You are on page 1of 7

የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን በካሬ ሜትር ማብራሪያ

የቤት ግብይት ለከተማዋ ወሳኝ የሚባሉ የገቢ አርዕስቶች ማለትም ገቢ ግብር፣ ግብር የሚከፈልበትን ሀብትን በማስተላለፍ
የተገኘ ጥቅም (ካፒታል ጌይን)፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ቴምብር ቀረጥ እና አሹራ የሚሰበሰብበት ወሳኝ ግብይት ነው።
የቤት ሽያጭ ውል ተዋዋዮች ይዘውት የሚመጡት የሁለት ወጎኖች ስምምነት አሁን ካለው ነባራዊ የገበያ ዋጋ እጅግ በጣም
ያነሰ ከመሆኑ ባሻገር ቴምብር ቀረጥ፣ ግብር የሚከፈልበትን ሀብትን በማስተላለፍ የተገኘ ጥቅም (ካፒታል ጌይን) እና አሹራ
የገቢ አርዕስቶች ላይ የተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች የተነሳ ሽያጭ ገቢ እንዲደበቅ በመደረጉ መንግስት ማግኝት
ያለበትን ገቢ በአግባቡ እንዳይሰበሰብ እና የህዝብ ጥያቄ በሚፈለገው ደረጃ ምላሽ እንዳያገኝ ተጽዕኖ አሳድሯል።

በቤት ግብይት ዙሪያ አሳንሶ መዋዋል፣ አሳንሶ መገመት፣ የስም ዝውውሩን ማዘግየት፣ ቤቱ በርካታ ጊዜ ግብይት
ቢፈጸምበትም በመንደር ውል እየተዋዋሉ ስም ዝውውር አገልግሎት ሳይጠይቁ ሙሉ ውክልና ወስደው ግብይቱን
አለማሳወቅ የሚታዩ ክፍተቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም በግብይቱ ዋጋ አሳንሶ መዋዋል እና ሽያጭ ባለማሳወቅ ምክንያት
ግብር የሚከፈልበትን ሀብትን በማስተላለፍ የተገኘ ጥቅም (ካፒታል ጌይን)15%፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15%፣ ቴምብር
ቀረጥ 2% ፣ አሹራ 4 % እና ንግድ ትርፍ ግብር እንደገቢ ሁኔታ ከ 10-35% የሚገኝ ገቢ መንግስት እያጣ መሆኑ
በዚሁ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የተጠናውን የቤት ሽያጭ የጥናት ወጤት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ አስፈላጊ
ነው፡፡

በመሆኑም በፌደራል መንግስት ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀፅ 3 መሠረት የተጠናውን የቤት
ሽያጭ ዋጋ ተመን በካሬ ወደ ስራ እንዲገባ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሽያጭ ዋጋ በካሬ ሜትር

የቦታው ደረጃ አማካይ ዋጋ በካሬ ሜትር


1/1 72,377
1/2 69,817

1
1/3 66,817
1/4 64,817
1/5 63,139

2
2/1 62,139
2/2 59,639
2/3 57,639
2/4 55,639
2/5 53,511
3/1 52,511
3/2 50,511
3/3 48,511
3/4 46,511
3/5 45,511
4/1 43,511
4/2 40,000
4/3 38,000

የቦታው ደረጃ አማካይ ዋጋ በካሬ ሜትር


1/1 123,937
1/2 119,937
1/3 116,937
1/4 113,937
1/5 97,296
2/1 96,296
2/2 94,296 2. አፓርት
መንት
2/3 92,296 ቤቶች
ሽያጭ
2/4 90,296 ዋጋ በካሬ
2/5 86,000 ሜትር

3/1 85,000
3/2 82,000
3/3 80,000
3/4 78,000
3/5 77,000
4/1 75,000 3
4/2 74,000
4/3 73,000
3. ሌሎች (ከኮንዶሚኒየም እና አፓርትመንት ውጭ ያሉ) ቤቶች የግንባታ ነጠላ ዋጋ በካሬ ሜትር እና
የመጠቀም መብት ዋጋ በካሬ ሜትር እንደሚከተለው ይሆናል

