የትርጉም ምንነት
የትርጉም ምንነት በተመለከተ የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ አተያይ አላቸው፡፡
ሀ. ካት ፎድ ጂ.ሲ፡-
“The linguistic Theory of translation” በሚለው መጽሐፍ ውስጥ፣ ትርጉም በሆነ አንድ ቋንቋ
የተዘጋጀን አንድ ሰነድ ወደሆነ ሌላ ቋንቋ መገልበጥ ነው ብሎ በይኗል፡፡
ለ. ፒተር ኒውማርክ፡-
“Approach to translation” በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ትርጉም በአንድ ቋንቋ የተላለፈን መልዕክት ወደ ሌላ
ቋንቋ የማስተላለፍ ቀረጻ ነው ይለዋል፡፡
ሐ. ናይዳና ታቦር፡-
“Theory and practice of Translation” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ፡- ትርጉም ለአቀባይ ቋንቋ ቅርብ
የሆነ፣ እማይጎርብጥ፣ ተቀራራቢ መልዕክት እና የአጻጻፍ ስልትን የተከተለ ምንባብ በተቀባይ ቋንቋ የማምረት ስራ
ነው፡፡
ተግባሩ ግቡ (ትኩረት) ምዘና
1. መተካት ምንባብ ተቀራራቢ
2. መተካት ምንባብ ተመሳሳይ
3. ማምረት መልዕክት ቅርብ
በትርጉም ፍፁም (የ 100%) አንድነት የለም፤ ምክንያቱም የቋንቃች መዋቅርና የሰዎች የህይወት ልምድ የተለያየ
በመሆኑ ነው፡፡ የትኛውም ትርጉም ውስጥ ምንጊዜም የፍቺ ኪሳራ አለ፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ከተርጓሚው ድክመት
አይደለም፡፡
ትርጉም በአቀባይ ቋንቋ በጽሁፍ የቀረበን መልዕክት በተቀባይ ቋንቋ በተለምዷዊና ከሞላ ጎደል አቻ በሆነ አባባል
መተካት ነው፡፡ በአቀባይ ቋንቋና በትርጉሙ ውስጥ ያለው የንባብ ይዘት አቻ መሆን አለመሆኑ የሚሰነው በያዘው
መልዕክት ነው፡፡ በትርጉም ሂት ቀዳሚው ነገር ፍቺ ሲሆን፣ በፍቺው ሂት ያለው ስልትም ሊለዋወጥ ቢችልም እርሱም
ሌላው ነጥብ ነው፡፡ በአንድ ምንባብ ውስጥ በአዝናንና በአስቂን መልኩ የተፃፈን መልዕክት ከረር ባለ ስሜት ማቅረብ
ይቻላል፡፡ ዋናው ነገር ለአንባቢው እንዲደርስ የሚፈለገውን ሀሳብ ብቻ መምረጥ ነው፡፡ የፍቺ አቻዊነትን ለመወሰን
ሁለት ጉዳዮችን በሚገባ ማጤን ያስፈልጋል፤ ይኸውም፡-
1. ስነ ልሳናዊ ፍቺን፡- በዚህ ሂደት ቃላቱ በቀጥታ የያዙትን ፍቺ የሚመለከት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ቤት
2. አውዳዊ ፍቺ፡- ይህ ፍቺ ከተባበት ሁኔታ /አውድ/ አንበሳ ጋር የሚፈታ ይሆናል፡፡ የትርጉምን ብያኔ ምንነት
ስናስብ ሶስት ነገሮች ላይ ማነጣጠር እንችላለን፡፡ እነዚህም፡-
1.1. Inter Semiotic
Semiotic ማለት የምልክቶች ጥናት ማለት ነው፡፡ በዚህ ሂት ከአንድ አይነት የምልክት ስርዓት ወደ ሌላ አይነት
የምልክት ስርዓት የሚተላለፍበት የትርጉም ሂደት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- o የትራፊክ መብራት o የመንገድ ላይ
ምልክቶች
1
o የዝብራ መተላለፊያ (Zebra crossing) o የተለያዩ አበቦች
1.2. Intra Lingual
በአንድ ቋንቋ ውስጥ የተለገፁን አንድ ሀሳብ በዚያው ቋንቋ በሌላ አይነት መንገድ መግለፅ ነው፡፡ ይህም አካሄድ
