You are on page 1of 1

የእኛ ሰዎች በሁሉም ዓይነት ሀብቶች የተትረፈረፉ ናቸው; … በሀብት በምድር ፊት ሁሉ ከእኛ ጋር የሚወዳደር

አይገኝም፡፡ ከጠላቶቻችን ጋር በኃይል ወደ ጦርነት ስንሄድ ፣ ከወርቅ እና ከብር ከከበሩ ድንጋዮች የተሠሩ 15
ትልልቅ ግሩም መስቀሎችን ለእያንዳንዳቸው በተዘጋጁ መንኮራኩሮች ላይ እንሰቅላለን እንይዛለን። ከእያንዳንዳቸው
መስቀሎች በስተጀርባ አሥራ ሁለት ሺህ ጦረኛ ወታደሮች ፥ መቶ ሺህ እግረኛ ወታደሮች መብልና መጠጥ
የሚያቀርቡ አምስት ሺህ ሰዎች ሳይቆጠሩ እናሰልፋለን ።
ምስጢራዊው የክርስቲያን ገዥ ፕሬስተር ጆን በ 1165 ለባዛንታይን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ማኑኤል በጻፈው
ደብዳቤው በመንግሥቱ ‘ከወገባቸው በላይ ሰው ከወገብ በታች ፈረስ የሆኑ ፍጥረታት ፣ በታሪክ የሚጠቀሱት
ኃያላት የሴት ጦረኞች’ እንደያዘ በመናገር ከገነት በሚፈሰው ወንዝ ውስጡ ኤሜራልድ(ደማቅ አረንጓዴ
ማዕድን) ፣ ሰንፔር እና ሌሎች ብዙ የከበሩ ድንጋዮች እንደሚገኙበት ገልጿል።በተጨማሪም የንጉሡ
ቤተመንግስት ‘የዕጸ ጸሊም(ዞጲ) ጣራ ያለው የ‹ ክሪስታል ›ቤተመንግስት ነበር እና በየቀኑ 30,000 ሰዎች
በኤመተስት አምዶች በሚደገፉ የወርቅ ጠረጴዛዎች ላይ ለመብላት ይቀመጣሉ። ታላቁ ገዥ እራሱ በእሳት ተራራ
ላይ በሚኖሩ በሰላማንደርን ሰዎች ከወርቅ የተፈተኑ ልብሶችን ነው የሚለብሰው፡፡

ይህ አስደናቂ ነገር ነበር ፣ ነገር ግን የመካከለኛው ዘመን አውሮፓን ቀልብ የሳበው ካህኑ ዮሐንስ 10,000
ፈረሰኞች እና 100,000 እግረኛ ወታደሮችን አዝምቶ ከአውሮፓውያን ጎን በመሰለፍ ቅድስቲቱን ሀገር
እየሩሳሌምን ከሙስሊሞች ቀምቶ ወደ ቀደመ ክብሯ እንደሚመልሳት የገባላቸው ቃል ነበር።፡
የክርስቲያን የመስቀል ጦረኞች ብዙ ምድር ያጡ ሲሆን ቅድስት ኢየሩሳሌምን ራሷን ሊያጡ ተቃርበው ነበር ፡፡
በዚህ የተነሳ የካህኑ ዮሐንስ ደብዳቤ ዜና በመላው ክርስቲያናዊ የአውሮፓ ሀገራት እንደ ሰደድ እሳት ተሰራጨ፡፡
በዚህም የተነሳ ነበር ፖርቹጋላውያን የአውሮፓን የአሰሳ ዘመን የጀመሩት።የመጀመሪያ አሰሳቸውን ያከናወኑትም
እሲያ ውስጥ ነበር ነገር ግን በዚያ የነበረው አሰሳቸው ውጤታማ ስላልነበረ ፊታቸውን ወደ ታላቂቱ ሀገር ኢትዮጵያ
አዞሩ።

Antony Zagoritis(Gemologist)

ይምርሃነ ክርስቶስ ከመንገሱ በፊት እየዞረ የሚሰብክ አስተማሪ እንደሆነ ይታወቃል።በክህነት በኩልም ቄስ
እንደሆነ ገድሉ ላይ ተጽፎ ይገኛል።ከነገሰ በኋላም እየቀደሰ ህዝቡን ያቆርብ እንደነበር ይታወቃል።ከዚህም
በተጨማሪ ውሃ ላይ ቤተመንግስቱን እና ቤተ ክርስቲያንን የሰራ ታላቅ ሰው ነው። በሱ ዘመንም በሀገሪቱ ሰላምና
ተድላ በዝቶ እንደነበረ ይነገራል።የቄሱ ንጉስ ይምርሃነ ክርስቶስ የንግስና ዘመን ልክ እንደ ካህኑ ንጉስ ዮሐንስ
የንግስና ዘመን በ12 መክዘ ነበር።
ካህኑ ንጉስ ዮሐንስ የጻፈውን ደብዳቤ ስናይ ብዙዎች የገለጻቸው ነገሮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል
ለአብነት ያህል ከገነት የሚፈስ ወንዝ የሚለው ግዮንን የሚወክል ሲሆን ኤሜራልድ የሚባል ማዕድን በወንዙ
ዙሪያ እንዳለ የገለጸውን ደግሞ አንቶንይ ዛጎሪቲስ የተባለ ጂሞሎጂስት “በከበረ ድንጋይ ጠፈር ውስጥ አዲስ
ኮከብ መወለዱን እየመሰከርን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኤመራልድ በዓለም ተወዳጅ ለመሆን ተዘጋጅቷል ፡፡ መሆንም
ይገባዋል ፣ ያምራል ፡፡ አዲሱን ግኝት እንመለከታለን ፡፡በከበረ ድንጋይ ጠፈር ውስጥ አዲስ ኮከብ መወለዱን
እየመሰከርን ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሜራልድ በዓለም ተወዳጅ ለመሆን ተዘጋጅቷል ፡፡ መሆንም ይገባዋል ፣
ያምራል፡፡” ብሎ ምስክር ሰጥቷል። ዋናው ነገር ደግሞ የካህኑ ንጉስ ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ መንግስት እና የካህኑ
ንጉስ ዮሐንስ ቤተ መንግስት ጣሪያ የተሰሩት ከተመሳሳይ እንጨት ከዞጲ መሆኑ ነው።
ስለ ካህኑ ንጉስ ይምርሃነ ክርስቶስ የተጻፉ ድርሳናትን ስናይ ንጉሱ ቀድሶ ሲያበቃ ህብስተ ሰማይ እየወረደለት
ህዝቡን ያቆርብ እንደነበረ እና ጸሐይ ላይ ስልጣን እንደነበረው ሁሉ ተጽፎ እናገኛለን።ይህን ለሚያደርግ ሰው
ደግሞ በደመና መጓዝ የሚከብድ ገቢር እይደለም በትንቢት መነጽር የሩቁን አቅርቦ ማየትም ጭምር።

You might also like