You are on page 1of 45

ትርጓሜ ስም፣ ግእዝ እና ባህላችን

አዘጋጅ፦ መምህር በትረማርያም አበባው


2015ዓ/ም
ትርጓሜ ስም

ስም ትርጉም
1 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ
2 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ
3 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ
4 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር
17 ዲና፦ፈረደ
18 ማኑሄ፦እረፍት
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ
21 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል
22 ሐና፦ ስጦታ
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ
25 ቶማስ፦ፀሐይ
26 ጎርጎርዮስ:-ንቁሕ የተጠበቀ
27 ማትያስ፦ፀሐይ
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና
30 ኖኅ፦ደስታ
31 ሴም፦ተሾመ
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው
36 እሴይ፦ዋጋየ
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው
42 ዮናስ፦ርግብ
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ
44 ራኄል፦በግዕት
45 ዕዝራ፦ረዳቴ
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት
51 ሶምሶን፦ፀሐይ
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
53 ማርታ፦እመቤት
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር
59 ሄኖስ፦ሰው
60 ሰሎሜ፦ሰላም
61 ሩሐማ፦ምሕረት
62 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል
63 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ
64 ኑኃሚን፦ደስታየ
65 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ
66 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል
67 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል
68 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
69 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ
70 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል
71 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል
72 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር
73 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ
74 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!
75 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል
76 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት
77 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
78 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ
79 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ
80 ሣራ፦ልዕልት
81 ስምዖን፦ሰማ
82 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
83 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
84 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል
85 አልዓዛር፦ትርጉሙ እግዚአብሔር ረድቷል
86 አስቴር፦ኮከብ
87 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ
88 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው
89 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ
90 አብራም፦ታላቅ አባት
91 አብርሃም፦የብዙዎች አባት
92 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው
93 አክዐብ፦የአባት ወንድም
94 ባሮክ፦ቡሩክ
95 አዳም፦መልካሙ
96 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
97 ባርቅ፦መብረቅ
98 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው
99 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል
100 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ
101 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል
102 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት
103 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
104 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ
105 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው
106 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው
107 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል
108 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
109 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
110 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል
111 ኤዶም፦ቀይ/የገነት ሌላ ስም ነው
112 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል
113 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው
114 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ
115 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ
116 ሰሎሞን፦ሰላማዊ
117 ኬብሮን፦ኅብረት
118 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል
119 ኤደን፦ደስታ
120 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
121 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል
122 ይሳኮር፦ ዋጋዬ
123 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ
124 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው
125 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው
126 ዮሴፍ፦ይጨምር
127 ዮናስ፦ርግብ
128 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
129 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል
130 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው
131 ምናሴ፦ማስረሻ
132 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል
133 ዲቦራ፦ንብ
134 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
135 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው
136 ጽዮን፦አምባ
137 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
138 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
139 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
140 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።

ምንጭ:-ቅዱሳት መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት


እንዲሁም የአንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት

ዕፀዋት በግእዝ ቋንቋ

ግእዝ__አማርኛ
ሰናፔ__ሰናፍጭ
ሐረፍ__ጎመንዘር/ቅባኑግ
መናሂ__ነጭ ጤፍ
ዳሂ____ጓያ
ሡራሕ_ድንች
ቤዴላህ____እንጉዳይ
በጢሕ_ዱባ
ሄላ____የወይን ዘለላ
ደንጎላ__ሱፍ
ስንዳሌ_ስንዴ
ሐምል__ጎመን
በድል/ፋል___ባቄላ
በጸል/ቱማ___ነጭ ሽንኩርት
እክል___እህል
ዚፋል___ሽንብራ
ቢጸልቱማ___ቀይ ሽንኩርት
ሕጥሜ_ጎመንዘር
ኅጥጥሜ___ጥጥ
ሐምሐም____ቅል
ሰገም___ገብስ
ሊጦስ/አስፈሊጦስ__ሰሊጥ
መለንስ_ኑግ
ሲላስ__አብሽ
ቆንደራጢስ/ዱሓን__ዳጉሳ
ተርሙስ____አተር
አለንስ__አጃ
ሕምር/ጥምዐት____እንሶስላ
ትለቤ/ከሙን__ተልባ
ሶመት_ነጭ ሽንኩርት
እንጎት_ትርንጎ
መርሳኒ_ቀጋ
መልጰጶን____ጎመን
ከሜን__ፌጦ
ከርካዕ_ሎሚ
ፔርካ__ሽንብራ
ጓልኬ_ሰናፍጭ
ሴዋ__ጌሾ
ቃሕዋ_ቡና
ሥርናይ___ስንዴ
ተቅዳ_ድንብላል
ስጕርንድ___ሽንኩርት
ሑስጱ_አሽክት
ክርዳድ_እንክርዳድ
ኵሓ____ከያ ዛፍ
ኤርጋሄ__አክርማ
ሰግላ___ሾላ
አሜከላ_እሾህ
ኩላ___ሙጫ
ሕንጽዋል___አረማሞ(የእፅዋት በሽታ)
ከርሜል__ችፍርግ
ቢሶም___ምሳና
በርሴም__ጽድ
በራቄኒም_ኮሸሽላ
ዖም_____ዛፍ
ተቢሳ___ሸንበቆ
ሜርሴንስ____ቀጋ
ቄድሮስ__ዋንዛ
ባሕሩስ_መቃ ሸንበቆ
ብሕውስ____መጭ/አብሾ/አስተናግር
ኤልያስ__ወይራ
ጠርቤንቶስ____ዋርካ
መዓረግራ_ሙጫ/አዶሮማር
ፐፒራ/አዛብ____እንዶድ
መምሬ_ወይራ
ተምር__ተምር
ዕጕስታር_ሬት
አጽፋር__አደይ አበባ
ሳቤቅ_ያረግ ሬሳ
ዘግባ_ዝግባ
ቀረብ_እንቧይ
ዐቃብ____ኮሸሽላ ሾኽ
ስት___ቄጤማ
አርቦት_ችባሓ
አቃኒ_ችፍርግ
ጳውቄና____ጽድ
ልብኔ_ልምጭ
ሰቂኖን_ኮክ
ሰኪኖን_እንዶድ
ሰውሳን_ሱፍ
ሰጥረጲሎን____ዋንዛ/ሽነት
ራምኖን_ዶግ
ቄድሮን__ዋንዛ
ተርሜን_ድድሆ/ክትክታ
ከርሜን_ድድሆ
ጢጤን_ዶቅማ
ጎሜዕ__ሸንበቆ/ቅርቅሀ
ሮዛ____ጽጌረዳ
አርዝ___ዛፍ
ፒርልዩ__ቀንጠፋ
ምግራይ____ግራር
መጽርይ_ቀጋ
ፐፒረለይ____እንዶድ
መድዮ___ጨፌ
ቀለምጤዳ____ቅንጭብ
ቀለምጼዳ_ቁልቋል
ተሐግ_____ሰርዶ

እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፋት በግእዝ

ግእዝ_አማርኛ
ቶራ_አጋዘን
ሐንዘር___አነር
ነምር____ነብር
አድግ____አህያ
አካሂ_ጥገት (አራስ ላም)
ካሂ__ጊደር
ተክሉ____የበግ አውራ
ኢናጦሊ__የግመል ጊደር
ጠሊ____ፍየል
ዳቤላ___የፍየል አውራ
በቅል___በቅሎ
ዕዋል___የአህያ ውርንጭላ
ዕጕል__ግልገል
ገመል__ግመል
ላሕም__ላም/በሬ
ሰቄዘሩ__አራስ ውሻ
ሦር____በሬ/ወይፈን
ከልብ___ውሻ
ሔሴሜት____ድመት
ቴፈን__ወይፈን
መሐስዕ_ጠቦት
በግዕ___በግ
በሐኵ__ጠቦት/አውራ
ጣዕዋ__ጥጃ
ሐርጌ__ጊደር/ሙክት
ሐርገፅ__አዞ
ተስጴዳ_ጥንቸል
ቀርዱ__ዝንጀሮ
ከማንዮ__ግስላ
ከራግልዮ_ዐሳማ
ሐለስትዮ__ጦጣ
ሆባይ _ዝንጀሮ
አርዌ___አውሬ
ግሔ____እሽኮኮ
ቢሕ____ጉማሬ
ዔሊ___ድንጋይ ልብሱ
ተኵላ__ተኵላ
መንተሌ_ጥንቸል
ሐራድል_ጅብ
ኀየል____ዋልያ
ቀይዘል_ሚዳቋ
ቍንጽል_ቀበሮ
ወይጠል____ፌቆ
አንበሳ____አንበሳ
ሐሪስ_አውራሪስ
ዋኖስ___ዋሊያ
ገሙስ__ጎሽ
ጋስ____የሜዳ አህያ
ፎቃንስ__ጉሬዛ
ራኩብ____የግመል ወሳብሬ
ዝእብ_ጅብ
ላጽቂት____ፌንጣ/እንሽላሊት
ሥርዐት____ድርጪት
ብሄሞት____ጉማሬ/ጎሽ
ተረቅት/ጽግነት_የሌት ወፍ
ጼዴነት____ድንጋይ ልብሱ/ዔሊ
ጻጹት___ጫጭት
ጽርኒ____አይጥ
ኦርና____ሚዳቋ
ማዖን____ድኩላ
ሰርኖን____ሰገኖ
ሰራግልዮን___ዐሳማ
ቅጥራቅጥሬን____ድንቢጥ
ተመን_ዘንዶ
ደስከን_ጎሽ
ደራጎን_ዘንዶ
ቀቀኖ_ርኩም
ደስከኖ_ጎሽ
እልልድኩ_አነር ድመት
ሐርማዝ_ጎሽ
ቅንፉዝ_ጃርት
ነጌ__ዝሆን
ጸያጴ____እንሽላሊት
መንጢጥ____ድምቢጥ ወፍ
አዲማ/ቶብኒ____ትኋን
ቃሕም____ገብረ ጉንዳን
ቆጶሮጢስ___የንብ አውራ
ንብሌስ_ፌንጣ
አክሳስ____ሺህ እግር/ቅንቡርስ/የእበት ትል
ዘንቢር____ተቆናጣጭ ዝንብ
ሐንቄ/ቆብኒ_ቅማል
ንህብ____ንብ
አቅራብ_ጊንጥ
ሣሬት__ሸረሪት
ሰኳዕት____ጉንዳን
ጸንጾላዕት___የእሳት ራት
ጽንጽንት____ነቀዝ/ብል
ቁንቁኔ___ነቀዝ
ሐሴን____አሸን
ቀርነናዕ____ትል
ቈርነናዕ____እንቁራሪት
ኮራኪ_ምስጥ/ጉንዳን
አንጼዋ____አይጥ
ከመዝ____የውሃ እናት
ትንንያ____ትንኝ
ጽንጽንያ____ዝንብ
ጕጋ__ቁንጫ
ዕፄ_ትል
ፃፄ__ብል/ነቀዝ
አንባጣ____አንበጣ
ኤርጌት____አውራ ዶሮ
ፍኅርት_ጫጭት
ዖፍ__ወፍ
ዶርሆ_ዶሮ
ዘርቤዶ_ዥግራ
ቆቅሕ___ቆቅ
ገምሉ___አለቅት
ኔስታሊ__የመስክ እባብ
ኤሉሊ__የእሳት ራት
ከይሲ_እባብ
ዓሣ__ዓሣ
ጋርሣ_አንባዛ
ሬክትም/ፊካትም_የውሃ እናት
ሰጳላክስስ/ገላሜዎስ____እስስት
አንበሪ/ዐንበር__ታላቅ ዓሣ
ጳልቃን_ርኩም
ሰገኖ_ሰጎን
ንስር_አሞራ
ዐንቄ____ጭላት
ርግብ___ርግብ
ማዕነቅ____ሽመላ
ቋዕ____ቁራ
ሶቤቃካ____ጅግራ
ኬሌሜዎን____እስስት
ዙዝዮን_አለቅት

ማስታዎሻ:-ለአንዱ የአማርኛ ቃል ብዙ የተለያዩ የግእዝ ቃላት


ሊኖሩት ይችላሉ። ለምሳሌ ርኩም ለሚለው የአማርኛ ቃል በግእዝ
"ጳልቃን" ወይም "ቀቀኖ" ይሆናሉ። ስለዚህ ከጽሑፉ የተደጋገመ
ነገር ብታዩ ተሳስቶ ሳይሆን ለአንዱ ቃል ብዙ አቻ ትርጓሜ ስላለው
መሆኑን እንድትገነዘቡ።

