯው እዚያው እዬተማሩ
አዴገው ከዚያ ከፌተኛ ዯረጃ ከሚናገሩ ዯግ ሰው ነበሩ። አማርኛ መናገር ብቻ ሳይሆን እንዱያውም
ከሚናገሩት የበሇጠ ማንበብ መፃፌ የሚያውቁ ነበሩ። አቶ ዘውዳ ማን መሆኔንና ሇምን ስራ ወዯ ሱዲን
እንዯ ተሊክሁ፥ እኔ ያስጠናሁዋቸውን ገሌፀው ካስተዋወቁኝ በሁዋሊ አቶ ዮሀንስ ከሶስት ቀን በፉት
ገንዘብ እነሱ ዘንዴ አስቀምጦ ሄድ እንዯሆነ ሲጠይቁዋቸው ማስቀመጡን አረጋገጡሌን።

ገንዘቡ የራስ እምሩ መሆኑንና ያን ገንዘብ በስማቸው ባንክ ሇማግባትም እያወጣሁ ያዘዙኝን ስራ
ሇመስራትም ሇኔ ሙለ ስሌጣን የሰጡበትን ፅሁፌ አሳይቼ «አቶ ዮሀንስ ከወታዯሮች ጋር እኔን ሱዲን
አዴርሶ ከመመሇስ በቀር ገንዘቡን ሇማስቀመጥም ሇማውጣትም ስሊሌታዘዘ እሱ የዘገዬ ወይም ጭራሽ
ያሌተመሇሰ እንዯ ሆነ፥ ገንዘቡን ሇኔ ማስረከብ አይቻሌም ወይ?» አሌሁዋቸው።

«አቶ ዮሀንስ ገንዘቡን ያስቀመጡትም ዯረሰኝ የተቀበለትም በስማቸው ስሇሆነ ሳያስቸግር


አይቀርም። ግን ሇሁለም አገረ - ገዢውን እናነጋግራቸው» አለና ፅሁፈን እዚያው ራሳቸው ወዯ
እንግሉዝኛ ተርጉመው በመኪና አስመትተው ወረቀቱንም እኔንም ይዘውን ወዯ አገረ - ገዢው ገቡና
ከፅሁፈም ከኔም እንዯ ተረደት ዯህና አዴርገው ገሇፁሊቸው።

«አቶ ዮሀንስ በሄደበት ቀን ማግስት እንዯሚመሇሱ ነበርኮ የነገሩን፤ አሌተመሇሱም?» አለ አገረ


- ገዡ።

«ከሄዯ አራተኛ ቀን ነው፤ ግን አሌተመሇሰም» አሌሁዋቸው።

«የተገናኘን እሇት ስንነጋገር ጣሉያኖች መተማን ሇመያዝ መቅረባቸውን ስሇነገናቸው መሳሪያ


የያዙ ወታዯሮች መተማ ትቼ መጥቻሇሁና ጣሉያኖች እንዲይማርኩዋቸው ቢቻሌ ወዯ ገሊባት
እንዱሻገሩሌኝ ያሇዚያም ሰዋራ ቦታ ይዘው እንዱቆዩኝ አዴርጌ ቶል እመሇሳሇሁ ብሇው ነበር የሄደ።
ታዱያ ጣሉያኖች መተማን ይዘዋሌ። ምናሌባት ወታዯርቶችንም እሳቸውንም ይዘዋቸው እንዯሆነ እስቲ

86
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ገሊባት በስሌክ ሌጠይቅ» ብሇው አገረ - ገዡ ከገሊባት አገረ - ገዢ ጋር ሳይያዙ የሸሹ መሆናቸውንና
በተሇይ ስሇ ዮሀንስ ግን የሰሙት ነገር አሇመኖሩን እንዲስታወቁዋቸው ነገሩን።

«እኔ ወዯዚህ የተሊክሁት አዛዣችን ራስ እምሩ ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ስሇ ወሰኑ፥ ሇወታዯሮቻቸው


ሌብስ መዴሀኒትና አንዲንዴ አስፇሊጊ የሆኑ ነገሮች ሇመግዛት ነው። ታዱያ ይህን ሇማዴረግ አንዴችሌ
ዮሀንስ ቶል ያሌተመሇሰ እንዯ ሆነ ገንዘቡን ሇኔ ሇማስረከብ ምን የሚያስቸግር ነገር አሇ?»
አሌሁዋቸው። ከዚያ ዮሀንስ ገንዘቡን መስሪያ ቤቱ እንዱያቀምጥሇት የጠዬቀበትን ፅሁፌና ከመስሪያ ቤቱ
የተቀበሇውን የዯረሰኝ ግሌባጭ አስመጥተው ከተመሇከቱ በሁዋሊ፥

«አቶ ዮሀንስ ይህን ገንዘብ እዚህ ያስቀመጠው በስሙ ነው፤ መስሪያ ቤታችንም የሰጠው ዯረሰኝ
የሱን ገንዘብ ባዯራ ያስቀመጠ መሆኑን የሚገሌፅ ነው፤ በሁሇቱም ውስጥ ገንዘቡ የራስ እምሩ መሆኑን
የሚያመሇክት አንዴ ቃሌ የሇም። ስሇዚህ ወይ እሱ ካሌመጣ ያሇዚያም ካሇበት ቦታ በመስሪያ ቤታችሁ
ያስቀመጥሁትን ገንዘብ ሇሀዱስ አስረክቡሌኝ ብል ካሌፃፇሌን ሊንተ ማስረከብ አንችሌም» ብሇው ቁርጡን
ነገሩኝ።

«ከራስ እምሩ ወረቀት እንዯሚያዩት፥ ሇዚህ ገንዘብ ባሊዯራ ያዯረጉኝ እኔን ብቻ ነውኮ! በወረቀቱ
ውስጥ ያቶ ዮሀንስ ስም እንዱያውም አሌተነሳም!» አሌሁዋቸው።

«እውነት ነው፤ በዚህ ወረቀት ውስጥ ያቶ ዮሀንስ ስም የሇም፤ ግን እሱ እዚህ መስሪያ ቤት


ባዯራ ያስቀመጠው ገንዘብ በራስ እምሩ ወረቀት ውስጥ የተመሇከተው ሇመሆኑ ላሊ፥ የራሱን ገንዘብ
ሊሇመሆኑ ምን ማስረጃ አሇ?» አለ እንግሉዛዊው ባሇስሌጣን እንዯ መሳቅ ብሇው። «ይሌቅስ» አለ ከተሌ
አዴርገው «በጣሉያኖች እጅ ካሌወዯቀ የሱዲንና የኢትዮጵያ ወሰን በጣም ረዢም ስሇሆነና ሇጊዜው
ጣሉያኖች የያዙት መተማን ብቻ ስሇሆነ ካሌተያዙት በሮች ባንደ በኩሌ አሌፍ እዚህ ይዯርስ ይሆናሌና
ተስፊ ሳንቆርጥ እስቲ እሱን እንጠንቀው» ብሇው አሰናበቱኝ።

መቸም ዮሀንስ ጣሉያኖች መተማን ሇመያዝ መቃረባቸውን ሲሰማ ባይዯነግጥና እዚያ


የተውናቸውን ወታዯሮች ከምርኮ ሇማዲን ባይቸኩሌ ኖሮ፥ በኔ ሊይ እንዱያ ያሇ ችግር የሚፇጥር ነገር
እንዯማያዯርግ እርግጠኛ ነኝ። ግን በዴንጋጤ ውስጥ በነበረበት ጊዜ በወታዯሮች ሊይ ያንዣበበውን አዯጋ
ብቻ ሲመሇከት ዴንገት ሳይመሇስ ቢቀር ገንዘቡን ካስቀመጠበት መስሪያ ቤት እኔም ሌሁን ላሊ ሰው
ማውጣት የማንችሌ መሆናችን እንዳት ሳይታዬው ቀረ?

ካገረ - ገዡ ከተሰናበትሁ በሁዋሊ፥ እሳቸው ፉት አሌቀርብም እንጂ በቀን አንዴ ጊዜ መስሪያ


ቤታቸውን ሳሌረግጥና ካቶ ሚካኤሌ በኪት ጋር ተገናኝቼ ሳሌናገር ውዬ አሊአውቅም። ነገር ግን በሄዴሁ
ቁጥር፥ እዚያ የማገኘው በዮሀንስ ውሬ ፊንታ ጣሉያኖች በኢትዮጵያ ይዞታቸውን እያስፊፈ መሄዲቸውን
ስሇ ነበረ፥ ሁሌ ጊዜ እያዘንሁና እዬተከዝሁ ነበር የምመሇሰ። ዘሪሁንም ያዘነና የተከዘ ፉቴን ሲያይ፥ ስሇ

87
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አቶ ዮሀንስ ከሰማሁት ዯስ የሚያሰኝ ወሬ አሇመያዜን ገምቶ ምን ወሬ ሰምቼ እንዯ መጣሁ መጠዬቁን
ተወ።

ካስራ አምስት ቀናት ያክሌ በሁዋሊ እኔ ከግዛቱ መስሪያ ቤት ተመሌሼ ዘሪሁን ምሳ፥ የማሰናዲት
ስራውን ጨርሶ እዯጅ ተቀምጠን ስናወራ፥

«አዋዋ፥ አቶ ዮሀንስ መጡ!» አሇ ዘሪሁን፤ ወሬያችነን አቁዋርጦ ወዯ አውራው ጎዲና ቀና ብል


አዬና። ያቶ ዘውዳ ግቢ ካውራው ጎዲና አጠገብ ስሇ ሆነ፥ እዯጅ ተቀምጦ አሊፉ አግዲሚውን መመሌከት
አንደ የጊዜ ማሳሇፉያችን ነበር።

«የት አሇ?» አሌሁ፤ የሱን አይን ተከትዬ አውራውን ጎዲና እዬተከተሇሁ፤ ዮሀንስን ብፇሌግ
ማየት ስሊሌቻሌሁ።

«ያቺ ተጭና ሰውዬው የሚስባት የምትሄዴ ጥቁር በቅል ያቶ ዮሀንስ «ምስንጅር» የሚለዋት
በቅል ናትኮ፤ የሚስባት ሰውዬም ያቶ ዮሀንስ አሽከር ነው» አሇ ዘሪሁን፤ አቶ ዮሀንስን ከጠፊበት እሱስ
አግኝቶ እንዲመጣው ሁለ ፉቱ በዯስታ በርቶ። እውነትም በቅልዋም ጭኖ እዬሳባት የሚሄዯው ሰውም
ያቶ ዮሀንስ ነበሩ። ያቺ «ምስንጅር» የሚለዋት ግመሌ የምታክሌ በቅል ጣሉያኖች በ «ዯባ ጉና»
ጦርነት ዴሌ ሆነው ሰፇራቸው ሲዘረፌ ባሊገር ዘርፍ ሇዮሀንስ የሸጠሇት የማታሳስት ነበረች።

«እስቲ ሩጥና ዮሀንስ የት እንዲሇ ጠይቀው» አሌሁት ዘሪኍንን። ዘሪሁን ሮጦ ባቶ ዮሀንስ


አሽከር ዯርሰበትና ቆመው ትንሽ ሲነጋገሩ ቆይተው አብረው ወዯኔ መጡ።

«ዮሀንስ የት ነው?» አሌሁት የዮሀንስ አሽከር ከተሳሳምን በሁዋሊ።

«ጌቶችማ - እንጃ! ወዲገራቸው የሄደ ይመስሇኛሌ!» አሇ።

«እንዳት? መቼ?»

«ጣሉያኖች መተማን የያዙ እሇት»

«ታዱያ አንተ እንዳት ተሇይተህ ቀረህ»

«እኔና ሁሇት ወታዯሮች ከተማ በገባንበት ጣሉያኖች ከተማውን ስሇ ከበቡት በግርግሩ ሾሌከን
ወጥተን ወዯ ሰፇራችን ብንመሇስ ሁለም ሄዯው ቆዩን። ከዚያ መሳሪያ ስሊሌነበረን ወዯ ገሊባት ተሻግረን
ሰንብተን ወታዯሮች እዚያው ቀሩ፤ እኔ ግን እናንተን ፌሇጋ ወዱህ መጣሁ» አሇ።

88
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እኛን ፌሇጋ ከሆነ የመጣህ በቅልውና አራግፌና አርፇህ ሁለንም ታጫውተናሇህ፤ አሁን
የነገርኸን እኔን ጭራሽ አሌገባኝም» አሌሁት። ከዚያ በቅልዋ ከተራገፇች በሁዋሊ ዘሪሁን ምሳችነን
አቅርቦሌን ሶስታችንም ተቀምጠን እዬበሊን ታሪኩን እንዯሚከተሇው ዘርዝሮ ተረከሌን።

«ጌቶች (አቶ ዮሀንስ) ከዚህ ወዯ ገሊባት የሄደ እሇት ካገረ ገዡ ጋር ሇመነጋገር እንዯሆነ
አሊውቅም፤ እዚያው ገሊባት አዴረው በማግስቱ ከረፇዯ በሁዋሊ ነው ወዯኛ የመጡ። ወዱያው እንዯ
ዯረሱ ወታዯሮቹንም እኛንም ሰብስበው ‹ጣሉያኖች መተማን ሇመያዝ በመንገዴ ሊይ ናቸውና ቁርስ
ያሌበሊችሁ ቶል ከተማ ገብታችሁ በሌታችሁ ከዚህ እንዴንነሳ› አለን። ከሁሇት ወታዯሮች በቀር
ወታዯሮች ሁለ ቀዯም ብሇው በተራ እየሄደ በሌተው ተመሌሰው ስሇ ነበረ ሁሇቱ፥ ወታዯሮችና እኔ
ከተማ ገብተን ቁርስ በመብሊት ሊይ እንዲሇን፥ እውጭ ጫጫጣ፤ ሆነ። ከዚያ ‹ምንዴነው› ብንሌ
‹ከተማውን ወታዯር ከበበው› አለን። እኛ የጣሉያን ጦር መቅረቡን ቀዯም ብሇው ጌቶች ነግረውን ስሇ
ነበረ ከባቢው እሱ መሆኑን አውቀን በግርግሩ ሾከን ወዯ ሰፇራችን ብንሄዴ ከዴንኩዋንና ከቃ በቀር
አንዴ ሰው የሇም፤ ሁለም አንዴ እቃ ሳያንጠሇጥለ መሳሪያቸውን ብቻ እዬያዙ ሸሽተዋሌ! ከዚያ
ዴንኩዋኖችን ትል ነቃቅሇን እቃውን ሰብስበን ይዘን መሳሪያ ባሇመያዛችን ስሊሌተከሇከሌን ወዯ ገሊባት
ተሻግረን ሰነበትን። ሁሇቱ ወታዯሮች እዚያው ቀሩ። እኔ ግን ሇዘመቻ ከተነሳንበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን
ዴረስ ዯመወዜን ጌቶች እንዱያስቀምጡሌኝ አዴርጌ ስሇ ነበረና አሁን ስሇ ተሇያዬን ‹ይቺን በቅል ብሸጥ
የዯመወዜን ያክሌ አሊጣባትም ይሆናሌ› ብዬ ‹በቅል በቅል ከገሊባት ይሌቅ ገዲሪፌ ይወዯዲሌ› ሲለኝ ጊዜ
እስዋን እዚህ ሇመሸጥና ወዱያውምም ‹እስዋን ባገኝ ስራ ፇሌገው ያስይዙኛሌ ብዬ› ወዯዚህ መጣሁ።
ገሊባት ሇመሰንበቻም ወዱህ ሇመምጫም ምንም ገንዘብ ስሊሌነበረኝ እያሇቀስሁ እንዯ ሙት ንብረት
የጌቶችን የመንገዴ አሌጋና ምንጣፌ የሌስብ ሳጥን እንዱሁም አንዲንዴ ነገር መሸጥ ግዴ ሆነብኝ። የጅ
ሻንታቸውንም ሰዎች ‹እንግዛ› ቢለኝ ምናሌባት የመንግስት ጉዲይ የተፃፇበት ወረቀት ይኖርበት እንዯሆነ
እስዎን ባገኝ ሳያዩት አሌሸጥም ብዬ እሱን አሌሸጥሁትም» አሇ።

ምሳ በሌተን ከጨረስን በሁዋሊ የጅ ሻንጣው መክፇቻ ከዮሀንስ ጋር በመሆኑ ዘሪሁንና የዮሀንስ


ሌጅ ሻንጣውን ገብያ ወስዯው እስከ ፌትወት እንዯ መጡ በውስጡ የነበሩትን ወረቀቶች እያወጣሁ ሳይ፥
ገዲሪፌ ግዛት ፅህፇት ቤት የተቀመጠውን የሰሊሳ ሽህ ብር ዯረሰኝ እዚያ ስሊገኘሁት የዯረሰኙ ሳይሆን
ገንዘቡ ያኔውኑ በጄ የገባ ያክሌ ነበር ዯስ ያሇኝ!

«ግሩም ነው! ይህን ሻንጣ አሇመሸጥ እግዚአብሔር መክሮህ እግዚአብሔር ሌትሌከው የሚገባህን
ትክክሇኛ መንገዴ አመሌክቶህ ነው። ግምትህ ትክክሌ ነው። ይህ ወረቀት ሇጊዜው በዮሀንስ እጅ የነበረ
ግን እኔ እዚህ አገር ስቆይ የሚያገሇግሇኝ ብርቱ የመንግስት ትእዛዝ ያሇበት ነው። ታዱያ ዮሀንስ እኔ
በላሇሁበት ጣሉያኖች መተማን ሉይዙ መቃረባቸውን ዴንገት ሲሰማ ቸኩል እንዯ ያዘው ሄድ ነበር።

89
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እና ቢጠፊ ኖሮ እኔን ብርቱ ችግር ይገጥመኝ ስሇ ነበረ እንዱያ ካሇ ችግር በማዲንህ በጣም ነው
የማመሰግህንህ!» ብዬ ስስመው እሱም ዯስ አሇው።

በማግስቱ ያን ዯረሰኝ ይዤ ወዯ ግዛቱ መስሪያ ቤት ሄጄ ሊቶ ሚካኤሌ በኪት ሳሳያቸውና ታሪኩን


በዝርዝር ስተርክሊቸው እንዯ ታምር ቆጥረውት ተገረሙ። ወዱያው ወዯ አገረ - ገዡ ይዘውኝ ገብተው
የሆነውን ሁለ እኔ እንዯ ተረክሁሊቸው አዴርገው ከነገሩዋቸው በሁዋሊ የዯረሰኙን ሲያሳዩዋቸው አገረ -
ገዡም ዯስ አሊቸው። ዴሮውንም አገረ - ገዡ የራስ እምሩን ወረቀት እንዲዩ የገንዘቡ ባሊዯራ እኔ
መሆኔን አምነው ነበር። ነገር ግን ዮሀንስ በስሙ አስቀምጦ በስሙ የዯረሰኝ የተቀበሇበትን ገንዘብ ሇኔ
ማስተሊሇፌ ህጋዊ የዯረሰኝ ከተመሇሰ በሁዋሊ እሱ ተቀዴድ የራስ እምሩ ገንዘብ በኔ ባሊዯራነት በግዛቱ
መስሪያ ቤት ባዯራ መቀመጡን የሚገሌፅ የዯረሰኝ እንዱሰጠኝ አዝዘውሌኝ ወዱያውኑ ተሰጠኝ።

ምእራፍ አስራ ሶስት

ሱዳን የቆዬንበት ጊዜ
ዘሪሁንና እኔ ሱዲን የቆዬንበት ጊዜ፥ ከግንቦት 1928 መጀመሪያ እስከ ነሏሴ 1928 መጨረሻ
ግዴም አራት ወራት ያክሌ ነበር። ካራቱ ወራት ሁሇቱን ወራት ያክሌ የቀረውን ካርቱም ነበር የቆዬን።
ገዲሪፌ አቶ ዘውዳ በሰጡን ካስራ አምስት እስከ ሃያ ቀናት ያክሌ ከቆዬን በኋሊ፥ ምንም እንኩዋ እሳቸው
አፊቸውን አውጥተው ባይናገሩ፥ እኛ ከያዝነው ላሊ እንግዲ የሚቀበለበት ቤት ያሌበራቸው መሆኑን
በማየት እዚያው ባጠገባቸው አንዴ ትንሽ ቤት ተከራይተን ወጣን። ግን ከግቢያቸው ብንወጣም ገዲሪፌን
እስከ ሇቀቀንበት ቀን ዴረስ ያቶ ዘዳ ርዲታ አሌተሇየንም። እንኩዋንስ ጠይቀናቸው ሳንጠይቃቸው
እሳቸው አውቀው የሚያዯርጉሌን ርዲታ ብዙ ነበር።

ካቶ ዘውዳ ላሊ፥ ገዲሪፌ በነበርንበት ጊዜ አይነተኛ ረዲታችን አቶ ሚካኤሌ በኪት ነበሩ። በተሇይ
እኔ ሬዱዮ ስሊሌነበረኝ ስሇ ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ሁኔታም ሆነ በጠቅሊሊው ስሇ አሇም ሁኔታ
የማውቀው ካቶ ሚካኤሌ በኪት ጋር በመነጋገር ነበር። መቸም ፅህፇት ቤታቸውን በቀን አንዴ ጊዜ
ሳሌረግጠው ውዬ አሊውቅም! ታዱያ፥ በሄዴሁ ቁጥር በዯስታ ተቀብሇው ቡና እየጋበዙን በየጊዜው
ጣሉያኖች በኢትዮጵያ ውስጥ የያዙዋቸውን ክፌልች እንዱሁም ሇአሇም ማህበር አባሌ ከሆኑት
መንግስታት እነማን ኢትዮጵያን ዯግፇው በኢጣሉያ ሊይ ቅጣት እንዱጣሌባት አሳብ እንዲቀረቡና እነማን
ቅጣቱን እንዯተቃወሙ ነግረውኝ ተስፊ እንዲሌቆርጥ አበረታተውኝ እሄዲሇሁ። ጃንሆይ ቤተሰባቸውንና
ብዙ መኩዋንንታቸውን ይዘው ወዯ ኢየሩሳላም መሄዲቸውን፥ ከዚያም ወዯ እንግሉዝ አገር የሚሄደ
መሆናቸውን መጀመሪያ የሰማሁ ካቶ ሚካኤሌ ነበር።

አቶ ሚካኤሌ በኪት፥ ምንም እንኩዋ ሱዲን ተወሌዯው አዴገው እዚያ በክብር የኖሩ ቢሆኑ
የኢትዮጵያ ነፃነት መጥፊት በጉያዋ አቅፊ የናትነት ፌቅርዋን እየመገበት እንዲሳዯገቻቸው

90
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ኢትዮጵያውያን አገር ወዲድች ሁለ ነበር ያሳመማቸው። ሙሶልኒ የጦር ሰራዊቱ አዱስ አበባ የገባበትን
ቀን አስታውቆ፥ ከዚያ ቀን ጀምራ ኢትዮጵያ ነፃ አገር መሆንዋ ቀርቶ የጣሉያን ቅኝ ግዛት እንዯ ሆነች
ማስታወቁን ሰምተው የነገሩኝ እሇት ከኔ ጋር ያሇቀሱትን መሪር ሌቅሶ አሌረሳውም አብሮኝ ይኖራሌ።

ኢትዮጵያ የጣሉያን ቅኝ ግዛት መሆንዋን ሙሶሉኒ ባዋጅ ካስታወቀ በሁዋሊ የኢትዮጵያ


የክብርዋና የነፃነትዋ ምሌክቶች የሆኑት ነገሮች ሁለ ተዋረደ ወዯቁ። በገዲሪፌ ግዛት መስሪያ ቤት
ያስቀመጥሁት የኢትዮጵያ ብርም ከነፃነትዋ ምሌክቶች አንደ ስሇ ነበረ ከኢትዮጵያ ነፃነት ጋር አብሮ
ወዯቀ፤ ዋጋ አጣ! ሳስቀምጠው ከሱዲን ብር ጋር አንዴ ሊንዴ የነበረው ባንዴ ጊዜ በግማሽ ወረዯ። እዚያ
ሊይም አሌቆመ፤ በዬቀኑ እየወረዯ እየወረዯ ሄድ በመጨረሻ ፇሊጊ አጣ። የሚፇሌጉት አንዲንዴ
ነጋዳዎች ቢኖሩ ሇመገበያያ ገንዘብነቱ ሳይሆን፥ ተነጥሮ ጥሩውን ብር ሇጌጣጌጥ መስሪያነቱ ብቻ ሆነ።
ያን ጊዜ ወዯ ሱዲን የተሊክሁበት አሊማ ከንቱ ሆኖ መቅረቱ ታዬኝና አዘኔ ከኔ አሌፍ አቶ ሚካኤሌንና
አቶ ዘውዳን አስጨንቆዋቸው እኔን ሇመርዲት ያሊሰቡትና ያሌሞከሩት ነገር አሌነበረም።

አንዴ ቀን አቶ ዘውዳን ጭምር አቶ ሚካኤሌ በኪት ጠርተውን እፅህፇት ቤታቸው ገብተን


እንዯ ተቀመጥን፤ «የሱን የወንዴማችንን ችግር የሚያቃሌሌ መስል የታኝዬን አሳብ እንዴሌገሌፅሌዎና
እንዴንመክርበት ነው፥ ዛሬ እርስዎ ጭምር እንዱመጡ ያስቸገርሁዎ» አለዋቸው «የሱን
የወንዴማችንን» ሲለ ወዯኔ እያመሇከቱ።

«ምንጊዜም ቢሆን ወዯስዎ መምጣት በስራዎ ጣሌቃ ገብቸ እንዲሊስቸግርዎ እሰጋሇሁ እንጂ
ሇኔስ ዯስታ ነው። ይሌቁንም የሱ ችግር የሚቃሇሌበት መንገዴ ከተገኘ እንኩዋንስ እርስዎ ዘንዴ ሩቅ
አገር ብሄዴ አይከብዯኝም» አለ አቶ ዘውዳ።

«እንዯሚያውቁት እዚህ እኛ ዘንዴ ያስቀመጠው ገንዘብ ዋሊ ስሊጣ፣ እንዯታሰበው ኢትዮጵያ


ውስጥ ከጠሊት ጋር ሇሚዋጉት ወታዯሮች ሌብስና መዴሀኒት ገዝቶ ሉወስዴሊቸው ሊይችሌ ነው ማሇት
ነው። ታዱያ እዚያ (ኢትዮጵያ) ያለት ኢትዮጵያውያን ሇጋራ አገራችን ነፃነት ህይወታቸውን ሲሰጡ እኛ
እዚህ ያሇነው ኢትዮጵያውያን ሇመዴሀኒትና ሇሌብስ የሚሆናቸው ገንዘብ እንዯያቅማቸው አዋጥተው
መስጠት ይበዛብናሌ? ሇኔ እንዯሚመስሇኝ ገዲሪፌ የምንኖረው ኢትዮጵያውያን ብዙ ስሇሆን ሴት ወንደ
ሌጅ አዋቂው እንዯያቅሙ ቢያዋጣ ይህን ዋጋ ያጣ ገንዘብ ይህን እንዯ ጠፊ የሚቆጠር ሰሊሳ ሺህ ብር
ሰብስቦ መተካት ይቻሊሌ። ስሇዚህ ይህን አሳብ መሰንበቻውን ብቻየን ሳሰሊስሌ ከሰነበትሁ በሁዋሊ ነው፤
ከሰዎቹ ጋር ከኔ የተሻሇ ግንኙነት ያሇዎ ከመሆንዎ፤ ከርስዎ ጋር እንዴንመካከርበት ፇሇግሁ።

«ማሇፉያ አሳብ አስበዋሌ ፇቃዯኞች ስንት እንዯሚሆኑ አናውቅም እንጂ ሁለም ፇቃዯኞች
ከሆኑማ ብዙ ገንዘብ መሰብሰብ ይቻሊሌ። አቅም የሚያንሳቸው ስሇሚኖሩ እነሱን ብንተዋቸው እንኩዋ
ከሚችለት ሰሊሳ ሺህ የሱዲን ብር መሰብሰብ ባይቻሌም የኢትዮጵያን ብር ሇጌጣጌጥ ስራ ገዝተው

91
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇሚነግደ አትራፉ ነጋዳዎች ባወጣው ዋጋ ሽጦ የሚጏዴሇውን የሚያሙዋሊ ገንዘብ ሇመሰብሰብ
የሚቻሌ ይመስሇኛሌ። ሇማናቸውም የሁሇታችሁም ፇቃዴ ቢሆን ስሇ ብሩ ሽያጭ ካንዲንዴ ነጋዳዎች
ስሇመዋጮው ካንዲንዴ ተዯማጭነት ካሊቸው ያገራችን ሰዎች ጋር ተነጋግሬ አሳባቸውን ካወቅሁ በሁዋሊ
እንዯ ገና እንነጋገርበት» አለ አቶ ዘውዳ።

«ማሇፉያ ነው። ብቻ ስሇ ብሩ ሽያጭ ካንዴ ብቻ ሳይሆን በርከት ካለ ነጋዳዎች ጋር ቀስ ብሇው


ውስጥ ሇውስጥ ተነጋግረው እያንዲንዲቸው ያቀረቡትን ዋጋ ካወቁ በሁዋሊ የስምምነት ቃሌዎን
ከመስጠትዎ በፉት እዚህ እንዯገና ብንነጋገርበት ይሻሊሌ። ይህን ያሌሁበት ምክንያት እኔም
የማውቃቸው አንዲንዴ ነጋዳዎች ስሊለ መጠየቄ አይቀርምና ሇሁሇታችን የቀረቡትን ዋጋዎች
አመዛዝነን መምረጥ እንዴንችሌ ነው» ብሇው አቶ ሚካኤሌ አሰናበቱን። ያነሇታ ጠፌቶ የነበረው
የመሌእክቴ አሊማ እንዯፉቱ ጠርቶ ጎሌቶ ባይሆንም ዯብዘዝ ብል በሩቅ ይታየኝና ዯስ እያሇኝ ወዯ ቤቴ
ተመሇስሁ።

አቶ ዘውዳ ሊቶ ሚካኤሌና ሇኔ እንዯ ነገሩን ክብር ነጋዳዎችና ስሇ መዋጮው ከኢትዮጵያውያን


ጋር በመነጋገር ሊይ እንዲለ አንዴ ቀን፥ አቶ ሚካኤሌ ፅህፇት ቤት ስዯርስ አዱስ ወሬ ቆዬኝ።

«ጣሉያኖች ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛታቸው መሆንዋን ካስታወቁ በሁዋሊ መገበያያ ገንዘብ በኢትዮጵያ፥


ብር ፊንታ የጣሉያን ሉሬ እንዱሆን አውጀው፥ አሁን ብሩን ከኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በወሰንዋ
ባለት አገሮች የሚገኘውንም በውዴ ዋጋ እዬገዙ መሰብሰብ ስሇ ጀመሩ ሇጊዜው የኢትዮጵያ ብር ዋጋ
ከፌ እያሇ መሄደን ሰማሁ። ስሇዚህ ከሱዲን ብር ጋር አንዴ ሊንዴ በሚሇወጥበት ዯረጃ ከዯረሰ፤ ‹ይዋሌ
ይዯር› ሳትሌ ቶል ብትሸጠው ይሻሊሌ። ይህን የምሌበት ምክንያት ጣሉያኖች መሰብሰቡን ሲያቆሙ
የብር ዋጋ ተመሌሶ መውዯቁ የማይቀር መሆኑን ስሇማወቅ ነው» አለኝ አቶ ሚካኤሌ። እኔም
ሳሊመነታ በሳቸው ተስማማሁ።

እውነትም በጥቂት ቀናት ውስጥ አቶ ሚካኤሌ እንዯነገሩኝ መተማን የያዙት ጣሉያኖች


የኢትዮጵያን ብር እየፇሇጉ በውዴ ዋጋ መግዛታቸው ገዲሪፌ በሰፉው ስሇተወራ፥ ቀዯም ብሇው አቶ
ዘውዳ ያነጋገሩዋቸው የብር ነጋዳዎች አንደን የኢትዮጵያ ብር አንዴ የሱዲን ብር ካንዴ መሀሇቅ
(ፒያስትር) ሂሳብ ገዙት። አስር መሀሇቅ (ፒያስትር) አንዴ የሱዲን ብር ስሇሆነ ሰሊሳው ሺህ የኢትዮጵያ
ብር ሰሊሳ ሶስት ሺህ የሱዲን ብር ሆነ ማሇት ነው። ስሇዚህ ያን ሰሊሳ ሶስት ሺህ ብር የሱዲን ብር ባንክ
አግብቼ «ኧሁ!» አሌሁ፤ አረፌሁ!

አቶ ዘውዳ ስሇ መዋጮው ከኢትዮጵያውያን ጋር ባዯረጉት ንግግር ዯስ የሚያሰኝና የተረጋገጠ


ተስፊ ማግኘታቸውን ሊቶ ሚካኤሌና ሇኔ ነግረውን ነበር። ገዲሪፌ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ሁለቃ፤
ገብተው ነበር። በተሇይ ሴቶች ወርቃቸውንና ላሊ ጌጣቸውን እዬሸጡ ሇማዋጣት ያስታውቁት ገንዘብ

92
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወርቃቸውንና ላሊ ጌጣቸውን እዬሸጡ ሇማዋጣት ያስታውቁት ገንዘብ ሲታይ መዋጮው ከአሰበው በሊይ
የሚገመት ነበር። ነገር ግን ያሌታሰበ አጋጣሚ ዯርሶ፥ የኢትዮጵያ ብር ከቀዴሞ ዋጋው እንኩዋ ከፌ
ብል ስሇ ተሸጠ አቶ ዘውዳ ሇሁለም ምስጋናችንን ገሌፀው መዋጮው የሚያስፇሌግ መሆኑን
እንዱያስታውቁሌን አዯረግን።

ራስ እምሩ ጎሬ መዴረሳቸውን አቶ ሚካኤሌ በኪት እዚያ በነበረው የቆንስሊቸው መስሪያ ቤት


በኩሌ አውቀው ነግረውኝ ነበር። ነገር ግን ምንም እንኩዋ አቶ ዮሀንስ ዯርሶባቸው ከተገናኙ እኔ ገዲሪፌ
መሆኔን ሳይነግራቸው እንዯማይቀር የታወቀ ሲሆን እስከዚያ ዴረስ ከራስ የዯረሰኝ መሌእክት
እንዯማይቀር የታወቀ ሲሆን እስከዚያ ዴረስ ከራስ የዯረሰኝ መሌእክት አሌነበረም። በመሀከለ የግሌ
ገንዘቤ እያሇቀ ስሇሄዯ ዘሪሁንና እኔ እንዳት አዴርገን መኖር እንዯምንችሌ በታም ያሳስበኝ ጀመር። ወዯ
ሱዲን እንዴንሄዴ ስንታዘዝ፥ የስዴስት ወር ዯመወዜን ከሶስት መቶ ብር በሊይ ተቀብዬ ነበር ከራስ
የተሰናበትሁ። እንዱሁም ሁሇቱን በቅልዎችን ገሊባት ሸጨ ከሞሊ ጎዯሌ ያኑ ያክሌ የሱዲን ብር
አግኝቻሇሁ። ያን ያክሌ ገንዘብ በኢትዮጵያ ሇሁሇት ሰዎች ሇብዙ ጊዜ በበቃ ነበር። ነገር ግን ሱዲን የኑሮ
ዋጋ ከኢትዮጵያ ይወዯዴ ስሇ ነበር፥ ሁሇት ወራት ሳያቆዬን ወዯ ማሇቁ ተቃረበ።

አንዴ ቀን ጥዋት ዘሪሁን ሇምግባችን የሚያስፇሌጉትን ነገሮች ሉገዛ ወዯ ገብያ መሄዴ ፇሌጎ፥
ገንዘብ ሲጠይቀኝ የነበረን ገንዘብ ትንሽ መሆኑን አይቼ «ዘሪሁን ከምትገዛው ነገር አንዲንደን ብትተው
ይሻሊሌ። እዚህ አገር ምን ያክሌ ጊዜ እንዯምንቆይ አናውቅም፤ ያሇን ገንዘብ ግን ብዙ ጊዜ የሚያቆዬን
አይዯሇም» አሌሁት። ዘሪሁን ማዘኔን ከፉቴ ሲያይ እሱም እንዯ ማዘን ብል ትንሽ አንገቱን ዯፌቶ
ሲያስብ ቆዬና፤

«የቀረን ገንዘብ አንዴ አህያ ሇመግዛት አይበቃም?» አሇ፤ አዝኖ የነበረ ፉቱ ከመቅፅበት በርቶ።

«አህያ? አህያ ሇምን እንገዛሇን ዘሪሁን?» አሌሁት።

«አዬህ አዋዋ! አንዴ ዯህና አህያ ከነውሀ መጫኛ ሸራው ሇመግዛት የሚበቃ ገንዘብ ካሇን፥
ስዴስት ወይም ሰባት ዘበኞች (ዯንበኞች) አብጅቼ ሇነሱ በዬቀኑ የሚያስፇሌጋቸውን ውሀ እዬቀዲሁ
ባቀብሌ፥ እንኩዋንስ ሊንተና ሇኔ ሇላሊም የሚተርፌ ገንዘብ ማግኘት እንችሊሇን። ስሇዚህ በገንዘብ
የምንቸገር መስልህ አይዞህ አትስጋ! እዚህ ውሀ ቀዴተው ሇዘቡኖቻቸው እያዯለ ሌጆቻቸውን
አስተምረው አባት እናቶቻቸውን ረዴተው ምንም ችግር ሳያገኛቸው የሚኖሩትን ብዙ ሰዎች አይታይም?
ስሇዚህ እግዚአብሔር ጤና ከሰጠን፥ ብዙ ፇገግ ባሇ የሚያበረታታ ፉት እንዯ ፇራ ህፃን እዬመሊሇሰ
«አይዞህ! አይዞህ!» እያሇ። ዘሪሁን እኔን ሇመርዲት ምን ያክሌ እንዯሚያስብ ካነጋገሩና ከሁኔታው ሁለ
ስንመሇከት ሌቤ ተነክቶ፣ አይኖቼ እንባ ሲያዝለ ስሊዬ፤

«ምነ አዋዋ? የሚያሳዝንህ ነገር ተናገርሁ?» አሇ እንዯ መዯንገት ብል።

93
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ኧረ የሇም! በጣም ዯስ የሚያሰኝ ግሩም አሳብ ነው ያሰብኸው ዘሪሁን! ምናሌባት ራስ ይፅፈሌን
እንዯ ሆነ ትንሽ እንጠብቅና ካሌፃፈሌን የኛ ገንዘብ ባይበቃም ተበዴረን ሞሌተን አሁን እንዲሌኸው
አህያውን እስከ መሳሪያው እንገዛና ኍዋሊ አንተ ሰርተህ ከምናገኘው ገንዘብ እዬቆጠብን ብዴራችንን
እንከፌሊሇን። ስታነጋግረኝ እንባ የመጣብህ ይህ ሁለ ችግር ባገራችን ሊይ የዯረሰው መከራ ያስከተሇው
መሆኑ ዴንገት ስሇታሰበኝ ነው» ብዬ ውሸቴን ነገርሁትና ገንዘብ ሰጥቸው እሱ ወዯ ገብያው ሲሄዴ እኔ
ወዲቶ ሚካኤሌ ፅህፇት ቤት ሄዴሁ።

ከዘሪሁን ጋር ስሇ ገንዘብ ችግር ከተነጋገርን በኋሊ፥ በሶስተኛው ይሁን ወይም ባራተኛው ቀን


እንዯ ሌማዳ ወሬ ሇመጠየቅ አቶ ሚካኤሌ ፅህፇት ቤት ስዯርስ ፇቃዯ፥ ስሊሴ ህሩይ እና ሲራክ ህሩይ
የሚባለ ሁሇት ሰዎች ከኢትዮጵያ ወዯ እንግሉዝ አገር ሲሄደ ካርቱም አርፇው ሇኔ መሌእክት ስሇያዙ
እስከ ሶስት ቀን ዴረስ ካርቱም ‹ሴንት ጀምስ ሆቴሌ› እንዯሚጠብቁኝ ስሌክ ማዴረጋቸውን ነገሩኝ።

ሌጅ ፇቃዯ ስሊሴ ህሩይና ሌጅ (ሁዋሊ ብሊታ) ሲራክ ህሩይ ሇብዙ ጊዜ፥ በጦርነቱ ጊዜ ጭምር
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዲይ ሚኒስትር የነበሩት የብሊቴን ጌታ ህሩይ ሌጆች ነበሩ። ሁሇቱንም በስም
ካሌሆነ አይቻቸው አሊውቅም። ሌጅ ሲራክ ህሩይ የውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ዋና ፀሀፉ መሆኑ እስማ
ነበር። ሌጅ ፇቃዯ ስሊሴ ህሩይ የክቡር ራስ እምሩ ሌጅ የወይዘሮ የምስራች እምሩ ባሇቤት ስሇ ነበሩ
በጎሬ በኩሌ አሌፇው እንዯሆነ የያዙሌኝ መሌእክት ከራስ ሳይሆን አይቀርም ብዬ ገመትሁ። ከዚያ
ግምቴ ሌክ መሆን አሇመሆኑን ሇማወቅ፤

«እኒህ ሁሇት ሰዎች ከኢትዮጵያ በየት በኩሌ ሱዲን ገብተው ይሆን ካርቱም የዯረሱ?»
አሌሁዋቸው አቶ ሚካኤሌን።

በሳሌስቱ ዘሪሁንና እኔ ቤት ነው ሱዲን የገቡ» ሲለኝ መሌእክቱ እርግጥ ከራስ መሆኑን


ስሊመንሁ እጅግ ዯስ አሇኝ!

በሳሌስቱ ዘሪሁንና እኔ ቤት ሊከራዩን ሰው የኪራዩን ውዝፌ ከፌሇን አቶ ሚካኤሌ በኪትንና አቶ


ዘውዳን ገዲሪፌ በቆዬንበት ጊዜ ስሊዯረጉሌን የማይረሳ ርዲታ አመስነንና ተሰናብተን በባቡር ወዯ ካርቱም
ተጉዋዝን። እዚያ፥ አቶ ሀብቴ ዯስታ አዴራሻውን ሰጥቶኝ ስሇ ነበር፤ የራሳችንን ቤት በሱ ርዲታ
እስክናገኝ በቀጥታ እሱ ቤት ሄዯን አረፌን። ወዱያው «ሴንት ጀምስ» ሆቴሌ ወስድ ከሌጅ ሲራክ ጋር
አገናኘኝ። ሌጅ ፇቃዯ ስሊሴ ህሩይን አሊገኘሁዋቸውም፤ ወዯ እንግሉዝ አገር ሄዯው ቆዩኝ። ሌጅ ሲራክ
ህሩይም እኔን ሇመጠበቅ ብቻ ነበር የቆዬው።

ሌጅ ሲራክ ገዝቼ ወዯ ጎሬ እንዴወስዴሊቸው ራስ ከሰጡት የዔቃ ዝርዝር ጋር፥ ከግንቦት 1928


እስከ ጥቅምት 1929 የስዴት ወር ዯመወዜን ጭምር በሱዲን ብር ስሇሰጠኝ በገንዘብ እጥረት ምክንያት
ተጭኖኝ የነበረው ከባዴ ያሳብ ጭንቀት ከትከሻየ ወርድ የወዯቀ መስል ተሰማኝና ቀሇሌ አሇኝ። ከዚያ

94
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በሁዋሊ ሁሇት ቀን እዬተገናኘን እሱ ጣሉያኖች ከገቡ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ስሇ ነበረው ሁኔታ
እዬነገረኝ እኔ ስሇ ሽሬ ገጠሙን አንዲንዴ ችግሮችም እያወራሁት ስንወያይ ቆይተን ወዯ እንግሉዝ አገር
ሄዯ።

ከሌጅ ሲራክ ጋር ተገናኝቼ መነጋገሬ በጣም ነበር የረዲኝ። ጣሉያኖች ሰራዊታቸው አዱስ አበባ
መግባቱንና ኢትዮጵያ የነሱ ቅኝ ግዛት እንዯሆነች ማስታወቃቸውን ስሰማ የክቡር ራስ እምሩ ወሬም
ሲጠፊኝ «ጠሊቶቻችን ኢትዮጵያን በሙለ ይዘው ያሇተቃውሞ ተዯሊዴሇው ተቀምጠው ይሆን?» የማሇት
ስጋት አዴሮብኝ ተስፊየ መመንመን ጀምሮ ነበር። ነገር ግን ጣሉያኖች አዱስ አበባ የገቡ እሇት ከዚያ
ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያ የነሱ ቅኝ ግዛት መሆንዋን ማስታወቃቸው እውነት ቢሆንም በሲዲሞና በባላ
በገሙጎፊና በኢለባቦርና በወሇጋ በጠቅሊሊው ከዯቡብ ምዔራብ እስከ ምዔራብ የኢትዮጵያ አገረ - ገዥዎች
ሁለም የጦር ሰራዊታቸውን እንዯያዙ በየቦታቸው እንዲለ ከመሆናቸው ላሊ ጃንሆይ የኢትዮጵያ
መንግስት መቀመጫ ጎሬ ሆኖ እሳቸው እስኪመሇሱ ቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅን ጠባቂ አዴርገው ሾመው
ከአሇም ማህበር እርዲታ ሉጠይቁ የሄደ መሆናቸውን ሌጅ ሲራክ ሲነግረኝ ቀዝቅዞ ከሞት አፊፌ ዯርሶ
የነበረው ጦርነቱን ቀጥል ዴሌ የመቀዲጀት ተስፊየ እንዯገና ሙቀትና ህይወት አገኘ። ሌጅ ሲራክ
እንዯነገረኝ ጣሉያኖች «ይዘናቸዋሌ» በሚለዋቸው አገሮች በትግራይ በቤገምዴርና በሰሜን በጎጃምና
በሸዋ እንኩዋ ከከተሞች በቀር መሀሌ አገሩ በኢትዮጵያውያን አርበኞች እጅ ነበር። ይህ ሁለ ትግለ
ሇረዥም ጊዜ ሉቀጥሌ የሚችሌ መሆኑንና «በመጨረሻ ዴለ ሇኢትዮጵያ ይሆን ይሆናሌ!» የማሇትን
ተስፊ የሚፇጥር ነበር።

ሌጅ ሲራክ ወዯ እንግሉዝ አገር እንዯ ሄዯ አቶ ሀብቴ ዯስታ፥ እኔንና ዘሪሁንን ካርቱም ይኖሩ
ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ካንዲንድቹ አስተዋወቀን እሱ ባስተዋወቀን ሰዎች አማካይነትም ከብዙ ላልች
ኢትዮጵያውያን ጋር ተዋወቅን።

ገዲሪፌ በቆየንበት ጊዜ ምንም እንኩዋ እዚያ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ብዙ ቢኢሆኑ ካቶ


ሚካኤሌ በኪትና ካቶ ዘውዳ በቀር ከላልች ጋር ይህን ያክሌ የተቀራረበ ግንኙነት አሌነበረንም።
ምናሌባት ገዲሪፌ ይኖሩ ከነበሩት ሰዎች በጣም የሚበዙት የጉሌበት ሥራ እዬሰሩ በዝቅተኛ ኑሮ
የሚኖሩ ስሇ ነበሩ እኛን ሇመንከባከብና ሇመርዲት ጊዜያቸውም ሁኔታቸውም ባይፇቅደሊቸው ይሆናሌ።
ካርቱም የነበሩት ኢትዮጵያውያን ግን በመግንስት የሰሊም የጦር አስተዲዯር ውስጥ በሹመት ሊይ ኖረው
በጡረታ የተገሇለም ባገሌግልት ሊይ የነበሩትም ነበሩ። እንዱሁም የንግዴና ሌዩ ሌዩ የግሌ ስራቸው
እየሰሩ ዯህና ኑሮ የሚኖሩት ብዙ ነበሩ። ታዱያ እኒያ ሰዎች የሚበዙት ዘሪሁንንና እኔን የጋራ ጠሊት
ከሆነው የፊሽስት ጦር ጋር ሲዋጉ ቆይተው ወዯ ሱዲን ከገቡት ኢትዮጵያውያን የመጀመሪያዎቹ እኛ
በመሆናችን እንዯሆነ አይታወቅም ‹እንዯ ክፈ ቀን እህሌ› እየተሻሙ በዬቤታቸው ይጋበዙን ስሇ ነበረ
ከቁስ በቀር ምሳን ራት እቤታቸው በዬቤታቸው ይጋበዙን ስሇ ነበረ ከቁርስ በቀር ምሳና ራት እቤታችን

95
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የምንበሊበት ጊዜ አሌፍ አሌፍ ሆነ። ይሌቁንም የሚጋበዙን ሁለ ዘሪሁንንና እኔን ብቻ ሳይሆን ሇኛ
ክብር ትሌቅ ዴግስ እዬዯገሱ ብዙ ሴቶችንና ወንድችን ኢትዮጵያውያን ጭምር ጋብዘው እዚያ ከመብለና
ከመጠጡ ጋር በሸክሊ የተቀረፀ ያገራችን ዘፇን እንጉርጉሮ ቀረርቶ ፈከራ፥…….ወዘተ በሙዚቃ ሲሰማ
ባንዴ ሊይ ሆነን ዯስ የሚያሰኘው ዯስ እያሰኘን የሚያሳዝነን የሚሸንጠው እዬነሸጠን አናሳሌፌ
የነበርንበትን ጊዜ ምንም ቢሆን አሌረሳውም፤ ትዝታው አብሮኝ ይኖራሌ።

አቶ ሀብቴ ዯስታ ካርቱም መጀመሪያ ካስተዋወቁኝ ኢትዮጵያውያን መሀከሌ ወዲገሬ እስኪመሇስ


ዴረስ በምክርና በስራም ዋና ረዲቴ የነበሩ አቶ «መንግስቱና ናይዝጊ» ነበሩ። አቶ መንግስቱ የኤላክትሪክ
ስራ አዋቂ ስሇ ነብሩ ከመንግስትም ከግሌ ዴርጅቶችና ሰዎችም ጋር የተዋዋለ እዬሰሩ ዯህና ንብረትና
በርከት ያለ ሌጆች የነበሩዋቸው ጭዋ ሰው ነበሩ። አቶ ሳሉም እና አቶ ኡመር የተባለ ከሀረር ሄዯው
በሱዲን ጦር ሰራዊት ውስጥ በመኮንንነት ማእረግ ሲያገሇግለ ኖረው ጡረታ የወጡ ሁሇት ሰዎችም ያቶ
መንግስቱን ያክሌ አይሁን እንጂ ዯህና ረዲቶቼ ነበሩ።

አቶ ሳሉም በጡረታቸው ሊይ ማሇፉያ የሌዩ ሌዩ ሸቀጦች ሱቅ ስሇ ነበራቸው ሀብት ካሊቸው


ኢትዮጵያውያን መሀከሌ አንደ ናቸው ሲባሌ እስማ ነበር። ግብዣ ከላሇኝ ብዙ ጊዜ እሳቸው ሱቅ
እዬሄዴሁ ነበር የማመሽ። ከሀይማኖት ጋር ተያይዞ በቆዬ ሌምዴ ይሁን ወይም በህግ የሚያስክር
መጠጥ መግዛት ሇሱዲኖች ክሌክሌ ስሇ ነበረና ሇኢትዮጵያውያን ግን ይፇቀዴ ስሇ ነበረ አንዴ አቶ ሳሉም
በጡረታ የተገሇለ የስሊም የጦር መኩዋንንት ጉዋዯኞቻቸው ገንዘባቸውን አዋጥተው ውስኪው፥ ቢራውና
ላሊው ሌዩ ሌዩ መጠጥ ባቶ ሳሉም ስም በገፌ ተገዝቶ እሳቸው ሱቅ እየተጠጣ ጭዋታውና ውካታው
በጣም ዯስ ያሰኝ ስሇ ነበረ እዚያ ማምሸት እወዴ ነበር። እኒያ ከሌጅነታቸው ጀምረው አብረው አዴገው፥
አብረው የሸመገለ ሰዎች እርስ በርሳቸው ሲጠራጠሩም ሲነጋገሩም ሲሰዲዯቡም ሌክ እንዯሌጅነታቸው
‹ስማ አንተ ሌጅ! ምን ማሇትህ ነው? አንተ ሌጅ! ምናባቱ ይኸ ሌጅ!› ነበር የሚባባለ። በጭዋታቸው
መሀከሌ እስበሳቸው አባት እናቶቻቸውን የሚሰዲዯቡባቸው ቃሊት በኛ ሌምዴ ከረኞች ሌጆች ካሌሆነ፥
ካዋቆች አፌ የማይወጡ ‹ነውር› ወይም ‹ፀያፌ› የምንሊቸው ነበሩ። ታዱያ እኔ አረብኛ መናገር
ባሌችሌም በመጠኑ መስማት ችዬ ስሇ ነበረ እኒያ ሽማግልች የሚሳዯቡባቸውን ቃሊት ስሰማ ሳቄን
መግታት ያቅተኝና ትንፊሽ እስኪያጥረኝ ከሌቤ ስስቅ እነሱ ዯግሞ እኔን እንዯ ቂሌ ቆጥረውኝ
«ኢነአሊቡክ!» ብሇው ትከሻየን እዬመቱ ይስቁብኛሌ።

ሇኛ ክብር ትሌቅ ዴግስ እዬዯገሱ በካርቱም ነዋሪዎች የነበሩትን ብዙ ኢትዮጵያውያን ከጋበዙት


ወይዛዝር መካከሌ በተሇይ እመይቴ ወይዘሮ ዯጊቱ ፇሇቀና እመይቴ ወዘርሮ ሊቀች (ያባታቸውን ስም
ረቻሇሁ) ዘሪሁንንና እኔን ሌክ እንዯ ቤተሰቦቻቸው ነበር የሚያዩን። ካርቱም እስክንሇቅ ዴረስ፥ እኒያ
ሁሇት ወይዛዝር ሌክ እንዯ ቤተሰቦቻቸው፥ ቀጠሮ ሳንጠይቅና ጊዜ ሳንጠብቅ ባሻን ጊዜ እቤታቸው
እዬገባን በሌተን ጠጥተን ተጫውተን የምንወጣባቸው ነበሩ።

96
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በጠቅሊሊው ዘሪሁንና እኔ ካርቱም የነበርንበት ጊዜ አገራችን በጠሊት እጅ የወዯቀችበት ከመሆኑ
ላሊ እኛ ወዯ ፉት ምን እንዯሚገጥመን የማናውቅ በመሆናችን በብርቱ ጭንቀት ውስጥ የነበርንበት ጊዜ
ነበር። ነገር ግን እዚያ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ሁለ በየበኩሊቸው እኛን ሇማስዯስት ያዯርጉሌን የነበረው
እንክብካቤ ርዲታቸው ፌቅራቸውና ጭዋታቸው የነበረብን ጭንቀት በሙለ ክብዯት እንዲይሰማን
የሚያዯርግና ብዙ ጊዜ እንዱያውም ጭንቀታችንን አስረስቶ ያዝናናን ስሇ ነበረ አሁን እንኩዋ
ሳስታውሰው ሌቤን ይነካዋሌ!

ካርቱም በቆዬንበት ጊዜ የጃንሆይ ዋና የሌፌኝ እስከሌካይ የነበሩት ‹ቀኛዝማች በሌሁ ዯገፈ›


ጃንሆይ ኢትዮጵያን ሇቀው ሲወጡ መጀመሪያ እስከ ኢዬሩሳላም ከዚያ፥ እስከ እንግሉዝ አገር
ሸኝተዋቸው ተመሌሰው እኛ ከመዴረሳችን ጥቂት ቀናት ቀዯም ብሇው በካርቱም በኩሌ ወዯ ጎሬ
ማሇፊቸውን ሰማን። በሌሁ ዯገፈ ጃንሆይን እንግሉዝ አገር አዴርሰው ወዯ ኢትዮጵያ የተመሇሱ ሇጠሊት
ሇመግባት ሳይሆን፥ ጠሊትን ሇመውጋት ነበር። ጣሉያኖች ኢትዮጵያን መያዛቸውን ካስታወቁ በሁዋሊ
አገራቸውን እየሇቀቁ ከወጡት ኢትዮጵያውያን መሀከሌ፥ በባእዴ አገር ስዯተኞች ሆኖ ከመኖር ቢከፊም
የኢትዮጵያ ዴሌ መመታት ያስከተሇውን ጠሊት ሁሇተኛ ዯረጃ ዜግነት እንዯ ህዝቡ ሁለ ተቀብል አገር
ውስጥ መኖርን መርጠው እንዯገና እዬተመሇሱ ወዯ ኢትዮጵያ የገቡ ብዙ መሆናቸውን ሰምቻሇሁ። ነገር
ግን በባእዴ አገር ተሰድ መኖርንም ባገር ውስጥ ሁሇተኛ ዯረጃ ዜጋ ሆኖ መኖርንም ተፀይፇው «ሇነፃነቴ
ወይ ሇሞቴ!» ብሇው ጠሊትን እስከ መጨረሻው ሇመዋጋት አብረዋቸው ከወጡት ተሇይተው በዚያ ብቻ
ወዯ ኢትዮጵያ የገቡ፥ እኔ እስከማውቀው ዴረስ በሌሁ ዯገፈ ብቻ ነበሩ!

ከቀኛዝማች በሁሌ በሁዋሊ ሌጅ ፇቃዯ ስሊሴ ህሩይም እንዯ ቀኛዝማች በሌሁ ከእንግሉዝ አገር
ተመሌሰው ሇጦርነት ወዯ ጎሬ መጥተው ከራስ እምሩ ጦር ሰራዊት ጋር ተጨምረዋሌ።

ክቡር ራስ እምሩ ገዝቼ እንዴወስዴሊቸው የፇሇጉትን የእቃ ዝርዝር ከሌጅ ሲራክ ከተቀበሌሁ
በሁዋሊ ከነበረን ገንዘብ ጋር እያነፃፀርሁ ስመሇከተው ምንም እንኩዋ ያገሩን ዋጋ ባሊውቅ እቃው ስሇበዛ
ገንዘቡ የማይበቃ መስል ታዬኝ። ራስ እንዴገዛ የፇሇጉት ሇወታዯር ዴንኩዋን የሚሆን ብዙ ጣቃ ካኪ፥
ሇቁስሌና ሇላልች ተራ ሇሆኑ በሽታዎች የሚሆን ሌዩ ሌዩ መዴሀኒት ሇስንቅ የሚሆን ዯረቃ ዯረቅና
በቆርቆሮ የታሸገ ሌዩ ሌዩ ምግብ እንዱሁም ብዙ ጥቃቅን ነገሮች ነበሩ። የእቃውን ዝርዝርና በባንክ
የነበረን ገንዘብ 33.000 የሱዲን ብር መሆኑን ሊቶ መንግስቱ ናይዝጊ አስታውቄ አሳባቸውን
ብጠይቃቸው እሳቸውም እንዯ እኔ ተጠራጠሩና የተፇሇጉት እቃዎች ከሚገኙባቸው እሳቸውም እንዯ እኔ
ተጠራጠሩና የተፇሇጉት እቃዎች ከሚገኙባቸው መዯብሮች ጠይቀን ጠቅሊሊ ግምት ብናገኝ የሚሻሌ
መሆኑን ስሇ ነገሩኝ ዞረን ጠይቀን ውዴ ሆነብን። ከዚያ ወዯ አቶ መንግስቱ ቤት ተመሌሰን ምን
ማዴረግ እንዯ ሚሻሇን ስንወያይ «እንዱህ እንዱህ ያለትን እቃዎች ሇመንግስት ወታዯሮችና ዴርጅቶች

97
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚሸጡ ኩባንያዎች እንዴንገዛ ፇቃዴ የምናገኝ ቢሆን ኖሮ በቀሊሌ ዋጋ ሇመግዛት እንችሌ ነበር»
አለኝ።

«ማን ይፇቅዴሌናሌ?» አሌሁዋቸው።

«እሱ ነው ችግሩ ዋናው አገረ - ገዥ ወዯ እንግሉዝ አገር ሄዯዋሌ። በምትካቸው የሳቸውን ስራ


የሚሰሩ ዋናው ፀሀፉ (ሲቪሌ ሴክሬታሪ) ናቸው። ታዱያ ዋናው ፀሀፉ ‹ሇመንግስት አገሌግልት
የማይውሌ እቃ ሇመንግስት በተተመነ ዋጋ ሇናንተ እንዱሸጡ ኩባንዮችን ማዘዝ አሌችሌም፥ ከስሌጣኔ
በሊይ ነው› ሳይለን የሚቀሩ አይመስሇኝም« አለ አቶ መንግስቱ።

«ዛሬ እኛ በምንገናኝበት ሁኔታ ሇሚገኙ ሁለ ሌዩ አስተያየት ተዯርጎ ፇቃዴ የሚሰጥባቸው


ምክንያቶች ይኖሩ ይሆናሌኮ። ታዱያ እንዱህ ያለ ምክንያቶች ይኖሩ እንዯ ሆነ ሉነግሩን ከሚችለ
የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እርስዎ የሚያውቁዋቸው የለም? ቢኖሩኮ ፇቃዴ ማግኘት የሚቻሌ መሆን
አሇመሆኑንና የሚቻሌ እንዯሆነም የሚኢያስችለትን ምክንያቶች ቢገሌፁሌን ይጠቅመን ነበር»
አሌሁዋቸው።

«እንጃ! እንዱህ እንዱህ ያሇውን የውስጥ ምስጢር ከሚያውቁት ሰዎች እንኩዋ የማውቀው ያሇ
አይመስሇኝም፤ ግን ዋናው ፀሀፉ ተቀብሇው እንዱያነጋግሩ ሉያዯርጉ ከሚችለ ሰዎች ጋር የሚተዋወቁ
ወዲጆች አሊጣም። ስሇዚህ ሇነሱ ሌንገራቸውና ዋናው ፀሀፉ ተቀብሇው የሚያነጋግሩህ ከሆነ ችግርህን
ነግረህ የምትፇሌጋቸውን እቃዎች ሇመንግስት በተተመነ ዋጋ ከሚሸጡ ኩባንያዎች ሇመግዛት ፇቃዴ
እንዱሰጡህ ጠይቃቸው። ቢፇቅደሌህ እሰዬ ነው! ባይፇቅዴሌህ መቸም ገንዘብህ ሉገዛ የሚችሇውን
ያክሌ ገዝተህ እንዲትሄ የሚከሇክሌህ የሇ! ምን ይቀርብሀሌ? ስሇዚህ እስቲ እንዴትገናኝ ሇማዴረግ
እንሞክር» አለ አቶ መንግስቱ። ከዚያ እኔም ባሳባቸው ተስማምቼ አንዴ ሳምንት ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ
ቀጠሮ ተዯርጏሌኛሌ ከ ‹ሲቪሌ ሴክሬታሪው› ጋር ተገናኘሁ።

ሲቪሌ ሴክሬታሪው ዯስ በሚያሰኝ ፇገግታ ሰሊምታ ሰጥተው ካስቀመጡኝ በሁዋሊ በኢትዮጵያ


ሊይ ፊሺስቶች ባዯረጉት የግፌ ወረራ እሳቸውም መንግስታቸውም እጅግ ያዘኑ መሆናቸውን ገሌፀው፥
ጣሉያኖች ኢትዮጵያን ሇመውጋት ገና የጦር ሰራዊትና መሳሪያ ወዯ ኤርትራና ወዯ ሱማሉያ በማጋዝ
ሊይ እንዲለም ጦርነቱን ከጀመሩ በሁዋሊም የእንግሉዝ መንግስት ካንዲንዴ መንግስቶች ጋር የግሌግሌ
አሳብ አቅርበው ጦርነቱ እንዱቀርና ነገሩ በእርቅ እንዱያሌቅ ብርቱ ጥረት አዴርገው ሙሶሉኒ
«አሻፇረኝ!» በማሇቱ የቀረ መሆኑን ነገሩኝ።

«ኢትዮጵያ የአሇም ማህበር አባሌ በመሆንዋ ነፃነትዋ እንዯሚጠበቅሊትና ከአባልቹ አንደ


ቢያጠቃት ማህበሩ አጥቂውን እንዯሚቀጣሊት ሙለ እምነት ነበራት። ስሇዚህ፥ እምነትዋን በማህበሩ ሊይ
ጥሳ ሳትጠነቀቅ በተቀመጠችበት ሙሶሉኒ የጦር ሰራዊቱንና መሳሪያውን በገፌ ወዯ ኤርትሪያና ወዯ

98
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሱማሉያ ማጋዝ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በያቅጣጫው እስከ ወሰናችን መገናኛ መንገድች ሰርቶና በወሰናችን
ዲር ሇዲር ምሽጎችን አጠንክሮ መሽጎ ስሇ ወጋን የሰሜን የመሀሌና የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች መያዝ
ችልዋሌ። ነገር ግን የነዚህ ክፌልች መሀሌ አገር አሁንም በኢትዮጵያ አርበኞች እጅ ነው። ከዚህ በሊይ
ዯግሞ በምእራብና በዯቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አገረ ገዥዎች ከነጦር ሰራዊታቸው በያገራቸው እንዲለ
ጦርነትቱን ሇመቀጠሌ በመሰናዲት ሊይ ናቸው። ስሇዚህ ጣሉያኖች የሰሜን የመሀሌና የምስራቅ
ኢትዮጵያ ከተሞች በመያዛቸው ጦርነቱ አያሌቅም ገና ይቀጥሊሌ። የምእራብ ዯቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ
ጣሉያኖች ባይሮፕሊን መዋጋት የማይችለበት ጫካ ብቻ ስሇሆነ በመጨረሻ አዴራጊዎች እኛ
እንዯምንሆን አንጠራጠርም!» አሌሁዋቸው አሊዋቂነቴን በሚገሌፅ የምነትና የዴፌረት አነጋገር።

«የኢትዮጵያውያን ጦረኝነትና ጀግንነት በአሇም ሁለ የታወቀሊቸው ነው። ሇዚህ በአፌሪቃ ካለት


አገሮች ሁለ እነሱ ብቻ ነፃነታቸውን ሇብዙ ሺህ ዘመን አስከብረው መኖራቸው አንዴ አይነተኛ ምስክር
ነው። ግን በታሪክ እንዯሚታየው ኢትዮጵያውያን ከውጭ ጠሊት ጋር ጦርነት ባዯረጉበት ቦታና ቤት
ሁለ የሌዩ ሌዩ አገረ ገዥዎችን ጦር ሰራዊት ባንዴነት እያስተባበሩ መርተው በዴሌ አዴራጊነት
የሚወጡ ነገስታት ነበሩ። ነገስታቱ ከላለ አገረ ገዥዎች እርስ በርሳቸው ይዋጋለ እንጂ ተባብረው
የጋራ ጠሊታቸውን አይወጉም ሲባሌ እንሰማሇን። እንዱሁም ንጉሱ አስተባብረው የሚመሩት የኢትዮጵያ
የጦር ሰራዊት ንጉሱ እጦርነት ውስጥ ቢወዴቁ ይበታተናሌ፤ እንጂ ተባብሮ ጠሊት መመከት አያውቅም
ሲባሌ እንሰማሇን። ሇምሳላ፥ እዚህ አገር ባፄ ዮሀንስ እየተመራ በመጣው የኢትዮጵያ ሰራዊትና በ
«መሀዱስቶች» የመራ በነበረው የሱዲን ሰራዊት መሀከሌ በተዯረገው ጦርነት ኢትዮጵያውያን አይሇው
ሱዲኖች የተሰሇፈበትን መስመር እዬሇቀቁ መሸሽ ከጀመሩ በሁዋሊ ዴንገት መሪው ዏፄ ዮሀንስ ተመተው
በመውዯቃቸው የኢትዮጵያ ጦር ፇርሶ መጨረሻ ዴለ ማህዱስቶች እንዯሆነ አንዲንዴ የዚህ አገር
ሽማግላዎች ጭምር ይተርካለ። ታዱያ አሁን የሁለም አስተባባሪ የነበሩት ንጉሱ አገራቸውን ሇቀው
በወጡበት ከአገረ ገዥዎች ያሊስተባባሪ ተባብረው በዘመናዊ የጦር ትምህርት ከሰሇጠነ የጦር ሰራዊትና
ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ካሇው ሀይሇኛ ጠሊት ጋር ጦርነቱን መቀጠሌ እንዳት ይችሊለ? በኔ አስተያየት
ከንግዱህ ወዱያ ጦርነቱን መቀጠሌ የሚፇሌግ ሰው ከንቱ ከመንገሊታትና ምናሌባትም ከመሞት በቀር
ዴሌ የማዴረግ ተስፊ ያሇው አይመስሇኝም። ከንግዱህ ወዱያስ አርፍ የተመቸ ጊዜ መጠበቅ ነው
የሚሻሇው» አለኝ።

«ጃንሆይ ከአሇም ማህበር ርዲታ ሇመጠየቅ እንጂ አንዴያቸውን አገራቸውን ሇቀው አሇመሄዲቸውን
የውጭ ጉዲይ ሚኒስቴራችን ዋና ፀሀፉ ሲራክ ህሩይ ወዯ እንግሉዝ አገር ሲሄዴ በቀዯም እዚህ
ተገናኝተን ነግሮኛሌ። ግን አንዴያቸውን ቢሄደ እንኩዋ ያገራችንን ሸሇቆና ጫካ ይዘው ስሊሌሄደ
ያገራአችን ሸሇቆና ጫካ ብዙ አመታት በውስጣቸው አቅፇው ሸሸተው ከጠሊታችን ተዋግተን ሇመጨረሻ
ዴሌ እንዴንበቃ ያዯርጉናሌ!» አሌሁዋቸው ከሞቅታ ጋር ‹ዴሌ የማዴረግ ተስፊ የሊችሁም› ሲለም
ዴንገት ስሜቴ ስሇታወከ ፉቴ ግልና አይኖቼ እንባ ሞሌተው።

99
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሲቪሌ ሴክሬታሪው በየዋህነቴ አዝነውሌኝ ይሁ ወይም፥ ታዝበውኝ ከቅርታ ፇገግታ ጋር ዝም
ብሇው ሲመሇከቱኝ ቆይተው፤ «እሺ እንግዱህ፤ እግዚአብሔር ይርዲችሁ! ታዱያ አሁን እኔ ምን
እንዴረዲህ ነው ሌታየኝ የፇሇግህ?» አለኝ።

«በሽሬ ግንባር የተዋጋው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት አዛዥ፥ ራስ እምሩ ጦርነቱን ሇመቀጠሌ


ወስነው ሰራዊታቸውን እንዯ ያዙ ወዯ ምእራብ ኢትዮጵያ ሲሄደ፥ እኔ ወታዯር ሌብስ፥ ስንቅና
መዴሀኒት ከዚህ ገዝቼ እንዴወስዴሊቸው ነበር ታዝዤ የመጣሁ። አሁን ተገዝቶ እንዱሄዴሊቸው
የሚፇሌጉትን የእቃ ዝርዝር ሲራክ ህሩይ አምጥቶ ሰጥቶኝ ከተመሇከትሁ በሁዋሊ የገብያውን ዋጋ ዞሬ
ብጠይቅ፤ ከሰጡኝ ገንዘብ በሊይ ሆኖ አገኘሁት። ስሇዚህ እርስዎን ሌሇምን የመጣሁ፥ ገንዘብ በሊይ ሆኖ
አገኘሁት። ስሇዚህ እርሶን ሌሇምን የመጣሁ፥ ሇመንግስት የጦርና የሰሊም ዴርጅቶች የሚያስፇሌጉትን
እቃዎች የሚሸጡ ኩባንያዎች ሇመንግስት በተተመነው ዋጋ ሇመግዛት ፇቃዴ እንዱሰጠኝ ነው ጌታዬ»
አሌሁ።

«ንጉሳችሁኮ ራስ እምሩ ከቤተሰባቸውና ከቅርብ ረዲቶቻቸው ጋር፥ በኢትዮጵያ አቅራቢያ


የእንግሉዝ መንግስት ከሚያስተዲዴራቸው አገሮች ወዲንደ ገብተው ሇመኖር እንዱፇቀዴሊቸው ጠይቀው፥
«ዩጋንዲ» ገብተው እንዱኖሩ ስሇታሰበ፥ የዩጋንዲ አገረ - ገዥ ተጠይቀው፥ የሳቸው መሌስ ነው
የሚጠበቀው። ታዱያ ራስ እምሩ ወዯ ዩጋንዲ የሚሄደ ከሆነ እቃውን መግዛት ሇምን ያስፇሌጋሌ?»
አለኝ።

«ጃንሆይ መቸ ነው ሇራስ እምሩ የእንግሉዝ መንግስት ከሚያስተዲዴራቸው አገሮች ወዲንደ


ገብተው እንዱኖሩ ፇቃዴ የጠዬቀሊቸው?»

