You are on page 1of 10

ይዘት

ይዘት ........................................................................................................................................................ 1
ረቂቅ ............................................................................................................................................................. 2
ዋና ማጠቃለያ .............................................................................................................................................. 3
1 መግቢያ ..................................................................................................................................................... 3
1.1 አላማ.................................................................................................................................................. 4
1.1.1 ዋና አላማ ................................................................................................................................. 4
1.1.2 ዝርዝር አላማ ........................................................................................................................... 5
1.2 ወሰን .................................................................................................................................................. 5
1.2.1 በኛ ወሰን ዉስጥ........................................................................................................................ 5
1.2.2 ከኛ ወሰን ዉጭ......................................................................................................................... 5
1.3 ራእይ ............................................................................................................................................... 5
2 የችግሮች መነሻ ሃሳቦች ............................................................................................................................ 6
2.1 ማህበራዊ ሚዲያ............................................................................................................................... 6
2.2 የሳይበር አለም ዘመን (ሳይበር ኤጅ) .............................................................................................. 6
2.3 ሃርድ ፓወር ከሶፍት ፓወር ሲነጣጠር ............................................................................................ 7
2.4 የሳይበር ደህንነት ሙያ ና የሳይበር ደህንነት ባለሞያዎች ............................................................ 7
2.5 አስግዳጅ የሳይበር ህግ ና የሳይበር ቴክኖሎጅ እንቅስቃሴ ............................................................ 7
2.6 c የሳይበር ደህንነት ድርጅት ........................................................................................................... 7
2.7 ድጅታል ሞብላይዜሽን .................................................................................................................... 7
3 መፍትሄ ..................................................................................................................................................... 8
መፍትሄ አንድ .......................................................................................................................................... 8
መፍትሄ ሁለት.......................................................................................................................................... 8
መፍትህ ሶስት ማህበራዊ ሚዲያ ማሰተዳደር ......................................................................................... 8
መፍትሄ አራት ማህበራዊ ሚዲያ መለየት......................................................................................... 9
መፍትሄ አምስት የፀጥታ ሃይሉን በቴክኖሎጅ ማጠናከር .................................................................. 9
3.1.3 ባህላዊ የደህንነት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን መጠቀም................................................................. 9

1|Page
ረቂቅ

መረጃ በአለም ላይ በተለይም በሳይበር ዘመን በጣም ውድ ንግድ ነው። መረጃ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን

ለማድረግ የመጀመሪያው አስፈላጊ ነገር ነዉ። ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማህበራዊ እንቅስቃሴ ባህላዊ

እንቅስቃሴ የግል እንቅስቃሴ ና ሌሎች ሊሆን ይችላል።ይህንን ወርቃማ ሃብት ለመጠበቅ ጠንካራ

የመረጃ አያያዝ መገንባት ዘዴ አለበት። የድጅታል ዘመኑ ትውልድ ለወርቃማው ሃብት ማለትም የጥሪ

መረጃ ትልቅ ሚና መጫወት ይኖርበታል። ማንኛውም ሰው መረጃውን ወይም ዳታን በሚስጥር ለመያዝ

ሶስቱን መስፈርቶች መከተል አለበት። እነሱም ሚስጥራዊነት ታማኝነት አቬሌቢሊቲ (CIA) ናቸው።

የመረጃ ደህንነት (CIA) ምስጢራዊነት፡ ያልተፈቀደ አጠቃቀምን ወይም መረጃን ይፋ ማድረግን

መከላከል። ታማኝነት፡ የመረጃን ትክክለኛነት እና ሙሉነት ይጠብቃል። አቬሌቢሊቲ የተፈቀደላቸው

ተጠቃሚዎች አስተማማኝ እና ወቅታዊ የመረጃ መዳረሻ አላቸው።

2|Page
ዋና ማጠቃለያ

መረጃ በሁሉም ዘርፍ የዘመኑ ወርቃማው ንግድ ነው። የቀን የሳይበር ወይም የድጅታል መረጃ ወርቃማ

ሃብት ምንጭ ና የፖለቲካል የድጅታል ድፕሎማሳዊ መፈጠሪያዉ ዋናዉ መንገድ ነዉ። ነገር ግን

የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ መሆን ካልቻለ አደጋዉም በዛዉ ልክ መጠነ ሰፊ ነዉ። ወደ ዝርዝር