ምግብና መጠጥ ነክ ነገሮች

ግእዝ_አማርኛ
ገይላ____አሞሌ ጨው
ተብሲል___ንፍሮ
ጼተሎ____ጉሽ ጠጅ
ጳኵሲማ____ዳቦ/አንባሻ
ልሔም_ዳቦ
ፕፕሬ____በርበሬ
መዓር_ማር
ሶከር_ስኳር
ሐሊብ____ወተት
ኅብስት____እንጀራ
አረቦናት____ፍትግ ክክ
አያያት_የማር ወለላ
ግብነት_አይብ
ሆሳዕና_መድኃኒት
መና_እንጀራ
ጸደና____የጣዝማ ማር
ዕቋን____ወገሚት
አክራጦን___የወይን ጠጅ
ወይን____ወይን
ጤጉን_ዳቦ ቆሎ
ሐምለ ብሒእ____ስልጆ
ፀቃውዕ_የማር ወለላ
ኮቤዝ_ዳቦ/አንባሻ
ማዕድ____ማዕድ/መሶብ
ቴሮጋ_እርጎ ወተት
ሱራጌ_መረቅ
አንቆቅሖ____እንቁላል
የአካል ክፍሎች

እራኅ_መሐል እጅ
ድማኅ____መሐል ራስ
ዳሌ__የጀርባ አጥንት
ሰይል_ሽል/ጽንስ
ዐፅም____አጥንት
ተኬሳ_ትክሻ
ሕዋስ_ሰውነት
ሐቌ_ወገብ
ቅርንብ____ቅንድብ
ዘነብ_ጅራት
ደርፍዑ____ሻኛ
ቀርን_ቀንድ
ተላዕ____ፍሪንባ
ጸኵ_ሹልዳ
መስቴካ____ጨጓራ
ገቦ__ጎን
መልታሕት___ፊት/ጉንጭ
ማዑት____አንጀት
መዝራዕት___ክንድ
ሥዕርት____ጸጉር
ኵሊት_ኩላሊት
ሰኮና_ተረከዝ
ሥን_ደም ግባት
እዝን____ጆሮ
ዓይን____ዓይን
ዘባን_ጀርባ
ጕርዔ____ጉረሮ
ሰንቡዕ____ሳንባ
ኵርናዕ_ክንድ
ሐልገዝ____የደም ሥር
መንኮብያ____አውራ ጣት
ክሳድ__አንገት
ከብድ__ሆድ
ቍይጽ__ጭን
መትከፍ_ትከሻ

#የቤት ዕቃዎች & አልባሳት
ቀርጠፋሉ____ቶፋ
ገብላ___ገንዳ/ገበታ
ቤረሌ___ብርሌ/ብርጭቆ
መሐፒል_ሳሙና
መንዲል_ሸማ ልብስ
ሰይቀል_እንዝርት
ጻሕል__ወጪት
ጽንጉል_ፍግ
ፍያል__ፍንጃል
ማዕሎ_አዷማ
ለንጳስ__ግምጃ
ኬጥሮጋውሎስ___የብረት ጋን
ፊላስ_የአልጋ ልብስ
ጌልዳቦሩ____ቡሃቃ
ምዕራ/መታግር_ጉልቻ
ቃሩራ____ጠርሙስ/ብርጭቆ
ንብቲራ_ኩስኩስት
ኮራ____ጋን/ጽዋ
ፓፒራ____ክብሪት
ጶደሬ____ግምጃ
ቢሶስ___አረንጓዴ ዓይነት ልብስ
ከፈር_ቅርጫት/እንቅብ
ጎሞር/ሜላቃ_ቁና
ጻሕር____ብረት ምጣድ
ፀምር____ግምጃ
መባሮ____መቆፈሪያ
መጕድዕ____መዶሻ
መሥነቅ____ስልቻ
መቀቅ_ሙገጫ
ቴውናቅ/ሱጣብ/ሱጣ__ወስከንበያ
ጸርቅ__ድሪቶ
ሶርቃቡ_እርሾ/ሊጥ
ድልጋቡ_አቅማዳ
መኩረቢ_መጥረቢያ
መሶብ_መሶብ
መዝረብ/ሰፌልያ____መዶሻ
መዝገብ_ሳጥን
ግራብ__ገንቦ
ጻሕብ__ማድጋ/ወጭት
ከረቦ__አገልግል
ክእቦ/ክቦ__ኩበት
ልሕኵት__ገንቦ
ሜላት_ሐር ግምጃ
መስብክት____ጋን
መሥነቅት____አቅማዳ
መቅጹት____ድስት/ምንቸት
መንኮክት____እንዝርት
ራግናት__ብቅል
ቀሡት_እንስራ
ዐራት_አልጋ
ወዲፈት____ዳውጃ/ግምጃ ጨርቅ
ጽህርት____ጋን
ጽፍነት____ስልቻ
ቴግኑ_ጉልቻ
ፓና____መብራት
ልጕን____ማሰሮ
ቆጶን____ጫማ
ጤገን____ብረት ምጣድ
ጵርዩን____መጋዝ
ግምዔ____ማሰሮ
ገልዕ____ገል
ፀፍዕ____አዛባ/ፋንድያ
መንካ____ማንኪያ
ማዕከክ_ማሰሮ/ቶፋ/ገንቦ
ማህው__ብርጭቆ/ብርሌ
ጠረጴዛ____ወንበር
ሰፌልያ____ድጅኖ/መዶሻ
አስፈሬዳ____እንቅብ/ቅርጫት
ወሳይድ_ትራስ
ሰንጎጕ_የብረት ዘንግ