«ቆይተዋሌ። የዩጋንዲ አገረ - ገዥ ከተጠየቁ እንኩዋ ካንዴ ወር በሊይ ሳይሆን የጻፈሌኝ


ወረቀትትና የእቃዎችን ዝርዝር ሲራክ ህሩይ አምጥቶ የሰጠኝ በዚህ ሳምንት ውስጥ ነውኮ! ስሇዚህ ሇኔ
እንዯሚመስሇኝ፥ ጃንሆይ ሇራስ እምሩ መኖሪያ የእንግሉዝን መንግስት ፇቃዴ የጠዬቁ የሳችውን ውሳኔና
ፇቃዴ ሳያውቁ በራሳቸው ፇቃዴ ሳይሆን አይቀርም። ይህን የምሌበት ምክንያት ራስ ጎሬ ከዯረሱ ጀምሮ
ከምእራብና ከዯብቡ ምእራብ ኢትዮጵያ አገረ - ገዥዎች ጋር ተሊሌከው ጦርነቱን ከህብረት ሇመቀጠሌ
የተስማሙ መሆናቸውን አሁን የእቃዎችን ዝርዝርና ሇኔ የተፃፇውን ትእዛዝ ከሳቸው ያመጣሌኝ፥ ሲራክ
ህሩይ ስሇ ነገረኝ ነው» አሌሁዋቸው።

«እንዲሌኸው ሉሆን ይችሊሌ» አለና ትንሽ ዝም ብሇው ቆይተው፤

«መግዛት የምትፇሌጋቸውን እቃዎች ዝርዝር አሁን ይዘሀሌ?» አለኝ።

100
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«አዎን ጌታየ» ብዬ በእንግሉዝኛ የተፃፇውን የእቃዎች ዝርዝር ከኪሴ አውጥቼ ሰጥቻቸው
ከተመሇከቱት በሁዋሊ አጥፇው እፉታቸው በጠረጴዛው ሊይ አስቀመጡና፤ «ስሇዚህ ፇቃዴ መስጠቱ
እንኩዋ አያስቸግርም፥ ቀሊሌ ነው። ሇዚህ ፇቃዴ መስጠቱን በላሊ ባይሆን ሇህሉና ከባዴ የሚያዯርገው
በዘመናዊ የጦር ትምህርት የስሇጠነና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ሰራዊት ካሇው ሀይሇኛ ጠሊት
ጋር ባድ እጃችሁን ያሇ መሪ ጦርነቱን ቀጥሊችሁ እንዴታሌቁ እንዯ መገፊፊትና እንዯ መዯፊፇር
የሚቆጠር መሆኑ ነው! የፊሽስቶችን ሀይሌ እናንተ አታውቁትም። ፊሽስቶች ወጣቶቻቸውን
ከሌጅነታቸው ጀምረው በዲቦ ፊንታ የጦር ትምህርት መግቢው እያሳዯጉ፥ ጠቅሊሊ ህዝባቸውን በሀብት
ፊንታ የጦር መሳሪያ እስኪከብዯው አሸክመው እያኖሩ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ‹አሇምን እንዯ
ሮማውያን አባቶቻችን እንገዛሇን› ብሇው የተነሱ እብሪተኞችና ሀይሇኞች ናቸው። ስሇዚህ በኔ አስተያየት
የኢትዮጵያ ጀግኖች በተሇይ እንዯናንተ ያሊችሁ በኔ አስተያየት የኢትዮጵያ ጀግኖች በተሊይ እንዯናንተ
ያሊችሁ ወጣቶች እንዱህ ባሇው ጎዯሇ ጊዜ፥ ያሊቀማችሁ ከሀይኛ ጠሊት ጋር ጦርነቱን ቀጥሊችሁ
ከምታሌቁ የተመቸ ጊዜ ሲያጋጥም አገራችሁ የሰው ዴሀ ሆና የሚያገሇግለዋት ሌጆች እንዲታጣ፥
የምትችለት ሁለ ይህን ጎዯል ጊዜ ዘወር እያሊችሁ ብታሳሌፈት የሚሻሌ ይመስሇኛሌ። ሇምሳላ አንተ
እንግሉዝኛ እንዯምትናገረው የምትፅፌ ከሆንህ፥ እዚህምን ቢሆን ስራ እዬሰራህ ሌትቆይ ትችሊሇህ»
አለኝ።

ሲቪሌ ሴክሬታሪው እንዱያ ያሇ ተስፊ የሚያስቆርጥና የሚያዯክም ነገር ሲነግሩኝ፥ ምናሌባት


እኒህ ሰው ፇረንጅ በመሆናቸው ወገኖቻቸውን ጣሉያኖችን ሇመርዲት ይሆን? ወይስ የጣሉያኖች ሀይሌ
የማይበገር፥ እጅግ ብርቱ ስሇሆነ እነሱን ሇመቁዋቁዋም መምከር ከማሇቅ በቀር ምንም ትርፌ የላሇው
መሆኑን ሊገኙዋቸው ኢትዮጵያውያን ሁለ እንዱሰብኩ ተገዝተው ይሆን? የማሇት ጥርጣሬ አዴሮብኝ
ነበር። ነገር ግን በረዥሙ ከተነጋገርን በሁዋሊ ያሊንዲች ማመንታት የጠዬቅሁት ፇቃዴ እንዱሰጠኝ
ሲያዯርጉ ሇምክር ብሇው የተናገሩትን በክፈ ተርጉሜ ስሇ ጠረጠርሁዋቸው ህሉናየ ወቀሰኝ።

«እኔ በሽሬ ግንባር ሇተዯረገው ጦርነት ተካፊይ ስሇ ነበርሁ፥ የፊሽቶች ሀይሌ ምን እንዯ ሆነ
አውቀዋሇሁ ጌታየ። የኢትዮጵያ መንግስት ሇአሇም ማህበር አባሌ በመሆኑ በማህበሩ ተማምኖ በሚገባ
ስሊሌተሰናዲ ፊሽስቶች በዚያ ተጠቅመው ከያቅጣጫው መንገድቻቸውን እስከ ወሰናችን ሰርተው
በወሰናችን ዲር ሇዲር ምቹ ቦታዎች እያዩ ምሽጎቻቸውን አጠንክረው መሽገው ጦርነቱ የተዯረገው
ወታዯርና መሳሪያ ሲያሌቅባቸው ከሁዋሊ ቶል በሚተኩባቸው ምሽጎቻቸው ሊይ ነበር። እንዱያም ሆኖ
ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ምሽግ ሰብረው ወይም አሌፇው እኒያን ‹ከሌጅነታቸው ጀምረው በዘመናዊ
የጦር ትምርት የሰሇጠኑ ፊሽስቶች› የጨበጣ ጦርነት ሲጋጠሙዋቸው ሬሳቸውን ቁስሇኞቻቸውንና
መሳሪያቸውን ጥሇው ይሸሹ ነበር! ሁዋሊ ብቻ አይሮፕሊኖቻቸውን አምጥተው ኢትዮጵያውያን
የተሰሇፈበትን ቦታን ከሁዋሊ ሲዯበዴቡ ኢትዮጵያውያን የያዙዋቸውን ምሽጎች ትተው ይሸሹና ፊሽስቶች
ከተጨማሪ ሀይሌ ጋር ሇቀዋቸው ወዯ ነበሩት ምሽጎቻቸው ይመሇሳለ። በዚህ አሆሁዋን ነው እስካሁን

101
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሰሜን፥ የመሀሌና የምስራቅ የኢትዮጵያን ከተሞች ሇመያዝ የቻለ። ወዯ ፉት ጦርነቱን ሇመቀጠሌ
የታሰበበት ኢትዮጵያ ምእራብና ዯቡብ ምእራብ ግን ፊሽስቶች መንገዴና ምሽግ ያሌስሩበት
አይሮፕሊኖቻቸው አሊማቸውን ተመሌክተው ሉመቱ የማይችለበት ጫካ ነው። ስሇዚህ እዚያ ምሽግና
አይሮፕሊን በላለበት የፊሽስትና የኢትዮጵያ ወታዯሮች ብቻ ሇብቻ በሚገጥሙበት ጦርነት እኔ ባዬሁት
መጠን ዴለ የኛ እንዯሚሆን ጥርጥር የሇውም!» አሌሁዋቸው፤ ከሞሊ ጎዯሌ ፈከራ በመሇስ አነጋገር።

«እሺ እንግዱህ ቅዴም እንዲሌሁህ የጠዬቅኸውን ፇቃዴ መሰጠቱ አያስቸግርም» ብሇው የገንዘብ
ክፌለን ሹም (ፊይናሻሌክ ሴክሬታሪ) በስሌክ ጠርተዋቸው መጥተው ከተነጋገሩ በሁዋሌካ ፇቃደ አሁን
ይሰጥሀሌ አለኝ። ከዚያ ፊይናንሻሌ ሴክሬታሪው» ሉሄደ ሲነሱ፥

«ይህ ወጣት ያሇኝን ሌንገርዎ!» አለዋቸው ሲቪሌ ሴክሬታሪው።

«ምን አሇ?»

«ንጉሳችሁ አገር ሇቀው ወጥተዋሌ። ያሇ መሪ ከሀይሇኛ ጠሊት ጋር ጦርነት መቀጠሌ እንዳት


ይሆንሊቸዋሌ?» ብሇው «ንጉሱ ያገራችንን ሸሇቆዎችና ጫካዎች ይዘው አሌሄደም፤ ሸሇቆዎቻችንና
ጫካዎቻችን ሇጠሊት አጋሌጠው አይሰጡንም በጉያቸው አቅፇው ሇመጨረሻ ዴሌ ያበቁናሌ» አሇኝ
አለዋቸው አኔ ባሌሁት ሊይም ጨማምረው።

«እውነቱ ነው አገር ካቀፇ በዘመናዊ መሳሪያ የሚዋጋን ጠሊት ባርበኝነት ከመከሊከሌ የተሻሇ
መንገዴ የሇም» አለና ፊይናንሻሌ ሴክሬታሪው «ፇቃደን አሁን ታገኛሇህ እማረፉያ ቤት ቆይ» ብሇውኝ
ወጡ። እኔም ሲቪሌ ሴክሬታሪውን አመስግኘ አቶ መንግስቱ ማረፉያ ቤት ተቀምጠው ይጠብቁኝ ስሇ
ነበረ ወዯሳቸው ሄጄ ፇቃደን ማግኘቴንም ከሲቪሌ ሴክሬታሪው ጋር የተነጋገርነውንም ባጭሩ
ስነገራቸው ዯስ አሊቸው። ከዚያ ምንም ያክሌ ሳንጠብቅ ፇቃዴ ወጥቶ ስሇ ተሊከሌን ወዲቶ መንግስቱ
ቤት ተመሇስን።

ምእራፍ አስራ አራት

ከካርቱም እስከ ጎሬ
የሲቪሌ ሴክሬተሪውን ፇቃዴ ካገኘን በሁዋሊ የፇሇግናቸውን እቃዎች ሇመግዛት እንኩዋንስ
ገንዘብ ሉያጥረን እንዱያውም መጠነኛ ገንዘብ ተረፇን። እቃዎችን እንዱሸጡ ከተፇቀዯሊቸው መዯብሮች
የመግዛቱንም ከተገዙ በሁዋሊ አሳስሮ በመርከብ የማስጫኑንም ስራ እኛ ምንም ሳንቸገር እንዱከናወን
ካዯረጉሌን ሰዎች ዋናዎቹ አቶ መንግስቱ ናይዝጊ አቶ ሀብቴ ዯስታና አቶ ዮሀንስ አንድም ያቶ መሇስ
አንድም፥ ወይዘሮ ጽዮን አንድምና የጄነራሌ አማን አንድም ወንዴም ነበሩ። ላልችም «ምን እንርዲ?»
የሚለ ብዙ ነበሩ።

102
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መቸም ያንዴ አገር ሰዎች ባገራቸው ሙለ ስምምነት ያሌነበራቸው ቢሆኑ እንኩዋ በባእዴ አገር
ሲገናኙ በመሀከሊቸው የነበረውን አሇመስማማት ረስተው ሇመቀራረብና ሇመረዲዲት እንዯሚፇሌጉ
የታወቀ ነው። ስሇዚህ ሱዲን ይኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያውያን፥ ዘሪሁንና እኔ የነሱም የኛም፤ የጋራ ጠሊት
ከሆነው የፊሽስት ጦር ሠራዊት ጋር ስንዋጋ ቆይተን ወዯ ሱዲን ስንሄዴ ያዯርጉሌን እንክባካቤና እኛን
ዯስ ሇማሰኘት ያዯርጉት የነበረው ርብራቦ ሁለ አያስገርም ይሆናሌ። የሚያስገርመው የሱዲኖች ነው።
ሱዲኖች አቶ ሳሉም ሱቅ ሲጫወቱ ከሚያመሹት ጀምሮ በላሊ ቦታም ዘሪሁንንና እኔን ከሚያገኙን
መሀከሌ የሚበዙት ከጦርነት መመሇሳችንን ሲሰሙ ሌክ እንዯ ዘመድቻቸው «እንኩዋን ዯህና
መጣችሁ!» እያለ እስኪጨንቀን እያቀፈ ይስሙን ነበር። ዘሪሁንና እኔ፥ ሱዲን በነበርንበት ጊዜ አገሩ
የእንግሉዝና የግብፅ «የጋራ ግዛት» (ኮንድሚኒየም) ነበር። ብቻ ሇስሙ «የጋራ ግዛት» ይባሌ እንጂ እኛ
ባዬነው መጠን የሰሊሙንም የጦሩንም አስተዲዯር የሚመሩት ሹማምንት እንግሉዞች ብቻ ነበሩ። ስሇዚህ
ሱዲኖች በገዛ አገር በባእዴ መገዛት ምን ያክሌ የውርዯት ውርዴት ምን ያክሌ ስሇዯረሰብን ስሇሚያውቁ
ያ! የሚያውቁት ውርዯትና ስቃይ በኛም ስሇዯረሰብን የውርዯትና የስቃይ ጉዋዯኞቻቸው የውርዯትና
የስቃይ ወገኖቻቸው በመሆናችን ይሆናሌ እንዯ ዘመድቻቸው ይመሇከቱን የነበር። እኛም እንዱያ
ሲያዝኑሌንና ያገራችን ነፃነት በመጥፊቱ ሲቆረቆሩ ስናይ ጠሊቶቻችነን ፊሽስቶችንም ከኛ ጋር ሲረግሙ
ስንሰማ እንዯ ወገኖቻችን እንጂ እንዯ ባእድች አናያቸውም ነበር። ስሇዚህ ዘሪሁንና እኔ ሱዲንን ሇቀን
ወዲገራችን ሇመመሇስ ከካርቱም ስንነካ አገራቸውን ትተው ከወገኖቻቸው ተሇይተው እንዯሚሄደ ሰዎች
ነበር ቅርታ የተሰማን።

መስከረም 1929 እንዯ ገባ፥ ዘሪሁንና እኔ በመርከብ ተሳፌረን ወዲ ወዲገራችን ሇመመሇስ


ተነሳን። ጥቂት ወዲጆቻችን አጅበውን እመሳፇሪያው ቦታ ስንዯርስ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን ዞረን
የተሰናበትናቸው ወይዛዝርና ሽማግልች እንኩዋ ሳይቀሩ ቀዴመው እዚያ ሲጠብቁን አገኘናቸው። በዚያ
አጭር ጊዜ ያፇራናቸው አንዲንዴ የሱዲን ወዲጆቻችንም ነበሩ። ከዚያ እቃችን ቀዯም ብል ተሳፌሮ ስሇ
ነበረ እኒያን ካርቱም በቆዬንበት ጊዜ እንዱያ ግሩም አዴርገው ያስተናገደንንና የረደነን ወገኖቻችነን ሁለ
አመስግነንና ተሰነባብተን፤ «በነጭ አባይ» ሊይ የመርከብ ጉዞዋችነን ጀመርን።

መርከብዋ ትሌቅ ካሇ መሆንዋም ላሊ ቁሌቁሌ የሚወርዯውን ውሃ እዬተጋፊች ሽቅብ ትሄዴ ስሇ


ነበረ ፌጥነት አሌነበራትም ቀስ ብሊ ነበር የምትጉዋዝ። ከካርቱም ተነስተን «ማሊካሌ» አጠገብ የ «ባሮ»
ወንዝ ከነጭ አባይ ጋር በሚገናኙበት እስክንዯርስ ስንት ቀን እንዯ ተጉዋዝን አሊስታውሰውም
ረስቸዋሇሁ። ነገር ግን ከካርቱም እስከ ጋምቤሊ የተጉዋዝነው በጠቅሊሊ፤ አስራ ሶስት ቀንና አስራ ሶስት
ላሉት እንዯ ሆነ ትዝ ይሇኛሌ። ግን ከዚህ፥ የባሮ መርከብ ዯርሳ፥ እቃሽን ከነጭ አባይ መርከብ ወዯ ስዋ
እስኪዛወር ማሊካሌ ሁሇት ቀንና ሁሇት ላሉት ስሇ ቆዬን ያ ሲቀነስ፥ በጠቅሊሊው በመርከብ የተጉዋዝነው
አስራ አንዴ ቀንና አስራ አንዴ ላሉት ነበር ማሇት ነው።

103
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ማሊካሌ ሁሇት ቀንና ሁሇት ላሉት ስንቆይ አንዴ የሱዲን ሴት አግብቶ በሚኖር አቶ «በየነ
አስፊው» በተባሇ ኢትዮጵያ ቤት ነበር ያረፌን። አቶ በየነ በመርከብ የሚሳፇሩትንና ከመርከብ
የሚወርደትን ሁለ የሚያስተናብር የመንግስት ሰራተኛ ስሇ ነበረ እቃችነን ከነጭ አባይ መርከብ ወዯ
ባሮ መርከብ ሇማዛወር አንዲች ችግር አሌገጠመንም ዘሪሁንና እኔ እየተቆጣጠርን የማዛወሩን ስራ እሱ
ነበር ያሰራሌን። እኒያ ዯጋግ ባሌና ምሽት እቤታቸው በቆዬንበት ጊዜ መጠነኛ ኑሮዋቸው በፇቀዯሊቸው
መጠን እኛን ዯስ ሇማሰኘት ያዯርጉት የነበረው መጣጣርና መቸጋገር ሌረሳው የማሌችሌ፤ ሁሌጊዜ ትዝ
ሲሇኝ የሚኖር ነው። የባሌና ምሽቱ ቤት አንዴ የነሱ ምኝታ ክፌሌና አንዴ እንዯ እንግዲ መቀበያም
እንዯ መብሌ ቤትም ሆኖ የሚያገሇግሌ በዴምሩ ሁሇት ክፌልች ብቻ የነበሩት ነበር። የመብሌና የመጠጥ
ችግር ያሌነበረ ከመሆኑ በሊይ ሁሇቱም ከማባበሊቸውና ከማቆሊመጣቸው ብዛት የተነሳ ዘሪሁንና እኔ
«በይለኝታ» ከጥጋብ በሊይ እዬበሊንና እዬጠጣን እንቸገር ነበር። በመኝታ ጊዜ ባሌና ምሽት የምኝታ
ክፌሊቸውን ሇኔ ሇቀው እነሱ ከዘሪሁን ጋር «እንግዲ መቀመያው ክፌሌ እንተኛሇን» ስሊለ ዘሪሁንና እኔ
እንግዲውም ያ ካሌሆነ ግን እውጭ እምኝታ ክፌሊቸው እንዴንተኛ ብሇምናቸውም ያ ካሌሆነ ግን
እውጭ እተኛ እንዯሆን እንጂ እነሱን አስሇቅቄ እምኝታ ቤታቸው እንዯማሌተኛ ባስፇራራቸውም
«ጭራሽ አናዯረገውም!» አለኝ።

«ሊንተ ብቻ ሳይሆን የተከበረ እንግዲ ስንቀበሌ ሁሌጊዜ የምናዯርገው ነው» አሇ አቶ በየነ።


ታዱያ በርከት ያሇ እቃ በመርከብ አስጭነን መጉዋዝችን ሌንከበር የሚገባን ሀብታሞች አስመስል
አሳይቶን እንዯሆነ እንጂ ዘሪሁንና እኔ በዴሜያችንም ሆነ በላሊ ሁኔታችን አንዲች የሚያስከብር ምሌክት
የሚታይብን አሌነበርንም። የሆነ ሆኖ አቶ በየነንና ባሌተቤቱን ሇምኘም አስፇራርቼም ውሳኔያቸውን
ማስሇወጥ ስሊሌቻሌሁ እየከበዯኝ መስተንግድዋቸውን ተቀብዬ፤ ማሊካሌን እስክንሇቅ ዴረስ እምኝታ
ቤታቸው ስተኛ እንዴቆይ ተገዯዴሁ።

የባሮ መርከብ ከነጭ አባይ መርከብ እንኩዋ በጣም ያነሰች ነበረች። የባሮ ወንዝም ከነጭ አባይ
ወንዝ በጣም ያንሳሌ። ሰዎች እንዯ ነገሩኝ በዋናው በጋ የባሮ ውሀ ሲጎዴሌ ያችን ትንሽ መርከብ
እንኩዋ ማስሄዴ ስሇማይችሌ መርከብዋ አገሌግልትዋን አቁዋርጣ የምትቆይበት ጊዜ አሇ። አንዲንዴ ቦታ
ወንዙ ከመጥበቡ የተነሳ መርከብዋ የግራና ቀኝ ግንድችን ሇመንካት ምንም ያክሌ አይቀራት። ስሇዚህ
ጠባቡን ቦታ እስክታሌፌ ቀስ ብሊ እየተጠነቀቀች ነበር የምትጉዋዝ።

መርከብዋ የባሮን ወንዝ ተከትሇው አሌፍ አሌፍ ከሚገኙት መንዯሮች አጠገብ ስትዯርስ
የሚወርደ መንገዯኞች ቢኖሩ ሇማውረዴና የሚሳፇሩ ቢኖሩ ሇማሳፇር ስትቆም፤ የመንዯሩ ነዋሪዎች
ሴቶች የሚበዙት፤ የሚወርደትንና የሚሳፇሩትን መንገዯኞች ሇማየት ብቻ ሳይሆን ገብያ ሇመገብየት
ጭምር የሚመጡ ናቸው። ከመስከረም ጀምሮ ወራቱ የሸት ስሇሆነ የተጠበሰም የተቀቀሇም በቀል

104
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አምጥተው ሇመንገዯኞች ይሰጡና በሇውጡ ስንቁ ያሇቀሇት ቆርቆሮ ጠርሙስ ወይም ላሊ እቃ
ይቀበሊለ።

የባሮን ወንዝ ተከትሇው እስከ ጋምቤሊ በሚገኙት መንዯሮች የሚኖሩት ነዋሪዎች ያንጊዜ
እንዲየሁዋቸው ሌብስ አሌሇበሱም፤ ራቁታችውን ነበሩ። ሴቶች ብቻ ከወገባቸው እስከ ጭናቸው አጋማሽ
ዴረስ ትንሽ ጨርቅ ያገሇዴማለ። ወንድች ግን እንዱሁ፥ እግዜር እንዴ እፇጠራቸው ርቃናቸውን
ናቸው። እንዱያውም «ተመሌካችን ይግረመው!» ብሇው በላልች ባህልች ሁለ እንዲይታይ መሸሸግ
ያሇበትን የወንዴነት አካሌ እነሱ የሰው አይን እንዱስብ ዙሪያውን ሊጭተው አካባቢውንና ራስ ዋናውን
በሌዩ ሌዩ ቀሇም ሸሌመው አስጊጠው ያሳዩታሌ ከዚህ ላሊ እኒያን በባሮ ወንዝ ዙሪያ የሚኖሩትን
ጥቁሮች ሁለ ከላልች የጥቁር ዘሮች ሌዩ የሚያዯርጋቸው የሚበዙት በቁመታቸው ልጋዎች በፉት -
መሌካቸው ሸጋዎች መሆናቸው ነው።

ከካርቱም ተነስተው የመርከብ ጉዞዋችነን ከጨረስን በሁዋሊ፥ ባስራ አራተኛው ቀን ይመስሇኛሌ


እጥዋቱ ሊይ ጋምቤሊ ዯረስን። የጋምቤሊ ከተማ በሁሇት ተከፌሊ የምስራቁ ክፌሌ በኢትዮጵያ
ባሇስሌጣኖች የምእራቡ ክፌሌ በእንግሉዝ ባሇስሌጣኖች ነበር የሚተዲዯሩ የመርከብዋ መቆሚያ
እንግሉዞች በሚያስተዲዴሩት ክፌሌ ስሇ ነበረ አቶ «ተክሇ ማርያም» የተባለ የኢትዮጵያ ጉምሩክ
አስተዲዯር ሹም ከጭፌሮቻቸው ጋርና ሇእንግሉዞች ክፌሌ አስተዲዲሪ የነበሩት እንግሉዛዊ ባሇስሌጣን
ካንዴ የንግሉዝ ሻሇቃ ጋር እዚያ ዴረስ መጥተው ተቀበለን። ሻሇቃው በጋምቤሊ የንግሉዝን ጥቅም
እንዱጠብቁና እዚያ ፀጥታ እንዱያስከብሩ ሇተመዯቡት ወታዯሮች አዛዥ ነበሩ።

ካቶ ተክሇ ማርያምና ከሰዎቻቸው ጋር ከተዋወቅን በሁዋሊ እሳቸው ከእንግሉዝ ባሇስሌጣኖች


ጋር አስተዋውቀውን እንግሉዞች ዯስ በሚያሰኝ ፇገግታ «እንኩዋን ዯህና መጣህ» እያለ ሰሊምታ
ሰጥተውኝና በውዲጅነት መንፇስ ሲያነጋግሩኝ ቆይተው ተሰነባብተን ሲሄደ እኔና ዘሪሁን እቃችን ወዲቶ
ተክሇ ማርያም መስሪያ ቤት ተግዞ እንዲሇቀ ከናቶ ተክሇ ማርያም ጋር ወዯ መስሪያ ቤታቸው ሇመሄዴ
መንገዴ ስንጀምር ራቅ ብል ቆሞ ሲጠባበቅ የቆዬ ሱዲናዊ ያስር አሇቃ፤ ሶስት ወታዯሮች አከትል
መጥቶ፥

«ወዯ ኢትዮጵያ ክፌሌ ከመሽገርህ በፉት ወዯኛ መስሪያ ቤት ሄዯህ ከእንግሉዛዊው አስተዲዲሪ
ጋር መነጋገር አሇብህ» አሇኝ ሇማስተዋሌ ያክሌ በሚበቃ እንግሉዝኛ።

«ካስተዲዲሪው ጋር አሁን እዚህ ስንነጋገር ቆይተን አሰናብተው ናሌኮ» አሌሁት።

«የሇም ከመስሪያ ቤታችን ዴረስ ሄዯን ማነጋገር አሇብህ!» አሇኝ ወታዯሮቹን ሲያዝ
እንዯሚያዯርገው ፉቱን ኮስተር አዴርጎ።

105
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ስራቱ እንዱህ ነው?» አሌሁ፥ ወዲቶ ተክሇ ማርያም ዘወር ብዬ።

«እስከ ዛሬስ እንዱህ ያሇ ስራት አሌነበረም፥ ግን አዱስ ስራት አውጥተው እንዯ ሆነ ምን


ይታወቃሌ? አስተዲዲሪው በቅርብ የመጥ፥ አዱስ ነው» አለኝ አቶ ተክሇ ማርያም።

«እስከ ዛሬ ተዯርጎ የማያውቅ ነገር ዛሬ በኔ የሚጀመርበት ምክንያት ምንዴነው? አሌሄዴም!»


አሌሁት ያስር አሇቃውን እገፊበት ይመስሌ አይኔን አፌጥጨ።

«እንዱያው ወዯ ኢትዮጵያ ክፌሌም አትሂዴ! ሁሊችሁም አትሄደ!» አሇ ያስር አሇቃ ከወታዯሮቹ


ጋር ቀዴሞ መንገዲችነን ዘግቶ።

«እስቲ ግዳሇም ሇማናቸውም ነገር አብረን እንሂዴ» አለ አቶ ተክሇ ማርያም።

«መሄዴ ካሌቀረስ፥ እኔ ሌሂዴና ችግር የተፇጠረ እንዯሆነ እሌክብዎታሇሁ» ብያቸው ከዘሪሁን ጋር


በወታዯሮች ታጅበን ወዯ እንግሉዞች መስሪያ ቤት ሄዴን። እዚያ ስንዯርስ ያስር አሇቃው አጥሩን
አስገብቶ ትቶን ወዯ አስተዲዲሪው ገብቶ ምን እንዯ ነገራቸው አሊውቅም እንግሉዛዊ አስተዲዲሪ ካጭር
ጊዜ በፉት ካየሁዋቸው ፌፁም ጭነን እንጋት ሊይ የሴሪቴን አቀበት ወጣን። አቀበቱን ስንወጣ፥ ሶስት
ጥምዴ «ባቱዎች» (ተሸካሚዎች) በተነጠፈ አሌጋዎቻቸው ሊይ መከዲዎቻቸውን አዴርገው ሶስት፥
ፇረንጆችን ተሸክመው ሲወርደ ተገናኘን። እኒያ ባሌጋ ሊይ ተኝተውም፤ ተቀምጠውም የሚጉዋዙ
ፇረንጆች በሽተኞች እንዯሆኑ ነጋዳዎችን ብንጠይቅ ላሉት፥ በበቅል ወዯ ጋምቤሊ መውረዴ ወይም
ከጋምቤሊ ቆሊውን መውጣት የማይፇሌጉ ፇረንጆችና አንዲንዴ የተመቻቸው ኢትዮጵያውያን ቀን በባቱ
መጉዋዛቸው የተሇመዯ መሆኑን ነገሩኝ።

ሴሪቴን ወጥተን «ቡሬ» ከምትባሌ ትንሽ ከተማ አጠገብ ስንዯርስ ጎጃም አስተማሪ ሳሇሁ አሇቃየ
ከነበሩት ካቶ (ሁዋሊ ፉታውራሪ) ወሌዯ ጊዮርጊስ ተዴሊ፥ ዯብረ ማርቆስ የራዱዮ ጣቢያው ሹም ከነበሩት፥
ካቶ (ሁዋሊ ዯጃዝማች) ገብረ መስቀሌ ሀብተ ማርያም ከሌጅ ሩት ካቶ (ሁዋሊ ዯጃዝማች) ገብረ መስቀሌ
ሀብተ ማርያም ከሌጅ (ሁዋሊ ዯጃዝማች) አሰጋኸኝ አራያና ካቶ ጉርሙ (ያባታቸውን ስም ረስቻሇሁ)
ጋር ተገናኘን። አቶ ጉርሙ ፇንሳይ አገር ስራ ይዘው ትዲር መስርተው ከሚኖሩበት ጣሉያን በኢትዮጵያ
ሊይ ጥርነት ስታዯርግ አገራቸውን ሇማገሌገሌ መጥተው ጦርነቱ በማሇቁ ወዯ ፇረንሳይ አገር
መመሇሳቸው ነበር። ላልች ተሰዯው ወዯ ሱዲን መሄዲቸው ነበር። ከናቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ ጋር እንዯ
ተገናኘን ነጋዳዎች ወዯ ጎሬ ጉዞዋቸውን እንዱቀጥለ አዴርገን ዘሪሁንና እኔ ከስዯተኞች ወገኖቻችን ጋር
ትንሽ አርፇን ሇመነጋገር ቡሬ ከተማ ገባን። እዚያ እናቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ ጠጅ ገዝተው እየጠጣን እነሱ
ስሇ ኢትዮጵያ ሁኔታ እኔ ስሇ ሽሬ ጦርነትና ከዚያ ከተመሇስን በሁዋሊ በሱዲን መንገዲችንም ሱዲን
በቆየንበት ጊዜም ስሊጋጠሙን መሌካምና ክፈ አጋጣሚዎች ስናወራ ካሰንበው በሊይ ቆዬን።

106
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ስሇ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስዯተኞች ወዲጆቼ ያወሩኝ ካርቱም ሌጅ ሲራክ ህሩይ ካወራኝ ብሩህ ተስፊ
የሚያሳይና የሚያበረታታ ወሬ ፌፁም የተሇዬ ነበር። እነሱ እንዯ ነገሩኝ ወሇጋን ጅማን ከፊን ባላን
ሲዲሞንና ጎምጎፊን ጣሉያኖች ገና ያሌያዙዋቸው መሆኑና ራስ እምሩ ከነዚህ አገሮች ገዥዎች
ካንዲንድቹ ጋር መሊሊካቸው እውነት ቢሆንም «ተባብሮ ጠሊትን ሇመቃወም በመሀከሊቸው ስምምነት
ተዯርጎ» የተባሇው እውነት አሌነበረም። ያን ጊዜ የተነጋገርንባቸው ቃሊት (ካንዲንዴ የረሳሁዋቸው በቀር)
በሙለ ትክክሌ ሉሆን ባይችለም በጠቅሊሊው የንግግራችን መስመር እንዯሚከተሇው ነበር።

«እንኩዋንስ ከጠሊት ተዋግቶ ነፃነታችነን የሚያስመሌስ ባሌተያዙት አገሮች ያሇውን የጦር


ሰራዊት ባንዴ ሊይ አስተባብሮ ሇመምራት ስሌጣኑን ሁለም አምነው የሚቀበለትና ጦርነቱን ዘሇግ ሊሇ
ጊዜ ሇመቀጠሌ የሚችሌ መሪ የሇም። እንዱያ ያሇ መሪ ቢኖርማ እኛስ አገራችነን ትተን የምሰዯዴ
ይመስሌሀሌ? እስካሁን ባሌተያዙት አገሮች ያለት አገረ - ገዥዎች ተባብረው ጠሊትን ሇመቃወም ሲለ
አንደ የላሊውን መሪነት ከመቀበሌ ይሌቅ ጠሊት ዯርሶ ሇየብቻቸው ተዋግተው ወይም ሳይዋጉ
ስሌጣናቸውን እስኪወስዴባቸው ዴረስ የበሊይ ሳይኖርባቸው መቆየቱን የሚመርጡ ናቸው። እንዱያውም
እንዯ ሰማነው ወሬና እኛም በዚህ አካባቢ እንዯ ተመሇከትነው ያሌተያዙት የምእራብና የዯቡብ ምእራብ
አገሮች ህዝብ ፉቱንም ጥሊቻ ቢኖረው ይሁን ወይም «ሇማያዘሌቅ ነገር አገራችነን የጦር ሜዲ
ያዯርጉብናሌ» ብል በመፌራት ይሁን፥ ከጠሊት ሇመዋጋት የተሰሇፈትን የኢትዮጵያ መንግስት ወገኖች
ሁለ እንኩዋንስ ሉረዲ ተቃዋሚነቱን ሇጠሊት ሇማሳዬት የሚፇሌግ ነው። ሇዚህ እንዯማስረጃ አዴርጌ
የምነግርህ የሆሇታ መኮንኖችና ወታዯሮች አብረዋቸው የነበሩት ሰሊማውያን ጭምር ሸሽተው ነቀምት
ከከረሙ በሁዋሊ እዚያ የወረዯውን የጣሉያን አይሮፕሊን አቃጥሇው ነጅውንና አብረውት የነበሩትን
ታሊሊቅ መኮንኖች ስሇገዯለ፥ ያገሩ ህዝብ ከዚያ እንዱባረሩ ማዴረጉን ነው። ስሇዚህ እንዱህ እንዱህ
ያሇውን ተቃውሞ እስኪያጋጥም ገሇሌ ብሇን መቆየቱ ይሻሌ ይሆናሌ› ብሇን ነው እያዘን አገራችነን
ትተን መሰዯዴን የመረጥን» አለ አቶ ወሌዯ ጊዮርጊስ ተዴሊ። ላልችም በዋናዎቹ የጦር ግንባሮች
የኢትዮጵያ ሰራዊት ዴሌ ከተመታ በሁዋሊ ከዬነበሩበት ቦታ የተመሇከቱትን እዬገሇፁ ተባብሮ ጠሊትን
ሇመቃወም የነበረው ተስፊ የመነመነ መሆኑን ነገሩኝ።

«ያገራችን ሰዎች ሲተርቱ፥ ‹ውሾች ቀን ባጥንት ይጣሊለ፤ ላት ጅብ ሲመጣባቸው እሱን


ሇመቃወም ይተባበራለ!› ይሊለ። ታዱያ ከውሾች የሚሻለት ሰዎች የጋራ ጠሊታቸው ሁለንም
እያጠቃቸው ሲመጣ እያዩ ተባብረው ያን የጋራ ጠሊታቸውን በመቃወም ፇንታ እንዳት እስበሳቸው
ሇመፊጀት ይነሳለ?» አሌሁ።

«አዬህ ሀዱስ! የሚበዛው የኢትዮጵያ ህዝብ ስሊሌተማረ መንግስትን ከሱ የተሇዬ እሱን እንዱገዛ
እግዚአብሔር በሊዩ የጫነበት ባሇስሌጣን አዴርጎ ነው የሚያየው። ስሇዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ቢገዛው
የጣሉያን መንግስት ቢገዛው ሌዩነት ያሇው መስል አይታዬውም። ስሇ ጣሉያን ዴሌ ማዴረግ ሰዎች

107
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሲነጋገሩ የሰማሁትን ሌንገርህ። ‹እኛ እንገዛ ይመስሌ እግዚአብሔር ከሰጠው ያበሻ ንጉስ ቢገዛ የፇርንጅ
ንጉስ ቢገዛ ምን አገባን? ‹እናቴን ያገባ ሁለ የእንጀራ አባቴ ነው› እንዯ ተባሇው አዯሌ› ሲሌ አንደ ‹ሌክ
ነው ሌክ ነው አለ ላልች። እየውሌህ የሚበዛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጦርነቱ የሁሇት ንጉሶች ወይም
የሁሇት ገዥዎች ጦርነት መሆኑንና የሱ ተግባር እግዚአብሔር ረዴቶት ዴሌ ሊዯረገው መገዛት ብቻ
መሆኑን የሚያምን ነው!» አለ አቶ ገብረ መስቀሌ ሀብተ ማርያም።

«መቸም ጦርነት የሚዯረገው ሇስሙ በመንግስቶች ወይም በገዥዎች መሀከሌ ይሁን እንጂ፤
ተዋጊው ሰራዊታቸው ወይም ህዝባቸው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም በረዥም ታሪኩ ከውጭ ጠሊቶቹ
ጋር ብዙ ጦርነቶች ሲያዯርግ ነገስታቱ ብቻቸውን ሄዯው የተዋጉበት ጦርነት የሇም ሁሌጊዜም ሰራዊቱ
ወይም ህዝቡ በጀግንነት ተዋግቶ ጠሊቱን ዴሌ እያዯረገ ነው ያገሩን ነፃነት አስከብሮ የኖረ። ስሇዚህ
እንዳት የኢትዮጵያ ህዝብ የጠሊት መንግስት ባገሩ ሊይ የሚያዯርገውን ጦርነት በንጉሱ ሊይ
እንዯሚያዯርገው እንጂ በሱ ሊይ እንዯሚያዯርግበት ስሇማይቆጥረው በግዳሇሽነት ይመሇከተዋሌ
ይለኛሌ? የውጭ መንግስቶች አገሩን የሚመሇከት ከሆነ ሇምን በብዙ ጦር ሜዲዎች ዯሙን እያፇሰሰ
ያገሩን ነፃነት ሲያከብር ኖረ?» አሌሁዋቸው።

«ይህ ያስተያየት ጉዲይ ያሇበት ስሇሆነ የሚያከራክር ነው። አዬህ? መቸም የኢትዮጵያ ወታዯር
ወይም በጠቅሊሊው የኢትዮጵያ ህዝብ ተፇጥሮው ጀግና መሆኑንና ባሇስሌጣን አክባሪ እንዯ መሆኑ
እንዱዋጋ ሲታዘዝ በጀግንነት ተዋግቶ ጠሊቶቹን ዴሌ እያዯረገ ያገሩን ነፃነት አስከብሮ የኖረ መሆኑ
በአሇም ሁለ የታወቀሇት ነው። ነገር ግን እንዱያ በጀግንነት እየተዋጋና ዯሙን እያፇሰሰ ያገሩን ነፃነት
አከብሮ የኖረ እንዱዋጋ ስሇታዘዘ ነው? ወይስ ባይታዘዝም ሊገሩ ነፃነት ሲሌ ተባብሮ እዬተነሳ
የመጣበትን ጠሊት ይዋጋ ኖሮዋሌ? ሁሇተኛ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ሊይ የሚያሳዩት ጀግንነት
ጦርነቱ፥ የሚቀሰቅሰው የተፇጥሮ ወኔ ነው? ወይስ ነፃነትን ሇማስከበር ካሊቸው ፅኑ ፌሊጎት የተነሳ ያገር
ፌቅር የሚቀሰቅሰው ነው? ወይስ ዯግሞ «ፇሪ» ተብል ሊሌመሰዯብ «ጀግና» ተብል ሇመከበር ነው?
ከነዚህ ጥያቄዎች ሁለ «ትክክሇኛው ይህ ነው» የምሌህ የሇኝም። እነዚህ ጥያቄዎች ሁለ በራሴ ውስጥ
ተነስተው መጉሊሊት የጀመሩ የቅርብ ጊዜ ወዱህ ነው። ዴሮ «በአፌሪቃ ምዴር ካለት አገሮች ሁለ
ኢትዮጵያ ብቻ ነፃነትዋን አስከብራ የኖረች ጀግኖች ሌጆችዋ በዬጊዜው ሉያጠቁዋት የመጡበትን ብርቱ
ጠሊቶች ሁለ ተባብረው ሇመቃወም በመቻሊቸው ነው» እዬተባሇ የሚተረከውን ታሪክ በሙለ ሌብ
እምኘ እኖርሊቸው ነው» እዬተባሇ የሚተረከውን ታሪክ በሙለ ሌብ አምኘ እኖር ነበር። ነገር ግን አሁን
ከጎጃም ተነስቼ እዚህ እስክዯርስ ከመኩዋንንቱ አንስቶ እስከ ተራው ህዝብ ሁለም የሚያዯርገውን ሳይና
የሚናገረውን ስሰማ የነበረኝ እምነት ተናጋብኝ። ይቅርታ አዴርግሌኝ ሀዱስ ወዯ ጦርነት ሇሚሄዴ ሰው
እንዱህ ያሇ የሚያዯክም ነገር ማናገር አይገባኝም ነበር። ግን ነገር ነገርን እየሳበ፥ ስሊስበው ብዙ መናገር
የማይገኝን ተናገርሁ» አለ አቶ ገብረ መስቀሌ።

108
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አቶ ወሌዯ ጊዮርጊስና አቶ ገብረ መስቀሌ በዴሜም ሆነ በውቀትና በአእምሮ ብስሇት ሇኔ
አስተማሪዎች የሚሆኑ አዋቂዎች ነበሩ። ሁሇቱም ፅኑ ያገር ፌቅር የነበራቸው መሆናቸውን ከማወቄም
ላሊ፥ የነገሩኝ ሁለ ከቅን ሌቡናና የህዝባችነን ሁኔታ ጠሌቆ ከማስተዋሌ የመነጨ መሆኑን
የሚያስጠረጥር አንዲች ምክንያት አሌነበረኝም። ይሁን እንጂ «ያ ብዙ ሽህ ዘመን ከሌዩ ሌዩ ሀይሇኞች
ጠሊቶች ጋር እየተዋጋ ነፃነቱን አስከብሮ የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ የሁለንም ጠሊቱን ሉያጠፊ የመጣ
ጠሊአቱ በፉቱ ተሰሌፍ እያዬው ተባብሮ የጋራ ጠሊቱን በመቃወም ፇንታ እስበሱ ተዋግቶ እንዲይተሊሇቅ
በሚያሰጋ ሁኔታ ሊይ ነው» ያለትን አስተያየት መቀበለ አስቸገረኝ። ግን «የጠሊት አይሮፕሊንና ታንክ
በሙለ ሀይሊቸው ተካፊዮች በማይሆኑበት ረዥም የጫካ ጦርነት ተባብረን ሀይሊቸው ተካፊዮች
በማይሆኑበት ረዥም የጫካ ጦርነት ተባብረን ጠሊታችነን አዴክመን መጨረሻ ዴሌ የኛ እንዯሚሆን»
የነበረኝ እምነት እነሱ የተናገሩትን ከሰማሁ በሁዋሊ መዴከሙ አሌቀረም።

የሆነ ሆኖ ከስዯተኞች ወዲጆች ጋር እንዱያ ያሇፇውንም የወዯፉቱንም ችግራችነን ሰፊ አዴርገን


ከተወያየን በሁዋሊ እየተሊቀስን በንባ ተሰነባብተን እነሱን እዚኢያው ትተናቸው ዘሪሁንና እኔ ወዯ ጎሬ
ጉዞዋችነን ቀጠሌን።

ምእራፍ አስራ አምስት

ጎሬ
ጎሬ እንዯ ዯረስን እቃውን እንዱረከቡ ክብር ራስ እምሩ ሇመዯቡዋቸው ሰዎች አስረክበን እኔም
ሂሳቤን አስወርጄ ተገሊገሌሁ ነፃ ሆንሁ። አቡነ አብርሃም፥ ሊቶ ዮሀንስ አብደና ሇኔ እንዱያስረክቡን
ተፅፍሊቸው የነበረውን ገንዘብ ስሇከሇከለን እቃው የተገዛው ከዯጃዝማች አያላው ሌጅ ከፉታውራሪ
መርሶ በተከብነው ገንዘብ ብቻ መሆኑን ሇራስ ስነገራቸው አቶ ዮሀንስ ሳይነግራቸው ቀርቶ እንዯሆነ
ወይም ነግሮዋቸው ረስተውት እንዯሆን አሊውቅም እንግዲ ሆኖባቸው ተገረሙ! አቶ ዮሀንስን ግን ጎሬ
አሊገኘሁትም ጎሬ እንዯ ዯረሰ ወዱያው ወዯ ሱዲን መሰዯደን ሰማሁ።

ትንሽዋ የጎሬ ከተማ በቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅ ተጠባባዊነት ሇተቁዋቁዋመው የኢትዮጵያ ጊዜያዊ
መንግስት መንበር በመሆንዋ ጦርነቱን ሇመቀጠሌ የወሰኑትም ገና ያሌወሰኑትም ሁለ ተሰብስበው
የሚገኝባት ስሇ ነበረች መቆያ ሇማግኘት ቀሊሌ አሌነበረም። እኔና ዘሪሁን ግን ራስ በነእብሩበት ሰፉ ግቢ
ውስጥ ሁሇት ክፌልች እንዴናገኝ ስሇ ታዘዘሌን ጎሬን እስክንሇቅ ዴረስ አሌተቸርንም። ያ፥ ራስ የነበሩበት
ሰፉ ግቢ በውስጡ ከነበሩት ማሇፉያ ቤቶች ጋር «ሌጅ ተዴሊ ሀይሇ ጊዮርጊስ» የተባለ የመንግስት ትሌቅ
ሹም ንብረቶች ኖረዋሌ። ታዱያ ሌጅ ተዴሊ ጦርነቱ ሲጀመር ከጣሉያኖች ጋር ሲሻረኩ ስሇ ተገኙ
እሳቸው በስቅሊት ተቀጥተው ንብረታቸው ሁለ የተወረሰ መሆኑ ያን ጊዜ በግሀዴ ይነገር ነበር።

109
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ዘሪሁንና እኔ ያመጣነውን እቃ አስረክበን የታዘዘሌንን ማረፉያ ካገኘን በሁዋሊ እኔ ከመንግስቱ
ተጠባቂ ከቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅ ጋር ሇመገናኘት ወዯ ጊዜያዊው ቤተ መንግስት ሄዴሁ። ቢትወዯዴ
ወሌዯ ፃዴቅ ሇኔና ሇጥቂት ጉዋዯኞቼ፥ ተፇሪ መኮንን ትምርት ቤት በነበርንበት ጊዜ የማይረሳ ርዲታ
ያዯረጉሌን ባሇውሇታችን ስሇ ነበሩ ማየት ነበረብኝ።

‹የቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅ ውሇታ› ያሌሁት ምንም እንኩዋ ከመንገዴ የወጣ ቢመስሌ በዚህ
መፅሀፌ ምእራፌ ሶስት ከተመሇከተው «ያበሻና የወዯሁዋሊ ጋብቻ» ከተባሇው ትያትር ጋር የተዛመዯ
ከመሆኑ ላሊ የሌጅነት አሰባችንን አሁን መሇስ ብዬ ሳስታውሰው፥ እኔን እያጫወተ እንዯሚያስቀኝ
«አንባቢዎችንም ሇማጫወትና ሇማሳቅ ያክሌ ያገሇግሌ ይሆናሌ» በማሇት ከዚህ ቀጥየ እፅፇዋሇሁ።

የተፇሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጊዜው ይሰጥ የነበረው ትምህርት አጥጋቢ ካሇ


መሆኑም ላሊ፥ አንዲንዴ አስተማሪዎች ችልታ ያሌነበራቸው በመሆናቸው እንዱሇወጡ ችልታ ካሊቸው
መሀከሌም አንዲንድቹ የስካር አመሌ ስሇ ነበራቸ በትምርት ጊዜ ሰክረው እቤታቸው የሚውለ
በመሆናቸው አቤቱታቸውን ዯጋግመው አሰምተው ምንም ስሊሌተዯረገሊቸው በፇትና ጊዜ አዴማ
አዴርገው «አንፇተንም» አለ። ወዱያው ባሇስሌጣኖች «እንዱያ ሊሇው አዴማ ጠንሳሾችም መሪዎችም
ባዲሪነት የሚማሩት ትሌሌቅ ተማሪዎች ሳይሆኑ ስሇማይቀሩ ከወሇጋ ሌጆች በቀር እዴሜያቸው
ተማሪዎች ሳይሆኑ ስሇማይቀሩ ከወሇጋ ሌጆች በቀር እሜያቸው አስራ ስምንት አመትና ከዚያ በሊይ
የሆኑ ላልች ተማሪዎች ሁለ ካዲሪነት ወጥተው በተመሊሊሽነት እንዱማሩ» የሚሌ ዯንብ አወጡ።
ወሇጎችን ከዚያ ጨካኝ ዯንብ ነፃ እንዱወጡ ያዯረጋቸው «የወሇጋ ገዥ የነበሩት ዯጃዝማች ሀብተ
ማርያም ገብረ እግዚአብሔር ሇያንዲንዲቸው ከመክፇሊቸው ላሊ ትምህርት ቤቱን ጠቅም ባሇ ገንዘብ
ይረደ ስሇ ነበረ ነው» ይባሌ ነበር። የሆነው ሆኖ ያ ዯንብ ከወጣ በሁዋሊ፥ በተመሊሊሽነት
ትምህርታቸውን መቀጠሌ የሚችለ አዱስ አበባ ዘመድች የነበሩዋቸው ካሌሆኑ ከየክፌሊተ ሀገሩ
ተሰብስበው ባዲሪነት ይማሩ የነበሩት አስራ ስምንት አመትና ከዚያ በሊይ እዴሜ የነበራቸው ሁለ
ትምህርታቸውን አቁዋርጠው «የትሜና» እንዱሄደ ተፇረዯባቸው ማሇት ነው! ስሇዚህ እዴሜያችን
አስራ ስምንት አመትና ከዚያ በሊይ የሆነ ትሌሌቅ ሌጆች ተሰብስን ትምርታችንን ሇመቀጠሌ ማዴረግ
የምንችሇው ነገር ባይኖርም ሳንበታተን ባንዴ ሊይ ሆነን እስከዚያ ዴረስ ተምረን ባገኘነው እውቀት
ያስተማረችንን አገራችንን የምንረዲበት መንገዴ ፇሌገን ማግኘት እንዲሇብን ተስማማን። ሁሇት ወይም
ሶስት ጊዜ ያክሌ በዴብቅ እየተሰበሰብን ከተመካከርን በሁዋሊ ማህበር እንዴናቁዋቁም ወስነን፥ እኔ ሰብሳቢ
ገብረ አብ ቢያዴግሌኝ ፀሀፉ ተወሌዯ ብርሃን ገንዘብ ያዥ ሆነን ተመረጥን።

የማህበሩ አሊማ ከትምርት ቤት ወጥተው ስራ የያዙ አባልች ሁለ በዯመወዛቸው መጠን


የተወሰነ መዋጮ አዋጥተው ስራ ካሌያዙት መሀከሌ ትያትር መዴረስ የሚችለት እዬዯረሱና
የማይዯርሱትን «በተዋናያንነት» እያሰሩ ገንዘብ ሰብስበው በኒህ በሁሇት መንገድች በሚገኘው ገንዘብ

110
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መጠን የህሌ ወፌጮዎች ማቁዋቁዋም ከዚያ በሁዋሊ ከዯመወዝ መዋጮ ከትያትርና ከወፌጮዎች
የሚገኘው ገንዘብ እየበረከተ ሲሄዴ ከህሌ ወፌጮ ተራምድ በኢትዮጵያ ከተሞች ሁለ በየተራ
የኤላክትሪክ ሀይሌና መብራት ማቁዋቁዋም ከዚያ ተራምድ የጨርቃ ጨርቅ የጫማና የብረት ማቅሇጫ
ፊብሪካዎች ማቁዋቁዋም ከዚያ በሁዋሊ እንዱያ ካንደ ተነስቶ፤ በዚያ ርዲታ ወዯ ላሊው እየተሸጋገሩ ሌዩ
ሌዩ ከባባዴ ፊብሪካዎችን በማቁዋቁዋም ኢትዮጵያን የሰሇጠኑት አገሮች በዯረሱበት እንዴትዯርስ ማዴረግ
ነበር! አቤ - ት እንዳት ቀሊሌ ነው! «ሌጆች ሰማይን እንዯሚያዩት ቅርብ መስልዋቸው ሉመቱት
ዯንጋይ ሽቅብ ይወረውሩበታሌ!» እንዯሚባሇው አዯሌ? ታዱያ በዚያ አሊማ በሌጆች ሸንጏ ተሰብስበን
ባንዴ ዴምፅ ተስማማን። ስሊፇፃፀሙ በመጀመሪያ ዯረጃ እኔ «ያበሻና የወዯሁዋሊ ጋብቻ» የተባሇ ትያርት
ዯርሼ ትምርት ቤት ሲዘጋ እንዱታይሌኝ ያንጊዜ የትምርት ሚኒስትር የነበሩትን «ብሊቴ ጌታ ህ ሳህላ
ፀዲለን» ጠይቄያቸው ከተመሇከቱት በሁዋሊ «ትምርት ቤት ቤት በሚዘጋበት ጊዜ የውጭ አገር አገር
ዱፕልማቶችና ሉኤልች ፇረንጆች ስሇሚገኙ በማያውቁት ቁዋንቁዋ እንዱያ ያሇ ረዥም ትያትር
ማሳየት አይገባም!» በማሇታቸው ሳይታይ ቀርቶ ስሇ ነበረ ቲኬት አሳትመን ሸጠን እሱን ሆቴሌ
ሇማሳየት ወሰን። ከዚያ በሁዋሊ አስቸጋሪው ነገር የትምህርት ሚኒስትሩ እንዲይታይ የከሇከለትን
ትያትር በተሇይ ጃንሆይ ካሌፇቀደ ማሳየት የማይቻሌ ስሇሆነ የብሊቴ ጌታ ሳህላ ፀዲለን ጥሌ ሳይፇራ
በትምርት ሚኒስቴር ስራ ገብቶ ጃንሆይን ሇማስፇቀደ የሚዯፌር ባሇስሌጣን የማግኘቱ ጉዲይ ነው።

በዚያ ጊዜ ያገር ግዛት ሚኒስትር የነበሩት ቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅ «ቅንና ሇሚያምኑበት ነገር
ከማንም ጋር ቢሆን ከመጋፇጥ ወዯ ሁዋሊ የማይለ ናቸው!» እየተባሇ ሲነገር እንሰማ ስሇ ነበረ
ወዯሳቸው ሄዯን እንዴንሇምናቸው ተስማማን። ስሇዚህ ገብረ አብ ቢያዴግሌኝና እኔ ሄዯን ስንሇምናቸው
ምንም ሳያመነቱ ትያትሩን አሳይተናቸው የሚጠቅም መሆኑ ከተረደት እንዯሚያስፇቅደሌን ተስፊ
ሰጥተውን በማግስቱ ወስዯን ሌናሳያቸው ቀጠሮ አዴርገውሌን ተመሇስን። በቀጠሮዋችን እሳቸው ከስራ
ከመመሇሳቸው ቀዴመን እግቢያቸው በቀጠሮዋችን እሳቸው ከስራ ከመመሇስቸው ቀዴመን እግቢያቸው
ገብተን ስንጠብቅ መጥተው ከኦተመቢሌ እንዯ ወረደ ሲያዩን ይዘውን ገቡ። ክረምት ስሇ ነበረ ይወይራ
ፌሌጥ «ግወ» ብሇው ነድ ቤቱን አሙቆት ነበር። ቢትወዯዴ ገብተው በተነጠፇ ዴሌዲሊቸው ሊይ ከቀኝና
ከግራ መከዲዎቻቸው መሀከሌ ከተቀመጡ በሁዋሊ ሁሇታንች ባጠገባቸው ቆመን እኔ ትያትሩን
ከመጀመሪያው ጀምሬ ማንበብ ጀመርሁ። አንዲንዴ ነጥቦች እንዱብራራሊቸው ሲጠይቁም፤ ሇማብራራትና
ላልች ጥያቄዎች ሰፊ ወዲሇ ክርክር ይመሩ ስሇ ነበረ፥ ስንከራከር ባንዴ ማታ ስናጨርስ ቀርተን፥
በተከታዩ ማታ እንዯ ገና ሄዯን ጨረስን።

«ማሇፉያ ትያትር አዘጋጅታችሁዋሌ፤ እግዚአብሔር ይባካችሁ ሌጆቼ። መማራችሁ እንዱህ


እንዱህ ያሇ ስራ እየሰራችሁ ያሌተማረውን እንዴታስተምሩ ነውና በርቱ። አሁን የት ሆቴሌ ነው
ሇማሳየት ያሰባችሁ?» አለ ቢትወዯዴ ዯስ ብልዋቸው።

111
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ማጀስቲክ ሆቴሌ በሚባሇው ነው»

«እንግዱህ ሉያዩት የሚገባ ማሇፉያ ትያትር መሆኑን አስረዴቼ ቢመቻሇው ጃንሆይ ራሳቸው
ሄዯው እንዱያዩሊቸው ባይመቻቸው ሇማሳየት እንዱፇቀዴሊችሁ እነገራቸዋሇሁ» ብሇው መሌሱን ከሶስት
ቀን በሁዋሊ እንዴንጠይቃቸው ቀጠሮ ሰጥተውን ተመሇስን። በቀጠሮዋችን ስንሄዴ ጃንሆይ ሆቴሌ ሄዯ
ትያትር ሇማየት የማይመቻቸው በመሆኑ ካሌጋ ወራሽ ጀምሮ፥ ራሶች፥ ዯጃዝማቾችና ላልች ታሊሊቅ
ሰዎች ትያትሩ ሆቴሌ በሚታይበት ቀን ሄዯው እንዱያዩ ባገር ግዛት ሚኒስትር ቀሊጢነት እንዱታዘዝ
የተረፇውን ቦታ ቲኬት ገዝቶ ማየት ሇሚፇሌግ ሁለ እንዴንሸጥ የተፇቀዯሌን መሆኑን ነገሩን። አቤ -
ት ያን ጊዜ የተሰማን ዯስታ! ያን ጊዜ የተሰማንን ዯስታ ሉገሌፁት የሚችለ ቃሊት አይገኙም! ያን ጊዜ
የሩቅ አሊማችንን የመታን መስል ተሰምቶን የምስራቹን፥ ሇማህበርተኞችን ሇመንገር በዯስታ እየፇነዯቅን
ሄዴን።

በተከተለት ሁሇት ሳምንቶች ከትምርት ቤቱ ዘበኞች ጋር ተሻርከን ላሉት ላሉት ሰው ሁለ


ሲተኛ የትያትር ማሳይውን አዲራሽ መስኮቶች እየዘጋን እዚኢያ ተዋንያኑ ሌምምዲቸውን ሲያዯርጉ
ሰነበቱ። ሌምምደ ዯህና ሆኖ ከተጠናቀቀ በሁዋሊ ትያትሩ ሶስት ሰአት ያክሌ እንዯሚፇጅ ስሇ ታወቀ፥
የሆቴለን የትያትር ማሳያ አዲራሽ ሇሶስት ሰዒት በሰማንያ ብር ተከራይተን እዚያ እንዱታይ አዯረግን።
ሇትያትሩ መክፇቻ እንዱሆን «ተነሱ ታጠቁ» የተባሇውን ያገር ፌቅር መቀስቀሻ መዝሙር የዯረስሁት
ሌምምደን እናዯርግ በነበርንበት ጊዜ ነው። በቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅ ቀሊጢነት ሇተጠሩት መሳፌንት
መኩዋንንትና ብዙ ታሊሊቅ ሰዎች እንዱሁም ቲኬት ሇገዙት ሁለ ያ ሰፉ አዲራሽ «አሌበቃ» ብል
በየመኮቱ ጠርዝ ተቀምጠውና ግንቡን እዬተዯገፈ ዙሪያውን ቆመው የሚያዩ ብዙ ነበሩ። በቢትወዯዴ
ቀሊጢነት ከተጠሩት መኩዋንንት መሀከሌ «አሞኛሌ» ብሇው ሳይመጡ የቀሩ ብሊቴን ጌታ ሳህላ ፀዲለ
ብቻ ነበሩ።

ሀበሻ ወዯ ሁዋሊን አግብታ ከመዯህየትዋና ከመንገሊታትዋ የተነሳ በሌቅሶ ብዛት አይነ በሽተኛ ስትሆን
ዝም ብሇው በመመሌከታቸው ሌጆቹዋን እየወቀሰች በፉታቸው ተቀምጣ በዜማ ስታሇቅስ ከተጠሩት
መኩዋንንትም ቲኬት ገዝቶ የሚያየው ህዝብም መሀከሌ፤ አብረዋት የሚያሇቅሱ ብዙ ነበሩ። ትያትሩን
ያዩት ሁለ ከመውዯዲቸ የተነሳ በጃንሆይ ትእዛዝ ከተጠሩት መሀከሌ ጥቂቱ የገንዘብ ስጦታ አዯረጉሌን።
ራስ ብዙ አንዴ መቶ ብር ላልች ካምሳ ብር ጀምሮ ወዯ ታች ሰጡ። ያን ትያትር ያዩት አይተው
በመውዯዲቸው ያሊዩት ካዩት ሰምተው ሉያዩት በመፇሇጋቸው ተዯግሞ እንዱታይ በጋዜጣ የፃፈት ስሇ
ብዙ፥ ባጭር ጊዜ ውስጥ ቲኬት አሳትመን ሽጠን ሁሇተኛ አሳዬነው። ሁሇተኛ ሲታይ ማጀስቲክ
ሆቴሌም ከመውዯደ የተነሳ ኪራይ ሳያስከፌሌ በነፃ እንዴናሳይ ፇቀዯሌን። ስሇዚህ ሊንዴ ጊዜ የሆቴሌ
ኪራይ ሇቲኬት ማሳተሚያና ሊንዲንዴ ጥቃቅን ወጪ ያዯረግነው ተቀንሶሇት ሁሇት ጊዜ ካሳዬነው
ቲያትር ከሰባት ሽህ ጠገራ ብር በሊይ ትርፌ አግኝተን ተወሌዯ ብርሃን (ገንዘብ ያዣችን) ባንክ

112
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዱያገባው አዯረግን። ከዚያ ወዱያስ? ከዚያ ወዱያማ ምንም ያክሌ ጊዜ አዱስ አበባ ሳንቆይ በስራ ወዯ
የጠቅሊይ ግዛቱ እንዴንበታተን ተዯረገ! ሊገራችን እዴገት የታሰበው ብርም፤ ባንክ እንዯ ተቀመጠ፥
ነፃነትዋን ሉያጠፈ ሇመጡት ፊሽስቶች ሆነ!

አሳባችን የሌጆች አሳብ እንዯ መሆኑ በህሌም ተራ እንዯ ሆነ እንጂ በዴገት እቅዴ ተራ ገብቶ
የሚታይ አሇመሆኑ መቸም የቅዴንና ያፇፃፀሙን ስራ ሇሚያውቁ ሁለ ግሌፅ ነው! ግን ቢትወዯዴ
ወሌዯ ፃዴቅን ጎሬ ከማግኘቴ ጋር ከብሊቴን ጌታ ሳህላ ፀዲለ ጋር በነበረን ፌሌሚያ የዋለሌን ውሇታ
ትዝታዎቻቸው እስከ ዛሬ ከሚያጫውቱኝ የሌጅነት አሳቦቻችንና ትግልቻችን አንደ ስሇ ሆነ፤
«አንባቢንም ያጫወት ይሆናሌ» በማሇት ነውና እዚህ ሊይ ያሇ ቦታው ጣሌቃ ያገባሁት፤ ይቅርታ
እንዯሚዯረግሌን ተስፊ አዯርጋሇሁ።

ቢትወዯዴ አሌረሱሌኝ ኖሮ ገና ሲያዩኝ ረዥም ጊዜ ተሇይቶዋቸው እንዯ ኖረ ዘመዲቸው አቅፇው


ሳሙኝ። ከዚያ ስሇ ራሴም ስሇሚያውቁዋቸው ጉዋዯኞቼም ጤንነትና የኑሮ ሁኔታ እየጠየቁኝ ስንነጋገር
ከቆየን በሁዋሊ ቤት አሊገኘሁ እንዯሆነ ከቤተ መንግስቱ ግቢ ውስጥ ሊገኝ እንዯምችሌ ስሇ ነገሩኝ
አመስግኘ ክቡር ራስ እምሩ ዯህና ቦታ ሰጥተውኝ እዚያ መሆኔን ነግሬያቸው ሌሂዴ ስነሳ በየጊዜው
እየሄዴሁ ባነጋግራቸው ዯስ የሚሊቸው መሆኑን ገሌፀውሌኝ ተሰናበትሁ። ከዚያ በሁዋሊ በየጊዜው
እየሄዴሁ ሳነጋግራቸው ተስፌፊቸውን ያሳረፈት በጃንሆይና በአሇም መንግስታት ማህበር ሊይ እንጂ ላሊ
«ጣሉያንን ዴሌ አዴርጎ ከኢትዮጵያ የሚያስወጣ ሀይሌ ይኖራሌ» ብሇው የማያምኑ መሆናቸውን
ከንግግራቸው ተረዲሁ።

«አየህ ሌጄ ጃንሆይ ሇአሇም መንግስታት ማህበር አቤቱታቸውን አቅርበው ማህበሩ በቃሌ ኪዲን
መሰረት ጣሉያንን አስገዴድ ካገራችን ካሊስወጣሌን አስተባብሮ የሚመራው መሪ በላሇበት የኢትዮጵያ
ሕዝብ ጦርነቱን ቀጥል ነፃነቱን ያስመሌሳሌ ብል ማሰብ ከንቱ ነው። ሁሊችንም ተስፊ የምናዯርገው
የአሇም መንግስታት ማህበር ሇጣሉያን ብል ቃሌ ኪዲኑን ማሊውን አያፇርስም ብሇን ነው» አለኝ
ቢትወዯዴ ስሇ ጦርነቱ መቀጠሌ ያሇውን ተስፊ መጀመሪያ የጠየቅሁዋቸው እሇት።

«ዴሮውንም ኢጣሉያ ዯፌራ አገራችንን የወረረች የአሇም መንግስታት ማህበር ሉያግዲት


እንዯማይችሌ ስሊወቀች ነውኮ ጌታየ። የጣሉያን ጦር ሰራዊት አዱስ አበባ እንዯ ገባ ኢትዮጵያ የጣሉያን
ቅኝ አገር መሆንዋን ሙሶሉኒ ባዋጅ ካስታወቀ ይኸው አምስት ወር ማሇፈ ነው። ግን እስካሁን የአሇም
መንግስታት ማህበር የጣሉያንን መንግስት እንኩዋንስ ጦሩን ከኢትዮጵያ እንዱያስወጣ ሉያስገዴዯው፤
ቃሌ ኪዲኑን በማፌረሱ ከማህበሩ እንዱወጣም የቀረበ አሳብ የሇ። እንዱያውም ከማህበርተኞቹ መሀከሌ
ኢትዮጵያ ነፃ አገር መሆንዋ ቀርቶ፥ የጣሉያን ቅኝ ግዛት መሆንዋን አውቀው የተቀበለ አለ ይባሊሌ።
ስሇዚህ ከአሇም መንግስታት ማህበር ርዲታ እናገኛሇን ብል ተስፊ ማዴረግ ከንቱ ነው» አሌሁዋቸው።

113
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እንግዱያውስ ላሊ ምን ተስፊ አሇን? ጃንሆይ ሙለ ተስፊ አዴርገው፥ ሇኛም ሙለ ተስፊ
ሰጥተውን የሄደ ከአሇም መንግስታት ማህበር ርዲታ አግኝተው እንዯሚመሇሱ ነበር። ግን አሁን አንተ
እንዲሌኸው ከሆነ አገራችን የጣሉያን ግዛት፥ ህዝብዋ የጣሉያን ባሮች ሆነን መቅረታችን ነዋ! ምነው
ይህን ሳሊይ ሳሌሰማ በሞትሁ! ይህን ሳያዩ ሳይሰሙ የሞቱ ምንኛ እዴሇኞች ናቸው!» አለ ቢትወዯዴ
ብስጭት በተቀሊቀሇበት አዘን ፉታቸው ካጭር ጊዜ በፉት ከነበረው ተሇውጦ።

በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት አባልች ከነበሩት መኩዋንንት የሚበዙት ሇአሇም ውትብትብ


ፖሇቲካ እንግድች የነበሩ ከመሆናቸው ላሊ ቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅ ስሇ አሇም ፖሇቲካ ተባራሪ ወሬ
እንኩዋ ከሚገኙበት ካዱስ አበባ ርቀው ጎሬ በመቆየታቸው ከኔ ጋር እስከ ተገናኙበት ጊዜ ዴረስ ጃንሆይ
ኢትዮጵያን ሇቀው ሲሄደ ከአሇም መንግስታት ማህበር ርዲታ አግኝተው እንዯሚመሇሱ የነገሩዋቸው
አምነው፤ ርዲታው እስኪዯርስሊቸው በተረጋገጠ ተስፊ የሚጠብቁ ነበሩ።

«ጌታየ ‹ከአሇም መንግስታት ማህበር ርዲታ የማናገኝ ከሆነ ላሊ ምን ተስፊ አሇን› ሊለት የአሇም
መንግስታት ማህበር ባሌነበረበት ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ የውጭ ጠሊቶቹን ሁለ ዴሌ እየመታ
ያገሩን ነፃነት አስከብሮ እንዯ ኖረ መቸም የታወቀ ነው። ስሇዚህ ወዯፉትም እንዯ ዴሮው ተባብሮ
ጦርነቱን ከቀጠሇ በመጨረሻ ጠሊቱን ዴሌ አዴርጎ ካገሩ ሉያስወጣ የሚችሌ መሆኑ የሚያጠራጥር
ስሇሆነ በአሇም መንግስታት ማህበር ርዲታ ተስፊ ከማዴረግ ይሌቅ በህዝባችን ጀግንነት ተስፊ ማዴረግ
ነው የሚገባ» አሌሁዋቸው።

«ንጉሠ ነገሥቱ ከሙለ ሠራዊታቸው ጋር ተዋግተው ያሌቻለትን ሀይሇኛ ጠሊት አስተባብሮ


የሚመራው ንጉስ ሳይኖረው ህዝቡ እንዳት አዴርጎ ካገሩ ሉያስወጣው ይችሊሌ ሌጄ?»

