You are on page 1of 8

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የትምህርት ክፍል = ሣልሳይ የመጀመሪያ ዙር ስም አሽቄ ዝናብ (ገ/ሚካኤል


የሐዲሳት ትርጓሜ
የማቴዎስ ወንጌል እንድምታ ምዕራፍ አንድ
1.ቅዱስ ማቴዎስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ላይ ትዕማር:ራኬብን እና ሩት በጌታ የዘር ሀረግ ከሌሎች ሴቶች
ይልቅ ለምን እንድትቆጠር አደርጋት?
 ትዕማር ማናት ራኬብ ማናት? ሩትስ? ከአህዛብ ወገን ሆነው ሳሉ ከክርስቶ የዘር ሐረግ የመቆጠራቸው ነገር
እንደምን ነው?

 ማቴ. 1፡3 «... ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ ...»


ይህን ጥቅስ ለመተርጎም በመጀመሪያ የነትዕማርንና የነፋሬስን የዛራንም ማንነት እንዲሁም ከይሁዳም ጋር ያላቸውን
ግንኙነት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ታሪኩም በዘፍጥረት 38 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ከታሪኩም ባጭሩ እንደሚከተለው
ይቀርባል፡፡
ይሁዳ ዔር፣ አውናንና ሴሎም የሚባሉ ልጆች ነበሩት፡፡ ለመጀመሪያ ልጁ ለዔርም አስተዋይ የሆነች ከአሕዛብ ወገን
የምትሆነውን ትዕማር የተባለች ሴትን አጋባው፡፡ እርሱ ግን «እኔ ከምርጦቹ ከእሥራኤል ወገን ስሆን እንዴት ከአሕዛብ
ከምትሆነው ሴት እጋባለሁ» ብሎ በትዕቢት ተናገረ፡፡ ይህም በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ስለነበር እግዚአብሔር ቀሰፈው፡፡
በሕገ ልቡናም ለወንድምህ ዘር አስቀርለት ብሎ ይሁዳ ለታናሹ ለአውናን ትዕማርን ይሰጠዋል፡፡ እርሱም እንዲሁ ክፉ
ስላደረገ ይቀሰፋል፡፡ በዚህን ጊዜ ይሁዳ ትንሹ ልጁም ሲሎምም ይሞትብ ኛል ብሎ ትዕማርን ወደ ዘመዶቿ ሄዳ
በመበለትነት እንድትቀመጥ ያደርጋል፡፡
ከዘመናት በኋላም የይሁዳ ሚስት ትሞትና በግ ለመሸለት ካገር ወዳገር ይዟዟር ስለነበር ትዕማር ወዳለችበትም ሀገር ሄደ፡፡
የይሁዳንም መምጣት ትዕማር በሰማች ጊዜ የመበለትነት ልብሷን አውልቃ እንደ ዘማውያን ለብሳ በመንገድ ጠበቀችው፡፡
ፊቷንም ሸፍና ስለነበር ምራቱ /የልጆቹ ሚስት/ መሆኗን ሳያውቅ ይደርስባትና ትፀንሳለች፡፡ ወደ እርሷም ስለመግባቱ ጠቦት
ሊሰጣት ተስማምተው እስከ ጊዜው ግን የጣቱን ቀለበትና አንባሩን የእጁንም በትር በማስያዣነት ሰጥቷት ስለነበር ይሁዳ
በውሉ መሠረት ጠቦቱን በመልእክተኛው በኤራስ ኤዶሎማዊ አማካኝነት በላከለት ጊዜ ሊያገኛት ስላልቻለ ጠቦቱን ይዞ
ተመልሷል፡፡ ከግዜ በኋላም ይሁዳ ትዕማር ከእርሱ መጽነስዋን በመያዣው አማካኝነት ተረዳ፡፡ ፋሬስና ዛራም መንትዮች
ሆነው ተወለዱ፡፡ በልደታቸውም ጊዜ ዛራ አስቀድሞ እጁን አወጣ አዋላጅቷም ቀይ ሐር አሰረችበት፡፡ ነገር ግን ዛራ እጁን
በመለሰ ጊዜ ፋሬስ ጥሶ አስቀድሞ ወጣ፡፡ ታሪኩ በአጭሩ ይህን ይመስላል፤ ይህ ሁሉ ምሳሌ ነው፡-

ምሳሌውም (ምስጢሩ)
ይሁዳ =የእግዚአብሔር አብ፣ አይሁድም ትንቢት ተነግሮላቸው ሱባኤ ተቆጥሮላቸው
ጌታን አልተቀበሉም፡፡
መልእክተኛው/ኤራስ አዶሎማዊ/= የቅዱስ ገብርኤል፣
አንድም
ጠቦቱ = የእግዚአብሔር ወልድ፣
ትዕማር = የቤተክርስቲያን ምሳሌ፡- ትዕማር ዘርን
ቀለበቱ = የሃይማኖት፣ ከአባትም ከልጆችም መቀበል እንዳልተጠየፈችም
አንባሩ = የአክሊለ ሦክ፣ ቤተክርስቲያንም ከአሕዛብም፣ ከሕዝብም፣ ከግዝሩም፣
ከቆላፋውም ወዘተ ያመኑትን ትቀበላለች፡፡ ወደ ጥቅሱ
በትሩ = የመስቀል ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ትርጉም እንመለስ፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ዐበይት ጥያቄዎች
ይኖራሉ፤
ትዕማር = የአይሁድ ምሳሌ ናት፡፡ ትዕማር ማስያዣውን
ይዛ ቀረች እንጂ ዋጋን /ጠቦቱን/ እንዳልተቀበለች፣

