You are on page 1of 128

የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

1
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በጠቅላላው ስለ ኢየሱስ በኢስላም ስለሚነገረው የተሳሳተ ትምህርት እና በተለይም፥ ‘ዒሳ


በቁርኣንና በወንጌል’ በሚል ርእስ ስር በሳዲቅ መሐመድ፥ ስለ ኢየሱስ ለተሰጠው የስሕተት
ትምህርት ምላሽ።

ዘላለም መንግሥቱ (© ፪ሺህ፲፫ ዓመተ ምሕረት)


ይህን መጽሐፍ ባለቤትነቱን ሳይወስዱና ለሽያጭ ሳያውሉ ጸሐፊውን በማሳወቅ ማባዛትም
ማሰራጨትም ይፈቀዳል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ የተወሰዱት ከ፲ ፱ ፻ ፶ ፬ ዓ. ም. የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ
ማኅበር ካሳተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
የሽፋን ገጽ ቅንብር፤ ዘመን ግራፊክስ።
*****

The Eesa of the Qur’an is not the Jesus of the Bible.

A Response to Islam’s misrepresentation of Jesus in general, and Sadiq


Mohammed’s Erroneous teachings in ‘Eesa in the Qur’an and the
Gospels’ in particular.

Zelalem Mengistu (© 2021)


This work can be reproduced and disseminated by only notifying the
author, without claiming ownership and so long as it is not for profit.
All Scripture quotations are from the 1962 edition of the Amharic Bible
published by the Bible Society of Ethiopia.
Cover Design: Zemen Graphics.

2
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ማውጫ
ርእስ፤ ገጽ
መግቢያ፤ 3
የመንደርደሪያ ጥቂት ነጥቦች፤ 5
ቃሉ ተበረዘ? ተከለሰ? ተለወጠ? 7
ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይ? 13
ኢየሱስ ከሥላሴ አካላት በሥጋ የመጣው ነው፤ 20
‘ሰውየው ብቻ ዒሳ’ እና ሰው የሆነው ኢየሱስ አሥራ ሁለት ነጥቦች፤ 32
የመስቀል ሞቱ፤ 73
የመስቀል ሞት ምንድር ነው? 91
ጌትነት፥ ሞና ትንሣኤ፤ 92
የትንሣኤው ምስክሮች፤ 93
የመስቀሉ ሞት ምንነት፤ 104
የእርግጠኛነታችን መሠረት፤ 105
መስቀሉ ከአራት ማዕዘናት ሲታይ፤ 107
መደምደሚያ፤ 124
ዋቢ መጻሕፍት፤ 127

3
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መግቢያ
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም፤ ከቶም አይደለም። የቁርኣኑ ዒሳ
ከስሙ ጀምሮ፥ ሥራውም፥ ማንነቱም የመጽሐፍ ቅዱሱ ክርስቶስ አይደለም።
በመጽሐፉ ገጾች ውስጥ ይህንን በዝርዝር እንመለከተዋለን።

ይህ አሁን የምታነብቡትን መጽሐፍ ሆኖ የተዘጋጀው ሥራ ከሁለት ዓመት በፊት


በፈረንጆች ቆጠራ በ2019 ሁለተኛ አጋማሽ (በኛ ከሰኔ 2011 እስከ ኅዳር 2012) ባሉት
ወራት ውስጥ በቪድዮ የተዘጋጀው ትምህርት በመጠኑ ዳብሮ የተሰናዳው ነው።
በቪድዮ የተሰራጨውን ትምህርት ለመመልከት ምንጩ እግርጌ ይገኛል።1

ከጥቂት ዓመታት በፊት ሳዲቅ መሐመድ፥ ‘ዒሳ በቁርኣንና በወንጌል’ በሚል ርእስ ስር
29 ክፍሎች ያሉት የስሕተት ትምህርት አሰራጭቶ ነበር። ጠቅላላው ስርጭት ከ6
ሰዓት በላይ የሆነ፥ የቁርኣኑ ዒሳ ትክክለኛው ኢየሱስ፥ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ
ደግሞ የሰዎች ፈጠራ መሆኑን ለማሳየት አስልቶ ያቀረበው የማደናገርና የስሕተት
ትምህርት ነው። እንደ ሌሎቹ የእስልምና ምካቴ እምነት ሰዎች ግቡ ሁለት ነው።
አንዱ፥ ሙስሊሞችን በአለማወቅ ጭጋግ ውስጥ ማቆየት ሲሁን ሁለተኛው
ክርስቲያኖችን ደግሞ ማደናገርና ስለ እምነታቸው ጥያቄ እንዲፈጠርባቸው ማድረግ
ነው። አንዳንድ ሰዎች ከቃሉ ያልተማሩትን ነገር ያስተምራሉ፤ ሲያስተምሩም
በድፍረት ነው። ስለማያውቁት ነገር ይናገራሉ፤ ሲናገሩም በግለት ነው። የሳዲቅ
መሐመድ መሠረታዊው ስሕተት እርሱ ዒሳ የሚለው ሰው፥ ያ ሰው የአዲስ ኪዳኑ
ኢየሱስ አለመሆኑን አለማወቁ ነው። ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በሥጋ መጥቶ
አገልግሎ፥ ሞቶ፥ ከሙታን ተነሥቶ ወደ አብ ካረገ ከ600 በላይ ዓመታት ቆይቶ
የተፈጠረ ፍጡር ነው።

የሳዲቅ መሐመድ አቀራረብ ኢየሱስ ያደረጋቸውን ነገሮች ያደረጋቸው እና የሆነው


ነገሮች የሆናቸው፥ የተናገራቸውን ነገሮች የተናገራቸው እና የሆኑበት ነገሮችም ሁሉ
የሆኑበት ሰው ብቻ፥ ፍጡር ብቻ በመሆኑ እንደሆነ ነው ሊያስረዳ የጣረው። ኢየሱስ

1
በቪድዮ የተሰራጩት ስምንት ክፍሎች እዚህ ይገኛሉ።
ክፍል አንድ፥ https://www.youtube.com/watch?v=twW-MZuZeNI
ክፍል ሁለት፥ https://www.youtube.com/watch?v=HZgjZ_s3fXc&t=1349s
ክፍል ሦስት፥ https://www.youtube.com/watch?v=hTKfnwfi3DI&t=337s
ክፍል አራት፥ https://www.youtube.com/watch?v=_GvH_2c-BXA&t=1502s
ክፍል አምስት፥ https://www.youtube.com/watch?v=snTkz5u4fn0&t=970s
ክፍል ስድስት፥ https://www.youtube.com/watch?v=FZkJcxHaY2A&t=1s
ክፍል ሰባት፥ https://www.youtube.com/watch?v=5bZbVbTADr0&t=2599s
ክፍል ስምንት፥ https://www.youtube.com/watch?v=cyRcEYwhrsE&t=483s

4
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሰው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስም ያስተምራል፤ ግን ሰው ሳይሆን እርሱ ሰው የሆነ


አምላክ ነው። በሥጋ የመጣ አምላክ ነው። ይህንን ነው፥ ‘ሳዲቅ መሐመድ
የማያውቀው ኢየሱስ’ በማለት፥ ስለሚያውቀው ዒሳ እና ስለማያውቀው ኢየሱስ
የተናገረ መሆኑን ያብራራሁት።

ይህ ጽሑፍ ለሳዲቅ መሐመድ የስሕተት ትምህርት ምላሽ ሆነ እንጂ ይህ ስለ ኢየሱስ


የተነገረ ትምህርት በመደበኛ ደረጃ ኢስላም በቁርኣን ዒሳ ስለሚባለው ስለ ኢየሱስ
የሚያስተምረው ነው። ስለዚህም፥ ይህ ለአንድ ሰው ሳይሆን ለጠቅላላው የተሳሳተ
ትምህርት የተሰጠ ምላሽ ነው።

በንባቡ ውስጥ ስለ መጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ያለን መረዳት ይበልጥ ግልጽ እንደሚሆን
እና ሙስሊሞችም ይህንን በሥጋ የተገለጠውን ኢየሱስ በእውነት ይረዱትና ያውቁት፥
ይቀበሉትና ይድኑበትም ዘንድ በመመኘት አበረክታለሁ።

ዘላለም መንግሥቱ።

5
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የመንደርደሪያ ጥቂት ነጥቦች።


አንደኛ፥ ሲጀመር፥ ዒሳ በአጠራሩም የቁርኣን እንጂ የዐረብኛ የኢየሱስ ስም
አለመሆኑን እንወቅ። የሱዋ ደግሞ የሹዋ የሚለው የዕብራይስጥ ስሙ አቻ ነው።
የዕብራይስጡ የሹዋ በግሪክ ኢየሱስ ወይም ዬሱስ (Ἰησοῦς) ይባላል፤ በሌሎች
ቋንቋዎችም ስሙ ለወጥ እየተደረገ ይጠራልና በዕረብኛ ዒሳ መባሉ ምን ችግር አለበት
ሊባል ይችላል። በዐረብኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖች ዘንድ ኢየሱስ የሱዋእ (‫ )ﯾﺴﻮع‬ነው
የሚባለው እንጂ ዒሳ አይባልም። ይህ ደግሞ ቀድሞም በዕረብኛ ተናጋሪዎች
ይጠራበት የነበረው ስም ነው። ደህና፥ ‘በዕረብኛ ዒሳ ይባላል’ እንበልና ዕረቦች
በሙሉና ክርስቲያን የዐረብኛ ተናጋሪዎችም ጭምር ኢየሱስን ዒሳ አሉት እንበል። ያ
ዒሳ ግን የአዲስ ኪዳኑ ኢየሱስ አለመሆኑን ለመረዳት ርቀን መሄድ እንኳን
አይኖርብንም። ዒሳ ፋቅ ፋቅ ስናደርገው ከቁርበቱ በታች ያለው ማንነት ኢየሱስ
አለመሆኑን በቀላሉ እናገኘዋለን። ሁለቱንም ምንጮች፥ ማለትም ወንጌላቱንም
ቁርኣንንም ከፍተን ስናይ ሁለት የተለያዩ እንጂ አንድ ገጸ ባሕርይ አለመሆናቸውን
በግልጽ እናያለን።

ሁለተኛ፥ የአዲስ ኪዳኑ ኢየሱስ ጌታ ነው፤ ጌታ ነው ማለት ሰዎችን፥ ‘ጌቶች!’


እንደምንለው የከበሬታ አጠራር ያለ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ጌትነት
የተቀዳጀ ጌታ ነው። ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው፤ በዚህ ሥጋዌው
ከኃጢአት በቀር፥በሥጋ የሆነ ሰው ሁሉ የሚሆነውን ሆኖአል፤ የሚሆነውም
ሆኖበታል፤ ሞቶአል፤ ከሙታንም ተነሥቶአል። ስለዚህ ኢየሱስን በተመለከተ ሦስቱ
የአዲስ ኪዳን ትልልቅ እና መሠረታዊ ትምህርቶች ጌትነቱ፥ ስቅለቱ ወይም ሞቱ፥ እና
ትንሣኤው ናቸው። እነዚህ ሦስቱም ደግሞ በቁርኣን የማይገኙና የተካዱ ናቸው።
በቁርኣን ኢየሱስ ጌታ አይደለም (ወይም አምላክ አይደለም)፤ አልተሰቀለም (ወይም
አልሞተም)፤ ከሙታንም አልተነሣም። ስለዚህ የቁርኣኑ ዒሳ የወንጌሉ ኢየሱስ ፈጽሞ
አይደለም ሲባል ስላልሆነ ነው።

ሦስተኛ፥ ቁርኣን የተጻፈው አዲስ ኪዳን ተጽፎ ከተጠናቀቀ ከስድስት እና ሰባት መቶ


ዓመታት በኋላ ነው። ሁሌም ምስክር መጥራት ያለብን ኦርጅናሌውን እንጂ
ደኃራዊውን ወይም በስፍራውና በጊዜው የሌለውን አይደለም። ስለ ኢየሱስ
የተነገረበት ኦርጅናሌው ምስክር አዲስ ኪዳን ነው። ስለዚህ ስለ ኢየሱስ ማወቅ
የሚፈልግ ሰው ከምንጩ ነው መቅዳት ያለበት። ይህ ሲነገራቸው ሙስሊም ዐቃብያነ
እምነት፥ ‘ይህ በእጃችሁ የሚገኘው የአሁኑ አዲስ ኪዳን ተበርዟል’ የሚል ማሳበቢያ
ያቀርባሉ። ይህ ድኩም ሰበብ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመጥቀስ ድፍረት እያገኙ፥
ከቁርኣን ጋር የማይስማማው ማናቸውም ምንባባትን ደግሞ፥ ‘የተበረዘ ነው’ ይላሉ።
ተበርዞ ከሆነ ያልተበረዘውን ማሳየት ትክክለኛው የመበረዙ ምስክር ይሆናልና ያንን
ማድረግ ነበረባቸው። ይህንን ማቅረብ የሚችል ግን ማንም ኖሮ አያውቅም። እንግዲህ
ማመን ያለብን ማንን ነው? ብለን መጠየቅ አለብን። ማመን ያለብን፥ የቅርቦቹ

6
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ጸሐፊዎች፥ በዓይኖቻቸው ያዩት፥ በጆሮቻቸው የሰሙት የመሰከሩትን ነው? ወይስ


ያላየው፥ ያልሰማው፥ ቃሉንም ያላነበበ፥ ማንበብም የማይችል ሰው የሆነው የኢስላም
ነቢይ ሙሐመድ የሰጠውን ምስክርነት? የቱ ነው መደመጥ ያለበት? መልሱ ግልጽ
ነው።

አራተኛ፥ ተበረዘ፥ ተከለሰ፥ ተሰረዘ ለሚባለው የሐሰት ክስ ደግሞ፥ የኢስላም ነቢይ


ሙሐመድ ራሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ይነበብ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ እና ዛሬ
በእጃችን የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ስለመሆኑ ለቁጥር የበዙ ማስረጃዎች
አሉን። ያኔ በሰባተኛውና በስምንተኛው ምዕት ዓመት በክርስቲያኖች እጅ የነበረው
መጽሐፍ አሁን ካለው የተለየ አለመሆኑ በብዙ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ነው። ከዚያ
በፊት በመቶዎች ዓመታትም የቀደሙ፥ ዛሬ በታላላቅ ቤተ መዘክሮች ውስጥ የሚገኙ
ቀዳሚ ጽሑፋት ይገኛሉ። እነዚያን እና ዛሬ በእጃችን ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ
ማመሳከር ይህ በእጃችን ያለው መጽሐፍ ያኔ በሙሐመድ ዘመን የነበረውና
ሙሐመድም ያጸደቀው መጽሐፍ መሆኑን መረዳት ይቻላል። ይህንን የቁርኣኑ ዒሳ
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ የአለመሆኑን ሙግት በዚህ፥ ‘መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል፤
ተከልሷል፤’ በሚሉት ድኩም መከራከሪያ ልጀምር።

ቃሉ ተበረዘ? ተከለሰ? ተለወጠ?


መጽሐፍ ቅዱስን፥ በተለይም አዲስ ኪዳንን ተበርዟል፥ ተከልሷል፥ ጎድፏል፥ ጠፍቷል
የሚሉ ሙስሊሞች ስላሉ ከላይ ከዘረዘርኳቸው አራት ነጥቦች ውስጥ ይህንን
አራተኛውን የመንደርደሪያ ነጥብ ላሰምርበትና ላብራራው እፈልጋለሁ። ምክንያቱም
እዚህ የምጽፍበት ጉዳይ ስለ ቁርኣኑ ዒሳ እና የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በመሆኑ
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ የሚለውን ለመቀበልና ላለመቀበል ምንጩ ማንና
የትኛው መጽሐፍ መሆን እንዳለበት ለማየት ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልእክት ወይም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያመለክተው


የእግዚአብሔር የማዳኑ ሥራ ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ ነው። ይህ ታሪክ
የተጻፈበት መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ደግሞ ቁርኣን ከመጽጻፉ በትንሹ ቢያንስ ከ500
ዓመታት በፊት ነው። ስናነጻጽር ቀድሞ የተጻፈው የቱ ነው? ምን ይላል? ያ
የተጻፈውስ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቁመናውን እንደጠበቀ ነው ወይስ
አይደለም? ካይደለ ወይም ከተለወጠ ተለወጠ የሚሉት ሰዎች ለመለወጡ
የሚያቀርቡት፥ መለወጡን የሚያሳዩበት ከኋላ ከተነገረውና ከተጻፈው ሳይሆን ቀድሞ
ከተጻፈው ናሙና ወይም ማስረጃ አላቸው ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።

7
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል፥ ተከልሷል የሚሉ ሰዎች ይህንን የሚሉት የነሱ መጽሐፍ
ከዚህ መጽሐፍ ጋር ሲጋጭ፥ እሱን ትክክል፥ ይህንን ስሕተት ለማድረግ ከመፈለግ
የተነሣ ብቻ ነው እንጂ የተበረዘ መሆኑን ለማሳየት፥ ‘ይኸው ኦርጅናሌው የሚለው
እንዲህ ነው፤ እናንተ እጅ ያለው መጽሐፍ የሚለው ደግሞ እንዲህ ነው።’ በማለት
አይደለም። እንዲህ ማለት የጀመሩት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን ቁርኣንም ጭምር
ተጽፎ ከተጠናቀቀ በብዙ መቶ ዓመታት በኋላ፥ ለትልልቅ ጥያቄዎች፥ ለትልልቅ
የመጽሐፍ ቅዱስ እና የቁርኣን ልዩነቶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገርባቸው ጉልህና
ግልጽ ጠያቂ ጉዳዮች መልስ ሲያጡ፥ ‘ይህ በእጃችሁ ያለው የተበረዘው ነው።
የቀድሞው ኦርጅናሌው ቢኖር ኖሮ የሚለው እንደዚህ፥ ልክ እንደ ቁርኣኑ ነው፤’
ይሉናል።

መሠረቱ የተሰነጠቀው የሙግት መነሻ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በኋላ በተነገረውና


በተጻፈው መፈተሻቸው ነው። የቀድሞው ትክክል መሆንና አለመሆኑን ለማረጋገጥ
ትክክል የመሆኑ ማረጋገጫ በኋላ የተጻፈው ይሆንና፥ አዲሱ የቀድሞውን እንዲመስል
ሳይሆን የቀድሞው አዲሱን ስላልመሰለ የቀድሞው ስሑት መደረጉ ነው። ስለ
መጽሐፍ ቅዱስ ስነ ጽሑፋዊ ሕያሴ (textual criticism) በጣም በሰፊው መጻፍ
ይቻላል:: መጽሐፍ ቅዱስ ባለፉት 400 ዓመታት በብዙ የፍተሻ ወላፈን የተገረፈና
በብዙ ወንፊቶች የተበጠረ፥ ተገርፎም ተበጥሮም ነጥሮ የወጣ መጽሐፍ ነውና እንደ
አዲስ የተበረዘና የተከለሰና የተለወጠ መሆኑን ኃላፊነቱን ወስዶ የማስረዳቱ ፈንታና
ኃላፊነት የኢስላም ነው መሆን ያለበት።

ከቅርብ ዘመን ወዲህ እና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢንጅል ተበርዟል፥ ተከልሷል


የሚሉ ሰዎች ብዙ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ግን አውቀው ይሁን ሳያውቁ የራሳቸውን
ነቢይ እየተጻረሩ ናቸው። ምክንያቱም፥ የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ የመጽሐፉ ሰዎች
የተባሉት የአይሁድ እና የነሳራዎች (የክርስቲያኖች ማለት ነው፤ ነሳራ ናዝራዊ
ከሚለው የወጣ ነው፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ተከታዮች ማለት ነው።) የነዚህ ሰዎች
መጽሐፍ የተበላሸ መሆኑን ሳይሆን ትክክል መሆኑን ነው የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ
ራሱ የመሰከረው። ሙሐመድ ያ መጽሐፍ ተበክሏል አንዴም፥ አንድም ቦታ፥
‘ተውራት ተበክሏል፥ ኢንጅል ተበርዟል፤ ዛቡር ተከልሷል፤’ አላለም። ካላለ፥ እና
መጽሐፉም ካልተበከለ፥ ይህን መጽሐፍ የሚያንኳስሱ ሰዎች መጽሐፉ የሚለውን ነገር
እንዳለ መቀበል አለባቸው፤ ምክንያቱም የራሳቸው መጽሐፍ እና የራሳቸው ነቢይ
አለመበከሉን ያረጋግጣልና።

ያንን የሚያረጋግጥ ጥቅስ ወይም አንቀጽ እንይ። ቁርኣን የአይሁድ መጽሐፍና


የክርስቲያኖች መጽሐፍ ትክክል መሆኑን ሲናገር፥ እግዚአብሔር እንዳወረደውም
ሲገልጥ፥ ሰዎቹን አይሁድና ክርስቲያኖችን፥ ‘የመጽሐፉ ሰዎች ወይም መጽሐፍ
የተሰጡት ሰዎች’ ይላቸዋል። ተውራትና ኢንጅልም የተወረዱ ወይም የወረዱ እንጂ

8
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተበከሉ መሆናቸውን አይናገርም። በሱረቱ አል-ዒምራን (ቁርኣን ምዕራፍ 3) እንዲህ


ይላል፤

3፥3-4 ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርአንን) ባንተ ላይ
ከፋፍሎ በውነት አወረደ። ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል።

(ከቁርአን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው) ፉርቃንንም አወረደ፤ እነዚያ በአላህ


ታአምራቶች የካዱ ለነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፤ አላህም አሸናፊ የመበቀል ባለቤት ነው።

ይህ የሚያስረዳን ሙሐመድ በነበረበት ጊዜ የነበሩትን የአይሁድ እና የክርስቲያኖች


መጻሕፍት ተውራትና ኢንጂል (ተውራት ኦሪት ነው፤ ኢንጂል ወንጌል ነው፤ ብሉይ
ኪዳንና አዲስ ኪዳን ማለት ነው) ትክክል መሆኑን መቀበሉን ነው። ልክ ቁርኣን
በወረደበት መልክ ወርደዋል ነው ያለው እንጂ፥ በርዘውታል፥ ቀይጠውታል፥
አትቀበሉት፥ ያልተበረዘውን ፈልጉና አግኙ አላለም። ታዲያ ምነው ያኔ ተቀባይነት
የነበረውን መጽሐፍ፥ የኢስላም ነቢይ የተቀበለውን መጽሐፍ ዛሬ የማይቀበሉት?

ከሙሐመድ ዘመን በፊት የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሙሐመድ በኖረበት ዘመን


የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ዛሬ በእጃችን ካለው ጋር ለውጥ የለውም። የአሁኑና የያኔው
ወይም ከ1ሺህ 4መቶ ዓመታት በፊት የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም አንድ ነው።
ያኔ የነበረው ዛሬ ባለው መልኩ እንደነበረ ለቁጥር የበዙ እጅግ ብዙ ማስረጃዎች
ይገኛሉ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ የቀድሞው ከአሁኑ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን
የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ያሉት ሌላ ጥንታዊነት ያለው መጽሐፍ በታሪክ ውስጥ
የለም። አሁን የሚነበበው መጽሐፍ ቅዱስ በሙሐመድ ዘመን ወይም ከዚያ በፊት
ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ስለመሆኑ የሚያረጋግጡ መቶ ወይ አምስት መቶ ወይ ሺህ
ሳይሆኑ ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ተጨባጭ ማስረጃ ጥንታውያን ጽሑፎች አሉ።

ለመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ከራሱ ከቁርኣኑ መጥቀስ የተገባ
ስለሆነ ነው ከቁርኣኑ የጠቀስኩት። አንድ ሁለት ልጨምር፤ በሱረቱ ዩኑስ (ሱራ
ወይም ምዕራፍ 10) ቁጥር 94-95 የተጻፈው በዚያን ጊዜ በእጃቸው የነበረው ወይም
አይሁድና ክርስቲያኖች ያነብቡት የነበረው መጽሐፍ የጥርጣሬያቸው ማስወገጃ
መጽሐፍ መሆኑን የሚናገር ክፍል ነው።

10፥94 ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾን እነዚያን ከአንተ በፊት


መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፤ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፤
ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን። 95 ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትኹን፤
ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና።

9
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ይህ የተባለው ለሙሐመድ ነው። ምንድርነው የሚለው? ላንተ የወረደውን


ከተጠራጠርክ፥ ይህ ነገር እውነት ከአላህ ነው ወይስ አይደለም ካልክ፥ ካንተ በፊት
መጽሐፉን የሚያነቡትን፥ ማለትም የመጽሐፉን ሰዎች (አይሁድና ክርስቲያኖችን
ማለት ነው) እነሱን ጠይቅ ተብሏል። የኢንጅል ባለቤቶች ወይም አንባቢዎች
ክርስቲያኖች ናቸው፤ በወንጌሉ ውስጥ በተጻፈው መፍረድ ይችላሉም ይጠበቅባቸዋልም
ማለት ነው። ደግሞም ኢንጅል ያልተሳሳተ መሆኑን እነዚህ አባባሎች ይመሰክራሉ።
መጽሐፋቸው የተበረዘ ቢሆን እነሱን ጠይቅ ይባል ነበር? ከሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)
እና አል-አንዓም (6) ጥቂት አንቀጾች እንይ።

5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ፤ አላህም ባወረደው


የማይፈርድ ሰው፣ እነዚያ አመጠኞች እነርሱ ናቸው።

5፥68 እላንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጅልን፣ ከጌታችሁም ወደናንተ


የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም
በላቸው፤ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው ቁርአን ከነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክሕደትን
በእርግጥ ይጨምርባቸዋል፤ በከሐዲያን ሕዝቦችም ላይ አትዘን።

ይህን በተመለከተ አንድ ሁለት የመጨረሻ ላክል፤ እነዚህ እንዲያውም ሰዎቹ መጽሐፍ
የተሰጡ ወይም የተሰጣቸው መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን፥ ቃላቶቹ የማይለወጡና
ለዋጭ የሌላቸው መሆናቸውን የሚመሰክሩ ናቸው፤

6፥114-115 እርሱ ያ መጽሐፉን የተብራራ ኾኖ ወደእናንተ ያወረደ ሲኾን «ከአላህ


ሌላ ዳኛን እፈልጋለሁን» (በላቸው)። እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው እርሱ ከጌታህ
ዘንድ በእውነት የተወረደ መኾኑን ያውቃሉ። ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን። የጌታህም
ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትሆን ተፈጸመች። ለቃላቱ ለዋጭ የለም። እርሱም ሰሚው
አዋቂው ነው።

18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ለቃላቶቹ ለዋጭ


የላቸውም፤ ከርሱም በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም።

እነዚህ ጥቅሶች ቃላቶቹ ይለወጣሉ፥ ይበረዛሉ አይሉም። በተቃራኒው ለቃላቶቹ


ለዋጭ የላቸውም ነው የሚለው። እነዚህን የመሰሉ ብዙ ጥቅሶች አሉ። ይበቃል።

እንግዲህ ከነዚህ መንደርደሪያዎች በመነሣት ነው ይህንን የተሳሳተና ኢየሱስ እየተባለ


የቀረበ ዒሳ የተባለ ሰው የምናየው። የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ
አይደለም። የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ነው ማለት፥ አንድ በጣም የታወቀ
ወይም የሚታወቅ ሰው ልጥቀስና፥ ለምሳሌ፥ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፥ ‘ዐፄ ኃይለ ሥላሴ
ስድስት ዓይን እና አምስት እግር ያላቸው፥ ቁመታቸው አሥራ አራት ሜትር ከስንዝር፥
ቀለማቸው አረንጓዴ የሆነ ቦርጫምና መላጣ ሰው ነበሩ’ እንደማለት ነው። ዐፄ ኃይለ

10
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሥላሴ እንደዚያ ያለ ሰው አይደሉም። ለነገሩ እንደዚያ ያለ ሰው ኖሮ አያውቅም።


ከተጠራጠርን ግን ሰነድ አገላብጠን፥ ስለ ቁመናቸውና ተክለ ሰውነታቸው የተጻፉ
በርካታ ማገናዘቢያዎችን መርምረን ዐፄው እንደዚያ ያለ ሰው አለመሆናቸውንና ይህ
አባባል ፈጠራ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን።

ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመጠኑ መለስ ብዬ ጽሑፋቱ በተዋረድ ከአንድ ዘመን ወደ


ቀጣዩ የተላለፉበት (Scriptural Transmission) ጥቂት ልበል። ዛሬ በእጃችን
የሚገኝ ማርቆስ ወይም ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፉት ኦርጅናሌ በኩረ ጽሑፋት የሉም።
ይህ እውነት ነው። የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ የኖረው ከ570-632 ሲሆን ከዚህ
ዘመን ወደ ሁለት መቶ ዓመታት የቀደሙ (ማለትም በአራተኛው መቶ ምዕት ዓመት
የሚገኙ) ጽሑፋት ክምችቶች ግን አሉ። ሙሐመድ በዘመኑ፥ ‘ወደ አንተም
ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን
የሚያነቡትን ጠይቅ፤’ ያለው ቀድሞ የተሰጠውን መጽሐፍ የሚያነብቡ መኖራቸውን
ይመሰክራል። ‘የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ፤’
ሲልም ቀድሞ በወረደው ሕግ የሚፈርዱ ሰዎች መኖራቸውን ተቀብሏል ማለት ነው።
ይህ ለክርስቲያኖች እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ተደርጎ የሚወሰድ ባይሆንም፥
ለሙስሊሞች ግን፥ ክርስቲያኖች የሚያነብቡት በዚያ ዘመን የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ
ትክክል የመሆኑ አረጋጋጭ ነው። ይህ መጽሐፍ ደግሞ ከዚያ በፊት የነበረውም ነው።
ዛሬም በእጃችን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ በዚያ ዘመን ከነበረው ፈጽሞውኑ የተለየ
አይደለም።

ዛሬ በእጃችን (በእጃችን ስል በገዳማት፥ በቤተ መዘክሮች ማለት ነው) የሚገኙት ከ25


ሺህ በላይ የሆኑ ከትናንሽ ቁራጮች እስከ መጽሐፎች የሚደርሱ መጽሐፎች
ተወስደው ሲመረመሩና ዛሬ በእጃችን ካለው መጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሲነጻጸሩ፥ በእጃችን
ያለው መጽሐፍ በኢስላም ነቢይ በሙሐመድ ዘመንና ከዚያም ቀድሞ ካለው ምንም
ያልተለየ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል። የመጽሐፍ ቅዱሱ ምሑር ዲ. ኤ. ካርሰን
እንደሚለው ከነዚህ የተላለፉልን ጽሑፋት ከ96-97% ኦርጅናሌ የሚባለውን በኩረ
ጽሑፍ እኩያ መጻፍ እንደሚቻል ያረጋግጣል።2

አንድ ጽሑፍ ተበረዘ ወይም ተቀየጠ ለማለት ዋናው ማረጋገጫ ከጽሑፉ በኋላ
የተፈጠረ ጥያቄ፥ ወይም ጥርጥር፥ ወይም ለሙግት መልስ ማጣት፥ ወይም ስሕተትን
ለመሸፈን መሞከር፥ ወይም ሌላ የግምትና የመላ ምት ድኩም ማጣጣያ ሳይሆን ወደ
ኋላ የተጓዘና፥ ‘አልተበረዘም’ የሚሉትን ሰዎች አፍ ማስያዝ የሚችል የምንጭ ሰነድ
በማቅረብ ነው መሆን ያለበት። መጽሐፍ ቅዱስ ተበረዘ የሚሉ ሰዎች የተበረዘ
መሆኑን ለማሳየት እጅግ ብዙ መልፋት የሚጠበቅባቸው መሆኑን ባለማወቅ ነው

2 Plummer p. 48.

11
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ይህንን ሙግት የሚያቀርቡት። ተጨባጭ ማሳመኛ የማቅረቡ ኃላፊነት እጅግ ከብዶ


በትከሻቸው ላይ የሚገኝ ሊያወርዱት የማይችሉት ሸክም ነው።

12
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይ?


ሳዲቅ መሐመድ ያወሳው የመጀመሪያው ነጥብ፥ (ከ29ኙ ክፍሎች በመጀመሪያው
በክፍል የተወሳው) ኢየሱስ ፍጡር ወይም ፍጥረት ነው የሚለው ነው። ይህ የሳዲቅ
ብቻ ሳይሆን የመላው ሙስሊሞች ትምህርት ነው። የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ
ኢየሱስ አለመሆኑ ዋናው ትምህርታችን ሆኖ ሙስሊሞች ከልባቸው ዒሳ የሚሉት
ኢየሱስን በመሆኑ የዚህ መጽሐፍ ምላሽ ኢየሱስ እነዚያን የሚሏቸውን ነገሮች
አለመሆኑን ማስረዳት ይሆናል።

ከሙስሊሞች ተደጋጋሚ የሙግት ጥያቄዎች አንዱ፥ ‘ኢየሱስ፥ መቼ እኔ


የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ አለ?’ የሚል እነዚህን ቃላት በትክክልና እነሱ በፈለጉበት
አቀማመጥ እንድናቀርብላቸው ነው። “በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው፥
‘የእግዚአብሔር ልጅ’ የሚለው ገላጭ ሐረግ ከራሱ ከኢየሱስ አንደበት በእውነት
እንደወጣ መነገር አይቻልም።”3 የሚለው አሳብ አቻ የለሽ ዘመናዊው ጥያቄ ነው። ግን
እውነት ነው? ይህንን እና ሌላውን ተደጋጋሚ፥ ‘ኢየሱስ፥ መቼ እኔ አምላክ ነኝ፤
አምልኩኝ አለ?’ የሚለውን በዚህ መጽሐፍ ገጾች እናያቸዋለን።

እውነት ኢየሱስ ሰው የሆነ ወይም በሥጋ የመጣ አምላክ ነው ወይስ ሰው ብቻ? እርሱ
ፍጡር ነው ወይስ ፈጣሪ? ሳዲቅ ኢየሱስን ደጋግሞ ፍጡር እና ፍጥረት በማለት
ተናግሯል። ሌሎችም የሚሉት ያንኑ ነው። ይህ ስሕተት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ
ኢየሱስ ፍጡር ወይም ፍጥረት መሆኑን አንዴም አይጠቅስም። ፍጡር ማለት
ያልነበረና ወደ መኖር በሌላው፥ በፈጠረው አማካይነት የመጣ ማለት ነው። አንድም
ቦታ እርሱ የተፈጠረ ፍጡር ወይም ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ መሆኑን መጽሐፍ
ቅዱስ አይናገርም። ኢየሱስ ፍጡር መሆኑ በቃሉ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከቶም
አይገኝም። ፈጣሪ መሆኑ ደግሞ በግልጽ እና በተደጋጋሚ ተጽፏል። ስለዚህ ኢየሱስ
ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለም። ፈጣሪ ደግሞ ፍጡር መሆን አይችልም። ምክንያቱም
እርሱ እራሱን መፍጠር አይችልምና። አንዳንድ የስሕተት አስተማሪዎች እግዚአብሔር
መጀመሪያ ኢየሱስን ፈጥሮ ከዚያ ኢየሱስ ሌሎቹን ነገሮች ሁሉ ፈጠረ የሚሉ አሉ።
ይህም የጨለመበት ስሕተት ነው።

ሳዲቅ ኢየሱስ ፍጡር መሆኑን ለማስረዳት ሰዎች በአራት መንገዶች እንደተፈጠሩና


ኢየሱስ ከነዚህ አራት መንገዶች አራተኛው መሆኑን ዘርዝሯል። አራቱ ነጥቦቹ ያለ
እናትና አባት መፈጠር (አዳም)፥ ከወንድ ብቻ መፈጠር (ሔዋን)፥ ከሁለቱም መፈጠር
(ሰዎች ሁሉ)፥ እና ከሴት ብቻ መፈጠር ብሎ ዒሳን ምሳሌ ሰጥቶአል። እዚህ ዝግጅት

3 Geisler and Saleeb, p. 234.

13
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ውስጥ የማወሳው የትምህርቱ አሳብ ስለሆነ ጠቅላላውን ቪድዮ ለማየት ስፍራው


ከግርጌ ይገኛል።4

ደጋግሞ ያወሳው ፍጥረት እና ፍጡር የሚለው ቃል ነው። አራቱን ከላይ የተጠቀሱትን


አፈጣጠሮች ያቀረበውም የስነ ፍጥረት ትንተና ለማቅረብ ሳይሆን ዋናው ጉዳይ
የኢየሱስ ማንነት ስለሆነ የኢየሱስ አፈጣጠር ልዩ ቢሆንም ያው አፈጣጠር መሆኑን
እና እርሱም ፍጡር መሆኑን ለማሳየት ነው። በነገራችን ላይ ቁርኣን ኢየሱስ ተወለደ
እንጂ ተፈጠረ ብሎ አያስተምርም። መወለዱ ደግሞ ሰው ሆኖ መምጣቱ፥ በሥጋ
መምጣቱ ነውና ይህንን መጽሐፍ ቅዱስም የሚያስተምረው ነው።

ስለ ማርያም በመናገርም እንዲህ ብሏል፤ ‘መርየም ማለት ኻዲማ ረብ ነው።’ ኻዲማ


ረብ ምን ማለት እንደሆነ አልተረጎመም፤ የረቢ ካዳሚ ማለት ይመስላል። ከሆነ፥
በምን ቋንቋ ነው ማርያም ማለት የረቢ ካዳሚ ማለት የሆነው? ምናልባት በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ማርያም ለገብርኤል፥ ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ
ይሁንልኝ አለች። የሚለው የሉቃ. 1፥38 ቃል ተወስዶ ይሆናል። ማርያም አይሁድ
ናት፤ ማርያም የሚለው ቃልም የዕብራይስጥ ቃል ነው እንጂ ዐረብኛ አይደለም።
የዕብራይስጡ ትርጉም ደግሞ ከዚያ ፈጽሞ የተለየ ነው። ይህ የቃል ትርጉም ትልቅ
ጉዳይ አይደለም ብለን መተው እንችላለን። ነገር ግን የስነ ትርጓሜው ሂደት ሆን ብሎ
ለማሳት መሆኑ መስተዋል አለበት። ማርያም የሚለው ስም ውስጥ ረቢ የሚል ቃል
የለም።

ቀደም ሲል ካነሳኋቸው ነጥቦች አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ከቁርኣን ቀድሞ የተጻፈ ሰነድ
ብቻ ሳይሆን ወንጌላት ኢየሱስን በቅርብ በሚያውቁ አብረውት በነበሩ እና፥
አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር አብረው በነበሩ ሰዎች የተጻፉ ታሪኮች፥ የተጻፉ ዜና
ሕይወቶች ናቸው። ስለ ኢየሱስ ማወቅ የሚፈልግ ማንም ሰው መሄድ ያለበት በግልጽ
እንደሚታወቀው የሚያውቁት ሰዎች ወደ ጻፉት እንጂ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ
እርሱን የማያውቀው፥ የስሚ ስሚ ስለ እርሱ ያወቀ ሰው ወደ ተናገረውና ያንን
የተናገረውን ሰምተው ሌሎች ወደጻፉት መጽሐፍ አይደለም።

ኢየሱስ ፍጡር መሆኑ በቃሉ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከቶም አይገኝም። ስለ


ኢየሱስ የተጻፉ ፈጣሪ መሆኑን የሚያሳዩ ደግሞ በርካታ ጥቅሶች ይገኛሉ፤ ጥቂት፥
ጥቅሶችን እንይ።

ዕብ. 1፥1-3 ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን
በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ
በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ
4 https://www.youtube.com/watch?v=0gOcq-Mh0bo

14
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት


በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።

እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ የፈጠረው በዘፍ. 1 እንደተገለጠው በስድስት ቀናት


ነው። ኢየሱስ ፍጡር ከሆነና ዓለማትን የፈጠረበት እርሱ ከሆነ፥ ዘፍ. 1፥1 ‘በመጀመሪያ
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።’ ነው የሚለው እና ያ እግዚአብሔር ካልሆነ
ፈጣሪው የተፈጠረ ፈጣሪ ሊሆን ነው። ችግሩ ያ ፈጣሪ በዘፍ. 1፥1 የተጻፈው
እግዚአብሔር ነው የተባለው። ደግሞ ነውም። ያ ፈጣሪ ደግሞ ማን መሆኑ እንዲህ
ተጽፎአል፤

ቆላ. 1፥13-16 እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን


ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። እርሱም የማይታይ አምላክ
ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም
አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና
ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤

ከፍጥረት በኩር ሲል አንዳንዶች በስሕተት እንደሚርረዱት ቀድሞ እርሱ ተፈጥሮ


ከዚያ እርሱ ሌሎች ነገሮችን ፈጠረ ማለት ሳይሆን ፍጥረት ሳይሆን በፊትም ቀዳሚው
መሆኑን አመልካች ነው። ተፈጠረ ከተባለ ያልተፈጠረበት፥ ያልነበረበት ጊዜ አለ
ማለት ነው። ከተፈጠረ ስለተፈጠረበት ጊዜ እና ሁኔታ ማስረዳት የማይችሉትንና
ማስረጃ የማያቀርቡበትን ነገር ማንሣት ውኃ መውቀጥ ነው። ከላይ እንዳየነውም
የዘፍጥረቱ ፈጣሪ እግዚአብሔር ( ‫ אֱלֹהִים‬ኤሎሂይም) ተብሎአልና ኢየሱስ ያንን
ከሆነ ያ ኤሎሂይም የተፈጠረ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም።

ዮሐ. 1፥1-3 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም


እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ
ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

እነዚህ ከብዙ ጥቂት ጥቅሶች ናቸው። እነዚህ የሚያሳዩን ኢየሱስ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር
አለመሆኑን ነው። ኢየሱስ ሰው ነው፤ ሰው ከሆነ ታዲያ እንዴት ነው ፍጡር
የማይሆነው? ሊባል ይችላል። ይህን በሌላ ክፍል እናነሣዋለን። በአጭሩ ግን ኢየሱስ
ሰው ብቻ ሳይሆን ሥጋ የለበሰ አምላክ ነው። አምላክ ነው፤ በአምላክነቱ ላይ ሥጋን
ወሰደ ወይም በሥጋ መጣ። የመጣው ደግሞ ለአንድ ዓላማ ነው። ያንንም
እንመለከታለን። እዚህ ግን ፍጡር አለመሆኑን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ አንድም
ስፍራ ኢየሱስን ፍጡር አለማለቱንና ደጋግሞ ግን ፈጣሪ መሆኑን መግለጡን ማየቱ
በቂ ነው።

15
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በዮሐ. 1፥14 ስላለው፥ ቃልም ሥጋ ሆነ ስለሚለው ቃል ሳዲቅ ሲናገር፥ ‘እኛ ቃልም


ሥጋ ሆነ አንልም’ ብሏል። ያለበት መንገድም፥ ‘የፈጣሪ ቃል አድራጊ እንጂ ተደራጊ
ባለመሆኑ እንደሆነ ተናግሯል። እዚህ ላይ ቆም ብለን ማየት ያለብን ዒሳ በቁርኣን
የአላህ ቃል መባሉንም ነው። ካሊማቱላህ ተብሎአል። ይህን የሚለው 4፥171 ነው።

4፥171 እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ


እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ
መርየም የጣላት (የሁን) ቃሉም ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤ በአላህና
በመልክተኞቹም እመኑ (አማልክት) ሦስት ናቸው አትበሉም፤ ተከልከሉ ለናንተ የተሻለ
ይሆናልና፤ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ለርሱ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው።
በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው። መመኪያም በአላህ በቃ።

ይህ ጽንሰ አሳብ ራሱ ምናልባት ክርስቲያኖች ኢየሱስን ቃል ከሚሉት ትምህርት


የተገኘ ሳይሆን አይቀርም። ብዙ ከብሉይና ከአዲስ ኪዳን የተወሰዱ የቁርኣን
ትምህርቶች መኖራቸው ሐቅ ነው። አንድ ቃል ከሌላ ምንጭ ከተወሰደ ቀድሞ ምንጩ
የተጻፈው ነው እንጂ ወሳጁ ምንጭ ሊሆን አይችልም። እዚህ ጥቅስ ውስጥ፥
‘አማልክት ሦስት ናቸው አትበሉ፤ . . . ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው።’ የሚለው
ይህ አባባል ክርስቲያኖችን የተመለከተ ና እነሱን ለመወንጀል የተሠራ ነው፤ ልጅ
ያለው ሲባልም የሥጋ ልጅን ማለቱ ነው። አብና ወልድ የሚሉ ሥላሴያውያን
ክርስቲያኖች ናቸው። ሥላሴ ራሱ ደግሞ አንድ አምላክ በሦስት አካላት መገለጡ
ሳይሆን ሦስት አማልክት ተደርጎ በኢስላም ስለሚታይና ክርስቲያኖችን ሦስት
አማልክት አምላኪዎች ተደርገው ስለሚታሰቡ ነው፥ ‘(አማልክት) ሦስት ናቸው
አትበሉም፤ ተከልከሉ’ የተባለው።

ይህ አንቀጽ የሚለው ኢየሱስ ቃል መሆኑን ነው፤ ወደ ማርያም የጣላት ቃል። ኢየሱስ


ቃል ነው። ቀደም ሲል ስለ ኢየሱስ ፈጣሪነት ስናይ በዮሐ. 1፥1 እንዳየነው፥
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር
ነበረ። እንደሚለው ቃል እርሱ ቃል ነው።

ሳዲቅ፥ የእግዚአብሔር ቃል አድራጊ ነው እንጂ ተደራጊ አይደለም ብሏል። እዚህ


ያለው፥ ይህንን ሲል በዮሐ. 1፥1 ያለውን ማለቱ ነው። ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ግን
ተደራጊ ሆነ ማለት አይደለም። ‘ቃል ሥጋ ሆነ’ ሳይሆን፥ ‘ቃል ሥጋ ተደረገ’ ቢባል
ኖሮ እውነትም ተደራጊ ነው ይባላል። ነገር ግን ቃል እንዲሆን ሳይደረግ፥ ቃል ሥጋ
ሆነ፤ ራሱ ቃል ሥጋ ሆነ። ማንም አላደረገውም፤ እርሱ ግን ሆነ። ይህ በጣም ግልጽ
የሆነ ሰዋሰው ነው። ለምሳሌ፥ እኔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም የኬንያ
ንጉሥ ብደረግ፥ ‘ተደረግሁ’ ይባላል፤ ያ ማለትም፥ ያደረገኝ አካል አለ ማለት ነው።
ነገር ግን፥ ማንም ሳያደርገኝ ብሆንስ? በሆነ መንገድ፥ መፈንቅለ መንግሥትም ይሁን
መገልብጠ መንግሥት ፈጽሜ፥ ግን ሆኜ ብገኝስ? ያኔ ተደረግሁ ሳይሆን፥ ‘ሆንኩ’
ይባላል። ቃል ሥጋ ተደረገ ማለት እና ቃል ሥጋ ሆነ ማለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።

16
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሥጋ ተደረገ አይልም፤ ቃልም ሥጋ ሆነ። ዮሐ. 1፥14 የሚለው


ንን ነው፤ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም
ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ማን አደረገው? ማንም
አላደረገውም። ስለ መደረግ አይናገርምና ጥያቄው ራሱ ሲጀመርም ልክ አይደለም።
ማንም አላደረገውም፤ ራሱ ቃል ሥጋ ሆነ።

የቃል ማንነት ወይም መለኮትነት የሚታየው በሥላሴ ማንነት ውስጥ ነው። እዚህ ላይ
ነገረ ሥላሴን በሌላ ስፍራ የምናየው ቢሆንም ሳዲቅ ራሱም፥ ዮሐ. 1፥1-2ን በመጥቀስ
ሁለት እግዚአብሔር ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል። ‘ቃል እግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ ብሎ ቃልም እግዚአብሔር ነው ካለ እግዚአብሔር ዘንድ ሌላ እግዚአብሔር አለ
ማለት ነው?’ ብሎአል። በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፥ እግዚአብሔር ሥላሴ ነው።
እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ሆኖ ሦስት አካላት የሆነ እግዚአብሔር ነው። አብ፥
ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ።

ቁርኣን ሥላሴን የሚያውቀው ወይም ክርስቲያኖች ሥላሴን የተረዱትና የሚሉት


አድርጎ የሚያስተምረው፥ ሦስቱ የሥላሴ አካላት፥ እግዚአብሔርን፥ ዒሳን፥ እና
ማርያምን ነው። ሱረቱ አል-ማኢዳህ (ሱራ 5) ቁጥር 116፤ ይህንን የተሳሳተ የቁርኣን
ነገረ ሥላሴ ነው የሚያሳየን፤

5፥116 አላህም፦ የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ ፦ እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ


ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፤ ጥራት
ይገባህ፤ ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፤ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ
አውቀኸዋል፤ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፤ ግን አንተ ዘንድ ያለውን
አላውቅም፤ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና ይላል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው ነገረ ሥላሴ ግን እግዚአብሔር ማርያምና ዒሳ


ሳይሆን አብ፥ ወልድ (ኢየሱስ)፥ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ነው። ኢየሱስ
ከአብ ጋር እኩልና ያልተናነሰ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስም ከአብና ወልድ ጋር
እኩልና ያልተናነሰ አምላክ ነው። ይህ ዋናው ትምህርት ስላልሆነ ወደ ዮሐ. 1፥1-2
ስንመጣ፥ ‘ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ’ ብሎ፥ ‘ቃልም እግዚአብሔር ነበረ’ ካለ
እግዚአብሔር ዘንድ ሌላ እግዚአብሔር አለ ማለት ነው?’ ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ፥
መልሱ፥ ‘በእርግጥም እግዚአብሔር ዘንድ ቃል ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።’
ነው። ያ ቃል ኋላ ሥጋ የሆነው ቃል ነው። እርሱም ኢየሱስ ነው። ዒሳ ፍጡር ከሆነና
ኢየሱስ ፍጡር ካልሆነ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ የቁርኣኑ ዒሳ አይደለም ማለት ነው።
የቁርኣኑ ዒሳ አስቀድሞ ቃል ኖሮ ኋላ ሥጋ አልሆነም። ከሆነ፥ ወይም ነበረ የሚባል
ከሆነም የኢየሱስን ዘላለማዊነት ይቀበላል ማለት ነው። ስለዚህ ነው ዒሳና ኢየሱስ
ከቶም አንድ ያልሆኑት።

17
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሌላው የሳዲቅ ጥያቄ ከመጀመሪያው ውስጥ የተሸጎረ ጥያቄ ሆኖ፥ ቃል ሥጋ ከሆነና


ሥጋ የሆነው ቃል እግዚአብሔር ከሆነ በዮሐ. 3፥16 ካለው ጋር አይጋጭም ወይ?
የሚል ነው። በእውነቱ አይጋጭም። ዮሐ. 3፥16 የሚለው፥ በእርሱ የሚያምን ሁሉ
የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን
እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ነው። እግዚአብሔር ሥላሴ መሆኑን
ከተቀበልን አብ ወደደ፤ ልጁን ሰጠ። ምን ይጋጫል? ምንም አይጋጭም። ግጭት
የሚሆነው ሥላሴን ሳንቀበል ስንቀር ወይም ስንክድ ነው። ለክርስትና አስተምህሮ ይህ
ግጭት አይሆንም። ልጅ ደግሞ ቃል፥ ሥጋ ሆኖ በመካከላችን አደረ። ምን ይጋጫል?
ምንም አይጋጭም። በወንጌላት ውስጥ እኮ ስለ አብና ወልድ መስተጋብር በብዛት
ተጽፎ ይገኛል። ስለዚህ አይጋጭም። ሳዲቅ ስለ መሆን እና መደረግ ሲጠይቅ፥ በዘፍ.
1፥3 ያለው ብርሃን ይሁን ሲባል እንደሆነው እዚህም ቃል ሁን የተባለው ነው ይላል።
ይህ ስሕተት ነው። ቃል ሥጋ ሆነ እንጂ ይሁን አልተባለም። ቃል ሥጋ ይሁን እና
ቃልም ሥጋ ሆነ አንድ አይደሉም።

ይህ ‘ሁን’ የተሰኘው በ4፥171 የተጻፈው ነው፤ ዒሳ ወደ መርየም የተጣለው ቃሉ፥


የሁን ቃሉ፥ ወይም ሁን የተባለው ቃሉ ነው ነው የሚለው፤

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት (የሁን) ቃሉም


ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤

(የሁን) የሚለው በቅንፍ ውስጥ መሆኑ የተጨመረ መሆኑ ገላጭ ነው። እዚያ
ዘፍጥረት ውስጥ ይሁን የተባለውና የሆነው ብርሃን ነው። ይሁን ተባለና ሆነ። እዚህ
ግን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው እና እግዚአብሔር የሆነው ቃል ራሱ ነው ሥጋ
የሆነውና በሥጋ የመጣው።

ኢየሱስን ወይም የእግዚአብሔር ልጅነትን በተመለከተ የሙስሊሞች የመረዳት


ጉድለት እኛ ክርስቲያኖች ቃሉ እንደሚል ኢየሱስ ወልድ ወይም ልጅ ነው ስንል
ማርያምና እግዚአብሔር አብ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርገው ልጅ እንደወለዱና
ኢየሱስ የዚያ ግንኙነት ውጤት እንደሆነ እንደምናስተምር ነው። አይወልድም
አይወለድም ሲሉም ያንን ማለታቸው ነው። ነገር ግን፥ መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ማንም
ክርስቲያን አስተማሪ እንደዚያ ያለ የስሕተት ትምህርት አያስተምርም።
በእግዚአብሔርና በማርያም መካከል የተደረገ ሩካቤ ሥጋ መኖሩን የሚያሳስብ ምንም
ቃል ብቻ ሳይሆን ፍንጭም የለም።

ኢየሱስ ሥጋ ሲሆን በሥጋ ሲመጣ፥ ሥጋን የነሣ ጊዜ ወይም ሰው የሆነ ጊዜ ተጀመረ


ማለት አይደለም። ሥጋ ሳይሆን በፊት በመለኮቱ የነበረ፥ የኖረ ጌታ ነው። እርሱ
ዘላለማዊ ጌታ ነው። ዮሐ. 1፥1-2 የሚገልጠው ያንን ዘላለማዊነት ነው። ሳዲቅ፥
‘ልጅነቱ የማርያም እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም’ ካለ በኋላ የኢየሱስ ልጅነት

18
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የእግዚአብሔር ሳይሆን የማርያም መሆኑን ለማረጋገጥ ከሉቃስ ወንጌል በማንበብ


ሊያብራራ ጥሯል። ያነበበው ክፍል፥ መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥
በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም
ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም
ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ ሉቃ. 1፥30-32።

ልጅነቱ ለማርያም እንጂ ለአላህ አይደለም ብሎ ይህንን ሊያብራራ የሞከረበት ምንባብ


ግን ራሱን የሚናገረውን ነገር የሚቃረን ነው። ይህንን ክፍል ኢየሱስ የማርያም ልጅ
መሆኑን ለማስረዳት የሚጠቀምበት ከሆነ ክፍሉን ይቀበለዋል ማለት ነው። ነገር ግን
ለማሳት እንጂ በመቀበል አለመጥቀሱን እናውቃለን። ምክንያቱን ጠቅላላውን አሳብ
አይቀበለውም። ይህ ክፍለ ምንባብ የማን ልጅ ይባላል አለ? የልዑል ልጅም ይባላል።
የማርያም ልጅ ሳይሆን የልዑል ልጅ። ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

ሳዲቅ ለምን ይህንን በራሱ ግምት የተሳሳተ የመሰለውን፥ ግን የራሱን ትምህርት


የሚሰብረውንና የሚቃወመውን ክፍል መርጦ እንዳነበበ አላውቅም። ካነበበው
በምንባቡ ይስማማል ማለት ነው። ከተስማማ ይህንን የሚያነበውን ክፍል ይቀበለዋል
ማለት ነው። የቪድዮ ትምህርቱን ሲጀምር ከክርስቲያኖቹ መጽሐፍ ከመጽሐፍ
ቅዱስም ትምህርቱን የሚደግፉ ክፍሎችን እንደሚያነብብ ገልጦ ነው የጀመረው።
ይህንን ክፍል ያንብበው እንጂ ክፍሉ ትምህርቱን የሚደግፍ ግን አይደለም። እርሱም
የምንባቡን አሳብ አይቀበለውም። ኢየሱስ የማርያም ልጅ ነው? አዎን በሥጋ ሲመጣ፥
ትሥጉት ሲሆን ከማርያም ነው የተወለደው። ስለዚህ በሥጋ የመጣ የማርያም ልጅ
ነው። ግን በሥጋ የመጣ ከዘላለምም የአብ ልጅ የሆነ አምላክ ነው።

የዚህ ክፍል ዋና አሳብ የቁርኣኑ ዒሳ የተፈጠረ ዒሳ መሆኑና የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ


ግን ያልተፈጠረ ፈጣሪ በመሆኑ ዒሳና ኢየሱስ አንድ ያለመሆናቸውን አንድ ማስረጃ
ያስጨብጠናል ማለት ነው። ከሙስሊሞች ጋር ስናወራ ዒሳ እያሉ ስለ ኢየሱስ
ሲነግሩን ስለ አንድ ሳይሆን ስለ ሁለት የተለያዩ አካላት እየተነጋገርን መሆኑን ይህንን
እንወቅ፤ እንንገራቸውም። ቃል ተደረገ እንጂ አልሆነም የሚለው አባባል የተፈጠረ
ስሕተት መሆኑን እንወቅ። ቃል ሥጋ ተደረገ የሚል ትምህርት በቁርኣንም በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥም አይገኝም። ይህ ፈጠራ ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ ፈጠራ ነው።

ይህንን የቃልን ሥጋነት ክፍል ስደመድም አንድ ጥያቄ ልጠይቅ። ይህ ጥያቄ የውይይት
ጥያቄም ሊሆን ይችላል። ጥያቄውም፥ እግዚአብሔር ቢፈልግ የፈለገውን፥ የወደደውን
መሆን ይችላል ወይስ አይችልም? የወደደውን ሊያደርግ ብቻ ሳይሆን የፈለገውን
ሊሆንም ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? እርሱ ያሻውን መሆን ይችላል? ወይስ እኛ
የገደብንለትን ሥልጣን ማለፍ የማይችል አምላክ ነው? ለምሳሌ፥ እግዚአብሔር ሰው
ልሁን ቢል፥ ሥጋ ልልበስ ቢል ይችላል ወይስ አይችልም?

