Professional Documents
Culture Documents
የዜግነት ጥሪ ለመንግሥት
የዜግነት ጥሪ ለመንግሥት
ተጻፈ ከፋንታሁን ዋቄ
ጳጉሜን ፭ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም.
ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን
የአገራችን የፖለቲካ ልሂቃን ሆይ! አንደ አንድ የጨነቀው ምሰኪን ዜጋ ምክረ-ሀሳብ ነውና
ለመስማት ሞክሩ፤ በለውጥ ስም የከፈታችሁትን የሲዖል በር ለመዝጋት ፈቃደኛ ከሆናችሁ ይህን ድምጽ
ስምታችሁ ለእናንተም መሪዎች እና ለእኛም ለተመሪዎች ከጥፋት እንድንተርፍ ” ለውጡን ለውጡት”።
ከዚህ ጽሑፍ የበለጠ ጮኾ የሚናገረው እየፈሰሰ ያለው የንጹሐን ደም፣ በቁማቸው በመከራ ውስጥ
እንዲገቡ የተደረጉ ዜጎች ዕንባ፣ አገር ውስጥ ተፈብርኮ እንዳይጠናቀቅ ተደርጎ የሚካሄደው የአገር ውስጥ ጦርነት
“ለውጡን ለውጡ” እያላችሁ ነው! ጽሑፉ ምናልባት ጩኸቱን በመየጠኑ ለማጉላት ይጠቅም ይሆናል።
በእኔ አረዳድ አገራችን አሁን የምትገኝበት አውድ፡- መንግሥት በሕዝቡ ዘንድ ሙሉ በሙሉ እንደ
መንግሥት ተአማኒነት አጥቷል። መንግሥት የጥቂት ልሂቃን ጠባብ ቡድን እንጂ የዜጎች አይደለም የሚል ዜጋ
አብላጫ ቁጥር አለው። መንግሥት በተወሰነ የብሔር ንዑስ ማንነት መሣሪያነት የሚያገለግል ብቻ ሳይሆን
በብሔረሰብ ሽፋን ጥቂት ልሂቃንና በሠልጣን ዙሪያ የተኮለኮለው ሙሰኛና የቁሳዊነት ሰቀቀን ሕሊናውን
የጋረዳቸው ቡድኖች አገልጋይ ሆኗል። በብሔር ፖለቲካ ሥር ራሳቸውን የሰወሩ በተለያዩ ቁሳዊና እምነታዊ ቡድን
የተደራጁ አካላት መንግሥትን እጅ አድርገው ብዙኃኑን ለመከራና ለስቃይ ዳርገዋል። አገሪቱ እነዚህ ቡድኖች
እንወክለዋልን በሚሉአቸው ክፍለ-ሕዝቦች እየማሉ በተቃራኒው ግን ከሕዝቡ ባህል፣ እምነት፣ እሴትና ዘለቄታዊ
የትውልድ ፍላጎት ውጭ ራሳቸውን ባደራጁ ጥቂት ራስወዳድ ልሂቃን ምናብ የተፀነሰችን ልዩ አገር ወይንም አካባቢ
ለመፍጠር በሚሠሩ ልሂቃን የተወጠረች አገር ሆናለች። የፖለቲካ ተቋማት ጠቃሚ ሀሳብ ከማመንጨት ያረጡ
የመከራ ምንጮች በመሆን የሚመሩትን ሕዝብ በቡድን መንጋነት አሥረው ወደባርነት የሚያግዙ መሣሪያዎች
አድርገዋዋል።
መንግሥት የተባለውን ተቋም የመመሥረቱ ቀዳሚ ዋና ዓለማ የእያንዳንዱን ዜጋ የመኖር ዋስትና ማረጋገጥ
ነበር፤ አሁን ያለው መንግሥት ግን በብሔር ንዑስ ማንነት መሠረት ላይ የቆመ መሆኑ ሰውን በሰውነቱ ለመቀበል
ፈተና ገጥሞታል። ትኩረቱ ለሥልጣን ዘለቄታዊነት አንዲያገለግለው ልዩነትን በቦታ፣ በቋንቋ፣ በባህል፣