የፕሮፖዛል አካል ከመሄዳችን በፊት፣ የሳይበር ደህንነት አጠባበቅ አስፈላጊነት በተመለከተ የጋራ ፍላጎት

ና አለማ ሊኖረን ይገባል። ይህ ወቅት የሳይበር ወይም የድጅታል ዘመን ሲሆን ብዙ ተጽእኖዎች

አሉት፣ ተጽኖው አወንታዊ ወይም አሉታዊ ሊሆን ይችላል። ባለፉት ሶስት ና አራት አመታት

የኢትዮጵያ የፖለቲካ የማህበራዊ ኢኮኖማዊ ና ድፕሎማሳዊ መከራከሪያ መድረክ ሳይበር ላይ ነበር

ይህም በጠረቤዛ ዙሪያ ከተደረጉ ክርክሮች ና ዉይይቶች በላይ ለውጦችን አምጥቶል። ሳይበሩ በፈጠረዉ

ትጽኖ ብዙ የጠረቤዛ ዙሪያ ዉሳኔዎች ተቀይረዋል። ስለዚህ ቀጣይ በድጅታል አለም የሚመጡ ለውጦች

ና የተለመዱ እንቅስቃሴዎች እንደ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ድፕሎማሳዊ ና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን

ሳይበር ላይ ለመቆጣጠር አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት በመገንባት የሳይበር ንግድ የጋራ ጥቅም

ልናስከብር ይገባል።

1 መግቢያ

ከቅረብ ጊዜ ወዲህ የቴክኖሎጂ እድገት የዓለምን ፖለቲካዊ, ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ና ድፕሎማሳዊ

እንቅስቃሴን በእጅጉ ለውጦታል። ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጂ እድገት ብዙ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ

ውጤቶች ሊያመጣ ይችላል። ስለሆነም ጥሩ ግንዛቤ እና ቀጣይነት ያለው ራስን የማጎልበት እንቅስቃሴ

ሊኖረውን ይገባል። በአለም አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ ጥናት እንደሚያሳየው በቴክኖሎጂ የሚከሰቱ

ችግሮች በተለይም በሳይበር ላይ የሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ አልባ ናቸዉ። በተለይ ጥናቱ

እንደሚያሳየዉ ያልተፈታ የቴክኖሎጂ ችግር በአፍሪካ 96% ገዳማ ሲሆን ከ96% በላይ የአፍሪካ

ድርጅቶች ከሚፈለገው የሳይበር ወይም የቴክኖሎጂ ምርት ከደረጃ በታች መስራታቸዉን ያረጋግጣል።

3|Page
በአገራችን አብዛኛው ህብረተሰብ በቀጥታም ይሁን በተዘዋሪ ከሳይበር አለም ጋር ቁርኝነት አለዉ።ከዚህ

በተጨማሪም፣ ንግድን፣ ባህልን ና መረጃን በዋናነት ሳይበር ምህዳሩን በመጠቀም ይለዋወጣሉ። በዚህ

ወቅት የሳይበር ጥቃት በህብረተሰቡ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጉዳት ያደርሳል። ለምሳሌ ሰዎችን

ከአካባቢው እንዲፈናቀሉ የሚያደርጋቸው በጣም አደገኛው የተሳሳተ የሳይበር መረጃ (የሃሰት

ፕሮፖጋንዳ) በመጠቀም ነዉ። ይህን ድሪጊት በቀጥታ ለመቆጣጠር ከባድ ነዉ ምክንያቱም ቨርቹዋል

አለም ዉስጥ ነው ድርጊቱ የሚካሄደዉ ይህ ማለት ውጤቱን እናየዋለን ነገርግን ድርጊቱ አድራጊ በቀላሉ

ማግኘት አንችልም። ሆኖም ግን ሁሉም የሳይበር መረጃዎች የተሳሳቱ ወይም አደገኛ ናቸው ማለት

የለብንም።

ሳይበር ኮምፒውተሮች በስፋት ጥቅም ላይ በመዋላቸዉ ሊገኙ የሚችሉ አዳዲስ ነገሮችን ለመግለጽ

በምንገለግልባቸዉ ቃላት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ቅድመ ቅጥያ ነው። ለምን ሳይበር ተባለ? ይህ

ስያሜ የተሰየመዉ በ1940ዎቹ ኖርበርት ዊነር በተባለ የሂሳብ ሊቅ የተስፋፋው “ሳይበርኔቲክስ”