19
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ኢየሱስ ከሥላሴ አካላት በሥጋ የመጣው ነው።


የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም የምንለው ሌላው ምክንያት ኢስላም
የኢየሱስን አምላክነትም፥ ነገረ ሥላሴንም የማይቀበል በመሆኑና ኢየሱስ ደግሞ
ከሥላሴ አካላት በሥጋ የመጣው በመሆኑ ነው። ይህንን ምላሽ በማዘጋጅበት ወቅት፥
በጽሑፍ አንድ መጽሐፍ መልስ እየሰጠሁ ነኝና ይህ እዚህ የማካፍለው ከዚያም
የተወሰደ ነው።5 በቀደመው ክፍል ኢየሱስ ፍጡር ሳይሆን ፈጣሪ መሆኑን አይተናል።
ጌታ በሥጋ የተገለጠ ወይም በሥጋ የመጣ አምላክ መሆኑ እንደገና ይሰመርበት።

እዚህ ሁለት ነጥቦችን እንመለከታለን። አንደኛው የሥላሴ ማንነት ሲሆን ሁለተኛው


ከዚህ የሥላሴ አካላት በሥጋ የተገለጠው አንዱ፥ ሁለተኛው አካል፥ ኢየሱስ ወይም
ወልድ ብቻ መሆኑን ነው።

መጀመሪያ የሥላሴ ማንነትን እንይ። ኢስላም አስተምህሮተ ሥላሴን ከቶም ያማያውቅ


ወይም የማይቀበል በመሆኑ የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ ወይም ክርስቲያኖች
የሚሰብኩትን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ተኪ በማድረግ ነው የሚያቀርበው። ኢየሱስ
ሰው ሲሆን አምላክ ታዲያ የት ገባ? ኢየሱስ ሲሞት፥ ኢየሱስ እግዚአብሔር ከሆነና
እግዚአብሔር ከሞተ እግዚአብሔር አልነበረም ማለት ነው? የሚሉ የተለመዱና
የተደጋገሙ አሳቦችና ጥያቄዎች ይሰነዝራሉ። እንዲህ ያሉ ጥያቄዎች ከአስተምህሮተ
ሥላሴ እና ከኢየሱስ ማንነት መረዳት ጎዶሎነት የመነጩ ጥያቄዎች ናቸው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፥ እግዚአብሔር ሥላሴ ነው። እግዚአብሔር አንድ


እግዚአብሔር ሆኖ ሦስት አካላት የሆነ እግዚአብሔር ነው። አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ
ቅዱስ አንድ አምላክ። ሥላሴ ምን እንዳልሆነ ጥቂት አሳቦችን በቅድሚያ እንይ።

ሀ) ቁርኣን ሥላሴን የሚያውቀውና የሚያሳውቀው እግዚአብሔርን፥ ዒሳን፥ እና


ማርያምን ሦስቱን በአንድ አድርጎ እንደሆነ ባለፈው ክፍል ከቁርኣን ሱረቱል ማኢዳህ
(5)፥116 በማንበብ ተመልክተናል። ጥቅሱ የሚለው ይህንን ነው፤

5፥116 አላህም፦ የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ ፦ እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ


ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፤ ጥራት
ይገባህ፤ ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፤ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ
አውቀኸዋል፤ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፤ ግን አንተ ዘንድ ያለውን
አላውቅም፤ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና ይላል።

5 እስላም እና ክርስትና (ንጽጽራዊ አቀራረብ) ዶ/ር ሙሓመድ ዓሊ አልኹሊ።

20
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሥላሴ የእግዚአብሔር የዒሳና የማርያም አንድነት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ


አያስተምርም። ሥላሴ ይህ አይደለም ማለት ነው። እንዲህ ያለ ሥላሴ በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። በክርስትና ታሪክ ውስጥም ይህ
አስተምህሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰጥቶ አያውቅም።

ለ) ሌላው ቁርኣን ሥላሴን የሚገልጥበት መንገድ የእግዚአብሔር፥ የዒሳና የማርያም


ጥምር ብቻ ሳይሆን፥ ሦስት አማልክት፥ ወይም ዒሳን የሦስቶች ሦስተኛ በማድረግ
ነው። የሦስቶች የማይገናኙ፥ ውስጣዊ አንድነት የሌላቸው አካላት ኅብረት ወይም
ጥምር ሦስተኛ ማለት ነው። የዩሱፍ ዓሊ የእንግሊዝኛ ቁርኣን ትርጉም ሱራ 5፥73ን
ሲተረጉም እንዲህ ይለዋል፤ They do blaspheme who say: Allah is one of
three in a Trinity: for there is no god except One Allah. If they
desist not from their word (of blasphemy), verily a grievous
penalty will befall the blasphemers among them. ይላል።

እዚህ ውስጥ የገባው፥ in a Trinity የሚለው ቃል የሌለና ራሱ የጨመረው ቃል


ነው። እንደዚህ የመሰሉ በቅንፍ ውስጥ እና ያለ ቅንፍ፥ ወይም በግርጌ ማስታወሻ
የሚጨመሩ፥ በሌሎች ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቁርኣኖች ውስጥ የሚገኙ ቃላት እጅግ
ብዙ ናቸው። ይህ ለምን እንደሆነ ሲጠየቅ የሚመልሱት፥ ‘ከዋናው ቋንቋ ወደ ተቀባዩ
ቋንቋ አሳቡን ማስተላለፍ ስለማይቻል ነው።’ ይላሉ። አሳቡ እንዲተላለፍ ሲባል
ደግሞ የሚጨመሩ ቃላትና ሐረጎች አሉ። ከላይ ባየነው ትርጉም ዩሱፍ ዓሊ Trinity
ያለው የአማርኛው 'የሦስት ሦስተኛ ነው' የሚለውን ነው። አማርኛውም ሥላሴ
የሚለውን በግርጌ ማስታወሻ ላይ ጽፎት ይገኛል። ዩሱፍ ዓሊ ቃሉን ሲጨምረው
በአማርኛውና በሌሎች ትርጉሞች በቅንፍ እንደተቀመጠው አስቀምጦ አላብራራም።
ይህ የአተረጓጎም ዘይቤ ቃልን ሳይሆን አሳብን የመተርጎም ዘይቤ ሆኖ የክርስትናን
አስተምህሮተ ሥላሴ ለመቃረን የታለመ ፕሮፓጋንዳዊ ትርጉም ነው። የአማርኛው
ጥቅስ ከነግርጌ ማስታወሻው ይህንን ይላል፤

5፥73 እነዚያ አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው (1) ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ ከአምላክም አንድ
አምላክ እንጅ ሌላ የለም፤ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ፣ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ
ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል። [የግርጌ ማስታወሻ 1፥ ከሦስት አማልክት አንዱ ነው ያሉ፤
በሥላሴ የሚያምኑ።]

ይህ የሚያስረዳው ኢስላም ሥላሴን የሚረዳው ሦስት አማልክት አድርጎ መሆኑን ነው።


ሦስት አማልክት ወይም ሦስት አምላኮች። የግርጌ ማስታወሻው ውስጥ ያለው ሦስት
አማልክት የሚለው እና ሥላሴ የሚለው ይህንን የተሳሳተ መረዳት የሚያረጋግጥ ነው።
ለዚህ ነው ሌሎች አማልክትን በአላህ ላይ እንደመጨመርና እንደ ማሻረክ ተደርጎ
የሚቆጠረው።

21
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ልክ አማርኛው በግርጌ ማብራሪያው 'በሥላሴ የሚያምኑ' እንዳለው ብጤ ነው ዩሱፍ


ዓሊም የተረጎመው። እርሱ ግን በግርጌ ማስታወሻና በቅንፍ ሳይሆን በቀጥታ እንደዚያ
እንደተባለ አድርጎ ነው የተረጎመው። የሦስት ሦስተኛና የሥላሴ ልዩነት የሦስት
አማልክት እና የአንድ አምላክና ሦስት አካላት ልዩነት ነው። ለሙስሊሞች የሦስት
ሦስተኛ ማለት ከሽርክ ጋር የሚያያዝ ስለሆነ ክርስቲያኖችን የሚያዩት እንደ ሦስት
አማልክት አምላኪዎችና አጋሪዎች ወይም ሸራኪዎች ነው። ይህ ሥላሴ የሚለው ቃል
የተጠቀሰው በቀጥታ የክርስቲያኖችን ትምህርት ብቻ ሳይሆን፥ አጋሪዎች ናቸው
በማለት ክርስቲያኖችንም ከሌሎች አጋሪዎች ወይም ሸራኪዎች ጋር ለማጥቃት
የታለመ ነው።

ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ፣ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ


ይነካቸዋል።

የሚለው ይህንን ጥቃት አመልካች ነው። በነገራችን ላይ፥ ቁርኣን ሁለት ምድቦች
አሉት፤ አንዱ መኪያ ይባላል እንደዚህ የሚባሉት የመካ ሱራዎች ናቸው። ሁለተኛው
መዲኒያ ይባላል በመዲና የተነገሩ ናቸው። መኪያዎች የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ
በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በመካ ሲኖር የተናገራቸው ሱራዎች ናቸው። ቁርኣን እንደ
መጽሐፍ ቅዱስ በጊዜ ቅደም ተከተል የተጻፉ ሱራዎች ወይም ምዕራፎች ስብስብ
ስላልሆ ሱራዎቹ ተሰባጥረው ነው የሚገኙት። ስብጥሩ ከትልልቅ ሱራዎች ወደ
ትንንሽ ነው። ከጠቅላላው 114 ሱራዎች 75% መኪያዎች ወይም የመካ ሱራዎች
ሆነው 25% መዲኒያዎች ወይም የመዲና ሱራዎች ናቸው። የመዲና ሱራዎች ከሂጅራ
ወይም ከመካው ስደት በኋላ በመዲና የተነገሩ ናቸው። እነዚህ የመዲና ሱራዎች
አጥላይነትና አግላይነት፥ እንዲሁም የአጥቂነትና የወራሪነት ስሜት የሚገለጥባቸው
ወይም የተገለጠባቸው ናቸው። ለምሳሌ ከመጀመሪያዎቹ 9 ሱራዎች ውስጥ 6ቱ
የመዲና ሱራዎች ናቸው። በነዚህ በስድስቱ ውስጥ ብቻ 110 በላይ የአጥቂነት ወይም
የጂሃድ ጥቅሶች ወይም አያዎች ይገኛሉ። ከሱራዎቹ ሁሉ በቅደም ተከተል
የመጨረሻው ሱራ ሱረቱል-ተውባህ የተባለው (ምዕራፍ 9) ሲሆን ይህ ሱራ
አጋሪዎችን ሁሉ ባገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሏቸው የሚለው ያለበት ነው።

አጋሪ ማለት ከአንዱ አላህ ሌላ የሚያመልኩ ማለት ነው። ከላይ እንዳየነው


ክርስቲያኖች ሥላሴያውያም አማኞች ስለሆኑ ሦስት አማልክት ያመልካሉ በማሰኘት
አጋሪ ናቸው ስለሚባል፥ ስለዚህ ከሚገደሉት መካከል ናቸው። ሱራ 9 ቁጥር 5 እና
29 ይህን ይላል፤

9፥5፥29የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸዉ፤


ያዙዋቸዉም፤ ክበቡዋቸውም፤ ለነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፤ ቢጸጸቱም፤
ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ፣ መንገዳቸውን ልቀቁላቸዉ አላህ
መሐሪ አዛኝ ነውና። . . . ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች፣ እነዚያን በአላህ
በመጨረሻዉ ቀን የማያምኑትን፣ አላህና መልክተኛዉ እርም ያደረጉትንም እርም

22
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የማያደርጉትንና እዉነተኛዉንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ሆነዉ


ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው። (ሱራ 9፥5 እና 29)።

ይህ ጥቅስ ከሥላሴ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ሆኖ አይደለም። ነገር ግን በሥላሴ ማመን


አጋሪነት ስለተባለና የኋለኞቹ ሱራዎች እንዴት ክርስቲያኖችና አይሁድ ላይ
እየተነጣጠሩ እንደመጡ ለማሳየት ነው። ክርስቲያኖች በሥላሴ ማመናቸው አጋሪ
አሰኝቶአቸዋል። አጋሪነት ደግሞ ያስገድላል።

ሌላው ከዚህ የቀድሞና የኋላ ሱራዎች (መኪያ እና መዲኒያ ሱራዎች) ጋር መታወቅ


ያለበት ነጥብ ደግሞ የኋላዎቹ አንቀጾች የቀድሞዎቹን ይሽራሉ። መሻር ወይም
በእንግሊዝኛ abrogation ይባላል። የሚሽረው ጥቅስ ወይም ሻሪው (ነሲክ ይባላል)
በኋላ የተነገረው ነው። የሚሻረው ወይም ተሻሪው ደግሞ መንሱክ ይባላል።
የሚሻረው ቀድሞ የተነገረው ነው። 2፥106 ይህን ይላል፤

ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን


እናመጣለን፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ (ቻይ) መኾኑን አታውቅምን? ፡፡

በዚህ አካሄድ የመካ ሱራዎች በቀላሉ የመዲና ሱራዎችን ይተካሉ ማለት ነው።
ለምሳሌ፥ የቀደመውን በመካው ሱራ፥ ‘በሃይማኖት ማስገደድ የለም።’ የሚለውን (2፥
256) ወይም በ109፥6 ‘ለናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ፤ ለኔም ሃይማኖቴ አለኝ።’
የሚለውን ምንም ማስፈራሪያ የሌለበትን የመካ ስብከት ይህኛው ከላይ ያየነው የሱራ
9 ቃል ይሽረዋል ማለት ነው። ይህ የመሻር ድንጋጌ የኋለኞቹን ትክክለኛ
ያደርጋቸዋል። አንቀጽን በአንቀጽ መለወጥ ይባላል፤ (2፥106፤ 16፥101)። ይህ የመሻር
ሕግ ራሱን ቁርኣንን ራሱን ያስተካከለ ወይም ያሻሻለ አድርጎ ስለሚያቀርበው
ዘላለማዊ የአለመሆኑ አንድ ውስጣዊ አስረጅ ነው።

የቀድሞዎቹ ሰላማዊ መሳዮች በኋለኞቹ አጥቂዎች መለወጣቸው በክርስቲያኖቹ


ትምህርትም፥ ማለትም፥ በሥላሴም ጭምር፥ እና በራሳቸው በክርስቲያኖቹም ላይ
የታለሙ የወረራና የአጥቂነት አንቀጾች ናቸው። በዓለም ላይ ካሉት ሃይማኖቶች ሁሉ
ከአንዱ በቀር ሁሉም ለሃይማኖታቸው ይሞታሉ እንጂ አይገድሉም። ከአንዱ በቀር
ያልኩት ኢስላምን ነው። ኢስላም ግን ይገድላል፤ እንዲገድሉ ግልጽ አንቀጾችን
ይሰጣል። ለምሳሌ፥ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸዉ፤ ይላል።

ሥላሴ ከአጋሪነት ጋር ስለተቆራኘና አጋሪነት ደግሞ የሚያስገድል ስለሆነ ይህ የሥላሴ


አስተምህሮ ለብዙ ነሳራዎች ወይም ክርስቲያኖች የሕይወት ዋጋ መክፈል ምክንያት
የሆነ ትምህርት ነው። ይሁን እንጂ፥ ሙሐመድም ሆነ የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች
የሥላሴን ምንነት አውቀውና ተረድተው ስሕተት ነው አላሉም። ስሕተት ነው ያሉት
ሳያውቁና ሳይረዱት ነው። ስላልተረዱት ነው፥ ‘የሦስት ሦስተኛ’ የተባለው።

23
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ስላልተረዱት ነው፥ ‘አላህ፥ ዒሳና መርየም’ ሥላሴ እንደሆኑ ተደርጎ የተነገረው።


በሙስሊሞች መረዳት ውስጥ ያለው ክርስቲያኖች የሚያመልኩት አንድ አምላክ
ሳይሆን ሦስት አማልክትን ነው።

ኢሳ ደግሞ የአላህ እና የማርያም አካላዊ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጤት ሆኖ


በክርስቲያኖች እንደሚታሰብ በመገመት አላህ እንዲያ ያለ ነገር ከማድረግና ልጅ ያለው
ከመሆን የጠራ ነው ይላል።

4፥171 እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ


እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ
መርየም የጣላት (የሁን) ቃሉም ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤ በአላህና
በመልክተኞቹም እመኑ (አማልክት) ሦስት ናቸው አትበሉም፤ ተከልከሉ ለናንተ የተሻለ
ይሆናልና፤ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ለርሱ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው።
በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው። መመኪያም በአላህ በቃ።

'አማልክት ሦስት ናቸው አትበሉ፤ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው' የሚለው


በክርስቲያኖች ላይ የተነጣጠረው ይህ የመዲኒያ ሱራ ጥቅስ መሆኑን ልብ እንበል።
ክርስቲያኖች ኢየሱስ ወልድ ወይም ልጅ ነው ስለሚሉ ነው፥ እርሱ ‘ልጅ ያለው
ከመሆን የጠራ ነው።’ የተባለው። ደግሞም፥ 'አማልክት ሦስት ናቸው አትበሉ'
የሚለው። ሦስት የተባሉትም ከላይ እንዳየነው፥ በጥቅሱ ውስጥ የተጻፉት አላህ፥
መርየም እና ኢሳ ናቸው። ምንም እንኳ የኢየሱስን እናት ማርያምን የሚያመልኩ
ሰዎች ያኔም ዛሬም ቢኖሩም፥ ሥላሴ ከቶም ያ መሆኑን ከቃሉ ጠቅሶ ማንም
አላስተማረም። ያስተማረም የለም። ልጅ ያለው ሲልም የሥጋ ልጅን ወይም በግብረ
ሥጋ ግንኙነት የሚወለድ የሥጋ ልጅን ማለቱ ነው። ልክ እግዚአብሔር ከማርያም ጋር
ሩካቤ ሥጋ ፈጽሞ ኢየሱስ እንደተወለደ ያለ መረዳት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው ሥላሴ በቁርኣን እንዳየነው የእግዚአብሔር


የማርያምና የዒሳ ጥምር አይደለም። የሦስት ሦስተኛም ሳይሆን እግዚአብሔር አንድ
እግዚአብሔር ነው። ሥላሴ ማለት ሦስት አማልክት ማለት አይደለም። ሥላሴ ሦስት
ሢሶዎች ተባብረው አንድ ያደረጉት የአንዱ ሙሉ አንድ ሦስተኛ ማለትም አይደለም።
ሥላሴ የሦስቶች፥ የሦስት እኩዮች ወይም አቻዎች ኅብረት ወይም ጥምር ወይም
ኮሚቴም አይደለም። ወይም ሥላሴ የሦስቱ ማንነት የፈጠረው አራተኛ ማንነትም
አይደለም።

ሥላሴያውያን ክርስቲያኖች የአንድ አምላክ፥ የአንድ እግዚአብሔር አምላኪዎች ናቸው


ሲባል ወይም በጥቅሉ ሥላሴ ሲባል የአማልክት ቁጥርን የሚመለከት ጽንሰ አሳብ
ሳይሆን የአምላክን ማንነት የተመለከተ ነው። ማንነቱም እግዚአብሔር አንድ
እግዚአብሔር ሆኖ በዚያው ቅጽበትና በዚያው ልክ ያው አንዱ እግዚአብሔር ሦስት
አካላት የሆነ እግዚአብሔር ነው። አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ።

24
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩልና ያልተናነሰ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስም ከአብና ወልድ
ጋር እኩልና ያልተናነሰ አምላክ ነው። ሥላሴ የአኀዝ ብዝኀነት ሳይሆን የአሐድ ማንነት
መግለጫ ቃል ነው። ቁጥርን ብቻ ሳይሆን፥ የአካል ቁጥር እንደተጠበቀ ሆኖ፥ ከቁጥር
በላይና ከቁጥር ይልቅ ማንነትን ገላጭ አሳብ ነው።

እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር መሆኑን ዘዳ. 6፥4 እንዲህ ይገልጠዋል፤ እስራኤል


ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው። አንተም አምላክህን
እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።

በአዲስ ኪዳንም ትምህርቱ ይኸው ነው። እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው። ጌታ


ከትእዛዛት ሁሉ ፊተኛይቱ የቷ መሆኗን ሲጠየቅ የመለሰው መልስ ይህንን ጥቅስ
በመጥቀስ ነው። ይህ ጌታ የተጠየቀበት ጥያቄና የሰጠው መልስ በሦስቱ ወንጌላት
ውስጥ ተጽፏል አንዱን ብቻ ብናይ፥ ማርቆስ የጻፈው ይህን ይላል፤ ማር. 12፥29
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤
ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፤ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ
በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት።
ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ይላል። ይህ የብሉይ ኪዳኑ ከላይ ያየነው ጥቅስ ነው።
ይህ የአዲስ ኪዳንም ትምህርት ነው። ቃሉ በቀጥታ ከዘዳግም ውስጥ የተጠቀሰ ነው።
በኢሳይያስም ይኸው ተነግሯል፤ ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ
ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል
እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። እኔ፥ እኔ
እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ኢሳ. 43፥10-11።

ይህ የእግዚአብሔር አንድነት እና ሦስት አካልነት የኛን ውሱን መረዳትና እውቀት


ስለሚፈታተንና ከተለመደው የራሳችን ማንነት፥ ማለትም፥ ከምናውቀው አንድ ሰው
አንድ አካል ከመሆኑ የተለየ ስለሆነ ለመረዳት ሊከብደን ይችላል፤ ይከብደናልም። ግን
ምስጢር ነው ብለን የምንሸፍነው ነገር አይደለም። ለመረዳት ይከብደናል ብለንም
የምናልፈው አይደለም። አስተምህሮተ ሥላሴ ለአንዳንድ ሃይማኖቶች፥ በተለይም
ለሙስሊሞች ግራ ገብ ነው። ተውሂድ ለሚባለው አስተምህሮም የማይገጥም ነው።
ተውሂድ በስነ መለኮት monad ወይም monadism ከሚባለው አስተምህሮ ጋር
አንድ ነው። ያም አንድ ነገር ወይም አንድ አካል፥ አንድ ማንነት፥ አንድ ባህርይ መሆን
ማለት ነው። ይህንን የተውሂድ አስተምህሮ ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጣው ነቢል
ቁሬሺ በቀላል ቋንቋ ሲያስቀምጠው እንዲህ ብሎታል፤

Let us consider again the basic teaching of tawhid: God is absolutely


one. This means that, in eternity past, before he had created anything,
Allah was alone. One person, all by himself. It was not until he chose
to create the universe that Allah had anything to relate with. This is a

25
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

significant theological problem because, through the ninety-nine


names and otherwise, Islam teaches that Allah is a relational being.
But if he had nothing to relate with before creating the universe, how
could he be a relational being?

ትርጉም፤ እግዚአብሔር ፍጹም አሐድ የሚለውን የተውሂድን መሠረታዊ ትምህርት


እናጢን፤ ይህ ማለት ከዘላለም፥ ምን ነገር ከመፍጠሩም በፊት አላህ አንድ ብቻውን
ነበረ፤ ብቻውን የሆነ አንድ ብቻ አካል ነበረ። ጽንፈ ዓለማትን እስኪፈጥር ድረስ
ምንም ዓይነት ግንኙነት የሚያደርገው ነገር አልነበረም። ይህ ትልቅ ስነ መለኮታዊ
ችግር ነው፤ ምክንያቱን በ99ኙ ስሞቹ እና በሌሎችም በኩል ኢስላም
የሚያስተምረው አላህ የግንኙነት ማንነት እንዳለው ነው። ነገር ግን፥ ጽንፈ ዓለምን
ከመፍጠሩ በፊት ምንም ግንኙነት የማያደርግ ከሆነ፥ እንዴት ሆኖ ነው የግንኙነት
ማንነት የሚኖረው?6

ነቢል ይህ እርስ በራስ የሚጣረስ ስለመሆኑ ለማሳየት ከአላህ ስሞች ሁለቱን ለምሳሌ
ያወሳል፤ አርራሕማን እና አርራሂም የተባሉት ስሞች፥ ሌላ አካል ካልኖረበት ፍጹም
አሐድ ጋር የማይሄዱ ስሞች ናቸው። አንድ አካል ብቻውን ከሆነ ለራሱ አይራራም
ወይም ራሱን አይምርም። ራሱንም አይወድድም። ራሱን ካልወደደ ወይም
የሚወድደው ሌላ እስኪመጣ ድረስ አል-ዉዱድ መሆን አይችልም ማለት ነው። ከላይ
በስነ መለኮት monad ወይም monadism ከሚባለው አስተምህሮ ጋር አንድ ነው
ያልኩት ነው ይህ ‘ፍጹም አሐድ።’ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ፍጹም አሐድ
ሳይሆን ሥሉስ አሐድ፥ ወይም በስነ መለኮቱ ቃል Triune ነው። እኔ አንድ ሰው ነኝ
አንድ አካል አለኝ። አንድ ሰው ሆኜ ሁለት አካል ሊኖረኝ አይችልም። እግዚአብሔር
ግን አንድ እግዚአብሔር ነው፤ አንድ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ሦስት አካል ነው። ይህ
አንድ ሆኖ ከአንድ በላይ አካል መሆን ዲበ አእምሮአዊ ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን
የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ነው።

ሥላሴ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አይገኝም፤ ልክ ተውሂድ የሚለው ቃል


በቁርኣን እንደሌለው ማለት ነው። ሆኖም እግዚአብሔር አንድ መሆኑ፥ አብ
እግዚአብሔር መሆኑ፥ ወልድ እግዚአብሔር መሆኑ፥ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር
መሆኑ የተገለጠ ነው። አብ እግዚአብሔር ከሆነ፥ ወልድም እግዚአብሔር ከሆነ፥
መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ከሆነ፥ ይህንንም ሆኖ እግዚአብሔር ደግሞ አንድ
ከሆነ፥ ይህ ነው፥ ‘አንድ እግዚአብሔር እና ሦስት አካላት የሆነ’ የሚባለው። ይህ ነው
ሥላሴ።

እግዚአብሔር ግን በሰው መረዳት ከምንለካውና ከምንተረጉመው በላይ የሆነ አምላክ


ስለሆነ እኛ ከምናውቀው የማንነት ወይም ምንነት መገለጫ፥ ወይም ከምናውቀው

6 Qureshi, Nabeel, No God but One: Allah or Jesus? ePub edition.

26
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የሰው ማንነት የተለየብን ቢሆን መቀበል እንጂ፥ ከኛ ሳጥን ውጪ ከሆነብን ወይም


ስለሆነብን ላለመቀበል መደራደር የለብንም። ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ አምላክ
ሆኖ አንድ አካል መሆኑን ቢገልጥልን ኖሮ የምንቀበለውን ያህል፥ አንድ አምላክ ሆኖ
ሁለት ወይም ሦስት ወይም አራት አካላት ቢሆን ልንቀበለው ግድ ነው። ይህ የማንነቱ
ዲበ አእምሯዊነት ወይም ከአእምሮ በላይነት እርሱ እግዚአብሔር ነውና ሊያስደንቀንና
ሊያስደምመን እንጂ ሊደንቀን የተገባ አይደለም።

የሥላሴ ትምህርት አዲስ የተፈጠረ ሳይሆን ቀድሞም የኖረና ኋላ የበራ፥ የተብራራ፥


ይበልጥ ግልጥና ገሐድ የሆነ እውነት ነው። ገና ከፍጥረት ጅማሬ ጀምሮ
የእግዚአብሔር ማንነት ሥላሴያዊ ነው። በእርግጥ ሥላሴ አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ
ቅዱስ መሆኑ የተገለጠው በአዲስ ኪዳን ቢሆንም ከጅምሩም የተመለከተ ንድፉም
የታየ ነው።

አንድ ነጠላ ባለቤት የብዙ ግስ ሲጠቀም፤ እንዲሁም የብዙ ባለቤት ነጠላ ግስ


ሲጠቀም ይታያል። ለምሳሌ፥ ዘፍ. 1፥1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን
ፈጠረ። በሚለው እግዚአብሔር ብዙ ነው፤ እግዚአብሔሮች እንደማለት ያለ ነው።
ቃሉ ኤሎሂይም የሚል ባለቤት ነው። ግሱ ደግሞ፥ ‘ፈጠረ’ ነው፤ የተባእት ግሥ ሆኖ
ነጠላ ነው። ይህ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ የምናገኘው አገላለጥ ነው።
አንድ ሰው፥ ‘ሰዎች ወደ ቤት ገባ።’ ቢል የቋንቋ ሰዋሰው ሕግ ስላጣረሰ ጠያፍ ነው።
ያም ልክ እንደዚህ ነው። ‘እግዚአብሔሮች ፈጠረ።’ ነው የሚለው። ግን የተለመደ
አገላለጥ ነውና ጠያፍ አይደለም።

በዘፍ. 1፥26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤


ይላል። እዚህ ባለቤቱም ግሱም ይስማማሉ። ሁለቱም የብዙ ናቸው።

ይህንን፥ ‘እኛ’ የሚለውን ቃል አንዳንዶች እንደ ግርማዊያዊ ‘እኛ’ አድርገው ያዩታል።


በብዙ አገሮችና ባህሎች ነገሥታት ይህንን ያደርጋሉ። ግርማዊያዊ ‘እኛ’ የሚባለውም
ለዚያ ነው። ራሳቸውን እኔ ሳይሆን እኛ እያሉ ይጠራሉ። ግርማዊያዊ እኛ majestic
plurality የሚባለው ነው። በቁርኣንም አላህ ‘እኛ’ እያለ ይናገራል። ለምሳሌ፥

5፥44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትሆን አወረድን፤

23፥14 ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን። የረጋውንም


ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን። ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን።
አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው። ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን
አስገኘነው። ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ።

27
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሲል ማንን ነው እኛ የሚለው? ማን ነው እኛ? ይህንን ስለ ግርማዊያዊ እኛ ነው


የምንለውን ያህል፥ ይህ ባይሆንስ? ብለን መጠየቅና፥ ካልሆነ ደግሞ፥ ‘ስለ ሥላሴያዊ
እኛ ሊሆን ቢችልስ?’ ማለት ለምን ይከብደናል?

መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ስፍራዎች ነጠላ ባለቤት ከነጠላም ከብዙም ግሶች ጋር


ተጽፏል፤ በዘፍ. 2፥7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤
በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
እዚህ ባለቤትና ግስ ይስማማሉ። ሁለቱም ነጠላ ናቸው። ባለቤቱ ኤሎሂይም ሳይሆን
የህዋህ የሚለው ስም ነው።

ዘፍ. 11፥6-7 እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ
ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት
አይከለከሉም። ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ
እንደባልቀው። እዚህ ደግሞ ነጠላ ባለቤትና የብዙ ግስ እናገኛለን።

በብሉይ ኪዳን እንዲህ ያሉ አገላለጦች ይኑሩ እንጂ እግዚአብሔር ሥላሴ መሆኑ


እጅግ የበራ ባይሆንም አንድ አምላክ መሆኑ ግን በግልጽ ተጽፎአል። ዘዳ. 6፥4-5

‫ח ֽד׃‬ ְ 4
ָ ֶ‫שׁמַע יִשְׂרָ אֵל י ְהו ָה אֱלֹהֵינו ּ י ְהו ָה ׀ א‬

ָ ְ‫בְתָּ אֵת י ְהו ָה אֱלֹהֶיך ָ בְּכָל־ל‬5ַ‫וְאָה‬


‫בבְך ָ וּבְכָל־נַפְשְׁך ָ וּבְכָל־מְאֹדֶ ֽך ָ׃‬

(ሽማዕ ዪስራኤል፥ ይህዋህ ኤሎሄይኑ ይህዋህ ኤኻድ፤ ውአሃባት ኤት ይህዋህ


ኤሎሄይካ ብኮል ልባብካ፥ ውብኮል ናፍሽካ፥ ውብኮል ምኦዴካ።) እስራኤል ሆይ፥
ስማ፤ ኤሎሄያችን ይህዋህ አንድ ይህዋህ ነው፤ አንተም ውደድ ኤሎሄህን ይህዋህን
(አምላክህን እግዚአብሔርን) በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ።

አንዳንድ መሠረታውያን አስተምህሮዎች ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን በተጓዙት


ጉዞ ልክ ይበልጥ የተብራሩ እየሆኑ ይሄዳሉ። ይህ በስነ መለኮት ርምደታዊ ግልጠት
ይባላል። እንዲህ ያለ ግልጠት ከተገለጠባቸው አስተምህሮዎች አንዱ ነገረ ሥላሴ
ነው። ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ይህ የሥላሴ
ማንነት ተገልጦ ይገኛል። የአብና የወልድ ግንኙነትም በብዙ ቦታዎች ተጽፏል፤
ለምሳሌ፥ ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥
ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። ማቴ.
11፥27። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ

28
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር


ነኝ። ማቴ. 28፥19-20። በተጨማሪ ዮሐ. 5፥19-26፤ እና 1ዮሐ. 2፥22-24 መመልከት
ይቻላል።

ከላይ ሁለት ነጥቦችን እንመለከታለን ካልኩት አንዱ እስካሁን ያየነው ነገረ ሥላሴ
ነው። ሁለተኛው ነጥብ፥ ከሥላሴ አካላት በሥጋ የመጣው ወልድ መሆኑ ነው። አብ
አልመጣም፥ መንፈስ ቅዱስ አልመጣም። ወልድ ግን መጥቷል። ስለዚህ መምጣት
1ዮሐ. 4፥2-3 ይህንን ይለናል፤ የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ
ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ
ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤
ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም
እንኳ በዓለም አለ።

በሥጋ መምጣት ማለት ቀድሞ ከነበሩበት ስፍራና ሁኔታ በዚህኛው ሁኔታ፥ ማለትም
በሥጋ ሁኔታ መምጣት ነው። ይህንን መምጣት የማይታመን መንፈስ፥ ይህንን
የማያምን፥ የማይቀበል መንፈስ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ኢየሱስ በሥጋ አልመጣም
የሚል መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም። ከላይ ባየነው በ1ዮሐ. 4፥2-3
ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው ተብሏል።

ይህ የክርስቶስ በሥጋ መምጣት ፈጽሞ፥ ሙሉ በሙሉ ሰውን መሆን ነው። እንደ ሰው


መሆን ሳይሆን ሰው መሆን ነው። ኢየሱስ ቀድሞም የሥላሴ አካል የሆነ አምላክ
ከሆነና ሰው ከሆነ ያ አምላክነት ምን ሆነ? ምንም አልሆነም። ሥጋ በመልበሱ መለኮቱ
ለኛ በመጋረጃ እንደ ተጋረደ ዓይነት ሆነብን ሆነ እንጂ ምንም መለኮት አልተቀነሰም።
ቀድሞ አምላክ ብቻ ሳለ 100% አምላክ እንደሆነው፥ ሰው ሲሆን ያ መለኮት
ቅንጣትም አልተቀነሰም፤ ያው 100% ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አምላክነቱ ቅንጣትም
ታህል ሳይቀነስ ሰውነትን ተላበሰ፤ ሥጋ ሆነ። ሰው ሆነ። ሰው ሲሆንም ጎዶሎ ሰው
ሳይሆን ሙሉ ሰው፤ 100% ሰው ነው የሆነው። እንደ ማናችንም ሰው ነው የሆነው፤
ከኃጢአት በቀር። በዚያች ሥጋ ከሆነባት ቅጽበት ጀምሮም ሰዋምላክ፥ ሰውና አምላክ
በአንድ አካል ሆነ። ይህ በሥነ መለኮት ቴአንትሮፖስ ይሰኛል። ሰውም አምላክም
ሆነ፤ በአንድ አካል። ሰው ሲሆን ከአምላክነቱ ምንም የጎደለው ባህርይ የለም። ሰው
በመሆኑ ግን ፈቃዱን ለአብ አስገዝቶአልና አንዳንዶቹን መለኮታዊ ባህርያት ወይም
ሥልጣናት በነጻነት እንደ መብትና እንደ ባለ ሥልጣን አልተጠቀመባቸውም።
መለኮታዊ ሥልጣንን አለመጠቀም ላለመጠቀም መውደድ እንጂ አለመሆን
አይደለም።

በሥጋው በመጋረጃ እንደ ተጋረደ መሆኑ ያዩት አይሁድ፥ በመካከላቸው


የተመላለሰባቸው ከተሞችና መንደሮች ሰዎች እርሱን ያዩትና ያወቁት እንደ ሰው ብቻ
መሆኑን አድርጎታል። ይህንን ሥጋውን እንደ መጋረጃ መጥራት በአዲስ ኪዳንም

29
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተጻፈ ምስያ ነው፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው


መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ
ድፍረት ስላለን፥ በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥ ከክፉ ሕሊና
ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት
እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤ ዕብ. 10፥19-22።

ኢየሱስ ሰው ሲሆን ሰው ሆነ እንጂ ሰው አልመሰለም። ሰውን መስሎ አልመጣም፤


ሰው ሆኖ መጣ እንጂ። ስለዚህ ሰው የሆነውን ነገር ሁሉ ከኃጢአት በቀር ሆኗል፤
በሰው የሚሆነውም ሆኖበታል። ሰው የሆነው ሁሉ አለው። ኢየሱስ ሰው ሲሆን
ደግሞ ለዓላማ ነው፤ ለአንድ ነገር ዓላማና ለሁለት ነገሮች ክንዋኔ ነው። ዓላማው አብ
እንዲከብር ነው። ግቦቹም፥ ኢየሱስ ሰው ሲሆን ሰው የሆነው፥ ሁለት ነገሮችን
ለመከወን ነው።

አንደኛ፥ እግዚአብሔርን ለመግለጥ፥ ለመተረክ፥ ለማሳየት ነው። እግዚአብሔርን


መግለጥን በተመለከተ ዮሐ. 1፥18 እንዲህ ይላል፤ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው
አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው። ይህ ተረከው የሚል
ቃል፥ ፈታው፥ ገለጠው፥ ከፈተው፥ ፈለቀቀው፥ አሳየው ማለት ነው። ኢየሱስ በሥጋ
መምጣቱ እግዚአብሔርን እንድናይ አድርጎናል። አምላክ ምን እንደሚመስል
ገልጦልናል። ኢየሱስ በሥጋ ባይመጣ እግዚአብሔርን በክርስቶስ በኩል ባወቅነው
እግዚአብሔርነቱ ፈጽሞ አናውቀውም ነበር። አዛኝነቱን፥ አፍቃሪነቱን፥ ደግነቱን፥
ይቅር ባይነቱን በተጨባጭ መረዳት አንችልም ነበር።

ሁለተኛ፥ ኢየሱስ ሰው የሆነበት ምክንያት ምትካዊ ሞታችንን ለመሞት ነው። በሥጋ


የመጣው ሊሞትልን ነው፤ ስለ ሞቱ ራሱ ኢየሱስም ደጋግሞ ተናግሯል። ጥቂት
ጥቅሶች ለማየት፥ ሉቃ. 18፥31-33 አሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ
አላቸው፦ እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው
ሁሉ ይፈጸማል። ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፥ ይዘብቱበትማል ያንገላቱትማል
ይተፉበትማል፤ ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል። ይህ
ከብዙ ጥቅሶች አንዱ ነው። ሉቃስ 22፥19-20 እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም
ሰጣቸውና፦ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት
አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ
በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው። ይላል። ኢየሱስ ለምን በሥጋ መጣ?
ሥጋው ሊቆረስ፥ ደሙ ሊፈስስ። ሊሞት መጣ። ለማን ሊሞት? ለእኛ። ይህ ምትካዊ
ወይም ተውላጣዊ ሞት የምንለው ነው።

ዕብ. 2፥14-15፤ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ
ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ
ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም

30
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

እንዲሁ ተካፈለ። ለምን መጣ? ሊሞት። በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት


እንዲሽር። ሥልጣኑን የሚሽረው በሞት ከሆነ መሞት አለበት፤ ይህ ግልጽ ነው።
ኢየሱስ መሞት ካለበት ደግሞ የሚሞት መሆን አለበት። እግዚአብሔር የሚሞት
አይደለም፤ በባሕርይው አይሞትም። መለኮት አይሞትም፤ ሊሞትም አይችልም።
ኢየሱስ መልአክ ሆኖ ቢመጣ ኖሮም መሞት አይችልም ነበር፤ መላእክትም
አይሞቱም። ስለዚህ የሚሞት ሊሆን በሥጋ መምጣት ነበረበት፤ አለበት፤ ስለዚህም
በሥጋ መጣ፤ ቃል ሥጋ ሆነ። ሰው ይሞታል። ስለዚህ ኢየሱስ ሰው ሆነ። ለምን?
ሊሞት። ለማን? ለእኛ።

31
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

‘ሰውየው ብቻ ዒሳ’ እና ሰው የሆነው ኢየሱስ


ሳዲቅ መሐመድ፥ ‘ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን የምናውቅባቸው መንገዶች’ ብሎ
የዘረዘራቸው አሥር ነጥቦች አሉ። አሥሩም ነጥቦች ሰው መሆኑን ያመለክታሉ፤
በትክክል ያመለክታሉ። ነገር ግን፥ ሰው መሆኑን እንጂ ፍጡር መሆኑን አይደለም።
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አለመሆኑን ቀደም ሲል ተመልክተናል።
ቀጥሎ የምንመለከተው ደግሞ፥ ‘ኢየሱስ ሰው ሆነ እንጂ ሰው ብቻ አይደለም’
የሚለውን አሳብ ነው።

አሥሩንም ነጥቦች በአንድ ላይ ደፍጥጦ መመለስ ይቻላል። ምክንያቱም አሥሩም ሰው


መሆኑን ይናገራሉ። ኢየሱስ ደግሞ በእርግጥም ሰው ነው። ሰው ሆኖ የመጣ ጌታ
ነው። አሥሩንም አንድ ላይ ጨፍልቆ አንድ ረጅም ምላሽ ከማቅረብ፥ በእያንዳንዱ
ነጥብ ትንሽ ትንሽ ምላሽ መስጠት የተሻለ ይሆናል።

1. ጾታ ያለው ወንድ መሆኑ።

ከአሥሩ ነጥቦች የመጀመሪያው፥ ጾታ ያለው ወንድ መሆኑ ነው። ወንድ መሆኑ፥


የወንድ ጾታዊ ብልት መያዙ ዒሳን ሰው ያሰኘዋል ብሎአል ሳዲቅ። መጀመሪያ ስለ
መላእክት፥ ሚካኤል ወይም ገብርኤል ብሏልና ስለነሱ ጥቂት ልበል። መላእክት
አያገቡም አይጋቡምም፤ አይወልዱም አይዋለዱምም፤ ስለዚህ የግብረ ሥጋ ብልት
ያላቸው አይመስሉም። አይመስሉም ያልኩት በግልጽ የተጻፈ ነገር ስለሌለ ነው።
ከሉቃ. 20፥35 ይህንን መረዳት እንችላለን፤ ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ
የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም፥ እንደ መላእክት ናቸውና። ይላል።
ሆኖም ግን መላእክት ጾታቢስ አይደሉም፤ በወንድ ጾታ ይጠቀሳሉ።

ይህ ጾታዊ አጠራር፥ ግዑዝ ባለቤት ባላቸው ቋንቋዎችም እንኳ ሳይቀር የሚደረግ


ነው፤ በወንድ ጾታ መጠራታቸው እውነት ነው። በአማርኛ ተባእት እና አንስት ባለቤት
ብቻ ነው ያለን። በአንዳንድ ሌሎች ቋንቋዎች፥ ለምሳሌ፥ በእንግሊዝኛ ወይም አዲስ
ኪዳን በተጻፈበት በግሪክ ሦስተኛ ባለቤት አለ፤ ግዑዝ ባለቤት ይባላል። ለግዑዛኑ
ባለቤቶች ጾታ ይሰጣቸው እንጂ ለሰዋሰዋዊ አነጋገር ካልሆነ በቀር ጾታ ግዑዝ
የለውም። ጾታ ሁለት ብቻ ነው። ስለዚህ ግዑዙ ባለቤት ከሁለቱ አንድ ጾታ
ይወስዳል። ይህ ለግዑዛን ብቻ ሳይሆን ለሕያዋንም ይሆናል። እግዚአብሔርንም አንተ
እንላለን። ሳዲቅም ቁርኣንም አላህን በአንተ ይጠራዋል፤ ጅብራኢልንም በአንተ፥
ሸይጣንንም በአንተ ይጠራቸዋል። እንጂ አንቺ አይላቸውም። ስለዚህ አንተ የሚባል

32
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሁሉ ወይም፥ ‘አንተ’ የሚያሰኝ የማንነት መለያ ያለው አካል ሁሉ ፍጡር ነው ማለት


አይደለም።

‘ኢየሱስ ጾታ ያለው መሆኑ ሰው መሆኑ አይደለም? ሰው ከሆነ ፍጡር መሆኑ


አይደለም?’ የሚል ነው የሳዲቅ ሙግት። ሰው መሆኑን በደንብ ይጠቁማል እንጂ!
መጠቆም ብቻ ሳይሆን ያረጋግጣልም። ኢየሱስ ሰው ሆኖ እንደመጣ ከተረዳን ሰው
ማለት ሰው ነው። አንድ ሰው ሰው ሲሆን ከተፈጠሩት ሁለት ጾታዎች አንዱን ሊሆን
ግድ ነው። ኢየሱስ ሲመጣ ወንድ ሆኖ መጣ። ወንድ ባይሆን ሴት ይሆን ነበር። ሴት
ሆኖ ቢመጣ ኖሮ ሳዲቅና እርሱን የመሰሉቱ እርግጠኛ ነኝ፥ ከዚህ የከፋ ተኩስ ይከፍቱ
ነበር። ሰው ሰው ከሆነ ከሁለት አንዱን፥ ወይ ወንድ ወይ ሴት ሊሆን ግድ ነው። ሌላ
ሦስተኛ ጾታ የለም። በሁለቱ መካከል ያለ ጾታም መኖሩ አይታወቅም። ስለዚህ
ኢየሱስ በጾታ ወንድ ነው።

‘ጾታ ወይም የወንድ ብልት ምን ይሠራለታል? እግዚአብሔር አይሸናም’ ብሏል ሳዲቅ።


ይህም ትክክል ነው። እግዚአብሔር አይሸናም። ኢየሱስ ግን በአምላክነት ላይ ሰው
ሆኗል፤ ሰው ደግሞ ይሸናል። ሌላውንም ሰው ሁሉ የሆነውን ሁሉ ይሆናል፤ ሰው
የሚያደርገውንም ሁሉ ነገር ያደርጋል። ኢየሱስ ሰው ሲሆን ከኃጢአት በቀር እንደኛ
የሆነ ሰው ነው። ያም በመለኮቱ ላይ የሆነው ማንነት ነው። ያ ሰው እኛ የሆንነውንና
የምናደርገውን ሁሉ ማድረግ የሚችል ነው። እንዳልኩት ከኃጢአት በቀር።

ኢየሱስ ለምን ወንድ ሆነ? ወንድ የሆነው በዔድን ገነት የተሰጠው ተስፋ ይፈጸም
ዘንድ ነው። ያ የዘፍ. 3፥15 ተስፋ መቅድመ ወንጌል ይባላል። ያ ተስፋ ሲሰጥ በተባእት
ወይም በወንድ ጾታ ነው የተነገረው፤ በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም
መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን
ትቀጠቅጣለህ። እርሷ ሳይሆን እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል ነው የተባለውና ‘እርሱ’ ሆኖ
ነው የመጣው። ሰኮናውን እንጂ ሰኮናዋን አልተባለም። ይቀጠቅጣል እንጂ
ትቀጠቅጣለች አልተባለም። ያ የተስፋ ቃል የተፈጸመበትን ሁኔታ ጳውሎስ በገላ. 4፥4
ሲናገር እንዲህ አለ፤ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት
የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ የተወለደውን እንጂ
የተወለደችውን አላለም፤ የተወለደውን ልጁን ላከ።

ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ደግሞ በኢሳይያስ ይህንን ተስፋ በትንቢት


ሲናገር፥ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው
ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ
ተብሎ ይጠራል። ኢሳ. 6፥9። ‘ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል’ አለ። ስለዚህ የተወለደው
ወንድ ነው። የወንድ ጾታ ያለው ሰው።

33
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በጾታ ወንድ መሆኑ የመሥዋዕትነቱም አመልካች ነው። በብሉይ ኪዳን ለኃጢአት


የሚቀርበው መሥዋዕት ተባት ጠቦት ወይም በግ ነው፤ ዘኁ. 7 እንዲሁም 29 ማየት
ይቻላል። ጌታ በሥጋ የመጣው ኃጢአታችንን ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን የበግ
መሥዋዕት ሊሸከምልንና በምትካችን ሊሞት ነው፤ ልክ እንደ ይስሐቅ ምትክ፤
አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ
ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፥ በልጁም ፋንታ መሥዋዕት
አድርጎ ሠዋው። ዘፍ. 22፥13። በጉንም ነው የሚለው እንጂ በጊቱን ወይም ጠቦቲቱን
አይልም። ወይም በኢሳይያስ እንደተነገረው ትንቢት፤ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም
አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥
እንዲሁ አፉን አልከፈተም። ኢሳ. 53፥7። እንደምትነዳ ጠቦት ወይም ዝም እንደምትል
በግ አልተባለም። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ የተናገረውም ይህንን ነበር።
ዮሐ. 1፥29፤ በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ
የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። ‘የምታስወግድ በጊት’ አላለም።
ስለዚህ ኢየሱስ ወንድ መሆኑ ሰው የመሆኑ ማንነት እንጂ ሰው ብቻ፥ ወይም ፍጥረት
ብቻ የመሆኑ ምልክት አይደለም።

‘አምላክ ሰው የሆነ ጊዜ አምላክ የት ነበር?’ ብሎ ሳዲቅ የጠየቀው ጥያቄ ቀደም ሲል


እንዳልኩት የፌዝ እና የስላቅ፥ እንዲሁም የነገረ ሥላሴ መረዳት ጉድለት ነው።
‘ኢየሱስ ሰው የሆነ ጊዜ አምላክ የት ነበር? የሞተ ጊዜ ታዲያ አምላክ የት ነበር?’
የሚሉና ይህን የመሰሉት ጥያቄዎች የእግዚአብሔርን ማንነት ካለመረዳት የሚመነጩ
ጥያቄዎች ናቸው። ኢየሱስ ሰው ሲሆን ወይም በሥጋ ሲመጣ፥ አምላክነቱን አልተወም
ወይም ከአምላክነት ወደ ሰውነት አልተለወጠም። ወይም ቀድሞ እግዚአብሔር
የነበረው እግዚአብሔር መሆኑ ቀረና አሁን ሰው አልሆነም። ሰው ከሆነ በኋላ ደግሞ
ሲሞት ያ ሰው የሆነው አምላክም ሲሞት አምላክ ሞተና ምድርና ሰማይ ያለ አምላክ
ቀሩ ማለት አይደለም። ደግሞም ኢየሱስ ሲሞት አምላክ የት ደረሰ? የት ገባ? እሱ
ሲሞት ምድርን ማን ያዛት? ማን ጠበቃት? እንዴት አልተደመሰሰችም? እንዴት
ምሕዋሯን ስታ እንጦርጦስ አልወደቀችም? ብሎ መጠየቅ የሥላሴን ማንነት
አለማጤንና የአለመረዳት ጥያቄ ነው።

ሳዲቅ በስሕተትና በድግግም፥ ‘አምላክ ሰው መስሎ’ የሚል ሐረግ ተጠቅሞአል።


ይህንን ሲል ለማሳት አስልቶ ነው እንጂ፥ ጌታ በሥጋ ሲመጣ ሰው መስሎ
አልመጣም። በሰው ተመስሎም አልመጣም። ሰው ሆኖ ነው የመጣው። መስሎ መጣ
የሚል ትምህርት ያላቸው አሉ። ይህ ዶኬሲስ ከሚባል ቃል የመነጨ ዶሴቲዝም
የሚባል ኑፋቄ ነው። ሳዲቅ ግን፥ ‘መስሎ መጣ’ ሲል ያንን ማለቱ ሳይሆን እንዲያው
ለማሳት ብሎ የተናገረው ነው።

34
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

2. ‘ዒሳ የአምላክነት ባህርይ አለው ወይ?’