«ከዚህ በፉት በትግራይና በኦጋዳን ግንባሮች የተዯረገው ጦርነት ሁሇቱም አገሮች የጫካ
ምሌክት የላሇባቸው ገሊጣዎች በመሆናቸው የጣሉያንን ጦር ሇዴሌ አብቅቶ አዱስ አበባ እንዱገባ
ያዯረገው የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከሇክሌበት ጫካ ስሊሌነበረው አይሮፕሊኖች ከሰማይ ያወርደበት
የነበረው ቦምብና የመርዝ ጋዝ ነው እንጂ የወታዯሩ ጀግነንት ወይም የላሊም መሳሪያ ብዛትና ጥራት
አሌነበረም። ወዯ ፉት ግን ጦርነቱ የሚዯረግ እስካሁን ባሌተያዙት ጫካ የሞሊባቸው አገሮች ስሇሆነና
እዚያ አይሮፕሊኖች እንዯ ሌብ ሇጦርነቱ ተካፊዮች ስሇማይሆኑ ጦርነቱን የሚወስነው፥ የኢትዮጵያና
የጣሉያን ወታዯሮች ጀግንነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያና የጣሉያን ወታዯር ጀግንነት ዯግሞ
አይሮፕሊን ባሌነበረበት ባዴዋ ጦርነት ታይቶዋሌ። ሇዚህ ነው፥ በወታዯሮቻችንና በጠቅሊሊው ህዝባችን
ጀግንነት ተስፊ ማዴረግ ይገባናሌ ያሌሁ።»

«ስማ ሌጄ» አለ ቢትወዯዴ ባሊዋቂነቴ የቅርታ ፇገግታ ፇገግ ብሇው። «አንተ ላሊ ላሊውን ነው
እንጂ ገና ሌጅ ስሇሆንህ ያገራችንን ሌማዴ አታውቀውም። የኢትዮጵያ ወታዯር መሰሌ የላሇው ጀግና

114
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መሆኑ እውነት ነው። ግን አስተባብሮ የሚመራው መሪ ያስፇሌገዋሌ። በሌማደ አገራችንን የሚወር
የውጭ ጠሊት ሲመጣ ንጉሠ ነገሥቱ ሁለንም የሚሾም የሚሽር የበሊይ ባሇስሌጣን በመሆኑ በያገሩ
ያለትን ንጉሦችና ራሶች ወይም ባሇላሊ ማእርግ አገረ - ገዥዎች ጦራቸውን አስከትተው በተወሰነ ጊዜ
ውስጥ ከተወሰነ ቦታ እንዱገኙ ያዝዛቸውና ሁለም ትእዛዙን አክብረው ጦራቸውን እየያዙ በተነገራቸው
ቦታ ሲገኙ ንጉሠ ነገሥቱ አስተባባሪና መሪ በመሆኑ ቦታ ቦታቸውን አስይዞ እያዋጋ ያው እንዲሌኸው
ጠሊቶቹን ዴሌ እየመታ ይመስሌ ነበር። ዛሬ ግን በውዴም በግዴም አዝዘው የሚመሩት ንጉሡ የለም፥
መሳፌንትና መኩዋንንትም ‹ማን በማን ታዝዞ ይዋጋሌ!› ባዮች ናቸው። ስሇዚህ ነገሩ ሊንተ እንዯ
መሰሇህ ቀሊሌ አይዯሇም አስቸጋሪ ነው። ‹መሪ የላሇው ሰራዊትና እረኛ የላሇው ከብት አንዴ ነው!›
እንዯሚባሇው ነው። እረኛ የላሇው ከብት አውሬ ቢመጣበት ሁለም ከመበሊት ሇመዲን በየፉናው
ይፇርጥጣሌ እንጂ፤ እንኩዋንስ ተባብሮ አውሬውን ሉቃወም፤ ባንዴ ተሰብስቦ እበረቱ መግባት
አያውቅም። አስተባብሮ የሚመራው የላሇው ሰራዊትም እንዯዚያ ነው» አለ ቢትወዯዴ።

«የጋራ ጠሊት ሲመጣ ተባብሮ በመከሊከሌ ፇንታ፤ ‹ማን በማን ይታዘዛሌ› መባባሌ ካሇማ፤
ምንም ማዴረግ እንዯማይቻሌ የታወቀ ነው። ግን ከብሊቴን ጌታ ህሩይ ሌጅ፤ ከሲራክ ህሩይ ጋር ሱዲን
ተገናኝተን ‹ጦርነቱን ባንዴነት ተባብረው እንዱቀጥለ፤ ክቡር ራስ እምሩ ከወሇጋ ከጅማው፤ ከከፊው፤
ከገሞጎፊው ከባላውና፤ ከሲዲሞው አገረ - ገዥዎች ጋር ተሊሌከው ተስማምተው፤ ክረምቱ እስኪወጣ
ነው የሚጠብቁ› ብልኝ ነበር። ታዱያ በራስና በኒያ ባሌተያዙት አገሮች ገዥዎች መሀከሌ ጦርነቱን
ሇመቀጠሌ ስምምነት አሌተዯረገም ማሇት ነው?»

«ራስ ሇሁለም የሊኩባቸው መሆኑን ሇኔም ነግረውኛሌ። ግን ራስ ዯስታ ዯጃዝማች ገብረ


ማርያምና ዯጃዝማች በየነ መርዔዴ ያለባቸው አገሮች ሲዲሞ ባላና ገምጎፊ ከዚህ ሩቅ በመሆናቸው
በክረምት የተሊኩ መሊክተኞች ዯርሰው እስኪመሇሱ ብዙ ጊዜ ስሇሚወስዴ መሌስ እንኩዋ የተገኘ
አይመስሇኝም። ቀረብ ያለት የወሇጋው መሌስ እንኩዋ የተገኘ አይመስሇኝም። ቀረብ ያለት የወሇጋው
ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም የጅማው ከንቲባ ጋሻው ጠናና የከፊው ዯጃዝማች ታየ ናቸው ከነሱም
የተጨበጠ ነገር አሇመኖሩን አሌሰማሁ። ስሇዚህ፥ ‹ራስ እምሩና ባሌተያዙት አገሮች ያለ አገረ ገዥዎች
ተባብረው ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ተስማምተዋሌ› ሇማሇት የሚቻሌ አይመስሇኝም» አለኝ።

ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ስሇ ታሰበው አሳብና ስሇ ታቀዯው እቅዴ ክቡር ራስ እምሩን


በጠየቅሁዋቸው ቁጥር ሁሌጊዜ ይሰጡኝ የነበረው መሌስ ክረምቱ ሲወጣ ጠሊትን ሇመውጋት እሳቸው
ከጎሬ ወዯ ውስጥ እንዯሚገቡና በዚያ ጊዜ ባሌተያዙት አገሮች የነበሩት አገረ - ገዥዎችም ጦራቸውን
አዘጋጅተው ሇጦርነት እንዱነሱ በሁለም የሊኩባቸው መሆኑን ብቻ ነበር። ስሇዚህ ራስ እምሩንም
ቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅንም በየጊዜው ካነጋገርሁዋቸው በሁዋሊ እንዯ ተረዲሁት እንኩዋንስ ከጠሊት ጋር
ሇመዋጋት በህብረት የተሰናዲ የጦርነት እቅዴ ሉኖር፥ ሌጅ ሲራክ እንዯ ነገረኝ ጦርነቱን ባንዴነት

115
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇመቀጠሌ በራስ እምሩና ቀዯም ብል ስማቸው በተነገረው አገረ - ገዥዎች መሀከሌ የተዯረገ ጠቅሊሊ
ስምምነትም አሌነበረ! እንዱያውም ባሌተያዙት አገሮች ከነበሩት ገዥዎች እነማን ጠሊትን ሇመቃወም
እነማን ጠሊትን ሇመቀበሌ ተሰሌፇው እንዯሚጠብቁ እንኩዋ አይታወቅም ነበር! ከነዚህ ላሊ ዯግሞ በኒያ
ባሌተያዙት አገሮች የሚኖረው ጠቅሊሊ ህዝብ ጦርነቱን ሇመቀጠሌ የሚፇሌጉን የኢትዮጵያ መንግስት
ወገኖች መርዲት የሚፇሌግ ወይስ ጦርነቱን መቀጠሌ እንዯማያዛሌ ወገኖች መርዲት የሚፇሌግ ወይስ
ጦርነቱን መቀጠሌ እንዯማያዛሌቅ በመረዲት የጣሉያንን ገዥነት ተቀብል በሰሊም መኖርን የሚፇሌግ ስሇ
መሆኑ አስቀዴሞ መረጃ ሇማግኘት የተዯረገ ምኩራ አሌነበረም። ስሇዚህ ሌጅ ሲራክ ሱዲን በነገረኝ
መሰረት ጦርነቱን በማስረዘም ጠሊታችንን አዴክመን ካገራችን ሇማስወጣትና ነፃነታችንን ሇማስመሇስ
የነበረኝ ፅኑ ተስፊ ጎሬ ከዯረስሁ በሁዋሊ ሁኔታውን ሁለ ስመሇከት ከተስፊ ዯረጃ ወርድ ከንቱ ምኞት
መሆኑን ተገነዘብሁ።

ከመስከረም 1929 መጨረሻ ግዴም ቀዯም ብል በክረምቱ ውስጥ፥ የሆሇታ መኮንኖችና


ወታዯሮች፤ ከወሇጋ ተገዯው ሲወጡ አብረዋቸው ከነበሩት መሀከሌ አቶ ይሌማ ዯሬሳ ድክተር
አመሇወርቅ በየነና የመቶ አሇቃ በኩረ የተባሇ ወጣት መኮንን ጎሬ መጥተው ከራስ ጋር ተገናኝተው
መመሇሳቸውን ሰማሁ። እኔ አግኝቼ አሊነገርሁዋቸውም። ነገር ግን አግኝተው ካነጋገሩኝ ሰዎች እንዯ
ሰማሁት ወሇጋን ሇቀው ወዯ ኢለባቦር ግዛት ከተሻገሩ በሁዋሊ ስሇ ዯጃዝማች ሀብተ ማርያምና ስሇ
ጠቅሊሊው የወሇጋ ህዝብ አቁዋም የሚያውቁት የተረጋገጠ ነገር አሌነበረም። እናቶ ይሌማ ተመሌሰው
ከሄደ በሁዋሊ የትምርት ቤት ጉዋዯኛየ፤ በትረ ፅዴቅ ካሳና በስም ብቻ የማውቀው ተመስገን ገብሬ ካዱስ
አበባ ሸሽተው ከሆሇታ ሰዎች ጋር የማውቀው ወዯኛ መጡ። እነሱም የሆሇታ መኮንኖች የጣሉያንን
አይሮፕሊን አቃጥሇው ነጂውንና አብረውት የነበሩትን ሹማምንት በመግዯሊቸው «ዯጃዝማች ሀብተ
ማርያም ከመኩዋንንታቸው ጋር መክረው ካገራቸው እንዱወጡ ማዴረጋቸው ከጣሉያኖች ጋር
ሇመቀራረብ ቢፇሌጉ ይሆናሌ» ብሇው ከመጠርጠር በቀር በዚያ ጊዜ የዯጃዝማችና የህዝባቸው አቁዋም
ምን እንዯ ነበረ እርግጠኛውን የማያውቁ መሆናቸውን ነገሩኝ። ታዱያ የዯጃዝማች ሀብተ ማርያም
አቁዋም መሆናቸውን ጠራጥር ሁኔታ እንዲሇ «ራስ እምሩ ከሳቸው ጋር ተባብረው በጠሊት ሊይ
ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ወዯ ወሇጋ ሉሂደ ነው» ተብል የተፊጠነ ዝግጅት ሲዯረግ ይታይ ነበር።

ያንጊዜ ከነበረው የክቡር ራስ እምሩ ጦር ሠራዊት የሚበዙት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ አብረዋቸው


የኖሩ መኩዋንንታቸውና ወታዯሮቻቸው ነበሩ። ከነሱም አንዲንድቹ እየጠበቁ ላልች በዴሜና በሌዩ ሌዩ
ምክንያት ራስ እያሰናበቱዋቸው ወዲዱስ አበባም ወዯ ያገራቸውም የገቡት ተቀንሰውሇታሌ። ከራስ ነዋሪ
ሰዎች ላሊ ጎጃም ከነበረው አንዴ ሻሇቃ የክብር ዘበኛ ጦር ባዛዡ፥ በሌጅ ግዛው ቡኔ ስር ጥቂት የክብር
ዘበኞች ነበሩ። እንዱሁም ጎጃም በግዛት ሊይ ከነበሩት መኩዋንንት ትዝ እንዯሚለኝ የጎጃም ተወሊጅ
ፉታውራሪ ዲምጠው ተሰማ እና ወሇየው ፉታውራር ከብዯ ያዘው ብቻ ከጥቂትት ከጥቂት ሰዎቻቸው
ጋር ነበሩ። ከነዚያ ላሊ በጉምሩክና ባንዲንዴ የመንግስት መስሪያ ይሰሩ የነበሩ ሹማምንትም ሰራተኞችም

116
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሉኤልች ግሇሰቦችም ነበሩ። ቀኛዝማች በሌሁ ዯገፈና ሌጅ ፇቃዯ ስሊሴ ህሩይ ሇጦርነት ከእንግሉዝ አገር
ከጃንሆይ እየተሰናበቱ መመሇሳቸውን ቀዯም ብዬ ስሊመሇከትሁ እነሱም ከጥቂት ሰዎቻቸው ጋር ነበር።
ስሇዚህ ክቡር ራስ እምሩ ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ከጎሬ ሲነሱ የነበራቸው ጦር ሰራዊት በዴምሩ ከሶስት
መቶ «ከፌ ቢሌ» ካራት መቶ ሰው የሚበሌጥ አይመስሇኝም።

ምእራፍ አስራ ስድስት

ከጎሬ እስከ (ጎይ?)


የጣሉያን ጦር ሰራዊኢት አዱስ አባባን እንዯ ያዘ ሙሶሉኒ ኢትዮጵያ የጣሉያን ቅኝ ግዛት
መሆንዋን ባዋጅ ካስታወቀ በሁዋሊ በየክፌለ ይዯረግ የነበረውን ጦርነት እኛና ጣሉያኖች በተሇያየ ስም
እንጠራው ነበር። በኛ በኩሌ «የኢትዮጵያ መንግስት መንበሩን ካዱስ አበባ ወዯ ጎሬ አዛወረ እንጂ
ስሊሌጠፊ በየክፌለ የሚዯረገው ጦርነት መንግስቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ የሚዋጋው ጦርነት ተከታታይ
ወይም ክፌሌ በመሆኑ ‹ጦርነቱን መቀጠሌ› ሉባሌ ይገባዋሌ» እንሌ ነበር። ጣሉያኖች በበኩሊቸው
«የጣሉያን መንግስት ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛቱ መሆንዋን ባዋጅ አስታውቆ የመንግስቱን ስሌጣን ከያዘ
በሁዋሊ በየክፌለ የሚዯረገው ጦርነት የሽፌተንት ጦርነት ነው» ባዮች ነበሩ። የሆነ ሆኖ እኛ በሰጠነው
ስምም ይሁን ወይም ጣሉያኖች በሰጡት ስም ጠሊትን ሇመውጋት ክቡር ራስ እምሩ ያን በትጥቅና
በስንቅ ወይም በህዝብ ዴጋፌ አዝሊቂ መተማመኛ የላሇው ጥቂት የጦር ሰራዊታቸውን ይዘው በጥቅም
1929 መጀመሪያ ግዴም፥ ወዯ ወሇጋው ገዥ ወዯ ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር
ሇመሄዴ ከጎሬ ተነሱ።

ዘሪሁንና እኔ ራስ ከጎሬ ከመነሳታችን ጥቂት ቀናት ቀዯም ብሇን «ቡኖ ዋቤኮ» ወዯ ሚባሌ አገር
ሄዴን። ዋቤኮ አቦ አባቴ ካገራቸው ከጎጃም ሄዯው ረዥም ጊዜ ይኖሩበት የነበረ ከወሇጋ መንገዴ ምንም
ያክሌ የማይርቅ አገር ነው። ስሇዚህ አባቴን አይቼ ወዱያውም በቅልዎችና በቂ ስንቅ ስሊሌነበሩኝ በዚያ
አጭር ጊዜ ውስጥ ሉገኝ የተቻሇውን ያክሌ ይዘን፤ ራስ በዚያ ሲያሌፈ እንዯምናገኝ አውቀን ነበር
የሄዴን።

አንዴ ሳምንት ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ ራስ እኛ ወዯ ነበርንበት አገር መቅረባቸውን ስሇ ሰማን አባቴ


የሰጡኝን ሁሇት በቅልዎችና ስንቅ ይዘን እሳቸው ጭምር «ሱጴ» እስከምትባሌ አገር ዴረስ አብረን
ሄዴን ከራስ ጋር ተገናኘን።

«ሌጅዎ ያሇ ስራው ከወታዯር ጋር ዘማች ሆኖ እንዯሚያዩት ካገር አገር ይዞራሌ። አሁን በዯህና
ከርሶ ጋር አገናኝተነዋሌና ከንግዱህ መክረው ከርስዎ ጋር እንዱቀር ያዯርጉት» አለዋቸው ራስ አባቴን
ተቀብሇው ሲያነጋግሩዋቸው። ከሌባቸው ይሁን ወይም የሚለትን ሇመስማት እንዯሆን አሊውቅም።

117
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እንኩዋንስ እሱን ከኔ ጋር እንዱቀር ሌመክረው ባሌሸመግሌ ኖሮ እኔም አብሬው ብሄዴ
በወዯዴሁ ነበር!» አለ አባቴ። ካባቴ ጋር ስሰነብት የጦርነቱ ነገር በተነሳ ቁጥር «የኢትዮጵያ አምሊክ
እግዚአብሔር ይርዲችሁ!» ከማሇት በቀር አንዴም ቀን ከጦርነቱ ቀርቼ ከሳቸው ጋር እንዴቆይ
እንኩዋንስ በቀጥታ ሉጠይቁኝ በተዘዋዋሪ መንገዴ አስተያይተውኝ አያውቁም። ስሇዚህ ያንሇት
«ሇይስሙሊ» ሳይሆንን ንከሌባቸው ነበር የተገናገሩት። ራስም ያ ጊዜ አሌፍ ነፃነታችን ከተመሇሰ በሁዋሊ
እንኩዋ ተገናኝተን ስሊባቴ ጤንነት ሲጠይቁኝ፤ ያንሇት ያለዋቸውን እንዲሌዯረሱት ይነግሩኝ ነበር፡

የሆሇታ መኮንኖችና ወታዯሮች እንዱሁም ካዱስ አበባና ከሌዩ ሌዩ ቦታዎች እየሸሹ አብረዋቸው
የቆዩት የጦርም፥ የሰሊምም ሰዎች ባንዴነት ተሰሌፇው ከራስ ጋር የተገናኙ ባሌሳሳት እዚያ ‹ሱጲ› ሊይ
ይመስሇኛሌ። አዛዡ ኮልኔሌ በሊይ ሀይሇ አብ የተባሇ አጠር ያሇ ቆፌጣና ወጣት መኮንን ነበር።
የሰሌፇኛውን መዝሙር እየመራ የሚያይዘመር «ይሌማ መንገሻ» የተባሇ ዘሇግ ያሇ ጠይም ጠጉረ ሊዛ
ነበር። ይሌማ መንገሻ አምቦ የርሻ ትምህርት ቤት ዱሬክተር የነበረ መሆኑን ሰማሁ። ይሌማ መንገሻ
ካኪ ሱሪና ሸሚዝ ብቻ ሇብሶ የተመዘዘ ጩቤውን በቀኝ እጁ ከራሱ በሊይ ከፌ አዴርጎ ይዞ «እረዯው!»
ሲኢሌ ጩቤውን ገዯም አዴርጎ የማረዴ ምሌክት እያሳየ «በሇው!» ሲሌ ጩቤውን ዘቅዝቆ የመውጋት
ምሌክት እያሳየ።

«እረዯው እረዯው አታርዯውም ወይ

ጥቁር አንበሳ አይዯሇህም ወይ!»

«በሇው በሇው አትሇው ወይ፥

ጥቁር አንበሳ አይዯሇህም ወይ!

«ኧረ በሇው ኧረ በሇው አትሇውም፥ አይ

ጥቁር አንበሳ አይዯሇህም ወይ!»

እያሇ፥ ሊቡ በፉቱ ሲወርዴ ከሩቅ እየታየ፤ የመዝሙሩን ቅኝት የተከተለ በዚያ ረዥም ቁመቱ
ሲዯረግ፤ የተቀባዩን ሰሌፇኛ ብቻ ሳይሆን የተመሌካቹን ስሜት ጭምር ማርኮ አብሮት ያስገረገርው ነበር!
ያ ትርኢት በውነት እንዳት ግሩም ነበር! እንዳት ሌብን በወኔ የሚያሞቅና፤ ሞትን የሚያስንቅ ነበር!
እኔ ብረሳው ይሆናሌ እንጂ መዝሙሩ ይህ፤ እዚይ የተጠቀሰው ብቻ አይመስሇኝም፤ ይህ «አዝማቹ»
ሳይሆን አይቀርም።

ከሰሌፈና ከመዝሙሩ ትርኢይት በሁዋሊ የሆሇታ መኮንኖች ወዯ ራስ ቀርበው በየስማቸውና


በየማእረጋቸው ተዋወቁ። ከዚያ ዴርጅታቸው እንዯ ተጠበቀ ሆኖ የራስን ትእዛዝ ሇነሱ እነሱ

118
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚፇሌጉት ጉዲይ ቢኖር ሇራስ እያስተሊሇፈ የሚያስፇፅሙ አማካይ መኮንን (ሇየዞን) ቀኛዝማች በሌሁ
ዯገፈ መሆናቸውን ሰማሁ። የሆሇቶች ጦር ከራስ ጦር ጋር ከተጨመረ በሁዋሊ በጠቅሊሊ ሰራዊቱ
በብዛት ብቻ ሳይሆን በጥራት ጭምር የተሻሇ እንዯ ሆነ አይጠረጠርም። ግን ብዛቱ እጅግም አሌነበር ግፊ
ቢሌ አንዴ ሽህ ያክሌ ቢሆን ነው። ያን ያክሌ መሆኑም የሚያጠራጥር ነው እጉዞ ሊይ በትእዛዝ ይሁን
ወይም እነሱ ፇሌገው እንዯሆነ አሊውቅም ሁሌጊዜ የጦር ሰራዊቱኡን ግንባር ይዘው ሲዋጉ የማይ
ሆሇቶችን ነበር። አንዴ ቀን ሆሇቶች ቀዴመው ላሊው ሰራዊት ተከትል ከዯዱሳ ሸሇቆ አፊፌ ሌንዯርስ
ትንሽ ሲቀረን አንዴ መጠነኛ ዲገት አጠገብ እንዯ ዯረስን እስሩ ከነበረው ጫካ ውስጥ ተዝናንቶ
በሚጉዋዘው ሰራዊት ሊይ ተኩስ ተከፇተ። ተኩሱን የከፇቱት የወሇጋ አገረ ገዥ ዯጃዝማች ሀብተ
ማርያም የክቡር ራስ እምሩን ሰራዊት እንዱወጋ ከሊኩት ጦር ጥቂት ሰዎች ነበሩ። ወዱያው በበቅል
የነበረው እየወረዯ ከግረኛው ጋር ባንዴነት ሆኖ ተኩስ ወዯ ተከፇተበት ቦታ ሩጫ ሆነ። ግን እኒያ
የተኮሱት ጥቂት ሰዎች በተሸሸጉበት ጫካ ውስጥ ምንም ያክሌ ሳይቆዩ እየዞሩ እየተኮሱ ዲገቱን
ወጥተው ሲሄደ ይታዩ ነበር።

ሆሇቶችና ከራስ ሰዎችም ቀዯም ያሌነው ተኩስ የከፇቱን ሰዎች እየተከተሌን ሮጠን ከዲገቱ
አናት ሊይ ስንዯርስ ከዲገቱ ጀርባ ቁሌቁሇቱን ወርዯው ከስሩ ያሇውን ዛፌና ቁጥቁዋጦ የሇበሰ ወንዝ
ተሻግረው ከማድ አቀበት ሊይ «ጉይ?» ከሚባሇው ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ባሇው ጫካ እየሮጡ ሲገቡ
አየናቸው።

መቸም ጠሊቶቻችን ያቀደት የጦርነት እቅዴ ግሩም የሆነ እቅዴ ነበር! እዚያ ከቤተ ክርስቲያኑ
ዙሪያ ባሇው ጫካ ውስጥ ብዙ ከባዴና ቀሊሌ መሳሪያ ጠምዯዋሌ! ከስሩ ባሇው ወንዝ ውስጥ ብዙ ባሇ
መትረየስና ሇባሇ ሌዩ ሌዩ መሳሪዑኢያ ጦር አስተኝተዋሌ! ዋናዎቹ ወጥመድች እኒህ ከቤተ ክርስቲያኑ
ዙሪያና በወንዙ ውስጥ የተጠመደት ናቸው። ታዱያ ወጥመድቻቸውን እንዱህ አዴርገው ካስናደ በሁዋሊ
እወጥመድቹ ውስጥ እኛን ስቦ የሚያገባሊቸው አንዴ ቡዴን ወዯ ፉት ሌከው በኛ ሊይ እየተኮሰ እንዱሸሽ
አዴርገዋሌ። የተሊከብን ጦር የዯጃዝማች ሀብተ ማርያም ይሁን እንጂ ያን እቅዴ ያቀደት ጣሉያኖች
መራሳቸው ወይም እነሱ የጦርነት እቅዴ ያስተማሩዋቸው ሰዎች መሆን አሇባቸው! እቅደ አስቀዴሞ
ያሌተጠነቀቀን ጠሊት ሲስት የማይችሌ እወጥመደ ውስጥ እንዱያገባ ሆኖ የታቀዯ ስሇ ነበረ አሳባቸው
ተሳካሊቸው እወጥመዲቸው ውስጥ ገባንሊቸው! ቀዴመን እዲገቱ አናት የዯረሰውም እኛን ተከትሇው
የዯረሱትም ሮጠው ወዯ ቤተ ክርስቲያኑ የገቡትን ሰዎች ብቻ እያየን እነሱን ሇመከተሌ ከዲገቱ አናት
ወርዯን እዯረቱ ሊይ ሆነን ዯረታችንን እንዯ ሰጠን ከማድ ቤተ ክርስቲያን በከባዴና በቀሊሌ መሳሪያ
የተተኮሰ ጥይት እንዯ መዒት ይወርዴብን ጀመር። ያን ጊዜ የሞተው ሞቶ የቆሰሇው ቆስል ዯህነኛው
በየዛፈና በየቁጥቁዋጦው ስር ተገን ፇሌጎ ያሌወዯቀ አሌነበረም። እንዲጋጣሚ ባጠገቡ ስሇ ነበርሁ ቆሞ
ያየሁት ኮልኔሌ በሊይ ሀይሇ አብን ብቻ ነበር። ከማድ የሚተኮሰው የሌዩ ሌዩ መሳሪያ ጥይት ከፉት
ከሁዋሊ ከቀኝ ከግራው እንዱያ እንዯ መአት እየወረዯ በዙሪያው የነበረውን የዛፌ ቅርንጫፌ ሁለ እንዱያ

119
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እየገነጣጠሇ ቁጥቁዋጦውን ሁለ እንዱያ እያብጠሇጠሇ ሲጥሌ ከዚያ መሀሌ ኮልኔሌ በሊይ የተመዘዘ፤
ያዛዥ ሰይፈን በቀኝ እጁ ከትከሻው ዝቅ አዴርጎ ዘርግቶ፤ ትንሽ እንኳ ስቅጥጥ ሳይሌ ዝም ብል ፉት
ሇፉት ያይ ነበር! ተኩሱ ፀጥ እስኪሌ ተገን ይዞ እንዱቆይ ከተኛሁበት ዛፌ ስር ጠርቸ ሇመንገር ካሰብሁ
በሁዋሊ በቅጡ ያሌተሇማመዴን ከመሆናችንም ላሊ «ምናሌባት ስሌታቸው ቢሆን ይሆናሌ» ብዬ ሌናገር
ያሰብሁትን መሌሼ ዋጥሁት። ትንሽ ቆይቶ ተኩሱ ጋብ ያሇ ሲመስሌ በሊይ ያዛዥ ሰይፈን ከትከሻው
ዝቅ አዴርጎ ከያዘበት ሁለም እንዱያ ሽቅብ ከራሱ በሊይ አውጥቶ እንዯገና ወዯ ፉት ወነጨፇና «አናቫ!»
(ወዯፉት) አሇ በጣ ጮሆ። ወዱያው አጭር ቁመናው በፇቀዯሇት መጠን እርምጃውን አስረዝሞ ወዯ ፉት
ስሄዴ በየዛፈም በየቁጥቁዋጦውም ስር ተገን ይዞ የነበረው ሁለ ከያሇበት እየወጣ ወዯ ፉት ሩጫውን
ያዘ። ያን ጊዜ እንዯገመትሁት ኮልኔሌ በሊይ ያን ትእዛዝ የሰጠ እዲገቱ ዯረት ሊይ የነበርንበት ቦታ
ከማድ ሇሚተኩስብን ጠሊቶቻችን ምቹ አዴርገን ስሇ ነበረ፥ ከዚያ ወርዯን ወንዙን የያዝን እንዯ ሆነ እሱን
ተገን አዴርገን ብርቱ ጉዲት ሳይዯርሰን ጠሊቶቻችንን ከስር ሇማጥቃት እንዯምንችሌ በማመን ሳይሆን
አይቀርም። አሳቡ ትክክሌ ይመስሊሌ። ጠሊቶቻችንም እንዱሁ እንዯሚታሰብ ስሊወቁ ነው፥ እቅዲቸውን
ሲያቅደ እዲገቱ ዯረቱ ሊይ የሚገኝ ሁለ ከማድ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ከሚተሶስበት ተገን ፌሇጋ ሸሽቶ
ወዯ ወንዙ መሄደ የማይቀር በመሆኑ ተቀብል የሚፇጅ ጦር እዚያ ወንዝ ውስጥ መሸሸጋቸው። እኔም
ወዯ ወንዙ ሩጫ ከጀመሩት ጋር ስሮጥ ከማሌፌበት ቁጥቁዋጦ ውስጥ ጣእር የሚያስጨንቀው ዴምፅ
«ሀዱስ» ሲሌ ስሇሰማሁ ዴምፁን ወዯ ሰማሁበት ቁጥቁዋጦ ዘወር ብሌ ጣሰው አይችለህም እዚያ
ወዴቆዋሌ።

ጣሰው፥ የመኮንንነት ትምህርት ሇመከታተሌ ወዯ ሆሇታ ከመሄደ በፉት ምኒሌክ ትምህርት


ቤት፥ እኔም ተፇሪ መኮንን ትምርት ቤት በነበርንበት ጊዜ ተዋውቀን የሩቅ ጉዋዯኝነት ነበረን። ቀረብ ብየ
ሳየው አንዴ ታፊው ተገንጥል ቆዲው እንዯ ያዘው በጏኑ ወዯ ወገቡ አፇንግጦዋሌ! ራሱ ተዘቅዝቆ እንዯ
ወዯቀ ሊቡ እንዯ ውሀ ፉቱን ያጥበዋሌ ካፈና ካፌንጫውም ዯም ይወርዲሌ! ያን ጊዜ ወንዙን ሇመያዝ
የሚሮጠው የኛ ጦር እስኪጠጋቸው ዴረስ እዚያ ውስጥ አንጥፇው የሚጠብቁት የጠሊት ሰዎች ገና
ተኩስ አሌከፇቱም ነበር። ስሇዚህ ጣሰው ቆስል የወዯቀው ቀዯም ብል በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ካሇው
ጫካ ውስጥ በተተኮሰ የከባዴ መሣሪያ ጥይት መሆን አሇበት። ወዱያውም የጠመንጃ ወይም የመትረየስ
ጥይት እንዱያ አዴርጎ ሉገነጥሌ የሚችሌ አይመስሌም። ታዱያ እኒዓ ቁስሇኛ የመርዲት ሌምዴ የላሇኝ
አይመስሌም። ታዱያ እኔ ቁስሇኛ የመርዲት ሌምዴ የላሇኝ ስሇ ነበርሁ የማዯርገው ቅጡ ጠፌቶኝ
ስርበተበት፥

«እባክህ ትንሽ ቀና አዴርገኝ» አሇ በዯከመ ዴምፅ።

ከወዯቀበት ቦታ አንዴ ሜትር ያክሌ ራቅ ብል አንዴ ትሌቅ ዛፌ ስሇ ነበረና ጣሰው ከኔ


የሚበሌጥ በመሆኑ ተሸክሞ ወዯዚያ መውሰደ ስሊቃተኝ ከሊይ ሁሇት ብብቶቹን ገብቼ ይዤ እየሳብሁ

120
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወስዴሁና ቀና አዴርጌ የዛፈን ስር ሳስዯግፇው ጭንቀቱ ትንሽ ቀሇሌ ያሇሇት መሰሇ። ታፊውም እንዯ
ተሇያዬ ይሁን እንጂ፣ ትንሽ ወዯ ወገቡ ወጥቶ፤ ወጥሮት የነበረው ወዯ ታች ወረዴ ስሊሇ ከሁኔታው
ስመሇከት ውጥረቱ ያስከተሇው ስቃይ የተቀነሰሇት መስል ተሰማኝ። እኔ ጣሰውን ስረዲ ከግርጊያችን
እወንዙ ውስጥ የተነሳው ተኩስ የቁዋያ እሳት የተቃጠሇ ይመስሌ ነበር! ብቻ እንዱያ እንዯሆነ ብዙ
አሌቆዬ፤ ትንሽ በትንሽ ከወንዙ እየራቀ ሄዯ፥ ወዯ ቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ የተፊፊመ ተኩስ ሲሰማ ቆየና
ከዚያም ጠፊ። ጣሰውን ቀና አዴርጌ የዛፈን ስር አንተርሸ አስተኝቼ፤ ካፈና ካፌንጫው የወጣውን የረጋ
ዯም በገዛ መሀረሙ ከጠራረግሁሇት በሁዋሊ፤ ከዚያ አሌፋ ምንም ሉያዯርግሇት የማይችሌ ስሇ መሰሇኝ፤
ሆሇቶች ጉዋዯኞቹ የተሻሇ ርዲታ ሉያዯርጉሇ ቢችለ ሄጄ ሇነሱ ሇመንገር ጠመንጃየን ካኖርሁበት ሳነሳ
አይቶ፤

«ውሀ አጠጣኝ» አሇ በዚያ በዯካማ ዴምፁ።

የዛፈን ስር ሇማንተራስ ስስበው ኮዲውን ከያዘበት ወስጄ ባጠገቡ አኑሬሇት ስሇ ነበረ፥ አንስቼ
ባየው ባድ ነው። ጣሰው በወዯቀበት ቁጥቁዋጦና በወንዙ መሀሌ አንዴ ትንሽ ሜዲ አሇች። እወንዙ
ውስጥ ተኩሱ አቁሞ ስሇ ነበረ፥ ከዚያ ሊመጣሇት ጠመጃየን እንዲነገትሁ ኮዲውን ይዤ ሮጥ ሮጥ
እያሌሁ ከቁጥቁዋጦው ወዯ ሜዲው ብቅ ስሌ ከወንዙ ውስጥ ብዙ ጥይት እሩምታ ስሇ ተተኮሰብኝ
ወዯቅሁ። ግን የተተኮሰብኝ ጥይት እንዲያገኘኝ ነው እንጂ አሌተመታሁም። በወዯቅሁበት እንዲሇሁ
ቆይቼ ተኩሱ ሲቆምሌኝ በጉብሴ ወዯ ጣሰው ተመሇስሁ። ተቁዋርጦ እወንዙ ውስጥ የቀሩ የጠሊት
ወታዯሮች እየተኮሱ አሊስቀርበኝ ስሊለ ውሀ ሇማምጣት አሇመቻላን ሇጣሰው ነገሁት። ወዱያው ድክተር
አሇመ ወርቅ መጣና ጣሰውን እዚያ ተኝቶ፥ እኔን ከፉቱ ቆሜ ሲያይ፤

«ጣሰው ቆስል ነው?» አሇ፥ ዯንግጦ። ድክተር አሇመ ወርቅ የከብት ሀኪም መሆኑን ቀዯም ብየ
ሰምቻሇሁ።

«አዎ፥ ክፈኛ ቆስልዋሌ» አሌሁት። ወዱያው ጏንበስ ብል ታፊውን ካየና የሌቡን ትርታ
ሲያዲምጥ ትንሽ ከቆየ በሁዋሊ ፉቱ በሀዘን ከብድ ራሱን እየወዘወዘ ቀና ሲሌ፥

«አሇመ ወርቅ፤ ውሀ አጠጣኝ፤ ተቃ - ጠሌሁ» አሇ ጣሰው፤ ዯካማ ዴምፁን ጣእር


እየጎተተው።

«ኮዲው ውሀ አሇበት?» አሇኝ ድክተር።

«የሇበትም፤ ከወንዙ ሊመጣ ብሞክር፤ እዚያ ተቁዋርጠው የቀሩ የጠሊት ወታዯሮች እየተኮሱ
አሊስቀርበኝ ስሊለ፤ ሳሌዯርስ ተመሌሼ መጣሁ።»

«ጠመንጃህን ይዘህ ኖሮዋሌ የሄዴህ?»

121
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«አዎ!»

«እስቲ ስጠኝ እኔ ሌሞክር» አሇና ድክተር አሇመ ወርቅ ጠመንጃውን አኑሮ፥ ኮዲውን ከኔ
ተቀብል ቁጥቁዋጦውን ወጣ አሇ። ወዱያው ሰሊማዊነቱን ሇማሳየት ኮዲ የያዘ እጁንም ባድ እጁንም
ከራሱ በሊይ ዘርግቶ እያሳየ ሜዲውን ሉገባ ሲሌ ሌክ በንዯኔ እንዯ ተዯረገው እሩምታ ተተኮሰበት። ወዯ
ቁጥቁዋጦው መሇስ ብል ቆይቶ እንዯገና ወዯ ሜዲው ብቅ ሲሌ፥ አሁንም ተተኮሰበት። ከዚያ በሁዋሊ
እሱም ተስፊ ቆርጦ ባድውን ተመሇሰ። ድክተር ከመመሇሱ ከያነሇት በፉት እቃ በኩታዋ እያዘሇች
ከሆሇቶች ጋር ስትጉዋዝ አያት የነበረች ሴት መጣችና፤

«ጋሼ ጌታየ ሇኔ ባዯረገው! እኔ አፇር በበሊሁ!» እያሇች ከጣሰው ፉት ተንበርክካ ስጥጮህ፤

«እባክሽ ውሀ አጠጭኝ» አሊት ሇኔም ሇድክተር አሇመ ወርቅም እንዲሇው። ወዱያው ያቺ ሴት


ኮዲውን ከድክተር አሇመ ወርቅ እጅ ነጥቃ ወንዙ ስትሮጥ፤

«ወንዙን የጠሊት ወታዯሮች ይዘው እየተኮሱ ስሊሊስቀረቡን ነውና የተመሇስን አትሂጂ


ይገዴለሻሌ» አሊት ድክተሩ። ሴትየዋ ግን እንኩዋንስ ሌትመሇስ የተናገረውን መስማትዋንም እንጃ! ዝም
ብሊ እየሮጠች ከቁጥቁዋጦው ወጥታ ወዯ ሜዲው ዝቅ ስትሌ በኛ እንዯ ተተኮሰብን እሩምታ
ተተኮሰባት። እስዋ ግን እንዯኛ በመመሇስ ፊንታ ኮዲዋን አንጠሌጥሊ ወዯ ሚተኩሱባት ሰዎች ሩጫዋን
ቀጠሇች። እኒያ ሰዎችም ሴት ስሇ ሆነች እንዯሆነ፥ ወይም በላሊ እስካሁን ሊውቀው ባሌቻሌሁ ምክንያት
ተኩሳቸውን አቁመውሊት ውሀውን ቀዴታ ተመሇሰች። ድክተር አሇመ ወርቅና እኔ የዚያችን ሴት
ጀግንነትና የኒያን ሰዎች መንፇሰ - ሇጋስነት አይተን፤ በጣም ተዯነቅን! ሴትየዋ ከጣሰው አፌ ዯሙን
ጠራርጋ ካመጣችሇት ውሀ ትንሽ ካጠጣችው በሁዋሊ፤ በረዥሙ ተንፌሶ፤ ሲወራጭ ቆየና አይኑን ገበብ
አዴርጎ ፀጥ አሇ። አይቺ ጀግና ሴት፤ ሇጣሰው ምኑ እንዯነበረችና ስምዋ ማን እንዯሚባሌ ያን ጊዜ
ድክተር አሇመ ወርቅን ሳሌጠይቀው መቅረቴ ሲያስፀፅተኝ ይኖራሌ።

«እስቲ እንዱህ ርዲታ ሉያገኝ ወዯ ሚችሌበት የሚያዯርሱ ሰዎች ፇሌጊኤ እስኪሌክሌሽ ዴረስ አብረሽው
ቆይ» ብልዋት ድክተር አሇመ ወርቅ እኒኢያ ተቁዋርጠው የቀሩት የጠሊት ወታዯሮች ከነበሩበት ከፌ
ብሇን ወዯ ወንዙ ሄዴን። እዚያ ወንዝ ውስጥና ዲርዲሩን፥ በዚያ አጭር ጊዜ ውስጥ ሞተውም ቆስሇውም
ወዴቀው የሚታዩት የኛና የጠሊት ሰዎች ብዙ ነበሩ። በዚያ የጨበጣ ጦርነት ከራስ መኩዋንንትና
ከወታዯሮች የሞቱትንም የቆሰለትንም ቁጥራቸውን አሊስታወሰውም እንጂ በርከት ያለ ነበሩ። ከሆሇቶች
ውስጥም፥ የሞቱና የቆሰለ - ወታዯሮች ሳይቆጥሩ - መኮንኖች ብቻ ስምንት መሆናቸውን ሁዋሊ ሰዎች
ነገሩኝ። ከሞቱት መሀከሌ ጣሰው አይችለህም ድክተር አሇመ ወርቅና እኔ እንዯ ተሇየነው ወዱያው
ህይወቱ ስሊሇፇ፥ እኔ ያየሁዋቸው እሱንና «አሰፊ ወሌዯ ሰማያት» የተባሇውን ወጣት መኮንን ነበር።
የጣሰው አይችለህምና ያሰፊ ወሌዯ ሰማያት ሞት ምንም ቢሆን አይረሳኝም። ምክንያቱም ጣሰውን

122
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከያንሇት በፉት አውቀው የነበረ ነው ሞት ጋር ፉት ሇፉት ተፊጥጣ ውሀ ቀዴታ ከተመሇሰች ጀግና ሴት
ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው። አሰፊ ሁዋሊ ሰዎች እንዯ ነገሩኝ ሆሇቶች ነቀምት በነበሩ ጊዜ ቡናይ ሊይ
ያረፇውን የጣሉያን አይሮፕሊን ከቃጠለትና ነጂውን አብረው ከነበሩት ብዙ የጣሉያን መኮንንኖች ጋር
ከፇጁት የሆሇታ መኮንኖች አንደ ከመሆኑ በሊይ፥ ያንሇት የሞተበት አሆሁዋን ሉረሳ የማይችሌ በመሆኑ
ነው። አሰፊ ወሌዯ ሰማያትና አንዴ ቀይ ሸበቶ መኮንን የጨበጣ ሲዋጉ አሰፊ ሸበቶውን መኮንን
ዯረታቸውን በሽጉጥ መትቶዋቸው እሳቸው በጎራዳ ግንባሩን ፇሌጠውት፥ እንዯ ተያዙ ባንዴ ሊይ
ወዴቀው ሲታዩ «ወንዴማሞች ያንዴ እናት ሌጆች፤ ምን ሰይጣን በመሀከሊችን ገብቶ እስበሳችን
እንዴንጋዯሌ አዯረገን!» እያለ በመሀከሊቸው ገብቶ ያጋዯሊቸውን ሰይጣን ባንዴነት የሚረግሙና ይቅርታ
የሚሇማመኑ ይመስለ ነበር! እኒያ ቀይ፤ ሸበቶ መኮነን የዯጃዝማች ሀብተ ማርያም አጋፊሪ የነበሩ
መሆናቸውን ‹እናውቃሇን› የሚለ ሰዎች ሁዋሊ ነገሩኝ።

ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም ዘመናዊና ሀገራቸውን የሚወስደ ሰው የነበሩ መሆናቸውን ብዙ


በቅርብ እናውቃቸዋሇን የሚለ ሰዎች ሲናገሩ እስማ ነበር። ዘመናዊ አስተሳሰባቸውን ባሰራር
የሚተረጉሙ ሇመሆናቸውም ባገራቸው ትምርት ቤት መክፇት የሚፇሌጉትን ሚሲዮናውያን
ከማበረታታቸው ላሊ ገንዘብ እየከፇለ ብዙ የወሇጋ ሌጆች ተፇሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሲያስተምሩና
ትምህርት ቤቱን በገንዘብ ሲረደ እንዯ ነበረ እኔም ስሇማውቅ ይህ ሁለ ዘመናዊ ሰው የነበሩ መሆናቸው
የሚያስረዲ። እንዱሁም ከሆሇታ መኮንኖች ጋር ከተሇማመዴን በሁዋሊ አንዲንድቹ እንዯ ነገሩኝ ሇነሱና
ከሱ ጋር ሇሀገራቸው ነፃነት ሇመታገሌ ከየቦታው ተጠራቅመው ወዯ ነቀምት ሇሄደት ሁለ፥ እዚያ
በቆዩበት ጊዜ የወር ዯመወዝ እየከፇለና በምክርም በላሊ በሚያስፇሌጋቸው ጉዲይ ሁለ እየረደና
እያበረታቱ ማቆየታቸው ሀገራቸውን የሚኢወደና ሇነፃነትዋ የሚያስቡ መሆናቸውን የሚያመሇክቱ
ናቸው። ታዱያ እኒያ ዘመናዊ አስተሳሰብ የነበራቸው እንዯ መሆናቸው መጠን የነፃነትና የባእዴ
ተገዥነትን ሌዩነት የሚያውቁ ሰው እኒያ ሀገራቸውን ወዲጅና ሇነፃነትዋ የሚያስቡ እንዯ መሆናቸው
መጠን ሇሀገራቸው ነፃነት የሚታገለት ሁለ ‹ርዲታና ዴጋፌ ያዯርጉሌናሌ› ብሇው ተስፊቸውን
ያሳረፈባቸው ሰው ሇኢትዮጵያ ነፃነትና ሇኢትዮጵያውያን ሁለ ዯህንነት የሚታአገሇውን የክቡር ራስ
እምሩን ሰራዊት የሚወጋ ጦር መሊካቸው ስሇሳቸው ሲነገርና ሲታመንም ከኖረው መሌካም ነገር ሁለ
ጋር ይስማማ ነበር።

ነፃነታችን ከተመሇሰ በሁዋሊ ካንዴ የወሇጋ ትሌቅ መኮንን ጋር ይህን ነገር አንስተን ስንነጋገር
ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም፥ ጦርነቱን እስከ መጨረሻ ሇመቀጠሌ ቆርጠን እንዯ ነበረና አሳባቸውን
እንዱተው ያስገዯደዋቸው ያባታቸው ትሌሌቅ መኩዋንንት እንዯ ነበሩ ነገሩኝ። «መኩዋንንቱ» አለ
የወሇጋው መኮንን «መኩዋንንቱ ንጉሠ ነገሥቱ የመሩትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሙለ ዴሌ ካዯረገው
ሀይሇኛ ጠሊት ጋር ገጥሞ ጦርነቱን መቀጠሌ፥ አገርን ከማስጠፊትና ህዝብን ከማስበዯሌ በቀር
የኢትዮጵያን ነፃነት ሉያስመሌስ አይችሌም» ብሇው ባንዴ ቃሌ ስሇ ተቃውሞዋቸውና ህዝቡም የነሱን

123
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሳብ እንዱከተሌ ቀስቅሰውት ስሇ ነበረ፥ ከጥቂት አሽከሮቻቸው ጋር ብቻ በመቅረታቸው የመጀመሪያ
አሳባቸውን ሇመተው ተገዯደ።

ይህ ሉሆን ይችሊሌ። ያን ጊዜ ባሌተያዙት አገሮች የነበሩት አገረ - ገዥዎች ሁለ


ሰራዊታቸውንና ህዝባቸውን ባንዴነት አስተባብረው ካሌተነሱ ሇየብቻቸው ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ
ሀይሇኛ ጠሊት ጋር ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ቢሞክሩ ሀገርህን ከማስጠፊትና ህዝብን ከማስበዯሌ በቀር፤
የኢትዮጵያ ነፃነት ማስመስሇ የማይችለ መሆናቸውም እውነት መሆኑ ታይቶዋሌ። ነገር ግን ዯጃዝማች
ሀብተ ማርያም ከዚህ በሊይ በተመሇከቱት ምክንያቶች ጦርነቱን ሇመቀጠሌ የነበራቸውን አሳብ ሇመተው
ቢገዯደም፤ እኒህን ምክኒያቶች ሇራስ ገሌፀው ወዯ ወሇጋ እንዲይሄደ፤ የወሇጋ መንገዲቸውን ሇውጠው
ወዯ ላሊ እንዱሄደ ሉሌኩባቸው አይችለም ኖሮዋሌ? ጦር ሲሌኩ ኢትዮጵያውያን ወንዴማሞች እስ
በሳቸው እንዯሚጋዯሎሌታያቸውም ኖሮዋሌ? ያሳዝናሌ!

የሆነ ሆኖ ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም ከሊኩት ኦር ተቁውርጠው ከቀሩት እወንዙ ውስጥ አንጥፍ
የነበረውም ከቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ከባዴና ቀሊሌ መሳሪያውን ጠምድ ባአገሪ ሲያጠቃን የነበረውም
ባጭር ጊዜ የሞተው ሞቶ የተረፇው ተርፍ ባንዴነት የዯዳሳን ሸሇቆ ወርድ ሄዯ። ከዚያ በሁዋሊ የተኩስ
ዴምፅ አሌተሰማም።

ራስ፥ ከሁዋሊ ዯርሰው ወንዙን ከሊይ በኩሌ ሉሻገሩ ከታች በኩሌ ተቁዋርጦ የቀሩ ጥቂት የጠሊት
ወታዯሮች መኖራቸውን ሲሰሙ «ባሊምባራስ ሌመንህ» ይባሌ የነበረውን የጭፌራ አሇቃ መኮንናቸውን
አስጠርተው እኒያን ሰዎች «እሺ» ቢለ እጃቸውን እንዱሰጡ ዯጋግሞ ጥሪ እንዱያዯርጉሊቸውና የሰሊም
ጥሪውን የማይቀበለ ከሆነ ባለበት እንዱጨርሳቸው ትእዛዝ ሰጥተውት አሇፈ። ሁውሊ ባሊምባራስ
ሌመንህ እንዯ ነገረኝ እጃቸውን እንዱሰጡ ከማስጠንቀቂያ ጋር ተዯጋግሞ የተዯረገሊቸውን የሰሊም ጥሪ
ባሇመቀበሊቸው እወንዙ ውስጥ እንዲለ ተከበው ያሇቁት፥ ጊዜው ጠሊቶቻችን ያዯረጋቸው ወንዴሞቻችን
አሥራ ሁሇት ነበሩ።

የሞቱትን ሇመቅበርም ሇቆሰለት ህክምና ርዲታ ሇመስጠትም እንዱመች ጦርነቱ ከተዯረገበት


አቅራቢያ ሰፇር ማዴረግ አስፇሊጊ ስሇ ነበረ ከጉይ ቤተ ክርስቲያን ግርጌ ሰፇር ሆኖ ሙታኑ እንዱቀበሩና
ቁስሇኞች እንዱታከሙ ተዯረገ። ከያነሇት ጀምሮ ረዲቶች ተዯርገውሊቸው ሇቁስሇኞች የህክምና ርዲታ
ሲሰጡ አይ የነበረ ወይዘሮ ስንደ ገብሩንና ያቶ ይሌማ መንገሻን እህት ወይዘሮ? (ወይዘሪት?) ጽጌ
መንገሻን ነበር።

124
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምእራፍ አስራ ሰባት

ከጉይ እስከ ጉማ
ጉይ ሊይ በተዯረገው ጦርነት ኢትዮጵያውያን ተባብረው የጋራ ጠሊታቸውን በመውጋት ፇንታ፥
እስ በሳቸው ተዋግተው መጋዯሊቸው እጅግ የሚያሳዝንና እንዲይዯርስ ሇማዴረግ የሚቻሌ ነበር።
ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም ከክቡር ራስ እምሩ ጋር ተባብረው ጠሊትን ሇመውጋት የማይችለበት
ምክንያት ያጋጠማቸው መሆኑን ገሌፀው ራስ ወዯ ሳቸው እንዲይሄደ ቢሌኩባቸው ኖሮ፥ ወይም ክቡር
ራስ እምሩ ስሇ ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም አቁዋምና በጠቅሊሊው ስሇ ወሇጋም ሆነ ስሇ አካባቢው ህዝብ
አሳብ የሚያስተማምን መረጃ ሳይገኝ እንዱሁም ዝም ብሇው ወዯ ወሇጋ ጉዞዋቸውን ባይጀምሩ ኖሮ ጉይ
ሊይ ጦርነት ተዯርጎ ኢትዮጵያን እስ በሳቸው አይጋዯለም ነበር። የዯጃዝማች ሀብተ ማርያምን አቁዋም
አጣርቶ ሇማወቅ ወዯ ወሇጋ ወሰን ቀረብ ብል ማዲመጥ አስፇሊጊ መስል ቢታይ እንኩዋ በጦርነት ጊዜ
እንዯሚዯረገውና ከጉይ ጦርነት በሁዋሊ በኛም ዘንዴ ማዴረግ እንዯ ተጀመረው ከሰራዊቱ ቀዴመው
መንገደና አካባቢው ካዯጋ ነፃ መሆናቸውን እያሰሱ የሚያረጋግጡ፥ ቃፉሮች ማዴረግ በተገባ ነበር። ነገር
ግን እንዱያ ያሇ ጥንቃቄ ባሇመዯረጉ፥ ጠሊታችን ከፉታችን ተሰሌፍ እንዯሚጠብቀን ሳናውቅ ባጠመዯው
ወጥመዴ ገብተን ያ ሌናመሌጠው እንችሌ የነበረና ሉዯርስብን የማይገባው ጉዲት ዯረሰብን።

ላሊው በኛ፥ በኩሌ የነበረ ጉዴሇት በቂ ስንቅና ትጥቅ ሳይኖረን «ጠሊታችነን በረዥም ጦርነት
አዴክመን ካገራችን እናስወጣሇን» ብሇን ስንነሳ ክቡር ራስ እምሩ ክረምቱን ሙለ ጎሬ ሲከርሙ
ሇስንቅም ሆነ ሇትጥቅ አይነተኛ አሇኝታችን የሆነው የዚያ ክፌሌ ህዝብ እንዱተባበረን ምንም የተዯረገ
ቅስቀሳ አሇመኖሩ ነበር።

የኢትዮጵያ ህዝብ በቅኝ አስተዲዯር ውስጥ ኖሮ ስሇማያውቅ፤ በነፃነትና በቅኝ አስተዲዯር መሀከሌ
ያሇውን ሌዩነት የሚያቁት ጥቂት ይሆናሌ። ስሇዚህ የቅኝ አስተዲዯር ህዝቡን ሊገሩ፥ ሇሀብቱ፥ ሇጉሌበቱ
ሇመብቱ ባሇቤት እንዲይሆን የሚያዯርግና ባንፃሩ እኛ ይህ ሁለ ፇጣሪ ከጥንት ጀምሮ ሇኢትዮጵያ ህዝብ
የሰጠው ፀጋ እንዲይወስዴበት ሇዚህ ሁለ ባሇቤት እንዯሆነ እንዱኖር የምታገሌ በመሆናችን የዚያ ክፌሌ
ህዝብ ሇራሱ ሲሌ በሀብቱ በጉሌበቱ፥ በህይወቱ እንኩዋ፥ እንዱተባበረን ቅስቀሳ ማዴረግ ይገባን ነበር።
ግን አሊዯረግንም። እንዱያውም እንዱተባበረን በመጣር ፇንታ አንዲንዴ ጊዜ ከኛ የሚሸሽበትን መንገዴ
ስንከፌትሇት እንታይ ነበር። ሇምሳላ፦ ከጉይ ጦርነት በሁዋሊ፤ ሰፇር በተዯረገበት ዙሪያ የሚኖረውን
ህዝብ ከብቶች ወታዯሮችን እንዯ አውሬ በጥይት ገዴሇው መብሊታቸውና እመንዯርም ገብተው
ነዋሪዎችን ማስቸገራቸው ሲታወቅ እንዱያ ባዯረጉት ወታዯሮች ሊይ እኑዋንስ ቅጣት ተግሳጥ
አሌዯረሰባቸውም። ምክንያቱን ከወታዯሮች አሇቃ አንደን ብጠይቃቸው «ጠሊቶቻችን ከቤተ ክርስቲያኑ
ዙሪኢያ ምሽግ ሰርተውና ከባዴ መሳሪያ ጠምዯው ከወንዴዙ ውስጥም የተዯራጀ ጦር አስተኝተው እኛን
የሚያጠፈበትን እቅዴ ሁለ ሲያቅደ በሰፇሩ ዙሪያ ያሇው ህዝብ እያዬ ላሊው ቢቀር እንዴንጠነቀቅ

125
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምሌክት ሉሰጠን ይችሌ ነበር። ነገር ግን በጠሊቶቻችን ወጥመዴ እስክንገባ ዝም ብል ተመሇከተን። እና
እንዱያ ማዴረጉ የነሱ ተባባሪ ቢሆን ነውና ከጠሊቶቻችን ሇይተን የምናይበት ምክንያት የሇም» ግን
የወታዯሮች አሇቃ እንዲለት «ህዝቡ ላሊው ቢቀር እንዴንጠነቀቅ ምሌክት ይሰጠን» የነበረ፤ ሇሱ ጥቅመ
የቆምን መሆናችነን አስረዴተን እንዱተባበረን፥ አስቀዴመን ጥረት ብናዯርግ ነበር እንጂ፥ ያን
ባሇማዴረጋችን ስሊሌተባበረን «ህዝቡን እንቀበሌ» ማሇት ጠሊት ከማብዛት በቀር ላሊ ትርፌ እንዯላሇው
ጉይ ብቻ ሳይሆን ከጉይ በሁዋሊ በሄዴንበት ሁለ እስከ መጨረሻው፥ ወሬ ነጋሪ እንኩዋ አጥተን በጉይ
የዯረሰብን ሲዯጋገም አዬን።

የክቡር ራስ እምሩ ሰራዊት ከጉይ ጦርነት ከሁዋሊ በሰፇረበት ቦታ ሁሇት ቀናት ያክሌ ቆይተን
ተመክረና ወዯ ወሇጋ ተጀምሮ የነበረው ጉዞ ሳይታሰብ ዴንገት በተዯረገው ጦርነት ምክንያት
አቅጣጫውን ወዯ ጅማ እንዱያዞር ስሇ ተወሰነ፥ ወዯ ጅማ ጉዞ ተጀመረ። ወዱያውም ሰራዊቱ በዬሇቱ
ጉዞውን ከመጀመሩ ሶስት ሰዒት ያክሌ እዬቀዯሙ እየሄደ የሚያሌፌበት መንገዴ ከአዯጋ ነፃ መሆኑን
እያሰሱ እንዱረጋገጡ «ፉታውራሪ ከበዯ ያዘው» እና «ቀኛዝማች (ሁዋሊ ፉታውራሪ) ዯጀኔ ርገጤ»
መመዯባቸውን ሰማሁ። ሁሇቱ በጀግንነታቸው የታወቁ የጭፌራ አሇቆች ሇቃፉርነት መመዯባቸው «ጅብ
ከሄዯ ውሻ ጮኸ» እንዯሚለት፤ ጉዲት ከዯረሰብን በሁዋሊ ከመሆኑ በቀር መቸም ሇወዯፉቱ መሌካም
የጥንቃቄ ዜዳ መሆኑ የታወቀ ነው። ግን ሇኔ ያን ጊዜ «ሇወዯፉቱ» የሚባሇው ነገር ትንሽ የተስፊ
ብሌጭታ የማይታይበ ጨሇማ ሆኖ ነበር የሚታዩኝ።

በጉይ ጦርነትና ከዚያ በሁዋሊ አቅጣጫችነን ወዯ ጅማ አዙረን መጉዋዝ ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ


መንገዴ ሇመንገዴ የተመሇከትሁት ሁለ ጦርነቱን በማስረዘም ጠሊታችነን አዴክመን ካገራችን ማስወጣት
እንዯምንችሌ የነበረኝን ተስፊ ከተስፊ ዯረጃ አውርድ ከንቱ ምኞት አዯረብኝና ተስፊ ቢስነት ባድነት
ተሰማኝ! ዙረታችን ዴካማችን ሞታን ሁለ አሊማ የሇሽ ሆኖ ታዬኝ!

