You are on page 1of 4

t he

eacher Bi-annual Bulletin November, 2011

የቆሎ ት/ቤት
ቤት - መካነ ቅኔ ሊቃውንት
ያሲን ዑመር
የኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት

ሁለት ሺህ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ የማንነታችን በሚገኘው ሩቅ ነገ ውስጥ የዕውቀት ስንቁንና


መገለጫ የሆነው ይህ ጥንታዊ ት/ቤት አገሪቱ የጥበብ ትጥቁን አሻግሮ ማየት የሚችል ባለ
በተጓዘችባቸው ረጅም ዘመናት ተማሩ ራዕይ መሆኑንም እንዲሁ፡፡
የተባሉትን ሊቃውንትና የሀገር መሪዎችን ያፈራ
በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪን ምንነት በውል
የተከማቸና የዳበረ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብት
ለመረዳት በአብዛኛው ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ
ለትውልድ ያስተላለፈ የትምህርት ቅርስ የአበው
ከሚሄድበት አንስቶ ከመሰሎቹና ከመምህሩ
ውርስ ነው(ዓለሙ፤1999)፡፡
ጋር እስካለው የአቀባበልና የአብሮ መኖር
እንደመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ መስተጋብር ድረስ ያለውን ሂደት በጥልቀት
መግቢያ አጅግ በርካታ የቅኔ ሊቃውንት የተቀዱባት ባህር መመርመር ተገቢ ነው የሚሉ ጥናትና ምርምር
ናት፡፡ ሊቃውንቱ አዕምሮአቸው ቅኔ ምስጢር አድራጊዎች አሉ፡፡ ይህንን ሂደት ሊቀ-ጉባኤ
ቅኔ፣ ሙዚቃ፣ ሥነ-ጽሑፍ ፣ ሥዕል ለሠለጠነም
የሚያፈላ፤ ስነ-ልቡናቸው በዕውቀት የተመላ ታረቀኝ (ጥቁም ሥራ)
ሆነ በመሠልጠን ላይ ላለ አንድ አገር በእጅጉ
ነበሩ፡፡ ጥልቅና ምጡቅ በሆነ ተሰጥዖአቸው
አስፈላጊ ነው ፡፡ የቅኔውን መንገድ ብናውቀው
እየተመሩ የቅኔን አዝመራ ለፍሬ ያበቁም ነበሩ፡፡
ተወዳዳሪ የሌለው የቅኔ አዝመራ እናመርታለን፡ ፡
ከሙዚቃ ባህር እንደፈለግን መቅዳት ብንችል ከላይ በጥቅሉ የቀረበውን
ስቃይን ልንታገስ የምንችልበትንና የትዕግስት መንደርደሪያ ታሳቢ በማድረግ በጥናታዊ ፅሁፉ
ጣፋጭ ፍሬ የሆነችውን ታላቅ ደስታ በኢትዮጵያ ባህላዊ የትምህርት ስርአት ውስጥ
የምንቀዳጅበትን መንፈስ እንፈጥራለን፡ ፡ የስነ- ጉልህ ስፍራ ያላቸውን የቆሎ ተማሪ ምንነትና
ጽሁፍ በረከትን መቋደስ ብንታደል በአንድ የቅኔ ትምህርት ሁለንተናዊ ገጽታ ለመዳሰስ
በኩል መጥፎ ልማድንና መጥፎ እምነትን፤ ጥረት ይደረጋል፡፡በጥረቱም፤- የቆሎ ተማሪ
መጥፎ አስተዳደርንና መጥፎ ህግን በማስወገድ ማነው ?ቅኔ ምንድን ነው ? የቅኔ አይነቶች
(በሌላ ወገን ከፍ ያለ ትምህርትና አብነት ምን ምን ናቸው? የቅኔ ግዕዛዊ ዋና ዋና ክፍሎች
በመቅሰም) ተጭኖን የኖረውን ድንቁርና ምንድን ናቸው? የቅኔዎቻችንን አዝመራ ለፍሬ
እናስወግዳለን፤መንፈሳችንን እናጎለምሳለን ( አቤ፤ ያበቁ ስመ-ጥር ባለቅኔዎች የት የት ይገኛሉ?
1962) ፡፡ እነማንስ ናቸው? ?የሚሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡
በዚህ መነሻነት ለዕውቀት ያደላ፤ድንቁርናን በ ቅ ደ ም ተከተላቸው ምላሽ
የጠላ ብሩህና ብልህ ወላጅ ስለልጁ የወደፊት ያገኛሉ፡፡በመጨረሻም የሀገራችን የቆሎ ት/ቤትና
ዕጣ ፈንታ ማሰብና ማስተዋል ያዘወትራል፡፡ የቅኔ ጥበብ መጻኢ ዕጣ ፈንታ ምን መሆን
የአብራክ ክፋይ ልጁ ዕውቀትና ጥበብን ፍለጋ እ ን ደ ሚ ገ ባ ው የ ሚ ጠ ቁ ም ማ ጠ ቃ ለ ያ
እንዲተጋ ይመክራል፡፡ከቀደሙት አዋቂዎች ተካትቷል፡፡
የዕውቀትና የጥበብን ማዕድ በመቋደስ
1.1 የቆሎ ተማሪ ማነው ?
ስነጥበብን፤ስነጽሁፍንና ኪነጥበብን ገንዘቡ
እንዲያደርግ ይዘክራል፡፡ በልጁ የአላዋቂነት የቆሎ ተማሪ ማለት ለዕውቀት ሲል
ጨለማ ላይ የዕውቀት ብ ር ሃ ን ከወገኑ ተለይቶ፤ቀዬውን ጥሎ፤ከሀገሩ ኮብልሎ፤
ወ ደ ሚ ፈ ነ ጥ ቅ በ ት ና የ ጥ በ ብ ወ ጋ ገ ን ከውሻ ጋር ታግሎ
ወደሚንተገተግበት የቆሎ ትምህርት ቤት ሄዶ ቢያገኝ ቁራሽ እንጀራ፤ቢያጣም ጥሬ ለምኖ፤
እንዲማር ይፈቅድለታል፡፡ ልጁ በቆሎ ተማሪነት ደበሎ ለብሶ፤ አኩፋዳ ተሸክሞ፤ ጉዝጓዝ
አንድ ያለውን የደበሎ ለባሽነት ጉዞ ደረጃ ተንተርሶ የሚኖር
በደረጃ በንባብ ቤት፤ በቅዳሴ ቤት፤ በዜማ
ቤት፤በቅኔ ቤትና በመጽሐፍ ቤት የዕውቀትና ለቀለም የተሰደደ፤ ለጥበብ የሚንከራተት
የጥበብ ጎዳና አቋርጦ የሊቃውንትነት ካባ ደርቦ መፃኢውን ኩነት አርቆ ተመልካች ነው (ሊቀ-
“ይበል” እንዲሰኝለትና እንዲመረቅለት ጉባኤ ታረቀኝ በ“ብሌን” ቁ.4፤ 1999 ውስጥ)
ይመኛል፡፡ ፡፡