መልክዐ ምድር እና ነገረ ሀገር

ሄላ_ምንጭ
ዔላ_የውሃ ጉድጓድ
ቀልቀል___ገደል አፋፍ
ደወል_አውራጃ/ቀበሌ
ዐምዓም___ረግረግ
ገዳም/ሊሳ_ዱር/በረሓ
መጽአሞ____ዋሻ/ግምጃ
ቆሮስ_መስፈሪያ ላዳን
ቀርሜሎስ____ለምለም ዱር
ቃዴስ____በረሓ
አርዮጳጌጤስ____መዝናኛ ቦታ
ባሕር____ባሕር
ወግር_ኮረብታ
ደብር_ተራራ
ሰንሰሪቁ/ኬርቃ____ስርጥ መንገድ
መርቄ____ቆላ
ሐይቅ____ወደብ/ዳር
መርሕብ____ሜዳ
ዐቀብ_ተራራ/ገደል
ግብ__ጉድጓድ
ምኔት_ገዳም
ሰኮት_አውራ መንገድ
ዐዘቅት____ጉድጓድ
ደሴት_የባሕር ጥጋጥግ
ገነት_ጓሮ/የተክል ቦታ
ጾማዕት/ጾላዕት___ዋሻ
ፂዖት____የከብት መሰማሪያ ክልክል
ፍኖት___ጎዳና
መዲና____ከተማ/አደባባይ
ፍና_መንገድ
ጕርን____አውድማ
ደደክ_ደጋ
ሐዝሐዝ____ረግረግ

የእርሻ እቃዎች

ላሕሎ_ወገል
ሰይራ_ወገል
ሞሰርት_ማረሻ
አርዑት_ቀንበር
አግልዕት____ማነቂያ
ገራህት____እርሻ
ጸጕራፍ____ጅራፍ

ነገረ ቤት

ትሄ_____መስኮት
ጽርሕ_አዳራሽ
ኰኵሕ_አለት ደንጊያ
መርኆ_መክፈቻ
ሶልላ__ኩረት፣ አሸዋ፣ አፈር
ጺላ___ጭቃ
ሶቶፍሌ_ምንቸት
መርጡል____አዳራሽ
ሩካም___ዕብነ በረድ
ተንከተም_ድልድይ/መሰላል
ናሕስ___የግንብ ቤት
ኤስኬዴሬ_እልፍኝ
ኆር____መስኮት
ጠፈር____ባጥ
ፍንዱቅ____ሆቴል
ኆኅት_ደጃፍ
ሐይመት____ድንኳን
ልገት_ጎጆ
መሬት_አፈር
ብርት__ብረት
ቤት_ቤት
ኀጺን_ብረት
ሜላንትሮን____ጉልላት
ዕብን_ድንጋይ
ጽንጕን____ጭቃ
ታዕካ____አዳራሽ
ሐኒክ____አፈር
ሰዋስው___መሰላል/ድልድይ
ዴዴ____ደጃፍ በር
ሐመድ____አመድ/ክሰል
ድድ_መሰረት
መምሠጥ____ቁልፍ
አንቀጽ_ደጃፍ/በር
ዕፅ___እንጨት

ለአንድ ቃል ብዙ ተመሳሳይ ትርጉሞች አሉት። ስለዚህ የተደጋገሙ


ቃላትን ስናይ በዚህ መልኩ እንደሆነ እናስተውል።
ለልጅዎ የግእዝ ስም ማውጣት ከፈለጉ ክፍል ፪

ግእዝ__አማርኛ
፩) መዓርዒር__ጣፋጭ
፪) አሜር__ፀሐይ
፫) አርያም_ሰማይ
፬) አምኃ_እጅ መንሻ
፭) ብሥራት___የምስራች
፮) ሰሎሜ_ሰላም
፯) አሜን__እውነት/ይሁንልኝ
፰) ሠዊት__እሸት
፱) ጸገየ___አበበ
፲) አስካል____ፍሬ
፲፩) ልዑል____ከፍ ያለ
፲፪) ሣህሉ____ይቅርታው
፲፫) ቀጸላ_አክሊል
፲፬) ሐመልማል___የለመለመ
፲፭) ከሃሊ_የሚችል ቻይ
፲፮) ጸዳሉ_መብራቱ
፲፯) ፈትለ ወርቅ____የወርቅ ፈትል
፲፰) ፊደል_ፊደል
፲፱) ማኅተም____ማተሚያ
፳) ሥዩም__የተሾመ ሹም
፳፩) ስብሐት____ምስጋና
፳፪) ስቡሕ_ምስጉን
፳፫) ተቅዋም_መቅረዝ
፳፬) ንጹሕ_የነጻ
፳፭) ሰላማ__ሰላም
፳፮) አዳም__ያማረ
፳፯) ዳግም_የደገመ
፳፰) ግሩም_ተፈሪ
፳፱) ጥዑም____የሚጣፍጥ
፴) ፍጹም__የተቀባ
፴፩) ይኄይስ____ተሻለ
፴፪) ሐዳስ/ሐዲስ___አዲስ
፴፫) ሕዳሴ__መታደስ
፴፬) ሰንኮሪስ_መምህር
፴፭) መቅደስ_ማመስገኛ
፴፮) ሞገስ__ባለሟል የተወደደ
፴፯) ትዕግሥት_መቻል
፴፰) ንጉሥ__የነገሠ
፴፱) ወራሲ__ወራሽ
፵) ውዳሴ__ምስጋና
፵፩) ጌራወርቅ____የወርቅ ሥራ
፵፪) ማኅደር_ማደሪያ
፵፫) ምሕረት_ይቅርታ
፵፬) መሓሪ__ይቅር ባይ
፵፭) ሠምረ__ወደደ
፵፮) ሥሙር_ተወዳጅ
፵፯) ሥምረት____መወደድ
፵፰) ነጸረ__ተመለከተ
፵፱) ምሥጢሩ____ምሥጢሩ
፶) መራሒ____መሪ
፶፩) ፍሥሓ_ደስታ
፶፪) አእመረ____አወቀ
፶፫) አእምሮ____እውቀት
፶፬) ፍቅር__መውደድ
፶፭) ክቡር__የከበረ
፶፮) ደብሩ__ተራራው
፶፯) ተግባር_ሥራ
፶፰) ረቂቅ__ረቂቅ
፶፱) መብረቁ____መብረቁ
፷) ነጸብራቅ__ነጸብራቅ

