You are on page 1of 3

መምህር አካለ-ወልድ እና ታሪካቸው

ደራሲ- አፎሚያ ሳለ-አምላክ


የመምህር አካለ ወልድ 2 ተኛ ትምህርት ቤት ከብዙ አመታት በፊት ስራውን የጀመረ በሆጤ ክፍለ ከተማ 09 ሮቢት ቀበሌ የሚገኝ
ደረጃውን የጠበቀ ውብ እና ፅዱ ትምህርት ቤት ነው። በመጀመሪያ ከጣውላ በተሰሩ 5 ህንጻዎች ጥቅምት 6 ቀን 1943 ዓ.ም ከ 1-5 ኛ
ክፍል በማካተት ስራ ተጀመረ። ደረጃውን ከፍ በማድረግ በአመቱ 1944 እስከ 8 ኛ ክፍል እንዲያድግ ተደረገ። በስተመጨረሻም
በመስከረም ወር 1997 ዓ.ም 80 መምህራኖችን እና 2060 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ ቻለ። ከገቢው ውጭ ላይ ሆነን
ስንመለከተው የተማሪዎች መግቢያ በር ፈዘዝ ባለ አረንጓዴ ቀለም ተውቦ እንመለከታለን ። በርከት ያላ ተማሪዎች ወለል ብሎ
በተከፈተው በር ሲገቡ ይታያል። ከበሩ ወደ ላይ አንገታችንን ቀና ስናደርግ “ መምህር አካለ ወልድ 2 ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ” ተብሎ
ጎላ ጎላ ባሉ ፊደላት ተጽፎ ጽሁፍ እንመለከታለን።
በዚያ በሰፊው በር እንደገባነ በስተግራ በኩል የጥበቃውን ቤት ስናገኝ አርፋጅ ተማሪዎችን ፟አትገቡመ ሰአት አልፏል ። ፟ እያሉ
ሲከራከሩ እንመለከታለን። ከጥበቃው ቤት አጠገብ መምህራኖች እና ተማሪዎች የሚገለገሉበት ሻይ ቤት ሲኖር የምግቡ ጠረን የጠገበን
ሰው እስኪያስርብ ድረስ ግሩም ነው። ተማሪዎች እና መምህራን በፈለጉት ሰአት የፈለጉትን መገልገል ይችላሉ። በስብሰባ ጊዜ በእረፍት
ሰአት ለአይን የሚማርኩ እንዲሁም ስንመገባቸውም የሚጣፍጡ ምግቦች ተዘጋጅተው ይቀርባሉ። ከዚያ ወጥተን አየር ለመውሰድ
ብንፈልግ በቁመቱ ረዘም ያለ አረንጓዴ መዝናኛ ቦታ ውስጥ መቀመጥ ደስታ ይሰጣል። ተማሪዎች በእረፍት ሰአት ተቀምጠው ሲያወሩ
መምህራኖችም በሻይ ሰአት እንዲሁም በእረፍት ሰአታቸው ተቀምጠው ሲወያዩ ትብብራቸው ያስቀና። ከሻይ ቤቱ ወጣ እንዳልን ብዙ
ተማሪውችን የሚያስገለግል የውሀ ቧንቧ ውሀ አለ። የውሃ ታንከሩ ከፍ ተደርጎ ተሰቅሏ። እንዲሁም ውሃ መጠጣት እና መታጠብ
ለሚፈልግ በየቦታው ይታያል። አንደኛው ከሻይ ቤቱ ጎን ፣ ሌላኛው በግራ በኩል ከአትክልቱ ወረድ ብሎ እና በቀኝ በኩል ወደ ሜዳ
በሚያሰኬደው አቅጣጫ ለተማሪዎች በሚመች መልኩ ተዘጋጅተው ተቀምጠዋለ። ከበሩ በስተቀኝ በኩል ስንመለከት ለአይናችን ማራኪ
የሆኑ እርካታ እና ደስታን የሚያጎናጽፉ በተለያዩ ቀለማት የተዋቡ አበቦች እይታቸው ደስታን ያጎናጽፋል። እነዚህን ውብ አበቦች ረጅም
ሰአት ብንመለከታቸው ''አትክልተኛው ምን ያህል ቢንከባከባቸው ነው።'' እስክንል ድረስ እጹብ ድነቅ ናቸው። ተማሪዎች፣ መምህራን
