You are on page 1of 2

የኮከቡ ሚስጢር

ይህ ባለስድስት ጉጥ ኮከብ የሰለሞን ማኅተም፥ የዳዊት ኮከብ ፥ የዳዊት ጋሻ ፥ የቴዎድሮስ ኒሻን ፥


የላሊበላ ጌጥ፥ የአክሱም ጌጥ፥ የፋሲል ጌጥ፥ የይምርኀነ ክርስቶስ ጌጥ ማኅተም በመባል ሲጠራ
አብዛኛውን ጊዜ ግን የሰለሞን ማኅተም አለያም የዳዊት ኮከብ በመባል ይታወቃል።

የዚህ ኮከብ አመጣጥ እንዲህ ነው፦

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚደጋገሙት ክስተቶች ውስጥ የኮከብ መታየት አንዱ ነው። ለምሳሌ ሙሴ
ሲወለድ ፥ ሰለሞን ቤተመቅደስ ሲሰራና ክርስቶስ ኢየሱስ ሲወለድ የታየው ኮከብ ለአብነት ተጠቃሽ
ነው። ይህ ሰለሞን አርማው አድርጎ በምኩራባት እንዲሰቀል ያዘዘው የኮከብ ቅርፅና በአገራችን ለብዙ
ዘመናት የቆየው የሰሎሞናዊው ሥርወ-መንግስት እንደአርማ ይጠቀምበት የነበረው ኮከብ ንጉሥ
ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ በፈለገ ጊዜ ከላይ ከሰማይ እያበራ የቤተመቅደሱን መሥሪያ
ሥፍራ የጠቆመው ኮከብ ነው።