፷፩) ይባቤ___እልልታ
፷፪) ጥበቡ___ብልሃቱ
፷፫) መሠረት__መሠረት
፷፬) ብሑት___ስልጡን
፷፭) ትሕትና___ትሕትና
፷፮) ተከሥተ__ተገለጠ
፷፯) ሃይማኖት_ሃይማኖት
፷፰) በየነ__ፈረደ
፷፱) መኰንን____ገዢ
፸) በጽሐ__ደረሰ
፸፩) መስፍን____የሚገዛ
፸፪) ምስፍና____ግዛት
፸፫) ክርስቲያን____ክርስቲያን
፸፬) ወሰን__ድንበር
፸፭) መዋዒ_አሸናፊ
፸፮) ትንሣኤ_መነሳት
፸፯) ነቅዐ ሕይወት_የሕይወት ምንጭ
፸፰) ገዛኢ__ገዢ
፸፱) ምሕርካ ክርስቶስ___የክርስቶስ ምርኮ
፹) ባራኪ____ባራክ
፹፩) መልአክ____አለቃ
፹፪) በረከት____በረከት
፹፫) ህላዌ_መኖር
፹፬) ኂሩት_ቸር የሆነች
፹፭) ልባዌ_ማስተዋል
፹፮) ቤዛዊት_ያዳነች የምታድን
፹፯) ስርጋዌ____ሽልማት
፹፰) ስርጉት____የተሸለመች
፹፱) ተስፋ_ተስፋ
፺) ኬንያ__ብልሃተኛ
፺፩) ኖላዊ__ጠባቂ
፺፪) መርዓዊ____ሙሽራ
፺፫) ማዕዶት____መሻገሪያ
፺፬) ወልታ____መከታ/ጋሻ
፺፭) ሐዋዝ____ያማረ
፺፮) ግእዛን____ነጻነት
፺፯) ሕሊና____ሕሊና
፺፰) ማኅሌት____ምስጋና
፺፱) ኅሩይ__ምርጥ
፻) ሲሳይ__ምግብ
፻፩) ሠናይ____ያማረ
፻፪) ፈታሒ____የሚፈርድ
፻፫) ሐሴት____ደስታ
፻፬) ትርሲት_ሽልማት
፻፭) ተዋናዪ_ተጫዋች
፻፮) ዐቢይ___ከፍ ያለ
፻፯) ትውፊት_ስጦታ
፻፰) ኃያል_የበረታ
፻፱) ጽጌ__አበባ
፻፲) ፍሬሕይወት____የሕይወት ፍሬ
፻፲፩) ምዕዳን_ምክር
፻፲፪) ንኡድ___ያማረ
፻፲፫) ነገደ___ሄደ
፻፲፬) ነጎድጓድ____ነጎድጓድ
፻፲፭) ጸዓዳ_ነጭ
፻፲፮) ሠረጸ_በቀለ
፻፲፯) ደምፀ____ተሰማ
፻፲፰) ሮሐ_ወለወለ/አራገበ/አናፈሰ
፻፲፱) ናርዶስ_ሽቱ
፻፳) እፀ ሕይወት___የሕይወት እንጨት

ክፍል ፩ ከዚህ ቀደም በዚሁ በቴሌግራም ቻናሌ ተለቆ ስለነበር


ወደኋላ ተመልክተው ያገኙታል።

ወንድ ወንዱ በጦርነት አልቆ ጥቂት ወንዶች ብቻ ይቀራሉ። ያን


ጊዜም ሴቱ ስለሚበዛ አንዱን ወንድ ሰባት ሴቶች አግባን ይሉታል። ያ
ጊዜ መቼ እንደሆነ ግን አልተገለጸም። ኢሳ. ፬፣፩ "በዚያም ቀን ሰባት
ሴቶች። የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤
ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን
ወንድ ይይዙታል" ተብሎ ተጽፏል። ይህ ለጊዜው በትንቢቱ
እንደተገለጸው ሰሙ ወንዱ አንሶ ሴቱ ይበዛልና ነው። ወርቁ ግን
ወንድ የተባለ ክርስቶስ ነው። ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ
ተብሏልና። ሰባት ቁጥር በዕብራውያን ትርጓሜ ፍጹም ነው። እስመ
ኍልቈ ሳብእ በኀበ ዕብራውያን ፍጹም ውእቱ እንዲል። ሴቶች
የተባሉ ምእመናን ናቸው። ሰባት ሴቶች ማለት ፍጹም ምእመናን
ማለት ነው። የገዛ እንጀራችንን እንበላለን ማለት ምግባር ትሩፋት
እንሰራለን ማለት ነው። ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ ማለት አንተ
ክርስቶስ እንደተባልክ እኛም ክርስቲያን እንባል ማለት ነው።
መሰደባችንን አርቅ ማለት ጣዖት አምላኪ መባላችንን አርቅ፣ አዳም
ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ ያለውን የዕዳ ደብዳቤ
ደምስስልን ማለት ነው። የስም ክርስቲያን አንሁን። በኑሮም፣
በንግግርም፣ በሥራም ክርስትናችንን የሚገልጽ እንሁን። የወሬ ብቻ
ሳይሆን የተግባር ክርስቲያንም እንሁን። ጥላቻን በፍቅር፣ በደልን
በይቅርታ እናስወግድና ሰላማውያን እንሁን።

ሥርዓተ ምግብ

እግዚአብሔር በቸርነቱ በዚህ ምድር እስካለን ድረስ ለሥጋ መቆያ


ምግብን ሠጥቶናል። የአበላልም ግን ሥርዓት አለው። ይህ
ሁላችንንም የሚመለከት ነው። 3 ነገሮችን እንመልከት። እኒህም
ቅድመ በሊዕ፣ ጊዜ በሊዕ፣ እና ድኅረ በሊዕ ናቸው።እነርሱን
እንመልከት።

ቅድመ በሊ ዕ፦ ከመብላታችን በፊት ምግብን የሚሰጥ


እግዚአብሔርን ስለሰጠን "አባታችን ሆይን እስከመጨረሻው" ብለን
ልናመሰግነው ይገባል። በኦሪት ዘመን ሊቀ ነቢያት ሙሴ ለሕዝቡ
ውሃ ሲያፈልቅላቸው ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ አመስግኖ
ይሰጣቸው ነበር። አንድ ቀን ግን ሕ ዝቡ አስቆጥቶት ስመ
እግዚአብሔርን ሳይጠራ እንኩ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው። በዚያ
ምክንያት ታላቅ መቅሰፍት መጣ። ሙሴም በዚህ ምክንያት ምድረ
ርስት ከነዓንን በሩቅ አይቶ ሳይገባባት ቀርቷል። ስለዚህ እኛም ወሀቤ
ኲሉ ሁሉን ሰጪ እግዚአብሔርን ከመብላታችን በፊት
እናመስግነው።ሳያመሰግኑ መብላት ሰይጣናዊ እንጃ ስልጣኔ
አይደለም።