ይህን አሳዘኝ የመከራ አውድየፈጠረው ርእዮት፣ አሠራርና መዋቅር በፍጥነትና በቁርጠኝነት ካልተቀየር
መንግሥትንም አገርንም ያጠፋዋል የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ። በአንድ አገር ሕዝብ መካከል ወገን የሆነ እና
ጠላት የሆነ በማለት ትርክትን የሚያራግበው ቡድንን እንጂ ሰውን የማያውቀው የለውጥ አቅጣጫ ቀጥሏል።
እኛም ተራው ዜጎች ኃጢአታችን በዝቶና በንስሐ ከመመለስ እጅግ ዘግይተን በመኖራችን ውጤቱ ከደርግ ወደ
ወያኔ ከዚያም ወደ ብልጽግና ዘረኛ የባሰ የእብደትና ውጥንቅጥ አጥፊ ፖለቲካ መሻጋገር ሆነብን። አሁንም
እንደሚገባ ንስሓ ገብትንና እርስበርሳችን ተፈቃቅረን ከሰውነት አስወጥተው በዘረኛ የቡድን ፖለቲካቸው
እየከፋፈላችሁ የምታጠፋፉንን ስላላስቆናችሁ መከራችን ቀጥሏል። ወደፊትም ከዚህ ፖለቲካ ካልወጣን ይቀጥላል።
የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓለማ እኛ እንደ ሕዝብ ንስሐ እንድንገባ እናንተ ለሂቃን እንደ ፖለቲካ ነዳፊዎችና መሪዎች
ከክፋታችሁ እንድትመለሱ፣ ሁላችንም አብረን ራሳችንን በራሳችን ከማጥፋት እንድንድን ማሳሰብ ነው።
እናንተ መሪዎች ሰማችሁም አልሰማችሁ እኛ ተመሪዎች አሁን ያለን አማራጭ እናንተንም መምከር እኛም
አንደ ሕዝብ ወደ ልቦናችን ተመለሰን ከቡድን እብደት ወደ ሰውነት ለመመለስ መመካከርና በተግባር መለወጥ
ነው። በሁለተኛ ደረጃ በሥልጣን ላይ የምትገኙና በፖለቲካ ተፎካካተሪነት ያላችሁ የወደፊት የአገር መሪዎች ምን
ያህል ተፈጥሮአዊ ያልሆነ፣ ከውጭም ያልመጣብን ችግር ፈጥራችሁ እንደምታሰቃዩን መለስ ብላችሁ
እንድትመለከቱ፤ በሶስተኛ ደረጃ ምን ብታደርጉ ከዚህ አጣብቂኝ ይዛችሁን ልትወጡ እንደምትችሉ የዜግነት
እይታን በማጋራት ከሕሊና ጫና እረፍት ለማግኘት ነው።
ለመልካም ለውጥ መጣን ብላችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከእናንተ አስቀድሞ የነበሩ የፖለቲካ ሥርዓታት በጣሉብን
ክፋት ላይ ጨምራችሁ፣ ክፋትን እንደ ልሕቀትና አዋቂነት በምትሠሩት ማስተዋል የጎደለው የቁማር ፖለቲካ
ለሕዝቡ ያፈራው ነገር፡- ጥርጣሬ፣ ስደት፣ መፈናቀል፣ ሞት፣ ሕገወጥነት እና ተስፋቢሰነት ነው። አሁን በኢኮኖሚ
ሥርዓት፣ በፍትሕ ሥርዓት፣ በማኅበራዊ መስተጋብር፣ በሕዝብ አሠፋፈር፣ በመንግሥት መዋቅር አድሎአዊነት
ወዘተ በምታደርጉት ተግባር ለውጡ ከአዎንታዊነት ወደ ባሰ ጥፋት የሚወስድ መሆኑን አስመስክራችኃል። ያንኑ
የቀደመ ሥረዓት ጥፉ ርእዮት አባብሳችሁና አክፍታችሁ ቀጠላችሁበታል። ይህን የሲኦል መንገድና በሩን