1|Page
የያዕቆብን ልደት በተናገረ ጊዜ ዔሳውን አልጠቀሰም ነበር፡፡ አሁን ግን ፋሬስና ዛራ ባንድነት መጠቀሳቸው ስለምንድን ነው?
የይስሐቅ ልደት በተናገረ ጊዜ ሳራን የያዕቆብን ልደት በተናገረ ጊዜ ርብቃን የይሁዳንና የወንድሞቹን ልደት በተናገረ ጊዜ
ደግሞ እነ ልያንና ራሄልን ሳይጠቅስ አሁን ትዕማርን የመጥቀሱ ምሥጢር ምንድን ነው?
ፋሬስና ዛራ ባንድነት የተጠቀሱት ምክንያት ስላላቸው ነው፡፡ እርሱም፡-
ፋሬስ የኦሪት ዛራ ደግሞ የወንጌል ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ዛራ እጁን አውጥቶ መመለሱ ወንጌል በመልከ ጼዴቅ ታይታ
የመጥፋትዋ ምሳሌ ነው፡፡ ፋሬስ ጥሶ እንደወጣ በመሀል ኦሪት ተሠርታለች፤ ዛራ ሁለተኛ እንደመወለዱ ወንጌልም ቆይታ
ተሠርታለች፡፡
መልከ ጼዴቅ ማነው᐀ መልከ ጼዴቅ በዘመነ አብርሃም የነበረ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፡፡ /ዘፍጥ.
14፤ ዕብ. 7/
ይህ ሰው አብርሃም ጠላቶቹን ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ አብርሃምን ሊቀበለውና ሊባርከው ኅብስትና
የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ ባረከውም አብርሃምም ደግሞ ለመልከ ጼዴቅ ከምርኮው አሥራት አወጣ፡፡ እንግዲህ ኅብስትና
ወይኑ የቅዱስ ቁርባን፣ መልከ ጼዴቅ የካህናት፣ አብርሃም የምእመናን ደግሞም አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ነበርና
ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌዎች መሆናቸው ነው፡፡ ይህ መልከ ጼዴቅ ክርስቶስን በአምስት ነገሮች ይመስለዋል፤
መልከ ጼዴቅ ማለት የጽድቅ ንጉሥ የሰላም ንጉሥ ማለት ነው፤ ክርስቶስም ደግሞ አምላከ ጽድቅ አምላከ ሰላም ነው፣
መልከ ጼዴቅ በኅብስትና በወይን ያስታኩት /ያመሰግን/ ነበር፤ ክርስቶስም ሥጋና ደሙን በኅብስትና በወይን ሰጥቶናል፣
መልከ ጼዴቅ በመጽሐፍ ቅዱስ እናቱና አባቱ አልተጠቀሱም ክርስቶስ ደግሞ ለሰማያዊ ልደቱ እናት ለምድራዊ ልደቱ አባት
የለውም፣
መልከ ጼዴቅ ከካም ዘር ተወልዶ ክህነትን ከልዑል እግዚአብሔር አገኘ ክርስቶስም ደግሞ ከይሁዳ ወገን ተወልዶ ክህነትን
ከሌዊ ሳይሆን ከልዑል እግዚአብሔር ተቀበለ፣
መልከ ጼዴቅ ለዘመኑ ጥንት ለሕይወቱ ፍጻሜ የለውም፣ ለክርስቶስም በመጀመሪያ ቃል ነበር ቃልም ሥጋ ሆነ ሲባል
ለልደቱ ጥንት የለውም አምላክነቱም ዘላለማዊ ነው፡፡
አንድም እደ ዛራ /የዛራ እጅ/ የቀሳውስት ቀዩ ሐር ደግሞ የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ቀሳውስት ሥጋ አምላክን በእጃቸው
ይፈትቱታልና፡፡
 ለትዕማር መጠቀስ ምክንያቶች ሆነው የሚቀርቡት ደግሞ፡-
አስቀድመን እንደተናገርነው ቅ/ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ለዕብራውያን የእነርሱን ወግና ሥርዓት በመጠበቅ ነበር፡፡ ስለዚህ
በአይሁድ ሥርዓት አንዲት ዕብራዊት ሴት በዘር ሐረግ ውስጥ ገብታ አትቆጠርም ስለዚህ እነ ሳራና ርብቃ ሊጠቀሱ
አልቻሉም፡፡ ትዕማር ግን ዕብራዊት ሳትሆን ከአሕዛብ ወገን በመሆኗና ክርስቶስ ከሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም
መወለዱን ለማሳየት በዘር ሐረግ ውስጥ ልትጻፍ ችላለች፡፡ ትዕማር በሃይማኖት እንደከበረች ከአሕዛብም በሃይማኖት
እንደሚከብሩ ለማጠየቅ፡፡
አንድም በእሥራኤል ዘለፋ ለአሕዛብ ተስፋ ለመስጠት፡፡ እሥራኤል በልደቱ ሥጋ ይመኩ ነበረና አሕዛብ ለእኛስ ክርስቶስ
ከትዕማር ተወልዶ የለምን እንዲሉ ትዕማር ተጠቅሳለች፡፡
 ማቴ. 1፡5 ሀ. «ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ ...»
ይህንንም ኃይለ ቃል ለመተርጎም የሰሎሞንን የራኬብንና የቦኤዝን ማንነት መረዳት ይጠቅማል፡፡ ታሪካቸውን በመጠኑ
ለመረዳት በመጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ምዕራፍ ሁለትንና ስድስትን ማንበብ ይቻላል፡፡ ታሪኩም በአጭሩ እንዲህ
ይቀርባል፡፡ እሥራኤላውያን በኢያሱ መሪነት ወደ ምድረ ርስት ሲጓዙ ሰጢን የተባለ ቦታ አርፈው ሳለ ኢያሱ ሁለት
ሰላዮችን /ሰሎሞንና ካሌብ/ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ በስውር ላከ፡፡ እነርሱም ኢያሪኮ በገቡ ጊዜ በመልካቸው በቁመታቸው
ስለተለዩ ወደ አንዲት ጋለሞታ ወደሆነች ረዓብ /ራኬብ/ የምትባል ሴት ቤት ይገባሉ፡፡ ሴቲቱም ሸሽጋ ከኢያሪኮ ንጉሥ እጅ