ጊዜ በሊዕ፦በምንበላት ጊዜ መጥነን ልንበላ ይገባናል። በቅዱሳት


መጻሕፍት ከሦስቱ አርእስተ ኃጣውዕ አንዱ ስስት ነው። በስስት
አንዷን እንጀራ አንድ ጉራሽ አድርጎ በእጅ እየሰገሰጉ መብላት
አይገባም። መጥነን ተረጋግተን ለቁመተ ሥጋ ያህል ልንበላ ይገባል።
ሌላው ቅዱሳን ሊቃውንት በየሐተታቸው ያስቀመጡት ከሰው ፊት
እጃችንን ሰደን ልንበላ አይገባም።

ድኅረ በሊዕ፦ ከምግብ በኋላ ደግሞ የበላነውን የጤና


እንዲያደርግልን ፈጣሪን "ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት
ለመንፈስ ቅዱስ።ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል
ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል የሚለውም እስከመጨረሻው
ልንደግማው ይገባል።ከዚህ በኋላ በእንተ አቡነ አቢብ ይቅር በለን
ብለን ሦስት ጉራሽ እንበላለን። (ይህን የምናደርግበት ምክንያት
እግዚአብሔር ለታላቁ ጻድቅና ሰማእት አቡነ አቢብ ቃል ኪዳን
ስለገባላቸው ነው። አቡነ አቢብ ማለት የክርስቶስን ስቅለት እያሰቡ
ሰውነታቸውን በስለት እየወጉ ይኖሩ የነበሩ ናቸው)። በቀጣይ ክፍል
ስለ አለባበስ የምጽፍ ይሆናል። ያው ባህላችንን እየረሳን መሠረቱ
ላልታወቀ ባዕድ ባህል ራሳችንን አሳልፈን እየሰጠን ስለሆነ ወደኛው
ውድ ባህል እንድንመለስ በማለት አስቤ ነው።

የአለባበስ ሥርዓት

በነገራችን ላይ ለምን እንደምትለብሱ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ብዙ


ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ራስን ከፀሐይ፣ ከውርጭ እና
ከመሳሰሉት ራስን ለመከላከል ነው። ነገር ግን የአለባበስ ሥርዓት ላይ
የምናጠብቅበት ዋናው ፍሬ ምክንያት ከዝሙት ጋር የተያያዘ ስለሆነ
ነው። በአለባበስ ዙሪያ ቅዱስ መጽሐፍ በተለያዩ ቦታዎች ተናግሯል።
የካህናት አለባበስ፣ የሴቶች አለባበስ ተገልጿል። ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ግን ራሳቸውን ይከናነቡ
ለምን አለ? ሙሴስ ሴት የወንድን ወንድ የሴትን ልብስ አይልበስ
ለምን አለ። የወንድ ልብስ ምንድን ነው? የሴት ልብስስ ምንድን
ነው? የሚለውን እንመልከት።

በማየት የሚመጣ ፍትወት ከሴት ይልቅ በወንድ ይጸናል። በመስማት


የሚመጣ ፍትወት ደግሞ ከወንድ ይልቅ በሴት ይጸናል። ወንድ ልጅ
የሴትን ገላ ካየ ፍትወት ይነሳበታል። ፍትወት ከተነሳበት ደግሞ "ወደ
ሴት አይቶ የተመኘ አመነዘረ" የሚለውን የፈጣሪ ሕግ ይሽራል። ሕግ
ከሻረ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት አይገባም። በነገራችን ላይ ይህን
ሰው መንግሥተ ሰማያት እንዳይገባ መሠናክል የሆነችው ሴትም
መሰናክል ስለሆነች መንግሥተ ሰማያት አትገባም። ከታናናሾቹ
ያሰናከለ ወዮለት ብሎ ጌታ የተናገረው ለዚያ ነው። ስለዚህ ብፁዕ
ጳውሎስ ሴቶች ራሳቸውን ይከናነቡ አለ። ከዚህ ላይ ሴቶች
የወንዶችን ልብስ አይልበሱ ሲል ሴቶች ሊለብሱት የሚገባ ልብስ
ተብሎ የተዘረዘረ ነገር የለም። ነገር ግን ከሐዋርያው ጳውሎስ ንግግር
እንደተረዳነው ተገልብቦ "መከናነብ" ራስን ላለማሳየት ነው። ስለዚህ
ሴቶች በየትኛውም መስፈርት አካላቸውን የሚያንጸባርቅ ልብስ
መልበስ የለባቸውም። ሰፋ ያለ ከአካላቸው ያልተጠበቀ ልብስ
ሊለብሱ ይገባል። ወንድ ልጅም እንዲሁ ሴቶችን ለፍትወት
የማይጋብዝ ልብስ ሊለብስ ይገባል። ልብስ የምንለብሰው
እንዲያምርብን እና ሌሎችን በፍትወት ለመሳብ ብለን ከሆነ ልብሱ
ምንም ይሁን ምን ሥርዓት አልባ አለባበስ ይባላል። በዋናነት ልብሱን
የለበስንበትን ምክንያት እንመርምረው።