የዚህ መጽሐፍ ገዢ አሳብ፥ ‘የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም’ የሚል


ነው። አንድ አለመሆናቸውን የሚያሳየው እውነት ሳዲቅ በቪድዮ ትምህርቱ አጥብቆ
ሊያስረዳ እንደሞከረው ዒሳ የአምላክነት ባሕርይ ከቶም የለውም። የቁርኣኑ ዒሳ
አምላክ አይደለም። ያ ዒሳ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ዒሳ አምላክ ላለመሆኑ ያወሳቸው ነጥቦች አሉ። አንደኛው፥ ‘ዒሳ የሚጠፋ በመሆኑ


ሰው ብቻ ነው።’ የሚል ነው። እርሱም እናቱ መርየምም ይጠፋሉ ይላል። በነገራችን
ላይ፥ እናቱ የሚላት መርየም የዒምራን ልጅ ማርያም ናት እንጂ የዮሴፍ እጮኛ
ማርያም አይደለችም። ስለዚህ የቁርኣኑ ዒሳ ብቻ ሳይሆን እናቱ ተብላ የተጠቀሰችው
መርየምም የኢየሱስ እናት ማርያም አይደለችም። ሞክሼ ናቸው ሊባል ይቻላል፤
መከራከሪያውም ሞክሼ መሆናቸው ነው፤ ነገር ግን ድኩም መከራከሪያ ነው። የቁርኣኗ
መርየም የዒምራን ልጅ ናት። ዒምራን የሙሴና የአሮን እና የእኅታቸው የማርያም
አባት ነው። በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንበረም የተሰኘው በዕብራይስጥ ዓምራም
የተባለው ነው። የዒምራን ልጅ ማርያም እና የአዲስ ኪዳኗ የኢየሱስ እናት ማርያም
ተሳክረው ቀርበዋል። ቁርኣን ይህንንም ያሳከረ መጽሐፍ ነው። ቁርኣን አንዳንድ
ታሪኮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እየቦጨቀ ይወስድና በተሳሳተ መረዳት ያቀርባል።
ስለዚህኛው መሳከር ራሱ ሳዲቅም በሌላ ቪዮ ያለው ነገር አለ። ይህንን የተሳከረ ጉዳይ
በሞክሼነት አጣብቆ ነው ለማስረዳት የሞከረው። ይህንን ስሕተት ለመደጋገፍ፥ ‘የለም
ሐሩን ወንድሟ የሙሴ ወንድም ሐሩን አይደለም፤ ሰዎች ደግሞ በቀደሙ የእምነት
ምሳሌዎች መጠራት የተለመደ ስለሆነ ነው እንጂ፤’ ይላሉ። ስሕተትን ለመሸፈን
የተደረገ ሙከራ መሆኑን እናስተውል። ቁርኣን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተሳክረው የተኮረጁ
ብዙ ነገሮች ያሉበትና ይህ የማርያም የዒምራን ልጅነት የተሳከረ ኩረጃ መሆኑን
ማስተዋል አለብን።

ዒሳ የአምላክነት ማንነት የሌለውና የሚጠፋ መሆኑ ሰው ብቻ መሆኑን ያሳያል ብሎ


ይህን አሳብ ሳዲቅ ሲደመድም፥ የሚጠፋ ነገር አምላክ ሊሆን እንደማይችል
በማብራራት፥ ‘አላህ ብቻ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ’ መሆኑን በመናገር ነው። የአምላክነት
ማረጋገጫ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ መሆን ከሆነ፥ ኢየሱስ አምላክ ለመሆን ይህንን
መሆን አለበት ማለት ነው። ፊት ያለና ኋላ ቀሪነት የአምላክ ባህርይ መሆኑን ቁርኣን
እንደሚያስተምር ሳዲቅ ተናግሯል። በእርግጥም ቁርኣንም ይህንን ይላል፤ ሱረቱል
ሐዲድ (57) ቁጥር 3 እንዲህ ይላል።

57፥3 እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ፣ ግልፅም ስውርም ነው፤ እርሱም ነገርን ሁሉ ዐዋቂ
ነው።

35
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መልካም፤ በዚህ እንስማማ። መጽሐፍ ቅዱስም ፊተኛና ኋለኛው እግዚአብሔር ብቻ


መሆኑን ይመሰክራል። በኢሳ. 41፥4 ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት
የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር፥ ፊተኛው በኋለኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ።
ይላል። እዚያው ኢሳ. 48፥12 ደግሞ፥ ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥
ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ። ይላል። ልክ ነው ፊተኛነትና
ኋለኛነት የመለኮት ባህርይ ነው። የአምላክነት ማረጋገጫ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ መሆን
ከሆነ፥ ፊተኛና ኋለኛ መሆን ከሆነ ኢየሱስ አምላክ ለመሆን ይህንን መሆን አለበት
ማለት ነው። ከሆነ ደግሞ ሳዲቅ ይህንን ሊቀበል የተገባው መሆኑ እሙን ነው። ሦስት
ጥቅሶች እንይ፤

ራእ. 1፥17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም


ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ። ይህን
ያለው ጌታ ክርስቶስ ነው። ይህን የተናገረውም፥ ዮሐንስ ጌታን ባየው ጊዜ ነው።

ራእ. 2፥8 በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ።


ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦ ይህ
ፊተኛውና መጨረሻው ሌላ ነው እንዳንል፥ እርሱ ራሱ መሆኑን እንዳንጠራጠር፥ ‘ሞቶ
የነበረው’ ብሎናል። ሞቶ የነበረ ፊተኛና መጨረሻ ሌላ የለም፤ ከኢየሱስ በቀር።

ራእ. 22፥13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ


ነኝ። ይህንንም ያለው ይህ ኢየሱስ ነው።

ይህ ጥቅስ ሲጠቀስ፥ ‘ይህ እኮ ዮሐንስ የተናገረው ነው።’ ይላሉ። ይህ ዮሐንስ የጻፈው


እንጂ የተናገረው አይደለም። ይህንን ያለው፥ ‘እኔ ነኝ’ እያለ ራሱ ኢየሱስ ነው። ይህንን
ካለ ወይ ነው፤ ወይም ውሸታም ነውና ጭራሽ ነቢይም አይደለም ብለን
እንደመድማለን እንጂ ሌላ ማዕረግ ልንሰጠው የተገባ አይደለም። የአምላክነት
ማረጋገጫ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ መሆን ከሆነ፥ ፊተኛና ኋለኛ፥ አልፋና ዖሜጋ መሆን
ከሆነ፥ ስሙ የተመሰገነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታና አምላክ ነው።

ከሥላሴ ውስጥ በአካል የመጣው፥ በሰውነት የተገለጠው አንዱ ብቻ፥ ወልድ፥


ወይም ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ እንዳየነው፥ ወልድ ወይም ልጅ በሥጋ ሲመጣ ተወለደ
እንጂ አልተፈጠረም። ኅልውናውም ሲወለድ አልጀመረም። እርሱ ዘላለማዊ አምላክ
ነውና። ስለዚህ ነው ፊተኛና ኋለኛ፥ መጀመሪያና መጨረሻ የሆነው። በነገራችን ላይ
ቁርኣን ኢየሱስ ተወለደ እንጂ ተፈጠረ ብሎ አያስተምርም። ስለዚህ የተፈጠረ ብሎ
ሲናገር፥ ይህ ራሱ ፈጠራ መሆኑን ማወቅ አለብን።

36
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ቀደም ባሉት ገጾች እንዳየነው ሳዲቅ ሰው በተለያየ መንገዶች እንደሚፈጠር


(ያለወንድና ያለሴት፥ ከወንድ ብቻ፥ ከወንድና ከሴት፥ ከሴት ብቻ) ያለው ልክ እንደ
ርችት ያለ የሽፋን ተኩስ ሆኖ በአራት አቅጣጫ ተደናግረን፥ ኢየሱስም ከአራቱ
መንገዶች በአንዱ ውስጥ የሚወድቅ ስለሆነ ኢየሱስ ፍጡር ነው እንድንል ነው።
ኢየሱስ ፍጡር ከሆነ ፊተኛና ኋለኛ፥ መጀመሪያና መጨረሻ መሆን አይችልም።ዒሳ
መወለዱን እንጂ አለመፈጠሩን ቁርኣንም ይመሰክራል። ለምሳሌ፥ 19፥33ን ኋላ ራሱ
ሳዲቅ ይጠቅሰዋል። 4፥171 የሚለው ነው።

እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን


እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት
(የሁን) ቃሉም ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ
(አማልክት) ሦስት ናቸው አትበሉም፤ ተከልከሉ ለናንተ የተሻለ ይሆናልና፤ አላህ አንድ
አምላክ ብቻ ነው። ለርሱ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው። በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ
የርሱ ነው። መመኪያም በአላህ በቃ።

ወደ መርያም የጣላት ቃሉ እና መንፈስ ብቻ ነው። ሁለቱንም ቃላት እናስተውል፤


ቃልም መንፈስም። ዒሳ ቃል ከሆነ ወደ ማርያም ሳይጣል በፊት ነበረ ማለት ነው፤
አይደል? ቃል ሆኖ ነበረ ማለት ነው። ለዚህም ነው ኢየሱስ የአላህ መንፈስ እና የአላህ
ቃል (ሩሃላህ እና ካሊማቱላህ) የሚባለው። መንፈስ ከሆነ፥ ቃል ከሆነ ደግሞ
ዘላለማዊ ነው ማለት አይደል? ነው። የአላህ ቃል ዘላለማዊ ነው ነው የሚሉት።
እንዲያውም ቁርኣንም፥ ቃሉ ስለሆነ፥ ዘላለማዊ ነው ነው የሚሉት። ሱራ 43፥3 ግን
ቁርኣን ዘላለማዊ አለመሆኑን ይመሰክራል። እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን
አደረግነው። ይላል። አደረግነው ከተባለ የተደረገ ነው፤ ከተደረገ ደግሞ ዘላለማዊ
መሆን አይችልም። ሆኖም ቃሉ ዘላለማዊ መሆኑን አጽንተው ይናገራሉ። በእውነቱ
ቃሉ ያልተፈጠረ ዘላለማዊ ከሆነ ከአላህ ሌላ ዘላለማዊ አካል አለ ማለት ነው። ቁርኣን
ዘላለማዊ ከሆነ ሁለት ዘላለማውያን አሉ ማለት ነው።

ታዲያ ስለ ኢየሱስ፥ በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ሲባል


ሳዲቅ፥ ‘እኛ እንዲህ አንልም’ ያለው ለምንድር ነው? ‘እዚህ ያለው እኮ ይሁን የሚል
ቃሉ ነው’ ሊል ይችላል። ግን ‘(የሁን) ቃሉ’ በሚለው ውስጥ ‘የሁን’ የሚለው በቅንፍ
ውስጥ ነው የሚገኘው። ያ ማለት የተጨመረ ቃል ነው ማለት ነው። እንዲህ ሲባሉ፥
‘የለም በዐረብኛው እንደዚያ ነው የሚለው’ ይሉናል። ታዲያ ለምን ይህኛው በቅንፍ
ከሚሆን፥ የተፈጠረው፥ ይሁን የተባለው እያሉ ከቅንፍ አውጥተው አያስቀምጡትም?
እንዲህ የሚያደርጉት ደግሞ በቋንቋዎች ሁሉ ነው። ከእንግሊዝኛ ትርጉሞች አንዱ
የSahih International ትርጉም ይህንኑ ጥቅስ የሚለውን እንይ፤

(The Messiah, Jesus, the son of Mary, was but a messenger of Allah and
His word which He directed to Mary and a soul [created at a command]

37
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

from Him.) ይለዋል።7 ይህኛው ደግሞ የሁን ቃሉ የሚለውን ከቅንፍ ውጪ እንደ


ቀጥተኛ ቃል አድርጎ፥ ግን [created at a command] ‘በትእዛዙ ተፈጥሮአል’ የሚል
በቅንፍ ጨምሮበታል። ይህ ሙሉ በሙሉ የተጨመረ ቃል ነውና ስለዚህ ነው በቅንፍ
ውስጥ የተቀመጠው። በቅንፍና በግርጌ ማስታወሻ የሚጨመሩ በጣም የበዙና እርስ
በርስ የሚጋጩ ነገሮች አሉ። አንዱ፥ ለምሳሌ፥ ይህ በቅንፍ የተቀመጠው ‘በትእዛዝ
የተፈጠረ’ created at a command የሚለው ነው። ቁርኣኑ ያንን ያለ ቢሆን ኖሮ
በትእዛዙ የተፈጠረ ተብሎ በሁሉም ቋንቋዎችና በአማርኛውም ጭምር ለምን
አልተጻፈም ነበር?

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አለመፈጠሩና ፈጣሪ መሆኑ፥ ደግሞም በሥጋ የመጣ፥


የተወለደና ሥጋ የሆነ መሆኑ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ነው። ‘ልጅ ያለው
ከመሆን የጠራ ነው’ የሚለውን ጥቅስ ባለፈው አይተን ነበር። ኢየሱስ ወልድ ወይም
ልጅ ነው ሲባል የአብ የሥጋ ልጅ ማለት ሳይሆን፥ ይህ ልጅነት የግንኙነት ወይም
የባህርይ መግለጫና መገለጫ ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔርና የማርያም ሩካቤ ሥጋ
ውጤት ሳይሆን ራሱ ቀድሞም የሥላሴ አንድ አካል የሆነው ቃል ሥጋ የሆነበት
ሁኔታ ነው። ኢስላም ክርስቲያኖችን የሚረዳበት የተሳሳተ አረዳድ፥ ቀደም ሲል፥
‘የመረዳት ጎዶሎነት’ ያልኩት ጉዳይ ነው። ኢየሱስ ልጅ ነው ሲባል የግብረ ሥጋ
ግንኙነት ውጤት አድርገን እንደምናስብ፥ እንደምንቀበልና እንደምናስተምር ነው
ተደርጎ እንዲታሰብ ነው የተሠራው። ሙስሊሞች በአማካዩ የሚያስቡትም እንደዚያ
ነው። ነገር ግን፥ ቃል ሥጋ መሆኑ በሥጋ መምጣቱ ነው። ኢየሱስ ከዚያ በፊት፥
ከመምጣቱ በፊት ዘላለማዊ ማንነት ያለው እግዚአብሔር ነው። የሥላሴ አንድ አካል
ነው። ሥጋ ሆነ እንጂ ሥጋ አልተደረገም። ተወለደ እንጂ አልተፈጠረም። ስለዚህ ዒሳ
እንደዚያ ሊሆን ይችላል እንጂ፥ ኢየሱስ፥ ‘ሁን!’ ተብሎ የተፈጠረ ፍጡር አይደለም።
ስለዚህ ነው የቁርኣኑ ዒሳ እና የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ከቶውኑም አንድ ያልሆኑት።

ልጅነት ወይም ወልድነት የግንኙነት ወይም የባህርይ መግለጫ ነው ስል፥ ራሳችንን


በሥጋ ያልተወለድንበት የዚያ ነገር ልጅ አድርገን እንደምናሳየው ማለት ነው። በሥጋ
ሳንወለድ፥ ከግንኙነት የተነሣ የዚያ ልጅ ተብለን እንጠራለን። ለምሳሌ፥ እኔ የአባቴ
የመንግሥቱ ልጅ ነኝ፤ ደግሞ የክርስትና አባቴ የመምሬ ጌቱ ልጅ ነኝ፤ ደግሞ
የተወለድኩባት የለኩ ልጅ እባላለሁ፤ የኢትዮጵያ ልጅም ነኝ፤ የቃለ ሕይወት ልጅም
እባላለሁ፤ የእግዚአብሔር ልጅ ደግሞ ነኝ። ይህ አንድ ምሳሌ ነው። ከመጀመሪያው፥
ከአባቴ ብቻ ነው በአካል ወይም በሥጋ ልጅነቴ እንጂ ከሌሎቹ ከሁሉም በሥጋ
አልተወለድኩም። ከሌሎቹ ጋር ያለኝ የአካል ሳይሆን የግንኙነት ልጅነት ነው።

7
Quran: English Translation: Saheeh International; http://tanzil.net/
Pdf: http://quranpdf.net/

38
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አንድ መሪ ወይም ሰልፈኛ፥ ‘የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ’ ሲባል ምንም አካላዊ


ልጅነት የለም። ግንኙነት እንጂ። በአዲስ ኪዳን ዮሐንስ እና ያዕቆብ የነጎድጓድ ልጆች
ተብለዋል። ምናልባት በባህርያቸው እንደ ነጎድጓድ ያሉ ስለሆኑ ይሆናል፤ እንጂ
በነጎድጓድ እና በእናታቸው መካከል ሩካቤ ተፈጽሞ አልተወለዱም። ወይም መጥምቁ
ዮሐንስ፥ ‘እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን
አመለከታችሁ?’ ሲል እውነት የእፉኝት የሥጋ ልጆች ሆነው አይደለም። በአንዳንድ
ቋንቋዎች የአካል ልጅነት እና የግንኙነት ልጅነት የተለያዩ ቃላት አሏቸው።
በዕብራይስጥ ለምሳሌ፥ ቤን እና ያላድ የሚባሉ ቃላት አሉ። በአማርኛ ልጅን
ለሁለቱም እንጠቀማለን። በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ለኢየሱስ ብዙ ጊዜ ወልድ
የሚለውን ቃል ብንጠቀምም፥ በግዕዝ ወልድ የሚለው ቃል ለኢየሱስ እንደሆነው
ሁሉ ለማንም የሚሆን ቃልም ነው።

ኢየሱስ የአብ ልጅ ሲባል ግን ከዘላለምም የአብ ልጅ ነውና የግንኙነት መግለጫ ነው።


ዮሐ. 17፥5 እና 24፤ ዕብ. 1፥2 እና 8፤ 1ዮሐ. 4፥9-14፤ 5፥9-20። እኛ የእግዚአብሔር
ልጆች የሆንንበት ልጅነት አለ፤ ኢየሱስ ግን ብቸኛው የአብ ልጅ ነው። ኢየሱስ የአብ
የአካል ወይም የሥጋ ልጅ አይደለም። የአካል ወይም የሥጋ ልጅ ከሆነ፥ ያንን
እስከሆነበት ጊዜ ድረስ ያልኖረበት ዘመን ሊኖር ነው። ይህ የመረዳት ጎዶሎነት ነው።
ከዚህ የተነሣ ሳዲቅ እና ሌሎችም፥ ‘ኢየሱስ ሰው በነበረ ጊዜ አምላክ የት ነበረ ታዲያ?
ሲሞትስ አምላክ የት ገባ? ሲያንቀላፋ ዓለምን ማን ነበር የያዛት? እንዴት ወድቃ
አልተሰበረችም?’ ብለው የሚጠይቁት። ይህ የኢስላም ተውሂድ ወይም ነጠላ አንድነት
የሚፈጥረው የመረዳት ጎዶሎነት ነው። ሥላሴን ካለመረዳት ወይም ካለመቀበል
ወይም ከሁለቱም የሚመጣ የእውቀት መጉደል እና የመለኮት ማጉደል ነው።
የመለኮት ማጉደል ስል፥ ከማንነቱ መቀነስ ነው። እነርሱ እኛን በአምላክ ላይ
ጨመራችሁ፥ አጋራችሁ ስለዚህ ከፈራችሁ፥ ኩፋር ሆናችሁ እንደሚሉት ሁሉ
በተቃራኒው እነርሱ ደግሞ ከአምላክ ማንነት ማጉደላቸው ነው። እግዚአብሔር ሥላሴ
ከሆነና፥ ‘የለም አይደለም፤ ነጠላ አንድ (ወይም ሞናድ) ነው እንጂ!’ ካሉ ይህ ማጉደል
ነው። እኛን ጨመራችሁ ባሉት ክስ ራሳቸውን እየከሰሱ ነው። በማጉደል ክስ።

3. ዒሳ ተመጋቢና አንቀላፊ ስለሆነ ሰው ብቻ ነው።

ሦስተኛው ዒሳ አምላክ ላለመሆኑ ተብሎ የቀረበው ‘ማስረጃ’፥ ተመጋቢ መሆኑ፥


ምግብ የሚበላ መሆኑ ነው። ከዚህ ጋር የሚጨፈለቀው ሌላው የሳዲቅ መሐመድ
ነጥብ 11ኛው ነጥቡ አድርጎ ያቀረበው፥ የሚተኛ፥ የሚያንቀላፋ መሆኑ ነው። ሁለቱም
ነጥቦች ስለሚቀራረቡና የሰውነቱ ምስክሮች ስለሆኑ አንድ ላይ 3ኛ ሙግቱ አድርጌ
ላንሣቸው።

39
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም። የሚለውን ዋናውን ነጥቤን


አንርሳው። የቁርኣኑ ዒሳ የተፈጠረና የሚጠፋ ፍጡር ብቻ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱሱ
ኢየሱስ ግን አምላክ፥ ምንም ያልጎደለው አምላክ፥ እንዲሁም ሰው፥ ምንም
ያልጎደለው ሰው፥ ሁለቱም በአንድ አካል ነው። እንከን የሌለው፥ ምንም ያልጎደለው
ሙሉ ሰው ነው። በዚያው ቅጽበት ምንም ያልጎደለው ሙሉ አምላክ ነው።

ሳዲቅ ስለ ኢየሱስ ሲናገር፥ ‘ይበላ ይጠጣ እንደነበር በመግለጽ አምላክ አለመሆኑን


አስተማረን’ አለ። አምላክ አይበላም፤ ኢየሱስ ይበላ ነበር፤ ስለዚህ አምላክ አይደለም።
ሎጂኩ ይህ ነው። ኢየሱስ ይበላና ይጠጣ የነበረው አምላክ ስላልሆነ ሳይሆን ሰው
ስለሆነ ነው። ይህ ሰው መሆን ወይም በሥጋ መምጣት በዚህ መጽሐፍ እንደ አታሞ
ደጋግሜ የምመታው፥ የምደልቀው ስለሆነ ሊያሰለች ይችላል። ምክንያቱም፥ በኢየሱስ
ላይ የቀረበውን ስሑት አስተምህሮ ዋና ነጥቡ አድርገው አንግተው የተነሡት ጥቂት
ወይም ብዙ ሙስሊሞች ሳይሆኑ ይህ የራሱ የቁርኣን ትምህርትም ነው። ሳዲቅ ከከዚህ
ብዙዎች አንዱ ነው። ‘ኢየሱስ ሰው ብቻ፥ ፍጡር ብቻ ነው’ የሚለው ተደጋግሞ
ስለሚወሳ፥ ስለ ኢየሱስ ስንካፈል እኔም ሰው ብቻ አለመሆኑን እደጋግመዋለሁ።
ልዩነታችን ግን ሳዲቅ፥ ‘ሰው ብቻ፥ ፍጡር ብቻ ነው’ ሲል፥ የኔ ምላሽ፥ ‘በእርግጥም
ሰው ነው፤ ኢየሱስ በሥጋ የመጣ አምላክ ነው፤ ሥጋ የሆነ ቃል ነው፤ በሥጋ የተገለጠ
ወይም ሰው የሆነ አምላክ ነው፤ ስለሆነም ሰው የሆነውን ሁሉ ሆኗል፤ ሰው
ያደረገውንም አድርጓል፤ ከኃጢአት በቀር’ የሚል ነው።

ምግብ መብላትና ውኃ መጠጣት አንዱ የሰው መሆን ባህርይ ነው። ምግብ መብላቱን
ሳዲቅ እንዳለው ቁርኣኑ ብቻ ሳይሆን ወንጌላቱም አሳምረው ገልጠውልናል፤
እንዲያውም፥ ማቴ. 11፥9 በላተኛ እንዳሉት በመጥቀስ እንዲህ ይላል፤ የሰው ልጅ
እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና
የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች። እግዚአብሔር ምግብ
መመገብ አያስፈልገውም። እውነት ነው፤ አያስፈልገውም። ኢየሱስ ግን ሰው በመሆኑ፥
ሰው ደግሞ ምግብ ስለሚመገብ፥ ምግብ ተመግቧል። ምግብ መብላቱ፥ ተመጋቢ
መሆኑ አምላክ አለመሆኑን ሳይሆን ሰው መሆኑን ያሳያል። መተኛቱም እንዲሁ።

ሳዲቅ እና ሌሎች ሙስሊሞች ይህንን የኢየሱስን መተኛት በፌዝ ይጠቅሱታል። ሳዲቅ


ይህንን ሲያስተምር ከእጁ የውሃ ጠርሙስ እንዲወድቅ በማድረግ ዓለም ኢየሱስ
ሲያንቀላፋ እንዴት እንደዚያ ወድቃ እንዳልተፈረካከሰች ለማስረዳት መሆኑ ነው።
በተለይም ኢየሱስ በታንኳ ሲሄዱ አንቀላፋ የሚለውን (ማቴ. 8፤ ማር. 4፤ ሉቃ. 8
የተጻፈውን) በመጥቀስ፥ ‘እግዚአብሔር ሲተኛና ሲያንቀላፋ ዓለሙን ማን ይይዘዋል?’
ብለው የሚጠይቁት ጥያቄ፥ የሥላሴን ምንነትና የኢየሱስን ማንነት የመረዳት ጎዶሎነት
ነው። በኢስላም መረዳት ኢየሱስ በሥጋ ሲመጣ የእግዚአብሔር ነጠላ አንድነት
(ቀደም ሲል ሞናድ ወይም ሞናዲዝም ብለን የተመለከትነው) አንዱ አምላክ ከአንዱ
ማንነት ወደ ሁለተኛው ማንነት እንደተለወጠ በስሕተት በመረዳት ነው።

40
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ነገር ግን፥ አንዱ ነጠላ ማንነት ወይም ሞናድ ወደ ሌላው አልተለወጠም። አብ ወደ


ወልድ፥ ወልድ ወደ መንፈስ ቅዱስ አልተለወጠም። ይህ የተሳሳተ መረዳት ወይም
የመረዳት ጎዶሎነት ነው። እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ሲወለድ ኢየሱስን ሆነ ብለን
እንደምናምን መታሱቡ ስሕተት ነው። የቁርኣኑን የተሳሳተ ‘ሥላሴ’ (እግዚአብሔር፥
ኢየሱስ እና ማርያም የሚሉትን) እንደምናምንና እንደምንቀበል ቢታሰብ እንኳ ኢየሱስ
ሲተኛ እግዚአብሔር እንዳልተኛ መረዳት ከባድ አልነበረም። እግዚአብሔር ሥላሴ
ከሆነና ከዚህ ማንነት ውስጥ ወልድ ብቻ በሥጋ መጣ ማለት ጠቅላላው የሥላሴ
ማንነት በአንዱ፥ በወልድ ውስጥ ተጠቅልሎ ገብቶ ወልድ በሥጋ ሲመጣ፥ ሲተኛና
እንቅልፍ ሲወስደው፥ ሲሞትና ሲቀበር ዓለምንና ጽንፈ ዓለማትን የሚቆጣጠር
እግዚአብሔር እንደተኛ፥ እንደሞተ መቁጠር መሳሳት ነው። ኢየሱስ በሥጋ ሲሞት
እንኳ በሥጋ ነው የሞተው እንጂ መለኮታዊ ማንነቱ አልሞተም፤ መለኮት አይሞትማ።

ኢየሱስ ተኛ፥ አንቀላፋ ሲባልም እውነት ነው፤ ኢየሱስ ሰው ነው፤ ሰው ብቻ ግን


አይደለም። ሰው ስለሆነ፥ ከኃጢአት በቀር፥ ሰው የሆነውን ሁሉ ሆኖአል። ሰው
ይደክመዋል፤ ደክሞአል። ሰው ያንቀላፋል፤ ይተኛል፤ ኢየሱስ አንቀላፍቶአል፤
ተኝቶአል። እግዚአብሔር አይተኛም፤ አያንቀላፋም። ቃሉም ይህንን በግልጽ ይላል፤
እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። እነሆ፥ እስራኤልን
የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም። መዝ. 121፥3-4። እግዚአብሔር አያንቀላፋም።
ኢየሱስ ግን በሥጋ የመጣ ሰው በመሆኑ፥ ሰው ይተኛልና፥ ያንቀላፋልና አንቀላፋ፤
ተኛ። ይህ አምላክ አለመሆኑን ሳይሆን ሰው መሆኑን ይመሰክራል። ኢየሱስ ሰው
መሆኑን እንስማማለን። እውነቱ ግን፥ ኢየሱስ ሰው ብቻ አይደለም፤ አምላክ ሳለ
በሥጋ የመጣ ሰው ነው። አዲስ ኪዳን ስለ ኢየሱስ የሚያስተምረው ይህንን ነው።
ስለዚህ ነው የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ያይደለው።

4ኛ ወደ ፊት ሟች ኢየሱስ

በኢስላም ትምህርት መሠረት ኢየሱስ ባለፈው በመጣ ጊዜ አልሞተም አልተሰቀለም፤


ወደ ፊት ግን ይሞታል። ወደ ፊት ሟች በመሆኑ አምላክ አይደለም። ባለፈው ኢየሱስ
ሰው የመሆኑን ምክንያት በትንሹ ሳወሳ፥ ‘ኢየሱስ ለምን ሰው ሆነ?’ የሚለውን ነጥብ
ስናይ፥ ሰው የሆነው፥ አንደኛ፥ እግዚአብሔርን ሊገልጥልን፥ ሊተርክልንና ሊያሳየን እና
ሁለተኛ፥ ሞታችንን ሊሞት ነው ብያለሁ። ለመሞት ሰው መሆን አለበት። አምላክ
አይሞትም፤ መላእክት አይሞቱም፤ ሰው ይሞታል። ይህንን የመሞቱን ጉዳይ ግዙፍ
ጉዳይ ነውና፥ በሌላ ራሱን በቻለ ነጥብ ለብቻ እመለስበታለሁ። እዚህ የተጠቀሰበትን
አሳብ ነካ አድርጌ ብቻ ልለፍ። እዚህ ላይ፥ ወደፊት ሟች መሆን የሚለውን ነጥብ
እናስተውል። ያለፈውን ሞቱን ሳይሆን ገና ወደፊት የሚሞተውን ሞት ነው የሚለው።

41
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተጠቀሰው ጥቅስ ሱረቱል መርየም (19) ቁጥር 33 ነው

19፥33 ሰላምም በኔ ላይ ነው፣ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞተበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ


በምቀሰቀስበትም ቀን፤

በተወለድሁ፥ በምሞትበት፥ በምቀሰቀስበት ቀን ካለ፥ መወለዱ ያለፈው መወለድ ሆኖ


ሞቱና ትንሣኤው ለምንና በምን ሂሳብ ነው ያለፈው ሞትና ትንሣኤ ያልሆነው? ቢባል
ባለፈው ስላልሞተ ነው ይባላል። ይሁን እንጂ፥ በምወለድበት ቀን የሚለው ግስ እና
በምሞትበት ቀን የሚለው ግስ በእውነት ልዩነት አላቸው ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ
ነው። ‘ያዉማ ወሊቱ’ እና ‘ወያውማ አሞቱ’ የግስ ሰዋስዋዊ ልዩነት አላቸው ወይ?
የቋንቋው ሊቃውንት የሚሉት እንደሌላቸው ነው። ልደቱ ያለፈው ሆኖ ሞቱ ያለፈው
የማይሆንበት፥ የሚመጣው የሚሆንበት ማስረጃ ደካማ ነው ማለት ነው። በነገራችን
ላይ፥ በምወለድበት ቀን ይላል እንጂ በምፈጠርበት ቀን አይልም። ቀደም ሲል
እንዳልኩት ኢየሱስ የተወለደ እንጂ የተፈጠረ አለመሆኑን አመልካች ጥቅስም ሆኖ
መወሰድ የሚችል ነው ይህ። ስለዚህ ኢየሱስ የተወለደ እንጂ የተፈጠረ ፍጡር
አለመሆኑን ይህም አንቀጽ ይመሰክራል ማለት ነው።

የሳዲቅ እና የኢስላም ትምህርት ነጥብ፥ ‘የቁርኣኑ ዒሳ ሟች ሰው በመሆኑ አምላክ


አይደለም’ ነው። ልክ ነው፤ የቁርኣኑ ዒሳ አምላክ አይደለም። የቁርኣኑ ዒሳ ደግሞ
ፈጽሞም የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም። ኢየሱስ ደግሞ ሞቷል፤ ገና ወደፊት
ሳይሆን ቀድሞውኑ ሞቷልና ይህ መሞቱ ሰው የመሆኑ አስረጅ ነው። የሞተው
በሰውነቱ ወይም በሥጋው እንጂ በመለኮቱ አይደለም። ገና ወደፊት የሚሞት ሳይሆን
የዛሬ 2ሺህ ዓመት ነው የሞተው። ሰው የመሆኑ አንድ ምክንያትም ይኸው ሞቱ ነው።
ቃል ሥጋ የሆነው ሊሞትልን ነው፤ ተውላጣዊ፥ ምትካዊ ሞታችንን ለመሞት ነው።
ክርስቲያኖች ስንሞት የት እንደምንሄድ እርግጠኛ የሚያደርገን እውነት ሞታችን
የተሞተ ሞት ስለሆነ ነው። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ከሞተ የቁርኣኑ ዒሳ
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ነው? ወይስ አይደለም ብለን መከራከርም አይገባንም።
በግልጽ፥ የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ወደ ፊት ይሞታል ማለት ቀድሞ አልሞተም ማለት ነው። ከላይ እንዳልኩት፥ ይህንን


ቀድሞ አለመሞቱን ሳዲቅ የሚሞግትበት ሌላ የብቻ ነጥብ አለውና ይህ ለብቻ
የምንመለስበት ጉዳይ ስለሆነ እዚህ መሞቱ የእውነት ሞት መሆኑን አስምሬበት ብቻ
አልፈዋለሁ። አለመሞቱን የሚያስረዳበት ቦታ ላይ በእርግጥ የመሞቱን ማጠናከሪያ
አቀርባለሁ። እዚያ የምንመለከተው፥ በ4፥157-158 የተጻፈውን አልገደሉትም
አልሰቀሉትምም የሚለው ሐረግ ነው።

42
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

5ኛ አምላክ አይደለሁም ይላል

በመጨረሻው ዘመን ዒሳ የሚጠየቀው ጥያቄ አለ።

5፥116 አላህም፦ የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ ፦ እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ


ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፤ ጥራት ይገባህ፤
ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፤ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ
አውቀኸዋል፤ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፤ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፤
አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና ይላል።

ይህ፥ ኢየሱስ እናቱንና እርሱን ከአላህ ጋር ሦስት አማልክት አድርጎ እንደሆነ ተጠይቆ
አልወጣኝም ያለበት ቃል። በኢስላም ሥላሴ ምን እንደሆነ ያለውን መረዳት
የሚገልጥልን ጥቅስም ይህ ነው። በሚሰጠው መልስ አምላክ አለመሆኑን መግለጡ
ነው። ግን ይህ ጥያቄ ቀድሞውኑ የተጠየቀ ጥያቄ ነው? ወይስ ገና ወደፊት የሚጠየቅና
የሚመለስ ጥያቄ ነው? ወደ ፊት የሚጠየቅ ከሆነ፥ እርሱ ገና ወደ ፊት የሚጠየቀውንና
የሚመልሰውን መልስ እኛ አሁን ማወቃችን ገራሚ ነው። ጥያቄውንም መልሱንም እኛ
አውቀነዋል። ዒሳ ግን ገና አላወቀም ማለት ነው? ይመስላል። ወይስ እርሱም አውቆ
መልስ እያዘጋጀ ነው? ወይስ መልሱ ይህ እኛም ያወቅነው ነው?

እዚህ ጥያቄው የሚቀርብበትንና የሚመለስበትን ሁኔታ ነው ሳዲቅ ያቀረበው።


ጥያቄው ስለ ሥላሴ ነው። ይህንን ጥያቄ ባለፈው ስለ ሥላሴ ስናይ አይተነዋል። እዚያ
ያየነው የኢስላም የሥላሴ መረዳት የእግዚአብሔር የኢየሱስና የማርያም ጥምር
መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ የክርስቲያኖች አስተምህሮተ ሥላሴ አይደለም። ሆኖም
አያውቅም። በየትኛውም በክርስትና ታሪክ ዘመን ውስጥ ሥላሴ ማለት የኢየሱስ፥
የእግዚአብሔርና የማርያም የሦስትዮሽ ኅብረት ነው የሚል ትምህርት ኖሮ አያውቅም።

ይህንን የሚጠየቀውና መልሱን የሚመልሰው የቁርኣኑ ዒሳ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ


ኢየሱስ ግን እንደዚያ ያለ ጥያቄ ቀርቦለት እንደዚያ ያለ መልስ አይሰጥም። ማርያም
የሥላሴ አካል አንዱ እንደሆነች ኢየሱስ አላስተማረማ! ለዚህ ነው የቁርኣኑ ዒሳ እና
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ከቶም አንድ ያልሆኑት። ሲጀመር፥ በዘመን ፍጻሜ ኢየሱስ
ፈራጅ እንጂ ተጠያቂ አይደለም። እርሱ ፍርድ ሁሉ በእጁ የተሰጠው ጌታ ነው። ዮሐ.
5፥22-23 ይህንን ይለናል፤ ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት
ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።
ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም። ይላል። እዚያው ምዕራፍ ቁጥር 27
የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው። ይላል። በሥጋ መምጣቱ
ካደረገው ነገሮች አንዱ ፈራጅነትም ነው።

43
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

6ኛ ጌታ ካለው ጌታ ሊሆን አይችልም

ሌላው የሙግት ነጥብ፥ ዒሳ አላህን ጌታዬና ጌታችሁ ብሎ በማስተማሩ አምላክ


እንዴት አምላክ ሊኖረው ይችላል? የሚል ነው። አምላክ አምላክ አይኖረውም፤ ሰው
ግን አምላክ ይኖረዋል፤ ኢየሱስ በሥጋ የመጣ አምላክ ሲሆን ሰው ሆኗል። ስለዚህ
እንደ ማንም ሰው፥ አብን አምላክ እና አምላኬ እያለ ገልጧል፤ ጠርቷል። ይህንን
መጽሐፍ ቅዱስም አሳምሮ ያስተምረዋል። በብዙ ዝርዝር ያስተምረዋል።

ዮሐ. 20፥17ን ሳዲቅ ጠቅሶታል፤ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤ ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ


አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ
አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት። እዚህ
ጥቅስ ላይ ያለውን፥ ‘ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ’ የሚለውን ሲጠቅስ ጎል
ጠባቂውን በጥበብ አልፎ ግብ እንዳስቆጠረ ጎል አግቢ በኩራት ነው የጠቀሰው።

መቼም፥ ‘ወደ አምላኬ’ ያለውን ቃል ዋቢ አድርጎ ከጠቀሰ ሳዲቅ ጥቅሱን፥ ዮሐ. 20፥
17ን ይቀበለዋል ማለት ነው። የሚደንቀኝ ነገር ሙስሊሞች ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲጠቅሱ
ልክ ያንን ቃል እንደሚቀበሉት አድርገው ሲሆን፥ ‘ይህንን ቃል እውነት እንደሆነ
እስክትጠቅሱት ድረስ ከተቀበላችሁት፥ በእውነት የጌታ ቃል ነው ብላችሁ
ትቀበሉታላችሁ?’ ሲባሉ የሚሠሩት ድራማ የሚደንቅ ነው። ሳዲቅ ይህንን ጥቅስ
ሲጠቅስ ጥቅሱን ስለሚቀበለው ነው የጠቀሰው? ወይስ ሳይቀበለው ግን ለመጥቀስ
ፈልጎ ነው የጠቀሰው? ወይስ ጎምዶ፥ የሚጎምድበትን ቦታ ደግሞ ራሱ መርጦ ነው
የሚቀበለው?

ቀደም ሲል ጥቅሱ መጀመሪያ ላይ ያለውን፥ ‘ወደ አባቴ አላረግሁምና’ ያለውንስ


ይቀበለው ይሆን? ለመሆኑ ኢየሱስ አብን አባቴ ማለቱን ከቶ ይቀበለዋል? እንዲያው
ሲጀመር፥ ኢየሱስ ከሞት መነሣቱንስ ይቀበላል? እንደሚያርግና እንዳረገስ ይቀበላል?
እውነቱ፥ ከአንዱ በቀር ሁሉንም ነገሮች አይቀበልም። አምላኬ ከሚለው በቀር። ወደ
አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ያለውን መከራከሪያ አድርጎ ካነሣ፥ ወደ አባቴና
ወደ አባታችሁ የሚለውን አይቀበልም። ለምን? ግልጽ ነው። እግዚአብሔር አባት
አይባልም፤ ምክንያቱም፥ ‘ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው።’ ይላል፤ ሱራ
4፥171። ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሰው ስለሚቀበለው ሳይሆን አንደኛ፥ አዋቂ
ለመምሰል፤ ሁለተኛ፥ ለማሳት ብቻ ብሎ፤ ሦስተኛ፥ መጽሐፉን ሲጠቅስ መጽሐፉን
የሚቀበል ለመምሰል ሲል ነው። ይህንን አሳችነት ወይም ተቂያ ይሉታል።

ስለዚህ ማንም ሙስሊም፥ ኢየሱስ አብን አምላኬ ብሎ የተናገረበትን ሲጠቅስ በምን


አፉ ነው የሚጠቅሰው? ከጠቀሰ ደግሞ ጠቅላላውን ለምን አይቀበልም? ከአንድ ጥቅስ
ውስጥ አንድ ሐረግ ወይም አንድ ቃል ብቻ እየወሰደ ሌላውን የሚወረውር ከሆነ ይህ

44
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ቃል ለቃሚነት፥ ቃል መንጣቂነት ይባላል። በመንጠቆ እንደሚመነጥቁት ያለ


መመንጠቅ። ለነገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ እና የክርስትና ከሳሽ ሙስሊሞች ከመጽሐፍ
ቅዱስ ሲጠቅሱ ከየምንባቡ የሚፈልጓትን ቃል ብቻ ነው የሚለቅሙት። ቃሊቷን፥
አንዷን ነው የሚወስዱት። ዐውድ የሚባል ነገር መኖሩን ጨርሶ አያውቁም፤
ቢያውቁም አይቀበሉም። እዚህም ስንመለከት፥ ከአንዲት ጥቅስ እንኳን ግማሹን
አንሥቶ ግማሹን ይጥለዋል። ከአንዲት ጥቅስ ኢየሱስ ሰው መሆኑን ለማሳየት አምላክ
እንዳለው ይጠቅሳል፤ አብን አባት ብሎ መጥራቱን ደግሞ ወዲያ ይጥለዋል፤
አይቀበልም።

ሳዲቅ ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ከቁርኣን በርከት አድርጎ ጠቅሷል፤ [3፥52፤ 5፥72፤
5፥117፤ 19፥36፤ 43፥64]። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ እርሱ እንዳለው፥ ‘ጌታዬና
ጌታችሁ’ የሚል የለም። ኢየሱስ አብን፥ ‘አባቴ’ ብሏል፤ ይህ ግንኙነቱን ይገልጣል።
‘አምላኬ’ ብሏል፤ ይህ ሰውነቱን ይገልጣል። ጌታዬ ግን አላለም። በመጽሐፍ ቅዱስ
ይህ ጌታ አብን አባትና አምላክ ማለቱ ደግሞ ተደጋግሞ ተጽፏል። ደቀ መዛሙርቱም
ይህንን ብለዋል። ለምን? እናስታውስ ኢየሱስ በሥጋ ሲመጣ፥ ሰው ሲሆን ሰው
የሆነውን ሁሉ ሆኗል፥ ሰው የሆነውን ሁሉ አድርጓል ከኃጢአት በቀር ብያለሁ።
በሰውነቱ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮአል፤ አባቴ ብሎ ለምኗል፤ አምላኬ ብሎ
ተናግሯል። ለምን? ሰው ስለሆነ። ጥቂት ጥቅሶች ልጨምርበት፤

ማር. 15፥34 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ


ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።

አብ የጌታ አባትና አምላክ መሆኑን፥ ይህንን ራሱም የተናገረውን እውነት ሐዋርያቱ


ጳውሎስም ጴጥሮስም ጠቅሰውታል፤

ኤፌ. 1፥3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን


የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

1ጴጥ. 1፥3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥


እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው
ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ
ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

ኢየሱስ አብን አባቴና አምላኬ ብሏል። ለምን? ሰው ስለሆነና ሰው ሲሆን አምላክ


ሊኖረው ግድ በመሆኑ። ሐዋርያቱም ያንን ጌታ ያለውን ተቀብለው አስተጋብተዋል።

45
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አብ ዘላለማዊ አባት ነው። ወልድም ዘላለማዊ ልጅ ነው። ስለዚህ የቁርኣኑ ዒሳ


የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ከቶም አይደለም።

7ኛ ኢብኑ አላህ ሳይሆን ኢብኑ መርየም ነው።

ሌላው በሳዲቅ የቀረበው ነጥብ የሐዋርያቱ ምስክርነት ነው በማለት ሐዋርያቱ ዒሳን፥


‘ኢብኑ መርየም አሉት እንጂ ኢብኑ አላህ አላሉትም፤’ የሚለው ነው። ወደዚህ ነጥብ
እመለሳለሁ። እዚህ ላይ ከሙግቶቹ ወጣ ልበልና ይህ ጉዳይ የኢየሱስን ወንድነት
የተመለከተ ጉዳይ ስለሆነ ይህንን ስለሚመለከተው የምካቴ ክርስትና አካሄድ ጥቂት
ልበል።

በዚህ እና እነዚህን በመሰሉ ስሕተቶች ላይ ምላሽ የምሰጠው ከምካቴ ክርስትና አንጻር


ነው። ምላሽ በምሰጥበት በዚህ ዝግጅት ትኩረቴ በስሕተት ትምህርቶች አማካይነት
በኢየሱስ ላይ የተቃጣውን ማጠልሸት በመግለጥ የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ መጽሐፍ
ቅዱስ በገለጠው ማንነቱ ለማሳየት ነው። ይህን የማደርገው ኢስላም ኢየሱስን
በሳለበት ምስል ብቻ ሳይሆን በሌሎች የስሕተት ትምህርቶችም ላይ ነው።

ከመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ውጪ ሌላ ኢየሱስ በየዘመናቱ ሲፈለሰፍ፥ ሲፈበረክና


ሲፈጠር ኖሯል። ገና በመጀመሪያው የክርስትና ዘመንም እንኳ ነበረ። ሐዋርያቱ
ዮሐንስ እና ጳውሎስም ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። 2ቆሮ. 11፥4 ላይ ጳውሎስ
ያስጠነቀቀው ይህንን ነው፤ የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥
ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥
በመልካም ትታገሡታላችሁ። ብሏል፤ ሌላ ኢየሱስ። ይህ እዚህ የምመልስበት ሳዲቅ
መሐመድ የሚያስተምረው ኢየሱስም የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ
ነው።

ዮሐንስም በ1ዮሐ. 4፥2-3 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ


ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ
ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤
ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም
እንኳ በዓለም አለ። ብሏል። ይህ ሳዲቅ መሐመድ የሚያስተምረው ኢየሱስ በሥጋ
ያልመጣው ሌላ ኢየሱስ ነው። በሥጋ የመጣ ማለት ባለፈው ትምህርት
እንዳብራራሁት አስቀድሞ ያልለ፤ ቀድሞ ያለ ሥጋ የነበረ፤ ኋላ በሥጋ የተገለጠ ማለት
ነው። ሌሎች ኢየሱሶች በዘመናት ውስጥ ሲሰበኩ ኖረዋል።

46
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ይህኛው ሳዲቅ ያቀረበው የቁርኣኑ ዒሳ ከብዙዎቹ ሌላ ኢየሱሶች አንዱ ነው። የቁርኣኑ


ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም። ሌላ ኢየሱስ ነው። ይህን የምላሽ ዝግጅት
በቪድዮ ማቅረብ ከጀመርኩ በኋላ አንዳንድ ጥያቄዎች ቀርበውልኛል። አንዱ ጥያቄ፥
‘የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ የማርያም ልጅ እንደሆነው የቁርኣኑ ዒሳም የማርያም ልጅ
ነውና እንዴት አንድ አይሆኑም? ከዚህ በፊት የተሰጡን የወንጌል ስርጭት ስልጠናዎች
ሁለቱም አንድ ናቸው ተብለን ነው የተማርነው።’ የሚል ነው። እነዚህ ስልጠናዎች
ተግባቦት እና መካከለኛ መድረክ ለመፍጠር የቀረቡ ሊሆኑ ይችላሉ። ያ የተግባቦት
መፈጠር ክፋት ላይኖርበት ይችላል። ሆኖም፥ ያ ከፊል እውነት ነው። ከፊል እውነት
ደግሞ ሙሉ እውነትን እንዳይፈጠር የሚከለክል ጠር ነው። ከፊል እውነት ከፊል ሌላ
ነገር አለበት። ያ ሌላ ነገር ብዙውን ጊዜ ውሸት ነው። ከፊል እውነት ያልኩትም
እውነት የሚመስል እንጂ ያልሆነ ነው። ዒሳ የመርየም ልጅ ነው። ግን ያቺ መርየም
ማን ናት? ብለን ስንመረምር የዒምራን ልጅና የሐሩን እኅት ናት። በኦሪት ዘጸአት
የምናገኛት ናት። በቁርኣን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወላግደው የተወሰዱ ታሪኮች አሉና ይህ
አንዱ ነው። እንዲያው፥ ‘የመርያም ወይም የማርያም ልጅ ነው፤’ ብለን ብንወስድ፥
ይህ የማርያም ልጅ ጌታ ነው ወይስ አይደለም? በመስቀል ሞቷል ወይስ አልሞተም?
ከሙታንስ ተነስቷል? ወይስ አልተነሣም? ብለን ብንጠይቅ፥ ይህ የምንነጋገርበት
ኢየሱስና ዒሳ የማርያምና የመርየም ልጅ ስለሆኑ ብቻ አንድ ናቸው ለማለት
የማንደፍር ብቻ ሳንሆን የማንሞክር ሆነን እንገኛለን።

ከዚህ በፊት ይህን ጽሑፍ ስጀምር እንዳልኩት፥ ስለ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አንድ የማንነት
ምስል አቅርቤ እንደነበረው ነው። ያንን አሳብ ጥቂት ሐረጎች ልጨምርበትና እንደገና
እንዲህ ልበለው፥ ‘በኋላ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተባሉት ተፈሪ መኮንን፥ ከአባታቸው
ከልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺመቤት አሊ
ሐምሌ 16 ቀን 1884 ዓ. ም. በኤጄርሳ ጎሮ የተወለዱ ስድስት ዓይን እና አምስት እግር
ያላቸው፥ ቁመታቸው አሥራ አራት ሜትር ከስንዝር የሆኑ፥ ከቶም ንጉሥ ያልነበሩ፥
ከደርግ ግድያ አምልጠው ወደ ሰማይ ያረጉ፥ አሁን ጃህ ተብለው የሚመለኩ አምላክ
ናቸው።’ ብል ከዚህ ውስጥ ከማን መወለዳቸው፥ የት መወለዳቸው እና መቼ
መወለዳቸው፥ ከእውነተኛው ታሪካቸው ጋር የሚመሳሰል ነው። በከፊል ተመሳሰለ
ማለት ግን አንቀጹ እውነት ነው ማለት አይደለም። የቁርኣኑን ዒሳ ስናስብም ቢበዛ
ጉዳዩ ይኸው ነው። ስለ ወንጌል ስርጭት ስልጠና የሚሰጡን ሰዎች ሊያመሳስሉ
የሚችሏቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ ነገሮች መኖራቸውን ብቻ በማየት መሳት
የለብንም።

የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ እንዲመስል እናቱ ማርያም ተብላለች፤ ያለ


ወንድ መወለዱ ተነግሯል፤ ከየት ወገን መሆኑ ተወስቷል፤ መመሳሰሉ እዚያ ላይ
ያበቃል። ልክ ከላይ እንዳቀረብኩት ምስስል ነው። ከዚያ ውጪ ዋናው ማንነቱና
ዋናው ገድሉ ተክዶ ያልሆነው ማንነቱና ዋና ያልሆነው ድርጊቱ ጎልቶ ተነግሯል።
ዋናው ማንነቱ፥ አምላክነቱና ሰውነቱ በአንድ አካል መሆኑ ሲሆን፥ ዋናው ገድሉ

47
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ደግሞ ሞቱና ትንሣኤው ነው። ይህ ተክዷል። ይህ ከውስጡ የወጣ ኢየሱስ ኢየሱስ


አይደለም።

በዚህ ጉዳይ ላይ ወረራውና ተኩሱ ከቁርኣን አቅጣጫ ሲሆን ምካቴዬና ምላሼ ከቃሉ፥
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። እውነተኛውን ክርስቶስ፥ ሌላ ያልሆነውን ክርስቶስ፥
የመጽሐፍ ቅዱሱን ክርስቶስ ማወቅ ሕይወት ነው። ዮሐ. 17፥1-3 ይህን ይነግረናል፤
ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ ሰዓቱ
ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥
ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው። እውነተኛ
አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች
የዘላለም ሕይወት ናት። አብን እና የተላከውን ወልድን ማወቅ የዘላለም ሕይወት
ነው። ወልድ የተላከ ስለመሆኑ ወደ ፊት ለብቻው አናየዋለን። ግን እሱን ማወቅ
የዘላለም ሕይወት ምንጭ መሆኑን እናስተውል። ይኸው ዮሐንስ በመልእክቱ ደግሞ፥
በወልድ የሚታመን አብ አለው፤ ወልድን የሚክድ አብ የለውም ይላል። 1ዮሐ. 2፥22-
23 ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና
ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ
የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው። ኢየሱስን ማወቅና በእርሱ መታመን
የሕይወት ምንጭነቱን አመልካች ትምህርቶች ናቸው።

ሌላ ኢየሱስ የሚያስተምሩ ሰዎች ይህንን የሕይወት ምንጭ አያሳዩም፤ ይሸፍኑታል።


በኢየሱስ ላይ፥ በትምህርቱም፥ በግብሩም፥ በማንነቱም ላይ ወረራዎችና የስሕተት
ትምህርቶች የተጀመሩት ደግሞ አሁን አይደለም። ገና ከመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን
ዘመን ጀምሮ ነው። ሐዋርያቱ በመጀመሪያ ምላሽ ሰጥተዋል። ቤተ ክርስቲያንም
በዘመናት ሁሉ ውስጥ በቂና ብቁ ምላሽ፥ ድንቅ ምላሽ፥ አጥጋቢ ምላሽ ስትሰጥ
ኖራለች። ዛሬም ስሕተቶቹ አልቆሙም፤ ምላሹም ይቀጥላል። ስሕተቶቹ
የሚያነጣጥሩት በኢየሱስ ማንነት፥ ትምህርት፥ እና ግብር ላይ መሆናቸውን እንወቅ።
ይህ የሚያሳየው የድነታችን ማዕከል ላይ ዒላማ መነጣጠሩን ነው። የሕይወት ምንጭ
ኢየሱስ ከሆነ ሰይጣን የሚፈልገው ዋና ናገር ሰዎችና ኢየሱስ እንዳይተዋወቁና
እንዳይገናኙ ነው።

በኢየሱስ ላይ የሚሰነዘር ማናቸውም ስሕተት ከመዳን መንገድ የሚያወጣ ስሕተት


ነው። ምክንያቱም መዳን በሌላ በምንም፥ በማንም የለም። ሐዋ. 4፥12 ይህንን
ያስተምረናል፤ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች
የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። ይላል። ሌላ የመዳኛ መንገድ የለም።
በኢየሱስ ጌትነት፥ ሞት፥ እና ትንሣኤ ላይ በሦስቱም፥ በጌትነቱ፥ በሞቱ፥ በትንሣኤው
ላይ የሚነጣጠር ማናቸውም ወረራ በሰው ልጆች ድነት ላይ የተነጣጠረ ነው።

48
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሮሜ 10፥9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን


እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ይላል። ኢየሱስ ምን እንደሆነ? ጌታ
እንደሆነ። እግዚአብሔር ከምን እንዳስነሣው? ከሙታን እንዳስነሣው። ሞቷል ማለት
ነው። ከሙታን ምን እንዳደረገው? እንዳስነሣው። ተነሥቷል ማለት ነው። እነዚህ
ሦስቱ መሠረታዊ የነገረ ክርስቶስ ማዕከላዊ አዕማድ ናቸው። በነዚህ በሦስቱ ውስጥ
ሥጋዌው አለ፤ የሞተው በሥጋ ስለሆነ። ግብሩና ገድሉ ሁሉ አለ፤ ያደረጋቸውን ሁሉ
ያደረገው በማንነቱ፥ ሰው በመሆኑና ጌታ በመሆኑ የፈጸማቸው ነገሮች ናቸው።

ለዚህ ነው ኢየሱስ ላይ የተነጣጠሩ የሐሰት ትምህርቶች ላይ በቂና መጽሐፍ ቅዱሳዊ


ምላሽ መሰጠት የኖረበት። ይህንን የማደርገውም ስለዚህ ነው። ወደ ሰባተኛው የሳዲቅ
ነጥብ ልለፍ። ነጥቡ የሐዋርያቱ ምስክርነት በማለት፥ ‘ሐዋርያቱ ኢብኑ አላህ
አላሉትም ኢብኑ መርየም አሉት እንጂ’ ብሏል። በወንጌላት ውስጥ ኢየሱስን፥
‘የማርያም ልጅ፥ ወይም የዮሴፍና የማርያም ልጅ’ ብለው የጠሩት ጥቂት አይሁድ
ነበሩ፤ ኢየሱስ ያደገበት የናዝሬት ሰዎች ናቸው እንደዚያ ያሉት። እነሱም ያንን ያሉት
የሚያውቁት ያንን በመሆኑ ብቻ ነው። አንድ ሁለት ጥቅሶች እንይ፤

ማቴ. 13፥55-56 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን?


ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ
ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።

ማር. 6፥3 እንዲህ ይላል፤ ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም
የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ፤
ይሰናከሉበትም ነበር።

የዮሴፍ ልጅ ያሉትም አሉ፤ ሉቃ. 4፥22፤ ዮሐ. 1፥46 እና 6፥12። ነገር ግን ኢየሱስ
የዮሴፍ ልጅ አለመሆኑ የታወቀ ስለሆነና ይህ ጥያቄ እንደ ሙግት መቅረብም
ስለማይችል ይህን እንለፈው። ከነዚህ የናዝሬት ሰዎች ብቻ በቀር ኢየሱስን፥ ‘የማርያም
ልጅ ወይም የዮሴፍ ልጅ ብሎ የጠራው’ በአዲስ ኪዳን ማንም የለም። ሳዲቅ
እንዳለው ሐዋርያቱ ኢየሱስን፥ ‘የማርያም ልጅ’ እያሉ አልጠሩትም። አንዴም
አልጠሩትም። እንደዚያ ብለው ጠርተውት ቢሆኑ ኖሮ ሐዋርያቱ የጻፉት ወንጌልና
መልእክቶች ብዙ ናቸውና በዚያ ውስጥ አንዴ እንኳን፥ አንዴ ብቻ እንኳን ባገኘን
ነበር። አንዴ ብቻ እንኳ። ግን አንድም የለም።

ሐዋርያቱ ኢብኑ አላህ አላሉትም ብሏል። ይህ ደግሞ ግዙፍ ውሸት። ጥሬ ውሸት


ነው። በእርሱ መረዳይ አላህ እግዚአብሔር ከሆነና የአላህ ልጅ (ወይን ኢብኑ አላህ)
ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ከሆነ፥ ሐዋርያቱ ይህንን ማለትና አለማለታቸው
ከአዲስ ኪዳን የሚረጋገጥ ጉዳይ ነው። ሲጀመር፥ ስለየትኞቹ ሐዋርያት እንደሚናገርም
ግልጽ መሆን አለበት።
49
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ፥ ‘የእግዚአብሔር ልጅ’ ተደጋግሞ ተብሏል። ስለ ኢየሱስ


ለማወቅ ከምንጩ ነው መቅዳት ያለብን። ስለ ኢየሱስ ማንነት ትክክለኛው እና ትኩሱ
ምንጩ አዲስ ኪዳን ነው። ወንጌላቱን የጻፉት ከጌታ ጋር የነበሩት ሐዋርያቱና ከእነርሱ
ጋር የነበሩ ወይም ከአፋቸው የሰሙ ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ። ስለ ኢየሱስ እውነተኛውን
ትምህርት ከሰባት መቶ ዓመታት በኋላ በስሚ ስሚና ከእጅ ወደ እጅ ከተላለፈ ታሪክ
ከተወሰደ ቃል ማግኘት አንችልም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የመሰከሩ
በአዲስ ኪዳን ብዙ ምስክሮች አሉ። እጠራለሁ፤ ሐዋርያቱን ጨምሮ ስምንት
ምስክሮች እጠራለሁ! ሐዋርያቱን ጨምሮ ያልኩት፥ እዚህ ኢየሱስን ኢብኑ መርየም
ያሉት ሐዋርያቱ ናቸው ተብሎ ስለተነገረ ነው። የለም፤ ሐዋርያቱ አንዴም ኢየሱስን፥
‘ኢብኑ መርየም’ ወይም፥ ‘የማርያም ልጅ’ አላሉትም፤ ብለውትም አያውቁም። ይህንን
አጠራር እንደ ‘ማዕረግ’ የምናገኘው በቁርኣን ውስጥ ብቻ ነው። ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ ወደ መሰከሩት ምስክሮች ልለፍ፤

ሀ. እግዚአብሔር አብ መስክሯል፤

ማቴ. 3፥17 እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ


ይህ ነው አለ።

ለሁለተኛ ጊዜ አብ ሲናገር፥ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥


እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት
የሚል ድምፅ መጣ። ማቴ. 17፥5።

ለ. ኢየሱስ ራሱ መስክሯል፤

ኢየሱስ የአብ ልጅ መሆኑን፥ ወይም በአንድ እግዚአብሔር ማንነት ውስጥ ኢየሱስ


ከአብ ጋር ያለው ግንኙነት የአብና የወልድ (የአባትና የልጅ) መሆኑን መስክሮአል።
ማቴ. 26፥63-64 እንዲህ ይላል፤ ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ
የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር
አምልሃለሁ አለው። ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ
የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው። በዚያን
ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን
ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።
እነርሱም፦ ሞት ይገባዋል ብለው መለሱ።
50
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ተሳድቦአል ያሉት እግዚአብሔርን መስደቡ አድርገው ነው። እግዚአብሔርን የሰደበ


ደግሞ በሕጉ ሞት ይገባዋል፤ ዘኁ. 15፥30፤ ዘሌ. 24፥10-16። ለዚህ ነው ሞት ይገባዋል
ያሉት። እግዚአብሔርን፥ ‘አባቴ’ ማለቱ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ማመሳሰሉና
ማስተካከሉ መሆኑን አይሁድ አውቀዋል። ስለዚህ ነው እግዚአብሔርን ሰደበ፤ ሞት
ይገባዋል ያሉት። በሉቃ. 22፥70-71 ደግሞ፥ ሁላቸውም፦ [ሽማግሌዎችና የካህናት
አለቆችና ጻፎች ማለት ነው] እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን? አሉት።
እርሱም፦ እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ አላቸው። እነርሱም፦ ራሳችን ከአፉ
ሰምተናልና ከእንግዲህ ወዲህ ምን ምስክር ያስፈልገናል? አሉ።

በዮሐ. 5፥18 እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን


ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ
ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ይላል። ኢየሱስ እግዚአብሔርን አባቱ ሲል
ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ መሆኑ ከአይሁድ የተሰወረ አልነበረም።
ኢየሱስ የአብ ልጅነቱን በግልጽ ቋንቋ ሲናገር፤ ወንጌላቱን የጻፉት ሐወርያትና ደቀ
መዛሙርት ደግሞ ባልደበዘዘ ቀለም ነው የጻፉልን። ከነዚህ ጥቅሶች ሌላ ኢየሱስ አብን
አባት እያለ የጠራባቸው ቦታዎች ሁሉ የዚህ ምስክሮች ናቸው። እጅግ ብዙ ናቸው፤
ለምሳሌ፥ ዮሐ. 17።

ይህ አብን አባቴ ማለት በአገልግሎት ዘመኑ ሁሉ የሆነና በመጨረሻዋ በሥጋ በሆነባት


ደቂቃ እንኳ ሳይቀር የተናገረው እውነት ነው። በመስቀል ላይ ሳለ እንኳ፥ ኢየሱስም፦
አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። . . . ኢየሱስም በታላቅ
ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ
ነፍሱን ሰጠ። ይላል፤ ማቴ. 23፥34 እና 46።

አንዳንድ ሙስሊሞች ኢየሱስ ይህን ያለው ልክ ሌሎች ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን


አባት ብለው በሚጠሩበት መልኩ ብቻ ነው ይላሉ። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው።
ኢየሱስ አብን አባት ሲል እኛ እግዚአብሔርን አባት በምንልበት መልክ አይደለም።
ኢየሱስ አንድያ ልጅ (μονογες υἱὸς) ነው። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም
ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ
ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሐ. 3፥16። እኛ ደግሞ ልጆች የተደረግን ልጆች ነን፤
የኛን ልጅነት የተመለከተው ቃሉም ልጅ መደረግ (υἱοθεσία) ነው፤ ሮሜ 8፥15 እና
23፤ ገላ 4፥5፤ ኤፌ. 1፥5። ጌታ ግን ልጅ የሆነ ልጅ ነው፤ እግዚአብሔር ወልድ ነው።

51
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሐ. መልአክ መስክሯል፤

ገብርኤል ወደ ማርያም መጥቶ የተናገራት ቃል ይህ ነው፤ መልአኩም መልሶ እንዲህ


አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ
ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። ሉቃ. 1፥35።

ይህንን የተናገረው ገብርኤል ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ መጥቶ፥ ‘ኢየሱስ


የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም፤ የመርየም ልጅ ነው እንጂ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ
አይባልም፤’ አላለም። ገብርኤል ይህንን አይልም፤ መሆኑን ያውቃላ! ራሱ ነዋ፥ ‘ከአንቺ
የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።’ ብሎ የተናገረው። መጥቶ
ማስተካከያውን ከተናገረም፥ ያኔ የተላከ ጊዜ ያልተባለውን ማለቱን አብሮ መመስከር
ነበረበት። ስለዚህ የቁርኣኑ ዒሳ ብቻ ሳይሆን የቁርኣኑ ጅብሪልም የመጽሐፍ ቅዱሱ
ኢየሱስ አይደለም ማለት ነው።

መ. መጥምቁ ዮሐንስ መስክሯል፤

እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ። ዮሐ. 1፥34።


ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ብዙ ነገሮችን መስክሯል። አንዱ ምስክርነቱ ይህ ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ የመሆኑ ምስክርነት ነው።

ሠ. ሐዋርያቱና ደቀ መዛሙርቱ መስክረዋል፤

ሐዋርያቱ ኢየሱስን፥ ‘ኢብኑ መርየም’ ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን


መመስከራቸውን ነው በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው። በማቴ 16፥16 ጴጥሮስ
እንዲህ አለ፤ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ
ነህ አለ። ጴጥሮስ ይህንን ያለው ሰዎች ጌታን ማን እንደሚሉት ከጠየቃቸውና
ከመለሱለት በኋላ እነርሱ ማን እንደሚሉት ለጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ባይሆን ኖሮ፥ ‘የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ላርምህ፤ ትልቅ
ስሕተት ተናግረሃልና ላርምህ፤ እኔ የማርያም ልጅ እንጂ የእግዚአብሔር ልጅ
አይደለሁም፤’ ይለው አልነበረም? ነበረ እንጂ!

52
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በታንኳይቱም የነበሩት፦ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት። ማቴ


14፥33። እዚህም፥ ‘አትሳቱ እኔ የማርያም ልጅ እንጂ የእግዚአብሔር ልጅ
አይደለሁምና ለእግዚአብሔር ስገዱ’ ይል ነበር። አላለም። ሌሎችም ብለዋል፤ ጥቂት
ልጨምር።

ዮሐ. 11፥27 እርስዋም፦ [የአልዓዛር እኅት ማርያም] አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም
የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።

ዮሐ. 6፥67-69 ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?


አለ። ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል
አለህ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል
አውቀናልም ብሎ መለሰለት።

ልብ ማለት ያለብን ነጥብ፥ እነዚህ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድ ናቸው። ሁሉም


አይሁዳውያን ናቸው። ለአይሁድ ፍጡርን የተለመደ ቋንቋቸው አይደለም። ፍጡርን
የእግዚአብሔር ልጅ ማለት የክህደት ጥግ ነው። ይህንን ቀደም ሲል፥ ‘እግዚአብሔርን
ሰድቦአልና ሞት ይገባዋል!’ ያሉበትን ስንመለከት አይተነዋል።

ረ. ጠላቶቹ የሆኑ አይሁድም መስክረዋል፤

እነዚህ አንድ የምስክር ቡድን ስለሆኑ እንደ እማኝ ልጥራቸው፤

ዮሐ. 5፥17-18 ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ
መለሰላቸው። እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን
ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ
ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ይህንን ጥቅስ ቀድሜ ጠቅሼዋለሁ። እነዚህ
ሰዎች ማለቱን መናገራቸው ቢሆንም ማለቱን ማረጋገጣቸውም ነው።

ዮሐ. 19፥6-7 ጲላጦስም፦ እነሆ ሰውዬው አላቸው። የካህናት አለቆችና ሎሌዎች


ባዩትም ጊዜ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ
አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት አላቸው። አይሁድም መልሰው፦ እኛ ሕግ
አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና
አሉት።

53
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

እነዚህ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ራሳቸውም አምነው መመስከራቸው ሳይሆን


ለመክሰስ ሲሉ ያንን ማለቱን መናገራቸው ነው። ቢሆንም ያንን ማለቱን መስክረዋል።
ይህ የሚያስገድለው ቢሆንም፥ ኢየሱስ፥ ‘ኧረ አልወጣኝም፤ አላልኩም፤ የውሸት
ምስክርነት ነው። ይኸው አሁንም እላለሁ፤ እኔ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለሁም!’
ብሎ ከሞት ሊድን በቻለም ነበር። አላለም።

ሰ. አሕዛብ መስክረዋል፤

አንድ ሮማዊ ወታደር ይህንን መስክሯል፤

ማር. 15፥39 በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ
ባየ ጊዜ፦ ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ አለ።

ሸ. አጋንንትም ሳይቀሩ መስክረዋል፤

አጋንንትን አጋንንት ናቸውና ማን ያምናቸዋል? እነዚህን ምስክር አድርገን ባንጠራም


ግን ማን መሆኑን አውቀው መስክረዋልና ቢያንስ ያሉትን እንስማ። አጋንንት
መናፍስት ናቸውና ቀድሞም ሳይወድቁ በፊት ፈጣሪያቸው ስለሆነ ያውቁታልና
የሚያውቁትን መስክረዋል።

ማቴ. 8፥29 እነሆም፦ ኢየሱስ ሆይ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን?


ጊዜው ሳይደርስ ልትሣቅየን ወደዚህ መጣህን? እያሉ ጮኹ።

ሉቃ. 4፥41 አጋንንትም ደግሞ፦ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ


እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ ገሠጻቸውም ክርስቶስም እንደ ሆነ አውቀውት
ነበርና እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም። አጋንንትም ቢሆኑ ያወቁትን መስክረዋልና ለዚህ
ነው እንደ ምስክር የቀረቡት።

ከዚህ በላይ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ ምን ምስክር ይጠራ? አብ


መሰከረ፤ ወልድ ራሱ መሰከረ፤ ገብርኤል፥ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሐዋርያቱ፥ ደቀ

54
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መዛሙርቱ፥ ጠላቶቹ የሆኑ አይሁድ፥ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ሮማዊ መስክረዋል።


አጋንንትም እንኳ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አውቀውት ተናግረዋል።

በተለይ ወደ ሐዋርያቱ ትምህርት ስንመጣ፥ ሳዲቅ፥ ‘ሐዋርያቱ ኢብኑ መርየም አሉት


እንጂ ኢብኑ አላህ አላሉትም’ ላለው ሐሰት ማረጋገጫ ለማቅረብ፥ የሐዋርያቱና የደቀ
መዛሙርቱ ስብከት ኢየሱስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ነበር፤

ሐዋ. 8፥37 ፊልጶስም፦ በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም፦


ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ።

ሐዋ. 9፥20 ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ


በምኵራቦቹ ሰበከ።

ሮሜ. 1፥1-4 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ
በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ይህም
ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት
የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

2ቆሮ. 1፥19 በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ


የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ
አዎን ሆኖአል።

ገላ. 2፥20 ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ


ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን
በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

ዕብ. 4፥14 እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ


ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።

ዕብ. 7፥3 አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም
ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ
ይኖራል።

55
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

1ዮሐ. 3፥9 ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤
ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።

1ዮሐ. 4፥15 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር


በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

1ዮሐ. 5፥5፥10፥12፥13 ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር


ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው? . . . በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር
አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር
ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። . . . ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ
የሌለው ሕይወት የለውም። . . . የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ
በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።

ራእ. 2፥18 በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦


እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ
እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦

የአዲስ ኪዳን ስብከትም ምስክርነትም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ነው።


በአዲስ ኪዳን ውስጥ፥ የናዝሬት ሰዎች በንቀት ከተናገሩት በቀር፥ ኢየሱስ አንዴም
የማርያም ልጅ ወይም፥ ‘ኢብኑ መርየም’ ተብሎ አልተጻፈም። የናዝሬት ሰዎችም
ለምን እንደዚያ እንዳሉ ቀደም ሲል ተመልክተናል። ይህ ማለት ኢየሱስ የማርያም
ልጅ አይደለም ማለት ነው? አይደለም። ነው እንጂ። ማርያም የኢየሱስ እናት ናት።
ኢየሱስ፥ ‘የማርያም ልጅ’ አልተባለም እንጂ ማርያም የኢየሱስ እናት እየተባለች
ተጠቅሳለች። ወልዳዋለች፥ አጥብታዋለች፥ አሳድጋዋለች፤ እርሷንም ዮሴፍንም
ይታዘዛቸው እንደነበር ተጽፏል፤ እየታዘዛቸውም አድጓል። የማርያም ልጅ ነው?
በትክክል፤ ነው። የማርያም ፈጣሪም ደግሞ ነው። ኢየሱስ አምላክ ነውና፥ ሙሉ
አምላክ፥ ሙሉ ሰው በአንድ አካል ነውና፥ ፈጣሬ ኩሉ ነው። ስለዚህ የማርያም
ፈጣሪም ነው። የሐዋርያቱ ምስክርነት፥ ‘ኢብኑ መርየም’ ሳይሆን፥ ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ነው። የአዲስ ኪዳን ምስክርነትም ስብከትም ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው
ብለን እኛም እንመሰክራለን። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ የቁርኣኑ ዒሳ
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ከቶም አይደለም።

8ኛ ኃይልና ፈቃድ የሌለው ነውና ፍጡር ብቻ ነው

56
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ኢየሱስ በራሱ ኃይልና ፈቃድ ምንም አለማድረጉ ወይም ሊያደርግ አለመቻሉን


በመጥቀስ ሳዲቅ ኢየሱስን ሰው ብቻ፥ ፍጡር ብቻ አድርጎ ስሎታል። የጠቀሰውን
ዮሐ. 5፥30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም
ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። የተላከ መሆኑን በሌላ ክፍል
ለብቻ እናየዋለን። እዚህ ላይ መሠረታዊው ስሕተት በራሱ ኃይልና ፈቃድ ምንም
ማድረግ አለመቻሉ ወይም አቅም የማጣቱ ጉዳይ ሳይሆን፥ ሰው በመሆኑ ፈቃዱን
ማስገዛቱ ነው። ይህንን ከሁለት አቅጣጫ እንየው።

አንዱ አቅጣጫ፥ ጌታ ሰው ሲሆን፥ ሰው ሁሉ፥ ማንም ሰው ለእግዚአብሔር ፈቃዱን


እንደሚያስገዛው ወይም ማስገዛት እንዳለበት ሁሉ ወልድም ፈቃዱን አስገዝቷል። ይህ
እስካሁን ስናይ እንደቆየነው ሰው መሆኑን ያሳያል። ጌታ ሰው ስለሆነ፥ ሰው የሆነውን
ሁሉ ሆኗል፤ አድርጓል፤ ከኃጢአት በቀር ያልኩት እንደገና ይሰመርበት። እንደ ሰው
በመመላለሱ ፈቃዱን አልፈለገም፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና ያለው
ያንን ነው።

በብዙ ቦታዎች ይህን የፈቃድ ማስገዛት እናያለን። እዚሁ ዮሐንስ በሚቀጥለው


ምዕራፍ፥ ዮሐ. 6፥38-40፤ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ
ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ
በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው። ልጅንም አይቶ
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም
በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ስለ ፈቃድ ሲያወሱ ሙስሊሞች ይህንን ክፍለ
ምንባብ አያነሡም፤ ምክንያቱም አብረውት የተወሱት ነገሮች ኢየሱስ አምላክ ብቻ
የሚያደርጋቸውን ነገሮችም አድራጊ ስለሆነ፥ ነገሮቹ ደግሞ አንድ ላይ ተያይዘው
የተጻፉ ስለሆኑ አይጠቅሱትም። በመጨረሻው ቀን አስነሺው እርሱ መሆኑና በእርሱ
ማመን የዘላለም ሕይወት መሆኑ ፈቃድ አድራጊ ፍጡር ብቻ አለመሆኑን አረጋጋጭ
ነው።

ማቴ. 26፥39 እና 42፤ ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥


ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ
እንደምወድ አይሁን አለ። . . . ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና፦ አባቴ፥ ይህች ጽዋ
ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን አለ። እዚህ መውደድ
የሚለው፥ እንደምትወድ፥ እንደምወድ የሚለው ፈቃድ ነው።

ሉቃ. 22፥42፤ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን
የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።

የጌቴሴማኒው ጸሎት የጭንቅ ጸሎት ነው። ያቺ ጽዋ መራራ ናትና እንደ ሰውነቱ


ለኢየሱስ ከባድ ናት፤ ግን የራሱን ፈቃድ ሳይሆን የአብን ፈቃድ መረጠ። ሰው
57
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

እንደሆነ አምላክ፥ የሰውን ኃጢአት ሊሸከም እንዳለው አምላክ፥ ይህ እንኳን


ለማድረግ፥ እንኳን ለመሆን፥ ለማሰብም የሚከብድ ነው። ጌታ የኃጢአተኛ ሰውን
ልዋጭ ሞት ሊሞት ነው። 1ቆሮ. 5፥21 ላይ የተጻፈውን፥ እኛ በእርሱ ሆነን
የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት
አደረገው። የተባለውን ሊሆን ነው። ይህ አንደኛው ሰው የመሆንና ፈቃድን የማስገዛት
አቅጣጫ ነው። ሰዎች ሰዎች ስለሆኑ ለእግዚአብሔር ፈቃዳቸውን ማስገዛት
ይጠበቅባቸዋል፤ ፈቃዳቸውን ሁሉ ያስገዛሉ ማለት አይደለም፤ ግን ማስገዛት
ጤናማው ግንኙነት ነው። ኢየሱስ ሰው ሆኗልና በሰውነቱ ይህንን የሰውነቱን የፈቃድ
ማስገዛት እናያለን። ሲያስገዛ ደግሞ ፈጽሞ ነው ያስገዛው። ይህ አንደኛው አቅጣጫ
ነው።

ሁለተኛው አቅጣጫ፥ የፈቃድ መጣመርና የፈቃድ መዋደድ ጉዳይ ነው። ለዚህ ነው


በዮሐ. 5፥30፥ እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ
ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። ያለው። ቁጥር 19
ላይም ይህንኑ አሳብ እናገኛለን፤ ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት
እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም
አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። እዚያው
ቁጥር 38፤ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ
ወርጃለሁና።

ይህ የፈቃድ መጣመርን፥ የፈቃድ መዋደድን ያሳያል እንጂ የአቅም ጉድለትን


አይደለም፤ የበላይነትና የበታችነት ጉዳይ አይደለም። ወልድና አብ በመለኮት እኩል
ናቸው። ይህንን የእኩልነት አሳብ እዚያው ዮሐ. 5 ውስጥ እናገኛለን።

ቁጥር 18 ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ . . .


መስተካከል።

ቁጥር 19 ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። . . .


ማድረግ።

ቁጥር 22-23 አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ . . . ወልድን


የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም። . . . ክብር።

ጥቅስን ከዐውዱ ነቅሎ፥ ጎምዶ፥ መንጥቆ ማየት ችግር እንዳለበት ቀደም ሲል


ጽፌአለሁ። ዙሪያውን ማየት አለብን፤ ይህ አተያይ ዐውደ ምንባባዊነት ወይም ዐውደ
ገብነት ይባላል። ለምሳሌ፥ ከዮሐ. 5 አንዲት ሐረግ ስንመዝዝ ዮሐንስ 5ን በመላው
ማየትና ማጤን አለብን። ‘ይህ ምዕራፍ ስለ ምን ያስተምራል?’ ማለት አለብን።

58
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ወደ ምዕራፉ መጀመሪያ በመሄድ ይህንን ዮሐንስ ምዕራፍ 5ን ስናየው ጌታ አንድ


ለ38 ዓመት ሽባ ሆኖ የኖረ ሰውን ፈወሰ። የፈወሰው በሰንበት ቀን ነው። በሰንበት ቀን
ስለፈወሰና፥ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ ስለመለሰላቸው።
ሊገድሉት ይፈልጉት ነበር። ቁጥር 18 እና 19 እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ
አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር
አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ስለዚህ
ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ
ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ
ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። አለ። ይህ ቁጥር 19 እና 30 ላይ ያለው ቃል
ተመሳሳይ አሳብ ነው፤ እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ
እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።

ጠቅላላው ምንባብ ለአይሁድ ተግዳሮት የተሰጠ መልስ ነው። ክሱ፥ ‘በሰንበት


ይፈውሳል፤ ሰንበትን ይሽራል፤ ስለዚህ ሐሰተኛ ነው፤’ የሚል ነው። ‘አባቴ እስከ ዛሬ
ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሏል፤ ደግሞም፥ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር
አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ብሏል፤ ስለዚህ ይህ ኃጢአተኛና ተላላፊ ነው፤
ከሐዲና ሐሳዊ ነው፤’ የሚል ክስ ነው። ይህ ለአይሁድ ጠንካራ ክስ ነው። የክሳቸውን
መሠረትም አበክረው ያውቁታል።

ዮሐ. 5 ለዚህ ተግዳሮት የተሰጠ ምላሽ ነው። ‘የማደርገው አብ የሚያደርገውን ነው።


እርሱ ይሠራል፤ እኔም እሠራለሁ። እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ፤ አልተቀበላችሁኝም።
እኔ የማደርገው ሁሉ የአባቴ ፈቃድ ነው። ፈቃዳችን አንድ ነው፤ የተስማማ ነው፤’
የሚል እውነት ነው የነገራቸው። ይህንን ነው የፈቃድ መጣመር ያልኩት። የአቅም
ጉድለት ወይም አለመቻል አይደለም። የፈቃድ ጥምረት እንጂ። ይህ ጥምረትና
አንድነት ትልቅ ጥርጥር ሳይሆን ኃጢአት ሆኖ ታይቷቸዋል። ፈቃድ ለሰው ልጆች
ሁሉ የተሰጠ የምርጫ ነጻነት ነው።

ይህ ማለት ኢየሱስ በራሱ ፈቃድ ምንም አያደርግም ማለት እንጂ ከቶም ምንም
ማድረግ አይችልም፤ ፈጣሪ ሳይሆን ፍጡር ነው፤ አቅም የለውም፥ ፈቃድም የለውም
ማለት አይደለም። እዚሁ ምዕራፍ ቁጥር 21 ላይ፥ አብ ሙታንን እንደሚያነሣ
ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን
ይሰጣቸዋል። ይላል። ይህ ለአብነት ያህል ነው። በሌሎች ብዙ ቦታዎች ሲፈውስ፥
ተአምራት ሲያደርግ፥ ይቅርታ ሲያደርግ በፈቃዱ ነው ያደረገው። የግል ፈቃዱን
አለማድረጉ፥ ማድረግ አለመቻሉ ሳይሆን፥ ፈቃዱን ማስገዛቱና ፈቃዱ ከአብ ፈቃድ
ጋር አንድ ፈቃድ መሆኑ አረጋጋጭ ነው። ስለዚህ፥ ‘በራሱ ኃይልና ፈቃድ ምንም
ሊያደርግ አለመቻሉ ፍጡር ብቻ የመሆኑ አረጋጋጭ ነው፤’ የተባለው ማጣጣያ ክስ
መሠረተቢስ ክስ ነው።

59
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

9ኛ የሩቅ ነገሮችን ቀድሞ ማወቅ አለመቻሉ

በበለሲቱ ፍሬ እንዳለና እንደሌለ አለማወቁ ወይም ፍጡርነቱን ያሳያል የሚል ሙግት


ሳዲቅ አቅርቦአል። እርሱ ብቻ ሳይሆን ይህን ብዙዎችም ያቀርቡታል።

ማቴ. 21፥18-22 በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ


አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ
ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ደቀ መዛሙርቱም ይህን
አይተው፦ በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ። ኢየሱስም መልሶ፦
እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ
አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት
ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው።

ማር. 11፥13-14 እና 20-24 ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች
ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል
በቀር ምንም አላገኘባትም። መልሶም፦ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ
አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ። . . . ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ
ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ትዝ ብሎት፦ መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ
ደርቃለች አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ።
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥
ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥
የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።

ይህንንም ከሁለት አቅጣጫ እንመልከተው። አንደኛው፥ ዐውደ ገብነት ነው።


ጠቅላላውን ታሪክ ማየት ያሻል። ልብ ብንል፥ ከዚያ በፊት (ማቴ. 14 እና ማር. 6)
ጌታ በሺህ የሚቆጠሩትን መግቧል። ያንን መመገቡን በግልጽ ተጽፎአል። በተአምር
መግቧል። እና ሲራብ ፍሬ ፍለጋ ከመሄድ ይልቅ መብል መፍጠር አይቻለውም ነበር?
ይቻለዋል። ግን ጌታ መለኮታዊ ሥልጣኑን የፈቃዱ ማስፈጸሚያ አድርጎ
አልተጠቀመም። እንዲያ ቢሆን ኖሮ ብዙ ነገሮችን ማድረግ እና በመስቀል ላይ
አለመሞትንም ጨምሮ እንዳይሆንበት መከልከል ይችል ነበር። ጭራሽ ሰው
አለመሆንንም፥ በሥጋ አለመምጣትንም ጨምሮ መሆን ወይም አለመሆን ይችል
ነበር።

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ይህ መርገም (ኢየሱስ ከፈጸማቸው


ተአምራት መርገም ያለበት ይህ ብቻ ነው) የእስራኤልን ማንነት እና ፍሬቢስነት
ለማመልከት ይመስላል ይላሉ። ሊሆን ይችላል። ግን በቀጥታ ስንወስደው ዛፊቱ ናት
የተረገመችው። ጌታ ስለ እስራኤል፥ ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥ ነው

60
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተባለው፤ ዮሐ. 19፥41። ስለ እስራኤል ብዙ ነገሮችን በምሳሌም በግልጽም


ተናግሮአል።

ለሐዋርያቱ ሊያስተምር የወደደው ነገር ያለም ይመስላል። በሁለቱም ክፍለ ምንባቦች፥


በማቴ. 21ም በማር. 11ም ስለ ጸሎትና ስለ እምነት ነው የተናገራቸው፤ ኢየሱስም
መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ
ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር
ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ
አላቸው። ማቴ. 21፥21። ይህ ለደቀ መዛሙርቱ ተግባራዊ ትምህርት የሰጠበት
አጋጣሚም ነው።

ሁለተኛው፥ መራቡም፥ መመኘቱም፥ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ


መምጣቱም ምን ያሳያል? ሰው መሆኑን። አምላክ አይራብም፥ ሁሉን ደግሞ
ያውቃልና፥ ‘ምናልባት’ ብሎ ሊፈትሽ አይሄድም። ሰው ግን ይራባል፤ ይመኛል፤
አንዳች ፈልጎም ይሄዳል።

ኢየሱስ በሌሎች ቦታዎች የሰዎችን ውስጣዊ አሳብ ሳይቀር ሁሉ ያውቃል። ዮሐ. 2፥


24-25 ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር
አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።
ይላል። በሌሎች በርካታ ቦታዎች አሳባቸውን እና የተነጋገሩትን አውቆ ይላል፤ ማቴ.
9፥4፤ 12፥25፤ ማር. 2፥8፤ 12፥15፤ ሉቃ. 9፥47፤ ዮሐ. 6፥61፤ ወዘተ።

ኢየሱስ ሰው በመሆኑ በጥበብም ወይም በእውቀትም ያድግ ነበር ሉቃ. 2፥52፤


ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ
ነበር። በራሱ ላይ እንዲሆን ወዶ በተቀበለው ሰው መሆን ወይም በሥጋ መምጣት
ራሱን በብዙ መንገዶች አጥሯል። ለምሳሌ በሥጋ በነበረ ጊዜ በአካሉ በሁሉ ስፍራ
አይገኝም ነበር። ይህ መታጠር ነው፤ መወሰን ነው። ማወቅን በተመለከተም ይህ
እውነት ነው። እንደ አምላክነቱ አምላክ ሁሉን አዋቂ ነውና ሁሉን ያውቃል። እንደ
ሰውነቱ ደግሞ እውቀቱ ውስን ነው፤ በእውቀት ያድጋል፤ ሁሉንም ነገርም አያውቅም።
ስለዚህ ተራበ፤ ተመኘ፤ ሊበላ ወዶ ሄደ፤ አጣ፤ ረገማት። ይህ ሁሉ ምንን ያሳያል?
ሰውነቱን። ሰው መሆኑን።

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ሰው የሆነ አምላክ ነው። ከኃጢአት በቀር ሰው የሆነውን


ሁሉ ሆኗል፤ ሰው ያደረገውን ሁሉ አድርጓል። ሳዲቅ ኢየሱስ የሩቆችን አለማወቁ
በማለት ካቀረባቸው ሁለት ነጥቦች አንዱ በለሲቱ ፍሬ እንዳለባትና እንደሌለባት
አለማወቁ ሲሆን፥ ሁለተኛው ነጥብ፥ ጌታ ተመልሶ የሚመጣበትን ቀን ባለማወቁ
ፍጡር ብቻ ነው ብሏል።

61
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ እንደ ጌታ የማይቀበሉት እንደ ሳዲቅ ያሉት ሰዎች ግዙፍ
ችግር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅስ ሲጠቅሱ የምትመቻቸው የሚመስላቸውን
አንዲት ቃል ወይም አንድ ሐረግ ብቻ ይወስዱና አጠገቡ ያለውን ወይም ያ ቃል
እውስጡ ያለበትን አሳብም አለመውሰዳቸው ነው። ለምሳሌ፥ ቀደም ሲል እንዳየነው፥
ሳዲቅ ኢየሱስ የተላከው መሆኑን ሲናገር ትኩረቱ የተላከ መሆኑ ላይ ብቻ ነበር።
‘ከተላከ፥ ማን ላከህ? ነው የምንለው’ ብሏል። ግን የስፍራው፥ የክፍለ ምንባቡ አሳብ፥
የዘላለም ሕይወት ምንጭ እርሱንና የላከውን አብን ማወቅ መሆኑን ወይም የሚለውን
ቃል አላወሳም። የተላከ መሆኑን ብቻ እንጂ የተላከው እርሱ ማን መሆኑን፥ ወይም
በክፍሉ ውስጥ፡ማን ተብሎ እንደተጠቀሰ እንኳ አላወሳም። ለምን? አሳቡ፥ ጥረቱ፥
ኢየሱስ የበታች መሆኑን፥ የላኪው ተላኪ ወይም ተላላኪ መሆኑን፥ ፍጡር መሆኑን፥
ለማሳየት ነው። ለዚህ ነው የተላከው የዘላለም ሕይወት ምንጭ መሆኑን ያላወሳው።

ይህ የሳዲቅ እና የብጤዎቹ ትልቁ ችግር ነው። ሌላ ምሳሌ ብናይ፥ በዮሐ. 12፥44 በእኔ
የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ ያለውን ሲወስድ፥ በላከኝ
ማመኑ ነው የሚለው ላይ ያተኩራል እንጂ፥ የኢየሱስና የአብ አንድ መሆን ላይ
አያተኩርም። ‘በእኔ የሚያምን’ ነው እኮ ያለው! በእኔ የሚያምን ካለ ኢየሱስ
የሚታመን ወይም የሚታመነው ነው ማለት ነው። ከአብ ጋር የሚታመነው ነው
ማለት ነው። በኢስላም ብዙ ሺህ ነቢያትና መልእክተኞች አሉ ይባላል፤ (ከ120ሺህ
በላይ) ከነዚህ ማንም፥ ‘በእኔ እመኑ!’ ያለ ረሱል ወይም መልእክተኛ የለም። ኢየሱስ
ግን ይህንን ብሏል። ይህንን የመታመን ነገር ወደ ጎን ገፍቶ የተላከ መሆኑ ላይ ብቻ
ማተኮር ማሳት ነው። ለቅሞ የሚፈልጉትን ብቻ ወስዶ የቀረው እስከመኖሩም መርሳት
ለማሳት ማደናገር ነው።

የሩቆችን የማያውቅ ባለው ስለ ዳግም ምጽአቱ ቀን አለማወቁን የተናገረው ነው። ማቴ.


24፥36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም
ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። ይህንን ክፍል ስናይ ጥቅሲቷን ብቻ ሳይሆን
ጠቅላላውን ምዕራፍ ነው ማየት ያለብን። ቢያንስ ከላይ ከፍ ብለን፥ ከታችም ዝቅ
ብለን ነው ማየት ያለብን። ጠቅላላውን ምዕራፍ፥ ማቴዎስ 24ን ስንመለከት ጌታ
ከመምጣቱ በፊት የሚሆኑት ምልክቶች ተነግረዋል። ጠቅላላው ማቴ. 24 የአንድ
ጥያቄ መልስ ነው። ያ ጥያቄ በማቴ. 24፥3 የሚገኘው ደቀ መዛሙርቱ ያቀረቡለት
ጥያቄ ነው። እንዲህ ይላል፤ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ
ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም
መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ይህን ጥያቄ በሰፊው ሲመልስላቸው ብዙ ምልክቶችን ሰጣቸው። ከምልክቶቹ


መካከል፥ ብዙዎች በስሙ ይመጣሉ፤ ጦርና የጦር ወሬ ይስሰማል፤ ሕዝብ በሕዝብ፥
መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣሉ፤ ራብ፥ ቸነፈር፥ የምድር መናወጥ ይሆናሉ።
እነዚህ የምጥ ጣር ጅማሬ ናቸው። ከዚያስ? ይቀጥላል፤ ተከታዮቹ ላይ ስደት ይበዛል፤

62
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ይሰደዳሉ፤ ይገደላሉ፤ ፍቅር ትቀዘቅዛለች፤ ወንጌል ይሰበካል፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶች፥


ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። ይቀጥላል፤ ከዚህ በኋላ
ወዲያው ወይም በፍጥነት በሰማይ ኃይላት ምልክት ይሆናል፤ በፀሐይ፥ በጨረቃ፥
በከዋክብት ላይ ምልክት ይሆናል፤ ከዚያ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል። ይህ
‘የሰው ልጅ’ የተባለው ኢየሱስ ነው። እነዚህን ሁሉ ምልክቶች መናገሩን ልብ እንበል።

ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ


ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። ከአባት ብቻ በቀር፤ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም
ሲል ከሁለት አንጻር እንመልከተው።

አንደኛ፥ ባለፉት በርካታ ነጥቦች እንዳየነው፥ ኢየሱስ ሰው ሲሆን መለኮታዊ


ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ አልተለማመደም። ፈቃዱን እንዳስገዛው ሰውነቱ ወይም
ስብእናው መለኮትነቱን እስኪሞት ድረስ ከአብ ፈቃድ ጋር አንድ ካልሆነ በቀር
አልተለማመደም። ለምሳሌ፥ ባለፈው ካየነው ብንወስድ፥ ሲራብ ምግብ መፍጠር
ይችል ነበር። ቀድሞ ፈጥሮ መግቧል። መፍጠር ለፈጣሪ ምኑም አይደለም። መፍጠር
ሲችል፥ ሌሎቹ እንዲበሉ እንደፈጠረው ወይም እንዳባዛው ለራሱ ግን አልፈጠረም።
የበለስ ፍሬ አይደለም፤ የበለስ ዳቦም መፍጠር ይችል ነበር። አላደረገም። በመስቀል
ላይ ኃጢአት ተሸክሞ አለመሞት ቢመኝም ይህ ከአብ ፈቃድ ጋር፥ ወይም ከመጣበት
ዓላማ ጋር የማይሄድ ነውና አላፈገፈገም፤ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር
ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃ. 22፥42። የኢየሱስ
ማወቅ በሰውነቱ ወይም ሰው በመሆኑ ውሱን መሆኑን ወይም በጥበብም ያድግ
እንደነበር ባለፈው ተመልክተናል። ኢየሱስ ዳግም የሚመጣባትን ቀኒቱንና ሰዓቲቱን
ካላወቀ፥ ወይም እንዲያውቅ ካልወደደ ይህ የሰውነቱ አንድ መግለጫ ነው። ፈቃዱን
በሙሉ ለአብ ሲያስገዛ እውቀቱም በፈቃዱ ውስጥ ነው። ይህ አንዱ ነጥብ ነው።

ሁለተኛ፥ እርሱ መለኮታዊ እውቀትን አለመለማመዱ ብቻ ሳይሆን ለሰዎችም፥


ለሰሚዎቹም መለኮታዊ ቀጠሮን ማወቅ አስፈላጊያቸው አይደለም። ኢየሱስ እነዚያን
ሁሉ ምልክቶች ከሰጠ ይህ በእውነቱ በቂና እውቀቱንም ገላጭ ነው። ‘የምመጣው
መስከረም 30 ቀን 2ሺህ 25 ዓመተ ምሕረት ነው።’ ቢል ምን የሚሆን ይመስለናል?
ማንም እንደሚገምተው፥ እስከ ጳጉሜ 2ሺህ 24 ድረስ እንዳሻቸው እየሆኑ፥ ሲፈነጥዙ
ቆይተው፥ የሆያሆዬ ቀን ወደ አዲሱ ዓመት አዲስ ባዲስ ሆነው ይገቡና ሰው መሳይ
በሸንጎ፥ መስከረም 30 መንግሥተ ሰማያት ደጅ ላይ ከች ይላሉ። እግዚአብሔር
የሚታለል አምላክ እንደሆነ በማሰብ።

ጌታ የተናገረው የሚመጣው ድንገት መሆኑንና ከዚያ ድንገት በፊት ያለው ጊዜ ግን


የሚታወቅ መሆኑን ነው። ድንገት የሚመጣ ከሆነ እንዴት ነው ቀኑን እንዲናገር
የምንጠብቀው? ምልክቶቹን እናስብ፤ የብዙዎች በስሙ መምጣት፥ ጦርና የጦር ወሬ
መሰማት፥ ሕዝብ በሕዝብ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሣት፥ ራብ፥ ቸነፈር፥

63
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የምድር መናወጥ፥ ስደት፥ መገደል፥ የፍቅር መቀዝቀዝ፥ የወንጌል መሰበክ፥ የሐሰተኞች


ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት መነሣትና ምልክትና ድንቅ ማሳየት፥ በሰማይ ኃይላት፥
በፀሐይ፥ በጨረቃ፥ በከዋክብት ላይ ምልክት መሆን። ከዚያ የሰው ልጅ ምልክት
በሰማይ መታየት። ይህ ሁሉ ምልክት ከመምጣቱ በፊት የሚሆን ነው።

ምሳሌ ደግሞ ሰጠ። ምሳሌ የሰጠው የኖኅን ዘመን ነው። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው
ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ
መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥
የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት
ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ማቴ. 24፥37-39።

በኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ እንደሚመጣ ይታወቃል፤ ኖኅ መርከብ እየሠራ


እግዚአብሔር ይታገሥ ነበር፤ ኖኅም ይሰብክ ነበር። ጴጥሮስ በ1ጴጥ. 3፥20 ጥቂቶች
ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት
በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም። ብሏል። እግዚአብሔር ይታገሥ ነበር።
2ጴጥ. 2፥5 ላይ ደግሞ፥ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን
የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥ ብሏል።
ኖኅ ይሰብክ ነበር። ኖኅም ይሰብክ፥ እግዚአብሔርም ይታገሥ ነበር። ውኃው ግን
መጣ። ሲመጣም በድንገት መጣ። የጌታም መምጣት ልክ እንደዚያ ነው።

እንደሚመጣ እናውቃለን፤ በድንገት እንደሚመጣ ተነግሯል፤ ተዘጋጅተን መኖር


እንዳለብን እናውቃለን፤ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አናውቅም። ጌታም አልተናገረም። ለምን
አልተናገረም? ማወቁ ለኛ አስፈላጊያችን ስላልሆነም ጭምር።

ከትንሣኤው በኋላም ይህንኑ ጥያቄ ጌታን ጠይቀውት ነበር፤ የሐዋ. 1፥6-7 እነርሱም
በተሰበሰቡ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን?
ብለው ጠየቁት። እርሱም፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን
ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ አላቸው። ይህ ከትንሣኤው በኋላ ነው፤ ያኔ
በሥጋው ወራት ስለሆነ ነው ያልተናገረው ቢባል፥ ‘ይህኛው ከትንሣኤው በኋላ ነውና
መናገር ይችል ነበር፤’ ማለት ይቻላል። ነገር ግን እዚህም አልተናገረም፤ ለምን? መልሱ
ግልጽ ነው፤ ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ ልናውቀው አልተሰጠንም።
መቼ እንደሚመጣ ማወቅ ቢያስፈልገን ኖሮ ጌታ በግልጽ ይነግረን ነበር። ቀኒቱን ብቻ
አይደለም፤ ሰዓቲቱንም በተናገረ ነበር፤ ግን ይህን ማወቅ ለእነርሱም፥ ለአኛም
አልተሰጠንም፤ አያስፈልገንም።

64
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

10ኛ እኔ ነቢይና መልእክተኛ ብቻ ነኝ ማለቱ፤

እነዚህን ሁለቱን ተቀራራቢ ናቸውና ጨፍልቀን በአንድ አድርገን እንመልከታቸው።


ግን ሁለቱም ራሳቸውን የቻሉ አሳቦች ስላሏቸው ለየብቻ እንያቸው። የሳዲቅ አንዱ
የሙግት ነጥብ፥ ‘ዒሳ እኔ ነቢይና መልእክተኛ ብቻ ነኝ በማለቱ ዒሳ አምላክ
አይደለም።’ የሚል ነው።

ኢየሱስ ነቢይ ነው? በእርግጥ ነው። አስቀድሞ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ ነው። በዘዳ.
18፥15-18 አምላክህን እግዚአብሔርን በኮሬብ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበት ቀን፦
እንዳልሞት የአምላኬን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ አልስማ፥ ይህችን ታላቅ እሳት
ደግሞ አልይ ብለህ እንደ ለመንኸው ሁሉ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል
ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።
እግዚአብሔርም አለኝ፦ የተናገሩት መልካም ነው፤ ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ
አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፥ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ
ይነግራቸዋል፤ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ።

አንዳንድ ሙስሊሞች ይህንን ከላይ ያየነውን ምንባብ ስለ ኢስላም ነቢይ ስለ


ሙሐመድ የተነገረ ነው ብለው ሊያስረዱ ይሞክራሉ። ይህን ለማድረግ የሚሞክሩት
ስለ ሙሐመድ የተነገረ ትንቢት በመጽሐፎች ውስጥ መኖሩ በቁርኣን ስለተመለከተ
ያንን ማረጋገጫ እንዲሆን ነው።

ሱረቱል አዕራፍ 7፥157

ለነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ
ነብይ የሆነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለሆኑት (በእርግጥ እጽፋታለሁ)፤ . . .

የሚል ይገኛል። ስለዚህ ከተውራትም፥ ከኢንጂልም ስለ ሙሐመድ የተነገረ ነገር


ተፈልጎ መገኘት አለበት። ከተውራት የሚጠቀሰው ይህ ነው። ከኢንጂል ደግሞ ከዮሐ.
14 እና 16 ስለ መንፈስ ቅዱስ የተነገረው ትንቢት ስለ ሙሐመድ ነው ብለው ይላሉ።

ይህን የዘዳ. 18፥18ን ትንቢት ለኢስላም ነቢይ ማድረግ በሦስት ምክንያቶች ስሕተት
መሆኑን ላሳይ፤

አንደኛ፥ ‘ከወንድሞችህ መካከል’ ነው የተባለው እንጂ ከሌላ አልተባለም። ሙሐመድ


አይሁዳዊ አይደለምና ከወንድሞችህ መካከል የተባለውን አያሟላም። ‘የለም፤ ወንድም
ሲባል እኮ ትርጉሙ ሰፊ ነው፤ እና ሙሐመድ ከእስማኤል ዘር ስለሆነ ወንድም

65
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ይባላል፤’ ይላሉ። ከእስማኤል ዘር ነው ብለን ብንወስድም እንኳ፥ እንዲህ ከሆነ፥


በዘዳ. 17፥14-15 ያለው ቃልም ተመሳሳይ ነውና ያም እንደዚያ ነው ብለን መውሰድ
አለብን ማለት ነው? ያ ጥቅስ የሚለው፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር
በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ
በላዬ ንጉሥ አነግሣለሁ ስትል፥ አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ
ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤
ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም። ይህ
በጣም ግልጽ ነው። አይሁድ ከዐረቦች ለራሳቸው ንጉሥ እንዲያነግሡ
አልተነገራቸውም። አድርገውም አያውቁም። እዚህ ከወንድሞችህ መካከል የተባለው
ከዐረቦች ወይም ከእስማኤላውያን ካልሆነ በዘዳ. 18 የተጻፈው በምን ሂሳብ ነው
ለዐረቦች ወይም ለእስማኤላውያን የሚሆነው?

