Professional Documents
Culture Documents
ድልየእውነተኞች ናት
ድልየእውነተኞች ናት
ይሁን?
በአለም ላይ የሙስሊሙ ቁጥር ከየትኛውም የሃይማኖት ተከታይ የበለጠ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው።
ነገር ግን ስንቶች ናቸው ራሳቸውን የኢስላም ዘብ አድርገው የሚያስቡት ብለን ስንጠይቅ ጥቂቶች ሆነው
እናገኛለን።
ታዲያ እኛ ሙስሊሞች ለለውጥ መጣር ያለብን ሁላችንም ወይስ የለውጡን ነገር ለጥቂቶች እንተወው? ማን
ለኢስላም ጠበቃ ይሁን ? ስልም ይህን ማለቴ ነው ።
የተለያዩ እስላማዊ የታሪክ ማህደሮችን ስናገላብጥ የሙስሊሙ መሪዎች፣ ኡለማዎች...ማን ለኢስላም ጠበቃ
ይሁን? ሲባል
-ሱለይማን አዳራኒ የተባሉ ታላቅ አሊም እንዲህ ይሉ ነበር፦ “ሰዎች ሁሉ ሃቅን (ኢስላምን)ቢተዉት እና
ብቻየን ብቀር ስለኢስላም እውነተኛነት ሳልጠራጠር ስራየን በቀጠልኩ ነበር! “ ብለዋል።
-በ ታላቁ ከሊፋ ዑመር ቢን አልኸጧብ- አላህ ስራችውን ይውደድላችው- ዘመን አመረማድ()عام الرماد
እየተባለ የሚታወቅ ትልቅ ድርቅ የደረሰበት አመት ነበር የኡመርን ጭንቀት ያስተዋሉ ጓደኞቻቸው እንዲህ
ብለው ነበር : “ አላህ ይህን ድርቅ ባያነሳልን ኖሮ ኡመር በጭንቀት ይሞታሉ ብለን ሰግተን ነበር!”
-ከለታት አንድ ቀን ኡመር - አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው- ቁጭ ብለው ያንቀላፉ ነበር ጓደኞቻቸውም :
ምነው ለምን አረፍ አይሉም? ሲሏችው “ ቀን ከተኛሁ የህዝቦቼን ሀቅ፣ ማታ ከተኛሁ ደሞ የገታዬን
ሃቅ(ኢባዳ) ላጎድል ነው! ” ብለው መለሱ።
-ኢማዱዲን ማህሙድ አዘንኪ ታላቅ ሙጃሂድ እና አላህን የሚፈራ ታላቅ የሙስሊሞች መሪ ነበር ኢብኑል
አሲር የተባሉ የታሪክ ጸሃፊ ስለሳቸው እንዲህ ብለው ነበር ፦ “ ፈሪሀ አላህ እና በፍትህ ኡማውን ያስተዳደረ
መሪ ከኡመር አ/አዚዝ በኋላ እንደ ማህሙድ ዘንኪ አላየሁም! ” በማለት መስክረውለታል ።
-ኡወይስ አልቀርኒ ማታ ማታ የተራበውን ካበሉ የታረዘውን ካለበሱ በኃላ እንዲህ ይሉ ነበር ፦ “ ጌታዬ ሆይ
በረሃብ ወይም በእርዛት ምክንያት አንድ ሙስሊም ቢሞት ተጠያቂ አታድርገኝ!”
ይህ እንግዲ ከብዙው ጥቂቱ ነው ታሪክም ነው ታሪክ ደሞ እራሱን ይደግማል ሲባል ነው የምናውቀው ታድያ
እኛ ሙስሊሞች ታሪክን መድገም ለምን ተሳነን? ወይስ አባባሉ ነው የተሳሳተው? ።
እኛ ሙስሊሞች ምን ያህል ለኢስላም እየተጨነቅን ነው? አንድ ቀን የኡማው ጉዳይ አስጨንቆን ራሳችንን
አሞን ያውቃል!?
ለኢስላም ምን ሰርተናል? ምንስ ለመስራት አስበናል? ማንንስ እየጠበቅን ነው? በተለይ እኛ ወጣቶች አላህ
በተለያዩ ዘርፎች የሰጠንን ተሰጥኦና ዝንባሌ ዲናችንን ለመርዳት እናውል እያልኩ እስላማዊ ጥሪየን
አቀርባለሁ።
ድል የእውነተኞች ናት!