ለኢትዮጵያ ሥልጣኔ የማይናቅ ከገለፃው የቆሎ ተማሪ ዕውቀትን


አስተዋጽዖ ላደረገው ጥንታዊው የቆሎ ፍለጋ የባይተዋርነትን አደጋና የረሃብን አለንጋ
ትምህርት ቤት ምስጋና ይግባውና እጅግ በርካታ የሚጋፈጥ መንፈሰ-ጽኑና ቆራጥ መሆኑን
ደበሎ ለባሽ ተማሪዎች የሊቃውንትነት ካባ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የሆዱን ረሃብ በመንፈሱ
ደርበው የየወላጆቻቸው ኩራት የሆኑባቸው ጥጋብ የሚያካክስና ከጉስቁልናው አድማስ ማዶ

65
Faculty of Teacher Education, St. Mary’s University College
t he
eacher Bi-annual Bulletin November, 2011

እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡ በመሆኑም ቅኔ ማለት ሲተረጎም ሰው


አንድ ተማሪ ወደ ማንኛውም የቅኔ ከራሱ አዕምሮ አንቅቶ ምስጋና ለማቅረብ
ቤት ሲሄድ በአብዛኛው ከቤተሰቡ
1.2. የቅኔ ትምህርት ሁለንተናዊ ገጽታ ሲያስብና ምሳሌ መስሎ፤ ምሥጢር አሻሽሎ ፤
ተሰውሮ( ተደብቆ) ነው፡፡ 1.2.1. ቅኔ ምንድን ነው ? ግጥም በመግጠም የልቡናውን ዕውቀት ፤
የሚይዘው አንዲት አኩፋዳ፤ አንዲት
ለምድና አንዲት ነጠላ አይሏት ጋቢ የአዕምሮውን ርቀት የሚገልፅበት ፤ ዕውቀቱን
ለቅኔ ምንነት ብያኔ ለመስጠት እጅግ
መለስተኛ ኩታ ሊሆን ይችላል፡፡ ስንቁ ግን የሚያስተምርበት ፤ የሰሚንም አዕምሮ
የማርያም ስምና የገበሬው ችሮታ በርካታ ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን የሚከተሉት
የሚያነቃቃበትና የሚያስታውቅበት የግጥም
ነው፡፡…ተማሪው ከሄደበት ተማሪ ቤት ለአስረጂነት ተጠቅሰዋል፡፡
ሲደርስ ተማሪዎች “ መኖር “ ብለው ጥበብ ነው ፡፡ ቅኔ በቃልና በኅሊና የሚያዝ
አክብረው ፤ እግሩን አጥበው ፤ ቅኔ ቀነየ ገዛ ካለው ግስ የተገኘ ወይም
ከለመኑበት አኩፋዳ ቁራሽ አዋጥተው ቀነየ ገዛ ያለውን አንቀፅ ያስገኘ ጥሬ ዘር ነው(
መኝታ ለቀው ያሳድሩታል፡፡ በማግስቱ መልክአ ብርሃን አድማሱ፤ 1963 )፡፡
መምህሩ ፊት በተማሪዎች አለቃ
አማካይነት ይቀርባል፡፡… መምህሩ ቅኔ የሚባለው ጥሬ ዘር መነሻው
ስሙንና የመጣበትን ምክንያት ጠይቀውና
አረጋግጠው ጎጆና ባልደረቦች መገኛው “ቀነየ ገዛ ካለው ግስ ሲሆን መገዛት
እንዲሰጡት ያዙለታል፡፡ የልመና ተብሎ በቀጥታ ይተረጎማል፡፡ ተቀነየ
መንደርም እንደሌሎቹ ወይም ከሌሎቹ ለእግዚአብሄር በፍርሃት እንዲል፡፡ አገዛዙም
ጋር ተካፍሎ ይከለልለታል፡፡ እንዲሁ ሳይሆን በአዲስ ምሥጋና አመስግኑ ነው
ትምህርቱንም ይቀጥላል፡፡ …. መጀመሪያ
ግስ ያጠናል፤ ያጠናውን ግስና ነባር ቃላት ‘‹ወንትቀነይ ለስምከ ቅዱስ› ‹በማመስገን
በየዕለቱ ከሚዘረፈው ቅኔ ጋር በማነፃጸር እንገዛለን› እንዲል መጽሐፉ (ጥዑመልሣን
ምስጢር ለማደላደል ይሞክራል፡፡ እንዲህ መኮንን፤ 1995፤19)፡፡
እንዲህ እያለ ከጉባኤ ቃና እስከ መወድስ
ቅኔ ደረጃ ይደርሳል፡፡ ቅኔ ማለት ግጥም አንድም የምስጋና
በማለት ይዘረዝሩታል፡፡ ግጥም ማለት ነው( ሀብተማርያም፤1963፤172)
ቅኔ የተለያዩና የተወሰኑ የዜማ ምጣኔዎች ያሉት
የቆሎ ተማሪውን መከራና ችግር
እንደ ግጥም ቤት የሚመታ ይዘቱ ውበትና ጥልቅ