2|Page
እንዲያመልጡ ታደርጋለች፡፡ እሥራኤልም ኢያሪኮን በያዙ ጊዜ ከነቤተሰብዋ ሊያድኗት ለሴቲቱ ተስፋ ሰጡዋት፡፡ መለያም
ይሆን ዘንድ በመስኮት ላይ ቀይ ሐር እንድታስር አስጠነቀቋት፡፡ እሥራኤልም አሕዛብን አጥፍተው ኢያሪኮን ያዙ ራኬብንም
ከነቤተሰብዋ አዳኗት፡፡ ኢያሱም ሰሎሞንንና ረዓብን ባረካቸው ተጋቡም ቦኤዝንም ወለዱ፡፡ ይህ ሁሉ ምሳሌ ነው፡-

ምሳሌውም (ምስጢሩ)
ኢያሱ = የጌታ፣ አጋንንትን አጥፍቶ ምእመናንን ገንዘብ አድርጓልና፡፡
መስኮት = የከናፍረ ምእመናን፣
ኢያሪኮ = የምእመናን፣
ሐር = የሥጋ ወደሙ ምሳሌ፤
አሕዛብ = የአጋንንት ምሳሌዎች ናቸው፤
ሰንደቅ አላማ = የመስቀል ምሳሌ
ኢያሱ አሕዛብን አጥፍቶ ኢያሪኮን እንደያዘ ጌታም
አንድምታ
ረዓብ /ራኬብ/ ደግሞ የአሕዛብ ምሳሌ ትሆናለች፡፡ ራኬብ ብዙ ወንዶች ስታገባ ስታስወጣ ከኖረች በኋላ በአንድ ሰሎሞን
እንደተወሰነች አሕዛብም ልዩ ልዩ ጣዖታትን ሲያመልኩ ኖረው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ተወስነዋልና፡፡
እዚህ ላይ እንደ ትዕማር ራኬብም በዘር ሐረግ ውስጥ መጠቀስዋ ለትዕማር ከተሰጠው ምክንያቱ ጋር አንድ ነው፡፡

 ለራኬብ መጠቀስ ምክንያቶች ሆነው የሚቀርቡት ደግሞ፡-


አስቀድመን እንደተናገርነው ቅ/ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ለዕብራውያን የእነርሱን ወግና ሥርዓት በመጠበቅ ነበር፡፡ ስለዚህ
በአይሁድ ሥርዓት አንዲት አሕዛባዊት ሴት በዘር ሐረግ ውስጥ ገብታ አትቆጠርም ስለዚህ እነ ሳራና ርብቃ ሊጠቀሱ
አልቻሉም፡፡ ራኬብ ግን ዕብራዊት ሳትሆን ከአሕዛብ ወገን በመሆኗና ክርስቶስ ከሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም መወለዱን
ለማሳየት በዘር ሐረግ ውስጥ ልትጻፍ ችላለች፡፡
 ማቴ 1፡5 ለ. «... ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ»
በአቤሜሌክ ቤተሰብ ላይ የደረሰው መከራና ኃዘን (1፡1-5)
ኑኃሚንና ሩት ወደ ቤተልሔም ተመለሱ (1፡6-22)
ሩት ቦዔዝን በመከር መሰብሰቢያ ስፍራ አገኘችው (2)
ሩት ወደ ቦዔዝ የአውድማ ስፍራ በመሄድ እንዲያገባት ጠየቀችው (3)
ቦዔዝ ሩትን አገባ፤ ወንድ ልጅም ወለዱ
ሐተታ
የሩት እና የኑኀሚን ታርክ
አንድ አቤሜሌክ የተባለ ሰው ሁለት ወንዶች ልጆቹን እና ባለቤቱን ኑኃሚንን ይዞ ከቤተልሄም ይሁዳ ወደ ሞአብ አገር
ሲሰደድ፤ በዚያም አቤሜሌክ ሁለቱን ለጆቹን ከሞአባውያን ሴቶች ጋር አጋብቶ ኖሩ፡፡አቤሜሌክን እና ሁለቱን ወንዶቸ
ልጆቹን ሲገድላቸው ኑኃሚን እና ሁለቱ ሞአባውያን ምራቶቿ ብቻቸውን ካለ ባልና ካለ ልጅ ቀሩ፡፡ በይሁዳ ምድር
የተከሰተው ረሃብ ተወግዶ የጥጋብ ዘመን መጣ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጎበኛቸው፡፡ ኑኃሚንም ይህንን የመጎብኘት ዜና
ካለችበት ከስደት ምድር ሆና በሰማች ጊዜ ከሁለቱ ምራቶቿ ጋር ለመመለስ መንገድ እንደ ጀመረች ሁለቱም ምራቶቿ ወደ
አባቶቻቸው ቤት እንዲመለሱ ግፊት ብታደርግባቸውም ሩት ግን አማትዋን መከተል ወደደች፡፡ ከአባቷ ቤት እና ከአገሯ፣
ከአማልክቶቿም ይልቅ የኑኃሚንን አምላክ ምጫዋ አድርጋ ለመከተል ወስና ከኑኃሚን ጋር ወደ ይሁዳ ምድር መጣች፡፡

