You are on page 1of 5

ትረካዊ ድራማ “ክርስቶስ ወገብረ ክርስቶስ”

በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊው ድንቅ ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ በአንድ የስዕል ትምህርት ቤት
ያስተምር ነበር፡፡ የሚያስተምራቸውም ከተለያየ የዓለም ክፍል የተወጣጡ ነጭ፣ ጥቁር፣ አማኒ፣ ኢአማኒ፣
ሴቶች እና ወንዶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ቀድሞ በሚያውቁት እውቀት አዕምሯቸውን የገነቡ ፤ የራሳቸው
የሆነ አቋም እና አመለካከት ያላቸው በአንድ ክፍል ውስጥ ያሉ ነገር ግን በተለያየ የአስተሳሰብ ደረጃ የሚገኙ
ተማሪዎች ነበሩ፡፡

ሠዓሊው ገብረ ክርስቶስ እነዚህን በአንድ ክፍል ግን በተለያየ ሃሳብ እና እምነት ውስጥ ያሉትን ተማሪዎቹን
አንድ በሚያደርገው ጥበብ፤ አንድ በሚያደርገው ሥዕል አንድ እያደረገ ያስተምራቸው ነበር፡፡
ሲያስተምራቸውም ጥበብ ለራቀበት እያረቀረበ ለረቀቀበት እያጎላ በአጠገባቸው ሲፈልጉት እየተገኘ
ያስተምራቸው ነበር፡፡

ጌታ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ዮሐንስን እንሚወደው ሁሉ፤ እኛም ደግሞ ከአንዱ የእጅ ጣታችን ሌላውን
እንደምንወደው ሁሉ ይህ ሠዓሊም ከሌሎቹ አብልጦ የሚወዳቸው ሁለት ድንቅ ጎበዝ ተማሪዎች ነበሩት፡፡
ዘወትርም ትምህርቱን አስተምሮ ከጨረሰም በኋላ ልዩ የቤት ሥራ ይሰጣቸውም ነበር፡፡

እንደ ተለመደው በአንዲቱ ቀን የትምህርት ክፍለ ጊዜ መጠናቀቅ በኋላ ለነዚህ ሁለት ድንቅ ተማሪዎቹ
እንደተለመደው የቤት ሥራ ሰጣቸው፡፡ ይህ የቤት ሥራ ለሁለቱም አንድ አይነት ቢሆንም በተለያየ አመለካከት
ያላቸው እነዚህ ሁለት ተማሪዎች መምህራቸው ካሰበው በተለየ እይታ አይተው ሁለቱም የቤት ሥራቸውን
ለመስራት ማውጠንጠን ጀመሩ፡፡

አንደኛው ተማሪ ይህ የቤት ሥራ ቀላል ቢሆንም የተለየ እና ውብ አድርጎ ሊስለው ፈልጓል፡፡ ሁለተኛው ተማሪም
በየትኛው ቀለም ቢስለው የተሻለ ሊሆን እንደሚችል ያስባል፡፡ ግን አሁንም የልባቸው አልደረሰም፡፡ ያስባሉ፤
ይንቆራጠጣሉ ፤ ግን አሁንም ምንም የተሻለ ሃሳብ እና ዘዴ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡

ስለዚህም ይህንን በሠዓሊው በገብረ ክርስቶስ የተቃኘውን ያንን በጎ አዕምሯቸውን ወደ ጎን በመተው


በጎጠኝነት እና በዘረኝነት የተበዘበዘውን ጭንቅላታውን ሊጠቀሙበት አሰቡ፡፡ አስበውም አልቀሩ ፡፡ ሸራውን
ዘረጉ ቀለሙን ሰደሩ፡፡ ባያስደስታቸውም አላስከፋቸውምና ዋናውን የስዕሉን ሃሳብ ትምህርት ረስተው
በራሳቸው ዓለም ውስጥ ሆነው ሳሉት፡፡

ሠዓሊው ገብረ ክርስቶስ በወረቀት ጽፎ የሰጣቸው የቤት ሥራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
በቀራንዮ አደባባይ ላይ ከነስቃዩ እና ከነመከራው ፤ ከመሐሪነቱ እና ከፈራጅነቱ ጋር አስተባብረው እንዲስሉ
ነበር፡፡