ቻይነትና ዕውቀትና ጥበብ ፈላጊነት
ምሥጢር እንዲኖረው ተደርጎ በልዩ ልዩ የቅኔ
ዕንባቆም(1958) እና ዓለሙ(1997)
መንገድ ዓይነቶች የሚቀናበርና በትምህርት
ይስማሙበታል፡፡ ይህንንም ተማሪው ከእናት
አማካይነት የሚቀሰም ሥነ ቃላዊ ድርሰት ነው(
አባት፤ ከዘመድ አዝማድ ከጓደኛና ወዳጅ ተለይቶ
አማርኛ መዝገበ ቃላት 1993፤180)፡፡
የተወለደበትንና ያደገበትን አካባቢ ትቶ ሩቅ አገር
መሄድ ይኖርበታል፡፡ በጉዞው ዳገት ቅኔ አንድ ቃል በሚሰጠው ቀጥተኛ
መውጣት፤ቁልቁለት መውረድ፤እንቅፋት ትርጉም ብቻ ሳይገታ ወይም ሳይወሰን
መመታት፤እሾህ መወጋት፤በቀን ሀሩር በሌት ቁር አስመስለን ጥልቅ በሆነ የተደበቀ ምሥጢርን
መንገላታት፤መራብና መጠማት ይኖራል፡፡ ቅኔ አጉልተን የምናይበት፤ የምንገልጽበት ዘዴ
ቤት ከደረሰም በኋላ ቢሆን አብዛኛውን ጊዜ ወይም የአነጋገር ሥልት ነው (ዓለሙ 1997፤
የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን የሚያገኘው “ 154) ፡፡
በእንተ ስሟ ለማርያም፤ ስለቸሩ እግዚአብሒር ” ቅኔ በሰምና በወርቅ በኅብርና በአንጻር
ብሎ ለምኖ ከመንደር ውሻ ጋር ታግሎና በመነገር ሁለትና ሦስት ትርጉምን አዝሎ በኅብርና
ተከላክሎ፣ፈንጣጣ፣ ተስቦና ወባ በመሳሰሉትና በምርምር ተጠማምሮ አንድን ምሥጢራዊ ሃሳብ
በሌሎች የውሃ ወለድ በሽታዎች ተጠቅቶ ነው፡፡ ለመግለጽ የበቃ እንደሆነ ቅኔ ይባላል፡፡(ንጉሤ
ይህንንና የመሳሰለውን ችግር ለመቋቋም 1993፤1) ቅኔ በቁሙ ሙሾ፤ ግጥም፤ ቅንቀና፤
የሚችለው በዕድሜ የበሰለ ወጣት ሲሆን ቁዘማ፤ የፍትሐት የልቅሶ ዜማ፤ ማኀሌት፤ ጉማ
ነው፡፡...የቅኔ ትምህርት ደረጃው ከጸዋትወ ዜማ ነው ( ኪዳነ ወልድ 1948፤798) ፡፡
ቀጥሎ ከትርጓሜ መጻሕፍት አስቀድሞ
በጉልምስና ወራት ነው፡፡ ምክንያቱም ትምህርቱ ቅኔ የቅኔ ሊቃውንት በመንፈሳዊም
የረቀቀና የጠለቀ በመሆኑ የትውልድ ሀገሩን ትቶ ሆነ በሥጋዊ ሐሳባቸውን የሚገልጹበት
ጎራ ዞሮ ወንዝ ተሻግሮ ወጥቶ ወርዶ ከውሻ ጋር የምርምርና የፍልስፍና ድርሰት ነው ፡፡ ቅኔ
ጦርነት ገጥሞ ቁራሽ እንጀራ ለምኖ ደበሎና ድሪቶ በአጋጣሚ በተሰጥዖና በልማድ የሚደርሱት
ለብሶ ብዙ ፈተና ተቀብሎ አይመስሉ መስሎ ቀይ ድርሰት አይደለም ፡፡ የቅኔ ትምህርት ቤት
የነበረው ጠቁሮ፤ ረጅም የነበረው አጥሮ ተጠምቶ ተከፍቶለት መምህር ተሰይሞለት ጉባኤ
ጸዋትወ መከራን ሁሉ ታግሶ የሚማሩት ተዘርግቶለት፤ ሥርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶለት
የተባህትወ ትምህርት ነው በማለት ያብራሩታል፡፡ ፤ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ፤ ከመምህር መምህር
ተመርጦ፤ደበሎ ለብሶ፤ ከውሻ ተከላክሎ፤ ቁራሽ
ከላይ የተጠቀሱት ጥናታዊ ጽሑፎች ለምኖ፤ ቆሎ ቆርጥሞ፤ የመምህሩን ቅኔ አጥንቶና
በጥቅሉ የሚጠቁሙት የቆሎ ተማሪው ዕውቀትና አስመስሎ ቆጥሮ ለመምህሩ አሳርሞ የሚማሩት
ጥበብን ፍለጋ ከረሃብ፤ ከጥማት፤ ከዕርዛትና ድርሰት ነው፡፡ ይህ በመሆኑ ቅኔ ትምህርታዊ
ከባይተዋርነት ጋር በቆራጥ ወኔና በፅኑ መንፈስ ድርሰት ነው፡፡ ቢሆንም ግጥማዊነቱን አንርሳ (
የሚዋጋ የትምህርት አርበኛ መሆኑን ነው፡፡ ዜና ማርቆስ 1994፤2)፡፡

