Professional Documents
Culture Documents
com
የትምህርቱ ዓላማዎች
በትምህርቱ መጨረሻ ላይ ተማሪዎች፡
❖ ትክክለኛ የሆኑ የጋብቻና ቤተሰብ ዓላማዎችን ይገልጻሉ፡፡
❖ ሰዎች ወደ ጋብቻ የሚገቡቧቸውን ትክክለኛ ያልሆኑ ዓላማዎችን ያብራራሉ፡፡
❖ ወደ ትዳር የገቡበትን ወይም ለመግባት ያሰቡበትን ዓላማዎቻቸውን
ይገመግማሉ፡፡
ሰዎች ለማግባት ሲያስቡ በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ እናገኛለን ብለው የሚያስቧቸው ነገሮች
ይኖራሉ፡፡ እነዚህ የተጋቢዎች ዓላማዎች ወይም ግቦች ይባላሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ተጋቢዎች ወደ ትዳር የሚገቡት በተሳሳተ ዓላማ ነው፡፡ የተሳሳተ ዓላማ ማለት
አሁንም ጥቂት ጊዜ ለጋብቻ ግንኙነታቸው ጠቃሚ ያልሆነ፣ በግንኙነት ላይ ሳይሆን በግንኙነቱ አማካኝነት
ወስዳችሁ ወደ ትዳር በሚገኙ ጊዜያዊ ጥቅሞች ላይ ያተኮረ፣ ተጨባጭ ነባራዊ እውነታን ያላገናዘበና ከአንዱ
የገባችሁበትን ምክንያቶች
የትዳር ጓደኛ የተሰወረ ግብ ነው፡፡
አስቡ፡፡ እናገኛለን ብላችሁ
ያላገኛችሁት ነገሮች ምን
እነዚህን የተሳሳቱ ግቦቻችሁን ከጻፋችሁ በኋላ ሌሎች ሰዎች ወደ ትዳር የሚገቡባቸውን
ምን ነበሩ?
ትክክለኛ ያልሆኑ ምክንያቶችን ተመልከቱ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ሙሉ በሙሉ ስህተት
ናቸው ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ምክንያቶች ብቻ ወደ ትዳር የገባ ሰው
መልካም ትዳር ለመለማመድ ፈተናው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ሰዎች ወደ ትዳር እንዲገቡ
ከሚያደርጓቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል፡-1
1
የእነዚህን ዝርዝር ሐሳቦች ማብራሪያ ከፈለጋችሁ ከበደ በከሬ፡ ጋብቻን እንዴት ልጀምር? የሚለውን መጽሐፍ
ማንበብ ትችላላችሁ፡፡
Page 1 of 4
Poimen Ministry – Email: poimenministry516@gmail.com
ጋብቻ ለሰዎች አስፈላጊ የሆነ ተቋም ነው፡፡ ሰዎች ጋብቻን ከመሠረቱ በኋላ በሕይወታቸው
በብዙ ነገር ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ ትክክለኛ የሆኑ ዓላማዎች የሚባሉት ተጋቢዎች በጋብቻ
ውስጥ ሊገኙ በሚችሉ ጥቅሞች ላይ ትኩረት በማድረግ እነርሱን ለማግኘት
የሚያስቀምጡት ግቦች ናቸው፡፡
ሳያገቡ መኖር የራሱ የሆነ በጎ ነገር ቢኖረውም፣ ማግባት ግን ሳያገቡ ከመኖር የተሻለ
ጥቅም አለው፡፡ ጥንዶች እነዚህ በጋብቻ ውስጥ በሚገኙ በረከቶች ላይ ትኩረት ሲያደርጉ
በትክክለኛው መስመር ላይ ናቸው ማለት ነው፡፡
Page 2 of 4
Poimen Ministry – Email: poimenministry516@gmail.com
መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው ብቻውን እንዳይሆን እግዚአብሔር ሴትን ፈጥሮ ሁለቱን በጋብቻ
አጣመራቸው፡፡
የሁለቱ ጥምረት ደግሞ ከማንኛውም ሰብዓዊ ግንኙነት እጅግ ተቀራራቢና የተጣበቀ ነው፡፡
ሰው ከአባትና ከእናቱ፣ ከወንድምና ከእህቱ ጋር ካለው ግንኙነት ሁሉ የሚቀርብ ወዳጅነት