ይህንን ስዕል በአንድ ቀን ጨርሰው መምህራቸው ገብረ ክርስቶስን ለማስደመም እና የመምህራቸውን አባታዊ
እና ሙያዊ አድናቆት እና ፍቅር ለማግኘት በዚያች ዕለት ጨርሰው ለማደር ሲስሉ የሥዕሉን ብርዕ ሲያሾሉ ፣
ቀለሙን ሲቀይጡ እና ሲስሉ አደሩ፡፡ እየሳሉም መሸ እየሳሉም ነጋ ፡፡ ሲጠበቡ አደሩ ፡፡ በራሳቸው ሃሳብ

የደ . ከ. አ . አረጋዊ እና ቅ . ገብረ ክርስቶስ ቤ . ክ ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት


ኪነ - ጥበብ ዋና ክፍል 1
ትረካዊ ድራማ “ክርስቶስ ወገብረ ክርስቶስ”

ክርስቶስን ከአይሁዳውያን ሃሳብ በከፋ ሃሳብ ሸራቸው ላይ ሲያሰቃዩት እና ሲሰቅሉት አደሩ፡፡ እያሳሉት አድረው
እያሳሉት ነጋ፡፡

በነጋውም ተማሪዎቹ በሙሉ ወደ ትምህርት ቤቱ በጊዜ ከትመው መምህራቸውን መጠባበቅ ይዘዋል፡፡ ነገር
ግን ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ መምህራቸው አርፍደዋል፡፡ ተማሪዎቹም የራሳቸውን ወሬ ይሰልቁ ጀመር፡፡
አንዱ ስለቤቱ አንዱ ስለ አዳሩ አንዲቱ ስለፍቅሯ አንዲቱም ስለጓዳዋ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ነገር ግን የተማሪው ቶሎ
መምጣት እንጂ መምህሩስ ፣ ሠዓሊውስ አላረፈዱም ነበር፡፡

ሠዓሊው ገብረ ክርስቶስ የጀንበሯን መፈንጠቅ ተከትሎ በአዲስ ስሜት እና መንፈስ ሊያስተምር ይልቁንም
ለነዚያ ለሚወዳቸው ለሁለቱ ተማሪዎቹ የሠጠውን የቤት ሥራ ለማየት ጓጉቶ፤ ያሰብኩትን ሃሳብ አግኝተውት
ይሆን ወይስ አደናግሯቸው ትተውት ይሆን ወይስ አቅቷቸው ትተውት ይሆን ወይስ ግሩም ሥዕል ያሳዩኝ ይሆን
እያለ ራሱን እየጠየቀ በእነዚህ ዥዋዥዌ ሃሳቦች መካከል ሲመላለስ ሳያስበው ከትምህርት ቤቱ በር ደረሰ፡፡

ጥያቄዎቹን እና ሃሳቡን ጥሎ በውጪ የተቀመጡትን ተማሪዎቹን በፍቅር በአባታዊ መሽቆጥቆጥ ሰላምታ


ሰጣቸው፡፡ ሰላምታ አሰጣጡን የተመለከተ አልፎ ሂያጅ ከግዳጅ ተርፎ ከረጅም ዓመት ቆይታ በኋላ የመጣ
ወታደር እንጂ ትናንት ከሰዓት ቻው ብሏቸው የሄደ መመህራቸው አይመስልም ሊል ይችላል፡፡ ከሰላምታው
ለጥቆ ተማሪዎቹም ይዟቸው ወደ ማስተማሪያ ክፍሉ ዘለቀ፡፡

ወደ ክፍሉም ሲገባ እኒያ ድንቅ ተማሪዎቹ የሰጣቸውን የቤት ሥራ ሰርተው በዚያው እንቅልፍ ድብን አድርጎ
ሞት ቅልቅል በሚመስል ሁኔታ ወንበራቸው ላይ ተቆልምመው ሲያንኮራፉ ተመለከተ፡፡ በመጀመሪያ
አዘነላቸው፡፡ እንደ አባትነቱም ሳይተኙ ሲለፉ ማደራቸውን ሲመለከት ከልቡ አዘነላቸው፡፡

ቀስ በሎ ሄዶም እንደ መወዝወዝ አድርጎ ከእንቅልፋቸው አነቃቸው፡፡ ሲነሱ ሕልምም ይመስላቸዋል፡፡ እውንም
ይመስላቸዋል፡፡ ድካም እና እንቅልፍ ድንግርግር ያለ ስሜት ውስጥ ከቷቸዋል፡ ግን ደሞ ከፊታቸው
መምህራቸውን ያን ጠቢብ ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስን ሲያዩ በቦታህ እንደተባለ ወቶአደር ተስተካክለው እንቅልፍን
ወዲያ ግድም አሽቀንጥረው ጥለው በፈገግታ ተመለከቱት፡፡