3|Page
ሩትም ሆነች ኦርፋ ስለ እግዚአብሔር ከኑኃሚን በሚገባ ሰምተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሩት በምጫዋ እግዚአብሔርን ስትመርጥ
ኦርፋ ግን አማትዋን ስማት ወደ አማልክቶቿና ወደ አባቷ ቤት ተመልሳለች፡፡ ሩት ወደ እግዚአብሔር ተጠጋች ከእርሱም ጋር
ተጣበቀች የማታውቀውንም ምድርና ሕዝብ በእምነት ተቀብላ መጣች ፍጻሜዋም በጎና ደስ የሚያኝ ነበረ፡፡ ምንም እንኳ
ኑኃሚን ቤተሰቧን በሞት ብትነጠቅም አንዲት ሞአባዊት ግን ወደ እግዚአብሔር ህዝብ አምጥታለች፡፡

ኑኀሚን በስደት ሳች ሁለት ልጆቿ ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አግብተው ነበር፡፡ ‹‹የኑኀሚን ባል አቤሜሌክ ሞተ፤ እርስዋና
ሁለት ልጆቿ ቀሩ፡፡ እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፤ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበር፡፡››
፣መጽ. ሩት 1÷3-4 ከጊዜያት በኋላ ግን ሁለት ልጆቿን በሞት አጣች፡፡ ወደ ሃገሯም ለመመለስ በተነሳች ጊዜ ሁለቱ
ምራቶቿ (የልጆቿ ሚስቶች) አብረዋት ሊሄዱ መንገድ ጀመሩ፡፡ ኑኀሚን ግን ባል አልባ ሁነው የቀሩት ምራቶቿ ደግሞ
ለእነርሱ ባዕድ በሆነ በኑኀሚን ሃገር በይሁዳ ስደተኛ ሆነው እንዲኖሩ አልፈቀደችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኑኀሚን የቀረ ሃብት
በሃገሯ የሚጠብቃት ስላልሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ችግርን ብቻዋን ለመታገል በበጎ አስተሳሰብ ወደ እናታቸው ቤት
እንዲመለሱ ነገረቻቸው፡፡ ‹‹እርሱዋም ከሁለት ምራቶቿ ጋር ከተቀመጠችበት ሥፍራ ወጣች ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ
በመንገድ ሄዱ፡፡ ኑኀሚንም ምራቶችዋን፤ ሂዱ ወደ እናታችሁም ቤት ተመለሱ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችሁ፤
እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችሁ፡፡›› መጽ.ሩት 1÷7-8 ‹‹ሩትም፡- ወደ ምትሄጂበት እሄዳለሁና፤ በምታድሪበትም
አድራለሁና… ሕዝብሽ ሕዝቤ፤ አምላሽም አምላኬ ይሆናልና..ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን
ያድርግብኝ፤ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች፡፡ ኑኀሚን ከእርሷ ጋር ለመሄድ እንደ ቆረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም
አለች፡፡›› መጽ.ሩት 1÷16-18 ከስደት ወጥታ ከእርሷ ጋር ወደ ሃገር ስትጓዝ ከከተማ በደረሰች ጊዜ ሕዝቡ ይህች ኑኀሚን
አይደለችምን እያሉ በደስታ በተናገሩ ጊዜ እርሷ ግን ራሷን ዝቅ አድርጋ ፍፁም በመንፈስ ድሃ በመሆን ‹‹በመንፈስ ድሆች
የሚሆኑ ብጽዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡›› ማቴ.5÷3

ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን። በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም። ልጄ
ሆይ፥ ሂጂ አለቻት። ሄደችም፥ ከአጫጆችም በኋኋኋ ላ በእርሻ ውስጥ ቃረ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ
ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።

እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፥ አጫጆችንም። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አላቸው። እነርሱም። እግዚአብሔር
ይባርክህ ብለው መለሱለት። ቦዔዝም በአጫጆች ላይ አዛዥ የነበረውን ሎሌውን። ይህች ቆንጆ የማን ናት? አለው።
የአጫጆቹም አዛዥ። ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ቆንጆ ናት፤ እርስዋም። ከአጫጆቹ በኋላ
በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ አለች፤ መጣችም፥ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ድረስ
ቆይታለች፤ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም አለው።

በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፤ የቃረመችውንም ወቃችው፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ።
አማትዋም። ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን አለቻት። እርስዋም። ዛሬ የሠራሁበት ሰው
ስም ቦዔዝ ይባላል ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት። ኑኃሚንም ምራትዋን። ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን
ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ። ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም
ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት።

ሞዓባዊቱ ሩትም። ደግሞ። መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ አለኝ አለቻት። ኑኃሚንም ምራትዋን ሩትን።
ልጄ ሆይ፥ ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው አለቻት። ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር
እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፤ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።

ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፤ እርሱ ዛሬ ሌሊት በዓውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል፡፡ እንግዲህ ታጠቢ፤
ተቀቢ፤ ልብስሽን ልበሺ፤ ወደ ዓውድማውም ውረጂ፤ ነገር ግን መብሉንና መጠጡን እስኪጨርስ ድረስ ለርሱ አትታይው፡፡
በተኛም ጊዜ የሚተኛበትን ሥፍራ ተመልከቺ፤ ገብተሸ እግሩን ግለጬ፤ ተጋደሚም፤ የምታደርጊውን እርሱ ይነግርሻል፡፡››
መጽ.ሩት 3÷1-5 ሩትም አመቷ ኑኀሚንን እጅግ ታከበራት ነበርና እንዳለቻት አረገች፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር ቦኤዝ ሩትን
ሚስት ያደረጋት፡፡ ‹‹ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ»