paraphrasing ይባላል፡፡ ምሳሌ፡- አማርኛን በአማርኛ ኦሮሚኛን በኦሮሚኛ
1.3. Inter Lingual
በሁለት የተለያዩ የተፈጥሮ ቋንቋዎች መካከል የሚደረግ የመልዕክት ማስተላለፍ ተግባር ነው፡፡ ይህንን በቀጥታ
አገላለፅ “Translation” ልንለው እንችላለን፡፡ ይህም ትርጉም (translation) በሁለት አይነት መንገድ
ሊገለፅ ይችላል፡፡
ትርጉም ፡- በቃል (interpretation)
በጽሁፍ (Translation) ይባላል
ምሳሌ፡- አማርኛን በኦሮሚኛ ኦሮሚኛን በአማርኛ
የትርጉምን ብያኔና ተግባር በተመለከተ የተለያዩ ምሁራን የተለያየ ብያኔ ሰጥተውት እናገኛለን፡፡
ከእዚህም መካከል፡- አንዳንዶች የትርጉም ተግባር፡- - መልዕክት ማስተላለፍ (transfer, transfuse) ነው
ሲሉ፣
- ሌሎች ደግሞ መተካት (Replacement) ነው የሚሉ አሉ
- እንዲሁም ደግሞ ዳግም መግለፅ (Reproducing) ነው የሚሉም
አልታዩም፡፡
ከዚሁ ጋር ጎን ለጎንም የሚተላለፈው ነገር ምንድነው ተብሎ ለሚጠየቀው ጥያቄ ደግሞ - ፍቺ (meaning)
- የምንባብ ይዘት (textual material)
- መልዕክት (message) ነው ይላሉ፡፡
በምን ሁኔታ ለሚለው ደግሞ ሁሉም ከአቀባይ ቋንቋ ወደ ተቀባይ ቋንቋ ነው ሲሉ፣ ተግባሩስ እስከምን ድረስ ነው
ተብለው ሲጠየቁ አንዳንዶች አቻዎነት (Equivalence) እስከሚገኝ ድረስ ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ ተቀራራቢና
ተላምዷዊ እስከሚሆን ድረስ ነው የሚሉም አሉ፡፡ እነዚህ ምሁራን ከላይ ይዘውት የተነሱትን ሀሳብ ይዘን
ስንመረምር፡-
ትርጉም የማስተላለፍ ተግባር ነው ካልን፣ ተቀባይ ቋንቋ ከዚህ ቀደም ባዶ ነበር የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
ለምሳሌ፡- እንደምን አደሩ? Good morning?
ስንት አመትህ ነው? How old are you?
በየቋንቋው፣ ቋንቋው ራስን የቻለ መግለጫ መንገድ ያለው ቢሆንም፣ እንደየቋንቋው ግን የአገላለፅ ልዩነት
ይኖረዋል፡፡ የምንተረጉመው ነገር ምንድነው? ምንባብ ማለት አንድ የተባለ ነገር ሲሆን፣ በምንባቡ ውስጥ ደግሞ
የማይጨበጡ በርካታ ነገሮች ይኖራሉ ለምሳሌ፡- የምንባቡ መልዕክት፣ አውድ፣ የተባለበት ምክንያት….
1.4 የትርጉም አስፈላጊነት
2
ያለንበት ዘመን የመረጃ ዘመን ነው፡፡ በዚሁ በመረጃ ዘመን ስለዘመናዊነት፤ ስለአለማቀፋዊነት መቀራረብ
በእጅጉ ይወሳል፡፡ በዚሁ ባለንበት ዘመን በአለም ላይ በርካታ ቋንቋዎች (ወደ ሰባት ሺህ (7,000) የሚደርሱ
ቋንቋዎች አሉ፡፡ ይህንን ያክል በርካታ ቋንቋዎች በአለማችን ላይ በመኖራቸው ምክንያት በቋንቋ የማይግባቡ በርካታ
ህዝቦች አሉ፡፡ እንግዲህ ይንን የመግባባት ችግር ለመፍታት ደግሞ ማስታረቂያው የትርጉም ሥራ ነው፡፡
በዓለማችን ላይ በርካታ ቋንቋዎች እስካሉ ድረስ፣ ሰዎች በቋንቋ አማካይነት ለመግባባት በእጅጉ ይቸገራሉ፤
ይህንን ችግር ለመፍታት ደግሞ የትርጉም ሥራ የግድ ይኖራል፤ ወይም በተለያዩ ቋንቋዎች የተከለሉ ህዝቦችን
ለማገናኘት የትርጉም ሥራ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ለመሆኑ በትርጉም ሥራ ውስጥ የሚካተቱት ምን ምንድን ናቸው?