ንጉሥ ዳዊት የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ የሚጠቁመውን በራዕይ ያየውን የኮከብ ቅርፅ ስሎ ቤተ
መቅደሱን እንደሚሰራ አስቀድሞ ለተነገረለት ልጁ አስቀምጦታል። ልጁም ስዕሉን ተጠቅሞ ኮከቡን
ከከዋክብት ለይቶ ባየው ጊዜ ኮከቡ ባበራለት ሥፍራ ላይ ቤተመቅደሱን ሰርቷል።
ወደ ሀገራችን ስንመጣ ደግሞ ደሸት የተባለ ታላቅ ፈላስፋ በታላቁ ወንዝ በግዮን ዳርቻ ሆኖ
በሚመራመርበት ጊዜ ምስለ ፍቁር ወልዳንና ይሄንን ባለስድስት ጉጥ ኮከብ በግዮን ውኃ ላይ ተስሎ
በማየቱ በሰሌዳ ስሎ ይህን የመሰለ ኮከብ በሰማይ ላይ ባያቹህ ጊዜ ተከተሉት ብሎ ለልጅ ልጆቹ
ስለነገራቸችው የሱ ዘሮች በተስፋ ይጠብቁት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ላይ እናገኘዋለን። የኩሽ
ልጆች (ኢትዮጵያዊያን) የዚህን ኮከብ በሰማይ መገለጥ ሲጠባበቁ ከኖሩ በኋላ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ
ኮከቡ በሰማይ ላይ ሲያበራ በመመልከታቸው ከአባቶቻቸው ጀምረው ይጠብቁት የነበረው ትንቢት
እንደደረሰ በማወቅ ኮከቡን ተከትለው ቤተልሔም ድረስ በመሄድ በከብቶች በረት ለተወለደው ለወልደ
እጓለ እመሕያው እጅ መንሻ እንደሰጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጽፏል።
.
የዚህ ኮከብና የኢትዮጵያዊያን ግንኙነት የሚጀምረው ከሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት አስቀድሞ የኖኅ
ልጅ ካም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበትና ኮከቡን በግዮን ውኃ ላይ ከተመለከቱበት ጊዜ
ነው።
.
እንግዲህ ከላይ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት የእሴይ ልጅ ዳዊት የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ
የሚያመለክተውን ኮከብ በትንቢት ካየ በኋላ በዙፋኑ፣ በጋሻውና በምኩራቦቹ ሁሉ እያስቀረፀ
አስቀምጦታል። የእርሱ ልጅ ሰሎሞንም በተመሳሳይ ኮከቡን በንግስና ዙፋኑና በሌሎች ቦታወች ሁሉ
ላይ ማስቀረጽ ጀመረ። ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ማክዳ (ንግስተ ሳባ ወይም ንግስተ አዜብ) የሰሎሞንን
ጥበብ በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ልትፈትነው ከብዙ እጅ መንሻ ጋር ወደ ሀገረ ኢየሩሳሌም ተጓዘች።
በእንግድነቷ ጊዜም ከንጉስ ሰለሞን ጸነሰች። የእስራኤል ቆይታዋን አጠናቅቃ ስትመለስም ንጉስ
እብነመለክ/አቤሜሌክ ወይም ቀዳማዊ ምንሊክን ወለደች። ንጉሥ ምኒልክ እድሜው በሃያዎቹ
መጀመሪያ በሆነ ጊዜ አባቱን የእስራኤልን ንጉሥ ሰለሞንን ጎብኝቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ብዙ
ሌዋውያን ካህናትንና ታቦተ ጽዮንን ከብዙ አጃቢ አይሁዶች ጋር ይዞ መጣ። ከዚህም በኋላ ምንሊክ
በኢትዮጵያ በነገሰ ጊዜ ቀድሞ በእናቱ ዙፋን ላይ ተቀርጾ የነበረውን የዘንዶ ምስል በማጥፋት ከአባቱ
ያገኘውን የኮከብ ምስል በዙፋኑና በእቃዎቹ እንዲሁም በጋሻውና በቤተመቅደሶች ሁሉ ላይ ቀረጸ።
.
ከዚህም በኋላ ዘራቸው ከሰለሞን የሚመዘዝ የሰሎሞናዊ ሥርወ ንግስት ነገስታት ሁሉ ይህን ኮከብ
እንደአርማ ይጠቀሙበት ነበር። ይህን ይመስላል የኮከቡ አመጣጥ።
.
የኮከቡ ትርጉም የሰፋ ቢሆንም Element encyclopedia of secret signs and symbols
ከተሰኘው የAlede Nozedar መጽሐፍ ያገኘሁትንና ሌሎችንም ተጨማሪ
ምንጮችን ተጠቅሜ ባገኘሁት መረጃ መሰረት
ምስሉ ላይ እንደሚታየው እያንዳንዳቸው የኮከቡ ጉጦች (ጫፎች) የተወከሉበት ቁጥር አላቸው።
ቁጥሮቹም በሁለንታ ውስጥ የሚገኙትን ፈለኮችን ይወክላሉ። ይኸውም፦
1=ጨረቃ
2=ቤነስ
3=ሜርኩሪ
4=ሳተርን
5=ማርስ
6=ጁፒተር
7=ፀሐይ ተብለው ይሰየማሉ። ይህም የሚያሳየው ምልክቱ ስለጠፈር የያዘው
ሚስጢር እንዳለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ መሀል ላይ መስቀሉ ሲጨመር
የመስቀሉን ብርሃናማነት[ፀሐይነት] ያሳያል።ላመኑበት መስቀል ብርሃን
ነው።ላመኑበት መስቀል የሀይል ምንጭ ነው።
.
ከዚህ በተጨማሪ ምልክቱ ለኢትዮጵያ የትንሳኤዋ አርማ ነው። በትንቢት እንደሚነገረው ይህ ኮከብ
በመጨረሻው ዘመን ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው ሳልሳዊው ቴዎድሮስ ሲወለድ በኢትዮጵያ ሰማይ
ላይ እያበራ በመታየት የትንሳኤዋን ብስራት ያውጃል። ይሄን የሰማው ካሣ ኃይሉ የንግስና ስሙን
ዳግማዊ ቴዎድሮስ በማለት ኮከቡን የአንገቱ ማዕተብ አድርጎት ነበረ። የጀግኖቹ የሽልማት ኒሻን ሁኖም
ነበር።
.
ኮከቡን በሚገባ ተጠቅመውበታል ተብለው በታሪክ መዛግብት የሚጠቀሱት ዳዊትና ልጁ ሰሎሞን
ናቸው። በተለይ ሰሎሞን
1-የአእዋፋትን ቋንቋ ለመስማት
2- የእንሰሳትን ቋንቋ ለመስማት
3-ሰይጣንን ለማሰርና
4-መናፍስትን ለማዘዝ ይጠቀምበት ነበር።

እኔ እገባለሁ
.
በአጠቃላይ ግን ይህ ኮከብ
1-የጥንቱን የአሁኑን እና የወደፊቱን ክስተት ሚስጢር ገላጭ
2-የደኅንነት አርማ። የእግዚአብሔርንና የሰውን በመስቀሉ መታረቅ የሚገልፅ የፍቅርና የነፃነት አርማ
ነው።
ወደ ላይ የሚያመለክተው ሶስት መዓዘን ሰማይን ሲወክል ወደታች የሚያመለክተው ደግሞ ምድርን
ይወክላል።መስቀሉ ሰማያዊዉንና ምድራዊውን ሶስት መዓዘን ማገናኘቱ በመስቀሉ ሰማያዊያንና
ምድራዊያን መታረቃቸውን ያሳያል።
3- Element encyclopedia of secret signs and symbols የተሰኘው የAlede Nozedar
መጽሐፍ እንደሚለው ከሆነ አእምሮን ያጎለብታል።
4-ሁሉም አጽናፈ ዓለማት በመስቀሉ ስር እንደሆኑ ያሳያል። እነሱም፦ ሰሜን፥ ደቡብ፥ ምስራቅ፥
ምዕራብ፥ አዜብ፥ መስእ፥ ባሕርና ሊባ ናቸው።

You might also like