እና የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች በእረፍት ሰአታቸው እዚያ ቦታ አካባቢ መቀመጥ ሰላምን ያጎናጽፋቸዋል።
ትምህርት ቤት እንደገባን ለተማሪዎች እንዳያስቸግር በማሰብ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ በኮብልስቶን ተሰርቷል። በቁጥራቸው በርካታ
የሆኑ ተማሪዎችን የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን ተማሪዎች በየቦታቸው እንዲሰለፉ በየክፍል ሴክሽኑ ተከፋፍሎ ተጽፏል። ተማሪዎችም ስነ
ስርአት ባለው መልኩ ቦታ ቦታቸውን ይዘው የታያሉ። በዚያ ፊት ለፊት ከፍ ብሎ የሚውለበለብ በአረንጓዴ ፣ቢጫ እና ቀይ ቀለማት
ያሸበረቀ ከመሃሉ ላይ በሰማያዊ የተከበበ የኮከብ ምልክት ያለው ኢትዮጵያዊነታችንን የሚገልጽ ባንዲራ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ደስታን
ይሰጣል። የባንዲራ ስነስርዓቱን ለማከናወን እንዲሁም የተለያዩ መልእክቶችን ለማስተላለፍ የምንጠቀምበት መድረክ ተማሪዎቹ
የሚነገረውን መልእክት በትኩረት እንዲያዳምጡት መንገዱን ይከፍታል። ይህ መድረክ ከባንዲራው መስቀያ በስተግራ በኩል ይገኛል።
ተማሪዎቹም ሆነ መምህራናቹ ባንዲራው በሚሰቀልበት ጊዜ በትኩረት ቀጥ ብለው ሲዘምሩ ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር ልባቸውን
ፈንቅሎ ይወጣል።
ወደ ቢሮ መግቢያ ቀጥታ ስንጓዝ ግርማ ሞገሳቸዉ የሚማርከው መምህር አካለ ወልድ ሠርጸ ወልድ ጥቁር ካባ ለብሰው የሚያሳይ
ምስል በትልቁ መስታወት ተቀምጧል ። ወደ ቢሮው ስንገባ መምህራኖች የሚፈርሙበት ወረቀት ነጭ ቀለም በተቀባ ሳጥን ላይ
ተቀምጧል። መምህራኖቹ በሰአታቸው በመገኘት ፊርማቸውን ያሰፍራሉ። ያንን አልፈን ስንሄድ የርዕሰ መምህሩ ቢሮ ይታያል።
በመቀጠልም በቀኝ በኩል ምክትል ርዕሰ መምህር ቢሮ አለ። አብዛኛውን ጊዜ ተማሪዎችም ሆነ መምህራን እዚያ ቢሮ አካባቢ
እንመለከታለን። ወደ ቀኝ ቀጥ ብለን በምንሄድበት ጊዜ የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሰ መምህር፣ የተማሪዎች ምክርና ድጋፍ ባለሙያ፣
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ የሰውነት ሀይል ባለሙያ እና የድንገተኛ ማእከል ሡፐር ቫይዘር ቢሮዎች ይገኛሉ፤ እንዲሁም
የመምህራኖች እስታፍ አለ። እዚያ ውስጥ በርከት ያሉ መምህራን ሲኖሩ በመማር ማስተማር ጊዜ የገጠማቸውን አጋጣሚዎች ይወያያሉ፤
እንዲሁም ከፍ ያለ ሳቅ እና ድምጽ ይሰማል። በርዕሰ መምህሩ ቢሮ በግራ በኩል የት/መ/መ/ ማዕከል ይገኛል። ቀጥታ ስንሄድ 12
የሚደርሱ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች የመምህራን ቢሮዎች አሉ። መምህራኖች ሲወጡ ሲገቡ ማየት የተለመደ ነው። በየቢሯቸው