o የተለያዩ የልብ ወለድ ጽሁፎች o ዜናዎች
o ከሸቀጣ ሸቀጦች ጋር የሚገቡ መመሪያዎች (Manuals) o ማመልከቻዎች
o ደንቦች o መመሪያዎች
ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች የሚግባቡት በትርጉም ነበር፡፡ በህይወት መስክ
ሁሉ በማናቸውም ጉዳይ የትርጉም ሥራ ይኖራል፡፡ አንድ እቃ ሲሸጥ አብሮ አጠቃቀሙን የሚያስረዳ መመሪያ በተለየ
ቋንቋ አብሮ ይኖራል፡፡ ስለዚህ በየትኛውም ቦታ ቋንቋዎች መግባባትን በገደቡበት ቦታ ሁሉ መግባባትን ለመፍጠር
ካስፈለገ ትርጉም የግድ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡
1.5 ትርጉም በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ
ትርጉም በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ምን መልክ አለው የሚለውን ነጥብ ከማንሳታችን በፊት በአለማችን ላይ ምን መልክ
ነበረው የሚለውን ነጥብ እናንሳ፡፡ ብዙ ነገር የት ተጀመረ ብለን ስንጠይቅ ብዙ ነገር የሚያመራን ወደ ግሪክና ወደ
ግሪክ ስልጣኔ ቢሆንም፣ የትርጉም ሥራን ስናስብ ግን በግሪክ ተጀመረ አንልም፡፡ ምክንያቱም ግሪካዊያን ቀደምት
ስልጣኔን የተቀላቀሉ ህዝቦች በመሆናቸው ከየትኛውም ሀገር በትርጉም የሚወስዱት ስልጣኔ አልነበራቸውም፡፡ ነገር
ግን በዘመኑ የግሪክን ስልጣኔ ለመቅዳት የሚሹ በርካታ ሀገሮች የግሪክን ስልጣኔ ወደ ራሳቸው ቋንቋ ተርጉመው
ወስደዋል፡፡ በዚህም ረገድ የመጀመሪያው የትርጉም ሥራ፣ የነበረው ሀገሮች የግሪክን ባህል ወደ ራሳቸው ባህል
ለማምጣት ባደረጉት ትርጉም የትርጉም ሥራ ነበር፡፡ ይህንንም በማድረግ ቀዳሚዎቹ ሮማዊያን ነበሩ፡፡ በወቅቱም
ከግሪክ ስልጣኔ ወደራሳቸው ባህል በትርጉም ባመጡት ሀገሮች ላይ የግሪክ ስልጣኔና አስተሳሰብ የራሱን አስተዋጽኦ
አድርጎም ነበር፡፡ ለምሳሌ የግብፅ ስልጣኔ መሠረቱ ግሪክ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የጽሁፍ ስራን ስንመረምር ደግሞ፣ የግድ መነሻችን የት እንደነበር መጠየቅ የግድ ይሆናል፡፡
ይህንንም ስናደርግ ወደኋላ ተመልሰን መነሻችን የሚሆነው በአክሱም ስልጣኔ ወቅት በድንጋይ ላይ ተፅፈው የተገኙት
ጽሁፎች ናቸው፡፡ እነዚህም ጽሁፎች እስከ 500 ዓ.ም. ድረስ ወደ ኋላ የሚመልሱን ሲሆን፣ ጽሁፎቹም የተገኙት
በግሪክና በሳባ ቋንቋ ነው፡፡
ኋላም ከክርስና ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጋር ተያይዞ በርካታ የትርጉም ሥራዎች በኢትዮጵያ ውስጥ
በቅጽበት ለመስፋፋት በቅተዋል፡፡ አንዳንድ ጸሃፍት (ምሁራን) የኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍን ስናስብ አብዛኛው የትርጉም
ሥራ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይላሉ፡፡ ለዚህም በማስረጃነት የሚያቀርቡት፡-
ሀ. የክርስትና ሃይማኖት በኢትዮጵያ በተጀመረበት ወቅት በርካታ ሃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ መመሪያዎች ከውጭ መጥተው
በወቅቱ ይነገር ወደነበረው ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተተረጎሙ፤
ለ. ፀሐፊዎቹ ራሳቸው (ለምሳሌ ከበደ ሚካኤልንና ሌሎቹንም ደራሲያን ጨምሮ፣ በአብዛኛው የትርጉም ሥራ ይሠሩ
እንደነበር ያወሳሉ፡፡
3
ሐ. ከ 1900 አንስቶ በ 1970 እና በ 1980 ዎቹም የነበሩ ጽሁፎች አብዛኞቹ ትርጉሞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም
ሀገራችን ትከተለው በነበረው ርዮተ አለም ምክንያት በርካታ የሶሻሊዝምን ርዕዮተ ዓለም የሚያስረዱ ጽሁፎች
ይተረጎሙ ነበር፡፡
ትርጉም አብዛኛው (ግማሽ) የህይወታችን ክፍል ነው ማለት ይቻላል ምክንያቱም አብዛኛው የቲቪ የሬዲዮና
በማስታወቂያ መልክ የሚለጣጠፉ ማስታወቂያዎችን ብንመለከት እንኳ በአብዛኛው ትርጉሞች ናቸው፡፡
ለምሳሌ:- ለህይወትህ ዋጋ ስጥ! (Value your Life!)
በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ ውስጥ የትርጉም ሥራ ይህንን ያህል ጎልቶ ቢታይም፣ እስካሁን ድረስ ስለትርጉም ቲዎሪ፣
ስለትርጉም አስፈላጊነትም ሆነ ስለትርጉም ጉዳት አንዳች ነጥብ እንኳን የጠቆመ ሰው የለም፡፡
የትርጉም ጥቅሞች፡- ሀ. የተሻሉ ስነ ጽሁፎችን ለማግኘት
ለ. የተሻለ ህይወትና አስተሳሰብ እንዲኖር
ሐ. የተሻለ የአፃፃፍ ስልትን ለመማር እድል ይሰጣል
1.6 ትርጉም የሚያመጣቸው አሉታዊ ነገሮች
ሀ. ትርጉም አላስፈላጊ የውጪ ባህሎች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ በር ሊሆን ይችላል፡፡
ለምሳሌ፡- የግብረ-ሰዶማዊነትን ተፈጥሯነት፣ የፍችን ቀላልነት፣ ከጋብቻ በፊት የግብረስጋ ግንኙነትን
አስፈላጊነትን፣ ኃይማኖት የለሽነትን፣ ቁሳዊነትን፣ የማህበራዊ ኑሮ አላስፈላጊነትንና የመሳሰሉ ባዕድ
አስተሳሰቦችን ሊያስተዋውቁ ይችላሉ፡፡
ሁ. ትርጉም ወሲብ ነክ ጽሁፎችና ፊልሞች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ በር ሊሆን ይችላል፡፡
ምሳሌ፡- የሲድኒ ሼልደን ድርሰቶች አይነት
አንድ ተርጓሚ የትርጉም ሥራውን ሲያከናውን የሚተረጉመው ድርሰት ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ ማሰብ አለበት፤ ይህ
ካልሆነ ችግሩ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም፡፡ አንድ ተርጓሚ ኢትዮጵያዊያንን በግብረገብነት ሊያንፅ የሚችል ሥራን
በትርጉም ወደሀገር ውስጥ ቢያስገባ ጠቀሜታው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት የትርጉምን ሥራና የተርጓሚውን
አላማ በሚገባ መለየት ያስፈልጋል፡፡
የትርጉም ንድፈ ሃሳቦች
2.1 ጠቋሚ ንድፈ-ሃሳብ (Reference Theory)
የቃላት ፍቺ በቃሉና በተወካዩ መካከል የሚመለከት ነው፡፡ ብዙ ቃላት የሚወክሉት ነገር የላቸውም፡፡
ለምሳሌ፡- ወደ፣ ገና፣ እንዴት…
Refenrece:- እንደፍቺ አለ፤ ይህ አስተሳሰብ ችግር አለበት የሚሉ ምሁራንም አሉ፡፡
2.2. ምስል ከሳች ንድፈ-ሃሳብ (Image Theory)
ቃላቱን ስንሰማ በአዕምሯችን የሚመጣው ምስል ፍቺ ነው፡፡ ብዙ ቃላት ፍቺ የላቸውም፤ ምስል አላቸው በሚሉት
ሰዎች ዘንድ እንካ አንድ አይነት ምስል በአዕምሯቸው ላይሳል ይችላል፡፡
2.3 የሀሳብ ማዕቀፍ ንድፈ-ሃሳብ (Concept Theory)
4
ቃላት በአዕምሯችን የሚፈጥሩት ምስል ነው ከማለት ይልቅ፤ አንድን ምስል ሊፈጥሩ የሚችሉ ንዑሳን ሐሳቦች ስብስብ
ነው የሚል ነው፡፡ እነዚያን ሀሳቦች በአንድ የሀሳብ ማዕቀፍ ሳንይዛቸው ፍቺ ይሰጡናል፡፡
2.4. ንድፈ ሃሳባዊ ትንታኔ (Conceptual Analysis)
ይህ የፍቺ የትንታኔ ዘዴ ሲሆን የአንድ ቃል ንዑሳን ሐሳቦች ፍቺ መሰባጠር ነው፡፡ ቃላት በየትኛው ይመሳሰላሉ?