ደረጃ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በካሬ ሜትር የመጠቀም መብት ዋጋ በካሬ ሜትር


1/1 30,000 61,369
1/2 30,000 60,369
1/3 30,000 59,369
1/4 30,000 58,369
1/5 30,000 56,295
2/1 30,000 53,295
2/2 30,000 50,295
2/3 30,000 47,295
2/4 30,000 44,295
2/5 30,000 40,974
3/1 30,000 35,974
3/2 30,000 31,974
3/3 30,000 28,974
3/4 30,000 24,974
3/5 30,000 22,175
4/1 30,000 19,175
4/2 30,000 18,175
4/3 30,000 17,000

4
ማሳያ 1፡- አንድ በደረጃ 1 የቦታ ደረጃ የሚገኝ የቦታ ስፋቱ 200 ካሬ ሜትር የሆነ እና የቤቱ ስፋት 140 ካሬ

ሜትር ስፋት ያለው መኖሪያ ቤት የቤት ሽያጭ ዋጋው ስሌት እንደሚከተለው ይሰላል።

ሀ = (ለ x ሐ) + (መ x ሠ)

ሀ = የቤት ሽያጭ ዋጋ

ለ = የይዞታ ስፋት

ሐ = አማካይ የመጠቀም መብት ዋጋ በካሬ ሜትር

መ = የቤት ስፋት

ሠ = አማካይ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በካሬ ሜትር

ሀ= (200 x 61,369.00) + (140 x 30, 000) = 16,473,800

ቤቱ መኖሪያ ቤት በመሆነ ካፒታል ጌን አይከፈልበትም።

አሹራ = 16,473,800 x 4% = 658,952

ቴምብር ቀረጥ = 20,335,390 x2% =329,476

በአጠቃላይ ለመንግስት የሚከፈል ክፍያ ብር= 658,952 + 329,476 = 988,428

5
ማሳያ 2፡- አንድ በደረጃ 1 የቦታ ደረጃ የሚገኝ የቦታ ስፋቱ 200 ካሬ ሜትር የሆነ እና የቤቱ ስፋት 140 ካሬ

ሜትር ስፋት ያለው የንግድ ቤት ሆኖ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ሰው የቤት ሽያጭ ዋጋው ስሌት እንደሚከተለው

ይሰላል። ( ቤቱ በ 2014 በ 10 ሚሊየን ብር የተገዛ ቢሆን የ 2015 ግሽበት ምጣኔው 32.38% ቢሆን)

ሀ = (ለ x ሐ) + (መ x ሠ)

ሀ = የቤት ሽያጭ ዋጋ

ለ = የይዞታ ስፋት

ሐ = አማካይ የመጠቀም መብት ዋጋ በካሬ ሜትር

መ = የቤት ስፋት

ሠ = አማካይ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በካሬ ሜትር

ሀ= (200 x 61,369.00) + (140x 30,000) = 16,473,800

የንግድ ቤት ሽያጭ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተቀናሽ ይሆናል።

=16,473,800x15%= 2,471,070

ካፒታል ጌን የሚሰላበት የሽያጭ ዋጋ ብር


= 16,473,800 - 2,471,070= 14,002,730

ካፒታል ጌን ታክስ = ሀ - (በ+ሸ)


ሀ = የቤት ሽያጭ ዋጋ
በ = ቤቱ የተገዛበት ዋጋ
ሸ= የግሽበት ማስተካከያ ዋጋ

ካፒታል ጌን ታክስ
= (14,002,730- (10,000,000+ (10,000,000 x0.3238))) x15%
=14,002,730 - (10,000,000+ 3,238,000)

6
=14,002,730 - 13,238,000 = 764,730 x15% = 114,709.5
ቴምብር ቀረጥ = 13,238,000 x2% = 264,760
አሹራ = 13,238,000 x4% = 529,520

በአጠቃላይ ለመንግስት የሚከፈል ክፍያ ብር


=2,471,070 + 114,709.5 + 264,760 + 529,520 = 3,380,059.5

ማስታወሻ፡- የሽያጭ ውሉ በዚህ በተተመነው ዋጋ የሚበልጥ በሚሆንበት ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው ዋጋ

በሽያጭ ውሉ የቀረበው ይሆናል።

You might also like