You are on page 1of 9

1.

መግቢያ
የክንዋኔ ጥበቦችን የሆኑትን የትወና፣ የዘፈን፣የሞዴሊንግ እንዲሁም የዳንስ ዝግጅቶችን ደረጃውን በጠበቀ
መልኩ ሊያቀርቡ የሚችሉ ባለሙያዎችን በማሳተፍ እርስ በእርስ የሚደረግ ውድድር ላይ ያተኮረ የቴሌቪዥን
ፕሮግራም ነው፡፡ የፕሮግራሙ ዋነኛ አላማ ደረጃውን የጠበቀ በውበቱ በጥራቱ የመጠቀ ዝግጅቶችን በማቅረብ
ተመልካችን ማዝናናትና በኢንዱስትሪው ውስጥ የጥራት ደረጃን በማመላከት ተፅእኖ መፍጠር ነው፡፡
የሚወዳደሩት ሰዎቹ ሳይሆኑ ሙያቸው ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች በፕሮግራሙ አዘጋጆች አናካኝነት አስፈላጊ
ሞያዊ ስልጠና እና ቴክኒካዊ ድጋፍ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ፕሮግራሙ እሁድ ከ 8 ስዓት አስከ 10 ስዓት የሚቀርብ የመዝናኛ ፕሮግራም ሲሆን ሁሉም ክንዋኔያዊ
ጥበቦች በአንድነት ተሰባጥረው የሚቀርቡ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ፕሮግራም በሴቶች የሚመራ ሲሆን እንዚህም
የፕሮግራም መሪዎች በዘርፉ አንቱ የተባሉና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ የሾው ፕሮግራም አቅማቸውን ያሳዩ
ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዳቸው የክንዋኔ ጥበቦች በስራቸው ብቁ የሆኑ ሶስት ሶስት ዳኞችን
እንዲሁም አምስት አምስት በሙያው ላይ ልምድ ያካበቱ ሰልጣኞች ይኖራቸዋል፡፡
እያንዳንዱ የክንዋኔ ጥበብ እራሱን ችሎ የሚቆምና ፕሮዳክሽናቸውም በተለያየ ቦታ እና ጊዜ የሚካሄድ
ነው፡፡ በዚሁም የመጨረሻ አሸናፊ ተወዳዳሪዎች በየዘርፋቸው ተሸላሚ የሚሆኑ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች
በቀዳሚነት የሚያገኙት የገንዘብ አልያም ተመጣጣኝ የሆነ ቁሳዊ ሽልማት ሲሆን በቀጣይም ለወደፊት
በኢንዱስትሪው ውስጥ ታዋቂ ሆነው ሊቆዩ የሚያስችላቸው የስራ ሁኔታ ይመቻችላቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች
በፕሮግራሙ አዘጋጆች አማካኝነት በሚከፈተው የስልጠና ተቋም በቂ የሆነ ስልጠና እንዲያገኙ ከመደረጉም
በላይ በሰለጠኑበት ዘርፍ ብቃት ደረጃው የተረጋገጠ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል፡፡
2. የፕሮግራሙ ራዕይ
በጥበባዊ ክንዋኔ የሙያ ዘርፍ በጥራትም ሆነ በውበት ደረጃውን የጠበቀ የመዝናኛ ፕሮግራም በማቅረብ
የሞያው ኮከብ ባለሙያዎችን ማስተዋወቅና በኢንዱስትሪው ውስጥ የብቃት ደረጃን ሊያሳይ የሚችል ስራን
በማቅረብ ለውጥ ማምጣት የሚችል አወንታዊ ተፅዕኖ መፍጠር፤
3. የፕሮግራሙ ዓላማ
1. በሞያው የላቀ ክህሎት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች አንጥሮ በማውጣት እና እነርሱን በመጠቀም
ብቃትና ደረጃውን የጠበቀ ስራ ለተመልካች ማቅረብ፤
2. በውበቱ የላቀ ብቃትና ደረጃውን የጠበቀ ፕሮግራም በማዘጋጀት ተመልካችን ማዝናናት እና
ፕሮግራሙን ብሎም የቴሌቪዥን ጣቢያውን ተወዳጅና ተናፋቂ ማድረግ፤
3. በሙያቸው የበቃ ክህሎት ኖሮአቸው ይህንን አቅማቸውን አሳይተው ኮከብ የሚሆኑበትን እድል
ላጡ ባለሙያዎችን አመቺ የሆነ መድረክ መፍጠር፤
4. ጥቂት ድጋፍ ቢያገኙ የሀገራቸው ኮከብ መሆን የሚችሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተታቸውን
በመሙላት ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፤
5. ለክዋኔ ጥበብ ኢንዱስትሪው ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ፈትሾና አንጥሮ በማሳየት እና ብቃታቸውን
እንዲያረጋግጡ በማስቻል ተሳታፊ እንዲሆኑ ማበርከት፤
6. በቀጣዩ አመት እያንዳንዱ የክንዋኔ ጥበብ ዘርፍ በተናጠል እርሱን ችሎ የሚቆም ፕሮግራም
ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማቅረብና ማስፋት፤
7. በቀጣይ ከእያንዳንዱ የክዋኔ ጥበብ ዘርፍ የተመረጡ ከ 40 በላይ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በቋሚነት
የሚሳተፉበት የቴሌቪዥን ፕሮግራም በጣቢያው ላይ በመጀመር ወደ ተግባራዊ ስራ የሚገቡበት
ሁኔታ መፍጠር፤
4. የድርጅቱ የስራ መዋቅር እና ሀላፊነት