ሌላው የወንድ ልብስ እና የሴት ልብስ የሚለውን በትውፊት


እናውቀዋለን።
እንደ ኢትዮጵያ ባህል ሴት ልጅ ዘረፍረፍ ያለ ሰፋ ያለ ቀሚስ ነው
የምትለብስ "ቀሚስ በመልበሷም የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ቃል
ትፈጽማለች"። በነገራችን ላይ ጥብቅ ያለ ቀሚስም ያው ሥርዓት
አልባ አለባበስ ነው። ምክንያቱም የአካልን ቅርጽ ያሳያልና። ሌላው
የካህናት አለባበስ በኦሪት ዘሌዋውያን በሰፊው ተገልጿል። ካህናት
ጠምጥመው ልዩ ልብስ የሚለብሱት ስለ ክብረ ወንጌል ነው። እንጂ
ካህናትም ይህንን አለባበሳቸውን ለተርእዮ ካዋሉት እንዲለብሱ
አይፈቀድም። ቅዱስ መጽሐፍ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ
ይላልና። በእኛ አለባበስ ምክንያት በሌላው ፈተና ከሆንን ሌላውንም
ራሳችንንም ወደ ገሐነም የምንልክ ስለምንሆን ወዮልን። ኢትዮጵያዊ
መጽሐፋዊ ትውፊታዊ አለባበስ ይኑረን። የባዕድ ሀገር አለባበስ ተገዥ
አንሁን። የእኛ ባህል አብዛኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ።ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ ከጉልበቱ በላይ ጸምር ወይም አጎዛ ብቻ ይለብስ
ነበር።እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በዚህ ምድር ስትኖር
ሁለት ቀሚስ ልብስ ብቻ ነው የነበራት። ዮሐንስ ወንጌላዊውን
ስታርፍ በአንዱ ቀሚሴ ገንዘኝ።አንዱን ቀሚሴን ደግሞ ለአንዲት ድሃ
ሥጥልኝ ብለዋለች። ልብስ ለከዲነ ዕርቃን ነው። ታላላቁ ቅዱሳንም
መንገድ ላይ የሆነ ልብስ ይጥሉና ሰው ንቆ ከተወው አንስተው
ይለብሱታል። አንስቶ ይዞት ከሄደ ግን ለሰው ይማርካል ማለት ነው
ስለዚህ ፈጣሪየ ከመልበስ አዳነኝ ብለው ይደሰቱ ነበር። ሥለዚህ
ዕርቃናችንን የሚሸፍን ጥብቅ ያላለ ሰፋ ያለ ልብስ እንልበስ።ይህ ነው
ኢትዮጵያዊው አለባበስ።

አነጋገር

በኢትዮጵያ ባህል የብልግና ቃላት አይነገሩም።ለሰሚው ምቾትን


የሚሰጡ ቃላት ተመርጠው ይነገራሉ እንጂ።አሁን አሁን ግን
የብልግና ቃላትን መናገር እንደ ሥልጣኔ እየተቆጠረ ነው።አንዴ
ሰብሰብ ብለን እያወራን አንድ ጓደኛችን ከመካከላችን ተነሳ። እንዴ
ወዴት ልትሄድ ነው? አልነው።እርሱም "አርዮስ ወደሞተበት" ብሎ
መለሰልን። አርዮስ የሞተ ሽንት ቤት አንጀቱ ተዘርግፎ ነው። እና ወደ
ሽንት ቤት እየሄድኩ ነው ሲለን ነው። ሽንት ቤት ከማለት ይልቅ
"አርዮስ የሞተበት" የሚለው ቃል ለሚሰማው የተመቸ ነው።
የብልግና ቃላት በአደባባይ የማይነገሩበት ምክንያት ምንድን ነው
ካልን በዋናነት የዝሙትን ነገር የሚናገሩ ከሆኑ ሰውን በዝሙት ሐሳብ
እንዳንጥለው ነው።በዚህ ምክንያት የኀልዮ በደል በድሎ መንግሥተ
ሰማያትን እንዳያጣ ነው። ቅኔ ቤትም በሌላም ቦታ ጸያፍ የሚባሉ
ቃላትን እንዳንጠቀም የምንከለከልበት ምክንያት ንግግራችንን ሁሉም
ቢሰማው የሚመች እንዲሆን ታስቦ ነው። ንግግራችን ሰሚውን አካል
እንዳይቆጣ እንዳይናደድ እንዳያዝን እንዳይሳደብ እንዳይበሳጭ እና
በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ሕግ የሚያወጡ ነገሮችን እንዳያስብ
እንዳይናገር የሚያደርግ መሆን አለበት።ቢቻል ሰውን ወደ መልካም
ሐሳብ የሚመሩ ንግግሮችን ልንናገር ይገባል።

ባህል ሰፊ ነው። ንግግርን አለባበስን አመጋገብን ያካተተ ነው።


ጴጥሮስ የጌታ ተከታይ መሆኑ የታወቀ በአነጋገሩ በአለባበሱ
በአጠቃላይ ሁኔታው ነው። በሥርዓት መናገር ምንድን ነው?
የሚለውን እንይ። እንግዲህ በንግግር ጊዜ ሦስት መሠረታዊ ነገሮች
ይታሰባሉ። እነዚህም፦
፩ ሞገሠ ቃል
፪ ሳዕስዐ አፍ
፫ ጣዕመ ነገር
ናቸው።እያንዳንዳቸውን በተወሰነ መልኩ እንያቸው።ንግግራችን
ሌላውን አስቆጥቶ ወደ በደል የሚያደርስ እንዳይሆን መጠንቀቅ።
ቁጥብ መሆን ሌላው ሀሳቡን ተናግሮ እንዲጨርስ በጥሞና
ማዳመጥ። ፈጠን ፈጠን አለማለት። ጉድይ ተኮር መሆን። ሰውየውን
ወደ መልካምነት የሚመራ መሆን አለበት።

ለመስማት የፈጠንክ ለመናገር የዘገየህ ሁን።ጌታችን በዚህ ምድር


ሲያስተምር ከእርጋታው የተነሳ የተቀጠቀጠ ሸንበቆ አይሰብርም
ተብሎ ተነግሮለታል። ክልብ ክልብ እያሉ መናገር ደንበኛ ባህል
አይደለም። መጀመሪያ የሌላውን ሰው ሀሳብ በትክክል መረዳት ከዚያ
የመናገሪያ ጊዜ ሲሰጥህ መናገር ይገባል። ታድያ ስትናገር ንግግርህ
ሞገሰ ቃል ጣዕመ ነገር እና ሳዕስዐ አፍ ሊኖርህ ይገባል።

ሞገሠ ቃል
አስወድዶ መናገር ነው። የሚሰማህ አካል እንድትናገር የሚጓጓ መሆን
አለበት። እንጂ ስልችት እስኪለውና መቼ ነው የሚጨርስ እስክትባል
መሆን የለበትም።

ጣዕመ ነገር
አስወድደህ ስትናገር ፍሬ የሌለው ነገር መናገር የለብህም። ነገርህ
የማይረሳና ሰማዕያኑ ሁልጊዜም እያስታወሱት ወደ መልካም ምግባር
ወደብ የሚያደርሳቸው መርከብ መሆን አለበት።