66
Faculty of Teacher Education, St. Mary’s University College
t he
eacher Bi-annual Bulletin November, 2011

እንጂ በወረቀት የማይሰፍር በውሣጤ አዕምሮ ጉባኤ ቃና------- ባለ ሁለት ቤት ነው፡፡ ከመንዝና ግሼ ሥላሴ በመለስ፤
ከሚገኝ ክሂል ድንገት የሚገነፍል ልዩ ፀጋ ነው ፡፡ እርሱም የትስብእትና የመለኮት ምሳሌ ነው፤ እንደ ንጋት ፀሐይ እንደ አጥቢያ
ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክና ኮከብ
ቅኔ ኪነ ጥበብ ነው ፡፡ ቅኔ የኢትዮጵያዊነት አንድ
አሻራ ነው ፡፡ ቅኔ የታሪካችን አካል ነው ፡፡ ፍፁም ሰው ለመሆኑ፤ ታሪካቸው ደምቆ ከሩቅ የሚነበብ፤
የቅኔው ሙያም በሌሎች ዓለማት የሌለ ዘአምላኪየ-------- ሦስት ቤት ያለውና የሥላሴ ነበሩ በሸዋ ከዋክብተ-ጥበብ፡፡
በሀገራችን ብቻ የሚገኝ የሀገራችን የጥበብ ቅርስ ምሣሌያቸው፤ በማለት ይመልሳሉ፡፡
የአበው ውርስ ነው ፡፡ በዚህ አያበቁም፤ የሀገራችንን የቅኔ ከዋክብት
ሚበዝኅ----------- ሦስት ቤት ያለውና የሥላሴ መገኛ ሐሰሳቸውን፤-
1.2.2. የቅኔ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው ምሣሌያቸው፤
ልቆጥራቸው ባልችል አንድ ባንድ ዘርዝሬ
? *ዋይ ዜማ---------- አምስት ቤት ያለውና የ5ቱ የቅኔን አዝመራ ያበቁ ለፍሬ
አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌ፤ ሊቃውንት ነበሩዋት ኢትዮጵያ
የቅኔ ዓይነቶችን ለማወቅ ሊቀ-
ለቃውንት ያሬድ የሰጡትን ትንተና ማንሳት *ሥላሴ ------------ ስድስት ቤት ያለውና የ6ቱ ሀገሬ፡፡
አስፈላጊ ነው፡፡ ከትንተናቸው “የጎንጅ፤ የዋድላና ቃላተ ወንጌል ምሳሌ፤ በማለት ቅኔ የመላይቱ ኢትዮጵያ ዘመን ዘለቅ
የዕውቀትና ጥበብ ቅርስ የአበው ውርስ መሆኑን
የዋሸራ ” ተብለው የሚታወቁ ሶስት የቅኔ *ዘይእዜ ----------- አምስት ቤት ያለውና የ5ቱ ያስገነዝባሉ፡፡
አይነቶች መኖራቸውን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ሊቀ- አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌ፤ በተጓዳኝ መገኛው በመላ ኢትዮጵያ
ሊቃውንቱ ገለጻቸውን በመቀጠል የቅኔዎቹ የሆነውን የቅኔ አዝመራ ለፍሬ ያበቁ ሊቃውንት
*መወድስ --------- ረጅም ቅኔ ነው፤ ቤቱም አንድ በአንድ በስም እያነሱ ያወድሳሉ፡፡ የስመ-
ልዩነት በግስ አገሳሰስና እርባታ፤ በሚገቡና
ዘጠኝ ነው፤ የ9 ሐፁረ መስቀል ምሳሌ ጥር የቅኔ ሊቃውንት ውዳሴያቸውን፡-
በማይገቡ የቃላት ጠባይ ፤ በዜማ ልክ፤ በቅኔ መሆናቸውን ይዘረዝራሉ፡፡
አገባብ ህግ፤ በቅኔ ስደራና በልውጥ ያሬዳውያን ጣና ዳር ቆሜ ዓባይ ወንዝ በመለስ፤
የዜማ ስፍሮች ወዘተርፈ መሆኑን ያብራራሉ፡፡ *ሊቀ ጉባኤ ታረቀኝ ከላይ በተራ ቁጥር( 4-7) እስኪ ከመቃብር ሊቃውንት “ልቀስቅስ፡፡
አያይዘውም ለቅኔዎቹ አይነት መለያየት መነሻ ስለቀረቡት የቅኔ ዋና ዋና ክፍሎች በመጠኑ በማለት ይጀምራሉ፡፡
