Professional Documents
Culture Documents
6 Input Device
6 Input Device
ኪይቦርድ Keyboard
ኪይቦርድ /Keyboard/ ዳታን ወደ ኮምፒዩተር ለማስገባት ከምንጠቀምባቸው ክፍሎች በዋነኛነት
የሚመደብ ሲሆን ተጠቃሚው ቦርድ ላይ የሚገኙትን የተለያዩ የፊደሎች፣ የቁጥሮች እና የተለያዩ ትዕዛዞች
ለማስገባት ይጠቀምበታል፡፡ እነኚህን ቁልፎች በምንጫንበት ወቅት እነሱን /ፊደሎች እና ቁጥሮች/
የሚወክል ኮድ ይፈጠራል፡፡
የኪቦርድ ቁልፍ ላይ ፊደላት፣ ቁጥሮች የሂሳብ ስሌት ምልክቶች እና ሌሎች አይነት ምልክት ለምሳሌ $, %,
&, #, @, },-----} እናገኛለን፡፡ የኪቦርዱ መጠን በላዩ ላይ እንደያዘው የተለያዩ አይነት ቁልፎች ይወሰናል፡፡
ስኬኘ ቁልፍን በመጠቀም በስራ ላይ ያለውን ኘሮግራም ወይም መመሪያ ለማስቆም፣ ለመሰረዝ፣ በስህተት
የታዘዙትን መመሪያ ለማስቆም እና አዲስ ትዕዛዝ ለመስጠት እንጠቀምበታለን፡፡
እንግሊዘኛ አለም አቀፍ ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም ኪቦርድ ላይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የምልክት
ቋንቋ እናገኛለን፡፡ ሆኖም እንደአገሩ ይህ ለአጠቃቀም ይመች ዘንድ በሀገሩ ቋንቋ አዘጋጅቶ መጠቀም
ይቻላል፡፡
ለአሁኑ የምናወራችሁ በእንግሊዘግ ለተዘጋጁ ኪቦርድ አይነት እንደመሆኑ መጠን የተሰጡትም ማብራሪያዎች
በእነዚህ አይነት ኪቦርድ ተንተርሶ ነው፡፡ ካኘስሎክ ቁልፍ የምንለው ለእንግሊዘኛ ቋንቋ ተጠቃሚዎች ቁልፍን
በመጫን ትልቁን የእንግሊዘኛ ፊደል ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ይረዳል፡፡
ሽፍት /Shift/ ቁልፍ ከሌሎች ቁልፎች ጋር በመጠቀም የሚያገለግል ነው፡፡ ለምሳሌ ሽፍት ቁልፍ በመጫን
የፊደል ቁልፎችን ብንደግም ትልቁን የእንግሊዘኛ ፊደል በእስክሪኑ ላይ ይፃፋል፡፡ በተጨማሪም ይህን ቁልፍ
ከሌሎች የቁጥር ቁልፎች ጋር አንድ ላይ ብንጫነው ከቁጥሩ በላይ የሚገኘውን ምልክት ይፅፋል፡፡
ኮንትሮል /ctrl/ ቁልፍ በጋራ ከፋክሽን ወይም ፊደል ቁልፎች ጋር በመሆን ትዕዛዞችን ለመላክ ወይም
በምስል መስታወት ላይ የተለያዩ ምልክቶችን እንዲታዩ የምናዝበት ቁልፍ ነው፡፡
በኪቦርድ ከላይ በመስመር ከF1 እስከ F12 የተደረደሩትን ፈንክሽን ቁልፍ ብለን እንጠራቸዋለን፡፡ እያንዳንዱ
ቁልፍ በመጫን የተለያዩ ስራን ማከናወን ይቻላላል፡፡ ለምሳሌ F1 በመጫን ስለምንጠቀምበት ፕሮግራም
ማንኛውንም የአጠቃቀም አጋዥ መጃዎችን ለማግኘት ይረዳናል፡፡
ረዘም ያለ ዝንግ የመሰለ ቁልፍ ኮቦርድ ከታች የሚገኝ ሲሆን አገልግሎቱን ቁልፉን በመጫን በጽሁፎች ወቅት
በቃላት መሀከል ባዶ ቦታ ለመፍጠር ነው፡፡
ስታተስ ላይት (Status lights) ወይም የሁኔታ መብራት የምንለው ኮምፒዩተሩ በስራ ላይ መሆኑን
(መብራቱን) ወይም ሌሎች የኮምፒዩተሩ ተጨማሪ አካላት በስራ ላይ መሆናቸውን የምንመለከትበት
አመልካች ብርሃን ሲሆን በኮምፒዩተሩ አካል ልይ ለመታየት በሚቻል መልኩ ይገኛል፡፡
በጽሁፍ ስራ ወቅት አዲስን መስመር ለመጀመር የምንጠቀምበት ቁልፍ ኢንተር ቁልፍ /Enter key/
እንለዋለን፡፡ ከዚያም በተጨማሪ እስፕራፍሽት (በሠንጠረዥ ስራ) በሚደረጉ ስራዎች ሠንጠረዡ ውስጥ
ጽሁፎችን ለመጨመር ቁለፍ እንጠቀማለን፡፡ ኢንተር ቁልፍ /Enter key/ መጫን የመስማማት ምልክት