የፕሮግራሙ ስራ አስኪያጅ

የኘ ሮግራ ሙ ስራ አስኪያ ጅ

የማ ስታ ወቂ ያ እና ህዝ ብ ግንኙት የኘ ሮዳክሽ ን ክፍል ሃላፊ የቢሮ አስተ ዳደር

የት ው ና እና ሞ ዲ ሊንግ የዳንስና እና ሙ ዚቅ ክፍል የቴ ክኒካል ክፍል ተ ወዳዳሪዎ ች


ክፍል ሃላፋ ሃላፊ ሃላፊ ሃላፊ

አጋዥ

የስልጠ አስ
የዳኞ ች የስልጣ ተ ወዳ ዳኞ ች
ና ተ ወዳዳ ተባ የቀ ረፃ እና የቀ ረፃ ቦታ
ሃላፊ ና ክፍል ዳሪዋ ሃላፊ
ሪዎ ች ባሪ
ኤ ዲ ቲ ንግ ክፍል
ተ ጠሪ እና ግብአት

ች ክፍል ዎች
ሃላፊ

ተ ወዳ
አሰል ተ ወዳ ዳኞ አሰል
ዳኞ ች ዳሪዎ
ጣኝ ዳሪ ች ጣኖች

4.1. የፕሮግራሙ ስራ አስኪያጅ
 ፕሮግራሙን በበላይነት ይቆጣጠራል ስራውን በሀላፊነት ይመራል፤
 በፕሮግራሙ ላይ ማናቸውንም ውሳኔዎች የመስጠት መብት አለው፤
 ግንኙነቱ በቀጥታ ከማስታወቂያ እና ህዝብ ግንኙነት፣ በፕሮዳክሽን ክፍል ሀላፊ እንዲሁም ከቢሮ አስተዳደር ጋር
ይሆናል፤
4.2. የማስታወቂያና የህዝብ ግንኙነት
 ዌብሳይት ዲዛይን ያደርጋል የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ፕሮግራሙን ያስተዋውቃል፤
 በፌስቡክ በዩቱዩብ እንዲሁም በሌሎች መንገዶች የሚሰሩትን የማስታወቂያ ስራዎችን ሀላፊነት ወስዶ ይሰራል፤
 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ ተጋባዥ ተመልካቾችን በእለቱ እንዲገኙ ያደርጋል፤
 በተለያዩ ቦታዎች የሚሰሩ ቢልቦርዶችን ዲዛይን ያደርጋል፤
4.3. የፕሮዳክሽን ክፍል ሀላፊ
 የእያንዳንዱ የክዋኔ ዘርፍ ሀላፊዎችን በበላይነት ይመራል፤
 የቴክኒክ ክፍል ሀላፊ በበላይነት ይመራል፤
 የተወዳዳሪ ጉዳይን የሚመለከት ተጠሪን ይመራል፤
 የስራ እቅድ ፕላን ያወርዳል ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
4.3.1. የቴክኒክ ክፍል ሀላፊ
 የቀረፃና የኤዲቲንግ ስራን በበላይነት ይመራ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
 ፕሮግራሞች በታሰበላቸው ቀን ስለመከናወናቸው ሀላፊነት ወስዶ ይሰራል፤
 ለቀረፃ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ከቀረፃው ቀን 5 ቀን በፊት መሞላታቸውን ያረጋግጣል፤