ያላቸው ትብብር ደስ ያሰኛል። የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን፣ ማስታወቂያዎችን እና ክፍለ ጊዜዎችን ማስቀመጣ ሰሌዳ ፊት ለፊት
ይገኛል።
ወደ ፎቅ በሚወስደው ደረጃ ስናቀና ተማሪወችን በረፍት ሰአት ለማዝናናት፣ ቁም ነገር ለማስጨበጥ፣ የተለዩ መልእክቶችን
ለማስተላለፍ የሚያገለግል የሚኒ ሚዲያ ክበብ ቢሮ ውስጥ ተማሪዎች መልእክት ሲያስተላልፉ ቀልብን ይገዛሉ። ፟የትምህርት ቤቱ
ተማሪዎች እና መምህራን እንዴት አረፈዳችሁ።፟ በሚል ድምጽጀምረው መልእክታቸውን ማሰተላለፍ ይጀምራሉ። በደረጃው ቀጥ ብለን
ስንወጣ በስተግራ በኩል የሪከርድ እና የማህደር ባለሙያ ቢሮ አለ። ተማሪዎች መታወቂያ ሲጠፋባቸው እዚያ ቢሮ በመሄድ አዲስ
መታወቂያ ያወጣሉ። የሆነ ድምፅ ይሰማል። ይሄ ድምፅ ከየት ነው ብየ ወደ ፊት ስሄድ ሰፊ የሆነ በአንድ ላይ በረካታ ሰዎችን የሚሰበስብ
አዳራሽ ውስጥ በቁጥራቸው በዛ ያሉ ሰዎች አራዳሹ ውስጥ ውይይት እያካሄዱ ነበር። በአዳራሹ የተለያዩ ውይይቶችን፣ ስብስባዎችን
እንዲሁም የተላዩ ተግባራቶችን ለማከናወን ይጠቀሙበታል።
ከአዳራሹ ጎን በፀጥታ የተሞላ ቤተ-መጸሀፍ ይገኛል። በቤተ መጽሃፍቱም ውስጥ ተማሪዎች ቦታ ቦታቸውን ይዘው በትኩረት
ያነባሉ። ቤተ-መጸሀፍቱ የተለያዩ መጽሀፍቶች እና የማትሊክ ጥያቄዎች በየክፍል ደረጃቸው እና በየትምህርት አይነታቸው ተከፋፍለው
ተቀምጠዋል። ተማሪዎችም ሆነ መምህራን የፈለጉትን መጽሀፍ መዋስም ሆነ መገልገል ይችላሉ። የመጽሀፍት አቅርቦቱ ተማሪዎች
ሳይቸገሩ የፈለጉተን መጽሀፍ በማቀናጀት መጠቀም ይችላሉ። ፀጥታው ሰላም ይሰጣል። ተማሪዎች ትኩረታቸውን ሰብስበው እንዲያጠኑ
ይህ ቤተ-መጸሀፍ ትክክለኛው ቦታ ነው።
በመምህር አካለ ወልድ ትምህርት ቤት በርካታ የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በ 2 የተለያየ አቅጣጫ ለሁለት የተከፈለ ነው።
በግራ በኩል በሚገኘው ፎቅ 21 የተማሪዎች መማሪያ ክፍል ይገኛል፤ እንዲሁም በቀኝ በኩል በሚገኘው ፎቅ 20 የመማሪያ ክፍሎች
ይገኛሉ። ክፍሎቹ ለተማሪዎች ምቹ በሆነ መልኩ በመሰራቱ በብርሀን የተሞላ ነው። መቀመጫውም ተማሪዎች ሳይጨናነቁ በነጻነት
ተመችቷቸው እንዲማሩ ያደርጋል። በየአንዳንዱ ክፍል የመማሪያ ፕላዝማ ይገኛል። የጥቁር ሰሌዳው ምቾት ጽሁፍን ያስውባል
መምህራኖችም ተመችቷቸው አስተምረው ይወጣሉ። በክፍሎቹ መሀል ላይ የሚያማምሩ ዛፎች እና የልዩ ልዩ አበቦች እይታ ደስታን
ይሰጣል። ተማሪዎች በረፍት ሰአት በዚያ

አካባቢ ተሠብስበው ይቀመጣሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ ቤተ መጽሐፍ በመሄድ መጽሐፍቾችን ይዋሳሉ።

You might also like