You are on page 1of 3

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ክፍሎችና የያንዳንዳቸዉ ዝርዝር ቋንቋ ዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩ እና የሚጻፉ ቋንቋዎችን እና የምልክት ቋንቋን ያጠቃልላል።


በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ 80 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት፡፡
በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ
ነዋሪዎች የመማሪያ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የፌዴራል መንግስቱ የሥራ ቋንቋ ሆኖ
የሚያገለግል ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና ትላልቅ የቋንቋ ክፍሎች
ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች ሲኖሩ
ናይሎ-ሳህራዊ ዉስጥ ደግሞ በሌላኛዉ ምድብ የቋንቋ ቤተሰብ ዉስጥ ይካተታል፡፡
ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች ወደ አራት ዋና ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። እነዚሁም
1. ኩሻዊ፦ ወደ 19 ቋንቋዎችን የያዘ
2. የአባይ-ሰሃራዊ፦ ወደ 20 ቋንቋዎችን የያዘ
3. ኦሞአዊ፦ ወደ 23 ቋንቋዎችን የያዘ እና
4. ሴማዊ፦ ወደ 12 ቋንቋዎች የያዘ ናቸው።
ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ
ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ፣ ኩናማኛ፣ ጉሙዝኛ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው።
እንደ ወላይትኛ፣ ጋሞኛ፣ ከፋኛ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ
አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ስልጢኛ፣ ሀደሪኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ።
የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ ትግርኛ ና አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን
ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት
ከቤተክርስትያን ውጭ ለዕለት ተዕለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።
በዝርዝር ስንመለከታቸዉ
1. አፍሮ እስያዊ ቋንቋዎች
1.1. ሴማዊ
1.1.1. ሰሜን
 ትግርኛ (በኤርትራም ይነገራል)
 ግዕዝ (በቤተ ክርስቲያን ብቻ ይነገራል)
1.1.2. ደቡብ
 በተለያዩ ቅላጼና ሥፍራ
o አማርኛ
o አርጎብኛ
o ሀደሪኛ ወይም ሐረርኛ
o የምሥራቅ ጉራጌ ቋንቋዎች
 ስልጤኛ (ኡልባረግና እነሞር)
 ወለኔኛ
 ዛይኛ
 የደቡብ ጉራጌ ቋንቋዎች
o ጋፋትኛ (የጠፋ)
o ሶዶኛ
o ሙኸርኛ
o ጎጎትኛ
o የምዕራብ ጉራጌ ቋንቋዎች
 እኖርኛ
 መስመስኛ (የጠፋ)
 መስቃንኛ
 ቸሃኛ ወይም ቸሃ (ሰባት ቤት ጉራጌ)
 እዣኛ
 ጉመርኛ
 ጉራኛ
 ግይጦኛ
 ኧንደገንኛ
 ኧነርኛ
1.2. ኩሻዊ
1.2.1. አገውኛ
 አውኛ (ኩንፋልኛ ዘዬ ወይም ቀበሌኛ ቋንቋን ጨምሮ)
 ቅማንትኛ
 ጫምታንግኛ
1.2.2. ምሥራቅ ኩሻዊ
 አፋርኛ (በኤርትራና ጅቡቲም ይነገራል)
 አላባኛ
 አርቦርኛ
 ባይሶኛ
 ቡሳኛ
 ቡርጂኛ
 ዳሳናችኛ (በኬንያም ይነገራል)
 ድራሻኛ
 ጋዋዳኛ
 ጌድዎኛ
 ሃድያኛ
 ከምባትኛ
 ኮንሶኛ ወይም
 ሊቢዶኛ
 ኦሮምኛ (በኬንያም ይነገራል)
 ሳሆኛ (በኤርትራም ይነገራል)
 ሲዳሞኛ
 ሶማልኛ (በሶማሊያም ይነገራል)
 ጻማይኛ
1.3. ኦሞአዊ
 አሪኛ
 አንፊሎኛ
 ባምባሲኛ
 ባስኬቶኛ
 ቤንችኛ
 ቦሮኛ ወይም ወይም ሺናሻ
 ጫራኛ
 ድሜኛ
 ዲዚኛ
 ዳውሮኛ
 ዶርዝኛ
 ገንዝኛ
 ጋሞኛ
 ጋይልኛ
 ጎፋኛ
 ሃመርኛ
 ሆዞኛ
 ቃጫማ-ጋንጁልኛ
 ከፋኛ
 ቃሮኛ
 ቁርቴኛ
 ማሌኛ
 መሎኛ
 ናይኛ
 ኦይዳኛ
 ሰዜኛ
 ሸኪቾኛ
 ሸኮኛ
 ወላይትኛ
 የምሳኛ
 ዛይሴ-ዘርጉላኛ
1.4. ናይሎ ሳህራዊ (አባይ ሰሃራዊ)
 አኙዋክኛ (በሱዳንም ይነገራል)
 በርታኛ
 ጉምዝኛ
 ቃጭፖ ባልስኛ (በሱዳንም ይነገራል)
 ቆሞኛ
 ቋማኛ
 ቀውግኛ
 ማጃንግኛ
 ምዕንኛ
 ሙርሌኛ (በሱዳንም ይነገራል)
 ሙርሲኛ
 ኩናምኛ (በኤርትራም ይነገራል)
 ኑርኛ (በሱዳንም ይነገራል)
 ንያንጋቶምኛ
 ኦጶውኛ
 ሻቦኛ
 ሱሪኛ
 ኡዱክኛ (በሱዳንም ይነገራል)
1.5. ያልተመደቡ
 ወይቶኛ (ወይጦኛ) (የጠፋ)
 ኦንጎትኛ (Ongota) (ለመጥፋት የተቃረበ)
 ረርበሬኛ (Rer Bare) (የጠፋ)

You might also like