 ለፕሮግራሙ መሳካት አስፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎችን በጉልበትም ሆነ በሙያ ዘርፍ ያሰባስባል ሀላፊነት ወስዶ
ይቆጣጠራል፤
 ሊቀረፁ የሚያስፈልጉ ቦታዎችን ከቀረፃው በፊት መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል ችግር በሚያጋጥመው ስዓት
ለሚመለከተው አካ ቀደም ብሞ ያሳውቃል፤
4.3.2. የክወና ዘርፍ ሀላፊዎች
 በዳኞቹ የሚቀርበውን ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል፤
 ለስልጠናው መሳካት ሀላፊነት ወስዶ ይሰራል፤
 የተወዳዳሪዎችን ጉዳይ ሀላፊነት ወስዶ ያስተባብራል፤
 ከሚመለከተው ክፍል ጋር በጋራ በመስራት በስዓቱና በጊዜው ስለተፈፃሚነቱ ይከታተላል፤
4.3.3. የተወዳዳሪዎች ሀላፊ
 የተወዳዳሪዎችን ምዝገባ ያስፈፅማል፤
 በውድድር ውስጥ ሲገቡ ተወዳዳሪዎች ፕሮግራም ያወጣል ያስተባብራል፤
 በመመካከር ማንኛውንም አሰልጣኞች ጋር የሚገኛኝ ግንኙነቶችን ሀላፊነት ወስዶ ይሰራል፤
 ሰልጣኞች ስልጠና በአግባቡ መውሰዳቸውን ይቆጣጠራል፤
 ለሰልጣኞች አስፈላጊውን መረጃ በስዓቱ ይሰጣል፤
 ለፕሮዳክሽኑ አባላት አስፈላጊውን መረጃ ያስተላልፋል፤
4.4. የቢሮ አስተዳደር
 በቢሮው ውስጥ የሚሰሩ አስተዳደራዊ ስራዎችን ይሰራል፤
 የሂሳብ ሰራተኛን በመቅጠር ስራዉን ይከታተላል፤
 የህግ ክፍል ባለሙያን በስሩ ያስተዳድራል
 የቢሮ ፀሀፊን ቀጥሮ ያሰራል፤
 ፕሮግራሙን በተመለከተ ባለጉዳዮችን ያነጋግራል ምላሽ ይሰጣል፤
 አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ቢሮውን ወክሎ ውሎችን ይፈራረማል፤
5. የፕሮግራሙ ዋና ባለድርሻ አካላት
የዚህ ፕሮግራም ባለቤት የዚህ ፕሮፖዛል አቅራቢ የሆነችው ማህሌት ሰለሞን ስትሆን ይህንን ፕሮግራም ከኢ.ኤን.ኤን የቴሌቪዥን
ጣቢያ ጋር በጋ ለመስራት ተስማምታለች፡፡ በዚህም የዚህ ፕሮቸግራም ዋና ባለድርሻ አካላት የማህሌት ሰለሞን ድርጅት እና
የኢ.ኤን.ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ ናቸው፡፡ እንዚህ ሁለቱ ድርጅቶች ስራዉን በጋራ የሚሰሩ ሲሆን የስራ ክፍፍላቸው እና የባለቤትነት