የሆኑት “ጎንጅና ዋሸራ” የተባሉት ስፍራዎች የተለየ ትንታኔ ይሰጣሉ፡፡
በውዳሴያቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ
በጎጃም፤ “ዋድላ” የተባለው መካነ ቅኔ ደግሞ በትንታኔው መሠረት፤ የጐጃምን የቅኔ ሊቃውንት ከትውልድ
በወሎ ክፍለ ሀገር መገኘታቸውን ይጠቁማሉ፡፡ 4. *ዋይ ዜማ--------- ሦስትም አምስትም ቤት መንደራቸው ጋር በማቀናጀት ያሞጋግሳሉ፡፡
እነዚህ አውራጃዎች ለብዙ ዓመታት የቅኔ አለው፤ ለአብነትም ተዋናይን ከጐንጅ ተራራ፤ መምህር
ትምህርት የአብነት ቦታ ሆነው በመቆታቸው ክፍለ ዮሐንስን ከአገው ምድር፤አራት ዓይና
5. * ሥላሴ ሦስትም ስድስትም ቤት አለው፤
ቅኔዎቹ በእነርሱ ስም ሊጠሩ መብቃታቸውን ጐሹን ከጐጃም፤ ገብረ ሥላሴን፡ ዮፍታሄ
ይጠቅሳሉ፡፡ 6. * ዘይእዜ--- ሦስትም ሰባትም ቤት አለው፤ ንጉሴን፡ አባ ቴዎፍሎስንና
7.*መወድስ -ኹለትም፤ሰባትም፤ስምንትም
በተጻራሪው ክነፈርግብ አታለል
ቤት አለው ይላሉ፡፡
“የግዕዝ ቅኔያት ታሪካዊ አመጣጥና ዕድገት
በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት መጣጥፍ 1.2.4. የቅኔዎቻችንን አዝመራ ለፍሬ
የቅኔ ዓይነቶችንና ምሳሌዎችን ለመዳሰስ ጥረት ያበቁ ስመ-ጥር ስመ ጥር ሊቃውንት የት የት
አድርገዋል፡፡ በጥረታቸውም የቅኔ መንገዶች ብዙ ይገኛሉ?
ይገኛሉ እነማንስ ናቸው? ናቸው
መሆናቸውን፤ በአጭር ጽሑፋቸው ሁሉንም
መዘርዘር አስቸጋሪ መሆኑንና ከ300 በላይ በላይ (1996) “የቅኔ ከዋክብት ”
መንገዶች እንደሚገኙ ገልጾ ማለፍ ግዴታ በሚለው የሥነ ግጥም መድብል ውስጥ
መሆኑን ያብራራሉ፡፡ ከገለጸዎቹ መረዳት የሀገራችን ስመ-ጥር የቅኔ
የሚቻለው የቅኔ ዓይነቶችን ወይም መንገዶችን ከዋክብት የት የት ይገኛሉ? የሚለውን ጥያቄ
ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ጥልቅ ጥናት ማድረግ ያነሳሉ፡፡
አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡ ያነሱትን ጥያቄም፤-
አዕምሮአቸው ቅኔ ምሥጢር የሚያፈላ፤
1.2.3. የቅኔ ግዕዛዊ ዋና ዋና ክፍሎች ሥነ-ልቡናቸው በዕውቀት የተሞላ፤
ምንድን ናቸው?
ናቸው ነበሩ ሊቃውንት በላስታ በዋድላ፤
ሊቀ-ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም በአክሱም በጎንደር ፤ ግሸን ላሊበላ፡፡
ማርቆስ / በአሁኑ ወቅት ብፁዕ አቡነ መልከ ረቂቁን ህዋስ የትርጓሜ ምሥጢር፤
ጼዴቅ/ ግዕዛዊው ቅኔ ሰባት ዋና ዋና ክፍሎች አጉልተው ያሳዩ በቅኔ መነፅር፤
እንዳሉት ይገልጻሉ፡፡ የቅኔውም ስምና ሙያ፤ ነበሩ ከዋክብት በትግራይ በጎንደር፤
የቤቱ ልክና የሚባልበት ጊዜ፤የያንዳንዱም ቅኔ
በወሎ በሸዋ ጎጃም በጌምድር፤
ትርጉምና አስተያየት ግዕዛዊው ቅኔ ሰባት ዋና ዋና
በመንዝና ግሼ በተጉለት አንኮበር፤
ክፍሎች እንዲኖሩት የሚያደርጉ ዓበይት
ምክንያቶች መሆናቸውን ያብራራሉ፡፡ የቅኔ ዋና ምሥራቅ ኢትዮጵያ አርሲ ባሌ ሐረር፤
ዋና ክፍሎቹ፡- ሲዳሞ ወለጋ ከፋ ኢሊባቦር፡፡
ሸዋ ተሻግሬም እስቲ ጥቂት ልጥቀስ፤

