You are on page 1of 39

 ቅዱስ ያሬድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ሲሆን ትውልዱ አኲስም ነው፡፡

 እናቱ ታውክልያ አባቱ ይስሐቅ ይባላሉ፡፡


 ሚያዚያ 5 ቀን ተወለደ፡፡
 አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡ የአኵሱም ቤተ ቀጢን (ቤተ ጉባኤ) መምህር የነበረው የእናቱ ወንድም አጎቱ
መምህር ጌዴዎን ይባል ነበር፡፡
 ቅዱስ ያሬድ የሰባት ዓመት ብላቴና በኾነ ጊዜ አባቱ ስለ ሞተ ከአጎቱ ዘንድ ለመማር ሄደ፡፡
 መምህር ለተማሪዎች “በሉ ፊደል አስቆጥሩት” አላቸውና ትምህርቱን ጀመረ፡፡
 ኾኖም ቃለ እግዚአብሔርን የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለነበር ዐብረው የሚማሩትም ሕፃናት “ያሬድ ዕንጨት ስበር
ውሃ ቅዳ” እያሉ አፌዙበት፤ቀለዱበት፡፡ አጎቱ ጌዴዎንም ከሕፃናቱ ጋራ ሊወዳደር ባለመቻሉና መዝሙረ ዳዊትን
ማጥናት አቅቶት ወደ ኋላ በመቅረቱ ከትምህርቱ ድክመት የተነሣ በጨንገር (በአለንጋ) ቢገርፈው ሕፃኑ ያሬድም በዚህ
ተበሳጭቶና ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር ወደ መደባይ ወለል ሲጓዝ ማይ ኪራህ ደረሰ፡፡
ለጥሙ ከምንጭ ውሃ ጠጥቶ ለድካሙ ከዛፉ ጥላ አረፈ፡፡
 ክሬዋሕ ከሚባል ዛፍ ሥር በውሃው ምንጭ ዳር ተቀምጦ ወደ ዛፉ
ተመለከተ አንድ ትል የዛፏን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደ ላይ እየወጣና
እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛው ጊዜ ወደ ዛፉ
ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ፡፡
 ተማሪ ያሬድም ከዚህ ትል ትዕግሥትን፣ ጽናትን፣ ጥረትን፣ ስኬትን
ትምህርት ወስዶ እኔም እኮ ተስፋ ሳልቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረግኹ
እግዚአብሔር ያሳካልኛል ብሎ በተስፋ ተጽናንቶ እንደገና ወደ
መምህሩ በመመለስ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ፡፡
 የአጎቱ ግርፋት ፣ምክርና ተግሣጽ ለሕይወቱ የሚጠቅም እንደኾነ በመረዳት ትምህርቱን በትጋት ቢማርና
ቢያጠና ያሰበው ደረጃ መድረስ እንደሚችል በመገንዘብ ወደ መደባይ ያደርገው የነበረውን ጉዞ ሠርዞ ወደ
አክሱም ከተማ ወደ መምህሩ ጌዴዎን ጉባኤ ቤት ተመለሰ፡፡
 አጎቱም ያሬድ ተጸጽቶ በመመለሱ በጣም ተደሰተ፡፡ ቅዱስ ያሬድም ዐይነ ልቡናውን ያበራለት ዘንድ
ፈጣሪውን እያለቀሰ በለመነ ጊዜ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ዕውቀትን ገለጸለት፡፡ “ተርኅወ
ኅሊናሁ፤ የያሬድ ኅሊናው ተከፈተ ማለት ልቡናው ብሩሕ ኾነ፡፡
 ቅዱስ ያሬድም መዝሙረ ዳዊትን፣ ውዳሴ ማርያምን፣ መሐልየ ነቢያትን፣ መሐልየ ሰሎሞንን፣
መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን ንባባቸውን እስከ አገባባቸው ዐወቀ፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቃሉ ይዞ ሲያስተምር ሳለ የትምህርቱን ጥራት፣ የሃይማኖቱን ጽናት፣
ደግነቱና ትዕግሥቱ፣ ትሕትናውና ተልእኮው በመምህሩ እና በካህናቱ ተመስክሮለት የአክሱም ጳጳስ አባ
ዮሐንስ ሢመተ ዲቁና ሾመው፡፡ ቅዱስ ያሬድ የታላቋ የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን
ኾነ፡፡
 ትምህርቱን በስፋት ስለቀጠለበት የመጻሕፍተ ብሉያት፣ የመጻሕፍተ ሐዲሳት እና የመጻሕፍተ ሊቃውንት
ትርጓሜ ሊቅ ኾነ፡፡ አጎቱ ጌዲዮን በሞት ሲለየው በአጎቱ ወንበር ተተክቶ ማስተማር ጀመረ፡፡
 ዐፄ ገብረ መስቀል በነገሡበት ዘመን ቅዱስ ያሬድን የወደደ፣ ሀገሪቷን ኢትዮጵያንም የመረጠ
እግዚአብሔር ለመረጠው ለቅዱስ ያሬድ የዘለዓለም መታሰቢያ እንዲቆምለትና ሀገሩ ኢትዮጵያም
በሚያስተምራት ማኅሌተ መላእክት እያመሰገነችው፣ እያከበረችው እንድትኖር ቅዱስ ፈቃዱ ስለሆነ ኅዳር
5 ቀን ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት (በሠለስት) ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን (መላእክት በአዕዋፍ
ተመስለው) እርሱ ወዳለበት ላከለት፡፡
 እነርሱም ያሬድ ባለበት ቦታ አንጻር በአየር ላይ ረብበው በግእዝ ቋንቋ “የተመሰገንክና የተከበርክ ያሬድ
ሆይ፥አንተን የተሸከመች ማሕፀን የተመሰገነች ናት፤ አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው” ብለው
አወደሱት፡፡ ቅዱስ ያሬድም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ወደ ሰማይ አንጋጦ ሦስቱን አዕዋፍ አየና “እናንተ
በሰው አንደበት የምትናገሩ ከወዴት መጣችኹ” አላቸው፡፡