በሚለው ግልጽ ያልሆነ ቃል አማካኝነት ነው። ሳይበርኔቲክስ በተሰኘው መጽሃፉ ዊነር ከመንግስት ወይም

ከአስተዳደር አካላት ጋር የተያያዘውን “ሳይበር” የሚል ጥንታዊ የግሪክ ቃል ሰይሞታል።

የሳይበር ደህንነት ቴክኒክ ና የተግባር ዲዛይን መረጃን ለመጠበቅ በዲጂታል መረጃ ላይ የሚተገበር

ሲሆን ይህም በተከማቸ በሚቀሳቀስ ና አገልግሎት እየሰጠ ባለ መረጃ ላይ የሚተገበር ይሆናል። የሳይበር

ደህንነት የመረጃ ደህንነት ና የስርዓት ደህንነት ማረጋገጫ መስፈርት ነዉ።መረጃን መጠበቅ ማለት

መረጃን ና የስራት ተደራሽነትን ሚስጥራዊ ማድረግ (ካልተፈቀደ አካል መከላከል) ና ( ካልተፈቀደ

ማሻሻያ መከላከል) ማለት ነዉ።

1.1 አላማ

1.1.1 ዋና አላማ

. የፕሮፖዛሉ ዋና አላማ በሳይበሩ ላይ የሚሰራ ምናባዊ የሳይበር ሃይል በመፍጠር ማንኛውንም የሳይበር

ጥቃት መከላከል መቻል ና የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ ባህላዊ ማህበራዊ ና ድፕሎማሳዊ እንቅስቃሴን

መደገፍ መቻል ነው።ንቅናቄው በሳይበር አካባቢ ላይ ትኩረት ለሚሰጠው ማህበራዊ ሚዲያ ያካትታል።

4|Page
1.1.2 ዝርዝር አላማ

o ተለዋዋጭ የሆነ የሳይበር ጥቃት መከላከያ ዘዴ መገንባት


o ቨርችዋል ግንኙነት በፍጠር የፖለቲካ ና የኢኮኖሚ መሪዎችን መደገፍ
o የሳይበር መነቃቃት በመፍጠር ወደ አንድነት መምጣት
o ሳይበር ባለሞያዎችን በመሰብሰብ ለፈጠራ ማነሳሳት
o የረጅሜ ጊዜ የሳይበር ጥቃት መከላከያ መፍትሄ ድዛይን ፕላትፎርም መዘርጋት
o በጠላት የሚመራ ልዩ ና ስልታዊ የሳይበር ጥቃት መከላከል

o የሳይበር አለምን በመጠቀም ማህበረሰባዊ ስነ ልቦና የሚያነጣጥሩ ስትራቴጂካዊ ጥቃቶችን

መከላከል

o የጋራ የሳይበር ፕላትፎርም በመፍጠር የፖለቲካ ና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚደግፍ ድምፅ

መሰሰብ
o በሂደት አዲስ የሳይበር ደህንነት ፕላትፎርም በመዘርጋት ማህበረሰቡን ከማንኛዉም ፖለቲካል
ኢኮኖሚካል ና ካልቸራል የሳይበር ጥቃት መጠበቅ

1.2 ወሰን

1.2.1 በኛ ወሰን ዉስጥ


• የሳይበር ድምፅ መሰብሰብ(የሳይበር ሃይል)
• በሳይበር የሚሰሩ ስራዎችን ማነቃቃት
• ሳይበር ታለንት መሰብሰብ

• ቅድሚያ የሚሰጠውን የሳይበር ደህንነት ስራ ማደራጀት ና መምራት (ለአሁኑ የሳይበር ጥቃት

ስጋቶች ትኩረት መስጠት)


• የቀጣይ የሳይበር ደህንነት የስራ እንቅስቃሴዎችን ማደራጀት
• አጥፊ የሳይበር ቫይረሶችን መለየት ና መፍትሄ መስጠት
• አዳዲስ የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን በመለየት ለሚመለከተዉ አካል ማስገንዘብ(ታርጌት ጉሩብ)
• የሳይበር ደህንነት ትንተና መስራት
• የሳይበር ደህንነት ሪሰርች መስራት