67
Faculty of Teacher Education, St. Mary’s University College
t he
eacher Bi-annual Bulletin November, 2011

ዶ/ር ኢሳይያስን ከደብረ ኤልያስ፤ መልዓከ ፀሐይ (የመካነ ቅኔ ሊቃውንት) መገኛም ናት ፡፡ አበባ፤ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡
ተገኜን ከአብማ፤ መምህር ውብሸትን ከብቸና፤ ለዘመናት የሊቃውንት ድሃ ሆና የማታውቀው ዕንባቆም ቃለ-ወልድ(1958)፡፡ ’’ስለቅኔ
መልዓከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬን ከደብረ እማማ ኢትዮጵያ በዘመነ ግሎባላይዜሽን ትምህርትና ስለ ጥቅሙ ”፤ለሦስተኛ
ዲማ፤ አለቃ ጌታሁንን ከሞጣ ጊዮርጊስ፤ መምህር የመካነ ቅኔ ሊቃውንት መገኛ የመሆኗን ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ
ኢሳይያስና መምህር ሪሳታዎስን ከመርጦ ብሥራት ነጋሪ የመፈለግ አዝማሚያ ማሳየት የቀረበ፤አዲስ አበባ፣ያልታተመ፡፡
ለማርያም፤ መምህር ቀስሙን ከደጋ ዳሞት፤ ጀምራለች፡፡
አለቃ ተክሌንና ማዕበሉ ፈንቴን ከዋሸራ ንጉሤ ነገዎ(1993)፡፡ ”የቅኔ አፈታት
ማርያም፤ መሪ ጌታ ጌቴን ከአዴት መድኃኔዓለም፤ በመሆኑም በቅኔ ጥበብ ዕውቀት የተካንንና ዘዴዎችና የምርምር ቅኔዎች ስብስብ ”ሜጋ
አቤ ጉበኛን ከይስማላ ጊዮርጊስ፤ ዕቡይ ካሣንና በትምህርት ሥራ ዘርፍ የተሠማራን ባለሙያዎች ማተሚያ ቤት፤ አዲስ አበባ፡፡
ማዕበሉ ደሴን ከጐንጅ፤ሊቀ ኅሩያን ዘገዬን ቅኔ የኢትዮጵያዊነት አንድ አሻራና የታሪካችን ኪዳነ ማርያም ጌታሁን (1948) ፡፡ ጥንታዊው
ከአዴት፤እማሆይ ገላነሽን ከጽላሎ አማኑኤል አካል መሆኑን ልናበሥርላት ይገባል፡፡ የቅኔው የቆሎ ተማሪ፤አዲስ አበባ፤ትንሣኤ ዘጉባኤ
መቃብር በመቀስቀስ ማወደሳቸውን መግለጽ ሙያም በሌሎች ዓለማት የሌለ በሀገራችን ብቻ ማተሚያ ቤት፡፡
ይቻላል፡፡ የሚገኝ የሀገራችን የጥበብ ቅርስ የአበው ውርስ
ክነፈርግብ አታለል (1997) ፡፡ “የደበሎው ዓለም
መሆኑንም እንዲሁ፡፡ ከዚሁ ጋር በተጓዳኝ
በቀጣዩ የውዳሴ ምዕራፍ ፈላስፋውን ት/ቤትና ተማሪዎች” በ “ፈለገ ጥበብ ”
ዘርዓ ያዕቆብን ከአክሱም ፤ ደቀመዝሙሩን መምህር ጥንታዊው የቆሎ ት/ቤት የዘመናዊው ትምህርት
መጽሔት
ወልደ ህይወትን ከእንፍራዝ ጎንደር፤በጽዮን ዘማሪ ሥርዓታችን መደላድል እንደሆነም ለተተኪው