መልሳችሁ ለመዝጋት እድል የምታገኙበትን እና የንስሐ እድል አግኝታችሁ መከራ ውስጥ ከከተታችሁት ሕዝብ
ጋር በአንድነት እንድትድኑ በገባኝ መጠን መውጫውን ልጠቁማችሁ።
ለሀገር ሰላምና አንድነት ሊያመጣ የሚችለው ይህን መንገድ መጠጋገንና ማሽሞንሞን ሳይሆን ሙሉ በሙሉ
መቀልበስ ብቻ ነው። ጥቆማው ተቀባይነት አግኝቶ እንደገመትኩት እናንተም እኛም ከተረፍን ደስተኞች እንሆናል።
ለውጥ ብላችሁ ስትነሱ መሪ ያደረጋችሁት ጥፋቱን ባስከተለው የማንነት ፖለቲካ ልሂቅነት አንቱ የተባሉ
ዘረኞችን ወደ ሥልጣን በማምጣትና አገራዊያን አዋቂዎችንና እሴቶቻቸውን፣ ሃይማኖታቸውንና እውቀቶቻቸውን
ሁሉ በጠላትነት በመፈረጅ ነበር። ስለዚህ ለእናንተ ለልሂቃኑ ከጀመራችሁት መንግድ የተለየ ሌላ የለውጥ
ምክር-ሀሳብ ማቅረብ የዋሕነት ሊመስላችሁ አንደሚችል እገምታለሁ። ቢሆንም በዝምታ ከማለፍ
ተናግሮ በደባባይ ምላሻችሁን መጠበቅ ይሻላል በሚል ይህችን አጭር መልዕክተ ልኬላችኋለሁ። ሀሳቤብ
ዋጋ ትሰጡት ይሆናል ብዬ እንዳስብ የሚደርገኝ አሁን የያዛችሁት መንገድ ሞት፣ ስደት፣ ጥርጣሬ፣ ጥላቻ፣
ሌብነት፣ ክፋት፣ ሐሰተኝነት፣ ጦርነት ብቻ በመሆኑ የምታጎርፉት የፕሮፓጋንዳ ወንዝ፣ በየጊዜው የምትሞክሩት
ብልጣብልጥ የልማትና የእምርታ ምስል ሊሸፍነው አለመቻሉ ፈጥጦ እንደወጣ መገንዘብ የጀመራችሁ
ስለሚመስለኝ ነው። በእኔ አምነት ከበለጠ ጥፋት ለመትረፍ ያለችንና የቀረችዋ አንዲት አማራጭ
“ለውጣችሁን መለወጥ” ብቻ ነው። ጭፍን አልኸኝነት፣ አማራጭ ሀሳብን በመቃወም ወደ ኃይልና ማሳደድ
መግፋት፣ ሀሳብን ከማሻሻል ይለቅ የብልጽግና መንገዱ “እነርሱ” የተባሉ ክፍሎችን ማሸነፍ፣ ማጥፋትና የበላይ
መሆን፤ በሐሰተኝነትና በእውነት መካከል ያለውን ድንብር ማደበዝዝና ማጥፋት፤ የቁማርተኝነት እንደማያወጣ
እየተካሄደ ያለው ጦርነት፣ የሰው መፈናቀልና እልቂት፣ በሁሉም ቦታ የሚካሄደው ሰቆቃ የሚጠቁማችሁ
ይመስለኛል።
1. መንግሥት ከሁሉ አስቀድሞ በዘውግ ፖለቲካና በፕሮፓጋንዳ ያልተበከሉትን የባህልና የእምነት መሪዎች፣
የአገር በቀል እውቀት ባለቤቶች፤ ከዘርኝነት፣ ባሳለፍናቸው የ50 ዓመታት ተከታታይ ፈተናዎች ሁሉ
ከሙስናና ከጽንፈኝነት ነፃ መሆናቸው የሚመሰከርላቸው፣ ከሙስና የጸዱ ኃይለ-ግብራት አማካሪዎችን
እግዚአብሔር በደላችንን ይቅር ብሎን ዘመነ ሉቃስ (2015 ዓ.ም.) የመደማመጥ፣ የእውነተኝነት፣
የፍትሐዊነት፣ የሰላም፣ የአንድነት ይሁንልን። ይህ እንዲሆን እኛም ተመሪዎች ተለውጠን፣ እናንተም መሪዎች
“ለውጣችሁን ለውጣችሁ” በቡድን ያይደለ በሰውነት ደረጃ ለመኖር ያብቃን!