መብታቸው እንደሚከተለው የሚገለፅ ይሆናል፡፡
5.1. የማህሌት ሰለሞን ድርጅት የስራ ድርሻ እና ሀላፊነት
 ከኢ.ኤን.ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ህጋዊ የውል ሰነድ ይፈራረማል የተዋዋለውን ውል ያከብራል፤
 የፕሮግራሙ ብራንድ ባለቤት ይህ ድርጅት ነው፤
 ፕሮግራሙን በሀላፊነት ሰርቶ በተያዘለት የአየር ስዓት ለስርጭት ያቀርባል፤
 በፕሮግራሙ ላይ ለሚፈጠር ማንኛውም የሞያዊ እና ቴክኒካዊ ችግር ሀላፊነት ወስዶ ይሰራል፤
 በውሉ መሰረት ኢ.ኤን.ኤንሀላፊነት ወስዶ በሚሰራባቸው ዘርፎች ላይ ለሚፈጠር ችግር ሀላፊነት አይወስድም፤
 ፕሮግራሙ የማስታወቂያም ሆነ የእስፖንሰር ገቢ አገኘም አላገኘም በፕሮፖዛሉ መሰረት ፕሮግራሙን አጣናቅቆ
የመጨረስ ግዴታ አለበት፤
 የሚገኘውን ማስታወቂያ ከቲቪ ጣቢያው ጋ በገባው ውል መሰረት ተፈፃሚ ሆኖ ይከፍላል፤
 በፕሮግራሙ የሚሳተፉ ማናቸውንም ሰዎች ይቀጥራል ያሰራል ይቆጣጠራል እንደአስፈላጊነቱ እርምጃ ይወስዳል ፤
 የፕሮግራሙን ቅርፅም ሆነ አቀራረብ እንዲሁም አተገባበር ሀላፊነት ወስዶ ይሰራል እንደአስፈላጊነቱ የመቀየር
መብት አለው፤
 በፕሮግራሙ ካርድ ላይ ባለ ሙሉ መብት ሲሆን ቴሌቪዥን ጣቢያውም ሆነ ሌላ አካል ከድርጅቱ ፍቃድ ውጭ
መጠቀም አይቻልም፤
 የቴሌቪዥን ጣቢያውን መተዳደሪያ ፖሊሲም ሆነ ማናቸውም ደንብ አክብሮ ይሰራል፤
 የሀገሪቱን ህጎች አክብሮ ይሰራል፤
5.2. የኢ.ኤን.ኤን የስራ ድርሻ
 ከማህሌት ሰለሞን ድርጅት ጋር ህጋዊ ሰነድ ይፈራረማል ተፈፃሚነቱን ይቆጣጠራል፤
 የፕሮዳክሽን ስራውን ሀላፊነት ወስዶ የቀረፃ ማቴሪያሎችን እና ባለሙያዎችን በማቅረብ ቀረፃውን ደረጃውን
በጠበቀ መልኩ ያከናውናል፤
 ተቀርፆ የመጣውን ፕሮግራም በወጣው ፕሮግራም መሰረት በተፈለገው ስዓት የኤዲቲንግ ስራውን ከዳይሬክተሩ
ጋር በመሆን ሰርቶ ያጠናቅቃል፤
 በፕሮግራሙ የተሰጠውን የአየር ስዓት ያከብራል እንደአስፈላጊነቱ ተነጋግሮ አዘጋጁ ካመነበት ሊቀየር ይችላል፤
 የፕሮግራሙን የጥራት ደረጃ ይቆጣጠራል ስራው በቀረበው ፕሮፖዛል መሰረት የማይቀርብ ከሆነ እርምጃ
ይወስዳል፤
 በተዋዋለው ውል መሰረት የተገኘውን ገቢ ይከፍላል
 እስፖንሰር ያፈላልጋል፤
 የፕሮግራሙን አዘጋጅ መብት ያስከብራል፤