የቅኔ ፈጣሪ ፈላስፋ ተርጓሚና አስተማሪ የተባለለትን ትውልድ መረጃውን የማቆየት አደራ እንዳለብን ዜና ማርቆስ እንዳለው(1994)፡፡ ቅኔ
አምነን ለተግባራዊነቱ የየድርሻችንን ጥረት ለወጣቶች፤አዲስ አበባ፤ሆራይዘን ማተሚያ ቤት
ዶሪን ከትግራይ ጨለቆት ሥላሴ፤ ዮሐንስ ገብላዊን
ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ፡፡
ከወሎ አማራ ሳይንት፤ ሰባቱ ከዋክብት የተባሉትን
እነ ድድቅ ወልዴን ከዋድላ ጨረቃ ዳውንት፤ በጥረቱም በዋናነት ሀገራዊው የቅኔ ጥዑመ ልሣን መኮንን(1995) ፡፡”ቅኔ፤ ፍኖተ ቤተ
የትርጓሜ ጠቢብ የቅኔ ነጐድጓድና የወሎ ነጸብራቅ ክርስቲያን”፣ ጎንደር
ሙያ ወጣቱ ትውልድ እንዲያውቀውና
የተባለለትን መምህር አካለወልድን ከቦሩ ሥላሴ፤
በተተኪው የነገ ትውልድ ውስጥም አብቦ
ለማን ከመቄት ደብረ አሮን መቃብር ቀስቅሰው
እንዲያፈራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ለዚህም
ያወድሳሉ፡፡
መምህራን ቅኔ በውጪውና በዓለማዊው
በሦስተኛው የውዳሴ ምዕራፍ አለቃ አባ ትምህርትና መጤ ባህል እየተበረዘ እንዳይሄድ
ገብረ-ሐናን ከናበጋ ጊዮርጊስ፤ ጌቱ ገሞራውን ስለጥቅሙና ጥንታዊነቱ ማስተማርና ማስረዳት
ከጎንደር፤ አክሊሉን ከደምቢያ አዘዞ፤ራስ ወልደ ይኖረባቸዋል፡፡ የጥናትና ምርምር ባለሙያዎች
ገብርኤልን ከትግራይ መኳንንት፤ ቀኛማች ተካልኝን በዘመናዊ የመቅረጸ ድምጽና ምስል እየቀረጹና
ከወሎ መሳፍንት፤ ማዕበል ወልደ ሕይወትን ከጣና በጥልቀት እያጠኑ ለመጭው ትውልድ
ዳር ሜጫ፤ ጥበቡ ገሜን ከደብረ ሊባኖስ ኩዩ
ለመዘክርነት ማስቀረት ይኖርባቸዋል፡፡
መቃብር ቀስቅሰው ያወድሳሉ፡፡
ሀገራዊው የቅኔ ሙያ በአዎንታዊ መልኩ
በአራተኛው የውዳሴ ምዕራፍ አድጎ፣በልጽጎና ዳብሮ ለቱሪስት መስህብ
የትውልድ መንደራቸውን ያልጠቀሱላቸውን እንዲሆንና ለኢኮኖሚው ዕድገት የበኩሉን
መንግስቱ ለማን፤ ዮሐንስ አድማሱን፤ ከበደ አስተዋጽዖ እንዲወጣ መደረግ ይኖርበታል፡፡
ሚካኤልን፤ ባለቅኔው ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅንን
ከ የ መ ቃ ብ ራ ቸ ው ቀ ስ ቅ ሰ ው ያ ወ ድ ሳ ሉ ፡ ፡ የመረጃ ምንጮች መዘርዝር
በመጨረሻም በላይ ሙታን የቅኔ ሊቃውንት ሀብተማርያም ወርቅነህ(1963)፡፡ ጥንታዊ
የቀሰቀሱበትን የውዳሴ ምዕራፍ፤-- የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት፤አዲስ
ልቆጥራቸው ባልችል አንድ ባንድ ዘርዝሬ አበባ፤ብርሃንና ሰላም፤ ማተሚያ ቤት፡፡