 ከሦስቱ አዕዋፍ አንዷም “ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ
ማኅሌትን ሰምተኽ እንድታዜም የተመረጥኽ መኾኑን
እንነግርህና እናበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልከን
መጥተናል” አለችው፡፡ ከዚያም ቅዱሳን መላእክት በዜማ
ወደሚያመሰግኑባት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በአካል ተነጠቀ፡፡
 በመጨረሻም እነዚያ አዕዋፍ ወደ እርሱ ተመልሰው መጡ፡፡
“ያሬድ ሆይ፤ የሰማኸውን አስተውለኸዋል?” ብለው ጠየቁት፡፡
“አላስተዋልኹም” ብሎ መለሰላቸው፡፡ “እንግዲያውስ አዲሱን
የእግዚአብሔርንምስጋና ጥራ፤ እርሱም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከእግዚአብሔር
መዘምራን ከቅዱሳን መላእክት በየዐይነቱ ዜማ ያለውን ማኅሌት ትማራለኽ፤ ታጠናለኽ” አሉት፡፡ ከዚህ በኋላ
ቅዱስ ያሬድ ማኅሌቱን በየዐይነቱ አውጥቶ “መልካምን ነገር ልቤ ተናገረ” እያለ ከቅዱሳን መላእክት ተማረ፡፡
 ቅዱስ ያሬድም የመላእክት ሥርዐታቸውን ዐይቶ፣ ማኅሌታቸውን አጥንቶ ኅዳር 6 በጠዋት ሦስት ሰዓት
ወደ ቀድሞ ቦታው ተመልሷል፡፡
 ከዚያም ኾኖ ፊቱን ታቦተ ጽዮን ወዳለችበት ወደ ምሥራቅ አዙሮ፥ እጆቹን ዘርግቶ እንዲህ ብሎ ሰማያዊ
ዜማውን አዜመ
“ለሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ
ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ
ይገብር ግብራ ለደብተራ” ብሎ በዓራራይ ዜማ አዜመ፡፡
ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት
የቀድሞ በቀድሞ ስሟ ዳውሮ ኢላ ተብላ ትጠራ ነበር ከዚህ በኋላ ”ሙራደ ቃል” (የቃል መውረጃ) እየተባለ
ይጠራል፡፡ ይህችንም ዜማ ”አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት
ነው፡፡ እርሷም ሳትጠፋ ለዘለዓለም ትኖራለች ፡፡
 ዐፄ ገብረ መስቀል የዜማውን ጣዕም ከሰሙና ከተረዱ በኋላ ሊቃውንቱንና ካህናቱን “ተቀበሉትና ለቤተ ክርስቲያን
መገልገያ ይኹን” ብለው አዘዟቸው፤ ነገር ግን ካህናቱና ሊቃውንቱ “ምን ምልክት ዐይተን እንቀበለው፤ እንደ
ሐዋርያት እጁንና እግሩን ለተሳለ ቀኖት (ችንካር)፣ አፉን ለምረረ ሐሞት ሰጥቶ አላየነው፤” ብለው መለሱላቸው፡፡
ንጉሡ “እንግዲያውስ ሱባዔ እንያዝና እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ይግለጽልን” ብለው ከታኅሣሥ አንድ ቀን
ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ሰባት ቀን ሱባዔ እንዲያዝ ዐወጁ ፡፡
 በዚያን ጊዜ ታኅሣሥ አንድ ቀን ሰኞ ዕለት ውሎ ነበርና ከሰኞ እሰከ እሑድ አንድ ሱባኤ ይዘው በየቀኑ የአኲሱም
ጽዮን ማርያምን ቤተ ክርስቲያን እየዞሩ አራት መቶ እግዚኦታና አርባ አንድ በእንተ ማርያም እያደረሱ ምሕላውን
አካሄዱ ፡፡
 በሰባተኛው ቀን እሑድ ዕለተ ምህላውን ጨርሰው ሲያሳርጉ ጌታ በዕለተ ዐርብ እንደተሰቀለ ኾኖ በአኲሱም ጽዮን
ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ተገለጸ፡፡
 በተገለጸው ምስክርነት መሠረት ዜማው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ መኾኑን አምነው ቤተ መንግሥቱ፣ ቤተ ክህነቱ
እና ሕዝቡ በአንድነት ተቀበሉት፡፡
 በዚህም ቀን ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ የተቀበለው ዜማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ብርሃኗ በራ በሰማያዊ
ምስጋና ቤተ መቅደሱ መላ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድን በእልልታ ተቀበለችው፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ስሙ እንደሚያመለክተው ሰማያዊ ዜማን ወደ ምድር አወረደ፤ ስም በተግባር ተገለጸ፤ “የመላእክት
እንጀራን የሰው ልጅ በላ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠኀቸው” የተባለው የቅዱስ ዳዊት የትንቢት ቃል
ፍጻሜ አገኘ፡፡
 ከዚህች ዕለት (ታኅሣሥ ሰባት ቀን) ጀምሮ የቅዱስ ያሬድ ዜማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ
መገልገያ ኾነ፡፡ ቅዳሴው በቅዱስ ያሬድ ጣዕመ ዜማ ተቀነባበረ፡፡
 የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ዜማ ከዓመት እስከ ዓመት ያለማቋረጥ የሚዘመርባት በምድር ያለች ሁለተኛ ጽርሐ
አርያም ኾነች፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ዜማውን በሚያዜምበት ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ሲሰሙ
አዕዋፍ በሰማይ ክንፋቸውን ረበው ሲጓዙ በመሬት እንስሳት