1.2.2 ከኛ ወሰን ዉጭ
• ቢሮ
• ኢንትርኔት አገልግሎት
• የስራ ማሰኬጃ በጀት(ፋይናስ)
• የደህንነት ድጋፍ(ጋረንት)

1.3 ራእይ
በአማራ ክልል ዉስጥ ባንድ ና በሁለት አመታት ዉስጥ ጠንካራ የሆነ ድጅታል ወታደር መፍጠር ነዉ

5|Page
2 የችግሮች መነሻ ሃሳቦች
2.1 ማህበራዊ ሚዲያ

. ማህበራዊ ሚዲያ በሳይበር ወይም በድጅታል ዘመን ዋነኛው የሳይበር ማጥቂያ መሳሪያ ነው። ባለፉት

አመታት "ማህበረሰባችን" በተለያዩ የጦር መሳሪያዎች አካላዊ ጥቃት ሲደርስበት ቆይቶል።በአሁኑ

ሰኣት ከኣካላዊ ጥቃት በተጨማሪ በሳይበር የማጥቃት ዘዴ በመጠቀም ስነ ልቦናዊ ጥቃት በህዝባችን

ተደቅኖበታል። በዋናነት አጥቂው አካል የሳይበር ምህዳሩን በመጠቀም የህብረተሰቡን ሞራል ና ማንነት

ላይ ያነጣጠረ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። ለማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ከሚውሉት መተግበሪዎች

መካከል ፌስቡ ቴሌግራም ትዊተር ና ሌሎችም ይገኙበታል። የማህበራዊ ሚዲያ አጥቂዎች

የሚከተሉትን ቴክኒኮች ይጠቀማሉ።

o የፌስቡክ የሳይበር ጥቃት


o ዋና ዋና መረጃ ምጮችን ማጥቃት
o ዋና ዋና የመረጃ ምጮችን ታማኝነት ማሳጣት
o ኮሚኒቲ ቫይረስ ማህበረሰቡ ላይ መለቀቅ
o በማህብራዊ ሚዲያ ላይ ዉጥረት መፍጠር
o ስሜታዊ የንግግር ቃላት መጠቀም(ታርጌትድ ጉርፕ ላይ)
o የጥላቻ ንግግር ማጋራት ና መለዋወጥ
o በሳይበር ማህብርሰቡ ጋር ተመሳስሎ ማጥቃት

2.2 የሳይበር አለም ዘመን (ሳይበር ኤጅ)

በየጊዜዉ አዳዲስ ቴክኖጂ ብቅ ማለት የዓለምን የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ማህበራዊ ስትራቴጂ የፖለቲካ

ስትራቴጂ ና የድፕሎማሳዊ ስትራቴጅ በእጅጉ ለዉጦታል። በሳይበር ወይም በድጅታል ዘመን ላይ

መሆናችን ባግባቡ ተረድተን ለዘመኑ ቴክኖሎጂ የሚመጥን ዝግጅት ያስፈልገናል። አንዳንዶቹ የሳይበር

አዲስ ስትራቴጂ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል።

o ሳይበር ፖለቲክስ
o ሳይበር ኢኮኖሚ
o ሳይበር አርሚ
o ሳይበር ጥቃት
o የሳይበር መከላከል
o ሳይበር ቅንጅት
o ሳይበር ድፕሎማሲ