እስከዚያ ጊዜ ዴረስ ተፅፍ ያነበብሁትም ባፌ ሲነገር የሰማሁትም «ኢትዮጵያውያን ብዙ ጊዜ


እስበሳቸው አዬተጣለ የተዋጉ ቢሆንም የውጭ ጠሊት ሲመጣባቸው የስበሳቸውን ጥሌ ወዯ ጎን ትተው
እዬተባበሩ ከውጭ የመጣ የጋራ ጠሊታቸውን መቃወም በማወቃቸው ያገራቸውን ነፃነት አስከብረው
ሇመኖር ቻለ» የሚሌ ስሇ ነበረ ያን አምኘ እኖር ነበር። ነገር ግን ያን ጊዜ ፊሽስት ኢጣሉያ ኢትዮጵያን
ሳትወር በጉይ ጦርነት ስሇ ኢትዮጵያም የጋራ ጠሊት ስሇሆነቺው ፊሽስት ኢጣሉያም ሆነው የሞቱ
ኢትዮጵያውያን ብቻ መሆናቸውን ሊይ በምናሌፌበት መንገዴ አቅራቢያ ከሚኖረው ህዝብ፥ የሚበዛው
ቤቱን እዬዘጋ ከኛ ሲሸሽ ያሌሸሸው በወገንነት ሳይሆን በጠሊትነት አይን ሲመሇከተን ሳይ ጫካችን እኛን
ከጠሊት በመተገን ፇንታ፥ የሚወጉንን በውስጡ እዬሸሸገ ሲያስወጋን ሊይ የሚበቃ ስንቅና ትጥቅ
ባይኖረንም ህዝባችን መግቦ ጫካችን ተግኖ ሇመጨረሻ ዴሌ እንዱያበቁን የነበረኝ ተስፊ ጥልኝ ጠፊ።

126
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ኢትዮጵያን ሇመያዝ በዬጊዜው የመጡትን ባእዲን መንግስታት
ጣሉያንን ጭምር ኢትዮጵያውያን ተባብረው ዴሌ እየመቱ ያገራቸውን ነፃነት አስከርበው ኖረዋሌ።
ታዱያ ያ ያስተባብራቸው የነበረው ያገር ፌቅር አሁን የት ዯረሰ? ወዳት ጠፊ? ያሁኑን ትውሌዴ ምን
ነካው?» እሊሇሁ፥ የወዯፉቱ ተስፊ ሲጨሌምብኝ አሳቤ ወዯ ሁዋሊ ተመሌሶ በትግራይ እነ ዯጃዝማች
ሀይሇ ስሊሴ ጉግሳ በጎጃም እነ ዯጃዝማች ገሰሰ በሇው በወሇጋ እነ ዯጃዝማች ሀብተ ማርያም ገብረ
እግዚአብሔር፥ እዚያ መንገዴ ሇመንገዴ ህዝቡ፥ የኢትዮጵያን ነፃነት ሇማጥፊት ከመጣው የጋራ ጠሊት
ጋር መተባበራቸውን አንዴ ባንዴ ይቆጠርና ከዚያ ኢትዮጵያ ትታየኛሇች! ኢትዮጵያ ከስታ ተንገሊታ
ተጎሳቁሊ እያሇቀሰች ትመጣና «እዩኝ እንዱህ ሆንሁ! አምሮብኝ ተከብሬ ታፌሬ እኖር የነበርሁይቱ፥
አሁን በናንተ ጊዜ እንዱህ ሆንሁ!» ብሊ ሌጆችዋን ኢትዮጵያውያንን ስትወቅስ ስትማጠን፤ ስትረግም
ትታየኛሇች።

ያን ጊዜ ከጉይ ተነስተን ወዯ ጅማ ስንሄዴ መንገዴ ሇመንገዴ፥ «የኢትዮጵያ ሌቅሶ» በሚሌ ርእስ


አንዴ ግጥም ገጥሜ ሌጅ ፇቃዯ ስሊሴ ህሩይ እንግሉዝ አገር ዯርሰው ሲመሇሱ ባመጡት የማባዣ
መኪና እያበዛን በሰራዊቱ መከሌም በላሊ ተቀባይ በተገኘበት ቦታም ሁለ እንበትን ጀመር።

ያን ግጥም «ሌጅ (ሁዋሊ ጀኔራሌ) ነጋ ሀይሇ ስሊሴ» ሱዲን በስዯት በነበረበት ጊዜ ሇወይዘሮ አበባ
ፇሇቀ ሰጥቶዋቸው ኖሮ፥ የኢትዮጵያ ነፃነት ከተመሇሰ በሁዋሊ እኔም ከጣሉያን እስር ቤት በ1936 የዛሬ
አርባ አራት ዒመት ግዴም መሆኑ ነው እንዯ ተመሇስሁ ወይዘሮ አበባ ከሱዲን መጥተው አዱስ አበባ
ነዋሪ መሆናቸውን ሰምቼ ሌጣይቃቸው ስሄዴ አሳዩኝ። ታዱያ ያን ጊዜ ሲያሳዩኝ በማባዣው መኪና
በተባዛው ሊይ ከስሩ ጄኔራሌ ነጋ፥ ተፇሪ መኮንን ትምህርት ቤት አብረው ስሇ ነበርን ስሇኔ ሰፊ አዴርጎ
እስከ ዛሬ በጃቸው ይኖር እንዯሆነ እንዱሰጡኝ ወይዘሮ አበባን ጠይቄያቸው ያን ጊዜ ያሳዩኝን ፇሌገው
ስሊጡት በዯብተር ገሌብጠው ያስቀመጡትን ሰጡኝ።

ግጥሙ በማዘዣ ከተባዛው ወዯ ዯብተር ሲገሇበጥ፥ አንዲንዴ የተዘሇለ ቃሊት መኖራቸው ከንባቡ
የሚታወቅ ከመሆኑና አንዲንዴ ቦታም የፉቱ ሁዋሊ የሁዋሊው ፉት እዬሆነ ከመገሌበጡ በቀር፥
በጠቅሊሊው ያው የኔ ግጥም ነው። ስሇዚህ ከዯብተሩ ያገኘሁትን ሳነብ የጎዯለትን ቃሊት
ያስታወስሁዋቸውን ያሇዚያም መሰሊቸውን ሞሌቼ ቦታ የተሇዋወጡትንም ቦዬቦታቸው አስጨምቸ
ሊንባቢዎች አቅርቤዋሇሁ። እንዱሁም ጀኔራሌ ነጋ ሀይሇ ስሊሲኤ ስሇኔ ካተተው፥ የውዲሴውን ክፌሌ
ትርፌ ስሇመሰሇኝ ትቼ ከግጥሙ ጋር የተዛመዯውን ክፌሌ ብቻ እንዯ መቅዴም እንዱሆን ከዚህ
እንዯሚከተሇው ፅፋዋሇሁ።

«ሀዱስ አሇማዪኤሁ፣………. የኢትዮጵያ መንግስት በፇረሰ ጊዜ ከራስ እምሩ ጋር ሆኖ ስሇ


ነፃነቱ በሚጋዯሌበት ጊዜ ቆሞም ተቀምጦም፥ ተኝቶም የሚያቃጥሇው ያገር ፌቅር ሌቡን እዬቀቀሇው
እንፊልት እየገነፇሇ አይኑን እንባ እዬሞሊ ስሇቸገረው በናቱ ስም «የኢትዮጵያ ሌቅሶ» ብል ሀዘኑን

127
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇወንዴሞቹ ሇኢትዮጵያውያን ሇማካፇሌ ሲሌ በንባው የፃፇሌንን የሚከተለትን ቃሊት ሇሀሳባችሁ
መሰረትና መሪ ይሆኑዋችሁዋሌ ስንሌ ተካፊይነታችነን እያረጋገጥንሊችሁ፤ ሀዘኑን በጎዯሇ ሞሌተን
ፅፇንሊችሁዋሌ»።

የኢትዮጵያ ሌቅሶ

፩. «ሌጆቼ በማመን፥ ባሇመጠርጠር፤

የሚዯፌረኝ የሇም፤ ይመስሇኝ ነበር።

«ግን አሁን ተዯፇርሁ ሊሌቅስ፥ እርሜን ሊውጣ፤

ጀግኖች ያሇቁብኝ፤ ስሇሆንኩ አይቶ አጣ።

«አዴምጡኝ ሌጆቼ ሊስጠንቅቃችሁ፤

ሳምናችሁ ብትከደኝ ስመካባችሁ፤

ዘሊሇም ውርዯት ነው ዯመወዛችሁ።

አየ ዋዬ ሌጆቼ እየ ዋዬ ከዲችሁ ወዬ።

፪. «ጀግና አሌተተካም ወይ፥ በቴዎዴሮስ ስፌራ፤

ጎበዝ አሌቆመም ወይ በዮሀንስ ስፌራ፤

ሰው የሇበትም ወይ በምኒሌክ ስፌራ፤

ጠሊቴ ሲወርረኝ ከቀኝ ከግራ፤

የሚሰማኝ ያጣሁ ብታራ ብጣራ።

ወይ እኔ ኢትዮጵያ የጀግኖች እናት፤

ሁለም አሇቁና ትተው ባድ ቤት፤

ዯርሶብኝ የማያውቅ አገኘኝ ጥቃት።

አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲሁኝ ወዬ።

፫. «ገንዘብ እዬዘራ ሲመጣ ጠሊት፤

128
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከማታሇሌ ጋራ፥ ውሸት ስብከት፤

ባጠመዯው ወጥመዴ እንዴትገቡሇት፤

ተንኮለን ሳታውቁ መስልዋችሁ እውነት፤

በግ ካራጁ ሁዋሊ እንዯሚጎተት፤

ትጎተታሊችሁ፥ እናንተም ሇሞት።

አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲችሁኝ ወዬ።

፬. ገንዘብ ተበዴሮ አሁን ሲሰጣችሁ፤

ሁጊዜም እንዯዚያው የሚያዯርግ መስልዋችሁ፤

እንዲትታሇለ ሁዋሊ ወዮሊችሁ።

አሁን ገንዘብ ሰጥቶ እንዲትታገለት ካረገ በሁዋሊ፤

እንኩዋንስ የራሱን ገንዝቡን ሉያበሊ፤

የናንተም ይሄዲሌ ይሰጣሌ ሇላሊ።

አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲችሁ ወዬ።

፭. አሁን ቢሰጣችሁ ገንዘብ ተበዴሮ፤

በጁ ስትገቡሇት እንዱህ ጥሮ ግሮ፤

ከዚያ በሁዋሊ ክንደን አጠንክሮ፤

ያጠፊውን ገንዘብ አንዴ ባንዴ ቆጥሮ፤

ይቀበሊችሁዋሌ ወሇደን ጨምሮ።

አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲችሁ ወይ።

፮. አይ ሞኞች ተሊሊዎች ሆይ፤

ዯሙን የሚያፇሰው በሰው አገር ሊይ፤

129
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እናንተን ሇማክበር መሰሊችሁ ወይ።

አሁን ስነግራችሁ ቢመስሊችሁ ዋዛ፤

በሁዋሊ መከራው ስቃዩ ሲበዛ፤

ሞትን ብትፇሌጉት በወርቅ አይገዛ፤

አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲችሁኝ ወዬ።

፯. ፀፀቱ ይውጣሌኝ እስቲ ሌንገራችሁ፤

ምናሌባት ብትሰሙኝ ትንሽ ቢቆጫችሁ፤

ጠመንጃው ጥይቱ እያሇ በጃችሁ፤

ደሩ ሸንተረሩ ሳሇ በዯጃችሁ፤

አሁን ጊዜ ሳያሌፌ ካሌተጋዯሊችሁ፤

ይህን ሁለ በጁ ካረገ በሁዋሊ አጥቂው ጠሊታችሁ፤

ቢጭኑት አጋሰስ ቢያርደት ሰንጋ ናችሁ።

አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲችሁኝ ወዬ።

፰. ከዚህ ወዱያ በቃኝ መክሬያችሁዋሇሁ፤

ሇኔም ሇናንተም ሞት፥ እርሜን አውጥቻሇሁ፤

መክሬያችሁዋሇሁ ሳይጠነክር አቅሙ፤

የናትነት ምክሬን ቃላን ብትፇፅሙ፤

እግዜር ይባርካችሁ አብቡ ሇምሌሙ፤

ግን ይህን ጩኸቴን ሌቅሶየን ባትሰሙ፤

በመሌእሌተ መስቀሌ የፇረሰው ዯሙ፤

ርጉም ያዴርጋችሁ እስከ ዘሊሇሙ።

130
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አየ ዋዬ ሌጆቼ አየ ዋዬ ከዲችሁኝ ወዬ»

ኮልኔሌ በሊይ ሀይሇ አብ ጭፌሮቹ ሁለ እንዱሰበስቡሇት ካዯረገ በሁዋሊ ያን ግጥም ይዞ አንዴ


ከፌተኛ ቦታ ሊይ ይቆምና ወይም ከፌተኛ ቦታ በላሇበት አንዴ ዛፌ ሊይ ይወጣና ግጥሞችን አንብቦ
«አዝማቹ» ሊይ በዯረሰ ቁጥር ትግሬ እንዯ መሆኑ «ዋይ ዋይ፥ ሌጆቼ ዋይ ዋይ ከዲችሁኝ ወይ» ሲሌ
በጋሇ ስሜት እጆቼን አንስቶ እዬነቀነቀ ምንም እንኩዋ ነገሩ የሚያሳዝንም የሚያበሳጭም ቢሆን፥ «ጥርስ
ባእዴ ነው» እንዯሚለት እንዲንታይ አፊችነን በጃችን ከዴነን፥ በዚያ ከግር እስከራሱ ወኔ ብቻ በሆነ ጎበዝ
እንስቅበት ነበር።

ከጉይ ተንስተን የኢለባቦርን ግዛት አሌፇን ጅማ ውስጥ «ጉማ» ከሚባሇው ክፌሌ እስክንዯርስ
ስንት ቀን እንዯወሰዯብን ረስቸዋሇሁ ምናሌባት አንዴ ሳምንት ወይም ከዚያ የበሇጠ ጊዜ ወስድብን
ይሆናሌ። የሆነ ሆኖ በተጉዋዝንበት መንገዴ አቅራቢያ ይኖር የነበረው ህዝብ፥ የጠሊት ስብከት እኛን
አስጠሌቶት ይሁን ወይም ጉይ ሊይ ወታዯሮቻችን የህዝብ ከብቶች ገዴሇው መብሊታቸውና እመንዯር
ገብተው ማስቸገራቸው ተሰምቶ አስፇርቶት ይሁን አይታወቅም፤ ቤቱን እዬዘጋ ከኛ ይሸሽ ነበር።
ያሌሸሸውም ሇኛ በጎ ፇቃዴ ያሇው ስሊሌነበረ በምንሄዴበት አገር ምን እንዯ ሚቆዬን ወሬ ነጋሪ
ባሇማግኘታችን ሳናውቅ እንዱሁ «እውር ዴንበራችነን» ነበር የምንሄዴ።

የጉዞዋችን አቅጣጫ ከወሇጋ ወዯ ጅማ እንዱሇወጥ የተወሰነበት አሊማ፥ ክቡር ራስ እምሩ


ከጅማው እንዯራሴ ከከንቲባ ጋሻው ጠና ጋር ተመካክረው ጠሊትን በህብረት ወግቶ ከኢትዮጵያ
ሇማስወጣት የሚያስችሌ እቅዴ ሇማቀዴ ነበር። ነገር ግን ጣሉያንን ከኢትዮጵያ ስሇምናስወጣበት መንገዴ
ሇመመካከር የምንሄዴባቸውን ከንቲባ ጋሻው ጠናን፥ ጉማ ጫካ ውስጥ አግኝተናቸው የጅማ ከተማ
በጣሉያኖች የተያዘ መሆኑንና እሳቸው ከተማውን ሇቀው ጫካ ከገቡ በርከት ያለ ቀናት ማሇፊቸውን
የሰማነው ከከንቲባ ከራሳቸውና አብረዋቸው ከነበሩት ነበር። ጅማ እስክንዯርስ የጅማን መያዝ አናውቅም
ነበር። እዚያ ጫካ ውስጥ ከከንቲባ ጋሻው ጠና ጋር፤ ከሰዎቻቸው ላሊ ያገኘናቸው መኩዋንንትና
ህዝቡም በጣም ብዙ ነበሩ። ከመኩዋንንቱ መሀከሌ ትዝ የሚለኝ (ላልችም ይሆናለ) የክብር ራስ
ቢትወዯዴ መኮንን እንዲሌካቸው ወንዴም (ወይም ቅርብ ዘመዴ) ፉታውራሪ አጥናፌ ሰገዴ ወሌዯ
ጊዮርጊስ የክቡር ራስ አዯፌርሰው ሌጅ ቀኛዝማች መኮንን አዯፌርሰውና ብሊታ ታከሇ ወሌዯ ሀዋርያት
ነበሩ። ወዱያው በተገናኘንበት እሇት ይሁን፥ ወይም በማግስቱ (ቀኑን ረስቻሇሁ) ራስና ከንቲባ ከላልች
ታሊሊቅ የጦርና የሰሊም (ሲቪሌ) መኩዋንንት ጋር ዘሇግ ያሇ ስብሰባ አዴርገው ቆይተው ተነሱ። መቸም
እንዱያ ባሇው የታሊሊቆች ስብሰባ ሇምክዴር የቀረቡት ጉዲዮች ምን እንዯ ነበሩና ምን እንዯተወሰነ
እርግጠኛውን ማወቅ አይቻሌ። አንዲንዴ «ጭምጭምታ ሰማን» ያለ ሰዎች እንዲወሩትና ሁዋሊ ሲሆን
ከታዬው መገመት እንዯሚቻሇው ግን ምክር የተዯረገባእው ጉዲዮች «የጅማን ከተማ የያዘውን የጣሉያን
ጦር እንምታ? ወይስ እሱን ትተን ዯጃዝማች ታዬ ጉሌሊቴ ወዲለበት፤ ወዲሌተያዘው አገር ወዯ ከፊ

131
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንሂዴ?» የሚለት ሲሆኑ የተወሰነው ጅማ ያሇውን የጣሉያን ጦር ከመምታት ወዯ ከፊ እንዴንሄዴ
ነው። ከስብሰባው እንዯተነሱ ብሊታ ታከሇ ወሌዯ ሀዋርያት ሰዎቻቸውን ይዘው ተሇይተውን ሄደ።
ወዳት እንዯሄደ አሊውቅም። ከዚያ በሁዋሊ ጭራሹ አሊዬሁዋቸውም። የተወራው ወሬ ግን «እስብሰባው
ሊይ በተወሰነው ውሳኔ ስሊሌተስማሙ በላሊ ክፌሌ ካለ አርበኞች ከነ ሻሇቃ (ሁዋሊ ራስ) መስፌን ስሇሽ
ጋር ሆነው ትግለን ሇመቀጠሌ ሄደ» የሚሌ ነበር።

ከነከንቲባ ጋሻው ጠና ዙሪያ ተሰብስቦ ጫካውን ሞሌቶት ያገኘነውና እኛም ከዯረስን በሁዋሊ
እዬመጣ በሊይ በሊዩ ይጨምር የነበረው ከያገሩ በየምክንያቱ እየሄዯ እዚያ ክፌሇ - ሀገር ይኖር የነበረ
ከሌዩ ሌዩ ዘር የተጠራቀመ ህዝብ ሲሆን ከዚያ የሚበዛው አማራነት ያሇው ነው። በጠቅሊሊው ከዚያ
ስዯተኛ ህዝብ መሀከሌ ዯምጎ ሽማግላው ባሌቴቱና ህፃኑ ይበዛ ነበር። ታዱያ እጉዞ ሊይ ራሳቸውን
ካሌቻለ ህፃናት በቀር ያ ሁለ ወንደ ከቤቱ ጋር ያሌተወውን ሇስዯቱ የሚያገሇግሇውን ቁሳቁስ ጠቅሌል
በራሱ ወይም በትከሻው ተሸክሞ ፌየለን በጁ ስቦ ወይም ድሮውን በቅፈ ታቅፍ ይሄዲሌ። ሴትዋ ሌጅዋን
ወይም ምጣዴዋን በጀርባዋ አዝሊ አገሌግሌዋን ወይም ላሊ እቃዋን በጅዋ አንጠጥሊ ትሄዲሇች። ታዱያ
ሇዚያ ሁለ ህዝብ መንገደ አሌበቃው ብል እየተተራመሰ ጫካ እዬጣሰ፥ አሞዋቸው ሲሊቀሱ ያን ረብሻ
ጫጫታ ያን ሁኔታ በጊዜው በቦታው ሊይ ተገኝቶ መመሌከቱ ብቻ ሳይሆን፤ ካሇፇም በሁዋሊ ትዝታው፤
የሚያሳዝን የሚዘገንን ነው።

«ያን ሁለ ህዝብ አንዲንደ ካባት ከናቱ ጀምሮ አንዲንደም ራሱ ሄድ ስራ እዬሰራ ቤት ንብረት


መስርቶ ዘመዴ ወዲጅ አበጅቶ የኖርንበትን አገር አስሇቅቆ እንዱያ ባሇ ችግር ውስጥ የጣሇው ምንዴነው?
ተብል ሲኢጠየቅ ያን ጊዜ ሲነገሩ የሰማሁዋቸው ምክንያቶች ሁሇት ነበሩ። አንደ ምክንያት «ያገሩ
ህዝብ ከላሊ አገር እዬሄዯ እዚያ የሚኖረውን በተሇይ አማራውን እንዱሇቅ ስሊስገዯዯው ነው» የሚሌ
ነበር። ሁሇተኛው ምክንያት «አባ ጆቢር» የተባለት ያገሩ ባሊባት፤ ያገሩ ተወሊጅ ያሌሆነው ሁለ
ካገራቸው እንዱያስወጣሊቸው በተሇይ አማራውን ግን ራሱን እዬቆረጠ ሇሚወስዴሊቸው ሽሌማት ሊንዴ
ያምራ ራስ ሰሊሳ (30) ብር እንዯሚሰጡ ሊገሬው በይፊ ስሊስታወቁና ያንዲንዴ ሰዎች ራስም ስሇተቆረጠ፥
አማራው ራሱ እንዲይቆረጥ ላሊው ‹ዛሬ ባማራው የዯረሰው ነገ በኔ ይዯርስ ይሆናሌ› ብል ፇርቶ መሸሹ
ነው» የሚሌ ነበር። ከነዚህ ከሁሇት ምክንያቶች የትኛው እውነት እንዯሆነ ማረጋገጥ አሌቻሌሁም
በግምት ግን ሁሇተኛው ምክንያት እውነት ይመስሊሌ።

አፄ ሀይሇ ስሊሴ እስከ ነገሱበት ጊዜ ዴረስ የየክፌሇ ሀገሩ አይተኛ ባሊባቶች፤ ከቅዴመ - ቅዴመ -
አያቶቻቸው ጀምሮ ተያይዞ የወረዯውን የዘር ሀገር ሳይሌቁ በያገራቸው በግዛት ሊይ የሚኖሩ ነበሩ። አፄ
ሀይሇ ስሊሴ ከነገሱ በሁዋሊ ከኒያ ባሊባቶች ብዙዎች ከግዛታቸው እንዱነሱ ተዯርጎ፥ በነሱ ቦታ ካዱስ አበባ
እንዯራሴዎች እየተሾሙ ስሇ ተተኩ በተሻሩት ባሊባቶች ብቻ ሳይሆን በያገራቸው ህዝብ መሀከሌ ጭምር
ጠቅሊሊ የቅርታ ስሜት ተፇጥሮ እንዯ ነበረ ህዝብ መሀከሌ ጭምር ጠቅሊሊ የቅርታ ስሜት ተፇጥሮ

132
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዯ ነበረ በምእራፌ፥ 3 ያ በያገሩ ባሊባቶች እዬተሻገሩ አዲዱስ የተናገሩትን አንባቢዎች ያስታውሳለ።
ስሇዚህ አባ ጆቢር የጅማ ባሊባት እንዯ መሆናቸው «ግዛቱ እንዯ ቆየው ሌማዴ ከኔ ቤት መውጣት
የሇበትም ከኔ ቤት ወጥቶ ካዱስ አበባ ሇተሊከ ባእዴ መስጠቱ በዯሌ ነው» ብሇው በመንግስት ሊይ ቂም
ቢይዙ፥ በጊዜው ግዛታቸው የተወሰዯባቸው ባሊባቶች ሁለ ያዘኑበት ጉዲይ ስሇነበረ ሊይፇረዴባቸው ይችሌ
ይሆናሌ። ነገር ግን በመንግስት ሊይ የያዙትን ቂም በተራው ህዝብ ሊይ ባሊባቶች ሲገዙ የነሱ ታዛዥ
ይኖር በነበረው ተራ ህዝብ ሊይ ጭምር መወጣት «የሚገባ ነው» ይባሌ እንዯ ሆነ ፌርደን ሊንባቢ
መተውን እመርጣሇሁ።

ምእራፍ አስራ ስምንት

ጌራ
የክብር ራስ እምሩ ሰራዊትና ከከንቲባ ጋሻው ጠና ጋር የነበረው እጅግ ብዙ ስዯተኛ ህዝብ ጉማ
ሊይ ተገናኝቶ፤ ከዚያ ወዯ ከፊ ሇመሄዴ በጀመረው ጉዞ ጌራ እስኪዯረስ ያሇፇበት መንገዴ ከምንዜውም
የከፊ አስመራሪ ነበር። መንገደ የሚያሌፇው አንዴ ቦታም ሳይቁዋረጥ ጥቅጥቅ ባሇ ዯን ውስጥ ነበር።
ጠሊት ጠመንጃና ጥይት ሰጥቶ እኛን እንዱወጉ እዚያ ዯን ውስጥ የሰገሰጋቸው ብዙ ምንዯኞች የሆኑ
ወገኖቻችን ከቀኝና ከግራ ሲተኩሱብን እንዯሚተኮሰው የጥይት ብዛት የተረፇ ሰው የሚኖር አይመስሌም
ነበር። ነገር ግን እኔ እንዲየሁትና ከላልችም እንዯ ሰማሁት እዚያ መንገዴ ሇመንገዴ በተዯረገብን ተኩስ
በሰዋችን የዯረሰውን የሞትና የመቁሰሌ ጉዲት «ከባዴ» የሚባሌ አሌነበረም።

«ቀን ሲከፊ ቀን ሲከዲ፤

ዘመዴ ይሆናሌ ባዲ።

«ቀን ሲከፊ ሲቸገር፤

አገር የሰው አገር»

ይሊለ በገና ዯርዲሪዎች። ስሇዚህ ቀን ከፊብንና ቀን ከዲንና «የጋራ ጠሊታችንን ዴሌ መትተን


አገራችንን ነፃ ሇማዴረግ በምንዋጋው ጦርነት ይተባበሩናሌ» ብሇው ሙለ እምነታችንን ያሳረፌንባቸው
ወገኖቻችን - ወዯው ይሁን ተገዴዯው አሊውቅም - የጠሊት ረዲቶች ሆነው ወገኑ! ከጠሊታችን ጋር
በምናዯርገው ረዥም ጦርነት «ሸሽጏ ተገን ሆኖ ሇመጨረሻ ዴሌ ያበቃናሌ» ብሇን የተማመንበት
ዯናችንም፤ በየዋህነት የጠሊት መሳሪያ ሇሆኑት ምንዯኞች መሸሸጊያ ሆኖ አስወጋን።

ከዚያ መንገዴ፥ ሇመንገዴ ብርቱ ተኩስ ከተዯረገብን ቀን በፉት በነበረው ላሉት ጉዋዯኛየ በትረ
ፅዴቅ ካሳ፥ ታምሞ አዴሮ ስሇ ነበረ፥ በተኩስ ቀን እሱን በበቅልየ አስቀምጨ እኔ ጠመንጃየን አንግቼ፥

133
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የኮርቻውን ዴሀራ ይዤ እየተነጋገርን እንሄዴ ነበር። ራስ በባሇበቅልዎች መኩዋንንትና በግረኞች
ታጅበው በበቅል ተቀምጨው ከኛ ትንሽ ራቅ ብሇው ፉት ፉት ይሄደ ነበር። ያ ብርቱ ተኩስ ይብስ
እየበረታ መሄደን በትረ ፅዴቅ አየና፤

«አንተ ሀዱስ ራስ እምሩ ሰው እንዯሚያከብራቸው ጥይትም የሚያከብራቸው መስልዋቸው ነው


ይህ ሁለ ጥይት እየተተኮሰ በበቅል ተቀምጠው የሚሄደ? ይሌቅ ተኩሱ በረዴ እስኪሌ ወርዯው ቦታ
ቢይዙና የሚተኩሱብንን ከጫካው ውስጥ እንዱያባርር ሇወታዯሩ ትእዛዝ ቢሰቱ አይሻሌም?» አሇኝ።

«እውነትህ ነው፤ ይሻሌ ነበር» አሌሁት።

«ታዱያ ሇምን ሄዯህ ይህኑ ሇፉታውራሪ ፇንታ አትነግራቸው?» አሇኝ። ፉታውራሪ ፇንታ ራስ
ከሚወደዋቸውና ከሚያከብሩዋቸው መኩዋንንታቸው አንደ ነበሩ። በትረ ፅዴቅ ተኩሱ በረዴ እስኪሌ
ራስ ከበቅል ወርዯው ቢቆዩ የሚሻሌ መሆኑን ሇኔ መንገር ከጀመሩ ትንሽ ቀዯም ብሇው ከመኩዋንንቱ
መሀከሌ ከበቅልዋቸው ወርዯው ጠመንጃቸውን አንግተው ሄዯው የራስን የኮርቻ ዯሀራ ይዘው
እያነጋገሩዋቸው መሄዴ ጀምረው ነበር። ሄጄ ከሁዋሊቸው ነካ አዴርጌ በትረ ፅዴቅ የነገረኝን
ስነግራቸው፣

«ስሇሱ ነው የምነጋገረው» አለኝ ፉታውራሪ። እኔ ዘወር ከማሇቴና ራስም ከበቅል ወርዯው


እግራቸው ሁሇተኛውን ርካብ ሇቅቆ መሬት ከመንካሩ ተቀምጠውባት የነበረችዋ በቅል በምንዯኞች
ጥይት ተመትታ እፉታቸው ወዯቀች። ያን ጊዜ በበቅል የነበረው ከበቅል እየወረዯ እግረኛው መንገደ
እየተው ሁለም ተገን ይዞ ሇመቆየት ወዯየዛፈ ስር ሄዯ። እመንገደ ሊይ የቀሩ በትረ ፅዴቅና የኔ በቅል
ብቻ ነበሩ። በትረ ፅዴቅ ከበቅልዋ ወርድ ፉቱን ወዯስዋ አዙሮ ሉስባት ቢሞክር «ገረገረችና» እስዋም
ወዯ ሁዋሊ ትስበው ጀመር። እንዱያ እሱ ወዯ ፉት በቅልዋ ወዯ ሁዋሊ እየተሳሰቡ በዚያ ተኩስ መሀሌ
እዚያ ገሊጣ መንገዴ ሊይ ስሇ ቀሩ ሁሊችንም ከያሇንበት በቅልዋን ሇቅቆ ወዲንዴ ዛፌ እንዱጠጋ
ጮኸንበት ነበር። ነገር ግን በትረ ፅዴቅ ከበቅልዋ ጋር እሌክ እንዯ ተጋባ ሁለ ከስዋ ጋር የገጠመውን
ትግሌ እንጂ በዙሪያው የሚወርዯውን የጥይት አመትም ሆነ የኛን ጩኸት ከቁም ነገር የጣፇው
አይመስሌም። ዯግነቱ እዚያ ጫካ ውስጥ ተሰግስገው የሚተኩስብንን ምንዯኞች፥ ወታዯሩ ገብቶ
እንዱመታ ታዝዞ ገብቶ ሲገጥማቸው እነሱ እየሸሹ ወታዯሩ እየተከተሇ ተኩሱ ከኛ እየራቀ ሄዯና
መንገደ አማን ሆነ።

«እኔም ላልችም ያን ያክሌ እየጮህንብህ ሇምን በቅልዋን ሇቅቀህ እንዯ ሁሊችን ተገን ፌሇጋ
አሌሄዴህ?» ብየ በትረ ፅዴቅን ሁዋሊ ብጠይቀው፤

«ስሇ ታመምሁ አንተ በግርህ እየሄዴህ የሰጠኸኝን በቅል ሇቅቄያት ጥይት ቢገዴሊት ወይም
ብትጠፊ ያንተንም የህሉናየንም ወቀሳ የማሌችሇው ስሇ መሰሇኝ ነው» አሇኝ። በትረ ፅዴቅ ካሳ

134
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የህሉናውንና የሰው ከሰውም ይሌቅ የህሉናውን ወቀሳ የሚፇራውን ያክሌ ሞትን የማይፇራ ቆራጥ ሰው
ነበር!

ወታዯሩ እዚያ ጭካ ውስጥ ተሰግስገው ይተኩሱብን የነበሩትን የጠሊት ምንዯኞች ካስሇቀቀሌን


በሁዋሊ የጠመጃ ዴምፅ ሳንሰማ፥ ጫካውን ጨርሰን እገሊጣው ክፌሌ ዯረስን። በዚያ ጫካ ውስጥ
እንጉዋዝ በነበርንበት ጊዜ ሁለ የጠሊት አይሮፕሊኖች አሌተሇዩንም በሊያችን ይመሊሇሱ ነበር። ነገር ግን
ከስራቸው እጫካው ውስጥ መሆናችንን ቢያውቁም ያሇንበትን በትክክሌ ሇይተው ሉያዩ ባሇመቻሊቸው
ቦምብ አሌጣለብንም። ያ ጫካ ካንዴ ወገን ወገን በጠሊት ሇተገዙ ምንዯኞች መሸሸጊያ ሆኖ ሲያስወጋን
ቢውሌም ከላሊ ወገን ሰራዊታችንን ያን ከጉማ ጀምሮ የተዯረገብንን እጅግ ብዙ ስዯተኛ ህዝብ ከጠሊት
አይሮፕሊኖች በመሸሸጉ ካሰን። ሰራዊቱና ያ ሁለ ብዙ ህዝብ የሚጉዋዝበት መንገዴ በጫካ ውስጥ
ባይሆን ኖሮ፤ ግሌጥ ቢሆን ኖሮ እኒያ በሊያችን ያሇ ማቁዋረጥ ሲመሊሇሱ የዋለት አይሮፕሊኖች ብርቱ
ጉዲት ያዯርሱብን እንዯ ነበረ አይጠረጠርም።

ከጫካው እንዯ ወጣን እንዯ መጠነኛ ኮረብታ አሌፇን፥ ከስሩ ያሇውን ጫካ የሇበሰ ወንዝ
ተሻገርንና ላሊ ከሊይ እስከ ታች በረዥሙ ጉብ ያሇ ሇሰፇርነት የሚስማማ ቦታ ስሇ ተገኘ እዚያ ሰፇርን።
ያ የሰፇርንበት ቦታ ሰውም ከብትም እስሩ ካሇው ወንዝ ውሀ እንዯ ሌብ የሚያገኝበት ከመሆኑ ላሊ
እንዲሌፌነው ጫካ ጥቅጥቅ ያሇ አይሁን እንጂ ብዙ ቅሌሌቅና ትንንሽ ዛፍች የሸፇኑት ስሇ ሆነ፥
አይሮፕሊኖች ከሊይ ኢሊማቸውን አነጣጥረው ሇመምታት የሚመች አሌነበረም። ከትንንሾቹ ዛፍች
የሚወዲዯር ዯገሊ ሳርም ሞሌቶበት ነበር። ያ ቦታና አካባቢው ከጅማ ግዛት ውስጥ «ጌራ» የሚባሇው
ክፌሌ መሆኑን ሰዎች ነገሩኝ።

ሰራዊታችንና አብሮት የሚጉዋዘው ስዯተኛ ሕዝብ ቀኑን ሙለ ፊታ ሳያገኝ የዋሇበትን


የሚያስመርር ጉዞ ጨርሶ በሰፇረበት ቦታ፥ ዯህና እረፌት አግኝቶ አዯረ። በማግስቱ እንጋት ሊይ ቃፉሮች
ፉታውራሪ ከበዯ ያዘውና ቀኛዝማች ዯጀኔ ርገጤ ከሰዎቻቸው ጋር እንዯ ተሇመዯው ሰራዊቱ
የሚጉዋዝበትን መንገዴ አማንነት ሇማረጋገጥ ቀዴመው ሄደ። ቆየት ብል ስዯተኛው ህዝብና
ከሰራዊቱም «ጉዋዝ» የሚባሇው ክፌሌ ተከትል መንገዴ ያዘ። ራስ ከዯረቅ ጦራቸው ጋር ቀዴመው
የሄዯው ብዙ ህዝብና ጉዋዙ እስኪርቅና መንገደ ነፃ እስኪሆንሊቸው ወዯ ሁዋሊ ቆዩ። አብሮዋቸው
ከቆዬው ሰራዊት መሀከሌ ቁርሱን አዴርጎ ጨርሶ፥ ሇጉዞ የሚሰጠውን ምሌክት የሚጠባበቀውም ገና
ቁርሱን ያሌጨረሰውም ነበረ። ሰራዊታችን በዚያ ሁኔታ እንዲሇ ከወንዙ ወዱያ ማድ ካሇው ኮረብታ
የከባዴ መሳሪያ ተኩስ ተሰማ። ወዱያው ተኩሱ ከተሰማበት አቅጣጫ፥ አንዴ «ዥም - ዥም - ዥም»
የሚሌ ነገር አየሩን እየሰነጠቀ መጥቶ እሰፇራችን ሊይ ፇነዲ። ጠሊት የተኮሰብን የመዴፌ እርሳስ ነበር!
ከዚያ ሁሇተኛው ከዚያ ሶስተኛው ከዚያ - ስንት እንዯ ሆነ እግዜር ይወቅ እየተከታተሇ ከማድው ከዚያ -
ስንት እንዯ ሆነ እግዜር ይወቅ እየተከታተሇ ከማድው ኮረብታ በተተኮሰ ቁጥር የመዴፈ እርሳስ እንዯ

135
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ፉተኛው እየተውዠመዠመ እየመጣ እሰፇራችን ሊይ ሲፇነዲ እንዯ መጋዝ ስሇታም ስብርባሪው
በዙሪያው ያገኘውን የዛፌ ቅርንጫፌ ሁለ እየቀነጣጠሰ ይጥሇው ጀመር። ያን ጊዜ አዯጋው ያሌተጠረጠረ
ዴንገተኛ ስሇ ነበረ በሰራዊታችን መሀከሌ መዯናገር የተፇጠፇ መስል ነበር። ነገር ግን ምንም እንኩዋ
የመዴፈ ተኩስ ባያቁዋርጥ፤ «ታጠቁ» ምሌክት የሆነው ጥሩንባ ሲነፊ ያ ጊዜያዊ መዯናገር አሇፇና
ሁለም ቀዋሚ ስራቱን በመከተሌ ወዯየቡዴን አሇቃው እየሄዯ ተሰብስቦ የሚሰጠውን ትእዛዝ በመጠባበቅ
ሊይ እንዴሇ «የጠሊት ወታዯር! የጠሊት ጦር! የጠሊት እግረኛ ጦር!» የሚሌ ዴምፅ ከያቅጣጫው ተሰማ።

እውነትም በጣም ብዙ የጠሊት እግረኛ ጦር ከማድው ኮረብታ እየወረዯ ከስራችን ያሇውን ወንዝ
ሇመያዝ ዘቅዝቆ ይሽቀዲዯማሌ! ግንባር ቀዯሙ እንዱያውም እወንዙ ሇመዴረስ ተቃርቦዋሌ! ያን ሲያዩ
የሆሇታ መኮንኖችና ወታዯሮቻቸው ከራስ ሰዎችም በከፉሌ ከጠሊት ቀዴመው ወንዙን ሇመያዝ እነሱም
እሽቅዴዴም ገጠሙ።

ወዱያው የራስ ዴንኩዋን ከነበረበት አጠገብ አንዴ ወርካ ይሁን ወይም ወርካ የሚመስሌ ትሌቅ
ዛፌ ስሇ ነበረ የመዴፈ እርሳስና የቦምብ ፌንጣሪ እንዲይገባ፥ የዛፈ ስር በግንባርም በቀኝና በግራም ግንዴ
እየተጏራረዯና ከረጢት አፇር እየተሞሊ ሰፊ ብል ታጥሮ ራስ እዚያ ሆነው፥ ወዯ ግንባር ሇሚሄደት
እንዱሄደ ተራቸው እስኪዯርስ በዯጅግንነት ተቆጥበው ሇሚቆዩት እንዱቆዩ ትእዛዝ እየሰጡ ጦርነቱን
ይመሩ ጀመር።

ወንዙን ሇመያዝ በኛ በጦርና በጠሊት ጦር መሀከሌ የነበረው ተኩስ ዯረቅ ጫካ እንዯሚያቃጥሌ የቁዋያ
እሳት ሲነጋጋ ራቅ ብል ሇሚያየውና ሇሚሰማው ያስፇራ ነበር። በዚያ ፇታኝ ጦርነት አንዲንዴ ጊዜ የኛ
ጦር አይል ወንዙን እጁ ሲያዯርግ አንዲንዴ ጊዜ የጠሊት ጦር አይል የኛን ጦር እያስሇቀቀ ሲይዝ፥ ያ
ወንዝ ብዙ ጊዜ የሁሇቱ ተፊሊሚ ጦሮች እጅ ከተሇዋወጠበት በሁዋሊ በመጨረሻ በኛ ሰራዊት እጅ እንዯ
ሆነ ቀረና፥ የጠሊት ጦር ሸሽቶ ከማድው ኮረብታ ጥግ ቦታ እንዱይዝ ስሇ ተገዯዯ እዚያ ሆኖ ይዋጋ
ጀመር። ታዱያ ያ ሸሽቶ፥ ከኮረብታው ዯረት ሊይ የያዘው ቦታ ወንዙን የያዘው የኛ ሰራዊት የመሳሪያ
ሀይለን አስተባብሮ ሇሚያወርዴበት የጥይት መአት አጋሌጦ ይሰጠው ስሇ ነበረ፥ የሚተገንበት አጥቶ
የተጨነቀ መሆኑን ከመሀከለ ብዙዎች ቦታ ሇመሇወጥ ሊይና፥ ታች ቀኝና ግራ ሲሩዋሩዋጡ ከሩቅ
መታየታቸው ያመሇክት ነበር።

የጠሊት ጦር እንዱያ ባሇ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲዋጋ ከቆየ በሁዋሊ በቀኝም በግራውም በኩሌ
ተጨማሪ የጦር ሀይልች አምጥቶ ጦርነቱ ከሚዯረግበት ሊይና ታች ወንዙን እንዱይዙ ሇማዴረግ
ሞከረ። ምናሌባት የጦርነቱን ግንባር ሇማስፊትና ያን የሰፊውን የጦርነት ግንባር ተከትል የኛ ሰራዊት
ወዯ ቀኝም ወዯ ግራም ዘርዘር ሲሌ መሀለ መዴከሙ ስሇማይቀር ያን የዯከመውን ክፌሌ አጥቅቶ ወዯ
ነበረበት ቦታ ወዯ ወንዙ ሇመመሇስ የሚሌች መስልት ይሆናሌ። ወይም ወንዙን የያዘው ሰራዊታችን
እዚያ ከቆየው የጠሊት ጦር ጋር እንዯ ተያያዘ አዱስ የመጡት የጦር ሀይልች ከቀኝና ከግራ ወንዙን

136
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ተሻግረው ሰራዊታችንን ሇመክበብ የሚችለ መስልት ይሆናሌ። ነገር ግን፥ የጠሊት አሳብ ያም ይሁን
ይህ አዱስ የጦር ሀይልችን ማምጣቱ በጦርነቱ ግንባር ምንም ያክሌ ሇውጥ አሊስከተሇም። በዯጀንነት
ተቆጥበው ከቆዩት የራስ የጭፌራ አሇቆችና ከከንቲባ ጋሻው ጠና ሰዎችም ታዝዘው ሄዯው በግንባር
ሲዋጉ ከቆዩት ጋር በመተባበር ወንዙን ወዯ ሊይም ወዯ ታችም ታዝዘው ሄዯው በግንባር ሲዋጉ ከቆዩት
ከቆዩት ጋር በመተባበር ወንዙን ወዯ ሊይም ወዯ ታችም በርዝመት ስሇ ያዙት አዱስ የመጡት የጠሊት
የጦር ሀይልች ያን ወንዝ ሇመያዝ፥ ወይም በሊይና በታች ተሻግረው ሰራዊታችንን ሇመክበብ ባዯረጉት
ሙከራ፥ ከብርቱ ትንቅንቅና ተጋዴል በሁዋሊ እንዯ ፉተኞች ጉዋዯኞቻቸው ወዯ ኮረብታው ጥግ
እንዱያፇገፌግ ተገዯደ።

ጠሊት፥ በሞትና በመቁሰሌ ከጦርነቱ ውጭ በሆኑት ወታዯሮች ምትክ ወይም በጠቅሊሊው


የግንባር ጦሩን ሇማበርታት አዲዱስ ተጨማሪ ሀይሌ ባመጣ ቁጥር እንዯ ማየሌ ብል እስከ ወንዙ
መዴረስ ይችሌና እዚያ ሊይ ብርቱ ትንንቅ ብርቱ ተጋዴል ከሆነ በሁዋሊ የኛ ወገን የዯረሰ ጉዲት
ዯርሶበት ጠሊቱን አሽሽቶ ወንዙን እንዯ ያዘ ይቀራሌ። እርግጥ የጠሊት ወገን ብቻ ሳይሆን የኛ አዛዦችም
በርከት ያለ ወታዯሮች በሞትና በመቁሰሌ ከጦርነቱ ውጭ በመሆናቸው ወይም ጠሊት ከማየለ፤ ብዙ
ጊዜ ዴጋፌ እየጠየቁ ራስ ሌከውሊቸዋሌ። ነገር ግን ጠሊት ከኮረብታው ጥግ የያዘው ቦታ ከኛ ወገን
ሇሚተኮስበት ጥይት አጋሌጦ የሚሰጠው ሲሆን የኛ ሰራዊት የሚዋጋው የወንዙን ግንጅና ጫካውን
ተተግኖ ስሇ ነበረ፥ ከኛ ወገን ይሌቅ በጠሊት ወገን የዯርሰው ጉዲት ይበሌጥ እንዯ ነበረ ገማቾች ሁለ
ይስማማለ። ጠሊት እንዯ ማየሌ ብል ወዯ ወንዙ በሚቀርብበት ጊዜ የሚተኩሰው የመትረየስና
የጠመንጃ ጥይት ከወንዙ ውስጥ በመሸገው ሰራዊታችን ሊይ ከሚያዯርሰው ይሌቅ የሰፇርንበት ቦታ
ኮረብታነት ስሇ ነበረውና ጠሊት ከያዘው ከፌተኛ ቦታ ኮረብታነት ስሇ ነበረውና የመትረየስና የጠመንጃ
ጥይት ወንዙን እያሇፇ የኮረብታውን ዯረት ወይም ስር መምታት ይቀናው ስሇ ነበረ እዚያ በነበረው
ሰዋችን ሊይ ያዯረሰው የሞትና የመቁሰሌ ጉዲት በቀሊለ የሚገመት አሌነበረም። እሰፇር የነበረው ሰዋችን
ጠሊት ከወንዙ አጠገብ በሚተኩሰው የመትረየስና የጠመንጃ ጥይት ብቻ አሌነበረም የተጎዲው። ከዚያ
የባሰ ከማድው ኮረብታ ሊይ ጠሊት ያሇ ማቁዋረጥ የሚተኩሰው የከባዴ መሳሪያ እርሳስና አይሮፕሊኖች
ያወርደበት የነበረው የ«እሳተ ገሞራ ቦምብ» ነበር በጣም የጎዲው።

ጥዋት ጦርነቱ ከተጀመረ በሁዋሊ ትንሽ ቆይተው ስንት እንዯ ነበሩ ረስቻሇሁ - የጠሊት
አይሮፕሊኖች መጥተው እሰፇራችን ሊይ የእሳተ - ገሞራ ቦምብ (ናፓሌም) ይጥለ ጀመር። ያ የእሳተ -
ገሞራ ቦምብ መጀመሪያ የገዯሇውን ሳር ያቃጥሌና ከዚያ ቦምቡ በወዯቀበትና ሳሩ በተቃጠሇበት ዙሪያ
ያሇውን ዛፌ ከዚያ ዘሌል ባጠገቡ ያገኘውን ሁለ ሲያቃጥሌ እንዱያ ካንደ ወዯ ላሊው እየተዛመተ
ጫካውን በሙለ የቁዋያ እሳት ተነስቶ የሚያቃጥሇው ይመስሌ ነበር። ሠፇር የነበረው ሰው ሁለ
ከየመጠሇያው እየወጣ እሳቱን ባፇርና በቅጠሌ ሇማጥፊት ሲሩዋሩዋጥ ከመሀከለ በቦምብና በከባዴ
መሳሪያ የርሳስ ፌንጣሪ ወይም በቀሊሌ መሳሪያ ጥይት እየሞቱም እየቆሰለም የወዯቁ ብዙ ነበሩ።

137
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እሰፇር የነበረው ሰው፥ በሙለ ባይሆን በከፉሌ እሳቱን ሇማጥፊት ፊታ የሚያገኝ አይሮፕሊኖች -
ከጥዋት ጀምሮ ወዯ ከፊ ጉዞ እይጀመረውን ስዯተኛ ህዝብና ጉዋዙን ሇመዯብዯብ ይሁን ወይም ቦምብ
አሌቆባቸው ሇመተካት ይሁን አይታወቅም - ከሰፇራችን ሊይ ሊጭር ጊዜ ጠፌተው ቆይተው እስኪመሇሱ
ነበር። እኒያ አይሮፕሊኖች እንዱያ እየተመሊሇሱ በግንባር ሇሚዋጋው ሰራዊት በዯጀንነት እስፇር
የቆየውንና ወዯ ከፊ በመጉዋዝ ሊይ የነበረውን ሰዋችንን ከጥዋት ጀምሮ ከእኩሇ ቀን በሁዋሊ እስከ
ስምንት ወይም እስከ ዘጠኝ ሰአት ግዴም ዴረስ ሲዯበዴቡ ውሇው ከሄደ በሁዋሊ አሌተመሇሱም።

ከጥዋት ጀምሮ እስከ ስምንት ወይም እስከ ዘጠኝ ሰአት ግዴም ዴረስ ሰራዊታችን በግንባር
ከጠሊት ሰራዊት በዯጀን ከእሳት ጋር በሁሇት ግንባሮች ሲዋጋ ነበር የዋሇ። ከዚያ በሁዋሊ አይሮፕሊኖች
መምጣታቸውን ሲያቆሙ ጦርነቱ ከወንዙ አካባቢ በሚዯረገው ተወስኖ፥ ጠሊት ተጨማሪ ሀይሌ ባገኘ
ቁጥር ወንዙን ሇመያዝ በሚያዯርገው ጥረት ውጊያው ተፊፌሞ ሲቃጠሌ ጉዲት በዝቶበት ወዯ ተራው
ጥግ ባፇገፇገ ቁጥር ውጊያው በመጠኑ በረዴ ሲሌ እንዱሁ የኛ ሰራዊት ከወንዙ አንዴ እርምጃ ወዯ
ሁዋሊ ሳይፇገፌግ ቀኑ ተገባዯዯ።

እኔ ያነሇት ራስ ጦርነቱን ከሚመሩበት ከፌተኛ ቦታ አጠገብ ስሇ ነበርሁ፥ ያ ቦታ የጠሊት ጦር


ወንዙን ሇማስሇቀቅ የኛ ጦር ሊሇመሌቀቅ ያዯርጉት የነበረውን ተጋዴል ዯህና አዴርጌ ሇመመሌከት
አስችልኝ ነበር። ወዯ አስርና አስራ አንዴ ሰአት መሀከሌ ጠሊት ሇመጨረሻ ጊዜ በተጨማሪ ጦር
ሀይለን አጠናክሮ የኛን ሰራዊት ከወንዙ ሇማስወጣት በጦርነቱ ግንባር ከሊይ እስከ ታች፥ ብርቱ
የማጥቃት ውጊያ አዯረገ። ያን ጊዜ ከመዴፈና ካዲፌኔው (ከሞርታሩ) እርሳስ ላሊ፥ የመትረየሱና
የጠመንጃው ጥይት ወንዙን አሌፍ እኛ በነበርንበት አካባቢ፥ በጢስ ተረብሾ እንዯ ወጣ የንብ ሰራዊት
«ጢዝ - ጢዝ - ጢዝ» እያሇ አየሩን ሞሌቶ ሲዋነብ፥ መዴረሻ ይሳጣ ነበር! በዚያ መሀሌ ቀኛዝማች
በሌሁ ዯገፈ ትንሽ ጏንበት ወይም - ተገን ፌሇጋ - ወዯ ቀኝ ይሁን ወዯ ግራ ሰግዯዴ አይለ እንዱሁ
ቀጥ እንዲለ ጠመንጃቸውን አንግተው ከጦርነቱ ግንባር እየተጎማሇለ መጥተው ራስን እጅ ነሱና አፇር
የተሞሊውን ከረጢት ምሽግ ከውጭ በሁሇት እጃቸው ዯገፌ ብሇው ቆመው ይነጋገሩ ጀመር። እዚያ
ቆመው ከራስ ጋር በሚነጋገሩበት ጊዜ ሁለ ጥይት ዙሪያቸውን ይዋነብባቸዋሌ ነገር ግን እሳቸው
በፌፁም ርጋታ በፌፁም ፀጥታ ንግግራቸውን ሲቀጥለ ዝንቦች የሚዞሩባቸውን ያክሌ የተቸገሩ
አይመለም ነበር! አንዲንዴ ጊዜ በንግግራቸው መሀከሌ ሲስቁ ይታያለ። የተቀመጥሁበት ቦታ ትንሽ ራስ
ያሇ ስሇ ነበረ ምን እንዯሚነጋገሩ ሊውቅ አሌቻሌሁም፥ የማጥቃት ውጊያ የሚያዯረግበት ጊዜ ስሇ ነበረ፥
በዯጀንነት ተቆጥበው የቆዩ የጭፌራ አሇቆች ቢኖሩ ሇርዴታ ወዯ ግንባር እንዱሊኩ ሇመጠየቅ መጥተው
ስሇሱ ኖሮዋሌ የሚነጋገሩ። ብቻ አሌቀናቸውም። ከጋሻጃግሬዎችና ራስን ሇመጠበቅ ከተመዯቡት ጥቂት
ሰዎች በቀር ዯጀን ሆነው የቆዩት የጭፌራ አሇቆች ሁለ፤ በዬተራ እየታዘዙ ወዯ ግንባር ሄዯው እዚያ
በመዋጋት ሊይ ነበሩ።

138
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከዚያ ቀኛዝማች በሌሁ ራስን እንዯ ገና እጅ ነስተው ጥይቱ እሳቸውን እንዯ ፇራ ሁለ እመሀሌ
ትቶ፥ በቀኝና በግራቸው ያሇውን የዛፌ ቅርንጫፌ ሁለ ሲጨፇጭፌ በመጡበት አሆሁዋን ረጋ ብሇው
እየተጎማሇለ ወዯ ጦርነቱ ግንባር ተመሌሰው ሄደ። በተቀመጥሁበት የዛፌ ስር እንዲሇሁ ካይኔ
እስኪጠፊ ዝም ብየ ስመሇከታቸው ቆይቼ ያ ሁለ የጥይት በረድ በዙሪያቸው ሲወርዴ ትንሽ ስቅጠጥ
የማይለ በመሆናቸው ሌባቸው ከቀዝቃዛ ብረት ወይም ካሇት ዴንጋይ እንዯ ተሰራ ሁለ ትንሽ ንቅንቅ
የማሇት ምሌክት የማይታይባቸው በመሆናቸው ከሌቤ አዯነቅሁዋቸው አከበርሁዋቸው!

ምንም እንኩዋ ጠሊት በተጨማሪ ጦር ሀይለን አጠናክሮ ከባዴና ቀሊሌ መሳሪያውን አስተባብሮ
በጦርነቱ ግንባር ከሊይ እስከታች ሇመጨረሻ ጊዜ - ያዯረገውን የማጥቃት ውጊያ ተቁዋቁሞ ሇመመሇስ
ቀኛዝማች በሌሁ የጠየቅሁትን ዴጋፌ ሳያገኙ ቢመሇሱ፤ ሰራዊታችን ያሇ ተጨማሪ ሀይሌ ከያዘው ቦታ
አንዴ ስንዝር ሳይሇቅ፤ ጦርነቱ እንዱያ ተፊፌሞ እንዯ ተቃጠሇ ቀኑ መሸ። ጨሇማው ከበዴ እያሇ ሄድ
አይን መያዝ ሲጀምር፤ ጠሊት ወንዙን ሇመያዝ ባዯረገው የማጥቃት ውጊያ ብርቱ የሞትና የመቁሰሌ
ጉዲት ከዯረሰበት በሁዋሊ፥ ሙከራው ሳይሳካሇት በመቅረቱ ወዯ ኮረብታው ጥግ አፇግፌጎ ከዚያ
የሚተኩሰው የመትረየስና የጠመጃ ጥይት እሰፇራችን ሳይዯርስ፥ ወንዙንና የሰፇርንበትን የኮረብታ ስር
ብቻ በመምታት ተወሰነ። ስሇዚህ ከራስ መምሪያ አጠገብ የነበርን ሁለ አሌፍ አሌፍ ከሚተኮስብን
የከባዴ መሳሪያ አዯጋ በቀር ከላሊ ስጋት ነፃ ሆነ። የከባዴ መሳሪያው እርሳስም ቢሆን፤ ብዙ ጊዜ እኛን
አሌፍ እየወዯቀ ሲፇነዲ ነበር የምንሰማው።

ቢበዛ፥ ከምሽቱ ወዯ አንዴ ሰአት ሊይ ቀኛዝማች በሌሁና ጥቂት ታሊሊቅ መኩዋንንት ከጦርነቱ
ግንባር ከወንዙ ወዯ ራስ መምሪያ መጡ። ወሩ ታህሳስ ስሇ ነበረ፥ ቀዯም ብል ጨሌሞ ነበር።
መኩዋንንቱ ሊጭር ጊዜ ከራስ ጋር ሲነጋገሩ ቆይተው ሲመሇሱ ፉታውራሪ ዲምተው ተስማ ሇንግግሩ
ስሇ ነበሩ፤ ምስጢር እንዲሌሆነ ምን ተነጋግረው እንዯ ወሰኑ ጠየቅሁዋቸው።

«ካንተ የሚሸሸግ አይዯሇም እንጂ ምስጢርነቱስ ምስጢርን ነው። ራስ አሁን ተነስተው ወዯ ከፊ


ጉዞዋቸውን እንዱቀጥለና ከኛ ወገን ተኩስ ሲቆም ጠሊት ግንባሩን ሇቅቀን መሄዲችንን አውቆ ወዱያውኑ
እንዲይከተሇን ፥ ቀኛዝማች በሌሁ የሆሇታን ሰዎች ይዘው ከራስ ሰዎችም አንዲንዴ የጭፌራ አሇቆች
ተጨምረው እስከ አምስት ሰአት ግዴም ዴረስ እዚሁ ወንዙን እንዯ ያዙ ሲተኩሱ ቆይተው ከዚያ
በሁዋሊ መንገደ ነፃ ስሇሚሆንና እነሱም ዯረቅ ጦር ስሇ ሆኑ በሩጫ እንዱከተለ ነው የተወሰነ» አለኝ።
ራስ ወዱያው ተነሱ፥ እኔ ግን በትረ ፅዴቅን ተሽልት ስሇ ነበረ እሱ ሰዎቻችንን ይዞ ጉዞውን እንዱቀጥሌ
ከተስማማን በሁዋሊ በቅልየን ብቻ አስቀርቼ የግንባሩን ሁኔታ እስከ መጨረሻ ሇማወቅ እዚያ እንዱቆዩ
ከተመዯቡት ከነቀኛዝማች በሌሁ ጋር መቆየት ፇሇግሁና እዚያው ቆየሁ።

ያ፥ ከንጋት እስከ ምሽት ዴረስ ቀኑን ሙለ እንዯ ተቃጠሇ የዋሇው የጌራ ጦርነት በጣም ብርቱ
ስሇ ነበር። በዚያ ጦርነት በጠቅሊሊው ስንት ሰው እንዲሇቀብን ሇኔ አሊውቅም፥ በመጨረሻ የጦርነቱን

139
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ግንባር እንዯ ያዘ የቀረው ጠሊት ያውቅ እንዯ ሆነ እንጂ ከኛ ወገን የሚያውቅ ሰው ያሇም
አይመስሇኝም። በባህሊችን በጦርነት ሜዲ ሲዋጉ የወዯቁትን ጀግኖች ቁጥር ሇቅሞ ማወቅ የተሇመዴ
አሌነበረም። የያንዲንደን ሰው ሞት የሚያውቅ የጦርነት ጉዋዯኞቹ ከዚያ ከፌ ሲሌ የቅርብ አሇቃው፥
ከዚያ በሁዋሊ ቤተሰቡ ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ ዴሌ ካዯረገችባቸውም ሆነ ዴሌ ከሆነችባቸው ብዙ
ጦርነቶች ባንዲቸው እንኩዋ የሞቱትን የቆሰለት ጀግኖችዋ ቁጥር በታሪክ ተመሌክቶ አይታይም።

በጌራ ጦርነት ምንም እንኩዋ የኛ ሰራዊት የወንዙን ግንጅና ወንዙ የሇበሰውን ጫካ ተገን
(ምሽግ) አዴርጎ ሲዋጋ የዋሇ በመሆኑ የዯረሰበት ጉዲት በጠሊት ከዯረሰው ጋር ሲመዛዘን ዝቅተኛ
እንዯሚሆን ቢገመት ባጠቃሊይ ያ ጦርነት በሰውና በጥይት ዯካማ የነበረ አቅማችንን ይብስ
እንዲዯከመው የማይጠርጠር መሆኑን ያነጋገርሁዋቸው መኩዋንንት ሁለ ተስማምተው ያረጋግጡ
ነበር። ከጌራ ጦርነት በሁዋሊ ሰራዊታችን የሰውና የጥይት፥ ከሰውም የባሰ የጥይት ዴሀ ሆነ። በወታዯሩ
ወገብ የሚታየው ዝናር ሁለ ከቁጥር የማይገቡ በጣም ጥቂት ጥይቶች ያለበት ወይም ምንም የላሇበት
ነበር!

ምእራፍ አስራ ዘጠኝ

ጎጀብ
ራስ ጦርነቱን ሲመሩ የዋለበትን ቦታ ሇቀው ወዯ ከፊ ጉዞዋቸውን ከቀጠለ በሁዋሊ ቀኛዝማች
በሌሁና የሆሇታ መኮንኖች ጠሊት ወንዙን እንዲይሻገር ሲጠብቅ እንዱቆይ ተመዴቦ የቀረውን ሰራዊት
በግንባሩ ከሊይ እስከ ታች ዘርዘር ብል ተሰሌፍ ተኩሱን እንዱቀጥሌ ስሊዯረጉ ተኩሱ ቀጠሇ። ብቻ ያ
ተኩስ ሁሇቱም ወገኖች - የኛም የጠሊትም - ከማድ የሚንቀሳቀስ ነገር ያዩ በመሰሊቸው ቁጥር ሇጥንቃቄ
ያክሌ፤ እንዱሁም በየቦታቸው መኖራቸውን ሇማስታወቅ ያክሌ ካሌሆነ መቸም በዚያ ጨሇማ «ጠሊትን
አነጣጥሮ ሇመምታት ይቻሊሌ» ተብል የሚተኮስ አሌነበር።

ከጠሊት ወገን ያሇማቁዋረጥ ከሚነጉዯው የከባዴ መሳሪያ ተኩስ በቀር ወንዙን ተከትል ከሊይ
እስከ ታች የሚተኮሰው የጠመንጃና የመትረየስ ተኩስ እንዯ ቀኑ ፊታ የማይሰጥ ሳይሆን፥ በረዴ ሲሌም
ሲፊፊምም ነበር። አንዲንዴ ጊዜ ፀጥ ብል ቆይቶ ያንደ ወገን ከማድ የሚንቀሳቀስ ነገር ያየ መልት
ተኩስ ሲከፌት የላሊው ወገን አጠፊውን ይመሌስና በግንባሩ ሊይ እስከ ታች የተፊፊመ ተኩስ ሲተኮስ
ይቆያሌ። ታዱያ፥ ያ ከፀጥታው በሁዋሊ ጠሊት የሚተኩሰው ተኩስ በቦታው መኖሩን ሇማስታወቅ እንጂ
ከዚያ አሌፍ የሚያስከትሇው ጉዲት እንዯላሇ ታውቆ ተሇመዯና እዚያ የነበሩት ሰዎቻችን የሞት ወይም
የመቁሰሌ ጉዲት እንዯማይዯርስባቸው መስጋቱን ረስተው በዚያ ፇንታ ፅኑ ርሀብ ተሰምቶዋቸው ሁለም
ሲነጋገሩ የሚሰሙት የሚባሊ ነገር ስሇሚገኝበት ዘዳ ሆነ።

140
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወታዯሮቹ የሚባሊ ነገር አጥብቀው መፇሇጋቸውን ቀኛዝማች በሌሁ እንዲወቁ ሰፇሩን ሇቅቆ ወዯ
ከፊ የሄዯው ሰራዊታችን ጥልት የሄዯ ስንቅ ቢገኝ በየሰፇሩ ዞረው የሚፇሌጉ ሰዎች ሊኩ። ነገር ግን
የተገኘው አንዴ ስሌቻ ማር ብቻ ነበር። ስሇዚህ አንዴ ሰው ከስሌቻው ውስጥ በሁሇት እፌኙ እየዛቀ
እዚያ ከቀኛዝማች አጠገብ ሇነበርን ሁለ ሰጥቶን በሊንና ሇግዚኤው ረሀባችነን አስታገሰሌን። ቆይቶ ግን
ግንባሩን ሇቅቀን በመንገዴ ሊይ እንዲሇን እኔ ብርቱ፥ ውሀ ጥም ስሇሇቀብኝ «ምነው ያን ማር ባሌበሊሁት
በቀረብኝ ኖሮ!» አሌሁ።

በጦርነቱ ግንባር እንዱያ ተኩስና ፀጥታ ሲፇራረቅ እስከ አምስት ሰአት ግዴም ቆይተን ሇቅቀን
በሰራዊታችን ሇመዴረስ የመነሻው ጊዜ ሲዯርስ ቀኛዝማች በሌሁ ግንባሩን ሲጠብቁ ሊመሹት የቡዴን
አሇቆች ሁለ ሰዎቻቸውን ይዘው እንዱነሱ በየተሰሇፈበት ቦታ መሊክተኞች ሊኩ። ከዚያ በቅልዎች
ከተኩሱ ራቅ ባሇ ሰዋራ ቦታ ተይዘው ሲጠብቁ ከቆዩበት እንዯ መጡሌን ባሇ በቅል በበቅልው እግረኛ
በግሩ ሰራዊታችን የሄዯንበትን የከፊን መንገዴ ይዘን ገሰገስን። ግን ቢበዛ ከአንዴ ሰአት ተኩሌ እስከ
ሁሇት ሰአት ተኩሌ ያክሌ ቢሆን ነው። ከዚያ በሁዋሊ ቀዴሞን በሄዯው ሰራዊታችን አንዴ ሰፉ ረግረግ
ሊይ ታግድ ቆይቶ የመጨረሻው ክፌሌ የታገዯበትን ቦታ ገና ሳይሇቅ ዯረስንበት። እዚያ ከነበረው ብዙ
ህዝብ ከረግረጉ ወዱያ ማድ ተራግፇው የቆዩ አጋሰሶቻቸውን የሚጭኑም ከረግረጉ ቀኝና ግራ አሌፍ
አሌፍ ባንዲንዴ ሊይ ተሰብስበው የሚንጫጩም ነበሩ። እንዯ ዯረስን ያን ብዙ ህዝብ ስናይ ጠሊት ቀዴሞ
መንገዴ ዘግቶበት የታገዯ መስልን ነበር። ነገር ግን፥ ጠሊት ያስታጠቃቸው ምንዯኞች ምቹ እዬያዙ
ማስቸገራቸው ባይቀርም፥ ሰራዊቱን እዚያ ቦታ ሊይ አግድ ያን ያክሌ ጊዜ ያቆዬው ብርቱ የጠሊት ጦር
ገጥሞት ሳይሆን በረግረጉ ምክንያት መሆኑን እዚያ የነበሩት ሰዎች ነገሩን።

የዚያን ሰፉ ረግረግ መሻገሪያ መሌካዎች ሇማግኘት ዲርዲሩን ወዯ ሊይ ወዯ ታች መሄዴ


ያስፇሌግ ነበር። ነገር ግን እዚያ የነበሩት ሰዎች እንዯ ነገሩን መሪዎች ካሇመኖራቸውም ላሊ ላሉት
በመሆኑ የተጫኑ ከብቶች ያለዋቸውም የላለዋቸውም እዬቸኮለ ቀጥታ መንገደን ይዘው እንዯ መጡ
ረግረጉ ውስጥ ይገባለ። እዚያ ከብቶች ከነጭነታቸው ሲወዴቁ እነሱን ተረዲዴቶ ሇማንሳትና
ጭነታቸውን አራግፍ በሸክም እያሻገሩ እንዯ ገና ሇመጫን እጅግ አስቸጋሪና ብዙ ጊዜ የሚፇጅ ስሇ ነበረ
ያን ችግር አሌፍ እንዯ ሌብ ሇመሄዴ አሌተቻሇም። ዯግሞ እኒያ ሰዎች እንዯ ተረኩሌን ችግሩን እጥፌ
ዴርብ አዴርጎ የዘጋው ያን ሁኔታ ሲያዩ ዲርዲሩን ወዯ ሊይም ወዯ ታችም ሄዯው መሌካዎችን እያገኙ
በዯህና የተሻገሩ ቢኖሩም፤ ብዙዎች ባሇ አጋሰሶችም በበቅል የተቀመጡና እግረኞችም ቀዴመዋቸው
ረግረጉ ውስጥ የገቡት መውጫ አጥተው ሲጨነቁ እያዩ እንዯ ዯረሱ ቀጥታ፥ እዚያ ረግረግ ውስጥ
እዬገቡ በሊይ በሊዩ መጨመራቸው ነው።

ያን የሚያሳዝን ታሪክ ሰዎች ሲተርኩን «ዴሌ ሆኖ የሚሸሽ ሰራዊት እንዯ በግ መንጋ በፉቱ
የሚሄዯውን እያየ መከተሌ እንጂ የሚሄዴበትት ገዯሌ ይሁን ሜዲ አይታየውም!» ሲባሌ የሰማሁት ትዝ

141
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሇኝ። ታዱያ ላሉት መሆኑ በጀ እንጂ ቀን ቢሆን ኖሮ እዚያ ረግረግ ውስጥና ዙሪያውን የነበርው እጅግ
ብዙ ህዝባችን እንዱያ እንዲሇ የጠሊት አይሮፕሊኖች ቢዯርሱበት ያገኘው የነበረው ጉዲት ምን ያክሌ
ይሆን እንዯ ነበረ እግዚአብሔር ይወቅ።

አጋሰሶቻቸውን ጭነው ያበቁትና ላልችም ጉዞዋቸውን ሲቀጥለ ጭነው ያሊበቁትና ላሉቱን


ዯጀን አዴርገው (ጠሊት በላሉት እንዯማይከተሊቸው አምነው) እዚያ ረግረግ ዲር ቆመው ተቀምጠውም
በርጋታ እያወሩ ብዙ ነበሩ። እኛ እነሱን እዚያ ትተን ከሚሄደት ጋር ተጨምረን ስንጉዋዝ አንዴ ቦታ
ሊይ አንዴ ሰው ከመንገደ ዲር እንዯ ተጋዯመ ፃእር የሚያስጨንቀው ዴምፁን ከፌ አዴርጎ ሲናገር ከሩቅ
ይሰማ ነበር። ሶት ወይም አራት የሚሆኑ ሰዎች በዙሪያው ቆመዋሌ። ታዱያ እንዱያው ያሇው ነገር
የተሇመዯ ሆነና፥ ከዚያ መንገደን ሞሌቶ ከሚሄዯው ህዝብ መሀከሌ ቀረብ ብል አይቶት ከንፇሩን
እዬመጠጠ ከሚሄዯው ህዝብ መሀከሌ ቀረብ ብል አይይቶት ከፌነሩን እዬመጠጠ የሚሄዴም ዘወር
ብል ሳያየው እንኩዋ የሚሄዴም ነበረ። እኔም እንዯ ዯረስሁ ቀረብ ብዬ ሳየው ባሊውቀውም የሇበሰው
ሌብስ የሆሇታ መኮንኖች መሇዮ ያሇበት ስሇ ነበረ፥ ከሆሇታ መኮንኖች አንደ መሆኑን ተረዲሁ። እጦርነቱ
ግንባር ቆስል እስከዚያ ዴረስ ሰዎች በሸክም ወስዯውት ይሁን ወይስ የት እንዯ ቆሰሇ ጠይቄ መሌስ
አሊገኘሁም። «ጎበዝ እባካችሁ ከነነፌሴ በጠሊት እጅ አንዲሌወዴቅ እናንተም እንዲሊስቸግር ገዴሊችሁኝ
ሂደ እባካችሁ! አንዴ ትይት ይበቃኛሌ አንዴ ጥይት አትንጉኝ!» ሲሌ ያስሇቅስ ነበር። «እባካችሁ
ተሸክመን እስከ ሰፇር ሌናዯርሰው አንችሌም?» አሌሁዋቸው በዙሪያው የነበሩትን ሰዎች።

«ቃሬዛ ቢኖር ነበራ! ቅስለ ሊንዴ ሰው ሸክም በማይመች ቦታ ስሇሆነ ያሇ ቃሬዛ አይቻሌም»
አሇኝ አንደ። የሆሇታ መኮንኖች ወይም ቀኛዝማች በሌሁ ምናሌባት ወዯ ሁዋሊ ሆነው ወይም ሳያዩት
በላሊ መንገዴ አሌፇው እንዯ ሆነ አሊውቅም እንጂ፤ ቢያዩት ኖሮ፥ እንዴያ ሲማጠን አሌፇውት
እንዯማይሄደ ርግጠኛ ነበርሁ። እዚያ ቆሜ ስመሇከተው ቆይቼ ብቻየን ምንም ሊዯርግሇት እንዯማሌችሌ
ስሇ ተረዲሁ እኔ አቁስዬ ጥዬው የሄዴሁ ይመስሌ የወንጀሇኛነት ስሜት ተስምቶኝ አፋን እዬመረረኝ
ጉዞዬን ቀጠሌሁ። ትንሽ ያፅናናኝ ሆሇቶች የጦርነቱ ግንባር ሲጠብቅ ሊመሸው የሰራዊታችን ክፌሌ ዯጀን
ሆነው ሁዋሊ የሚከተለ ሰምቼ ስሇ ነበረ «እነሱ ይዯርሱሇት ይሆናሌ» የማሇቱ ተስፊ ነበር። እውነትም
የሆሇታ ጉዋዯኞቹ ሁዋሊ ዯርሰው እንዱገዯሌ ማዴረጋቸውን ሲወራ ሰማሁ። መገዯለ እውነት ቢሆንም
ማን እንዯ ገዯሇው ወይም ከተወሩት ሁሇት ወሬዎች የትኛው እውነት እንዯ ሆነ ሊረጋግጥ
አሌቻሌሁም።

አንዯኛው ወሬ «ሆሇቶች ከመሀከሊቸው አንዴ ቁስሇኛ ሇመዲን ተስፊ ያሇው ከሆነ ምንም ብርቱ
ችግር ቢገጥማቸው ትተውት እንዲይሄደ ሇመዲን ተስፊ የላሇው ከሆነ ግን ገዴሇውት እንዱሄደ ቃሌ
ኪዲን ስሇ ነበራቸው ያ መኮንን የማይተርፌ መሆኑ ከተረጋገጠ በሁዋሊ አንዴ መኮንን እንዱገዴሇው
ተዯረገ» የሚሌ ነበር።

142
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሁሇተኛው ወሬ «ቁስሇኛው እንዯማይተርፌ ከተረጋገጠ በሁዋሊ የጎረሰ መሳሪያ ተሰጥቶት ራሱን
አንዱገዴሌ ተዯረገ» የሚሌ ነበር። ያ እንዯማይተፌ ሆኖ በመቁሰለ የሞት ፌርዴ ተፇርድበት የተዯሇ
መኮንን «ሻምበሌ ሇማ አያባሬ» ይባሌ ነበር።

የጌራ ጦርነት የተዯረገበትን ቦታ የተጉዋዝንበት ክፌሌ አሌፍ አሌፍ ጫካ ቢኖርበትም


በጠቅሊሊው ከመንገደ ቀኝና ግራ የሚታዬው አዝመራ ነበር። ያን ያሇፇን ዘንባባዎችና ላልች ሌዩ ሌዩ
ዛፍች በርከት ብሇው የሚታዩበት ካካባቢው ትንሽ ከፌ ያሇ ቦታ ስንዯርስ እዚያ ሊይ ሰፇር ተዯርጎ ቆየን።
እኔ ረሀብና ዴካም ተዯራርበው አዝሇውኝ ስሇ ነበረ ሰዎቼ የሰፇሩበትን ቦታ መፇሇጉ ያመት መንገዴ
መስል ታይቶኝ እንዯማሊገኘው አስቀዴሜ ተስፊ ቆርጨ ቅርብ ሆኖ ወዯ ታዬኝ ዛፌ ሄጄ በቅልየን ከዛፈ
ጋር በሇኮው አሰርሁና የኮርቻውን ምቹ አንጥፋ ኮቴም ሱሪየም ቁምጣዎች ስሇ ነበሩ ግሊሱን ሇብሼ
ጠመንጃየን ተንተርሼ እዚያ ዛፌ ስር ገዯም አሌሁ። ወዱያው ከባዴ እንቅሌፌ ወስድኝ ዝናሙ ዘንሞ
እስኪያባራ አሌነቃሁም ነበር። ስነቃ የሇበስሁትን ግሊስና ያነጠፌሁትን ምቹ ዝናም አበስብሶዋቸው ብርቱ
ብርዴ እንዯ ወባ ሲያንቀጠቅጠኝ አገኘሁ። በቅልየም ሌጉዋሙን በታሰረበት ዛፌ ፇግፌጎ አውሌቆ ከፉቴ
ጥልሌኝ ሇኮውን ቆርጦ ሄድዋሌ። ከዚያ ተነስቼ ጠመንጃየንና የበቅልውን ሌጉዋም እንዱሁም ዝናም
ያበሰበሳቸውን ምቹና ግሊስ ይዤ የምሄዴበትን ሳሊውቅ አእምሮየ ሳይሆን እግሬ በመራኝ
እየተንቀጠቀጥሁ ትንሽ እንዯ ሄዴሁ የሌጅ ቢተውን (ያባቱን ስም ረስቻሇሁ) ዴንኩዋን አዬሁ። ሌጅ
ቢተው የክቡር ራስ እምሩ ሌዩ ፀሏፉ ነበር። ባሌተቤቱ ወይዘሮ ዋጋየ (የሳቸውንም ያባት ስም
ረስቻሇሁ) በሽሬ ዘመቻ መኖራቸውን አሊስታውስም እንጂ ከጎሬ ጀምሮ በምእራብ በተዯረገው ትግሌ
ሁለ ከባሊቸው ሳይሇዩ ተካፊይ የሆኑ ብርቱ ወይዘሮ ነበሩ።

«ሌጅ ቢተው ሌጅ ቢተው» ብዬ ተጣራሁ ወዯ ዴንኩዋኑ በር ቀረብ ብዬ።

«ማነው!» አሇ ሌጅ ቢተው ከውስጥ።

ማን መሆኔን ከተናገርሁ በሁዋሊ ወይዘሮ ዋጋየ ቶል የፊና መብራት አብርተው አስገቡኝ።


ጠመንጃየን ባንዴ ትከሻየ ዝናም ያበሰበሳቸው የበቅል እቃዎቼን በላሊው ትከሻየ ተሸክሜ
እዬተንቀጠቀጥሁ ስገባ ባሌና ምሽት አይተው መጀመሪያ ሁሇቱም ዯንግጠው የሚያዯርጉትን አጡ ከዚያ
ዋጋየ ከዴንጋጤያቸው ወጥተው የተሸከምሁትን ሁለ ካሊየ ወስዯው ወዱያ አስቀመጡና «ወባ አሇብህ?»
አለኝ።

«የሇብኝም፤ ብርዴ ነው» አሌሁዋቸው። ወዱያው ከየት አምጥተው ምን ጊዜ አንዲነጠፈት


ሳሊይ፤

«በሌ እዚያ ተኛ» አለኝ፣ ከነሱ ምኝታ ትንሽ ራቅ ብል የተነጠፇ ምንጣፌ አመሌክተው። ግማሽ
ራቁቴን ባሳዩኝ ምንጣፌ ሊይ ስጋዯም ቶል ጫማየን አውሌቀው በወፌራም ጋቢ ከራሴ እስከ እግሬ

143
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከጠቀሇለኝ በሁዋሊ በሱ ሊይ ከነሱ ብርዴ ሌብስ አንደን ዯግሞ በዚያ ሊይ ምን እንዯሆነ አሊውቅም ላሊ
ነገር ዯራርበው እስኪከብዯኝ አሸከሙኝ። ትንሽ ቆይቼ ሰውነቴ ፀጥ እያሇ ሄዯና እንቅሌፌ ወሰዯኝ። ብቻ
ምንም ያክሌ ተንቀሌፌቼ ሳይቆይ፤ ከውጭ ሰዎች ሲንጫጩ ነቅቼ፥ የተከናነቡትን ሌብስ ገሇጥ ባዯርግ
ነግቶ የዴንኩዋን ውስጥ ሁለ ብርሃን ሆኖዋሌ። ወዱያው የበቅልየ መጥፊት ትዝ ስሊሇኝ ቶል ተነስቺኤ
ጫማየን ሳጠሌቅ ባሌና ምሽት ነቅተው፥

«አሁን ተነስተህ ወዳት ሌትሄዴ ነው? ብርደ ገና አሌሇቀቀምኮ» አሇኝ ሌጅ ቢተው።

«ጉዞ ሳይጀመር በቅልየን ሌፇሌገው ጉዞ ከተጀመረ በሁዋሊ አሊገኘውም» ብዬ ተነሳሁ።

«እንግዱያውስ ጋቢውን እንዯሇበስህ ሂዴ» አለኝ እመይቴ።

ቁምጣ ኮቴንና ቁምጣ ሱሪየን ከውስጥ የገሊየ ከሊይ ተዯራርቦ የተጫነኝ የሌብስ ሙቀት
አዴርቀውኛሌ። ምቹውና ግሊሱ ግን፥ እንዯ ረጠቡ ነበሩ። ጋቢየን ተከናንቤ ጠመንጃየንና ርጥቡ የበቅል
እቃየን ተሸክሜ በጎ አዴራጊዎቼን ከሌብ አመስግኘ በቅልየን ሌፇሌግ ወጣሁ።

እዴሌ ሁሇት መሌክ የሇውም። ወይ ቀና ወይ ጠማማ ነው። ታዱያ ያነሇት ከንጋት አቅራቢያ
ጀምሮ ቀና እዴሌ ገጠመኝና ከዚያ እንዯ ወባ በሽታ ከሚያንቀጠቅጥ ብርቱ ብርዴ በነሌጅ ቢተው
የማይረሳ ርዲታ ተገሊግዬ ከነሱ ዴንኩዋን እንዯ ወጣሁ ብዙ ሳሌሄዴ፥ በርከት ያለ ከብቶች (በቅልዎች
አህዮችም) ባንዴነት ሲግጡ በሩቁ አዬሁ። ቀረብ እያሌሁ ስሄዴ ከመሀከሊቸው አንደ በቅል ባድ ኮርቻ
የተጫነ መሆኑን ሳይ «የኔ በቅል ሳይሆን አይቀርም» ብዬ ገመትሁ። እውነትም የኔ በቅል ነበር።
ከጠባቂዎቹ አንደ የማውቀው የፉታውራሪ ዲምተው ተሰማ አሽከር ስሇ ነበረ የተሸከምሁትን ኮተት
ሲያይ እንዯ መዯንገጥ ብል እዬሮጠ መጥቶ ሸክሜን ተቀበሇኝና፤

«ምን ጉዴ ነው? እነዘሪሁን ምን ሆኑ? በቅልውስ ይህን ሁለ እቃ ሊንተ ጥል ኮረቻ ብቻ


ተጭኖ እንዳት ወዱህ መጣ?» አሇኝ።

እኔም ከነዘሪሁን የተሇየሁበትን ምክንያትና ከዚያ በሁዋሊ የሆነውን ባጭሩ ነገርሁትና ምናሌባት
እነ ዘሪሁን የሰፇሩበትን ያውቅ እንዯሆነ ብጠይቀው የማያውቅ መሆኑን ነገረኝ።

ከዚያ ያ ሌጅ በቅልየን ሇጉሞ ርጥብ ምቹና ግሊሱንም ብዬቦታቸው አዴርጎ ሲሰጠኝ ርቦኝ ስሇ
ነበረ ወዯ ሌጅ ቢተው ዴንኩዋን ተመሌሼ ቁስ በማዴረግና ስዎቼ የሰፇሩበትን በመንፇሇግ መሀከሌ
መቁረጡ አስቸግሮኝ ሳመንታ ቆየሁ። ሁዋሊ ጉዋዝ ከመነሳቱ በፉት ሰዎቼን ፇሌጌ ካሊገኘሁ ሇያነሇት
ጭራሹን ሊገኛቸው የማሌችሌ መስል ስሇታዬኝ እነሱን መፇሇጉን መረጥሁና መንገዳን ስጀምር፤

144
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እነ ዘሪሁንን ያገኘሀቸው እንዯ ሆነ በከፊ መንገዴ ከሰፇሩ መውጫ ሊይ ተቀምጨ
የምጠብቃቸው መሆኑን ንገርሌኝ። አሁን ሰፇር - ሇሰፇር ዞሬ እንዲሌፇሌጋቸው ስሊገኛቸው ሰራዊቱ ጉዞ
የጀመረ እንዯሆነ እንዲያመሌጡኝ ነው» ብዬ ሇሌጁ ነግሬ እንዯ ምንም ተጎትቼ በበቅልየ ሊይ ተቀምጬ
የከፊን መንገዴ ይዤ እስከ ሰፇሩ ወሰን ሄዴሁ። አንዴ ትንሽ ወንዝ ተሻግሬ በመንገዴ የሚያሌፇውን
ማየት የምችሌበት ከፌተኛ ቦታ አገኘሁና እዚያ ተቀምጨ ስጠብቅ ሰፇርተኛው መጉዋዝ ከጀመረ በሁዋሊ
ብዙ ቆተው ሰዎቼን ሲመጡ አዬሁዋቸው። አቶ በትረ ፅዴቅ ገና ከሩቅ ሲአይየኝ እዬሮጠ መጥቶ ስሞኝ
ሰፇር ሳሌዯርስ ያዯርሁበትን ምክንያትና ወዳት እንዲዯርሁ ሉጠይቀኝ ሲጀምር የዘሪሁን ፈከራ
አቁዋረጠው።

ዘሪሁን ሁሇት ጠምጃዎች የራሱን አንግቶ ላሊውን በጁ ይዞ አንዴ ጉሌበቱን እንበርክኮ ሲፇክር
ሲፇክር ቆዬና፥

«እኔ ያንተ ወንዴም እኔ ያንተ አሽከር እንዱህ ነኝ!» ብል በጁ የያዘውን ጠመንጃ ከፉቴ
አስቀመጠው። ማታውን እጉዞ ሊይ ጠሊት ያስታጠቃቸው ምንዯኞች በሚጉዋዘው ሰራዊታችን ሊይ አዯጋ
ጥሇው ሲታኮሱ፥ ከነሱ የማረከው ጠመንጃ ነበር።

«ጠመንጃውን መርቄሌሀሇሁ። በሌ እንግዱህ የምበሊው ነገር ስጠኝ» አቶ በትረ ፅዴቅ ያነሇት፥


እንኩዋንስ ሉስቅብኝ በመራቤና በመንገሊታቴ በጣም ነበር ያዘነ። ሁዋሊ ግን የኢትዮጵያ ነፃነት ከተመሇሰ
በሁዋሊ እንኩዋ በኔ ሇማሳቅ ሲፇሌግ ከሚያነሳቸው ማሳቂያዎች አንደ የዚያነሇት ሁኔታየ ነበር።

«ሀዱስ» ይሊሌ በትረ ፅዴቅ ሉያስቅብኝ ሲፇሌግ። «ሀዱስ፥ ሁሇት ቀን ጦሙን እዬዋሇ አዴሮ፥
በሶስተኛው ቀን ከእህሌ በቀር ላሊ ነገር አሌታየው ባሇበት አሽከሩ የሚያስገርም የጀብዴ ስራ ሰርቶ በወጉ
አሽከሮች በጌቶቻቸው ፉት እዴነሚያዯርጉት የማረከውንጠመጃ ከፉቱ ጥል ሲፇክር ‹እባክህ ይህን
ፌከራህን ሇላሊ ጊዜ አቆይና ይሌቅስ አሁን የምበሊው ነገር ስጠኝ!› አሇው» ብል እየሳቀ ያስቅብኝ ነበር።
ታዱያ እውነቱ፥ በትረ ፅዴቅ ሉያስቅብኝ ፇሌጎ ይሇው የነበረው አዯሇም። ዘሪሁንን የምበሊው እንዱሰጠኝ
የጠየቅሁት እንዯ ወጉ ፌከራውን አስጨርሼ እንዯ ወጉ የጣሇውን ምርኮ (ጠመንጃውን) ተቀብዬ
ከመረቅሁሇት በሁዋሊ ነበር። የሆነ ሆኖ ዘሪሁን ቶል ከወንዝ ውሀ አምጥቶ፥ በሶ አሰናዴቶሌኝ ከበሊሁ
በሁዋሊ ከዚያው ከበሶው በጥብጦ በትሌቅ ዋንጫ ስጠኝና ያን ጠጥቼ እኔ እስካርፌ እዚያው ቆይተው
ጉዞዋችነን ቀጠሌን።

ያንጊዜ ጅማና ከፊ የተሊያዩ ጠቅሊይ ግዛቶች ስሇ ነበሩ ያነሇት ሰፇር የተዯረገበት ቦታ የሁሇቱ
ግዛቶች ወሰን ከነበረው ከጎጀብ ወንዝ አጠገብ ነበር። የከፊው ገዥ ክቡር ራስ ጌታቸው አባተ ከጃንሆይ
ጋር ወዯ ሰሜን ግንባር ሇዘመቻ ታዝዘው ሲሄደ ክቡር ዯጃዝማች ታዬ ጉሌሊቴ ከሚመራ አውራጃ
ተነስተው የከፊ ጠቅሊይ ግዛት ጥብቅ ገዢ እንዱሆኑ ተዯርጎ ነበር። አንባቢዎች እንዯሚያስታውሱት

145
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ክቡር ራስ እምሩ ክረምቱን ጎሬ ሲከርሙ ተባብረው ጠሊትን እንዱቃወሙ ከፃፈሊቸውና እንዯሚስማሙ
እምነት ተጥልባቸው ከነበሩት ታሊሊቅ መኩዋንንት አንደ ዯጃዝማች ታዬ ስሇ ነበሩ እሳቸውና የከፊ
ህዝብ ጠሊትን የሚቃወሙና ሇኢትዮጵያ ነፃነት የቆሙ ሇመሆናቸው አንዲች ጥርጣሬ የነበረ
አይመስሌም። ስሇዚህ ማታ ጥሩንባ እዬተነፊ ከሞሊ ጎዯሌ የሚከተሇው ማስጠንቀቂያ ሲሇፇፌ አመሸ።

«ከነገ ጀምሮ የምንጉዋዝበት አገር ህዝብ ጠሊትን፥ የሚቃወምና እኛን የሚረዲ በመሆኑ በመንገዴም ሆነ
በሰፇር ባሊገሩ በፇቃደ ሇሽያጭ የሚያቀርበውን በገንዘብ ከመግዛት በቀር ወታዯር ወይም ከወታዯር ጋር
የሚጉዋዝ ማነኛውም ሰው ባሊገሩን በምንም አይነት ሲያስቸግር ቢገኝ ወይም ማስቸገሩን ያይን ምስክር
ቢነግርበት በብርቱ የሚቀጣ መሆኑን እንዴታውቁት!»