4|Page
ትዕማር፣ ራኬብ፣ ሩት እነዚህ ሦስት ሴቶች የተነሡበት ምክንያት ተስፋ ከተሰጣቸው ከእስራአል ወገን ሳይሆን
ትንቢት ካልተነገረላቸው ከአሕዛብ ወገን ስለሆኑ ነው፡፡ በዚህም የጌታ ልደት ከእስራኤል ብቻ ሳይሆን
ከአሕዛብም መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ወንጌላዊው ማቴዎስ ለወገኖቹ ለዕብራውያን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት የተነገረለት
ሱባዔ የተቆጠረለት መሲሕ እርሱ መሆኑን ለማስረዳት የጌታን የዘር ሐረግ በመተንተን ወንጌሉን መጀመሩን
ባለፈው እትማችን ተገልጿል፡፡ ከዚያ የሚቀጥለው እነሆ፡-
በጌታችን የትውልድ ቁጥር ውስጥ ከአሕዛብ ወገን የነበሩ ሴቶች የመጠቀሳቸው ምክንያት ባለፈው የተገለጸ
ሲሆን ዕብራዊትዋ ቤርሳቤህ /የኦርዮ ሚስት/ ለምን ተነሳች? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፡፡ አይሁድ
ክርስቶስ በዳዊት ከበረ ይላሉና፡፡ ዳዊት በክርስቶስ ከበረ እንጂ እሱማ ኦርዮንን አስገድሎ ሚስቱን የቀማ
አልነበረምን ለማለት እንዲመቸው ነው ሲሉ መተርጉማን ተርጉመውልናል /ወንጌል አንድምታ/፡፡
ጌታ የተወለደው ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆኖ ሳለ ወንጌላዊው ለዮሴፍ የተወለደ ይመስል ቆጥሮ
ቆጥሮ ዮሴፍ ላይ ማቆሙ ለምንድር ነው?
በዕብራውያን ሥርዓት የትውልድ ሐረግ የሚቆጠረው በወንድ በኩል እንጂ በሴት አይቆጠርም በዚሁም ላይ
አይሁድ ጌታን የዳዊት ልጅ እያሉ ይጠሩት የነበረው በአንዳር በአሳዳጊው በዮሴፍ በኩል ነበርና ዓላማውም
የዳዊት ወገን መሆኑን መግለጽ በመሆኑ በዮሴፍ በኩል ቆጠረ፡፡ ዳሩ ግን ጌታ ከእመቤታችን በኅቱም ድንግልና
ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና መወለዱ የታወቀ ነው፡፡ ማቴ.1፥34-36፣ ኢሳ.7፥14፡፡
ዮሴፍና እመቤታችን ዘመዳሞች መሆናቸውን ወንጌላዊው በእጅ አዙር ገልጿል፡፡ አልአዛር በወንጌሉ
እንደተገለጸው ማታንን ብቻ ሳይሆን የወለደው ቅስራንም ነው፡፡ ማታን ያዕቆብን ሲወለድ፡፡ ቅስራ ደግሞ
ኢያቄምን ወለደ፡፡ ያዕቆብ ቅዱስ ዮሴፍን /የእመቤታችንን ጠባቂ/ ወለደ፡፡ ኢያቄም እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያምን፡፡ ዝምድናቸው በጣም የቀረበ /ሦስት ቤት/ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡ ሁለቱም የዳዊት
ወገን ናቸው፡፡ ዳሩ ግን ክርስቲያኖች ጌታን የዳዊት ልጅ የምንለው በአንጻር በዮሴፍ ሳይሆን በእናቱ በቅድስት
ድንግል ማርያም ነው፡፡
ዮሴፍ የእመቤታችን እጮኛ ተብሎ መጠራቱ እንዴት ነው? እመቤታችን ለዮሴፍ በእጮኝነት ስም መሰጠትዋ
ስለብዙ ምክንያት ነው፡፡ ከእነዚህም ጥቂቶቹ፡-
ሴት ልጅ ናት ጠባቂ ያስፈልጋታልና በእጮኛ ስም እንዲጠብቃት ነው፡፡ እንዲሁም ዮሴፍ ምክንያት ባይሆን
እመቤታችን ጌታን በግብረ መንፈስ ቅዱስ በፀነሰችበት ጊዜ መከራ ላይ በወደቀች ነበር፡፡ ስለዚህ ምክንያት ሆኖ
ከመደብደብ ከመንገላታት እንዲያድናት ነው፡፡
ክርስቶስ ያለ ወንድ ዘር መወለዱን ዐይተው እናቱ ቅዱስት ድንግል ማርያምን ከሰማይ የመጣች ኃይል
አርያማዊት ናት እንጂ የአዳም ዘር ሰው አይደለችም፡፡ ክርስቶስም ከመልአክ የተገኘ መልአክ ነው የሚሉ
መናፍቃን እንደሚነሱ ያውቃልና ከመላእክት ወገን ብትሆንማ ኖሮ እንዴት ለማረጋገጥ ለዮሴፍ ታጨች
ለማለትና የአዳም ዘር መሆንዋን ለማረጋገጥ፡፡
በመከራዋ በስደትዋ ጊዜ እንዲያገለግላት እንዲላላክላት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ጥበብ ድንግል ማርያም በውጭ የዮሴፍ እጮኛ እንድትባል ማድረጉ ከላይ ስለተጠቀሱት
ምክንያቶች ነው እንጂ ዘር ለማስገኘት ሔዋን ለአዳም ረዳት ሁና እንደተሰጠችው ዮሴፍ ልጅ ለማስገኘት
ረዳት እንዲሆናት አይደለም፡፡ አያይዞም ወንጌላዊው ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን ሲገልጽ፡፡
“እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች” ብሏል፡፡