በየትኛው ይለያያሉ? የሚለውን ካወቅን የትኛው ቃል በየትኛው አውድ ተመራጭ እንደሆነ ለመወሰን ያስችላል፡፡
ለምሳሌ፡- Chair Sofa Bench Ha
Sitting Sitting Sitting Sitting
One One/more more person one person
Support Support no support no support
See look watch gaze
2.5 የፍቺ ትንታኔ
በአንድ ምንባብ ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱ የፍች አሃድ (Semantic Unit) ለጠቅላላው ምንባብ መልዕክት
የሚበረክቱት የፍቺ አስተዋፅኦ መገንዘብ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ደግሞ ምንባቡን በዝርዝር መገንዘብ ነው፡፡ ቃላት
በምንባብ ውስጥ የሚፈቱት በሚገኙበት ዓ.ነገር ውስጥ (በአውዳቸው) ነው፡፡ ዓ.ነገር ከቃላት የሚመሰረት ስለሆነ
ስለቃላት ፍቺ ማውራት (ማሰብ ማለት) ስለ ዓ.ነገር ፍቺ ማውሳት ማለት ነው፡፡
2.6 የአውድ አይነቶች
ሀ. ስነ ልሳናዊ (Linguistics) አውድ
በአንድ ምንባብ ውስጥ ያሉ ቃላት፣ ሀረጋት፣… ወዘተ text – context እየሁኑ መሄዳቸውን የሚመለከት ነው፡፡
ለ. ተግባራዊ (Situational/programatic) አውድ ነው፡፡
ተግባቦት በሚካሄድበት ዙሪያ ገባ፣ ርዕሱን፣ ቦውን፣ ተናጋሪውን ወዘተ የሚመለከት
የቃላት ፍቺ በሚገኙበት ዓ.ነገር ውስጥ በሁለት አይነት መንገድ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይኀውም፡-
1. ቅንጅታዊ፡- ከዓ.ነገሩ መዋቅር አኳያ የሚገኙበትን የቅንጅት (syntactic marking of meaning
ስፍራና ፍቻቸውን ይመለከታል፡፡ ለምሳሌ፡- ቃል በዓ.ነገሩ ውስጥ የገባበት ስፍራ ባለቤት፣ ተሳቢ ወይም ግስ ይሆናል
ብለን እንገምታለን፡፡
2. በዓ.ነገሩ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ቃላት ጋር የሚኖረው የፍቺ መስተጋብር ነው፡፡ (meaning intaction
semotactic marking of meaning) ምሳሌ፡- The book is on the table
The multiplication table
የተለያዩ ቃላት የፍቺ ተመሳሳይነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ አንድ ቃል የተለያ ግን ተዛማጅ ፍቺዎች ሊኖሩት
ይችላሉ፡፡
2.7. የቃላት እና የፍቺ ተዛምዶ ሁኔታ
5
የቃላትን ፍቺ ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት ይቻላል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
ሀ. ከተዋረድ ዝምድና (Hierarchical)
አንዱ የሌሎችን ፍቺ በውስጡ ሲይዝ (Generic specific) ምሳሌ፡- ዛፍ ጥድ ዛፍ የሚለው ጥድን ሊተካ ይቻላል
የቃላትን ስርዓታዊ ተዛምዶ ማወቅ የቃላዊ ፍቺ ሲፈጠር (Lexical gap ሲኖር) እንዴት መተካት እንዳለብን
ለማወቅ ይረዳናል፡፡
ለ. Scientific – Kingdom – phylum Class
ሐ. የፍቺ መስክ (Semantic Field) ቃላት በአንድ የፍቺ መስክ ሊገኙ ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ፡- እንቅስቃሴ፡- ሮጠ፣ ዘለለ፣ ተንከባለለ… ግንኙነታቸው ተዋረዳዊ አይደለም፡፡ አንዱ አንዱን