አራዊት ይከተሉት ነበር፡፡ የተጠመዱ በሬዎች እንኳን ሳይቀሩ
ዜማውን ያዳምጡ ነበር ፡፡ በጎንደር ክፍለ ሀገር ወገራ አውራጃ
በአምባ ጊዮርጊስ ወረዳ ልዩ ስሙ ሰርዶ ሜዳ በሚባል ቦታ ቅዱስ ያሬድ
“ዘሪ ሊዘራ ወጣ ሲዘራም አንዳንዱ ቅንጣት ባልሆነ ስፍራ ወደቀ”
 ማቴ. 13 ተብሎ በምሳሌ ዘር የተነገረውን በዜማው አግብቶ ቃሉን ከፍ አድርጎ እያዜመ በሚሔድበት ጊዜ ተጠምደው
በእርሻ ላይ ያሉ በሬዎች እያዳመጡ አልንቀሳቀስም ስላሉ ገበሬዎች ተሰብስበው ቅዱስ ያሬድን፡- “አንተ ሥራ ፈት
ተማሪ ፤ራስህ ሥራ ፈተኽ ሌላውን ሥራ ታስፈታለኽ” በማለት ገርፈውታል፡፡ ለዚህም ነው ወገረ ከሚለው የግእዝ
ግሥ ወገራ የሚለው ቃል ወጥቶ የአካባቢው መጠሪያ የሆነው፡፡ ቦታውም “ወርቀ ደሞ ” እየተባለ እስከ ዛሬ ድረስ
ይጠራል ፡፡ ወርቃማ ደሙ የፈሰሰበት ማለት ነው ፡፡
 ሀገሪቱ ቅዱስ ያሬድን ስለገረፈችው ለብዙ ዘመናት በድርቅና በተለያዩ
ችግሮች ስትፈተን ኖራለች ፡፡ በቦታውም ከትልቅ ማዕርግ የደረሰ ሰው
ሳይወጣባት እንደ ቆየ አባቶች ይናገራሉ ፤ ብዙ አባቶችም
“የቅዱስ ያሬድን ታቦት አምጥታችኹ ቤተ ክርስቲያን ሠርታችኹ
ብታቋቁሙት ረድኤቱ ይመለስላችኋል፤ መርገሙ ይሻርላችኋል
እንዲሁም መታሰቢያውን ብታደርጉ ዝክሩን ብታዘክሩ ስሙን
ብትጠሩ ይህ ሁሉ ችግር ይቃለልላችኋል” እያሉ ምክር ሲለግሷቸው ቆይተው በ1956 ዓ.ም በአንዲት መበለት
ምክንያት ጥላጌ መስክ ላይ ምህረት ተለምኗል፡፡
 ደልደሊት ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታቦቱ ስለገባ ፍጹም በረከት ወርዶላታል ፡፡ በየጊዜው ዝናም ለዘር ጠል
ለመከር የማይለያት፣ ጥቂት ቢዘሩ ብዙ የሚያመርቱባት፣ ሰው ሁሉ በፍጹም ተድላ የሚኖርባት ሀገር ኾናለች ፡፡
ይኸውም የጻድቁ ይቅርታ መኾኑ ታውቆ በዕለተ ሰንበት መዝሙር በየወሩ መኅሌት እየተቆመ መታሰቢያው ይደረጋል
፡፡ በዙሪያው ያሉ መምህራንና መዘምራን ካህናት ስላሉ ክብረ በዓሉ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡
 ፡፡
 ቅዱስ ያሬድ በቅድስት አኲሱም ወንበር ዘርግቶ፣ ጉባኤ
አስፍቶ ደቀ መዛሙርቱን እያስተማረ ሲኖር በጾመ ፵ ሱባዔ
ላይ ሳለ አንድ ቀን በምኩራብ ሰሞን ስለምናኔው እያስታወሰ
በተመስጦ ሲዘምር የዜማው ጣዕም እንኳን ሌላውን ራሱን እጅግ
ይመሥጠው ነበር፡፡ በጣዕመ ዝማሬው ተመሥጦ ሲያዳምጥ
የነበረው ኢትዮጵያዊው ንጉሥ የዐፄ ካሌብ ልጅ ዐፄ ገብረ
መስቀል ዐይን ዐይኑን እየተመለከተ ሳይታወቀው በመስቀል
ሰላጢኑ (በበትረ መንግሥቱ ዘንግ) ጫፍ የቅዱስ ያሬድን
እግር ወጋው፡፡ቅዱስ ያሬድ ግን ከሰማያት የተገኘች ቃለ
ማኅሌቱን እስኪፈጽም ድረስ ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ሕመሙ
ሳይታወቀው ቀጠለ፤ ደሙም ያለማቋረጥ ፈሰሰ፡፡
ቅዱስ ያሬድ የጀመረውን በፈጸመ ጊዜ ንጉሡ ደንግጦ በትሩን ከቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ቢነቅለው ደሙ
በኀይል ይፈስ ጀመር፡፡ ያን ጊዜ ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀል የቅዱስ ያሬድን ትዕግሥት ባየ ጊዜ በመደነቅ፣
በመገረምና በመደንገጥ ዝም በማለት አፉን ይዞ ቆመና ምድራዊ ዋጋ የሚፈልግ መስሎት “ካህን ያሬድ ሆይ
የምትፈልገውን የደምህን ዋጋ ጠይቀኝ” አለው፡፡ ቅዱስ ያሬድም መልሶ “የፈለግኹትን እንዳትከለክለኝ ቃል
ኪዳን ግባልኝ” አለው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀልም የጸና ቃል ኪዳን ለቅዱስ ያሬድ ገባለት፡፡ ቅዱስ ያሬድም
“ከዚህ ሐላፊ ዓለም ክብር ተለይቼ መናኝ ሆኜ እንድኖር ተወኝ አሰናብተኝ” ብሎ አሳቡን ገለጸለት፡፡
 ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀልም የቅዱስ ያሬድን ቃል በሰማ ጊዜ እጀግ ደንግጦ “ወዮልኝ! ወዮልኝ!
በዘመነ መንግሥቴ እግዚአብሔር የሰጠኝ እንዲህ ያለ ካህን አይገኝም ወዮ! ወየው! በሰማያዊ ጣዕመ
ዜማው በተከበርኹ ፈንታ በኀዘን ባሕር ውስጥ ወደቅኹ ወዮ! ወየው! ወዮልኝ! የዐይኔ ብርሃን
የራሴ ዘውድ፣ የገበዘ አኲሱም ሽልማቷ፣ ጌጧ እና ግርማ ሞገሷ” እያለ አለቀሰ፡፡ ያን ጊዜ በቤተ
መንግሥቱ ታላቅ ኀዘን ኾነ፡፡ ካህናቱ እና ሕዝቡም በሙሉ ስለ ካህን ቅዱስ ያሬድ መለየት አዘኑ፡፡
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ያሬድ ካህን የጠየቀውን እንዳይከለክለው ከአፉ የወጣውን
መሐላ አስቦ በምናኔ አሰናበተው እንጂ ሊከለክለው አልቻለም፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ካህን ዘመኑን ሁሉ በመላእክት ማኅሌት እግዚአብሔርን በማገልገልና ይህን ማኅሌት ለሚከተሉት ደቀ
መዛሙርት በማስተማር ዘመኑን ፈጽሞ ከ22 ዓመታት በላይ በምናኔ ታግሦ በገድሉና በጣዕመ ዜማው ጸላኤ ሠናያትን