6|Page
o ሳይበር ቢዝነስ

2.3 ሃርድ ፓወር ከሶፍት ፓወር ሲነጣጠር

ሁለቱ ዓይነት የደህንነት ዘዴዎች ለአንድ ድርጅት የጀርባ አጥንት ናቸው. አካላዊ የፀጥታ ዘርፍ

በአብዛኛዉ በአብዛኛው የለመደው የደህንነት ዘዴ ሲሆን ባህላዊ የጸጥታ ዘዴ በመባል ይታወቃል።

በንፅፅር ቨርቹዋል ሴኪዩሪቲ (ሳይበር ሴኪዩሪቲ) ብዙ ያልተለመደ ቢሆንም በዚ የድጅታል ዘመን ግን

ለሁሉም የፀጥታ ዘርፍ የጀርባ አጥንት ነዉ።ስለዚህ አሁን ያለው የሳይበር ደህንነት ና የወደፊት የሳይበር

ትንተና ትልቅ አጀንዳ መሆን አለበት።

2.4 የሳይበር ደህንነት ሙያ ና የሳይበር ደህንነት ባለሞያዎች

ባሁኑ ሰኣት በአፍሪካ ከዘጠና ስድስት በላይ (>96) ድርጅቶች ከሳይበር ደህንነት መስፈርቶች በታች

ና ሳይበር ደህንነት ሙያ በሌላቸዉ ሰራተኞች ያሰራሉ። ምክንያቱም በአፍሪካ የሳይበር ደህንነት ሙያ

እና የሳይበር ደህንነት ባለሙያ ላይ ትኩረት አልተሰጣቸውም። በዚህ የድጀታል ዘመን የሳይበር ደህንነት

ባለሙያዎችን መሰብሰብ ና የሳይበር ደህንነት ሙያ ስኬቶችን ማጠናከር ግዴታ ነው።

2.5 አስግዳጅ የሳይበር ህግ ና የሳይበር ቴክኖሎጅ እንቅስቃሴ


➢ በሁሉም ሁኔታ ጥገኛ ነን
o የፖለቲካ የሳይበር ጥገኝንት
o የኢኮኖሚ የሳይበር ጥገኝነት
o የወታደራዊ ሃይል የሳይበር ጥገኝነት
o የማህበራዊ ሳይበር ጥገኝነት
o ግለሰባዊ ሳይበር ጥገኝነት

2.6 የሳይበር ደህንነት ድርጅት

• አዲስ የቨርቹዋል ንዑስ አደረጃጀት መፍጠር

• ፕሮፌሽናል መሪ መፍጠር

• መርጃ ማምረት ና መጠቀም

• ታማኝነት መፍጠር

2.7 ድጅታል ሞብላይዜሽን


o ፖለቲካዉን ላማጠንከር ድጅታል ፖለቲካል ንቅናቄ መፍጠር

7|Page
o ድጅታል ማህበራዊ ንቅናቄ መፍጠር
o ድጅታል ኢኮኖማዊ ንቅናቄ መፍጠር
o ኣዳዲስ ድጅታል ፕላትፎረሞችን ቶሎ መቀበል
o ድጅታል ፕላትፎርም ተጠቅመን የጥላቻ ንግግሮችን ማስወገድ
o ድጅታል ድምፆችን ማነቃቃት
o ድጅታል ቢዝነስን ማነቃቃት

3 መፍትሄ
መፍትሄ አንድ
o በዚህ ጦረነት አማራ ላይ የተደቀነዉን ደጅታል ስጋት መከለስ ና መተንተን(ድጅታል ወያኔ)
o አሁን ላይ ድጅታል መድረኩ ላይ ያለዉን የፖለቲካ ና የማህበራዊ እቅስቃሴ አሰላለፍ መከለስ
o አጫጭር ጥናቶችን በማከሄድ በፖለቲካዉ ና በማህበራዊ እንቅስቃሴዉ ላይ ሳይበሩ የፈጠረዉን
ተፅኖ መተንተን
o ሳይበሩ ምህዳሩ ላይ ጥናቶችን በመለት የመፈትሄ ሃሳቦችን ማስቀመጥ
o የተለዩ እዉቀቶችን ና ታለቶችን በመጠቀም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ባግባቡ በኮማድ ስር
በማስተዳደር በዘርፍ የሚቃጣዉን የሳይበር ጥቃት መከላከል(ለምሳሌ በቅርቡ አመራሮች ላይ
እየደረሰ ያለዉን ሚዲያ ዘመቻ ማየት በቂ ነዉ)
o ፖዘቲቭ ሃሳብ ያላችውን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ባንድ ኮማንድ ስር ማስተዳደር
o ለፖዘቲቭ አለማ ማህበራዊ ሚዲያ አካዉንት በመከፍት ተከታይ ማፍራት
o ማህበራዊ ሚዲያን በማዳረጃት የመረጃ አጣሪ ቡድን መስርት
o ተማኝ መረጃዎችን በመልቀቅ በቡድኑ ላይ እምነት መጣል
o በመጨረሻም በሳይበሩ የሚመጡ ማንኛዉም ጥቃት መከላከል