ሁለተኛ፥ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን ስለሚል ይህ ነቢይ በያህዌህ ስም መናገር


አለበት። ሙሐመድ በአላህ እንጂ ከቶም በያህዌህ ስም አልተናገረም፤ ተናግሮም
አያውቅም፤ የያህዌህን ስም ጠርቶም አያውቅም። ይህ ሁለተኛው ነጥብ ሙሐመድ
የተነገረለት ነቢይ የአለመሆኑ ምስክር ነው።

ሦስተኛ፥ ይህ ትንቢት በኢየሱስ የተፈጸመ ትንቢት መሆኑ በግልጽ ተነግሯል። በማን


እንደተፈጸመም በግልጽ ተጽፎ ይገኛል። በሐዋ. 7፥38 ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች፦
እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት
ያላቸው ሙሴ ነው። ካለ በኋላ ቀጥሎ በዝርዝር የተናገረው ስለ ክርስቶስ ነበረ፤ ቁጥር
52-53 ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ
የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት
እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም። ይህንም በሰሙ ጊዜ
በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። ይላል። ስለማን ሲናገር ነው
በጣም የተቆጡትና ጥርሳቸውን ያፋጩት? ስለ ክርስቶስ። ይህን የተናገረው ፊልጶስ
የብሉይ ኪዳኑን ትንቢት በኢየሱስ መፈጸም አያይዞ ነው የተናገረው።

ጴጥሮስም በበዓለ ኀምሳ ቀን ስብከቱ ይህንን መሰከረ፤ ሐዋ. 2፥21-26፤ እግዚአብሔር


ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን
ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና። ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን
እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን
ስሙት። ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ።
ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ
ወራት ተናገሩ። እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር
ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።
ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን
ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው። አለ። ስለ ማን ሲሰብክ ነው ይህን

66
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ያለው? ስለ ክርስቶስ። ስለዚህ በዘዳ. 18፥18 የተነገረው ስለ ሌላ ስለ ማንም ሳይሆን


ስለ ክርስቶስ ነውና ያ የተነገረለት ነቢይ ነው ክርስቶስ ነው ማለት ነው።

ጌታ ነቢይ መሆኑም ተደጋግሞ ተጽፎአል። ማቴ. 13፥57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ
አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። ይላል። ይህን ጌታ ነው
በናዝሬት የተናገረው። የተናገረው የተለመደ አባባልን ቢሆንም ራሱን እንደ ነቢይ
በማድረግ አቅርቧል። በሉቃ. 13፥33ም ተቀራራቢ ነገር ተናግሯል፤ ዳሩ ግን ነቢይ
ከኢየሩሳሌም ውጭ ይጠፋ ዘንድ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም ልሄድ
ያስፈልገኛል።

ማቴ. 21፥45-46 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ


እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤ ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት
ፈሩአቸው። ሕዝቡ እንደ ነቢይ ያዩት ነበር።

ሉቃ. 7፥16 ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸውና፦ ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል፥
ደግሞ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐበኘ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ይህም
የሕዝቡ መረዳትና ስሜት ነው።

ሉቃ. 24፥19 እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦


በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ
ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤ እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ
እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ
ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ
ሦስተኛው ቀን ነው። የኤማሁስ መንገደኞች፥ የጌታ ደቀ መዝሙሮች ናቸው።

ስለዚህ ትንቢቱም፥ ጌታም፥ ደቀ መዛሙርቱም፥ አይሁድም ነቢይ መሆኑን


ተረድተዋል፤ መስክረዋልም። ነቢይ ሴማዊ ቋንቋ ነው። በዕብራይስጥም፥ በዐረቢም፥
በአማርኛም ነቢይ ነው የምንለው፤ ሴማውያን ቋንቋዎች ስለሆኑ። ነቢይ ማለት
የእግዚአብሔርን ቃል፥ የሕዝቡን ሁኔታ፥ የወደፊቱንም ነገር ለሕዝቡ የሚናገር ማለት
ነው። ኢየሱስ ይህን አድርጓል? አድርጓል። ስለዚህ ነቢይ ሊባል ይቻላል።

ሁለተኛው ሳዲቅ ያነሣው ሙግት፥ ‘መልእክተኛ’ የሚለው ነው። ዒሳ ረሱል አላህ ነው


ነው ያለው ሳዲቅ። ኢየሱስ የተላከ መሆኑን ቀደም ሲል አይተናል፤ የተላከ ከሆነ
መልእክተኛም ነው። አምላክ ሳለ ሰው ሲሆን፥ በሥጋ ሲመጣ መጣ ማለት ነው።
ሲመጣ መእልክተኛ ነው፤ ወይም በዐረብኛ ረሱል ነው። ይህንንም ነው የሆነው።
ኢየሱስ የተላከ መሆኑን በብዛት ተናግሯል።

67
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ቀደም ሲል፥ ‘ሌላ ኢየሱስ’ የሚባል ስለመኖሩ ተናግሬ ነበር። ሌላ ያልሆነውን


ክርስቶስ የሰበኩ ብዝይ ነበሩ። እውነተኛውን ክርስቶስ፥ የመጽሐፍ ቅዱሱን ክርስቶስ
ማወቅ ሕይወት ነው፤ የዘላለም ሕይወት። ይህ እርሱን ማወቅ የዘላለም ሕይወት
መሆኑ በተጻፈበት ክፍል በዮሐ. 17፥1-3 እርሱ የተላከ መሆኑንም ተወስቶአል። ክፍሉ
እንዲህ ይላል፤ ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦
አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን
እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን
አክብረው። እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን
ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የዘላለም ሕይወት አብን እና የላከውን
ወልድን ማወቅ ነው። አብን እና (እና ይሰመርበት) ወልድን ማወቅ ነው። እና እና
ደግሞም አንድ ናቸው። 17፥3ን በተጻፈበት ቃል ብናየው ይህ ግልጽ ይሆናል፤

αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ይህችም (ይህች ደግሞ) ናት የዘላለም ሕይወት፤


ἵνα γινώσκωσί σε τὸν μόνον ἀληθινὸν Θεὸν ያውቁ ዘንድ [እነርሱ]
አንተን እውነተኛውን አምላክ ብቻን፤ καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.
ደግሞም (እንዲሁም ወይም እና) አንተ የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን።

ኃይለ ቃሉ የዘላለም ሕይወት ምንጭ ምንነት ነው። ምንድር ነው የዘላለም ሕይወት


ምንጭ? አብን እና ወልድን ማወቅ። አብ እውነተኛ አምላክ ብቻ ተብሎ፥ ኢየሱስ
የተላከው ተብሎ በእኩል ቀርበዋል። የዘላለም ሕይወት ምንጭ ሆነው አብንም
ወልድንም ማወቅ በእኩል ተጠቅሰዋል። ይህ ቃል ጸሎት መሆኑን አንርሳ። ሲጸለይ
የሚነገረው ሌላ ጊዜ ለሌላው ከሚነገረው ይልቅ ቀጥተኛ ወይም በቀጥታ የሚነገር
ነው።

11ኛ እኔ አምላክ ነኝ አለማለቱ

ይህ መሟገቻ የመጨረሻው ነው፤ በጠቅላላ ሳዲቅ ያቀረባቸው ነጥቦች 12 ናቸው


ሁለቱን ተመጋቢ መሆን እና ማንቀላፋት የሚሉትን በአንድ ስለመለስኳቸው ነው 11
የሆኑት። የመጨረሻው ነጥብ ይህ፥ ‘አምላክ ነኝ ብሎ ባለመናገሩ’ የተባለው ነው።

አምላክ ነኝ ብሎ ባለመናገሩ ዒሳ አምላክ አይደለም የሚለው እጅግ ብዙ ጊዜ


የሚጠቀስ እና ግን ደካማ የሆነ መከራከሪያ ነው። ሳዲቅ ኢየሱስ፥ ‘አምላክ ነኝ መች
አለ?’ ብሎ አለማለቱን ተናግሮአል። ይህቺኛዋ በአምላክነቱ ላይ የተቃጣች ጥፊ
ስለሆነች ጥቂት በስፋት አንመለከታታለን። ብዙ ጊዜ ከብዙ ሙስሊሞች እንደ ሰልፍ
እየተከታተለ የሚመጣ አንድ ጥያቄ አለ፤ ያም፥ ‘ኢየሱስ እርሱ፥ 'እኔ አምላክ ነኝ፤
68
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አምልኩኝ፤ ስገዱልኝ’ ብሎአል ወይ? መቼ ነው እንደዚህ ያለው? የትጋ ነው እንደዚህ


ያለው? እኔ እምላክ ነኝ፤ አምልኩኝ ብሎ ቃል በቃል የተናገረበትን ቦታ አሳዩኝ።'
የሚል ነው። አንዳንዶቹ ሲወራረዱ፥ ‘እኔ እምላክ ነኝ፤ አምልኩኝ ብሎ ቃል በቃል
የተናገረበትን ቦታ አሳዩኝና እኔ ክርስትና እነሣለሁ።' የሚሉም አሉ።

ይህ አቀራረብ ኢየሱስ፥ 'አምላክ ነኝ' አላለምና አምላክ አይደለም ለማሰኘት ግን


ጉልበት የሌለው አቀራረብም ድምዳሜም ነው። ለዚህ ሙግት፥ እንደ ጥያቄው
አቀራረብ፥ በቀላሉ፥ ‘ኢየሱስ፥ እኔ አምላክ አይደለሁምና አታምልኩኝ፤ አትስገዱልኝ'
ብሎስ መቼ ተናገረ? የትጋ ተናገረ? እንዲህ ስላልተናገረ አምላክ ነው ማለት ነው።’
በሚል አጭር አጸፋ መመለስም ይቻላል። ለዚህ ነው ጉልበት የሌለው አቀራረብም
ድምዳሜም ነው ያልኩት።

አምላክ አይደለሁም መች አለ? ሲባልም፥ ‘እኔ ሰው ብቻ ነኝ እንጂ ሌላ ምንም


አይደለሁም፤ ረሱሉ አላህ ብቻ ነኝ፤ የምሞትና የማልነሣ ነኝ መች አለ?’ እንደ ማለት
ነው። እንዲህ ያለውን ሙግት ለማቅረብ መነሻ መሆን ያለበት ያላለው ሳይሆን ያለው
ነገር ነው። ያላለውማ ብዙ ነገር አለ። ‘አምላክ ነኝ መች አለ?’ ባልነው መንገድ፥ ‘እኔ
ግመል ነኝ’ አላለምና ኢየሱስ ግመል ነው ማለት ወይም ‘እኔ ብራና ነኝ፤ ወይም ፍየል
ነኝ፤ ወይም ከብት አርቢ ነኝ፤’ አላለምና ብራና፥ ወይም ፍየል፥ ወይም ከብት አርቢ
ነው እንደማለት ነው፤ ይህ ደካማ መነሻ ነው። ደካማ መነሻ ብቻ ሳይሆን ወደተሳሳተ
መድረሻ የሚመራም ነው። ያላለውንና ያላለው ላይ ሳይሆን ወይም ያልሆነው ላይ
ሳይሆን የሆነውን ነው መግለጥና የሆነው ላይ ማተኮር ያለብን።

ኢየሱስ፥ 'እኔ አምላክ ነኝ፤ አምልኩኝ፤' ብሎ በቀጥታ መናገሩ በመጽሐፍ ቅዱስ


አልተጻፈም። እንዲህ ቢል ኖሮ ይህ አቀራረብ ወይም ይህንን ማለቱ አይሁድ ኢየሱስን
በተሳሳተ መልኩ እንዲያዩትና በማንነቱ እንዳይቀበሉት የሚያደርጋቸው ነው።
ኢየሱስ፥ 'እኔ አምላክ ነኝ፤ አምልኩኝ' ብሎ እያስተማረ ቢመጣ በአይሁድ መረዳት
ኢየሱስን እንደ አብ መውሰድ ሊሆን ነው። ኢየሱስ ደግሞ ወልድ እንጂ አብ
አይደለም። እግዚአብሔርም ሥላሴ እንጂ ነጠላ አንድ (ወይም ተውሂድ ወይም በስነ
መለኮት ሞናድ) አይደለም። ስለ እርሱም ሆነ ስለ ሥላሴያዊው ስነ መለኮት
ትክክለኛው መረዳት እንዲኖራቸው እርሱ ወልድ መሆኑን እና አብም አብ መሆኑን
ነው ደጋግሞ ያስተማረው። በግልጽና በዝርዝር ኢየሱስ ይህንን አስተምሮአል። ይህ
እውነት የገባቸው ገብቷቸዋል። የገባቸው ሲሰግዱለትም ሆነ ስለ እርሱ እውነቱን
ሲመሰክሩ አላገዳቸውም። እኔ አምላክ አይደለሁም፤ እኔ ስግደት አልቀበልም፤
አትስገዱልኝ ብሎ አልተከላከለም።

ኢየሱስ ራሱን ሰው ብቻ ሳይሆን ከሰውም በላይ መሆኑን አሳውቋል። ለነገሩ አምላክን


የምናውቀው፥ ‘አምላክ ነኝ! አምላክ ነኝ! ውደቁልኝ! ስገዱልኝ!’ በማለቱ ብቻ
አይደለም። ሳይሆኑ ውደቁልኝ ስገዱልኝ የሚሉ አሉ። እንዲያ ስላሉ ናቸው ማለት

69
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አይደለም። ባይልስ? ሳይልስ? ማወቅ ይቻላል? በትክክል ይቻላል። አንድ ሰው ስለ


ራሱ፥ ‘ሰው ደብዳቢ ነኝ፤ ጥፍር ነቃይ ነኝ! ነፍሰ ገዳይ ነኝ!’ እያለ ሳያውጅ፥
እየደበደበና እያሰቃየ፥ ጥፍር እየነቀለና እየገደለ ቢዞር፥ እና ሰዎች ያንን ሰው፥ ያንን
እንደሚያደርግ አውቀው፥ 'ይህ ክፉ፥ ጨካኝ፥ አረመኔ፥ ወይም ነፍሰ ገዳይ!' ቢሉት
ተሳስተዋል? አልተሳሳቱም። ይህ ሰው በአፉ አላለም፤ በድርጊቱ ግን ብሏል። ሌላ ሰው
ደግሞ፥ በሉቃ 10 እንደተጻፈው እንደ ደጉ ሳምራዊ፥ ከመስመሩ ወጥቶ ችግረኞችን
እየረዳ፥ በጎ እያደረገ፥ የተራቡትን እያበላ፥ የተጠሙትን እያጠጣ፥ የታረዙትን
እያለበሰ፥ የታመሙትንና የታሰሩትን እየጎበኘ፥ በጎ እያደረገ ቢዞር፥ ይህም ሰው ስለ
ራሱ ምንም ጡሩምባ ባያስነፋ ባይለፍፍ፥ ሰዎች ይህንን ሰው፥ ‘ምግባረ ሰናይ፥ ገባሬ
ሰናይ፥ ደግ አድራጊ፥ በጎ አድራጊ' ቢሉት ተሳስተዋል? አልተሳሳቱም። ሰውየው ያንን
ነዋ! ቃላችን ብቻ ሳይሆን ድርጊታችንም ማንነታችንን ይገልጠዋል።

በዚህ ዓይነት አንዱ መጥቶ አምላክ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም ሊያደርግ የማይቻለውን


ነገር ቢያደርግስ? ሰዎች ኢየሱስን አምላክ ወይም ጌታ ቢሉት ሰምተውና አይተው
ነውና አልተሳሳቱም። የኢየሱስ አምላክነት በወንጌላት ውስጥ በገሃድ ይታያል።
ኢየሱስ አምላክ የመሆኑ ወይም የአምላክነቱ ሌላ አስረጅ የሚሆነው አምላክ ብቻ
ሊያደርጋቸው የተገቡ ነገሮችን፥ ወይም ሰው ሊያደርጋቸው የማይችላቸውን ነገሮች
ማድረጉ ነው። ተአምራትን ማለቴ አይደለም። ተአምራትን ማድረግ የአምላክ ችሎታ
ቢሆንም እግዚአብሔር በሰዎች አማካይነትም ተአምራትን በማድረጉ እዚህ
አልጠቅሰውም። ነገር ግን፥ የአምላክ ብቻ ሥልጣን የሆኑ እና ኢየሱስ ያደረጋቸውና
የተቀበላቸው አሉ። ጥቂቱን እንይ፤

ሀ. ኃጢአትን ይቅር ማለቱ፥ (ማቴ. 9፥2-5፤ ሉቃ. 7፥48)፤ ይህ የበደሉንን ይቅር


ማለት አይደለም። ያንን እኛም እናደርጋለን። ግን ጠቅላላውን በደል፥ ኃጢአት ይቅር
ማለት ወይም መማር ወይም ማስተስረይ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ማንም
የማያደርገው ነው።

ለ. ጌታ ተሰኝቶ ስግደት ሲቀርብለት መቀበሉ። ማቴ. 14፥33፤ ሉቃ. 24፥52፤ ዮሐ.


20፥28፤ ራእ. 19፥10። እነዚህ እዚህ የቀረቡት ስግደቶች የአክብሮት ዝቅ ማለት ወይም
የሰላምታ ማጎንበሶች አይደሉም። ለአምላክ የቀረቡ የአምልኮ ስግደቶች ናቸው።
ኢየሱስ አምላክ ባይሆን ኖሮ እንዳያደርጉት ይከለክላቸው ነበር። አልከለከለም።
ተቀበለ እንጂ።

ሐ. ዘላለማዊ መሆኑ። በዮሐ. 8፥59 አይሁድ ኢየሱስን ሊወግሩት ድንጋይ


ማንሣታቸው ተጽፎአል። ለአይሁድ መውገር ማለት የሞት ቅጣትን መቅጣት ነው።
በሐዋ. 7 እስጢፋኖስን እንደወገሩት። እስጢፋኖስን የወገሩት ኢየሱስን በመስበኩ
ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን በአብ ቀኝ ቆሞ አየሁ በማለቱ ነው። እራሱን ከአብ ጋር
ያስተካከለውንማ እንዴት አይወግሩት! ይህ በቀኝ መቆም ኢየሱስንና አብን

70
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ማስተካከል ወይም ኢየሱስን እግዚአብሔር እንደሆነ መግለጥ ነው። አይሁድ


ኢየሱስን ለመውገር ድንጋይ ያነሡት ኢየሱስ፥ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ
ነኝ ስላላቸው ነበር (ቁጥር 58)። ከቁጥር 56 ጀምሮ እንዲህ ይላል፤ አባታችሁ
አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም፦ ገና
አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም፦ እውነት እውነት
እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ
አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።

ይህ እኔ ነኝ የሚለው ሐረግ ዘላለማዊነቱን መናገሩ ሲሆን ዘላለማዊነት ደግሞ


የመለኮት ብቻ ባህርይ ነው። እርሱ ዘላለማዊ አምላክ መሆኑን ቀደም ሲል ዮሐ. 1፥1-
2ን ስናይ ተመልክተናል። በዮሐ. 1፥1-2 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም
በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው
በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ይላል። ከዚህ ክፍል የምንገነዘበው ቃል እግዚአብሔር
መሆኑን እና ይህም ቃል በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ እንደነበረ ሲሆን በዚሁ
ምዕራፍ ቁጥር 14 ይህ ቃል ሥጋ መሆኑ ተጽፎአል። ይህ ሥጋ የሆነው ቃል ኢየሱስ
መሆኑም ተብራርቶአል። ስለዚህ ይህ ሥጋ የሆነው ኢየሱስ ከዘላለምም የነበረው ቃል
ነው፤ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውና እግዚአብሔር የሆነው ነው።

መ. አምላክ ሲሰኝ አለማስተባበሉ። ሌላ ሁለተኛ ኢየሱስን ለመውገር ድንጋይ


የተነሣበት ጊዜም ነበረ። በዮሐ. 10፥33 አይሁድም፥ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤
ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው
መለሱለት። የሚል ቃል አለ። ጥቂት ጥቅሶችን ወደላይ ከፍ ብለን ስንመለከት አይሁድ
ሊወግሩት ድንጋይ እንዳነሡና ይህን ያደረጉትም፥ 'እኔና አብ አንድ ነን' በማለቱ
እንደሆነ እናነብባለን።

ከቁጥር 26 ጀምሮ እንዲህ ይላል፤ እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ


አታምኑም። በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም
የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም
አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው
ማንም አይችልም። እኔና አብ አንድ ነን። አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ
አነሡ። ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው
ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው። አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ
አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው
እንጂ ብለው መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት
ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና
እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ
ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ
ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ

71
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ
ሥራውን እመኑ።

ኢየሱስ የተናገረው ንግግር ለአይሁድ አሻሚና አደናጋሪ አልነበረም። ምን ማለቱ


መሆኑን እነርሱ አልጠየቁትም፤ እርሱም አላስተባበለም። እጅግ በጣም ግልጽ ነው።
አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ሲሉት፥ መች ወጣኝ?
መቼ ነው ያልኩት ብሎ ማስረዳት አይችልም ነበር? ይችል ነበር። አለ? አላለም።
ለምን? አምላክ ነዋ! ኢየሱስ የመለሰላቸው ይህንን እውነት የሚያጠነክር እንጂ
የሚያስተባብል አይደለም። ለአይሁድ ኢየሱስ ያለውና የተናገረው ገብቶአቸዋል።
ሊወግሩት የፈለጉትና ኋላም እንዲሰቀል ያደረጉትና ያስደረጉት ስለዚህ ነው። ስለ
ምን? አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ እንዳሉት፥ ሰው
ሳለ ራሱን አምላክ ያደረገ ነው የመሰላቸው። የመሰላቸው ለእነርሱ ሳይሆን የሆነ
መሰላቸው እንጂ እውነቱ ግን ያንን የጠረጠሩትን ነገር ነው። እርሱ አምላክ ነው።

ዮሐ. 5፥18 እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን


ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ
ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ይላል፤ ሊገድሉት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፈለጉ፤
እስኪገድሉት ድረስም መፈለጋቸውን አላቆሙም፤ በመጨረሻም ገደሉት፤ ለምን?
ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር በማስተካከሉ። ራሱን ማስተካከሉ አምላክነቱ ነው።

የኢየሱስ አምላክነት ከወንጌላቱ ባሻገርም በተደጋጋሚ የተነገረ እውነት ነው። በሐዋ.


20፥28 ቤተ ክርስቲያን፥ በገዛ ደሙ የዋጃት የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን
ተብላለች። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ
ተጠንቀቁ። ይላል ቃሉ። የገዛ ደሙ የተባለው የተዋጀችበት ደም ነው። ደሙ ደግሞ
የእግዚአብሔር ደም ተብሎአል። የገዛ ማለት የራሱ ማለት ነው። በገዛ ደሙ ማለት
በራሱ ደም ማለት ነው። ይህ ከሆነ የፈሰሰው ደም የእግዚአብሔር ደም ነው ማለት
ነው። በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደም የማን መሆኑ ገሃድ ነው። የኢየሱስ ደም ነው። ያ
ደም የኢየሱስ ከሆነና እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በገዛ ደሚ ከዋጃት፥ ያ ደም
ደግሞ የኢየሱስ ደም ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

ይህ የደም መፍሰስ ነው ኢየሱስ አምላክ ሳለ ሰው የሆነበት ምክንያት። ደም


እንዲኖረው ሰው መሆን አስፈለገው። የብዙዎች ኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ
የሚወገድበት ሥርዓት ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ መስዋዕትን ከፍቅር
የተነሣ አዘጋጀ። ደም ይፈስስ ዘንድ አምላክ ሰው መሆን ኖረበት፤ ደግሞም ምንም
ኃጢአት የሌለበት መሆን ተገባው፤ እንዲያው ሰው ብቻ ከሆነ ሁሉ ኃጢአትን
ሠርተዋልና ንጹህ መሆን ባልቻለም ነበር። ደግሞም ለራሱ ኃጢአት ብቻ ነበር
የሚሞተው እንጂ ሌላውን መወከል አይችልም። ስለዚህ ሰው ብቻ ሳይሆን ሰው የሆነ

72
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አምላክ መሆን ኖረበት፤ ይኸውም በምትክነት የሚስሠዋው ቁጥር ስፍር ለሌለው


ኃጢአትና እጅግ ብዙ ለሆኑ ኃጢአተኞች በመሆኑ ነው።

በሌሎችም ስፍራዎች ኢየሱስ በግልጽ አምላክ ተሰኝቶአል፤ ለምሳሌ፥ ቲቶ 2፥13፤ ዕብ.


1፥8፤ 2ጴጥ. 1፥1። እዚህ የተጠቀሰው የአምላክነት ስያሜ የመለኮት ብቻ፥ የአምላክ
ብቻ ሥልጣን ነው። እነዚህን ካደረገ፥ ይህንን ከሆነ፥ ኢየሱስ አምላክ ነው። አምላክ
ከተባለም አምላክ ነው። ልክ በነጥቦች የሚሠሩ ስዕሎችን አይተን ምንነቱን
እንደምናውቅ፤ ይህንንም እናውቃለን፤ በመጀመሪያ የምናየው ነጥቦች ብቻ ነው፤
ቁጥሮችን ተከትለን ነጥቦቹን ስናገናኝ ግን ስዕሉ ፍጥጥ ብሎ፥ ግልጥ ሆኖ ይታያል።
ስለ ክርስቶስ የሚናገሩትን እነዚህን ነጥቦች ስናገናኝ የምናገኘው እውነት፥
የሚያስተጋባ፥ ጎልቶ የሚደመጥ፥ ‘አዎን፥ ኢየሱስ አምላክ ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር
ወልድ ነው፤’ የሚል ነው።

የመስቀል ሞቱ
የኢየሱስ በመስቀል መሞት ዒሳ ኢየሱስ አለመሆኑን አረጋጋጭ ነው። ባለፉት ክፍሎች
ዒሳ ፍጡር ነው፤ አምላክ አይደለም በማለት መሐመድ ሳዲቅ ላቀረባቸውን 12 ነጥቦች
ምላሽ ስሰጥ የምላሼ ዋና አሳብ፥ እርሱ ዒሳ የሚለው ሰው የመጽሐፍ ቅዱሱን
ኢየሱስን አለመሆኑን ማሳየት ነው። ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠ ወይም ሥጋ የለበሰ
አምላክ መሆኑን በስፋትና በዝርዝር አይተናል። ከላይ ካየናቸው ብዙ ገጾች አሳቦች
እነዚህ ሁለቱ፥ የቁርኣኑ ዒሳ እና የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በቅርበት ሲፈተሹ
ፈጽሞም አንድ እንዳልሆኑ ማረጋገጥ ከባድ አይሆንም። እስካሁን ያየናቸው ነጥቦችም
ያንን አሳይተውናል። ቀጥሎ የምንመለከተው ነጥብም ይህንን ይበልጥ ያረጋግጥልናል።

ቀጥሎ የምናየው ዋና አሳብ ሥጋ የለበሰበት ዋና ምክንያት የሆነው የኢየሱስ መሰቀሉና


መሞቱ፥ ከሙታንም መነሣቱ ነው። በቁርኣን ኢየሱስ አልተሰቀለም፥ አልሞተም፥
አልተቀበረም፥ አልተነሣም። ስለዚህ፥ ይህ ብቻውን እንኳ ኢየሱስ ዒሳ አለመሆኑን
በአሥር ጣት ፈርሞ ይመሰክርልናል። እዚህ መመልከት የምንጀምረው ይህ የሞቱና
የስቅለቱ ጉዳይ ነው።

የሙስሊም ተከራካርያንና እዚህም የሳዲቅ ነጥብ፥ ‘ዒሳን አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትም’


ነው። የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ባይሆንም፥ ሳዲቅም ሆነ ሌሎች
ሙስሊሞች ዒሳ የሚሉት ኢየሱስን ስለሆነ፥ ይህ፥ ‘ኢየሱስ አልሞተም አልተሰቀለም’
የሚሉት ነገር ፈጽሞ ውሸት መሆኑንና የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በእርግጥም
መሰቀሉንና መሞቱን፥ መነሣቱንም ከቃሉ እናያለን። ከቃሉ ብቻ ሳይሆን፥ ይህ

73
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

እውነት ከቃሉ ውጪ ታሪክም የዘገበው ጉዳይ መሆኑንም እናያለን። ከዚህ ጋር


በቀጥታ ባይገናኝም በተዘዋዋሪ ስለሚገናኝ አስቀድሜ ሦስት ነጥቦችን እግረ መንገድ
በማየት ልጀምር።

አንደኛው ነጥብ፥ ሳዲቅ፥ ‘የውርስ ኃጢአት ብሎ ነገር የለም፤ የምትክ ሞትም የለም፤’
ብሏል። በቀጥታም ባይሆን ግንኙነቱ የኢየሱስ ሞት ምትካዊ ሞት በመሆኑ ነው።
ሌላው ቢቀር፥ ኢየሱስ ለኛ ሞተ የሚባለው ነገር ወደ ጎን ቢቀመጥ፥ ለኛም አልሞተም
ቢባል፥ ኢየሱስም በመስቀል ላይ አልሞተም ብንል፥ ቁርኣኑ እንደሚለው ኢየሱስ
አልተሰቀለም፤ አልሞተም ብለን ብንወስድ ያልሞተበት ምክንያት አለ አይደል? ይህንን
አንርሳ። እነሱ አልሞተም ነው የሚሉት። ለምን አልሞተም? እንዴት አልሞተም ሲባል
የሚሰጡት ምክንያት ራሱን የሚገድል ምክንያት ነው።

‘ዒሳ ካልሞተ፥ ያልሞተው በምን ምክንያት ነው?’ ቢባል፥ ‘በምትኩ ሌላ ሰው ተሰቅሎ


ሞቶ ነው፤’ ይላሉ። ይህንን ጉዳይ እናየዋለን፤ ግን የምትክ ሞት የለም ማለትና በዒሳ
ምትክ ሌላ ሰው፥ እርሱን የመሰለ፥ በእርሱ የተመሰለ ሞተ ከተባለ እርስ በርሱ
አይጋጭም ይህ አባባል? ያ ምትክ ባይሞትና ባይሰቀል ኖሮ እኮ ኢየሱስ ይሰቀል
ነበር። አይደል? ራሱን በራሱ የሚገድል ሙግት ነው ያልኩት ይህንን ነው።

እንደዚህ ያሉ ሌሎች ምሳሌዎችንም መጥቀስ እንችላለን። አንድ ሁለት ልጨምር፤


ለምሳሌ፥ በይስሐቅ (እነሱ እስማኤል ነው የሚሉት፤ ይሁን ደኅና፥ በእስማኤል
እንበለው፤ በእስማኤል) ፈንታ የታረደው በግ ምትካዊ አይደለም? ወይስ ነው? በጉ
ባይታረድ ይስሐቅ (ወይም እስማኤል) ይድን ነበር? አይድንም፤ ስለዚህ ምትካዊ ሞት
ብሎ ነገር የለም ማለት ይቻላል? መልሱ ግልጽ ነው። ሌላ አንድ ምሳሌ ልጨምር።
በሐዲስ ውስጥ ደግሞ ሙስሊሞች ከጀሃነም እንዲወጡ በእነርሱ ፈንታ ካፊሮች
(ክርስቲያኖች ማለት ነው) ወደ ሲዖል ይጣሉና እነሱ ወደ ጀነት ይገባሉ ይላል።
ሙስሊማን ከገነት እንዲወጡ ካፊሩን ወደ ጀሃነም መጣላቸው ምትካዊነት አይደለም?
እንዲህ ያሉ ምትካዊ ሞትና ቅጣቶችን ማውሳት ይቻላል። የምትክ ሞት የለም ያለው
ራሱን መጣላቱ እንደሆነ እንዲታይ ነው።

ሁለተኛው ነጥብ፥ ትልቅ ጉዳይ አይደለም፤ የእግረ መንገድ ነጥብ ነው። ደጋግሞ፥ እነ
አዳም ቅጠል በሉ ይላል፤ የምን ቅጠል እንደሚያወራ ግልጽ አይደለም። ጫት የቃሙ
አስመሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስም ቁርኣንም ላይ ጫት ቃሙ፤ ወይም ቅጠል በሉ
አይልም። አል አዕራፍ 7፥22

ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ እፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው፤ ከገነት ቅጠልም


በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመር፤

74
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ነው የሚለው። ከየት አመጣው? ሱረቱ ጣሃ 20፥121

ከርሷም በልሉም፤ ለነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፤ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ


ይለጥፉ ጀመር

ከርሷም የተባለው በቁጥር 120 ከተጻፈችው ዛፍ ማለት ነው፤ ቅጠል አልበሉም።


በግልጽ የተጻፈው ፍሬ መብላታቸው ነው። ይህ አሳብ በቀጥታ ባይገናኝም እዚህ
ለማንሣት የፈለግሁበት ምክንያት የዔድን ገነት ክስተት በአዳም በኩል የሰው ልጆች
ሁሉ ውድቀት መሆኑን እንድናስታውስ ነው። ይህ ከላይ ካየነው የውርስ ኃጢአት ጋር
የተቆራኘ ሆኖ ሁላችንም በአዳም ውስጥ ነበርንና፥ ‘አዳም ለራሱ ለብቻው ነው
የወደቀው፤’ ማለት እንደማንችል ለማመልከት ነው።

ሦስተኛው ነጥብ፥ ይህም የእግረ መንገድ ነጥብ ነው። እነአዳም ያኔ የወደቁት


በራሳቸው ኃጢአት ስለሆነ ቅጣታቸውም የራሳቸው ብቻ ነው፤ የያኔዎቹ ያደረጉት
እኛን አይወክለንም ያለበት ስሕተት ነው። ስለያኔዎቹ፥ ስለቀድሞዎቹ ሲናገር
ከአሁኖቹ ጋር አንድና እኩል መሆንን ተናግሮ ነበር። ‘ለምን እኩል አልሆኑም? ያኔ
ሌሎቹ ብዙ መቶ ዓመት ከኖሩ ዛሬ ለምን አይኖሩም?’ ሲል የራሱን አሳብ መቃረኑ
መሆኑን አላስተዋለም። ያኔ ያለው መቼን ነው? ዔድን ገነት የኖሩበትን ጊዜ ከሆነ
በዔድን ገነት የኖሩት ከሰዎች አዳምና ሔዋን ብቻ ነበሩ። የቀሩት በሙሉ የኖሩት
ከገነት ውጪ ነው። የቀሩት ሁሉ የተወለዱት ከውድቀት በኋላ ነው። ደግሞም
ዕድሜያቸው እስከ ኖኅ ዘመን ድረስ እጅግ ረዣዥም ነበረ። ‘የራሱን አሳብ መቃረኑ
መሆኑን አላስተዋለም’ ያልኩት፥ የዕድሜ ማጠር በቀጥታም በተዘዋዋሪም የውድቀት
ውጤት ከሆነ፥ ሰው ደግሞ አልወደቀም፥ ሲፈጠርም ኃጢአት የለበትም ካለ
በተቃራኒው እንዲያውም የሰው ዕድሜ ከጥፋት ውኃ በፊት እንደነበረው መሆን
ነበረበት እንጂ! ዛሬም ስምንት እና ዘጠኝ መቶ ዓመት የሚኖሩ ሰዎች መኖር
ነበረባቸው።

የሰው ዕድሜ ያጠረው ከጥፋት ውኃ በኋላ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ የምድር ስነ


ምሕዳር ፈጽሞ ተለወጠ። የሰማይ መስኮቶች ሲከፈቱ (ምናልባት ከozone በላይ
ያለው የበረዶ ግግር ሳይሆን አይቀርም) እና የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሲነደሉ ምድር
እንደነበረችው ያለች አልሆነችም። የሰው ዕድሜ ያጠረው ከጥፋት ውኃ ወዲህ ነው።
ይህ ረጅም ዕድሜ ኃጢአተኛ ስላለመሆን መከራከሪያ መሆን አይችልም። የሰው
ዕድሜ ማጠር በተዘዋዋሪ የውድቀት ውጤት ነው። የወደቀ ሰው ደግሞ ቤዛ
ያስፈልገዋል። የክርስቶስ ሞት ያ ቤዛነት ነው።

ወደ መስቀል ሞቱ እንምጣ። የክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ


ነጥብ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ልጥቀስ ብሎ ኢየሱስ ስላለመሞቱ ሳዲቅ የጠቀሰው
ዮሐ. 7፥32-34ን ነው። ፈሪሳውያንም ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጕሩ

75
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሰሙ፤ የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ሊይዙት ሎሌዎችን ላኩ። ኢየሱስም፦ ገና


ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ። ትፈልጉኛላችሁ
አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አለ። የሚለው ነው።

ማስረጃው በቃ ይኸው ነው? ሳዲቅ ኢየሱስ ላለመሞቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ


አቀርባለሁ ሲል፥ አልገደሉትም አልሰቀሉትም የሚል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያቀርባል
ብለን እንድንጠብቅ በሚያስደርግ መልኩ ነው። ‘አልሰቀሉትም; አልገደሉትምም፤’
የሚል ወይም ያንን የሚመስል ያወጣል ብዬ ጠብቄ ነበር። አላወጣም። ለምን? ከየት
ያወጣል? ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ? እንዴት አድርጎ? መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላው
የሚያመለክተው ወዴት ሆነና? መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ተሰቀለ፥ ሞተ፥ ተነሣ ይላል
እንጂ አልሰቀሉትም አልገደሉትም አይልም። አልሰቀሉትም አልገደሉትም ያለው አንድ
ብቻ ነው፤ ያም ከተሰቀለ ከ700 ዓመታት በኋላ የተጻፈው በቁርኣን የሚገኘው ጥቅስ
ነው፤ በሱረቱ አል-ኒሳእ 4፥157-158 ይገኛል።

4፥157 ፦ እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው


(ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ
እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት፣ ከርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፤ ጥርጣሬን
ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ በእርግጥም አልገደሉትም።

4፥158 ይልቁኑስ፣ አላህ ወደርሱ አነሳው፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

ሱረቱ አል-ኒሳእ ከመዲና ሱራዎች አንዱ ነው። የመዲና ሱራዎች የኋለኞቹ ሱራዎች
ናቸው። ይህንን አሳብ ቀደም ባለው ክፍል እንደጠቀስኩት በቁርኣን መሻር የሚባል
ድንጋጌ አለ፤ (በእንግሊዝኛ abrogation ይሉታል፤) የኋለኞቹ የቀደመውን የሚሽሩት
ናቸውና የመዲና ሱራዎች የመካ ሱራዎችን ይሽራሉ። ይህ የመዲና ሱራ ነው።
ክርስቲያኖችንና አይሁድን ለማጥቃት ከተሰነዘሩትና እምነታቸውን ለማጠልሸትና
መጽሐፎቻቸውን ለማጥላላት የተነገሩት አያዎች (አንቀጾች) ያሉባቸው ሱራዎች ደግሞ
የመዲና ሱራዎች ናቸው። ሙስሊሞች መጽሐፎቹን አናጥላላም ሊሉ ይችላሉ፤ ግን
የሚለውን አለመቀበል እኮ ማጥላላትና ማዋደቅ ነው። ያ ብቻ አይደለም፤ መሻር እኮ
መከለስና መበረዝም ነው። ይህንን ለመቀበል አያስቡም።

መጽሐፉን፥ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቅሱታል፤ ነገር ግን ስሕተታቸውን


የሚያሳየውን እውነት ከመጽሐፉ አውጥተው ሲያሳዩአቸው፥ ‘ይህኛው በኋላ
የተጻፈው፥ የተበረዘው፥ የተከለሰው ነው’ ይላሉ። በመካና በመዲና ሱራዎች መካከል
የተደረገውን ብረዛ ግን መበረዝ አይሉትም። የሚገርመው እውነት ግን፥ በኢስላም
ነቢይ በሙሐመድ ዘመን የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ፥ ቀደም ሲል ለማሳየት በትንሹ
እንደሞከርኩት ከዚያም በፊት በነበሩት መቶዎች ዓመታት የነበረው መጽሐፍ ቅዱስና
ዛሬ በእጃችን የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ተመሳሳይና ያልተበረዘ መሆኑን እናውቃለን።

76
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተበረዘ ቢሆን ኖሮ የመጽሐፉ ሰዎች የኢንጅል ባለቤቶች በውስጡ ባለው ሕግ


ይፍረዱ ብሎ የኢስላም ነቢይ አይናገርም ነበር። ለምሳሌ፥ በሱረቱ ዩኑስ ቁጥር 94-
95 የተጻፈው በዚያን ጊዜ በእጃቸው የነበረውን ወይም አይሁድና ክርስቲያኖች
ያነብቡ የነበረውን መጽሐፍ የጥርጣሬያቸው ማስወገጃ መሆኑን የሚናገር መጽሐፍ
መሆኑን ነው።

10፥94 ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾን እነዚያን ከአንተ በፊት


መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፤ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፤
ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን። 95 ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትኹን፤
ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና።

በሱረቱ አል ማኢዳህ ደግሞ እንዲህ ይላል፤

5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ፤ አላህም ባወረደው


የማይፈርድ ሰው፣ እነዚያ አመጠኞች እነርሱ ናቸው።

5፥68 እላንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጅልን፣ ከጌታችሁም ወደናንተ


የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም
በላቸው፤ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው ቁርአን ከነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክሕደትን
በእርግጥ ይጨምርባቸዋል፤ በከሐዲያን ሕዝቦችም ላይ አትዘን።

የኢንጅል ባለቤቶች ክርስቲያኖች ናቸው፤ በወንጌሉ ውስጥ በተጻፈው መፍረድ


ይችላሉም እንዲፈርዱና እንዲበይኑም ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ደግሞም ኢንጅል
ያልተሳሳተ መሆኑን እነዚህ አባባሎች ይመሰክራሉ። የተሳሳተ፥ የተበረዘ፥ የተከለሰ፥
የተበላሸ ቢሆን ኖሮ በመጽሐፉ እንዲፈርዱ ባልተናገረም ነበር።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አናቅጽ የሚያሳዩት በዚያን ጊዜ የነበረውን፥ በእርሱ ዘመን


የነበረውን መጽሐፍ ቅዱስ የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ ተቀብሎት እንደነበር ነው።
የአይሁድ እና የክርስቲያኖች መጻሕፍትን ተቀባይነት የሚጠቅሱ ብዙ ሱራዎች አሉ፤
ጥቂት እነሆ፥ 2፥40-42 እና 285፤ 3፥3-4፥71፥93፤ 4፥47 እና 136፤ 5፥47-49፤ 6፥
91፤ 6፥114-115፤ 10፥37፤ 10፥94፤ 18፥27፤ 21፥7፤ 29፥46፤ 35፥31፤ 46፥12። እነዚህ
ሁሉ አንቀጾች በሙሐመድ ዘመን የነበረው የአይሁድ እና የክርስቲያኖች መጻሕፍት
ትክክል መሆናቸውን ያወሳሉ እንጂ ከቶም መሳሳታቸውን፥ መጥፋታቸውን፥
መለወጣቸውን፥ መበረዛቸውን፥ መከለሳቸውን አይናገሩም። እንዲያውም ቃላቶቹ
የማይለወጡ መሆናቸውን መስክሮአል፤ ሱረቱ አል ክሀፍ ይህን ይላል፤

18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ለቃላቶቹ ለዋጭ


የላቸውም፤ ከርሱም በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም።

77
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም ማለት ለዋጭ የላቸውም ነው። አራት ነጥብ። መጽሐፉን
መለወጥ የሚችል ማንም ሊኖር አይችልም። ይህ መጽሐፍ ያኔ ሙሐመድ እርሱ
የተቀበለው ከነበረ አሁን ለምን አይቀበሉትም? የዚህ አጭር መልስ ከተቀበሉ ከሁለቱ
አንዱ ብቻ ትክክል መሆኑ የሚታይ ስለሆነና ያንን መገዳደር የሚችል ማረጋገጫ
ባለመኖሩ ነው። ወይ ተሰቅሏል ሞቷል ትክክል ነው፤ ወይም አልተሰቀለም አልሞተም
ትክክል ነው። ሁለቱም ትክክል መሆን አይችልም። አንዱ ከሌላው ጋር ተቃራኒ ነውና
ሁለቱም ትክክል አለመሆንም አይችሉም። ከሁለቱ አንዱ ብቻ ትክክል ነው። መቼም
ይህ መጽሐፍ ከኢስላም ነቢይ በኋላ ተለወጠ ወይም ተበረዘ እንዳይባል ከላይ
እንዳልኩት ያኔ የነበረውና ከዚያም በፊት የነበረው አዲስ ኪዳን ከአሁኑ ጋር ፍጹም
አንድ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ ሺህ፥ ከ25 ሺህ በላይ የጽሑፍ ቁራጮች ብቻ
ሳይሆኑ በሙሉ ይዘት የተደጎሱ መጽሐፎችም አሉ። አይቶ ማረጋገጥ የሚወድ በቀላሉ
ሊያይ እስከሚችል ድረስ የነዚህ ሰነዶች የሚነበብ ጽሑፋቸውና የሚታይበ፥ አካል
በቤተ መዘክሮችም፥ በምስል በኢንተርኔትም ይገኛል።

ወደ ጀመርነው ወደ ኢየሱስ አለመገደልና አለመሰቀል ስለሚናገረው በሱረቱ አል-ኒሳእ


4፥157-158 ስላለው ጥቅስ እንደገና እንምጣ።

4፥157 ፦ እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው


(ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ
እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት፣ ከርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፤ ጥርጣሬን
ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ በእርግጥም አልገደሉትም።

4፥158 ይልቁኑስ፣ አላህ ወደርሱ አነሳው፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ ብዙ ግጭቶች አሉበት። አንድ አምስት ያህል ጉልህ ግጭቶች
አሉበት። ከዚያም ሊበዙ ይችላሉ፤ ለኔ የታዩኝ አምስቱ እነዚህ ተራና አላፊ ሳይሆኑ
መሠረታዊ ስሕተቶችና ግጭቶች ናቸው።

አንደኛ፥ ‘እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን


በማለታቸው’ የሚለው ነው። አይሁድ መሢሕ ኢየሱስን ገደልነው አላሉም። ብለውም
አያውቁም። ሲጀመር አይሁድ ኢየሱስን መሢሕ ብለው አልጠሩትም። ጠርተውትም
አያውቁም። አይሁድ ኢየሱስን እንደ መሢሕ አይተውትም፥ ተቀብለውትም
አያውቁም። ከቶም አልተቀበሉትም። ቃሉም የሚለው፥ የሚያረጋግጠው
እንዳልተቀበሉት ነው። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
ነው፤ ዮሐ. 1፥11። እውነቱ አለመቀበላቸው ነው።

አይሁድ ሳይሞት በፊት፥ ‘አጋንንት አለበት፥ ሕዝቡን ያስታል፤ አሳች ነው’ ነበር
የሚሉት እንጂ መሢሕ ብለውት አያውቁም። ከሞተ በኋላም እንኳ፥ ‘ያ አሳች’ ነበር

78
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ያሉት፤ ሲኖር ሳይሆን፥ ከሞተ በኋላ እንኳ። ማቴ. 27፥63-66፤ ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች
በሕይወቱ ገና ሳለ፦ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን። እንግዲህ ደቀ
መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም፦ ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥
የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን
ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት። ጲላጦስም፦ ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ
እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው። እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው
መቃብሩን አስጠበቁ። ይህንን አይሁድ ያሉት ለጲላጦስ ነው። ያ አሳች ነው ያሉት፤ ‘ያ
መሢሕ፤ ያ የገደልነው መሢሕ’ አላሉም።

ግጭቱ ይህ ነው። አይሁድ መሢሕ ኢየሱስን ገደልነው አላሉም። መሢሕ ብለውት


አያውቁም። እርግጥ መሢህ ብለው የጠሩት አይሁድ አሉ። እነዚህ በጣም ጥቂት የሆኑ
የእርሱ ተከታዮች ናቸው። እነዚህ ደግሞ ገደልነው ብለው የሚፎክሩ አይደሉም።
አልገደሉትም፤ ከገደሉት ጋርም ተባባሪ አልነበሩም። ደግሞም ተከታዮቹ እንጂ ገዳዮቹ
ሊሆኑ አይችሉም። ከዚህ በላይ ደግሞ፥ ይህ የተጠቀሰው ቃል፥ ‘እኛ የአላህን
መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን’ አሉ የሚለው የሌለና ተፈልጎም
የማይገኝ የተፈጠረ ቃል ነው። አንድም ቦታ፥ ‘እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ
አልመሲሕ ዒሳን ገደልን’ የሚሉ አይሁድ መኖራቸው የተጻፈበት ታሪክ አልተገኘም።
ይህ ተጽፎ የተገኘው ከ700 ዓመታት በኋላ ከተጻፈው ቁርኣን ውስጥ ብቻ ነው።

ሁለተኛ፥ በዚህ አንቀጽ ውስጥ ያለው ሌላው ውስጣዊ ችግር እነዚህ፥ ‘እኛ የአላህን
መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን’ ያሉት ሰዎች መረገማቸው ነው።
ገደልን በማለታቸው (ረገምናቸው)፤ ‘ረገምናቸው’ የሚለው በቅንፍ ውስጥ ሆኖ ነው
የተጻፈው። ይህ ማለት የተጨመረ ቃል ነው ማለት ነው? ይሁን እንጂ፥ በቅንፍ
ሆኖም ግን ተጽፏል፤ ሰዎቹ ተረግመዋል ማለት ነው። ረጋሚው ማን ነው? እንደ
ጥቅሱ አሳብ አላህ ነው። አላህ ረጋሚም ነው ማለት ነው።

የሚረግመው ደግሞ ወንጀለኞችን ሳይሆን ምንም ጥፋት ያላጠፉትን ንጹሐን ሰዎች


ነው። ንጹሐን መሆናቸውን በቀጣዩ ነጥብ እንመለከታለን። እንደዚህ ጥቅስ አሳብ
እነዚህ ሰዎች አልሰቀሉትም፤ አልገደሉትም። ታዲያ ካልገደሉት ለምን ተረገሙ?
አለመግደላቸውን እያወቀ፥ አለመስቀላቸውን እያወቀ አላህስ ለምን ነው የረገማቸው?
ገደልነው ስላሉ ነው የተረገሙት? አለመግደላቸውን አያውቅም ኖሯል ረጋሚው?
ወይስ ሳይገድሉት ገደልነው በማለታቸው ነው የረገማቸው?

79
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሦስተኛ፥ የመምሰሉ ጉዳይ ነው። ይህ ግዙፍ ውስጣዊ ተቃርኖ ነውና በመጠኑ ሰፋ


አድርገን እንየው። ነጥቡ፥ ‘ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ’ የሚለው ነው።
የእንግሊዝኛው የዩሱፍ አሊ ትርጉም፥ That they said (in boast), "We killed
Christ Jesus the son of Mary, the Messenger of Allah.;- but they
killed him not, nor crucified him, but so it was made to appear
to them, and those who differ therein are full of doubts, with no
(certain) knowledge, but only conjecture to follow, for of a surety
they killed him not:- Nay, Allah raised him up unto Himself; and
Allah is Exalted in Power, Wise;- ይላል።

ተመሰለ ማለት መሰለ የሌላውን መልክ ያዘ ማለት ነው። የተገደለው በዒሳ ተመሰለ
ከተባለ፥ ይህ የተመሰለው ሰው ያንን ሰው አይደለም ማለት ነው። ካልሆነ ይህ ሰው
ያንን ሰው አለመሆኑን በመናገር፥ ራሱን ለመከላከል ምንም እርምጃ አይወስድም?
ልብሱን ሲገፍፉት፥ አካሉን ሲገርፉት፥ ሲጎስሙት፥ ሲከፉበት፥ ሲተፉበት፥
ሲያላግጡበት፥ ሲዘብቱበት፥ የእሾክ አክሊል ሲያደርጉበት፥ መስቀል ሲያሸክሙት፥
ሲሰቅሉት፥ አንድ ጊዜ እንኳ፥ ‘እኔ እሱ ሰውዬ አይደለሁም!’ ማለት አይችልም ነበር?
በተለይ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ፥ ‘የአይሁድ ንጉሥ ነህን?’ ብሎ ሲጠይቀው፥ ‘ኧረ እኔ
እሱን አይደለሁም!’ እንዴት አላለም? ‘አይደለሁም’ ብሎ በአንዲት ቃል ነጻ መውጣት
አይችልም ነበር? ወይስ መልኩ ሲቀየር ዱዳም ሆኖ ነበር? ‘እኔ ያንን ሰው አይደለሁም’
ብሎ መትረፍ እየቻለ አለማድረጉ ግዙፍ ውስጣዊ ግጭት ነው።

ይህ እንዲመስል የተደረገው ሰው ግን ማን ነው? ለዚህ የተለያዩ መላ ምቶች


ይቀርባሉ። ብዙዎች ያ በኢየሱስ የተመሰለው ማን ነው? ሲባሉ የአስቆሮቱ ይሁዳ ነው
ይላሉ። እሺ፤ ይህ የተመሰለው ይህንን፥ ‘እኔ እርሱን አይደለሁም’ እንዳይልም ተደረገ
እንበል፤ አልተናገረም እንበል። ግን ይህ የተሰቀለው የተናገራቸው ነገሮች ደግሞ አሉ።
ይህ ኢየሱስን ያልሆነ ሰው የተናገረውን ነገርስ እንዴት ተናገረ? ልብ እንበል፤ ኢየሱስ
ከያዙት ጊዜ ጀምሮ እስከ መስቀሉ ድረስ አፉ አልታተመም፤ አልተዘጋም። እርሱ
ኢየሱስ ራሱ መሆኑን የሚገልጡ ነገሮችንም ተናግሯል። ለምሳሌ፥ ካህናት ፊት ቀርቦ፥
ጲላጦስም ሲጠይቀው መልሷል፤ እናቱን ማርያምን፥ ‘እነሆ ልጅሽ’ ብሏታል። ሌላ
ሰው፥ ለምሳሌ፥ ተመሰለ የተባለው የአስቆሮቱ ይሁዳ፥ ማርያምን እንደዚያ ይላል?
ማለትስ ይችላል? የአስቆሮቱ ይሁዳ፥ ‘አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር
በላቸው’ ይላል? ወይስ ይህ የተመሰለው ሰው ይህንንም እንዲል ተደረገ? ተደርጎ ከሆነ
ማሳቱ አይበዛም? የተመሰለው የአስቆሮቱ አለመሆኑ ግልጽ ነው። የዚህኛው ይሁዳ
ታሪክና አሟሟቱ ደግሞ በግልጽ ተጽፎልን ይገኛል። የአስቆሮቱ ይሁዳ በዛፍ ላይ
ተሰቅሎ ወይም ታንቆ ነው የሞተው። ታዲያ ይህኛው በዛፍ ተሰቅሎ የሞተው ማነው?
ቢባል፥ ‘እርሱም በይሁዳ ተመሰለ እንጂ ይሁዳ አይደለም’ ሊሉ ነው? ምናልባት ይባል
ይሆናል።

80
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ኢስላም በአንድ ወገን ምትካዊ ሞትን አያምኑም። ግን ‘አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም


ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ’ የሚለውን ይጠቅሳሉ። እዚህ ላይ አንድ
ሰው በዒሳ ምትክ ተሰቅሏል ማለት ነው። ይህ ነገር ታዲያ ምትካዊ ሞት ነው ወይስ
አይደለም? አንድ ሰው በሌላው ምትክ ከሞተ ምትካዊ ሞት ሊባል ይቻላል ወይስ
አይቻልም? ከሆነ ቁርኣን የራሱን ትምህርት ራሱም ተጻረረ ማለት አይደለም? ነው።
ውስጣዊ ግጭትና ተቃርኖ። ይህኛው በምትኩ የሞተለት ሰው ሞት ምትካዊ ሞት ነው
ከተባለ ደግሞ የኢየሱስ ሞት ምትካዊ ሞት መሆኑ ለምን እንግዳ ነገር ይሆናል?

'ይህ ሌላ ሰው ማን ነው?' በሚለው ጥያቄ ላይ ሙስሊሞች የሚያቀርቡት ማስረጃ


መሠረት የሌለው ብቻ ሳይሆን በማንነቱ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የቀረቡት መልሶችም
ብዙና እርስ በርስ የሚቃረኑ ናቸው። የተሰቀለው ሰው ጌታ በናይን ኢየሱስ ከሞት
ካስነሣው ወጣት እስከ ኢየሱስ ወጣት ደቀ መዝሙር፥ ከቀሬናው ስምዖን፥ እስከ
አስቆሮቱ ይሁዳ እና በመካከል ያሉ ሰዎችንም ይጨምራል። ከሙስሊሞች ይህ ሰው
ማን መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚችል ማንም ሰው የለም። ቁርኣንም ማንነቱን
አይናገርም። እንዲያው ቢያንስ ለኢየሱስ ምትክ ሆኖ ስለሞተ ሊመሰገን መጠቀስ
አልነበረበትም? ይህንን ሰው ማን እንደመረጠውና እንዴት እንደተመረጠም
የሚያውቅ የለም።

የኢስላም አንድ ቅርንጫፍ የሆኑት አሕመዲያ የተባሉ ሙስሊሞች ደግሞ ይህንን ሌላ


ሰው በፈንታው ተሰቀለ የሚለውን አሳብ ጭራሹን የሚቃወሙ ናቸው። ኢየሱስ
በመስቀል ላይ መሞቱንም ጭምር አይቀበሉም። ይህንን በሌላ ክፍል አወሳለሁ።
ሙስሊም ሆነውም ሱረቱ አል-ኒሳዕ ቁ. 157-8ን የማይቀበሉም አሉ ማለት ነው።
ሁለቱ የተሳሳቱ ነጥቦች ስንመለስ፥ የመጀመሪያው ነጥብ የተመሰለው ማን ነው? ሲሆን
ሁለተኛው ያስመሰለውስ ማን ነው? የሚለው ነው።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የኢየሱስ ሞት ምትካዊ ሞት ነው፤ በእኛ ምትክ፥


ወይም ለእኛ ሲል ፈቅዶ ነው የሞተው። ኢስላም ይህንን ሞት መካዱ ብቻ ሳይሆን
ለምትካዊ ሞት ክሕደት ሌላ ምትክ ማስፈለጉ ነው አሳዛኙ ስሕተት። ይህ ኢየሱስ
ያይደለው ኢየሱስን እንዲመስል የተገደደና የተመሰለ ተለውጦ የተሰቀለው ሰው ማን
ነው? ደግሞስ በትክክል በወንጌሉ ውስጥ እንደተጻፈው ያለውን ኢየሱስን የሚወክልና
የሚመስል ሰው ነው? በተለያዩ ሰዎች ምናባዊ ግምቶችና ከተነገሩ ተረቶች ሌላ ማን
መሆኑን ለማረጋገጥ የተደረገ ሙከራ አለ?