ድል አድርጎ ከዚህ ዓለም ድካምና መከራ የሚያርፍበትና ከደቀ መዛሙርቱ ተለይቶ በጠለምት ዋሻ ውስጥ
የሚሠወርበት ቀንና ሰዓት መድረሱን በጸጋ በዐወቀ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ “ይቤ ጳውሎስ ኃላፊ ንብረቱ ለዝንቱ
ዓለም አኃውየ አስተፋጥኑ ገቢረ ሠናየ አንሰ በድረየኒ ፈጸምኩ ወሃይማኖትየኒ ሠለጥኩ እንከሰ ጽኑሕ ሊተ አክሊል
ዘየዓሥየኒ መኰንነ ጽድቅ፤ጳውሎስ የዚህ ዓለም ንብረት ኃላፊ ነው አለ፤ ወንድሞቼ መልካም ለማድረግ ተፋጠኑ እኔ
ሩጫዬን ጨረስኹ፤ ሃይማኖቴን ጠበቅኹ ከእንግዲህ ወዲህ የእውነት ገዢ የሚሰጠኝ አክሊል ይቆየኛል” (2ኛ ጢሞ.
4፥7-8) እያለ በሚያራራ ቃል ምክሩን ሰጥቶ ተሰናበታቸው፡፡ እነርሱም ምክሩን ተቀብለው “አባ አቡነ፣ አባ መምህርነ
አይቴ ተሐውር ወለመኑ ተኀድገነ፤ አባታችን መምህራችን ወደ የት ትሔዳለኽ? ለማንስ ትተወናለኽ?” እያሉ ሲያዝኑ
ሲያለቅሱ በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ግንቦት 11 ቀን ተሠወረ
 ቅዱስ ያሬድ የሚመንንበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለደረሰ የመሰናበቱን ጉዳይ ፈጽሞ ከቤተ ክርስቲያን ወጣ፡፡
ከዚያም እንደ ኪሩቤልና ሱራፌል ያደረጋቸውን መዘምራን ካህናት ለአኲሱም ጽዮን አበርክቶላት ለመሄድ ተነሣ፡፡
በዚህ ጊዜ የሚወዱት ካህናት፣ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ተከትለውት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት፡፡ ከእርሱ
በሚለዩበትም ጊዜ “ሰላመ ነሳእነ ወሰላመ ኃደግነ ለክሙ ወሰላመ እግዚአብሔር የሃሉ ምስለ ኵልክሙ&(ሰላም፣ድጓ)
ሰላምን ከእናንተ ተቀበልን ለእናንተም ሰላምን ተውንላችሁ የእግዚአብሔር ሰላምም ከሁላችሁ ጋራ ይኹን” ብሎ በዜማ
ተሰናበታቸው፡፡
 ሀ. ግእዝ ዜማ - የግእዝ ዜማ በባሕርዩም ሲታይ በጣም ጠንካራና ኃይለኛ ነው:: ግእዝ የዜማ ስልት የእግዚአብሔር
አብ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የግእዝ ጠንካራነት እግዚአብሔር አብ በአካል ሥጋ ለብሶ ያልተገለጠ በባህርዩ የማይደረስበት
ልገልጥ ባለ ጊዜ ለፍጥረቱ በዘፈቀደ የሚገለፅ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ግእዝ የመጀመሪያው ዜማ ስም እንደሆነ ሁሉ
እግዚአብሔር አብም ለአዳም የገባውን መሐላ ወይም ቃል ኪዳን ለመፈጸም ዐምስተኛው ሺኽ ተፈጽሞ ስድስተኛው
ሺኽ ሲጋመስ በጽኑ ቀጠሮውና በታማኝ ቃሉ ኀይሉና ክንዱ የሆነውን እግዚአብሔር ወልድን ወደዚህ ዓለም የመላኩን
ማለትም በፈቃድ አንድ መሆናቸውን ምስጢሩ ያሳያል፡፡
 ለ. ሕዝል /ዕዝል/ ዜማ :- ሕዝል /ዕዝል/ የሚለው ቃል ታዛይ ወይም ተደራቢ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ከግእዝ ጋር
ተደርቦ የሚዜም ዜማ ማለት ነው፡፡ ዕዝል በዜማ ባሕርዩም ማኅዘኒ ወይም አሳዛኝ ማለት ነው፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታ
በተሰቀለበት በዕለተ ዐርብ የሚዜም ይህ ዕዝል የተባለው ዜማ ነው፡፡ የዕዝል ዜማ የእግዚአብሔር ወልድ ምሳሌ ነው፡፡
ይኸውም የዕዝል ዜማ ስም እዛይ፣ታዛይ ወይም ተደራቢ እንደመሆኑ ከግእዝ ዜማ ቀጥሎ እንደሚጠራ ከእግዚአብሔር
አብ ቀጥሎም እግዚአብሔር ወልድ የሚጠራ መሆኑን በምሳሌነቱ ይገልጻል፡፡ ግእዝና ዕዝል መተዛዘላቸው
እግዚአብሔር አብና ወልድ አንድ መሆናቸውን የማይለያዩ መሆናቸውን ያሳያል፡፡
 ሐ. ዓራራይ ዜማ
 ዓራራይ ማለት የሚያራራ፣ ልዩ ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ ማለት ነው፡፡ ይህ ዜማ በዐምስቱ የዜማ ድርሰቶች
ሁሉ ያለ ቢሆንም በተለይ በቅዳሴ ዜማ በዝቶ የሚታይ ነው፡፡
 የዓራራይ ዜማ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡ ይኸውም የዓራራይ ዜማ ርኅራኄ ያለው ወይም አራኅራኂ
የሆነ ልዩ ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ እንደሆነና የአራራይ ስም ከዕዝል ቀጥሎ እንደሚጠራ የእግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ ስምም ከእግዚአብሔር ወልድ ቀጥሎ የሚጠራ መሆኑን ይገልጻል፡፡ የዓራራይ ዜማ ባሕርይ ጣዕም
ያለው ልብን የሚመስጥ ዓራኅራኂ እንደሆነ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም የምእመናንን ልብ በደስታ የሚሞላ
በርኅራኄው ኀጢአትን የሚያስተሰርይ መሆኑን፣ ዜማው ዓራኅራኂ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም የምእመናንን
ኀጢአት ይቅር እያለ በርኅራኄ የሚጠብቃቸው መሆኑን ምሥጢሩ ይገልጻል፡፡
᎔ ድፋት ፡- ድፋት ማለት ድምፅንና አንገትን ወደታች እርግጥ አድርጎ ወይም ደፍቶ ትንፋሽን ወደ ሆድ ውስጥ