የፕሮግራሙ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች


የዚህ ፕሮግራም ቀጥተኛ ተሳታፊዎች

1) የኢ.ኤን.ኤን ቲቪ ጣቢያ፤
2) ማህሌት ፕሮዳክሽን፤
3) ተወዳዳሪዎች፤
4) ዳኞች፤
5) የፕሮግራሙ አዘጋጅ ፣ አስተባባሪ፣ አስተዋዋቂ፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች፤
6) የተወዳደሪ አሰልጣኞች፤
7) አጋዥ ባለሙያዎች፤
8) እስፖንሰር አድራጊዎች፤
9) ፕሮሞሽን እና ፐፕሊኬሽን፤
10) ሂሳብ ሰራተኛ እና የህግ ባለሙያ፤

የፕሮግራሙ አጋር ድርጅቶች

1) እስፖንሰር አድራጊ ተቋሞች፤


2) ፕሮግራሙ የሚቀረፅባቸው ሆቴሎች፤
3) ሲኒማ ቤቶች፤
4) የትያትር አዳራሾች፤
5) ትምህርት ቤቶች፤
6) የመንግስት ተቋማት፤
7) የባህል ቢሮ፤
8) ቴ/ሙ/ት/ስ ተቋማት፤
9) በሀገሪቱ ያሉ የመድረክ ድምፅ እና መብራት ስራ የሚሰሩ ድርጅቶች ፤
6. የፕሮግራም መርሀ ግብር
6.1. የጥር ማስታወቂያ
 ሰኔ 15-30 የሚፈፀም፤
 ኢ.ኤን.ኤን እና የማህሌት ድርጅት በጋራ የማስታወቂያ ቀረፃ ያካሂዳሉ፤
 በከተማው 6 ቦታዎች የሚሰቀሉ ቢልቦርድ ማስታወቂያዎች ተዘጋጅተው ይሰቀላሉ፤
 የቀረፃ ማስታወቂያ ኤዲት ተደርጎ ይጠናቀቃል፤
 ይህ ቀረፃ ከሀምሌ 1-ጳጉሜ 5 ባለው ጊዜ የሚተላለፍ ይሆናል፤
6.2. የተወዳዳሪዎች ቅበላ እና አሰሳ
 ከሀምሌ 1- ነሀሴ 30 ተፈፃሚ ይሆናል፤
 ተመዝጋቢ ተወዳዳሪዎች ሀሎ ካሽን ፣የስልክ መስመርን ፣የፕሮግራሙን ዌብሳይት እንዲሁም የሚዘጋጁ ቢሮዎችን
በመጠቀም ይመዘገባሉ፤
 ዳኞች የፕሮዳክሽን አባላትን በመያዝ የሚያምኑባቸውን ባለሙያዎች ያሉበት ድረስ እየሄዱ በማሰስ ለውድድር
ይጋብዟቸዋል፤
 ከሀምሌ 15- ነሀሴ 30 ድረስ ሁሉም ዳኞች ፕሮግራም አግኝተው የአሰሳ ቀረፃቸውን ያካሂዳሉ፤
 ይህ ቀረፃ ከመስከረም 1-30 ፕሮግራም ሆኖ በቴሌቪዥን የሚተላለፍ ይሆናል፤
 ከሁሉም የክህሎት ሞያ በአጠቃላይ 40 ተወዳዳሪ ይመለመላል 15 ተዋናየ ፣ 15 ሙዚቀኛ ፣ 5 ዳንስ ፣ 5 ሞዴል፤
6.3. የተመዝጋቢ ተወዳዳሪዎች ማጣሪያ
 ከመስከረም 2-25
 ሁሉም የክህሎት ሞያዎች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት በተዘጋጀላቸው የቀረፃ ቦታ በመገኘት
ተወዳዳሪዎችን ያጣራሉ፤
 ተወዳዳሪዎች በተዘጋጀላቸው ፕሮግራም መሰረት ተገኝተው ውድድራቸውን ያካሂዳሉ፤