5|Page
ጌታም ልደቱን ያለወንድ ዘር ያደረገበት ምክንያት ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት መወለዱን ለማስረዳት ነው፡፡
የመጀመሪያው ልደት በኋላኛው ልደት ታውቋልና፡፡ ቀዳማዊ አዳም ከኅቱም ምድር እንደተገኘ ሁሉ ሁለተኛው
አዳም ጌታም ከኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡ እመቤታችን እናትም ድንግልም ስትባል መኖሯ አምላክ ወሰብእ
/ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው/ ሲባል ለመኖሩ ምሳሌ ነውና፡፡ ለትውልድ ማኅተመ ድንግልናዋ አለመለወጡ ሰው
ሲሆን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ ምሳሌ ናትና፡፡
“የበኲር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም” ሲል ምን ማለቱ ነው?
የበኲር ልጅ ለመባል የግዴታ ተከታይ ሊኖረው አይገባም፡፡ አንድ ብቻ ቢሆንም በኲር ይባላል፡፡ ከእርሱ በፊት
የተወለደ የለምና፡፡ ዘጸ 13፡1-2፡፡ የጌታ በኲር መባል የመጀመሪያም የመጨረሻም ብቸኛ ልጅዋ ስለሆነ ሲሆን
ከድንግል የተወለደውም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ የአብ ልጁ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ዕብ.1፡6፡፡
በሌላም በኩል ከፍጥረታት በፊት ያለና የነበረ፡፡ ፈጣሬ ኲሉ ዓለም መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፡፡ ይህንንም የቤተ
ክርስቲያን የንጋት ኮከብ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል “….. ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኲር ነው ሁሉ
በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል እርሱም ከሁሉ በፊት ነው፡፡” ቆላ.1፡17፡፡
“እስከ” የሚለውን ቃል አገባብ በተለያየ ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት እንደገባ በሚከተሉት
ምሳሌዎች እንመልከት፡፡
1. “የሳኦል ልጅ ሜልኮል አስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለችም” 2 ሳሙ.6፡23፡፡ አባባሉ ከሞተች
በኋላ ልጅ ወለደች የሚል ይመስላል፡፡ ዳሩ ግን ሰው ከሞተ በኋላ ሊወልድ ስለማይችል ትክክለኛው
ትርጉም ሳትወልድ መሞትዋን ለመግለጽ የተጠቀሰ መሆኑን ይገነዘቧል፡፡
2. “ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ” ሮሜ.5፡7፡፡ የሞት ንግሥና ከሙሴ በኋላ አለመቅረቱ
የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ አነጋገሩ መቀጠሉን የሚገልጽ ነው እስከ ጌታ ሞት ድረስ፡፡
3. “እግዚአብሔር ጌታዬን ጠላቶችህን ለእግርህ መረጋገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው”
መዝ.110፡1፡፡ ጠላቶቹን ካሸነፈ በኋላ በቀኝ መቀመጡ ቀረን ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታ በመስቀሉ ላይ
ዲያብሎስን ድል ካደረገ በኋላ /ቆላ.2፡14 ና 15/ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ሆኖ ያየው መሆኑን
ተናግሮአል፡፡ የሐዋ ሥራ 7፡55፡፡ የእስከ አገባብ በዚህ ላይ ፍጻሜ የሌለው ሆኖ እናገኛለን፡፡
4. “እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ማቴ.28፡20፡፡ ከዓለም ፍጻሜ በኋላ
ከእናንተ እለያለሁ ማለቱ አይደለም፡፡ ከላይ በተገለጸው መሠረት “እስከ” የሚለው ቃል ፍጻሜ ላለው
ነገር እንደሚገባ ሁሉ ፍጻሜ ለሌለው ነገርም ይገባል፡፡ ስለሆነም ወንጌላዊው ማቴዎስ “እስከትወልድ
ድረስ አላወቃትም” በማለት ዮሴፍ ጌታን ከወለደች በኋላ በሴትና በወንድ ግብር ፍጹም አላወቃትም
ማለቱ ነው፡፡
† የዮሴፍ ልደት በዋነኛነት ለምን ተጠቀሰ ?
ከእመቤታችን የሚወለደው ክርስቶስ ከይሁዳ ከዳዊት ወገን እንደሆነ ትንቢት ተነግሯል፡፡ /ኢሳ. 11፡1/ ነገር ግን ከእናት
ብቻ እንጂ አባት ስለሌለው ዮሴፍ ከዳዊት ዘር ነውና ክርስቶስ በእናቱ እጮኛና ዘመድ በዮሴፍ የዳዊት ልጅ ተብሎ
እንዲቆጠር ነው፡፡ ምነው በእናቱ የዳዊት ልጅ አይባልምን᐀ ቢባል አይሁድ ሴትን ከትውልድ ቁጥር አግብተው አይቆጥሩም
እና የእናቱን ከትውልድ መቆጠር ስለማይቀበሉት ነው፡፡ ስለዚህ በእናቱ እንዳይቆጠሩ አይሁድ ስለማይቀበ ላቸው
ወንጌላውያን የክርስቶስን ትውልድ ሲቆጥሩ በዮሴፍ በኩል ቆጥረዋል፡፡
/አልዓዛር ማታንና ቅስራን ይወልዳል፤ ማታን የዮሴፍ አባት ያዕቆብን ቅስራ ደግሞ የእመቤታችን አባት ኢያቄምን
ይወልዳሉ፡፡/
እመቤታችን ለዮሴፍ ለምን ታጨች ?