ሊተካ አይችልም፤ ነገር ግን ሁሉም በአንድ የፍቺ መስክ ይገኛሉ፡፡
2.8. የፍቺ ገፅታዎች (Aspects of meaning)
1. ጠቋሚ (Referncial meaning) ፍቺ፡- ራሱን ነገሩ የሚወክለው፣ ለምሳሌ፡- ልብ (heart)
– Reference: Bear in your heart (ቂም ያዘ)
– Bear in your mind (አስታወሰ)
2. ምስል ክሳች (Figarative meaning) ፍቺ ፡-
ከጠቋሚ በላይ ትርጉም ሲኖረው ነው፡፡ Metaphore፡ Beyond Reference ምሳሌ፡- ልጆች አበቦች ናቸው
3. ፈሊጣዊ (Indomatic meaning) ፍቺ፡- ከሰዋሰዋዊ ቅንጅታቸው ውጪ የተለየ ፍቺ ያላቸው ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- እግረ ደረቅ Tall tale - ለማመን የሚቸግር
4. ፍካሬያዊ (Connotative meaning) ፍቺ፡-
ቃሉ ከመደበኛ ትርጉሙ ውጪ የሚሰጠው አውዳዊ ትርጉም ነው፡፡
ምሳሌ፡- ልጁን ውሃ በላው፣ ክሱ እንዲፈረድለት በእጁ ሄደ (ጉቦ ሰጠ)
ምዕራፍ ሶስት
ለተርጓሚነት የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ችሎታዎች
ትርጉም ሳይንሳዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የትርጉም ሥራ ስርዓታዊ በሆነ መንገድ ይጠናልና፡፡ በተለይም ደግሞ
የስነልሳን ግኝቶች፣ የሚባሉት ንጽጽራዊ ስነ ልሳንና ስነፍች በሂደቱ በጣም ስለሚያስፈልጉ፣ የትርጉም ሥራ
ሳይንሳዊ ያደርጉታል፡፡ በንጽጽራዊ ስነ ልሳን፡- የሚተረጎመው ጽሑፍ ቋንቋና የተተረጎመው ጽሁፍ በቋንቋው
ይጠናል፡፡ የትርጉሙ ትክክለኝነት ይመረመራል፤ የተለያዩ ዘዴዎችን ከትሎም የሚሄዱ በመሆኑ ሳይንሳዊነት የጎላ
ይሆናል፡፡ ይህንን በተመለከተ የስነ ትርጉም ምሁራን ከሚባሉት መካከል ናይዳ ሰፊ ሀተታ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ አንድ
ተርጓሚ የትርጉም ስራውን ከመጀመሩ በፊት ስለትርጉምና የአተረጓጎም ሂደት መጠነኛ ግንዛቤና ችሎታዎች
ያስፈልጉታል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
3.1 የአቀባይና የተቀባይ ቋንቋ ችሎታ፡-
6
ይህም ማለት በአንድ የትርጉም ስራ ላይ የተሰማራ ሰው፣ የተፃፈውን ቋንቋ በሚገባ አንብቦ መልዕክቱን መረዳት
አለበት፤ የሚረጉምበትን ቋንቋም በሚባ ማወቅ አለበት፡፡ በዚህ ሂደት የአቀባዩንም ሆነ የተቀባዩን ቋንቋ
ሰዋሰው፣ የቋንቋዎችን ባህላዊ ገፅታ፣ የቋንቋዎችን አባባሎች፣ ባህላዊ አገላለፆችን መገንዘብና ባህላዊ
እሳቤዎችን በሚባ ማወቅና መረዳት አለበት፡፡ ይህ ሲባል ግን አንትሮፖሎጂስት መሆን አለበት ማለት አይደለም፤ ነገር
ግን ቋንቋን ማወቅ ማለት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ባህልን ማወቅ ማለት ነው፡፡
3.2 ሐሳብን በቋንቋ በተለይም በጽሁፍ የመግለጽ፡-
ችሎታ ጽሁፍን በቋንቋ ከመናገር የበለጠ፤ የማቀናበር ችሎታን የትርጉም ስራ ስለሚጠይቅ፣ ተርጓሚ ወደ ደራሲነት
ችሎታ እንዲያዘነብል የሚገደድ ይሆናል፡፡
3.3 የሚረጉምበትን የእውቀት ዘርፍ የማወቅ ችሎታ፡-
አንድ ተርጓሚ በትርጉም ስራው የሁሉንም የሙያ መስኮች ሊካን አይችልም፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ የህግ ባለሙያ አንዳንድ
ህግ ነክ ስያሜዎችን ሲተረጉም፣ ከቋንቋ ማወቁ ችሎታ በተለየ መልኩ የህግ እውቀት ሊኖው ይገባል፡፡ ጋዜጠኛም