ከቁርኣን መጽጻፍ በፊት ከእውነትና ከእውነታ የራቁ ቢሆኑም እነዚህን የመሰሉ ነገሮች
ኖረው አያውቁም ማለት አይደለም፤ ያውቃሉ። አንዳንዶቹ በአካል ሌላ ሰው ነው
ሲሉ ሌሎች አካል መሰለ እንጂ አካል አልነበረም የሚሉ ናቸው። በጉልህ
የሚታወቀው ዶሴቲዝም የሚባለው ቀደም ሲል አንዴ የጠቀስኩት በሁለተኛው ምዕት
ዓመት ብቅ ያለ ኑፋቄ ነው። ቃሉ δόκησις (ዶኬሲስ) δοκεῖν (ዶኬይን)

81
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መሳይነት፥ መምሰል ማለት ነው። እነዚህ የዚህ ስሕተት ተከታዮች ዶሴቲስቶች


ይባላሉ። ኢየሱስ ሥጋ የለበሰ መሰለ እንጂ የአዳምን ሥጋ አልለበሰም ይላሉ። እነዚህ
ይህን ማለታቸው ግን 'የተሰቀለው ሰው ክርስቶስን መሰለ' የሚለውን አሳብ ለቁርኣን
አበድሮ ወይም አውሶ ይሆናል እንጂ የዶሴቲስቶች አሳብ ክርስቶስ ሰውን መሰለ እንጂ
ጭራሹን ሰው አይደለም፤አምላክ ብቻ ነው፤ አምላክ ደግሞ ሊሰቀል አይችልም፤
አይገባውምም፤ ስለዚህ የተሰቀለው ሌላ መሆን አለበት ወይም የተሰቀለ መሰለ የሚል
ነው። ሥጋ መልበሱን፥ 'ሥጋ የለበሰ መሰለ' ይበሉ እንጂ አምላክነቱን ግን ይቀበላሉ።
እንዲያውም ሥጋ ያልለበሰ ነው በማለታቸው አምላክነቱን ያገነኑ ይመስላቸዋል።
የቁርኣን 'ተመሰለ' የሚለው ትምህርት ምንጭ ምናልባት ከዶሴቲስቶች ሊሆን
ይችላል።

ባሲለደስ የተባለ ከ117-137 በእስክንድርያ ያስተምር የነበረ ሰው ኢየሱስ ደክሞ ሳለ


መስቀሉን የተሸከመው የቀሬናው ስምዖን ኢየሱስን እንዲመስል ተደርጎ ተሰቀለ፤
በዚያው ቅጽበት ደግሞ ኢየሱስ የቀሬናውን ስምዖንን መስሎ ቆመው ከሚያዩትና
በተሰቀሉት ከሚስቁት አንዱ ነበር ይላል። ይህ ሰው ያስተማረውን ይህንን ነቅፎ
የጻፈው ኢሬኔዎስ የተባለ መካቴ እምነት ነው።8

ኢብን ከቲር የተባለው ታዋቂ የቁርኣን ፈቺ (ከሙሐመድ ከ700 ዓመታት በኋላ


ከ1300-1373 የኖረ ነው።) ስለዚህ ስለ 4፥157 ‘አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትም’ ጥቅስ
በተፍሲሩ በ61ኛው ምዕራፍ ላይ ሲያብራራ ኢየሱስም ከ12ቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር
ሳለ፥ በመልኩ እኔን መምሰል የሚፈልግና በኔ ፈንታ የሚሞት ቢኖር በገነት ከኔ ጋር
እንዲኖር አደርገዋለሁ ይላቸዋል። ከደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ወጣት የሆነው አንድ
ጎልማሳ ፈቃደኛ ሆነ። ኢየሱስም እንዲቀመጥ ነገረውና ደግሞ ጥያቄውን አቀረበለት።
አሁንም ያ ወጣት ፈቃደኛ ሆኖ ቆመ። አሁንም እንዲቀመጥ ነግሮ ጥያቄውን
ደገመለት። ለሦስተኛ ጊዜ ወጣቱ ሲቆም፥ "እንግዲያውስ አንተ ነህ" አለው። ያኔውኑ
የኢየሱስ መልክ በወጣቱ ላይ ተለጠፈበትና ኢየሱስን ሲመስል አላህ ኢየሱስን
በጣራው ቀዳዳ አድርጎ ወሰደው። ሊይዙት የመጡትም ያንን ወጣት ወሰዱትና
ሰቀሉት።9

አይሁድ፥ ‘ገደልነው!’ ብለው እንደ ፎከሩ የተባለው ይህ ነው እንግዲህ።


ክርስቲያኖችም የገደሉት መስሏቸው ተታለሉ። ክርስቲያኖች እሺ ተታለሉ እንበል።
እዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መታለላቸው ግን ከሁሉን የሚገርም ነው። ምክንያቱም
በነሱ ፊት ነው ነገሩ ሁሉ፥ የቅየራው ሥርዓት የተፈጸመው፤ የተደረገው። እነዚህ
ሐዋርያቱ ደግሞ ላመኑበት እውነት የኖሩ፥ ያገለገሉና ነፍሳቸውንም የሰጡ ናቸው።
ለውሸት ነው ነፍሳቸውን የሰጡት? ይህ ከመታለሎች ሁሉ የከፋ መታለል አይደለምን?

8 Irenaeus, Book 1 Ch. 24, 4.


9 Tafsir Ibn Kathir, ch. 61.

82
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የሐዋርያቱ ስብከት ግን የተለወጠለት ሰው ሞተ የሚል ሳይሆን ክርስቶስ ራሱ


መሞቱን ነው። ልዋጭ ሰውን ኢየሱስ ነው ብሎ መስበክ ማጭበርበር ሆኖ ለልዋጭ
ሰው ብሎ እምነትን ገልጦ መሞት ከንቱ ቂልነት አይደለምን?

አንዳንድ ሙስሊሞች አጥብቀው የሚጠቅሱትና በአንዳንድ ሙስሊም ምሑራን በጣም


የተወደደው የበርናባስ ወንጌል የተባለው በ15ኛው መቶ የተጻፈ የፈጠራ መጽሐፍ
ነው። ልብ እንበት የተጻፈው በ15ኛው መቶ ነው። ግን በርናባስ የተባለው በሐዋርያት
ሥራ ውስጥ የምናገኘው የወንጌል ሰባኪ እንደጻፈው ተደርጎ የሚነገር ፈጠራ ነው።
በዚህ መጽሐፍ ከምዕራፍ 215 ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ፥ በተለይ ከ215-217
ድረስ ይሁዳ በኢየሱስ መልክ ተለውጦ ስለተሰቀለበት ሁኔታ በግሩም አተራረክ
ይተርካል። ይሁዳ ኢየሱስን ሲመስል ኢየሱስን ግን አራት መላእክት ሚካኤል፥
ገብርኤል፥ ዑራኤል፥ እና ሩፋኤል ወደ ሦስተኛው ሰማይ ወስደው አስቀመጡት።
በፈንታው ይሁዳ መከራ ተቀበለ። ሲሰቀልም እንኳ፥ 'እግዚአብሔር ሆይ! ወንጀለኛው
አምልጦ እኔ ያለ ፍትሕ እንድሞት ለምን ተውከኝ?' እያለ ይጮህ ነበር።

ይሁዳ ሲሰቀል፥ ኢየሱስን ወንጀለኛ ማለቱ ለሙስሊሞች ለራሳቸውም ሳይቀፋቸው


የሚቀር አይመስለኝም። ምክንያቱም በጤና የሚያስብ ማንም ሙስሊም ዒሳ ወንጀለኛ
ነው ብሎ ማሰብን አያስብም። ይሁን እንጂ፥ ይህ፥ ' . . . እያለ ይጮኽ ነበር' የሚለው
አገላለጽ አንድ ጉልህ ጥያቄ እንድንጠይቅ ያስገድደናል። በወንጌላቱ ውስጥ ኢየሱስ
(ወይም ቁርኣን እንደሚለው ኢየሱስን የመሰለው ሰው) ተሰቅሎአል። ይህ የተሰቀለ
ሰው ኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስን የመሰለ ሰው ከሆነ ከላይ እንዳየነው በበርናባስ ወንጌል
የተጻፈውን የመሰለ በጣም ብዙ ነገር መናገር አለበት።

የበርናባስ ወንጌል የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ በስም እየተጠቀሰ የተጻፈበትና አንድ


ቦታ እንዲያውም ኢየሱስ ራሱ የሙሐመድን የጫማውን ጠፍር ለመፍታት ዕድል
ቢያገኝ እንደ መታደል የሚቆጠርለት መሆኑን የተናገረበትም የፈጠራ መጽሐፍ ነው።
መቼ እንደተፈጠረም ስለሚታወቅ፥ አላዋቂዎች ካልሆኑ በቀር ብዙ ሙስሊሞች
ይህንን መጽሐፍ አይጠቅሱትም።

ፋሪስ አል ቃይራዋኒ (Faris Al-Qayrawani) የተባለ ጸሐፊ በመጽሐፉ ውስጥ ሌሎች


ምንጮችን (ወሃብ ቢን ሙናባህ፥ ቀታዳ፥ ሙጃሂድ፥ አላማ ባጋዊ የሚባሉት)
በመጥቀስ ሰባ ደቀ መዛሙርቱ እርሱን መሰሉ፤ ከነዚያ አንዱ ተያዘና ተሰቀለ ይላሉ
ብሎአል።10 ሰባ ኢየሱስን የሚመስሉ ሰዎች፤ ይታዩአችሁ። ከነዚያ ሰባ ተመሳሳይ
ሰዎች የትኛው ኢየሱስ መሆኑን አውቀው ነው የሰቀሉት? ወይስ የቱም ይሁን ብቻ
አንድ ሰው መሰቀል አለበት ብለው ነው የሰቀሉት? የሰባው ሰዎች መልክስ በዚያው

10 Was Christ Really Crucified?e.v.

83
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ቀረ ወይስ ኋላ ወደ ነበረበት ተመለሰ ይሆን? እንዲህ ያሉት ልብ ወለዶች ለፊልም


ደራሲዎች የሚመቹ ናቸው።

አቡ ሙሳ አል ሐሪሪ የተባለ ጸሐፊ ስምዖን (ምናልባት የቀሬናው?) እንደተሰቀለ


ጽፎአል። ይህንን እንዲመስል ያደረገው ደግሞ ኢየሱስ ራሱ መሆኑንም ጽፎአል።11
እንዲህ የመሰሉ ብዙ ፈጠራዎች፥ ነሲቦችና ግምቶች ብዙ ናቸው።

ይህ መሳይ የሆነ፥ የመሰለ፥ ወይም የተመሰለ ሰው ሊመልሳቸው የማይችላቸው ነገሮች


መኖራቸው እውነት ነው። እንዲያው ሆነ ቢባል፥ ለመምሰሉ ማንም ይምሰል ወይም
ይመሰል፤ ይሁዳ ይሁን ወይም ስምዖን፥ ቶማስ ወይም መሰለ፥ ማንም ይሁን ብቻ ያ
ሰው ኢየሱስን መስሎ ወይም በኢየሱስ ተመስሎ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሸንጎ፥ እንዲሁም
ወደ ጲላጦስ ቀርቧል ማለት ነው። ይህ ኢየሱስን ያልሆነ ሰው ወደነዚህ መርማሪዎች
ሲቀርብ ሊል የሚችለውን ነገር በትክክል እናውቃለን። ማንም ሰው ያውቀዋል።
ራሳችንን በዚያ ሰው ምትክ እንደተለወጠ ሰው አድርገን ብናስቀምጥ የምንመልሰውን
መልስ እናውቀዋለን። መልሳችን ያ ሰው ከሚመልሰው መልስ ጋር ይገጣጠማል። ግን
ይህ ሰው ከቀረበ በኋላ ኢየሱስ የመለሰውን መልስ ሊመልስ እንዴት ይችላል? ወይስ
መልኩ ብቻ ሳይሆን እውቀቱና አእምሮውም ተለወጠ?

ይህ የተለወጠ ወይም የተመሰለ ሰው ከተያዘበት ጀምሮ እስከተሰቀለና እስከ ሞተበት


ድረስ ሊላቸው የማይችላቸውን ነገሮች ለመመልከት፥ ከአንዱ ወንጌል ብቻ ትንሽ
ቆርሰን እንይ። ከወንጌላቱ በመጠንና በዝርዝር አነስተኛ የሆነውን የማርቆስን ወንጌል
እንይ፤ ኢየሱስን ያልሆነ ሰው፥ 'እኔ እርሱ አይደለሁም! በስሕተት ነው የያዛችሁኝ!
ልቀቁኝ!' እያለ ይለፈልፋል እንጂ፥ እነዚህን ነገሮች በእውን ይላል?

ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን? በመቅደስ


ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍት
ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ አላቸው። ማር. 14፥48-49።

ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፥ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው።


ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ
ታያላችሁ አለ። ማር. 14፥61-62።

11Faris Al-Qayrawani, Was Christ Really Crucified? electronic version at:


http://www.the-good-way.com/eng/books/4360/format-xml

84
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ጲላጦስም ደግሞ፥ አንዳች አትመልስምን? እነሆ፥ በስንት ነገር ያሳጡሃል ብሎ


ጠየቀው። ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም። ማር.
15፥4-5።

እነዚህ ሦስት ጥቅሶች ናሙና ብቻ ናቸው። ከማርቆስ ወንጌል ሌሎች ጥቅሶችን ወይም
ሌሎቹን ሦስቱን ወንጌላት ብንጨምር ብዙ ይህን የሚመስሉ እናቀርባለን። (ማቴ. 26-
27፤ ሉቃ. 22-23፤ ዮሐ. 18-19 ተመልከቱ።) የተሰቀለው ሌላ ሳይሆን ኢየሱስ
ለመሆኑ ይህ አስረጅ ነው። ይህ ሰው ኢየሱስን ሳይሆን ኢየሱስን እንዲመስል
የተደረገውና የመሰለው ሰው ቢሆን ከላይ የተጻፈውን አለመናገር ብቻ ሳይሆን፥
'በሐሰት ነው የምከሰሰው! እናንተ ሰዎች አይገባችሁም እንዴ?!' ይል ነበር፤ የተሰቀለው
ሰው ግን ይህንን አላለም። ዲዳ ካልሆነ በቀር መከላከያውን ማቅረብ ይችል ነበር።
ዲዳ አለመሆኑ ደግሞ ግልጽ ነው፤ በመናገሩ ይታወቃል።

የተሰቀለውን ሰው አላህ መልኩን ቀይሮ ኢየሱስን ሲያስመስለው ውስጡንም ቀይሮ


ራሱን ኢየሱስን እንደሆነ አድርጎ እንዲቀበል አደረገው ካልተባለ በቀር፥ ኢየሱስን
ያልሆነ ሰው እንዲያው ዝም ብሎ ነፍሱን ላልፈጸመው ጥፋት አሳልፎ አይሰጥም። ያን
ሁሉ የፍርድና የዳኝነት ሂደት (በሮም ባለ ሥልጣኖች 3 ጊዜ፥ በአይሁድ ሸንጎ 3 ጊዜ)
ተፈትሾ ሲያልፍ ያ ሁሉ መርማሪ ይህ ሰው ኢየሱስ አለመሆኑን አለማወቃቸው ምንኛ
የሚገርም ብቻ ሳይሆን የሚያስቅም ነው! ስለ ሮም የፍርድ ሂደት ማወቅ ያለብን አንድ
ነገር አለ፤ ያም፥ የሮም ፍርድ አሰጣጥ አካሄድ የነፍስ ቅጣት ከመፍረዱ በፊት
በጥንቃቄ ችሎቱን የማካሄዱ ሂደት የታወቀና የተዘገበ ጉዳይ ነው። ወንጀለኛ ያልሆነ
ሰው በአፍንጫቸው ስር አልፎ ለመስቀል ሞት ዳረጉ ማለት ታሪክ የሚንቀው ክስ
ነው።

ኢየሱስን የመሰለው ሰውም እየጮኸ አለመሆኑን በመናገር ፈንታ፥ ክርስቶስ


መሆኑንም፥ ሲያስተምራቸው መኖሩንም፥ የቡሩክ ልጅ መሆኑንም በግልጽ ተናገረ።
ይህ ሰው ያልሆናቸውን እነዚህን ነገሮች ካለ ወይም ከተናገረ ቀጣፊ ነው። ደግሞም
ሰው ሁለት ነፍስ የለውምና ለአንዲቱ ይቆማል እንጂ በሐሰትና ለሐሰት ራሱን ለሞት
አሳልፎ አይሰጥም። ይሁዳ ከሆነ ተሰቀለ የሚባለው ለ30 ብር ብሎ ጌታውን አሳልፎ
የሰጠ ሰው ሆኖ እያለ፥ ለ30 ብር የተስገበገበ ሰው ለነፍስያው ሳይሳሳ ራሱን ሰጠ
ማለት ማንም የማያምነው ግምትና መላ ምት ነው። በመስቀል ላይ ሲሞት ጠላቶቹንና
ያሰቃዩትን፥ 'የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው' ሊል የሚችል ከኢየሱስ በቀር
ሌላ ማን ሊሆን ይችላል? ይሁዳ? ይሁዳ አያደርገውም።

የኢየሱስ እናት ማርያም እንኳ ኢየሱስ ከመስቀል ሲናገራት ያ ድምጽ የሌላ መሆኑን
አልጠረጠረችም። የተቀየረው ሰው መልኩ ብቻ ሳይሆን ድምጹም ተቀይሮ ነበር
ማለት ነው? አላህ መልኩን ከቀየረና መቀየር የሚችል አምላክ ከሆነ ድምጽ፡መቀየርም

85
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አይከብደው ይሆናል። ደግሞም ይህ ሰው ማርያም እናቱ ሳትሆን ልክ እንደ እናቱ


አድርጎ ይናገር ነበር። ይህም ሌላ ሸፍጥ ነው።

እንግዲህ በጥቅሉ ሲታይ ይህ ተመሰለ የሚባለው ነገርና ተመሰለ የተባለው ሰው


ማስረጃ የሌለውና እርስ በርስ የተቀዋወመ ነው። በእርግጥ የሞተው ኢየሱስ መሆኑ
ግልጽ ነው። እርሱ መሆኑን እና የመሞቱንም አስፈላጊነት እመለስበታለሁ። ከዚያ
በፊት ግን የተመሰለውን ልናይ እንደሞከርን ያስመሰለውንም ደግሞ እንይ።

አራተኛ፥ ከሁሉም ነጥቦች በላይ ይህኛው በጣም አስቸጋሪው ጉዳይ ነው። ይህ


በተሰቀለው ኢየሱስ ተመሰለ የተባለው ሰው ሳይሆን ከተሰቀለና ከመሰለ፥ ወይም
ለሌሎች እንዲመስል ከተደረገ፥ ይህ ትልቅ የሆነ ማሳት ወይም ሌሎችን ምንም
የማያውቁ ሰዎችን ማሳሳትና ማጭበርበር አይደለም? ነው እንጂ! ኢየሱስ የተሰቀለ
መስሏቸው እነዚያ ሁሉ የኢየሱስ ተከታዮች ተሳስተዋል ማለት ነው። በዚህ ስሕተት
ምክንያትም የክርስትና እምነትም ተጀመረ ማለት ነው። ስለዚህ፥ ለዚህ ሁሉ መሳትና
መሳሳት እና ለክርስትና እምነት መጀመር ምክንያቱና ተጠያቂው ማን ሊሆን ነው? ያ
ያስመሰለው ወይም ኢየሱስን ያልሆነው መስሎ እንዲሞት ያደረገው አድራጊ ነው
ማለት ነው።

አድራጊው ማን ነው? ያስመሰለው (እንዲመስል ያደረገው) ማን ነው? አሳችና ለዋጩ


ማን ነው? የተለወጠው ሰው ማንነት ብቻ ሳይሆን የለዋጩ ማንነትም መታየት
አለበት። ይህንን ያደረገውና ያልሆነውን ያስመሰለው፥ በዚያም ያሳተው ማን ነው
ማለት ነው? አላህ! የተመሰለው የሞተው ነው፤ እንዲመስል ያደረገው ደግሞ አላህ
ነው። ክርስትናን ራሱን የጀመረው አላህ ነው ማለት ነው። ከሆነ፥ ሌላ ሰው
እንዲሰቀል በማድረግና የተሰቀለው ኢየሱስን እንዲመስላቸው በማድረግ የጀመረው
አላህ ራሱ ከሆነ፥ ለክርስቲያኖች መሳትና መሳሳት ተጠያቂው ማን ሊሆን ነው? አላህ።
ይህ እውነት ሲሆን ለሙስሊሞች ለመቀበል እጅግ የሚያስቸግራቸውና የሚቀፍፋቸው
ጉዳይ ነው።

ይህ ሁሉ የሆነው፥ የነገሩ ዓላማና ግብ ምንድርን ነው? ክርስቲያኖችን ማሳት ነው፤


አይደል? የሞተላቸው መሰላቸውና እሱን ተከተሉት። ያልሞተላቸው የሞተላቸው
መስሏቸው ከተከተሉት ሳቱ፤ ተሳሳቱ፤ ተታለሉ። ይህን ሁሉ ማሳትና ማታለል
ያደረገው ማን ነው? ኢየሱስን ማንም ሳያይ፥ ማንም ሳያውቅ ወስዶት በፈንታው
በምትኩ ሌላውን እርሱን እንዲመስል መልኩን ቀይሮ እንዲሞት ያደረገ ማን ነው?
አላህ። ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲስቱና በስሕተት ኢየሱስ መስሏቸው ኢየሱስን
ያልሆነውን እንዲከተሉት ያደረገ ማን ነው? አላህ። ሳዲቅ እና ሙስሊሞች
የሚያስረዱን እኮ ይህንን ነው። እርሱን ወሰደው፤ ማንም ሳያይ፥ ማንም ሳያውቅ።
በፈንታው ሌላውን እርሱን እንዲመስል አደረገ፤ የተደረገው ያ ሞተ። ሌሎቹ
መሰላቸው፤ ይህ ከማሳቶች ሁሉ የበለጠው ማሳት አይደለምን?

86
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አላህ እንዳይስቱ ቢፈልግ ለሙሉ እንዲያውቁ፥ ሁሉ እያዩ፥ በግልጽ፥ በገሃድ፥ በጠራራ


ፀሐይ አልወሰደውም? ምክንያቱን አልነገረንም። ብቻ በስውር ማንም ሳያይና ሳያውቅ
ወስዶት፥ ሌላው እሱን እንዲመስል አድርጎ ሠራርቶት፥ ያ ሌላ ሰው በምትኩ ተሰቀለ፤
አዲስ ሃይማኖት ተጀመረ፤ ክርስትና የሚባል ነገር ተፈጠረ። ማን ፈጠረው? ወይም
ማን እንዲፈጠር አደረገ? አላህ። እንዴት? ኢየሱስን ያልሆነውን ኢየሱስ በመስቀል
ላይ እንዲሰቀል አድርጎ። ይህ ትልቁ መፍታት የማይቻል ተቃርኖና ግጭት ነው።

ይህ ትልቅ የማሳትና ማሳሳት ስሕተት እንዲፈጠር ምክንያት የሆነ መኖሩ መታወቅ


ያለበት ጉዳይ ነው። ጥቅሱን እንደገና እንይ፤

እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው


(ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ)
ተመሰለ።

በመጀመሪያ፥ ቀደም ሲል እንዳየነው አይሁድ የማርያምን ልጅ መሢሑን ኢየሱስን


ገደልነው ብለው አላሉም። ይህ ተፈልጎ የማይገኝ ቃል ነው። ታዲያ ካልገደሉት ለምን
ተረገሙ? ገደልነው ስላሉ? ይህ ፍርደ ገምድልነት መሆኑንም ቀደም ሲል አይተነዋል።
‘አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትም፤’ የተባሉት አይሁድ ናቸው። አይሁድ በመስቀል ላይ
ሰውን ሰቅለው መግደል ወጋቸው አይደለም። የመስቀል ሞት ሮማውያን ሮማዊ
ያልሆነ ሰውን የሚቀጡበት የስቃይ ቅጣት ነው። በመገደሉ የተደሰቱ አይሁድ
የማርያምን ልጅ ኢየሱስን፥ 'ይህን ሐሰተኛ ገደልነው' ነው የሚሉት እንጂ መሢሕ
ብለው አይጠሩትምና፥ 'የአላህን መልክተኛ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን' አይሉም።
መሢሓቸው አይደለምና። ተከታዮቹ ብቻ ናቸው መሢሕ፥ ክርስቶስ ብለው
የሚጠሩት። መሢሕ ብለው የሚጠሩቱ ደግሞ 'ገደልነው' ብለው አያቅራሩም፤
አይገድሉትምና። ይህ ከቁርኣን ውስጣዊ ግጭቶች አንዱ ነው።

እንደ ቁርኣን ትምህርት ይህ ሰውን የመለወጥ ችሎታ የማንም ሰው ሳይሆን የአላህ


ብቻ ነው። ይህ የተገደለው በዒሳ መመሰል ደግሞ ትልቅ ማሳሳትና ማሳት መሆኑ
ግልጽ ነው። ይህ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ የከፋው ማሳት ደግሞ እነዚያ ሁሉ የኢየሱስ
ተከታዮች ኢየሱስ ሳይሞት የሞተ መስሏቸው ተሳስተዋልና፥ ከዚያ ደግሞ ምናልባት
እርሱን የሚመስል ሰው በሦስተኛው ቀን የተነሣ መስሎ ታይቷቸዋልና ለዚህ
ስሕተትና ለክርስትና እምነት መጀመር ምክንያት የሆነው ይህ አላህ የፈጠረው
ስሕተት ነው ማለት ነው። የሞተው፥ የተመሰለው ነው ከተባለ ታዲያ ከሞት
የተነሣውስ? እና ከተነሣ በኋላ ኢየሱስ ነኝ እያለ እየታየ ቀጠለ? ወይስ ጨርሶ
አልተነሣም ይህኛውም?

አላህ ኢየሱስን መውሰድ ከቻለ ሌላ ሰው እርሱን መስሎ እንዲሰቀል ማድረግ


ሲጀመርስ ለምን አስፈለገው? ወስዶ ብቻ መተው አይችልም ኖሯል? ደግሞም

87
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በምስጢርና በማታለል ሳይሆን በግልጽ ማድረግ አይችልም ኖሯል? ይሁን፤


በምስጢርም ያድርግ፤ ግን ሌላ ምትክ ሳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር? ይህ
መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው። ዓይናቸው እያየች መውሰድ ሲችል፥ ሰው እርሱን
እንዲመስል፥ ያ ሰው ተሰቅሎ መከራ እንዲያይ፥ በዚያ ላይ ደግሞ ክርስትና የሚባል
ሃይማኖት እንዲፈጠር ምክንያት ለምን አስፈለገ? ይህ መመለስ ያለበትና መመለስ
የማይችሉት ጥያቄ ነው።

ኢየሱስ አይሁድም ሮማውያንም እያዩት ቢወሰድ እኮ ስሕተታቸው ገብቶአቸው ንስሐ


ለመግባት ዕድል ያገኙ ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ከተወሰደና በፈንታው እርሱን
የሚመስል ከተሰቀለ ሰዎች ኢየሱስ የተሰቀለ መስሏቸው ሊሳሳቱ ነው፤ ሊሳሳቱም
በቅተዋል። ይህ አሳሳችነት ነው። ሐዋርያቱ የሰበኩት ኢየሱስ የተሰቀለው ኢየሱስ
ሳይሆን በፈንታው የተሰቀለው ሌላ ኢየሱስ ነውና ይህ ስሕተት ደግሞ እስከ 600
ዓመታት ድረስ ያልተስተካከለ ስሕተት ሆኖ ቆይቶ የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ
ተገልጦለት ያሳወቀው ጉዳይ ነውና አውቆም ለክርስቲያኖቹ አልነገራቸውምና ለዚህ
ሁሉ ስሕተት ተጠያቂው ማን ነው? አላህ። ስለዚህ አላህ ያሳስታል፥ ያስታል ማለት
ነው። ቢያንስ ማረሚያው ከ600 ዓመታት በኋላ እስኪላክ ድረስ የነበሩት ሰዎች ሁሉ
ስተዋል። አሁን ያለው ክርስትናም በዚያ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ እስከ አሁን ያሉቱም
ክርስቲያኖችና ከዚህ በኋላም ያሉት ሁሉ ተሳስተዋል። በጠቅላላው ክርስትና
እንዲፈጠር በማድረጉ ተጠያቂው አላህ ነው ማለት ነው። ይህ ሁሉ ሕዝብ ወደ
ስሕተትና ወደ ዘላለማዊ ጥፋት እንዲሄድ ያደረገው አላህ ነው ማለት ነው።

ኢየሱስ ተአምራት ማድረግ ይችላል፤ ቁርኣንም እንደሚመሰክረው ብዙ ተአምራት


አድርጎአል። ሊይዙት የመጡትን ዶግ አመድ ማድረግ ሲችል ለምን ዝም አላቸው?
ለምን ሌላ በፈንታው እስኪለወጥለት ድረስስ ዝም አለ? ወይም ለምን ራሱ ሌላው
እርሱን እንዲመስል ለወጠ? ይህ ባህርይ የኢየሱስን ይመስላል? እንኳን የመጽሐፍ
ቅዱሱን ኢየሱስ፥ የቁርኣኑን ዒሳንም አይመስልም። አይሁድ ሊገድሉት ሲሞክሩ ይህ
የመጀመሪያው አይደለም። ከዚህ በፊት አምልጦአል፤ ጊዜው ስላልደረሰ። አሁንም
ቢፈልግ ማምለጥ ይችላል። ግን አልሞከረም፤ ጊዜው ስለሆነ። ሲችል ለምን
አላደረገም? ይህም መመለስ አለበት? እንደ ቁርኣን አስተምህሮ ዒሳ ገና እሕፃንነቱና
ከልጅነቱ ጀምሮ ተአምራት ያደረገ መሆኑ ተጽፎአል። ታዲያ እዚህ ተአምራቱ አበቃና
በማሳት ውስጥ ተሳታፊ ሆነ?

ሌላው ኢየሱስን መስሎ እንዲሞት ለማድረግ ኢየሱስ በመጀመሪያ ለመሞት


አለመፈለግ አለበት። አንዳንድ ሙስሊሞች ጌታ በጌቴሴማኒ የጸለየውን በመጥቀስ፥
'ሊሞት ሳይፈልግ ነው የሞተው' ሊሉ ይሞክራሉ። ኢየሱስ ከመጀመሪያም
እንደሚሞትና ምን ዓይነት ሞት እንደሚሞትም በግልጽ ደግሞ ደጋግሞ ተንብዮአል።
ሞትን አልሸሸም። ሲሸምሽ ከቶም አልታየም። የመጣውም ስለዚህ ነው። ለመሞት
እንዲያውም ፈቃደኛ ነበረ። ማንም አላስገደደውም። ሥጋ የለበሰውም ስለዚህ ነው።

88
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በፈቃዱ ነው ነፍሱን ያኖራት፤ ዮሐ. 10፥18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ


ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ
ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ ብሎአል። ወደ ጌቴሴማኒ የሄደው አልፎ
እንደሚስሰጥ አውቆ ሊጸልይ እንጂ ሊደበቅ አይደለም። ሰይፍ እንዲገዙ የነገራቸው
ትንቢቱ እንዲፈጸም እንጂ እንዲከላከልበት ወይም እንዲያጠቃበት አይደለም። ዓሳ
አጥማጆች በሁለት ሰይፎች የሮምን ወታደሮች እንደማይገጥሙ ለዓለሙ ሁሉ የታወቀ
ነው። አሳማኝ ምላሽ መሰጠት አለበት እንጂ እንደ ዓለት የጠጠረውን ሐቅ ለመሸሽ
ሱራ 5፥157-158 ብቻ መጠቀስ የለበትም። አዲስ ኪዳንን የሚያህል፥ ራቁን ቁርኣንን
የሚያህል፥ ትልቅ እና ሙሉ መጽሐፍ መጽሐፍ እና ከአዲስ ኪዳን በኋላ ብዙ መቶ
ዓመታት ቆይቶ የተነገሩ ሁለት ጥቅሶች መነጻጸር እንዴት ይችላሉ?

አላህ ይህንን ኢየሱስን ወስዶ፥ ሌላው ሰው ደግሞ፥ 'ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው


በዒሳ) ተመሰለ' እንደሚለው ካደረገ ምን እንዳደረገ እንመልከት። ቢያንስ አራት
ትልልቅ ኃጢአቶች ወይም ቢያንስ ወንጀሎች ተፈጽመዋል። አራተኛው ከሁሉም
የከፋው ነው።

አንደኛ፥ ከመጀመሪያም እንደሚሞት ነቢያቱ የተናገሩለትና ራሱም እንደሚሞትና


በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ የተነበየው ኢየሱስ እንዳይሞት (ወይም እንዳልሞተ)
ተደርጓል። አንዳንዶች የአላህ ነቢይ እንዲያ ያለ የስቃይ ቅጣት መቀጣት የለበትም
ይላሉ። ሊባል ይቻላል፤ ግን ራሱ ሙሐመድም እንዴት ባለ የስቃይ ሞት እንደሞተ
ስናይ ይህ አባባል ትርጉም ያጣል። ሙሐመድ አንዲት አይሁዳዊት ከምግብ ጋር
ባበላችው መርዝ ተመርዞ ሲሰቃይ ከርሞ ነው የሞተው።

ሁለተኛ፥ ያለ ፈቃዱ አንድ ሰው እንዲገደል ተደርጓል። ማንም ሳይሞት በግልጽና


በገሃድ፥ ኢየሱስ እየታየ መወሰድ ሲችል በስውር ተወስዶ፥ በፈንታው አንድ ይህ
ሊሆንበት ያልተገባው ንጹሕና ሰላማዊ ሰው ክፉና ጭካኔ የተሞላበትን የሮማውያን
ቅጣት ሊቀበል ተደርጓል። ይህ ፍትሕ ሳይሆን ኢፍትሐዊ ፍርደ ገምድልነት ነው።

ሦስተኛ፥ ሰዎች ሁሉ ያ ሰው ኢየሱስን እንዲመስላቸው ሆነዋል ወይም ተደርገዋል።


ይህ ጅምላ የሆነ፥ ሰዎች ሁሉ ያልሆነ ነገርን ነው ብለው እንዲቀበሉና እንዲያምኑ
የተደረጉበት አዚም ውስጥ ማስገባት የተፈጠረው በአላህ ነው። ሰዎች የሆነውን
አልሆነም፤ ያልሆነውን ሆነ ብለው እንዲቀበሉ የተገደዱበት ሁኔታ ውስጥ ያለ ምንም
አማራጭ ገብተዋል። ይህንንም ያደረገው አላህ ነው።

አራተኛ፥ በዚህ ሁሉ ማሳት ውስጥ ክርስትና የሚባል ሃይማኖት እንዳይፈጠር ማድረግ


ሲችል እንዲፈጠር በማድረጉ ትልቁን ኃጢአት ሠርቷል። ይህ ከኢስላም አንጻር
ሲታይ ትልቁ ጥፋት ነው። ኢየሱስን በግልጥ፥ የሰዎች ሁሉ ዓይን እያየች ወደ ሰማይ
ሊወስድና ሊነጥቅ ሲችል ይህን ባለማድረጉ ሰዎች ሁሉ ተታልለው፥ ደቀ መዛሙርቱ
89
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ተታልለው፥ ሮማውያን ተታልለው፥ አይሁድ ተታልለው "እኛ የአላህን መልክተኛ


አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው" (ረገምናቸው) 4፥157። እንግዲህ ከዚህ
ማስመሰል የተነሣ ይህ ክርስትና የተባለ ሃይማኖት ተፈጠረ።

አምስተኛ፥ እና የመጨረሻው ተቃርኖና ግጭት፥ የተመሰለው እሺ ሞተ፤ ከሙታን


የተነሳውስ ማን ነው? ያው የተመሰለው ነው ከሞት የተነሣው? እና ከተነሣ በኋላ
ኢየሱስ ነኝ እያለ እየታየ ቀጠለ? ወይስ ጨርሶ አልተነሣም? ኢስላም ሲጀመርም
አልሞተምና መነሣት ብሎ ነገር የለም ነው የሚለው። በእርግጥ በኢስላም ውስጥ
ቁጥራቸው ብዙ ባይሆንም አሕመዲያ የሚባል ቡድን ወይም ቤተ እምነት አለ፤
እነዚህ ኢየሱስ ተሰቅሏል፥ ሳይሞት ተቀብሯል፤ ከዚያ ተነሥቶ ሕንድ አገር ሄዶ ኖሮ
ሞተ የሚሉ አሉ። ግን ኢየሱስ መሞቱንና መሰቀሉን ከሙታንም መነሣቱን እርግጥ
የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶችና ማስረጃዎች አሉ። እነዚህን በቀጣዩ ክፍል እናያለን።

እነዚህ ከላይ ያሳየኋቸው አምስት ቅራኔዎች የሱረቱ አል-ኒሳእ 4፥157-158 ውስጣዊ


ግጭቶችና ቅራኔዎች ናቸው። ሳዲቅ ኢየሱስ ስላለመሞቱ ከዮሐንስ ወንጌል ስለሆነ
የጠቀሰው፥ መሞቱ በሁሉም ወንጌሎች ውስጥ በዝርዝር የተጻፈ ቢሆንም ከዚሁ
ከዮሐንስ ብቻ እስኪ ጥቂት ጥቅሶች እንይ፤

ዮሐ. 3፥14-15 ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን
ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
[ስቅለት]

ዮሐ. 6፥62 እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት


ይሆናል? [ትንሣኤ]

ዮሐ. 12፥23-24 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ


ሰዓቱ ደርሶአል። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ
ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። [ሞት]

ዮሐ. 12፥32-34 እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።


በምን ዓይነትም ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክታቸው ይህን ተናገረ።
እንግዲህ ሕዝቡ፦ እኛስ ክርስቶስ ለዘላለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው
ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?
ብለው መለሱለት። [የሞቱ ዓይነት]

90
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የመስቀል ሞት ምንድር ነው?

እነዚህን አምስት ግጭቶች ካየን በኋላ የሞተው ኢየሱስ ራሱ የመጽሐፍ ቅዱሱ


ኢየሱስ መሆኑን ክርስቲያን ካልሆኑ ምስክሮች ከኢስላምም ጭምር እንመልከት።
አስቀድመን የመስቀል ሞት ምን ስለመሆኑ፥ ስለ መስቀል ሞት ጥቂት ልግለጽ።

የመስቀል ሞት ማለት ክፉ የቅጣት ሞት ነው። ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት የስቃይ


ሞት ነው። ትንፋሽን እንኳ በጣዕር የሚተነፍሱበት ጣዕረ ሞት ነው። በመስቀል
የሚሞት ወንጀለኛ ከመሰቀሉ በፊት ይህ ነው የማይባል የጭካኔ ድብደባና ግርፋት
የሚቀበልበት ጭንቅ ነው። ወንጀለኞቹ የሚገረፉበት መግረፊያ አለንጋ ወይም ጅራፍ
ብቻ አይደለም፤ በመግረፊያው ጫፎች ላይ ሹል ብረትና የአጥንት ስንጣሪዎች ይገቡና
ይገመዱበታል። በግርፋቱ ሥጋ እየተቦጨቀ ይነሣል።

በጣም ፈጣንና ቀልጣፋ የግድያ መንገዶች አሉ፤ ተወግቶ መገደል፥ ለአውሬ ተሰጥቶ
መበላት፥ በእሳት መቃጠል ቀላል፥ ቀልጣፋና ፈጣን ሞት ናቸው ከመስቀል ጋር
ሲነጻጸሩ። መስቀል በማሰቃየት መግደያ መሳሪያ ነው። በመስቀል ላይ የሚሰቀሉ
አንዳንዶቹ አስቀድሞ በሚቀበሉት ድብደባና ግርፋት ለሞት የቀረቡ ሆነው ነው
የሚሰቀሉት። እጃቸው ተዘርግቶ ደረታቸው ስለሚወጠር የሳቡትን አየር ለማውጣት
ወይም ወደ ውጪ ለመተንፈስ ጭንቅ ነው። አየር ለመሳብ በተቸነከረው እግራቸው
ረግጠው ከፍ ማለት አለባቸው። ይህ ደግሞ ቀላል አይደለም፤ ችንካር ነው። ከፍ ብሎ
መተንፈስ ለመቻል የችንካሩን ቁስል ስቃይ ችለው ነው የሚረግጡትና ከፍ የሚሉት።
ብቻ መተንፈስ ስላለባቸው እንደምንም ከፍ ብለው ወደ ውስጥ ይስቡና ዝቅ ሲሉ
ወደ ውጪ ይተነፍሳሉ። ጥቂት ቆይተው መተንፈስ አቅቷቸው እንደ ታፈነ ሰው
ተሰቃይተው ይሞታሉ። ካልሞቱና ቶሎ መሞት ካለባቸው ጭናቸው እንዲሰበር
ይደረጋል። ጭናቸው ከተሰበረ በእግራቸው ረግጠው ቀና ማለት አይችሉምና
መተንፈስ አቅቷቸው ይሞታሉ። የመስቀል ሞት በጥብቅ የሚሸሹት፥ ወይም
ተገድደው የሚሞቱት እንጂ ፈቅደው የሚሞቱት ሞት አይደለም። ጌታ ግን ወድዶ፥
ወድዶን ነው በመስቀል ላይ የሞተልን።

በኢየሱስ የተመሰለውና ኢየሱስን ያልሆነው ይህ ሰው ንጹሕ መሆኑን፥ እርሱ


አለመሆኑን ሳይመሰክር፥ ሳይከራከር፥ ሳይንፈራገጥ፥ ፈቅዶ እየተነዳ ወደ መስቀል
ሞት፥ ክፉና አሰቃቂ ወደሆነው ወደ መስቀል ሞት ሄደ? ይህ ፈጽሞ የማይመስል
ግምት ነው። ደግሞ ማወቅ ያለብን ኢየሱስ ይህንን ሞት ነው የሞተልን። ኢየሱስ
ይህንን ሞት መሞት ብቻ አይደለም። ከዚህ ክፉ ሞት በኋላ ከሙታንም ተእሥቶአል።
ትንሣኤውን አረጋጋጭ ማስረጃዎች በቀላሉ የሚወረወሩ አይደሉም። ትልቁ አረጋጋጭ
ደግሞ ከትንሣኤው በኋላ ያዩት ኢየሱስ ምትሐት ሳይሆን እውን መሆኑን ስላወቁ ደቀ
መዛሙርቱ አንድያ ነፍሳቸውን ሳይሳሱ የሰጡ መሆናቸው ነው። ማን ነው ለተፈጠረ

91
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ነገር፥ እውነት ላልሆነ ነገር፥ ውሸት መሆኑን ነፍስያው ለምታውቀው ነገር ነፍሱን
የሚሰጥ? ተታልሎ ሰጠ ማለት ይቻላል? ከሆነ፥ ያታለለውስ ማን ነው? ያስ ሌሎቹን
አታልሎ ያስሞተ ሰው እንዴት ሆኖ ሞተ?

ጌትነት፥ ሞትና ትንሣኤ


ነገረ ክርስቶስ (Christology) ከክርስትና ትምህርቶች ውስጥ ጉልሁ ነው። ክርስትና
የኖረው ከክርስቶስ የተነሣ ነው። ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ተከታይ ወይም
የክርስቶስ የሆነ ማለት ነው። ክርስቲያን የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው በሐዋ. 11፥25-26 ነው፤ በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ
ጠርሴስ መጣ፤ ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ
ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ
በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ። መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ የተባሉት የጌታ
ደቀ መዛሙርት ናቸው። ደቀ መዝሙር ማለት ደግሞ ተከታይ ተማሪ ማለት ነው።
ስለዚህ በቀላል አፈታት፥ ክርስቲያን ማለት የጌታ ደቀ መዝሙር፥ ተማሪ፥ ተከታይ
የሆነ ማለት ነው። ክርስቲያን ከክርስትና፥ ክርስትናም ከክርስቶስ ተለይተው መታየት
አይችሉም።

ክርስቶስን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸው ሦስት ዐበይት ትምህርቶች


አሉ። እነዚህም፥ ጌትነቱ፥ ሞቱ እና ትንሣኤው ናቸው። ሥጋዌው ወይም ሥጋ
መልበሱም ትልቅ ነጥብ ነው፤ ግን ሥጋዌው በሞቱ ውስጥ የሚጠቀለል ነው።
ምክንያቱም፥ የሞተው ሥጋ ስለሆነ ወይም በሥጋ ስለመጣ ነው። እና ሦስቱ ግዙፋን
ትምህርቶች ጌትነት፥ ሞት፥ ትንሣኤ ናቸው። ሮሜ. 10፥9 እነዚህን ሦስት አሳቦች
በአንድ ጥቅስ፥ በአንድነት ጠፍሮ ይዟል። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር
እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና።

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር - ምን እንደሆነ? ጌታ። ጌታ ሲል


መለኮትነቱን ማወጁ ነው። ሰዎች በተለምዶ፥ ‘ጌታ፥ ጌታው’ ሊባሉ ይችላሉ። እዚህ
ጳውሎስ እየጻፈ ያለው ጌትነት ግን፥ የአክብሮት ‘ጌታ’ ወይም ‘ጌታው’ አይደለም። ጌታ
ሲል አምላክነቱን መግለጡ ነው።

እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው - ከምን? ከሙታን። ሞቶአል ማለት ነው።

92
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው - ከምን? ከሙታን። ምን እንዳደረገው?


እንዳስነሣው። ከሞት ተነሥቶአል ማለት ነው።

በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ እነዚህን ነገሮች ማመን ወይም አለማመን የመዳንና


የአለመዳን ልዩነት የታሰረበት እውቀት ወይም መንገድ ነው። አንድ ሰው ለመዳን፥
ድነትን ለማግኘት በልቡ እነዚህን ሦስት ነገሮች ማመን አለበት። ጌትነቱን፥ ሞቱን፥
ትንሣኤውን።

በሚገርም ሁኔታ እነዚህ ሦስቱም ነጥቦች ደግሞ በቁርኣን የማይገኙ ብቻ ሳይሆኑ፥


ቁርኣን አጥብቆ የሚቃወማቸው ናቸው። በቁርኣን ኢየሱስ ጌታ አይደለም (ወይም
አምላክ አይደለም)፤ አልተሰቀለም (ወይም አልሞተም)፤ ከሙታንም አልተነሣም።
ስለዚህ ምክንያት ብቻ የቁርኣኑ ዒሳ የወንጌሉ ኢየሱስ ፈጽሞ አይደለም ማለት
እንችላለን። ሌላ ምንም ሳይጨመር፥ በሮሜ 10፥9ን ብቻ በመጥቀስ ዒሳና ኢየሱስ
ሁለት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ማረጋገጥ እንችላለን። የቁርኣኑ ዒሳ በፈንታው
ሌላው እርሱን መስሎ የተሰቀለለትና እርሱ ሳይሞት ወደ ሰማይ የተወሰደው ነው።
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ጌታ የሆነው፥ የሞተው፥ የተቀበረውና የተነሣው ነው።

የትንሣኤው እውነትነት እና ምስክሮች


እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ
እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል
በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ . . . 1ቆሮ. 15፥3-4። ይህ ጳውሎስ፥ መጽሐፍ እንደሚል ብሎ
የጻፈው ቃል በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ጊዜ የነበረው የእምነት መግለጫ ነው
ብለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይስማማሉ። ‘መጽሐፍ እንደሚል’ የተባለው
በወንጌል ወይም በወንጌላት የተጻፈው የሞቱና ትንሣኤው ታሪክ ነው። ይህ
የሚያሳየው ጌታ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ወዲያው ብዙም ሳይቆይ፥ ይህ እውነት በጳውሎስ
ዘመን የእምነት መግለጫ ሆኖ ተጽፎ ነበር፤ ይጠቀስም ነበር ማለት ነው።

ሞቱን እውን ያደረገው ደግሞ ትንሣኤው እውን መሆኑ ነው። ቁርኣን እንደሚለው
አልሰቀሉትም፥ አልገደሉትም ተወሰደ እንጂ የሚለው ሐሰት መሆኑን የምናውቀው
ትንሣኤው የሐዋርያቱን ሕይወት ፈጽሞ የገለበጠው ጉዳይ በመሆኑ ነው። ኢየሱስ
ከተወሰደ በአካል ሊታይ አይችልም። ያ የተሰቀለውን በሌላ እንዲመሰል ያደረገው ሌላ
የተነሣ ሰውም አስመስሎ ካላቀረበ በቀር። ግን የተነሣው ደግሞ ራሱ ኢየሱስ መሆኑን
በተለያዩ ማስረጃዎች ሲያረጋግጥ አርባ ቀን ቆይቷል። ሐዋ. 1፥3 ደግሞ አርባ ቀን
እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ

93
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። ይላል። በብዙ ማስረጃ


(τεκμήριον ቴክሜሪዮን) የሚለው ቃል የሕግ ወይም የፍርድ ቤት ቃል ነው።
በብዙ እርግጠኛ የሚያደርግ ማረጋገጫ ከሕማማቱ (ከመከራው፥ ከስቃዩ፥
ከመስቀሉና ከሞቱ) በኋላ እየታያቸው ራሱን አሳያቸው። ሞቱን የሚያረጋግጠው
ትንሣኤው ነው። ትንሣኤው የሞቱ አረጋጋጭ ነው። ሞቱ፥ ተሰቅሎ መሞቱ እውን
መሆኑን የሚመሰክረው ትንሣኤው ነው። ከሞት የተነሣው ተፈጥሮም፥ ኃጢአትም፥
ሞትም በማይገዙት ወይም ሊሠለጥኑበት በማይችሉት እንደገና ሊሞት በማይችል
መንፈሳዊ አካል ነው።

የኢየሱስ በመስቀል መሞት፥ መሞቱ እንዲመስላቸው የተደረጉ የተታለሉ ጥቂት


አይሁድ ተከታዮቹ ብቻ የጻፉት ታሪክ አይደለም። እነሱ ተታልለው ጻፉ ቢባሉ
እንኳ፥ ያልተታለሉ ሌሎችም ጽፈዋል። ክርስቲያን ያልሆኑ እንዲያውም ጸረ ክርስትናና
ጸረ ክርስቲያኖች የሆኑ ሰዎችም እንኳ መሞቱን አምነው ጽፈዋል። ስለዚህ መሞቱ
እውነት መሆኑ ነው መኖሩን እውነት የሚያደርግላቸው። የኢየሱስ ሞት ታሪክም
የዘገበው እውነት ነው። ክርስቲያኖች ማመናቸው እምነታቸው ነውና የተታለሉት
ስለሆኑ የነሱን ምስክርነት አንቀበልም ማለት ቢሞከር እንኳ፥ ክርስቲያን ያልሆኑም
ይህንን እውነት ተቀብለው የጻፉ የታሪክ ዘጋቢዎች ጥቂት አይደሉም። ጎልተው
የሚታወቁትን አወሳለሁ፤

ምስክር አንድ፤

ከሙስሊም ምስክሮችም የኢየሱስን በመሰቀል መሞት የሚቀበሉ መኖራቸውን


መርሳት የለብንም። ከሙስሊሞች የዒሳን መሞት ከሚቀበሉት በመጥቀስ ልጀምር።

በኢስላም አልተሰቀለም፤ አልተገደለም የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፥ ተሰቅሏል ግን አልሞተም


የሚሉም አሉ። በኢስላም ውስጥ ቁጥራቸው ብዙ ባይሆንም ተሰቅሏል ግን አልሞተም
የሚሉ አሕማዲያዎች አሉ። አሕመዲዎች ወይም አህማዲያ የሚባለው ቡድን ወይም
ቤተ እምነት ሰዎች ኢየሱስ ተሰቅሏል፥ ግን አልሞተም፤ ሩሁን ስቶ፥ ከዚያ ከመስቀል
ወርዶ፥ ሳይሞት ተቀብሮ፥ አገግሞ ድኖ፥ ተነሥቶ፥ ከእናቱ ከማርያም፥ ከሚስቱ
ከመግደላዊት ማርያምና ከደቀ መዝሙሩ ከቶማስ ጋር ወደ ምሥራቅ ወደ ሕንድ አገር
ሄዶ፥ በካሽሚር ኖሮ፥ አገልግሎ፥ አርጅቶ ሞተ፤ መቃብሩም ስሪንጋር ውስጥ ሮዛ ባል
(Roza Bal - መካነ መቃብር ማለት ነው) ይገኛል የሚሉ ናቸው።

94
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ በመስቀል ላይ አልሞተም ብቻ ሳይሆን ዳግም ምጽአቱም


ተፈጽሟል ይሉናል፤ ሚርዛ ጉላም አህመድ (Mirza Ghulam Ahmad) የተባለው
የአህማዲያ ሃይማኖት ጀማሪ ዳግም የመጣው ኢየሱስ ነው ይሉናል። አሕመዲዎች።

ኢስማኢሊዎችም የኢስላም ሌላ ቅርንጫፍ ናቸው። እነዚህም ስለ ዒሳ ሞት የሚሉት


አላቸው። ኢስማኢሊዎች ሺዒዎች ወይም የሺዓ ኢስላም ተከታዮች ናቸው። ከነዚህ
ውስጥ Abu Hatim al-Razi የተባለው የኢስማኢሊ ፈላስፋ በማቴ. 10፥28
የተጻፈውን የወንጌል ቃል በመውሰድ፥ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል
የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን
ፍሩ። የሚለውን በመውሰድ የኢየሱስን ሥጋውን ነው የሰቀሉት እንጂ ነፍሱን
አይደለም ይላል። ይህንን የአል-ራዚን አሳብ ካሊል አንዳኒ የተባለ ኢስማኢሊ ሰው
በጽሑፉ ውስጥ ሲያብራራ፥ እንዲህ ይላል፤ (ትርጉም የራሴ ነው)

ስቅለትን በተመለከተ የኢስማኢሊ አቋም ሲጠቀለል እንዲህ ነው፤ በታሪክ ውስጥ


ኢየሱስ ተሰቅሏል ሞቷል፤ ‘በፈንታው የሞተ ልዋጭ’ የለም፤ ይህ፥ ‘ለነሱ ተመሰለ’
(ሹቢሃ ላሁም) የሚለው የኢየሱስ አካሉ ወይም ሰብአዊ ባህርዩ (ናሱት) ነው፤
የሰማያዊው ባህርይ መገለጫ የሆነችው የክርስቶስ ነፍስ ሰማያዊቱ ባህርይ (ላሁት)
ልትገደል አትችልም፤ ቁርኣን አልገደሉትም፥ አልሰቀሉትም የሚለው ያንን ነው።
እንዲህ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ እና ቁርኣን ስቅለቱን በተመለከተ አይጋጩም።
ይላል።

The Isma‘ili position on the Crucifixion can be summarized as follows:


Historically, Jesus was crucified and killed; there was no ‘substitute’.
That which ‘appeared to them’ (shubbiha lahum) as being crucified
was precisely the body or human nature (nasut) of Jesus. Christ’s
soul, as the manifestation of his divine nature (lahut), could not be
killed and this is what the Qur’an speaks of when it says “they killed
him not, nor did they crucify him”. The Bible and the Qur’an are thus
in agreement over the Crucifixion.12

ይህ የብዙዎቹ ሺዒ ኢስማኢሊዎች እምነት ነው። የአል-ራዚ ብቻ ሳይሆን ከ10ኛውና


11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በኖሩ በታሪካቸው ውስጥ የጎሉ ኢማሞቻቸው፥
ለምሳሌ፥ ኢማም አል-ሳዲቅ፥ ኢክዋን አል-ሳፋ፥ አል-ሲጂስታኒ፥ ጃፋር ኢብን-
ማንሱር፥ የሌሎቹም ትምህርት ነው።

12Khalil Andani, ገጽ 10። https://www.themathesontrust.org/papers/islam/andani-


crucifixion.pdf

95
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ከዘመናችን ሺዒዎች መካከል Reza Aslan የተባለው ኢራናዊ አሜሪካዊ ምሑርና


Zealot የተባለውን መጽሐፍ የጻፈ ሙስሊም ጸሐፊ ነው። ይህ መጽሐፍ ኢየሱስ
ቀናተኞቹ ከሚባሉት የሮምን መንግሥት በመገርሰስ የእግዚአብሔርን መንግሥት
ለማቆም ይጥሩ ከነበሩት በፍጻሜ ዘመን ከሚያምኑ ፖለቲከኞች አንዱ መሆኑን
ይተርካል። የመጽሐፉን መታተም ተከትሎ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2012 በተደረገለት
ቃለ ምልልስ Aslan ኢየሱስ እንደተሰቀለና እንደሞተ እንደሚያምን ተናግሯል።

እነዚህ ከኢስላምም ኢየሱስ ሞቷል የሚሉ፥ አልሞተም አልተሰቀለም የሚለውን


የማይቀበሉ መኖራቸውንም ያሳያል። አህመዲዎች፥ ኢስማኢሊዎችና፥ ከሺዒ
ኢስላሞችም ውስጥ የተወሰኑ አንዳንድ መኖራቸው ስለ ኢየሱስ አለመሞት
ከሙስሊሞችም ምስክር መጥራት እንደሚቻል ያሳያል።