መምህሩ ገብረ ክርስቶስም ለእንዚያ ድንቅ ተማሪዎቹ ያንን የሚያስቀና እና የሚያስደስት የተለመደ
ሰላምታውን ሰጣቸው፡፡ አቀፋቸው ሳማቸውም፡፡ እነርሱም የሰጣቸውን ጨርሰዋልና ለማሳየት እና
ከመምህራቸው እንደ ተለመደው የሚሰጣቸውን አድናቆት እና አስተያየት ለመቀበል ቅጣት ምት
እንደሚመታለት በረኛ አቆብቁበው ቁመዋል፡፡

መምህሩም የተሸፈነውን የመጀመሪያውን ተማሪ የሥዕል ሸራ ሽፋኑን አንሸራትቶ አየው፡፡ ቀጥሎም


የሁለተኛውን፡፡ ግን ከወትሮው በተለየ ፊቱ ላይ ግርታ እና ቅር መሰኘት ይታይ ነበር ፡፡አንደኛው ተማሪ
ክርስቶስን በጥቁር ሰው አምሳል ስሎ ፤አንደኛው ደሞ ክርስቶስን በነጭ ሰው አምሳል ስሎ ነበር፡፡ ገብረ
ክርስቶስም ሃሳባቸውን ከውጣቸው ያየ በሚመስል ሁኔታ ፊቱ ላይ ከፊል ዳመና የመሰለ ግርታ ታየ፡፡

የደ . ከ. አ . አረጋዊ እና ቅ . ገብረ ክርስቶስ ቤ . ክ ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት


ኪነ - ጥበብ ዋና ክፍል 2
ትረካዊ ድራማ “ክርስቶስ ወገብረ ክርስቶስ”

አንደኛው ተማሪ የመመህሩን ፊት አይቶ ግር እንዳለው በማየት ምናልባት ግርታው በማስረዳት ከለቀቀ ብሎ . .
. . . ልክ የተቃኘውን ቅኔ ሊፈታ እንደ ተዘጋጀ ተማሪ ታጥቆ ቆመ፡፡ እንዲህም ብሎ ማስረዳት ጀመረ፡፡
“መምህሬ ሆይ በሰጠኸኝን የቤት ሥራ እንዲህ አድርጌ ስዬዋለው፡፡ ከወትሮውም በተለየ ክርስቶስን በጥቁር
ቀለም አድምቄ የአንድ ጥቁር ሰው ፊት መልክ እንዲይዝም አድርጌዋለው፡፡ ምክንያቱም ጥቁር ኃያል ነው፡፡
ለዚህም ኢትዮጵያውያን ነጫጭባዎችን ማሸነፋችሁን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡ደግሞም ክርስቶስ
የተወለደው ከጥቁሮች ወገን ከምትሆን አንዲት ሴት ነው፡፡ ደግሞም ነጮች ክፉ ናቸው፡፡ ክርስቶስ ከደጋጎቹ
ከጥቁሮች ወገን እንጂ ከክፉዎቹ እና ከቀማኞቹ ከነጮች ወገን ስላልሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ በእውነት
በጥቁር ቀለም መሳሌ ቦታውን እና ጊዜውን የሚያውቅ ሠዓሊ የሰራው ያስመስለዋል” እያለ የሚያስረዳ
መስሎት እንደ መርዶ አርጂ ፍሬ አልባ ዲስኩሩን ይደሰኩር ነበር፡፡

በሠዓሊው በገብረ ክርስቶስ ፊት ላይ ያለው ግርታ ሳይለቅ ወደ ሁለተኛው ተማሪው ዘወር ብሎ አስረዳኝ
በሚል እይታ ዓይን ዓይኑን የሙጥኝ አለ፡፡ ሁለተኛው ተማሪም በመጀመሪያው ተማሪ እጅግ ተናዶ እና በሽቆ
ኖሮ ለማስረዳት ቃላት እስከሚያጥረው ድረስ ለማስረዳት ቸኮለ፡፡ እንዲህ ሲልም ተናገረ፡፡ “ክርስቶስማ ነጭ
ነው፡፡ ጥቁር ደካማ ነው፡፡ በነጭ ሲገዛ የዋለ እንደነበር በታሪክ ማየት ይቻላል፡፡ ደግሞም ክርስቶስ የዘር ግንዱ
ከነገሥታት ዘር ነው፡፡ በታሪክም ከጥቁር ወገን ነገሠ ተብሎ ሲወራም ሰምተንም አናውቅም፡፡ ክርስቶስ ኃያል
አምላክ ነውና በነጭ ሰው ፊት አምሳል የሳልኩት” ብሎ ግዳይ እንደጣለ ጀግና የጎቢጥ ጓደኛውን ያየው ጀመረ፡፡