በማግስቱ ጥዋት እንዯ ተሇመዯው መንገደ አማን መሆኑን እያሰሱ የሚያረጋግጡት ቃፉሮች
ፉታውራሪዑ ከበዯ ያዘውና ቀኛዝማች ዯጀኔ ርገጤ ከሰዎቻቸው ጋር ቀዯም ብሇው ተነስተው ሄደ።
ቆይተው ስዯተኛው ህዝብና ከጉዋዙ የሚበዛው ክፌሌ ተከተለ። ከሁለም በሁዋሊ ራስ ከመኩዋንንቱና
ከሆሇታ መኮንኖች ጋር መንገዲቸውን ያዙ። ዯብረ ማርቆስ የነበሩት የክብር ዘበኞች አሇቃ ሌጅ (ሁዋሊ
ቀኛዝማች) ግዛው ቡኔ መትረየሳቸውን አስጭነው እሳቸው በበቅል ተቀምጠው ከራስ ፉት ሇፉት ይሄደ
ነበር። ከራስና ከመኩዋንንቱ በሁዋሊ አቶ በትረ ፅዴቅና እኔ ተዝናንተን እያወራን ስንሄዴ ሁሇት
ወታዯሮች አንዴ የጣሉዑያን መሇዮ ያሇበት ቆብ በራሱ የዯፊ ሰው ቀኝና ግራ ክንድቹን ይዘው እየሮጡ
ባጠገባችን አሌፇው ወዯ ራስ ቀረቡና ይነጋገሩ ጀመር። ራስም ሰውዬውን እዬጠዬቁት ሲመሇስ ከሩቅ
እናይ ነበር። ምን እንዯጠዬቁትና ምን እንዯ መሇሰ አሌተሰማንም። ሁዋሊ እንዯ ሰማነው ግን «ጣሉያኖች
ከፊን መያዛቸውንና ያን መሇዮም ያገኘው ሇጣሉያን ወታዯርነት ከተቀጠሩ የከፊ ጉዋዯኞቹ መሆኑን
ተናገረ» አለን። ሰውዬው በወታዯሮቹ እንዯተያዘ እንዱቆይ ወዯ ሁዋሊ ተመሇሰ። ጉዞው ግን
አሊቁዋረጠም፥ ይቀጥሌ ነበር። የከፊን መያዝ ከሰውዬው የሰሙ ከሁሇት ወታዯሮች በቀር ራስና
ባጠገባቸው የነበሩት ብቻ ስሇ ነበሩ ላሊው «አገር አማን ነው» ብል በሰሊም ጉዞውን ይቀጥሌ ነበር።

ወዯ ጎጀብ እዬቀረብን ስንሄዴ ቀኙና ግራው ጥቅጥቅ ያሇ ጫካ ይህን እንጂ ጥርጊያው መንገዴ
በጣም ሰፉ ስሇ ነበረ ያን ጥርጊያ መንገዴ በወርደም በቁሙም ባሇበቅል መኩዋንንትና እግረኛ ወታዯር
ሞሌቶት ሁለም ባንዴነት እንዯ ማእበሌ ሲጥመሇመሌ ማየቱ እንዳት ዯስ ያሰኝ ነበር!

ጎጀብ ወንዝ ዲር ስንዯርስ ሶስት ይሁን አራት ረዣዥም ፇረንጆች ዴንገት፥ ከዬተሸሸጉባቸው
አጫጭር ቁጥቁዋጦዎች እዬወጡ ቀጥ ብሇው ቆሙ። በኪሳቸው ምን እንዯ ያዙ እነሱና እግዜር
ይወቁት እንጂ በጃቸው የመሳሪያ ምሌክት አይታይም ነበር! ወዱያው ያ በሰሊም እያወራና እዬተዝናና
ይጉዋዝ የነበረው ሰራዊት «ቁም!» እንዯ ተባሇ ሁለ ሁለም ባንዴ ጊዜ ቀጥ አሇ! ወሬውና መዝናናቱም
እንዱሁ ዝም ፀጥ አሇ! ፇረንጆች የጠሊት መትረየሶች ተዯግነውባቸው እያዩ እንዱያ ባድ እጃቸውን
ዯረታቸውን ገሌብጠው መቆማቸው እኛን? ወይስ ሞትን? ማናቸነን ቢንቁ እንዯሆነም እንዱሁ ከነሱና

146
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከግዜር በቀር የሚያውቅ የሇ! ያም ሆነ ይህ እኔ እስከ ዛሬ ዴረስ አዯንቃቸዋሇሁ። ዯቂቃ ባሌመሊ ጊዜ
ውስጥ ያን ፀጥታ አቁዋርጠው፥

«በሇው!» ካለ በሁዋሊ ሌጅ ግዛው ቡኔ፥ «እንበሊቸው?» አለ እንዯገና ወዯ ራስ ዘወር ብሇው።

«ተው ቆይ እስቲ! ‹ምንዴን ናቸው?› በለዋቸው» አለ ራስ በጃቸው የያዙትን አሇንጋ ይሁን


ወይም ላሊ ነገር ሊይና ታች እያወዛወዙ። ወዱያው ከኛ ዘንዴ ጠያቂ ሳይሄዴ ከፇርንጆቹ ዘንዴ አንዴ
የምናውቃቸው ሰው እየሮጡ መጥተው ራስን እጅ ነሱ። እኒያ ሰው ቀኛዝማች መጊዴ ይባለ ነበር።
ቀኛዝማች መጊዴ የሻሇቃ ዮሀንስ አብደ እና የአቶ ዲዊት አብደ የእንጀራ አባት መሆናቸውን ጎሬ
በቆየሁበት ጊዜ ሰምቻሇሁ። ከቀኛዝማችነት ማእረግ ጋር የጎሬ ከተማ ገዥ ሆነው መሾማቸውንም የዚያ
ሌንነሳ አቅራቢያ ሰምቸ ነበር።

«ምንዴን ናቸው እነዚህ?» አለዋቸው ራስ፥ ቀኛዝማች መጊዴን።

«ኮልኔሌ ሚኒቲ? ማላቲ (ስሙን ረስቼዋሇሁ) እና ረዲቶቻቸው ጣሉያኖች ናቸው ጌታየ።


ኮልኔለ ክቡርነትዎን የከበበው የጣሉያን ጦር አዛዥ ናቸው። ከመጡበት መንገዴ ቀኝና ግራ ያሇውን
ጫካ የጣሉያን ጦር ይዞታሌ። ከወንዙ ወዱያ ማድም መዴፍችና ሌዩ ሌዩ ከባዴ መሳሪያዎች
ተጠምዯዋሌ። ስሇዚህ ‹ተከበዋሌ መውጫ የሇዎትምና እጅዎን ቢሰጡ ይሻሊሌ!› ነው የሚለት» አለ
ቀኛዝማች መጊዴ።

«እጃችነን ባንሰጥስ?» አለ ራስ ትንሽ ዝም ብሇው ቆይተው።

«ይህኑ ሌንገራቸውና መሌሱን ሊምጣ» ብሇው ቆይተው።

«ይህኑ ሌንገራቸውና መሌሱን ሊምጣ» ብሇው ቀኛዝማች እየሮጡ እንዯ መጡ እየሮጡ ወዯ


ጣሉያን ሹማምት ሄዯው ዘሇግ ያሇ ጊዜ ሲነጋገሩ ከቆዩ በሁዋሊ ተመሌሰው፥ የኮልኔለን መሌስ ሇራስ
አስታወቁ። መሌሱ ከሞሊ ጎዯሌ እንዱህ ነበር።

«ተከበዋሌና በከንቱ ሰው ከሚያሌቅ በፇቃዴዋ እጅዎን እንሰጡ እንጠይቅዎታሇን። ፇቅዯው


እጅዎን የማይሰጡ ከሆነ ግን እስካሁን ባዯረጉት ሁለ ሇርስዎ ከፌ ያሇ አክብሮት ስሊሇን እንዱህ
በዴንገት አዯጋ ጥሇን አንይዝዎትም በጦርነት ህግ የተዯነገገውን ስነ - ስራት በመከተሌ ተዋግተን ነው
የምይዝዎ። ስሇዚህ ምርጫውን ሇርስዎ እንተዋሇንና መክረው አስበው ውሳኔዎን ያስታውቁን። እስከዚያ
ዴረስ እኛ፥ ከወንዙ ወዱያ ማድ ሄዯን እንቆያሇን።»

147
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወዱያው ጣሉያኖች ወንዙን ተሻግረው ሲሄደ ራስ መኩዋንንታቸውንና የሆሇታን መኮንኖች
እንዱሁም ከጅማ መጥተው የተጨመሩትን መኩዋንንት ሰብስበው ከመንገደ አጠገብ ወዯ ጫካው ትንሽ
ገባ ብሇው ምክር ያዙ።

ያነሇት የጣሉያን የጦር አሇቆች ያሳዩትን ጭዋነትና ዯመ - በራዴነት በሽሬ፥ የጦር ግንባር -
ሇማስፇራራት ሲለ ብቻ - ይሸሽ የነበረውን ሰራዊት በእሳተ - ገሞራ ቦምብ ከማቃጠሊቸውና እንዯ ተባይ
በመርዝ ከመፌጀታቸው ጋር ሳነፃፅረው ጣሉያኖች ባንዴ አካለ ሁሇት የተሇያዩ መሌኮች ያለት ሰው
መስሇው ታዩኝ

ያነሇት ጎጀብ ወንዝ ሊይ የሆነው ሁለ በእሇቱ ብቻ ሳይሆን ካሇፇ በሁዋሊም መሇስ ብል


ስያስቡት የሚያስገርሙና የማይገቡ ነገሮች ያለበት ነው! ከሁለ አስቀዴሞ መንገደን እያሰሱ አማን
መሆኑን እንዱያረጋግጡ ከሰዎቻቸው ጋር ቀዯም ብሇው የሄደት ፉታውራሪ ከበዯ ያዘውና ቀኛዝማች
ዯጀኔ ርገጤ ጎጀብ ወንዝ ሊይ ዴንገት በጣሉያን ወጥመዴ ውስጥ ሲገቡ፥ እጃቸውን ከመስጠት በቀር ላሊ
ማማረጫ ባይኖራቸውስ ቃፉር ሇሆኑሇት ሰራዊት አንዲች ያዯጋ ምሌክት ማሳየት አይችለም ኖሮዋሌ?
ከዚያ ቆይቶ የተከተሇው ስዯተኛ ህዝብና ጉዋዙ እንዳት ነው አንዴ ወሬ ነጋሪ እንኩዋ ወዯ ሁዋሊ
ሳይተው እወንዙ እንዯ ዯረሰ እዬተሻገረ እጁን የሰጠ? ከዚያ በሁዋሊ ዯግሞ ከራስ ሰራዊት ብዙ
የራባቸው የዯከማቸውና ጥይት ያሇቀባቸው አባልች ተስፊ ቆርጠው ራስና መኩዋንንቱ ከመንገደ
አጠገብ ተሰብስበው በመምከር ሊይ መሆናቸውን እያዩ፥ «ምን ይለን» ሳይለ በገሀዴ መሳሪያቸን
እያስረከቡ እጃቸውን ሲሰጡ ይታዩ ነበር! ይህስ ምን ይባሊሌ? የሚያስገርም አዯሇም? ዛሬ ከብዙ
አመታት በሁዋሊ ሇሚሰሙት የሚያስገርም ነው! በእሇቱ እዚያ ቆመን እናይ ሇነበርን ግን የሚያስገርም
ብቻ ሳይሆን የሚያስዯነግጥና የሚያስሇቅስ ስሇ ነበረ አንዲችን የዴካማችን ሁለ መጨረሻ መሆኑ
ተሰምቶን አሇቀስን። በምክሩ ሊይ ከመዋጋቱ እጅ መስጠቱ የተመረጠበት ምክንያትም ይህ ሁለ ታይቶ
መሆኑን እዚያ የነበሩ ሰዎች ነገሩኝ። እኒያ ሰዎች እንዯ ነገሩኝ የሰራዊቱ እምራብና መዴከም የጥይት
ማሇቅ ከሁለም ይሌቅ ያካባቢውን ህዝብ ዴጋፌ ማጣት ይህ ሁለ ሰፉ ክርክር ከተዯረገበት በሁዋሊ
እንዱህ ባሇ ሁኔታ ሆነን ጦርነት መግጠሙ ሰው ከማስጨረስ በቀር ወዯ ግባችን ስንዝር የማያራምዴ
ስሇሆነ አንዲንዴ ውሇታዎች ተጠይቀው ጣሉያኖች የሚቀበለ ከሆነ እጅ መስጠቱ የሚሻሌ በመሆኑ
ተወሰነ። «ተጠየቁ» ከተባለት ውሇታዎች የማስታውሳቸው የሚከተለት ነበሩ።

፩ኛ፦ ሇኢትዮጵያ ነፃነት ሇመዋጋት ከኢጣሉያ የጦር ሰራዊት አምሌጠው በዚያ ጊዜ ከራስ እምሩ
ጦር ጋር የነበሩት ኤርትራውያን ከላልች የራስ ሰራዊት አባልች የተሇዬ ቅጣት እንዲያገኛቸው ሙለ
ምህረት እንዱዯረግሊቸው፤

፪ኛ፦ ወሇጋ ውስጥ ቡናያ ሊይ የጣሉያንን አይሮፕሊን ባቃጠለትና በውስጡ የነበሩትን ጣሉያኖች
በገዯለት የሆሇታ መኮንኖች ሊይ ያን በማዴረጋቸው የተሇዬ ቅጣት እንዲይዯረግባቸው፤

148
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፫ኛ፦ ራስ እምሩን ተከትሇው እስከዚያ ቀን ዴረስ በኢጣሉያ ሊይ ጦርነቱን ሲቀጥለ በቆዩት ሁለ
ሊይ ያን በማዴረጋቸው ከላልች ኢትዮጵያውያን የተሇየ ምንም አዴርጎት እንዲይዯረግባቸውና
በዬሀገራቸው ገብተው እንዯ ላልች ኢትዮጵያውያን ሁለ ሰሊማዊ ኑሮ ሇመኖር እንዱፇቀዴሊቸው»
ከዚህ በሊይ ያመሇከትሁዋቸው አሁን የማስታውሳቸው አይነተኞች ጥያቄዎች ሲሆኑ የረሳሁዋቸው
ላልችም ሉኖሩ ይችሊለ።

ራስና መኩዋንንቱ በምክር ሊይ እንዲለ አንዴ ከጣሉያን ሹማምንት የተሊከ መሊክተኛ እዬሮጠ
መጥቶ ከራስ ጋር እንዱገናኝ ጠየቀ። ሰውዬው የያዘው መሌእክት ጌራ ሊይ የወሇጋን የጣሉያንጦር
ከሁዋሊችን መዴረሱን አስታውቆ ያ ከሁዋሊ የመጣ ጦር፥ ባሇበት እንዱቆም እንጂ ወዯ ፉት እንዲይገፊ
ሇማዴረግ የጣሉያንን ባንዱራ የያዙ መሊክተኞች መሊክ አስፇሊጊ ሆኖ በመገኘቱ ባንዱራውን የያዙት
መሊክተኞች በራስ ሰራዊት መሀከሌ ሇማሇፌ እንዱፇቀዴሊቸው ሹማምንቱ መጠየቃቸውን የሚያመሇክት
ነበር። ራስም በጉዲዩ ከመኩዋንንቱ ጋር አሳብ ከተሇዋወጡ በሁዋሊ መፌቀዲቸውን አስታውቀው አንዴ
የጣሉያንን ባንዱራ የያዘ ሰው በጥቂት ሰዎች ታጅቦ «ዯረሰ» ወዯ ተባሇው ጦር ሇመሄዴ በሰራዊታችን
መሀከሌ ሲያሌፌ አዬን። እውነት - እንዯ ተባሇው - አዱስ ጦር ከሁዋሊችን ዯርሶ እንዯሆነ ወይም
የተከብንበት ዙሪያ መስመር የተዘጋና መውጫ የላሇን አስመስል አሳይቶ ራስ እጃቸውን ሇመስጠት
የሚጠይቁዋቸው ውሇታዎች እንዲይበዙና አስቸጋሪዎች እንዲሆኑ ተፅእኖ ሇማዴረግ የተፇጠረ ዘዳ
እንዯሆነ መቸም እኛ «መጣ» የተባሇውን ጦር ስሊሊዬን እናውቅ!

የሆነ ሆኖ፥ ራስ እጃቸውን ሇመስጠት ያቀረቡዋቸው ውሇታዎች ሇጣሉያን ሹማምንት ተሊሌፇው


ሹማምንቱ በበኩሊቸው በውሇታዎቹ ውስጥ ከተጠየቁት ጥያቄዎች ሊንዲንድቹ መሌስ መስጠት የሚችለ
ከነሱ በሊይ ባሇስሌጣኖች እንጂ እነሱ ባሇ መሆናቸው ቦንጋ ሇዋናው አዛዥ ምናሌባትም ሊዱስ አበባ
በቴላግራም አስተሊሌፇው መሌስ እንዲገኙ የሚያስታውቁ መሆናቸውን ገሇፁ። ከዚያ ሁሊችንም
በያሇንበት ሆነን ስንጠብቅ ውሇን ከቀትር በሁዋሊ አስር ወይም አስራ አንዴ ሰአት ግዴም ሹማምንቱ
ወዯ ራስ መጥተው ጥያቄዎቻቸው ሁለ ባዱስ አበባ በኩሌ ሇሙሶሉኒ ተሊሌፇው ሙሶሉኒ
መቀበሊቸውን ሲያስታውቁዋቸው ራስም፥ ያቀረቡዋቸውን ውሇታዎች መሆናቸውን መንግስት የተቀበሇ
ከሆነ እጃቸውን ሇመስጠት የወሰኑ መሆናቸውን አስታውቀው ሁለም በዚያ አሇቀ። የጦርነቱ
የመንከራተቱ የነፃነቱ ባገራችን ጫካ ውስጥ በተስፊ የመቆየቱ ነገር እንኩዋ ሇኛ ያነሇት በዚያ አሇቀ።
ነገር ግን በተስፊ የመቆየቱ ነገር እንኩዋ ሇኛ ያነሇት በዚያ አሇቀ። ነገር ግን ቀኑ መሽቶ ስሇ ነበረ
ከነመሳሪያችን በነበርንበት አዴረን የመሳሪያ ርክክብ የተዯረገና ወዯ ቦንጋ የተጉዋዝን በማግስቱ ነበር።
ታዱያ እዚያ ከመንገደ ቀኝና ግራ ባሇው ጫካ ተሰግስገን ስናዴር «ጫካውን በሙለ የጣሉያን ጦር
ይዞታሌ» ተብል ተነግሮን የነበረ ቢሆንም የጣሉያንን ጦር እዚያ መኖር የሚያሳይ አንዲች ምሌክት
አሊዬንም። ሁሇተኛ ከጣሉያን ሰራዊት አምሌጠው ከራስ እምሩ ጋር የነበሩት ኤርትራውያን «ሙሶሉኒ
ምህርት አዴርገውሊቸዋሌ ተብል አዯሩ። ከዚያም ከኢትዮጵያ ሇመውጣት መቻሊቸውን ሁዋሊ ሰማሁ።

149
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ስሇዚህ መጀመሪያ ዴንገት ከጣሉያኖች ጋር ስንገናኝ ቀኛዝማች መጊዴ «ከመንገደ ግራና ቀኝ ያሇው
ጫካ በሙለ በጣሉያን ጦር ስሇተያዘ ተከበዋሌ» ብሇው ሇራስ የነገሩዋቸውን እነዚህ የተመሇከቱት ሁሇት
ነገሮች ያስተባብለዋቸዋሌ።

ምእራፍ ሃያ

ቦንጋ
ክቡር ራስ እምሩ አብረዋቸው ከነበሩት መኩዋንንት ጋር ጎጀብ ወንዝ ሊይ መክረው ያካባቢውን
ህዝብ ዴጋፌ ካሇማግኘትም ላሊ የስንቅና የትጥቅ እጥረት በሰራዊቱ ሊይ ብርቱ የመንፇስና የአካሌ
ዴካም ያስከተሇ መሆኑን በመገንዘብ እጃቸውን ሇመስጠት መወሰናቸውን ባሇፇው ምእራፌ
አመሌክቻሇሁ። ያን ውሳኔ ሇማዴረግ የተጠየቁትን ውሇታዎች ጣሉያኖች መቀበሊቸውን እስኪያስታውቁ
ቀኑ ስሇመሸ ላሉቱን እዚያው ማዯራቸውን በዚያ ምእራፌ ተነግሮዋሌ።

በማግስቱ ወንዙን እየተሻገርን መሳሪያችንን ሇጣሉያኖች ካስረከብን በሁዋሊ አርበኝነታችን ቀርቶ


ምርኮኞች ስሇሆን፥ ብዙ ምርኮኞች ወዯ ተሰበሰቡበት ወዯ ቦንጋ ተወስዯን። ቦንጋ ስንዯርስ የማረኩን
ሹማምንት ሇበሊያቸው፥ በዚያ ክፌሌ የጣሉያን ጦር ሰራዊት ዋና አዛዥ ሇነበሩት ሇኮልኔሌ (ሁዋሊ
ጀነራሌ) ማሌታ አስረከቡን።

ኮልኔሌ ማሌታ ባችር ጊዜ (ከጥቅምት እስከ ታህሳስ 1929) ምእራብ ኢትዮጵያ የያዙበትን
ፌጥነትና የጦርነትም የፖሇቲካም ስሌታቸውን ወይም እቅዲቸውን ተከታትል የተመሇከተ ሁለ ጠሊት
እንኩዋ ቢሆን እንዱያዯንቃቸው ይገዯዲሌ!

ፊሽስት ኢጣሉያ የኢትዮጵያን ነዋሪ ነፃነት ሇማጥፊትና ህዝብዋን በቅኝ ግዛት ቀንበር ጠምዲ
ሇመጨቆን የተነሳችሇትን የእብሪት አሊማ ሇማስፇፀም የቆሙ የዚያ ክፈ አሊማ መሳሪያ በመሆናቸው
ኢትዮጵያዊ እንዯ መሆኔ ኮልኔሌ ማሌታን አጥብቄ እጠሊቸዋሇሁ። ነገር ግን እቅዲቸውን በጥንቃቄ
ሰርተው ጊዜና የሰው ህይወት በከንቱ በማይባክንበት ትንሽ የማያቃውስባቸው መሪ በመሆናቸው ጠሊት
እቅዲቸውን ትንሽ የማያቃውስባቸው መሪ በመሆናቸው ጠሊት ብሆንም በሙያቸው እንዲዯንቃቸው
እገዯዲሇሁ። የእቅዴ አሰራራቸውን ዘዳና ፌጥነታቸውን የተቻሇውን ያክሌ አሳጥሬ በሚከተለት
መስመሮች ሊንባቢዎች መግሇስጽ እወዲሇሁ።

እስከ ጥቅምት 1929 አጋማሽ ወይም እስከዚያ ወር መጨረሻ ግዴም፤ ክቡር ራስ እምሩና እኛም
ከሳቸው ጋር ጎሬ ስሇ ነበርን ያን ጊዜ ጣሉያኖች ወዯ ምእራብ ኢትዮጵያ አሇመዴረሳቸውን እናውቃሇን።
ስሇዚህ ኮልኔሌ ማሌታ በምእራብ ኢትዮጵያ ዘመቻውን የጀመሩ በትቅምት 1929 መጨረሻ ግዴም ነው
ማሇት ነው። እንግዱህ በዚያ በጥቅምት መጨረሻ ግዴም ወዯ ሰዬ (ወሇጋ) ይዘምቱና በጦር

150
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በማስፇራራትም ይሁን በፖሇቲካ በማግባባት የሰዬን ባሊባቶችና ህዝቡን ያሳምናለ። ከዚያ ሰዬ
ከዯጃዝማች ጆቴ ሌጆች ወሰና የሚባለትን ሾመው እዚያው ይተውና ሁሇተኛውን ሌጅ ዯጃዝማች ዮሀንስ
ጆቴን ይዘው ወዯ ኢለባቦር ይሻገራለ። ኢለባቦር ሇጊዜው የኢትዮጵያ መንግስት እንዯራሴ ሆነው ጎሬ
የተቀመጡትን ቢትወዯዴ ወሌዯ ፃዴቅን ከሌጅ ሌጃቸው ጋር ይይዛለ። ከዚያ እነሱንም ይዘው ወዯ ከፊ
ይሻገሩና የከፊን ጥብቅ ገዥ ዯጃዝማች ታዬ ጉሌሊቴን ይይዛለ። ከዚያ ክቡር ራስ እምሩ ወሇጋና ጅማ
ተይዘው ሲቆዩዋቸው ወዯ ከፊ ቦንጋ የሚሄደ መሆናቸውን እቅዲቸውን ጎጀብ ሊይ ያጠምደና ሲጠብቁ
ይቆያለ። ከዚያ ያ ጎጀብ ሊይ የተጠመዯ ወጥመዴ አንዴ ጥይት ሳይተኮስ የጎጃሙን ጠቅሊይ ገዥ ክቡር
ራስ እምሩን ብቻ ሳይሆን የጅማውን ገዥ ከንቲባ ጋሻው ጠናን ጭምር ይይዝሊቸዋሌ። ከዚያ በሁዋሊ
ከዯጃዝማች ሀብተ አምርያም በቀር የምእራብ ኢትዮጵያን ጠቅሊይ ገዥዎች ሁለ ምርኮኞቻቸውን
አዴረገው ባንዴ ሊይ ይሰበስቡና ቦንጋ ያስቀምጡዋቸዋሌ። ምእራብ ኢትዮጵያንም እንዱያ ባሇ ጭምር
ጊዜ ከሰሜንና ከመሀሌ ኢትዮጵያ ጋር ተጨምሮ የጣሉያን ቅኝ ግዛት እንዱሆን ሇማዴረግ ይችሊለ!
የሚያስዯንቅ ችልታ ነው! ምናሌባትም ኯልኔሌ ማሌታ በምእራብ ኢትዮጵያ ያሳዩት ችልታቸው
ይሆናሌ ወዱያው ከኯልኔሌ ማሌታ በምእራብ ኢትዮጵያ ያሳዩት ችልታቸው ይሆናሌ ወዱያው
ከኮልኔሌነት ወዯ ጀነራሌነት ማእርግ ሇማዯግ ያበቃቸው!

በምእራብ ኢትዮጵያ ጦራችን እንዱያ ባጭር ጊዜ ተፇትቶ ያ የኢትዮጵያ ክፌሌ በጣሉያኖች


መያዙ የማይሻር የመንፇስ ስብራት ነበር ያዯረሰብን። አንባቢዎች እንዯሚያስታውሱት ክቡር ራስ እምሩ
ተከዜ ሸሇቆ ውስጥ በሰፇርንበት እኔን ወዯ ሱዲን ሉሌኩኝ አስጠርተውኝ ስንነጋገር ጦራችንን በሽሬ
ግንባር ዴሌ ሳይሆን ሇምን ወዯ ሁዋሊ እንዯ መሇሱት በጠየቅሁዋቸው ጊዜ «ረዥም ጊዜ ሌንዋጋበት
የምንችሌ ሇኛ የሚመች ቦታ ይዘን ጦርነቱን ሇመቀበሌ አስበን ነው» ብሇው ጦርነቱን ሇመቀጠሌ፥
ከሰሜን ኢትዮጵያ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚሻሌበትን ምክንያት ዘርዘር አዴርገው ሲነገሩኝ በሰጡኝ
ምክንያት እኔም አምኘበት ዯስ ብልኝ ነበር ወዯ ተሊኩበት የሄዴሁ።

ራስ እንዲለት ጦራችን ረዥም ጊዜ ጦርነቱን ሇመቀጠሌ ከሰሜን ኢትዮጵያ የምእራቡ ክፌሌ


አገራችን የሚስማማ እንዯሚሆን ታምኖባቸው የነበሩት ምክንያቶች አጥጋቢ መሆናቸውን ሇማስረዲት
ሁሇቱ ክፌልች (ሰሜንና ምእራብ) በዚያ ጊዜ የነበሩትን ሁኔታ በማነፃፀር ሌዩነታቸውን ከዚህ
እንዯሚከተሇው ባጭሩ ሇማሳየት እሞክራሇሁ።

፩ኛ፥ ሰሜን ኢትዮጵያ፡- ፊሽስት ኢጣሉያ ኢትዮጵያን ሇመውረር መነሳትዋ ከወሌወሌ ግጭት
ጀምሮ የታወቀ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት እምነቱን በአሇም ማህበር ሊይ ጥል ሳይሰናዲ ጣሉያኖች
በምስራቅና በመሀሌ ትግራይ አዱግራትን መቀላን፥ አዴዋን አክሱምንና የዚያን አካባቢ ሁለ አሌፇው
እስከ ተምቤን ዯርሰው ነበር። በምእራብ ትግራይ በኩሌ እንዱያውም የትግራይን ግዛት በጠቅሊሊው
ይዘው ተከዜ አፊፌ አጠገብ ዲባጉና ሊይ መሽገው ነበር። ታዱያ በዚያ በያዙት የትግራይ ክፌሌ ሁለ

151
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምቹ ቦታዎች እየመረጡ ምሽጎቻቸውን መሽገው እርድቻቸውን የመኪና መንገድች ሰርተው ስሇ ነበረ፥
ወታዯርና ትጥቅም ስንቅም ላሊም ሇጦርነት የሚያስፇሌግ ነገር ሁለ የማመሊሇስ ችግር ሉያገኛቸው
ሇጦርነት ታዝዞ ሉዋጋ ሲሄዴ ባገሩ መሬት ቀዴሞት ምሽጉን መሽጎና እርደን አርድ ከሚጠብቀው
ጠሊት ጋር ነበር የሚዋጋ። በሰሜን አሉያኖች የኢትዮጵያን ሰራዊት አስቀዴመው ባሰናደዋቸው
ምሽጎችና እርድች ተተግነው ብቻ ሳይሆን ቦምብና መርዝ እንዯ እንዯ ዝናም ከሰማይ እያወረደ ጭምር
ነበር የሚወጉት። አይም ሁለ ሁኖ «በመጀመሪያው የተንቤን ጦርነትና በዲባጉና ጦርነት
ኢትዮጵያውያን ጠሊትን ሳይቀር ባስገረመ ጀግንነት ምሽግ እየጣሱ ገብተው ጣሉያኖችን በጨበጣ ውጊያ
እያሸነፈ ከምሽጋቸው አስወጥተው ዴሌን ተቀዲጅተው ነበር! እንዱሁም «በሰሇክሇካ» ጦርነት
ኢትዮጵያውያን የመጨረሻ ዴሌ አያግኙ እንጂ የጣሉያኖች ምሽግ ጥሰው ገብተው ከብርቱ የጨበጣ
ውጊያ ቦሁዋሊ ጣሉያኖችን ከምሽጋቸው አስወጥተው ሇማባረር መቻሊቸውን ራሴ የተመሇከትሁ ያይን
ምስክር ነኝ! እንዱያ ያሇው የኢትዮጵያውያን ጀግንነት ጠሊት አስቀዴሞ ባገራችን ምሽጎችን ሳይመሽ ግና
ጦሩ ሲጎዲበት አዱስ ጦር ሇመተካት መሳሪያና ስንቅ ሲጎዴሌበት ሇመሙሊት መንገድችን ሳይሰራ ቢሆን
ኖሮ ኢትዮጵያና የጣሉያን ሰራዊቶች በግሌጥ ሜዲሌ ፉት ሇፉት ገጥመው የሚዋጉበት ጦርነት ቢሆን
ኖሮ ምናሌባት ያ የኢትዮጵያውያን ጀግንነት በሰሚአን ኢትዮጵያ ያዴዋን ዴሌ ሇመዴገም ሳያበቃን
አይቀርም ነበር! ነገር ግን ጠሊታችን አስቀዴሞ ባገራችን ባሇቤት ሆኖ እኛ ሌናሰናዲው ይገባን የነበረውን
መከሊከያ አሰናዴቶ እዚያ ሊይ እንዴንዋጋ ሳሌስገዯዯን የኢትዮጵያውያን ጀግንነት «የእሳት እራት»
ጀግንነት ሆኖ ቀረ!

፪ኛ፦ ምእራብ ኢትዮጵያ፦ የምእራብ ኢትዮጵያ ሁኔታ ከሰሜኑ ፇፅሞ የተሇየሌ ነበር። ከሁለ
አስቀዴሞ፤ ምእራብ ኢትዮጵያ እንዯ ሰሜን ጣሉያኖች አስቀዴመው በመረጡሊቸው ቦታዎች
ምሽጎቻቸውን ያሌመሸጉበት ሰራዊታቸውንና ሇሰራዊታቸው የሚያስፇሌገውን ትጥቅና ስንቅ ከመነሻው
እስከ ምሽጏቻቸው ሇማመሊሇስ መንገድች ያሌሰሩበት ነበር። እንዱሁም ምእራብ ኢትዮጵያ ዯናማ
በመሆኑ የጣሉያን አይሮፕሊኖች በሰሜን እንዲዯረጉት ኢትዮጵያውያንን በግሊጭ አግኝተው በቦምብና
በመርዝ ሇማጥቃት የሚችለበት ነበር። ባንፃሩ ሇኢትዮጵያውያን ከማናቸውም የጠሊት ጥቃት
ሇመከሊከሌና ጠሊትን ተሸሽጏ ሇማጥቃት የሚያችሌ ምቹ ነበር። ስሇዚህ ያ በሰሜን ኢትዮጵያ የታየው
የኢትዮጵያውያን ቆራጥነትና ጀግንነት በምእራብ ኢትዮጵያም ቢኖር ኖሮ የምእራብ ኢትዮጵያ ጠቅሊይ
ገዥዎችም «ማን በማን ውስጥ ሆኖ ማን የማንን ትእዛዝ ተቀብል ጦርነት ሉዋጋ!» እየተባባለ እስበስ
በመናናቅ ፇንታ እንዱያ ያሇውን ምስኪን አስተሳሰብ ሇመቁዋቁዋም ፇቃዯኞች ቢሆኑ ኖሮ የምእራብ
ኢትዮጵያ ጦርነት ባሇቀበት ሁኔታ ባሊሇቀ ነበር! ኮልኔሌ ማሌታም ምንም ያክሌ የጦርነትና የፖሇቲካ
እቅዴ መስራት አዋቂና የሰሩትን እቅዴ በሚያስገርም ፌጥነት ወዯ ፌፃሜ ሇማዴረስ ችልታ ቢኖራቸው
ከዚያ ሁለ ችልታቸው ጋር የምእራብ ኢትዮጵያን ጦርነት ሶስት ወራት ተካክል ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ
ሇመጨረስ ባሌተሳካሊቸው ነበር! ነገር ግን የኢትዮጵያ ጠቅሊይ አገረ ገዢዎች ታዝዘው እንጂ በስምምነት

152
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ተባብረው መስራት የሇመደ አሌነበሩም። ወታዯሩ ከትጥቅና ከስንቅ እጥረት ላሊ ያካባቢው ህዝብ ዴጋፌ
ስሊሌነበረው ተስፊ የቆረጠ ነበር። ህዝቡም የቅኝ ግዛት አስተዲዯር ስሇሚያከትሇው የባርነት ኑሮም ሆነ
በዚያ የባርነት ኑሮ ሉያኖር የመጣን ጠሊት መቃወም የራስን ጥቅም መጠበቅ ስሇ መሆኑ አስቀዴሞ
አንዲች ገሇፃ ወይም ቅስቀሳ አሌተዯረገሇትም ነበር። ስሇዚህ በጠሊት ገንዘብና መሳሪያ እየተባበሇ፤ ጠሊትን
በመቃወም ፇንታ ሇጠሊት ረዲት ሆነ። በዚህ ሁለ ምክንያት ሇማውራት በሚያሳፌር አጭር ጊዜ ውስጥ
ዴሌ ሆነን፤ እጃችንን ብቻ ሳይሆን ምእራብ ኢትዮጵያን ጭምር ሇጠሊት ሰጠን!

ቦንጋ ክቡር ራስ እምሩ ከንቲባ ጋሻው ጠናና ከነሱ ጋር የነበሩት ታሊሊቅ መኩዋንንት እንዱሁም
የሆሇታ መኮንንኖችና ከፇረንጅ አገር ትምህርታቸውን ጨርሰውም ሳይጨርሱ አቁዋርጠውም ሊገራቸው
ሉዋጉ የመጡ ምሁራን ኯልኔሌ ማሌታ በነበሩበት ባገረ - ገዡ ግቢ ከቅጥር ውስጥ በዴንኩዋን
እንዱሰፌሩ ተዯርጎ ነበር። ስሇዚህ ጎሌቶ አይታይ እንጂ፣ በነሱ ሊይ ቁጥጥር መኖሩን ባንዲንዴ ምሌክት
እናውቅ ነበር። በጠቅሊሊ ሰራዊቱ ግን ካገረ - ገዡ ግቢ ቅጥር ውጪ ተበታትኖ ስሇ ነበረ የሰፇረ አንዲች
ቁጥጥር የነበረበት አይመስሌም። ኖሮ እንዯ ሆነም ሇኛ አይሰማንም ነበር። አቶ በትረ ፅዴቅ ካሳና እኔ
ከሰዎቻችን ጋር ከግቢው ቅጥር ውጪ ካንዴ ወንዴ አጠገብ ሰፌረን ከዚያ በፇሇግን ጊዜ ራስንና እግቢው
ውስጥ የሰፇሩትን ወዲጆቻችንን ሌናይ ስንሄዴ እንኩዋንስ ችግር ሉገጥመን «ሇምን መጣችሁ» ተብሇን
ተጠይቀን አናውቅም። ላልችም ከግቢው ቅጥር ውጪ የሰፇሩት ሁለ እንዱሁ እንዯ ሌብ ማግባትና
መውጣት ከተማ ውስጥም መዘዋወር ይችለ ነበር።

በምግብ ብኩሌ ከቅጥር ውጪ ከሰፇርነው እውስጥ የሰፇሩት ምርኮኞች በመጠኑም ቢሆን ይሻለ
ነበር። እግቢ በምንገባበት ጊዜ እንዯ ተመሇከትነው ድክተር አሇመወርቅ በየነ ጣሉያኖች ምግብ
ከሚያከፊፌለበት እንዯ ዲቦ፥ በቆርቆሮ የታሸገ ምግብ ስኩዋርና ሻይ እንዱሁም አንዲንዴ አስፇሊጊ የሆኑ
ነገሮች እያሸከመ አምጥቶ እዚያ ሇሰፇሩት የኛ ሰዎች ሲያከፊፌሌ እናይ ነበር። ድክተር አሇመወርቅ
እዚያ ሇሰፇሩት ምርኮኞች ተተሪ ሆኖ መመዯቡን ያን ጊዜ ሰማሁ።

ከፇረንጅ አገር ከተመሇሱት ምሁርና እና ከሆሇታ መኮንኖች መሀከሌ ብዙ የሲጋራ ሱሰኞች


ነበሩ። ታዱያ ድክተር አሇመወርቅ ያመጣው ሲጋራ በማይበቃበት ጊዜ፥ ሳጥኑ እየተከፇተ አንዲንዴዋን
ሲጋራ ሁሇት ሰዎች የጋራ እንዱያጤስዋት ስትሰጣቸው «እኔ አንዴ ጊዜ ስመጥ አንተ ሁሇት ጊዜ
መጠጥህ እኔ ባጭሩ ስስብ አንተ በረዥሙ ሳብህ» በመባባሌ በኒያ ሱሰኞች መሀከሌ የነበረው ፌጅት
የሚያስቅም የሚያሳዝንም ነበር!

የቦንጋ ከተማ (ወይስ መንዯር ሌበሇው?) ያን ጊዜ ከማናቸውም ከተማ ወይም አገር ጋር


የሚያገናኝ የመኪና መንገዴ ያሌነበረው ከመሆኑ ላሊ ያይሮፕሊን ማረፌያም አሌነበረው። እዚያ ሇነበረው
የጣሉያን ስራዊት ምግብ ሆነ ላሊ ሇእሇት ኑሮ አስፇሊጊ የሆነ ነገር ሁለ በአይሮፕሊን ነበር የሚዯርስ።

153
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ገብያ በማይውሌባቸው ቀኖች አይሮፕሊኖች ይመጡና ዝቅ ብሇው ሉያወርደ የፇሇጉትን ሁለ እገብያው
ሜዲ ሊይ በዣንጥሊ (ፓራሹት) አውርዯው ይሄዲለ።

ስሇዚህ የመኪና መንገዴ እስኪከፇት ዴረስ የምግብና የላሊ ሇእሇት ኑሮ አስፇሊጊ የሆነ ነገር
ሁለ እጥረት ስሇ ነበረ፥ ከቅጥር ውጪ የነበረውን ምርኮኞች ከማራኪዎቻችን አንዲች የምናገኘው ነገር
አሌነበረም። ነገር ግን አስራ አምስት ቀናት ይሁን ሶስት፥ ሳምንት ያክሌ ቦንጋ፥ በቆየንበት ጊዜ ባሇ
መጋዘን መኪና ቀዴሞ ጫካውን ሲጠርግ ቡሌዯዘር ተከትል መሬቱን እያስተካከሇ ጊዜያዊ መንገዴ
ተከፇተና ስንቅም ላሊ ሇሰራዊቱ የሚያስፇሌግ ነገርም የጫኑ ካሚዮኖች ቦንጋ መግባት ጀመሩ። ብቻ
ምግብ የጫኑ ካሚዮኖች መግባት እንዯ ጀመሩ ቦንጋን ስሇ ሇቀቅን የምግቡ መዴረስ የኛን ሁኔታ ምንም
አሌሇወጠም።

ቦንጋን የሇቀቅን ከፇረንጆች አዱስ አመት በሁዋሊ ነበር። ሊመት በአለ መዴፌ ሲተኮስ በትረ
ፅዴቅና እኔ፥ እነ ክቡር ራስ ዯስታ ዲምጠው መጥተው በኮልኔሌ ማሌታ ሊይ አዯጋ የጣለ መስልን
ዯስታችን ቅጥ መጠኑን ያጣ ሆኖ ነበር።

ያን ጊዜ ራስ ዯስታ ዲምጠው ዯጃዝማች ገብረ ማርያምና ዯጃዝማች በየነ መርእዴ


ከነየሰራዊታቸው እጃቸውን ሳይሰጡ፥ በሲዲሞ በባላና በገምጎፊ በየግዛታቸው እንዲለ ነበሩ። ታዱያ
መነሻው ያሌታወቀ ወሬ «ራስ ዯስታ ዯጃዝማች ገብረ ማርያምና ዯጃዝማች በየነ፥ በአዱስ አበባ ሊይ
ሉዘምቱ ተነስተዋሌ፥ ጅማን ሉይዙ ተቃርበዋሌ ወዯ ከፊ መጥተው ኮልኔሌ ማሌታን ሉዋጉዋቸው ነው»
እየተባሇ ይናፇስ ስሇ ነበረ «ምኞት ባሇበት አሰቱም ይመስሊሌ እውነት» እንዯሚባሇው እንመኘው የነበረ
ነገር ሆነና ከሶስቱ ጠቅሊይ አገረ - ገዥዎች አንደ ወይም ሶስቱ ባንዴነት በኮልኔሌ ማሌታ ሊይ አዯጋ
የጣለ መሰሇን። ነገር ትንሽ ቆይተን ተኩሱ ሇበአለ ክብር መሆኑን ስንሰማ፥ ዯስ ያሇንን ያክሌ የሀዘን
ስሜት እንዯ ገና ዴሌ የመሆን ስሜት ተሰማን። ያነሇት ሇበአለ ክብር ኮልኔሌ ማሌታ ሇጣሉያኖች ብቻ
ሳይሆን ከቅጥር ውስጥ ሇሰፇሩት ኢትዮጵያውን ምርኮኞች ጭምር ግሩም የሆነ ግብዣ ማዴረጋቸውን
ሁዋሊ ሰማን።

በአለ እንዲሇፇ ማራኪዎቻአችን ወዳት እንዯሚወስደን ሳናውቅ ክቡር ራስ እምሩና አብረናቸው


የነበርን ምርኮኞች የጅማን መንገዴ ይዘን ጉዞ ጀመርን። ክቡር ዯጃዝማች ታዬ ጉሌሊቴም አብረውን
ነበሩ። የጎጀብን ወንዝ፥ በተማረክን ጊዜ በተሻገርንበት ሳይሆን በሺቪ ግንባር ተሻግረን እሜዲው ሊይ
አርፊ የቆየችን አይሮፕሊን ክቡር ራስ እምሩንና ዯጃዝማች ታዬን ይዛ ሄዯች። ያን ጊዜ ራስና ዯጃዝማች
ወዳት እንዯ ተወሰደ ከጣሉያኖች በቀር ያወቀ ሰው አሌነበረም። ሁዋሊ ግን አዱስ አበባ አይሮፕሊን
ማረፉኢያ ወርዯው አጭር ጊዜ ቆይተው፥ ከዚያ ከተማ እንኩዋ ሳይገቡ በቀጥታ ወዯ ጣሉያን አገር
መወሰዲቸውን ሰማን። የቀረውነው ምርኮኞች ጉዞዋችንን ቀጥሇን - በስንተኛ ቀን እንዯሆነ ረስቸዋሇሁ -
ጅማ አይሮፕሊን ማረፉያው አጠገብ ሰፇርን። ከዚያ በማግስቱ ይመስሇኛሌ ከምሁራኑና ከከመኩዋንንቱ

154
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መሀከሌ ጥቂት በአይሮፕሊን ወዯ አዱስ አበባ ተወሰደ። ከተከታዩ ቀን ከቀትር በሁዋሊ ግዴም
በአይሮፕሊን ወዯ አዱስ አበባ ከተወሰደት ምርኮኞች መሀከሌ አንደ እኔ ነበርሁ።

ምእራፍ ሃያ አንድ

አዲስ አበባ
አዱስ አበባ እንዯ ዯረስን ካይሮፕሊን ማረፉያ በቀጥታ የ «ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት» ወዯ ተባሇው
ቦታ ተወሰዴን። ያ ቦታ ዴሮ «ገነተ ሌዐሌ ቤተ መንግሥት» ይባሌ የነበረው አሁን «አዱስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ» የሚባሇው ነው። እዚያ ‹ሲኞች ማርቻኖ› የተባለ አማርኛ ግሩም አዴርገው የሚያውቁ
ጣሉያን የስማችንን ዝርዝር ከጅማ እስከ አዱስ አበባ ካዯረስን ሰው ተቀብሇው ሁሊችንንም በተራ በየስም
ከናባታችን እየጠሩ እዴሜያችንን የተወሇዴንበትን አገርና እንዱያ እንዱያ ያሇውን ሇመታወቂያነት
የሚያገሇግሌ ነገር ሁለ እየጠየቁ ይመዘግቡ ነበር። የኔ ተራ ዯርሶ ሲጠሩኝ «አቤት» ብየ ከምርኮኞች
ጉዋዯኞቼ ተሇይቼ እሳቸው ተቀምጠው በሚመዘግቡበት እስክዯርስ ዝም ብሇው በመገረም አይን
ይመሇከቱ ነበር። በዴሜ ሌጅ ከመሆኔም ላሊ የሇበስሁት የካኪ ቁምጣ ኮትና ሱሪ ስሇ ነበረ ይብሱን ሌጅ
ያስመስሇኝ ነበር።

«ሀዱስ አሇማየሁ ማሇት አንተ ነህ? ግሩም ነው! ‹ቤት ሰው ከላሇበት ቁንጫ ይፇሊበታሌ!›
የሚለት ተረት አሰት አይዯሇምኮ! ባገሩ ሰው ሲጠፊ ጊዜ አይዯሇም እንዯናንተ ያሊችሁ ህፃናት ወዯ
ትምህርት ቤት በመሄዴ ፇንታ ወዯ ጦርነት ከዚያ አሌፊችሁ ዱፕልማቶች እየሆናችሁ ውሌ
ሇመፇራረም ወዯ ውጭ መንግስታት የምትሊኩ? ግሩም ነው! እሺ ታዱያስ የኛ ዱፕልማት፤ የንግሉዝ
መንግስት ምን ያክሌ የጦር ሰራዊትና ምን አይነት የጦር መሳሪያ ሇራስ እምሩ ሉሰጥ አንተስ ስሇ ራስ
እምሩ ምን ሌትሰጥ ተፇራርመህ መጣህ?» አለ ሲኞር ማርቻኖ ንግግራቸውን ብቻ ሳይሆን
ፇገግታቸውንና አስተያየታቸውን ጭምር ባሽሙር ቀሇም አስጊጠው እፉታቸው እንዯ ቆምሁ አይኔን
እየተመሇከቱ።

እስከያነሇት ዴረስ እንዱያ ያሇ ጥሩ አማርኛ የሚናገር ፇረንጅ አጋጥሞኝ ስሇማያውቅ ሇጠየቁኝ


ጥያቄ በመመሇስ ፇንታ ሳይታወቀኝ አይኔን ብቻ ሳይሆን አፋን ጭምር በሰፉው ከፌቼ እመሇከታቸው
ኖሮዋሌ! በውነት ዯንግጫሇሁ! ከጥያቄያቸው ይሌቅ አማርኛቸው ነበር ያስዯነገጠኝ!

«ሇጥያቄየ መሌስሇኝ እንጂ! የጠየቅሁህን አሌሰማህም እንዳ! የንግሉዝ መንገስ ምን ያክሌ የጦር
ሰራዊትና ምን አይነት የጦር መሳሪያ ሇራስ እምሩ ርዲታ ሉሰጥና ራስ እምሩስ ምን ሉያዯርጉ
ተፇራርመህሊቸው መጣህ? ብዬ ጠይቄህ ነበርኮ!» አለኝ።

155
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«የጠየቁኝን ሰምቻሇሁ፤ የጦር ሰራዊትና የጦር መሳሪያ ውሌ ሌፇራረም ወዯ እንግሉዝ
መንግስት አሌተሊክሁም» አሌሁ።

«ምነው የራስ እምሩ ጦር ሽሬ ዴሌ ከሆነ በሁዋሊ፥ ወዯ ሱዲን ተሌከህ አሌሄዴህም?»

«መዴሀኒትና ሇወታዯር ሌብስም ዴንኩዋንም የሚሆን ካኪ ከገብያ ሌገዛ ሄዯው እንጂ የጦር
ሰራዊትና የጦር መሳሪያ ውሌ ከንግሉዝ መንግስት ጋር ሇመፇራረም አሌነበረም ወዯ ሱዲን የሄዴሁ»
ስሊቸው ፇገግ ብል የነበረ ፉታቸውን ኮስተር አዴርገው ሊጭር ጊዜ ዝም ብሇው ሲመሇከቱኝ ቆዩና «በሌ
ዯግ ነው» ብሇው እዴሜየን የተወሇዴሁበትን አገርና እንዱሁም ላልችን ጥያቄዎች እየጠየቁኝ
ነግሬያቸው ከመዝገቡ በሁዋሊ አሰናበቱኝ።

ሲኞር ማርቻኖ ምዝገባቸውን እስኪጨርሱ መሽቶ ስሇ ነበረ ቀኛዝማች ‹መሊኩ ታዬን›


አስጠርተው ሁሊችንንም ወዯ ቤቱ ወስድ አሳዴሮ በማግስቱ ጥዋት እንዱመሌስሌን አስረከቡት።
ቀኛዝማች መሊኩ ታዬ የክቡር ዯጃዝማች ታዬ ጉሌሊቴ ሌጅ ነው። ሁሇታችንም በሌጅነታችን ተፇሪ
መኮንን ትምህርት ቤት ስንማር እንተዋወቅ ነበር። ነገር ግን ምንም እንኩዋ የተሇያዬንበት ጊዜ በጣም
ረዢም ባይሆን «ምናሌባት ረስቶኝ ይሆናሌ፤ ባይረሳኝም የጣሉያን ምርኮኛ ሆኘ ሲያየኝ የማያውቀኝ
መስል መታየቱን ይመርጥ ይሆናሌ» ብየ እንዯማሊውቀው ሁለ፥ አየት አዴርጌው ዝም አሌሁ። እሱም
እንዯኔ ሊንዴ አፌታ አየት አዴርጎኝ ዝም አሇ።

ያነሇት እቀኛዝማች መሊኩ ቤት የተምራን ምርኮኞች ምናሌባት ባስራ አምስትና በሀያ መሀከሌ
እንሆን ይሆናሌ። ታዱያ ሇዚያ ሁለ ሰው የቀረበው መስተንግድ፥ (መብለና መጠጡ) ባይነቱም ሆነ
በብዛቱ ባጭር ጊኤ የተሰናዲ አይመስሌም፤ ግሩም ነበር! ከራት በሁዋሊ - ምናሌባት ሁሊችንን ባንዴ ሊይ
ሇማስተኛት እንዴንተኛ ወዯየተሰናደሌን ክፌልች እንዯገባን ከቤቱ ሌጆች አንደ መጥቶ ቀኛዝማች
መሊኩ ሉያየኝ እንዯሚፇሌግ ነገረኝ። ሌጁን ተከትዬ ስሄዴ ቀኛዝማች ከሌፌኙ በራፌ ቆሞ ይጠብቀኝ
ኖሮ ገና በሩቅ ሲያየኝ አብረን እንዲሊመሸንሁለ እየሮጠ መጣና አንገቴን አቅፍ እስኪጨንቀኝ ዴረስ
እያገሊበጠ ሳመኝ። ከዚያ ወዯ እሌፌኙ ይዞኝ ገብቶ መጠጥ እንዴጠጣ ቢሇምነኝ፥ በራት ጊዜ ከጠጣሁት
በሊይ ብጨምር ጤና እንዯማሊገኝ ስሊስረዲሁት እንዱሁ ተቀምጠን እንጫወት ጀመር።

«ታውቃሇህ? እዚያ መስሪያ ቤት ካየሁህ ጀምሬ እንዱህ ብቻህን እስካገኝህ ምን ያክሌ ናፌቄ
እንዯ ሊስረዲህ አሌችሌም!» አሇኝ።

«እኔምኮ እዚያ በማሊውቀው ሰው ሁለ መሀከሌ አንተን ብቻ የማውቅህ በማግኘቴ ዯስ ብልኝ


መጥቼ ሌስምህ ፇሌጌ ነበር። ነገር ግን አሁን የምገኝበትን ሁኔታ ሳስብ፥ ‹ሊንተ አይበጅ ይሆናሌ› ብየ
ነው የተውሁት» አሌሁት። ከዚያ እሱ ስሇ ዘመቻውም ስሇ አርበኝነቱም እኔ ጣሉያኖች አዱስ አበባ ከገቡ

156
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጀምረው ስሊዯረጉት እየተጠያየቅን ብቻችንን ስናወራ ቆይተን ወዯ የምኝታችን ከመሄዲችን በፉት
በማግስቱ ሊዯርገው ስሇሚገባኝ ምክር ስጠኝ።

«ነገ ጥዋት ወዯ ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት መሌሼ እንዴ ወስዲችሁ ሲኞር ማርቻኖ አዝዘውኛሌ።
ከዚያ በሁዋሊ ምን እንዯሚያዯርጉዋችሁ ከነሱ በቀር ምቸም የሚያውቅ የሇ። እስከ ዛሬ ዴረስ እንኩዋ
ጣሉያኖች - ምናሌባት ሰው እንዲይሸሻቸው ሉሆን ይችሊሌ - ፇቅዯውም ሆነ ወይም በሀይሌ ተገዯው
በሚገቡት አርበኞች ሊይ ክፈ ሲሰሩ አሊየሁም። ነገር ግን ራስ እምሩንና የኔ አባት ወዯ ጣሉያን አገር
የወሰደዋቸው በእስረኝነት እንዯሆነ እስከ ዛሬ ይከተለት የነበረውን ፖሇቲካ ሉሇውጡ አስበው ሉሆን
ይችሊሌና፥ ነገ በናንተ ሊይ ስሇሚያዯርጉትም እርግጠኛ መሆን አይቻሌ! ስሇዚህ ሇማናቸውም ነገ ጥዋት
እነሱ እጅ ከመግባትህ በፉት እስካሁን ዯህና መሆንህንና ላሊም ሇዘመድችህ የምትሌከውን መሌእክት
የሚያዯርስሌህ፥ የታመነ ሰው እንዲሇህ ሰጥተህ ላልችን ይዤ ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት ግቢ ከመግባቴ
በፉት ዴረስብኝ» አሇኝ።

«የታመነ ሰውስ አሇኝ፤ ግን አንተን የሚያሰጋ አይሆንም?»

«ምኑ?»

«ቅዴም እንዲሌኸው ነገ የሚሆን እስኪታወቅ፥ ሇጊዜው እስረኛ ነኝኮ! ታዱያ አሳዴረህ


እንዴትመሌስ የተሰጠሁህን እስረኛ መሌቀቅህ ቢታወቅ አያሰጋህም?»