 አጠቃላይ ኦረንቴሽን ሁሉም ተወዳዳሪዎች ሁሉም ዳኞች በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር ይካሄዳል፤
 በእለቱ የመክፈቻ ስነስርዓት አጭር ትያትር ፣ ዳንስ ፣ ፋሽን ሾው ዘፈን በተጋባዥ ባለሙያዎች ይቀርባል
የከተማው ታዋቂ ሰዎች እንዲገኙ ይደረጋል፤
 ይሄ የማጣሪያ ውድድር እና የመክፈቻ ስነስርዓት ከጥቅምት እስከ ታህሳስ 15 ለሁለት ወር ከሁለት ሳምንት
በቴሌቪዥን ፕሮግራም ይተላለፋል፤
 ከሁሉም የክህሎት ሙያ በአጠቃላይ 70 ተወዳዳሪዎች ይለያሉ 25 አክተር፣ 25 ሙዚቃ ፣ 10 ዳንስ 10 ሞዴል፤
6.4. የመጀመሪያ ዙር ልምምድ
 ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 የሚፈፀም ይሆናል፤
 110 ተሳታፊ ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፤
 ተወዳዳሪዎች በተመደበላቸው አሰልጣኝ መሰረት ስልጠና ይወስዳሉ ለቀጣይ ዙር ለሚያቀርቡት ስራ ዝግጅት
ያደርጋሉ፤
 ተወዳዳሪዎች የህይወት ታሪካቸው ፕሮፋይል ይሰራላቸዋል ኢንተርቪው ይደረጋሉ፤
 ከታህሳስ 15-22 ለሁለት ሳምንት ፕሮግራም ሆኖ ይቀርባል፤
6.5. የመጀመሪያ ዙር ውድድር ቀረፃ
 ከህዳር 1-15 የሚፈፀም ይሆናል፤
 እያንዳንዱ የክጅሎት ዘርፍ በተዘጋጀለት ቦታ የተወዳዳሪዎች ቀረፃ ያካሂዳል፤
 በዚህ ዙር 110 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ 40 ተዋናይ፣40 ሙዚቀኛ፣ 15 ተወዛዋዥ እና 15 ሞዴል፤
 ከጥር 1-መጋቢት 7 ለሁለት ወር ከአንድ ሳምንት የሚታይ ፕሮግራም፤
6.6. የሁለተኛው ዙር ልምምድ
 ከህዳር 20-30 ተፈፃሚ ይሆናል፤
 68 ተወዳዳሪዎች 24 ተዋናይ፣24 ሙዚቀኛ፣10 ዳንሰኛ ፣10 ሞዴል ተሳታፊ ይሆናል፤
 ተወዳዳሪዎች ልምምድ ያደርጋሉ ልምምዳቸው ይቀረፃል፤
 መጋቢት 15 ለአንድ ቀን ሾው ሆኖ ይቀርባል፤
6.7. ሁለተኛ ዙር ወድድር ቀረፃ
 ከታህሳስ 1-10 ተፈፃሚ ይሆናል፤
 68 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፤
 ሁሉም ክህሎቶች በተዘጋቸላቸው የጊዜ እና ቦታ ፕሮግራም ተገኝተው ውድድሩ ይካሄዳል አላዎች ይለያሉ፤
 ከዚህ ውድድር 12 ተዋናይ፣ 12 ሙዚቀኛ፣ 8 ሞዴል ፣ 6 ዳንሰኛ ተጣርቶ ይቀራል በአጠቃላይ 38 ተወዳዳሪዎች
