You are on page 1of 3

የቤተክርስትያናችን ታሪክ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ


በአጭሩ።
በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት አመጣጥ።
ምንኩስናና ገዳማት በኢትዮጵያ።
መጽሐፍ ቅዱስ።
የቤተ ክርስቲያንዋ እምነት መርሆዎች።
ሥርዓተ ቅዳሴ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ
ውጭ።
በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያናት የሚሰጡት መንፈሣዊና ማህበራዊ
አገልግሎቶች።
ከሌሎች አብያተ ክርስቲይናት ጋር ያለ ግንኙነት።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ታሪክ በአጭሩ።
ኢትዮጵያ የጁዲዮ የክርስትያን እምነትና ባሕል ያላት ጥንታዊት አገር ስትሆን
የክርስትና እምነት ተከታዮች በብዛት የሚግኙባት ነች። አስገራሚ ታሪክ፣
ድንቅ ሥልጣኔዋ፣ባሕልና ሃይማኖታዊ የሆነው የሕዝቧችዋ አኗኗር ልዩ
ያደርጋታል። በኦሪት ዘፍጥረት እንደተጻፈው “የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን
ነው፣እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።” (ዘፍ. 2፥13) በዳዊት
መዝሙር ደግሞ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” (መዝ.
67(68)፥31)። ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ በብዙ የታሪክ መዛግብትና መጽሐፍት
ላይ ስለ ኢትዮጵያ ተዘግቧል። በተጨማሪ ታሪካዊና አርኬኦሎጂካል ግኝቶች
የሚያስገርሙ ሃቆችን ስለ ኢትዮጵያ እየገለጹ ነው። ኢትዮጵያ የራስዋ የሆነ
ፊደል ከነአጻጻፉና ሥርዓቱ ጋር ያላት ብቸኛ አፍሪካዊት አገር ነች።
ጥንታዊ የግሪክ ባለ ቅኔዎች፣ ገጣሚዎችና የታሪክ ጸሐፊዎች ስለኢትዮጵያ
ብዙ ጽፈዋል፤ ከነዚህ መካከል ሆሜር ስለአገሪቱና ስለሕዝቧ ሲገልጽ “እንከን
የሌለባቸው ዘሮች” ሲል ሔሮዶቱስ ደግሞ የኢትዮጵያን የመልክዐ ምድር
አቀማመጥን እንዲህ ሲል ገልጾታል፣ “ከግብፅ በስተደቡብና የቀይ ባሕር
አካባቢን ይዞ እስከ ሕንድ ወቂያኖስ የሚጠጋ ግዛት ነው” ስለሕዝቧም
ሲናገር “የረጅም እድሜ ባለፀጎችና እውነተኛ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው”ብሏል።

በብሉይ ኪዳን ንግሥተ ሳባ ንጉሥ ሰለሞንን ለመጎብኘት ወደ የኢየሩሳሌም


ያደረገችውን ጉዞ በ1ኛ ነገ. 10፥1-13 ተጽፎ ሲገኝ በኢትዮጵያውያንም ዘንድ
ይህ ጉዞ ብሉይ ኪዳን በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ያደረገና፤ የንጉሥ ሰለሞንና
የንግሥት ሳባ ልጅ የሆነው ቀዳማዊ ምኒሊክ ጽላተ ሙሴን ወደ ኢትዮጵያ
እንዲመጣ ያደረገ ነው ተብሎ ይታመናል።
ከዚያን ጊዜ በኋላ የአይሁድ እምነትና ሥርዓተ አምልኮ የሕዝቧ እምነትና
የቀን ተቀን ኑሮ መመሪያ ሆኗል። በቀዳማዊ ምኒሊክ የተመሰረተው
የአክሱም ሥርወ መንግሥት ተብላ ትታወቅ ነበር። በተጨማሪ ብዙ የታሪክ
መረጃዎች እንደሚያስረዱት በኢትዮጵያ ነፃ መንግሥት የተመሰረተው ከ
4,522 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። የዛሬይቱ አክሱም የጥንታዊት
ኢትዮጵያ ዋና መዲና፣የሥልጣኔ መገኛና የክርስትና እምነት መወለጃ
እንደሆነች ዛሬ የሚታዩት የሕዝቧ ኣኗኗርና ሃይማኖታዊነት፣ ታሪካዊ
ቅርሶችዋ፣የቆሙት ሐውልቶችዋና ልዩ ልዩ የሥነ ጥበብ ሥራዎቿ ሲመሰክሩ
አክሱም አሁንም ዋነኛ የሃይማኖት መንጸባረቂያ ቅድስት ቦታ ነች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሊቃውንቶችና የተማሩ


ቀሳውስቶች ያላት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ከሰላሳ ሺህ በላይ የሆኑ
አብያተ ክርስቲያናት ከሦስት መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ቀሳውስቶችና ወደ
አርባ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ምዕመናን ያላት አገር ስትሆን በዚህም
ከምሥራቃውያን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ አገሮች በምዕመናን ብዛት
የቀዳሚነትን ሥፍራ ይዛለች።

You might also like