/ok/ ነው፡፡
L.. አሮው ቁልፎች /Arrow key/
በኪቦርድ የቁልፍ አቀማመጥ በአራት አቅጣጫ የሚያመለክቱ አራት የተለያዩ ቁልፎች በዓይነት አሮው ኪ
እንላቸዋለን፡፡ አገልግሎታቸውም እንደሚያመለክቱበት አቅጣጫ በምስል መስታወቱ ውስጥ ወደ ምንፈልግበት
ቦታ ለመያዝ ይረዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ፕሮግራሙ ዓይነት የተመረጠን ክፍል ለማጥበብና ለማስፋት
እንጠቀምበታለን፡፡
የቁጥር ቁልፎች /Number keypad/ የምንላቸው የቁጥር ዓይነቶች ከ0-9 ያሉትን ለመጠቀም
የሚያገለግሉ የኪቦርድ አካላት ናቸው፡፡
Mouse
ማውስ ከስተሩ የፕላስቲክ ኳስ ያለበት መገልገያ ሆኖ እስክሪኑ ላይ የሚገኙትን የተለያዩ ነገሮች ለመምረጥ
የሚያገለግል በተኖች አሉት ማውዙ የኳሱን እንቅስቃሴ እያገናዘበ እስክሪን ላይ የሚገኘውን ጠቋሚ ቀስት
የተለየዩ ነገሮችን ለመምረጥ በሚያመች መልኩ ያንቀሳቅሰዋል፡፡ በማውስ ውስጥ ባለው ኳሱ እንቅስቃሴ
መሰረት ወደ ኮምፒዩተሩ መግባት የሚገባውን መረጃን ለመመልከት እና ለመምረጥ እንገለገልበታለን፡፡
የማውዝ አጠቃቀም በተመለከተ በጠፍጣፋ ቦታ ላይ በእጅ በማንሸራተት በኮምፒዩተሩ የምስል መስታወት
ላይ ወደተፈለገው አቅጣጫ የማውዝ ጠቋሚውን ቀስት መከተል ያስፈልጋል፡፡ ማውዝን በመጠቀም
በኪቦርድ የምንጠቀምባቸው የተለያዩ ትዕዛዞች በቀላሉ ማከናወን እንችላለን ፡፡
የአብዛኛው ማውስ ቅርጽ ከላዩ ለአንድ እጅ አያያዝ አመቺ ሆኖ የተሰራ ሲሆን ከስሩ ጠፋጣፋና ተንሸራታች
ባህሪይ አለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከላዩ እና ከዚያም በላይ በእጅ የምንጫናቸው ቁልፎች አሉት፡፡
አብዛኛው ማውስ በላዩ ሁለትና ከዚያ በላይ በእጅ የምንጭናቸው ቁልፎች ሲኖሩት እነዚህን ቁልፎች
በመጫን የምንፈልገውን ምልክት ከምስል መስታወቱ ላይ በመምረጥ ወደ ኮምፒዩተሩ ትዕዛዞች
እናስተላልፋለ፡፡የማውስን ቅርጽ በላይ በተመለከትነው ስዕል ላይ የተገለጸ ሲሆን የትዕዛዙን
እንቅስቃሴ የምንመለከትበት ቅርጾች የተለያዩ ናቸው ለምሳሌ ፡-
ስካነር Scanner
ስካነር የምስል መቀበያ መሳሪያ ሲሆን አገልገሎቱም የተለያዩ የምስል ምጃዎችን ለምሳሌ ስዕል ፡-
ስዕል (ዲዛይኖች ቻርት እና ግራፊክስ) ማግኔቲክ ጨረር በመጠቀም ወደ ኮምፒዩተሩ ለማስገባት
እንጠቀምበታለን፡፡ ኮምፒዩተሩ ለሚጠቀምበት ጠቋሚ መረጃ የምስል መረጃዎችን በብርሃን ወይም
ኤሌልትሮን ማግኔቲክ ጨረር በመጠቀም የሚደረግ ሂደት ኢሜጅ ፕሮሰሲንግ /Image
processing/ ብለን እንጠራዋለን፡፡
ማይክራፎን Microphone
የምንጠቀምበት ኮምፒዩተር ዘርፈብዙ ጥቅም /Multimedia System/ ወይም አገልግሎት
የሚሰጥ ከሆነ መረጃን በድምጽ መልክ ከተጠቀመው ወደ ኮምፒዩተሩ ለማስገባት ማይክራፎን
እንጠቀማለን፡፡
ላይት ፔን Light pen
ላይት ፔን (Light pen) ዳታን ወደ ኮምፒዩተር ማስገባት መሳርያ ሲሆን በብርሃን አማካኝነት በማሳያ
እስክሩኑ ላይ የተለያዩ ክፍሎችን ለመምረጥ ያገለግላል፡፡ ላይት ፔን (Light pen) ከማውስ ጋር
ተመሳሳይነት አለው ነገር ግን ላይት ፔን (Light pen) ስንጠቀም የኤሌክትሮኒስ ጫፍ ያለውን
እስክሪብቶ በማንቀሳቀስ እስክሪኑ ላይ የምንፈልገውን ክፍል በቀጥታ በመጠቆም እንመርጣለን፡፡
ጆይስቲክ Joystick