ነው፡፡ በዚህ ወዳጅነት ውስጥ ሁለንተናዊ ሕይወትን መጋራት ይገኛል፡፡ በዚህ ግንኙነት
ውስጥ ባልና ሚስት አንዱ ለሌላው በሚመች መንገድ አብረው ይኖራሉ፡፡
በባልና ሚስት መካከል ያለው አንድነት ጠንካራ ነው፣ ዘላቂነት አለው፡፡ ሁለቱም
በመደጋገፍና በመተባበር አብረው የሕይወትን ጉዞ ይጓዛሉ፡፡ የተለያዩ ውጣ-ውረዶች
ቢያጋጥሟቸውም ሁለቱ ያላቸውን ችሎታ፣ ጥበብ፣ እውቀት፣ ልምድ፣ …. በመጠቀም
በመክ.4፡9-12 መሠረት፣ ወደፊት ይሄዳሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት (መክ4፡9-12) ያለውን
በባልና ሚስት መካከል ክፍል አንብቡ፡፡
ያለው አንድነት ምን
ጥቅም አለው? ባልና ሚስት በኑሮአቸው እርስ በርስ እየተደጋገፉ ይኖራሉ፡፡ ሁለቱም እውቀታቸውን፣
ክህሎታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ያላቸውን ነገሮች ሁሉ አንድ ላይ በማቀናጀት ኑሮአቸውን
ለማሻሻል መጣር ይገባቸዋል፡፡ ሁለቱም የምችሉትን ሁሉ ማድረግ ይገባቸዋል እንጂ አንዱ
በሌላው ላይ ጥገኛ መሆን አይጠበቅበትም፡፡
የተፈጠሩ ወንድና ሴት በ(ዘፍ1፡31) ላይም እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ሰዎች ባረካቸው ይላል፡፡ የባረካቸውም
እንዴት ተባዝተው ምድርን ‹‹ብዙ ተባዙ፣….›› በማለት ነበር፡፡
መሙላት ይችላሉ?
ወንድና ሴት ተባዝተው ምድርን መሙላት የሚችሉት ልጆችን ሲወልዱ ነው፡፡ ልጆችን
ለመውለድ ደግሞ ሁለቱ ወሲብ መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ በዚህም ክፍል ወሲብ
ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ እንደተጠቀሰ መመልከት ትችላላችሁ፡፡ በ(ዘፍ4፡1) ላይም
‹‹አዳምም ሚስቱን አወቀ›› ካለ በኋላ እርሷም ልጅ እንደ ወለደች ይናገራል፡፡ ወሲብን
Page 3 of 4
Poimen Ministry – Email: poimenministry516@gmail.com
ዘርን ለመተካት
ሦስተኛው የጋብቻ ዓላማ ዘርን መተካት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ
ከፈጠረ በኋላ በመጀመሪያ ሲባርካቸው ‹‹ብዙ ተባዙ ….›› (ዘፍ1፡31) አላቸው፡፡
እግዚአብሔር የወንድና የሴትን የዘር ፍሬ ከባረከ፣ ልጆችን መውለድ በረከት ነው፡፡ ልጆች
የሚወለዱት ባልና ሚስት ወሲብ ሲፈጽሙ ነው፡፡ ወሲብ ደግሞ መፈጸም ያለበት በጋብቻ
ውስጥ ነው ብለናል፡፡ እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ቃል ልጆች መወለድ ያለባቸው በትዳር
ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ዐይነት መንገድ ከተወለዱ፣ ልጆች ከወላጆቻቸው ተገቢውን ሁለንተናዊ
እንክብካቤ በማግኘት ማደግ ይችላሉ፡፡
ተጋቢዎች በትዳር ውስጥ ከዚህ በታች የተጠቀሱ ግቦችን ለማግኘት ቢሠሩ ደስታና ሰላም
የበዛበት ግንኙነት ይኖሯቸዋል፡፡
በጋብቻ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች በርካታ ጥቅሞችን ደግሞ የማግባት ጥቅሞች በሚለው
ርዕስ ሥር ወደፊት እንመለከታለን፡፡
ጥያቄዎች
❖ ……………………………………………..……….
❖ ………………………………………………………
Page 4 of 4