ምስክር ሁለት፤

ከታሪክም ከዓለማውያን ወይም ክርስቲያን ያልሆኑ ታሪክ ጸሐፍትም ይህን የመሰከሩ


ብዙ አሉ። ታሪካዊ ምስክሮች ከሁሉ በፊት መታየት፥ መፈተሽ አለባቸው። ታሪካዊ
ምስክሮች ሲባል በጣም ለታሪኩ የቀረቡት ይበልጥ ተአማኒዎች ናቸው። በጣም ከራቁ
በጣም ታማኞች አይደሉም። ከአይሁዳውያን፥ ሮማውያን፥ ግሪካውያንም ታሪክ
ጸሐፍት ኢየሱስ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን በመስቀል ተሰቅሎ መሞቱን ጽፈዋል።
ጥቂት እንመልከት፤

ሀ) ፑብልዮስ ቆርነሌዎስ ታሲቶስ (ታሲተስ) አንዱ ነው። ይህ የታሲተስ መጽሐፍ


የተጻፈው በ116 ዓ. ም. ነው። ታሲቶስ የኖረው ከ55-120 ዓ. ም. ሲሆን ሁለት ትልልቅ
መጽሐፎችን ጽፎአል። Annals የተባለው አንዱ ነው። ይህ ሰው ክርስቲያን
አይደለም፤ ግን በመልካምነቱና ታማኝነቱ የታወቀ ሰው ነው። ታሲቶስ ታሪክ ጸሐፊ
ብቻ ሳይሆን ባለ ሥልጣንም ነው። ስለ ክርስቲያኖች ያወቀው ባለ ሥልጣን በመሆኑ
መንግሥታዊ ሰነዶችን የመመርመር ዕድል ስላለው ሳይሆን አይቀርም። ስለ
ክርስቲያኖች፥ ስለ ስያሜያቸው፥ ስለ ጅማሬያቸውና ከይሁዳ እስከ ሮም ስለ
መድረሳቸው በስፋት ጽፎአል። በዚህ ውስጥ ክርስቶስ በጴንጤናዊው ጲላጦስ
ተፈርዶበት መሞቱንም ጽፎአል። ታሲተስ Annals በተባለው መጽሐፉ 15፥44 ስለ
ሮም መቃጠልና የሮምን ቃጠሎ በክርስቲያኖች ላይ ስለመለጠፍ ነው የሚናገረው፤
ግን በክፍሉ ስለ ክርስቲያኖች ሲናገር እንዲህ ይላል፤

But all human efforts, all the lavish gifts of the emperor, and the
propitiations of the gods, did not banish the sinister belief that the

96
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

conflagration was the result of an order. Consequently, to get rid of


the report, Nero fastened the guilt and inflicted the most exquisite
tortures on a class hated for their abominations, called Christians by
the populace. Christus, from whom the name had its origin, suffered
the extreme penalty during the reign of Tiberius at the hands of one
of our procurators, Pontius Pilatus, and a most mischievous
superstition, thus checked for the moment, again broke out not only
in Judæa, the first source of the evil, but even in Rome, where all
things hideous and shameful from every part of the world find their
centre and become popular. Accordingly, an arrest was first made of
all who pleaded guilty; then, upon their information, an immense
multitude was convicted, not so much of the crime of firing the city,
as of hatred against mankind.13

ትርጉም፤

በመጨረሻም ክሱን ለማስወገድ ሲል ኔሮ ወንጀሉን ሕዝቡ ስለሚጠየፋቸውና


በጥላቻ ‘ክርስቲያን’ ብሎ በሚጠራቸው ሰዎች ላይ ጭኖ እጅግ የከፋ ቅጣት
ቀጣቸው። እነዚህ ስማቸውን ያገኙበት ክርስቶስ የተባለው በጢባርዮስ ዘመነ
መንግሥት ከገዢዎቻችን መካከል አንዱ በሆነው በጴንጤናዊው ጲላጦስ እጅ
እጅግ የከፋውን ቅጣት የተቀበለው ነው። ይህ አምልኮ ከተቀጨ በኋላ እንደገና
የክፋት ምንጭ በሆነችው በይሁዳ ተጫረና አስቀያሚና አሳፋሪ ነገሮች ከዓለሙ
ሁሉ መጥተው ታዋቂ በሚሆኑበት በሮምም ጭምር ናኘ። (ትርጉም የራሴ።)

በዚህ ጽሑፍ ስለ ክርስቶስ ሲናገር፥ ‘እነዚህ ስማቸውን ያገኙበት ክርስቶስ የተባለው


በጢባርዮስ ዘመነ መንግሥት ከገዢዎቻችን መካከል አንዱ በሆነው በጴንጤናዊው
ጲላጦስ እጅ እጅግ የከፋውን ቅጣት የተቀበለው ነው።’ ብሏል። እጅግ የከፋውን
ቅጣት ያለው የመስቀል ቅጣትን ነው። ታሲቶስ ስለ ክርስቶስ ይህን ለመናገር
ያስገደደው የለም። ታሪክን ነው የጻፈው። ታሪክን የጻፈው ደግሞ እንደ ታሪክ ዘጋቢ
እንጂ እንደ ክርስቲያን ሆኖ አይደለም። ታሲቶስ ክርስቲያን አልነበረም።

የከፋው ቅጣት የተባለው የመስቀል ቅጣት ምን ያህል የከፋ ሞት መሆኑን ከላይ


አይተናል። ሮማውያን የሚቀጡት ከፍተኛው የስቃይ ቅጣት ነው። በእንጨት መሰቀል
ለአይሁድም እንኳ እርግማን ነው፤ ዘዳ. 21፥22-23።

ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኃጢአት ቢሠራ፥ እንዲሞትም ቢፈረድበት፥


በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው፥ በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ

13 Tacitus, Annals 15ኛ ቅጽ 44ኛ ምዕራፍ።

97
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር


ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው። ዘዳ. 21፥
22-23፤ በእንጨት ላይ የሚሰቅሉት የከፋ ኃጢአተኛ ስለሆነና ምድሪቱን በኃጢአቱ
እንዳያረክስ ነው።

ገላ. 3፥10-13 ይህንን የዘዳግምን አሳብ ጠቅሶ ከክርስቶስ ጋር አቆራኝቶ ይገልጥልናል፤


ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ
ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና። ጻድቅ በእምነት
ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።
ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን፦ የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።
በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ
እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤

እነዚህ እንደ ታሲቶስ ያሉት ምስክሮች የአይሁድን ሕግ ያጠኑ ሊቃውንት ወይም


የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትና ተከታዮች አይደሉም። የፍርዱ አካሄድ፥ የችሎቱ ሂደት፥
በሮም መንግሥት የተመረመረበት ዝርዝር ተጽፎአል። በሮማዊ ሕግ 3 ጊዜ፤
በጲላጦስ፥ በሔሮድስ፥ እንደገና በጲላጦስ፥ በአይሁድ ሸንጎ 3 ጊዜ በሐናና በቀያፋ።
የክሱ ፋይል የሮም መንግሥት ቸል የሚለው ጉዳይ አይደለም። ‘የአይሁድ ንጉሥ’
ተብሎ ነው የተከሰሰው። ይህ ትልቅ ፖለቲካዊ ወይም ፕሮፓጋንዳዊ ወንጀል ጉዳይ
ነውና በቀላል የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ ዓይነት ችሎት ታይቶ የሚበየን ጉዳይ አይደለም።
ፍርዱ ፍትሕ የጎደለው ቢሆንም ሂደቱ የፍርድ ሂደት ነበር። ፍርዱም፥ ስቅለቱም፥
ሞቱም ሰዎች የሰሙት፥ ያዩት፥ ያረጋገጡት ነገር ነው።

የኢየሱስ ፍርድ የተደረገው በድብቅና በስውር አልነበረም። የቄሣር ወኪል ባለ


ሥልጣን፥ የይሁዳ ገዢ፥ የገሊላ ገዢ፥ ካህናት፥ ሊቀ ካህናቱ አሉበት። የአይሁድ
ሸንጎና የሮም ሥልጣን ቢሮ ያየው ጉዳይ ነው። የተሰቀለው ኢየሱስ አይደለም
የሚለው ውኃ የማያነሣ ቀሽም መከራከሪያ መሆኑን ይህ ሊያረጋግጥልን ይችላል።
እነዚህ ሁሉ ሰዎች የተሳሳተ ሰው ወስደው ሰቀሉ ለማለት የሚደፍር ሰው ሰነፍና
አላዋቂ ደፋር ነው። የሮም ሕግ ኢየሱስ አይደለሁም የሚልን ሰው፥ ‘ነህ እንጂ!’
ብለው ለፍርድ አሳልፎ አይሰጥም። የተከሰሰው ደግሞ ወንጀለኛ ሆኖ ከተገኘ ፍርዱን
በትክክልና ሙሉ በሙሉ መቀበሉን እርግጠኛ ሳይሆኑ አያቆሙም።

ለ) ፍላብዮስ ዮሴፍ (Josephus) ከ37-97 የኖረ አይሁዳዊና ለሮማውያን የአይሁድን


ታሪክ የዘገበ ሰው ነው። የአይሁድ ጥንተ ታሪክ (Antiquities of the Jews)
በተባለው ሥራው 18ኛው መጽሐፍ 3ኛ ምዕራፍ 3ኛ አንቀጽ ላይ እንዲህ ጽፎአል፤

3. Now there was about this time Jesus, a wise man, if it be lawful to
call him a man; for he was a doer of wonderful works, a teacher of

98
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

such men as receive the truth with pleasure. He drew over to him
both many of the Jews and many of the Gentiles. He was [the] Christ.
And when Pilate, at the suggestion of the principal men amongst us,
had condemned him to the cross, those that loved him at the first did
not forsake him; for he appeared to them alive again the third day; as
the divine prophets had foretold these and ten thousand other
wonderful things concerning him. And the tribe of Christians, so
named from him, are not extinct at this day.14

ትርጉም፤ ‘እነሆ በዚህ ዘመን ኢየሱስ የተባለ ጠቢብ ሰው ነበረ፤ ሰው መባሉ ሕጋዊ
ከሆነ፤ ምክንያቱም እርሱ ተምራትን አድራጊና እውነትን የሚወድዱ ሁሉ በደስታ
የሚሰሙት ነበረ። ከአይሁድም ከአሕዛብም ብዙዎችን ወደራሱ ስቦ ነበር። እርሱ
ክርስቶስ ነበረ። ከኛ መካከል አለቆቻችን ባቀረቡለት አሳብ ተስማምቶ ጲላጦስ
እንዲሰቀል በፈረደበት ጊዜ ከቀድሞ የወደዱት አልከዱትም ነበር። ከዚያም
የእግዚአብሔር ነቢያት ይህንና ሌሎችንም እልፍ ድንቅ ነገሮች እንደተናገሩለት
በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሥቶ ታያቸው። በእርሱ ስም የተሰየሙትና ክርስቲያን
የተባሉት ሕዝቦች እስከ ዛሬ ድረስም አልጠፉም።’ (ትርጉም የራሴ።)

ዮሴፍ የጻፈው ይህ ሥራ እንዲያውም በኋላ ክርስቲያኖች በጽሑፉ ውስጥ የሳጉት


ሥራ ነው ተብሎ በአንዳንድ ሊቃውንት ተነቅፎአል፤ ግን ከግምት በቀር ለነቀፌታው
ማስረጃ ሊያቀርቡ አልቻሉም። ዮሴፍ እንደ አይሁዳዊ ይህን ታሪክ ከታሪክ አንጻር
ሊያቀርብ እንደጣረ ይታያል። ደግሞም በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የሕይወት ዘመን
ነው የኖረውና ስለ ክርስትና ሲጽፍ ስለ ክርስቶስ ከሚያውቁት የቀዳ ሳይሆን
አይቀርም።

ሐ) ማራ ወልደ ሰራጵዮን (Mara Bar-Serapion) የተባለ እስረኛ ለልጁ በጻፈው


ደብዳቤ (የደብዳቤው ዘመን በትክክል አይታወቅም፤ ግን ከ73 እስከ 200ዎቹ
መጨረሻ ድረስ መሆኑ ይገመታል) አይሁድ ጠቢብ ንጉሣቸውን ስለ መግደላቸው
ጽፎአል።

መ) ታለስ (Thallus) ሌላው የሮም ጸሐፊ በ52 ዓ. ም. አካባቢ የጻፈውን በመጥቀስ


ዩልዮስ አፍራቅያኖስ (Julius Africanus) የተባለ ሌላ ጸሐፊ ጽፎአል። የታለስ ጽሑፍ
በሌሎች ጥቅስ ውስጥ ተጠቅሶ ብቻ ነው የሚገኘው እንጂ ራሱን እንደቻለ ሆኖ
አልተገኘም። አፍራቅያኖስ ታለስን ጠቅሶ የጻፈውም በ221 ዓ. ም. ነው። ኢየሱስ
በሞተ ጊዜ ስለሆነው ጨለማ ታለስ ጨለማው የፀሐይ ግርዶሽ ብቻ እንጂ ሌላ
አይደለም ብሎ አጣጥሎ የጻፈውን በመቃወም ነበር የጻፈው ነው። እንደ ማስረጃ
ያቀረበውም የአይሁድ ፋሲካ በዓል ሙሉ ጨረቃ ላይ የዋለ ሲሆን በሙሉ ጨረቃ

14 Antiquities: Book 18, Ch. 3, Electronic version.

99
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ጊዜ ቀን ላይ የፀሐይ ግርዶሽ ሊኖር አለመቻሉን በማብራራት ነው።15 ሙሉ ጨረቃ


ሲሆን ኢየሱስ በሞተበት ከሰዓት በኋላ በ9 ሰዓት የፀሐይ ግርዶሽ ሊኖር አይችልም።
ሙሉዋ ጨረቃ ማታ ላይ ነው የምትታየውና በ9 ሰዓት ፀሐይን ልትጋርድ
በምትችልበት ስፍራ አትገኝም። ይህንን የቀን ጨለማ የአርዮስፋጎሱ ድዮናስዮስ
(Dionysius the Areopagite) የተባለው ሰውም ጠቅሶታል።

ሠ) የሳሞሳታው (ግሪካዊው) ሉቅያኖስ (Lucian of Samosata) ይህ ሰው የፌዝ


ወይም የስላቅ ጽሑፎችን የሚጽፍ ሰው ነበረ። ስለ ክርስቲያኖችም እያፌዘ የጻፈ ሰው
ነው። የኖረው ከ125 እስከ 180 ዓ. ም. ገደማ ነው። ስለ ክርስቲያኖች በጻፈው ጽሑፉ
ውስጥ ክርስቲያኖች በመስቀል ላይ የተሰቀለውን መሪያቸው ወይም ሕግ ሰጪያቸው
የሆነውን ሰው እንደሚያመልኩ ጠቅሶአል።16 ሉቅያኖስ የኖረው ከክርስቶስ ሞትና
ትንሣኤ በኋላ ከ100 ዓመታት በኋላ ሲሆን ይህ የክርስቶስ ሞት ለግሪካውያን
ዓለማውያን ተረት ሳይሆን ታሪክ ነው። እያፌዘባቸው ነው በመስቀል የተሰቀለ መሪ
ያመልካሉ እያለ የምጸት ጽሑፍ የጻፈው።

ረ) የጲላጦስ ሥራ ወይም ግብረ ጲላጦስ (Acts of Pontius Pilate.) የተባለውን


ሰነድ ሰማዕቱ ኢዮስጢን (Justin Martyr) እና ጠርጡልያኖስ (Tertullian)
በመጥቀስ የክርስቶስ መሰቀልና ሞት የተረጋገጠ መሆኑን ጽፈዋል። እነዚህ ጸሐፊዎች
(ኢዮስጢን እና ጠርጡልያኖስ) ክርስቲያኖች ናቸው የጠቀሱት ሰነድ ግን ሮማዊ
ምንጭ ነው። ኢዮስጢን በ150 ዓ. ም. አካባቢ ጠርጡልያኖስ ደግሞ በ220 ዓ. ም.
አካባቢ ነው የጻፉት።17 ኢዮስጢን እና ጠርጡልያኖስ ክርስቲያኖች ሲሆኑ የጠቀሱት
ምንጭ ግን ክርስቲያን ያልሆነ ሰው ሥራ ነው። ስለዚህ ያላመኑ ሰዎችም የክርስቶስን
ሞት ጽፈዋል።

ሰ) ሶይቶኒዮስ፤ የቄሣር አድርያን (Emperor Hadrian) (የኖረው 78-138 ዓ. ም.


የነገሠው 117-138) ጸሐፊ የሆነው ሶይቶኒዮስ (Suetonius) ለክርስቲያኖች ስደት
ምክንያት ስለሆነው ስለ ተሰቀለው ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤም ጽፎአል።18

ሸ) በ140 ዓ. ም. ገደማ ቄልስዮስ (Celsius) የተባለ የክርስትና ጠላት የሆነ ጸሐፊም


ስለ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቃይቶ መሞት ጽፎአል።

15 F. F. Bruce: The New Testament Document, IVF & Tyndale Press., London 1960, p.
113, 143.
16 Habermas, Gary R. The Verdict of History, Thomas Nelson, Nashville, 1982, pp. 100.
17 Ibid., pp. 107-108.
18 Ibid., pp. 89-90.

100
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ቀ) አይሁድ በትውፊትና ኋላም በታሪክ ባስቀመጧቸው ሰነዶች የክርስቶስን ሞት


ጽፈዋል። ጠልሙድ (Talmud) የአይሁድ ስነ ቃልና ስነ ጽሑፍ የታሪክ ሥራ ነው።
ስነ ቃላዊው ሥራ ሚሽና የተባለው ሲሆን ይህ ትውፊት በ2ኛው መቶ በጽሑፍ
ሊቀመጥ በቅቶአል። በጽሑፍ የተቀመጠው ትውፊት (ሚሽና) ገማራ ይባላል፤ ገማራ
ስብስብ ወይም መድብል ማለት ነው። ሚሽና ስድስት ክፍሎች አሉት። በ4ኛው ክፍል
ውስጥ ሳንሂድሪን ስለተባለው ስለ አይሁድ ሸንጎ በተጻፈው ውስጥ ስለ ሸንጎው ፍርድ
ሂደት ዝርዝር ተወስቶአል። ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ፍርድም ተጽፏል።

On the Eve of Passover they hung Yeshu the Notzarine. And the
herald went out before him for 40 days [saying]: “Yeshu the
Notzarine will go out to be stoned for sorcery and misleading and
enticing Israel [to idolatry]. Any who knows [anything] in his defence
must come and declare concerning him.” But no-one came to his
defence so they hung him on the Eve of Passover.19

ትርጉም፤ በፋሲካ ዋዜማ የናዝሬቱን የሱስ ሰቀሉት። አዋጅ ነጋሪው ከእርሱ በፊት
40 ቀናት ቀድሞ፥ ‘የሱስ የናዝሬቱ ስለ ጥንቆላ እና እስራኤልን (በጣዖት አምልኮ)
ስለማሳት በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል። ስለ እርሱ ምንም ነገር የሚያውቅና
የሚሟገት ማንም ሰው ቀርቦ መናገር አለበት።’ እያለ ለፈፈ። ነገር ግን ሊሟገትለት
የመጣ ማንም አልነበረምና በፋሲካ ዋዜማ ሰቀሉት።

ከዚህ የምንረዳው አይሁድ እንኳ በጽሑፋቸው የተሰቀለው ኢየሱስ እንጂ ኢየሱስን


የመሰለ አለመሆኑን ያረጋግጣሉ። አይሁድ የጻፉልን ሌላ ጽሑፍ ቶሌዶት ዬሹ
(Toledoth Jeshu) የሚባል ልብ ወለዳዊ ሥራም አለ። ይህ ጽሑፍ የኢየሱስ ደቀ
መዛሙርት በድኑን ሊሰርቁ ማሰባቸውን አንድ ይሁዳ የተባለ አትክልት ጠባቂ ሰምቶ
በሌሊት መጥቶ የኢየሱስን በድን ከዮሴፍ መቃብር ወስዶ አዲስ በተቆፈረ ጉድጓድ
ቀበረው። ደቀ መዛሙርቱም ወደ መቃብሩ መጥተው የኢየሱስን በድን ባጡ ጊዜ
ተነስቶአል እያሉ ተመለሱ። የአይሁድ አለቆችም መጥተው መቃብሩ ባዶ ሆኖ
አገኙት። አትክልት ጠባቂው ግን ወስዶ አዲሱን መቃብርና የኢየሱስን በድን
አሳያቸው።20 ይላል።

ይህ በማቴ. 28፥11-15 ከተጻፈው በድኑን ሰረቁት ከሚለው ወግ ጋር ይቀራረባል። ነገር


ግን የቀላል ሚዛን ውሸትነቱን የሚገልጠው ብዙ ቀዳዳዎችም ያሉበት ተረት ነው።
ለምሳሌ፥ አትክልት ጠባቂው መቃብሩን ይጠብቁ የነበሩትን የሮም ወታደሮችና

19
Sanhadrin 43a (http://www.tyndale.cam.ac.uk/Tyndale/staff/Instone-
Brewer/prepub/Sanhedrin%2043a%20censored.pdf).
20 Habermas, Gary R. The Verdict of History, Thomas Nelson, Nashville, 1982, p. 99.

101
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የታተመውን መቃብር እንዴት አልፎ ያን ገድል ፈጸመ? ደህና፤ ፈጸመ እንበል።


አይሁድ ኢየሱስ ተነሣ ሲባል ሐሰትነቱን ለማረጋገጥ አዲሱን መቃብርና ሬሳውን
ስለምን አላሳዩም? ይህ፥ 'ተሰረቀ' ለተባለው ፈጠራ መደገፊያ የተሠራ ልብ ወለዳዊ
ትረካ ነው። ይሁን እንጂ የሞተውና የተቀበረው ኢየሱስ እንጂ ሌላ ኢየሱስን የመሰለ
ሰው መሆኑን ይህም ተረት አያወሳም።

እነዚህ ሁሉ ከላይ የተዘረዘሩት ክርስቲያናዊ ያልሆኑና ታሪካዊ ጽሑፎች ናቸው።


ታሪክን የዘገቡ ሰነዶች ናቸው። ከነዚህ ጽሑፎች በየትኛውም የሞተው ሰው ላዩት
ሰዎች በኢየሱስ ተመሰለ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስን መሰለ የሚል እንኳን ቃል፥ መናኛ
አሳብ እንኳ አናገኝም። ስለዚህ፥ በቁርኣን 4፥157 ‘እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን
ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው (ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤
አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ . . .’ የሚለው ከ600
ዓመታት በኋላ የተፈጠረ የፈጠራ ቃል እና ስሕተት ነው።

እስካሁን ያየናቸው ሁለት ቡድን ምስክሮች ክፍል አንድ ሙስሊሞች፥ እና ክፍል


ሁለት ከክርስትና ውጪ የሆኑ የታሪክ ምስክሮች ማኅደር ነው።

ምስክር ሦስት፤

ከነዚህ የውጪ ምስክሮች ሌላ በርካታ ክርስቲያን ጸሐፊዎችንም መጥቀስ ይቻላል።


ስለ ጌታ የጻፉ ክርስቲያን ጸሐፊዎች እጅግ ብዙ ናቸው። ለሙስሊም ተከራካሪዎች
ክርስቲያን ጸሐፊዎችን መጥቀስ ላይጥም ይችላል፤ ግን እነዚህ የተከበሩ ጸሐፊዎች
ናቸው፤ ጽሑፋቸውም የመጀመሪያዎቹን ክርስቲያኖች እምነት የሚያንጸባርቅ ነው።
ስለዚህ ጸሐፊዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ክርስቲያኖቹም በእምነት የቆሙበትን አንሸራታች
ያልሆነ ዓለት ማየት ይቻላል። ያንን እምነት ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያትና ደቀ
መዛሙርት እንደተቀበሉትና እንደኖሩበትም መረዳት ይቻላል። ቢያንስ ጥቂት ስሞችን
ብቻ ከመጀመሪያው መቶ ምዕት ዓመት ለአብነት ላውሳ፤

የሮሜው ቀሌምንጦስ (ከ30-100 ዓ. ም.)

አግናጤዎስ (ከ35-107 ዓ. ም.)

ጳጵያስ (ከ60-130 ዓ. ም.)

102
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ፖሊቃርጶስ (ከ65-155 ዓ. ም.)

የነዚህንና ከነዚህ በኋላ የኖሩትንና ከአዲስ ኪዳን ጥቅሶች እየጠቀሱ የጻፉትን የአባቶች
ጽሑፎች በመሰብሰብ ጠቅላላውን አዲስ ኪዳን በሙሉ (ከ17 ጥቅሶች በስተቀር)
እንደገና መጻፍ ይቻላል ይላል የምካቴ ክርስትናው ምሑር ጆሽ ማክደዌል።21 ጆሽ
ማክደዌል የክርስቶስን ሞትና በተለይም፥ ትንሣኤ እውነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ
ሰፊና ጥልቅ ምርመራ ካደረገ በኋላ የትንሣኤው ማስረጃ ክብደቱና ብዛቱ ከሞት
የተነሣውን ጌታ በማመንና በመከተል ክርስቲያን ከመሆን ሌላ አማራጭ ሊሰጠው
ስላልቻለ በ1959 ክርስቲያን የሆነ ሰው ነው።

ምስክር አራት፤

አራተኛውና የመጨረሻው ምስክር ቅዱስ ቃሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላው፥


በተለይም አዲስ ኪዳን ሞቱን፥ ስቅለቱን ቀብሩን፥ ትንሣኤውን ገልጦ ይናገራል።

አይሁድ መሢሕ ይሰቀላል ብለው እንኳን አስበው፥ አልመውም አያውቁም። አይሁድ


የሚጠብቁ የነበረው መሢሕ ነጻ አውጪ፥ አሕዛብን በብረት በትር ቀጥቅጦ የሚገዛ፥
ድል ነሺ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አንበሳ ነው። በመስቀል የሚሞት መሢህ ጭራሽ
አይታሰብም። መሰቀል እርግማን ነዋ! በእንጨት የሚሰቀል የተረገመ፥ መሬት ላይ
ቢሞት መሬትን የሚያረክስ እንደሆነ የሚታሰብ ስለሆነ መሬት ላይ ሞቶ መሬት
እንዳያረክስ በእንጨት ከፍ ብሎ አየር ላይ መሞት የተገባው ርጉም ነው። መስቀል
የሚለው ቃልና መስቀል የሚባለው አሳብ በራሱ አሳፋሪ ነገር ሆኖ እያለ፥ እራሱ
በመስቀል ላይ የሞተ መሢሕ መከተል ደግሞ ይበልጡን አሳፋሪ የሆነ ነገር። ራሱን
እንኳ ማዳን የማይችል አዳኝ እንዴት ሌላውን ያድናል? ተቃርኖ ይመስላል።

ነገር ግን በመስቀል ላይ መሞቱ ብቻ ሳይሆን፥ የተደረገው ድርጊትም ብቻ ሳይሆን፥


ምክንያቱም፥ ለምን መሞቱም ነው ለተከታዮቹ የገባቸውና የተከተሉት። ገባቸውና
ተከተሉት እንጂ መስቀል ማለት ሞኝነትና አሳፋሪ፥ መሰናክልም የሆነ ጉዳይ ነው።
1ቆሮ. 1፥18 እና 22-24፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን
የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ
ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም
ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ

21 Mc Dowell, Josh: Evidence that Demands a Verdict, Campus Crusade for Christ
International, Arrowhead, San Bernadino, CA, 1977, pp. 54-55.

103
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ


ነው።

እዚህ ሁለት ቃላት ላይ እናተኩር፤ ማሰናከያ እና ሞኝነት በሚሉ ሁለት ቃላት።


ማሰናከያ የሚለው ቃል ማፈሪያ ወይም አሳፋሪ ነገር ማለት ነው። ነውር ወደ ማለት
የተጠጋ ቃል ነው። የተሰቀለ አዳኝ? ያሳፍራል! የመስቀሉ ቃል አሳፋሪነቱ
ለሃይማኖተኞች ነው። ለአይሁድ መስቀል፥ የተሰቀለ ሰው፥ የተሰቀለ አዳኝ ነውር
ነው። ተሰናከሉበት።

ሞኝነት ደግሞ ሞኝነት ነው፤ ቂልነትና ጅልነት ነው። ማሰናከያ ለሃይማኖተኞች


እንደሆነው ሞኝነት ደግሞ ተማርን ለሚሉ ለጠቢባን፥ ለግሪኮች፥ ለምክንያታውያን፥
በስነ አመክንዮ ለተራቀቁ ሰዎች የመስቀል ሞት እና በመስቀል ላይ የሞተ አንድ ሰው
ሌሎችን ሊያድን የመቻሉ ነገር ቂልነት ነው።

ለማያምኑትና ለማይቀበሉት ግራ የሆነው ይህ የመስቀል ጉዳይ ለተጠሩት ግን፥


ለሚያምኑት ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ሆነ። ምኑ? የመስቀሉ ቃል፤ ይህ
መሢሑ በመስቀል ላይ የመሞቱና በሞቱ የማዳኑ ቃል፤ የማዳኑ ትምህርት።

ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ውስጥ በገሃድ እንደሚታየው እንደ ቁርኣን ትምህርት


ኢየሱስ አልሞተም። የተሰቀለና የሞተ ሰው አለ፤ ግን ያ ሰው ኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስን
እንዲመስል የተደረገ ሌላ ሰው ነው። ስለዚያ ሰው ማንነት እና በዚህ የመምሰልና
የአለመሆን ጉዳይ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ውስጣዊ ግጭቶችን ቀደም ሲል
ተመልክተናል።

የመስቀል ሞት ምንነት
መስቀሉ የክርስትና እምነት እንብርት መሆኑ የታወቀ ነው። ቀደም ሲል
እንደተመለከትነው ክርስቶስን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸው ሦስት
ዐበይት ትምህርቶች አሉ። እነዚህም፥ ጌትነቱ፥ ሞቱ እና ትንሣኤው ናቸው። ብዬ
ነበር። ሥጋ መልበሱም ትልቅ ነጥብ ነው፤ ግን ሥጋዌው በሞቱ ውስጥ የሚጠቀለል
ነው። የሞተው ሥጋ ስለለበሰ ወይም በሥጋ ስለመጣ ነው በማለት እነዚህን ሦስት
ግዙፋን ትምህርቶች ጌትነት፥ ሞት፥ ትንሣኤ የሚለውን ጠቅልሎ፥ ጠፍሮ የያዘልን
አንድ ጥቅስ አይተን ነበር፤ ሮሜ. 10፥9፤ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር
እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና።

104
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር - ምን እንደሆነ? ጌታ። ጌታ ሲል


ገዢነትን፥ ሉዓላዊነትን፥ መለኮትነትን መግለጡ ነው።

እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው - ከምን? ከሙታን። ከሙታን ከተነሣ


ሞቶአል ማለት ነው። ለምን ሞተ? እንመለከተዋለን።

እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው - ምን እንዳደረገው? እንዳስነሣው። ከምን?


ከሙታን። ከሞት ተነሥቶአል ማለት ነው። የትንሣኤውን አስፈላጊነትም እናያለን።

እነዚህ ሦስቱም ነጥቦች ደግሞ በቁርኣን የማይገኙ ብቻ ሳይሆኑ፥ ቁርኣን አጥብቆ


የሚቃወማቸው ናቸው። በቁርኣን ኢየሱስ ጌታ አይደለም (ወይም አምላክ አይደለም)፤
አልተሰቀለም (ወይም አልሞተም)፤ ከሙታንም አልተነሣም። ታዲያ፥ ስለዚህ
ምክንያት ብቻ የቁርኣኑ ዒሳ የወንጌሉ ኢየሱስ ፈጽሞ አይደለም ማለት አንችልም?
እንችላለን። የቁርኣኑ ዒሳ በፈንታው ሌላው እርሱን መስሎ የተሰቀለለትና እርሱ
ሳይሞት ወደ ሰማይ የተወሰደው ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ደግሞ የሞተው፥
የተቀበረውና የተነሣው ነው።

መስቀሉ የክርስትና እምነት እንብርት የሆነው፥ የአሮጌው ኪዳን ማብቂያና የአዲሱ


ኪዳን ጅማሬ ስለሆነ ነው። የኪዳናቱ ድንበር መስቀሉ ነው። አዲሱ ኪዳን
የተጀመረው በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደም ነው። ይህን መካድ ከዚህ ኪዳን ውጪ
መሆን ነው። የሰው ልጆች ደኅንነት ይህን እውነት በመቀበልና ባለመቀበል ላይ
ባላቸው ውሳኔ ላይ የጸና ነው። መስቀሉን ለመካድ ወይም ክርስቶስ በመስቀል ላይ
አልተሰቀለም ለማለት ብዙ፥ እጅግ ብዙ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ማስረጃዎችንና
ምስክሮችን በጅምላ መካድ አስፈላጊ ነው። ይህንን ደግሞ ሕሊናና አእምሮ
አይቀበለውም። ይህ የመስቀሉ ገድል ክርስቲያኖች የሚያምኑት እውነትና
እውነትነቱም በቃሉ የተጻፈ ነው።

መስቀሉ የእርግጠኛነታችን መሠረት ነው።


መስቀሉ ሞቱን እርግጠኛ የሚያደርግ እውነት አለበት። የእግዚአብሔር ይቅርታ
በተፈጸመ ሥራ ላይ፥ በተከፈለ ዋጋ ላይ የተመሠረተ ይቅርታ ነው። በመስቀሉ ላይ
የእግዚአብሔር ምሕረትና ቁጣው፥ ፍርድና ፍትሕ አብሮ ተገልጦአል። ጸጋውና ጽድቁ
አብሮ ታይቶአል። በሞት ለተገኘ ሕይወት የሕይወት ሞት ዋጋ የተከፈለበት ስፍራ
ነው መስቀሉ።

105
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ዋጋ ከተከፈለ እርግጠኛ የሚያደርግ ዋስትና አለ ማለት ነው። የተከፈለው ዋጋ ደግሞ


ሙሉ ዋጋ ነው። እንኳን ሙሉ ዋጋ ተከፍሎ ቀብድ እንኳ ሰጥቶ አንድ ዕቃ የኔ ነው
ማለት ይቻላል። መስቀሉ የኃጢአት ዋጋ፥ ሙሉው ዋጋ የተከፈለበት ስፍራ ነው።
ኃጢአት መቀጣት አለበት፤ በመስቀል ላይ ኃጢአት ተቀጣ። ቅጣቱ ደግሞ ኃጢአትን
ያስወግዳል፤ ኃጢአት ተወገደ። ዕዳ ከተከፈለ ባለ ዕዳነት የለም። ተከፍሏላ!
ክርስቲያኖችን እፎይ ያሰኘው እውነት ይህ የተከፈለ ዕዳና የኃጢአት ስርየት ነው።

መስቀሉ በሥራና በጥረት መዳንን ያበቃበት ስፍራና ያበቃው ድርጊትም ነው።


መልካም ሥራን ለመዳን ተብሎ ሲደረግና ከተዳነ በኋላ ሲደረግ ፈጽሞ የተለያዩ
ነገሮች ናቸው። የክርስትና መልካም ሥራ ከተዳነ በኋላ እርግጠኛ የሆነ መዳንን
የማሳየት ድርጊት ነው፤ በጌታ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለውና ያንን ለመመስከርና
ሌሎችም ያንን እንዲያገኙ የሚደረግ ምስክርነት ነው እንጂ ለመዳን ተብሎ የሚደረግ
ሥራ አይደለም። የዳነ ሰው የሚሠራው ሥራ በውስጡ ያለው የክርስቶስ ሕይወት
የሚያፈልቀው ነገር እንጂ ጥረት አይደለም።

የመስቀሉ፥ ‘ተፈጸመ’ የጥረት ፍጻሜ ነው። እግዚአብሔርን በራስ ሥራ ለማስደሰት


የመልፋት ልፋት ፍጻሜ ነው። ተከፍሎልኛል፤ በደሌ ተወግዶልኛል፤ በፈንታዬ እርሱ
ፈጽሞልኛል፥ ከውኖልኛል አረፍኩ፤ እፎይ ማለት ነው።

በሥራ ለመጽደቅ ለሚሞክር ሃይማኖት ይህ የኃጢአት ይቅርታ የተገኘበት መንገድ


መስቀሉ መሆኑ የማይዋጥ ትምህርት ነው። ልፋት የለበትማ! ዋጋ መክፈል፥ ዐቀበት
መውጣት፥ ቁልቁለት መውረድ የለበትማ! ንስሐ፥ መናዘዝ፥ ራስን መጉዳት፥ ማጎሳቆል
የለበትማ! ሌላውን ማጎሳቆልና መግደልም የለበትማ! የልፋት ወይም በሥራ የመጽደቅ
ሃይማኖቶች ስርየት፥ ይቅርታ፥ የዘላለም ሕይወት በነጻ መቀበል ከሆነ ርካሽ
ይመስላቸዋል። ስርየት፥ ይቅርታና የዘላለም ሕይወት ነጻ ነው ማለት ግን ርካሽ ነው
ማለት አይደለም። ለሕይወት የሚያስፈልጉን ትልልቅ ነገሮች ነጻ ናቸው፤ ርካሽ ግን
አይደሉም። ለምሳሌ፥ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት ነጻ ነው፤ አየር ነጻ ነው፤ እነዚህ ረከስ
ባለ ዋጋ ፈልገንና አማርጠን ወይም ተከራክረንና ተደራድረን ዋጋ አስቀንሰን
አንገዛቸውም።

የዘላለም ሕይወትም ነጻ ነው፤ ርካሽ ግን አይደለም። ዋጋው ተከፈለ ማለት እኛ


ከፋዮቹ ስላልሆንን፥ ስላልከፈልን ርካሽ ነው ማለት አይደለም። 'እግዚአብሔር ሁሉን
ቻይ በመሆኑ ይቅር ሊል ከወደደ ይችላል' ለሚሉ የመስቀል ላይ ሞት ትርጉም
አይሰጥም። ኃጢአት ደመወዝ አለው፤ ዋጋ አለው። ደመወዙ፥ ዋጋው መከፈል
አለበት። ደመወዙ፥ ዋጋው ሞት ነው። አንተ መሞት አለብህ፤ አንቺ መሞት አለብሽ፤
እኔ መሞት አለብኝ፤ ወይም ሌላው በፈንታዬ መሞት አለበት።

106
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

'እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ በመሆኑ ይቅር ሊል ከወደደ ይችላል' ለሚሉት የመስቀል


ላይ ሞት ትርጉም አይሰጥም ያልኩትን ላብራራው። ይህ አማራጭ ተደርጎ
የሚወሰደው የይቅርታ መንገድም ዋስትናን የሚያስጨብጥ አይደለም። እርግጠኛ
የሚያደርግ አይደለም። 'እግዚአብሔር አዛኝ ነው፤ ርኅሩኅ ነው፤ ይቅርታ አድራጊ ነው'
ማለትና፣ 'እርግጠኛ ነኝ ይቅርታ አድርጎልኛል፥ ተቀብሎኛል' ማለት የተለያዩ ናቸው።
አንድ ሰው የይቅርታው እርግጠኛ መሆን የሚችለው መቼ ነው? እስከ ምን ድረስ
ራሱን አጎሳቁሎ ነው? መናዘዝና ንስሐ፥ ዋጋ መክፈልና ራስን ማጎሳቆል እስከ ምን
ድረስ ሊሆን ነው? ይቅርታው ለመገኘቱስ ምን ማስረጃና ማረጋገጫ ሊኖር ይችላል?
አይችልም። በሥራ እግዚአብሔርን ለማስደሰትና ደኅንነትን፥ ዘላለማዊ ሕይወትንና
መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ፈጽሞ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ፈጽሞ
አይቻልም።

ያ ሰው እግዚአብሔር እንደተደሰተበት ፈጽሞ እርግጠኛ አይሆንም። ቢበዛ፥ 'ፈጣሪ፥


እርሱ ያውቃል' ብቻ ነው የሚለው። ይህ እስልምናን ጨምሮ ሁሉንም በሥራ
የሚታመኑ ሃይማኖቶችን የሚመለከት ነው። በተለይ በእስልምና እርግጠኝነት ስለሌለ
ማንም ከሞት በኋላ ወዴት እንደሚሄድ የተረዳ ኖሮ አያውቅም። ሙሐመድም እንኳ
ከሞት በኋላ የት እንደሚሄድ እርግጠኛ አልነበረም። አንድ እግሩ ወደ ጀነት ከገባ
በኋላ እንኳ አላህ አውጥቶ ሊወረውረው እንደሚችል ተናግሯል። ወደ ክርስትና
ስንመጣ ግን ይህንን እርግጠኝነት እውን የሚያደርገው የሞተውና ሞቶ የተነሣው ጌታ
ቃል ነው።

ወደ መስቀሉ እውነት ስንመጣም መስቀሉ የክርስትና እምነት እንብርት ነው። በሞቱ


ነዋ ሕይወት ያገኘነው። በትንሣኤው ነዋ የጸደቅነው። መስቀሉ ከውስጡ ከወጣ
ክርስትና ምውት ነው። ክርስትናንን ምውት ለማድረግ ሰይጣን የሚፍጨረጨርበት
አንድ መንገድ መስቀሉን ማስካድ መሆኑ ማስገረም የለበትም። መስቀሉ ሰይጣን
እራሱ የተቀጠቀጠበት ስፍራ ነውና (ዘፍ. 3፥15) ሰይጣን የሚጠላውና የሚታወክበት
አንድ ማዕከላዊ ሥራ ቢኖር ሌላ ምንም ሳይሆን መስቀሉ ነው። ሰዎችም
እያዳያውቁትና እንዳይቀበሉት የሚፍጨረጨርበት ትልቅ ጉዳይ መስቀሉ ነው። በዚያ
መስቀል ላይ የተሰቀለው ኢየሱስ እንጂ ቁርኣን እንደሚለው ሌላ ማንም አልነበረም።

መስቀሉ ከአራት ማዕዘናት ሲታይ


የመስቀሉን እውነት ከቃሉ ከአራት ነገሮች አንጻር እንይ። 1. ከአስፈላጊነቱ፥ 2.
ከትንቢት፥ 3. ከድርጊት፥ እና 4. ከዓይን ምስክሮች።

107
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አስፈላጊነቱ ስል የኃጢአት ዋጋ የመከፈሉ ጉዳይ፥ የመከፈሉ አስፈላጊነት ማለቴ ነው።


ትንቢቱ ስል ሌሎች ነቢያት የተናገሩትና ራሱ ጌታም እንደሚሞት የተናገረው ቃል እና
የትንቢቶቹ መፈጸም የሞቱ ምስክር መሆኑ ነው። ድርጊቱ ፍጻሜው ነው፤ የተነገሩት
ትንቢቶች ተፈጸሙ። ምስክሮቹ ሲሰቀልና ሲሞት ተገኝተው በጆሮ የሰሙት፥ በዓይን
ያዩት፥ መሞቱን ያረጋገጡት፥ የቀበሩት፥ ከሙታን ከተነሣ በኋላ መነሣቱን ያዩት፥
የዳሰሱት፥ ያረጋገጡት፥ የጻፉት፥ የተለወጠ ሕይወት ያሳዩት፥ በዓላማ የኖሩትና ሞትን
ሳይፈሩ የሞቱት ምስክሮች ናቸው።

ኢየሱስ ከሞተ ከ600 ዓመታት በኋላ የተነገረ አልሞተም፥ አልተሰቀለም የሚል


ክህደት እነዚህን ማስረጃዎች የሚሸከምበት ጉልበትም ትከሻም የለውም።
በሙስሊሞች ዘንድ ኢየሱስ በሕይወቱ መጨረሻ ምን እንደሆነ የተስማማ
አመለካከትም የለም። አንዳንዱ ሞቶ ተነሥቶ እንደተወሰደ ያምናሉ። አንዳንዱ
ሳይሞት እንደተነጠቀና ገና መጥቶ እንደሚሞት ያምናሉ። አንዳንዱ ተሰቅሎ
እንደነበርና ከተሰቀለበት ሳይሞት ተቀብሮ፥ አገግሞ ድኖ፥ ኖሮ እንደሞተ ያምናሉ።
አንድ አይደሉም። ክርስቶስ አልሞተም አልተሰቀለም የሚሉት ይህንን፥ 'አልገደሉትም፤
አልሰቀሉትምም፤ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ' የሚለውን ጥቅስ ብቻ
በመውሰድ ነው። ለዚህ አንድ ጥቅስ ሌላው ሁሉ ማስረጃ እንደ ባለ አእምሮ
ሳይመዘንና ሳይመረመር ውድቅ ተደርጎአል። ይህ አእምሮን በርካሽ መሸጥ ነው። ወደ
አራቱ ማዕዘናት እይታ እንለፍ።

1. የመስቀሉ አስፈላጊነት

የሞት አስፈላጊነት የኃጢአትን ክብደት የሚያሳይ ነገር ነው። እግዚአብሔር ፍጹም


ቅዱስ አምላክ ነውና ኃጢአት በእርሱ ዘንድ ከቶም ሊገኝ የተገባ አይደለም። የኃጢአት
ዋጋ ሞት ነው (ዘፍ. 2፥17፤ ሮሜ 6፥23)። ኃጢአትን ፈጽሞ የሞትን ዋጋ የማይጠብቅ
ማንም ሰው የለም። የሰው ልጅ ሁሉ የሚሞተው በኃጢአት ምክንያት ነው። ሞት
ወደ ሰው ሕይወት ውስጥ የገባው በኃጢአት ምክንያት ነው። ሞት ዋጋ ካለው ዋጋው
መከፈል አለበት። እርሱ ኃጢአትን ያደረገው ሰው መሞት አለበት ወይም ስለ እርሱ
ሌላው መሞት አለበት።

ይህ ሌላው መሞት አለበት የሚባለው ነገር ነው ለመረዳት የሚከብደው። ለጥፋቱ


ዋጋው መከፈሉ አስፈላጊ ሆኖ፥ ተፈላጊ ሆኖ ሳለ፥ አንዱ አጥፍቶ ሌላው ዋጋ መክፈሉ
ኢፍትሐዊ ነው። እርግጥም ያለ ፍላጎት አንዱ በሌላው ፈንታ ከሞተ ወይም
እንዲገደል ከተደረገ ይህ ኢፍትሐዊነት ነው። ኃጢአትን ለመክፈል የሚሞተው
ለመሞት ፈቃደኛ ሆኖ ከተገኘ ግን ይህ ኢፍትሐዊነት ተወግዶ ሞቱ ፍትሐዊ ይሆናል
ማለት ነው። ክርስቶስ ለመሞት ፈቃደኛ ነበረ። አልተገደደም፤ ላለመሞት ይችል
108
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ነበር። ላለመሞት ከአገር መውጣት ይችል ነበር። አገር ጥሎ አልወጣም። ጥሎ


አልሸሸም። ለንጽሕናው መከራከሪያ ማቅረብ ይችል ነበር፤ አላቀረበም። እነዚህ ነገሮች
በመስቀል ላይ እንዳይሞት ሊከላከሉለት ይችሉ ነበር። ግን መከላከልን አልሞከረም።

ሰው በመልካም ሥራው ሊድንና ሊጸድቅ ይችላል የሚል ማናቸውም ሃይማኖት


ለኃጢአት ዋጋ መከፈል እንዳለበት በመጠኑ ቢቀበልም ከፋዩና ከፍሎ የሚድነውና
የሚጸድቀው ኃጢአተኛው ሰው በራሱ ችሎታ መሆኑን ያስተምራል። ንስሐ መግባትና
መልካም ሥራ መሥራት በቂ ናቸው ብሎ ያምናል። አንዳንዶች፥ ሰው የግብረ አዳም
ኃጢአት ወይም ጥንተ አብሶ እንዳለበት ሲያምኑ ሌሎቹ ሰው ንጹሕና ምንም ኃጢአት
የሌለበት ሆኖ ተፈጥሮአል። ከተፈጠረ በኋላ ስላደረጋቸው በደሎች ንስሐ በመግባትና
መልካም በማድረግ መዳንና መንግሥተ ሰማያትን መቀዳጀት ይችላል ብለው
ያምናሉ። ሌላው ስለ በደለኛው የመሞቱና ዋጋ የመክፈሉ አስፈላጊነት በእነዚህ ዘንድ
ስፍራ የለውም።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ግን በብሉይ ኪዳን ዘመን፥ ከነአዳም ዘመን ጀምሮ
ለመሥዋዕት ደም ይፈስስ ነበር። ደም ሕይወት አለበት፥ ነፍስ አለበት፤ ጥቂት
ጥቅሶችን ላሳይ፤

ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፤ ዘፍ. 9፥4፤

የሥጋ ሁሉ ሕይወትና ደሙ አንድ ነውና ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች፦ የሥጋ ሁሉ


ሕይወት ደሙ ነውና የሥጋውን ሁሉ ደም አትብሉ፤ የሚበላውም ሁሉ ተለይቶ
ይጥፋ አልኋቸው። ዘሌ. 17፥14፤

ነገር ግን ደሙ ነፍሱ ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባህምና ደሙን


እንዳትበላ ተጠንቀቅ። ዘዳ. 12፥23።

ደም ያስተሰርያል። ደም የሚያስተሰርየው ሕይወት ስላለበት ነው። የኃጢአት ዋጋ


ክብደቱን የምናውቀው ሕይወትን በመጠየቁ ነው። ደም ሳይፈስ ስርየት ከቶውኑም
የለም፤ ዕብ. 9፥22። የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው፤ ሮሜ. 6፥23 ይህን ይላል፤
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ
በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። የኃጢአት ዋጋ ሞት ነውና ኃጢአት ሞትን
ይጠይቃል። ሞት ማለት ሕይወትን የሚጠይቅ፥ ሕይወትን የሚወስድ ማለት ነው።
ይህንን አሳብ በሦስተኛው ነጥብ፥ በመስቀሉ ድርጊት ላይ አነሣለሁ። የመስቀሉን
አስፈላጊነት አየን፤ የመስቀሉን ትንቢት እንመልከት።

109
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

2. የመስቀሉ ትንቢት

የመስቀሉ ትንቢት ሌሎች ነቢያት የተናገሩትና ራሱ ጌታም እንደሚሞት የተናገረው


ቃል ነው። የጌታ ለሞት መምጣቱ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍትም በአዲስ ኪዳንም
በራሱ በጌታ የተነገረ ነው። ገና በዔድን ገነት በዘፍ. 3፥15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥
በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥
አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። ተብሎ ተጽፎአል። ከሴት ዘር የሚመጣ አናት
ቀጥቃጭ ይጠበቅ ነበር። ገላ. 4፥4-5 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ
እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ
ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። አለ። ይህ የተፈጸመው
የዔድን ገነት ትንቢት ቃል ነው። ጌታ መጣ፤ ለምን? ይዋጅ ዘንድ። መዋጀት ዋጋ
ከፍሎ ማዳን ነው። ጌታ የከፈለው ዋጋ የዎጆ ዋጋ ነው። የነፍስ ዋጋ ነው፤ ዋጋውም
ነፍሱ ናት፤ ሕይወቱ ናት።

ከብሉይ ኪዳን ብዙ ትንቢቶች መዝ. 22ን እና ኢሳ. 53ን ብቻ መጥቀሱ በቂ ነው።


መዝ. 22 ገላጭ በሆነ ቋንቋ መስቀሉን ያሳያል። ገና ሲጀምር 'ኤሊይ ኤሊይ ላማህ
አዘብታኒ' ይላል። ይህ የዕብራይስጥ ቃል ነው። በጌታ አገልግሎት ዘመን በሚነገረው
የሱርስጥ ወይም አራማይስጥ ቋንቋ፥ 'ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ' የተባለው፥
በመስቀል ላይ ጌታ የጮኸው የጣዕር ጩኸት ቃል ነው። ይህ የሰቆቃ ጥያቄ ብቻ
ሳይሆን የትንቢቱ ፍጻሜም ነው።

ከዚሁ መዝ. 22 ቁጥር 8 በእግዚአብሔር ተማመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ቢወድደውስ


ያድነው እንዳሉት ተጽፎ በማቴ. 27፥43፥ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ የእግዚአብሔር
ልጅ ነኝ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው በሚለው ቃል ተፈጽሞአል። መዝ.
22፥16 የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። ያለው ቃል በቃል
የተፈጸመ ነው።

መቸንከር ትንቢቱ በተነገረበት ዘመን በአይሁድ ዘንድ የመቅጫ መሳሪያና መንገድ


አልነበረም። አይሁድ ሰውን ቸንክረው አይገድሉም። መስቀል የአይሁድ የመቅጫ
መሣሪያ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም። መዝ. 22፥18 ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥
በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ ይላል፤ ዮሐ. 19፥24 ደግሞ የትንቢቱን ፍጻሜ እንዲህ
ሲል ይገልጣል፤ ስለዚህ እርስ በርሳቸው፥ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት
እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም። ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ
ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

ኢሳ. 53 መጨነቁን፥ መሰቃየቱን፥ በሸላቾች ፊት እንዳለ በግ አፉን አለመክፈቱን


ወይም ዝም ማለቱን፥ መቃብሩ ከክፉዎች፥ ሞቱም ከባለጠጎች ጋር መሆኑን
ተንብዮአል። ሞቱን ብቻ ሳይሆን ስለምን እንደሞተም ይነግረናል፤ እርሱ ግን ስለ
110
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ


ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። . . . ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ
በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ
ይከናወናል። ‘ስለ’ የሚለውን ቃል እናስተውል። ስለ መተላለፋችን፥ ስለ እኛ
መተላለፍ። ስለ በደላችን፥ ስለ እኛ በደል። የደኅንነታችን ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤
የማን? የእኛ፤ በማን ላይ? በእርሱ ላይ።

ጌታ ራሱ ደግሞ ደጋግሞ ተናግሮታል፤ እንደሚሰቀልና እንደሚሞት፥ በሦስተኛውም


ቀን እንደሚነሣ በግልጽና በማያጠራጥር ቋንቋ ተናግሮታል። ጥቂቱን እንይ፤

ማቴ. 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና


ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን
ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

ማቴ. 17፥ 22-23 በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ
ዘንድ አለው፥ ይገድሉትማል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው። እጅግም አዘኑ።

ማቴ. 20፥17-19 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፥ በመንገድ አሥራ ሁለቱን


ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ፥ እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥
የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥
ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፥
በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።

ማር. 9፥30-31 ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ያስተምር


ስለ ነበር ማንም ያውቅ ዘንድ አልወደደም፤ ለእነርሱም፦ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ
አልፎ ይሰጣል፥ ይገድሉትማል፥ ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል ይላቸው ነበር።

ማር. 10፥32-34 ወደ ኢየሩሳሌምም ሊወጡ በመንገድ ነበሩ፥ ኢየሱስም ይቀድማቸው


ነበርና ተደነቁ፤ የተከተሉትም ይፈሩ ነበር። ደግሞም አሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ
አቅርቦ ይደርስበት ዘንድ ያለውን ይነግራቸው ጀመር። እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም
እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፥ የሞት ፍርድም
ይፈርዱበታል፥ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፥ ይዘብቱበትማል ይተፉበትማል
ይገርፉትማል ይገድሉትማል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።

ሉቃ. 9፥21-22 እርሱ ግን፦ የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል በሽማግሌዎችም


በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊጣል ሊገደልም በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ይገባዋል
ብሎ ለማንም ይህን እንዳይናገሩ አስጠንቅቆ አዘዘ።
111
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሉቃ. 18፥31-33 አሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ወደ


ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።
ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፥ ይዘብቱበትማል ያንገላቱትማል ይተፉበትማል፤
ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።

ሉቃ. 24፥6-9 [ከትንሣኤው በኋላ መላእክቱ የተናገሩት ቃል] የሰው ልጅ


በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ
ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ። ቃሎቹንም አሰቡ፥ ከመቃብሩም
ተመልሰው ይህን ሁሉ ለአሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው።

ሉቃ. 24፥46-48 [ከትንሣኤ በኋላ ራሱ ኢየሱስ] እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ


መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት
ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።
እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። [ይህ ጠቅላላው የብሉይ ኪዳን አሳብ ፍጻሜና
ድምዳሜ ነው።]

የጌታ ሞትና ትንሣኤ በግልጽ የተነገረ ትንቢት ፍጻሜ ነው። ጌታ ይህ እንደሚደርስበት


ከተናገረና ተናግሮ ካልሞተ ውሸታም እንጂ ነቢይ ሊባል አይገባውም። ውሸታም
ካልሆነ ደግሞ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ከሆነም የተናገረውን ልንቀበል የተገባ ነው።
የሐዋርያቱ ስብከትም ይህ ነበር። ምስክሮች ናችሁ እንደተባለ ምስክሮች ሆኑ እንጂ
ከመናገር አልተቆጠቡም። የስብከታቸው ዋና ጉዳይ የክርስቶስ ለኃጢአታችን መሞቱና
ከሙታን መነሣቱ ነው።

የክርስቶስ ሕይወት፥ ስቅለት፥ ሞትና ትንሣኤ፥ ከተፈጸመና በወንጌላት ከተጻፈ ከ600


እና 700 ዓመታት በኋላ የተጻፈው ቁርኣን፥ 'አልገደሉትም፥ አልሰቀሉትምም፤
መሰላቸው እንጂ' በሚል ማስረጃ የለሽ አንድ አንቀጽ ይህንን ታሪካዊ ድርጊት
ሊገፋው ይሞክራል። ግን ይህ እውነት እንደ ተተከለ ዓለት የጸና እንጂ መገፋት
የሚቻል ቀላል በርሜል አይደለም። የጌታ ሞቱ ስለ መሞቱ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜ
ነው።

3. የመስቀሉ ድርጊት

የመስቀሉ ድርጊት ፍጻሜው ነው። ይህ የተነገረው ትንቢት የተፈጸመበት ድርጊት


ነው። መሥዋዕት ወይም ቤዛነት በክርስቶስ የመስቀል ሞት ተፈጸመ እንጂ
አልተጀመረም። መሥዋዕት ማቅረብ የኃጢአት ስርየትን የሚያስሰጥ ሥርዓት ነው።

112
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ገና እነ አዳም ከገነት ሲወጡ ነው ይህ የተጀመረው። ዕርቃናቸው የተሸፈነበት ቁርበት


የመጣው ደም ከፈሰሰበት እንሰሳ ነው። ስርየት ማለት ቃሉ ራሱ በዕብራይስጥ
መሸፈን፥ መክደን ማለት ነው። ምሳሌነቱም ኃጢአትን መሸፈን ነው። ቤዛ ማለትም
መሸፈኛ፥ መክደኛ ማለት ነው።

የክርስቶስ ሞት፥ ምትካዊ ወይም ተውላጣዊ ሞት ነው። ምትካዊ ቅጣት ያላጠፋው


በአጥፊው ፈንታ ወይም ምትክ ቅጣትን ሲቀበል ማለት ነው። ምትካዊ ሞት
ለሙስሊሞች ለመቀበል የሚከብድ ትምህርት ነው። እንደ ኢስላም ትምህርት ሰው
ለራሱ ኃጢአት ብቻ ነው ተጠያቂ የሚሆነው እንጂ ስለሌላው አይደለም። ያም ሆኖ፥
እርግጠኛ አይሁን እንጂ ጸልዮና ለምኖ ይቅርታ ማግኘት ይችላል። አንዱ የሌላውን
ኃጢአት መውሰድ አይችልም፤ ሌላውም ለአንዱ ኃጢአት መቀጣት የለበትም።
አዳማዊ ኃጢአት ወይም የውርስ ኃጢአት ወይም ጥንተ አብሶ የሚባል ነገር የለም።
ኢየሱስን በተመለከተም ኢየሱስ ሲጀመርም አምላክ አይደለም፤ አምላክ ሳለ ሰው
አልሆነም፤ አንድ ሰው የሌላውን ኃጢአት ስለማይወስድ ስለ ሌላ ወይም ስለ ሌሎች
አልሞተም፤ ሊሞትም የተገባው አይደለም።

ይህ ምትካዊ ሞት ለሙስሊሞች ለመቀበል ይክበድ እንጂ በቁርኣንም የተጻፈ ይህንን


መሳይ አለው። በሱረቱ አል ሷፋት 37፥107 በታላቅ ዕርድም (መሥዋዕት)
ተቤዠነው። ይላል። ዕርዱ ወይም መሥዋዕቱ በአብርሃም ልጅ በይስሐቅ (ቁርኣን
እስማኤል ይለዋል) ፈንታ የተሠዋ መሆኑ ግልጽ ነው። እዚህ ታላቅ ዕርድ የተባለው
በፈንታው የሞተው እንስሳ ነው። አንዱ እንዲተርፍ ሌላው ሞቶ ነበር ማለት ነው።
ስለዚህ አንዱ የሌላው ምትክ ሆኖ ሊሞት ይችላል ማለት ነው። የመስቀሉ ሞት ዓላማ
ምትካዊነትም ይህ ነው። ቤዛነት ወይም መቤዠት ነው። የኃጢአት ስርየት ነው።
በይስሐቅ ፈንታ የታረደው በግ የተሰቀለው የኢየሱስ ተምሳሌት ነው። የዓለምን
ኃጢአት የሚያስወግድ ብሎ ዮሐንስ የመሰከረለት እርሱ ነው፤ ዮሐ. 1፥29።

ሌላ ምሳሌ ከቁርኣን እንይ። ይህን አሳብ ቀደም ሲልም አውስቼዋለሁ። ይህ እያየን


ያለነው፥ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ
የሚለው ጥቅስ ራሱ እንኳ ስለ ልዋጭ ሞት የሚነግረን ነገር የለም? አለ። ይህን ጥቅስ
በጥሬው ከወሰድነው ኢየሱስ እንዳይሞት በፈንታው፥ በምትኩ ሌላ ሰው ሞቶአል
ማለት ነው። አላህ ኢየሱስን በግልጥ መንጠቅና ማንም ሰው እንዳይሞት ማድረግ
ካልቻለና በስውር ማንም ሳያውቅ ሊወስደው ከፈለገ አንድ ሰው በፈንታው መሰቀል
አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። ይህ በፈንታው ሌላ የመሰቀል ነገር አልሆነም እንጂ ቢሆን
ኖሮ ታዲያ ይህ ተውላጣዊ ሞት ሊባል አይቻልም? ይቻላል። ስለዚህ ተውላጣዊ ሞት
ለቁርኣንም እንግዳ ነገር አለመሆኑን ልናውቅ ግድ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው ከዚህ በፊት ባየናቸው ክፍሎችም እንዳየነው


አዳም በኃጢአት ሲወድቅ የአዳም ዘር ሁሉ ነበር የወደቀው። ሮሜ. 5፥14-15 ነገር ግን

113
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ


ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። ነገር ግን
ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ
ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ
የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ። ይላል። ሰው ሁሉ በአዳም ውስጥ ነበረ።
1ቆሮ. 15፥21-22 ደግሞ፥ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል
ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን
ይሆናሉና። ይላል። ሰው ሁሉ በአዳም ሞቶ በክርስቶስ ትንሣኤ በኩል ግን ዘላለማዊ
ሕይወትን እንደሚቀዳጅ ነው እነዚህ ክፍሎችና እነዚህ የመሰሉት ሌሎችም
የሚያሳዩት።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው ሰው በመጀመሪያ የተፈጠረው ሊሞት


አልነበረም። ሊሞት ካልነበረና አዳም ከሞተ በኋላ የአዳም ልጆች ሁሉ ከሞቱ ይህ
የአዳም ኃጢአትና ቅጣት ወደ ዘሩ የመተላለፉ አንድ አመልካች ነው። ይህ ባይሆን
ኖሮ እያንዳንዱ የአዳም ዘር ልክ እንደ አዳም በዔድን ገነት የመኖርና ፈተናን የማለፍን
ወይም የመውደቅን ዕድል ሊሰጠው በተገባ ነበር። የሰው ዘር ሁሉ መዋቲ መሆኑ
የአዳምን ኃጢአት ወራሽ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የውርስ ኃጢአት ከኖረ የኃጢአቱ
መፍትሔም መኖር አለበት። ከላይ ያየናቸው ጥቅሶች ይህንን ነው የሚያሳዩት።

ከነ አዳምም ጀምሮ ለኃጢአት ስርየት ደም ይፈስስ እንደነበር ብሉይ ኪዳን በሰፊው


ያስተምራል። ደም ሕይወት ወይም ነፍስ እንዳለበትና የኃጢአት ዋጋ ክብደቱ ነፍስን
መጠየቁንና ደም ሳይፈስ ስርየት እንደሌለም አይተናል። የኃጢአት ዋጋ ሕይወትን
የጠየቀ ነው። የክርስቶስ ሞት ይህንን ዋጋ የከፈለ ነው።

መስቀሉ የመዳን ዋና መንገድ ሳይሆን ብቸኛው መንገድ ነው። ሙሴም በምድረ በዳ


እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው
እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። ዮሐ. 3፥14-15። በዚህ ጥቅስ
ሌሎች የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ መሰቀል የተገባው የሰው ልጅ የተባለው
ኢየሱስ ነው። ይህ፥ ‘የሰው ልጅ’ የሚለው ሐረግ በብዙ ቦታዎች የተጠራበት
መጠሪያና ኢየሱስም ራሱ በጣም የተጠቀመበት ቃል ነው። የምድረ በዳው የናስ
እባብ በዓላማ ላይ የመሰቀሉ ታሪክ በዘኁ. 21 ይገኛል። በምድረ በዳ የነበረው
የእስራኤል ሕዝብ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ በመናገራቸው ምክንያት
እግዚአብሔር ሊቀጣቸው እባቦችን ሰደደ። ሕዝቡ ተነደፉ፤ ብዙዎችም ሞቱ። ኋላ
በድለናል ብለው ሲጸጸቱ ይህ የናስ እባብ ተሠርቶ በዓላማ ወይም ረጅም እንጨት
ላይ እንዲሰቅል እግዚአብሔር ለሙሴ ነገረው። የተነደፉት ሁሉ የናሱን እባብ ባዩ ጊዜ
ዳኑ፤ በሕይወትም ኖሩ። የምድረ በዳው የናስ እባብ መሰቀልና የኢየሱስ መሰቀል
መመሳሰል አይቶ ወይም አምኖ መዳን ነው። ኢየሱስ የተሰቀለው የመዳን መንገድ
ይሆን ዘንድ ነው።

114
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ሁሉ ኃጢአት መሥራታቸውና ከእግዚአብሔር ክብር የጎደሉ መሆናቸው እና


የኃጢአት ደመወዝ ሞት መሆኑ በቃሉ ውስጥ ተጽፎአል፤ ሮሜ. 3፥23፤ ሮሜ 6፥23።
ኃጢአተኛ ሁሉ የኃጢአቱን ደመወዝ ወይም ዋጋ መቀበል አለበት። ወይም መሞት
አለበት። ይህ ሞት በሥጋ መሞት ብቻ ሳይሆን ከዚህ የከፋው ሞት ነው፤ ያም፥
ዘላለማዊ ሞት ወይም ከቅዱስና አፍቃሪ አምላክ ለዘላለም መለየት ነው። በሮሜ 6፥
23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት መሆኑ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር የጸጋ ወይም
ፍጹም ነጻ ስጦታ የዘላለም ሕይወት መሆኑም ተጽፎአል። ይህም ስጦታ በክርስቶስ
ኢየሱስ በኩል ነው። በብሉይ ኪዳን የሰዎች ኃጢአት ይወገድ የነበረው በምትካቸው
ይፈስስ በነበረው የእንስሳ መሥዋዕት ወይም ደም ነበር። ያ የብሉይ ኪዳን
የመሥዋዕት ሥርዓት የአንድን ሰው ኃጢአት ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያስወግድ ጊዜያዊ
ሥርዓት ነበር።

ዘላቂው መንገድ የክርስቶስ ሞት ነው። የብዙዎች ኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ


የሚወገድበት ሥርዓት ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ መስዋዕትን ከፍቅር
የተነሣ አዘጋጀ። ይህ ምትክ ሆኖ ለሰው ልጆች የሚሞተው ማሟላት ስላለበት ነገሮች
ዊልያም ማክዶናልድ ከጻፈው ልውሰድ። ይህ የኃጢአት ማስተስረያ ምትክ ማሟላት
ያለበት መስፈርቶች አራት ናቸው፤ እነዚህም፥

1ኛ፥ ሰው መሆን አለበት፤ 2ኛ፥ ምንም ኃጢአት የሌለበት መሆን ይገባዋል


(ያለዚያ ለራሱ ኃጢአት ብቻ ነው የሚሞተው)፤ 3ኛ አምላክ መሆን አለበት፤
ይኸውም በምትክነት የሚሰዋው ቁጥር ስፍር ለሌለው ኃጢአትና እጅግ ብዙ
ኃጢአተኞች በመሆኑ ነው። ሰው ብቻ ከሆነ ከሰው ይህን ማድረግ የሚችል
ንጹሕ ሰው የለም። ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና። 4ኛ፥ ራሱን ለሌሎች ኃጢአት
ሲል አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን አለበት።22 ይህ ምትክ ነው በመስቀል ላይ
የሞተው።

በ3ኛው መስፈርት ላይ፥ 'አምላክ መሆን አለበት' ተብሎአል። ይህን ላብራራው።


አንድ ሰው ስለሌላ ሰው ቢሞት ያ ሰው የዚያን አንድ ሰው ኃጢአት ብቻ ሊሸከም
ይችል ይሆናል። ለዚያውም ከቻለና ብቃት ከኖረው ነው። የብዙዎችን ኃጢአት
ለማስወገድ ግን ያ ሰው ሰው ሆኖ፥ ግን ከሰው በላይ የሆነ ሰው መሆን አለበት።
ኃጢአት የሌለበት መሆን አለበት። ኃጢአት የሌለበት ሰው ደግሞ የለም። ሊኖርም
አይችልም፤ ምክንያቱም፥ ሁሉ በአዳም ወድቀዋል። መልአክ መጥቶ በሰው ፈንታ
ሊሞት አይችልም። መላእክት የተላኩበትን ለመፈጸም በአካል ለጊዜው ይገለጣሉ
እንጂ አካል የላቸውም፤ መላእክት መናፍስት ናቸውና ሊሞቱም አይችሉም። ስለዚህ
ጌታ ራሱ ሰው መሆን ኖረበት።

God's Answers to Man's Questions, MacDonald, William, ትርጉም ታቢ ዘወልድ፤ ለሰው


22
ጥያቄ የእግዚአብሔር መልስ፤ ቫንኩቨር፥ ካናዳ፤ ገጽ 5።

115
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መላእክት ሊሞቱ ካልቻሉ አምላክማ ይልቁን እንዴት ሊሞት ይችላል? አይችልም።


ስለዚህም ነው ሰው የሆነው። አምላክነቱን ሳይደመስስ፥ ሳይሰርዝ ሰው ሆነ።
አምላክም ሰውም የሆነ አንድ አካል ሆነ። ሙሉና ያልጎደለ አምላክ ሳለ ኃጢአት
የሌለበት ንጹሕና ፍጹም ሰው ሆነ። ይህ ሰው የሆነ አምላክ ነው በመስቀል ላይ
የሰውን ምትካዊ ሞት የሞተው። የክርስቶስ በመስቀል ላይ በኃጢአተኞች ፈንታ
መሞት ምትካዊ ወይም ተውላጣዊ ሞት ነው። ክርስቶስ ለዚህ የመስቀል ሞት ፈቅዶ
ታዘዘ፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል
ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊል. 2፥8።

ጌታ በሞተበት ዘመን የመስቀል ቅጣት ሮማዊ ላልሆኑ ወንጀለኞች፥ በተለይም


ለባሪያዎችና ለዘራፊዎች የሚሰጥ ስቃይ የተሞላና ደም የሚፈስስበት የከፋ ቅጣት
ነው። ኋላ ኋላ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ላሉ ዜጎችም ደረሰ እንጂ ሮማዊ ዜግነት ያላቸው
ሰዎች ቅጣት መቀጮና ግዞት ነው። በከፍተኛ የመንግሥት ክህደት ወንጀል ካልተያዙ
በቀር የሚሞቱ ከሆነ ፈጣንና ቀልጣፋ ሞት እንዲሞቱ ይደረጋል እንጂ በተጓተተና
ስቃይ በሞላበት የመስቀል ሞት እንዲቀጡ አይደረግም። ባለፈው እንዳመለከትኩት
የመስቀል ሞት የስቃይ ሞት ነው። ለተመልካቾች ከወንጀለኞች፥ 'እኔን ያየህ ተቀጣ'
መልእክት እንዲተላለፍ የሚደረግበት የጭካኔ ቅጣት ነው። በመስቀል ላይ የሚሰቀሉ
ሰዎች ሳይሞቱ የሚቆዩበት ጊዜ እንደ ሰዎቹ ጤናማነትና ጥንካሬ፥ እንደ አሰቃቀሉና
እንደ አየሩ ሁኔታ ከጥቂት ደቂቃዎች እስከ ጥቂት ቀናት ሊደርስ ይችላል። ሰዎቹ
እየተሰቃዩ ቆይተው በመጨረሻ የራሳቸውን ሰውነት ከፍ አድርገው ለመተንፈስ እንኳ
አቅም አጥተው ነው የሚሞቱት።

የመስቀል ሞት የአይሁድ የቅጣት መሣሪያ አይደለም። በየአገሩና በየባህሉ፥


በየሕዝቡም የነፍስ ቅጣት የሚፈጸምባቸው የተለያዩ የቅጣት መንገዶች አሉ።
በእንጨት መስቀል ለአይሁድ ፈጽሞ ፈጽሞ የማያውቁት ባይሆንም ያልተለመደ ነው።
ይህ ምድሪቱንም የሚያረክስ የመርገም ሞት ነው። ስለዚህ የተሰቀለው በዚያው ቀን
መቀበር አለበት፤ ዘዳ. 21፥22-23።

አይሁድ ጥፋተኛን በሞት ቅጣት ለመቅጣት የሚያደርጉት በድንጋይ መውገር ነው።


በድንጋይ ከሚያስወግሩ ጥፋቶች መካከል ለምሳሌ፥ ዘርን ወይም ልጅን ለጣዖት
መሠዋት (ዘሌ. 20፥2)፤ ጣዖትን ማምለክና ማስመለክ (ዘዳ. 13፥10፤ 17፥2-5)፤
መናፍስት ጠሪነት (ዘሌ. 20፥27)፤ የእግዚአብሔርን ስም መስደብ (ዘሌ. 24፥10-14
እና 23)፤ ሰንበትን ማርከስ (ዘኁ. 15፥ 32-36) ይገኛሉ። አይሁድ ጌታን ሊወግሩት
ቃጥተው ነበር፤ ዮሐ. 8፥54-59፤ 10፥27-33። ይህን ያደረጉት ራሱን ከአብ ጋር
በማመሳሰሉ ነው።

የጌታ ሞት የፈቃድ ሞት ነው። አለመሞት ቢፈልግ አለመሞት ይችል ነበር። ቀደም


ሲል እንደተመለከትነው ጌታ ራሱ በመስቀል እንደሚሞት ደጋግሞ ተናግሮአል።

116
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተናገረው ራሱ ነው። ቀደም ሲል የቀደሙት ነቢያት ስለ መሢሕ መከራ ቢተነብዩም


ጌታ እነዚህ ትንቢቶች በእርሱ እንደሚፈጸሙ ያውቅ ነበርና ራሱም እንደሚሞት
አስቀድሞ በመናገር አሰመረባቸው። ጌታ ለመሞት ባይፈልግ ገለል ይል ወይም አገር
ለቅቆ ይሸሽ ነበር እንጂ ሮማውያንን መጋፈጥ አይኖርበትም ነበር። ነገር ግን
እንደሚሞት ራሱ ትንቢቶቹንም ተናግሮ፥ ለዚህ እንደመጣም መስክሮ ነው ራሱን
በፈቃዱ የሰጠው። የጌታ ምትካዊ ሞት የሙሉ ፈቃድ ሞት ነው።

4. የመስቀሉና የትንሣኤው ምስክሮች

ኢየሱስ ተሰቅሎ ለመሞቱና ከሞት ለመነሣቱ ማስረጃው የበዛ መሆኑ መልስ


ለመስጠት ለሙስሊሞች ያስቸግራቸዋል። ሞቱና ትንሣኤው ከ600 ዓመታት በኋላ
በተጻፈች በአንዲት አንቀጽ ብቻ (በ4፥157-158) በቀላሉ ሊክዱትና ሊጥሉት
የማይችሉት ጉዳይ ነው። መልስ የመስጠቱ ጉዳይ በሜዳቸው ያለ፥ በትከሻቸው ላይ
ያለ ትልቅ ሸክም ነው። ማስረጃዎችን ሁሉ እንደሌሉ አድርጎ መቁጠር ከማንም
ፍትሕን ለመፈጸም ከሚወድ ዳኛ የማይጠበቅ ነው። ምስክሮቹን እንይ።

የደቀ መዛሙርቱ ምስክርነት

ጌታ ሲሰቀልና ሲሞት፥ ከሞትም ተነሥቶ ያዩት ብዙ ምስክሮች አሉ። ሲያዝ፥


ሲፈረድበት፥ ሲጎሳቆልና ሲተችበት፥ ሲሰቀልና ሲሞት ተገኝተው የነበሩ፥ መሞቱን
ያረጋገጡ፥ መቀበሩን ያዩና የቀበሩ፥ ከሙታን ከተነሣ በኋላ መነሣቱን ያዩ፥ የዳሰሱት፥
ያረጋገጡት፥ የጻፉት ብዙ ናቸው። ይህንን ሰምተውና አይተው ፍጹም የተለወጠ
ሕይወት የታየባቸው፥ መኖርን በዓላማ የኖሩና ሞትን ሳይፈሩ የሞቱ ምስክሮች
ሁለትና ሦስት ሳይሆኑ ብዙ ናቸው። ነገር በሁለትና ሦስት ምስክር ስለሚጸና ሁለትና
ሦስት ብቻ ቢሆኑም እንኳ በቂ ናቸው።

የመጀሪያዎቹ የፍርዱ ሂደት፥ የስቅለቱ፥ የሞቱንና የትንሣኤው ምስክሮች የራሱ የጌታ


ደቀ መዛሙርት ናቸው። ከአፉ ትንቢቱን ሰምተዋል። እንደሚሞት ሲናገር አንዳንዴ
ቃሉ ተሰውሮባቸው አልገባቸውም፤ ሌላ ጊዜ ይህን በማለቱ ገስጸውታል፤ ማቴ. 16፥
21-22፤ 20፥19፤ ማር. 10፥32-34፤ ሉቃ. 18፥30-34። ከነዚህ ደቀ መዛሙርት
ጭፍሮች መጥተው ሲይዙት ብዙዎቹ ቢበታተኑም እስከ ገዢው ግቢና እስከ መስቀሉ
የተከተሉት ነበሩ። ከመስቀል ሆኖ ያናገረውም አለ። በድኑን ከመስቀል አውርደው
ከፍነው የቀበሩትም ነበሩ። ከትንሣኤው በኋላ ያዩት፥ ያወሩት፥ የሰሙት፥ የዳሰሱት

117
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ነበሩ። ከትንሣኤው በኋላ ጌታ አንድ ቀንና፥ አንድ ጊዜ ብቻ ታይቶ አልነበረም


ያረገው። ያም እንኳ ቢሆን ተቀባይነትን እንዲያጣ አያደርገውም። ነገር ግን በ40
ቀናት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች፥ ለተመሳሳይ ሰዎች በተደጋጋሚና ለተለያዩ
ሰዎች ጭምር መታየቱ ምትሃት አይደለም።

ማን ለውሸትና ለተረት ይሞታል? ‘ሐዋርያቱ፥ ደቀ መዛሙርቱና የመጀመሪያዎቹ


አማኞች የድፍረት ሞት ለመሞት ያልፈሩት ለምንድርን ነው?’ ብለን ብንጠይቅ፥
መልሱ፥ ያዩት ነገር በመኖሩ ነው። ማን ለውሸት ይሞታል? ኢየሱስ የሞተ መስሏቸው
ነው ወይም የተሰቀለው ኢየሱስን መስሏቸው ነው ቢባል እንኳ ትንሣኤውን
መስሏቸው ነው ማለት አይቻልም። ጌታ ባይነሣ ኖሮ ይህንን ሊያውቁት ይችሉ ነበር
እንጂ ሳይነሣ የተነሣ ሊመስላቸው አይችልም። የኢየሱስ ከሞት መነሣት እውነት
ባይሆን ኖሮ ከሞት ተነሥቶ ያላዩት ሰዎች ሞትን ለምን አልሸሹም? በትውፊታዊና
ታሪካዊ ጽሑፎች የተጻፈልን እውነት ሐዋርያቱ ሁሉ ሰማዕታት ሆነው እንደሞቱ
ነው። እነዚህ ሰዎች ያልተነሣውን ኢየሱስን ተነሥቶአል ብለው ተረት ፈጥረው፥
ሌሎችን አታልለው ሌሎች እንዲሞቱ አጋፈጧቸው ብንል እንኳ፥ እራሳቸውስ እንዴት
ሊሞቱ በቁ? የፈጠሩት ተረቱ እውነት ሆኖባቸው ነው ለውሸት የሞቱት ማለት ከቶም
የማይመስልና ማንም የማይቀበለው ስንፍና ነው።

የደቀ መዛሙርቱ ሕይወት ደግሞ ሬሳ የሰረቁና የደበቁ ዓይነት አልነበረም። በተለይ


ከበዓለ ኀምሳ በኋላ ከቶም ታይቶባቸው የማያውቅ ድፍረትና ቆራጥነት ነበር
የታየባቸው። ለመመስከር ፈጣኖች፥ ለመስበክ ደፋሮች፥ ለመሰደድ ቆራጦች፥ ለመሞት
ወደ ኋላ የማያፈገፍጉ ነበሩ። በጌቴሴማኒ ጥሎት የሸሸውና በሊቀ ካህናቱ ግቢ
የካደውን ጴጥሮስን፥ በበዓለ ኀምሳ ቀን ያየው ሰው፥ ያ ጴጥሮስ ነው ብሎ ለማመን
አይችልም። ለውጡን ምን አመጣው? ኢየሱስ ወደ አላህ ተወስዶ ኢየሱስን ያልሆነ
ሰው ተሰቅሎ ነው? አይደለም! የተሰቀለውን ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ ስላየው እንጂ!
ይህ እንደ ባለ አእምሮ ስንዳኝ የምንቀበለው ምስክርነት ነው። የደቀ መዛሙርቱ
ሕይወት ለውጥና ላመኑበት መሞት ጉልህና ደማቅ ምስክር ነው።

መታየቱ

የጌታን ትንሣኤ ባዶው መቃብር ብቻውን ሊመሰክር አይችልም። መቃብር ባዶ ሊሆን


ይችላል። የአይሁድ አለቆች እንዳሉት ደቀ መዛሙርቱ ሬሳውን ሊሰርቁና ሊደብቁት
ከቻሉ መቃብሩ ባዶ ሊሆን ይችላል። የመቃብር ባዶ መሆን ትንሣኤን አያረጋግጥም።
የተነሣው ጌታ ከታየና ከተዳሰሰ ግን በእርግጥም ተነሥቶአል! እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን
ሳይሆን እርሱን የሚመስል ሰው አዩ ማለት በቀላል የሚታለፍ ጉዳይ ሊሆን
አይታሰብም።
118
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ከትንሣኤው በኋላ መጀመሪያ ከታያት ከማርያም ጀምሮ ትንሣኤውን በተለያዩ ጊዜያት


እስካዩት በቁጥር ከአንድ እስከ 11 እስከሚደርሱ ሰዎች እንዲሁም 500 የሚበልጡ
ሰዎች በአንድ ጊዜ ያዩት መሆኑ ተጽፎአል። ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ
ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን
አንቀላፍተዋል፤ 1ቆሮ. 15፥6። በአንድ ጊዜ ከአምስት መቶ በሚበዙ ሰዎች መታየት
ምንም ማስተባበያ ሊቀርብበት አይችልም። ቅዠት፥ ወይም ምትሐት ነው ሊባል
አይችልም። 500 ሰዎች ቀርቶ አምስት ሰዎች እንኳ በአንድ ጊዜ አንድ ዓይነት ቅዠት
ሊያቃዣቸው አይችልም።

የአንዱ ተጠራጣሪ የቶማስ ምስክርነት ብቻውን እንኳ ትልቅ ነው። ቶማስ ጠርጣሪና
አእምሮውን የሚተማመን ሰው ነበረ። ካየው በኋላ ግን ጌታዬና አምላኬ ነበር ያለውና
የሰገደለት፤ ዮሐ. 20፥28።

የሮም ፍርድ

ምስክሮቹ የራሱ ደቀ መዛሙርትና ተከታዮቹ ብቻ አይደሉም። ተከታዮቹ የጻፉት


ቢታይ ማስረጃው ወደ ጎን ለመግፋት የማያስሞክር ነው። የፍርዱ አካሄድ፥ የችሎቱ
ሂደትም ምስክር ነው። በሮም መንግሥት 3 ጊዜ፥ በጲላጦስ፥ በሔሮድስ፥ እንደገና
በጲላጦስ፥ በአይሁድ ሸንጎ 3 ጊዜ የተመረመረበት ዝርዝር ተጽፎአል። የክሱ መዝገብ
የሮም መንግሥት ቸል የሚለው ጉዳይ አይደለም። ‘የአይሁድ ንጉሥ’ ተብሎ ነው
የተከሰሰው። ፍርዱ ፍትሕ የጎደለው ቢሆንም ፍርድ ነበር። ፍርዱም፥ ስቅለቱም፥
ሞቱም ሰዎች የሰሙት፥ ያዩት፥ ያረጋገጡት ነገር ነው።

የኢየሱስ ፍርድ የተደረገው በድብቅና በስውር አልነበረም። የቄሣር ወኪል ባለ


ሥልጣን፥ የይሁዳ ገዢ፥ የገሊላ ገዢ፥ ካህናት፥ ሊቀ ካህናቱ አሉበት። የአይሁድ
ሸንጎና የሮም ሥልጣን ቢሮ ያየው ጉዳይ ነው። የተሰቀለው ኢየሱስ አይደለም
የሚለው ውኃ የማያነሣ መከራከሪያ መሆኑን ይህ ሊያረጋግጥ ይችላል። እነዚህ ሁሉ
ሰዎች የተሳሳተ ሰው ወስደው ሰቀሉ ለማለት የሚደፍር አጉል ደፋር ነው። የሮም ሕግ
ኢየሱስ አይደለሁም የሚልን ሰው፥ ‘ነህ እንጂ፤ እራስህ ነህ!’ ብለው ለፍርድ አሳልፈው
አይሰጡም። በእርግጥ የተከሰሰው ደግሞ ፍርዱን በትክክል መቀበሉን፥ ቅጣቱን
መቀበሉን ወይም ነጻ መውጣቱን እርግጠኛ ሳይሆኑ ግማሽ መንገድ ሄደው
አያቆሙም።

119
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

የተጻፈው ቃል

ተጽፎአል ሲባል ሙስሊሞች የተጻፈው የተሳሳተ ነው ሊሉ ይቃጣቸዋል። ግን


የተጻፈውን እነርሱ ናቸው የተሳሳተ ነው ያሉት እንጂ ነቢያቸውም የተሳሳተ ነው
አላለም፤ አንዴም አላለም። ይህንን በዚህ ሒሳዊ ግምገማ የመጀመሪያ ክፍሎች
ተመልክተናል። በኢስላም ነቢይ በሙሐመድ ዘመን የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ
ዛሬ በእጃችን ያለው ለመሆኑ ማረጋገጫው ለቁጥር የበዛ ነው። ቁርኣን አንድም ስፍራ
የመጽሐፉ ሰዎች መጽሐፍ የተበረዘ፥ የተበከለ ነው አላለም። በሙሐመድ ዘመን
የነበረው መጽሐፍ ዛሬም ያለው ነውና እርሱ የመሰከረለትን መጽሐፍ መቀበል ብቻ
እንጂ፥ ‘ተለወጠ፥ ተቀየጠ፥ ተበረዘ፥ ተደለዘ’ ማለት አይቻልም።

መጽሐፍ ቅዱስ አለመበረዙንና አለመበከሉን የሚያረጋግጡ ወደ 25 ሺህ ያህል


የጽሑፍ ቁራጮችና ቅጅዎች ሲኖሩ እነዚህ ሁሉ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ
ከሚያረጋግጠው መጽሐፍ ጋር ይስማማሉ እንጂ ቁርኣኑ የሚለውን አለመሰቀሉን፥
አለመሞቱንና አለመነሣቱን አያወሱም።

መጽሐፍ ቅዱስና ቁርኣን እርስ በርሳቸው ይቃረናሉ። ማናቸውም ሁለት ነገሮች እርስ
በርስ ከተቃረኑ ወይ ሁለቱም ስሕተት ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወይም ከሁለቱ አንዱ ብቻ
ትክክል ነው እንጂ ሁለቱም እርስ በርስ የሚቃረኑ ነገሮች በአንድ ጊዜ ትክክል ሊሆኑ
አይችሉም። ቁርኣንና መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስን፥ ስቅለቱን ሞቱንና ትንሣኤውን
በተመለከተ የተራራቁ ሳይሆኑ ፈጽሞ የተቃረኑ ናቸው። ተሰቅሏል፤ አልተሰቀለም።
ሞቷል፤ አልሞተም። ተነሥቷል፤ አልተነሣም ነው ልዩነቱ። ይህ ከሆነ የክርስቶስን
ሞትና ትንሣኤ በተመለከተ ከሁለቱ አንዱ ብቻ ትክክል ነው እንጂ ሁለቱም ትክክል
ሊሆኑ አይችሉም።

እንግዲህ ከሁለቱ አንዱ ብቻ ትክክል ከሆነ፥ ሞቱና ትንሣኤው ደግሞ በሺህ


የሚቆጠሩ ምስክሮች የሚጠራ ከሆነ፥ አለመሞቱና አለመነሣቱ ደግሞ ከ600 ዓመታት
በኋላ የተጻፈ አንድ ምስክር ብቻ የሚጠራ ከሆነ ምስክር ፍለጋ መሯሯጥ ያለበት ማን
መሆኑ ግልጽ ነው።

የአይሁድ አለማስተባበል

አይሁድ በመጀመሪያ የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤ የሰበኩት በኢየሩሳሌም ነው።


ኢየሩሳሌም ኢየሱስ የሰበከባት፥ የሞተባት፥ የተቀበረባት ከተማ ናት። የአይሁድ
መሪዎች ማጣፊያው ሲያጥራቸው አስከሬኑን በሌሊት ደቀ መዛሙርቱ ሰረቁ ብለው

120
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

አስወሩ። ያቀረቡት ኤግዚቢት ግን አልነበረም። ኋላ በዚህ በክርስቶስ ስም


እንዳይሰብኩ አስፈራርተው ሊያስቆሙ ሞክረው ነበር። ከማስፈራራት የሚቀልለው
መንገድ ትንሣኤው ውሸት መሆኑን ማረጋገጥ ነበር። ለማረጋገጥ ደግሞ አስከሬን
ማሳየት ብቻውን በቂ ነበር። ይህ ሊሆን አልቻለም፤ ለምን? አስከሬን የለማ!

ሙስሊሞች፥ 'የኢሳን አስከሬን ከየት ያመጣሉ? አላህ ወስዶታል!' ሊሉ ይችሉ


ይሆናል። እንደ ሙስሊሞች አባባል ኢየሱስ ተወሰደ እንጂ ኢየሱስን መስሎ
የተሰቀለው ሰው በድንስ ተቀብሮ የል እንዴ? ያንን አስወጥተው ወይም አሳይተው
ይህን ናላቸውን ያዞረውን አዲስ ሃይማኖት በእንጭጩ እንዲቀጭ ማድረግ ይችሉ
አልነበረም? የሞተው በዒሳ ተመሰለ ነው የተባለውና የተቀበረው ያ የእርሱ አምሳያ
መሆኑ የታወቀ ነው። ግን አላደረጉም። ደግሞስ፥ 'አላህ ወስዶታል' የሚለው ቃል
መቼ ነው የመጣው? ከ600 ዓመታት በኋላ! ከዚያ በፊት ከመሞቱ በፊት ተወስዶአል
የሚል ቃል ሌላ ጸሐፊ ጠቅሶት አልተገኘም። ለመነሣቱ ግን ለቁጥር የበዙ የዓይን
ምስክሮች ነበሩ።

ሰንበት

ሰንበት ሌላው የትንሣኤው ምስክር ነው። የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ነው። ጌታ


ከሙታን የተነሣው ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ነው። ያም እሁድ ነው። እንደገና
በሳምንቱ የታያቸው በዚያው በእሁድ ቀን ነው። ጌታ የተነሣበት ቀን ልዩና ታሪካዊ
በመሆኑ ደቀ መዛሙርቱ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን መሰብሰብ ጀመሩ። ይህ
ለአይሁድ ትልቅ ኃጢአት ነው። የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርትና ሐዋርያቱ በሙሉ
አይሁድ ናቸው። ይህን ለውጥ ለመፍጠር ምን አነሳሣቸው? ትንሣኤው ነው። ቤተ
ክርስቲያን ይህን ቀን 'የጌታ ቀን' በማለት በዚህ ቀን መሰብሰብና ማምለክ አብሮ
መቁረስንም አዲሱ ባህላቸው አደረጉት። የክርስቲያኖች በየሳምንቱ መጀመሪያ ወይም
እሁድ መሰብሰብ የትንሣኤው ምስክር ነው።

ጳውሎስ

የጳውሎስን ሕይወት በጥንቃቄ ስንመረምር ከሞት የተነሣው ጌታ ከጠራራ ፀሐይ


በላይ በሆነ ዓይን የሚያጠፋ ብርሃን ተገናኝቶት ነው የተለወጠው። ጳውሎስ ሳውል
ይባል በነበረበት ጊዜ ድንበር አቋራጭ የክርስቲያኖች አሳዳጅ ነበረ። ኋላ ስለ ክርስቶስ
ስም መከራን ተቀበለ። መከራን ብቻ አይደለም ሕይወቱንም ሰጠ። ጳውሎስ

121
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ከአሳዳጅነት ወደ ተሰዳጅነት የተለወጠው ዕብድነት ኖሮበት ሳይሆን ከሞት የተነሣው


የጌታን ድምጽ ሰምቶ ነው። በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን
ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ
የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል
አለው። ሐዋ. 9፥4-5።

ጳውሎስ ክርስትናን እንደፈጠረ ወይም እንደቀረጸ የሚገምቱ ሰዎች ነገር እውነት ከሆነ
ጳውሎስ ይህንን ክርስትና የተባለ ተረት ፈጥሮ፥ እርሱ ለፈጠረውና እውነት ላልሆነው
ተረት ነው እንዲያ የተንገላታውና ዋጋ የከፈለው ማለት ነው? የመጨረሻው የከፈለው
ዋጋ ደግሞ ነፍሱን መስጠቱ ነበር። ማነው ለተፈጠረ ውሸት፥ ያውም ራሱ ለፈጠረው
ውሸት የሚሞት? ራሱ ለፈጠረው ውሸት የሚሞት ሰው ካየን ዕብድ ሰው አየን ማለት
ነው። የጌታን ሐዋርያት ስናስተውላቸው ውሸት ሕያው ሆኖ እንዲቆይ ብለው ለውሸት
ነፍሳቸውን የሚሰጡና ራሳቸውን የሚሸጡ ሳይሆኑ ውሸትን የሚጸየፉ ሰዎች
ለመሆናቸው በቃሉ ውስጥ የምናያቸው ታሪካቸው ይመሰክራል።

እንግዲህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ከመጽሐፍ


ቅዱስ ውጪም እጅግ የበዙ ማስረጃዎችና ምስክሮችን አይተናል። ኢየሱስ መሞቱና
ከሞትም መነሣቱን የሚያረጋግጡ ይህን የሚያህሉ ምስክሮች መጥራት ተችሏል።
ሳዲቅ መሐመድም ሆነ ሙስሊሞች በአጠቃላይ ኢየሱስ ተሰቅሎ ስላለመሞቱ
የሚሰጡት ሰብዓዊ ማስረጃ ከአንድ ጥቅስ ባሻገር እንደ ደመና የበዙ ምስክሮችን
የሚረታ ማስረጃ በማቅረብ መሆን አለበት።

እስካሁን ባየናቸው በርካታ ነጥቦች የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ


አለመሆኑን የሚያረጋግጡ እጅግ ብዙ ማስረጃዎችን ተመልክተናል። በእርግጥም
የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስና የቁርኣኑ ዒሳ የተለያዩ ናቸው። ኢየሱስ አምላክ
ስላለመሆኑ ወይም ነቢይ ብቻ ስለመሆኑ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልሳችን፥ ‘ኢየሱስ
አምላክ ካልሆነ ራሱን ከአብ ጋር አንድ ያደረገ ሐሰተኛ ነውና እንደ መልካም ሰው
ወይም እንደ ነቢይም መታየት የለበትም’ የሚል ነው። ራሱን ከአብ ጋር አንድ ሳይሆን
አንድ ካደረገ ውሸታም እንጂ ነቢይም ሊባል የተገባው አይደለም።

ይህን አመለካከት በተመለከተ C. S. Lewis የተባለው እንግሊዛዊ ክርስቲያን ምሑር


Mere Christianity በተባለ መጽሐፉ ውስጥ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ነበር፤
(ትርጉም የራሴ)

ልከላከል የምፈልገው አንድ ነገር አለ፤ ያም፥ አንዳንድ ሰዎች ስለ ኢየሱስ፥


'ኢየሱስን እንደ ታላቅ የሞራል መምህር አድርጌ እቀበላለሁ፤ አምላክነቱን ግን
አልቀበልም' የሚሉትን ነው። ይህ ማለት የሌለብን አንድ ነገር ነው። እንዲያው
ሰው ብቻ የሆነ ሰው ኢየሱስ የተናገራቸውን ነገሮች ከተናገረ ታላቅ የሞራል

122
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መምህር ሊሆን አይችልም። ይህ ሰው ወይ ዕብድ ነው፤ 'እኔ የተቀቀለ እንቁላል ነኝ'


እንደሚል ያለ ዕብድ፤ ያለዚያ ከሲዖል የመጣ ሰይጣን ነው። ምርጫህን መምረጥ
አለብህ። ይህ ሰው ወይ የእግዚአብሔር ልጅ የነበረና የሆነ ነው፤ ወይም ዕብድ፥
ወይም ከዚያ የከፋ ነው። ከፈለግክ ዘግተህ ዝም ልታሰኘው፥ ምራቅህን ጢቅ
ልትልበት፥ ወይም እንደ ዲያብሎስ ቆጥረህ ልትገድለው ትችላለህ፤ ያለዚያም
ከእግሩ ስር ወድቀህ ጌታ እና እግዚአብሔር ልትለው ትችላለህ። ነገር ግን፥ 'ታላቅ
የሞራል መምህር' ወደሚል የንቀት ንግግር አንምጣ። ይህንን ለምርጫችን
አላቀረበልንም፤ ይህ አሳቡም አልነበረም።23

በቁርኣን የምናገኘው ዒሳ ነቢይ ብቻ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ግን ጌታ ነው፤


ማለትም አምላክ ነው። ሰው የሆነ አምላክ ነው። በሥጋ የመጣ ወይም ሥጋ የለበሰ
አምላክ ነው። ይህ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ማንነት የመጽሐፍ ቅዱስ ማንም
ክርስቲያን የሚቀበለው አስተምህሮ ነው። ‘ኢየሱስ ጌታ ነው።’ ስል፥ ‘የለም ጌታ
አይደለም፤ ፍጡርና ሰው ብቻ ነው።’ የሚል ከኖረ በእርግጥ ስለተለያየ ነገር
እየተናገርን መሆናችንን ምንም ምርምር የሚያሻው ጉዳይ አይደለም።

23 Mere Christianity, p54-56.ትርጉም የራሴ።

123
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መደምደሚያ
እንደ መደምደሚያ ቃል የኢየሱስን አንድያነት በመናገር ልጨርስ። አንድያ ልጅ
የሚለው ቃል ለክርስቶስ መግለጫ ሲሆን መሳይ ወይም ቀዳሚና ተከታይ የሌለው
መሆኑን የሚያሳይ ቃል ነው። በብሉይ ኪዳን ቋንቋ ለሰዎችም የተጠቀሰ ቃል ሆኖ
ብቸኛ ልጅን ያመለክታል፤ ለምሳሌ፥ ኤር. 6፥26፤ አሞ. 8፥10፤ ዘካ. 12፥10። ቃሉ
ּ‫ יָחִיד‬ያኺይድ አንድና ብቸኛ መሆንን እንዲሁም የተወደዱ መሆንንም ያሳያል።
በመዝ. 22፥20 ብቻነት፥ በመዝ. 68፥6 ብቸኞች የሚለውም ቃል ከዚህ አንድ ነው።
በዘፍ. 22፥2፥12፥16 ብቸኛ ሳይሆን ልዩ ወይም የተወደደ ልጅነትን ያሳያል። ይህንኑ
ታሪክ የዕብራውያን ጸሐፊ በአዲስ ኪዳን አንድያ ልጅነት አድርጎ ያቀርበዋል፤ ዕብ. 11፥
17።

መሳ. 11፥34 ብቸኛ ወይም አንድ ብቻ ልጅነትን ያሳያል። ይህ ቃል ብሉይ ኪዳን ወደ


ጽርዕ በተመለሰበት የሰባ ሊቃናት ትርጉም ልክ በአዲስ ኪዳን ስለ ክርስቶስ የተጻፈው
μονογενής (ሞኖጌኔስ) የሚል ቃል ነው። ይህ ቃል በአዲስ ኪዳንም ለሌሎችም
ብቸኛ ልጆች ተጠቅሶአል፤ ለምሳሌ፥ ሉቃ. 7፥12፤ 8፥42፥ 9፥38። እነዚህ የሉቃስ
ጥቅሶች ልጆቹ ብቸኞች ወይም ቀዳሚና ተከታይ የሌላቸው መሆናቸውን
አያስረዳንም። በዕብ. 11፥17 ላይ ያለው ቃልም ሞኖጌኔስ ነው። ይህ ቃል የሚናገረው
ስለ አብርሃም ሲሆን ልጁ ይስሐቅ ሞኖጌኔስ ተብሎአል። አብርሃም በኋላ ሌሎች
ልጆች እንዳሉት የታወቀ ነው። እዚህ ላይ ንጽጽሩ ከእስማኤል ጋር ነው። ይስሐቅ
አንድያ የሆነው በብቸኛነት ሳይሆን የተስፋው ቃል ልጅ በመሆኑ ነው። ስለዚህ
ሞኖጌኔስ ብቻነትን ሳይሆን ልዩነትን የያዘ ቃል ነው።

የኢየሱስን አንድያ ልጅነት (ሞኖጌኔስነት) በተመለከተ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እንይ።

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ


እግዚአብሔር አንድያ ልጁን (μονογενής) እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ
ወዶአልና። ዮሐ. 3፥16

በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ


(μονογενής) ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ዮሐ. 3፥18

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም


(μονογενής) ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሐ. 1፥14

124
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ
(μονογενής) እርሱ ተረከው። ዮሐ. 1፥18

በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር
ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን (μονογενής) ወደ ዓለም ልኮታልና። 1ዮሐ. 4፥9

ኢየሱስ አንድያ ልጅ የሆነው ወይም የተባለው ታሪክን የሚያጣርሱ እንደሚናገሩት


በኒቅያ ጉባዔ አይደለም። የዮሐንስ ወንጌል ከኒቅያ ጉባዔ በፊት መኖሩን ካልካድን
በቀር 'አንድያ ልጅ' የሚለውን ቃል ከኒቅያ ጋር ልናቆራኝ ከቶም አንችልም።

ለክርስቶስ ስለተነገረው ስለዚህ ቃል ስንመጣ ግን ይህ ቃል ክርስቶስ ብቸኛ፥ መሳይ


የሌለው፥ በዓይነቱ ልዩ፥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አመልካች ነው። ሞኖጌኔስ
በሁለት ቃላት የተሠራ ጥምር ቃል ሲሆን እንደ አማርኛው አንድያ ልጅ ማለት ነው።
ሞኖ አንድ ብቻ ማለት ሲሆን ጌኔስ የተወለደ፥ ልደት፥ ልደት ያገኘ ማለት ነው።
ካልተንዛዛ በቀር ጌኔስ ልጅ ማለት ነው። በአማርኛ እየተነጋገርንና እየተጻፈም
በእንግሊዝኛ በርካታ ትርጉሞች 'only begotten' ተብሎ ስለተተረጎመና beget
ደግሞ በሥጋ መውለድ ስለሆነ፥ በሥጋ መውለድ ደግሞ ወሲባዊ ግንኙነትን
ስለሚያስገድድ ኢየሱስ 'only begotten' ሲባል በወሲብ ፈቃድ የተወለደ ልጅ ነው
ማለት ነው የሚል ሰንካላ መከራከሪያ ይቀርባል። በቅርብ ከአንድ ሙስሊም ጋር
ስንነጋገር beget የሚለውን ቃልና ትልቅ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ነበር ይዞ
የመጣው። የቃሉን ምንነት ለመረዳት ወደ ሌላ ቋንቋ ከተሄደ ከአማርኛ ተዘልሎ ወደ
እንግሊዝኛ ሳይሆን ወደ ምንጩ ነው መኬድ ያለበት። መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ
በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ አይደለም የተጻፈው።

ሌሎች የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው የተጠሩ አሉ፤ ለምሳሌ፥ እስራኤል እንደ አንድ
ሕዝብ በዚህ ስም ተጠርተዋል፤ ዘጸ. 4፥23። እኛም የክርስቶስ ተከታዮች
የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዮሐ. 1፥12፤ 11፥52፤ ሮሜ 8፥14-21፤ ገላ. 3፥26፤ ፊል. 2፥
14-15፤ 1ዮሐ. 3፥2። ይህ ልጅነት እኛ በክርስቶስ በኩል ያገኘነው ልጅነት ሲሆን
ብቸኛና መሳይ የለሽ ልጅነት አይደለም። የክርስቶስ μονογενής ወይም አንድያ ልጅ
መሆን ብቸኛና መሳይ የለሽ ልጅነት ነው። የአብ አንድያ ልጅ ሲባል በሥላሴ ውስጥ
ያለው ዘላለማዊ ስፍራና ባህርይ እንጂ ልጅ ከአባት በኋላ እንደሚገኝ አብ ቀዳሚ
ወልድ ተቀዳሚ ማለት አይደለም። አብ አስቀድሞ የነበረ፥ ወልድ ቀድሞ ሳይኖር
ቆይቶ ኋላ መኖር የጀመረ ማለት አይደለም።

ወልድ ወልድ የተሰኘው ከድንግል ተወልዶ ሥጋ በመልበሱ ምክንያት፥ ጽድቅን ሁሉ


ለመፈጸም በመፍቀዱ፥ ራሱን ዝቅ በማድረጉ፥ ራሱን ለምትካዊ ሞት አሳልፎ
በመስጠቱ፥ በመታዘዙ ነው እንጂ ኋላ በመገኘቱ ከቶም አይደለም። በኅልውና ወልድ

125
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

ከአብ፥ ወይም መንፈስ ቅዱስ ከወልድ አይተናነሱም። አይቀዳደሙም። ኢየሱስ በሥጋ


የተገለጠ አምላክ በመሆኑ ከመወለዱ በፊትም ነበረ። የት? ዓለማትን ሲፈጥር
በእግዚአብሔር ዘንድ ወይም ከአብ ጋር ነበረ፤ ዮሐ 1፥1-2፤ 17፥5።

ይህ ወልድ ነው፤ ይህ ኢየሱስ ነው። እርሱ ጌታችን፥ መድኃኒታችንም ነው።

የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ከቶም አይደለም።

126
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

Al-Qayrawani, Faris; Was Christ Really Crucified? The Good Way


Publishing, 2010. electronic version at: http://www.the-good-
way.com/eng/books/4360/format-xml

Andani, Khalil Article, The Crucifixion in Shi’a Isma’ili Islam.


https://www.themathesontrust.org/papers/islam/andani-
crucifixion.pdf

Bruce, F. F. The New Testament Document, IVF & Tyndale Press.,


London 1960.

Geisler, Norman L. and Saleeb, Abdul, Answering Islam, The


Crescent in the Light of the Cross, Baker Books, Grand Rapids,
Michigan, 2003.

Habermas, Gary R. The Verdict of History, Thomas Nelson,


Nashville, 1982.

Irenaeus, Against Heresies, Book 1 Ch. 24, 4 (electronic version).

Josephus, Flabius. Antiquities: Book 18, Ch. 3, Electronic version.

Klein, William W., Blomberg, Craig L., and Hubbard, Robert L.,
Jr. Introduction to Biblical Interpretation, Copyright © 1993,
2004, 2017 by ZONDERVAN, ePub Edition Edition ©
February 2017.

Lewis, C. S., Mere Christianity, Collins, London , 1952.

Mc Dowell, Josh: Evidence that Demands a Verdict, Campus


Crusade for Christ International, Arrowhead, San Bernadino,
CA, 1977.

Plummer, Robert L. 40 Questions About Interpreting the Bible,


Kregel Inc. Grand Rapids, MI., 2010.

127
የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም።

Quran: English Translation: Saheeh International; http://tanzil.net/


Pdf: http://quranpdf.net/

Quran: Abdulla Yusuf Ali Abdullah Yusuf Ali - The Meaning of


the Holy Qur'an. Electronic version.

Qureshi, Nabeel, No God but One: Allah or Jesus? Zondervan,


Grand Rapids, MI. 2016.

Sanhadrin electronic version. Document 43a


(http://www.tyndale.cam.ac.uk/Tyndale/staff/Instone-
Brewer/prepub/Sanhedrin%2043a%20censored.pdf).

Tacitus, Publius. The Annals. e.v.


https://penelope.uchicago.edu/Thayer/E/Roman/Texts/Tacitus/
home.html

Tafsir Ibn Kathir, electronic version, ch. 61, electronic version.


http://www.tafsir.com.

መጽሐፍ ቅዱስ፤ ብርሐንና ሰላም ማተሚያ ቤት አዲስ አበባ፤ 1954 ዓ. ም.።

ሙሓመድ ዓሊ አልኹሊ፤ እስላም እና ክርስትና (ንጽጽራዊ አቀራረብ)፤ ተርጓሚ፥


አይታወቅም፤ ሑዳ ፕሬስ ሊሚትድ፤ አዲስ አበባ፤ 1989።

ቅዱስ ቁርኣን፤ ነጃሺ አሳታሚ ድርጅት፤ አዲስ አበባ፤ 1961 ዓ. ም.።

128

You might also like