«ሇምን ይታወቃሌ? አንተ አዋጅ እየተናገርህ አትሄዴ!» አሇ በቀሌዴ እንዯ መሳቅ ብል።

«የተነገረ ነገር ምንም ቢሆን መታወቁ አይቀር!» አሌሁት።

«ግዳሇህም፤ በዚህ አትስጋ። ብቻ በሶስት ሰአት ስሇ ሆነ ግቢኢ የምንገባ በጣም በጥዋት ሄዯህ
ጉዲይህን ፇፅመህ ሇሶስት ሰአት አስር ዯቂቃ ጉዲይ እንዴትመሇስና «አንበሳ በር» ይባሌ በነበረው
የግቢው የምስራቅ በር እንዴትጠብቀኝ» አሇኝ። እክዚያ አንዴ ሌጅ ጠርቶ በጥዋት ስወጣ እንዲይከሇክሇኝ
ዘብ ሇሚጠብቀው ወታዯር ነግሮኝሌ እንዱያዴር እዘዘሌኝና እዚያው እሱ እሌፌኝ አንዴ ትንሽ ክፌሌ
ውስጥ የምተኛበት ተሰናዴቶሌኝ እዚያ አዯርሁ።

ቀኛዝማች መሊኩ ታዬ፥ አሳዴሮ እንዱመሌስ የተሰጠሁትን እስረኛ ያሊንዲች ጠባቂ ጉዲየን
ፇጽስሜ እንዴመሇስ መሌቀቁ የጣሇብኝን እምነት የማሊጎዴሌ መሆኔን ስሊመነ ይሆን? ወይስ የጣሇብኝን
እምነት አጉዴዬ ባመሌጥም በኔ ምክንያት የመጣውን ሁለ እስከ መቀበሌ ዴረስ ይወዯኝ ስሇ ነበረ
ይሆን? በማናቸው ምክንያት መሆኑን አሊውቅም። ብቻ ያም ይሁን ይህ፥ ከዚያ በሁዋሊ ባንገናኝም
እዴሜ ሌኬን ሳስታውሰው የምኖር ውሇታ ጥልኝም ቀረ።

157
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በጥዋት ተነስቼ ሇዘብ ጠባቂው ወታዯር ስሜን ነግሬ አባቴ ‹ቄስ ባዴማ ያሇው› ወዯ ሚኖሩበት
እንጦጦ ስዊዴን ሚስዮን ትምርት ቤት ሄዴሁ። ቄስ ባዴማና በሌተቤታቸው ወይዘሮ የሽመቤት ተገኝ፥
ሌጆቻቸውም ሁለ ከቤተሰቡ አባልች አንዲንዴ ይቆጥሩኝ ስሇ ነበረ መዝመቴንና ከዘመድቻቸው
አሇመመሇሴን ሰምተው ኖሮ፥ ሲያዩኝ ዯስታቸው እጅግ ታሊቅ ሆነ። እመይቴ የሽመቤትና ሌጃቸው
ወይዘሮ አዱስ አሇም ባዴማ «እሌሌ» ሲለ እዚያ ግቢ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ብዙዎች ሰምተው
ተሰበሰቡ። እቤት ገብተን ጎጃም ሇዘመድቼ እንዱተሊሇፌሌኝ የፇሇግሁትን መሌእክት ቶል ቶል አሰናዴቼ
ሊባቴ ቀኤስ ባዴማ ሰጥቼ ቁርሴን በሌቼ እርሳቸውም በኔ፥ ሊይ የሚወስዯውን ሇማወቅ ስሇ ፇሇጉ
አብረውን ወዯ ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት ሄዴን።

ከቀኛዝማች መሊኩ ጋር በተቃጠርንበት አንበሳ በር ቆመን ስንጠብቅ ቀኛዝማች መሊኩ በበቅልው


ተቀምጦ በብዙ እስረኞች ታጅቦ ዯረሰና ይዞን ወዯ ግቢ ገባ። እዚያ አንዴ ባንዴ እየተጠራን ወዯ ሲኞር
ማርቻኖ ፅህፇት ቤት ገብተን አዱስ አበባ የምንቆይበትን ቦታ እያስመዘገብን፥ ከኔ በቀር ላልች ሁለ
ያነሇት ወይም በማግስቱ የሚዋሱዋቸውን ሰዎች ይዘው ቀርበው እንዱያስፇርሙ ግዳታ እየገቡ
መውጣታችውን ነገሩኝ። እኔ ግን አባቴ ቄስ ባዴማ ቤት የምቆይ መሆኔን ካስመዘገብሁ በሁዋሊ እሳቸው
እዚያ ስሇ ነበሩ በተፇሇግሁ ጊዜ ሉያቀርቡኝ ዋስ ሆነው ፇረሙና ሌንወጣ ስንሌ፤

«ስሊንተ የመጨረሻ ሁኔታ የሚወሰነው እስኪነገርህ ዴረስ በየቀኑ - ጥዋት ከሶስት እስከ ሰባት
ሰአት ባሇው ጊዜ ውስጥ - እየመጣህ ከዘብ ጠባቂው ጋር በምታገኘው ዯብተር እንዴትፇርም!» ብሇው
ሲኞር ማርቻኖ ሇኔ ከነገሩኝ በሁዋሊ «አንዴ ቀን ሳይፇርም ቢቀር በሀሊፉነት የሚጠየቁ እርስዎ
መሆንዎን ማወቅ አሇብዎ!» አለ ወዲባቴ ቄስ ባዴማ ዘወር ብሇው። ሁዋሊ ጠይቄ እንዯ ተረዲሁት
ከጅማ አብረን ከመጣን እሰረኞች መሀከሌ በየቀኑ እንዱፇርም የታዘዘ ከኔ በቀር አሌነበረም።

አባቴ ቄስ ባዴማና እኔ ከፖሇቲካ ፅህፇት ቤት ወዯሳቸው ቤት እንዯ ተመሇስን አቶ «ብርሃኑ


ወንዴምና» አቶ «መኯንን ቸኮሌ» የኔን ወሬ ሰምተው መጡ። ከሁሇቱም ጋር ሇከፌተኛ ትምርት ወዯ
«በይሩት» እስኪሄደ ዴረስ ከሚሲዮን ትምህርት ቤት እስከ ተፇሪ መኮንን ትምህርት ቤት ዴረስ አብረን
ስንማር የኖርን፥ ጉዋዯኞች ነበርን። ከበይሩት ሲመሇሱ እኔ ጎጃም በስራ ሊይ የነበርሁ በመሆኔ፥ ገና
ያነሇት መገናኘታችን ስሇ ነበረ ከጦርነቱ በዯህና ተመሌሼ ሲያዩኝ በጣም ነበር ዯስ ያሊቸው።

ብርሃኑና መኮንን፥ ባንዴነት ትንሽ የሻይ ቤት ከፌተው ቄስ ባዴማ ከሚኖሩበት የሚሲዮን


ትምርት ቤት ጎረቤት ስሇ ነበረ የሚኖሩ የወዯፉት እየጣየ እስኪጣሌ፥ ምግቤ ከነ ቄስ ባዴማ ቤት ሆኖ
ምኝታየ ከነሱ ጋር እንዱሆን በመሀከሊችን ስምምነት ተዯረገ። ከዚያ በየቀኑ ወዯ ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት
እየሄዴሁ እየፇረምሁ፥ ካባቴ ቄስ ባዴማና ከሁሇቱ ጉዋዯኞች ጋር አንዴ ሳምንት ያሌሞሊ ጊዜ አዱስ
አበባ እንዯቆየሁ አንዴ እሁዴ አባቴ ቄስ ባዴማ ከቤተ ክርስቲያን ሲመሇሱ «የመጨረሻ ሁኔታየን
ውሳኔ» የሚያመሇክት ወሬ ይዘውሌኝ መጡ።

158
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ጣሉያኖች ሌጅ ይሌማ ዯሬሳንና አንተን ወዯ ጣሉያን አገር ሉወስደዋቸው መወሰናቸው
ይወራሌ። ከግንሉዞች የተገኘ ወሬ ስሇ ሆነ እርግጥ ነው» አለኝ። በንግሉዝ ሇጋሲዮንም በንግሉዝ
ቆስሊም አሰርጉዋሚዎችና የቅርብ ረዲቶች እየሆኑ ይሰሩ ከነበሩት ብዙ ጊዜ በሚሲዮን ትምርት ቤት
የተማሩ ስሇ ነበሩ፥ እንግሉዞች የሰሙትን ሲያካፌለዋቸው እነሱም በበኩሊቸው ሇኢትዮጵያውያን
የሚሲዮን መምህራን ያካፌሊለ። ስሇዚህ ስሇኛ የተወራውም ያን የተሇመዯ መንገዴ ተከትል የመጣ ወሬ
ሉሆን ይችሊሌ።

«ሇመሆኑ ከብዙ ባሇስሌጣኖችና የተማሩ ሰዎች መሀከሌ ሁሇታችን ብቻ ተሇይተን ወዯ ጣሉያን


አገር የምንወስዴበት ምክንያትስ ታውቆ ይሆን?» አሌሁ፤ ወሬው ስሊስዯነገጠኝ ትንሽ ዝም ብዬ ቆይቼ።

«ሌጅ ይሌማ በውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ካይነተኞች ሹማምንት መሀከሌ የነበረ ከመሆኑ ላሊ ራስ
እምሩ እጃቸውን ሇመስጠት ከጣሉያኖች ጋር ንግግር ባዯረጉ ጊዜ ዋና አማካሪያቸው የነበረ ስሇሆነ፥
አንተ እንግሉዞች ርዲታ እንዱያዯርጉሊቸው ራስ እምሩ ሌከውህ ወዯ ሱዲን ሄዯው ስሇ ነበረ ነው
ይባሊሌ» አለኝ።

«ስማ ሀዱስ» አለ አባቴ ቄስ ባዴማ ትንሽ ዝም ብሇው ሲያስቡ ቆይተው ቀና አለና። «ዛሬ
ማታ ወዯ ‹ውጊያ› ሌውሰዴህና ዘመድችዋ በሚያውቍት አሌባላ መንገዴ አባይን አሽግረው አገርህ
ጎጃም እንዱያገቡህ እንዴታዯርግ ሌንገራት። ከዚያ በሁዋሊ ብትፇሌግ ወዯ ሱዲን ትሄዲሇህ ያሇዚያም
ጫካ ውስጥ ካለት አርበኞች ጋር ተጨምረህ እነሱ እንዯ ሆኑት ትሆናሇህ!» ‹ወይዘሮ ወጊድ› የሚባለት
ሱለሌታ የሚኖሩ ሇቄስ ባዴማ ቤተሰብ የረዥም ጊዜ ወዲጅ ስሇ ነበሩ የጠየቁዋቸውን ሁለ
እንዯሚያዯርጉሊቸው ያምኑ ነበር።

«እንኩዋንስ ጠፌቼ ‹አንዴ ቀን ሳሌፇርም ብቀር በሀሊፉነት እንዯሚጠየቁ› ሇኔ ዋስ ሆነው


ሲፇርሙ እኒያ የጣሉያኑ ሹም ያስጠነቀቁዎን ረሱት እንዳ» አሌሁዋቸው።

«አሌረሳሁትም። ታዱያ አንተ ብትጠፊ እኔን ምን የሚያዯርጉኝ መሰሇህ? ስሊንተ ጣሉያን አገር
ወስዯው የሚያስሩኝ መሰሇህ?»

«ስሌጣን ሁለ በጃቸው ነው፤ ከፇሇጉ ዛሬ ሇማዴረግ የማይችለት ነገር ምን አሇ? እንኩዋንስ


ጣሉያን አገር ወስድ ማሰር ቢገዴለስ ማን ጠያቂ አሇባቸው?»

«አይምሰሌህ ምንም አያዯርጉኝ! አየህ? የሚሲዮን ሰራተኛ ስሇሆንሁ እዚህ ግቢ ውስጥ ገብተው
እኔን አንዴ ነገር ቢያዯርጉኝ ሚሲዮናችንን ብቻ ሳይሆን የስዊዴንን መንግስት ጭምር የሚያሳዝን
ይሆናሌ። ስሇዚህ፥ ዛሬ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛታቸው መሆንዋን ብዙ መንግስታት እንዱያውቁሊቸው

159
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በሚፇሌጉበት ጊዜ አንተ በመጥፊትህ ብቻ የስዊዴንን መንግስት የሚያሳዝን አንዲች ነገር የሚያዯርጉ
አይመስሌህ!» አለና አሁንም ትንሽ ዝም ብሇው ቆይተው፥

«ዯግሞ ምንም አያዯርጉ እንጂ ቢያዯርጉስ እኔኮ ያገሌግልት ዘመኔን ወዯ መጨረሻ አዴርሼ
ሞት መጥቶ እስኪወስዯኝ በመጠባበቅ ሊይ ያሇሁ ሽማግላ ነኝ! እናንተ ግን ያገሌግልት ዘመናችሁን
ሇመጀመር ገና በመሰናዲት ሊይ ስሇሆናችሁ ሇሀገራችሁና ሇወገናችሁ ተስፊዎች ናችሁና የናንተ ህይወት
መጠበቅ ይገባሌ። ከንግዱህ ወዱያ ያሇው የኛ ህይወት ዋጋም የሇው። ስሇዚህ ማታ እወስዴሀሇሁና
ተሰናዲ» አለኝ አሳባቸውን የማሌቀበሌ መሆኔን ወዱያው ሌነገራቸ ብፇሌግ ስሜቴ ስሇ ታወከብኝና
እንባየ ስሇ ተናነቀኝ መናገር ባሇ መቻላ ዝም ብዬ ቆየሁ። ከዚያ ትንሽ ፀጥ ስሌ «እንዱህ ያሇውን አሳብ
አሌቀበሌምና ዲግመኛ እንዲያስነሱብኝ!» አሌሁዋቸው።

«እንዳት?»

«የርስዎ ህይወት የብዙ ሰው ህይወት ነው እንጂ የርስዎ ብቻ አይዯሇምኮ! አያርገውና እርስዎ


አንዴ ነገር ቢሆኑ ብዙ ሰው መጠጊያ ያጣሌ! ስሇኔም የሆነ እንዯ ሆነ እንዴኖር የእግዚአብሔር ፇቃዴ
ከሆነ ጣሉያን አገር ስሇ ተወሰዴሁ አሌሞት! ስሇዚህ በኔ ወዯ ጣሉያን አገር መወሰዴ አይጨነቁበት»
ብየ በውሳኔየ ስሇ ፀናሁና ቢቆጡኝም ቢያባብለኝም አሳቤን የማሌሇውጥ ስሇሆንሁ ተቆጥተው ትተውኝ
ሄደ።

በማግስቱ ይሁን በሳሌስቱ - ቀኑን ረስቸዋሇሁ - ሌፇርም ወዯ ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት በሄዴሁበት


ከዚያ በሚከተሇው ቀን «በሶስት ሰአት የፖሇቲካው ዋና ሹም «ማጆሬ ፓርሊቨቸኒ» ሉያዩኝ ስሇሚፇሌጉ
ቀዯም ብዬ እዚያ እንዴዯርስ ተነገረኝ። በተቀጠርሁበት ቀንና ሰአት ፖሇቲካ ፅህፇት ቤት ዯርሼ
ሹማምቱ ገና ስሊሌገቡ ቆሜ ስጠብቅ ሌጅ ይሌማ ዯሬሳ መጣ። እሱንም እንዯኔ፥ ማጆሬ ፓርሊቪቸኒ
እንዲስጠሩት ሲነግረኝ ሇምን እንዲስጠሩኝ ያውቅ እንዯሆነ ብጠይቀው እንኩዋንስ የሚያውቀው በግምት
የሚጠረጥረው እንኩዋ አሇመኖሩን ነገረኝ። ጣሉያኖች እሱንና እኔን ወዲገራቸው ሉወስደን
መወሰናቸውን - ከእንግሉዞች የተገኘ ወሬ ነው ብሇው - አባቴ ቄስ ባዴማ ከሁሇት ይሁን ከሶስት ቀን
በፉት ነግረውኝ እንዯ ነበረ ስነግረው ማመኑም አሇማመኑም አስቸግሮት ዝም ብል ሲያስብ ቆይቶ፥

«ታዱያ አመንህ?» አሇኝ።

«እስከ ዛሬ ጥርጥር ነበረኝ ዛሬ ግን አመንሁ» አሌሁት።

«ሇምን?»

«በቀዴመ አባቴ ቄስ ባዴማ ሁሇታችን ሌንወሰዴ መወሰኑን ነግረውኝ ዛሬ ሁሇታችን ባንዴ ሊይ


ስሇ ተጠራን።»

160
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እውነት ነው፤ ይመስሊሌ» አሇ። ትንሽ ቆይተን ተጠራን።

ስንገባ «ማጆሬ ፓርሊቪቺኒ» ከክፌሊቸው መሀከሌ ቆመው ነበር። ሇሁሇታችንም የጅ ሰሊምታ


ከሰጡን በሁዋሊ፥

«ይሌማ ዯሬሳ ማንኛችሁ ናችሁ?» አለ፤ ፇገግ ብሇው።

«እኔ ነኝ» አሇ ሌጅ ይሌማ።

«በሇንዯን የኢኮኖሚ ትምርት ቤት የኢኮኖሚክ ሳይንስ ምሩቅ መሆንህን አውቃሇሁ፤ አንተም


ሀዱስ አሇማየሁ መሆንህን አውቃሇሁ። ኑ፥ ተቀመጡ፤ ወዲጆቼ» ብሇው ከጠረጴዛቸው ፉት በነበሩ
ሁሇት ወንበሮች አስቀምጠውን ዞረው በወንበራቸው ተቀመጡ። እንግሉዝኛ ሲናገር የሰማቸው
«እንግሉዛዊ አዯለም» ቢለት ሉያምን አይችሌም፤ እንዯ ተማሩ እንግሉዛውያን ፇፅሞ የጠራ እንግሉዝኛ
ነበር የሚናገሩ። ቡና ይሁን ሻይ አዝዘውሌን ስንጠጣ ስሇ ተጠራንበት ጉዲይ ከመንገዴ የወጣ መጣጣርና
ክፈ ስራችውን በጎ ሇማስመሰሌ ይቀባቡት የነበረው የውሸት ቀሇም ሁለም ውሸት መሆኑን ይብስ
አጉሌቶ ያሳያቸው ነበር።

«ኢትዮጵያ» አለ ማጆሬ ፓርሊቪቸኒ፥ «ኢትዮጵያ የጥንታዊኢ ስሌጣኔና ባህሌ ባሇ ፀጋ የሆነች


አገር ስሇ ሆነች፥ እንዯ ላልች የአፌሪቃ አገሮች ስሊሌሆነች ኢጣሉያ፣ እንዯ ላልች የአውሮፓ ገዢዎች
ህዝብዋን ሇመግዛትና ሀብትዋን ሇመዝረፌ የመጣች አሇመሆንዋን የኢትዮጵያ ህዝብ በተሇይ እናንተ
የተማራችሁት እንዴታውቁሌን እንፇሌጋሇን። የኢትዮጵያን ጥንታዊ ስሌጣኔ ተባብረን አዴሰን፥ ያሌሇማ
ሀብትዋን ተባብረን አሌምተን የጋራ ሇመጠቀም ነው የምንፇሌግ። ተባብሮ ሇመስራት ዯግሞ፥ የሁሇቱን
ወገኖች የጣሉያኖችንና የኢትዮጵያን መግባባትና መተማመን ያስፇሌጋሌ። ስሇዚህ የኢትዮጵያ ታሊሊቅና
የተማሩ ሰዎች፥ ከታሊቁ ንጉሳችንና ከመሳሪያችን ከሙሶሉኒ ጋር እየተገናኙ የጣሉያን መንግስት
ኢትዮጵያን ሇመጥቀም እንጂ ሇመጉዲት ፌፁም የማይሻ መሆኑን ከነሱ ከንጉሱና ከሙሶሉኒ አፌ ሲሰሙ
እንዯሚያምኑ ስሇ ታውቀ ነው፥ አሁን ራስ እምሩና ዲጃች ታዬ ተጋብዘው ወዯ ጣሉያን አገር የሄደ።
ራስ እምሩና ዯጃች ታዬ ከንጉሱና ከሙሶሉኒ ጋር ተገናኝተው የጣሉያን መንግስት አሳብ ከተገሇፀሊቸው
በሁዋሊ በጣሉያን አገር የተሰራውን ሌዩ ሌዩ ዘመናዊና ታሊሊቅ ስራ እየተዘዋወሩ አይተው ሲመሇሱ
ከነሱና እንዯስነሱ በየጊዜው እየተጋበዙ የጣሉያንን ስራ ጎብኝተው ከሚመሇሱት ኢትዮጵያውያን ጋር
ተባብረን ኢትዮጵያን ባጭር ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ አገር ሌታዯርጋት ነው የምንፇግሌ።

«ራስ እምሩና ዯጃች ታዬ ጣሉኢያን አገር እንዯ ዯረሱ ይህ ሁለ ተገሌፆሊቸው ከተማሩት ሰዎች
መሀከሌ ከነሱ ጋር ንጉሱንና የመንግስቱን መሪ ሙሶሉኒን ተገናኝንተው በጣሉያን አገር የተሰሩትን
የሌማት ስራዎች ጎብኝተው ሲመሇሱ እዚያ ባዩት አይነት ከኛ ጋር ተባብረው አገራቸውን ሇማሌማት
ፌሊጎትም ችልታም ያሊቸውን ሰዎች ስም እንዱሰጡ ተጠይቀው የናንተን የሁሇታችሁን ስም ስሇ ሰጡ

161
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ነው፥ እነሱ ወዲለበት እንዴትሄደ አሁን የጠራናችሁ። በጣሉያን አገር ተወሌዯው ኖረው እስኪሞቱ
ዴረስ ከንጉሱና ከሙሶሉኒ ፉት ቀርበው ሇመነጋገር የታዯለ ምን ያክሌ ጥቂት ይመስለዋችሁዋሌ!
እናንተ ግን ይኸው ሳትፇሌጉ ተፇሌጋችሁ ከታሊቁ ንጉሳችንና ከታሊቁ መሪያችን ከሙሶሉኒ ጋር
ተገናኝታችሁ ሌትነጋገሩ ነው! በውነት እዴሇኞች ናችሁ! ራስ እምሩና ዯጃች ታዬ እናንተ
እስክትዯርሱሊቸው እየጠበቁ ከንጉሱና ከሙሶሉኒ ጋር ገና አሌተገናኙምና ቶል መሄዴ አሇባችሁ።

«ከምፅዋ በመርከብ ተሳፌራችሁ ወዯ ጣሉያን አገር ስትሄደም ጣሉያን አገር ስትዯርሱም


የሚያስፇሌጋችሁ ገንዘብ ተሰናዴቶ ይጠብቃችሁዋሌ። ግን እስከ ምፅዋ ኪሳችሁ ባዲ እንዲይሆን ያክሌ፥
ትንሽ ገንዘብ ያስፇሌጋችሁ ይሆናሌ» አለ የፖሇቲካው ዋና ሹም የፖሇቲካ «ሀ. ሁ» የማያውቅ
መሀይም በማያምነው ረዢም ስብከታቸው ካሰሇቹን በሁዋሊ።

«እግዚአብሄር ይስጥሌን፤ ሁሇታችንም የኪስ ገንዘብ አሇን» አሇ ሌጅ ይሌማ ምንም እንኩዋ


የኔን አሳብ ባያውቅ ስሇ ራሱም ስሇ እኔም ሆኖ። እውነትም ሁዋሊ እስበሳችን ስንነጋገር እንዯ
ተገሊሇፅነው፥ እኔ ትንሽ እሱ ከኔ የተሻሇ ገንዘብ ነበረን። ስሇዚህ ይሌማ የፖሇቲካውን ሹም «ገንዘብ
አሇን፤ የርስዎን የኪስ ገንዘብ አንፇሌግም» ሲሊቸው በጣም ነበር ዯስ ያሇኝ! ነገር ግን እሳቸው
ጉርሻቸውን ሊሇመቀበሌ የፇሇግንበት በኩራት መንፇስ መሆኑን አውቀው ይሁን ወይም ሳያውቁ
እንዴንቀበሌ አስገዯደን።

«የነበራችሁበትን ስሇማውቅ ገንዘብ እንዯላሊችሁም አውቃሇሁ! ስሇዚህ አስመራ ስትዯርሱ


የፇሇጋችሁትን ያክሌ ገንዘብ እንዱሰጡዋችሁ ሊገረ - ገዡ አሁን በስሌክ እነገራቸዋሇሁ፤ እስከዚያ ዴረስ
ኪሳችሁ ባድ እንዲይሆን ይህን ተቀበለኝ እባካችሁ ወዲጆቼ» ብሇው አምስት መቶ ሉሬ የያዘ እጃቸውን
ሇይሌማም ሇኔም በየተራ ሲዘረጉ ሇመናው አብቅቶ ትእዛዝ እንዲይመጣ ፇርተን ተቀበሌንና ወዯ ጣሉያን
አገር የምነሳበት ቀን ተነግሮን ወጣን።

ምእራፍ ሃያ ሁለት

ካዲስ አበባ እስከ ፓንዛ


ሌጅ ይሌማ ዯሬሳና እኔ በጥር 1929 ምርኮኞች ሁለ ተሇይተን በግዞት ወዯ ጣሉያን አገር
ሌንወስዴ መወሰኑ ሲሰማ ዘመድቻችንና ወዲጆቻችን ብቻ ሳይሆኑ በሩቅ፥ ከሚያውቁን መሀከሌም፥
ብዙዎች አዝነውሌን ነበር። ትንሽ ቆይቶ በየካቲ 12 1929 ማርሻሌ ግራሲያኒን ሇመግዯሌ ሙከራ
ከተዯረገ በሁዋሊ የምርኮ ጉዋዯኞቻችን ሁለ በመብራት እየተፇሇጉ ተሇቅመው ማሇቃቸው ሲታይ ግን
የኛ ቀዯም ብል በግዞት ከኢትዮጵያ መውጣት መዲኛችን ሆኖ በመገኘቱ እኛንም አዝነውሌን የነበሩትን
ሁለም አስገረመን! ከክቡር ራስ እምሩና ከከንቲባ ጋሻው ጠና ጋር ከነበሩት መኩዋንንትም ከሆሇታ
መኮንኖችና ከፇርንጅ አገር ከተመሇሱት ምሁራንም፥ ከጅማ አዱስ አበባ እንዯ ገቡ ወዯ ባሊገር ሸሽተው

162
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወይም ከዘመዴ ቤት ተሸሽገው ካመሇጡት አንዲንዴ በቀር ሁለም አሇቁ! ሌጅ ይሌማና እኔ ፖንዛ
ከዯረስን በሁዋሊ ነበር ማርሻሌ ግራሲያኒ አዯጋ ተጥለባቸው መቁሰሊቸውን የሰማን።

በጥር 1929 እኩላታ ግዴም በጣም ጥዋት ጀንበር ከመውጣትዋ እንኩዋ በፉት በአይሮፕሊን
ካዱስ አበባ ተነስተን መስሪኢያ ቤት ተዘግቶ ከሰባት ሰአት በሁዋሊ አስመራ ዯረስን። (በዚያ ጊዜና ባሁን
መሀከሌ አይሮፕሊኖች የጨመሩት ፌጥነት የሚያስገርም መሆኑን ይህ ያሳያሌ!) አስመራ መስሪያ ቤት
እስኪከፇት ወዯ ጦር ሰራዊት ሰፇር ተወስዯን እዚያ ሲጠብቀን እንዱቆይ የተረከበን ወታዯር እስከ ዛሬ
ዴረስ ሉገባኝ ምክንያት ሲያስቸግረን የቆየውን አሌረሳውም!

ከአይሮፕሊን ማረፉያ እስከ ጦር ሰራዊት ሰፇር በካሚዮን የወሰዯን የጣሉያን የጦር መኮንን
ከካሚኢዮን አውርድ ሇወታዯሩ በጣሉያንኛ የነገረውን ነግሮት ስሇኛ ካዱስ አበባ ያመጣውን ወረቀትም
ሰጥቶት ከሄዯ በሁዋሊ ያ ወታዯር አንዴ ትንሽ ቤት ከፌቶ እዚያ እንዴንገባ በቁጣ አዘዘን። ቤቱ
የሲሚንቶ ሸክሊ የተነጠፇ ከመሆኑ በቀር የላሊ ምንጣፌ ወይም የወንበር ምሌክት አይታይበትም፤ ፌፅም
ባድ ነበር!

«ተቀመጡ!» አሇ ወታዯሩ በቁታ።

«እዚህ እግራችንን አጥፇን ሇመቀመጥ ስሇሚኢያስቸግረን እባክህ ወንዴሜ ውጪ እዯረጃው ሊይ


እንቀመጥ» አሇው ሌጅ ይሌማ።

«ተቀመጡ ብያሇሁ፤ ውጪ አትወጡም!»

«እንግዱያው ውጪ መውጣታችን የሚያስፇራ ከሆነ በሩን ይዝጉብንና ባይሆን መቀመጣችን


ቀርቶ እዚሁ እንቁም» አሌሁ፤ አስታራቂ አሳብ ያገኘሁ መስልኝ።

«ማነው እናንተን የሚፇራ! እኔ ነኝ እናንተንም የምፇራ? ተቀመጡ አሁን!» አሇ ቁታው


ይብሱኑ ግል ግል የጠመጃውን አፇሙዝ አስቀዴሞ ወዯኛ እየመታ። ያን ጊዜ ሰውዬው ክፈ ነገር
ሇማዴረግ ምክንያት የሚፇሌግ መል ስሇ ታየን ምንም ሳንመሌስ እዚኢያ ሲሚንቶ ወሇሌ ሊይ
እግራችንን ዘርግተን ተቀመጥን። እሱም እየተሳዯበ ቤቱን ዘግቶ ወጣና እዯጅ ይንሸራሸር ጀመር።
እንዱያ ሲንሸራሸር ይቆይና በቤቱ መስኮት አንገቱን አስገብቶ ሰዴቦን ይሄዲሌ። ብዙ ጊዜ እየተመሊሇሰ
ሲሰስቡን ከቆዩ በሁዋሊ እንዯ ገና በሩን ከፌቶ ገብቶ፥

«ንጉስ ሀይሇ ስሊሴ ተሸንፇው አገር ሇቀው ሲሄደ እናንተ የጣሉያንን መንግስት ሌታሸንፈ ነው
ሽፌቶች የሆናችሁ? እናንተ ርጉማን?» አሇ፥ እግራችንን ዘርግተን እንዯ ተቀመጥን ከፉታችን ቆሞ።

«ተነሱ!» አሇ ቀጥል። ስንነሳ፥

163
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ውጡ!» አሇ በሁዋሊችን እንዯ ሆነ የጠመንጃውን አፇሙዝ ወዯኛ አዴርጎ። ወጥተን እበረንዲው
ሊይ ቆመን ተከታዩን ትእዛዝ ስንጠብቅ፥

«ዯረጃው ሊይ ተቀመጡ!» አሇ መጀመሪያ እንዯ ሇመንነው። እንዲዘዘን እዯረጃው ሊይ ስንቀመጥ


እሱ ዯረጃውን ወርድ እታች ብቻውን በትግርኛ እየተናገረ ሲንሸራሸር ከቆየ በሁዋሊ ወዯኛ መጥቶ
በፉታችን ቆመና ላሊ ሰው እንዲይሰማው የፇራ ይመሌስ ጎንበስ ብል አፈን ወዯኛ ቀረብ ዴምፁን ዝቅ
አዴርጎ፥

«አንተ!» አሇ። «አንተ! የናንተ ጌታ የናንተ ንጉስ ሀይሇ ስሊሴና እናንተ ርጉማን ሁለ ብዙ ሽህ
አመታት ነፃ ሆና የኖረችውን አገር ኢትዮጵያን የጣሌያን ግዛት አዯረጋችሁ፤ የኢጵያን ህዝብ የጣሉያን
ባሪያ አዯረጋችሁ። ኢትዮጵያን ነፃ እንዯ ሆነች ቆይታ ስትሰሇጥንና ስትበረታ እኛን ጭምር ረዴታ
አብረን ነፃ ሆነን እንዴንኖር ተስፊ ነበረን። አሁን ንጉሳችሁ ሀይሇ ስሊሴን እናንተ የኢትዮጵያን ነፃነትም
የኛን ተስፊም ባንዴ ሊይ አጠፊችሁ! እዝግሄር ያጥፊችሁ!» አሇ ቁጣው በፉቱ ሊይ እንዴ እሳት ሴንዴ
እየታየ። እንዱያ ጎንበስ ብል በዝቅተኛ ዴምፅ ሇኛ ሲናገር ምንም እንኩዋ ባቅራቢያው ላሊ ሰው ባይኖር
የፇራው ነገር እንዯ ነበረ ሁለ በየቅፅበቱ ቀኝና ግራ እየተገሊመጠ ያይ ነበር! ትንሽ ቆይቶ መስሪያ ቤት
የሚከፇትበት ጊዜ ዯርሶ አንዴ ትንሽ ካሚዮን የሚነዲ ሰው መጥቶ ያው ሲነዘንዘን የዋሇው ወታዯው
እጅቦ ወዲገረ - ገዡ ፅህፇት ቤት ወሰዯን።

ሹማምንቱም ላልች ሰራተኞችም ወዯየ ፅህፇት ቤታቸው የሚገቡ ባሇ ጉዲዮች ተቀምጠው ተራ


በሚጠብቁበት ክፌሌ አሌፇው ስሇ ነበረ እዚያ እንዯ ተቀመጥን አንዲንዴ ሹም አሌፍ በሄዯ ቁጥር፥

«ተነሱ፤ ባሇጌ!» ይሇናሌ ወታዯሩ ባጠገባችን ቆመ።

እዚያ ከተቀመጡት መኩዋንንት መሀከሌ አንዴ የማውቃቸው የትግራይ ወይም የኤርትራ


መኮንን ነበሩ። እኒያ መኮንን በሽሬ ግንባር እጦርነት ሊይ በነበርንበት ጊዜ በራሳቸው ስም ይሁን ወይም
ከላሊ ሰው ተሌከው ክከቡር ራስ እምሩ ጋር ሉነጋገሩ መጥተው ጥቂት ቀናት ሇብቻ እየተገናኙ ሲነጋገሩ
ቆይተው እስኪሄደ እንተያይ ነበር። ባሌሳሳት ስማቸው ፉታውራሪ ወሌዯ ስሊሴ ይመስሇኛሌ።
ፉታውራሪ ወሌዯ ስሊሴ ያን ያስቸግረን የነበረውን ወታዯር ጠርተው ምን እንዯ ነገሩት አናውቅም፤
ወዯኛ እያመሇከቱ የነገሩትን ከነገሩት በሁዋሊ «ተነሱ ተቀመጡ!» እያሇ ማስቸገሩን ተወንና አርፇን
ቆየን። ከዚያ እኛን ጉዲይ የሚመሇከቱት ሹም ስሊስጠሩን ወታዯሩ ይዞን ገብቶ ካዱስ አበባ ያመጣን ሰው
ከሰጠው ወረቀት ጋር አቀረበን።

ሹም ካዱስ አበባ የመጣውን ወረቀት ካዩ በሁዋሊ ወዯ ጣሉያን አገር የምትሄዯዋ መርከብ፥


ያንሇት ማታ ከምፅዋ ስሇምትነሳ፥ ከመነሳትዋ በፉት ሇመዴረስ ቶል ሇመሄዴ እንዲሇብን አዘዙ። ያ፥
ሲነዘንዘን የዋሇው ወታዯር እስከ ምፅዋም አጅቦ ወስድ እዝያ ሇሚያረከቡን ሰዎች እንዱያስረክብ ጠይቆ

164
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ነበር። ወታዯሩ ሹሙን የጠየቀው በጣሉያንኛ ስሇ ነበረ ምን እንዯ ተናገረ እኔን አሌገባኝም ነበር። ሌጅ
ይሌማ ግን ከኔ የተሻሇ ፇረንሳይኛ ያውቅ ስሇ ነበረና! ጣሉያንኛ ሇፇርንሳይኛ ቅርብ በመሆኑ ሰውዬው
የጠየቀው ከሞሊ ጏዯሌ ገብቶት ኖረዋሌ። ስሇዚህ፥ ያ ሰው ሲያስቸግረን የዋሇ መሆኑን ገሌፆ፥ እክሰ
ምፅዋ ላሊ ጠባቂ እንዱያዯርጉሌን ሹሙን በፇረንሳይኛ ስሇ ጠየቃቸው ወታዯሩን ተቆጥተው
ከቢሮዋቸው አስወጥተው ትርፌ አጃቢ ሳያስፇሌ መሳሪያ ያሇው ሰው በኦቶመቢሌ እንዱያዯርሰን ስሇ
ተወሰነ ማእርጉ ምን እንዯ ሆነ የማሊስታውሰው የጣሉያን የወታዯር ሹም እንዱወስዯን ታዘዘ።

ካስመራ እስከ ምፅዋ የሄዴንበት ኦቶመቢሌ በነጂውና ሁውሊ በተቀመጥነው በኛ መሀከሌ ያሇው ቦታ
ጥይት ሉሰብረው በማይችሌ መስትዋት የተዘጋ ነበር። እንዱሁም በቀኝና በግራችን ያለት መስኮቶች
ጥይት ከማይሰብረው መስትዋት የተሰሩ ሆነው ስሇ ተዘጉ አየር አናገኝም ነበር። ነጂው ብቻ በጎኑ
ያሇውን መስኮት ከፌቶ ሇኛ አያስተርፌሌንም እንጂ፥ ሇራሱ አየር እንዯ ሌብ ያገኘ ስሇዚህ ያ ነጂ
መትረየሱን ባጠገቡ አስቀምጦ መርከብዋ የምነሳበት ጊዜ ሳይዯርስ ምፅዋ ሇመዴረስ ሲዯርስ ሙቀቱ
የበረታ በሄዯ መጠን ሌጅ ይሌማም እኔም ሰውነታችን ታውኮ ተቸገርን። ይሌቁንም እኔ የቅሌሽሌሽ
ስሜት ስሇ ፀናብኝ መታገስ አቅቶኝ በኛና በነጂው መሀከሌ ያሇውን መስተዋት አጥር መሊሌሼ ስመታ
ነጂው ኦቶመቢለን ከመንገደ ዲር አቁሞ መትረየሱን ይዞ መጣና ከውጪ የተቆሇፇውን የኦቶመቢሌ በር
ከፌቶ ራስኑ ነቅነቅ እያዯረገ በጣሌያንኛ ተናገረ። እኔ ያን ጊዜ አንዴ የጣሉያን ቃሌ አሊውቅም ነበር።
ነገር ግን የነጂው አነጋገር በራሱና በጁ ያሳያቸው ከነበሩት ምሌክቶች ጋር «ምን ትፇሌጋሊችሁ?»
የሚሌ ጥያቄ መሆኑን ገምቼ እኔም ባፋና በጄ የ«እውኪያ» ምሌክት አሳየሁት። ያን ጊዜ ቶል በሩን
በሰፉው ከፌቶሌን ወዯ ሁዋሊ ፇንጠር ብል ቆሞ እንዴንወጣ ምሌክት ሰጠን። ወጠውን ንፁህ አየር
እየተነፇስን ትንሽ እንዯ ቆየን ዯህና ሆነን ማቅሇሽሇሹንም ተወኝ። ግን በሱ ፇንታ ብርቱ ራብ ተሰማኝ።
ያነሇት ከነጋ ጀምሮ ሌጅ ይሌማም እኔም ምንም አሌቀመስን፤ ባድ ሆዲችንን ነበርን። ወዱያው ጥዋት
እኔ ፉቴን ስታጠብ ከጏዋዯኞቼ ከብርሃኑናን ከመኮንን አንደ «ትንሽ አርፊችሁ እህሌ የምትቀምሱበት
እዴሌ ያጋጠማችሁ እንዯሆነ «ሳንዴዊች» እዚህ በሽንጣህ ኪስ አስቀምጠንሊችሁዋሌ» ያሇኝ ትዝ አሇኝ።

«አሌራበህም? እኔን በጣም ራበኝ!» አሌሁት ሌጅ ይሌማን።

«ቢርበኝ ምን ሊዴርግ እችሊሇሁ እንጂ እኔንም ርቦኛሌ» አሇ።

«ጥዋት ጉዋዯኞቼ ሳንዴዊች በሻንጣየ ውስጥ ያስቀምጡሌን መሆናቸውን ነግረውኝ ነበር፤ እስቲ
አውጥተን እንዴንበሊ ይፇቅዴሌን እንዯሆነ ይህን ሰውየ እንጠይቀው» አሌሁት።

«በምን ቁዋንቁዋ እንጠይቀዋሇን? ፇረንሳይኛ ያውቅ ይሆን?» አሇና በፇረንሳይ ሉያነጋግረው


ቢሞክር ሰውየው ራስኑ ነቀነቀ። ከዚያ እኔ የሰው ዘር ሁለ በሚግባባበት ቁዋንቁዋ በጥቅሻ ስሌጠይቀው

165
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሰብሁና ሻንጣየ በኦቶመቢለ የእቃ መጫኛ ሊይ ስሇ ነበረ፥ ወዯሱ እያመሇከትሁ በእጄ የመጉረስ ባፋ
የማሊመት ምሌክት ሳሳየው ሰውየው እየሳቀ ሰአቱን አይቶ አውርዯን እንዴንበሊ ፇቀዯሌን።

ሻንጣውን አውርጄ ስከፌት ተከዴኖ ሇብቻው በሻንጣው ኪስ በተቀመጠ እቃ አራት ከጠጠበሰ


ስጋና ከሰሊጣ ተዯባሌቆ የተሰናዲ ሳንዴዊች አገኘሁ። ከዚያ ይሌማና እኔ አንዲንዴ ይዘን ሁሇቱን ከነቃው
ሇጣሉያኑ ስናቀርብሇት መጀመሪያ እሱም አንደን አንስቶ ላሊውን እኛ እንዴንበሊው በምሌክት አሳይቶን
ነበር። ነገር ግን እሱ እንዱበሊሌን መፇሇጋችንን እኛም በምሌክት ስናሳየው እሱንም እንዯኛ ርቦት ኖሮ
እኛ አንዲንደን እሱ ሁሇቱን ባንዴ ጊዜ ጨረስን! ከዚያ በሁዋሊ ጣሉያኑና እኛ ወዲጆች ሁነን ተማመንና
አጠገባችን ከነበረች ትንሽ ወንዝ ውሀ እንዴንጠጣ በምሌክት ስንሇምነው አፇምሙዙን ወዯኛ አዴርጎ በጁ
ይዞት የቆየውን መትረየሱን በትከሻው አንግቶ አብረን ውሀ ጠጥተን ተመሇስን። ከኦቶመቢለ ውስጥ
አስገብቶ ከቆሇፇብን በሁዋሊም አየር እንዴናገኝ የመስኮቱን መስትዋት ካንዴ ወገን ትንሽ ዝቅ
አዯረገሌን። ከዚያ ምፅዋ ሇመዴረስ ምንም ያክሌ ጊዜ አሌፇጀብንም፤ ቶል ዯርሰን፤ ጣሉያን አገር
ሇሚረከበን ባሇስሌጣን ሇሚያስተሊሌፈን የመርከቡ ሹማምንት ተሰጠን።

ከምፅዋ እስከ ናፖሉ (ጣሉያን አገር) የሄዴንበት መርከብ በኢትዮጵያ ሲዋጉ የቆዩትን ወታዯሮች
ይዞ የሚመሇስ ነበር። ቁጥራቸውን በትክክሌ ባሊውቅም ወታዯሮቹ ብዙ ነበሩ። ያ ሁለ ወታዯር
የሚበሊበትና የሚተኛበት በቂ ቦታ ስሊሌነበረ ሁለም መቁነኑን በየቁናው እየያዘ ባገኘው ክፌት ቦታ
ተቀምጦ በሌቶ ክፌት ቦታ በተገኘበትና በመከቡ ጣራ ሊይ ነበር የሚተኛ። የመርከቡ የምኝታ ክፌልችና
የመብሌ አዲራሹ ሇመኮንኖች ብቻ የተመዯቡ ነበሩ። ሌጅ ይሌማና እኔ እንዯ መኮንኖች የምንተኛበት
አንዴ የጋራ ክፌሌ ተሰጥቶን መብሌ ቤት ከመኮንኖች ጋር ተስርቶሌን ነበር የምንበሊ። የወታዯሮች ዋና
አዛዥ አንዴ ኮልኔሌ ነበሩ። አዛዣቸውም «የሻምበሌ» ማእርግ የነበራቸው ቄስ ነበሩ።

ኮልኔሌ እንዯ ነገሩን ካንዯኛው የአሇም ጦርነት በሁዋሊ ከአውስትርያ ተከፌሊ ሇኢጣሌያ
የተጨመረች «ቲሮሌ» የምትባሌ አገር ተወሊጅ ነበሩ። ቄሱ ግን ቱባ ጣሉያን ነበሩ። ሁሇቱም እንግሉዝ
ዯህና አዴርገው ያውቁ ስሇ ነበረ ብዙ ጊዜ ወዯኛ ክፌሌ እየመጡ በየተራ መጠጥ አዝዘው አስመጥተው
እየጠጣን ስንጫወት እናመሽ ነበር።

በጭዋታው መሀከሌ ኢጣሉያ ኢትዮጵያን በጦርነት ይዛ ቅኝ ግዛትዋ የማዴረግዋ ነገር ሲነሳ


ቄሱ ተገቢ መሆኑን ኮልኔሌ ተገቢ አሇመሆኑን ሇማስረዲት ሲጩዋጩዋሁ ተጣሌተው የሚሇያዩ
ይመስሌ ነበር ግን አይጣለም።

የቄሱ አስተይየት ከሞሊ - ጎዯሌ «ኢጣሉያ ምንም እንኩዋ በዘመናዊው የሳይንስና የቴክኖልጂ
እውቀት ከቀዯሙት አገሮች አንዴዋ ብትሆን በህዝብዋ ብዛት መጠን መሬትዋ በጣም ጠባብ በመሆኑ
ህዝብዋን በቴክኖልጂ እንዯ ቀዯሙት አገሮች ህዝብ በምቾት ሌታኖር አሌቻሇችም። ባንፃሩ ኢትዮጵያ

166
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መሬትዋ ሰፉ ህዝብዋ ጥቲት ስሇ ሆነ ወዯ ፉትም ሇብዙ መቶ አመታት ህዝብዋ በዝቶ የመሬት ችግር
የሚያሳስባት አገር አይዯሇችም። አሁን ኢትዮጵያን የሚያሳስባት ሀብታም መሬትዋን በዘመናዊ
የሳይንስና ቴክኖልጂ እውቀት እሌምቶ የህዝብዋን ኑሮ ማሻሻሌ ነው። ስሇዚህ ኢጣሉያ ሀብትዋን
የቴክኖልጄ እውቀትዋን ይዛ ኢትዮጵያ ገብታ የሀዋርያነት ስራዋን እየሰራች የኢትዮጵያን ህዝብ
ብትጠቅምና ራስዋም ብትጠቀም ሇሁሇቱም ወገኖች ይበጃሌ እንጂ ሇማንም አይከፊም። ይህ ካሌሆነ ግን፥
ሇጣሉያን መንግስት ያሇው ማማረጫ አንዴ ብቻ ነው፤ ይኸውም ያገሩ ሀብት ሉያኖር የሚችሇውን
ያክሌ ህዝብ አስቀርቶ የቀረውን ማጥፊት! ይህ ዯግሞ በሰውም በእግዚአብሔርም ህግ የተከሇከሇ ነው!»
የሚሌ ነበር።

የኮልኔሌ አስተያየት ዯግሞ፦ እንዱሁ ከሞሊ ጏዯሌ - «ኢጣሉያ ብዙ ሀብት ያሊትና፥ ኢትዮጵያ
የላሊትን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ብዙ የጦር ሰራዊት ያሊት አገር መሆንዋ ኢትዮጵያን በጦርነት
ይዛ ቅኝ ግዛትዋ ሇማዴረግ መብት አይሰጥዋትም። እነዚህ የተባለት ምክንያቶች መብት የሚሰጡ
የሚሰጡ ከሆነ፥ ከኢጣሉያ የተሻሇ የጦር መሳሪያና የበዛ የጦር ሰራዊት ያሊቸው አገሮችም ኢጣሉያን
በጦር ሀይሌ ይዘው ቅኝ ግዛታቸው ሇማዴረግ መብት ይኖራቸዋሌ ማሇት ነው! በጠቅሊሊው ብርቱዎች
ዯካማዎችን ትሌቆች ትንሾችን ሇመግዛት ዯካማው ከብርቱ ትንሹ ከትሌቁ ጋር የሰው ማህበር
መስርተው የሚኖሩበት መሆኑ ቀርቶ ዯካማውን ብርቱው ትንሹን ትሌቁ የሚበሊለበት ያራዊት ማህበር
ይሁን ማሇት ነው! እንዱሁም ‹ኢጣሉያ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛትዋ አዴርጋ ከብዙ ህዝብዋ ከፌሊ
ሌታሳርፌትበት ካቻሇች፤ የቀራትን የቀረውን ጥፊት ብቻ ነው!› ያለት እውነት አዯሇም፤ ላሊ ማማረጫ
አሇ። ኢጣሉያ ኢትዮጵያን ሇመውረር ካጠፊችው ብዙ ሀብትዋ ትንሹን ክፌሌና የቴክኖልጂ እውቀትዋን
ይዛ ገብታ የርሻ የንደስትሪ የመገናኛና ላልችን የሌማት ስራዎች ሇመስራት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር
የመተባበርና የወዲጅነት ስምምነት ብታዯርግ በሁሇቱ ሕዝቦች መሀከሌ በጠሊትነት ፇንታ ወዲጅነትን
አትርፊ በቅኝ ገዥነት ከምታገኘው በይበሌጥ ያሊነሰ ጥቅም ታገኝ እንዯ ነበር አይጠረጠርም!» የሚሌ
ነበር።

ይህ ኢጣሉያ ኢትዮጵያን በጦርነት የመያዝዋ ነገር ሲነሳ ሌጅ ይሌማና እኔ የጭዋታው


ተካፊዮች መሆናችን ቀርቶ ተመሌካቾች በመሆን እንወስን ነበር። ኮልኔለና ቄሱ መጀመሪያ በዚህ ጉዲይ
ሊይ ሲከራከሩ ቆይተው ከሄደ በሁዋሊ፤

«እባክህ! እነዚህ ሰዎች የኢጣሉያን አሸናፉነትና የኢትዮጵያን ተሸናፉነት ካሊጡት ቦታ እኛ ዘንዴ


መጥተው የሚያወሩ ይሌቁንም ቄሱ ኢትዮጵያ የጣሉያን ቅኝ ግዛት ሌትሆን እንዯሚገባት እኛ ዘንዴ
መጥተው በዴፌረት የሚሰብኩ ሆነ ብሇው እኛን ሇማናዯዴና ሇማሳዘን ነው? ወይስ የሚያስዝን ሌብ
እንዯላሇን በዴኖች ቆጥረውን ይሆን?» አሌሁ ሳይታወቀኝ በሌጅ ይሌማ ሊይ በቁጣ አይኔን አፌጥጨ።

167
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ታዱያ ይህን ቁጣህን ማዴረግ በቄሱ ሊይ ነበር እንጂ በኔ ሊይ ነው?» አሇ ሁኔታየን ሲያይ
እየሳቀ። ከዚያ ትንሽ ዝም ብል ሲያስብ ቆየና፤

«ምናሌባት በጉዞዋችን ሊይ ሁለ፥ ዛሬ የተነጋገሩትን የመሰሇ ነገር እየተነጋገሩ የኛን ስሜትና


ሁኔታ ሲያጠኑ ቆይተው በመጨረሻ ሇሚረከቡን ባሇስሌጣኖች ምን አይነት ሰዎች መሆናችንን
ሇማስረዲት ይሆናሌ። ወይም እንዱሁ ሇሰው ስሜት የማያስቡ ግዳሇሾች ቢሆኑ ይሆናሌ። ያም ሆነ ይህ
አሁን ባሇበት ሁኔታ ከዚህ የከፊ ሉዯርስብን ስሇሚችሌ የሚዯርሰውን ሁለ ሇመቀበሌ ተሰናዴቶ
መጠበቅ ይሻሊሌ!» አሇኝ። ግን ከምፅዋ እስከ ናፖሉ እስክንዯርስ ዴረስ፥ ከዚያ የከፊ ነገር አሌገጠመንም፤
እንዱያውም እዚያ መርከብ ሊይ የነበሩት ሁለ እንዯ እስረኞች ሳይሆን እንዯ ክብር እንግድች ይመሇከቱን
ስሇ ነበረ እኛም እስረኞች መሆናችንን ሌንረሳው ትንሽ ቀርቶን ነበር!

ናፖሉ እንዯ ወረዴን «የጣሉያን - ምስራቅ - አፌሪቃ ጉዲይ ፅህፇት ቤት» የሚባሇው መስሪያ
ቤት ሰራተኞች መጥተው ስሇኛ ከተፃፇው መሸኛ ሰነዴ ጋር በመርከብ ካመጡት ሹማምንት ተረከቡን።
ከዚያ ወዯ መስሪያ ቤታቸው ወስዯው ካሇቃቸው ጋር አገናኙን። ከዚያም ወዯ መስሪያ ቤታቸው
ካሇቃቸው ጋር አገናኙን። በናፖሉ የጣሉያን ምስራቅ አፌሪካ ፅህፇት ቤት ዋና ሹም - ሻሇቃ ወይም
ኮልኔሌ መሆናቸውን አስታውሳሇሁ። እኒያ መኮንን ስንገባ ተነስተው የጅ ሰሊምታ ሰጥተው
ከጠረጴዛቸው ባሻገር በፉት ሇፉታቸው ካስቀመጡት በሁዋሊ ቡና አዝዘው እሳቸው ጭምር ስንጠጣ
ጣሉያንኛ ወይም ላሊ ያውሮፓውያን ቁዋንቁዋ እናውቅ እንዯ ሆነ ጠየቁን። እንግሉዝኛና ፇረንሳይኛም
በመጠኑ እንዯምናውቅ ሌጅ ይሌማ ሲነገራቸው እሳቸው ካገራቸው ቁዋንቁዋ ላሊ እንግሉዝኛ
ፇረንሣይኛና የስፓኝ ቁዋንቁዋ የሚያውቁ መሆናቸውን ነግረውን በንግሉዝኛ እንነጋገር ጀመር።
እውነትም መኮንኑ የተማሩ ሰው ከመሆናቸው ላሊ እንዯ ነገሩን ወዯኛው አሇም ወዯ አፌሪቃ መጥተው
ባያውቁም በአውሮፓ ውስጥ አንዲንዴ አገሮችን ተዘዋውረው የጎበኙ ስሇ ነበሩ ሰፊ ያሇ አስተያየት
የነበራቸውና ጭዋ ነበሩ። አብረናቸው የቆየንበት ጊዜ ዘሇግ ያሇ ቢሆንም በዚያ ጊዜ ስሇ ኢጣሉያና ስሇ
ኢትዮጵያ ጦርነት አንዴ ቃሌ አሌተናገሩም። ስንነጋገር የቆየን ስሇ ጉዞዋችን ኢትዮጵያ ውስጥ ስሇ
ተወሇዴንበት አገር ትምርታችንን ወዳት እንዯ ተማርን ምን ስራ እንዯ ነበርንና እነሱን ስሇመሳሰሇው
ያሇፇ ኑሮዋችን እየጠየቁን ስንመሌስ እንዱሁም በዚያ ሳቢያ በሚነሱ አንዲንዴ ጉዲዮች ሊይ አስባ
ስንሇዋወጥ ነበር። ታዱያ፥ ምንም እንኩዋ እፅህፇት ቤታቸው በቆየንበት ጊዜ ሌጅ ይሌማና እኔ
የተናገርነው ሇጠየቁን በመመሇስና ባንዲንዴ ጉዲዮች ሊይ አጫጭር አስተያየት በመስጠት የተወሰነ
ቢሆንም ስሇ ኢትዮጵያውያን መንግስታቸው ሲሰብከው የኖረው ፕሮፓጋንዲ እኛን ከሰውነት ዯረጃ ዝቅ
አዴርጎ የሚያሳይ ስሇ ነበር እኒያው፥ ሇጥያቄዎቻቸው የመሇስናቸውን ባንዲንዴ ጉዲዮች ሊይ የሰጠናቸው
አጫጭር አስተያዬቶች እንኩዋ ያስገረሙዋቸው፥ እንዱያውም ያስዯነግጡዋቸው መሆናቸው ከፉታቸው
ይታወቅ ነበር። መኮነኑ እፅህፇት ቤታቸው ስንገባ ጀምረው በጭዋነት የተቀበለትን ቢሆንም ባነጋገሩን
መጠን ሌባቸው እያከበረን የሄዯ መሆኑ ከሁኔታቸው ሁለ ይታይ ነበር። ይኸውም ከገባን በሁዋሊ

168
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሉያስከብረን የሚገባ ሌዩና ትሌቅ ነገር ስናዯርግ አይተው ወይም ስንናገር ሰምተው ሳይሆን እዚህ ሊይ
እንዲሌሁት እኛን ዝቅ አዴርጎ ሇማሳየት ሲሰብክ ሲሰሙት ከኖሩት ሌዩ ሆነን ስሊገኙን ይመስሇኛሌ።
ሇምሳላ ከተገረሙባቸ ትናንሽ ነገሮች አንደ ትግራይ ውስጥ ‹አንቲጮ› የሚባሇውን ቦታ እሳቸውና
ረዲቶቻቸውን በርካታ (መሌክአምዴር) ሊይ ፇሌገው አጥተውት ኖሮ እኔ በዘመትሁበት በሽሬ ግንባር
የነበረ በመሆኑ አውቀው ስሇነበረና ስሊሳየሁዋቸው ነበር! መቸም ከዚህ ያነሰ ነገር የሇ፤ ግን መኮንኑን
አስገረማቸው!

«አገራችነን ኢጣሉያ ከዛሬ በፉት ታውቁታሊችሁ? ወይስ ገና አሁን ማየታችሁ ነው?» አለ


መኮንኑ ‹አንቲጮን› ከሁዋሊቸው እግንቡ ሊይ በተሰቀሇው ካርታ አሳይቻቸው እንዯ ተቀመጥሁ።

«ከዛሬ በፉት አናውቅም፤ አሁን ማየታችን ነው» አሇ ሌጅ ይሌማ።

«ከዚህ የምትሄደበት ቦታስ ተነግሮዋችሁዋሌ?»

«አሌተነገረንም» አሇ አሁንም ሌጅ ይሌማ።

«ፓንዛ የሚባሌ ዯሴት ነው። አገሩ እንኩዋ እኔ አይቸው ባሇውቅም በበጋ የከተማ ሰዎች
ሇእረፌት የሚሄደበት ጥሩ ቦታ መሆኑን ሰምቻሇሁ፤ ግን ወዯዚያ ከመሄዲችሁ በፉት የጣሉያንን አገር
ትንሽ ተዘዋውራችሁ ማየት ብትችለ መሌካም ነበር። ላሊው ቢቀር ሮምን እንኩዋ ብታዩ ኢጣሉያ
እንዳት ያሇች አገር እንዯ ሆነች አንዴ አሳብ ይኖራችሁ ነበር! አለ፥ እንዯ ማዘን ብሇው።

«ግዳሇም፤ አሁን ባይሆን ወዯ ፉት እዴሌ ይኖረን ይሆናሌ» አሇ ሌጅ ይሌማ። ከዚያ መኮንኑ፥


አንዴ የመቶ አሇቃ በስሌክ ጠርተው እዚያው ከፅህፇት ቤታቸው ውስጥ ገሇሌ ብሇው ሲነጋገሩ ቆይተው
መጡና፥

«በዚህ ምክንያት የሚመጣ ችግር ቢኖር አሊፉነቱን እኔ ሇመቀበሌ ዝግጁ ስሇሆንሁ፥ የመቶ
አሇቃ ዛሬ በማታው ባቡር ወዯ ሮም ወስድ፥ ቅዲሜና እሁዴ ቱሪስቶች ከያገሩ እየመጡ
የሚጏበኙዋቸውን ታሪካዊ ቦታዎች እያዞረ ካሳያችሁ በሁዋሊ ሰኞ ማታ ተመሌሳችሁ ማክሰኞ ወዯ
ፓንዛ ትሄዲሊችሁ። የመቶ አሇቃ ከኔ የተሻሇ እንግሉዝኛ ያው ቃሌ፤ ሇዚህ ነው እሱን የመረጥሁሊችሁ»
አለ ፇገግ ብሇው የመቶ አሇቃውን ሇኛ እያመሇከቱ። ማውታውን በባቡር ወዯ ሮም ተጉዋዝን።

የመቶ አሇቃው፥ ሮምን ዯህና አዴርጎ የሚያውቅ ኖሮ፥ በዯረጃው መሀከሇኛ ቢሆንም ምቾት
ባሌጎዯሇው ሆቴሌ አሳርፍ ቅዲሜና እሁዴ ሉታዩ የሚገባቸውን ታሪካዊና አዱሶችም ቢሆኑ ስመጥር
የሆኑትን ቦታዎች እያዞረ አሳዬን። የናፖሉው አሇቃው ስሇኛ የነበራቸውን መሌካም አስተያየት
ተመሌክቶ ይመስሇኛሌ፤ የመቶ አሇቃው በብርቱ ጥንቃቄና በትህትና ነበር ሲያስተናግዯን የሰነበተ።

169
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ትናንት ምሳ በበሊንበት ሆቴሌ አንዲንዴ የዋንው መስሪያ ቤት (የቅኝ ግዛቶች ሚኒስቴር)
ሰራተኛ አይተዋችሁ ከየት እንዯ መጣችሁ ጠይቀውኝ ከኢትዮጵያ የመጣችሁ መሆናችሁን
ነግሬያቸዋሇሁ። ስሇዚህ እዚህ መዴረሳችሁ ከታወቀ ወዯ ዋናው መስሪያ ቤት ወስጃሇሁ የክፌለን አሊፉ
አይታችሁ ብትሄደ የሚገባ አይመስሊችሁም?» አሇ የመቶ አሇቃው በትህትና ሰኞ ጥዋ እቁርስ ሊይ።

«የመስሪያ ቤቱን ስነ ስራት የሚያውቁ እርስዎ ስሇሆኑ የርስዎን አሳብ እንቀበሊሇን» አሇው ሌጅ
ይሌማ።

ከቁርስ በሁዋሊ ወዯ ቅኝ ግዛት ሚኒስቴር ሄዯን፥ የምስራቅ - አፌሪቃ ክፌሌ ሹም ከሆኑት አንዴ
ሻሇቃ ተገናኘን። ሻሇቃው እንኩዋንስ ኢትዮጵያን፥ ኢጣሉያ ቀዯም ብሊ የያዘችውን ኤርትራያን
ሶማሉያንም ስማቸውን ካሌሆነ መሌካቸውን የሚያውቁ አሌነበሩም። ስሇዚህ ቅኝ አገር ቆይተው
የተመሇሱት ሹማምንት እንዯሚያዯርጉት እንዯ አሽከሮች ሳይሆን እንዯ እንግድች የጅ ሰሊምታ እዬሰጡ
አስቀምጠው ባንዴ ኤርትራዊ አነጋጋሪነት ትንሽ ሲያነጋግሩን ከቆዩ በሁዋሊ ወዯ ሚኒስቴሩ ዋና
ዱሪክተር ሊኩን።

የቅኝ ግዛቶች ጉዲይ ሚኒስቴር (ዋና ዱሪክተር) የተባሇው ሰው ከወጣትነቱና ገና ውፌረት


ያሌተጫነው ከመሆኑ በቀር መሌኩና በጠቅሊሊ ሁኔታው «ሲኞር ሙሶሉኒን» በጣም ይመስሌ ነበር።
ስሙን ምን ጊዜም አሌረሳው፤ «ድክቶር ሚቸላ» ይባሌ ነበር። የመቶ አሇቃውንና ኤርትራውያን
አነጋጋሪ ተከትሇን ገብተን ያንገት ሰሊምታ ስንጥስ ግንባሩ ቁዋጥሮ ዝም ብል ሲመሇከትን ቆይቶ፥

«ሮም መቸ መጣችሁ? ሇምን መጣችሁ? በሊቸው» አሇ፤ ግን ባሩን እንዯ ቁዋጠረ ወዯ


አነጋጋሪው ዘወር ብል። ሮም የሄዴን አርብ መሆኑንና የፓንዛ መርከብ የሚነሳበት ቀን እስኪዯርስ
ታሪካዊ ቦታዎችን ሇማየት መሄዲችነን እንዱነግርሌን ሌጅ ይሌማ በንግሉዝኛ ሇመቶ አሇቃው ሲነገረው
ዋናው ዱሪክተር በታም ተቆጥቶ፥

«እስረኞች ናችሁ እንጂ ቱሪስቶች አሇመሆናችሁን ማወቅ አሇባችሁ! ዯግሞ በኛ ፉት ከጣሉያንኛ


በቀር በማናቸውም የአውሮፓውያን ቁዋንቁዋ እንዴትናገሩ አንፇሌግም። ጣሉያንኛ እስክታውቁ ባነጋጋሪ
አማካይነት ባገራቸው ቁዋንቁዋ መናገር ትችሊሊችሁ ባሊቸው» አሇው አነጋጋሪውን። ያረፌንበትን ጠይቆ
ሆቴሌ መሆኑን የመቶ አሇቃው ሲነገረው እዚያ ከመስሪያ ቤቱ አጠገብ ኤርትራውያን ሰራተኞች
በሚኖሩበት በማሳረፌ ፇንታ ሆቴሌ በማሳረፈ እሱንም ተቆጣው። ከዚያ ያኑሇት ወዯ ናፖሉ በሚሄዯው
የመጀመሪያ ባቡር ወስድ፥ ወዱያውኑ ወዯ ፓንዛ እንዴንሄዴ እንዱያዯርግ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጥቶና
እስከዚያ ዴረስ ባስተናገደን ሹማምንት ዯግነት ምክንያት ሌንረሳው ትንሽ ቀርቶን የነበረውን
እስረኝነታችነነም አስታውሶ ወዯ እስር ቤታችን አባረረን!

170
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምእራፍ ሃያ ሶስት

ፓንዛ
ፓንዛ ከናፖሉ ብዙ ሳይርቅ በምእራብ መሀከሇኛ - ባህር የሚገኝ አነስተኛ ዯሴት ነው። በውስጡ
የባህሩን ዙሪያ ጠረፈን ተከትሇው፥ በዬራሳቸው ስም የሚጠሩ ጥቂት መንዯሮች አለበት። ከኒያ ታናሽ
መንዯሮች አንደ «ፍርና» ይባሊሌ። ክቡር ራስ እምሩ ሀይሇ ስሊሴና ክቡር ዯጃዝማች ታዬ ጉሌሊቴ፥
መጀመሪያ ወዯ ጣሉያን አገር እንዯ ሄደ ያረፈት «ፍርና» ነበር። ብዙ ህዝብ ያሇበትና የመንግስት
መስሪያ ቤቶችም በገብያው ያለበት ግን በጠቅሊሊው የዯሴቱን መጠሪያ ስም የያዘው «ፓንዛ» ነው።
እዚያ ፓንዛ የመንግስቱ ተቃዋሚዎች የሆኑ ብዙ ግዞተኞች (ኮንፉናቲ) ይኖሩ ነበር። ያን ጊዜ
እንዯዯማነው በኒያ ግዞተኞች መሀከሌ በጣሉያን አገር ስመ - ጥር የሆኑ ፇሊስፊዎች ፕሮፋሰሮች
ጋዜጠኞችና ባሇ ሌዩ ሌዩ ሙያ የፖሇቲካ ሰዎች ነበሩባቸው። ሌጅ ይሌማና እኔ ከመርከብ ፓንዛ እንዯ
ወረዴን፥ ወዯ አስተዲዯሩ መስሪያ ቤት ሄዯን ከተመዘገብንና ካገረ - ገዡ (ኮሚሳሪዮ) ከተገናኘን በሁዋሊ
ራስ እምሩና ዯጃዝማች ታዬ ወዯ ነበሩበት ወዯ ፍርና ተወሰዴን።

ፍርና ራስ እምሩና ዯጃዝማች ታዬ የነበሩት እኛም ከዯረስን የገባንበት ያንዴ ሴት ቤት ነበር።


ሴትዮዋ ባሇቤታቸው ሞተው ከሽማግላ አባታቸውና ከሁሇት ወጣት ወንድች ሌጆቻቸው ጋር ይኖሩ
ነበር። ታዱያ እርስ በርሳቸው ከነቤተሰባቸው ከሚኖሩበት ላሊ ሁሇት ትፌር ቤቶች ስሇ ነበሩዋቸው
እኒያን ትርፌ ቤቶች ሇኛ መኖሪያ ሇመንግስት አከራይተው በዚያ ሊይ ምግባችንንና የፅዲትም ላሊም
የሚያስፇሌገንን አገሌግልት እሳቸው ችሇው በየወሩ ሂሳባቸውን ከመንግስት ይቀበሊለ። ስሇዚህ ፍርና
አምት ወር ወይም ከዚያ ትንሽ በሇጥ ያሇ ጊዜ ስንቆይ በገንዘብ መሌክ እየራሳችን ከነበረን ትናንሽ ጥሪት
በቀር የምናገኘው ነገር አሌነበረም እንጂ በምግብና በሚያስፇሌገን አገሌግልት በኩሌ አንዲች ችግር
አሌነበረብንም።

አገረ - ገዡ «ኮሚሳሪዮ ሳሌቫቶሪ» እውነት መሆኑን አናውቅም እንጂ ፊሽስት አሇመሆናቸው


ይወራሊቸው ነበር። የሆነ ሆኖ ሇኛ በጣም ዯግ ነበሩ። በተሇይ ሇክቡር ራስ እምሩ እጅግ ከፌ ያሇ
አክብሮትና አዴንቆት ነበራቸው። ፇረንሳይኛ ያውቁ ስሇ ነበረ ተገናኝተው በሚነጋገሩበት ጊዜ ሁለ
«ኤክሰሊንስ» ክቡርነትዎ ከማሇት በቀር አንዴ ቀን «ራስ እምሩ» ብሇው በስማቸው ሲጠሩዋቸው ሰምቼ
አሊውቅም። ሇሌጅ ይሌማም፥ - ሇንዯን ዩኒቬርሲቲ የኢኮኖሚክ ሳይንስ ምሩቅ መሆኑን ስሊወቁ -
አክብሮትም የተሇዬ ፌቅርም ነበራቸው። ብዙ ጊዜ «የሱን ያክሌ ትምርት ያሇው እዚህ በመሀከሊችን
አንዴ የሇም!» እያለ በርከት ያለ ሰዎች ባለበት ሲናገሩ ሰምቻሇሁ። አንዲንዴ ቀን ኮሚሳሪዮው በሾፋር
የሚነዲ ኦቶመቢሊቸውን ትተው በሞተር ቢስክላት መጥተው ሌጅ ይሌማን አፇናጥጠው ወስዯው
አብረው ይውለና ማታ ይመሌሱታሌ። በጠቅሊሊው ኮሚሳሪዮ ሳሌቫቶሬ ሇኛ ምን ያክሌ ዯግ እንዯ ነበሩና
ከፌ ያሇ አክብሮት እንዯነበራቸው ምስክር ሆኖ ሉጠቀስ የሚችሇው እሳቸው አገረ - ገዢ ሆነው ፖንዛ

171
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በቆዩበት ጊዜ ሁለ እኛን ስሇሚመሇከት ጉዲይ - ትእዛዝም ይሁን ላሊ - ሉነጋግሩን ሲፇሌጉ ራሳቸው
እኛ ወዲሇንበት መጥተው አነጋግርውን ከመሄዴ በቀር አንዴ ቀን እንኩዋ ወዯ ፅህፇት ቤታቸው
ጠርተው የማያውቁ መሆናቸው ነው። ታዱያ እሳቸው ስሇኛ የነበራቸውን አስተያየት በመመሌከት
የመስሪያ ቤቱ ሹማምንትና ሰራተኞችም የፀጥታ ክፌሌ ሰራተኞችና ካራቢኔሪዎችም (ፖሉሶችም)
የዯሴቱ ህዝብ ሳይቀር በዯህና ይመሇከቱን ስሇ ነበረ በጠቅሊሊው በሀገራችን በኢትዮጵያና በህዝብዋ
ሇዘሇቄታው በዯረሰው መከራ ከማዘን በቀር በእሇት ኑሮዋችን የሚያሳዝነን ነገር አሌነበረም።

ራስና ዯጃዝማች ይኖሩበት የነበረው ቤት ባሇ ሁሇት ክፌልች ሆኖ፥ አንደ ክፌሌ ሁሊችንም
ባንዴ ሊይ ተቀምጠን የምንጫወትበትና ወዱያውም መብሌ ቤታችን ሲሆን ሁሇተኛው ክፌሌ የሁሇቱ
(የራስና የዯጃዝማች) ምኝታ ቤት ነበር። ሁሇተኛው ቤትም፥ እንዱሁ ባሇ ሁሇት ክፌልች ሆኖ፤ አንደ
ክፌሌ ሌጅ ይሌማና እኔ የምንተኛበት ሁሇተኛው የሚጠብቁን ፖሉሶች (ካራቢኔሪዎች) የሚኖሩበት
ነበር።

አንዴ ማታ ራስ በሌተን ሁሊችንም ወዯዬምኝታ ቤታችን ከሄዴን በሁዋሊ በራችን ስሇተመታ


ብንከፌት ያገረ - ገዢው ሾፋር እዚያ ቆሞ አንዲችነን ኮሚሳሪዮ ሉያነጋግሩን እንዯሚፇሌጉ ነገረን።
እሳቸውም ከኦቶመቢሊቸው ወጥተው እዝያው ባጠገቡ ቆመው ነበር። ሌጅ ይሌማና እኔ ገና በቀን
ሌብሳችን እንዴሊእን ስናወራ ስሇ ነበረ በራችን የተመታ ሁሇታችንም ቶል ወዯ ኮሚሳሪዮው ሄዯን
ሰሊምታ ስንሰጣቸው በምኝታ ጊዜ መጥተው በማስቸገራቸው ማዘዛቸውን ገሌፀው ከመንግስቱ መሪ
ከሲኞር ሙሶሉኒ የተሊኩ ትሌቅ ሰው ክቡር ራስ እምሩን ሇማነጋገር እንዯሚፇሌጉ ነገሩን። ከሙሶሉኒ
የተሊኩት ሰው ከኦቶመቢለ ውስጥ እንዯ ተቀመጡ ነበሩ።

«መቸ?» እሳቸው ሌጅ ይሌማ።

«ነገ ጥዋት መመሇስ ስሊሇባቸው አሁን ማነጋገር ነው የሚፇሌጉ።»

«አጉሌ ጊዜ መጥተን በማስቸገራችን እኔም የቅኝ ግዛቶች ዋና ዱሪክተርም እናዝናሇን፤ ነገር ግን


የቅኝ ግዛቶች ዋና ዱሪክተር የመጡ ሇዚህ ጉዲይ ብቻ ስሇሆነና ነገ በጥዋት ሇመመሇስ የሚቸኩለበት
ጉዲይ ስሊሊቸው አሁን ተገናኝተው ማነጋገር ይፇሌጋለ» አለ አገረ - ገዡ። ከዚያ ሌጅ ይሌማና እኔ
እያዘንም እዬፇራንም ሄዯን በር ስንመታ ትንሽ ከቆዬን በሁዋሊ ራስ በላት ሌብሳቸው ሊይ የጥዋት
ሌብሳችውን ዯርበው መጥተው በሩን ከፇቱና በዚያ ሰዒት በቀን ሌብሳችን ሲያዩን፥

«ምነ ምን ሆናችሁ?» አለ እንዯ መዯንገት ብሇው። ሁዋሊ እንዯ ነገሩን የዘመዴ ሞት መርድ
ይዘንባቸው የሄዴን መስልዋቸው ኖሮዋሌ።

172
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ዯህና ነን። አገረ ገዡ፥ የቅኝ ግዛቶችን ዋና ዱሪክተር ይዘው መጥተው ክቡርነትዎን ሇማነጋገር
ከሙሶሉኒ ተሌከው መጥተዋሌና አሁን ንገሩሌን ስሊለን ነው። አሁን ሁሇቱም እውጭ ቆመዋሌ»
አሊቸው ሌጅ ይሌማ።

«ምነው አይነጋም? ወይስ እንዱህ ላሉት እንቅሌፌ መከሌከለም ከቅጣታችን አንደ ክፌሌ
ይሆን?» አለ ራስ በስጨት ብሇው።

«ወዯ ምኝታ ቤት ክገቡ መቆዬትዎንና ሳይተኙ እንዯማይቀሩ ስንነግራቸው ኮሚሳሪዮው በጣም


ነው ያዘኑ። ስሇዚህ መቸም ተነስተዋሌና አነጋግረዋቸው ቢመሇሱ የሚሻሌ አይመስሌዎትም?» አሇ ሌጅ
ይሌማ ብስጭታቸውን ሇማብረዴ የሚናገራቸውን ቃሊትም የሚናገርበትን ስሌትም በጥንቃቄ እዬመረጠ።

