You are on page 1of 2

ኮምፒዩተር

 በሌላ ቋንቋ ለማንበብ


ለመከታተል
Edit
ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ
ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው።
ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-
ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።

ኮምፒዩተር

ታሪክ Edit

ቀድሞ አስሊ ማለት አንድ በሒሳባዊ ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር።
እስከ 20 ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ።
እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች(አስሊዎች) ጋር ሲወዳደሩ በጣም ትልቅና ቀርፋፋ ናቸው።

የኮምፒዩተር ዐይነቶች Edit


 ሜን ፍሪም
 ሱፐር ኮምፒዩተር
 ዎርክ ስቴሽን
 ማይክሮ ኮምፒዩተር-(ዴስክቶፕ፣ ላፕቶፕ፣ ፓልምቶፕ)
 ሚኒ ኮምፒዩተር

ዋና የኮምፒየተር ዐይነቶች እንደሚከተለው ነው፦

የኮምፕዩተር ክፍሎች Edit

የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1.ሞኒተር(የምንሰራውን ነገር እንዲያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ፣ ቪዲዮ ወይም ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል)


ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡

14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከምስል ማሳያው አንድ ጥግ እስከ ሌላኛው ጥግ ያለውን ርቀት በመለካት
ነው፡፡(ስዕሉን ይመልከቱ፡፡)

በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ሬሾ (ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4 በ 3(በትክክል ሲጻፍ 4:3 ይሆናል)
ነበር፡፡

አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (widescreen) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡

2.ማዘርቦርድ(እናት ሰሌዳ)(ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች)የሚቀዳጁበት)


3.ሲፒዩ(የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእምሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡)
4.ሜሞሪ(ማስታወሻ)(የምንሰራውን ስራ ወይም ፋይል በጊዚያዊነት አስቀምጠንበት የምንሰራበት)
ሜሞሪ(ማስታወሻ) በባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች
ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች
ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት
(gigabyte) እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡

ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡

5.ኤክስፓንሽ ስሎት
6.የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረቢያ (power supply)
7.የሲዲ ማሰሪያ (cd drive)
8.ሀርድ ዲስክ (የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ)
9. መሎጊያ (ማውስ)
10.የፊደል ገበታ (ኪቦርድ)
ዊኪፒዲያ ላይ ያለውን ምስል ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡

ኮምፕዩተሮች እንዴት እንደሚሰሩ Edit


ታዋቂ ዋና ዋና የኮምፕዩተር አምራቾች

You might also like