በመመለስ ማዜም ማለት ሲሆን ከላይ ወደ ታች መውረድን ያመለክታል፡፡

᎘ ሂደት ፡- ሂደት ማለት እንደ ሜዳ፣ እንደ መንገድ፣ እንደ ቦይ ውሃ ሰተት ብሎ እንደሚሄድ ተጓዥ አንተም

ሳታቆም ወይም ሳታቋርጥ ምንም ነገር ሳይዝህ ሰተት ብለህ ሂድ ወይም አዚም ማለት ነው፡፡

᎕ ቅናት ፡- ቅናት በቅርጽነቱ ደጋን የመሰለና ከቀኝ ወደግራ የተሰመረ ወልጋዳ መስመር ይመስላል፡፡ ቅናት ማለት

በዜማው ቃል መጨረሻ ያለውን ቃል አንዱን ፊደል ይዘህ አንገትህን ወደላይ በማቅናትና ድምፅህን እንቅ
በማድረግ አዚም ማለት ነው፡፡
 ይዘት፡- ይዘት ማለት በፍጥነት ከዜማው ዘር አንዱን የፊደል ሆሄ ያዝ በማድረግ አዚም ማለት ሲሆን ምንም ተጨማሪ
የሌለውን አንድ ብቻ የሆነን ነገር የሚያመለክት ነው፡፡
᎙ ቁርጥ፡- ቁርጥ ማለት ዜማውን በምታዜምበት ጊዜ ድምፅን በመጠኑ በመቀነስ ትንፋሽን ወደታች
በማመቅ እንደገናም ድምፅን በማጋነን አገጭን ወደፊት በማድረግ አዚም ማለት ነው፡፡

᎖ ጭረት ፡- ጭረት ማለት በዜማው መካከል ያለውን ንባብ አንዱን ፊደል ጎተት ወይም ሳብ አድርገህ
አንገትህን ወደላይ አቅንተህ አዚም ማለት ነው፡፡