«ዴግ ነው፤ ሌብሴን ሇብሼ ሌምጣ» ብሇው ወዯ ምኝታ ቤታቸው ሲገቡ እኛም ኮሚሳሪዮውና
የቅኝ ግዛቶች ዋና ዱሪክተር ወዲለበት ሄዴን ያነሇት ማታ ከሲኞር ሙሶሉኒ ወዯ ክቡር ራስ እምሩ
ተሌኮ የመጣው የቅኝ ግዛቶች ዋና ዱሪክተር ባሇፇው ምእራፌ የማሇከትሁትን አንባቢዎች
እንዯሚያስታውሱት ሮማን፥ በመጎብኘታችን ተቀጥቶ ወዱያውኑ ወጥተን ወዯ ፓንዛ እንዴንሊክ ጥብቅ
ትእዛዝ ሰጥቶ ያባረረ «ድክተር ሚቸሉ» የተባሇው ወጣት ነው። ድክቶር ሚቸሉ ሮማ ፅህፇት ቤቱ
ተቀምጦ ካነጋገርን ፌፁም የተሇዬ ሆን ታዬን። ኮሚሳሪዮው በዬስማችን ሲያስተዋውቁን፥ ከዚያ በፉት
አይቶን እንዯማያውቅ ሁለ በፇገግታ የጅ ሰሊምታ ሰጥቶ፥ ያገሩ አዬርና የኑሮው ሁኔታ ተስማምቶን
እንዯ ሆነ ትንሽ እንዯ ጠያዬቀን ራስ ሇብሰው ወዯ መብሌ ቤት ሲመሇሱ በመስኮት ስሊዬን፥ መጀመሪያ
ሌጅ ይሌማ ሄድ፥ አነጋገሮዋቸው ተመሇሰና ሁሊችንም እንዴንገባ ምሌክት አሳዬን።

ከመብሌ ቤቱ ውስጥ ራስ ከተቀመጡበት ላሊ አንዴ ወንበር ብቻ ነበር። በጠቅሊሊው የነበሩን


ወንበሮችም በቁጥራችን ሌክ አራት ስሇ ነበሩ ባንዴ ተቀምጠን በምጫወትበትና በምንበሊበት ጊዜ ወዯ
መብሌ ቤት እንወስዲቸዋሇን፤ በምንተኛበት ጊዜ፥ ሇሌብሳችን ማስቀመጫ እንዱሆኑ ወዯዬምኝታ ቤታችን
እንወስዲቸዋሇን፤ ስሇዚህ ያንሇት ማታ የሌጅ ይሌማና የኔ ወንበሮች እምኝታ ቤታችን ስሇ ነበሩ እመብሌ
ቤት የነበሩ የራስና የዯጃዝማች ወንበሮች ብቻ ነበሩ።

ክቡር ራስ ተነስተው ሇኮሚሳሪዮው የጅ ሰማታ ከሰጡና፥ ከዚያም ኮሚሳሪዮው ከቅኝ ግዛቶች ዋና


ዱሪክተር ጋር ካስተዋወቁዋቸው በሁዋሊ ተቀምጠው ኮሚሳሪዮውን እንዱቀመጡ ጋበዙዋቸው።
ኮሚሳሪዮው በበኩሊቸው እዚያ የነበረው ባድ ወንበር አንዴ ብቻ መሆኑን ሲያዩ የቅኝ ግዛቶችን ዋና
ዱሪክተር እንዱቀመጡ ጋብዙዋቸው። ዋናው ዱሪክተር ግን ኮሚሳሪውን አቁሞ እሱ መቀመጥ
አሇመፇሇጉን ራሱን በመነቅነቅ ገሌፀ። እኔ ሶስተኛ ወንበር ባሇመኖሩ የተፇጠረውን ችግር የተገነዘብሁት
የሁሇቱን (የኮሚሳሪዮውንና የዋናውን ዱሪክተር) መገባበዝ ከተመሇከትሁ በሁዋሊ ነበር። ያን ጊዜ እንዯ
መዯንገጥ አሌሁና እኛ ምኝታ ቤት ወንበር ሇማምጣት ሌወጣ ስሌ፥ ራስ ተመሌክተው፥

173
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«ሀዱስ ወንበር ሇማምጣት እንዯሆነ የምትሄዴ አያስፇሌግም» ስሊለኝ መሇስ አሌሁ። ከዚያ
እንዱያ ራስ ተቀምጠው ሁሇቱ ሹማምንት ቆመው በዝምታ ትንሽ ተፊጥጠው ከቆዩ በሁዋሊ፥

«ነገ በጣም ጥዋት ወዯ ሮማ የምመሌስበት ብርቱ ጉዲይ ስሊስገዯዯኝም ምንም እንኩዋ


የያዝሁዋቸው መሌእክቶች ዯስ እንዯሚያሰኙዎ ባምን አጉሌ ጊዜ መጥቼ ከምኝታዎ እንዱቀሰቀሱ
በማዴረጌ አዝናሇሁ። የመንግስታችን መሪ ክቡር ቤንቶ ሙሶሉኒ ሁሇት መሌክቶች እንነግርዎ ሌከውኝ
ነው የመጣሁ። አንዯኛው መሌእክት ቤት - ንብረትዎ ርስትዎና ማናቸውም የርስዎ የነበረው ሁለ
እንዱመሇስሌዎ ገናናው የጣሉያን መንግስት ስሇ ፇቀዯ እርስዎ ከዚህ ወዯ ሀገርዎ እስኪመሇሱ ዴረስ
ስሇርስዎ ሆኖ የሚረክብሌዎን ሰው በፅሁፌ እንዱያስታውቁ ነው። ሁሇተኛው መሌእክት» ብል የቅኝ
ግዛቶች ዋና ዱሪክተር ሉቀጥሌ ሲሌ ራስ አቁዋርጠው ከተቀመጡበት ተነሱና፥

«እግዚአብሄር ይስጥሌኝ፥ የኔ ቤት - ንብረት ርስትና ማናቸውም የኔ የነበረው ሁለ የኢትዮጵያ


ነፃነት ሲጠፊ አብሮ ጠፌቶዋሌ! አሁን ቤት - ንብረት ርስትና ማናቸውም የኔ የሆነ ነገር የሇኝም!
ሁለንም የጣሉያን መንግስት ሇወዯዯው ይስጠው?» ሲለ የመራራ ንግግራቸው ተቃራኒ በሆነ ፇገግታ
ፉታቸው ሁለ በርቶ ሁሊችንም በዴንጋጤ ዝም ብሇን እንመሇከታቸው ጀመር። እንዱያ ዝም ብሇውን
ትንሽ ከቆዬን በሁዋሊ የቅኝ ግዛቶች ዋና ዱሪክተር በቆመበት እንዲሇ የቃሌ ሰሊምታ ብቻ ሰጥቶ ዘወር
አሇ። ከዚያ ኮማሳሪዮውም የቃሌና የጅ ሰሊምታ ሇራስም ሇኛም ሰጥተው ዋናውን ዱሪክተር ተከትሇው
ወጡ።

የጣሉያን ሹማምንት ከሄደ በሁዋሊ ዯጃዝማች ከተኙበት ተነስተው እኛ ወዯ ነበርንበት


መጥተው የሆነውን ሁለ ስንነግራቸው እሳቸውም እንዯኛ እንዱያውም ከኛ ጠንከር ባሇ ቁዋንቁዋ በራስ
ሊይ ፇረደ።

ክቡር ራስ እምሩና ክቡር ዯጃዝማች ታዬ፥ በሁለ ባይሆን በብዙ ነገር የተሇያዬ እምነት የተሇያዬ
አስተሳሰብና ያሰራር ስሌት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። ክቡር ዯጃዝማች ታዬ፥ በዴሮው የኢትዮጵያውያን
እምነት የፀኑ በዴሮው አስተሳሰብና ያሰራር ስሌት የሚያምኑ ነበሩ። ክቡር ራስ እምሩ ምንም እንኩዋ
ጥንታዊውን የኢትዮጵያውያን እምነትና አስተሳሰብም ያሰራር ስሌትም ጭራሽ ዋጋ ባያሳጡ ሇዘመናዊው
እምነትና አስተሳሰብም ያሰራር ስሌትም ክብዯት የሚሰጡ ነበሩ። ታዱያ ሁሇቱ ሲከራከሩ ሌጅ ይሌማና
እኔ አብረናቸው ተቀምጠን መስማቱ ዯስታን ብቻ ሳይሆን ትምርትን ጭምር ይሰጠን ነበር።

«አሁን ሁሊችሁም በኔ የፇረዲችሁብኝ እኮ ወይ እኔ አሳቤን እንዱገባችሁ አዴርጎ መግሇፅ


አሌቻሌሁ ይሆናሌ፤ ወይም እናንተ እንዱገባችሁ አሌፇሇጋችሁ ይሆናሌ እንጂ፥ አሳቤን ከተረዲችሁሌኝ
ሌትፇርደብኝ አትችለም። እኔ ያሌሁት «ይህ ቤት የኛ ቤት አዯሇም የጣሉኢያን መንግስት ሰርቶም
ይሆን ተከራይቶ እኛን በእስረኝነት ያስቀመጠበት ቤቱ ነው። ስሇዚህ ሇኛ ሹማምንቱ ሲመጡ

174
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚቀመቱበትም በቂ ወንበር እንዱኖር ማዴረግ የባሇቤቱ የመንግስት ፇንታ ነው። እንጂ የኛ ፇንታ
አይዯሇም። እኛ እስረኝነታችነን ትተን ሇሹማምንት መቀመጫ ወንበር ሌንበዯር አንሄዴም፤ ወይም
ስሊሰሩን ውሇታቸውን ሇመመሇስ የተቀመጥንበትን ወንበር እኛ ተነስተን ሇነሱ አንሰጥም» ነው፤ ይህ
ዯግሞ «እሌከኛ አያሰኝም» አለ ራስ።

«ስማኝ ራስ» አለ ዯጃዝማች። «ስማኝ፤ ይህ ሁለ አሁን ሇክርክር ያመጣኸው ነው። እኛ


ወንበር ሇመዯበዯር ባሇመሄዴህ ሳይሆን እቤታችን ያሇው ወንበር እንዲይመጣ ከሌክሇህ ሉጎደህም
ሉጠቅሙህም የሚችለትን ባሇሥሌጣኖች በማሳዘንህ ነው የፇረዴንብህ። ዯግሞ ከብርቱ ጠሊት ጋር
መከራከርና መፇካከር በጁ ሳይገቡ ነው እንጂ በጁ ከገቡ በሁዋሊ እግዚአብሄር «በቃ» እስኪሌ ዴረስ
አመሌን አሳምሮ የታዘዙትን ፇፅሞ ካሌኖሩ በባሰ ችግር ሊይ በባሰ ውርዯት ሊይ መውዯቅን ያስከትሊሌ።
አሁን እግዚአብሔር ሊንተ ቆሞ «ተው!» ባይሊቸው መንግስት የሊካቸውን ሹማምንት «እኔ ተቀምጨ
እናንተ ቆማችሁ መሌእክቱን ንገሩኝ» ስትሊቸው ተቆጥተውው ፖሉሳቸውን ከውጪ ጠርተው እጅህን
ጎትቶ እንዱያነሳህና እነሱ ባንተ ወንበር ተቀምጠው፥ አንተ ቆመህ መሌእክቱን እንዴትሰማ ሇማዴረግ
አይችለም ኖሮዋሌ? ይህስ ያንተን ክብር የሚነካ አይሆንም ኖሮዋሌ? በኔ አስተያየት እንዱህ ያሇው
ሳያስፇሌግ ራስን ሊዯጋ ማጋሇጥ ነው። እንዱህ ያሇው ባገራችን ‹ከተያዙ በሁዋሊ መፇራገጥ ጀርባን
ወይም ጎንን ሇመምሇጥ› እንዯሚለት ያሇ ነው።»

«እጀን በፖሉስ አስጎትተው ማስነሳትና እነሱ በኔ ወንበር ተቀምጠው እኔ ቆሜ መሌእክቱን


እንዴሰማ ማዴረግ ይችሊለ። ነገር ግን እንዱያ ማዴረግ የማይገባ ግፌ መሆኑን ስሇማምን በግዴ ስሸነፌ
አዯርገዋሇሁ እንጂ ወዴጄ በፇቃዳ አሊዯርገውም። ‹ማዴረግ የማትወዯውን ነገር ጠሊትህ አስገዴድህ
ስታዯርግ ክብርህ የሚነካህ አይሆንም ወይ?› ስሊለት እኔ አስተያየት ሰው ሇሚያምንበት ነገር ወይም
ሇመብቱ ከብርቱ ጠሊት ጋር ተከራክሮ ታግል ሲሸነፌ የሚያምንበትን ነገር ቢተውና መብቱን ቢያጣ
አይዋረዴም፤ ክብሩም አይነካም። የሚዋረዴና ክብሩ የሚነካ ገና ሇገና ጠሊቴ ሀይሇኛ ስሇሆነ ሳያሸንፇኝ
አይቀርም ብል ፇርቶ ሳይከራከር ሳይታገሌ የሚያምንበትን ነገር የትወና መብቱን ፇቅድ የሰጠ እንዯ
ሆነ ነው» አለ ራስ።

«በጠሊት እጅ ሳይገቡ በጠሊት እጅ እንዲይገቡ መታገሌና መጋዯሌማ ያባት ነው። አሁን


የምነጋገረው በጠሊታችን እጅ ከገባን በሁዋሊ በጠሊታችን ስሌጣን ስር ከዋሌን በሁዋሊ ስሇተዯረገውና
ሉዯረግ ስሇሚገባው ነው። ሇዚህ ነው አሁን ሇክርክር ብሇህ ያመጣኸው ነው ያሌሁህ» ብሇው ዯጃዝማች
ሲነሱ ላሉቱ ተገባዴድ ስሇነበረ ሁሊችንም ተሰነባብተንና ወዯዬምኝታ ቤታችን ሄዴን። ባማግስቱ
ኮሚሳሪዮ ሳሌቮቶሬ ጥዋት የቅኝ ግዛቶችን ዋና ዱሪክተር ሸኝተው ከቀትር በሁዋሊ ወዯ አስራ አንዴ
ሰአት ግዴም ወዯኛ መጥተው ትናንቱን ማታ ስሇዯረሠው ቅር የሚያሰኝ ነገር ክቡር ራስን ይቅርታ
ከሇመኑ በሁዋሊ ዋናው ዱሪክተር ሳይነግረን ወዝፍ የተወውን ከሙሶሉኒ የተሊከ መሌእክት ነገሩን።

175
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መሌእክቱ አንዯኛ እስከዚያ ጊዜ ዴረስ እንኖርበት የነበረው ቤት ባሇቤት ሇቤት ኪራይ ሇምግብ
ሇፅዲትና ሇላሊ ሇኛ ሇሚሰጥ ማናቸውም አገሌግልት ሁለ ሂሳባቸውን ሇመግንስት ባሇስሌጣኖች
እያቀረቡ ይከፇሌ በነእብረው ፇንታ ከተከታዩ ወር ጀምሮ ሇክቡር ራስ እምሩና ሇክቡር ዯጃዝማች ታዬ፥
በወር አንዲንዴ ሽህ ሉሬ እንዱከፇሇንና ሇቤት ኪራይ ሇምግብ ሇሰራተኛ ዯመወዝና ሇማናቸውም
ሇሚያስፇሌገን ነገር ሁለ ወጪ ራሳችን ከዚያ በዬወሩ ከሚሰጠን ገንዘብ እንዴንከፌሌ፤ ሁሇተኛ በዯህና
ቦታ ሊይ የገንዘብ አቅማችን በሚችሇው ኪራይ ቤት እንዯ ተገኘ ተከራይተን ከፍርና ወዯ ዋናው ከተማ
ወዯ ፓንዛ እንዴንዛወር መፇቀደን የሚገሌፅ ነበር። ወዱያው አንዴ ወር ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ ፓንዛ
ከባህሩ ዲር ማሇፉያ ቤት በዯህና ዋጋ ስሇተገኘሌን ተከራይተን ምግብ የማሰናዲቱንና የፅዲቱን ስራ
የምትሰራ አንዴ ሰራተኛ ቀጥረን ወዯዚያ ተዛወርን።

ፓንዛ ክቡር ዯጃዝማች ታዬ፥ አንዴ አመት ያክሌ የቀረነው ሶስታችን ሁሇት ዒመት ካስር ወር ስንቆይ
ኮሚሳሪዮ ሳሌቫቶሬ አገረ - ገዢ እስከነበሩበት ጊዜ ዴረስ አንዲች የምናማርረው ነገር አሌገጠመንም፤
ኑሮዋችን በግዞተኞች ኑሮ አይን ሲታይ በውነቱ ዯናህ ነበር። ሌጅ ይሌማና እኔ ወዯ ግሇኞች ቤት
አንገባም እንጂ ቀን ከሆነ በዯሴቱ ውስጥ በፇሇግነው ጊዜ ወጥተን የፌሇግነው ያክሌ ሽር ሽር ሇማዴረግ
እንችሌ ነበር። ራስንና ዯጃዝማችን ብቻ ሲወጡ አንዴ «የካራብኔሪ» (የፖሉስ) ሹምና ሁሇት ተራ
ካራቢኔሪዎች ይከተለዋቸው ነበር። ሌጅ ይሌማንና እኔን ግን ከነሱ ጋር መውጣት ስንፇሌግ ካሌሆነ
ካራቢኔሪዎችም አይከተለን። ፓንዛ፥ ካይነተኞች መዋኛዎች አንደ ከኛ ቤት አጠገብ ያሇው ስሇሆነ በበጋ
እዚያ፥ ሁሊችንም ከውጭ ከሚመጣውና ከዯሴቱ ህዝብ ጋር ስንዋኝ እንውሌ ነበር። የፇሇግናቸውን
መፃሀፌት ከውጭ አገር አዝዘን አስገብተን ማንበብም እንችሌ ነበር። ራዱዮ ገዝተን እቤታችን ውስጥ
የአሇም ወሬ ያሇተቆጣጣሪ መስማት እንችሌ ነበር። በጠቅሊሊው እስራታታችን «እዚያ ከነበሩት የጣሉያን
ግዞተኞች የቀሇሇ ነበር« ሇማሇት ይችሊሌ።

ክቡር ዯጃዝማች ታዬ፥ አንዴ አመት ያክሌ ፓንዛ ከኛ ጋር ከቆዩ በሁዋሊ «ምህረት
ተዯርጎሌዎታሌ» ተብሇው ወዯ ሀገራቸው ከመመሇሳቸው በፉት እዚያው በኢጣሉኢያ ውስጥ «አቨሉኖ»
ወዯ ሚባሌ አገር ሄደ። እንዯሚወራው ወሬ - እውነት መሆኑ እንኩዋ አጠራጣሪኢ ነው - አቨሉኖ
የጣሉያንን ጥንታዊና ዘመናዊ ስራዎች እየዞሩ ጎብኝተው ከሲኞር ሙሶሉኒና ከላልች የጣሉያን ታሊሊቅ
ሹማምንት ጋር ተገናኝተው ተዋውቀው እንዱመሇሱ የሚጋበዙ የኢትዮጵያ ታሊሊቅ መኩዋንንትና
ወይዛዝር አርፇው ሚቆዩበት ቦታ ነበር።

ኮሚሳሪዮ ሳሌቫቶሪ፥ ከፓንዛ ገዢነታቸው ተሽረው በምትካቸው ላሊ ኮሚሳሪዮ ሲሾሙ የኛም


የኑሮ ሁኔታ ከመሌካም ወዯ ክፈ ተሇወጠ።

፩ኛ፡ - ጥዋት ከሶስት ሰአት በፉት ከቤታችን እንዲንወጣና ማታ ካስራ ሁሇት ሰአት በሁዋሊ
ከቤታችን ውጪ እንዲንገኝ ታዘዝን።

176
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፪ኛ፡ - በዯሴቱ ውስጥ ሇሽርሽር መሄዴ የምንችሌባቸው ቦታዎች ተወሰኑ።

፫ኛ፡ - ያገሩ ህዝብ በማይዋኝበት ጊዜ ሇብቻችን ካሌሆነ፥ ጣሉያኖች በሚዋኙበት ጊዜ እንዲንዋኝ


ተከሇከሌን። ባጭሩ ሁኔታችን ከግዞተኝነት ሇእስረኝነት የቀረበ ሆነ። ዯግነቱ ኮሚሳሪዮ ሳሌቫቶሬ ተሽረው
በቦታቸው አዱሱ ኮሚሳሪዮ ከተተኩ በሁዋሊ ፓንዛ ብዙ ጊዜ አሇመቆየታቸውን ነው። አዱሱ ኮሚሳሪዮ
በተሾሙ በጥቂት ወራት ውስጥ «ሉፓሪ» ወዯ ሚባሌ ላሊ ዯሴት ተዛወርን።

ምእራፍ ሃያ አራት

ሊፓሪ
ሉፓሪ በጣሉያን አገር «ሲሲሉያ» ከሚባሇው ክፌሌ ሰሜን በምእራብ መሀከሇኛ ባህር የሚገኝ
ዯሴት ነው። በሮማውያን ተረት፥ (ላጅንዴ) ሉፓሪ «የነፊሶች አምሊክ የሚኖርበት መናገሻ ከተማው
ነው» ይባሌ ነበር። በነፊሱ ሀይሇኛነትና ባዬሩ ጠባይ ቶሌ ቶል ተሇዋዋጭሰነት ሉፓሪ ባጠገቡ ካለት
የዯቡብ ጣሉያን ክፌልች (ከሲሲሉያና ከካሊብሪያ) የተሇዬ መሆኑ እሙን ቢሆንም «በጣም ክፈ» የሚባሌ
አይዯሇም።

ክቡር ራስ እምሩን ሌጅ ይሌማንና እኔን አንዴ የፀጥታ ጥበቃ ሹም አምስት ያክሌ ጭፌሮቹ
ከፓንዛ በመርከብ ወስዯው ሉፓሪ ሲያወርደን እዚያ አንዴ የፀጥታ ጥበቃና የፖሉስ (የካራቢሬኔ)
ሹማምንት ከጥቂት የዬዴርጅታቸው አባልች ጋር ሆነው ተቀበለን። የሉፓሪ ከተማ ዙሪያውን በዲገት
ተከበው ከዲገቱ ስር ባሇ ሸሇቆ ውስጥ ነው። ከምስራቅ ወገን ባሇው ዲገት አናት ሊይ፥ ትሌሌቅ ያረጁ
ህንፃዎችና የህንፃ ፌራሾች ባንዴነት በሸበት አሮጌ ግንብ ታጥረው ይታያለ። በዚያ በሽበታም ግንብ
በታጠረው ሰፉ ግቢ ውስጥ ቁጥራቸውን የማሊስታውሰው ብዙ ዩጎስሊቮች ይኖሩ ነበር።

እኒያ ሉፓሪ አሮጌ ግንብ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዩጎስሊቮች እንዯ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1934
የዩጎስሊቪያ ንጉስ የነበሩትን ንጉስ አላክሳንዴርን ያስገዯሇው ኡስታሽ የተባሇው የዩጎስሊቪያ አቢዮታዊ
ዴርጅት አባልች መሆናቸውን ሰማን። ንጉስ አላክሳንዴር የፇረንሳይ መንግስት ጋብዞዋቸው ሄዯው፥
ማርሴይ በሚባሇው የወዯብ ከተማ ሲወርደ በጊዜው የፇረንሳይ የውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር የነበሩት ሉዊስ
ባርቱ ይቀበለዋቸዋሌ። እዚያ፥ ሁሇት (ንጉሡና የውጭ ጉዲይ ሚኒስትር ባርቱ) ጎን - ሇጎን ሲሄደ፥
የኡስታሽ አባልች ባንዴ ሊይ ይገዴለዋቸውና ከላልች ያሳብም የግብርም አበሮቻቸው ጋር ሆነው ወዯ
ጣሉያን አገር ሸሽተው ይሄዲለ። «በንጉስ አላክሳንዴር መገዯ የጣሉያንና የሀንጋሪ መንግስቶች ነበሩበት
እዬተባሇ ይወራ ሇነበረው ወሬ ምናሌባት የኒያ ዩጎስሊቮች ያንጊዜ ጣሉያን አገር ሉፓሪ ግንብ ውስጥ
መኖር እንዯ ምስክርነት ሉጠቀስ ይችሌ ይሆናሌ።

177
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያ፥ ዩጎስሊቮች ይኖሩበት የነበረው ባሮጌ ግንብ የታጠረ ግቢ፥ ሇኛም ሉፓሪ በምንቆይበት ጊዜ
መኖሪያ እንዱሆን ተወስኖ ኖሮ በመርከብ ወሰደና ከመርከብ ስንወርዴ የተቀበለን ሹማምንትና
ጭፌሮቻቸው ይዘውን ወዯዚያ ሄደ። ግን፥ ግቢው አንዴ ይሁን እንጂ ሇኛ መኖሪያ እንዱሆን
የተመዯበሌን ቤት ዩጎስሊቮች የሚኖሩበትን አሌፍ ሇብቻው ፇንጠር ብል ካጥሩ ጥግ የተሰራ ዘመናዊ
መጠነኛ ቤት ነው። እዚያ ዋና ዋናዎቹ ሹማምንት ተሰብስበው ይጠብቁን ነበር። እነዙም የዯሴቱ ዋና
አስተዲዲሪ (ኮሚሳሪዮ) የፀጥታ ጥበቃ ሹምና አንዴ የፖሉስ (የካራቤኔሬ) ኮልኔሌ ነበሩ። ከመርከብ
መውረጃው ሇመኖሪያ እስከ ተመዯበሌን ቤት ዴረስ ራቅ ያሇ ቢሆንም በግራችን ነበር የሄዴን። እዚያ
እንዯ ዯረስን የተቀበለን ሹማምንት እኛን ሇሰሊምታ ያክሌ እንኩዋ ሳያነጋግሩን ከወሰደን የፀጥታ ጥበቃ
ሰዎች ጋር ሲነጋገሩ ቆይተው የፖሉሱ ኮልኔሌ ወዯኛ መሇስ አለና፥ ሻንጣዎቻችነን እዬከፇትን
እንዴናሳይ አዘዙን።

«ከያዛችሁን ጀምሮ እስካሁን ዴረስ እኛም፥ ሻንጣዎቻችንም በናንተ እጅ ነን። ፓንዛ ስንኖርም
ከዚያ ተነስተን እዚህ እስክንዯርስ ስም የጠባቂዎቻችሁ አይን ሊንዴ አፌታ አሌተሇዬንም፤ ታዱያ
እንዱያው እኛን ሇማስቸገር ካሌሆነ፥ አሁን በሻንጣችን ውስጥ ‹ምን ይገኛሌ› ብሊችሁ ነው ‹ክፇቱ ዝጉ›
የምትለን?» ሲለ ራስ ባማርኛ ሌጅ ይሌማ በጣሉያንኛ ተረጎመሊቸው።

«ቀዋሚ ስራታችን ነው እንጂ፥ እናንተን ሇማስቸገር የምናዯርገው አይዯሇም፤ ስሇዚህ


ሻንጣዎቻችሁ ሁለ ከፌታችሁ ማሳዬት አሇባችሁ?» አለ ኮልኔለ ንግግራቸውንም ፉታቸውንም ከረር
አዴርገው።

«መክፇቻ የሇኝም፤ ሁለንም እዬሰበራችሁ እዩ በሇው» አለ ራስ በቁጣ።

«ሻንጣዎች ቢሰብሩኮ የምንጎዲ እኛ ነን! ታዱያ ብንከፌትሊቸውና ቢያዩ አይሻሌም?» አሊቸው


ሌጅ ይሌማ። እኔም የሱን አሳብ ዯግፋ ነበር። ነገር ግን ራስ፥ እኛን ገሊመጡና በኮልኔለ ሊይ
አይናቸውን አፌጥጠው «ሮምፕሬ ቪዳሬ!» (ሰብራችሁ እዩ!) አለ፤ በዯካማ ጣሉያንኛቸው። የጣሉያን
ሹማምንት ግን ሻጣን ወዯ መስበሩ በመሄዴ ፇንታ ባንዴ ሊይ ሰብሰብ ብሇው በዝቅተኛ ዴምፅ ይመካከሩ
ጀመር። በዚያ ፇንታ እኛም ራስን ሇምነን፥ መክፇቻዎቻቸውን ሇሌጅ ይሌማ እንዱሰጡ ሇማዴረግ
ቻሌን። ከዚያ ኮልኔለ መጀመሪያ ከራስ ሻንጣዎች አንደ እንዱከፇት አዝዘው ተከፌቶሊቸው ከፀጥታ
ጥበቃ ሰዎች አንደ፥ በሻንጣው ውስጥ ያሇውን እቃ በጥንቃቄ ገሇጥ፥ እያዯረገ ሲያይ፥ ከስር ባንዴ
የተሸፇነ ትንሽ ሳጥን ውስጥ የጣሉያን መንግስት የነገስታት ተወሊጆች ሇሆኑ ሌኡሊን የሚሸሌመውን
ኒሻን ስሊገኘ፥

«ይህ ምንዴነው?» ሻንጣ ፇታሹ ኒሻኑን ከሳጥኑ ውስጥ አውጥቶ እዚያ ሇነበርነው ሁለ
እያሳዬ። ሹማምንቱ ያን ኒሻን ከብበው እያዩ እስበሳቸው ሲነጋገሩ ቆይተው፥

178
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«መቸ ያገኙት ነው?» አለ ኮልኔለ ራስ ሻንጣቸው ሲበረበር ፇንጠር ብሇው ቆመው ወዯ
ምሚመሇከቱበት ዘወር ብሇው።

«ነፃ በነበርን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስትና የጣሉያን መንግስት፥ ሇመሳፌንቶቻቸውና


ሇሚኒስትሮቻቸው ሽሌማት ሲሇዋወጡ ያገኘሁት ነበር» አለ ራስ።

«ይህ፥ ከነገስታት ሇተወሇደ መሳፌንት ብቻ የሚሰጥ እጅግ የተከበረ ሽሌማት ስሇሆነ በጥንቃቄ
ሉጠብቁት ይገባሌ» ሲለ ኮልኔለ፤

«እኔ አሁን፥ ይህን ኒሻን ከምንም አሌቆጥረው! አሁን ይህ ኒሻን ሇኔ፥ ከዚህ ከመሬቱ አሸዋ
ምንም ሌዩነት የሇውም! ብትፇሌጉ ውሰደት!» አለ ራስ፥ ኒሻኑን በመፀየፌ አይን እያዩ። ከዚያ በሁዋሊ
ያሌተከፇቱት የራሽ ሻንጣዎች የሌጅ ይሌማና የኔ ሻንጣዎችም ሳይከፇቱ እዚያ እኛን ሇመጠበቅ
ከተመዯቡት ፖሉሶች (ካራቢኔሬዎች) በቀር፥ የጣሉያን ሹማምንት ተከታዮቻቸውን ሁለ ይዘው፥ የቃሌ
ሰሊምታ ብቻ ሰጥተውን ሄደ።

እንዱህ በዬቦታው ካጋጠሙን የጣሉያን ሹማምንት አንዲንድቹ ስሌጣናቸውን ሇማሳዬት ትንሽ


ከመንገዴ የወጣ ነገር ሲያዯርጉ ካዩ ክቡር ራስ እምሩ፥ ሇዚያ ሇትንሹ ከመንገዴ የወጣ ነገር ትሌቅ
ከመንገዴ የወጣ ነገር ሳይመሌሱ አሳሌፇውት አያውቁም። ታዱያ፥ አዴርጎታቸው ከባዴ የእስረኝነት
ኑሮዋቸውን ይብሱን እንዲያከብዴባቸው ሰግተን ነገሩ ካሇፇ በሁዋሊ ያዯረጉት ወይም የተናገሩት
የማይገባ መሆኑን ስንነግራቸው ከኛ ጋር ይስማማለ። ነገር ግን በትኩሱ ያሰቡትን ሳይናገሩ ወይም፥
ሳያዯርጉ አይመሇሱም። ብቻ የሚያስገርመው፥ ያ አይነት ጥጥር አቁዋማቸው ቀንበራቸውን በማክበዴ
ፇንታ ሲያቀሌሊቸው በጣሉያን ሹማምንት ሁለ ፉት ሲያከብራቸው ይታይ ነበር።

ሉፓሪ በገባንበት ቀን ማግስት፥ የሚጠብቁን ካራቢኔሬዎች ሹም (አፑንታቶ) ሌጅ ይሌማንና


እኔን «ተጠርታችሁዋሌ» ብል ወዯ አገረ - ገዥው ፅህፇት ቤት ወሰዯን። እዚያ ኮሚሳሪዮው ተቀብሇው
ትንሽ ካነጋገሩን በሁዋሊ ስሇ ማንነታችን ቅፅ እንዴንሞሊ ወዯ ክፌለ ሰራተኛ ሊኩን። ያነሇት በኔ
የዯረሰው ሇክቡር ራስ እምሩና ሇሌጅ ይሌማ የብዙ ቀን መሳቂያ ሆናቸው። ወዯ ሀገራችን ተመሌሰን
አመታት ካሇፈ በሁዋሊ እንኩዋ ሌጅ ይሌማ በጭዋታ መሀከሌ በኔ ሉያስቅብኝ ሲፇሌግ ከሚያወራቸው
ወሬዎች አንደ ያ «በኔ ዯረሰ» ያሌሁት ነበር። ታሪኩ ከሞሊ ጎዯሌ የሚከተሇው ነው።

ፓንዛ እስክንዯርስ ዴረስ ስሇያንዲንዲችን የተመዘገበው መታወቂያችን ስም ከናባታችን


የተወሇዴንበት ክፌሇ ሀገር እስከ ቀበላው የተወሇዴንበት አመተ ምህረት የተፃፇበት ነበር እንጂ የናት
ስም አሌነበረበትም። ፓንዛ ስንገባ ግን የናቶቻችነንም ስም እንዴናስመዘግብ ስሇ ተጠዬቅን ሌጅ ይሌማ
አስመዝግቦ እስኪጨርስ እኔ አንዴ አሳብ መጥቶብኝ እሱን አውጥቼ አውርጄ ወዱያው አንዴ ውሳኔ
አዯረግሁ። ‹አሁን ይህን ሁለ የሚፅፈትኮ› አሌሁ ባአቤ። ‹አሁን ይህን ሁለ የሚፅፈት ምናሌባት፥

179
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መሌካም እዴሌ አጋጥሞን ከዚህ ማምሇጥ ብንችሌ የወሊጆቻችን ስም እስከሚኖሩበት ቦታ ስሇሚያውቁ
እነሱን ይዘው ሇማሰቃየት ነው። ታዱያ ምን ይሻሇኛሌ? ስም ከተማረክሁበት ቀን ጀምሮ በዬዯረስሁበት
ቦታ የተፃፇ ስሇ ሆነ መቸስ እግዚአብሔር ይሁናቸው እንጂ አሁን ምንም ማዴረእግ አሌችሌ። እናቴን
ግን አሁን የውሸት ስም ፇጥሬ ብሰጥ ሊዴናት እችሊሇሁ› አሌሁና ወዱያው አገሬ ሳሇሁ ከማውቃቸው
ሴቶች መሀከሌ ስም መረጣ ጀመርሁ። ከዚያ በህይወት ያለ ሴቶች ስም የሰጠሁ እንዯ ሆነ እናቴን
ሇማዲን እነሱን አሳሌፍ ሇስቃይ መዲረግ የማይገባ መሆኑን ህሉናየ ጮሆ ስሇ ነገረኝ የሞተች ሴት ስም
ፌሇጋ ሄዴሁ። ወዱያው ሌጅ ሳሇሁ ከጎረቤታችን የጎዋዯኛየ እናት ሞታ እዚያ መሰንበቻውን የነበረው
ሌቅሶ ትዝ አሇኝና የስዋን ስም ሇመስጠት ወስኘ፥ ከማስመዝገቤ በፉት ሇሌጅ ይሌማ ስነግረው «አንተን
ሇማምሇጥ ያብቃህ እንጂ እናትህን ፌሇጋ የሚሄዴ ሰው የሇምና ይሌቅ ዝም ብሇህ የውነተኛ ስማቸውን
ብታስመዘግብ ይሻሌሊ» አሇኝ። ነገር ግን እኔም እሱም ምክንያታችነን ሇማስረዴት ጊዜ ስሊሌነእብረን
በውሳኔየ ፀንቼ ያን የውሸት ስም አስመዝግቤ ነበር። ከዚያ በሁዋሊ ፓንዛ ሁሇት አመት ካስር ወር
በቆዬንበት ጊዜ ስሇ ማንነታችን ቅፅ መሙሊት አስፇሊጊ ስሌነበረ ችግርም አሌነበር። ነገር ግን ወዯ
ሉፓሪ ስንዛወር፥ ቅፅ መሙሊት አስፇሊጊ ሆኖ ተገኘ። ስሇዚህ መዝጋቢው በሌጅ ይሌማ ጀምሮ ሌክ
ፓንዛ የተጠዬቅናቸውን እዬጠዬቀ መጣና «የናት ስም?» ሲሌ ስሰማ ፓንዛ ሇናቴ ፇጥሬ የሰጠሁዋትን
የውሸት ስም ሇማስታዎስ ብፇሌግ ጠፊኝ። መዝጋቢው ሌጅ ይሌማን እየጠዬቀ መዝግቦ እስኪጨርስ ያን
የውሸት ስም መስጠቴኢ እንኩዋ ትዝ አሇሌኝ አሇ። ያን የጠፊ ስም እንዱወሌዴ አሳቤን ባስጨነቅሁት
መጠን፥ እንኩዋንስ የጠፊውን ሉገኝ የያዘውም እዬተበተነበት መሰብሰብ አቃጠው። ዯግነቱ መዝጋቢው
የሌጅ ይሌማን ምዝገባ በመጨረስ ሊይ እንዲሇ ኮሚሳሪዮው አስጠርተውት ሄዯ።

«ኧረ ጉዴ ፇሊሌህ!» አሌሁት ሌጅ ይሌማን፤ መዝጋቢው ተጠርቶ እንዯ ወጣ።

«የምን ጉዴ ነው የፇሊው?»

«ፓንዛ ቅፅ ስናስሞሊ ሇናቴ የሰጠሁዋት የውሸት ስም ጠፊኝ?» ስሇው ገርሞት ዝም ብል


ቆይቶ፥

«እየውሌህ ያነሇት ‹እባክህ ዝም ብሇህ የናትህን የውነተኛ ስም አስመግብ› ብዬ ስሇነበር


‹አሻፇረኝ!› ብሇህ አሁን ራስህን ብቻ ሳይሆን እኛን ጭምር የሚያዋርዴ ነገር ሌታዯርስብን ነው!» አሇኝ።

«እናንተን ጭምር የሚያዋርዴ ምን ነገር አዯረግሁ?»

«ፓንዛ ሇናትህ ያስመዘገብኸው የውሸት ስም ከጠፊ እዚህስ የውሸት ስም ሌታስመዘግብ አዯሌ?


ታዱያ እዚህ የምታስመዘግበው ፓንዛ ካስመዘገብኸው የተሇዬ ሆኖ ሲገኝ ውሸታሞች ናቸው መባሊችን
ይቀራሌ?»

180
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እኔ ‹ስሇዋሸሁ እናንተ የምትዋረደበት ምክንያት አይታዬኝምና ይሌቅ እሱን ትተህ መዝጋቢ
ሳይመጣ ፓንዛ ስሇዚህ ነገር ከተነጋገርነው የምታስታውሰው አሇ እንዯሆነ ይረዲኝ ይሆናሌና ንገረኝ»

«እኔ፥ አንተ ከዚህ ማምሇጥ አትችሌም እንጂ ማምሇጥ ከቻሌህ፥ እናትህን ማንም አያገኛቸውና፥
የሞተች ሴት ስም ከማስመዝገብ የውነተኛ ስማቸውን ብታስመዘግብ ይሻሊሌ› ብዬ መምከሬ እንጂ ላሊ
የማስታውሰው የሇኝም» ሲሌ፤

«ኦ - እቴቴ ያጤነሽ!» አሌሁ እዬሳቅሁ። «እቴቴ ያጤነሽ» ስምዋን ሇናቴኢ የሰጠሁት የሞተቹ
የጉዋዯኛዬ እናት ነበረች። ሌጅ ይሌማ «የሞተች ሴት ስም ከማስገብ የናትህን የውነተኛ ስም
ብታስመዘግብ ይሻሊሌ» ሲሌ የሞተች ሴት ስም ማስመዝገቤና የሞተችቱ ሴትም የጉዋዯኛየ እናት
«እቴቴ ያጤነሽ» መሆንዋን አስታወስሁ።

«እኔን የብዙ ቀን መሳቂያ አዯረገኝ» ያሌሁት ታሪክ ከሞሊ ጎዯሌ ከዚህ በሊይ ያመሇከትሁት ሆኖ
ሳሇ፥ ሌጅ ይሌማ ያነሇት ከኮሚሳሪዮ ፅህፇት ቤት እንዯ ተመሇስን ሇክቡር ራስ እምሩ ያወራውና
ሁዋሊም ሇብዙ ሰው ያወራው የነበረ በኔ ሇማሳቅ እንዱመቸው ታሪኩን ትንሽ ሇውጥ እያዯረገ ነበር።

«ሀዱስ» ይሊሌ፤ ወሬው እውነት እንዱመስሌሇት አስቀዴሞ እዬሳቀ። «ሀዱስ፥ ሉፓሪ ከሚሳሪዮ
ፅህፇት ቤት መዝጋቢው «የናትህን ስም ንገረኝ» ቢሇው ከመዯንገጡ የተነሳ የናቱ ስም ጠፌቶት እኔ
አስታዎስሁት! ታዱያ እሊይ እንዯ ተመሇከተው እናቴን በኔ ምክንያት ሉዯርስባት ከሚችሌ አዯጋ
ሇመሰወር የፇጠርሁት የውሸት ስም ነበር እንጂ የጠፊኝ የውነተኛ ስምዋ አሌነበረም። ብቻ እሱ
የሚፇሌገው በኔ ማሳቅን ስሇ ነበረ አሰማምሮ ሲያወራ እንኩዋንስ ላልችን እኔንም ያስቀኝ ነበር!

እኛ ሉፓሪ ገብተን አጭር ጊዜ እንዲሳሇፌን፥ ዩጎስሊቮች ከዚያ ሄደ። ወዲገራቸው ተመሌሰው


ወይም ወዯ ላሊ ሀገር ሄዯው እንዯሆን ግን አናውቅም። ስሇዚህ፥ እዚያ ባሮጌ ግንብ በታጠረ ሰፉ ግቢ
ውስጥ እኛን ከኛ ራቅ ብሇው ካጥሩ በር አጠገብ እየኖሩ ግቢውን የሚጠብቁ ሽማግላ ከቤተሰባቸው ጋር
ቀረን። አመት ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ ሌጅ ይሌማም «ምህረት ተዯርጎሌሀሌ» ተብል ወዯ ሀገሩ ስሇ
ተመሇሰ፥ ከእስረኞች፥ ክቡር ራስ እምሩና እኔ ብቻ ቀረን።

ክቡር ራስ እምሩና፥ እኔ ከሁሇት አመት በሊይ ሉፓሪ ስንቆይ እኔን ፓንዛ የጀመረኝ
«የብሮንካይቲስ» በሽታ - ባዬሩ ጠባይ ተሇዋዋጭነት ምክንያት - እዬጠነከረብኝ ከመሄደ በቀር፥
ከሹማምንቱ ሆነ ከዯሴቱ ህዝብ በኩሌ አንዲች ችግር ገጥሞን አያውቅም ነበር። በገንዘብ በኩሌ ሉፓሪ
በማንከፌሌበት የመንግስት ቤት እንኖር ስሇ ነበረ እንዱያውም ከፓንዛ ይሻሇን ነበር። እንዱሁም ፓንዛ
በኮሚሳሪዮ ሳሌቫቶሬ ቦታ የተተኩት አገረ - ገዥ ከተወሰነ ጊዜ በሁዋሊ ከቤታችን ውጪ እንዲገኘና
ከተወሰነ ጊዜ በፉት ከቤታችን እንዲንወጣ በዯሴቱ ውስጥ ከተወሰነ ቦታ አሌፇን እንዲንሄዴና ብቻችነን

181
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ካሌሆነ ካገሩ ህዝብ ጋር እንዲንዋኝ ከሌክሇውን የነበረውን ሁለ የሉፓሪው ኮሚሳሪዮ ፇቅዯውሌን ስሇ
ነበረ፥ የሉፓሪው የእስረኝነት ኑሮዋችን ፓንዛ ወዯ መጨረሻው ጊዜ የነበረውን ያክሌ ከባዴ አሌነበረም።

የሉፓሪው ኮሚሳሪዮ፥ በተሇይ እኔ በወጣትነት እዴሜዬ በባእዴ አገር የእስረኝነት ኑሮ መኖሬ


አንሶ ዯግሞ በዚያ ሊይ ጤና አጥቼ የምሰቃይ በመሆኔ ያዝኑ እንዯ ነበረ ከነገሩዋቸው ሰዎች
ከመስማቴም ላሊ ባዴራጎታቸው ይታይ ነበር። ሇምሳላ ሀኪም ቤት ሄጄ መታከሜን ከዘበኞች ወይም
ከላሊ የሰሙ እንዯ ሆነ ብዙ ጊዜ ሇምርመራም ሆነ ሇህክምናና ሇመዴሀኒት የከፇሌሁትን ፊክቱር አየው
- በገንዘብ ያሌተቸገርሁ መሆኔን እዬነገርሁዋቸው - በግዴ ይመሌሱሌኝ ነበር። እንዱሁም የምችሌ
ብሆን ኖሮ ሊቲን ሇመማር ፌሊጎት እንዯ ነበረኝ ከነገርሁዋቸው ሰዎች ሰምተው ከዯሴቱ ጳጳስ ጋር
ተነጋግረው አንዴ መነኩሴ በነፃ እንዱያስተምሩኝ አዴርገውሌኝ ያሇ ጠባቂ ብቻየን ወዯ ጳጳሱ ግቢ
እዬሄዴሁ እማር ነበር። በመጨረሻ በሽታየ እያዯር እዬጠነከረብኝ መሄደን ሲያይ የዯሴቱ ዋና ሀኩም
ወዯ ሉፓሪ ከተዛወርሁ ጀምሮ የጤናየን ሁኔታ በተከታተሇው መጠን በሽታየ እዬከፊ እንጂ እዬተሻሻሇ
የማይሄዴ መሆኑን ሲያረጋግጥ ቢቻሌ ወዯ ተወሇዴሁበት አገር እንዴመሇስ የማይቻሌ ከሆነ ግን ያዬሩ
ጠባይ ቶሌ ቶል ወዯማይሇዋወጥበት የጣሉያን «የብስ» ክፌሌ እንዴንዛወር የውነተኛ (ፕሮፋሽናሌ)
አስተያየቱን እንዱሰጥ ስሇነገሩት እሳቸው ያስመሩሇትን መስመር ተከትል አስተያየት ሰጠ። ከዚያ
የሀኪሙን «ሪፖርት» መሰረት አዴርገው ወዯ ተወሇዴሁበት አገር እንዴመሇስ ያ ባይቻሌ ግን ጣሉያን
አገር ወዯ «የብሱ» ክፌሌ እንዴዛወር የበሊይ ባሇስሌጣኖች ጠይቀው ረዢም ጊዜ ሳይፇጅ «ካሊብርያ»
ወዯ ሚባሇው የጣሉያን የብስ ክፌሌ እንዴዛወር መፇቀደን የሚያበስር መሌስ ዯረስን። የዯረሰን መሌስ
ካንዴ ወገን ፊታ ከማይሰጥ «የብሮንካይቲስ» በሽታየ የሚያሳርፇኝ ስሇመሰሇኝ ዯስ ቢያሰኘኝ፥ ከላሊ
ወገን፥ ራስን ብቻቸውን ትቻችወ እኔም አንዴ ኢትዮጵያዊ በላሇበት ብቻየን ሇመኖር የመሄደ ሃሳብ
ከብድኝ በመሄዴና ባሇሁበት ከስቃይ ጋር በመቆዬት መሀከሌ መወሰን አቅቶኝ ተቸግሬ ነበር። ነገር ግን
ሀኪሙና ኮሚሳሪዮው ብቻ ሳይሆን ራስ ጭምር ሉፓሪን ሇቅቄ እንዴሂዴ አጥብቀው ስሇመከሩኝ
«ከሊብሪያ» ውስጥ «ልንጎብኮ» ወዯሚባሌ ቦታ ሄዴሁ።

ምእራፍ ሃያ አምስት

ሎንጎቡኮ
ልንጎቡኮ በዯቡብ ጣሉያን «ካሊብርያ» በሚባሇው ካንዴ ከፌተኛ ተራራ ዯረት ሊይ የሚገኝ ትንሽ
ከተማ ነው። «ከተማ» ከመባሌ እንኩዋ ምናሌባት፥ «የጠገር መንዯር» ቢባሌ ከእውነተኛ ሁኔታዎች ጋር
በተስማማ! ከህዝቡ የሚበዛ በርሻና በከብት እርባታ የሚኖር ባሊገር ከመሆኑ ላሊ ከጥቂት ትናንሽ ሱቆች
በቀር፥ ከፌተኛ የንግዴ ቤቶች ወይም ፊብሪካዎች አሌነበሩበትም። የነበረው ትምህርት ቤት አንዴ እስከ
አራተኛ ክፌሌ ዴረስ የሚማሩበት ያንዯኛ ዯረጃ ትምህርት ቤት ብቻ ነበር። የጤና አገሌግልት
የሚሰጠውም አንዴ ክሉኒክ ብቻ ነበር። ከዚያ ከፌ ያሇ ትምርትና ህክምና የሚፇሌግ ሰው ቢኖር

182
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ተራራውን ወርድ ሮሳኖ ወዯ ተባሇ ከተማ ወይም ራቅ ወዲለ ላልች ከተሞች መሄዴ ነበረበት።
በጠቅሊሊው ልንጎቡኮ በከንቲባዎችና በከተሞች ስራት ይተዲዯር የነበረ ከመሆኑ በቀር «ከተማ» የሚያሰኝ
ላሊ ምክንያት አሌነበረውም።

ልንጎቡኮ እስኪዯርስ ዴረስ እዚያ ወይም በላሊ የጣሉያን ክፌሌ የኢጣሉያን ክፌሌ የኢትዮጵያ
እስረኞች መኖራቸውን አሊውቅም ነበር። እርግጥ ከነክቡር (ሁዋሊ ሌኡሌ) ራስ እምሩ ጋር «ፓንዛ»
ሳሇን «ማርሻሌ ግራሲያኒን» ሇመግዯሌ ሙከራ ከተዯረገ በሁዋሊ «ሳርዳኒያ» ውስጥ «አሲናራ» በሚባሌ
ዯሴት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ታስረው እንዯ ነበረ ሰምተናሌ። ታዱኢያ እኒያ ያሲናራ
እስረኞንች ሁለ ምህረት ተዯርጎሊቸው ወዯ ሀገራቸው መመሇሳቸውን ይጠብቁን የነበሩት የፀጥታ ክፌሌ
ሰራተኞችና ፖሉሶች (ካራቢኔሬዎች) ነግረውን ነበር። ነገር ግን ግንጎቡኮ ስንዯርስ አስራ አዴስት ያክሌ
እስረኞች አገኘሁ። እነሱም፦

፩. ዯጃዝማች (ሁዋሊ ቢትወዯዴ) መንገሻ ውቤ ከላልች እስረኞች ተሇይተው እዚያ ባጠገብ ሇብቻ
ይኖሩ የነበር።

፪. ባሊምባራስ (ሁዋሊ ፉታውራሪ) እማኙ ይመር፥

፫. ሙሱእ አብርሃም ከኢትዮጵያዊት ባሌተቤታቸውና ካራት ወንድች ሌጆቻቸው ጋር።

፬. ሌጅ (ሁዋሊ ዯጃዝማች) ግርማቸው ተክሇ ሀዋርያት፥

፭. ሌጅ ቴዎዴሮስ ወርቅነህ፥

፮. ሌጅ (ሁዋሊ ኮልኔሌ?) ኮስሮፌ በጏሲያን፥

፯. ሌጅ (መሀንዱስ) አበበ ገብረ ፃዴቅ፥

፰. አቶ ሳሙኤሌ ገብረ የሱስ፥

፱. አቶ በርሄ ክፌለም፤

፲. አቶ ብርሃነ ሀብተ ሚካኤሌ፤

፲፩. አቶ ግራዝማች ሇገሰ ገብሬ ነበሩ ፡

እኒህ እስረኞንች መጀመሪያ - እዚህ ሊይ እንዯ ተመሇከተው ማርሻሌ ግራሲያኒን ሇመግዯሌ


በተዯረገው ሙከራ ምክንያትን «አሲናራ» በሚባሇው ዯሴት ታስረው ከነበሩት ብዙ ኢትዮጵያውያን ጋር
ነበሩ። ሁዋሊ፥ የሚበዙት በምህረት ወዯ አገራቸው ሲመሇሱ ከመሀከሊቸው እነሱና ላልች ተመርጠው

183
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ልንጎቡኮ እንዱቆዩ ተዯረገ። ከነዚያ ዯግሞ «ነጋዴራስ ወዲጆ አሉ» እዚያው ሲሞቱ አሁንም በርከት
ያለት በምህረት ተመሌሰው አስራ አዴስቱ ቀሩ። እኒህ አስራ አዴስቱ ተሇይተው የቀሩበት ምክንያት
ምን እንዯ ሆነ አሌተገሇፀሊቸውም። «ከሁለ ተሇይተው ወዯ ሁዋሊ መቅረታቸው ከሁለ የበሇጠ አዯገኞች
በመሆናቸው ወዯ ሀገራቸው የተመሇሱ እንዯ ሆነ በጣሉያን ባሇሥሌጣኖች ሊይ ችግር እንዲይፇጥሩ
የተዯረገ ነው» ሲባሌ ይሰማ ነበር፤ ሉመስሌም ይችሊሌ። ነገር ግን መጀመሪያ እስረኞች ወዯዬስርቤቱ
የተሰዯደበትም ሆነ ሁዋሊ በምህረት የሚበዙት ሲመሇሱ ጥቂቱ ተመርጠው ወዯ ሁዋሊ የቆዩበት ሁኔታ
ሲታይ እንዱሁ በዘፇቀዯ እውር የበቀሌ ጥምን ሇማርካትና ቁጥር ሇመሙሊት እንጂ የተገዯለት ወይም
የታሰሩት ሰዎች አዯገኞች መሆኑ አሇመሆናቸው በጥናት ተዯርሶበት አሇመሆኑ ግሌፅ ነበር።

‹አብርሃ ዯቦጭና ሞገስ አስገድም› የተባለ ወጣቶች የማርሻሌ ግራሲያኒን ህይወት ሇማጥፊት
በሰነዘሩት አዯጋ ምክንያት ከክቡር (ሁዋሊ ሌኡሌ) ራስ እምሩ ጋር የነበሩት የሆሇታ መኮንኖችና
ወታዯሮች ካሇቃቸው ከኮልኔሌ በሊይ ሀይሇ አብ ጋር እንዱሁም የራስ መኩዋንንትና አዱስ አበባ
የነበሩት ምሁራንም መኩዋንንትም በዬተገኙበት በገፌ እዬተያዙ ተገዴሇው እንዯ ጥራጊ ባዴነት በሰፊፉ
ጉዴጉዋዴ ከተጣለ በሁዋሊ የተረፈት እዬተሰበሰቡ በዬቦታው ታጏሩ። ከዚያ በተከተለት ጥቂት ቀናት፥
ሇይምሰሌ ያክሌ እንኩዋ «ምርመራ» የሚባሌ ነገር ሳይሞክር ከኒያ በዬቦታው ከታጏሩት እስረኞች
ብዙዎች እንዯ በግ እዬተጏተቱ እዬወጡ ሲታረደ ሰነበቱ።በመጨረሻ ከመጉዯሌ፥ የተረፈት በእስረኝነት
ናኩራ ዯናኔ አሲናራ፥…..ወዘተ ወዯ ተባለ ቦታዎች ተሊኩ። አንዲንድቹ ተይዘው ወዯ እስር ቤት
የተሊኩበትን ሁኔታ ራሳቸው ሲያወሩ ከማስገረም አሌፍ ያስቅ ነበር። ያቶ «በርሄ ክፌልም» ታሪክ
ትንሽ ረዘም ቢሌም ሇምሳላነት መጥቀሱ በዚያ ጊዜ የተዯረገውን ሇማሳዬት ይረዲሌ።

አቶ በርሄ ክፌለም እንዲወራን በትግራይ ክፌሇ ሀገር ተወሌድ፥ አስመራ በሚሲዮን ትምህርት
ቤት የጣሉያን ቁዋንቁዋ የተማረ ነበር። እዚያ (አስመራ) ነጋዴራስ ወዲጆ አሉን ያገኝና አዱስ አበባ
ወስዯው የመንግስት ቤት ተቀእምጦ ስራ ሲፇሌጉት ጣሉያኖች ኢትዮጵያን ይይዙና የመንግስት ስራ
የመያዙ ተስፊ ከንቱ ሆኖ ይቀራሌ። ከዚያ ጣሉያንኛ የሚያውቅ በመሆኑ ሁዋሊ አዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የተባሇው የጃንሆይ ግቢ የብዙ ጣሉያን ሹማምንት ፅህፇት ቤት ሆኖ ስሇ ነበረ እዚያ በተሊሊኪነት
ተቀጥሮ ያገሇግሌ ኖሮዋሌ። ግራሲያኒን ሇመግዯሌ በተዯረገው ሙከራ ምክንያት ያሇቁት ኢትዮጵያውያን
አሌቀው ወዯዬእስር ቤቱ እንዱሊኩ የተመዯቡት የስም ዝርዝር ወጥቶ ከሚጠባበቁት መሀከሌ ወዯ
አሲናር እንዱሄደ የተወሰነባቸው «ፉታውራሪ በርሄ ተስፊይ» የተባለ መኮንን ኖረዋሌ። እስረኞቹን
ከያቅጣቸው የሚወስደት ካሚዮኖች ቀርበው የስም፥ ዝርዝር የያዙት የአሉያን ሹማምንት እያንዲንደን
እስረኛ በስሙ እዬጠሩ በካሚዮን በሚጭኑበት ጊዜ፥ ፉታውራሪ በርሄ ተስፊይ ቢጠሩ ላሉቱን ሾሌከው
አምሌጠው ኖሮ «የውሀ ሽታ» ይሆናለ! «ፉታውራሪ በርሄ ተስፊይ ፉታውራሪ በርሄ ተስፊይ!» ቢባሌ
በያቅጣጫው «አቤት» ባይ ይጠፊሌ። ከዚያ አንዴ ታሉያን «ቆይ በርሄ ያሇበትን እኔ አውቃሇሁ» ብል

184
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እዬሮጠ ሄድ፥ «ተሊሊኪ በርሄ ክፌልምን» ይዞ ይመጣና «ያውሌህ በርሄ!» ብል ሇስም ዝርዝር ጠሪው
ይሰጠዋሌ።

«አንተ ፉታውራሪ በርሄ ተስፊይ ነህ?» ይሊሌ የስም ዝርዝር ጠሪው።

«ኧረ ፉታውራሪ በርሄ ተስፊይ አይዯሇሁም፤ እኔ በርሄ ክፌልም ነኝ» ይሊሌ በርሄ ክፌልም።

«ፉታውራሪ ባትሆንም አባትህ ተስፊይ ባይሆንም አንተ ‹በርሄ› ከሆንህ ግዳሇም ይበቃሌ፤ ሂዴ
ግባ፥ ጊዜየን አታጥፊብኝ!» ብል የስም ዝርዝር ጠሪው ጣሉያን እዬገፊ እካሚዮኑ ውስጥ ያስገባውና
በርሄ ወዯ ምፅዋ፥ ከዚያ ወዯ አሲናራ ከተወሰደት እሰረኞች ጋር ይወሰዲሌ! እስረኞች አሲናራ የቆዩትን
ያክሌ ከቆዩ በሁዋሊ ዯግሞ ሇብዙዎቹ ምህረት ተዯርጎሊቸው ወዯ ሀገራቸው ሲመሇሱ፥ በርሄ ተመርጠው
ልንጎቡኮ በእስረኝነት እንዱቆዩ ከተወሰነባቸው ጋር እንዱቀር ይወሰንበታሌ! ስሇዚህ «ተመርጠው
ልንጎቡኮ በእስረኝነት እንዱቆዩ ከተወሰነባቸው ጋር እንዱቀር ይወሰንበታሌ! ስሇዚህ «ተመርጠው ወዯ
ሁዋሊ የቀሩት ከሁለ የከፊ አዯገኞች ስሇሆኑ ነው» ከተባሇ ከነሱ አንደ በርሄ ክፌልም መሆኑ ነው!
እንግዱህ የበርሄ፥ ክፌልምን ረዢም ታሪክ ሇማውራት ከመስመሪ ስሇወጣሁ ያንባቢዎችን ይቅርታ
እዬሇመንሁና እንዲሌካቸው ተስፊ እያዯረግሁ ወዯ ዋናው ታሪክ እመሇሳሇሁ።

ካስራ ስዴስቱ እስረኞች ሙሴ አብራህም ከባሌተቤታቸውና ከሌጆቻቸው ጋር መንግስት


በተከራዬው ቤት ሇብቻቸው ይኖሩ ነበር። ላልች እስረኞች፥ ሁለም ባንዴ ምዴር ቤትና ፍቅ ያሇው
ትሌቅ ቤት ነበር የሚኖሩ። ያ ቤትም እንዱሁ መንግስት ከግሇሰብ የተከራዬው ነበር። ቤቱ ትሌቅ
ከመሆኑ የተነሳ የቅርብ ጉዋዯኞች ከሆኑት አንዲንዴ ክፌሌ ሇሁሇት የያዙ ቢኖሩም የሚበዙት
ሇዬብቻቸው ክፌሌ ነበራቸው። ሌጅ ግርማቸው ተክሇ ማርያም ሇዬብቻቸው ክፌሌ ከያዙት አንደ ስሇ
ነበረ እኔ ከሱ ጋር እንዴዲበሌ ተዯረ። ከጥቂት ወራት በሁዋሊ ግን ሌጅ ግርማቸው ወዯ ክቡር (ሁዋሊ
ሌኡሌ) ራስ እምሩ እንዱሄዴ ጠይቆ ስሇ ተፇቀዯሇትና ስሇ ሄዯ ብቻዬን የክፌለ ባሇቤት ሆንሁ።

እኔ ልንጎቡኮ ስዯርስ እዚያ የነበሩ እስረኞች በወር የተወሰነ ገንዘብ እዬተሰጣቸው በዚያ ገንዘብ
ምግባቸውን እያሰናደ የሚመገቡ ራሳቸው ነበር። ሇሌብሳቸው ሆነ ወይም ሇላሊ ሇሚያስፇሌጋቸው
ጉዲይ ሁለ፥ ያንኑ በወር የሚያገኙትን እንዱበቃ ማዴረግ የነሱ ፇንታ ነበር። ቀዯም ብል ግን - እነሱ
እንዯነገሩኝ - «ሮማኖ» የተባሇ ቤተሰብ የምግብ ማሰናጃ ትንሽ ሆቴሌ ስሇ ነበረ እዚያ፥ እየተመገቡ
ሂሳቡን መንግስት ይከፌሌ ኖሮዋሌ። እንዱሁም ሇሌብስ ሇመዴሃኒትና ሇላሊ መንግስት አስፇሊጊነቱን
ሊመነበት ጉዲይ ይከፌሌሊቸው ኖሮዋሌ። ታዱያ በዚያ ጊዜ እነሱ አስፇሌጊያቸው በመሆኑ እንዱገዛሊቸው
የሚፇሌጉት ነገር ሇመንግስት ባሇስሌጣኖች አስፇሊጊ ሆኖ ስሇማይታያቸው ባሇስሌጣኖቹን ሇማስረዲት
ብርቱ ችግር የነበረ ከመሆኑ ላሊ ባሇ ሆቴለም ትርፈን ሇማብዛት ሇሚከፌሇው ገንዘብ ተመጣጣኝ የሆነ
ምግብ ባሇማቅረቡ ፅኑ ርሀብ እንዯነበረባቸው ይናገሩ ነበር።

185
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሁዋሊ፥ ፊሽስት ኢጣሉያ ኢትዮጵያን ከመውረርዋ በፉት ብዙ አመታት ኢትዮጵያ የኖሩ፥
ኢጣሉያዊ ካቶሉክ መነኩሴ እስረኞችን ሇመጎብኘት ወዯ ልንጎቡኮ ሄዯው፥ በተሇይ በምግብ በኩሌ
መጎዲታቸውን ስሇ ተረደ መንግስት ሇያንዲንዲቸው በዬወሩ የተወሰነ ገንዘብ እዬሰጣቸው በዚያ
ምግባቸውን እንዱችለ አስዯረጉሊቸው። እኔም ሌጅ ግርማቸው ተክሇ ሀዋርያት ወዯ ክቡር ራስ እምሩ
ከሄዯ በሁዋሊ የምኝታ ክፌላ ሇብቻየ ይሁን እንጂ የምግብ ጉዋዯኝነቴን ካቶ ሳሙኤሌ ገብረ የሱስ ከሌጅ
አበበ ገብረ ፃዴቅና ካቶ በርሄ ክፌልም ጋር አዴርጌ ምንም እንኩዋ ያ ጊዜ በጦርነቱ ምክንያት
በጠቅሊሊው የጣሉያን ህዝብ ሊይ ችግር እዬተባባሰ የሄዯበት ጊዜ ቢሆን ያገኘነውን፥ እዬተረዲዲን ሰርተን
እዬተመገብን ወዯ ሀገራችን እስክንመሇስ ዴረስ የተሇዬ ችግር ሳይይዯርስብን ቆዬን።

የፓንዛና የሉፓሪ ነዋሪ ህዝብ፥ እዚያ የነበርነውን እስረኞች በዯህና አይን ያየን እንዯ ነበረ ሁለ
የልንጎቡኮ ነዋሪ ህዝብም እዚያ ሇነበሩት እስረኞች ማዘን ብቻ ሳይሆን ፌቅርም አክብሮትም ነበረው።
ሇዚህ ምክንያቶች ነበሩ። እነሱም፦

አንዯኛ፥ ምንም እንኩዋ በሙሶሉኒ ጊዜ ሇጣሉያን ህዝብ ቢያንስ ያንዯኛ ዯረጃን ትምህርት
መጨረስ በህግ ግዳታ የነበረ በመሆኑ ከልንጎቡኮ ህዝብ እስከ አራተኛ ክፌሌ በሚማሩበት ያንዯኛ ዯረጃ
ትምህርት ቤት ገብሮ ያሌወጣ ባይኖር አብዛኛው ህዝብ ከትምርት ቤት ከወጣ በሁዋሊ ወዯ እርሻውና
ወዯ ከብት እርባታው ስሇ ሚሄዴ በጥቂት አመታት ውስጥ ያን ሇማንበብና ሇመፃፌ ያክሌ የተማረውን
ትምርት ይረሳዋሌ። ስሇዚህ ሇማዘጋጃ ቤት ሇፖሉስ ፅህፇት ቤት ወይም ሇላሊ መስሪያ ቤት ማመሌከቻ
ማግባት ከሚፇሌጉት የልንጎቡኮ ነዋሪዎች መሀከሌ ሇብዙዎች ማመሌከቻቸውን ያሇ ምንም ዋጋ
የሚፅፈሊቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች ነበሩ።

ሁሇተኛ፥ ካንዯኛ ዯረጃ በሊይ ትምህርታቸውን መቀሌጠሌ ሇሚፇሌጉ የልንጎቡኮ ወጣቶች


መሸጋገሪያ ትምርት (ኢንተሚዱየሪ ኮርስ) የሚሰጥ ዴርጅት ወይም ሰው ስሊሌነበረ ወጣቶቹን ወዯ
ሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርት ቤት ወይም ወዯ ኮላጅ ሇመግባት የሚያበቃ የመሸጋገሪያ ትምህት ያሇ ምንም
ዋጋ የሚሰጥ «አበበ ገብረ ፃዴቅ» ነበር። አበበ በመሀንዱስነት የፇረንሳይ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነበር።
እንዱሁም ኮስሮፌ በጎሲያ (በትምርት ይሁን በሌምዴ አሊውቅም) እንስሳትን ማከም ይችሌ ስሇ ነበረ
የልንጎቡኮ ባሊገሮች ከብቶቻቸው ሲታመሙባቸው ወዯሱ እዬወሰደ ያሇ ዋጋ ያክምሊቸው ነበር። ስሇዚህ
አበበንና ኮስሮፌን ልንጎቡኮ በስማቸው የሚጠራቸ አሌነበረም፤ ሁለም አበበን «እንጀኜሬ» ኮስሮፌን
«ድቶሬ» ነበር የሚሊቸው።

ስሇዚህ የልንጎቡኮ፥ ህዝብ እነዚህን በሊይ ያመሇከትሁዋቸውን የመሳሰለትንም ላልችንም እንዯ


መሌካም ጠባይና እንዯ ጭዋነት ያለ ነገሮች በኢትዮጵያውያን ሊይ ሲያይ ኢትዮጵያውያን ፊሽስቶች
ይሰብኩት እንዯ ነበረው አውሬዎችና ፌፁም ዯንቆሮዎች ሳይሆኑ፥ እንዯ ላሊው ህዝብ ሁለ ዯግነትም
እውቀትም ያሊቸው ሰዎች የነበሩባቸው በመሆናቸው ይወዲቸውና ያከብራቸው ነበር። አንዲንዴ

186
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የፊሽስትን ስራት አጥበው ይጠለ የነበሩ አዋቂዎች ኢትዮጵያውያንን ከመውዯዲቸው የተነሳ
እንዱያውም፥ ሊገራቸው ሰዎች ዯፌረው የማይናገሩትን ምስጢር ሇኛ ይነግሩን ነበር።

ከኒያ የፊሽት ጠሊቶች መሀከሌ አንዴ ቄስ ሊቶ ሳሙኤሌ ገብረ የሱስና ሇኔ የነገሩንን ሇምሳላ
ያክሌ፥ ከሞሊ ጎዯሌ ከዚህ፥ እንዯ ሚከተሇው እፅፇዋሇሁ።

«ሙሶሉኒ ስሌጣን ከያዘ ጀምሮ የጣሉያን ህዝብ ከችግር ወጥቶ ስሇማያውቅ ያን የውስጥ ችግር
ሇማስረሳት ባገር ፌቅርና እውን ሉሆን በማይችሌ ከንቱ የታሊቅነት ህሌም የህዝቡን መንፇስ መሸንገሌን
በስሌጣን ሊይ ሇመቆዬት የሚያስችሌ አይነተኛ ዘዳ አዴርጎ የያዘ ነው። ስሇዚህ ኢጣሉያን ካንዴ ጦርነት
ወዯ ላሊ ጦርነት እዬመራ እያገባ የሀብትና የወጣት ዴሀ አዯረጋት! ዛሬ የቅኝ ግዛቶች ያለዋችወ
መንግስታት የማያዛሌቅ መሆኑን ተረዴተው የያዙዋቸውን ግዛቶች የሚሇቁበትን ሁኔኢታ ሲያመቻቹ
በሚታዩበት ጊዜ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ሇማዴረግ ያን ያክሌ ህይወትና ሀብት እንዱጠፊ ያዯረገበት
ምክንያትና የኢትዮጵያ ጦርነት ከማሇቁ «የጀነራሌ ፌራንኮን» የፊሽስት ስራት ሇማበርታት ‹በስፔይን›
ጦርነት ኢጣሉያ ጣሌቃ እንዴትገባ ማዴረጉም የዚያ ዘዳው ክፌልች ናቸው። የስፔይን ጦርነት ስያሌቅ
እንኩዋ ሙሶሉኒ በስሌጣን እስካሇ ዴረስ ኢጣሉያ የወጣቶችዋን ህይወትና የተረፇ ትንሽ ሀብትዋን
የምታጠፊበት ጦርነት መፌጠሩ አይቀርም» እውነትም ቄሱ እንዲለት፥ እንዯ «ጎሪጎሪዮስ» አቆጣጠር
በ1939 ሁሇተኛው የአሇም ጦርነት ከተነሳ በሁዋሊ በ1940 ሙሶሉኒ ኢጣሉያ የአሇም የጃፓን የጦር ባሇ
ቃሌኪዲን መሆንዋን ባጅዋ አስታውቀ።

ቄሱም ላልችም ይለት እንዯ ነበረው የጣሉያን ህዝብ ችግር እዬተባባሰ የሄዯ በተሇይ ኢጣሉያ
ኢትዮጵያን ከወረረችበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። በዚያ ጊዜ በሙለ ኢጣሉያ የቃ እጥረትና የዋጋ ግሽበት ስሇ
ነበረ በገብያ የሚገኘውን ያክሌ መጠነኛ እቃ በውዴ ዋጋ እዬገዙ የሚጠቀሙ ሀብት ያሊቸው ነበሩ።
የሚበዛው ህዝብ የሚኖርበትን የችግር ዯረጃ በዬቤቱ ገብተን በባናይም ስራቱን የሚያቃወሙት ሰዎች
ይናገሩት የነበረው እውነት መሆኑን በውጭ የሚታዬው ይመሰክር ነበር። ሇምሳላ ተራው ሰው ይቅርና
በመንግስት ሰራተኞች መሀከሌ እንኩዋ መቀመጫውና ጉሌበቱ የተጣፇ ሱሪ ወይም አንገቱና ክርኑ
የተጠቃቀመ (የተዯረተ) ኮት ሇብሶ መሂዴ የተሇመዯ የማስነውር ነገር ሆኖ ነበር። ወዲጆች ይሁኑ
ወይም ጉዋዯኞች በመንገዴ ሲገናኙ ከሰሊምታ ቀጥሇው «ዛሬ ምን በሊህ? አንተስ ምን በሊህ?» ተባብሇው
ሲጠያየቁ መስማትም ሌክ እንዯ ሰሊምታው የማይቀር፥ የተሇመዯ ነበር። ታዱያ ምንም እንኩዋ
ጣሉያኖች ኢትዮጵያን ይዘው በቆዩበት ጊዜ ሁለ እነሱ አገር በስረኝነት ስሇ ነበርሁ ኢትዮጵያ ውስጥ
እንዳት ይኖሩ እንዯ ነበረ ባሊይ የነሱ የምቾት ኑሮና የቃው በያይነቱ መትረፌረፌ የሚያስገርም እንዯ
ነበረ በዚያ ጊዜ ኢትዮጵያ የነበሩት ሁለ የሚናገሩት ነው። ቀዯም ብሇው በኤርትራ ይኖሩ የነበሩት
ጣሉያኖችም እንዱሁ ከፌ ባሇ ዴልት ይኖሩ እንዯ ነበረ የሚያውቁ ሰዎች ይናገሩ ነበር። ታዱያ
ባገራቸው የሚኖሩትን ጣሉያኖች ምቾትና የቃ መትረፌረፌ ስሰማ «ከቶ በሚገዙት ህዝብ አይን ምንም

187
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የማይጎሊቸው ‹ምለእ በኩሇሄ› መስል ሇመታየት ሇፕሮፓጋንዲ የሚያዯርጉት ይሆን? ብዬ ራሴን
ጠየቅሁ።

አንዴ ቀን አቶ ሳሙኤሌ ገብረየሱስና እኔ ሇሽርሽር በወጣንበት ካንዴ ዛፌ ስር ተቀምጠን ስናወጋ


የእስረኞች (የኛ) ጠባቂ የነበሩት «ሹምባሽ ገብረ ፃዴቅ» መጥተው ባጠገባችን ከመቀመጣቸው አንዴ
ያረጀ ሌብስ ሇብሳ ባድ እግርዋን የምትሂዴ የጣሉያን ሴት ጆንያ - ሙለ የጉቶ እንክትካች በራስዋ
ተሸክማ፥ ባጠገባችን ከነበረው ጫካ ውስጥ ብቅ አሇች። ያች መሀከሌ እዴሜ የነበራት ሴት እንዯ ማቶት
(የጋን፥ ወይም የንስራ ማስቀመጫ) ክብ ሆኖ በወፌራሙ የተጠቀሇሇ የጨርቅ መዯሊዴሌ በራስዋ ሊይ
አስቀምጣ፥ በዚያ እምዯሊዴሌ ሊይ የጉቶ እንክትካች የሞሊ ትሌቅ ጆንያዋን አመቻችታ ተሸክማ በግራና
ቀኝ እጆችዋ ወገብዋን ዯገፌ አዴርጋ ባድ እግርዋን፥ ቀጥ ብሊ ፇጠን እያሇች ስትራመዴ እንኩዋንስ ጆንያ
ሙለ የጉቶ እንክትካች የተሸከመች፥ አንዴ ቁና እህሌ የያዘች አትመስሌም ነበር። አቶ ሳሙኤሌና እኔ፥
ያች ሴትዮ በሁሇት እጆችዋ ወገብዋን ዯግፊ እንዱያ በፌጥነት ስትሄዴ፥ ጆንያው ከራስዋ ጋር የታሰረ
ወይም በጅዋ የዯገፇችው ይመስሌ ትንሽ እንኩዋ ንቅንቅ አሇማሇቱ አስገርሞን ስንነጋገር፥

«ወይ ግሩም አንታ! መቆዬትኮ መሌካም ነው፤ ብዙ ነገር ያሳያሌ!» አለ ሹምባሹ ሴትዬዋ ከኛ
እስክትርቅም ዝም ብሇው ሲመሇከቱ ቆይተው። ሹምባሹን ያስገረማቸው ጉቶው ያሇ ማሰሪያ ወይም ያሇ
ዴጋፌ በሰው ራስ ሊይ ተቀምጦ መሄደ ሳይሆን አንዴ የጣሉያን ሴት ጫማ ሳታዯርግ ባድ እግርዋን
አሮጌ ሌብስ ሇብሳ ጆንያ ሙለ ጉቶ በራስዋ ተሸክማ ስትሄዴ ማየታቸው ነበር!