የቅኔን አዝመራ ያበቁ ለፍ ሊቃውንት ሊቀ ጉባኤ ታረቀኝ ደምሴ በ “ብሌን” ቁ.4፤


ነበሩዋት ኢትዮጵያ ሀገሬ፡፡ (1999)፡፡ “ግዕዛዊው የኢትያጵያ ቅኔ ከየት
እስከ የት”
በማለት አጠናቅቀዋል፡፡
መልክአ ብርሃን አድማሱ(1963) ”መጽሐፈ ቅኔ
በጥናታዊ ጽሑፉ በዝርዝር ለማየት (ዝክረቃውንት)”፤አዲስ አበባ፡፡
እንደተሞከረው በቆሎ ት/ቤት የቀሰመው የቅኔ
ሙያ የዚህ ወይም የዚያኛው ብሔር ተብሎ በላይ መኮንን (1996)፡፡ የቅኔ ከዋክብት፡
የማይመደብና በሌሎች ዓለማት የሌለ ሥነ-ግጥም፤ጣና ማተሚያ ቤት፡፡
የታሪካችን አንድ አካልና ማንነታችን መገለጫ ዓለሙ ኃይሌ(1997)፡፡ ”ጥንታዊ የቅኔ
መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ”፡፡

ማጠቃለያ አማርኛ መዝገበ ቃላት (1993)፡፡ የኢትዮጵያ


ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል፤አዲስ አበባ
ሰው ዘርና የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤት አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡
የሆነችው ኢትዮጵያ የረቂቅና ምጡቅ የቅኔ 
ጥበብ ሊቃውንት የሚማሩባት የቆሎ ት/ቤት አቤ ጉበኛ(1966)፡፡ መስኮት፤አዲስ

68
Faculty of Teacher Education, St. Mary’s University College

You might also like