፡ ርክርክ ፡- ርክርክ በቅርጹ ሲታይ የሚንጠባጠቡ ነገሮችን ያመለክታል ርክርክ ማለት ረጅም የሆነውን

ዜማ በላዩ ላይ ርክርኩ በመጨመር በረጅሙ አዚም ማለት ነው፡፡

᎑ ደረት፡- ደረት ማለት ደረትን ከፍ በማድረግ ፊት ለፊት ቀጥ ብሎ በጉልህ ድምፅ በጉሮሮ የሚዜም
ማለት ሲሆን ቅርጹ አንድ ተኝቶ የነበረ ሰው አፈፍ ብሎ ሲነሣ የሚያሳይ ይመስላል፡፡
ስ ድርስ ፡- ድርስ ማለት የቃሉ መጨረሻ የሆነውን አንዱን የፊደል ሆሄ ያዝ በማድረግና ድምፅን ወደ ኋላ በመሳብ

ዜማውን እስከመጨረሻው ማዜም ማለት ነው፡፡

ር አንብር፡- አንብር ማለት አስቀምጥ አሳርፍ ማለት ሲሆን የአንዱን ዘር የመጨረሻ ሆሄ ያለምንም ተጨማሪ
ድምጽና ርክርክ በማስቀመጥ ወይም በማቆም አዚም ማለት ነው፡፡
᎔ ድፋት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ከልዕልናው ወርዶ ወደዚህ ዓለም መምጣቱንና ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው መሆኑን ይገልጻል፡፡

᎘ ሂደት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዚህ ዓለም ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ በባሕር በየብስ እየተመላለሰ ማስተማሩን እንዲሁም አይሁድ አንድ ጊዜ ከሐና ወደ ቀያፋ፣ ከቀያፋ
ወደ ጲላጦስ፣ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ፣ እየወሰዱ እንዲንገላታ ማድረጋቸውን የሚያስረዳ ነው፡፡
᎕ ቅናት፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክነቱ በሽተኞችን መፈወሱ ለምጻሞችን በማንጻቱ፣ ዕውራንን ማብራቱ፣ ሙታንን ማስነሣቱና ጎባጣ የሆኑትን ማቅናቱ ያስቀናቸው ካህናተ
አይሁድ ጠማማ በሆነ አእምሯቸው ቀንተው፣ ተመቅኝተው እንዲሰቀል ማድረጋቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
 ይዘት ምሳሌነቱም ከጽድቅ በቀር ሌላ ኀጢአትና በደል ወይም ጥፋት የሌለበት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድ በትምህርቱና በተአምራቱ ቀንተው ከሳሽ መስካሪ ሆነው
በሐሰት ማስያዝያቸውንና ዓለምን በእጁ (በመዳፉ) የያዘ አምላክ መሆኑን ያስተምረናል፡፡
᎙ ቁርጥ ሲሆን ምሳሌነቱም አይሁድ በሐሰት መስክረው ጌታችንን ቢያስይዙትም መከራ ቢያደርሱበትም በሲዖል ተግዞ የነበረውን አዳምና ልጆቹን ለማዳን ቆርጦ መነሣቱንና በፈቃዱ
ራሱን ለመከራ አሳልፎ በመስጠት ነፍሱን ከሥጋው ለመለየት ቁርጥ ውሳኔ ማድረጉን ያመለክታል፡፡

᎖ ጭረት ፡- ምሳሌነቱም ራሰ ጠማማ ራሰ ጎባጣ በሆነ በትር /ዘንግ/ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መመታቱን ያመለክታል፡፡

፡ ርክርክ ፡- ጌታችን ሲገረፍና ሲሰቀል ከሰውነቱ የተንጠባጠበውን የደሙን ነጠብጣብ ያመለክታል፡፡

᎑ ደረት፡- ፡ ምሳሌነቱም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ከሞተና ከተቀበረ በኋላ ሞትን ድል አድርጎ በራሱ ክብርና ሥልጣን ከመቃብር አፈፍ ብሎ በመነሣት ሁሉን
ከፈጸመ በኋላ በክብር በውዳሴ፣ በቅዳሴ በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ ማረጉን ያስተምራል፡፡
ስ ድርስ ፡- ነቢያት ጌታ ይወርዳል፤ ይወለዳል፤ ይሞታል፣ ይነሣል፣ ወደ ሰማይ ያርጋል፣ ሲሉ የተናገሩት ትንቢትና የተቆጠረው ሱባዔ መድረሱን
ር አንብር፡- ጌታ የማዳን ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ በአብ ቀኝ መቀመጡን የሚያስረዳ ነው፡፡
 የቅዱስ ያሬድ ለሀገራችን ያደረገው አስተዋጽኦ የጠለቀ ግንዛቤ አለመኖሩ ሥራዎቹ ፣
ከሀገርም አልፎ ለዓለም እንዳይተርፍ አድርጎታል፡፡

 ቅዱስ ያሬድ ያበረከተው ዜማ በየትኛውም ክፍለ ዓለማት የማይገኝና ለኢትዮጵያ


ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ከእግዚአብሔር የተበረከተ ጸጋ ሲሆን
ሀገራችን ኢትዮጵያም የዚህ ሐብት ብቸኛ ባለቤት ያደርጋታል፡፡

 ቅዱስ ያሬድ ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለዓለም ያደረገውን አስተዋጽኦ በጥቂቱ ከዚህ