ይቀራሉ፤
 ይህ ቀረፃ ከመጋቢት 22-30 ለአንድ ወር ከ 2 ሳምንት ጊዜ ይተላለፋል፤
6.8. የሶስተኛ ዙር ዝግጅት
 ከታህሳስ 11- ጥር 15 ድረስ ተፈፃሚ ይሆናል፤
 38 ተወዳዳሪዎች የሚያሳፍ ይሆናል፤
 የተወዳዳሪዎች የውድድር ስራ ዝግጅት ይካሄዳል፤
6.9. የሶስተኛ ዙር ውድድር የቀረፃ ጊዜ
 ከጥር 15--የካቲት 30 ድረስ ተፈፃሚ ይሆናል፤
 38 ተወዳዳሪዎች ከተዘጋጁላቸው አዘጋጆች በመታገዝ በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ቀረፃቸውን ያካሂዳሉ፤
 በዚህ ውድድር 8 ተዋነወያን፣8 ዘፋኝ፣4 ሞዴል፣4 ዳንሰኛ ይቀራሉ በዚህም 24 ተወዳዳሪዎች ይቀራሉ፤
 ከግንቦት 7-30 ለአንድ ወር የሚቀርብ ፕሮግራም፤
6.10. የአራተኛ ዙር ውድድር ዝግጅት
 ከየካቲት 30- ግንቦት 1 የሚፈፀም ይሆናል፤
 ተወዳዳሪዎች የመዝጊያ ፕሮግራም ዝግጅት ልምምድ ስክሪፕት ይወስዳሉ፤ ተጋባዥ ባለሙያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ
ምልመላው አብሮ ይካሄዳል፤
 ተዋናይ የትያትር ልምምድ ይጀምራሉ፤
 ሙዚቀኛና ዳንሰኞች የኮንሰርት ዝግጅት ልምምድ ይጨርሳሉ፤
 ሰኔ 1-ሰኔ 15 የሚተላለፍ የሁለት ሳምንት ፕሮግራም፤
6.11. አራተኛ ዙር ውድድር
 ከግንቦት 1- ሰኔ 30 ተፈፃሚ የሚሆን፤
 ተዋንያን የትያትር ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ፤
 ዳንሰኞች የዳንስ ፕሮግራም ከሙዚቃ ኮንሰርት ጋር ያቀርባሉ፤
 የፋሽን ሾው ፕሮግራም ይቀርባል (ሊቀር ይችላል )፤
 24 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ (ተጋባዥ ባለሙያዎች እንደአስፈላጊነታቸው ይወሰናል)፤
 ከሰኔ 22-ሀምሌ 15 ለአንድ ወር የሚተላለፍ ፕሮግራም፡፡
6.12. የተወዳዳሪዎች ቅስቀሳ እና ልምምድ
 ከሀምሌ 1 አስከ ነሀሴ 30 የሚፈፀም፤
 የመዝጊያ ፕሮግራም ዝግጅት የሙዚካ ድራማ ልምምድ፤
 የማስታወሻ ፕሮግራሞች፤
 ከሀምሌ 15- ነሀሴ 7 ቅስቀሳ እና ትውስታ ይካሄዳል፤
 ከነሀሴ 15 - ጳጉሜ የሚዚካ ድራማ ዝግጅት ይተላለፋል፡፡
6.13. የመዝጊያ ፕሮግራም
 መስከረም 1 የሚከናወን ላይቭ ፕሮግራም፤
 ካልተቻለ ቀድሞ የሚቀረፅ ፕሮግራም፤
 አሸናፊዎች ይለያሉ ሽልማት ይወስዳሉ፡፡

You might also like