You are on page 1of 5

ባሇጌ እውነት

"ዛሬ አንቺን እንዲህ እንደሚያደርግሽ እኔንም እንዲሁ ያደርገኝ ነበር፤ አሌፈንበት ነው እቴ


ዝም ያሌነው እንጂሳናውቅ ቀርተን እንዳይመስሌሽ…ተወደድኩ ብሇሽ አትበይ ደንበር ደንበር
እኛንም አንጊዜ እነዲህ አድርጎን ነበር" ...በእድሜ ተኮንነው ያጡትን የወጣትነት ዘመን ውበትና
ቁንጅና ንቀውት እንዳሇፉ ሁለ ትተነው ነው እያለ የሚያወሯት ነገር አይገባትም
…በወጤነታቸው ዘመን የሇየሊቸው አሇላ እንደሆኑ ሰፈሩ ምስክር ነው…ዛሬ ምንም ዋጋ የሇው
የሚለትን ሁለ ሇማጣጣም ሲለ የእድሜአቸውን እኩላታ አባክነዋሌ…"ከአንዱ ወደአንዱ
መንዛሇሌ ቁም ነገር አይምሰሌሽ" ካለ ከአንዱ ወደአንዱ ይዛሇለ ነበር ማሇት ነው፡፡ የእድሜ
ፍርሃት ጭነት ያመጣባቸው ጉብጠት ተንጠራርቶ ከወጣትነት ፍሬ ሇመቀንጠፍ ስሇከሇከሊቸው
ይሆን ወይ ደግሞ ያሳሇፉት ህይወት መናነቱን በእድሜ መዝነው አይተው እንደሁ ከንቱ ነው
የሚለት ግሌጽ አይደሇም…

"ሰሇሞን እንኳ ስንቱን ካሽሞነሞነ በኋሊ ሁለ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ያሇው"

"ሰሇሞን እኮ ብዙ ዓመት ኖሯሌ፤በዛ ሊይ እንደው እውነቱን ሇመናገር እሱ ያየውን እንደው


ማየቱ ይቅርና አስበነው እራሱ መች እናውቃሇን…ደግሞ እኮ ሇሰሇሞን የደበረው ነገር
ሇላሊውም እኮ ያስጠሊዋሌ ማሇት አይደሇም"

"ሇሰሇሞን ጊዜ ሲሆን አፍሽን ታሞጠሙጫሇሽ እንግዲህ ኖሮ ያየ ሰው አይበጅም ካሇ መቀበሌ


ነው እንጂ ኖሬ ካሊየሁ አሊምንም ማሇት የህጻን ሌጅ ድርጊት ነው፤ የዘመኑ ወጣት ሲነገራችሁ
አትሰሙ ሁለን ካሊየሁ ማሇት"

"እሺ እሱን ተይው እና አንድ ነገር እኮ እድሜው በገፋ ቁጥር ያረጅና በላሊ ነገር ይተካሌ
ሇእውነትም እነደዚሁ ነው የአንድ ዘመን እውነት እውነታነቱ ሇዘመኑ ብቻ ነው" አቋርጠዋት
ይገባለ

"እና እውነትሽን አስረጂኛ እስኪ፤እናም የእኔን እውነታ ውሸት መሆኑንም አሳዪኝ"

"አታምኚኝማ" እጇን ከአናቷ በሊይ እያወረጨች፤ ስትበሳጭ እንዲህ ደርጋታሌ

"ድሮንስ ሊምንሽ ፈሌገሽ ነበር"

"ካሊመንሽኝ ታድያ ሇምን አስረዳሻሇው?"

ሳሚ ባቲ Page 1
@samibati for telegram users
"እንጃባሽ ቆይ ቀድሞ ነገር ቢቀርብሽስ፤የምን መሟዘዝ ነው እቴ ያንቺ ደግሞ ሌክ አጣ ማርም
ሲበዛ እኮ ይመራሌ" ማሩን በሌተው መረራቸው ያህሌ ፊታቸው ቀጨመ