መፍትሄ ሁለት
o የድጅትል ዘርፉን የሚመራ ምቹ ድርጅት መገንባት
o አለም ላይ ያሉ በዘርፉ ፕሮፌሽናል የሆኑ የራሳችን ሰዎችን ቨርችዋሊ መሰብሰብ
o የጋራ የሆነ የሳይበር ደህንነት ዲዛይን ፕላትፎርም መዘርጋት
o የሳይበር ደህንነት ፕላት ፎርም ተግባራዊ ማድረግ
o ፕሮፌሽናሎች የሳይበር ደህንነት ንቅናቄ ማስጀመር
o ህጋዊ የሳይበር ሃይል መዋቅር መዘርጋት

መፍትህ ሶስት ማህበራዊ ሚዲያ ማሰተዳደር

ማህበራዊ ሚዲያን ማስተዳደር ማለት ማህበራዊ ሚዲያን በሃላፊነት የመጠቀም ና መጥፎ መረጃ

በምህዳሩ ሲለዋወጥ የማረም እንቅስቃሴ ማስኬድ ማለት ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ለሰው ልጅ አስፈላጊ

ከሆኑ ቴክኖሎጂዎች አንዱ ነው ።ህብረተሰቡ ጉልበቱን ጊዜውን ኢኮኖሚውን በመቀነስ ና የኑሮ

ፈተናን ለማቃለል ይረዳዋል።በተጨማሪም ማህበራዊ ሚዲያ በትንሿ መንደር ውስጥ ዓለማትን

የመሰብሰብ ና ሃሳቦችን የመለዋወጥ ሃይል ጠቀሜታ አለዉ። በሌላ በኩል ማህበራዊ ሚዲያውን በአግባቡ

8|Page
ማስተዳደር ካልቻልን ብዙ የጎንዮሸ ጉዳቶች አሉት። ባጭሩ የማህበራዊ ሚዲያ ጥቅምም ጉዳትም

አለው ነገርግን ጥሩ የማህበራዊ ሚዲያ የአስተዳደር ቴክኒኮችን ከተከታተልን ጉዳቱን አስወግደን

ጥቅሙን ልንጠቀምበት እንችላለን እሱን ለማስተዳደር ከዚህ በታች ያሉትን የአሰራር ዘዴዎች መጠቀም

እንችላለን።

መፍትሄ አራት ማህበራዊ ሚዲያ መለየት

የማህበራዊ ሚዲያን ችግር ለመቆጣጠር ወይም ለመቆጣጠር የመጀመሪያው እርምጃ እያንዳንዱን

የማህበራዊ ሚዲያ አይነት በአጭሩ መለየት እና መግለጽ ነው። በአለም ላይ ብዙ አይነት የማህበራዊ

ሚዲያ አለ ነገርግን በአገራችን እይታ መዘርዘር እንችላለን። እነዚህም

✓ ፌስቡክ
✓ ቴሌግራም
✓ ቲዉተር
✓ ዋትሰአፕ
✓ ኢኔስታግራም
✓ ዩቱብ
✓ ዊቻት
✓ ሊከድን

መፍትሄ አምስት የፀጥታ ሃይሉን በቴክኖሎጅ ማጠናከር


➢ ጀኦ ኢንትለጀንስ
➢ ሲግናል ኢንትለጀንስ
➢ ሳይበር ኢንፍራ ስትራክቸር
➢ ኤሌክትሮኒክ ዋር ፌር
➢ ኢቲካል ሃኪንግ
➢ ዲጅታል ፍሮሲክ

3.1.3 ባህላዊ የደህንነት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን መጠቀም


ባለፈዉ ዘመን አባቶቻችን የእንሰሳት ና አእወፍ ደምፅ በመተርጎም ና በመለየት የጌዜዉን ሁኔታ
በመረዳት ቅድመ ዝግጅት በማካሄድ ሁሉንም አቀፍ ፈተናዎች ተጋፍጠዉ አሸንፈዉ አልፈዋል። ከዚህ
በተጨማሪ ምጡቅ አምሮ ያላቸዉ አባቶቻችን የፀሃይን የጨረቃን የክዋክብት ና የንፈስ አቅጣጫ ና
ባህሪን በመረዳት ና በመተንተን በወቅቱ ሊደርስ ይችል የነበረዉን ስጋት ሁሉ መክትዉ አልፍዋል።
ይሁን እንጅ በዚህ ወቅትም ባሃላዊ የደህንነት ምስጠራ ዘዴዎችን ፈጠራ ታክሎበት በንጠቀምበት የተሻለ
ዉጤት ማግኘት ይቻላል።

9|Page
10 | P a g e

You might also like