ብንወሰድ፣ ከሙያው መስክ አንፃር የጥያቄ አወጣጥ፣ የአተረጓጎም ችሎታ፣ የጥያቄ አጠያየቅ፣ ጽፎ የማስተላለፍ…
ወዘተ የመሳሰሉትን ችሎታዎችን በተመለከተ በደንብ ማወቅ አለበት፡፡ ምሳሌ፡- Money Laundaring:-
የገንዘብ እጥበት የገንዘብ ብክነት (ከሙስና ጋር የተያያዘ ሀሳብ ነው)
3.4 የአተረጓጎም ችሎታ፡-
ሦስት የተለያዩ ሀሳብ ነው ሳይንስን፣ ጥበብንና ክሂልን በአንድነት አስተባብሮየመሰረተ ሂደትን በቀጥታ የሚመለከት
ይሆናል፡፡ የትርጉም ትምህርት ከተግባራዊ ትምህርት ወይም ከልምድ የሚገኝ ነው፡፡ ሁለት ቋንቋዎችን የሚችል ሰው፣
ሁለቱንም ቋንቋዎች በእኩል ደረጃ ይችላል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ይንን ችሎታ የተካኑ ሰዎች
ባይጠፋም፡፡
አንድ ተርጓሚ በትንሹ ከሚችለው ቋንቋ ወደ በደንብ ወደሚችለው ቋንቋ ቢተረጉም ነው፡፡ ምክንያቱም፣ በየትኛውም
ቋንቋ ብንመለከት ከምንረዳበት (ከመረጃ) ችሎታ ይልቅ የመግለጫ ችሎችን ያነሰ ነው፡፡ አንድን ጽሁፍ
በምንተረጉምበት ወቅት የተሰጠንን ጽሁፍ አንብበን ለመረዳት የሚያስፈልጉን በዚያው በጽሁፍ ውስጥ የስፍራውን ያህል
ብ ነው ነገር ግን ያንን ጽሁፍ ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም የሚያስፈልገን ክሂል ግን ካነበብነው ጽሁፍ በበለጠ፣
የመቀበያ ቋንቋ ችሎታችን ከፍተኛ መሆን አለበት፡፡
የመረዳት ችሎታችን ከመግለጫ ወይም ከመተርጎሚያ ችሎታችን ያነሰ ነው፡፡ ምክንያቱም በትርጉም ሂደት ቃላትን
መምረጥ፣ የአገላለፅ ስልትን መመዘንንና ሌሎች ጉዳዮችን ስለሚጠይቅ ነው፡፡
ምዕራፍ አራት የትርጉም ምዘና
አንድ የትርጉም ስራ ጥሩ ነው ወይም መጥፎ ነው ለማለት እንደመመዘኛ ከምንጠቀማቸው መመዘኛዎች መካከል፡ አቻዊነትና
ተፈጥሯዊነት ዋነኞቹ ናቸው።
4.1. አቻዊነት (Equivalence)
የአቻዊነት መመዘኛ ምንድነው? በአንድ ትርጉም ውስጥ አቻዊነት የሚመዘነው በአቀባይና በተቀባይ ቋንቋ ውስጥ ያለው
መልዕክት መቀራረብ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተርጓሚው አላማ አቻዊነትን የሚወሰን ጉዳይ ይሆናል፡፡ የትርጉም
ሥራ ሲሰራ፣ ትርጉም በፍፁም ሳይፋለስና ሳይሸራረፍ መተርጎም አይቻልም፤ ምክንያቱም በየቋንቋው ባህል የሚከሰት
ልዩነት ይኖራልና፡፡ ይህ ደግሞ (Semantic deficit) ይባላል፡፡ በትርጉም ሥራ አንድ ተርጓሚ ስራውን
የሚያከናውነው አቻዊነትን እስከሚያገኝ ድረስ ነው፡፡
7
Grammatical and Lexical adjustment to produce the message
በማንኛውም አካሄድ ከቅርፁም ሆነ በይዘቱ ተመሳሳይ የሆነ የቋንቋ ትርጉም አይገኝም፡፡ ምክንያቱም ቋንቋዎች
ራሳቸው በአገባባቸው፣ በቅርጻቸው፣ በባህላቸው… መዋቅር ይለያሉና፡፡
በትርጉም ሂደት ፍፁም የሆነ ትርጉም ስለማይገኝ ትኩረታችን መሆን ያለበት የፍቺን ትክክለኝነት፣ ተለምዷዊነት
እንጂ የቅርፅ አንድነትን አይደለም፡፡
4.2. ተለምዷዊነት (Natural Equivalence)
ተለምዷዊነት ሲባል የቋንቋውን የፍቺ ተቀራራቢነት (አቻዊነት) በዋናነት የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ሲባል በአቀባይ
ቋንቋ በጽሁፍ የቀረበ መልዕክት፣ በተቀባይ ቋንቋ ተመጣጣኝና ተለምዷዊ በሆነ አቻ አገላለፅ የሚገለፅ ተግባር