"እሺ አንቺ ማር እስኪመርሽ ድረስ በሌተሸ ታውቂያሇሽ?" የተንኮሌ ፈገግታ ፊቷ ሊይ አሇ

"ቀድሞ ነገር ማር የሚባሌ ነገር በሌጅነቴ ማር ውስጥ ንብ ሞታ ካየሁ ወዲህ እንደማሌወድ


ታውቂያሇሽ አይደሌ እንዴ…

"እኮ ታድያ ማሩን ሳትበይ ስሇማሩ መምረር እንዴት ሌታውቂ ቻሌሽ?" ተንኮሎ ግቡን
እንደመታ ተሰማት መሰሌ

"ከአባባለ ከሆነ ችግርሽ እንግዲህ ሌቀይርሌሻ…እም..." ከአፋቸው የሚወጣውን ሃሳብ ባርኮት


እንደሚቀበሌ ሰው በጉጉት ትጠባበቃሇች…ሃሳቡን ከጣርያ ያወርዱት ይመስሌ ጣርያው ሊይ
አፍጥጠውበት ቆዩ፤ጣርያው ሳይገጅር አሌቀረም መሰሌ ተስፋ ቆርጠው ወሇለን በአይናቸው
ዳበሱት፤ ምናሌባት ከጣርያው የወደቀ ሃሳብ እየፈሇጉ ይሆናሌ…መሬት ደግ አይደሇችም
የፈሇጉትን ሃሳብ ሳይሆን የፈሇገቸውን ሃሳብ ሰጠቻቸው...ያቺ ሌኬሇሽ የቤት ኪራዩን ገንዘብ
አዘግይታ መስጠቷ ሳያንስ ሙለውን መክፈሌ አሌችሌም ብሊ በእንባ የታጀበ ጎዶል ብር ነው
የሰጠቻቸው፤ሇቀጣይ ወርም ማገኘቷን እንጃ…ተከራይ ሆኖ በየወሩ የአከራይን ካዝና
ሇጣርያቸውና ሇግድግዳቸው ቸርነት ሲለ መሙሊትን ያውቁታሌ ታድያ በእሳቸው የሆነውን
በላሊ ሊሇመድገም ሲለ ሇተከራይ የማያሳዩት ቸርነት አሌነበረም የቤት ኪራይን ከመተው
አሌፎም የወር አስቤዛን እስከማካፈሌ…የሌኬሇሽ ግን ሌክ አጣ ሇጣርያውና ሇግድግዳው
ባትከፍሌ መብራቱና ውሃው በነጻ አሌመጣ ታድያ ምን የሚለት ፈሉጥ ነው የሞሊኑሮ እየኖሩ
ወር በደረሰ ቁጥር ሇቤት ኪራይ ማሇቃቀስ…ጎዶል ብሩን ሲቀበለ በኃይሇ ቃሌ
ተናግረዋታሌ…እናም ፈጣሪ ቸርነት አድርጎ ዛሬ አከራይ ቢያደርጋቸው ተከራይ ሊይ እንዱህ
መሆናቸው ፈጣሪን ያስከፋ ድርጊት የፈጸሙ፤ ፈጣሪም በዚህ ተናዶ በተዓምራቱ ከኪራይ ቤት
እንዳወጣ በተአምራቱ ወደኪራይ ቤት እንዳይመሌሳቸው ሰግተዋሌ…የተዓምር ጥሩ እንጂ
እንዴት ክፉ ይኖረዋሌ ግን ፈጣሪስ መሌካሙን እንጂ እንዴት እነዲህ ያሇ ነገር
ያደርጋሌ?...ይሄኔ ነው የአባ ደምሴ ቃሌ ከራሱ ሊይ ጥምጥሙን ጠምጥሞ
የሚመጣባቸው…እግዚአብሄር ድሃን ማበሌጠግ እንደሚያውቅ ሁለ ባሇጠጋን ማደህየትም
እንዲሁ ያውቅበታሌ…ፈጣሪ እንዴት ችግር ይፈጥራሌ ታድያ?...ሃብታሙን ሇማደህየት
የሚያወጣውን ኃይሌ ምናሇ አንዱን ድሃ ኃብታም ቢያደርግበት? እንደው ዝም ብል ኃይለን

ሳሚ ባቲ Page 2
@samibati for telegram users
በረባ ባሌረባው መጨረስ ምን የሚለት ነው?…ሳያስቡት ከፈጣሪ ሙግት መጀመራቸው
እንደክፉ ነጥብ ተቆጥሮ በድህነት እንዳይቀጡ በፍርሃት ይባሱን ሌባቸው ራደ...ሇዚህ
አስተሳሰባቸው ፈጣሪ እመንበሩ ሊይ ሆኖ "ምን ያህሌ ብትጠግቢ ነው ከእኔ የምትሟገች!!!"
ብል ድህነትን ስያሰፍራባቸው ታያቸውና ዘገነናቸው…አሁንስ ቢሆን የትኛው ሃብታቸው
ነው…ቢያንስ ምንም ሳይሰሩ ወር እየቆጠረ ብር የሚያመጣ የኪራይ ቤት አሊቸው….እሱንስ
ማን አየበት ተመስገን ነው ብሇው እንዳያመሰግኑ የሌኬሇሽ ሌክ አሌባ ሇቅሶ እፊታቸው
ይደነቀራሌ…እንባ ገንዘብ ይሆን ይመስሌ መንታ መንታ እንባ የምታወርደው…

"እየጠበቅኩሽ እኮ ነው የማሩን አባባሌ በላሊ እሇውጥሌሻሇሁ ብሇሽ ዝም አሌሽ" ፈገግ ብሇው ያ


የሃሳብ ባሇጠጋ የሆነ መሬት በፈገግታ አዩት…መሬቱ ፈገግታቸው አሞቀው ይሁን የሇጉትን
ሃሳብ ወረወረ…

"ውሃም ሲበዛ ሽንት ይሆናሌ"

"እና ታድያ ውሃ ተጠጥቶ ምን ሉሆን ነው ድሮስ?"