«መቆየት አዯሇም እዚህ አገር መጥቼ አሮጌ ሌስብ የሇበሰ አበሻ ሲያዩ የሚፀዬፈት የጣሉያን
ሴቶች አሮጌ ሌብስ ሇብሰው ያሇ ጫማ ያህያ ጭነት ተሸክመው ሲሄደ እንዲይ ያዯረገኝ? አሁን አገሬ
ተመሌሼ እዚህ ያዬሁትን ሁለ እዚህ የጣሉያን ህዝብ የሚኖርበትን የኑሮ ሁኔታ ሁለ ባወራ ማን
ያምነኛሌ? ያገሬ ሰው ሁለ ‹ውሸታ ወይም እዴብ ነው› ኮ የሚሇኝ!» አለ።

በዚያ ጊዜ በጣሌያን አገር ስሇ ነበረው ችግር ሙሶሉኒንና የፊሽስትን ስራት ይጠለ የነበሩ ሰዎች፥
ከዚህ የሚከተሇውን ይነግሩን ነበር።

«መቸም ሙሶሉን ስሌጣን ከያዘ ጀምሮ የጣሉያን ህዝብ ከችግር ወጥቶ አያውቅ! ነገር ግን
ችግሩን ይህን ያክሌ አክፌቶ የእሇት ኑሮ ሇመኖር የማይቻሌ ያዯረገው አገር በማያፇራው ብቻ ተወስኖ
መኖር (አውታርኪያ) የተባሇው ትእዛዝ ከወጣና ብስራ ሊይ ከዋሇ በሁዋሊ ነው። ኢጣሉያ ኢትዮጵያን
በወረረች ጊዜ፥ የአሇም መንግስታት ማህበር ወዯ ኈሌቱ አገሮች (ወዯ ኢጣሉያና ወዯ ኢትዮጵያ) የጦር
መሳሪያ እንዲይገባ የእገዲ ውሳኔ አሳሌፍ ነበር። ነገር ግን ውሳኔው፥ የጦር መሳሪያን እንጂ እንኩዋንስ
ሇሰሊማዊ ኑሮ አስፇሊጊ የሆኑትን እቃዎች የጦር መሳሪያ ሇመስራት የሚያገሇግለትን ጥሬ እቃዎችም
አሌከሇከሇም። ብቻ ሇሙሶሉኒ ያን ውሳኔ ምክንያት አዴርጎ፥ አገር ውስጥ የማይገኙበትንና ቢገኙም

188
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በብቃት የማይገኙትን ሇሰሊማዊ፥ ኑሮ አስፇሊጊ የሆኑ እቃዎች «በአውታርኪያ» ትእዛዝ መሰረት ከውጭ
እንዲይገቡ እገዲ ሇማዴረግ ተመቸው። ታዱያ ካንዴ በኩሌ ‹በጣሉያን አገር ብርቱ የእቃ እጥረትና የዋጋ
ግሽበት እንዱፇጠር ያዯረገው የአሇም መንግስታት ማህበር ያሳሇፇብን የእገዲ ውሳኔ› ነው እያሇ የውሸት
ፕሮፓጋንዲውን እየነዛ ከላሊ በኩሌ ሇሰሊማዊ ኑሮ አስፇሊጊ የሆኑትን እቃዎች ከውጭ ገዝቶ ሇማስገባት
ሉውሌ ኑሮ አስፇሊጊ የሆኑትን እቃዎች ከውጭ ገዝቶ ሇማስገባት ሉውሌ በሚገባው ገንዘብ ሇጦር
መሳሪያ የሚሆኑትን ጥሬ እቃዎች ብቻ እዬገዛ እያስገባ የጦር መሳሪያ ሀብት ከማምከን በቀር ሀብት
ይወሌዴ ይመስሌ፥ ያው እሱን እዬሰራ በሊይ በሊዩ እየከመረ፥ ህዝቡን በብርቱ ችግር እንዱኖር
አዯረገው!»

በኢትዮጵያ «ያንዴ ሰው ቤት ሲቃጠሌ በጎረቤቱ እጨሇማ ውስጥ ሊለ ብርሃንን ራቁት ሇሆኑ ሙቀትን
ይሰጣሌ!» ይባሊሌ። እንዯዚያ ሁለ ሁሇተኛው የአሇም ጦርነት ተነስቶ ኢጣሉያ በ1940 እጦርነቱ ውስጥ
መግባትዋ ሲታወጅ ምንም እንኩዋ ያ ጦርነት የብዙ ህዝብ ህይወትና ንብረት የሚያጠፊ መሆኑን እንጂ
ውጤቱ ምን እንዯሚሆን ባናውቅ እኛ ነፃነታችነን ተገፇን ዙሪያው ጨሇማ ሆኖብን እንኖር የነበርን
ኢትዮጵያውያን እስረኞች «ምናሌባት ኢጣሉያና የጦር ጉዋዯኞችዋ ዴሌ ሆነው ነፃነታችነን የምናገኝበት
ጊዜ ይዯርስ ይሆናሌ» ብሇን ተስፊ የነፃነት ፌሊጎታችነን ሇመቀስቀስና ጊዜያዊ ዯስታን ሇመስጠት ያክሌ
እንጂ ከዚያ የማያሌፌ አሌነበረም። ይሁን ሇማሇትም ምሌክንያቶች ነበሩ፤

አንዯኛ ያ ጊዜ ጀርመን በአውሮፓ ጃፓን በሩቅ ምስራቅ ብርቱ ተቃውሞ ሳይገጥማችወ ዴሌ


በዴሌ እያከታተለ የተቀዲጁበት ጊዜ ነበር። ሁሇተኛ፥ በአውሮፓ አድሌፌ ሂትሇርና ዮሴፌ ስታሉን
መስኮብ ምስራቅ ፖሊንዴን የቦሌቲክን አገሮችና ፉንሊንዴን ሇመያዝ ጀርመን፥ መሀሌ አውሮፓን ሇመያዝ
በሚወስደት እርምጃ አንደ ላሊውን እንዲያሰናክሌ የምስጦር ውሌ ከተዋዋለ በሁዋሊ ጀርመን ወዱያው
ከስዊዴን በቀር የሰሜንንና የመሀሌ አውሮፓን አገሮች የያዘበት ጊዜ ነበር። እንዱሁም ጀርመን ሇርዲታ
እፇረንሳይ አገር ገብቶ ይዋጋ የነበርውን የእግሉዝ ሰራዊት ዴሌ አዴርጎ ወዯ አገሩ አባርሮ ያስወጣበትና
የእንግሉዝ ራስዋ ፌታ ሳታገኝ በጀርመን ያዬር ሀይሌ በብርቱ ከመዯብዯብዋ የተነሳ የወዯፉት ሁኔታዋ
አጠራጣሪ የነበረበት ጊዜ ነበር። ሙሶሉኒም «ሲያመነታ ቆይቶ በመጨረሻ ኢጣሉያ የጀርመንና የጃፓን
የጦር ባሇቃሌኪዲን ሆና እንዴትገባ የወሰነ እኒያ ሁሇቱ አገሮች (ጀርመን እና ጃፓን) ዴሌ አዴራጊዎች
እንዯሚሆኑ ርግጠኛ ስሇሆነ የምርኮው ተካፊይ መሆን እንዲይቀርበት ከምርኮው ዴርሻውን ሇማግኘት
ብል ነው» ይባሌ ስሇ ነበረ ባጠቃሊይ በዚያ ጊዜ የነበረው ሁኔታ «የአክሲስ መንግስታት» ይባለ
የነበሩትን (ጀርመን ጃፓን ኢጣሉያ) ዴሌ የሚያዯርጉ አስመስል የሚያሳይ ነበር። ስሇዚህ ሇኛ የነፃነት
ተስፊችን ሞቶ ተቀብሮ በፌፁም ጨሇማ ውስጥ እንኖር ሇነበርን ኢትዮጵያውያን እስረኞች የኢጣሉያ
እጦርነቱ ውስጥ መግባት ብቻ ያሌታሰበ አዱስ ምእራፌ ስሇ ከፇተ ያ ሞቶ የነበረ ተስፊችን እንዯ ገና
ህይወት ያገኘ መስል ተሰምቶን ሇጊዜው ዯስ ቢሇንም፥ ከዚህ በሊይ በተመሇከቱት ምክንያቶች ዯስታችን

189
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሞቀና የዯመቀ አሌነበረም። ነገር ግን እያዯር የጦርነቱን መሌክ የሇወጡ አዲዱስ ሁኔታዎች ስሇ ዯረሱ
የኛም ተስፊ በዚያው መጠን ከቀዴሞው እዬጠነከረ ይሄዴ ጀመር።

በእንግሉዝ አገር ከጦርነቱ በፉትና በጦርነቱም ጊዜ፥ ጀርመን የእንግሉዝ የጦር ሰራዊት ዴሌ
አዴርጎ ከፇረንሳይ አገር ሲይስወጣ ጠቅሊይ ሚኒስትር የነበሩት ኒቪሌ ቸምበርሉን ስሌጣን ሇቅቀው
ሰርዊንስተር ቸርችሌ ጠቅሊይ ሚኒስትር ሆኑ። ስሇዚህ የቸርችሌ ጠቅሊይ ሚኒስትር መሆንና ያሜሪካም
የእንግሉዝ ተባባሪዎች የሆኑት መንግስታትም (ኮመንዌሌዝ) እጦርነቱ ውስጥ መግባት የጦርነቱን
መሌክ ከሇወጡት አይነተኛዎች ነበሩ። እንዱሁም «ጀነራሌ ቻርሌስ ዯጎሌ» ተሰዯው እንግሉዝ አገር
ከነበሩት «ነፃ ፇረንሳይ» ይባሌ ሇነበረው ክፌሌና ሇፇረንሳይ የቅኝ ግዛት ህዝብ በሳቸው መሪነት ሇነበረው
ክፌሌና ሇፇረንሳይ የቅኝ ግዛት ህዝብ በሳቸው መሪነት ሇነፃነቱ ትግሌ ታጥቆ እንዱነሳ ያዯረጉት ጥሪ፥
በተሇይ የፇረንሳይ ህዝብ ያገር ፌቅር ስሜት ቀስቅሶት ባጭር ጊዜ በቂ ሰራዊት በዙሪያቸው ሇማስሇፌ
ችሇው ነበር። ስሇዚህ ያ በጀነራሌ ዯጎሌ ይመራ የነበረው የፇረንሳይ የጦር ሰራዊት በጠቅሊሊው ሇነፃነቱ
ጦርነት ጠቃሚ አስተዋፅኦ ያዯረገ መሆኑ በጊዜውም ከጦርነቱ በሁዋሊም ይነገርሇት ነበር።

«ሰር ዊንስተር ቸርችሌ» የጠቅሊይ ሚኒስትርነቱን ስሌጣን ሲይዙ ያዯረጉት ንግግር ጦርነቱ ወዯ
መጨረሻው የዯረሰ መስልዋቸው ከምርኮውም ከክብሩም ሇመካፇሌ ሲለ ጦርነት ሇገቡት ሇሙሶሉኒና
በጣሉያን አገር የፊስሽትን ስራት ይዯግፈ ሇነበሩት ሁለ እጅግ አሳሳቢና አስጊ የነበረ መሆኑ በግሌፅ
ይታይ ነበር። በንግግሩ ውስጥ ከሞሊ ጎዯሌ እንዱህ የሚሌ ነበረበት። «ጦርነቱ ምንም ያክሌ ረዥም ጊዜ
ቢወዴስ፥ ይህች አገራችን እንግሉዝም የምትያዝ ቢሆን እንኩዋ መንግስታችነን የእንግሉዝ ተባባሪዎች
ከሆኑት አገሮች (ኮመንዌሌዝ) ወዯ አንደ አዛውረን ትግሊችነን እንቀጥሊሇን እንጂ የጦርነቱ ጊዜ
ስሇረዘመና አገራችን ስሇ ተያዘች መጨረሻው አይሆንም። ሇምንም ያክሌ የረዥም ጊዜ ጦርነት የሚብቃ
ህዝብና የሚበቃ ሀብት ስሊሇን የጦርነቱ መጨረሻ «የአክሲስ» መንግስታት (ጀርመን ጃፓን ኢጣሉያ)
ዴሌ ሆነው የጦር ሀይሊችን ሲዯመሰስ ብቻ ነው!» ይህን የመሰሇ ንግግር ሇኛ፥ የጣመንን ያክሌ ወይም
ከዚያ የበሇጠ በችግር ሊይ ሇነበረው ሇጣሉያን ህዝብ መራራ ነበር።

በተሇይ ሇኛ ሇኢትዮጵያውያን እስረኞች ጠቅሊይ ሚኒስትር ቸርችሌና ያሜሪካው ፕሬዝዯንት


«ፌራንክሉን ዲሊኖ ሮዝቨሌት» አትሊንቲክ ውቅያኖስ ሊይ በመርከብ ተገናኝተው ከተነጋገሩ በሁዋሊ፥
ጦርነቱ ስሇሚዋጉበት አሊማ ያወጡት «አትሊንቲክ ቻርተር» በተባሇ ስም የታወቀ መግሇጫ የነፃነት
ተስፊችነን ከምንጊዜውም የበሇጠ አጉሌቶና አበርትቶ ዯስታችነንም በዚያ መጠን አብዝቶት ነበር።
የመግሇጫው ፌሬ ነገር ሁሇቱ ሀያሊን መንግስታት (እንግሉዝና አሜሪካ) ተባባሪዎቻቸው ጭምር
ጦርነቱን እስከ መጨረሻ የሚዋጉበት አሊማ «የአክሲስ» መንግስታት (ጀርመን ጃፓን ኢጣሉያ) ዴሌ
አዴርገው እኒያ ሶስት መንግስታት በሁሇተኛው የአሇም ጦርነት የያዙዋቸው አገሮች ሁለ ሙለ

190
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ነፃነታቸውን እንዱያገኙ ማዴረግ እንጂ በኒያ ባጥቂዎች ቦታ ተተክተው ቅኝ ግዛቶቻቸው ሇማዴረግ
ፌፁም ሙሊት የላሊቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነበር።

ያን «የአትሊንቲክ ቻርተን» መግሇጫ ከሰማንበት ጊዜ ጀምሮ ራሳችነን ባካሌ ባይሆን በመንፇስ


በግብር ባይሆን ባሳብ የአሜሪካ የእንግሉዝና የተባባሪዎቻቸው የጦር ባሇ ቃሌኪዲኖች አዴርገን ቆጥረን
በእስር ቢዑታችን እንዲሇን የነፃነቱን ጦርነት አብረናቸው እንዋጋ ጀመር! ሲቀናቸው ዯስታ ሳይቀናቸው
ብስጭትና አዘን እንዯነሱ እዬተፇራረቁብን የነፃነቱን ትሌ አብረናቸው እንታገሌ ጀመር!

ካንዴ ወገን እንግሉዝ ተጠናክረው አሜሪካና የእንግሉዝ ተባባሪዎች (ኮመንዊሌዝ) ተጨምረው


የሚዋለሇትን አሊማ ጥርት አዴርገው ገሌፀው ጦርነቱን ባዱስ መንፇስ መጀመራቸው ዯስ ሲያሰኘን
ከላሊ ወገን መስኮብ በጦርነቱ አሇመግባቱ የሩቅ ተመሌካች ሆኖ መቅረቱ ያናዴዯን ነበር። አሜሪካና
እንግሉዝ ከተባባሪዎቻቸው ጋር፥ በአውሮፓ ጀርመንና ጣሉያንን ከፉት ሲወጉ መስኮብ ጀርመንን
ከጀርባው የሚወጋው ቢሆኖ ኖሮ ዴሌ አዴራጊዎች መሆናችን የተረጋገጠ ከመሆኑ ላሊ የጦርነቱ
መጨረሻም ይፊጠን እንዯ ነበረ እናምን ነበር። ነገር ግን ከዚህ ከፌ ብል እንዯተመሇከተው አድሌፌ
ሂትሇርና ዮሴፌ ስታሉን፥ መስኮብ ምስራቅ ፖሊንዴ የቦሌቲክን አገሮችና ፉንሊዴን ሇመያዝ ጀርመን
መሀሌ አውሮፓን ሇመያዝ ቀዯም ብሇው «መጥወኒ እመጥወክ» (አጉርሰኝ ሊጉርስህ) ተባብሇው
የምስጢር ውሌ የተዋዋለ በመሆናቸው ኮሚኒስት መስኮብ ሁሇቱ ወገኖች ጠሊቶቹ እስኪተሊሇቁ
ያሇዚያም እስኪዲከሙ ሲጠብቅ የሚቆይ መስል ታይቶን እንናዯዴ እናዝን ነበር።

አንዴ ቀን አበበ ገብረ ፃዴቅና እኔ ከፍቅ በረንዲችን ሊይ እየተመሊሇስን ስናወራ፥ እታች ኮስሮፌ
ከወዯ አዯባባዩ እዬሮጠ ወዯኛ ሲመጣ፥ አይተን «ምን ሆኖዋሌ» ስንሌ እሱም ቀና ብል አዬንና፥ «ሌጆች
የምስራች!» አሇ።

«ምስር ብሊ! ምንዴን ነው የምስራቹ?» አሌሁ እኔ።

«ጀርመን መስኮብን ዩክሬንን ወረረ!»

«መቼ?»

«ትናንት»

አቤ - ት፥ ያ ጊዜ ዯስታችን! «ያንደ ቤት ሲቃጠሌ ሇላሊው ብርሃንንና ሙቀትን ይሰጣሌ»


እንዯሚለት አዯሌ? ኮስሮፌ እኛ ዘንዴ ሲዯርስ ሁሇታችንም እያቀፌን ስመነው፥ «በቃ፤ ዴሌ አዯረግን!
ዴሌ አዯረግን! ያውም ነገ!» ተባብሇን በዯስታ እንዘሌ ጀመር። ብቻ ዴለ እንዲሰብነው የኛ መሆኑ እውን
ቢሆንም የጦርነቱ መጨረሻ እንዲሰብነው «ነገ» ወይም ከነገ - ወዱያ አሌሆነም፤ ረዢም ጊዜ ፇጀ።
ጀርመን መስኮን የወረረበት እንዯ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር 1942 በጀነራሌ አይዘንሀወር ይመራ የነበረው

191
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያሜሪካ የንግሉዝና የተባባሪዎቻቸው የጦር ሀይልች የነበሩ ነፃ አውጪ ሰራዊት በሰሜን አፌሪካ ወርድ
ያሇ ብርቱ ተቃውሞ ሰፉ ቦታ መያዙን ሰማን። ያነሇት «እሰይ የዴሌ በር ተከፇተ!» ብሇን ዯስታችን
ቅጥ መጠን ያጣ ሆነ። ጀነራሌ አይዘንሀወር በአውሮፓ የጦር ግንባር የነፃ አውጪው ሰራዊት ጠቅሊይ
አዛዡ ነበሩ።

እኛም አብዛኛው የልንጎቡኮ ህዝብም ራዱዮ ስሊሌነበረን ወሬውን መስማት የምንችሌ በከተማው
ዋና አዯባባይ የራዱዮ ማጉያ ስሇ ነበረ ከቀኑ በሰባት ሰአት እዚያ የተሰበሰብን ነበር። ታዱያ እዚያ
በጣሉያን ራዱዮ ሲነገር እንሰማው የነበረ ሁለ የውሸት ፕሮፓጋንዲ ነበር። ጀርመን ጃፓንና ጣሉያን
በየጦር ግንባሩ ይዯረግ በነበረው ግጥሚያ የዯረሰባቸው ጉዲት አይነገርም ነበር፤ አንዲንዴ ጊዜ
የሚነገረው ይህን ያክሌም ከጉዲት ቁጥር የማይገባ ፇፅሞ «ጉዲት» ሉባሌ የማይችሌ ነበር። ያን ጊዜ
የጣሉያን ራዱዮ እያጋነነ ይናገር የነበረ በዬጦር ግንባሩ ከመጠን ያሇፇ ጉዲት የሚዯርሰው ባሜሪካኖች
በንግሉዞችና በተባባሪዎቻቸው ሊይ መሆኑን ነበር። ካሜሪካ ከንግሉዝና ከተባባሪዎቻቸው በዬቀኑና
በዬጦር ግንባሩ የሚወዴቀው አይሮፕሊን የሚዯመስሰው ታንክና የሚገዴሇው ወይም እስከ አሇቆቹ
የሚማረከው ወታዯር የጣሉያን ራዱዮ እንዯሚያወራው ቢሆን ኖሮ ሰራዊታቸውና መሳሪያቸው አሌቀው
በጥቂት ወራት እየጦርነቱ ፌፃሜ የሚህን ይመስሌ ነበር! ነገር ግን ጦርነቱ ይበሌጥ እዬተፊፊመ
ይቀጥሌ ነበር። ስሇዚህ የጣሉያን ራዱዮ፥ የጀርመንና የጣሉያን ሰራዊቶች የበረቱ፤ ያሜሪካ የንግሉዝና
የተባባሪዎቻቸው ሰራዊቶች ወታዯርና መሳሪያ አሌቆባቸው የዯከሙ አስመስል ያወራ የነበረው ምኞት
እንጂ እውነት አሇ መሆኑን አውቀን ወሬ በምንሰማበት አዯባባይ እንዯቆምን እኛ እስረኞች እስበሳችን
እየተጠቃቀስን ያሹሙር ፇገግታ እንሇዋወጥ ነበር። ታዱያ ሇካስ ያን ሁኔታችንን ሁለ ይመሇከቱ
ከነበሩት መሀከሌ አንዲንድቹ እየሄደ ሇባሇስሌጣኖች ይነግሩብን ኖሮ ወዯ አዯባባይ እየሄዴን ወሬ
እንዲንሰማ ተከሇከሇን። እኛም አዴራጎታችን የማይገባ መሆኑን ተረዴተን፥ በሱ ተቆጥተውና ያገር ፌቅር
ገፊፌቶዋቸው ሇባሇስሌጣኖች የነገሩብንም የራዱዮን ወሬ ወዯሚሰማበት አዯባባይ እንዲንሄዴ የወሰኑብን
ባሇስሌጣኖችም ጥፊት እንዲሌነበረባቸው ጥፊት የራሳችን እንዯ ነበረ አምነን «እንዱያውም ሲያንሰን
ነው!» ብሇን ውሳኔውን በጥሞና ተቀብሇን በወሬ ጊዜ እንኩዋንስ ወዯ አዯባባይ ሌንሄዴ ከቤት
መውጣቱንም ተወን። ይሁን እንጂ ሙሶሉኒንና የፊሽስት ስራት ይጠለ ከነበሩት ሰዎች አንዲንድቹ
ካዯባባይ ሲመሇስ ወዯኛ እየመጡ የሰሙትን ይነግሩን ስሇ ነበረ ወዯ አዯባባይ እንዲንሄዴ በመከሌከሊችን
በየቀኑ በራዱዮ ይነገር የነበረው ወሬ ከሞሊ ጎዯሌ አያመሌጠንም ነበር።

መቸም የውሸጥ ፕሮፓጋንዲ አሌፍ አሌፍ ባንዲንዴ ተጨባጭ እውነት ካሌተዯገፇ ፕሮፓጋንዲ
በሚነዛው ሰውም ሆነ መንግስት ትዝብትንና ንቀትን ማስከተለ የማይቀር ነው። በጣሉያን መንግስት
የዯረሰውም ይህ ነበር። ጦርነቱ በሰሜን አፌሪካ እሰከ ግብፅ ወሰን ሲዯርስና በተሇይ የነፃ አውጪው
ሰራዊት ያዬር ሀይሌ የመሬት ውጊያ በሚዯረግበት በሰሜን አፌሪካ ብቻ ሳይወስን ከዚያ አሌፍ
የጣሉያንን አገርም ጀርመኖች የያዙትን ምእራብ አውሮፓንም መዯብዯብ ሲጀምር እኛ በነበርንበት ክፌሌ

192
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዯ ተመሇከትነው፣ የጣሉያን ህዝብ መንግስቱ በራዱዮ ስሇሚነዛው የውሸት ፕሮፓጋንዲ ትዝብቱንና
ንቀቱን በስውር ሳይሆን በግሌፅ ማሰማት ጀመረ።

በኢትዮጵያ «ማሰሪያውን ቆርጦ የወጣ በቅል መብረር ታፌኖ የኖረ ሰው መናገር ከጀመረ በፉት
አዯጋ ቢኖር አይታዬውም!» እንዯሚባሇው የጣሉያን ህዝብ አፌኖት ይኖር የነበረው የፊሽስት ብርቱ
ክዴን ዯከም ያሇ ስሇ መስሇው እስከዚያ ጊዜ ዴረስ በመንግስቱ ሊይ መናገር ይቅርና መስማት እንኩዋ
ይፇራ የነበረው ነቀፊና ዘሇፊ እስበሱ ሳይፇራራ በዴፌረት መነጋገር የተሇመዯ ሆነ። በጦር ጉዋዯኝነት
ጣሉያን አገር የነበሩትን የጀርመን ወታዯሮችም እንዯ ጦር ጉዋዯኞች ሳይሆኑ አገሩን ሉይዙበት እንዯ
መጡ የጠሊት ወራሪ ወታዯሮች ቆጥሮዋቸው በጥሊቻ አይን የመሇከታቸው ጀመር። ይህ ሁለ
በኢጣሉያን አገር ከዚያ በፉት ከነበረ ሁኔታ ፇፅሞ የተሇየ ትሌቅ ሇውጥ ሆኖ ታይቶን፥ ቀኑ መቸ
እንዯሚሆን ባናውቅም ሙሶሉኒ የሚወዴቅበት ጊዜ ሩቅ እንዯማይሆን አምነን፥ ከሙሶሉኒ በሁዋሊ
በጣሉያን አገር የሚዯረገው ሇውጥ «በሬቮለሽን ይሆን ወይስ በሰሊም?» በሚሇው ጥያቄ ሊይ እስበሳችን
እንከራከር ጀመር።

የጄነራሌ አይዘንሀወር ነፃ አውጪ ሰራዊት ሞሮኮን ቱኒስያንና አሌጀሪያን አሌፍ ሉቢያ መዴረሱ
እንዯ ታወቀ ከዚያ ዯቡቡ የጣሉያን ክፌሌ ሩቅ ስሊሌ ሆነ «በቅርቡ ወዯዚያ ክፌሌ ሳይሻገር አይቀርም?»
እየተባሇ ይወራ ጀመር። ወዱያው በዚያ ጊዜ ይወራ በነበረው ወሬ ምክንያት ይሁን ወይም በአጋጣሚ
ክቡር ራስ እምሩና ሌጅ ግርማቸው ተክሇ ሀዋርያት ከሲሲሉ ሰሜን ሉፓሪ በሚባሇው ዯሴት ከነበሩት
እኛ ወዯ ምንኖርበት ወዯ ልንጎቡኮ እንዱዛወሩ ተዯረገ። ነገር ግን ልንጎቡኮ ከኛ ጋር ሳይሆን መንግስት
የተሇዬ ቤት ተከራይቶ ነበር ያስቀመጣቸው። ቢሆንም እንዲንገናኝ ስሊሌተከሇሌን እየተገናኘን በጠቅሊሊው
ስሇ ጦርነቱም በተሇይ ስሇ ሀገራችንም ሇመወያየት ተመቸን።

ነፃ አውጪው ሰራዊት መጀመሪያ ሰሜን አፌሪካ ሲወርዴ የገጠመው ተቃውሞ «እጅግ ብርቱ»
የሚባሌ አሌነበረም። ነገር ግን ጀርመናዊው ፉሌዴ ማርሻሌ ሮሜሊ የጀርመንና የጣሉያን ሰራዊቶች
ባንዴነት አጠናክሮ እዬመራ የመከሊከያ ጦርነት በመዋጋት ሳይወሰን የማጥቃት ጦርነትም መዋጋት
ከጀመረ በሁዋሊ ጦርነቱ በጣም ጠንክሮ እዚያው ሰሜን አፌሪካ ሊይ ወዯ ፉትና ወዯ ሁዋሊ ሲመሊሇስ
ዘጠኝ ወራት ያክሌ ቆዬ። ሮሜሊ፥ የሚያስገርም ችልታ የነበረው የጦር አዛዥ መሆኑን ጠሊቶቹ ሁለ
ተስማምተው በአዴንቆት ይመሰክሩሇት ነበር። ከዚያ ጀነራሌ አይዘንሀወር ሰራዊት በማየለ በሀምላ ወር
1943 ከሰሜን አፌሪካ ተራምድ በዯቡብ ኢጣሉያ ሲሲሉ የተባሇውን ክፌሌ መውረር ጀመረ። ከላልች
የኢጣሉያ ክፌልችም ብዙ ከተሞችን ባዬርና በጠረፌ ያለትን በመርከብ መዯብዴቡ ከጊዜ ወዯ ጊዜ
እየከፊ ይሄዴ ጀመር። ያን ጊዜ ችግርና ጦርነት ተዯራበው ያመረሩት የጣሉያን ህዝብ «ሰሊም
እንፇሌጋሇን፤ ከጦርነቱ እንውጣ!» እያሇ እስከዚያ ዴረስ ያዯርገው እንዯ ነበረ በማጉረምረም ሳይሆን
ዴምፁን ከፌ አዴርጎ በየቦታው ማሰማት ጀመረ።

193
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሲሲሉ ጦርነት ብዙ አሌቆየም። በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ዯሴቱ በሙለ በነፃ አውጪው ሰራዊት
ተያዘ። ከዚያም ነፃ አውጪው ሰራዊት «የመሲናን የባህር ሰሊጢ» ተሻግሮ ካሊብርያንና ላልችን የዯቡብ
ኢጥሉያ ክፌልች ሇመውረር በመሰናዲት ሊይ እንዲሇ የኢጣሉያ ንጉስ ቪቶሪዮ አማኑኤሌ ሙሶሉኒ
ስሌጣኑ ሇማርሻሌ ፔትሮ ባድሉዮ እንዱያስረክቡ ማዘዛቸው በይፊ ተገሇፀ። ስሇዚህ በዚያው በሀምላ ወር
1934 ሙሶሉኒ ስሌጣኑን ሇባድሉ ሇቅቆ፥ «ፓንዛ» በሚባሌ ዯሴት በግዞት እንዱቆይ መዯረጉን ሰማን።
«ፓንዛ» ሙሶሉኒና የፊሽስትን ስራት ይቃወሙ የነበሩ ብዙ የፖሇቲካ ሰዎች ፇሊስፍችና ፀሀፉዎ በዞት
ይኖሩበት የነበረ ቦታ ከመሆኑ ላሊ፥ አንባቢዎች በላሊ ምእራፌ ያመሇከትሁትን እንዯሚያስታውሱት
ክቡር ራስ እምሩ ክቡር ዯጃዝማች ታዬ ሌጅ ይሌማ ዯሬሳና እኔም መጀመሪያ በእረኝነት ወዯ ጣሉያን
አገር እንዴሄዴ እዚያው ፓንዛ ነበር የቆይነው። ስሇዚህ የሙሶሉኒን በግዞት ወዯ ፓንዛ መወሰዴ ስንሰማ
«ታሪክ አሽሙር ነው!» የሚባሇውን ዘይቤ አስታውሰን ተገረምን።

«ማርሻሌ ባድሉዮ ከሙሶሉኒ ስሌጣን እንዱረከቡ የተዯረገበት ዋና ምክንያት ህዝቡ ሰሊም ስሇ


ፇሇገ በተቻሇ መጠን የኢጣሉያ ክብርም ጥቅምም የማይጎዲበት የእርቅ ስምምነት ከዴሌ አዴራጊዎች
መንግስታት ጋር ሇመነጋገር እንዱመች ነው» ሲባሌ ይሰማ ነበር። ነገር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ ባድሉዮ
ስሌጣን በያዙ ባርባ ቀናት ውስጥ መስከረም 3 1934 ኢጣሉያ ዴሌ መሆንዋን ተቀብሊ ያሇምንም ውሇታ
(ኮንዱሽን) እጅዋን ሰጠች። ኢትዮጵያ ከኢጣሉያ ነፃ የሆነች እንዱያውም ኢጣሉያ ዴሌ ሆና እጅዋን
ከመስጠትዋ በፉት በ1940 – 41 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1933) ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ነፃነት
ከኢጣሉያ ዴሌ መሆን ጋር የተያያዘ መሆኑን እናምን ስሇ ነበረ ያገራችን ነፃነት እውን መሆን ተቀብሇን
እስበሳችን «የምስራች!» እየተባባሌን። ኢጣሉያ ዴሌ ሆና እጅዋን መስጠትዋን በሰማ ጊዜ ነበር።

ምእራፍ ሃያ ስድስት

ነፃነት
ኢጣሉያ እንዯ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በመስከረም መጀመሪያ 1943 ሊይ ዴሌ መሆንዋን ተቀብሊ
እጅዋን ብትሰጥም በጣሉያን አገር ጦርነቱ አሌቆመም፥ ይቀጥሌ ነበር። በዚያ ጊዜ ነፃ አውጪው ሰራዊት
የያዘው ከዯቡብ ኢጣሉያ ጥቂቱን ክፌሌ ብቻ ስሇ ነበረና የሚበዛው የጣሉያን ክፌሌ ገና በጀርመን
ሰራዊቱ እንዯ ተያዘ ስሇ ነበረ በዚያ የጀርመን ሰራዊት በያዘው ክፌሌ ብርቱ ጦርነት ይካሄዴ ነበር።
ዋናው ከተማ ሮም እንኩዋ በነፃ አውጪው ሰራዊት የተያዘ ኢጣሉያ እጅዋን ከሰጠች በሁዋሊ ዘጠኝ
ወራት ያክሌ ቆይቶ፥ በሰኔ ወር መጀመሪያ 1944 ነበር። ከዚያ በሁዋሊም ቢሆን፥ በሰሜኑ የኢጣሉያ
ክፌሌ በነፃ አውጪው ሰራዊትና በጀርመን ሰራዊት መሀከሌ ብርቱ ጦርነት እንዯ ተካሄዯ ነበር።
እንዱያውም ነፃ አውጪው ሰራዊት በሰሜን ኢጣሉያ ብቻ ሳይሆን በጠቅሊሊው ምእራብ አውሮፓን
ወርሮ ጀርመን የያዛቸውን አገሮች ሇማስሇቀቅ አይነተኛውን የማጥቃት ጦርነት የጀመረ በዚያው በሰኔ

194
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወር 1944 ነበር። ያሜሪካ የንግሉዝና የተባባሪዎቻቸው ሰራዊት ከምእራብ የመስኮብ ሰራዊት ከምስራቅ
ሀይሊቸውን አስተባብረው ጀርመንን መውጋት የጀመሩም በዚያ ጊዜ ነበር።

መቸም የምእራቡ ክፌሌ ነፃ አውጪ ሰራዊት መሰናድውን፥ በንግሉዝ ሀገር ካጠናቀቀ በሁዋሊ
በስኔ መጀመሪያ 1944 ወራሪ ሰራዊቱን በፇረንሳይ አገር ሇማወዴ ያሰሇፇው የመርከብና ያዬር ሀይሌ
«ከዚያ በፉት በታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅ» ይባሊሌ። ከታች የጠሊትን መከሊከያ እየዯመሰሰ
ወታዯሩን በፇረንሳይ መሬት ያወረዯው መረከብ ብዛት ከ4000 በሊይ ሲሆን እመሬት የወረዯውን
ወታዯር ከጠሊት አዯጋ ሇመጠበቅና ሇመከሊከሌ የፇረንሳይን ጠፇር እንዯ ጉም የሸፇነው ያይሮፕሊን
ብዛት ከ3000 በሊይ እንዯ ነበረ ይናገራሌ። ከዚያ በሁዋሊ ጦርነቱ በየቦታው ሁለ ነፃ አውጪው ሰራዊት
የማጥቃት ጀርመን የመከሊከሌ ጦርነት የሚዋጉበት ሆነ።

ሁሇተኛው የአሇም ጦርነት እንዳት እንዯ ተነሳና እንዯ ተፇፀመ በያንዲንደ የጦርነት ቦታ
ተፊሊሚ ሀይልች ምን ምን ያክሌ ሰራዊት አሰሌፇው በምን አይነት መሳሪያ እንዯ ተዋጉና በየቦታውስ
ማን አሸናፉ ማን ተሸናፉ እንዯ ሆነ በመጨረሻም ጦርነቱን ያነሱት ዱክቴተሮች ፌፃሜያቸው ምን እንዯ
ሆነ ይህን ሁለ ሇመረዲት የሁሇተኛውን አሇም ጦርነት ዝርዝር ታሪክ ማንበብ ያስፇሌጋሌ። ነገር ግን
እኔ ከዚህ ከሁሇተኛው የአሇም ጦርነት ከኢትዮጵያና ከኛ ከኢትዮጵያውያን እስረኞች ጋር የተዛመዯውን
ክፌሌ ብቻ ሇማመሌከት ያክሌ እንጂ በጠቅሊሊው የጦርነቱን ታሪክ ሇመፃፌ አሳቡም አስፇሊጊው ጠሇቅ
ያሇ ጥናትም ስሇላሇኝ እሱን ሇታሪክ ፀሀፉዎች ትቼ እኛን እስረኞችን ወዯሚከተሇው ክፌሌ
እመሇሳሇሁ።

አንዴ ቀን እስረኞች በርከት በሇን ከፍቅ በረንዲችን ሊይ ተቀምጠን ስናወራ ቴዎዴሮስ ወርቅነህ
ከጥቂት ወታዯሮች ጋር ወዯኛ ሲመጣ አየን። ወታዯሮች የሇበሱት መሇዮ የጣሉያን አሇመሆኑን
ብናውቅም፥ የምን አገር መሆኑን ሌናውቅ ሳሊሌቻሌን «የምን ወታዯሮች ይሆኑ?» እየተባባሌን
እስበሳችን ስንጠያየቅ እኛ ባሇንበት ዯረሱና ቴዎዴሮስ አስተዋወቀን። የ ‹ካናዲ› ወታዯሮች ነበሩ።

በመሌእክት ሊይ የነበሩ ጉዋዯኞቻቸው ከኛ፥ በሊይ በገዯሊማው ቦታ መኪና ተሰናክልባቸው


ከሊካቸው የጦር ሰፇር ርዲታ እንዯሚዯርስሊቸው በራዱዮ አመሌክተው ኖሮ፥ እነሱን ሇመርዲት የሚሄደ
ወታዯሮች ነበሩ። ልንጎቡኮ ሲዯርሱ ቁርስ ቀምሰው ሇማሇፌ «ሮማና ሆቴሌ» ገብተው የፇሇጉትን
ሇሆቴለ አስተናጋጆች ሇመንገር እነሱ ጣሉያንኛ የሆቴለ አስተናጋጆች እንግሉዝኛ ባሇማወቃቸው
የመግባባት ችግር ስሇ ተፇጠረ፥ ባጋጣሚ ቴዎዴሮስ እዚያ ተገኝቶ በሱ አስተርጉዋሚነት የፇሇጉት
ቀርቦሊቸው እየተመገቡ ከቴዎዴሮስ ጋር ሲጫወቱ ስሇሱም ስሇነሱም ማነንት በሰፉው ተነጋግረው
ይተዋወቃለ። ቴዎዴሮስ እንግሉዞች ባፄ ቴዎዴሮስ ሊይ በዘመቱ ጊዜ አፄ ቴዎዴሮስ - እጃቸውን
ሇጠሊት ከመስጠት ራሳቸውን መግዯሌ መርጠው በገዛ መሳሪያቸው ህይወታቸውን ሲያሳሌፈ አባቱን
ሀኪም ወርቅነህን በሕፃንነታቸው ወስዯው እያስተማሩ ካሳዯጉዋቸው በሁዋሊ ሀኪም ወርቅነህ

195
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከእንግሉዛዊት እናት የወሇደት ስሇ ነበረ በእንግሉዝኛ አነጋገሩት በመሌኩም ሌክ እንግሉዞችን ነበር
የሚመስሌ።

ቁርሳቸውን እንዯ ጨረሱ የካናዴያኑ ሹም (የመቶ አሇቃ ነበር) ሶስት ወታዯሮች አስከትል
የቀሩትን ከመኪናዎቻቸው ጋር እዚያው ትትወ ከቴዎዴሮስ ጋር እኛን ሇማየት መጡ። ወዱያው፥
ወንበሮችን ከየክፌለ ሰባስበን አስቀመጥናቸውና ስሇኛም ስሇነሱም መነጋገር ጀመርን። ቡና እንዱጠጡ
ብንሇምናቸው በችግር ሊይ ሇነበሩ ጉዋዯኞቻቸው ሇመዴረስ መቸኮሊቸውን ምክንያት አዴርገው ግብዛችንን
አሌተቀበለም። ቢሆንም ኢጣሉያ ኢትዮጵያን ወርራ ከያዘችበት ከ1936 (በጎርጎርዮስ አቆጣጠር) ጀምሮ
ከሰባት አመት በሊይ በእስረኝነት ጣሉያን አገር የኖርን መሆናችንንና ኢጣሉያ ከሀገራችን ከወጣች
በሁዋሊም በሁሇቱ አገሮች (በኢጣሉያና በኢትዮጵያ) መሀከሌ ግንኙነት ባሇ መኖሩ በእስረኝነታችን
እንዲሇን መሆናችንን ስንነግራቸው በትእግስት ሇማዲመት ያክሌ ጊዜ ሰጡን። ከዚያ እነሱ አባልች
የሆኑበት የነፃ አውጪው ሰራዊት ዋና መምሪያ «ባሪ» በሚባሇው የወዯብ ከተማ በመሆኑ ሇርዲታ
ከሚሄደበት ቦታ እንዯ ተመሇሱ እኛ ስሇምንገኝበት ሁኔታ የተረደትን ሇሰራዊቱ ጠቅሊይ አዛዥ ነግረው
ባንዴ ሳምንት ውስጥ ነፃ የሚያወታን ባሇስሌጣን እንዯሚሊክሌን የመቶ አሇቃው የተጋረጠ ተስፊ
ሰጠውን ሄደ።

እዴሜውን ሙለ ታውሮ የኖረ ሰው «ነገ ትበራሇህ» ቢለት «ዛሬን እንዳት አዴሬ?» አሇ


እንዯሚባሇው እኛም ከሰባት አመታት በሊይ በእስረኝነት ኖረን «ባንዴ ሳምንት ውስጥ ነፃ ትሆናሊችሁ»
ሲለን ሳምንቱን በጣም ረዢም ቢጎቱት የማይዯርስ መስል ታየን። ሁውሊ ያ ሳምንት እንዯ ምንም
እያዘገመ ዯረሰ ነፃ የሚያወጣን ባሇስሌጣን ግን አብሮ አሌዯረሰንም። ያን ጊዜ እንዳት ተሰቀቅን «ምነው
እኒያን ካናዲውያን ባሊገኘንና የነፃነትን ወሬ ባሊሰሙን ኖሮ!» እያሌን ማሌካም ወሬ ያሰሙንን ሰውፕች
ወቀስን! ታዱያ ካንዴ ወገን ያ ስንመኘው የነበረው ነፃነት «ያዝነው ጊዜንና ያመሇጠን መስልን ስናዝን
ከላሊ ወገን ሰውና ሁኔታው ጊዜንና ጊዜ የሚወሌዲቸውን አዲዱስ ሁኔታዎች ተከትሇው የሚሇዋወጡ
መሆናቸውን ስንገረም እየተመሇከትን ሰነበትን!

ኢጣሉያ ዴሌ ሆና፥ እጅዋን ከሰጠች በሁዋሊ በጣሉያን አገር ሊስራ አንዴ ወራት ያክሌ መንግስት
አሌነበረም። ሰሜኑ ክፌሌ የጀርመንና የነፃ አውጪው ሰራዊቶች የሚዋጉበት ዯቡብ ክፌሌ በነፃ
አውጪው ሰራዊት ቁጥጥር ስር ነበሩ። ስሇዚህ የነፃ አውጪው ሰራዊት አካሌ የሆኑት ካናዲውያን
ጉዞዋቸውን አቁዋርጠው ወዯኛ መጥተው አነጋግርውን መሄዲቸው በልንጎቡኮ ህዝብ መሀከሌ ሲታወቅ
በእረኝነት በኖርንበት አገር እንዯ እስረኞች መታየታችን ቀርቶ የነፃ አውጪው ሰራዊት ወገኖች ሆነን
ታየን! ስሇዚህ ወዲጅነታችንን የሚፇሌገው ሰው በዝቶ ሰነበተ። ከህዝቡ መሀከሌ እንኩዋ -
እስከምናውቀው ዴረስ - እኛን በመሌካም በክፈ አይን የሚያየን ፉቱንም ብዙም እንዲሌነበረ እናምናሇን።
ከሹማምንቱ መሀከሌ ግን እንዲንቸገር ሉረደን የሚሞክሩም ትናንሽ ምክንያቶችን እየተቆጣጠሩ

196
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያስቸግሩን የነበሩም ነበሩዋቸው። ታዱያ እንዲንቸገር ያስቸግሩን የነበሩት ከበሊይ የተሰጣቸው ትእዛዝ
ወይም መመሪኢያ አስገዴድዋቸው የሰሩት አንዲንዴ ስራ አሳዝኖን ሆነ «ይቅር» እንዴንሌና የነፃ
አውጪው ሰራዊት ሹማምንት ቢመጡ በመሌካም እንጂ በክፈ እንዲአስተዋውቃቸው ሲያስተባብለን
ሰነበቱ።

የካናዲ ወታዯሮች ከመቶ አሇቃቸው ጋር አነጋግረውን ከሄደ በሁዋሊ በሶስተኛው ሳምንት


አጋማሽ ግዴም እስረኞች ሁለ ከክቡር ራስ እምሩና ከሌጅ ግርማቸው በቀር ወዯ ከንቲባው መስሪያ ቤት
ተጠርተን ስንዯርስ አዯባባዩን ብዙ ወታዯሮችና ካሚዮኖች ሞሌተውት አገኘን። እኒያ ወታዯሮችና
ካሚዮኖች ነፃ አውጪው ሰራዊት እኛን ነፃ ሇማውጣት ከ«ባሪ» የሊከቸው ነበሩ። እኛ ከመዴረሳችን
በፉት የወታዯሮቹ አዛዥ እንግሉዛዊው ሻሇቃ ክቡር ራስ እምሩ ወዯ ነበሩበት ቤት ሄዯው እሳቸውንም
ሌጅ ግርማቸውንም አነጋግረው መመሇሳቸውን ሁዋሊ ሰማን። ዯጃዝማች (ሁዋሊ ቢትወዯዴ) መንገሻ
ውቤም እኛ ከነበርንበት ትንሽ ራቅ ባሇ ቦታ ስሇ ነበሩ፥ እዚያ አሌነበሩም። ወዯ ከንቲባው ፅህፇት ቤት
ስንገባ እንግሉዛዊው ሻሇቃ ዋናውን ቦታ ይዘው በዙሪያቸው ከንቲባውና ላልች የዚያ አገር ሹማምንት
ተቀምጠው ነበር። ሻሇቃ ተነስተው ሇሁሊችንም የጅ ሰሊምታ ሰጥተውን እስኪቀመጡ ዴረስ፥ ከንቲባውም
የዚያ አገር የፀጥታውና የፖሉሱ ሹማምንትም እኛን ሇማስከበር ሳይሆን እንግሉዛዊውን መኮንን ሇማጀብ
አብረዋቸው ተነስተው ቆመው ቆዩ።

ከዚያ የንግሉዙ ሻሇቃ እዚያ አገር በእስረኝነት ስንኖር በምግብ በሌብስ በህክምና እጦትና በላሊ
በማናቸውም ነገር የዯረሰብን በዯሌ ቢኖር እንዴንናገር ጠየቁን። እኛም ከመግባታችን በፉት
የምንጠይቀው ጥያቄ ቢኖር በሁሊችን ስም ባሊምባራስ እማኙ ይመር በቴዎዴሮስ ወርቅነህ
አስተርጉዋሚነት እንዱመሇሱ ተስማምተን ስሇ ነበረ፥ እሳቸው መሌስ ሰጡ።

ባሊምባራስ በሰጡት መሌስ «እስረኞች እንዯ መሆናችን ከቤት ወጥተውን የምንገባበት ጊዜና
የምዯርስበት ቦታ የተወሰኑ ከመሆናቸውና እንዱሁም በእስረኞች ሉዯርሱ ከሚችለ እንዲንዴ ነገሮች
በቀር የዯረሰብን ሌዩ በዯሌ የሇም። ሇምግብ ሇሌብስ ሇመዴሀኒትና በጠቅሊሊው ሇሚያስፇሌገን ሁለ
በየወሩ እንዱከፇሇን ከተመዯበው ገንዘብ ያሇፇው ወር እስከ ዛሬ ባይከፇሇንም ወዯ ፉት እንዯሚከፇሇን
ተስፊ ስሇ ተሰጠን ችግር አሌዯረሰብን፤ እግዚአብሔር ይስጥሌ« ሲለ እንዯሚያበቁት ወቀሳው
እንዲይመር በምስጋና አጣፌጠው ሻሇቃውና ከንቲባው ሳቁ። ከንቲባው እንግሉዝኛ ማወቃቸውን ገና
ያነሇት ነበር ሁሊችንም የተረዲን።

«እውነት ነው ገንዘብ ይሊክሌን ከነበረበት ቦታ ባንዲንዴ ችግር ምክንያት ሳይሊክሌን ቆይቶ ስሇ


ነበረ ያሇፇው ወር ከሚመጣው ወር ጋር ተጨምሮ የሚክፇሌ መሆኑን ነግረናቸው ነበር። አሁንም
በሁሇት ቀናት ውስጥ የሁሇቱ ወራት ባንዴ ሊይ እንዱከፇሊቸው እናዯርጋሇን» አለ ከንቲባው።

197
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
«እንግዱህ የሁሇቱ ወራት ገንዘባችሁ በሁሇት ቀናት ውስጥ የሚከፇሊችሁ መሆኑን ይሄው
አሁን ከከንቲባው ስምታችሁዋሌ፤ ላሊም የጎዯሊችሁ ነገር መኖሩን አሌነገራችሁን። ስሇዚህ እዚህ
የምትፇፅሙት ጉዲይ እንዲሊችሁ ፇፅሙና ጉዋዛችሁን አሰናዴታችሁ እንዲበቃችሁ ወዯ «ባሪ»
እንወስዲችሁዋሇን፤ ከዚያም ወዯ ሀገራችሁ ትሄዲሊችሁ፤ እንኩዋን ከእስረኝነት ነፃ ሇመሆን አበቃችሁ!»
ብሇው ሻሇቃው እንዯ ገና ተነስተው ሇሁሊችንም የጅ ሰሊምታ ሲሰጡን አብረዋቸው ተቀምጠው የነበሩት
የጣሉያን ሹማምንትም ተነስተው «እንኩዋን ዯስ ያሊችሁ!» እያለ የጅ ሰሊምታ ሰጡንና እያመሰገን
ተሰናብተን ወጣን። ከዚያ ጀምሮ ካሳሪዎቻችን ወዯ ነፃ አውጭዎቻችን እጅ ተሊሇፌን። እሰረኞች ሆነን
በጣሉያን አገር ከሰባት አመታት በሊይ ከኖርን በሁዋሊ ነፃ ሆን!

የልንጎቡኮ ከንቲባ፥ በንግሉዛዊው ሻሇቃ ፉት በሰጡት ቃሌ መሰረት በሁሇት ቀናት ውስጥ የሁሇት
ወራት ገንዘባችንን እንዯ ሰጡት በየሱቁ የነበረንን «ደቤ» ከፊፇሌን ከእንዲችንም ነፃ ሆነን። ከዚያ
የምንይዘውን እቃ (ሌብስና መፃህፌት) እያሰናዲን ሶስት ቀናት ያክሌ ልንጎቡኮ ስንቆይ ከእቃ ማሰናዲቱ
በተረፇ ጊዜ ባካባቢያችን አይተናቸው የማናውቀውን የሚያማምሩ ተራራዎችና ጫካዎች ከንግሉዝ
ወታዯሮች ጋር ሆነን እንዯ አገር ጏብኝዎች እየዞርን ስናይ ሰነበትን። ከዚያም እቃችንን በካሚዮኖች
አስጭነን፥ በጠሊት አገርም ወዲጆች ስሇ ማይጠፈ ከወዲጆቻችን ጋር ተሰነባብተን ተነሳን። ዯጃዝማች
መንገሻ ወቤ አቶ በህርነ ሀብተ ሚካኤሌና ጠባቂያችን የነበሩት ሹምባሽ ገብረ ፃዴቅ ሇጊዜው እዚያው
ቆዬ። ላልች እንዯ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥቅምት ወር መጨረሻ 1936 አካባቢ ክቡር ራስ እምሩ
ከእግንሉዛዊው መኮንን ጋር በኦቶመቢሌ የቀረ ነው ሁሊችንም ከእቃችን ጋር በካሚዮኖች ተሳፌረን
ከልንጎቡኮ በዚያ ክፌሌ የነፃ አውጪው ሰራዊት ዋና ሰፇር ወዯ ነበረው ወዯ «ባሪ» ተጉዋዝን። ሹምባሽ
ገብረ ፃዴቅ ልንጉቦኮ የቀሩበት ምክንያት ዴሮውንም እዚያ የነበሩ እስረኞችን የጣሉያን መንግስት
ስሊዘዛቸው እንጂ ራሳቸው እስረኛ ስሊሌነበሩ ነው። ዯጃዝማች መንገሻ ውቤና አቶ ብርሃነ ሀብተ
ሚካኤሌ ከኛ ተሇይተው ልንጎቡኮ የቆዩበትን ትክክሇኛ ምክንያት ግን እኔ አሊወቅሁትም።

ኢትዮጵያ በፊሽስት ኢጣሉያ ከተያዘች በሁዋሊ እንዯ ገና ነፃ መሆንዋና እኛም በኢትዮጵያ ነፃነት
ምክንያት ከኛ በፉት ጠሊቶቻችን ምህረት እያዯረጉሊቸው አገራቸው እንዯ ገቡት ጉዋዯኞቻችን ሳይሆን
እነሱ (ጠሊቶቻችን) ዴሌ ተመትተው በሙለ ነፃነት ወዯ አገራችን ሇመግባት በመሰናዲት ሊይ መሆናችን
እንዯ ታምር ሆኖ ነበር የታየን! መቸም ታምር ማሇት ያስተሳስብን ስነ ስራት ተከትል ይሆናሌ
የተባሇው ሳይሆን ሲቀር «አይሆንም» የተባሇው ሆኖ ሲገኝ ነው። የኢትዮጵያን የኛ ነፃት መሆንም
አያስተሳስብን ስነ ስራት ተከትል ሇተመሇከተው «ሉሆን ይችሊሌ» የማይባ ነበር።

በየጦር ግንባሩ ተሰሌፍ የነበረው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ዴሌ ተመትቶ ጠፌቶ እንዯ ቀዯሙት
ነገስታት የክፌሊተ ሀገሩን ህዝብ አስተባብረው እየመሩ ጠሊትን መቁዋቁዋም ይችለ የነበሩት ንጉሰ
ነገስቱ አገራቸውን ትተው ተሰዯው በየጫካው ተበታትነው ይገኙ ከነበሩት አርበኞች በቀር፥ በብሄራዊ

198
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ዯረጃ የተዯራጀ አንዲች ሀይሌ ባሌነበረበት ፊሽስት ኢጣሉያ ትዮጵያን ከያዘች በሁዋሊ እስዋን (ኢጣሉያ)
አስወጥቶ ኢትዮጵያን እንዯ ገና ነፃ የሚያዯርግ ሀይሌ ይገኛሌ ማሇ ከማንም አሳብ የራቀ ነበር። ሇኛ
ሇእስረኞችም ቢሆን ሁሇተኛው የአሇም ጦርነት ከመነሳቱ በፉት ተስፊችን ከስረኝነት ወጥተን፥ ወዯ
ሀገራችን ተመሌሰን ቢቻሌ ወዯ ላሊ አገር ማምሇጥ፥ ካሌተቻሇ እዚያው ፊሽስት ኢጣሉኢያ የጫነችብንን
የባርነት ቀንበር ከወገኖቻችን ጋር ተሸክሞ ሇመኖር ካሌሆነ በቀር ነፃነት የምንመኘው ምኞት ወይም
የምናሌመው ህሌም እንጂ «እናገኘው ይሆናሌ» ብሇን ተስፊ የምናዯርገው አሌነበረም። እንገር ግን እኛ
ሳናስበው ሁሇተኛው የአሇም ጦርነት ተነስቶ ኢጣሉያ በመጨረሻ ሄዲ ዴሌ ከተመቱት መንግስታት ወገን
ተሰሌፊ ስሇ ተገኘች ቅኝ ግዛቶችዋን እንዴትሇቅ በመንገዴዋ ኢትዮጵያ ነፃ ሆነች! እኛም ህሌማችን
እውን ሆኖ ነፃ ሆነ! «ዯስታ ቀሉሌ» ያባቶች ብሂሌ ነው! መሌካም ትሌቅ ነገር ሁለ ሲጠፊ
የሚከብዯውን ያክሌ ሲገኝ ዯስታው ብዙ ጊዜ አብሮ የማይቆይ ቀሊሌ ይሆናሌ። «ዯስታ ቀሉሌ!!»

እኛ በእረኝነት እንዲሇን ላልች ጉዋዯኞቻችን በየጊዜው «የጣሉያ መንግስት ምህረት


አዴርጎሊችሁዋሌ» እየተባሇ ወዯ ሀገራቸው በገቡ ቁጥር ተሇይተን በመቅረታችን እናዝን ነበር። ነገር ግን
ሁሇተኛው የአሇም ጦርነት ተነስቶ፥ የአሜሪካን የንግሉዝ መንግስታት ከተባባሪዎቻቸው ጋር ጦርነቱን
የሚዋጉበትን አሊማ «አትሊንቲ ቻርተር» በተባሇው ማስታወቂያ ካስታወቁ በሁዋሊ አሳባችንን ሇወጥን።
በዚያ ማስታወቂያ የሚዋጉበት አሊማ «የአክሲስ» መንግስታት (ጀርመን ጃፓን ኢጣሉያ) በጦርነት
የያዙዋቸውን አገሮች ሁለ ነስጻ እንዱወጡ ማዴረግ መሆኑን ከገሇፀበት ጊዜ ጀምሮ ቀዯም ብየ
እንዲመሇከትሁት እኛም ራሳችንን የነሱ (የነፃ አውጪዎች) ባሇ ቃሌኪዲኖች አዴዴርገን ቆጥረን በአካሌ
ባይሆን በንመፇስ በግብር ባይሆን በአሳብ ጦርነቱን አብረናቸው እንዋጋ ነበር! ስሇዚህ ጠሊቶቻችን ዴሌ
ተመትተው ከእስረኝነታችን ነፃ ስንወጣ «እንኩዋንም እስረኞች እንዯሆን ቆየን! እንኩዋንም በጠሊቶቻችን
ምህረት ሳይሆን እነሱ ዴሌ ተመትተው በኛ አሸናፉነት ነፃ ወጣን!» ብሇን ዯስታችን እጥፌ ዴርብ ሆነ!
እውነትስ ነፃነትን የቀማ ጠሊት ወዴድ ሳይሆን ተገዴድ ራርቶ ሳይሆን ዴሌ ተመትቶ የቀማውን ነፃነት
ሲመሌስ ዯስታን እጥፌ ዴርብ የሚያዯርግ አዯሇም? ነፃነት የቀማ ጠሊት ባሸናፉነቱ ኮርቶ በንቀት
ቁሌቁሌ እያዬ «ምህረት እዴርጌሊችሁዋሇሁ!» ከሚሌ ዴሌ ተመትቶ ተንበርክኮ ሽቅብ እያዬ የዯስታ
ሁለ ቁንጭሊሊት የሚያዯርግ ነው! ይህን የምሌም በበቀሌ መንፇስ አሇመሆኑን መግሇጽ እወዲሇሁ።
ሁሌጊዜም ቢሆን ከበዯሇኛ ቅጣት እንጂ ምህረት አዯሇም የሚፇሌገው! የበዯሌ መካሱ እንጂ ዲረጎት
ማጉረሱ የተበዯለትን ክብር አይመስሌም! ተበዴሇው ተዯብዴበው እንኩዋ ዲረጎት ሲያዯርጉባቸው ዯስ
የሚሊቸው ውሾች እንጂ ሰዎች አይዯለም! ስሇዚህ ሰዎች እንዯ መሆናችን ጠሊቶቻችን ራርተው በችሮታ
ሳይሆን ዴሌ ተመትተው በግዳታ በጌትነታቸው ዲረጎት ከሚያጎርሱን ተገዯው ነፃነታችንን በመመሇስ
እንዯ አቻዎች ሲክሱን ይህ ሁለ ሲሆን ነፃነታችንን በመመሇስ እንዯ አቻዎች ሲክሱን ይህ ሁለ ሲሆን
ማየቱ ተገፌፇን የነበረው የሰውነት ክብራችን ተቀምጠን የነበረው ነፃነታችን ሇመመሇሱ ማረጋገጫ

199
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በመሆኑ የፊሽስቶች ዴሌ መሆንና በዚያ ምክንያት «ያሇውዴ በግዴ ያዯርጉት የነበረው ሁለ ዯስታችንን
የዯስታ ቁንጭሊሊት አዯረገው!» ያሌሁ በዚህ መንፇሴ እንጂ በበቀሌ መንፇስ አዯሇም።

ከልንጎቡኮ ተነስተን ባሪ እንዯ ዯረሰን እዚያ የክፌለ ነፃ አውጪ ሰራዊት አዛዥና


መኩዋንንታቸው ባንዴ ትሌቅ ሆቴሌ ዴሌ የተመታችዋ የጣሉያን የጦር መኩዋንንት ባጠገቡ በላሊ
ሆቴሌ እንዯ ሚኖሩ ሰማን። የጣሉያን የጦር መኩዋንንት ቡናና ላሊ መጠጥ በሚጠጣበት አዯራሽ
ሇመግባት ቢፇቀዴሊቸውም የነፃ አውጪው ሰራዊት የጦር መኩዋንንት በሚኖሩበት ሆቴሌ ሇመኖር
ያሌተፇቀዯሊቸው መሆኑንም ሰማን። ሇኛ ግን የነፃ አውጪው ሰራዊት መኩዋንንት በነበሩበት ሆቴሌ
ቦታ ተሰጥቶን እዚያ አረፌን። አመሻሹ ሊይ አራት ወይም አምስት የምንሆን ኢትዮጵያውያን ቡና
ሇመጠጣት ወዯ አዲራሹ ወርዯን ባንዴ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጥን። ከኛ ትንሽ ፇቀቅ ብል በነበረ ጠረጴዛ
ዙሪያ ተቀምጠን ሌዩ ሌዩ መጠጥ እየጠጡ የሚጫወቱ ሰዎችም ነበሩ። አሳሊፉው መጥቶ ቡና
እስክናዝዝ በመጠበቅ ሊይ እንዲሇ እኒያ ሰዎች እኛን እየተመሇከቱ ሲነጋገሩ ቆዩና ከመሀከሊቸው አንዴ
ትሌቅ የጦር መኮንን ከተቀመጡበት ዴንገት ብዴግ ብሇው እኛን እየተገሊመጡ እያዩ እንዯሚሸሽ ሰው
ፇጠን ፇጠን ብሇው ወጡ።

መኮንኑ የሸሹበትና እኛን እየገሊመጡ፥ ያዩበት የነበረው ሁኔታ የተመሌካችን አይን የሚጠራ ስሇ
ነበረ ሁሊችንም ወዯሳቸው ማየት ስንጀምር «ጀነራሌ ናዚ! ጀኔራሌ ናዚ!» አለ ከመሀከሊችን ጀኔራሌ ናዚ
ናዚን አዱስ አበባ ያወቁዋቸው የነበሩት እየተቀባበለ። ጀኔራሌ ናዚ፥ የጣሉያን እንዯራሴ፥ ምክትሌ ወይም
ዋና ባሇስሌጣን ሆነው ኢትዮጵያ በሰሩበት ጊዜ የፖሇቲካም በጦርም ያመራር ችልታቸው በብዙ
ኢትዮጵያውያን ዘንዴ፥ ከላልች ፊሽስቶች የተሻሇ ከፌተኛ ግምት የተሰጣቸው ሰው ነበሩ። ታዱያ ያነሇት
«ያባረሩዋቸው ይመስሌ ያን ያክሌ የሸሹ ምናሌባት እንዱያ እክፌ ብሇው ይታይና ይከበሩ በነበሩበት
አገር ሰዎች በኢትዮጵያውያን ፉት ምርኮኛ ሆነው መታየቱ አሳፌሮዋቸው ይሆናሌ!» ብሇን ገምተን
ከመሀከሊችን አንዲንድቹ ሲያዝኑሊቸው ላልች «እንኩዋን እግዚአብሔር ይህን ሇማየት አበቃን!» እያለ
ዯስታቸውን ገሇፁ። ወዱያው ዯስታቸውን ከገሇፁት አንደ ቀጥል ያሇውን ግጥም ነገሩን።

«ሊይኞቹ ሲወርደ ታችኞች ሲወጡ፥

የሚጫወቱበት ቦታ እየተሇወቱ፥

ይህ ነው ሊስተዋሇው የዚህ አሇም ነገር፤

ቦታውን ሳይሇውጥ በሊይ እንዯ ሆነ ዘሊሇም የሚኖር

ከቶ ምንም የሇ፥ ከፇጣሪው በቀር»

200
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ባሪ በቆየንባቸው ጥቂት ቀናት ቴዎዴሮስ ወርቅነህ እንግሉዝኛ ጣሉያንኛ አዋቂ በመሆኑ
እንግሉዞችን እየረዲ ጣሉያን አገር ሇመቆየት ፇቃዯኛ እንዯ ሆነ ተጠይቆ ስሇ ፇቀዯ ከኛ ተሇይቶ
ከእንግሉዞች ጋር እንዱቆይ ተዯረገ። ሁዋሊ ግን ከስንት ወራት በሁዋሊ መሆኑን አሊስታውስም እንጂ
እሱም ልንጎቡኮ የቀሩትንም እንዯኛ አገራቸው ገቡ።

201
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss

You might also like