ነው፡፡ በትርጉም ሂደት ከትርጉም አቻዊነት ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች አንድ ተርጓሚ የትርጉም ሥራውን በሚያከናውንበት
ወቅት ስለአቀባይ ቋንቋ ማወቅ ያለበት፡፡
ሀ. እያንዳንዱ ቋንቋ የራሱ ልዩ ባህርይ፣ ልዩ አቅም እንዳለው ማወቅ አለበት፡፡
ለ. የመልዕክት ይዘቱን ለመጠበቅ የማስተላለፊያ ቅርፁን መቀየር አንድ ተርጓሚ የሚረጉምበት ቋንቋና የሚያውቀው
ቋንቋ ተፅዕኖውን እንዳያሳርፍበት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡
ለምሳሌ፡- የእንግሊዘኛ ምንባብ ወደ አማርኛ የሚተረጉም ሰው፣ በትርጉም ሂደቱ የአማርኛው ተፅዕኖ በትርጉም
ውስጥ እንዳይኖርበት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በእንግሊዘኛ ለሚባለው ለእያንዳንዱ አገላለፅ ተቀራራቢ
ሀሳቡን ከአማርኛ ፈልጎ ማግኘት አለበት፡፡
ምሳሌ፡- Good morning? እንደምን አደርክ? ይህ በጣም የተለመደ እና እማይጎረብጥ ነው፡፡
ሐ. በአንድ ቋንቋ የተገለፀ ነገር በሌላ ቋንቋ ሊገለፅ ይችላል፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ቅርፁ ሊለወጥ ሲችል
እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ጽሁፍ መተርጎም ያለበት የመጀመሪያ ፀሐፊ ሀሳቡን በገለፀበት መንገድ
ነው፤ ይህ ካልሆነ ግን የትርጉም ትክክለኛው ሥራ ተካሂዷል ማለት አይቻልም፡፡
እያንዳንዱ ቋንቋ የራሱ የሆነ የመግለፅ ችሎታ አለው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን የፎርማን አስገዳጅነት ሳይኖር
ሲቀር ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በሬሳላይ፡- ይህንን ቃል ብንወስድ ቃል ሚስጥር አዘል ነው፡፡ ይህንን ቃል በእንግሊዘኛ
ለየብቻው መግፅ ይቻላል፤ ሆኖም ግን ሁለቱን በአንድነት መግለፅ አይቻልም፡፡
We find Ourselves working hard to meet other peoples standard of
success.
ተክለሃይማኖት አይንህን ያጥፋው (Plant religion dismissed your eye)
ከመሬት ተነስቶ ነገር ይፈልገኛል (stand from the ground he find me matter)
እንዴት ነህ? We have አለን
የትርጉም አይነቶች
ትርጉም ከሚከናወንበት መንገድ አንጻር ሲታይ በሶስት ሊከፈል ይችላል፡፡ ሀ. የማሽን ትርጉም፣ ለ. በማሽን የታገዘ
ትርጉም እና ሐ. የገጽ ትርጉም ተብሎ ይከፈላል፡፡
6.1. የማሽን ትርጉም
8
የማሽን ትርጉም በአለማችን ላይ በ 20 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረ ጠንካራ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የማሽን ትርጉም
የሚከናወነው ኮምፒተሮችን በመጠቀም ሲሆን ለዚሁ አገልግሎት ተብለው የሚዘጋጁ የተለያዩ መተግበሪያዎችንም
ይጠቀማሉ፡፡
6.2. በማሽን የታገዘ ትርጉም
በማሽን የታገዘ ትርጉም ከማሽን ትርጉም የሚለየው ማሽኑ ከተረጎመ በኋላ ሰዎች የማሟሸት ስራን ስለሚሰሩ ነው፡፡
በማሽን የታገዘ ትርጉም ከማሽን ትርጉም ይልቅ ማራኪ፣ ሳቢ እና ትክክል ነው፡፡
6.3. የስክሪን ትርጉም
የስክሪን ትርጉም ማናቸውንም በኤለክትሮኒክ ቁሳቁስ መስኮት (ስክሪን) በድምጽ የሚተላለፉ መልእክቶችን ከአቀባይ
ቋንቋ ወደ ሌላ ተቀባይ ቋንቋ መተርጎም ነው፡፡