6|Page
=> አንድም ሴት ናትና ያውም መልከ መልካም ጠባቂ ስለሚያስፈልጋት በእጮኛ ስም ሊጠብቃት፣
=> አንድም ክርስቶስ ካለወንድ ዘር መወለዱን አይተው እናቱ ማርያም ከሰማይ የመጣች ኃይል ናት እንጂ የአዳም ዘር
አይደለችም፡፡ ክርስቶስም ከመልአክ የተገኘ መልአክ ነው የሚሉ መናፍቃን በኋላ እንደሚነሱ ስለሚያውቅ ከሰማይ የመጣች
ኃይል ብትሆንማ ለዮሴፍ መች ትታጭ ነበር᐀ ብሎ ነገራቸውን ለማፍረስ እንዲመች እመቤታችን እውነት የአዳም ዘር
እንደሆነች ለማስረዳት በእጮኛ ስም ለዮሴፍ እንድትሰጥ አደረገ፣
መታጨቷ ለዚህ ምክንያት እንደሆነም አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ገልጾታል፡፡ ገብርኤል መልአክም ወደ ድንግል ብቻ እንደተላከ
አልተናገረም፡፡ «ስሙ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ድንግል» አለ እንጂ፡፡ የወንድ እጮኛ በማለቱ እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም በእውነት ሴት እንደሆነች ያስረዳል ብሏልና፡፡
=> አንድም አገልጋይዋ ተላላኪዋ እንዲሆን ነው፡፡ ሄሮድስ ልጅዋን ሊገድለው ባስፈለገው ጊዜ ወደ ግብፅ ስትሰደድ ዮሴፍ
አብሯት ተሰዶ እንዲረዳት እግዚአብሔር ለዮሴፍ እንድትታጭ አደረገ፣
=> አንድም ከመደብደብ ከመወገር ሊያድናት በዘኁ. 5፡19 በተጠቀሰው መሠረት አንዲት ሴት ከባልዋ ሌላ ፀንሳ ብትገኝ
ማየ ዘለፋ ያጠጧት ነበር፡፡ እንዲሁም አንዲት ሴት ባል ሳታገባ ብትፀንስ በሙሴ ሕግ መሠረት ደብድበው ይገድሏት ነበር፡፡
ስለዚህ እመቤታችን ለዮሴፍ ሳትታጭ ፀንሳ ቢሆን አይሁድ ለድብደባ ባበቋት ነበር፡፡
ስለዚህ ድንግል ማርያም ለዮሴፍ መታጨቷ እኒህንና ይህን ለመሳሰሉ ምክንያቶች ነው እንጂ ለሚስትነት አይደለም፡፡ ለዚህስ
ቢሆን ኖሮ ለዮሴፍ ትታጭ ሲል ተአምራትን ባላሳየ ነበር፡፡ ለዚህም ቢሆን ኖሮ አንዲትን ሴት ለአንድ ወንድ ለማጋባት
በትር እስከማለምለም ባላስፈለገም ነበር፡፡
ከዚህም ሌላ ዮሴፍ ለእመቤታችን ለባልና ሚስት ወግ እጮኛ እንዳልሆነ ቅዱስ መጽሐፍ በግልጽ ያስረዳናል፡፡ ይኸውም
እመቤታችን ጌታን ከመውለድዋ በፊት የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም እየተገለጸ ሲያናግረው ለምሳሌ «እጮኛህን
ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ»< ነበር፡፡ ጌታን ከወለደች በኋላ ግን እጮኛህን የሚለውን መልአኩ ፈጽሞ
አልተጠቀመበትም፡፡ ነገር ግን «ሕፃኑንና እናቱን» የሚለውን አባባል ይጠቀም ነበር እንጂ እንደ ቀድሞው ሕፃኑንና
እጮኛህን አላለውም /ማቴ. 2፡13-15፣ 2፡20-21፤ ሉቃስ 2፡4-6፤ 2፡33-43/
ዳግመኛ ሚስቱ ብትሆን ኖሮ ባል ለሚስቱ ቀናተኛ ነውና ዮሴፍ ሕገ ኦሪትን ይፈጽም ነበር ማለት ማየ ዘለፋ እንድትጠጣ
ያደርግ ነበር፡፡ እርሱ ግን ይህን ሁሉ አለማድረጉ ጠባቂዋ ተላኪዋ መሆኑን ያሳያል፡:
† «ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን» ሲል ምን ያመለክታል ?
ክርስቶስ የፅርዕ ቋንቋ ነው፡፡ በዕብራይስጥ ማስያስ፣ በዓረብኛ መሲህ በግዕዝ ቅቡዕ ይባላል፡፡ ክርስቶስ የሚለው ስም
የትስብእት /የሰውነቱ/ ብቻ ወይም የመለኮት ብቻ አይደለም፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ
ቢሆን የወጣለት ስም ነው እንጂ፡፡ አምላክ ሰው ቢሆን የወጣለት ስም ነው፡:
«ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን» ብሎ ማቴዎስ ሲጽፍ ሐዋርያት ሲያደርጉ እንደነበር ሁሉ ከእመቤታችን የተወለደው
ኢየሱስ ትንቢት የተነገረለት ሱባኤ የተቆጠረለት እሥራኤል ዘሥጋ በተስፋ ሲጠባበቁት የነበረው ክርስቶስ መሆኑን
መመስከሩ ነው፡፡ /የሐዋ. 18፡28፤ የሐዋ. 2፡36/
 አላወቃትም … ከወለደች በኋላ አወቃት መለት ነዉን?

1. እመቤታችን በድንግልና እስክትወልድ ድረስ ወልድ የተባለዉ እርሱ ድንግል የትባለች እርሷ እንደሆነች አላወቀም

አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም መባሉ መጻህፍት በኩር ያሉት እመቤታችን በድንግልና
እስክትወልድ ድረስ ወልድ የተባለ እርሱ ድንግል የተባለች እርሷ እንደሆነች አላወቀም፡፡ ምነው መልአኩ ነግሮት የለም ወይ
ቢሉ በጊዜው የመልአኩን ቃል ይቀበለው እንጂ በፍጹም ምስጢር አልተረዳውም ምክንያቱም የዚህ አይነት ልጅ ከዚህ
በፊት አልተገኘምና አንድ አይን ቢያዩበት አያስረግጥ አንድ ምስክር አያስደነግጥ ነውና ይህንን ሁሉ ተፈጸሞ በዐይኑ