ሠዓሊው ገብረ ክርስቶስም በጥሞና ሲያዳምጥ ቆይቶ ንዴቱ እስከሚታወቅበት ድረስ በእጅጉ ተበሳጨ፡፡
ተንቆራጠጠም፡፡ ተማሪዎቹ ማን ስሕተት ሰርቶ ይሆን እያሉ እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀምረዋል፡፡

ሠዓሊውም “እውነት ክርስቶስ በደሙ ነው ወይስ በፊቱ ቀለም ነው ያዳነን” ሲል በክፍሉ የነበሩት ተማሪዎች
ጠየቃቸው፡፡ ከዚያም መልሱን ሳይጠብቅ ሁሉንም ተማሪዎች እንዲከተሉት አዝዞ በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ
ካለ ኮረብታማ መሰል ዳገት ላይ ይዟቸው ወጥቶ መሳል ጀመረ፡፡
.
.
.

የደ . ከ. አ . አረጋዊ እና ቅ . ገብረ ክርስቶስ ቤ . ክ ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት


ኪነ - ጥበብ ዋና ክፍል 3
ትረካዊ ድራማ “ክርስቶስ ወገብረ ክርስቶስ”

እዩት ይሄን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ፤ በቀይ እየወጋ፤ በደም እየሣለው፤


እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው
ቀራንዮ ሆነ የወጠረው ሸራ
ጎልጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ
አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ፡፡

ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር


ብሩሹን አሹሎት እንደ ጎኑ ጦር
እየወጋ ሣለው በጣም ጨከነበት
ገብረ ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ
የቆዳው ዓይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ

እየወጋ ሣለው
እየሣለ ወጋው
ዘሩ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር
የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው ሀገር
እንዳንለው ፈረንጅ፤ እንዳንለው ጥቁር፤ እንዳንለው ቀይ
በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ
በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው
በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው
ከቀናት ባንዱ ዕለት
ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩበት
በተመጻዳቂ የምሑር አንደበት
ባንዱ አፍ ሲጠቁር
ባንዱ አፍ ሲነጣ
መታገስ አቃተው ሠዓሊው ተቆጣ!

ስሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ


ሐሣቡን የሚገልጽ ቀለም እስከሚያጣ
ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ
አልወጣልህ አለው ፍቅርን ሥሎ ሥሎ

የደ . ከ. አ . አረጋዊ እና ቅ . ገብረ ክርስቶስ ቤ . ክ ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት


ኪነ - ጥበብ ዋና ክፍል 4
ትረካዊ ድራማ “ክርስቶስ ወገብረ ክርስቶስ”

ሥሎ … ሥሎ … ሥሎ …
ፍቅርን ሥሎ ሥሎ
በሣለው እየወጋ በደማው እየቀባ
ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም
እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይኽ አይደለም
እያለ እስኪናገር የሥዕሉ አንደበት
ገብረ ክርስቶስም ለክርስቶስ 'ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት
በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት

ቀለም ቀይ ቀለም
የደም ቀለም የጥላ ቀለም
የሁሉም ነው እንጂ የማንም አይደለም
ፍቅር ዘር አይደለም

ዲ/ን ያሬድ አበባው

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን /ቴዲ አፍሮ/

ዲ/ን ስለሺ ወርቁ


ሰዓሊ ኤርምያስ መኮንን

ዲ/ን ያሬድ አበባው

ሰዓሊ ኤርምያስ መኮንን

ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ - አርክቴክት በቃሉ


ነጭ ተማሪ - ሺመልስ ዓለሙ
ጥቁር ተማሪ - ዲ/ን አካል በለጠ
ተማሪ 1 – አዲስዓለም ኃ/ሚካኤል
ተማሪ 2 -ትዕግሥት ሙሉቀን

የደ . ከ. አ . አረጋዊ እና ቅ . ገብረ ክርስቶስ ቤ . ክ ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት


ኪነ - ጥበብ ዋና ክፍል 5

You might also like