You are on page 1of 1

“Your Kids Our Kids! “ “ልጆችዎ ልጆቻችን ናቸው!

+251(0)116-607203 +251(0)911-469878 3628 www. Safari-academy.com Addis Ababa, Ethiopia

የ፳፻፲፮ ዓ.ም የት/ት ዘመን የ ፱ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ት/ት ማስታወሻ

ሥነ-ጽሁፍ
ሥነ-ጽሁፍ የሚሇው ቃል በቁሙ ሲታይ በጽሁፍ የተቀረጸ የቋንቋ ጥበብን የሚያመሇክት
ቢሆንም ከዚህ የቁም ፍቺው ባሇፈ የሰው ልጅ የጽህፈት ባህል ከመጀመሩ አስቀድሞ
ስሜቱን የገሇጸባቸው ወደፊትም የሚገልጽባቸው ቃላዊ ፈጠራዎችንም ያጠቃልላል፡፡
ሥነ-ጽሁፍን ቃላዊ ሥነ-ጽሁፍ እና ጽሁፋዊ ሥነ-ጽሁፍ በመባል መክፈል ይቻላል፡፡የሥነ-
ጽሁፍ ዘሮች ከሚባለት ውስጥ፡-
-ስነ-ቃል
-ልቦሇድ
-ስነ-ግጥም
-ተውኔት እና
-ዘይቤ ይጠቀሳለ፡፡
ሥነ-ጽሁፍ ቃለ እንደሚያመሇክከተው ሥን (ሥነ)-ማሇት ውበት ማሇት ሲሆን ሥነ-ጽሁፍ
ደግሞ የጽሁፍ ውበት ማሇት ነው፡፡ሥነ-ጽሁፍ በአገላሇጽ ትባቱ፣በህይወት (ኑሮ) ማሳያነቱ፣
በሳቢነቱና የአንድ ደራሲ ወጥ ስራ በመሆኑ የተዋጣሇትና ኪነ-ጥበባዊ ብቃቱ
የተመሰከረሇት የፈጠራ ስራ ነው፡፡ ሥነ-ጽሁፍ የሚሇው ቃል በትክክል የሚያመሇክተው
የተመሰከረሇት የጥራት ደረጃ ያላቸውና በዝርው ወይም በግጥም የተጻፉ ስራዎችን ብቻ
ነው፡፡ ሥነ ጽሁፍ ከሰው ልጅ ህይወት ጋር የጠበቀ ቁርኝነት አሇው፡፡የሥነ-ጽሁፍ ዋነኛ
ጉዳይ የሰው ልጅ ነው፡፡ምንጩ ፈጣሪውም ተቀባዩም ሰው ነው፡፡በመሆኑም ሥነ-ጽሁፍ
የሰው ልጅ በህይወቱ ከሚያልፍበት ውጣ ውረድ ይቀዳል፤በሰው ተፈጥሮ መልሶ ሇሰው
ይነገራል፡፡ሇዚህም በማህበረሰቡ ዘንድ ልዩ ቦታ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡

ሇሥነ-ጽሁፍ መኖር ምክንያት ሦስት ዋና ዋና ነጥቦች ይጠቀሳለ፡፡ የመጀመሪያው ሰው


ስሇህይወት የተገነዘበውን በጎም ሆነ ክፉ ነገር ሇመሰሎቹ ማካፈል በመፈሇጉ(ደራሲያን
ከሌላው ሰው በተሇየ ስሇሕይወት የመናገር ፍቅር ስላላቸው እነሱ ባዩበት መነጽር ሌላው
እንዲመሇከት ከመፈሇግ)፣ ሁሇተኛው ደራሲያን ሇሰው ልጅ ጥልቅ ፍቅርና ሰውን ሇማወቅ
ጽኑ ፍላጎት ስላላቸው፣ ሰዎች ምን አይነት ፈጡሮች ናችው? ከየት መጡ? ወዴት
ይሄዳለ? ባህሪያቸውስ? ወዘተ ጥያቄዎች መሳጭ መልስ ሇመስጠት፣ሦስተኛው የሰው ልጅ
ሇውበት ያሇው ፍቅር ነው፡፡ ማራኪነትና ሳቢነት በአንድ ቅርፅ ሲዘጋጅሇት ደስ የሇዋል ይህ
የውበት ፍቅር ደግሞ ደራሲው ሁሌም እንዲፅፍ ያደርገዋል፡፡ ደራሲ ሕይወትን፣ፍቅርን እና
ውበትን ከሚገልጽባቸው ዘውግ አንዱ ልቦሇድ ነው፡፡

“ፈጣሪ የተወደዱ ልጆቻችንን ፣ ሀገራችንንና ህዝባችንን ይጠብቅልን!”

የ ፱ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ማስታወሻ

You might also like