"እህሌም ሲበዛ ያቅራሌ እኮ" መሇወጫውን ሰጡ

"የማያቅረው ስንት ሰው አሇ ሆደ ስሌቻ" ቁጣቸው ገነፈሇ

ምነው ከእኔ በሊይ እውቀት ሇአሳር አሌሽ…ማርም እኮ ሲበዛ…" ሳይጨርሱት ሳቅ


አደናቀፋቸው

"ይሄን እድሜ ኖረን አሌፈንበታሌ ፎንቸር ፎንቸር ኋሊ መዘዙ ብዙ ነው"

"እኔ እኮ አንቺ እነደምታስቢኝ አይነት ሰው አይደሇሁም የሚጎዳኝን እና የሚጠቅመኝን ሇይቼ


የማውቅ ሰው ነኝ"

"የሚጊዳሽን እነደማታውቂማ እያሳየሽኝ አይደሇ"

"ቆይ አንቺ አትተማመኚብኝም ማሇት ነው"

"እንዴት ሌመንሽ እቴ አካሌሽ ከቀን ቀን እንደአበባ ውበቱ እየፈነዳ ይወጣሌ…ወንዱ እንደው


ከአዳም አንስቶ አእምሮ ብሊሽ ሆኖ ነው የተፈጠረው ይሄን አካሌ አይቶ ስሜቱን የትኛው
ወንድ ነው የሚያስታግስ ነገ እኮ ሆድሽን አሳብጠሽ ብትመጪ እኔን ምንም አትጎጂኝ

ሳሚ ባቲ Page 3
@samibati for telegram users
እንዲያውም አያት አድርገሽኝ በጊዜ ወግ ታሳይኛሇሽ ሰው ስሇሚያወራውም ግድ የሇኝ ዲቃሊ
ታቀፈች ይበለኝ እንዲህ መባሌ ብርቄ አይደሇም አንቺንም ስወሌድ እንዲህ ነው የተባሌኩት…"
ንግግራቸውን ሇአፍታ ገታ አደረጉ ዓይናቸው ከአድማስ ባሻገር የሚያይ ይመስሊሌ

"…እኔ የሚያሳስበኝ የአንቺ ህይወት ብቻ ነው፤ ደጀን የሚሆን ባሌ ቢኖርሽ በዛ ሊይ ወንድ ሌጅ


ምንም ከላሇሽ መጫወቻ ነው የሚያደርግሽ ቢያንስ ተምረሽ ከቤት ወጣ ስትይ ነው በቅናት
ከማን ውሊ ይሆን እያሇ ሌቡ የሚሰቀሇው፤ ወንዶች አሊዋቂነታቸውን እንደምታውቅ ሴት
የሚፈሩት ነገር የሇም" ደመቀ እሳቸውን ትቶ የተማረች አገባ መባለን መቼም ቢሆን
ከአእምሯቸው የሚያወጡት ሃሳብ አይደሇም

"ፍርሃትሽ እኮ ይገባኛሌ ግን የእኔና የዴቭ ግንኙነት አንቺ እንደምታስቢው አይደሇም"

"ወንድና ሴት ተገናኝተው አኔ ካሰብኩት ውጭ ምን ያደርጉና ነው?"

"አይደሇማ እኛ ሁለንም ነገር በጊዜው ሇማድረግ ቃሌ ተገባብተናሌ"

"እኮ ቃሊችሁን እንዴት ሌመን እንደጎመን አበባ የሚፈካ ውበትሽን እያየሁ እሱስ ከቃሌ ኪዳኑ
ቢያፈነግጥ ይፈረድበታሌ እንዴ" የጎመን አበባ ደብዛዛ ወበት እንዳሇው ዘንግተው ይሆን
የሌጃቸውን ውበት እንደጎመን አበባ ውበት ማመሳጠር ፈሌገው እንደው እሳቸውም የገባቸው
አይመስሌ

