You are on page 1of 5

አፀደ ሕፃናት ት/ቤት

የፕሮጀክት ጥናት

ግንቦት፣2015 ዓ.ም
ጎርጎራ
1. የፕሮጄክቱ ማጠቃለያ

/EXCUTIVE SUMMARY/

 የፕሮጀክቱ ባለቤት፡-ምዕራፈ ቅድሳን ጎርጎራ ድብረ ሲና ማርያም


 የፕሮጀክቱ ስም/ስያሜ/፡- የገዳሙ ስም የአፀደ ሕፃናትና የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት
 የፕሮጀክቱ ቦታ፡- ጎርጎራ ከተማ
 የፕሮጀክቱ ዓላማ፡- የአጭርና የረጅም ጊዜ አላማዎችን ተግባራዊ ማድረግ
 የፕሮጀክቱ መነሻ ካፒታል፡ ብር 3,000,000
 የፕሮጀክቱ ፋይናንስ ምንጭ፡- በ ጎርጎራ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን እና በጎ አድራጊ ማህበራት፥ ግለሰቦች
 የፕሮጀክቱ አስፈፃሚ አካል፡- የማኅበሩ የቦርድ አባላት
 ቁጥጥርና ክትትል፡- የማኅበሩ አባላት በሚያቋቁሙት ቡድን
2. መግቢያ

/ INTRODUCTION/

ጎርጎራ ከተማ ከ 5,000 በላይ ሕዝብ ይኖርባታል ተብሎ ይገመታል፡፡ በ ከተማዋ የ አጸደ ሕፃናትና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መክፈት
የሚኖረው ጠቀሜታ በጣም ከፍተኛ ነው”” በዚህም መሠረት ይህ የፕሮጀክት ጥናት በውስጡ የችግሩን ግዝፈትና የፕሮጀክቱን
አስፈላጊነት \ የፕሮጀክቱን ግብ \ ዓላማና ተግባራት \ የፕሮጀክቱን ተጠቃሚዎችና የሚያስፈልገውን በጀትና አጠቃላይ ግብዓት የያዘ
ሲሆን በመጨረሻም የፕሮጄክቱ አዋጭነትና የአስተዳደር/MANAGEMENT/ ሁኔታ እንዲካተት ተደርጋል””
የፕሮጀክቱ መነሻ አስፈላጊነትና የችግሩ ግዝፈት
የፕሮጀክቱ መነሻ
ይህ የአፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤት ፕሮጀክት እንዲጠና መነሻ የሆነው በጎርጎራ ከተማ ዉስጥ የሚገጘ የግል አፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤት
ልማት አለመኖሩ ና የመንግስት የትምህርት ልማት ዘርፍ በዉጤታማነትና በተደራሽነት ረገድ ዉስን መሆኑ እና በአጸደ ህጻናት
ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየዉ የእዉቀት፣የክህሎት ፣የስነምግባርና የአመላከከት ችግር ከፍተኛ ሆኖ መታየቱ ነዉ፡፡
የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት
አንደሚታወቀዉ በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በትምህርቱ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነዉ፡፡ስለሆነም ትዉልዱ
በእዉቀት፤በክህሎት፤ በስነምግባር እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህል ትዉፊት የሚጠብቁና አርአያነት ያላቸዉ እንዲሆኑ ከመንግስተ ጎን
በመሰለፍ የግሉ ሴክተር አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ገዳሙ በ ጎርጎራ ከተማ ት/ቤቱን መክፈቱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የፕሮጀክት
ፕሮፖዛል እንዲዘጋጅ ተደርጎል””

የችግሩ ግዝፈት / PROBLEM STATEMENT/

በማዕከላዊ ጎንደር ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ትምህርት ቢሮ የ 2014 ዓ.ም ሪፖርት እንደሚያሳየዉ የግል አጸደ ኅጻናት ትምህርት ቤት
በጎርጎራ ከተማ አልመኖሩን እና 1 የምንግስት ትምህርት ቤት ብቻ ይገኝል፡፡ ሆኖም ግን ጥራት ያለዉን ትምህርት ለማህበረሰቡ
ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ዉስንነት እንደሚታይባቸዉ የተለያዩ አመላካች ነገሮች ይታያሉ፡፡ በተለይ ከማስተማር ስነ ዘዴ፣ በመንግስት
የተቀመጠዉን ስርዓተ ትምህርት በጥልቀትና አመርቂ በሆነ ደረጃ ከመተግበር አንጻር፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናትን በስነ ምግባር በማነጽ
እና አገር በቀል እዉቀቶችን ከዘመናዊ እዉቀቶች ጋር አጣምሮ ከማቅረብ አኳያ ዉስንነት ይታያል፡፡ ስለሆነም የ ጎርጎራ አጸደ ህጻናት
ትምህርት ቤት ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች በመቅረፍ ረገድ የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ወረዳዉ ዉስጥ በግሉ የትምህርት ልማት
ዘርፍ የሚታየዉን ክፍተት ለመሙላት ታስቦ የተመሰረተ ነዉ፡፡
የፕሮጀክቱ ግብና ዓላማዎች/ GOALS AND OBJECTIVES/
የፕሮጀክቱ ግብ
1. ህፃናት በጥሩ ሥነ ምግባር ታንፀውና ሁለንተናዊ ስብዕናቸው ተሟልቶ ለአገራቸው የበኩላቸውን አስተዋፅዎ
እንዲያበረክቱ ማድረግ
የፕሮጀክቱ ዓላማዎች
ሀ . የአጭር ጊዜ አላማዎች

1. ሕፃናትን ተቀብሎ በማስተማር በጥሩ ሥነ ምግባር ታንፀው እንዲወጡ ማድረግ፡፡

2. ለወገኖች የሥራ እድል መፍጠር ፡፡

ለ. የረጅም ጊዜ አላማዎች

1. የግዕዝና የሥነ ምግባር ትምህርት በማስተማር ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ በምግባር የታነፁ ህፃናት
ማፍራት
2. በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ለመጠበቅ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ለድህነት ቅነሳ
ፕሮግራሙየበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት
3. ተማሪዎች በሁለንተናዊ ስብዕናቸዉ /በአዕምሮ በአመለካከትና በክህሎት/ የዳበሩ እንዲሆኑ በማድረግ
ኢትዮያዊ ማንነታቸዉ ባልተዛባ መልኩ መቅረጽ ነዉ፡፡
5. የፕሮጄክቱ ራዕይና ተልዕኮ /VISION AND MISSION/

5.1 (VISION):-
በቀለም ትምህርት፣በፈጠራ እና በሳይንስና ቴክኖሎጅ ተወዳዳሪ የሆኑና በበጎ የታነፁ
5.2 (MISSION):-ታገዝ
ብቃት ባላቸዉ ባለሙያዎች አማካኝነት ዘመኑን የዋጀ ትምህርት ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በግልና
በህብረት ጠንክሮ መስራት የሚወድ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ብሎም በስነ ምግባር የታነጸ ትዉልድ መፍጠር፡፡

You might also like