የሚከተሉት ናቸው፡፡
 በተለይም በዋናነት በከበሮ፣ በጸናጽልና በመቋሚያ ቅንጅት የሚዜመው ዝማሬ
ከመንፈሳዊ ጥቅሙ ባሻገር ሽብሸባው ዕይታን የሚስብና ለጎብኚዎች እጅግ አስደናቂ
መኾኑ በሀገር ገጽታ ግንባታ ላይ ያለው ድርሻ ጉልህ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን
በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት መካከል መስከረም 16 ቀን የመስቀል ደመራ በዓል፣
ታህሣሥ 29 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ፣ ጥር 11
ቀን የጥምቀት በዓል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ በመስቀል
አደባባይ፣ የልደት በዓል በቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጥምቀት በዓል
በአዲስ አበባ በጃን ሜዳና በጎንደር ፋሲለደስ በተለየ ድምቀት ይከበራል፡፡ እነዚህ በዓላት
ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች ዘጠና በመቶ (90/100) የሚሆነው በቅዱስ ያሬድ ዜማ
የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን የበዓል ሥነ -
ሥርዓት ለመመልከት በየዓመቱ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት ጎብኚዎች ወደ ሀገራችን
ይመጣሉና ከዚህ አንጻር የቅዱስ ያሬድ ዜማ በጎብኚዎች መስብህነትና ለሀገራችን ገጽታ
ግንባታና ገቢ በማስገኘትና የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ትልቅ ጥቅም አለው፡፡
 የቅኔ ትምህርት የተጀመረው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ፀዋትወ ዜማ ሲደርስ አብሮ ደርሶታል፡፡
 ቅኔ በቤተክርስቲያናችን ራሱን የቻለ ትምህርት ቤት ያለው ከፍተኛ ትምህርት ነው፡፡
የቅኔ ትምህርት ደቀ መዛሙርትን ተመራማሪዎች፣ የቅኔ ዘራፊዎችና የምርምር ሰዎች
ወይም ፈላስፎች የሚደርግ ከሣቴ ጥበብ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ቦታ
ይሰጠዋል፡፡ ቅኔ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜና ምሥጢር መፈተኛ፣ የአዕምሮ ማጽኛ፣
የዕውቀት ማጎልመሻና የምርምር ዋሻ ነው፡፡

 በዓለምላይ ለሚታወቁ ቅኔዎች መሠረት የጣለው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡


 የዜማ ምልክት ማለት ዜማውን እንዴት ማዜም እንዳለብን ሊመራን ፣ ሊያስረዳን፣
ሊያሳውቀንና ሊያረጋግጥልን የሚችል ጠቋሚ ምልክት ነው፡፡
 ለምሳሌ አንድ ሰው ዜማውን ሲጠራጠር ወይም ዜማው ሲጠፋው መጽሐፉን ገልጦ
ምልክቱን በማየት የተጠራጠረውን ወይም የጠፋበትን ዜማ በምልክቱ ጠቋሚነት
ያገኘዋል ማለት ነው፡፡
 ቅዱስ ያሬድ መጀመሪያው የዜማ ምልክት አዘጋጅ ነው፡፡ ድፋት፣ ሂደት፣ ቅናት ፣
ይዘት፣ ቁርጥ፣ ጭረት፣ ርክርክና ደረት በማለት የፊደል ቅርጽ በሌላቸው ያዘጋጃቸው
ምልክቶች አንድ ሺ አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠሩ ናቸው፡፡
 የዜማ ምልክቶችን (ኖታዎችን) በማዘጋጀት በዓለም ላይ የመጀሚረያው ቅዱስ ያሬድ
ነው፡
 የቅ/ያሬድ አስተዋጽኦ እና በብዙዎች ዘንድ የማይታወቀው ሥራው በኢትዮጵያ ውስጥ
የመጀመሪያው ደራሲ እሱ መሆኑ ነው። እስካሁን በተደረገው ጥናት የኢትዮጵያ
ጽሑፎች እስከ ያሬድ መነሳት ድረስ ትርጉሞች (በተለይ ከግሪክ ቋንቋ) ነበሩ። ብሔራዊ
(ሀገር በቀል) ድርሰትን በኢትዮጵያ የጀመረ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ በመሆኑ ለኢትዮጵን
ደራሲያን የደራሲነትን በር የከፈተ እርሱ ነው፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ከመሬት ውጪ በላይ በፀፍፀፈ ሰማይ ስላሉ ግኡዛን አካላትም በመንፈስ
ቅዱስ እየተቃኘ ዘምሯል፡፡
 ስለከዋክብት፣ስለጸሐይና ስለጨረቃ አነዋወር ፣ የብርሃናቸውን ዑደት በተመለከተ
ተናግሯል፡፡
 ስለ ፀሐይ ፣ስለ ጨረቃ እንዲሁም ስለከዋክብት መሠረታዊ ባሕሪያቸውን ፣ተፈጥሮአዊ
እንቅስቃሴያቸውን፣ ዝግመተ ለውጣቸውን አሠራራቸውን ያደንቃል፡፡ የፀሐይና ጨረቃ
የብርሃናቸውን መበላለጥ የከዋክብት ውበታቸውን የሰሌዳቸውን ስፋትና ጥበት
አነዋወራቸውን ዘውጋቸውን ሳይቀር በዜማው አድንቋል፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ስለ ምድር ስነ ተፈጥሮ አቀማመጥ ፣ዝግመተ ለውጥ በእርሷ ስለሚኖሩ
የሰው ልጆች አሰፋፈር በምድር ላይ ስላላቸው አኗኗር ይተነትናል ያብራራል፡፡
 “በጥልቁ መሠረት ውስጥ ተመላልሰሃልን? ከግርማህ የተነሳ የሞት ብረት
ተከፍተውልሃልን? ከሰማይ በታች በምድር ስፋት አስተውለሃልን? መጠኑ ምን ያህል
እንደሆነ እሰኪ ንገረኝ?”
 ስለ ወንዙ፣ ስለ ሸንተረሩ፣ ስለሸለቆው ጥልቀት፣ ስለ ተራራው ርዝመት፣ ስለ
ኮረብታው ስለባሕሩና ስለውቅያኖሱ ስፋት ስለ አፍላጋቱ ፍሰት ስለ ቀላያቱ
ስለምድረበዳው ስለ ጭንጫው በአጠቃላይ ዓለምአቀፋዊ መልክአ ምድር በመዳሰስ
የምድርን ገጽታ የፈጣሪን ችሎታ በማድነቅ ያስቃኘናል፡፡
 አፍሪካውያን ለተፈጥሮ ዐይን የላቸውም ትኩረት አይሰጡም ለሚለው የምእራባውያን
ትችት ቅዱስ ያሬድ ከአንድ ሺ አምስት መቶ ዓመታት በፊት መልስ እንደሰጣቸው
እንረዳለን፡፡
 ቅዱስ ያሬድ ስለ ምድር ስነ ተፈጥሮ አቀማመጥ ፣ዝግመተ ለውጥ በእርሷ ስለሚኖሩ
የሰው ልጆች አሰፋፈር በምድር ላይ ስላላቸው አኗኗር ይተነትናል ያብራራል፡፡
 “በጥልቁ መሠረት ውስጥ ተመላልሰሃልን? ከግርማህ የተነሳ የሞት ብረት
ተከፍተውልሃልን? ከሰማይ በታች በምድር ስፋት አስተውለሃልን? መጠኑ ምን ያህል
እንደሆነ እሰኪ ንገረኝ?”
 ስለ ወንዙ፣ ስለ ሸንተረሩ፣ ስለሸለቆው ጥልቀት፣ ስለ ተራራው ርዝመት፣ ስለ
ኮረብታው ስለባሕሩና ስለውቅያኖሱ ስፋት ስለ አፍላጋቱ ፍሰት ስለ ቀላያቱ
ስለምድረበዳው ስለ ጭንጫው በአጠቃላይ ዓለምአቀፋዊ መልክአ ምድር በመዳሰስ
የምድርን ገጽታ የፈጣሪን ችሎታ በማድነቅ ያስቃኘናል፡፡
 አፍሪካውያን ለተፈጥሮ ዐይን የላቸውም ትኩረት አይሰጡም ለሚለው የምእራባውያን
ትችት ቅዱስ ያሬድ ከአንድ ሺ አምስት መቶ ዓመታት በፊት መልስ እንደሰጣቸው
እንረዳለን፡፡
 የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድነትን በመጠበቅ ረገድ የቅዱስ ያሬድ ዜማ
የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፡፡
 ይህም ማለት ዜማው አንድና ወጥ የኾነ ሥርዓትን በመዘርጋት የቤተ ክርስቲያኗን
ሁለንተናዊ ሕይወትን በአጠቃላይ በቅዱስ ያሬድ ዜማ ዐሥሮ ቋጥሮታል፡፡
 ማንም ሰው ሊፈታው ወይም ሊበጥሰው የማይችል ጠንካራ አንድነት እንዲፈጠር
አድርጎታል፡፡
 ዜማው በየትኛውም አካባቢ የምትገኝ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት
መዝሙር፣ አንድ ዓይነት ቅዳሴ፣ አንድ ዓይነት ማኅሌት፣ አንድ ዓይነት ሥርዓት
በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፡፡
 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መለያየትና መከፋፈል እንዳይፈጠር ጥበቃውን ዐሳይቷል፡፡
ስለሆነም የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት በመጠበቅ ከፍተኛ ጥቅም አስገኝቷል፡፡
1. ማስተዋል፣ትዕግሥት፣ተስፋ አለመቁረጥን ጽናት፣
ጥረት፣ ስኬት እንማራለን
2. የመጠየቅና የማንበብ ጥቅም እንማራለን
3. ጊዜውን በአግባቡ የመጠቀምና የአገልግሎት ትጋትን
እንማራለን
 ለጸሎት
 ለማስተማር
 ለማንበብ
 ለመጠየቅ
 ሐዋርያዊ አገልግሎት
 ለመጻፍ
5. የጸሎት የሱባኤ የምናኔ ሕይዎትና ዓላፊውን ዓለምና
ንብረቱን መናቅ አለመገዛትን እንማራለን
 ቅዱስ ያሬድ በንጉሡ ዐፄ ገብረመስቀል፣ በካህናቱ፣ በመከንንቱና በምዕመናኑ ዘንድ ትልቅ
ከበሬታ ነበረው ይህንን ጥሎ ምናኔን መረጠ

6. ተተኪ ትውልድ ማፍራትና የማስተላለፍ ትጋት እንማራለን


 አራቱ ደቀ መዛሙርትን ተክ ቷ ል
 ዙር አምባ ዝማሬ መዋሥዕቱን ጽፎ አዘጋጅቱ ደቀ መዛሙርቱን አፍርቷል
ዛሬ ዙር አምባው የዝማሬ መዋሥዕት ምሥሠከር ከቅዱስ ያሬድ ጀምሮ 46ኛ ናቸው
 እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ለነ ልሣነ ዕፍረት የእርሱ ደቀመዛሙርት ያፈራቸው ናቸው

6. ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሕብረት መትጋትን እንማራለን


ቅዱስ ያሬድ በቅዳሴው ፣ በዜማው በአገልግሎቱ ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ጸንታ እንድትኖር
ከዓመት እስከ ዓመት የምንገለገልበትን ሥርዓት ሠርቶልናል በዚህም ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ
ጸንታ ቆይታለች

You might also like