7|Page
እስኪያይ ድረስ አላወቀም ነበር፡፡ነብዩ ኢሳያስ አልተናገረውም ወይ ቢሉ እርሱም በደፈናው ድንግል አለ እንጂ ለይቶ
አልተናገረም ወልድን ትወልዳለች አለው እንጂ አምላክን ትወልዳለች አላለውም በዚህ ሁሉ ምክንያት የበኩር ልጇን
እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ነበር፡፡ኢሳ 7÷14 ፤ ማቴ 1÷25
2. የሰብአሰገልን መምጣት እስኪያይ ድረስ አላወቃትም
ሰብአሰገል(የጥበብ ሰዎች) ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ዘኁ 24÷17-18 የሚለውን ትንቢት በማንበብ በኮከብ ተመርተው
ወደቤተልሄም በመድረስ በበረት ለተኛው ሕፃን ያቀረቡትን በረከት(መስዋዕት) አረጋዊ ዮሴፍ ይህንን ሁሉ ባየ ጊዜ በዚያች
በከብቶች በረት የተኛው ሕፃን የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ የሚሰገድለት እጅ መንሻ የሚቀርብለት አምላክ መሆኑ እናታችን
ማርያም ወላዲተ አምላክ መሆንዋን አወቀ ተረዳ፡፡ ነገር ግን የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቀም ነበር ፡፡ ሉቃ
2÷7 ማቴ 2÷1

3. ቅዳሴ መላእክትን እስኪያይ ድረስ አላወቃትም


ለእንግዶች ማረፊያ(ማደሪያ) ስፍራ ስላልነበራቸው የሰማይና የምድር ፈጣሪ በከብቶች በረት በቤተልሔም ተወለደ ላሞች
በትንፋሻቸው አሞቁት ቤተልሔም በብርሃን ተጥለቀለቀ በከንቶች ዙሪያ አእላፋት መላእክት እንደ ሻሽ እየተነጠፉ
እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር በአንድነት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱሰ እግዚአብሔር እያሉ ሲያመሰግኑ ወደተኛው ሕፃን እና እናቱ
ዘንድ ሲሰግዱ አረጋዊው ዮሴፍ በተመለከተ ጊዜ የመላእክት ፈጣሪ ዝማሬ የሚገባው አምላክ መሆኑን አወቀ እርሷም
የመላእክት እህት እመ አምላክ መሆንዋን ተረዳ፡፡ነገር ግን በኩር የተባለውን መድኃኔአለም ክርስቶስን በድንግልና
እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ነበር፡፡ሉቃ 2÷7
4. የእረኞችን መምጣት እስኪያይ ድረስ አላወቃትም
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኋልና ይህም ምልክት ይሁንላችሁ ህፃን ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታዩታላችሁ
(ታገኙታላችሁ) መልአኩ ባላቸው መሰረት እረኞችም ይህንን የሆነውን ነገር እስከ ቤተልሔም ሔደን እንይ በለው ሰግደው
ከበጎቻቸው ግልገል በበረት ለተኛው ለተወለደው አምላክ እጅ መንሻ ሰጠ አረጋዊው ዮሴፍ ይህንን ነገር ባየ ጊዜ
ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና የተወለደው ሕፃን የእንስሳት ሁሉ ፈጣሪ የሰዎች ጌታ መሆኑን አወቀ ፡፡
የሕፃኑ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እመ ብዙሃን መሆንዋን ተረዳ፡፡ የእረኞችን መምጣት እስኪያይ ድረስ
አላወቃትም ነበር፡፡
5. የእመቤታችንን መልክ ለይቶ አላወቃትም
ነበር አረጋዊው ዮሴፍ እግዚአብሔርና ካህናት እንዲጠበቅ አደራ ሰተውት ወደቤቱም በወሰዳት ጊዜ የእመቤታችን መልክ
ስለሚለዋወጥበት አጥርቶ አላወቃትም ፈጽሞ ማየትም አልተቻለውም እመቤታችን ጌታን ከፀነሰች ጊዜ አንስቶ መልኳ
ይለዋወጥ ነበር ይህም የሆነው ነቢያት ምስጢረ ሥጋዌውን በብዙ ህብረ መልክ ትንቢት ይናገሩ ነበር አረጋዊው ዮሴፍ
ህብረ መልኳን አላወቀም ነበር፡፡ለዚህ ነው ወንጌላዊው ማቴዎስ የበኩር ልጇንእስክትወልድ አላወቃትም ያለው፡፡

6. የሰሎሜን ምስክርነት እስኪሰማ ድረስ አላወቃትም ነበር


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመውለጃዋ ጊዜ ሲደርስ ልጇን ወለደች ሰሎሜም እመቤታችንን እንደሌሎች እናቶች
ምጥእና ጭንቀት እንደሌለባት በድንግልናም እንደወለደች ባየች ጊዜ በዚህ ተገርማ የእመቤታችንን አንቀጸ ድንግልና በእጆቿ
በዳሰሰች ጊዜ እጆቿ በእሳት እንደተፈጅ እርር ኩምትር ብለው ተቃጠሉ ወዲያውኑም የተወለደውን ሕፃን መድኃኔ አለም
ክርስቶስን በዳሰሰች ጊዜ ያረሩና የተኮማተሩ እጆቿ ለመለሙ አረጋዊው ዮሴፍ ይህንን ሁሉ ተአምራት ሲያይ በእውነት
በእውነት እመቤታችን እሳተ መለኮትን በማህፀኗ የተሸከመች የስግው ቃል እናት መሆኗን አወቀ፡፡ሕፃኑም የሰሎሜን እጅ
ባለመለመ ጊዜ ነፍስና ስጋን ከመቃጠል የሚያድን አምላክ እንደ ሆነ አናቱም የህይወት እናት መሆንዋን አወቀ፡፡ ከእነዚህ
ሁሉ ግብራት በፊት ግን ማንነቷን አልተረዳም፡፡

8|Page

You might also like