"አንቺ ደግሞ አካበድሽው" ያ ሃሳበኛ መሬት እጁን አውሇብሌቦ እንደጠራቸው ሁለ


አፈጠጡበት፤ አሁንም የሃሳብ ሸማ እየሸመነ ያሇብሳቸው ጀመር…ዳግማዊ ምኒሌክ ትምህርት
ቤት…ቆንጂት ሻይ ሌበሌሻ ቡና ሌበሌሻ…ታስፈራ እንደሁ ብሊ ፊቷን ታኮሳትራሇች…ስትኮሳተሪ
ውበትሽ እንደገኃነም አበባ ይበሌጡን ይደምቃሌ…መኮሳተሯ ስሇታወቀባት ይሆን ሇፈገግታ
ያደሊ ገጽ ትሇቅቃሇች…ያን ፈገግታ ከሃሳብ ባህር ተቀድቶ የእውኑ አሇም ገጻቸው ሊይ ፈሰሰ…

"ምነው ፈገግ አሌሽ?" ፈገግታቸው እንደነውር አስደነገጣቸው ፈገግ ያስባሇኝ ይሄ ነው ብሇው


ቢናገሩት እና ትዝታቸውን በንግግር ነፍስ ቢዘሩበት ምንኛ በወደዱ ግን አይደሇም ትዝታቸውን
ነግረዋት እንዲሁም እሷ አክሇፍሌፏታሌ…

"ቆይ እሺ እሱን ስታውቂው ምን ያህሌ ጊዜሽ ነው" ትዝታቸውን መናገር አስጨንቋቸው


የተናገሩት ነው፤ እንዲያው ይህን ርዕስ ሇማዛወር ምን ብሌ ይሻሌ ይሆን ብሇው

ሳሚ ባቲ Page 4
@samibati for telegram users
"አንቺ ደግሞ አሁን ብነግርሽ ጊዜው ስሊጠረ በደንብ ምንነቱን አታውቂውም ሌትይኝ ነዋ"

"አጭር ጊዜ ነው ማሇት ነው?"

"ቆይ ሇአንቺ አጭር ጊዜ ማሇት ምን ያህሌ ጊዜ ነው?" ደመቀን አራት አመት ነበር ደጅ
ያስጠኑት፤ ታድያ ጊዜ አብሮ ሇመቆየት ጋሻ አያደሇም እንዴ እንዴት ትቷቸው ሄደ?
ምናሌባት ብዙ ስሊስጠበቁት ፍቅሩ ተገቢው ቦታ ሳይደርስ በጊዜ ብዛት አርጅቶ ከጥቅም ውጪ
ሆኖ ይሆን…ፍቅር እና ገንፎ በትኩሱ ይባሌ የሇ¡ ገንፎው ቀዝቅዞ ከሻገተ ኋሊ ይሆን
የደረሱበት!?…ጊዜ ሲረዝም ፍቅር ያጸና ይመስሌ ታድያ ሇምን የጊዜውን ርዝመት መጠየቅ
አስፈሇጋቸው…የግብዝ ጥያቄ እንደጠየቁ ተሰማቸው

"አንቺ መናገሩ ምን አስፈራሽ እኔ የፈሇግሁትን ሌበሌ"

"አይደሇማ"…የማይሰሙ ቃሊቶችን አፏ ውስጥ ተጉሞጠሞጠች አሌተፋችውም


ዋጠቻቸው…ከዴቭ ጋር ፍቅረኛ መሆን ቶምቦሊ እንደመቁረጥ ነው ቶምቦሊ መቁረጥም ብቻ
ሳይሆን በቶምቦሊ መሸሇምም ነው…ቶምቦሊን እሌፍ ቢመኘው እንደማያገኘው ሁለ ዴቭንም
ማግኘት እንዲሁ እድሌ ይጠይቃሌ በስንት ሴቶች ሲፈሇግ አሌገኝ ያሇ ወንድ በራሱ ተነሳስቶ
ፍቅሩን ከተናዘዘ እንዴት ወደኋሊ ይባሊሌ?...

"እማ ወንድ ሌጅ እኮ ሴት ሌጅን ትቶ የሚሄደው ሴት ሌጅ አያያዙን ሳትችሌበት ሲቀር


ነው"...ብሊ ብትናገር እናቷን ወንድ አያያዝ ስሊሌቻሌሽበት ነው አባዬ ትቶሽ የሄድሽው ብል
መሳሇቅ ሆነባት…ዴቭን ከእሷ የሚያቆይ የሆነ ብሌሃት እንዳሊት ግን ይሰማታሌ፤እሱን
ብትናገር የእናቷን ስጋት ታቀሌሌ መስል ታያት ግን እንዴት አድርጋ ትናገረው…ቢናገሩ
ትዕዝብት ባያወሩ አሊዋቂነት! ምን ይሻሊሌ እንደው!…

ሳሚ ባቲ Page 5
@samibati for telegram users

You might also like