ሳዕስዓ አፍ
ንግግርህ የተከናወነ ቅደም ተከተል ያለው ያልተድበሰበሰ ጥርት ያለ
መሆን አለበት።
በጠቅላላው ንግግራችን ረጋ ያለ፣ ፈጠን ፈጠን ያላለ፣ ነገረ ዘርቅ
የሌለበት። ለሰሚው የሚመቹ፣ የማያስጠሉ፣ የተመረጡ ቃላትን
ልንናገር ይገባናል።ሌላው ንግግራችን ትዕቢት የሌለበት ትሕትናን
የተሞላ መሆን አለበት። ልባቸው የገዘፈ እና የደነደነ ሰዎችን በሐሜት
ላይ በተመሰረተ መረጃ ሳይሆን በተረጋገጠ ማስረጃ ተመሥርተን
ሳንፈራ መገሠጽ ይገባል። ያዘኑትን ደግሞ ልናጽናናቸው ይገባናል።

ሌሎች ምርጥ ባህሎቻችን

ተጋግዞ በደቦ መሥራት፣ የተቸገረን ሰው በእድር ማገዝ ታላላቅ


መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትነት ያላቸው ባህሎቻችን ናቸው።
በኢትዮጵያችን "ዘበልአ ባሕቲቶ ይመውት ባሕቲቶ" ብቻውን የበላ
ብቻውን ይሞታል የሚል ስነ ቃልም አለን። ይህ ማለት የጎረቤታችን
ደስታው ደስታችን ኀዘኑ ኀዘናችን መሆኑን ያመለክታል።
ኢትዮጵያዊው ባህል ግለኝነት(Individualism) ወይም ራስ
ወዳድነት አይደለም። ሁሉም ሰው ስለ ሁሉ ያስባሉ። አንዱ
ስለሁሉም ያስባል። ሁሉም ደግሞ ስለ አንዱ ያስባሉ። (ይህ ውድ
እሴታችን አሁን በዘረኞች እየተሸረሸረ ስለሆነ ልንታገለው
ይገባናል)። ሕገ እግዚአብሔር መጨረሻው ፍቅር ነው። የሌላውን
ደስታ ደስታ ማድረግ እና የሌላውን ኀዘን ኀዘን ማድረግ አንደኛው
የፍቅር መገለጫ ነው። በሌላው የደረሰው ችግር ሁሉ በራሳችን
እንደደረሰ አስበን መፍትሔ መፈለግ ነው ኢትዮጵያዊው እና
ኦርጅናሉ ባህላችን።

የሥራ ባህላችን

ኢትዮጵያዊው ገበሬ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ይነሳና በሬዎቹን ፈትቶ


ጭድ ወይም ገለባ አብልቶ ሞፈሩን እርፉን ቀንበሩን አዘጋጅቶ፣
ውዳሴ ማርያሙን ደግሞ፣ ቁርሱን በልቶ ጠዋት 12 ሰዓት ወደ
እርሻው ማሳ ሄዶ ይጠምዳል። ልክ ማታ 12 ሰዓት ይጨርሳል። አርሶ
አምርቶ ይኽው ከተሜውንም ገጠሬውንም እየመገበ ይኖራል።
ካመረተው እህልም ለቤተክርስቲያን አሥራቱን በኩራቱን አውጥቶ
ይሰጣል። እርሱ እንዲህ ሲያደርግ ሚስቲቱ ደግሞ አክርማ ወይም
ሰበዝ ቀጭታ፣ ጥጥ አባዝታ፣ ያንን ጥጥ በእንዝርት ፈትላ፣ ለባሏም
ለልጆቿም ለእርሷም ልብስ ታዘጋጃለች። ሰበዙን ደግሞ በወስፌ
ሰፍታ መሶበ ወርቅ፣ ወስከንባያ ሠርታ ለቤቷ አስፈላጊ እቃወችን
ታሟላለች፣ ለቤተክርስቲያን ደግሞ ሙዳይ አዘጋጅታ ትሰጣለች።
በዚህ ጠንካራ የሥራ ባህላችን ሙሉ በሙሉ ከጥገኝነት ወጥተን
ቀጥታ ከተፈጥሮ የሚያስፈልገንን እናሟላ ነበር። አሁን ግን በራሳችን
የምንሰራው ነገር እየጠፋ ፍላጎቶቻችን በሌላው አቅርቦት ላይ
የተመሠረቱ እየሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ምናልባት ወደፊት ለአደገኛ
ባርነት ያመቻቸናል። ስለዚህ ሀገር በቀል እውቀቶችን ባንተዋቸው እና
ብናሳድጋቸው መልካም ነው። የሥራ ባህላችን እንዲህ ያለ ጠንካራ
ነበር። አሁን አሁን ግን የእኛን የድሮውን ትተን የውጭ ፍለጋ
መሄዳችን የባርነት መጀመሪያ ይመስላልና እንመለስ።
ማንበብ እውቀት

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ደረቅ ሐዲስ እየተባለ የሚጠራውን ትንቢተ


ኢሳይያስ ሲያነብ እንደነበረ የሐዋ.8 ተገልጿል። ንግሥተ ሳባም
የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት እስራኤል ድረስ ሄዳለች።
ኢትዮጵያውያን ለጥበብ የተለየ ፍቅር ነበረን። ለትምህርት እና
ለእውቀትም ልዩ ክብር ነበረን። የአብነት ተማሪው ባዶ እጁን
ከቤተሰቡ ተለይቶ ሩቅ ሀገር ሄዶ ሲማር ምግቡን ልብሱን ችለው
የሚያስተምሩት የሄደበት ሀገር ሰዎች ናቸው። ሌላው ፈሪሀ
እግዚአብሔር ባህላችን ነበረ። አንድ ሰው በአንዱ በደል ሲያደርስበት
እግዚአብሔርን ፈርቼ ነው እንጂ... ይለዋል። እግዚአብሔርን ፈርቶ
ማድረግ ከሚችሉት ወንጀል መከልከል ድንቅ ባህል ነው። የራሳችን
ባህል የሆኑትን ነገሮች መሠረታቸውን ሳናውቅ በባዕድ ትምህርት
ሚዛንነት ብቻ ማጣጣልና መናቅ አይገባም።

ረድዔተ እግዚአብሔር አይለየን ።

You might also like