You are on page 1of 1

ጥበቃ . . .!

(ከበእርሱፈቃድ

የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ ነው እንጅ #እረኝነቴን አልወደውም። በጎች አስቸግረውኝ አያውቁም። ወዳልኋቸው ይሄዳሉ . . .
ወደ ግርግማቸው . . . ወደ መስክ . . . ወደ የትም!(ግን ይሰለቻል) የስራ ውበቱ ፈታኝነቱ ነው። ተፈትኖ ማለፉ ነው ትልቁ
እርካታ። እርካታ የሌለው ስራ ደግሞ ይሰለቻል።

የዛን እለት ማታ ሌሎች እረኞች አንቀላፍተው እኔ ብቻ ነበር የቀረሁት።(እያሰብኩ) እንዴት ከዚህ ስራ መላቀቅ
እንደምችል . . . ጌቶቼን በምን አሳምኘ የተሻለ ስራ እንዲሰጡኝ እንደማደርግ . . . እንዲህ እያሰብኩ ሳለሁ ርቀቱ
ከከዋክብቱ መሀል የሚመስል የህፃን ለቅሶ ሰማሁ። ፀጥ አልኩ(ከሀሳቤ)። ለቅሶው ቀጠለ (ከተራራዎች መሀል . . .) ተነስቼ
ድምፁን ወደ ሰማሁበት መሮጥ ፈልጌ ነበር ግን ፈራሁ። እየቆየ ድምፁ ወደ ከተማው መሀል . . . ከዛም አጠገብ ካለው
#የከብቶች_ግርግም ገብቶ ተሰወረ። ውስጤ ሲቀዘቅዝ ተሰማኝ። ድምፁ ወደ ተሰወረበት ቦታ ልፈልገው ተነሳሁ።
ከቦታው ስደርስ ሁለት #ሴት እና #ወንድ ለከብቶች ምግብ በተዘጋጀ ሳር ላይ የተኛን #ህፃን አይናቸውን ተክለውበት
አገኘኋቸው። አስተያየታቸው ግን ለየቅል ነበር። ሴቷ #በእናታዊ_ፍቅር ወንዱ ደግሞ . . . (የወንዱ አስተያየት እንዴት
ይገለፃል? አባታዊ አይደለም። ሌላ ነው) ህፃኑን በአትኩሮት አየሁት የተኛ ይመስላል። ፊቱ ላይ ግን ቅድም የሰማሁት #ሳቅ
አለ። አሃ! ሳቅ አይደለም ለቅሶ ነው። (እንዴት ተምታታብኝ?) ዝቅ አልኩ ወደ ህፃኑ። አልደረስህ አለኝ . . . ተንበረከክሁ!
አጁን በእጄ ይዤ ሳምኩት። ስሜቱ ግን ተቃራኒ ነበር (እጄን በእጁ ይዞ የሳመኝ አይነት) ከኋላየ ከብዶኝ ዘወር ስል መቼ
እንደመጡ ያላየኋቸው ተኝተው የነበሩ እረኞች ከበው ህፃኑን በስስት ያዩታል። ቆይቶ ህፃኑ አይኑን ገለጠ። ነገሮች
ተገለበጡብኝ . . . #ከበን_ማየታችን ቀርቶ #ከቦ_ሚያየን መሰለኝ። እይታችንን ሰለበው! ከቀናት በኋላ በረቱን ለቀው
ሲሄዱ ከማንነቴ የጎደልኩ ያህል ተሰማኝ። ከዛን ቀን ጀምሮ ስራ ቀየርኩ። #በግ_መጠበቄን ባላቆምም ከልቤ የምጠብቀው
ግን የዛን አይነት ህፃን መወለድ ነበር። ሌሊቱን ነቅቼ ምጠብቀው በጎቹን ሳይሆን የህፃን ለቅሶ ሆነ።

እሱን ሚመስል ህፃን በበረቱ እስኪወለድ ልደቱን አከብርለታለሁ . . .!

#ሰናይ_በዓል!

You might also like